"እንግዲህ፡ንስሓ፡ግባ፤አለዚያ፡ፈጥኜ፡ እመጣብሃለሁ፡፡" ራዕ 2፥16
🕊 💖 🕊
[ የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ]
💖
[ 🕊 ቅድስት 🕊 ]
ቅድስት ማለት የከበረች የተለየችና የተመሰገነች ማለት ነው ፤ ይኸውም በባሕርዩ ቅዱስ የሆነው ጌታ ጾምን ቀድሶ የጀመረባት ዕለት በመሆኑ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይህ ሳምንት ቅድስት የሚል ሥያሜ ሰጥቶታል::
ይህ ሳምንት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ እግዚአብሔር የባሕርይ ቅድስና እንዲሁም ቅዱስ እግዚአብሔር ስለቀደሳቸው ቅዱሳን አካላት [ ጾም ቅድስት ፣ ሰንበት ቅድስት ፣ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ወዘተ እያለች ] የምታስተምርበት ሳምንት ነው።
ሰው ሁሉ በቅድስና መንገድ በመመላለስ የክብሩ ባለቤት የመንግሥቱ ወራሽ እንዲሆን እግዚአብሔር " እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ " በማለት ስለማስተማሩ ስፊ ትምህርት ይሰጥበታል።
እግዚአብሔርን ማየትና የእግዚአብሔር የሆነውን ሥርዓት መከተል ስለሚያስችል ዕለት ዕለት መልካም በማድረግ ቤተ መቅደስ ተብሎ የተነገረለትን ሰውነታችንን በንጽሕና በመጠበቅ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕቃ ሆነን መቅረብ እንደሚገባን ይዘከርበታል።
እግዚአብሔር አምላካችን ቅዱስ ነው እያልን በልባችን አምነን በአፋችን መስክረን በተግባር ግን ከቅድስና ርቀን እንዳንኖር እግዚአብሔር እንደቀደሰንና ልጅነትን እንደሰጠን በማመን በተቀደሰ ሁኔታ መኖር ይገባናል።
🕊 💖 🕊
🕊
[ † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
† 🕊 ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ 🕊 †
† በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከእመቤታችን በቀር ከቅዱሳን ሐዋርያት የሚበልጥ አልተነሳም:: "ሐዋርያ" ማለት "ፍንው: ልዑክ: የተላከ: የጽድቅ መንገደኛ" እንደ ማለት ነው:: በምሥጢሩ ግን "ባለሟል" ብለው ሊቃውንቱ ተርጉመውታል::
ይህስ እንደምን ነው ቢሉ :-
¤የፍጥረታት ሁሉ ጌታ: የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ከድንግል ማርያም ተወልዶ: አድጐ: ተጠምቆ: ጾሞ: ከገዳመ ቆረንቶስ ሲመለስ ቀዳሚ ሥራው ያደረገው ደቀ መዛሙርቱን መጥራት ነበር::
ከተከተሉት የ፭ [5] ገበያ ሕዝብ መካከል "ወሐረየ እምሰብአ ዚአሁ አሠርተ ወክልኤተ ሐዋርያተ" እንዲል በመጀመሪያ ፲፪ [12] ቱን ሐዋርያት መረጠ::
† እሊህም :-
፩. ዼጥሮስ የተባለ ስምኦን
፪. እንድርያስ [ወንድሙ]
፫. ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
፬. ዮሐንስ [ወንድሙ]
፭. ፊልዾስ
፮. በርተሎሜዎስ
፯. ቶማስ
፰. ማቴዎስ
፱. ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ
፲. ታዴዎስ [ልብድዮስ]
፲፩. ናትናኤል [ቀናተኛው ስምዖን] እና
፲፪. ማትያስ [በይሁዳ የተተካ] ናቸው:: [ማቴ.፲፥፩] [10:1]
† እነዚህን ፲፪ [12] አርድእቱን ከጠራ በሁዋላ ለ፫ [3] ዓመታት ከ፫ [3] ወራት ከዋለበት ሲማሩ ይውሉ ነበር:: ሌሊት ደግሞ ምሥጢር ሲያስተረጉሙ ያድሩ ነበር::
ጌታ እንደሚገባ ካስተማራቸው በሁዋላ ከፍ ያለ ኃላፊነትን ሾማቸው:: ለዓለም እረኞች: የእርሱም ባለሟሎች ሆኑ:: እጅግ ብዙ መከራ እንደሚገጥማቸው ነገራቸው:: [ማቴ.፲፥፲፮] (10:16), [ዮሐ.፲፮፥፴፫] (16:33) በዚያው ልክ ክብራቸውንም አከለላቸው:: [ማቴ.፲፱፥፳፰] (19:28)
ሥልጣናቸው ደግሞ እስከዚህ ድረስ ሆነ:: "በምድር ያሠራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል: በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል::" [ማቴ.፲፰፥፲፰] (18:18) "ይቅር ያላችሁዋቸው ኃጢአታቸው ይቀርላቸዋል: ያላላቹሃቸው ግን አይቀርላቸውም::" [ዮሐ.፳፥፳፫] (20:23)
የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ [ማቴ.፲፮፥፲፱] (16:19): እረኝነትን [ዮሐ.፳፩፥፲፭] (21:15) ተቀበሉ:: ጌታ በንጹሕ አንደበቱ ሐዋርያቱን እጅግ ሲያከብራቸው "ጨው: የዓለም ብርሃናት" [ማቴ.፭፥፲፫] (5:13) አላቸው:: ወንድሞቹም ተባሉ:: [ዮሐ.፯፥፭] [7:5] ከዚህም በሚበልጥ በሌላ ክብር አከበራቸው::
ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ በጌታ ሕማማት ጊዜ ገና ነበሩና አንዳንዶቹ ፈርተው ተበተኑ:: ተመልሰው ግን በጽርሐ ጽዮን ሲጸልዩ ሰንብተው የጌታን ትንሳኤ ተመለከቱ:: እጆቹን: እግሮቹንም ዳስሰው ሐሴትን አደረጉ::
ለ ፵ [40] ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓት: ሌላም በፍጡር አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢራትን ተምረው: ጌታ ሊቀ ዽዽስናን ሹሟቸው ዐረገ::
ለ ፲ [10] ቀናት በእመ ብርሃን ሥር ተጠልለው ሲጸልዩና በአንድ ልብ ሲተጉ ሰንብተው መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው:: በአንዴም ከፍርሃት ወደ ድፍረት ተመልሰው ፍጹማን: ብርሃናውያን ሆኑ:: ፸፩ [71] ልሳናትን ነስተው በአንዲት ስብከት ብቻ 3ሺ ነፍሳትን ማረኩ:: [ሐዋ.፪፥፵፩] (2:41)
ቅዱሳን ሐዋርያት በኅብረት ለአንድ ዓመት ያህል በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ እየተመላለሱ አስተምረው ብዙ እሥራኤላውያንን ወደ ክርስትና ማርከዋል:: ከዚህ በሁዋላ ግን እንደ ትውፊቱ ዓለምን በእጣ ለ ፲፪ [12] ተካፈሏት::
ይህ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ አብሯቸው ነበርና ለእያንዳንዳቸው እንደሚገባቸው አሕጉረ ስብከቶች ደረሷቸው:: እነርሱም ደቀ መዛሙርቶቻቸውን አስከትለው ለታላቁ መንፈሳዊ ዘመቻ ወረዱ::
በሔዱበት ቦታም ከተኩላ: ከአንበሳና ከነምር ጋር ታገሉ:: በጸጋቸውም አራዊትን [ክፉ ሰዎችን] ወደ በግነት መልሰው ለክርስቶስ አስረከቡ:: በየሃገሩ እየሰበኩ ድውያንን ፈወሱ:: ለምጻሞችን አነጹ:: እውራንን አበሩ:: አንካሶችን አረቱ:: ጐባጦችን አቀኑ:: ሙታንንም አስነሱ:: እልፍ አእላፍ አሕዛብንም ወደ መንጋው ቀላቀሉ::
ስለዚህ ፈንታም ብዙዎቹ በእሳት ተቃጠሉ:: ቆዳቸው ተገፈፈ:: በምጣድ ተጠበሱ:: ደማቸው በምድር ላይ ፈሰሰ:: ከአንድ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በቀር ሁሉም ይህችን ዓለም በሰማዕትነት ተሰናበቱ:: ጨው ሆነው አጣፍጠዋልና: ብርሃንም ሆነው አብርተዋልና እናከብራቸዋለን:: "አባቶቻችን: መምሕሮቻችን: ጌቶቻችንና ሊቆቻችን" እንላቸዋለን::
ቅዱስ ማትያስ ስም አጠራሩ ይክበርና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተሰቦቼ ብሎ ከመረጣቸው ፻፳ [120] ቅዱሳን አንዱ : ፫ [3] ዓመት ከ፫ [3] ወር ከጌታችን እግር ቁጭ ብሎ የተማረ: በይሁዳ ፈንታ ከ፲፪ [12]ቱ ሐዋርያት ይቆጠር ዘንድ መንፈስ ቅዱስ የመረጠው ሐዋርያ ነው::
ቅዱሱ ሐዋርያ በዕጣ በደረሰው ሃገረ ስብከቱና በሌሎቹም ዓለማት ለወንጌል አገልግሎት ብዙ ደክሙዋል:: በተለይ የሰውን ሥጋ ወደሚበሉ ሰዎች ሃገር ገብቶ ወንጌልን ቢሰብክላቸው ዓይኖቹን አውጥተው ከብዙ ስቃይ ጋር ለ ፴ [30] ቀናት ሣር አብልተውታል::
እሱ ግን በትእግስትና በፈጣሪው ኃይል ድንቅ ተአምር አድርጐ አሳምኖ አጥምቋቸዋል:: ከብዙ ተጋድሎና ቅድስና በሁዋላም በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና አርፏል::
† አምላከ ቅዱሳን ሐዋርያት ቸርነቱን ያብዛልን:: በምልጃቸው ከክፉ ጠብቆ ከበረከታቸው ይክፈለን::
🕊
[ † መጋቢት ፰ [ 8 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ [ከ፲፪ [12] ቱ ሐዋርያት]
፪. ቅዱስ አርያኖስ ሰማዕት [በዘመነ ሰማዕታት ብዙ ክርስቲያኖችን ያሳድድ የነበረና ጌታ በንስሃ የጠራው]
፫. ቅዱስ ዮልዮስ ሊቀ ዻዻሳት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
፪. ኪሩቤል [አርባዕቱ እንስሳ]
፫. አባ ብሶይ [ቢሾይ]
፬. አቡነ ኪሮስ
፭. አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
† " . . . እንዲህም ብለው ጸለዩ:: 'አቤቱ ልብን ሁሉ የምታውቅ አንተ ከእነዚህ ከሁለቱ የመረጥከውን አንዱን ግለጥ?' . . . ዕጣ አጣጣሉአቸው ዕጣውም በማትያስ ላይ ወጣ:: ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋርም ተቆጠረ::" † [ሐዋ.፩፥፳፬]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
ቅዳሜ - መጋቢት 07 2016 ዓም
ማቴዎስ 24-28
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የማቴዎስ ወንጌልን ከምዕራፍ 24-28 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ስለ ጌታችን ዳግም ምጽአቱ እና ስለ ዓለም ፍጻሜ ምልክቶች፥ ስለ ሰዓትዋና ስለ ዕለቲቱ፥ ስለ ዐሥሩ ደናግል፥ ስለ መክሊቶቹ የተሰጠ ምሳሌ፥ ስለ ክርስቶስ ሁለተኛ መምጣት፥ ስለ አይሁድ ምክር፥ ጌታችንን ሽቱ ስለ ቀባችው ሴት፥ ስለ አስቆሮቱ ይሁዳ፥ ስለ ፋሲካ በዓል፥ ስለ ምሥጢረ ቁርባን ሥርዓት፥ ጌታችን በጌቴሴማኒ ስለ መጸለዩ፥ ስለ መያዙ፥ ጴጥሮስ ስለ መካዱና መመለሱ፥ ስለ ይሁዳ የሕይወት ፍጻሜ፥ ስለ ጌታችን መከራ እንዲሁም ስለ መሰቀሉ፥ ስለ መሞቱ እና ስለ ትንሳኤው እናነባለን።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) ጌታችን ስለ ዓለም ፍጻሜ ምልክቶች ምን ተናገረ?
2) ጌታችን ስለ መክሊቶች የሰጠው ምሳሌ ምን ነበር? እናንተስ ከዚህ ምሳሌ አንጻር መክሊታችሁን አትርፌያለሁ ብላችሁ ታስባላችሁ?
3) በጌታ ዳግም ምጽአት ጊዜ ምን እንደሚፈጠር ተጽፏል? በአጭሩ ግልጹ።
4) የምሥጢረ ቁርባን ሥርዓት ስለተመሰረተበት ሁኔታ ምን ተጽፏል?
5) ጌታችን ከሰቀሉት በኋላ የሰቀሉት ሰዎች ምን ያደርጉ ነበር?
6) ጌታችን የተቀበረበትን ሁኔታ በአጭሩ ግለጹ።
7) ጌታችን ከማረጉ አስቀድሞ ለሐዋርያት የሰጣቸው ትእዛዝ ምን ነበር?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
ምስጢረ ተክሊል
@kooblife
@kooblife
#Join & share
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
/channel/+Tzj6PS4vttnGfrWW
▬ ▬ ▬▬ ▬▬ ▬▬
ስለ "ማህተብ" መጽሃፍ ቅዱስ ላይ የት ነው የማገኘው? ጥቅስ share adtgulign
Читать полностью… †
† 🕊 ዘ ወ ረ ደ 🕊 †
[ የጾምን መግባት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ ትምህርት ! ]
💖
[ ክፍል አራት ]
" ጾምም እንደዚህ ናት ፤ ዕረፍተ ነፍስን ትሰጣለች፡፡ ለሽማግሌዎች ውበትን ታጎናጽፋቸዋለች ፤ ወጣቶችን በቀና ጎዳና ትመራቸዋለች ፤ ማስተዋልን ትለግሳቸዋለች ፤ ኹሉንም ሰው እንደ ዘውድ እንደ አክሊል ያማረ የተወደደ ታደርገዋለች፡፡
እንግዲያውስ ዛሬ ምንም ዓይነት ሁካታ አይኑር፡፡ ሁካታስ ይቅርና ምልክቱም አይኑር፡፡ የምግብ ዓይነትን ለማንጋጋት የሚራወጥ ማንም አይገኝ፡፡ ኹሉም ሰው ከእንደዚህ ዓይነት ግብር ይራቅ፡፡ ከተማችን እንደ ተወደዱ ቈነጃጅት አመለ ሸጋና የምትማርክ ትኹን፡፡
በአንድ ሌሊት ውስጥ ምን ያህል ለውጥ እንዳለ ስመለከትና የትናንቱን ጫጫታ ሳስታውሰው ጾም እንደ ምን ያለች ፍቱን መድኃኒት መኾንዋን ዐይቼ በእጅጉ እደነቃለሁ፡፡ የእያንዳንዱን ሰው አመለካከት እንደ ምን እንደምትቀይር ተመልክቼ በእጅጉ መደነቅን ይይዘኛል ፡ የገዢዎችን ብቻ ሳይኾን የተገዢዎችንም ፣ የጌቶችን ብቻ ሳይኾን የባሮችም ፣ የወንዶችን ብቻ ሳይኾን የሴቶችንም ፣ የባለፀጎችን ብቻ ሳይኾን የድኾችንም ፣ ቃለ እግዚአብሔር የሚያውቁትን ብቻ ሳይኾን የማያውቁትንም እንደ ምን ልበ ንጹሀን እንደምታደርጋቸው ተመልክቼ አብዝቼ እደነቃለሁ፡፡
የገዢዎችን ብቻ ሳይኾን የተገዢዎችንም ብዬ መናገሬስ ስለ ምንድን ነው ? ነገሥታትም ከነዘውዳቸውና ከነሙሉ ማዕርጋቸው ኾነው ራሳቸውን ለጾም ስለሚያስገዙ ነዋ ! ዛሬ በባለጸጋውና በድኻው ማዕድ ልዩነት የለውም፡፡ ኹሉም ሰው ተርታ ኑሮን የሚመራ ነው፡፡ የቅምጥልነትን ሕይወት የሚመራ የለም፡፡ ታይታን የሚፈልግ የለም፡፡ ኹሉም ሰው በቤቱ ካለው የሰባ ፍሪዳና ወይን ይልቅ እዚህ በቤተ ክርስቲያን ያለውን ሰማያዊውን ማዕድ ሽቶ የመጣ ነው። "
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
ሐሙስ - መጋቢት 05 2016 ዓም
ማቴዎስ 14-18
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የማቴዎስ ወንጌልን ከምዕራፍ 14-18 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ስለ ሄሮድስና ስለ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ጌታችን እንጀራና ዓሳ አበርክቶ ስለማብላቱ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለሚተዉ ሰዎች፥ ብዙዎችን ከደዌ ስለ መፈወሱ፥ ከሰማይ ምልክት ስለሚሹ ሰዎች፥ ከፈሪሳውያን ትምህርት ራስን ስለመጠበቅ፥ ስለ ራሱ እንደጠየቃቸው እና ሕማሙንና ሞቱን ስለ መግለጡ እናነባለን። በተጨማሪም ክብሩን በደብረ ታቦር ስለ መግለጡ፥ ጋኔን የሚጥለውን ሰው እንደፈወሰ፥ ትሕትናን እንዳስተማረ፥ ስለ ጠፋው በግ እና ስለ ንጉሡ እና አገልጋዮቹም ምሳሌ እንደሰጠ ተጽፎ እናገኛለን።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) ጌታችን በአምስት እንጀራ እና በሁለት ዓሳ ያደረገው ተዓምር ምንድር ነው? ይኽስ በሕይወታችሁስ እጃችሁ ላይ ያለው ነገር ትንሽ በሆነ ጊዜ እግዚአብሔርን ስለማመን ምን ያስተምራችኋል?
2) ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ ጌታ በውሃ ላይ በሄደ ጊዜ ምን ተፈጠረ? ከተፈጠረው ነገር በመነሳት፥ በሕይወታችሁ ውስጥ ባለው ማዕበል ላይ ያተኮራችሁበትን፥ እንዲሁም በክርስቶስ ላይ ያተኮራችሁበትን ጊዜ በማነጻጸር ልዩነቱን ግለጹ።
3) ጌታችን ሰውን የሚያረክሰው ምንድር ነው አለ? ከምላሹ በመነሳት፥ ውጫዊ ድርጊታችሁ ብቻ ሳይሆን ልባችሁም በእግዚአብሔር ዘንድ ንጹህ እንዲሆን ምን ማድረግ ይኖርባችኋል?
4) ከነዓናዊቷ ሴት ጌታችን ልጇን ይፈውስላት ዘንድ በለመነችው ጊዜ ምን ተፈጠረ? እምነት እና አዘውትሮ ያለመሰልቸት ወይም ተስፋ ባለመቁረጥ እግዚአብሔርን መጠየቅ ስለሚያስገኘው ጥቅምስ ምን ያስተምራችኋል?
5) ‘የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?’ ለሚለው ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ የመለሰው ማነው? የጌታችንስ ምላሽ ምን ነበር? እናንተስ፥ የሰውን ልጅ ማን ትሉታላችሁ?
6) ጌታችን መስቀላችንን ተሸክሞ እርሱን ስለመከተል ምን አስተማረ? በየቀኑ ጌታችንን በመከተል ውስጥስ መስቀላችንን መሸከም የሚገባን እንዴት ነው?
7) ጌታችን ክብሩን በደብረ ታቦር ከገለጠ በኋላ፥ ሐዋርያቱ ስለ ኤልያስ መምጣት ለጠየቁት ጥያቄ የሰጣቸው ምላሽ ምንድር ነው? ይህስ ነገሮችን ሁሉ በቀጥታ መተርጎም ስለሚያመጣው የአረዳድ መዛባት ምን ያስተምራችኋል?
8 ) ጌታችን የሰናፍጭ ቅንጣት የምታህልን እምነት መሠረት አድርጎ ምን አስተማረ?
9) ጌታችን አንድን ሕፃን ልጅ በመጠቀም ስለ መንግሥተ ሰማያት ያስተማረው ትምህርት ምንድር ነው? ይህ ትምህርት በሕይወታችሁ ውስጥ ትሑት ስለመሆን ምን ያስተምራችኋል?
10) ጌታችን የጠፉትን ስለመፈለግ የመሰለው ምሳሌ ምንድር ነው?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
/channel/c/2014228571/1
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] 🕊
▷ " ት ክ ክ ለ ኛ ጸ ሎ ት "
[ " በቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ... ! " ]
[ 🕊 ]
----------------------------------------------------
" ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።" [ ፊልጵ.፬፥፮ ]
🕊 💖 🕊
[ የማይሰለች ተጋዳይ ፤ የክብር ኮከብ ! ]
" እንግዲህ ከሰው ተለይቶ ወደ ጫካ ገባ ፤ በዚያም ኖረ። በበጋው ፡ ሓሩር ፡ በክረምቱ ፡ ቍር ፡ እየተሠቃየ ፡ ኖረ ። በሰውነቱ ላይ ፡ ልብስን ፡ አልለበሰም ፡ ዕራቁቱን ፡ ነበረ እንጂ ራቁቱን ፡ በብርድ ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ይጸልይ ነበር ፤ ወገቡንም ፡ በማቅ ፤ በሠንሰለት ታጥቆ ነበር ። ከዚያ ፡ ጫካ ፡ ቅዝቃዜ ፡ የተነሣም ፡ ሰውነቱ ፡ አልቆ አጥንቱ ፡ ደርቆ ፡ ነበር።
ሰውነቱንም ፡ በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ዕራቁትሽን ፡ ትቆሚአለሽና ፡ እወቂ ፥ ጽኚ በርቺ ፡ ጨክኚ ፡ ይላት ፡ ነበር ፤ እንደዚህ ፡ ባለ ፡ ሥራ ፡ በጾምና ፡ በጸሎት ፡ በስግደትና ፡ በብዙ ፡ ትጋት ፡ ቀንም ፡ ሌሊትም ፡ ጽሙድ ፡ ሆኖ ፡ ኖረ።
ያለ ዕረፍት ብዙ ፡ ጸሎትን ፡ ይጸልይ ፡ ብዙ ፡ ስግደት ይሰግድ ነበር ። ሥጋው እስኪደርቅ : ቍርበቱም ፡ ከአጥንቱ እስኪጣበቅ ፡ ድረስ ከእንጨት ፡ ፍሬና ሥራ ሥር ፡ ወይም ፡ ከአትክልት ፡ ወይም ገዳማውያን ፡ ከሚመገቡት ፡ ከሌሎች ፡ ፍሬያት ፡ ምንም፡ ምን ፡ የሚመገበው አልነበረውም : ለሥጋውም ፡ ምንም ፡ ምን ፡ ምክንያት ፡ አልሰጠም።
መላእክትም : ዘወትር : ይጎበኙት ፡ ነበር ፤ በሥራውም ፡ በቃሉም፡ እንደነሱ ፡ ነበርና ፤ በገድልና ፡ በትሩፋት ፡ የሚመስለው : ማነው ፡ምድራዊ : ምግብ : የተመገበበት : ጊዜ : የለም ፤ ውሃን አልጠጣም ፤ ምንም ፡ ምን ፡ ልብስ ፡ አልለበሰም ፤ ፈጽሞ ፡ ለሥጋው አላደላም ።
በእውነትም ፡ አቡነ ፡ ገብረ : መንፈስ : ቅዱስ : መላእክትን : መሰለ ፤ በዚህ ፡ በኃላፊው ፡ ዓለም ፡ ለመብል ፥ ለመጠጥ ፥ አላሰበም። ስለ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብሎ ፡ ተራበ ተጠማ ። "
[ ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
''እውነተኛ ጿሚ ራሱን ከክፉ ምግባራት የከለከለ፤ ከንቱ የሆኑ ንግግሮችን ከመናገር የተቆጠበ፣ ሐሰትን የማይናገር፣ ሐሜተኛ ያልሆነ፣ በማንም ላይ የማይፈርድ፣ሽንገላን የማይወድና እኒህንም ከመሰሉ ነገሮች ራሱን የተጠበቀ ፣የማይቆጣ፣ የማይበሳጭ ፣ተንኮለኛ ያልሆነ ፣ ቂመኛ ያልሆነና፣ እነዚህን ከመሳሰሉ ክፋቶች ሁሉ የራቀ ሰው ነው፡፡
ሕሊናህ ኃጢአትን ከማሰብ ይጡም፡ አእምሮህም ኃጢአትን ከማስታወስ ይከልከል፡፡ ክፉን ከመመኘት ሁሉ ጡም፡፡ ዐይኖችህ ከንቱ የሆኑ ነገሮችን ከመመልከት፣ ጆሮህም ከንቱ ከሆኑ ዘፈኖችና ከሐሜተኞች ሹክሹክታዎች ጠብቅ፡፡ አንደበትህ ከሐሜት፣ በሌላው ላይ ከመፍረድ ፣ ከስድብ፣ ከውሸት ፣ከማታለል፣ከሽንገላ ንግግሮች እንዲሁም ከማይጠቅሙና አጸያፊ ከሆኑ ቃላት ይጡሙ፡፡ እጆችህም ሰውን ከመግደልና የሌላውን ንብረት ከመዝረፍ ይጡሙ፡፡ እግሮችህም ኃጢአትን ለመፈጸም ከመሄድ ይጡሙ፡፡ ከክፉ ተመለስ መልካምንም ፈጽም፡፡''
#ቅዱስ_ኤፍሬም
እኛስ እውነተኛ ጿሚ መባል ይገባን ይሆን?
የተክሌ አቋቋም ዝማሜ ምልክት
@kooblife
@kooblife
#Join & share
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
/channel/+Tzj6PS4vttnGfrWW
▬ ▬ ▬▬ ▬▬ ▬▬
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] 🕊
▷ " ት ክ ክ ለ ኛ ጾ ም "
[ " በቅዱሳን አባቶቻችን አንደበት ... ! " ]
[ 🕊 ]
----------------------------------------------------
" በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ ፥ ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትና ለመታገሥ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ ፥ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ ፥ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን።" [ ቆላ.፩፥፲ ]
🕊 💖 🕊
†
† 🕊 ዘ ወ ረ ደ 🕊 †
[ የጾምን መግባት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ ትምህርት ! ]
💖
[ ክፍል ሁለት ]
" እንኪያስ እጅግ የምወዳችሁ ምእመናን ሆይ ! ከኹሉም በፊት እነዚህን ነገሮች በስፋት እንነጋገርባቸው ዘንድ ፤ ዳግመኛም አንዳች የሚረባንን ነገር ይዘን ወደ ቤታችን እንመለስ ዘንድ ቃላችንን በታላቅ ትጋትና ጉጉት ሆናችሁ ትቀበሉት ዘንድ አሳስባችኋለሁ፡፡
ኹላችንም ወደዚህ ጉባኤ ስንመጣ እንዲሁና ያለ ዓላማ አይደለም፡፡ ወሬ ለማውራት ፣ ምን እንደተባለ እንኳን ሳንሰማ ለማጨብጨብ ፣ ከዚያም ምንም የሚረባ ነገርን ሳንይዝ ወደ ቤታችን ለመመለስ ወደዚህ ጉባኤ አልመጣንም፡፡ እኔ የመጣሁት ለነፍሳችሁ ድኅነት የሚጠቅም አንዳች ነገርን ለመናገር ነው ፤ እናንተም ስትመጡ በእኔ በባሪያው አድሮ እግዚአብሔር የሚናገረውን ነገር አድምጣችሁ ለመጠቀምና አንዳች የሚረባ ነገርን ይዛችሁ ወደ ቤታችሁ ለመመለስ ነው፡፡
ተመልከቱ ! ቤተክርስቲያን ማለት ቤተ ድኅነት ናት፡፡ ወደ እርሷ የሚመጡትም ለችግራቸው ተገቢውን መድኃኒት አግኝተው መሔድ አለባቸው፡፡ ተግባራዊ የኾነ ለውጥ ሳያመጡ ቃለ እግዚአብሔርን መማር ብቻ ምንም ጥቅም እንደሌለው ሲናገርም ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ እንዲህ ብሏል ፦
"በእግዚአብሔር ፊት የሚጸድቁት ሕግን የሚያደርጉት እንጂ ሕግን የሚሰሙ አይደሉም፡፡" [ሮሜ.፪፥፲፫]
በቃል መነገሩ ፣ በልብ መታሰቡ ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መዘገቡ ከፍ ከፍ ይበልና አምላካችን ክርስቶስም ሲያስተምር ፦
"በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡" ብሏል [ማቴ.፯፥፳፩] ስለዚህ ተወዳጆች ሆይ ! ቃሉን በመስማታችን ብቻ አንዳች የምንጠቀመው ነገር ስለሌለ የሰማነውን የምናደርግ እንጂ የምንሰማ ብቻ አንሁን፡፡ እንዲህ ከሆነም እምነታችን ሕይወት ያለው እምነት ይሆናል፡፡
በመኾኑም ስለ ጾም የሚሰጠውን ስብከት ለማዳመጥ እዝነ ልቦናችሁን ክፈቱ፡፡ ከትሕትና እና ዓይናፋር ሙሽሪት ጋር ለማነጻጸር ያህል ፦ ሙሽሪቱን በሰርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች አስቀድመው ቤቱን ያስጌጡታል ፡ ይጠርጉታል፡፡ የቆሸሸ ልብስን የለበሰ ሰው ወደ ሰርጉ አዳራሽ እንዳይገባ ያደርጉታል፡፡ ወደ አዳራሹ መግባት የሚችለው የሰርግ ልብስ የለበሰ ሰው ብቻ ነው፡፡
እናንተም እንዲሁ ልታደርጉ ይገባችኋል ፦ ልቡናችሁን በማንጻት ፣ አብዝቶ ከመብላትና ራስን ካለመግዛት በመራቅ - የምግባር እናት ፣ የማስተዋልና የሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትሆን ጾምን ደጀ ልቡናችሁን በመክፈት ልትቀበሏት ይገባችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ታላቅ ሐሴት ታደርጋላችሁ ፤ እርሷም ቁስለ ነፍሳችሁን ትፈውስላችኋለች፡፡
ሌላ ምሳሌ መስዬ ብነግራችሁ ፦ ሐኪሞች በህሙማን ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻና መርዘኛ ፈሳሽን ማስወገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ ሕሙማኑ ምግበ ሥጋን ከመውሰድ እንዲቆጠቡ ያደርጓቸዋል፡፡ ሕሙማኑ ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከሉ ግን ሐኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት የተፈለገውን ያህል ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም የነፍስንና የሥጋን ቁስል የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚህ በላይ ልንሆን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡ ድህነትን የምንሻ ከሆነ ልቡናችንን ንጹህና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል ፤ እንዲህ ካልሆነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡"
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
✨🍃✨🍂✨🍃✨🍂✨🍃✨🍂✨
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ለዐቢይ ጾም ሁለተኛው እሑድ በአዘጋጀው ምስጋና አማካኝነት ዕለቱ ‹‹ቅድስት›› የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ትርጉሙም
‹‹የተለየች፣ የተመረጠች፣ የከበረች›› ማለት ነው።
መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ገጽ ፯፻፹፬
“ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ፤ ሀቡ ስብሐተ ለስሙ፤ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ፤ ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት ኀበ ፃፄ ኢያማስኖ ወኢይረክቦ ሰራቂ፤ ድልዋኒክሙ ንበሩ ዘበላዕሉ ጸልዩ ኀበ ሀሎ ክርስቶስ”
“ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ሥራውንም ለአሕዛብ ንገሯቸው፤ ለስሙም ምስጋናን አቅርቡ ሰንበትን አክብሩ፤ እውነትንም አድርጉ፤ ብል የማያበላሸው ሌባም የማያገኘው በሰማያት ያለ መዝገብን ለእናንተ ሰብስቡ፤ ተዘጋጅታችሁም ተቀመጡ፤ ክርስቶስ ወዳለበት ወደ ላይ አስቡ፡፡“
†
[ የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ]
[ 🕊 ቅድስት 🕊 ]
💖
" ቅድስት " ማለት ‹ የተለየች ፣ የነጻች ፣ የከበረች › ማለት ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን ጾም የጀመረባት ፣ ልዩ ፤ የተቀደሰች ፤ የከበረች ፤ ልዩ ፣ ንጹሕ ፣ ክቡር በሚኾን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጾመች መኾኗን ያመላክታል፡፡
ይህች ጾም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አራት የተገለጠችው የጌታችን ጾም ስትኾን ፣ ስያሜዋና የዕለቷ የምስጋና ሥርዓትም የቅዱስ ያሬድ ነው፡፡አምላካችን በገዳመ ቆሮንቶስ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት በጾመበት ጊዜያት እነዚህ ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል አድርጓል፡፡
ሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ የሚባሉትም ፦ ትዕቢት ፣ ስስትና ፍቅረ ንዋይ ናቸው፡፡ በእነዚህ ሦስት ኃጢአቶች ጌታችን በዲያሎስ በተፈተነ ጊዜ በትዕቢት ቢመጣበት በትሕትና ፤ በስስት ቢመጣበት በትዕግሥት ፤ በፍቅረ ንዋይ ቢመጣባት በጸሊዓ ንዋይ ጌታችን ዲያሎስን ድል አድርጎታል፡፡ ለእኛም እነዚህን ድል ለማድረግ የምንችልበትን ጥበብ – ጾምን ገልጦልናል፡፡
ትዕቢት ያልተሰጠንን መሻት ፣ ስስት አልጠግብ ባይነት ስግብግብ መኾን ፣ ፍቅረ ንዋይ ለገንዘብ ሲሉ ፈጣሪን መካድ ነው፡፡ አንደ ክርስቲያን ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል ካደረገ ሌሎችን ኃጣውእ በቀላሉ ድል ማድረግ ይቻለዋል፡፡
[ በመምህር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ ]
🕊 💖 🕊
†
[ 🕊 ድምፀ ተዋሕዶ 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
[ ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ። ]
[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊
[ " ቅ ዱ ሳ ት መ ጻ ሕ ፍ ት ! " ]
[ ክፍል ዘጠኝ ]
" ይህን በመጀመሪያ እወቁ ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ፤
ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።" [፪ጴጥ.፩፥፳]
💖 ድንቅ ትምህርት 💖
[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]
" የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል።" [ ምሳ.፩፥፴፫ ]
† † †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
👇
ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወተአምራቲሁ
በግእዝና አማርኛ
አሳታሚ የምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳምና የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም በአንድነት
@kooblife
@kooblife
#Join & share
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
/channel/+Tzj6PS4vttnGfrWW
▬ ▬ ▬▬ ▬▬ ▬▬
†
[ 🕊 መዝሙረ ተዋሕዶ 🕊 ]
🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒
[ ኦርቶዶክሳዊ የተቀደሰ ያሬዳዊ ዝማሬ ሰዓት ]
[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]
🕊
በስመ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ንጹሕና የተቀደሰ ነው ፥ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ልመና የሚቀርብበት ፣ ይቅርታና ምሕረት የሚጠየቅበት ፣ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚዘጋጅ ንጹሕ መስዋዕት ነው ፥ በአበው ጸሎት ይዘጋጃል ፥ ከስጋዊና ከደማዊ ሀሳብ የራቀ ነው ፥ ልቦናን ወደ ንስሐ ይጠራል ፥ ከኃጢአትና ከክፉ ሥራ የመለየት ኃይል አለው ፥ ክፉ መንፈስን ከሰው ልብ ያርቃል ፥ መረጋጋትን ልቦናን ዘልቆ የሚሰማ ውስጣዊ ሰላምን ይሰጣል ፥ በአሚነ ሥላሴ ያጸናል ፥ የክርስቶስን የባህርይ አምላክነትና መሐሪነት ይመሰክራል ፥ የእመቤታችንን ፍቅር በልቦና ያሳድራል ፥ በእናትነቷና በምልጃዋ እንድንታመን ያደርጋል ፥ በቅዱሳን ጸሎትና በቃል ኪዳናቸው ያጸናል ፥ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እናውቅ ዘንድ መንገድ ይመራናል ፥ ፈሪሐ እግዚአብሔርንና ፍቅረ እግዚአብሔርን ያጎናጽፈናል፡፡
† † †
ተወዳጆችሆይ ፦ በተቀደሰ ሰማያዊ ያሬዳዊ ዜማ ነብሳችንን እናስጊጣት፡፡ ከደጋጎቹ አባቶቻችን ጋር ከዓለም ርኩሰት በተለየ የተቀደሰ ዝማሬ አምላካችን እግዚአብሔርን እናመሥግን፡፡ ለስጋዊ ጆሮዎች ከሚመች ከረከሰ የተሃድሶ የኑፋቄ እርሾ ልቦናችንን እንጠብቅ፡፡ ገንዘብን ስለመውደድ ከሆነ ከሥጋዊ ሥራ ፈጽሞ እንለይ፡፡
🍒
[ 🕊 ወደዚች አገር አወጣው ! 🕊 ]
[ ከአገርህና ከዘመዶችህም ወጥተህ ወደማሳይህ ወደ ማንኛውም ምድር ና አለው።
በዚያን ጊዜ ከከለዳውያን አገር ወጥቶ በካራን ተቀመጠ። ከዚያም አባቱ ከሞተ በኋላ እናንተ ዛሬ ወደምትኖሩባት ወደዚች አገር አወጣው። ]
{ ሐዋ. ፯ ፥ ፫ }
† † †
💖 🕊 💖
🕊
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞
መጋቢት ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
✞ ሰማዕትነት በቅዱስ ቴዎዶጦስ ሕይወት ✞
🕊 † ቅዱስ ቴዎዶጦስ † 🕊
በ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ጊዜው ለክርስቲያኖች ሁሉ ፍጹም የመከራ ከመሆኑ የተነሳ "ዘመነ-ሰማዕታት" ሲባል በወቅቱ ከ፵፯ [47] ሚሊዎን በላይ ክርስቲያኖች ተጨፍጭፈዋል::
የዘመኑ ክርስቲያኖች ለመሞት የሚያደርጉትን እሽቅድምድም እያዩ አሕዛብ "ወፈፌዎች" እያሉ ይጠሯቸው ነበር:: [ዓለም እንዲህ ናትና!] እብዶቹ ጤነኞችን "እብድ" ማለታቸውኮ ዛሬም አለ::
[ለነገሩ "ግደልና ጽደቅ" ከሚል መመሪያ በላይ ጤና ማጣት አይኖርም)]
ታዲያ በወቅቱ አንድ ቴዎዶጦስ የሚሉት ወጣት በምድረ ግብጽ ይኖር ነበር:: ወጣቱ እጅግ ብርቱ ክርስቲያን ነበርና እንደ ዘመኑ ልማድ ተከሦ በነፍሰ ገዳዮች ፊት ቀረ:: ክሱ አንድ ብቻ ነው:: "ክርስቶስን አምልከሃል" የሚል::
ከሥጋ ሞት ለማምለጥ ደግሞ መንገዱ ያው አንድ ብቻ ነው:: ፈጣሪውን ክርስቶስን ክዶ ለአሕዛብ አማልክት [ አጋንንት ] መገዛት:: ቅዱስ ቴዎዶጦስ በገዳዮቹ ፊት ቆሞ ተናገረ :-
"እኔ ክርስቲያን ክርስቶሳዊ የክርስቶስ ነኝ:: ምንም ብታደርጉኝ ከክርስቶስ ፍቅር ልትለዩኝ አትችሉም"[ሮሜ.፰፥፴፭] አላቸው::
እነሱ ግን ነገሩ እውነት አልመሰላቸውምና ሊያሰቃዩት ጀመሩ::
- ገረፉት
- አቃጠሉት
- ደበደቡት
- ሌላም ሌላም ማሰቃያዎችን በእርሱ ላይ ተጠቀሙ:: የሚገርመው ግን እሱ ሁሉን ሲታገሥ ገዳዮቹ ግን ደከሙ::
በመጨረሻም ወደ ገዢው ዘንድ አቅርበው "ብዙ አሰቃይተነዋል:: ግን ሊሳካልን አልቻለም" በሚል ሰይፍ [ሞት] ተፈረደበት:: በአደባባይ ሊሰይፉት ሲወስዱት ግን ትንሽ አዘኑለት መሰል ጨርቅ አምጥተው "ፊትህን ሸፍን" አሉት:: [ያኔ ትንሽም ቢሆን ሰብአዊነት ሳይኖር አይቀርም]
ቅዱስ ቴዎዶጦስ ግን ገዳዮቹን በመገረም እየተመለከታቸው ተናገረ:- "እኛ ክርስቲያኖች ሞትን አንፈራም:: ሞት ለእኛ ወደ ክርስቶስ መሸገጋገሪያ ድልድያችን ነውና የምንፈራው ሳይሆን የምንናፍቀው ነው::" "ኢትፍርሕዎሙ [አትፍሯቸው]" [ማቴ.፲፥፳፰]
ይህን ብሎ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ጌታውን አመሰገነ:: ፊቱ ላይ ደስታ እየተነበበ ጨካኞቹ አንገቱን ሰየፉት:: በብርሃን አክሊልም ቅዱሳን መላእክት ከለሉት::
- መሠረታዊው ነገር ቅዱስ ቴዎዶጦስ ለምን አልፈራም? ነው::
አጭር መልስ ካስፈለገን ቅዱሱ ያልፈራው ከልቡ ክርስቶሳዊ በመሆኑ ነው:: ትኩረት እንድንሰጠው የሚያስፈልገው ግን የሰማዕታት ምስጢራቸው :-
፩. በጽኑ የክርስትና መሠረት ላይ መመሥረታቸው
፪. ዕለት ዕለት የክርስቶስን ፍቅር መለማመዳቸው
፫. ከወሬ [ንግግር] ይልቅ ተግባርን መምረጣቸው
፬. በንስሃ ሕይወት መመላለሳቸው
፭. ሥጋ ወደሙን የሕይወታቸው ዋና አካል ማድረጋቸው
፮. ከእነሱ የቀደሙ ቅዱሳንን ዜና ሕይወት ከልብ ማንበባቸው
፯. በቃለ እግዚአብሔር መታነጻቸው . . . መጠቀስ የሚችሉ መገለጫዎቻቸው ናቸው::
" ዛሬስ "
ዓለማችን ከጠበቅነው በላይ ነፍሰ በላነቷ እየጨመረ ነው:: ዛሬ የክርስትና ጠላቶች ከጉንዳን በዝተዋል::
- የራሳችን ማንነት
- ክርስትናችን በአፋችን ላይ ብቻ መሆኑ
- እረኞችና በጐች መለያየታቸው . . . ሁሉ እኛ ልናርማቸው የሚገቡ ናቸው::
- አሸባሪዎች
- አሕዛብ
- የመዝናኛው ዓለም
- ሰይጣን አምላኪ ዝነኞች [Celebrities]
- ሚዲያው
- ማሕበራዊ ድረ ገጾችና መሰል ነገሮች ደግሞ ልንጠነቀቅባቸው የሚገቡና እኛን ውስጥ ለውስጥ በልተው የፈጁን የሰይጣን መሣሪያዎች ናቸው::
ስለዚህም ከዛሬ ጀምረን ባለ መታወክ ክርስትናችንን ከአፋችን ወደ ልባችን: ከብዕራችን ወደ አንጀታችን እንድናወርደው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አደራ ትላለች::
ዛሬ ነገሮችን ረስተን ሌሎች አላስፈላጊ ነገሮችን ከጀመርን እጅግ አሳፋሪ መሆኑ አይቀርም:: በጐውን ጐዳና ተከትለን በሃይማኖትና በፍቅረ ክርስቶስ ከጸናን ግን ማንም ቢመጣም ፈጽሞ አንናወጥም::
ይልቁኑ
"አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን:
ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው:: ስለዚህም ምድር ብትነዋወጥ: ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም::" [መዝ.፵፮፥፩] እያልን ከቅዱስ ዳዊት ጋር እንዘምራለን::
" ለዚህ ደግሞ ደመ ሰማዕታት ይርዳን:: በረከታቸው ይድረሰን:: የጌታ ፍቅርም አይለየን "
🕊 † ጻድቁ ንጉሥ ቴዎድሮስ † 🕊
በሃገራችን ታሪክ በጣም ተወዳጅ ከነበሩ ነገሥታት ጻድቁ ቴዎድሮስ ቅድሚያውን ይወስዳል:: በርግጥ በርካቶቻችን የምናውቀው ስለ ሃገሩ ፍቅር ራሱን የሰዋውን ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስን [1845-1860] ነው:: በበጎ ሥራውና በቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ግን ዛሬ የምናስበው ቀዳማዊው ነው::
ቀዳማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ የደጉ ዐፄ ዳዊት [ግማደ መስቀሉን ያመጡት] እና የተባረከችው ሚስታቸው ፅዮን ሞገሳ ልጅና የጻድቁ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ታላቅ ወንድም ነው:: በኢትዮዽያ ለ፫ [3] ዓመታት [ከ1396-1399] ብቻ ነግሦ እያለ እንደ ንጉሥ ሳይሆን-
- ከጠዋት እስከ ማታ ድሃ እንዳይበደል ፍርድ እንዳይጉዋደል ይታትር የነበር::
- ጾምና ጸሎትን የሚያዘወትር::
- ወገቡን ታጥቆ ነዳያንን የሚያበላ::
- ለአብያተ ክርስቲያናትም የሚጨነቅ ደግ ሰው ነበር::
- ስለዚህም በሕዝቡ እጅግ ተወዳጅ ነበር:: በነገሠ በ፫ [3] ዓመቱ ዐርፎ በዝማሬና በለቅሦ ሥጋውን ተሸክመው ሲሔዱ ወንዝ ተከፍሎላቸዋል:: ከመቃብሩም ላይ ጸበል ፈልቁዋል::
ዘለዓለም ሥላሴ ደግ መሪና ሰላማዊ ዘመንን ያድሉን::
🕊
[ † መጋቢት ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ጻድቁ ኢትዮዽያዊ ንጉሥ ዐፄ ቴዎድሮስ
፪. ቅዱስ ቴዎዶጦስ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ፊልሞን ሰማዕት
፬. ቅዱስ አብላንዮስ ሰማዕት
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ሥሉስ ቅዱስ [ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ]
፪. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
፫. አባ ሲኖዳ [ የባሕታውያን አለቃ ]
፬. አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
፭. አባ ባውላ ገዳማዊ
፮. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
፯. ቅዱስ አግናጥዮስ [ ለአንበሳ የተሰጠ ]
" ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ:: ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና:: ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው:: ስለዚህ ባ ለሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል:: . . . ለሁሉ እንደሚገባው አስረክቡ:: ግብር ለሚገባው ግብርን: ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን: መፈራት ለሚገባው መፈራትን: ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ::" [ሮሜ.፲፫፥፩-፰]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ዐቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ ] 🕊
▷ " ት ሕ ት ና "
[ " በቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ... ! " ]
[ 🕊 ]
----------------------------------------------------
" በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም ፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ " [ ኤፌ.፬፥፪ ]
🕊 💖 🕊
ሚስት አጣሁ 🤔
꧁ ውድ አንባቢያን 2 ደቂቃ እንዎሶትና ይህንን አስተማሪ ታሪክ ላካፍላችሁ ꧂
አንድ ወጣት ሚስት ማግባት ፈለገ። በዙሪያውም ብዙ ቆነጃጂት ሞልተዋል።ወጣቱ ግን ለአይኑ እምትሞላ ፣ ለትዳሩ የምትበጅ ፣ ሙሉ የሆነች ቆንጆ ና ውብ ሴት የሚላት የትኛዋ እንደሆነች መምረጥ ተቸገረ። ሴት በሞላበት ሀገር ሚስት ፍለጋ ቢናውዝም ይችን ላግባ ብሎ መምረጥ እና መወሰን ተሳነው። ብቻ ቢፈልግም ቢያስፈልግም ሚስት አጣ።
ከዕለታት አንድ ቀን ምን ይሻላ ብሎ ሰው ሲያማክር እራቅ ወዳለ ሀገር አንድ ጠቢብ ሰው ስላሉ እሳቸው ጋር ቢሄድ አንዳች መፍትሄ እንደሚያገኝ ነገሩትና እርሱም ወደዛ አሉ ወደተባሉ ጠቢብ ሽማግሌ ዘንድ ይሄዳል። ጠቢቡ ዘንድም ደርሶ የበቆሎ ማሳ ቁጭ ብለው ሲጠብቁ አገኛቸው። ሚስት ያጣው ወጣትም ከማሳው ዳር ካለው የእርሻው ዲብ ላይ ጺማቸውን አንጀርግገው በግርማ ሞገስ ቁጭ ብለው የበቆሎ ማሳ ወደሚጠብቁት ጥበበኛ ሽማግሌ ጠጋ አለና እንደምን ዋሉ አባቴ አላቸው።እርሳቸውም እግዚያብሔር ይመስገን እንደምን ዋልክ ልጀ አሉት። ጥበበኛ ነወት ተብየ መምጣቴ ነው አላቸው። እርሳቸውም በእርጋታ ትኩር ብለው እያዩት " ምን እንድረዳህ ፈልገህ ነው የመጣኸው? " ብለው ጠየቁት። እርሱም "ሚስት አጣሁ !..."ብሎ የመጣበትን ጉዳይ አንድ በአንድ አስረዳቸው።
እርሳቸውም " አይይ ልጄ !! በል ና ተከተለኝ " ብለው ከበቆሎው ማሳ ዳር ቆሙና " የመጣህበትን እንድነግርህ ከዚህ ከምታየው የበቆሎ ማሳ ከዚህ ከቆምንበት ጀምርና እስከ ዳር ድረስ ውስጥ ለውስጥ ገብተህ ከዚህ ሁሉ የበቆሎ እሸት በመጠኑ ከፍ ያለ እና አሪፍ እምትለውን አንድ ብቻ የበቆሎ እሸት ዘንጥለህ አምጣልኝ ። ነገር ግን ማሳሰቢ ልስጥህ ።
1ኛ ከዚህ ከቆምክበ ከፊትህ ካለው እሸት ወደ ውስጥ ብገባም ከዚህ የበለጠ እሸት አላገኝም ብለህ ካመንክ እዚሁ ዘንጥለህ ልትሰጠኝ ትችላለህ።
2ኛው ማሳሰቢያ ከዚህ ጀምረህ እስከ ማሳው ዳር ድረስ ወደፊት እየተራመድክ መምረጥ ትችላለህ ነገር ግን ልብ በል አንዴ ያለፍከውን እሸት እንደገና ወደ ቡሀላ ተመልሰህ መቁረጥ አትችልም ወደፊት ብቻ።
3ኛው ማሳሰቢያ አጥቻለሁ ብለህ ባዶ እጅህን መምጣት አትችልም።
4ኛው እና የመጨረሻው ደግሞ ከዚህ ሰፊ የበቆሎ ማሳ አንድ የበቆሎ እሸት ብቻ ነው ቆርጠህ እምታመጣልኝ።
መጀመር ትችላለህ " አሉትና ተመልሰው ቁጭ አሉ ወጣቱም ወደ በቆሎው ገባና የተሻለ የሚለውን በቆሎ መፈለግ ጀመረ። ሁሉም እሸት አማረው አይን አዋጅ ሆነበት ትንሽ ገባ እንዳለ በጣም የሚያማልል እሸት አየና ሊቆርጥ አሰበና " ወደፊት ከዚህ ከሚታየኝ የበለጠ ትልልቅ እና እሚያማምር ቢኖርስ ? ብሄድ ይሻላል"። ብሎ ፍለጋውን ቀጠለ። ነገር ግን ወደ ፊት በሄደ ቁጥር እንደ ቅድሙ የሚያምር ሳይሆን ጥራቱ እየቀነሰ ሄደ። አሁንም ወደ ፊት ጥሩ እሸት አገኛለሁ እያለ መዳከር ያዘ። ነገር ግን ጭራሽ ከቅድሙ የባሰ በመጠኑ ያነሰ፣ ገና ለጋ የሆነ እና ትል የበላው እየሆነ መጣ። ወጣቱም ወደ ኋላ መመለስ አትችልም ስለተባለ ምናለ ቅድም ዳር ላይ ቆርጨ በነበር እያለ እየተፀፀተ አሁንም ተስፋ ሳይቆርጥ ወደፊት ልክ ቅድም ስገባ እንዳየሁት እሚያማምር እሸት አገኝ ይሆናል እያለ በተስፋ ወደ ፊት ፍለጋውን ቀጠለ። እሚያሳዝነው የተባለውን እሸት ሳይቆርጥ በገባበት ተቃራኒ የእርሻው ዳርቻ ሊወጣ ሲዳረስ እንዳለ ግማሹን ወፍ የጠረጠረው እየሆነ መጣ።" እስኪ እንደ ቅድሙ ዳር ላይ ጥሩ በቀሎ ባገኝ ብሎ የእርሻው ጫፍ ላይ ብቅ አለ ነገር ግን እሚገርመው ጭራሹንም ወፍ እልም አድርጎ የጨረሰውና ቆረቆንዳ ብቻ ሁኖ አገኘው።ወደ ቡሃላ እንዳይመለስ ወደ ኋላ መመለስ አትችልም ተብሏል። ባዶ እጁን እንዳይመለስ ምንም ቢሆን ባዶ እጅህን እንዳትመለስ ተብሏል። ስለዚህ አማራጭ ስላጣ ወፍ የበላውን የበቆሎ ቆረቆንዳ አንዱን ዘንጥሎ ወደ ጠቢቡ ተመለሰ እና ከፊታቸው ቆመ።
✍ እርሳቸም "እስኪ ያመጣኸውን አሳየኝ "አሉት። እርሱም አንድም በላዩ ላይ ጥሬ የሌለውን ቆረቆንዳ ሰጣቸውና በሀፍረት ፀጥ ብሎ ቆመ።"ይህንን ነው የተሻለ ያገኘኸው?" ብለው ቢጠይቁት እርሱም በሀፍረት አባቴ ያው የተሻለ አገኛለሁ ብየ ስፈልግ ሳላስበው ወፍ ከበላው ደረስኩ " አለ እየተንተፋተፈ። ቁጭ በል እስኪ አሉና "አየህ የኔ ልጅ ሚስት እያማረጡ አንዷን ከአንዷ እያመረጡ መኖርም ልክ እንደዚህ ነው።
👉 አብዝቶ መምረጥ መጨረሻ ከምራጭ ይጥላልና ሚስት ከእግዚያብሔር ስለሆነች በአንተ ምርጫ አይሆንም። ከፊትህ ያለችውን ሚስት አድርግ "አሉት
ለሴቶችም በተመሳሳይ
ምን ተማራችሁ❓
❤❤ውብ አሁን❤❤
/channel/Fabulous212
🕊
[ † እንኳን ለጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † አቡነ ገብረ ሕይወት † 🕊
† ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ [ንሒሳ አካባቢ] ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ: የቅዱሳን የበላይ: ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው::
የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አንደበት ይኖራል?
- እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል?
- ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?
አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ ፭፻፷፪ [562] ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ :-
- እህል ያልቀመሱ [ምግባቸው ምስጋና ነውና]
- ልብስ ያልለበሱ [ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና]
- ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት::
- ሃገራችንን አስምረው: አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል::
ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም : ገብረ ሕይወትም ይባላሉ:: በ፭፻፷፪ [562] ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል:: በዚህም በሚሊየን [አእላፍ] ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል::
ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል:: እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል:: ለየት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው:: ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና::
የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮዽያ ልዩ ፍቅር አላቸው:: ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ ፻ [100] ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል:: ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው::
ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ፳፻ [2,000] በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት:: በ8ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት ፭ [5] ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል::
ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ::
"ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ::
ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ::
ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ::
ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ::
ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ::" እንዲል::
† የጻድቁ በዓል ጥቅምት ፭ [5] ቀን የሚከበረው ብዙ ጊዜ መጋቢት ፭ [5] ዐቢይ ጾም ውስጥ ስለሚውል ተውላጥ [ቅያሪ] ሆኖ ነው::
† ቸር አምላክ ከጻድቁ ዋጋና በረከት ይክፈለን::
🕊
[ † መጋቢት ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ [አባ ገብረ ሕይወት]
፪. ቅዱስ አባ ሰረባሞን [በምድረ ግብፅ ምንኩስናን ካስፋፉ ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ]
፫. አባ ግርማኖስ ጻድቅ [ሶርያዊ]
፬. ቅድስት አውዶክስያ ሰማዕት [ከከፋ የኃጢአት ሕይወት ተመልሳ ለቅድስና የበቃች እናት]
፭. ቅዱሳን ስምዖንና ሚስቱ አቅሌስያ [የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወላጆች]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪. ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ
፫. ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
፬. ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
† " ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም::" † [ማቴ.፲፥፵፩] [10:41]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
†
† 🕊 ዘ ወ ረ ደ 🕊 †
[ የጾምን መግባት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ ትምህርት ! ]
💖
[ ክፍል ሦስት ]
" የዛሬው ንግግሬ ለአንዳንዶቻችሁ አዲስና እንግዳ እንደሚሆንባችሁ ዐውቃለሁ፡፡ ነገር ግን በዓላማ [ ድኅነትን ለማግኘት ብለን ] እንጹም እንጂ እንዲሁ የልማድ ባርያዎች አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡
በየቀኑ ከልክ በላይ በመብላትና በሆዳምነት የምታገኙት ጥቅም ምንድነው ? ጥቅምስ ይቅርና ጭራሽ የከፋ ጉዳትን የሚያመጣባችሁ ነው፡፡ ተመልከቱ ከልክ በላይ በመጠጣትና በመስከር የማስተዋል ልቡና ሲታወር የጾም ጥቅምዋም ምንም ምልክትን ሳያስቀር ያጠፋዋል፡፡
እስኪ ልጠይቃችሁ ፦ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ብዙ ወይንን ከሚጠጡ በየመሸታ ቤቱ አድረው ፀሐይ ከምትወጣባቸው ፣ ለሚያገኛቸው ሰው ኹሉ ደስ ከማያሰኙ ፣ ለቤተ ሰቦቻቸው ግድ ከሌላቸው ፤ ሕፃን ዐዋቂው ከሚሳለቅባቸው ፣ ራሳቸውን ባለመግዛታቸውና ያለጊዜው በኾነ ደስታ ደስ በመሰኘታቸው ምክንያት ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን ካጡ ከእነዚህ ሰዎች በላይ ማን ጎስቋላ ሰው አለ?
ቅዱስ መጽሐፍስ እንዲህ የሚል አይደለምን ? ፦ “ሰካሮች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም” [ ፩ኛ ቆሮ.፮፥፲ ]፡፡ ወዮ ! እንደ ጠዋት ጤዛ ለሚጠፋ ያውም እጅግ ከባድ ጉዳትን የሚያመጣ እርካታን ለማግኘት ብለው የዘለዓለምን መንግሥትን የሚያጡት እነዚህ ሰዎች ከሚያገኛቸው መከራ በላይ ምን መከራ አለ ?"
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
ረቡዕ - መጋቢት 04 2016 ዓም
ማቴዎስ 11-13
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የማቴዎስ ወንጌልን ከምዕራፍ 11-13 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ከመጥምቁ ዮሐንስ ስለ ተላኩት መልእክተኞች፥ ጌታችን ኢየሱስ መጥምቁ ዮሐንስን በምን መልኩ እንዳመሰገነው፥ ያለመኑትን ከተማዎች መንቀፉ፥ ስለ ሰንበት እና ስለ አከባበርዋ መናገሩ፥ እጁ ደርቃ ስለ ነበረችው ሰው፥ ብዙ ሰዎችን ስለማዳኑ እና ምልክት ስለ ጠየቁ ሰዎች ተጽፎ እናገኛለን። በተጨማሪም፥ ስለ ዘርና ስለ ዘሪው ምሳሌ፥ ስለ ስንዴና እንክርዳድ ምሳሌ፥ ስለ ሰናፍጭ ቅንጣት ምሳሌ፥ ስለ እርሾ ምሳሌ፥ ስለ እንክርዳዱና ስለ ስንዴው እንዲያውም ስለ ተቀበረው ወርቅ መናገሩንም እናነባለን።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) መጥምቁ ዮሐንስ ወደ ጌታችን የላካቸው ሰዎች ምን ጠየቁ? የጌታስ ምላሽ ምን ነበር?
2) በሕይወታችሁ ውስጥ በጣም የደከማችሁበትን ወይም የዛታችሁበትን ጊዜ አስቡት። ጌታችን ሸክማቸው ለከበዳቸው ሰዎች ያቀረበው ግብዣ እናንተን የሚመለከተው እንዴት ነው?
3) ደቀ መዛሙርቱ በሰንበት እሸት ቆርጠው በበሉ ጊዜ ፈሪሳውያን ተቃውመው ነበር። በዚህ ጊዜ ጌታችን ስለ ሰንበት እውነተኛ ምንነት ምን አስተማረ?
4) ከዚህ በፊት ያለማሰብ እና ያለማስተዋል የተናገራችኋቸውን ንግግሮች አስቡ። ጌታችን ስለ ንግግር ያስተማረውን ትምህርት መሠረት በማድረግ፥ ለወደፊቱ ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባችኋል?
5) እስቲ ስለ መንግሥተ ሰማያት በጥሞና አስቡ። ጌታችን ስለ ስንዴ እና እንክርዳድ የሰጠው ምሳሌ፥ ስለ መንግሥተ ሰማያት ያላችሁን አረዳድ በምን መልኩ ይለውጠዋል?
6) ሰዎች የጌታችንን የሚደንቅ ትምህርት በሰሙ ጊዜ ምን ተባባሉ? እናንተስ፥ የጌታችን ትምህርት ደንቋችሁ ለራሳችሁ ወይም ለሌላ ሰው ያላችሁት ነገር ትዝ ይላችኋል?
7) የጌታችንን ትምህርቶች መቀበል ያልፈለጉ ሰዎች ትምህርቱን ለማናናቅ ምን ይሉ ነበር? እናንተስ እውነተኛይቱን ሃይማኖት ላለማመን ሰዎች ምን አይነት ምክንያቶችን ሲሰጡ ሰምታችኋል?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks
†
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ በመለኮቱ ሥልጣን ሞትን አጠፋው ! ]
--------------------------------------------------
" ሥጋም በታመመ ጊዜ መለኮት ከሱ አልተለየም ፥ ከእርሱ ጋር ተዋሕዶ ነው እንጂ፡፡ በመለኮቱ ሥልጣን ሞትን አጠፋው ፤ በእርሱም ሠለጠነበት፡፡ በሥጋው መከራን ስለ ተቀበለ ስለ ሞተ ፈንታ በፈራሽ ነገራቸው የሚቃወሙትን ኃፍረትን አጎናፀፋቸው፡፡
እነሆ ሞትን ድል ነሣው ፤ በሲኦል ተግዘው የነበሩ ነፍሳትንም ማረከ፡፡ ክብሩን ገልጦ በመለኮቱ ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ።
እንኪያስ መናፍቃን ይገሠፁ ፤ ይመከሩ፡፡ የሚገባ ሥርዓት እንደመደሆኑ ሃይማኖትን አጽንተው ይያዙ፡፡ የመጻሕፍትን ቃል ምሥጢር ባለማወቃቸው ፀብ ክርክርን አያምጡ።
በመጽሐፉ ቃል አለን እያሉ ሃይማኖትን ለሚቃወሙ ለአለአዋቆች ዝንጋዔ ነው፡፡ ዳግመኛም በሃይማኖት አንድ ነን እያሉ እርስ በርሳቸው በነገር ለሚከራከሩ ሰዎች ኃጢኣት ክሕደት ነው።
እኛ ግን ሥጋን የተዋሐደ አምላክ እንደ ሆነ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገርነው ነገራችን ይህ ነው፡፡ እርሱ አንድ ነው ፤ እርሱ ፡ ሰማያዊ ነው ፥ ምድራዊም ነው።
ኃያል አምላክ ሲሆን በሥጋ መከራ ተቀበለ፡፡ እንኪያስ አለ ዐዋቆች ትስብእት [ሥጋ] ከመለኮት አንድ መሆኑን ይመኑ ፤ እርስ በእርሳቸው በከንቱ አይከራከሩ ፤ በመናፍቃን ክሕደት አይውደቁ፡፡
ቅድስት ቤተክርስቲያን ከዚህ ሁሉ የነፃች በመሆኗ ይቅኑ እንጂ፡፡ አሜን፡፡ "
[ አቡሊዲስ ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።
† † †
💖 🕊 💖
🕊
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
✝ መጋቢት ፬ [ 4 ] [ ድርሳነ መስቀል ] ✝
[ ✞ እንኩዋን ለታላቁ ነቢይ : ጠቢብና የእሠራኤል ንጉሥ "ቅዱስ ሰሎሞን" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]
🕊 † ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እሥራኤል † 🕊
- መፍቀሬ ጥበብ::
¤ ጠቢበ ጠቢባን::
¤ ንጉሠ እሥራኤል::
¤ ነቢየ ጽድቅ::
¤ መስተሣልም [ ሰላማዊ ] . . . እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ሰሎሞን የታላቁ ነቢይና ንጉሥ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እና የቅድስት ቤርሳቤህ [ ቤትስባ ] ልጅ ነው:: ከ፫ [3] ሺ ዓመታት በፊት የተወለደው ቅዱስ ሰሎሞን እስከ ፲፪ [ 12 ] ዓመቱ ድረስ በቤተ መንግሥት ከአባቱ ጋር አድጉዋል::
ቅዱስ ዳዊት ፸ [ 70 ] ዘመን በሞላው ጊዜ የአካሉን መድከም አይቶ : አዶንያስ በጉልበት እነግሣለሁ ቢልም አልተሳካለትም::
እግዚአብሔር ሰሎሞንን መርጧልና ገና በ፲፪ [12] ዓመቱ ነገሠ:: ልበ አምላክ አባቱ ዳዊት ነፍሱ ከሥጋው ከመለየቷ በፊት መከረው:: "ልጄ ሆይ! ልብህን ስጠኝ:: ፈጣሪህንም አምልክ" አለው::
ቅዱስ ሰሎሞን እንደ ነገሠ በገባዖን ለእግዚአብሔር መስዋዕትን አቀረበ:: ጌታም ተገልጾ "ምን ትፈልጋለህ?" አለው:: ሰሎሞንም ልክ እንደ አባቱ ማስተዋልን : ልቡናን ለመነ:: በዚህም ጌታ ደስ ስለተሰኘ "አልቦ እምቅድሜከ : ወአልቦ እምድኅሬከ - ከአንተም በፊት : ከአንተም በሁዋላ እንዳንተ ያለ ጠቢብና ባለጠጋ ሰው የለም : አይኖርም" ብሎት ተሠወረ:: ቅዱስ ሰሎሞን ለ፵ [40] ዓመታት በእሥራኤል ላይ ነገሠ::
ግሩም በሆነ ፍትሑ : በልዩ ጥበቡ ዓለም ተገዛለት:: እግዚአብሔር የመረጣት የእኛዋ ንግስተ ሳባ / አዜብ / ማክዳም ትፈትነው ዘንድ ሒዳ ምኒልክን [እብነ_መለክን] ጸነሰች:: በሁዋላም ታቦተ ጽዮንና ሥርዓተ_ኦሪት መጣልን::
ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን ድንግል ማርያም ከእነሱ ዘር እንደምትወለድ ነግሮት ነበርና ያበጀሁ መስሎት ሴቶችን አብዝቶ ነበር::
- ነገር ግን :-
¤ አንደኛ ሰው [ሥጋ ለባሽ] ነውና::
¤ ሁለተኛ ደግሞ ከብዙ ሴቶች መካከል ከአንዷ እመ ብርሃን ትገኛለች መስሎት ነበር:: ነገሩ መንገድ ስቶበት ከአሕዛብ [ከፈርዖን ልጅ] ጋር በመወዳጀቱ ለጣዖት አሰገደችው:: እግዚአብሔር እጅግ አዘነ::
በራዕይ ተገልጦ "ስለ ወዳጄ ስለ ዳዊት ስል በአንተ ላይ ክፉን አላደርግም" አለው:: ታላቁ ነቢይ ሰሎሞን ይህንን ሲሰማ ወደ ልቡ ተመለሰ:: ማቅ ለብሶ : አመድ ነስንሶ በፍጹም ልቡ አለቀሰ:: ንስሃ ገባ:: መፍቀሬ ንስሃ ጌታችንም ንስሃውን ተቀበለው::
የይቅርታው መገለጫም ተወዳዳሪ የሌላቸውን ፭ [ 5 ] መጻሕፍት ገለጠለት:: ተናገራቸው:: ጻፋቸው:: እሊሕም :-
፩. መጽሐፈ ጥበብ
፪. መጽሐፈ ተግሣጽ
፫. መጽሐፈ መክብብ
፬. መጽሐፈ ምሳሌ
፭. መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ናቸው::
ቅዱስ ሰሎሞን ልዩ የሆነውን ቤተ መቅደስ በመስራቱም ይደነቃል:: ደጉ ንጉሥ : ጠቢብና ነቢይ ሰሎሞን በዚህች ዕለት በ፶፪ [52] ዓመቱ ዐርፎ ወደ ፈጣሪው ሔዷል:: [እንደ ድርሳነ መስቀል ኢትዮጵያዊ ትውፊት]
ከመፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን በረከት ይክፈለን፡፡
🕊
[ † መጋቢት ፬ [ 4 ] የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት ]
፩. መፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን
[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ [ወንጌላዊው]
፪. ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
፫. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ [ሰማዕት]
" የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ : ፀሐይ : ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ : ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ::
ሰባኪው:- "ከንቱ : ከንቱ : ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል::" [መክ.፲፪፥፩-፱]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
ማግሰኞ - መጋቢት 03 2016 ዓም
ማቴዎስ 6-10
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን! በዛሬው የዐቢይ ጾም ንባባችን የማቴዎስ ወንጌልን ከምዕራፍ 6-10 ድረስ እናነባለን።
ከንባብ በፊት የሚደረግ ጸሎት፡ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
በዛሬው ንባባችን ላይ ጌታችን ስለ ምጽዋት መስጠት፥ ስለ ጸሎት እና ጾም፥ በሰማያት መዝገብ ስለማስቀመጥ፥ ስለ ምግብ እና ልብስ፥ በሌሎች ላይ ስላለመፍረድ፥ ስለ ጠባቢቷ በር እና የአብን ፈቃድ ስለማድረግ ያስተማረውን እናነባለን። በተጨማሪም፥ ጌታችን ለምጻሙን ሰው፥ የመስፍኑን ልጅ፥ የጴጥሮስን አማት እና ሌሎችንም ስለማዳኑ፥ ማዕበሉን ስለ መገሰጹ፥ አጋንንት ያደረባቸውን ስለመፈወሱ፥ ስለ መፃጉዕ መፈወስ፥ ደም ስለሚፈሳት ሴት እና ስለ ሐዋርያትም መጠራት ተጽፎ እናገኛለን።
*የክለሳ ጥያቄዎች*
1) በማቴዎስ 6 መሠረት፥ ጌታችን ስለ ምጽዋት፥ ስለ ጾም እና ስለ ጸሎት አስተምሯል። ጌታችን ባስተማራቸው ነገሮች ላይ መሠረት በማድረግ፥ የምጽዋት፥ የጾም እና የጸሎት ሕይወት ላይ ምን አይነት ማስተካከያ ማድረግ ይገባል?
2) ጌታችን ስለ ምግብ፥ መጠጥ እና ልብስ መጨነቅን በተመለከተ ምን አስተማረ? ትምህርቱን ከሕይወታችሁ ጋር ስታነጻጽሩት ምን አይነት ክፍተት ይታያችኋል?
3) ጌታችን በሌሎች ላይ ስለመፍረድ ምን አስተማረ? ውጤቱስ ምንድር ነው? በአሁኑ ሰዓት በሕይወታችሁ ተቻኩላችሁ የፈረዳችሁበት ሰው ይኖር ይሆን? ከሆነስ፥ በጌታችን ትምህርት መሠረት እንዴት አመለካከታችሁን ልታስተካክሉ ትችላላችሁ?
4) ጌታችን ወደ መንግሥተ ሰማያት ስለሚገቡ ሰዎች ምን ተናገረ? ከዚህ አንጻር መንፈሳዊ ሕይወታችሁን ስትመረምሩትስ አስቀድማችሁ ማስተካከል የሚኖርባችሁ ነገር ምንድር ነው?
5) የጌታችንን ትምህርት ሰምተው ስለሚያደርጉ እና ስለማያደርጉ ሰዎች የተመሰለው ምሳሌ ምንድር ነው?
6) በማቴዎስ 8 መሠረት፥ ጌታችን እምነቱን ያደነቀለት ሰው ማን ነው? ምን ተደረገለት? በሕይወታችሁ ይህንን ሰው በምን አይነት መንገድ ልንመስለው ይገባል ብላችሁ ታስባላችሁ?
7) ጌታችን እርሱን መከተል የሚፈልግ ሰው ምን ማድረግ እንዳለበት አስተማረ? ከዚህ በመነሳት፥ ጌታችን ባስተማረው መሠረት ሕይወታችሁን ስትመረምሩት፥ እርሱን በመከተል ረገድ ከሁሉ አስቀድሞ ልታስተካክሉት የሚገባ ነገር ምንድር ነው?
8 ) ጌታችንን ለፈውስ የቀረቡት ሁለት ዕውሮች “ማረን” ባሉት ጊዜ የጠየቃቸው ጥያቄ ምንድር ነው? ለዚህ ጥያቄ በሕይወታችሁ ውስጥ ለጌታ የምትሰጡት መልስስ ምንድር ነው?
9) ጌታችን ብዙ ሕዝብ እየተከተለው ባየ ጊዜ ምላሹ ምን ነበር? ለደቀ መዛሙርቱስ ምን አላቸው?
10) ጌታችን ሥጋን ገደለው ነፍስን መግደል ስለማይችሉት ምን አስተማረ?
መልካም ንባብ!
/channel/OrthodoxTewahdoBooks