በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
ስለ ስደት የበገና መዝሙር
በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።
የአራተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ
🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀
ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
........................................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም ፣
ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፡፡
መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢት ዓለም ፣
መልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም ፣
እም አምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም፡፡
ዚቅ:
ፈጠርካሆሙ ለመላእክት ከመ ይትለአኩከ ፣
ግብረ እደዊከ አዳም አሠርጎከ ለሰማይ በከዋክብት ፣
ወለምድርኒ በስነ ጽጌያት ፣
ግብረ እደዊከ አዳም ፣
እግዚኦ ፈድፋደ ቃልከ ጥዑም ፡፡
ማኅሌተ ጽጌ:
ናሁ ጸገየ ወወሀበ መዓዛ ፣
ተአምርኪ ናርዶስ ለቤተክርስቲያን ዘይውሕዛ ፡፡
እንዘ ታረውጽኒ ቦቱ ማርያም ፍኖተ ቤዛ ፣
አጉይዪኒ ከመ ወይጠል ወከመ ኃየል ወሬዛ ፣
እምገጸ ኃጢአት አጎተ አርዌ ዘይቀትል ኀምዛ፡፡
ትርጉም፦ ቤተክርስቲያንን የሚያስጌጣት ናርዶስ የተባለ ተዓምርሽ እነሆ አብቦ መዓዛን ሰጠ ማርያም ሆይ በድኅነት ጎዳና እያስሮጥሽኝ እንደ ፌቆና እንደ ዋልያ አውራ አሽሺኝ፡፡
ወረብ:
ናሁ ጸገየ ወወሀበ መዓዛ ተአምርኪ ናርዶስ (2) ይሐውዛ ለቤተክርስቲያን (2)
እንዘ ታረውጽኒ ቦቱ ፍኖተ ቤዛ (2) ማርያም ፍኖተ ቤዛ (2)
ዚቅ:
ነፍሳተ ጻድቃን እውያን አመ ይሁቡ መዓዛ ፣
ለዘምግባረ ጽድቅ አልብነ ይኩነነ ቤዛ ፣
ንግደትኪ ማርያም እስከ ደብረ ቁስቋም እምሎዛ፡፡
ማኅሌተ ጽጌ:
እእሚርየ ማርያም ከመ ዘልፊ ታፈቅሪ ፣
ሰላም መልአከ ለኪ አንተ ጽጌረዳ ትፈሪ፡፡
ለለአማኅኩኪ ባቲ ከመ ገብርኤል አብሣሪ ፣
አፈዋተ ጽጌ እምልሳንየ ትፀርሪ ፣
ትእምርቶ ለሠናይትኪ ምስሌየ ግበሪ ፡፡
ወረብ:
እእሚርየ ማርያም (ከመ) ዘልፊ ታፈቅሪ ሰላመ መልአክ (2)
አንተ ጽጌረዳ ትፈሪ ሰላመ (2) መልአክ (2)
(ለለአማኅኩኪ ከመ ገብርኤል አብሣሪ አፈዋተ ጽጌ (2) )
ዚቅ:
ሃሌ ሉያ ጸረሐ ገብርኤል ልዑለ ቃል ወይቤ ፣
ጽገዩ ገዳም ተፈሥሒ ገዳም ፣
እስመ ናሁ ናርዶስ ወሀቦ መዓዛሁ ፡፡
ማኅሌተ ጽጌ:
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስት ወራብዕተ ፣
ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ ፣
ካዕበ ትመስል ሰብእተ ዕለተ ፣
እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ ፣
ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኩ ዕረፍተ ፡፡
ትርጉም፦ ማርያም እናትሽ አበባን ያስገኘች ሦስተኛይቱ ቀን ማክሰኞን ትመስላለች ዳግመኛም ሰባተኛይቱ ቀን ቀዳሚትን ትመስላለች በሰማይና በምድር ላሉ ፍጥረታት ዕረፍት የሆንሽ የነፃነት ምልክት አንቺን አፍርታለችና አስገኝታለችና፡፡
ወረብ:
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እምኪ (2)
ዘወለደት ጽጌ (2) ወፀሐየ ዓለም (2)
ዚቅ:
እምኩሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ፣
ወእምኩሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ፣
ከመ ትኩኖ ማሕደረ ለመንፈስ ቅዱስ ፣
ወምስጋድ ለኩሉ ዓለም፡፡
ወረብ:
እምኩሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ (2)
ወእምኩሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ከመ ትኩኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ (2)
ማኅሌተ ጽጌ:
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፣
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ ፡፡
ትርጉም፦ ነጭና ቀይ መልክ ያለው አበባ ልጅሽን ታቅፈሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ርግቤ ከሐዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነይ የእኔ አዛኝ ደስ ካለው ከገብርኤል እንደ አንቺ ሩኅሩኅ ከሚኾን ከሚካኤል ጋር ነይ፡፡
ወረብ:
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ (2)
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ ሠናይትየ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ (2)
ዚቅ:
ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን ፣
ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን ፣
ንዒ ርግብየ ሠናይት ፣
ወይቤላ መልአክ ተፈሥሒ ፍሥሕት ፣
ቡርክት አንቲ እም አንስት ፣
ንዒ ርግብየ ሠናይት፡፡
ወረብ:
ንዒ ርግብየ (2) ምስለ ሚካኤል (2)
ወንዒ ሠናይትየ (2) ምስለ ገብርኤል ፍሱሕ (2)
ማኅሌት
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፣
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፣
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፣
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፣
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
ትርጉም፦ በስሙ ምልክትና የሞቱ መታሰቢያ የታነፀብሽ ከሚያበራ ወርቅ ይልቅ እንደ ዕንቁ የጠራ ንጽህና ያለሽ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ኹሉን ለእርሱ ታሰግጂለታለሽ እርሱም ለአንቺ ይሰግዳል፡፡
ወረብ:
ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየኀቱ እምዕንቁ ባሕርይ (2)
ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀፀላ መንግሥቱ (2)
ዚቅ:
ይእቲ ተዓቢ እም አንስት ፣
አሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት ፣
መድኃኒቶሙ ለነገሥት አክሊል ንፁህ ለካህናት ፣
ብርሃኖሙ ለከዋክብት፡፡
ወረብ:
ይእቲ ተዓቢ እም አንስት እሞሙ ለሰማዕት ተዓቢ (2)
መድኃኒቶሙ ለነገሥት ፋሲለደስ ወኢያሱ መድኃኒቶሙ (2)
ሰቆቃወ ድንግል:
አይቴኑ መልአክ ዘአብሠረኒ ፣
ብካይየ ይርአይ ወይርድአኒ ፣
ወአልብየ ሰብእ ዘየአምረኒ ፣
እንዘ ትብሊ ድንግል እራኅራኅከኒ ፣
በገዳም አመ ነሥኡኪ ልብሰ ወልድኪ ረቡኒ ፣
ጸላኢ ወተቃራኒ ፈያታይ ማኅዘኒ ፡፡
ወረብ:
አይቴኑ መልአክ ዘአብሰረኒ (2) ገብርኤል ወይርድአኒ (2)
እንዘ ትብሊ ድንግል እራኅርከኒ አልብየ ሰብእ ዘየአምረኒ (2)
ዚቅ:
አመ ወጽአት በፍርሃት እም ሀገረ ዳዊት ዘይሁዳ ፣
በብሥራተ መልአከ እንግዳ ፣
ኢረከበት ማየ በፍኖት ዘታሰቅዮ ለወልዳ፡፡
መልክአ ውዳሴ:
ለኪ ይደሉ ውዳሴ ወስባሔ ፣
በአፈ መላእክት ወሰብእ እለ ይነብሩ ውስተ ኩለሄ ፣
ማርያም ድንግል ማርያም አመ ኤሎሄ ፣
ከመ ሰብሐዊ ፍቁርኪ አቀረብኩ እማኄ ፣
ለዝክረ ስምኪ ዘይምዕዝ እምርኄ፡፡
ዚቅ:
ለኪ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወስግደት ፣
እምኀበ ሰብእ ወመላእክት ፡፡
መዝሙር:
ሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት ፣
ኩሉ ነባሪ ወቀናዪ ያዕርፉ ባቲ ፣
ግብረ እደዊከ አዳም ፣
ለሐኮ ለሰብእ በአርአያከ ወበአምሳሊከ ፣
ግብረ አደዊከ አዳም ፣
ፈጠርካሆሙ ለመላእክት ከመ ይትለአኩከ ፣
ግብረ እደዊከ አዳም ፣
አሠርጎከ ለሰማይ ወለከዋክብት ፣
ወለምድርኒ በስነ ጽጌያት ፣
ግብረ እደዊከ አዳም ፣
እግዚኦ ፈድፋደ ቃልከ ጥዑም፡፡
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
#ዘጠኙ ቅዱሳን
(በ5ኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ ክርስትናን ለማስፋፋት የተሰደዱ ክርስቲያን ሚሲዮናውያን)
ዘጠኙ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት አከፋፈል መሰረት “ ጥንታዊው የታሪክ ዘመን” ተብሎ በሚጠራው ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ዘጠኝ የውጭ ሀገር ታላላቅ የክርስትና ሃይማኖት አባቶች ናቸው ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ የሆነ መንፈሳዊ አስተዋጽኦን ማለትም በመንፈሳዊ ህይወት ፣ በስብከተ ወንጌል፣ገዳማዊ እና የምንኩስና ሕይወትን በማስፋፋት ፣ መጽሐፍትን በመተርጎም፣ አበርክተዋል፡፡
ለአገራችን ሥነ-ፅሑፍ እድገት ጉልህ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ ከደጋግ ነገስታት ጋር በመሆን ለትምህርት ፣ ለማህበራዊ ኑሮ ወዘተ መሠረት የሆኑ ገዳማትን ከመመስረት ከቤት ክርስቲያን አልፎ ለአገራችን ኢትዮጵያ አያሌ አበርክቶት አድርገው አልፈዋል፡፡ በአገራችን ለቅድስናና ምንኩስና ፣ ለመፈንሳዊነት ትልቅ አብነት አላቸው፡፡ ከሮም ፣ ታናሽ እስያ፣ቁስጥንጥንያ ፣ ቂሳሪያ እና ሌሎች የእስያና ኤሮፓ አገሮች ቢመጡም ግዕዝን አጥንተው የአገሩን ባህልና አኗኗር ለምደው ክርስትናን በምድረ ኢትዮጵያ አስፋፍተዋል፡፡
ክርስትናን ወሰን አይገድበውምና ፣ ክርስቲያን ሃይማኖት እንጂ የድንበር አገር የለውምና የመጡበትን ቦታ ሳይሆን ህዝቡ መንፈሳዊ አባትነታቸውን ተቀብሎ! ቤተክርስቲያንም ውለታቸውን ቆጥራ የቅድስና ማዕረግ ሰጥታ ታከብራቸዋለች፡፡ ዕለት ተሰይሞላቸውም ክብር ይደረግላቸዋል፡፡
ከተለያዩ አካባቢ መምጣታቸውም ከየመጡበት አገር ወደ ግዕዝ መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ አያሌ መንፈሳዊ መጽሐፍትን እንዲተረጉሙ አስችሏቸዋል፡፡ በዚህች ትንሽ ርዕስ ስለተሰዓቱ ቅዱሳን ይህን ያክል ካነሳን በሚከተለው አንቀጽ ደግሞ ማንነታቸውን እናስተዋውቃችኋለን፡፡ ስም የመጡበት አገር የገደሙበት ቦታ የመታሰቢያቸው ቀን:-
፩- አቡነ አረጋዊ ሮም ደብረዳሞ ጥቅምት ፲፬
፪- አቡነ ጰንጤሌዎን ሮም አክሱም ጥቅምት ፮
፫- አቡነ የማታ ቆስይ ገርዓልታ ጥቅምት ፳፰
፬- አቡነ ገሪማ ሮም መደራ/ዓድዋ/ ሰኔ ፲፯
፭- አባ ጽሕማ አንጾኪያ እንደ አባ ድሕማ/ይዲያ ጥር ፲፮
፮- አባ አፍፄ ታናሽ እስያ የሓ ግንቦት ፳፱
፯- አባ ሊቃኖስ ቁስጥንጥንያ አክሱም ህዳር ፳፰
፰- አባ አሌፍ ቂሳርያ ደብረ ሃሌሉያ መጋቢት ፲፩
፱- አባ ጉባ ኪልቂያ አድዋ አጠገብ ግንቦት ፳፱
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የቅዱስ ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ መልእክት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጐጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ዓመቱን ጠብቆ ስለ አጠቃላይ ተልእኮአችን ለመወያየት በዚህ ጉባኤ የሰበሰበን አምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን፡፡
“ወይእዜኒ ግብኡ ኀበ ኖላዊሃ ወዓቃቢሃ ለነፍስክሙ፤ አሁንም ወደ እረኛችሁና ወደ ነፍሳችሁ ጠባቂ ተመለሱ” (1 ጴጥ 2÷!5)
ሁሉን የሚችል አምላካችን እግዚአብሔር በፍቅሩና በፍቅሩ መነሻነት ብቻ ፍጥረታትን በሙሉ እንደፈጠረ ቅዱስ መጽሐፍ ያስተምረናል፤ ከፈጠረም በኋላ የክብሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ወዶ ክብሩን አድሏቸዋል፡፡እግዚአብሔር ለፍጡራኑ ካደላቸው ነገሮች አንዱ በየዓይነታቸው ጠባቂና መሪ እያደረገ በፍጡራን ላይ ፍጡራንን መሾሙ ነው፤ ይህ ስጦታ በሰማይም ሆነ በምድር ላሉ ፍጥረታት የተሰጠ የሱታፌ መለኮት ስጦታ ነው፡፡
ይህም በመሆኑ ሁሉም ፍጡራን አራዊትም ሆኑ እንስሳት ይብዛም ይነስ ጠባቂና መሪ እንዳላቸው እናስተውላለን፤ በተለይም የፍጥረታት ቁንጮ የሆኑ መላእክትና ሰዎች መሪና ሹም እንዳሏቸው የማንክደው ሃቅ ነው፡፡ ቅዱስ መጽሓፍም ይህንን ደጋግሞ ያስረዳል፤ የነዚህ ሁሉ ላዕላዊ ጠባቂና መሪ ደግሞ እግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በፍጡራን ላይ ፍጡራንን ጠባቂዎች አድርጎ ሲሾም ፍጡራንን የክብሩ ተሳታፊ ለማድረግ እንጂ የእሱ ጥበቃ አንሶ ወይም ድጋፍ ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ፍጹምና ላዕላዊ የሆነ ጥበቃው ሁሉንም ያካለለ ነውና ከእሱ ቊጥጥርና ጥበቃ ውጭ አንድም ነገር እንደሌለ የምንስተው አይደለም ፡፡
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
በአምሳለ እግዚአብሔር በተፈጠረውና በክብር መልዕልተ ፍጡራን በሆነው ሰው ላይ በዚህ ዓለም የተሾሙ ሁለት አካላት አሉ፤ እነሱም የመንፈስና የዓለም መሪዎች ናቸው፡፡ በተለይም የመንፈስ መሪዎችና ጠባቂዎች የተባሉት በመንፈስ ቅዱስ ተሹመን በዚህ ክርስቶሳዊ ጉባኤ የተሰበሰብነው እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ነን፡፡
ይህ ጉባኤ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን መሪና ጠባቂ ነው፤ ከዚያም ባሻገር እንደ ቃሉ እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ቃሉን በመስበክ ፍጥረተ ሰብእን በሙሉ የመጥራት ተልእኮ ለእኛ የተሰጠ የቤት ሥራ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የተሰጠን ኀላፊነት እጅግ በጣም ታላቅ እንደመሆኑ የሚጠበቅብን ውጤትም በዚያው ልክ ትልቅ ነው፤ ብዙ ከተሰጠው ብዙ ይፈለግበታል ያለው የጌታችን አስተምህሮም ይህንን ያስታውሰናል፡፡
ሁላችን እንደምንገነዘበው አሁን የምንገኝበት ዘመን የጸላኤ ሠናያት መንፈስ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ከምንም ጊዜ በበለጠ ጦሩን ሰብቆ የተነሣበት ጊዜ ነው፤ አሁን ያለው ዓለም በሀገራችንም ሆነ በሌላው ክፍለ ዓለም ላሉ ኦርቶዶክሳውያን ከባድ ፈተና ደቅኖብናል፡፡
ክፉው መንፈስ የሰውን አእምሮ በማዛባት ምእመናንን በቅዱስ መጽሐፍና በሕገ ተፈጥሮ ከተመደበላቸው የጋብቻ ሕግ በማስወጣት እንስሳት እንኳ የማይፈጽሙት ነውረ ኃጢአት እንዲፈጽሙ በመገፋፋት ላይ ይገኛል፡፡ በአማንያን ልጆቻችን ላይም በረቀቀ ስልት ግድያ፣ እገታ፣ አፈና፣ የመብት ተጽዕኖ እና አድልዎ በማድረግ እንደዚሁም በአስመሳይ ስብከትና አምልኮ ጣዖትን በማለማመድ ሕዝቡ ሳይገባውና ሳይጠነቀቅ ከእግዚአብሔር መንግሥት እንዲወጣ እያደረገ ነው፡፡
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
ክፉው መንፈስ በተራቀቀና በተራዘመ ስልት ሊውጠን በተነሣ ልክ እኛም ከእሱ እጥፍ በሆነ መለኮታዊ ኃይል ልንመክተው ካልቻልን በፈጣሪም ሆነ በትውልድ እንደዚሁም በታሪክ ፊት በኀላፊነት መጠየቃችን አይቀርም፡፡ መከላከል የምንችለውም ችግሩን በውል ከመረዳት አንሥቶ ሕዝቡን በደምብ በማስተማርና በመጠበቅ እንደዚሁም ለመሪነታችን ዕንቅፋት ከሚሆኑን ዓለማዊ ነገሮች ራሳችንን በማራቅ ነው፡፡
ሕዝቡም በዚህ ዙሪያ ሊያደምጠንና ሊከተለን የሚችለው መስለን ሳይሆን ሆነን ስንገኝለት ነው፡፡ ሕዝቡ ሊከተለን የሚችለው እሱን በብቃት ለመጠበቅ ዓቅሙም ተነሣሽነቱም ቁርጠኝነቱም እንዳለን ሲመለከት፣ እንደዚሁም ከዕለት ተዕለት ተግባራችንና አኗኗራችን የሚያየው ተጨባጭ እውነታ ኅሊናውን ሲረታ እንደሆነ አንርሳ፡፡
የምናስተምረው ሌላ የምንሠራው ሌላ ከሆነ ግን ከሕዝቡ አእምሮ መውጣታችን እንደማይቀር መገንዘብ አለብን፤ በመሆኑም በሰብእናችን፣ በአስተዳደራችን፣ በአመራራችንና በጥበቃችን ሁሉ እንደቃሉና እንደቃሉ ብቻ ለመፈጸም መትጋትና በቁርጥ መነሣት ጊዜው አሁን ነው እንላለን፡፡ ይህ ሲሆን በምእመናንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት አስተማማኝና እንከን የለሽ ይሆናል፤ ይህ ከሆነ እውነትም የመሪነት፣ የእረኝነትና የመልካም ተምሳሌነት ኀላፊነታችንን በትክክል ተወጥተናል ማለት እንችላለን፡፡
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
የሰው ልጆች በዚህ ዓለም ሲኖሩ የተሟላ ሰላምና ጣዕመ ሕይወት ሊኖራቸው የሚችለው በመንፈሳዊ ኑሯቸው የተሻለ ነገር ስላገኙ ብቻ አይደለም፡፡ ሰዎች ከሥጋዊ ክዋኔም ጭምር የተፈጠሩ እንጂ እንደመላእክት ሥጋ የሌላቸው መንፈስ ስላይደሉ ለኑሮአቸውና ለሥጋዊ ክዋኔአቸው የሚሆን ነገር ያስፈልጋቸዋል፡፡ በዚህም ዓለማዊው አስተዳደር የተመቻቸ መደላድል ሊፈጥርላቸው ግድ ነው፤ ዓለማዊው አስተዳደርም የመለኮትን ተልእኮ ለመፈጸም የተሾመ ሹመኛ እንደመሆኑ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በትክልል መምራት ይጠበቅበታል፡፡ ምንም ቢሆን የተቀበለው ኀላፊነት የእግዚአብሔር ነውና በሚሠራው ሁሉ በሿሚው አምላክ ከመጠየቅ አያመልጥም፡፡
እኛም በዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ወኪሎች ስለሆንን ቢሰሙንም ባይሰሙንም ዓለማውያን ሹማምንትን የማስተማርና የመምከር ኀላፊነት አለብን፡፡ ይህ የሁለታችን ኀላፊነት እንደ እግዚብሔር ፈቃድ ስንፈጽም የሕዝብ ሰላምና በረከት፣ ፍቅና አንድነት፣ ዕድገትና ልማት በአስተማማኝ ሁኔታ ይረጋገጣል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም፤ አለመግባባት በዝቶአል፣ ማኩረፍና መቀያየም ሰፍቷል፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡
ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቷል፤ ይህ ለአንድ ሀገር ወይም ሕዝብ የውድቀት ምክንያት ከሚሆን በቀር ከቶውኑም የዕድገት ምልክት ሊሆን አይችልም፡፡
ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ክፉ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው በእኛው ልጆች በኢትዮጵያውያን መሆኑ ነው፤ ስለሆነም በከተማም፣ በጫካም፣ በገጠርም በየትኛውም ስፍራ የምትገኙ ልጆቻችን ምንም ይሁን ምን ሀገርንና ሕዝብን ከመጉዳት ተቆጠቡ፡፡
በተለይም ከቤተ ክርስቲያንና ከሀገር እንደዚሁም ሕዝቡን ከሚያገለግሉ ካህናትና ሲቪል ሠራተኞች እባካችሁ እጃችሁን አንሡ፤ ቤተ ክርስቲያን እኮ የእናንተና የሕዝቡ ሁሉ እናት ናት፤ በእናታችሁ ላይ መጨከንን እንዴት ተለማመዳችሁት? አሁንም ንስሐ ግቡ ያለፈው ይበቃል፡፡
መዝሙር ዘሳልስ ሰንበት
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እም፤
ዘወለደት ጽጌ(፫) ወፀሐየ ዓለም።
ሥላሴ ትትረመም
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"የአምላክ አቃቤ ሕግ"
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ጥቅምት ፳፯
መድኃኔዓለም ክርስቶስ
ጌታችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት::
¤ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::
ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት::
¤ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት::
¤ራሱንም በዘንግ መቱት::
¤እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::
¤በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት::
በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6666 ገረፉት::
ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: 6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት::
7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን ተናገረ:: ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ::
በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ::
11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ::
ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::
ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::
+በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱ ይማረን ለሀገራችን ሰላሙን ይላክልን፤ አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ማኅሌተ ጽጌ ዘሐምሳይ ሳምንት በዓለ ተክለሃይማኖት
🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀
ለማንኛውም ወርኃዊ እና ዓመታዊ ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
.....................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
ገባሬ ኩሉ-
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።
ዚቅ
ዛቲ ይእቲ እኅተ ትጉሃን መላእክት፤ ወለተ ኄራን ነቢያት፤ እሞሙ ለሐዋርያት፤ ሞገሶሙ ለጻድቃን ወሰማዕት።
ወቦ መልክዓ ሥላሴ(ሌላ)
ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ
ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤ወተክለ ሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዐጽሙ፡፡
ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ንዕዱ ማዕዶተ ንትካፈል ርስተ ኀበ ጽጌ ዘሠምረ ኀበ አስተዳለወ ዓለመ ክቡረ ምስለ ተክለሃይማኖት ንትፈሳሕ ሀገረ
ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፣ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ
ወረብ፦
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ገብርኤል ፍሡሕ ሊቀ መላእክት/፪/
ዚቅ፦
በሰላም ንዒ ማርያም፤ትናዝዝኒ ኃዘነ ልብየ፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሱራፌል ወኪሩቤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ኲሎሙ ቅዱሳን፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ወልድኪ አማኑኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ለናዝዞ ኩሉ ዓለም።
ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘይኀቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
ዚቅ፦
ሰአሊ ለነ ማርያም አክሊለ ንጹሐን ብርሃን ቅዱሳን።
ዓዲ ዚቅ፦
አክሊሎሙ ለሰማዕት ተስፋ መነኮሳት ሠያሚሆሙ ለካህናት፤ነያ ጽዮን መድኃኒት
ማኅሌተ ጽጌ፦
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማህበረ ጻድቃን ተወደሰ፤ ወፈድፋድሰ በላዕለ ኃጥአን ነግሠ፤ እስመ አንሥአ ሙታነ ወሕሙማነ ፈውሰ፤ ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ፤ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ
ወረብ፦
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማህበረ ጻድቃን ተወደሰ ተአምረ ፍቅርኪ/፪/
ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ/፪/
ዚቅ፦
ይዌድስዋ ኵሎሙ ወይብልዋ እኅትነ ነያ ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ በሰማያት ኵሎሙ መላእክት
ማኅሌተ ጽጌ፦
ለምንት ሊተ ኢትበሊ እምአፈ ኃጥእ ውዳሴ፤ ይበቁዓኒ ዘብየ እምአፈ ጻድቃን ቅዳሴ፤ጽጌ መድኃኒት ማርያም ዘሠረፅኪ እምሥርወ እሴ፤ እመ ተወከፍኪ ኪያየ አባሴ፤ተአምረኪ የአኵት ብናሴ
ወረብ-
ለምንት ሊተ ኢትበሊ ድንግል ውዳሴ እምአፈ ኃጥእ/፪/
ይበቁዓኒ ዘብየ ቅዳሴ እምአፈ ጻድቃን/፪/
ዚቅ፦
አዘክሪ ለኃጥአን ወአኮ ለጻድቃን አዘክሪ ለርሱሐን ወአኮ ለንጹሐን
ሰቆቃወ ድንግል
እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሔልዊ፤ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤ለክብረ ቅዱሳን በከመይቤ ኦዝያን ዜናዊ፤እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።
ወረብ
በከመ ይቤ ኦዝያን ኦዝያን ክብረ ቅዱሳን/፪/
እምግብጽ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡ/፪/
ዚቅ
ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን ጸዋዕክዎ
መዝሙር በ5-
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ጸገየ ወይን ወፈረየ ሮማን፤ወፈረዩ ኩሉ ዕጽወ ገዳም ቀንሞስ ዕቁረ ማየ ልብን፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ጸገዩ ጽጌያት ጸገዩ ደንጎላት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር በስነ ጽጌያት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ ምሕረት፤ማ፦ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ።
አመላለስ፦
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ወለመድኃኒት/፬/
©ያሬዳውያን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እም፤
ዘወለደት ጽጌ(፫) ወፀሐየ ዓለም።
ከአቡነ አረጋዊ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ የተገኘ በ፲፯ኛው ክፍለ ዘመን የተሳለ የቅዱሳኑ ምስል
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"አቡነ አረጋዊ"
ጽድቅህ ጠርቶናል አባትነትህ
በቅድስና ያማረ ሕይወትህ
ጌጥ ውበታችን አባ አረጋዊ
መናኝ መነኩሴ መልአክ ምድራዊ (፪)
ተቃኝተህ ስላደግክ በመንፈስ ቅዱስ
ወደ ፅርዕ ተጓዝክ ወደ አባ ጳኩሚስ
ተዘጋጅተህ ነበር ለችግር ፈተና
ዘሚካኤል አለህ ሰጥቶህ ምንኩስና (፪)
አዝ---
ለኢትዮጵያ ምእመናን አባት ተብለሃል
ወንጌል በማስተማር ብዙ አትርፈሃል
መጻሕፍት ተርጉመህ ያበረከትክ ለአበው
የአንተስ ትሩፋት እፁብ ነው ድንቅ ነው (፪)
አዝ---
የዓለም ጨው ሆነህ አጣፈጥካት ምድርን
በልባችን ሳልካት ቤተ ክርስቲያንን
ደብረ ሀሌ ሉያ ደብረ ዳሞ ቅድስት
የፈውስ ቦታ ናት መካነ ትኅርምት (፪)
አዝ---
ልክ እንደ አባቶችህ አስተዋይ ስለሆንክ
ገና ወጣት ሳለህ አረጋዊ ተባልክ
የሥጋን ሞት ሳታይ ተሰውረህ ከምድር
ብሔረ ሕያዋን ተቀላቀልክ በክብር (፪)
አዝ---
በቦሌ ደብረ ገነት ቅ/ጊዮርጊስ እና ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ጥቅምት ፲፬
ጻድቁ አቡነ አረጋዊ
‹‹ወበዛቲ ዕለት ኮነ ተዝካሩ ለዐብይ ወክቡር አቡነ አረጋዊ ዘይሰመይ ዘሚካኤል››
‹‹በዚህች ቀን የታላቁ እና የከበረ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዘሚካኤል የሚባለው መታሰቢያ ነው››
አባታችን ‹‹አቡነ አረጋዊ›› በሀገራችን ስም አጠራራቸው ከከበሩ አባቶች አንዱ ጻድቅ ናቸው፡፡ ጻድቁ የተወለዱት በ5ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አከባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው አባታቸው ንጉሥ ይስሐቅ እናታቸው ደግሞ ቅድስት እድና ይባላሉ፡፡ የተወለዱት ደግሞ በታላቋ ሮም ነው፡፡ ስማቸው ብዙ አይነት ነው ወላጆቻቸው ‹‹ ዘሚካኤል›› ሲሏቸው፣ በበረሀ ‹‹ገብረ አምላክ ››ተብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ደግሞ ‹‹አረጋዊ›› ይባላሉ፡፡ አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጽሐፍ ተምረዋልና ጠፍተው ገዳም ገቡ፡፡ በዚያም በገዳሙ ዳውንስ (ግብፅ) የታላቁ ቅዱስ "ጳኩሚስ" ደቀ መዛሙርት ሆነው ከነአባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል፡፡ ከመነኮሱ ከዓመት በኋላ ወደ ሀገራቸው ሮም ተመልስው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግሥት ስዎች ወደ ምናኔ ማርከዋል ፡፡
451 ዓ.ም በተካሄደው የኬልቄዶን ጉባዔ ላይ የሁለት ባሕርይ ትምህርት አንቀበልም በማለታቸው በቤዛንታይን ነገሥታት ስቃይ እና መከራ ፀናባቸው :: በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ ከሁለት ባሕርይ ትምህርት የፀዳች እና ታላቅ አምልኮተ እግዚአብሔር እንደሚፈፀምበት ስለ አወቁ ከሌሎች ስምንት ቅዱሳን ጋር በሁለተኛው የኢትዮጲያ ጳጳስ በአባ ሚናስ ጊዜ በንጉሥ አልዓሜዳ ዘመነ መንግሥት በ5ተኛው መቶ ክ/ዘመን ማብቂያ 480/81 ዓ.ም ወደ ሀገራችን ገቡ፡፡ ከአባታችን ከአቡነ አረጋዊ ጋር የነበሩት ስምንቱ ቅዱሳን ከሮም ፤ከቤዛንታይን ፤ ታናሿ እስያ፤ሶሪያ ግዛትና አካባቢዎች የመጡ ናቸው፡፡ ስማቸውም አባ ገሪማ (አባ ይስሐቅ) ፣ አባ ጰንጠሌዎን፣ አባ አፍፄ፣ አባ ጉባ ፣አባ ሊቃኖስ ፣ አባ ይምዓታ ፣አባ ጽሕማ፣አባ አፍጼ ናቸው :: ስለ ተሰዓቱ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ የገቡበት መንገድ ሁለት ዓይነት ምንጮች ይገኛሉ፡፡ የመጀመሪያው አምደ ሃይማኖት ኢትዮጲያዊው ቄርሎስ የሚባለው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ቅዱሳኑ ወደ ኢትዮጲያ ሲመጡ ነገሥታት እና መኳንንትን አስከትለው መጽሐፍትን ይዘው ስለነበር የመጡት ሀገር ለመውረር መስሏቸው ኢትዮጲያውያን ደንግጠው ነበር ፡፡ ነገር ግን በእጃቸው የተለያየ ተአምራትን ማየት ስለቻሉ ለመንፈሳዊ ተልዕኮ መምጣታቸውን ተረዱ ከተአምራቱ መካከል በዕራፈ የእሳት ፍም የቋጠሩ፣ ጠዋት ዘርተው ለሠርክ ቅዳሴ ማድረሳቸው (አቡነ ገሪማ)፣ በወንፊት ውሃ ተሸክመው መሄዳቸው፣ አሥሩ የእጅ እና የእግር ጣቶቻቸው እንደ ፀሐይ ያበሩ መሆናቸውን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጠቅሰዋል ሁለተኛው ምንጭ አባታችን አቡነ አረጋዊ መጀመሪያ ብቻቸውን መጥተው የኢትዮጲያውያንን ደግነት እና ታማኝነት ስለተረዱ ተመልሰው ሄደው ለ8ቱ ቅዱሳን በመግለፅ ይዟቸው መጥተዋል የሚሉ ምንጮች ናቸው ::
አባታችን አቡነ አረጋዊ ሲመጡ እናታቸው ቅድስት እድና እና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ :: ንጉሡም ተቀብለው በቤተ ቀጢን ( አክሱም) አሳረፏቸው በዚያ ተቀምጠው መጽሐፍትን እየተረጎሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል፡፡ አባታችን ለብዙ ጊዜ በዓት ፍለጋ ደክመዋል በመጨረሻም ደብረዳሞ ማርካቸዋለች ፡፡ፃድቁ አባታችን እያስተማሩ ደብረዳሞ ሲደርሱ ወደሰማይ ቀጥ ያለች ተራራ ሰው በምንም መንገድ ሊደርስበት ወይም ሊወጣበት የማይቻለውን ቦታ እሳቸው ተመኙ፡፡ ‹‹ አሁን ይህንን ተራራ በምን ልወጣ እችላለሁ›› እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግር ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነብዩ ዳዊት ላይ አድሮ እንደተናገረ ( መዝ 90 (91) ÷11-16) የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስድስት ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ ሚካኤል ሠይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል ፡፡ ወዲያው “ሀሌ ሉያ ለአብ ሀሌ ሉያ ለወልድ ሀሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው አመስግነዋል። ቦታውም <<ደብረ ሀሌ ሉያ>> ተብሏል ፡፡ በዚህችም እለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ምድራዊ ህብስትን አልበሉም፡፡ በሰንበተ ክርስቲያን ከቅዳሴ በኋላ ህብስተ ሰማይ እያመጡላቸው ይመገቡ ነበር ፡፡
ፃድቁ አባታችን የምንኩስና ኑሮ ሥነ ሥርዓት በማስተማራቸውና በማስፋፋታቸው <<አቡሆሙ ለመነኮሳት ዘኢትዮጵያ፤ የኢትዮጵያ መነኮሳት አባት>> ይባላሉ። ግዕዝን በመማር መጽሐፍ ወደ ግዕዝ ቋንቋ ተርጉመዋል። ከአፄ ገ/መስቀል እና ከቅዱስ ያሬድ ጋርም ወዳጆች ነበሩ፡፡ በደብረዳሞ ተራራ ግርጌ የኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ለሴቶች ገዳም አድርገው ሰጥተዋል። ቀዳሚ መነኩሴም የሆኑት እናታቸው ቅድስት እድና ናቸው፡፡ በመጨረሻም ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስማቸውን ለሚጠራ መታሰቢያቸውን ለሚያደርግ ቃልኪዳን ተቀበሉ፡፡ በመምህራቸው አባ ጳኩሚስ እንደተማሩት ለልጆቻቸው መነኮሳት ሥርዓተ ማኅበርን ሰሩላቸው፤ ከዚያ በኋላ በእግዚአብሔር ቸርነት እንደሄኖክ እንደ ኤልያስ ከሞት ገፅ ጥቅምት 14 ቀን በደብረ ዳሞ ተሰወሩ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በፃድቁ ጸሎት ይማረን፤ በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ልብ በሉ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት አይበጅም፤ ሰውን መጉዳትና እግዚአብሔርን መዳፈር አቁሙ፤ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሥርዓተ አምልኮም ያለቦታው አታውሉ፤ ጥያቄአችሁን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዕድል ስጡ፡፡ በእግዚአብሔር ስም ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንና ልጆቻችን የምናስተላፈው ወቅታዊ መልእክታችን ይህ ነው፡፡
በመጨረሻም
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የሥራ አፈጻጸም ላይ ለመምከርና ለመወሰን ኀላፊነት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት መደበኛና ዓመታዊ ጉባኤውን የጀመረ መሆኑን ለሕዝበ ክርስቲያኑ እናበስራለን፡፡
እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ!
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን::
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ደጅሽ ላይ ቆሟል
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🌹 ልጅሽ ደጅ ላይ ቆሟል 💧
-------------------------------
ከመስከረም 26-እስከ ሕዳር 6 ባሉ አንድ ቅዳሜ ማታ ከ3 ሰዓት በኋላ ማሕሌተ ጽጌን ለመቆም ወደየካ ደብረ ሳሕል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየሄድኩ ነው . . . መንገዱ ጭር ብሏል፤ አንድ ሱቅ ላይ ግን ደምበኛ (ገዢ) ቆሟል፤ እኔ መንገዴን እየቀጠልኩ ነው፡፡ ደንበኛው ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ እና ‹‹አባ ይበርኩኝ?›› አለኝ
‹‹ካህን አይደለሁም›› አልኩት፣ በለበስኩት ነጠላ ጋቢና በእጄ የያዝኩት የጸሎት መጽሐፍ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደምሄድ አውቆ ነው፡፡
‹‹አውቃለሁ›› አለኝ እና ‹‹ወደየትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው የምትሄደው?›› ጠየቀ መለስኩለት፤
‹‹እባክህን ልሸኝህ?›› አለኝ አዲስ ቪ 8 መኪና እያሳየኝ
‹‹ብዙም ሩቅ ስላልሆነ በእግሬ ነው የምሄደው›› አልኩት . . . ግለሰቡ የጠጣ ይመስላል፣ በእርግጥም የመጠጥ ሽታ ሸትቶኛል፤ በእጁ ፓኬት ሲጋራ ይዟል፣ ከሱቁ ሲመጣ ከፓኬቱ ውስጥ አንዱን አውጥቶ ከንፈሩ ላይ አድርጎ ነበር ሲቀርበኝ በጣቶቹ መሃል ያዘው፣ ምልከታዬን አስተውሎ ነው መሰለኝ የያዘውን ሲጋራ በሙሉ ጣለና በእግሩ ረጋገጠው፡፡
‹‹አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ልትል ነው አይደል?›› አለኝ
ከዚህ ንግግር በኋላ ስካሩ ሙሉ ለሙሉ ሲጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡
ሁሉንም የመኪናውን በሮች ከፈተና ‹‹እንዲናፈስ ፈልጌ ነው . . . በሲጋራና በመጠጥ ሽታ የታጠነ መኪና ውስጥ እንዳትገባ›› አለኝ፤ በግርምት ቆምሁ፤
‹‹እባክህ አሁን እንሂድ?›› የጋቢናውን በር ብቻ ትቶ ሌሎቹን ዘጋጋና መኪናውን ለመንዳት ተዘጋጀ፤ በእምነት ገባሁና ተቀመጥኩ
መንገድ ስንጀምር በጣም ባዘነ ድምጸት
‹‹ሽሮ ሜዳ ነው ያደግሁት . . . ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን . . . ጽጌን በፍቅር ቆሜ ነው ያደግኩት . . . ለረጅም ዓመታት . . . አክሊለ ጽጌ ብዬ . . . ክበበ ጌራ ወርቅ ብዬ ›› ዓይኖቼን ከመንገዱ ነቅዬ ወደርሱ ሳዞር መንታ መንታ ሆነው የሚወርዱ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም መስማት ብቻ
‹‹ዲግሪዬን ከያዝኩ በኋላ አንድ ዓለም አቀፍ ኤን ጂ ኦ ገባሁ . . . በከፍተኛ ደመወዝ በቃ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ተለያየሁ. . . አልሳለም፣ ኪዳን አላደርስ፣ አላስቀድስ፣ አላድር፣ አላነግስ ከሀገር ሀገር መዞር ከጓደኞቼ ጋር መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ . . . ይኸውልህ ሚስትና ልጆች እያሉኝ ነው እዚህ ያገኘኸኝ፣ የመጠጥና የሲጋራ ጓደኞቼ በልጠውብኝ ነው ያገኘሁህ. . . ውስኪአቸውን ይዘው እየጠበቁኝ ነው ›› ያለቅሳል፣ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ግን በሥርዓት ረጋ ብሎ ይነዳል፤ መናገሩን ይቀጥላል
‹‹ተረጋግቼ ማሰብ አልፈልግም . . . ምክንያቱም ከተረጋጋሁ ልጅነቴን ማሰብ እጀምራለሁ . . . ልጅነቴን ማሰብ ከጀመርሁ ቤተ ክርስቲያንን ማሰብ እጀምራለሁ . . . ደጀ ሰላሟን ማሰብ እጀምራለሁ. . . መቅደሷን ማሰብ እጀምራለሁ፣ . . . የዕጣኑን ሽታ ማሰብ እጀምራለሁ . . . ማልቀስ እጀምራለሁ . . . ፍቅሯን አስባለሁ . . . የጸናጽሉ፣ የከበሮው ድምጽ ይሰማኛል፣ በመሃል ሰይጣኔ ይመጣና እውነቴን ነው ስጠራው ነዋ የሚመጣው . . . ለጓደኞችህ ደውል ይለኛል . . . በመጠጥ ራስህን ደብቅ ይለኛል እታዘዘዋለሁ ልጆቼንና ሚስቴን ጥዬ እወጣለሁ›› አሁን ወደ ቤተክርስቲያን ታጥፈናል፤ ወደ ግቢው የሚያስገባ በር ጋር ስንደርስ ቆመ፣ ወደውስጥ ለመግባት በሮቹ የተከፈቱ ቢሆንም አልገባም፤
‹‹ወደውስጥ ገብተህ ትንሽ ቆይተህ አትሄድም?›› አልኩ ሀዘኑ ተጋብቶብኝ
‹‹አልገባም ግን ድሮ የሚወድሽ ልጅሽ ደጅ ቆሟል በላት›› አለና ሳግ ተናንቆት መሪውን ተደግፎ ድምጽ አሰምቶ አለቀሰ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ለምን እንዳለቀሰ፣ እንዴት እንዳለቀሰ በዓይኔ ያየሁ መሰለኝ፤
‹‹እባክህን ግባና አልቅስ›› አልኩ፣ የቻለውን ያህል አልቅሶ እንዲወጣለት ፈለግሁ፣
‹‹ማን . . . እኔ? አልገባም ግን ንገርልኝ አሁንም ይወድሻል በልልኝ . . . እዚህ በር ላይ ቆሟል በልልኝ›› አለኝ፣ እያለቀሰ ወረድሁ
ቅዱስ ዳዊት ‹‹በኃጥአን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ›› መዝ 84፣10 ያለው ለምን እንደሆነ ይበልጥ ገባኝ
ሳላውቀው የእኔም እንባ መንገዱን ጀምሯል፤ ‹‹ማን ስለሆንኩ ነው እንዲህ በፍቅርህ የተሸከምከኝ›› አልኩ አምላኬን፣
በላዔ ሰብዕ ትዝ አለኝ በልጅነቱ የሚያስታውሳትን የድንግልን ድንቅ ስሟን ሲሰማ ከክህደት እንደተመለሰና ለመዳን ምክንያት እንደሆነችው፡፡ እናም ‹‹በልጅነቱ ይወድሽ የነበረውን ልጅሽን አስቢው ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢለት›› አልኳት
‹‹በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ ውስጥ እንገናኝ›› ነህ 6፡10
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።
ስርዓተ ማኅሌት ዘሣልሳይ ጽጌ በዓለ መስቀል
🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀
ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
........................................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡
ዚቅ
ዝኬ ዘተዘርዓ ቃለ ጽድቅ በትውክልተ መስቀል፤ ወፍሬሁኒ ኮነ መንፈሰ ህይወት፤ ተስፋሆሙ ለእለ ድኅኑ፤ ወበጽጌሁ አርዓየ ገሃደ አምሳለ ልብሰተ መለኮት፤ ዕቊረ ማየ ልብን፤ ጽጌ ወይን ተስፋሆሙ ለጻድቃን።
ማኅሌተ ጽጌ
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል፤ ወጸገይኪ ጽጌ በኢተሰቅዮ ማይ ወጠል፤ ወበእንተዝ ያሬድ መዓርዒረ ቃል፤ ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ወይብል፤ ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል።
ወረብ፦
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል/፪/
ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ያሬድ ወይብል ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል/፪/
ዚቅ፦
በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ወባቲ ይገብሩ ተአምረ በውስተ አህዛብ እስመ አርአያ መስቀል ይዕቲ
ማኅሌተ ጽጌ
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤ካዕበ (ወካዕበ) ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤ ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ።
ወረብ፦
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እም/፪/
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪/
ዚቅ
እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ወእምኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ከመ ትኩኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለመ።
ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፣ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ
ወረብ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/
ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ተመየጢ ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ በአምሳለ ወርቅ ይግበሩ ለኪ ኮሰኮሰ ዘብሩር፤ አመ ወለደቶ አርአያ ወሰደቶ፤ በትእምርተ መስቀል፤ ትፍሥሕትኪ ውእቱ፤ ብርሃንኪ ውእቱ ሰላምኪ።
ዓዲ ዚቅ
ወይቤላ ንዒ ንሑር፤ኀበ ደብረ ከርቤ ውስተ አውግረ ስኂን፤ እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት
ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
ዚቅ
ነያ ሠናይት ወነያ አዳም፤ አግዓዚት ማርያም ጽርሕ ንጽሕት፤ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤ ወዲበ ርእሳኒ አክሊል፤ ፅሑፍ በትምህርተ መስቀል
ዓዲ ዚቅ፦
በወርቅ ወበዕንቍ ወበከርከዴን፤ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት፤ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ፤ትርሢተ መንግሥቱ አንቲ መድኃኒቶሙ ለነገሥት
ሰቆቃወ ድንግል
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።
ወረብ፦
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም/፪/
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ተዓይል/፪/
ዚቅ
አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤ አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤ እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ፤እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ
ወረብ፦
አመ አመ አጒየይኪ ዕጓለኪ በሐቂፍ/2/
እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ/2/
ሰቆቃወ ድንግል(ሌላ)
ኀበ አዕረፍኪ እግዝዕትየ ማርያም ታሕተ ጽላሎተ ዕፅ እምፃማ፤ፈያት ክልኤቱ ሶበ በጽሑኪ በግርማ፤እምትሕዝብተ ሞቱ ማሕየዊ ለወልድኪ ንጉሠ ራማ፤እፎኑ አዕይንትኪ ማያተ አንብዕ አዝንማ፤አዕይትየ ለገብርኪ ክልኤሆን ይጽለማ
ዚቅ
ሐፃቤ ርስሐትየ ይኩን አንብዕኪ ዘአንፀፍፀፈ ዲበ ምድር አመ ወልድኪ ይፄዓር በመልዕልተ
መዝሙር፦
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፣ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘዓቀምከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወከመ ወሬዛ ኀይል መላትሒሁ፤ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ሰማይ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ በከዋክብት ሠማይ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኩሉ ዕለት፤ማ፦ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፥ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ።
አመላለስ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ/፪/
ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ/፪/
©ያሬዳውያን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
# ቅድስት ሥላሴ
በ ‹‹ምሥጢረ ሥላሴ›› ትምህርት እንደምንረዳው ቅድስት ሥላሴ አንድም ሦስትም ናቸው፡፡ ‹‹ሥላሴ›› የሚለው ቃል ‹‹ሠለሰ፤ ሦስት አደረገ›› ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ (መጽሐፍ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ገጽ ፮፻፷፱)
ቅድስት ሥላሴ ስንልም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ማለታችን ነው፡፡ ‹‹ቅድስት›› ተብሎ ደግሞ በሴት አንቀጽ /ቅድስት ሥላሴ/ ይጠራል፤ ‹‹ቅድስት›› እና ‹‹ልዩ ሦስት›› የሚባልበትም ሃይማኖታዊ ምሥጢር፡-
፩. ቅድስት
ሥላሴ ‹‹ቅድስት›› ተብለው በሴት አንቀጽ መጠራታቸው ሴት /እናት/ ልጅዋን መውለዷን እንደማትጠረጥረው ሁሉ ሥላሴም ይህን ዓለም መፍጠራቸውን ስለማይጠረጥሩ ነው፡፡ ሁሉም ከእነርሱ፣ ለእነርሱ፣ በእነርሱ ሆኗልና፡፡ ሴት ወይንም እናት ልጅዋ ቢታመምባት እንዲሞትባት አትሻም፤ ሥላሴም ከፍጥረታቸው አንዱ እንኳን በጠላት ዲያብሎስ እንዲገዛባቸው አይፈቅዱም፡፡ ሴት ፈጭታ ጋግራ ቤተሰቦቿን እንደምትመግበው ሥላሴም በዝናም አብቅለው በፀሐይ አብስለው ፍጥረቱን ሁሉ ስለሚመግቡ ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እያልን እንጠራቸዋለን፡፡
፪. ልዩ ሦስትነት
በትምህርተ ሃይማኖት ሥላሴ በቅድምና፣ በፈጣሪነት፣ በሥልጣን፣ በመመስገን፣ በክብር፣ በፈቃድ አንድ /እግዚአብሔር/ ሲሆኑ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት መሆናቸውን ይገልጻል፡፡
ሀ. በስም
የቅድስት ሥላሴ የስም ሦስነትነት አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ተብለው መጠራታቸው ነው፡፡ አብ በራሱ ስም አብ ይባላል እንጂ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አይባልም፡፡ ወልድም ወልድ ይባላል እንጂ አብ ወይንም መንፈስ ቅዱስ አይባልም፡፡ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ቢባል እንጂ አብ ወይንም ወልድ አይባልም፤ ስማቸው ፈጽሞ የማይፋለስ ነውና፡፡
ከቅዱስ ጴጥሮስ ቀጥሎ በሦስተኛነት በአንጾኪያ ተሹሞ የነበረው ቅዱስ አግናጥዮስ ‹‹አብሂ ውእቱ አብ ወኢኮነ ወልደ ወኢ መንፈሰ ቅዱሰ፣ ወልድሂ ውእቱ ወልድ ወኢኮነ አበ ወኢ መንፈሰ ቅዱሰ፣ ወመንፈስ ቅዱስሂ መንፈስ ቅዱስ ውእቱ ኢኮነ አበ ወኢ ወልደ፣ ኢይፈልስ አብ ለከዊነ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፣ ወኢ ወልድ ለከዊነ አብ ወወልድ፤ ወኢ መንፈስ ቅዱስ ለከዊነ አብ ወወልድ፤ አብም አብ ነው እንጂ ወልድን መንፈስ ቅዱስን አይደለም፤ ወልድም ወልድ ነው እንጂ አብን መንፈስ ቅዱስንም አይደለም፡፡ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ አብን ወልድን አይደለም፤ አብ ወልድን መንፈስ ቅዱስን ወደመሆን አይለወጥም፤ ወልድም አብን መንፈስ ቅዱስን ወደመሆን አይለወጥም፤ መንፈስ ቅዱስም አብን ወልድን ወደመሆን አይለወጥም›› ብሏል፡፡ (ሃይ. አበው ዘቅዱስ አግናጥዮስ ምዕ. ፲፩. ገጽ. ፴፯)
የቅድስት ሥላሴ ስማቸው ከአካላቸው፣ አካላቸው ከስማቸው ሳይቀድም ቅድመ ዓለም የነበረ ስም ነው እንጂ ድኅረ ዘመን የተገኘ አይደለም፡፡ ቅድምናቸው ዘመኑን ቢወስነው እንጂ ዘመኑ ቅድምናቸውን አይወስነውምና፡፡ (መንገደ ሰማይ-በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ገጽ. ፴፪)
ስለዚህም ሊቁ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት ‹‹ወናሁ ንቤ ካዕበ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወአኮ እሉ አስማት ዘቦኡ ላዕሌሆሙ ድኅረ አላ እሙንቱ እስመ አካላት፡፡ ወብሂለ ሰብእሂ አኮ ውእቱ ስም ዳዕሙ ፍጥረት ውእቱ… ወአካሎሙኒ ለሥሉስ ቅዱስ ወአስማቲሆሙ አልቦ ውስቴቶሙ ዘይዴኀር አላ እሉ እሙንቱ ብሉያነ መዋዕል እምቀዲሙ ዘእንበለ ጥንት ወዘመን፤ አሁን ደግሞ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እንላለን ግን አካላት ተቀድመው ተገኝተው እሊህ ስሞች ኋላ የተጠሩባቸው አይደለም፤ ሰው ማለት ኋላ የወጣ ስም አይደለም፡፡ ባሕርዩ ነው እንጂ የሥላሴ አካላቸውም ቀድሞ ስማቸው ከአካላቸው በኋላ የተገኘ አይደለም፡፡ ጥንት ሳይኖራቸው ዘመን ሳይቀድማቸው የነበሩ ናቸው እንጂ›› ብሎ ተናግሯል፡፡ (ሃይ-አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት ፲፫፥፬-፰ ገጽ ፵)
ለ. በአካል
የቅድስት ሥላሴ የአካል ሦስትነታቸው ደግሞ አብ ፍጹም አካል፣ ፍጹም ገጽ፣ ፍጹም መልክእ አለው፡፡ ወልድም ፍጹም አካል፣ ፍጹም ገጽ፣ ፍጹም መልክእ አለው፡፡ መንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል፣ ፍጹም ገጽ፣ ፍጹም መልክእ አለው፡፡ ሊቁ አቡሊዲስ ስለ ሥላሴ የአካል ሦስትነት ሲገልጽ ‹‹ነአምን በአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ከመ ሠለስቱ ገጻት ፍጹማነ መልክእ ወአካል እሙንቱ እንዘ አሐዱ መለኮቶሙ ዘበአማን፤ ባሕርያቸው በእውነት አንድ ሲሆን በመልክ፣ በአካል ፍጹማን እንደሆኑ ሦስት ገጻት እንደሆኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን›› ብሏል፡፡ (ሃይ. አበ. ዘአቡሊዲስ ምዕ. ፴፱፥፫ ገጽ ፻፴፯)
ሐ. በግብር
የቅድስት ሥላሴ የግብር ሦስትነታቸው ሲተረጎም የአብ ግብሩ መውለድ ማሥረፅ ነው፤ ወልድን ወልዷል፣ መንፈስ ቅዱስንም አሥርፇልና፡፡ የወልድ ግብሩ መወለድ ነው፤ ከአብ ተወልዷልና፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረፅ ነው፤ ከአብ ሠርፇልና፡፡
አብ ወልድን ቢወልድ፣ መንፈስ ቅዱስንም ቢያሠርፅ እንጂ አይወለድም፣ አይሠርፅም፡፡ ወልድ ቢወለድ እንጂ አይወልድም፤ አይሠርፅም፤ አያሠርፅም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቢሠርፅ እንጂ አይወለድም፤ አያሠርፅም፤ በመሆኑም ቅድስት ሥላሴ በዚህ ግብራቸው አብ ወላዲ፣ ወልድ ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ ተብለው ይጠራሉ፡፡
በእርግጥ ምሥጢረ ሥላሴን በሚገባ መርምሮ መረዳት ለማንም ቢሆን አይቻለውም፡፡ እርሱ ባወቀ ግን ምሥጢረ ሥላሴ በምሥጢረ ጥምቀት ተገልጧል፡፡ እንግዲህ እምነታችንን በቅድስት ሥላሴ ላይ በማድረግ በቀናች ሃይማኖት ልንጸና ይገባል፡
©Mahibere kidusan
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox