በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
ጭፍሮቹም በዚሁ ዕለት ሌሊት የክብር ባለቤት የሆነውን ጌታችንን ይዘው ወደፊት፣ ወደኋላ እየጐተቱ፣ እያዳፉ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ወስደውታል።
መዝሙረ ዳዊት ምንባባት
በአንድ ሰዓት፡- "አፉ ከቅቤ ይልቅ ለዘበ ፤ በልቡ ግን ሰልፍ ነበረ ፤ ቃሎቹም ከዘይት ይልቅ ለሰለሱ ፤ እነርሱ ግን እንደ ተመዘዘ ሰይፍ ናቸው" (መዝ፶፬(፶፭)፡፳፩)
በሦስት ሰዓት፡- "የጻድቅን ነፍስ ያደቡባታል፤ በንጹህ ደምም ይፈርዳሉ፡፡"(መዝ፺፫(፺፬):፳፩)
በስድስት ሠዓት፡- "የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁና በዙሪያው ፍርሃት ነበረ በላዬ በአንድነት በተሰባሰቡ ጊዜ ፤ ነፍሴን ለመንጠቅ ተሰባሰቡ፡፡"(መዝ፴ (፴፩):፲፫
በዘጠኝ ሰዓት፡- "እግዚአብሔር እረኛዬ ነው ፤ የሚያሳጣኝም የለም ፤ በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፡፡" መዝ፳፪(፳፫):፩-፪
ኅጽበተ እግር ሲጀመር ደግሞ "በሂሶጵ እርጨኝ እነጻማለው እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለው፡፡" (መዝ፶:(፶፩):፯)
በመጽሐፈ ግብረ ሕማማት፡- "ከዚህ በኋላ የእግር እጥበት ሥርዓት ነው ፤
ዲያቆን ሁለት ኩስኩስቶች ያቅርብ በውስጣቸውም ውኃ ይምላባቸው አንዱ
ለእጅ መታጠቢያ እንዲሆን ካህኑም እስከ መጨረሻው ጸሎተ አኮቴት ይበል ፤
ጸሎተ ዕጣኑንም ደግሞ ዕጣንን ያሳርግ ፤ ስለ ሰላም ስለ ሊቀ ጳጳሳት ስለ ማኅበር ይጸልይ፡፡ ሕዝቡም ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን ይበሉ፡፡ አቡነ ዘበሰማያትም ይበሉ ፤ ኀምሳኛውንም የዳዊትን መዝሙር ይበሉ፡፡" (ግብረ ሕማማትገጽ፭፻፵፪)
"ከዚህ በኋላ ሕዝቡ ይነሱ አርባ አንድ ጊዜ ኪራላይሶን ይበሉ ካህኑም መስቀል ይዞ ውኃውን ሦስት ጊዜ አሐዱ አብ ቅዱስ (ልዩ ክቡር ንጹሕ ጽኑዕ ነው) ፤ አሐዱ ወልድ ቅዱስ (ልዩ ክቡር ንጹሕ ጽኑዕ ነው) ፤ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ (ልዩ ክቡር ንጹሕ ጽኑዕ ነው) እያለ ሦስት ጊዜ ውኃውን ይባርክ፡፡" (ግብረ ሕማማት ገጽ ፭፻፶፱)
"ከዚህ በኋላ ካህኑ እንደ ሥርዓቱ ኅጽበተ እግርን ያድርግ (ይፈጽም) ከዚህ በኋላም ጥቁር ልብስ ለብሰው ሥርዐተ ቅዳሴውን ይጀምሩ የቃጭል ድምጽንም አያሰሙ፡፡" (ግብረ ሕማማት ገጽ፭፻፷፩)
በአሥራ አንድ ሰዓት፡- "በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ ጽዋዬም የተረፈ ነው" (መዝ፳፪(፳፫):፭-፮)
የአይሁድ ካህናት ያለበደል እና ያለጥፋት ንጹሑን ክርስቶስን ለመስቀል ሞት እንዲደርስ በጭካኔ በዕለተ ሐሙስ ከሌሊቱ 3፡00 ጀምሮ ብዙ መከራ አደረሱበት ፤ እጅጉን ተሰቃየ ፤ እያዳፉ አንዳች ሳይናገር አሰቃዩት ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ በትንቢት መነጽር የተመለከተውን የጌታችንን ስቃይ እንዲህ ሲል ያመጣዋል፡-
"ተጨነቀ ተሠቃየም አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም፡፡ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? ከክፉዎቹም ጋር መቃብሩን አደረጉ..."(ኢሳ፶፫:፩-፰)
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን!
ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🩸"በዕፀ መስቀል ላይ"🩸
በዕጸ መስቀል ላይ በዚያ አደባባይ/2/
አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ ተንገላታህ ወይ
አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ መከራ አየህ ወይ
አዝ
መስቀል አስይዘው ኪርያላይሶን
ወደ ጎልጎታ " "
ሲገርፉህ ሲያዳፉህ " "
ስትንገላታ " "
አዝ
ያንን አቀበት ኪርያላይሶን
ያንን ዳገት " "
ጀርባህ ተገርፎ " "
ስትቃትት " "
አዝ
አንተን እያዩ ኪርያላይሶን
ሴቶች ሲያለቅሱ " "
እናቶች ቀርበው " "
ላብህን ዳበሱ " "
አዝ
መስቀል አስይዘው ኪርያላይሶን
እንዲያ ሲያዳፉህ " "
የቀሬናው ሰው " "
ስምኦን አገዘህ " "
በዘማሪት ማርታ ኃይሉ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት
ረቡዕ
በዚህች ዕለት ያስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሰጠውና ሌሎችም ይታሰባሉ። በቅዱስ ማቴዎስና በቅዱስ ማርቆስ አመዘጋገብ መሠረት በዕለተ ረቡዕ የሚከተሉት ሦስት ነገሮች ተፈጽመዋል፦
፩. ምክረ አይሁድ ይባላል
የካህናት አለቆች፣ የሕዝብ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ፈሪሳውያን በጌታችን ላይ ተማክረዋል፤
፪. የመልካም መዓዛ ቀን ይባላል
ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ቤት ሳለ አንዲት የተጸጸተች ሴት ሽቱ ቀብታዋለች፡፡
፫. ከዳተኛው ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመስጠት ከጸሐፍት ፈሪሳውያንና ከካህናት አለቆች ዘንድ ሠላሳ ብር ለመቀበል ተስማምቷል፡፡
የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሹማምት በጌታችን ላይ ይሙት በቃ ለመወሰን የሰበሰቡት ሸንጐ ‹ሲኒሃ ድርየም› ይባላል፡፡ በዚህ ሸንጐ ላይ በአብዛኛው የተሰየሙት ሰዱቃውያን ሲኾኑ ሌሎቹ ደግሞ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ነበሩ፡፡
ሸንጐው በአጠቃላይ ሰባ ሁለት አባላት የነበሩት ሲኾን የሚመራውም በሊቀ ካህናቱ በቀያፋ ነበር፡፡ በዕለቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት ይዘው እንደሚገድሉት አይሁድ በዚህ ሸንጎ መክረዋል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳም ጸሐፍት ፈሪሳውያንና የካህናት አለቆች በጌታን ላይ የነበራቸውን ጥላቻ ያውቅ ስለነበር ‹‹ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ? እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤›› በማለት ጌታችን አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተስማቷል፡፡
ጌታችን ያስተምር በነበረበት ወቅት የአስቆሮቱ ይሁዳ ከምእመናን ለሚገባው ገንዘብ ሰብሳቢ (ዐቃቤ ንዋይ) ነበር፡፡ ከሚሰበሰበው ሙዳየ ምጽዋት ለግል ጥቅሙ እየቀረጠ የማስቀረት የእጅ አመል ነበረበት፡፡ ይሁዳ ፍቅረ ንዋይ እንደሚያጠቃው ድብቅ አመሉ ጎልቶ የወጣው ጌታችን በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው ውድ የኾነ ሽቱ በቀባችው ጊዜ ነው፡፡ በዚያች ዕለት ይሁዳ የተቃውሞ ድምፅ ካሰሙት አንዱ ነበር፡፡
‹‹ይህ ሽቱ ተሽጦ ለድሆች ቢሰጥ መልካም ነበር፤›› በማለት ያቀረበው አሳብ ‹‹አዛኝ መሳይ ቅቤ አንጓች›› እንደሚባለው ነበር፡፡ ሽቱ ሲሸጥ የሚያገኘው ጥቅም አለ፤ ሽቶው በጌታችን እግር ሥር ከፈሰሰ ለእርሱ የሚተርፈው የለም፡፡
ይሁዳ ተቆርቋሪ መስሎ ያቀረበው አሳብ ተቀባይነት በማጣቱም ማኩረፊያ ያገኘ
መስሎት በቀጥታ ከካህናት አለቆች ዘንድ ሔዶ ጌታንን በሠላሳ ብር ለመሸጥ ተዋዋለ፡፡ ይህ ታሪክም በሦስቱ ወንጌላት ውስጥ በሚከተሉት ምዕራፎች ተመዝግቦ እናገኛዋለን፤ ማቴ. ፳፮፥፫-፲፮፤ ማር. ፲፬፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፪፥፩፮፡፡
የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ተምሯል፡፡ በረከተ ኅብስቱን ተመግቧል፡፡ ልዩ ልዩ ተአምራት በጌታችን እጅ ሲደረጉ ዅሉ ተመልክቷል፡፡
ጌታችንም ከሌሎች ሐዋርያት ሳይለየው እግሩን አጥቦታል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳ ግን ለሐዋርያነት የጠራውን፣ ተንበርክኮ እግሩን ያጠበውን ጌታ ለሞት አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ‹‹የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሔዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት!›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፮፥፳፬)፡፡ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ዘንድ ፍቅሩን ገንዘብ ሲያደርጉ ይሁዳ ግን እርግማንን ነው ያተረፈው፡፡ ‹‹ገንዘብ የኃጢአት ሥር ነው፤›› ተብሎ አንደ ተነገረ የኃጢአት ሥር የተባለው ገንዘብ የክርስቲያኖችን ሕይወት ያዳክማልና ምእመናን እንደ ይሁዳ በገንዘብ ፍቅር እንዳንወድቅ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሰው ‹‹ይህን ዓለም ቢያተርፍ ነፍሱን ከጐዳ ምን ይጠቅመዋል?›› ተብሎ የተነገረውን ቃል ልብ ማለት ጠቃሚ ነው፡፡
ክርስቲያን ነን በማለት የክርስትናውን ስም በመያዝ እምነታቸውን፣ የቆሙበትን ዓላማ በመገንዘብ የሚለውጡ ሰዎች ዛሬም እንደ ይሁዳ ጌታችንን እየሸጡት እንደ ኾነ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ለድሆች መመጽወት ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡
ዳሩ ግን በድሆች ስም የሰውን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋል እጅግ የከፋ ኃጢአት ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ለገንዘብ ብለው ድሆችን ለረኃብ ለችግር ባልንጀራቸውን ለመከራ እና ለሞት አሳልፈው ሲሰጡ ምንም አይጸጽታቸውም፡፡
እውነተኛ ክርስቲያኖች ግን ሕይወታችንን ለገንዘብ ፍቅር ሳይኾን ለእምነታችንና ለባልንጀራችን አሳልፈን መስጠት ይኖርብናል፡፡ በፍቅረ ንዋይ ተጠምደን ሰዎችን አሳልፎ በመስጠት ለአይሁዳዊ ሸንጐ ምቹ ኾነን መገኘት እንደሌለብን መገንዘብ አለብን፡፡
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን!
ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት-ማክሠኞ
✅የጥያቄ ቀን
✅የትምህርት ቀን
@Ethiopian_Orthodox
🩸"ዓለምን ለማዳን"🩸
ዓለምን ለማዳን የተሰቀለው
ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው /፪/
ጌታችን ተሰቅሎ ሲያዩት መላእክት
በዝማሬ ፈንታ አለቀሱለት
ሚካኤል ዝም አለ ገብርኤል ገረመው
አምላኩን እርቃኑን ተሰቅሎ ስላየው
አዝ=====
ነፍሱን ለወዳጁ የሚሰጥ ቢገኝም
ለጠላቱ የሚሞት በጭራሽ አይኖርም
ጠላቶቹ ስንሆን ለእኛ የሞተው
በመስቀል የዋለው በፈቃዱ ነው
አዝ=====
እውሩን ቢያበራ የሞተ ቢያስነሳ
በመመስገን ፈንታ ሆነበት ወቀሳ
ከመከራ ሊያድን ቢገለጥ በስጋ
የእሾህ አክሊል ደፋ ቀኝ ጎኑ ተወጋ
አዝ=====
የጸሎተ ሐሙስ ዕለት እራት የሆነው
አርብ በመስቀል ላይ የተሰቀለው
ፍቅር አስገድዶት ለእኛ የሞተው
መልካሙ እረኛችን መድኃኔዓለም ነው /፪/
በዘማሪት ፋንቱ ወልዴ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት
ሰኞ
፩. መርገመ በለስ (በለስ የተረገመችበት) ዕለት ነው።
አንድምታ፡
ወንጌሉ እና ግብረ ሕማማቱ ላይ እንደተገለጸው
☞በለስ የቤተ እስራኤል እና ፍሬ የሃይማኖትና የምግባር ምሳሌ ናቸው ፡፡ ጌታችን ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈለገ፤ አላገኘም፡፡ ስለዚህም እስራኤል ሕዝበ እግዚአብሔር መባልን እንጂ፣ ነቢይነት፣ ካህንነት፣ መሥዋዕት አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ በመርገሙ ምክንያት ትንቢት ክህነት መሥዋዕት ከቤተ እስራኤል ጠፉ፡፡
☞በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት "ኦሪትና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽር አልመጣሁም፡፡" በማለት ፈጸማት ፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና ፍሬ ባንቺ አይሁን አላት ፤ ድኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በአዲስ ኪዳን የድኅነት ዘመንም ተተካች፡፡
☞በለስ ኃጢአት ናት ፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ "በአንቺ ፍሬ አይገኝ" ማለቱም
"በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር" ማለት ነው፡፡ በለሷም ስትረገም ፈጥና መድረቋ፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በአምላካችን እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡
፪. አንጽሖተ ቤተመቅደስ የተከናወነበት ዕለት ነው።
ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው "ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች… እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት" ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፣ ገርፎም አስወጣቸው...'' እንዲል። (ማቴ ፳፩፡፲፫)
ምስጢሩ :-
☞ቤተመቅደስ የሆንን እኛ የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ አንጽሖተ ቤተመቅደስ የተፈጸመበት ሰኞም በማለት ሊቃውንት ይገልጹታል።
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን!
ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
እብኖዲ፣ ትስቡጣ ፣ ማስያስ ፣ ታኦስ ፣ ናይናን እና ኪርያላይሶን ትርጉማቸው ምንድን ነው???
@Ethiopian_Orthodox
በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ ባዕድ ቃላት
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡
ኪርያላይሶን ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዚእነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡ ፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡
ናይናን-የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡
እብኖዲ-የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው።
ታኦስ-የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡
ማስያስ-የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው።
ትስቡጣ-«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው።
አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡
አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ – ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው።
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ-የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡
@Ethiopian_Orthodox
የ፵፩/41 ስግደት ምን እየተባለ ይሰገዳል?
አንድ ክርስቲያን በጾም ጊዜ ከጸሎት በኋላ የጌታን መከራና ለእኛ ያሳየውን ፍቅር እያሰበ ከሐጢያቱ ብዛት ከአምላኩ ይቅርታ ያገኝ ዘንድ ፵፩/41 ጊዜ እንዲህ እያለ ይስገድ:-
፲፪/12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
፲፪/12 ጊዜ በእንተ እግዝዕትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ
፲፪/12 ጊዜ ኪርያላይሶን
፭/5 ጊዜ ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት፣አዴራ፣ሮዳስ(አምስቱ የጌታ ችንካሮች)
እነዚህም ቢደመሩ ፵፩/41 ይሆናሉ፡፡
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሥርዓተ ጸሎት ዘሰሙነ ሕማማት ፩
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🩸 ሰሙነ ሕማማት 🩸
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከዕለተ ትንሣኤ በፊት ያለውን ሳምንት "ሰሙነ ሕማማት" በማለት ታከብረዋለች። "ሕማማት" የሚለው ቃል "ሐመ" ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን የዚህ ስያሜ መነሻም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መከራው፣ሕማሙና ሞቱ የሚዘከርበት ከአዳም እስከ ክርስቶስ የነበረው የዓመተ ፍዳ የዓመተ ኩነኔ ወቅትም የሚታሰብበት ስለሆነ "ሰሙነ ሕማማት" ተብሏል።
በዚህ ልዩ በሆነ ሳምንት ካህናትና ምእመናን በነግህ፣ በሠልስት፣ በቀትር፣ በተሰዓትና በሠርክ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመጓዝ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማተ መስቀል የሚያዘክረውን ምዕራፍ ከቅዱሳት መጻሕፍት በማንበብና በመጸለይ ሕማሙንና ሞቱን ያዘክራሉ፤ ቅዱስ ያሬድ በመጨረሻው ሳምንት በየዕለቱ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተፈጸመውን ነገረ መስቀል በተመለከተ ያዘጋጀውን መዝሙር ይዘምራሉ፤ አብዝተው ስግደትን ይሰግዳሉ፡፡
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ሆኖ ሳለ ሕማማትን መቀበሉ ስለምን ነው ቢሉ፡-
☞ፍቅሩን ለመግለጽ፡- ለፍጥረቱ ይልቁንም ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅሩን ይገልጽ ዘንድ(ዮሐ ፫÷፲፮) ምንም በደል ሳይኖርበት ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ(ዮሐ ፲፭÷፲፫)
☞የኃጢአትን ፍዳ ከባድነት ለማሳየት፡- እርሱ ጻድቅና ንጹህ ሆኖ ሳለ ሰውን ወዶ ይህን ያህል መከራ ከተቀበለ ሰው ኃጢአት በመሥራት ቢመላለስ የኃጢአትን ውጤት ከባድነት ያስተምረናል፡፡ ራሱ ጌታችንም ከጲላጦስ ግቢ እስከ ቀራንዮ አደባባይ መስቀል ተሸክሞ ሲንገላታ ላለቀሱለት የኢየሩሳሌም እናቶች <<በእርጥብ እንጨት የሚያደርጉ ከሆነ በደረቀውስ እንዴት ይሆን>> በማለት ገልጾለታል፡፡ (ሉቃ ፳፫÷፳፪)
☞ቤዛ ለመሆን፡- በኦሪት ዘመን ሰዎች ለሠሩት ኃጢአት ኃጢአታቸውን ለማስተሰርይ ነውር የሌለበትን በግ ቤዛ እንዲሆናቸው መስዋዕት ያቀርቡ ነበር ይህ ግን ከአዳም የተሰወረውን ኃጢአት ማስቀረት ስላልቻሉ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሁኖ መጣ <<እነሆ የእግዚአብሔር በግ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ>>(ዮሐ ፪÷፳፮)
☞እርግማናችንን ለማስቀረት፡- <<በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፏልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን>>(ገላ ፫÷፲፫) በማለት ቅዱስ ጳውሎስ እንደጻፈው እርግማናችንን ተሸክሞ ሕማማትን መቀበሉ የቀድሞው ኃጢአት ምንም ያህል ከባድ ቢሆን በታላቅ መስዋዕትነት እንዳስቀረልን ሊያስተምረን ነው፡፡ (ዘዳ ፳፩÷፳፫)
☞የድኅነታችንን ክቡርነት /ውድነት/ ሊያስረዳን ፡- ድኅነታችንን የእግዚአብሔር ልጅ ደሙን እስኪያፈስለት ድረስ እጅግ ውድ መሆኑን ሊያስተምረን፡፡ (ራዕ ፭÷፱)
@Ethiopian_Orthodox
ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎች የዐቢይ ጾም ሳምንታት ልዩ የሚያደርገው ሥርዓት አለ፡፡
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰሙነ ሕማማት :
ሊሰሩ ያልተፈቀዱ በርካታ ናቸው:: በመስቀል መባረክ፣ መሳቅ፣ መሳሳም፣ ከሴት ጋር መገናኘት(ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 593)፣ ኑዛዜ መፈጸም ፈጽሞ የተከለከለ ሲሆን የ5500ው የጨለማ ዘመን መታሰቢያ በመሆኑ መንበሩ በጥቁር ልብስ ይሸፈናል ካሕናትም ጥቁር ይለብሳሉ:: በዚህ ሳምንት ለሞተ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይለትም፣ ክርስትናም እንዲሁ አይፈጸምም:: "እግዚአብሔር ይፍታህ" አይባልም(ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 600)፤ ሳምንቱ የሚታሰበው ሕማሙን ሞቱን በማሰብና በስግደት ነው:: የግዝት በዓላት(12፣21 እና 29) እንኳ ይሰገድባቸዋል:: የዚህ ሳምንት ጾም የቻለ ሁለት ሁለት ቀን ያልቻለ እስከ ጀንበር ግባት ድረስ ነው:: ምግቡም ቆሎ ዳቦ የላመ የጣመ ያልሆነ ደረቁን በበርበሬ ነው፤ መጠጡም ንጹህ ውኃ ነው:: ጠጅ ያንቆረቆረ ጮማ የቆረጠ እድል ፈንታው ጽዋእ ተርታው በጌታ ሞት ከተደሰቱት ከአይሁድ ጋር ነው።(ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 578)
ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም። ጸሎቱ ውዳሴ ማርያም፣ አንቀጸ ብርሃን፣ መልክአ ሕማማትና መዝሙረ ዳዊት ናቸው።
ስናጠቃልለው የተከለከሉ ነገሮች ምን ምን ናቸው ካሉ፡
1. መሳሳም
2. ሩካቤ ሥጋ ማድረግ
3. መስቀል ማሳለም እና መሳለም
4. ክርስትና ማስነሣት
5. ለሙታን ፍትሐት ማድረግ
6. ክህነት መስጠት
7. የላመ የጣመ ምግብ መመገብ
8. መሳቅ መጫወት መጨፈር
9. አብዝቶ ጠግቦ መመገብ
10. መስከር ወዘተ ናቸው፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሣዕና ይከናወናሉ፡፡
@Ethiopian_Orthodox
የሰሙነ ሕማማት ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች:
፩. አለመሳሳም ፡- ከላይ እንዳየነው በሰሙነ ሕማማት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች መስቀል እንደማይሳለሙት ሁሉ መጨባበጥ፣ መሳሳምን የትክሻ ሰላምታ መለዋወጥን አይፈጽሙም፡፡ ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት አይሁድ ጌታን ለመስቀል ሰኞ እና ማግሰኞ መከሩ አልሰመረላቸውም፡፡ ምክራቸው የተፈጸመው ረቡዕ ነው፡፡ ስለዚህ አይሁድ እያንሾካሾኩ እንስቀለው ፤እንግደለው ብለው ይማከሩ ነበር፡፡ በዘመነ ፍዳ ወቅት ሠላምና ፍቅር አለመኖሩን የሚገልፅልን በመሆኑ ያንን ለማስታወስ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡
፪. ሕፅበተ እግር፡- ጌታ በፍጹም ትህትና የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበበት፣ ከሐዋርያት ጋር ግብር የገባበትና የክርስትና ህይወት ማሕተም የሆነውን ምስጢረ ቁርባን ያከናወነበት ዕለት ነው። ጸሎተ ሐሙስ ሕፅበተ እግር ጌታችን በዚህ ዕለተ እናንተ ለወንድማችሁ እንዲሁ አድርጎ ለማለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት የተሰጠ ምሳሌ ነው፡፡
፫. ጉልባን እና ቄጠማ ፡- ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጀና የጸሎት ሐመስ እለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብጽ ተሰደው በሚነጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ያን ጊዜ ያልቦካው ሊጥ እያጋገሩ ቂጣ መብላት ንፎሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበር፡፡ ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና ጉልባን በማዘጋጀት በዓል ይታሰባል፡፡ [በጸሎተ ሐሙስ ዕለት በስፋት የምናየው ይሆናል።]
ቄጠማ (ቀጤማ)፡- በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱን ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለ አዋዲ/ እየመቱ "ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሳኤሁ አግሃደ" የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠ እና ትንሳኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመኑም ለቤተ ክርስቲን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ ቀጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሰሩበትን ድርጊት የሚያስተውስ ነው፡፡ በዚህ እለት ልብስ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲቆናትን ቄጠማ ተሸክመው ቃጭል ሲቃጭሉ መታየታቸው እለተ ትንሳኤውን ለምዕመናን ትልቅ ብስራት ነው።
ሰ) ድንግልናን ጠብቆ መኖር ጋብቻ ሳይዘገይ በጊዜው እንዲፈጸም ይገፋፋል፡፡ ምክንያቱም ማንኛውም ጤናማ ሰው የተቃራኒ ፆታ አቻውን የመሻት ዝንባሌ አለው። ታዲያ ይህ በውስጡ የሚገኝ ሩካቤ መሻትና ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ሕገ ወጥ ሩካቤን ላለመፈጸም (ድንግልናውን ጠብቆ ለመኖር) የሚያደርገው ጥረት የሚታረቁለት ሲያገባ ብቻ በመሆኑ ድንግልናውን ጠብቆ እስከ ጋብቻ ለመቆየት ዓላማ ያለው ሰው በውስጡ ያለውን የፍትወት ግፊት ለማብረድ ሲል ቶሎ ብሎ ማግባት እንዳለበት ይሰማዋል፡፡
ድንግልናን ስለመጠበቅ ግድ የሌላቸውና ቅድመ ጋብቻ የሚደረግ ዝሙትን የተለማመዱ ሰዎች ግን ጋብቻን እንደ መታሰር ስለሚቆጥሩትና በውስጣቸው ያለውን የፍትወት ግፊት እንደ ፈቃዱ እያስተናገዱት በመሆኑ ወደ ጋብቻ የሚገፋቸው ውስጣዊ ኃይል ስለሚቀንስ ከማግባት ይቦዝናሉ። ስለዚህ በዘማዊያን ዘንድ ዘግይቶ ማግባት የተለመደ ነው፡፡ ድንግልናቸውን ጠብቀው የኖሩ ሰዎች ግን ወደ ጋብቻ ለማምራት ቆራጦች በመሆናቸው ውሳኔያቸው እጅግ ፈጣን ነው።
ጋብቻ ለመፈጸም የሩቅ ቀጠሮ ያላቸው ሰዎች እንኳን ከጋብቻ በፊት ምንም ዓይነት ሩካቤ ማድረግ እንደማይፈቀድላቸው ሲያውቁ የጋብቻ ቀጠሮአቸውን በማሳጠር የአግቡኝ ሮሮ የሚያሰሙት በዚህ ምክንያት ይመስላል።
ሸ) ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ሩካቤ ሥጋ የጋብቻን ቀነ ቀጠሮ እንዲራዘም ከማድረጉም በላይ ለመለያየትም በር ከፋች ነው። የተጋቡ ሰዎች ሩካቤ ለመፈጸም የማይችሉበት ሁኔታ ሲፈጠር ለመለያየት እንደሚገፋፉ ሁሉ ያልተጋቡም ሰዎች ሩካቤ መፈጸማቸው እንዲለያዩ ዓይነተኛ ምክንያት ይሆናል።እንደ አምኖን የሚሹትን ሲያገኙ «ለዚህ ሴትነትሽ ነውን?» የሚሉ ወንዶች ቁጥር እጅግ በርካታ ነው። 1ኛ ሳሙ 13÷14-16
ቀ) አስቀድሞ የምንኩስና ዝንባሌ ያለው ስው ከጋብቻ በፊት ሩካቤ መፈጸሙ የበለጠ ወደ ምንኵስና እንዲገፋፋ ይሆናል፡፡ ይህ አካሄድ ግን ለፈተና የሚመጣ እንጂ ለመልካም አይደለም፡፡ በእግዘአብሔር ፈቃድ የሚሆን ምንኩስና አይሆንምና፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው በመጀመሪያ የሥጋ ፈተና ጨርሶ የራቀለት ይመስልዋል።በመቀጠልም ቢመነኩስ ሥርየት እንደሚያገኝ ይሰማዋል፡፡ ከዚህ ይልቅ ግን የሌላውን ሕይወት አበላሽቶ መመንኮስ እንደማይገባው ቢሰማው የተሻለ ነበር፡፡ ለራሱም ቢሆን ጣዕመ ዓለምን ባይቀምስ መልካም ነበር፡፡ ለምንኩስናውም ይረዳው ነበር:: ነገር ግን ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ሰይጣን በስሜት እየነዳ እንዲመነኩስ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ከጋብቻ በፊት የሚፈጸም ሩካቤ በምንም መልኩ ጠቀሚ አይደለም:: ለምንኩስና መገፋፋቱም አሉታዊ እንጂ አዎንታዊ ገፅታው አይደለም።
በአጠቃላይ ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ግንኙነትና ድንግልናን ማጣት በባልና በሚስት መካከል ደስታን፣ መተማመንን፣ ፍቅርን ይቀንሳል፡፡ መጸጸትንና ሰላም ማጣትን በመካከላቸው ይፈጥራል፡፡ ለልዩ ልዩ በሽታዎችና ላልታሰበበት እርግዝና ከዚያም አልፎ ለውርጃ ያጋልጣል:: ያለ ጋብቻ መዘግየትን ያመጣል:: አለመጽናት” አለመታገሥን፣ አለመታመንንና የመሳሰሉትን ያመለክታል:: ብዙ መንፈሳዊ ጸጋዎችንም ያሳጣል፡፡ ያለ አግባብ ለመመንኮስ ወይም ደግሞ ለባሰ የዝሙት ተግባር ሊገፋፋም ይችላል፡፡
በቀጣይ ምዕራፍ ስምንት ክፍል አምስት:
👉 ድንግልናን የሚያሳጡ አደገኛ ወቅቶች፣ቦታዎችና አጋጣሚዎች በሚል ይቀጥላል....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
«ይህንንም ለራሳችሁ ጥቅም እላለሁ፣ በአገባብ እንድትኖሩ ሳትባክኑም በጌታ እንድትጸኑ ነው እንጂ ላጠምዳችው ብዬ አይደለም »1ቆሮ7÷35
ሀ) የመጀመሪያው በድንግልና የመኖር ጥቅም «በአገባብ መኖር» ነው:: «በአገባብ መኖር» ሕግና ሥርዓትን እየፈጸሙ በአግባቡና በሥነ ሥርዓት¸ መኖር ማለት ነው።በድንግልና መኖር አግባብ ነው፡፡ዝሙት ግን ግብረ ገብነትን ማጣት ነው፡፡ድንግልናን ጠብቆ ለመኖር የሚደረገው ትግል ሕጋዊ ሰው ሆኖ መኖርን ያለማምዳል።ታዲያ ድንግልናን መጠበቅ እንደ አሸዋ ሽክም ከከበደውና ንጽሕናን ከናቀ ከዚህ አመንዝራ ትውልድ ግብረ ገብነትን መጠበቅ ከዝንብ ማር እንደ መጠበቅ አይሆንምን?
ለ) ሁለተኛው በድንግልና የመኖር ጥቅም «ሳይባክኑ» መኖር ነው፡፡ በድንግልና የሚኖር ሰው አይባክንም ወዲህና ወዲያ አይልም።ዝሙት ግን መባከን ነው:: ለምን ቢባል ዝሙተኛ ኃጢአቱን ለመደበቅ፣ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ምን ያመጣብኝ ይሆን? በማለትና ዝሙቱ ቢታወቅ በሌሎች ዘንድ ምን ሊባል እንደሚችል በማሰብ በስጋትና በመባከን ይኖራል፡፡ ዝሙት ያባክናልና፡፡ በተጨማሪም ዛሬ ዛሬ በዝሙት ጠንቅ በሚመጣ በሽታ ተይዤ ይሆን” ከማለት የሚበልጥ መባከን ምን አለ?
ቅዱስ ዳዊት «ወተአውከት እምመዓት ዓይንየ» በማለት ተናግሯል፡፡ እንዲህም ማለቱ «ሴቶችና ሕፃናት ሲቆጧቸው ከእሁን አሁን ዱላ ጣሉብን በማለት ዓይናቸው እንደሚባክነው እኔም ጕልማሳ ገድዬ በጎልማሳ ሚስት በማመንዘሬ ምን ትቀጣኝ ይሆን? በማለት ባከንኩኝ› ለማለት ነው:: መዝ6፥1-3 ስለዚህ ዝሙት በዚህ ብቻ ሳይሆን በሌላም በብዙ መንገድ ሰውን ሲያባክነው ይታያል:: ድንግልናን ለመጠበቅ የሚጣጣር ሰው ግን ዝሙት ከሚያመጣው መባክን ፈጽሞ የዳነ ነው:: መዝ6 ፥ 2-3
ሐዋርያው ሰዎች በድንግልና እንዲኖሩ የሚያበረታታበትን ምክንያት ሲገልጽ «ያለ ሐሳብ ልትኖሩ እወዳለው» ብሏል:: 1ቆሮ7፥32 ምክንያቱም ያገባ ‹‹የዓለምን ነገር ያስባልና፤ ልቡም ተከፍሏል›› ይላል:: 1ቆሮ7፥33 በዝሙት ከመኖር በጋብቻ መኖር ሐሳብ ያቀላል፡፡ በጋብቻ ከመኖር ደግሞ በድንግልና መኖር የበለጠ ከሐሳብ ነጻ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው «ያለ ሐሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ» በማለት መክሯል:: ከዚህ የሐዋርያው ቃል በመነሣት «ሳይባክኑ መኖር» ድንግልናን ከመጠበቅ የሚገኝ ዋነኛ ጥቅም መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡
ሐ) ሐዋርያው በጥቂት ገጸ ንባብ ካሰፈራቸው ድንግልናን የመጠበቅ ጥቅሞች ውስጥ ሦስተኛውና የመጨረሻው «በጌታ እንድትጸኑ» የሚለው ነው፡፡ ድንግልናን መጠበቅ በጌታ ያጸናል፡፡ ይህም ማለት ስለ ፍትወት ብለው ኮረዳና ጎልማሳ ፍለጋ ብዙዎች ሃይማኖታቸውን እንደተዉ የሚታወቅ ነው፡፡ «በመዳራታቸውም ብዙዎች ይከተሏቸዋል» እንደተባለው ብዙዎች በዝሙት ማዕበል እየተገፉ ከሃይማኖት ወጥተዋል:: ድንግልናውን ለመጠበቅ የቆረጠ ሰው ግን የሃይማኖት ሙቀቱ ሳይበርድበት ለፈጣሪው ባለው ፍቅር ጸንቶ ይኖራል። 2ጴጥ2፥1-2
ይህም ብቻ ሳይሆን ድንግልናን መጠበቅ ራሱ ጽናትንና ትዕግሥትን ይጠይቃልና ስለዚህ <በጌታ እንድትጸኑ>አለ፡፡ በተጨማሪም «ድንግልናውን በልቡ ይጠብቅ ዘንድ ቢጸና›› 1ቆር:7፥37 በማለት ሐዋርያው የተናገረው ቃል «ጽናት» ከድንግልና ጋር ያለውን ትሥሥር ያሳያል፡፡ ድንግልናን በመጠበቅ ጽናትንና ትዕግሥትን የመሳሰሉ መንፈሳዊ ተግባራትን እንማርበታለን፡፡ ስለዚህ ድንግልናውን ለመጠበቅ የቆረጠ ሰው በዓላማው ሁሉ ትዕግሥተኛና ጽኑ ሰው መሆኑን መናገር ይቻላል፡፡ ታዲያ ይህን የመሰለ ጥቅም ማግኘትን የሚያህል ምን ነገር አለ? አንተ ሰው ጽኑ ነህን? ለማለት ድንግልናህን ጠብቀህ እስከ አሁን አለህን? ቢባል ስንቶቻችን ፅናት እንደሌለን ይረጋገጥ ይሆን?
መ) ድንግልናን ጠብቆ መኖር ታማኝነትን ያረጋግጣል፡፡ ምክንያቱም ድንግልና በሥርዓት ጠብቀን እንድንይዘው በአደራ እንደ ተሰጠን የከበረ ንብረት ነውና፡፡ ባለ አደራው ፈጣሪያችን በሚያስፈልግ ጊዜና ሰዓት ለትዳር አጋራችን እንድንሰጠው ይጠብቅብናል፡፡ በዚህ ጊዜ ድንግልናው ጠብቆ እስከ ጋብቻ ጊዜው ድረስ ያልቆየ ሰው አደራ በሊታ ይባላል፡፡ ታማኝነትም የጐደለው ይሆናል፡፡ ሰው ደግሞ በዚህ ካልታመነ በሌላ ነገር በምን ሊታመን ይችላል?
ድንግልናን መጠበቅ «በባልና በሚስት መካከል መተማመንን› ይፈጥራል የሚባለው የታማኝነት ምልክት ስለሆነ ነው:: ባል ሚስቱን በምን ይመን? ለእግዚአብሔር ትእዛዝ ያልታመነች በሰው ዘንድ ታማኝ ልትሆን እንዴት ትችላለች? ስለዚህ ድንግልናን ጠብቆ በመኖር ታማኝነትን ማስመስከር ይገባል:: ማኅተመ ድንግልና የታማኝነት ማረጋገጫ ምስክር ነውና፡፡
ድንግልና በሩካቤ ሥጋ ይጠፋል፡፡ ይህ ተግባር ደግሞ በዓይን እንደ መጥቀስና እንደ ማስነጠስ በቅጽበትና ሳይታሰብ የሚከናወን ተግባር አይደለም:: ሩካቤን ለመፈጸም የሚያስችል ምቹ ቦታ ለማስናዳት ከሚደረግ ጥረት አንሥቶ ብዙ ሂደቶችን በማለፍ የሚከናወን በመሆኑ በእጅ እንደያዙት ብርጭቆ ድንገት ሳላስበው ወድቆ ተስበረብኝ የሚባል ነገር አይደለም፡፡ በመሆኑ ድንግልናን ያለ ጊዜው ማጥፋት ታማኝነትን እንደ ማጣት እንጂ እንደ እንድ ተራ ቅጽበታዊ ስሕተት ለመቁጠር ያስቸግራል፡፡
በሩካቤ ጊዜ ባል ለሚስቱ ድንግልናውን ያስረክባል:: ምንም እንኳን በግዘፍ ልዩ ምልክት ባይኖረውም ረቂቅ የፍቅር ቋንቋ አለውና ይግባቡበታል።ሚስት ደግሞ በረቂቅም በግዘፍም ድንግልናዋን በከበረ ስጦታነት ለባሏ ታበረክታለች። በዚህ ጊዜ ለባሏ እንድትሰጥ እግዚአብሔር በሚስቱ ያቆየለትን አደራ ባል ሲቀበል (ድንግልናዋን ሲያገኝ) ሚስቱን በአደራ ጠባቂነት እንዲያያት፣ እንዲያምናት፣ እንዲያከብራትና እንዲወዳት ያደርገዋል:: ባልና ሚስት እንዲፈቃቀሩ፣ እንዲተማመኑና እንዲከባበሩ ድንግልናን ጠብቆ መገኘት ወሳኝ የሚሆነው ስለዚህ ነው።
ድንግልናን መጠበቅ ችሎታ ነው:: ምክንያቱም በውስጡ ጽናት፣ ብርታት፣ ትዕግሥት፣ ታማኝነት አለበትና፡ድንግልናን መጠበቅ ፍቅር፣ ባልን ማክበርን፣ ራስን ማክበርና የመሳሰሉት በውስጡ ይገኙበታል፡፡
"ወዳንቺ የመጣው"
ወዳንቺ የመጣው በብሩህ ደመና
ከሦስቱ አካል አንዱ ክርስቶስ ነውና
የጠፋ በግ አዳም ታደሰ በጌታ
በአንቺ ተፈጸመ የሰው ልጆች ደስታ
በደይን የተጣለች ሄዋን ተደሰተች
የደስታ መፍለቂያ አንቺን ስላገኘች
የበረከት ፍሬ ካንቺ ተገኘልን
የወይን ቦታ ነሽ ድንግል እናታችን
ወልድም ባህሪሽን ባህሪ አድርጎት
ለፍጥረታት ጌታ መዓዛሽ ተስማምቶት
ካንቺ ይወለድ ዘንድ ፍጹም ሊላላክሽ
በጥቂቱ አደገ ተልኮና ታዞሽ
ከድንግልና ጋር አንድ የሆነ ሐሊብ
በሩካቤ ሳይሆን በብስራት እንደ ንብ
ከሆድ መጥበብ ጋራ የመለኮት ስፋት
አንቺ ሆነሽ ሳለ ታናሿ ሙሽሪት
በፍጡር ሊና የማይመረመር
እፁብ ነው ድንቅ ነው የመጽነሷ ነገር
እሳት ወነበልባል በሆድሽ ውስጥ ሲያድር
ነደ ነበልባሉ አልፈጀሽም ነበር
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
መጋቢት ፳፱
በዓለ ወልድ (የጌታችን ጽንሰት)
መጋቢት ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የከበረ መልአክ ገብርኤል የምሥራች የነገረበት ድኅነትን የተመላች ታላቅ በዓል ናት በዚህም የከበረ ወንጌል ምስክር ሁኗል እንዲህ ሲል፦ ኤልሳቤጥ ከፀነሰች በኋላ በስድተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል የገሊላ ክፍል የሆነች ናዝሬት ወደምትባል አገር ከዳዊት ወገን ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ።
የድንግሊቱም ስም ማርያም ነው። መልአኩም ወደርሷ ገብቶ ደስተኛ የሆንሽ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አላት። እርስዋም አይታ ከንግግሩ የተነሣ ደንግጣ እንዴት እንዲህ ያለ ሰላምታ ይቀበሏል ብላ አሰበች።
መልአኩም እንዲህ አላት ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ እርሱ ታላቅ ነው የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል።
እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል ለያዕቆብ ወገንም ለዘላለም ነግሦ ይኖራል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም።
ማርያምም መልአኩን ወንድ ሳላውቅ ይህ እንደምን ይሆናል አለችው።መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ያድርብሻል የልዑል ኃይልም ያጸናሻል ከአንቺ የሚወለደው ከሶስቱ አካል አንዱ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ይባላል።
እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ፀንሳለች ወንድልጅም አገኘች ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ማርያምም እነሆኝ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለችው።
ያን ጊዜም ድንግል ስትሆን ረቂቅ ፅንስን ተቀበለች የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል ወልድ ዋህድ ለኩነተ ሥጋ ወርዶአልና ይህም አንድ ባሕርይ አንድ ህልውና ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ የነበረ በማይመረመር ድንቅ በሆነ ተዋሕዶ እንዴትም እንደሆነ በማይታወቅ በቅድስት ድንግል ማርያም ማሕፀን አደረ ፅንስ ሆኖ ኖረ።
በዚያን ጊዜም የኋላ ኋላ መለየት ከቶ የሌለውን ፍጹም ሰውነት ነሥቶ ተዋሐደ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ ያለ መለያየት አንድ ሆኖአልና። ይቺም ዕለት የበዓላት ሁሉ በኵር ናት በእርሷም የዓለም ድኅነት ተጀምሮዋልና። ይሕች ቀን ለቤተ ክርስቲያን በእጅጉ ልዩ ናት:: በዓመቱ ከሚከበሩ በዓላትም አንደኛውን ሥፍራ ትይዛለች::
የዛሬዋ ዕለት በሚከተሉት ድርብርብ በዓላት ምክንያት "ርዕሰ በዓላት"(የበዓላት ራስ)፣ "በኩረ በዓላት" እየተባለች ትጠራለች:: ይኸውም:-
፩. አስቀድሞ ዓለም የተፈጠረችበት (መዝ ፻፩:፳፭)
፪. መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ያበሠረባት፣ (ሉቃ ፩:፴፩)
፫. ክብር ይግባትና እመቤታችን ድንግል ማርያም መድኅን ክርስቶስን የፀነሰችበት፣ (ሉቃ ፩:፴፩ ማቴ ፩:፳፫)
፬. በዕለተ ዓርብ በዕፀ መስቀል ነፍሱን በፈቃዱ ስለእኛ አሳልፎ ከሰጠ በኋላ በዕለተ እሑድ ከሙታን ተለይቶ የተነሣባት (መዝ ፻፲፯:፳፬፣ መዝ ፸፯:፷፭-፷፮፣ ዮሐ ፲፱:፩፣ ፩ኛ ቆሮ ፲፭:፳)
፭. ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ የሚመጣባት ቅድስት ዕለት ናት። (ራእ ፳፪:፲፪ ፣ መዝ ፵፱:፪ ፣ ማቴ ፳፬:፵፬)
አምላካችን ከዕለቷ ረድኤትና በረከት ይክፈለን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት
ሐሙስ
ከስቅለትና ከትንሣኤ በፊት ያለው ሐሙስ በቤተክርስቲያን ልዩ ልዩ ስያሜዎች
አሉት፡፡
ሀ. ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።
የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ይለምን ይማልድ የነበረን ሥጋን የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፤ (ማቴ 26፤36-46፣ ዮሐ.17)
ለ. ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል ።
ሕጽበተ እግር፦ ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፤ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳትና የደብር አስተዳዳሪዎች በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብሕን ኃጢአት እጠብ ሲሉ ከአገልጋዮቹ ጀምረው በቤተክርስቲያን የተገኙትን ምእመናን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡ ያረፍዳሉ፡፡
ሐ. የምሥጢር ቀን ይባላል ።
ከሰባቱ ምሥጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፤ ይኸውም ‹‹ይህ ስለእናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ›› ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ ‹‹ይህ ስለእናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱ ጠጡ›› በማለት እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን መንገድ ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ቅዳሴ ይቀደሳል፤ የሚቀደሰውም በለሆሳስ ሲሆን እንደ ቃጭል ሆኖ የሚያገለግለውም ጸናጽል ነው፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ሲመጡ ድምጻቸውን ዝግ አድርገው፣ በለሆሳስ እየተነጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ ነው፤ በቅዳሴውም ጸሎተ ተአምኖ፣ ኑዛዜ አይደረግም፤ ሥርዓተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል፤ ይህም ጌታችን የሰጠውን ዘለዓለማዊ ቃል-ኪዳን ለማሰብ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ተዘጋጅቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል፡፡
መ. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡
ጸሎተ ሐሙስ ( የፋሲካ እራት) ፦ ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹ይህ ጽዋዕ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱም ጠጡ››በማለቱ ይታወቃል፡፡ (ሉቃ.22፤20) ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊ ቃል-ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት መሆኑን በማሰብ የቃል-ኪዳኑ ፍጻሜዎች፣ ጠባቂዎች መሆን እንደሚገባን እንማራለን፡፡
ሠ. የነጻነት ሐሙስ ይባላል።
ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ራሱ ጌታችን ስለሰው ልጅ ነፃነት ሲናገር ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፡፡›› በማለቱ(ዮሐ.15፤15) ከባርነት የወጣንበት ቀን መሆኑን መጽሐፍ በግልጥ ያስረዳናል፡፡
ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኃጢአት ባርነት ተላቅቆ፤ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርበታል፡፡
እርሱ ጠላቶቹ ስንሆን ወዳጆቹ አድርጐናልና፡፡
ረ. አረንጓዴ ሐሙስ አምላካችን የጸለየበትን የአትክልት ቦታ ወይም ጌቴሴማኒ ለማሰብ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል።
ጌታ እንዴት፣ ምን እና ለምን ጸለየ?
እንዴት ጸለየ?
አምላካችን የምሥጢር ሐዋርያቱን (ዮሐንስ ፣ ያዕቆብ እና ጴጥሮስ ) አምስት ትእዛዝን (ተቀመጡ ፣ ትጉ ፣ ጸልዩ ፣ ተኙ ፣ ዕረፉ ) በማዘዝ ግንባሩን ምድር አስነክቶ ሰግዶ ጸለየ።(ማቴ፳፮:፴፮-፵፭)
ምን ጸለየ?
ሦስት ጊዜ ደጋግሞ የጸለየው ጸሎት አንድ ዓይነት ነው ይኸውም:- "አባቴ ቢቻልስ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ ፣ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ።"(ማቴ፳፮:፴፮-፵፭)
ለምን ጸለየ?
፩. ምሣሌ ይሆነን ዘንድ ነው።
፪. ፈቃዱን ማስቀደም እንዳለብን እናውቅ ዘንድ ነው።
፫. ወደፈተና እንዳንገባ መጸለይ እንደሚገባ እናውቅ ዘንድ ነው።
የጸሎቱ ትርጓሜ ምንድን ነው?
፩. ዓለም እንድትድን እና ክብርን እንድታገኝ ለሞት ተላልፎ እንደሚሰጥ ገልጿል።
"ያለ እኔ ሞት የዓለሙ ደኅንነት ያለ እኔ ሐሳር የዓለሙ ክብር አይቻልም እንጂ የሚቻልስ ከሆነ ይህ ጽዋዓ ሞት ይለፍልኝ። ነገር ግን ያንተ ፈቃድ ይደረግ እላለሁ እንጂ የኔ ፈቃድ ይደረግ አልልም።" (ወንጌል አንድምታ ገጽ፪፻፸፱)
፪. ሞት እንዲቀርልን እንደ ሞተ ገልጿል። "በኔ ሞት የዓለም ደኅንነት በኔ ኃሣር የዓለም ክብር የሚቻልስ ከሆነ እኔ ከሞትሁላቸው ከኔ ሞት የተነሳሣ ይህ ጽዋዕ ሞት ይቅርላቸው።(ወንጌል አንድምታ ገጽ፪፻፸፱)
፫. አብነት ይሆነን ዘንድ ሞትን እንደሚቀምስ ገልጿል። " ከኔ ለምዕመናን ይለፍላቸው ። እኔን አብነት አድርገው ይሙቱ ። ነገር ግን የኔ ፈቃድ ካንተ ፈቃድ ልዩ ሁኖ የኔ ፈቃድ ይሁን አልልም። የኔ ፈቃድ ካንተ ፈቃድ ጋራ አንድ ነውና ያንተ ፈቃድ ይሁን እላለሁ እንጂ። " (ወንጌል አንድምታ ገጽ፪፻፸፱)
በዚህ ዕለት በወንጌላት የተመዘገቡ ድርጊቶችን ቀጥለን እንመልከት፡
ሀ. የፋሲካ ዝግጅት የተደረገበት ዕለት ነው ።
ዝግጅቱ በሦስቱ ወንጌላት ላይ ተመዝግቧል፡፡ (ማቴ.26፤17-19፣ ማር 14፤1-16፣ ሉቃ.22፤6-13) ፋሲካ ማለት ማለፍ ማለት ነው፤ ይኸውም እሥራኤላውያን በግብጽ ምድር ሳሉ መልአኩን ልኮ እያንዳንዱ እሥራኤላዊ የበግ ጠቦት እንዲያርድና ደሙን በበሩ ወይንም በመቃኑ እንዲቀባ ለሙሴ ነገረው፤ ሙሴም ለሕዝቡ ነገረ፤ ሁሉም እንደታዘዙት ፈጸሙ፤ መቅሰፍተ ከእግዚአብሔር ታዞ መልአኩ የደም ምልክት የሌለበትን የየግብጻውያን ቤት በሞተ በኵር
ሲመታ፤ የበጉ ደም ምልክት የእሥራኤላውያንን ቤት ምልክቱን እያየ ማለፉን ለማመልከት ነው፡፡ (ዘዳ.12፤1-13) በዚህ መነሻነት በየዓመቱ እሥራኤላውያን በመጀመሪያ ወራቸው በዐሥራ ዐራተኛው ቀን በግ እያረዱ የፋሲካን በዓል ያከብራሉ፡፡ ሀገራችንም አስቀድማ ብሉይ ኪዳንን የተቀበለች ሀገር እንደመሆኗ ይህ ድርጊት ይፈጸምባት ነበር፡፡ በአንጻሩም ዛሬ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ፋሲካ ተብሎ የተጠራበት ምክንያት በዚህ በፋሲካ በዓል ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ደሙን ስላፈሰሰልን ነው፡፡ በደሙ መፍሰስ ሞተ በኵር የተባለ ሞተ ነፍስ ቀርቶልናልና፡፡ ‹‹ፋሲካችንም ክርስቶስ ነው፡፡›› (1ኛ
ቆሮ.5፤6፣ 1ኛ.ጴጥ.1፤10)
ለ. በዚህ ዕለት እንደ ማክሰኞ ለደቀመዛሙርቱ ረጅም ትምህርት አስተምሯል።
ምሥጢረ ሥላሴ የሦስትነት ትምህርት፤ ምሥጢረ ሥጋዌ (የአምላክ ሰው መሆን)፤ በዮሐ.14፤16የሚገኘው በጠቅላላ የዚህ ዕለት ትምህርት ነው፡፡ የትምህርቱም ዋና ዋና ክፍሎች ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታንና የዳግም ምጽአቱ ነገር ነው፡፡
እነዚህም በስፋትና በጥልቀት መማር እንደሚገባ ሲያስረዳን፤በተአምራት ሊገልጥላቸው ሲችል በረጅም ትምህርት እንዲረዱት አድርጓል፡፡ ተማሪዎቹን እሱ እያስተማራቸው ሳለ ያልገባቸውን እየጠየቁ ተረድተዋል፡፡ከዚህም እያንዳንዳችን በቤተክርስቲያን ተገኝተን መማርና ያልገባንን ጠይቆ መረዳት እንደሚገባን እንማራለን፡፡
ሐ.ይህ ዕለት ከደቀመዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ የተባለ ጌታ ሆይ፣ መምህር ሆይ ብሎ በመሳም አሳልፎ የሰጠበት ዕለት ነዉ።
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት-ረቡዕ
✅ምክረ አይሁድ
✅የመልካም መዓዛ ቀን
✅ከዳተኛው ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመስጠት ከጸሐፍት ፈሪሳውያንና ከካህናት አለቆች ዘንድ ሠላሳ ብር ለመቀበል ተስማምቷል።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🩸"ጌታ ሆይ" 🩸
ጌታ ሆይ አይሁድ አማፅያን ሰቀሉህ ወይ
የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ/2/
የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመሰቀል
የሄዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት/2/
ንጹህ ክርስቶስ ሆንክ በደለኛ ብለህ ስለኛ
መስቀል አሸክመው አሥረው ገረፉህ እያዳፉህ/2/
እጅና እግርህ በችንካር ተመታ የዓለም ጌታ
የእሾህ አክሊል ደፍተህ ጎንህን ተወጋህ አልፋ ኦሜጋ/2/
ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው
ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጎዱ/2/
በመስቀል ላይ ተጠማሁ ስትል ታላቅ በደል
ሃሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው/2/
ይቅር ባይ ግልጽ በደላችን ሁሉን ሳታይ
አንተ ይቅር በለን በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ/2/
በሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት
ማክሰኞ
በዚህ ዕለት አምላካችን ለጥያቄዎች በሙሉ መልስ የሰጠበት እና በስፋት ያስተማራቸው ትምህርቶች የሚታሰቡበት ዕለት ነው።
፩. የጥያቄ ቀን ትባላለች።
በዚህ ዕለት አምላካችን ስለ ሥልጣኑ በካህናት አለቆችና በሕዝብ አለቆች"በምን ሥልጣንህ እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን የሰጠህ
ማነው?"(ሉቃ፳:፩-፵፩) የሚል ጥያቄ ለፈተና የተጠየቀበት ዕለት በመሆኑ የጥያቄ ቀን ትባላለች፡፡
ጥያቄዎቹ በቁጥር አምስት ናቸው። እነዚህም:-
፩. ሥልጣኑን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፪) ለክፋት የቀረበ ጥያቄ በመሆኑ ጥያቄውን በጥያቄ መልሶታል።
፪. በወይን አትክልት መስሎ ጥያቄ አቅርቦላቸዋል። (ሉቃ፳:፱)ይህ ምሳሌ በቀጥታ ከእነርሱ ጋር እንደሚገናኝ ተረድተውም ነበር።
፫. ግብርን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፳፪) ይህንንም በድንቅ ጥበቡ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ብሎ መልሶላቸዋል።
፬. ትንሣኤ ሙታንን የተመለከተ ጥያቄ ቀርቦለታል። (ሉቃ፳:፴፫) ከጋብቻ ጋር በተገናኘ ምድራዊ አስተሳሰብ ሰማያዊውን ኑሮ አውርደው ለጠየቁት ለሰዱቃውያን ከሞት በኋላ እንደ መላእክት ያለን ኑሮ የመኖር ዕድል እንዳለው የሰው ልጅ መልሶላቸዋል።
፭. ክርስቶስን የዳዊት ልጅ ለምን ይሉታል የሚል ጥያቄ አቅርቦላቸዋል።(ሉቃ፳:፵፩)
መልስ ላጡበት ጥያቄ ራሱ በመመለስ እርሱ የዳዊት ጌታ መሆኑን አስተምሯቸዋል።
፪. የትምህርት ቀን ትባላለች።
በዚህ ዕለት ደቀ መዛሙርቱን ሰፊ ትምህርትን ስለ መጨረሻው ዘመን ምልክቶች አስተምሯቸዋልና የትምህርት ቀን ተብላ ትጠራለች። (ሉቃ፳:፵፬-፵፯) ያስተማራቸው ትምህርቶች
፩. የአምልኮ መልክ ካላቸው ተጠንቀቁ
፪. ታይታን ከሚወዱ ተጠንቀቁ
፫. ለራሳቸው ክብርን ከሚሰጡ ተጠንቀቁ
፬. የባልቴቶችን ገንዘብ ከሚበሉ ተጠንቀቁ
፭. በምክንያት ጸሎት ከሚያረዝሙ ተጠንቀቁ
ሌላው በግብረ ሕማማት ካህናት በዚህች ዕለት ስለሚያከናውኗቸው ስራዎች እንዲህ ተብሎ ተገልጿል:-"ከዚህ በኋላ በከበረች ቤተክርስቲያን ማክሰኞ ከሌሊቱ መጀመሪያው ሰዓት ካህናት ይሰብሰቡ። ተዘከሮ እግዚኦ የሚለውን የዳዊት መዝሙር ወአሰሰልኩ ዕለተ እስከሚለው ድረስ ጸልዩ። ውዳሴ ማርያምም የቀዳሚትን ይድገሙ።" ግብረ ሕማማት (ገጽ፪፻፴፪)
የመዝሙረ ዳዊት ምንባባት
በ፩ ሰዓት (መዝ፴፬:፬-፭)
በ፫ ሰዓት (መዝ፻፲፰:፻፶፬)
በ፮ ሰዓት (መዝ፲፯:፲፯)
በ፱ ሰዓት (መዝ፳፬:፩)
በ፲፩ ሰዓት (መዝ፵፬:፮)
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን!
ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
በሰሙነ ሕማማት ይህንን አድርጉ
ሰሙነ ሕማማት አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ቤዛ ሆኖ ተላልፎ መሰጠቱን የምናስታውስበት ሳምንት ነው።
ይህንን ምክንያት በማድረግ የሥርዓት ለውጥ ሲደረግ ሲመለከቱ ግራ የሚጋቡና ሥርዓተ አምልኮውን በሚገባ ከመከታተል ይልቅ ሥርዓት የጣሱ እየመሰላቸው የሚጨነቁ ስላሉ ልናደርገው የሚገባንን እጽፍላችኋለሁ።
1️⃣. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ ፊትንና መላ ሰውነትን በትዕምርተ መስቀል {በመስቀል ምልክት} ማማተብ አይከለከልም። ከካህን እጅ ቡራኬ አንቀበልም በካህኑ እጅ ያለውን መስቀል አንሳለምምና ማማተብም የለብንም በሚል ፍልስፍና ካልሆነ ማማተብ ክልክል ነው ተብሎ የተጻፈበት ቦታ የለምና።
2️⃣. የሚከለከል ጸሎት የሌለ መሆኑን አውቃችሁ ያስለመዳችሁትን ጸሎት በትጋት ጸልዩ። መሥዋዕት ካለመሠዋታችን ቅዳሴ ካለመቀደሳችን በቀር በዚህ ሳምንት ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጀምሮ እስከ ሊቃውንት ድርሳናት ድረስ በቤተ ክርስቲያን የማይጸለይ ጸሎት የለምና።
3️⃣. ሰላምታ መስጠት ከጸሎተ ሐሙስ ዕለት በቀር አልተከለከለም፤ እሱም ቢሆን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በይሁዳ ሰላምታ ተላልፎ መሰጠቱን ለማስተዎስ እንጅ ሌላ የተለየ ምክንያት ስለሌለው በመርሳት ወይም በሌላ ከድፍረት በተለየ ምክንያት ሰላምታ ያቀረበላችሁን ሰው ልታስደነግጡና ትልቅ ኃጢአት እንደሠራ አድርጋችሁ ልታስጨንቁት አይገባም።
4️⃣. “በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ” ብሎ መጻሕፍትን ማንበብ ወይም ሌላ ሥራን መጀመር ይቻላል። ስመ እግዚአብሔር መጥራት የምንከለከልበት ጊዜ መቸም የለምና።
5️⃣. የጌታችንን ሕማሙንና ሞቱን የሚያስታውሱ መጻሕፍትን በማንበብና በመስማት ጊዜአችንን መወሰን ይገባናል።
6️⃣. በዚህ ሳምንት ተድላ ደስታን ሲያደርጉ መገኘት ከአይሁድ ጋር እንደ መተባበር የሚያስቆጥር ስለሆነ አብዝቶ በመብላትና በመጠጣት፣ ያማረውንና ጌጠኛውን ልብስ በመልበስ፣ ባልና ሚስት በምንጣፍ በመገናኘት እንዲሁም በልዩ ልዩ ምክንያት ከምናደርጋቸው ተድላ ደስታዎች መራቅ ይገባናል። ቅዱሳን በዘመናቸው ሁሉ ባሰቡት ጊዜ የሚያስጨንቃቸውን የክርስቶስን መከራ እያሰብን ለጥቂት ጊዜም እንኳን ቢሆን የክርስቶስን መከራ በሰውነታችን ማሰብ ይገባናል።
የተቻለው እንደ ጴጥሮስ የራሱን ኃጢአት እያሰበ እንደ ማርያም መግደላዊት የክርስቶስን ሞት እያዘከረ ሊያለቅስ ይገባዋል።
በወዲያኛው ዓለም ከማልቀስ የሚያድነን ዛሬ የራሳችንን ኃጢአት አስበን የክርስቶስን ሞት አዘክረን የምናለቅሰው ለቅሶ ነው እንጅ ዛሬ ከተደሰትን ደስታችንን በዚህ ዓለም ማድረጋችን አይደለምን?
7️⃣. በተቻለን መጠን በቤተ ክርስቲያን መዋል ይገባናል፤ ሕማማተ መስቀልን የሚያስታውሱ መጻሕፍት የሚነበቡበት ሳምንት ስለሆነ ነው። ነገር ግን በልዩ ልዩ ምክንያት በቤተ ክርስቲያን መዋል እንኳን ባይቻላችሁ ባላችሁበት ቦታ ሁናችሁ እየዋሻችሁ በሐሰት የከሰሱትን፣ እየቀማችሁ ልብሱን የገፈፉትን፣ ሰው እየደበደባችሁ በጅራፍ የገረፉትን፣ በወንድሞቻችሁና በእኅቶቻችሁ ላይ እየፈረዳችሁ በክርስቶስ ላይ የፈረዱበትን፣ በሰዎች ላይ እየተዘባበታችሁ የተዘባበቱበትን፣ በሳቅና በሽንገላ ሰውን እየሸነገላችሁ ሽንገላ በተሞላበት ሰላምታ ጌታውንና መምህሩን አሳልፎ የሰጠ ይሁዳን ልትመስሉ አይገባም።
ይልቁንም በአይሁድ እጅ ተላልፎ ቢሰጥም ንጹሓ ባሕርይ መሆኑን በማመን እስከ ቀራንዮ የተከተሉትን ደቀመዛሙርት ልትመስሉ ይገባል። እግራችሁ በመቅደሱ ውስጥ ባይቆምም ልባችሁን ከመቅደስ ልታወጡት አይገባም። እያዘናችሁ ባላችሁበት ቦታ ዋሉ።
8️⃣. በቤታችሁም ሆነ በቤተ ክርስቲያን አብዝታችሁ ስገዱ። ስለሁላችንም ቤዛ የሚሆን ክርስቶስ በፊታችን መስቀል ተሸክሞ ሲወድቅ እያያችሁት ትቆማላችሁን? አይሁድ ገፍተውት አንድ ጊዜ ወደ ምድር በወደቀ ጊዜ ለወደቀው መውደቅ ዘመናችንን ሙሉ ብንወድቅ ብንነሣ ውለታ መክፈል እንችል ይመስላችኋል?
ቅዱሳን ሳያቋርጡ ሲሰግዱ የሚኖሩት ክርስቶስ በፊታቸው በአይሁድ እጅ እየተገፋ መስቀሉን እንደተሸከመ ሲወድቅ በዓይነ ሕሊናቸው ስለሚያዩት ነው።
በስንክሳር ተጽፎ የምናገኘው ዜና ሞታቸው እየሰገዱ ሳሉ ሞት ነፍሳቸውን ከሥጋቸው ለይቶ እንደሚወስዳትና ለስገደት ታጥቀው እንደተንበረከኩ እንደሚገኙ ይነግረናል። የተሰቀለውን ክርስቶስን የሚያስብ ሰው ለሰውነቱ ዕረፍትን አይሻም።
9️⃣. ከሁሉም ሰው ጋር ፍቅርን አድርጉ። ሰውን ለመውደድ ምክንያት አታብጁ። ክርስቶስ አሳልፎ የሰጠውን ይሁዳን “ወዳጄ” ብሎ ሲጠራው አትሰሙትም?
እግዚአብሔርን አንተን ያለ ምክንያት እንደ ወደደህ አንተም ያለ ምክንያት ሰውን መውደድ ልመድ። ክርስቶስ አንተን ጠላቱ ሆነህ ሳለ ፍቅርን ካላጎደለብህ ለጠላትህ ፍቅርን አታጉድልበት።
ክርስቶስ ይሁዳን ‘’ወዳጀ’’ ብሎ ከጠራው አንተም ይሁዳዎችህን ወዳጀ ብለህ ጥራቸው። አውቃለሁ ጠላትን መውደድ መራራ ሐሞትን ከመጠጣት በላይ መራራ ነው። ነገር ግን እኔም ለይሁዳዎቻችን ፍቅርን እንስጥ ማለቴ መራራ ሐሞት የጠጣ ክርስቶስን እንድንመስለው ነው።
1️⃣0️⃣. ለሁሉም መስጠት በምትችሉት መጠን ስጡ እንጅ አትቀበሉ። ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነውና በመስጠታችሁ ብፁዓን ተብለው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገቡት ትቆጠራላችሁ።
ምናልባትም የምትሰጡት ገንዘብ ባይኖራችሁ ዕዳ ይሆንባችሁም ቢሆንም ገንዘብ ለሰጧችሁ ባለጠጎች የምትሰጡት ጸሎት ሊኖራችሁ ይገባል። ከምንጊዜውም የበለጠውን ስጦታ የተቀበልንበት ሳምንት መሆኑን እያሰባችሁ አንዳች የምትሰጡት ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ስጦታ የሌላችሁ ባዶዎች እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ።
ከሁሉ በላይ የሆነውን ስጦታ የጌታን ሥጋና ደም እነሆ ተቀብለናል።
ክርስቶስ መድኃኒነ
መጽአ ወሐመ በእንቲአነ
ወበሕማማቲሁ ቤዘወነ‼
© ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአከ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት-ሰኞ
✅መርገመ በለስ
✅አንጽሖተ ቤተ መቅደስ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሥርዓተ ጸሎት ዘሰሙነ ሕማማት ፪
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
፬. በሰሙነ ሕማማት ዕለተ ዐርብ የስቅለቱ መታሰቢያ ነው፦ ምእመናኑ በሰሙነ ሕማማት የሰሩትን ይናዘዛሉ፡፡ ካህናቱን በወይራ ቅጠል ትከሻቸውን እየጠበጠቡ ቀን ከሰገዱት ስግደት በተጨማሪ ሌላ ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ ምሳሌ ነው፡፡ ጥብጠባው የሚደረግለት ሰው በህማማቱ ወቅት የፈጸመው በደል ወይም ኃጢአት ካለ ይህንኑ በመናገር የስግደቱ ቁጥር ከፍ እያለ እንዲል ያደርጋል፡፡
፭. አክፍሎት፡- በሰሙነ ሕማማት ዕለተ ዐርብ ከስግደት በኋላ ምእመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ለቁመተ ሥጋ ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ በዓል/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡ ከዓርብ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ማክፈል የብዙዎች ነው፡፡ አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታቸን ያዕቆብ እና ዩሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህል ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡
ከሰኞ እስከ ሐሙስ ዕለት የሚካሄደው የሰሙነ ሕማማት የጸሎት ሥርዓት እንደሚከተለው በምስል ቀርቧል:
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
“ሆሣዕና”
በዘማሪ አቤል ተስፋዬ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሆሣዕና
የዐብይ ጾም ስምንተኛ እሑድ(ሳምንት)
ሆሣዕና ከጌታችን አምላካችን ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከኢየሩሳሌም ወደ ቤተ መቅደስ ለመግባት በፈለገ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ፊታችው ባለው ሀገር "ሂዱና አህያ ከውርጭላዋ ጋራ ታስራ ታገኛላችው ፈታችው እምጡልኝ። 'ምን ታደርጋላችሁ?' የሚላችሁ ሰው ካለ 'ጌታቸው ይፈልጋቸዋል' በሉ" ብሎ ላካቸው ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ እንዳዘዛቸው ሄደው ፈተው አመጡለት በዚያም የተሰበሰቡት ሁሉ በአህዮች ላይ ልብሳቸውን ጎዘጎዙለት ጌታችንም በሁለቱ አህዮች ላይ ተቀመጠ ከሌሎቹ እንስሳት አህዮችን መርጦ በአህዮች ተቀምጧል፡ አህዮች በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ታሪክ አላቸውና።
✅የበልአም አህያ የመልአኩን ክብር ለመግለጥ አፍ አውጥታ ተናግራለች። (ዘሁል 22+28)
✅ጌታችን በተወለደ ጊዜ አህዮች ከከብቶች ጋር በበረት እስትፋሳቸውን ገብረዋል። (ቅዳሴ ማርያም)
የሆሣዕና እህዮች ከሁሉ ተመርጠው አምላካችን ተቀምጦባቸዋል: 'ለምን የተዋረዱት አህዮችን መረጠ?' ቢባል:-
፩. ደመናን አዝዞ : ነፋስን ጠቅሶ : በእሳት መንኮራኩር ላይ የሚረማመድ አምላክ ሲሆን ነገር ግን የመጣው ትሕትናን ለማስተማር : የትሕትና ጌታ መሆኑን ለመግለጽ ነውና በአህያ ተቀመጠ።
፪. ትንቢቱን ለመፈጸም <<አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሁትም ሁኖ በአህያም በውርንጭላቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም ያጠፋል>> ብሎ ዘካርያስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈጸም ነው። ዘካ ፱÷፩
፫. ምሳሌውን ለመግለጽ
ምሳሌ- ቀድሞ ነቢያት ዘመነ ጸብእ ከሆነ በፈረስ ተቀምጠው ዘገር ነጥቀው ይታያሉ ዘመነ ሰላም ከሆነ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታዩ ነበርና ጌታችንም ዘመነ ሰላም ነው ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል።
፬. ምሥጢሩን ለመግለጽ
ምሥጢር- በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም አሳዶም አይዝም እሱም ካልፈለጋችሁኝ አልገኝም ከፈለጋችሁኝ አልታጣም ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል።
ህድግት የእስራኤል ምሳሌ ህድግት ቀንበር መሸከም የለመደች ናት= እስራኤልም ህግ መጠበቅ ለምደዋልና
እዋል የአህዛብ ምሳሌ
እዋል ቀንበር መሸከም አልለመደችም=አህዛብም ህግ መጠበቅ አልለመዱምና (አንድም) ህድግት የኦሪት ምሳሌ ህድግት ቀንበር መሸከም እንደለመደች=ኦሪትም የተለመደች ህግናትና
እዋል የወንጌል ምሳሌ
እዋል ቀንበር መሸከም አልለመደችም=ወንጌልም ያልተለመደች አዲስ ህግ ናትና
በሁለቱም ላይ መቀመጡ ኦሪትንም ወንጌልንም የሰራሁ እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡ ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ ፲፮ ምእራፍ ነው ፲፬ቱን ምእራፍ በእግሩ ሂዶ ሁለቱን ምእራፍ በአህያይቱ ሂዷል በውርጭላይቱ ሁኖ ፫ ጊዜ ቤተ መቅደሱን ዙሯል ፲፬ ምእራፍ የአስርቱ ትእዛዛትና የአራቱ ኪዳናት ምሳሌ፤ አስሩ ምእራፍ የአስርቱ ትአዛዛት፣ አራቱ ምእራፍ የአራቱ ኪዳናት ምሳሌ ነው፣ አራቱ ኪዳናት የሚባሉት እነዚህ ናቸው፦ ኪዳነ ኖህ : ክህነተ መልከ ጼዴቅ :ግዝረተ አብርሀም እና ጥምቀተ ዮንሐስ ናቸው፡፡
በአህያይቱ ላይ ልብሳቸውን አንጥፈውለታል::
ልብስ በአካል ያለውን ነውር ይሸፍናል አንተም ከባቴ አበሳ ነህ ሲሉ።
በአህያዋ ላይ ኳርቻ ሳያደርጉ ልብስ አንጥፈውለታል :-
ኳርቻ ይቆረቁራል ልብስ አይቆረቁርም የማትቆረቁር ህግ ሰራህልን ሲሉ ነው።
ስለምን ልብሳቸውን አነጠፉለት ቢባል ? በእዩ ልማድ ነው ፡
እዩ የተባለው ሰው በእስራኤል ላይ ሲነግሥ እስራኤል ልብሳቸውን አንጥፈውለት ነበረና በዚያ ልማድ አንጥፈውለታል እኩሌቶቱ ደግሞ ዘንባባ አንጥፈውለታል ። 🌴
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ? (ማቴ. ፳፩÷፩-፲፯፣ ማር. ፲፩÷፩-፲፣ ሉቃ. ፲፱÷፳፱-፴፰፣ ዮሐ. ፲፪÷፲፪-፲፭)
የዘንባባ ዝንጣፊ
✅ ዘንባባ የድል ምልክት የደስታ መግለጫ የምስጋና መስጫ ነው፡፡
✔️ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል።
✔️ይስሐቅም ያእቆብን በወለደ ጊዜ አምላኩን በዘንባባ አመስግኗል።
✔️እስራኤል ከግብጽ በወጡ ጊዜ በዘንባባ ንሴብሆ እያሉ እህተ ሙሴ ማርያም ከበሮ እየመታች አምላካቸውን አመስግነዋል፡፡
✔️ዮዲት እስራኤልን እየገደለ ያስቸገረው ሆለፎርኒስን አንገቱን ቆርጣ በገደለችው ጊዜ እስራኤል ዮዲት መዋኢት ዮዲት ኀያሊት ብለው በዘንባባ አመስግነዋታልና።
✅ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
✅ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው።
✅ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
✅ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው።
✅ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡
የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ
✅የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ህይወታችንን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
✅ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው:- አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
✅ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
✅ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።
የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ
✅ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
✅ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
✅ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
✅ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።
ከፊት ከኋላ ያሉት "ሆሣዕና በዓርያም ለዳዊት ልጅ መድኀኒት መባል ይገባዋል" እያሉ አመስግነውታል የምስጋና ጌታም በአህዮች ተቀምጦ ወደ መቅደስ ገብቷል።
በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች፦
-ዕብ ፱፥፲፩ እስከ ፍጻሜ
-፩ጴጥ ፬፥፩-፲፪
-ሐዋ ፳፰፥፲፩ እስከ ፍጻሜ
ምስባኩም፦ መዝ፰፥፪
"እመ አፈ ደቂቅ ወሕጻናት አስተዳሎከ ስብሐተ በእንተ ጸላኢ ከመትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ"
"ከሕጻናት አንደበት ምስጋናን አዘጋጀህልኝ፡፡ ስለ ጠላትና ቂመኛን ለማጥፋት"
ወንጌሉም፦ ዮሐ፭፥፲፩-፲፫
ቅዳሴ ፦ ዘጎርጎርዮስ (ነአኵቶ)[በዕዝል ዜማ]
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሠ) ድንግልናን መጠበቅ መጠንቀቅ ነው፡፡ እንዲያው፡ መጠንቀቅ ተብለው ከሚወሰዱ ማንኛውም ዓይነት ሌሎች እርምጃች ምንም ዓይነት ሰብአዊ ቀውስ ሳያስከትል መከናወን የሚችል ተገቢ የጥንቃቄ ዓይነት ነው:: ከበሽታ፣ ያለ አግባብ ወይም ሳያገቡ ከመውለድ፣ ክብርንና መልካም ስምን ከማጣት፣ ከመጸጸት በአጠቃላይ ለወደፊት መንፈሳዊም ሆነ ሥጋዊ ችግር ከሚፈጥሩ የኑሮ ጠንቆች ሁሉ መቶ በመቶ ሊሰውር የሚችል መጠንቀቅ ቢኖር ድንግልናን መጠበቅ ነው::
ረ) አንዲት ሴት በድንግልና ኖራ ብታገባ ልቧ አይከፈልምና ፈጣሪዋን እጅግ አድርጋ ታስደስተዋለች፡፡ ሐዋርያው «ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ» ያለው ስለዚህ ነው:: ድንግል ሴት በድንግልና ኖራ ስታገባ ደግሞ ባሏን በጣም ታስደስተዋለች፡፡ ማንኛውም ባል ሚስቱን ድንግል ሆና ቢያገኛት ይደሰታልና፡፡ ድንግል ባትሆን ግን ባልዋን እንዴት ልታስደስተው ትችላለች? በእርግጥ ባልን ማስደሰት የሚቻለው በዚህ ብቻ ባይሆንም የሚጀምረው ግን ከዚህ ነው፡፡
ድንግልናን ካጠፉ በኋላ የሚደረግ ጋብቻ አግብቶ የፈታ ሰው እንደሚፈጽመው እንደ ሁለተኛ ጋብቻ ይቆጠራል:: ምክንያቱም የተጋቡ ሰዎች ብቻ ሊፈጽሙት የሚገባውን ሩካቤ ሥጋ ከጋብቻ በፊት ፈጽሞ በመገኘቱ ነው፡፡ ለመመንኮስ ተስሎ የነበረ ሰው ቢያገባ የተሳለው ስእለት እንደ መጀመሪያ ጋብቻ ተቆጥሮ የሚፈጽመው ጋብቻ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚያገባ ሰው እንደሚቆጠርበት ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ይናገራል፡፡
ይህ እንዲህ ከሆነ ድንግልናቸውን ያጡ ስዎች የሚፈጽሙት ጋብቻ እንደ መዓስባን ወይም እንደ ሁለተኛ ጋብቻ መቆጠሩ ምንም አያስደንቅም:: እዚህ ላይ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ለሁለተኛ ጊዜ የሚያገባ ሰው ማለትም ሚስቱ ሞታበት ወይም ለፍቺ በሚያበቃ ምክንያት ተለያይተው ከሆነ ፈቅዶ እንዳደረገው እንደ መጀመሪያ ጊዜ ጋብቻው ደስተኛ እንደማይሆን ነው:: እንደዚሁም ሁሉ ፈት ሆኖ ማግባት ድንግል ሆኖ እንደ ማግባት አያስደስትም ወይም ፈትን ማግባት ድንግልን እንደ ማግባት አያስደስትም፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንደሚያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፡ ልቡም ተከፍሏል፡፡» ስለሴቶች ደግሞ «የተጋባች ግን ባሏን እንዴት ደስ እንደምታሰኘው የዓለም ነገር ታስባለች::» 1ቆሮ7፥33-34 ብሎ በተናገረው መሠረት ያገቡ ሰዎች ልቡናቸው እንደሚከፈልና እግዚአብሔርን በአንድ ልብ ሆነው ለማምለክ እንደሚቸገሩ ሁሉ ድንግልናቸውን ካጡ በኋላ ያገቡ ሰዎችም እንደዚሁ ልቡናን የሚከፍል ተግባር የፈጸሙ በመሆኑ በሙሉ ልብ አንዳቸው አንዳቸውን ማስደሰት ይሳናቸዋል፡፡
እንደዚህ ያሉ ባለትዳሮች ሩካቤ በሚፈጽሙበት ጊዜ ከዚያ አስቀድሞ ድንግልናቸውን ያጡበትን መንገድ ክፉም ሆነ ደግ መስለ በታያቸው መልኩ በሕሊናቸው ማሰላሰላቸው የማይቀር ነገር ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ የሐሳብ መክፈል ደግሞ እየፈጸሙት ባለው ሕጋዊ ሩካቤ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያመጣል፡፡ ስለዚህ ባል ሚስትን ሚስት ደግሞ ባሏን በሙሉ ልብ ማስደሰት አይችሉም መባሉ ትክክል ነው፡፡ ይህ የልቡና መከፈል የሚፈጠረው ድንግልናውን ባልጠበቀው ወገን ብቻ ላይሆን ይችላል፡፡ ድንግልናውን ጠብቆ የኖረውም ወገን ድንግልናውን ስላጣው (ስላጣችው) ወገን ሕይወት በሕሊናው መመራመር ይፈጠርበታል፡፡ ስለዚህ ምንም በአካል መዋሐድ ቢችሉም የልቡና ተዋሕዶ ለመፍጠር ይቸገራሉና ደስታቸው በእጅጉ ይቀንሳል፡፡
ይህን ለመሰለ ችግር መፍትሔው ከሁሉ አስቀድሞ ድንግልናን ማጣት የሚያስከትለውን አካላዊና ሕሊናዊ ቀውስ በመረዳት ድንግልናን መጠበቅ ሲሆን በተረፈ ግን በተቻለ መጠን ያለፈን ሕይወት አምኖ በመቀበል መርሳትና ለወደፊቱ የሚበጀውን ብቻ ማድረግ ይሆናል፡፡
ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
ምዕራፍ ስምንት ክፍል ዐራት
.................................................
ድንግልናን የመጠበቅ ጥቅም
በጎ ተግባር ጥቅም ሊኖረው ይገባል። ክርስቲያኖች እንኳን የሚጐዳ ሥራ ይቅርና ባይጐዳ እንኳን ምንም ለማይጥቅም ሥራ መልፋት የለባቸውም።ጥቅም ሲባልም በዋናነት የሚጠቀሰው የነፍስ ጥቅም ነው። «ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢከስር ምን ይጠቅመዋል።» በማለት ጌታችን የተናገረው ቃል በመጀመሪያ መታየት ያለበት የነፍስ ጥቅም መሆኑን ያስረዳል።ማቴ16፥26
መጽሐፍ ቅዱስ ሥራ ሁሉ ከጥቅም ጋር መያያዝ እንዳለበት ይናገራል፡፡ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «ሁሉ ተፈቅዶልኛል ሁሉ ግን የሚጠቅም አይደለም፡፡»በማለት ያንን ነገር ለማድረግ መብት ቢኖረንም ጥቅም ከሌለው ግን አለማድረግ መሻሉን ተናግሯል፡፡1ኛ ቆሮ10÷23 :6÷12
ሐዋርያው በተጨማሪ አንዳንድ ሥልጠናዎችና ልምምዶች ለሥጋዊ ነገር እንደሚጠቅሙ ከገለጸ በኋላ ድንግልናን ለመጠበቅ የሚደረግ መንፈሳዊ ልምምድ ግን ጥቅሙ ለሁለት ዓለም በመሆኑ ይበልጥ መጥቀሙን ሲገልጽ «ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔር መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለነገር ሁሉ ይጠቅማል፡፡» 1ጢም4፡8 በማለት ተናግሯል።
ይኸው ሐዋርያ ደግሞ ስለ ክብረ ድንግልና መላልሶ ካስተማረ በኋላ ለምን እንዳስተማረ ሲናገር «ይህንንም ለራሳችው ጥቅም እላለሁ» በማለት በድንግልና መኖር እንደሚጠቅም ተናግሯል።በድንግልና መኖር ጥቅሙ ለራስ እንጂ ለሌላ አይደለም።1ቆሮ7፥35
በድንግልና መኖር ከሚያስገኘው ሰማያዊ ጠቀሜታ በፊት በምድር ላይም ብዙ ጥቅምን ያስገኛል።ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹን ጠቅለል በማድረግ በአንድ ስፍራ በጥቂት ገጸ ንባብ ሐዋርያው እንዲህ ሲል ገልጿቸዋል።
"ኒቆዲሞስ"
በዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
ኒቆዲሞስ/፪/ክቡር፣/፪/
ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር፣/፪/
በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ፣
በመከራው ጽናት ይህን ዓለም ናቀ፣
መምህር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ፣
የትዕቢትን ጅረት : በትህትና : ተዋርዶ አደረቀ።
°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ።
°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°
ፍርሀትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ፣
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ፣
የመግነዙን በፍታ በሽቱ ያከበረ፣
ከመቅደሱ አንቀጽ : ላይረሳ : አምድ ሆኖ ታጠረ።
°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ።
°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°
ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ነገረች፣
ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች፣
ከጨለማው ኃጢአት ነቅታ ብርሃን ካየች፣
እንደ ኒቆዲሞስ : ነፍስህም : ተምራ ተመለሰ።
°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox