ethiopian_orthodox | Unsorted

Telegram-канал ethiopian_orthodox - የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

30344

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Subscribe to a channel

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጥር ፲፪
ቃና ዘገሊላ


"የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች"
ዮሐ ፪:፭

@Ethiopian_Orthodox

ቃና ከናዝሬት ከተማ በሰሜናዊ ምዕራብ በገሊላ አውራጃ የምትገኝ ከተማ ስትሆን በወቅቱ ትንሽና ገጠራማ መንደር ናት፡፡ ነገር ግን በውስጧ በተደረገው ተአምር መጽሐፍ ቅዱስ ስለመዘገባት ሁሌም የሚታወስ ታሪክ ያላት ሥፍራ ናት፡፡

ቃና ጌታችን ሁለት ታላላቅ ተአምራት ያደረገባት መንደር ስትሆን አንዱን ተአምር በቅርበት (በአካል ተገኝቶ) ሁለተኛውን ደግሞ በርቀት (ቃል ብቻ ተናግሮ) ያደረገው ተአምር እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ይህውም የጌታችን ቀዳሜ ተአምር የሆነው ቃና ሠርግ ቤት ተአምር ሲሆን፤ ሁለተኛው በቅፍርናሆም የንጉሥ ባለሟል የሆነ አንድ ሹም ጌታ ወደ ገሊላ እንደመጣ ሰምቶ ከቅፍርናሆም ሠላሳ ኪሎ ሜትር ተጉዞ በመምጣት ልጁ በንዳድ (yellow fever) መታመሙን ነግሮት ወደቤቱ ወርዶ እንዲፈውስለት ለመነው ፡፡ ዛሬ በሚሊየን የሚቆጠሩ ህጻናትና ነፍሰጡር እናቶች በአፍሪካና ኢስያ ብሎም በኢትዮጵያ ለሞትና ለስቃይ የሚዳረጉበት ህመም መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡ ለአፍሪካ ህጻናትና እናቶች ሞት ይርቅ ዘንድ ጌታ ሆይ ቃል ተናገር ሞት ሰምቶ ይደንግጥ ያለ እድሜ ሞት ይጥፋ እንበለው፡፡ጌታ ግን ለሹሙ ልጁ እንደማይሞት ሲነግረው ይህንን አምኖ ሄደ ልጁ ባለበት ቦታ ሆኖ ጌታ በተናገረበት ሰዓት ተፈወሰለት፡፡ ይህንን ነው በርቀት የተደረገ ተአምር የምንለው፡፡ ዮሐንስ ፬፥፵፮-፶፬

የቃና ዘገሊላ ሠርግ የጌታችን የመጀመሪያ ተአምር ነው ሲባል ከልጅነቱ ጀምሮ ተአምራትን ያደርግ እንደነበር ቅዱሳት መጻሕፍት ያስረዱናል፡፡ ነገር ግን በግልጥ በአደባባይ በህዝብ ፊት ማስተማር የጀመረው ከሠላሳ ዓመቱ በኋላ ነበር፡፡ይሄውም በብሉይ ልማድ ለማስተማር በነቢያነት የሚመረጡትና የሚላኩት ከሠላሳኛው እድሜ በኋላ ነበርና ነው፡፡ የቃና ገሊላ ሠርገኞችን ስም መጽሐፍ ቅዱስ በስም ባይጠቅስልንም ሊቃውንት ዶኪማስ እንደሆነ ሲያስተምሩ ለእመቤታችን ዘመድ መሆኑንም የሚጽፉም አሉ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ይህንን ተአምር ሲናገር “እንዲህ በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሠርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ ይላል”፡፡ በሰርጉ ጌታ የተገኘው ብቻውን አይደለም እናቱና ደቀመዛሙርቱ ነበሩ፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ቤተክርስቲያን ፈጣሪ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ስትሰብክ እመቤታችንን ቅዱሳንን የማትለየው፡፡ ይህንን እንድንሰብክ የነገረን ቅዱስ ዮሐንስ ነው፡፡

በክርስቲያኖች ልብ በህይወታችን በኑሮአችን ጌታን እንደማንለየው ድንግል ማርያምን ቅዱሳንን አንለይም፡፡እርሱ በአምላክነቱ ድንግል ማርያም በእናትነትዋ ቅዱሳን በምልጃቸው አንለያቸውም ፡፡ “እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ”። ዮሐ ፲፭፥፭ ዛሬ የአለም ሩጫ የመናፍቃን ተንኮል ትውልዱን ከድንግል ማርያም መለየት ከቅዱሳን መለየት አላማቸው አድርገውታል፡፡ ምናልባት መብቱን ቢያገኙ ቅዱስ ዮሐንስን በዚህ ምዕራፉ ጌታን አልሰበከም ይሉት ይሆን?

ጌታ በቃና ዘገሊላ ተአምር የጀመረው በሠርግ ቤት መሆኑን ቅዱስ ዮሐንስ ሲናገር በቃና ሠርግ ነበር ነው የሚለው፡፡ ይሄውም ሠርግ ቤትን የተአምር መጀመሪያ ያደረገበት ምክንያት ሰይጣን የሰውን ልጅ የመጀመሪያ ኃጢያት በማሰራት ያፈረሰው የጋብቻን አንድነት በመሆኑ በማዳኑም ሂደት የጉሰቆለ ጋብቻን ወደ ቀደመ ቅድስናው ለመመለስ ጋብቻን ለመባረክ በሠርግ ቤት ጀመረ፡፡

ሰይጣን አዳምንና ሔዋንን ከእግዚአብሄር ከለያቸው (ዕፀ በለስን ከበሉ) በኋላ መግባባት መስማማት አቃታቸው፤ አንዱ አንዱን ይከስ ጀመር አንድ አካል መሆናቸው ቀረ፡፡አዳም ህይወቴ ያላትን ሔዋንን አጥፊዬ ናት አላት፡፡ የጋብቻ አንድነት ጠፋ፤ ውድቀት ወደ ቤተሰብ ገባ፡፡አለመታዘዝ በዘር ወደ ሰው ልጅ ሁሉ ደረሰ፡፡ “ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ”፡፡ ሮሜ ፭፥፲፪

ስለሆነም ጋብቻን ይቀድስ ያከብር ዘንድ የሰው ልጆችን ብሎም የአዲሲቷን የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተክርስቲያን መሰረት የሆነው ቤተሰብ የሚመሠረተው ከተቀደሰ ቤተሰብ በመሆኑ ጋብቻን መባረክ የመጀመሪያ ተአምር እንዳደረገ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይነግረናል፡:

የቃና ገሊላ ሠርግ የጌታችን ፍጥረታት የሚታዘዙት፤ እንዲሁም የእመቤታችን ምልጃ የተገለጠበት ተአምር ነበር ፡፡ይህንንም የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፦ “የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው”። ሠርጉ መካከል ላይ ወይን ጠጅ አለቀ ይህ ለሰርገኛው ትልቅ ሀፍረት ነው ነገር ግን እርሷ ግን ጭንቀታቸውን፤ችግራቸውን ስላወቀች ያውም ሳያማክሯት የልባቸውን ሐዘን አውቃ ወይኑ ማለቁን ነገረችው፡፡ ከዚህ በላይ ለእመቤትችን የምልጃ ማስረጃ ምን ይሆን? ፡፡ዛሬም እንደዶኪማስ ሠርግ ሕይወታችን ብዙ ነገር ያልቅበታል። በተለይ ያለንበት ዘመን በሰዎች ዘንድ ፍቅር፤እምነት፤ሰላም የጠፋበት መተማመን የጎደለበት በመሆኑ እመቤትችን ልጅዋን ፍቅር እኮ የላቸውም፤ እምነት እኮ የላቸውም፤ ሰላም እኮ የላቸውም፤ በማለት የጎደለንን እዲሞላልን ትጸልያለች፤ጌታም ልመናዋን ወዶ ሲመልስ ጊዜዬ ገና አልደረሰም ሲል አማናዊውን ወይን ደሜን የምሰጥበት ጊዜ ገና አልደረሰም ማለቱ ነው፡፡ ጌታም ለእናቱ ልመና ይህንን የማላደርግበት ምክንያት የለም በማለት ሲመል፤ “ኢየሱስም፦ አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት”። ይህንን ቃል ነው እንግዲህ ካንቺ ጋር ምን አለኝ ስላላት ምልጃዋን አልተቀበለም በማለት ትርጉሙን ማጣመም የሚፈልጉት፡፡ ነገር ግን የንባቡም ሆነ ትርጉሙ ልመናሽን የማልቀበልበት የማላደርግበት ምክንያት የለም ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ይህንንም ቅዱሳት መጻሕፍት ሲያስረዱ፡- ኤልያስን በቤቷ የተቀበለች የሰራጵታዋ ሴት ልጅዋ በሞት ሲለይባት ታገለግለው የነበረውን የእግዚአብሔር ሰው ኤልያስን፦ "የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ ኃጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?" አለችው። ፩ኛ ነገ ፲፯፥፲፰ ይህን ማለቷ በእኔና ባንተ መካከል ምን ጠብ አለ ለማለት እንጂ የንቀት አነጋገር እንዳልሆነ መገንዘብ ይገባል፡፡
ከሰው የወጣው መናፍስት ኢየሱስን ባየው ግዜ “በታላቅ ድምፅም እየጮኸ፦ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ አለ” በማለት ሲናገር አንተ እኔን ማዘዝ አትችልም የሚል ትርጉም አይሰጥም፡፡

በዚህም መሰረት የእናቱን ልመና ስለተቀበለ "እርሷም እናቱም ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው፡፡" ይላል በዚህም ሰው አምላኩን ፈጣሪውን ይሰማ ይታዘዝ ዘንድ እንዲገባ አስተማረችን፡፡ የስራውን መጀመሪያ ባደረገው በዮርዳኖስ ሲጠመቅ እግዚአብሄር አብ የኢየሱስን ተወዳጅ ልጅነት እንዲሁም በደብረ ታቦር ላይ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ”። ማቴ 17፡5 እመቤታችንም የተናገረችው እግዚአብሄር አብ በዮርዳኖስ የተናገረውን በደብረ ታቦር ስለ ልጁ የመሰከረውን ቃል ነው፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
"ከውኃ እንዴት እንወለዳለን የሚል ሰው ካለ እንዴት ከአፈር ተወለድን ብዬ እጠይቀዋለሁ!!!" ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሰን፥ አደረሳችሁ።
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሥርዓተ ማኅሌት ዘጥምቀት

"ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአእዛኒክሙ አናቅጸ ጸሎት ሠናይ፤ ምሥጢራተ ሰሚዕ ሥላሴ ዘይተልዎ ርእይ፤ በአብትረ ያዕቆብ በርሀ ሥላሴክሙ ፀሐይ፤ ወተመሰሉ ሰብአ ዓይን አባግዓ ላባ ወማይ፤ ለኀበ አባግዕ ዘዮም ወጥምቀት ዓባይ።

ዚቅ
መኑ ይወርድ ውስተ ቀላይ፤ ክርስቶስ ውእቱ ዘወጽአ እማይ፤ እመንፈስ ቅዱስ ሠለስቲሆሙ፤ እለ አሐዱ እሙንቱ ፫ቲሆሙ፤ እለ ይከውኑ ሰማዕተ ፫ቲሆሙ፤ ለሊሁ ወረደ መንፈስ ቅዱስ፤ ከመ ይቀድስ ማያተ፤ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፤ ጸጋ ወጽድቅሰ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ኮነ።

ነግሥ
ሰላም ለማየ ዮርዳኖስ ዮሐንስ ዘአተቦ፤ መንፈስ ቅዱስ ከመ አጥበቦ፤ ሶበ መጽአ ቃል እምሰማይ ለተናብቦ፤ ነድ ለማየ ባሕር ከበቦ፤ ማይ ኀበ የሐውር ጸበቦ።

ዚቅ
ርእዩከ ማያት እግዚኦ፤ ርእዩከ ማያት ወፈርሑ፤ ደንገፁ ቀላያተ ማያት ወደምጸ ማያቲሆሙ።

ወረብ
ርእዩከ 'እግዚኦ'/፪/ ርእዩከ ማያት/፪/
'ደንገፁ'/፪/ ቀላያተ ማያት ደንገፁ ቀላያተ ማያት/፪/

ትምህርተ ኅቡዓት
እምሰማያት እምኀበ አብ አይኅዓ፤ በሕማማተ ሥጋሁ ቤዘወነ፤ ወደሞ ክቡረ መንፈሰ ሕይወት፤ ወቅድሳተ መንፈስ ወሀበነ፤ ወማየ መንጽሔ ዚአነ።

ወረብ
'ወደሞ ክቡረ'/፪/ መንፈሰ ሕይወት ወቅድሳተ መንፈስ ወሀበነ/፪/
ወማየ መንጽሔ ዚአነ/፬/

ምልጣን
ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ፤ ወለደነ ዳግመ እማይ ወእመንፈስ ቅዱስ፤ እሙነ ኮነ ለፀሐየ ጽድቅ አስተርእዮቱ፤ አማን፤ መንክር ስብሐተ ጥምቀቱ።

ወረብ
ክርስቶስ ተወልደ ክርስቶስ ተጠምቀ ክርስቶስ ተወልደ/፪/
'ወለደነ ዳግመ'/፪/ እመንፈስ ቅዱስ ወማይ/፪/

እስመ ለዓለም
ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ኀበ ዮሐንስ፤ ከመ ያጥምቆ በፈለገ ዮርዳኖስ፤ ወወጺኦ እማይ ተርኅወ ሰማይ፤ መጽአ ቃል እምደመና ዘይብል ዝንቱ ውእቱ ወልድየ፤ ዘአፈቅር ሎቱ ስምዕዎ።

ወረብ
ሖረ ኢየሱስ እምገሊላ ኀበ ዮሐንስ/፪/
ከመ ያጥምቆ በፈለገ ፈለገ ዮርዳኖስ/፪/

ዕዝል
ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል፤ ቃለ እግዚአብሔር፤ ውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ፤ ወተገሠ በሥጋ፤ መንፈስ ዘኢይትገሠሥ ወዘኢይትለከፍ፤ ዘመልዕልተ ሰማያት ዘመልዕልተ ሥልጣናት፤ ወገብረ መንጦላዕተ ሥጋ ሰብእ መዋቲ፤ ወረደ ዲበ ምድር፤ ወአንሶሰወ ውስተ ዓለም፤ በበህቅ ልህቀ በ፴ ክረምት፤ በዮርዳኖስ ተጠምቀ።

ምልጣን
ዘመልዕልተ ሰማያት ዘመልዕልተ ሥልጣናት፤ ወገብረ መንጦላዕተ ሥጋ ሰብእ መዋቲ።

አመላለስ
ወገብረ መንጦላዕተ/፪/
ሥጋ ሰብእ መዋቲ/፪/

አቡን
በ፭: እስመ ሰምዓ ይቀውም ሎቱ አብ ናዛዚ በርእየተ ርግብ ውስተ ምጥማቃት እንዘ ይብል፤ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር፤ ዘኪያሁ ሠምርኩ ይቤ፤ ወበይእቲ ሥጋ እንተ ነሥአ መድኅን እምቅድስት ድንግል፤ ኪያሃ ሠምረ አብ በሥጋ ምጽአቶ።

ቅንዋት
እምሰማያት ወረደ፤ ወእማርያም ተወልደ፤ ከመ ይሥዓር መርገማ ለሔዋ ዲበ ዕፅ ተሰቅለ፤ በ፴ ክረምት በዮርዳኖስ ተጠምቀ፤ ዘነቢያት ሰበክዎ ወአስተርአየ ገሃደ።

ሰላም
ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ፤ ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ፤ ወበእንተ ጥምቀቱ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ ገብአ ወወጽአ በሰላም።

ምልጣን
ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ፤ ቆመ ማዕከለ ባሕር፤ ገብአ ወወጽአ በሰላም።

ወረብ
ኃዲጎ ፺ወ፱ ነገደ/፪/
ማዕከለ ባሕር ቆመ ማዕከለ ባሕር/፪/

💠 መልካም በዓል! 💠

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ርዕዩከ ማያት
ርዕዩከ ማያት እግዚኦ ፥ ርዕዩከ ማያት ወፈርሁ፣/፪/
ደንገጹ ቀላያተ ማያት፥ ወደምጸ ማያቲሆሙ።/፬/ኧኸ

አቤቱ፥ ውኆች አዩህ፥ ውኆችም አይተውህ ፈሩህ፣/፪/
ጥልቆች ተነዋወጡ፥ ውኆችም ጮኹ።/፬/ኧኸ
              ~ መዝ ፸፯፥፲፮ ~

©በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከተራ

ከተራ ማለት ምን ማለት ነው!?
የበዓለ ጥምቀት ዋዜማ የታቦቱ ወደ ወንዝ መውረድና ባሕረ ጥምቀቱን ማዘጋጀት ሃይማኖታዊ ታሪክና ምሳሌ አለው። የቃልኪዳኑን ታቦት አክብሮ መጓዝና ወደ ወንዝ መዉረድ የተጀመረዉ በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነዉ።
እያሱ በሙሴ እግር ተተክቶ ሕዝበ እስራኤልን እየመራ ከዮርዳኖስ ወንዝ ሲደርስ ባሕሩ ለሁለት ይከፈልና ወራጅም ይቆም/ይከተር/ነበር። እስራኤል ዘስጋ ወደምድር ርስት ለመግባት ሲሻገሩ ፤ድንካን ጥለዉ የቃል ኪዳኑ ታቦት በድንካኑ ዉስጥ አድርገዉ ለዋዉያኑ በዙርያው ፣ካህናት ደግሞ በዉስጥ ሁነዉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አድረው በማለዳ ተሻግረዋል (ኢያሱ3፥8-9)። ካህናቱ የቃልኪዳኑን ታቦት አክብረዉ የወንዙን ዳርቻ በረገጡ ጊዜ እንደ ክረምት ማዕበል ይወርድ የነበረው ዉሀ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደግድግዳ ወደ ላይ ይቆማል ።

➱ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ታቦተ ፅዮንን ያከበሩት ካህናት ከወንዙ መሀል ይቆሙ ነበር። በዚሁ መሰረት "ወተጠምቀ እገሪሆሙ ለካህናት "ወይም የካህናት እግሮቻቸው የዮርዳኖስ ዉሀን በመርገጣቸዉ እንደክረምት ሆኑአቸው ።
በሐዲስ ኪዳን ጌታችን ለመሰረተዉ ሥርዓተ ጥምቀት ምሳሌ ነበረ።ቤተክርስቲያንም የጥምቀት ዋዜማ ከተራ ብላ የጠራቺዉ ከዚህ በመነሳት ነዉ።

➱ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ የላይኛዉ ሸሽቶ ወደላይ ተመልሶ ሽቅብ ፈሷል።የታቹም ወደላይ ሸሽቷል የላይኛዉ ፈሳሽ ተቋርጦ እንደክምር ተቆልሎ ቀርቷል።

ቅዱስ ዳዊት የተመለከተዉ ይሄንኑ ነዉ።ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ቤዛነት ተቋርጦ ፣የታቹም ፈፅሞ መድረቁ ኃጢአተ አዳም የመጥፋቱ ምሳሌ ነዉ። እስራኤል ፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ኢያሪኮ መሄዳቸው ምእመናን የጥምቀት ከኃጢአት ቁራኝነት ተላቀዉ እግራቸዉ ወደ ልምላሜ ገነት ወደ እረፍት መንግስት ሰማያት አቅንተዉ ለመሄዳቸዉ ምሳሌ ነዉ።
🌿ኢያሱ እንደ ጌታ
🌿እስራኤልን እንደ ምእመናን
🌿ዮርዳኖስን ጥምቀት
🌿ምድረ ርስት ለገነት መንግስተ ሰማያት ምሳሌ ነዉ።
🌿ታቦቱን አክብሮ የሚሄደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ ፣ታቦቱ የጌታችን፣ ባሕረ ጥምቀት የዮርዳኖስ ወንዝ።

ታቦቱን አጅበው የሚሄዱት በዓሉን የሚያከብሩ ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐን ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩት ሰዎች ምሳሌ ናቸውና ።

ታቦታቱ በጥምቀት ዋዜማ ከመንበራቸው ወደ ጥምቀት ባሕር መዉረዳቸዉና በዚያን ማደራቸዉ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከማታዉ ጀምሮ መዉረድንና ተሰልፎ ተራዉን ሲጠብቅ ማደሩን ያጠይቃል ።

🌿ጥምቀት የሞቱና የትንሳኤዉ ምሳሌ ነዉ። ከኃጥአን ጋር ተቆጥሮ እንዲጠመቅና እንዲሰቀል የተፃፈዉ ቃል ንስሐን ጥምቀትን የማያስፈልገዉ ሲሆን ነገር ግን ፍፁም ኃጥእ መስሎ በዮሐንስ እጅ ጥምቀትን ለመፈፀም በማየ ዮርዳኖስ እግር ተጠመቀ (ኪ.ወ.ክ517)
🌿ጌታችን የተጠመቀው በወርሐ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናብ ፣የበረዶ ጊዜያት ነዉ። ከወንዝ ዳር ያለመጠለያ መዋልና ማደር አልቻሉም በመሆኑም ከዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄድ ሰዎች ሁሉ በዮርዳኖስ ዙርያ ድንኳናቸው ተክለዉ ያርፉ ነበረ።

🌿በዚህ አንፃር ዛሬም በባሕረ ጥምቀት ዙርያ ድንዃኖች ዳሶች ይጣላሉ ።

👉በሀገራችን በተለያዩ አከባቢዎች በተለይም በአክሱም የንግስተ ሳባ መዋኛን፣ ጎንደር የአፄ ፋሲለደስ መዋኛን፣በላስታ የላሊበላን መዋኛ፣በሸዋ የዘርአ ያዕቆብም ፍርድ መስጫ አደባባይ ፣አርባ አራቱ ታቦት የሚያድርበት የሸንኮራ ሜዳን"ራብቴ ወንዝን"፣በአዲስአበባ ደግም ጃን ሆይ ሜዳ(ጃን ሜዳን)ወዘተ የመሳሰሉትን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል ።
👉እነዚህ ቦታዎች ዛሬም ድረስ ተከብረዉ ይገኛሉ። እኛ በዚህ ወቅት ታቦት ይዘን ፣ከወንዝ ወርደን፣ድንኳን ተክለን ማክበራችን ይፈፀማል ።

ከተራ በመባል የሚታወቀው በዋዜማው ሠርገዉ/1981፣8/እንደገለፁት
ከተራ የሚለዉ ቃል ከተረከበ ካለዉ የግእዝ ግስ ነዉ። ከተራ ፍቺዉ ውኃ መከተር ፣ወይም መገደብ ማለት ነዉ።ብለዉ ሲፈቱ ደስታ ተክለወልድ /1962፣694/ ደግሞ የጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 የጠራ ወራጅ ውኃ የሚከተርበት ፣ ታቦትና ሰዉ ወደ ዠማ ወንዝ የሚወርድበት ጊዜ ነዉ በማለት ሊቃዉንት ይፈቱታል በየዓመቱ ጥር 10ቀን የምእመናኑን አብዛኛው ስራ ውኃን መከተርና መገደብ መሆኑ ዕለቱ ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል ውኃው የሚከተረዉ በማግስት ጥር 11 ቀን የጥምቀት በዓል ስለ ሚከበር ለህዝቡ መጠመቂያ እንዲሆን ነዉ።በየሰበካዉ ቦታ ተለይቶና ተከልሎ ታቦቱ በዳስ ወይም በድንኳን የሚያድርበት የተለያዩ የውኃ ግድብ የሚበጅበት ስፍራ (ባሕረ ጥምቀት ) የታቦት ማደሪያ እየተባለ ይጠራል።ባሕር ፦የውኃ ማሰባሰቢያ (ምእላደ ማይ፣ የውኃ ማከማቻ )ምቁመ ማይ።በሌላ አነጋገር የውኃ አገር ዓለም ማይ ነዉ።

እንኳን አደረሳችሁ!

🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩
🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨
🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የከተራ፣ የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓል መዝሙራት ስብስብ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"እምሥራቀ ፀሐይ"
እምሥራቀ ፀሐይ አስከነ አረብ ይት አኮት ስሙ ለእግዚአብሔር አምላክነ ኪያከ ወልዶ ዘፈነወለነ{፪}
ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀካህናቲነ አስተጋብአነ(፪) ሀበ ትረፍቅ መካነ{፪}

ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ የአምላችን የእግዚአብሔር ስሙ ይመስገን ልጁ ወዳጁን አንተን ልኮልናልና{፪}
ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህናትን ወደ አንተ ሰብስበን(፪) እኛ እኛን ልጆችህን{፪}

©በዘማሪት በላይነሽ አሰፋ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጥር ፮
በዓለ ግዝረቱ ለክርስቶስ


ጥር ስድስት በህዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጸመ ልሳነ ዕፍረት ሐዋርያው ጳውሎስ ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ ብሎ እንደተናገረ።

ለብዙዎችም ጌታችን ወደ ቤተ ግዝረት እንዳልገባና እንዳልተገረዘ ይመስላቸው ነበር እነርሱ እንዳሰቡት ሁኖ ቢሆን ኑሮ አይሁድ ታላቅ ምክንያትን የሚያገኙ በሆኑ ነበር ጌታችን ግን የግዝረትን ሕግ ፈጸመ ለእኛ በግዝረት ፈንታ የክርስትና ጥምቀትን ሰጠን የፋሲካውንም ቂጣ በላ በእርሱም ፈንታ ሥጋውንና ደሙን ሰጠን።

የከበረ ወንጌል ስምንተኛው ቀን በተፈጸመ ጊዜም ሕፃኑን ሊገዝሩት ወሰዱት ሳትፀንሰው መልአኩ እንዳወጣለት ስሙን ኢየሱስ አሉት እንዳለ ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ማርያም ጻድቅ አረጋዊ ዮሴፍን "እንደ ሕጉ ልጄን እንዲገርዘውና ስሙንም እንድንሰይመው ብልህ የሆነ ገራዥ ሰው አምጣልኝ" አለችው። ዮሴፍም ሔዶ የሚገርዝ ባለሙያ አመጣ ያ ባለሙያም ሕፃኑን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በእናቱ በንጽሕት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ አየው "እንድገርዘው ሕፃኑን በጥንቃቄ ያዙት" አላቸው።

ሕፃን ጌታ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው "ባለሙያ ገራዥ ሆይ ደሜ ሳይፈስ ትገርዘኝ ዘንድ ትችላለህን በዚያች ዕለት ካልሆነ በቀር ደሜ አይፈስምና ጐኔን በጦር ሲወጉኝ ያን ጊዜ ውኃና ደም ይፈሳል ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆቹ መድኃኒት ይሆናል።"

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ያ ባለሙያ በሰማ ጊዜ አደነቀ ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሥቶ ከሕፃኑ ጌታ እግር በታች ሰገደ ያንጊዜም ምላጮቹ በእጆቹ ላይ ቀልጠው እንደ ውኃ ሆኑ የከበረች ድንግል እመቤታችንን ማርያምን "ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ይህ ልጅሽ ስለርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው" አላት።

ሕፃኑም ለዚያ ባለሙያ ዳግመኛ መልሶ እንዲህ አለው "እኔ ነኝ ትገዝረኛለህን ወይስ ተውክ ወይም ያባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ እኔ ላድርግ" ያም ባለሙያ "የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው" አለው ሕፃን ጌታችንም "አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ የሕዝቡ ሁሉ አባቶች የሆኑ ናቸው ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጣቸው" ባለሙያውም "እኔ ከአንተ ጋር እናገር ዘንድ አልችልም በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና" አለው።

በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ ጌታችን ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ "አባት ሆይ ለአብርሃም ለይስሐቅ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ" አለ። ያን ጊዜ ያለ ሰው እጅ በሕፃኑ ሥጋ ላይ ግዝረት ተገለጠች። ድንግልናዋ ሳይለወጥ ከድንግል ማሕፀን እንደ መውጣቱ የጌታችን ግዝረቱ የማይመረመር ሆነ እንዲሁ ወደ ሐዋርያት በተዘጋ አዳራሽ መግባቱና መውጣቱ እንደማይመረመር እንዲሁ እንደ ፈቀደ ከረቀቀ ጥበቡ ችሎታውን በመገረዝ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቆረጥ ገለጠ።

አዳምንና ልጆቹን ያድናቸው ዘንድ በፈቃዱ ከጐኑ በመስቀል ላይ የሚፈሰው ደምና ውኃ ካልሆነ በቀር ብዙም ሆነ ጥቂት ሊሆን አይችልም እርሱ በፈቃዱ ሕጉ እንዲፈጸም አስቀድሞ አዘዘ እንጂ።

ያም ባለሙያው ገራዥ ይህን ተአምር ባየ ጊዜ የሕፃኑንም ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ የክብር ባለቤት ከሆነ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር በታች ሦስት ጊዜ ሰገደና "በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ የእስራኤልም ንጉሥ ነህ" አለው። ከዚህም በኋላ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተአምራቱ ያየውንና የሰማውን እየተናገረ ወደ ቦታው ሔደ።

ለእርሱ ለጌታችን ከቸር አባቱ ጋራ ማሕየዊ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋራ ክብር ምስጋና ስግደትም ይሁን: አሜን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት  ወቅታዊ  ጉዳዮችን አስመልክተው  አባታዊ የሰላም ጥሪ አስተላለፉ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በአጠቃላይም የመጽሀፍትን ትርጉምና የአነጋገር ዘይቤ ካለማወቅ የሚመጣ ስህተት ከመሆኑም ባሻገር ለገዛ ጥፋት መጻሕፍትን የሚያጣምሙ ስለመኖራቸው፤ ሲናገር “ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ”። ፪ኛ ጴጥ. ፫፥፲፮
ከዚያም በውሃ የተሞሉ ጋኖች ወደ ወይን ተለወጡ፡፡ ይህ ተአምር በዮሐንስ ወንጌል ከተጻፉት አምላክነቱን ከገለጸባቸው ሰባት ምልክቶች (ተአምራት) ውስጥ ሲሆን በፍጥረታት ላይ ስልጣን እንዳለው ያሳየበትም ነበር፡፡ መርከቢቱን ከማእበል መናወጽ ፤ደቀመዛሙርቱን ከመጨነቅ አድኖ ማእበሉን ጸጥ ባደረገ ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ፍጥረታት ለእርሱ መታዘዙን ሲያዩ፤”ነፋሳትና ባሕርስ ስንኳ የሚታዘዙለት፥ ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው? እያሉ ተደነቁ “። ይላል፡፡ ከዚህም ባሻገር እርሱ ሰው ሆኖ ተገልጦ የሰውን አልጫ ማንነት በእርሱ የድህነት ሥራ ለወጠ፡፡ የብዙዎቻችንን የትላንት ማንነት በኃያአት ያሳለፍነውን ጊዜ ውሃችንን ለውጦት ነው በቤቱ እንድንኖር ያደረገን፡፡ ኢሱስም ቀድተው ለአሳዳሪው እንዲሰጡ አዘዘ፡፡

በዚህመ ዶኪማስ ተደነቀ በደስታ ተሞላ ታዳሚዎቹም የተለወጠው ወይን ጠጅ ከመጀመሪያው በእጅጉ በመብለጡ ተገርመው “ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው”። ሰውም በአግዚአብሄር ሲለወጥ እንዲሁ ነው። በኃጢአት ያሳለፈው ህይወት መራራ ነው። በእግዚአብሔር መደገፍ ሲጀምር፤ ማመን ሲጀምር፤ የመረረ ሀይወቱ ተለውጦ ለሌሎች መጣፈጥ ይጀምራል፡፡ ሰው የእግዚአብሔርን ፍቅር ካልቀመሰ በቀር ሊያውቀው አይችልም፤ እርሱን ለማወቅ ቃሉን መጠጣት፤ ስጋውና ደሙን መንፈሳዊውን ምግብ መመገብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ነው የክርስቲያኖች እምነት መንፈሳዊ ህይወት የሚቀይረው፤ ለመንግስቱ የሚያበቃው፡፡ ደቀመዛሙርቱ ይህንን ቃና ወይን መለወጥ ባዩና በቀመሱ ግዜ እምነታቸው ጨመረ “ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ” ይለናል፡፡ በአጠቃላይ የቃና ዘገሊላ በዓል ብዙ የምንማርበት ሲሆን የጌታ ህይወት ለዋጭነት፤ የድንግል ማርያምን አማላጅነት ተገልጦ፤ ያየንበት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ነው፡፡

የአምላካችን ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

©መ/ር ንዋይ ካሳሁን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መጽዐ ቃል እም ደመና ዘይብል ዘይብል፤(፪)
ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር።(፪)

መጣ ቃል ከደመና እንደዚህ የሚል፤(፪)
የምወደው የማፈቅረው ልጄ ይኽ ነው።(፪)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"መኑ ይወርድ"
መኑ ይወርድ ውስተ ቀላይ{፪}
አሐዱ እምነ ሠለስቱ ወልድ/ክርስቶስ ውእቱ{፪}

ዳዊት በመዝሙሩ የተነበየለት
ውኆች አይተው ደንግጠው የሸሹት
ኮረብቶች እንደእንቦሳ ዘለው ያከበሩት
በውኃ የተጠመቀው እርሱ(፪) ነው መድኃኒት

በልዩነት መንፈስ ታጥሮ ለነበረው
ህዝብና አህዛብ ተብሎ ለተለየው
በዮርዳኖስ ተጠምቆ አንድ ያደረገን
ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ እግዚአብሔር ነው

በአዳም እና ሄዋን የነበረውን እዳ
ደምስሶ ሊያድነን ከዘለዓለም ፍዳ
በሰውነቱ ረቅቆ በአምላክነቱ የሻረው
ወልደ እግዚአብሔር ወልደ(፪) ማርያም ነው

ጌታችን ሲጠመቀ በዮሐንስ እጅ
ምሥጢር ተገለጠ የድኅነት አዋጅ
መንፈስ ቅዱስ በእርግብ አብም በደመና
ተገልጠው አሳዩ ወልድ ወልደ አምላክ ነውና

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጥር ፲፩
ጥምቀተ ኢየሱስ


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላሳ ዓመት ሲመላው ዮሐንስ ሰላሳ ዓመት ከስድስት ወር ሲሆነው በዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ሄደ፤
🌿 ለምን ወደዮሐንስ ሄደ ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ ለምን አልመጣም ቢሉ ባሪያ በጌታው እጅ ይጠመቃል እንጂ ጌታ በባሪያው እጅ ይጠመቃልን ቢሉ ?

1. ለትህትና

ጌታችን ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ሰው የሆነው ለትህትና ነው እንጂ ለልእልና አይደለምና

2. አብነት ለመሆን

ጌታችን ዮሐንስን መጥተህ አጥምቀኝ ቢለው ዛሬ ነገሥታት መኳንንት ሀብታሞች መጥታችሁ አጥምቁን ይሉ ነበርና ሂዳችው ተጠመቁ ለማለት።

🌿 ከሌሎች ወንዞች ለይቶ ጥምቀቱን ለምን በዮርዳኖስ አደረገው ቢሉ?

1. ትንቢቱን ለመፈፀም

ዮርዳኖስ ወደሃላው ተመለሰ ብሎ መዝሙረኛው ዳዊት ስለ ዮርዳኖስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈፀም ነው።

2. የአዳምና የሄዋን የእዳ ደብዳቤአቸውን ለመደምሰስ

ከእለታት አንድ ቀን ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን ላይ የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ ስቃይ አጽንቶ ስመ ግብርናታችውን ጽፋችሁ ብትሰጡኝ ስቃይ አቀልላችኋለሁ ብሏቸው ስቃዩን ያቀለለልን መስሏቸው።

አዳም የዲያብሎስ ባሪያ ነው ሔዋን የዲያብሎስ ባሪያ ናት ብለው ጽፈው ሰጡት።

ያን ተቀብሎ በሁለት እብነ ሩካም ጽፎ አንዱን ሲኦል አንዱን ዮርዳኖስ ጥሎት ነበርና በዮርዳኖስ የተጣለውን በጥምቀቱ ለመደምሰስ ዮርዳኖስን መርጧል።

ሲጠመቅም እንደአምላክነቱ አቅልጦ እንደ ሰውነቱ ረግጦ የእዳ ደብዳቤአቸውን አጥፍቶላቸዋል ።

በሲኦል የጣለውን በዕለተ ዓርብ በአካለ ነፍስ ወርዶ ደምስሶታል።

ጌታችን ዮሐንስን "አጥምቀኝ" ሲለው

"ሌላውን
በአንተ ስም
በአብ ስም
በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠምቃለው አንተን በማን ስም ላጥምቅህ?" አለው።

"የቡሩክ አብ ልጁ ብርሃንን የምትገልጥ ይቅር በለን የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ እነሆ ክህነትህ እንደ መልከጼዴቅ ክህነት ለዘለአለም ነው" እያልክ አጥምቀኝ አለው።

+የአብ ልጅ መሆኑን

+ብርሃን የሚገልጥ መሆኑን

+ይቅር ባይ መሆኑን

+የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ መሆኑን

+ክህነቱ ዘለዓለማዊ መሆኑን እየመሰከረ አጥምቆታል

🌿ጥምቀቱን በውሃ ያደረገው ስለምን ነው ቢሉ?

+ውሃ በዙፋን ካለ ንጉሥ በአደባባይ እስካለ ጽኑስ ለሁሉ የሚገኝ ነው።

+ውሃ ጽንፍ እስከ ጽንፍ ይፈሳል ጥምቀትም ጽንፍ እስከ ጽንፍ ይደርሳልና

+ውሃ ከእድፍ ያነጻል ጥምቀትም ከኀጢአት ያነጻልና

+ውሃ የወሰደው ፍለጋ የለውም በጥምቀትም የተሰረየ ኀጢአት በፍዳ አያስዝምና

+ውሃ መልክ ያሳያል መልክ ያለመልማል

ጥምቀትም መልክአ ነፍስ ያሳያል መልክአ ነፍስ ያለመልማልና

+በውሃ የታጠበ ልብስ እየቀደም እየነፃ ኃይል ግዘፍ እየነሳ ይሄዳል

ምእመናንም ተጠምቀው ገድል ትሩፋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰሩ እየጨመሩ ይሄዳሉና

+ርብቃ ለይስሐቅ የታጨችው ውሃ ስትቀዳ ነው

ምእመናንም ለክርስቶስ ሙሽራነት የሚታጩት በውሃ ተጠምቀው ነውና

+በውሃ ቀድሞ ሰብአ ትካት ሰብኣ ግብጽ ጠፍተው ነበርና ውሃ ለመአት እንጂ ለምሕረት አልተፈጠረም ብለውት ነበርና ለመአትም ለምሕረትም እንደተፈጠረ ለመግለጽ ከሁሉም ውሃን መርጦ በውሃ ተጠመቀ።

በመአር በወተት በወይን በዘይት ተጠምቆ ቢሆን ኑሮ ሀብታሞች እንጂ ድሃዎች አያገኙትምና ሁሉ በሚያገኘው በውሃ ተጠመቀ።

ሲጠመቅም መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዷል።

🌿መንፈስቅዱስን ስለምን ርግብ አለው ቢሉ?

+ርግብ ሀዳጊተ በቀል ናት መንፈስ ቅዱስም ሀዳጌ በቀል ነውና

+ርግብ በኖህ ጊዜ ኀፀ ማየ አይኅ ነትገ ማየ አይኅ ስትል ቆጽለ እፀ ዘይት ይዛ ተገኝታለች መንፈስ ቅዱስም ተስፋ መስቀልን ያበስራልና

+ርግብ ክንፋን ቢመቷት እንቁላልዋን ቢሰብሩባት ቤታን ካላፈረሱባት ቦተዋን አትለቅም መንፈስ ቅዱስም ኀጢአት ቢሰሩም ለንስሓ ይጠራል እንጂ ፈፅሞ ካልካዱት አይርቅምና ።

🌿ጥምቀቱን በመአልት ያላደረገው በሌሊት ያደረገው ስለምነው ቢሉ?

በመአልት አድርጎት ቢሆን መንፈስ ቅዱስ በቁሙ ርግብ ነው ብለው በተጠራጠሩ ነበና

🌿አሁንስ ርግብ አለመሆኑ በምን ይታወቃል ቢሉ ?
ጌታችን የተጠመቀ ከሌሊቱ አስር ሰአት ነው ፤በአስር ሰአት ወፎች ርግቦች አይበሩም ተሀዋስያን ከቦታቸው አይንቀሳቀሱምና በዚህ ርግብ አለመሆኑ ይታወቃል።

መንፈስ ቅዱስ የወረደው ከውሀው ከወጣ ከዮሀንስ ከተለየ በሇላ ነው፤ ከውሃው ሳለ ወርዶ ቢሆን ለቀድሶተ ማያት የወረደ ነው ባሉ ነበርና።

ከዮሐንስ ጋራም ሳለ ቢሆን ስለ ክብረ ዮሐንስ የወረደ ነው ባሉ ነበርና ።

ሲወርድም ረቦ ወርዷልቢሉ
አብ ምሉእ ነው ፤አንተም ምሉእ ነህ
እኔም ምሉእ ነኝ ሲል ነው።

አንድም አሰይፎ ወርዷል ቢሉ፤ የብሉየ መዋእል የአብሕይወት ነኝ፤የብሉየ መዋእል የአንተም ህይወት ነኝ።

እኔም ብሉየ መዋእል ሕይወት ነኝ ሲል ነው።
ወርዶም ራሱን ቆንጠጥ አድርጎ ይዞታል

አብ አኃዜ ዓለም ነው
አንተም አኀዜ ዓለም ነህ
እኔም አኀዜ ዓለም ነኝ ሲል ነው።

መውረዱ ለአብነት ነው

እናንተም ስትጠመቁ እንደዚህ እወርድላችዋለው ሲል ነው።

ከዚህ በሃላ አብ በደመና ሁኖ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት ብሎ ልጁ መሆኑን መስክሯል።

🌿ጌታችን ሲጠመቅ አንድነት ሶስትነት ተገልፇል

ወልድ በመጠመቅ
መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በመውረድ
አብ በደመና ሁኖ በመመስከር

አንድ ሲሆኑ ሶስት ሶስት ሲሆኑ አንድ መሆናቸው ተገልጧል ማቴ 3÷13-17።

+++መልካም በዓል+++

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"እግዚኡ መርሐ"
እግዚኡ መርሐ ዮርዳኖስ አብፅሃ /፪/
ወበህየ ዮሐንስ ወበሕየ ፍፁመ ተፈሥሐ /፪/

ጌታውን መራና ዮርዳኖስ አደረሰው /፪/
በዚህም ዮሐንስ በዚህም ፈጽሞ ደስ አለው /፪/

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ቅዱስ እግዚአብሔር"
ቅዱስ እግዚአብሔር ኃያል ሕያው ዘኢይመውት/፪/
ዘተወልደ እማርያም ወተጠምቀ በዮርዳኖስ
ዘተወልደ እማርያም ተሰሀለነ/፪/

ቅዱስ እግዚአብሔር ኃያል ሕያው የማይሞት/፪/
ከድንግል የተወለድክ በዮርዳኖስ የተጠመቅክ
ከድንግል የተወለድክ ይቅር በለን/፪/

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጾመ ገሃድ /ጾመ ድራረ ጥምቀት/

ጾመ ገሃድ (ጋድ)፦ የቃሉ ትርጕም «ገሃድ» ሲል መገለጥ፥ «ጋድ» ሲል ለውጥ ማለት ነው። ይኸውም የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መገለጥን የምናስብበት ነው። አንድም ጋድ ተብሎም ይጠራል፤ ጥምቀት ረቡዕ፣ ዓርብ ቢውል በዚያ ለውጥ ማግሰኞና ሐሙስ ይጾማልና።

ጋድ /ጾመ ድራረ ጥምቀት/፦ ይህ ጾም የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት በማሰብ የጥምቀትን ዋዜማ ከምግብ መከልከል ነው። የሚቆርብ ሰው አክፍሎ የሚያድር ስለሆነ የጥምቀት ድራር /ዋዜማ/ ጾም ነው።

የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ዕለት በሚውልበት ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ ማግሰኞንና ሐሙስን በመጾማችን ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል። በዚህም የጾምና የበዓል ማክበር ይከናወንልናል።

የጥምቀት ዋዜማ ሰኞ፣ ማግሰኞ፣ ሐሙስ ከሆነ ጾም ነው፤ በአጋጣሚ ደግሞ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ከጥሉላት ምግቦች ብቻ ይጾማል። ሆኖም ጥምቀት በየትኛውም ዕለት ቢውል በየዓመቱ ሁልጊዜ የጥምቀትን ዋዜማ እስከ ዕርበተ ፀሐይ እንጾም ዘንድ አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብንና ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ይሆን ዘንድ ሥርዓትን ሠርተውልናል።

በ2017 ዓ.ም የጌታችን በዓለ ጥምቀት ጥር 11 ቀን በዕለተ እሑድ ስለሆነ ጾመ ጋድ /ገሃድ/ ጥር 10 ቀን በዕለተ ቅዳሜ ይሆናል ማለት ነው። ስለሆነም በቀዳሚት ሰንበት መጾም አይገባምና ጠዋት ከቅዳሴ በኋላ ከጥሉላት የተለየ ምግብ ይበላል። ነገር ግን የጥሉላት ምግቦችን(ሥጋ፣ እንቁላል፣ ወተት፣ ዓሣ ወዘተ..) መመገብ ፈጽሞ የተከለከለ ነው

ምንጭ፡
- የጽድቅ በር /አለቃ አያሌው ታምሩ/
- ሰባቱ አጽዋማትና ታሪኮቻቸው /በመ/ር ኃ/ሚካኤል ተፈራ/

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ቅድመ ዓለም ንጉሥ ዘለዓለም ሥላሴ"

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጥር ፯
በዓለ ሥሉስ ቅዱስ ሕንጻ ሰናዖርን ያፈረሱበትና ቅዳሴ ቤታቸው ነው

ጥር ሰባት በዚች ቀን በዓለ ሥላሴ የሚከበረው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን ሌላው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው::

ሕንጻ ሰናዖር
ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም: ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር:: ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ::

ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ:: በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ::

ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ:: ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል:: ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል::

መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል:: ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው:: ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን::

ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም:: የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና:: ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ::

ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ:: እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ:: ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት:: ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል::

ቅዳሴ ቤት
በ1684 ዓ.ም አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::

ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን: ሠራዊት: መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል:: በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል: ደግ: ጥበበኛ: አስተዋይ: መናኝ ንጉሥ ነውና::

ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ.ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::

ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ"
በዘማሪት አዜብ ከበደ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጥር ፬
ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ

ጥር አራት በዚህች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደው የከበረና የተመሰገነ ወንጌልን የጻፈ የሐዋርያው ዮሐንስ የፍልሰቱ መታሰቢያ ሆነ።
----------------------------------
ስ ዮሐንስ ሀገሩ የገሊላ አውራጃ ሲሆን ከወንድሙ ከያዕቆብና ከአባቱ ከዘብዴዎስ ጋር ዓሣ እያጠመደ ይኖር ነበር። እናቱም ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ እንደሆነችና ማርያም እንደምትባል የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ይመሰክራል። ዮሐንስ ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ የታላቁ ያዕቆብ ታናሽ ወንድም ነው።

ለዚህም ቅዱስ ወደ እስያ ሀገር ይሔድ ዘንድ ዕጣው በወጣ ጊዜ እጅግ አዝኖ አለቀሰ እነርሱ ክፉዎች ከሀዲዎች ልባቸው የደነደነ መሆናቸውን አውቋልና ግን ከጌታችን ኃይልን መጽናናትን አግኝቶ ከደቀ መዝሙሩ ከአብሮኮሮስ ጋር ወጥቶ ወደ ክፍሉ ሔደ።

ወደ ኤፌሶንም ሊሔድ ወዶ በመርከብ ላይ ተሳፈረ መርከቡም ተሰበረ እየአንዳንዱ በመርከብ ስባሪ ሠሌዳ ላይ ተንጠለጠለ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስንም የባሕሩ ማዕበል ወደአንዲት ደሴት አደረሰው ቅዱስ ዮሐንስ ግን በባሕሩ ማዕበል መካከል አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ኖረ።

ከዚህም በኃላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስ ወዳለበት ወደ የብስ ባሕሩ ተፋው ስለ መገናኘታቸውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት በዚያን ጊዜም ተነሥተው ወደ ኤፌሶን ከተማ ገቡ ግን በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰብኩ ዘንድ አልተቻላቸውም እነዚያ ያገር ሰዎች እጅግ የከፉ ናቸውና።

ስለዚህም ምክንያት ፈጥረው ዮሐንስ ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤት እሳትን የሚያነድ ሆነ ረድኡ አብሮኮ ሮስም አጣቢ ሆነ ያቺ ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ነበር መጻተኞችም ስለሆኑ ታጉሳቁላቸዋለች ትደበድባቸዋለች ትረግማቸዋለች ባሮቿም እንደሆኑ ጽፈውላታልና ለእርሷ ባሮች አደረገቻቸው በዚህ በታላቅ ጒስቊልና ውስጥ ኖሩ።

ከዚህም በኃላ በአንዲት ዕለት ይታጠብ ዘንድ የአገረ ገዥው ልጅ ገባ በዚያም የውሽባ ቤት ከተሠራ ጀምሮ የሰይጣን ኃይል አለ የመኰንኑንም ልጅ አንቆ ገደለው በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ለዚያ ለሞተው ሊያለቅሱለት ተሰበሰቡ የከበረ ዮሐንስም ከእርሳቸው ጋር መጥቶ እንደ ሰው ሁሉ ሊያይ በዚያ ቆመ።

ሮምናም በአየችው ጊዜ ረገመችው "አንተስ በጌታዬ ልጅ ሞት ደስ ብሎህ ልትዝትብኝ መጣህ" አለችው ቅዱሱ ግን በቅንነት "አይዞሽ አትዘኝ" አላት ይህንንም ብሎ ወደ ሞተው ቀረብ ብሎ በመስቀል ምልክት አማተበበት በፊቱም ላይ እፍ አለበት። በዚያንም ጊዜ ያ ሞተው ድኖ ተነሣ የአገር ሰዎችም ደነገጡ ሮምናም ወዮልኝ እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን አለች።እርሱም አይደለሁም እኔ አገልጋይ ሐዋርያው ነኝ እንጂ አላት በእነርሱ ላይ የሠራችውን በደል ሁሉ ይቅር ይሏት ዘንድ መሪር ልቅሶ በማልቀስ ሐዋርያትን ለመነቻቸው እነርሱም አረጋጓት አጽናኗትም።

ከሀገሩም ሰዎች ብዙዎቹ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው በፊታቸውም ብዙዎች የሆኑ ድንቆች ተአምራትን አደረገ ይህንንም አይተው የሀገሩ ሰዎች ሁሉም በጌታችን አመኑ።ከጣዖታቱ አገልጋዮች በቀር እነርሱም ሰይጣን በእርሱ ላይ ስለሚያነሣሣቸው ሊገድሉት ይሹ ነበር ነገር ግን ምርጦቹን እግዚአብሔር ጠበቃቸው።

የከበረ ዮሐንስም ሁሉንም እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ እስከመለሳቸው ድረስ ታላቅ ድካምና ጭንቅ የሆነ መከራ ደረሰበት።የከበረ ሐዋርያ ጳውሎስም ስለ ልቡናቸው ደንዳናነት ጣዖታትን ስለመውደዳቸውም ስለ እነርሱ መስክሮአል።እርሱም ዮሐንስ በታላቅ ድካም ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው።ከዚህም በኋላ ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትን ዲያቆናትን ሾመላቸው።

ከዚህም በኋላ ከእስያ በዙሪያዋ ወዳሉ አገሮች ሁሉ ወጥቶ አስተማረ እግዚአብሔርንም ወደማወቅ መለሳቸው።ይህም የከበረና የተመሰገነ ዮሐንስ በዚህ ዓለም ዘጠና ዓመት ኖረ እጅግም ሸመገለ ግን እንደ ባልንጀሮቹ እንደ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አልቀመሰም።ስለ ድንግልናውና ስለ ንጽሕናው ይህ ሆነ ሁሉም በክብር ይስተካከሉ ዘንድ እርሱም ወንጌልን ቀለምሲስ የሚባለውን ራእይ ሦስት መልእክታትን የጻፈ ነው።ራት ሲበሉ በጌታ ኢየሱስ አጠገብ የተቀመጠውና "አቤቱ የሚያሲዝህ ማነው" ያለው ይህ እርሱ ነው።

ጌታችንም በተሰቀለ ጊዜ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በመስቀሉ አጠገብ የቆመ እናቱንም "እነሆ ልጅሽ" ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው።

ጴጥሮስም እርሱን ሲከተለው ባየው ጊዜ ስለእርሱ ጌታ ኢየሱስን "አቤቱ ይህስ እንዴት ነው" ብሎ የተናገረ ጌታ ኢየሱስም "እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ከወደድኩ አንተ ምን አለህ አንተ ግን ተከተለኝ" ያለለት ይህ ነው ።

የተመሰገነ ዮሐንስም ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ሰዓት እንደ ቀረበ በአወቀ ጊዜ ሕዝቡን ጠራቸው ጸሎትንም ጸለየና ኅብስቱን ባርኮ ቆረሰ ይህም የጌታችን ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ባረካቸው አጽናናቸውም።

ከዚህም በኃላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ። ከኤፌሶንም ከተማ ውጭ ወጣ ጐድጓድ እንዲቆፍሩም አዘዘ ከውስጥዋም ወርዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ ከአንድ የበፍታ ቀሚስ በቀር አላስቀረም። እጆቹንም አንሥቶ ጸለየና ወደ ከተማ ይመለሱ ዘንድ አሰናበታቸው በክርስቶስም ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝቡ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዛቸው በጎ ሥራዎችንም ይሠሩ ዘንድ ጌታችን ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፈለው ዘንድ አለውና።

ሁለተኛም እንዲህ አላቸው "እኔ ከሁላችሁም ደም ንጹሕ ነኝ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራችሁ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩኝም።"

ይህንንም በተናገረ ጊዜ አለቀሱ እጆቹንና እግሮቹን ስመው በጒድጓዱ ውስጥ ትተውት ወደ መንገድ ተመለሱና የሆነውን ሁሉ ለሰዎች ነገሩዋቸው ሁሉም ደንግጠው መጡ ግን ልብስና ጫማ እንጂ መቃብሩን አላገኙም እጅግም አደነቁ ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን በዚህ በጎ ዕረፍት ያሳረፈው እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ የተለያዩ ስሞች ተሰጥተውታል፡
🌿ወልደ ዘብዴዎስ - አባቱ ዘብዴዎስ ስለሆነ
🌿ፍቁረ እግዚእ - በሕይወቱና በኑሮው ጌታን በመምሰል ጌታ ይወደው ስለነበር
🌿ነባቤ መለኮት (ታዖሎጎስ) - ነገረ መለኮትን ከሌሎች በበለጠ አምልቶ አስፍቶ በጥልቀት በማስተማሩ
🌿ቦአኔርጌስ (ወልደ ነጎድጓድ) - የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት በመግለጡና ለጌታችን ባለው ቅንዓት ባሳየውም የኃይል ሥራ
🌿ባለራእይ (አቡቀለምሲስ) - ኃላፍያትንና መጻእያትን በራእይ በመግለጡ
🌿ቁጹረ ገጽ (ፊቱ በኃዘን የተቋጠረ) - በዕለተ ዓርብ በእግረ መስቀሉ ተገኝቶ የጌታችንን መከራ መስቀል በማየቱ ከዚያች ዕለት ጀምሮ ፊቱ በኃዘን ተቋጥሮ ይኖር ስለነበር
----------------------------------
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ አባት በሐዋርያ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"መጽአ ወልድ"
"ሃሌ ሉያ መጽአ ወልድ ውስተ ዓለም፣ ሃሌ ሉያ ውስተ(፪)
ወለብሰ ሥጋነ ሰብአ ኮነ በአርአያ ዚአነ።(፪)"

"ሃሌ ሉያ ወልድ መጣ ወደ ዓለም፣ ሃሌ ሉያ ወደ ዓለም።(፪)
ሥጋችንን ለበሰ ሰውም ሆነ በእኛ አርአያ ሰው ሆነ።(፪)"

©በማኅበረ ቅዱሳን ዘማርያን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ስለ አምላክ ሰው መሆን የሃይማኖት አባቶቻችን በመደነቅ እንዲህ አሉ፦

«ኃይለኛ ተዋጊ ሆኖ ገብቶ በእርሷ ማኅፀን ፍርሃትን ለበሰ፤ የሁሉ መጋቢ ሆኖ ገብቶ ረሃብን ተቀበለ፡፡ ለሁሉም መጠጥን የሚሰጥ ሆኖ ገብቶ ጥምን ተቀበለ፡፡ ለሁሉ ልብስን የሚሰጠው ከእርሷ ማኅፀን ራቁቱን ሆኖ ተወለደ፡፡

ከሕሊናት ሁሉ ለራቀ ለዚህ ድንቅ ምሥጢር አንክሮ ይገባል፤ ምድራዊት ሴት ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃልን ወለደችው፥ ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው፤ እርሱም እናቱን ፈጠረ፤ ከእርሷም እርሱ የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ።
  ተዋርዶ በእኛ ባሕርይ ተወለደ፤ እርሱም እኛን ስለመውደዱ ፈጠረን ፤በእኛ ባሕርይ ወለደችው ፤ ፈጣሪም እንደሆነ ታወቀ።
  እርሱ ሊዋሐደው ሥጋን ከድንግል ፈጠረ ፤ ባሕርይዋን ባሕርይ አደረገ ፤ ፍጡራንን ሁሉ የፈጠረ ሲሆን ባሕርዩ ያልነበረ ሥጋን ተዋሐደ የተዋሐደውንም ባሕርይ የፈጠረ እርሱ ነው ።
  የድንግልን ሥጋ መረጠ ፤ሰው መሆኑን ሊያስረዳ ፍጹም አካሉን በማሕፀኗ ፈጠረ።>> ማር ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

<<ቀዳማዊ አምላክ ዛሬ ተወለደ ጥንቱን ገንዘቡ ባይደለ ባሕርይ ተገኘ ፤ እርሱ ቀዳማዊ አምላክ ነው ሰው በመሆኑም ከባሕርዩ አልተለወጠም።
  የመለኮቱ መገኘትም ከእመቤታችን ከተወለደ ወዲህ አይደለም ፤ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ጥበብ ነው እንጂ የማይታመም እርሱ ከባሕርየ መለኮቱ ሳይለወጥ ሕማም የሚስማማውን ሥጋን ተዋሐደ ።
ዳግመኛም በልዑል ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ያለ እርሱ ፡ በበረት ተጣለ ሥጋ ሳይሆን የነበረ የማይዳሰስ ወልድ ዋሕድ ዛሬ ሥጋን በመዋሐድ ተዳሰሰ ፤ ኃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ።
የማይወሰን እግዚአብሔር በድንግል ማኅፀን እንደ ተወሰነ ማን አየ? ማን ሰማ? ሰማያት ለማይወስኑት እርሱ የድንግል ማኅፀን አልጠበበውም ባሕርዩ ሳይለወጥ ከእርስዋ ተወለደ እንጂ ፤ ከመለኮቱ የተለየ ዕሩቅ ብእሲ አይደለም ።
.
ብልህ ሸክላ ሠሪ የሚሠራውን የለዘበ ጭቃ በአገኘ ጊዜ ከእርሱ መልካም ዕቃ እንዲሠራ እንደዚህ ጌታችን የዚህችን ድንግል ንጹሕ ሥጋዋን ንጽሕት ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ፤ ነፍስ ያለችውን ሥጋ ሊዋሐደው ፈጠረ።
እንደ ወደደ ከድንግል ነፍስን ሥጋን ፈጥሮ ለበሰ፤ እርሱንም ተዋሕዶ ዛሬ ተወለደ ፤ ሕጸጽ ያለበት ነው ብሎ ባሕርያችንን አልተወውም ፤ ሥጋን በተዋሐደ ጊዜ ቃል ከምላቱ አልተወሰነም ፤ ሥጋ የፈጣሪ አካል ባሕርይ በሆነ ጊዜ ፍጹም አምላክነትን አገኘ እንጂ።
ሸክላ ሠሪ አስቀድሞ በእጁ ጭቃ ሳይዝ መሥራት እንደ ማይቻለው ፤ በፍዳ ተይዞ የነበረ ባሕርይ ዳግመኛ ያለ እግዚአብሔር እጅ በዘር ተፈጠረ ሊሉት አይገባም፤ ፈጣሪ ይዋሐደው ዘንድ ያለዘር በእደ እግዚኣብሔር ተፈጠረ እንጂ።
ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እርሱ ትንሽ ሕፃን ሆኖአልና፤ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ፤ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተወለደ፤ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሠሥ የነበረ በምድራውያን እጅ ተዳሠሠ፤  ኀጢአት የሚያስተሠርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፤ ይህን ወዶአልና።
ክብሩ ተለይቶ የነበረ ሥጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው ፤ የጸጋ ገዥነትን አጥቶ የነበረ ሥጋንም የባሕርይ ገዥ ሊያደርገው ወደደ ፤ አዳም ከእኛ እንዳንዱ ሆነ ያለውንም ሰው በመሆን ሊገልጠው ወደደ።>> ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

<<የሰው ልጅ ሕይወት እና መዳን የሆነው ጌታ ተወልዷል፣ ዛሬ እርቅ ከመለኮት ለሰው ልጅ፥ ከሰውም ለመለኮት ተደረገ። ዛሬ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ዘሏል። ከላይ ያሉት ወደ ታች ላሉት፥ ከታች ያሉትም ወደ ላይ ላሉት ተላኩ፤ ዛሬ ሞት ለጨለማ፥ ሕይወት ደግሞ ለሰው ልጆች ኾነ። ዛሬ ለሰዎች ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚወስድ እና ወደ ነፍስም የሚገባ የእግዚአብሔር መንገድ ተደረገ።>> ቅዱስ መቃርስ ታላቁ

እንኳን አደረሳችሁ!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…
Subscribe to a channel