በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
"ቅድመ ዓለም ንጉሥ ዘለዓለም ሥላሴ"
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ጥር ፯
በዓለ ሥሉስ ቅዱስ ሕንጻ ሰናዖርን ያፈረሱበትና ቅዳሴ ቤታቸው ነው
ጥር ሰባት በዚች ቀን በዓለ ሥላሴ የሚከበረው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን ሌላው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው::
ሕንጻ ሰናዖር
ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም: ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር:: ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ::
ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ:: በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ::
ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ:: ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል:: ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል::
መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል:: ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው:: ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን::
ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም:: የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና:: ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ::
ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ:: እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ:: ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት:: ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል::
ቅዳሴ ቤት
በ1684 ዓ.ም አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::
ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን: ሠራዊት: መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል:: በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል: ደግ: ጥበበኛ: አስተዋይ: መናኝ ንጉሥ ነውና::
ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ.ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::
ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ"
በዘማሪት አዜብ ከበደ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ጥር ፬
ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
ጥር አራት በዚህች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደው የከበረና የተመሰገነ ወንጌልን የጻፈ የሐዋርያው ዮሐንስ የፍልሰቱ መታሰቢያ ሆነ።
----------------------------------
ቅዱስ ዮሐንስ ሀገሩ የገሊላ አውራጃ ሲሆን ከወንድሙ ከያዕቆብና ከአባቱ ከዘብዴዎስ ጋር ዓሣ እያጠመደ ይኖር ነበር። እናቱም ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ እንደሆነችና ማርያም እንደምትባል የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ይመሰክራል። ዮሐንስ ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ የታላቁ ያዕቆብ ታናሽ ወንድም ነው።
ለዚህም ቅዱስ ወደ እስያ ሀገር ይሔድ ዘንድ ዕጣው በወጣ ጊዜ እጅግ አዝኖ አለቀሰ እነርሱ ክፉዎች ከሀዲዎች ልባቸው የደነደነ መሆናቸውን አውቋልና ግን ከጌታችን ኃይልን መጽናናትን አግኝቶ ከደቀ መዝሙሩ ከአብሮኮሮስ ጋር ወጥቶ ወደ ክፍሉ ሔደ።
ወደ ኤፌሶንም ሊሔድ ወዶ በመርከብ ላይ ተሳፈረ መርከቡም ተሰበረ እየአንዳንዱ በመርከብ ስባሪ ሠሌዳ ላይ ተንጠለጠለ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስንም የባሕሩ ማዕበል ወደአንዲት ደሴት አደረሰው ቅዱስ ዮሐንስ ግን በባሕሩ ማዕበል መካከል አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ኖረ።
ከዚህም በኃላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስ ወዳለበት ወደ የብስ ባሕሩ ተፋው ስለ መገናኘታቸውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት በዚያን ጊዜም ተነሥተው ወደ ኤፌሶን ከተማ ገቡ ግን በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰብኩ ዘንድ አልተቻላቸውም እነዚያ ያገር ሰዎች እጅግ የከፉ ናቸውና።
ስለዚህም ምክንያት ፈጥረው ዮሐንስ ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤት እሳትን የሚያነድ ሆነ ረድኡ አብሮኮ ሮስም አጣቢ ሆነ ያቺ ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ነበር መጻተኞችም ስለሆኑ ታጉሳቁላቸዋለች ትደበድባቸዋለች ትረግማቸዋለች ባሮቿም እንደሆኑ ጽፈውላታልና ለእርሷ ባሮች አደረገቻቸው በዚህ በታላቅ ጒስቊልና ውስጥ ኖሩ።
ከዚህም በኃላ በአንዲት ዕለት ይታጠብ ዘንድ የአገረ ገዥው ልጅ ገባ በዚያም የውሽባ ቤት ከተሠራ ጀምሮ የሰይጣን ኃይል አለ የመኰንኑንም ልጅ አንቆ ገደለው በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ለዚያ ለሞተው ሊያለቅሱለት ተሰበሰቡ የከበረ ዮሐንስም ከእርሳቸው ጋር መጥቶ እንደ ሰው ሁሉ ሊያይ በዚያ ቆመ።
ሮምናም በአየችው ጊዜ ረገመችው "አንተስ በጌታዬ ልጅ ሞት ደስ ብሎህ ልትዝትብኝ መጣህ" አለችው ቅዱሱ ግን በቅንነት "አይዞሽ አትዘኝ" አላት ይህንንም ብሎ ወደ ሞተው ቀረብ ብሎ በመስቀል ምልክት አማተበበት በፊቱም ላይ እፍ አለበት። በዚያንም ጊዜ ያ ሞተው ድኖ ተነሣ የአገር ሰዎችም ደነገጡ ሮምናም ወዮልኝ እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን አለች።እርሱም አይደለሁም እኔ አገልጋይ ሐዋርያው ነኝ እንጂ አላት በእነርሱ ላይ የሠራችውን በደል ሁሉ ይቅር ይሏት ዘንድ መሪር ልቅሶ በማልቀስ ሐዋርያትን ለመነቻቸው እነርሱም አረጋጓት አጽናኗትም።
ከሀገሩም ሰዎች ብዙዎቹ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው በፊታቸውም ብዙዎች የሆኑ ድንቆች ተአምራትን አደረገ ይህንንም አይተው የሀገሩ ሰዎች ሁሉም በጌታችን አመኑ።ከጣዖታቱ አገልጋዮች በቀር እነርሱም ሰይጣን በእርሱ ላይ ስለሚያነሣሣቸው ሊገድሉት ይሹ ነበር ነገር ግን ምርጦቹን እግዚአብሔር ጠበቃቸው።
የከበረ ዮሐንስም ሁሉንም እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ እስከመለሳቸው ድረስ ታላቅ ድካምና ጭንቅ የሆነ መከራ ደረሰበት።የከበረ ሐዋርያ ጳውሎስም ስለ ልቡናቸው ደንዳናነት ጣዖታትን ስለመውደዳቸውም ስለ እነርሱ መስክሮአል።እርሱም ዮሐንስ በታላቅ ድካም ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው።ከዚህም በኋላ ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትን ዲያቆናትን ሾመላቸው።
ከዚህም በኋላ ከእስያ በዙሪያዋ ወዳሉ አገሮች ሁሉ ወጥቶ አስተማረ እግዚአብሔርንም ወደማወቅ መለሳቸው።ይህም የከበረና የተመሰገነ ዮሐንስ በዚህ ዓለም ዘጠና ዓመት ኖረ እጅግም ሸመገለ ግን እንደ ባልንጀሮቹ እንደ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አልቀመሰም።ስለ ድንግልናውና ስለ ንጽሕናው ይህ ሆነ ሁሉም በክብር ይስተካከሉ ዘንድ እርሱም ወንጌልን ቀለምሲስ የሚባለውን ራእይ ሦስት መልእክታትን የጻፈ ነው።ራት ሲበሉ በጌታ ኢየሱስ አጠገብ የተቀመጠውና "አቤቱ የሚያሲዝህ ማነው" ያለው ይህ እርሱ ነው።
ጌታችንም በተሰቀለ ጊዜ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በመስቀሉ አጠገብ የቆመ እናቱንም "እነሆ ልጅሽ" ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው።
ጴጥሮስም እርሱን ሲከተለው ባየው ጊዜ ስለእርሱ ጌታ ኢየሱስን "አቤቱ ይህስ እንዴት ነው" ብሎ የተናገረ ጌታ ኢየሱስም "እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ከወደድኩ አንተ ምን አለህ አንተ ግን ተከተለኝ" ያለለት ይህ ነው ።
የተመሰገነ ዮሐንስም ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ሰዓት እንደ ቀረበ በአወቀ ጊዜ ሕዝቡን ጠራቸው ጸሎትንም ጸለየና ኅብስቱን ባርኮ ቆረሰ ይህም የጌታችን ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ባረካቸው አጽናናቸውም።
ከዚህም በኃላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ። ከኤፌሶንም ከተማ ውጭ ወጣ ጐድጓድ እንዲቆፍሩም አዘዘ ከውስጥዋም ወርዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ ከአንድ የበፍታ ቀሚስ በቀር አላስቀረም። እጆቹንም አንሥቶ ጸለየና ወደ ከተማ ይመለሱ ዘንድ አሰናበታቸው በክርስቶስም ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝቡ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዛቸው በጎ ሥራዎችንም ይሠሩ ዘንድ ጌታችን ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፈለው ዘንድ አለውና።
ሁለተኛም እንዲህ አላቸው "እኔ ከሁላችሁም ደም ንጹሕ ነኝ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራችሁ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩኝም።"
ይህንንም በተናገረ ጊዜ አለቀሱ እጆቹንና እግሮቹን ስመው በጒድጓዱ ውስጥ ትተውት ወደ መንገድ ተመለሱና የሆነውን ሁሉ ለሰዎች ነገሩዋቸው ሁሉም ደንግጠው መጡ ግን ልብስና ጫማ እንጂ መቃብሩን አላገኙም እጅግም አደነቁ ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን በዚህ በጎ ዕረፍት ያሳረፈው እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።
ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ የተለያዩ ስሞች ተሰጥተውታል፡
🌿ወልደ ዘብዴዎስ - አባቱ ዘብዴዎስ ስለሆነ
🌿ፍቁረ እግዚእ - በሕይወቱና በኑሮው ጌታን በመምሰል ጌታ ይወደው ስለነበር
🌿ነባቤ መለኮት (ታዖሎጎስ) - ነገረ መለኮትን ከሌሎች በበለጠ አምልቶ አስፍቶ በጥልቀት በማስተማሩ
🌿ቦአኔርጌስ (ወልደ ነጎድጓድ) - የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት በመግለጡና ለጌታችን ባለው ቅንዓት ባሳየውም የኃይል ሥራ
🌿ባለራእይ (አቡቀለምሲስ) - ኃላፍያትንና መጻእያትን በራእይ በመግለጡ
🌿ቁጹረ ገጽ (ፊቱ በኃዘን የተቋጠረ) - በዕለተ ዓርብ በእግረ መስቀሉ ተገኝቶ የጌታችንን መከራ መስቀል በማየቱ ከዚያች ዕለት ጀምሮ ፊቱ በኃዘን ተቋጥሮ ይኖር ስለነበር
----------------------------------
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ አባት በሐዋርያ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"መጽአ ወልድ"
"ሃሌ ሉያ መጽአ ወልድ ውስተ ዓለም፣ ሃሌ ሉያ ውስተ(፪)
ወለብሰ ሥጋነ ሰብአ ኮነ በአርአያ ዚአነ።(፪)"
"ሃሌ ሉያ ወልድ መጣ ወደ ዓለም፣ ሃሌ ሉያ ወደ ዓለም።(፪)
ሥጋችንን ለበሰ ሰውም ሆነ በእኛ አርአያ ሰው ሆነ።(፪)"
©በማኅበረ ቅዱሳን ዘማርያን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ስለ አምላክ ሰው መሆን የሃይማኖት አባቶቻችን በመደነቅ እንዲህ አሉ፦
«ኃይለኛ ተዋጊ ሆኖ ገብቶ በእርሷ ማኅፀን ፍርሃትን ለበሰ፤ የሁሉ መጋቢ ሆኖ ገብቶ ረሃብን ተቀበለ፡፡ ለሁሉም መጠጥን የሚሰጥ ሆኖ ገብቶ ጥምን ተቀበለ፡፡ ለሁሉ ልብስን የሚሰጠው ከእርሷ ማኅፀን ራቁቱን ሆኖ ተወለደ፡፡
ከሕሊናት ሁሉ ለራቀ ለዚህ ድንቅ ምሥጢር አንክሮ ይገባል፤ ምድራዊት ሴት ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃልን ወለደችው፥ ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው፤ እርሱም እናቱን ፈጠረ፤ ከእርሷም እርሱ የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ።
ተዋርዶ በእኛ ባሕርይ ተወለደ፤ እርሱም እኛን ስለመውደዱ ፈጠረን ፤በእኛ ባሕርይ ወለደችው ፤ ፈጣሪም እንደሆነ ታወቀ።
እርሱ ሊዋሐደው ሥጋን ከድንግል ፈጠረ ፤ ባሕርይዋን ባሕርይ አደረገ ፤ ፍጡራንን ሁሉ የፈጠረ ሲሆን ባሕርዩ ያልነበረ ሥጋን ተዋሐደ የተዋሐደውንም ባሕርይ የፈጠረ እርሱ ነው ።
የድንግልን ሥጋ መረጠ ፤ሰው መሆኑን ሊያስረዳ ፍጹም አካሉን በማሕፀኗ ፈጠረ።>> ማር ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
<<ቀዳማዊ አምላክ ዛሬ ተወለደ ጥንቱን ገንዘቡ ባይደለ ባሕርይ ተገኘ ፤ እርሱ ቀዳማዊ አምላክ ነው ሰው በመሆኑም ከባሕርዩ አልተለወጠም።
የመለኮቱ መገኘትም ከእመቤታችን ከተወለደ ወዲህ አይደለም ፤ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ጥበብ ነው እንጂ የማይታመም እርሱ ከባሕርየ መለኮቱ ሳይለወጥ ሕማም የሚስማማውን ሥጋን ተዋሐደ ።
ዳግመኛም በልዑል ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ያለ እርሱ ፡ በበረት ተጣለ ሥጋ ሳይሆን የነበረ የማይዳሰስ ወልድ ዋሕድ ዛሬ ሥጋን በመዋሐድ ተዳሰሰ ፤ ኃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ።
የማይወሰን እግዚአብሔር በድንግል ማኅፀን እንደ ተወሰነ ማን አየ? ማን ሰማ? ሰማያት ለማይወስኑት እርሱ የድንግል ማኅፀን አልጠበበውም ባሕርዩ ሳይለወጥ ከእርስዋ ተወለደ እንጂ ፤ ከመለኮቱ የተለየ ዕሩቅ ብእሲ አይደለም ።
.
ብልህ ሸክላ ሠሪ የሚሠራውን የለዘበ ጭቃ በአገኘ ጊዜ ከእርሱ መልካም ዕቃ እንዲሠራ እንደዚህ ጌታችን የዚህችን ድንግል ንጹሕ ሥጋዋን ንጽሕት ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ፤ ነፍስ ያለችውን ሥጋ ሊዋሐደው ፈጠረ።
እንደ ወደደ ከድንግል ነፍስን ሥጋን ፈጥሮ ለበሰ፤ እርሱንም ተዋሕዶ ዛሬ ተወለደ ፤ ሕጸጽ ያለበት ነው ብሎ ባሕርያችንን አልተወውም ፤ ሥጋን በተዋሐደ ጊዜ ቃል ከምላቱ አልተወሰነም ፤ ሥጋ የፈጣሪ አካል ባሕርይ በሆነ ጊዜ ፍጹም አምላክነትን አገኘ እንጂ።
ሸክላ ሠሪ አስቀድሞ በእጁ ጭቃ ሳይዝ መሥራት እንደ ማይቻለው ፤ በፍዳ ተይዞ የነበረ ባሕርይ ዳግመኛ ያለ እግዚአብሔር እጅ በዘር ተፈጠረ ሊሉት አይገባም፤ ፈጣሪ ይዋሐደው ዘንድ ያለዘር በእደ እግዚኣብሔር ተፈጠረ እንጂ።
ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እርሱ ትንሽ ሕፃን ሆኖአልና፤ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ፤ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተወለደ፤ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሠሥ የነበረ በምድራውያን እጅ ተዳሠሠ፤ ኀጢአት የሚያስተሠርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፤ ይህን ወዶአልና።
ክብሩ ተለይቶ የነበረ ሥጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው ፤ የጸጋ ገዥነትን አጥቶ የነበረ ሥጋንም የባሕርይ ገዥ ሊያደርገው ወደደ ፤ አዳም ከእኛ እንዳንዱ ሆነ ያለውንም ሰው በመሆን ሊገልጠው ወደደ።>> ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
<<የሰው ልጅ ሕይወት እና መዳን የሆነው ጌታ ተወልዷል፣ ዛሬ እርቅ ከመለኮት ለሰው ልጅ፥ ከሰውም ለመለኮት ተደረገ። ዛሬ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ዘሏል። ከላይ ያሉት ወደ ታች ላሉት፥ ከታች ያሉትም ወደ ላይ ላሉት ተላኩ፤ ዛሬ ሞት ለጨለማ፥ ሕይወት ደግሞ ለሰው ልጆች ኾነ። ዛሬ ለሰዎች ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚወስድ እና ወደ ነፍስም የሚገባ የእግዚአብሔር መንገድ ተደረገ።>> ቅዱስ መቃርስ ታላቁ
እንኳን አደረሳችሁ!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"የምስራች ደስ ይበለን"
የምስራች ደስ ይበለን (፪)
የዓለም መድኃኒት ተወለደልን
ምስራች ደስ ይበለን
ኢየሱስ የዓለም ቤዛ (፪)
የዓለም ቤዛ (፫) ለኛ ተወለደልን
አዝ = = = = =
ንጉሥ ሄሮድስ ይህን ሲሰማ (፪)
ፈልጋችሁ አምጡት በቀን በጨለማ (፪)
አዝ = = = = =
ሰብዐ ሰገል እንደታዘዙት (፪)
በኮከብ ተመርተው ህፃኑን አገኙት (፪)
አዝ = = = = =
ሰገዱለት ከመሬት ወድቀው (፪)
ወርቅ እጣን ከርቤውን በረከቱን ሰጥተው (፪)
አዝ = = = = =
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ታኅሣሥ ፳፱
ልደተ ክርስቶስ
ታኅሣሥ ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን የከበረና የተመሰገነ ታላቅ የልደት በዓል ሆነ የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከከበረች ድንግል ማርያም የተወለደባት ዕለት ከበዓላት ሁሉ ተለይታ ከፍ ከፍ ያለች ናት።
የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶቻችን የከበረ የልደትን በዓል በሁለት ቀኖች ያከብሩ ዘንድ በምክራቸው ተስማሙ ከወደኋላ ባለ በሃያ ስምንት ሌሊቱ የልደት በዓል ነው በሃያ ዘጠኝ መዓልቱ ጳጉሜን ስድስት በሆነ ጊዜ በዚያች ዓመት የልደት በዓል በሃያ ስምንት በመዓልት ይከበራል። ጳጉሜን አምስት ከሆነ ግን በሃያ ዘጠኝ ይሆናል ስለዚህ የበዓላት ሁሉ ራስ የሆነ የከበረ የልደት በዓል በሁለቱ ቀኖች እንዲከበር አዘዙ ወሠኑ።
የበዓላት ራስ ስለሆነ ስለ ከበረ የልደት በዓል የከበረ ወንጌል እንዲህ አለ። በንጉሡ በኄሮድስ ዘመን በይሁዳ ዕፃ በቤተልሔም ጌታ ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ እነሆ የፍልስፍና ሰዎች ከምሥራቅ መጥተው ወደ ኢየሩሳሌም ደረሱ። ኮከቡን በምሥራቅ አይተን እንሰግድለት ዘንድ መጥተናልና የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው እያሉ።
እሊህ ፈላስፎች ከበለዓም ወገን ናቸው እነርሱም በከዋክብት የሚፈላሰፉ ናቸው በመጽሐፋቸው በበለዓም መጽሐፍም የአይሁድ ንጉሥ ሊወለድ እንዳለው ተጽፎአል እርሱ በለዓም ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል ከእስራኤልም ንጉሥ ብሎ ነበርና።
ይቅር ባይ እግዚአብሔርም በረቀቀ ጥበቡ አለበማቸው በሚያምኑበትም ሳባቸው እነርሱ ከዋክብትን በመጠባበቅ የሚፈላሰፉ ናቸውና ይህንንም ኮከብ ገለጠላቸው በአዩትም ጊዜ ደስ አላቸው መልኩ በብዙ አይነት ልውጥ ነውና። ሕፃን የታቀፈች ድንግል ብላቴናን ይመስላል እርሱም በቀን ይጓዛል በሌሊትም ይሠወራል ከሰውም ሲገናኙ ይሠወርና ሲቆሙ በሌላ አንጻር ይገለጥላቸዋል።
እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ ያ ኮከብ ተሠወራቸው እጅግ አዘኑ የሚያደርጉትንም አላወቁም ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ገብተው ስለተወለደው ንጉሥ ጠየቁ። የእሊህም ሰዎች ቊጥራቸው ሠላሳ ሽህ ነው ነገሥታቱ ሦስት ናቸው ለየእንዳንዱ ንጉሥ ዐሥር አሥር ሽህ ሠራዊት አለው።
ንጉሡ ኄሮድስም በሰማ ጊዜ ደነገጠ ኢየሩሳሌምም በመላዋ ከእርሱ ጋር ደነገጠች። የካህናት አለቆችና የሕዝቡን ጸሐፊዎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ በየት ይወለዳል ብሎ ጠየቃቸው። በይሁዳ ዕፃ በቤተልሔም ነው አሉት በነቢይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና።
የኤፍራታ ዕፃ ቤተልሔም አንቺም ከይሁዳ ነገሥታት አታንሺም ወገኖቼ እስራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ካንቺ ይወለዳልና። ከዚህም በኋላ ኄሮድስ ሰብአ ሰገልን በጭልታ ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከነሱ ተረዳ።
ሒዳችሁ የዚያን ሕፃን ነገር እርግጡን መርምሩ ያገኛችሁትም እንደሆነ እኔም መጥቼ እሰግድለት ዘንድ በኔ በኩል ተመልሳችሁ ንገሩኝ ብሎ ወደ ቤተልሔም ሰደዳቸው። የነገራቸውንም ሰምተው ከንጉሡ ሔዱ እነሆ በምሥራቅ ያዩት ከከብ ወደ ቤተልሔም እስኪያደርሳቸው ይመራቸው ነበር ሕፃኑ ካለበትም ዋሻ ላይ ደርሶ ቆመ።
ኮከቡንም ባዩ ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር አገኙት ወድቀውም ሰገዱለት ሣጥናቸውንም ከፍተው ወርቅ ከርቤ ዕጣን እጅ መንሻ አቀረቡለት።
በእግዚአብሔርም ፈቃድ ዮሴፍ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሕፃኑ ጌታ ኢየሱስም በዚያች ዕለት ወደ ቤተልሔም መጡ ስለዚህም ሰብአ ሰገል አገኙአቸው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ናዝሬት በሌላ ቦታ አላደገምና ከተወለደም ዕድሜው ሁለት ዓመት ሆኖት ነበር።
አምላክ ነውና ስለ መንግሥቱ ወርቅን ገበሩለት ክህነትም ገንዘቡ ነውና ዕጣንን ገብሩለት ማሕየዊ ለሆነ ሞቱ ምልክትም ከርቤን ገበሩለት። ወደ ኄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ነገራቸው በሌላ መንገድም ወደ አገራቸው ተመልሰው ገቡ። አምላክ በሥጋ ስለመገለጡ ዓዋጅ ነጋሪዎችና ሰባኪዎች ሆኑ።
ይችም ዕለት ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት ስለርሷ የተናገረላት ናት እንዲህ ብሎ እነሆ ድንግል ፀንሳ ወንድ ልጅን ትወልዳለች ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።
ስለዚችም የከበረች ድንግል ነቢይ ሕዝቅኤል እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ እግዚአብሔርም አለኝ ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች አትከፈትም የሚገባበትም የለም የእስራኤል ፈጣሪ እግዚአብሔር እንደተዘጋች ይገባባታልና ተዘግታ ትኑር አለ።
ነቢዩ ዳንኤልም አለ ሌሊት በራእይ አየሁ እነሆ ታላቁ እንደ ሰው ልጅ በሰማይ ደመና መጣ ዘመኑን ወደ ሚያስረጅ ደረሰ ከፊቱም አቀረቡት የዘላለም አገዛዝ ጌትነት መንግሥት ተሰጠው ሕዝቡና አሕዛቡ ሁሉ መንደር መንድረው የሚኖሩትና ነገዱም ነገሥታቱም ሁሉ ይገዙለታል አገዛዙም የዘላለም አገዛዝ ነው መንግሥቱም የማያልፍ የማይጠፋ ነው።
ዳግመኛም ኢሳይያስ እግዚአብሔር እንደ እኔ የሥጋ መጋረጃ በመጋረድ ተገለጸልኝ አለ። አሁንም ደግሞ አዲስ ሰማይ አዲስ ምድር እሠራ ዘንድ አለኝ አለ ሁለተኛም ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች ከእርሷም ጽጌ አበባ ይወጣል አለ። ዳግመኛም ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶልናልና ይኸውም ሥልጣን በጫንቃው የሆነ ክርስቶስ ነው። ስሙም ድንቅ መካር የዘላዓለም አባት የሰላም አለቃ ይባላል አለ።
ኤርምያስም አለ እግዚአብሔር እንዲህ አለ በዚያን ወራት ለዳዊት ብርሃንን አወጣለሁ በምድርም የቀና ፍርድን ያደርጋል እግዚአብሔርም ያመኑበትን ያድናቸዋል።
ኤልሳዕም እንዲህ አለ።እ ግዚአብሔር ከሰማይ ይወርዳል በእስራኤል ልጆች አደባባይም በመመላለስ ለሕዝቡ ዕውነትን ያስተምራቸዋል ከአብርሃም ልጅነት ልዩ ከሆኑ ወገኖች በቀር አሕዛብ ሁሉ ይታዘዙለታል። ናሆም ነቢይም እንዲህ አለ። እግዚአብሔር በእኔ አርአያ ይመጣል ልብሱም እንደልብሴ ነው።
ነቢዩ ኢዩኤልም እንዲህ ተናገረ የእግዚአብሔር ዙፋን የሆነች ብላቴና ድንግልን አየሁ እርሷም እንደ እሳት ያልባት ነበር ስለርሷም ይቺ ማን ናት ብዬ ኪሩብን ጠየቅሁት ከአዳም ልጆች የተመረጠች የእግዚአብሔር ዙፋን ይህች ድንግል ናት በርሷም የተጐሳቈሉ አሕዛብ ይድናሉ ለአመነባትም ረድኤትና መጠጊያ ናት።
ዳዊትም በመዝሙሩ እንዲህ አለ እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ ዛሬም በተዋሕዶ ወለድኩህ አለኝ። ለምነኝ አሕዛብን ርስት አድርጌ እሰጥሃለሁ ግዛትህም በመላው ዓለም ነው። ዳግመኛም አብ አለ ቀዳማዊ ወልድ በኃይል ቀን ካንተ ጋራ ሳለሁ ከአጥቢያ ኮከብ በፊት ከሆድ ወለድኩህ እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለሙ አገልጋይ ካህን ነህ ብሎ እግዚአብሔር ማለ ከማለም አይጸጸትም።
ቤዛ ይስሐቅ በግዕ ከኅቱም ዕፀ ሳቤቅ እንደተገኘ ለእስራኤልም በበረሀ ውስጥ ከኅቱም አለት ውኃ እንደ ፈለቀ የደነቀች የአሮን በትርም እንደለመለመችና እንደ አፈራች። በሶምሶንም እጅ ውስጥ ከአህያ መንጋጋ ዐጥንት ውኃ እንደ ፈሰሰ።
እንዲሁ የጌታችን ልደት በኅቱም ድንግልና ሆነ። በዕፀ ጳጦስ ውስጥ እሳት እንደ ነደደች ዕፂቱም እንዳልተቃጠለች እንዲሁ የመለኮቱ እሳት ድንግልን አላቃጠላትም።
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
እንኳን አደረሳችሁ!
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ጌታችን ስለተወለደባት ምሽት ቅዱስ ኤፍሬም አንዲህ አለ.....
‹‹ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡ ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!
ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም! ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡ ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን! ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው እንዳይታበይባት! ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን አንበቀልባት! የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት! የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት!
ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው! ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡ ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ!
የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት! ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!››
እንኳን ለአምላካችን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ፤
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፤
በምሉእ ፍቅሩ ሰውን ከባርነት ወደ ነጻነት ለመመለስ በሥጋ ሰብእ የተወለደው ጌታችን ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡
“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዘሠምሮ ለሰብእ፤ ክብር በሰማያት ለእግዚአብሔር ይሁን›› በምድርም እጅግ ለወደደው የሰው ልጅ ሰላም ይሁን” (ሉቃ ፪÷፲፬)
ይህ ቃለ ሰላም በጌታችን ዕለተ ልደት የተነገረ ነው፣ ቃሉ የተነገረው እንዲሁ እንደ ተራ ነገር ሳይሆን በቃለ መዝሙር እየተደጋገመ ነው፡፡ የተዘመረውም በምድራውያን ደራሲዎች ሳይሆን በሰማያውያን መላእክተ እግዚአብሔር ነው፣ የያዘው መልእክትም ሰማያውያንና ምድራውያንን ሁሉ ያካለለ ነው፡፡ የመልእክቱ ገዢ ሓሳብም አምላክ ከሰውነታችን ጋር ባለመለያየት፣ ባለመጠፋፋት፣ ባለመቀላቀል፣ ባለመዋዋጥ፣ ባለመለዋወጥና ያለባዕድና አንድ አካል፣ አንድ ክዋኔ፣ አንድ ጠባይ ሆኖ በተዋሕዶ ተገልጾኣልና እግዚአብሔር ይክብር ይመስገን፡፡ የተዋሕዶውም ምስጢር ሰላምን ያሰፍናልና እግዚአብሔር ሰውን በእጅጉ መውደዱ ከዚህ ተዋሕዶ ዓውቀናል የሚል ነው፡፡
"ኖላዊነ ኄር- መድኃኔዓለም "
ኖላዊነ ኄር መድኃኔዓለም
ለነፍስ ወለሥጋ ወለኵሉ ዓለም
ዕቀበነ (፫) ለዓለመ ዓለምን
ድምጼን ይለዩታል በጎቼ በሙሉ
አያስታቸውም መንገደኛ ሁሉ
በራሱ በአምላክ የተባለላችሁ
በጎች ተሰብሰቡ ወደ በረታችሁ
አዝ...
ነብይ ነኝ የሚል የሠፈር ዜናዊ
አድርጎ የሾመ ራሱን ወንጌላዊ
ነጣቂ ተኩላው ተበራክቷልና
መንጋህን ጠብቀው በእምነት እንዲጸና
አዝ...
ከአምላክ የተላከ እውነተኛ እረኛ
ለመንጋው የሚያስብ ያይደለ ምንደኛ
ፊት የተማረ ነው ኋላም የተሾመ
በሐዋርያዊ ክህነት በእውነት የታተመ
አዝ...
ከጌታ የመጣ ካልሆነ ክህነቱ
ከአበው የተለየ ከሆነ ትምህርቱ
በበሩ ያልገባ ሌባ ነው ስላለ
ምዕመናን አትስሙት አሳቹ ስላለ
አዝ...
ጩኸታችን ሰምተህ ጭንቀታችን ዓይተህ
በየዘመናችን የሚታደግ ልከህ
እውነተኛው መምህር የበጎች እረኛ
አንተው አሰማራን ተመልከት ወደ እኛ
በዘማሪ ቀሲስ እስክንድር ወልደማርያም
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ቸር ጠባቂ ለበጎቹ መልካም መሰማርያን ያዘጋጃል፤ ያሰማራቸዋልም።
ቸር ጠባቂ በጎቹን በመልካም ስፍራ ለማሰማራት መሰማርያን ያዘጋጃል። ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፤ የሚያሳጣኝም የለም፤ በለመለመ መስክ ይመራኛል(መዝ 22፡1)።›› እንዳለው ቸር ጠባቂ በጎቹን በለመለመ መስክ ያሰማራቸዋል። ‹‹በሙሴና በአሮን እጅ ህዝብህን እንደ በጎች መራሀቸው›› መዝ 76፡20 እንደተባለም በበጎ ይመራል። የለመለመ መሰማርያ የተባለም የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ የአገልግሎት ዘርፍ ነው።
ምንደኛ ግን ራሱን ያሰማራል። በትንቢተ ሕዝቅኤል በምዕራፍ 43 ቁጥር 2 ላይ እንደተገለፀው ክፉ እረኛ ራሱን በበጎቹ መካከል ያሰማራል። ጠቦቶቹንም ያርዳቸዋል፤ ይበላቸዋልም። ‹‹ጮማውን ትበላላችሁ፤ ጠጉሩንም ትለብሳላችሁ፤ የወፈሩትንም ታርዳላችሁ፤ በጎቹን ግን አታሰማሩም (ሕዝ 34፡23)።›› እንዳለ መሰማርያውንና ውኃውን ይረግጣል፤ ያፈርሳልም። ለራሱና ለራሱ ብቻ መሰማርያን ያዘጋጃል። ለእኛ ግን ለነፍስም ለሥጋም የሚሆን መሰማርያን የሚያዘጋጅልን እርሱ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ቸር ጠባቂ በጎቹን ያበዛል።
ቸር ጠባቂ በበረት ያሉትንና በውጭ ያሉትን በጎች አንድ ለማድረግ ይተጋል። በውጭ ያሉትን በጎች ወደ በረት ለማስገባት ሌትና ቀን ይሠራል። ይህንንም መርህ በማድረግ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን ለዓለም በመስበክ በጎችን አብዝተዋል። ቅጥረኛ ግን በውጭ ያሉት በጎች በዚያው ቢቀሩ አይገደውም። በበረት ያሉትንም ጭምር በመከፋፈል ከበረት አስወጥቶ ይበትናል። እርሱ ስለራሱ ጥቅም እንጂ ስለበጎቹ ምንም የማይገደው ምንደኛ ነውና። ነገር ግን ‹‹የማሰማሪያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው (ኤር 23፡1)።›› እንደተባለ በመጨረሻው ቀን መጠየቁ አይቀርም። እኛ ግን የጠፉትን የሚፈልግ፣ ያሉትን የሚያፀና እውነተኛ ጠባቂያችን እርሱ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብለን እናምናለን።
ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት ‹‹እኔ ባሪያህ የአባቴን በጎች ስጠብቅ አንበሳና ድብ ይመጣ ነበር፥ ከመንጋውም ጠቦት ይወስድ ነበር። በኋላውም እከተለውና እመታው ነበር፥ ከአፉም አስጥለው ነበር፤ በተነሣብኝም ጊዜ ጕሮሮውን ይዤ እመታውና እገድለው ነበር (1ኛ ሳሙ 17፡34)። ›› እንዳለው ከዲያብሎስ ጉሮሮ ከአንበሳም መንጋጋ ያዳነን እውነተኛው ጠባቂያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ቸር ጠባቂ ስለበጎቹ መስዋእት ይሆናል።
ቸር ጠባቂ ራሱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ይሰጣል። ተኩላ ሲመጣ ጥሎ አይሸሽም፤ ከበጎቹ ቀድሞ ይዋጋል እንጂ። ‹‹ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከማኖር ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም (ዮሐ 15፡13)።›› እንደተባለ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ መስዋእት ይሆናል። ምንደኛ ግን በጎቹን ስለ ራሱ አሳልፎ ይሰጣል። ተኩላ ሲመጣም በጎቹን ጥሎ ይሸሻል፤ በጎቹም ለምድር አራዊት መብል ይሆናሉ።
‹‹ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ። ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍሱን ይሰጣል። ጠባቂ ያይደለ፥ በጎቹም ገንዘቡ ያልሆኑ ምንደኛ ግን ቅጥረኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም መጥቶ በጎቹን ይነጥቃቸዋል፤ ይበትናቸዋልም። ምንደኛስ ይሸሻል፤ ስለ በጎቹም አያዝንም፤ ምንደኛ ነውና። ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፥ የእኔ የሆኑትን መንጋዎቼን አውቃለሁ፡፡ የእኔ የሆኑትም ያውቁኛል፡፡ አብ እኔን እንደሚያውቀኝ እኔም አብን አውቀዋለሁ፤ ለበጎች ቤዛ አድርጌ ሰውነቴን አሳልፌ እሰጣለሁ (ዮሐ 10፡11-15)።›› እንዳለ ነፍሱን ስለ በጎቹ አሳልፎ የሰጠ እውነተኛ ጠባቂያችን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እንደተናገረው ቸር ጠባቂ እርሱ ነው፤ በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎቹ ትልቅ ጠባቂ የሆነው እርሱ ነው (ዕብ 13፡20)። የነፍሳችን ጠባቂ የሆነው እርሱ ነው (1ኛ ጴጥ 2፡23)። የእስራኤል ዘነፍስ ጠባቂ የሆነውም እርሱ ነው (መዝ 79፡1)። እውነተኛም ጠባቂ እርሱ ነው (ዮሐ 10፡7)።
በጎችን የመጠበቅ ኃላፊነትና ተጠያቂነት
በጎችን የመጠበቅ ኃላፊነት ከተጠያቂነት ጋር አብሮ ለጠባቂዎች (ለሐዋርያትና ከሐዋርያት ቀጥሎ እስከ ዕለተ ምጽዓት ለሚነሱ እውነተኛ መምህራን) ተሰጥቷል። ‹‹ግልገሎቼን አሰማራ፤ ጠቦቶቼን ጠብቅ፤ በጎቼን አሰማራ።›› ብሎ የመጠበቅ ኃላፊነትን በጴጥሮስ በኩል ለሐዋርት ሰጥቷል (ዮሐ 21፡15-17)። ‹‹በጎቼን ከጠባቂዎች እጅ እፈልጋለሁ›› ብሎም በጎችን የመጠበቅ አገልግሎት ተጠያቂነትም እንዳለበት ተናግሯል (ሕዝ 34፡10)። በጎች (ምዕመናን) የክርስቶስ ተከታዮች እንጂ የእረኞቹ ተከታዮች አይደሉም፤ ጠባቂዎችም ባለአደራዎች እንጂ የበጎቹ ባለቤቶች አይደሉምና።
ዛሬስ የጠባቂዎች ድርሻ ምንድን ነው?
ጌታችን እንዳስተማረው የጠባቂዎች (የካህናትና የመምህራን) ድርሻ የሚከተሉትን ያጠቃልላል።
በበሩ መግባት፡- በተዋሕዶ ላይ መመሥረት፣ በሥርዓት መመራት፣ በእምነት መኖር
በጎቹን ማወቅ፡- በግና ተኩላን ለይቶ ማወቅ፣ የራስንና የሌላውን ለይቶ ማወቅ፣ ለበጎቹም ግልፅ መሆን
በጎቹን መጠበቅ፡- በጎችን ነቅቶ መጠበቅ (እንዳይነጠቁ)፣ ባክነው እንዳይጠፉ መንከባከብ
መሠማርያውን ማዘጋጀት፡- የሚያስፈልጋቸውን ትምህርት፣ ተግሳፅና ምክር መስጠት
በመልካም ስፍራ ማሰማራት፡- ከፊት ሆኖ በመምራት (በማገልገል) ለሥጋ ወደሙ ማብቃት
አንድነትን ማጠናከር፡- ከውጭ ያሉትን በማምጣትና ከውስጥ ያሉትን በማፅናት አንድነትን ማጠናከር
መስዋዕትነትን መክፈል፡- እውነትን በመመስከር መልካም አርአያ መሆን
የበጎች (የተጠባቂዎች) ድርሻስ ምንድን ነው?
በጌታችን ትምህርት መሠረት በጎች (ተጠባቂዎች) ጠባቂያቸውን በሚገባ ድምፁን ማወቅና እርሱንም መከተል፣ እውነተኛ ጠባቂ ያልሆነውን (ክፉውን እረኛ ወይም ምንደኛውን) መለየትና ከእርሱም መራቅ፣ ዛሬ እውነተኛ የሆነው ጠባቂያቸው ወደ ምንደኛነት ቢቀየር እንኳን ቶሎ ነቅቶ መለየት መቻልና ራሳቸውንም መጠበቅ ይኖርባቸዋል። እውነተኛና ቸር ጠባቂያችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም በጎች ያድርገን፤ አርአያ የሚሆኑ ደገኞች ጠባቂዎችንም አያሳጣን።
የኖላዊ ክብረ በዓል ከታህሳስ 21-27 ባለ እሁድ ቀን ብቻ የሚከበር ሲሆን ይህ በዓል በተለይም በምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በጣባ የጎደና ቀበሌ በኢትዮጵያ ብቸኛ በሆነው ጣባ ኖላዊ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ይከበራል ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"እምሥራቀ ፀሐይ"
እምሥራቀ ፀሐይ አስከነ አረብ ይት አኮት ስሙ ለእግዚአብሔር አምላክነ ኪያከ ወልዶ ዘፈነወለነ{፪}
ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀካህናቲነ አስተጋብአነ(፪) ሀበ ትረፍቅ መካነ{፪}
ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ የአምላችን የእግዚአብሔር ስሙ ይመስገን ልጁ ወዳጁን አንተን ልኮልናልና{፪}
ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህናትን ወደ አንተ ሰብስበን(፪) እኛ እኛን ልጆችህን{፪}
©በዘማሪት በላይነሽ አሰፋ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ጥር ፮
በዓለ ግዝረቱ ለክርስቶስ
ጥር ስድስት በህዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጸመ ልሳነ ዕፍረት ሐዋርያው ጳውሎስ ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ ብሎ እንደተናገረ።
ለብዙዎችም ጌታችን ወደ ቤተ ግዝረት እንዳልገባና እንዳልተገረዘ ይመስላቸው ነበር እነርሱ እንዳሰቡት ሁኖ ቢሆን ኑሮ አይሁድ ታላቅ ምክንያትን የሚያገኙ በሆኑ ነበር ጌታችን ግን የግዝረትን ሕግ ፈጸመ ለእኛ በግዝረት ፈንታ የክርስትና ጥምቀትን ሰጠን የፋሲካውንም ቂጣ በላ በእርሱም ፈንታ ሥጋውንና ደሙን ሰጠን።
የከበረ ወንጌል ስምንተኛው ቀን በተፈጸመ ጊዜም ሕፃኑን ሊገዝሩት ወሰዱት ሳትፀንሰው መልአኩ እንዳወጣለት ስሙን ኢየሱስ አሉት እንዳለ ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ማርያም ጻድቅ አረጋዊ ዮሴፍን "እንደ ሕጉ ልጄን እንዲገርዘውና ስሙንም እንድንሰይመው ብልህ የሆነ ገራዥ ሰው አምጣልኝ" አለችው። ዮሴፍም ሔዶ የሚገርዝ ባለሙያ አመጣ ያ ባለሙያም ሕፃኑን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በእናቱ በንጽሕት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ አየው "እንድገርዘው ሕፃኑን በጥንቃቄ ያዙት" አላቸው።
ሕፃን ጌታ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው "ባለሙያ ገራዥ ሆይ ደሜ ሳይፈስ ትገርዘኝ ዘንድ ትችላለህን በዚያች ዕለት ካልሆነ በቀር ደሜ አይፈስምና ጐኔን በጦር ሲወጉኝ ያን ጊዜ ውኃና ደም ይፈሳል ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆቹ መድኃኒት ይሆናል።"
የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ያ ባለሙያ በሰማ ጊዜ አደነቀ ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሥቶ ከሕፃኑ ጌታ እግር በታች ሰገደ ያንጊዜም ምላጮቹ በእጆቹ ላይ ቀልጠው እንደ ውኃ ሆኑ የከበረች ድንግል እመቤታችንን ማርያምን "ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ይህ ልጅሽ ስለርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው" አላት።
ሕፃኑም ለዚያ ባለሙያ ዳግመኛ መልሶ እንዲህ አለው "እኔ ነኝ ትገዝረኛለህን ወይስ ተውክ ወይም ያባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ እኔ ላድርግ" ያም ባለሙያ "የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው" አለው ሕፃን ጌታችንም "አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ የሕዝቡ ሁሉ አባቶች የሆኑ ናቸው ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጣቸው" ባለሙያውም "እኔ ከአንተ ጋር እናገር ዘንድ አልችልም በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና" አለው።
በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ ጌታችን ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ "አባት ሆይ ለአብርሃም ለይስሐቅ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ" አለ። ያን ጊዜ ያለ ሰው እጅ በሕፃኑ ሥጋ ላይ ግዝረት ተገለጠች። ድንግልናዋ ሳይለወጥ ከድንግል ማሕፀን እንደ መውጣቱ የጌታችን ግዝረቱ የማይመረመር ሆነ እንዲሁ ወደ ሐዋርያት በተዘጋ አዳራሽ መግባቱና መውጣቱ እንደማይመረመር እንዲሁ እንደ ፈቀደ ከረቀቀ ጥበቡ ችሎታውን በመገረዝ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቆረጥ ገለጠ።
አዳምንና ልጆቹን ያድናቸው ዘንድ በፈቃዱ ከጐኑ በመስቀል ላይ የሚፈሰው ደምና ውኃ ካልሆነ በቀር ብዙም ሆነ ጥቂት ሊሆን አይችልም እርሱ በፈቃዱ ሕጉ እንዲፈጸም አስቀድሞ አዘዘ እንጂ።
ያም ባለሙያው ገራዥ ይህን ተአምር ባየ ጊዜ የሕፃኑንም ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ የክብር ባለቤት ከሆነ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር በታች ሦስት ጊዜ ሰገደና "በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ የእስራኤልም ንጉሥ ነህ" አለው። ከዚህም በኋላ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተአምራቱ ያየውንና የሰማውን እየተናገረ ወደ ቦታው ሔደ።
ለእርሱ ለጌታችን ከቸር አባቱ ጋራ ማሕየዊ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋራ ክብር ምስጋና ስግደትም ይሁን: አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው አባታዊ የሰላም ጥሪ አስተላለፉ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"ላሊበላ ቅዱስ"
በቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ታኅሣሥ ፳፱
ልደቱ ለጻድቅ ካህን ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ
ቅዱስ ላሊበላ ከአባቱ ዣን ስዩምና ከእናቱ ኪርወርና በታኅሣሥ ፴፱፣ ፲፻፩ ዓ.ም በላስታ ቡግና ወረዳ ልዩ ስሟ ሮሀ በተባለችው ሥፍራ ተወለደ፡፡ አባቱ በላስታ አውራጃ የቡግናው ገዢ ነበር፤ እናቱ ደግሞ አገልጋይ ነበረች፡፡ የልደቱን ነገር አስቀድሞ ቅዱስ ሚካኤል ለእናቱ ነግሯት ነበር፤ ቅዱስ ላሊበላ በተወለደ ጊዜም ብዙ ነጫጭ ንቦች መጥተው በሰውነቱ ላይ አርፈው እንደ ማር እየላሱት ስለታዩ እናቱ ‹‹ልጄን ንብ ዘበኛ ሆኖ ይጠብቅልኛል›› ስትል ስሙን ‹‹ላል ይበላል›› ብላዋለች፡፡ ‹ላል› በአገውኛ ‹ንብ› ማለት ነው፡፡ በጊዜ ብዛት በተለምዶ ነው ‹‹ላሊበላ›› ተብሎ መጠራት ተጀመረ፡፡ ንቦቹ ግን ሥጋዊ ንቦች ሳይሆኑ በንብ የተመሰሉ መላእክት ናቸው፡፡ ንጉሥ መሆኑን እያመለከቱ ሃይማኖትና ምግባር ማር ከእርሱ እንደሚቀዳ ለማመልከት በንብ ሠራዊት ተመስለው ሰውነቱን ላሱት፡፡ እንደ ዮሐንስና እንደ ኤርምያስም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ሞልቶበታል፡፡
ወላጆቹም እግዚአብሔርን በመፍራትና በበጎ ምግባር አሳደጉት፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ካደገ በኋላም ስለ ቅድስናውና ስለ ንግሥናው ትንቢት እየተነገረ ስለነበር ወንድሙ ቀናበት፡፡ በዚህም የተነሣ ላሊበላ ሀገሩን ለቅቆ ወደ ኢየሩሳሌም አቀና፤ በዚያም ለብዙ ዓመታት ቆየ፡፡
ቅዱስ ላሊበላም ከስደት እንደተመለሰ ወንድሙ መልእክቶኞችን ልኮ ካስመጣው በኋላ ምክንያት አድርጎ ከሦስት እስከ ሰባት ሰዓታት ያህል እንዲገረፍ አደረገ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ከግርፋቱ ሠውሮት ስለነበር ምንም ጉዳት አልደረሰበትም፡፡ ወንድሙም ከፊቱ ባቆመው ጊዜ ይህን ተአምር አይቶ ከመኳንንቶቹ ጋር አደነቀ። ይቅርታ እንዲያደርግለትም ቅዱስ ላሊበላን ጠይቆት እርቅ ሆነ፡፡ ከዚህም በኋላ መስቀል ክብራን አገባ፡፡ በ፲፻፩፻፶፮ ዓ.ም ‹ገብረ መስቀል› ተብሎም ነገሠ፡፡
በዘመነ መንግሥቱም ዘወትር ለድሆችና ለምስኪኖች እንዲሁም ለችግረኞች ይመጸውት ነበር፡፡ በአንድ ወቅትም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦለት ወደ ሰማያት አወጣው፤ ዐሥሩን አብያተ ክርስቲያናትንም እንዴት መሥራት እንደሚችል አሳየው፡፡ ወደ ምድርም ተመልሶ መንፈስ ቅዱስ እንዳረቀቀው በአስደናቂ ጥበብ አብያተ ቤተ ክርስቶያናቱን አነጻቸው፡፡
ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናቱ በሦስት መደብ የተከፋፈሉ ናቸው፤ ሁሉም የመሬት ውስጥ ለውስጥ መተላለፊያም አላቸው፡፡ በመጀመሪያው መደብ ውስጥ ‹ቤተ መድኃኒዓለም፣ ቤተ ማርያም፣ ቤተ-መስቀል፣ ቤተ-ደናግል፣ ቤተ-ጎለጎታ እና ቤተ-ሚካኤል ሲገኙ፤ በሁለተኛው መደብ ውስጥ ደግሞ፣ ቤተ-አማኑኤል፣ ቤተ-መርቆሪዮስ፣ ቤተ-ሊባኖስ እና ቤተ-ገብርኤል› ይገኛሉ፡፡
በሦስተኛው መደብ ውስጥ የሚገኘው ‹ቤተ-ጊዮርጊስ› ነው፡፡ ቤተ-ጊዮርጊስ ከሁሉም አብያተ ክርስቲያናት በስተመጨረሻ የተሠራና እጅግ ያማረ፣ በኪነ ሕንፃ ውበቱም ከሁሉም የላቀ ነው፡፡
ይህም የአብያተ ክርስቲያናቱ ሠሪዎች በሥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተራቀቁ የመምጣታቸው ምሥክር ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ሲወሱ የሚታየው ምስል የዚሁ የቤተ-ጊዮርጊስ ምስል ነው፡፡ ገድለ ላሊበላ እንደሚያስረዳው የፍልፍል አብያተ ክርስቲያናቱ ሥራ የተጀመረው በላሊበላ ዐሥረኛ ንግሥ ዘመኑ ነው፡፡ ሥራውን ለማጠናቀቅም ፳፫ ዓመት ፈጅቷል፡፡ አብያተ ክርስቲያነቱንም አንጾ ከጨረሰ በኋላ መንግሥቱን ለወንድሙ አወረሰው፡፡
ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በብርሃን ሠረገላ ተቀምጦ የሚስፈራ መብረቅን የተጎናጸፉ አእላፍት ሠራዊቶቹ ዙሪያውን ሆነው ወደርሱ መጥቶ እንዲህ አለው፤ ‹‹ወዳጄ ላሊበላ ሆይ ሰላም ይሁንልህ፤ እኔ በማይታበል ቃሌ እነግርሃለሁ፤ ማደሪያህ በክብር ሁሉ ከከበሩ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያቶቼ ጋር ይሁን፡፡ በጸሎትህና በቃል ኪዳንህ ለሚታመን እምነቱ እንደ ጴጥሮስና ጳውሎስ ደም መፍሰስ ይሆንለታል፡፡ ወደ ቤተ መቅደስህም የሄደ በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደሴ እንደ ሄደ ይሆንለታል፤ መቃብርህንም የተሳለመ የሥጋዬን መቃብር እንደተሳለመ ይሆንለታል፡፡ በዓመታቱ ወሮች ሁሉ የተራቡትን እያጠገበ የተጠመቁትንም እያጠጣ መታሰቢያህን ለሚያደርግ እኔ የተሠወረ መና እመግበዋለሁ፤ የሕይወት ጽዋንም አጠጣዋለሁ፡፡ በመታሰቢያህ ቀንም ዕጣን ወይም ስንዴ የሚያገባውን እኔ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት በውስጠኛው መጋረጃ አስቀምጬ ከተቆረሰው ሥጋዬ አቆርበዋለሁ፤ በአማላጅነትህም እየታመነ የገድልህንና የቃል ኪዳንህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ያንተ ስም በተጻፈበት ቦታ እኔ ስሙን እጽፋለሁ፤ በፍጹም ልቡ ለሚያምን ይህን የማይታበል ቃል የተናገርኩ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ እኔ ነኝ፡፡›› ቅዱስ ላሊበላም ይህን ቃል ኪዳን በተሰጠው ጊዜ ጌታችንን እያመሰገነ በምድር ወድቆ ሰገደ፡፡ ጌታችንም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ በክብርና በምስጋና ወደ ሰማያት ዐረገ።
ቅዱስ ላሊበላ ከዚህ በኋላ ጥቂት ታሞ በሰላም ዐረፈ፤ የብርሃን መላእክትም ነፍሱን ተቀብለው የዘለዓለም ሕይወት ማደሪያ ወደሆነው ማረፊያው ገነት አስገቡት።
እግዚአብሔር አምላክ በቅዱስ ላሊበላ ጸሎት ነፍሳችንን ይማርልን፤ አሜን፡፡
©ገድለ ቅዱስ ላሊበላ
©መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ሰኔ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🔊ልደትን በባለልደቱ ቤት!
በእርግጥም እግዚአብሔር ሰውን ለመውደዱ ከዚህ የበለጠ ማሳያ ወይም ማስረጃ የለም፤ እንከን የለሽ ንጹህ አምላክ የእኛን ኃጢአተኛ ሰውነት አካሉ አድርጎ ተወለደ ሲባል ላስተዋለው ሰው ምንኛ ቢወደን ነው የሚለው ጥልቅ አድናቆትን ያጭራልና ነው፡፡ይህ ብቻም አይደለም በዚህ ነገረ ተዋሕዶ ምክንያት ሰውነታችን አምላክ ሆኖ በመንበረ ጸባኦት እንዲቀመጥ መብቃቱ የድኅነታችንና የክብራችን ከፍታ ምን ያህል አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደደረሰ መንፈሳችን በአንክሮ ይረዳዋል፡፡ድምር ውጤቱም በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ፍጹምና አስተማማኝ ሰላም መፈጠሩን ያስረዳናል፤ ሰማያውያኑ መላእክተ እግዚአብሔር በመዝሙራቸው ያበሰሩን ይህንን የምስራች ነው፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
እኛ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር በእጅጉ ይወደናል ስንል እንዲሁ ከሜዳ ተነሥተን ኣይደለም፡፡ በበደላችንና በኃጢአታችን ሳይጸየፈን ሰውነታችንን በረድኤት ወይም በኅድረት ያይደለ በኩነት ተዋሕዶ ወደ አምላክነት ደረጃ ከፍ ስላደረገው ነው እንጂ፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ፍጹምና ምሉእ ፍቅሩ ሰውነታችንን በመበረ ጸባኦት ኣስቀምጦ መላእክት ሳይቀሩ ፍጥረታትን በሙሉ እንድንገዛ አድርጎናል፤ ምክንያቱም መላእክት በዕለተ ልደት የዘመሩለት በተዋሕዶ አምላክም ሰውም ለሆነ ለቤተ ልሔሙ ሕፃን እንጂ ለመለኮት ብቻ ኣይደለምና ነው፡፡ የዕለተ ልደት መዝሙር ዛሬም በሰማያትም ሆነ በምድር በተዋሕዶ ሰውም ኣምላክም የሆነ አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለክበታል፣ ይመሰገንበታል፡፡የሰማዩና የምድሩ ዕርቅ ወደ ኋላ ላይመለስ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ ተከናውኖኣል፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሰውም አዋጭ ምርጫ ይህ ዕርቅ ተጠብቆ እንዲኖር ነው፣ ያለ ዕርቅ ሰላም ሕይወት የለውምና፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
የእግዚአብሔር ክብርና ሰላም በእጅጉ የተሳሰሩና የተቆራኙ ናቸው፤ እኛ እግዚአብሔርን ካከበርነው፣ ካዳመጥነው፣ ከታዘዝነውና ከተከተልነው ሰላም አለ ማለት ነው፡፡ ለሱ ካልታዘዝንና እሱን ካላከበርን ግን ዘላቂ ሰላምን ማግኘት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው፤ ምክንያቱም ሰላምን ጨምሮ መልካም ነገር ሁሉ ያለው በእግዚአብሔር እጅ ነውና፡፡ ዛሬ በሁሉም የዓለማችን ማዕዘን የሚታየው የሰላም መደፍረስ እግዚአብሔርን ካለማክበራችንና ለሱ ካለመታዘዛችን የተነሣ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም፡፡ ዓለም ከእግዚአብሔር ቃል ርቃ ለመሄድ በእጅጉ እየኳተነች ነው፤ በዚህ እኩይ ተግባርዋ ደግሞ እግዚአብሔር ለስጋትና ለጉስቁልና አሳልፎ እየሰጣት ነው፡፡ እግዚአብሔር በምስጢረ ሥጋዌው ቢታረቃትም ዕርቁን ማክበር አቅቶአታል፤ ይህንን የእግዚአብሔር ጸጋ ቸል ብላ የምታደርገው ሩጫ የትም ሊያደርሳት እንደማይችል ብታውቅና በንስሓ ብትመለስ እግጅ ተጠቃሚ ትሆናለች፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
የእግዚአብሔር ቃል “እናንተስ ከማይጠፋ ዘር ተወለዳችሁ” ብሎ ተስፋውን እንደነገረን ምድባችን ከማይጠፋ ዘር እንዲሆን ክርስቲያኖች የሆን ሁላችን በአእምሮ ጐልብተን፣ በሥነ-ምግባር ኣምረን፣ ጤናማ ሕይወትን ልንመራ ይገባናል፡፡
የአምላካችንን በዓለ ልደት ስናከብር ነገረ እግዚአብሔርን፣ ነገረ ፍቅርን፣ ነገረ ዕርቅንና ነገረ ሰላምን በማኅበረሰባችን የማሥረጽ አጀንዳ ይዘን ልናከብር ይገባል፡፡
ጠቡ ፣ ጥላቻው፣ መለያየቱ፣ መጠፋፋቱ፣ ለወንድሜ ከማለት ይልቅ ለኔ ለኔ ማለቱ ሲጎዳን እንጂ ሲጠቅመን ኣላየንም፡፡ አሁንም ወደ ልባችን እንመለስና በፍቅር፣ በዕርቅና በእኩልነት፣ በስምምነትና በወንድምነት ወደሚገኝ አንድነት እንምጣ፤ የልደቱ መዝሙር ያስተማረን ይህና ይህ ብቻ ነውና፡፡ በሌሎቹ ክፍለ ዓለማት እንደሆነው ሁሉ በሀገራችን የተከሠተው አላስፈላጊ ግጭት ብዙዎችን አሳጥቶናል፤ ብዙዎችንም ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎ ሜዳ ላይ ፈሰው የሰቆቃ ኑሮ እንዲገፉ አድርጎብናል፡፡ የሀገር ሀብት እንዲወድም ሆኖአል፤ ልጆቻችን ምናለ ከእንግዲህ ወዲህ ቢበቃንና ምድሪቱን የሰላም አየር እንድትተነፍስ ብንፈቅድላት፤ ይህ የወቅቱ የቤተክርስቲያናችን ዋነኛ መልእክትና ጥሪ ነው፡፡
በመጨረሻም፡-
በዓለ ልደት የእግዚአብሔር በዓል ነውና፣ እግዚአብሔር በምድራችን ሰላምን ያወርድ ዘንድ ካለን ከፍለን ለተፈናቃዮች፣ ለነዳያን እና ለአካል ጉዳተኞች በመለገስ በዓሉን በመንፈሳዊ ደስታና በሰላም እንድናከብር አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤
መልካም በዓለ ልደት ያድርግልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ
ተክለሃይማኖት
ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
@Ethiopian_Orthodox
"ሣር ቅጠሉ ሰርዶው"
ሣር ቅጠሉ ሰርዶው ሰንበሌጥ ቄጤማው
በዚያች ቀን በዚያች ወር ለምለም የነበረው
በእልልታ ዘመሩ በደስታ ተሞልተው
ጌታ መወለዱን የምስራች ሰምተው
እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌ ሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ (፪)
ያ ትሁት እረኛ ሳለ በትጋት
ብርሃንን ለበሰ በእኩለ ሌሊት
ጥሪ ተደርጎለት ከሰማይ ሠራዊት
ለመመልከት በቃ የጌታውን ልደት
አዝ= = = = =
የእረኝነት ሥራ ተንቆ እንዲቀር
ብሎ ሰው በልማድ ደንግጎ ነበር
የብዙ ሰው ራስ መሆኑን እረኛ
ክርስቶስ ሲወለድ ተረዳነው እኛ
አዝ= = = = =
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ጾመ ገሐድ እና በዓለ ልደት
ገሐድ፡- መገለጥ፣ ማታየት፣ መታወቅ፣ ማለት ሲሆን፤
ጋድ፡- ማለት ደግሞ ምትክ፣ ለውጥ፣ ቅያሪ ማለት ነው፡፡
በዓለ ልደት በመጣ ጊዜ ሁሉ በተለይም በዓሉ ዓርብና ረቡዕ ከዋለ ጥያቄዎች ይበዛሉ፡፡ የጥያቄው ምክንያት ደግሞ ደንታ-ቢስነት፣ አለመማር፣ ጥያቄን እንጂ መልስን አለመያዝ ያመጣው ጣጣ ነው፡፡
ማንኛውም ክርስቲያን ስለ ሰባቱ አጽዋማት በቂ ዕውቀት መያዝ አለበት፡፡ ትምህርቱም ከአንድ ቀን የማያልፍ ግፋ ቢል በሁለት ቀን ቁጭብሎ መማር በሚገባ ሊታወቅ የሚችል ቀላል ትምህርት ነው፡፡ አብዛኛው ክርስቲያን ግን ለሃይማኖታዊ ጉዳዮች የሚሰጠው ጊዜና ትኩረት ዝቅ ያለና በደንታ-ቢስነት የተመላ ስለሚሆን እንደዚህ ያሉ ቀላል ጉዳዮች ሳይቀሩ በየዓመቱ ጥያቄ ሁነው እንዲኖሩ አድርጓቸዋል፡፡
ወቅሶ ከማለፍ ድርሻን መወጣት ይሻላልና ቀላል ትምህርት ነው ያልኩትን ጾም ከተነሣሁበት ከገሐድ ጀምሬ ለማብራራት ልሞክር ሰባት ዓመት የሞላው ጤነኛ ክርስቲያን ሊጾማቸው የታዘዙ ሰባት የአዋጅ አጽዋማት አሉ። እነርሱም፦
1. ገሐድ [ጋድ] ትርጉሙን ከላይ ስላስቀመጥኩት ወደ ምሥጢሩ ስገባ ይህ ጾም የልደትና የጥምቀት ዋዜማ ነው። ፍትሐ ነገሥቱ አንቀጽ 15 ቁጥር 567 ላይ ‹‹እንደ ዐቢይ ጾም በመጠንቀቅ የሚጾም አለ ብሎ ሌሎቹን ከዘረዘረ በኋላ…ወጾመ ድራረ ልደት ወጾመ ድራረ ጥምቀት፡- የልደትና የትምቀት ዋዜማ ጾም ነው ይላል፡፡ አንዳንዶች በጾም ላይ ጾም የለምና ለገና ጋድ የለውም ለማለት ይሞክራሉ ቁምነገሩ ግን ጾሙን ደርበን ሳይሆን ለብቻ አንድ ዕለት ጨምረን ነው እየጾምን ያለንው፡፡
ከኅዳር 15 እስከ ታኅሣሥ 28 ያለው ቀን ሲቆጠር 44 ነው፡፡ ይኸውም 40ው የነቢያት ጾም ነው ሦስቱ ቀናት አንዱ የመበሥር የጌታ፣ ሁለተኛው የተበሣሪ የእመቤታችን ሦስተኛው የአብሣሪ የቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በሌላ መንገድ ሦስቱ ቀን የአብርሃም ሦርያዊ ጾም ነው፡፡ ይህ አባት በሦስት ቀን ሱባኤ ተራራ ማፍለሱን ታኅሣሥ 6 የሚነበበው ስንክሳር ይነግረናል፡፡ ስለዚህ ከ44ቱ ቀናት 40ው የነቢያት፣ ሦስቱ የጌታ፣ የእመቤታችን፣ የቅዱስ ገብርኤል /የአብርሃም ሦርያዊ/ የፊልጶስ ደቀ መዛሙርቱ ሊቀብሩት ሥጋው ተሠውሮባቸው ሦስት ቀን ጹመው ያገኙበት/፣ 44ኛዋ ቀን ግን ያለምንም ተቀናቃኝ ገሐድ ወይም ጋድ ናት፡፡ ገሐድ መገለጥ ነው፤ በባሕርየ መለኮቱ የማይታየው ጌታ በተዋሕዶተ ትስብእት ስለተገለጠልን መቀበያ አድርገን እንጾመዋለን።
ጋድ ባለው ግን የጥምቀትና የልደት በዓል ዓርብና ረቡዕ ቢውሉ ጾም የለምና ለዚያ ምትክ ማለት ነው፡፡ ይህንን ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 566 እንዲህ ገልጾታል፦ "ወዓዲ ረቡዐ ወዓርበ በኵሉ ሱባኤ ዘእበለ መዋዕለ ኃምሳ ወበዓለ ልደት ወጥመቀት ሶበ ኀብሩ ቦሙ፤ ዳግመኛም ረቡና ዓርብን በየሳምንቱ ሊጾሙ ይገባል፤ ከበዓለ ኃምሳ በስተቀር እንዲሁም ልደትና ጥምቀት ጊዜ ገጥሟቸው ረቡና ዓርብ ከሚውሉበት ጊዜ በቀር፡፡" ከዚህ የምንረዳው ልደትና ጥምቀት ዓርብና ረቡዕ ሲውሉ ጾም አለመኖሩን ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በምትካቸው አንድ ቀን የምንጾምላቸው መሆኑ ነው፡፡
የጥር 11 ቀን ስንክሳርም እንዲህ ይላል፥ ከላይ የገሐድን ነገር እያብራራ ከመጣ በኋላ…... በዚች ዕለት ምእመናን እስከምሽት እንዲጾሙ ያዘዙበት፣ ምክንያቱ ይህ ነው፡፡ የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል (ሥጋ፣ ወተት፣ ዕንቁላል) በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲያከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላት ናቸውና፡፡
እኛ በዚህ በኃላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን…... እያለ ይቀጥላል፡፡
ይህ ሁኖ ሳለ አንዳንድ ሰዎች በዚሁ በጥር 11 ቀን ስንክሳር መጨረሻ ላይ ያለውን አርኬ ጠቅሰው ከላይ የተነበበውን ሙሉ ንባብ ዘንግተውና ትተው ለገና ገሐድ የለውም ለማለት "ሰላም እብል ለጾመ ዕለት ዋሕድ፤ ዘስሙ ገሐድ ፤ ስሙ ገሐድ ለሚባል የአንድ ቀን ጾም ሰላም እላለሁ" የሚለውን ይጠቅሳሉ።
ጥቅሱ ቁርበተ ነክ ነው። ሙሉ ስንክሳሩ ሲነበብ አንቀላፍቶ ወይም ስንክሳሩን ሳይሰማ ከአርኬው ብቻ ለደረሰ ሰው ይመስለዋል እንጂ የጥር 11ዱ ስንክሳርስ በማያሻማ ሁኔታ በግልጽና በዝርዝር አስቀምጦታል። ገሐድም ለለልደትም ለጥምቀትም የተሠራ ነው፡፡ ዋሕድ ያለው የልደትና የጥምቀት ገሐድ አንድ ተብሎ ስለሚቆጠር ነው 44ቱ ጾመ ነቢያት አንድ ተብሎ እንደሚቆጠር፡፡
ገሐድ የሌላቸው ጾመ ሐዋርያት፣ ጾመ ፍልሰታ.... ፋሲካቸው ከረቡዕና ከዓርብ ላይ ሲሆን ይጾማሉ፡፡
2. ከላይ ዝርዝሩን የገለጽነው ጾመ ነቢያት (ከኅዳር 15 እስከ ታኅሥሥ 28)
3. ጾመ ነነዌ (የነነዌ ሰዎች ከእሳት የዳኑበት)
4. ዐቢይ ጾም (ዐቢይ እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሁኖ የጾመው)
5. ጾመ ሐዋርያት (አባቶቻን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ለስብከተ ወንጌል ከመውጣታቸው በፊት የጾሙት)
6. ጾመ ፍልሰታ ለማርያም (ጾመ ማርያም ሐዋርያት የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት ለማየት ያበቃቸው ጾም)
7. ጾመ ረቡዕ ወዓርብ፤ (ረቡዕ የጌታችን ሞቱ የተወሰነበት፣ ዓርብ ተሰቅሎ የሞተበት ነው) ይህን ዐውቆ የማይጾም እየጾመም የማያውቅ ክርስቲያን ሰነፍ ደካማ ይባላልና እናት ተምራ ለልጇ፣ አባት ተምሮ ለልጁ ሊያስተምረው ይገባል።
©መ/ር ኃይለማርያም ዘውዱ
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ኖላዊ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የበዓላት ቀኖና መሠረት ከህዳር 15 እስከ ጌታችን ልደት (ታህሳስ 28/29) ድረስ ያለው ወቅት በዘመነ ብሉይ የነበሩ ቅዱሳን ነቢያት የጌታን ልደት በተስፋ እየጠበቁ የገቡትን ሱባኤ፣ የጾሟቸውን አጽዋማት በማሰብ ልዩ ልዩ ክብረ በዓላት ይከበራሉ። ለእያንዳንዱ በዓልም የተለየ የቅዱሳት መጻሕፍት ንባብና ትርጓሜ፣ የተለየ የምስጋና መዝሙር ይዘመራል። በጾመ ነቢያት ውስጥ ያሉት የመጨረሻዎቹ ሦስት ሣምንታት በተለየ መልኩ ይከበራሉ። ወቅቱም ትንቢተ ነቢያትን በማሰብ ዘመነ ስብከት ይባላል። የነቢያት የስብከታቸው ማዕከል የክርስቶስ ሰው የመሆን ተስፋ ነውና።
የዘመነ ስብከት የመጀመሪያው ሣምንት ስብከት ይባላል(ከታኅሣሥ 7-13)፤ ሁለተኛው ሣምንት ብርሃን ይባላል(ከታኅሣሥ 14-20)፤ ሦስተኛው ሳምንት ኖላዊ ይባላል(ከታኅሣሥ 21-27)። ኖላዊ ማለት ጠባቂ ማለት ሲሆን ቅዱሳን ነቢያት እውነተኛው ጠባቂ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ይገለጣል ብለው በትንቢት መናገራቸውና ኢየሱስ ክርስቶስም ቸር ጠባቂ መሆኑን እያሰበች ቤተክርስቲያን የምትዘምርበት፣ የምታመሰግንበትና የምታስተምርበት ዕለት በመሆኑ ኖላዊ ተብሎ ተሰይሟል። በዚህ ዕለት ጌታችን በወንጌሉ እርሱ ቸር ጠባቂ እንደሆነ ያስተማረበት ዮሐ 10፡1-22 ያለው የወንጌል ክፍል ይነበባል፣ ከተያያዥ የቅዱሳት መጻሕፍት ምስጢራት ጋርም ይሰበካል፣ ይተረጎማል።
የዚህ የጌታችን ትምህርት መነሻ ‹‹እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች ስፍራ በበሩ የማይገባ በሌላም በኩል የሚገባ ሌባ፥ ወንበዴም ነው፤ በበሩ የሚገባ ግን የበጎች ጠባቂ ነው። ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ አውጥቶም ያሰማራቸዋል። ሁሉንም አውጥቶ ባሰማራቸው ጊዜ በፊት በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ቃሉን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ ከሌላው ግን ይሸሹታል እንጂ አይከተሉትም፥ የሌላውን ቃሉን አያውቁምና(ዮሐ 10፡1-5)። ›› የሚለው ነው።
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ‹‹ቸር ጠባቂ›› የተባውን ትምህርት ስለ ሦስት ምክንያቶች አስተምሯል። የቸር ጠባቂ መገለጫዎችን ለይቶ ለማሳወቅ፤ የቸር ጠባቂና የምንደኛን ልዩነት ለማስረዳትና ቸር ጠባቂ እርሱ መሆኑን ለመግለጽ ያስተማረው ነው። በትምህርቱም ሰባት የቸር ጠባቂ መገለጫዎችን አስቀምጧል። እነዚህም፡-
ቸር ጠባቂ በበሩ ይገባል፤ በበሩም ይወጣል።
ቸር ጠባቂ ወደ በጎች በረት በበሩ ብቻ ይገባል፤ በበሩም ብቻ ይወጣል። በጎቹን ከበረታቸው አውጥቶ ሊያሰማራ በግልፅ በበሩ ይገባል፤ ይዟቸውም በግልፅ (በብርሃን) በበሩ ይወጣል። የሌሊት ጠባቂውም ይከፍትለታል። ሌባ ግን አጥር ጥሶ ቅጥር አፍርሶ ይገባል እንጂ በበሩ አይገባም፤ እንደዚያውም ይወጣል። በጨለማ ይገባል እንጂ በግልፅ (በብርሃን) አይገባም። ምንደኛ መምህርም እንደዚሁ እምነትን አጉድሎ ሥርዓትን አፍርሶ ወደ ቤተክርስቲያን በተንኮል ይገባል።
የበጎች በር የተባለውም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በእርሱ ያላመነ (በበሩ ያልገባ) እውነተኛ ጠባቂ ሊሆን አይችልምና። እምነትን ሥርዓትን ያልጠበቀ እውነተኛ ጠባቂ ሊሆን አይችልም። በበሩ የገባ (ተመስክሮለት የመጣ) በበሩም መግባትን ያስተማረን ጠባቂ እርሱ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የክርስቶስን አርዓያ የተከተሉ ደገኛ መምህራንም በበሩ ይገባሉ፤ በበሩ ይወጣሉ።
ቸር ጠባቂ በጎቹን ያውቃቸዋል፤ እነርሱም ያውቁታል።
ቸር ጠባቂ በጎቹን በየስማቸው ይጠራቸዋል። እነርሱም ድምፁን ይሰሙታል፤ ያውቁታልም። በትክክለኛው ስማቸው (ግብራቸውን በሚገልፅ) ይጠራቸዋል። እነርሱም ድምፁን ስለሚያውቁ ይሰሙታል። ቃሉን (አስተምህሮውን) ያዉቁታል። ወንበዴ ግን የበጎቹን ስም ከቶ አያውቅም፤። በጎቹም ድምፁን አያውቁትም። እንደ ይሁዳ ዘገሊላ እንደ ቴዎዳስ ዘግብፅ ያሉት እንደዚህ ሐሰተኛ ጠባቂዎች ነበሩ (ሐዋ 5፡33-39)። አስተምህሮአቸው ከእግዚአብሔር ስላልሆነ ለጊዜው ተከታይ ቢያገኙም ምዕመናን አልሰሟቸውም። እነርሱም ጊዜአቸው ሲደርስ ጠፍተዋል። በጎቹን የሚያውቅ እነርሱም ድምፁን የሚያውቁት እውነተኛ እረኛችን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ‹‹ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ፥ የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድምጥ፤ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ፥ ተገለጥ (መዝ 79፡1)።›› እንደተባለ የቤተክርስቲያን ጠባቂዋ እርሱ ነው። የክርስቶስን አርዓያ የተከተሉ ደገኛ መምህራንም በጎች የተባሉ ምዕመናንን ሐዋርያዊ ትምህርትን እያስተማሩ በምግባር በሃይማኖት ያጸኗቸዋል።
ቸር ጠባቂ በጎቹን ይመራቸዋል፤ እነርሱም ይከተሉታል።
ቸር ጠባቂ በበጎቹ ፊት ፊት ይሄዳል። እነርሱም እርሱን እየተከተሉት ይሄዳሉ። እርሱ ቀድሞ በጎቹ ይከተሉታል። ወደ መሰማርያችውም ይመራቸዋል። አንድ በግ ቢቀርበት ወይም ቢጠፋበት እንኳን ሌሎቹን ትቶ የጠፋውን ይፈልጋል (ሉቃ 15፡2ሌባ ግን ከበጎቹ ኋላ ኋላ ይሄዳል፤ በጎቹንም ሊሠርቅ ከኋላ ሆኖ በጎቹን በአይነ ቁራኛ እየተመለከተ ይከተላል። በጎቹ ቢጠፉም አይገደውም፤ ሊሠርቅ እንጂ ሊመራቸው አልመጣምና። እኛን ወደ ለመለመ መስክ የሚመራን እኛም ድምፁን ሰምተን የምንከተለው እውነተኛ ጠባቂያችን እርሱ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
የሰቡትና የወፈሩት አንዳንድ በጎች፣ ምስኪኖችንና የከሱትን በጎች እየገፉ ከበረት ሲያስወጡአቸው፣ በቀንዳቸው ሲወጉአቸው፣ ሲያቆስሉአቸው፣ ሲያደሙአቸው፣ የሚጠጡትን ውኃ ሲያደፈርሱባቸው፣ ምግባቸውን ሲረግጡባቸው እያዩ ከመቀመጫቸው ላለመነሳት ዝም ብለው እንደሚያዩ ምንደኞች ያይደለ እውነተኛ እረኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የክርስቶስን አርዓያ የተከተሉ ደገኛ መምህራንም በጎች የተባሉ ምዕመናንን በእውነተኛ ትምህርት ይጠብቋቸዋል። ምንደኛ የሆኑ ክፉ መምህራን ግን በጎች የተባሉ ምዕመናንን አቁስለውና አድምተው ከበረት ያወጧቸዋል፤ በሌሎች ፈተናዎች ምዕመናንን ከመጠበቅ ቸል ይላሉ።
ቸር ጠባቂ በጎቹን ይጠብቃል፤ ይንከባከባቸዋልም።
ቸር ጠባቂ በጎቹን ከክፉ ሁሉ ይጠብቃል፤ የሚያስፈልጋቸውንም ነገር ሁሉ ያውቃል። ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማቸዋል። የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል (ኢሳ 40፡11)። ጭቃውን ሳይጠየፍ ይሸከማቸዋል፤ ይንከባከባቸዋል (ሉቃ 15፡6)። ምንደኛ የሆነ እረኛ ግን የራሱን ፍላጎት እንጂ የበጎቹን ፍላጎት አያውቅም፤ እነርሱም አያውቁትም። በጎቹን ይበትናቸዋል፤ በጎቹን ይጠቀምባቸዋል እንጂ አይጠብቃቸውም፤ አይጠቅማቸውምም። ጠፍተን ሳለ የፈለገን የሚንከባከበንና የሚመግበን ቸር ጠባቂያችን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
እንደ ምንደኛ (ቅጥረኛ) በጎቹን በማሰማራት ፈንታ ወደ እረፍት መስክ ራሱን ያላሰማራ፤ በአደራና በጠባቂነት የተሰጣቸውን በጎች እያረዱ እየበሉ አውሬ በላቸው እንደሚሉ ቅጥረኞች ያይደለ፤ በጎች እሰከሚበርዳቸው ድረስ ያለ አግባብ ፀጉራቸውን እንደሚሸልቱ ቅጥረኛ ያልሆነ፤ ታማሚ በጎችን እንዳላከሙ፤ ደካሞችን እንዳላዳኑ፤ ሰባራዎችን እንዳልጠገኑ፤ የጠፉትን በጎች ወደ መንጋው በመመለስ ፈንታ ወሬያቸውን በመሰለቅ በወንበራቸው ተቀምጠው እንዳልሰበሰቡ እረኞች ያይደለ የጠፉትን የሚሰበስብ የቤተክርስቲያን ጠባቂዋ እርሱ ነው።