ethiopian_orthodox | Unsorted

Telegram-канал ethiopian_orthodox - የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

30344

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Subscribe to a channel

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

Do you enjoy reading this channel?

Perhaps you have thought about placing ads on it?

To do this, follow three simple steps:

1) Sign up: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
2) Top up the balance in a convenient way
3) Create an advertising post

If the topic of your post fits our channel, we will publish it with pleasure.

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

   አንዳንድ ጊዜ በጠና የታመሙ ሰዎች በጸበል ለመፈወስ ክትትል ሲጀምሩ ልዮ ልዩ ፈተና ያጋጥማቸዋል፡፡ ከፈተናዎቻቸውም ውስጥ አንዱና ዋነኛው ሴቶች ከሆኑ በየወሩ ይታያቸው የነበረው የወር አበባ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ያለማቋረጥ ወይም በተደጋጋሚ መከሠቱ ነው:: ይህን የመሰለ ፈተና ሲከሰት ከሰይጣን ጋር እልክ መጋባትና ዝም ብዬ ብጠመቅ ምን አለበት? ማለት ሞኝነት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ «ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አታሸንፍ>> ይላልና ሥርዓት እየጣሱ ሰይጣንን ለመርታት አለመሞከር ጥሩ ነው፡፡  ሮሜ12፥21 ሰይጣን ጸበል በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን ሥርዓት በማክበርና በመታዘዝም ይሸነፋል «ያለኝ ዕድል መጠመቅ ብቻ ነው» ማለት ያለ ጸበል ሰይጣን የሚረታበት ነገር የለም ያሰኛል፡፡
   ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆች ሁሉ ባለጋራ የሆነ ዲያብሎስ በምን በምን ድል እንደሚሆን ባስተማረ ጊዜ በመጀመሪያ ከልብ ጋር የተስማማ እምነት እንደሚያስፈልግ ገልጿል፡፡ በማስከተልም «ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጾም በቀር አይወጣም›› በማለት አብሮ አደግ ሰይጣንን አሳፍሮ ለማባረር ጾምና ጸሎት ዓይነተኛ መሣሪያዎች መሆናቸውን ጠቁሟል:: ማቴ 17፥21 ስለዚህ ጸበል ለመጠመቅ የነበረን ዕድል በዚህ መልኩ ፈተና ሲገጥመው ተስፋ ሳይቆርጡ በጾም፣ በጸሎትና በመሳሰሉት መንፈሳዊ አማራጮች በመታገዥ ባለጋራን ድል ማድረግ ይቻላል፡፡
   በሌላ አቅጣጫ ወሳኙ እምነት በመሆኑ ካልተጠመቅሁ አይሆንም ከማለት ይልቅ በሕመም ምክንያት መጾምና ቆሞ መጸለይ ባይቻል እንኳን በጸበሉ መተሻሸትና መጠጣት ከመጠመቅ እኩል ነው:: መተሻሸትና መጠጣት እንዴት ይቻላል? እንዳይባል እድፍን ማጥራት እንዳይሆን በሚል መጠመቅ ተከለከለ እንጂ መጠጣት አልተከለከለም፡፡
   ከላይ የተጠቀሱትን አማራጭ መንገዶች መጠቀም ያልተቻላቸው ደካሞችና ሕመምተኞች እንደ ልቡናቸው የእምነት ደረጃ ለመጓዝ እንዲችሉ መምህራነ ቤተ ክርስቲያንን ማዋየትና በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን መመራት ይኖርባቸዋል። ካህናተ ቤተ ክርስቲያን በዚህ መልኩ የሚቸገሩን እናቶችና እኅቶች እንዲጠመቁ በመፍቀድም ሆነ ሌለኞች አማራጮችን በማመቻቸት ሊረዷቸው ይችላሉ:: መርሐ ጽድቅ ባህለ ሃይማኖት የተሰኘ መጽሐፍ ‹ይቁረብ አይቁረብ» በሚል አርዕስት ሥር ባቀረበው ሐተታ «ከደመ ጽጌዋ ያልነፃች ሴት ከታመመች ለሥጋ ወደሙ አጋፋሪ የለውምና ትቁረብ›› በማለት የግል አስተያየቱን ይሰጣል፡፡ ይህ አስተያየት ፅነት ያለው (ችግር ያለበት፣ ሊቀበሉት የማይገባና ግትር) ነው:: ምክንያቱም ሥጋ ወደሙ አጋፋሪ የለውም አይባልም፡፡ መላእክት፣ ካህናትና እያንዳንዱ ምእመን የሥጋ ወደሙ አጋፋሪዎች ናቸውና፡፡ ማለትም ማንም በማይገባ መንገድ ሥጋ ወደሙን እንዳይቀበል ይቆጣጠራሉ፡፡ ሆኖም ከላይ እንደተጠቀሰው አንዳንዶች ደፍረው ከደመ ጽጌ ያልነጹ ሴቶችን ቢታመሙ ይቁረቡ እስከ ማለት ድረስ ፈቃድ ከሰጡ እንዲጠመቁ መፍቀድ ለካህናት ቀላል ተግባር መሆኑን ያመለክታል::
   ይኸው መጽሐፍ «ይሁን እንጂ ለሞት የምታሰጋ ብትሆን ነው እንጂ የማታሰጋ ከሆነ የቤተ ክርስቲያን ሕግ በሚያዘው መሠረት ወደ ቤተ ክርስቲያን አትገባም» በማለት አስተያየቱን ይደመድማል፡፡ ስለዚህ ይህን የመሰለ ፈቃድ በጸና ለታመሙ እንጂ ውለው አድረው ለመጠመቅ ፋታ ላላቸው ሁሉ አለ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡

3. ከመቁረብ
   ምንም እንኳን ለቁርባን የሚያስፈልገውን ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቁ ቢሆኑም ሴቶች ከደመ ፅጌ ሳይነጹ ሥጋ ወደሙ መቀበል አይችሉም፡፡ ይህን ሥርዓት ተላልፎ ሴቶችን ከወር አበባ ሳይነጹ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲገቡና ሥጋውና ደሙን እነዲቀበሉ ያደረገ ቢኖር ዲያቆንም ሆነ ቄስ ከክህነቱ እንዲሻር ፍትሐ ነገሥት እንዲህ ሲል ይደነግጋል:: «ወለእመ ተዓደጠ ፩ሂ እምቀሳውስት ወዲያቆናት ወአብአ ብእሲተ ትክተ ኅበ ቤተ ክርስቲያን ወመጠዋ ቁርባነ በመዋዕለ ትክቶሃ ይደቅ እመዓርጊሁ» ይህ ዐረፍተ ነገር «ከግዳጅዋ ያልነጻችውን ሴት በደሟ ወራት ከቤተ ክርስቲያን አግብቶ ሥጋውን ደሙን ያቀበላት ከመዓርጉ ይሻር» ማለት ነው:: ፍት.ነገ.6፤ ዘሌ7፥19-21 ስለዚህ ሴቶች ከወር አበባ ሳይነጹ ሥጋውንና ደሙን መቀበል አይኖርባቸውም፡፡
  ይህን በተመለከተ የመጽሐፉ አስደናቂ አገላለጽ ደግሞ «እቴጌም ብትሆን›› ማለቱ ነው፡፡ «እቴጌም ብትሆን›› ማለት የንጉሥ ወይም የንግሥት እናት ወይም ራሷ ንግሥት ብትሆንም እንኳን ከደሟ ሳትነጻ ሥጋውና ደሙን ልትቀበል አትችልም ማለት ነው፡፡ አገላለጹ ሥርዓቱ ጽኑ መሆኑን ያስረዳል፡፡ ስለዚህ ሥጋ ወደሙን መቀበል የጓጓንበት ታላቅ በዓል ቢኖር፣ ሰርግ ወይም ሌላ ታላቅ ጉዳይ ቢኖርብንም በምንም አመካኝተን ቢሆን በወር አበባ ላይ ሳለን መቁረብ (ሥጋውንና ደሙን መቀበል) አንችልም:: ከማንኛውም የኛ ጉዳይ ስለ ሥጋ ወደሙ የተሠራው ሥርዓት ይበልጣልና፡፡ ስለዚህ በቁርባን የሚጋቡ ሰዎች የሰርግ ቀናቸውን ከመወሰናቸውና የሰርግ ዝግጅት ከመጀመራቸው በፊት የሴቷን የወር አበባ ዑደት ለይቶ ማወቅና ከሰርግ ቀኗ ጋር አንድ እንዳይሆን መጠንቀቅ አለባቸው:: ስለምን ቢባል በወር አበባ ላይ ያለች ሴት በምንም ዓይነት ማስተዛዘኛ ለመቁረብ ስለማይፈቀድላት ነው፡፡

4. ቤተ መቅደስ ከመግባት
   ሴት ልጅ መዋዕለ ንጽሕናዋን ሳትፈጽም በደመ ጽጌዋ ሳለች ወደ ቤተመቅደስ እንዳትገባ ሥርዓት ተሠርቷል:: ከግዳጅዋ ከነጻች በኋላ ገላዋን ታጥባ ትገባለች፡፡ ፍት.ነገ.አን 6 ሠለስቱ ምዕት በድጋሚ «ሐራስ ወትክት ኢትባእ ውስተ ቤተ ክርስቲያን» በማለት መዋዕለ ንጽሕናዋን ያልፈጸመች ወላድና ከደመ ጽጌዋ ያልነጻች ሴት ቤተ መቅደስ እንዳትገባ አዘዋል፡፡
    በወር አበባ ላይ ያለች ሴት ወደ ቤተ ክርስቲያን አትግባ ማለት ቤተ ክርስቲያን አትሂድ ማለት አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሄዳ የመጀመሪያውን ቅጽር (አጥር) ከገባች በኋላ በመጠለያና በገረገራ ውስጥ ሆና ተጸልይ፣ ትማር፣ ማንኛውንም መንፈሳዊ ነገር ትከታተል እንጂ ወደ ቤተ መቅደስ ተደፋፍራ አትግባ ማለት ነው፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አምጥተው «በመካከልም እርሷን አቁመው መምህር ሆይ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች» ማለታቸው በግልጽ ተጽፏል፡፡ ዮሐ 8፥1- 5 ይልቁንም በቁጥር 2 እና 20 ላይ የተጻፉት «ወደ ቤተ መቅደስ ደረሰ» እና «ኢየሱስም በመቅደስ ሲያስተምር» የሚሉት ሐረጎች ይህ ታሪክ የተፈጸመው በቤተ መቅደስ መሆኑን በጉልህ ያሳያሉ፡፡
   በዘመነ ኦሪት እንኳን ያመነዘረ ሰው ይቅርና በትዳሩም ቢሆን ሩካቤ የፈጸመ ሰው ዕለቱን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት አይችልም ነበር። ታዲያ ይህች ሴት ስታመዝር ተገኝታ ተይዛ ሳለ በቤተ መቅደስ ያውም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት በክስ ለመቆም እንዴት ቻለች?
  በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 8 ቁጥር 3 እና 20 ላይ እንደተተረጎመው ቤተመቅደስ ሦስት ቅጽር ነበራት፡፡ ስለዚህ ድቀት ያገኘው ማለትም በዝሙት የተሰነካከለ፣ ሕልመ ሌሊት ያየ ሰውና በወር አበባ ላይ ያለች ሴት የመጀመሪያውን አጥር ብቻ አልፈው ገብተው ይሳለሙና መባቸውን ሰጥተው፣ ተምረው፣ ሌላም መንፈሳዊ ተግባር አከናውነው ይመለሳሉ:: ወደ ውስጥ ግን ዘልቀው መግባት አይችሉም ነበር። ስለዚህ ከላይ ስታመነዝር ተገኝታ የተያዘችውም ሴት የገባችው የመጀመሪያውን አጥር ብቻ ነው:: በዚህ ታሪክ መሠረት በወር አበባ ላይ የሚገኙ ሴቶች ወደ ቤተ መቅደስ መግባት አይፈቀድላቸው

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት
ምዕራፍ ሰባት ክፍል ሁለት
....................................................


የወር አበባ «ርኩሰት» ነውን?
ምንጩ ባይታቅም በወር አበባ ላይ ያሉ አንዳንድ ሴቶች መስቀል ሊያሳልሟቸው ሲሉ «ርኩስ ነኝ አያሳልሙኝ!» ሲሉ ይደመጣሉ:: ሌለኞች ደግሞ ደመ ፅጌ ሲታያቸው ከጸሎት፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከማንበብ፣ አልፎ ተርፎም ለዝክርና ለጸዲቅ የሚሆን ማንኛውንም ሥራ ከመሥራት ይከለከላሉ፡፡ ማለትም ስንዴ ከመልቀም፣ አሻሮ ከመቁላት፣ እንኩሮ ከማነኮር እስከ መከልከል ይደርሳሉ፡፡ በእርግጥ የወር አበባ ርኩሰት ነውን? ርኩስስ ያሰኛልን?
በእርግጥ በዘመነ ኦሪት የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በዘመነ ኦሪት የወር አበባ የምታይን ሴት ለመጥቀስ «በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች>> እና ‹ባለ መርገም ሴት>> ሲል ይገኛል:: ዘሌ.18፥19፣ 20፥18 ከወር አበባዋ የነጻችን ሴት ለመጥቀስ ደግሞ <<ከርኩሰትዋ ነጽታ ነበርና>> በማለት ይገልጻል። 1ሳሙ11፥4 እነዚህ ጥቅሶች በሙሉ የወር አበባ በዘመነ ኦሪት የመርገምና የርኩሰት ምልክት ነበር ያልነውን ለማጉላት በዋቢነት የሚጠቀሱ ናቸው::
ይህ የሆነበት ምክንያት የወር አበባ የተከሰተው ሔዋን ደመ ፅፀ በለስን በማፍሰሷ ምክንያት እግዚአብሔር «ወበከመ አድመውኪያ ለዛቲ ዕፅ ከማሁ ድምዊ ለለወርኁ» ብሎ ከረገማት በኋላ በመከሠቱ ነው፡፡ ትርጓሜውም «የዚህችን ዕፀ በለስ ደሟን እንዳፈሰስሽ የአንቺም ደም በየወሩ ይፍሰስ›› ማለት ነው፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ውድ የ"የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች" ቻናል ተከታታዮች፥ የዕለቱን መርሐ ግብሮች፤ በNetwork ምክንያት ጊዜውን ጠብቀን ባለማቅረባችን ይቅርታ እንጠይቃለን!🙏

@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

አለ ክቡር ዳዊት። ስለዚህም ሁሉ ነገር አቤቱ ማራቸው ይቅርም በላቸው መፃተኛዋ ባሪያህንም ኃጢአቷን አታስብባት እያለች ወደፈጣሪዋ መሪር ዕንባን አለቀሰች። ያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ግርማ ወደስዋ መጣ። በታላቅ ግርማ ሆኖ ባየችውም ጊዜ ደነገፀች ከእግሩ ሥርም ወደቀች። ከዚህ በኋላ ነውር በሌለባቸው ንዑዳት ክቡራንና ንጹሐን በሆነ እጆቹ አነሣት። ቀጥሎም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ አትደንግጭ ነገር ግን የልብሽን ሃሳብ ንገሪኝ" አላት። እስዋም "አቤቱ ባሪያህንስ በባለሟልነት ካሠለጠንካት አባታችን አዳምን በአርአያህና በአምሣልህ ስለምን ፈጠርከርው። በእንጨት መስቀልስ ላይ ለምን ተሰቀልክ ስለአዳምና ስለልጆቹ አይደለምን?" አለችው። "አዋን ስለነሱ ስል ተሰቅያለሁ" አላት። "እግዲያውስ መሰቀልህ ወይም የተሰቀልከው ስለነሱ ከሆነ ከአቤል ጀምሮ እስከ ዛሬ የሞቱን ከዛሬም በኋላ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የሚሞቱትን አቤቱ ማራቸው ይቅርም በላቸው" አለችው። "አንተ ቸር ይቅር ባይ መዓትህ የራቀ ምሕረትህ የበዛ ነህና ከአንተ ሌላ አምላክ የሌለ እውነተኛ አምላክ ነህ ሁሉ ይቻልሃልና የሚሣንህ ነገር ከቶ የለምና ዓለም በጠቅላላዋ በእፍኝህ አትሞላም" በማለት እያለቀሰች ለመነችው። በዚያ ጊዜ ጌታ መልሶ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እስኪ አንቺ ራስሽ ፍረጅ አዳም ከነልጆቹ ከሠራው ኃጢአት እና እኔ በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን በቀያፋና በሐና አደባባይ በዕለተ ዓርብ ከተቀበልኩት ሕማማተ መስቀል ቢመዘን የትኛው ይመዝን ይመስልሻል?" አላት። ይህንም ባላት ጊዜ ደነገጠችና ከመሬት ላይ ወደቀች። በዚህ ጊዜ ቅዱሳት በሆኑ እጆቹ ከወደቀችበት አነሣትና "እንግዲህ ይህን ሁሉ መከራ የተቀበልኩ ለማን ወይም በማን ምክንያት ይመስልሻል" አላት።

ጌታም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እስኪ የልብሽን ሃሳብ ወይም ፍላጐትሽን ንገሪኝ" አላት። በዚህን ጊዜ "አቤቱ ፈጣሪየ ፈቃድህስ ቢሆን የአዳም ልጆች ከሥቃይ ከኵነኔ ይድኑ ዘንድ ዲያብሎስን ይቅር ትለው ወይም ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ። የኃጥእን መመለሱን እንጂ ጥፋቱን አትወድምና" አለችው። "የምለምንህ ወይም ማረው የምልህ ዲያብሎስን ወድጄው አይደለም ነገር ግን እርሱ ከተማረ በአዳም ልጆች ላይ ሥቃይና ኵነኔ ሊኖር አይችልም ብየ በመገመት እንጂ። የነሱ ሥጋ ሥጋየ እንደሆመኑ መጠን የኔም ሥጋ ሥጋህ ነውና" አለችው። ይህንም ባለችው ጊዜ ጌታ ፍግግ ብሎ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ሌሎች ካንቺ በፊት የነበሩ ካንቺም በኋላ የሚነሱ የማያስቡትን እጅግ የሚያስደንቅ ልመና አቀረብሽ" አላት። ይህንም ካለ በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ጠርቶ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ዲያብሎስን ማርልኝ ስትል ልመና አቅርባለችና እሺ ካላት ታወጣው በንድ ወደሲዖል ይዘሃት ሂድ" ብሎ አዘዘው። በዚህ ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እሺ ብሎ ሰግዶ እጅ ነሥቶ ወደሲዖል ይዞአት ሄደ። አብረው በሚጓዙበትም ጊዜ "እንግዲህ ዲያብሎስ ከታረቀ ወይም ከተማረ የሰው ልጆች ሁሉ ያርፋሉ" እያለች ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ታሳስበው ነበር። ይህን አምላክነትን ሲሻ ከክብሩ የተዋረደ ዲያብሎስ ምሕረት ለማግኘት ይሻ መስሏት ነበርና።

ከሲዖል አፋፍ በደረሱም ጊዜ የተመለከተችው ሥቃይ ተነግሮ የማያልቅ ነው ሰዎች ከሰዎች ጋር እንደውሻ ይናከሱ ነበር። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል "ምሕረት የሚፈልግ ከሆነ እስኪ በይ ዲያብሎስ ብለሽ ጥሪው" አላት። በዚህ ጊዜ በመላእክት ቋንቋ ሦስት ጊዜ "ሣጥናኤል ሣጥናኤል ሣጥናኤል" በማለት ጠራችው። ዲያብሎስም "ከዚህ በብዙ ሠራዊት ላይ ነግሼ ከምኖርበት አገር ማን ነው እሱ የሚጠራኝ" እያለ በታላቅ ቃል አሰምቶ ተናገረ። ከዚህም በኋላ "ለብዙ ዘመን ስፈልግሽ ወይም ሳድንሽ ቆይቼ ነበር ዛሬ ግን ከምኖርበት ቤቴ ድረስ መጣሽን" አላት። እርሷም "ጌታ ይቅርታ አድርጓልሃልና ከዚህ ከሥቃይና ከመከራ ቦታ ከወገኖችህ ጋራ ና ፈጥነህ ውጣ" አለችው። ይህንም በለችው ጊዜ ልቡ እንደ እሳት ነደደ አፈፍ ብሎ ተረማምዶ በግራ እጁዋን ይዞ ከሲዖል ረግረግ ውስጥ ወረወራት። በዚያን ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የእሳት ሰይፍ ይዞ ከኋላ ከኋላዋ ይከተላት ነበርና ይህን ምሕረት የሌለው ዕቡይ ዲያብሎስ በያዘው ሰይፍ ቢቀጣው የሲዖል ደጃፍ ተከፈተች። በዚህ ሰዓት ታላቅ ጨኸትና ውካታ ወይም መደበላለቅ ሆነ በሲዖል ያሉ የሰዎች ነፍሳት እንደንብ ከበቧት ወይም ሠፈሩባት። በዚያን ጊዜ በቅዱስ ሚካኤል ክንፍና በስዋም በተሰጣት ክንፈ ረድኤት ከሲዖል የወጡት ነፍሳት ቁጥር ዓሥር ሺህ ያህል ነበር። እነዚህ ከመከራ ያመለጡ ከሥቃይ የወጡ ነፍሳትን ባየች ጊዜ እጅግ አድርጋ ተደሰተች ከደስታዋም ብዛት የተነሣ የእናቱን ጡት እየጠባ እንደሚዘል እምቦሳ ጥጃ በመካከላቸው ትዘል ነበር።

ከዚህም በኋላ ወደ ፈጣሪዋ ሄዳ "አቤቱ ፍርድህ ከቶ እንደዚህ ነውን?" እያለች አደነቀች። ጌታም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ዲያብሎስን ድል አድርገሽ ጥቂት ምርኮን አገኘሽን" አላት። እስዋም  "አዋ ጌታዬ በኃይልህና በቸርነትህ አገኘሁ" አለችው። ከዚህ በኋላ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሚካኤል ጠርቶ "እሊህን ነፍሳት ዓለም ሳይፈጠር ወደ አዘጋጀሁላት ወደ ክርስቶስ ሠምራ መኖሪያ ቦታ ውሰዳቸው" አለው። በዚህ ጊዜ "አቤቱ ፈጣሪየ የእኔ መኖሪያየ ወዴት ነው?" አለችው። ጌታም "መኖሪያሽ ከእናቴ ከድንግል ማርያም ጋራ ነው እነሆ በትረ ማርያም ብየ ሰየምኩሽ መቀመጫሽን ወይም ደረጃሽን ከእርስዋ ቀጥሎ ሁለተኛ አደረግሁልሽ የባለሟልነት ግርማ አጐናጸፍኩሽ አንቺን የሚወዱ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው" አላት። ይህንም ባላት ጊዜ ፈጽማ ደስ ተሰኘች ወደ ኋላዋም መለስ ብላ ብትመለከት ለዓይን የሚያንፀባርቁ ዓሥር አክሊላት አየች። በየአንዳንዳቸው አክሉል ላይ ዐራት ከዋክብት አሉ ባቸው የእሊህ ከዋክብት ቊጥራቸው ሲደመር አርባ ይሆናል። በዚህ ጊዜ ከስዋ ጋራ የነበረውን መልአክ "እሊህ በላያቸው ብርሃናውያን ከዋክብት ያሉባቸው አክሊላት ለማን የተዘጋጁ ናቸው ሰውነቴ እጅግ አድርጋ ወዳቸዋለችና" አለችው። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም "ላንቺ ቢሆን ደስ አይልሽምን?" አላት። እርስዋም "አዎን ጌታየ ለኔ ቢሆን እወዳለሁ" አለችው። "እንግዲያስ ላንቺ የተዘጋጁ ናቸው" አላት። "በምን ሥራዬ ለኔ ተሰጡኝ" አለችው። "ዐሠርቱ ቃላት ኦሪትን ስድስቱን ቃላተ ወንጌል ጠብቀሽ ቤትሽን ጥለሽ ይህን ዓለም ንቀሽ አጥቅተሽ የክርስቶስን ቀምበር ተሸክመሽ ፈጣሪሽን ስለተከተልሽው ነው" አላት። ይህንንም በአላት ጊዜ እጅግ አድርጋ ተደሰተች ሁሉን ማድረግ የሚችል እግዚአብሔርንም ፈጽማ አመሰገነች።
ምንጭ፦ ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ

የቅድስት እናታችን ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ለተክለ ሃይማኖት ጻድቅ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ግንቦት ፲፪
አቡነ ተክለ ሃይማኖት


በዚህችም ዕለት የኢትዮጵያ ብርሃኗ ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፍልሠተ ዐፅማቸው ስለመከናወኑ፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከብዙ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸው በኋላ ተዘዋውረው ወንጌልን ለመስበክ የማይችሉት ዕድሜ ላይ ደረሱ፡፡ በዚህም ጊዜ ‹‹ለሌሎች አበራሁ ለራሴ ግን ጨለምኩ፣ ዓለም አጣፈጥሁ እኔ ግን አልጫ ሆንኩ…›› ብለው በዓት አጽንተው ከቆሙ ሳይቀመጡ፣ ከዘረጉ ሳያጥፉ ለ7 ዓመት ቆመው ጸለዩ፡፡ ከ1267-1289 ዓ.ም ባለው ጊዜ ደግሞ በደብረ ሊባኖስ ካለችው ገዳመ አስቦ ዋሻ በመግባት 8 ጦሮችን ተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት፣ ነገረ መስቀልን በማሰብ በተመስጦ ሌትና ቀን ያለማቋረጥ በጾምና በጸሎት በአርምሞ ተወስነው ሲጋደሉ ከቁመት ብዛት የተነሣ ጥር 4 ቀን 1289 ዓ.ም. አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራለች፡፡ ቅዱስ አባታችን በመዓልትና በሌሊት በትጋትና በቁመት በተጋድሎ ብዛት አንዲት የአገዳ እግራቸው ስትሰበር ዕድሜያቸው 92 ዓመት ሆኗቸው ነበር፡፡

ከ1289-1296 ዓ.ም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው በመቆም ያለምግብና ያለውኃ በትኅርምት ሌትና ቀን እንቅልፍ በማጣት እንደ ምሰሶ ጸንተው፤ በተመስጦ በትጋት ለሰው ዘር ሁሉ ድኅነትን ሲለምኑ ኖረዋል፡፡ ከሰባቱ ዓመታት ውስጥ ጥቂት ውኃ የቀመሱት በአራተኛው ዓመት ብቻ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ጌታችን ተገልጦላቸው በሰው አእምሮ ሊታሰብና ሊለካ የማይችል ትልቅና ልዩ የመንግሥት አዳራሽ ከሰጣቸው በኋላ የመለኮትን ነገር የሚናገር የእሳት አንደበት ያላቸው የመንግሥት ልብስ አለበሳቸው፡፡ በመስቀል ምልክት የተጌጡት ሰባት የሕይወት አክሊላትን አቀዳጅቷቸዋል፡፡ ይኸውም ‹‹ስለ ቀናች ሃይማኖትህ፣ ሃይማኖትን ለማስተማር መላዋን ኢትዮጵያን ስለመዞርህ፣ ከአረማውያን ሕዝብ ጋር በሃይማኖት ስትታገል ደምህን ስለማፍሰስህ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ወርደህ ልዩ ልዩ የቅዱሳን ቦታዎች ስለመሳለምህ፣ በሰባት ዓመታት ቊመት የአንዱ አገዳ እግርህ ስለመሰበሩ፣ ስለብዙ ጾም ጸሎት ስግደትህ፣ ስለልብህ ንጽሕናና ቅድስና›› በማለት የሕይወት አክሊላትን ካቀዳጃቸው በኋላ ዝክራቸውን በማዘከር መታሰቢያቸውን የሚያደርጉ ሁሉ በዚህ ዓለምም ሆነ በወዲያኛው ዓለም ፍጹም ዋጋና ፍጹም ክብር እንደሚሰጣቸው ጌታችን ታላቅ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ሥጋቸውም ወዴት ይቀበር ዘንድ እንዳላቸው ሲነግራቸው ‹‹እስከ 57 ዓመት ሥጋህ ከዚህ ይቀበራል፤ ከ57 ዓመት በኋላ ግን ይህች ዋሻ ትናዳላች፤ በዚህም ገዳም አደባባይ በስምህ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ልጆችህ ሠርተው ሥጋህን አፍልሰው በውስጡ ያኖራሉ›› አላቸው፡፡

ቅዱስ አባታችን በሞት ከማረፋቸው በፊት አስቀድሞ ጌታችን እንደነገራቸው ሥጋቸው ከነፍሳቸው ከተለየች ከ57 ዓመት በኋላ የካቲት 19 በጸሎት ላይ ለነበሩት ለአቡነ ሕዝቅያስ ተገልጠውላቸው ‹‹ጌታ የገባልኝ ቃል ይፈጸም ዘንድ ሥጋዬ የሚፈልስበት ደረሰ፣ ቀኒቱንም በምስጋናና በጸሎት መንፈሳዊ በዓል አድርጉ፤ እኔ ኃጥኡ በሞትኩበት ቀን እንደነበረው ምስጋና አቅርቡ፡፡ ሄደህ ለ12 መምህራንና ለልጆቼ ግንቦት 12 እንዲያከብሩ ንገራቸው፡፡ በፍልሰቴ ቀን አባቴ አባቴ የሚለኝ ሁሉ ይምጣ ያኔ እኔ ወዳጄ ሚካኤልና ልጄ ፊልጶስ አብረን መጥተን እንባርካለን፡፡ ምልክት ይሆንህም ዘንድ በምመጣበት ጊዜ የጠፋው የመቅረዙ መብራት ይበራል›› አሉት፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ ሕዝቅያስ በአባታችን ተባርከው ሄደው በአራቱም አቅጣጫ ላሉት 12 መምህራንና ለክርስትያኖች ሁሉ አባታችን የነገሩትን የፍልሰታቸው በዓል ስለማድረግ ወደ ፍልሰቱ በዓል ያልመጣም በዚያች ቀን (በሰማይ ለምልጃ) አባቴ እንዳይለው እርሱም ልጄ እንዳይለው ጨምሮ መልእክቱን ላከላቸው፡፡ እነርሱም ከያሉበት ተሰብስበው መጥተው የቅዱስ አባታችንን ሥጋቸውን አውጥተው ወደ ቤተ ክርስቲያን አፍልሰው 3 ጊዜ መቅደሱን አዙረው በዓሉንም አባታችን እንዳሉት በዝማሬና በምስጋና አክብረው ወደ ውስጥ አስገቡት፡፡ በዚህም ጊዜ ብፁዕ አባታችን ተክለ ሃይማኖት አስቀድመው እንደተናገሩት ጠፍቶ የነበረው መብራት ቦግ ብሎ በራ፡፡ ከቅዱስ ሚካኤልና ከልጃቸው ከአቡነ ፊልጶስ ጋር በመሆንም በዓሉን ያከብር የነበረውን የተክለ ሃይማኖት የጸጋ ልጆቻቸውን ሁሉም ይባርኩ ነበር፡፡

የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ረድኤት በረከታቸው ይደርብን! በጸሎታቸውም ይማረን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ግንቦት ፲፪
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


ግንቦት አስራ ሁለት በዚህች ዕለት የዓለሙ ሁሉ መምህር የሆነ የከበረ አባት ዮሐንስ አፈወርቅ አረፈ፡፡ ይህም አባት ከእስክንድርያ አገር ሰዎች ወገን ነው የአባቱም ስም አስፋኒዶስ የእናቱም ስም አትናሲያ ነው እሊህም እጅግ ባለጸጎች ነበሩ ይህንንም ልጃቸውን በመልካም አስተዳደግ አሳደጉት ትምህርትንና ጥበብንም ሁሉ አስተማሩት እርሱ ወደ አቴና ሒዶ በመምህራን ቤት ተቀምጦ ትምህርትን ሁሉ ተምሮ በዕውቀቱ ከብዙዎች በላይ ከፍ ከፍ ብሏልና።

ከዚህም በኋላ ገና በታናሽነቱ መነኰሰ የዚህንም የኃላፊውን ዓለም ጣዕም ንቆ ተወ ከእርሱም ቀድሞ በዚሁ ገዳም ቅዱስ ባስልዮስ መንኵሶ ነበር በአንድነትም ተስማምተው ብዙ ትሩፋትን ሠሩ ወላጆቹም በሞቱ ጊዜ ከተውለት ገንዘብ ምንም ምን አልወሰደም ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠ እንጂ ከዚያም በምንኵስና ሥራ በመጠመድ ፍጹም ገድልን እየተጋደለ ኖረ።

በዚያም ገዳም ሶርያዊ ጻድቅ ሰው ስሙ ሲሲኮስ የሚባል መነኰስ ነበረ እርሱም ወደፊት የሚሆነውን በመንፈስ ቅዱስ ያይ ነበር በአንዲት ሌሊትም ለጸሎት እየተጋ ሳለ ሐዋርያትን ጴጥሮስንና ዮሐንስን አያቸው ወደ ዮሐንስ አፈወርቅ ገብተው ጴጥሮስ መክፈቻ ሰጠው ወንጌላዊ ዮሐንስም ወንጌልን ሰጠው እንዲህም አሉት በምድር ያሠርከው በሰማይ የታሠረ ይሆናል በምድርም የፈታኸው ደግሞ በሰማያት የተፈታ ይሆናልና በውስጥህ መንፈስ ቅዱስ ያደረብህ አዲስ ዳንኤል ሆይ የክብር ባለቤት ከሆነ ከታለቅ መምህር ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወደ አንተ ተልከናልና ዕወቅ እኔም የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ የተሰጠኝ ጴጥሮስ ነኝ። ሁለተኛውም እኔም በመጀመሪያው ስብከቴ በከበረ ወንጌል ቃል አስቀድሞ ነበረ ያልኩ ይህም ቃል በጠላት ላይ የእሳት ሰይፍ የሆነ ዮሐንስ ነኝ። ለአንተም ከክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወገኖችህ ምእመናንን በቀናች ሃይማኖት ታሳድጋቸው ዘንድ ዕውነተኛ አእምሮ ደግሞ ተሰጥቶሃል። ጻድቅ ሲሲኮስም ይህን ራእይ በአየ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ቸር ታማኝ እረኛ ሁኖ እንደሚሾም ዐወቀ። ከዚህም በኋላ በቅዱስ ዮሐንስ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በላዩ ወርዶ አደረበትና ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ ዲያቆን ሁኖ ሳለም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ብሉያትንና ሐዲሳትን ተረጎመ።

በአንዲት ሌሊትም ቅዱስ ዮሐንስ ሲጸልይ የእግዚአብሔር መልአክ በድንገት እንደ በረድ ነጭ በሆነ ልብስ ተገለጠለት ቅዱስ ዮሐንስም ሲያየው ደንግጦ በምድር ላይ ወደቀ መልአኩም አርአያውን ለውጦ እንደ ሰው ሁኖ ታየው ወዳጄ አዲስ ዳንኤል ሆይ አትፍራ ተነሣ አለው የቅዱስ ዮሐንስም ልቡ ተጽናንቶ ጌታዬ አንተ ማነህ ግርማህ አስፈርቶኛልና አለው የእግዚአብሔር መልአክም ትሠራው ዘንድ የሚገባህን ልነግርህ ወዳንተ የተላክሁ ነኝ። አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ያዘዘህን ለመሥራት ልብህን አበርታ ቃልህ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በአራቱ ማእዘን ይደርሳልና እልፍ አእላፋትም ትምህርትህን ተቀብለው ትእዛዝህን ሰምተው ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር ተመልሰው ይድናሉና በእግዚአብሔር መንግሥትም ውስጥ የጸና የብርሃን ዐምድ ትሆናለህና። እነሆ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አንተ ይመጣል ከእርሱም ጋራ ሁሉም ካህናትና ዲያቆናት በየማዕረጋቸው የሚያዝህንም አድርግ የእግዚአብሐር ትእዛዝ ነውና ልትተላለፍ አይገባህም አለው።

ከዚህም በኋላ ያ መልአክ ለአባ ፊላትያኖስ ተገልጦ ቅዱስ ዮሐንስን ቅስና እንዲሾመው አዘዘው በማግሥቱም ሊቀ ጳጳሳቱ መጣ ከርሱ ጋራም ካህናት አሉ ይህን ቅዱስ ዮሐንስንም ይዞ ቅስና ሾመው። የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳትም በአረፈ ጊዜ ንጉሥ አርቃድዮስ ልኮ አስመጥቶ ቅዱስ ዮሐንስን በቍስጥንጥንያ ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾመው አባቶቻችን ሐዋርያት እንደሚአደርጉት በሊቀ ጵጵስናው ሥራ ላይ ጸና ሕይወትነት በአላቸው ትምህርቶችና ተግሣጾች ሕዝቡን ሁልጊዜ የሚአስተምር ሆነ። ከኤጲስቆጶሳትም ሆነ ከመንግሥት ወገን ሕግን የሚተላለፉትን ሁሉ ይገሥጻቸዋል ማንንም አይፈራም ፊት አይቶም አያደላም።

የንጉሥ አርቃድዮስ ሚስት አውዶክስያም ገንዘብ ወዳጅ ስለሆነች የአንዲት ድኃ መበለት ቦታዋን በግፍ ወሰደች ያቺ መበለትም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥታ ንግሥት አውዶክስያ ቦታዋን እንደነጠቀቻት ነገረችው እርሱም የደኃዋን ቦታዋን መልሺላት ብሎ ከብዙ ምክር ጋር እንድትመልስላት ንግሥት አውዶክስያን ለመናት እርሷ ግን እምቢ በማለት አልታዘዘችለትም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውን ደሙን እንዳትቀበል አውግዞ ለያት።

ቍጣንና ብስጭትንም ተመልታ ስለ ክፉ ሥራቸው ከሹመታቸው እርሱ የሻራቸውን ኤጲስቆጶሳት ሰበሰበች እነርሱም ንግሥቲቱን ስለ ተቃወመ ስደት እንደሚገባው በእርሱ ላይ ተስማምተው ጻፉ እርሷም አጥራክያ ወደ ሚባል ደሴት ሰደደችው። ከዚያም በደረሰ ጊዜ የዚያች ደሴት ሰዎች በክፉ ሥራ ጸንተው የሚኖሩ ከሀድያን ሁነው አገኛቸው ቅዱስ ዮሐንስም አስተማራቸው ገሠጻቸውም በፊታቸው ስለ አደረጋቸው ድንቆች ተአምራት ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው።

የሮሜ ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳቱ ዮናክኒዶስ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ስደት በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ በንጉሥ አርቃድዮስ ላይም በመቆጣት እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፈው ላኩ ከዚህ ከክፉ ሥራ ተጠበቅ ትእዛዛችንንም ተቀብለህ የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ ከአልመለስከው በአንተና በእኛ መካከል ሰላም አይኖርም።

መልእክታቸውንም በአነበበ ጊዜ እጅግ አዘነ ሚስቱንም አግዶ ልኮ ቅዱስ ዮሐንስን ከስደቱ መለሰው በተመለሰ ጊዜም የቍስጥንጥንያ ሰዎች በመመለሱ ታላቅ ደስታ አደረጉ። ከጥቂት ቀኖች በኋላም ንግሥቲቱ ወደ ክፋቷ ተመልሳ ሁለተኛ ወደ አጥራክያ ደሴት ሰደደችውና በዚያው አረፈ።

ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳት ዮናክኒዶስም በሰሙ ጊዜ መልእክትን ላኩ ሊቀ ጳጳሳቱም የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ እስከምትመልሰው ድረስ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል አውዶክስያን አወገዛት።

ከዚህም በኋላ የከበረ ዮሐንስን ይመልሱት ዘንድ ንጉሥ ላከ ግን ሙቶ አገኙት ሥጋውንም ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ አደረሱት። የከበረ ዮሐንስም በተሰደደበት አገር እንደአረፈና ሥጋውንም ወደ ቍስጥንጥንያ ከተማ እንዳመጡ ወደ አባ ዮናክኒዶስ መልእክት ጽፈው አስረዱት። ሁለተኛም የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል ልኮ አውድክስያን አወገዛት እየለመነችውም ስምንት ወር ያህል ኖረች በብዙ ልመናም ፈታት። ነገር ግን ጭንቅ በሆነ ደዌ እግዚአብሔር አሠቃያት ያድኗት ዘንድ ገንዘቧን ለባለ መድኃኒቶች ጥበበኞች እስከ ሰጠች ድረስ ግን አልዳነችም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መቃብርም ሔዳ በእርሱ ላይ ያደረገችውን በደል ይቅር ይላት ዘንድ እየሰገደችና እያለቀሰች ለመነችው እርሱም ይቅር አላት ከደዌዋም ፈወሳት። ጌታችንም ከሥጋው ታላላቅ ድንቆች ታአምራትን ገለጠ።

ስለርሱም እንዲህ ተባለ በአንዲት ዕለትም ከንጉሥ አርቃዴዎስ ጋር ተቀምጦ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው አባቴ ሆይ ስለ አንድ ቃል እንድታስረዳኝ እለምንሃለሁ። ይህም ቃል ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በልቤ ውስጥ ይመላለሳል ወንጌላዊ ማቴዎስ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምን የበኵር ልጅዋን እስከ ወለደች ድረስ ዮሴፍ አላወቃትም ስለምን አለ ወንዶች ሴቶችን እንደሚአውቋቸው ዮሴፍ አወቃትን አለው።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

   ከዚህ በኋላ ውስጥ ለውስጥ ያረካት የነበረው ውኃ ዝናብ ሆኖ እየመጣ ምድርን ከውጭ ያጨቀያት ጀመር፡፡ ምድር ለሔዋን ምሳሌ ናት ሰው ምድር ይባላልና፡፡ «እስመ አንተ ምድር፣ ዘምድረ ሰብሰ» የሚሉት መጽሐፍ ቅዱሳዊና መንፈሳዊ ጥቅሶች ሰው ምድር ለመባል ምስክሮች ናቸው፡፡ ዝናብ ደግሞ የወር አበባ ምሳሌ ነው:: ከውስጥ ለውስጥ ይሄድ የነበረው ውኃ ከጊዜ በኋላ በውጭ ተገልጦ ምድርን ማጨቅየቱ በሔዋን ባሕርይ የነበረ ደም ከጊዜ በኋላ በአፍአ መታየት መጀመሩን ያስረዳል::
    በዚህ ምስጢር መሠረት ሔዋን የወር አበባ ማየት የጀመረችው ከገነት ውጭ ነው፡፡ ጊዜውም አዳምና ሔዋን የፈጣሪን ትዕዛዝ ተላልፈው ከገነት ከተባረሩ በኋላ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

በወር አበባ ወቅት የሚያጋጥም የሕመም ስሜት
    ለዐቅመ ሔዋን የደረሰች ሴት ደመ ፅጌ በምታይባቸው ዕለታት የጡንቻና የአጥንት መልፈስፈስ (ድካም) ያጋጥማታል:: በተጨማሪም የጀርባ ወይም የወገብ ሕመም ሆድ ቁርጠት፣ የምግብ መንሸራሸር ችግርና የምግብ ፍላጐት ማጣት ለመሳሰሉት የሕመም ስሜቶች ስለምትጋለጥ በአመጋገብና በቂ ዕረፍት በማግኘት ረገድ ምቾት ያስፈልጋታል፡፡
    በቂ ዕረፍት ማለት ተኝቶ መዋል ማለት አይደለም፡፡ በወር አበባ ወቅት የሚኖረውን የሕመም ስሜት ለመቀነስ በቂ ዕረፍት ማግኘት እንደተጠበቀ ሆኖ ቀልጣፋ የተግባርና የእንቅስቃሴ ሰው ሆኖ መገኘት እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ይስማሙበታል፡፡
    ከሚኖረው የሕመም ስሜት በተጨማሪ ትዝብት ላይ እስከ መውደቅ የሚያደርስ መቅበጥበጥና አንዳንድ ጊዜም የመደበር (መደበትና) በሆነው ባልሆነው በቀላሉ የመከፋት ሁኔታ ሊንጸባረቅ ይችላል፡፡
     ከላይ የተጠቀሱትን የሕመም ስሜቶችንና በጠባይ ላይ የሚከሰቱትን ለውጦች መረዳት በወር አበባ ላይ የሚገኙትን ሴቶች በሚገባ ለመንከባከብ ይረዳል:: በዚህ ወቅት የሚገኙ ሴቶችን መንከባከብ እንደሚገባ ከቀደሙት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪኮች መረዳት ይቻላል::
    ላባ የተባለ ሰው የጠፋበትን ዕቃ በሚፈልግበት ጊዜ በወር አበባ ላይ ትገኝ የነበረችውን ልጁን ራሔልን ከተቀመጠችበት ቦታ ላለማስነሣት የተቀመጠችበትን ስፍራ ከመበርበር ተቆጥቧል፡፡ በምን አውቆ ቢባል እርሷም አባትዋን «በፊትህ ለመቆም ስላልቻልኩ አትቆጣብኝ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛል» አለችው ስለሚል ከዚህ የይቅር በለኝ ቃሏ ያለችበትን ሁኔታ ለመገንዘብ ችሎ ነበር፡፡ ዘፍ 31፥35 ይህ የላባ ታሪክ በወር አበባ ላይ ለሚገኙ ሴቶች ሌሎች ሰዎች ሁሉ ማድረግ ያለባቸውን እንክብካቤ በግልጽ ያስረዳል፡፡

በቀጣይ ምዕራፍ ሰባት ክፍል ሁለት <<የወር አበባ «ርኩሰት» ነውን?>> በሚል ይቀጥላል...

ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

.                      ምዕራፍ ሰባት
                          የወር አበባ

አሰያየሙ
  ሀ. በመንፈሳዊያን መጻሕፍት የወር አበባ ልዩ ልዩ ስያሜዎች አሉት፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ስለ አብርሃምና ስለ ሚስቱ ሕይወት በሚተርክበት ጊዜ «አብርሃምና ሣራም በዕድሜያቸው ሽምግለው ፈጽመው አርጅተው ነበር፤ በሴቶችም የሚሆነው ልማድ ከሣራ ተቋርጦ ነበር» በማለት ተናግሯል:: በዚህም ትረካው ነቢዩ ሙሴ የወር አበባን «በሴቶች የሚሆነው ልማድ» በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ ሰይሞታል፡፡ ዘፍ 18፥11 ከዚህ የሊቀ ነቢያት ሙሴ አሰያየም በመነሣት ሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍትና መምህራነ ቤተ ክርስቲያን የወር አበባ ለማለት «ልማደ አንስት» ሲሉ ይገኛሉ::

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

.                   ምዕራፍ ስድስት
       ለዐቅመ ሔዋን የመድረስ ምልክቶች

    እንደ ወንዶች ሁሉ ሴቶችም ለዓቅመ ሔዋን ሲደርሱ የተለያዩ አካላዊ ለውጦች ይታዩባቸዋል:: በኮረድነት ዓመታት ፈጣን የሆነ የቁመት ማደግና የክብደት መጨመር ከመከሰቱም ሌላ የሽንጥ መርዘም፣ የደረት መጋጠሚያ መጐድጐድ፣ የትከሻ መስፋትና የአንገት መወፈር ተያይዘው ይመጣሉ፡፡ በአንዳንድ ሴቶች ላይ ደግሞ ብጉር በሰውነታቸው በተለይም በፊታቸው ላይ በዝቶ የሚታይ ሲሆን የፊት ቅርጽም ቀስ በቀስ እየተለወጠ ይሄዳል፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

💠ከሰማያት ወርዶ💠

ከሰማያት ወርዶ ሥጋን በመልበሱ
በዓለም መድኃኒት ነጻ ወጣን በእርሱ
የጨለማው ገዢ ዲያብሎስ አፈረ
በጌታ ትንሣኤ የሞት ኃይል ተሻረ(፪)

እልል እልል ደስ ይበለን(፪)
ሞትን ድል ነስቶ ተነሣልን(፪)

አዳም ሆይ በሲኦል ለዘመናት ኖረ
ዛሬ በትንሣኤው ብርሃንን አገኘ
የተስፋው ቃልኪዳን ይኸው ተፈጽሟል
ላንተም ለልጆችህ ዛሬ ሰላም ሆኗል(፪)

አዝ---

የአጋንንት ግዛት ሲኦል ባዶ ቀረ
ነፍሳት ነጻ ወጡ ጠላትም ታሰረ
የብርሃን ግርማ ጸዳል ምድርን ሞላት
በትንሣው ብርሃን አገኘን ድኅነት(፪)

አዝ---

የድኅነትን ሥራ በሞቱ ፈጸመ
የዲያብሎስ ሴራ ሥልጣኑ አከተመ
በዕለተ ሰንበት ክርስቶስ ተነሥቷል
የሲኦል እስራት ገመዱ ተፈትቷል(፪)

እልል እልል ደስ ይበለን(፪)
ሞትን ድል ነስቶ ተነሣልን(፬)
በማኅበረ ሰላም መዘምራን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

እንጂ ከቅጽረ ቤተክርስቲያን ገብተው ጸልየውና ተምረው ወይም ማንኛውም መንፈሳዊ ተግባር አከናውነው መመለስ የሚከለክላቸው የለም፡፡

በቀጣይ ምዕራፍ ሰባት ክፍል ሦስት <<ወደ ቤተ መቅደስ ለምን አይገባም?>> በሚል ይቀጥላል..

ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ይሁን እንጂ የረከሰ በተቀደሰበት፤ የተረገመ በተባረከበት በዚህ በአዲስ ኪዳን ዘመን የወር አበባን ርኩሰት ነው ማለት ቀርቶ መታሰብም የለበትም: የወር አበባ ርኩሰት መሆኑ ቀርቷል፡፡ ርኩሰት አይደለም፣ ርኩስም አያሰኝም፡፡ እኛ ባለንበት በዚህ በአዲስ ኪዳን ዘመን የወር አበባን ርኩሰት ነው ማለት ከባድ ኃጢአት ከመሆንም አልፎ ክህደት ይባላል፡፡ በአዲስ ኪዳን ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈጸመው ቤዛነት መርገምነቱና ርኩሰትነቱ ተወግዷልና፡፡
   አንድ መዘንጋት የሌለበት ነገር የወር አበባ ርኩሰት ባይሆንም አደፍ ነው፡፡ አደፍ (እዳሪ) ነው ማለትና ርኩስት ነው ማለት ከፍተኛ ልዩነት አላቸው:: ርኩሰት ውሳጣዊ ነው፡ በንስሐ እንጂ በውኃ አይጠራም፡፡ አደፍ ግን አፍአዊና በግዘፍ የሚታይ ነው:: ስለዚህ ውኃ ያጠራዋል:: እንደዚህም ሁሉ የወር አበባ አደፍ (እዳሪ) ነው ሲባል ሰውነታችን እንደሚያስወግዳቸው ማንኛውም ሌሎች ነገሮች አፍአዊ ቆሻሻ ነው ማለት ነው::"
   የወር አበባ በሴቶች ባሕርይ ሳለ እንደ ቆሻሻ አይቆጠርም:: ሰውነት ሲያስወግደው ግን ይቆጠራል:: ለምሳሌ:- ዛሕል (ንፍጥ)፣ ሽንት፣ ምራቅ፣ ዓይነ ምድር (እዳሪ)፣ ላብ እነዚህ ሁሉ በሰው ባሕርይ በሰውነት ውስጥ ሳሉ ጠቃሚና አስፈላጊ ነበሩ፡፡ ሰውነት ሲያስወግዳቸው ግን እንደ ጉድፍ ይቆጠራሉ፡፡ የወር አበባም እንዲሁ ነው፡፡ ዛሕል (ንፍጥ) ካፍንጫ ከወጣ እዳሪ ነው፡፡ ርኩሰት ግን አይደለም የወር አበባም እንዲሁ ነው፡፡
   የወር አበባ ርኩሰት ባለመሆኑ መስቀል ከመሳም፣ ከመጸለይ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከማንበብና ከመድገም አያግድም:: ያግዳል እንጂ የሚል ካለ አቡነ ዘበሰማያትን ጨምሮ ሰላም ለኪንና ሌሎች የጸሎት ዓይነቶችን በቃላቸው የሚነዱ ምዕመናት በብዙ ቁጥር ይገኛሉ፡፡ በወር አበባ ወቅት ቅዱሳት መጽሕፍትን ለማንበብ ከተከለከሉ በቃላቸው የያዙትን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ምን ሊያደርጉት ነው? ደግሞም ወረቀቱንና ብራናውን የሚያከብረው ቅዱስ ቃሉ አይደለምን? ቅዱሱን ቃል በልቡናቸው ይዘው ሳለ መጽሐፉን አትንኩት አታንቡት ማለት ግብዝነት አይሆንምን? የትኛው ይበልጣል? ወረቀቱና ብራናው ነውን? ወይስ ወረቀቱንና ብራናውን የሚያከብረው ቅዱስ ቃሉ? ብራናውንና ወረቀቱን እንዳይነኩና እንዳያነቡ የሚከለከሉ ከሆነ ቅዱስ ቃሉንም በቃላቸው አንዳይዙና እንዳያጠኑ መክልክል በተገባቸው ነበር፡፡ ከተፈቀደላቸው ግን መጻሕፍቱን ከማንበብና ከመድገም የሚከለክላቸው ማን ነው? ስለዚህ በወር አበባ ላይ የሚገኙ ሴቶች እነዚህን ተግባሪት ከማከናወነን አይከለከሉም፡፡
   ከላይ የተጠቀሰውን ሐሳብ ከዚህ በታች የሰፈረው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ንጽጽራዊ በሆነ መንገድ ሲያጠናክረው እናገኘዋለን፡፡ <<እናንተ ማንም በቤተ መቅደስ የሚምል ምንም የለበትም ማንም በቤተ መቅደስ ወርቅ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል የምትሉ ዕውሮች መሪዎች ወዮላችው:: እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች ማናቸው ይበልጣል? ወርቁ ነውን? ወይስ ወርቁን የቀደሰው ቤተ መቅደስ? ደግማችሁም:- ማንም በመሠዊያው የሚምል ምንም የለበትም ማንም በላዩ ባለው መባ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል ትላላችው፡፡ እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው? እንግዲህ በመሠዊያው የሚምለው በእርሱና በእርሱ ላይ ባለው ሁሉ ይምላል፡፡ በቤተ መቅደስም የሚምለው በእርሱና በእርሱ ላይ በሚኖረው ይምላል፡፡ በሰማይም የሚምለው በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል::>> ማቴ 23፥16-22

በወር አበባ ወቅት መከልከል የሚገባው ከምን ከምን ነው?
    ሴቶች ደመ ፅጌን በሚያዩበት ወቅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አራት ዋና ዋና ነገሮች እንዳይፈጸሙ በመንፈሳዊ ሕግ ተከልክለዋል፡፡ እነዚህ ነገሮች ለምን እንደተከለከሉና ለመከልከላቸውም የሚቀርቡ መጽሐፋዊ መረጃዎች ተያይዞው ቀርበዋል፡፡

1. ከሩካቤ
የወር አበባን የምታይ ሴት ባለትዳር ከሆነች በደሟ ወቅት ምንም እንኳን ባሏ ቢሆንም ሩካቤ መፈጸም በመንፈሳዊ ሕግ አይፈቀድላትም:: የሕክምና ባለሙያዎችም ቢሆኑ በደም ወራት የሚደረግ ሩካቤ በአብዛኛው ለአባለ ዘር፣ ለልዩ ልዩ ተላላፊ በሽታዎችና እንዲሁም ለልክፋት (ለኢንፌክሽን) በቀላሉ ለመጋለጥ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ይናገራሉ::
   በመንፈሳዊ አስተምህሮ ስንመለከተው ደግሞ የሰው ልጅ ዘር ክቡር ነው፡፡ ስለዚህ ሴት ልጅ በትክት (በወር አበባ) ላይ እያለች ሩካቤን መፈጸም ክቡር ዘርን እዳሪ ከሆነ ደም ጋር ማዋሐድ ነውና ከባድ ኃጢአት ሆኖ ይቆጣራል፡፡
   መጽሐፍ ቅዱስ ሴት ልጅ ከግዳጅዋ ሳትነፃ የሚፈጸም ሩካቤን ሲከለክል እንዲህ ይላል፡- «እርሷም በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች ኀፍረተ ሥጋዋን ትገልጽ ዘንድ ወደ ሴት አትቅረብ:» ዘሌ 18፥ 19 ይህንን ሕግ ተላልፎ ኀጢአት የሠራ ሰው ስለሚገባው ቅጣት ሲናገር ደግሞ:- «ማንኛውም ሰው ከባለመርገም ሴት ጋር ቢተኛ ኀፍረተ ሥጋዋንም ቢገልጥ እርሷም የደሟን ፈሳሽ ገልጣለችና ሁለቱም ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ፡፡» ይላል። ዘሌ20፥18
   ትክቶ (የወር አበባ) ምንም እንኳን በአዲስ ኪዳን መርገም ወይም ርኩሰት ስላልሆነ በዚህ ወቅት ሩካቤ የሚፈጽሙ ሰዎች እንደ ኦሪቱ ዘመን በድንጋይ ተወግረውና በእሳት ተቃጥለው እንዲጠፉ ባይደረግም ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በመተላለፋቸው በመንፈሳዊ ቅጣት (በቀኖና) መቀጣታቸው አይቀርም:: ምክንያቱም በወር አበባ ወቅት የሚፈጸም ሩካቤ በአዲስ ኪዳንም ክልክል ስለሆነ ነው:: የወር አበባን ጨምሮ ባልና ሚስት ሩካቤ ከመፈጸም የሚታቀቡባቸው ወቅቶችና ዕለታት በ«ትዳርና ተላጽቆ› መጽሐፍ በምዕራፍ ስምንት ላይ በሚገባ ተዘርዝረዋልና ያን ይመልከቱ፡፡

2. ከመጠመቅ
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ «ይህም ውኃ ደግሞ ማለት የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም:: ለእግዚአብሔር ጥምቀት የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ» በማለት ተናግሯል፡፡ 1ጴጥ 3፥21 ስለዚህ ጥምቀት ሥጋዊ እድፍን ማስወገጃ ስላልሆነ ከመጠመቅ በፊት ተጣጥበው ከአፍአዊ እድፍ ከጠሩ በኋላ መጠመቅ ይገባል እንጂ ከእድፍ ጋር ለመጠመቅ መቅረብ ተገቢ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የሥጋ ንጽሕና ለነፍስ ንጽሕናና ለንስሐ የመዘጋጀት ምልክት (ምሳሌ) ነውና፡፡
  እንዲህ ከሆነ የወር አበባ ከላይ እንደተገለጸው አደፍ ይባላልና በወር አበባ ላይ ሳሉ መጠመቅ ክልክል ነው፡፡ ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ «ወለእመ ተዳደቃ ወረከባ ለብእሲት ደመ ትክቶ ትጽናሕ እስከ ትነጽሕ›› ማለትም «በምትጠመቀው ሴት በምትጠመቅበት ቀን አደፍ ቢመጣባት እስክትነፃ ድረስ ትቆይ» በማለት በወር አበባ ወቅት የሚደረግ ጥምቀትን ይከለክላል፡፡
   በእርግጥ ከላይ የሰፈረው የፍትሐ ነገሥት ጥቅስ የሚመለከተው ለዓቅመ ሔዋን ከደረሱ በኋላ ክርስትና ለመነሣት የሚመጡ የንዑሰ ክርስቲያንን ጥምቀተ ክርስትና ነው፡፡ ቢሆንም ይኸው ራሱ ጥቅስ ማንኛውም ክርስቲያን ከበሽታ ለመፈወስም ሆነ ለበረከት በየጊዜው ለሚጠመቀው የፈውስ ጥምቀት ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ምክንያቱም በወር አበባ ወቅት መጠመቅ የተከለከለበት ምክንያት ለየትኛውም የጥምቀት ዓይነት ቢሆን ምስጥሩ ያው በመሆኑ ነው፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

Do you enjoy reading this channel?

Perhaps you have thought about placing ads on it?

To do this, follow three simple steps:

1) Sign up: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
2) Top up the balance in a convenient way
3) Create an advertising post

If the topic of your post fits our channel, we will publish it with pleasure.

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ግንቦት ፲፪
ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ


በዚህችም ዕለት ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ነው፡፡ በሸዋ ከፍለ አገር በቡልጋ አውራጃ ልዩ ስሟ ቅዱስ ጌዬ የተባለች አገር ነበረች ይህችም የእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የትውልድ አገሯ ናት። በዚህም አገር በወርቅና በብር በሐር እና በልዩ ልዩ ልብስ በወንድና በሴት አገልጋዮች በፈረስና በበቅሎ የከበረ አንድ ስሙ የታወቀ ሰው ነበር። የዚህ ሰው ስሙ ቅዱስ ደረሳኒ ሲሆን የሚስቱም ስም ቅድስት ዕሌኒ ይባላል ሁለቱም ባልና ሚስቱ እግዚአብሔር የሚፈሩ ደጋግ ሰዎች ስለነበሩ በጎ ሥራቸው በዓለም ሁሉ የታወቀ ነበር። እሊህም ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠችና የከበረችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ወልደው በደም ግባቷና በጠባይዋ እየተደሰቱ አሳደጓት ከዚያም የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ሥርዓቶችንም ሁሉ አስተማሯት። ባደገችና ለአቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ የንጉሥ ባለሟል የሆነ ትውልዱ፤ ነገዱ ከአባ ፃሠርጓ ወገን የሆነ ለኢየሱስ ሞዓ ልጅ ለሠምረ ጊዮርጊስ በሕግ አጋቧት። እሱም በዚህ ዓለም ገንዘብ በጣም የከበረ ከመሆኑም በላይ በይበልጥ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው ነበረ። ከደም ግባቷ የተነሣ ሙሽራይቱ ማለት እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን እጅግ አድርጎ ወደዳት። አሟቷ ኢየሱስ ሞዐም ይህች ብላቴና "በታላቅ ቁም ነገር የተመረጠች ነች" በማለት ትንቢት ይናገርላታል ስለዚህ እንደ እመቤቱ አድርጐ ያከብራት ነበር። ከዚህም በኋላም ለሕጋዊ ባሏ ለሠምረ ጊዮርጊስ ዓሥራ አንድ ልጆች ወለደችለት ከነዚህም መካከል ዘጠኙ ወንዶች ሁለቱ ሴቶች ነበሩ። ልጆችዋንም ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች በክብር በሥርዓት አሳደገቻቸው።

በዚያን ዘመን የእግዚአብሔር ባለሟል የሚሆን ዓፄ ገብረ መስቀል የሚባል የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበር። እርሱም ዝናዋን ሰምቶ ሥነ ምግባሯን ተመልክቶ ይልቁንም በሷ ላይ ያደረውን ኃይለ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ስለገለጸለት እጅግ አድርጐ ይወዳትና ያከብራት ነበር። ከዕለታት ባንድ ቀን በጸሎትሽ አስቢኝ በማለት በራሱ በንጉሡ ቤተ መንግሥት ከሚያገለግሉ አገልጋዮች ወይም ሠራተኞች መካከል እንዲያገለግሏት 174 አገልጋዮች ላካላት። ዳግመኛም ፈረስና በቅሎ ከነሥራታቸው እንደዚሁም ለነሥታት ሚስቶች የሚገባ ከሐርና ከወርቅ የተሠራ ልብስና የወርቅ ጫማ ላከላት። ነገር ግን እሷ ይህን ሁሉ ክብር አልፈለገችም ይልቁንም ለዓላማየ ዕንቅፋት ወይም ከንቱ ውዳሴ ይሆንብኛል በዚያውስ ወርቁ ጌጡ ልብሱ ተሸጦ ለነዳያን ይመጸወታል ለቤተ ክርስቲያን መባዕ ይሰጣል እኒህን አገልጋዮች ግን ምን አደርጋቸዋለሁ በማለት ወደ እግዚአብሔር እያመለከተች ቆየች።

ከአገልጋዮችዋ መካከል ምግባሯ የከፋ የምታናድዳትና የምታበሳጫት አገልጋይ ነበረች። ከዕለታት በአንድኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ በጣም ተበሳጨችና በዚያች አገልጋይ አፍ ውስጥ የእሳት ትንታግ ጨመረችባት።  ያም እሳት ትንታግ በአገልጋይዋ ጉረሮ ድረስ ዘለቀና ገደላት። በዚህን ጊዜ ቤተሰቦችዋ መጥተው የአገልጋይቱን አስከሬን ወደሌላ ክፍል ወሰዱት። ብፅዕት ክርስቶስ ሠምራም ደንግጣ ካለችበት ቤት ውስጥ ወደ ሌላው ክፍል ገባችና ወደ ሰማይ አቅንታ "ወይኔ ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ የካህን ሚስት ስሆን ነፍስ ገዳይ ሆኛለሁና። ሰውስ ምን ይለኛል ለነፍሴስ ምን እመልስላታለሁ ከእግዲህ ከክርስቲያን ወገን ልቆጠር አይገባኝም በደሌንስ እንደምን አድርጌ ልሸሸሽጋት እችላለሁ" እያለች አለቀሰች።

ከዚህ በኋላ እንዲህ ስትል ለእግዚአብሔር ብፅዓት አደረገች "አቤቱ ይህችን በእኔ እጅ የሞተችውን አገልጋይ ነፍስዋን ከሥጋዋ አዋህደህ ብታሥነሣልኝ ልጆቼን ቤቴን ንብረቴን ትቼ ባለ ዘመኔ ሁሉ አንተን እከተላለሁ። አንተን ከመከተል ከቶ ወደኋላ አልልም። ለሰውነቴ ጌጥ ወይም ግርማ ሞገስ የሚሆናት ወይም የሚሞቃት ልብስ ከቶ አልለብስም ሥጋዬን የሚያረካ ምግብም አልመገብም። አቤቱ ጌታዬ ሆይ ጸሎቴን ስማኝ ልመናዬም በፊትህ ፈጥኖ ይድረስ አቤቱ ፊትህን ከኔ ከባሪያህ አትመልስ"። እንዲህ እንዲህ እያለች በልቅሶና በኀዘን ለብዙ ሰዓት ከጸለየች በኋላ ድካም ተሰማትና ዕረፍት አደረገች። ከዚህ በኋላ ቤተሰቦችዋ እስዋ ወዳለችበት ክፍል መጥተው "እመቤታችን ሆይ ሙታ የነበረችው አገልጋይሽ በእግዚአብሔር ኃይልና በአንቺ ጸሎት ተነሥታለችና ደስ ይበልሽ" አሏት። በዚህ ጊዜ ፈጥና ተነሥታ ደስ እያላት ሙታ የነበረችው አገልጋይ ካለችበት ቦታ ደረሰችና ሕይወት አገኘቻት ከዚያም ቃሏን ከፍ አድርጋ "ልመናዬን ቸል ያላለ ቸርነቱንም ከኔ ከባሪያው ያላራቀ ፈጣሪ ይክበር ይመስገን" ብላ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔር አመሰገነች።

ከዚህ በኋላ አስቀድሞ ከአፏ የወጣውን ከአንደበቷ የተነገረውን ቃል አስባ ልብሰ ምንኵስናዋን ማለት ቆቧን ቀሚሷን አጽፏን መታጠቂያዋን አዘጋጀች። ቤተሰቦቿና አገልጋዮቿም "እመቤታችን ሆይ ይህ የምታዘጋጂው የምናኔ ልብስ ለምንሽ ነው ወይስ ለማን ነው የምታዘጋጂው" አሏት። እርሷም " ሃይማኖት ያስተማሩኝ አባቴ ልብስ አልቆባቸዋል ሲሉ ሰምቼ ለሳቸው ነው የማዘጋጀው" አለቻቸው።

ከዚህም በኋላ ከዕለታት ባንደኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ አገልጋዮቿን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሄድ ዘንድ ተዘጋጁ አለቻቸውና እነሱም አሺ በጎ ብለው አጅበዋት ወደቤተ ክርስቲያን ሄዱ። ከዚያም እንደደረሱ "በሉ እንዲህ እኔ ከዚህ ጥቂት እቆያለሁና እናንተ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ ለኔ ይህች አንድዲት አገልጋይና ይህ ሕፃን ልጅ ብቻ ይበቁኛል አለቻቸው። በዚያኑ ጊዜ አገልጋዮቿ እጅ እየሱ ወይም እየተሰናበቱ ወደቤታቸው ተመለሱ። ከዚያም ከዳዊት መዝሙር "ልቤ ጽኑ ነው አቤቱ ልቤ ጽኑ ነው እግዚአብሔርን ፈጽሜ አመሰግነዋለሁ እግዚአብሔር የደህንነቴ መብራት ስለሆነ ምን ያስደነግጠኛል እግዚአብሔር የሕይወቴ መተማመኛ ነው ምንስ ያስፈራኛል የሚለውን እየጸለየች የሚያልፈን ዓለም በማያልፈው ዓለም ለመተካት ወይም ለመለወጥ አውጭኝ እግሬ ብላ ገሠገሠች። ያ በልስላሴና በእንክብካቤ የኖረ እግር ከመንገዱ ብዛት እንደዚሁም ከቅርቅፍቱና ከእንቅፋቱ የተነሣ ፈለግ ሲያወጣ ሥጋውን እየቆረጠች ስትጥለው ደሙ እንደጒርፍ ውሃ ይወርድ ነበር። ያች የተከተለቻት አገልጋይ ግን ከእመቤቷ እግር እየተቆረጠ የሚወድቀውን የአካል ቊራጭ እያነሳች በልብሷ ትቋጥረው ነበር። በዚህ ዓይነት ችግርና ፀሐይ ሐሩር የብዙ ጐዳና ጉዞ ተጉዛ ከአሰበችበት አገር ደረሰች። በደብረ ሊባኖስ አቅራቢያ ወይም አካባቢ ስትደርስ የራስ ፀጒራን ይዛው በነበረ ምላጭ ላጨች ልብሷንም አውልቃ ለነዳያን አከፋፈለች የያዘችውንም ገንዘብ በመንገድ ላይ ላገኘችው ሁሉ መፅውታ ጨረሰች። ከዚያም አስቀድማ ያዘጋጀችውን ልብስ ምንኵስና ማለት ቀሚስዋን አጥልቃ አጽፋን ተጐናጽፋ ቆቧን ደፍታ ደብረ ሊባኖስ ከሴቶች ገዳም ደረሰች። የገዳሙ መነኰሳትም በታላቅ ክብር ተቀብለው ወደበዓታቸው አስገቧት ...

እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ለሳጥናኤል ምሕረት እንደለመነች፦ ከዕለታት በአንድኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ጓንጉት በምትባል ደሴት ውስጥ ዓርብ ዕለት ከቀኑ በስድስት ሰዓት ላይ ስለሰው ልጆች ስትጸልይ ሣለ። ዓለሙ ሁሉ ከንቱ እንደሆነና የሰውም ልጅ ሕይወት እንደጥላ ኃላፊ ጠፊ መሆኑን ፈጽማ ተመለከተች። ነቢዩ ዳዊት "ሰው ከንቱ ነገርን ይመስላል ዘመኑ ወይም ሕይወቱ እንደጥላ ያልፋል" ሲል ተናግሯልና። ዳግመኛም "ሰው ክብር እንኳ ቢሆን ሊኖር አይችልም እንደሚጠፋ ወይም ማስተዋል እንደሌለው እንስሶች መሰለ...

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የኢትዮጵያ ብርሃኗ ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ኦ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የከበረ ዮሐንስም ንጉሥ ሆይ እንዲህ አትበል እንዲህ አንተ እንደምትለው አይደለም የከበረች ድንግል እመቤታችንስ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሆድዋ ውስጥ በነበረ ጊዜ የእርሱ ኅብረ መልክ በሚለዋወጥ ጊዜ ከእርሱ ጋር መልኳ ይለወዋወጥ ነበር። በንጹሕ ብርሌ ውስጥ ውኃ በጨመሩ ጊዜ ውኃ መስሎ እንደሚታይ ወይን ጠጅም ቢጨምሩ ያንኑ መስሎ እንደሚታይ ወይም ከውስጡ በተጨመረው ቀይም ቢሆን ቀልቶ እንደሚታይ ቅጠልያም ቢገባበት ቅጠልያ መስሎ እንደሚታይ።

ድንግልም በሆድዋ ውስጥ የልጅዋ መልክ በሚለዋወጥ ጊዜ ከእርሱ ጋራ መልኳ ይለዋወጥ ነበር። እንደ ሮማን አበባ የምትቀላበት ጊዜ አለ እንደናርዶስም የምታብለጨልጭበት ጊዜ አለ የለመለመ ቅጠል የምትመስልበትም ጊዜ አለ ከወለደች በኋላ ግን አልተለወጠችምና ዮሴፍ በአንድ በቀድሞው ኅብረ መልኳ ተወስናለት መልኳን ተረዳ ማለት ነው አለው። በዚያን ጊዜ በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ ከወርቅ የተሠራ የእመቤታችን አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ሥዕል ነበረችና አፈ ወርቅ ዮሐንስ ልሳነ ወርቅ ዮሐንስ አፈ በረከት ዮሐንስ መልካም ተናገርክ የሚል ቃል ከእርሷ ወጣ።

ንጉሡና ከእርሱ ጋር ያሉት በሰሙ ጊዜ እጅግ አደነቁ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት በዚያን ጊዜ ንጉሥ አዝዞ ወርቅ ሠሪ አስመጥቶ ለከበረ ዮሐንስ የወርቅ ልሳን አሠርቶ ለሚያየው ሁሉ መታሰቢያ ምልክት ሊሆን አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ሥዕል ዘንድ ሰቀለው። ቅዱስ ዮሐንስንም ከዚያች ቀን ወዲህ ልሳነ ወርቅ ብሎ ጠራው አፈ ወርቅም ተብሎ እስከዛሬ ተጠራ።

እግዚአብሔር አምላካችን ከሊቁ በረከት ያሳትፈን! አሜን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ዋይ ዜማ ዘሰማዕኩ በሰማይ እመላዕክት ቅዱሳን እንዘይብሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር መላ ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ስብሀቲከ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ግንቦት ፲፩
ቅዱስ ያሬድ ካህን ወማኅሌታይ


ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳላቸው የሆነ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ያሬድ የተሰወረበት ነው። ይህም ቅዱስ ከአባ ጌዴዎን ዘመዶች ወገን ነው እርሱም በኢትዮጵያ አገር ከታነፁ አብያተ ክርስቲያናት ለምትቀድም ከአክሱም ካህናት ውስጥ ነው እርሷም አስቀድሞ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በውስጥዋ የተሰበከና አምላክን በወለደች በእመቤታችን በከበረች ድንግል ማርያም ስም የከበረች ናት።

ይህም አባ ጌዴዎን ትምህርትን ሊአስተምረው በጀመረ ጊዜ መቀበልም ማጥናትም እስከ ብዙ ዘመን ተሳነው። በአንዲት ዕለትም መምህሩ በእርሱ ላይ ተበሳጭቶ መትቶ አሳመመው። ያሬድም ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ ከኀዘኑም ብዛት የተነሣ ከዛፍ ሥር ተጠለለ። ወደ ዛፉ ላይም ትል ሲወጣ አየ ትሉም ከዛፉ እኩሌታ ደርሶ ይወድቅ ነበረ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ከአደረገ በኋላ በጭንቅ ከዛፉ ላይ ወጣ።

ቅዱስ ያሬድም የትሉን ትጋት በአየ ጊዜ ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ተመልሶ አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝና እንደ ወደድክ አድርገኝ አለው መምህሩም ተቀበለው።

ከዚህ በኋላ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ሆኖለት በአጭር ጊዜ የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን ተምሮ ፈጸመ ዲቁናም ተሾመ።

በዚያም ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ። እግዚአብሔርም መታሰቢያ ሊያቆምለት በወደደ ጊዜ ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን ላከለት እነርሱም በሰው አንደበት ተናግረውት ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ከእሳቸው ጋራ አወጡት በዚያም ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የሚያመሰግኑበትን ማኅሌታቸውን ተማረ።

ወደ አነዋወሩ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ በአክሱም ዳር ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን በሦስት ሰዓት ገባ በታላቅም ቃል ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ የጽዮንም ደገኛዋ ሰማይን ፈጠረ። ዳግመኛም እንዴት እንደሚሠራት የድንኳንን አሠራር ለሙሴ አሳየው አስተማረው አለ።

ይቺንም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራት። የቃሉንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ንጉሡም ንግሥቲቱም ጳጳሱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ የመንግሥት ታላቆችና ሕዝቡ ሁሉ ወደርሱ ሮጡ ሲሰሙትም ዋሉ።

ከዚያም በኋላ ከዓመት እስከ ዓመት በየክፈለ ዘመኑ በክረምትና በበጋ በመጸውና በጸደይ በአጽዋማትና በበዓላት በሰንበታትም እንዲሁም በመላእክት በዓል በነቢያትና በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልም በዓል የሚሆን አድርጎ በሦስቱ ዜማው ሠራ ይኸውም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ነው።

የሰው ንግግር የአዕዋፍ የእንስሳትና የአራዊት ጩኸት ከዚህ ከሦስቱ ዜማው አይወጣም።
በአንዲት ዕለትም ቅዱስ ያሬድ ከንጉሥ ገብረ መስቀል እግር በታች ቁሞ ሲዘምር ንጉሡም የያሬድን ድምፅ እያዳመጠ ልቡ ተመሥጦ የብረት ዘንጉን በያሬድ እግር ላይ ተከለው ከእርሱም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ያሬድም ማኅሌቱን እስከ ሚፈጽም አልተሰማውም።

ንጉሡም አይቶ ደነገጠ በትሩንም ከእግሩ ላይ ነቀለ ስለ ፈሰሰው የደምህ ዋጋ የፈለግኸውን ለምነኝ ብሎ ለያሬድ ተናገረው ያሬድም ላትከለክለኝ ማልልኝ አለው። ንጉሥም በማለለት ጊዜ ወደገዳም ሔጄ እመነኲስ ዘንድ አሰናብተኝ አለው ንጉሡም ሰምቶ ከመኳንንቱ ጋራ እጅግ አዘነ ተከዘም እንዳይከለክለውም መሐላውን ፈራ እያዘነም አሰናበተው።

ከዚህ በኋላም ቅዱስ ያሬድ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ፈጽሞ የከበረሽና የተመሰገንሽ ከፍ ከፍም ያልሽ የብርሃን መውጫ የሕይወት ማዕረግ የሆንሽ የሚለውን ምስጋና እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ከፍ አለ።

ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሒዶ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያ ፈጸመ። እግዚአብሔር ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጥቶታል።

የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች
፩. ድጓ
፪. ጾመ ድጓ
፫. ዝማሬ
፬. መዋሥዕት
፭. ምዕራፍ  ናቸው።

የዜማ ዓይነቶች
፩. ግዕዝ
፪. ዕዝል
፫. አራራይ ናቸው።

የቅዱስ ያሬድ ረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

  ለ. ከእናታችን ከሣራ በኋላ ዘግይታ የተነሣችው የያዕቆብ ሚስት ራሔል ደግሞ «ልማደ አንስት»ን በሌላ ስፍራ በ«ሴቶች የሚደረስ ግዳጅ» ብላ ስትጠራው እናነባለን። ዘፍ 31፡35 ከዚህም በመነሣት መንፈሳዊያን መጻሕፍት ‹‹ከወር አበባ ነፅታ ነበር›› ለማለት «ከግዳጅዋ ጠርታ ነበር» ይላሉ:: በዚህ ዘመን የሴቶች ግዳጅ በብዙኃን ዘንድ ተለይቶ የሚታወቀው «የወር አበባ» በመባል ነው::
  ሐ. የወር አበባ የ«ወር» የተባለበት ምክንያት በየወሩ የሚታይ ስለ ሆነ በመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገውም:: «አበባ›› የተባለበት ምክንያት ግን ሴቶች ልጆች ራሳቸው በዕፅ፣ በየወሩ የሚያዩት ደም በአበባው፣ የሚወልዷቸው ልጆች ደግሞ በፍሬው ስለሚመሰሉ ነው፡፡
    መጽሐፈ ሥነ ፍጥረት ከመጽሐፈ ምሥጢር ጠቅሶ ከላይ ለተብራራው ሐሳብ የሚሆን መረጃ እንዲህ ሲል ይሰጣል:- «እስመ ዕፅ ይቀድሞ ለጽጌ ወይተልዎ ፍሬ ወለአንስትኒ ይቀድሞን ጽጌ ደመ ትክቶ ወይተልዎን ፍሬ ውሉድ» ይህም «ለአንድ ተክል አበባው ቀድሞ ፍሬው እንደሚከተል ለሴቶች ልጆችም በመጀመሪያ የወር አበባ ቀድሞ ይታያቸውና በኋላ ልጅ ለመውለድ ይበቃሉ» ማለት ነው፡፡ በመጨረሻም «ወለዕፅሰ እምከመ ተነግፈ ጽጌሁ ወየብሰ ቆጽሉ ኢይትረከብ ፍሬ ላዕሌሁ ወለአንስትኒ እምከመ በጠለ ደመ ትክቶሆን በርስዓን ኢይረክባ ውሉደ እስመ ኀለፈ መዋዕሊሆን› ይላል፡፡ ይህም ወደ አማርኛ ሲተረጎም «አንድ ተክል አበባው ከረገፈና ቅጠሉ ከደረቀ በኋላ ፍሬ እንደማያስገኝ ሴቶች ልጆችም በእርጅና ምክንያት ደም ከቆረጡ ወይም ካረጡ በኋላ መውለጃ ጊዜያቸው አልፏልና ልጅ ለማግኘት አይችሉም» ይላል:: ይህ ለምን እንደሚሆን የመጽሐፈ ምሥጢር ጸሐፊ ምክንያቱን ሲያስረዳ «እስመ ጽጌ ውእቱ ደመ ትክቶሆን» በማለት ይደመድማል:: ይህም «ሴቶች በየወሩ የሚያዩት ደም አበባ ነውና» ማለት ነው፡፡ ከዚህም ሴቶች በየወሩ የሚያዩት ደም «የወር አበባ›› መባሉን ብቻ ሳይሆን ለምን የወር አበባ እንደተባለም ጭምር እንረዳለን:: (መጽሐፈ ሥነ ፈጥረት ዘዓርብ)
  መ. እውነኛ ጻድቅ የሚባለው ሰው ምን ዓይነት ምግባር ያለው ሰው እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሲመሰክር እንዲህ ይላል:- «አደፍም መዳለባት ሴት ባይቀርብ... እርሱ ጻድቅ ነው ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል፡፡ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ... ብሏል::» ሕዝ 18፡7-9 በዚህ ዐረፍተ ነገር ውስጥ አደፍ የተባለው የወር አበባ ነው፡፡ ይህንኑ ቃል በግዕዙ ብንመለከት ‹‹ደመ ትክቶ» ሲለው እናነባለን፡፡
  ሠ. የወር አበባ «ደመ ፅጌ» ይባላል፡፡ «ደመ ፅጌ» ማለት «የአበባ ደም» ማለት ነው፡፡ ይህም ያበቡ ወይም በአበባነት ዘመን ያሉ : ሴቶች የሚያስገኙት ደም እንደ ማለት ነው፡፡ መምህራነ ቤተ ክርስቲያን የወር አበባን «ደም» የሚሉበት ምክንያት የወንድ ዘር ካላገኘ ከማኅፀን ግድግዳ ፍራሽ ጋር በደም መልክ ስለሚፈስና የኋለኛው ማንነቱ ደምነት ስለሆነ ነው:: ይህ የማኅፀን ግድግዳ ፍራሽ በሥነ ሕይወት ትምህርት ከኦቫሪ (ከዘር ከረጢት) በየወሩ ከሚለቀቅ የወንድ ዘር ካላገኘ ኦቫ (ሴቴ ዘር) ወይም እንቁላል ጋር በየወሩ በደም መልክ እንደሚፈስ ይታወቃል፡፡
   የወር አበባ መታየት ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ ሴቶች እስከሚያርጡበት ጊዜ ድረስ በየወሩ ይመጣል፡፡ ይህ ልማደ አንስት በእርግዝና ወቅት ይቋረጥና ልጅ ከተወለደ(ች) በኋላ ጤናማ ሂደቱን ይቀጥላል::
   ይህ ወርኃዊ ዑደት የሚጀምርበት፣ የሚቋረጥበት ዕድሜና መታየት ከጀመረበት እስከሚቋረጥበት ድረስ የሚወስደው ጊዜ ከሰው ወደሰው ይለያያል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጉዳይ መተከዝ በከንቱ መጨነቅ ነው:: የወር አበባ ሴት ልጅ ፈጣሪ ለመደበላት ዕጥፍ የሕይወት ሚና ማለትም ሚስትና እናት ለመሆን መድረሷን የሚያመለክት በመሆኑ ሳትከፋ በጸጋ ልትቀበለው ይገባታል፡፡
   ብዙ ሴቶች የወር አበባን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያዮ መደንገጥ፣ መፍራትና መጨነቅ ይታይባቸዋል:: ሆኖም ጤናማ የሆነ የዕድገት እመርታ በመሆኑ ንጽሕናን ለመጠበቅ የሚያስችል ጥንቃቄ የሚያስፈልግ ቢሆንም የሚያሳፍርና እንደ ልዩ ነገር የሚታይ አለመሆኑን ማወቅ ይገባቸዋል::
      እናቶች ለልጆቻቸው ስለ ወር አበባ አስቀድመው በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ይጠበቅባቸዋል:: ይህን የሕይወት ጎዳና ያለፉበት በመሆኑ እናቶች ይመረጡ እንጂ አባቶችም ይህን በመሰለ ነገር ላይ ራሳቸውን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ካደረጉ ልጆቻቸውን ከመደንገጥ፣ ከመረበሽና ከመሳሰሉት ነገሮች ሊያድኗቸው ይችላሉ፡፡
   ልጆችም ይህን በመሰለ ጉዳይ ላይ ከማንኛውም ሰው ይልቅ ወላጆች እንደሚረዷቸው ዐውቀው በግልፅ ወላጆቻቸውን ማማከር ይኖርባቸዋል፡፡ ራሔል «በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛል» በማለት ለአባቷ ለላባ ስትነግረው ምንም እንዳላስፈራትና እንዳላሳፈራት ሁሉ ልጆችም ስለ ጉዳዩ በቂ ግንዛቤ ባይኖራቸው እንኳን «ይህ ነገር ምንድር ነው?›› በማለት ስለ ወር አበባ ወላጆቻቸውን ሳይፈሩ በግልጽ ቢያማክሩ መልካም ነው፡፡ ዘፍ 31፥35
   ወጣት ሴቶች የወር አበባን በተመለከተ የሚሰጡትን መንፈሳዊ ትምህርቶች መከታተል፣ አበው መምህራንን መጠየቅና ከዚህ ጋር ተያይዘው የተሠሩትን የቤተክርስቲያን ሥርዓቶችን በሚገባ ማወቅ ይኖርባቸዋል:: በተጨማሪ የወር አበባን በተመለከተ ምርቱን ከግርድ እየለየ ለተመለከታቸው የሥነ ሕይወትና የሥነ ተዋልዶ መጻሕፍት መጠነኛ ጠቀሜታ አላቸው::
    እመቤታችን ድንግል ማርያም በስእለት ተሰጥታ በቤተ መቅደስ እየኖረች ሳለ ለዐቅመ ሔዋን ስትደርስ አይሁድ እንደ ለሌሎች ሴቶች አይተዋት ቤተመቅደሳችንን በልማደ አንስት ታሳድፍብናለች ብለው አስወጥተዋታል:: ይሁን እንጂ ከእናቷ ማኅፀን ጀምራ በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀች እመቤታችን ግን በዚህ ዓለም ለ64 ዓመታት ስትኖር ልማደ አንስት አላገኛትም:: ከእርሷ በቀር ግን ልማደ አንስት ሳያገኛት ዓቅመ ሔዋንን የምታልፍ ጤናማ ሴት የለችም፤ አትኖርምም፡፡

              የወር አበባ መቼት
  «መቼት» ማለት መቼና የት ማለት ነው፡፡ የወር አበባ መቼት አለው:: መቼቱ አዳምና ሔዋን በኃጢአት ከወደቁ በኋላ ከገነት ውጭ ነው፡፡ አዳምና ሔዋን በገነት በነበሩበት ጊዜ ምንም እንኳን በሔዋን ባሕርይ ደመ ጽጌ የነበረ ቢሆንም ደሟ በኣፍአ አታይም ነበር።
ዕፀ በለስን በልተው አዳምና ሔዋን ፈጣሪያቸውን በበደሉ ጊዜ ግን ሔዋን ደመ ዕፅ በለስን አፍስሳለችና «ወበከመ አድመውኪያ ለእንትኩ ዕፅ ከማሁ ድምዊ ለለወርኁ› በማለት ደሟ በየወሩ እንዲፈስ ፈጣሪ ፈረደባት፡፡ ስለዚህ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሔዋን ከገነት ውጭ ሆና ስትኖር ደሟ በየወሩ ይፈስ ጀመር፡፡
   

እንደሚታወቀው ዝናብ መዝነብ የጀመረው በምድር ላይ ኃጢአት እየበዛ መጥቶ እግዚአብሔር ዓለምን በጥፋት ውኃ እንድትጠፋ ካደረገ በኋላ ነው:: ከዚያ አስቀድሞ ውስጥ ለውስጥ በሚሄድ ጉም ምድር ትረሰርስ ነበር እንጂ ዝናብ አይዘንብም ነበር፡፡ ከጥፋት ውኃ በኋላ ግን ጌታ እግዚአብሔር ክረምትና በጋን ለማፈራረቅ ለኖህ በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት ዝናብ መዝነብ ጀመረ። ዘፍ 8 ፥22

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

አንዳንድ ጊዜ ይህ የሴቶች የዕድገት እመርታ ከሕዋሳት በአንዱ ላይ ፈጣን ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት እጆች ወይም እግሮች ከሌሎች የአካል ክፍሎች ጋር ሲነፃፀሩ ይበልጥ የረዘሙ መስለው ይታዩ ይሆናል:: ይሁን እንጂ ሁሉም ሕዋሳት ጊዜ ጠብቀው ተመጣጣኝ መሆናቸው አይቀርም፡፡
    በዚህ የልጃገረዶች የሽግግር ዘመን በብብትና በብሽሽት (ኀፍረተ አካል) አካባቢ ከሚታየው የጸጉር መበቀል ጋር ዳሌዎች ይሰፋሉ፡፡ ልጃገረዶች የሚኖራቸው ሰፋ ያለ ዳሌ ወሊድን ብቻ ሳይሆን ከወለዱ በኋላ ሕፃናቸውን ለማዘልና ለማቀፍ ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል፡፡
    መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ ትንሽ ሴት ልጅን ለመጥቀስ «እኛ ጡት የሌላት ታናሽ እኅት አለችን» ይላል መኀ 8:8 በዚህ መሠረት ልዩ ክሥተት ካልሆነ በቀር ጡት ጨርሶ አለመኖሩ ወይም እድገቱን ያልጨረሰ «ትንሽ› መሆኑ የልጅነት ምልክት ሲሆን ጡት ማጐጥጐጥ ደግሞ ለዐቅመ ሔዋን የመድረስ ጉልህ ምልክት ነው፡፡
    አንዲት ኮረዳ የሚኖሩአት ሁለት ጡቶች ልጅ በምትወልድበት ጊዜ ለሕፃኑ ምግብ የሚሆነውን ወተት ማመንጨት ይጀምራሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ «ጡትዋ ሁልጊዜ ታርካህ፣ በፍቅርዋም ሁልጊዜ ጥገብ›› ምሳ5 ፥ 19 እንደተባለው እውነተኛ ባሏን ደስታ እንድታጠግብበት እግዚአብሔር የሰጣት ብርቅ ሕዋስ ነው፡፡ ባልዋ የሚደሰተው ጡቶቿን በመሳም፣ በመነካካትና በመደባበስ (በገሢሥ) መሆኑ ግልፅ ነው:: ምንም ቃሉ የተጠቀሰው በሕገ ወጥ መንገድለኖሩ ሰዎች ቢሆንም ድርጊቱ በሕጋዊ መንገድ በሚኖሩ በባልና በሚስት መካክል የሚከናወን የወንድና የሴት ተግባር በመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ገልጾታል:- «የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር›› ሕዝ 23፡8፤ 23፥3 ይህ ሁሉ ሲሆን ደግሞ እርስዋም ከባልዋ ጋር አብራ ደስ እንደሚላት የታወቀ ነው፡፡
   ወደ ዐቅመ ሔዋን እየደረሱ ያሉ ሴቶች ጡቶቻቸውን በተመለከተ ያልተዛባ አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ አንዳንድ ወጣት ሴቶች ከባልንጀሮቻቸው ጡቶች ጋር የራሳቸውን ጡቶች ሲያስተያዩ የነሱ እጅግ ያነስ ወይም የተለቀ ይመስላቸዋል:: በዚህ ምክንያት መጠኑን የቀነሱ እየመሰላቸው ነፍሳቸው እስክትወጣ ድረስ በጡት መያዣ ሲወጠሩ፣ሌሎች ደግሞ ጡቶቻቸው ያነሱ ሲመስላቸው የገንዘብ ዐቅም ባይኖራቸው እንኳን ምናምን እየወታተፉ እነርሱ ልከኛ ያሉትን ጡት ለማስመሰል ሲደክሙ ይታያሉ፡፡ የጡታቸውን ቅርፅና መጠን ለማስተካክል ቀዶ ጥገና እስከ ማድረግ የደረሱና ለማድረግም ምቹ ጊዜን የሚጠባበቁ ብዙ ቆነጃጅት በዙሪያችን ይገኛሉ፡፡
    አበው ሠለስቱ ሞዕት በሃይማኖተ አበው «ወኢትትመየጥ ኀበ ካልዕ አርአያ እሰመ ዘዚአከ የአክለከ» ማለትም «ሌላ መልክ አትሻ (መነቀስ፣ መጠቆር፣ መታገም) በተፈጥሮ ያገኘኸው ይበቃሃል» በማለት የተናገሩትን ቃለ ምዕዳን ወደ ጐን በመተው የዘመኑ ወጣት ሴቶች ጡቴ ተለቀ! ወደቀ! አነሰ! በማለት መጨነቃቸው እጅግ የሚያሳዝን ነው:: ጡት ምንም ቢመስል ምንም ቢያህል የተፈጠረበትን ዓላማ አያጓድልም:: በዚህ ጉዳይ መጨነቅ ራስን መበደል ነው::
    በተጨማሪም ጡት በቀላሉ ሊጐዳ የሚችል ሕዋስ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ:: ስለዚህ ከመጨነቃችን የተነሣ የማናውቃቸውን ነገሮች እንደመሰለን መጠቀም ጉዳት ላይ ሊጥለን ይችላል፡፡ ይህን በመሰለ ሙከራቸው ለጡት ካንሰርና ለመሳሰሉ ልዩ ልዩ ደዌያት የተጋለጡ በርካታ ሴቶች መኖራቸውንም መዘንጋት የለብንም:: ከሰውነት ቅርፅ ጤናማነት ይበልጣል፡ መጨነቅ የሚገባው ከቅርፅና ከውበት ይልቅ ለጤንነትና ለመልካም አስተሳሰብ ነው፡፡
    ሴቶች በሚወልዱበት ጊዜ ልጆቻቸውን እያጠቡ የማሳደግ ኃላፊነት አለባቸው:: እንደ «ጡቴ ይወድቃል» እና የመሳሰሉትን ርካሽ ምክንያቶች በማቅረብ ሕፃናትን ከማጥባት መቦዘን አይገባም፡፡ ለሕፃናት የእናት ጡት ወተትን የሚተካ ምንም ዓይነት ምግብ እንደሌለ ሰው ሁሉ የሚፈርደው ነው:: አበውም በፍትሐ ነገሥት ‹‹ወአትሀብ ውሉዳ ለሐፃንያን» ማለትም «ልጆቿን ለሞግዚቶች አትስጥ» ይሉና ምክንያቱን ሲገልፁ:- አንደኛ መከራን መሰቀቅ ነው፡፡ ሁለተኛ ዝሙትን መውድድ ሲሆን ሦስተኛ ደግሞ እግዚአብሔር የሰጠውን ምግብ መከልከል ስለ ሆነ ግፍ ነው ይላሉ፡፡ ስለዚህ ጡት የተፈጠረበት ዋነኛ ዓላማው ልጆችን ለማሳደግ ምግብ ለመስጠት ነው እንጂ ጌጥና ውበት እንዲሆን አይደለም፡፡ ለጡት ልጆችን ከማሳደግ በላይ ምን ሥራ፥ ሊመጣለት ይችላል? ውበት ሥራ እንጂ መልክ መሆን የለበትም:: ስለዚህ የጡት ውበቱ ልጆችን ማሳደጉ ነው!
   ሌላው ሴቶች ለዐቅመ ሔዋን መድረሳቸውን የሚያበስር ዋነኛ ምልክት የወር አበባ መታየት መጀመሩ ነው:: ስለ ወር አበባ አሰያየም፣ ምንነትና ተያያዥ ሥርዓቶች ከዚህ በታች ራሱን ችሎ በተብራራ መልኩ ተጽፏል::

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም:
ተነስቷል በዚህ የለም(2):
መድኃኔዓለም
ሞት የማይችለው የበረታ:
ኃያል ነው ማይረታ ማኅተሙን የፈታ:
የትንሳኤው ጌታ።
*አዝ*
ገዳዩ ሞት በእርሱ ድል መንሳት ተዋጠና:
ሰንሰለቴን ቀንበሬን ተካው በበገና:
ሞት ሆይ መውጊያህ የታል እያልን ምንዘምረው:
መስቀልህ ጦር ስምህ ጋሻችን ሆኖልን ነው :
ዳንን የምንልው።
*አዝ*
ተሻግረናል ስላሻገርከን ለዘለዓለም:
በመቃብር ሞት ይይዝህ ዘንድ ከቶ አልቻለም:
ኃይለኛውን በኃይል አስረኸው ላይፈታ:
ዘመርንልህ አሸናፊ ነህ የእኛ ጌታ:
ከፍ በል በእልልታ።
*አዝ*
ሞቶ ማዳን ለማን ተችሏል ካንተ በቀር:
ጌትነትህ ሥራህ ይኖራል ሲመሰከር:
ወዳጄ ሆይ ውበትህ ውብ ነው የሚያበራ:
ተጨነቀ ተንቀጠቀጠ ጠላት ፈራ:
ዕፁብ ያንተ ሥራ።
*አዝ*
መስክሩለት የምስራች ነው ታላቅ ዜና:
መላዕክቱ ነጭ ለብሰዋል ድል ነውና:
ከተማዋ አንዳች ሆናለች በለሊቱ:
በዝማሬ ተንቀጠቀጠ ወኅኒ ቤቱ:
ከበሮውን ምቱ።

በዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
እሁድ
ዳግማይ ትንሣኤ

ዳግማይ ትንሣኤ ማለት ጌታችን በተደጋጋሚ ለሐዋርያቱ እና ለተለያዩ ሰዎች በተለያየ ሥፍራ መገለጡን የምናስብበት ሳምንት ነው፡፡
ቤተክርስቲያን ከትንሣኤው እስከ ዳግማይ ትንሣኤው ያለውን ሳምንት እንደ አንድ ቀን ነው የምታየው ክብር ይግባውና የትንሣኤው ጌታ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው ዕለት ጀምሮ ከመግደላዊት በመጀመር ለልዩ ልዩ ሰዎች ተገልጧል፡፡
፩. ለመግደላዊት ማርያም ተገልጧል፡፡(ዮሐ፳፡፲፩)
፪. ለሴቶች ተገልጧል፡፡(ማቴ፳፰፡፱)
፫. ለሐዋርያው ጴጥሮስ ተገልጧል፡፡(ሉቃ፳፬፡፴፬)
፬. ለኤማውስ መንገደኞች ተገልጧል፡፡(ሉቃ፳፬፡፲፫)
፭. ከሐዋርያው ቶማስ በቀር ለሐዋርያት ተገልጧል፡፡(ዮሐ፳፡፲፱)
፮. ሐዋርያው ቶማስ ባለበት ለደቀ መዛሙርቱ በዝግ ቤት ተገልጧል፡፡(ዮሐ፳፡ ፳፮)
፯. በጥብርያዶስ ለሰባቱ ሐዋርያት ( ጴጥሮስ ቶማስ ናትናኤል ሉቃስ ኒቆዲሞስ ይሁዳ ያዕቆብ ) ተገልጧል፡፡
፰. ለአምስት መቶ ሰዎች ተገልጧል፡፡(፩ቆሮ፲፭፡፮)
፱. ለሐዋርያው ያዕቆብ ተገልጧል፡፡(፩ቆሮ፲፭፡፯)
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተገለጠባቸው በእያንዳንዱ መገለጦች ውስጥ ለሐዋርያቱ ሦስት አደራዎችን ሰጥቷቸዋል፡፡ እነዚህም :-
በመጀመሪያው የትንሣኤ ዕለት የኃጢአት ስርየት የማድረግን ሥልጣን ሰጥቷቸዋል(ዮሐ፳፡፳፫)
በሁለተኛው ደግሞ የማስተማር ጸጋ ሰጥቷቸዋል(ማቴ፳፰፡፲፮-፳)
በሦስተኛው ሕጻናትን ፤ ወጣትን እና ሽማግሌዎችን የመጠበቅና የመምራት ኃላፊነት ሰጥቷቸዋል፡፡(ዮሐ፳፩፡፲፭-፲፰)
በዚህም ሐዋርያዊት ወይም የሐዋርያትን ፍኖት የተከተለች በሐዋርያት በኩል ይህንን ሁሉ ጸጋ ያገኘች ቅድስት ፣ አንዲት ፣ ኩላዊት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ሁሉንም አደራ እና መመሪያ ተግባራዊ እያደረገች ትገኛለች፡፡
ሐዋርያዊት የሆነች ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በዚህ ዕለት ልክ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ጋር በነበሩበት ዘመን ይሰማቸው የነበረውን ደስታ በማሰብ ሥርዓተ አምልኮቷን ትፈጽማለች፡፡
በግጻዌው መሰረት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናትም ሆነ ገዳማት የሚዘመረው
መዝሙር "ይትፌሳህ ሰማይ ወትትሐሰይ ምድር" ትርጉም "ሰማይ ይደሰታል ምድርም ሐሴት ታደርጋለች" የሚለው ሲሆን ምስባኩ ደግሞ "ይትነሣእ እግዚአብሔር ወይዘረው ጸሩ ወይጎይዩ ጸላእቱ እምቅድመ ገጽ ከመ የሀልቅ ጢስ ከማሁ የሀልቁ" ትርጉም እግዚአብሔር ይነሳ ጠላቶቹ ይበተኑ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ ጢስ እንደሚበን እንዲሁ ይብነኑ" (መዝ፷፯(፷፰)፩-፪)
ቅዳሴው የዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ሲሆን ወንጌሉ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ሃያ ከቁጥር አሥራ ዘጠኝ እስከ ፍጻሜ ነው፡፡ በዚህ ወንጌል ላይ ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ ያላቸውን ሐዋርያት እናገኛለን፡፡ "ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው፡፡" (ዮሐ፳፡፳)
ያም ቀን ዕለተ እሑድ ማታ ላይ ነበር፤ የጨለማው መጨለም ፤ የአይሁድ ዛቻና ማስፈራራት ሐዋርያትን እጅጉን አስጨንቋቸዋል ከአሁን አሁን ገደሉን ፤ በቃ ጠፋን፤ይህን እና ይህን ብቻ እያሰቡ በራቸውን እንዳይከፍቱት በጠንካራ ቁልፍ ቆልፈው የጭንቀታቸው መጠን እየጨመረ እየጨመረ... ባለበት በዚህ ጊዜ ምንም እንኳን ከመከራው እና ከጭንቀቱ ብዛት በሩን ዘግተው ሞታቸውን ቢጠባበቁም በሞት ላይ ስልጣን ያለው ተስፋን መቀጠል የሚችል አምላክ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ብሎ መካከላቸው ሲቆም ከመቅጽበት ጌታን ባዩ ጊዜ በሐዘን የጨፈገገው ፊታቸው በደስታ በራ፡፡ ክብር ለአምላካችን ይሁን፡፡ የእኛንም የተዘጋ ቤታችንን ከፍቶ ገብቶ በሐዘን እና በጭንቀት የጨፈገገው ፊታችንን በደስታ አብርቶ ሰላማችንን ይመልስልን፡፡ አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…
Subscribe to a channel