ethiopian_orthodox | Unsorted

Telegram-канал ethiopian_orthodox - የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

30344

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Subscribe to a channel

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በብዙ ወጣቶች ዘንድ ያልተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም ፍሬያማ ግብር (ስኬት) ማለት የተመኙትን ሁሉ ማግኘት ይመስላቸዋል:: ነገር ግን ከዚህ የሚበልጥ ስኬታማነት አለ፡፡ እርሱም ራስን በመግዛት ምኞትን መመጠን ነው:: ምኞትን ከመመጠን ጋር ስናወዳድረው የተመኙትን ለማግኘት መልፋት በጣም ቀላል ነገር ነው:: ከባዱ ነገር አለመመኘት ወይም ምኞትን በልክ ለማድረግ መቻል ነው፡፡.
ታዋቂና ዝነኛ ሰው መሆን ብትፈልግ ብዙ ጥረትና ጊዜ ይፈጅብህ ይሆናል እንጂ ታገኘዋለህ:: ነገር ግን የተናቀ ሰው ለመሆን አስበህ ታውቃለህን? ብታስበውስ የሚቻል ይመስልሃልን? ትልቅ ሰው ከመሆን ትንሽ ሰው መሆን እጅግ ይከብዳል:: ታዲያ ችሎታ መባል ያለበት የቱ ነው? ትልቅ ሰው መሆን ባትችል እንኳን ጥረቱ ያም ባይሆን ፍላጐቱ ይኖርሃል፡፡ ስለዚህ ትንሽ ነህ አትባልም:: ትንሽ ለመሆን ግን እንኳን መጣር ይቅርና ሐሳቡንም አምኖ ለመቀበል ይከብድሃል፡፡ ለምን ይመስልሃል? ትንሽ ስለ ሆንክ ይመስልሃልን? አይደለም፡፡ እንደዚህ ለማድረግ ችሎታ ስላሌለህ ነው::
በወጣትነት ዘመን ይህ የተሳካላቸው ያለ ምንም ጥርጥር ጻድቃንና ቅዱሳን ናቸው፡፡ ለዚህ ማዕረግ የበቁት ብዙ ሀብት በማካበትና ብዙ በመማር ሳይሆን የኢየሱስ ክርስቶስን ፈለግ በመከተል ራሳቸውን ብዙ ስላዋረዱ ከዚህም ዓለም ምንም ስላልፈለጉ ነው።
ቅዱስ ዳዊት ያሰበውና የሚሠራው ሁሉ የሚከናወንለት ምስጉን ሰው ምን ዓይነት ሰው እንደ ሆነ ሲገልጽ እንዲህ ይላል:- «ምስጉን ነው : በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይልዋል፥ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል:: እርሱም እንደተተከለች፥ ፍሬዋን በውኃ ፈሳሾች በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል›› ይልና በመጨረሻም «የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል» ይላል፡፡ ከዚህ የበለጠ ስኬታማነት ሊኖር አይችልም:: ይህ የሚገኘው ደግሞ ከላይ የተገለጡትን መንፈሳዊ ጎዳናዎችን በመከተል ነው:: የስኬት መሠረት መንፈሳዊነት ነው የተባው ስለዚህ ነው።
ሰው ከእግዚአብሔር ርቆ ስኬታማ መሆን አይችልም:: የያዕቆብ ልጅ ዮሴፍ በሥጋም ሆነ በነፍስ ነገሮች ሁሉ የተሳኩለት ወጣት እንደ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይመስክራል፡፡ «እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ፣ በግብፃዊው ጌታውም ቤት ነበር። ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ፣ እርሱ የሚሠራውም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ፡፡»
ዛፍ ከግንዱ ተለይቶ ለማፍራት እንደማይችል እንዲሁ የሰው ልጅም ከፈጣሪው ተለይቶ ፍሬያማ መሆን አይችልም። ሰው ሠራሽ አበባ መልኩ ይመር እንጂ ምንም ዓይነት መልካም መዓዛና ሕይወት እንደሌለው ሁሉ በችኮላና ከፈጣሪ ተለይተው ያፈሩት ነገር ሁሉ ውስጣዊ ደስታና ዘላቂነት የሌለው በመሆኑ መጨረሻው አሳዛኝ ነው፡፡ ብዙ ነገር ኖሮህ በኃዘን ከመዋጥህ የተነሣ ምንም እንደሌለው ከምትሆን ትንሽ ነገር ኖሮህ በደስታ ብትኖር አይሻልህምን? ስልዚህ «የሰው ሕይወቱ በገንዘቡ መጠን አይደለምና» ነገሮችን መሻትህ ከፈጣሪህ እንዳይለይህ ተጠንቀቅ! ከመጎምዠትም ተጠበቅ ! ሉቃ12÷15
ሰው ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ቢሆን ነገሮች ሁሉ ይሳካሉ፡ ይከናወኑማል፡፡ ራሱ ፈጣሪ «ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም» ብሏልና፡፡ ዮሐ15፥4-7 ያለ ረድኤተ እግዚአብሔር መማር ማስተማር መጻፍ መደጎስ በአጠቃላይ ማንኛውም ሥራ ከፍጻሜው ሊደርስ አይችልም:: ነቢዩ ነህምያም «እኛ ባሮቹ ተነሥተን እንሠራለን የሰማይ አምልክም ያከናውንልናል» ያለው «ማከናወን» የፈጣሪ ድርሻ ስለሆነ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ «ወጢንሰ እምኀበ ሰብእ» በማለት እንደተናገረው «መጀመር›› የሰው ድርሻ ሲሆን መፈጸም ግን የእግዚአብሔር ነው:: ነገሮች ከፊጻሜ ሳይደርሱ ደግሞ ስኬት የሚባል ነገር ሊኖር አይችልም:: ስለዚህ «መፈጸም» የፈጣሪ ከሆነ የሰው ስኬት የተያዘው በእግዚአብሔር እጅ ነው ማለት ነው::
መንገድ እንዲቃናልህ የምትሠራውም ሁሉ እንዲከናወንልህ ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ከዚህ በታች የሰፈረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በልብህ አኑረህ ተጠቀምበት:: ቃሉም እንዲህ ይላል:- «የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፡ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፡ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም፡፡» ኢያ1፥8

ቀጣይ የመጨረሻው ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ክፍል ዐራት :
👉 «በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ» በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በእርግጥ የማያሳፍርና የሚያሳፍር ነገርን ለይቶ ማወቅ ለሰው ሁሉ የሚገባ ነገር ነው።ምክንያቱም ከመለመዱ የተነሣ የማያሳፍረው ሲያሳፍር፤ የሚያሳፍረው ደግሞ ሲያስመካ ማየት የዘወትር ክሥተት አየሆነ መጥቷልና፡፡
በዚህ ዘመን ውሽት በሚናገሩበትና በሚያታልሉብት ጊዜ ፊትን ሳያጥፉ ድርቅ ብሎ መፋጠጥ እንደ ጉብዝና ተቆጥሯል:: ይህን የሚያደንቁና ሲዋሹ የሌላውን ፊት ትኩር ብሎ ለማየት ራሳቸውን የሚያለማምዱ በርካታ ሰዎች በዙሪያችን ይገኛሉ፡፡ ለጊዜው ይህ ጉብዝና ሊመስል ይችል ይሆናል ውሎ አድሮ ግን ከፍተኛ ጸጸት ማስከተሉ አይቀርም፡፡
እፋራምነት የመልካም ሥነ ምግባር መገለጫ ነው:: ሆኖም ብዙዎች እንደ ጭቆናና ብዝበዛ መሣሪያ አድርገው ስለሚቆጥሩት በምንም አጋጣሚ ማፈር አይፈልጉም:: እንዲያውም አንዳንድ ደፋር ነን ባዮች ዓይናፋርነትህን አውቀው በአንድ ወቅት ሳያሾፉብህና ሳያስጨንቁህ አይቀሩም፡፡ ይህ አጋጣሚ ራስህን በጣም እንደ ተጠቃ ሰው ቆጥረህ እንደ እነርሱ «ደረቅነትን» ለመለማመድ በቁጣ እንድትነሣሣ ለማድረግ ለሰይጣን በር ይከፍትለታል፡፡ ስለዚህ ይህንና ይህን የመሳሰሉ ገጠመኞች ዓይናፋርነትህ ብዙ እንዳጐደለብህ እንዲስማህ በማድረግ እንድታማርረው ወይም ደግሞ እሽቀንጥረህ እንድትጥለው ያደርጉሃል:: ነገር ግን ይህን ካደረግህ በዚህ ዓለም ስትኖር በባሕር ላይ ሆነህ መልሕቅህን እንደ ጣልከው ቁጠር፡፡
ኀፊረ ገጽ ብተለይ በወጣትነት መንፈሳዊ ሕይወትን ለመምራት በእጅጉ ይጠቅማል፡፡ ተገቢ ባልሆነ ተግባርህ ብቻህን ስትሆን ሕሊናህን፤ በቤት ውስጥ ወላጆችህን፣ በሌላ ስፍራ ደግሞ አለቆችህን፣ መምህራንንና ሌሎች ታላላቅ ሰዎችን ማፈርና ማክበር ይኖርብሃል፡፡ ሰው እኮ የሚመከረው ሕሊና ሲኖረው ወይም የሚፈራውና የሚያከብረው ሰው ሲኖረው ነው:: እነዚህ የሌሉት በማን ይመከራል?
ማፈርና መፍራት ከሰዎች እየራቁ በመሄዳቸው በሀገራችን ብዙ ችግሮች ተበራክተዋል፡፡ ሽማግሌን አፍሮ መታረቅ እንኳን እንደ ከዚህ ቀደሙ ቀላል ነገር አልሆነም:: ብዙ ሴቶች እኅቶቻችን ለሻካራ ንግግርና <<ደረቅ>> ለሚያሰኛቸው አለባበስ ተጋልጠዋል:: በየፌርማታው፣ በየመጓጓዣ መኪና፣ በየመንገዱና በየፈፋው መሳሳምና መዳራት አበጀህ እንደሚያሰኙ ተግባራት ተደርገው ተወስደዋል፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ደግሞ መደባበቁና ጨለማን ተገን ማድረጉ ቀርቶ በሕዝብ መድረኮችና በአደባባይ ላይ በዝሙት መንፈስ መዳራትና መሳሳም የጥበብ መግለጫ ሆነው በየፊልሙና በየድራማው መሃል እንደ ሳጋ ተሰግስገው ይታያሉ፡፡ በዚህ ፍጥትነታችን ከቀጠልን ዝሙትን እንደ ባህል እንደሚቆጥሩ ሀገሮች ግብረ ዝሙትን በገሃድ በፊልምና በቴአተር ቤቶች መድረክ የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።
የዚህ ሁሉ ምንጩ ኀፊረ ገጽ ከኢትዮጵያውያን ልቡና ተገፍቶ እንዲወጣ ስለተደረገ ነው፡፡ ይህም ሁሉ ሆኖ ወጣቶች ገና ባለመንቃታቸው ዓለም ዓይናቸውን በጨው ላጠቡ ስዎች እንደምትመች አድርገው በመቁጠር ራሳቸውን «ደረቅ» ለማድረግ ይጥራሉ፡፡
ለበጎና ለሚገባ ነገር ደፍሮ መሰለፍ ስማዕትነት ነው:: ነገር ግን ለሰይጣን ፈቃድ ደፍሮ መሰለፍ ምን ይባላል? ክርስቲያን አፋራም ነው ማለት ለመብቱ አይከራክርም፣ ዝም ብሎ ይጨቆናል፣ ይረገጣል ማለት አይደለም:: ማፈር የማይፈልግ ሰው ከሚያሳፍሩ ነገሮች መለየት ይገባዋል እንጂ ደፋርነትን መለማመድ መፍትሔ አይሆንም፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የኤፌሶን ክርስቲያኖችን በመከረበት አንቀጽ «...የሚያሳፍር ነገርም፥የስንፍና ንግግርም ወይም ዋዛ የማይገቡ ናቸውና አይሁኑ።» በማለት ተናግሯል፡፡ «የሚያሳፍር ነገርም» ሲል ሐሳብም፣ ንግግርም፣ ሥራም የሚያሳፍሩ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገልጻል፡፡ እነዚህ ሦስቱም «ነገር» ይባላሉና፡፡ ኤፌ 5፥4
ከሥነ ተዋልዶ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የሰውነት ክፍሎች፣ ፆታ ነክ ተግባራትን፣ ፆታ ነክ ውይይቶችን ማየት መስማት፣ ማውራትና ማከናወን በሕግ በሥርዓት፤ ዘልክና በፈሊጥ መሆን አለበት፡፡ እነዚህ ነገሮች ከማፈር ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት አላቸው:: የእነዚህ ነገሮች በሙሉ ጌጣቸው ማፈር ነው።ማፈር የሌለበት የሥነ ተዋልዶ አካል እንደ አሻንጉሊት አካል ነው፡፡ ምነው? ቢባል ግብረ ነፍስ የለበትምና ስለዚህ ነው:: ማፈር ደግሞ የለባዊት ነፍስ ጠባይ እንጂ የሥጋ መታወቂያ አይደለምና፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ማፈር አለማፈርን በቀጥታ ከአለባበስ ጋር አያይዞ ገልጾታል:: «እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ::»1ጢሞ2÷10 አንቺ ወጣት «በሚገባ ልብስ›› በማለቱ የሚገባና የማይገባ ልብስ እንዳለ ሐዋርያው መናገሩን አስተዋልሽን? ራስሽን መሸለም (ማስጌጥ) ከወደድሽም እንደ ሐዋርያው ምክር «ከእፍረት» ጋር አድርጊው ያለ እፍረት ብታጌጪ ጌጥሽ ጌጥ አይሆንም፡፡ ታላቁ ጌጥ ‹‹ኀፊረ ገጽ» ነውና፡፡

ቀጣይ ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ክፍል ሦስት :
👉 «ስኬታማነት» በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መልካም ስም ያለውን ጠቀሜታ ለመረዳት ቀላል ነው።እንኳን በብዙ አቅጣጫ ብዙ መልካም ስም ኖሮህ ይቅርና «እገሌ ታማኝና እውነተኛ ነው» በሚል ስም ብቻ ብትታወቅ ብዙ ጥቅሞች ይከቡሃል፡፡ ለምሳሌ፦ እውነተኛ ሰው በብዙዎች ዘንድ ታማኝነትና አክብሮትን ያተርፋል:: የሚያገኛቸው ወዳጆቹ እውነተኝነቱን አድንቀውና ወደው የሚቀርቡ በመሆናቸው አብዛኞቹ ራሳቸው እውነተኞች መሆናቸው የማይቀር ነውና፥ እውነተኛ በመሆንህ እውነተኞች ጓደኞችን እንድታገኝ ረዳህ ማለት ነው።ይህ ደግሞ ታላቅ ትርፍ ነው።የሰው ሁሉ ችግር ታማኝ ባልንጀራ ማፍራት አለመቻል ነውና።
ከዚህም ሌላ በመልካም ስም መታወቅ ሌላም የሚያስገኘው ጥቅም አለ፡፡ የንግዱ ዓለም ብዙ ማጭበርበር ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ሆኖም አሠሪዎችና ሠራተኛ ቀጣሪዎች ለታማኝነት ከፍ ያለ ዋጋ ሰጥተው እውነተኞችንና ታማኞችን መቅጠር ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ አንተ በታማኝነት መታወቅህ ብቻ በሥራ ችሎታ ብዙ የሚበልጡህ ሰዎች ቢኖሩም እንኳን ሥራ የማግኘትና ሌሎች ከሥራ በሚባረሩበትም አጋጣሚ በሥራህ የመቆየት ዕድል ይገጥምሃል፡፡ ይህም «ታማኝ» የሚል መልካም ስም ማትረፍ ብቻ ምን ያህል እንደሚጠቅም ያስረዳል።
ባልና ሚስት በታማኝነት የሚተዋወቁ ከሆነ ጥርጣሬንና አለመተማመንን አስወግደው በፍቅር ለመኖር ይረዳቸዋል። ታማኝ ልጆችም በወላጆቻቸው ዘንድ ሙሉ አመኔታን ያተርፋሉ፡፡ ልጆች በወላጆች ዘንድ «ታማኝ» በሚል መልካም ስም ከታወቁ ቀስ በቀስ ሰፊ ነፃነት እያገኙ ይመጣሉ።እውነቱን መናገር ተግሣጽን እንኳን ቀላል የሚያደርግበት ሁኔታ አለ፡፡ አንድ ታዳጊ አጥፍቶ በሚቀጣበት ጊዜ ቢክድ የቅጣቱ መጠን ሊጨምር ይችላል፡፡ ቢያምንና ይቅርታ ቢጠይቅ ግን ቅጣቱ ይቀልለታል፡፡ በወኅኒ ቤትም ሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ቢሆን ሐቁ ይህ ነው።
ሰው ሁሉ በሕይወት ዘመኑ ሌሎች እንዲያምኑትና ቃሉን እንዲቀበሉት በብርቱ የሚፈልግበት አንድ አጋጣሚ ሳይመጣበት አይቀርም፡፡ ታማኝ የሚል ስም ያለው ሰው በዚህ ሁሉ ሳይቸገር ነገሩን ሌሎች በቀላሉ ሊያምኑለት ይችላሉ፡፡ በአጠቃላይ «ታማኝ»የሚል መልካም ስም ያተረፈ አንድ ሰው ተዘርዝረው የማያልቁ ብዙ ጥቅሞችን ያገኛል፡፡
ከላይ የተጠቀሰው ስለ «ታማኝነት» ብቻ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ሐቀኛ፣ የተከበረ፣ ጨዋ፣ ሰው አክባሪ፣ ቁጥብ፣ ቁም ነገረኛ፣ ዐዋቂ፣ ትሑት፣ የሚሉ ሌሎች መልካም ስሞችን ብታተርፍ ምን ያህል በነፍስና በሥጋ እንደምትጠቀም ገምት። እነዚህ ነገሮች ያሉት ለሥራ፣ ለጓደኝነት፣ ለትዳር በአጠቃላይ ለሁሉም ጉዳይ በመብራት እንደሚፈለግ ጥርጥር አይኑርህ።
መልካም ስም እንዲሁ በቀላሉ አይገነባም። ብዙ ድካምና ጥረት ከመጠየቁም ሌላ ብዙ ጊዜ ይወስዳል። የሚያስደንቀው ግን ጥሩ ስም ሲበላሽ ምንም ጊዜ አለመፈለጉ ነው።ስለዚህ መልካም ስምን እንደ ዓይን ብሌን ሊጠነቀቁለት ይገባል። መልካም ስም ገንዘብ፣ የትምህረት ደረጃ ወይም ሌላ መስፈርት ኣይጠይቅም።ፈቀደኛ ከሆንክ የነፍስህ ዕውቀት ብቻ መልካም ስም እንዲኖርህ ለምትሠራው ሥራ ሁሉ በቂ ናት፡፡
የመልካም ስምን ጠቀሜታ መዘርዘር በአንፃሩ የመጥፎ ስምን ጉዳት መዘርዘር ነው።በመጥፎ ስም ከታወቅህ የእናትህ ልጅ እንኳን አያቀርብህም። ስለዚህ በስካራምነት፣ በቅብጠት፣ በአባካኝነት፣ በውሸት፣ በቀልድና በመዘበት፣ በመልከስከስ፣ በገንዘብ ወዳድነት፣ በትዕቢት፣ በክህደት፣ በስሜታዊነት፣ በተናጋሪነትና በመሳሰሉት መጥፎ ስሞች እንዳትታወቅ ተጠንቀቅ። በገዛ እጅህ ሁሉ ነገር ርቆብህ ቁጭ ብለህ የምታለቅስበትን የኀዘን ገመድ ለምን ትጎትታለህ?
ወጣት ከሆንክ መጥፎ የተባሉትን ነገሮች ለመላቀቅ አልቻልኩም አትበል፡፡ አስቀድሞ እንደተገለጠው መጥፎና ጥሩ ነገር የሚወስዱት ጊዜ የተለያየ ነው። ከክፉ ጠባዬ ብታረምም ተቀባይነት ግን አላገኘሁም በማለት ተስፋ መቁረጥ አይገባም።ይህ ሁሉ የመጀመሪያ ክፉ ሥራህ ደሞዝ እንደሆነ አምነህ ራስህን እየወቀስህ ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ ተቀባይነት ለማምጣት ተጣጣር እንጂ ወደ ኋላህ አትመለስ።መቼም ቢሆን «ከመልካም ሽቶ መልካም ስም» ይሻላልና፡፡መክ7፥1
አንተ ጥሩ የትምህርት ደረጃና ሙያ ይዘህ ሥራ አጥተህ ስተቀመጥ መልካም ስም የያዙ ሌሎች ያለምንም ማስረጃና የሥራ ልምድ የምትቀናበትን ሥራ ሲሠሩ አይተህ አታውቅምን? ይህ አገላለጽ ትምህርትና ዕውቀትን ለማቃለል ሳይሆን የመልካም ስምን ታላቅነት ለማጉላት ነው። በትምህርትና በሥራ ልምድህ ላይ የመልካም ሥነ ምግባር ባለቤት መሆንህ ከተነገረ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመትም አያስቸግርም።
የመልካም ስም ቁልፉ መንፈሳዊነት ነው።ትምህርተ ሃይማኖትና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ሰው በሥነ ምግባር መታነፁና የመልካም ስም ባለቤት መሆኑ አያጠራጥርም።የዚህ ዓለም ምስኪን ማለት መንፈሳዊ ተብሎ መልካም ስም የሌለው ነው።መልካም ስም እንዲኖርህ ትፈልጋለህ? ታዲያ ገጸ ልቡናህን ወደ ፈጣሪህ ለምን አትመልስም?

ቀጣይ ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ክፍል ኹለት :
👉 «ኀፊረ ገጽ» በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ውድ የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች ቻናል ተከታታዮች :
ከወደ ምስራቅ (ድሬ) ወንድሞች አግዘውት ከፕሮቴስታንቱ ዓለም ወደ ክርስትና የተመለሰ አንድ ወንድማችን ነበር : ክርስቲያን ከሆነ በኋላ ራቅ ካለ ቦታ ወንድሞች ወዳሉበት ወደ ድሬ ስለመጣ እነርሱ እያገዙት የቤት ኪራይም የት/ቤት ክፍያም የእለት ጉርስም እያብቃቃ ነበር የኖረው። አሁን ግን ጊዜው እንደሚታወቀው ለመኖር ከባድ ነውና ነገሩ ከአቅሙ በላይ ሆኖ መማርም አልቻለም፤ለምግብም እስከመቸገር ደርሷል።

ብንችልና አቅሙ ቢኖረን ቋሚ የሆነ ራሱን የሚለውጥበት ነገር ብናደርግ መልካም ነበር ቢያንስ ግን ለአሁኑ የት/ት፣ የቤት ኪራይ ወጪውን ከዕለት ጉርሱ ጋር የምትሞላለት ነገር ብንተባበረው አግዙን ብለን መጥተናል።🤲

በዚህኛው ጾም የአንድ ክርስቲያን ወንድማችንን ጭንቀት በማቅለል ጥቂት በረከት ብንካፈል መልካም ነውና መቶም ሁለት መቶም አንድ ሺህም ብትሆን በቅዱሳን ሐዋርያት ስም በልጁ አካውንት እናስገባለት።🙏

CBE 1000267371044
በረከት ግርማ ቱፋ

(በባንክ አስገብታችሁ ደረሰኝና የክርስትና ስማችሁን በ @Ethiopian_Orthodox_bot በኩል አድርሱን🤲)

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ረ ሊያጠፋው ምክንያት ይፈልግበት ነበር፡፡ ለዐፄ ገብረ ማርያም በእናትም በአባትም እኅት የምትሆነው ለላሊበላ ግን በአባት ብቻ እኅት የሆነችው ዮዲት ላሊበላን ለመግደል በማሰብ ቀን ከሌሊት አጋጣሚን ትጠብቅ ነበር፡፡ ቅዱስ ላሊበላም ጌታችን መራራ ሐሞት መጠጣቱንም እያሰበ ሁልጊዜ ዓርብ ዓርብ ከጾምና ጸሎት በኋላ መራራ ኮሶ ይጠጣ ነበርና ይህን አጋጣሚ በመጠቀም አንድ ቀን እንደጠማው አውቃ በጠላ ውስጥ መርዝ ጨምራ ሰጠችው፤ ቅዱስ ላሊበላም መርዝ የተቀላቀለበትን ጠላ ጠጣው፡፡ እርሱ ከመጠጣቱ በፊት ያገለግለው የነበረው ዲያቆን ቀምሶት ወዲያው ሲሞት አየ፡፡ ዲያቆኑ ያስመለሰውን የጠጣው ውሻም ወዲያው ሞተ፡፡ ቅዱስ ላሊበላም ይህን ሲመለከት በሐዘንና በፍጹም ፍቅር ሆኖ ‹‹አገልጋዬ ለእኔ የተዘጋጀውን መርዝ ጠጥቶ እንደሞተ ሁሉ እኔም መሞት ይገባኛል›› በማለት ያን መርዝ ስለወዳጁ ፍቅር ሲል ጠጥቶ ለመሞት ቆረጠና ጠጣው፡፡ ጌታችን በወንጌሉ ስለራሱ ‹‹ስለ በጐቹ ቤዛ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ የሚሠጥ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም›› (ዮሐ 15፡13) ብሎ የተናገረውን ቃል ቅዱስ ላሊበላም ስለ ወዳጁ ሞት ሲል ራሱን ለሞት አሳልፎ ሰጠ፡፡ ነገር ግን መርዙ እንኳን ሊጎዳው ይቅርና በሆዱ ውስጥ ከልጅነቱ ጀምሮ የነበረበትን የሆድ ሕመም ነቅሎ አወጣለት፡፡ በዚህም ጌታችን በወንጌሉ ‹‹የሚገድል መርዝም ብትጠጡ ምንም አትሆኑም›› (ማር 16፡18) ያለው ቃል ተፈጽሞለታል፡፡ መርዙ ለበጐ ሆኖለት ከሆዱም ውስጥ የነበረው ጥፍሮች ያሉት አውሬ መሰል ፍጡር ወጣለትና የሆድ ሕማሙ ፈጽሞ ተወው፡፡ ያን ጊዜም ቅዱስ ላሊበላ በወቅቱ ለሦስት ቀንም ያህል እንደሞተ ሆኖ የቆየ ቢመስልም ቅዱስ ገብርኤል ግን በመንፈስ ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ ሰባቱ ሰማያትን ያሳየው ሲሆን በጌታችን ፊትም አቅርቦት አስባርኮታል፡፡ ጌታችንም ቅብዓ መንግሥት ቀብቶት ትልቅ ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡
ጻዲቁ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ ቅድስናን ከንግሥና፣ ክህነትን ከንጽሕና፣ ጥበብ መንፈሳዊን ከጥበብ ሥጋዊ ጋር አንድ አድርጐ አስተባብሮ የያዘ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ፣ ቅዱሳን መላእክትም ይራዱት እንደነበርና ጌታችንም ትልቅ ቃልኪዳን እንደሰጠው ከቅዱስ ገድሉ ላይ እናገኛለን፡፡ ከጌታችን ዘንድ የተሰጠውንም ቃልኪዳን በሦስት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ በዚህም መሠረት፡-
1ኛ. መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን እየመራው ከላስታ ወደ አክሱም ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም አድርሶ በዚያ የሚገኙትን ቅዱሳት መካናት ሁሉንም ካሳየው በኋላ ‹‹ወደ ሀገርህ ሮሐ ተመልሰህ በእነዚህ ምሳሌ ታንጻለህ›› ብሎታል፡፡ ወደ ሀገሩም ተመልሶ በአሽተን ማርያም ተራራ ላይ ሱባኤ ይዞ በጾም ጸሎት ተወስኖ ሳለ እግዚአብሔር የሚሠራቸውን መቅደሶች በግልጽ በራእይ አሳይቶታል፡፡

2ኛ. ከላይ እንዳየነው ለሞት ተብሎ የተሰጠው መርዝ ለሕይወት ሆኖለት በመሬት ላይ ወድቆ ሳለ በነፍስ መልአክ ነጥቆት እስከ ሰባተኛው ሰማይ ጽርሐ አርያም ድረስ ደርሶ በጌታ ፊት ቀርቦ ከጌታ ዘንድ ‹‹እኔ አከበርኩህ ቃሌ አይታበይም፣ ከአንድ ቋጥኝ እነዚያን በራእይ ያሳየሁህን አብያተ ክርስቲያናት ታንጻለህ›› የሚል ቃልኪዳን ተቀብሏል፡፡

3ኛ. ከኢየሩሳሌምም ተመልሶ የንግሥናውን ዙፋን ከቅዱስ ገብረ ማርያም ከተረከበ በኋላ በተሰጠው መንፈሳዊ ሀብትና ባየው ራእይ መሠረት አብያተ ክርስቲያናቱን አንጾ ከጨረሰ በኋላ በቀኝና በግራው ዓሥር ዓሥር ኪሎ የሚመዝን የዓለት ድንጋይ ተሸክሞ ለ7 ዓመት ሲጾም ሲጸልይ ጌታችን ተገልጦለት ‹‹…ያነጽካቸውን ቤተ መቅደሶች የተሳለመውን ኢየሩሳሌምን እንደተሳለመ አድርግለታለሁ›› የሚለውን የመጨረሻውን ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡ (ይህን ቃልኪዳኑን መጨረሻ ላይ በዝርዝር እናየዋለን) እነዚህን ሦስት ዋና ዋና ቃልኪዳኖቹን በቅድሚያ ማንሳት የፈለኩበት ምክንያት ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ስለ ቅዱስ ላሊበላ ድንቅ ሥራዎች ከማሰባችንም ሆነ ከመናገችን በፊት በቅድሚያ ስለ ራሱ ስለ ቅዱስ ላሊበላ የቅድስና ሕይወቱና ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ግንኙነት ማወቁ የግድ አስፈላጊ መሆኑን ለመጠቆም ነው፡፡ አሁን አሁን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሆን ተብሎ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ውቅር አብያተ ክርስቲያናቶቹ በቱሪስት መስህብነታቸው ብቻ እየታዩ የቅድስና ታሪካችንም እየተጨፈለቀና መንፈሳዊ እሴቶቻችንንም ለማጥፋትም ጥረት እየተደረገ ስለሆነ እውነተኛውን ነገር በደንብ ማወቅና በእጅጉ መጠንቀቅ ስላለብን ነው ይህን የማነሳው፡፡ ስለዚህ የቅዱስ ላለበላን የቅድስና ሕይወትና ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ግንኙነት ስንረዳ እነዚያ እጅግ ድንቅ የሆኑ ሥራዎቹ በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና በሰማያውያን መላእክት እርዳታ የተሠሩ መሆናቸውን እንረዳለን፤ እግዚአብሔርም ለእኛ የሰጠንን ድንቅ የምሕረትና የቃልኪዳን ስጦታዎቻችን መሆናቸውን እንረዳለን፡፡ ያንጊዜም ውቅር አብያተ ክርስቲያናቶቹን ዓለም ከሚመለከትበት የተለየ መንፈሳዊ ዐይን ይኖረናል፡፡ የቃልኪዳኑም ተጠቃሚዎች ለመሆን መንፈሳችን ይነሳሳል፡፡ በዚህ ደግሞ አሁን ያለውም ሆነ ወደፊት የሚመጣው ትውልድ ታሪኩን ከማጉደፍና ከጥፋት ይጠበቃል፣ አኩሪ ታሪኩንም ጠንቅቆ ለማወቅ መንፈሳዊ ቅናትም ስለሚያድርበት ራሱንም ከውጪው የባሕል ወረራና ጥቃት ይጠብቃል፡፡ በሀገራችን ያሉትን እጅግ ጥልቅ የሆኑ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ምሥጢሮችን ጠንቅቀው የተረዱት እነ ፕሮፌሰር ፓንክረስት ‹‹ክርስቶስ ከነጮች ይልቅ ለኢትዮጵያውያን ቅርበት አለው›› በማለት ምስክርነታቸውን እየሰጡ ባለበት ወቅት የዘመኑ የሀገራችን ወጣት ማንነቱን ጠንቅቆ ቢያውቀው ኖሮ የእነርሱን (የነጮቹን) ባሕል ለመከተል ባልዳዳው ከዘመናዊ ባርነትም ራሱን በጠበቀ ነበር፡፡

4.መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለቅዱስ ላሊበላ ስለ ቤተመቅደሶቹ አሠራር በዝርዝር እንዳስረዳው፡- በተራ ቁጥር ሁለት ላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በቅዱስ ገድሉ ላይ ከገጽ 117-127 ድረስ በጣም በስፋትና በዝርዝር እንደተጠቀሰው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ላሊበላን እስከ ሰባተኛው ሰማይ ድረስ በመላእክት ተነጥቆ በፊቱ እንዲቆም ካደረገው በኋላ ቤተ መቅደሶቹን እንዴት እንደሚያንጽ ቃል በቃል ነግሮታል፡፡ እግዚአብሔር ለኖህ መርከቡን እንዴት እንደሚሠራ ከነልኬቱ ጭምር በዝርዝር እንደነገረው ሁሉ ለቅዱስ ላሊበላም ዝርዝር ሁኔታዎችን ጭምር እንዲህ በማለት ትእዛዝ ሰጥቶታል፡- ‹‹መልአኩም ክብሩ ከሰማያት ሁሉ ክብር ወደሚበልጥ ወደ ሰባተኛው ሰማይ አደረሰው፣ ቅዱስ ላሊበላም ይህንን አይቶ በግንባሩ ተደፋ፣ ከኪሩቤል ዘንድ ይነሳ የሚል ቃል ተሰማና አንዱ ሱራፌል መጥቶ አነሣው፡፡ ልቡንም አጽንቶ አቆመው…እግዚአብሔርም ተናገረው፡- ‹በምድር ላይ ቤተመቅደስ ትሠራልኝ ዘንድ የማሳይህን አስተውል፤ እዝነ ልቡናህንም ግለጥ፡፡ ከሰው ጋር ስለምኖር በሰማያት የምትኖር አባታችን እያሉ ከሚጠሩኝ በሃይማኖት ከተጐናፀፈኝ ስሜን ከሚያመሰግኑ ከመረጥኳቸው ከሕዝብ አንደበት በምመሰገንበት ገንዘብ እኔ ፈጥሬያቸዋለሁና፡፡

ከመጀመሪያይቱ ድንኳን ውስጥ በተሣለው ላይ ምስላቸው የተሠራ ከሚንቀሳቀሱ ከኪሩቤል አምሳል ለሙሴ እንደተናገርኩት አይደለም፡፡ ወዳጄ ሙሴ የመጀመሪያይቱን ድንኳን አርአያ በደብረ ሲና እንዳሳየሁት ድንኳንን እንደሠራ ሁሉ እንደሁ አንተም እንዳሳየሁህ ትሠራ ዘንድ ዕወቅ፣ አስተውል፣ ተጠንቀቅም፡፡ የማሳይህ ግን ለሙሴ እንዳሳየሁት አይደለም፤ መቅደሴን የምትሠራልኝም ሙሴ እንደሠራው አይደለም፤ ሙሴስ ከተፈተለ ልብስና ከእንጨት ድንኳን ሠራ፤ አንተ ግን ለምሰሶውም ሆነ ለመቀኑ ለመድረኩ እንጨትን

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ነዋ ሚካኤል መልአከ ክሙ
ይስአል ለክሙ በእንተ ምሕረት
በዘማሪት መቅደስ ከበደ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ እነርሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እርሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡

በሰኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡ ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና "የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?" በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡ ለጊዜው "በእኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም" ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእርሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ በመቀጠልም ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ሰይጣናዊ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን "ድረስልኝ" እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሰኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡

ምልጣን ዘሰኔ ሚካኤል
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ፤
ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ፤
ፀሐይ ፀልመ ወወርኅ ደመ ኮነ፤
ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኵሉ፤

ትርጉም

አይሁድ ጌታችንን በሰቀሉት ጊዜ
ሚካኤል ዝም አለ ገብርኤልም ተደነቀ
ፀሐይ ጨለመ ጨረቃ ደም ኾነ
ከመስቀሉ ወርዶ ለኹሉ አበራ።
ቅዱስ ያሬድ

ከበዓሉ በረከትን ያሳትፈን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሰኔ ፲፪
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል አፎምያን ያዳነበት ዕለት ነው፡፡ ዳገመኛም ይኽች ዕለት የባሕራንን የሞት ደብዳቤ ቀዶ እርሱን ለታላቅ ክብር ያበቃባት ዕለት ናት፡፡

ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ' ካ-ከመ' ኤል- አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ መኑ ከመ አምላክ (እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው) ማለት ነው፡፡ አንድም ለእግዚአብሔር አሸናፊ ድል አድራጊ የቸርነትና የርህራሄ መገኛ መዝገብ ማለት ነው፡፡

ይህ ታላቅ መልአክ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራዕዩ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ›› ብሎ ከተናገረላቸው መላእክት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን የሰባቱም ሊቃነ መላእክት አለቃ እንዲሆን እግዚአብሔር መርጦ ሹሞታል፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ያደረጋቸው የሠራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ ተአምራት አሉት፡፡ ስለዚህ ስለ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፤ ጠባቂነትና አማላጅነት ከአባቶቻቸው የተማሩትን በኑሮአቸው ያዩትን አባቶቻችን ጽፈዋል፡፡ ስለ ቅዱስ ሚካኤል ከጻፉት አባቶች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያክል፡- ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ኤዎስጣቴዎስ ዘአንፆኪያ፣ ቅዱስ መቃርዮስ፣ ቅዱስ ያሬድ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እና የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አባዲማቴዎስ ናቸው፡፡ እኛም የአባቶቻችንን አንደበት አንደበታችን አድርገን በኅዳር ፲፪ ክቡር ገናና የሆነ ቅዱስ ሚካኤል ካደረጋቸውና ከሠራቸው ብዙ ተአምራት ውስጥ የተወሰኑትን በመልአኩ ተረዳኢነት እንዲህ ብለን እንናገራለን አንጽፋለን፡፡
ጥንተ ነገሩ እንዲህ ነው፡- ንግስት ክሌዎፓትራ ‹‹ሳተርን›› ለሚባለው ጣዖት የሠራችው ቤተ ጣዖት በእስክንድርያ ነበር፡፡ ይህ ቤተ ጣዖት እስከ እስክንድርያው ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ /፫፻፲፪ - ፫፻፳፮/ ዘመን ድረስ ነበር፡፡ እለ እስክንድሮስ ሊያጠፋው ሲነሣ ሕዝቡ ከልቡ ገና የአምልኮ ጣዖት ስላልጣፋ "፲፰ ፓትርያርኮች ያልነኩትን አንተ ለምን ታፈርስብናለህ?" ብለው ተቃወሙት፡፡ እለ እስክንድሮስም ሕዝቡን መክሮና አስተምሮ የሳተርን በዓል ይውልበት በነበረው ዕለት የቅዱስ ሚካኤልን በዓል እንዲያከብሩ አውጆ ቤተ ጣዖቱንም በቅዱስ ሚካኤል ስም ሰይሞ ቤተክርስቲያን አደረገው፡፡

ሕዝቡ በየዓመቱ መሥዋዕት እየሠው ተረፈ መሥዋዕቱን እየተመገቡ እየዘፈኑ እያጨበጨቡ ያከብሩ ነበር፡፡ ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ቁስጠንጢኖስ "አብያተ ጣዖታት ይዘጉ አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ" ብሎ ካወጀ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት እለ እስክንድሮስ ቤተ ጣዖቱን አፍርሶ ከቦታው ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ታቦተ ሚካኤልን አግብቶ በዓሉን በደስታ በሐሴት አሳለፉት፡፡ እለ እስክንድሮስም ሕዝቡን የጣዖቱን በዓል ተው "ይህን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል አክብሩ" ብሎ በየዓመቱ በዚህ ቀን በዓል እንዲሆን ሥርዓት ሠራላቸው፡፡ ይህንንም የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ከሚያከብሩ ምእመናንን አንዱ የባሕራን አባት ነበር፡፡
እርሱም እግዚአብሔርን እጅግ አድርጐ የሚፈራ ወር በገባ በየዐሥራ ሁለቱ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን የሚዘክርና ይልቁንም በኅዳር ዓሥራ ሁለትና በሰኔ ዓሥራ ሁለት ቀን በታላቅ ክብር የሚያከብር አንድ ሰው ነበር። ለዚህ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰውም ርኅራኄ የሌለው በእርሱም ላይ ጥላቻ ያደረበት አንድ በለጸጋ ጐረቤት ነበረው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በሚያከብርበት ጊዜ ሁሉ ይዘብትበት ይሳለቅበት ነበር። ይህ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ሰውዬ በዚህ ዓይነት በጐ ሥራ ብዙ ጊዜ ከኖረ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ያርፍ ዘንድ የሞቱ ጊዜ ቀረበ። ሚስቱንም ጠርቶ "በጐ ስራ ከመሥራት ለድኃ ከመመጽወት ቸል አትበይ የቅዱስ ሚካኤልንም በዓል በየወሩ ከማክበር አትቦዝኝ ይልቁንም በኅዳር ዓሥራ ሁለትና በሰኔ ዓሥራ ሁለት ቀን ከፍ ባለ ሥነ ሥርዓት እንድታከብሪ አደራ እልሻለው" አላት፡፡ በሚሞትበትም ጊዜ ሚስቱ ፀንሳ ነበር። ይህም ደገኛ ሰው በሰላም ዐረፈና ፍጹም መንግሥተ ሰማያትን ወረሰ።

ከዚህም በኋላ ሚስቱ የመውለጃዋ ጊዜ ተቃርቦ ነበርና ምጥ ይዟት በታላቅ ጭንቅ ላይ እንዳለች "አንተ የእግዚአብሔር መልአክ ሆይ በእኔ ላይ ይቅርታን አውርድ ከዝህ ከደረሰብኝም ጭንቅ ይገላግለኝ ዘንድ ስለኔ እግዚአብሔርን ለምንልኝ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ባለሟልነት ተሰጥቶሃልና" እያለች ለመነች። ይህንንም በምትልበት ጊዜ ያለችበት ቤት በብርሃን ተመላ ከጭንቋም ዳነችና መልኩ በጣም ያማረ ልጅ ወለደች። የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ያን ሕፃን ባረከውና "ቸርነት ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለጸጋ ገንዘብና ሀብት እርሻውንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዟል" አለ። ያን ጊዜ ያ ባለጸጋ በሴትዮዋ ቤት መስኮት አጠገብ ሆኖ ሁኔታውን ሁሉ ይመለከት ነበርና ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ልቡ በታላቅ ኅዘን ተነካ፤ ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ብላቴናውን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀው ነበር።

ብላቴናውም ዓሥር ዓመት በሆነው ጊዜ እናቱ በጣም ችግር ፀናባት፡፡ በዚህን ጊዜ እምነት የጐደለው ያ ባለጸጋ "አንቺ ችግረኛ ስለሆንሽ ይላከኝ ያገለግለኝ ዘንድ ልጅሽን ስጭኝና ምግቡንና ልብሱን ምንም ሳላጐድል ተንከባክቤ አኖረዋለው ለአንቺም ሃያ ወቄት ወርቅ እሰጥሻለው" አላት። ይህንንም ባላት ጊዜ ስለ ችግሯ በጣም በመደሰት ልጅዋን ሰጠችውና ሃያውን ወቄት ወርቅ ተቀበለች፡፡ ብላቴናውንም በወሰደ ጊዜ እንግዲህ ሃሳቤ ሁሉ ዛሬ ተፈጸመልኝ እያለ በጣም ደስታ ተሰማው፡፡ ከዚህ በኋላ በልጅ ቁመት ልክ ሳጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሣጥኑ ውስጥ አግብቶ በላዩ ላይ ቆለፈበትና ሣጥኑን ወስዶ ከባሕር ጨመረው፤ እንዲሁም የሣጥኑን ቁልፍ መክፈቻ አብሮ ወረወረው። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሰጥም በባሕሩ ላይ እየተንሳፈፈ ከዚያች አገር ርቃ ወደምትገኝ የባሕር ወደብ ደረሰ።
በባሕሩ አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበርና ያንን ሣጥን ባየው ጊዜ ከባሕሩ አወጣውና ወደ ቤቱ ወሰደው። እቤቱም በደረሰ ጊዜ "ይህን ሣጥን በምን እከፍተዋለሁ?" እያለ ሲያወጣ ሲያወርድ ተመልሶ ወደ ባሕሩ ይሄድ ዘንድ እግዚአብሔር አሳሰበው፤ በሄደም ጊዜ አንድ ዓሣ የሚያጠምድ ሰው አገኘና ዓሣ አጥማጁን "በኔ ስም መረብህን ወደ በሕር ጣልና የተሠገረው ዓሣ ለኔ ይሆናል ዋጋውን ግን እከፍልሃለው" አለው፡፡ ዓሣ አሥጋሪውም እንደ ተነጋገሩት መረብን ከባሕር ቢጥል ታላቅ ዓሣ ተያዘና ለሰውየው ሰጥቶት ዋጋውን ተቀበለ። እሱም ያንን ዓሣ ከቤተሰቦቹ ጋር ጠብሶ ይበላ ዘንድ በችኮላ ወደ ቤቱ ሄደና ያሣውን ሆድ ቢሰነጥቀው የዚያን የሣጥን ቁልፍ መክፈቻ አገኘ፡፡ በዚያን ጊዜ ይህ መክፈቻ የዚህ ሣጥን ቁልፍ መክፈቻ መሆን አለበት ሲል አሰበና ቁልፉን ለመክፈት ቢሞክር ወለል ብሎ ተከፈተ። በዚህም እየተደነቀ ሳለ ሣጥኑን ቢከፍተው ያ ባለ ፀጋ ሊገድለው ያሰበውን ሕፃን በሣጥኑ ውስጥ አገኘው። ባየውም ጊዜ እጅግ ተደስቶ በባሕር ውስጥ ስላገኘው ስሙን "ባሕራን" ብሎ ሰየመውና እንደ ልጁ አድርጐ ይንከባከበው ዘንድ ወሰነ፡፡
ከባሕራን ሀገር የበግ ጠባቂው አገር የዓሥር ቀን ጐዳና የሚያስኬድ ርቀት ነበረው። ከብዙ ዓመታት በኋላ ያ ባለ ጸጋ ሰው ለንግድ ከሀገሩ ወጣ፡፡ በጉዞውም ላይ ሳለ ፀሐይ ስትገባ ከዚያ የበግ ጠባቂው ዘንድ ደረሰ። በግ ጠባቂውንም "ወንድሜ ሆይ ባንተ ዘንድ የማድርበት ቢኖር ታሳድረኝ ዘንድ እለምንሃለው፣ ኪራዩንም እከፍልሃለው" ብሎ ጠየቀውና ያ በግ ጠባቂ ወደ ቤቱ አስገባው። ባለጸጋውም ገብቶ ጥቂት ካረ

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጠቃሚ ነገር በልክ ተምሮ መሥራት ነው፡፡ ብዙ ተምረው ምንም ሳይሠሩ ሕይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቁጥር ጥቂት አይደለም፡፡ ስለዚህ ትምህርትን መመጠን ነገር ግን ሥራን ማብዛት ይገባል፡ ጠቢቡ ሰሎሞን «ብዙ መጻሕፍትን ማድረግ ፍጻሜ የለውም ፥ እጅግም ምርምር ሰውነትን ያደክማል›› በማለት የተናገረው ሰው የሚጠቀመው ብዙ በመማሩ ሳይሆን በልክ ተምሮ ብዙ ሲሠራ መሆኑን ለመጠቆም ብሎ ነው፡፡ መክ12፥12 በተጨማሪም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በልክ ስለመኖር የሰጠው ምክር በልክ ስለ መማርም ሊጠቀስ ይችላል፡፡ 2ጢም4፥5
መንፈሳዊያን ሰዎች መንፈሳዊ ትምህርት ቤትን እንደ መካነ ገድል (ገድል መፈጸሚያ ቦታ) በመቁጠር መላ ዘመናቸውን በትምህርት ቤት ለማሳለፍ ይወስናሉ፡፡ ይህ ድርጊት የዓለምን ጥቀርሻ ሳይቀቡና ከዓለም ምንም ሳይፈልጉ ለመኖር የሚወሰን የምናኔ ኑሮ በመሆኑ ጊዜን እንደ ማባከን አይቆጠርም፡፡ ታውቆ የተወሰነ ውሳኔ በመሆኑም ምንም ዓይነት ጸጸት አያስከትልም፡
ሆኖም እንዲህ ያለ የምናኔ ሐሳብ የሌላቸው ሰዎች በመንፈሳዊ ትምህርትም ላይ ቢሆን ያለ አግባብ ጊዜ ማጥፋት የለባቸውም፡፡ ብዙ ተምሮ ምንም ሳያገለግሉ፣ የሚሹትንም ሳያገኙ እየተቆጩጬ ኖረው ከመሞት በመጠኑ ተምሮ የተማሩትንም በአግባቡ ተጠቅመውበት ማለፍ ይመረጣል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሕይወት የሚገኝበትን ጥልቅ መንፈሳዊ ትምህርቷን ለሰው ሁሉ እንዲዳረስ የበለጠ ጥረት ማድረግ አለባት።
እግረ መንገዴንም ሳልጠቁም የማላልፈው ነገር ቢኖር የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ቢያስቡበት ሰፋ ያለ ጊዜ የሚጠይቁት የንባብ፣የቅዳሴ፣ የዜማ፣ የአቋቋም፣ የቅኔና የመጻሕፍት ትርጓሜ ትምህርቶቿ አሁን ከሚወስዱት እጅግ በጣም ባነሰ ጊዜ ውስጥ መጠቃለል የሚችሉ መሆናቸውን ነው፡፡እስከሚሆን ድረስ ደግሞ የመንፈሳዊ ትምህርት ጥማት ያለባቸው ምእመናን ሁኔታዎች እስከ ፈቀዱላቸው ድረስ በግላቸውም ቢሆን እንኳን ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን ከማጥናት መቦዘን የለባቸውምደ
2) ሰው ምንም ቢማር ራሱን እንደ አዋቂ መቁጠር አይገባውም፡፡ አዋቂ እንደ ሆነ የሚሰማው ሰው በትዕቢት ይይዛል፡፡ «ማንም አንዳች ያወቀ ቢመስለው ሊያወቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም።» 1ቆሮ8፥2 በማለት ቅዱስ ጳውሎስ ተናግሯል፡፡ መታወቅ ያለበትን ትህትናን ሳያውቃት ሰው አዋቂ ሊባል አይችልም፡፡ ትሕትና ደግሞ አዋቂ ነኝ አታሰኝም። በዚህ ዓለም ካሉት ነገሮች ከቁጥር የማይገባን ጥቂት ነገር አውቆ አዋቂ ነኝ ማለት እጅግ የሚያሳፍር ነው፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «ዕውቀት ያስታብያል» 1ቆሮ8÷2 በማለት እንደተናገረው ዕውቀት ሲያስታብይ ፍቅር ግን ያንጻል፡፡ከዕውቀት ፍቅር በብዙ ይበልጣል፡፡ስለዚህ አንተ ብዙ ዕውቀት ቢኖርህ ትንሽ ፍቅር ያለው ሰው ይበልጥሃልና መታበይ አይገባህም፡፡
ሰው ሁሉ ከትዕቢት ለመዳን ያወቀውን ዕውቀት ከሌሎች ሰዎች እንዳገኘውና በዕውቀት ከርሱ የተሻሉ በርካታ ሰዎች እንዳሉ ቢያስብ በጣም ይጠቀማል። ከዚህም በላይ ዕውቀትን እንደ ገበቴ ውኃ ማፍሰስ (ማጥፋት) የሚቻለው ፈጣሪም እንዳለ ባይዘነጋ ጥሩ ነው፡፡ ከአንተ አስቀድሞ የነበሩ ብዙ አዋቂዎች እንደ ቀለም ቀንድ ተሰብረው ተቀብረዋል፡፡ ሌሎችም የትምህርት ማስረጃቸውን እያሳዩ የሚለምኑ ሆነዋል:: ከፊሎቹ ደግሞ አብደውና አእምሮአቸውን አጥተው የሚናገሩትን እንኳን አያውቁትም።ታዲያ አንተ ከእነዚህ እንደ አንዱ ባለመሆንህ ማመስገን ሲገባህ የምትኩራራው ከእግዚአብሔር እጅ የምታመልጥ ይመስልሃልን? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «ዕውቀትም ቢሆን ይሻራል» በማለት የተናገረውን ቃል አስበህ ዕውቀትን የሚስጥና የሚነሣ የሰማይን አምላክ አመስግን እንጂ አትታበይ፡፡ 1ቆሮ13÷9
ትዕቢት በእጅጉ ይጐዳል፡፡አንተ በዕውቀትህ የምትታበይ ሰው ትዕቢት መጉዳቷን እንኳን ሳታውቅ አዋቂ ነኝ እንዴት ትላለህ? በማወቅህ ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ ትዕቢትና ትምክህት የሚያመጡብህ ጉዳት ትምህርት ከሚሰጥህ ጥቅም በእጅጉ ይከፋል፡፡ ታዲያ ተምሮ ትዕቢተኛ ከመሆን ደንቁሮ ትሑት መሆን አይሻልም ትላለህን?
የአንድ የፈጠራ ሙያ ባለቤት ብትሆን እንኳን ልትመካ አትችልም፡፡ ምክንያቱም እርሱም ቢሆን መሠረቱን ማየት ከቻልክ የሌሎች መሆኑን ትገነዘባለህ:: በዙሪያ የምታያቸው ነገሮች በአብዛኞቹ የአንድ ሰው የፈጠራ ውጤት ሳይሆኑ የብዙ ሰዎች የሐሳብ ጥርቅም ውጤቶች ናቸው:: ወይም በአንድ ሰው ክተጀመሩ በኋላ በሌሎች ሰዎች እየዳበሩ አሁን የምታያቸውን አኽለዋል:: ለምሳሌ፡- መቀመሪያ (ኮምፒውተር)፣ ሰዓት፣ ስልክ፣ ነፋሰ ድምፅ (ሬዲዮ)፣ ነፋሰ ሥዕል (ቴሌቪዥን)፣ መብራትንና ሌሎችንም ነገሮች ብትመለከት ስለግኝታቸው አንድ መሠረት የጣለ ስው ቢጠቀስላቸውም አሁን ላሉበት ደረጃ የበቁት ግን የብዙ ሰዎች ሐሳብ ተጨምሮባቸው ነው፡፡ መሠረት ጣለ የተባለውም ሰው ከእርሱ በፊት የነበሩ ሰዎች ለግኝቱ መሠረት የሆነ ሐሳብ በሆነ መንገድ ባይለግሱት ኖሮ መሠረት የተባለውን ሐሳብ አንኳን ለማግኘት አይበቃም ነበር፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ዕውቀት የባሕርይው የሆነ የዕውቀት ባለቤት አእምሮውንና የተገለገለባቸውን ቁሳቁሶች ባይፈጥርለት ኖሮ ማንም ሰው የፈጠራ ሙያ ባለቤት ባልሆነም ነበር፡፡ ታዲያ ይህን ሁሉ ያስተዋለ በፈጠራ ሙያው ፈጣሪን ማመስገን እን እንጂ መመካት አይገባውም፡፡የሚመካውን ግን ሐዋርያው እንዲህ ሲል ይገሥጻል:- «አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጐሃል? ያልተቀበልከውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው?›› 1ቆሮ4÷7

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ትምህርት ጉዳት ይኖረዋል?
ቅዱሳት መጻሕፍትና ትምህርቶቻቸው የተገኙት ከማይሳሳት ከእግዚአብሔር በመሆናቸው ፍጹምና እንከን የለሽ ናቸው:: ቅዱስ ዳዊትም «በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር የእግዚአብሔር ቃል የነጻ ቃል ነው::›› በማለት የመንፈሳዊ መጻሕፍትን ፍጹምነት መስክሯል። መዝ11፥6 በዚህ ምክንያት ቅዱሳት መጻሕፍትን ማሻሻል፣ በዙ ብሎ መቀነስና አንሰዋል በማለት ለመጨመር መሞከር ከባድ መንፈሳዊ ቅጣት ያስከትላል፡፡ራእ 22÷18-19 ፤ዘዳ4÷2
እነዚህን ቅዱሳት መጻሕፍት የሰው ልጅ በሚገባ ባለመማሩ ይጐዳል እንጂ እነርሱን በመማሩ የተነሣ የሚጐድልበትና የሚጐዳበት አንዳችም ነገር የለም:: ሰው ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሮ ከተጐዳችግሩ ያለው ከራሱ ወይም ከመምህሩ እንጂ ከቅዱሳት መጻሕፍቱ ሊሆን አይችልም። ችግር የሚፈጠረው በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት የተጻፈውን ቅዱስ መጽሐፍ በርኩስ መንፈስ አጋዥነትና በራስ ፈቃድ ተነሣሥቶ ለመተርጐም በሚሞከርበት ጊዜ ነው። 2ጴጥ1፥20-2፤ ሐዋ8፥30-31 መንፈሳዊ ትምህርት ዓላማውን ሳይለቅ በሚገባ ቢማሩት ምንም ዓይነት ጉዳት የሌለው ፍጹም ጠቃሚ ትምህርት ነው።
ዓለማዊ (ሥጋዊ) ትምህርት ግን ፍጹምነት የለውም፡፡ በየጊዜው በሚደረስባቸው አዳዲስ ግኝቶች የተነሣ በአቀራረጹ ብቻ ሳይሆን በመሠረታዊ ሐሳቡም ከጊዜ ወደ ጊዜ የመለዋወጥና እያደገ የመሄድ ባሕርይ አለው።ይህ ሂደት ዘመናዊ ትምህርት ምንም እንኳን ጥልቅ ቢመስልም ገና ዕድገቱን ሙሉ በሙሉ ያልጨረሰ እንጭጭ እንደሆነና ፍጹምነት እንደሚጎድለው ያሳያል። እስከ አሁንም ድረስ ወደ ሙሉ የዕውቀት ደረጃ ባለመድረሱ አዲስ ሐሳብ ሲገኝ ብቻ ጉዳታቸው የሚገለጥ ዛሬ ግን በጠቃሚነታቸው ብቻ ጐልተው የሚታወቁ ብዙ ስሕተቶችን አካቶ ይዟል።
የዘመናዊ ትምህርት ፅንሰ ሐሳቦች በሙሉ በቤተ ሙከራ ተፈትሸው የወጡ አይደሉም፡፡ ሙከራ ሊደረግባቸው የማይችሉ ብዙ የዘመናዊ ትምህርት ክፍሎች አሉ፡፡ እነዚህ በሙከራ ያልታዩ ይልቁንም በዕድል፣ በመላምትና በግምት የተገኙ ጭብጥ የሌላቸው ሐሳቦች (ሃይፖተቲካልስ) ጉድለታቸው እስኪታወቅ ድረስ የሰውን ልጅ በተሳሳተ አመለካከት ተቀርጾ እንዲያድግ በማድረግ፣ በማኅበራዊ ኑሮው፣ በጤናው፣ በምግባሩና በሃይማኖቱ ላይ ይህ ነው የማይባል አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደራቸው አይቀርም።ይህም የዘመናዊ ትምህርት ዋነኛና ቀጥተኛ ጉዳት ተደርጐ ይጠቀሳል። ሃይማኖት የሌላቸውና ለመንፈሳዊ ነገር ግድ የሌላቸው ሰዎች ዘመናዊ ትምህርት ጥቅም ብቻ እንጂ ጉዳት ያለው አይመስላቸውም፡፡ ነገር ግን ዘመናዊ ትምህርት በመንፈሳዊ ትምህርት ከተመዘነ በብዙ ጎዳና ሊጎዳ እንደሚችል መታዘብ ይቻላል።

ቀጣይ ምዕራፍ ዐሥር ክፍል ዐራት :
👉 «የትምህርት ተዛማጅ ጉዳቶች» በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

አሳዛኝ ውጤቶችን በሚያስከትሉ በጾታ ብልግና፣ በአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት፣ በሌብነት፣ በቡድን ጸብና በመሳሰሉት ልዩ ልዩ የዓመፅ ተግባራት የተመረዙ ባልንጀሮችህን ጨምርሮ በርካታ ሰዎች በዙሪያህ ይገኛሉ፡፡ይህን ከመሳሰሉት ሰዎች ጋር መዋል ቅር ሳያሰኝህ አይቀርም፡፡ ምንም እንኳን ከነዚህ ሰዎች ጋር ያለህን ግንኙነት በቀላሉ ለማስቀረት ያስቸገረህ ቢሆንም ትምህርትህን በሚገባ ብትከታተል ግን እንዲህ ካሉ መጥፎ ሰዎች ጋር ያለህን የጠበቀ ግንኙነት ቀስ በቀስ ለመቅረፍ ትችላለህ፡፡ ለትምህርት ጥሩ ትኩረት በምትሰጥበት ጊዜ ሰፊ ጊዜህን ይይዝልሃል፡፡ ይህም ሥነ ሥርዓት ከጐደላቸው ሰዎች ጋር የሚኖርህን ግንኙነት ውስን ያደርገዋል፡፡ እንደዚህ ያሉ ሰዎች ፍላጐትህ ትምህርትህን በሚገባ መከታተል ብቻ መሆኑን ሲያዩ ከጊዜ በኋላ ሊተዉህ ይችላሉ፡፡ይህም ከትምህርት የምታገኘው «ጥበቃ» ነው።
መጽሐፈ መነኮሳት የማንበብ ልምድና ትምህርት በንጽሕና ተጠብቆ ለመኖር አጋዥ መሆናቸውን እንዲህ ሲል ይገልጻል:- «ፃማ ሥጋዊት ወአንብቦ መጻሕፍት አሞላካውያት የዐቅብዋ ለንጽሕና» በአማርኛ «በሥጋ መድከምና አምላካዊያት መጻሕፍትን ማንበብ ንጽሕናን ይጠብቋታል» ማለት ነው:: (ማር.ይስ.አን.ሣልስ.ምዕ 9)
የመንፈሳዊ ትምህርት ጥቅም
ያለንበት ዘመን ከየትኛውም ጊዜ ይልቅ የትምሀርት ጥቅም ጎልቶ የሚታይበት ዘመን ሆኗል። ከላይ በጥቂቱ የተገለጹት ዕሤቶች ከሥጋዊ ትምህርት የሚገኙ ናቸው። ሥጋዊ ትምህርት እንደዚህ የሚጠቅም ሆነ መንፈሳዊ ትምህርት ደግሞ እጅግ በተሻለ ሁኔታ እንደሚጠቅም ጥርጥር የለውም:: ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ማንኛውም ሥጋዊ ነገር ያለው ጠቀሜታ ከመንፈሳዊ ነገር ጠቀሜታ ጋር ሲነጻጸር እጅግ ጥቂት" እንደ ሆነ እንዲህ በማለት ይገልጻል፡፡ «ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለነገር ሁሉ ይጠቅማል፡፡»1ጢሞ4፥8 ስለዚህ መንፈሳዊ ትምህርት የሚሰጠው ጠቀሜታ ከሥጋዊ ትምህርት እጅግ የላቀ ነው።
በስሕተታቸው ጸንተው የሚኖሩ ሰዎች ሥራዬ ትክክል ነው ብለው የሚያምኑ ወይም መሳሳታቸውን በውል ያልተረዱ ናቸው፡፡ ከዚህ ካለፈ ደግሞ ስሕተታቸውን ቢያውቁም ከዘለቄታዊ ጥቅም ይልቅ ለጊዜው የፍላጐታቸውን መሳካት የሚወዱ ከመሆን አይዘሉም።ካለማወቅ የተነሣ የተሳሳቱ ሰዎች መላልሰው ሥራቸውን ቢመረምሩትና በቂ ግንዛቤ እስኪያገኙ ድረስ ስለ ሥራቸውም አስከፊነት ቢማሩ ከስሕህተት ይታረማሉ፡፡መማር ከመሳሳት ያድናልና፡፡
የማይሳሳት የለም፤ ከስሕተት ሁሉ የሚከፋው ግን በሃይማኖታችን ላይ የምንፈጥረው ስሕተት ነው፡፡ ለምን ቢባል ጉዳቱ የነፍስ ስለሆነ ነው።ከዚህም ዓይነት ስሕተት ቢሆን መዳን የሚቻለው በመማር ነው። አለማወቅ ለሕህተት መንሥኤ ከሆነ መማርና ማወቅ ከስሕተት ለመዳን መፍትሔ መሆኑ ግድ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤ ላይ ባላቸው እምነት ችግር ለነበረባቸው ለሰዱቃውያን የስሕተታቸው መነሻ ምን እንደ ነበር ሲነግራቸው ‹‹መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችው» ብሏቸዋል።ማቴ22፥29 ስለዚህ ትምህርት ካሉት ዋና ዋና ጥቅሞች መካከል ‹‹ከስሕተት ለመዳን›› የሚለው በአንደኛነት ይጠቀሳል።
ከስሕተት ለመዳን ብቻ ሳይሆን ለማመንና እግዚአብሔርን ፈርቶ ለመኖርም ትምህርት ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሳይማሩ ሃይማኖተኛ ሰው መሆን እጅግ አስቸጋሪ እንደ ሆነ «ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?›› በማለት ተናግሯል።ሮሜ10፥14 ቅዱስ ዳዊት ደግሞ «ልጆቼ ሆይ ስሙኝ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ» መዝ33÷11 በማለት ማመን ከትምህርት እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡ በዓይን ያላዩትን እግዚአብሔርን መፍራት ማመን ይባላል፡፡
ለማመን ብቻ ሳይሆን መልካም ሥራ ለመሥራትም መማር ያስፈልጋል፡፡ የማያውቁትን መሥራት ስለማያስቸግር ለመሥራት ማወቅ፣ ለማወቅ ደግሞ መማር ግድ ነው፡፡ ማወቅ ለመሥራት ብቻ ሳይሆን በሥራችን የትክክለኛለነት ስሜት እንዲስማንና ያለማቋረጥ በጉጉት እንድንሠራው ያግዘናል፡፡ በአጠቃላይ በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ጐዳና የሚሠሩ ሥራዎችን ለማከናወን መማር ያስፈልጋል።ለዚህም ነቢዩ ኢሳይያስ «መልካም መሥራትን ተማሩ» በማለት የተናገረው ቃል በቂ ማስረጃ ነው፡፡ ኢሳ1፥17፤ 26፥9-10

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጾመ ድኅነት

ጾመ ድኅነት ስሙ እንደሚያመለክተው የመዳን ጾም ማለት ሲኾን፣ ይህም በብሉይ ኪዳኑ አጽዋማት በጾመ አስቴር እና በጾመ ዮዲት የተተካ የሐዲስ ኪዳን ጾም ነው፡፡

በብሉይ ኪዳን በሐማ ምክንያት በእስራኤል ላይ ታውጆ የነበረው ሞት በጾመ አስቴር እንደ ተሻረ ኹሉ፣ በሐዲስ ኪዳንም በዕለተ ረቡዕ በጌታችን ላይ በተፈጸመው ምክር የሰይጣን ሴራ ፈርሷልና በጾመ አስቴር ምትክ ረቡዕን እንጾማለን፡፡

እንደዚሁም በብሉይ ኪዳን በጾመ ዮዲት ምክንያት ሆሎሆርኒስ ድል እንደ ተደረገበት ኹሉ፣ በሐዲስ ኪዳንም መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ በከፈለው መሥዋዕትነት ዲያብሎስ ድል ተደርጓልና በጾመ ዮዲት ምትክ ዓርብን እንጾማለን፡፡
የእነዚህ የሁለቱ ቀናት (የረቡዕና ዓርብ) ጾም ጾመ ድኅነት ይባላል፡፡

ጾመ ድኅነት እንደ ጾመ ነነዌ፣ ዐቢይ ጾም እና ጾመ ሐዋርያት የበዓላትና የአጽዋማት ማውጫ ቀመርን ተከትሎ የሚመጣ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል የሚመደብ ጾም ነው፡፡

ጾመ ድኅነት ከበዓለ ኀምሳ በስተቀር ዓመቱን ሙሉ የሚጾም ጾም ነው፡፡

ዕለተ ረቡዕ የጌታ ሞት የተመከረበት፤ ዓርብም አምላካችን የተሰቀለበት ዕለት ነውና በመስቀሉ መሥዋዕትነት ያገኘውን ድኅነት ዘወትር ማሰብ ስለሚገባን ሁልጊዜ እንድንጾማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ሥርዓት ተሠርቶልናል፡፡

በዚህ ዓመት ጾመ ድኅነት ሰኔ ፬(4) ቀን ይጀመራል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጾመ ሐዋርያት
ሰኔ 2
ጾመ ሐዋርያት በወርኃ ሰኔ ስለሚጾም በምእመናን ዘንድ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፤ ከሰባቱ የዐዋጅ አጽዋማትም አንዱ ነው፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡
ይህም ጾም ከበዓለ ኀምሳ በኋላ የሚጾም ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ቅዱሳን ሐዋርያት በጸሎት ይተጉ ወደ ነበረበት ቤት በመሄድ ደቀመዛሙርቱን ይዟቸው ከቤት በመውጣት መንገድ ጀመረ፡፡ እርሱ ከፊት እየመራቸው እነርሱ እየተከተሉት ወደ ረጅሙና በረጃጅም ዛፎች ወደ ተሞላው ደብረ ዘይት ተራራ ይዟቸው ወጣ፡፡ ይህንንም እየነገራቸው ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ፤ከፍ አለ፡፡ ነጭ የሆነች ብሩህ ደመናም አምላካችንን ተቀበለችው፡፡ከዓይናቸውም እየራቀ፤ከእይታቸው በርቀት ሳይሆን በርኅቀት ተሰወረባቸው፡፡ሐዋርያትም ኢየሱስ ክርስቶስን በጣም ይወዱት ስለነበር ሲለያቸው አዝነው አተኩረው ሰማዩን ለረጅም ሰዓት ተመለከቱ፡፡ ድንገትም ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ቅዱሳን መላእክት በአጠገባቸው ቆመው ታዩአቸው፡፡መላእክትም ሐዋርያትን እንዲህ አሏቸው፤ ‹‹እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን  ቆማችኋል፡፡ ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል›› አሏቸው፤ (ሐዋ. ፩፥፰-፲፩)፡፡ ሐዋርያትም የመላእክትን ማረጋጊያ ቃል ከሰሙ በኋላ  በኢየሩሳሌም ወደ ምትገኘው ቤተ መቅደስ በመሄድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገራቸው እስኪፈጸም ድረስ ቀን ከሌሊት በአንድነት ሆነው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከመካከላቸው አድርገው በጾምና በጸሎት እየተጉ ቆዩ፡፡
የጾመ ሐዋርያት የጊዜ ቀመር ሥሌት በዓለ ጰራቅሊጦስ እንደ ገባ ባለው የመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ በዚህም መሰረት የዘንድሮ ጾመ ሐዋርያት ሰኔ ፪(2) ይገባል። ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት እንዲህ ተናግሮ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። ‹‹እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት›› (ማቴ.፱፥፲፬)።  ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ ጌታችን እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር፡፡‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው  ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ያንጊዜም ይጾማሉ›› (ማቴ.፱፥፲፭)፡፡
እኔ ሳለሁ አይጾሙም ማለቱ እርሱ ካልሞተና ካላረገ፤ መንፈስ ቅዱስም ካልተሰጣቸው በመንፈስ ቅዱስ ባልታደሰ ሰውነት ጾመው ድል መንሳት ስለማይቻላቸው ነው፡፡ ይህን ጾም የምንጾመው ሐዋርያት ጾመው ጸልየው ድል ያደረጉትን ዓለም እኛም የምናሸንፍበት ኃይል እንዲሰጠን ፈጣሪያችንን አምላከ ሐዋርያት ተለመነን እያልን ለመማጸን ነው፡፡
ይህን ጾም እንደ ሌሎቹ አጽዋማት ሁሉ እያንዳንዱ ምእመን ሊጾመው የሚገባ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን አብዛኛው ምእመን ‹‹የቄስ ጾም›› ነው በማለት ከጾሙ ሽሽት ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተክርስትያንን መሠረት ያደረገ ባለመሆኑ መስተካከል ይገባዋል፡፡
ሐዋርያትን አብነት በማድረግ ጾመን በረከትን ልናተርፍ ይገባናል፡፡
የአምላካችን የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት፣
የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣
የቅዱሳን ሐዋርያት በረከት፣
የጻድቃን የሰማዕታት ጸሎት እና ምልጃ አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን፡፡

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት (የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ክፍል ሦስት
.................................................
➺ስኬታማነት

ወጣት ከሆንክ ቢያንስ አንድ ነገር እንዴት እንደሚሳካልህ ሳያስጨንቅህ አይቀርም::የምታሰበው ሁሉ እንዲፈጸምልህና ስኬታማ ሰው እንድትሆን ትፈልጋለህ? ከፈለግህ በመጀመሪያ በሕይወትህ መንፈሳዊ ሰው ሁን፡፡ የስኬት መሠረት መንፈሳዊነት ነውና፡፡ እንዲህ ሳትሆን ብዙ ነገር ቢሳካልህ እንኳን ተመልሶ እንዳልተወጠነ ሊሆን እንደሚችልና ውሸት እንደ ሆነ አስብ፡፡
ማንም ሰው ደስተኛና ስኬታማ ሆኖ መኖር ይፈልጋል:: ወጣቶችም ይህን መፈለጋቸው መልካም ነገር ነው፡፡ ስኬታማ ዕድሜን ያረዝማል፣ በተስፋ፣ በጥንካሬ ያቆያል፡፡ መቸገር፣ ማጣትና ማዘን ግን ያለጊዜው ያስረጃል፡፡ ደራሲው «እንበለ ጊዜ በላህ ኢይርሳዕ ወሬዛ» እንዳለ «ያለ ጊዜዬ በኀዘን ምክንያት እንዳላረጅ›› ለማለት ነው:: (መልክዐ ሚካኤል) ሆኖም ግን ደስተኛና ስኬታማ ለመሆን መታወቅ ያለባቸው ብዙ ነገሮች አሉ።
ፍሬያማ ግብር (ስኬት) ማለት ሰው በሥጋዊ ሕይወቱ ተጨባጭ የሆኑ ነገሮችን ማግኘቱ ብቻ አይደለም:: የሰው መንፈስም (ነፍስም) የምትመኘው ብዙ ነገር አላት፡፡ የነፍስ ምኞቶች በሙሉ እንደ እርስዋ ረቂቃን ናቸው:: የነፍስ ምኞቶች ሐዋርያው «የመንፈስ ፍሬዎች» በማለት የገለጣቸው ሲሆኑ እነርሱም:- ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃትና ራስን መግዛት ናቸው:: ገላ5÷22 ሰው ስንል ነፍስም ሥጋም እንደመሆኑ መጠን በሥጋ የሚመኛቸው ግዙፋን ነገሮች ስለተሟሉለት ብቻ ደስተኛና ስኬታማ ሊባል አይችልም፡፡ ክላይ የተጠቀሱት «የመንፈስ ፍሬዎች›› የሌሉት ሰው ስኬታማ አይደለም።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት (የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ክፍል ኹለት
.................................................
➺«ኀፊረ ገጽ»

እግዚአብሔር በሰው ልጆች መካከል መተፋፈር እንዲኖር አድርጓል:: ይልቁኑም «ወከደና በኀፍረት» እንደ ተባለው ሴቶች በማፈር እንዲያሸበርቁ ልዩ መጐናጸፊያ ሰጥቷቸዋል፡፡
«ኀፊረ ገጽ» ማለት የሌላውን ሰው ገጽ አይቶ መፍራትና ማፈር ማለት ነው:: ይህ እጅግ ውድ ስጦታ ነው:: በመፍራት ውስጥ ማክበር በማክበር ውስጥ ደግሞ መፍራት እንዳለ ሁሉ በማፈርም ውስጥ ማክበርና መፍራት አሉ፡፡ ሰውን የማይፈራ እግዚአብሔርንም አይፈራም ለማለት ያስደፍራል፡፡ ምክንያቱም ሰውን መፍራት እግዚአብሔርን የመፍራት መገለጫ ነውና፡፡ 1የሐ3÷17
ቅዱሳት መጻሕፍት መፍራትና ማፈር የማያውቅ ደረቅ ሰውን ያወግዛሉ:: ማር ይስሐቅ ከሌላ መጽሐፍ ያገኘውን «ዘኢየኃፍር ገጸ ከይሲ ውእቱ ዘይሴሰይ መሬተ» ፤ «የሰውን ገጽ አይቶ የማያፍር አፈርን እንደሚበላ እባብ ነው» ማለት ነው::
ቅዱሳን አበው የሃይማኖት ዓይን ስላላቸው እንኳን በአካል ገዝፎ በአጠገባቸው የሚገኝ ሰውን ይቅርና የሚጠብቃቸውን መልአክ በማፈር ከማያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ ተጠንቅቀው ይኖሩ ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ ጠባቂ መልአካቸውን በማፈር ለብቻቸው ሳሉ እንኳን ከልብስ ተራቁቶና ተገላልጦ ዘና ማለት የማይሆንላቸው እንደ ነበሩ ዜና ሕይወታቸው ይናገራል።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት (የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ክፍል አንድ
.................................................
➺ «መልካም ስም»

ጠቢቡ ሰሎሞን ስለ ስም ሲናገር «ከመልካም ሽቶ መልካም ስም ይሻላል» ብሏል። መክ 7፥1 እግዚአብሔር ስምን የብዙ ነገሮች ምልክት አድርጎታል፡፡ ስም መብት፣ ክብር፣ ገንዘብ፣ መርዳት፣ ችግር፣ ውድቀት፣ ሲሆን ለማየት በዙሪያህ ያሉትን ነገሮች መመርመር ብቻ በቂ ነው።ምንም የሚያስከብር ነገር ላይኖራቸው በቀደመ ማንነታቸው ብቻ ሰዎች ሲከበሩ አይተህ አታውቅም?በስም ብቻ ገንዘብ የሚገኝበት ሁኔታስ ገጥሞህ አያውቅም?
ነገር ግን ብዙ ወጣቶች «መልካም ስም» ያለውን ከፍተኛ ዋጋ አያውቁም፡፡ እንዲህ የሚያስብለው ስማቸውን በክፉ የሚያጠፋ ርካሽ ተግባር ዘወትር ሲፈጽሙ መገኘታቸው ነው።መጥፎ ነገሮች ምን ጊዜም ክፉ ስም ያስገኛሉ።በሥውርና በድብቅ ቢፈጸሙ እንኳን ከጥቂት ቆይታ በኋላ በአደባባይ መውጣታቸው የማይቀር ነው።«ድብቁን የምትገልጽ የውስጡን ወደ ውጭ የምታወጣው ሆይ» የሚባል እግዚአበሔር ሥራውን አይዘነጋምና።
መልካም ስም ከመልካም ሽቶ ጋር የተነጻጸረው ያለ ምክንያት ኣይደለም። መልካም ሽቶ ርቆ ሄዶ ከመሽተቱም በላይ ስሜትን ይማርካል፣ ይስባልደ መልካም ስምም አንተ ካላሰብከው ቦታ ደርሶ ያሳውቅሃል፣ ያስወድድሃል፡፡ክፉ ስም ደግሞ እንደ ክፉ ሽታ ነው።ያ ከሩቅ መጥቶ እነደሚበክል ተደብቆ የተሠራም ክፉ ሥራ ርቆ ሄዶ ስምን ይበክላል፡፡ ስለዚህ በዘመንህ ሁሉ ከቁሳዊና ከብልጭልጭ ነገሮች ይልቅ ጥሩ ስም እንዲኖርህ ተጣጣር፤መልካም ስም ካለህ የተመኘኸውን ሁሉ ሳታገኝ አትቀርምና። መልካም ስም የመልካም ሥራ ነው እንጂ የፈጠራና የማስመሰል ውጤት አይደለም።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ቅዱስ ላሊበላ"

በገርጂ ጊዮርጊስ የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት መዘምራን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የምትፈልግ አይደለህም፤ ለጠፈራቸው መማገሪያ ገመድ የምትሻ አይደለህም፣ እንጨትንም ለማገር፣ ለምሰሶዋቸውም ገበታ፣ ለዙሪያቸውም ለማያያዣ ጭቃን የምትፈልግ አይደለህም፡፡ የቤተመቅደሶችን ፈቃድ ሁሉ ከአንድ ቋጥኝ ድንጋይ ትፈጽማለህና፡፡ የማሳይህ እኚህ የቤተ መቅደሶች አኗኗር ከምድር ልብ ውስጥ እስከዛሬ አለ፡፡ ከአሁን ጀምሮ በእጅህ እስኪገለጡም ድረስ በምድር ልብ ይኖራሉ፡፡ በሰው ልጅ ጥበብ ያይደለ በእኔ ሥልጣን ከምድር ልብ ውስጥ ታወጣቸው ዘንድ መረጥሁህ፡፡ ሕዝቦቼ ተወልጄ አድጌ ሞቼ ተቀብሬ ከሞትም የተነሳሁባትን ሀገር ለማየት ኢየሩሳሌም በመሄድ ግማሹም በበረሃ ይቀር ነበር አሁን ግን አንተ ኢየሩሳሌምን በሀገርህ ትሠራለህ፡፡ በማንም እጅ ዳግመኛ ሊሠሩ የማይችሉ ቤተ መቅደሶቼን እንዳሳየሁህ ትሠራለህ፡፡ አንተም እንዳሳየሁህ በልብህ ውስጥ አኑራቸው፡፡ ስትሠራቸውም እየልካቸው ይሁን፤ ከእርዝመታቸውም በላይ ቢሆን፣ ከወርዳቸውም በላይ ቢሆን፣ በመወጣጫቸውም ላይ ቢሆን አንዳች እንዳትጨምር፡፡ ያሳየሁህ እሊህ ዐሥሩ መቅደሶች ከአንዲት ቋጥኝ ድንጋይ ሲወጡ አይተሃልና….› እያለ ጌታችን ሲነግረው ጻዲቁ ንጉሥ “ይህ እንዴት ይሆናል?” በማለት ይጠይቃል፡፡ ጌታም እውነት እልሃለሁ እነዚህ ያሳየሁህ መቅደሶች በሰው ኃይል የሚሠሩ ሆነው አይደለም፤ ጀማሪያቸው ሠሪያቸውና ፈጻሚያቸው እኔ ነኝ ነገር ግን ኃይሌ በአንተ እጅ እንዲገለጽ ለምክንያት ተልከሃል፤ አንተ አነጽካቸው እየተባለ እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ ስምህ ይጠራባቸዋል…›› እያለ ይቀጥላል የቅዱስ ላሊበላ ገድል፡፡ ቤተ መቅደሶቹንም ለመሥራት ቦታውን ያውቅ ዘንድ ሱባኤ ገብቶ ሳለ ዛሬ ቤተ ማርያም ካለችበት ቦታ ላይ ቅዱሳን መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ታይተውት በቦታው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መቅደሱን መሥራት ጀመረ፡፡ ዓሥሩን ቤተ መቅደሶች ሲሠራ እርሱ አንድ ክንድ ሠርቶ እንደሆነ ሌሊቱን አድሮ በቀጣዩ ቀን አሥር ክንድ ሆኖ ያገኘው ነበር፣ ቀንም በማይታወቁ ሰዎች አምሳል እየተገለጡ መላእክት ይራዱት ነበር፡፡

5. አንዳንድ ነገሮች ስለ ቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፡- ቅዱስ ላሊበላ ዓሥሩም ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በጣም በሚያስገርም ሁኔታ በውስጥና በውጭ ያሉት ብዙ ቅርጾች ነገረ ድኅነትን በምሳሌ እንዲወክሉ አድርጎ ነው ያነጻቸው፡፡ የክርስቶስን መከራና በእርሱም የተገኘውን ፍጹም ዘላለማዊ ድኅነት በእያንዳንዱ ቤተ መቅደስ ውስጥ እንዴት አድርጎ በምሳሌ እንዳስቀመጠው እጅግ አስገራሚ ነው፡፡
በላስታ ቅዱስ ላሊበላና አካባቢው የሚገኙ ሌሎች አስደናቂ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፡- ከአሥሩ የቅዱስ ላሊበላ አስደናቂ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በተጨማሪ የቅዱስ ነአኵቶለአብና የቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም አሸተን ማርያም በዋናነት ሕዝበ ክርስቲያኑ የሚጐበኛቸው ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ናቸው፡፡ በላሊበላና አካባቢው ግን እጅግ ጥንታዊና አስደናቂ የሆኑ በጣም በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ሣርዝና ሚካኤል፣ ብልባላ ቂርቆስ፣ ብልባላ ጊዮርጊስ፣ አርባዕቱ እንስሳ፣ ትርኩዛ ኪዳነምሕረት፣ ገነተ ማርያም፣ ቀንቀኒት ሚካኤል እነዚህ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ሲሆኑ እንዲሁም ዋልድቢት ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም፣ አቡነ ዮሴፍ ገዳም፣ ገብረ ክርስቶስ ዋሻ ቤተክርስቲያን፣ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን፣ ቀደሊት ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ እመኪና መድኃኔዓለምና እመኪና ልደታ፣ ማውሬ እስጢፋኖስ፣ የቅዱስ ገብረ ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ማይ ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ተከዜ ኪዳነምሕረትና መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዳንዶቹ ከ485-536 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በዐፄ ካሌብ ዘመነ መንግሥት የታነጹ ናቸው፡፡ ሌሎቹንና በሰሜን ላስታ ያሉትን ደግሞ እነ ላሊበላና ይምርሃነ ክርስቶስ አንጸዋቸዋል፡፡

ቅዱስ ላሊበላ እኛ ከምናውቃቸው ከድንቅ ሥነ ሕንፃዎቹ ሥራ በተጨማሪ ከሺህ ዓመታት በፊት በሥዕል፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በሃይማኖት፣ በኢኮኖሚ፣ በውጭ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙትና በመሳሰሉት ሁሉ እጅግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ከሺህ ዓመታት በፊት አዳራሾችን፣ ፎቆችን፣ የውስጥ ለውስጥ መተላለፊያዎችን፣ የእንግዳ መቀበያዎችን፣ የሕፃናት ማሳደጊያዎችን፣ የሕሙማን መፈወሻዎችን፣ የሕንፃ መሳሪያዎችን፣ የትምህርት ማዕከሎችን፣ የመደጎሻ ቦታዎችን ያቋቋመ መሆኑን የብራና ገድሉ እንደሚናገር የደብሩ አባቶች ይገልጣሉ፡፡ ወደፊት ተርጎመው እንሚያቀርቡልን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ከዚህ በተጨማሪ የግእዝ ቋንቋን በጽሑፍ አበልፅጎ ያቆየ ባለውለታ ነው፡፡ ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ውጭ ሌሎችንም በርካታ ቤተ መቅደሶች ሠርቷል፤ ከሀገራቸንም አልፎ በሱማሌ ሞቃዲሾ ላይ መቅደሰ ማርያም የተባለች ቤተክርስቲያን ሠርቷል፡፡ ክርስትናን ከግብፅ ምድር ጨርሰው ለማጥፋት ተንባላት በተነሡ ጊዜ ዓባይን ሊያግድባቸው ሲነሣ በብዙ ምልጃና ልመና ስለማራቸው በሀገሪቱ ውስጥ ክርስትና እስካሁን እንዲቆይ የራሱን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ በአጠቃላይ ቅዱስ ላሊበላ ነቢይም ሆኖ፣ ሐዋርያም፣ ጻዲቅም፣ ሰማዕትም ሆኖ ጥበብ መንፈሳዊንና ጥበብ ሥጋዊን ከእግዚአብሔር ተሰጥቶት ንግሥናንና ክህነትን፣ ቅድስናንና ንጽሕናን በሚገባ አስተባብሮ በማያዝ እግዚአብሔርንም ሰውንም በቅንነት ሲያገለግል ኖሮ ሰኔ 12 ቀን 1197 ዓ.ም ከፈጣሪው ታላቅ ቃልኪዳን ተቀብሎ በዝማሬ መላእክት፣ በመዝሙረ ዳዊት ቅድስት ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ ሰማያዊ ክብርን ወርሷል፡፡ ክቡር ሥጋውም ራሱ ባነጸው ቤተ ሚካኤል መቅደስ ሥር በክብር ዐርፏል፡፡

(ምንጭ፡- ገድለ ቅዱስ ላሊበላ፡- የቅዱስ ላሊበላ ደብር በ2003 ዓ.ም ያሳተመው፣ ስንክሳር ዘወርሃ ሰኔ)
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሰኔ ፲፪
ቅዱስ ላሊበላ
ቅዱስ ገብርኤል ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ ሰባቱ ሰማያትን ካሳየውና በጌታችን ፊት አቅርቦት ካስባረከው በኋላ ጌታችንም በቅዱስ ቃሉ ‹‹ሕዝቦቼ የመከራና የሥቃዬን ቦታ ለማየት ኢየሩሳሌም በመሄድ በመንገድ እየቀሩ ስለሆነ አሁን ግን አንተ በሀገረ ሮሀ ኢየሩሳሌምን ትሠራለህ›› በማለት የቤተ መቅደሶቹን አሠራር በዝርዝር የነገረው ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ ዕረፍቱ ነው፡፡

ቅዱስ ላሊበላ ጌታችን የጠጣውን መራራ ሐሞት በማሰብ ሁልጊዜ ዓርብ ዓርብ ኮሶ ይጠጣ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ላሊበላን ኢየሩሳሌም ወስዶት በዚያ ያሉ ቅዱሳን መካናትን ሁሉ አሳይቶ አሳልሞታል፡፡ ወደ ሰማይም ነጥቆ ወስዶ ሰባቱ ሰማያትን ያሳየው ሲሆን በጌታችን ፊትም አቅርቦት አስባርኮታል፡፡ ጌታችንም ‹‹ሕዝቦቼ የመከራና የሥቃዬን ቦታ ለማየት ኢየሩሳሌም በመሔድ በመንገድ እየቀሩ ስለሆነ አሁን ግን አንተ በሀገረ ሮሀ ኢየሩሳሌምን ትሠራለህ›› በማለት የቤተ መቅደሶቹን አሠራር በዝርዝር ነግሮታል፡፡ ከነገሠም በኋላ ሱባኤ ገብቶ ቤተመቅደስ የሚሠራበትን ቦታ በጸሎት ሲጠይቅ ዛሬ ቤተ ማርያም ካለችበት ቦታ ላይ የብርሃን አምደ ወርቅ ተተክሎ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ስላየ ቦታው እግዚአብሔር የፈቀደው መሆኑን አውቆ ሥራውን ጀመረ፡፡ ጌታችን ቀድሞ ‹‹እኔ ራሴ ነኝ እንጂ ቤተ መቅደሶቹን የምትሠራቸው አንተ አይደለህም፣ ነገር ግን በአንተ ስም እንዲጠራ ስለፈቀድኩ ሄደህ ሥራ›› ብሎ እንዳዘዘው ቅዱስ ገድሉ ይናገራል፡፡ ላሊበላ ዓሥሩን ቤተመቅደሶች ሲሠራ እርሱ አንድ ስንዝር ሠርቶ እንደሆነ ሌሊቱን ዓሥር ስንዝር ሆኖ ያገኘው ነበር፡፡ ቀንም ሲሠራ ቅዱሳን መላእክት በማይታወቁ ሰዎች አምሳል ሆነው ይራዱት ነበር፡፡ በመጨረሻም ጌታችን በገሃድ ተገልጦለት በቦታው ላይ እጅግ አስገራሚ ቃልኪዳኖችን ሰጥቶታል፡፡

ከ10ኛው እስከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (920-1253 ዓ.ም ድረስ) በላስታ ቡግና ምድር የነገሡ የላስታ ቡግና ተወላጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ነገሥታት የንግሥናቸው መጠሪያ ‹‹የዛጉዌ ሥርወ መንግሥት›› ወይም ‹‹የላስታ መንግሥት›› በመባል ይታወቃል፡፡

የላስታ ነገሥታት የዘር ሀረጋቸው ከንጉሥ ሰሎሞን ዘር ሲያያዝ የመጣ ነው፡፡ ከላስታ (ከዛጉዌ) ነገሥታት መካከል ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ፣ ቅዱስ ገብረ ማርያም፣ ቅዱስ ላሊበላና ቅዱስ ነአኵቶለአብ እነዚህ አራቱ ነገሥታት እንደ መልከጼዴቅ (ዘፍ 14፡18) ክህነትን ከንግሥና፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ እግዚአብሔርንም ሰውንም በቅድስና አገልግለው አልፈዋል፡፡ በንግሥናቸው ሀገራችንን በመልካም ሥራና በቅድስና ከማስተዳደራቸው በተጨማሪ ቅዱሳን ጻድቃን ሆነው እግዚአብሔርን በብዙ ድካም በመልካም ተጋድሎአቸው ያገለገሉና አገልግሎታቸውም ሆነ ቅድስናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ ስለተመሰከረላቸው ጌታችን የሰጣቸውን ቃልኪዳን መሠረት በማድረግ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን የቅድስና ማዕረግ ሰጥታ፣ በስማቸው ቤተክርስቲያን አንጻ፣ ጽላት ቀርፃ በዓላቸውን እያከበረች መታሰቢያቸው ተጠብቆ ለዘለዓለም እንዲኖር አድርጋለች፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን የቅዱስ ላሊበላን እጅግ ድንቅ የሆኑ ሥራዎቹን ዓለም ከሚመለከትበት የተለየ መንፈሳዊ ዐይን ሊኖረን ይገባል፡፡ ስለዚህም የቅዱስ ላሊበላን የቅድስና ሕይወትና ከእግዚአብሔር ጋር ስለነበረው ግንኙነት ገድለ ቅዱስ ላሊበላን መነሻ በማድረግ ብዙ ነገሮችን ቀጥሎ እናያለን፡-
1. ቅዱስ ላሊበላ ከአባቱ ዣን ስዩምና ከእናቱ ኪርወርና ጌታችን በተወለደበት ዕለት ታኅሣሥ 29 ቀን 1101 ዓ.ም በላስታ ቡግና ወረዳ ልዩ ስሟ ሮሀ በተባለችው ሥፍራ ተወለደ፡፡ የልደቱን ነገር አስቀድሞ ቅዱስ ሚካኤል ለእናቱ ነግሯት ነበርና በተወለደ ጊዜ ብዙ ነጫጭ ንቦች መጥተው በሰውነቱ ላይ አርፈው እንደ ማር እየላሱት ስለታዩ እናቱ ‹‹ልጄን ንብ ዘበኛ ሆኖ ይጠብቅልኛል›› ስትል ስሙን ‹‹ላል ይበላል›› ብላዋለች፡፡ ላል በአገውኛ ንብ ማለት ነው፡፡ በጊዜ ብዛት በተለምዶ ነው ‹‹ላሊበላ›› ተብሎ መጠራት የተጀመረው፡፡ ንቦቹ ግን ሥጋዊ ንቦች ሳይሆኑ በንብ የተመሰሉ መላእክት ናቸው፡፡ ንጉሥ መሆኑን እያመለከቱ የሃይማኖትና የምግባር ማር ከእርሱ ይቀዳል ሲሉ በንብ ሠራዊት ተመስለው ሰውነቱን ላሱት፡፡ እንደ ዮሐንስና እንደ ኤርምያስም በእናቱ ማኅፀን ሳለ ነው መንፈስ ቅዱስ የሞላበት፡፡

ከዚህ ቀጥሎ በገድሉ ውስጥ የተጠቀሱ አንዳንድ አስደናቂ ነገሮችን እናያለን፡፡
2. ቅዱስ ላሊበላ ያነጻቸውን አብያተ ክርስቲያናት መመልከት ያለብን በቅርስነታቸውና በቱሪስት መስህብነታቸው ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ የተገኙ ብቸኛ መንፈሳዊ ሀብቶቻችን መሆናቸውን ነው፡- ስለ ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ከማንሳታችን በፊት በመጀመሪያ እውነተኛ የሕይወት ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን መመልከት የግድ ያስፈልጋል፡፡ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀድሞ በሕገ ልቡና ከዚያም በሕገ ኦሪት እግዚአብሔርን ስታመልክ ኖራለች፡፡ በሐዲስ ኪዳንም ሐዋርያቱ እንኳን ለስብከት ከኢየሩሳሌም ሳይወጡ ነው በ34 ዓ.ም በራሷ ሐዋርያ በጃንደረባው ባኮስ አማካኝነት በክርስቶስ ማመንንና ጥምቀትን ወደ ሀገሯ ያመጣችው፡፡ የዚህ ደግሞ ምስክሩ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ 1ኛ ነገ 10፡1-13፣ ሐዋ 8፡26-40፡፡ በዚህ መረጃ መሠረት ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ እስከ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ወደ ኢየሩሳሌም እየሔዱ ሃይማኖታዊ ጉዞ ያድርጉ ነበር፡፡

ከ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ ግን ከኢትዮጵያ ተነስቶ በሱዳን በግብፅ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም በእግርና በእንስሳት ጉዞ ለማድረግ የመንገዱ አድካሚነትና በረሃማነት የሚባክነው ጊዜ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ተሻግሮም እስከ ግብፅና ሱዳን ድረስ የእስልምና ሃይማኖት ስለተጠናከረ ለኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ወደ ኢየሩሳሌም ለመጓዝ አስቸጋሪ ስለሆነባቸው ለሃይማኖታዊ አምልኮና ስግደት ወደ ኢየሩሳሌም የሚያደርጉት ጉዞ ተቋረጠ፡፡ ይህ ሁኔታም ሲያያዝ እስከ ቅዱስ ላሊበላ ዘመን ደርሷል፡፡

ቅዱስ ላሊበላም የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ወደ ኢየሩሳሌም ያደርጉት የነበረው ጉዞ በመቋረጡ በእጅጉ እያዘነ ተግቶ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር፡፡ የኢየሩሳሌምንም አምሳያ የሆኑ አብያተ ክርስቲያናትን በሀገሩ ለመሥራት ይመኝ ነበር፡፡ ጥቂት ነገር ሲለምኑት አብዝቶ መስጠት ለእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነውና ላሊበላ ምድራዊ ኢየሩሳሌምን በሀገሩ ለመሥራት ሲያስብ ልዑል እግዚአብሔር በጥበቡ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ (2ኛ ቆሮ 12፡1-7) ወደ ሰማይ አሳርጎት ሰማያዊት ኢየሩሳሌምን አሳይቶታል፡፡ ጌታችንም ‹‹ሕዝቦቼ የመከራና የስቃዬን ቦታ ለማየት ኢየሩሳሌም በመሄድ በመንገድ እየቀሩ ስለሆነ አሁን ግን አንተ በሀገረ ሮሐ ኢየሩሳሌምን ትሠራለህ›› በማለት የቤተ መቅደሶቹን አሠራር ሁሉ በዝርዝር ነግሮታል፡፡ በሰማያዊት ኢየሩሳሌምም ምሳሌ በሀገሩ ላይ ወጥ ከሆኑ የዓለት ድንጋዮች መላእክት እየተራዱት ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እንዲያንጽ ነግሮታል፡፡
3. ጠላት ለክፉ ያሰበውን እግዚአብሔር ለበጎ ያደርገዋል፡- ወደኋላ ተመልሰን የቅዱስ ላሊበላን የልጅነት ሕይወቱን እናንሳ፡- ቅዱስ ላሊበላ እናትና አባቱ ከሞቱበት በኋላ ወደ ጎጃም በመሄድ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን፣ ብሉይና ሐዲስን በደንብ ተምሮ ከጨረሰ በኋላ ወደ ደብረ ሮሐ ተመልሶ መጥቶ ነግሦ ከነበረው ከወንድሙ ከገብረ ማርያም ዘንድ ተቀመጠ፡፡ ‹‹ከገብረ ማርያም ቀጥሎ የሚነግሠው ላሊበላ ነው›› ተብሎ ትንቢት ስለተነገ

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ፈ በኋላ በግ ጠባቂው ያን ብላቴና ባሕራን ብሎ ሲጠራው በሰማ ጊዜ "ልጅህ ነውን?" ብሎ ጠየቀው። በግ ጠባቂውም "አዎን ይህ አሁን ጐልማሳ ሆኖ የምታየው ወጣት ገና ሕፃን ሆኖ ሳለ በሣጥን ተከቶ ከባሕር ውስጥ ተጥሎ አግኝቼው ወስጄ አሳድጌዋለሁና ልጄ ነው" አለው። ባለጸጋውም በባሕር ውስጥ የጣለው ሕፃን መሆኑንም ስላወቀ ይህንን ነገር በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደነገጠ፤ ይገድለውም ዘንድ ፈለገ፡፡

በበነጋውም መንገዱን ለመሄድ ሲዘጋጅ ልዩ ልዩ ምክንያት (ሰይጣናዊ ሃሳብ) በመፍጠር በግ ጠባቂውን "ወንድሜ ሆይ አንድ የማስቸግርህ ጉዳይ አለኝ ይኸውም በቤቴ የረሳሁት ነገር ስላለ ዕገሊት ወደ ምትባል ሀገር ሄዶ መልእክት ያደርስልኝ ዘንድ ይህን ብላቴና እንድትሰጠኝ ነው የድካሙንም ዋጋ ሃያ ወቄት ወርቅ እከፍላለሁ" አለው።
ያም በግ ጠባቂ ስለ ወርቁ ስጦታ ደስ በመሰኘት ያን ጐልማሳ ጠርቶ "ልጄ ባሕራን ሆይ ይህ ክቡር ሰው ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤቱ ሊልክህ ይፈልጋልና መልእክቱን አድርስለት እግዚአብሔር በሰላም ያግባህ" ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም "እሺ መልካም ነው አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁ ነኝ" አለው። ከዚህም በኋላ ያ ባለጸጋ "ይህችን የመልእክት ደብዳቤ ይዞ ወደ አንተ የመጣውን ስሙ ባሕራን የተባለውን መልእክቷ በደረሰችህ ጊዜ ፈጥነህ ግደለው ገድለህም ሬሣውን ከጉድጓድ ጣለው እኔ በሰላም ተመልሼ እስክመጣ ድረስ ማንም ማን ይህን ምሥጢር አይወቅ" የሚል ጽሑፍ ለሹሙ ጽፎ አዘጋጀ፡፡ እንዲሁም በሹሙና በእርሱ መካከል የሚተዋወቁበትን ማኅተም በደብዳቤው ላይ አትሞ ለባሕራን ሰጠው፡፡ ለመንገዱም የሚሆነው ስንቅ ሰጥቶ ላከው።

ባሕራንም መልእክቱን ለማድረስ ዘጠኝ ቀን ተጉዞ የአንድ ቀን ጎዳና ሲቀረው እነሆ ክቡር የሚሆን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በንጉስ ጭፍራ አምሳል በፈረስ ተቀምጦ ወደሱ ደረሰና ወዴት እንደሚሄድ ጠየቀው፡፡
ባሕራንም "ከአንድ ባለጸጋ ሰው የተጻፈ ደብዳቤ ይዤ እርሱን ለማድረስ ዕገሊት ወደምትባል አገር እሄዳለሁ" አለው። ንዑድ ክቡር የሚሆን ቅዱስ ሚካኤልም "እስኪ የመልእክቱን ደብዳቤ አሳየኝ?" አለው፡፡ ባሕራንም "ጌታዬ ለማንም አታሳይ ብሎኛል" አለው፡፡ መልአኩም "እሺ ያም ባይሆን እንደተጠቀለለ አሳየኝ" አለው፡፡ ባሕራንም አሳየው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በሞቱ ደብዳቤ ላይ እፍ ቢልበት የሞቱን ትእዛዝ አጥፍቶ የሕይወት ትዕዛዝ ጽፎበታል፡፡ በደብዳቤው ላይ የተጻፈውን የሞት መልእክት ደምስሶ "ከእኔ ከባለጸጋ ዕገሌ የተጻፈ" ይልና "ይህን መልእክት ይዞ ለመጣሰው ዕገሊት የምት ባለዋን ልጄን አጋቡት (ዳሩለት) በዱር የተሰማራውን ከብቴን በቤት ያለውን ሀብቴን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረቴን በሙሉ አውርሼዋለሁና እኔ እስክመጣ ድረስ አትጠብቁ በሄድኩበት ሀገር የምቆይበት ጉዳይ አለኝና፤ በቤቴና በንብረቴ ላይ ሙሉ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና የወደደውን ያደርግ ዘንድ አትከልክሉት ስለዚህም በእኔና በአንተ መካከል የምንተዋወቅበትን ምልክት አድርጌበታለሁ" የሚል ጽሑፍ ጽፎ ሰጠውና "እንግዲህ ወደ ባለጸጋው ቤት ሂድና ይህን መልእክት አድርስ ነገሩ እንዳይገለጽብህ ከእኔ ጋር መገናኘታችንንና የመልእክቱን ጽሑፍ እንደለወጥኩልህ ለማንም አትንገር" ሲል አስጠነቀቀው፡፡ ባሕራንም "እሺ ጌታዬ እንዳዘዝከኝ አደርጋለሁ" ብሎ ጉዞውን ቀጠለና የዚያን የባለፀጋ ቤት እየጠየቀ ከደረሰበት በኋላ ደብዳቤውን ለሹሙ ሰጠው።

ያም ሹም ደብዳቤውን ተቀብሎ ሲያነብ የታተመበት ማኅተም ዕውነተኛ መሆኑን ከአረጋገጠ በኋላ እግዚአብሔር እንዳዘዘው በቤተ ክርስቲያን ደንብ የባለጸጋውን ልጅ በተክሊል አጋባው፣ የሠርጉንም በዓል እስከ ዐርባ ቀን ድረስ በታላቅ ደስታ አከበሩ። ከሠርጉም በዓል ፍጻሜ በኋላ ያ ባለጸጋ ሰው ከሄደበት አገር ወደ ሀገሩ ተመልሶ ገባና በቤቱ አካባቢ ሲደርስ የደስታና የዘፈን ድምፅ ስለሰማ "ይህ የምሰማው ድምፅ ምንድነው?" ሲል ጠየቀ፡፡ ሰዎቹም "ባሕራን የተባለ ጐበዝ ካንተ ዘንድ ልጄን ዳሩለት የሚል ትእዛዝ አምጥቶ ልጅህን አግብቶ በሠርጉ ምክንያት ይዘፍናሉ ይደሰታሉ እነሆ እየበሉና እየጠጡ በቀንና በሌሊት እየዘፈኑ ሲደሰቱ ዐርባ ቀን ሆኗቸዋል በመልእክትህም እንዳዘዝከው ገንዘብህን የወንድና የሴት ባሮችህን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረትህን ሁሉ በሙሉ አስረክበውታል" አሉት።

ያም ባለጸጋ ያህን ቃል በሰማ ጊዜ ከድንጋጤው የተነሳ በታላቅ ቃል በመጮኽ ከመሬት ላይ ተከስክሶ ሞተና ነፍሱን አጋንንት ተረክበው ወደ ሲኦል አወረዷት። ከዚህም በኋላ ባሕራን የተባለ ያ ጐልማሳ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ እያከበረ ዝክሩን እየዘከረ ይኖር ጀመር። በዚያን ጊዜ በጉዞ ላይ ሳለ ተገልጾለት የሞቱን መልእክት ወደ ሕይወት የለወጠለት ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነም አወቀ ተረዳ። ንዑድ ክቡር የሚሆን የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ሊቆጥሩት የማይቻል ብዙ ስለሆነ በኛም ላይ ኃይለ ረድኤቱ አድሮብን ይኑር እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን።
+ + +

ቅድስት አፎምያ፡- ቅድስት አፎምያ ሀገሯ ኪልቅያ ነው፡፡ ባለቤቷ አስተራኒቆስ መስፍነ ኪልቅያ ነበረ፡፡ እርሷም በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ደገኛ ሴት ናት፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ ነበር፡፡

ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እርሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡ ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ ባሏም ታሞ ሞቶ ከሀብቷ ከንብረቷ እየሰጠች እየመጸወተች በጾም በጸሎት ተወስና ትኖር ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ደግ መነኩሴ መስሎ አጋንንትን መነኮሳይያት አስመስሎ መጥቶ ከደጅ ሆኖ አስጠራት፡፡ እርሷም "ከቤት ገብታችሁ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ጸልዩልኝ" አለቻቸው፡፡ ሰይጣናቱም "እኛማ በነግህ ጸልየናል?" አሏት፡፡ ቀጥሎም ሰይጣን "...እንደው አንቺ ግን ይህ ሁሉ ጾም ጸሎት ምን ያደርገልሻል? ሀብትሽን ሰጥተሸ መጨረስሽስ ስለምንድን ነው? በዚያ ላይ አንቺ ስትደክሚ የሚደግፍሽ ስታረጂ የሚጦርሽ ልጅ የለሽም ሁለተኛ ማግባት ኃጢአት መስሎሻልን? እነ አብርሃም እነ ዳዊ ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች ወልደው የለምን? አሁንም ቤት ሰሪ ጎመን ዘሪ ልጅ ያስፈልግሻልና ባል አግቢ፣ እሺ በይኝ" አላት፡፡
ቅድስት አፎምያም "አባ ቆብህ መልካም ነበር ንግግርህ ግን ክፉ ነው፣ አትጹሚ አትጸልዩ ያልከኝ ጌታ ምጽዋት አበድር እመስዋዕት ብሎ የለምን? ሁለተኛ ባል አግቢ ማለትንስ ከምን አገኘኸው? እርግቦች እንኳ ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ከሌላ ወንድ አይቀርቡም ታዲያ ጥንቱን በንጽሕና ሊኖር የተፈጠረ ሰው ሁለተኛ አላገባም ቢል ዕዳ ፍዳ ሊሆንበት ነውን?" ብላ ሞገተችው፡፡

የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ አይቷታልና ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ ከላይ እንዳየነው በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ ሌላ ባል አግብታ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡ ቅድስት አፎምያ ግ

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

3) መንፈሳዊ ትምህርት መንፈሳዊ ዓላማ ሲኖረው ሥጋዊ ትምህርት ደግሞ በአመዛኙ ሥጋዊ ዓላማ አለው፡፡ መንፈሳዊ ትምህርትን ከዓላማው ወጥቶ መብያና መጠጫ ቢያደርጉት ፈጣሪን ማስደሰት አይችልም፡፡ አልፎ ተርፎም እንደ ቅኔ ባለ መንፈሳዊ ትምህርት ፈጣሪን ለማመስገን መራቀቅ ሲገባ ፍጡርን ሲሹ እንደፈጣሪ ለማወደስ አልያም ደግሞ እንደ ዲያብሎስ ለመደምሰስ ቢጠቀሙበት ያለ ዓላማው ነውና ማስጠየቁ አይቀርም። ስለዚህ በተማሩት ትምህርት ከመጠየቅና ከመጐዳት በአግባቡ በሥራ ላይ በማዋል መጠቀም ያሻል።መኮትኮቻን መፍለጫ፡ መፍለጫን ደግሞ መኮትኮቻ ማድረግ ያለፋል እንጂ ምንም አይጠቅምም:: እንደዚሁም ሁሉ መንፈሳዊ ትምህርትን ያለ ዓላማው ቢያውሉት ያስጐዳል እንጂ አይጠቅምም።
4) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ።» ሉቃ12፥15 በማለት አስተምሮአል:: የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለም ማለት ባለው ነገር መጠን አይደለም ማለት ነው:: ስለዚህ የሰው ሕይወት በጉልበቱ፣ በመልኩ፣ በወገኑ፣ በዕውቀቱ ልክ አይደለም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን ዛሬ ዛሬ ሕይወት በትምህርት ልክ መስሏቸዋል። በዚህ ምክንያት በትምህርታቸው ማነስ ተስፋ በመቁረጥ በእጅጉ ያዝናሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ ብዙ ከማዘን መማር የሚችሉበት መንገድ ካለ መማር የሌለ ከመሰላቸውም ምንም ሳይማሩ የተሻለ ኑሮ የሚኖሩትን ሰዎች በመመልከት እነርሱም እንደዚያ ከመኖር የሚያግዳቸው ነገር እንደሌለ በማመን ጠንክሮ መሥራት ይኖርባቸዋል:: ስለ ትምህርት ባለን የተዛባ አመለካከት የምንጐዳው እኛው ራሳችን ነን፡፡ «ያልተማረ ይታሰር ወይም ይገደል!» ተብሎ እስካልታወጀ ድረስ ጥሩ አስተሳሰብና ስብእና ካለህ የምትሠማራበት የሥራ መስክ ይለይ ይሆናል እንጂ ከተማረ ሰውም በተሻለ መልኩ ለመኖር ትችላለህ።ይህን መቀበል ካቃተህ ግን ትምህርት አምላኪ ከመሆንም ባሻገር ብትማርም እንኳን የትግል መንፈስ የለህምና ስኬታማ አትሆንም። ስለዚህ ያልተማረ ብትሆንም ሙሉ ሰውነት ይሰማህ እንጂ አትሸማቀቅ። አልተማርኩም ብሎ ተስፋ መቁረጥ ባልተማሩ ሰዎች ዘንድ አልፎ አልፎ የሚታይ የትምህርት አንጻራዊ ጉዳት ነው፡፡
5) ለማወቅ ብትጓጓና ጎበዝ ተማሪ ለመሆን ብትመኝ መልካም ነው፡፡ ምኞትህም ከግብ እስኪደርስ ጠንክረህ ተማር፡፡ ሕይወትን መና በሚያስቀሩ ልዩ ልዩ ዕፀዋቶች ታግዘህ ለመማር አትሞክር። አንዳንዶች ለጥናት ይረዳል በማለት ጫት ከመቃም አንሥቶ ዕውቀት ይገልጻሉ የተባሉትን ልዩ ልዩ ዕፀዋት በመጠቀም በጤናቸው፣ በጠባያቸውና በመሳሰሉት ማንነታቸው ላይ የማይሽር ጠባሳ አስቀምጠዋል፡፡ ለመማር አገዙኝ የምትላቸው እነዚህ ዕፀዋት ሱስ ወደ መሆን ይለወጡና የሠራህበትን ገንዘብ በሙሉ «ያስተማርነበት ነው!» በማለት እንደሚያስገብሩህ መዘንጋት የለብህም፡፡
6) ከተማርህ በኋላ በተማርከው የትምህርት ዘርፍ ተያያዥ የሆነ ሥራ ብታገኝ መልካም ነው።ይህ ግን ሊሳካም ላይሳካም የሚችል ነገር በመሆኑ በመስክህ ሥራ አላገኘኽም ማለት ሥራ ፈጽሞ የለም ማለት አይደለም፡፡ ማንኛውምን ሥራ ለመሥራት የተነሣሣ ልቡና ይኑርህ፡፡ ገቢ ባይኖረውም እንኳን የሥራ ልምድ የሚሆንህን መንገድና ዕድል ተጠቀምበት እንጂ አትናቀው፡፡መሥራትም ትምህርት ነውና ገቢ ባይኖረውም ከመቦዘን መሥራት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ሥራ ስታጣ አስብና ፈጥረህ ሥራ እንጂ ሥራን ከመንግሥት ብቻ አትጠብቅ፡፡ እንዲህ ማድረግ ተስፋ ከመቁረጥ ያድንሃል፡፡ ተምረህ ሥራ ማጣትህ ካልተማረ ይልቅ ተስፋ ካስቆረጠህ መማርህም ያጠራጥራል፡፡ ምክንያቱም መማር ማለት በተሻለ መልኩ ማሰብ ማለት ነዋ!

ቀጣይ ምዕራፍ ዐሥራ አንድ ክፍል አንድ :
👉
«መልካም ስም» በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት (የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ዐሥር ክፍል ዐራት
.................................................

የትምህርት ተዛማጅ ጉዳቶች
1) ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ በዘመናዊ ትምህርት ምክንያት ሲከሠት የሚስተዋለው ጉዳት ሰዎች ለትምህርት ከሚሰጡት ጊዜ ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ይኸውም አንዳንድ ሰዎች ትምህርት ለሰው ከሚያስፈልጉት ነገሮች እንደ አንዱ ብቻ በነጠላ ሊታይ የሚገባው ነገር መሆኑን ይዘነጉታል፡፡ ለሚያስፈልጓቸው ሌሎች ተግባራት ማዋል ያለባቸውን ጊዜ በሙሉ ለትምህርት ብቻ በማዋል የኋላ ኋላ ሲጸጸቱ ይታያል፡፡ ለምሳሌ:- አንዲት ልጃገረድ ትምህርቷን ባለመመጠንዋ ምክንያት የመውለጃ ዕድሜዋ ቢያልፍባት ተምራ ያገኘችው ማዕረግ የተሳናትን ልጅ መውለድ ሊመልስላት ወይም ኑሮዋን ደስተኛና የተሟላ ሊያደርገው አይችልም:: ስለዚህ ጊዜን አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ማብቃቃት እንጂ መላ ዕድሜን ለትምህርት ብቻ መስጠት ብልህ አያሰኝም፡፡
ትምህርት ሰው እራሱን ካልመጠነ በቀር ፍጻሜ የሌለው ነገር ነው:: አንድ ሰው በዓለም ላይ ያሉትን ነገሮች ጠቅሎ ሊያውቅ አይችልም። በአንድ ርእሰ ጉዳይ ግን የተሻለና ጠለቅ ያለ ዕውቀት ሊኖረው ይችላል፡፡ ሐዋርያው «ከዕውቀት ከፍለን እናውቃለን›› በማለት የተናገረው አንድ ሰው የሚያውቀው ጥቂት ነገርን ያውም በክፊል መሆኑን ለማስረዳት ነው። 1ቆሮ 13፥9

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መንፈሳዊ ትምህርት ለበጎ ሥራ ያዘጋጃል።«የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ» በማለት ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረው ቃል ከላይ የተጠቀሰውን ሐሳብ ይደግፋል፡፡ 2ጢም3፥16 መንፈሳዊ ትምህርት ለበጎ ሥራ የሚያዘጋጅ፣ የሃይማኖት ሰው እንድንሆን የሚያደርግ በመሆኑ በነፍስም ሆነ በሥጋ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ የመንፈሳዊን ትምህርት ጥቅም በአጭር ቃል ስናጠቃልለው «መዳን የሚገኝበት ጥበብ›› እንለዋለን፡፡ 2ጢሞ3፥15 ምክንያቱም ይህ ጥበብ ሰው የእምነትንና የምግባርን እርካብ እየረገጠ ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመውጣት ስለሚያስችለው ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ መንፈሳዊ ትምህርት ወደ አእምሮ የሚገበትን የዘመናዊ ትምህርት ዕንስ ሐሳቦችንና ማንኛውም ዓይነት ዕውቀቶችን ምን ያህል እውነተኛና ጠቃሚ እንደሆኑ ለመመዘን ይረዳል።መንፈሳዊ ትምህርት ከዘመናዊ ትምህርት መቅደም የሚኖርበትም ስለዚህ ነው፡፡ አንድ ሰው አስቀድሞ መንፈሳዊውን ትምህርት በሚገባ የተማረ ከሆነ ለወደፊት ሕይወቱ የሚበጀውንና ከእግዚአብሔር አንድነት እንዳይለይ የሚረዳውን ነገር ሁሉ ለይቶ ያውቃል።
«ሥራ» ተብለው ነገር ግን ከመንፈሳዊ ሕይወት ጋር ፍጹም የሚቃረኑ ብዙ መስኮች አሉ፡፡ አንድ ክርስቲያን አስቀድሞ መንፈሳዊ ግንዛቤ ካለው ከፈጣሪ አንድነት የሚለዩትን እነዚህን ነገሮች እየተማረና እያጠና ገንዘቡንና ጊዜውን አያባክንም። ለምሳሌ:- ቤተ ክርስቲያን ከመጽሐፍ ቅዱስ መረጃ በመጥቀስ «ዘፋኝነትን» ታወግዛለች፡፡ አንድ ሰው ደግሞ ደግሞ መንፈሳዊነትን መላበስ እየፈለገና የቤተ ክርስቲያን ልጅ ሆኖ ሳለ አንድን የሙዚቃ መሣሪያ አጨዋወትና ጥሩ ዘፋኝ ለመሆን የሚያስችል የድምጽ አወጣጥ ጥበብን ቢያጠና በሕይወቱ ብዙ ነገሮች አይቃወሱበትም? ምክንያቱም ሌላ ሥራ እንዳይሠራ ገንዘቡንና ጊዜውን አቃጥሎ ያገኘው ሙያ ቢኖር የሙዚቃ መሣሪያ መጫወትና ዘፋኝነት ነው፡፡ እንዳይተወው ደግሞ ምን ሠርቶ ይኑር? በዚሁ ሥራው ተሰማርቶ እንዳይኖር ደግሞ ከፈጣሪው ጋር ያለው ግን በእጅጉ ይበላሽበታል፡፡ ለዚህ ሁሉ ችግር መፍትሔ የሚሆነው በምን መልኩ ብንጓዝ እንደምንጠቀም ከወዲሁ ለይተን እንድናውቅ የሚረዳንን መንፈሳዊ ትምህርት አስቀድመን ብንማር ነው።
ብዙ ክርስቲያኖች ጥሩ መንፈሳዊ ሰው መሆን ያልቻሉት ከላይ የተጠቀሰው ዓይነት ውስብስብ ችግር ስላጋጠማቸው እንጂ መሆን ሳይፈልጉ ቀርተው አይደለም፡፡ እንዲህ ያለ ችግር ያጋጠማቸው ሰዎች ቀስ በቀስ ሥራቸውን በሌላ አማራጭ እየተከ ከፈጣሪ ጋር ያላቸውን ዘምድና ከማጠናከር ውጭ ባሉበት ሁኔታ ጥሩ መንፈሳዊ ሰው መሆን የሚችሉበት ምንም ዓይነት መንገድ
የለም።ከዚህ ሁሉ የሚከፋው ደግሞ «ካፈርኩ አይመልሰኝ» እንደሚባለው ሥራቸው በቅዱስ መጽሐፍ የተወገዘ ሆኖ ሳለ አንድ ጊዜ ስለገቡበት ብቻ ሥራቸውን መጽሐፍ ቅዱስ እንደማይቃወመው አድርገው ለማስረዳት የሚሞክሩ ሰዎች መኖራቸው ነው፡፡ ተሳስቻለሁ ! እኔ በሄድኩበት እንዳትሄዱ ብሎ ማስረዳት አንዱ መንፈሳዊነት ሆኖ ሳለ ሌሎችም ተጨምረው እንዲሳሳቱ «ሥራዬ ልክ ነው» ማለት «እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል» የሚል ዓይነት የምቀኝነት ሥራ ነው፡፡ አንተ ወጣት የምትማረው ትምህርትና የወደፊት የሥራ መሰማሪያህ በመንፈሳዊ ሕይወት ለአንድ ክርስቲያን መኖር እስከሚገባው ድረስ ዘልቆ ከመሄድ የሚያግድህ እንዳይሆንብህ ትጠነቀቃለህ? ከሆነ ደህና ካልሆነ ግን ለነፍስህ ምንም እንዳላሰብክላት እወቅ፡፡ ስለ ወደፊት መንፈሳዊ ማንነቱ ምንም የማያስብ ሰውስ እንዴት ክርስቲያን ሊባል ይችላል?

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ዐሥር ክፍል ሦስት
.................................................

በትምህርት መኖር «ጥበቃ» ነው!
ቦዘኔ አእምሮ ብዙ ክፉ ሐሳቦችን ሲወልድ ይውላል።«ሥራ ፈት አእምሮ የሰይጣን ቤተ ሙከራ ነው» መባሉ ተገቢ ነው።ሰዎች ጊዜያቸውን ለመልካም ነገር ካልተጠቀሙበት ለክፉ ተግባር የሚያወሉት የተትረፈረፈ ጊዜ ይኖራቸዋል። በመልካም ተግባር! ወይም በመማር የተጠመዱ ከሆኑ ግን ክፉ ሐሳብ ቢፈጠርባቸው እንኳን ከጊዜ እጥረት የተነሣ ሳያከናውኑት ይቀራሉ፡፡
ለብዙ ወጣቶች የሥነ ምግባር ጉድለቶች ተጠቃሽ የሚሆነው ቦዘንተኝት ወይም ሥራ አጥነት ነው።የእነዚህ ሰዎች አእምሮ በሥራ ባለመጠመዱ ምክንያት ወደ ልዩ ልዩ ክፉ ጐዳና ይተማል፡፡ የአብዛኞቹ ሰካራሞች፣ የጫት ቃሚወች፣ የሲጃራ አጫሾች፣ የአደንዛዥ ዕፀዋትና መድኃኒት ሱሰኞች ሕይወት ቢፈተሽ ለሥራና ለትምህርት ግድ የለሾች መሆናቸውን መረዳት ይቻላል።ይህ ማለት ግን ከሠራተኞችና ከምሁራን ይህን በመስለ ርካሽ ተግባር የተመረዙ የሉም ማለት አይደለም።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሐዋርያት ተባበሩ፤
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ፤
ቃሉን አስተማሩ።

ካረገ በኋላ በአስረኛው ቀን፤
ወደ አለም ላከው ጰራቅሊጦስን።

በዝግ ቤት ውስጥ ቆዩ ቀኑን ሲጠብቁ፤
የተሰጣቸውን ተስፋውን እስኪያውቁ።

ቀኑም ደረሰና በሃምሳኛው እለት፤
ተሰብስበው ሳሉ በአንድነት ፀሎት፤
መንፈስ ቅዱስ ታየ በነደ እሳት።

ያ የተነገረው ያ የተስፋ ቃል፤
ወረደ ከሰማይ በእሳት አምሳል።

ጴጥሮስ አሳመነ ሶስት ሺ ነፍሳት፤
ያን ጊዜ ገሊላ በሰጠው ትምህርት።

ከሶስት አካል አንዱ መንፈስ ቅዱስን፤
ልኮ አናገራቸው ሁሉን በልሳን።

ሐዋርያት ተባበሩ፤
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ፤
ቃሉን አስተማሩ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ስለተባለበትና ተስፋ በተሰጣቸው በኀምሳኛው ቀን ወርዶ ስለ ሠራው ሥራ እንዲህ በማለት ያብራራል። ‹‹ወመንፈስ ቅዱስኒ ኢተሰምየ ጰራቅሊጦስሃ ዘእንበለ አመ ይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ እፌኑ ለክሙ ካልአ ጰራቅሊጦስሃ። ጰራቅሊጦስ ብሂል ናዛዚ ብሂል በነገረ ጽርዕ ……መንፈስ ቅዱስም ጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሌላውን አጽናኝ እልክላችኋለሁ›› ከማለቱ በፊት ጰራቅሊጦስ አልተባለም ጰራቅሊጦስ ማለት በጽርዕ ቋንቋ አጽናኝ ማለት ነው ስለምን አጽናኝ ተባለ ደቀ መዛሙርቱ ወልድ ካረገበት ቀን ጀምሮ ጰራቅሊጦስ እስከ ወረደበት ቀን ድረስ ያለቅሱ ነበረና ስለዚህም ወልድ መንፈስ ቅዱስን ጰራቅሊጦስ አለው። የስሙ ትርጓሜ ግን አስቀድመን እንደተናገርነው አጽናኝ ማለት ነው። (ዮሐ. ፲፬፥፲፭)

በዓለ ጰራቅሊጦስ የሚከበረው ርደተ መንፈስ ቅዱስን መሠረት በማድረግ በመሆኑ ምክንያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል ነው፤ በዕለቱም ኢየሩሳሌም በተባለችው ቤተክርስቲያን ስለመጽናት፤ ከግለኝነት ይልቅ መንፈሳዊ አንድነትን ስለማስቀደም እና ስለመጸለይ እንማራለን፡፡
በዓለ ትንሣኤውን በቸርነቱ በሰላም እንድናሳልፍ ፈቅዶ እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ጠበቀን፣ አሁን ደግሞ በጾም፣ በጸሎት ሆነን እርሱን የምናመሰግንበትን ወቅት ስላመጣልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁን፤ አሜን፡፡
ምንጮች፤

መዝገበ ታሪክ፣ ክፍል ፪፤ መምህር ኅሩይ ኤርምያስ፤ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም፤ ገጽ ፹፬-፹፭፡፡

መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፲፰ ቀን፣ መጽሐፈ ምሥጢር፡፡

መጽሐፈ ግጻዌ፡፡

ማኅቶተ ዘመን፣ መምህር በሙሉ አስፋው፤ ፳፻፩ ዓ.ም፤ ገጽ ፻፺፭-፪፻፬፡፡


ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…
Subscribe to a channel