በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
ሐዋርያት ተባበሩ፤
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ፤
ቃሉን አስተማሩ።
ካረገ በኋላ በአስረኛው ቀን፤
ወደ አለም ላከው ጰራቅሊጦስን።
በዝግ ቤት ውስጥ ቆዩ ቀኑን ሲጠብቁ፤
የተሰጣቸውን ተስፋውን እስኪያውቁ።
ቀኑም ደረሰና በሃምሳኛው እለት፤
ተሰብስበው ሳሉ በአንድነት ፀሎት፤
መንፈስ ቅዱስ ታየ በነደ እሳት።
ያ የተነገረው ያ የተስፋ ቃል፤
ወረደ ከሰማይ በእሳት አምሳል።
ጴጥሮስ አሳመነ ሶስት ሺ ነፍሳት፤
ያን ጊዜ ገሊላ በሰጠው ትምህርት።
ከሶስት አካል አንዱ መንፈስ ቅዱስን፤
ልኮ አናገራቸው ሁሉን በልሳን።
ሐዋርያት ተባበሩ፤
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ፤
ቃሉን አስተማሩ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ስለተባለበትና ተስፋ በተሰጣቸው በኀምሳኛው ቀን ወርዶ ስለ ሠራው ሥራ እንዲህ በማለት ያብራራል። ‹‹ወመንፈስ ቅዱስኒ ኢተሰምየ ጰራቅሊጦስሃ ዘእንበለ አመ ይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ እፌኑ ለክሙ ካልአ ጰራቅሊጦስሃ። ጰራቅሊጦስ ብሂል ናዛዚ ብሂል በነገረ ጽርዕ ……መንፈስ ቅዱስም ጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሌላውን አጽናኝ እልክላችኋለሁ›› ከማለቱ በፊት ጰራቅሊጦስ አልተባለም ጰራቅሊጦስ ማለት በጽርዕ ቋንቋ አጽናኝ ማለት ነው ስለምን አጽናኝ ተባለ ደቀ መዛሙርቱ ወልድ ካረገበት ቀን ጀምሮ ጰራቅሊጦስ እስከ ወረደበት ቀን ድረስ ያለቅሱ ነበረና ስለዚህም ወልድ መንፈስ ቅዱስን ጰራቅሊጦስ አለው። የስሙ ትርጓሜ ግን አስቀድመን እንደተናገርነው አጽናኝ ማለት ነው። (ዮሐ. ፲፬፥፲፭)
በዓለ ጰራቅሊጦስ የሚከበረው ርደተ መንፈስ ቅዱስን መሠረት በማድረግ በመሆኑ ምክንያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል ነው፤ በዕለቱም ኢየሩሳሌም በተባለችው ቤተክርስቲያን ስለመጽናት፤ ከግለኝነት ይልቅ መንፈሳዊ አንድነትን ስለማስቀደም እና ስለመጸለይ እንማራለን፡፡
በዓለ ትንሣኤውን በቸርነቱ በሰላም እንድናሳልፍ ፈቅዶ እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ጠበቀን፣ አሁን ደግሞ በጾም፣ በጸሎት ሆነን እርሱን የምናመሰግንበትን ወቅት ስላመጣልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁን፤ አሜን፡፡
ምንጮች፤
መዝገበ ታሪክ፣ ክፍል ፪፤ መምህር ኅሩይ ኤርምያስ፤ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም፤ ገጽ ፹፬-፹፭፡፡
መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፲፰ ቀን፣ መጽሐፈ ምሥጢር፡፡
መጽሐፈ ግጻዌ፡፡
ማኅቶተ ዘመን፣ መምህር በሙሉ አስፋው፤ ፳፻፩ ዓ.ም፤ ገጽ ፻፺፭-፪፻፬፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"ቅዱስ ላሊበላ"
በገርጂ ጊዮርጊስ የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የምትፈልግ አይደለህም፤ ለጠፈራቸው መማገሪያ ገመድ የምትሻ አይደለህም፣ እንጨትንም ለማገር፣ ለምሰሶዋቸውም ገበታ፣ ለዙሪያቸውም ለማያያዣ ጭቃን የምትፈልግ አይደለህም፡፡ የቤተመቅደሶችን ፈቃድ ሁሉ ከአንድ ቋጥኝ ድንጋይ ትፈጽማለህና፡፡ የማሳይህ እኚህ የቤተ መቅደሶች አኗኗር ከምድር ልብ ውስጥ እስከዛሬ አለ፡፡ ከአሁን ጀምሮ በእጅህ እስኪገለጡም ድረስ በምድር ልብ ይኖራሉ፡፡ በሰው ልጅ ጥበብ ያይደለ በእኔ ሥልጣን ከምድር ልብ ውስጥ ታወጣቸው ዘንድ መረጥሁህ፡፡ ሕዝቦቼ ተወልጄ አድጌ ሞቼ ተቀብሬ ከሞትም የተነሳሁባትን ሀገር ለማየት ኢየሩሳሌም በመሄድ ግማሹም በበረሃ ይቀር ነበር አሁን ግን አንተ ኢየሩሳሌምን በሀገርህ ትሠራለህ፡፡ በማንም እጅ ዳግመኛ ሊሠሩ የማይችሉ ቤተ መቅደሶቼን እንዳሳየሁህ ትሠራለህ፡፡ አንተም እንዳሳየሁህ በልብህ ውስጥ አኑራቸው፡፡ ስትሠራቸውም እየልካቸው ይሁን፤ ከእርዝመታቸውም በላይ ቢሆን፣ ከወርዳቸውም በላይ ቢሆን፣ በመወጣጫቸውም ላይ ቢሆን አንዳች እንዳትጨምር፡፡ ያሳየሁህ እሊህ ዐሥሩ መቅደሶች ከአንዲት ቋጥኝ ድንጋይ ሲወጡ አይተሃልና….› እያለ ጌታችን ሲነግረው ጻዲቁ ንጉሥ “ይህ እንዴት ይሆናል?” በማለት ይጠይቃል፡፡ ጌታም እውነት እልሃለሁ እነዚህ ያሳየሁህ መቅደሶች በሰው ኃይል የሚሠሩ ሆነው አይደለም፤ ጀማሪያቸው ሠሪያቸውና ፈጻሚያቸው እኔ ነኝ ነገር ግን ኃይሌ በአንተ እጅ እንዲገለጽ ለምክንያት ተልከሃል፤ አንተ አነጽካቸው እየተባለ እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ ስምህ ይጠራባቸዋል…›› እያለ ይቀጥላል የቅዱስ ላሊበላ ገድል፡፡ ቤተ መቅደሶቹንም ለመሥራት ቦታውን ያውቅ ዘንድ ሱባኤ ገብቶ ሳለ ዛሬ ቤተ ማርያም ካለችበት ቦታ ላይ ቅዱሳን መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ታይተውት በቦታው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መቅደሱን መሥራት ጀመረ፡፡ ዓሥሩን ቤተ መቅደሶች ሲሠራ እርሱ አንድ ክንድ ሠርቶ እንደሆነ ሌሊቱን አድሮ በቀጣዩ ቀን አሥር ክንድ ሆኖ ያገኘው ነበር፣ ቀንም በማይታወቁ ሰዎች አምሳል እየተገለጡ መላእክት ይራዱት ነበር፡፡
5. አንዳንድ ነገሮች ስለ ቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፡- ቅዱስ ላሊበላ ዓሥሩም ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በጣም በሚያስገርም ሁኔታ በውስጥና በውጭ ያሉት ብዙ ቅርጾች ነገረ ድኅነትን በምሳሌ እንዲወክሉ አድርጎ ነው ያነጻቸው፡፡ የክርስቶስን መከራና በእርሱም የተገኘውን ፍጹም ዘላለማዊ ድኅነት በእያንዳንዱ ቤተ መቅደስ ውስጥ እንዴት አድርጎ በምሳሌ እንዳስቀመጠው እጅግ አስገራሚ ነው፡፡
በላስታ ቅዱስ ላሊበላና አካባቢው የሚገኙ ሌሎች አስደናቂ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፡- ከአሥሩ የቅዱስ ላሊበላ አስደናቂ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በተጨማሪ የቅዱስ ነአኵቶለአብና የቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም አሸተን ማርያም በዋናነት ሕዝበ ክርስቲያኑ የሚጐበኛቸው ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ናቸው፡፡ በላሊበላና አካባቢው ግን እጅግ ጥንታዊና አስደናቂ የሆኑ በጣም በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ሣርዝና ሚካኤል፣ ብልባላ ቂርቆስ፣ ብልባላ ጊዮርጊስ፣ አርባዕቱ እንስሳ፣ ትርኩዛ ኪዳነምሕረት፣ ገነተ ማርያም፣ ቀንቀኒት ሚካኤል እነዚህ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ሲሆኑ እንዲሁም ዋልድቢት ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም፣ አቡነ ዮሴፍ ገዳም፣ ገብረ ክርስቶስ ዋሻ ቤተክርስቲያን፣ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን፣ ቀደሊት ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ እመኪና መድኃኔዓለምና እመኪና ልደታ፣ ማውሬ እስጢፋኖስ፣ የቅዱስ ገብረ ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ማይ ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ተከዜ ኪዳነምሕረትና መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዳንዶቹ ከ485-536 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በዐፄ ካሌብ ዘመነ መንግሥት የታነጹ ናቸው፡፡ ሌሎቹንና በሰሜን ላስታ ያሉትን ደግሞ እነ ላሊበላና ይምርሃነ ክርስቶስ አንጸዋቸዋል፡፡
ቅዱስ ላሊበላ እኛ ከምናውቃቸው ከድንቅ ሥነ ሕንፃዎቹ ሥራ በተጨማሪ ከሺህ ዓመታት በፊት በሥዕል፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በሃይማኖት፣ በኢኮኖሚ፣ በውጭ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙትና በመሳሰሉት ሁሉ እጅግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ከሺህ ዓመታት በፊት አዳራሾችን፣ ፎቆችን፣ የውስጥ ለውስጥ መተላለፊያዎችን፣ የእንግዳ መቀበያዎችን፣ የሕፃናት ማሳደጊያዎችን፣ የሕሙማን መፈወሻዎችን፣ የሕንፃ መሳሪያዎችን፣ የትምህርት ማዕከሎችን፣ የመደጎሻ ቦታዎችን ያቋቋመ መሆኑን የብራና ገድሉ እንደሚናገር የደብሩ አባቶች ይገልጣሉ፡፡ ወደፊት ተርጎመው እንሚያቀርቡልን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ከዚህ በተጨማሪ የግእዝ ቋንቋን በጽሑፍ አበልፅጎ ያቆየ ባለውለታ ነው፡፡ ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ውጭ ሌሎችንም በርካታ ቤተ መቅደሶች ሠርቷል፤ ከሀገራቸንም አልፎ በሱማሌ ሞቃዲሾ ላይ መቅደሰ ማርያም የተባለች ቤተክርስቲያን ሠርቷል፡፡ ክርስትናን ከግብፅ ምድር ጨርሰው ለማጥፋት ተንባላት በተነሡ ጊዜ ዓባይን ሊያግድባቸው ሲነሣ በብዙ ምልጃና ልመና ስለማራቸው በሀገሪቱ ውስጥ ክርስትና እስካሁን እንዲቆይ የራሱን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ በአጠቃላይ ቅዱስ ላሊበላ ነቢይም ሆኖ፣ ሐዋርያም፣ ጻዲቅም፣ ሰማዕትም ሆኖ ጥበብ መንፈሳዊንና ጥበብ ሥጋዊን ከእግዚአብሔር ተሰጥቶት ንግሥናንና ክህነትን፣ ቅድስናንና ንጽሕናን በሚገባ አስተባብሮ በማያዝ እግዚአብሔርንም ሰውንም በቅንነት ሲያገለግል ኖሮ ሰኔ 12 ቀን 1197 ዓ.ም ከፈጣሪው ታላቅ ቃልኪዳን ተቀብሎ በዝማሬ መላእክት፣ በመዝሙረ ዳዊት ቅድስት ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ ሰማያዊ ክብርን ወርሷል፡፡ ክቡር ሥጋውም ራሱ ባነጸው ቤተ ሚካኤል መቅደስ ሥር በክብር ዐርፏል፡፡
(ምንጭ፡- ገድለ ቅዱስ ላሊበላ፡- የቅዱስ ላሊበላ ደብር በ2003 ዓ.ም ያሳተመው፣ ስንክሳር ዘወርሃ ሰኔ)
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሰኔ ፲፪
ቅዱስ ገብርኤል ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ ሰባቱ ሰማያትን ካሳየውና በጌታችን ፊት አቅርቦት ካስባረከው በኋላ ጌታችንም በቅዱስ ቃሉ ‹‹ሕዝቦቼ የመከራና የሥቃዬን ቦታ ለማየት ኢየሩሳሌም በመሄድ በመንገድ እየቀሩ ስለሆነ አሁን ግን አንተ በሀገረ ሮሀ ኢየሩሳሌምን ትሠራለህ›› በማለት የቤተ መቅደሶቹን አሠራር በዝርዝር የነገረው ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ ዕረፍቱ ነው፡፡
ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ፡- ቅዱስ ላሊበላ ጌታችን የጠጣውን መራራ ሐሞት በማሰብ ሁልጊዜ ዓርብ ዓርብ ኮሶ ይጠጣ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ላሊበላን ኢየሩሳሌም ወስዶት በዚያ ያሉ ቅዱሳን መካናትን ሁሉ አሳይቶ አሳልሞታል፡፡ ወደ ሰማይም ነጥቆ ወስዶ ሰባቱ ሰማያትን ያሳየው ሲሆን በጌታችን ፊትም አቅርቦት አስባርኮታል፡፡ ጌታችንም ‹‹ሕዝቦቼ የመከራና የሥቃዬን ቦታ ለማየት ኢየሩሳሌም በመሔድ በመንገድ እየቀሩ ስለሆነ አሁን ግን አንተ በሀገረ ሮሀ ኢየሩሳሌምን ትሠራለህ›› በማለት የቤተ መቅደሶቹን አሠራር በዝርዝር ነግሮታል፡፡ ከነገሠም በኋላ ሱባኤ ገብቶ ቤተመቅደስ የሚሠራበትን ቦታ በጸሎት ሲጠይቅ ዛሬ ቤተ ማርያም ካለችበት ቦታ ላይ የብርሃን አምደ ወርቅ ተተክሎ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ስላየ ቦታው እግዚአብሔር የፈቀደው መሆኑን አውቆ ሥራውን ጀመረ፡፡ ጌታችን ቀድሞ ‹‹እኔ ራሴ ነኝ እንጂ ቤተ መቅደሶቹን የምትሠራቸው አንተ አይደለህም፣ ነገር ግን በአንተ ስም እንዲጠራ ስለፈቀድኩ ሄደህ ሥራ›› ብሎ እንዳዘዘው ቅዱስ ገድሉ ይናገራል፡፡ ላሊበላ ዓሥሩን ቤተመቅደሶች ሲሠራ እርሱ አንድ ስንዝር ሠርቶ እንደሆነ ሌሊቱን ዓሥር ስንዝር ሆኖ ያገኘው ነበር፡፡ ቀንም ሲሠራ ቅዱሳን መላእክት በማይታወቁ ሰዎች አምሳል ሆነው ይራዱት ነበር፡፡ በመጨረሻም ጌታችን በገሃድ ተገልጦለት በቦታው ላይ እጅግ አስገራሚ ቃልኪዳኖችን ሰጥቶታል፡፡
ከ10ኛው እስከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (920-1253 ዓ.ም ድረስ) በላስታ ቡግና ምድር የነገሡ የላስታ ቡግና ተወላጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ነገሥታት የንግሥናቸው መጠሪያ ‹‹የዛጉዌ ሥርወ መንግሥት›› ወይም ‹‹የላስታ መንግሥት›› በመባል ይታወቃል፡፡
የላስታ ነገሥታት የዘር ሀረጋቸው ከንጉሥ ሰሎሞን ዘር ሲያያዝ የመጣ ነው፡፡ ከላስታ (ከዛጉዌ) ነገሥታት መካከል ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ፣ ቅዱስ ገብረ ማርያም፣ ቅዱስ ላሊበላና ቅዱስ ነአኵቶለአብ እነዚህ አራቱ ነገሥታት እንደ መልከጼዴቅ (ዘፍ 14፡18) ክህነትን ከንግሥና፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ እግዚአብሔርንም ሰውንም በቅድስና አገልግለው አልፈዋል፡፡ በንግሥናቸው ሀገራችንን በመልካም ሥራና በቅድስና ከማስተዳደራቸው በተጨማሪ ቅዱሳን ጻድቃን ሆነው እግዚአብሔርን በብዙ ድካም በመልካም ተጋድሎአቸው ያገለገሉና አገልግሎታቸውም ሆነ ቅድስናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ ስለተመሰከረላቸው ጌታችን የሰጣቸውን ቃልኪዳን መሠረት በማድረግ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን የቅድስና ማዕረግ ሰጥታ፣ በስማቸው ቤተክርስቲያን አንጻ፣ ጽላት ቀርፃ በዓላቸውን እያከበረች መታሰቢያቸው ተጠብቆ ለዘለዓለም እንዲኖር አድርጋለች፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን የቅዱስ ላሊበላን እጅግ ድንቅ የሆኑ ሥራዎቹን ዓለም ከሚመለከትበት የተለየ መንፈሳዊ ዐይን ሊኖረን ይገባል፡፡ ስለዚህም የቅዱስ ላሊበላን የቅድስና ሕይወትና ከእግዚአብሔር ጋር ስለነበረው ግንኙነት ገድለ ቅዱስ ላሊበላን መነሻ በማድረግ ብዙ ነገሮችን ቀጥሎ እናያለን፡-
1. ቅዱስ ላሊበላ ከአባቱ ዣን ስዩምና ከእናቱ ኪርወርና ጌታችን በተወለደበት ዕለት ታኅሣሥ 29 ቀን 1101 ዓ.ም በላስታ ቡግና ወረዳ ልዩ ስሟ ሮሀ በተባለችው ሥፍራ ተወለደ፡፡ የልደቱን ነገር አስቀድሞ ቅዱስ ሚካኤል ለእናቱ ነግሯት ነበርና በተወለደ ጊዜ ብዙ ነጫጭ ንቦች መጥተው በሰውነቱ ላይ አርፈው እንደ ማር እየላሱት ስለታዩ እናቱ ‹‹ልጄን ንብ ዘበኛ ሆኖ ይጠብቅልኛል›› ስትል ስሙን ‹‹ላል ይበላል›› ብላዋለች፡፡ ላል በአገውኛ ንብ ማለት ነው፡፡ በጊዜ ብዛት በተለምዶ ነው ‹‹ላሊበላ›› ተብሎ መጠራት የተጀመረው፡፡ ንቦቹ ግን ሥጋዊ ንቦች ሳይሆኑ በንብ የተመሰሉ መላእክት ናቸው፡፡ ንጉሥ መሆኑን እያመለከቱ የሃይማኖትና የምግባር ማር ከእርሱ ይቀዳል ሲሉ በንብ ሠራዊት ተመስለው ሰውነቱን ላሱት፡፡ እንደ ዮሐንስና እንደ ኤርምያስም በእናቱ ማኅፀን ሳለ ነው መንፈስ ቅዱስ የሞላበት፡፡
ከዚህ ቀጥሎ በገድሉ ውስጥ የተጠቀሱ አንዳንድ አስደናቂ ነገሮችን እናያለን፡፡
2. ቅዱስ ላሊበላ ያነጻቸውን አብያተ ክርስቲያናት መመልከት ያለብን በቅርስነታቸውና በቱሪስት መስህብነታቸው ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ የተገኙ ብቸኛ መንፈሳዊ ሀብቶቻችን መሆናቸውን ነው፡- ስለ ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ከማንሳታችን በፊት በመጀመሪያ እውነተኛ የሕይወት ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን መመልከት የግድ ያስፈልጋል፡፡ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀድሞ በሕገ ልቡና ከዚያም በሕገ ኦሪት እግዚአብሔርን ስታመልክ ኖራለች፡፡ በሐዲስ ኪዳንም ሐዋርያቱ እንኳን ለስብከት ከኢየሩሳሌም ሳይወጡ ነው በ34 ዓ.ም በራሷ ሐዋርያ በጃንደረባው ባኮስ አማካኝነት በክርስቶስ ማመንንና ጥምቀትን ወደ ሀገሯ ያመጣችው፡፡ የዚህ ደግሞ ምስክሩ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ 1ኛ ነገ 10፡1-13፣ ሐዋ 8፡26-40፡፡ በዚህ መረጃ መሠረት ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ እስከ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ወደ ኢየሩሳሌም እየሔዱ ሃይማኖታዊ ጉዞ ያድርጉ ነበር፡፡
ከ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ ግን ከኢትዮጵያ ተነስቶ በሱዳን በግብፅ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም በእግርና በእንስሳት ጉዞ ለማድረግ የመንገዱ አድካሚነትና በረሃማነት የሚባክነው ጊዜ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ተሻግሮም እስከ ግብፅና ሱዳን ድረስ የእስልምና ሃይማኖት ስለተጠናከረ ለኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ወደ ኢየሩሳሌም ለመጓዝ አስቸጋሪ ስለሆነባቸው ለሃይማኖታዊ አምልኮና ስግደት ወደ ኢየሩሳሌም የሚያደርጉት ጉዞ ተቋረጠ፡፡ ይህ ሁኔታም ሲያያዝ እስከ ቅዱስ ላሊበላ ዘመን ደርሷል፡፡
ቅዱስ ላሊበላም የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ወደ ኢየሩሳሌም ያደርጉት የነበረው ጉዞ በመቋረጡ በእጅጉ እያዘነ ተግቶ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር፡፡ የኢየሩሳሌምንም አምሳያ የሆኑ አብያተ ክርስቲያናትን በሀገሩ ለመሥራት ይመኝ ነበር፡፡ ጥቂት ነገር ሲለምኑት አብዝቶ መስጠት ለእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነውና ላሊበላ ምድራዊ ኢየሩሳሌምን በሀገሩ ለመሥራት ሲያስብ ልዑል እግዚአብሔር በጥበቡ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ (2ኛ ቆሮ 12፡1-7) ወደ ሰማይ አሳርጎት ሰማያዊት ኢየሩሳሌምን አሳይቶታል፡፡ ጌታችንም ‹‹ሕዝቦቼ የመከራና የስቃዬን ቦታ ለማየት ኢየሩሳሌም በመሄድ በመንገድ እየቀሩ ስለሆነ አሁን ግን አንተ በሀገረ ሮሐ ኢየሩሳሌምን ትሠራለህ›› በማለት የቤተ መቅደሶቹን አሠራር ሁሉ በዝርዝር ነግሮታል፡፡ በሰማያዊት ኢየሩሳሌምም ምሳሌ በሀገሩ ላይ ወጥ ከሆኑ የዓለት ድንጋዮች መላእክት እየተራዱት ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እንዲያንጽ ነግሮታል፡፡
3. ጠላት ለክፉ ያሰበውን እግዚአብሔር ለበጎ ያደርገዋል፡- ወደኋላ ተመልሰን የቅዱስ ላሊበላን የልጅነት ሕይወቱን እናንሳ፡- ቅዱስ ላሊበላ እናትና አባቱ ከሞቱበት በኋላ ወደ ጎጃም በመሄድ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን፣ ብሉይና ሐዲስን በደንብ ተምሮ ከጨረሰ በኋላ ወደ ደብረ ሮሐ ተመልሶ መጥቶ ነግሦ ከነበረው ከወንድሙ ከገብረ ማርያም ዘንድ ተቀመጠ፡፡ ‹‹ከገብረ ማርያም ቀጥሎ የሚነግሠው ላሊበላ ነው›› ተብሎ ትንቢት ስለተነገ
ፈ በኋላ በግ ጠባቂው ያን ብላቴና ባሕራን ብሎ ሲጠራው በሰማ ጊዜ "ልጅህ ነውን?" ብሎ ጠየቀው። በግ ጠባቂውም "አዎን ይህ አሁን ጐልማሳ ሆኖ የምታየው ወጣት ገና ሕፃን ሆኖ ሳለ በሣጥን ተከቶ ከባሕር ውስጥ ተጥሎ አግኝቼው ወስጄ አሳድጌዋለሁና ልጄ ነው" አለው። ባለጸጋውም በባሕር ውስጥ የጣለው ሕፃን መሆኑንም ስላወቀ ይህንን ነገር በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደነገጠ፤ ይገድለውም ዘንድ ፈለገ፡፡
በበነጋውም መንገዱን ለመሄድ ሲዘጋጅ ልዩ ልዩ ምክንያት (ሰይጣናዊ ሃሳብ) በመፍጠር በግ ጠባቂውን "ወንድሜ ሆይ አንድ የማስቸግርህ ጉዳይ አለኝ ይኸውም በቤቴ የረሳሁት ነገር ስላለ ዕገሊት ወደ ምትባል ሀገር ሄዶ መልእክት ያደርስልኝ ዘንድ ይህን ብላቴና እንድትሰጠኝ ነው የድካሙንም ዋጋ ሃያ ወቄት ወርቅ እከፍላለሁ" አለው።
ያም በግ ጠባቂ ስለ ወርቁ ስጦታ ደስ በመሰኘት ያን ጐልማሳ ጠርቶ "ልጄ ባሕራን ሆይ ይህ ክቡር ሰው ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤቱ ሊልክህ ይፈልጋልና መልእክቱን አድርስለት እግዚአብሔር በሰላም ያግባህ" ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም "እሺ መልካም ነው አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁ ነኝ" አለው። ከዚህም በኋላ ያ ባለጸጋ "ይህችን የመልእክት ደብዳቤ ይዞ ወደ አንተ የመጣውን ስሙ ባሕራን የተባለውን መልእክቷ በደረሰችህ ጊዜ ፈጥነህ ግደለው ገድለህም ሬሣውን ከጉድጓድ ጣለው እኔ በሰላም ተመልሼ እስክመጣ ድረስ ማንም ማን ይህን ምሥጢር አይወቅ" የሚል ጽሑፍ ለሹሙ ጽፎ አዘጋጀ፡፡ እንዲሁም በሹሙና በእርሱ መካከል የሚተዋወቁበትን ማኅተም በደብዳቤው ላይ አትሞ ለባሕራን ሰጠው፡፡ ለመንገዱም የሚሆነው ስንቅ ሰጥቶ ላከው።
ባሕራንም መልእክቱን ለማድረስ ዘጠኝ ቀን ተጉዞ የአንድ ቀን ጎዳና ሲቀረው እነሆ ክቡር የሚሆን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በንጉስ ጭፍራ አምሳል በፈረስ ተቀምጦ ወደሱ ደረሰና ወዴት እንደሚሄድ ጠየቀው፡፡
ባሕራንም "ከአንድ ባለጸጋ ሰው የተጻፈ ደብዳቤ ይዤ እርሱን ለማድረስ ዕገሊት ወደምትባል አገር እሄዳለሁ" አለው። ንዑድ ክቡር የሚሆን ቅዱስ ሚካኤልም "እስኪ የመልእክቱን ደብዳቤ አሳየኝ?" አለው፡፡ ባሕራንም "ጌታዬ ለማንም አታሳይ ብሎኛል" አለው፡፡ መልአኩም "እሺ ያም ባይሆን እንደተጠቀለለ አሳየኝ" አለው፡፡ ባሕራንም አሳየው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በሞቱ ደብዳቤ ላይ እፍ ቢልበት የሞቱን ትእዛዝ አጥፍቶ የሕይወት ትዕዛዝ ጽፎበታል፡፡ በደብዳቤው ላይ የተጻፈውን የሞት መልእክት ደምስሶ "ከእኔ ከባለጸጋ ዕገሌ የተጻፈ" ይልና "ይህን መልእክት ይዞ ለመጣሰው ዕገሊት የምት ባለዋን ልጄን አጋቡት (ዳሩለት) በዱር የተሰማራውን ከብቴን በቤት ያለውን ሀብቴን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረቴን በሙሉ አውርሼዋለሁና እኔ እስክመጣ ድረስ አትጠብቁ በሄድኩበት ሀገር የምቆይበት ጉዳይ አለኝና፤ በቤቴና በንብረቴ ላይ ሙሉ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና የወደደውን ያደርግ ዘንድ አትከልክሉት ስለዚህም በእኔና በአንተ መካከል የምንተዋወቅበትን ምልክት አድርጌበታለሁ" የሚል ጽሑፍ ጽፎ ሰጠውና "እንግዲህ ወደ ባለጸጋው ቤት ሂድና ይህን መልእክት አድርስ ነገሩ እንዳይገለጽብህ ከእኔ ጋር መገናኘታችንንና የመልእክቱን ጽሑፍ እንደለወጥኩልህ ለማንም አትንገር" ሲል አስጠነቀቀው፡፡ ባሕራንም "እሺ ጌታዬ እንዳዘዝከኝ አደርጋለሁ" ብሎ ጉዞውን ቀጠለና የዚያን የባለፀጋ ቤት እየጠየቀ ከደረሰበት በኋላ ደብዳቤውን ለሹሙ ሰጠው።
ያም ሹም ደብዳቤውን ተቀብሎ ሲያነብ የታተመበት ማኅተም ዕውነተኛ መሆኑን ከአረጋገጠ በኋላ እግዚአብሔር እንዳዘዘው በቤተ ክርስቲያን ደንብ የባለጸጋውን ልጅ በተክሊል አጋባው፣ የሠርጉንም በዓል እስከ ዐርባ ቀን ድረስ በታላቅ ደስታ አከበሩ። ከሠርጉም በዓል ፍጻሜ በኋላ ያ ባለጸጋ ሰው ከሄደበት አገር ወደ ሀገሩ ተመልሶ ገባና በቤቱ አካባቢ ሲደርስ የደስታና የዘፈን ድምፅ ስለሰማ "ይህ የምሰማው ድምፅ ምንድነው?" ሲል ጠየቀ፡፡ ሰዎቹም "ባሕራን የተባለ ጐበዝ ካንተ ዘንድ ልጄን ዳሩለት የሚል ትእዛዝ አምጥቶ ልጅህን አግብቶ በሠርጉ ምክንያት ይዘፍናሉ ይደሰታሉ እነሆ እየበሉና እየጠጡ በቀንና በሌሊት እየዘፈኑ ሲደሰቱ ዐርባ ቀን ሆኗቸዋል በመልእክትህም እንዳዘዝከው ገንዘብህን የወንድና የሴት ባሮችህን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረትህን ሁሉ በሙሉ አስረክበውታል" አሉት።
ያም ባለጸጋ ያህን ቃል በሰማ ጊዜ ከድንጋጤው የተነሳ በታላቅ ቃል በመጮኽ ከመሬት ላይ ተከስክሶ ሞተና ነፍሱን አጋንንት ተረክበው ወደ ሲኦል አወረዷት። ከዚህም በኋላ ባሕራን የተባለ ያ ጐልማሳ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ እያከበረ ዝክሩን እየዘከረ ይኖር ጀመር። በዚያን ጊዜ በጉዞ ላይ ሳለ ተገልጾለት የሞቱን መልእክት ወደ ሕይወት የለወጠለት ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነም አወቀ ተረዳ። ንዑድ ክቡር የሚሆን የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ሊቆጥሩት የማይቻል ብዙ ስለሆነ በኛም ላይ ኃይለ ረድኤቱ አድሮብን ይኑር እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን።
+ + +
ቅድስት አፎምያ፡- ቅድስት አፎምያ ሀገሯ ኪልቅያ ነው፡፡ ባለቤቷ አስተራኒቆስ መስፍነ ኪልቅያ ነበረ፡፡ እርሷም በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ደገኛ ሴት ናት፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ ነበር፡፡
ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እርሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡ ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ ባሏም ታሞ ሞቶ ከሀብቷ ከንብረቷ እየሰጠች እየመጸወተች በጾም በጸሎት ተወስና ትኖር ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ደግ መነኩሴ መስሎ አጋንንትን መነኮሳይያት አስመስሎ መጥቶ ከደጅ ሆኖ አስጠራት፡፡ እርሷም "ከቤት ገብታችሁ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ጸልዩልኝ" አለቻቸው፡፡ ሰይጣናቱም "እኛማ በነግህ ጸልየናል?" አሏት፡፡ ቀጥሎም ሰይጣን "...እንደው አንቺ ግን ይህ ሁሉ ጾም ጸሎት ምን ያደርገልሻል? ሀብትሽን ሰጥተሸ መጨረስሽስ ስለምንድን ነው? በዚያ ላይ አንቺ ስትደክሚ የሚደግፍሽ ስታረጂ የሚጦርሽ ልጅ የለሽም ሁለተኛ ማግባት ኃጢአት መስሎሻልን? እነ አብርሃም እነ ዳዊ ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች ወልደው የለምን? አሁንም ቤት ሰሪ ጎመን ዘሪ ልጅ ያስፈልግሻልና ባል አግቢ፣ እሺ በይኝ" አላት፡፡
ቅድስት አፎምያም "አባ ቆብህ መልካም ነበር ንግግርህ ግን ክፉ ነው፣ አትጹሚ አትጸልዩ ያልከኝ ጌታ ምጽዋት አበድር እመስዋዕት ብሎ የለምን? ሁለተኛ ባል አግቢ ማለትንስ ከምን አገኘኸው? እርግቦች እንኳ ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ከሌላ ወንድ አይቀርቡም ታዲያ ጥንቱን በንጽሕና ሊኖር የተፈጠረ ሰው ሁለተኛ አላገባም ቢል ዕዳ ፍዳ ሊሆንበት ነውን?" ብላ ሞገተችው፡፡
የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ አይቷታልና ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ ከላይ እንዳየነው በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ ሌላ ባል አግብታ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡ ቅድስት አፎምያ ግ
"በማእከለ አስዋክ"
በዘማሪት መቅደስ ዓለሙ
@Ethiop_tewahido
@Ethiop_tewahido
@Ethiop_tewahido
ሰኔ ፰
የእመቤታችን ማርያም ቅዳሴ ቤት
ሰኔ ስምንት በዚች ቀን አምላክን የወለደች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የእመቤታችን ማርያም የታወቀችው በውኃ ምንጭ ዘንድ ያለች የቤተ ክርስቲያንዋ ቅዳሴ ነው። እርሱም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ጋር ወደ ግብጽ አገር ተሰዶ ሲመለስ ያፈለቀው የተባረከ መታጠቢያ ነው።
ይህም እንዲህ ነው ለጻድቁ ዮሴፍ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገልጾለት ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ አገር ሒድ አለው። ዮሴፍም ነቅቶ ተነሣ ክብር ይግባውና ሕፃኑን ጌታችንን እናቱንና እኅቷ ሰሎሜን ይዞ ወደ ግብጽ አገር ሔዱ በዚያም በውስጧ ባሉ በብዙ አገሮች እየዞሩ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ኖሩ።
ሄሮድስም ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ሁለተኛ ተገለጠለት ወደ እስራኤልም አገር ሕፃኑንና እናቱን ይዞ እንዲመለስ አዘዘው። በሚመለሱም ጊዜ ወደ መዓልቃ ደረሱ ከዚያም ወደ መጣርያ አገር ደረሱ ይቺም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውኃ ያፈለቀባትና የመታጠቢያ ቦታ የሆነች ናት እርሷም እስከ ዛሬ አለች ሰዎችም ከአገሩ ሁሉ ከየነገዱ ሁሉ መጥተው አምላክን ወደ ወለደችና በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደ ጸናች ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ይለምናሉ ከተባረከውም የውኃ ምንጭ ታጥበው ከደዌያቸው ሁሉ ይድናሉ በዛሬዪቱ ቀን ከከበረች ቤተ ክርስቲያንም ይባረካሉ።
እርሷን እመቤታችንን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እናቱ ላደረጋት ስለርሷም ዘመድ ለሆነንና ወደርሱ ላቀረበን ወራሾቹም ላደረገን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
@Ethiop_tewahido
@Ethiop_tewahido
@Ethiop_tewahido
ምስባክ፦
ዐረገ እግዚአብሔር በይባቤ ፤
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን፤
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"ማርያም አንቲ"
ማርያም አንቲ ደመና ሰማይ ዘአኃዝኪ ዝናመ(፪)
ተክላተ መሬት አዳም ወሔዋን ዘፈረዩ ብኪ ዳግመ(፪)
ከመሬት የተገኙ አዳምና ሔዋን ሕይወት ያገኙብሽ(፪)
ዝናምን የያዝሽ የሰማይ ደመና ማርያም አንቺ ነሽ(፪)
በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ግንቦት ፳፩
ደብረ ምጥማቅ
ከሠላሳ ሶስቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ነው። ደብረ ምጥማቅ በግብፅ ሀገር በምኔተ ገምኑዲ አቅራቢያ የምትገኝ ቦታ ናት። እመቤታችን በስደት ሳለች ጌታ በዚህ ቦታ በስምሽ ዐብይ ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ ስሙንም ደብረ ምጥማቅ ይሉታል ብሎ ነግሯት ነበር። ይኸውም አልቀረ፤ በዚሁ ቦታ በእመቤታችን ስም ቤተክርስቲያን ታንጾ ስሙ ደብረ ምጥማቅ ተብሏል።
በዚህም ዕለት እመቤታችን ከፀሐይ ሰባት እጅ አብርታ ከጉልላቱ ላይ በመንበረ ብርሃን ተቀምጣ መላእክት ሊቃነ መላእክት ከበው ሲያመሰግኗት ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት እጅ ሲነሷት ታይታለች። “እንዘ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኃምሰ ዕለታተ” እንዳለ ደራሲ በልጇ የመለኮት ብርሃን አሸብርቃ መላእክት: ሊቃነ መላእክት: ኪሩቤል: ሱራፌል ከበዋት ነቢያት: ሐዋርያት: ሰማዕታት: ደናግላን: መነኮሳት ሄሮድስ ያስፈጃቸው ሕፃናት ይመጣሉ። ሱራፌል ማዕጠንት ይዘው በእያንዳንዱ እያመሰገኑ ያጥኑ ነበር። ከሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ተከትሎ ቅዱስ መርቆርዮስ በጥቁር ፈረስ በየተራ እየመጡ ይሰግዱላታል።
ከፊቷ ብርሃን የተነሣ 5 ቀን ሌሊቱና ቀኑ አይታወቅም ነበር። በዚህ ጊዜ ልብሳቸውን ወደ ላይ ሲወረውሩላት የፈቀደችውን ተቀብላ ትልክላቸዋለች። ከዚያም ለበረከት ይካፈሉታል። ከተሰበሰቡትም እስኪ እገሌን አስነሺልን እያሉ ሲለምኗት አስነሥታ በሕይወተ ሥጋ ታሳያቸው ነበር። እንዲህ እየሆኑ በፍጹም ደስታ ሰንብተዋል። እስከ አምስት ቀንም ምዕመናኑን አረማውያኑንም አንድ ወገን አድርጋ ስትባርክ ሰንብታለች። ከዚህም በኋላ ምዕመናኑም አረማውያኑም በየዓመቱ እኚህን አምስት ዕለታት በደብረ ምጥማቅ ተሰብስበው የሚያከብሩ ሆነዋል። የበዓሉ መታሰቢያ ከግንቦት 21 እስከ 25 ቀን ነው።
ግንቦት 21 በደብረ ምጥማቅ በገሃድ ተገልጻ ታላቅ ተአምር ያደረገችበት፡፡
ግንቦት 22 በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡
ግንቦት 23 በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡
ግንቦት 24 እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ይዛ ከአረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በመሰደድ ግብፅ አገር የገባችበት ዕለት፡፡
ግንቦት 25 ተወዳጅ ልጇ የደረቁ በትሮችን ተክሎ በተአምራት ያለመለመበት ዕለት፡፡
በዚህ ዕለትም እናታችን፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ለ5 ቀን በግልጽ መታየቷ የሞቱት መነሳታቸው ብርሃን መሆኑ ጨለማ መጥፋቱ የሰውን ልመና መቀበሏ ወዘተ ይነገራል። የቅድስት እናታችን ረድኤት በረከቷ አማላጅነቷ አይለየን፣ ጣዕሟን ፍቅሯን አይለይብን። የዓመት ሰው ይበለን፣ አሜን!
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
“ድንግል ሆይ በሁሉ አንደበት መመስገን የተገባሽ ስለሆነ በሰማይ ካሉ መላእክትና በምድር ከሚኖሩ ደቂቀ አዳም ሁል ጊዜ ምስጋና ይቀርብልሻል።” ቅዳሴ ማርያም
“ሰላም ለእለ ርእዩኪ ከመ ዐይነ ወለት ኀበ እማ፣
መዋዕል ኃምስ እስከ ይትፌጸማ፣
ማርያም ንግስት ዘደብረ ምጥማቅ ከተማ፣
ብፁዓት አዕይንት ዘነጸራኪ በግርማ፣
ወብፁዓት አእጋር ቅድሜኪ ዘቆማ።” እን ዐርኬ
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ምንጭ፡ መዝገበ ታሪክ 2 ገጽ 87፣ መድብለ ታሪክ ገጽ 383
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2. የወር አበባ ርኩሰት ባይሆንም እንኳ እዳሪ (አደፍ) መሆኑ ተገልጿል:: ስለዚህ ከወር አበባ ሳይነጹ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ነውርና ጸያፍ የሆነ ነገርን ይዞ እንደ መግባት ይቆጠራል። በቤተክርስቲያን እንትፍ (አክ) ማለት ነውር እንደሆነ የወር አበባም እንዲሁ ነውና ወደ ቤተ መቅደስ አያስገባም፡፡ የዚህ ምስጢር ከወንዶች ሕልመ ሌሊት ጋር ይመሳሰላልና ያንን ማንበብ ያሻል፡፡
ውሻን ከቤተ እግዚአብሔር ማኖር የማያስፈልግበት ምክንያት ከሌሎች እንስሳት እርሱ የተለየ ሆኖ አይደለም:: ነገር ግን በየደረሰበት ለመሽናት እግሩን ያነሣልና በዚህ ምክንያት ውሻ ወደ ቤተ እግዚአብሔር እንዳይገባ ይደረጋል፡፡ ውሻን ቤተ እግዚአብሔር ገብቶ ያገኘው ሰው ሁሉ አባርሮ ያስወጣዋል፡፡ ይህ በመለመዱ ብዙዎች ፊት የነሡት አንድ ሰው «ከቤተ እግዚአብሔር የገባ ውሻ አደረጉኝ!» እያለ በራሱ ይተርታል:: የውሻ አለመፈለግ ለቤተ እግዚአብሔር ንጽሕና ሲባል ብቻ ነው፡፡ ሰውም ቢሆን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሲሄድ ከሥጋዊ እድፍም ንጹሕ መሆን ይኖርበታል። ዘፍ19፥14
3. <<መቅደሴን ፍሩ» በማለት ፈጣሪያችን እግዚአብሔር መቅደሱን እንድንፈራ አዝዞናል፡፡ መቅደሱን መፍራትና ማክበር እርሱን መፍራትና ማክበር ነውና፡፡ ዘሌ 26፥2 ቅዱስ ዳዊትም «አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ» በማለት በቤተ መቅደስ ፈሪሃ እግዚአብሔር እንደሚያስፈልግ ገልጿል፡፡ መዝ 5፥7 ሕግና ሥርዓት ከሌለ አክብሮትና ፍርሃት አይኖርም ሕግ ሲኖር ግን ፍርሃት ይኖራል:: የወር አበባን የመሰሉ ወደ ቤተ መቅደስ ከመግባት የሚያግዱ ሥርዓቶችም ቤተ መቅደስ የሕግ ባለቤት የእግዚአብሔር መኖሪያ መሆኗን በማስረዳት ፍርሃት በሰው ልቡና እንዲሳል ይረዳሉ፡፡
ቤተ መቅደስ እንደፈቀዱ የሚገቡባትና የሚወጡባት ብትሆን ኖሮ ቀላ ትገኝ ነበር:: ይህ ባለመሆኑ ግን እስከዛሬ ድረስ ግርማ ተጐናጽፋ ትገኛለች:: "በወር አበባ ላይ ሳላችሁ ሕልመ ሌሊት አግኝቷችሁ ወደ ቤተ መቅደስ አትግቡ፣ አደግድጉ፣ ጫማችውን አውልቁ፣ የወንድ፣ የሴትና የካህናትን መቆሚያ ለይታችሁ ቁሙ ፣ አትሣቁ፣ ተራ ወሬ አታውሩ" የሚሉት ትእዛዛት ፍርሃት አያሳድሩምን? ይህን የመሳሰሉ ሥርዓቶችና ትእዛዛት ቤተ ክርስቲያን ባይኖሯት ኖሮ ዛሬ እንደምናያቸው የመናፍቃን አዳራሾች መጋዘንና በረት ባልሆነችም ነበርን?
4. በብዙ ክርስቲያኖች ዘንድ መንፈሳዊ ሥራ በስሜትና በልማድ ይሠራል:: በዚህ መልኩ ሥራን መሥራት አእምሮን ያለ ፍሬ ያስቀራል:: ልማድና ስሜት በማስተዋል ወደ ተግባር መቀየር አለባቸው እንጅ በልማድነታችው ሲዘልቁ ጉዳት አላቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከየት እንደጀመርንና የት መፈጸም እንዳለብን ሳናስተውል በልማድ የምንጸልይበት ጊዜ አለ:: ሌላ ጊዜ ደግሞ ከልማድ የተነሣ የድርጅቶችንና የትምህርት ቤቶችን ሰፊ ደጅአፍ እንደ ቤተክርስቲያን ቆጥረን አማትበን የምንሣለምበት ጊዜ አለ፡፡ ይህ የሚሆነው ከልብ ሳንሆን ስንቀርና በልማድ አማካኝነት ነው።
በወር አበባ ወቅትና በሌሎች ክስተቶች ወደ ቤተክርስቲያን እንዳንገባ መከልከላችን ከልማድ ወጥተን በአእምሮ እንድንመላለስ ይረዳል:: መቼ መግባት መቼ አለመግባት እንዳለብንና ለምን እንደማንገባ ማሰብ ራስን ለመመርመር የሚያግዝ መንገድ ነው:: ራሳችንንና ያለንበትን ሁኔታ መርምሮ ማወቅ ደግሞ ትልቅ ጥቅም ነው::
በልማድ ቤተ እግዚአብሔር የሚመላለሱ ሰዎች ቤተ እግዚአብሔር አለመሄድንም ከተለማመዱ ቀልጠው ይቀራሉ፡፡ ልማድ በልማድ ይሸነፋልና፡፡ ነገር ግን ለምን እንደሚመላለሱ ምክንያቱንና ጥቅሙን እያስተዋሉ ከልማድ ወጥተው በማስተዋል የሚመላለሱ ሰዎች ግን «በእግዚአብሔር ቤት እንደተተከለና እንደለመለመ የወይራ ዛፍ ይሆናሉ» መዝ51፥8
ወደ ቤተ መቅደስ እንዳንገባ የተከለከልንባቸው ወቅቶችና ሁኔታዎች እንደ ሱስ በልማድ ብቻ ወደ ቤተ መቅደስ እንዳንጓዝ ከልማድ ያወጡናል:: በአንጻሩ በማስተዋል እንድንመላለስ ያደርጉናል፡፡ ብንሄድ የምናገኘውን ጥቅም ባንሄድ ደግሞ የሚቀርብንን ጸጋ ዓይናችንን ገልጠው የሚያሳዩን እነዚህ ሥርዓቶች ናቸው::
5. እናታችን ሔዋን ደመ ዕፀ በለስን በማፍሰሷ ምክንያት ከገነት ተባረረች:: ደሟም በየወሩ እንዲፈስ ተፈረደባት:: ነገር ግን ከእርሷ አብራክ ከተገኘች ከድንግል ማርያም የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ደሙን በማፍሰሱ መርገም ተወገደ፡፡ ዛሬ ሴቶች በወር አበባ ምክንያት ወደ ቤተ መቅደስ ከመግባት ሲከለከሉ የቀደመ ታሪካቸውን ያስታውሳሉ፡፡ ራሳቸውን በመውቀስም ትኍት ይሆናሉ፡፡ ተመልሰውም ወደ ገነት እንዲገቡ በፈጣሪ የተደረገላቸውን ውለታ በማስታወስ ፈጣሪን ያመሰግናሉ፡፡ ስለዚህ በወር አበባ ወቅት ወደ መቅደስ መግባት መከልከሉ የቀድሞውን ዘመን ለማስታወስ ይረዳል ማለት ነው፡፡
6. ቤተ መቅደስ የገነት ምሳሌ ናት፡፡ እናታችን ሔዋን ከአዳም ጋር ለሰባት ዓመታት በገነት ስትኖር የወር አበባ አታይም ነበር። ቤተ መቅደስ ለገነት ምሳሌ መሆኗ የተሟላ እንዲሆን የወር አበባ የምታይ ሴት ወደ ቤተ መቅደስ አትገባም፡፡
«ትገብእ ነፍስ ኀበ ፈጣሪሃ ወታቀድም ሰጊደ ለልዑል» እንደ ተባለው «ነፍስ ወደ ፈጣሪዋ ትመለሳለች:: ያን ጊዜ አስቀድማ ለልዑል እግዚአብሔር ትሰግዳለች» ይኽችውም ነፍስ ጻድቅ የሆነች እንደሆነ ከልካይ ሳይኖርባት ወደ ፈጣሪዋ ገብታ ቀርባ ትሰግድና የተዘጋጀላትን ክብር ትወርሳለች፡፡ ነገር ግን የኃጥእ ሰው ነፍስ የሆነች እንደሆነ በሩቅ ሰግዳ ትመለሳለች እንጂ ወደ ፈጣሪዋ አትገባም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በዚህ ዓለም ወደ ቤተ መቅደስ ለመግባት የማያስችል ማንኛውም እክል የገጠመው ሰው ቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ብቻ አልፎ ገብቶ ይሳለምና እጅ ነሥቶ ይመለሳል እንጂ ወደ መቅደስ ተደፋፍሮ ሊገባ አይገባውም፡፡ (ትምህርተ ኅቡአት ትርጓሜ) ወደ ቤተ መቅደስ ከማያስገቡ እክሎች መካከል ደግሞ የወር አበባ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡
7. ሰው ላልያዘውና ላላገኘው ነገር ጉጉ እንደሆነ ሁሉ የጓጓለትንም ነገር ያገኘ እንደሆነ ቶሎ የሚሰለች ፍጡር ነው:: ስለዚህ ወደ ቤተ መቅደስ እንዳንገባ በምንከለከልበት ጊዜ ትላንት የገባንበትን ቤተ መቅደስ ከመሰልቸት ይልቅ በአዲስ መልኩ ገብቶ ለማስቀደስ እንድንጓጓ ያደርገናል፡፡ ስለዚህ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ማስቀደስ ብርቅ እንዲሆንብንና እንድንጓጓ ለማድረግ ይህን የመሰሉ ሥርዓቶች ያላቸውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ መረዳት ይግባል፡፡
በእርግጥ በማስተዋልና በመረዳት ከሆነ ተግቶ ወደ ቤተ መቅደስ መመላለስ አይሰለችም:: ነገር ግን ይህ ማስተዋልና ትጋት በሁሉ ዘንድ አይገኝምና ስለ ሥጋ ድካም ሲባል እንደዚህ ዓይነት ሥርዓቶች ተሠርተዋል:: በነዚህም ሥርዓቶች ከጽኑ ሰው ይልቅ ስልቹ ሰው በይበልጥ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ይህ ሥርዓት ስልቹ ሰውን በናፍቆት ወደ ቤተ እግዚአብሔር እንዲገሠግስ ያደርገዋል፡፡ ስልቹ ያልሆነ ሰው ግን ምንም እንኳን ልዩ ልዩ እክሎች ወደ ቤተ መቅደስ እንዳይገባ ቢከለክሉትም በቀላሉ ተዘናግቶ ቤተ ክርስቲያን ከመሄድ አይሰንፍም፡፡
ጾመ ሐዋርያት
ጾመ ሐዋርያት በወርኃ ሰኔ ስለሚጾም በምእመናን ዘንድ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፤ ከሰባቱ የዐዋጅ አጽዋማትም አንዱ ነው፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡
ይህም ጾም ከበዓለ ኀምሳ በኋላ የሚጾም ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ቅዱሳን ሐዋርያት በጸሎት ይተጉ ወደ ነበረበት ቤት በመሄድ ደቀመዛሙርቱን ይዟቸው ከቤት በመውጣት መንገድ ጀመረ፡፡ እርሱ ከፊት እየመራቸው እነርሱ እየተከተሉት ወደ ረጅሙና በረጃጅም ዛፎች ወደ ተሞላው ደብረ ዘይት ተራራ ይዟቸው ወጣ፡፡ ይህንንም እየነገራቸው ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ፤ከፍ አለ፡፡ ነጭ የሆነች ብሩህ ደመናም አምላካችንን ተቀበለችው፡፡ከዓይናቸውም እየራቀ፤ከእይታቸው በርቀት ሳይሆን በርኅቀት ተሰወረባቸው፡፡ሐዋርያትም ኢየሱስ ክርስቶስን በጣም ይወዱት ስለነበር ሲለያቸው አዝነው አተኩረው ሰማዩን ለረጅም ሰዓት ተመለከቱ፡፡ ድንገትም ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ቅዱሳን መላእክት በአጠገባቸው ቆመው ታዩአቸው፡፡መላእክትም ሐዋርያትን እንዲህ አሏቸው፤ ‹‹እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል፡፡ ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል›› አሏቸው፤ (ሐዋ. ፩፥፰-፲፩)፡፡ ሐዋርያትም የመላእክትን ማረጋጊያ ቃል ከሰሙ በኋላ በኢየሩሳሌም ወደ ምትገኘው ቤተ መቅደስ በመሄድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገራቸው እስኪፈጸም ድረስ ቀን ከሌሊት በአንድነት ሆነው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከመካከላቸው አድርገው በጾምና በጸሎት እየተጉ ቆዩ፡፡
የጾመ ሐዋርያት የጊዜ ቀመር ሥሌት በዓለ ጰራቅሊጦስ እንደ ገባ ባለው የመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ በዚህም መሰረት የዘንድሮ ጾመ ሐዋርያት ሰኔ ፲፯(17) ይገባል። ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት እንዲህ ተናግሮ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። ‹‹እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት›› (ማቴ.፱፥፲፬)። ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ ጌታችን እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር፡፡‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ያንጊዜም ይጾማሉ›› (ማቴ.፱፥፲፭)፡፡
እኔ ሳለሁ አይጾሙም ማለቱ እርሱ ካልሞተና ካላረገ፤ መንፈስ ቅዱስም ካልተሰጣቸው በመንፈስ ቅዱስ ባልታደሰ ሰውነት ጾመው ድል መንሳት ስለማይቻላቸው ነው፡፡ ይህን ጾም የምንጾመው ሐዋርያት ጾመው ጸልየው ድል ያደረጉትን ዓለም እኛም የምናሸንፍበት ኃይል እንዲሰጠን ፈጣሪያችንን አምላከ ሐዋርያት ተለመነን እያልን ለመማጸን ነው፡፡
ይህን ጾም እንደ ሌሎቹ አጽዋማት ሁሉ እያንዳንዱ ምእመን ሊጾመው የሚገባ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን አብዛኛው ምእመን ‹‹የቄስ ጾም›› ነው በማለት ከጾሙ ሽሽት ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተክርስትያንን መሠረት ያደረገ ባለመሆኑ መስተካከል ይገባዋል፡፡
ሐዋርያትን አብነት በማድረግ ጾመን በረከትን ልናተርፍ ይገባናል፡፡
የአምላካችን የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት፣
የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣
የቅዱሳን ሐዋርያት በረከት፣
የጻድቃን የሰማዕታት ጸሎት እና ምልጃ አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን፡፡
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
በዓለ ጰራቅሊጦስ
መንፈስ ቅዱስ ከሚጠራባቸው ስሞች አንዱ ጰራቅሊጦስ ናዛዚ መጽንዒ መስተፍሥሒ፤ የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ የሚል ትርጉም አለው፡፡ አጽናኝም የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ‹‹አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል፤ እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋ›› ብሎ ተናግሯል፡፡ በሌላም በኩል ደግሞ ‹‹እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ ጰራቅሊጦስ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል›› እንዲል። (ዮሐ.፲፬፥፳፮፤ ፲፭፥፲፮)
ጰራቅሊጦስ የሚለው የመንፈስ ቅዱስ ስም የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ መሆኑም ከማሳየት በላይ፤ ፍጹም አካል ያለው አምላክ እንደሆነ አመልካች ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጰራቅሊጦስ ማለት መሪ፣ አጽናኝ፣ ረጂ ማለት መሆኑን በስፋት ካስተማሩ ሊቃውንት በቀዳሚነት ይነሳል። ጰራቅሊጦሰ የተባለው መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው። ሐዋርያዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ያላትን እምነቷን ስትገልጥ ‹‹ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማኅየዊ ዘሠረፀ እም አብ ንሰግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ››፤ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረፀ ከአብ ከወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን፣ እናመሰግነዋለን፤›› የሚል ነው።
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ፤ የቅድስናም ምንጭ ነው። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ‹‹ወስመ መንፈስ ቅዱስ ነቅዐ ቅድሳትየ፤ የመንፈስ ቅዱስም ስም የቅድስናየ መገኛ ነው›› በማለት ገልጾታል። (መጽሐፈ ምሥጢር)
ቅዱስ ባስልዮስም በቅዳሴው ‹‹ሃሌ ሉያ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር መንፈስ ቅዱስ ንጹሕ ክቡር ልዩ ነው›› በማለት አምላካዊ ስሙን ጠርቶ አመስግኖታል። ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ዕለት ዕለት በምታከናውነው ሥርዓተ ቅዳሴ ‹‹መንጽሒ ወመጽንዒ የሚሆን መንፈስ ቅዱስ ክቡር ምስጉን ነው›› እያለች የአምላክነት ስሙን ጠርታ ታመሰግነዋለች።
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ሊያጸኑ ከሓድያንን ሊለዩ (ሊያወግዙ) ሲሰባሰቡ በመካከላቸው ተገኝቶ ውሳኔ ያስወስናቸው የነበረው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ሲገልጹ ጰራቅሊጦስ የተባለ ስሙን ጠርተው እንዲህ ብለዋል፣ ‹‹ወሀሎ ምስሌሆሙ ኅብረ መንፈስ ቅዱስ …. ጰራቅሊጦስ የሚያነጻና የሚያጸና መንፈስ ቅዱስም በጉባኤያቸው ነበረ፡፡›› (መጽሐፈ ምሥጢር)
ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ሰባ ሁለቱ አርድእት እና ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ሆነው በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ‹‹እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤›› ሲል ለሐዋርያቱ በሰጣቸው የተስፋ ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል (ሉቃ. ፳፬፥፵፱)፡፡ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በሁሉም ላይ አረፉባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሁላቸውም መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየሀገሩ ቋንቋዎች ሁሉ ተናገሩ፡፡ (ሐዋ.፪፥፩-፬)
ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ዐሥራቱን፣ በኵራቱን፣ ቀዳምያቱን ካህናተ ኦሪት ስለሚቀበሉበት በብሉይ ኪዳን በዓለ ሠዊት ተብሎ ይከበር ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ስለ ተቀበሉበት በበዓለ ሠዊት ምትክ በዓለ ጰራቅሊጦስ ተብሎ ይከበራል፡፡ የበዓለ ትንሣኤ መነሻው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ማለትም በግብጽ፣ እስራኤል ከሞት የዳኑበት የመታሰቢያ በዓል እንደ ሆነው ሁሉ፣ ለበዓለ ጰራቅሊጦስም መነሻው ይኸው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ነው፡፡ የአይሁድ ፋሲካ ከተከበረ ከሰባት ሳምንታት በኋላ በኀምሳኛው ቀን የሩቆቹ ከከተሙበት ወጥተው፣ የቅርቦቹ ከተሰባሰቡበት ተገናኝተው ለበዓሉ ፍጻሜ የሚሆነውን በዓለ ሠዊት (የእሸት በዓል) ያከብሩ ነበር፡፡
ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰባስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጐልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ሆነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል፡፡ ቀድሞ ይናገሩት ከነበሩት ቋንቋ በተጨማሪ ፸፩ ቋንቋዎች ተገልጠውላቸው ምሥጢራትን በልዩ ልዩ ቋንቋ መተርጐም ጀምረዋል፡፡ ሐዋርያት በየሀገሩ ቋንቋ ሲናገሩ የሰሙ በዚያ የነበሩ ሰዎችም በሐዋርያት ተገረሙ፡፡ አንዳንድ የአይሁድ ወገኖች ግን በሐዋርያት ላይ ያዩት ክሥተት አዲስ ነገር ስለሆነባቸው ‹‹ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ሰክረው የሆነ ያልሆነውን ይቀባጥራሉ›› እያሉ ሐዋርያትን ያሟቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ይህንን ሐሳባቸውን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ‹‹ሰክረዋል የምትሉ እናንተ እንደምትጠራጠሩት አይደለም፡፡ ጊዜው ማለዳ፣ ሰዓቱም ገና ሦስት ሰዓት ነውና፡፡ ግን በነቢዩ ኢዩኤል ‹ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ፣ ይህንን ድንቅ ተአምር ያደረገው እናንተ የሰቀላችሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤››በማለት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥቷቸዋል፡፡ (ኢዩ.፪፥፳፰)
በትምህርቱም ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት፣ምሳሌ የመሰሉለት አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ማረጉንና ዳግም በክብር በምስጋና መጥቶ በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈረድ መሆኑን ሐዋርያት እንደሚመሰክሩ በአይሁድ ፊት አሰምቶ ተናገረ፡፡በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም ‹‹ምን እናድርግ?››ብለው በጠየቁት ጊዜ ከክፋታቸው ተመልሰው፣ንስሓ ገብተው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ ነገሯቸዋል፡፡ በዚያችም ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ተጠምቋል፡፡(ሐዋ.፪፥፩-፵፩)
ቅዱሳን ሐዋርያት፤ ‹‹በዚህች ቀን በሦስት ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና በላያችን ኃይልን ሞላ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን እንዳለው በአዲስ ቋንቋ ተናገርን፤›› በማለት በዕለቱ ያዩትንና የተደረገላቸውን፣ እንደዚሁም የበዓሉን ታላቅነት ከመሰከሩ በኋላ ይህንን በዓል ማክበር እንደሚገባ አዝዘዋል፤ በዚህ ወቅት መጾምና ማዘን ተገቢ አለመሆኑንም ተናግረዋል፡፡ (ዲድስቅልያ ፴፥፴፰-፴፱፤ ፴፩፥፷፱-፸)
ቅዱሳን ሐዋርያትም ‹‹ከአብ የሠረፀ የሁላችንም መጽናኛ የሚሆን ዓለሙንም ሁሉ ያዳነ ከአብና ከወልድ ጋር ህልው የሚሆን መንፈስ ቅዱስን ላከልን፡፡ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስም አንድ ነው›› ብለዋል። በሌላም ነቢዩ ዳዊት ስለመንፈስ ቅዱስ ‹‹መንፈስህን ከእኔ አታርቅ አለ፤ ዳግመኛም በሰውነቴ እውነተኛ መንፈስን አጽናልኝ፣ ከሁሉ በሆነ መንፈስ ቅዱስ አጽናኝ አለ›› በማለት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መንፈስ ቅዱስን ጰራቅሊጦስ አጽናኝ መካሪ መባሉን አስተምሯል። (መዝ. ፶፥ ፲-፲፪፤ መጽሐፈ ምሥጢር)
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በበዓለ ኀምሳ ምንባብ ላይ እግዚአብሔር
ረ ሊያጠፋው ምክንያት ይፈልግበት ነበር፡፡ ለዐፄ ገብረ ማርያም በእናትም በአባትም እኅት የምትሆነው ለላሊበላ ግን በአባት ብቻ እኅት የሆነችው ዮዲት ላሊበላን ለመግደል በማሰብ ቀን ከሌሊት አጋጣሚን ትጠብቅ ነበር፡፡ ቅዱስ ላሊበላም ጌታችን መራራ ሐሞት መጠጣቱንም እያሰበ ሁልጊዜ ዓርብ ዓርብ ከጾምና ጸሎት በኋላ መራራ ኮሶ ይጠጣ ነበርና ይህን አጋጣሚ በመጠቀም አንድ ቀን እንደጠማው አውቃ በጠላ ውስጥ መርዝ ጨምራ ሰጠችው፤ ቅዱስ ላሊበላም መርዝ የተቀላቀለበትን ጠላ ጠጣው፡፡ እርሱ ከመጠጣቱ በፊት ያገለግለው የነበረው ዲያቆን ቀምሶት ወዲያው ሲሞት አየ፡፡ ዲያቆኑ ያስመለሰውን የጠጣው ውሻም ወዲያው ሞተ፡፡ ቅዱስ ላሊበላም ይህን ሲመለከት በሐዘንና በፍጹም ፍቅር ሆኖ ‹‹አገልጋዬ ለእኔ የተዘጋጀውን መርዝ ጠጥቶ እንደሞተ ሁሉ እኔም መሞት ይገባኛል›› በማለት ያን መርዝ ስለወዳጁ ፍቅር ሲል ጠጥቶ ለመሞት ቆረጠና ጠጣው፡፡ ጌታችን በወንጌሉ ስለራሱ ‹‹ስለ በጐቹ ቤዛ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ የሚሠጥ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም›› (ዮሐ 15፡13) ብሎ የተናገረውን ቃል ቅዱስ ላሊበላም ስለ ወዳጁ ሞት ሲል ራሱን ለሞት አሳልፎ ሰጠ፡፡ ነገር ግን መርዙ እንኳን ሊጎዳው ይቅርና በሆዱ ውስጥ ከልጅነቱ ጀምሮ የነበረበትን የሆድ ሕመም ነቅሎ አወጣለት፡፡ በዚህም ጌታችን በወንጌሉ ‹‹የሚገድል መርዝም ብትጠጡ ምንም አትሆኑም›› (ማር 16፡18) ያለው ቃል ተፈጽሞለታል፡፡ መርዙ ለበጐ ሆኖለት ከሆዱም ውስጥ የነበረው ጥፍሮች ያሉት አውሬ መሰል ፍጡር ወጣለትና የሆድ ሕማሙ ፈጽሞ ተወው፡፡ ያን ጊዜም ቅዱስ ላሊበላ በወቅቱ ለሦስት ቀንም ያህል እንደሞተ ሆኖ የቆየ ቢመስልም ቅዱስ ገብርኤል ግን በመንፈስ ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ ሰባቱ ሰማያትን ያሳየው ሲሆን በጌታችን ፊትም አቅርቦት አስባርኮታል፡፡ ጌታችንም ቅብዓ መንግሥት ቀብቶት ትልቅ ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡
ጻዲቁ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ ቅድስናን ከንግሥና፣ ክህነትን ከንጽሕና፣ ጥበብ መንፈሳዊን ከጥበብ ሥጋዊ ጋር አንድ አድርጐ አስተባብሮ የያዘ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ፣ ቅዱሳን መላእክትም ይራዱት እንደነበርና ጌታችንም ትልቅ ቃልኪዳን እንደሰጠው ከቅዱስ ገድሉ ላይ እናገኛለን፡፡ ከጌታችን ዘንድ የተሰጠውንም ቃልኪዳን በሦስት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ በዚህም መሠረት፡-
1ኛ. መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን እየመራው ከላስታ ወደ አክሱም ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም አድርሶ በዚያ የሚገኙትን ቅዱሳት መካናት ሁሉንም ካሳየው በኋላ ‹‹ወደ ሀገርህ ሮሐ ተመልሰህ በእነዚህ ምሳሌ ታንጻለህ›› ብሎታል፡፡ ወደ ሀገሩም ተመልሶ በአሽተን ማርያም ተራራ ላይ ሱባኤ ይዞ በጾም ጸሎት ተወስኖ ሳለ እግዚአብሔር የሚሠራቸውን መቅደሶች በግልጽ በራእይ አሳይቶታል፡፡
2ኛ. ከላይ እንዳየነው ለሞት ተብሎ የተሰጠው መርዝ ለሕይወት ሆኖለት በመሬት ላይ ወድቆ ሳለ በነፍስ መልአክ ነጥቆት እስከ ሰባተኛው ሰማይ ጽርሐ አርያም ድረስ ደርሶ በጌታ ፊት ቀርቦ ከጌታ ዘንድ ‹‹እኔ አከበርኩህ ቃሌ አይታበይም፣ ከአንድ ቋጥኝ እነዚያን በራእይ ያሳየሁህን አብያተ ክርስቲያናት ታንጻለህ›› የሚል ቃልኪዳን ተቀብሏል፡፡
3ኛ. ከኢየሩሳሌምም ተመልሶ የንግሥናውን ዙፋን ከቅዱስ ገብረ ማርያም ከተረከበ በኋላ በተሰጠው መንፈሳዊ ሀብትና ባየው ራእይ መሠረት አብያተ ክርስቲያናቱን አንጾ ከጨረሰ በኋላ በቀኝና በግራው ዓሥር ዓሥር ኪሎ የሚመዝን የዓለት ድንጋይ ተሸክሞ ለ7 ዓመት ሲጾም ሲጸልይ ጌታችን ተገልጦለት ‹‹…ያነጽካቸውን ቤተ መቅደሶች የተሳለመውን ኢየሩሳሌምን እንደተሳለመ አድርግለታለሁ›› የሚለውን የመጨረሻውን ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡ (ይህን ቃልኪዳኑን መጨረሻ ላይ በዝርዝር እናየዋለን) እነዚህን ሦስት ዋና ዋና ቃልኪዳኖቹን በቅድሚያ ማንሳት የፈለኩበት ምክንያት ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ስለ ቅዱስ ላሊበላ ድንቅ ሥራዎች ከማሰባችንም ሆነ ከመናገችን በፊት በቅድሚያ ስለ ራሱ ስለ ቅዱስ ላሊበላ የቅድስና ሕይወቱና ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ግንኙነት ማወቁ የግድ አስፈላጊ መሆኑን ለመጠቆም ነው፡፡ አሁን አሁን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሆን ተብሎ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ውቅር አብያተ ክርስቲያናቶቹ በቱሪስት መስህብነታቸው ብቻ እየታዩ የቅድስና ታሪካችንም እየተጨፈለቀና መንፈሳዊ እሴቶቻችንንም ለማጥፋትም ጥረት እየተደረገ ስለሆነ እውነተኛውን ነገር በደንብ ማወቅና በእጅጉ መጠንቀቅ ስላለብን ነው ይህን የማነሳው፡፡ ስለዚህ የቅዱስ ላለበላን የቅድስና ሕይወትና ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ግንኙነት ስንረዳ እነዚያ እጅግ ድንቅ የሆኑ ሥራዎቹ በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና በሰማያውያን መላእክት እርዳታ የተሠሩ መሆናቸውን እንረዳለን፤ እግዚአብሔርም ለእኛ የሰጠንን ድንቅ የምሕረትና የቃልኪዳን ስጦታዎቻችን መሆናቸውን እንረዳለን፡፡ ያንጊዜም ውቅር አብያተ ክርስቲያናቶቹን ዓለም ከሚመለከትበት የተለየ መንፈሳዊ ዐይን ይኖረናል፡፡ የቃልኪዳኑም ተጠቃሚዎች ለመሆን መንፈሳችን ይነሳሳል፡፡ በዚህ ደግሞ አሁን ያለውም ሆነ ወደፊት የሚመጣው ትውልድ ታሪኩን ከማጉደፍና ከጥፋት ይጠበቃል፣ አኩሪ ታሪኩንም ጠንቅቆ ለማወቅ መንፈሳዊ ቅናትም ስለሚያድርበት ራሱንም ከውጪው የባሕል ወረራና ጥቃት ይጠብቃል፡፡ በሀገራችን ያሉትን እጅግ ጥልቅ የሆኑ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ምሥጢሮችን ጠንቅቀው የተረዱት እነ ፕሮፌሰር ፓንክረስት ‹‹ክርስቶስ ከነጮች ይልቅ ለኢትዮጵያውያን ቅርበት አለው›› በማለት ምስክርነታቸውን እየሰጡ ባለበት ወቅት የዘመኑ የሀገራችን ወጣት ማንነቱን ጠንቅቆ ቢያውቀው ኖሮ የእነርሱን (የነጮቹን) ባሕል ለመከተል ባልዳዳው ከዘመናዊ ባርነትም ራሱን በጠበቀ ነበር፡፡
4.መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለቅዱስ ላሊበላ ስለ ቤተመቅደሶቹ አሠራር በዝርዝር እንዳስረዳው፡- በተራ ቁጥር ሁለት ላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በቅዱስ ገድሉ ላይ ከገጽ 117-127 ድረስ በጣም በስፋትና በዝርዝር እንደተጠቀሰው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ላሊበላን እስከ ሰባተኛው ሰማይ ድረስ በመላእክት ተነጥቆ በፊቱ እንዲቆም ካደረገው በኋላ ቤተ መቅደሶቹን እንዴት እንደሚያንጽ ቃል በቃል ነግሮታል፡፡ እግዚአብሔር ለኖህ መርከቡን እንዴት እንደሚሠራ ከነልኬቱ ጭምር በዝርዝር እንደነገረው ሁሉ ለቅዱስ ላሊበላም ዝርዝር ሁኔታዎችን ጭምር እንዲህ በማለት ትእዛዝ ሰጥቶታል፡- ‹‹መልአኩም ክብሩ ከሰማያት ሁሉ ክብር ወደሚበልጥ ወደ ሰባተኛው ሰማይ አደረሰው፣ ቅዱስ ላሊበላም ይህንን አይቶ በግንባሩ ተደፋ፣ ከኪሩቤል ዘንድ ይነሳ የሚል ቃል ተሰማና አንዱ ሱራፌል መጥቶ አነሣው፡፡ ልቡንም አጽንቶ አቆመው…እግዚአብሔርም ተናገረው፡- ‹በምድር ላይ ቤተመቅደስ ትሠራልኝ ዘንድ የማሳይህን አስተውል፤ እዝነ ልቡናህንም ግለጥ፡፡ ከሰው ጋር ስለምኖር በሰማያት የምትኖር አባታችን እያሉ ከሚጠሩኝ በሃይማኖት ከተጐናፀፈኝ ስሜን ከሚያመሰግኑ ከመረጥኳቸው ከሕዝብ አንደበት በምመሰገንበት ገንዘብ እኔ ፈጥሬያቸዋለሁና፡፡
ከመጀመሪያይቱ ድንኳን ውስጥ በተሣለው ላይ ምስላቸው የተሠራ ከሚንቀሳቀሱ ከኪሩቤል አምሳል ለሙሴ እንደተናገርኩት አይደለም፡፡ ወዳጄ ሙሴ የመጀመሪያይቱን ድንኳን አርአያ በደብረ ሲና እንዳሳየሁት ድንኳንን እንደሠራ ሁሉ እንደሁ አንተም እንዳሳየሁህ ትሠራ ዘንድ ዕወቅ፣ አስተውል፣ ተጠንቀቅም፡፡ የማሳይህ ግን ለሙሴ እንዳሳየሁት አይደለም፤ መቅደሴን የምትሠራልኝም ሙሴ እንደሠራው አይደለም፤ ሙሴስ ከተፈተለ ልብስና ከእንጨት ድንኳን ሠራ፤ አንተ ግን ለምሰሶውም ሆነ ለመቀኑ ለመድረኩ እንጨትን
ነዋ ሚካኤል መልአከ ክሙ
ይስአል ለክሙ በእንተ ምሕረት
በዘማሪት መቅደስ ከበደ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ እነርሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እርሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡
በሰኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡ ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና "የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?" በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡ ለጊዜው "በእኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም" ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእርሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ በመቀጠልም ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ሰይጣናዊ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን "ድረስልኝ" እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሰኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡
ምልጣን ዘሰኔ ሚካኤል
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ፤
ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ፤
ፀሐይ ፀልመ ወወርኅ ደመ ኮነ፤
ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኵሉ፤
ትርጉም
አይሁድ ጌታችንን በሰቀሉት ጊዜ
ሚካኤል ዝም አለ ገብርኤልም ተደነቀ
ፀሐይ ጨለመ ጨረቃ ደም ኾነ
ከመስቀሉ ወርዶ ለኹሉ አበራ።
ቅዱስ ያሬድ
ከበዓሉ በረከትን ያሳትፈን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሰኔ ፲፪
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል አፎምያን ያዳነበት ዕለት ነው፡፡ ዳገመኛም ይኽች ዕለት የባሕራንን የሞት ደብዳቤ ቀዶ እርሱን ለታላቅ ክብር ያበቃባት ዕለት ናት፡፡
ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ' ካ-ከመ' ኤል- አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ መኑ ከመ አምላክ (እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው) ማለት ነው፡፡ አንድም ለእግዚአብሔር አሸናፊ ድል አድራጊ የቸርነትና የርህራሄ መገኛ መዝገብ ማለት ነው፡፡
ይህ ታላቅ መልአክ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራዕዩ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ›› ብሎ ከተናገረላቸው መላእክት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን የሰባቱም ሊቃነ መላእክት አለቃ እንዲሆን እግዚአብሔር መርጦ ሹሞታል፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ያደረጋቸው የሠራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ ተአምራት አሉት፡፡ ስለዚህ ስለ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፤ ጠባቂነትና አማላጅነት ከአባቶቻቸው የተማሩትን በኑሮአቸው ያዩትን አባቶቻችን ጽፈዋል፡፡ ስለ ቅዱስ ሚካኤል ከጻፉት አባቶች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያክል፡- ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ኤዎስጣቴዎስ ዘአንፆኪያ፣ ቅዱስ መቃርዮስ፣ ቅዱስ ያሬድ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እና የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አባዲማቴዎስ ናቸው፡፡ እኛም የአባቶቻችንን አንደበት አንደበታችን አድርገን በኅዳር ፲፪ ክቡር ገናና የሆነ ቅዱስ ሚካኤል ካደረጋቸውና ከሠራቸው ብዙ ተአምራት ውስጥ የተወሰኑትን በመልአኩ ተረዳኢነት እንዲህ ብለን እንናገራለን አንጽፋለን፡፡
ጥንተ ነገሩ እንዲህ ነው፡- ንግስት ክሌዎፓትራ ‹‹ሳተርን›› ለሚባለው ጣዖት የሠራችው ቤተ ጣዖት በእስክንድርያ ነበር፡፡ ይህ ቤተ ጣዖት እስከ እስክንድርያው ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ /፫፻፲፪ - ፫፻፳፮/ ዘመን ድረስ ነበር፡፡ እለ እስክንድሮስ ሊያጠፋው ሲነሣ ሕዝቡ ከልቡ ገና የአምልኮ ጣዖት ስላልጣፋ "፲፰ ፓትርያርኮች ያልነኩትን አንተ ለምን ታፈርስብናለህ?" ብለው ተቃወሙት፡፡ እለ እስክንድሮስም ሕዝቡን መክሮና አስተምሮ የሳተርን በዓል ይውልበት በነበረው ዕለት የቅዱስ ሚካኤልን በዓል እንዲያከብሩ አውጆ ቤተ ጣዖቱንም በቅዱስ ሚካኤል ስም ሰይሞ ቤተክርስቲያን አደረገው፡፡
ሕዝቡ በየዓመቱ መሥዋዕት እየሠው ተረፈ መሥዋዕቱን እየተመገቡ እየዘፈኑ እያጨበጨቡ ያከብሩ ነበር፡፡ ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ቁስጠንጢኖስ "አብያተ ጣዖታት ይዘጉ አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ" ብሎ ካወጀ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት እለ እስክንድሮስ ቤተ ጣዖቱን አፍርሶ ከቦታው ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ታቦተ ሚካኤልን አግብቶ በዓሉን በደስታ በሐሴት አሳለፉት፡፡ እለ እስክንድሮስም ሕዝቡን የጣዖቱን በዓል ተው "ይህን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል አክብሩ" ብሎ በየዓመቱ በዚህ ቀን በዓል እንዲሆን ሥርዓት ሠራላቸው፡፡ ይህንንም የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ከሚያከብሩ ምእመናንን አንዱ የባሕራን አባት ነበር፡፡
እርሱም እግዚአብሔርን እጅግ አድርጐ የሚፈራ ወር በገባ በየዐሥራ ሁለቱ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን የሚዘክርና ይልቁንም በኅዳር ዓሥራ ሁለትና በሰኔ ዓሥራ ሁለት ቀን በታላቅ ክብር የሚያከብር አንድ ሰው ነበር። ለዚህ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰውም ርኅራኄ የሌለው በእርሱም ላይ ጥላቻ ያደረበት አንድ በለጸጋ ጐረቤት ነበረው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በሚያከብርበት ጊዜ ሁሉ ይዘብትበት ይሳለቅበት ነበር። ይህ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰውዬ በዚህ ዓይነት በጐ ሥራ ብዙ ጊዜ ከኖረ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ያርፍ ዘንድ የሞቱ ጊዜ ቀረበ። ሚስቱንም ጠርቶ "በጐ ስራ ከመሥራት ለድኃ ከመመጽወት ቸል አትበይ የቅዱስ ሚካኤልንም በዓል በየወሩ ከማክበር አትቦዝኝ ይልቁንም በኅዳር ዓሥራ ሁለትና በሰኔ ዓሥራ ሁለት ቀን ከፍ ባለ ሥነ ሥርዓት እንድታከብሪ አደራ እልሻለው" አላት፡፡ በሚሞትበትም ጊዜ ሚስቱ ፀንሳ ነበር። ይህም ደገኛ ሰው በሰላም ዐረፈና ፍጹም መንግሥተ ሰማያትን ወረሰ።
ከዚህም በኋላ ሚስቱ የመውለጃዋ ጊዜ ተቃርቦ ነበርና ምጥ ይዟት በታላቅ ጭንቅ ላይ እንዳለች "አንተ የእግዚአብሔር መልአክ ሆይ በእኔ ላይ ይቅርታን አውርድ ከዝህ ከደረሰብኝም ጭንቅ ይገላግለኝ ዘንድ ስለኔ እግዚአብሔርን ለምንልኝ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ባለሟልነት ተሰጥቶሃልና" እያለች ለመነች። ይህንንም በምትልበት ጊዜ ያለችበት ቤት በብርሃን ተመላ ከጭንቋም ዳነችና መልኩ በጣም ያማረ ልጅ ወለደች። የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ያን ሕፃን ባረከውና "ቸርነት ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለጸጋ ገንዘብና ሀብት እርሻውንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዟል" አለ። ያን ጊዜ ያ ባለጸጋ በሴትዮዋ ቤት መስኮት አጠገብ ሆኖ ሁኔታውን ሁሉ ይመለከት ነበርና ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ልቡ በታላቅ ኅዘን ተነካ፤ ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ብላቴናውን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀው ነበር።
ብላቴናውም ዓሥር ዓመት በሆነው ጊዜ እናቱ በጣም ችግር ፀናባት፡፡ በዚህን ጊዜ እምነት የጐደለው ያ ባለጸጋ "አንቺ ችግረኛ ስለሆንሽ ይላከኝ ያገለግለኝ ዘንድ ልጅሽን ስጭኝና ምግቡንና ልብሱን ምንም ሳላጐድል ተንከባክቤ አኖረዋለው ለአንቺም ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሻለው" አላት። ይህንንም ባላት ጊዜ ስለ ችግሯ በጣም በመደሰት ልጅዋን ሰጠችውና ሃያውን ወቄት ወርቅ ተቀበለች፡፡ ብላቴናውንም በወሰደ ጊዜ እንግዲህ ሃሳቤ ሁሉ ዛሬ ተፈጸመልኝ እያለ በጣም ደስታ ተሰማው፡፡ ከዚህ በኋላ በልጅ ቁመት ልክ ሳጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሣጥኑ ውስጥ አግብቶ በላዩ ላይ ቆለፈበትና ሣጥኑን ወስዶ ከባሕር ጨመረው፤ እንዲሁም የሣጥኑን ቁልፍ መክፈቻ አብሮ ወረወረው። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሰጥም በባሕሩ ላይ እየተንሳፈፈ ከዚያች አገር ርቃ ወደምትገኝ የባሕር ወደብ ደረሰ።
በባሕሩ አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበርና ያንን ሣጥን ባየው ጊዜ ከባሕሩ አወጣውና ወደ ቤቱ ወሰደው። እቤቱም በደረሰ ጊዜ "ይህን ሣጥን በምን እከፍተዋለሁ?" እያለ ሲያወጣ ሲያወርድ ተመልሶ ወደ ባሕሩ ይሄድ ዘንድ እግዚአብሔር አሳሰበው፤ በሄደም ጊዜ አንድ ዓሣ የሚያጠምድ ሰው አገኘና ዓሣ አጥማጁን "በኔ ስም መረብህን ወደ በሕር ጣልና የተሠገረው ዓሣ ለኔ ይሆናል ዋጋውን ግን እከፍልሃለው" አለው፡፡ ዓሣ አሥጋሪውም እንደ ተነጋገሩት መረብን ከባሕር ቢጥል ታላቅ ዓሣ ተያዘና ለሰውየው ሰጥቶት ዋጋውን ተቀበለ። እሱም ያንን ዓሣ ከቤተሰቦቹ ጋር ጠብሶ ይበላ ዘንድ በችኮላ ወደ ቤቱ ሄደና ያሣውን ሆድ ቢሰነጥቀው የዚያን የሣጥን ቁልፍ መክፈቻ አገኘ፡፡ በዚያን ጊዜ ይህ መክፈቻ የዚህ ሣጥን ቁልፍ መክፈቻ መሆን አለበት ሲል አሰበና ቁልፉን ለመክፈት ቢሞክር ወለል ብሎ ተከፈተ። በዚህም እየተደነቀ ሳለ ሣጥኑን ቢከፍተው ያ ባለ ፀጋ ሊገድለው ያሰበውን ሕፃን በሣጥኑ ውስጥ አገኘው። ባየውም ጊዜ እጅግ ተደስቶ በባሕር ውስጥ ስላገኘው ስሙን "ባሕራን" ብሎ ሰየመውና እንደ ልጁ አድርጐ ይንከባከበው ዘንድ ወሰነ፡፡
ከባሕራን ሀገር የበግ ጠባቂው አገር የዓሥር ቀን ጐዳና የሚያስኬድ ርቀት ነበረው። ከብዙ ዓመታት በኋላ ያ ባለ ጸጋ ሰው ለንግድ ከሀገሩ ወጣ፡፡ በጉዞውም ላይ ሳለ ፀሐይ ስትገባ ከዚያ የበግ ጠባቂው ዘንድ ደረሰ። በግ ጠባቂውንም "ወንድሜ ሆይ ባንተ ዘንድ የማድርበት ቢኖር ታሳድረኝ ዘንድ እለምንሃለው፣ ኪራዩንም እከፍልሃለው" ብሎ ጠየቀውና ያ በግ ጠባቂ ወደ ቤቱ አስገባው። ባለጸጋውም ገብቶ ጥቂት ካረ
ዐረገ በስብሀት ዐረገ በእልልታ :
ሞትን ድል አድርጎ የሠራዊት ጌታ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ዕርገት
ከጌታችን ፱ቱ አበይት በዓላት ውስጥ አንዱ ዕርገት ነው፡፡
“እያዩት ወደሰማይ ዐረገ”(ሉቃ 24÷50 የሐዋ 1÷9)
ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ ለሰላሳ ዘጠኝ ቀናት ያህል ለሐዋርያቱ በተለያየ ጊዜ እየተገለጠ ለአገልግሎት ሲያዘጋጃቸው እና ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምስጢር እያስተማራቸው ከቆየ በኋላ በ፵ኛው ቀን በሐዋርያቱ ፊት አርጓል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው የጌታችንንአበይት በዓላት አንዱ ዕርገት ነው።
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተነሣ በ፵ኛው ቀን ወደ ሰማይ አረገ ያረገበትም ቦታ ቢታንያ አጠገብ የሚገኘውደብረ ዘይት የሚባለው ተራራ ነው። አሥራ አንዱ ሐዋርያትን እዚያ ድረስ ከወሰዳቸው በኋላ ባርኳቸው እያዩት ዐረገ። ደመና ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ። ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቀደመ ክብሩ፤ በመለኮታዊ ክብሩ ወደ ሰማይ አርጎ በአባቱ ቀኝ ተቀመጧል። ጌታችን ያረገውም በለበሰው ሥጋ በመሆኑ እና ለሁለተኛ ጊዜ ለፍርድ በሚመጣበት ጊዜ ይህን ክብር እኛም እንድናገኝ ምሳሌ ሲሆነን ነው።
በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣንበክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ኤፌ . ፪፡፮ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዕርገቱ አስመልክቶ ከተናገራቸው ሦስት ነገሮች ውስጥ፦
#የመጀመሪያው፤ እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ። ዮሐ . ፲፪፡፴፪
#ሁለተኛው ደግሞ፤ ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ዮሐ .፲፬፡፲፰
#ሶስተኛው፤ እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። ዮሐ . ፲፮፡፯
የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ለእኛ ትልቅ ተስፋ ነው ስለዚህም ሐዋርያት ጌታችን ሲያርግ ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ይመለከቱት እንደነበር እኛም በታላቅ ተስፋ የጌታን ነገር ልናስብ ይገባል። ነቢዩ ዳንኤል ስለ ጌታችን ዕርገት እና በአብ ቀኝ ስለመቀመጡ እንዲህ ሲል በትንቢት ተናግሮ ነበር፤ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የሰው ልጅየሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ
በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም
የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥መንግሥቱም የማይጠፋ ነው። ዳን. ፯፡፲፫ - ፲፬ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ስንል ጌታ ከአብ ጋር እኩል ነው ማለታችን ነው።
ከ፬ቱ ወንጌላት ውስጥ ይህን የዕርገቱን ታሪክ የመዘገቡት የማርቆስ ወንጌልና የሉቃስ ወንጌል ናቸው። ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ።እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው፤ እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደታያት ሲሰሙ አላመኑም። ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ባላገር ሲሄዱ በመንገድ በሌላ መልክ ተገለጠ፤ እነርሱም ሄደውለሌሎቹ አወሩ፤ እነዚያንም ደግሞ አላመኑአቸውም። ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ተገለጠ፥ ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ። እንዲህም አላቸው። ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥ የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ። ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ። ማር. ፲፮፡፱-፲፱ እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ። እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ። እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየወደ ሰማይም ዐረገ። ሉቃ. ፳፬፡፵፰-፶፩
ቅዱስ ሉቃስ የሐዋርያት ሥራን ሲጽፍ ስለ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት አብራርቶ ጽፎታል። እንዲህ ሲል፦ ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖለእነርሱ ራሱን አሳያቸው። ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፥ ነገር ግን። ከእኔ የሰማችሁትንአብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ፤ ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ። እነርሱም በተሰበሰቡ ጊዜ። ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሥትን ትመልሳለህን? ብለውጠየቁት። እርሱም አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤ ነገር ግንመንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድርዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ። ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎችበአጠገባቸው ቆሙ፤ ደግሞ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው። ሐዋ. ፩፡፫-፲፩
ክርስቲያኖች በሰማያት ስፍራ ከጌታችን ከመድሃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረው እንደሚቀመጡ የእርሱ ዕርገት ያረጋግጥልናል። ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ጌታችን እርገት እንዲህ ሲል ይመክረናል፤ እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ። በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና። ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበትጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ። ቆላ. ፫፡፩-፬
ኖርንም ሞትንም የክርስቶስ ነንና ዘላለማዊ ሕይወትን እንወርስ ዘንድ አምላካችን ይርዳን። ልዑል እግዚአብሔር በኑሮአችን ሁሉ ባርኮን፤ ቀድሶን፤ በእርሱ ፈቃድ እንድንኖር ይርዳን። የምንሻትን መንግስተ ሰማያትን ያወርሰን ዘንድ የእናቱ የድንግል ማርያም አማላጅነት፤ ስለ እርሱ ክብር ሲሉ ሕይወታቸውን ሰውተው ያለፉት ቅዱሳን ሰማዕታት ምልጃ እና ጸሎት አይለየን አሜን።
[በዲያቆን ንጋቱ አበበ]
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መግለጫ እንደሚከተለው ይነበባል።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሄድ ሰንብቷል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1.በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤
2.በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል፤
3.በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሱ የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታ በመስጠትና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ መልሶ ማልማት እንድትገባ ድጋፍ በማድረግ፤ በተለይም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በፈረሰው የጽርሐ ምኒልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃ ምትክ በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጭ ተጨማሪ ምድር ቤትና የቦታ ስፋት ያለው B+G+4 ሕንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባትና የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ኃላፊ አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ማድርጋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከምስጋና ጋር የተቀበለው ሲሆን በተሰጠን ምትክ ቦታ ላይም የከተማው ፕላን በሚፈቅደው መሠረት የመልሶ ማልማት ሥራው እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
4.የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
5.የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስምልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችን ምልዐተ ጉበኤው ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ አሳልፏል፤
6.የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
7.በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑ ቢታወቅም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገለጸ ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
8.ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
9.በደቡብ የሀገራችን ክፍል የቤተ ክርስቲያኒቱን አብነት ትምህርት ከማስፋፋትና ከፍ ያለ መዐርግ ከመስጠት አንፃር የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት ማስመስከሪያ ትምህርት ቤት እንዲሆን በቀረበው ጥናት መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ለምሥክር ጉባኤ ቤቱ ዕውቅና በመስጠት ወደ ትግበራ እንዲገባ ወስኗል፡፡
10.ከሀገራችን ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ በሙያ ብቃታቸው፣ በምግባራቸውና በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
11.የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሠረት ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
12.በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
8. ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተመሠረተች ነች፡፡ በውስጧም ሊፈስ የሚገባው በደሙ የዋጃት የክርስቶስ ደም ብቻ ነው:: ስለዚህ በየዕለቱ በካህናት እጅ ሥጋው ይፈተታል ደሙም ይቀዳል፡፡ ምዕመናንም ከዚህ ምስጢር በአግባቡ በመሳተፍ ሥርየተ ኃጢያትና ሕይወተ ነፍስ ያገኛሉ:: ይህን ምስጢር ለመጠበቅ ሲባል በቤተክርስቲያን የፍጡር ደም መፍሰስ የለበትም፡፡ ማንኛውም ሰው በማንኛውም ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ሳለ ደም ቢወጣው ደሙ በቤተ እግዚአብሔር እንዳይነጥብ መጠንቀቅ ከባሰም ከቤተ መቅደስ መውጣት ይኖርበታል፡፡ ሴቶች ደግሞ ደም የሚታያቸው በታወቁ ዕለታት ስለሚሆን አስቀድመው ወደ ቤተ መቅደስ ከመግባት መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል::
ከደመ ፅጌ ሳይነጹ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት አለብኝ ማለት እጅግ በጣም ድፍረት ነው:: በመሠረቱ ቤተ እግዚአብሔር የሚገባው በእግዚአብሔር ቸርነት ነው እንጂ ሰው በራሱ ብቁ ስለሆነ አይደለም፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ዳዊት «እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፡፡» ብሏል:: መዝ 5፥7 ታዲያ ንጹሕ እንደሆን በሚሰማን ጊዜ እንኳን ቤተ እግዚአብሔር እንድንገባ የሚያደርገን የእግዚአብሔር ቸርነት እንጂ ንጽሕናችን ካልሆነ ወደ ቤተ መቅደስ የማያስገባ ግልጽ ምክንያት እያለብን መግባት ይገባኛል ማለት ድፍረት አይሆንምን?
ሰው በቤተ መቅደስ ሲኖር በፍርሃት፣ በቅድስና፣ በፅኑ እምነትና በማስተዋል መሆን አለበት። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ቅዱስ ልጁ ለጢሞቴዎስ «በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ› ያለው ቃል ይህን ያረጋግጣል፡፡ 1ጢሞ 3፥14 ስለዚህ «ከመሥዋዕት መታዘዝ ይበልጣል›› ብለን በወር አበባ ወቅት ተደፋፍሮ ቤተ መቅደስ ከመግባት ብንቆጠብ «በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት» እንዴት መኖር እንደሚገባ በደንብ ተረድተናል ያሰኛል፡፡
ቤተ ክርስቲያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ሕግና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም› ማቴ 5፥17 ባለው መሠረት በመሥዋዕተ ኦሪት መሥዋዕተ ወንጌልን ተክታ በደመ ክርስቶስ ታድሳ የምትኖር የአዲስ ኪዳን ሙሽራ ናት፡፡ ፈጣሪዋ እንዲያልፉ ያደረጋቸውን አሳልፋ ያጸናቸውን ደግሞ አጽንታ ትኖራለች፡፡ ነገር ግን መዋዕለ ንጽሕ ያልፈጸመች ሴት በወር አበባ ላይ ሳለች ወደ ቤተመቅደስ አትግባ የሚለውን ሥርዓት «ኦሪታዊነት» ነው በማለት የሚነቅፉ መምህራን ነን ባዮች ፍርሃተ እግዚአብሐርን ከምዕመናን ልቡና ለማራቅ ሲሯሯጡ ይገኛሉ፡፡ ምዕመናን ግን ከእንደነዚህ ዓይቶቹ «የምን አለበት» መምህራን ኑፋቄ መጠንቀቅ፥ በስሜትና በአጉል ፍልስፍና እየተፍገመገሙ ወደ ክህደት ዐዘቅት ከመውደቅ ራስን ማዳን ይጠበቅባቸዋል፡፡
በሥርዓትና በአግባብ መኖር የማይዋጥላቸው አንዳንድ ሰዎች « በወር አበባ ላይ የምትገኝ ሴት ወደ ቤተ መቅደስ አትግባ የሚለው ሥርዓት የተሠራው በድሮ ጊዜ ንጽሕናን ለመጠበቅ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ስላልነበረ ነው:: አሁን ግን ንጽሕናን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂ ያፈራቸው ልዩ ልዩ መገልገያዎች ስላሉ እነርሱን እየተጠቀምን ቤተ መቅደስ ብንገባ ምን አለበት?» ሲሉ ይደመጣል፡፡
በመሠረቱ በወር አበባ ወቅት ወደ ቤተ መቅደስ የማይገባበት ምክንያት ንጽሕናን በተመለከተ ብቻ ወይም በወቅቱ ንጽሕናን ለመጠበቅ ስላልተቻለ ብቻ አይደለም:: ጥያቄውን የሚያነሡት ሰዎች ‹‹በወቅቱ ንጽሕናን ለመጠበቅ ስለሚያዳግት ነበር» የሚሉት አሁን ግን ንጽሕናን ለመጠበቅ ምንም ችግር ስለሌለ ብንገባስ ለማለት እንዲረዳቸው ነው፡፡ ምክንያት ሰጪ ራሳቸው ምክንያቱንም አፍራሾች ራሳቸው ናቸው፡፡ ወደ ቤተ መቅደስ የማይገባበት ትክክለኛ ምክንያት ግን ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 ባለው በዝርዝር ተጽፏል፡
በቀድሞ ጊዜ ንጽሕናን ለመጠበቅ ምቹ ሁኔታ ስላልነበረ ይህ ሥርዓት ተሠራ ማለት ሥርዓቱ የተሠራው ለጊዜው አማራጭ እስኪገኝ ድረስ ብቻ ነበር እንደማለት ይቆጠራል:: በተጨማሪም ይህ ሥርዓት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት አልተሠራም ወይም ራሱ መንፈስ ቅዱስም ቢሆን ክብር ይግባውና መጪውን ጊዜ አያውቅም ወይም የቴክኖሎጂን ዕድገት ከግምት ውስጥ አስገብቶ ሥርዓቱን አልሠራም እንደ ማለት ነው፡፡
በተጨማሪም በዚህ ዘመን እንኳን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ብንመለከት የዘመኑ ቴክኖሎጂ ያፈራውን በመጠቀም በወር አበባ ጊዜ ከሚከሠት የንጽሕና ጉድለት ለመዳን የሚችሉ ሴቶች ቁጥር እጅግ ጥቂት ነው፡፡ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ወይም በገጠር አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች ኑሮአቸው ከድሮው ጊዜ ባልተለየ መልኩ መሆኑ ይታወቃል። ታዲያ ከላይ በተገለጸው መልኩ ንጽሕናቸውን ለመጠበቅ ለቻሉ ሰዎች ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ቢፈቀድ ያልቻሉትስ? የሚል ጥያቄ ማስነሣቱ አያቀርም፡፡ ላልቻሉት እንደቀድሞው ቢከለክሉ ደግሞ ቤተክርስቲያን በሀብታምና በድኃ መካከል ልዩነት ፈጥራ የምታስተዳድር ፍትሐዊነት የሌላት ትሆናለች።
ከእኛ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር ኅብረት ያላቸው እኅት አብያተ ክርስቲያናት ከኛ የሚለዩበት ብዙ ቀኖና እንዳለ የታወቀ ነው፡፡ እነርሱ በወር አበባ ወቅት ሴት ልጅ ቤተ መቅደስ እንዳትገባ ሥርዓት ሠሩም አልሠሩም ከእኛ የሚጠበቀው የራሳችንን አክብሮ መያዝ ነው። በዚህ መልኩ እነርሱን መምሰል ይገባናል ማለት ዐላዋቂነት እንጂ ሥልጣኔ ሊሆን አይችልም፡፡
በልዩ ልዩ ምክንያት ባሕር ማዶ ተሻግሮ ከአገር ርቆ መኖር ያለ ቢሆንም ከሥርዓት መውጣት ግን አይገባም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደካማነታቸው፣ የውስጥ ስሜታቸውና እምቅ ክህደታቸው የሚገለጠው ባሕር ሲሻገሩ ነው:: የእነዚህ ዓይነት ሰዎች የክህደታቸው ማራገፊያ ወደቦች ደግሞ ሥርዓት ማፍረስ ሥልጣኔና ዘመናዊነት መስሎ የሚታያቸውና ማንነታቸው የጠፋባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ በምንም ዓይነት ሁኔታና በየትኛውም ቦታ ሆኖ ለሥርዓት ተገዥ መሆን በእጅጉ ይጠቅማል፡፡ ስለዚህ «ሴት ልጅ በወር አበባ ላይ ሳለች ወደ መቅደስ አትግባ›› የሚለውን ትዕዛዘ አበው በየትኛውም ቦታ ልናከብረው ይገባል፡፡
የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት በሌላ መንፈስ መመልከት ተገቢ አይደለም፡፡ በሴቶች ላይ የወር አበባ እንዳለ ሁሉ በወንዶችም ላይ ወደ ቤተ መቅደስ እንዳይገበ የሚያግዳቸው ዝንየት (ሕልመ ሌሊት) የሚባል ምክንያት አለባቸው፡፡ ስለዚህ ይህ ሥርዓት ሴቶችን ለመጨቆን ወይም ከወንዶች ለማሳነስ ሆን ተብሎ የተሠራ ባለ መሆኑ ከመብትና ከጾታ እኩልነት አንፃር ማየት ፖለቲከኛ እንጂ ሃይማኖተኛ ሊያደርገን አይችልም::
በቀጣይ ምዕራፍ ስምንት <<ድንግልና ምንድር ነው?>> በሚል ይቀጥላል...
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሕይወተ ወራዙት
ምዕራፍ ሰባት ክፍል ሦስት
..............................................
ወደ ቤተ መቅደስ ለምን አይገባም?
የወር አበባ ርኩሰት አለመሆኑ ከዚህ በፊት በሚገባ ተብራርቷል፡፡ ታዲያ ርኩሰት ካልሆነ በዚህ ወቅት ሴቶች ወደ ቤተ መቅደስ እንዳይገቡ ሥርዓት የተሠራው ለምን ይሆን? ለዚህ ጥያቄ መልስ ሊሆኑ የሚችሉ ዋናዋና ነጥቦች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፡፡
1. በወር አበባ ወቅት ድካምና ልዩ ልዩ የሕመም ስሜቶች እንደሚከሰቱ ከላይ በቂ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ወዲህና ወዲያ ሳይሉና ሳይንቆራጠጡ መንፈሳዊውን ሥርዓተ ጸሎት ማድረስ እንደሚገባ የሚያስረዳ ሥርዓት አላት:: ሆኖም በወር አበባ ላይ የሚገኙ ሴቶች በሚሰማቸው ሕመም ምክንያት ጐንበስ ቀና በማለትና በመንቆራጠጥ የሌላውን ጸሎተኛ ልቡና እንዳያውኩና ራሳቸውም ምቾት እንዳያጡ በማሰብ ከቤተ መቅደስ እንዳይገቡ ተከልክለዋል፡፡ በዚህ ዓይነት የሕመም ስሜት ላይ ሆኖ ሕሊናን ሰብስቦ በተረጋጋ መንፈስ መጸለይ እጅግ ያስቸግራል፡፡ በእርግጥ በወር አበባ ወቅት ሕመም የማይሰማቸው አንዳንድ ሴቶች መኖራቸው ቢታወቅም ሥርዓት የሚሠራው ብዙኃኑን ከግምት በማስገባት መሆኑን መዘንጋት የለበትም፡፡ ስለዚህ በወር አበባ ላይ የሚገኙ ሴቶች በሚሰማቸው ሕመም ምክንያት ተረጋግተው የማይጸልዩ፣ የማያስቀድሱ ..…ወዘተ ከሆነ ወደ ቤተ መቅደስ ለምን ይገባሉ? ቤተ ክርስቲያን የጸሎትና የመንፈሳዊ ተግባር ማከናወኛ ቤት ናት እንጂ ሌላ ዓላማ የላትምና፡፡