29777
በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
ኅዳር ፳፭
ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት (ፒሉፓዴር)
ኅዳር ሃያ አምስት በዚች ቀን የስሙ ትርጓሜ መርቆሬዎስ የሆነ ፒሉፓዴር በሰማዕትነት አረፈ። መርቆሬዎስም ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው በሁለተኛ ትርጓሜ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው።
ይህም ቅዱስ አስሊጥ ከምትባል አገር ነው እርሷም የአባቱና የአያቱ አገር ናት እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው። የአባቱና የአያቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ነበር በአንዲት ዕለትም እንደልማዳቸው ለማደን ወጡ ከገጸ ከለባት ወገንም ሁለት ወንዶች ተገናኙአቸውና የቅዱስ መርቆሬዎስን አያት በሉት። ሁለተኛም አባቱን ሊበሉት ፈለጉ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክም ከለከላቸው፤ ከእርሱ የሚወጣ መልካም ፍሬ ስለአለ አትንኩት አላቸው።
ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ዙሪያቸውን በእሳት ከበባቸው። በተቸገሩ ጊዜም ወደ ቅዱስ መርቆሬዎስ አባት መጥተው ሰገዱለት። በዚያንም ጊዜ እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደ በጎች የዋሆች ሆኑ። አብረውትም ወደ መንደር ገቡ።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ በተወለደ ጊዜ ስሙን ፒሉፓዴር ብለው ጠሩት። የውሻ መልክ ያላቸውም በእነርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት የሚኖሩ ሆኑ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ። የቅዱስ መርቆሬዎስ ወላጆች አስቀድሞ አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትንም ጸጋ በተቀበሉ ጊዜ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ኖኅ ብለው ሰየሙት። እናቱንም ታቦት አሏት። ፒሉፓዴርንም መርቆሬዎስ ብለው ሰየሙት።
የውሻ መልክ ያላቸው ግን የእግዚአብሔር መልአክ በተገለጸላቸው ጊዜ እንደ ነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ። ንጉሡም የኖኅንና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜና በሰማ ጊዜ ወደርሱ አስቀረባቸው በዚያንም ጊዜ እግዚአብሔር በንጉሡ ፊት የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው ንጉሡ ያቀረባቸውን ሁሉንም አራዊት አጠፏቸው።
ንጉሡም ይህን በአየ ጊዜ እጅግ ፈራ፤ የአራዊትንም ተፈጥሮአቸውን ያርቅ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲማልድ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ለመነው። እርሱም በለመነ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ።
ከዚህም በኋላ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ንጉሡ ወስዶ ገዥና የሠራዊት አለቃ አድርጎ ሾመው። የውሻ አርአያ ያላቸውም ይታዘዙለት ነበር። ከእርሳቸውም የተነሣ ሁሉም ይፈሩ ነበር።
ከዚህም በኋላ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የሾመውን ንጉሥ ይወጋ ዘንድ ከሀዲ ንጉሥ ተነሣ። ንጉሡም ከጦር ሠራዊት ጋር የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ላከው። ከሀዲው ንጉሥ ግን እነዚያን የውሻ አርአያ ያላቸውን አባብለውና ሸንግለው ወደርሱ ያመጧቸው ዘንድ ወታደሮችን ላከ። በአመጧቸውም ጊዜ ሃይማኖታቸውን ይለውጡ ዘንድ አብዝቶ ሸነገላቸው፤ ባልሰሙትም ጊዜ ሊአሠቃያቸው ጀመረ አንዱ አምልጦ ሸሽቶ ወደ ጌታው ሔደ። ሁለተኛውም በሰማዕትነት ሞተ።
ከጦር ሜዳ የቅዱስ መርቆሬዎስ አባት በተመለሰ ጊዜ ሚስቱንና ልጁን ፈለጋቸው ግን አላገኛቸውም። ንጉሡ የሱ ወገኖች ድል እንደሆኑ በሰማ ጊዜ የቅዱስ መርቆሬዎስ አባት መኰንኑ የሞተ መስሎት ነበርና የቅዱስ መርቆሬዎስን እናት ወስዶ ሊአገባት ፈለገ። ከንጉሥ ወታደሮችም አንዱ ንጉሡ ያሰበውን በጽሙና ነገራት። እርሷም ይህንኑ ወታደር ከሀገር ውስጥ በሥውር ያወጣት ዘንድ ለመነችውና ከልጇ ከብፁዕ መርቆሬዎስ ጋር ወጥታ ወደ ሌላ አገር ሔደች።
ንጉሡም ከእርሱ የሆነውን የመኰንኑም የመርቆሬዎስን አባት ሚስቱን ለማግባት ማሰቡን እንዳይነግሩት አዘዘ። የውሻ መልኮች ያላቸው ከእርሱ ጋር እንዳሉ የተቆጣም እንደሆነ እንደሚአመጣቸውና አገሮችን ያጠፋሉ ብሎ ይጠራጠራልና ስለዚህ እጅግ ይፈራዋል።
ከዚህም በኋላ ደግሞ በንጉሡ ላይ ጦርነት ተነሣ። የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት ወደ ጦርነቱ ወጣ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ይዘው ማረኩት። ወደ ሮሜውም ንጉሥ አቀረቡት ንጉሡም ክርስቲያን ነበርና የተማረከው መኰንን ክርስቲያን መሆኑን በአወቀ ጊዜ አልገደለውም። በክብር አኖረው እንጂ እጅግም ወደደውና ከጥቂት ቀኖች በኋላ በመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ላይ ገዥ አድርጎ ሾመው።
ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ፈቃድ ሚስቱና ልጁ መርቆሬዎስ ወዳሉበት አገር ደረሰ። ሚስቱም በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ በአየችው ጊዜ ባሏ አንደሆነ አወቀችው። እርሱ ግን አላወቃትም።
በአንዲትም ዕለት እርሱና ጭፍሮቹ ከእንግዳ ማረፊያ ቤት በወጡ ጊዜ ልጅዋን መርቆሬዎስን ወስዳ ያማሩ ልብሶችን አልብሳ ሒዶ ከመኰንኑ ፈረስ ላይ እንዲቀመጥ አዘዘችው። እርሱም አባቱ ነው። በተቀመጠ ጊዜም ጭፍሮች ይዘው ወደ መኰንኑ ፊት አቀረቡት መኰንኑም ልጁ እንደሆነ አላወቀምና በእርሱ ላይ ተቆጣ።
የመርቆሬዎስም እናት መጥታ ጌታዬ ሆይ እኛ መጻተኞች ነን አንተም መጻተኛ እንደሆንክ በአወቅሁ ጊዜ ልጅህ ሁኖ ልጄ ከአንተ ጋር እንዲሆን አሰብኩ አለችው። እርሱም ጠየቃት እንዴት እንደተሰደደችም መረመራት እርሷም ሚስቱ እንደሆነች ነገረችው በዚያንም ጊዜ አወቃት ልጁን መርቆሬዎስንም አወቀው እጅግም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑት ያንንም የእንግዳ ማረፊያ ቤት ቤተ ክርስቲያን አደረጉት እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በአንድነት ኖሩ።
ከዚህም በኋላ አባቱና እናቱ በሞቱ ጊዜ ንጉሡ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወስዶ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው። ቅዱስ መርቆሬዎስም መኰንንነትን በተሾመ ጊዜ ያ ገጸ ከልብ ከርሱ ጋር ነበር ወደ ጦርነትም አብሮት የሚወጣ ሆነ።
ለመዋጋትም በሚሻ ጊዜ የቀድሞ የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን እግዚአብሔር ይመልስለት ነበር ማንም ሊቋቋመው የሚችል የለም። ለቅዱስ መርቆሬዎስም ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠው ዜናውም በሁሉ ቦታ ተሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎችም ከፍ ከፍ አለ።
እንዲህም ሆነ ያን ጊዜ በዚያን ወራት በሮሜ አገር ጣዖትን የሚያመልክ ዳኬዎስ የሚባል ንጉሥ አለ። ጠላቶቹም የበርበር ሰዎች ተነሡበት። እርሱም ከእርሳቸው ጋር ሊዋጋ ሠራዊቱን ሰብስቦ ወጣ። እነርሱ ግን እንደ ባሕር አሸዋ ብዙ ነበሩ ብዛታቸውንም በአየ ጊዜ ደንግጦ እጅግ ፈራ። ቅዱስ መርቆሬዎስም እግዚአብሔር ያጠፋቸው ዘንድ በእጃችንም አሳልፎ ሊሰጣቸው አለውና አትፍራ አለው።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ የእግዚአብሔርን መልአክ በውጊያው ውስጥ አየው የተሳለ ሰይፍም በእጁ ውስጥ አለ ያቺንም ሰይፍ ሰጠውና እንዲህ አለው ጠላቶችህን ድል በአደረግህ ጊዜ ፈጣሪህ እግዚአብሔርን አስበው።
ጠላቶቹንም ድል አድርጎ በሰላም ተመለሰ መልአኩም ዳግመኛ ተገልጦለት ለምን የፈጣሪህን የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ረሳህ አለው።
ጦርነቱም ከተፈጸመ በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን ሊያደርግ ወደደ። ቅዱስ መርቆሬዎስም ለበዓል ማክበር አብሮት አልወጣም ወደ ቤቱ ሔደ እንጂ። ሰዎችም ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳልመጣና ዕጣንን በማሳረግም እንዳልተባበረ አስረዱት።
በዚያንም ጊዜ ንጉሥ መልእክተኞችን ልኮ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወደርሱ አስመጣው። በመዘግየቱም አድንቆ ለአማልክት ዕጣን ለማሳረግ ከእኔ ጋር ያልመጣህ የእኔን ፍቅር እንዴት ተውህ አለው። በዚያንም ጊዜ ትጥቁንና ልብሱን ወረወረለትና ንጉሡን እንዲህ አለው። እኔ ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም።
ንጉሥ ዳኬዎስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ። እርጥብ በሆኑ የሽመል በትሮች እንዲደበድቡት አዘዘ። ሁለተኛም ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ይገርፉት ዘንድ አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዘ ይህን ሁሉ አደረጉበት።
"እናታችን ጽዮን"
እናታችን ጽዮን ይድረስሽ ምስጋና፤
መጠጊያ ማረፊያ ጥላችን ነሽና።
ከገነት ብንወጣ ማረፊያ ሆንሽን፤
የምሕረት ደመና ውኃ ሰጠሽን፤
የሕይወት እንጀራ አመጣሽልን፤
በአስራትም በአደራም ለአንቺ ተሰጠን።
አዝ
የኤልሳቤጥ አጽናኝ የጭንቅ ቀን ደራሽ፤
የኃጢአታችን ብዛት ዳገት ሳይሆንብሽ፤
ምሥራችን ደስታን ይዘሽልን መጣሽ፤
ማርያም ስንልሽ ደረስሽልን ፈጥነሽ።
አዝ
ውለታሽ ብዙ ነው ከልብ የማይጠፋ፤
ስምሽ መጽናኛ ነው አዝኖ ለተከፋ፤
በእንተ ማርያም ብሎ ለለመነ፤
የሰማይ የምድርም ማንም አልጨከነ።
አዝ
በትራችን አንች ነሽ የምትደግፊን፤
ባሕረ እሳትን የምታሳልፊን፤
ጽርሐ ሥላሴ ነሽ ማኅደረ መለኮት፤
ሁልጊዜ አንጠግብሽም እንላለን ብጽእት።
አዝ
©በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ኅዳር ፳፩
ጽዮን ማርያም
ኅዳር ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓሏ መታሰቢያ ነው።
“ታቦተ ጽዮን” የሚለውንም ስያሜ ያገኘችው ጽዮን ተብላ በምትጠራው የእስራኤል ከተማ ስም ነው፡፡ ጽዮን ማለት ተፀወነ፡ ተጠጋ፣ ተማጠነ ማለት ነው፡፡ ክቡረ ዳዊትም ጽዮንን አምባ፣ መጠጊያ አድርጎ ብዙ ጠላቶቹን ተዋግቶ አሸንፎ ድልን ተጎናጽፏል።
ጽዮን የተባለችው የታላቁ የዳዊት ከተማ የተገፉና የተበደሉ ሕዝቦች ሁሉ እውነተኛ ፍርድ ለማግኘት፣ ተሰብስበው የሚሰነብቱባት ከተማ ስለነበረች፣ ጽላተ ሙሴም በዚያ ስለነበረች በርሷ ተማጽነውም ችግራቸው ሰለሚቃለል ታቦቷ “ታቦተ ጽዮን” ተብላለች፡፡
ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን፣ ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች። "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው። "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው።
"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው። ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል። ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው። በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን። (2ቆሮ.6፥16 ፣ ራዕይ.11፥19)
የአምላክ ማደሪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በቃል ኪዳን ታቦት ትመሰላለች ይኽቺም ፦
✿ የእግዚአብሔር የጌትነቱ መግለጫ የኾነችው፤
✿ በፍልስጥኤም ይመለክ የነበረ ጣዖትን ቀጥቅጣ ያጠፋች፤
✿ በድፍረት ሊነካት የሞከረ ኦዛን የቀሰፈች፤
✿ በታላቅ ክብር ወደ ሀገሯ ስትመለስ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በታላቅ መንፈሳዊ ደስታ በፊቷ የዘመረላት ፤
✿ ልጁ ሰሎሞንም ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርቶ በክብር ያኖራት ናት፡፡
ጌታ የታቦቷን አሠራር ሲነግረው "ሽምሽር ስጢን ከሚባል ከማይነቅዝ እንጨት ቀርጸኽ አብጅ ከታች እንደ ዙፋን አራት እግር አውጣለት ሞላልነቱን ኹለት ክንድ ከስንዝር ቁመቱ ክንድ ከስንዝር ወርዱን ክንድ ከስንዝር ኹለት ክንድ ከስንዝር ምስሃል ለዚኽ ቁመት የለውም አራት ቀለበት ኹለት ሙሎጊያ አበጅለት አፍአውን ውስጡን በንጹሕ ወርቅ ለብጠው በምስማኩና በምስማኩ ኹለቱን ኪሩቤል እንደሚናተፉ አውራ ዶሮዎች አንገታቸውን ደፋ አድርገኽ በላይ ሣልበት ዙሪያውን ፈለግ አውጣለት ብጽብጽ ወርቅ አፍስበት ጽላቶቹን በውስጡ አኑር" ብሎታል፡፡
ይኸውም ምሳሌ
✅ታቦት ፡- የእመቤታችን
✅ወርቅ፡- የንጽሕናዋ የቅድስናዋ
✅ታቹ መቀመጫው ፡- የንጽሓት እንስት
✅ላዩ መግጠሚያው ፡- የንጹሓን አበው
✅ግራ ቀኙ ፡- የሐና የኢያቄም
✅ወደ ውስጥ የገባችው:-የድንግል ማርያም ያቺ በመኻከላቸወም እንደኾነች እመቤታችንም ከሐና ከኤያቂም ለመገኘቷ ምሳሌ ነው።
✅ኹለት ክንድ ከስንዝር:- ከአዳም እስከ ኖኅ ባለው ዘመን 2260 ዘመን ይመስላል ይኸውም በኖኅ ዘመን አርአያ ድንግል ታቦተ ኖኅ ለመገኘቷ ምሳሌ፡፡
✅አንድ ክንድ ከስንዝር ቁመቱ :- ከኖኅ እስከ ሙሴ ባለው ዘመን ይመስላል ይኸውም 1600 ዘመን ነው። በዚህ ዘመን አርአያ ድንግል ጽላተ ሙሴ ለመገኘቷ ምሳሌ ነው፡፡
✅አንድ ክንድ ከስንዝር ወርዱ:- ከሙሴ እስከ እመቤታችን ባለው ዘመን ይመስላል ይኽውም 1640 ዘመን ይኾናል ይኽ በኾነ አርአያ ድንግል ታቦተ ኖኅ አርአያ ድንግል ጽላተ ሙሴ ምሳሌዎቿ የሚሆኑ አማናዊት ድንግል ማርያም ለመገኘቷ ምሳሌ ነው፡፡
✅አራቱ ቀለበት:- የአራት ወገን ንጽሕናዋ ምሳሌ ይኸውም ከርእይ /ኃጢአትን ከማየት/፤ ከሰሚዕ/ኃጢአትን ከመስማት/ ፤ ከገሲስ/በእጅ ዳሰሶ ኃጢአትን ከመሥራት እና ከአጼንዎ /የኃጢአት መዐዛን ከማሽተት/ እመቤታችን ከነዚኽ ኹሉ ተጠብቃለችና
✅ኹለቱ ቀለበት:- የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ ምሳሌ
✅ኹለቱ ሥዕለ ኪሩቤል:- የጠባቂ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልና የአብሳሪ መልአክ የቅዱስ ገብርኤል ምሳሌ ናቸው ይኽውም የብሉይ ሊቀ ካህናት በዓመት አንድ ቀን ገብቶ ከኹለቱ ኪሩቤል መካከል ቃል ሰምቶ ይወጣ ነበር ቅድስት ድንግል ማርያም በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ተጠብቃ ከቅዱስ ገብርኤል ቃል ሰምታ አካላዊ ቃልን በግብረ መንፈስ ቅዱስ ያለ ዘር ያለ ሩካቤ ፀንሳ ተገኝታለችና።
ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ ይኽንን መንፈሳዊ ምስጢር በጥልቅት በመመርመር ድንግል ማርያምን ፡-
👉በምስጢር የተመላች ታቦት
👉 እሳትን የተመላች ታቦት
👉የቅዱስ ቃል ታቦት
👉የቃል ኪዳን ታቦት በማለት ገልጿታል፡፡
ኅዳር 21 ቀን የሚከበረውም የእመቤታችን ምሳሌዎች የተገለጡበት እና የተለያዩ ሥራዎች የተሰሩበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ እነዚህም፡-
1. ነቢዩ ዘካርያስ ሁለንተናው ወርቅ የሆነ፣ የዘይት ማሰሮ በራሱ ላይ የነበረበትንና ሰባት መብራቶች ያሉትን መቅረዝ ሲያበራ ያየበት ዕለት ነው፡፡ ዘካ. 4፤1-2። ዘካርያስ ያየው ብርሃን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ ዮሐ. 8፤12፡፡ ይህ ብርሃን የታየባትና የተገለጠባት መቅረዝ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፡፡ ብርሃን መቅረዝ እንዲያዝና እንዲገለጥ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ተገልጦልናል፡፡ ጨለማ ዓለምን አብርቷል፡፡ ብርሃን ክርስቶስን ወልዳለችና እርሷም እመ ብርሃን / የብርሃን እናት/ ትባላለች፡፡
2. ታቦተ ጽዮን ዳጎንን ገልብጣ በመጣል ኃይሏን የገለጠችበት ዕለት ነው፡፡ በፍልስጥኤማውያን ተማርካ ቤተ ጣዖት ወስደው ከጣዖታቸው ከዳጎን በታች አስቀምጠዋት ነበር፡፡ ታቦተ ጽዮን ግን በላይዋ ያለውን ዳጎንን ገልብጣ ጥላ እርሷ ከላይ ተቀመጠች፡፡ በታቦት የሚገለጠው የእግዚአብሔር ኃይል ነው፡፡ ምክንያቱም በታቦቱ ላይ ያለው ሕገ እግዚአብሔርና ስመ እግዚአብሔር ነው፡፡ የእግዚአብሔር ስም የጸና ክንድ ነውና ሁሉን ያሸንፋል። ስለዚህ ምንም እንኳ ለጊዜው ስትማረክ ደካማ ብትመስልም መማረኳ ግን ኃይሏን ለመግለጥ፣ ለአሕዛብ የጣዖትን ከንቱነት የታቦትን ክቡርነት ለመግለጥ ነበር፡፡
3. ቀዳማዊ ምኒልክ ታቦቱን ይዞ አክሱም የገባበት፣ ንግሥት ሳባ ታላቅ በዓል አድርጋ የተቀበለችበት፣
4. አብረሃ ወአጽብሐ በአክሱም ከተማ 12 ቤተ መቅደስ ያለው ቤተ ክርስቲያን በአስደናቂ ሁኔታ ሠርተው ከጨረሱ በኋላ ቅዳሴ ቤቱን ያከበሩበት፣ እንዲሁም
5. በ9ኛው መ/ክ/ዘመን ዮዲት ክርስትና ለማጥፋት በተነሳች ጊዜ በእርሷ ምክንያት ታቦተ ጽዮን ወደ ዝዋይ ሐይቅ የተሰደደችበት፡፡ በኋላም የሰላሙ ዘመን ሲመጣ ተመልሳ አክሱም የገባችበት በዚሁ በኅዳር 21 ስለሆነ በእነዚህ በተደራራቢ ታሪኮች ምክንያት በየዓመቱ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል “ኅዳር ጽዮን በአክሱም ጽዮን” የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡
የእመቤታችን ልመናዋ ክብሯ አማላጅነቷም ከእኛ ከህዝበ ክርስቲያን ጋር ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር! አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ፈቃዴ ነው
አዝ.....
አዝ.....
አዝ.....
አዝ.....
አዝ.....
"እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ"
ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሌላው ላይ መፍረድ እንደማይገባ አስተምሯል፡፡ በዚህ ትምህርቱም “እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፡፡”ማቴ ፯÷፩ ብሏል፡፡ ይህም ንጹሕ ሳትሆኑ ወይም ሳትሾሙ ብትፈርዱ ይፈረድባችኋል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ተሾመው የፈረዱ አሉና፡፡ ለምሳሌ፡- ሙሴ በስለጰዓድ፣ ኢያሱ በአካን፣ ቅዱስ ጴጥሮስ በሐናንያና ሰጲራ፣ ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ በበርያሱስ ፈርደዋል ዘኁ.27፡1-15፣ 36፡2-12፣ ኢያ.7፡1-26፣ የሐዋ.5፡1-11፣ 13፡4-12፡፡ አንድ ሰው ንጹሕ ሳይሆን በፈረደው ፍርድ እንደሚፈረድበት ከንጉሡ ከዳዊት ሕይወት መማር ይቻላል 2ኛ ሳሙ.12፡1-15፡፡
ቅዱስ ጳውሎስም በመልእክቱ “ስለዚህ አንተ የምትፈርድ ሰው ሁሉ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኰንናለህና፤ አንተው ፈራጁ እነዚያን ታደርጋለህና፡፡ እንደዚህም የሚያደርጉት ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነተኛ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ አንተም እንደዚህ በሚያደርጉ የምትፈርድን ያንን የምታደርግ ሰው ሆይ አንተ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃልን?” ብሏል፡፡
ለዚህም ነው ጌታችን በወንድምህ ዓይን ያለውን ጉድፍ ከማውጣትህ በፊት በዓይንህ የተጋረድውን ምሰሶ አስወግድ ያለው፡፡ ጉድፍ የተባሉት ጥቃቅን ኃጢአቶች ሲሆኑ ምሰሶ የተባሉት ደግሞ ታላላቅ ኃጢአቶች ናቸው፡፡ ይህም ጥቃቅኗን ኃጢአቶች እየተቆጣጠርክ በባልንጀራህ ከመፍረድህ በፊት አንተው ራስህ ታላላቆቹን ኃጢአቶችህን በንስሐ አስወግደህ እንዳይፈረድብህ ሁን ማለት ነው፡፡
እዚህ ላይ የባልንጀራ ኃጢአት ትንሽ የራስ ኃጢአት ደግሞ ትልቅ የተባለበት ምክንያት ሰው የባልንጀራውን ኃጢአት የሚያውቀው በከፊል የራሱን ግን የሚያውቀው ሙሉ በሙሉ በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ተላልፎ እገሌ እንዴት ኃጢአት ይሠራል ብሎ በሌላው መፍረድ ፈሪሳውያንን መሆን ነው ማቴ.23፡1-39፡፡
............ ✞ ✞ ✞ ...........
ይልቁኑም እነዲህ ብለን እንጸልይ :-
"አቤቱ ጌታ ሆይ የራሴን ጥፋት አስመልክተኝ እንጂ በወንድሜ ላይ እንድፈርድ አታድርገኝ" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
\\በፆም ትትፌወስ//
በጾም ትትፌወስ ቁስለ ነፍስ
ወበጸሎት ትትሀሰይ መንፈስ /2/
አዝ………….
መአልትና ሌሊት በጾም ጸሎት ተግቶ
አሳይቷል ጌታ ስርዓትን ሰርቶ
አይቀርም ፈተናው ትጋት ከሌለበት
ስጋ ካልደከመች በጾምና ጸሎት
አዝ………….
ሙሴ የተባለው ያ የእግዚአብሔር ሰው
ፊቱን የበራለት አርባ ቀን ጾሞ ነው
በሲና ተራራ ተቀብሎ ህግን
እርሙን እንድንተው አሳየን መንገድን
አዝ………….
የጸሎት እናቷ ስለሆነች ጾም
ትህትናን ይዘን ደግሞም አንድ ሆነን
ብንተጋ በጸሎት ከንስሀ ጋራ
ጾም ታደርሰናለች ከጽዮን ተራራ
አዝ………….
አንድበትም ይጹም ኃይልም ይረጋጋ
ጆሮም ክፉ ሰምቶ ነፍሱን እንዳይወጋ
ድኅን ከመበደል ልብም ተመልሶ
መጾምስ እንዲህ ነው የበደለን ክሶ......
በዘማሪ አቤል ተስፋዬ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ኅዳር ፲፭
ጾመ ነቢያት
ጾም በሃይማኖት ምክንያት ከምግብና መጠጥ ተጠብቀው (ተከልከለው) ከአምላክ ጋር የሚነጋገሩበት መንፈሳዊ ዘር የሚዘራበት የአምላክ ፈቃድ ብቻ የሚፈፀምበት የፅድቅ (የህይወት) በር ነው። ከቤተክርስቲያናችን የሥርዓተ ቀኖና መፅሀፍ የፆምን ትርጉም አንዲህ ብሎ ይተረጉመዋል። 'ሰው ህግን ለሰራለት ለክርስቶስ እየታዘዘ ሐጢአቱን ለማስተስረይ ብዙ ዋጋ ለማግኘት ፈልጎ የፍትወት ሃይል ደካማ ሥጋ ለነባቢት ነፍስ ይገዛለት ዘንድ በህግ በታወቁ ጊዜያት ከመብል መከልከል ማለት ነው።'
ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ለልጆቿ ከምታስተምራቸውና ለመንፈሳዊ ተጋድሎ ለሥጋዊ ፈቃድ መግቻ ልጓም ለፈቃደ ነፍስ መፈፀሚያ መንገድ ሆኖ ለአማኒያኖቿ ከሰራቻቸው ስርዓቶች አንዱ ፆም ነው። ይህም የድኅነት በር ነው። የፅድቅ መንገድ ነው። ይህም ለአንድ ኦርቶዶክሳዊ አማኝ በሃይማኖት ሲኖር ራሱን እየመረመረና እየፈተነ (2ኛ ቆሮ. 13፥5) የዲያብሎስን ሃይል ድል መንሻ የመንግሰተ ሰማያት መውረሻ ስንቁን ትጥቁን የሚያሳድግበት ብርቱ ጥሩር እንደሆነ ቤተክርስቲያን ሥርዓት ሰርታ ልጆቿን ታስተምራለች።
የፆም ወቅት መንፈሳዊ ተጋድሎ የሚበዛበት የጌታን ፍቅር የምንገልፅበት ዲያብሎስን ተዋግተን ድል የምናገኝበት የጦር እቃ የምንለብስበት እግዚአብሔርን በንስሃ ምህረት ቸርነት የምንጠይቅበት አባታዊ ፍቅርን ቤተሰባዊ ግንኙነታችንን የምናዳብርበት የውስጣችንን ምስጢር ለአምላካችን የምንነግርበት እንዲሁም ምህረትን የምናደርግበት፣ ድሃ አደጎችን ፣ የታመሙትን፣ የሞቱ ነፍሳትን የምናስብበትን ጊዜ ሲሆን በአጠቃላይ በፆም አማካይነት ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ መውደዳችንን የምናሳይበት ከፈቃደ ሥጋ ይልቅ ፈቃደ ነፍስን የምንፈፅምበት ወቅት ነው።
የነቢያት ጾም የሚገባው ኅዳር ፲፭ (15) ቀን ሲሆን ጾሙ የሚፈታው በገና በዓል ታኅሣሥ ፳፱ (29) ነው:: ወይም ደግሞ በአራት ዓመት አንዴ በዘመነ ዮሐንስ ታኅሣሥ ፳፰(28) ቀን ይፈታል።
ጾመ ነቢያት የተባለበትም ምክንያት ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለ ተፈጸመበት እንዲሁም በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምሥጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ የረቀቀው ገዝፎ እየተመለከቱ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ስለ ጾሙ ስለ ጸለዩ ነው፡፡
እንዲሁም ነቢያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ፣ እና ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍጻሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑት፡፡ በየዘመናቸው «አንሥእ ኃይለከ፣ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ እጅህንም ላክ» እያሉ ጮኹ (መዝ 143/144/:7-8)፡፡ በጾምና በጸሎት ተወስነውም ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ ... ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር «የማያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር» ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ፡፡ ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩት እነ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋልም (ኢሳ 58:1)፡፡ በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለ ተፈጸመበት ይህ ጾም «የነቢያት ጾም» ይባላል፡፡
ስለ ጾሙ መግቢያ የእኛ ቤተ ክርስቲያን የሥርዓታችን መጽሐፍ ፍትሐ ነገሥታችን እንዲህ ይላል፦ <<ወይከውን ከመ ረቡዕ ወዓርብ፤ ወውእቱ ጾም ዘይቀድም እምልደት፤ ወጥንተ ዚኣሁ መንፈቀ ሕዳር ወፋሲካሁ በዓለ ልደት። /የነቢያት ጾም እንደ ረቡዕና እንደ ዓርብ የሆነ፤ ይኸውም ከልደት አስቀድሞ የሚጾም መጀመሪያው የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል የሆነ ጾም ነው።>> (ፍት.ነገ. ፲፭፥፭፻፷፰)::
እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን በረከት የምናገኝበት ያድርግልን! አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🌟Join our cryptocurrency community now and get 50 USDT registration experience for free!
🌟Limited time benefits, seize the opportunity!
🌟We will share the latest and most accurate cryptocurrency market trends and investment advice with you every day to help you easily grasp investment opportunities. There
🌟are rich professional exchanges and practical sharing in the exclusive community group, providing you with one-stop cryptocurrency investment support. Hurry up! The number of places is limited, join and enjoy the benefits!
🔗https://lihi.cc/Ubwrc
Click the link to join the community and receive 50 USDT registration experience!
ወረብ
አንተኑ ሚካኤል መና/፪/ ዘአውርደ{፪}
ወአንተኑ ለእስራኤል መና ዘአውርደ{፪}
.
"ኦ አንተኑ ሚካኤል"
በዘማሪ ዲ/ን ሙሉቀን ከበደ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ምግባችንን አውጥተን ለነዳያን መስጠትና መንፈሳዊ ጉዞ በምናከናውንበት ወቅት አውጥተን መጠቀም እንዳንችል ተደርጓልም ብለዋል፡፡
የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ኀላፊ አቶ አበበ በዳዳ ዩንቨርሲቲው በመጀመሪያው ረቂቅ መመሪያ ያወጣቸው ሕጎች ለኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች በጣም አስቸጋሪ ነበሩም ብለዋል፡፡
ነገር ግን በተማሪዎች በተቋቋመ ኮሚቴ በመመሪያው አንዳንድ አንቀጾች ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ በቀረበው አስተያየት መሠረት ከበፊቱ የተሻለ ቢሆንም አሁንም ግን የተማሪዎችን ሃይማኖታዊ መብት የሚጋፋ መመሪያ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የማስተባበሪያው ኀላፊ አክለውም በተለይም ነጠላን አላስፈላጊ ልብስ በማለት የተገለጸው መመሪያ አግባብነት የሌለው ነውም ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ይህ አካሄድ ሀገርን የማይጠቅም በመሆኑ ሊታሰብበት እንደሚገባ አሳስበው ዩንቨርሲቲው አሳማኝ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሰዎች በልዩ ሁኔታ ሃይማኖቱ የሚፈቅደውን አለባበስ መልበስ ይችላሉ የሚል መመሪያ ስላለው የሚመለከታቸው አካላት ውይይትና ምክክር እንዲያደርጉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
"የተሻለ ነገር"
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
አርባዕቱ እንስሳ
አንቅዕተ ማኅሌት አንቅዕተ ውዳሴ
ምግባቸው ምስጋና ልብሳቸው ቅዳሴ
ዘወትር ይቀኛሉ ለቅድስት ሥላሴ /፪/
ዐይኖቻቸው ብዙ ክንፎቻቸው ስድስት የሥላሴን መንበር የሚሸከሙት
ሱራፌል ኪሩቤል መገብተ ስብሐት /፪/
አዝ.....
ሰአሉ ለነ አርባዕቱ እንስሳ ገጸ ሰብእ ወገጸ አንበሳ
ገጸ ላሕም ወገጸ ንስር /፪/
አዝ.....
ዘወትር አይለዩም ከመንበሩ ዙሪያ ያመሰግናሉ ብለው ሃሌ ሉያ
ይሏታል ድንግልን እኅትነ ነያ /፪/
አዝ.....
ኪሩቤል ሱራፌል ምሉዓነ ግርማ ምስጋናቸው ሲፈስ ድምፃቸው ሲሰማ
ልብን ይመስጣል የምስጋናው ዜማ /፪/
አዝ.....
ሰአሉ ለነ አርባዕቱ እንስሳ ገጸ ሰብእ ወገጸ አንበሳ
ገጸ ላሕም ወገጸ ንስር /፪/
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ኅዳር ፰
አርባዕቱ እንስሳ
ኅዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው የአርባዕቱ እንስሳ በዓላቸው ሆነ።
እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።
የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።
የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።
ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።
የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።
ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።
በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።
እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።
ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።
ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።
በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።
ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው። ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።
ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።
©ስንክሳር
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
✞ንብ ሁኑ ዝንብ አትሁኑ!
አንዳንድ ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚመለከቱት ትክክል ያልሆኑ ነገሮች እጅግ ሐፍረት እንደሚሰማቸው በማዘን ይነግሩኛል። ለነዚህ ሰዎች እንዲህ ብዬ እነግራቸዋለሁ:- ዝንብን “እዚህ አካባቢ አበቦች ይታዩሻል” ብላችሁ ጠይቋት።
ዝንቧም “ ስለ አበባዎች አላውቅም። ነገር ግን እዚያ ጋር ትልቅ የቆሻሻ ክምር አለ በዚያ የምትፈልጉትን አይነት የሚሸት ቆሻሻ ታገኛላችሁ” ብላ ትመልስላችኋለች። ካስፈለገ ስለ ቆሻሻው ዝርዝርና በቦታው ስለሚገኝ ንጹህ ያልሆነ ነገር በቂ ማብራሪያ ትሰጣችኋለች። ንብን ደግሞ “በዚህ አካባቢ ንጹሕ ያልሆነ ቆሻሻ ቦታ ታውቂያለሽ” ብላችሁ ብትጠይቋት “ ቆሻሻ? በጭራሽ! እዚህ አካባቢ አይቼም አላውቅም! ይህ ቦታ እጅግ ውብ በሆኑ ቆንጆ መዓዛ ባላቸው አበቦች የተሞላ ነው” ብላ ትመልስላችኋለች። በአትክልት ስፍራውና በሜዳው ስላሉ አበቦች ውበትና ዝርዝርም ትነግራችኋለች። አስተዋላችሁ? ዝንብ የምታውቀው ቆሻሻንና ቆሻሻ ያለበትን ቦታ ነው ንቢቱ ግን ውብ አበቦች እና ሰናይ መዓዛ ያለበትን ቦታ ነው የምታውቀው።
አንዳንድ ሰው እንደ ዝንብ ነው። አንዳንድ ሰው ደግሞ እንደ ንብ። እንደ ዝንብ የሚያስቡት በሁሉም አጋጣሚ የሚያዩት መጥፎውን ሲሆን በመጥፎው ሃሳብም ቀድመው የተሞሉ ናቸው። መልካም ቢኖር እንኳ አይታያቸውም። ንቦቹ ግን በሚመለከቱት ነገር ውስጥ ሁሉ መልካሙን ያያሉ። ስሑት የሆነ እና በጎ ሕሊና የሌለው ሰው ሁሉን ነገር ስሑት አድርጎ ያስባል። ሁሉንም ነገር በመጥፎ መንገድ ይመለከታል። በጎ ሕሊና ያለው ሰው ግን ምንም ዓይነት ነገር ቢመለከት ምንም አይነት ነገር ብትነግሩት መልካምና ቀና ሀሳብን እንደያዘ ይቀጥላል።
አንድ ጊዜ የሆነ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪ ወደኔ በዓት መጣና በበሩ ላይ ባለው የመጥሪያ ብረት አንኳኳ። በወቅቱ በርግጥ ብዙ ደብዳቤዎችን እያነበብኩ ቢሆንም ምን እንደፈለገ ወጥቼ ለማየት ወሰንኩ። “ ምን ፈለግክ የኔልጅ?” አልኩት። “ የአባ ፓይሲዮስ በዓት ነው?” ሲል ጠየቀኝ። አክሎም “አባ ፓይሲዮስን ላገኛቸው እፈልጋለሁ” አለኝ። “በርግጥ የአባ ፓይሲዮስ በዓት ነው ነገር ግን አባ ፓይሲዮስ ሲጋራ ሊገዛ ወጥቷል” ስል መለስኩለት። “ የሆነ ሰው ሊረዱ ነው የሄዱት በርግጠኝነት” ሲል መለሰልኝ። “አይ ለራሱ ነው የሚገዛው ሲጋራውን” አልኩት። “የነበረውን በሙሉ አጭሶ ጨርሷቸዋል። ሲጋራ በጣም ነው የሚወደው። እኔን እዚህ ብቻዬን ትቶኝ ነው የሄደው መቼ እንደሚመለስ እንኳን አላውቅም። የሚቆይ ከሆነ እኔ ራሱ ጥዬ መሄዴ ነው” አልኩት። የተማሪው ዐይን እንባን አቅርሮ ውስጣዊ ስሜቱን አሳበቀበት። ነገር ግን አሁንም በበጎ ሕሊና እና በቀና ሀሳብ “አባ ፓይሲዮስን እንደኔ ያለነው ነን ያሰቃየናቸው” ሲለኝ “ ቆይ ለምን ልታገኘው ፈለግህ” አልኩት “ቡራኬ ልቀበል ነው” አለኝ “ አንተ ሞኝ ከእርሱ ምን አይነት ቡራኬ ነው የምትጠብቀው ለራሱ የተታለለ ሞኝ ነውኮ! እኔ በደንብ አውቀዋለሁ። በርሱ ውስጥ ምንም ጸጋ እግዚኣብሔር የለም። ይመለሳል ብለህ እሱን በመጠበቅ ጊዜህን አታባክን ጠጥቶም ሊሆን ይችላል የሚመጣው በጣም ጠጪም ነው በዛ ላይ” አልኩት። ይህንን ሁሉ እየነገርኩት ሁሉ ያ ወጣት ልጅ አሁንም መልካም ማሰቡንና በጎ ሕሊናውን አልጣለም። በመጨረሻም “ ይኸውልህ እኔ እስኪመጣ ጥቂት እጠብቀዋለሁ ምን ልንገርልህ ንገረኝና ሂድ” ስለው “ የምሰጣቸው ደብዳቤ አለ በዚያም ላይ ሲመጡ ቡራኬ ተቀብዬ ነው የምሄደው” ብሎ ከነገርኩት ከዚህ ሁሉ ቆሻሻ ውስጥ መልካም ነገር ብቻ እንዴት እንዳየ ተመለከታችሁ? ምንም ያህል መጥፎ ነገር ብነግረው በመልካም ሀሳብ ነበር የሚወስዳቸው። ስለ ሲጋራ እንኳ እየነገርኩት አይኑ እንባ አቅርሮ “የሆነ ሰው ሊረዱ ሄደው ነው” ብሎ ያስብ ነበር። ብዙ የተማሩና ታላላቅ ነገሮችን ያነበቡ ሰዎች እንኳ የዚህን ወጣት ተማሪ ያህል በጎ ሕሊና የላቸውም። መልካም ሀሳቡን በመጥፎ ስታጠፉበት ደግሞ ሌላ በጎ ሀሳብ ይፈጥርና በዚያም ተመስርቶ በጎ ድምዳሜ ላይ ይደርሳል። በርሱ በጣም ተደነቅሁ እንዲህ ያለ ነገር ሳይ የመጀመሪያዬ ነው።
ንብ እንሁን ዝንብ አንሁን!
ንብ እንሁን ዝንብ አንሁን!
ንብ እንሁን ዝንብ አንሁን!
መምህር ኢዮብ ይመኑ እባላለሁ!
በኢኦተቤ ሰባኬ ወንጌል ነኝ!
መምህራን በተለያዩ ቦታዎች እየተዘዋወርን ወንጌልን እናዳርሳለን! እርስዎ የማኅበረ ቅዱሳንን ዩቱዩብ ሰብስክራይብ በማድረግና በማጋራት ብቻ ወንጌልን ለዓለም ማድረስ እንደሚችሉ ያውቃሉ?
እኔ ዘመቻውን ተቀላቅያለሁ እናንተስ?
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
🗣እሑድ ጾም ነው!
ጾመ ነቢያት የሚገባው እሑድ ህዳር 15 ሲሆን: የጾም ማሰሪያ ቅዳሜ ነው:እሑድ ከጥሉላት ምግቦች እንጾማለን።
እንደ ቀኖናም ጾም ሁሉ ሰኞ ይገባል የሚል አዋጅ የለም። ግዴታ ሰኞን ጠብቀው የሚገቡ አጽዋማት ነነዌ: ሁዳዴ(ዓቢይ ጾም): ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም) ብቻ ናቸው። ሌሎች አጽዋማት በሰኞ ሊገቡም ላይገቡም ይችላሉ።ይህ ጾም ደግሞ ያለ ተውሳክ የሚወጣ ስለሆነ ቀንን እንጂ ዕለትን አይጠብቅም።
ይህ ጾም የአጽዋማት ሁሉ መሠረት ነው። የተስፋ: የሱባኤ ጾም ነው: ከአዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉ ቅዱሳን የጮሁት ጩኸትም ነው። የሌሎች አጽዋማት መወለድ በዚህ ጾም ምክንያት ነው።
ነቢያት የአምላክን በሥጋ መገለጥ: የንጉሡን ከድንግሊቱ መወለድ ተስፋ በማድረግ ጾመውታል: በርግጥም ተስፋቸው ተፈጽሞ ጌታችን ስለእኛ ከድንግል ማርያም ተወልዷል: በጨለማ ለምንኖር የማይጠፋ ብርሃን በራልን:ወንጌል ወይም የምስራች መባሉም ዋነኛ ምክንያት ይህ ነው።
ታዲያ ለምን እንጾመዋለን? ጌታ አንዴ ተወልዶ የለም ወይ? የሚል ጥያቄ ሊነሣ ይችል ይሆናል:መልሳችን ጌታ ኢየሱስ በልባችን ገና ስላልተወለደ ነው! የሚል ይሆናል።
ባዶ ሆድ ከመሆን እንዲሁ ከመራብ ከፍ ያለ ጾም ያርግልን :ልባችንም ቤተልሔም ይሆን ዘንድ ፈቃዱ ይሁን!
©ዲ/ን ኤርምያስ ተፈራ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
✝️ደጉ ሳምራዊ
ደጉ ሳምራዊ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ሳምራዊ ማለት ሀገር ጠባቂ ማለት ነው፥ ኢየሱስ ክርስቶስም እረኛችን ጠባቂያችን ነው፤ ዮሐ 10፥11 ፣1ኛ ጴጥ 2፥24። ሀገር ጠባቂ ሀገርን የሚጠብቀው ራሱን ለሞት አሳልፎ በመስጠት ነው፥ ኢየሱስ ክርስቶስም እኛን በነፍስም በሥጋም የጠበቀን ራሱን ለመስቀል ሞት አሳልፎ ሰጥቶ ነው፤ ደጉ ሳምራዊ ቊስለኛውን በሩቅ አይቶ አዘነለት ፥ቀርቦም በቊስሉ ላይ ወይንና ዘይት አፈሰሰለት፤ ወይኑ፦ የቊስለኛውን ደም እንዲያቆምለት እንዲያደርቅለት ነው። ቊስል ቶሎ የሚደርቀው ከላይ ነው፥ ወዲያውም እየተሰነጣጠቀ ያሰቃያል፤ ለዚህም መከላከያ እንዲያለሰልስለት ዘይቱን አፍስሶለታል። ጌታችንም በሩቅ ማለትም በሰማይ መንበሩ ተቀምጦ ቊስለኛውን አዳም በዓይነ ምሕረቱ አየው፥ ገጸ ምሕረቱን መለሰለት፤ ቀረበውም። (ባሕርዩን ባሕርይ አደረገ ፥ የባሕርዩ መመኪያ ከሆነች ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ፥ ተዋሕዶ ሰው ሆኖ ተወለደ)።ወይን እንደማፍሰስ፦በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ፥ ሥጋውን ቆረሰለት ደሙን አፈሰሰለት። ጌታችን የጸሎተ ኀሙስ ዕለት ወይኑን በጽዋ አድርጎ፦ «ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው፤» ያለው ለዚህ ነው። ማቴ 26፥27።
እንደ ዘይት ደግሞ የመንፈሰ ቅዱስን ጸጋ ሰጥቶታል። ይኽንን በተመለከተ ቅዱስ
ዳዊት፦«ወይን (የክርስቶስ ደሙ) የሰውን ልብ ደስ ያሰኛል፥ ዘይትም ፊትን ያበራል፥
(መንፈስ ቅዱስ ሰውን ብሩኅ መልአክ ያስመስለዋል) ፥ እህልም (የክርስቶስ ስንዴ ሥጋው) የሰውን ጉልበት (ነፍስን) ያጠናክራል።» ብሏል። መዝ 103፥15 ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም፦
«እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋልና ሁሉንም ታውቃላችሁ።» ያለው ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ነው።
ደጉ ሳምራዊ ከአህያው ወረዶ ቊስለኛውን ማስቀመጡ የሚያመለክተው፦ ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ መንበሩ መውረዱንና የአዳምን በሰማይ መንበሩ ማስቀመጡን ነው።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ «በኢየሱስ ክርስቶስ በሰማያዊ ሥፍራ ከእርሱ ጋር አስቀምጠን፤» ያለው ይኽንን ምሥጢር ይዞ ነው። ኤፌ 2፥7። ምክንያቱም በተዋሕዶ አምላክ የሆነ ሥጋ በሰማይ የእሳት መንበር ተቀምጧልና።
ደጉ ሳምራዊ፦ ያከመውን ቊስለኛ ለእንግዶች ቤት ጠባቂ ማስረከቡ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ፈሳሽነት ያከማቸውን ምእመናን ለመምህራን የማስረከቡ ምሳሌ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስን፦«ግልገሎቼን አሰማራ፥ ጠቦቶቼን ጠብቅ ፥ በጎቼን አሰማራ፤» ያለው ለዚህ ነው። ዮሐ 21፥15። ሁለት ዲናሮች ደግሞ የሁለቱ ማለትም የብሉይ ኪዳንና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ምሳሌዎች ናቸው። የሰው ሕይወቱ የሚጠበቀው በእነዚህ ነውና። በሁለት ዲናር የተመሰሉ ቅዱሳት መጻሕፍት ምግበ ነፍስ ናቸውና። ቅዱስ ዳዊትም፦ «ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ጣፈጠኝ።» ብሏል። መዝ 118፥103።
ደጉ ሳምራዊ የእንግዳ ቤት ጠባቂውን፦ «ከሁለት ዲናር በላይ ብታወጣ እኔ በተመለስኩ ጊዜ እከፍልሃለሁ፤» አለው እንጂ፥ «ዋጋ የለህም፤» አላለውም። ይህም የሚያመለክተው፦ መምህራን የተሰጣቸውን፦ ሁለት ዲናር (ብሉይ ኪዳንን እና አዲስ ኪዳንን) ይዘው ፥
የምእመናንን ሕይወት ለመጠበቅ ሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍትን ቢጽፉ፥ ጌታ ሲመጣ
የድካማቸውን ዋጋ እንደሚከፍላቸው ነው። ቅዱሳን ሊቃውንት፦ መጽሐፍ ቅዱስን
ለማብራራት ፥ ንባቡን በመተርጐም ፥ ምሥጢሩን በማራቀቅ አያሌ መጻሕፍትን ጽፈዋል። እነዚህም አዋልድ መጻሕፍት ይባላሉ። የቅዱሳት መጻሕፍት ልጆች ማለት ነው። የገድል የድርሳን እና የተአምር መጻሕፍት ቊጥርም ከአዋልድ መጻሕፍት ነው። እነርሱም የእግዚአብሔር ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንደፈጸሙ፥ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን የሚያሳይ ነው። መጻፍ ማጻፍም ፥ መስማት ማሰማትም ዋጋ አለው። እንግዲህ በተሰጡን
ሁለት ዲናሮች ሥራ እንድንሠራ ፥ ሌሎችንም ቅዱሳት መጻሕፍት በመጻፍና በማጻፍ እንድንመከርና እንድንመክር ፥ የተሰጠንን አደራ እንድንጠብቅ ፥ በዚህ ዓለም ተዋርደን ምእመናን የሚከብሩትን ግብር ይዘን እንድንገኝ፥ የሚያዝን ልቡና እንዲሰጠን ፥ የምናቆስል ሳይሆን የቆሰሉትን የምናክም እንዲያደርገን፥ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም
አማላጅነት አይለየን አሜን።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
Kezih betach yemilekekew mastawekia slemaytekm elefut.
Читать полностью…
ኅዳር ፲፪
ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት
ኅዳር ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
ዳግመኛ በዚህች ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን የተራዳበት ቀን ነው።
ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሁኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው ከእኛ ሰዎች ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ አለው። እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወዳንተ መጥቻለሁ አለው ።
ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል አለው ። የእግዚአብሔር የሠራዊቱም አለቃ ሚካኤል ኢያሱን የቆምክባት ምድር የከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው ኢያሱም እንዳለው አደረገ ።
እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው በውስጧ ያለውን ንጉሧን ከኃያላኑና ከአርበኞቹ ጋር በእጃችሁ ኢያሪኮን እነሆ አስገባታለሁ ። ይህም የከበረ መልአክ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር በመሆን ገድላቸውን እስከ ሚፈጽሙ የሚያጸናቸውና የሚያስታግሣቸው ነው ።
ስለዚህም ስለ ልዕልናውና ስለ አማላጅነቱ በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠራለት እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲአወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲአደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲአደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናልና። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ይማረን የቅዱስ ሚካኤል በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሃይማኖታዊ ነጻነታችንን የሚጋፋ መመሪያ አውጥቷል ሲሉ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ገለጹ፡፡
ተማሪዎቹ ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ያወጣውን የሥነ መግባርና ዲሲፕሊን መመሪያ ተከትሎ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ወደ መመገቢያ አዳራሽ ሲሄዱ ነጠላ እንዳይለብሱና ምግብ እንዳያወጡ ሃይማኖታዊ መብታቸውን የሚጋፋ የሥነ ምግባርና ዲሲፕሊን መመሪያ መውጣቱን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ ኀላፊ አቶ አበበ በዳዳ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል።
አቶ አበበ በዳዳ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ኦርቶዶክሳውያን የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ሃይማኖታዊ የመብት ጥሰት እንዳይፈጸምባቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መወያየት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
ዩንቨርሲቲው በ2017 ዓ.ም ባወጣው የሥነ ምግባር ዲስፕሊን መመሪያ የተለያዩ እምነት ተከታይ ተማሪዎች በግቢው ስለሚያስተናገዱ ከሃይማኖትና ከበዓላት ጋር የተያያዙ የአለባበስ ሥርዓቶች የማንነትና የእምነት መገለጫዎች በመሆናቸው ሊከበሩ ይገባቸዋል ይላል፡፡
በሌላ በኩል የኒቨርሲቲው ሃይማኖታዊ ነጻነታችንን የሚጋፋ መመሪያ አውጥቷል ሲሉ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በምግብ ሰዓት የህሊና ጸሎት ካልሆነ በቀር ጸሎት እንዳናደርግና ከዳቦ ውጭ ምግብ እንዳናወ እንዲሁም በመመግቢያ አዳራሽ ውስጥ ነጠላ እንዳንለብስ መመሪያ ወጥቷል ብለዋል፡፡
ተማሪዎች አክለውም የወጣውን መመሪያ ምክንያት በማድረግ በአንዳንድ የጥበቃ አካላትና ግለሰቦች ጫና እየተደረገብን ነው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡
✞የምፈልገውን ሳይሆን ፤ የሚያስፈልገኝን ስጠኝ
በአንድ ወቅት አንድ መነኩሴ የወይራ ዘይት ዛፍ ተከለና ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል መጸለይ ጀመረ ፤ "ጌታ ሆይ ለዛፌ ይጠቅም ዘንድ ዝናብን አዝንብልኝ" አለ። እግዚአብሔርም ጸሎቱን ተቀብሎ ዝናቡን አዘነበለት ፤ ዛፉም ውኃን በጣም ጠግቦ አፈሩ ረሰረሰ። ለዛፉ ይጠቅም ዘንድ ግን ከመጠን በላይ የረሰረሰው አፈር መድረቅ ያስፈልገው ነበር። ስለሆነም መነኩሴው ወደ እግዚአብሔር ጸለየ "ጌታ ሆይ ብዙ ፀሐይ በዛፉ ላይ እንድታወጣ እለምንሃለሁ" አለ። እግዚአብሔርም በለመነው መሠረት ፀሐይ አወጣለት ፤ ዛፉም አደገለት። መነኩሴው ልመናውን ቀጠለ "ጌታ ሆይ የዛፉ ሥር እና ቅርንጫፍ ይጠነክር ዘንድ ጥቂት ውርጭ ላክልኝ" አለ። እግዚአብሔርም በጠየቀው መሠረት ውርጩን ላከለት ፤ ከዚያም ዛፉ ከውርጩ የተነሣ ጠወለገ ሞተም።
መነኩሴው በኹኔታው በጣም ተናድዶ ወደ አንድ መነኩሴ ሔዶ የገጠመውን ታሪክ እና ቅሬታውን ያለማጉደል አጫወተው ኀዘኑን አካፈለው። ሁለተኛው መነኩሴ ታሪኩን ከሰማ በኋላ "እኔም እንደ አንተ የወይራ ዘይት ዛፍ አለኝ ተመልከት" አለው ፤ የእርሱ ዛፍ በመልካም ኹኔታ አድጋለች። ሁለተኛው መነኩሴም ቀጥሎ "እኔ ግን ከአንተ በተለየ መልኩ እጸልያለሁ ፤ ይህን ዛፍ የፈጠረው እርሱ ነውና ፤ ከእኔ የተሻለ የሚያስፈልገውን እንደሚያውቅ ለእግዚአብሔር ነገርኹት ፤ እግዚአብሔርም እንዲንከባከበው በጸሎት ጠየቅኹት ፤ እርሱም ጸሎቴ ሰምቶ ተንከባከበው" በማለት አስረዳው።
በእኛም ሕይወት እንዲህ ነው ፤ የሚያስፈልገንን በትክክል የምናውቅ መስሎን እንለምናለን ፤ ነገር ግን ለእኛ የሚያስፈልገንን ያለማጓደል የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ስለዚህ "በሙሉ ልብ እንመነው! "የምፈልገውን ሳይሆን የሚያስፈልገኝን ስጠኝ" እንበለው።
✞✞✞
" ኢየሱስ ግን፦ የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ፥ እኔ የምጠመቀውንስ ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን? አላቸው።"
(የማርቆስ ወንጌል 10: 38)
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ደም ወማይ
ደም ወማይ ወሐሊብ እምነ ክሳዱ ፈልፈለ/፪/
ሶበ ተከለለ/፪/ጊዮርጊስ ሶበ ተከለለ/፪/ኧኸ/፫/
ትርጉም፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰይፍ አንገቱን በተሰየፈ ጊዜ ደም ውኃና ወተት ፈሰሰ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ኅዳር ፯
የቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕት ቅዳሴ ቤቱ ከበረች
ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን የልዳ ሀገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ።
ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ሊአፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው፤ ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ። በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲያኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዱው ራስ ደርሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልንጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጐሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ ሀገራቸው አፍረው ተመለሱ።
ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ ሀገር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሔደ በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ።
ክብር ይግባውና ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቁስጠንጢኖስን በእግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox