በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
ሰውም ይህን ፍቅሩን የሚቀበልበትና ለዚህ ፍቅር የሚገዛበት መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን አንድነት ጠብቆ መኖር ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በጠላት የተከናወነው ጥቃት በዚህ አንፃር የተቀናበረ ስለነበር ሰው ከእግዚአብሔር ፍቅር እንዲወጣ ትዕዛዙን እንዲያፈርስ ከአምላኩ አንድነት እንዲለይ ተደረገ "ብትወዱኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ" /ዮሐ 14÷15 / ማለት ሰው በጠላት ምክር ተነዳ ከእግዚአብሔር ፍቅር ወጥቶ ሕጉን በመተላለፍ ከእግዚአብሔር አንድነት ተለይቶ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ በመቃብር መውርድ ሲኦል መውረድ አገኘው ባሕርይው አደፈ ሥነ ተፈጥሮው ጎሰቆለ በጠላት መዳፍ ላይ ለዘላለም በባርነት ወደቀ፡፡
እግዚአብሔር ግን ከኔ ካልጎደለ በገዛ እጁ ባመጣው ሳይል ሰውን ከፈጠረበት ጽኑ ፍቅሩ ተነስቶ የሰውን ልጅ ሊፈልገው ወደደ፡፡ እግዚአብሔር ቃል ሰው ሆነ ጸጋና እውነትን ተሞልቶ በእኛ አደረ ይህ ማለት እግዚአብሔር ሰውን አልተወውም ሊፈልገው መጣ ይህ ፍቅር ደግሞ ልዩ ነው ስለሆነም እግዚአብሔር ሰውን ከፈጠረበት ሰውን ያዳነበት ምስጢር ይበልጣል ይደንቃል ተባለ ይህ ፍቅር ከሰማይ እንዲወርድ አድርጎታል፣ ይህ ፍቅር ሰው እንዲሆን አድርጎታል፣ ይህ ፍቅር በአደባባይ እንዲከሰስ ያለበደሉ እንዲገረፍ ያለ ኃጢአቱ እንዲሰቀል ስለ ሰው እንዲሞት አድርጎታል፡፡ በዚህ ቤዛነቱ ሞታችንን በሞቱ ሽሮ በመነሳት ለእኛ ሕይወትና ትንሳኤ ሆኖናል፡፡
ከዚህ በኋላ ለሰው ልጅ በክርስቶስ ከሆነው ብዙ ጸጋ አንዱ ደግሞ ከበደል እንደገና መመለስ ከኃጢአት በመናዘዝ መንጻት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰው ከበደሉ በንስሐ ወደርሱ እንዲመለስ እድል መስጠቱ ንስሐ እግዚአብሔር በሰው ልጅ ላይ ያለውን የማያባራ ፍቅር ማረጋገጫ ሆኖ የተሰጠ ጸጋ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ እስከ ዓለም ማለፍ ቤተክርስቲያን መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለች እግዚአብሔር ለእርሷና ለአማኞች የሰጠውን ጸጋ ስታውጅ ትኖራለች፡፡
፨መግቢያ
በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአእምሮ ሕሙማን ሲኖሩ እነዚህን ሕሙማን ለማከምና ለማዳን የሚሰሩ ባለሙያዎች የሥነ አእምሮ ባለሙያዎች ይባላሉ፡፡ እነዚህ ባለሙያዎች ቁጥራቸው ጥቂት አይደለም በየዕለቱም ብዙ የአእምሮ እረፍትና ሰላም የሌላቸው ሰዎች ችግሮቻቸውን ሲናዘዙላቸውና እነርሱም በአጠፌታው ምክራቸውን ሲለግሷቸው ይውላሉ፡፡
አስገራሚው ነገር እነዚህ የሥነ አእምሮ ባለሙያዎች ባልተነሱበት ጊዜ ከአስራ ስምንተኛው ከፍለ ዘመን አስቀድሞ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ይህን መንገድ ስትሰራበት አማኞቿን ስታገለግልበት ቆይታለች፡፡
ለመሆኑ ሰዎች በውስጣቸው አንድ ነገር አፍነው ሲይዙና አፍነው በያዙት ሰላም የሚነሳ ጉዳይ ሲጎዱ ሁለንተናቸው እንዴት ይዘበራረቃል? የሚለውን ስንመለከት በሥጋ በነፍስ የኑዛዜ አስፈላጊነትን በሚገባ እንገነዘባለን፡፡
ኑዛዜ በቃል ብቻ የሚነገር እና ጥቅሙን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ሂደቱን የአፈፃፀም ደረጃውን መገንዘብ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ኑዛዜ ቀጣዩን አኗኗራችንን የመቀየር ቁርጠኝነትን የምናረጋግጥበት የትላንቱን ያደፈ ሕይወት ያስጠላን ቀሪ ሕይወታችንን ለአምላካችን አስረከቦ ለመኖር የሚያስችል ሰላማዊ ሕይወትን የሚያጎናጽፍ መንፈሳዊ ኃይል ነው፡፡
ይህ ደግሞ በትክክለኛ ጸጸት ያለፍንበትንና ያለንበትን ስህተት ከማመን ኃጢአትን በኃጢአትነቱ ተመልከቶ ከመጥላት የሚገኝ ነው፡፡ ስለዚህ ኑዛዜ የነፍስና ሥጋ ድህነት ዋስትና ሲሆን በቀጣዩ ዘላለማዊ ሕይወታችን ላይ ወሳኝ ስለሆነ ቀጠሮ የማይሰጠውና በሕይወተ ሥጋ ሳለን ሳናመነታ ልንፈጽመው የሚገባ የቀሪ ሕይወታችን እረፍትና ሰላም መጎናፀፊያ መንገድ ነው፡፡
“ወደ እኔ ኑ" /ማቴ 11÷28/ ሲል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊታችን ወዳቀረበው የዘላላም ተስፋና ሕይወት ከሚያደርሱን መንገዶች በአንዱና በዋነኛው የሕይወት መንገድ ከርሱ ጋር መመላለስ እንችላለን ማለት ነው፡፡ ይህን መረዳታችን ደግሞ ለኑዛዜ እንድንቀርብ የሚያበረታን ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የንስሐ ሕይወታችንንም ጽኑ ያደርግልናል፡፡
ቀጣይ ምዕራፍ አንድ ክፍል አንድ :
👉 "የኑዛዜ ምንነት" በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
“ኃይሌ ብርታቴ”
በዘማሪ ታዴዎስ ግርማ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሐምሌ ፯
ቅድስት ሥላሴ
ሐምሌ ሰባት በዚህች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡
አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡
ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡
እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሐምሌ ፭
ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ
1. ትውልዳቸው
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ፡-በገሊላ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው በቤተሳይዳ ተወለደ፡፡ የአባቱ ስም ዮና የእናቱ ስም ሃውኒን ይባላል፡፡ ከ 5 ዓመቱ ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ነው የመጀመሪያው ስሙ ስምዖን ሲሆን ይህንንም እናቱ በነገዷ ስም እንዳወጣችለት ይነገራል፡፡ ጴርቴዋ የምትባል ሚስት ነበረችው፡፡ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር ዓሣ በማጥመድ ይተዳደር ነበር፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፡- ከብንያም ነገድ ነው፡፡ አባቱ ዮስአል ሲሆን የተወለደውም ጌታ በተወለደ በ5 ዓመት በጠርሴስ ከተማ ነው፡፡ ጠርሴስ በንግድዋ የታወቀች የኬልቅያ ዋና ከተማ ናት፡፡ ሮማውያን በሥራቸው ለሚተዳደሩት ሕዝቦች ሮማዊ ዜግነት ይሰጡ ስለነበር የቅዱስ ጳውሎስ አባት በዜግነት ሮማዊ ነበር፡፡ ይህም ለቅዱስ ጳውሎስ ተላልፎለታል፡፡ ቀዳሚ ስሙ ሳውል ሲሆን ትርጓሜውም ጸጋ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በ15 ዓመት ዕድሜው ወደ ትውልድ ሐገሩ በመመለስ በኢየሩሳሌም ከታላቅ እኅቱ ቤት ተቀምጦ ከመምህር ገማልያል ሕገ ኦሪትን መጻሕፍተ ነቢያትን ሲማር አድጓል፡፡ በ3ዐ ዓመቱም የአይሁድን ሸንጐ አባል ሆኖ ተቆጠረ፡፡ ሐዋ22÷3
2. አጠራራቸው እና ሕይወታቸው
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ
በጐልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ ማሥገር ጀመረ፡፡ ለደቀመዛሙርትነት ሲመረጥ እድሜው 55 ዓመት ሲሆን ወደጌታችን ያመጣውም ወንድሙ እንድርያስ ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረውን መረቡን ታንኩዋውን እንዲህም አባቱን ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው፡፡ በቂሳርያ ከተማ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቀ ጊዜ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ ለአይሁድ ሊቃውንት የተሰወረ ምሥጢረ ተዋሕዶ ገልጦ በመመስከሩ ጌታችን አንተ ጴጥሮስ ነህ ብሎታል ትርጓሜውም «ዐለት» ማለት ነው በአረማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ይወድ ነበር፡፡ ፍቅሩ ግን ቅንዓት የተቀላቀለ በመሆኑ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የሞቱን ነገር ቀድሞ ሲነግራቸው አይሁንብህ በማለት ተከራክሯል፡፡ ማቴ 16፥23 በኋላም ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም ብሎ በራሱ ቅንዓት ተማምኖ ተናግሮ ነበር፡፡ ጌታችን ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ቢለው እንኳን ከአንተ ጋር መሞት እንኳ የሚያስፈልገኝ ቢሆን ከቶ አልክድህም በማለት የተናገረ ሰው ነው፡፡ ማቴ 26፥34
ቅዱስ ጴጥሮስ አስቀድሞ የተናገረውን ቃል ለመጠበቅ ሞክሮ ነበር፡፡ ጌታ የሰው ልጅ አሳልፎ ይሰጣል ብሎ አስተምሯቸው ነበር፡፡ ጌታ ተላልፎ የሚሰጥበት ሌሊት ቅዱስ ጴጥሮስ ጭፍሮችም ጌታን ለመያዝ ሲጠጉ የሊቀ ካህናቱን ባርያ ማልኮስ ጆሮውን በሰይፍ ቆረጠው፡፡ ዮሐ 18፥1ዐ ጌታችን ግን ሞቱ በፍቃዱ ለድኀነተ ዓለም ነውና ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ ሲል ገሠጸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታ በሐናና በቀያፋ በሮማ መኳንንትና ወታደሮች መከራን ሲቀበል በሩቅ ይከተለው ነበር፡፡ ጌታን ወደ ሊቀካህናት ቀያፋ ግቢ ባስገቡትም ጊዜ ተከትሎ ገባ፡፡
ነገር ግን አይሁድ ከሮም ወታደሮች ጋር አብረው በጌታ ላይ ያደርሱት የነበረው መከራ ለሰው ልጅ ህሊና የሚከብድ በመሆኑ እውነተኛ ፍርድ መጥፋቱን የተመለከተው ጴጥሮስ እሳት ወደሚሞቁት ተጠጋ፡፡ በዚያም እያለ የገባውን ቃል አጥፎ 3 ጊዜ አላውቀውም ብሎ ካደ፡፡ ያን ጊዜም ዶሮ ጮኸ፡፡ቅዱስ ጴጥሮስ የሚታወቅበት ሌላው ትልቁ ነገር ንስሐው ነው ጌታው የነገረው መድረሱን ቃል የገባለት አምላኩን መበደሉን እንዳወቀ ከግቢው ወጥቶ አለቀሰ፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ በዕድሜው ታላቅነት በሐዋርያት ዘንድ እንደ አባት ይታይ ስለነuር ጌታ በተለየው ጊዘ? ሐዋርያቱን ሊመግብ ወደሚያውቀው ሙያ ዓሣ ወደማስገሩ ተሠማራ ጌታም አስቀድሞ የመረጠው እርሱ ነውና ቢከዳው እንኳን በንስሐ በመመለሱ ንስሐውን መቀበሉን ዛሬም እንደሚወደው ይገልጽለትም ዘንድ በጥብርያዶስ ባሕር ተገለጠለት፡፡ አሁን ቅዱስ ጴጥሮስ በራስ መተማመኑ እንዳላዋጣው አውቆ ትወደኛለህ ተብሎ ሲጠየቅ አንተ ታውቃለህ ነበረ መልሱ የራሱ እውቀት የት እንዳደረሰው ያውቃልና ጌታችንም ኀዳጌ በቀል /በቀልን የሚተው/ ነውና ዛሬም እንደሚወደው በንሰሐ ተመልሷልና ዛሬም ለእርሱ የሰጠውን ክብር እንደማያጐልበት ሲነግረው ግልገሎቼን አሠማራ ጠቦቶቼን ጠብቅ በጐቼን አሠማራ በማለት አደራውን አስረከበው፡፡ ዮሐ 21፥15-17
ጌታ በዐረገ በ10ኛው ቀን መንፈስቅዱስን ተቀብሎ የሚያውቀው ጸንቶለት የማያውቀው ተገልጾለት በአንድ ቀን ስብከት 3000 ሕዝብ አሳምኗል፡፡ሐዋ2÷41
ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለጸሎት ወደ ምኩራብ ሲገቡ እግሩ ልምሾ ሆኖ የተወለደ አንድ ሰውን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነስ ተመላለስ ብሎ አድኅኖታል፡፡ በኢዮጴ ስምዖን ሰፋዬ አሣዕንን(ቁርበት ፋቂ)፣ ሊቀ ሐራ ቆርነሌዎስን አስተምሯል፣ጣቢታን ከሞት አስነሥቷል(ሐዋ9÷36)፣ በልዳም ኤንያ የተባለ የ8 ዓመት የአልጋ ቁራኛ ፈውሷል፡፡ ሐዋ9÷32 በሰማርያ ጸጋ እግዚአብሔርን በወርቅ በሀብቱ እገዛለሁ ያለውን ሲሞን መሠርይን ድል ነስቶታል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ስለነበረ በአይሁድ ሸንጐ አባልነት ለ2 ዓመታት በሠራበት ወቅት እምነቱ ቀናተኛ ፊሪሳዊ በመሆኑ ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣማ> ይቃወም ነበር፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ሲያርፍም የወጋሪዎችን ልብe ይጠብቅ የነበረው እርሱ ነው፡፡
በ32 ዓመት ዕድሜው ከኢየሩሳሌም 223 ኪ.ሜ ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ወደ ሊቀ ከህናቱ ቀርቦ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የሚያስችKውን የፈቃድ ደብዳቤ ጠይቆ ከአገኘ በኋላ ጭፍሮችን አስከትሎ ወደ ደማስቆ አመራ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ከተማዋ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው ነበር ከሰማይ የወረደው ብርሃን አካባቢውን ያለበሰውና ሳዖል ሳዖል ስለምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምጽ የሰማው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስም ጌታ ሆይ ማን ነህ? ብሎ ጠየቀ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል ሲል መድኃኒታችን ተናገረው፡፡ ያንን በወደቀበት ሆኖ እየተንቀጠቀጠ ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ ሲል ጠየቀው ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ወደ ደማስቆ እንዲገባ ተነገረው፡፡ የሐዋ 9፥1
የሐዋርያው ዓይኖች ለማየት አልቻሉም፡፡ እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ ለ3 ቀናት ያህልም እህል ሳይቀምስ ቆየ በዚያች ዕለት እግዚአብሔር አምላክ በደማስቆ ለሚገኘው እና ሐናንያ ለተባለው አባት በራዕይ ተገለጠለት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ያለበትን አድራሻ ነገረውና እንዲያጠምቀው አዘዘው፡፡ ሐናንያ አስቀድሞ የቅዱስ ጳውሎስን ማንነት ያውቃል፡፡ አብዛኞቹ በደማስቆ የሚገኙት ክርስቲያኖች ከኢየሩሳሌም በስደት ጊዜ የመጡ ናቸው፡፡ ያን ስደት ያስነሳው ደግሞ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ የደረሰው መከራ ነው፡፡ በዚህ በቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ደግሞ ዋናው ተዋናይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነበርና ነው፡፡ ሐናንያ ቅዱስ ጳውሎስን ካጠመቀውና ካስተማረውም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዓረብ ሐገር መሄዱን ራሱ ተናግሯል፡፡ ገላ 1÷17 ለሦስት ዓመታት በዓረቢያ በረሃ ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ፡፡ በዚያም በነበሩ አይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ፡፡ ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱና
◈ ያልተወለደው ባለ ቅኔ ◈
በእርግጥም መጥምቁ ዮሐንስ ገና ሳይወለድ በእናቱ ሆድ ጰራቅሊጦስ የተደረገለት ሐዋርያ ነው፡፡ ሐዋርያት 'እናንተ ግን ከላይ ኃይል አስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ' ተብለው እንደታዘዙ ዮሐንስም 'በአናትህ ማሕፀን ሳለህ ኃይልን አግኝ' የተባለ የእናቱ ሆድ ውስጥ ጸንቶ የቆየ ደቀ መዝሙር ነበር፡፡ ሉቃ. ፳፬፥፵፱ ሐዋርያት በአንድ ልብ ሆነው ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በወረደላቸው ጊዜ ድንግል ማርያም በመካከላቸው እንደነበረች ዮሐንስ እና እናቱ በመንፈስ በአንድ ልብ ሆነው ባመሰገኑባት በዚህች ዕለትም ድንግሊቱ ከመካከላቸው ነበረች፡፡ ሐዋ፩÷፲፬፣ ሉቃ ፩÷፵፩
ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ ከመካከላቸው ተነሥቶ ጴጥሮስ በሰበከው ስብከት ልባቸው የተነኩትን ሕዝቡን 'ምን እናድርግ' እንዳሰኘ ከእናቱ ጋር መንፈስ ቅዱስ የተቀበለው ዮሐንስም ከተወለደ በኋላ በሰበከው ስብከት ሕዝቡን 'ምን አናድርግ?' አሰኝቷል፡፡ ሐዋ.፪÷፴፯ ፣ሉቃ፫÷፲ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ የዮሐንስም የጴጥሮስም የስብከታቸው ርእስ 'ንስሓ ግቡ' ነበረ፡፡ ማቴ. ፫፥፩ ፣ ሐዋ. ፪፥፴፰
ቅዱስ አቡሊዲስ ዘሮሜ ስለ ዮሐንስ ሲናገር:- “እርሱም ማርያም ሰላምታ ስታቀርብላት ሰማ ፤ ደስ አያለውም በእናቱ ሆድ ውስጥ ዘለለ ፤ በድንግል ሆድ ውስጥ የፀነሰችውን የእግዚአብሔርን ቃል አይቶአልና'ሰምዐ : እንዘ፡ ትትአምኃ : ማርያም : አንፈራዓጸ : በከርሠ: እሙ : እንዘ ፡ ይትፌሣሕ፡ እስመ፡ ይሬኢ፡ ዘውስተ: ከርሠ : ድንግል፡ ዘፀንሰት፡ ቃለ፡ እግዚአብሔር' ብሏል፡፡
"ዝናማትም ዘነሙ ወንዞችም ጎረፉ" 🌧🌧🌧🌧🌧🌧🌧🌧
በዘማሪት ማርታ ኃ/ሥላሴ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ዘመነ ክረምት በኢትዮጵያ
በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሥርዓተ አስተምህሮ በቅዱስ ያሬድ የዜማ መጻሕፍት እና በመጽሐፈ ግጻዌ መሠረት፣እንዲሁም በሀገራችን ኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ስሌት መሠረት ወቅቶች በአራት ይከፈላሉ፡፡ እነዚህም ወቅቶች ዘመነ መጸው (መከር)፣ ዘመነ ሐጋይ (በጋ)፣ ዘመነ ጸደይ (በልግ) እና ዘመነ ክረምት ይባላሉ፡፡
ከአራቱ ወቅቶች መካከልም ከሰኔ ፳፮ እስከ መስከረም ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ጊዜ (አሁን የምንገኝበት ወቅት) ዘመነ ክረምት ተብሎ ይጠራል፤ ቃሉን ለማብራራት ያኽል፣ "ክረምት" የሚለው ቃል ‹ከረመ – ከረመ› ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን፣ ትርጕሙም የዝናም፣ የአዝርዕት፣ የአረም ጊዜ፣ እንደዚሁም ዕፀዋት፣ አዝርዕትና አትክልት በቅለው፣ ለምልመው የሚያድጉበት፣ ምድር በአረንጓዴ ዕፀዋትና በልምላሜ የምታሸበርቅበት ወቅት ማለት እንደሆነ የአማርኛ መዝገበ ቃላትና ልዩ ልዩ ድርሳናት ያስረዳሉ።
በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት አራቱ ወቅቶች የጌታችንና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ወንጌል በጻፉት በአራቱ ወንጌላውያን እንደሚመሰሉ ማለትም: ዘመነ ክረምት - በወንጌላዊው ማርቆስ፣ ዘመነ ፀደይ - በወንጌላዊው ማቴዎስ፣ ዘመነ ሀጋይ - በወንጌላዊው ዮሐንስ እና ዘመነ መፀው - በወንጌላዊው ሉቃስ እንደሆነ ሊቃውንት ያስተምራሉ።
ከአራቱ ወቅቶች መካከል ከሰኔ ፳፮ እስከ መስከረም ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ጊዜ (አሁን የምንገኝበት ወቅት) በወንጌላዊው ማርቆስ የተመሰለው ዘመነ ክረምት ተብሎ ይጠራል፡፡
በዓተ ክረምት (የክረምት መግብያ)
ከሰኔ ፳፮ እስከ ሐምሌ ፲፰ ቀን ድረስ ያለው የመጀመሪያው የክረምት ክፍለ ጊዜ "በዓተ ክረምት" ወይም ‹ዘርዕ፣ ደመና› ይባላል፡፡ ‹በዓተ ክረምት› ማለት <የክረምት መግቢያ፣ መጀመሪያ› ማለት ነው፡፡ በዚህ ወቅት በቤተክርስቲያናችን ስለክረምት መግባት፣ ስለዘርዕ፣ ስለደመና እና ስለዝናም የሚያዘክሩ መዝሙራትና ምንባባት ይዘመራሉ፣ ይነበባሉ፡፡ ይህ ወቅት ደመና ሰማዩን የሚሸፍንበት፣ የዝናም መጠን የሚያይልበትና መሬት በዝናም ረክታ ዘር የምታበቅልበት ጊዜ ነውና፡፡
በዘመነ ክረምት መጀመርያ (መግቢያ) ሳምንት በቤተክርስቲያናችን የሚቀርበው የቅዱስ ያሬድ መዝሙር የሚከተለው ነው፤ ‹‹ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ሶበ ይዘንም ዝናም ይጸግቡ ርኁባን ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ሶበ ይዘንም ዝናም ይትፌሥሑ ነዳያን ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ወሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ደምፀ እገሪሁ ለዝናም›› የመዝሙሩ ቀጥተኛ ትርጕም፡-‹‹የዝናም ኮቴው ተሰማ፣ ዝናም በሚዘንም ጊዜ የተራቡ ይጠግባሉ፡፡ የዝናም ኮቴው ተሰማ፡፡ ዝናም በሚዘንም ጊዜ ድሆች ይደሰታሉ፡፡ የዝናም ኮቴው ተሰማ፣ አምላካችን ለሰው ልጅ ዕረፍት ሰንበትን ፈጠረ፤ የዝናም ኮቴው ተሰማ፡፡ የዝናም ኮቴው ተሰማ፡፡>>
ይህ መዝሙር ከሰኔ ፳፮ ጀምሮ ያለው ወቅት ክረምቱ የሚገባበት እና ዝናም በብዛት የሚጥልበት ጊዜ መኾኑን የሚያበሥር ሲኾን፣ በተጨማሪም ዝናም በሚዘንብበት ጊዜ የሚበቅለውን እኽልና የምንጮችን መብዛት ተስፋ በማድረግ የተራቡ እንደሚጠግቡ፤ የተጠሙም እንደሚረኩ የሚያትት ምሥጢር ይዟል፡፡ እንደዚሁም ጊዜ ለበጋ፣ጊዜ ለክረምት የሚሰጥ አምላክ ለሰው ልጅ ማረፊያ ትኾን ዘንድ ዕለተ ሰንበትን መፍጠሩንም ያስረዳል፡፡
አያይዞም ቅዱስ ዳዊት "ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና ወያስተዴሉ ክረምተ ለምድር ዘያበቍል ሣዕረ ውስተ አድባር፡፡››መዝ ፻፵፮፥፰ ትርጕም፡- ‹‹ሰማዩን በደመና የሚሸፍን፣ ለምድርም ዝናምን የሚያዘጋጅ፣ ሣርን በተራሮች ላይ የሚያበቅል እርሱ ነው፡፡>> እግዚአብሔር ሰማዩን በደመና የሚሸፍን፤ ዝናምንም (ክረምትን) ለምድር (ለሰው ልጅ) የሚያዘጋጅ፤ እንደዚሁም በተራሮች ላይ ሣርን (ዕፀዋትን) የሚያበቅል አምላክ መኾኑን ያስገነዝባል። ዘመነ ክረምት በየትኛውም ክፍለ አኅጉር ወቅቶችን እየቀያየረ ምድርን ሲያድስ የሰው ልጆችንም ሕልውና አብሮ በማደስ ሰውና ክረምት ያለውን ቁርኝት ዘላለማዊ አድርጎታል።
ስለሆነም ክረምት እና በጋውን በማፈራረቅ ምድርን በልምላሜ እና አበባ የሚያሸበርቀውን ፤ በዘመናት መካከል በፀጋና በረከት የሚያኖረውን የዘመን ባለቤት አምላካችን እግዚአብሔርን ከልባችን እያመሰገንን ለዘላለማዊ ክብሩ በመገዛት እንኑር። በክረምት የሚሠሩትን ሥራዎች በሙሉ በመከወን ለፍሬያማው ወቅት እግዚአብሔር ያደርሰን ዘንድ አብዝተን እንጸልይ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
© በመ/ር ሽፈራው እንደሻው
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሕይወተ ወራዙት (የወጣቶች ሕይወት)
ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ክፍል ዐራት
.................................................
➺«በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ››
ጠቢቡ ሰሎሞን ለወጣቶች በሙሉ ዘለዓለማዊ መመሪያ የሚሆን የሕይወት ቃል ተናግሯል:: ቃሉም «የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ›› የሚል ነው:: መክ12፥1 «በጉብዝናህ ወራት» ያለው ወጣቶችን ለመጥቀስ ፈልጎ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ወጣቶች «ጎበዞች» ይባላሉና፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በመልእክቱ «ጎበዞች ሆይ ብርቱዎች ስለ ሆናችው የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ እጽፍላችዋለሁ፡፡››ብሎ በጻፈ ጊዜም ወጣቶች «ጎበዞች» እንደሚባሉ ማጠናከሪያ ሰጥቷል፡፡ 1ዮሐ3፥14
«ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ» ማለቱም «ክፉ» የሚባለውን የወጣትነት ምኞት ስለ አሸነፋችሁ ማለቱ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ «ከክፉ የጎልማስነት ምኞት ሽሽ»በማለት የክርስትና ልጁ ጢሞቴዎስን እንደመከረው የወጣትንት ምኞት «ክፉ» ይባላልና፡፡ ወጣቶች ፈጣሪያቸውን ማሰብ እንደሚኖርባቸው ተለይተው የተጠቀሱት ለምንድር ነው? ፈጣሪን ማሰብ ማለትስ እንዴት ነው?
በመሠረቱ ፈጣሪን ማሰብ የሚኖርባቸው ወጣቶች ብቻ አይደሉም፡፡ ልጆችም ሆኑ አረጋዊያን ፈጣሪን ማሰብ ይኖርባቸው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ግን ወጣቶችን ለይቶ ፈጣሪን ማሰብ እንዳለባቸው የተናገረበት ምክንያት አለው፡፡ ይኸውም ከልጆችና ከአረጋዊያን ይልቅ ወጣቶችን እግዚአብሔርን እንዲረሱ የሚገፋፋቸው ብዙ ነገር ስላለ ነው፡፡
በብዙ ወጣቶች ዘንድ ያልተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም ፍሬያማ ግብር (ስኬት) ማለት የተመኙትን ሁሉ ማግኘት ይመስላቸዋል:: ነገር ግን ከዚህ የሚበልጥ ስኬታማነት አለ፡፡ እርሱም ራስን በመግዛት ምኞትን መመጠን ነው:: ምኞትን ከመመጠን ጋር ስናወዳድረው የተመኙትን ለማግኘት መልፋት በጣም ቀላል ነገር ነው:: ከባዱ ነገር አለመመኘት ወይም ምኞትን በልክ ለማድረግ መቻል ነው፡፡.
ታዋቂና ዝነኛ ሰው መሆን ብትፈልግ ብዙ ጥረትና ጊዜ ይፈጅብህ ይሆናል እንጂ ታገኘዋለህ:: ነገር ግን የተናቀ ሰው ለመሆን አስበህ ታውቃለህን? ብታስበውስ የሚቻል ይመስልሃልን? ትልቅ ሰው ከመሆን ትንሽ ሰው መሆን እጅግ ይከብዳል:: ታዲያ ችሎታ መባል ያለበት የቱ ነው? ትልቅ ሰው መሆን ባትችል እንኳን ጥረቱ ያም ባይሆን ፍላጐቱ ይኖርሃል፡፡ ስለዚህ ትንሽ ነህ አትባልም:: ትንሽ ለመሆን ግን እንኳን መጣር ይቅርና ሐሳቡንም አምኖ ለመቀበል ይከብድሃል፡፡ ለምን ይመስልሃል? ትንሽ ስለ ሆንክ ይመስልሃልን? አይደለም፡፡ እንደዚህ ለማድረግ ችሎታ ስላሌለህ ነው::
በወጣትነት ዘመን ይህ የተሳካላቸው ያለ ምንም ጥርጥር ጻድቃንና ቅዱሳን ናቸው፡፡ ለዚህ ማዕረግ የበቁት ብዙ ሀብት በማካበትና ብዙ በመማር ሳይሆን የኢየሱስ ክርስቶስን ፈለግ በመከተል ራሳቸውን ብዙ ስላዋረዱ ከዚህም ዓለም ምንም ስላልፈለጉ ነው።
ቅዱስ ዳዊት ያሰበውና የሚሠራው ሁሉ የሚከናወንለት ምስጉን ሰው ምን ዓይነት ሰው እንደ ሆነ ሲገልጽ እንዲህ ይላል:- «ምስጉን ነው : በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይልዋል፥ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል:: እርሱም እንደተተከለች፥ ፍሬዋን በውኃ ፈሳሾች በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል›› ይልና በመጨረሻም «የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል» ይላል፡፡ ከዚህ የበለጠ ስኬታማነት ሊኖር አይችልም:: ይህ የሚገኘው ደግሞ ከላይ የተገለጡትን መንፈሳዊ ጎዳናዎችን በመከተል ነው:: የስኬት መሠረት መንፈሳዊነት ነው የተባው ስለዚህ ነው።
ሰው ከእግዚአብሔር ርቆ ስኬታማ መሆን አይችልም:: የያዕቆብ ልጅ ዮሴፍ በሥጋም ሆነ በነፍስ ነገሮች ሁሉ የተሳኩለት ወጣት እንደ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይመስክራል፡፡ «እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ፣ በግብፃዊው ጌታውም ቤት ነበር። ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ፣ እርሱ የሚሠራውም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ፡፡»
ዛፍ ከግንዱ ተለይቶ ለማፍራት እንደማይችል እንዲሁ የሰው ልጅም ከፈጣሪው ተለይቶ ፍሬያማ መሆን አይችልም። ሰው ሠራሽ አበባ መልኩ ይመር እንጂ ምንም ዓይነት መልካም መዓዛና ሕይወት እንደሌለው ሁሉ በችኮላና ከፈጣሪ ተለይተው ያፈሩት ነገር ሁሉ ውስጣዊ ደስታና ዘላቂነት የሌለው በመሆኑ መጨረሻው አሳዛኝ ነው፡፡ ብዙ ነገር ኖሮህ በኃዘን ከመዋጥህ የተነሣ ምንም እንደሌለው ከምትሆን ትንሽ ነገር ኖሮህ በደስታ ብትኖር አይሻልህምን? ስልዚህ «የሰው ሕይወቱ በገንዘቡ መጠን አይደለምና» ነገሮችን መሻትህ ከፈጣሪህ እንዳይለይህ ተጠንቀቅ! ከመጎምዠትም ተጠበቅ ! ሉቃ12÷15
ሰው ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ቢሆን ነገሮች ሁሉ ይሳካሉ፡ ይከናወኑማል፡፡ ራሱ ፈጣሪ «ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም» ብሏልና፡፡ ዮሐ15፥4-7 ያለ ረድኤተ እግዚአብሔር መማር ማስተማር መጻፍ መደጎስ በአጠቃላይ ማንኛውም ሥራ ከፍጻሜው ሊደርስ አይችልም:: ነቢዩ ነህምያም «እኛ ባሮቹ ተነሥተን እንሠራለን የሰማይ አምልክም ያከናውንልናል» ያለው «ማከናወን» የፈጣሪ ድርሻ ስለሆነ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ «ወጢንሰ እምኀበ ሰብእ» በማለት እንደተናገረው «መጀመር›› የሰው ድርሻ ሲሆን መፈጸም ግን የእግዚአብሔር ነው:: ነገሮች ከፊጻሜ ሳይደርሱ ደግሞ ስኬት የሚባል ነገር ሊኖር አይችልም:: ስለዚህ «መፈጸም» የፈጣሪ ከሆነ የሰው ስኬት የተያዘው በእግዚአብሔር እጅ ነው ማለት ነው::
መንገድ እንዲቃናልህ የምትሠራውም ሁሉ እንዲከናወንልህ ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ከዚህ በታች የሰፈረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በልብህ አኑረህ ተጠቀምበት:: ቃሉም እንዲህ ይላል:- «የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፡ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፡ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም፡፡» ኢያ1፥8
ቀጣይ የመጨረሻው ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ክፍል ዐራት :
👉 «በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ» በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
በእርግጥ የማያሳፍርና የሚያሳፍር ነገርን ለይቶ ማወቅ ለሰው ሁሉ የሚገባ ነገር ነው።ምክንያቱም ከመለመዱ የተነሣ የማያሳፍረው ሲያሳፍር፤ የሚያሳፍረው ደግሞ ሲያስመካ ማየት የዘወትር ክሥተት አየሆነ መጥቷልና፡፡
በዚህ ዘመን ውሽት በሚናገሩበትና በሚያታልሉብት ጊዜ ፊትን ሳያጥፉ ድርቅ ብሎ መፋጠጥ እንደ ጉብዝና ተቆጥሯል:: ይህን የሚያደንቁና ሲዋሹ የሌላውን ፊት ትኩር ብሎ ለማየት ራሳቸውን የሚያለማምዱ በርካታ ሰዎች በዙሪያችን ይገኛሉ፡፡ ለጊዜው ይህ ጉብዝና ሊመስል ይችል ይሆናል ውሎ አድሮ ግን ከፍተኛ ጸጸት ማስከተሉ አይቀርም፡፡
እፋራምነት የመልካም ሥነ ምግባር መገለጫ ነው:: ሆኖም ብዙዎች እንደ ጭቆናና ብዝበዛ መሣሪያ አድርገው ስለሚቆጥሩት በምንም አጋጣሚ ማፈር አይፈልጉም:: እንዲያውም አንዳንድ ደፋር ነን ባዮች ዓይናፋርነትህን አውቀው በአንድ ወቅት ሳያሾፉብህና ሳያስጨንቁህ አይቀሩም፡፡ ይህ አጋጣሚ ራስህን በጣም እንደ ተጠቃ ሰው ቆጥረህ እንደ እነርሱ «ደረቅነትን» ለመለማመድ በቁጣ እንድትነሣሣ ለማድረግ ለሰይጣን በር ይከፍትለታል፡፡ ስለዚህ ይህንና ይህን የመሳሰሉ ገጠመኞች ዓይናፋርነትህ ብዙ እንዳጐደለብህ እንዲስማህ በማድረግ እንድታማርረው ወይም ደግሞ እሽቀንጥረህ እንድትጥለው ያደርጉሃል:: ነገር ግን ይህን ካደረግህ በዚህ ዓለም ስትኖር በባሕር ላይ ሆነህ መልሕቅህን እንደ ጣልከው ቁጠር፡፡
ኀፊረ ገጽ ብተለይ በወጣትነት መንፈሳዊ ሕይወትን ለመምራት በእጅጉ ይጠቅማል፡፡ ተገቢ ባልሆነ ተግባርህ ብቻህን ስትሆን ሕሊናህን፤ በቤት ውስጥ ወላጆችህን፣ በሌላ ስፍራ ደግሞ አለቆችህን፣ መምህራንንና ሌሎች ታላላቅ ሰዎችን ማፈርና ማክበር ይኖርብሃል፡፡ ሰው እኮ የሚመከረው ሕሊና ሲኖረው ወይም የሚፈራውና የሚያከብረው ሰው ሲኖረው ነው:: እነዚህ የሌሉት በማን ይመከራል?
ማፈርና መፍራት ከሰዎች እየራቁ በመሄዳቸው በሀገራችን ብዙ ችግሮች ተበራክተዋል፡፡ ሽማግሌን አፍሮ መታረቅ እንኳን እንደ ከዚህ ቀደሙ ቀላል ነገር አልሆነም:: ብዙ ሴቶች እኅቶቻችን ለሻካራ ንግግርና <<ደረቅ>> ለሚያሰኛቸው አለባበስ ተጋልጠዋል:: በየፌርማታው፣ በየመጓጓዣ መኪና፣ በየመንገዱና በየፈፋው መሳሳምና መዳራት አበጀህ እንደሚያሰኙ ተግባራት ተደርገው ተወስደዋል፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ደግሞ መደባበቁና ጨለማን ተገን ማድረጉ ቀርቶ በሕዝብ መድረኮችና በአደባባይ ላይ በዝሙት መንፈስ መዳራትና መሳሳም የጥበብ መግለጫ ሆነው በየፊልሙና በየድራማው መሃል እንደ ሳጋ ተሰግስገው ይታያሉ፡፡ በዚህ ፍጥትነታችን ከቀጠልን ዝሙትን እንደ ባህል እንደሚቆጥሩ ሀገሮች ግብረ ዝሙትን በገሃድ በፊልምና በቴአተር ቤቶች መድረክ የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።
የዚህ ሁሉ ምንጩ ኀፊረ ገጽ ከኢትዮጵያውያን ልቡና ተገፍቶ እንዲወጣ ስለተደረገ ነው፡፡ ይህም ሁሉ ሆኖ ወጣቶች ገና ባለመንቃታቸው ዓለም ዓይናቸውን በጨው ላጠቡ ስዎች እንደምትመች አድርገው በመቁጠር ራሳቸውን «ደረቅ» ለማድረግ ይጥራሉ፡፡
ለበጎና ለሚገባ ነገር ደፍሮ መሰለፍ ስማዕትነት ነው:: ነገር ግን ለሰይጣን ፈቃድ ደፍሮ መሰለፍ ምን ይባላል? ክርስቲያን አፋራም ነው ማለት ለመብቱ አይከራክርም፣ ዝም ብሎ ይጨቆናል፣ ይረገጣል ማለት አይደለም:: ማፈር የማይፈልግ ሰው ከሚያሳፍሩ ነገሮች መለየት ይገባዋል እንጂ ደፋርነትን መለማመድ መፍትሔ አይሆንም፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የኤፌሶን ክርስቲያኖችን በመከረበት አንቀጽ «...የሚያሳፍር ነገርም፥የስንፍና ንግግርም ወይም ዋዛ የማይገቡ ናቸውና አይሁኑ።» በማለት ተናግሯል፡፡ «የሚያሳፍር ነገርም» ሲል ሐሳብም፣ ንግግርም፣ ሥራም የሚያሳፍሩ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገልጻል፡፡ እነዚህ ሦስቱም «ነገር» ይባላሉና፡፡ ኤፌ 5፥4
ከሥነ ተዋልዶ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የሰውነት ክፍሎች፣ ፆታ ነክ ተግባራትን፣ ፆታ ነክ ውይይቶችን ማየት መስማት፣ ማውራትና ማከናወን በሕግ በሥርዓት፤ ዘልክና በፈሊጥ መሆን አለበት፡፡ እነዚህ ነገሮች ከማፈር ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት አላቸው:: የእነዚህ ነገሮች በሙሉ ጌጣቸው ማፈር ነው።ማፈር የሌለበት የሥነ ተዋልዶ አካል እንደ አሻንጉሊት አካል ነው፡፡ ምነው? ቢባል ግብረ ነፍስ የለበትምና ስለዚህ ነው:: ማፈር ደግሞ የለባዊት ነፍስ ጠባይ እንጂ የሥጋ መታወቂያ አይደለምና፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ማፈር አለማፈርን በቀጥታ ከአለባበስ ጋር አያይዞ ገልጾታል:: «እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ::»1ጢሞ2÷10 አንቺ ወጣት «በሚገባ ልብስ›› በማለቱ የሚገባና የማይገባ ልብስ እንዳለ ሐዋርያው መናገሩን አስተዋልሽን? ራስሽን መሸለም (ማስጌጥ) ከወደድሽም እንደ ሐዋርያው ምክር «ከእፍረት» ጋር አድርጊው ያለ እፍረት ብታጌጪ ጌጥሽ ጌጥ አይሆንም፡፡ ታላቁ ጌጥ ‹‹ኀፊረ ገጽ» ነውና፡፡
ቀጣይ ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ክፍል ሦስት :
👉 «ስኬታማነት» በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
መልካም ስም ያለውን ጠቀሜታ ለመረዳት ቀላል ነው።እንኳን በብዙ አቅጣጫ ብዙ መልካም ስም ኖሮህ ይቅርና «እገሌ ታማኝና እውነተኛ ነው» በሚል ስም ብቻ ብትታወቅ ብዙ ጥቅሞች ይከቡሃል፡፡ ለምሳሌ፦ እውነተኛ ሰው በብዙዎች ዘንድ ታማኝነትና አክብሮትን ያተርፋል:: የሚያገኛቸው ወዳጆቹ እውነተኝነቱን አድንቀውና ወደው የሚቀርቡ በመሆናቸው አብዛኞቹ ራሳቸው እውነተኞች መሆናቸው የማይቀር ነውና፥ እውነተኛ በመሆንህ እውነተኞች ጓደኞችን እንድታገኝ ረዳህ ማለት ነው።ይህ ደግሞ ታላቅ ትርፍ ነው።የሰው ሁሉ ችግር ታማኝ ባልንጀራ ማፍራት አለመቻል ነውና።
ከዚህም ሌላ በመልካም ስም መታወቅ ሌላም የሚያስገኘው ጥቅም አለ፡፡ የንግዱ ዓለም ብዙ ማጭበርበር ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ሆኖም አሠሪዎችና ሠራተኛ ቀጣሪዎች ለታማኝነት ከፍ ያለ ዋጋ ሰጥተው እውነተኞችንና ታማኞችን መቅጠር ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ አንተ በታማኝነት መታወቅህ ብቻ በሥራ ችሎታ ብዙ የሚበልጡህ ሰዎች ቢኖሩም እንኳን ሥራ የማግኘትና ሌሎች ከሥራ በሚባረሩበትም አጋጣሚ በሥራህ የመቆየት ዕድል ይገጥምሃል፡፡ ይህም «ታማኝ» የሚል መልካም ስም ማትረፍ ብቻ ምን ያህል እንደሚጠቅም ያስረዳል።
ባልና ሚስት በታማኝነት የሚተዋወቁ ከሆነ ጥርጣሬንና አለመተማመንን አስወግደው በፍቅር ለመኖር ይረዳቸዋል። ታማኝ ልጆችም በወላጆቻቸው ዘንድ ሙሉ አመኔታን ያተርፋሉ፡፡ ልጆች በወላጆች ዘንድ «ታማኝ» በሚል መልካም ስም ከታወቁ ቀስ በቀስ ሰፊ ነፃነት እያገኙ ይመጣሉ።እውነቱን መናገር ተግሣጽን እንኳን ቀላል የሚያደርግበት ሁኔታ አለ፡፡ አንድ ታዳጊ አጥፍቶ በሚቀጣበት ጊዜ ቢክድ የቅጣቱ መጠን ሊጨምር ይችላል፡፡ ቢያምንና ይቅርታ ቢጠይቅ ግን ቅጣቱ ይቀልለታል፡፡ በወኅኒ ቤትም ሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ቢሆን ሐቁ ይህ ነው።
ሰው ሁሉ በሕይወት ዘመኑ ሌሎች እንዲያምኑትና ቃሉን እንዲቀበሉት በብርቱ የሚፈልግበት አንድ አጋጣሚ ሳይመጣበት አይቀርም፡፡ ታማኝ የሚል ስም ያለው ሰው በዚህ ሁሉ ሳይቸገር ነገሩን ሌሎች በቀላሉ ሊያምኑለት ይችላሉ፡፡ በአጠቃላይ «ታማኝ»የሚል መልካም ስም ያተረፈ አንድ ሰው ተዘርዝረው የማያልቁ ብዙ ጥቅሞችን ያገኛል፡፡
ከላይ የተጠቀሰው ስለ «ታማኝነት» ብቻ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ሐቀኛ፣ የተከበረ፣ ጨዋ፣ ሰው አክባሪ፣ ቁጥብ፣ ቁም ነገረኛ፣ ዐዋቂ፣ ትሑት፣ የሚሉ ሌሎች መልካም ስሞችን ብታተርፍ ምን ያህል በነፍስና በሥጋ እንደምትጠቀም ገምት። እነዚህ ነገሮች ያሉት ለሥራ፣ ለጓደኝነት፣ ለትዳር በአጠቃላይ ለሁሉም ጉዳይ በመብራት እንደሚፈለግ ጥርጥር አይኑርህ።
መልካም ስም እንዲሁ በቀላሉ አይገነባም። ብዙ ድካምና ጥረት ከመጠየቁም ሌላ ብዙ ጊዜ ይወስዳል። የሚያስደንቀው ግን ጥሩ ስም ሲበላሽ ምንም ጊዜ አለመፈለጉ ነው።ስለዚህ መልካም ስምን እንደ ዓይን ብሌን ሊጠነቀቁለት ይገባል። መልካም ስም ገንዘብ፣ የትምህረት ደረጃ ወይም ሌላ መስፈርት ኣይጠይቅም።ፈቀደኛ ከሆንክ የነፍስህ ዕውቀት ብቻ መልካም ስም እንዲኖርህ ለምትሠራው ሥራ ሁሉ በቂ ናት፡፡
የመልካም ስምን ጠቀሜታ መዘርዘር በአንፃሩ የመጥፎ ስምን ጉዳት መዘርዘር ነው።በመጥፎ ስም ከታወቅህ የእናትህ ልጅ እንኳን አያቀርብህም። ስለዚህ በስካራምነት፣ በቅብጠት፣ በአባካኝነት፣ በውሸት፣ በቀልድና በመዘበት፣ በመልከስከስ፣ በገንዘብ ወዳድነት፣ በትዕቢት፣ በክህደት፣ በስሜታዊነት፣ በተናጋሪነትና በመሳሰሉት መጥፎ ስሞች እንዳትታወቅ ተጠንቀቅ። በገዛ እጅህ ሁሉ ነገር ርቆብህ ቁጭ ብለህ የምታለቅስበትን የኀዘን ገመድ ለምን ትጎትታለህ?
ወጣት ከሆንክ መጥፎ የተባሉትን ነገሮች ለመላቀቅ አልቻልኩም አትበል፡፡ አስቀድሞ እንደተገለጠው መጥፎና ጥሩ ነገር የሚወስዱት ጊዜ የተለያየ ነው። ከክፉ ጠባዬ ብታረምም ተቀባይነት ግን አላገኘሁም በማለት ተስፋ መቁረጥ አይገባም።ይህ ሁሉ የመጀመሪያ ክፉ ሥራህ ደሞዝ እንደሆነ አምነህ ራስህን እየወቀስህ ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ ተቀባይነት ለማምጣት ተጣጣር እንጂ ወደ ኋላህ አትመለስ።መቼም ቢሆን «ከመልካም ሽቶ መልካም ስም» ይሻላልና፡፡መክ7፥1
አንተ ጥሩ የትምህርት ደረጃና ሙያ ይዘህ ሥራ አጥተህ ስተቀመጥ መልካም ስም የያዙ ሌሎች ያለምንም ማስረጃና የሥራ ልምድ የምትቀናበትን ሥራ ሲሠሩ አይተህ አታውቅምን? ይህ አገላለጽ ትምህርትና ዕውቀትን ለማቃለል ሳይሆን የመልካም ስምን ታላቅነት ለማጉላት ነው። በትምህርትና በሥራ ልምድህ ላይ የመልካም ሥነ ምግባር ባለቤት መሆንህ ከተነገረ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመትም አያስቸግርም።
የመልካም ስም ቁልፉ መንፈሳዊነት ነው።ትምህርተ ሃይማኖትና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ሰው በሥነ ምግባር መታነፁና የመልካም ስም ባለቤት መሆኑ አያጠራጥርም።የዚህ ዓለም ምስኪን ማለት መንፈሳዊ ተብሎ መልካም ስም የሌለው ነው።መልካም ስም እንዲኖርህ ትፈልጋለህ? ታዲያ ገጸ ልቡናህን ወደ ፈጣሪህ ለምን አትመልስም?
ቀጣይ ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ክፍል ኹለት :
👉 «ኀፊረ ገጽ» በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ውድ የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች ቻናል ተከታታዮች :
ከወደ ምስራቅ (ድሬ) ወንድሞች አግዘውት ከፕሮቴስታንቱ ዓለም ወደ ክርስትና የተመለሰ አንድ ወንድማችን ነበር : ክርስቲያን ከሆነ በኋላ ራቅ ካለ ቦታ ወንድሞች ወዳሉበት ወደ ድሬ ስለመጣ እነርሱ እያገዙት የቤት ኪራይም የት/ቤት ክፍያም የእለት ጉርስም እያብቃቃ ነበር የኖረው። አሁን ግን ጊዜው እንደሚታወቀው ለመኖር ከባድ ነውና ነገሩ ከአቅሙ በላይ ሆኖ መማርም አልቻለም፤ለምግብም እስከመቸገር ደርሷል።
ብንችልና አቅሙ ቢኖረን ቋሚ የሆነ ራሱን የሚለውጥበት ነገር ብናደርግ መልካም ነበር ቢያንስ ግን ለአሁኑ የት/ት፣ የቤት ኪራይ ወጪውን ከዕለት ጉርሱ ጋር የምትሞላለት ነገር ብንተባበረው አግዙን ብለን መጥተናል።🤲
በዚህኛው ጾም የአንድ ክርስቲያን ወንድማችንን ጭንቀት በማቅለል ጥቂት በረከት ብንካፈል መልካም ነውና መቶም ሁለት መቶም አንድ ሺህም ብትሆን በቅዱሳን ሐዋርያት ስም በልጁ አካውንት እናስገባለት።🙏
CBE 1000267371044
በረከት ግርማ ቱፋ
(በባንክ አስገብታችሁ ደረሰኝና የክርስትና ስማችሁን በ @Ethiopian_Orthodox_bot በኩል አድርሱን🤲)
📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚
ሰላም ውድ የ"የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች" ቻናል ተከታታዮች በኃያሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንደምን ሰነበታችሁ? ከዚህ በፊት በመጻሕፍት አምዳችን "ተግባራዊ ክርስትና" እና "ሕይወተ ወራዙት ፩" የተሰኙ መጻሕፍትን ወደ እናንተ ማድረሳችን ይታወቃል። እነሆ አሁን ደግሞ "እንዴትና ምን ብዬ ልናዘዝ?" በሚል ርዕስ በመ/ር የሺጥላ ሞገስ የተዘጋጀውን እጅግ ጠቃሚ መጽሐፍ በመጽሐፉ ምዕራፍ መሠረት በክፍል ከፋፍለን ወደ እናንተ ማድረስ እንጀምራለን። ስለሆነም አንብባችሁ ትጠቀሙበት ዘንድ እንዲሁም ለሌሎችም ያነበባችሁትን ታጋሩ ዘንድ እናሳስባለን። ይልቁንም ደግሞ ያነበብነውን ወደ ተግባራዊ ህይወት ቀይረን እንኖረው ዘንድ መልዕክታችን ነው።
መልካም ንባብ!
==================================
እንዴትና ምን ብዬ ልናዘዝ?
...............................................
፨መቅድም
ንስሐ እግዚአብሔር በሰው ልጅ ላይ ያለው የማያባራ ፍቅር ማረጋገጫ ሆኖ የተሰጠ ጸጋ ነው
የሰው ተፈጥሮ እራሱ የእግዚአብሔር ፍቅር መግለጫና ውጤት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ብቻውን መኖር አቅቶት አልያም ለህልውናው ከሰው ልጅ የሚፈልጋቸው ግብዓቶች ኖረው አልያም ያለ እኛ መኖር ስለማይችል አይደለም ፍቅር የሆነው እግዚአብሔር ፍቅሩ በሚፈጥረው ሰው ላይ እንዲገለጽ ሽቶ እንጂ፡፡ “ሰውን በመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር፡፡” /ዘፍ 2÷18/
"ወይቤሎሙ ሑሩ"
በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰብክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት፡፡ በዚያም የተነሣ የደማስቆ ክርስቲያኖች በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ አይሁድ ጳውሎስን እንደሚያውቁት እና እንደለመዱት ሆኖ ስላላገኙት ሊገድሉት ተነሱ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቲያኖች የቅዱስ ጳውሎስን መመለስ ሊያምኑ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻ ግን በርናባስ ወደ ሐዋርያት ዘንድ ወስዶ የጳውሎስን መመለስ በመተረክ እንዲያምኑት አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም በድፍረት በማስተማሩ አይሁድ ስለተቃወሙት ከተማዋን ትቶ በቂሳርያ በኩል ወደ ትውልድ ሐገሩ ጠርሴስ ተመለሰ፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጠርሴስ ከተማ ለ9 ዓመታት ቆይቷል፡፡ ከኢየሩሳሌም ውጭ የአሕዛብ ከተማ በነበረችው በአንጾኪያ የክርስትና ሃይማኖት ተስፋፋ፡፡ ከዚህም በኋላ ሐዋርያው ሦስት ታላላቅ ሐዋርያዊ ጉዞዎችን አድርጓል፡፡ በመጀመሪያው ጉዞው ወደ 2ዐዐዐ ኪ.ሜ የሚደርስ መንገድ በእግር ተጉዟል፡፡ ይህም የተከናወነው በ46 ዓ.ም ነው፡፡ በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከ18 በላይ ከተሞችን ሸፍኗል፡፡ ጉዞውም በ5ዐ ዓ.ም የተደረገ ነው፡፡ በሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከ2ዐ በላይ ከተሞችን ሸፍኗል፡፡ ጉዞውም በ54 ዓ.ም የተደረገ ነው፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በጥበብ ነበር የሚያስተምረው፡፡ ጣዖት የሚያመልኩትን መምለኬ ጣዖት መስሎ፣ ሕሙማንን ሕሙም መስሎ አስተምሯል፡፡ 1ኛ ቆሮ9÷21 በአንጾኪያ ከሞተ 2 ወር ያለፈውን የንጉሡን ልጅ ከሙት አስነሥቷል፡፡ ብዙም ጊዜ በቁም እሥር በብዙም መከራ ሥቃይ እንግልት ያለፈ ታላቅ ሐዋርያ ነው፡፡
3. ዕረፍታቸው
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ
ንጉሡ ኔሮን ቄሣር መምለኬ ጣዖት ነበር፡፡ በሃይማኖት ምክንያት አስሮት ነበር፡፡ ወደ ጦር ግንባር ዘምቶ ጠላቱን ድል ነሥቶ ሲመለስ ለጣዖት ስገድ ቢለው አልሰግድም አለ፡፡ በችንካር ተቸንክሮ በመስቀል ተሰቅሎ ይሙት ብሎ ፈረደበት፡፡ ከዚያ በፊት አሕዛብ ሊጣሉት ሲነሱ ወደ ጌታ ሲያመለክት እሳት ከሰማይ ወርዳ ታጠፋለት ነበር፡፡ አሁንም ትብላቸው ብሎ ወደ ጌታ ቢያመለክት ጌታ በመስቀል ተሰቅሎ ታየው ዳግመኛ በሮም ሰቀሉህን አለ አንተ ብትፈራ እንጂ አለው፡፡ ፈቃድህስ ከሆነ ብሎ እንደ ጌታዬ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ስቀሉኝ አላቸው ፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ በጨካኙ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት ቁልቁል በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ሥጋውንም ደቀመዝሙሩ መርቄሎስ ከመስቀሉ አውርዶ በወተት አጥቦ ሽቱ ቀብቶ በነጭ ሐር ገንዞ እንዳይፈርስ በማር በተመላ ሣጥን አድርጎ ቀብሮታል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
ለ 2 ዓመት ከ6 ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ከቆየ በኋላ በ74 ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት አንገቱን በሠይፍ ተሠይፎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም በሰማዕትነት አረፈ፡፡
አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ረድኤት በረከታቸው ይክፈለን፡፡ አሜን!!!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የድንግል ማርያምን ድምፅ ሲሰማ የተሰማውን ደስታ መናገር ባይችልም ፣ 'የተባረክሽ ነሽ' ብሎ ለማመስገን ባይታደልም እናቱ ኤልሳቤጥ ግን ልጅዋን ወክላ 'በደስታ ዘለለ' ብላ ተናገረችለት፡፡ እርሱ ቃል አውጥቶ ማመስገን ባይችልም እናቱ የጌታን እናት አመስግና የልቡን አደረሰችለት፡፡ እርሱ በመዝለልና በመስገድ እናቱ ደግሞ በታላቅ ድምፅ በማመስገን ድንግል ማርያምን ተቀበሏት፡፡
በእናቱ ሆድ ውስጥ ያለ ሕፃን 'ኖር' ብሎ እጅ ነሥቶ የሚቀበላት ክብርት እንግዳ ከድንግል ማርያም በቀር ወዴት አለች? ገና ያልተወለደ ልጅ ድምፅዋን ሰምቶ ከእናቱ ሆድ ለመውጣት ከጓጓላት ማርያም ስም በቀርስ ሴት ልጅ ምጥ ላይ በሆነች ጊዜ ልጁን ልውጣ ልውጣ ለማሰኘት ሊጠራ የሚገባው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስም ምን አለ?
ዮሐንስ በእናቱ ሆድ ሳለ የድንግል ማርያምን ድምፅ ስለሰማ ከተወለደ በኋላ የዓለምን ድምፅ መስማት አስጠልቶት ወደ በረሃ ሸሸ፡፡
አረጋዊው ስምዖን 'ዓይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ' እንዳለ ዮሐንስም 'ጆሮዎቼ የእናትህን ድምፅ ሰምተዋልና ባሪያህን አሰናብተኝ' ብሎ ለዓለም የሞተ ሆኖ በበረሃ ኖረ፡፡ ድንግሊቱን የሰሙ ሰዎች ልባቸው ወደ ምናኔ ሕይወት ያዘነብላል፡፡ ወደ ምድረ በዳ ሔደው ድንጋይ ተንተርሰው ሲተኙ ደግሞ እንደ ያዕቆብ እግዚአብሔር በላይዋ የተቀመጠባትን መሰላል ያያሉ፡፡
በማሕፀን የነበረውን ዮሐንስን በትኩረት ሳስበው በቤተ ክርስቲያን ያሉ የዋሀን ምእመናንን ይመስለኛል፡፡ በድንግል ማርያም ፍቅር ልባቸው እየነደደ ስምዋን ሲሰሙ ፣ ምስጋናዋን ሲያዩ የሚናገሩት የሚጠፋቸው ፣ እመብርሃንን እየወደዷት ቃላት አሳክተው ስለ እርስዋ ለመናገር ግን አንደበት የሚያጥራቸው ምእመናን ይታዩኛል፡፡ በቅኔ ማኅሌቱ ዳር ቆመው ማኅሌት ሲቆም ለጌታና ለእናቱ ምስጋና ሲቀርብ እንደ ዮሐንስ የሚይዙት የሚጨብጡትን አጥተው በደስታ የሚዘልሉ ፣ አንድም ቃል ከአፋቸው ሳይወጣ በሐሴት የሚሰግዱ ብዙ የዋሃን ምእመናን ትዝ ይሉኛል፡፡
ወዳጄ አንተም ድንግሊቱን ለማመስገን እንደ ዮሐንስ መናገር ካቃተህ ብዙ አትጨነቅ፡፡ መንፈስ ቅዱስን የተመላች እናትህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከኤልሳቤጥ በላይ ለድንግሊቱ የሚሆን ብዙ ምስጋና አላትና ለንግግርህ ሳትጨነቅ በደስታ እየዘለልህ አጅባት፡፡ በእናትህ ቤተ ክርስቲያን ሆድ ውስጥ እንደ ያዕቆብና ኤሳው ለብኵርና እየተጣላህ ሆድዋን መርገጥህን ትተህ እንደ ዮሐንስ ለምስጋናና ስግደት ከተጋህ ቤተ ክርስቲያን ፍቅርህን አይታ ምስጋናን ታስተምርህና እርስዋ 'የጌታዬ እናት አንዴት ወደ እኔ ትመጣለች' እንዳለች አንተም ነፍስ ስታውቅ እንደ ዮሐንስ 'ጌታ ሆይ አንተ አንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?' ብለህ ለመናገር ትበቃለህ፡፡
እዚህ ላይ ለዘጠኝ ወር ዲዳ የነበረው የሊቀ ካህናቱ ዘካርያስን ነገር ሳስበው እጅግ አሳዘነኝ፡፡ ድንግሊቱ በቤታቸው ሦስት ወራት ስትቆይ ዘካርያስም የማገልገሉ ወራት ተፈጽሞአልና በዚያ ነበረ፡፡ ሆኖም የድንግል ማርያምን ድምፅዋን እንዳይሰማ መልአኩ ጆሮውን ዘግቶታል፡፡ የድንግል ማርያም ድምፅ በኤልሳቤጥ ጆሮ ሲንቆረቆርና ዮሐንስን ሲያዘልል ዘካርያስ ግን ከማየት በቀር አምላክን ፀንሳ የመጣችዋን ድንግል ድምፅ ለመስማት አልቻለም፡፡ ስለ እርስዋ ለመናገር እና ገብርኤል እንደነገረው የዘለለው ሕፃን ዮሐንስ ለጌታ መንገድ የሚያሰናዳ መሆኑን እንዳይናገር አንደበቱ ተይዞአል፡፡ የዘካርያስ ሁኔታ ጊዜያዊም ቢሆን እጅግ ያሳዝናል፡፡ በኋላ ግን ተአምረኛው ልጁ 'የሚጮኽ ሰው ድምፅ' የተባለ ዮሐንስ ሲወለድ ስሙን በመጻፍ ብቻ ልሳኑ ተከፍቶለት ከድንግሊቱ መዝሙር ጋር የሚመሳሰል ምስጋናን ቢያቀርብም ድንግል ማርያም ቤቱ በከረመችበት ጊዜ ስለእርስዋ ቤቱ እያለች መናገርም ሆነ እርስዋን መስማትም አለመቻሉ ያሳዝናል፡፡
ዘካርያስስ ተይዞ ነው ፤ የበለጠ የሚያሳዝኑት ግን ስለ ድንግል ማርያም መናገርም ፣ መስማትም የማይወድዱ ሰዎች ናቸው፡፡ የድንግል ማርያምን ድምፅ ሰምተው እንደ ዮሐንስ የሚዘልሉትንና በታላቅ ድምፅ የሚጮኹትን በትዝብት እያዩ ምንም ተሳትፎ የሌላቸው ! ልሳን እያላቸው ስለ ድንግል ማርያምና ልጅዋ የማይናገሩ ፣ ጆሮ እያላቸው ውዳሴዋን የማይሰሙ ሰዎች ግን መልአክ ሳይቀሥፋቸው ራሳቸውን የቀሠፉ ናቸው ብል እንደ መሳደብ ይሆንብኝ ይሆን? ከሆነስ ይቅር፡፡
("የብርሃን እናት" /በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ/ ከሚል የተወሰደ)
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"በተራራማው"
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሰኔ ፴
ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
ሰኔ ሠላሳ በዚህች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ። ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው። በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጐረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው።
በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን አይሆንም ዮሐንስ ይባል አለች። ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም አሏት። አባቱንም ጠቅሰው ማን ሊባል ትወዳለህ አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም 'የልዑል ነቢይ' እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ።
ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው።
ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ።
"የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ" እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እነሆ ብሎ ኢሳይያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለሱ እንዲህ አለ። "በፊትህ ጐዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልእክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ።'
ራሱ መድኃኒታችንም ስለርሱ ሲናገር "ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም" ብሏል። ይህ የእግዚአብሔርን ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና።
ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ፡፡
©ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
እግዚአብሔርን ማሰብ ማለት ሕጉንና ትእዛዙን በቤት ሲቀመጡ፣ በመንገድ ሲሄዱ፣ ሲተኙና ሲነሡም መጫወት ማለት ነው:: ዘዳ6፥4-9 በተጨማሪም ቃሉን በልቡና መያዝና በፍጹም ልብና በፍጹም ነፍስ እግዚአብሔርን መውደድ ማለት ነው:: በዚህ መልኩ ፈጣሪን ማሰብ ይገባል፡፡ ለምን ቢባል? ነቢዩ ዳዊት «እግዚአብሔርን የሚረሱ ይጠፋሉ፡፡›› ብሏልና፡፡
ፈጣሪን ማሰብ ማለት «ሕጉን በቀንና በሌሊት ያስባል›› በማለት ቅዱስ ዳዊት እንደ ተናገረው የእግዚአብሔርን ሕግ በደስታ ማሰብ ማለት ነው:: መዝ1÷2 ተግባር የተለየው ማሰብ ብቻውን ምግባር የተለየው እምነት ሆነ ማለት ነው።ምግባር የተለየው እምነት ደግሞ ነፍስ እንደ ተለየው ሥጋ የሞተ መሆኑ በግልጽ ተነገሯል፡፡ ያዕ1÷26
እግዚአብሔርን ማሰብ ማለት በሥራ በሚገለጥ ነገር እግዚአብሔርን ማክበር ማለት ነው እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አይደለም፡፡ አግዚአብሔርን አስበዋለው ማለት በሥራ ካልተገለጠ ምንም አይጠቅምም፡፡ ሚስት ለባሏ «ሁል ጊዜ አስብሃለሁ እናፍቅሃለሁ ከራሴ አብልጨ እወድሃለሁ» ብትለው ነገር ግን ባሏ ከሚወደው ነገር አንዱንም ባትሠራ «እወድሃለሁ» ማለቷ ብቻ ባሏን ሊያስደስተው ይችላልን? ፈጣሪንም ብዙ ትእዛዛቱን ወደ ኋላ ጥሎ «አስብሃለሁ» ማለት ብቻ ምንም አያስደስተውም፡፡
ሩቅ ሀገር ያለ ወዳጃችንን በደስታው ጊዜ እንኳን ደስ ያለህ በኀዘኑ ጊዜ ደግሞ እግዚአብሔር ያበርታህ ለማለት ካልጣርን በሚያስፈልገውም ሁሉ የማንረዳው ከሆነ «ሁል ጊዜ አስብሃለሁ» ማለት ብቻ ምን ይጠቅመዋል። በዚህ መልኩ መራራቅ የሞት ያህል ነውና ያረሳሳል።ፍቅርንም ያጠፋል እንጂ መተሳሰብም አይባልም፡፡ ፈጣሪንም ቢሆን ጠዋት ማታ ካልጸለዩ፣ ካላመሰገኑት፣ ካልለመኑት፣ ሕጉን ካላከበሩ«አስብሃለው» ቢሉት ጨርሶ በዚህ አይደሰትም።
የያዕቆብ ልጅ ዮሴፍ የጠጅ አሳላፊዎችን አለቃ «ነገር ግን በጎ ነገር በተደረገልህ ጊዜ እኔን አስበኝ» ሲል ምን ማለቱ ነበር? «ምሕረትን አድርግልኝ፥ የእኔንም ነገር ለፈርዖን ነግረህ ከዚህ ቤት አውጣኝ» በማለት በግፍ ከተጣለበት ወኅኒ ቤት እንዲያስወጣው መናገሩ አልነበረም? ዘፍ40፥14 ስለዚህ «በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ›› ማለትም አንድ ተገቢ ነገር ሥራ ማለት ነው እንጂ በሕሊና ፈጣሪህን አሰላስለው ማለት ብቻ እንዳልሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡
ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቀኝ ተሰቅሎ የነበረው ሽፍታ «አቤቱ በመንግሥትህ በመጣ ጊዜ አስበኝ» ሲል ምን ማለቱ ነበር? ጌታ የማያውቀው ሆኖ ራስን ማስተዋቁ ነበርን? ወይስ ፈጣሪ በመጣ ጊዜ «አስበኝ ብለኽኝ ነበር» እንዲለው ብቻ ነበርን? ይቅርታ እንዲያደርግለትና መንግሥቱን እንዲያወርስው መለመኑ እንደ ነበር አያጠራጥርም:: ሉቃ23÷42-43 ታዲያ የ«ማሰብ›› ትርጓሜ እንዲህ ከሆነ «በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ» ሲባልም ሕጉን ጠብቅ፣ ጸልይ፣ አመስግን፣ ማለት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ» በማለት ለለመነው ወንበዴ «እውነት እውነት እልሃለው ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ» ብሎ የመለሰለት መልስ «ማሰብ›› የሚለውን ቃል በሌላ መልኩ እንድናየው ግድ ይለናል:: «አስበኝ» ላለው ወንበዴ «ከእኔ ጋር ትኖራለህ» ካለው ‹‹ማሰብ›› ማለት ከራስ ጋር አብሮ ማኖር የሚል ትርጓሜ እንዳለው ያስረዳል:: ፊያታዊ ዘየማንም (በቀኝ የተሰቀለው ሽፍታም) «አስበኝ» ሲል «ከራስህ ጋር አኑረኝ›› ማለቱ እንደ ነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ከእኔ ጋር ትኖራለሀ» በማለት ከመለሰለት መልስ እንገነዘባለን:: ሉቃ23፥42 43
ከላይ በተሰጠው ሐተታ መሠረት «ማሰብ›› ማለት «ከራስ ጋር ማኖር» ማለት ከሆነ «በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ» ማለት ምን ማለት ሊሆን ይችላል? በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህ ካንተ የማይለይበትን ሥራ አድርግ ማለት ነው፡፡ ማለትም ሰውን ከፈጣሪው የሚለየው ኃጢአት ነውና ከኃጢአት ሽሽ! ኢሳ59፥2 በአንጻሩ ደግሞ መልካም ሥራን ሁሉ አድርግ፡ በደልህን ሁሉ አምነህ ንስሐ ግባና ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀበል። በዚህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሆናል፡፡ ዮሐ6፥56 ይህን ሁሉ አድርገህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ሲሆን «በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ» የሚለውን ትእዛዝ በእውነት የፈጸምክ ትሆናለህ፡፡
አኮቴት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ለዘአፈጸሙኒ በዳኅና ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን!
~ ተፈጸመ~
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"ማርያም ድንግል"
በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሠኔ ፳ እና ፳፩ በእመቤታችን ስም የተሠራች የመጀመሪያዋ ሕንፃ ቤ/ክ እና ቅዳሴ ቤት የእመቤታችን ፪ኤቱ ክብረ በዓላት ታሪክ
በሠኔ ፳ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በፊልጵስዩስ የተሠራችው ሕንፃ ቤ/ክ ትታሰባለች፤ ይኸውም የቤ/ክ ታሪክ እንደሚያስረዳን ጳውሎስና በርናባስ ወደ ፊልጵስዩስ ከተማ ገብተው ባስተማሩ ጊዜ ሕዝቡ “መካነ ጸሎት ለዩልን” ብለዋቸዋል፤ ይኽነንም ለጴጥሮስ በነገሩት ጊዜ ጌታችን የሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን አሠራር እንዲገልጽላቸው ሱባዔ ገቡ፤ ሱባዔውም ሲፈጸም ጌታ ሐዋርያትን የሞቱትን አስነሥቶ ያሉትን ጠርቶ በሕይወተ ሥጋ በፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፨
“በናቴ ስም አብያተ ክርስቲያናት ሊታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ላሳያችኊ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናትን ላስተምራችኊ ሰብስቤያችኋለኊ” ብሏቸው፤ ወደ ምሥራቅ አገር ይዟቸው ወጣ፤ በዚያ በምሥራቅ ሀገር ሦስት ደንጊያዎች ነበሩ ተራርቀው የነበሩትን አቀራረባቸው፤ ጥቃቅን የነበሩትን ታላላቅ አደረጋቸው፤ ቁመቱን ወርዱን ለክቶ ሰጣቸው፤ ቁመቱ 24 ወርዱ 12 ክንድ ነው፡፡
፳፬ቱ የ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ አምሳል ነው፤ ፲፪ቱ የ፲፪ቱ ሐዋርያት ምሳሌ ነው፤ ከዚኽ በኋላ ሥራ ጀመሩ፤ ሲሠሩትም ሰም እሳት ሲያሳዩት እንዲለመልም በእጃቸው ላይ እየተሳበ ሠርተው ፈጽመውታል፤ ይኽ የኾነ እመቤታችን ባረገች በአራተኛው ዓመት በሠኔ ፳ ቀን ነው፨
በሠኔ ፳፩ኛው ቀን ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ መጣ፤ እመቤታችንን ታቦት፤ ሐዋያትን ልኡካን አድርጎ፤ ጌታ ዐቢይ ካህን ኾኖ ቀድሶ አቊርቧቸዋል፤ ከዚያም “እምይእዜሰ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ” (ከእንግዲኽ ወዲኽ እናንተ እንዲኽ ሥሩ) ብሎ አዝዟቸው ዐርጓል፤ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የተጀመረ በቅድስት ድንግል ስም ነው፡፡
ሦስቱ ደንጊያዎች የሥላሴ አምሳል ናቸው፤ ከታች አቀማመጣቸው ፫ ከላይ ሕንፃቸው ፩ ነው ይኽም የአንድነታቸው የሦስትነተኛው አምሳል ነው፤
አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ፡-
“በሠላስ አእባን ገጸ ሥላሴሁ ለአምሮ
ሐኒጸ ቤትኪ ድንግል ድኅረ ፈጸመ ሣርሮ
አመ ወረደ ለበዓል ምስሌኪ በአማኅብሮ
እንዘ ይብላ ቃለ ለዘምሮ
ልዑል ቀደሰ ማኅደሮ
ደናግል ለጽጌኪ ዘበጣ ከበሮ”
(ድንግል በአካል ሦስት መኾኑን ለመግለጽ በሦስት ድንጋዮች ቤትሽን መሥራት ከፈጸመ በኋላ፤ ከአንቺ ጋር ለበዓል በተገለጸ ጊዜ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ እያሉ ልጅሽን ለማመስገን ደናግል በከበሮ ምስጋናን አቀረቡ) በማለት ገልጸዋል፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሠራሯ በሰማያት አምሳል እንደኾነ ሊቃውንት ይተነትናሉ፤ ይኸውም የመጀመሪያዋ ሰማይ “ጽርሐ አርያም” ስትባል ከእሳት ብርሃኗን ነሥቶ ከብርሃን ብርሃንን ጠምቆ አጥርቶ፤ ኹለንተናዋን በብርሃን ቀለም ሸልሟታል “አልቦ ሰማይ ዘይጼልል ላዕሌሃ እስመ መልዕልታዊት ወጽንፋዊት ይእቲ ወኲለንታሃ ብርሃን ፍጹም ዘኢይትነገር በልሳነ ኲሉ ፍጡር ወኲሎሙ ብርሃናት አምሳለ ቀለምጺጸ እሳት በኀቤሃ” ይላል ፤ ብርሃኗን ማንም ከቶ ሊገልጸው አይችልም፤ ከርሷ ብርሃን አንጻር ሲታዩ ሌሎቹ ብርሃናት የእሳት ፍንጣሪ ያኽላሉ፤ ከሰማይ ኹሉ በላይ ስትኾን ከርሷ በላይ ምንም ሰማይ የለም፤ ከዚኽ የተነሣ “ሰማየ ሰማያት” ትባላለች (ዘዳ ፲፥፲፬፤ ፩ነገ ፰፥፳፯)፡፡
ምሳሌነቷን ሊቃውንት በመጽሐፈ ቅዳሴ መቅድም ላይ የሰማይ ሥርዓት በምድር ላይ ስለመሠራቱ ሲተነትኑ በጽርሐ አርያም ውስጥ መንበረ ብርሃን፣ ታቦተ ብርሃን፣ መንጦላዕተ ብርሃን፣ አራቱ ጸወርተ መንበር፣ ኻያ አራቱ ዐጠንተ መንበር ይኖራሉ፤ ጽርሐ አርያም የመቅደስ፤ መንበረ ብርሃን የመንበር፤ ታቦተ ብርሃን የታቦት፤ መንጦላዕተ ብርሃን የመንጦላዕት፤ አራቱ ጸወርተ መንበር የአራቱ ሊቃነ ጳጳሳት፤ ፳፬ቱ ዐጠንተ መንበር የጳጳሳት የኤጲስ ቆጶሳት አምሳል ናቸው፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ሰዓታቱ ላይም “ወኊልቈሙ ለእሙንቱ መላእክት ወሊቃነ መላእክት... ወቡርክት ዛቲ ቤተ ክርስቲያን እንተ አሕዛብ ትመስል ኀይለ ሰማያት” (የእነዚኽ መላእክት የመላእክት አለቆች ቊጥርም መናብርትና ሥልጣናት፣ አጋዕዝትና ኀይላት፣ ሊቃናት፣ ኪሩቤልና ሱራፌል ነው፤ እየጮኹም እንዲኽ ይላሉ የእስራኤል አምላክ ይመስገን የሕዝቡ የአሕዛቡ የምትኾን የተባረከች ቤተ ክርስቲያን የሰማያት ኀይልን ትመስላለች) ይላል፡፡
ሊቁ ሰራዊተ መላእክትን በሚያመሰግንበት በዚኽ ክፍል ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሠራሯና እና አከፋፈሏ በመላእክት ከተማ እና በአሰፋፈራቸው ልክ የተመሰለች መኾኗን አስረግጦ አስተምሯል፡- ይኸውም ሦስቱ የቤተ ክርስቲያን ክፍሎች (መቅደስ፣ ቅድስት፣ ቅኔ ማሕሌት) የሦስቱ ዓለመ መላእክት ምሳሌ ሲኾን ይኸውም መቅደስ የኢዮር፤ ቅድስት የራማ፤ ቅኔ ማሕሌት የኤረር ምሳሌ ናቸው፡፡
ኢዮር በተባለችው ሰማይ ኪሩቤል፣ ሱራፌል፣ ኀይላት ይኖራሉ፡፡ ራማ በተባለችው ሰማይ አርባብ፣ መናብርት፣ ሥልጣናት ይኖራሉ፡፡ ኤረር በተባለችው ሰማይ ሊቃናት፣ መኳንንት፣ መላእክት ይኖራሉ፡፡ እነዚኽ 9ኙ ነገድ የ፱ቱ መዓርጋተ ቤተ ክርስቲያን አምሳል ናቸው፡፡
ይኸውም በኢዮር ከሚኖሩት መላእክት ውስጥ ኪሩቤል የሊቃነ ጳጳሳት፤ ሱራፌል የጳጳሳት፤ ኀይላት የኤጲስ ቆጶሳት አምሳል፡፡
በራማ ሰማይ ከሚኖሩት ነገደ መላእክት ውስጥ አርባብ የቆሞሳት፤ መናብርት የቀሳውስት፤ ሥልጣናት የዲያቆናት አምሳል፡፡
በኤረር ሰማይ ከሚኖሩት ነገደ መላእክት ውስጥ ሊቃናት የንፍቀ ዲያቆናት፤ መኳንንት የአናጒንስጢሳውያን፤ መላእክት የመዘምራን አምሳል ናቸው፡፡
ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ ስለ ክብረ ቤተ ክርስቲያን፦
✍️ “እንተ ተሐንጸት በስሙ፤ ወተቀደሰት በደሙ ወተዐትበት በዕፀ መስቀሉ ጊሡ ኀቤሃ እስመ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ” (በስሙ ታነጸች፤ በደሙም ከበረች፤ በዕፀ መስቀሉም ተባረከች፤ ወደ ርሷ (ቤተ ክርስቲያን) ኺዱ የእግዚአብሔር ኀይል በርሷ ላይ ነውና) ይላል፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ተአምኆ ቅዱሳን በሚባለው ታላቅ መጽሐፉ ላይ፡-
“ሰላም ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማኅደረ ስብሐት ምዕዋደ መላእክት እመ ኲሉ ሕዝብ” (የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ (ቦታ) የምስጋና ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ይገባል) ብሏታል፡፡
ይኸው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ በተመሳሳይ መልኩ እናትነቷን በሰባቱ ጊዜያት የሕማማት ሰላምታው ላይ፡-
“ሰላም ለኪ ቤተ ክርስቲያን እምየ ዘትጼንዊ መጽርየ ብኪ ጸናዕኩ እምከርሠ እምየ
ቤተ ክርስቲያን አክሊለ ርእስየ ሰላም ለኪ”
(እንደ ቀጋ የምትሸትቺ ቤተ ክርስቲያን እናቴ ሰላምታ ለአንቺ ይገባል፤ ከእናቴ ማሕፀን ዠምሮ በአንቺ ጸናኊ፤ የራሴ አክሊል የምትኾኚ ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ለአንቺ ይገባሻል)
“በሐኪ በሐኪ ቤተ ክርስቲያን እምነ
ግበሪ ሰላመ ማእከሌነ እምኀይለ ጸላኢ ወፀር ዕቀቢ ኪያነ ትንብልናኪ የሀሉ ምስሌነ፤ ሰላም ለኪ”
(ሰላምታ የተገባሽ እናታችን ቤ/ክ ሰላም ሰላም እንልሻለን፤ በመኻከላችን ሰላምን አድርጊ፤ ከፍጹም ጠላት እኛን ጠብቂ፤ ልመናሽም ከእኛ ጋራ ይኹን) በማለት እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አወድሷል፡፡
በተጨማሪም ሠኔ ፳፩ ቀን ቅድስት ድንግል ማርያም በጎልጎታ ቃል ኪዳን መቀበሏም ይታሰባል።
የቅድስት ቤተ ክርስቲያን በረከት ይደርብን፡፡
በመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሕይወተ ወራዙት (የወጣቶች ሕይወት)
ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ክፍል ሦስት
.................................................
➺ስኬታማነት
ወጣት ከሆንክ ቢያንስ አንድ ነገር እንዴት እንደሚሳካልህ ሳያስጨንቅህ አይቀርም::የምታሰበው ሁሉ እንዲፈጸምልህና ስኬታማ ሰው እንድትሆን ትፈልጋለህ? ከፈለግህ በመጀመሪያ በሕይወትህ መንፈሳዊ ሰው ሁን፡፡ የስኬት መሠረት መንፈሳዊነት ነውና፡፡ እንዲህ ሳትሆን ብዙ ነገር ቢሳካልህ እንኳን ተመልሶ እንዳልተወጠነ ሊሆን እንደሚችልና ውሸት እንደ ሆነ አስብ፡፡
ማንም ሰው ደስተኛና ስኬታማ ሆኖ መኖር ይፈልጋል:: ወጣቶችም ይህን መፈለጋቸው መልካም ነገር ነው፡፡ ስኬታማ ዕድሜን ያረዝማል፣ በተስፋ፣ በጥንካሬ ያቆያል፡፡ መቸገር፣ ማጣትና ማዘን ግን ያለጊዜው ያስረጃል፡፡ ደራሲው «እንበለ ጊዜ በላህ ኢይርሳዕ ወሬዛ» እንዳለ «ያለ ጊዜዬ በኀዘን ምክንያት እንዳላረጅ›› ለማለት ነው:: (መልክዐ ሚካኤል) ሆኖም ግን ደስተኛና ስኬታማ ለመሆን መታወቅ ያለባቸው ብዙ ነገሮች አሉ።
ፍሬያማ ግብር (ስኬት) ማለት ሰው በሥጋዊ ሕይወቱ ተጨባጭ የሆኑ ነገሮችን ማግኘቱ ብቻ አይደለም:: የሰው መንፈስም (ነፍስም) የምትመኘው ብዙ ነገር አላት፡፡ የነፍስ ምኞቶች በሙሉ እንደ እርስዋ ረቂቃን ናቸው:: የነፍስ ምኞቶች ሐዋርያው «የመንፈስ ፍሬዎች» በማለት የገለጣቸው ሲሆኑ እነርሱም:- ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃትና ራስን መግዛት ናቸው:: ገላ5÷22 ሰው ስንል ነፍስም ሥጋም እንደመሆኑ መጠን በሥጋ የሚመኛቸው ግዙፋን ነገሮች ስለተሟሉለት ብቻ ደስተኛና ስኬታማ ሊባል አይችልም፡፡ ክላይ የተጠቀሱት «የመንፈስ ፍሬዎች›› የሌሉት ሰው ስኬታማ አይደለም።
ሕይወተ ወራዙት (የወጣቶች ሕይወት)
ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ክፍል ኹለት
.................................................
➺«ኀፊረ ገጽ»
እግዚአብሔር በሰው ልጆች መካከል መተፋፈር እንዲኖር አድርጓል:: ይልቁኑም «ወከደና በኀፍረት» እንደ ተባለው ሴቶች በማፈር እንዲያሸበርቁ ልዩ መጐናጸፊያ ሰጥቷቸዋል፡፡
«ኀፊረ ገጽ» ማለት የሌላውን ሰው ገጽ አይቶ መፍራትና ማፈር ማለት ነው:: ይህ እጅግ ውድ ስጦታ ነው:: በመፍራት ውስጥ ማክበር በማክበር ውስጥ ደግሞ መፍራት እንዳለ ሁሉ በማፈርም ውስጥ ማክበርና መፍራት አሉ፡፡ ሰውን የማይፈራ እግዚአብሔርንም አይፈራም ለማለት ያስደፍራል፡፡ ምክንያቱም ሰውን መፍራት እግዚአብሔርን የመፍራት መገለጫ ነውና፡፡ 1የሐ3÷17
ቅዱሳት መጻሕፍት መፍራትና ማፈር የማያውቅ ደረቅ ሰውን ያወግዛሉ:: ማር ይስሐቅ ከሌላ መጽሐፍ ያገኘውን «ዘኢየኃፍር ገጸ ከይሲ ውእቱ ዘይሴሰይ መሬተ» ፤ «የሰውን ገጽ አይቶ የማያፍር አፈርን እንደሚበላ እባብ ነው» ማለት ነው::
ቅዱሳን አበው የሃይማኖት ዓይን ስላላቸው እንኳን በአካል ገዝፎ በአጠገባቸው የሚገኝ ሰውን ይቅርና የሚጠብቃቸውን መልአክ በማፈር ከማያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ ተጠንቅቀው ይኖሩ ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ ጠባቂ መልአካቸውን በማፈር ለብቻቸው ሳሉ እንኳን ከልብስ ተራቁቶና ተገላልጦ ዘና ማለት የማይሆንላቸው እንደ ነበሩ ዜና ሕይወታቸው ይናገራል።
ሕይወተ ወራዙት (የወጣቶች ሕይወት)
ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ክፍል አንድ
.................................................
➺ «መልካም ስም»
ጠቢቡ ሰሎሞን ስለ ስም ሲናገር «ከመልካም ሽቶ መልካም ስም ይሻላል» ብሏል። መክ 7፥1 እግዚአብሔር ስምን የብዙ ነገሮች ምልክት አድርጎታል፡፡ ስም መብት፣ ክብር፣ ገንዘብ፣ መርዳት፣ ችግር፣ ውድቀት፣ ሲሆን ለማየት በዙሪያህ ያሉትን ነገሮች መመርመር ብቻ በቂ ነው።ምንም የሚያስከብር ነገር ላይኖራቸው በቀደመ ማንነታቸው ብቻ ሰዎች ሲከበሩ አይተህ አታውቅም?በስም ብቻ ገንዘብ የሚገኝበት ሁኔታስ ገጥሞህ አያውቅም?
ነገር ግን ብዙ ወጣቶች «መልካም ስም» ያለውን ከፍተኛ ዋጋ አያውቁም፡፡ እንዲህ የሚያስብለው ስማቸውን በክፉ የሚያጠፋ ርካሽ ተግባር ዘወትር ሲፈጽሙ መገኘታቸው ነው።መጥፎ ነገሮች ምን ጊዜም ክፉ ስም ያስገኛሉ።በሥውርና በድብቅ ቢፈጸሙ እንኳን ከጥቂት ቆይታ በኋላ በአደባባይ መውጣታቸው የማይቀር ነው።«ድብቁን የምትገልጽ የውስጡን ወደ ውጭ የምታወጣው ሆይ» የሚባል እግዚአበሔር ሥራውን አይዘነጋምና።
መልካም ስም ከመልካም ሽቶ ጋር የተነጻጸረው ያለ ምክንያት ኣይደለም። መልካም ሽቶ ርቆ ሄዶ ከመሽተቱም በላይ ስሜትን ይማርካል፣ ይስባልደ መልካም ስምም አንተ ካላሰብከው ቦታ ደርሶ ያሳውቅሃል፣ ያስወድድሃል፡፡ክፉ ስም ደግሞ እንደ ክፉ ሽታ ነው።ያ ከሩቅ መጥቶ እነደሚበክል ተደብቆ የተሠራም ክፉ ሥራ ርቆ ሄዶ ስምን ይበክላል፡፡ ስለዚህ በዘመንህ ሁሉ ከቁሳዊና ከብልጭልጭ ነገሮች ይልቅ ጥሩ ስም እንዲኖርህ ተጣጣር፤መልካም ስም ካለህ የተመኘኸውን ሁሉ ሳታገኝ አትቀርምና። መልካም ስም የመልካም ሥራ ነው እንጂ የፈጠራና የማስመሰል ውጤት አይደለም።
"ቅዱስ ላሊበላ"
በገርጂ ጊዮርጊስ የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox