በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
በ. ስለራሳቸው በጣም የሚኮሩ ሰዎች ኩራታቸውን የሚያሳዩት ብዙ ጊዜ ስለ አለባበሳቸው ከመጠን በላይ በመጨነቅ ነው፡፡ በልብሳቸው ወይም በመልካቸው ሁል ጊዜ «ሌሎችን አስንቀው» ለመታየት ይፈልጋሉ።ይህንንም ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንዲህ ሲል ገልጾታል፦ «ከመ ትዘኀሪ መትትመክሒ በላዕለ ብዙኃት አንስት ነዳያት ወትትዐበዪ በቅድመ አዕይንቲሆን ወትምስዊ አልባቢሆን ወታድውዪ ነፍሳቲሆን ወትወስኪዮን ንዴተ በዲበ ንዴቶን» ይህም አንቺ ሴት አጊጠሽ መውጣት የምትፈልጊው «ልብስ በሌላቸው በድሆች ላይ ልትመኪ፣ በፊታቸው ልትታበዪ፣ ልቡናቸውን በቅንአት እንደ ሰም ልታቀልጪ፣ ሰውነታቸውን በቅንአት ልታሳምሚና በኃዘናቸው ላይ ኃዘን ልታመጪባቸው ወደሽ ነው እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም።» ማለት ነው:: አንቺ ራስሽ «ዝንጥ» ያልሽ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ስሜት ተሰምቶሽ አያውቅም? ተግ.ዮሐ28
ውድና ጌጠኛ ልብስ መልበስ ያኮራሻል? ይህ የሚያኮራሽና ከሌላው ሰው የበለጥሽ መስሎ የሚሰማሽ ከሆነ ሰነፍ ሴት ነሽ፡፡ አላዋቂ በመሆንሽም ታሳዝኛለሽ እንጂ አታስጎመጂም፡፡ ምክንያቱም እንኳን ዐዋቂው የሰው ልጅ ይቅርና ፈረስና በቅሎ እንኳን የሰው ያህል ዕውቀት ሳይኖራቸው በጣም የሚደሰቱት ጌጣጌጥ አድርገውላቸው ከሚነዷቸው ይልቅ አራግፈው ሲያቀሉላቸው ነው።ስለዚህ ዐዋቂ የሚባል የሰው ልጅ ወርቁን ሐሩን በራሱ ቢሸከመው በወገቡ፣ በደረቱ፣ በእጁና በጣቱ ቢያጠልቀው በአንገቱም ቢያንጠለጥለው ሊያፍር እንጂ ሊኮራ አይገባውም ነበር፡፡
ያደረገው የወርቅና የሐር ጌጥ ዕወቀትና ሕይወት የሌለው ፍጡር በመሆኑ ነው እንጂ ኩራት የሚገባው ለእርሱ ነበር። ለባሕርይው የማያሻው ነገር ከተጫነበት ሰው ይልቅ ጌጡ ቢከብር ምን ይደንቃል? በላዩ የተቀመጠበት ሳይኮራ ተሸካሚው የሰው ልጅ መኩራቱና መደሰቱ እጅግ የሚያሳዝንና ዐላዋቂነት ነው። ተመልካቾችም ስለዚህ ሽክም ምክንያት ሊያዝኑለት ሲገባቸው ቢቀኑበት ወይም ቢያከብሩት ቅዱስ ያዕቆብ ለወርቅና ለብር በመሳሳታቸው የነቀፋቸው ከንቱዎች ናቸውና አይመሰገኑም፡፡ ዐዋቂ ግን ሌላውን ባለው ወርቅና ብር ብዛት አያከብርም።ለራሱም ቢሆን በሀብቱ ብዛት እናደሚከበር አያስብም አይቀበለውምም፡፡
በሌላ አቅጣጫ ስንመለከተው ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ስለ ልብስ «ግድ የለሽ» መሆንም ኩራትን ወይም ራስ ወዳድነትን ሊያሳይ ይችላል፡፡ በአለባበሱ የተዝረከረከው ግለሰብ ስለ አለባበሱ ግድ የለሽ የሆነው በስንፍና ምክንያት ሊሆን ቢችልም አለባበሱ በሌሎች ላይ ለሚያሳድረው ተጽዕኖ «ምን ቸገረኝ!» የሚል ዓይነት ዝንባሌ ያለው ሰው መሆኑን ሊጠቁም ይችላል፡፡
ተ. እኛ ራሳችንን ከምንመለከተው በላይ ሌሎች ሰዎች ይመለከቱናል፡፡ ታዲያ ሌሎች ሲመለከቱን መልካም ነገር ከእኛ እንዲያገኙ መጣር የለብንምን? ይህም ስለ ስሜታቸው እንደምንጠነቀቅላቸው የሚያሳይ መሆን አለበት፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች ግን ነገረ ሥራቸው በሙሉ ወዳጆቻቸው ስለራሳቸው በሚያስቡበት ጊዜ እንዲሸማቀቁ የሚያደርግ ነው:: በዚህም ተግባራቸው «እያንዳንዳችን እንድናንጸው እርሱን ለመጥቀም ባልጀራችንን ደስ እናሰኝ» በማለት ሐዋርያው የተናገረውን ምክር ቀኑን ሙሉ ሲሽሩት ይውላሉ፡፡ ሮሜ 12÷2
ቸ. አንቺ ሴት እስኪ ነፍስሽን ትሕትና አስተምሪያት።ሁልጊዜ ደምቆና አሽብርቆ መታየት ብቻ ሳይሆን ተራና መናኛ ልብስን መልበስንም ተለማመጂ።«ሞትን የምታለብስና ወደ ሲኦል የምታወርድ አፍአዊ ጌጥን» ከልክ በላይ አትውደጂ:: ይህ በነፍስ እንደ ማጌጥ በእግዚአብሔር ፊት አያኮራሽምና፡፡ ለአፍአዊ ጌጥ የማትጓጓ ሴት ዘውድ ከደፋ ንጉሥ ትበልጣለች፡፡ እንዴት? ቢባል ሰው ሁሉ ለቁሳቁስ ሲገዛ እሷ አትገዛምና፡፡
ነ. አንዳንድ ሰዎች ስለ አለባበስ ባይሰበክ ይመርጣሉ።ብዙዎች ደግሞ «ለምን ስለ ሌላ ነገር አታስተምሩም? ከዚህ ይልቅ ብዙ አንገብጋቢ ርእሰ ጉዳይ የለምን?» ይላሉ።አርግጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ይኖር ይሆናል፣ ሆኖም የአለባበስ ጉዳይም በክርስትና ዐቢይ ነገር ነው።ያ ባይሆን ኖሮ ሐዋርያትም ሆኑ ሊቃውንት ስለ አለባበስ ብዙ ባልጻፉ ነበር፡፡ ይህ ጉዳይ ተራ ነው የምትዪ ከሆነ አለባበስሽን በማስተካከል ተራነቱን አንቺ ራስሽ አስቀድመሽ ማሳየት ይገባሻል፡፡ ካልሆነ በጉዳዩ በየጊዜው ላለመገሠጽ ብለሽ ትምህርቱን ማናናቅሽ አስተዋይ አያደርግሽም።
ቀጣይ ምዕራፍ ዘጠኝ ክፍል ዐራት :
👉አለባበስሽ ስለ አንቺ በደንብ ይናገራል!
👉አፋዊ ጌጥን መውደድ "አምልኮ ጣዖት ነው!" የሚባለው ለምንድር ነው? በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
ምዕራፍ ዘጠኝ ክፍል ሦስት
.................................................
➺በአልባሳት በምታጌጪበት ጊዜ ልታስተውያቸው የሚገቡ ነገሮች!
ሀ. ወጣት በምትሆኚበት ጊዜ ስለ አለባበስሽና ስለ ውጫዊ ማንነትሽ የምትጨነቂው በአብዛኛው እኩዮችሽ ስለ አንቺ ምን እንደሚያስቡ በማሰብ ነው። በዚህ ጉዳይ ብዙ አትልፊ እነርሱ ራሳቸው በመለወጥ ላይ ያሉ ገና ታዳጊዎች መሆናቸውን መዘንጋት የለብሽም።ስለዚህ ዛሬ በአድራጎትሽ ቢደሰቱ ነገ በጭራሽ ላይደሰቱ ይልቁንም ነገሮች ሲገቧቸው ባሳደርሽባቸው ተጽዕኖ ሊያዝኑብሽም ይችላሉ፡፡
እኩዮችሽን ያስደስታል ብለሽ የምታደርጊው ነገር ወላጆችሽንና በአንቺ ግምት የምታከብሪያቸውን፣ የምታደንቂያቸውንና ከፍ አድርገሽ የምትመለከቻቸውን ሰዎች በእጅጉ ሊያሳዝናቸው ይችላል።ለምን ቢባል ከእኩዮችሽ ይልቅ አድራጎትሽ የሚያስከትለውን ቀውስ መመርመር ስለሚችሉ ነው።በወላጆችሽና እንደነዚህ ባሉ ሰዎች ዘንድ ዝቅ ተደርገሽ እንዳትታዪና እንደ ትልቅ ሴት እንድትቆጠሪ ከፈለግሽ ከአለባበስሽ ይልቅ ስለመልካም ሴትነትሽ ተጨነቂ፡፡
ለ. ሴቶች ያገቡ ወይም ያጩ ከሆነ ልብስ በሚለብሱበት ጊዜ ስለ ትዳራቸው በትኩረት ማሰብ ይኖርባቸዋል፡፡ ልብስ ከግብረ ዝሙት ጋር የጠበቀ ትስስር ስላለው ባሎች የሚስቶቻቸውን አለባበስ በጥንቃቄ ይከታተላሉ፡፡ ለአፋቸው ልበሺው «ያምርብሻል» ቢሉም እንኳን ሚስቶች ለባሎቻቸው ሕሊና መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ቸል ብላ የምታልፍ ሴት የገዛ ትዳሯን በራሷ እጅ እያፈረስች መሆኗን ማወቅ አለባት።ምክንያቱም የሴቶች አለባበስ በወንዶች ስሜት ላይ ያለውን ሚና ወንዶች ከራሳቸው በመነሣት በሚገባ ስለሚያውቁ ያንቺ አለባበስ የሚያስከትለውን መዘዝ ለመገመት ለባልሽ በጣም ይቀለዋል።
➺«የሚገባ ልብስ»
ክርስቲያኖች ሊለብሱት የሚገባና የማይገባ የልብስ ዓይነት አለ፡፡ ለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ «ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራስን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ።› በማለት የተናገረው ቃል ምስክር ነው:: 1ጢሞ2፥10
የማይገባ ልብስ የሚባለው አካልን ለእይታ የሚያጋልጥና ፀረ ክርስትና መልእክት ያለው ልብስ ሁሉ ነው።በላዩ ላይ የዝሙት መልእክት ያለው ሥዕልና ጽሑፍ ያዘለ ከሆነ፡ ስስና ዘርዛራ ወይም ከገላ ጋር የሚጣበቅ ሆኖ ገላን የሚያሳይና ቅርጽን የሚያወጣ ከሆነ ወይም በማናቸውም መልኩ ክርስቲያናዊ ዓላማን የሚፃረር ከሆነ ክርስቲያኖች ሊለብሱት አይገባም።
የማይገባ አለባበስ የሚባለው የሴቶች ሱሪ መልበስ ብቻ አይደለም።ቀሚስም የማይገባ ልብስ ሆኖ የሚገኝበት ብዙ መንገድ አለ፡፡ ለምሳሌ እጅግ ቢያጥር ወይም ተሰንጥቆና ሳስቶ ሰውነትን ለእይታ ካጋለጠ ቀሚስ በመሆኑ ብቻ «የሚገባ ልብስ» ሊሆን አይችልም::
አንዲት ልጃገረድ ለአቅመ ሔዋን ስትደርስ በሰውነቷ ላይ የሚታየው ለውጥ ለአቅመ አዳም የደረሱ ወንዶችን በኃይል የሚማርክ ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት ሴቶች በወንዶች በተደጋጋሚ ይፈተናሉ፡፡ አንቺም ወደ ትልቅ ሴትነት ስትቀርቢ ተመሳሳይ የሆነ ፈተና ያጋጥምሻል:: እውነተኛ የልብና የሕሊና ስላም ለማግኘትና ዘለቄታዊ ሰላምሽን የሚያደፈርሱ ችግሮች እንዳይደርሱብሽ የምትፈልጊ ከሆነ ራስሽን መቆጣጠርና ትክክኛ ለሆነው ነገር ጠንካራ አቋም ማሳየት ይጠበቅብሻል፡፡
ከወሊድ ጋር ተዛምዶ ያላቸውን የሰውነትሽን ክፍሎች ለማሳየት ቁምጣና አጣብቂኝ የሆኑ ጉርድ ቀሚሶችን፣ አጭር ቀሚስና ጠባብ ሹራቦችን፣ ስስና ዘርዛራ ልብስ፣ ጠባቃ ሱሪ፣ እየለበስሽ ሆን ብለሽ ትኩረት መሳብ ይገባሻልን? እንዲህ ያደረግሽ እንደሆነ የወጣት ሴቶች ፆር በሆነው የምንዝር ጌጥ ፍቅር (ትውዝፍት) ተይዘሻል ማለት ነው።በዚህ መቀጠልሽ ደግሞ የተቃራኒ ጾታዎችን ፍትወተ ሥጋ የመቀስቀስ ሚና ይጫወታል፡፡ ከዚያስ በኋላ ምን እንደሚከተል ታውቂያለሽ?
በዚህ ዓይነት አድራጎትሽ የተሳቡ ወንዶች የሚያቀርቡልሽን ፈተና ሁሉ ለመቋቋም ምን ያህል ችሎታ አለሽ? ፈተናው እንደ ስኳር በሚጣፍጥ ወይም ሥውር በሆነ ማባበልና ማታለል፣ በውዴታ፣ ገፋ ካለም በግዴታ ሊሆን ይችላል፡፡ ታዲያ ገና በማደግ ላይ ያለሽ ስትሆኚ ይህን ሁሉ እንዴት ችለሽ ታልፊዋለሽ? አካላዊ ዕድገት አሳይተሽ ይሆናል ፡ ነገር ግን ምን ያህል ለጋብቻና እናት ለመሆን የሚያስፈልገው የአእምሮና የስሜት ብስለት አለሽ? በአካል ማደግሽ ብቻ በቂ አይደለም::
ዕድገቱን የጨረሰ ነገር ግን ያልበሰለ አረንጓዴ ሙዝ አይተሽ ታውቂ ይሆናል፡፡ ይህ ሙዝ ከተቆረጠ በኋላ እንኳን ለመበላት ገና መብሰል አደሚያስፈልገው አታውቂምን? አንቺም እንዲሁ በአካል የደረስሽ ቢመስልሽም ይህን ለመሰለ ጾታዊ ግንኙነት ለመጀመር ገና መብሰል እንደሚቀርሽ ራስሽን አሳምኚው:: ብትጣደፊ ግን ጊዜው ሳይደርስ የጽጌሬዳን እንቡጥ ለመክፈት እንደ መሞከር ይሆንብሻል፡፡ ይህም ትርፉ አበባን ማበላሸትና ወደ ፊት ሊገኝ የሚችለውን ውበት መጉዳት ብቻ ነው::
ጋብቻ ማለት ሙሽራ መሆን ብቻ እንዳልሆነም አትዘንጊ የቤት አደራጅ፣ ምግብ አዘጋጅና ልብስ አጣቢ መሆንንም ያካትታል፡፡ እናት መሆንም ልጆችን ተንከባክቦ በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ትዕግሥትና ጽናት የሚጠይቅ ነው።ይህ ሁሉ ደግሞ በጥሩ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በክፉ ጊዜም በሕመምና በጤንነት ጊዜ ሁሉ ጭምር ሳይቋረጥ መደረግ የሚያስፈልገው የሕይወት እንቅስቃሴ ነው::
ከዚህ በተጨማሪ ለጋብቻ ዝግጁ እንደሆንሽ ቢሰማሽ እንኳን ልታገቢው የምትፈልጊው ምን ዓይነት ባልን ነው? አንድ ወጣት ወንድ የተማረከው አንዲት ልጃገረድ በጾታ ግንኙነት በኩል ልትሰጠ ው በምትችለው እርካታ ላይ ብቻ በማተኮር ከሆነ ጥሩ ባል የሚሆን ይመስልሻል? ታዲያ ሰውን በአለባበስና በውጫዊ ውበት ለመማረክ ከመሞከር ይልቅ ውስጣዊ ማንነትሽን ተመልክቶ ማለትም በአእምሮሽና በልብሽ ውስጥ ያለውን አይቶ ዘላቂ ወዳጅነት እንዲመሠረት ብትፈልጊ በጣም የተሻለ አይመስልሽምን? ይህን ለማድረግ የምትችዪው ደግሞ ለአለባበስሽ ከመጠን በላይ ከመጨነቅ ይልቅ ሌሎችን የሚስቡ መልካም ጠባዮችን በማፍራት ነው። ማለትም በግልጽና በበሳል አነጋገር፣ ስለ ሕይወት ባለሽ ደስተኛና ጤናማ አመለካከት፣ እንደዚሁም ለታማኝነት፣ ለግብረ ገብነት፣ እግዚአብሔርን ለመፍራትና ለመሳሰሉ መልካም ነገሮች ያለሽን በጎ ፍላጎት በቃልና በሥራ ለማሳየት በመጣር ነው።
ከዚህ አልፈሽ የትዳር ዓላማ ሳይኖርሽ መረን በወጣ የዝሙት ተግባር ለመኖር አስበሽ አለባበስሽን ያበላሽሽ ከሆነ ዘግየት ብሎ ማዘንሽ አይቀርም፡፡ አለባበሳችን ኑሮአችንን ደስተኛ ወይም ኀዘን ያጠላበት ለማድረግ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው።ደስተኛና መልካም ስብእና የሞላበት ኑሮ ለመኖር የሚደረግ ጥረት አለባበስን ቁጥብ ከማድረግ ይጀምራል፡፡ አስተውሎ መልበስ የመልካም ስብእና መገለጫ ሲሆን ስድ አለባበስ የሚፈጥረውን የስሜት መገለባበጥ መሠረት ያደረገ የአኗኗር መንገድን መከተል ከሰውነት ደረጃ ዝቅ ያደርጋል::
ስለዚህ ሆን ብለሽ ጥፋትን ዓላማ ያደረገ አለባበስ ከመልበስ ተጠንቀቂ! በአለባበስሽ አንድን ወንድ ብትማርኪ አንቺም ሆንሽ እርሱ አትደነቁም:: ምክንያቱም እርሱ በእንስሳዊ ጠባይ የሚማረክ ደካማ ሲሆን አንቺም ደግሞ በስሜት ብቻ እንጂ በውስጣዊ ማንነትሽ በአእምሮአቸው በሳል የሆኑ ሰዎችን መማረክ ያቃተሽ ደካማ ነሽና። ጎበዝ ከሆንሽ ከስሜት ይልቅ በበሳል አስተሳሰብና በጨዋነት የሚሳቡትን ሰዎች ለመማረክ ጨዋና ግብረ ገብነት ያለው ሰው ለምን አትሆኚም?
በወጣትነትሽ ለፈጣሪሽ ታማኝ ሁኚ! ለውጫዊና ለጊዜያዊ ደስታ ብለሽ መልካም ጠባያትን ንቀሽ አትጣያቸው:: ውስጣዊውን ንቀሽ ለሥጋዊና ለውጫዊ ነገሮች ተገዝተሽ መኖርሽ ከፈጣሪሽ ጋር በእጅጉ ያራርቅሻል።እርሱ እንዲህ ብሏልና «በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሠወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ» 1ጴጥ3፥4 ስለዚህ ስለውስጣዊ ማንነትሽ እንጂ ስለውጫዊው ማንነትሽ ብዙም አትጨነቂ፡፡
ቀጣይ ምዕራፍ ዘጠኝ ክፍል ሦስት :
👉በአልባሳት በምታጌጪበት ጊዜ ልታስተውያቸው የሚገቡ ነገሮች በሚል ይቀጥላል....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
ምዕራፍ ዘጠኝ ክፍል ሁለት
.................................................
➺የልብስ ምሳሌነትና ምሥጢር
ልብስ የጸጋና የክብር ምሳሌ ነው። አዳምና ሔዋን ሕግ በጣሱ ጊዜ የእግዚአብሔር ክብር እንደራቃቸው ያወቁት ልብሳቸው በመገፈፉ ነው።ልብስ የክብር ምልክት ነውና፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ንዋያተ ቅድሳትንና ምስጢራትን በሙሉ በመንጦላዕት እናከብራቸዋለን፡፡ (በመጋረጃ) እና በአልባሳት በመሸፈን እናከብራቸዋለን።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ሐፍረትን ንቆ» ዕርቃኑን የተሰቀለው ራሱን እስከ መጨረሻው አዋርዶ፣ ተዋርዶ የነበረ አዳምን በልዕልና ስፍራ ማስቀመጡን ለማመልከት ነበር። በልብስ መሸፈን የክብር ምልክት ከሆነ መራቆት ደግሞ የውርደት ምሳሌ መሆኑ ግድ ነውና፡፡ እንዲሁም የእስራኤልን ውርደት ለማመልከት እግዚአብሔር ከነቢያት አንዱን ዕርቃኑን እንዲሄድ ያደረገበት ጊዜ ነበር፡፡
ይልቁንም ለኛ ለኢትዮጵያውያን እግዚአብሔር በጥበቡ ምሥጢር ያለው አለባበስ ያለበሰን መሆኑን «ፍኖተ አእምሮ» በተባለው መጽሐፋቸው እንዲህ ሲሉ ጽፈው ነበር:: « ብዙዎቻችን የአለባበሳችንን ምሥጢር ሳናውቅ ብንለብስም የፈጣሪ ፈቃድ ያለበት ነውና ምሥጢሩን ዐውቀን እናጽናው እንጂ አንለውጠው::»
ምሥጢሩም "የመኳንንትና የወታደር ሱሪና እጀ ጠባብ ሠላጤ ጫፉ እንደ ጦር ራሱ እንደ ልብ ሆኖ መስፋቱ ለጊዜው ሲሮጡ፣ ሲሄዱ፣ ሲቀመጡም ሆነ ሲነሡ የማያስቸግርና ልከኛ እንዲሆን ነው:: ምሳሌው ግን ቅዱ አንደ ጦር መሆኑ ልባችን ለድፍረት ሰውነታችን ለስለት የተመረጠ የጦር ሰዎች ነን ለማለት ነበር፡፡"
አለ ክቡር ዳዊት። ስለዚህም ሁሉ ነገር አቤቱ ማራቸው ይቅርም በላቸው መፃተኛዋ ባሪያህንም ኃጢአቷን አታስብባት እያለች ወደፈጣሪዋ መሪር ዕንባን አለቀሰች። ያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ግርማ ወደስዋ መጣ። በታላቅ ግርማ ሆኖ ባየችውም ጊዜ ደነገፀች ከእግሩ ሥርም ወደቀች። ከዚህ በኋላ ነውር በሌለባቸው ንዑዳት ክቡራንና ንጹሐን በሆነ እጆቹ አነሣት። ቀጥሎም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ አትደንግጭ ነገር ግን የልብሽን ሃሳብ ንገሪኝ" አላት። እስዋም "አቤቱ ባሪያህንስ በባለሟልነት ካሠለጠንካት አባታችን አዳምን በአርአያህና በአምሣልህ ስለምን ፈጠርከርው። በእንጨት መስቀልስ ላይ ለምን ተሰቀልክ ስለአዳምና ስለልጆቹ አይደለምን?" አለችው። "አዋን ስለነሱ ስል ተሰቅያለሁ" አላት። "እግዲያውስ መሰቀልህ ወይም የተሰቀልከው ስለነሱ ከሆነ ከአቤል ጀምሮ እስከ ዛሬ የሞቱን ከዛሬም በኋላ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የሚሞቱትን አቤቱ ማራቸው ይቅርም በላቸው" አለችው። "አንተ ቸር ይቅር ባይ መዓትህ የራቀ ምሕረትህ የበዛ ነህና ከአንተ ሌላ አምላክ የሌለ እውነተኛ አምላክ ነህ ሁሉ ይቻልሃልና የሚሣንህ ነገር ከቶ የለምና ዓለም በጠቅላላዋ በእፍኝህ አትሞላም" በማለት እያለቀሰች ለመነችው። በዚያ ጊዜ ጌታ መልሶ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እስኪ አንቺ ራስሽ ፍረጅ አዳም ከነልጆቹ ከሠራው ኃጢአት እና እኔ በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን በቀያፋና በሐና አደባባይ በዕለተ ዓርብ ከተቀበልኩት ሕማማተ መስቀል ቢመዘን የትኛው ይመዝን ይመስልሻል?" አላት። ይህንም ባላት ጊዜ ደነገጠችና ከመሬት ላይ ወደቀች። በዚህ ጊዜ ቅዱሳት በሆኑ እጆቹ ከወደቀችበት አነሣትና "እንግዲህ ይህን ሁሉ መከራ የተቀበልኩ ለማን ወይም በማን ምክንያት ይመስልሻል" አላት።
ጌታም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እስኪ የልብሽን ሃሳብ ወይም ፍላጐትሽን ንገሪኝ" አላት። በዚህን ጊዜ "አቤቱ ፈጣሪየ ፈቃድህስ ቢሆን የአዳም ልጆች ከሥቃይ ከኵነኔ ይድኑ ዘንድ ዲያብሎስን ይቅር ትለው ወይም ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ። የኃጥእን መመለሱን እንጂ ጥፋቱን አትወድምና" አለችው። "የምለምንህ ወይም ማረው የምልህ ዲያብሎስን ወድጄው አይደለም ነገር ግን እርሱ ከተማረ በአዳም ልጆች ላይ ሥቃይና ኵነኔ ሊኖር አይችልም ብየ በመገመት እንጂ። የነሱ ሥጋ ሥጋየ እንደሆመኑ መጠን የኔም ሥጋ ሥጋህ ነውና" አለችው። ይህንም ባለችው ጊዜ ጌታ ፍግግ ብሎ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ሌሎች ካንቺ በፊት የነበሩ ካንቺም በኋላ የሚነሱ የማያስቡትን እጅግ የሚያስደንቅ ልመና አቀረብሽ" አላት። ይህንም ካለ በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ጠርቶ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ዲያብሎስን ማርልኝ ስትል ልመና አቅርባለችና እሺ ካላት ታወጣው በንድ ወደሲዖል ይዘሃት ሂድ" ብሎ አዘዘው። በዚህ ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እሺ ብሎ ሰግዶ እጅ ነሥቶ ወደሲዖል ይዞአት ሄደ። አብረው በሚጓዙበትም ጊዜ "እንግዲህ ዲያብሎስ ከታረቀ ወይም ከተማረ የሰው ልጆች ሁሉ ያርፋሉ" እያለች ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ታሳስበው ነበር። ይህን አምላክነትን ሲሻ ከክብሩ የተዋረደ ዲያብሎስ ምሕረት ለማግኘት ይሻ መስሏት ነበርና።
ከሲዖል አፋፍ በደረሱም ጊዜ የተመለከተችው ሥቃይ ተነግሮ የማያልቅ ነው ሰዎች ከሰዎች ጋር እንደውሻ ይናከሱ ነበር። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል "ምሕረት የሚፈልግ ከሆነ እስኪ በይ ዲያብሎስ ብለሽ ጥሪው" አላት። በዚህ ጊዜ በመላእክት ቋንቋ ሦስት ጊዜ "ሣጥናኤል ሣጥናኤል ሣጥናኤል" በማለት ጠራችው። ዲያብሎስም "ከዚህ በብዙ ሠራዊት ላይ ነግሼ ከምኖርበት አገር ማን ነው እሱ የሚጠራኝ" እያለ በታላቅ ቃል አሰምቶ ተናገረ። ከዚህም በኋላ "ለብዙ ዘመን ስፈልግሽ ወይም ሳድንሽ ቆይቼ ነበር ዛሬ ግን ከምኖርበት ቤቴ ድረስ መጣሽን" አላት። እርሷም "ጌታ ይቅርታ አድርጓልሃልና ከዚህ ከሥቃይና ከመከራ ቦታ ከወገኖችህ ጋራ ና ፈጥነህ ውጣ" አለችው። ይህንም በለችው ጊዜ ልቡ እንደ እሳት ነደደ አፈፍ ብሎ ተረማምዶ በግራ እጁዋን ይዞ ከሲዖል ረግረግ ውስጥ ወረወራት። በዚያን ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የእሳት ሰይፍ ይዞ ከኋላ ከኋላዋ ይከተላት ነበርና ይህን ምሕረት የሌለው ዕቡይ ዲያብሎስ በያዘው ሰይፍ ቢቀጣው የሲዖል ደጃፍ ተከፈተች። በዚህ ሰዓት ታላቅ ጨኸትና ውካታ ወይም መደበላለቅ ሆነ በሲዖል ያሉ የሰዎች ነፍሳት እንደንብ ከበቧት ወይም ሠፈሩባት። በዚያን ጊዜ በቅዱስ ሚካኤል ክንፍና በስዋም በተሰጣት ክንፈ ረድኤት ከሲዖል የወጡት ነፍሳት ቁጥር ዓሥር ሺህ ያህል ነበር። እነዚህ ከመከራ ያመለጡ ከሥቃይ የወጡ ነፍሳትን ባየች ጊዜ እጅግ አድርጋ ተደሰተች ከደስታዋም ብዛት የተነሣ የእናቱን ጡት እየጠባ እንደሚዘል እምቦሳ ጥጃ በመካከላቸው ትዘል ነበር።
ከዚህም በኋላ ወደ ፈጣሪዋ ሄዳ "አቤቱ ፍርድህ ከቶ እንደዚህ ነውን?" እያለች አደነቀች። ጌታም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ዲያብሎስን ድል አድርገሽ ጥቂት ምርኮን አገኘሽን" አላት። እስዋም "አዋ ጌታዬ በኃይልህና በቸርነትህ አገኘሁ" አለችው። ከዚህ በኋላ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሚካኤል ጠርቶ "እሊህን ነፍሳት ዓለም ሳይፈጠር ወደ አዘጋጀሁላት ወደ ክርስቶስ ሠምራ መኖሪያ ቦታ ውሰዳቸው" አለው። በዚህ ጊዜ "አቤቱ ፈጣሪየ የእኔ መኖሪያየ ወዴት ነው?" አለችው። ጌታም "መኖሪያሽ ከእናቴ ከድንግል ማርያም ጋራ ነው እነሆ በትረ ማርያም ብየ ሰየምኩሽ መቀመጫሽን ወይም ደረጃሽን ከእርስዋ ቀጥሎ ሁለተኛ አደረግሁልሽ የባለሟልነት ግርማ አጐናጸፍኩሽ አንቺን የሚወዱ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው" አላት። ይህንም ባላት ጊዜ ፈጽማ ደስ ተሰኘች ወደ ኋላዋም መለስ ብላ ብትመለከት ለዓይን የሚያንፀባርቁ ዓሥር አክሊላት አየች። በየአንዳንዳቸው አክሉል ላይ ዐራት ከዋክብት አሉ ባቸው የእሊህ ከዋክብት ቊጥራቸው ሲደመር አርባ ይሆናል። በዚህ ጊዜ ከስዋ ጋራ የነበረውን መልአክ "እሊህ በላያቸው ብርሃናውያን ከዋክብት ያሉባቸው አክሊላት ለማን የተዘጋጁ ናቸው ሰውነቴ እጅግ አድርጋ ወዳቸዋለችና" አለችው። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም "ላንቺ ቢሆን ደስ አይልሽምን?" አላት። እርስዋም "አዎን ጌታየ ለኔ ቢሆን እወዳለሁ" አለችው። "እንግዲያስ ላንቺ የተዘጋጁ ናቸው" አላት። "በምን ሥራዬ ለኔ ተሰጡኝ" አለችው። "ዐሠርቱ ቃላት ኦሪትን ስድስቱን ቃላተ ወንጌል ጠብቀሽ ቤትሽን ጥለሽ ይህን ዓለም ንቀሽ አጥቅተሽ የክርስቶስን ቀምበር ተሸክመሽ ፈጣሪሽን ስለተከተልሽው ነው" አላት። ይህንንም በአላት ጊዜ እጅግ አድርጋ ተደሰተች ሁሉን ማድረግ የሚችል እግዚአብሔርንም ፈጽማ አመሰገነች።
ምንጭ፦ ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
የቅድስት እናታችን ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ለተክለ ሃይማኖት ጻድቅ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ግንቦት ፲፪
አቡነ ተክለ ሃይማኖት
በዚህችም ዕለት የኢትዮጵያ ብርሃኗ ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፍልሠተ ዐፅማቸው ስለመከናወኑ፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከብዙ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸው በኋላ ተዘዋውረው ወንጌልን ለመስበክ የማይችሉት ዕድሜ ላይ ደረሱ፡፡ በዚህም ጊዜ ‹‹ለሌሎች አበራሁ ለራሴ ግን ጨለምኩ፣ ዓለም አጣፈጥሁ እኔ ግን አልጫ ሆንኩ…›› ብለው በዓት አጽንተው ከቆሙ ሳይቀመጡ፣ ከዘረጉ ሳያጥፉ ለ7 ዓመት ቆመው ጸለዩ፡፡ ከ1267-1289 ዓ.ም ባለው ጊዜ ደግሞ በደብረ ሊባኖስ ካለችው ገዳመ አስቦ ዋሻ በመግባት 8 ጦሮችን ተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት፣ ነገረ መስቀልን በማሰብ በተመስጦ ሌትና ቀን ያለማቋረጥ በጾምና በጸሎት በአርምሞ ተወስነው ሲጋደሉ ከቁመት ብዛት የተነሣ ጥር 4 ቀን 1289 ዓ.ም. አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራለች፡፡ ቅዱስ አባታችን በመዓልትና በሌሊት በትጋትና በቁመት በተጋድሎ ብዛት አንዲት የአገዳ እግራቸው ስትሰበር ዕድሜያቸው 92 ዓመት ሆኗቸው ነበር፡፡
ከ1289-1296 ዓ.ም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው በመቆም ያለምግብና ያለውኃ በትኅርምት ሌትና ቀን እንቅልፍ በማጣት እንደ ምሰሶ ጸንተው፤ በተመስጦ በትጋት ለሰው ዘር ሁሉ ድኅነትን ሲለምኑ ኖረዋል፡፡ ከሰባቱ ዓመታት ውስጥ ጥቂት ውኃ የቀመሱት በአራተኛው ዓመት ብቻ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ጌታችን ተገልጦላቸው በሰው አእምሮ ሊታሰብና ሊለካ የማይችል ትልቅና ልዩ የመንግሥት አዳራሽ ከሰጣቸው በኋላ የመለኮትን ነገር የሚናገር የእሳት አንደበት ያላቸው የመንግሥት ልብስ አለበሳቸው፡፡ በመስቀል ምልክት የተጌጡት ሰባት የሕይወት አክሊላትን አቀዳጅቷቸዋል፡፡ ይኸውም ‹‹ስለ ቀናች ሃይማኖትህ፣ ሃይማኖትን ለማስተማር መላዋን ኢትዮጵያን ስለመዞርህ፣ ከአረማውያን ሕዝብ ጋር በሃይማኖት ስትታገል ደምህን ስለማፍሰስህ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ወርደህ ልዩ ልዩ የቅዱሳን ቦታዎች ስለመሳለምህ፣ በሰባት ዓመታት ቊመት የአንዱ አገዳ እግርህ ስለመሰበሩ፣ ስለብዙ ጾም ጸሎት ስግደትህ፣ ስለልብህ ንጽሕናና ቅድስና›› በማለት የሕይወት አክሊላትን ካቀዳጃቸው በኋላ ዝክራቸውን በማዘከር መታሰቢያቸውን የሚያደርጉ ሁሉ በዚህ ዓለምም ሆነ በወዲያኛው ዓለም ፍጹም ዋጋና ፍጹም ክብር እንደሚሰጣቸው ጌታችን ታላቅ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ሥጋቸውም ወዴት ይቀበር ዘንድ እንዳላቸው ሲነግራቸው ‹‹እስከ 57 ዓመት ሥጋህ ከዚህ ይቀበራል፤ ከ57 ዓመት በኋላ ግን ይህች ዋሻ ትናዳላች፤ በዚህም ገዳም አደባባይ በስምህ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ልጆችህ ሠርተው ሥጋህን አፍልሰው በውስጡ ያኖራሉ›› አላቸው፡፡
ቅዱስ አባታችን በሞት ከማረፋቸው በፊት አስቀድሞ ጌታችን እንደነገራቸው ሥጋቸው ከነፍሳቸው ከተለየች ከ57 ዓመት በኋላ የካቲት 19 በጸሎት ላይ ለነበሩት ለአቡነ ሕዝቅያስ ተገልጠውላቸው ‹‹ጌታ የገባልኝ ቃል ይፈጸም ዘንድ ሥጋዬ የሚፈልስበት ደረሰ፣ ቀኒቱንም በምስጋናና በጸሎት መንፈሳዊ በዓል አድርጉ፤ እኔ ኃጥኡ በሞትኩበት ቀን እንደነበረው ምስጋና አቅርቡ፡፡ ሄደህ ለ12 መምህራንና ለልጆቼ ግንቦት 12 እንዲያከብሩ ንገራቸው፡፡ በፍልሰቴ ቀን አባቴ አባቴ የሚለኝ ሁሉ ይምጣ ያኔ እኔ ወዳጄ ሚካኤልና ልጄ ፊልጶስ አብረን መጥተን እንባርካለን፡፡ ምልክት ይሆንህም ዘንድ በምመጣበት ጊዜ የጠፋው የመቅረዙ መብራት ይበራል›› አሉት፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ ሕዝቅያስ በአባታችን ተባርከው ሄደው በአራቱም አቅጣጫ ላሉት 12 መምህራንና ለክርስትያኖች ሁሉ አባታችን የነገሩትን የፍልሰታቸው በዓል ስለማድረግ ወደ ፍልሰቱ በዓል ያልመጣም በዚያች ቀን (በሰማይ ለምልጃ) አባቴ እንዳይለው እርሱም ልጄ እንዳይለው ጨምሮ መልእክቱን ላከላቸው፡፡ እነርሱም ከያሉበት ተሰብስበው መጥተው የቅዱስ አባታችንን ሥጋቸውን አውጥተው ወደ ቤተ ክርስቲያን አፍልሰው 3 ጊዜ መቅደሱን አዙረው በዓሉንም አባታችን እንዳሉት በዝማሬና በምስጋና አክብረው ወደ ውስጥ አስገቡት፡፡ በዚህም ጊዜ ብፁዕ አባታችን ተክለ ሃይማኖት አስቀድመው እንደተናገሩት ጠፍቶ የነበረው መብራት ቦግ ብሎ በራ፡፡ ከቅዱስ ሚካኤልና ከልጃቸው ከአቡነ ፊልጶስ ጋር በመሆንም በዓሉን ያከብር የነበረውን የተክለ ሃይማኖት የጸጋ ልጆቻቸውን ሁሉም ይባርኩ ነበር፡፡
የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ረድኤት በረከታቸው ይደርብን! በጸሎታቸውም ይማረን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ግንቦት ፲፪
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ግንቦት አስራ ሁለት በዚህች ዕለት የዓለሙ ሁሉ መምህር የሆነ የከበረ አባት ዮሐንስ አፈወርቅ አረፈ፡፡ ይህም አባት ከእስክንድርያ አገር ሰዎች ወገን ነው የአባቱም ስም አስፋኒዶስ የእናቱም ስም አትናሲያ ነው እሊህም እጅግ ባለጸጎች ነበሩ ይህንንም ልጃቸውን በመልካም አስተዳደግ አሳደጉት ትምህርትንና ጥበብንም ሁሉ አስተማሩት እርሱ ወደ አቴና ሒዶ በመምህራን ቤት ተቀምጦ ትምህርትን ሁሉ ተምሮ በዕውቀቱ ከብዙዎች በላይ ከፍ ከፍ ብሏልና።
ከዚህም በኋላ ገና በታናሽነቱ መነኰሰ የዚህንም የኃላፊውን ዓለም ጣዕም ንቆ ተወ ከእርሱም ቀድሞ በዚሁ ገዳም ቅዱስ ባስልዮስ መንኵሶ ነበር በአንድነትም ተስማምተው ብዙ ትሩፋትን ሠሩ ወላጆቹም በሞቱ ጊዜ ከተውለት ገንዘብ ምንም ምን አልወሰደም ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠ እንጂ ከዚያም በምንኵስና ሥራ በመጠመድ ፍጹም ገድልን እየተጋደለ ኖረ።
በዚያም ገዳም ሶርያዊ ጻድቅ ሰው ስሙ ሲሲኮስ የሚባል መነኰስ ነበረ እርሱም ወደፊት የሚሆነውን በመንፈስ ቅዱስ ያይ ነበር በአንዲት ሌሊትም ለጸሎት እየተጋ ሳለ ሐዋርያትን ጴጥሮስንና ዮሐንስን አያቸው ወደ ዮሐንስ አፈወርቅ ገብተው ጴጥሮስ መክፈቻ ሰጠው ወንጌላዊ ዮሐንስም ወንጌልን ሰጠው እንዲህም አሉት በምድር ያሠርከው በሰማይ የታሠረ ይሆናል በምድርም የፈታኸው ደግሞ በሰማያት የተፈታ ይሆናልና በውስጥህ መንፈስ ቅዱስ ያደረብህ አዲስ ዳንኤል ሆይ የክብር ባለቤት ከሆነ ከታለቅ መምህር ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወደ አንተ ተልከናልና ዕወቅ እኔም የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ የተሰጠኝ ጴጥሮስ ነኝ። ሁለተኛውም እኔም በመጀመሪያው ስብከቴ በከበረ ወንጌል ቃል አስቀድሞ ነበረ ያልኩ ይህም ቃል በጠላት ላይ የእሳት ሰይፍ የሆነ ዮሐንስ ነኝ። ለአንተም ከክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወገኖችህ ምእመናንን በቀናች ሃይማኖት ታሳድጋቸው ዘንድ ዕውነተኛ አእምሮ ደግሞ ተሰጥቶሃል። ጻድቅ ሲሲኮስም ይህን ራእይ በአየ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ቸር ታማኝ እረኛ ሁኖ እንደሚሾም ዐወቀ። ከዚህም በኋላ በቅዱስ ዮሐንስ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በላዩ ወርዶ አደረበትና ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ ዲያቆን ሁኖ ሳለም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ብሉያትንና ሐዲሳትን ተረጎመ።
በአንዲት ሌሊትም ቅዱስ ዮሐንስ ሲጸልይ የእግዚአብሔር መልአክ በድንገት እንደ በረድ ነጭ በሆነ ልብስ ተገለጠለት ቅዱስ ዮሐንስም ሲያየው ደንግጦ በምድር ላይ ወደቀ መልአኩም አርአያውን ለውጦ እንደ ሰው ሁኖ ታየው ወዳጄ አዲስ ዳንኤል ሆይ አትፍራ ተነሣ አለው የቅዱስ ዮሐንስም ልቡ ተጽናንቶ ጌታዬ አንተ ማነህ ግርማህ አስፈርቶኛልና አለው የእግዚአብሔር መልአክም ትሠራው ዘንድ የሚገባህን ልነግርህ ወዳንተ የተላክሁ ነኝ። አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ያዘዘህን ለመሥራት ልብህን አበርታ ቃልህ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በአራቱ ማእዘን ይደርሳልና እልፍ አእላፋትም ትምህርትህን ተቀብለው ትእዛዝህን ሰምተው ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር ተመልሰው ይድናሉና በእግዚአብሔር መንግሥትም ውስጥ የጸና የብርሃን ዐምድ ትሆናለህና። እነሆ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አንተ ይመጣል ከእርሱም ጋራ ሁሉም ካህናትና ዲያቆናት በየማዕረጋቸው የሚያዝህንም አድርግ የእግዚአብሐር ትእዛዝ ነውና ልትተላለፍ አይገባህም አለው።
ከዚህም በኋላ ያ መልአክ ለአባ ፊላትያኖስ ተገልጦ ቅዱስ ዮሐንስን ቅስና እንዲሾመው አዘዘው በማግሥቱም ሊቀ ጳጳሳቱ መጣ ከርሱ ጋራም ካህናት አሉ ይህን ቅዱስ ዮሐንስንም ይዞ ቅስና ሾመው። የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳትም በአረፈ ጊዜ ንጉሥ አርቃድዮስ ልኮ አስመጥቶ ቅዱስ ዮሐንስን በቍስጥንጥንያ ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾመው አባቶቻችን ሐዋርያት እንደሚአደርጉት በሊቀ ጵጵስናው ሥራ ላይ ጸና ሕይወትነት በአላቸው ትምህርቶችና ተግሣጾች ሕዝቡን ሁልጊዜ የሚአስተምር ሆነ። ከኤጲስቆጶሳትም ሆነ ከመንግሥት ወገን ሕግን የሚተላለፉትን ሁሉ ይገሥጻቸዋል ማንንም አይፈራም ፊት አይቶም አያደላም።
የንጉሥ አርቃድዮስ ሚስት አውዶክስያም ገንዘብ ወዳጅ ስለሆነች የአንዲት ድኃ መበለት ቦታዋን በግፍ ወሰደች ያቺ መበለትም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥታ ንግሥት አውዶክስያ ቦታዋን እንደነጠቀቻት ነገረችው እርሱም የደኃዋን ቦታዋን መልሺላት ብሎ ከብዙ ምክር ጋር እንድትመልስላት ንግሥት አውዶክስያን ለመናት እርሷ ግን እምቢ በማለት አልታዘዘችለትም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውን ደሙን እንዳትቀበል አውግዞ ለያት።
ቍጣንና ብስጭትንም ተመልታ ስለ ክፉ ሥራቸው ከሹመታቸው እርሱ የሻራቸውን ኤጲስቆጶሳት ሰበሰበች እነርሱም ንግሥቲቱን ስለ ተቃወመ ስደት እንደሚገባው በእርሱ ላይ ተስማምተው ጻፉ እርሷም አጥራክያ ወደ ሚባል ደሴት ሰደደችው። ከዚያም በደረሰ ጊዜ የዚያች ደሴት ሰዎች በክፉ ሥራ ጸንተው የሚኖሩ ከሀድያን ሁነው አገኛቸው ቅዱስ ዮሐንስም አስተማራቸው ገሠጻቸውም በፊታቸው ስለ አደረጋቸው ድንቆች ተአምራት ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው።
የሮሜ ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳቱ ዮናክኒዶስ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ስደት በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ በንጉሥ አርቃድዮስ ላይም በመቆጣት እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፈው ላኩ ከዚህ ከክፉ ሥራ ተጠበቅ ትእዛዛችንንም ተቀብለህ የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ ከአልመለስከው በአንተና በእኛ መካከል ሰላም አይኖርም።
መልእክታቸውንም በአነበበ ጊዜ እጅግ አዘነ ሚስቱንም አግዶ ልኮ ቅዱስ ዮሐንስን ከስደቱ መለሰው በተመለሰ ጊዜም የቍስጥንጥንያ ሰዎች በመመለሱ ታላቅ ደስታ አደረጉ። ከጥቂት ቀኖች በኋላም ንግሥቲቱ ወደ ክፋቷ ተመልሳ ሁለተኛ ወደ አጥራክያ ደሴት ሰደደችውና በዚያው አረፈ።
ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳት ዮናክኒዶስም በሰሙ ጊዜ መልእክትን ላኩ ሊቀ ጳጳሳቱም የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ እስከምትመልሰው ድረስ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል አውዶክስያን አወገዛት።
ከዚህም በኋላ የከበረ ዮሐንስን ይመልሱት ዘንድ ንጉሥ ላከ ግን ሙቶ አገኙት ሥጋውንም ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ አደረሱት። የከበረ ዮሐንስም በተሰደደበት አገር እንደአረፈና ሥጋውንም ወደ ቍስጥንጥንያ ከተማ እንዳመጡ ወደ አባ ዮናክኒዶስ መልእክት ጽፈው አስረዱት። ሁለተኛም የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል ልኮ አውድክስያን አወገዛት እየለመነችውም ስምንት ወር ያህል ኖረች በብዙ ልመናም ፈታት። ነገር ግን ጭንቅ በሆነ ደዌ እግዚአብሔር አሠቃያት ያድኗት ዘንድ ገንዘቧን ለባለ መድኃኒቶች ጥበበኞች እስከ ሰጠች ድረስ ግን አልዳነችም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መቃብርም ሔዳ በእርሱ ላይ ያደረገችውን በደል ይቅር ይላት ዘንድ እየሰገደችና እያለቀሰች ለመነችው እርሱም ይቅር አላት ከደዌዋም ፈወሳት። ጌታችንም ከሥጋው ታላላቅ ድንቆች ታአምራትን ገለጠ።
ስለርሱም እንዲህ ተባለ በአንዲት ዕለትም ከንጉሥ አርቃዴዎስ ጋር ተቀምጦ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው አባቴ ሆይ ስለ አንድ ቃል እንድታስረዳኝ እለምንሃለሁ። ይህም ቃል ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በልቤ ውስጥ ይመላለሳል ወንጌላዊ ማቴዎስ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምን የበኵር ልጅዋን እስከ ወለደች ድረስ ዮሴፍ አላወቃትም ስለምን አለ ወንዶች ሴቶችን እንደሚአውቋቸው ዮሴፍ አወቃትን አለው።
➺አለባበስን በተመለከተ ስለ ወንዶችስ ምን ሊባል ይችላል?
አለባበስን በተመለከተ ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ወንዶችም ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው።ሠለስቱ ምዕት በሃይማኖተ አበው «ወይኩን አልባሲከ በተዓቅቦ፣ አለባበስህ በጥንቃቄ ይሁን» በማለት አዘዋል፡፡ ሊቃውንት አባቶቻችን አሁንም በሃይማኖተ አበው የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ «ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም አንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው። » ራእይ16፥15 በማለት የተናገረውን ምሥጢረ ብዙ ኃይለ ቃል ዋቢ በማድረግ እነርሱም «ወዓዲ ተዐቀብ ከመ ኢትትዐረቅ እምልብስከ ቅድመ መኑሂ ዘእንበለ ዳዕሙ ሶበ ይረክበከ ምክንያት ለተዐርቆ» ብለዋል፡፡ ይህም በአማርኛ «ዳግመኛ በማንም ፊት ከልብስህ ራቁትህን እንዳትሆን ተጠበቅ የምትራቆትበት ምክንያት ቢያገኝህ ነው እንጂ፡፡» ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ስለዚህ በሐኪም ፊት አንድንራቆት የሚያደርግ በሽታን የመሰለ ነገር ሳያገኘን ተራቁቶ መታየት ያስጠይቃል።
የኖኅ መራቆት የልጅ ልጁን ከነዓንን ለእርግማን ዳርጓል፡፡ ዘፍ8÷22-25 የቤርሳቤህ ከልብስ ተራቁቶ መታየት ራሷንና ዳዊትን ለዝሙት ዳርጓል፡፡ 2ሳሙ11፥2-4 ስለዚህ መራቆት የማያስፈልገው በቤተሰብም ሆነ በተመሳሳይ ፆታዎች መኻል ነው እንጂ ዘመድ ባልሆነና በሩቅ ሰው ዘንድ ብቻ አይደለም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ «ወንድ የሴትን ልብስ አይልበስ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና» ይላል፡፡ ዘዳ22፥5 ሆኖም ግን ብዙ ጊዜ «ሴት የወንድን ልብስ አትልበስ» የሚለው ቃል ብዙ የመጠቀሱን ያህል ይህ ቃል አይጠቀስም፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ቃል ወንዶች በአለባበስና ለባሕርያቸው በማይስማማ ሥራ አርአያቸውን ወደ ሴት መቀየር እንደሌለባቸው ያስረዳናል፡፡
ቀጣይ ምዕራፍ ዘጠኝ ክፍል ሁለት :
👉 የልብስ ምሳሌነትና ምሥጢር
👉 «የሚገባ ልብስ» በሚል ይቀጥላል....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
ምዕራፍ ዘጠኝ ክፍል አንድ
.................................................
ትውዝፍት (የምንዝር ጌጥ)
እግዚአብሔር የሰው ልጆች እንዲታረዙ (እንዲራቆቱ) አይፈልግም፡፡ስለዚህ አዳምና ሔዋን ትእዛዙን አፍርሰው የጸጋ ልብሳቸውን በተገፋፉ ጊዜ «የቁርበት ልብስ አደረገላቸው፤ አለበሳቸውም» ዘፍ3፥21 ነገር ግን ከልክ በላይ ከፍተኛ ዋጋ በማውጣትና ግብረ ገብነት በጎደለው መልኩ ማጌጥ መልበስ የሚያስፈልግበትን ትክክለኛ መንፈሳዊ ትርጉም ያጠፋል፡፡
በልብስ የሚጠቀመው ሥጋ ቢሆንም ልብስ ግን አስፈላጊነቱ ለነፍስ ነው። ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ነፍስ ብትለየው አያፍርም፣ አይለብስም።ልብሰ መግነዝ እንኳን የሚያለብሱት መልበስ ተገቢ መሆኑን የሚያውቁ ነፍስ ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ሆኖም በመልበስ ከቁርና ከብርድ የሚድነው ሥጋ በመሆኑ ልብስ ጠቃሚነቱ ለሥጋ እንደ ሆነ ተደርጎ ይነገራል፡፡
ትርጓሜ ወንጌል «ስለነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት ወይም ስለ ሰውነታችው በምትለብሱት አትጨነቁ» የሚለውን ሲተረጉም እንዲህ ይላል፦ ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል «ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት አትጨነቁ» ያለው ነፍስ ሥጋዊ መብል የምትበላ ሥጋዊ መጠጥም የምትጠጣ ሆና አይደለም። ነገር ግን የበሉት የጠጡት ደም ይሆናል (ከሰውነት ጋር ይዋሐዳል)።የበሉት የጠጡት ደም በመሆኑ ደግሞ ተጠቃሚዋ ነፍስ ናት።ምክንያቱም «እስመ ነፍስ ተኀድር በደም ፣ ነፍስ በደም ታድራለችና» ተብሎ ተጽፏልና፡፡ ደም ባይኖር ወይም ቢደርቅ ነፍስ በምን ታድራለች? ደም ፈሶ ሲያልቅ ሰው የሚሞተው ነፍስ ማደሪያዋን በማጣቷ ምክንያት ስለምትለይ ነው።ስለዚህ ተመጋቢው ምንም ሥጋ ቢሆን በዋናነት ተጠቃሚዋ ነፍስ በመሆኗ መብል መጠጥ ለነፍስ እንደሆነ ተደርጎ ይነገራል፡፡
ድንግልናን ማቃለል ያስቀሥፋል!
ድንግልና ወጀብ የበዛበትን የዓለም ባሕር የምንሻገርበት መርከብ ነው። ስለዚህ ድንግልና ከመከራ ይሠውራል። ድንግል ማርያም ሄሮድስ ሊያደርስባት ካሰበው ኀዘንና መከራ እንዴት እንደዳነች መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር እንዲህ ይላል፦ «ከእባቡም ፊት ርቃ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሃ እንድትበር ለሴቱቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።» ራእይ12፥14 እንደሚታወቀው እመቤታችን ከሄሮድስ ፊት ሸሽታ ወደ ግበፅ በረሃ ሄዳለች:: ለዚህም የረዷት ሁለት ክንፎች ንጽሐ ሥጋዋና ንጽሐ ነፍሷ ናቸው።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመከራ የተሠወረችው በንጽሕናዋ ነው፡፡ ንጽሕና ከመከራ ይሠውራልና።በሁለት ወገን በነፍስና በሥጋ የሚገኝ ድንግልናዋም ሁለት የንሥር ክንፍ ተብሏል፡ ድንግልና ክንፍ ይባላልና፡፡ ስለ ድንግልና ስያሜ በመግቢያ ላይ እንደ ተገለጠው አረጋዊ ዮሴፍ «ኦ ወለተ እስራኤል መኑ ቀረጸ አክናፈ ድንግልናኪ፣ አንቺ የእስራኤል ልጅ የድንግልናሽን ክንፍ ማን ገሠሠው?» በማለት የተናገረው ቃል ድንግልና «ክንፍ› ለመባሉ ምስክር ነው።
ድንግልናን መጠበቅ ከመከራ ከሠወረ ድንግልናን አለመጠበቅ ለመከራ እንደሚያጋልጥ ግልጽ ነው፡፡ ክብርን አለመጠበቅ ያስቀጣል፡፡ ሕግን ያለመጠበቅ የሚያመጣውን ቅጣት ድርሳነ ሚካኤል ‹‹ወይ ለክን አሌ ለክን እለ ታማስና ድንግልናክን ዘእንበለ ጊዜሁ እስመ ሀለወክን አፍሐመ እሳት ዘይበልዓክን ዘእንበለ ዓቅም- ድንግልናችሁን ያለ ጊዜው በማይገባ የምታጠፉ እናንተ ወዮላችሁ ወዮታ አለባችሁ! እናንተንም የሚበላ የገሃነም እሳት ተዘጋጅቷልና» በማለት ይናገራል፡፡ በገሃነም ከመጣል የሚበልጥ ምን መቅሠፍት አለ? ድንግልናን መጣል በገሃነም ያስጥላል፡፡ (ድርሳነ ሚካኤል ዘጥቅምት)
በእስራኤላዊያን ዘንድ አንዲት ሴት ሳታገባ በአባቷ ቤት ሳለች ድንግልናዋን ብታጠፋ በድንጋይ ተወግራ ትገደል ነበር፡፡ ይህን እንዲፈጽሙ ነቢዩ ሙሴ «ነገሩ እውነት ቢሆን፡ በብላቴናይቱም ድንግልናዋ ባይገኝ፡ ብላቴናይቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያወጡአት፥ በእስራኤልም ዘንድ የማይገባውን ነገር አድርጋለችና በአባቷም ቤት አመንዝራለችና የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይወገሩአት፡ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ፡፡» በዳ22÷20-21 በማለት አዝዟቸው ነበር:: በዘመነ ኦሪት በሕይወት ዘመን ለልዩ ልዩ መከራ ከማጋለጥና በኋላም በገሃነም እሳት ከማስኮነን ሌላ ድንግልናን አለመጠበቅ የሚያመጣው ተጨማሪ መቅሠፍት በድንጋይ ተወግሮ መሞት ነበር፡፡
እግዚአብሔር ነገደ ብንያምንም ስለ ክፉ ሥራችው ለመበቀል ፈልጐ እስራኤላዊያንን ለጦርነት እንዲወጡ ትእዛዝ ባስተላለፈ ጊዜ ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ እግዚአብሔር ጉባዔ ወደ ምጽጳ ያልወጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ ባልወጡት ሰዎች ላይ የጉባዬው ውሳኔ «ሂዱ በኢያቢስ ገለዓድም ያሉትን ሰዎች ከሴቶችና ከሕፃናት ጋር በሰይፍ ስለት ግደሉ፡፡ የምታደርጉትም ይህ ነው:: ወንድን ሁሉ ከወንድ ጋር የተኛችይቱንም ሴት ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ ብለው አዘዟቸው፡፡ ወንድ ያላወቁ አራት መቶ ቆነጃጅት ደናግሎች በኢያቢስ ገለዓድ በሚኖሩ መካከል አገኙ፥ በከነዓንም አገር ወዳለችው ወደ ሴሎ ወደ ሰፈሩ አመጡአቸው።>> መሳ21፥10-12
ከላይ ከተጻፈው ታሪክ ሕፃናትን ጨምሮ ከወንድ ጋር የተኙና ድንግልናቸውን ያልጠበቁ ሴቶች በሙሉ በሰይፍ ስለት ስያልቁ ለመዳን የቻሉ ግን አራት መቶ የሚሆኑ ድንግልናቸውን የጠበቁ ቆነጃጅት ብቻ ነበሩ፡፡ እነዚህ ከጦርነት መቅሠፍት የተረፉ ደናግላን መዳናቸው ብቻ ሳይበቃቸው መልካም ትዳር ለማግኘት በቅተዋል፡፡ ይህም በቁጥር 14 ላይ «ከኢያቢስ ገለዓድም ሴቶች ያዳኗቸውን ሴቶች አገቡአቸው።» በማለት በማያሻማ መልኩ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡
ዛሬም ቢሆን ድንግልናን መጠበቅ ከመቅሠፍት ያድናል፡፡ ድንግላዊ ካልሆነ በቀር ኤድስን ጨምሮ ከተለያዩ የአባለዘር በሽታዎች ነጻ የመሆን ስሜት የሚሰማው ማን ነው? በዚህ ዘመን ድንግልናን ባልጠበቁ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር ያዘዘው መቅሠፍት እንደ ኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ሰይፍ የታጠቁ ወታደሮችን ሳይሆን ልዩ ልዩ ደዌን፤ ሰላም ማጣትን፣ የአእምሮ ጭንቀትን፣ ሥጋትን፣ ግጭትን፣ ጥርጥርን፣ አለመግባባትን፣ መለያየትንና የመሳሰሉትን ነው፡፡ እንደ አያቢስ ገለዓድ ሰዎች ድንግልናቸውን ያለ ጊዜውና ያለ አግባብ ያጠፉትን ሰዎች የሚቀሥፍ ወታደር (መልአክ) ዛሬም የሚላክ ቢሆን ኖሮ ስንቶቻችን በሕይወት እንተርፍ ነበር? ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ኀጢአታችን አላደረገብንምና ፈጣሪያችን ይክበር ይመስገን!
ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
ምዕራፍ ስምንት ክፍል ሰባት
.................................................
ስለ ድንግልና ማልቀስና መጾም ይገባል!
በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኩ የተመዘገበለት ዮፍታሔ የተባለው መስፍን አንዲት ሴት ልጅ ነበረችው:: ከእርሷም በቀር ወንድ ወይም ሴት ሌላ ልጅ አልነበረውም:: ይህች ሴት ልጁ ወንድ የማታውቅ ድንግል ነበረች:: በድንግልና ሆና እስከ መጨረሻው ለመኖር ውሳኔ ነበራት፡፡
ከዕለታት በአንድ ቀን ዮፍታሔ ለጦርነት ሲወጣ ጦርነቱን በድል ከፈጸምኩኝና «በደኅና በተመለስኩ ጊዜ ሊገናኘኝ ከቤቴ ደጅ የሚወጣው ማንኛውም ለእግዚአብሔር ይሆናል፣ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አቀርበዋለሁ።» ብሎ ለእግዚአብሔር ስእለት ተሳለ ጦርነቱንም በድል በፈጸመ ጊዜ «እነሆም ልጁ ከበሮ ይዛ እየዘፈነች ልትገናኘው ወጣች» ይላል።እንደ ስእለቱም እርሷን መሠዋት ነበረበትና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይህን አሳወቃት። በዚህ ጊዜ ምንም _ ሳታቅማማ በፍጹም ታዛዥነት በአፍህ እንደተናገርህ አድርግብኝ›› አለችው፡፡ መሳ11÷29-40
ነገር ግን ከመሠዋቷ በፊት አባቷን «ለድንግልናዬ እንዳለቅስ ሁለት ወር አሰናብተኝ» መሳ11፥37 በማለት አባቷን ተማጸነችው፤ አባቷም ፈቀደላት፡፡ ከዚህ በኋላ «በተራሮች ላይ ስለድንግልናዋ አለቀሰች» መሳ11÷ 29 ይህች ሴት ያለቀሰችው ለምንድር ነው? ምክንያቷ ምንም ይሁን ምን ለእኛ ግን ስለድንግልና ማልቀስ አስተማረችን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በየዘመኑ ብዙ ደናግላን መኖራቸውን ገልጾ ይናገራል፡፡ ለምሳሌ፦ «በስድስተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨት ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ›› ይላል፡፡ ይህን የወንጌላዊ ቃል መምህራን ሲተረጉሙ ብዙ ገሊላዎች አሉና ከእነዚያ ለመለየት «የናዝሬት ከተማ» ሲል ብዙ ዮሴፎች አሉና አረጋዊ ዮሴፍን «ከዳዊት ወገን ለሆነው» በማለት ለይቶ ጠቅሶታል:: በዚያው ዘመን ደግሞ ብዙ ደናግል ነበሩና ከእነዚያ ለመለየት «ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል» በማለት ተናገረ ይላሉ፡፡ ይህም ትርጓሜ በየዘመኑ ብዙ ደናግላን መኖራቸውን ያስረዳል። ሉቃ 1÷26-27
ሐቁ ይህ ሆኖ ሳለ ይህ ትውልድ ግን ዛሬ ዛሬ ደናግላንን ማግኘት ጭንቅ እንደሆነ ይናገራል፡፡ የዚህ ነገር ዐቢይ ምክንያት ይህ ትውልድ አመንዝራ በመሆኑና ሁሉን የሚመለከተው እንደ ራሱ ስለሆነ ነው:: ይህ ሐሳብ የተጋባባቸው አንዳንድ ደናግላንም ድንግልናቸውን እነሱ ብቻ ጠብቀው እንደሚኖሩ ይሰማቸዋል:: ነገር ግን የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና ድንግልናዊ አኗኗርን ከምታወድስ ከቤተ ክርስቲያን ዘልቀው ቢመለከቱ በየጊዜው እንደ ዕንቁ የሚያበሩ ደናግላን ምእመናንን በዐፀዷ ዙሪያ ተኮልኩለው መመልከት ይቻላል:: በዚህ ምክንያት ሰይጣን ብዙ ሴሰኞች ዓይኖቻቸውን በቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ እንዲያነጣጥሩ ማድረጉ ሊታወቅ ይገባል::
ዛሬ ዛሬ ድንግልና የሚገኘው በማዋለጃ ሆስፒታል ውስጥ በሚገኙ ሕፃናት ዘንድ ብቻ እንደሆነ ተደርጎ የሚናኘው ቀልድ መሰል አሉባልታ እጅግ የተጋነነ የሰይጣን ወሬ ነው፡፡ ይህ ዓይነት የተጋነነ ወሬ ድንግልናቸውን ያፈረሱ ሰዎች ከመጸጸትና ንስሐ ከመግባት ይልቅ «በእኔ አልተጀመረ» እያሉ እንዲጽናኑ ሲያደርጋቸው፣ ሌሎችን ደግሞ «በድንግልና የምገኝ እኔ ብቻ ነኝ» በማለት በትዕቢት እንዲወደቁ አድርጓቸዋል።
ደናግላን በቁጥር ብዙ መሆናቸው መታወቁ ማንም በድንግልናው እንዳይመካ ያደርጋል። ብዙ ሰው በያዘው ነገር መመካት አይመችምና፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በድንግልናው የሚመካ ሰው ራሱን ቢመረምር አንዳይመካ የሚያደርገውና ለድንግልናዊ ኑሮው የማይስማማ እጅግ በጣም ብዙ የልቡና ርኩሰት ይገኝበታል፡፡ ለምሳሌ፡- መመካት፣ በሌላው መፍረድ፣ መታበይ፣ ማማት፣ ክፉ ፍትወት፣ ሰዶማዊነት፣ ትምክህት የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ታዲያ ከእነዚህ ሁሉ የረከሱ ሥራዎች ጋር እንደ ትኋን ተጣብቀው እየኖሩ «ድንግል ነኝ እኮ!» እያሉ መመካት አያሳፍርም?
አንዳንዶች ደግሞ በድንግልናቸው ይመኩ እንጂ እነርሱ ራሳቸው በልዩ ልዩ መንገድ ሲያቃልሉት ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ፡- ድንግልና በገንዘብ የማይተመን ሆኖ ሳለ አንዲት ልጃገረድ «ድንግል ነኝኮ» እያለች የሚመጣላትን ባል «አንዱን ዕውቀት፣ አንዱን ሹመት፣ አንዱን ገንዘብ፣ አንዱን ንብረት ሌላውን ደግሞ ማራኪ ቁመናና ውበት የለውም» በማለት ከድንግልና ጋር የማይወዳደሩ ነገሮችን ብታማርጥበት ንጽሕናዋን ለተጠቀሱት ነገሮች እንደ መሸጥ አይቆጠርባትምን? ስለ ንጽሕናዋ ንጽሕናን መሻትና መመልከት ሲገባት የሀብትን መጠንና ሌሎች ነገሮችን በማየቷ ድንግልናን እንደሚገባው መጠን ታከብራለች ለማለት አያስደፍርም፡፡ ስለ ድንግልና እንዲህ ዓይነት የተዛባ አመለካከት ይዞ በድንግልና መመካት እንዴት ያሳፍራል?
በመጨረሻም ማስተዋል ያለብን ድንግልናችንን ለመጠበቅ የመጀመያዎቹ ተጠቃሾች እኛው ራሳችን ብንሆንም ዐስበ ድንግልናችንን (የድንግልናችንን ዋጋ) ለማግኘት ያህል ነው እንጂ ድንግልናችንን የሚጠብቅልን ራሱ እግዚአብሔር ነው:: መጽሐፈ አርጋኖን ስለ መንፈስ ቅዱስ "ንጹሐን ደናግልን ያበረታቸው እርሱ ነው።"ይልና «በድንግልናም ጊዜ የንጽሕና መንፈስ ነው» በማለት ይናገራል፡፡ (አርጋኖን ዘእሁድ) ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ደግሞ «እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂ በከንቱ ይደክማል» መዝ126÷1 በማለት ተናግሯል፡፡ ትርጓሜውም እግዚአብሔር በከተማ የሚመስለውን ሰውነትን በንጽሕና በድንግልና ካልጠበቀ ራሴን ጠብቄ ድንግልናዬን እቆያለው ማለት ከንቱ ድካም ነው ይለናል፡፡
ሚስቶች አለባበስን በተመለከተ የራሳቸውን ስሜት ብቻ ሳይሆን የባሎቻቸውንም ሁኔታ ከግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለባቸው ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ተናግሯል።በሚስቶች ተገቢ ያልሆነ አለባበስ ባሎች የሚሰማቸውን ሲናገርም"ወሶበሂ ኢኀፈረ ነቢበ እንበይነ ዘእንበለ ዳእሙ ያት ሒዘበኪ በልቡ።
ወታመጽኢ ቅንአተ በርእስኪ፡፡ ወታኀጥኢ ኩሎ ተድላ በእንቲአሁ፡፡ ወባሕቱ ትጻልኢ፡ ወትሴስሊ እምኔሁ፡፡"ይህም «በማይገባ ልብስ አጊጠሽ ባየ ጊዜ ሕጌ ይፈርስብኛል ብሎ ሊናገርሽ ቢያፍር እንኳን በልቡ ይጠረጥርሻል፡፡ በሥራሽ ቅንአትን ታመጭበታለሽ፡፡ ስለ ቀናም ከእርሱ የምታገኚውን ተድላ ታጫለሽ፡፡ ትነቀፊያለሽ ስለዚህ ከባልሽ ተፋተሽ ትሔጃለሽ» ማለት ነው:: ዳግምኛም በልብስ ዘማ አጊጣ ስትወጣ ባያት ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን የምትሔድ እንኳን ቢሆን «ባይከለክላት እንኳን ይጠረጥራት የለምን? ከቤት ሳለች እንዲህ የማታጌጠው ለምንድር ነው? ምን አምሯት ይሆን?» ማለቱ አይቀርም።ይህም ቃል በግእዙ እንዲህ ይነበባል፡ «ወእምኒ ኢከልኣ አኮኑ እምተሐዘባ፡፡ ወይቤ ለምንት ኢትሠረገው ውስተ ቤት ወኢትሤነይ፡፡ ወምንትኑ መፍቅዳ፡፡» (ተግ.ዘዮሐ 28)
ሐ. እኔ እንዲህ የማጌጠው ባሌ ውጭ ውጭ እንዳይልብኝ ነው ! » በማለት ልብሰ ዘማ (የዘማዊያንን ልብስ) መልበስ አትለማመጂ፡፡ ከዚያ ይልቅ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተናገረው ‹ንጹሑን ኑሮሽን እየተመለከተ» ባልሽ ባንቺ እንዲማረክ አድርጊ፡፡ 1ጴጥ3፥1-6 ባልሽን በአለባበስሽ እንዲማረክ ማድረግ የበለጠ ሴሰኛ ማድረግ መሆኑን አታውቂምን? ባልሽ «ንጹሕ» ሰው ከሆነ የሚማረከው በ«ንጹሕ» አኗኗርሽ እንጂ በአለባበስሽ አይደለም።«ወእመሰ ተሠርገውኪ በዘዚአሁ ሠርጉ ወኮነ ምትኪ ዘማዌ የሐውር ኀበ ካልእት ማለትም «ባልሽ ሴሰኛ ከሆነ ግን ምንም በጌጦች ዓይነት ሁሉ ብታጌጪ ካንቺ ወደ ሌላ መሄዱ አይቀርም፡፡» ምክንያቱም በማጌጥ አንዷ ሴት አንዷ መብለጧ አይቀርምና፡፡ (ተግ.ዘዮሐ 28)
መ. ከወሊድ ጋር ተዛምዶ ያላቸውን አካላት የሚያጋልጥ ልብስ ለብሶ ወደ ገበያና ሥራ ቦታ መሄድ እጅግ ያሳፍራል፡፡ ለሥራም የሚመች አይደለም፡፡ ይልቁኑም ለክርስቲያኖች ሰውነትን እንደ ከብት የሚያስገምት ልብስ ለብሶ በመዋኛና በመታጠቢያ ስፍራዎች ወዲህና ወዲያ ማለት እንዴት ያስነውራል? ከዚህ ሁሉ ግን የሚያስወቅስው በልብሰ ዘማ አጊጦና ተገላልጦ ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባት ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ «ቦኑ ትትቃወሚዮ ለቃለ ሐዋርያ ብፁዕ ጳውሎስ» በማለት እንደ ተናገረው ወደ ቤተ ክርሰቲያን የምትሔጂው «ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ራስዋን ታዋርዳለች» በማለት የተናገረውን ቅዱስ ጳውሎስን ለመቃወም ነውን? 1ቆሮ11፥5
ሠ. የማይገባ አለባበስ በክርስቲያኖች ዘንድ ቢታይ በማያምኑ ሰዎች ፈጣሪያቸውን ያሰድቡታል፡፡ ለምሳሌ፦ አንዲት ሴት እጅግ በጣም ከፍተኛ ዋጋ በሚያወጣ ልብስ ተሸልማ የሚበሉትና የሚጠጡትን አጥተው የተቸገሩ ድሆች ቢያይዋት ስለ ፈጣሪ የሚያስቡት ምንድር ነው? «እኛ እንዲህ ስንቸገር አንተ ሰብስበህ ለአንዲቱ ይህን ሁሉ ታሽክማታለህን? አንተንስ ፋንድያ ማጠን ነው!» አይሉትምን? እንዲህም ባይሉት ፈጣሪ የማይወዳቸው እየመሰላቸው ተስፋ መቁረጣቸው አይቀርም፡፡ አሕዛብንም ቢሆን ግብረ ገብነት የጎደለው አለባበሳችን ወደ ሃይማኖታችን እንዳይሳቡ ሊያደርጋቸው ይችላል።
ረ. አለባበስን በተመለከተ የራስን ስሜት፣ የትዳራችንን ሁኔታ፣ የድሆችንና የማያምኑ ሰዎችን ሕሊና ላለመጉዳት ከማሰብ በላይ ከፈጣሪ ሕግ ላለመውጣት ጥረት ብናደርግ አለባበሳችን በዘመናችን ሁሉ ብዙ እጅግ በጣም ተለዋዋጭ እንዳይሆን ለማድረግ ባልቸገረንም ነበር። ስለዚህ ልብስ ከፈጣሪ አይበልጥምና አለባበስን በተመለከተ «ፈጣሪዬ ከኔ የሚሻው ነገር ምንድር ነው?» እያሉ በአግባቡ መመላለስ ይገባል፡፡
ሰ. ሕይወት በእንቅሰቃሴ የተሞላች ናት፡፡ ከቤት ለአንድ ዓላማ ብለሽ ከወጣሽ በኋላ እግረ መንገድሽን ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ሌላ ቦታ መድረስ ያስፈልግሽ ይሆናል፡፡ ታዲያ አለባበስሽ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ የማያግድሽ ሁለገብ እንዲሆን ለምን አትጥሪም? ለአንቺም ቢሆን እኮ የምታከብሪያቸውን ሰዎች ስታዪና በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትሄጂ በመሳቀቅ ከምታልቂ አንድ ፊቱን በእግዚአብሔርና በመልካም ሰዎች ዘንድ የተወደደ አንድ ወጥ የአለባበስ መንገድ ብትከተዪ መልካም ነው::
ሸ. ልብስ ስትለብሺ በእንቅስቃሴ ወቅት እንዴት እንደምትሆኚ አስቢ እንጂ እንደ ልብስ ማሳያ አሻንጉሊት ይመስል የሰቀሉብሽን ወይም ያምርብሻል ያሉሽን ሁሉ አትልበሺ፡፡ አንቺ እኮ! በመኪና ቁጭ ብለሽ የምትጓዢ፣ በቢሮ ቁጭ ብለሽ የምትጽፊ፣ አጎንብሰሽ የወደቀ የምታቀኚና ልብስ የምታጥቢ በአጠቃላይ በእንቅስቃሴ የተሞላ ሕይወት ያለሽ ፍጡር ነሽ፡፡ ታዲያ በነዚህ እንቅስቃሴዎችሽ ውስጥ አጭርና ጠባቃ ልብስ ብትለብሽ ለሌሎች እይታ የምታጋልጫቸውን ሕዋሳቶችሽንና ሊፈጠርብሽ የሚችለውን አንዳንድ መጥፎ ገጠመኝ ለምን አታስተውዪም። እኔ በግሌ አጭር ልብስ ለብሶ ማርዘም ላይቻል ሲጎትቱ ከመዋል ረጅሙን መርጦ መልበስ ይሻላል እላለሁ።
ቀ. አንዳንድ ወጣቶች ኋላ ቀር መስለው እንዳይታዩ በጣም አዲስ ከሆነው ፋሽን ጋር መራመድ እንደሚገባቸው አድርገው ያስባሉ።ምን ጊዜም ከመጠን ያለፈ «ወግ አጥባቂ» በመሆንና በጣም «ዘመናዊ» በመሆን መካከል አንድ አማካይ ቦታ ይኖራል፡፡ ይህን መሀከለኛነት ከያዝሽ ሁል ጊዜ ጥሩ አለባበስ ይኖርሻል፡፡ በየጊዜው ለሚመጣው የፋሽን ለውጥ ተገዥ ከመሆንም ትድኛለሽ፡፡
በተጨማሪም ስለ ፋሽን በጣም በመጨነቅሽ የምትጠቅሚው ማንን ነው? መልሱ ራስሽን ሳይሆን ፋሽኖችን የሚያቀርበውንና የሚያበረታታውን የንግዱን ዓለም ነው።እነርሱ አንድ ዋነኛ ዓላማ አላቸው፤ እርሱም ገንዘብ ማግኘት ነው።በእነርሱ ሥራ ውስጥ የሰይጣንን ሚና ከተመለከትሽ ደግሞ ዓላማው በብልሹ አለባበስ ምክንያት በዓለም ላይ የሥነ ምግባር ጉድለት እንዲንሰራፋ፣ ስለ እግዚአብሔር ማሰብ በቁሳዊ ነገር እንዲተካ ማድረግ ሆኖ ታገኝዋለሽ፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜ ፋሽን ተከታይ ከሆንሽ አንቺ ምንም ሳትጠቀሚ ገንዘብሽን ጨምሮ የምታጫቸው ነገሮች በርካታ ናቸው::
ሰበር ዜና
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል፦
1. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤
2. ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
3. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን የሐዲያ ሀ/ስብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
4. ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዘኮሎራዶን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤
5. ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሜኒሶታን እንደያዙ የኮሎራዶ ሀ/ስብከትን እንዲመሩ፤
6. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳ ጳስ፤
7. ብፁዕ አቡነ ዕንባቆምን የገዳማት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ፤
8. ብፁዕ አቡነ ሙሴ አውስትራልያን እንደያዙ የግቢ ቅዱስ ገብርኤልና የበዐታ ለማርያም ገዳም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።
➼ የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፲፯ ዓ/ም
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሴቶች ሠላጤ የሌለው ሱሪ መልበሳቸው ደግሞ ለጊዜው ለእይታ ሲጋለጡና ወደ ደርብ (ሰገነት) ሲወጡ ለአካላቸው መከለያ እንዲሆን ነው።ምሥጢሩ ግን እንደ ወንዶች የምንዋጋበት ዐቅም የምንደፍርበት ልብ የለንም፡፡ የአካላችንም ቅርጽ ከወንዶች አካል ቅርጽ ልዩ ነው እንደ ማለት ነበር፡፡ ስለዚህ የሱሪያቸው ስም ትርጉም ባለው አጠራር «ልብ አልባ» ይባላል፡፡
የካህናትና የባላገሮች ሱሪና እጀ ጠባብም ሠላጤውን እንደ ወታደር አድርገው መስፋታቸው የተፈጥሮ አካላችን ቅርጹ ከእናንተ ጋር አንድ ነው ማለት ሲሆን፡ የእጅና የእግር ማስገቢያውን ደግሞ የሌላ ሰው እጅና እግር ደርቦ የሚያስገባ ያኽል ቦላሌ አያያ መስፋታቸው ለጊዜው ሲሠሩና ሲንቀሳቀሱ እንዳያልባቸው እንዲያናፍስላቸውና ቶሎ እንዳያልቅባቸው በማለት ነበር፡፡ ምሥጢሩ ግን የሌላውን ሰው እጅና እግር ደርቦ የሚያስገባ ያህል ሰፊ አድርገው መሥራታቸው አርሰን የምንመገበው አስተምረንና አማልደን የምናጸድቀው በተፈጥሮ ወንድማችን ለሆነ ሁሉ ነው እንጂ ለራሳችን ጥቅም ብቻ ስንል አይደለም ለማለት ነው። ሠላጤውንም እንደ ወታደር አድርገው መታየታቸው ስለ ሁላችሁ እንሥራ ብለን ለክህነት ራሳችንን ለየን አንጂ እንደ ወታደርም የጦር ሥራ ለመሥራት የምንችል ነን ለማለት ነው:: ስለዚህ ልብስ የሰው የሥራውና የተፈጥሮው ልዩነት መታወቂያ ነው እንጂ ነፋስና ብርድን መከላከያ ብቻ ወይም የፋሽን ገበያ ማሞቂያ አይደለም:: እንዲህ ከሆነ ክርስቲያኖች የልብሳቸውን አርአያ እንደፈለጉ ከመቀያየር ተቆጥበው በሥርዓትና በአግባቡ ማጌጥ አለባቸው።
ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ግንቦት ፲፪
ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
በዚህችም ዕለት ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ነው፡፡ በሸዋ ከፍለ አገር በቡልጋ አውራጃ ልዩ ስሟ ቅዱስ ጌዬ የተባለች አገር ነበረች ይህችም የእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የትውልድ አገሯ ናት። በዚህም አገር በወርቅና በብር በሐር እና በልዩ ልዩ ልብስ በወንድና በሴት አገልጋዮች በፈረስና በበቅሎ የከበረ አንድ ስሙ የታወቀ ሰው ነበር። የዚህ ሰው ስሙ ቅዱስ ደረሳኒ ሲሆን የሚስቱም ስም ቅድስት ዕሌኒ ይባላል ሁለቱም ባልና ሚስቱ እግዚአብሔር የሚፈሩ ደጋግ ሰዎች ስለነበሩ በጎ ሥራቸው በዓለም ሁሉ የታወቀ ነበር። እሊህም ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠችና የከበረችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ወልደው በደም ግባቷና በጠባይዋ እየተደሰቱ አሳደጓት ከዚያም የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ሥርዓቶችንም ሁሉ አስተማሯት። ባደገችና ለአቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ የንጉሥ ባለሟል የሆነ ትውልዱ፤ ነገዱ ከአባ ፃሠርጓ ወገን የሆነ ለኢየሱስ ሞዓ ልጅ ለሠምረ ጊዮርጊስ በሕግ አጋቧት። እሱም በዚህ ዓለም ገንዘብ በጣም የከበረ ከመሆኑም በላይ በይበልጥ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው ነበረ። ከደም ግባቷ የተነሣ ሙሽራይቱ ማለት እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን እጅግ አድርጎ ወደዳት። አሟቷ ኢየሱስ ሞዐም ይህች ብላቴና "በታላቅ ቁም ነገር የተመረጠች ነች" በማለት ትንቢት ይናገርላታል ስለዚህ እንደ እመቤቱ አድርጐ ያከብራት ነበር። ከዚህም በኋላም ለሕጋዊ ባሏ ለሠምረ ጊዮርጊስ ዓሥራ አንድ ልጆች ወለደችለት ከነዚህም መካከል ዘጠኙ ወንዶች ሁለቱ ሴቶች ነበሩ። ልጆችዋንም ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች በክብር በሥርዓት አሳደገቻቸው።
በዚያን ዘመን የእግዚአብሔር ባለሟል የሚሆን ዓፄ ገብረ መስቀል የሚባል የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበር። እርሱም ዝናዋን ሰምቶ ሥነ ምግባሯን ተመልክቶ ይልቁንም በሷ ላይ ያደረውን ኃይለ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ስለገለጸለት እጅግ አድርጐ ይወዳትና ያከብራት ነበር። ከዕለታት ባንድ ቀን በጸሎትሽ አስቢኝ በማለት በራሱ በንጉሡ ቤተ መንግሥት ከሚያገለግሉ አገልጋዮች ወይም ሠራተኞች መካከል እንዲያገለግሏት 174 አገልጋዮች ላካላት። ዳግመኛም ፈረስና በቅሎ ከነሥራታቸው እንደዚሁም ለነሥታት ሚስቶች የሚገባ ከሐርና ከወርቅ የተሠራ ልብስና የወርቅ ጫማ ላከላት። ነገር ግን እሷ ይህን ሁሉ ክብር አልፈለገችም ይልቁንም ለዓላማየ ዕንቅፋት ወይም ከንቱ ውዳሴ ይሆንብኛል በዚያውስ ወርቁ ጌጡ ልብሱ ተሸጦ ለነዳያን ይመጸወታል ለቤተ ክርስቲያን መባዕ ይሰጣል እኒህን አገልጋዮች ግን ምን አደርጋቸዋለሁ በማለት ወደ እግዚአብሔር እያመለከተች ቆየች።
ከአገልጋዮችዋ መካከል ምግባሯ የከፋ የምታናድዳትና የምታበሳጫት አገልጋይ ነበረች። ከዕለታት በአንድኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ በጣም ተበሳጨችና በዚያች አገልጋይ አፍ ውስጥ የእሳት ትንታግ ጨመረችባት። ያም እሳት ትንታግ በአገልጋይዋ ጉረሮ ድረስ ዘለቀና ገደላት። በዚህን ጊዜ ቤተሰቦችዋ መጥተው የአገልጋይቱን አስከሬን ወደሌላ ክፍል ወሰዱት። ብፅዕት ክርስቶስ ሠምራም ደንግጣ ካለችበት ቤት ውስጥ ወደ ሌላው ክፍል ገባችና ወደ ሰማይ አቅንታ "ወይኔ ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ የካህን ሚስት ስሆን ነፍስ ገዳይ ሆኛለሁና። ሰውስ ምን ይለኛል ለነፍሴስ ምን እመልስላታለሁ ከእግዲህ ከክርስቲያን ወገን ልቆጠር አይገባኝም በደሌንስ እንደምን አድርጌ ልሸሸሽጋት እችላለሁ" እያለች አለቀሰች።
ከዚህ በኋላ እንዲህ ስትል ለእግዚአብሔር ብፅዓት አደረገች "አቤቱ ይህችን በእኔ እጅ የሞተችውን አገልጋይ ነፍስዋን ከሥጋዋ አዋህደህ ብታሥነሣልኝ ልጆቼን ቤቴን ንብረቴን ትቼ ባለ ዘመኔ ሁሉ አንተን እከተላለሁ። አንተን ከመከተል ከቶ ወደኋላ አልልም። ለሰውነቴ ጌጥ ወይም ግርማ ሞገስ የሚሆናት ወይም የሚሞቃት ልብስ ከቶ አልለብስም ሥጋዬን የሚያረካ ምግብም አልመገብም። አቤቱ ጌታዬ ሆይ ጸሎቴን ስማኝ ልመናዬም በፊትህ ፈጥኖ ይድረስ አቤቱ ፊትህን ከኔ ከባሪያህ አትመልስ"። እንዲህ እንዲህ እያለች በልቅሶና በኀዘን ለብዙ ሰዓት ከጸለየች በኋላ ድካም ተሰማትና ዕረፍት አደረገች። ከዚህ በኋላ ቤተሰቦችዋ እስዋ ወዳለችበት ክፍል መጥተው "እመቤታችን ሆይ ሙታ የነበረችው አገልጋይሽ በእግዚአብሔር ኃይልና በአንቺ ጸሎት ተነሥታለችና ደስ ይበልሽ" አሏት። በዚህ ጊዜ ፈጥና ተነሥታ ደስ እያላት ሙታ የነበረችው አገልጋይ ካለችበት ቦታ ደረሰችና ሕይወት አገኘቻት ከዚያም ቃሏን ከፍ አድርጋ "ልመናዬን ቸል ያላለ ቸርነቱንም ከኔ ከባሪያው ያላራቀ ፈጣሪ ይክበር ይመስገን" ብላ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔር አመሰገነች።
ከዚህ በኋላ አስቀድሞ ከአፏ የወጣውን ከአንደበቷ የተነገረውን ቃል አስባ ልብሰ ምንኵስናዋን ማለት ቆቧን ቀሚሷን አጽፏን መታጠቂያዋን አዘጋጀች። ቤተሰቦቿና አገልጋዮቿም "እመቤታችን ሆይ ይህ የምታዘጋጂው የምናኔ ልብስ ለምንሽ ነው ወይስ ለማን ነው የምታዘጋጂው" አሏት። እርሷም " ሃይማኖት ያስተማሩኝ አባቴ ልብስ አልቆባቸዋል ሲሉ ሰምቼ ለሳቸው ነው የማዘጋጀው" አለቻቸው።
ከዚህም በኋላ ከዕለታት ባንደኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ አገልጋዮቿን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሄድ ዘንድ ተዘጋጁ አለቻቸውና እነሱም አሺ በጎ ብለው አጅበዋት ወደቤተ ክርስቲያን ሄዱ። ከዚያም እንደደረሱ "በሉ እንዲህ እኔ ከዚህ ጥቂት እቆያለሁና እናንተ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ ለኔ ይህች አንድዲት አገልጋይና ይህ ሕፃን ልጅ ብቻ ይበቁኛል አለቻቸው። በዚያኑ ጊዜ አገልጋዮቿ እጅ እየሱ ወይም እየተሰናበቱ ወደቤታቸው ተመለሱ። ከዚያም ከዳዊት መዝሙር "ልቤ ጽኑ ነው አቤቱ ልቤ ጽኑ ነው እግዚአብሔርን ፈጽሜ አመሰግነዋለሁ እግዚአብሔር የደህንነቴ መብራት ስለሆነ ምን ያስደነግጠኛል እግዚአብሔር የሕይወቴ መተማመኛ ነው ምንስ ያስፈራኛል የሚለውን እየጸለየች የሚያልፈን ዓለም በማያልፈው ዓለም ለመተካት ወይም ለመለወጥ አውጭኝ እግሬ ብላ ገሠገሠች። ያ በልስላሴና በእንክብካቤ የኖረ እግር ከመንገዱ ብዛት እንደዚሁም ከቅርቅፍቱና ከእንቅፋቱ የተነሣ ፈለግ ሲያወጣ ሥጋውን እየቆረጠች ስትጥለው ደሙ እንደጒርፍ ውሃ ይወርድ ነበር። ያች የተከተለቻት አገልጋይ ግን ከእመቤቷ እግር እየተቆረጠ የሚወድቀውን የአካል ቊራጭ እያነሳች በልብሷ ትቋጥረው ነበር። በዚህ ዓይነት ችግርና ፀሐይ ሐሩር የብዙ ጐዳና ጉዞ ተጉዛ ከአሰበችበት አገር ደረሰች። በደብረ ሊባኖስ አቅራቢያ ወይም አካባቢ ስትደርስ የራስ ፀጒራን ይዛው በነበረ ምላጭ ላጨች ልብሷንም አውልቃ ለነዳያን አከፋፈለች የያዘችውንም ገንዘብ በመንገድ ላይ ላገኘችው ሁሉ መፅውታ ጨረሰች። ከዚያም አስቀድማ ያዘጋጀችውን ልብስ ምንኵስና ማለት ቀሚስዋን አጥልቃ አጽፋን ተጐናጽፋ ቆቧን ደፍታ ደብረ ሊባኖስ ከሴቶች ገዳም ደረሰች። የገዳሙ መነኰሳትም በታላቅ ክብር ተቀብለው ወደበዓታቸው አስገቧት ...
እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ለሳጥናኤል ምሕረት እንደለመነች፦ ከዕለታት በአንድኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ጓንጉት በምትባል ደሴት ውስጥ ዓርብ ዕለት ከቀኑ በስድስት ሰዓት ላይ ስለሰው ልጆች ስትጸልይ ሣለ። ዓለሙ ሁሉ ከንቱ እንደሆነና የሰውም ልጅ ሕይወት እንደጥላ ኃላፊ ጠፊ መሆኑን ፈጽማ ተመለከተች። ነቢዩ ዳዊት "ሰው ከንቱ ነገርን ይመስላል ዘመኑ ወይም ሕይወቱ እንደጥላ ያልፋል" ሲል ተናግሯልና። ዳግመኛም "ሰው ክብር እንኳ ቢሆን ሊኖር አይችልም እንደሚጠፋ ወይም ማስተዋል እንደሌለው እንስሶች መሰለ...
የኢትዮጵያ ብርሃኗ ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
❤ ኦ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ❤
ኦ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ አስተብቁዕ ለነ ለዉሉድከ ደቂቀ አዳም/፪/
ሰሚዐነ ተግሣጸከ ከመንድኃን እሳቱ ዘኢይጠፍእ ወዕፄሁ ዘኢይነውም/፪/
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የአዳም ልጆችን እኛን አማልደን/፪/
ተግሣጽህን ሰምተን እንድን ዘንድ ከማይጠፋው እሳት ትሉም ከማያንቀላፋ/፪/
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የከበረ ዮሐንስም ንጉሥ ሆይ እንዲህ አትበል እንዲህ አንተ እንደምትለው አይደለም የከበረች ድንግል እመቤታችንስ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሆድዋ ውስጥ በነበረ ጊዜ የእርሱ ኅብረ መልክ በሚለዋወጥ ጊዜ ከእርሱ ጋር መልኳ ይለወዋወጥ ነበር። በንጹሕ ብርሌ ውስጥ ውኃ በጨመሩ ጊዜ ውኃ መስሎ እንደሚታይ ወይን ጠጅም ቢጨምሩ ያንኑ መስሎ እንደሚታይ ወይም ከውስጡ በተጨመረው ቀይም ቢሆን ቀልቶ እንደሚታይ ቅጠልያም ቢገባበት ቅጠልያ መስሎ እንደሚታይ።
ድንግልም በሆድዋ ውስጥ የልጅዋ መልክ በሚለዋወጥ ጊዜ ከእርሱ ጋራ መልኳ ይለዋወጥ ነበር። እንደ ሮማን አበባ የምትቀላበት ጊዜ አለ እንደናርዶስም የምታብለጨልጭበት ጊዜ አለ የለመለመ ቅጠል የምትመስልበትም ጊዜ አለ ከወለደች በኋላ ግን አልተለወጠችምና ዮሴፍ በአንድ በቀድሞው ኅብረ መልኳ ተወስናለት መልኳን ተረዳ ማለት ነው አለው። በዚያን ጊዜ በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ ከወርቅ የተሠራ የእመቤታችን አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ሥዕል ነበረችና አፈ ወርቅ ዮሐንስ ልሳነ ወርቅ ዮሐንስ አፈ በረከት ዮሐንስ መልካም ተናገርክ የሚል ቃል ከእርሷ ወጣ።
ንጉሡና ከእርሱ ጋር ያሉት በሰሙ ጊዜ እጅግ አደነቁ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት በዚያን ጊዜ ንጉሥ አዝዞ ወርቅ ሠሪ አስመጥቶ ለከበረ ዮሐንስ የወርቅ ልሳን አሠርቶ ለሚያየው ሁሉ መታሰቢያ ምልክት ሊሆን አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ሥዕል ዘንድ ሰቀለው። ቅዱስ ዮሐንስንም ከዚያች ቀን ወዲህ ልሳነ ወርቅ ብሎ ጠራው አፈ ወርቅም ተብሎ እስከዛሬ ተጠራ።
እግዚአብሔር አምላካችን ከሊቁ በረከት ያሳትፈን! አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ዋይ ዜማ ዘሰማዕኩ በሰማይ እመላዕክት ቅዱሳን እንዘይብሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር መልዓ ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ግንቦት ፲፩
ቅዱስ ያሬድ ካህን ወማኅሌታይ
ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳላቸው የሆነ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ያሬድ የተሰወረበት ነው። ይህም ቅዱስ ከአባ ጌዴዎን ዘመዶች ወገን ነው እርሱም በኢትዮጵያ አገር ከታነፁ አብያተ ክርስቲያናት ለምትቀድም ከአክሱም ካህናት ውስጥ ነው እርሷም አስቀድሞ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በውስጥዋ የተሰበከና አምላክን በወለደች በእመቤታችን በከበረች ድንግል ማርያም ስም የከበረች ናት።
ይህም አባ ጌዴዎን ትምህርትን ሊአስተምረው በጀመረ ጊዜ መቀበልም ማጥናትም እስከ ብዙ ዘመን ተሳነው። በአንዲት ዕለትም መምህሩ በእርሱ ላይ ተበሳጭቶ መትቶ አሳመመው። ያሬድም ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ ከኀዘኑም ብዛት የተነሣ ከዛፍ ሥር ተጠለለ። ወደ ዛፉ ላይም ትል ሲወጣ አየ ትሉም ከዛፉ እኩሌታ ደርሶ ይወድቅ ነበረ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ከአደረገ በኋላ በጭንቅ ከዛፉ ላይ ወጣ።
ቅዱስ ያሬድም የትሉን ትጋት በአየ ጊዜ ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ተመልሶ አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝና እንደ ወደድክ አድርገኝ አለው መምህሩም ተቀበለው።
ከዚህ በኋላ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ሆኖለት በአጭር ጊዜ የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን ተምሮ ፈጸመ ዲቁናም ተሾመ።
በዚያም ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ። እግዚአብሔርም መታሰቢያ ሊያቆምለት በወደደ ጊዜ ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን ላከለት እነርሱም በሰው አንደበት ተናግረውት ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ከእሳቸው ጋራ አወጡት በዚያም ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የሚያመሰግኑበትን ማኅሌታቸውን ተማረ።
ወደ አነዋወሩ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ በአክሱም ዳር ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን በሦስት ሰዓት ገባ በታላቅም ቃል ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ የጽዮንም ደገኛዋ ሰማይን ፈጠረ። ዳግመኛም እንዴት እንደሚሠራት የድንኳንን አሠራር ለሙሴ አሳየው አስተማረው አለ።
ይቺንም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራት። የቃሉንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ንጉሡም ንግሥቲቱም ጳጳሱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ የመንግሥት ታላቆችና ሕዝቡ ሁሉ ወደርሱ ሮጡ ሲሰሙትም ዋሉ።
ከዚያም በኋላ ከዓመት እስከ ዓመት በየክፈለ ዘመኑ በክረምትና በበጋ በመጸውና በጸደይ በአጽዋማትና በበዓላት በሰንበታትም እንዲሁም በመላእክት በዓል በነቢያትና በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልም በዓል የሚሆን አድርጎ በሦስቱ ዜማው ሠራ ይኸውም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ነው።
የሰው ንግግር የአዕዋፍ የእንስሳትና የአራዊት ጩኸት ከዚህ ከሦስቱ ዜማው አይወጣም።
በአንዲት ዕለትም ቅዱስ ያሬድ ከንጉሥ ገብረ መስቀል እግር በታች ቁሞ ሲዘምር ንጉሡም የያሬድን ድምፅ እያዳመጠ ልቡ ተመሥጦ የብረት ዘንጉን በያሬድ እግር ላይ ተከለው ከእርሱም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ያሬድም ማኅሌቱን እስከ ሚፈጽም አልተሰማውም።
ንጉሡም አይቶ ደነገጠ በትሩንም ከእግሩ ላይ ነቀለ ስለ ፈሰሰው የደምህ ዋጋ የፈለግኸውን ለምነኝ ብሎ ለያሬድ ተናገረው ያሬድም ላትከለክለኝ ማልልኝ አለው። ንጉሥም በማለለት ጊዜ ወደገዳም ሔጄ እመነኲስ ዘንድ አሰናብተኝ አለው ንጉሡም ሰምቶ ከመኳንንቱ ጋራ እጅግ አዘነ ተከዘም እንዳይከለክለውም መሐላውን ፈራ እያዘነም አሰናበተው።
ከዚህ በኋላም ቅዱስ ያሬድ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ፈጽሞ የከበረሽና የተመሰገንሽ ከፍ ከፍም ያልሽ የብርሃን መውጫ የሕይወት ማዕረግ የሆንሽ የሚለውን ምስጋና እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ከፍ አለ።
ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሒዶ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያ ፈጸመ። እግዚአብሔር ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጥቶታል።
የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች
፩. ድጓ
፪. ጾመ ድጓ
፫. ዝማሬ
፬. መዋሥዕት
፭. ምዕራፍ ናቸው።
የዜማ ዓይነቶች
፩. ግዕዝ
፪. ዕዝል
፫. አራራይ ናቸው።
የቅዱስ ያሬድ ረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
እንደዚሁም ሁሉ ልብስ ለሰውነት (ለሥጋ) ተነግሯል። በዚህ ትርጓሜ መሠረት ወንጌላዊው «ለነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት ስለ ሰውነታችሁም ደግሞ በምትለብሱት አትጨነቁ» ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው።ማቴ6፥25 እንኳን ትርፍ ስለ ሆነ ስለ «ማጌጥ» ይቅርና ዕርቃን የሚያስቀር የልብስ አጦት ችግር ቢፈጠር እንኳን «መጨነቅ» እንደማያስፈልግ ይገልጻል፡፡
ስለ አለባበስ ትኩረት ሰጥቶ ማሰብ ባያስነቅፍም መጨነቅ ግን የሚገባ ነገር አይደለም።«መጨነቅ» ከማሰብ ከፍ ያለ መጠን አልባ ነገር ነው።ጌታችን በወንጌል «ስለምትልበሱት አትጨነቁ» ብሏል። ብዙዎች የሚለብሱትን በማጣት ሳይሆን መምረጥ አቅቷቸው ይጨነቃሉ፡፡ ይህ እጅግ የሚያሳዝን ነው።እንኳን «ያስኬዳል አያስኬድም» እያልን ቀርቶ የምንለብሰው ባይኖረን እንኳን አዳምንና ሔዋንን ቁርበት ያለበሰ አምላክ ያለብሰኛል ማለት ይገባናል፡፡ዘፍ 3:2
ደግሞስ እስራኤላዊያን በምድረ በዳ ለአርባ ዓመታት ሲንከራተቱ «ጫማቸው ሳይፈታ፣ በትራቸው ሳይወድቅ፣ ልብሳቸው ላያልቅ» ያኖራቸው እግዚአብሔር አይደለምን? ስለዚህ እስራኤል ዘነፍስ የተባልኩኝ እኔንም አይተወኝም ማለት እንዴት ያቅተኛል?
ይብላኝ እንጂ ለእኔ እምነት ለጎደለኝ «የሜዳ አበቦችን የሚያለብሳቸው» እርሱ እኔን ማልበስ አይሳነውም።ማቴ 6፥28 በእምነት ጠንክሬ እንደ ቅዱስ ዳዊት ‹እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝም የለም» እያልኩኝ የምዘምረው መቼ ይሆን? መዝ 22፣1 እንደ ቅዱስ ጳውሎስስ «ምግብና ልብስ ከኖረን ግን እርሱ ይበቃናል» በማለት ለመመሰከር እበቃ ይሆን? 1ጢሞ6፥8
➺ የሰው ነፍስ ስለ አለባበስ በቂ ግንዛቤ አላት!
ልብስ የሚያስፈልግው ለነፍስ እስከ ሆነ ድረስ ነፍስ ስለ ልብስ ማንም ሳያስተምራት በደንብ ታውቃለች፡፡ አዳምና ሔዋን ጸጋቸው በተገፈፈ ጊዜ «የበለስ ቅጠሎችን ቆርጠው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ» ይህን ማን አስተምሯቸው ነው? ነፍስ መልበስ እንደሚገባ ስለምታውቅ አይደለምን? ዘፍ3:7 ከዚህ አንቀጽ ሳንዘል ነፍስ ስለ ልብስ ያላትን ግንዛቤ በሚገባ መመርመር ይኖርብናል። ምክንያቱም ነፍስ ልብስ አስፈላጊ መሆኑን ብቻ ሳይሆን መልበስ ያለብንን የልብስ ዓይነትና በዋናነት መሸፈን የሚገባውን የአካል ክፍል ለይታ ማወቋን ይጠቁመናልና፡፡
በዘመነ አዳም ሌሎች ፍጥረታት፡ ለምሳሌ፡ እንስሳት ልብስ አልለበሱም ነበር። አዳምና ሔዋን ግን ለራሳቸው «አገለደሙ» እንጂ እነርሱን አይተው እኛም መልበስ አያስፈልገንም አላሉም፡፡ ከሁሉ- የሚደንቀው ደግሞ ብዙ ፅፀዋት እያሉ ከእነዚያ መካከል በለስን መምረጣቸው ሳያንስ ያን ሰፍተው ማገልደማቸው ነው:: የለበሱት ብርድን ለመከላከል ብቻ ቢሆን ኖሮ ከማገልደም ይልቅ ሌላ አካላቸውንም ጨምረው ባለበሱ ነበር።ነገር ግን ነፍስ ቅድሚያ መልበስ ያለበትንም አካል ታውቃለችና «አገለደሙ» እንጂ ሙሉ ለሙሉ አልለበሱም። ልብሳቸው የበለስ ቅጠል ሆኖ በመቸገራቸው እንጂ ከወሊድ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ሌሎች ሕዋሳቶቻቸውንም ጨምረው ይሽፍኑ እንደ ነበር ጥርጥር የለውም።ነገር ግን ከነበረባቸው የልብስ ችግርና ማንም ሳይመክራቸው እንዲህ ማድረጋቸውም ለኛ ብዙ ትምህርት ያስጨብጠናል። አካላቸውን የሸፈኑት በለስ እስከ መስፋት ተቸግረው ነውና፡፡ እኅቴ ሆይ እስኪ ልጠይቅሽ! አንቺ ይህን ያህል ተቸግረሽ ሰውነትሽን ለመሸፈን ትጥሪያለሽ? ወይስ የሚያስጨንቅሽ ሕዋሳቶችሽን በዘዴ አጋልጦ ሌሎች እንዲያዩሽ ለማድረግ አለመቻልሽ ነው?
አዳምና ሔዋን ማገልደማቸው ብቻ በቂ አለመሆኑን ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የቁርበት ልብስ እንዲለብሱ በማድረጉ አስረድቶናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ «አለበሳቸው» ይላል እንጂ ግልድም ሰጣቸው አይልም፡፡ እኛንም ግልድማችንን አስወልቆ እንደ እነርሱ ያልብሰን፡፡ አሜን! ዘፍ3፡21
ከአዳምና ከሔዋን ታሪክ ሌላም ቁም ነገር እንማራለን፡፡ ሰው ምን ዓይነት ልብስ መልበስ እንዳለበት ሌላውን ሰው መጠየቅ አይኖርበትም፡፡ ከዚህ ይልቅ ራሱን ይመርምር፣ ነፍሱንም ይጠይቅ፡፡ ሕሊናውን የሚሰማ ከሆነ በቂ መልስ ያገኛል።ብዙ እኅቶች ግን ስሜታቸውን እንጂ የነፍሳቸውን ፈቃድ አይከተሉም፡፡ ሆኖም ነፍስ መሆን ያለበትን መጠቆሟን፣ መንፈስ ቅዱስም «በማይገባ ልብስ» ስንሽለም መውቀሱን ስለማይተው ሴቶቻችን የለበሱት ተገቢ ልብስ አለመሆኑ ይታወቅ ዘንድ ሲያፍሩ፣ አጠረ ብለው የለበሱትን ሲጎትቱና ወይም በልዩ ልዩ ዘዴ የተራቆተውን የሰውነት ክፍል ለመሸፈን ሲሞክሩ ይታያሉ። ከዚህ ሁሉ ግን ይበልጥ የሚጠቅመው የነፍስን ፈቃድ አዳምጦ ተገቢ ልብስ መልበስ ነበር።
ድንግል ሴት ትፈልጋለህ ?
ምንም እንኳን ሰዎች ሁሉም ባይሆኑም ብዙ ስዎች ግን የሚያገቧት ሴት ድንግል እንድትሆን ይፈልጋሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ መፈለግ ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያ መስፈርታቸው ያደርጉታል፡፡ ይህ እጅግ ደስ የሚያሰኝ አቋም ነው፡፡ ምክንያቱም የሁሉም ሰው አቋም እንዲህ ቢሆን ኖሮ ሴቶች ሁሉ በንጽሕና መኖርን ለወደፊት ትዳራቸው መቃናት ሲሉ ስለሚለማመዱት ነው::
ታዲያ ሚስቱ ድንግላዊ ሆና ቢያገኛት የሚመኝ ሰው እርሱም ድንግልናውን የጠበቀ ሆኖ መገኘት እንዳለበት ለአፍታም እንኳ ቢሆን መዘንጋት የለበትም፡፡ ስለዚህ ይህን የሚመኝ ራሱን ይጠብቅ።ካላገባሃት ሴት ጋር አንሶላ መጋፈፍን አትሻ።ልታገባ አንድ ቀን የቀረህ ቢሆን እንኳን ሳታገባት ይህን መሞክር የለብህም:: በሰዓታትና በቅጽበት ውስጥ በእቅፍህ ያለች እጮኛህ ያንተ ሚስት መሆን የማትችልበት ሁኔታ ይፈጠር እንደ ሆነ አታውቅምና፡፡ አንተ ራስህ ከነድንግልናህ የምትፈለግበት ጋብቻ ከፊትህ ይጠብቅሃል፡፡ እርሷንም በምትሄድበት ቦታ ባሏ ከነ ሙሉ ክብሯ ይሻታል፡፡ ታዲያ ካላገባሃት ሴት ጋር ለምን ትተኛለህ?
ካላገቧት ሴት ጋር ምንጣፍ መጋራት በሰው ቤት መግባትና ከባለ ትዳር ሴት ጋር እንደ ማመንዘር ነው።ያላገባች መሆኗ ልዩነቱ ባሏን መቅደምህ ብቻ ነው።አንተ በሰው ተዳር እንዲህ የምትገባ ከሆነ ሌሎች ደግሞ አንተ የምታገባትን ሴት ከክብር አሳንሰው ንጽሕናዋን ገፈው ያቆዩልሃል፡፡ አንተ ድንግል ሳትሆንና የብዙዎችን ሕግ አፍርሰህ ድንግል ሴት መፈለግህ አያስገርምም?
ሰው የራሱን ድንግልና ቢጠብቅ እግዚአብሔር ደግሞ በድንግልና የተጠበቀች ሚስት እንደፍላጎቱ ሊሰጠው ተስፋ ሰጥቷል፡፡ ሰው የራሱን «ዕቃ» ቢጠብቅ ለእርሱ የሚገባውን «ዕቃ≫ እግዚአብሔር በክብር ይጠብቅለታል:: በመጽሐፍ ቅዱስ «ዕቃ የሚባለው አባለ ዘርዕ (ኀፍረተ አካል) ነው ቅዱስ ዳዊት «በእውነት ከወጣን ጀምረን እኛ ሰውነታችንን ከሴቶች ሦስት ቀን ጠብቀናል፣ የብላቴኖችም ዕቃ የተቀደሰች ናት፣ ስለዚህ ዛሬ ዕቃቸው የተቀደሰች በመሆኗ እንጀራው እንደሚበላ እንጀራ ይሆናል።» 1ሳሙ21÷5 በማለት የተናገረው ቃል ኀፍረተ አካል «ዕቃ» እንደሚባል በሚገባ ያስረዳል::
የራሱን ንጽሕና የጠበቀ ሰው ለእርሱ የምትሆነው ሚስቱ ከነቅድስናዋ፣ ከነንጽሕናዋና ከነሙሉ ክብሯ (ድንግልናዋ) እንደሚያገኛት ማወቅ አለበት ሲል ሐዋርያው «ከእናንተ እንያንዳንዱ የራሱን ዕቃ (ሚስቱ የምትሆነውን) በቅድስናና በክብር (ከነድንግልናዋ) ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ» በማለት ይናገራል:: «ዕቃ» የሚለው ኀፍረተ አካልን መሆኑ ከላይ በማያሻማ መልኩ ተገልጿል፡፡ ስለዚህ ድንግልን ማግባት የሚፈልግ ሰው የራሱን ክብር መጠበቅ ይኖርበታል:: 1ኛተሰ 4፥5
በቀጣይ ምዕራፍ ዘጠኝ ክፍል አንድ :
👉 ትውዝፍት(የምንዝር ጌጥ)
👉 የሰው ነፍስ ስለ አለባበስ በቂ ግንዛቤ አላት!
👉 አለባበስን በተመለከተ ስለ ወንዶችስ ምን ሊባል ይችላል ?
በሚል ይቀጥላል....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
አንቺ ወጣት ሴት ስለ ድንግልናሽ ምን ታስቢያለሽ? እግዚአብሔር ከነድንግልናሽ እንዲጠብቅሽ ጸልየሽ ታውቂያለሽን? ወይስ «እኔን ወንዶች የማይቀርቡኝ ምን አድርገህ ፈጥረኸኝ ነው?» ብለሽ በእግዚአብሔር ላይ ታለቅሽበታለሽ? በድንግልና ሆኖ እግዚአብሔርን ማገልገልስ ታስቦሽ ያውቃል? ቤተሰቦችሽ አንቺን ከአደጋ ለመጠበቅ ሲሉ የሚያደርጉትን ቁጥጥር በምን መልኩ ታይዋለሽ? ይህን አትልበሺ፣ አምሽተሽ አትግቢ የሚል ቁጥጥር እኮ ጭቆና አይደለም:: ነው እንዴ?
ድንግልናን መጠበቅ ብርቱ ትግል ይጠይቃል። ያ ባይሆን ኖሮ «ድካማቸውን ይቀበል ዘንድ ስለ ደናግል እንማልዳለን›› ተብሎ ስለ ደናግል ድካም ባልተጻፈ ነበር፡፡ ታዲያ ይህን ድካም እግዚአብሔር ሳይረዳሽ ትችይዋለሽን? የእግዚአብሔርን እርዳታ ለማግኘት ደግሞ መጸለይ ያስፈልጋል ያውም ከዕንባ ጋር፡፡ (ሥርዓተ ቅዳሴ በእንተ ቅድሳት)
ቤተ ክርስቲያን አንቺን _ ጨምሮ ስለ ደናግል ሁሉ ትጸልያለች፡፡ ዘወትር በቅዳሴ «እግዚአብሔር የድንግልናቸውን ዋጋ (አክሊል) ይሰጣቸው ዘንድ ለእግዚአብሔር ወንዶችም ሴቶችም ልጆች ይሆኑ ዘንድ ድካማቸውንም ይቀበል ዘንድ ስለ ደናግል እንማልዳለን::» ትላለች። ቤተ ክርስቲያን ስለ አንቺ እየጸለየች" የጉዳዩ ባለቤት አንቺ ግን ባትጸልዪ አሜን ለማለት እንኳን እንደኮራሽ ይቆጠርብሻል፡፡
ፈጣሪ አንድ ቀን ድንግልናችንን በተመለከተ እንድንቆጭ ማድረጉ አይቀርም። እንዲያገባን የምንቋምጠው ወንድ ካለን ሌላ ነገር ሁሉ ይልቅ ድንግልና ቢኖረን የሚወድ ይሆንና አንድ ቀን እናዝን ይሆናል፡፡ ወይም ሌላ የምንሻቸው ነገሮች ድንግልናችንን ባለመጠበቃችን የተነሣ እናጣቸውና እንቆጫለን። ለምሳሌ:- በዚህ ምክንያት ለሥርዓተ ተክሊል ወንዶች ደግሞ ለድቁናና ለሌላም መንፈሳዊ ማዕርግ የማንበቃ እንሆንና የምናዝንበት ጊዜ ይኖራል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው ድንግልና ያለውን የከበረ ዋጋ እንድናውቅ እግዚአብሔር ስለሚፈልግ ነው:: ክብርን ባለመጠበቅ ምክንያት የሚፈልጉትን ማጣት እጅግ ያሳዝናል፡፡ አያሳዝንም እንዴ?
እርግጥ ነው ድንግልናቸውን ያቃለሉ ሰዎች ስለ ናቁት ድንግልናቸው ምርር ብለው በቁጭት የሚያለቅሱበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ይህም ስለ ክብረ ድንግልና ጥልቅ መንፈሳዊ ትምህርት በሚሰሙበት ጊዜ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ከዚያ በፊት ደናግል ሆነው ሳለ እንደ ዮፍታሔ ልጅ ስለ ድንግልናቸው የሚያለቅሱ ሰዎች እንዴት የተመሰገኑ ናቸው? እንደ ዮፍታሔ ልጅ ሁሉ ከማኅበረ ደናግል ተለይታ ወደ ዝሙት ዓለም የገባች አንዲት ሴት ተጸጽታ ስታለቅስ ጓደኞቿም አብረው ያለቅሱላት ነበር። በኋላም የእርሷና የጓደኞቿ ዕንባ ከበደሏ ጋር ቢመዘን ኀዘኗ በልጦ ስለ ተገኘ በድጋሚ ከመኀበረ ደናግል ገብታ መቆጠሯን ተአምረ ማርያም ይናገራል፡፡ ይህም ስለ ድንግልና ማልቀስ እንደሚገባ ያሳያል:: ደናግላን ክብራቸውን ለማቆየት እያለቀሱ ከዕንባ ጋር መኖር ከተገባቸው ክብራቸውን ያልጠበቁ ሰዎች እንዴት ይልቅ ማዘንና ማልቀስ ይገባቸው ይሆን?
ድንግልናን ጠብቆ ለመቆየት ራስን መግዛት ያስፈልጋል፡፡ ራስን ለመግዛት ደግሞ ጾም ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል:: ስለቢህ ጾምን ጠልቶ ድንግልናን ጠብቆ ማቆየት አዳጋች ነው። በድንግልናዊ አኗኗራቸው የምናወድሳቸው ቅዱሳን በሙሉ የጾምና የትሕርምት ሰዎች ነበሩ:: ለምሳሌ:- ነቢዩ ኤልያስን ብንወስድ ምንም እሀል ሳይቀምስ አስከ አርባ ቀን ድረስ ለመቆየት የቻለ የጾም ሰው እንደ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይተርክልናል፡፡ 1ነገ19፥8
ማር ይስሐቅ ‹‹እስመ ጾም ወስኖሙ ለድንግልና ወለቅድስና» ማለትም «የድንግልናና የቅድስና ውበታቸው ጾም ነውና» በማለት ተናግሯል፡፡ ይህም ጾምና ድንግልና ያላቸውን ጥብቅ ዝምድና ያስረዳል። ቤተ ክርስቲያን «ድካማቸውን ይቀበል ዘንድ» እያለች ስለ ደናግል የምትጸልየው ደናግላን ድንግልናቸውን ጠብቆ ለማቆየት በብዙ ጾም፣ ጸሎትና ስግደት ስለሚደክሙ አይደለምን? ስለዚህ በድንግልና ለመቆየት የሚፈልግ ሰው ጾምን መውደድ አለበት፡፡
እያንዳንዱ ሰው የገዛ ሕይወቱን ቢመረምር ከላይ የተጠቀሰውን የእግዚአብሐር ጠባቂነት የሚያረጋግጥ ገጠመኝ ይኖረዋል፡፡ በዝሙት ለመውደቅ ባለው ኃይል ተጠቅሞ ሲጣጣር፣ ከሰው ሲደበቅ፣ ሥውር ቦታ ሲሻ፣ ምቹ ጊዜ ሲጠባበቅ ባልጠበቀው ሁኔታ እግዚአብሔር ዕቅዱን ያላፈረሰበት ድንግል ነኝ ባይ ከቶ አይገኝም፡፡ እንደ ሰውዬው ፈቃደኝነት፣ የልቡና ምኞትና ለዝሙት መዘጋጀት ቢሆን ኖሮ ድንግልናውን ከጊዜያት በፊት ባፈረሰው ነበር። እንደዚህ ከሆነ እግዚአብሔር ጠብቆ ባቆየው ድንግልና መመካት ይገባልን? በጭራሽ ይልቁኑም «ጥበቃውን ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን» እያሉ ፈጣሪን ማመስገን ለሁሉም የሚገባ ነው።
ከተፈጥሮተ ሥጋ ተፈጥሮተ ነፍስ እንደሚበልጥ ከድንጋሌ ሥጋም ድንጋሌ ነፍስ ይበልጣል። ታዲያ በሥጋ ድንግል መሆናችን ትዕቢትና ትምክህት ፈጥሮ የነፍስ ድንግልና እንዳይኖረን የሚያደርግ ከሆነ እግዚአብሔር ትሑት ሆነን የነፍስ ድንግልናችን እንዲጠበቅልን ለማድረግ የሥጋ ድንግልናችንን በማይረባ ምክንያት እንዲጠፋ ጥበቃውን ከእኛ የሚያርቅበት ጊዜ አለ። እግዚአብሔር «ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣልና» ያዕ 4÷6
የሐሳዌ መሢሕ (የሐሰተኛው ክርስቶስ) እናት ከነገደ ዳን የተወለደች ናት፡፡ የሐሰት ነቢያት «በድንግልና ፀንሰሽ በድንግልና ትወልጃለሽ› እያሉ ትንቢት ይናገሩላታል፡፡ ለጊዜው ድንጋሌ ሥጋ ነበራትና ትዕቢት ያድርባታል:: ከዚያ በኋላም ከመቃብረ አረሚ (የአረማዊያን መቃብር) ቆማ ስትጸልይ ከነገደ ዔሳው የተወለደ አንድ ዓይና ጎልማሳ ከወደ ምሥራቅ ይመጣና ከክብር ያሳንሳታል፡፡ በዚህ ጊዜ ፀንሳ ልጅ ትወልዳለች፡፡ አንድ ጊዜ መንፈሰ ትዕቢት አድሮባታልና በድንግልና ፀንሼ በድንግልና ወለድሁት ትላለች፡፡ ልጇም ተወልዶ ሲያድግ አምልክ ነኝ ፈጣሪ ነኝ ማለት ይጀምራል፡፡ (ራእ13÷1 ትርጓሜ)
ከላይ የተጠቀሰችው የሐሳዌ መሢሕ እናት ገና ለወደፊት የምትመጣ ናት፡፡ ሆኖም ግን ትዕቢቷና ክፉ ግብሯ አስቀድሞ ታውቆ ተገልጧል።ትዕቢቷና በድንግልናዋ መመካቷ ለመደፈር አበቃት።ሰው ሲመካ ረድኤተ እግዚአብሔር ይለየዋል። በዚህ ጊዜ ከላይ እንደ ተጠቀሰችው ሴት ለብዙ ክፉ ነገሮች ይጋለጣል፡፡ አንችም እኅቴ በድንግልናሽ ብትመኪ ዕጣሽ ከዚህ የተለየ አይሆንም:: በድንግልናዋ የምትመካና ድንግል ሳትሆን «ድንግል ነኝ» እያለች የምትዋሽ ሴት ሁሉ በግብርዋ የሐሳዌ መሢሕ እናትን መምሰሏ ጥርጥር የለውም፡፡
እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን እጅግ የሚያስደንቅ ትሕትናን ተጐናጽፋ እናያታለን፡፡ ትንቢተ ኢሳይያስን በምታነብበት ጊዜ «እነሆ ድንግል ትፀንሳለች» ከሚለውን አንቀጽ ስትደርስ «አምላክን ለመውለድ ለታደለች ለዚያች ሴት ከዘመንዋ በደረስኩና ወጥቼ ወርጄ ባገለገልኳት ትል ነበር እንጂ እኔ ብሆን ወይም እኔ ነኝ›› አላለችም:: በዚህ ሐሳቧና ንግግሯ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴው «ደብር ነባቢት በትሕትና፣ በትሕትና የምትናገር ተራራ» በማለት አወድሷታል:: (ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘረቡዕ)
አምሳያ ከሌለው ድንግልናና ንጽሕናዋ ጋር ይህን የመሰለ ትሕትና ይዛ በመገኘቷ «ወደ ትሑት፡ በቃሌም ወደ ሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ፡፡» ኢሳ66÷2 በማለት የተናገረ እግዚአብሔር በድንግል ማርያም ማኅፀን አደረ፡፡ ድንግል ማርያም ከትሕትናዋ ብዛት የሁሉን ፈጣሪ ከፀነሰች በኋላ እንኳን ስትጸልይ «የባሪያውን ትሕትና ተመልከቷልና› አለች እንጂ, «የእናቱን ትሕትና» አላለችም:: መመካት ቢያስፈልግ ከድንግል ማርያም በቀር የሚያስመካ ድንግልና ያለው የሰው ዘር አልነበረም፡፡ እርሷ ካልተመካች ሊመካ የሚችል ማን ይኖራል? ሉቃ1÷ 48
በሥጋ ንጽሕናና በድንግልና መመካትና በሌሎች መፍረድ አይገባም። ይህ ትዕቢት ነውና፡፡ ትላንት በትዕቢታቸው ምክንያት ብዙዎችን ያዋረደና ያሳፈረ እግዚአብሔር ዛሬም በድንግልናቸው የሚመኩትን ሰዎች ብቃታቸው ከራሳቸው እንዳልሆነ ያውቁ ዘንድ በሚያሳፍር ሁኔታ ሊጥላቸው ይቻለዋል፡፡ በድንጋሌ ሥጋ ከሚመካ ትዕቢተኛ ድንጋሌ ሥጋ የሌለው ትሑት ሰው በእጅጉ ይሻላልና መመካት አያስፈልግም::
በቀጣይ ምዕራፍ ስምንት ክፍል ሰባት :
👉 ስለ ድንግልና ማልቀስና መጾም ይገባል!
👉 ድንግልናን ማቃለል ያስቀስፋል!
👉ድንግል ሴት ትፈልጋለህ? በሚል ይቀጥላል....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
ምዕራፍ ስምንት ክፍል ስድስት
.................................................
ድንግልና ያስመካል?
ድንግልናን መጠበቅ መልካም ነገር ቢሆንም የሚያመጻድቅና ብዙ የሚያስመካ ግን መሆን የለበትም:: «ድንግል ነኝ እኮ!» ብሎ መመጻደቅ የሚያስከትለው ወቀሳና መዘዝ ድንግልናን ከማጣት በላይ ነው። አንድ ሰው በድንግልናው የሚመጻደቀው መንፈሳዊነት ሲጐድለውና ዕውቀቱም ያነሰ ሲሆን ነው፡፡
ነቢዩ ኤልያስ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ድንግላዊ ኑሮ ነበረው፡፡ በተጨማሪም ለእግዚአብሔር ቀናዒና ንጹሕ የሆነ አምልኮት የነበረው ታላቅ ነቢይ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ መልኩ የሚኖረው እሱ ብቻ ይመስለው ነበር፡፡ ስለዚህ አንድ ቀን ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር «እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ» ሲል እናነባለን፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር «ከእስራኤል ጉልበታቸውን ለበኣል (ለጣዖት) ያላንበረከኩትን ሁሉ፣ በአፋቸውም ያልሳሙትን ሁሉ ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀራለሁ።» በማለት መልሶለታል፡፡ 1ነገ19፥14(18)
ዛሬም ቢሆን ደናግላን የሉም ማለት አይቻልም።ጉልበታቸውን ለዝሙት ያላንበረከኩ የልጅ ፍቅር፣ የሴት ከንፈር ያልማረካቸው ወንዶችና የወንድ ፍቅር ያላገበራቸው ብዙ ሴቶች አሉ፡፡ በንጽሕና ኖረው ለምናኔ፣ ለምንኩስና የሚበቁ «ሰባት ሺህ» የመንግሥተ ሰማያት ዜጐች ለእግዚአብሔር አሉት፡፡«ሰባት» ቁጥር በዕብራውያን ፍጹም ቁጥር ነውና፤ «ሰባት ሺህ ዜጎች ለእግዚአብሔር» አሉት ማለት ፍጹም ብዙ ቁጥር ያላቸው ወዳጆች አሉት ማለት ነው፡፡