ethiopian_orthodox | Unsorted

Telegram-канал ethiopian_orthodox - የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

30344

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Subscribe to a channel

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"አባ ተክለ ሃይማኖት"
አባ አቡነ አባ መምህርነ/፪/አባ ተክለ ሃይማኖት /፪/
እም አእላፍ/፪/ ኅሩይ እም አእላፍ ኅሩይ/፪/

አዝ…
አምላክ የጠራህ ለታላቅ ክብር፣
ተክለ ሃይማኖት ትጉ መምህር፣
ሐዋርያ ነህ በዚች በምድር፣/፪/
ጸሎት ምኅላህ በእውነት ተሰማ፣
ክብርህ ታወቀ በላይ በራማ።/፪/

አዝ…
ደብረ ሊባኖስ ተቀደሰች፣
በእጅህ መስቀል ተባረከች፣/፪/
ኤልሳዕ ልበልህ ቅዱስ ዮሐንስ፣
ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ ነህ ቅዱስ።/፪/

አዝ…
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ፣
ጸሎትህ ሆኖናል መድኃኒትና ፈውስ፣/፪/
ዛሬም ስንጠራህ ቃል ኪዳንህን አምነን፣
ጠለ በረከትህ ለሁላችን ይሁን።/፪/
አዝ…

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መንፈስ ቅዱስ›› ብሎ የሹመትን ሀብት አሳደረባቸው፡፡ ዳግመኛም ‹‹በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሁን፤ በምድርም የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሁን፤ አንተን የሰማ እኔን መስማቱ ነው፤ የላከኝ አባቴንም መስማቱ ነው፡፡ አንተን እንቢ ያለ እኔን እንቢ ማለቱ ነው፡፡ የላከኝ አባቴንም እንቢ ማለቱ ነው፡፡ ይህን ሥልጣን ቀድሞ ለሐዋርያት ሰጥቻቸው ነበር፡፡ ከሐዋርያትም ሹመትን የተቀበለ ጳጳሱ ትሾምና ትሽር፣ ትተክልና ትነቅል ዘንድ ሥልጣንን ሰጠህ፡፡ ይህንንም ያደረኩልህ የጳጳሱን ቃል በመናቅ አይደለም፡፡ የፍቅሬን ጽናት ባንተ እገልጽ ዘንድ ነው እንጂ፡፡ ሐዋርያት ወዳልደረሱበት ሕዝብ በመምህርነት እልክህ ዘንድ በሚካኤል ቃል አዲስ ስም አወጣሁልህ፡፡ አንተም በማናቸውም ሥራ ከእነርሱ አታንስም፣ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጌሃለሁና፡፡ ሰውን ሁሉ በእኔ ስም እያስተማርክ ታሳምን ዘንድ፣ ሚካኤልም ባሰብከው ሥራ ሁሉ ረዳት ይሁንህ፣ ሁል ጊዜ ካንተ አይለይም፤ በምትሄድበትም ጎዳና ሁሉ እርሱ መሪ ይሁንህ፤ እኔም ባለ ዘመንህ ሁሉ አልለይህም›› ካላቸው በኋላ ሰላምታ ሰጥቷቸው ዐረገ፡፡

ብፁዕ አባታችንም እጅ ነሥተው ‹‹ለእኔ ለኀጥኡ የማይገባኝ ሲሆን ይህን ሁሉ ጸጋ የጠኸኝ ስምህ በሰማይ በምድር የተመሰገነ ይሁን›› አሉ፡፡ ከዚያች ቀን ጀምሮ ሀብተ ኃይልን የተመሉ ሆኑ፡፡ ወደቤታቸው ተመልሰው ያላቸውን ሀብት ንብረት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን፣ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጥተው ጨረሱ፡፡ ከዚያም ‹‹አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደተከፈተ ተውኩልህ›› ብለው ቤታቸውን እንደተከፈተ ትተው ወንጌልን ለማስተማር ወጡ፡፡ ጻድቁ አባታችን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ኃይማኖት ስለመለሱት በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ተብለዋል፡፡

የአባታችን ረድኤት በረከታቸው በእኛ በምና'ምን ክርስቲያኖች ላይ እጥፍ ድርብ ይሁንልን! አሜን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ጥሩልኝ ዳዊትን"
ዘማሪ አቤል ተስፋዬ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ታኅሣሥ ፳፫
ዕረፍቱ ለልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት


ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል:- "እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ: አይጸጸትም::" (መዝ. 131:11) አሁን በእግዚአብሔር መጸጸት ኑሮበት አይደለም:: ቅዱስ ዳዊት የማያጸጽት ፍጹም ወዳጅ መሆኑን ሲገልጥ ነው እንጂ:: ጌታ ቅዱስ ዳዊትን "እንደ ልቤ የሆነ: ፈቃዴን የሚፈጽም: ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁት" (መዝ. 88:20)
እንደ አምላክ ልብ ሆኖ መገኘት ምን ይረቅ?! ምንስ ይደንቅ? ለዚህ አንክሮ ይገባል።

ቅዱስዳዊት አባቱ እሴይ እናቱ ሁብሊ ይባላሉ። በነሐሴ 13 ቀን ተጸነሰ በሚያዝያ 6 ቀን በይሁዳ በቤተልሔም ሀገር ተወለደ። (1ሳሙ. 16፡10-11) ዳዊት ማለት ልበ አምላክ ማለት ነው። እረኛና ብላቴና ነበር።
የፍልስጤማውያኑን ሰው ጎልያድን በ12 ዓመቱ 5 ጠጠርን ከወንዝ ለቅሞ በወንጭፍ ወርውሮ የገደለ (1ሳሙ.12፡45-51)፣ ንጉሥ ሳዖል በጌልቦአ ተራራ በራሱ እጅ ከሞተ በኋላ አስቀድሞ በይሁዳ 7 ዓመት በመላው እስራኤል 33 ዓመት የነገሠ (2ሳሙ. 2፡4፤ 2ሳሙ. 5፡1-5) ቅዱስ አባት ነው።
“እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሆነ ሰው መርጧል” (1ሳሙ.13፡14) ተብሎ በእግዚአብሔር የተመረጠና ነገረ ሥጋዌን፣ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታንን፣ ዳግም ምጽዓትን፣ ነገረ ማርያምን፣ ክብረ ቅዱሳንን፣ በስፋትና በጥልቀት የተናገረ የብሉይ ኪዳን “ወንጌላዊ” ነበር።
🌿(መዝ.21 (22)፡ 16-18 “ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዙኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ። አጥንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም። ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።…”፣
🌿መዝ. 46(47)፡4-5 አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።”
🌿መዝ.49(50)፡ 1-5 “ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል። አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊት ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ።”፣
🌿መዝ. 44(45)፡9 “የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።”

ዳዊት ታላቅና ገናና ንጉሥ ከመሆኑ የተነሳ መንግሥቱ የመሲህ መንግሥት ምሳሌ ሆኗል፤ መሲሁም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳዊት ስም ብዙ ጊዜ በመጽሐፍቅዱስ ተጠቅሶ ይገኛል። (ት.ኢሳ.9፡7፣ ኤር.23፡5-6፣ ኤር.3314-17፣ ህዝ. 34፡23፣ሆሴዕ 3፡5)
ቅዱስ ዳዊት 7 ሀብታት የተሰጡት አባት ነበር፤ እነዚህም:
፩. ሀብተ ክህነት
፪. ሀብተ መንግሥት
፫. ሀብተ መዊዕ
፬. ሀብተ ትንቢት
፭. ሀብተ ኀይል
፮. ሀብተ በገና
፯. ሀብተ ፈውስ ናቸው።

እድሜ ዘመኑን እግዚአብሔርን በማገልገልና በመፍራት ኖሮ በታህሳስ ፳፫ ቀን አርፎ በኢየሩሳሌም ተቀብሯል።

የልበአምላክ ቅዱስ ዳዊት ረድኤትና በረከቱ ከእኛ ከምናምን ክርስቲያኖች ጋር ለዘለዓለም ይኑር: አሜን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"▫️እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

▫️በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቀም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

▫️ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

▫️የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

▫️በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

▫️ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

▫️በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

▫️በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

▫️ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው።

▫️ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

▫️አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።

✨በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9"

(➥አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ - መንፈሳዊው መንገድ መጽሐፍ አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"አይ ሞኝነቴ ሞቴን መርሳቴ"

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ላመስግንህ የእኔ ጌታ"
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

#ውዳሴ_ከንቱ

፪. እኛ ስለ ሰዎች
ምስጋና ከእኛ ስለ ሰዎች በሚቀርብበት ወቅትም ልናስተውላቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡በእርግጥ ሰዎችን ማመስገንና እንዲመሰገኑ መፈለግ ከክርስቲያኖች የሚጠበቅ የበጎ ምግባር መገለጫ ነው፡፡
እንደ ዲያቢሎስ መመስገን ብቻ እንጂ ሰውን ማመስገንና ማበረታታት የማይፈልጉ ሰዎች አሉና፡፡ ነገር ግን የምስጋናውን ልክ የምናልፍ ከሆነ ለተመስጋኙ ጥቅም ከመሆን ይልቅ ፈተና የምንሆንበት ዕድል የሰፋ ነው፡፡በውዳሴ ከንቱ የወደቀ ከሆነም መሰናክል የሆንነው እኛ በመሆናችን እንቀጣለን፡፡ "ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ቢኖር የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ከጥልቅ ቢጣል ይሻለው ነበር” ተብሎ ተጽፏልና፡፡ ማቴ 18÷6 ስለዚህም መመስገን የሚገባውን ሰው መለየትና መመስገን በሚገባው ልክ ማመስገን ከእኛ የሚጠበቅ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ደግሞም “ከጠላት መሳም የወዳጅ ንክሻ ይሻላል” ተብሎ እንደ ተፃፈ ለሰዎች ከሚቀርብላቸው ምስጋና ይልቅ ወቀሳና ምክር ለመሻሻል ይጠቅማቸዋልና ማመስገን ብቻ ሣይሆን መውቀስና መምከር ተገቢ ነው፡፡ጌታችን የአይሁድ መምህር የሆነ ኒቆዲሞስን “አንተ የአይሁድ መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን?” ብሎ አለማወቁን ገስፆ መምህርነቱን አመስግኖ እንደ ተናገረው ዮሐ. 3÷10
፫. እኛ ስለ እኛ
ውዳሴ ከንቱ ሰዎች እኛን በሚያመሰግኑበት ወቅት ባለን አቀባበል ወይም እኛ ለሰዎች በምናቀርበው ምስጋና ልክ ብቻየ ሚመዘን አይደለም፡፡እኛ ስለ ራሳችን ባለን አስተያየትና በምናቀርበው ምስጋናም ጭምር እንጂ፡፡ በእርግጥ ለራስ ጥሩ አመለካከት መያዝና ራስን ማበረታታት ተገቢ ነው፡፡ይህ ሁኔታ ልክ ከሌለው ግን ለራሳችን ብቻ የምናዜም በውይይት መሃል እኛ ብቻ መነሳት የምንፈልግ ከእኛ ይልቅ ሌላ ሰው ቢነሣ ቅር የሚለን ገፍተንም ስለራሳችን ጥሩነት የምናወራ እንሆናለን፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ “የሌላ ሰው አፍ ያመስግንህ ” ተብሎ መጻፉ ሰው በራሱ አንደበት መመስገን እንደሌለበት የሚያስረዳ ነው፡፡በወንጌልም የታዘዙትን ሁሉ በፈፀሙ ጊዜ አገልጋዮች ምን ማለት እንዳለባቸው የተቀመጠላቸው ትዕዛዝ “የማንጠቅም ባሪያዎች ነን በሉ” የሚል ነው ሉቃ. 17፡10 ፡፡ ይህም ሰው ከልክ አልፎ ለራሱ ቦታ እንዳይሰጥና በውዳሴ ከንቱ እንዳይወድቅ ለመጠበቅ የታዘዘ ነው፡፡ ርዕሳችን ውዳሴ ከንቱ በመሆኑ በማይጠቅም ውዳሴ ላይ ብቻ አተኮርን እንጂ የሚገቡና የሚጠቀቅሙ የታዘዙም ምስጋናዎች አሉ፡፡ “ የማይጠቅም ውዳሴ ” የሚለውን ርዕስ በራሱ የሚጠቅም ውዳሴ መኖሩን የሚጠቁም ነው፡፡

➥ቀጣይ:- የሚጠቅም ውዳሴ.....

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ስብከት"
የዘመነ ስብከት መጀመሪያ ሳምንት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የበዓላት ቀኖና መሠረት ከህዳር ፲፭/15 እስከ ጌታችን ልደት (ታኅሣሥ ፳፰/፳፱-28/29) ድረስ ያለው ወቅት በዘመነ ብሉይ የነበሩ ቅዱሳን ነቢያት የጌታን ልደት በተስፋ እየጠበቁ የገቡትን ሱባኤ፣ የጾሟቸውን አጽዋማት በማሰብ ልዩ ልዩ ክብረ በዓላት ይከበራሉ። ለእያንዳንዱ በዓልም የተለየ የቅዱሳት መጻሕፍት ንባብና ትርጓሜ፣ የተለየ የምስጋና መዝሙር ይዘመራል። በጾመ ነቢያት ውስጥ ያሉት የመጨረሻዎቹ ሦስት ሳምንታት በተለየ መልኩ ይከበራሉ። ወቅቱም ትንቢተ ነቢያትን በማሰብ "ዘመነ ስብከት" ይባላል። የነቢያት የስብከታቸው ማዕከል የክርስቶስ ሰው የመሆን ተስፋ ነውና።

የዘመነ ስብከት የመጀመሪያው ሳምንት "ስብከት" ይባላል(ከታኅሣሥ ፯/7-፲፫/13)፤ ሁለተኛው ሳምንት "ብርሃን" ይባላል(ከታኅሣሥ ፲፬/14-፳/20)፤ ሦስተኛው ሳምንት "ኖላዊ" ይባላል(ከታኅሣሥ ፳፩/21-፳፯27)።

ስብከት
ስብከት ማለት በቁሙ "የምስራች፣ አዲስ ዜና መንገርን" የሚመለከት ሲሆን ዋናው ምሥጢር ግን ከነገረ ድኅነት (ከመዳን ትምሕርት) ጋር የተገናኘ ነው።

በዚህ ዕለት (ሳምንት) ሁሉም ነቢያት ከነ ትንቢታቸው ይታሰባሉ። ይህም ከታሕሳስ ፯/7 እስከ ፲፫/13 ያለውን ይይዛል። ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ እግዚአብሔር አዳምን በ፯/7 ሃብታት አክብሮ በገነት ቢያኖረው "አትብላ" የተባለውን ዕፀ በለስ በላ። በዚህም ከፈጣሪው ተጣልቶ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ፣ በርደተ መቃብር፣ ርደተ ገሃነም ተፈረደበት። በኋላ ግን ንስሃ ስለ ገባ "ከ፭/5 ቀን ተኩል (፶፻፭፻/5500 ዘመን) በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ቃል ኪዳንን ሰጠው።

ከዚህ በኋላ ለ፶፻፭፻/5500 ዘመናት ጊዜ ወደ ታች ይቆጠር ጀመር። ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆንና ዓለምን ማዳንም ትንቢት ይነገር፣ ሱባኤ ይቆጠር፣ ምሳሌም ይመሰል ገባ።

ከአዳም እስከ ሙሴ (ዘመነ አበው) ምሳሌያት ይበዛሉ። ከሙሴ እስከ ዳዊት (ዘመነ መሣፍንት) ምሳሌያቱ እየጐሉ መጥተዋል:: ከልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እስከ ቅዱስ ሚልክያስ ድረስ (በዘመነ ነቢያት/ነገሥት) ግን ትንቢቶች ስለ ክርስቶስና ስለ ማደሪያ እናቱ እንደ ጐርፍ ፈስሰዋል።

ነቢያትም የመሲህን መምጣት እየጠበቁ በጾም፣ በጸሎትና በትሕርምት ኑረዋል። እንባቸውንም አፍስሰው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶላቸዋል። መድኅን ክርስቶስም ተወልዶ አድኗቸዋል።

በዘመነ ስብከት የመጀመሪያው ሰንበት (እሑድ) በኦሪተ ሙሴ፣ በነቢያትም አስቀድሞ ስለ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን ትንቢት ተነግሮ፣ ምሳሌ ተመስሎ፣ ሱባዔ ተቆጥሮ እንደ ነበር ይነገራል፤ ይሰበካልም፡፡
"እምኦሪተ ሙሴ እስከ ነቢያት ሰበኩ ምጽአቶ ንህነ ነአምን ስብከቶ ፣ ከኦሪተ ሙሴ አንስቶ እስከ ነቢያት የወልደ እግዚአብሔርን መምጣት ሰበኩ አስተማሩ እኛም ሙሴና ነቢያት የሰበኩት ስብከት አምነን እንቀበላለን" እንዳለ (ቅዱስ ያሬድ )
በተጨማሪም በዚህ ሳምንት ከአብርሃም እስከ ዳዊት ባለው ትውልድ ውስጥ ስለ ክርስቶስ ሰው መሆን የተሰበከው ስብከት ይታሰባል፡፡
የነቢያት ስብከት: በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙሴ በሕግ ነቢያትም በትንቢት እንደ ጻፉለት የሚናገረው ወንጌል ይነበባል (ዮሐ 1፡44)፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊትም ‹‹ፈኑ እዴከ እም አርያም » እጅህን ከአርያም ላክ አድነኝም› (መዝ 143፡7) በማለት ስለክርስቶስ ማዳን በትንቢት መነጽር ተመልክቶ የዘመረው የመዝሙር ክፍል እንዲሁ ይሰበካል፡፡ ከዐበይት ነቢያት አንዱ የሆነው ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስም ‹‹ሰማዮችን ቀደህ ምነው ብትወርድ! ተራሮችም ምነው ቢናወጡ›› (ኢሳ 64፡1) ብሎ ስለክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት መውረድ፣ ከድንግል ማርያምም መወለድ የተናገረውን ትንቢት ቤተክርስቲያን ትሰብካለች፡፡
የቤተክርስቲያናችን ስብከት: ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ “እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን” (2ኛ ቆሮ 4፡5) እንዳለው ቤተክርስቲያን በተለይ በዘመነ ስብከት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች የሰጠውንና የፈጸመውን የማዳን ተስፋ ትሰብካለች፡፡ ቅዱስ ያሬድም በመዝሙሩ “ከዓለም በፊት የነበረውንና መድኃኒት የሆነውን ወልድን እንሰብካለን” እንዳለ ቤተክርስቲያናችን ፣ በጊዜውም አለጊዜውም፣ በችግርም በደስታም ስለ ኃጢአታችን የሞተውንና አምላክ ወልደ አምላክ ክርስቶስን ትሰብካለች።

አምላካችን እግዚአብሔር ከአባቶቻችን በረከት ያድለን፣ አሜን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

#ውዳሴ_ከንቱ

ውዳሴ ከንቱ የሚለው ቃል የማይረባ የማይጠቅም ውዳሴ የሚል ትርጓሜ ያለውሲሆን ውዳሴ ብጡል (የተናቀ፤ተርታ) ውዳሴ ተብሎም ይጠራል፡፡የቃሉ ትርጉም በዚህ መልኩ የሚፈታ ይሁን እንጂ “ የማይጠቅም “ ከመሆን አልፎ ሰውን ሊጎዳ የሚችል ነገር በመሆኑ የቤተክርስቲያናችን መጻሕፍት አጥብቀን ልንሸሸው እንዲሚገባ ያስተምራሉ፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግሩ ስር ተቀምጣ ቃላት ታዳምጥ የነበረችውን የማርታ እህት ማርያምን “ማርያምስ የማይቀሟትን በጎ ዕድል መረጠች ” ሉቃ10÷42 ብሎ ያመሰገነበትን ቃል አበው ሲተረጉሙ “ መማር ውዳሴ ከንቱ የለውም “ አላውቅም ማለት ነውና፡፡ ስለዚህም አጋንንት የማይቀሟትን (ዋጋዋን ) የማያስቀሩባትን መማርን መረጠች ማለት ነው ብለው መተርጎማቸው ‹‹ውዳሴከንቱ›› የሰውን የልፋት ዋጋ በምድራዊ ክብር የሚያስቀር ከንቱ ነገር መሆኑን ያስረዳል፡፡ አበው ከውዳሴ ከንቱ እንድንጠበቅ ማስተማራቸው የመልካም ስራችን ዋጋ ሰዎች በሚያቀርቡልን የምስጋና ስጦታ ምክንያት በምድር እንዳይቀርብን በማሰብ ነው፡፡ በወንጌልም ጌታ ከሰዎች ምስጋና በመሻት መልካም ሥራቸውን በሰው ፊት ስላደረጉ ፈሪሳውያን ሲናገር “እሙንቱሰ ነሥኡ እሴቶሙ… እነዚህስ ዋጋቸውን ተቀብለዋል” ማቴ6÷2 በማለት ከሰው የተቀበሉት ምስጋና ሰማያዊ ዋጋቸውን እንዳሳጣቸው አስተምሯል፡፡
እንዲህ ስንል ግን በሰው የተመሰገነ ሁሉ ውዳሴ ከንቱ ሆኖበታል ያልተመሰገነ ደግሞ አልሆነበትም ማለትም አይደለም፡፡ በልቦናው የመመስገን መሻት ኖሮት መልካም ሥራ የሠራ ነገር ግን በለስ ያልቀናው ያልተመሰገነ ሰው ሊሰርቅ ሄዶ አጥር ፀንቶበት፣ ውሻ ጮሆበት፣ጠባቂ ነቅቶበት የተመለሰ ሰውን ይመስላል፡፡ መሻቱ በልቦናው ስላለ ሰዎች ባያመሰግኑትም ቅሉ ለመመስገን በመሻት አስቀድሞ ወድቋልና ከሰው ውዳሴ ሳይፈልግ የሠራ ሰውም ሰው ቢያመሰግነው እንኳ አይሻውምና በውዳሴ ከንቱ ወደቀ አያሰኝም፡፡ ይህም ውዳሴ ከንቱ ኃይል አግኝቶ ሰውን የሚጥለው የተዘጋጀ ልቦና ሲኖረው መሆኑን እንገነዘባለን፡፡
➥ውዳሴ ከንቱ በሦስት ዓይነት መንገድ ሲቀርብ እንደ አቀራረቡና አቀባበሉም ሰዎችን ሊጎዳ ይችላል፡፡
፩. ሰዎች ስለ እኛ
ውዳሴ ከሰዎች ለእኛ በሚቀርብበት ወቅት የሚያመሰግነን ሰው ማን ነው? ምስጋናውስ ለእኛ የሚገባን ነውን? የሚሉትን ጥያቄዎች ራሳችንን መጠየቅ ከጉዳት ይጠብቀናል፡፡ የሚያመሰግነን ሰው ማነው? የሚለውን ማሰባችን ተወዳጅነትን ለማትረፍና በአፀፋ ለማመስገን ከሚመጡ ሰዎች ሲጠብቀን ምስጋናው ለእኔ ይገባልን? የሚለውን ማሰብ ደግሞ ምስጋናውን ይገባናል ብሎ ከመቀበል ይጠብቀናል፡፡ በወንጌል ጌታችን “ ቸር መምህር ሆይ “ ብሎ የቀረበው ሰው መመስገንንና ተወዳጅነትን ለማትረፍ ሲሉ ምስጋና ከሚያቀርቡ ሰዎች የሚመደብ ነው፡፡ (ማር 10÷17) ምስጋናን “ለእኔ የሚገባ ነውን?” ብሎ መርምሮ መቀበልን የተማርነው ከቅዱሳን እናቶቻችንና ከቅዱሳን አባቶቻችን ነው፡፡
ክብር ይግባትና በሚገባት ግብር የተመሰገነች እመቤታችን “እፎኑ ከመ ዝኑ እንጋ አምኃ ይትአምኁ - እንዲህ ያለውን ሰላምታ እንዴት ይቀበሉታል?” ሉቃ 1÷29 ማለቷ ቅዱሳን በሚገባቸው ገንዘብ ቢመሰገኑ እንኳ (በትሕትና ) አይገባንም እንደሚሉ የሚያስረዳ ነው፡፡
በትንሣኤ ዘጉባኤም “ተርቤ አብልታችሁኛልና፣ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና ….” ተብለው የሚመሰገኑ ቅዱሳን “መቼ ተርበህ አበላንህ?፣መቼ ተጠምተህ አጠጣንህ?.....” ሲሉ ሠርተው እንዳልሰሩ ሆነው በትሕትና እንዲመልሱ ተጽፏል፡፡ ማቴ 25÷44
አቡነ ተክለሃማኖትም ከብዙ ትሩፋትና ተጋድሎ በኋላ “አሌ ሊተ ወይ ሊተ ለዘኢገበርኩ ምንተ - ወዮ ለኔ ምንም ላልሠራሁት” እያሉ ምርር ብለው ማልቀሳቸውን ገድላቸው ዘግቦታል፡፡
እኛም ምንም እንኳ ከእነርሱ መዐርገ ትሕትና ደርሰን አይገባንም ማለት ባንችል በብሩህ ፊት ሆነን ውዳሴን እያጣጣሙ ከመቀበል መለየት ይገባናል፡፡ይልቁንም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ እንዳሉት በምንመሰገንበት ወቅት የከፉ ኃጢአቶቻችንን እያሰብን ራሳችንን መገሰጽ ይገባናል፡፡

፪.እኛ ስለሰዎች ........ይቀጥላል .....

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

✝️እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሐሪ ነው፡፡

"እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥ ከቍጣ የራቀ፥ ምሕረቱም ብዙ ነው፡፡" መዝ 144(145)÷8

ስለ እግዚአብሔር ርኅሩኅነትና መሓሪነት ማወቅ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ቁልፍ ነው፡፡ እኛ ሰዎች በደል የማያጣን ነን፡፡ ድካም የማይለየን ነን፡፡ ርኅሩኅነቱን ስንረዳ ሳናውቅ በስህተት አውቀን በድፍረት ለሰራነው ኃጢአት እንደሚምረን እንረዳለን፡፡

በመንገድ ስንሄድ መኪና ሰው ገጭቶ እናያለን፡፡ ሹፌሩ መግጨት ፈልጎ ነው ሰው የሚገጨው ? አይደለም፡፡ መቼም ማንም ሰው ሆን ብሎ ሰው አይገጭም፡፡ አንዳንዶቻችን እንደዚህ ነን፡፡ ሆን ብለን ኃጢአት ማድረግ አንፈልግም፡፡ ግን ደግሞ ስጋችን ደካማ ስለሆነ ሳንፈልግ እናደርጋለን፡፡ፈልጎ ማድረግና ሳይፈልጉ ማድረግ ይለያያል፡፡ ሆን ብሎ ሰው ያልገጨ ሹፌር እንዴት እንሚሆን አይታችሁታል? በሰራው ስህተት ከልቡ ያዝናል፡፡ እግዚአብሔርን ሆን ብለን መበደል የማንፈልግ ሰዎች አለን፡፡እርሱን ደስ ለማሰኘት ጠዋት ስንወጣ ሰላም አውለኝ ብለን ተማጽነነው ወደ ተግባራችን የምንወጣ ሰዎች አለን፡፡ እንዲህ ያልነው እግዚአብሔርንም እንዳንበድለው ፈልገን ጭምር ነው፡፡

በተሳሳትነው ነገር እስከ ተጸጸትን ድረስ አምላካችን እንደሚራራልን መረዳት አለብን፤ ውኃ ውስጥ ገብቶ እየሰመጠ እየሰመጠ እንደሚሄድ ሰው አንዳንዶቻችን ግን ሁሌ እየበደልኩት እንዴት ይቅር ይለኛል? በሚል አነገጋገር ውስጥ እየሰመጥንና እየሰመጥን ስንሄድ እንገኛለን፡፡እግዚአብሔር ርኅሩኅ ነው ፡፡ ርኅሩኅነቱን ስናስብ እየሰመጥን ካለንበት (ሁሌ እየበደልኩት ይቅር አይለኝም ከሚል አባባል) ያወጣናል፡፡

ከእጃችሁ አምልጦ የተሰበረ ብርጭቆ ተመልሶ ብርጭቆ መሆን እንደማይችል እኛም ይቅር እንደማንባልና እንደ ብርጭቆው ተስፋ የሌለን አድርገን ማሰብ የለብንም፡፡ ርኅሩኅ ነውና ይራራልናል ፤ መሐሪ ነውና ይምረናል፡፡መልሰን በእግዚአብሔር ፊት በመቅረብ፡- 'አባት ሆይ ማረን 'ልንል ይገባል እንጂ የጤና ችግር ኖሮበት ሰው ፊት እንደማይቀርብ እንዲሁ ፊቱ መቅረብ መተው የለብንም፡፡

ሰዎች ሰውን መጉዳት ሲፈልጉ ከሚያደርጉት ነገር አንዱ ስለ ጠሉት ሰው የተዛባ ነገር ማስወራት ነው፡፡ ጠላት ዲያብሎስም እኛ እግዚአብሔርን በበደልን ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር እንደማይለንና ፊቱ መቅረብ እንደማንችል ይነግረናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ርኅሩኅና መሐሪ መሆኑን ስናውቅ ግን አሉባልታውን ወደ ጎን ትተን ፊቱ በመቅረብ ማረን የምንልበት አዲስ ምዕራፍ እንከፍታለን፡፡

እናት ያለቀሰ ልጅዋን እያሻሸች እንደምታጽናና እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሐሪ ነው የሚለው ቃል እጅግ የሚያጽናና ነው፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሔር ለቁጣ የዘገየ(የማይቸኩል)፣ ምሕረቱም ብዙ እንደሆነ ቃሉ ይነግረናል፡፡

ወንጀል ሰርተሃል ተብሎ ፍርድ ቤት በየቀጠሮው ሲመላለስ የከረመ ሰው እስራት የማያሰጥህ ነው ተብሎ መዝገቡ ሲዘጋለት እየተደሰተ ወደ ቤቱ እንደሚመለስ ሰው የእግዚአብሔር ርኅሩኅነት፣ መሐሪነት፣ ከቁጣ የዘገየና ምሕረቱ ብዙ መሆኑን ስንሰማ የተጨነቀች ነፍሳችንን ደስ በጣም ደስ ያሰኛታል፡፡ነፍሳችን የሰማችው ቃል(ስለ ርኅሩኅነቱና መሐሪነቱ) እንደ ማግኔት እየሳበ ሁልጊዜም ከፊቱ እንድትቀርብና እንድትጸልይ ያደርጋታል፡፡

ርኅሩኅና መሐሪ አምላካችን ሆይ እናመሰግንሃለን ::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር! አሜን፡፡

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ታኅሣሥ ፮

ቅድስት አርሴማ ድንግል
እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው:: መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና" (ማቴ. 5:11) የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል::
*ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት::
*ቅድስት አርሴማ ይህ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት::
*ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት::
*ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት::
*ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት::
➺ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:
+አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቁዋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው:: በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት:-
1.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት
2.ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት
3.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት::
+ቅዱሱ 3ቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ:: ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት:: መከራው ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ: ይጾሙ: ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር::
+ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው:: በሁዋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኩዋ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ::
+በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ:: ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው:: የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ::
+በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ:: በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር:: መከራው ግን አለቀቃቸውም:: ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው::
+ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት:: ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ: አይሆንም" አለችው:: ሊያስፈራራት ሞከረ:: ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው::
+አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው:: እጅግ ስላፈረ አስገረፋት: አሰቃያት: ዐይኗንም አወጣ:: በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት::
+ከነገር ሁሉ በሁዋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው::
+የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ:: የንጉሡ እህት ስታለቅስ በራዕይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን-ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው:: ወዲያውም ቆፍረው አወጡት::
+ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም:: ለ15 ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው::
ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው::
+የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ኢትዮዽያ እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል:: ለዚህም ይመስላል ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮዽያውያን ልዩ ፍቅር ያላት:: በዋናው ገዳሟ (ወሎ /ኩላማሶ/ : ስባ : ውስጥ የሚገኝ ነው) ጨምሮ ስሟ በተራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና::
+ነገር ግን ወንድሞቼና እሕቶቼ በቅድስቷ እናታችን ስም የሚነግዱ ሥጋውያን ሰዎች በዝተዋልና እንጠንቀቅ:: የሰማዕቷ ክብር ብዙ ነውና በሕልም ላይ ብቻ አንታመን:: አባ እንጦንስ እንዳሉት "በሕልሙ የሚታመን ሰው ከንቱ ነውና::" (መዝ. 75:5)
+በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል:: ይህች እናት እመ-ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት: ታጸናት: ከጐኗም ትቆምላት ነበር:: ረሃቧን: ጥሟን: ስደቷን: መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች:: በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች::

ይህች ዕለት ለቅድስት አርሴማና ለተከታዮቿ ሰማዕታት የፍለሰትና የቅዳሴ ቤት መታሰቢያ ናት።

©ስንክሳር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

#ዘፋኝነት
በዘመናችን የሥልጣኔ፣ የፍልስፍና የዘመናዊነት መገለጫ ዘፋኝነት የሚመስላቸው በርካታ ሰዎች አይጠፉም፡፡ በተለይም ‹‹ዘመናዊ›› ነን ብለው ራሳቸውን በሚቆጥሩ ሰዎች ዘፈን የማይዘፍን ወይም የማያዳምጥ ኋላ ቀር ተደርጎ ይታሰባል፡፡ አበው ‹‹ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በቅጠሉ›› እንዲሉ የተሰጥኦ ውድድር በሚል ሰበብ በትውልዱ ላይ የዘፋኝነት መንፈስ በውስጡ አስርጸዋል፡፡ ከዚህ ከተሳሳተ ድርጊታቸው እንዲታረሙ ለማስገንዘብና የዘፋኝነት ሱስ ተጸናውቶን ከእግዚአብሔር መንግሥት እንዳይለየን ለማስተማር ይህን ርዕሰ ጉዳይ ማንሳት አስፈልጓል፡፡
ዘፈን ምንድን ነው?የሚል ጥያቄ ለምናቀርብ ዘፈን ማለት ዝላይ፣ እስክስታ፣ በቅኔና በግጥም ከልዩ ልዩ መሣሪያ ጋር እየተቀነባበረ የሚቀርብ የደስታ ምልክት ነው ፡፡ በዘፈን ላይ ጥናት አድርገናል የሚሉ አንዳንዶች ደግሞ ‹‹የመንፈስ እርካታ›› ‹‹የሕይወት ቅመም›› እያሉ ለሥጋቸው መደሰቻ የሚመች ትርጉም ሲሰጡትም ይደመጣሉ፡፡
መዝሙር ከዘፈን ጋር ያለውን ልዩነት ምን እንደሆነ መለየት እንድንችል መዝሙር ፈጣሪያችን እግዚአብሔርን፤እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምና ቅዱሳንን የምናመሰግንበት፤ጸጋ እግዚአብሔር የሚያሰጥ፤ ሰማያዊ መንግሥቱን እንድንወርስ የሚያሳስብ ነው፡፡ ዘፈን ደግሞ በተቃራኒው ፈቃደ ሥጋን የሚያነሳሳ፤ ከእግዚአብሔር መንግሥት የሚለይ እኩይ ተግባር ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዘፈን ቅዱስ ጳውሎስ የሥጋ ፈቃዳት ብሎ ከዘረዘራቸው የሚመደብ ነው፡፡ ለዲያብሎስና ጭፍሮቹ አጋንንት የሚቀርብ መስዋዕት እንደሆነም ከዚህ በታች መጽሐፍ ቅዱስን ዋቤ አድርገን እናያዋለን፡፡
የሥጋ ፈቃድ ነው
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ገላቲያ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች በላከው መልእክቱ ‹‹የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት ርኩሰት መዳራት ጣዖትን ማምለክ ምዋርት ጥል ክርክር ቅንዓት ቁጣ አድመኝነት መለያየት መናፍቅነት ምቀኝነት መግደል ስካር ዘፋኝነት ይህንም የሚመስል ነው›› በማለት ዘፋኝነት ከሥጋ ፈቃዳት አንዱና ዋነኛው እንደሆነ ተናግሯል ፡፡
የዲያብሎስ መሥዋዕት ነው
ዘፈን ዲያብሎስና ሠራዊቱን ለማስደሰት የሚቀርብ መሥዋዕት ነው፡፡ ለእግዚአብሔር አምላካችን የሚቀርበው መስዋዕት ምስጋና ሲሆን፤ የዲያብሎስ ፈቃድ የሚፈጽሙ ሰዎች ደግሞ የሚያቀርቡ መስዋዕት ዘፈን ነው፡፡ ሕዝበ እስራኤል በእግዚአብሔር ቸርነት በሙሴ መሪነት ከግብጽ ባርነት ከወጡ በኋላ ከፈርዖን የግፍ አገዛዝ ያጣቸውን እግዚአብሔርን በመርሳት ለአምላካቸው በሰገዱበት እግራቸው ለጣዖት ሰግደዋል፡፡ እግዚአብሔርን ባመሰገኑበት አንደበታቸው ለዲያብሎስ ዘፍነዋል፡፡ ከሰማይ መና ወርዶላቸው እንዳልተመገቡ ለዲያብሎስ የቀረበ መስዋዕት በልተዋል፡፡ በዚህ ክፉ ሥራቸው እግዚአብሔር አምላካቸውን አሳዝነዋል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ለዲያብሎስ ያቀረቡት የዘፈን መሥዋዕት እንዲህ በማለት ገልጾታል ‹‹ሕዝቡም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ ሊዘፍኑም ተነሡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖትን የምታመልኩ አትሁኑ ›› /ዘጸ. 321-7/፡፡ ነብየ እግዚአብሔር ኢሳይያስም አጋንንት ዘፈን እንደሚስማማቸው ‹‹በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ ›› ብሎ በግልጽ ዘፈኝነት የአጋንንት ሥራ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ከዚህ አንጻር የምንዘፍን ሰዎች ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ አጋንንት መሥዋዕት እያቀረብን እንደሆነ አስተውለን ይሆን?
ዘፈኝነት የሚያስከትለው ችግር ከክብር ማሳነስ ነው፡፡ የያዕቆብ ልጅ ዲና የአሕዛብ ሴቶች ዘፈንና ጨዋታ ልታይ ሔዳ የኤሞር ልጅ ሴኬም ከእሷ ጋር በመተኛት ከክብር አሳንሳ እንድትመለስ አድርጓታል፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴም ይህን ታሪክ መግልጽ አስቀምጦታል፡፡ ‹‹ለያዕቆብ የወለደችለት የልያ ልጅ ዲናም የዚያን አገር ሴቶች ልጆችን ለማየት ወጣች፡፡ የአገሩ አለቃ የኤዊያዊ ሰው የኤሞር ልጅ ሴኬም አያት ወሰዳትም ከእርሷም ጋር ተኛ አስነወራትም ›› ብዙዎች ዘፈን የሚያመጣውን ጣጣ ባለማወቅ ለመዝናናት በሚል ሰበብ ከቤታቸውን ወጥተው ድንግልናቸውን በማጣት ከክብር አንሰው ይመለሳሉ፡፡ ላልተፈለገ እርግዝና ተጋልጠው ከዓላማቸው ተሰነካክለው ይቀራሉ፤ በራሳቸው መንገድ ባመጡ ኃጢአት እግዚአብሔርን ያማርራሉ፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ በዘፈን ምክንያት ከሚመጣ ኃጢአት ራሳችንን እንድንጠብቅ እንዲህ ይለናል ‹‹ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ፤ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር ›› በማለት ይመክረናል፡፡
ከዚህ መልእክት ልንወስደው የሚገባን ዓብይ ቁም ነገር በዘፈን ምክንያት ከሚመጡ የኃጢአት ሥራዎች ራሳችንን በመጠበቅ እንዳለብን ነው፡፡ ዘፋኝነት እግዚአብሔርን የሚያስቀይም፣ ሰዎችኝ ወደ ኃጢአት የሚጋብዝ፣ ከመንግሥተ ሰማያት በአፍአ የሚያደርግ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም ዘፋኝነት ሥራችን የሆነ ሰዎች እግዚአብሔር በሰጠን አንደበት እንዘምርበት፤ ዘፈን በመስማት ራሳችንን ለኃጢአት ያጋለጥን ሰዎች ንስሐ ገብተን መዝሙር እናዳምጥ! አምላካችንን ልዑል እግዚአብሔር የዘፋኝነት መንፈስ ከውስጣችን ያስወግድልን፡፡ በዘፈን ምክንያት ከምንሠራው ኃጢአት ይጠብቀን፡፡ አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ታኅሣሥ ፳፬
ልደቱ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት


ታኅሣሥ ሃያ አራት በዚህች ዕለት ጌታችን በቃሉ ''ሐዲስ ሐዋርያ'' ብሎ የሾማቸው የኢትዮጵያ ብርሃኗ የሆኑ የደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ልደታቸው ነው፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ማለትም ‹‹አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነውታል፡፡ ወላጆቻቸውም ስማቸውን ፍሥሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ይኸውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ የወላጆቻቸው የቀድሞ ስማቸው ዘርዐ ዮሐንስና ሣራ ይባል ነበር፡፡

ቅዱሳን አባቶቻችን እነ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና እነ አቡነ ዜና ማርቆስ ሌሎቹም እነ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ፣ አቡነ ሕፃን ሞዐ፣ አቡነ አኖሪዮስ(ትልቁ)፣ አቡነ ገላውዲዮስ፣ አቡነ ማትያስ ዘፈጠጋርና አቡነ ቀውስጦስ ዘመሐግል የትውልዳቸው መሠረት ኢያሱ ለሌዋውያን ክፍል ትሆን ዘንድ ከለያት ከኢየሩሳሌም ነው፡፡ ስማቸው የተጠቀሱት እነዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን የወንድማማቾች ልጆች ሲሆኑ ከአዳም ጀምሮ 61ኛ ትውልድ ናቸው፡፡ ይኸውም እንዴት ነው ቢሉ ትውልዱ ከአዳም ጀምሮ በካህኑ አሮን በኩል የሆነውና የሌዋዊያን ሊቀ ካህን የነበረው የሳዶቅ ልጅ አዛርያስ በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ከታቦተ ጽዮንና ከብዙ ሌዋዊያን ካህናት ጋር ሊቀ ካህን ሆኖ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ አክሱም ተቀምጦ ኖረ፡፡ የኦሪትንም ሕግ እየዞረ ለኢትዮጵያ ሰዎች አስተማረ፡፡ ትውልዱም በአብርሃ ወአጽብሓና በአባ ሰላማ ዘመን እስከነበረው እንበረም የሚባለው ጻድቅ ድረስ ደረሰ፡፡ የእንበረምም ትውልድ ደገኛው ሕይወት ብነ በጽዮን ድረስ ደረሰ፡፡ ሕይወት ብነ በጽዮንም የደማስቆ ምድር ከሚሏት ከወለቃ ሀገር የመኮንን ልጅ የሆነችውን ወለተ ሳውልን አግብቶ አበይድላን ወለደ፡፡ አበ ይድላም በንጉሡ ድልዓዥን ዘመነ መንግሥት ለ150 ካህናት አለቃ ሆኖ በወለቃ ሀገር የክርስቶስን የወንጌል ሕግ እያስተማረ ብዙዎችን አጠመቀ፡፡ እስከ ሸዋ ምድር ድረስ እያስተማረ መጥቶ በሸዋ ምድር ተቀመጠ፡፡ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳነጸ፡፡ እጅግ አስደናቂ ተአምራትንም ያደርግ ነበር፡፡ ‹‹በሸዋ ጽላልሽ ተቀምጦ ሲያስተምርም በአንዲት ቀን እስከ ሁለት መቶ ሺህ ሕዝብ ያጠምቅ ነበር›› በማለት ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ይመሰክርለታል፡፡

አበይድላ በመጨረሻ በፈቃደ እግዚአብሔር ከሸዋ ጽላልሽ ምድረ ዞረሬ ሚስት አግቶ ሀበነ እግዚእን ወለደ፤ ሀበነ እግዚእም በኩረ ጽዮንን ወለደ፤ በኩረ ጽዮንም ሕዝበ ቀድስን ወለደ፤ እርሱም ነገደ እግዚእ የተባለ ነው፡፡ ሕዝበ ቀድስም ብርሃነ መስቀልን ወለደ፤ እርሱም ዐቃቢነ እግዚእ የተባለ ነው፡፡ ብርሃነ መስቀልም ሕይወት ብነን ወለደ፤ እርሱም ሴትን ወለደ፡፡ ሴትም ወረደ ምሕረትን ወለደ፡፡ ወረደ ምሕረትም ዘካርያስን ወለደ፡፡ ዘካርያስም የእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት የሆኑ 6 ወንድማማች ልጆችን ወለደ፡፡ እነርሱም እንድርያስ፣ አርከሌድስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብ፣ ቀሲስ ዮሐንስና ቀሲስ ዮናስ ናቸው፡፡ እንድርያስም ሳሙኤል ዘወገግን ወለደ፤ አርከሌድስም ሕፃን ሞዐን ወለደ፤ ዘርዐ አብርሃምም ታላቁን አኖርዮስን ወለደ፤ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብም ተክለ ሃይማኖትን ወለደ፤ ቀሲስ ዮሐንስም ዜና ማርቆስን ወለደ፣ ቀሲስ ዮናስ ደግሞ የፈጠጋሩን ማትያስንና ገላውዲዮስን ወለዳቸው፡፡ ገላውዲዮስም የመሐግሉ ቀውስጦስን ወለደ፡፡ እነዚህ ደጋግ ቅዱሳን በእናታቸውም በኩል እንዲሁ በዝምድና የተሳሰሩ ናቸው፡፡ ማቴዎስ የተባለው ደገኛ ክርስቲያን የሸዋ ገዥ የነበረ ሲሆን አንድ ወንድ ልጅ መድኃኒነ እግዚእንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ወለደ፡፡ ሶስቱ ሴቶች ልጆችም እምነ ጽዮን፣ ትቤ ጽዮንና ክርስቶስ ዘመዳ ይባላሉ፡፡ ሦስቱ እኅትማማቾችም ደጋጎቹን አባቶቻችንን ወለዱልን፡፡ እምነ ጽዮን የእነ ዜና ማርቆስን እናት ማርያም ዘመዳንና ወለደች፡፡ ትቤ ጽዮንም ሕፃን ሞዐን ወለደች፡፡ ክርስቶስ ዘመዳ ደግሞ ታላቁን አኖሬዎስን ወለደች፡፡ የፈጠጋሩ ገዥ መድኃኒነ እግዚእ ደግሞ የተክለ ሃይማኖትን እናት እግዚእ ኀረያን ወይም በሌላ ስሟ ሣራን ወለደ፡፡

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከልጅነታቸው ጀምሮ በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በ15 እና በ22 ዓመታቸው ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ከአቡነ ቄርሎስ (ጌርሎስ) ዲቁናንና ቅስናን ተቀብለዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ቅድስት ቤተክርስቲያንን በወጣትነት ዕድሜያቸው ያገለግሉ እንደነበር በዚህ ይታወቀል፡፡

ከዕለታት በአንዱ ቀን አባታችን ከጓደኞቻቸው ጋር ለአደን ወደ ዱር ሄደው ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ታያቸው፡፡ ቅዱስ አባታችንም ‹‹እንደዚህ ባለ ገናንነት የማይህ ጌታዬ ማነህ?›› ባሉት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹ዘወትር የምጠብቅህ ካንተ የማልለይ እናትህንና አባትህንም ስላንተ ከውኃ ስጥመትና ከምርኮ ያዳንኳቸው እኔ ሚካኤል ነኝ፡፡ ከእንግዲህ አውሬ አዳኝ አትሁን፤ ሰውን ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ሰውን በትምህርት የምታድን ሁን እንጂ፡፡ እነሆ እግዚአብሔር ጽኑዕ ሥልጣን ሰጥቶሃልና፤ ሙት ታስነሣለህ፤ ድውያንን ትፈውሳለህ፤ አጋንንትም አንተን በመፍራት ይሸሻሉ፡፡ ስምህ ፍሥሐ ጽዮን አይሁን፤ ተክለ ሃይማኖት ይሁን እንጂ፡፡ ትርጓሜውም ተክለ አብ፥ ተክለ ወልድ፥ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው›› አላቸው፡፡
ቅዱስ ሚካኤል ይህን ሲነግራቸው ጌታችን በሥጋ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እንደነበር ሆኖ መልከ መልካም ጎልማሳ መስሎ ታያቸው፡፡ ጌታችንም ‹‹ወዳጄ እንዴት ሰነበትክ? ቸር አለህን?›› አላቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ‹‹ጌታዬ ሆይ አንተ ማነህ?›› ብለው ሲጠይቁት ጌታችንም ‹‹እኔ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ነኝ፤ በናትህ ማኅፀን ፈጥሬህ ያከበርኩህ እኔ ነኝ፡፡ በተወለድክ በሦስተኛው ቀን አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለህ ታመሰግነኝ ዘንድ የምስጋና ሀብት ያሳደርኩብህ እኔ ነኝ፡፡ በርሃብ ዘመን በቤት የሚያሻው ምግብ ሁሉ ቅቤው፣ የስንዴው ዱቄት በእናት በአባትህ ቤት ይመላ ዘንድ በእጅህ ሀብተ በረከት ያሳደርኩብህ እኔ ነኝ፡፡ ያንን ሰው አንተን በተጣላ ጊዜ በነፋስ አውታር የሰቀለኩት በመዓት ጨንገር የገረፍኩት እኔ ነኝ፡፡ ውኃ ጠምቶህ በለመንከኝ ጊዜ ከደረቅ መሬት የጣፈጠ ውኃ ያመነጨሁልህ እኔ ነኝ፡፡ ከልጅነትህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ተአምራት እያደረግሁ በአንተ እጅ የታመሙትን ያዳንኳቸው እኔ ነኝ፡፡ ወደፊትም አደርግልሃለሁ›› አላቸው፡፡ ይህንን ብሎ በእጆቹ ባረካቸውና ‹‹ንሣእ

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ባሰማት ጊዜ"
ስሙ ገብርኤል የተባለ ለድንግል ነገራት መልካም ዜና
እንደምትወልደው ወልድን በድንግልና(፪)

ባሰማት ጊዜ ቃሉን ቅዱስ ገብርኤል በለዛ(፪)
ድንግል ቀረበች ወደእርሱ ፍጹም ትሕትናን ይዛ(፪)

ትጸንሻለሽ ሲላት መልአኩ ፋጹም በልቧ ሳትመካ
እንደቃልህ ይሁን አለቺው በቃሉ ተማርካ(፪)
አዝ---
የዓለም መድኃኒት ነውና ካንቺ የሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ
ትሰይሚዋለሽ ስሙን ብለሽ ኢየሱስ(፪)
አዝ---
እፁብ ድንቅ ነው ሁልጊዜ ለድንግል ማርያም የተሰጣት ክብር
የአምላክ እናት መሆን መመረጥ ከሴቶች መካከል(፪)
አዝ---
ጸጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ ይገባሻል አንቺ ክብርና ምስጋና
የክብር ባለቤት ሁልጊዜ ካንቺ ጋር ነውና(፪)
አዝ---

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ታኅሣሥ ፳፪
ብሥራተ ገብርኤል

ታኅሣሥ ሃያ ሁለት በዚህች ዕለት ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን አምላክን እንደምትወልድ ያበሰረበት መታሰቢያ ነው፡፡ ይኸውም ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው። ይኸውም ‹‹ልዑል እግዚአብሔር ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን ‹ሂድና ለጽዮን ልጅ ለድንግል የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ወደአንቺ መጥቶ ኃይለ ልዑል ወልድ ሥጋሽን ለብሶ ሰው ይሆናል፤ ይኸውም ካንቺ የሚወለደው ጽኑዕ ነው ብለህ ንገራት› አለው፡፡ ‹ደንቆሮዎች የሚሰሙበት፣ ድዳዎቸ የሚናገሩበት፣ ዕውራንም የሚያዩበት፣ ሙታን የሚነሡበት፣ ለምጻሞች የሚነጹበት፣ ሐንካሳዎች የሚሄዱበት፣ በጨለማ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ብርሃን የሚያዩበት ጊዜ እነሆ ደረሰ ብለህ ንገራት› አለው፡፡
ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ሰምቶ በግንባሩ ተደፍቶ ልዑል እግዚአብሔርን ‹ጌታ ሆይ! የምትነግረኝ ይደረግ ዘንድ እንደምን ይሆናል?› አለው፡፡ ጌታም ‹የጀመርኩትን ቸርነት ፈጸምኩ፣ የወይን ግንድ ይቆረጣል (ወልደ እግዚአብሔር ይሞታል)፣ ወይራም ከበለስ ጋር ይተከላል (መስቀል ይተከላል)፣ ቅጽሮችም ይቀጸራሉ (ምግባር ከሃይማኖት ጋር ይሠራል)፣ የኤልፍና የሌሚ ወገን ይነሣል፡፡ ገብርኤል ሆይ! ሄደህ ለዳዊት ልጅ ‹እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ› ብለህ አብሥራት› አለው፡፡ ‹ለዘለዓለም ነግሦ የሚኖረውን እነሆ ትፀንሳለሽ በላት› አለው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ሰምቶ ሰገደ፡፡ ልብሱንም በላዩ ይዞ በመስቀል ቀኝ ይወርድ ዘንድ ወደደ፡፡ ጌታም ‹መግባትህና መውጣትህ በፍቅር አንድነት ይሁን› አለው፡፡ ‹ዘካርያስን ረግመህ አንደበቱን እንዳሰርህ እርሷን እንዳታሳዝናት ይልቁንም አብዝተህ ደስ አሰኛት አንጂ› አለው፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ሰምቶ ፈጽሞ ደስ እያለው ሊባኖስ ከሚባል ተራራ እስኪሰማ ድረስ ክንፉን እያማታ ወረደ፡፡ በዚህም ጊዜ በዙሪያው ያሉ ሁሉ ‹ይህ የምንሰማው ምንድነው?› ይሉ ነበር፡፡ የተደረገበትንም ቦታ አላወቁትም ነበር፡፡››
እመቤታችንን በ3 ዓመቷ እናትና አባቷ ብፅዓት አድርገው ለእግዚአብሔር ሰጥተዋታልና ካህናትም በቤተ መቅደስ ከመካነ ደናግል አስገብተዋት በመልአኩ በቅዱስ ፋኑኤል አማካኝነት ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየመጣላት ያንን እየተመገበች ቅዱሳን መላእክት እየጎበኟት 12 ዓመት ኖራለች፡፡ በ15 ዓመቷ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ጌታችንን እንደምትወልድ በዚህች ዕለት አብሥሯታል፡፡ በመጀመሪያ እመቤታችን ውኃ ቀድታ ስትመለስ የጠተማ ውሻ እያለከለከ ሲመጣ ብታየው ለፍጥረት ሁሉ የምትራራ ናትና በወርቅ ጫማዋ ለዛ ለተጠማው ውሻ ውኃ ስታጠጣ አብሯት የነበሩ ሴቶች ‹‹ማድጋሽን አጎደልሺው፣ ቀድቼ እሞለዋለሁ እንዳትይ ጉድጓዱ ጥልቅ ነው መቅጃም የለሽም›› አሏት፡፡ ክብርት እመቤታችንም ‹‹ውሃ የሚገኘው ከወደላይ ነው እንጂ ከወደታች ነውን? ፍጥረቱን ያጠጣ ጌታ ይሞላልኛል›› አለቻቸው፡፡ ማድጋዋም በተአምራት ሞልቶ ተገኘ፡፡ ሴቶቹም ዳግመኛ ‹‹በዚህ ዘመን አምላክ ከድንግል ይወለዳል ይላሉ ካንቺ ይሆን?›› እያሉ ሲዘብቱባት ወዲያው ከወደኋላዋ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ‹‹እነሆ ትጸንሻለሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም ዞር ብትል የተናገራትን አጣችው፡፡ በዚህም ጊዜ ‹‹አባቴን አዳምን እናቴን ሔዋንን ያሳተ ጠላት ይሆናል›› ብላ ሄደች፡፡
ዳግመኛም እመቤታችን ከቤት ደርሳ ማድጋዋን ስታስቀምጥ መልአኩ አሁንም በድምፅ ‹‹እነሆ ትጸንሻለሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም ይህን ጊዜ ‹‹ምነው ይህስ ነገር ደጋገመኝ እንዲህ ያለውን ነገር ቤተ መቅደስ ሄደው ሊረዱት ይገባል›› ብላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዳ ወርቅና ሐር እያስማማች ስትፈት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እሁድ ቀን በ3 ሰዓት በገሃድ ተገለጸላትና እጅ እየነሳ እየሰገደ አበሠራት፡፡ ‹‹የዕውነተኛ ንጉሥ እናቱ እመቤታችን ላንቺ ፍቅር አንድነት ይባል›› አላት፡፡ ዳግመኛም ‹‹አንቺ ከሴቶች ይልቅ ተለይተሸ ንዕድ ክብርት ነሽ›› አላት፡፡ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናቸ ክብርት እመቤታችንም የብርሃናዊውን መአልክ የቅዱስ ገብርኤልን ቃል በሰማች ጊዜ ‹‹እንዲህ ያለውን ሰላምታ እንደምን ይቀበሏል! እንዴትስ መቀበል ይቻላል? እንጃ›› አለችው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ‹‹ማርያም ሆይ! መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፣ ኃይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ይለብሳልና አይዞሽ አትፍሪ›› አላት፡፡ ዳግመኛም ‹‹ይህ ካንቺ የሚወለደው ጽኑ ከሃሊ ነው፡፡ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ፣ እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፣ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፣ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፣ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም›› አላት፡፡ እመቤታችንም መልአኩን ‹‹ምድር ያለ ዘር ፍሬን አትሰጥምና እኔ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?›› አለችው፡፡ መልአኩም መልሶ ‹‹መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፣ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ እርሷ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፡፡ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፣ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችንም ይህን ጊዜ ‹‹እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ›› አለችው፡፡ መልአኩም ከእርሷ ዘንድ ሄዶ ተሠወረ፡፡ አካላዊ ቃልም በማኅፀኗ አደረ፡፡ በዚያችም ቅጽበት የእመቤታችን የፊቷ መልክ ተለወጠ፣ እንደፀሐይም አሸበረቀ፡፡
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
‹‹እንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ ወሪዳ ምድረ ቆላ ገብርኤል መጽአ እንዘ ይረውጽ በሰረገላ ክንፎ ክንፎ ክንፎ ጸለላ ተፈስሒ ተፈስሒ ለድንግል ይቤላ፤
ትርጉም ፦ወደ ቆላው ምድር ወርዳ እመቤታችን ወርቅን ከሐር ጋር አስማምታ እየፈተለች ሳለች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ እየሮጠ መጣ፣ ክንፉንም እያማታ እየሰገደ ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ አላት››

"ተፈሥሒ ፍሥሒት ኦ ምልዕተ ጸጋ፤ ጸጋን የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ" ሉቃ 1፡28

…ደስ የተሰኘህ ሆነህ ምሥራችን የተናገርክ መልአኩ ገብርኤል ሆይ የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው። ወደኛ የመጣ የጌታን ልደት ነገርኸን ለድንግል ማርያም ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ ብለህ አበሰርኻት ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን ።…

እንኳን አደረሳችሁ!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"የራማው ልዑል ገብርኤል"
የራማው ልዑል ገብርኤል (፪)
ተመላለስ መሐላችን ስምህን ጠርተን ና ስንልህ(፪)
      ብርሃን ልብሱ እሳታዊ መልአክ
      አንተ አማልደን ከመሐሪው አምላክ (፪)
              አዝ….
የምስራች ነጋሪ ድንቅ ልደት አብሳሪ
የጽድቅ ፋና የምሕረት ጎዳና (፪)
              አዝ….
      ላመኑብህ ለተማጸኑህ
      ፈጥኖ ደራሽ አለኝታቸው ነህ (፪)
             አዝ….
የአናንያ የአዛርያ የሚሳኤል ከለላቸው
ከእሳት ነበልባል ያዳንካቸው (፪)
            አዝ….
     ምሰሶ አምዳችን መጠጊያችን
     ቅዱስ ገብርኤል ጠባቂያችን (፪)
            አዝ….
ዕለት ዕለት የምንማልድህ
ልጀችህን ይምራን መንፈስህ(፪)
አዝ....

©ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ታኅሣሥ ፲፱
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል


ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ያዳነበት ነው፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር ከአባታቸው ከይሁዳው ንጉሥ ከኢዮአቄም ጋር የማረካቸው አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ እግዚአብሔር በዚህች ዕለት መልአኩን ልኮ ታላቅ ተአምር አድርጎላቸዋል፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር እነዚህን ወጣቶች በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ጥበብን እያስተማረ ካሳደጋቸው በኋላ በባቢሎን ሀገሮች ሁሉ ውስጥ ሾማቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ የወርቅ ምስል በሠራ ጊዜ መኳንንቱንና በግዛቱ ውስጥ ያሉ ሁሉ ለዚያ ምስል እንዲሰግዱ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ለጣዖቱ ባለመስገድ እግዚአብሔርን ብቻ በማምለክ የጸኑት እነዚህ ሦስት ወጣቶች ብቻ ነበሩ፡፡ ስለ እነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡-
‹‹ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው፡፡ ንጉሡም ናቡከደነፆር መኳንንትንና ሹማምቶችን፥ አዛዦችንና አዛውንቶችን፥ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፣ መጋቢዎችንም፣ አውራጃ ገዦችንም ሁሉ ይሰበስቡ ዘንድ፣ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ፡፡ በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምቶቹ፣ አዛዦቹና አዛውንቶቹ፣ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ፣ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዦቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰበሰቡ፤ ናቡከደነፆርም ባቆመው ምስል ፊት ቆሙ፡፡ አዋጅ ነጋሪውም እየጮኸ እንዲህ አለ፡- ‹ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የምትናገሩ ሆይ! የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፣ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል፡፡ ተደፍቶም የማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል፡፡› ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፣ የመሰንቆውንና የክራሩን፣ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፣ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፤ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ፡፡

በዚያን ጊዜም ከለዳውያን ቀርበው አይሁድን ከሰሱ፡፡ ለንጉሡም ለናቡከደነፆር ተናገሩ እንዲህም አሉ ‹ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ፡፡ አንተ ንጉሥ ሆይ የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ፤ ተደፍቶም የማይሰግድ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል ብለህ አዘዝህ፡፡ በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፤ አማልክትህን አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም፡፡› ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ፤ እነዚህንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው፡፡ ናቡከደነፆርም ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ! አምላኬን አለማምለካችሁ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን? አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው?›› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡን ‹ናቡከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም፡፡ የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! እርሱ ባያድነን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ› አሉት፡፡

የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፡፡ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፡፡ እርሱም ተናገረ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ፡፡ ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ፡፡ የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ፡፡ የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም ‹ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?› ብሎ ተናገራቸው፡፡ እነርሱም ‹ንጉሥ ሆይ! እውነት ነው› ብለው ለንጉሡ መለሱለት፡፡ እርሱም ‹እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል› ብሎ መለሰ፡፡ የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ ‹እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም! ኑ ውጡ› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ፡፡

መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፣ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡ ናቡከደነፆርም መልሶ ‹መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፣ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ፡፡ እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ፣ ቤቶቻቸውም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ› አለ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም በባቢሎን አውራጃ ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፡፡›› ትንቢተ ዳንኤል 3፡1-30፡፡

አምላካችን ከቅዱስ ገብርኤል ረድኤት በረከት ያካፍለን ፤ የመልአኩ ፈጣን ምልጃ አይለየን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

#ተዘክሮተ_ሞት

«ለመተኛት ወደ አልጋህ ባመራህ በቀረብህ ጊዜ አልጋዬ፡ ምን አልባት በዚህ ሌሊት ለእኔ መቃብሬ ልትኾኚ ይኾን ይኾናል፤ በጊዜአዊው ዕንቅልፍ ፈንታ በዚህ ሌሊት ያኛው እንቅልፍ (ሞት) ይመጣብኝም እንደ ኾነ አላውቀውም በላት ።ስለዚህ ነጻ እግሮች እያሉህ ከመልካም ሥራ በኋላ ሩጥ፤ ከታሠሩ መፈታት በማይችሉበት ማሰሪያ ከመታሠራቸው በፊት፡፡ የእጆችህ ጣቶችም እስካሉህ ድረስ ሞት ከመምጣቱ በፊት በጸሎት ፊትህንና መላ ሰውነትህን በተእምርተ መስቀል አማትብ፡፡ ዐይኖች እስካሉህ ድረስ በአቧራ ከመሽፈናቸው በፊት በእንብዕ(በእንባ) ምላቸው።ሰው ሆይ ከዚህ ዓለም መለየትህን አስብ፣ እንዲህም በል፡- እነሆ የታዘዘ መልአክ ከበር ቆሞአል (ደርሶአል)፣ እኔንም ይከተለኛል። ለምን ሊል ዘሊል እኾናለሁ? መመለሻ የሌለው ዘለዓለማዊ መንገድ አለ፡፡መለኮት ደግነት የተነሣ የሰውን ልብ የሚገዛውና ነፍስን ወደ ሕይወት የሚመራት የመጀመሪያው ትምህርት ተዘክሮተ ሞት ነው።.ተዘክሮተ ሞት በሰይጣን እጅግ በብዙ ይጠላል፡፡ እርሱም ከሰው ተዘክሮን ለመንቀል በሙሉ ኃይሉ መሞከርን አይተዉም፡፡ የሚቻለውስ ቢኾን በምድራዊ ሕይወት አሳብ ተብትቦ ተዘክሮተ ሞትን ከሰው ልብ (አእምሮ) ለማስወገድ ምድራዊ መንግሥታትን ለሰው በሰጠው ነበር፡፡ አታላዩ ሰይጣን ተዘክሮተ ሞት በሰው ሁልጊዜም ካለ፣ አሳቡ ለአሁኑ ሕይወት መታለሎች የተጣበቀ ኾኖ እንደማይቀር አልያም የሰይጣን ማታለሎች ሰውን ሊቀርቡት እንደማይችሉ ያውቃል፡፡"

ማር ይስሐቅ ሶርያዊ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

#ውዳሴ_ከንቱ

የሚጠቅም ውዳሴ (ውዳሴ ዘይረብሕ)
ቅድስት ቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት በማድረግ ጎጂነቱን አውቃ የከለከለችው ከንቱ ምስጋና እንዳለ ሁሉ ተገቢ ነው ይጠቅማል ብላ የፈቀደችው ያዘዘችውም የምስጋና ዓይነት አለ፡፡ ይህ የምስጋና አይነት የተለየ ስያሜ ባይኖረውም ከውጤቱ በመነሳት ውዳሴ ዘይረብሕ (የሚረባ-ረብ ያለው ውዳሴ)፣ ውዳሴ ዘይበቊዕ (የሚጠቅም ውዳሴ) ልንለው እንችላለን፡፡
ለአምላካችን እግዚአብሔር ፤ ለቅዱሳን፤ በሥራቸው ሊመሰገኑ ለሚገባቸው ቅን ሰዎች፤ አንዳንዴም በምስጋና ልናበረታቸው ለሚገቡ ድኩማን የሚደረጉ ምስጋናዎች ከዚህ ዓይነቱ ምስጋና ውስጥ የሚመደቡ ናቸው፡፡
ለእግዚአብሔርና ለቅዱሳን የሚቀርቡ ምስጋናዎች አመስጋኙን ብቻ ሲጠቅሙ የቀሩት ደግሞ የሚጠቅሙበት ጎዳና ቢለያይም አመስጋኙንም ተመስጋኙንም የሚጠቅሙ ናቸው፡፡ ምስጋና አመስጋኙን ብቻ ሊጠቅም እንደሚችል የሚያሳይ በቅዳሴ ማርያም ላይ “ዘንተ ቅዳሴ ዘይቄድስ ካህን አኮ ማርያምሃ ዘይቄድስ አላ ውእቱ ይትቄደስ - ይህን ቅዳሴ የሚቀድስ ካህን ማርያምን የሚቀድሳት አይደለም ራሱ ይቀደሳል እንጂ” የሚል ንባብ ይገኛል፡፡ ከጥቅማቸው ከፍታ አንፃር ካየነው ደግሞ ለእግዚአብሔርና ለቅዱሳን የሚቀርብ ምሥጋና ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ራሱን የቻለ ሰፊ ሐሳብ በመሆኑም በዚህ ጽሑፍ የምንዳስሰው አይሆንም፡፡ ይልቁን ከሰዎች ጋር ባለን ማኅበራዊ ሕይወት ስለሚያጋጥሙንና ጥንቃቄ ስለሚፈልጉ ምስጋናዎች በጥቂቱ እንመለከታለን፡፡
መልካም ለሚሠሩና ቅን ለሆኑ ሠዎች ምስጋና እንደሚገባቸው በቅዱስ ዳዊት የመዝሙር መጽሐፍ “ወለራትዓን ይደልዎሙ ክብር - ለቅኖችም ምስጋና ይገባቸዋል” መዝ 33:1 ተብሎ የተጻፈ ሲሆን ልጁ ሰሎሞን ደግሞ መልካም ስለምትሠራ ልባም ሴት በጻፈበት የምሳሌ ክፍል “ልጆችዋ ይነሣሉ ምስጋናዋንም ይናገራሉ ባልዋ ደግሞ እንዲህ ብሎ ያመሰግናታል።መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ። ውበት ሐሰት ነው ደም ግባትም ከንቱ ነው እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች። ከእጅዋ ፍሬ ስጡአት ሥራዎችዋም በሸንጎ ያመስግኑአት።” ምሳ 31:28 በማለት ጽፏል፡፡ ከእነዚህ ጥቅሶች መልካም ለሚሠሩ ሁሉ ምስጋና የሚገባ መሆኑን ብንረዳም ጎን ለጎን ልናደርጋቸው የሚገቡ በቂ ጥንቃቄዎችም አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል፡-
፩- በመጠንና በተገባ ነገር ማመስገን
ምስጋናው ያልተመጠነና የተጋነነ ከሆነ በአንድ በኩል ተመስጋኙ በደንብ አንዲሠራ ከማድረግ ይልቅ በምስጋናው እየተደሰተ ተዘናግቶ እንዲኖር የሚያደርገው ሲሆን በሌላ መልኩ ደግሞ በውዳሴ ከንቱ እንዲወድቅ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ አመስጋኙም ለውድቀት ምክንያት በመሆኑ ከመቀጣት አይድንም፡፡
፪-ከጕሕሉት(ከሽንገላ) እና ከውሸት የፀዳ መሆን
ብዙ ሰዎች ዘመን የወለደውን ንጉስ የወደደውን ተከትለው በልባቸው ባያምኑበት እንኳ መስሎ ለማደር ብለው ሰዎችን ያመሰግናሉ፡፡ ተመስጋኙ ይህ ከልብ ነው፣ ይህ አይደለም ብሎ መለየት ባይችልም ልብና ኲላሊትን የሚመረምር አምላክ ይፈርድብኛል ብለን “በአፉሆሙ ይድህሩ ወበልቦሙ ይረግሙ - በአፋቸው ይመርቃሉ በልባቸውም ይረግማሉ፡፡” መዝ 62:4 ከተባሉት እንዳንቆጠር መጠንቀቅ ይገባናል፡፡
፫ ምስጋናን ሱስ እስኪሆን አለማስለመድ
ምስጋና ከተለመደ እንደሌሎቹ ልማዶች ሱስ ሊሆን ይችላል፡፡ አበው “ኀዲገ ልማድ ፅኑዕ ውእቱ - ልማድን መተው ከባድ ነው” እንዳሉ በውዳሴ ሱስ የተጠመደ ሰውም ከዚህ ልማድ መውጣት ሊከብደው ሲቀር ቅር ሊሰኝ አልፎም ለምን አልተመሰገንኩም ብሎ ሊቆጣ ይችላል፡፡ ሰው እንዲህ ካለ ክፉና አስተቺ ልማድ ውስጥ እንዲገባ ምክንያት መሆን ከባድ ፍርድ ያለበት በመሆኑ ሱስ እስኪሆንበት በነጋ ጠባ ሰውን ከማመስገን መጠበቅ ተገቢ ነው፡፡
በቅዱሳት መጻሕፍት መልካም ለሚሠሩና ቅን ለሆኑ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ምስጋናው ለማይገባቸውና የእነርሱ ባልሆነ ነገር ሰዎችን ማመስገን ጠቃሚ ሆኖ የሚገኝበት ጊዜ እንዳለም ተጽፏል፡፡ በሥጋዊ ትምህርት ጎበዝ ያልሆነውን ተማሪ ጎበዝ በማለት ተነሳሽነቱ እንዲጨምርና እንዲሻሻል ማድረግ እንደሚቻል በመንፈሳዊ ሕይወቱ ያልበረታን ሰውንም በማመስገን ማበርታት እንዲሁ ይጠቅማል፡፡ ይህን በተመለከተ በመጽሐፈ መነኮሳት ላይ “ወድሶ ለሰብእ በዘኢኮነ ሎቱ ወድሶ ለሰብእ በዘኢኮነ ድልወቱ እስመ ወድሶ ለሰብእ ይወስክ ኃይለ - ሰውን የእርሱ ባልሆነና ባልተገባው ነገር አመስግነው ምስጋና ለሰው ኃይልን ይጨምራልና” ተብሎ ተጽፏል፡፡
ከላይ ስለተገለጡት ተገቢ ምክንያቶች ማመስገን በዚህ ጽሑፍ ተነግረው የማያልቁ እጅግ ብዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ “ብጹዕ ሕዝብ ዘየአምር የብቦ - እልልታን (ምስጋናን) የሚያውቅ ሕዝብ ምስጉን ነው፡፡” መዝ 89:15 ተብሎ እንደተጻፈ ሰዎችን ለማመስገን መነሳት በራሱ የሚያስመሰግን ደግ ተግባር ነው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ አምላክ “በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል” ማቴ 5:22 ብሎ ካስተማረን ወንድሙን ያመሰገነ ምን ዓይነት ሽልማት ይገባው ይሆን? “ዘይፀርፍ ላዕለ እኁኁ ዘረፈኬ ላዕለ እግዚአብሔር ልዑል - በወንድሙ ላይ የተሳደበ በእግዚአብሔር ላይ ተሳደበ” ተብሎ ከተጻፈ ወንድሙን ያመሰገነ ምን ዓይነት ክብር ይጠብቀው ይሆን?
............. ✞✞✞ .............

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"እናምናለን እኛ ሁለት ልደታትን"
ሐዋርያት አበው እንዳስተማሩን
ስለሰው ልጅ ድኅነት አምላክ ሰው መኾኑን
በስሙ የተጠራን እኛ እናምናለን
መለኮት ከሥጋ ተዋሕዷል ብለን

እናምናለን እኛ ኹለት ልደታትን
የአብ ልጅ ከድንግል ዳግም መወለዱን/፪/

ስግደት የሚገባው የአብ አካላዊ ቃል
ከክቡር ዙፋኑ ከሦስትነት ሳይጎድል
በዚህ ዓለም መጥቶ ሰው ሆኗል ከድንግል
ከአብ አንድነቱ ከቶ ሳይከፈል
አዝ---
ቃልም ሥጋ ሆኖ በእኛ ላይ አድሮ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም በተዋሕዶ ከብሮ
ፍጹም የአምላክ ልጅ ፍጹም ሰውነቱ
ተገልጧል በድንግል በዳግም ልደቱ
  አዝ---

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ከንቱ ነኝ"
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከሰዎች ማነው እንደ እኔ ትእዛዝህን ሻሪ/፪/ከአማልክትስ ማነው እንዳንተ መሐሪ /፪/

የኃጢአት ሸክም ከብዶብኝ ሲያስጨንቀኝ
ጠላቶች ከበው በእኔ ላይ ሲዝቱብኝ
ብቸኝነቴን አይተህ ስለደረስክልኝ
ተመስገን እንጂ ላንተ ሌላ ምን አለኝ

አዝ...../፪/

በደሌን አይተህ በቅፅበት ያላጠፋኸኝ
እንደ ጥፋቴ በቁጣ ያልተበቀልከኝ
ቸር እና የዋህ አምላክ እንዳንተማ አይገኝ /፪/

አዝ...../፪/

እንደ ሕዝቅያስ ጸሎቴን አምላክ ስማኝ
እንደ ዳዊትም ልመናዬን ተቀበለኝ
በዘመኔ እኩሌታ አምላኬ አትውሰደኝ
ወሰን በሌላት ፍቅርህ ታግሰህ ጠብቀኝ

አዝ...../፪/


@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"የአርማንያ ሰማዕት |አርሴማ|"
ለሰማያዊ ክብር በወንጌል|፪| ያስጌጠሽ
ለቃሉ ምስክር አምላክ  የጠራሽ
የአርማንያ ሰማዕት|፪|  አርሴማ አንች ነሽ፣
 
          አዝ...........
የምሥጢር ዋሻ ነሽ የሰማይ ሙሽራ፣
በዓለማት ሁሉ ክብርሽ የሚያበራ።
ምግባር|፪| እና እምነትን አስተባብረሽ ይዘሽ፣
በመንግሥተ ሰማይ አክሊል ተቀዳጀሽ።
አዝ.........
በእውነት ቢያምርም የሰው ልጅ ውበቱ፣
ምግባር ከታጣበት በሰማይ አባቱ።
ያልሆነለት|፪| እሱ ውበት ሃይማኖቱ፣
ብለሽ ተናግረሻል ይቀራል በከንቱ።
አዝ.....
የጽናት ምስክር  ለቃለ ወንጌሉ ፣
ከሁሉ ይበልጣል  የፈጣሪ ኃይሉ።
ጸንተው|፪| ለሚኖሩ በሃይማኖታቸው ፣
አርሴማ እናታችን አብነት ሆንሻቸው።
አዝ........
ለሰማያዊ ክብር ስለሆንሽ ምክንያት፣
እኛ እንልሻለን የሁላችን  እናት።
ለምናምን|፪| ሁሉ በምልጃ ኪዳንሽ፣
ምሕረትን አሰጪን ለምነሽ ከአምላክሽ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"በቤተ መቅደስህ ያሳደግከኝ"

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ንጽህተ ንጹሀን ከዊና፣
ከመታቦት ዘዶር ዘሲና፣
ውስተ ቤተ መቅደስ፣
ነበረት(፪) በድንግልና፣
ሲሳይያ ኅብስተ መና፣
ወስቴሃኒ ስቴ ጽሞና።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…
Subscribe to a channel