በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
አመ ፳ወ፮ ለመስከረም ዘቀዳማይ ጽጌ በዓለ ቶማስ ወሀብተማርያም ማኅሌት
ለማንኛውም ወርኃዊ እና ዓመታዊ ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
.....................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም።
ዚቅ፦
ለሥሉስ ቅዱስ ጥዑም ቃሎም፤ናርዶስ ጸገየ ዉስተ አፍሆሙ፤
መግቢያ ዘማኅሌተ ጽጌ
ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት፤ተሠርገወት ምድር
(🌹#በህብረት_ሁሉም🌹)
በስነ ጽጌያት፤ለመርዓዊሃ ትብሎ መርዓት፤ወልድ እኁየ ወረደ ውስተ ገነት።
ማኅሌተ ጽጌ፦
ጽጌ አስተርአየ ሠሪጾ እምዓጽሙ፤ለዘአምኃኪ ጽጌ ለገብርኤል ምስለ ሰላሙ፤ወበእንተዝ ማርያም ሶበ ሐወዘኒ ጣዕሙ፤ለተአምርኪ አኀሊ እሙ፤ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ፡፡
ወረብ
መዓዛ ጣዕሙ ለተአምርኪ ሶበ ሶበ ሐወዘኒ/፪/
ወበእንተዝ ማርያም አኅሊ ለተዓምርኪ/፪/
ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ናሁ አስተርአየ ጽጌ መርዓቱኒ ትቤ ወልድ እኁየ ይምዕዝ ከርቤ፤ ዕንባቆም ነቢይ ግብረ ምግባሩ ለወልድ አንከርኩ ይቤ፤ ንጉሠ ሰላም ክርስቶስ ዓቢይ ልዕልናከ ወመንክር ስብሐቲከ፤ለዕረፍት ሰንበት ሠራዕከ፤
ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፣ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ
ወረብ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ /፪/
አመ ቤተ መቅደስ ሠናይትየ ሠናይትየ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ/፪/
ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ፤እንተ ሐዋርያት ይሴብሑኪ፤መላእክት ይትለአኩኪ፣ፃዒ እምሊባኖስ ስነ ሕይወት
ማህሌተ ጽጌ
ጽጌኪ ማርያም ኮነኒ ሲሳየ ወአራዘ፤ወጸግወኒ እምትካዝ ተአምረኪ መናዝዘ፤ቶማስ ሎቱ አመ ገቦሁ አኃዘ፤እንዘ ይብል ከርቤ እምእዴየ ውኅዘ፣ረከበ በውስተ ቁስሉ አፈወ ምዑዘ
ወረብ-
አመ ገቦሁ ቶማስ ሎቱ አኃዘ/፪/
እንዘ ይብል ከርቤ እምእዴየ ውኅዘ ረከበ አፈወ ምዑዘ/፪/
ዚቅ-
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወልድ እኁየ ፈነወ ዕዴሁ እንተ ስቊረት፤ለከፎ ሶቤሃ ርስነ መለኮት
ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ/፪/
ዚቅ
ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት፤ ወስብሕት በሐዋርያት፤አክሊለ በረከቱ ለጊዮርጊስ፤ ወትምክህተ ቤቱ ለ፳ኤል።
ሰቆቃወ ድንግል
በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ ሕፀተ ግጻዌ ዘአልቦ፤ሰቆቃወ ድንግል እጽሕፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ፤ወይሌ ወላህ ለይበል ዘአንቦ፤ከማሀ ኀዘን ወተሰዶ ሶበ ለኩለሄ ረከቦ፤ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ
ወረብ፦
ከማሀ ኀዘን ከማሀ ኀዘን ወተሰዶ ኀዘን/፪/
ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ ዓይነ ልብ ዘቦ/፪/
ዚቅ፦
እወ አማን እምውሉደ ሰብእ አልቦ፤ምንዳቤ ወግፍዕ ዘከማኪ በዉስተ ኩሉ ዘረከቦ፤
መዝሙር ፦
በ ፬
ትዌድሶ መርዓት ፤ እንዘ ትብል ነዐ ወልድ እኁየ ፤ ንፃእ ኀቅለ ፤ ት ፡ ንርአይ ለእመ ጸገየ ወይን ፤ ወለእመ ፈረየ ሮማን ፤ ት ፡ አሰርገወ ሰማየ በከዋክብት ፤ ወምድረኒ በሥነ ጽጌያት ፤ ት ፡ እስመ ውእቱ ወልድ ዋሕድ ፤ እግዚኣ ለሰንበት ፤ ትዌድሶ መርዓት ወትብሎ ፤ ወልድ እኁየ ቃልከ አዳም ።
አመላለስ፦
ትዌድሶ መርዓት ወትብሎ/፪/
ወልድ እኁየ ቃለከ አዳም/፬/
©ያሬዳውያን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
እኔ አላዝንም
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
💠የመንፈስ ፍሬዎች💠
፮.በጎነት
✞ በጎነት ለራስም ለሌላውም መልካም መሆን ነው። ደግነት እና ቅንነት ይመሳሰሉታል። ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ሲባል ለመልካም ነው ለማለት ነው። የመልካምነት መለኪያው የእግዚአብሔር ቃል ነው። አንድ ሰው በጎ የሚባለው እንደ እግዚአብሔር ቃል ሲኖር ነው። በሌሎች ሰዎች ክፉ አለማድረግና ለሌሎች ሰዎች መልካም
ማድረግ በጎነት ነው። ስለሌሎች ሰዎች ጥሩ አስተያየት አነጋገር ካለው በጎ ነው ይባላል። ብናጠፋ፣ ብንበድል እንኳ እግዚአብሔር ፈጥኖ አያጠፋንም። ለእኛ በጎ ስለሆነ የንሥሓ እድሜን ይሰጠናል። እንዲህ ከሆነ ታድያ አንዳንድ ክፉዎችን እግዚአብሔር ፈጥኖ የሚያጠፋቸው ስለምንድን ነው? ቢባል ቢቆዩ ኃጢዓትን
አብዝተው ስለሚሰሩ በሰማይም ፍዳቸው ይቀንስ ዘንድ ቶሎ ያጠፋቸዋል። አንዳንድ መልካሞችንስ ወዲያው የሚያጠፋቸው ለምንድን ነው? ከተባለ ከቆዩ ኃጢዓት ሊሰሩ ይችላሉና። በአሁኑ ጽድቃቸው ዋጋቸውን ለመስጠት ነው። አንዳንድ መልካሞች ብዙ ዘመን ይቆያሉ ለምንድን ነው? ከተባለ ለክብር የሚያበቃቸውን
ሥራ አብዝተው ይሰሩ ዘንድ እና ለኃጥዓን ተግሣጽ ይሆኑ ዘንድ ነው። አንዳንድ ክፉዎችን ደግሞ ብዙ ያቆያቸዋል ለምንድን ነው? ቢሉ የሰሯት መልካም ሥራ ካለች እርሷን በዚህ ምድር በድሎት እንዲኖሩ አድርጎ በሰማይ ፍዳቸው ይበዛ ዘንድ ነው። አንዳንድ ኃጢዓተኞች በዚህ ምድር ደስተኛ ሆነው ይኖራሉ አንዳንድ ኃጢዓተኞች ደግሞ በዚህ ምድር በመከራ ይኖራሉ ለምንድን ነው? ከተባለ። በዚህ ምድር ደስተኛ የሆኑት እንደ ነዌ በሰማይ ፍዳቸው የሚበዛ ሰዎች ናቸው። በዚህ ምድር ኃጢዓተኛ ሆነው በመከራ የሚኖሩት ደግሞ የኃጢዓታቸውን ፍዳ ጥቂቱን በዚህ ምድር ስለተቀበሉ በሰማይ ይቀልላቸዋል።ድኃው አልዓዛር በዚህ ምድር ለምን ተሰቃየ ቢሉ ምንም እንኳ ጻድቅ ቢሆን ሰው ከድንግል ማርያም በስተቀር ጽነት አያጣውምና ለዚያ ፍዳውን በዚህ ምድር ተቀብሎ በሰማይ ዋጋው ይበዛለት ዘንድ ነው። ሰው በዚህ ምድር እስካለ ድረስ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ስለማያውቀው ሁልጊዜም ለሁሉም ሰው በጎ ሊሆን ይገባል። አንዳንዱን በደለኛ እግዚአብሔር ወዲያው ይቀስፈዋል ለምን ቢሉ በሕይወተ ሥጋ ላሉት ምሳሌ ይሆን ዘንድ ነው። አንዳንዱን በደለኛ እግዚአብሔር በዚህ ምድር ያቆየዋል ለምን ቢሉ ንሥሓ ይገባ ዘንድ ነው። በማንኛውም ጊዜ በማንኛውም ቦታ በማንኛውም ሁኔታ በጎ እንሁን።
👉'እምነት' ይቀጥላል ..........
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"ቸርነትን አድርግ"
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
" እሰይ አበራ መስቀሉ " ዘማሪት ትርሃስ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
Enjoy our content? Advertise on this channel and reach a highly engaged audience! 👉🏻
It's easy with Telega.io. As the leading platform for native ads and integrations on Telegram, it provides user-friendly and efficient tools for quick and automated ad launches.
⚡️ Place your ad here in three simple steps:
1 Sign up
2 Top up the balance in a convenient way
3 Create your advertising post
If your ad aligns with our content, we’ll gladly publish it.
Start your promotion journey now!
+ቅዱስ ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: (መዝ. 59:4)
+በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት:: ስለዚህም " መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም: መሠረተ ቤተ ክርስቲያን" ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::
+ ቅዱስ ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን ይነግረናል:: ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስም ስለ መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን ነውና:: (1ቆሮ. 1:18, ገላ. 6:14)
+አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል:: የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ: የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ: ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ በወዴት አለና::
+ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን: እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት: ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን ተሻግረዋል::
+በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ ምስክርን አንፈልግም::
+"+ በዓለ_መስቀል +"+
በሃገራችን ኢትዮጵያ መስቀልን በሚመለከት ከሚከበሩ በዓላት ውስጥ የደመራ መስቀል በዓል /መስከረም 16ና 17/ እንዲሁም መጋቢት 10 የመስቀለ ኢየሱስ በዓል ተያያዥነት ያላቸውና ዋነኞቹ ናቸው፡፡ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ከጌታችን ሞትና ትንሣኤ በኋላ በቀራንዮ አደባባይ ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ጌታችንን የገነዙት #ዮሴፍና #ኒቆዲሞስ ከቀራንዮ ወደ ጎልጎታ (ጌታችን ተቀብሮባት ወደነበረው መካነ መቃብር) ወስደው አኑረውታል፡፡
አበው ሐዋርያት ወደየሀገረ ስብከታቸው ሲሄዱ የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ሐዋርያው #ያዕቆብ በኃላፊነት እንዲጠብቀው አድርገዋል፤ ከየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱም በእግረ መስቀሉ ሥር እየተሰበሰቡ ይጸልዩ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያምም ጠዋትና ማታ በመስቀሉ ሥር ትጸልይ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ታሪኩንና ቦታውን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን ክቡር መስቀሉን ለማየት ያመኑትም በረከት ለማግኘት ከየአቅጣጫው ይመጡ ነበር፡፡ በመስቀሉ ተዓምራት ብዙዎች ከተለያዩ ደዌ /በሽታ/ ተፈውሰዋል፡፡ ይህም በጣም ብዙ ሰዎች ክርስቶስን ወደ ማመን ስቧቸዋል፡፡ ይህን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ የክርስቶስ ሰቃዮች /ሰቃልያነ ክርስቶስ/ በሁኔታው ባለመደሰታቸው ሕይወት የሆነውን የጌታ መስቀሉን ከጎልጎታ አንስተው ቀብረውት #ለ300 ዓመታት ያህል የከተማው ጉድፍና ጥራጊ እየጣሉበት የተቀበረበት ቦታ ኮረብታ እስኪሆን ድረስ ቆይቷል ‹‹በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ፤ መስቀልከ ዕፀ ሕይወት፥ ዕፀ መድኀኒት›› እንዲል፡፡ ሆኖም #በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ለክርስቲያኖች ነፃነት የሚያስብና የሚያስከብር ንጉሥ በሮም ተነሣ፡፡ የንጉሡም ስም ቈስጠንጢኖስ ይባል ነበር፡፡ ይህ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እንዲወድ ያደረገው በጠላቱ በማክሴንዲዩስ (መክስምያኖስ) ላይ በዘመተበት ጊዜ ገና በጉዞ ላይ እያለ ‹‹በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀርከ (በዚህ የመስቀል ምልክት ጠላትህን ድል ታደርጋለህ)›› የሚል በመስቀለኛ ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ በጠፈር ሰማይ አይቶ በመስቀል ምልክት #ድል በማድረጉ ነው፡፡
የንጉሥ #ቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት #እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባት፥ ታሪኩ በውስጧ የሰረጸባት ቅድስት እናት ነበረች ቈስጠንጢኖስም በዘመነ መንግሥቱ በትዕምርተ መስቀል ብዙ የድል ሥራ ስለሠራ ለመስቀሉ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ነበረው፡፡ ንግሥት እሌኒም መስቀሉን ለማግኘት ሰው ብትጠይቅ የሚያውቅ አላገኘችም፡፡ በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመሆኑ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊና መቃርስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ አገኘች፡፡ ከእነዚህም አረጋዊው ኪራኮስ ዕድሜው የሸመገለና በእስራኤል ባህልና ደንብ ያደገ ነበር፡፡ እሌኒም እሱን ጠይቃ መስቀሉን ለማግኘት እንዲተባበራት ጠየቀችው ሆኖም ሊተባበራት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ረሃብና ጽም ስታበዛበት ግን የረሃብና የጽሙን መጽናት ተመልክቶ ከእነዚህ ከሦስት ተራሮች አንዱ እንደሆነ ነገራት፤ ከሦስቱ ተራራ የትኛው እንደሆነ ለማወቅ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሱባኤ እንድትይዝ ነገራት፤ ሱባኤም ያዘች፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር #መልአኩን ልኮ እንዲህ አላት ‹‹አንቺም ሰውም በከንቱ አትድከሙ እንጨት አሰብስበሽ፥ ደመራ አስደምረሽ፥ በእሣት አያይዘሽ፥ በፍሕሙ ላይ ዕጣን አፍስሽ፤ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን ተመልክተሽ ጢሱ ያረፈበትን ቦታ አስቆፍሪው›› አላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንዳላት እንጨት አሰብስባ #ደመራ አስደመረች ዕጣንም አፈሰሰችበት #ጭሱም ሰማይ ደርሶ ቅድመ ሥላሴ ሰገዶ ወደ ምድር ሲመለስ ቦታውን አመለከታት ይህም የሆነው #መስከረም_16 ቀን ነው፡፡ እኛ ደመራ ብለን የምናከብረው ይህን አብነት በማድረግ ነው፡፡
+"+ ቅዱስ_አውዶኪስ_ቀሲስ +"+
=>ይህ ቅዱስ ሰው ለቅዱስ መስቀሉ ከነበረው ፍቅር የተነሳ በብዙ ድካም ወደ #ኢየሩሳሌም በእግሩ ተጉዞ ነበር:: ከብዙ መንገደኞች ጋር በጐዳና ላይ ሳሉ ታዲያ አንድ አይሁዳዊ (ሰማርያዊ) ተቀላቀላቸው:: በወሬ በወሬ የት እንደሚሔዱ ሲጠይቃቸው "መካነ መስቀሉን ለመሳለም ወደ #ጐልጐታ ነን" አሉት::
+እሱ ግን ከት ብሎ ስቆ "እንዴት እንጨት ትሳለማላችሁ" በሚል አፌዘባቸው:: የፀሐዩ ሐሩር እጅግ ጠንቶ ነበርና ቅዱስ አውዶኪስ ኃይለ መስቀሉን ሊያሳይ ወደደ:: በመንገድም መርዝነት ያለው ውሃ ነበርና ቅዱሱ ቀርቦ ጸልዮ በመስቀሉ ባረከውና ፈጥኖ ወደ ጣፋጭነት ተቀየረ::
+ምዕመናኑ ደስ ብሏቸው ሲጠጡ ያ አይሁዳዊ 'እጠጣለሁ' ብሎ ቢቀርብ ወደ ነበረው ተመለሰበት:: 'በኮዳ የያዝኩትን እማልጠጣ' ብሎ ቢከፍተው ደግሞ ተልቶ አገኘው:: እጅግ ደንግጦ አለቀሰ:: በጣም ጠማው: ግን ምኑን ይጠጣ!
+አማራጭ ሲያጣ ወደ ቅዱስ አውዶኪስ ሒዶ እግሩ ላይ ወድቆ አለቀሰ:: በመስቀሉ ቢማጸን መራራው ጣፈጠለት:: በዚህ ምክንያትም ወደ ክርስትና ተመልሷል:: ቅዱሱ በመልካም ሽምግልና ሲያርፍ ውሃው የተቀየረበት ቦታ ላይ ቤተ መቅደስ ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል::
+"+ ቅድስት ታኦግንስጣ +"+
=>በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረችው ሮማዊቷ እናት መንገድ ላይ ቁማ ወንጌል ስታነብ በንጉሥ ወታደሮች ተማርካ ወደ ሕንድ ተወስዳለች:: በዚያም በመስቀል አማትባ ሙት በማስነሳቷ የሃገሩ ሰው ወደ ክርስትና ከነ ንጉሡ ተመልሰዋል:: እርሷም ገዳም አንጻ: ደናግሉን ሰብስባ በንጽሕና ኑራለች:: በዚህ ቀን ዐርፋ ሲቀብሯት የብርሃን መስቀል መቃብሯ ላይ ተተክሏል::
=>አምላከ ቅዱሳን በኃይለ መስቀሉ: በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን:: ከበረከቱ አሳትፎ በዓሉን የሰላም ያድርግልን::
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"አላማርርህም"
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"እውነተኛ ሰላም"
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል"
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ተቃውሞ አዲስ ዘመቻ ተጀምሯል። ቻናላችን ትግሉን ከአምስት ዓመታት በፊት ነበር የጀመረው።
👇👇
/channel/Ethiopian_Orthodox/490
💠የመንፈስ ፍሬዎች💠
✝️ "የመንፈስ ፍሬ ግን:ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።"ገላ 5÷22
፩.ፍቅር
✞ በክርስቲያናዊ ሕይወት ከሁሉም የመንፈስ ፍሬዎች የሚቀድመውና የሚበልጠው የመንፈስ ፍሬ ፍቅር ነው።ምክንያቱም፤ ፍቅር የእግዚአብሔር ባሕርይ ስለሆነ ነው 1ዮሐ. 4:16 ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ ስለሆነ ነው ሮሜ. 13.8 ማር. 12:28
✞ የእግዚአብሔር ቃል ይህንን ሲያስረዳ እንዲህም ከሆነ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር፣ እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፡፡ ከነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው ይላል 1ቆሮ.13:13፡፡ በሌላ ክፍል ፍቅርን “የፍጻሜ ማሰሪያ”ብሎታል ቆላ.3:14፡፡ ስለዚህ ክርስቲያኖች ከሁሉ የሚበልጠው ይህ የመንፈስ ፍሬ እንዲታይባቸው እግዚአብሔርንም ሰውንም ከልብ ሊያፈቅሩ ይገባቸዋል፡፡ ሌሎቹን የመንፈስ ፍሬዎች ከማሰባችን በፊት ፍቅር ሊኖረን ፍቅርን ልንከታተል ያስፈልጋል 1ቆሮ.14:1፡፡
✞ ፍቅር የአንዱን ድካም አንዱ ሲሸከም ነው። ሰማዕትነት የሌለበት ፍቅር ፍቅር አይባልም። በአፍ ብቻ እወድሃለሁ እወድሻለሁ ማለት ውሸት ነው። ይህንንስ ባላገሩ "የአፍ ዘመድ ከገበያም አይገድ" ብሎ ተርቶበታል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሐ. ፲፭፣፲፫ "ነፍሱን ስለወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" ብሎ የፍቅርን ትርጓሜ አስተማረን። ፍቅር በአፍ የሚናገሩት ብቻ አይደለም በሕይወት የሚኖሩትም ነው እንጂ። ለዚያም ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን በቃል ከተናገረ በኋላ በተግባር ደግሞ አዳምን ለማዳን በመስቀል የተሰቀለ። መስቀል ፍቅር በተግባር የተገለጠበት አደባባይ ነው። ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት ብሎ ሊቁ የገለጠው ይህንን ነው። ፍቅር ራሱ እግዚአብሔር ነው። ፩ኛ ዮሐ.፬፣፰-፳ "ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም እግዚአብሔር ፍቅር ነውና----ማንም እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው" ይላል። ይህ የሚነግረን በፍቅር ጥላቻ እንደሌለ ነው። ፍቅር ሌላውን እንደ ራስ መውደድ ነው። ማቴ. ፯፣፲፪ "ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው" ተብሎ እንደተጻፈ ሰውን መውደድ በእኛ ሊደረግብን የማንፈልገውን በሌላውም እንዲደረግ አለመፈለግ ሲሆን እግዚአብሔርን መውደድ ደግሞ ትእዛዙን በመፈጸም ይገለጣል።ዮሐ. ፲፬፣፳፩ "ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው" እንዲል።
✞ ማቴ. ፯፣፳፩-፳፫ "በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ይሉኛል። የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም እናንተ አመፀኞች ከእኔ ራቁ ብየ እመሰክርባቸዋለሁ" እንዲል የጌታን ስም ብዙ ጊዜ ብትጠራ፣ በስሙ ተአምራትን ብታደርግ፣ በስሙ ትንቢትን ብትናገር፣ በስሙ አጋንንትን ብታወጣ ይህ የፍቅር ምልክት ተደርጎ አይያዝም። እግዚአብሔርን የመውደድ ዋናው ምልክቱ ፈቃዱን መፈጸም ነው። ፈቃዱ ምንድን ነው ከተባለ ዘጸ. ፳፣፩ ጀምሮ ያሉ አስሩን ሕግጋት መፈጸም ነው። ማቴ. ፲፱፣፲፯ "ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ" እንዳለ። ዮሐ. ፲፪፣፶ "ትእዛዙም የዘለዓለም ሕይወት እንደሆነች አውቃለሁ"እንዲል።
✞ ቅዱስ ጳውሎስ ፍቅርን ጠቅለል አድርጎ ሲያቀርበው እንዲህ ብሎታል። ፩ኛ ቆሮ. ፲፫፣፪-፰ " ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድኾችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሣል፣ ቸርነትንም ያደርጋል፣ ፍቅር አይቀናም፣ ፍቅር አይመካም፣ አይታበይም፣ የማይገባውን አያደርግም፣ የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ በደልን አይቆጥርም፣ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለዓመፃ ደስ አይለውም። ሁሉን ይታገሣል፣ ሁሉን ያምናል፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም" ብሎ ገልጾታል።
👉'ደስታ' ይቀጥላል ...........
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"አክሊለ ጽጌ"
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
“ጽጌ መዓዛ ሠናይ”
🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ያለውን ወቅት ወርኃ ጽጌ ትለዋለች። ወርኃ ጽጌ የእመቤታችን ስደት የሚታሰብበት ወቅት ነው። ስደት አድካሚ ጉዞ አለው። ረኀብና ጥምም መገለጫው ነው። ጠቢቡ "እነሆ ክረምት ዐለፈ ዝናቡም አልፎ ሔደ፤ አበቦችም በምድር ላይ ተገለጡ፤ የዜማም ጊዜ ደረሰ፤ የቁርዬም ቃል በምድራችን ተሰማ" (መኃ. ፪÷፲፩-፲፪) ብሏል። “ክረምት ዐለፈ” ያለው የአዳም የመከራ ዘመን ማለፉን ሲናገር ነው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድም እመቤታችንን መዓዛ ባላቸው ጽጌያት መስሎ "መዓዛሆሙ ለቅዱሳን " ብሏታል።
አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፈ ምሥጢር" አዳም እንኳን ተሳሳተ ፣አዳም እንኳን ወደቀ በገነት ውስጥ ቢኖር ኑሮ አዳም ከሔዋን ጋር ዕፀ-ሕይወትን እየበላ ይኖር ነበር እንጂ እኛ አናገኛትም ነበር።፣አዳም ባይሳሳት ኑሮ አንቺ አትወለጅም ነበር። ስለዚህ በገነት የተነፈግነውን ዕፀ-ሕይወት አንቺ ሰጥተሽናልና እናመሰግንሻለን” ብሏታል።
ቅዱስ ዮሐንስ "ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ፤ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች። እርስዋም ፀንሳ ነበር፤ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች። ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት፤ በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ"(ራእ. ፲፪÷፫) ብሏል። ፀሐይ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ በቀንም፣ በሌሊትም የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን ነው። ፲፪ የክብር አክሊል የተባሉት ፲፪ ሐዋርያት ናቸው። ቅዱሳን ሐዋርያት ለድንግል ማርያም ጌጦች በመናቸው አክሊል አላቸው። ድንግል ማርያምም ለሐዋርያት ጌጣቸው ናት። "ሞገሶሙ ለሐዋርያት" እንዲል ቅዳሴ ማርያም። በጨረቃ የተመሰለው ዮሐንስ መጥምቅ ነው። ጨረቃ ሠርቅ ካደረገችበት ጀምሮ ብርሃኗ እየጨመረ በ፲፭ኛው ቀን ሙሉ ትሆናለች። ቅዱስ ዮሐንስም አንገቱን ከተቆረጠ በኋላ ፲፭ ዓመት አስተምሯል። ጨረቃን ተጫምታ ነበር ማለት ዮሐንስ ገና ከእናቱ ማኅፀን ሁኖ ለድንግል ማርያም ሰገደ ማለት ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ "ምጥ" ያለው ድንግል ማርያም የገጠማትን ጭንቅ ነው። ቅዱስ አትናቴዎስ " ያለ ዘር ፣ያለ ምጥ ወለደችው" (ሃይ.አበው ምዕ•፳፰ ክ፲፬ ቊ ፲፱) በማለት የወለደችው ያለ ምጥ መሆኑን ተናግሯል። እመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሦስት ነገሮች ብትጨነቅም ክርስቶስን ስለመውለድ አልተጨነቀችም። ድንግል ማርያም የተጨነቀችው ልጇ በቀራንዮ በተሰቀለ ጊዜ፣ ስለ ኃጥአን ለመከራ መዳረግ እና የሦስት ዓመቱ የግብፅ በረሃ ስደቷ ያስጨንቃት ነበር።
እርሷም "ከእንግዲህ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል” በማለት ትውልደ ሴም፣ ትውልደ ካም፣ ትውልደ ያፌት እንደሚያመሰግናት ተናግራለች። “እነሆ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ሁኖ ወደ ምድረ ግብፅ ይመጣል፤ የግብፅ ጣዖታትም በፊቱ ይርዳሉ"(ኢሳ ፲፱÷፩) ተብሎ የተነገረው በስደቷ ወቅት የተፈጸመውን ነው። ሆሴዕም "ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድኩት፤ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት"(ሆሣ ፲፩÷፩:) ብሏል። ጌታችን የተሰደደው ግብፅን እና ኢትዮጵያን ለመባረክ ነው። አንድም ሰይጣንን ከሰው ልቡና አስወጥቶ ለመስደድ ነው።
በድንግል ማርያም ስደት ምክንያት ክርስቲያኖች የሰማዕትነትን በረከት አግኝተዋል። ሰሎሜ ጌታን በማዘል ድንግል ማርያምን ስትረዳ የመከራዋ ተካፋይ በመሆን አብራ ተንከራታለች። ጥጦስም ጌታን በትከሻው ተሸክሞ ሸኝቷቸዋል። በቅዳሴያችን "በቀኝ የተሰቀለውን ሽፍታ በመስቀል ላይ እንዳሰብከው አቤቱ እኛንም በመንግሥትህ አስበን" በማለት እንማጸናለን። በእመቤታችን ስደት በረከትን ያጡት ሄሮድስ፣ ትዕማር፣ዳክርስ እና መሰሎቻቸው ናቸው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ የድንግል ማርያምን ስደት በማሕሌት፣ በዝክርና በቅዳሴ ታስባለች። በዚህ ምክንያት ድንግል ማርያምን “አንቲ ውእቱ ጽጌ መዓዛ ሠናይ” በማለት እናመሰግናታለን። 🌺
የእመቤታችን ፍቅሯ በልባችን ምስጋናዋ በአንደበታችን እጥፍ ድርብ ሆኖ በእኛ በምናምን ክርስቲያኖች ላይ ይደርብን!
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
💠የመንፈስ ፍሬዎች💠
፯.እምነት
✞ እምነት አካሌን የሰጠ፣ የሚያስፈልገኝን ነገር ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር እስከ ዕለተ ሞቴ ይመራኛል ብሎ ሙሉ ተስፋን በእግዚአብሔር ላይ ማድረግ ነው።እምነት ካለመኖር የፈጠረኝ እግዚአብሔር በመግቦት ያኖረኛል ብሎ ቁርጥ ሀሳብን ለእግዚአብሔር መስጠት ነው። ብዙዎቻችን እምነት የለንም። እምነት ያለው ሰው ስለምንም አይጨነቅም። ከምንም በላይ የሆነው እግዚአብሔር አለኝ ብሎ በልቡ ስለሚያምን የሚያሳስበው የሚፈራው እና የሚያስጨንቀው ጉዳይ አይኖርም። እምነት ከመንፈስ ፍሬዎች አንዱ ነው። ገላ. ፭፣፳፪። እምነት ያለው ሰው ተስፋ አይቆርጥም። ምክንያቱም ምንም ዓይነት ፈተና ውስጥ ቢኖር እግዚአብሔር በጥበቡ ከዚያ እንደሚያወጣው ተስፋ ያደርጋልና። እምነት ያለው ሰው እንደ ዳንኤል አንበሳ ጉድጓድ ውስጥ ሊጣል ይችላል። ነገር ግን እግዚአብሔር አንበሶች እንዳይበሉት ያደርጋል። እምነት ያለው ሰው ሰማዕት ሊሆን መከራ ሊደርስበት ይችላል። ነገር ግን ከሁሉም የምትበልጠውን መንግሥተ ሰማያት ያገኛል። መዓልትና ሌሊትን፣ ክረምትና በጋን እያፈራረቀ የሚመግበን የሚያኖረን እግዚአብሔር ስላለን አንፈራም አንጨነቅም። ሰው እምነት እያጣ ሲሄድ ይጨነቃል፣ ያዝናል። ነገር ግን ከእኛ የሚጠበቀውን የድርሻችንን እየተወጣን ረድኤተ እግዚአብሔርን እየጠየቅን በተስፋ እንኑር። እምነታችን አይጉደል። ቀድሞ ቅዱሳንን የረዳ እግዚአብሔር ነው። አሁንም ያለው ራሱ ነው። እኛንም ይረዳናል። ይረድአነ አምላክነ ወመድኃኒነ። አምላክነሰ አምላከ አድኅኖ። ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ። እግዚአብሔርን በሙሉ ልባችን እንመነው። መልካም የሆነውን ሁሉ ያደርግልናል።
👉'የዋህነት ' ይቀጥላል .............
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የመስቀሉ ነገር ሲገባን
በሊ/መ ይልማ ኃይሉ
የመስቀሉ ፍቅር ሲገባን (፬)
እመቤታችንን እንወዳታለን
የመስቀሉ ፍቅር የገባቸው (፬)
እመቤታችን አለች ከጎናቸው
የመስቀሉ ነገር የገባቸው (፬)
እመቤታችን አለች ከጎናቸው
አባ ሕርያቆስ አባታችን
የመስቀሉ ነገር ቢገባው
ልቤ አፈለቀ አለ መልካም ነገር
ከእመቤቴ ጋራ ሲነጋገር
ከድንግል ማርያም ጋር ሲነጋገር
አዝ---
ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ነይ ነይ ቤዛዊት ዓለም{፪}
አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (፪)
አንዱ ሃገር ስትሄድ መድኃኔዓለም አለችው
አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (፪)
አንዱ ሃገር ስትሄድ ኢየሱስ አለችው
አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (፪)
አንዱ ሃገር ስትሄድ ክርስቶስ አለችው
አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (፪)
ለመናኒው ፀሎት ልዩ እጣን
የዋሻው ሻማ ነሽ እመብሃን
መአዛሽ ሸተተኝ ከግሸን
ትናፍቂኛለሽ ምን ልሁን
ትርቢኝማለሽ ምን ልሁን
የመስቀሉ ነገር ሲገባን(፬)
እመቤታችንን እንወዳታለን
ዳዊት በመዝሙሩ ያነሳሻል
የያዕቆብ ድንኳን ነሽ ይልሻል
የእግዚአብሔር ሃገር የሚሉሽ
እመቤቴ ማርያም አንቺ ነሽ (፪)
ቤተልሔም ስሄድ አይሻለሁ
ቀራኒዮ ስሄድ አይሻለሁ
ፍጹም አትለይም ከልጅሽ
የአንቺስ ልዩ ነው ፍቅርሽ (፪)
የመስቀሉ ነገር ሲገባን(፬)
እመቤታችንን እናያታለን
ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ነይ ነይ ቤዛዊት ዓለም{፪}
አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (፪)
አንዱ ሃገር ስትሄድ አማኑኤል አለችው
አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (፪)
አንዱ ሃገር ስትሄድ ክርስቶስ አለችው
አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (፪)
አንዱ ሃገር ስትሄድ አንድዬ አለችው
አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው (፪)
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
መስከረም ፳፩
ብዙኃን ማርያም
በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው።
ጉባዔ ኒቅያ
በ፫፻፳፭ ዓ.ም አርዮስ የሚባል መናፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡
በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡
ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ (2348) መካከል ፫፻፲፰ (318) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡
፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "ብዙኃን ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡
@Ethiopian_Orthodox
ዕፀ መስቀል/ግሸን ማርያም
በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤
ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡
ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡
መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡
ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡ መጽሐፉ እንደሚለው በሃገራችን ያለው ግማደ መስቀሉ (የቀኝ እጁ) ብቻ ሳይሆን ሙሉው ዕፀ መስቀል ነው።
የእመቤታችን ማርያም ምልጃና ጥበቃ አይለየን!
©ማኅበረ ቅዱሳን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
💠የመንፈስ ፍሬዎች💠
፭.ቸርነት
✞ ቸርነትን ግእዙ "ምጽዋት" ይለዋል። ከተቀባዩ ምንም ሳይፈልጉ የሚሰጡት ስጦታ ነው። አሁን ያሉ የኢትዮጵያ የአብነት መምህራን በችግር ተምረው ያገኙትን እውቀት በነጻ ያስተምራሉ። እውቀት ይመጸወታል። ገንዘብ ይመጸወታል። ጉልበትም ይመጸወታል። ሁሉም የቸርነት ሥራዎች ናቸው። ቸሩ እግዚአብሔር እንዲምረን እኛም ቸር እንሁን። ሰው በቸርነት ፈጣሪውን ይመስላል። እግዚአብሔር ቸር ስለሆነ እኛነታችንን፣ አካላችንን፣ ተፈጥሮን ሰጥቶናል። ከዚህ በኋላ በታናናሾች አድሮ ምጽዋትን እየተቀበለ ሰማያዊ ዋጋን ይሰጠናል። በኋላ በምጽአት ጻድቃንንና ኃጥዓንን ሲለይ በዋናነት የሚጠይቀው ቸርነትን (ምጽዋትን) ነው። ብራብ አብልታችሁኛል፣ ብጠማ አጠጥታችሁኛል፣ ብታረዝ አልብሳችሁኛል፣ እንግዳ ብሆን ተቀብላችሁኛል፣ ብታመም ጠይቃችሁኛል፣ ብታሰር አስፈትታችሁኛል የሚሉት ቃላት
ምሥጢራቸው ቸርነት ነው። ምጽዋት (ቸርነት) ሰው ፈጣሪን የሚመስልበት መልካም ሥራ ነው። ፈጣሪ ሁሉን በነጻ እንደ ሰጠን የሚመጸውት ሰውም ፈጣሪ ከሰጠው ጸጋ በነጻ የሚሰጥ ነው። ቸርነት (ምጽዋት) በከንቱ ዘነሳእክሙ በከንቱ ሀቡ ያለውን የሐዋርያውን ቃል በተግባር ማዋል ነው። ቸርነት ሰው ሌላውን ሰው
እንደራሱ ከመውደዱ የተነሳ የሚደረግ የመንፈስ ፍሬ ነው። ለዚያ ነው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች የመንፈስ ፍሬዎችን ሲነግራቸው አንዱ ቸርነት ነው ያላቸው። ገላ. ፭፣፳፪። የቸርነት ሥራዎች ለከንቱ ውዳሴ ከዋሉ ዋጋ አያሰጡም። ጌታ ሲያስተምር ቀኝህ የሰጠችውን ግራህ አትወቅ ምጽዋትህ ሰው ይይልኝ ብለህ
ሳይሆን በስውር ይሁን ያለን። አሁን ሰው መጽውቶ በማኅበራዊ ሚዲያ ካልተነገረለት ይከፋል። መምህር አስተምሮ ማስተማሩ በሁሉ ካልታወቀለት ይከፋዋል። ቸርነትና ውዳሴ ከንቱ አይስማሙም። በአደባባይ ከመወደስ በአደባባይ መሰደብ ይሻላል። ቸሩ መድኃኔዓለም ይቅር እንዲለን ቸርነትን ገንዘብ እናድርግ።
👉' በጎነት ' ይቀጥላል ...........
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
መስከረም 17 ቀን ማለትም የደመራ በዓል ማግስት የምናከብረው የመስቀል በዓል ደግሞ ንግሥት እሌኒ ደመራ አስደምራ እጣን አጢሳ (አስጢሳ) የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ #ቁፋሮውን_ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤ በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ አጋዥነት ቁፋሮ በተጀምረ ከ5 ወር ከ23 ቀን በኋላ መስቀሉ መጋቢት 10 ተገኝቷል፤ ከ10 ዓመት በኋላም ቤተ መቅደሱ ታንጾ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡ መስቀሉም እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽባዎችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡ ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡ ይህ የጌታ #ዕፀ መስቀልም በዓፄ #ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በተለያዩ ቅዱሳት መካናት (እንጦጦ #ማርያም፣ ጋራ #መድኃኔዓለም፣…..) ሲያርፍ ቆይቶ በስተመጨረሻው ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል›› ተብሎ ለዓፄ #ዘርዓ ያዕቆብ በተነገረው መሠረት በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም በክብር አርፏል፡፡ እኛንም በመስቀሉ ፈዋሽነት ይማረን የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ይሳልብን አሜን፡፡
* "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" /ሊቁ ቅዱስ #ያሬድ/
* ‹‹ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።›› /ብርሃነ ዓለም ቅዱስ #ዻውሎስ ገላ.6፥14፣ 1ኛቆሮ.1፥18/
የመስቀል ክብረ በዓላት
መስከረም 16 የደመራ በዓል
መስከረም 17 የመስቀል በዓል
መስከረም 10 ተቀጸል ጽጌ
መጋቢት 10 መስቀሉ የተገኘበት በዓል
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ጥልን በመስቀሉ ገደለ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
መስቀል
🌋✝
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ ማርያም እግዝእት በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ መከራ መስቀልን ተቀብሎ:
¤ከግራ ቁመት:
¤ከገሃነመ እሳት:
¤ከሰይጣን ባርነት:
¤ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::
=>+"+ እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ +"+ እንዳለ ሊቁ::
+ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም ራሷ አርአያ ትዕምርተ መስቀል ናት::
+እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት (ዘፍ. 4:15) ጀምሮ
¤ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት (ዘፍ. 22:6):
¤ቅዱስ ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል (ዘፍ. 28:12):
¤ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ (ዘፍ. 48:14):
¤ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው የሙሴ በትር (ዘጸ. 14:15):
¤የናሱ ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት (ዘኁ. 21:8) ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::
💠የመንፈስ ፍሬዎች💠
፬.ትዕግሥት
✞ አሁን አሁን ከትዕግሥተኞች ይልቅ ስለ ትዕግሥት የሚያወራው ይበልጣል። ትዕግሥት የክብር እናት ናት።ከክርስቶስ መስቀል በረከትን ማግኛ ነው። ክርስቶስ እኛን ለማዳን በመስቀል ተሰቀለ። እስኪ ራስህን አድን እያሉ አይሁድ ሲሳለቁበት፣ ምራቃቸውን ሲተፉበት፣ ተነበይ ለነ ክርስቶስ መኑ ጸፍዐከ እያሉ በጥፊ ሲመቱት እነርሱን ማጥፋት እየቻለ ለእኛ ትዕግሥትን ያስተምረን ዘንድ መከራውን ሁሉ በዝምታ ተቀበለ። ሰማዕታት ስለ እውነት መራራ ሞትን ታገሡ። ወተዐገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግሥተ ሰማያት እንዲል። የታገሠ የድል አክሊል ያገኛል። ይህችውም መንግሥተ ሰማያት ናት። አባቶቻችን ዕጉሣን ነበሩ። ለመናገር የዘገዩ ለመስማት የፈጠኑ ነበሩ። ታጋሽ ሰው ሕይወቱ የተረጋጋ ነው። አርምሞ (ዝምታ) የትዕግሥት አጋዥ ነው። ትዕግሥት የጠብ ማብረጃ ነው።
✞ ትዕግሥትን እንለማመዳት። ሲታገሡ ያማል። ሕመሙ ግን አጭር ነው። ከሕመሙ በኋላ ያለው ደስታ ልዩ ነው። እናት ልጇን ስትወልድ የምጥ ጊዜዋ አስጨናቂ ነው። ነገር ግን ልጇን ከወለደች በኋላ ወንድ ልጅ ወለድሽ ብለው ሲያስታቅፏት
ያለፈውን መከራ ሁሉ በልጇ ትረሳዋለች። ስንሰደብ ዝም ስንል ልናዝን እንችላለን። ነገር ግን እየቆየ ሲሄድ ምን ስድብማ አየር የሚወስደው አይደለምን ብለን ደስ ይለናል። ቅዱሳንም ይህችን ዓለም ያሸነፏት በትዕግሥት ነው። ሊቁ መዋዕያነ ዓለም አንትሙ በብዙኅ ትዕግሥት ያለው ይህንን ነው።
✞ ታጋሽ ሰው የሰማእታቱ የእነ ቅዱስ መርምህናም፣ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የእነ ቅዱስ ፊቅጦር፣ የእነ ቅዱስ መርቆሬዎስ፣ የእነ ቅዱስ ፋሲለደስ፣ የእነ ቅዱስ ገላውዴዎስ፣ የእነ ቅዱስ ቂርቆስ እንዲሁም የቅዱሳን ሰማእታት ሁሉ ወዳጅ ነው። ታጋሽ ሰው የመነኮሳቱ የእነ ቅዱስ መቃርስ፣ የእነ አባ እንጦንስ እንዲ የቅዱሳን መነኮሳት ሁሉ ወዳጅ ነው። ታጋሽ ሰው የቅዱሳን ሁሉ ወዳጅ ነው። እግዚአብሔር ይወደዋል። በሉ ኑ ታጋሽነትን እንለማመድ። ታጋሽ እንሁን።
👉'ቸርነት' ይቀጥላል ...........
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
💠የመንፈስ ፍሬዎች💠
፫. ሰላም
✞ ቅድስት ድንግል ማርያምን ሰላማዊት ይላታል። ልጇም ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ይባላል። አንድ ሰው ውስጣዊ ሰላም ይሰማኛል ሲል ብትሰማው የሐሳብ ስምምነት የአእምሮ ዕረፍት እንዳገኘ ትረዳለህ። ውስጣዊ ሰላም የሕዋሳቶቻችን ስምምነት ውጤት ነው። ሰላም ተሳለመ_ተፈቃቀረ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ዘመድ ዘር ነው። ሰላም ፍቅር ማለት ነው። ምሥጢራዊ ትርጓሜው ግን ከተሰናእዎ ጋር ይቀራረባል። የነገር እና የሐሳብ ስምምነት ማለት ነው። ሰላም ሆነ ማለት ስምምነት ላይ ተደረሰ ማለት ነው። አምላከ ሰላም ክርስቶስ ሰላምን እሰጣችኋለሁ ብሏል። ለሰውነታችን የተስማማች ገነትን ሰጥቶም አረጋገጦልናል። ሲኦል ግን ለእኛ ሰውነት የማይስማማ ቦታ ነው። በሲኦል ሰላም የለም። ሁከት ብጥብጥ ዋይታ ለቅሶ ይበዛል። ውስጣዊ ሰላም የሚገኘው በድለን ከነበረ ንሥሓ ገብተን ኃጢዓታችንን አስወግደን መልካም ሥራ ስንሰራ ነው። ነገር ግን ሌላውን እያስቀየምን፣ እያናደድን፣ እየተሳደብን ውስጣዊ ሰላም ይሰማናል ብንል ውሸታም እንባላለን። ነቢዩ ኤርምያስ እንደተናገረው "ወይቤሉ ሰላም ሰላም ወአልቦ ሰላም" እንዳሉት ሐሰተኛ ነቢያት እንሆናለን። የልቡና ሰላም የሚገኘው እውነትን ፍቅርን ትሕትናን ስንይዝ ነው። ፍጹም ሰላማዊት ወደ ሆነችው መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ከተጣላናቸው ጋር በይቅርታ ታርቀን፣ የበደልነውን ክሰን በፍቅር እንኑር።
✞ ክርስቶስ ሰላምን የሰጠን በደላችንን ይቅር ብሎ ነው። እኛም በትክክለኛ ፍትሕ ያጠፋው ክሶ፣ የተበደለው ተክሶ በሰላም እንኑር። ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት ከፈለጉ የተጣሉትን ይታረቁ፣ ቂም በቀል ጥላቻ ዘረኝነት ካለብዎ ያስወግዱ። ከእርስዎ የሚጠበቀውን መልካምነት ያድርጉ። የድርሻዎትን ይወጡ። ከመንፈስ ፍሬዎች አንዱ ሰላም ነው። ገላ. ፭፣፳፪።
👉'ትዕግሥት' ይቀጥላል ..............
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
መስከረም ፲
ጼዴንያ ማርያም
ጼዴንያ በምትባል ሀገር ማርታ የምትባል ደግ ሴት ነበረች፡፡ ይህች ደግ ሴት በቤቷ ትልቅ አዳራሽ ሠርታ እንግዶችን እንደ አባታችን አብርሃም ተቀብላ አብለታ አጠጥታ ማደሪያ ቦታም ሰጥታ ታስተናግድ ነበር፡፡ አባ ቴዎድሮስ የሚባል ኢትዮጵያዊ መነኩሴ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ መሽቶበት ከማርታ ቤት በእንግድነት አደረና ጠዋት ሊሄድ ሲነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚሄድ ሲነግራት ‹‹የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተህ አምጣልኝ ዋጋውን ልስጥህ›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ገንዘቡን ሥዕሉን ሳመጣልሽ ትሰጪኛለሽ›› ብሏት ሄደ፡፡ ኢየሩሳሌምም ደርሶ ቅዱሳት መካናትን ተሳልሞ ሥዕሉን ረስቶ ሳይገዛ ሲመለስ «አደራ ጥብቅ አይደለምን? ያቺ ሴት አደራ ያለችህን ለምን ረሳህ» የሚል ድምፅ ሰማ፡፡ በጣም ደንግጦ ተመልሶ ሄዶ ገዝቶ በረሃ በረሃውን መጓዝ ጀመረ፡፡ በመንገድም እየተጓዘ አንበሳ ሊበላው እየሮጠ ወደ እርሱ ሲመጣበት አየ፡፡ መነኩሴው አንበሳውን ከመፍራት የተነሣ ደነገጠ፣ ተንቀጠቀጠ ደንግጦ ቁሞ ሳለ ያች ሥዕል ከአንበሳው ጩኸት ሰባት እጅ በሚበልጥ አስፈሪ ድምፅ ጩሃ ተናገረች፡፡ ያን ጊዜ አንበሳው ደንግጦ ፈጥኖ ሸሸ፡፡ መነኩሴውም መንገዱን ቀጠለ፡፡ በመንገዱም ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ወጥተው ወንበዴዎች ሊቀሙትና ሊገድሉት ከበቡት፡፡ ከሥዕለ ማርያሟም እንደ መብረቅ ያለ ታላቅ ቃል ወጣ፡፡
ወንበዴዎችም እጅግ ፈርተው ሸሽተው ከጫካው ውስጥ ገቡ፡፡ ያም መነኩሴ እነኚህን የሚያስደንቁ ተአምራት በተመለከተ ጊዜ በልቡ «ለእኔ ረዳት ትሆነኝ ዘንድ ወደ ሀገሬ ይዣት እሄዳለሁ እንጂ ለላከችኝ ሴት አልሰጥም» ብሎ ወደ ሀገሩ ሊሄድ በመርከብ ተሳፈረ፡፡ በባሕር ላይም ሳለ ጽኑ ነፋስ ተነስቶ መርከቡን እየገፋ ማርታ ወዳለችበት ሀገር ወደ ጽዴንያ ዳርቻ አደረሰው፡፡ ማደሪያም ስለሌለው ወደ ደጓ ሴት ወደ ማርታ ቤት ከእንግዶች ጋር አብሮ ገብቶ አደረ፡፡ ሲነጋ ወጥቶ ሊሄድ ከደጃፍ ሲደርስ ደጃፉ ጠፍቶት ከአጥሩ ሲታገል ዋለ፡፡ ማርታም «አባቴ ያመመህ የደከመህ ትመስላለህ ዛሬ ደግሞ እዚህ እደርና ነገ ትሄዳለህ» አለችውና አደረ፡፡ በሁለኛውም ዕለት እንደ መጀመሪያው ቀን በሩን አልፎ መሄድ አቃተውና እዚያው ማርታ ቤት አደረ፡፡ በሦስተኛው ቀን መውጣት ፈልጐ አሁንም ከአጥሩ ጋር ሲታገል አይታ «አባቴ የሆንከው ምንድነው? እነሆ ዛሬ ሦስተኛ ቀንህ ነው» አለችው፡፡
መነኩሴውም «ይህችን ተአምረኛ ሥዕል አልሰጥም ብዬ ነው፡፡ እኔኮ ሥዕል ከኢየሩሳሌም ግዛልኝ ያልሽኝ መነኩሴ ነኝ» ብሎ ሥዕለ ማርያምን አውጥቶ ሰጣት፡፡ እርሷም እጅግ በጣም ተደስታ እግዚአብሔርን አመሰገነች፡፡ በሥዕሏም ፊት ሰግዳ ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ምስጋናን አቀረበች፡፡ ተቀብላም ሥዕል ቤት አሠርታ በክብር አስቀመጠቻት፡፡ ይህችም ሥዕል ቅዱስ ሉቃስ የሳላት ናት፡፡ ሥጋ የለበሰች ትመስላለች፡፡ ከፊቷም ወዝ ይንጠባጠባል፡፡ በዚህችም ሥዕል ብዙ ተአምራት ተደረገ ሕሙማን ተፈወሱ፣ ዐይነ ስውራን ማየት ቻሉ፡፡ በዚያ ዘመን የነበረው ሊቀ ጳጳስ ተአምሯን ሰምቶ ሥዕሏ ወደ ማርታ ቤት የገባችበት ዕለት መስከረም ፲ ቀን እንዲከበር ሥርዓት ሠራ፡፡ ይህም በዓል በቤተ ክርስቲያናችን ሁልጊዜ ይከበራል፡፡
የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ ፍቅሯን ጣዕሟን ታሳድርብን፣ ልጇ አምላካችን በጸሎቷ ይማረን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
💠የመንፈስ ፍሬዎች💠
፪. ደስታ
✞ ደስታ በምናየውና በምንሰማው፣ በምንቀምሰው ነገር በተፈጸሙ ክስተቶች የሚሰማን የህሊና እርካታ ነው፡፡ በክርስቲያናዊ ሕይወት ደግሞ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ከእግዚአብሔር ጋር በመኖር የሚገኝ መንፈሳዊ የርካታ ስሜት ነው፡፡ ደስታችንም የሚፈጸመው በዓለም ከሚገኘው ጊዜያዊ ደስታ በተለየ መልኩ ነው፡፡
✞ አራት ዓይነት ደስታዎች አሉ። እነዚህም:-
፩) ፍሥሓ መላእክት
፪) ፍሥሓ ኖሎት
፫) ፍሥሓ ቍንጽል (የቀበሮ ደስታ)
፬) ፍሥሓ መስቴማ ናቸው።
◈ ፍሥሓ መስቴማ ማለት የሰይጣን ደስታ ማለት ነው። ሰይጣን ሌሎች ሰዎች ሲሳሳቱ፣ ሲወድቁ፣ ሲሞቱ፣ ሲጎዱ በጣም ይደሰታል። በሌሎች ሰዎች ኀዘን እና ጉዳት የሚደሰቱት ደስታ የሰይጣን ደስታ ይባላል።
◈ ሁለተኛው የደስታ ዓይነት የቀበሮ ደስታ ነው። ቀበሮ የጣዝማ ማር ስታገኝ ከደስታዋ ብዛት የተነሳ ማሩ እስኪጠፋት ትዘላለች። የደስታዋ ምንጭ የሚበላ አገኘሁ ብላ ነው። የሰው ልጅ በሥጋዊ ነገሮች የሚደሰተው ደስታ የቀበሮ ደስታ ይባላል።
✞ ሦስተኛው ደስታ የእረኞች ደስታ ነው። እኒህም ጌታ በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ የተደሰቱት ደስታ ነው። ይህ ደስታ ነፍሳዊ ደስታ ነው። በጌታ መወለድ በሲኦል ተግዞ የነበረ አዳም ወደ ገነት የሚመለስበትን የምሥራች ከመልአኩ የሰሙበት ነውና። እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘይከውን ፍሥሓ ለክሙ እንዲል።
✞ የመላእክት ደስታ የፍጹማን ደስታ ነው። መላእክት አንድ ኃጥእ ንሥሓ በገባ ጊዜ በሰማያት ታላቅ ደስታ ይሆናል ተብሎ የተነገረላቸው ናቸው። የመላእክትደስታ ከግላዊ ጥቅም የተለየ ደስታ ነው። ሌላው ሲጠቀም፣ ሌላው ሲያገኝ፣ ሌላው ሲሾም፣ ሌላው ሲደሰት የሚደሰቱት ደስታ ነው።
✞ እንግዲህ ገላ. ፭፣፳፪ ደስታ የመንፈስ ፍሬ ነው የተባለው በሁለቱ ዓይነት ደስታዎች ነው። እነዚህም ፍሥሓ ኖሎት እና ፍሥሓ መላእክት ናቸው። ትክክለኛው ደስታ የሚገኘው በቁስ አይደለም። በእግዚአብሔር ነው። መዝ. ፺፬፣፩ "ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን" ተብሏል። ቅዱስ ጳውሎስም በመልእክቱ ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ብሏል። በሌላ ቦታ ቅዱስ ዳዊት "ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ" ብሏል። ደስታ የሚገኘው ከእግዚአብሔር ቤት ነውና። ደስታ የራቃችሁ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ። ያን ጊዜ ደስ ይላችኋል። ሰማእታት እየተገደሉ ግን ደስተኞች ነበሩ። ለምንድን ነው ስንል የደስታቸው ምንጭ እግዚአብሔር ስለሆነ ነው። እግዚአብሔር ደግሞ ሕይወተ ሕይወት ብርሃነ ብርሃን መሠረተ መሠረት ስለሆነ ነው። ደስታችንን በእግዚአብሔር እናድርግ።
👉'ሰላም' ይቀጥላል ..............
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"ፍቅርን ከክርስቶስ"
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox