ethiopian_orthodox | Unsorted

Telegram-канал ethiopian_orthodox - የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

30344

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Subscribe to a channel

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

+ቅዱስ ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: (መዝ. 59:4)

+በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት:: ስለዚህም " መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም:  መሠረተ ቤተ ክርስቲያን" ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::

+ ቅዱስ ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን ይነግረናል::  ብርሃነ ዓለም  ቅዱስ ዻውሎስም ስለ መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን ነውና:: (1ቆሮ. 1:18, ገላ. 6:14)

+አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል:: የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ: የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ: ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ በወዴት አለና::

+ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን: እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት: ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን ተሻግረዋል::

+በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ ምስክርን አንፈልግም::

+"+ በዓለ_መስቀል +"+

    በሃገራችን ኢትዮጵያ መስቀልን በሚመለከት ከሚከበሩ በዓላት ውስጥ የደመራ መስቀል በዓል /መስከረም 16ና 17/ እንዲሁም መጋቢት 10 የመስቀለ ኢየሱስ በዓል ተያያዥነት ያላቸውና ዋነኞቹ ናቸው፡፡ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ከጌታችን ሞትና ትንሣኤ በኋላ በቀራንዮ አደባባይ ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ጌታችንን የገነዙት #ዮሴፍና #ኒቆዲሞስ ከቀራንዮ ወደ ጎልጎታ (ጌታችን ተቀብሮባት ወደነበረው መካነ መቃብር) ወስደው አኑረውታል፡፡

   አበው ሐዋርያት ወደየሀገረ ስብከታቸው ሲሄዱ የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ሐዋርያው #ያዕቆብ በኃላፊነት እንዲጠብቀው አድርገዋል፤ ከየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱም በእግረ መስቀሉ ሥር እየተሰበሰቡ ይጸልዩ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያምም ጠዋትና ማታ በመስቀሉ ሥር ትጸልይ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ታሪኩንና ቦታውን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን ክቡር መስቀሉን ለማየት ያመኑትም በረከት ለማግኘት ከየአቅጣጫው ይመጡ ነበር፡፡ በመስቀሉ ተዓምራት ብዙዎች ከተለያዩ ደዌ /በሽታ/ ተፈውሰዋል፡፡ ይህም በጣም ብዙ ሰዎች ክርስቶስን ወደ ማመን ስቧቸዋል፡፡ ይህን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ የክርስቶስ ሰቃዮች /ሰቃልያነ ክርስቶስ/ በሁኔታው ባለመደሰታቸው ሕይወት የሆነውን የጌታ መስቀሉን ከጎልጎታ አንስተው ቀብረውት #ለ300 ዓመታት ያህል የከተማው ጉድፍና ጥራጊ እየጣሉበት የተቀበረበት ቦታ ኮረብታ እስኪሆን ድረስ ቆይቷል ‹‹በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ፤ መስቀልከ ዕፀ ሕይወት፥ ዕፀ መድኀኒት›› እንዲል፡፡ ሆኖም #በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ለክርስቲያኖች ነፃነት የሚያስብና የሚያስከብር ንጉሥ በሮም ተነሣ፡፡ የንጉሡም ስም ቈስጠንጢኖስ ይባል ነበር፡፡ ይህ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እንዲወድ ያደረገው በጠላቱ በማክሴንዲዩስ (መክስምያኖስ) ላይ በዘመተበት ጊዜ ገና በጉዞ ላይ እያለ ‹‹በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀርከ (በዚህ የመስቀል ምልክት ጠላትህን ድል ታደርጋለህ)›› የሚል በመስቀለኛ ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ በጠፈር ሰማይ አይቶ በመስቀል ምልክት #ድል በማድረጉ ነው፡፡

     የንጉሥ #ቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት #እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባት፥ ታሪኩ በውስጧ የሰረጸባት ቅድስት እናት ነበረች ቈስጠንጢኖስም በዘመነ መንግሥቱ በትዕምርተ መስቀል ብዙ የድል ሥራ ስለሠራ ለመስቀሉ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ነበረው፡፡ ንግሥት እሌኒም መስቀሉን ለማግኘት ሰው ብትጠይቅ የሚያውቅ አላገኘችም፡፡ በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመሆኑ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊና መቃርስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ አገኘች፡፡ ከእነዚህም አረጋዊው ኪራኮስ ዕድሜው የሸመገለና በእስራኤል ባህልና ደንብ ያደገ ነበር፡፡ እሌኒም እሱን ጠይቃ መስቀሉን ለማግኘት እንዲተባበራት ጠየቀችው ሆኖም ሊተባበራት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ረሃብና ጽም ስታበዛበት ግን የረሃብና የጽሙን መጽናት ተመልክቶ ከእነዚህ ከሦስት ተራሮች አንዱ እንደሆነ ነገራት፤ ከሦስቱ ተራራ የትኛው እንደሆነ ለማወቅ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሱባኤ እንድትይዝ ነገራት፤ ሱባኤም ያዘች፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር #መልአኩን ልኮ እንዲህ አላት ‹‹አንቺም ሰውም በከንቱ አትድከሙ እንጨት አሰብስበሽ፥ ደመራ አስደምረሽ፥ በእሣት አያይዘሽ፥ በፍሕሙ ላይ ዕጣን አፍስሽ፤ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን ተመልክተሽ ጢሱ ያረፈበትን ቦታ አስቆፍሪው›› አላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንዳላት እንጨት አሰብስባ #ደመራ አስደመረች ዕጣንም አፈሰሰችበት #ጭሱም ሰማይ ደርሶ ቅድመ ሥላሴ ሰገዶ  ወደ ምድር ሲመለስ ቦታውን አመለከታት ይህም የሆነው #መስከረም_16 ቀን ነው፡፡ እኛ ደመራ ብለን የምናከብረው ይህን አብነት በማድረግ ነው፡፡

+"+ ቅዱስ_አውዶኪስ_ቀሲስ +"+

=>ይህ ቅዱስ ሰው ለቅዱስ መስቀሉ ከነበረው ፍቅር የተነሳ በብዙ ድካም ወደ #ኢየሩሳሌም በእግሩ ተጉዞ ነበር:: ከብዙ መንገደኞች ጋር በጐዳና ላይ ሳሉ ታዲያ አንድ አይሁዳዊ (ሰማርያዊ) ተቀላቀላቸው:: በወሬ በወሬ የት እንደሚሔዱ ሲጠይቃቸው "መካነ መስቀሉን ለመሳለም ወደ #ጐልጐታ ነን" አሉት::

+እሱ ግን ከት ብሎ ስቆ "እንዴት እንጨት ትሳለማላችሁ" በሚል አፌዘባቸው:: የፀሐዩ ሐሩር እጅግ ጠንቶ ነበርና ቅዱስ አውዶኪስ ኃይለ መስቀሉን ሊያሳይ ወደደ:: በመንገድም መርዝነት ያለው ውሃ ነበርና ቅዱሱ ቀርቦ ጸልዮ በመስቀሉ ባረከውና ፈጥኖ ወደ ጣፋጭነት ተቀየረ::

+ምዕመናኑ ደስ ብሏቸው ሲጠጡ ያ አይሁዳዊ 'እጠጣለሁ' ብሎ ቢቀርብ ወደ ነበረው ተመለሰበት:: 'በኮዳ የያዝኩትን እማልጠጣ' ብሎ ቢከፍተው ደግሞ ተልቶ አገኘው:: እጅግ ደንግጦ አለቀሰ:: በጣም ጠማው: ግን ምኑን ይጠጣ!

+አማራጭ ሲያጣ ወደ ቅዱስ አውዶኪስ ሒዶ እግሩ ላይ ወድቆ አለቀሰ:: በመስቀሉ ቢማጸን መራራው ጣፈጠለት:: በዚህ ምክንያትም ወደ ክርስትና ተመልሷል:: ቅዱሱ በመልካም ሽምግልና ሲያርፍ ውሃው የተቀየረበት ቦታ ላይ ቤተ መቅደስ ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል::

+"+ ቅድስት ታኦግንስጣ +"+

=>በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረችው ሮማዊቷ እናት መንገድ ላይ ቁማ ወንጌል ስታነብ በንጉሥ ወታደሮች ተማርካ ወደ ሕንድ ተወስዳለች:: በዚያም በመስቀል አማትባ ሙት በማስነሳቷ የሃገሩ ሰው ወደ ክርስትና ከነ ንጉሡ ተመልሰዋል:: እርሷም ገዳም አንጻ: ደናግሉን ሰብስባ በንጽሕና ኑራለች:: በዚህ ቀን ዐርፋ ሲቀብሯት የብርሃን መስቀል መቃብሯ ላይ ተተክሏል::

=>አምላከ ቅዱሳን በኃይለ መስቀሉ: በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን:: ከበረከቱ አሳትፎ በዓሉን የሰላም ያድርግልን::

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"አላማርርህም"

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"እውነተኛ ሰላም"

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል"

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ተቃውሞ አዲስ ዘመቻ ተጀምሯል። ቻናላችን ትግሉን ከአምስት ዓመታት በፊት ነበር የጀመረው።
👇👇
/channel/Ethiopian_Orthodox/490

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

💠የመንፈስ ፍሬዎች💠

✝️ "የመንፈስ ፍሬ ግን:ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።"ገላ 5÷22

፩.ፍቅር
✞ በክርስቲያናዊ ሕይወት ከሁሉም የመንፈስ ፍሬዎች የሚቀድመውና የሚበልጠው የመንፈስ ፍሬ ፍቅር ነው።ምክንያቱም፤ ፍቅር የእግዚአብሔር ባሕርይ ስለሆነ ነው 1ዮሐ. 4:16 ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ ስለሆነ ነው ሮሜ. 13.8 ማር. 12:28

✞ የእግዚአብሔር ቃል ይህንን ሲያስረዳ እንዲህም ከሆነ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር፣ እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፡፡ ከነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው ይላል 1ቆሮ.13:13፡፡ በሌላ ክፍል ፍቅርን “የፍጻሜ ማሰሪያ”ብሎታል ቆላ.3:14፡፡ ስለዚህ ክርስቲያኖች ከሁሉ የሚበልጠው ይህ የመንፈስ ፍሬ እንዲታይባቸው እግዚአብሔርንም ሰውንም ከልብ ሊያፈቅሩ ይገባቸዋል፡፡ ሌሎቹን የመንፈስ ፍሬዎች ከማሰባችን በፊት ፍቅር ሊኖረን ፍቅርን ልንከታተል ያስፈልጋል 1ቆሮ.14:1፡፡

✞ ፍቅር የአንዱን ድካም አንዱ ሲሸከም ነው። ሰማዕትነት የሌለበት ፍቅር ፍቅር አይባልም። በአፍ ብቻ እወድሃለሁ እወድሻለሁ ማለት ውሸት ነው። ይህንንስ ባላገሩ "የአፍ ዘመድ ከገበያም አይገድ" ብሎ ተርቶበታል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሐ. ፲፭፣፲፫ "ነፍሱን ስለወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" ብሎ የፍቅርን ትርጓሜ አስተማረን። ፍቅር በአፍ የሚናገሩት ብቻ አይደለም በሕይወት የሚኖሩትም ነው እንጂ። ለዚያም ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን በቃል ከተናገረ በኋላ በተግባር ደግሞ አዳምን ለማዳን በመስቀል የተሰቀለ። መስቀል ፍቅር በተግባር የተገለጠበት አደባባይ ነው። ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት ብሎ ሊቁ የገለጠው ይህንን ነው። ፍቅር ራሱ እግዚአብሔር ነው። ፩ኛ ዮሐ.፬፣፰-፳ "ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም እግዚአብሔር ፍቅር ነውና----ማንም እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው" ይላል። ይህ የሚነግረን በፍቅር ጥላቻ እንደሌለ ነው። ፍቅር ሌላውን እንደ ራስ መውደድ ነው። ማቴ. ፯፣፲፪ "ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው" ተብሎ እንደተጻፈ ሰውን መውደድ በእኛ ሊደረግብን የማንፈልገውን በሌላውም እንዲደረግ አለመፈለግ ሲሆን እግዚአብሔርን መውደድ ደግሞ ትእዛዙን በመፈጸም ይገለጣል።ዮሐ. ፲፬፣፳፩ "ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው" እንዲል።

✞ ማቴ. ፯፣፳፩-፳፫ "በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ይሉኛል። የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም እናንተ አመፀኞች ከእኔ ራቁ ብየ እመሰክርባቸዋለሁ" እንዲል የጌታን ስም ብዙ ጊዜ ብትጠራ፣ በስሙ ተአምራትን ብታደርግ፣ በስሙ ትንቢትን ብትናገር፣ በስሙ አጋንንትን ብታወጣ ይህ የፍቅር ምልክት ተደርጎ አይያዝም። እግዚአብሔርን የመውደድ ዋናው ምልክቱ ፈቃዱን መፈጸም ነው። ፈቃዱ ምንድን ነው ከተባለ ዘጸ. ፳፣፩ ጀምሮ ያሉ አስሩን ሕግጋት መፈጸም ነው። ማቴ. ፲፱፣፲፯ "ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ" እንዳለ። ዮሐ. ፲፪፣፶ "ትእዛዙም የዘለዓለም ሕይወት እንደሆነች አውቃለሁ"እንዲል።

✞ ቅዱስ ጳውሎስ ፍቅርን ጠቅለል አድርጎ ሲያቀርበው እንዲህ ብሎታል። ፩ኛ ቆሮ. ፲፫፣፪-፰ " ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድኾችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሣል፣ ቸርነትንም ያደርጋል፣ ፍቅር አይቀናም፣ ፍቅር አይመካም፣ አይታበይም፣ የማይገባውን አያደርግም፣ የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ በደልን አይቆጥርም፣ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለዓመፃ ደስ አይለውም። ሁሉን ይታገሣል፣ ሁሉን ያምናል፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም" ብሎ ገልጾታል።

👉'ደስታ' ይቀጥላል ...........

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

እነርሱም በታላቅ ጉስቁልና ውስጥ እየኖሩ እያለ በአንዲት ዕለት የአገረ ገዥው ልጅ ለመታጠብ ወደ ውሽባው ቤት ገባ፡፡ በውሽባ ቤቱም የሰይጣን ኃይል ስለነበረበት የመኰንኑን ልጅ አንቆ ገደለው፡፡ የአገሪቱም ሰዎች ሁሉ ለሞተው የመኰንን ልጅ ሊያለቅሱ ሲሰበሰቡ ቅዱስ ዮሐንስም አብሮ ቆሞ ሲመለከት ሮምና መጥታ "በጌታዬ ልጅ ሞት ልትደሰት መጣህን" እያለች ረገመችው፡፡ እርሱም "አይዞሽ አትዘኚ" አላትና ወደ ሞተው ልጅ ቀርቦ በመስቀል ምልክት ካማተበበት በኋላ በፊቱ እፍ አለበት፡፡ የሞተውም ልጅ ድኖ ተነሣ፡፡ የሀገሪቱም ሰዎች እጅግ ደነገጡ፡፡ ሮምናም ደንግጣ "እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን" ብላ ጠየቀችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም "በፍጹም እኔ አምላክ አይደለሁም፣ እኔ የእርሱ አገልጋዩና ሐዋርያው ነኝ እንጂ" አላት፡፡ ሮምናም ስለበደለቻቸው በደል ሁሉ መሪር ዕንባን እያለቀሰች ይቅር እንዲሏት ለመነቻቸው፡፡ እነርሱም አረጋጉዋት፡፡ ከሕዝቡም ውስጥ ብዙዎቹ በጌታችን አመኑ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ሌሎች ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ ወንጌልን እየሰበከ ከጣዖት አገልጋዮች በቀር ሁሉንም አሳምኖ አጠመቃቸው፡፡ አገልጋዮችን ኤጲስቆጶሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ከሾመላቸው በኋላ ወደ ሌሎች አቅራቢያ አገሮች ሄደ፡፡

በመጨረሻም በከሃዲውና በጨካኙ በድምጥያኖስ ዘመን በጣዖት አምላኪዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ፡፡ በፈላ ውኃ ካሠቃዩት በኋለ በፍጥሞ ደሴት አጋዙት፡፡ በዚያም ሳለ ራእዩን ተመልክቶ ጻፈው፡፡ ድምጥያኖስም ከተገደለ በኋላ ከግዞቱ ተመልሶ ሦስቱን መልእክታቱንና ቅዱስ ወንጌሉን ጽፏል፡፡ ጌታችንም አስቀድሞ ሞትን እንደማይቀምስ ለዮሐንስ ቃል ገብቶለት ነበርና (ዮሐ 21፡22) ጥር 4 ቀን እንደ ኤልያስና ሄኖክ ሞትን እንዳያይ ወደ ብሔረ ሕያዋን ወስዶታል።

ጌታችን ለዮሐንስ ያልነገረው እርሱም ያላስተማረው ምሥጢር የለም፡፡ ወንጌሉን መጻፍ ሲጀምር "በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ…" ብሎ የጌታችን ነገር ተመራምሮ ለመድረስ ሲል በመሀል መልአኩን በዮርዳኖስ ባሕር ላይ ሲሄድ አገኘው፡፡ መልአኩም የዮርዳኖስን ባሕር በእንቁላል ቅርፊት እየጨለፈ ወደ ውጭ ሲያፈስ ተመለከተው፡፡ ዮሐንስም ተገርሞ "ምን ማድረግህ ነው" አለው፡፡ መልአኩም "የዮርዳኖስን ባሕር ቀድቼ እየደፋሁ ልጨርሰው ነው" ሲለው ዮሐንስም መልሶ "ታዲያ በእንቁላል ስባሪ ነውን?" አለው፡፡ መልአኩም "አዎን" አለው፡፡ ዮሐንስም "በከንቱ ደከምክ" አለው፡፡ ይህን ጊዜ መልአኩም መልሶ "አንተስ እንጂ ደግሞ የአምላክን መገኘት፣ አኗኗሩንም ተመራምረህ በጥበብ ለማግኘት ብለህ 'በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ..' ብለህ ጀምረህ የለምን? አንተ ጌታን ተመራምረህ ካገኘህና ከደረስክበት እኔም የዮርዳኖስን ወንዝ በዚህ እንቁላል ቅርፊት ቀድቼ እጨርሰዋለሁ" አለው፡፡ ዮሐንስም ይህን ጊዜ ደንግጦ ዝቅ ብሎ "ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ…" ብሎ ሀሳቡን ለወጠና ሌላ ታሪክ ቀጠለ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ክርስቲያኖችን ሁሉ ወክሎ እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ እርሱም ለመቤታችን በአደራ የተሰጠ ሲሆን እመቤታችንን ከወሰዳት በኋላ ለ16 ዓመት እየተንከባከበ ጠብቋታል፡፡ እናቱም በሕፃንነቱ ስለሞተች እመቤታችን ናት እየተንከባከበች ያሳደገችው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በመልኩም ከጌታችን ጋር ይመሳል ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ሥዕል የመሳል ተሰጥኦም ነበረው፡፡ ጌታችን በተሰቀለበት ዘመን የነበረው ጢባርዮስ ቄሳር ልጁ በሽተኛ ነበር፡፡ የጌታችንን የማዳን ሥራ እየሰማ እነ ጲላጦስም ስለጌታችን የሚጽፉለትን ይሰማ ስለነበር ልጁን ከጌታችን መቃብር ላይ እንዲያኖሩለት ላከው፡፡ ልጁም ፈጥኖ ተፈወሰለት፡፡ ጢባርዮስ ቄሳርም በልጁ መዳን ምክንያት የጌታችንን ውለታ ማስቀመጥ ፈልጎ የጌታችንን ሥዕሉን የሚሥልለትን ሲያጠያይቅ ዮሐንስን አገናኙት፡፡ ዮሐንስም ጌታችንን ልክ በዕለተ ዓርብ እንደተሰቀለ አድርጎ በመሣል ለጢባርዮስ ቄሳር ሰጠው፡፡ ሲሥለውም በመጀመሪያ ጌታችንን ልክ እንደተሰቀለ አድርጎ ራቁቱን ነበር የሳለው፡፡ ዮሐንስ የሳለው የጌታችን ሥዕልም አፍ አውጥቶ "በመጀመሪያ አይሁድ በኢየሩሳሌም ራቁቴን ሰቀሉኝ፣ አሁን ደግሞ አንተ ድጋሚ በሮም ራቁቴን ትሰቅለኝን?" ብሎ ተናገረው፡፡ ዮሐንስም እጅግ ደንግጦ "እንዴት አድርጌ ልሳልህ?" ብሎ የሳለውን ሥዕል ቢጠይቀው ሥዕሉም "ከለሜዳ አልብሰህ ሳለኝ" አለው፡፡ ዮሐንስም እንዳለው ከለሜዳ አልብሶ ከሳለው በኋላ ሥዕሉን ትኩር ብሎ ተመልክቶ ቢስመው ከንፈሩ አንድ ቀን ተኩል ያህል ተጣብቆ ቆይቷል፡፡ ዛሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የምትጠቀምባቸውን የጌታችንን ስነ ስቅለት የሚያሳዩ ሥዕሎች መገኛቸው ይህ ወንጌላዊው ዮሐንስ የሳለው ሥዕል ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፦
👉በሕይወቱና በኑሮው ሁሉ ጌታችንን ለመምሰል ይጥር ነበርና ጌታችንም እጅግ ይወደው ስለነበር "ፍቁረ እግዚእ" ተባለ፣
👉 የታላቁ ያዕቆብ ታናሽ ወንድም ስለሆነና አባቱም ዘብድዮስ ስለሚባል "ዮሐንስ ወልደ ዘብድዮስ" ተባለ፣
👉ለጌታችን ባለው ቅናትና ከወንድሙ ጋር ሆነው ባሳዩት የኃይል ሥራ እንዲሁም የጌታችንን አምላክነት በመግለጡ "ቦአኔርጌስ ወይም ወልደ ነጎድጓድ" ተብሏል:
👉ነገረ መለኮትን ከሌሎቹ በበለጠ ሁኔታ አስፍቶና አምልቶ በማስተማሩ "ነባቤ መነኮት ወይም ታዖሎጎስ" ተብሏል።
👉ኃላፊውንና መጻዒውን ጊዜ በራእዩ ስለገለጠ "አቡቀለምሲስ" ተባለ፣ ይህም በግሪክኛ ባለራእይ ማለት ነው፡፡
👉የጌታችንን መከራ መስቀሉን እያስታወሰ ፸ ዘመን ሙሉ እያለቀሰ ስለኖረና ፊቱም በሀዘን ስለተቋጠረ "ቁጹረ ገጽ" ተብሏል፡፡

የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱ አይለየን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

🌼ባርክ ለነ🌼
ባርክ ለነ እግዚኦ ዘንተ ዓመተ ምሕረትነ በብዝኃ ኂሩትከ ለሕዝብከ ኢትዮጵያ/አፍሪካዊያን/ ከመ ንግነይ ለስምከ ቅዱስ /፪/
ወከመ ይኩን ንበረተነ በሰላም ወበዳኅና በዝንቱ ዓመት/፪/

ባርክልን አቤቱ ይህንን የምሕረት ዓመታችን በቸርነትህ ብዛት ለሕዝቦችህ ኢትዮጵያን/አፍሪቃዊያን/ እንድንገዛ ለቅዱስ ስምህ /፪/
እንዲሆንልን ኑሮአችን የሠላም የደህና በዚህ ዓመት /፪/

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መስከረም ፪
ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ

መስከረም ሁለት በዚህች ቀን የካህኑ የዘካርያስ ልጅ የከበረ አጥማቂው ዮሐንስ ሕግን አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ ሰማዕት ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ነቢዩ ዮሐንስ በገሠጸው ጊዜ ፊልጶስ ወንድሙ ስለሆነ ቅዱስ ዮሐንስም የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም ይለው ነበርና።

ቅዱስ ዮሐንስም ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር። ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ። ስለዚህም ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው።

ሄሮድስም ዮሐንስን ይፈራው ነበር ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር። ሄሮድስ የተወለደባትን ቀን በዓል የሚያከብርባት ዕለት ነበረች መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ግብር አገባ።

የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና የምትሺውን ለምኚኝ እሰጥሻለሁ አላት። እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት።

ወጥታም እናቷን ምን ልለምነው አለቻት እናቷም የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አለቻት። ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን እንድትሰጠኝ እሻለሁ ብላ ለመነችው። ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ እምቢ ሊላት ግን አልወደደም።

ያን ጊዜም ባለወጎችን ላከ በእሥር ቤትም ሳለ የዮሐንስን ራስ ቆረጡ ራሱንም በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጡአት እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች። በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ ከእጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረረች ታላቅ ድንጋፄ ሆነ።

ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም እያለች በመጮኽ ዘልፋዋለችና። ደቀ መዛሙርቱም በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት።

ከሰማዕቱ፤ ከጻድቁ፤ ከካህኑ፤ ከነቢዩ ከቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ረድኤትና በረከት ይክፈለን: አሜን!

©ስንክሳር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
"ወትባርክ፡አክሊለ፡ዓመተ፡ምሕረትከ፡ወይጸግቡ፡ጠላተ፡ገዳም"
              መዝ ፷፬÷፲፩    
 "በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ  ምድረ በዳዎችም ጠልን ይጠግባሉ።"
            መዝ 64÷11         

ዐውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ ዐውደ ዓመት:
ንዒ ማርያም ለምሕረት ወሣህል።
           ~~~
እሰይ ደስ ደስ ይበላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ:
ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ።
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ አሸጋገራችሁ አሸጋገረን።                         
 
          
    መልካም አዲስ ዓመት!
       🌼እንቁጣጣሽ🌼                                        
         
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox                              
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

2.4. ዘመነ ክረምት
ዘመነ ክረምት ማለት ዘመነ ውሃ ማለት ነውና በዚህ ዘመን ውኃ ይሰለጥናል፡፡ ውሃ አፈርን ያጥባል፣ እሳትን ያጠፋል፣ ቢሆንም በብሩህነቱ ከእሳት፣ በቀዝቃዛነቱ ከነፋስ፣ በእርጥብነቱ ከመሬት ጋር ተስማምቶ ይኖራል፡፡
ክረምት በውስጡ አራት ወራትን /ሐምሌ፣ ነሐሴ፣ ጳጒሜንና መስከረም/ የያዘ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ “ያረሁ ክረምተ በበዓመት፣ ይሰምዑ ቃሎ ደመናት፣ በየዓመቱ ክረምትን ያገባል፤ ደመናትም ቃሉን ይሰሙታል” ሲል በድጓው እንደነገረን የዘመናት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር በየዓመቱ አዙሮ የሚያመጣልን ወቅት ነው፡፡ ደመናትም
ለቃሉ ትእዛዝ ተገዢዎች በመሆን ዝናመ ምሕረቱን ጠለ በረከቱን የሚያወርዱበት ጊዜ ነው፡፡ ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ድረስ ያለውን ጊዜ ይይዛል፡፡

3. ዓመተ ወንጌላውያን
የሦስቱ ወንጌላውያን ማለትም የዮሐንስ፣ የማቴዎስና፣ የማርቆስ ዘመናት እያንዳንዳቸው ከመስከረም 1 ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 5 ድረስ 365 ቀን ከስድስት ሰዓት ነው፡፡ ዘመነ ሉቃስ ግን ከመስከረም 1 እስከ ጳጉሜን 6 ቀን በመሆኑ 366 ቀናት ይኖሩታል፡፡

4. ወራት
በግዕዝ ቋንቋ “ወርሃ” የምንለው ቃል በአማርኛ ወር እንለዋለን ይህም ወደ ብዙ ቁጥር ሲለወጥ ወራት ይሆናል፡፡ በኢትዮጵያ ዘመን አቈጣጠር እያንዳንዳቸው 30 ቀናት ያሏቸው 12 ወራት፣ 5 ወይም በየአራት ዓመት 6 ቀናት የሆነች ጳጉሜን ያሉ ሲሆን በአውሮፓውያን
አቈጣጠር ግን የየወሩ የቀናት ቁጥር ለየት ይላል፡፡

የወራቱ ስም የግዕዝ መገኛው አማርኛው ትርጉም:
1 መስከረም— ከረመ ከረመ/ረ ይጠብቃል/
2 ጥቅምት —ጠቀመ ጠቀመ/ቀ ይጠብቃል/
3 ኅዳር –ኀደረ አደረ
4 ታኅሣሥ— ኀሠሠ ፈለገ
5 ጥር —ጠየረ መጠቀ/ወደ ላይ ተመረመረ
6 የካቲት —ከተተ ሰበሰበ
7 መጋቢት— መገበ መገበ/ገ ይጠብቃል/
8 ሚያዝያ —መሐዘ ተጐዳን
9 ግንቦት— ገነባ ገነባ
10 ሰኔ —ሠነየ አማረ
11 ሐምሌ — ሐምለ ለመለመ
12 ነሐሴ— ነሐሰ ሠራ

5.ሳምንት
ሳምንት “ሰመነ” ስምንት አደረገ ከሚለው ከግዕዝ ቃል የተገኘ ነው፡፡ በሕገ ዑደት መሠረት ዕለት ከተነሣበት ማለትም ከእሑድ እስከ እሑድ ያለው ጊዜ ሳምንት ተብሎ ይጠራል፡፡ በዚህ ሳምንት ውስጥ ያሉት ቀናት እያንዳንዳቸው 24 ሰዓት ያላቸው ናቸው፡፡

እሑድ ማለት “አሐደ” አንድ አደረገ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ
ስለሆነ ትርጉሙ አንድ ማለት ነው፡፡
ሰኞ ሁለተኛ ፣ ማክሰኞ /ማግስት/ ሦስተኛ፣ ረቡዕ አራተኛ፣ ሐሙስ
አምስተኛ፣ ዓርብ ስድስተኛ ፣ቅዳሜ ሰባተኛ ቀን ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን በስድስት ቀናት /ከእሑድ - ዐርብ/ ፈጥሮ ያረፈባትና ሰዎችም እንዲያርፉበት ያዘዛት ሰባተኛዋ ቀን በግዕዝ ቀዳሚት ሰንበት ተብላ ትጠራለች፡፡

6. የዕለታት ስያሜ
1. እሑድ ፡ አሐደ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አንድ አደረገ /የመጀመሪያ ሆነ/ ማለት ነው፡፡
በዚህ ቀን ፍጥረታት መፈጠር ስለጀመሩ እሑድ ተብሏል፡፡
2. ሠኑይ /ሰኞ/፡ ሠነየ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሁለት አደረገ ማለት ነው፡፡ ለሥነ ፍጥረት ሁለተኛ ስለሆነ ሰኑይ/ ሰኞ/ ተብሏል፡፡ አንድም ሠናይ (ያማረ) ማለት ነው።
3. ሠሉስ/ማክሰኞ/ ፡ ሠለሰ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ሦስት አደረገ ማለት ነው፡፡ ማክሰኞ የሚለው የሰኞ ማግስት ማለት ነው፡፡
4. ረቡዕ ፡ረብዐ /አራት አደረገ/ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ለሥነ ፍጥረት አራተኛ ቀን ማለት ነው፡፡
5. ሐሙስ፡ ሐመሰ /አምስት አደረገ/ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ለሥነ ፍጥረት አምስተኛ ቀን ማለት ነው፡፡
6. ዓርብ ፡ ዓረበ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ተካተተ ማለት ነው፡፡ ፍጥረታት እሑድ መፈጠር ጀምረው አርብ ስለተካተቱ /ተፈጥረው ስለተፈፀሙ/ አርብ ተብሏል፡፡
7. ቅዳሜ፡ ቀዳሚት ማለት ሲሆን ሰንበተ ክርስቲያን ከሆነችው ከዕለተ እሑድ ቀድማ ስለምተገኝ ቀዳሚት ሰንበት /ቅዳሜ/ ተብላለች፡፡

«ወይእዜኒ በጽሃ ጊዜሁ ለነቂህ እምነዋም ኀለፈት ሌሊት ወመጽአት መዓልት ወንግድፍ እምላእሌነ ምግባረ ጽልመት ወንልበስ ወልታ ብርሃን ከመናንሰሉ በምግባረ ፅድቅ።
ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ ካመንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቧል፤ ሌሊት አልፏል፤ ቀኑ ቀርቧል፤ እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃን ጋሻ ጦር እንልበስ፤ በቀን እንደምንሆን በአግባቡ እንመላለስ። በዘፈንና በስካር በዝሙትና በመዳራት አይሁን፤ በክርክር እና በቅናት አይሁን»
ሮሜ ፩፫፥፩፩

«የአክለክሙ መዋእል ዘሃለፈ ፥ ያለፈው ዘመን ይበቃችኋል» እንደተባለ
(፩ኛ ጴጥሮስ ፬ ፥ ፫- ፬ ) በኃጢአት፣ በርኩሰት፣ በጠብ፣ በክርክር፣ በቁጣ፣ በቂም በቀል፣ በስካር ያለፈው ይብቃ። መጪውን ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የንስሐ ያድርግልን።

ስብሐት ለእግዚአብሔር ዘሃሎ በአርያም
ወለወላዲቱ ድንግል ማርያም
ወለመስቀሉ ክቡር ዕፀ ፍቅር ወሰላም
አሜን‼️

©ዲ/ን ጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

🌼 አቡሻኽር 🌼

ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ
በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥
መዝሙር ፷፬ ÷፲፩


አቡሻኽር የተለያዩ የዘመን ቀመሮችን ያጠና ዘመን ቀማሪ የቁጥር ሰው (Mathematician) ነው። ሙሉ ስሙ አቡሻኽር ወልደ አቤል ሔሬም ሲሆን ዮሐንስ ፍቁርም ይሉታል። በ፲፱፻፷፪ በታተመው የአቡሻኽር መጽሐፍ ላይ የአቡሻኽርን ቁጥርና ሐሳብ የመረመሩ (የተነተኑ) ፱ ሊቃውንትን ይዘረዝራል። እነዚህም ሰዒድ ወልደ በጥሪቅ፣ ማኅቡብ መንበጋዊ፣ ስዒዳውያን አይሁድ፣ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቄርሎስ፣ ኤጲፋንዮስ፣ ዮሐንስ ዘደማስቆ፣ ማርቆስ ወልደ ቀምበር እና ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ (ሃሚድም ይላሉ) ናቸው። አቡሻኽር መጽሐፉን የጻፈው እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ ፲፩፻፵፱ ነው ይላሉ። አንዳንዶች እስከ ፲፩፻፺፫ ድረስ ከፍ ያደርጉታል።
መጽሐፉን የሀገራችን ሊቃውንት መርምረውታል፣ ሐተታ ጭረውበታል፣ አስተምረውታል። በዚህ ሂደትም ከሀገራችን የቁጥር መጻሕፍት ይመደባል።

አቤቱ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትክ ሰማያትም የጅህ ስራ ናቸው፤ አነርሱ ያልፋሉ አንተ ግን ትኖራለህ፤ ሁላቸውም አንደ ልብስ ያረጃሉ አንደ መጎናጸፊያ ትለውጣቸዋለህ። አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ ዓመቶችህም ከቶ አያልፉም። መዝ ፻፩፤፪፬-፪፰

የአዲሱን ዓመት 2017 ዓ/ም መባቻ፣ ወንጌላዊና ዘመኑን እንዴት በቀላሉ ማስላት ይቻላል ቢባል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዘመን አቆጣጠርን ባሕረ- ሐሳብ ወይም አቡሻኽርን መሠረት በማድረግ እንደሚከተለው በቀላሉ ማስላት ይቻላል።
ከአዳም እስከ ክርስቶስ ያለው 5500 ዘመን ዓመተ ኩነኔ (ፍዳ) ሲሆን፣ ከክርስቶስ መወለድ እኛ እስካለንበት ያለው ዘመን ደግሞ ዓመተ ምሕረት ይባል። የኹለቱ ድምር ዓመተ ዓለም ይባላል።

ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምሕረት ➕ ዓመተ ኩነኔ (ፍዳ)
= 2017 ➕ 5500
= 7517
ወንጌላዊ፦ በየ4 ዓመቱ አንድ ጊዜ የሚሾም ማለት ነው፡፡
ወንጌላዊ = ዓመተ ዓለም ➗ 4
= 7517 ➗ 4
= 1879 (ቀሪ 1️⃣ )
1879፦ መጠነ ራብዒት ይባላል፡፡ አንድ አራተኛ (1/4) ማለት ነው።
= 7517➖ ( 4 ✖️1879)
= 7517➖ 7516
= 1
ቀሪው '1️⃣‘ ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ
ቀሪው ' 2️⃣ ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ
ቀሪው ' 3️⃣ ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ
ቀሪው ' 0️⃣ ' ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይሆናል።
ስለዚህ ቀሪው '1️⃣' ስለሆነ የዘንድሮው ወንጌላዊ (2017) ማቴዎስ ሲሆን ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ ይባላል።
በሌላም በኩል ዓመተ ምሕረቱንም ለ4ቱ ወንጌላውያን ብናካፍለው የዘመኑን ወንጌላዊ ማወቅ እንችላለን።
2017 ➗ 4 = 504 (ቀሪ '1️⃣' )
ቀሪው ' 1 ' በመሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ እንደሆነም በዚህ ይታወቃል።

ዕለተ ቀመር፦ መስከረም አንድ የሚውልበት ቀን ነው፡፡
ዕለተ ቀመር = (ዓመተ ዓለም ➕ መጠነ ራብዒት) ➗ 7
= (7517➕ 1879) ➗ 7
= 9396 ➗ 7
= 1342 ቀሪ 2
ቀሪው '0️⃣ 'ከሆነ ሰኞ
ቀሪው '1️⃣'ከሆነ ማክሰኞ
ቀሪው '2️⃣ 'ከሆነ ረቡዕ
ቀሪው '3️⃣ 'ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው '4️⃣'ከሆነ ዓርብ
ቀሪው '5️⃣ 'ከሆነ ቅዳሜ
ቀሪው '6️⃣ 'ከሆነ እሑድ መባቻ ይሆናል።

በመሆኑም ዘንድሮ ቀሪው ''2️⃣ ' ስለሆነ ዕለተ ቀመር ረቡዕ ይሆናል ወይም አዲሱ ዓመት 2017 ዓ/ም መባቻ መስከረም አንድ ቀን በዕለተ ረቡዕ ይውላል ማለት ነው። ዘንድሮ ዕለተ ቀመር ጥንተ ዮን (ዖን) ከተባለችው ረቡዕ ጋር መገጣጠሙ ነው።
ሥነ ፍጥረት የተጀመረባት እሑድ ጥንተ ዕለት፣ ዘመን አቆጣጠር የተጀመረባት ማክሰኞ ጥንተ ቀመር እንዲሁም ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት የተፈጠሩባት ዕለተ ረቡዕ ጥንተ ዮን (ዖን) ትባላለች።

በተመሳሳይ ፤
መስከረም 1 በዋለበት ሚያዝያ 1 ይውላል
ጥቅምት 1 በዋለበት ግንቦት 1 ይውላል
ኀዳር 1 በዋለበት ሰኔ 1 ይውላል
ታኅሣሥ 1 በዋለበት ሐምሌ 1 ይውላል
ጥር 1 በዋለበት ነሐሴ 1 ይውላል።

በዚህ መሠረት የ2017 ዓ/ም መስከረም 1 ቀን ረቡዕ ስለሚውል በተመሳሳይ ሚያዝያ 1 ቀንም ረቡዕ ይውላል ማለት ነው።
የዚህ ዓመት ጳጉሜን 5 በዋለበት ዕለት የቀጣይ ዓመት በዓለ ልደት (ገና) ይውላል። ይህም ማለት የ2016 ዓ/ም ጳጉሜን 5 ማክሰኞ ቀን ስለዋለች የ2017 ዓ.ም፡
🌼
በዓለ ልደት ( ገና ) ማክሰኞ ታኅሣሥ 29፣
🌼
መስቀል መስከረም 17 ቀን ዐርብ፣
🌼
ጥምቀት ጥር 11 ቀን እሑድ ፣
🌼
ጾመ ነነዌ የካቲት 3 ቀን ሰኞ፣
🌼
ዐቢይ ጾም የካቲት 17 ቀን ሰኞ፣
🌼
ደብረ ዘይት መጋቢት 14 ቀን እሑድ፣
🌼
ሆሳዕና ሚያዝያ 5 ቀን እሑድ፣
🌼
ስቅለት ሚያዚያ 10 ቀን ዐርብ፣
🌼
ትንሣኤ ሚያዚያ 12 ቀን እሑድ፣
🌼
ርክበ ካህናት ግንቦት 6 ቀን፣
🌼
ዕርገት ግንቦት 21 ቀን ሐሙስ፣
🌼
ጰራቅሊጦስ ሰኔ 1 ቀን እሑድ፣
🌼
ጾመ ሐዋርያት ሰኔ 2 ቀን ሰኞ፣
🌼
ጾመ ድኅነት ሰኔ 4 ቀን ረቡዕ የሚውሉ ይሆናል


አዳም የተፈጠረው በዕለተ ዓርብ ነው። ከ40 ቀን በኋላም ወደ ገነት እግዚአብሔር አስገባው። አዳምም የእግዚአብሔርን ሕግ እየጠበቀ 7 ዓመት ከ1 ወር ከ17 ቀን በገነት ተቀመጧል። ከዚያ በኋላ አትብላ የተባለውን እጸ በለስ ስለበላ ተፈረደበት። አዳምም ንሥሓ በገባ ጊዜ እግዚአብሔር ከ5500 ዘመን በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ የሚል ተስፋ ሰጠው። የአዳም ልጆችም ይህን ይዘው ጌታ ሰውን ለማዳን የሚመጣበትን ጊዜ በፀሐይ በጨረቃ በከዋክብት እየቆጠሩ ይኖሩ ነበር። የዘመን ቁጥር የተጀመረበት ምክንያቱ ይህ ነው።

ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፤
ዓለም ከተፈጠረ በ5500 ዘመን በዘመነ ዮሐንስ መጋቢት 29 እሑድ ቀን በ 3:00 ሰዓት ተጸነሰ፤
ዓለም ከተፈጠረ በ5501 ዘመን ወይም በ1 ዓመተ ምሕረት በዘመነ ማቴዎስ ታኅሳስ 29 ቀን ማክሰኞ ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ተወለደ።
በ5531 ዘመን ወይም በ31 ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሉቃስ ጥር 10 ቀን ለ11 አጥቢያ ማክሰኞ ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ተጠመቀ።
በ5533 ዘመን ወይም በ33 ዓመተ ምሕረት ዘመነ ማቴዎስ ነሐሴ 13 እሑድ ቀን በቀትር ጊዜ ብርሃነ መለኮቱን ለሐዋርያት በደብረ ታቦር ገለጠ።
በ5534 ዘመን (በ34 ዓ.ም) በዘመነ ማርቆስ መጋቢት 22 ቀን እሑድ በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ (ሆሣዕና)።
በ5534 ዓ.ዓ (በ34 ዓ.ም) በዘመነ ማርቆስ መጋቢት 26 ቀን ሐሙስ በሠርክ ጌታችን መስዋዕተ ኦሪትን በመስዋዕተ ወንጌል የተካበት ነው።
በ5534 ዓ.ዓ (በ34 ዓ.ም) በዘመነ ማርቆስ መጋቢት 27 ቀን ቀትር በ6:00 ሰዓት ተሰቅሎ በ9:00 ሰዓት ነፍሱን ከሥጋው ለይቶ ሠርክ በ11:00 ሰዓት የተቀበረበት ነው።
በ5534 ዓ.ዓ ( በ34 ዓ.ም) በዘመነ ማርቆስ መጋቢት 29 ቀን እሑድ መንፈቀ ሌሊት ከሙታን ተለይቶ የተነሣበት ነው።
በ5534 ዓ.ዓ (በ34 ዓ.ም) በዘመነ ማርቆስ ግንቦት 8 ቀን በ 3:00 ሰዓት ያረገበት ነው።

ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ ጀምሮ እስከ ዛሬ ያለው ዘመን በዓመተ ፀሐይ ሲቆጠር 7516 ዓመተ ዓለም ነው።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጳጉሜን ፫
ቅዱስ ሩፋኤል


ሰማያውያን ከሆኑ ከመላአክት አለቆች ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ቀጥሎ 3ተኛ ነው፡፡ "ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል፡፡ ጦቢት 12፡15፡፡ ሩፋኤል የሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል መልአክ የሰላምና የጤና መልአክ ይባላል፡፡ በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ሆነ ቁስል ይፈወስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” መጽሐፈ ሄኖክ 6፡3፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል የሰው ልጆች ከተያዙበት የኃጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ “በበሽታ ሁሉ ላይ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡” በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል፡፡ ሄኖክ 10፥13 ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ በማኅፀን ላለ ችግርና ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም፡፡ ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት በማሕፀን እያለ ማለትም በሥላሴ አርአያ መልኩ መሳል ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡ በመውለጃቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነት ያለን ረቂቅ ርኩስ መንፈስ ያውቃል፡፡ አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ጭን ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሠቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል። ጦቢት 3፡8-17
ይኽም ጻድቅ ጦቢት በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ዕውነትና ቅን በሆነ ሕግ ጸንቶ የሚኖር ነው፡፡ ከወገኖቹ ጋራ ከመማረኩ በፊት ለችግረኞች ብዙ ምጽዋትን ይሰጥ ነበር፣ ብዙ ጊዜም የበጎቹን ጠጉርና ከእህሉም ዓሥራት በኩራቱን ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣ ነበር፡፡ ከገንዘቡም ከሦስት አንዱን ለድኆች ይሰጣል፡፡ በዚያን ጊዜም ሕዝቡ ሁሉም ክደው በአልና ደማሊ ለሚባሉ ጣዖታት ይሰዉ ነበር፡፡
የቅዱስ ጦቢት ወገኖቹ ነነዌ በተማረኩ ጊዜ ሁሉም የአሕዛብን እህል በሉ፤ እርሱ ግን ሰውነቱን ይጠብቅ ነበር፡፡ የአሕዛብንም መብል እንዳይበላ እግዚአብሔርን ያስበው ነበርና፡፡ በአንዲት ዕለትም በአደባባይ የወደቀ በድን አግኝተው ነገሩት፡፡ እርሱም እህል ሳይቀምስ ተነሥቶ ሔደ፡፡ ፀሐይም እስከሚገባ ወደ አንድ ቤት ውስጥ አስገብቶ አኖረውና ፀሐይ ሲገባ ቆፍሮ ቀበረው፡፡ በዚያችም ሌሊት እንደኃጢአተኛ ሆኖ በእድሞ ሥር ተኝቶ አደረ፡፡ በእድሞውም ላይ ወፎች መኖራቸውን ስላላወቀ ፊቱን ገልጦ ሳለ ወፎች እርኩሳቸውን ዐይኖቹ ላይ ጣሉበትና ዐይኖቹ ተቃጠሉ፡፡ ከዐይኖቹም ጢስ ወጣ፡፡ ታወሩም፡፡ ባለ መድኃኒትም ሊያድነው አልቻለም፡፡ መልአኩን ልኮ ነፍሱን እንዲወስዳት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ በዚያችም ዕለት የራጉኤል ልጅ የሣራ እና የጦቢት ጸሎታቸው ተሰማላቸው፡ ይህችም ሣራ አስማንድድዮስ የሚባል የሚባል ጋኔን በጭኗ አድሮ ሰባት ባሎቿን በየተራ የገደለባት ናት፡፡

ጦቢትም በገባኤል ዘንድ በአደራ ያስቀመጠውን ገንዘብ ያስመጣለት ዘንድ ልጁን ጦቢያን አሽከር እንዲፈልግ ነገረው፡፡ ጦቢያም ለአባቱ ታዛዥ ሆኖ አሽከር ሲፈልግም መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ስሙን አዛርያ ነኝ ብሎ በሰው አምሳል ተገለጠለትና ጦቢት አንድ ላይ ላካቸው፡፡ ጤግሮስ ወንዝ በደረሱ ጊዜ ጦብያ ሊታጠብ ባለ ጊዜ ታላቅ ዓሣ ሊውጠው ሲል መልአኩ ‹‹አትፍራው ያዘውና ጉበቱንና ልቡን አውጣ›› አለው፡፡ እንዳዘዘውም አደረገ፡፡ ጦቢያም ‹‹አንተ ወንድሜ አዛርያ ሆይ! ይህ የዓሣ ሐሞት፣ ጉበትና ልቡ ምን ይሠራል?›› አለው፡፡ አዛርያ የተባለው ቅዱሱ መልአክም ‹‹ጉበቱና ልቡ ከደቀቀ ዕጣን ጋራ ቢያጤሱት ጋኔን ያደረበትን ጢሱ ያድነዋል፤ ሐሞቱም ዐይኖቹ የታወሩበትን ሰው ቢኩሉት የታወረ ዐይኖቹ ይበራሉ›› አለው፡፡
ዳግመኛም አዛርያ የራጉኤልን ልጅ ሣራን እንዲያገባት ነገረው፡፡ እንዳይፈራም አጽናናው፡፡ ወደ ራጉኤል ቤት በደረሱም ጊዜ ሣራ ተቀብላ ደስ አሰኘቻቸው፡፡ ጦቢያም ሣራን ወደዳትና እርሷን ይሰጠው ዘንድ አባቷን ጠየቀው፡፡ አባቷም ካሁን በፊት ለሰባት ባሎች ሰጥቷት ሰባቱም እንደሞቱ ቢነግረው ጦቢያም ‹‹የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን›› አለው፡፡ አባቷም ሣራን ሰጠውና ወደ ጫጉላ ቤት ባገቧቸው ጊዜ ጦቢያ አዛርያ የነገረውን አስታወሰ፡፡ የዓሣውን ጉበትና ልብ ከደቀቀ ዕጣን ጋራ ቢያጤሰው ጋኔኑ አስማንድድዮስ ሸሸ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልም ይዞ ለዘለዓለም አሠረው፡፡ ከዚህም በኋላ ጦቢያ ሚስቱን ሣራን ወስዶ ወደ አባቱ ቤት ተመለሰ፡፡ የአባቱንም ዐይኖች በኳለ ጊዜ እንደ ጭጋግ ሆኖ ከዐይኖቹ ተገፈፈ፡፡እርሱም ዳነና ማየት ቻለ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልም ራሱን ገለጠላቸውና ብዙ ምሥጢርን ከነገራቸው በኋላ ዐረገ፡፡

ከዚህም በኋላ ጦቢት ከወገኖቹ ጋራ ታላቅ የደስታ በዓል አደረገ፡፡ ስለ ጌታችንም መከራ ትንቢት ሲናገር ‹‹እርሱ በኃጢአታችን ይገርፈናል፣ ደግሞ እርሱ ይቅር ይለናል፣ ይፈውሰናልም፡፡ ሁለተኛም መከራህን የሚያስቡ የተመሰገኑ ናቸው፣ እነርሱ ክብርህን ባዩ ጊዜ በአንተ ደስ ይላቸዋልና›› አለ፡፡ ከዚህም በኋላ ጦቢት ብዙ ትንቢቶችን ተናገረ፡፡ ስለ ኢየሩሳሌም መታነጽና የእስራኤል ምርኮኞች ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመለሱ ትንቢትን ተናገረ፡፡ ልጁን ጦቢያንም ‹‹ልጄ ሆይ! ምጽዋት እንደምታድንና እንደምታጸድቅ ተመልከት›› አለው፡፡ ይህንንም ተናገሮ በአልጋው ላይ ሳለ በ158 ዘመኑ በሰላም ዐረፈ፡፡
ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው” ሄኖክ 3፡5-7፡፡ በዚህ መሠረት ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሄኖክ 2፥18 ሰማያውያን መዛግብት በእጁ የሚጠብቃቸው እግዚአብሔር እንዳዘዘዉ የሚከፍታቸዉ የሚዘረጋቸዉ ይህ ታላቅ መልአክ ነው፡፡
የምሕረትና የረድኤት መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሥራዎቹ አንፃር በተለያየ ስም ይጠራል፡፡ "ፈታሄ ማህጸን" ይባላል-እናቶች ሲወልዱ ምጥ እንዳይበዛባቸዉ የሚራዳ መልአክ ስለሆነ አያሌ ክርስቲያኖች ማርገዛቸዉን ካወቁ ጀምሮ ድርሳኑን በማንበብ መልኩን በመድገም ጠበሉን በመጠጣት ሰውነታቸዉን በመቀባት ይለምኑታል፡፡ እንደ እምነታቸው ጽናት ይደረገላቸዋል፡፡ ዳግመኛም "ዐቃቤ ኖኀቱ ለአምላክ" ይባላል-ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠበቅ ስለሆነ ነው፡፡ ዳግመኛም "መራሔ ፍኖት" ይባላል-ጦቢትን በቀና መንገድ መርቶታልና ነው፡፡ እንዲሁም "መላከ ክብካብ" ይባላል-ጦቢያና ሣራን ያጋባ ጋብቻቸዉን የባረከ በመሆኑ ነው፡፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያደረገው ተዓምር ይህ ነው፡፡ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በዓል እስኪፈፀም ድረስ በከበረ ሊቀ ጳጳስ አባ ቴዎፍሎስ ዘመን በምድረ ግብጽ ውስጥ ከእስክንድርያ ውጭ በታናፀች አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን ከዓሣ አንበሪ ላይ የታነፀች ነበረች፡፡ ነገር ግን በወደቡ አጠገብ ከነበረ ግዙፍ አንበሪ ጀርባ ላይ መታነጿን ቀድሞ ያነጿት ሰዎች ቢሆኑ ከካህናትም ቢኾን ያወቀ አልነበረም፡፡
ያ አንበሪም የቤተክርስቲያኑ ህንጻ በከበደው ጊዜ ፈጽሞ ተንቀሳቀሰ፡፡ ከአሸዋማው መሬት ላይ በባህሩ ዳርቻ የታነፀች

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መስቀል
🌋✝

ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ ማርያም እግዝእት በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ መከራ መስቀልን ተቀብሎ:
¤ከግራ ቁመት:
¤ከገሃነመ እሳት:
¤ከሰይጣን ባርነት:
¤ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::

=>+"+ እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ +"+ እንዳለ ሊቁ::

+ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም ራሷ አርአያ ትዕምርተ መስቀል ናት::

+እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት (ዘፍ. 4:15) ጀምሮ
¤ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት (ዘፍ. 22:6):
¤ቅዱስ ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል (ዘፍ. 28:12):
¤ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ (ዘፍ. 48:14):
¤ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው የሙሴ በትር (ዘጸ. 14:15):
¤የናሱ ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት (ዘኁ. 21:8) ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

💠የመንፈስ ፍሬዎች💠

፬.ትዕግሥት

✞ አሁን አሁን ከትዕግሥተኞች ይልቅ ስለ ትዕግሥት የሚያወራው ይበልጣል። ትዕግሥት የክብር እናት ናት።ከክርስቶስ መስቀል በረከትን ማግኛ ነው። ክርስቶስ እኛን ለማዳን በመስቀል ተሰቀለ። እስኪ ራስህን አድን እያሉ አይሁድ ሲሳለቁበት፣ ምራቃቸውን ሲተፉበት፣ ተነበይ ለነ ክርስቶስ መኑ ጸፍዐከ እያሉ በጥፊ ሲመቱት እነርሱን ማጥፋት እየቻለ ለእኛ ትዕግሥትን ያስተምረን ዘንድ መከራውን ሁሉ በዝምታ ተቀበለ። ሰማዕታት ስለ እውነት መራራ ሞትን ታገሡ። ወተዐገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግሥተ ሰማያት እንዲል። የታገሠ የድል አክሊል ያገኛል። ይህችውም መንግሥተ ሰማያት ናት። አባቶቻችን ዕጉሣን ነበሩ። ለመናገር የዘገዩ ለመስማት የፈጠኑ ነበሩ። ታጋሽ ሰው ሕይወቱ የተረጋጋ ነው። አርምሞ (ዝምታ) የትዕግሥት አጋዥ ነው። ትዕግሥት የጠብ ማብረጃ ነው።

✞ ትዕግሥትን እንለማመዳት። ሲታገሡ ያማል። ሕመሙ ግን አጭር ነው። ከሕመሙ በኋላ ያለው ደስታ ልዩ ነው። እናት ልጇን ስትወልድ የምጥ ጊዜዋ አስጨናቂ ነው። ነገር ግን ልጇን ከወለደች በኋላ ወንድ ልጅ ወለድሽ ብለው ሲያስታቅፏት
ያለፈውን መከራ ሁሉ በልጇ ትረሳዋለች። ስንሰደብ ዝም ስንል ልናዝን እንችላለን። ነገር ግን እየቆየ ሲሄድ ምን ስድብማ አየር የሚወስደው አይደለምን ብለን ደስ ይለናል። ቅዱሳንም ይህችን ዓለም ያሸነፏት በትዕግሥት ነው። ሊቁ መዋዕያነ ዓለም አንትሙ በብዙኅ ትዕግሥት ያለው ይህንን ነው።

✞ ታጋሽ ሰው የሰማእታቱ የእነ ቅዱስ መርምህናም፣ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የእነ ቅዱስ ፊቅጦር፣ የእነ ቅዱስ መርቆሬዎስ፣ የእነ ቅዱስ ፋሲለደስ፣ የእነ ቅዱስ ገላውዴዎስ፣ የእነ ቅዱስ ቂርቆስ እንዲሁም የቅዱሳን ሰማእታት ሁሉ ወዳጅ ነው። ታጋሽ ሰው የመነኮሳቱ የእነ ቅዱስ መቃርስ፣ የእነ አባ እንጦንስ እንዲ የቅዱሳን መነኮሳት ሁሉ ወዳጅ ነው። ታጋሽ ሰው የቅዱሳን ሁሉ ወዳጅ ነው። እግዚአብሔር ይወደዋል። በሉ ኑ ታጋሽነትን እንለማመድ። ታጋሽ እንሁን።

👉'ቸርነት' ይቀጥላል ...........

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

💠የመንፈስ ፍሬዎች💠

፫. ሰላም

✞ ቅድስት ድንግል ማርያምን ሰላማዊት ይላታል። ልጇም ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ይባላል። አንድ ሰው ውስጣዊ ሰላም ይሰማኛል ሲል ብትሰማው የሐሳብ ስምምነት የአእምሮ ዕረፍት እንዳገኘ ትረዳለህ። ውስጣዊ ሰላም የሕዋሳቶቻችን ስምምነት ውጤት ነው። ሰላም ተሳለመ_ተፈቃቀረ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ዘመድ ዘር ነው። ሰላም ፍቅር ማለት ነው። ምሥጢራዊ ትርጓሜው ግን ከተሰናእዎ ጋር ይቀራረባል። የነገር እና የሐሳብ ስምምነት ማለት ነው። ሰላም ሆነ ማለት ስምምነት ላይ ተደረሰ ማለት ነው። አምላከ ሰላም ክርስቶስ ሰላምን እሰጣችኋለሁ ብሏል። ለሰውነታችን የተስማማች ገነትን ሰጥቶም አረጋገጦልናል። ሲኦል ግን ለእኛ ሰውነት የማይስማማ ቦታ ነው። በሲኦል ሰላም የለም። ሁከት ብጥብጥ ዋይታ ለቅሶ ይበዛል። ውስጣዊ ሰላም የሚገኘው በድለን ከነበረ ንሥሓ ገብተን ኃጢዓታችንን አስወግደን መልካም ሥራ ስንሰራ ነው። ነገር ግን ሌላውን እያስቀየምን፣ እያናደድን፣ እየተሳደብን ውስጣዊ ሰላም ይሰማናል ብንል ውሸታም እንባላለን። ነቢዩ ኤርምያስ እንደተናገረው "ወይቤሉ ሰላም ሰላም ወአልቦ ሰላም" እንዳሉት ሐሰተኛ ነቢያት እንሆናለን። የልቡና ሰላም የሚገኘው እውነትን ፍቅርን ትሕትናን ስንይዝ ነው። ፍጹም ሰላማዊት ወደ ሆነችው መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ከተጣላናቸው ጋር በይቅርታ ታርቀን፣ የበደልነውን ክሰን በፍቅር እንኑር።

✞ ክርስቶስ ሰላምን የሰጠን በደላችንን ይቅር ብሎ ነው። እኛም በትክክለኛ ፍትሕ ያጠፋው ክሶ፣ የተበደለው ተክሶ በሰላም እንኑር። ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት ከፈለጉ የተጣሉትን ይታረቁ፣ ቂም በቀል ጥላቻ ዘረኝነት ካለብዎ ያስወግዱ። ከእርስዎ የሚጠበቀውን መልካምነት ያድርጉ። የድርሻዎትን ይወጡ። ከመንፈስ ፍሬዎች አንዱ ሰላም ነው። ገላ. ፭፣፳፪።

👉'ትዕግሥት' ይቀጥላል ..............

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መስከረም ፲
ጼዴንያ ማርያም


ጼዴንያ በምትባል ሀገር ማርታ የምትባል ደግ ሴት ነበረች፡፡ ይህች ደግ ሴት በቤቷ ትልቅ አዳራሽ ሠርታ እንግዶችን እንደ አባታችን አብርሃም ተቀብላ አብለታ አጠጥታ ማደሪያ ቦታም ሰጥታ ታስተናግድ ነበር፡፡ አባ ቴዎድሮስ የሚባል ኢትዮጵያዊ መነኩሴ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ መሽቶበት ከማርታ ቤት በእንግድነት አደረና ጠዋት ሊሄድ ሲነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚሄድ ሲነግራት ‹‹የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተህ አምጣልኝ ዋጋውን ልስጥህ›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ገንዘቡን ሥዕሉን ሳመጣልሽ ትሰጪኛለሽ›› ብሏት ሄደ፡፡ ኢየሩሳሌምም ደርሶ ቅዱሳት መካናትን ተሳልሞ ሥዕሉን ረስቶ ሳይገዛ ሲመለስ «አደራ ጥብቅ አይደለምን? ያቺ ሴት አደራ ያለችህን ለምን ረሳህ» የሚል ድምፅ ሰማ፡፡ በጣም ደንግጦ ተመልሶ ሄዶ ገዝቶ በረሃ በረሃውን መጓዝ ጀመረ፡፡ በመንገድም እየተጓዘ አንበሳ ሊበላው እየሮጠ ወደ እርሱ ሲመጣበት አየ፡፡ መነኩሴው አንበሳውን ከመፍራት የተነሣ ደነገጠ፣ ተንቀጠቀጠ ደንግጦ ቁሞ ሳለ ያች ሥዕል ከአንበሳው ጩኸት ሰባት እጅ በሚበልጥ አስፈሪ ድምፅ ጩሃ ተናገረች፡፡ ያን ጊዜ አንበሳው ደንግጦ ፈጥኖ ሸሸ፡፡ መነኩሴውም መንገዱን ቀጠለ፡፡ በመንገዱም ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ወጥተው ወንበዴዎች ሊቀሙትና ሊገድሉት ከበቡት፡፡ ከሥዕለ ማርያሟም እንደ መብረቅ ያለ ታላቅ ቃል ወጣ፡፡
ወንበዴዎችም እጅግ ፈርተው ሸሽተው ከጫካው ውስጥ ገቡ፡፡ ያም መነኩሴ እነኚህን የሚያስደንቁ ተአምራት በተመለከተ ጊዜ በልቡ «ለእኔ ረዳት ትሆነኝ ዘንድ ወደ ሀገሬ ይዣት እሄዳለሁ እንጂ ለላከችኝ ሴት አልሰጥም» ብሎ ወደ ሀገሩ ሊሄድ በመርከብ ተሳፈረ፡፡ በባሕር ላይም ሳለ ጽኑ ነፋስ ተነስቶ መርከቡን እየገፋ ማርታ ወዳለችበት ሀገር ወደ ጽዴንያ ዳርቻ አደረሰው፡፡ ማደሪያም ስለሌለው ወደ ደጓ ሴት ወደ ማርታ ቤት ከእንግዶች ጋር አብሮ ገብቶ አደረ፡፡ ሲነጋ ወጥቶ ሊሄድ ከደጃፍ ሲደርስ ደጃፉ ጠፍቶት ከአጥሩ ሲታገል ዋለ፡፡ ማርታም «አባቴ ያመመህ የደከመህ ትመስላለህ ዛሬ ደግሞ እዚህ እደርና ነገ ትሄዳለህ» አለችውና አደረ፡፡ በሁለኛውም ዕለት እንደ መጀመሪያው ቀን በሩን አልፎ መሄድ አቃተውና እዚያው ማርታ ቤት አደረ፡፡ በሦስተኛው ቀን መውጣት ፈልጐ አሁንም ከአጥሩ ጋር ሲታገል አይታ «አባቴ የሆንከው ምንድነው? እነሆ ዛሬ ሦስተኛ ቀንህ ነው» አለችው፡፡
መነኩሴውም «ይህችን ተአምረኛ ሥዕል አልሰጥም ብዬ ነው፡፡ እኔኮ ሥዕል ከኢየሩሳሌም ግዛልኝ ያልሽኝ መነኩሴ ነኝ» ብሎ ሥዕለ ማርያምን አውጥቶ ሰጣት፡፡ እርሷም እጅግ በጣም ተደስታ እግዚአብሔርን አመሰገነች፡፡ በሥዕሏም ፊት ሰግዳ ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ምስጋናን አቀረበች፡፡ ተቀብላም ሥዕል ቤት አሠርታ በክብር አስቀመጠቻት፡፡ ይህችም ሥዕል ቅዱስ ሉቃስ የሳላት ናት፡፡ ሥጋ የለበሰች ትመስላለች፡፡ ከፊቷም ወዝ ይንጠባጠባል፡፡ በዚህችም ሥዕል ብዙ ተአምራት ተደረገ ሕሙማን ተፈወሱ፣ ዐይነ ስውራን ማየት ቻሉ፡፡ በዚያ ዘመን የነበረው ሊቀ ጳጳስ ተአምሯን ሰምቶ ሥዕሏ ወደ ማርታ ቤት የገባችበት ዕለት መስከረም ፲ ቀን እንዲከበር ሥርዓት ሠራ፡፡ ይህም በዓል በቤተ ክርስቲያናችን ሁልጊዜ ይከበራል፡፡
የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ ፍቅሯን ጣዕሟን ታሳድርብን፣ ልጇ አምላካችን በጸሎቷ ይማረን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

💠የመንፈስ ፍሬዎች💠

፪. ደስታ

✞ ደስታ በምናየውና በምንሰማው፣ በምንቀምሰው ነገር በተፈጸሙ ክስተቶች የሚሰማን የህሊና እርካታ ነው፡፡ በክርስቲያናዊ ሕይወት ደግሞ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ከእግዚአብሔር ጋር በመኖር የሚገኝ መንፈሳዊ የርካታ ስሜት ነው፡፡ ደስታችንም የሚፈጸመው በዓለም ከሚገኘው ጊዜያዊ ደስታ በተለየ መልኩ ነው፡፡
✞ አራት ዓይነት ደስታዎች አሉ። እነዚህም:-
፩) ፍሥሓ መላእክት
፪) ፍሥሓ ኖሎት
፫) ፍሥሓ ቍንጽል (የቀበሮ ደስታ)
፬) ፍሥሓ መስቴማ ናቸው።

◈ ፍሥሓ መስቴማ ማለት የሰይጣን ደስታ ማለት ነው። ሰይጣን ሌሎች ሰዎች ሲሳሳቱ፣ ሲወድቁ፣ ሲሞቱ፣ ሲጎዱ በጣም ይደሰታል። በሌሎች ሰዎች ኀዘን እና ጉዳት የሚደሰቱት ደስታ የሰይጣን ደስታ ይባላል።
◈ ሁለተኛው የደስታ ዓይነት የቀበሮ ደስታ ነው። ቀበሮ የጣዝማ ማር ስታገኝ ከደስታዋ ብዛት የተነሳ ማሩ እስኪጠፋት ትዘላለች። የደስታዋ ምንጭ የሚበላ አገኘሁ ብላ ነው። የሰው ልጅ በሥጋዊ ነገሮች የሚደሰተው ደስታ የቀበሮ ደስታ ይባላል።
✞ ሦስተኛው ደስታ የእረኞች ደስታ ነው። እኒህም ጌታ በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ የተደሰቱት ደስታ ነው። ይህ ደስታ ነፍሳዊ ደስታ ነው። በጌታ መወለድ በሲኦል ተግዞ የነበረ አዳም ወደ ገነት የሚመለስበትን የምሥራች ከመልአኩ የሰሙበት ነውና። እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘይከውን ፍሥሓ ለክሙ እንዲል።
የመላእክት ደስታ የፍጹማን ደስታ ነው። መላእክት አንድ ኃጥእ ንሥሓ በገባ ጊዜ በሰማያት ታላቅ ደስታ ይሆናል ተብሎ የተነገረላቸው ናቸው። የመላእክትደስታ ከግላዊ ጥቅም የተለየ ደስታ ነው። ሌላው ሲጠቀም፣ ሌላው ሲያገኝ፣ ሌላው ሲሾም፣ ሌላው ሲደሰት የሚደሰቱት ደስታ ነው።

✞ እንግዲህ ገላ. ፭፣፳፪ ደስታ የመንፈስ ፍሬ ነው የተባለው በሁለቱ ዓይነት ደስታዎች ነው። እነዚህም ፍሥሓ ኖሎት እና ፍሥሓ መላእክት ናቸው። ትክክለኛው ደስታ የሚገኘው በቁስ አይደለም። በእግዚአብሔር ነው። መዝ. ፺፬፣፩ "ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን" ተብሏል። ቅዱስ ጳውሎስም በመልእክቱ ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ብሏል። በሌላ ቦታ ቅዱስ ዳዊት "ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ" ብሏል። ደስታ የሚገኘው ከእግዚአብሔር ቤት ነውና። ደስታ የራቃችሁ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ። ያን ጊዜ ደስ ይላችኋል። ሰማእታት እየተገደሉ ግን ደስተኞች ነበሩ። ለምንድን ነው ስንል የደስታቸው ምንጭ እግዚአብሔር ስለሆነ ነው። እግዚአብሔር ደግሞ ሕይወተ ሕይወት ብርሃነ ብርሃን መሠረተ መሠረት ስለሆነ ነው። ደስታችንን በእግዚአብሔር እናድርግ።

👉'ሰላም' ይቀጥላል ..............

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ፍቅርን ከክርስቶስ"

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መስከረም ፬
ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ

መስከረም አራት በዚህች ዕለት ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ከእናቱ ማርያም ባውፍልያ ከአባቱ ዘብዴዎስ የተወለደበት ዕለት እንደሆነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌልን ለመስበክ ዕጣ የደረሰው እስያ ስለነበር ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን አስከትሎ ሄደ፡፡ ይኽችውም ኤፌሶን በጥንቱ በታናሽ እስያ በዛሬው የቱርክ ግዛት ውስጥ ከተማ ናት፡፡ ዛሬ ኢያዞሎክ ተብላ የጥንት ታሪኳ ጠፍቷል፡፡ አስቀድሞ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ሰብኮባታል፡፡ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ጢሞቴዎስንም በከተማዋ ላይ ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾሞት ነበር፡፡ እርሱም በግፍ እስከተገደለበት ጊዜ ድረስ ቅዱስ ዮሐንስን እየረዳው በከተማዋ ብዙ አገልግሏል፡፡ በኋላ ግን በግፍ ገድለውታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ኤፌሶን ለመሄድ በመርከብ ሲሳፈር መርከቡ በማዕበል ተሰበረ፡፡ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን መዕበሉ ወደ አንዲት ደሴት አደረሰው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በመርከቡ ስባሪ ተንጠልጥሎ በባሕሩ ማዕበል መካከል 40 ቀንና 40 ሌሊት ከኖረ በኋላ ማዕበሉ ተፍቶ አብሮኮሮስ ካለበት ደሴት አደረሰውና ተያይዘው ኤፌሶን ከተማ ገቡ፡፡ የከተማይቱም ሰዎች እጅግ ክፉዎች ስለነበሩ መጀመሪያ ላይ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ አልቻሉም ነበር፡፡ እነርሱም እጅግ ክፉዎች መሆናቸውን ስላወቀ ቅዱስ ዮሐንስ ገና ዕጣው ሲደርሰው በሀዘን አልቅሶ ነበር፡፡ አሁንም ከተማው በገቡ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ምክንያት በመፍጠር ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤቷ እሳት አንዳጅ ሆኖ አብሮኮሮስም ዕቃ አጣቢ ሆነው ተቀጠሩ፡፡ የቀጠረቻቸው ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ጀመር፡፡ ባሮቿ እንደሆኑ ተስማምተው ስለጻፉላት ትደበድባቸውም ነበር፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ዘከመ:መተሮ:ለዮሐንስ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

🌼 ዐውደ ዓመት 🌼
ዐውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ ዐውደ ዓመት:
ንዒ ማርያም ለምሕረት ወሣህል።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ዘመናት ሲቆጠሩ ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ እና ዘመነ ዮሐንስ ናቸው። ሁልጊዜም ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ ስንሸጋገር ጳጒሜን 6 ትሆናለች። ይህ እንዴት ሆነ?
3ቱ ዓመታት ( ዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ) 365 ቀናት ከ6 ሰዓት ይይዛሉ። ስለዚህ የሦስቱ ዓመታት የ6 ሰዓታት ጥርቅም 18 ይሆናል። ዘመነ ሉቃስ ተገባዶ ወደ ዘመነ ዮሐንስ ስንሸጋገር 18+6=24 ሰዓት ( አንድ ቀን) ይሆናል። ስለዚህ በየአራት ዓመቱ ጳጉሜን 6 ትሆናለች። በፈረንጆቹ leap year ይሉታል እሱም February ወር 29 ቀናትን ይይዛል ። በእኛ መጠነ ራብዒት ማለትም ዘመነ ዮሐንስ የሚውልበት ነው።
ቀደምት አባቶች ጳጒሜን 7 ቀናትን የምትይዝበት ዓመት እንዳለ ጽፈው አስቀምጠዋል። ይህም በ600 ዓመት አንዴ ይከሰታል። በቀን በ24 ሰዓታት ውስጥ ተጨማሪ 0.4 ሰከንድ አለ። ሪና መዐልትና ሪና ሌሊት የሚል ሌላም ስሌት አለ። በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር አንድ ዓመት 365 ቀናት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት ወይንም 365 ቀናት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ነው። ስለዚህ 2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ተጠራቅሞ ጳጒሜን 7 ያደርጓታል። ካልዒት ማለት 24 ሰከንድ ማለት ነው። የ5 ዓመት 30 ካልዒት የ10 ዓመት 60 ካልዒት ነው። 60 ካልዒት ደግሞ 24 ሰከንድ ነው። የ100 ዓመት 240 ሰከንድ ወይም 10 ኬክሮስ የ200 ዓመት 20 ኬክሮስ፣ የ300 ዓመት 30 ኬክሮስ፣ የ400 ዓመት 40 ኬክሮስ፣ የ500 ዓመት 50 ኬክሮስ፣ የ600 ዓመት 60 ኬክሮስ። 60 ኬክሮስ 1440 ደቂቃ ወይም 24 ሰዓት ይሆናል።ስለዚህ በ600 ዓመት አንድ ጊዜ ጳጒሜን 7 ይሆናል።

ባሕረ ሐሳብ ማለት ምን ማለት ነው?
ባሕረ ሐሳብ ማለት ቁጥር ያለው ዘመን ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽም የሐሳብ ባሕር ማለት ነው፡፡ በዓላት እና አጽዋማትን ለማውጣት የመደመር፣ የመቀነስ፣ የማባዛት ስሌትን ብቻ ሳይሆን ሐሳበ ፀሐይን፣ ሐሳበ ወርኅን፣ ሐሳበ ከዋክብትን ሐሳበ ዐበቅቴን ወዘተ አጠቃሎ የያዘ እንደ ባሕር የሰፋ በመሆኑ የሐሳብ ባሕር ተብሏል፡፡ የዘመን አቈጣጠር ማለት ስለማሕበራዊ ኑሮ ጠቄሜታና የሃይማኖት ተግባሮች ለማከናወን በሚያገለግል መልኩ ተፈጥሮአዊውን የወቅቶች ክፍፍል እርስ በርሳቸው የማመቻቸት ዘዴ ነው፡፡
ሐሳበ ዘመን የዘመን አቆጣጠር ማለት ሲሆን የሐሳበ ዘመን ትምህርት ባሕረ ሐሳብ ይባላል፡፡ ባሕረ ሐሳብ የሚለው ቃል ሐሰበ ቆጠረ ከሚለው ግስ የወጣ ዘመድ ዘር ነው፡፡ ስለዚህ ባሕረ ሐሳብ ማለት ቁጥር ያለው ዘመን ወይም ዓመተ ዓለም ማለት ነው፡፡ ባሕረ ሐሳብ
መባሉም የባሕር አዝዋሪቱ፣ መንገዱን፣ ጥልቀቱና ስፋቱ ረዥምና ሰፊ እንደሆነ የባሕረ ሐሳብ ትምህርትም መንገዱን ስፋቱ ልዩ ልዩ በሆነ የአጽዋማትና የሱባዔያት ምሥጢር የተሰናዳ ስለሆነ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር /የጊዜ ቀመር/ አንድ ዓመት በውስጡ ዐሥራ ሦስት ወራትን የያዘ ሆኖ በአራት ወቅቶች የተከፈለ ነው፡፡
አራቱ ክፍላተ ዘመን የሚባሉት፡-
ክረምት ከሰኔ 26 ቀን - መስከረም 25 ቀን፣
መፀው /መከር/ ከመስከረም 26 ቀን - ታኅሣሥ 25 ቀን፣
በጋ / ሐጋይ/ ከታኅሣሥ 26 ቀን - መጋቢት 25 ቀን፣
ጸደይ / በልግ/ ከመጋቢት 26 ቀን - ሰኔ 25 ቀን ናቸው፡፡

ከክረምት በስተቀር እያንዳንዱ ወቅት በውስጡ ዘጠና ዘጠና ቀናት ይዟል፡፡ ክረምት ግን ለብቻው 95 ቀናትን የያዘ ነው፡፡

2. አራቱ ክፍላተ ዘመን
የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች ጊዜ፣ ወር፣ ዘመን አላቸው፡፡ አንድን ዓመት በአራት ክፍለ ዘመን በመክፈል ድርሰቱን ውሱን አድርጎታል፡፡ ዘመኑም እንዲሁ በድርሰቱ የተወሰነ ሆኗል፡፡ እነዚህም ዘመናት ዘመነ መፀው፣ ዘመነ ሐጋይ፣ ዘመነ ጸደይ፣ ዘመነ ክረምት በመባል ይታወቃሉ፡፡

2.1. ዘመነ መፀው
መፀው በሌላ አነጋገር ጥቢ ይባላል፡፡ እንደ ሌሊት ከብዶ የሚታየው ክረምት አልፎ መስከረም ከጠባ በኋላ በ4ኛው ሳምንት ስለሚጀምር ነው ጥቢ የሚባል ተጨማሪ ስያሜ የተሰጠው፡፡
ዘመነ መፀው ከመስከረም 26 እስከ ታኅሣሥ 25 ድረስ ያለው ጊዜ ነው፡፡ የዕለቱ ቁጥርም 90 ይሆናል፡፡ ከዘመነ ክረምት ቀጥሎ በመሆኑ ዘመነ ክረምትን በማስቀደም ጽጌንና መፀውን በማስተባበር ቅዱስ ያሬድ የሚከተለውን ብሏል፡፡ “ግሩም በሆነው ኃይልህ እንመካ ዘንድ አንተ ዘመናትን ሠራህ ክረምትን ለዝናባት መፀውን ለአበቦች
ሰጠህ” ድጓ ዘጽጌ ኩፋሌ 2 ኢዮ.2÷23 ኤር.5፥24/

መፀው መሬት በክረምት የተሰጣትን ዘር አበርክታ፣ አብዝታ ለፍሬ የምታደርስበት የምርት ወቅት ነው፤ መፀው በአብዛኛው የአዝመራ መሰብሰቢያ ጊዜው ነው፡፡ በዚህ ክፍለ ዘመን በዋናነት ሦስት ወራት ያገኛሉ፤ እነርሱም ጥቅምት፣ ኅዳርና ታኅሣሥ ናቸው፡፡ ይህ ወቅት
በኢትዮጵያ ምድር አበቦች በየሜዳው በየሸንተረሩና በየተራራው ፈክተው የሚታዩበት አዝርእት የሚያሸቱበትና ለፍሬ የሚበቁበትን ወራት ይዞ ይገኛል፡፡

2.2. ዘመነ ሐጋይ /በጋ/
ዘመነ ሐጋይ ይህ የበጋ ወቅት ነው፡፡ “ሐጋይ”…. በጋ ሆነ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው፡፡ ይህም ከታኅሣሥ 26 እስከ መጋቢት 25 ቀን ያለውን ጊዜ ያጠቃልላል፡፡ ሐጋይ በጋ የጥርን፣ የየካቲትንና የመጋቢትን ወር ይይዛል፡፡
ዘመነ ሐጋይ የቃሉ ትርጓሜ ዘመነ ፀሐይ ማለት ሲሆን ሥርወ ቃሉም ኃገየ … ከሚለው ግዕዝ የተገኘ ነው፡፡ ከአራቱ ክፍላተ ዘመን አንዱ እጅ ወይም አንድ አራተኛው ሐጋይ ይባላል፡፡ የሐጋይ ፍቺ በጋ እንደሆነ ሁሉ እንዲሁም መፀውም ጸደይም በእርሱ ስም በጋ ይባላሉ፡፡
“ዘጠኝ ወር በጋ” እንዲሉ፣ አንዳንድ ጊዜም መጽሐፍት በሁለት ከፍለው ይናገራሉ፡፡ “ክረምትና በጋን አንተ ሠራህ” ፤ “በበጋም በክረምትም እንዲህ ይሆናል” / መዝ.75፥17፣ ዘካ.14፥10፣ ዘፍ.10፥22/ እንዲል
ኃጋይ ማለት መገኛ መክረሚያ በጋ፣ ፀደይ፣ ደረቅ ወቅት ነው፡፡ በዚህ ወቅት በመፀው ያሸተውና ያፈራው መኸር የሚታጨድበት፣ የሚሰበሰብበትና በየማሳው ከተከመረ በኋላ የሚበራይበት፣ በጎተራ የሚከተትበት በመሆኑ “የካቲት” የሚለውን ወር ይዞ እናገኘዋለን፡፡ የግብርናው ኅብረተሰብ እህሉን በጎተራው ከትቶ ለተወሰነ ጊዜ
የሚያርፍበት በመሆኑ የዓመት በዓላት እንደ ልደት፣ ጥምቀት ያሉት፣ ዘመነ መርዓዊ የሚባለው የጋብቻ ዘመን በዚህ ወቅት የተካተቱ ናቸው፡፡

2.3. ዘመነ ጸደይ /በልግ/
ዘመነ ጸደይ ማለት የቃሉ ትርጉም ዘመነ በልግ (የበልግ ዘመን) ማለት ነው፡፡ ጸደይ በበጋና በክረምት መካከል የሚገኝ በውስጡ የሚያዝያን፣ የግንቦትንና የሰኔ ወራትን የያዘ ክፍለ ዘመን ነው፡፡ በመሆኑም ጸደይ የሌሎች ወቅቶችን ባሕርያት አሳምሮ የያዘ ነው፡፡ ምክንያቱም በአንድ በኩል የበልግ አዝመራ የሚታጨድበት የሚወቃበትና የሚዘራበት ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለክረምት የሚዘራ ማሳ የሚታረስበት /ለዘር ዝግጁ የሚሆንበትን ጊዜ ነው፡፡ በአብዛኛው ግን ዘመነ በልግ ነው፡፡
ቅዱስ ያሬድ በድጓው “ይሁብ ዝናመ ተወን” የበልግ ዝናምን ይሰጣል እንዳለው የበልግ ወቅት ነው፡፡ ይህም ወቅት በልግ አብቃይ በሆነው የሀገራችን ክፍል የበልግ አዝመራ የሚዘራበት፣ በልግ አብቃይ ባልሆነው ክፍል ደግሞ መሬት ለክረምቱ የዙር ጊዜ የሚያዘጋጅበት ነው፡፡
“አንድ ሰኔ የነቀለውን ሁለት ሰኔ አይተካውም” እንደሚባለው የግብርናው ኅብረተሰብ ቀጣይ የግብርና ሥራውን በትጋት የሚሠራበት ወቅት ነው፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"እግዚአብሔር ፈዋሽ"

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ይህች ቤተ ክርስቲያንም ከመሰረቷ አናወጻት፡፡ ያን ጊዜ ትልቁም ትንሹም ወንዱም፣ ሴቶችም፣ የተሾሙ ዲያቆናት፣ ካህናት፣ ሕዝቡም ሁሉ ደነገጡ ታወኩ፡፡ ዓሣ አንበሪው ግን መንቀሳቀሱን አልተወም፡፡ በመንቀሳቀሱም የቤተ ክርስያኗ ሕንፃ እኩሌታ ይሰነጠቅ ዘንድ ጀመረ፣ ምድርም ተናወፀች፣ ንጉሱና፣ ሊቀ ጳጳሳቱም፣ ካህናቱም፣ ዲያቆናቱም፣ ህዝቡም፣ ሁሉም ካሉበት በባህሩ ወደብ ከተሰራች ከዚህች ቤተ ክርስቲያን መናወጥ የተነሳ ፍርሃት መንቀጥቀጥ በላያቸው ወረደ፡፡ ያ አንበሪ ግን በባህሩ ውስጥ ወደፊት መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗም በጀርባው ላይ ነበረች፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ያሉትም ሁሉ ያ ዓሣ አንበሪ ወደ ባሕሩ ውስጥ ሊያሰጥመን ነው ሲሉ አሠቡ፡፡ ያን ጊዜም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ስዕል ፊት በጽኑ አለቀሱ፡፡ በአንድ ቃልም "ገናናው የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ ርዳታህ ፈጥኖ ይደርስልን ዘንድ በቅድስት ቤተክርስቲያን ወደተሰበሰብን ወዳጆችህ ተመልከት" እያሉ ይጸልዩ ጀመር፡፡ ያንጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሰማይ ወርዶ ያችን ቤተክርስቲያን በብሩሃት ክንፎቹ እንደደመና ጋረዳት፡፡ በእጁ በተያዘ የብርሃን በትረ መስቀሉ ያን ዓሣ አንበሪ ወግቶ "በኢየሱስ ክርስቶስ ሃይል ከቦታህ ሳትንቀሳቀስ እስከትውልድ ፍፃሜ ዘመን ለዘለዓለም ትኖር ዘንድ አዝዝሃለሁ" አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያኗን ከነመዓዘኗ ከግርግዳዎቿ ከመሠዊያዋ በውስጧ ተተክለው ካሉት ሁሉ ጋር ከጀርባው ላይ እያለች ያንን ዓሣ አንበሪ ወግቶ በያዘበት ብርሃናዊ በትረ መስቀሉ ወደቀድሞው የባሕሩ ወደብ ጎተተው፡፡ ያንጊዜም ግንቡ ቦታውን ሳይለቅ እርስ በእርሱ ተጣበቀ፡፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ዓሣ አንበሪውን በቀድሞ ሥፍራው ያቺን ቤተክርስቲያን በቀደመ መሠረቷ ላይ አጽንቷቸዋልና፡፡ ሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤልም አዳኝ የሆነ የጌታው የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ጠርቶ ከሞት እንዳዳናቸው ሁሉም አስተዋሉ፡፡ በድንቅ ተዓምራቱ የዳኑ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ በሊቀመላእክቱ ቅዱስ ሩፋኤል ላይ አድሮ ድንቅ ተዓምራቱን ስለገለጸላቸው የቅዱስ ሩፋኤልን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ የዚህች ቤተክርስቲያን ታሪክም በዓለም ሁሉ በየአውራጃዎቹም ተሰማ፡፡ የቅርብም የሩቅም ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው ታላቁ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል የለመኑትን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ የነገሩትን ያማልዳቸው ዘንድ በውስጧ ይጸልያሉ፡፡ በዚችም ቤተክርስትያን ብዙ ውስጥ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ታኅሣሥ 13 ቀንም ተአምራቶቹ ከተፈጸመባቸው ዕለታት አንዷ ናት፡፡ ቅዳሴ ቤቱም በዚሁ ዕለት ተከናውኗል፡፡

በዚኽች ዕለት ታስበው የሚውሉት ቅዱሳን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል፣ የካህኑ መልከጼዴቅ፣ የአቡነ ሰራጵዮን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

አምላክ ሆይ ማረን
እውነተኛው ንጉሥ ለፍርድ ሲመጣ
ጻድቁን ሊያከብር ኃጥኡን ሊቀጣ
መለከት ሲነፋ ነጐድጓድ ሲሰማ
ክርስቶስ ሲገለጥ በሚያስደንቅ ግርማ 
    አምላክ ሆይ ማረን 
    ማረን አምላክ ይቅር በለን
የነበረው ሁሉ ሲሆን እንዳልነበር
ተነሥተው ሲቆሙ ሙታን ከመቃብር
ፀሐይ ስትጨልም ሰማያትም ሲያልፉ
ምድር ቀውጢ ስትሆን ቀላያት ሲጠፉ
     አዝ---
ፍጥረት ሲናድ ዲርስ ግርማ እያስፈራው
የአዳም ዘር በሙሉ ሲቆም ከነሥራው
ማነው የሚገኘው በጐ ምግባር ሠርቶ
ቅዱሳንን መስሎ በሃይማኖት ጸንቶ
   አዝ---
በምድራዊ ሕይወት ትሩፋት የሠሩ
ጻድቃን ሲደሰቱ ተግተው ሲዘምሩ
ኃጥአን ሲጠፋቸው የሚሰወሩበት
እኛስ ከየት ይሆን የምንገኝበት

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…
Subscribe to a channel