habeshagay1 | Adults only

Telegram-канал habeshagay1 - ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

1099

Subscribe to a channel

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣0⃣

#አንዳንዴ_አረፍ_በሉ!

በፈለጓችሁ ጊዜ ሁሉ ጊዜያችሁን፣ በቸገራቸው ጊዜ ሁሉ ገንዘባችሁን፣ ስሜታቸው ወረድ ባለ ጊዜ ሁሉ ትኩረታችሁን፣ ባጠፏችሁ ጊዜ ሁሉ ይቅርታችሁን፣ ባስቸገሩ ጊዜ ሁሉ ትእግስታችሁን . . . ካለምንም መከልከል የምታፈሱላቸው ሰዎች ያንን ባደረጋችሁ መጠን የማይገነዘቧችሁ ከሆነ፣ ከምንም የማይቆጥሩት ከሆነ፣ ግዴታችሁ እንደሆነ የሚያስቡ ከሆነ፣ ሆን ብለው የሚጎዷችሁ ከሆነና እነዚህ መሰል ግድ-የለሽ ስሜቶች የሚሳዩ ከሆነ ያንን ሁሉ ታግሳችሁ ተጨማሪ አመታቶችን መቆየት ከቻላችሁ ግፉበት፣
#ፈጣሪም_ጸጋውን_ይስጣችሁ፡፡

ምናልባት ግን አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ሰዎች ትምህርትን የሚያገኙት እናንተ ወጥራችሁ የያዛችሁትን ለእነሱና ለእነሱ ብቻ የመኖር የውዴታ ግዴታችሁን ለቀቅ አድርጋችሁ ለራሳችሁ ጤንነት ለመስራት አረፍ ስትሉ እንሆነ ላስታውሳችሁ፡፡
#አንዳንድ_ሰዎች_የሚማሩት_እናንተ_ለእነሱና_ለእነሱ_ብቻ_ከመኖር_ትንሽ_አረፍ_ስትሉ_ብቻ_ነው፡፡

በቃ እንደዛ ነው!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋል

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣8⃣

ለመልቀቅ ተዘጋጁ!

በእጃችሁ ያሉትን መልካም የሆኑ የፈጣሪ ስጦታዎች በሙሉ ተመልከቷቸውና ፣ እነዚህ ውብ የሆኑ ስጦታዎች የእናንተ በመሆናቸው
#ምን_ያህል_ደስተኞች_እንደሆናችሁ_አስቡት፡፡ እግረ-መንገዳችሁን እነዚህ ውብ ነገሮች ምን ያህል #እንደምትንከባከቧቸውና_በጥንቃቄ_እንደምትይዟቸውም_አስቡ፡፡ 

ጥሩ ፍቅረኛ፣ መልካም ቤተሰብ፣ ጤንነት፣ ገንዘብ . . . እና የመሳሰሉት በእጃችን የሚገኙ የፈጣሪ በረከቶች በቅጡ ካልተያዙ ፈጠነም ዘገየም ከእጃችን ይወሰዳሉ፡፡ ይህ ጉዳይ ጊዜ ሊሰጠው የማይገባና አሁኑኑ ታስቦበት የማስተካከያ እርምጃ ሊወስድበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

እነዚህንና መሰል መልካም ስጦታዎች በሚገባ ካልያዛችኋቸው መቼ ከእናንተ ሊሄዱ ወይም ሊወሰዱ እንደሚችሉ አታውቁምና ለመልቀቅ ተዘጋጁ፡፡ ለመልቀቅ ዝግጁ እንዳልሆናችሁ ከተሰማችሁ ግን
#አያያዛችሁን_የማስተካከል_ጉዞን_ዛሬውኑ_ጀምሩ፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

El Houb - The Love (2022)
Original title: El Houb

👨🏼‍🤝‍👨🏻
#ElHoubTheLove 👨🏼‍🤝‍👨🏻

✏️Sub: English
🌏 Country: Netherlands
📝 Language:
#Arabic #English #Dutch
🌟 Score: 7.0/10
🎭 Genre: Drama
🎬 1h 42min

✨ Storyline: Moroccan-Dutch Karim returns to his family home and opens up to his parents about being into men. Their reaction inspires a journey of discovery through Karim's isolation as he attempts to break an ingrained culture of silence.

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

👇🏽👇🏽👇🏽

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ህግ ፀረ ፍቅር ነው !

#በጣም_ህጋዊ_ከሆንክ_አንድ_ሰው_ማፍቀር_አትችልም። ምክንያቱም የፍቅር ዋናው ብቃት ድንገታዊነት ነውና።

#ፍቅር የሚመጣው በድንገት ነው።
#ፍቅር በድንገትም ሊጠፋ ይችላል።
#ፍቅር ምክንያት፤ምንም መመርያ የለውም #ፍቅር እንደ ታዓምር ነው የሚከሰተው።
#ፍቅር ምትሃታዊ ነው፣ፍቅር ስለምን እንዴት? እንደሚከሰት ማንም አያውቅም።


#ፍቅር ፀረ-ህግ ነው፣#ፍቅር ፀረ-ስበት ነው፣ #ፍቅር ፀረ-ሳይንስ ነው፣ #ፍቅር ከሁሉም ሎጂክ እና ህግ በተቃርኖ ውስጥ ነው።
-------------------
ኦሾ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣5⃣

#የፍቅር_ቋንቋዎች_መለማመድ #ክፍል_ሶስት

3፡- ስጦታን መቀበል
ስጦታ ማለት በእጆችህ በመያዝ “ይህ ሰው እኮ እኔን ስለሚያስበኝ ይህንን ስጦታ ሰጠኝ” የምንለው ነገር ነው፡፡ ለአንድ ሰው እኮ ስጦታን ለመስጠት ስለዚያ ሰው ማሰብ አለብህ፡፡ ስጦታው ትልቅም ሆነ ትንሽ ሰውየው እንዳሰበን አመልካች ነው፡፡

ዛሬ ለፍቅር አጋራችህ አንድን የፍቅር ስጦታ በመስጠት እሱ ለእናንተ ምን ያህል ልዩ እንደሆነ ለማሳየት ሞክር፡፡ በተጨማሪም ልደታቸውን፣ በዓላትንና የጋብቻ ቀናችሁን በማስታወስ ስጦታን በመስጠት ፍቅራችሁን ለመግለጽ  ሞክሩ፡፡ 

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣4⃣

#የፍቅር_ቋንቋዎች_መለማመድ #ክፍል_ሁለት

#ጥራት_ያለው_ጊዜን_ማሳለፍ


ጥራት ያለው ጊዜን ማሳለፍ (Quality Time)፡፡ ጥራት ያለው ጊዜ ማለት ለአጋራችን ያልተከፋፈለ ትኩረትንህን መስጠት ማለት ነው፡፡ ዛሬ በቀን ውስጥ ከፍቅረኛችሁ ጋር ምን ያህል ጊዜን እንደምታሳልፉና የእነዚህ ጊዜያችሁ ጥራት ምን ያህል እንደሆነ በማሰብ ጀምሩ፡፡

ቀናቸውንና ውሏቸውን እንዲናገሩ በመፍቀድ ሙሉ ትኩረት መስጠትን፣ ስልክንና ሌሎች ሚዲያዎች በመዝጋት ከእነሱ ጋር ብቻ መሆንንና የመሳሰሉትን ልምምዶች ተግባራዊ ለማድረግ ሞክሩ፡፡

ፍቅራችሁ የበረከት ይሁንላችሁ!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

እንኳን በጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ
2016ኛ አመት የልደት በአል በሰላም በጤና አደረሳችሁ
ወንድሞች

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟


@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣2⃣

#ጥሩውን_ተስፋ_አድርጉ#ለተሻለው_ግን_ስሩ!

ተስፋ ሁል ጊዜ ተስፋ ነው፡፡ ሊመጣ የሚችል፣ ነገር ግን ከቁጥጥራችን ውጪ የሆነ ነገር ነው፡፡ የግል ጥረትና ስራ ግን እንደ ግንባታ ነው፣ በገነባነው ቁጥር እያደገና እርግጠኛ እየሆነ ይሄዳል፡፡

•  የኑሮው ሸከምና ትግል ትንሽ ቀለል እንዲል ተስፋ ማድረግ ጥሩ ነው፣ ግን እስከሚቀል ድረስ ከባድ ሸክም መሸከም የሚችል አቅም እየገነባችሁ ብትቆዩ መልካም ነበር፡፡

•  የሰዎች አስቸጋሪ ባህሪይ እንዲስተካከል ተስፋ ማድረግ ጥሩ ነው፣ እስከዚያው ግን እናንተ በሰው አያያዝ ጥበብ እየበሰላችሁ ብትቆዩ መልካም ነው፡፡


በየፊናችሁ ሆናችሁ የቀሩትን የተስፋና የስራ ገጽታዎች ከግል ምልከታችሁ አንጻር ሙሏቸውና ተስፋ እያደረጋችሁ ወደ ስራ!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ


@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#እንደምትሄድ_ባውቅ

በእግሬ አንተን  ጋ ለመምጣት ከቃሊቲ አራብሳ እሄድ ነበር ?
አናደድከኝ ብዬ ብዙ አረቄ በባዶ ሆዶ አጠጣ ነበር ?
ደክሞኝ ዝዬ አልጋ ላይ እንደበድን ተንጋልዬ <<አንገናኝ ወይ?>> ስትለኝ ተወርውሬ ያለህበት እመጣ ነበር ?

እንደምቴድ ባቅ ....!

ድብን ፤ቅንት ፤ እርር ብዬ ስሜቴን አፍን ነበር  ?
ሁሉን ትቼ ካንተ በቀር ብዬ አለምን ችላ እል ነበር ?

እንደምቴድ ባቅ ...!
ሳልሳሳ በደንብ  እስምህ እተኛህ አልነበር?
በራስህ ጥፋት የተጣላኸውን ተደርቤ ጠላት አደረገው ነበር ?
ደብሮኝ ተደሰተ ብዬ እቦርቅ ነበር ?

እንደምቴድ ባቅ ...

ብቻዬን ሆኜ ሳልም እቅዴ ውስጥ አኖርህ ነበር?
ገመናህን ገመናዬን  እንደዛ አርቀን እንገላለጥ ነበር?

እንኳን እንደምቴድ አላወኩ ይሄን ሁሉ ትዝታ ከየት አመጣ ነበር ?!😏😏😏😢



@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣0⃣9⃣

#ልታጧቸው_የማይገባችሁ_ሰዎች!

ጤና በሆንንባቸው አመታት ትዝም የማይለን የጤንነት አስፈላጊነት ልክ ጤናውን ስናጣው ነው የሚገባን፡፡ አንዳንድ በሕይወታችን ያሉ ሰዎች ልክ እንደ ጤንነት ናቸው፡፡ አጠገባችን ባሉበት ጊዜ የእነሱ መኖር ጥቅም ብዙም ትዝም አይልም፡፡ እንዲያውም ስንኮንናቸው፣ ስንከሳቸው፣ ጥፋታቸውን ስናበዛ፣ መልካም ነገር ባደረጉ ቁጥር ከማመስገን ይልቅ ያላደረጉልንን ስንቆጥርባቸው . . . ራሳችንን እናገኘዋለን፡፡

በዚህ ምድር ላይ ልክ እንደ ጤንነት ፈጽሞ ልታጧቸው ከማትፈልጓቸው ነገሮች መካከል
#ለእናንተ_ጥሩ_የሆኑ_ሰዎች ይገኙበታል፡፡ ባህሪያችሁን ተሸክመው፣ ለእናንተ ኖረው፣ በራሳችሁ ጥፋት እርቅ ፈልገው . . . የሚኖሩ ሰዎች ብርቅና የማይገኙ እንቁዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ሰዎች ከማጣታችሁ በፊት ብትጠነቀቁላቸው ጥቅሙ ለእናንተው ነው፡፡ አንዴ ካጣችኋቸው እንደገና ስላማታገኟቸው ማለት ነው፡፡

ነገሩን ስንገለብጠው ከላይ የጠቀስነው አይነት ታማኝነት እያሳያችኋው የተገለጸውን አይነት ባህሪይ የሚያሳይዋችሁ ሰዎች ካሉ የእናንተ አለመኖር ምን ያህል ሊያጎድልባቸው እንደሚችል ማሳየቱ አንድ አማራጭ መሆኑን አትርሱ፡፡ ከእነሱ ንዝንዝ ጋር መኖር ከቻላችሁ
#ከእነሱ_ንዝንዝ_ውጪ መኖር አያቅታችሁም ፡፡ እስቲ ዘወር በሉላቸውና ይዩት!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣0⃣8⃣

#ራስን_የመቀበል_ጉዞ_እንጀምር


እኔና እናንተ ስንሰራ ጥሩ ቤተሰብ እንገነባለን፡፡ ጥሩ ቤተሰብ ስንገነባ ደግሞ ጥሩ ሕብረተሰብና ሃገር እንገነባለን፡፡ ስለዚህ መማር፣ መወያየት፣ ሃሳብ መለዋወጥ አናቆምም፡፡

ራሳችሁን በመለወጥ ጎዳና ውስጥ ልትለማመዷቸው ከምትችሏቸው መልካም ልምምዶች መካከል አንዱ ራስን የመቀበል ጉዳይ ነው፡፡

አንድ ሰው በፍጹም ካልተመቻችሁ ለማስተካከል ትሞክራላችሁ፣ ካልቻላችሁና ከአቅማችሁ በላይ ከሆነ ትለዩታላችሁ፡፡
#ራሳችሁን_ግን_እደዚያ_ማድረግ_አትችሉም፡፡ ሁል ጊዜ ከእናንተው (ከራሳችሁ) ጋር ስለሆናችሁ ራሳችሁን በደንብ አድርጋችሁ መቀበል አለባችሁ፡፡


መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ሰውረን!!!😂😂😂

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

Beneath the Skin (2015)

👨🏼‍🤝‍👨🏻
#BeneaththeSkin 👨🏼‍🤝‍👨🏻

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣0⃣6⃣

#ራስን_የመቀበል_ጉዞ_እንጀምር

#የመጨረሻ_ክፍል
#ራስን_በመቀበል_የሰዎችን_ምሳሌነት_መከተል

ራስን በመቀበል የሰዎችን ምሳሌነት መከተል ማለት ማንነቴን በማይነካ መልኩ የሰዎችን አርአያነት መከተል ማለት ነው፡፡ ራሱን በሚገባ የተቀበለ ሰው ራሱን ሳይጥልና ሳይተው መልካም ምሳሌ የሆኑ ሰዎችን በማየት ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ምሳሌነታቸውን ይከተላል፡፡

መልካም ምሳሌዎችን የመምሰል ጤናማ ጎዳና የሚያጠቃልላቸው እውነታዎች፡-

1. 
#ከስህተት_በመታረም_ደረጃ
ራስን ስነ-ምግባር በመምራትና እየሄደበት ካለው የስህተት ጎዳና ተመልሶ ፥ በእውነተኛው መንገድ ላይ ለመሄድ አርአያ የሆኑ ሰዎችን መምሰል መልካም ልምምድ ነው፡፡ እንዲያውም፣ ይህ ሁኔታ ራሱን በሚገባ በመቀበል ለማደግ የሚፈልግ ሰው ምልክት ነው፡፡


#ማሕበራዊ_ጤናማነትን_በመጠበቅ_ደረጃ
ከግል ሕይወታችንም ሆነ ከስራችን አንጻር ለማሕበራ ግንኙት የማይመችን ማንኛውንም ጤና ቢስ የሕይወት ዘይቤ  በማስወገድ ደረጃ አርአያ ያረግነውን ሰው ምሳሌነት መከተል እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣0⃣5⃣

#ራስን_የመቀበል_ጉዞ_እንጀምር

#ክፍል_አራት
#ራስን_ያለመቀበል_መንስኤዎችን_መለየት

ራሳችንን ጥለን ወደ ሌላኛውና የእኛ ወዳልሆነው ማንነት እንድንማረክ ጥሪ የሚያደርጉ ሁኔታዎች በዙሪያችን ሞልተዋል፡፡ እነዚህ ጥሪዎች ካለን የውስጥ ስነ-ልቦናዊ  ፍላጎቶች ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ በውስጣችን ያለውን የመወደድና ተቀባይነት የማግኘት ፍላጎት ለማሟላት ብዙ ነገሮችን ለማድረግ ይቃጣናል፡፡ ሳናስበውም ራሳችንን ማለቂያ የሌለው ጉዞ ውስጥ ገብቶ እናገኘዋለን፡፡ ይህ እንዳይሆን በውስጣችን ያሉትን ስነ-ልቦናዊ ፍላጎቶች በማወቅ ትክክለኛ መረጋጋት የምናገኝበትን መንገድ መፈለግ አለብን እንጂ ራስን ባለመቀበል ስቃይ ውስጥ መማቀቅ የለብንም፡፡

ከራሳችን ለመሸሽ ራሳችንን ያሳመንንባቸው ስውር ስነ-ልቦናዊ ምክንያቶች፡-

1. 
#ሰዎች_እንዲቀበሉን፡፡
ሰዎች ቤተሰባቸውን ለማስደሰት፣ ፍቅረኛ እንዲቀበላቸው፣ እንዲሁም አንድ ቡድን ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘት ራሳቸውን ለመለወጥ ይሞክራሉ፡፡ መጨረሻው ግን አያምርም፡፡ መፍትሄው ራስን ሆኖ መኖር ነው፡፡

2. 
#የዘመኑን_ሰው_መስሎ_ለመገኘት፡፡
የዘመኑን ፋሽን፣ የዘመኑን ቁመና፣ የዘመኑን የንግግር ዘይቤ … ለመጨበጥ የሚደረግ መፍጨርጨር አስጊ ነው፡፡ የዘመኑ ነገር ጤናማ ባህል ወደ መሆን መጥቶ እኛንም ከነካካን ችግር የለበትም፡፡ ከእውነተኛ ማንነታችን ካስወጣን ግን መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡

3. 
#ስኬታማ_መስሎ_ለመታየት፡፡
አንዳንድ ሰዎች በስራውም ሆነ በኑሮ ሁኔታ ስኬታማ መስሎ ለመታየት የማያደርጉት ጥረት የለም፡፡ ስኬት ግን የታይታና የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን ሂደትና የኑሮ ዘይቤ ነው፡፡ መነሻውም ራስን ሆኖ መገኘት ነው፡፡

ይቀጥላል . . .

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣9⃣

ትንሽ ታገሱ!

ለጥንዶች . . .

የፍቅር ወራት የመተዋወቂያና የመግባቢያ ወቅት መሆኑን አትዘንጉ፡፡ በእነዚህ ወራት ውስጥ ልክ እናንተ የፍቅረኛችሁ ሁኔታ፣ ባህሪይ ልማድና የሕይወት ዘይቤ ግነኙነቶቀቀ እንደሚላችሁ ሁሉ፣ ፍቅረኛችሁም ገና እናንተን ለማወቅ እየታገለ መሆኑ/ አትርሱ፡፡ ስለዚህ ትንሽ ታገሱ!

በፍቅረኛችሁ ሁኔታ ላይ የማትወዱትን ነገር እየለቀማችሁ ከማዋከባችሁ፣ ከማኩረፋችሁ፣ ከመበሳጨታችሁ፣ ስሜታዊ ከመሆናችሁና “በቃ እንለያይ” አይነት ሃሳብ ከመሰንዘራችሁ በፊት በቅድሚያ ለፍቅርና ለመተዋወቅ ጊዜ ስጡት፡፡

በተቻላችሁ መጠን አብራችሁ ብዙ ጊዜ አሳልፉ፣ ብዙ ተነጋገሩ፣ ብዙ ጥያቄን በመጠያየቅ አንዱ ስለሌላው ለማወቅ ሞክሩ፣ ተናበቡ፣ የምትግባቡበትንም ሆነ የማትግባቡበትን ሃሳብና አቋም አንሸራሽሩ፣ አንዱ በሌላው ላይ የማይወደውን ነገር በግልጽ ተወያዩ . . . ፡፡

ለፍቅር ትንሽ ጊዜ ስጡት! 

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

El Houb - The Love (2022)
Original title: El Houb

👨🏼‍🤝‍👨🏻
#ElHoubTheLove 👨🏼‍🤝‍👨🏻

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣7⃣

#ፍቅርን_አታደራርቡ!

ከአንድ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት ከጀመራችሁ በኋላ ቀዳሚው ስራችሁ የግንኙነቱን አይነት ትርጉም በመስጠት መግባባት ነው፡፡ ይህም ማለት ያላችሁ ግንኙነት የቀላል ጓደኝነት ይሁን አልያም የፍቅር ግንኙነት ይሁን፣ ሁለታችሁም ግልጽ በሆነ መልኩ በመነጋገር ከነትርጓሜያቸው መግባባት አለባችሁ፡፡

ግንኙነታችሁ የቀላል ጓደኝነት (Friendship) ደረጃ ላይ ካለ፣ ከመገናኘት፣ ከመጠናናትና ከመግባት ያለፈ ደረጃ ስለሌለው አንዱ የሌላኛውን ማንንም ሰው የማግኘት ነጻነት ሊጠብቅ ይገባዋል፡፡

አንድ ጊዜ እናንተ የእነሱ፣ እነሱ ደግሞ የእናንተ እንደሆናችሁ ከተግባባችሁና የፍቅረኛነትን (Lovers) ጎዳና ከጀመራችሁ በኋላ፣
#በዚያ_ፍቅረኛ ላይ ሌላ ፍቅረኛ ደርቦ የመያዝ ልማድ ካላችሁ እጅግ የከሰረን የወደፊት ሕይወት እንደጀመራችሁ አትዘንጉ፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣6⃣

ለትንሹም ለትልቁም ጥፋት ካለምንም መታለፍ ቤተሰብ ወይም አሳዳጊ
#ቅጣትና_ስድብ_ሲያቀምሱት_ያደገ_ሰው ይዞ የሚያድገው የስነ-ልቦና ቀውስ ይህ ነው አይባልም፡፡  ይህ ቀውስ የማንነታችንን ዋጋ ካለፈው ታሪካችን አንጻር እንድንተምነው ያደርገናል፡፡

ይህ ሲሆን፣ ሰው ለሰራው ስህተት ሁሉ አንድም ሳይታለፍ ልኩን ሊገባና ሊቀጣ ይገባዋል የሚል ዝንባሌ እናዳብራለን፡፡

በሁሉ ነገር ተቀጥቶ ያደገ ሰው ዘወትር ስህተትን ከቅጣት ጋር አያይዞ ነው የሚመለከተው፡፡ ይህ፣ “ሰው ለሰራው ስህተት ሁሉ ልኩን መቅመስ አለበት” የሚል የቅጣት ዝንባሌ ነው፡፡

ይህ ዝንባሌ ያለው ሰው ለተከሰተ ማንኛውም አይነት ስህተት የሚያውቀው ምላሽ ቅጣት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም፣ አንድ ስህተት ሲገኝ አንድ ሰው የግድ መቀጣት አለበት፡፡ ይህ አመለካከት ደግሞ ስህተት ሲገኝ ራስን በመውቀስ ወይም የሚወቀስ ሰው ፈልጎ በመውቀስና በመቅጣት ሊገለጥ ይችላል፡፡

በየእለቱ የአንድን ሰው ስህተት ለአፍታ አንኳን ሳናልፍ የሚወገር ሰው ፍለጋ የምንተጋው ለዚህ ይሆን?

እስቲ በሰዎች ላይ ያለንን ጭካኔ ትንሽ መለስ እናድረገው!


መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

✅ ЯНГИ ҚУРИЛАЁТГАН УЙЛАРДАН УЙ ҚИДИРЯПСИЗМИ?

⚡️ 2024-йилда қурилаётган уйлар ва уларнинг нархлари
⚡️12 ойдан 120 ойгача муддатли тўлов
⚡️Буларнинг барчаси
@YangiBinolar телеграм каналимизда

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣3⃣

#የፍቅር_ቋንቋዎች_መለማመድ #ክፍል_አንድ

የፍቅር ቋንቋ 1፡-
#የሚገነቡና_የሚያጸኑ_ቃላት


ውጤታማ የፍቅር ተግባቦትን ለማዳበር ከፈለግን የፍቅር አጋራችንን ቀደምተኛ የፍቅር ቋንቋ ለመማር ፈቃደኞች መሆን አለብን . . . የተለያዩ ቋንቋ ከሚናገሩ ሰዎች ጋር ለመግባባት
#የእነሱን_ቋንቋ_መናገር የግድ እንደሆነ ሁሉ ፥ ከፍቅረኛችንም ጋር ለመግባባት #የእነሱን_የፍቅር_ቋንቋ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡

ሌላውና ዋንኛው ደግሞ ፍቅርን በስሜት መግለጫው መንገድ የሚገነቡንና የሚያበረታቱን ቃላት በመለዋወጥ ነው፡፡

ዛሬ ለፍቅረኛችሁ ምንም አይነት አሉታዊ፣ የወቀሳ፣ የክስና ድካምን የሚያጎላ ቃላት ላለመናገር ሞክሩ፡፡ በዚያ ምትክ የሰሩትን መልካም ነገር ማድነቅ፣ ያቃታቸውን ነገር ማበረታተት፣ ውበታቸውን ማድነቅ፣ እነሱ በመኖራቸው ምክንያት ስላገኛችሁት መልካም በረከት እና የመሳሰሉትን ቃላት ንገሯቸው፡፡

ግንኙነታችሁ የሰላምና የደስታ ይሁንላችሁ!
አልጨረስንም

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

እምወደውን  በዙርያዬ አጥቼ ስለማላቅ፣ የሚወዱኝ ሰዎች እንዳሉኝ ሲለሚታወቀኝ ፣ ደስታ ከልቤ ፣  ደስታ ከኑሮዬ፣ ደስታ በምወዳቸው ሰዎች ጭርሶ ስለማይጠፋ...

የተደረገልኝ ፣የተዋለልኝ ሳይነገረኝ ስለሚገባኝ ።
መርህ ስላለኝ ፣ ሳጠፋ ስለሚሰማኝ  ። የወዳጆቼ ስኬት ደስ ስለሚያሰኘኝ ።

ተመስገን ብዬ ስለተደረገልኝ ነገር ደስ ስለምሰኝ ።

ስለሆነልኝ ሁሉ አመስጋኝ ነኝ 🙏❤

መልካም በዓል❤

እንኳን አደረሳችሁ ወንድሞች

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣1⃣1⃣

#የትውስታዎቻችን_ተጽእኖ

በአንድ ጥናት መሰረት ሰዎች ከዚህ ቀደም ያሳለፏቸውን ደስ የማያሰኙ ልምምዶች ለ5 ደቂቃዎች መለስ ብለውና ጠልቀው እንዲያስቡት ሲደረጉ የሰውነታቸው በሽታን የመከላከያ አቅም #55 በመቶ ይወርዳል፣ ከዚያም ለ6 ሰዓታት በዚያ ሁኔታ ይቆያል፡፡

ከዚያ በተቃራ ደግሞ ደስ የሚያሰኙ ልምምዶቻቸውን ለ5 ደቂቃዎች ጠልቀው እንዲያስቡት ሲደረጉ የሰውነታቸው በሽታን የመከላከያ አቅም #40 በመቶ ከፍ ይላል፡፡

የእንደዚህ አይነት ጥናቶች ውጤቶች እንደየአጥኚዎቹ የመለዋወጡ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሃሳቦቻችን በጤንነታችን ላይ ባላቸውን ተጽእኖ ላይ ግን ብዙል ልንለያይ አንችልም፡፡ ይህ ጥናት ደስ የማያሰኘንን ያለፉ ልምምዶቻችንንና ታሪኮቻችንንች ቁጭ ብለን ከማሰላሰል ይልቅ ደስ በሚያሰኙት ላይ የማተኮር ልምምድ የላቀ እንደሆነ የሚያስታውሰን ጥናት ነው፡፡

ደስ የማያሰኙ ልምምዶቻችንን ፈጽሞ እንዳልተፈጠሩ ማድረግ ባንችልም፣ ለሁኔታው በቂ ትኩረትና ጊዜ ከሰጠንና ተገቢውን ትምህርት ካገኘን በኋላ መልካም መልካሙን እያሰላሰሉ ወደፊት!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣0⃣

#ሚዛን_ያልጠበቀ_የአንድዮሽ_ግንኙነት_ምልክቶች

ትክክለኛ የፍቅር ግንኙነት
#ሁለትዮሽ ነው፡፡ ይህም ማለት የሁለትን ሰዎች የጋራ ፍቅር፣ መሰጠትና ጥረት የሚጠይቅ ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ ጊዜ በሁሉ ነገር የሚጦዘው አንደኛው ወገን ብቻ ሲሆን የሆነ የተዛባ ነገር እንዳለ ጠቋሚ ነው፡፡

1.  በስልክ፣ በአካልም ሆነ በቻት እናንተ ካላናገራችኋቸው እነሱ ንግግርን የማያነሳሱ ሰዎች . . .
2.  አብሮ የማሳለፍን ጥያቄ እናንተ ካልጠየቃችሁና ካላነሳሳችሁ እነሱ በፍጹም ፍላጎት የማያሳዩና የማያነሳሳ ሰዎች . . .
3.  አለመግባባት ሲፈጠር እናንተ ብቻ ይቅርታ ካልጠየቃችሁ ጥፋታቸው ሆኖ እንኳን በፍጹም ይቅርታ የማይጠይቁ ሰዎች . . .
4.  ለሁሉም ሁኔታ መስዋእትነት ከፋዮች እናንተ እንድትሆኑ የሚጠብቁ ሰዎች . . .
5.  ለግንኙነቱ ጤናማነት ሲባል መስዋእትነትን እናንተ ብቻ እየከፈላችሁ እነሱ ግን የማይከፍሉ ሰዎች . . .
6.  እጅግ በጣም አስቸጋሪ የሆነውን ባህሪያቸውን ዝም ብላችሁ እንድትሸከሙ የሚፈልጉ ሰዎች . . .
7.  ሆን ብለው በማንኛውም ጊዜ ትተዋችሁ ሊሄዱ እንደሚችሉ አይነት ስሜትን የሚሰጧችሁና ሰዎች . . .
8.  የእናንተ ፍላጎትና ዓላማ ሙሉ በሙሉ በእነሱ ፍላጎትና ዓላማ ስር እንዲጠቃለል የሚፈልጉ ሰዎች . . .
9.  ሁሉንም ነገር (ስራ፣ ጓደኛ፣ መዝናናት …) ከእናንተ የሚያስቀድሙ ሰዎች . . .
10.  እናንተ እቅዳችሁን ከእነሱ አንጻር ስታወጡ እነሱ ግን ከራሳቸው አንጻር ብቻ የሚያወጡ ሰዎች፡፡

#ሚዛኑ_ይጠበቅ!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ትዝ ይልሃል?… "መርሳት ባንችል ኖሮ ሁላችንም እናብድ ነበር"የሚለውን አባባል ሰምተን የሳቅን ቀን?

…አንተ እንዲያውም በጣም ነበር የሳቅከው።ከልክ በላይ መሳቅህ አስገርሞኝ ያሳቀን ነገር አንድ አይደለም ይሆናል ብዬ እንድታብራራልኝ ጠየቅኩህ። «መርሳት ምን ይገርማል ብዬ ነዋ… እስኪያሳብደኝ ድረስ መርሳት ሲያቅተኝ አስበኸዋል?»ብለኸኝ አሁንም ሳቅክ።

ጨዋታችንን ወደ ቁም ነገር ወሰድኩት።ኮስተር አልኩ።«እኔንም ቶሎ ትረሳኛለህ?…»አልኩህ።«ያው ከተለያየን ህይወት መቀጠሉ ይቀራል…?»አልከኝ…  እንዳልናደድ ፈራ ተባ እያልክ።

እኩል እንደማንዋደድ የገባኝ በዛች ቅፅበት ነበር። ያን ጊዜ ደነገጥኩኝ።ድንጋጤ እና ፍርሃት አንድ ላይ ሰፈሩብኝ።አንተን የማጣት ይሁን ወይ አንተን መርሳት ያለመቻል፤ የትኛው እንደሆነ በቅጡ ያልተረዳሁት ፍርሃት ወረረኝ።

ሁለታችንም በተለያየ perspective እንደሳቅን ሲገባኝ በጣም አዝኛለሁ።አንተ«እንኳንና አንተን ስንቱን ረስቼዋለሁ» በሚል።እኔ ደግሞ«አንተን ከምረሳ ማበድ አይቀለኝም?»በሚል ነበር የሳቅነው።

ተለያየን።

ከተለያየን ደግሞ ብዙዙዙ ጊዜ ሆነን።አንተ ህይወቴ ውስጥ ከመምጣትህ በፊት እንዴት እኖር እንደነበር ጠፋብኝ።ወደዛ ለመመለስ ሞክሬያለሁ።ግን ረሳሁት። ብሞክርም ላስታውሰው አልቻልኩኝም።

አንተ ደግሞ እኔን ረስተከኛል።እኔ ግን ልረሳህ በመታገሉ ውስጥ ራሴን እያበድኩኝ አገኘሁት። ከመርሳቱ እና ከማበዱ የቱ እንደሚቀድምልኝ አላውቅም።ቶሎ በረሳሁህ።አንተን ስለመርሳት እያሰብኩኝ ባላስታወስኩህ።አንተን ስለመርሳት ራሱ በረሳሁ።

ብቻ…ከዚህ ሁሉ ስቃዬ ግን አንዱ ቶሎ እንዲገላግለኝ በፅኑ አፈልጋለሁ።የቱ ነፃ እንደሚያወጣኝ የቱ እንደሚያድነኝ ግን አላውቅም።

ወይ መርሳቴ ወይ ደግሞ ማበዴ..

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈
በውጪ ላላችሁ እንዲሁም ለምታከብሩ

HAPPY NEW YEAR
2024


🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣0⃣7⃣
#ልክ_እንደ_ጥላ

አንድ ሰው የፍቅር ጣእም በሚሰጥ መልኩ የሕይወታችሁ አካል ሆኖና የተወሰነ ጎዳና አብራችሁ ከተጓዘ በኋላ ካለምንም ማብራሪያ በድንገት ሲጠፋ ሁኔታውን Ghosting እንለዋለን፡፡ ልክ አካል እንደሌለው እንደ “ጥላ” አሁን እዚህ በኋላ ደግሞ የት እንዳለ የማይታወቅ ባህሪይ ለማመልከት ነው፡፡

#በድንገት_ስልክ_መደወልም_ማንሳትም_ማቆም#በተለምዶ_ከሚገናኙበት_አካባቢ_መጥፋት#ያሉበትን_አለማሳወቅ#ግንኙነትን_ማቆምና የመሳሰሉት ሁኔታዎች እንደምሳሌ ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ በተለይም ያለንበት የማሕበራዊ መገናኛ ፍቅር በተበራከተበት ዘመን አንድ ሰው ከሌላው ሰው በድንገት የመሰወርን ልምምድ ለመለማመድ እጅግ ቀላል የሆነበት ጊዜ ነው፡፡

ብዙ ሰዎች በፍጹም በአካል ካላዩት ሰው ጋር “በቻት” (Chat) ብቻ በፍቅር የሚወድቁበትና የስሜት ትስስር የሚፈጥሩበት ዘመን ላይ ነን፡፡ ይህ ሁኔታ በአካል ከመገናኘት ይልቅ በድንገት ለመቁረጥና “ብሎክ” ለማድረግ አመቺ ነው፡፡  

ሰዎች ልክ እንደ ጥላ ድንገት የሚጠፉበት..

↪️ አንዳንዶቹ ለእኛ ፍላጎት ሲያጡ ያንን በግልጽ ከመናገር ይልቅ መጥፋትን ይመርጣሉ፡፡
↪️ አንዳንዶቹ በፍቅር ሽፋን ስም ድብቅ አጀንዳቸው አልሳካ ሲላቸው ይሰወራሉ፡፡
↪️  አንዳንዶቹ በአንድ ጊዜ ከተለያዩ ሰዎች ጋር የፍቅር ግንኙነትን የመያዝን ጨዋታ ይጫወቱና በመጨረሻ ወደሚያዛልቃቸው ዘወር ማለት ሲፈልጉ ደብዛቸው ይጠፋል፡፡

የእነሱ ምክንያት ያም ሆነ ይህ እናንተ ለሚኖራችሁ የፍቅር ነክ ግንኙነት የስሜትን ትስስር በልኩ የማድረግና የመሳሰሉትን ልምምዶች በማዳበር ራሳችሁን ብትጠብቁ ይመረጣል፡፡  

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

Beneath the Skin (2015)

👨🏼‍🤝‍👨🏻
#BeneaththeSkin 👨🏼‍🤝‍👨🏻

🌏 Country: UK, Canada
📝 Language:
#English
🌟 Score: 4.3/10
🎭 Genre: Drama, Romance
🎬 1h 27min

✨ Storyline: After his family falls apart Joshua is forced to move to Canada to live with his estranged father. It is there he meets Jay, a local tattoo artist. The two becomes closer despite the negativity that surrounds them.
👇🏽👇🏽👇🏽
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#ከሱ_ጋ_ስሆን_ደስስ_ይለኛል

እርግት ማለቱ ፣ሳወራ የሚያሳየኝ አስተያየት..😍 ጉንጬን እየነከሰኝ የሚስመኝ አሳሳም፣እቤት ውስጥ ስራ እንዲያግዘኝ ስጠይቀው ፥ እጁን ለድብድብ በሚመሰስል እየሰበሰበ  "ምን ላግዝ?" ሲለኝ 😘😘

የነገርኩትን ቀልድ "ደግመህ ንገረኝ" እያለ ደግሞ የሚስቅልኝ "መሀሙድ አህመድን ዝፈንልኝ " ሲለኝ በኔ ድምፅ ብዬ ስደነግጥ የሚስቀው ሳቅ 😂😂😂

ብሶቱን እየነገረኝ "አለሁልህ የት አባቱንና!!!" ብዬ አንገቱን ስስመው... ሲረጋጋልኝና..... "ታሾፋለህ ኣ?" ሲለኝ....

ሁለታችንም ደረት ከምንመታ ብዬ ነው ስላት ከብሶቷ ጋ ታግላ እየሰደበቺኝ   የምትፈግገው ፈገግታ ።

አርፍጄበት የሚገላምጠኝ መገላመጥ... አንገቱን ግንባሩን ጉንጩን ለመለማመጥ የምስመው አሳሳም፣ የሚስመኝ አሳሳም😘😘😘
                   ታድዬ - እወደዋለሁ ❤

#መልካም_ጁምአ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣0⃣4⃣#ራስን_የመቀበል_ጉዞ_እንጀምር

#ክፍል ሶስት- #ራስን_ያለመቀበል_መገለጫዎችን_መመርመር

ራስን ያለመቀበል መገለጫዎችን መመርመር ማለት ራሴን ያለመቀበሌን ጠቋሚ የሆኑ ምልክቶችን በመለየት ማወቅ ማለት ነው፡፡ ራሳችንን ያለመቀበላችን ጉዳይ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም በዙሪያችን ላሉ ሰዎች የሚታይ ነው፡፡ እነዚህን ሁኔታዎች መለየት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም
#አንዳንድ_ጊዜ_ራስን_ያለመቀበል_ችግር_እንዳለብን_እንኳ_በቅጡ_አናውቀውም፡፡ ምልክቶቹን ስናስተውል ብቻ የችግራችንን ምንጭ በማወቅ መፍትሄን የማግኘት እርምጃ መውሰድ እንጀምራለን፡፡

ራስህን አለመቀበልህን ለመለየት መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-

1. 
#ንግግርህን_ተመልከተው
አንዳንድ ራሳቸውን ያልተቀበሉ ሰዎች አነጋገራቸው ዝቅተኝነትን ያመለክታል፡፡ ሌሎች ግን ያንን የውስጥ ትግል ለማሸነፍ ሳያስቡት የትእቢትን ቃላት ይለምዳሉ፡፡ በአጭሩ፣ ንግግርህን ብታጤነው ምልክትን ማየትህ አይቀርም፡፡

2. 
#አለባበስህን_አጢነው
አንዳንድ ሰዎች ማንነታቸውን ለመደበቅ ቀላል ሆኖ የሚያገኙት መንገድ የአለባበስ ሁኔታ ነው፡፡ በአጭሩ ይህንን ጥያቄ ጠይቅ፣ “አለባበሴ ከእኔ ጋር የማይመጣጠን አንድን ነገር ለመደበቅ ወይም ለማጉላት እንደሆነ ያሳያል?”

3. 
#አጠቃላይ_ሁኔታህን_አስተውለው
አንዳንድ ሰዎች ሁኔታቸው “የእነሱ” አይደለም፡፡ እንቅስቃሴአቸው፣ አረማመዳቸው፣ ሰላምታ አሰጣጣቸው … የእነሱ እንዳልሆነ ያስታውቃል፡፡ እስቲ ሁኔታህን አጢነውና ከአንተነትህ ውቺ የሆነ ነገር ካስተዋልክ ወደ ትክክለኛው ማንነትህ ለመመለስ ሞክር፡፡ 

ይቀጥላል . . .


@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…
Subscribe to a channel