ethiopian_orthodox | Unsorted

Telegram-канал ethiopian_orthodox - የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

30344

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Subscribe to a channel

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በዕፀ መስቀሉ
በዕፀ  መስቀሉ የተከፈለልኝ
የኢየሱስ ፍቅር  ምንኛ ማረከኝ
ከፍቅርም በላይ ሆነና መሠጠኝ
ከመስቀል ሥር ሁኜ ፊቱን እያየሁኝ

ዓለምን በፍቅሩ ያሸነፈ ጌታ
የጸብን ማዕበል በፍቅሩ የገታ
ሕይወቴን ጸጥ አድርጎ ይምራት በምልሐቱ
እኔ ምን አለፍኝ አልደክምም በከንቱ
አዝ.....
ደሙ ከወዙ ጋር ተዋሕዶ ሲወርድ
በእኔ በደል ጌታዬ ቀረብልኝ ለፍርድ
ሀጥያቴን በጫንቃዉ ተሸክሞልኛል
በደሌን ደምሥሶ ንፁሕ አድርጎኛል
አዝ......
የቀራንዮ ግፍ በአንተ ላይ የሆነዉ
ሰይጣንን ጠርቆ ከመንገድ አወጣዉ
እሾሕ አሜኬላዉ ተደምስሶልናል
የንጹሕ በግ ደም አዳምን ታድጓል
አዝ......
ይኽንን ሥጋዬን ብሉ ይላችሁዋል
ይኽንን ደሜንም ጠጡ ይላችሁዋል
ከመስቀል ሥር ሆነን ደሙን እንቀበል
ሥጋዉን እንብላ ሠዉ ሆይ ችላ አንበል

ሊቀመዘምራን ይልማ ኃይሉ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መጋቢት ፲
በዓለ ቅዱስ መስቀል


መጋቢት አስር በዚህች እለት የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የተገለጠበትና የተገኘበት ነው። የዚህም የከበረ ዕፀ መስቀል መገለጡና መገኘቱ ሁለት ጊዜ ሆኗል።

መጀመሪያ የጻድቁ ንጉስ የቆስጠንጢኖስ እናት በሆነች በንግሥት እሌኒ እጅ ነው።
እርሷ ለእግዚአብሔር ተስላ ነበርና ልጇ ቆስጠንጢኖስ ወደ ክርስቲያን ሃይማኖት ቢገባ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዳ መስቀሉን እስከ አገኘችው ድረስ ልትፈልግው በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ልታንፃቸው ነው።

ከዚህ በኋላ ልጇ አምኖ የክርስትና ጥምቀትን በተጠመቀ ጊዜ እሌኒ ቅድስት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች ከእርሷ ጋርም ብዙ ሰራዊት ነበር ደርሳም ስለ ከበረ መስቀል መረመረች የሚያስረዳት አላገኘችም የአይሁድ ወገን የሆነ አንድ ሽማግሌ ሰው አስራ በርሀብና በጥማት አስጨነቀችው።
በተጨነቀም ጊዜ ለንግሥት እሌኒ "የጎሎጎታን ኮረብታ አስጠርጊ" ብሎ ነገራት እርሷም ይጠርጉ ዘንድ አይሁድን አዘዘቻቸው።

ቤቱን የሚጠርግ ሰው ሁሉ ጥራጊውን በውስጡ የከበረ መስቀል በአለበት በጌታችን መቃብር ላይ እንዲጥል አይሁድ አስቀድመው አዝዘው ነበርና ንግሥት እሌኒ እስከደረሰችበት ጊዜ ከሁለት መቶ አመት በላይ ጥራጊያቸውን ሲጥሉበት ኖሩ ኮረብታም ሆነ። አይሁድም በጠረጉ ጊዜ ሶስት መስቀሎች ተገለጡ የክብር ባለቤት ክርስቶስ የተሰቀለበት የትኛው እንደሆነ አላወቁም።
የሞተ ሰውም አግኝተው አመጡ። አንዱንም መስቀል አምጥተው በሞተው ሰው ላይ አኖሩት አልተነሳም ደግሞ ሌላውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አኖሩ አሁንም አልተነሳም ከዚህም በኋላ ተኛውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አደረጉት ያንጊዜ የሞተው ሰው ተነሳ እሌኒም የክርስቶስ መስቀል እንደሆነ አውቃ ሰገደችለት የክርስቲያንም ወገኖች ሁሉ ሰገዱለት።

ለልጇ የላከችው ይህ መስቀል ነው የሚል በሌላ መጽሐፍ ይገኛል የቀረው ግን ግንዱ በውስጡ ተተክሎበት የነበረው ከእርሱም እኩሌታውን ከቅንዋቱ ጋራ ወደ ልጅዋ የላከችው ነው።

ከዚህም በኋላ ሥርዓታቸውና የህንፃቸው ነገር በመስከረም ወር በዐሥራ ሰባት ተጽፎ የሚገኝ አብያተ ክርስቲያናትንና የከበሩ ቦታዎችን አነጸች።

ሁለተኛው በሮሙ ንጉሥ በህርቃል ዘመን የሆነው ሲሆን የፋርስ ሰዎች በግብፅ አገር ሳሉ ወደ አገራቸው ሊመለሱ ወደዱ። ከሹማምንቶቻቸው አንዱ የጦር መኰንን ተነጥሎ ወደ ኢየሩሳሌም አልፎ ደረሰ ወደ ከበረ መስቀል ቤተ ክርስቲያንም ገባ። መስቀሉም በላዩ በተተከለበት ግንድ ፊት ታላቅ ብርሃን ሲበራ አይቶ ሊያነሳው እጁን ዘረጋ። እሳትም ወጥታ እጁን አቃጠለችው።

ከክርስቲያን በቀር ማንም ሊነካው እንደማይችል የመስቀልን የክብሩን ነገር ሰዎች ነገሩት። ሁለት ዲያቆናትንም ይዞ የከበረ መስቀልን እንዲሸከሙ አዘዛቸው ከኢየሩሳሌምም ብዙ ሰዎችን ማርኮ ወደ አገሩ ተመለሰ።

የፋርስ ሰዎች ኢየሩሳሌምን እንዳጠፏት ብዙዎች ሰዎችንም እንደማረኩና የከበረ የክርስቶስንም መስቀሉን እንደወሰዱ የሮም ንጉሥ ህርቃል በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ። ስለርሱም እንዲጾሙ ምእመናንን አዝዞ ወደፋርስ ዘምቶ ወጋቸው ብዙዎችንም ገደላቸው የከበረ ዕፀ መስቀልንም እየፈለገ በሀገራቸው ሁሉ ዞረ ግን አላገኘውም።

ያ ዲያቆናቱና መስቀሉን የወሰደ መኰንን ከቦታዎች በቤቱ አንፃር ባለ በአንድ ቦታ ላይ ወስዷቸው ጥልቅ ጉድጓድ እንዲቆፍሩ አዝዞ በዚያ የከበረ መስቀልን አስቀበረ እነዚያንም ዲያቆናት ገደላቸው።

ነገር ግን ያ መኰንን የማረካት የካህናት ወገን የሆነች በእርሱ ቤት የምትኖር አንዲት ብላቴና ነበረች። እርሷም የከበረ መስቀልን ሲያስቀብርና ሁለቱን ዲያቆናት ሲገድላቸው በቤቱ ውስጥ ሁና በመስኮት ትመለከት ነበር ወደ ንጉሥ ህርቃልም ሂዳ መኰንኑ ያደረገውን ሁሉ ነገረችው።
ይህም ንጉሥ ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያቺ ብላቴናም መራችው ከእርሱም ጋራ ብዙ ሠራዊት ሆኖ ኤጲስቆጶሳትና ካህናትም ነበሩ ።ወደ ቦታውም እስከምታደርሳቸው ያቺን ልጅ ተከተሏት ቆፍረውም የከበረ ዕፀ መስቀልን አገኙት ከአዘቅቱም አወጡት ንጉሡና ሠራዊቱም ሰገዱለት።

በልብሰ መንግሥቱም አጎናጸፈው ታላቅ ክብርንም አከበረው ከሰራዊቱም ጋር እጅግ ደስ አለው። የዚህም መስቀል ሁለተኛ የተገለጠበትና የተገኘበት በዚች ቀን በመጋቢት አስር ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ንጉሡ የከበረ እፀ መስቀልን ተሸክሞ ወደ ቁስጥንጥንያ ከተማ ወሰደው፡፡

የመድኃኒታችን የመስቀሉ በረከት ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

©ስንክሳር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ገብረ መንፈስ ቅዱስ አቡነ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መላእክትም በእሳት ሰይፍ መተሩአቸው በመብረቅም አጨዱ አቸው አመድም ሆነው በነፋስ በተኑአቸው። የእነዚያም አጋንንት ቁጥራቸው ሰባት መቶ ሺህ እልፍ ከአንዱ ሺህ ነበር። ከዚህም በኃላ ጌታ ክርስቶስን የካዱ ወዳሉበት ወደ ምእራብ ሀገር ወሰደው። ነገስታቱና መሳፍንቱ መኳንንቱም በሚወ

ጡበትና በሚገቡበት ጉዳና ላይ አቆመው ጌታችንም በዚች ጉዳና ብዙ መከራ ያገኝሀል ግን በርታ ታገስ ብሎት በዚያ ተወው። በዚያን ጊዜም የአርብ ንጉስ ጣዖታቱን አስይዞ መኳንንቱን ሰራዊቱን አስከትሎ በዚያች ጎዳና መጣ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን በጎዳና ውስጥ በተገናኙት ጊዜ ጣኦታቱ ወድቀው ተሰባበሩ።

ንጉሱም አባታችንን በአየው ጊዜ አንተ ጠጉር ለባሽ ምንድነህ ሰው ነህን አለው።አባታችንም አዎን ክብር ያለው የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያው የሆንኩ ሰው ነኝ ብሎ ለከሀዲው ንጉስ መለሰለት። ንጉሱም ዳግመኛ አባታችንን በዚያ አይሁድ በሰቀሉት ታምናለህን አለው አባታችንም በሰው ፊት አምንበታለሁ።ስለ እኔ በተሰቀለው አላፍርበትም ስለ እኔ ብቻ የተሰቀለ አይደለም ስለ አንተና ከአንተ ጋራ ስለ አሉትም ነው እንጂ ንጉስ ሆይ የዘላለም ህይወትን ታገኛላችሁ እመኑበት አለው።

ንጉሱም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ተቆጣ ሰራዊቱንም ጠርቶ በፍጥረት እሳትን አንድዱ ለተሰቀለው ለናዝሬቱ ሰው ባሪያው ነኝ የሚለውን ጠጉር ለባሽ ወስዳችሁ ጨምሩት አላቸው። የእሳቱም ነበልባል በረጅም ዛፍ መጠን ከፍ ከፍ እስከሚል አነደዱ። አባታችን ግን ንጉሱና ሰራዊቱ ሁሉ እያዩት አልፎ በፈቃዱ ወደ እሳቱ ገባ። እሳቱም እንደወንዝ ውኃ ሆነ ሰረዊቱም እጅግ አደነቁ እኩሌቶቹም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ንጉሱም ሲያደንቁ በአየ ጊዜ ፈፅሞ ተቆጣ ከሰባ ሰባት አርበኞቹ ጋራ በቁጣ ተነስቶ ያደነቁትንና ያመኑትን አንገታቸውን ቆረጠ ።

በዚያችም ቀን የተቆረጡ አርባ መቶ ሺህ ሆነው ተቆጠሩ።ንጉሱም የአባታችንን አንገት ሊቆርጥ ሰይፉን መዞ ተወርውሮ ሄደ። ያን ጊዜም ከመብረቅና ከነጎድጓድ ጋራ ታላቅ ንውፅውፅታ ሆነ ንጉሱንም ከሰራዊቱ ጋራ አጠፋው ከከሀዲው ንጉስ ጋራ የሞቱት ቁጥራቸው አራት ሺህ እልፍ ሆነ።

ጌታችንም አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን ጠላቶችህንና የኔንም ጠላቶች አጠፋሁልህ አለው።አባተችን ግን በመብረቅ የሞቱትን ሬሳቸውን ነፍሳቸውንም መላእክተ ፅልመት ወደ ስቃይ ሲወስዱአቸው በአየ ጊዜ መድኃኒታችንን እሊህን ስሁታን ማርልኝ ሰው ስሁትና ከዳተኛ ነውና አቤቱ አንተ ግን መሀሪ ይቅር ባይ ታጋሽም ነህ አለው።አባታችንም ይህን ሲናገር ጌታችን ተሰወረ።

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም ከዚያ ሄደ ታላቅ ገደልም አገኘ እግሮቹንም በገመድ አስሮ በገደሉ ውስጥ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ።ሰይጣንም መጥቶ ያቺን ገመድ ቆረጣት ወደ ታችም ተወርውሮ ወረደ።ቅዱስ ሚካኤልም ቀድሞ አባታችንን ያዘው በእግርህ ላቁምህ ወይም በራስህ አለው በራሴ እቆም ዘንድ ተወኝ አለው ትቶት ሄደ።

በዚያም በራሱ ቁሞ በጥርሶቹም ደንጊያ ነክሶ እስከ ሰላሳ አመት ኖረ አንጀቱና ናላው ሁሉ እየፈሰሰ አልቆ መላ አካሉ እንደእንጨት ቅርፊት ሆነ። ከሰላሳ አመትም በኃላ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባታችንን ገብረ መንፈስ ቅዱስ እያለ ሶስት ጊዜ ጠራው። እርሱም እነሆኝ ጌታዬ አለ ጌታችንም እነዚያን ከሀዱዎች ምሬልሀለሁ ከዚህ ተነሳ አለው።ያን ጊዜ የነከሰውን ደንጊያ ትቶ ተነሳ።ጥርሱም ተነቅሎ በድንጊያ ተተክሎ ቀረ። ክንፎችም ተሰጥተውት እየበረረ ከእግዚአብሔር ፊት ደረሰ ጌታውንም ከማርክልኝ ከስጋቸው ጋራ ተነስተው በመጠመቅ ክርስቲያኖች ይሁኑ ብሎ ለመነው። መድኃኒታችንም በሽተኞችን ልትፈውስ ሙታንን ልታስነሳ ስልጣን ሰጥቼሀለሁ አሁንም ወደተገደሉት ሄደህ በመስቀል ምልክት በላያቸው አማትብ ህይወት መድኃኒት በሆነ ስሜም አስነሳቸው አለው።ያን ጊዜም በድኖቻቸው ወዳሉበት ሂዶ አስነሳቸው አጥምቆም ክርስቲያኖች አደረጋቸው ከእርሳቸውም ሄደ።

ከዚህ ዓለም የሚለይበት በቀረበ ጊዜ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነሆ ተገለጠለት። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ እስከ አስራ አምስት ትውልድ የምህረት ቃል ኪዳን ሰጠው።የእድሜውም ዘመናት አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ሲሆን በሰላም በፍቅር አረፈ። ጌታችንም ነፍሱን ተቀበለ አቅፎም ሳማት በመላእክትና በቅዱሳን ሁሉ ምስጋና አሳረጋት።

በጸሎቱ ያስምረን:ሀገራችንን ኢትዮጵያን ከገባችበት ፈተና በጸሎቱና በተሰጠው ቃልኪዳን ያድናት: አሜን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በተለይም መዋቅራዊ ድጋፍ እየተሰጠው በሚመስል መልኩ የጥላቻ ንግግሮች ተባብሰው መቀጠላቸው እና ይኸው ጥላቻም በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ብቻ ሳይሆን በሜንስትሪም እና በመጽሐፍትም ጭምር ሲካሄድ መቆየቱ እና እየተካሄደ መሆኑ በርካታ ምእመናንን ያሳዘነና ያስቆጣ መሆኑ ተመላክቶአል።

መንግስት እነዚህን የጥላቻ አራማጆች እና ጸረ ሃይማኖት ግለሰቦችን በሕግ አግባብ እንዲጠይቅም ምእመናን ጥሪ አቅርበዋል።

©ተሚማ
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ምኩራብ"
ኧኸ     ኧኸ     ኧኸ
ቤትህ ቅዱስ ነው መቅደስህ

ለዘለዓለም መርጬዋለው
በረድኤቴ እገለጣለው
ልቤ እና አይኔ በዚያ ነውና
እሰማለሁኝ ጸሎት ምስጋና
               አዝ===
ቤትህን ከበው ገንዘብ ለዋጮች
የሚሸጡበት በግ እና ርግቦች
እንዲገለበጥ መደባቸው
የቤቱ ጌታ አንተ ጎብኘው
               አዝ===
የቤትህ ቅናት በላኝ እንደ እሳት
ክፋት ጥላቻ ሲበረቱባት
የአህዛብ ዛቻው የአህዛብ ፈረስ
አስተናገደች የክብር መቅደስ
               አዝ===
ለፍርድ ተነሳ ዝም አትበል ጌታ
እንዲፈራርስ የሻጭ ገበታ
መለያየቱ በልጧል ከትላንት
ዛሬም አምላክ ሆይ ቤትህን ጎብኛት

©በዲያቆን ዘማሪ ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ምኩራብ
የዐብይ ጾም ሦስተኛ እሑድ(ሳምንት)


ሦስተኛው ሰንበት ምኩራብ ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት በዚሁ ዕለት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ሰላሙ ድረስ በዕለተ ሰንበት «ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ» «ምኩራብ» ማለትም ቀጥተኛ ፍችው ኮረብታ፣ ተራራ የሚያኸል ታላቅ ሕንጻ ማለት ነው፡፡

ከዚህም የተነሣ የአይሁድ ቤተ ጸሎት ወይም ቤተመቅደስ ማለት ይሆናል፡፡ ዐቢይ ፍሬ ቃሉ ግን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያነ ሥጋን በትምህርቱ፣ ድውያነ ነፍስን በታምራቱ ሲፈውስ በምኩራብ እየተገኘ የፈጸመውን የማዳን ሥራ በኀሊና እያሳሰበ የሚያስተምር ሦስተኛ ሳምንት ነው፡፡

ዮሐ. 2:12 «ኢየሱስ በሰንበት ቀን ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ» እያለ ኢየሱስ በአይሁድ ምኩራብ ማስተማሩን እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ይህን ሰንበት ለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ እየገባ ለማስተማሩና በምኩራብ የሚሸጡ የሚለውጡ ነጋዴዎችን ለማስወጣቱ ቤተ መቅደሱን ለማስከበሩ መታሰቢያ ሳምንት ነው።

የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡

ትርጉም:-
ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው ፡፡ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል (እያለ የሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው፡)፡ ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ።

ምስባኩም፦ መዝ ፷፰፥፱
"እስመ ቅንዐት ቤትከ በልዐኒ ትዕይርቶሙ ለእለይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ"
"የቤትህ ቅናት በልቶኛል የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆብኛልና ነፍሴን በጾም አስመረርኳት"

በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች
-ቆላ ፪፥፲፮ እስከ ፍጻሜ
-ያዕ ፪፥፲፬ እስከ ፍጻሜ
-የሐዋ ሥራ ፲፥፩-፱

ወንጌሉም፦ ዮሐ ፪፥፲፪ እስከ ፍጻሜ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ነዋ ጊዮርጊስ
ነዋ ጊዮርጊስ አሐዱ እም ቅዱሳን ሰማዕት
መጽአ ይርድአኒ ይቤ ምኒልክ ንጉሥ።

ትርጉም
ንጉሥ ምኒልክ አለ እነሆ ከቅዱሳን ሰማዕት አንድ የሆነ ጊዮርጊስ ሊረዳኝ መጣ።

©MK
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የካቲት ፳፫
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት በዓድዋ


የካቲት ሀያ ስሶት በዚህች ቀን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት አባቶቻችንን ዓድዋ ላይ የረዳበት ነው፡፡ በዚያን ወራት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ከአንድ ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ አራት ዓመት በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ በነገሡ በሃያ ስድስት ዓመት የምኒልክ የጦር አለቃ ገበየሁ ድል ከአደረጋቸው በኋላ እንደገና ምኒልክን ወግተው ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ሊገዙ የሮም ሰዎች መጡ።

ከዚህም በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት፡ ዳግማዊ አጤ (ዓፄ) ምኒልክ መስከረም ፯ ቀን ፲፰፻፹፰ (1888 ዓ.ም) ላይ "እግዚአብሔር በቸርነቱ፡ እስከ አሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም እስከ አሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ እንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉ ነውና ስለ እኔ ሞት አላዝንም፡፡ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፡፡ እንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፤ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት፤ እግዚአብሔር የወሰነልንን የባህር በር አልፎ መጥቷልና እኔም የአገሬን ከብት ማለቅ፤ የሰውን መድከም አይቼ እስከ አሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር፡፡ አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም፡፡ የአገሬ ሰው፤ ከአሁን ቀደም የበደልሁህ አይመስለኝም አንተም እስከ አሁን አላስቀየምኸኝም፡፡ ስለዚህ ስንቅህን በአህያ አመልህን በጉያህ ይዘህ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ፡፡ ጉልበት የሌለህ ለልጅህ፤ለሚስትህ፤ ለሃይማኖትህ ስትል በኀዘን እርዳኝ፡፡ ወስልተህ የቀረህ ግን በኋላ ትጣላኛለህ አልተውህም፡፡ ማርያምን! በዚህ አማላጅ የለኝም"፡፡ ዘመቻዬም በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ" ብለው አዋጅ አስነገሩ፡፡ ዳግኛም በፈረሶታቸው መጣብር ላይ በጦራቸው አንደበት ላይ የመስቀል ምልክት እንዲያደርጉ ጭፍሮችን አዘዛቸው መስቀል ጠላትን ድል አድራጊ እንደሆነ አስቀድሞ ያውቅ ነበርና።

አዋጁን ካስነገሩ በኋላ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ትግራይ ክፍለ አገር ዘመቱና ከትግራይ አውራጃ አንዷ የምትሆን አድዋ የምትባል አገር ደረሱ፡፡ የሣህለ ማርያም (ዳግማዊ ምኒልክ) ሚስት ወለተ ሚካኤል (እቴጌ ጣይቱም) በንጉሡ ትዕዛዝ ታቦተ ጊዮርጊስን አስይዘው ከሊቀ ጳጳሱ ከአባ ማቴዎስ እንዲሁም ከቀሳውስቱና ከመነኰሳቱ ጭምር ከንጉሡ ጋር ወደ ጦርነቱ ተጓዘች፡፡በዚያም ጊዜ የአክሱም ጽዮን መነኰሳትና ካህናት የእመቤታችንን ሥዕል ይዘው ወደ ንጉሡ ወደ ምኒልክ መጥተው ከሊቀ ጳጳሱ ከነአቡነ ማቴዎስ ጋር ተቀላቀሉ ከዚያም ሌሊቱን ሙሉ ጸሎት ምሕላ ሲያደርሱ አደሩ።

ቅዳሜ ማታ ለእሑድ አጥቢያ የካቲት ሃያ ሁለት ቀን ነው ንጉሡ ሣህለ ማርያም (ምኒልክ) የጦር ልብሱን ለብሰው ከሠራዊቱ ጋር ወደ ጦር ግንባር ሄደ፡፡ ከዚያም ከሮማውያን የጠላት ጦር ጋር ተገናኝቶ ከሌሊቱ ዐሥራ አንድ ሰዓት ጦርነቱን ጀመረ፡፡ የንጉሡ የሣህለ ማርያም (የምኒልክ) ሚስት ወለተ ሚካኤል (እቴጌ ጣይቱም) ሌሊት በታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስና በእመቤታችን ሥዕል ፊት በጸሎትና በስግደት እያደረች ሲነጋ ወደጦርነቱ ቦታ በመሄድ እጅግ ለሚያስደንቅ የአነጋገሯ ኃይል ቃል በጦርነቱ መካከል እየተገኘች ለንጉሡ ወታደሮች የሞራልና የብርታት ድጋፍ ትሰጣቸው ነበር። በእውነትም ለተመለከታት ሁሉ እንደ ኃይለኛ ተጋዳይ አርበኛ ትመስል ነበር እንጂ የሴቶች የተፈጥሮ ባሕርይ በእርሷ ላይ አይታይባትም ነበር። የንጉሡም ወታደሮች የንግሥቲቱን የጀግንነት አነጋገር በሰሙ ጊዜ በእሳት ላይ እንደተጣደ የብረት ምጣድ ልባቸው ጋለ ይልቁንም ላም እንዳየ አንበሳና የፍየል መንጋ እንዳየ ነብር እየተወረወሩ በጦርነቱ መካከል በመግባት የጠላትን ጦር በሰይፍ ይጨፈጭፋት ነበር። መጽሐፍ ሹመትን ሽልማትን ያየ አርበኛ ከጦርነት ከሰልፍ ወደኋላ አያፈገፍግም ብሎ ተናግሯልና፡፡ በዚያም ጊዜ ንጉሡ ሣህለ ማርያም (ምኒልክ) በጦርነቱ መካከል ሳለ ሊቀ ጳጳሱ አባ ማቴዎስ እንዲሁም የአክሱም መነኰሳትና ሌሎቹ ካህናት በሙሉ ታቦተ ጊዮርጊስንና ሥዕለ ማርያምን ይዘው ከንጉሡ በስተኋላ በደጀንነት ቆመው ጸሎተ ምህላ ያደርሱ ነበር። ንግሥቲቱ ወለተ ሚካኤል (እቴጌ፡ጣይቱም) በጸሎት ጊዜ በመዓልትም በሌሊትም ከእነርሱ አትለይም ነበር። የጽዮን አገልጋዮችም በእግዚአብሔር የሕጉ ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር።

በዚህም ዕለት ይኸውም የካቲት ሃያ ሦስት ቀን በሮማውያንና በኢትዮጵያውያን መካከል ከፍተኛ ጦርነት ሆነ በዚህም ጊዜ በሰማይ ታላቅ ተአምር ተደረገ። ማለትም የቀስተ ደመና ምልክት ታየ ከዚያም ከቀስተ ደመናው ውስጥ መልኩ አረንጓዴ የመሰለ ጢስ ይወጣ ነበር፡፡ ከዚህም ጢስ ውስጥ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ያለ ድምጽ ተሰማ፡፡ ከዚህም የነጐድጓድ ድምጽ የተነሳ በሮማውያን ወታደሮች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሽብር ሆነ ለመዋጋት አልቻሉም፡፡ ይልቁኑ ኃያሉ ገባሬ ተአምር ማር ቅዱስ ጊዮርጊስ በአምባ ላይ ፈረሱ ተቀምጦ ከነፋስ ሩጫ ይልቅ እየተፋጠነ በአየር ላይ በተገለጸ ጊዜ በግንባራቸው ፍግም እያሉ ወደቁ፡፡ "የኢትዮጵያ ህዝብ አምላካቸው ሊረዳቸው መጣ እንግዲህ ማን ያድኅነናል" አሉ ምድርም ጠበበቻቸው በዚህን ጊዜ የኢትዮጵያ ሠራዊት የሮምን የጦር ሠራዊት ፈጁዋቸው የተረፉትንም ማረኳቸው ፈጽመውም እስኪያጠፏቸው ድረስ በሮማውያን ላይ በእግዚአብሔር ሥልጣን የኢትዮጵያውያን እጅ እየበረታ ሄደ፡፡ ከዚህም በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሣህለ ማርያም (ምኒልክ) በእግዚአብሔር ኃይልና በተአምራት አድራጊው በቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳይነት የሮማውያንን የጦር ሠራዊት ድል አድርገው የድል አክሊል ተቀዳጅተው ተመለሱ፡፡

ስለዚህም በዳዊት የምስጋና ቃል የድል ዘውድ ያቀዳጀኝን እግዚአብሔር "ባለ ዘመኔ ሁሉ አመሰግነዋለሁ ለፈጣሪዬ እዘምራለሁ" አለ ሕዝቡም ሁሉ "በክብር ከፍ ከፍ ያለ እግዚአብሔርን በፍጹም ምስጋና እናመስግነውለን የሮማውያንን ኃይል ቀጥቅጦ አጥፍቷልና ሠረገሎቻቸውንም ሠባብሯልና ሠራዊቱንም ሁሉ በምድር ላይ በትኗልና" እያሉ አመሰገኑ። በፈጣሪው በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል በጦርነቱ መካከል የረዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስንም በፍጹም ማድነቅ አደነቁ። የሮማም የጦር ሠራዊት በኢትዮጵያውያን ፊት ተዋረዱ ዳግመኛም በኢትዮጵያ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም። በምኒልክም ዘመነ መንግሥት ኢትዮጽያ ከጦርነት ለዓርባ ዓመት ያህል አረፈች።

የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ ከአደዋ ጦርነት ከተመለሱ በኋላ በአዲስ አበባ በምትበል ከተማው መካከል በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ቤተክርስቲያን አሠራ። ስሟንም ገነተ ጽጌ ብለው ሰየሟት። ቅዱስ ጊዮርጊስ በጦርነት ቦታ ሁሉ ይረዳው ነበርና። ልመና ክብሩ በኛ ለዘላለሙ በዕውነት ይደረግል። በረከቱ ከእኛ ጋር ትሁን እኛንም በቅዱስ ጊዮርጊስ አማላጅነት ይማረን ለዘለዓለሙ አሜን!!! (ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተአምር 17)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቅድስት
የዐብይ ጾም ሁለተኛ እሑድ(ሳምንት)


ቅድስት የሚለው ቃል ግሱ “ቀደሰ” ሲሆን "ለየ፣ አከበረ፣ መረጠ" የሚል ትርጉም ይይዛል።
ቅድስት ማለት የተለየች፣ የተመረጠች፣ የከበረች ማለት ነው። ቅዱስ የሚለው ቃል እንደየአገባቡ ለፈጣሪም ለፍጡርም ያገለግላል። ለፈጣሪ ሲነገር እንደ ፈጣሪነቱ ትርጉሙ ይሰፋል ይጠልቃል ለፍጡር ሲነገር ደግሞ እንደ ፍጡርነቱ እና እንደ ቅድስናው ደረጃ ትርጉሙ ሊወሰን ይችላል።

እግዚአብሔርን ቅዱስ ስንል የባህሪይው የሆነ፣ ኃጢአት የማይስማማው ፣ ለቅድስናው ተወዳዳሪ ተፎካካሪ የሌለው፣ ወደር የማይወጣለት፣ ዘለዓለማዊ የሆነ ማለታችን ሲሆን ፍጡራንን ግን ቅዱሳን ስንል ቅድስናቸው የጸጋ የሆነ፤ ከእግዚአብሔር ያገኙት፤ እንደነጭ ልብስ ጽድቁም ኃጢአቱም እንደ ዝንባሌአቸው የሚስማማቸው፤ ለቅድስናቸው ማዕረግ ደረጃ የሚወጣለት እንደ ገድል ትሩፋታቸው መጠን ሊጨምርም ሊጎድልም የሚችል ማለታችን ነው። ከፍጡራን መካከል ለእግዚአብሔር የተለዩ ሁሉ በጸጋ የቅድስናው ተሳታፊ ሊሆኑ ይችላሉ። መላእክት፣ ሰዎች፣ መካናት፣ ዕለታት፣ አልባሳት፣ ንዋያት ሁሉ ለእግዚአብሔር እስከተለዩ ድረስ ከቅድስናው በረከት ይሳተፋሉና እንደየደረጃቸው ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ።

በዚህ ዕለት ስለ ቅድስና እንዲሁም ዘወትር በዕለተ ሰንበት ከሌሎች ቀናት በተለየ ሁኔታ ለጽድቅ ሥራ እንድንበረታ፣ ለቅድስና እራሳችንን እንድንለይ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይሰበካል ይነገራል። የሚዘመረውም መዝሙር “ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ ሀቡ ስብሐተ ለስሙ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት ኀበ ፃፄ ኢያማስኖ ወኢይረክቦ ሰራቂ ድልዋኒክሙ ንበሩ ዘበላዕሉ ጸልዩ ኀበ ሀሎ ክርስቶስ ፥ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ሥራውንም ለአሕዛብ ንገሯቸው፤ ለስሙም ምስጋናን አቅርቡ፤ ሰንበትን አክብሩ፤ እውነትንም አድርጉ፤ ብል የማያበላሸው ሌባም የማያገኘው በሰማያት ያለ መዝገብን ለእናንተ ሰብስቡ፤ ተዘጋጅታችሁም ተቀመጡ፤ ክርስቶስ ወዳለበት ወደላይ አስቡ፡፡”

በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ እንደዘመረልን በተለይ ሰንበት ነገረ እግዚአብሔር በተለየ ሁኔታ የሚዘከርባት፤ ኅሊናችን ከምድራዊው ሃሳብ ወጥቶ ወደ ሰማያዊው የሚነጠቅባት፤ ለቅድስና የተለየች ቅድስት ዕለት መሆኗን ይጠቁማል። በቅዱስ መጽሐፍም “የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ” (ዘፀ. ፳፥፰) ተብሏል፡፡ የሰንበትን ቀን አስቀድሞ የቀደሰ የባረከ እራሱ እግዚአብሔር ነው "እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና"(ዘፍ.፪፥፫) እንግዲህ “የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ” የተባለው እግዚአብሔር አስቀድሞ የባረከውን የቀደሰውን እኛ ድጋሚ የምንቀድስ የምንባርክ ሆነን ሳይሆን በዕለተ ሰንበት እራሳችንን በተለየ ሁኔታ ለቅዱስ ተግባር እንድንለይ ለሥጋችን ከምንፈጽማቸው ተግባራት ይልቅ ለተግባረ ነፍስ እንድናደላ ያስረዳናል። ምንም እንኳን ለስጋችን ስንባክን ጊዜ ቢያጥረን በዕለተ ሰንበት ግን ቅዳሴ ከማስቀድስ ቅዱስ ቃሉን ከመስማት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ከመቀበል እንዳናስታጉል በሥርዓት ቤተ ክርስቲያን ታዝዘናል፡፡

ሊቃውንቱ በፍትሐ ነገሥት "ተጋብኡ ኩሎ ዕለት ኀበ ቤተ ክርስቲያን ወፈድፋደሰ በዕለተ ሰንበት ወበበዓላት ወበዕለተ ትንሣኤ ዘውእቱ ዕለተ እሑድ፤ ሁልጊዜ በቤተ ክርስቲያን ተሰብሰቡ፤ ይልቁንም በዕለተ እሑድ፣ በዕለተ ቀዳሚት፣ በጌታ በዓላት ወደ ቤተ ክርስቲያን ተሰብሰቡ፡፡” (ፍትሐ ነገሥት ገጽ ፪፻፶፬) ብለው ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ከሌሎች ቀናት በተለየ ሁኔታ ትኩረት የምንሰጥበት የምንቀደስበት ዕለት ቅድስት ሰንበት እንደሆነች ተናግረዋል። ሐዋርያዊው ቅዱስ አትናቴዎስም በቅዳሴው ላይ ሰንበት የተቀደስች እና ሕይወታችን እንዲቀደስባት የተለየች ቀን መሆኗን ሲያስረዳ እንዲህ ይላል፡፡ “ወንበል ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር ንትፈሣሕ ወንትሐሰይ ባቲ ፥ ይህች ዕለት እግዚአብሔር የሠራት ያከበራት ዕለት ናትና በእርሷ ፈጽሞ ደስ ይበለን”። ሰንበት ለክርስትያኖች ለመንፈሳዊ ደስታ የተለየች ቀን ናት። የመንፈሳዊ ደስታ ምንጩ በነፍስ የሚገኝ መንፈሳዊ በረከት ነው። ሰው የኃጢአትን ሸክም በንስሃ ሲያራግፍ፤ ነፍሱ በጸጋ እግዚአብሔር ስትቃኝ የሚሰማውን ደስታ በሌላ በምንም መንገድ ሊያገኘው አይችልም። ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ሰንበት ቅድስትና ለቅድስና የተለየች ቀን መሆኗን ያስተማረን አስቀድሞ በነብያት ትንቢት ያናግር የነበረ መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶት ነው።

ስለ ሰንበት መለየትና መቀደስ እንዲሁም የመንፈሳዊ ሐሴት ቀን ለመሆኗ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት መዝሙሩ እንዲህ ብሎ ነበር “እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።” (መዝ. ፻፲፯፥፳፬) ቅዱስ ዮሐንስም በራእዩ ሰንበት የጌታ ቀን ስለመሆኗ እንዲህ ይላል “በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ” (ራእ. ፩፥፲) ሰንበት የእኛ ቀን ሳትሆን ለጌታችን የምንሰራባት የምንለይባት ፣ የምንቀደስባት፣ ነገረ እግዚአብሔርን የምንዘከርባት የጌታ ቀን ናት። ለቅድስና የተለየች ቅድስት ቀን ናት ። በተለይ የክርስቲያን ሰንበት እሑድ “በኵረ በዓላት” ትባላለች በኵር ታላቅ እና መጀመርያ ማለት ነው፤ የመዳናችን መሰረት የተወጠነባት የጌታ የጽንሰቱ ቀን ዕለተ ሰንበት ናት፤ የመዳናችን ማረጋገጫ፣ የእምነታችን መሰረት ፣ የበዓላት ሁሉ ዓቢይ ትንሳኤው የተፈጸመው በዕለተ ሰንበት ነው። እንግዲህ በዚች ቅድስት ዕለት፥ ለቅድስና በተለየች ዕለትስ ሥጋውንም ነፍሱንም በሚያረክስ ተግባር የተሰማራስ ለነፍሱ ምን ዋስትና ይኖረዋል?

ቅድስት በተባለች በሰንበት እሑድ ማንም በምንም ምክንያት ወደ ቤተ እግዚአብሔር ከመሄድ እንዳያስታጉል በሥርአተ ቤተክርስትያን ተቀምጦልናል። ሌላው ቀርቶ በዕዳ በብድር በቀረጥ በግብር በአስራት በበኩራት ይሉኝታ ፈርቶ ማንም ቅድስት በምትባል በእሑድ ሰንበት ቅዳሴ እንዳያስታጉል ማንም ማንንም በዚህች ቅድስት ዕለት ምንም አይነት እዳ እንዳይጠይቅ ታዝዟል።

“ወኢይኅሥሥ መኑሂ በይእቲ ዕለት ንዋዮ እምካልኡ ወኢይጽሐቅ አሐዱሂ እምእመናን በእንተ ኃሥሠ ዕዳ ። አው ተጻልኦ አው በዘይመስሎ ለዝንቱ። ወይሑሩ ቦቱ ኩሉሙ ሰብእ ኀበ ቤተ ክርስቲያን ወይምጽኡ ኲሉ ለለ ፩ እምእመናን ኅቤሃ በንጽሕ ወበትህትና ዘእንበለ ፍርሃት እምነ መኮንን ወእም በዓለ ዕዳ አው እምፈታሒ አው ዘይመስሎ። ወእመሰ ተሀበለ ፩ሂ ክርስቲያን ምክዕቢተ ይፍዲ ፥ ከምእመናን ወገን አንድስ እንኳ በእሑድ ቀን ለገንዘብ መትጋት፤ገንዘቤን አምጣ ብሎ መጣላት፣ ዋስ መያዝ አይገባውም ። ሁሉም ምእመናን ወደ ቤተክርስቲያን በንጽሕና በትሕትና ሆነው ይምጡ እንጂ ። ዳኛ ግብሬን፣ አበዳሪ ብድሬን ፣ኤጲስቆጶስ ዐሥራት በኵራት ፣ ነጋድራስ 'ቀረጥ አምጡ' ይሉናል ብለው ሳይፈሩ ይምጡ። ከነጋድራሶች አንዱ እንኳ ወደ ቤተክርስትያን ከሚሄዱ ሰዎች ቀረጥ ይቀበል ዘንድ የድፍረት ሥራ የሠራ ቢሆን እጽፍ አድርጎ ይክፈል።” (ፍትሐ ነገሥት ገጽ ፪፻፶፰-፪፻፶፱) ቅድስት ቤተክርስቲያን ይህን ያህል ጥንቃቄ የምታደርገው ሰዎች በተለያየ ምክንያት ከቤተ እግዚአብሔር እንዳይርቁ ከዛም አልፎ ተበዳይም ሆነ በዳይ

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ኪዳነ ምሕረት እናቴ"
ኪዳነ ምሕረት እናቴ አማልጅኝ እኔን ከልጅሽ
የፍቅር እናት ነሽና አማልጅኝ እኔን ከልጅሽ
የሰላም እናት ነሽና አስታርቂኝ እኔን ከልጅሽ

የተገለጠው ብርሃን ከምሥራቅ የተወለደው
በፍቅር ሰንሰለት ታስሮ ዓለምን ሁሉ አዳነው(፪)

አዝ===

በረሃውን ባሰብኩት ጊዜ ያንን የአሸዋ ግለት
አንቺ ትንሽ ብላቴና ኧረ እንዴት ቻልሽው በእውነት(፪)

            አዝ===

ዝም ብዬ ይደንቀኛል የአምላክን ሥራ ሳስበበው
ምክንያት አንቺን አድርጎ ይህንን ዓለም አዳነው(፪)

            አዝ===

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"መጻጉዕ"
ሰው የለኝም ያለ በሰው የተረሳ፣
የዳነው መጻጒዕ ያዳነውን ረሳ።

በአምስቱ እርከኖች በአዕማደ ሚስጥራት፣
ቤተ ሳይዳ ላለች ከመቅደስ ላኖርካት፣
በበደል ለምናዝን ምሕረትን ፍለጋ፣
በንሰሐ ማረፍ ከዐራተ ዝንጋኤ ከኃጢአት አልጋ።

        አዝ= = = = =

በጠበሉ ደጃፍ ለጸኑት የሚላክ፣
ለቀድሶተ ማይ የሚወርደው መልአክ፣
በመንገድ ጠብቆ ሞትን የሚያሳልፍ፣
ዛሬም ይድረስልን ቀድመው ከገቡት ጋር ነፍሳችን እንድታርፍ።

        አዝ= = = = =

አልጋው ተሸክሞት ደክሞ ለሚጨነቅ፣
አልጋን አሸክመህ ሕመም የምታርቅ፣
ደዌያችንን ነስተህ ቆስለህ የምትፈውስ፣
የመጻጒዕ ረዳት የነፍሳት መጠጊያ መድኃኒት ክርስቶስ።

        አዝ= = = = =

የባሰ እንዳያየው ቃሉን ያልጠበቀ፣
እጁን ሰዶ ጸፍቶ ከደዌው ታረቀ፣
'ሰንበት የሻረ' ከሚሉት እንዳንውል፣
ለትንሣኤው ደስታ የሰንበትን ጌታ አርብን እንከተል።
       
©በዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መጻጉዕ
የዐብይ ጾም አራተኛ እሑድ(ሳምንት
)

መጻጉዕ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ላይ ታሪኩ የተጻፈው ለ፴፰ ዓመት አልጋ ላይ ተኝቶ የኖረ በቤተ ሳይዳ/በቤተ ዛታ ስፍራ ይዞ የመልአኩን መምጣት ፤የውሃውን መባረክ፤ የውሃውን መናወጥ እና ድኅነቱን በተስፋ የሚጠብቅ ግን ድኅነቱ በሳምንት አንዴ እርሱም አንድ ሰው ብቻ ስለሆነ የሚያገኘው ይህን እድል ማግኘት ያቃተው ተሸክሞ ወደ ውሃው የሚያደርሰው በተባረከ ጊዜ እንዲድን የሚያግዘው ሰው አልባ ህመምተኛ ነው።
ጌታችንም ወደ ቤተ ሳይዳ መጥቶ የልቡን ሃሳብ ያውቃልና "ልትድን ትወዳለህን?" አለው
ጌታችን መጻጉዕ የሚፈልገው ጠፍቶት ሳይሆን 'ሙሉ ሰው ነህና መስክር ፍላጎትህ ከአንደበትህ ይውጣ' በሚል ነው።
ይህም ታማሚ እዛጋ ለብዙ ዘመን ያየው የነበረው በሰዎች ተረድተው ወደ ተቀደሰው ውሃ ገብተው ድነው ሲወጡ ነበርና ብቸኛ መሆኑን መዳን እየቻለ ግን ወደ ውሃው የሚያደርሰው ጎረምሳ ስለፈለገ "ሰው የለኝም" አለ። አንድም ጌታችን ገና የ፴ ዓመት ወጣት ነበርና 'ተሸክሞ ያደርሰኛል' ወይም ከርሱ ጋር ብዙ ሰዎች ነበሩና 'ሰው ቢያዝዝልኝ' በሚል ሰው የለኝም አለ።

ጌታችንም "ለ፴፰ ዓመት አልጋህ አንተን ተሸክማለችና አሁን ተነስ አልጋህን ይዘህ ሂድ" አለው። ያላሰበው ደስታ አደናግሮት ማን እንደ አዳነው እንኳን ሳያውቅ ነበረ የተነዳው በዚህም ገጠመኝ በሰንበት ሥራ አይሠራም የሚሉ አይሁዶች ያዙትና "እንዴት በሰንበት አልጋ ትሸከማለህ?" ብለው ያዙት ፴፰ አመት ሲተኛ ግን ማንም አልጠየቀውም። "ያዳነኝ እርሱ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ" ብሎ መለሰላቸው። "ማን ነው ያዳነህ?" ይህ ምላሽ እርሱ ባይመልስም ለእነርሱ ግልጽ ነው በዛ ሰዓት ከእርሱ ከመድኃኔዓለም ውጪ እንዲህ አይነት ተግባር የሚሠራ አልነበረምና። መጻጉዕ በውስጡ ዘወትር ማን ነው ያዳነኝ የሚለውን ጥያቄ አንግቦ ጌታም በመቅደስ አግኝቶት "ኃጢአትህ ተሰርዮልኻል ግን ዳግመኛ ከዚ በላይ እንዳያገኝህ ደግመህ አትበድል" ሲለው ምስክር አይሉት ፈጥኖ ሄደና ለአይሁድ "ያዳነኝ እርሱ ነው" ብሎ ተናገረ። ሕማማተ መስቀል ላይ አባቶቻችን የጌታ ፊት በጥፊ ጸፍቶታል ይላሉ።
ከ፴፰ አመት በላይ አልጋ ላይ የነበረውን "ከዚህ በላይ እንዳያገኝህ" ሲል 'ሲኦል እንዳትገባ ከዚህ የከፋ ስቃይ እሳት እንዳያገኝህ ደግመህ አትበድል' ሲል ነው።

እኛ ስንቶቻችን ዳግማዊ መጻጉዕን ሆነናል!?: በቤቷ ኖረን፣ የሥጋችን ፈውስ ከፀበል ከእምነቱ ተደባብሰን ድነን፣ ለነፍሳችን ንስሓ ከአባቶች አግኝተን፣ ሥጋውንም በልተን ደሙንም ጠጥተን ዛሬ ግን ከእርሷ ርቀን፣ በውሸት መስክረን ሁለተኛው ንጉሥ ገንዘብን ያነገሥን ዳግማዊ መጻጉዕ ሆነን የተገኘን! ዛሬ ካለው መከራ የባሰ የወደፊቱ የቆየው መከራ ሳያገኘን ሮጥ ብለን እንድናመልጥ አምላካችን ይርዳን።
በዚህ ሳምንት መጻጉዕ ብቻ ሳይሆን ጌታችን በመዋለ ሥጋዌ ዘመን ያዳናቸው ድውያን ሁሉ ይታወሳሉ።
እኛም የሥጋ የነፍስ በሽታ አለብንና እርሱ በቸርነቱ ይታደገን ይፈውሰን አሜን።

በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ጥቅሶች
-ገላ ፭፥፩ እስከ ፍጻሜ
-ያዕ ፭፥፲፬ እስከ ፍጻሜ
-የሐዋ ሥራ ፫፥፩-፲፪

ምስባኩም፦ መዝ ፵፥፫-፬
"እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ ወይመይጥሎቱ ኩሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣህለኒ"
"እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል መኝታውን ሁሉ ለበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል እኔስ አቤቱ ማረኝ"

ወንጌሉም፦ ዮሐ ፭፥፩-፳፭

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መጋቢት ፭
እረፍቱ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ


መጋቢት አምስት በዚህች ቀን ተአምራቱና ትሩፋቱ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነ ቅዱስ አባት ተጋዳይ አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የእረፍቱ ቀን መታሰቢያ ሆነ፡፡ ይህም ቅዱስ አባት በተወለደባት ቀን ድንቅ የሆነ ስራን ሰራ ተነስቶ ከእናቱ እቅፍ ወርዶ ከጨለማ ወደ ብርሀን ላወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን እያለ ለስላሴ ሰግዷልና ምስጋናም አቅርቧልና።

ህፃኑም ሶስት አመት በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር መልክተኛ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ህፃኑን ከእናቱ እቅፍ አንስቶ ብዙ ባህታውያን ወዳሉበት ገዳም ወስዶ በደጅ አኖረው ወደ አበምኔቱ ወደ አባ ዘመደ ብርሀንም ገብቶ ስለ ህፃኑ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ነገረው።

በዚያን ጊዜም ነገሩ እውነት እንደሆነ ይረዳ ዘንድ አባ ዘመደ ብርሀን ተነስቶ ወደ ደጅ ወጣ። መልአኩም እንደ ነገረው ህፃኑ ከበር ተቀምጦ ፈገግታን ተሞልቶ አገኘው። እጅግም ደስ ብሎት ለእግዚአብሄር ሰገደ ህፃኑንም አንስቶ ሳመው ታቅፎም ወደ በአቱ አስገባው።

በፍቅር በስነስርአት አሳደገው። የዳዊትን መዝሙርና ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸውን መፃህፍት ሁሉ ብሉይንና ሀዲስን አስተማረው። ከዚያም በኃላም ክህነት ይሰጠው ዘንድ ስሙ አብርሀም ወደሚባል ጳጳስ ወሰደው ጳጳሱም በአየው ጊዜ ደስ አለው።የዲቁና ማእረግንም ሾመው እንደ ቀዳሜ ሰማእት እስጢፋኖስም ፀጋንና ሞገስን የተመላ ሆነ።

ከጥቂት ቀኖች በኃላም በጌታችን ትእዛዝ ቅስና ተቀበለ። በፆም በፀሎት በስግደት በብዙ ትጋትም እየተጋደለ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ኖረ። በበረሀም ብዙ ዘመናትን ሲኖር ነፍሱን "ነፍሴ ሆይ እወቂ በእግዚአብሔር ፊት ራቁትሽን ትቆሚ ዘንድ እንዳለሽ እንግዲህስ ፅኚ በርቺ ታገሺ!" ይለት ነበር። ቆዳው ከዐጥንቱ እስቲጣበቅ ያለ መብልና ያለ መጠጥ በእንዲህ ያለ ግብር በገድል ተጠምዶ ኖረ።ከእፅዋት ፍሬዎች ወይም ከእንጨት ስሮች አልተመገበምና ለስጋውም የሚጠቅም ምንም ምን ምክንያት አልፈለገም።

ለገብረ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ አለው ከእንግዲህ በአለም ካሉ ሰዎች ከካህናት ከመነኮሳት ወይም ከምእመናን ህዝባውያን እንዳያውቁህ አደርግልሀለሁ። እንዳንተ ካሉ በቀር አንተ ራስህ ብትፈቅድ እንጂ መላእክትም ይጎበኙሀል። የብርሀን ሰረገላም ይሁንልህ መድረስ ወደምትሻበት ሁሉ ብረር እኔንም ማየትና በፈለግህ ጊዜ ከአባቴና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በሶስትነቴ ታየኛለህ። አሁንም ወደ ኢትዮጵያ ምድር ሂድ በዚያም ከደይን የምታወጥቸው ነፍሳት አሉህ አለው።

ከዚህም በኃላ ስልሳ አንበሶች ስልሳ ነብሮች በፊት በኃላ አጅበውት ወደ ኢትዮጵያ ምድር ተጓዙ። የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ገብርኤልም ከአንበሶችና ከነብሮች ጋር በነፋስ ሰረገላ አሳፍሮ ይመራው ነበር። ወደ ምደረ ከብድም አደረሰው ከዚያም ወደ ልዩ ተራራ ወደ ደብረ ዝቋላ ወሰደው።

አባታችንም በባህሩ ቁሞ ምስራቁን ምዕራቡን ሰሜኑን ደቡቡን አራቱን ማእዘን ተመለከተ።የኢትዮጵያ ሰዎች የሚሰሩትን ኃጢአታቸውን በአይኖቹ ፊት የተገለጠ ሆኖ አየ። በራሱም ተዘቅዝቆ ተወርውሮ ወደ ባህሩ ውስጥ ገባ እሊህን የእጅህ ፍጥረቶች የሆኑትን ካልማርካቸው ከእዚህ ባህር እንዳልወጣ በእግሮቼም እንዳልቆም በህያው ስምህ እምላለሁ እያለ ማለ እንዲሁም ሆኖ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ኖረ።

ስምህን የጠራውን መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሀለሁ የሚል ቃል በመልአክ አማካይነት ወደ አባታችን መጣ። አባታችንም መልአኩን መላውን የኢትዮጵያን ሰው ካልማረልኝ ከዚህ ባህር አልወጣም አለው መልአኩም ከአጠገቡ ሄደ።

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም በዚያ ባህር ውስጥ መቶ ዓመት ኖረ ስጋው ሁሉ አለቀ ደሙም በባህሩ ውስጥ ፈሰሰ አጥንቶቹም እንደበረዶ ነጭ ሆነው ታዩ። አጋንንትም ከአራቱ ማእዘን በየቀኑ ሰባት መቶ ሽህ ሶስት መቶ ሽህ እየሆኑ በመምጣት በቀስታቸው ይነድፉታል እስከ መቶ አመትም አጥንቶቹን በሻፎ ድንጋይ ይፍቁታል ይህን ሁሉ መከራ በትእግስት ሲቀበል ኖረ።

ከዚህም በኃላ ጌታችን ወደርሱ መጥቶ ከባህሩ ዳር ቆመ። አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስንም መላውን የኢትዮጵያ ሰው ምሬልሀለሁና ተነስተህ ውጣ አለው ያንጊዜም ወጣ አጥንቶቹም እንደ ወንፊት ቀዳደሰ የተበሳሱ ሆነው ተገኙ ጌታም ዳሰሰውና ጤነኛ አደረገው ወደ ምድር ከብድም ሰደደው።

ከዚያም ወደ ላይ ወጥቶ ከፀሀ ከሰማይ በታች እስከ ሰባት አመት ኖረ። ዳግመኛም ወደ ምድረ ከብድ ተልኮ እንደ አምድም የተተከለ ሆኖ ሰባተረ አመት ቆሞ ኖረ። ወደ ሰማይም ሲመለከት ቅንድቦቹን አልከደነም ራሱንም ወደ መሬት ዝቅ አላደረገም ነበር እጆቹም ወደ ሰማይ ተዘርግተዋል። እነሆ ሰይጣንም በቁራ ተመስሎ መጣ አይኖቹንም ወደ ሰማይ ያንጋጠጡ ሁለቱን አይኖቹን አንቁሮ አሳወረው። እርሱ ግን ምንም ሳያጓድል እስከ ሁለት ሳምንት ድረስ እንደ ቀድሞው በመትጋት ሲፀልይ ኖረ።

ከዚህም በኃላ ሚካኤልና ገብርኤል መጥተው በፊቱ ቆሙ በሁለቱ አይኖቹ ላይም እፍ አሉበት ብርሀንም ተሰጥቷቸው እንደ ቀድሞው አዩ። ከሰማይ ታላቅ ኃይል ተሰጥቶሀልና ጠላቶችህን ትበቀላቸው ዘንድ ወደ ዝቋላ ሂድ አሉት ከዚያም መላእክት ከአጠገቡ ሄዱ። እርሱም ተነስቶ ወደ ዝቋላ ተጓዘ በጎዳናም ሲጓዝ ሶስት ሽማግሌዎች ከእንጨት ጥላ በታች ተቀምጠው አየ አባታችንም በአያቸው ጊዜ ልሰውራቸው ብሎ በልቡ አሰበ። እንርሱም ፈጥነው በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጥነናልና ሶስታችንንም በጀርባህ እያዘልክ አንዳንድ ምእራፍ ሸኘን እንጂ አትተውን ብለው ተጣሩ። በመጣም ጊዜ ሁለመናቸውን ሽበት የከበባቸው የደከሙ ሽማግሎች ሁነው አገኛቸው አንደኛውንም አንስቶ በጀርባው አዘለው ወደ አንድ ምእራፍም አደረሰው ሽማግሌውም ከዚህ አሳርፈኝ አንተ ደክመሀል የማትበላ የማትጠጣ ስለሆንክ አለው አባታችንም ሽማግሌ ሆይ በምን አወቅከኝ አለ።

ሽማግሌውም ሂደህ ባልንጀሮቼን አምጣልኝ አለው ተመልሶ ሁለቱ ወደአሉበትም ደርሶ ሁለተኛውን ሽማግሌ በጀርባው አዝሎ ወደ ቀደመው ሽማግሌ አድርሶ አብሮ አስቀመጠው ሶስተኛም ተመልሶ ሶስተኛውን ሽማግሌ አዝሎ ሁለቱ ወዳሉበት አድርሶ በአንድነት አኖረው፡፡ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም እነዚያን አረጋውያን እናነተ ከወዴትናችሁ መአዛችሁ ልብ ይመስጣል እጅግም ደስ ያሰኛል አላቸው።እነርሱ ግን ተነስተው ቆሙ አንድ ሲሆኑ ሶስት ሶስት ሲሆኑ አንድ መሆናቸውን ገለጡለት የአባቶች አለቃ አብርሀም እንደ አየ።

ያንጊዜም የእግዚአብሔርን የጌትነቱን ክብር አየ የእሊያ አረጋውያንም ፊታቸው ተንቦገቦገ ከፀሀይና ከመብረቅ ብልጭታም ሰባት እጅ በራ አባታችንም በምስጢራት ጎርፍ የተዋጠ ሆኖ ፈራ ተንቀጠቀጠ በምድር ላይም ወደቀ። ህልምን የሚአልምም መሰለው ከዚያም ጌታችን አባታችንን አነቃውና መቶ አመት ያህል ስጋህን ሲነዱፉህ አጥንቶችህን ሲፍቁህ የኖሩ አጋንንትን ታጠፋቸው ዘንድ ወደ ዝቋላ ተራራ ውጣ አለው።

እኔ እንደ ወሰድኩህ ባለማወቃቸው በባህር ውስጥ አለ በማለት በትእቢት ላይ ናቸው ሰባቱ ሊቃነ መላእክትም ይረዱሀል መባርቅትም በፊት በኃላ ሆነው ይከተሉሀል አለው።

ያን ጊዜ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ በመብረቅ ላይ ተጭኖ በረረ እነዚያ አጋንንት ወደአሉበትም ወረደ። ደመናትም ከበቡአቸው

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የጥቃት ዓላማ ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እንዲቆሙ ምእመናን ጠየቁ !

መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዒላማ ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እና መልእክቶች በአፋጣኝ እንዲቆሙ እና መንግስትም ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ቲኤምሲ ያነጋገራቸው ምእመናን ገልጸዋል።

ማናቸውም ቤተ እምነቶች መብቶቻቸው እንዲከበር እንደሚፈልጉትና የሃይማኖታቸውን አስተምህሮ በነጻነት ማስተላለፍ ሕገ መንግስታዊ መብታቸው እንደሆነ የጠቆሙት አስተያየት ሰጪ ምእመናኑ በተመሳሳይም ሁሉም ቤተ እምነቶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነት እና አስተምህሮ ባከበረ መልኩ ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት ነጻነታቸውን ተጠቅመው በማናቸውም መልኩ ሃይማኖታቸውን ማራመድ ሕገ መኖግስታዊ መብታቸው ቢሆንም የሌላውን እምነት ማንቋሸሽ፣ ማኮሰስ እና ማጥላላት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እና ግጭት ቀስቃሽና ጸረ ሰላም እንቅስቃሴ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ባለፉት ጊዜያት ከአንዳንድ ቤተ እምነት ተከታዮች ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ቅዱሳን፣ ስለ ንዋያተ ቅድሳት ብሎም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት በምታስተምቸው ትምህርቶች ላይ ትኩረት ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች ሲተላለፉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የብፁዕ  ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  ፲፪ኛ ዓመት  በዓለ ሢመት እየተከበረ ይገኛል

የካቲት ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፲፪ኛ በዓለ ሢመት  በዛሬው ዕለት  የካቲት ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከናወነ ነው።

©Eotc broadcast

@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ቅድስት"
በኩር ናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእርሷ ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን
               አዝ===
በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና
መልካም ስራ ሚሠራባት ሰንበት ቅድስት ናትና
ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነጻነት
እግዚአብሔር ይህን ሰጠን ደስ ይበለን በሰንበት
               አዝ===
ለአብርሃም ተገልጣለች ለሙሴም በደብረ ሲና
በነቢያት የታወቀች ሰንበት ደሀራዊት ናትና
በሳምንቱ ሠለጠነች ተሰበከች በሀዋሪያት
ሀሌሉያ እለተ ሰንበት ተሰጠችን ልናርፍባት
               አዝ===
በእልልታ እንሞላ እንደነቢዩ አሳፍ
በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ
በመቅደሱ ናቸውና ቅዱስነት እና ግርማ
ቅዳሴአችን ይሰማልን ከምድር እስከ ኢዮር ራማ
               አዝ===
እግዚአብሔር አብ የባረካት እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት
ከእለታት ሁሉ መርጦ መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያረጋት
በእርሧ ሀሴት እናድርግ እናክብራት እንድንከብር
ከደጀ ሰላሙ ታዛ ከመቅደሱ እንሰብሰብ

©በዲያቆን ዘማሪ ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

፣በዕዳ የሚጠየቅም ሆነ የሚጠይቅ ሁለቱም በአንድነት ቅዱስ ቃሉን ሲሰሙ ዋሽቶ የሰው ዕዳ ያልከፈለውም ተጸጽቶ ይክሳል ወራት ብሶበት ቀን ጥሎት መክፈል ላልቻለውም ምህረት ይቅርታ እንዲያገኝ ቅዱስ ቃሉ ጸሎቱ ምክንያት ይሆነዋል ። በዚህም የተነሳ ሁለቱም ወገኖች በክፉ ከመፈላለግ ይልቅ የይቅርታ የምህረት ሰዎች ይሆናሉ። በዚህች በኵረ በዓላት በምትሆን በቅድስት በዕለተ ሰንበት የምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት ይባረካል ይቀደሳል በዚህ ታሳቢነት ዕለቱም ዕለተ ቅድስና መሆኑን ለማጠየቅ ቅድስት ተብሏል ።

ቅድስና የተፈቀደልን ብቻ ሳይሆን የታዘዝነውም ጭምር ነው “እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ” (ዘሌ.፲፱፥፪) በዚህ ኃይለ ቃል ውስጥ ቅድስና እንደ ፈቃድም እንደ ትእዛዝም ሆኖ ተሰጥቶናል፤ እግዚአብሔር ያልፈቀደውን ነገር አድርጉ ሁኑ ብሎ አያዝም።የቅድስና ሕይወት መሰረቱ የእግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ ሆኖ ሳለ ለመቀደስ የእኛ መሻት መፈለግ ዝንባሌም ወሳኝ ነው። ለዚህም ነው ሐዋርያው እንዲህ ሲል የጻፈልን “ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥” (ዕብ. ፲፪፥፲፬) ምንም አንኳን ቅድስና የተፈቀደና የታዘዘ ቢሆንም የውዴታ እና የነጻ ፈቃድ ውጤት እንጂ የምንገደድበት አይደለም፡፡እግዚአብሔር ፍቅሩ ገብቶን ወደን እና ፈቅደን በፈቃዱ እና በትእዛዙ ስንመራ ያስደስተዋል እንጂ ተገደን ፈርተን ተንቀጥቅጠን እንድንገዛለት አይወድም፡፡

ወደ ቀደመ ነገራችን ስንመለስ ዕለተ ሰንበትም ቅድስት መባሏ ከላይ ያብራራነውን መሰረታዊ ሃሳብ በተከተለ መልኩ ነው። ዕለቲቱ ቅድስት መባሏ ዋና ዓላማ በሰዎች እና በእግዚአብሔር መካከል ለቅድስና ሕይወት ምልክት ማስታወሻ እንድትሆን ነው። በባህሪው ቅዱስ የሆነ አምላክ ዓለምን የማዳን ስራውን የጀመረበትን ጽንሰቱን እንዲሁም የማዳን ስራውም አጠናቆ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ዘላለማዊ ሕይወትን ያበሰረበትን ትንሳኤውን የምናስብበት በመሆኑ የዕለቱ ቅድስና የፈጣሪን ቅዱስ ተግባር የምናደንቅበት ከማንኛውም የሥጋ ሥራ ተለይተን የዋለልንን ውለታ ከፍ ከፍ እያድረግን እርሱን የምናመሰግንበት ዕለት ነው። ይህም እኛን ወደ በለጠ የቅድስና ሕይወት የሚያሸጋግረን ከመሆኑም በላይ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ፍቅር በየጊዜው እንድናስብና በፍቅሩም እንድንኖር ያግዘናል፡፡
©ተሚማ

ምስባኩ፦ መዝ ፺፭፥፭
"እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ አሚን ወሠናይት ቅድሜሁ ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ"
"እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ ምስጋና ውበት በፊቱ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው"

በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ መልእክታት
-፩ኛ ተሰ ፬፥፩-፲፫
-፩ኛ ጴጥ ፩፥፲፫ እስከ ፍጻሜ
-የሐዋ ሥራ ፲፥፲፯-፴

ወንጌሉም፦ ማቴ ፮፥፲፮-፳፭

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ዘወረደ"
በእርሱ ፍቃድ በአባቱ ፍቃድ
በመንፈስ ቅዱስ ፍቃድ
ከሰማያት ወረደ ከድንግል ማርያም ተወለደ።

ዓለሙን እንዲሁ ወደደና
ከሰማያት በላይ ወረደና
በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት
ተወሰነ አምላከ አማልክት

  ከሰማያት የወረደው ፍቅር ስቦት የመጣዉ
  ወልደ አብ ወልደ ማርያም ኢየሱስ ፈራጅ ነዉ
               አዝ===
ቅድመ ዓለም ተወልዶ ያለ እናት
ድህረ ዓለምም ያለ አባት
የእግዚአብሔር ልጅ በእርግጥም ሰው ሆነ
ሁሉ በእርሱ ይኸው ተከናወነ

  ከሰማያት የወረደው ፍቅር ስቦት የመጣዉ
 ወልደ አብ ወልደ ማርያም ክርስቶስ አምላክ ነዉ
               አዝ===
የማይታይ ታየ በምድር
ረቂቁ ገዘፈ ስለፍቅር
ሥጋን ተዋሕዶ ሆነልን ፈውሥ
አማኑኤል የነገስታት ንጉሥ

ከሰማያት የወረደው ፍቅር ስቦት የመጣዉ    
ወልደ አብ ወልደ ማርያም እግዚአብሔር እርሱ ነዉ

©በዲያቆን ዘማሪ ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ዘወረደ
የዐብይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት

የመጀመሪያ የዐብይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል። በዚህ ቀን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ ወደ ምድር መውረድ ይሰበካል ይዘመራል። ሰውም በታላቅ ፍርሃት ወደ አምላክ መቅረብ እንዳለበት ይነገርበታል።

ደግሞም ጾመ ሕርቃል ይባላል። ስያሜውም በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱንም አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅዱሳን ዘረፈ: 60 ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3 ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማውንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል።
በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተስብሰበው ከ14 ዓመት በኃላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲያኑ የሮም ንጉስ ሕርቃል ይነግሩታል። እርሱም "ሐዋሪያት ሰው የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው?" አላቸው "እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማን" ብለን አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል።

ምስባኩም:- መዝ ፪፥፲፩
"ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሰዩ ሎቱ በረዓድ አፅንእዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐፅ"
"ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ በርአድም ደስ ይበላችሁ ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቆጣ"

በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡት ጥቅሶች:
-ዕብ ፲፫፥፯-፲፯
-ያዕቆብ ፬፥፮ እስከ ፍጻሜ
-የሐዋ ሥራ ፳፭፥፲፫ እስከ ፍጻሜ

ወንጌሉም:- ዮሐ ፫፥፲-፳፭
"¹⁰ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን?
¹¹ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም።
¹² ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?
¹³ ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።
¹⁴-¹⁵ ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።
¹⁶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
¹⁷ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።
¹⁸ በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።
¹⁹ ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው።
²⁰ ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤
²¹ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።
²² ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ፥ በዚያም ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ ያጠምቅ ነበር።
²³ ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና ያጠምቅ ነበር፥
²⁴ እየመጡም ይጠመቁ ነበር ዮሐንስ ገና ወደ ወኅኒ አልተጨመረም ነበርና።
²⁵ ስለዚህም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል ስለ ማንጻት ክርክር ሆነ።"

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ዐብይ ጾም
-------------------------------
@Ethiopian_Orthodox
-------------------------------
ጾም ማለት "ተወ"፣ "ታቀበ" ፣"ታረመ" ካለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው። ፍቺውም ምግብ መተው ፤መከልከል፤ መጠበቅ ማለት ነው።
ጾም ማለት ሰውነት ከሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል፤ መወ'ሰን ማለት ነው። ወይም ሰውነት የሚያምረውን የሚያስጎመጀውን ነገር መተው ማለት ነው። ጾም ከሃይማኖት ጋር ዝምድና ስላለው ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ጾም አለ።
✳️ ጾም በብሉይ ኪዳን ከፍተኛ ቦታ አለው።
ነብያት ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ወራት እህል ውሃ በአፋቸው አይገባም ነበር። (ዘፀ 30÷34-28)
✳️ በኃጢአት ብዛት የታዘዘውን የእግዚአብሔርን መዓት የሚመልሰው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑት ሲማልዱት ነበር። (ዮሐ 2÷7-10)
✳️ በሐዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሰራሽ ህግ ሳይሆን እራሱ መድኃኒታችን በመዋዕለ ሥጋዌው የሥራ መጀመሪያ አድርጎ የሰራው ህግ ነው።
✳️ ይህ ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር መንፈስ እርኩስ ሰይጣን እንኳን በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግራል።(ማቴ 17÷21)
✳️ ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ የታዘዙት ሐዋርያትም ከመንፈስ ቅዱስ በየጊዜው ትዕዛዝ የሚቀበሉበት በጾም እና በጸሎት ላይ እንዳሉ ነበር።(ሐዋ 13÷2)
✳️ ለስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናት ቀሳውስት የሚሾሙት በጾምና በጸሎት ነበር። (ሐዋ 13÷3)

ጾምስ በታወቀው እለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ መከልከል ነው።
ጾም ማለት ጥሉላት ማባልዕት ፈፅሞ መተው ሰውነትንም ከመብልና ከመጠጥ ከሌላውም ክፉ ነገር ሁሉ መጠበቅ፣ መግዛት፣ መቆጣጠር፣ በንስሐ ታጥቦ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ "ይቅር በለኝ" በማለት ቅድመ እግዚአብሔር በመንበረከክ ምሕረት ለአምላክ ለመቀበል መዘጋጀት ነው።

ፆም ነፍስን ቁስልን የምትፈውስ፣ ሀይለ ፍትወትን የምታደክም የበጎ ምግባር ሁሉ መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጸጋን የምታሰጥ የወንጌል ስራ መጀመሪያ ፣ የፅሙዳን ክብራቸው፣ የደናግል የንፅህና ጌጣቸው ፤የንፅህና መገለጫ ፣ የጸሎት ምክንያት እናት፤ የእንባ መናኛ መፍለቂያ አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ስራ ሁሉ የምታነቃቃ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትህትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት።
ከህገ ልቦና ከነበሩ አበው አንስቶ በዘመነ ኦሪት እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ ቀደምት አበው ነቢያት፣ ነገሥታት፣ ካህናት በፆምና በጸሎት ፅመድ ሆነው እግዚአብሔር አምላካቸው ከክፉ ነገር እንዲሰውራቸው በይቅርታ እንዲጎበኛቸው ሀይልም እንዲጎናፅፋቸው ተማፅነው ሀሳባቸውን ፈፅሞላቸዋል።

በሀዲስ ኪዳን ጾም ስለ ፅድቅ ተብሎ መከናወን ያለበት አብይ ተግባር ነው።// ማቴ 5÷6//
ስጋዊ ጥቅምን ለማግኘት ተድላ ሰጋን በመሻት ሳይሆን ዘላለማዊ መንግስት ለመውረስ ስለ ፅድቅ ተብሎ የሚፈፀም ነው።
ጾም እንደምን ነው ቢሉ የስጋ ምግባር ነው። ምፅዋት የገንዘብ ግብር እንደሆነች አንድም ምፅዋት ስጋን መገበር ነው።
ምፅዋት ገንዘብ መገበር እንደሆነች ~~~ ስለዚህም የሚፆም ሰው በፈቃደ ስጋው ላይ ድልን ይቀዳጃል።
በእምነት ሆኖ የለመነውን እግዚአብሔር ይሰጠዋል። ሰማያዊ የሆነውን ምስጢር ለማየት ከዓለማዊነት ነገሮች ተለይቶ ይነጠቃል። በዓለም እየኖረ ከዓለሙ ይለያል። ከዓለም አይደለምና //ዮሐ 15÷19//

🔰ዐብይ ጾምም ቤተክርስቲያናችን እንድንጾም ካወጀችልን ጾም አንዱ ነው።
አብይ ጾም የተለያዩ ስሞች አሉት:
፩. ዐብይ ጾም: ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም በመሆኑ እንዲሁም ዐብይ እግዚአብሔር ወዓቢይ ኀይሉ ዓቢይ እግዚአብሔር ወብዙኃ አኰቴቱ የተባለ ጌታ የጾመው ስለሆነ፣ //መዝ 47÷1 መዝ 146÷5//
ዐብይ ጾም መባሉ ትልቅና ታላቅ ጾም መሆን ለማሳወቅ ነው። ይህ ጾም ታላቅ መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መጾሙና ከሌሎች አፅዋማት ጋር ሲነጻጸር በቁጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንጦስ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያና ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የጾመው ጾምም በመሆኑ ነው።

፪. ሁዳዴ ጾም: ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት ሥራ ሁዳድ ስለሚባል ሲሆን ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ኃያሉ አምላካችን ስለጾመው ነው።፣ /አሞ 7÷1 //
፫. በዓተ ጾም : ፆም መግቢያ፣ መባቻ ወይም ጾሙ የሚሰፍርበት በዓል ማለት ነው
፬. ጾመ አርቦ: ጌታችነ ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመዉ 40// አርባ ቀን ስለሆነ ነው //ማቴ 4÷1
፭. ጾመ ኢየሱስ : ጾሞ ፣ ጹሙ ብሎ ስላዘዘን፣
፮. ጾመ ሙሴ : ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ሰኞ "ዕዝል ከመዝ ይቤ ሙሴ እስመ ለዓለም ፣ ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት" እያለ በጾመ ድጓ ስለ ዘመረ ነው።

🌿ዐብይ ጾም ጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው። //ማቴ 4÷1
ምእመናንም ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል።
🌿ዐብይ ጾም ስምንት ሳምንታት //55 ቀኖች // አሉት። 7//ሰባት ቅዳሜ 8//ስምንት እሁድ ይገኛሉ። አስራ አምስት ቀን 55//ማለት ነው። ከጥሉላት እንጂ ከእህል ወኃ ስለማይጾሙ የጾሙ ወራት አርባ ቀን ብቻ ይሆናል።

የዐብይ ጾም ሶስት ክፍሎች
፩. ዘወረደ ( ጾመ ሕርቃል)፦ ይህም ጾሙ ከሚገባበት ሰኞ ጀምሮ እስከ እሁድ ያረሰ ያለው 7 ቀን ነው።
፪. የጌታ ጾም፦ ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው አርባ ቀን ነው።
፫. ሕማማት፦ ይህ ጌታችን በአልዓዛር ቤት ለማዕድ ከተቀመጡበት የሆሳዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሥዑር ቅዳሜ ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት ነው።
ይህም ፯+፵+፰=፶፭(7+40+8=55)ቀን ይሆናል።

የዐብይ ጾም ሳምንታት 8 ሲሆኑ:
፩. ዘወረደ
፪. ቅድስት
፫. ምኲራብ
፬. መጻጉዕ
፭. ደብረ ዘይት
፮. ገብርሔር
፯. ኒቆዲሞስ እና
፰. ሆሣዕና ናቸው።

ጾሙን ጾመን ድኅነት የምናገኝበት የበረከት እንዲሁም ቤተክርሰቲያናችንንና ሐገራችንን ከመዓት የምንታደግበት ያድርግልን! አሜን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…
Subscribe to a channel