ethiopian_orthodox | Unsorted

Telegram-канал ethiopian_orthodox - የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

30344

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Subscribe to a channel

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሠ) ድንግልናን መጠበቅ መጠንቀቅ ነው፡፡ እንዲያው፡ መጠንቀቅ ተብለው ከሚወሰዱ ማንኛውም ዓይነት ሌሎች እርምጃች ምንም ዓይነት ሰብአዊ ቀውስ ሳያስከትል መከናወን የሚችል ተገቢ የጥንቃቄ ዓይነት ነው:: ከበሽታ፣ ያለ አግባብ ወይም ሳያገቡ ከመውለድ፣ ክብርንና መልካም ስምን ከማጣት፣ ከመጸጸት በአጠቃላይ ለወደፊት መንፈሳዊም ሆነ ሥጋዊ ችግር ከሚፈጥሩ የኑሮ ጠንቆች ሁሉ መቶ በመቶ ሊሰውር የሚችል መጠንቀቅ ቢኖር ድንግልናን መጠበቅ ነው::
ረ) አንዲት ሴት በድንግልና ኖራ ብታገባ ልቧ አይከፈልምና ፈጣሪዋን እጅግ አድርጋ ታስደስተዋለች፡፡ ሐዋርያው «ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ» ያለው ስለዚህ ነው:: ድንግል ሴት በድንግልና ኖራ ስታገባ ደግሞ ባሏን በጣም ታስደስተዋለች፡፡ ማንኛውም ባል ሚስቱን ድንግል ሆና ቢያገኛት ይደሰታልና፡፡ ድንግል ባትሆን ግን ባልዋን እንዴት ልታስደስተው ትችላለች? በእርግጥ ባልን ማስደሰት የሚቻለው በዚህ ብቻ ባይሆንም የሚጀምረው ግን ከዚህ ነው፡፡
ድንግልናን ካጠፉ በኋላ የሚደረግ ጋብቻ አግብቶ የፈታ ሰው እንደሚፈጽመው እንደ ሁለተኛ ጋብቻ ይቆጠራል:: ምክንያቱም የተጋቡ ሰዎች ብቻ ሊፈጽሙት የሚገባውን ሩካቤ ሥጋ ከጋብቻ በፊት ፈጽሞ በመገኘቱ ነው፡፡ ለመመንኮስ ተስሎ የነበረ ሰው ቢያገባ የተሳለው ስእለት እንደ መጀመሪያ ጋብቻ ተቆጥሮ የሚፈጽመው ጋብቻ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚያገባ ሰው እንደሚቆጠርበት ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ይናገራል፡፡
ይህ እንዲህ ከሆነ ድንግልናቸውን ያጡ ስዎች የሚፈጽሙት ጋብቻ እንደ መዓስባን ወይም እንደ ሁለተኛ ጋብቻ መቆጠሩ ምንም አያስደንቅም:: እዚህ ላይ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ለሁለተኛ ጊዜ የሚያገባ ሰው ማለትም ሚስቱ ሞታበት ወይም ለፍቺ በሚያበቃ ምክንያት ተለያይተው ከሆነ ፈቅዶ እንዳደረገው እንደ መጀመሪያ ጊዜ ጋብቻው ደስተኛ እንደማይሆን ነው:: እንደዚሁም ሁሉ ፈት ሆኖ ማግባት ድንግል ሆኖ እንደ ማግባት አያስደስትም ወይም ፈትን ማግባት ድንግልን እንደ ማግባት አያስደስትም፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንደሚያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፡ ልቡም ተከፍሏል፡፡» ስለሴቶች ደግሞ «የተጋባች ግን ባሏን እንዴት ደስ እንደምታሰኘው የዓለም ነገር ታስባለች::» 1ቆሮ7፥33-34 ብሎ በተናገረው መሠረት ያገቡ ሰዎች ልቡናቸው እንደሚከፈልና እግዚአብሔርን በአንድ ልብ ሆነው ለማምለክ እንደሚቸገሩ ሁሉ ድንግልናቸውን ካጡ በኋላ ያገቡ ሰዎችም እንደዚሁ ልቡናን የሚከፍል ተግባር የፈጸሙ በመሆኑ በሙሉ ልብ አንዳቸው አንዳቸውን ማስደሰት ይሳናቸዋል፡፡
እንደዚህ ያሉ ባለትዳሮች ሩካቤ በሚፈጽሙበት ጊዜ ከዚያ አስቀድሞ ድንግልናቸውን ያጡበትን መንገድ ክፉም ሆነ ደግ መስለ በታያቸው መልኩ በሕሊናቸው ማሰላሰላቸው የማይቀር ነገር ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ የሐሳብ መክፈል ደግሞ እየፈጸሙት ባለው ሕጋዊ ሩካቤ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያመጣል፡፡ ስለዚህ ባል ሚስትን ሚስት ደግሞ ባሏን በሙሉ ልብ ማስደሰት አይችሉም መባሉ ትክክል ነው፡፡ ይህ የልቡና መከፈል የሚፈጠረው ድንግልናውን ባልጠበቀው ወገን ብቻ ላይሆን ይችላል፡፡ ድንግልናውን ጠብቆ የኖረውም ወገን ድንግልናውን ስላጣው (ስላጣችው) ወገን ሕይወት በሕሊናው መመራመር ይፈጠርበታል፡፡ ስለዚህ ምንም በአካል መዋሐድ ቢችሉም የልቡና ተዋሕዶ ለመፍጠር ይቸገራሉና ደስታቸው በእጅጉ ይቀንሳል፡፡
ይህን ለመሰለ ችግር መፍትሔው ከሁሉ አስቀድሞ ድንግልናን ማጣት የሚያስከትለውን አካላዊና ሕሊናዊ ቀውስ በመረዳት ድንግልናን መጠበቅ ሲሆን በተረፈ ግን በተቻለ መጠን ያለፈን ሕይወት አምኖ በመቀበል መርሳትና ለወደፊቱ የሚበጀውን ብቻ ማድረግ ይሆናል፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ስምንት ክፍል ዐራት

.................................................
ድንግልናን የመጠበቅ ጥቅም
በጎ ተግባር ጥቅም ሊኖረው ይገባል። ክርስቲያኖች እንኳን የሚጐዳ ሥራ ይቅርና ባይጐዳ እንኳን ምንም ለማይጥቅም ሥራ መልፋት የለባቸውም።ጥቅም ሲባልም በዋናነት የሚጠቀሰው የነፍስ ጥቅም ነው። «ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢከስር ምን ይጠቅመዋል።» በማለት ጌታችን የተናገረው ቃል በመጀመሪያ መታየት ያለበት የነፍስ ጥቅም መሆኑን ያስረዳል።ማቴ16፥26
መጽሐፍ ቅዱስ ሥራ ሁሉ ከጥቅም ጋር መያያዝ እንዳለበት ይናገራል፡፡ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «ሁሉ ተፈቅዶልኛል ሁሉ ግን የሚጠቅም አይደለም፡፡»በማለት ያንን ነገር ለማድረግ መብት ቢኖረንም ጥቅም ከሌለው ግን አለማድረግ መሻሉን ተናግሯል፡፡1ኛ ቆሮ10÷23 :6÷12
ሐዋርያው በተጨማሪ አንዳንድ ሥልጠናዎችና ልምምዶች ለሥጋዊ ነገር እንደሚጠቅሙ ከገለጸ በኋላ ድንግልናን ለመጠበቅ የሚደረግ መንፈሳዊ ልምምድ ግን ጥቅሙ ለሁለት ዓለም በመሆኑ ይበልጥ መጥቀሙን ሲገልጽ «ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔር መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለነገር ሁሉ ይጠቅማል፡፡» 1ጢም4፡8 በማለት ተናግሯል።
ይኸው ሐዋርያ ደግሞ ስለ ክብረ ድንግልና መላልሶ ካስተማረ በኋላ ለምን እንዳስተማረ ሲናገር «ይህንንም ለራሳችው ጥቅም እላለሁ» በማለት በድንግልና መኖር እንደሚጠቅም ተናግሯል።በድንግልና መኖር ጥቅሙ ለራስ እንጂ ለሌላ አይደለም።1ቆሮ7፥35
በድንግልና መኖር ከሚያስገኘው ሰማያዊ ጠቀሜታ በፊት በምድር ላይም ብዙ ጥቅምን ያስገኛል።ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹን ጠቅለል በማድረግ በአንድ ስፍራ በጥቂት ገጸ ንባብ ሐዋርያው እንዲህ ሲል ገልጿቸዋል።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ኒቆዲሞስ"
በዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ

ኒቆዲሞስ/፪/ክቡር፣/፪/
ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር፣/፪/

በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ፣
በመከራው ጽናት ይህን ዓለም ናቀ፣
መምህር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ፣
የትዕቢትን ጅረት : በትህትና : ተዋርዶ አደረቀ።

°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ።
°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°

ፍርሀትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ፣
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ፣
የመግነዙን በፍታ በሽቱ ያከበረ፣
ከመቅደሱ አንቀጽ : ላይረሳ : አምድ ሆኖ ታጠረ።

°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ።
°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°

ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ነገረች፣
ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች፣
ከጨለማው ኃጢአት ነቅታ ብርሃን ካየች፣
እንደ ኒቆዲሞስ : ነፍስህም : ተምራ ተመለሰ።
°°°°°°°°°°°°°°✧°°°°°°°°°°°°°°°
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የዓቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ኒቆዲሞስ
የዐብይ ጾም ሰባተኛ እሑድ(ሳምንት)


ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የነበረው ሰው ነው፡፡ የአይሁድ አለቆች አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ምልክት አሳየን›› እያሉ ይፈታተኑት ነበር፡፡ ጌታችን ስለ ሞቱና ትንሣኤው በምሳሌ እያስረዳ ቢያስተምራቸውም እነርሱ ግን አልገባቸውም ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ ጌታችን በተአምራቱ የታመሙትን ሲፈውስ
‹‹ሕጋችን ተሻረ›› ይሉ ነበር፡፡ በዚህ ዅሉ ተአምራትና ትምህርት የአይሁድ አለቆች ክርስቶስን ለመክሰስ በሚፈልጉበት ወቅት ከአይሁድ አለቆች አንዱ ኒቆዲሞስ በቀን እንዳያደርገው አይሁድን ቢፈራ፣ አንድም ጊዜ ባያደርሰው እንደ ባልንጀሮቹ ክርስቶስን ሳይቃወም በሌሊት ወደ ጌታችን ዘንድ እየሔደ ወንጌልን ይማር ነበር፡፡
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነፍስ የታመሙትን በቃሉ፣ በሥጋ የታመሙትን በተአምራቱ ሲፈውስ ኒቆዲሞስ ሰምቶ፣ ተመልክቶ በመምህርነቱ ሳይኮራ አለቅነቱን መመኪያ ሳያደርግ በልቦናው የተሳለውን እውነትን የመፈለግ ስሜት አንግቦ ከጌታው፣ ከመምህሩ ከክርስቶስ ዘንድ በሌሊት ይገሰግስ ነበር (ዮሐ. ፫፥፩)፡፡ ምስክርነቱንም እንዲህ ሲል መስጠት ጀመረ፤
‹‹መምህር ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከኾነ
በቀር አንተ የምታደርገውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል
የለምና፤›› (ዮሐ. ፱፥፳፬፤ ሐዋ. ፲፥፴፰)፡፡
ይህን ምስክርነቱን በሚሰጥበት ጊዜም ጎዶሎን የሚሞላ፤ አላዋቂነት በአዋቂነት የሚለውጥ፤ ከምድራዊ ዕውቀት ወደ ሰማያዊው ምሥጢር የሚያሸጋግር አምላክ ‹‹ዳግመኛ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን
መንግሥት ለማየት አይችልም፤›› በማለት የአይሁድ መምህር ለኾነው ኒቆዲሞስ ቢያስተምረው ምሥጢሩ አልተገለጠለትም ነበርና ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ
ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ
ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?›› በማለት ጥያቄ አቅርቧል (ዮሐ. ፫፥፮፤ ፩ኛጴጥ. ፩፥፳፫)፡፡
‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ
ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ
አይችልም፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስም
የተወለደ መንፈስ ነውና፤›› (ኤፌ. ፭፥፳፮) በማለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ ቢያስረዳውም ምሥጢሩ ከአቅሙ በላይ ስለ ኾነበት እንደምን ይቻላል? በማለት ጠይቋል፡፡
አበ ብዙኃን አብርሃም ከአምላኩ ሞገስን አግኝቶ የሰዶምና ገሞራ ጥፋት እንዳይደርስ ለመማለድ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር እንደ ነበረ፤ ኒቆዲሞስም አላዋቂነቱን አምኖ ያልገባውን ምሥጢር ከአምላኩ በጠየቀ ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስም፡- ‹‹አንተ የእስራኤል
መምህራቸው ኾነህ ሳለ ይህን ነገር አታውቅምን?
በምድር ያለውን ስንነግራችሁ ካላመናችሁ በሰማይ
ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ
ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም …
ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅ
እንዲሁ ይሰቀላል፡፡ ያመነበት ዅሉ ለዘለዓለም ሕያው ኾኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፋ አይደለም ...፤›› እያለ ሰው በመብል ምክንያት የአምላኩን ትእዛዝ አፍርሶ ከእግዚአብሔር ቢለይም የሰው ልጅ ያጣውን ልጅነት ለመመለስ፣ ስመ ክርስትናን፣ ሀብተ ወልድን ለመስጠት ጌታችን መምጣቱን አስረዳው (ዮሐ. ፫፥፲፬)፡፡ ይህን የክርስቶስን የማዳን ሥራና በሥጋ መገለጥም
‹‹ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ አመከርከኒ
ወኢተረከ ዐመፃ በላዕሌየ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ
እጓለ እመሕያው፤ ልቤን ፈተንኸው፡፡ በሌሊትም
ጐበኘኸኝ፤ ፈተንከኝም፡፡ ምንም አላገኘህብኝም፡፡ የሰውን
ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፤›› (መዝ. ፲፮፥፫) በማለት ቅዱስ ዳዊት ከኒቆዲሞስ ሕይወት ጋር በማዛመድ አመሥጥሮታል፡፡
በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምሥጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ቀድሞ በአደባባይ ሔዶ መማርን ይፈራ እንዳልነበረ ምሥጢሩ ሲገለጽለት ግን አይሁድ ጌታችንን በሰቀሉት ዕለት ፍርኃት ርቆለት ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ፡፡ ‹‹ወአልቦ ፍርኃት
ውስተ ተፋቅሮትነ፤ ፍጹም ፍቅር ፍርኃትን አውጥቶ
ይጥላል›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፯፥፶፰፤ ፩ኛዮሐ. ፬፥፲፰)፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ያመነ፣ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ፣
ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል›› (ማር. ፲፮፥፮) በማለት በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት በአምላክነቱ አምነን የመንግሥቱ ወራሾች እንኾን ዘንድ ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን እንደ ገለጸ ለእኛም ይግለጽልን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

 በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች
-ሮሜ ፯፥፩-፱
-፩ኛ ዮሐ ፬፥፲፰ እስከ ፍጻሜ
-የሐዋ ሥራ ፭፥፴፬ እስከ ፍጻሜ

ምስባኩም፦ መዝ ፲፮፥፫
"ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመጻ በላዕሌየ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ ዕጓለእመሕያው"
"ልቤን ፈተንከው በሌሊትም ጎበኘኸኝ ፈተንኸኝ ምንም አላገኘህብኝም የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው"

ወንጌሉም፦ ዮሐ ፫፥፩-፳

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል።
በለኒ መሐርኩከ/በለኒ መሐርኩኪ በእንተ ማርያም ድንግል።
እስመ ኢኀሎ ሔር እንበሌከ ቃል።"

"ከአንተ (ከቃል) በቀር ቸር የለምና በቀራንዮ የተሰቀልህ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ሆይ! ስለ ማርያም ድንግል (ስለ እናትህ) ብለህ ምሬሀለሁ/ምሬሻለሁ በለኝ።"
(መልክአ መድኃኔ ዓለም)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መጋቢት ፳፯
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ


መጋቢት ሃያ ሰባት በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ። ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተዘርግቶ ተሰቅሎ በአየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት ሐዋርያ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳትለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር። እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋራ አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደሲኦል ወረደች።

መድኃኔዓለም ክርስቶስ ስለ ዓለም ሁሉ ድኅነት በሥጋ ተሰቅሏልና ሞቱን በአንክሮ እናዘክር ዘንድ የልቡናችን ዐይን ወደ ቀራንዮ እናንሳ! እነሆ ክፉዎች አይሁድ ሰይጣን ልባቸውን አስቶታልና እንደ ወረንጦና እንደ ወስፌ እንደመርፌም ያለ 300 እሾህ ያለው ስረወጽ አድርገው አክሊል ሠርተው ከፍላት አግብተው በጉጠት አንስተው ‹ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ነህ ዘውድ ይገባሃል› ብለው በራሱ ላይ ደፉበት፡፡ ለአክሊለ ሦኩም 73 ስቁረት ነበረው፡፡ እራሳቸው እንደ መሮ፣ ወርዳቸው እንደ ሞረድ 4 ማዕዘን አሠርተው ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸውን እንደ ወስፌ አድርገው 73 ችንካር ሠርተው በ73ቱ ስቁረት አግብተው በጌታችን በራሱ ላይ ቢመቱበት ሥጋ ለሥጋ ገብቶ መሐል ልቡን ወጋው፡፡ አክሊለ ሦኩን በራሱ ላይ አድርገው ሲያበቁ ከቤት ወደ አደባባይ እያመላለሱ ‹‹ንጉሥ ሆይ!...›› እያሉ ምራቃቸውን እየተፉበት ተዘባበቱበት፡፡ መስቀል አሸክመው ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ እያዳፉ ሲወስዱት 136 ጊዜ በምድር ላይ ጣሉት፡፡ ከኋላ ያሉት ‹‹ፍጠን›› እያሉ ገፍትረው ይጥሉታል፣ ከፊት ያሉት ደግሞ ‹‹ምን ያስቸኩልሃል?›› እያሉ መልሰው ገፍትረው ይጥሉታል፡፡ ከዚህ በኋላ ክፉዎች አይሁድ ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር ስለታቸው ደግሞ እንደ ወስፌ የሆኑ 5 ችንካሮችን ሠርተው ሳዶር በሚባለው ችንካር ቀኝ እጁን፣ በአላዶር ግራ እጁን፣ በዳናት ሁለት እግሮቹን፣ በአዴራ መሐል ልቡንና በሮዳስ ደረቱን ቸንክረው የአዳም ራስ ቅል ባለበት ቀራኒዮ አደባባይ ላይ ሰቅለውታል፡፡

ክፉዎች አይሁድ መድኃኔዓለም ክርስቶስን እንደያዙት የኋሊት አስረው አፍንጫውን 25 ጊዜ ቢመቱት ደሙ በመሬት ላይ እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ከጌቴሴማኒ እስከ ሐና ቤት ድረስ አስረው የፊተኞቹ ሲጎትቱት የኋለኞቹ እየለቀቁት የኋለኞቹም በተራቸው ሲጎትቱት የፊተኞቹ ይለቁታል፡፤ እንዲህ እያደረጉ 65 ጊዜ ከመሬት ጋር አጋጭተውታል፡፡ ሳውል በእግሩ ሲረግጠው ጌታችን ‹‹መመለስህ ላይቀር ለምን ትረግጠኛለህ?›› ቢለው ስለዚህ ንግግርህ ብሎ ሳውል 440 ጊዜ አስገረፈው፡፡

ክፉዎች አይሁድ መድኃኒታችንን በሁለት ግንዶች መካከል አድርገው 65 ጊዜ ከግንዱ ጋር አጋጩት፡፡ ቀያፋ በሚመረምረው ጊዜ ጌታችን ‹‹አምላነቴን አንተው ራስህ ተናገርኽ›› ቢለው አይሁድ በእጃቸው ሲመቱት እጃቸውን ቢያማቸው ድንጋይ ጨብጠው 120 ጊዜ ፊቱን ጸፉት፡፡ አይሁድ ወደ ጲላጦስ ዘንድ ሲወስዱት ‹‹ምናልባት ጲላጦስ ባይፈርድበት እንኳ እንዳይቆጨን›› ብለው 305 ጊዜ በሽመል ደብድበውታል፡፡ በአምላክነቱ ቻለው እንጂ የአንዱ ምት ብቻ በገደለው ነበር፡፡ በርባን የይሁዳ የሚስቱ ወንድም (አማቹ) ስለነበር እርሱ እንደፊታለትም ከዋጋው ከ30ው ብር ጋር አብሮ ተደራድሮበት ነበር፡፡
ሰይጣን ልባቸውን ለክፋት ያስጨከናቸው ክፉዎች አይሁድ በጲላጦስ አደባባይ የጌታችንን ፂሙን 80 ጊዜ ነጭተውታል፡፡ ጲላጦስ እንደ ሕጋቸው 41 ብቻ ገርፈው እንዲለቁት ቢያዝም ክፉዎች አይሁድ ግን ጌታችንን ሲገርፉት ‹‹አሠቃቂ ግርፋቱን አይተን ልባችን እንዳይራራ›› ብለው ሰንጠረዥ ገበጣ ሰርተው ሲጫወቱ አንዱ ተነስቶ እስከ 60 እና 70 ድረስ ይገርፍና ሲደክመው ‹‹ቆጠራችሁን?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ‹‹አልቆጠርንም›› ሲሉት ከድካሙ የተነሣ ‹‹እኔው ልግረፍ እንደገና እኔው ልቁጠር›› ብሎ ትቶት ሲቀመጥ ሌላኛው ይነሣና እንደዛኛው ሁሉ በተራው 60 እና 70 ይገርፈዋል፡፡ ሁሉም እንዲህ እያሳሳቱ የራሳቸውን ሕግ እየተላለፉ አይሁድ ጌታችንን ሥጋው አልቆ አጥንቱ እንደበረዶ ነጭ ሆኖ እስኪታይ ድረስ 6666 ጊዜ ጽኑ ግርፋትን ገረፉት፡፡ በእነዚህ ሁሉ ግርፋቱ ወቅት 366 ጊዜ ሥጋው ተቆርሶ መሬት ላይ ወድቋል፡፡

የመድኃኔዓለም ወገኖች ሆይ! የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ መሆኑንና የትዕግሥቱን ብዛት አይተን እናደንቅ ዘንድ ከመጻሕፍት ጠቅሰን እንነግራችኋለን፡፡ አይሁድ ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ በፊት እርሱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን አምላክ መሆኑን ቢነግራቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፡፡ እሱ ግን ጊዜው ገና ነበርና ተሰውሮአቸው በመካከላቸው አልፎ ሲሄድ በፍጹም አላዩትም ነበር፡፡ በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። አይሁድም:- ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም:- እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ፡፡›› ዮሐ 8፡56-59፡፡

ዳግመኛም በዮሐንስ ወንጌል ላይ እንደተጻፈው አይሁድ መድኃኔዓለምን ሊይዙት የጦር መሣሪያቸውን ሰብስበው ወደ ጌቴሴማኒ በመጡ ጊዜ ‹‹ማንን ትፈለጋላችሁ?›› ቢላቸው ‹‹የናዝሬቱን ኢየሱስን እንፈልጋለን›› ሲሉት ‹‹እኔ ነኝ›› ቢላቸው ከአንደበቱ የወጣውን መለኮታዊ ቃል ብቻ መቋቋም አቅቷቸው መሬት ላይ ወድቀው ተዘርረዋል፡፡ ይህም ክስተት በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡ (ዮሐንስ ወንጌል ላይ ምዕራፍ 18 ከቁጥር አንድ ጀምሮ ይመለከቷል፡፡) እናም የጌታችን ሞቱ በፍጹም ፈቃዱ ባይሆን ኖሮ በጌቴሴማኒ ሊይዙት የመጡት ክፉዎች አይሁድን እንደመጀመሪያው ሁሉ በተሠወራቸው ነበር አሊያም ከአንደበቱ በሚወጣው አምላካዊ ቃሉ ብቻ ባጠፋቸው ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን ጌታችን ወደዚህች ምድር የመጣበትን ዓላማ ይፈጽም ዘንድ እንዲገድሉት በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ቢሰጣቸው ያን ሁሉ እጅግ አሠቃቂ መከራ አደረሱበትና ለመስቀል ሞት አበቁት፡፡

ወዮ ለዚህ ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል! ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፡፡ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡ በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፡፡ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፡፡ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!! ለዚህ ባሕርይው አንክሮ ይገባል፡፡

በመድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞት በአንድነት እናለቅስ ዘንድ ቅዱሳን ሁላችሁ ኑ! መድኃኒታችን ሙቷልና ፍጥረታት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ መያዝንና መታሠርን የተቀበለ መድኃኒታችን ሙቷልና፡፡ ጥፊንና ግርፋትን የተቀበለ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ መደብደብንና መመታትን የታገሰ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ ሄኖክ እግዚአብሔር ‹‹በሴም ቤት ይደር›› ብሎ አብ ስለራሱ የተናገረለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አብርሃም ቃልኪዳን የገባልህን

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ወደ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ስንመጣ ደግሞ አንድ ሰው ድንግልናውን ጠብቆ ለመኖር ከተሳለ በኋላ እንደ ገና ወደ ማግባት ቢመለስ ጋብቻው ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚያገባ ሰው ተቆጥሮ ሥርዓተ ተክሊል አይፈጸምለትም ። (ፍት.ነገ.አን.24) ስለዚህ ድንግልናን ተስሎ ኋላ ከመቸገር ሳይሳሉ በልብ ንጽሕናን ለመጠበቅ መወሰንና ሲያቅት ወደ ጋብቻ መሄድ ይሻላል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «ድንግልናውን በልቡ ይጠብቅ ዘንድ ቢጸና» በማለት እንደ ተናገረው ድንግልና የሚጠበቀው በልብ እንጂ በአፍ አይደለምና፡፡ (1ቆሮ7÷37)

«ድንግል ነኝ!» ብዬ እጮኛዬን ዋሸሁት! ምን ይሻለኛል?
ምንም ዓይነት ሩካቤ ሳይፈጸም ድንግልና ሊወገድ የሚችልባቸው ብዙ ሁኔታች ተዘርዝረዋል:: አንዳንድ ደካማ ሴቶች ድንግልናቸውን አስመልክቶ ለሚጠየቁት ጥያቄ ያሳለፉት ማንነታቸው ትችት ውስጥ ሳይገባ መልስ ለመስጠት በቂ ምክንያት ያገኙ እየመሰላቸው በዚህ ምክንያት ተሰነካክለዋል፡፡ ማለትም ድንግል ሳይሆኑ «ድንግል ነኝ» ይላሉ፡፡ ድንግል አለመሆናቸው የሚገለጥበት ጊዜ ሲመጣ ማለትም ሊያገቡ ሲሉ ደግሞ «ዝሙት ፈጽሜ አላውቅም ነገር ግን ድንግልናዬ በምን ምክንያት እንደ ጠፋ አልገባኝም!» በማለት ደረቅ ውሸት የሚዋሹ ብዙዎች ናቸው፡፡ ሌሎች ሴቶች ደግሞ እውነቱ በሚገለጥበት ጊዜ ‹‹በዚህ ምክንያት ይሆናል እንጂ እኔ ዝሙት ፈጽሜ አላውቅም!›› ብዬ ምክንያት በሚል እሳቤ ድንግል አለመሆናቸው እያወቁ ወደ ፊት የሚያገቡትን ሰው «ድንግል ነኝ› እያሉ መዋሸታቸው ብዙ መዘዝ ሲያመጣባቸው ይታያል፡፡ ግመል ቢሰርቅ በዚያ ቁመቱ ጐንበስ ብሎና ተደብቆ ማምለጥ አለመቻሉን ለመግለጽ «ግመል ሰርቆ አጐንበሶ› እየተባለ ይተረታል፡፡ በአንድ ወቅት በግድ ይፋ የሚሆን ነገርን ለመደበቅ መጣር ሞኝነት ነው፡፡ ታዲያ አንዳንድ ሴቶች ድንግልናቸውን በተመለከተ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፈጦ የሚታየውን እውነት መደበቃቸው ምን ይባላል? ውሸት በምንም መልኩ መልካም ባይሆንም የዚህ ዓይነት ውሸት ግን ጨርሶ መሞከር የሌለበትና ከሁሉ የሚከፋ ነው፡፡ «እውነቱን ተናግሮ ከመሸበት ማደር» እንደሚባለው እውነቱን ተናግሮ ከዚያ ተያይዞ የሚመጣውን ክፋም ሆነ መልካም ነገር መቀበል የተሻለ አማራጭ ነው:: ይህ ሲባል ግን ባል ሚስትን ሚስት ደግሞ ባልን ይህን በመሰለ ነገር መደባበቅና መወሻሸት እንደሌለባቸው ለመናገር ነው እንጂ ለማንኛውም ሰው ይህን እውነት ወይም የግል ሕይወት መናገር አለብን ለማለት አይደለም፡፡ ሰው ሁሉ ይህን የግል ኑሯችንን የማወቅ መብት የለውምና፡፡
ድንግልና ከሩካቤ ውጭ በተለያየ መንገድ ሊጠፋ መቻሉን ሴቶች ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ወንዶችም የሚያውቁት ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን ወንዶች ይህን ብቻ ሳይሆን ይህ ዓይነት ሁኔታ ሊፈጠር የሚችልበት አጋጣሚ በጣም ጠባብ መሆኑንም ያውቃሉ:: ስለዚህ ብዙ ወንዶች በምንም ተአምር ሚስቴ ከወንድ ጋር ግንኙነት ሳይኖራት ድንግልናዋን በሌላ መንገድ አጣች ብሎ ለማመን ይቸገራሉና፡፡ ይህን ማወቅ ዕወቀት ብቻ ከመሆን አልፎ የሚሰጣቸው ጥቅም አይኖርም፡፡
በዚህ ምክንያት ምንም እንኳን ልዩ ልዩ ምክንያቶች ይዘውት ሐሳብሽን የተቀበለ ቢመስልም በልቡናው የሚኖረውን ጥርጥር ይህን በመሰለ ምክንያትሽ ከነ ሰንኮፉ ማውጣት አይቻልሽም:: ታዲያ በትዳር ዘመንሽ በሙሉ ሳትታመኚ እየተጠረጠርሽ ከምትኖሪ ያሳለፍሽውን ሕይወት በግልጽ ተናግሮ መተማመን አይሻልሽምን?
እውነት ተናግረሽ ቢሆን ኖሮ ባልሽ እንዲቀበልሽ መንፈስ ቅዱስ ያግዝሽና ባልሽን ሊያሳምንልሽ ይችል ይሆናል፡፡ ይህ ሐሳብ በይሆናል የተገለጸው የመንፈስ ቅዱስን የማሳመን ችሎታ በመጠራጠር ሳይሆን የባልሽን ማመን በመጠራጠር ነው፡፡ ታዲያ ይህን በመሰለ ጉዳይ እውነት እንኳን ቢነግሩት ለማመን የሰው ልጅ የሚቸገር ከሆነ ውሸት ተናግረሽ ለማሳመን ምን ዐቅም አለሽ? ስለዚህ የዚህ መድኃኒቱ በመጀመሪያ ንጽሕናን ጠብቆ መኖር ሲሆን መሰናከል ካገኘሽም ግልጹን ተናግሮ ወደ ትዳር ማምራት ብቻ ነው፡፡
መዋሸት ኃጢአት ነው፡፡ ድንግል እንኳን ብትሆኚ "ኃጢአት የነገሠብኝ ነኝና ድንግል መባል አይገባኝም" የሚል የትሕትና ንግግር የሚጠበቅብሽ ክርስቲያን ስትሆኚ በአንጻሩ ድንግል ሳትሆኚ ይህን የመሰለ ማዕረግ ለራስሽ መስጠትሽ ትዕቢትሽን ያጐላዋል::
ባልና ሚስት አንድ አካል ናቸው:: ባል የሚስት ራስ ነው፡፡ ሰው ራሱን ይዋሻል? ሚስት ባሏን ዋሸች ማለት ራሷን ዋሸች ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በትንሹም ቢሆን አለመታመን ነው:: ዛሬ ባልሽን ዋሽሽ ነገ የንስሐ አባትሽን ከዚህ በኋላ ቤተ ክርስቲያንን እንደማትዋሺ በምን ይረጋገጣል? ቤተ ክርስቲያንን መዋሸት ደግሞ ጌታውን የዋሸና አሳልፎ የሰጠ ይሁዳን መምሰል ነው፡፡
በዘመነ ኦሪት አንዲት ባለትዳር ሴት ባሏ ምንም ግልጽ የሆነ ነገር ሳይዝ እንኳ ቢጠረጥራት «ማየ ዘለፋ» እንድትጠጣ ትደረግ ነበር። «ማየ ዘለፋ» እርግማንን የሚያመጣ ‹መራራ ውኃ> ነው:: በዝሙት የተጠረጠረችው ያች ሴት እውነት አመንዝራ ከሆነ በብዙ መቅሠፍት ትመታ ነበር፡፡ የባሏ መጠራጠር በከንቱ ከሆነ ግን ምንም ክፉ ነገር አያገኛትም ነበር፡፡ የ«ማየ ዘለፋ» አጠቃላይ ዝርዝር አፈጻጸሙ በኦሪት ዘዳግም ተጽፏል። ዘዳ 5÷11-31 ከዚያ አልፋ ብታመነዝር ወይም ድንግልናዋ ሳይገኝ ቢቀር በድንጋይ ተወግራ ትገደል ነበር፡፡ ዘዳ 22÷20-24 ይህ ዓይነት አሠራር በአዲስ ኪዳን ቀርቷል:: ሆኖም አንዳንድ ባሎች የሚስታቸውን ድንጋሌ ሥጋ ሲያጡ "ለምን ተዋሸሁኝ?" በማለት እልክ ውስጥ በመግባት ለብዙ ተገቢ ያለሆነ እርምጃ የተጋለጡ አሉ፡፡ አንዳንዶቹ መስቀልንና ቅዱሳት መጻሕፍትን አስጨብጠው ሚስቶቻቸውን ያስምላሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ውሸት ተናግረውና ኃጢአት ሠርተው የመጡትን ሰዎች «አያሳልፉም» በተባሉ የአንዳንድ ቅዱሳት መካናት ዋሻዎችና አጣብቂኞች እንዲያልፉ ካላደረግን ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ይህ ሁሉ ኀዳጌ በቀል (በደልን ይቅር የሚል) አለመሆንና ኢ-ክርስቲያናዊ አስተሳሰብ ነው:: በዘመነ ወንጌል እንዲህ ማሰብ ኦሪታዊ ሆኖ መገኘት ነው፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ቸር አገልጋይ ማነው"
ቸር አገልጋይ ማነው ለንጉሥ  የታመነ
መክሊቱን ያልቀበረ አትርፎ የከበረ (፪)

ባለ አምስቱ መክሊት መልካም ያደረገው
በመውጣት በመውረድ አትርፎ መጥቶ ነው
በጥቂቱ ታምኖ በብዙ የተሾመው
ባለ አምስቱ መክሊት ሊቀ ጳጳሱ ነው

አዝ= = = = =
ሳይሰለች የተጋ ባለሁለት መክሊት
የታመነ እረኛ በፍቅርና በእምነት
ግባ የተባለው ወደ ጌታው ደስታ
አጥምቆ ያቆርባል ካህኑ የጌታ

አዝ= = = = =
ለሚበልጠው ጸጋ ተጠርቶ የነበረ
መክሊቱን ደብቆ ቆፍሮ የቀበረ
ሰነፍ ባርያ ተብሎ ወደ ፍርድ ተጣለ
ማኔ ቴቄል ፋሬስ በአምላክ ፊት ቀለለ

አዝ= = = = =
ፈቃድህን ማድረግ ነፍሱ ለምትወደው
ወንጌልህን መግለፅ የየዕለት ግብሩ ነው
ህግህ ለዘለላም ተጽፎ ይኖራል
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህ ይነገራል

©በዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ተብለን ወደ ውርደት አዘቅት እንዳንላክ መጠንቀቁ አይከፋም፡፡ የመሾም የመሻር የማሳደግና የማውረድ ሥልጣን የእግዚአብሔር ነውና፡፡ “ከእናንተ መካከል አንዱን እንኳ እንዳናስቸግር ቀንም ሌሊትም እንሠራ ነበር” (፩ኛ ተሰ. ፪፥፱) በጎና ታማኝ አገልጋዮች ሆነን እንድንገኝ ጠንክረን ልንሠራ ይገባናል፡፡

 በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች
-፪ኛ ጢሞ ፪፥፩-፲፮
-፩ኛ ጴጥ ፭፥፩-፲፪
-የሐዋ ሥራ ፩፥፮-፱

ምስባኩም፦ መዝ ፴፱፥፰
"ከመ እግበር ፈቃድከ መከርኩ አምላኪየ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ"
"አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድኩ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው በታላቅ ጉባዔ ጽድቅህን አወራሁ"

ወንጌሉም፦ ማቴ ፳፭፥፲፬-፴፩

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ገብር ኄር
የዐብይ ጾም ስድስተኛ እሑድ(ሳምንት)


ይህን ሳምንት ቅድስት ቤተክርስቲያን ”ገብርኄር” የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች፡፡ ገብርኄር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ. 25:14-30 ነው፡፡

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ መስሎ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ የዛሬው ወንጌል አስተማሪ የሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል፡፡ በተለይ ምንም እንኳን የቤተክርስቲያን ሓላፊነት የእገሌና የእገሊት ተበሎ ባይወሰንም ቤተ ክርስቲያን ባላት የአገልግሎት መዋቅር መሠረት የሓላፊነትን ቦታ ይዘው ለሚያገለግሉ ሰዎች አትኩሮት ሊሰጡባቸው የሚገባቸውን ነጥቦች ይጠቁማል፡፡ ይህን ለማየት ያመቸን ዘንድ ከታሪኩ የመጀመያ ክፍል በመነሣት ዋና ዋና የሆኑ ዐሳቦችን በአትኩሮት መመርመር  ጠቃሚ ነው፡፡

በምሳሌያዊው ታሪክ መጀመሪያ ላይ የምናገኘው አንድ መንገድ ሊጀምር ያሰበ ሰው ከመሔዱ በፊት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን ለአንዱ አምስት ለአንዱ ሁለት እንዲሁም ለሌላኛው አንድ መክሊት ነግደው ያተርፉበት ዘንድ እንደሰጣቸው ነው፡፡ ገና ከታሪኩ መጀመሪያ እንደምንረዳው የአገልጋዮቹ ጌታ ምንም እንኳን እርሱ ለመንገድ ቢዘጋጅም ሀብቱ ግን በተዘጋ ቤት ውስጥ ተቆልፎበት እንዲቀመጥ አልፈለገም፡፡ በዚህም አገልጋዮቹን ጠርቶ ገንዘቡን በአደራ ተቀብለው እንዲያተርፉበት ማዘዙን እንደማስረጃ ልናቀርብ እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ማትረፍ በመፈለጉ ብቻ ገንዘቡን ያለአግባብ አልበተነም፡፡ ነገር ግን ለእርሱ ቀረቤታ የነበራቸውን አገልጋዮቹን ጠርቶ ያውም እንደየችሎታቸው መጠን ሓላፊነቱ ሳይከብዳቸው እንዲሠሩበት ገንዘቡን አከፋፈላቸው፡፡

ይህ ጌታ ቅንነትና ርኅራኄ የበዛለት እንደሆነ የሚያመላክተን ነገር አለ፡፡ ይኸውም ለአገልጋዮቹ ሓላፊነትን ቢሰጥም እንኳን ከእነርሱ ጋር በነበረው ቀረቤታ ማን ምን መሥራት ይችላል የሚለውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለእያንዳንዳቸው እንደ ሓላፊነት የመሸከም አቅማቸው አምስት ሁለት አንድ እያደረገ መስጠቱ ነው፡፡ ምናልባት ስስት ባልተላቀቀው ስሜት ለሚያስብ ሰው የዚህ ጌታ መክሊት አሰጣጥ አድልዎ ያለበት ሊመስለው ይችላል፡፡ ታሪኩን እስከ መጨረሻው ብንከታተለው ግን የሚያሳየን የባለ መክሊቱን ባለቤት ቅንነት ነው፡፡ ቀጥለን እንደምናነበው ይህ ጌታ ለአገልጋዮቹ አትርፉበት ብሎ መክሊቱን ሰጥቷቸው በሔደበት ሀገር አልቀረም፡፡ ይልቁንም እያንዳንዱ በተሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩበት ሊቆጣጠራቸው እንደመጣ እናነባለን፡፡ ስለዚህ አገልጋዮቹ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩ እንደሚጠይቃቸው እያወቀ ከአቅማቸው በላይ የሆነ መክሊትን በመስጠት ምን ሠርተው የተሰጣቸውን መክሊት ያህል ማትረፍ እንደሚችሉ በማሰብ እንዲጨነቁ አልፈለገም፡፡ በተቃራኒው የምናየው ያለምንም ጭንቀት ከአእምሯቸው በላይ ሳይሆን ባላቸው ኀይል ተጠቅመው መሥራትና ማትረፍ የሚችሉትን ያህል መክሊት እንደሰጣቸው ነው፡፡

ከብዙ ጊዜም በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ በሰጣቸው መክሊት ምን እንደሠሩበት ሊቆጣጠራቸው ሲመጣ አምስት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሌላ አምስት እንዲሁም ሁለት መክሊት ተቀብሎ የነበረው ሌላ ሁለት መክሊት አትርፎ ጌታቸው ፊት እንደቆሙ ያ ጌታም በእነዚህ አገልጋዮቹ ታማኝነት ተደስቶ ወደ ደስታው እንዳስገባቸው እናያለን፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ያ አንድ መክሊት ተቀብሎ የነበረው ምድርን ቆፍሮ ያተርፍባት ዘንድ የተሰጠችውን መክሊት እንደቀበረ ከዚህም አልፎ ምን አደረክባት ተብሎ ሲጠየቅ የአመጽ ንግግር እንደተናገረ በዚህ ከፊቱ ያዘነው ጌታውም ያን ክፉ አገልጋይ እንዲቀጣ እንዳደረገው አናነባለን፡፡

በዚህኛው ክፍል ከተጠቀሰው ታሪክ ሦስቱን አካላት ማለት የመክሊቱን ሰጪ ጌታ፣ በጎ የተባሉ አገልጋዮችና ክፉ እና ሰነፍ የተባለውን አገልጋይ በተናጥል እንመልከታቸው፡፡

1. የአገልጋዮቹ ጌታ፡–

ይህ ሰው ለገንዘቡ ጠንቃቃ ከመሆኑ ባሻገር በአገልጋዮቹ ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለው እናያለን፡፡ በክፉው አገልጋይ ላይ ባለመታዘዙ ምክንያት የፈረደበትን ፍርድ /ልቅሶና ጥርስ ማፏጨት ወዳለበት በውጪ ወዳለ ጨለማ እንደአወጡት/ ስንመለከት የሚያሳየን የአገልጋዮቹን ጌታ ታላቅ ሥልጣን ነው፡፡ ምንም እንኳን ሥልጣኑ ጽኑ ቢሆንም ይህ ጌታ ፍርዱ ግን በእውነት ላይ የተመረኮዘ መሆኑን ደግሞ በድካማቸው ታግዘው በተሰጣቸው መክሊት ላተረፉት በጎ አገልጋዮች የሰጣቸውን ፍጹም ደስታ መጥቀስ ይቻላል፡፡

2. በጎ አገልጋዮች:-

በአገልጋዮቹ ጌታ በጎ አገልጋዮች የተባሉት አምስት መክሊት የተቀበለውና ሁለት መክሊት የተቀበለው ናቸው፡፡ እዚህ ጋር ማስተዋል የሚገባው እነዚህ ሁለቱ አገልጋዮች በጎ አገልጋዮች ለመባል ያበቃቸው አስቀድመው ብዙ ወይንም የተሻለ ቁጥር ያለው መክሊት ለመቀበል መብቃታቸው አይደለም፡፡ ጉዳዩ የመክሊቱ ቁጥር ሳይሆን በተሰጣቸው መክሊት መጠን የሚገባቸውን ያህል ደክመው ማትረፍ መቻላቸው ነው፡፡ ወይንም ያ ባለ አንድ መክሊት አገልጋይ ከሁለቱ ያሳነሰው ከአንድ በላይ መክሊት መቀበል የማይችል መሆኑ ሳይሆን በዚያችው በአንዷ መክሊት እንኳን መሥራት አለመቻሉ ነው፡፡

3. ክፉና ሰነፍ አገልጋይ:-

ይህ ሰው የተጠቀሱ ሦስት መሠረታዊ ችግሮች አሉበት፡፡

የአገልጋዮቹ ጌታ ወደ መንገድ ሊሔድ በተዘጋጀበት ወቅት አገልጋዮቹን ጠርቶ ለእያንዳንዳቸው እንደችሎታቸው ገንዘቡን ሲሰጣቸው አትርፈው እንዲቆዩት ነው፡፡ ከላይ እንደተነገጋገርነው እንደ አቅማቸው መስጠቱም አቅማቸው በሚፈቅደው የሥራ ደረጃ እንዲሰማሩ በማሰብ ነበር፡፡ ይህ ሰነፍ አገልጋይ ግን ያደረገው ከታዘዘበት ዓላማ በተቃራኒው መልኩ ነው፡፡ ሊሠራበት የሚገባውን መክሊት ቀበረው፡፡ ይህም ለጌታው ትዕዛዝ ያለውን ቸልተኝነት ያሳያል፡፡

ጌታው በመጣ ጊዜ አመጽ የተመላበት የሐሰት ንግግር ተናግሯል፡- ከሔደበት ቦታ ተመልሶ ጌታው በተሰጠው መክሊት ምን እንዳደረገ ሲጠይቀው «አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበትም የምትሰበሰብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ አውቃለሁ ስለፈራሁም ሔድሁና መክሊትህን በምድር ውስጥ ቀበርሁ፡፡» ሲል መለሰለት፡፡ ይህ ንግግር ከአመጽ ንግግርነቱ በተጨማሪ ውሸት አለበት፡፡ ምክንያቱም እርሱ እንዳለው ጌታው ካልዘራበት የሚያጭድ ካልበተነበት የሚሰበሰብ ጨካኝ ሰው ቢሆን ኖሮ ያደርግ የነበረው ምንም መክሊት ሳይሰጠው ከነትርፉ ሁለት መክሊቶችን ይጠይቀው ነበር፡፡ ነገር ግን ተጽፎ የምናነበው ትርፉን ከመጠየቅ በፊት አንድ መክሊት ሰጥቶት እንደበረ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አስቀድሞ ገንዘቡን ዘርቶ ነበር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ጌታ ዘርቷልና ማጨድ ይገባዋል፤ በትኗልና መሰብሰብም መብቱ ነው፡፡

እርሱ መሥራት ሲሳነው እንኳን ዕድሉን ለሌሎች አልሰጠም፡- ይህ ሰው የተሰጠው መክሊት በትርፍ ሊመለስ እንደሚገባው ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ምክንያቱም ገና ሲቀበል ከጌታው የተቀበለው ትዕዛዝ ነውና፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን መውጣት መውረዱ ቢከብደውም ወጥተው ወርደው ማትረፍ ለሚችሉ ሰዎች አለመስጠቱ ተጨማሪ ጥፋቱ ነው፡፡ ይህን እንዳያደርግ ያሰረው ደግሞ ውስጡ የተቀረጸው የአመጽ መንፈስ ነው፡፡ ጌታው መጥቶ ስለ ትርፉ ሲጠይቀው የሚመልስለትን ረብ የለሽ ምክንያት እንደ መከላከያ አድርጎ ማሰቡ አእምሮው ሌላ አማራጭ እንዳያስብ የዘጋበት ይመስላል፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መ. ሌላውን መንፈሳዊና ተገቢ ምክንያት ወደ ጐን በመተው አንድ ጊዜ ከነድንግልና ያጫቸውን ሰው በማክበርና በመፍራት ብቻ ድንግልናቸውን የሚጠብቁ ሴቶች አሉ። እነዚህ ሴቶች ያጫቸው ሰው ሳያገባቸው ሕጋቸውን ቢወስድ ማንም እንደፈቀደ እንደሚገባበትና እንደሚወጣበት እንደ ክፍት በር ሆኑ ማለት ነው። ምክንያቱም ባል በገዛ እጁ መጠበቂያ ማኅተሙን ስላፈረሰው ከዚያ በኋላ በምንም መንገድ መቆጣጠር ስለማይችል ነው።
ድንግልናቸውን ላጫቸው ሰው ብለው የሚጠብቁ ሰዎች ባጫቸው ሰው እጅ ድንግልናቸው ከተወሰደ ከዚያ በኋላ ከዝሙት ተጠብቀው እንዲኖሩ የሚያደርጋቸው ምንም ዓይነት ምክንያት አይኖርም፡፡ ሰው ደግሞ ንጽሕናውን የሚጠብቅበት ምንም ዓይነት ዓላማና ምክንያት ሳይኖረው ንጽሕናዬን ልጠብቅ ሊል አይችልም። በዚህና በመሳሰሉ ምክንያቶች አንድ ጊዜ ድንግልናን ማጥፋት የባሰ ዘማዊ ማድረጉ ግልጽ ነው።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስታመነዝር የተያዘችውን ሴት «ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ» ያላት አንድ ጊዜ ዝሙት በመሥራቷ ተስፋ ቆርጣ መላልሳ እንዳታመነዝር ለማስጠንቀቅ ነበር። ዮሐ 8፥11 አንድ ጊዜ በማመንዘር ስሜ ከጠፋ አይቀር በማሰኘት የበለጠ ዘማዊ ያደርጋልና።
ያጨሃትን ሴት ላታገባት አትድረስባት። ከዚህ ወጥተህ ድንግልናዋ ቢያጓጓህና ብትደርስባት በሁለት መንገድ ራስህን ጐድተሃል። አንደኛ አመንዝራ ትባላለህ፤ የራስህንም ክብር ታጣለህ ሁለተኛ ደግሞ እርሷንም ካንተ ወጥታ ለማመንዘር እንዲመቻት አድርገሃልና በራስህ ጠንቅ አመጣህ ማለት ነው። ምክንያቱም ከዚያ በኋላ እርሷ አንተን የምትፈራበት አንተም እርሷን የምትጠብቅበት ምንም ምልክት የለህም፡፡ ምልክቱን በገዛ እጅህ አፍርሰኸዋልና። እንዲህ ከሆነ አግዚአብሔር ይጠብቅልኝ እንጂ ካገባኋት በኋላስ ማመንዘር ትችል የለምን? እንዳትል እርግጥ ነው ትችላለች ቢሆንም ማግባቷም ራሱ የድንግልናዋን ያህል ጥበቃ ሊያደርግላት መቻሉን አትርሳ፡፡

ድንግልናና ሥርዓተ ተክሊል
ድንጋሌ ሥጋ ላላቸው ሰዎች በጋብቻቸው ጊዜ የሚደረግላቸው ጸሎት ለመዓስባን (ደናግል ላልሆኑ) ሰዎች ከሚደረገው ይለያል፡፡ ጉልህና ተጨባጭ ድንግልና (ድንጋሌ ሥጋ) ስላላቸው በግዘፍ የሚታይ፣ የሚሰማ ሥርዓት ማለትም ሥርዓተ ተክሊል ይፈጸምላቸዋል፡፡ ለእነዚህ ደናግላን በግልጽ በዓይነ ሥጋ ከሚታየው ሥርዓተ ተክሊል ባሻገር በንስሐ ሕይወት ድንጋሌ ነፍስም ያላቸው በመሆኑ በዓይነ ነፍስ ብቻ የሚታይ ረቂቅ የብርሃን ልብስ፣ የብርሃን አክሊል ይደረግላቸዋል፡፡
ታዲያ ሥርዓተ ተክሊል በድንጋሌ ሥጋ አንጻር የሚደረግ ከሆነ በንስሐ በተደጋጋሚ ከሚገኝ ከድንጋሌ ነፍስ አንጻር ደግሞ ረቂቅና በዓይነ ሥጋ የማይታይ የብርሃን አክሊል የሚደረግ ከሆነ ድንጋሌ ሥጋ የሌላቸው ነገር ግን በንስሐ ለተመለሱ ሰዎች በንስሐ ስላገኙት ድንጋሌ ነፍስ ረቂቅ የብርሃን አክሊል ብቻ አይበቃቸውምን? ለእነዚህስ ሰዎች በግዘፍ ያለ ድንጋሌ ሥጋ ሳይኖራቸው በግዘፍ የሚታይ ሥርዓተ ተክሊል መፈጸም ተገቢ አካሄድ ነውን?
በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት አንድ ሰው ድንግልናውን ጠብቆ ለመኖር ከተሳለ በኋላ እንደ ገና ወደ ማግባት ቢመለስ ጋብቻው ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚያገባ ሰው ተቆጥሮ ሥርዓተ ተክሊል አይፈጸምለትም። (ፍት.ነገ.አን.24) ይህ ሰው ንጽሐ ሥጋውን ሳያጠፋ ስእለት ተስሎ ስላፈረሰ ብቻ ክብረ ተክሊል ከቀረበት ንጽሐ ሥጋውን ያፈረሰ ሰው እንዴት ይልቅ ተክሊል ከማድረግ አይክለከል?

«ድንግል›› ልባል እችላለሁን?
ይህ ጥያቄ የብዙዎች ነው:: ልዩ ልዩ የግብረ ሰዶም ተግባራትን ያከናወኑ ሰዎች፣ዘራቸውን በሜዳ ያፈስሱ የነበሩ ወንዶች፣በአደገኛ ሁኔታ ለዝሙት የተጋለጠ መዳራት ይፈጽሙ የነበሩና በሌላም ልዩ ልዩ የዝሙት ጐዳና የተጓዙ ሰዎች በመጨረሻ ይህን መጠየቃቸው አይቀርም፡፡
ግን ለምን?

ሰይጣነ ዝሙት ሰው እንዳይጸጸትና በቀደመ ሥራው ንስሐ እንዳይገባ ለማድረግ የማይገ'ባ ጭንቀትና ተስፋ ያሳድርበታል በመጀመሪያ በኃጢአት እንዲወድቁ የሚያደርግ እርሱ ነው፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ከመጸጸት፣ ንስሐ ከመግባትና ጥፋታቸውን ከማስብ ይልቅ ያጡትን ነገር እንዲያስላስለ ያደርጋቸዋል። መጽሐፈ መነኮሳት ስለዚህ ነገር ሲናገር፦ «ወያገርሮ ለልብ ኀበ ምግባረ ዝሙት ቅድመ ይትሀወክ በእንተ ዘቀደመ ንጽሑ - ንጽሐ ልቡናው ስለፈረሰበት ንጽሐ ሥጋ ይፈርስብኝ ይሆን እያለ ይታወካል፡፡» ይላል:: ድንግል ነኝን? የሚል ጥያቄ የሚፈጠረውም በዚህ ምክንያት ነው:: ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲፈጠር የሚበጀው ያጡትን ማሰላሰል ሳይሆን ይቅር በለኝ ብሎ ንስሐ መግባት ነው፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ድንግልናን ከንጽሕና ጋር «እንደ ንጽሕት ድንግል>> በማለት አቆራኝቶ ስለገለጸው ድንጋሌ ሥጋን ከንጽሕና ተግባር ጋር አንድ አድርጐ መያዝ ይገባል፡፡ 2 ቆሮ11÷2 የቅድስና ሥራ የተለየው በአንጻሩ ደግሞ ርኩሰት የተዋሐደው ድንጋሌ ሥጋ አለ። በቅዳሜ ዕለት የሚነበብ የእመቤታችን ምስጋና «ተፈስሒ ኦ ምልዕተ ጸጋ ድንግል ዘእንበለ ርኩስ» ይላል፡፡ ትርጓሜውም «ያለ ርኩሰት ድንግል የሆንሽ ምልዕተ ክብር ሆይ ደስ ይበልሽ!» ማለት ነው፡፡ (ውዳሴ ማርያም ዘቀዳም) ይልቁኑም «ያለ ርኩሰት ድንግል የሆንሽ›› የሚለው ቃል ሰዎች በሥጋ ድንግል ሆነው ብዙ ርኩሰት ሊኖርባቸው እንደሚችል ሲያስረዳ የእመቤታችን ድንግልና ግን ፍጹምና ያለ ርኩሰት መሆኑን ያስገነዝበናል::
ደናግላን ቆነጃጅት ይባላሉ፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ የጠቀሳቸው አሥር ቆነጃጅት ደናግላን ናቸው፡፡ አምስቱ ልባሞች ሲሆኑ አምስቱ ግን ሰነፎች ነበሩ። ማቴ. 25፥13 እነዚህ ሰነፍ ደናግላን መብራታቸውን ይዘው ለመብራት የሚሆን ዘይት ግን አልያዙም ነበር፡፡ ዘይቱን ሳይይዙ መብራት መያዛቸው ብቻ ሙሽራው በመጣ ጊዜ አብረውት ሠርጉ ቤት ለመግባት አላበቃቸውም፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ንጽሐ ሥጋን ይዞ ንጽሐ ነፍስን ሳይዙ መገኘት ምንም አይጠቅምም፡፡ ድንጋሌ ሥጋንም ያለንጽሕና ከብዙ ርኩሰት ጋር መያዝ ምንም እንደማይጠቅም በትርጓሜው ተብራርቷል፡፡ ድንጋሌ ሥጋ እንደ መብራት ድንጋሌ ነፍስ ደግሞ እንደ ዘይት ነውና፡፡
እንዲህ ከሆነ ከብዙ ነውረኛነት ጋር በሥጋ ብቻ ድንግል ብትሆን ምን ትጠቀማለህ? ምንም ሳይማሩ (ሳያውቁ) በመመረቂያ ልብስ (ጋዋን) ማሸብረቅና ምንም የንጽሕና ጐዳና ሳይከተሉ በሥጋ ብቻ ድንግል መሆን አንድ ናቸው:: ምነው ቢባል ቢያሳፍሩ እንጂ አያስከብሩምና፡፡ ስለዚህ በፈቶች (ድንግልና በሌላቸው) ሰዎች ዘንድ እንኳን የማይታይ የዝሙት ዓይነት እያፈራረቁ በሥጋ ብቻ ድንግል መሆን አያስመካምና ድንግልናን ከንጽሕና ጋር መጠበቅ ተገቢ ነው፡፡
ድንግል ነኝን? ከሚለው ይልቅ ዋናው ጥያቄ መሆን ያለበት ድንግልናችንን እንድንጠራጠር ያደረገን ተግባር ኃጢአት ነውን? የሚለው ነው:: ማኅተመ ድንግልና ካልፈረሰ ኃጢአት (ዝሙት) አልተፈጸመም ማለት አይደለም:: ሰውን መግደል ዝሙት አይደለም ኃጢአትነቱ ግን እጅግ ታላቅ ነው:: «ወዘመዉ በጣዖቶሙ» ጣዖት ማምለክ ዝሙት ነው ፤ ድንጋሌ ሥጋን ግን አያጠፋም፡፡ ግብረ ሰዶምም ማኅተመ ድንግልናን ላያጠፋ ይችል ይሆናል ዝሙት መሆኑን ግን ማንም አይክድም:: ስለዚህ የማይጠቅም ጥያቄ በማንሣት ጉልጭ አልፋ ክርክር ከመከራከር ኃጢያትን ማቆም ብልህነት ነው።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በጨቅላ ዕድሜያቸው ያገቡ ልጆች ጋብቻቸው እንደማይጸናና ችግር እያጋጠማቸው እንደ ሆነ ሁሉ ሳያገቡ ድንግልናቸውን የሚያጠፉና ስድ የለመዱ የዛሬ ተጋቢዎችም ራሳቸውን ገትቶ መያዝ ስለማይሆንላቸው ከትዳር በኋላ ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ማየት የዘወትር ክሥተት ሆኗል፡፡ ስለዚህ ድንግልናን የመጠበቅ ጥቅም ይህ ነው ተብሎ ከሚጠቀሰው በላይ ስለሆነ የትዳር ሕይወቱን ጤናማነት የሚሻ ሁሉ ከጋብቻ በፊት ድንግልናውን ሳያስደፍር መኖር ይኖርበታል፡፡  እንደዚሁም እስራኤላዊያን ከጋብቻ በፊት ድንግልና እንዳይጠፋ የሚቆጣጠሩበት ከባድ መንፈሳዊ ሕግ ፈጣሪ ሰጥቷቸው ነበር። ማለትም ከጋብቻ በፊት ድንግልናውን የሚያጠፋ ሁሉ በድንጋይ ተወግሮ፣ በእሳት ተቃጥሎ ይገደል ነበር። ዛሬ ዛሬ በአንዳንድ የሀገራችን ገጠራማ አካባቢዎች እንደሚደረገው ሁሉ በእስራኤላውያንም ዘንድ አንድ ሰው ሁነኛ የትዳር አጋሩን አግኝቶ እስከሚያገባ ድረስ ድንግልናውን ጠብቆ ይኖር ነበር፡፡ እነዚህ የታሪክ ማስረጃዎች እስከ ጋብቻ ድረስ ድንግልናን ጠብቆ መቆየት አግባብ እንደነበር ያስረዳሉ::
   ወደ ጥንታዊው ግሪክ ዓይነ ልቡናችንን የመለስን እንደሆነ ደናግል ተለይተው የሚኖሩበት በዕውቀትና በሥልጣኔ ይጎለምሱበት የነበረ ቦታ ተለይቶ «ፓርቴናጎግዮን» የሚል ስያሜ እንደነበረው አስከ አሁን ድረስ ያሉ የግንቦቹ ፍራሽና ታሪክ ያስረዳሉ፡፡ ድንግልናን መጠበቅ ለጊዜው (እስከ ጊዜው) የሚባለው እስከ ትዳር ለማለት ነው፡፡ ከትዳር በኋላ ግን ወንዱ ድንግልናውን በከበረ ስጦታነት በረቂቅ መንገድ ለሚስቱ ሲያስረክብ ሴቲቱ ደግሞ እንደዚሁ ሕጓን በገሢሥ ሊታወቅ በሚችል መልኩ (በግዘፍ) ለባሏ ትሰጣለች፡፡ ይህ ሲሆን በባልና በሚስት መካከል ጥልቅ የሆነ መከባበር፣ መተሳሰብ፣ መተማመንና መፈቃቀር ይጎለብታል፡፡
   እንደ ምንኩስና ሁሉ ጋብቻም በድንግልና ተጠብቀው ከኖሩ በኋላ ሊገባበት ይገባል፡፡ ጋብቻ እንደ ፈቀዱ በኃጢአት ሲጨማለቁ ከኖሩ በኋላ በመጨረሻ የሚፈጸም ሥርዓት አይደለም፡፡ ምንም እንኳን ደናግላን ካልሆኑ ማግባት አይቻልም ባይባልም በድንግልና ሆነው የሚፈጽሙት ጋብቻ ግን ብዙ ጸጋና በረከት አለበት:: ጋብቻ በደናግላን ያምራል:: የብዙ ቅዱሳን ወላጆችም በድንግልና ኖረው በቅዱስ ጋብቻ የተወሰኑ ናቸው::
   ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ድንግልና በተናገረበት አንቀጽ «ስለ ደናግል የጌታ ትእዛዝ የለኝም» 1ቆሮ 7፥25 በማለት የተናገረው በሕይወት ዘመን በሙሉ በድንግልና ስለ መኖር ነው እንጂ እስከ ጋብቻ ጊዜ ድረስ በድንግልና ለመኖር ሥርዓትም ትእዛዝም የለም ለማለት አይደለም:: እስከ ጋብቻ ጊዜ ድረስ ማንኛውም ሰው ድንግልናውን ጠብቆ የመኖር መንፈሳዊ ግዴታ አለበት::
    ድንግልናን እስከ ጋብቻ ድረስ ጠብቆ ማቆየት ለሰው ልጅ በሙሉ የተሰጠ ችሎታ ነው:: ስለዚህ ይህ በውዴታ መደረግ ያለበት ነገር ብቻ አይደለም:: መንፈሳዊ ግዴታና ትእዛዝም እንዳለበት መታወቅ አለበት:: መላ ዘመንን በድንግልና ኖሮ ለመፈጸም ግን አስቀድሞ እንደተገለጸው መመረጥና መታደል ያስፈልጋል:: ማቴ 19፥11 በዐዋጅ የተደነገጉትን አጽዋማት በተሠራላቸው ቀኖና መሠረት መጾም ለሁሉ የሚቻል ነው:: ሥርዓቱ የተሠራው የሰውን ሁሉ ዐቅም በሚያውቅ በመንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡ ከዚያ አብልጦ ምንም እህል ሳይቀምሱ እንደ ሙሴና እንደ ኤልያስ ለዐርባ ቀናት ለመጾም ግን መመረጥንና መታደልን ይጠይቃል:: መላ ዘመንን በድንግልና ለመኖርም እንዲሁ ሲሆን እስከ ጋብቻ በንጽሕና ለመቆየት ግን ለሰው ሁሉ የታወጀ ነው:: ዘፀ 34 ÷ 28፤1ኛ ነገ19÷8

በድንግልና መኖር የማይቻል ነገር ነው?
አንዳንድ ሰዎች ድንግልናን መጠበቅ የማይቻል ነገር እንደሆነ አድርገው ሲናገሩ ይደመጣል፡፡ እውነት ድንግልናን መጠበቅ ይቻላል? አዎን! በደንብ ይቻላል:: የማይቻል ቢሆን ኖሮ ፈጣሪ የፈጠረውን ፍጥረት ይዘት ያውቃልና እስከ ጋብቻ ጊዜ ድረስ ድንግልናችንን እንድንጠብቅ ባላዘዘንም ነበር። ከበሬ መራገጥን፣ ከአህያ ደግሞ መዋጋትን የሚጠብቅባቸው የለም፡፡ ለዚህ ስላልተፈጠሩ አይቻላቸውምና፡፡ እግዚአብሔርም ለሰው የማይቻለውን አያዝዘውም አይጠብቅበትምም፡፡
  ሩካቤ ሥጋን እንደምንተነፍሰው አየር፣ እንደምንጠጣው ውኃና እንደምንመገበው ምግብ መቁጠር የለብንም፡፡ ምክንያቱም እነዚህን ያጣ ሰው ብዙ ሳይቆይ ወደ ሞት ይሄዳል፡፡ ሰው ግን ሩካቤ ባለማድረግ ብዙ ሊፈተን ይችል ይሆናል እንጂ አይሞትም:: ስለዚህ ሩካቤ ሥጋ የማይቋቋሙት ነገር አይደለምና ድንግልናን መጠበቅ ይቻላል፡፡
ድንግልናን መጠበቅ አይቻልም በማለት የሚያምኑ ሰዎች ከግትር አቋማቸውና ከድክመታቸው የተነሣ ብዙ ደናግላንን እንደምሳሌ ቢያቀርቡላቸው እንኳን አያምኑም፡፡ ወይም ጤናማነታቸውን እንጠራጠራለን በማለት ምክንያት ይደረድራሉ፡፡ ነገር ግን ንጽሕና መጠበቅ የመሰለ ጤናማነት የለም:: ከኃጢአት ተለይቶ ድንግልናን በመጠበቅና ነፍስን ጤናማ ማድረግ ከጤናማነትም በላይ ነው፡፡ ጤና ማጣትስ እንደ ክፍት ቤት የዘማውያን መናኽሪያ መሆን ነው፡፡ ስለዚህ በአዎናባጆች አሉባልታ በመደናገጥ ጤናችንን እስከመጠራጠር ደርሰን ራሳችንን ለመፈተሽ ወደ ዝሙት ከማምራት በሠራነው ሥራ መልካምነት ሙሉ እምነት ኖሮን ድንግልናችንን መጠበቅ ይገባናል፡፡
በዝሙት መሸነፍ የሚጀምረው ድንግልናን መጠበቅ የማይቻል ነገር እንደሆነ ከማሰብ ነው:: አልችልም ያለ ተሸንፏልና፡፡ ነገር ግን ለሚያምን እንኳን ድንግልናን መጠበቅ ይቅርና ከዚያም በላይ የሆነ ነገር ይቻላል፡፡ «በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱም ደግሞ ያደርጋል:: ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል።» በማለት የሁሉ ፈጣሪ ለሰው ልጆች የገባው ቃል ኪዳን የሚሻር አይደለምና።ዮሐ 14÷12-73
  ሰው ድንግልናውን ለመጠበቅ ዝንባሌ ሲኖረው መንፈስ ቅዱስ ይደግፈዋል፡፡ ስለዚህ ራሱን ለመግዛትና ስሜቱን አሸንፎ ለመኖር ይችላል፡፡ከመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎችም አንዱ «ራስን መግዛት› ነውና ገላ 5፥23 ስለዚህ ንጽሕናውን ለመጠበቅ የኃይሉ ምንጭ መንፈስ ቅዱስ ከሆነ ድንግልናን ጠብቆ መኖር አይቻልም ለማለት አያስደፍርም፡፡ ሐዋርያው «ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ» በማለት የተናገረው ቃል ድንግልናን ጠብቆ መኖርንም ይመለከታል:: ፊል. 4፥13 ስለዚህ በእምነት አየታገዙ ድንግልናን ጠብቆ መኖር ይቻላል::ማቴ 17፥20
በቅዱስ መጽሐፍ«ለሚያምን ሁሉ ይቻላል» እንደተባለው እንኳን ድንግልናን መጠበቅ ይቅርና ለማያምኑ ሰዎች የማይቻል የመሰለ ነገር ሁሉ ለሚያምኑ ሰዎች ይቻላል፡፡ መንፈሳዊነት ማለት ረቂቅነት ማለት ነው፡፡ ረቂቅነት ማለት ደግሞ ረቂቅ ነገሮችን ማሰብና ማድረግ መቻል ማለት ነው፡፡ አንድ ክርስቲያን ድንግልናን መጠበቅ እንደማይቻል ነገር አድርጎ ካመነ መንፈሳዊ ነው ማለት እንዴት ይቻላል?
ድንግልናን መጠበቅ በኛ ዘመን የተጀመረ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ አዳም ከመሳሳቱ በፊት ለሰባት ዓመት ከሁለት ወር በገነት የኖረው ኑሮ ነው:: ኖኅም ለጋብቻና ለፍሬ የበቃው ለአምስት መቶ ዓመታት በድንግልና ከኖረ በኋላ ነው:: «ወዓቀበ ኖኅ ድንግልናሁ ሐምስተ ምዕተ ዓመተ ወነበረ እንዘ ይትለአክ ለሥጋ አቡነ አዳም በትእዛዘ እግዚአብሔር» ማለትም «ኖኅም በእግዚአብሔር ትእዛዝ የአባታችን የአዳምን ሥጋ እየጠበቀ ለአምስት መቶ ዓመታት ያህል በድንግልና ኖረ» ማለት ነው::(ስንክሳር ጥር6)

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ደብረ ዘይት"
ለፍርድ ይመጣል አምላካችን

ኧኸ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን
ለፍርድ ይመጣል አምላካችን
ዋጋ ሊከፍል ለሥራችን
በኃይል በስልጣን ይገለጣል
የወጉትም ሁሉ ያዩታል

ኧኸ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን

አንደበትም ሁሉ ዝም ይላል
የተከፈተ አፍ ዲዳ ይሆናል
መጻሕፍት ሁሉ ተዘርግተው
ይገለጣል የሁሉ ሥራው

ኧኸ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን

ዓለም በኃጢአቱ ይቀጣል
የትዕቢቱ ኩራት ይሻራል
ይዋረዳሉ ጨካኞቹ
ይከበራሉ ትሁቶቹ

ኧኸ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን

ለአሕዛብ ሊሆን ምሥክር
የመንግሥቱ ወንጌል ሲነገር
ቅዱሱ ወንጌል ይህን ብሏል
ፍጻሜ ዘመን ያኔ ይሆናል

ኧኸ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን

እንዲወጣ መብረቅ ከምስራቅ
እስከ ምዕራብ እንዲዘልቅ
የጌታ መምጣት እንደዚህ ነው
መንግሥትና ፍርዱ በእጁ ነው

ኧኸ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን

እንጠብቀው ተዘጋጅተን
ልባሞች ሆነን መብራት ይዘን
አናውቅምና ቀኒቱን
የሙሽራውን መምጫውን
አናውቅምና ሰዓቱን
የሙሽራውን መምጫውን
ኧኸ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን

©በዲያቆን ዘማሪ ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቅዱስ ጳዉሎስም “የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸዉን እየለወጡ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞ ሠራተኞች ናቸው። ይህም ድንቅ አይደለም ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለዉጣልና” ብሏል /2ቆሮ.11፥13-15/። ሐዋርያት ሁሉ በየመልእክቶቻቸው ከሐሰተኞች አስተማሪዎች እንድንጠበቅ ደጋግመው አሳስበዋል። ብዙ ሰው ግን በየዋሕነት ስለሚጓዝ የነዚህ ተኩላዎች ሰለባ ሆኗል።
ጊዜው ክፉ ነውና የሐሰተኞች ነቢያት መረብ ጠልፎ ወደ ሐሰተኞች ክርስቶሶች እንዳይወስደን በጥንቃቄ መጓዝ ይጠበቅብናል። ሐዋርያዉ ቅዱስ ይሁዳም በመልእክቱ ቁ.3  “ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ” ሲል እንደመከረን በተቀደሰ እምነታችን እስከመጨረሻ ጸንተን እንጋደል።

በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች
-፩ኛ ተሰ ፬፥፲፫ እስከ ፍጻሜ
-፪ኛ ጴጥ ፫፥፯-፲፭
-የሐዋ ሥራ ፳፬፥፩-፳፪

ምስባኩም፦ መዝ ፵፱፥፫
"እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ"
"እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይቃጠላል"

ወንጌሉም፦ ማቴ ፳፬፥፩-፴፮

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

«ይህንንም ለራሳችሁ ጥቅም እላለሁ፣ በአገባብ እንድትኖሩ ሳትባክኑም በጌታ እንድትጸኑ ነው እንጂ ላጠምዳችው ብዬ አይደለም »1ቆሮ7÷35
ሀ) የመጀመሪያው በድንግልና የመኖር ጥቅም «በአገባብ መኖር» ነው:: «በአገባብ መኖር» ሕግና ሥርዓትን እየፈጸሙ በአግባቡና በሥነ ሥርዓት¸ መኖር ማለት ነው።በድንግልና መኖር አግባብ ነው፡፡ዝሙት ግን ግብረ ገብነትን ማጣት ነው፡፡ድንግልናን ጠብቆ ለመኖር የሚደረገው ትግል ሕጋዊ ሰው ሆኖ መኖርን ያለማምዳል።ታዲያ ድንግልናን መጠበቅ እንደ አሸዋ ሽክም ከከበደውና ንጽሕናን ከናቀ ከዚህ አመንዝራ ትውልድ ግብረ ገብነትን መጠበቅ ከዝንብ ማር እንደ መጠበቅ አይሆንምን?
) ሁለተኛው በድንግልና የመኖር ጥቅም «ሳይባክኑ» መኖር ነው፡፡ በድንግልና የሚኖር ሰው አይባክንም ወዲህና ወዲያ አይልም።ዝሙት ግን መባከን ነው:: ለምን ቢባል ዝሙተኛ ኃጢአቱን ለመደበቅ፣ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ምን ያመጣብኝ ይሆን? በማለትና ዝሙቱ ቢታወቅ በሌሎች ዘንድ ምን ሊባል እንደሚችል በማሰብ በስጋትና በመባከን ይኖራል፡፡ ዝሙት ያባክናልና፡፡ በተጨማሪም ዛሬ ዛሬ በዝሙት ጠንቅ በሚመጣ በሽታ ተይዤ ይሆን” ከማለት የሚበልጥ መባከን ምን አለ?
ቅዱስ ዳዊት «ወተአውከት እምመዓት ዓይንየ» በማለት ተናግሯል፡፡ እንዲህም ማለቱ «ሴቶችና ሕፃናት ሲቆጧቸው ከእሁን አሁን ዱላ ጣሉብን በማለት ዓይናቸው እንደሚባክነው እኔም ጕልማሳ ገድዬ በጎልማሳ ሚስት በማመንዘሬ ምን ትቀጣኝ ይሆን? በማለት ባከንኩኝ› ለማለት ነው:: መዝ6፥1-3 ስለዚህ ዝሙት በዚህ ብቻ ሳይሆን በሌላም በብዙ መንገድ ሰውን ሲያባክነው ይታያል:: ድንግልናን ለመጠበቅ የሚጣጣር ሰው ግን ዝሙት ከሚያመጣው መባክን ፈጽሞ የዳነ ነው:: መዝ6 ፥ 2-3
ሐዋርያው ሰዎች በድንግልና እንዲኖሩ የሚያበረታታበትን ምክንያት ሲገልጽ «ያለ ሐሳብ ልትኖሩ እወዳለው» ብሏል:: 1ቆሮ7፥32 ምክንያቱም ያገባ ‹‹የዓለምን ነገር ያስባልና፤ ልቡም ተከፍሏል›› ይላል:: 1ቆሮ7፥33 በዝሙት ከመኖር በጋብቻ መኖር ሐሳብ ያቀላል፡፡ በጋብቻ ከመኖር ደግሞ በድንግልና መኖር የበለጠ ከሐሳብ ነጻ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው «ያለ ሐሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ» በማለት መክሯል:: ከዚህ የሐዋርያው ቃል በመነሣት «ሳይባክኑ መኖር» ድንግልናን ከመጠበቅ የሚገኝ ዋነኛ ጥቅም መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡
ሐ) ሐዋርያው በጥቂት ገጸ ንባብ ካሰፈራቸው ድንግልናን የመጠበቅ ጥቅሞች ውስጥ ሦስተኛውና የመጨረሻው «በጌታ እንድትጸኑ» የሚለው ነው፡፡ ድንግልናን መጠበቅ በጌታ ያጸናል፡፡ ይህም ማለት ስለ ፍትወት ብለው ኮረዳና ጎልማሳ ፍለጋ ብዙዎች ሃይማኖታቸውን እንደተዉ የሚታወቅ ነው፡፡ «በመዳራታቸውም ብዙዎች ይከተሏቸዋል» እንደተባለው ብዙዎች በዝሙት ማዕበል እየተገፉ ከሃይማኖት ወጥተዋል:: ድንግልናውን ለመጠበቅ የቆረጠ ሰው ግን የሃይማኖት ሙቀቱ ሳይበርድበት ለፈጣሪው ባለው ፍቅር ጸንቶ ይኖራል። 2ጴጥ2፥1-2
ይህም ብቻ ሳይሆን ድንግልናን መጠበቅ ራሱ ጽናትንና ትዕግሥትን ይጠይቃልና ስለዚህ <በጌታ እንድትጸኑ>አለ፡፡ በተጨማሪም «ድንግልናውን በልቡ ይጠብቅ ዘንድ ቢጸና›› 1ቆር:7፥37 በማለት ሐዋርያው የተናገረው ቃል «ጽናት» ከድንግልና ጋር ያለውን ትሥሥር ያሳያል፡፡ ድንግልናን በመጠበቅ ጽናትንና ትዕግሥትን የመሳሰሉ መንፈሳዊ ተግባራትን እንማርበታለን፡፡ ስለዚህ ድንግልናውን ለመጠበቅ የቆረጠ ሰው በዓላማው ሁሉ ትዕግሥተኛና ጽኑ ሰው መሆኑን መናገር ይቻላል፡፡ ታዲያ ይህን የመሰለ ጥቅም ማግኘትን የሚያህል ምን ነገር አለ? አንተ ሰው ጽኑ ነህን? ለማለት ድንግልናህን ጠብቀህ እስከ አሁን አለህን? ቢባል ስንቶቻችን ፅናት እንደሌለን ይረጋገጥ ይሆን?
መ) ድንግልናን ጠብቆ መኖር ታማኝነትን ያረጋግጣል፡፡ ምክንያቱም ድንግልና በሥርዓት ጠብቀን እንድንይዘው በአደራ እንደ ተሰጠን የከበረ ንብረት ነውና፡፡ ባለ አደራው ፈጣሪያችን በሚያስፈልግ ጊዜና ሰዓት ለትዳር አጋራችን እንድንሰጠው ይጠብቅብናል፡፡ በዚህ ጊዜ ድንግልናው ጠብቆ እስከ ጋብቻ ጊዜው ድረስ ያልቆየ ሰው አደራ በሊታ ይባላል፡፡ ታማኝነትም የጐደለው ይሆናል፡፡ ሰው ደግሞ በዚህ ካልታመነ በሌላ ነገር በምን ሊታመን ይችላል?
ድንግልናን መጠበቅ «በባልና በሚስት መካከል መተማመንን› ይፈጥራል የሚባለው የታማኝነት ምልክት ስለሆነ ነው:: ባል ሚስቱን በምን ይመን? ለእግዚአብሔር ትእዛዝ ያልታመነች በሰው ዘንድ ታማኝ ልትሆን እንዴት ትችላለች? ስለዚህ ድንግልናን ጠብቆ በመኖር ታማኝነትን ማስመስከር ይገባል:: ማኅተመ ድንግልና የታማኝነት ማረጋገጫ ምስክር ነውና፡፡
ድንግልና በሩካቤ ሥጋ ይጠፋል፡፡ ይህ ተግባር ደግሞ በዓይን እንደ መጥቀስና እንደ ማስነጠስ በቅጽበትና ሳይታሰብ የሚከናወን ተግባር አይደለም:: ሩካቤን ለመፈጸም የሚያስችል ምቹ ቦታ ለማስናዳት ከሚደረግ ጥረት አንሥቶ ብዙ ሂደቶችን በማለፍ የሚከናወን በመሆኑ በእጅ እንደያዙት ብርጭቆ ድንገት ሳላስበው ወድቆ ተስበረብኝ የሚባል ነገር አይደለም፡፡ በመሆኑ ድንግልናን ያለ ጊዜው ማጥፋት ታማኝነትን እንደ ማጣት እንጂ እንደ እንድ ተራ ቅጽበታዊ ስሕተት ለመቁጠር ያስቸግራል፡፡
በሩካቤ ጊዜ ባል ለሚስቱ ድንግልናውን ያስረክባል:: ምንም እንኳን በግዘፍ ልዩ ምልክት ባይኖረውም ረቂቅ የፍቅር ቋንቋ አለውና ይግባቡበታል።ሚስት ደግሞ በረቂቅም በግዘፍም ድንግልናዋን በከበረ ስጦታነት ለባሏ ታበረክታለች። በዚህ ጊዜ ለባሏ እንድትሰጥ እግዚአብሔር በሚስቱ ያቆየለትን አደራ ባል ሲቀበል (ድንግልናዋን ሲያገኝ) ሚስቱን በአደራ ጠባቂነት እንዲያያት፣ እንዲያምናት፣ እንዲያከብራትና እንዲወዳት ያደርገዋል:: ባልና ሚስት እንዲፈቃቀሩ፣ እንዲተማመኑና እንዲከባበሩ ድንግልናን ጠብቆ መገኘት ወሳኝ የሚሆነው ስለዚህ ነው።
ድንግልናን መጠበቅ ችሎታ ነው:: ምክንያቱም በውስጡ ጽናት፣ ብርታት፣ ትዕግሥት፣ ታማኝነት አለበትና፡ድንግልናን መጠበቅ ፍቅር፣ ባልን ማክበርን፣ ራስን ማክበርና የመሳሰሉት በውስጡ ይገኙበታል፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ወዳንቺ የመጣው"
ወዳንቺ የመጣው በብሩህ ደመና
ከሦስቱ አካል አንዱ ክርስቶስ ነውና
የጠፋ በግ አዳም ታደሰ በጌታ
በአንቺ ተፈጸመ የሰው ልጆች ደስታ

በደይን የተጣለች ሄዋን ተደሰተች
የደስታ መፍለቂያ አንቺን ስላገኘች
የበረከት ፍሬ ካንቺ ተገኘልን
የወይን ቦታ ነሽ ድንግል እናታችን
         
ወልድም ባህሪሽን ባህሪ አድርጎት
ለፍጥረታት ጌታ መዓዛሽ ተስማምቶት
ካንቺ ይወለድ ዘንድ ፍጹም ሊላላክሽ
በጥቂቱ አደገ ተልኮና ታዞሽ
         
ከድንግልና ጋር አንድ የሆነ ሐሊብ
በሩካቤ ሳይሆን በብስራት እንደ ንብ
ከሆድ መጥበብ ጋራ የመለኮት ስፋት
አንቺ ሆነሽ ሳለ ታናሿ ሙሽሪት
      
በፍጡር ሊና የማይመረመር
እፁብ ነው ድንቅ ነው የመጽነሷ ነገር
እሳት ወነበልባል በሆድሽ ውስጥ ሲያድር
ነደ ነበልባሉ አልፈጀሽም ነበር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መጋቢት ፳፱
በዓለ ወልድ (የጌታችን ጽንሰት)

መጋቢት ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የከበረ መልአክ ገብርኤል የምሥራች የነገረበት ድኅነትን የተመላች ታላቅ በዓል ናት በዚህም የከበረ ወንጌል ምስክር ሁኗል እንዲህ ሲል፦  ኤልሳቤጥ ከፀነሰች በኋላ በስድተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል የገሊላ ክፍል የሆነች ናዝሬት ወደምትባል አገር ከዳዊት ወገን ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ።

የድንግሊቱም ስም ማርያም ነው። መልአኩም ወደርሷ ገብቶ ደስተኛ የሆንሽ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አላት። እርስዋም አይታ ከንግግሩ የተነሣ ደንግጣ እንዴት እንዲህ ያለ ሰላምታ ይቀበሏል ብላ አሰበች።

መልአኩም እንዲህ አላት ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ እርሱ ታላቅ ነው የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል።

እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል ለያዕቆብ ወገንም ለዘላለም ነግሦ ይኖራል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም። 

ማርያምም መልአኩን ወንድ ሳላውቅ ይህ እንደምን ይሆናል አለችው።መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ያድርብሻል የልዑል ኃይልም ያጸናሻል ከአንቺ የሚወለደው ከሶስቱ አካል አንዱ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ይባላል።

እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ፀንሳለች ወንድልጅም አገኘች ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ማርያምም እነሆኝ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለችው።

ያን ጊዜም ድንግል ስትሆን ረቂቅ ፅንስን ተቀበለች የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል ወልድ ዋህድ ለኩነተ ሥጋ ወርዶአልና ይህም አንድ ባሕርይ አንድ ህልውና ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ የነበረ በማይመረመር ድንቅ በሆነ ተዋሕዶ እንዴትም እንደሆነ በማይታወቅ በቅድስት ድንግል ማርያም ማሕፀን አደረ ፅንስ ሆኖ ኖረ።

በዚያን ጊዜም የኋላ ኋላ መለየት ከቶ የሌለውን ፍጹም ሰውነት ነሥቶ ተዋሐደ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ ያለ መለያየት አንድ ሆኖአልና። ይቺም ዕለት የበዓላት ሁሉ በኵር ናት በእርሷም የዓለም ድኅነት ተጀምሮዋልና። ይሕች ቀን ለቤተ ክርስቲያን በእጅጉ ልዩ ናት:: በዓመቱ ከሚከበሩ በዓላትም አንደኛውን ሥፍራ ትይዛለች::

የዛሬዋ ዕለት በሚከተሉት ድርብርብ በዓላት ምክንያት "ርዕሰ በዓላት"(የበዓላት ራስ)፣ "በኩረ በዓላት" እየተባለች ትጠራለች:: ይኸውም:-
፩. አስቀድሞ ዓለም የተፈጠረችበት (መዝ ፻፩:፳፭)
፪. መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ያበሠረባት፣ (ሉቃ ፩:፴፩)
፫. ክብር ይግባትና እመቤታችን ድንግል ማርያም መድኅን ክርስቶስን የፀነሰችበት፣ (ሉቃ ፩:፴፩ ማቴ ፩:፳፫)
፬. በዕለተ ዓርብ በዕፀ መስቀል ነፍሱን በፈቃዱ ስለእኛ አሳልፎ ከሰጠ በኋላ በዕለተ እሑድ ከሙታን ተለይቶ የተነሣባት (መዝ ፻፲፯:፳፬፣ መዝ ፸፯:፷፭-፷፮፣ ዮሐ ፲፱:፩፣ ፩ኛ ቆሮ ፲፭:፳)
፭. ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ የሚመጣባት ቅድስት ዕለት ናት። (ራእ ፳፪:፲፪ ፣ መዝ ፵፱:፪ ፣ ማቴ ፳፬:፵፬)

አምላካችን ከዕለቷ ረድኤትና በረከት ይክፈለን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጌታ ሆይ አይሁድ ዓማፅያን ሰቀሉህ ወይ
የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ(፪)
የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመገደል
የሔዋን ስሕተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት (፪)
ንጹህ ክርስቶስ ሆንክ በደለኛ ብለህ ስለኛ
መስቀል አሸክመው አሥረው ገረፉህ እያዳፉህ (፪)
እጅና እግርህ በብረት ተመታ የዓለም ጌታ
የሾህ አክሊል ደፍተህ ጎንህም ተወጋ አልፋ ኦሜጋ (፪)
ግብዞች እንደ ራሳቸው መስሏቸው
ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጐዱ (፪)
በመስቀል ላይ ቃልን አሰምተህ ተጠማሁ ስትል
ሐሞት እና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው (፪)
ይቅር ባይ የሰዎችን በደል ሁሉን ሳታይ
አንተ ይቅር በለን በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ (፪)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ይስሐቅ ከሰይፍ ቤዛ የሆነህን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ያዕቆብ በበረሃ የታገለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮብ በደመና የታየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሙሴ ስለ እርሱ ‹እንደእኔ ያለ ነቢይ ይነሣል› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳዊት ‹‹እነሆ በኤፍራታ ሰማነው፣ በበረሃ ዛፍም አገኘነው›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤርሚያስ ‹‹የክቡሩን ዋጋ ሠላሳ ብር ተቀበሉ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡

ኢሳይያስ ‹‹ወልድ ሰው ለመሆን ተገለጠልን፣ ሕፃን ተወለደልን፣ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅኤል ‹‹አምላክ ወደ ተዘጋች ደጃፍ ገባ፣ ከተዘጋች በርም ወጣ›› ብለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳንኤል ነጭ ሐር ለብሶ ያየኸውን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤልያስ ከሞት በፊት የሰወረህ በእሳት ፈረሶች ያሳረገህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅያስ የፀሐይ መግባቱን ያሳየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ምናሴ ችንካሮችህን ከእግር ብረት የፈታ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮስያስ ፋሲካውን ያደረግህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል ከእሳት ምድጃ ያዳናች የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አብያና ሲላ ፌንቶስ ከመወለዱ አስቀድሞ ያመናችሁበት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ የቀድሞ አባቶች ነቢያት ሁላችሁ ከፋራን ተራራና ከቴማን ይመጣል ያላችሁት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ኑ፡፡ አሞፅ በአድማስ ቅጥር ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዘካርያስ በተራራዎች መካከል ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዕዝራ በአርፋድ በረሃ ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡

ስምዖን በክንድህ የታቀፍከውን ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዮሴፍ እንደ አንተ የተሸጠ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ጠራቢ ዮሴፍ በትከሻህ ያዘልከው በክንድህ የተሸከምከው ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ከሕፃንነትህ ጀምሮ በበረሃ ያለ እናት ያለ አባት ያሳደገህ መንገዱንም እንድትጠርግለት ያዘጋጀህና መለኮትን እንድታጠምቅ የመረጠህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡

ኢያቄምና ሐና ሆይ የልጃችሁን ልቅሶዋን የልቧንም መዘንጋት ታዩ ዘንድ ኑ፡፡ ከሔዋን እስከ ፋኑኤል ልጅ እስከ ሐና ያላችሁ ሁላችሁ ቅዱሳት ሴቶች የድንግልን ልቅሶዋን ታዩ ዘንድ ኑ፣ አንድ ልጇ ሙቷልና፡፡ የለመለመ የሥጋ ሞት ሕንፃ የተጀመረበት የአቤል ተከታዩ፣ ከጎኑ የፈሰሰው ደም ሔዋንን ከጥፋት ያዳናት የተገደለ መድኃኒታችን ነው፡፡ የናቡቴ ጓደኛው የተገፋው መድኃኒታችን ነው፡፡ አቤል ስለሚስቱ ሞተ፡፡ ናቡቴም ስለ ወይኑ ቦታ ሞተ፡፡ መድኃኒታችን ግን በቀኙ ያነጻት ዘንድ ስለቤተክርስቲያን ሞተ፡፡ ነፍሳችሁን ይወስዷታልና መውረዱንም አላወቁምና ስለ ወገኖቹ ኃጢአት እስከ ሞት ደረሰ ብሎ ስለ እርሱ የተናገረ አባቱን እንስማው፡፡ ሙሴም እርሱን ያውቁት ዘንድ አላሰቡትም፣ በሚመጣበት ቀንም አላወቁትም አለ፡፡ ዕዝራ በባሕር ጥልቅ ያለውን ማወቅ እንዳይችሉ ወልድንም ማወቅ እንዲሁ ሆነባቸው አለ፡፡ ጳውሎስም ብታውቁትስ ኖሮ የክብርን ጌታ እግዚአብሔርን ባልሰቀላችሁት ነበር አለ፡፡

በመሰደድ፣ ያለምንም በደልም በፍርድ አደባባይ በመቆም መከራ መስቀልን በመሸከም አብነት የሆናችሁ ሰማዕታት ሁላችሁ ኑ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት አስባችሁ በጋራ አልቅሱለት፡፡ ሁሉ የእርሱ ከእርሱ ለእርሱ ተፈጥሮ ሳለ በምድር ላይ ምንም ሳይኖረው ራሱን እንኳን የሚያስጠጋበት ቤት ሳይኖረው አብነት የሆናችሁ ባሕታውያንና መነኮሳት ሁላችሁ ኑ በዛሬዋ ዕለት ስለሞተው አምላካችሁ መሪር ዕንባን አልቅሱለት፡፡ ሕግ ጠብቆ፣ ሥርዓት አክብሮ፣ ነዳያንን በመመገብና ያዘኑትን በማጽናናት 33 ዓመት በምድር ላይ ኖሮ አብነት የሆናችሁ እናንት በዓለም ሆናችሁ ሕግ ጠብቃችሁ፣ አሥራት በኩራቱን አውጥታችሁ፣ ድሆችን በመርዳት የምትኖሩ ክርስቲያኖች ሁላችሁ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት ታስቡ ኑ፡፡

‹‹የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና›› ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደጻፈልን (1ኛ ጴጥ 2፡21) እርሱ ንጹሕ ባሕርይ ሲሆን ወደ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ወደ ዮርዳኖስ በመሄድ ለተጠመቅን ለእኛ ለተነሣሕያን ለሁላችን አብነት የሆነን መድኃኒታችን ስለእኛ ሞቷልና ሞቱን እናስብ ዘንድ ኑ በቤቱ ተሰብስበን እናልቅስለት፡፡ መታሰያውንም እናድርግለት፡፡ ጌታችን ሞቶ ተቀብሮ ካረገ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳን አባቶቻችን ለእነ አቡነ መባዓ ጽዮን፣ ለእነ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እንደነገራቸው የሞቱን መታሰቢያ የሚያደርግ ኃጠአተኛ እንኳ ቢሆን ሲኦልን አያያትም፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ ቢኖር ሲኦል ራሷ አፍ አውጥታ ‹‹ይህችን ነፍስ ወደኔ አታምጡብኝ›› ብላ ትጮሃለች እንጂ ችላ አትቀበለውም፡፡

የጌታችን ወዳጆቹ ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በድርብ በፍታና በመቶ ወቄት ሽቱ ገንዘው በሐዲስ መቃብር ሊቀብሩት ቢሉ ጌታችን ያን ጊዜ ዐይኑን ክፍቶ ‹‹በሰውነቴ መዋቲ ብሆን በመለኮቴ ሕያው ነኝ እንጂ ምነው እንደ እሩቅ ብእሲ ዝም ብላችሁ ትገንዙኛላችሁን?›› አላቸው፡፡ ይህን ጊዜም ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በታላቅ ድንዳጤ ሆነው ‹‹አቤቱ ጌታችን ሆይ! እንግዲያስ ምን እያልን እንገንዝህ?›› አሉት፡፡ መድኃኒታችንም እንዲህ እያላችሁ ገንዙኝ አላቸው፡- ‹‹ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ተሣሃለነ እግዚኦ› እያላችሁ ገንዛችሁ ቅበሩኝ አላቸው፡፡›› ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ለወዳጆቹ ለ12ቱ ሐዋርያት፣ ለ72ቱ አርድእት፣ ለ36ቱ ቅዱሳት አንስት ‹‹እስከ ሦስት ቀን እነሣላችኋለሁ እዘኑ አልቅሱ፣ እህል ውኃ አትቅመሱ በሏቸው›› ብሎ ለዮሴፍና ለኒቆዲሞስ አክፍሎት አስተማራቸው፡፡

ዳግመኛም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዕርገቱ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሞቱን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ነግሯቸዋልና፡፡ ሕማሙንና ሞቱንም እንዲዘክሩ አዟቸዋልና አሁንም ያንን ሁሉ የመድኃኔዓለምን ሞቱን ያላሰበና የሞቱን መታሰቢያ በዓል ያላከበረና እርሱንም የማይወደው ቢኖር ዕድል ፈንታው ጽዋ ተርታው ከአይሁድ ጋር ነው፡፡
የአምላካችንን የመድኃኔዓለምን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ ለመተባበር ያብቃን።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ድንግልናዬን መጠበቅ የሚኖርብኝ ለምንድር ነው?
ብዙ ሰዎች ድንግልናቸውን የሚጠብቁበት ምክንያት ይለያያል፡፡ የአንዳንዶቹ ምክንያት ከመንፈሳዊ ነገር ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም:: የሌለቹ ደግሞ መንፈሳዊ አካሄድ ቢመስልም ዋናውን መሠረት የለቀቀ ይሆናል:: እንደውም አንዳንዶች ሰይጣናዊ በሆነ መንገድ ለመጓዝ ሲሉ ድንግልናቸውን የሚጠብቁበት ጊዜ አለ፡፡ የምክንያቶቹ መለያየት ድንግልናን በጽናት ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አለው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የድንግልናን ዋጋ (ዐስበ ድንግልናን) የሚከፍለው እግዚአብሔር በመሆኑ ምክንያቱ ተገቢና መንፈሳዊ ካልሆነ እንኳን ዋጋ ልናገኝበት ይቅርና ቅጣትም ሊያስክትልብን ይችላል:: ሰዎች ድንግልናቸውን ከሚጠብቁባቸው ምክንያቶች መካከል ጥቂቶቹን ለመግለጽ ያህል ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡
ሀ. እንደ ብሔረሰቡ ልማድና ባሕል ይለያያል እንጂ ርእሰ ብሔር (ንጉሥ ወይም ንግሥት) ለመሆን ድንግል ሆኖ መኖር ግዴታ የሚሆንበት ብሔረሰብ አለ፡፡ በዚህ ዓይነት መንገድ ደናግላን ሆነው የሚኖሩ ሰዎች «ፓላስ ቨርጅንስ› ይባላሉ፡፡ ከዚህም አልፎ የቤተ መንግሥት ጠባቂዎችና ሠራተኞች የነገሥታት ሴቶች ልጆችን እንዳያባልጉ ሲባል ሕጽዋን (ጃንደረባ) ይደረጉ ነበር፡፡ ይህም ከቤተ መንግሥት እንብላ እንጠጣ በማለት ከሴት ሳይደርሱ ለመኖር ይህን ዓይነት ውሳኔ የሚወስኑ ሰዎች መኖራቸውን ያሳያል፡፡ ማቴ 19፥12 ትርጓሜ
ለ. በድሮ ጊዜ ብዙ የፍልስፍና ሰዎች ሩካቤ ጥበብን ይሠውራል (ዕውቀትን አይገልጽልንም) ብለው ያምኑ ነበር። ስለዚህ በተቻላቸው ሁሉ ድንግልናቸውን ጠብቀው ለመኖር የወሰኑ ብዙዎች ነበሩ:: ይህን የሚያስረዳ ታሪክ በፊልክስዩስ መጽሐፍ ይገኛል፡፡ ፈላስፎች ባሕታውያንን ሊፈትኗቸው ሄዱ« እናንተ ትጾማላቸው እኛም እንጾማለን። እናንተ ድንግልናችሁን እንደምትጠብቁት እኛም እንጠብቃለን ታዲያ እናንተ ከእኛ የምትበልጡት በምንድር ነው?» አሏቸው፡፡ ከባሕታዊያኑ መካከል አንዱ አረጋዊ ሲመልስ እንዲህ አለ:- «ንሕነሰ ነዓቅብ አልባቢነ» ማለትም «እኛ ከእናንተ የምንለየውና የምንበልጣችሁ ልባችንን ስለምንጠብቅ ነው» አላቸው፡፡ ዛሬም ቢሆን በልዩ መንፈሳዊ ያልሆነ አመለካከት፣ ከፍርሐት፣ በብዙ ሥራ ከመጠመድ የተነሣ በድንግልና የሚኖሩ አንዳንዶች አሉ፡፡ የመንፈሳዊያን ሰዎች ድንግልና አጠባበቅ ግን ከእነዚህ ዓይነት ሰዎች ድንግልና አጠባበቅ በዓላማም ሆነ በይዘት በእጅጉ ይለያል:: (ፊልክ. ክፍ.6 ተስ.78)
ሐ. ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች ድንግልናቸውን የሚጠብቁ ሰዎች በእርግጥ ድንግልናቸው ምን ያህል እውነት ይሆናል? የሚለው ጥያቄ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ሰይጣንም ራሱ ደግሞ በግልጽ "በድንግልና ሆናችው አገልግሉኝ" የሚልበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ለጣዖት አምልኮ የተለዩ ደናግላን «ፔስት ቨርጅንስ›› ይባላሉ::
ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ድንግልናን መጠበቅ ለሰዎቹ ምንም እንኳን እንደ ሐሳባቸው የፈለጉትን ያገኙ ቢመስላቸውም ድንግልናን መጠበቅ ከሚያስፈልግበት ትክክለኛ መንገድ በተቃራኒው መንገድ በመፈጸሙ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከፍተኛ ወቀሳና ቅጣት ያስከትላል፡፡ ምክንያቱም ይህን ፈታኝ ጉዳይ ሰይጣንን ደስ ለማሰኘት ብሎ ለመፈጸም መቻል በከፍተኛ ሁኔታ ለሰይጣን መገዛትን ስለሚያመለክት ነው::
መ. ዛሬ ዛሬ ደግሞ ሁሉም ነገር ወደ ገንዘብ እየተመነዘረ በመምጣቱ ድንግልናን ለረጅም ዓመታት በመጠበቅ ነጥብ ወይም «ሪከርድ» ለማስመዝገብ ውድድር ውስጥ መግባት ተጀምሯል፡፡ ይህን ለመሰለ ጉዞም ራሳቸውን የሚያዘጋጁ አያሌ ሴቶች አይጠፉም::
ሠ. ከላይ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች ውጭ በመንፈሳዊ ጐዳና በባል ዘንድ ተወዳጅ ለመሆንና ላለመነቀፍ ሲሉ ድንግልናቸውን የሚጠብቁ ብዙ ሴቶች አሉ:: ሌሎች ደግሞ ደናግል ባይሆኑ የሚቀርባቸው ክብረ ተክሊልና መንፈሳዊ የሠርግ ሥርዓት እየታያቸው ድንግልናቸውን ይጠብቃሉ:: በእነዚህ ምክንያቶች ድንግልናን መጠበቅ የሚያስነቅፍ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ድንግልናን ከምንጠብቅባቸው መንፈሳዊ ምክንያቶች ውስጥ በንዑስ ምክንያትነት የሚጠቀሱ በመሆናቸው ነው::
ድንግልናን መጠበቅ የሚያስፈልገው ሐሳብ ሳይከፈል በምናኔ ለመኖርና ፈጣሪን በሙሉ ኃይል ለማገልገል ብቻ አድርጎ ማሰብ ስሕተት ነው፡፡ በእርግጥ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረው ይህ ራሱ አንዱ ምክንያት ነው። 1ኛ ቆሮ 7፥32-35 ሆኖም ግን ሰፊና ጥልቅ ምክንያቶች ያሉትን ድንግልናዊ ኑሮ በዚህች ጠባብ ምክንያት ማጠር ግፍ ነው:: ምክንያቱም ከበቂ በላይ እውነተኛ አገልጋዮች በዓለም ላይ የሞሉ ቢሆን እንኳን ድንግልናዊ ኑሮ የተሻለ መንፈሳዊ የኑሮ ዘርፍ እንደ መሆኑ መጠን ሊቀር የሚገባው ነገር ባለመሆኑ ነው:: በተጨማሪም ዕድሜን ከጠገቡ በኋላ በሞት አፋፍ ላይ ሳሉ ) የሚመነኩሱ ሰዎች አሉ:: ይህም ምናኔ ወይም ምንኩስና ለአገልግሎት ብቻ ሲባል የሚደረግ ነገር ሳይሆን አንዱ መንፈሳዊ የኑሮ ዘርፍ መሆኑን ያሳያል፡፡
ረ. ድንግልና ሊጠበቅ የሚገባው እግዚአብሔርን ስለመፍራትና መታዘዝ ተብሎ ነው፡፡ ሌሎች ምክንያቶች መፍረሻ ምክንያት ስላላቸው ምክንያትነታቸው ሲቀር ድንግልና መጠበቅም አብሮ ሊቀር ይችላል፡፡ ስለዚህ መቼም ቢሆን መቅረት የሌለበት ነገር እግዚአብሔርን መፍራት ስለሆነ ድንግልናንም የምንጠብቅበት መሠረታዊ ምክንያት እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ሲባል መሆን አለበት:: እንዲህ ከሆነ ሰው ድንግልናውን እስከ ተፈለገው ጊዜ ድረስ ጠብቆ ለመኖር ይችላል::

በቀጣይ ምዕራፍ ስምንት ክፍል ዐራት:
👉
ድንግልናን የመጠበቅ ጥቅም በሚል ይቀጥላል....

ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ስምንት ክፍል ሦሥት

.................................................
ድንግልናን መሳል ኃጢአት ነው?
በድንግልና ለመኖር መሳል ኃጢአት አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ፈታኝና አስቸጋሪ ነገር በመሆኑ በፍጥነትና በችኮላ መደረግ የለበትም፡፡ ስለዚህ ነገር ጠቢቡ ሰሎሞን እንዲህ ብሏል፡፡ «እግዚአብሔር በሰማይ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፡፡ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኩል፡፡ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ይሁን።» መክ5፥2 ስእለት አለመሳል መብት ሲሆን የተሳሉትን መፈጸም ግን ግዴታ ነው። ስለዚህ «ተስለህ የማትፈጽም ከምትሆን ባትሳል ይሻላል›› መክ5፥5 የተሳሉትን አለመፈጸም ኃጢአት ነውና፡፡
በድንግልና ለመኖር መሳል ምን ያህል አስቸጋሪ መሆኑን አንጋፋ ደራሲ የተባሉት ሐዲስ ዓለምአየሁ «ፍቅር እስከ መቃብር›› በተሰኘ መጽሐፋቸው «በዛብህ» በተባለው ገጸ ባሕርይ ላይ እንዲታይ አድርገዋል፡፡ ስለዚህ በተለይ ወላጆች እነርሱ የማይኖሩትንና የማይቻላቸውን ኑሮ በልጆች ላይ መጫንና ልጆቻቸውን በድንግልና ኖረው ዘመናቸውን እንዲፈጽሙ ማስገደድ የለባቸውም፡፡ እስከ ጋብቻ ድረስ በድንግልና እንዲቆዩ ለማድረግ ግን ከመምከርና ከማስተማር አንሥቶ ተገቢ የሆነውን እርምጃ ሁሉ የመውሰድ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ስንመጣ ደግሞ አንዲት ሴት በድንግልና ለመኖር ብትሳል ወላጆቿም ሆኑ ባሏ ሰምተው ከተቃወሙ ስእለቷ ሊፈርስባት ይችል ነበር፡፡ በሰሙበት ዕለት ካልተቃወሟት ግን ስእለቷ: ይጸና ነበር፡፡ (ዘ2-30፥1-16)

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የመጽሐፍ ቅዱስ መተርጉማን አባቶች የዚህን ምሳሌያዊ ታሪክ ምስጢር ሲያስተምሩ የአገልጋዮቹ ጌታ የፍጡራን ጌታ የሆነ የእግዚአብሔር ምሳሌ እንደሆነ እንዲሁም ሦስቱ አገልጋዮች በተለያየ ደረጃ ያሉ ምዕመናንን እንደሚወክሉ ያስተምራሉ፡፡

ከዚህ የወንጌል ክፍል ምን እንማራለን?

ከተጠቀሰው ታሪክ የምንማራቸው ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ዓበይት የሆኑትን ሁለቱን እንመልከታቸው፡፡

ለእያንዳንዳችን ከእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ እንዳለ እንረዳበታለን

እግዚአብሔር እያንዳንዳችን በሃይማኖት ሆነን የምናፈራውን ፍሬ ይፈልጋል፡፡ ምንም እንኳን ከእኛ ፍሬን ቢፈልግም ያን ፍሬ ማፍራት የምንችልበትን ኃይል ግን የእግዚአብሔርን ልጅነት ካገኘንበት ከዕለተ ጥምቀት ጀምሮ እንደሚያስፈልገን መጠን እየሰጠን ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀበልናቸው ስጦታዎች በቁጥር እጅግ ብዙ ቢሆኑም በዓይነታቸው ግን ለሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው እያንዳንዱ ክርስቲያን ዳግመኛ በመወለድ ምስጢር ያገኘው የእግዚአብሔር ልጅነት ጸጋና ከልጅነት ጋር በተያያዘ የሚሰጡ ስጦታዎች ናቸው (ዮሐ.3፥3)። ሁለተኛው ዓይነት ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድና እንደ ሰውየው አቅም ለተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ማስፈፀሚያ ይሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔር የሚሰጡ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ትንቢት መናገር ፣ በተለያዩ ልሳናት መናገር ፣ አጋንንትን ማስወጣት … የመሳሰሉት ከዚህኛው ዓይነት ስጦታ የሚመደቡ ናቸው (1ኛ ቆሮ.12፥4)፡፡

በመጀመሪያውም ይሁን በሁለተኛው ዓይነት ስጦታ ተቀባዮች ዘንድ ግን ብዙ የሚያሳዝኑ ችግሮች አሉ፡፡ በዳግመኛ መወለድ ምሥጢር (በ40 ና 80 ቀን ጥምቀት) ስላገኘነው የልጅነት ጸጋ ጊዜ ሰጥቶ የሚያስብ ክርስቲያን ማግኘት በዚህ ዘመን በጣም አዳጋች ነው፡፡ በዓመት ውስጥ ክርስቲያንነቱ ለጥምቀት በዓልና ለመስቀል ደመራ ካልሆነ ትዝ የማይለው ቁጥሩ ቀላል አይደለም፡፡ ከዚህ የከፋው ደግሞ ከቤተ ዘመድ አንድ ሰው ምናልባትም ራሱም ሊሆን ይችላል ነፍሱ ከሥጋው ካልተለየች ወደ ቤተ ክርስቲያን ደጅ ብቅ አይልም፡፡

እግዚአብሔር ለእኛ የልጅነትን ጸጋ በመስጠቱ ለእኛ ያለውን ጥልቅ ፍቅሩን አሳይቶናል፡፡ ምክንያቱም ልጅነታችን ዋጋ ተከፍሎበታልና፡፡ እንዲሁ በቀላሉ አይደለም ልጆች የተባልነው፡፡ እኛ ልጅነትን እንድንቀበል አምላክ መከራን ተቀብሏል፡፡ የጥምቀታችን ውሃ የፈሰሰው በጦር ከተወጋው ከጌታ ጎን ነው (ዮሐ.19፥24)፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ይሄንን ሁሉ ሲያመለክት ”የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደሰጠን እዩ፡፡” (1ኛ ዮሐ.3-1) እኛ ልጆቹ እንሆን ዘንድ እግዚአብሔር ካሳየን የአባትነት ፍቅር በተጨማሪ ልጆቹ ስለመሆናችን የገባልንም ተስፋ ከአዕምሮ በላይ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ምዕመናን በላከው መልእክቱ ”እንኪያስ እናንተ ልጆች ናችሁ እንጂ ባሮች አይደላችሁም፡፡ ልጆች ከሆናችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሾች ናችሁ፡፡” (ገላ.4:7) በማለት  ስለሚጠብቀን ተስፋ ነግሮናል፡፡

ስለዚህ በጣም ልንጠነቀቅበት የሚገባን የመጀመሪያው መክሊታችን ልጅነታችን መሆኑን መረዳት ያስፈልገናል፡፡ በዚህም መክሊት እንድንሰራ የታዘዝናቸውን ምግባራት እንድናፈራ የሚጠበቅብንን ፍሬዎች ማፍራት አለብን፡፡ ያለበለዚያ መክሊቱን እንደቀበረው ሰው መሆናችን ነው፡፡

እያንዳንዱ ስጦታ እንደሚያስጠይቅ እንረዳለን

እግዚአብሔር ያለ አንድ አላማ ለሰዎች ሓላፊነትን የሚያሰከትል ስጦታ አልሰጠም አይሰጥምም፡፡ ማንም ከእግዚአብሔር የተቀበለ ሰው የተሰጠው ስጦታ ለሆነ አላማ ነውና ጥያቄ አለበት፡፡ ጠያቂው ደግሞ የስጦታው ባለቤት ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ ማንም ይሁን ማን ግን ስለተሰጠው መክሊት ባለቤቱ ከፊቱ አቁሞ እንደሚጠይቀው መዘንጋት የለበትም፡፡እንግዲህ በአጠቃላይ መክሊት የተባለ ጸጋ ስጦታ ሲሆን እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የተለያየ ስጦታ ሰጥቶናል፡፡ በተሰጠንም ስጦታ ልናገለግልበት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪ መክሊት ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡ የሰማናትን ቃለ እግዚአብሔር ለሌላው ማሰማት ይገባናል ፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው ማሰማቱ ብቻ ነው፡፡ በልቦናው አድሮ ሥራ የሚሠራ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነውና፡፡ በመሆኑም እርሱ በሰጠን የአገልግሎት በር ጸጋ በታማኝነት በማገልገል በሕይወት ዘመናችን ሁሉ መንፈሳዊውን ሀብት የምናተርፍ እንሆን ዘንድ የተላለፈልን አምላካዊ ምክር ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ የተጠራነው ፍሬ ልናፈራና ሌላውንም ልናተርፍ መልካም ሥራን ልንሠራ እንጂ የሥጋችንን ፈቃድ በመከተል የኃጢአት ባሮች ልንሆን አይደለም፡፡ መጽሐፍ እንደሚነግረን  ¨ሁሉ እንደተጠራ እንዲሁ ይኑር” (፩ኛ ቆሮ. ፯፥፳) ይላልና።

አሁን ባለንበት ወቅት በጎና ታማኝ አገልጋይ መሆን እንዳንችል ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ የችግሮቹም መሠረታዊ ምንጭ በተጠሩበት ጸንቶ መቆም ፈጽሞ አለመቻልና ለሥጋዊ ጥቅም ብቻ በማድላት ሓላፊነትን መዘንጋት ናቸው፡፡ በሥጋዊ አምሮት ፍላጎትና ምርጫ ውስጥ ደግሞ መንፈሳዊ ጸጋንና በረከትን ለማግኘት የሚያስችለንን የታማኝነት ሥራን መሥራት አይቻልምና በታማኝነት ከምናድነው ሰው ይልቅ መክሊታችንን በመቅበር ባለመታመን መሰናክል የምንሆንበት ሰው ሊበዛ እንደሚችል አያጠራጥርም፡፡ በመሆኑም ከእርሱ ዘንድ እንደ ዓቅማችን የተሰጠንን መንፈሳዊ ዕውቀት ሀብትና አገልግሎት ለሌላው በማድረስ መክሊታችንን ልናበዛ የምንችለውና አገልግሎታችን ወይም ክርስትናችን ውጤታማ የሚሆነው ምርጫችንን አውቀን እንደቃሉ ሆነንና ጸንተን ስንገኝ ብቻ ነው፡፡ ይህ ባለመሆኑ ነው ዛሬ ብዙዎቻችን በሕይወታችን ሌላውን ማትረፍ አቅቶን በእግዚአብሔርና በሰውም ዘንድ በሚያስወቅስ የስንፍና መንገድ ላይ ቆመን የምንገኘው፡፡ ስለዚህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው “ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ” (ማቴ. ፳፬፥፵፪) ብሎናል፡፡

ቃሉን የሰማንና የምናውቅ ሁላችን በሞቱ ላዳነን፣ በልጅነት ጸጋም ላከበረን፣ በትንሣኤውም ላረጋጋን፣ በመስቀሉ ጥልን ገድሎ ከራሱ ጋር ላስታረቀን፣ በውኂዘ ደሙም ሕይወትን፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ በረከትንና ዘለዓለማዊ ደስታን ለሰጠን አምላካችን በመታዘዝ አቅማችን በሚፈቅደው አገልግሎት ጸንቶ መገኘት ተገቢ ነው፡፡ በአገልግሎት የመጽናት ምልክቱ ደግሞ አትራፊነት ነው፡፡ ቅዱሳን ነቢያት፣ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ቅዱሳን ሊቃውንት በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ በአትራፊነት ይታወቃሉ፡፡ ለማትረፍ ግን ራሳቸውን ለእውነት ለአገልግሎት ለመከራ አሳልፈው በመስጠት ነው፤ በትንሹ መታመን ሲባል የእኛ አገልግሎት ከፈጣሪ ቸርነት ጋር ስለማይመጣጠን ነው፤ በብዙ እሾምሃለሁ ማለቱም በመንግሥተ ሰማያት ለዘለዓለም ከብሮ መኖርን ነው፡፡

ከቅዱሳን ነቢያትም ሐዋርያትም ሰብአ አርድእትም ሊቃውንትም የሰማነውና ያየነው እውነት ምንጊዜም ትጉህ ሠራተኛ የሚሠራው መልካም ሥራ ሁሉ ለቤተ ክርስቲያንም ለሀገርም የሚሰጠው ጥቅም እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ዘመን ልዑል እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን፤ ምእመናንን፤ ሀገርንና ሕዝብን ለመምራት የጠራንና የመረጠን፤ በአገልግሎት ዐደባባይ ያስቀመጠን ሰዎች እጅግ ዕድለኞች ነን፤ ምክንያቱም የሕዝብን ችግርና አቤቱታ ሰምቶ ተቀብሎ መፍትሔ መስጠት ትርፋማነት ነውና፤ ትርፋማነት ደግሞ ወደ ትልቁ የሹመት መሰላል መውጣት ነው፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ አገልግሎታችን ተደናቅፎ የሕዝባችን ችግር ሳይፈታ ቀርቶ የአገልግሎታችን ተቆጣጣሪ አምላካችን ቢጎበኘን “አንተ ሰነፍ አገልጋይ”

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

  ድንግል ነኝን? የሚለው ጥያቄ ብዙ ጊዜ የሚፈጠረው ሰይጣን ሲተናኮል ነው፡፡ ምክንያቱም ሁለት ልብ ያለው መወሰን ስለማይችል በመባክን መሥራት ያለብንን ሳንሠራ እንድንቀር ዳግመኛም ደናግል እንደሆንን ቢነገረን ከባድ ኃጢአት እንዳልሠራን ቆጥረን እንድንጽናናና እንድንዘናጋ ለማድረግ ሲሆን በመጨረሻም ድንግል እንደማንባል ቢነገረን ደግሞ ከአሁን በኋላ ለምኔ እጠነቀቃለው? በማሰኘት ተስፋ እንድንቆርጥ አድርጐ ወደ ዝሙት እንድንሄድ ለመገፋፋት ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ምሕዋረ ሰይጣን ተገንዝቦ ካለፈ መጥፎ ተግባር መሸሽ ብቻ የሚበጅ ይሆናል::
  ከዚህም በተጨማሪ ከላይ የተጠቀሰው ዓይነት ጥያቄ የሚፈጠረው ፍቅረ እግዚአብሔር ሲጐድልብንና ራስ ወዳድ ስንሆን ነው:: ምክንያቱም ግብረ ሰዶምን የመሰለ ብዙ ኅብረ ዝሙት እየፈጸምን ያሳሰበን በደልነቱ ሳይሆን የድንግልናችን መጥፋትና አለመጥፋት በመሆኑ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ «የቤተ ፈት» አስተሳሰብ ይባላል፡፡ «ቤተ ፈት» የምትባለው ባል አግብታ እየኖረች ከጊዜ በኋላ ባሏን ፈትታ የኮበለለች ሴት ናት፡፡ ከሄደችበትም ችግር ሲያጋጥማት የሚታያት ባሏን መበደሏ ሳይሆን ከባሏ ጋር በመትኖርበት ጊዜ የነበራት ምቾትና ክብር ነው፡፡
  አባታችን አዳምን ግን የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም፡፡ ማለትም ኃጢአት ሠርቶ ከገነት በተባረረ ጊዜ ፈጣሪዬን አስቀየምኩት እያለ ስለ በደሉ ያለቅሰ ነበር እንጂ የገነት ተድላ ደስታ ቀረብኝ እያለ ስላጣው ነገር አያዝንም ነበር:: «አልቦቱ ካልዕ ሕሊና ለአዳም ዘእንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢአቱ - ስለ ኃጢአቱ ከማልቀስ በቀር ለአዳም ሌላ ሐሳብ አልነበረወም» የተባለው ስለዚህ ነው፡፡ (መቅድመ ወንጌል)
  እንደዚሁም ሁሉ ሰው በልዩ ልዩ ኃጢአት በተሰነካከለ ጊዜ «ድንግል ነኝን?» እያለ ያጣውንና ያገኘውን እያሰበ ከመተከዝ «አንተን ብቻ በደልሁ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ» በማለት ኃጢአቱን እያሰበ ቢያለቅስ በንስሐ አዳምን መስሎታልና የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም ይባላል:: መዝ50 ፥ 4
  በመጨረሻም ድንግል ነኝን? የጋብቻዬስ አፈጻጸም ምን ይመስላል? ማለትም በተክሊል ማግባት እችላለሁ? ወይስ አልችልም? እያሉ በማሰላሰል ከመጨነቅ ባለፈው ክፉ ሥራ በመጸጸት ለወደፊቱ ደግሞ በመጠንቀቅና በመጠበቅ ከመምህረ ንስሐ ጋርም ውይይት በማድረግ በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን በመመራት ልቡናን በአንድ ሐሳብ ማጽናት ይገባል፡፡

በቀጣይ ምዕራፍ ስምንት ክፍል ሦስት:
👉ድንግልናን መሳል ኃጢአት ነው?
👉«ድንግል ነኝ» ብዬ እጮኛዬን ዋሸሁት ምን ይሻለኛል?
👉ድንግልዬን መጠበቅ የሚኖርብኝ ስለ ምንድር ነው?
በሚል ይቀጥላል....

ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መታጨት፣ ማጨትና ማግባት በድንግልና ሊደረጉ ይገባል!
  እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ሕግና ሥርዓት ማንኛውም ሰው ድንግልናውን ጠብቆ ማጨት፣ ካጨም በኋላ ድንግልናውን ጠብቆ እስከ ጋብቻው መቆየትና ማግባት ይኖርበታል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሱስ ክርስቶስን በሙሽራ ቤተ ክርስቲያንን ደግሞ በሙሽሪት መስሎ በተናገረበት አንቀጽ «እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ላንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና» በማለት በወርቁ የክርስቶስ ሙሽራ የምትባል ቤተ ክርስቲያን በቅድስና የተዋበች መሆኗን አመልክቶ በሰሙ ደግሞ መተጫጨት መደረግ ያለበት ንጽሕናን ጠብቀው በድንግልና እየኖሩ መሆኑን ተናግሯል። 2ቆሮ 11÷2 ሊቀ ነቢያት ሙሴ በኦሪት «ማንኛውም ሰው ድንግልና ያላትን ልጃገረድ ቢያጭ» በማለት የተናገረው ቃል በድንግልና ሆኖ ማጨትና መታጨት አንደሚገባ ለማስረዳት ተጨማሪ መረጃ ይሆናል፡፡
«ከተጫጨን ወዲህ መጋባታችን አይቀር ታዲያ የፈለገነውን ብናደርግ ምን አለበት?» በማለት ወደ ሩካቤ ማምራት አይቻልም። ሳይጋቡ የሚደረግ ሩካቤ ነውረኛ ያሰኛልና።2ሳሙ 13፥12-1 በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ የታጨችን ሴት «ልጃገረድ» እያለ ደጋግሞ መጥራቱ ያልተጋቡ ሰዎች ምንም ቢተጫጩ ሩካቤ መፈጸም የማይገባቸው መሆኑን ያስረዳል።
የተጫጩ ወንድና ሴት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጋብቻ ሳይፈጸምላቸው <ካህኑ ፈቅደውልን ነው፣ ተማምለን ቃል ተገባብተናል፣ ልንጋባ የቀረን ጥቂት ቀን ወይም ትንሽ ነገር ብቻ >የሚሉና ተቀባይነት የሌላቸው ሌሎችንም ምክንያቶች በመደርደር ሩካቤ ማድረግ አይገባቸውም። የማይገባቸውም ላይጋቡ ሊቀሩ ይችላሉ ከሚል ስጋት ብቻ ሳይሆን ቢጋቡም እንኳን ከመጋባታቸው በፊት በእጮኝነታቸው ወራት የፈጸሙት ሩካቤ ሕጋዊ ባለመሆኑ ዝሙት ሆኖ ስለሚቆጠር ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው አንድ እስራኤላዊ ሚስት አግብቶ ድንግልና ባያገኝባት ሚስቱን መክሰስ ይችል ነበር፡፡ መንፈሳዊ ሕጉ እንደሚያዝዘውም በልዩ ልዩ መንገድ የሴቲቱ ክስ ይጠናና ክሷ ሐሰት ሆኖ ከተገኘ ከሳሽ ባሏ በእስራኤል ድንግል ላይ ክፉ ስም አምጥቷልና «መቶ የብር ሰቅል» ከተቀጣ በኋላ የከተማዋ ሽማግሌዎች ገርፈውት ዕድሜ ልኩን እንዳይፈታት ሥርዓት ያደርጉበት ነበር።ዘዳ 22፥13-19 ክሱ እውነት ሆኖ ቢገኝና ‹‹በብላቴናይቱም ድንግልናዋ ባይገኝ በአባቷ ቤት አመንዘራለችና በድንጋይ ተወግራ ትገደል ነበር፡፡»ዘዳ 22÷20-24 ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ የድንግልናን ክብር ከማስረዳቱም በላይ ማንኛውም ሰው ወደ ትዳር መግባት ያለበት ድንግልናውን እንደጠበቀ መሆን እንዳለበት ያስተምራል
ሐዋርያው "ድንግሊቱም ብታገባ ኃጢአት አትሠራም(አይሆንባትም)" ይላል። 1ቆሮ 7፥28 ለወንዱ ደግሞ «ዳሩ ግን ማግባት ወደሚገባው ዕድሜ በደረሰ ጊዜ ስለ ድንግልናው ያፈረ ሰው ቢኖር የወደደውን ያድርግ (ማለት ከፈለገ ያግባ ካልፈለገ ደግሞ አያግባ)፣ ቢያገባም ኃጢአት የለበትም»1ቆሮ 7፥36 በማለት ድንግልናን ጠብቆ መኖር የሚያስፈልገው የግድ ለመመንኮስ ብቻ ሳይሆን ዘግይተው ማግባትም እንደሚችሉ ኃጢአትም እንደማይሆንባቸው ይገልጻል።
የድንግልና ሕይወት የንጽሕና፣ የቅድስናና የታማኝነት ምሣሌ ሆኖ በጽኑ ቃል ኪዳን መገኘትን የሚያመለክት በመሆኑ ልዩ ክብር አለው። በተለይም ከክብረ ክህነት ጋር በተያያዘ መልኩ አንድ ካህን ለክብረ ክህነቱ ሲባል ድንግሊቱን እንጂ ጋለሞታይቱን (ፈት የሆነችውን) እንዳያገባ በሕግ ተከልክሏል። ሕጉም እንዲህ ይላል «በራሱም ላይ የቅባት ዘይት የፈሰሰበት፥ የክህነትም ልብስ ይለብስ ዘንድ የተቀደሰ ከወንድሞቹ የበለጠው ካህን ራሱን አይግለጥ ልብሱንም አይቅደድ። እርሱም ሚስትን በድንግልናዋ ያግባ: ባሏ የሞተባትን፣ ወይም የተፋታችውን፣

ወይም ጋለሞታይቱን አያግባ። ነገር ግን ከሕዝቡ ድንግሊቱን ያግባ። እኔም የምቀድሰው እግዚአብሔር ነኝና በሕዝቡ መካከል ዘሩን አያጎስቁል» ዘሌ 21፥11-14 ድንግልናን ከጣሉ በኋላ ማግባት ዘርን ማጎስቆል መሆኑን ተረዳህን? ስለዚህ ክብርህን ጠብቅ ከዚያ በኋላ ክብሯን የጠበቀች ሴት ፈልግና አግባ።
በተለይ ለካህን ስለ ክብረ ክህነት ሲባል ሕጉ ይጥበቅ እንጂ ማንኛውም ሰው ቢሆን ማግባት የሚኖርበት ራሱ ድንግልናውን ጠብቆ ከኖረ በኋላ እንደ እርሱ ድንግልናዋን ጠብቃ የኖረችውን ሴት ነው። በዝሙት ሲዘሉ ከኖሩ በኋላ ከማግባት ድንግልናን ጠብቀው ከቆዩ በኋላ ማግባት ለሕሊና፣ ለጤና፣ ለተሳካና መልካም ትዳር እዲሁም ለመንፈሳዊ ሕይወት ምቹና የተሻለ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከላይ ለተጠቀሱት ሐሳቦች ሁሉ መቋጫ የሚሆነውን ቃል «ድንግልን ያገባ መልካም አደረገ›› 1ቆሮ. 7፥38 በማለት ፈት (ድንግልን ያልሆነችን) ሴት ከማግባት ድንግልና ያላትን ሴት ማግባት ብልጫ እንዳለው አስረድቷል፡፡
ከጋብቻ በፊት ድንግልናን መጣል የበለጠ «ሴሰኛ» ያደርጋል!
ሀ. «ያላዩት አገር አይናፍቅም» እንደሚባለው ዝሙትን የማያውቁ ሰዎች ዝሙትን እንደቀመሱት አይሆኑም። ምክንያቱም ስለማያውቁት ነው። አንድ ጊዜ ድቀት ካገኛቸው በኋላ ግን የያዘውን እንደተቀማ አንበሳ መሬት አይበቃቸውም። ለምን ቢባል ጣዕመ ዝሙትን ቀምሰዋልና ስለዚህ ነው።
ለ. ያላገቡ ሰዎች ስለወደፊት ትዳራቸው በማሰብ ድንግልናቸው ይጠብቃሉ። አንዳንዶቹ ባሌ ድንግል ሆኜ ቢያገኘኝ ይደሰታል ብለው ስለሚያምኑ ይሆናል። ሌሎቹ ደግሞ ለራሳቸውም ክብረ ተክሊል እንዳይቀርባቸው በመስጋት ይሆናል። «ላለሁበት ማዕረግና የሕይወት ጐዳና ተስማሚ አይደለም፤ ስሜን ያጐድፋል» በማለት ራሳቸውን ከዝሙት የሚቆጥቡ ሰዎችም በርካታ ናቸው። ሌሎች ደግሞ በባህል ተፅዕኖ በድንግልና ተጠብቀው ይኖራሉ፡፡ ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን ድንግልናን መጠበቁ ጠቃሚ ነው። ነገር ግን እንደዚህ ዓይነት ሰዎች በአንድ ቀን ስሕተት ድንግልናቸውን ሲያጡ ከዚያ በኋላ «ራስን መጠበቅም ሆነ አለመጠበቅ ልዩነት የለውም›› በማለት ከመጠንቀቅ ይቦዝናሉ። እኅቴ ሆይ! አንድ ጊዜ መሳሳት ብቻ ተስፋ በማስቆረጥ የሚፈጥረውን ቸልተኝነት አየሽን? አንቺ ግን እኅቴ ሆይ እንደዚህ አይነት ቸልተኝነት ወደ ልብሽ እንዲገባ አትፍቀጅለት፡፡
ሐ. "ከዚህ ቀደም የምጠነቀቀው ስለድንግልናዬ ብዬ ነበረ ድንግልናዬን ካጣሁ በኋላ ስለምን እጠነቀቃለሁ?" የሚለውን የሕሊና ፈተና በድል መወጣት አቅቷቸው ብዙዎች ተስፋ በመቁረጥ በዝሙት ጐርፍ ተጥለቅልቀዋል። ምንም እንኳን አንድ ጊዜ ቢሳሳቱ ተስፋ ባለመቁረጥ ለወደፊቱ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ክብረ ድንግልና ከተወሰደ በኋላ የሚደረግ ዝሙት እንደ ዝሙት አይቆጠርም የሚል ሕግ የለምና።
ለመጀመሪያ ጊዜ በሚፈጸም ዝሙት ማኅተመ ድንግልና እንደሚወገድ ሁሉ ከዚያ በኋላ በሚደረግ የተደጋጋመ ዝሙትም የሚወገድ ሌላ ሥጋዊ ድንግልና ባይኖርም በፈጸምነው ዝሙት ብዛት የምናጣው ክብረ ነፍስ ግን አለ። ድንጋሌ ሥጋ ለክብረ ነፍስ አምሳል ነው። ድንጋሌ ሥጋ አንድ ሲሆን ክብረ ነፍስ ግን እጅግ በጣም ብዙ ነው። የነፍስ ድንግልናዋ በብዙ ጐዳና ነው። ስለዚህ በምንፈጽመው የዝሙት ቁጥር ብዛት ነፍሳችን የምታጣው ጸጋና ክብርም እንዲሁ ይበዛል እንጂ ከድንግልና መወገድ በኋላ የሚፈጸሙ ዝሙቶች በጥቅሉ እንደ አንድ ጊዜ ስሕተት አይቆጠሩም፡፡ በየጊዜው የሚፈጸሙት የዝሙት ተግባራት የሚያስከትሉት ጉዳትና ክብር ማጣት ድንግልናችንን ለማጣት ካበቃን የመጀመሪያ ጊዜ ዝሙት ጋር እኩል ነው።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ስምንት
ክፍል ሁለት
...............................................
እስከ ጋብቻ ጊዜ ድረስ መደንገል
  በሀገራችን በኢትዮጵያ የድንግልና ሕይወት ከጥንት አባቶቻችን ጀምሮ የተከበረና በማንኛውም ሰው ዘንድ ዋጋ ያለው ነገር ነበር። ይኸውም ይታወቅ ዘንድ የድሮ ሰዎች ልዩ ልዩ ዘዴና ጥናት አድረገውለት ሲሠሩበት ቆይተዋል:: ማለትም አንድ ሰው ዕድሜው ወይም ችሎታውና ስሜቱ የኑሮ ደረጃውም ማግባት እስከሚፈቅድለት ድረስ በድንግልና መኖር ግዴታው ነበር። ስለዚህ ሴቷና ወንዱ እንዳይተያዩ፣ እንዳይገናኙና እርስ በእርሳቸው ስሕተት እንዳይሠሩ በማለት በልዩ ልዩ ዘዴ ይጠበቁ ነበር፡፡
   በሀገራችን የ«ታላላቅ» ሰዎች ልጆች የተባሉት ሴቶች የሆኑ እንደሆነ በሞግዚቶችና በወላጆች እየተጠበቁ በክብር በማዕርግ ያድጉ እንደ ነበር ወንዶች የሆኑ እንደሆነ ደግሞ እንደ ገዳም እንደ አምባ ያለ ከሰው የተለየ ቦታ ተሰጥቷቸው በንጽሕናና በድንግልና የያድጉ እንደነበር ታሪክ በሰፊው ያስረዳናል።
   በ«ዝቅተኛውም» ማኅበረ ሰብእ ቢሆን እንደ ዛሬ ጊዜ ሳይዘገዩ በፍጥነት ስለሚጋቡ እስከዚያው ድረስ ግን ድንግልናን ጠብቆ ለመቆየት የተቻላቸውን ሁሉ ሳያደርጉ አይቀሩም ነበር፡፡ ዛሬ ዛሬ ደግሞ እጅግ በዛ እንጂ በሁሉም ረገድ እስኪደረጁ ድረስ ሳያገቡ መዘግየቱ መልካም ሆኖ ሳለ ስለ ንጽሕናቸው አጠባበቅ ደግሞ ምንም የተወሰደ እርምጃ ስለ ሌለ የድንግልና ሕይወት እየቀለለና ዋጋ እያጣ መጥቷል::

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ደብረ ዘይት
የዐብይ ጾም አምስተኛ እሑድ(ሳምንት)

(የዐብይ ጾም እኩሌታ)
ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ነው፡፡ቦታው ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኝ የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ሲሆን ስሙም ከወይራ ዛፉ:- ደብረ ዘይት (የወይራ ዛፍ ተራራ) በመሰኘት ተገኝቷል። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ዘይት በዓል ሆኖ የሚከበርበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረዘይት ተራራ ላይ ሳለ ለቅዱሳን ደቀመዛሙርቱ ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ስለ ዳግም ምጽአቱ ስላስተማራቸዉ በጌታችን ትምህርት መሠረት ነገረ ምጽአቱን እንድናስታውስ ወይም እያሰብን እንድንዘጋጅ ለማድረግ ነው።

ስለ ዓለም መጨረሻና ስለ ዳግም ምጽአቱ ምልክቶች ምን እንደሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ላይ በሦስት መሠረታዊ ክፍሎች ከፍሎ ጽፎልናል፡፡

፩. ሃይማኖታዊ ምልክቶች

"እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ" /ማቴ 24፥5/፡፡

፪. ፖለቲካዊ ምልክቶች

“ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ” /ማቴ 24፥6/ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና” /ማቴ 24፥7/

፫. ተፈጥሯዊ ምልክቶች

“ረሐብም ቸነፈርም የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል” /ማቴ.24፥7/

ከላይ ያየናቸውን ምልክቶች በዓለማችን ላይ ዕለት ዕለት የምናየው የምንሰማው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የነገራቸውን ምልክቶች የቤተ ክርስቲያናችን አራት ዐይና ሊቃውንት የወንጌሉን ገጸ ንባብ እንዲህ ብለው ያመሰጥሩታል፡፡

“እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያዎች ናቸው” /ማቴ.24፥8/

ምጥ ሲመጣ አስቀድሞ የምጡ መጀመሪያ ሕመም (ጣር) እንዳለ ሁሉ የዓለምም ፍጻሜ በጣር ነው የሚጀምረው። ይህንንም ጌታችን በግልጽ አስረድቶናል፦ ጦርና የጦር ወሬ መሰማት፣ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ መነሳት፣ ርሃብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ መታየት ለዓለም ፍጻሜ የምጥ ጣር መጀመሪያዎች ናቸዉ። እነዚህ ነገሮች በሁሉም ቦታ በአንድ ጊዜ ላይከሰቱ ይችላሉ፤ ነገር ግን በልዩ ልዩ ቦታዎች ለብዙ ዘመናት ታይተዋል፤ እየታዩም ናቸው።

“ስለ ስሜ በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ” /ማቴ.24፥9/

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ስለ ስሜ ክርስቲያኖች በመሆናችሁ በዓለም ዘንድ ትጠላላችሁ" ብሎናል። ዓለም ክፉ ስለሚሠራ የጥሩ ነገር ተቃራኒ ሆኖ ለብዙ ዘመናት ቆይቷል። ጌታችን “ብርሃንም ወደ ዓለም ስለመጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፣ሥራዉም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል” /ዮሐ. 3፥19-21/ እንዳለን በክፉ ሥራ ውስጥ ያለው ይህ ዓለም በጎ ሥራ የሚሠሩትን የክርስቶስን ተከታዮች ይጠላል። ጨለማ ብርሃንን ብርሃንም ጨለማን እንደሚጠላ፤ ይህ ዓለም እኛን እንዲጠላን፣ እኛ ክርስቲያኖች ደግሞ ይህንን ዓለም ልንጠላው ይገባል።
አሁን ባለንበት ዘመን ክርስትና እየተጠላ፣ እየተናቀ ነው ያለው። “ባደጉት” ዓለማት ባዶ አብያተ መቅደሶች ቀርተው እነሆ እንመለከታቸዋለን፤ ትውልዱ በዓለም ስሜትና በሥጋ ፈቃድ ብቻ እየሔደ ነው። ክርስቲያን ነን በሚሉትም አውሮፓውያን ዘንድ የአንገት በላይ የማስመሰል ክርስትና እንጂ እንደ ቅዱስ ቃሉ የሚጓዝ አማኝ ማግኘት አይቻልም። እውነተኞች አይወደዱም፤ ይገፋሉ፤ ይናቃሉ። ሁኔታው የዘመኑ ፍጻሜ እጅግ እየቀረበ መምጣቱን በእርግጥ ያስረዳል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህም በላይ “ስለ ስሜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችሁማል” ብሏል። ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ማንንም ሳይበድሉ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ በልዩ ልዩ ሀገራት ክርስቲያኖች ሰማዕትነትን እስከ አሁን ድረስ እየተቀበሉ ነው፡፡ቅዱስ ጳዉሎስ  “ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን” /ሮሜ 8፥36/ እንዳለው። ይህ በቅዱሱ በክርስቶስ ስም መጠላትና መከራ መቀበል ከዓለም የሚጠበቅ የፍጻሜዉ ዘመን ምልክት መሆኑን አውቀን መዘጋጀትና ከሐዋርያው ጋር “በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን” /ሮሜ 8፥37/ እያልን በእምነታችን ጸንተን መጋደል ይገባናል።

የክርስቲያኖች ቁጥር እያነሰ መምጣት፣ የአብያተ ክርስቲያናት መዘጋት፣ ሰው ሰው የሚያሰኘውን ክብርና ሞገስ ትቶ በግብሩ እንስሳትን ሲመስል የቅድስና ሕይወት ሲጠላና ሲናቅ፤ በአንጻሩ ደግሞ የሰው ልጅ ለረከሰው ለዚህ ዓለም ምኞትና ፈቃድ ሲገዛ ስናይ የዚህ ዓለም ፍጻሜ ጊዜው እየደረሰ መሆኑን አውቀን፤ ኖኅ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ቢኖርም ራሱን በቅድስና ጠብቆ እንደኖረ /ዘፍ.6-8/፤ ሎጥም እንዲሁ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ሲኖር በነርሱ ኃጢአት እንዳልተባበረ /ዘፍ. 19/ ከዚህ ዓለም ክፉ ሥራ ተለይተን ራሳችንን በቅድስና በመጠበቅ እንጋደል። ዓለሙ ስለ እምነታችን ቢጠላንም እኛም ስለ ክፉ ሥራው ንቀነው መኖር የግድ መሆኑን እንወቅ እንጂ ስለ እምነት፣ ስለ ቅድስናም ከዓለም በጎ ነገር አንጠብቅ። በተለያዩ ሁኔታዎች የሚደርሱብንን ፈተናዎች ሁሉ በትዕግስት እንቀበላቸው እንጂ በማማረር አንዘን፤ ምክንያቱም ስለ ስሜ በዓለም ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ተብለናልና።

“የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል!” ማቴ.24፥15/

ዓለም ራሱን በማርከስ ብቻ ሳይወሰን በፍጻሜ ዘመን በተቀደሰው ስፍራ እንኳን ሳይቀር የጥፋትን ርኩሰት ያቆማል። የተቀደሰው ስፍራ የተባለው በተቀደሰ ሃይማኖት የሚኖሩትን ሀገራት፣ ሕዝቦች የሚመለከት ነው። እንደ ኢትዮጵያ የመሳሰሉትን ሀገራት ዲያብሎስ በመልእክተኞቹ ላይ አድሮ በብዙ ርኩሰት ተፈታትኗቸዋል፤ እየተፈታተናቸውም ነው። የየሀገራቱን እምነትና ታሪክ ለማጥፋት ጥሯል፤ ብዙውንም የቅድስና ሥርዓት በርዟል፤ የቻለውንም ከነጭራሹ አጥፍቶታል። አሁን እንኳ አምልኮተ እግዚአብሔር በሚፈጸምባቸዉ ቅዱሳት መካናትና ገዳማት ሳይቀር በልዩ ልዩ ምክንያት የጥፋት ርኩሰት አዉጇል። ይህም የፍጻሜ ዘመኑ አንዱ ምልክት ስለሆነ አንባቢዉ ያስተዉል እንደተባለ የዘመኑን መፍጠን የጊዜውን መድረስ በመረዳት መዘጋጀት ይገባናል።

“ብዙ ሐሰተኛዎች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ” /ማቴ.24፥11/፡፡

ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት በየዘመኑ ተነስተው እውነተኛይቱን ቤተ ክርስቲያን ታግለዋታል፤ ሊያጠፏት ባይችሉም እንኳን ብዙ ልጆቿን ነጥቀው ወስደውባታል። የነዚህን ሐሰተኞች ሠራተኞች አመጣጥ ከባድ የሚያደርገው በተአምራትና በድንቅ ምልክቶች መምጣታቸው ነው። ጌታችን እንደተናገረ “ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳን እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ” /ማቴ.24፥24/ ስለዚህ በምትሐታዊ ምልክቶቻቸው የብዙ የዋሃንን ልብ በማታለል ከተቀደሰ እምነታቸው እያስኮበለሉ አጥፍተዋቸዋል፤ በማጥፋትም ላይ ይገኛሉ። ስለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ  “ወዳጆች ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነዉ እንደሆነ መርምሩ”/1ዮሐ 4፥1-3/ አለን።

Читать полностью…
Subscribe to a channel