ethiopian_orthodox | Unsorted

Telegram-канал ethiopian_orthodox - የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

30344

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Subscribe to a channel

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

እያንዳንዱ ሰው የገዛ ሕይወቱን ቢመረምር ከላይ የተጠቀሰውን የእግዚአብሐር ጠባቂነት የሚያረጋግጥ ገጠመኝ ይኖረዋል፡፡ በዝሙት ለመውደቅ ባለው ኃይል ተጠቅሞ ሲጣጣር፣ ከሰው ሲደበቅ፣ ሥውር ቦታ ሲሻ፣ ምቹ ጊዜ ሲጠባበቅ ባልጠበቀው ሁኔታ እግዚአብሔር ዕቅዱን ያላፈረሰበት ድንግል ነኝ ባይ ከቶ አይገኝም፡፡ እንደ ሰውዬው ፈቃደኝነት፣ የልቡና ምኞትና ለዝሙት መዘጋጀት ቢሆን ኖሮ ድንግልናውን ከጊዜያት በፊት ባፈረሰው ነበር። እንደዚህ ከሆነ እግዚአብሔር ጠብቆ ባቆየው ድንግልና መመካት ይገባልን? በጭራሽ ይልቁኑም «ጥበቃውን ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን» እያሉ ፈጣሪን ማመስገን ለሁሉም የሚገባ ነው።
ከተፈጥሮተ ሥጋ ተፈጥሮተ ነፍስ እንደሚበልጥ ከድንጋሌ ሥጋም ድንጋሌ ነፍስ ይበልጣል። ታዲያ በሥጋ ድንግል መሆናችን ትዕቢትና ትምክህት ፈጥሮ የነፍስ ድንግልና እንዳይኖረን የሚያደርግ ከሆነ እግዚአብሔር ትሑት ሆነን የነፍስ ድንግልናችን እንዲጠበቅልን ለማድረግ የሥጋ ድንግልናችንን በማይረባ ምክንያት እንዲጠፋ ጥበቃውን ከእኛ የሚያርቅበት ጊዜ አለ። እግዚአብሔር «ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣልና» ያዕ 4÷6
የሐሳዌ መሢሕ (የሐሰተኛው ክርስቶስ) እናት ከነገደ ዳን የተወለደች ናት፡፡ የሐሰት ነቢያት «በድንግልና ፀንሰሽ በድንግልና ትወልጃለሽ› እያሉ ትንቢት ይናገሩላታል፡፡ ለጊዜው ድንጋሌ ሥጋ ነበራትና ትዕቢት ያድርባታል:: ከዚያ በኋላም ከመቃብረ አረሚ (የአረማዊያን መቃብር) ቆማ ስትጸልይ ከነገደ ዔሳው የተወለደ አንድ ዓይና ጎልማሳ ከወደ ምሥራቅ ይመጣና ከክብር ያሳንሳታል፡፡ በዚህ ጊዜ ፀንሳ ልጅ ትወልዳለች፡፡ አንድ ጊዜ መንፈሰ ትዕቢት አድሮባታልና በድንግልና ፀንሼ በድንግልና ወለድሁት ትላለች፡፡ ልጇም ተወልዶ ሲያድግ አምልክ ነኝ ፈጣሪ ነኝ ማለት ይጀምራል፡፡ (ራእ13÷1 ትርጓሜ)
ከላይ የተጠቀሰችው የሐሳዌ መሢሕ እናት ገና ለወደፊት የምትመጣ ናት፡፡ ሆኖም ግን ትዕቢቷና ክፉ ግብሯ አስቀድሞ ታውቆ ተገልጧል።ትዕቢቷና በድንግልናዋ መመካቷ ለመደፈር አበቃት።ሰው ሲመካ ረድኤተ እግዚአብሔር ይለየዋል። በዚህ ጊዜ ከላይ እንደ ተጠቀሰችው ሴት ለብዙ ክፉ ነገሮች ይጋለጣል፡፡ አንችም እኅቴ በድንግልናሽ ብትመኪ ዕጣሽ ከዚህ የተለየ አይሆንም:: በድንግልናዋ የምትመካና ድንግል ሳትሆን «ድንግል ነኝ» እያለች የምትዋሽ ሴት ሁሉ በግብርዋ የሐሳዌ መሢሕ እናትን መምሰሏ ጥርጥር የለውም፡፡
እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን እጅግ የሚያስደንቅ ትሕትናን ተጐናጽፋ እናያታለን፡፡ ትንቢተ ኢሳይያስን በምታነብበት ጊዜ «እነሆ ድንግል ትፀንሳለች» ከሚለውን አንቀጽ ስትደርስ «አምላክን ለመውለድ ለታደለች ለዚያች ሴት ከዘመንዋ በደረስኩና ወጥቼ ወርጄ ባገለገልኳት ትል ነበር እንጂ እኔ ብሆን ወይም እኔ ነኝ›› አላለችም:: በዚህ ሐሳቧና ንግግሯ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴው «ደብር ነባቢት በትሕትና፣ በትሕትና የምትናገር ተራራ» በማለት አወድሷታል:: (ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘረቡዕ)
አምሳያ ከሌለው ድንግልናና ንጽሕናዋ ጋር ይህን የመሰለ ትሕትና ይዛ በመገኘቷ «ወደ ትሑት፡ በቃሌም ወደ ሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ፡፡» ኢሳ66÷2 በማለት የተናገረ እግዚአብሔር በድንግል ማርያም ማኅፀን አደረ፡፡ ድንግል ማርያም ከትሕትናዋ ብዛት የሁሉን ፈጣሪ ከፀነሰች በኋላ እንኳን ስትጸልይ «የባሪያውን ትሕትና ተመልከቷልና› አለች እንጂ, «የእናቱን ትሕትና» አላለችም:: መመካት ቢያስፈልግ ከድንግል ማርያም በቀር የሚያስመካ ድንግልና ያለው የሰው ዘር አልነበረም፡፡ እርሷ ካልተመካች ሊመካ የሚችል ማን ይኖራል? ሉቃ1÷ 48
በሥጋ ንጽሕናና በድንግልና መመካትና በሌሎች መፍረድ አይገባም። ይህ ትዕቢት ነውና፡፡ ትላንት በትዕቢታቸው ምክንያት ብዙዎችን ያዋረደና ያሳፈረ እግዚአብሔር ዛሬም በድንግልናቸው የሚመኩትን ሰዎች ብቃታቸው ከራሳቸው እንዳልሆነ ያውቁ ዘንድ በሚያሳፍር ሁኔታ ሊጥላቸው ይቻለዋል፡፡ በድንጋሌ ሥጋ ከሚመካ ትዕቢተኛ ድንጋሌ ሥጋ የሌለው ትሑት ሰው በእጅጉ ይሻላልና መመካት አያስፈልግም::

በቀጣይ ምዕራፍ ስምንት ክፍል ሰባት :
👉 ስለ ድንግልና ማልቀስና መጾም ይገባል!
👉 ድንግልናን ማቃለል ያስቀስፋል!
👉ድንግል ሴት ትፈልጋለህ? በሚል ይቀጥላል....

ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ስምንት ክፍል ስድስት
.................................................


ድንግልና ያስመካል?
ድንግልናን መጠበቅ መልካም ነገር ቢሆንም የሚያመጻድቅና ብዙ የሚያስመካ ግን መሆን የለበትም:: «ድንግል ነኝ እኮ!» ብሎ መመጻደቅ የሚያስከትለው ወቀሳና መዘዝ ድንግልናን ከማጣት በላይ ነው። አንድ ሰው በድንግልናው የሚመጻደቀው መንፈሳዊነት ሲጐድለውና ዕውቀቱም ያነሰ ሲሆን ነው፡፡
ነቢዩ ኤልያስ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ድንግላዊ ኑሮ ነበረው፡፡ በተጨማሪም ለእግዚአብሔር ቀናዒና ንጹሕ የሆነ አምልኮት የነበረው ታላቅ ነቢይ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ መልኩ የሚኖረው እሱ ብቻ ይመስለው ነበር፡፡ ስለዚህ አንድ ቀን ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር «እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ» ሲል እናነባለን፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር «ከእስራኤል ጉልበታቸውን ለበኣል (ለጣዖት) ያላንበረከኩትን ሁሉ፣ በአፋቸውም ያልሳሙትን ሁሉ ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀራለሁ።» በማለት መልሶለታል፡፡ 1ነገ19፥14(18)
ዛሬም ቢሆን ደናግላን የሉም ማለት አይቻልም።ጉልበታቸውን ለዝሙት ያላንበረከኩ የልጅ ፍቅር፣ የሴት ከንፈር ያልማረካቸው ወንዶችና የወንድ ፍቅር ያላገበራቸው ብዙ ሴቶች አሉ፡፡ በንጽሕና ኖረው ለምናኔ፣ ለምንኩስና የሚበቁ «ሰባት ሺህ» የመንግሥተ ሰማያት ዜጐች ለእግዚአብሔር አሉት፡፡«ሰባት» ቁጥር በዕብራውያን ፍጹም ቁጥር ነውና፤ «ሰባት ሺህ ዜጎች ለእግዚአብሔር» አሉት ማለት ፍጹም ብዙ ቁጥር ያላቸው ወዳጆች አሉት ማለት ነው፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ዮም ፍሰሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም"
ዘማሪ ፍቃዱ አማረ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

🌿 "ኢያቄም ወለዳ" 🌿
ኢያቄም ወለዳ ኢያቄም(፪)
ዳዊት ዘመዳ ኢያቄም ወለዳ።(፬)

ከሰማይ እግዚአብሔር ክንዱንም ሰደደ
ማደሪያው እንድትሆን ጽዮንን ወደደ
ከእሴይ ዘር ሐረግ ከዳዊት ወገን
መረጣት ንጉሱ ማደሪያው እንድትሆን

ዳዊት ዘመዳ ኢያቄም ወለዳ(፬)

ሁለቱ አዕሩግ ቅዱሳን የሆኑ
በምግባር ትሩፋት በዕምነት የጸኑ
ኢያቄም ወሐና የሐይማኖት ፍሬ
የአምላክን እናት አስገኙልን ዛሬ

ዳዊት ዘመዳ ኢያቄም ወለዳ(፬)

ኢያቄም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት
የሐና ማኅጸን ምንኛ ድንቅ ናት
ማርያም ሆይ ልደትሽ ጽልመትን ገለጠ
መልአከ ሞት ፈራ ሰይጣን ደነገጠ

ዳዊት ዘመዳ ኢያቄም ወለዳ(፬)

ሰላም ለልደትሽ ለሰው ዘር ለሆነው
ለጽንሰትሽ ሰላም ድውያንን ላዳነው
እግዚአብሔር ከፍጥረት ዘር ባያስቀርልን
ሰዶምን በመሰልን ገሞራንም በሆንን

ዳዊት ዘመዳ ኢያቄም ወለዳ(፬)

ኢያቄም ወለዳ ኢያቄም(፪)
ዳዊት ዘመዳ ኢያቄም ወለዳ(፬)
በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

.....ያሳታትን ዲያብሎስ በቅድስና መንገዷን ሰውራ የምታስተውን (ግራ የምታጋባውን) መድኃኒት ልጇን ተወልዳ አይታ በደስታ አነባች፡፡ የፍጥረት እናትና አባት የሆኑ አዳምና ሔዋን ልጃቸውን እናታችን፣ ካሳችን፣ መድኃኒታችን፣ ሰማያችን ተወለደች እያሉ ሲደሰቱ ሲያመሰግኑ ልጆቻቸውም ከእነርሱ ጋር የባሕርያችን መመኪያ የድኅነታችን ቀርን ዛሬ ተወለደች እያሉ ተደሰቱ፡፡ ከአንድ ከዲያብሎስ በቀር ሁሉም ደስ አላቸው። እርሷም በኋላ እንኳን የቀደመው የኋላው ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል አለች። እንግዲያስ በእርሷ መወለድ እንደ ዲያብሎስ አይክፋን፤ ይልቁንም የፍጥረት ሁሉ አባትና እናት እንደሆኑት እንደ አባታችን አዳምና እንደ እናታችን ሔዋን፣ እንደ ነቢያትና አበው ሁሉ አብረን ደስ ይበለን፡፡ እንኳን ደስ አለን፤ ዛሬ የባሕርያችን መመኪያ፣ ሰማይ የደረሰችው መሰላል፣ እግዚአብሔር ከእርሷ ጋር ሆኖ አማኑኤል ተብሎ ከእኛም ጋር እንዲሆን ምክንያት የሆነችልን የእመቤታችን ልደት የእኛም የሁላችን ልደት ነውና፡፡
ሰማይ የደረስሽው መሰላል፣ ከምድር ባሕርያችን የተሠራሽ ሰማይ ሆነሽ የጽድቅ ፀሐይን ያወጣሽልን ሰማይ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ዛሬም የዲያብሎስ ግሣት የሆነውን ዘረኝነትን፤ መለያየትን እና ርኩሰትን አስወግጅልን፡፡ የባሕርያችን መመኪያ ሆይ ለአጋንንትና ለመናፍቃን መሳለቂያ አታድርጊን፡፡ በእኛ ጉድለት ምክንያት ታምነውባት አፈሩ፣ ተማጽነውባት መልስ አጡ እያለ ዝንጉዎችን እንዳያጠራጥር ቸሪቱ አማላጂቱ ሆይ በልደትሽ ስላስደሰትሻቸው ከሐፍረትና ከውረደትም ስላዳንሻቸው እናትና አባትሽ ስለኢያቄምና ስለሐና ፣ ስለአዳምና ሔዋን ብለሽ ድረሽልን፡፡
በእሥራኤል ትውፊት እሥራኤል በተጨነቁ ቁጥር ራሔል ስትጮህ ይሰማቸው እንደነበረ ዛሬም አንቺ ከጮሕሽ ልጅሽ ይምራልና በእውነት ይቅር ይለን ዘንደ ለምኝልን፤ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

በክርስትናው ለሚያምን ሁሉ እንኳን ደስ አለን፤ እንኳንም ለእናታችን ልደት ለሁላችንም የጋራ የልደት በዓል አደረሰን፡፡
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"መልክአ ማርቆስ"
በኆኅተ መንግስተ ሰማያት ሰንበት ትምህርት ቤት

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሚያዝያ ፴
ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ

ሚያዝያ ሠላሳ በዚች ቀን ለእስክንድርያ ሊቃነ ጳጳሳት አለቃ የሆነ ወንጌልን የጻፈ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት አረፈ።

የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አርስጦቡሎስ ነው እርሱም ከአምስቱ አገሮች የሆነ የእናቱም ስም ማርያም ነው እርሷም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ተጽፋለች እርሱም አስቀድሞ ስሙ ዮሐንስ ነው። በግብረ ሐዋርያት ማርቆስ በተባለ በዮሐንስ እናት ቤት ሐዋርያት ይጸልዩ ነበር ተብሎ እንደ ተጻፈ። እርሷም ባለጸጋ ነበረችና የዮናናውያንን የሮማይስጥን የዕብራይስጥን ትምህርት ለልጅዋ ለማርቆስ አስተማረችው።

በአደገም ጊዜ በርናባስ ወንጌልን ለመስበክ ከጳውሎስ ጋራ ሲሔድ ይዞት ሔደ በእነርሱም ላይ የሚደርስባቸውን መከራ አይቶ በጵንፍልያ ከተማ ሳሉ ትቷቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።

ሐዋርያትም በተመለሱ ጊዜ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን አሕዛብ እንደ ተመለሱ እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ላይ ድንቅ ተአምራትን እንዳደረገ ተናገሩ። ይህ ብላቴና ማርቆስም ከእርሳቸው ስለ መለየቱ አዘነ ተጸጸተ።

ከዚያም አብሮአቸው ሊሔድ ፈለገ አስቀድሞ ትቷቸው ስለተመለሰ ጳውሎስ ሊአስከትለው አልወደደም በርናባስ ግን ወሰደው አጎቱ ነውና። በርናባስም ከአረፈ በኋላ ወደ ሮሜ አገር ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሒዶ ለእርሱ ደቀ መዝሙሩ ሆነ በዚያም ቅዱስ ጴጥሮስ የተረጐመለትን ወንጌልን ጻፈ በሮሜ አገርም አስተማረበት። ከዚያም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትእዛዝና በሐዋርያትም ትእዛዝ ወደ እስክንድርያ አገር ሔደ። በውስጥዋም የከበረ ወንጌልን አስተማረ ደግሞም በአፍራቅያና በአምስቱ አገሮች በርቃ በሚባልም አገር ወደ እስክንድርያ ከተማ በገባ ጊዜ ጫማው ተቆረጠ።

በዚያም በከተማው መግቢያ ጫማ ሰፊ ነበረ። ቅዱስ ማርቆስም እንዲሰፋለት ለርሱ ሰጠው ሲሰፋም ጣቱን ወግቶ ሰነጠቀው ከእርሱም ደም ፈሰሰ በዮናኒም ቋንቋ ኢታስታዖስ አለ ትርጓሜውም አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ማርቆስም ስሙን የምትጠራው አውቀኸው ነውን አለው እንጠራዋለን እንጂ አናውቀውም አለ።

እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ አባታችን አዳም ትእዛዙን እንደተላለፈ የጥፋት ውኃም እንደ መጣ ሙሴንም እንደላከውና እስራኤልን ከግብጽ እንዳወጣቸው ሕግንም እንደ ሠራላቸው ናቡከደነጾርም ወደ ባቢሎን ማርኮ እንደወሰዳቸውና ከሰባ ዓመት በኋላ ወደ አገራቸው ኢየሩሳሌም እንደ ተመለሱ ክርስቶስ ሥጋ በመልበስ ወደ ዓለም ስለ መምጣቱ ነቢያት ትንቢት እንደ ተናገሩ ያስተምረው ዘንድ ጀመረ።

ከዚያም በኋላ ወደ ምድር ምራቁን ትፍ ብሎ ጭቃ አድርጎ ጣቱን ቀባው ወዲያው ዳነ በጌታችንም አመነ። ያም ሰፊ ስሙ አንያኖስ ነው። ቅዱስ ማርቆስንም ወደ ቤቱ ወስዶ ልጆቹን ዘመዶቹንም ወደ ርሱ አቀረበ እርሱም አስተምሮ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው።

በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ሰዎች በበዙ ጊዜ የቅዱስ ማርቆስን ዜና ሰምተው የአገር ሰዎች ሊገድሉት ተሰበሰቡ እርሱም አንያኖስን ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሹሞ ልጆቹን ቄሶችና ዲያቆኖች አድርጎ ከዚያም ወደ በርቃ ወደ አምስቱ አገሮችም ወጥቶ አስተማረ። በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው በእርሳቸውም ዘንድ ሁለት ዓመት ኖረ ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው።

ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ተመለሰ ምእመናንም ተጨምረው በዝተው በታወቁ ቦታዎች ሁሉ በባሕሩም ዳር በላሞች መካበቢያ በሚባለውም አብያተ ክርስቲያን ሠርተው አገኛቸው።

ከሀድያንም የከበረ ሐዋርያን ይገድሉት ዘንድ በብዙ ድካም ፈለጉት እርሱም አምስቱን አገሮች ሲጐበኝ በሥውር ወደ እስክንድርያ ከተማ ይገባ ይወጣ ነበር። በአንዲትም ዓመትም ከአምስቱ አገሮች ተመልሶ ሚያዝያ ዐሥራ ሰባት ቀን በመድኃኒታችን የትንሣኤ በዓል ወደ ቤተክርስቲያን ገባ ሕዝቡም ሁሉ በዙሪያው አሉ። ከሀድያንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው በአንገቱ ውስጥ ገመዶችን አድርገው በከተማው ሁሉ ጎተቱት። እነርሱም ገና እንደፍየል ሙክት እንጎትተዋለን እያሉ ይጮኹ ነበር። በላሞች መካበቢያና በሀገሪቱ አደባባይ በከተማውም ዙሪያ በየቀኑ ሲጎትቱት ኖሩ።

ሌሊትም በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐዋርያት ጋራ በነበረበት አርአያ ሁኖ ተገለጠለት ሰላምታም ሰጥቶ አጽናናው ቃል ኪዳንም ሰጠው። እነሆ አንተ ከወንድሞችህ ሐዋርያት ጋር ተካከልህ አለው። እርሱም በልቡናው ፈጽሞ ደስ አለው። በማግሥቱም ሁለተኛ ገመዶችን በአንገቱ አድርገው በአገሮች ሁሉ ጎተቱት በቀኑም መጨረሻ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።

ከሀዲዎችም ታላቅ እሳትን አንድደው የቅዱስ ማርቆስን ሥጋ ከውስጡ ጨመሩ። በክብር ባለቤት ጌታችን ፈቃድም ንውጽውጽታ ጨለማ ቀዝቃዛ ነፋስ መብረቅና ነጐድጓድ ሆነ። ፀሐይም ጨለመ ከሀዲዎችም ሸሹ ምእመናንም መጥተው የሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስን ሥጋ ወሰዱ ምንም ጥፋት ሳይደርስበት ደኀና ሆኖ አገኙት በመልካም ልብስም ገንዘው በጥሩ ቦታ አኖሩት መታሰቢያውንም አደረጉ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ማርቆስ ጸሎት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

  ከዚህ በላይ በጣም የሚያሳዝነው ይህ የዝሙት ተግባር በመንፈሳዊነት ሰበብ ሲከናወን ማየት ነው፡፡ ልጸልይልሽ፣ ላስጠምቅሽና ላጥምቅሽ፣ በሚሉ ሰዎች ብዙ ሴቶች ክብራቸውን አጥተዋል። ይህ የሚሆነው ሰውን ከመጠን በላይ ማመን ሲደራ ነው:: ጉዳዩ መንፈሳዊ መሆኑ ደግሞ ሰዎቹን የበለጠ እንዳይጠራጠሩ ያደርጋል። ይህን በመሰለ ነገር ብዙዎች ተሰነካክለዋልና አስቀድሞ እንደተገለጸው በሰው ብዙ አለመተማመን መልካም ነው። ፈዋሽ ጠበል አለ ወደ ተባለበት ቦታ ሁሉ «እግዚአብሔር አለ ምን እሆናለሁ?!» እያሉ ፈጣሪን መፈታተን አይገባም፡፡ ይልቁንም ብዙ ሰው ወደማይኖርባቸውና በየጫካዎች ወደሚገኙ የጠበል ቦታዎች ጨለማን እንኳን ሳይፈሩ ረጅም መንገድ እጓዛለሁ ማለት እጅግ መታወር ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ምንም ጉዳት ባይደርስብን እንኳን ከዚህ በኋላ መሞክር አይኖርብንም፡፡ በዚህ ምክንያት ተማሮ ጨርሶ ከቤተ ክርስቲያን ከመራቅ ከወዲህ መጠንቀቅ ይገባል።
ሌላውን ማስታመም ያንቺን የንጽሕና ኑሮ አደጋ ላይ የሚጥለው ከሆነ አለማስታመም ወይም ታማሚም ብትሆኚ አስታማሚ ማጣትሽ ይመረጣል፡፡ ከሥጋ ሕመም ቅድስናን ማጣት ይከፋልና፡፡ ሰይጣን ዝሙትን ለማስፈጸም ታማሚ ወይም አስታማሚ የሚያደርግበት ጊዜ አለ፡፡ ትዕማር የተባለች የዳዊት ልጅ ድንግልናዋን ያጣችው አምኖንን አስታምማለሁ ብላ ስትንጎዳጎድ ነው። 2ሳሙ13÷7-17 ይህ ታሪክ ለምን የተጻፈ ይመስልሻል? እግዚአብሔር አንቺን ለማስተማር ፈልጐ አይደለምን? ማስታመም ብቻ ሳይሆን አንቺ ራስሽ ብትታመሚም በምትጎጂበት መንገድ አስታማሚ አትፈልጊ፡፡ አስታማሚ አግኝቶ ንጽሕናን ከማጣት ከነንጽሕና መሞት ይመረጣል። ብታምኚ ግን እግዚአብሔር አስታማሚ የላትም ብሎ ለሞት አያበቃሽም። እርግጥ ሕመም መግቢያ ያሳጣልና ወደማንፈልገው ነገር በግድ እንድንገባ የሚያደርግበት ጊዜ አለ:: ሰይጣንም ወጥመዱን በሕመም ምክንያት የሚዘረጋው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ሆኖም ለዘለዓለም ሕይወት የሚበጀውን አውቆ መጠንቀቅና እርምጃ መውሰድ የሰው ፋንታ ነው::

ተ. ሴቶች ድንግልናቸውን እንዳይጠብቁ ለማጥመድ ሰይጣን በዚህ ዓለም የዘራው ብዙ ዓይነት የተሳሳተ አመለካከት አለ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ ሩካቤ ማድረግ በወንዶች ዘንድ ፍቅርን የሚያጸና (መወደድን የሚያመጣ) አድርጐ ማሳሰብ ነው፡፡ ስለዚህ ብዙ ሴቶች ድንግልናቸውን አሳልፈው ላላገቡት ወንድ ይሰጣሉ፡፡ ይህ አስተሳሰብ ፍጹም ቂልነት ነው፡፡ ምንም እንኳን ድርጊቱን የፈጸመው ራሱ ቢሆን ለእርሱ ይህ አይታሰበውም፡፡ ከዚህ ይልቅ ሳላገባት እንዲህ ካደረገች ከሌላም ካላገባችው ሰው ጋር ቢሆንም አንዲሁ ናት ብሎ በልቡናው ይታዘብሻል እንጂ ሊወድሽ አይችልም:: ፍቅር ምንም ምክንያት አያሻውም እውነተኛ ወዳጅ እንዲሁ ይወዳል፡፡ በምክንያት የሚወድ ግን በምክንያት ይጠላል፡፡ ራስሽን ስትሰጪው የወደደሽ የመሰለሽ ሰው አንዴ ብትቀሪበት እንደሚጠላሽ አታውቂምን? ወይስ እንዳንቺ ራሷን አሳልፋ የምትሰጠው ሴት ቢያገኝ ትቶሽ እንደሚሄድ አታስተውይምን? ምክንያቱም ይህ ሰው የሚወደው ሲሰጡት ብቻ ነውና፡፡
«ወንዶች አብራቸው የተኛችን ሴት ያፈቅራሉ» የሚለው አመለካከት ፍጹም የተዛባ መሆኑን የሚያረጋግጥልን አንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ አለ፡፡ ይኸውም የትዕማር ታሪክ ነው፡፡ አምኖን የተባለው ሰው ትዕማር የተባለች ከሌላ እናት የምትወለደውን የገዛ እኅቱን ወደደ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አምኖን ለትዕማር የነበረውን ፍቅር ሲገልጽ «አምኖንም ከእኅቱ የተነሣ እጅግ ስለተከዘ ታመመ፣ ድንግልም ስለነበረች አንዳችም ያደርጋት ዘንድ በዓይኑ ፊት ጭንቅ ሆነበት ይላል፡፡» 2ሳሙ13÷2 ይህን የመስለ ፍቅር የነበረው አምኖን አብሯት ከተኛና ሕጓን ከወሰደ በኋላ ግን ምን እንደ ተሰማው ሲገልጽ «ከዚያ በኋላ አምኖን ፈጽሞ ጠላት አስቀድሞ ከወደዳት ውድ ይልቅ በኋላ የጠላት ጥል በለጠ ይላል።» 2ሳሙ13፥15 ታዲያ ሕጌን ቢወስድ ይወደኛል ማለት ቂልነት መባሉ አያንሰውምን? በዚህ ዓይነት አስተሳሰብ ሄደው ክብራቸውን ያጡ፣ ያረገዙ፣ ለውርጃ የተጋለጡ ብዙ የመንፈስ ስብራት ያገኛቸውን ሴቶች ቤት ይቁጠራቸው።
ቸ. ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ስለ ንጽሕናቸው በትኵረት ማሰብ ይገባቸዋል፡፡ አንድ በዙሪያቸው የሚከናወንን ነገር ፍጻሜው ወዴት እንደሚሆን በጥንቃቄ መመርመር አለባቸው። የነገር መነሻ ላያሳስብ ይችላል፡፡ ወይም ከፍጻሜው ጋር የማይገናኝ ይመስል ይሆናል፡፡ በደንብ ያስተዋለ ግን በእርግጥ የሚያገናኛቸው ነገር መኖር አለመኖሩን ሊረዳ ይችላል:: ለምሳሌ፡- መጽሐፈ መነኮሳት «ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው ትሕትና የለውም›› ይላል፡፡ እዚህ ላይ አንድ ሰው ነጭ ልብስ ከትዕቢት ጋር ምን አገናኘው? ብሎ ሊጠይቅ ይችላል:: ለዚህ ሐተታ ሲሰጥ ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው ከሱ ይልቅ ሊከበር የሚገባው ሰው ተነሥቶ ልብስህ እንዳይቆሽሽ እዚህ ላይ ተቀመጥ ብሎ በራስ መቀመጫ ላይ እንዲቀመጥ ቢያስተናግደው ሳይግደረደርና ምንም ሳያቅማማ ሄዶ ይቀመጣል፡፡ ታዲያ አይገባኝም ማለት ሲገባው ለልብሱ ሲል የትሕትና ሥራ አጉድሎ ግብዣውን ሳያቅማማ መቀበሉ ትሕትና ጎደለበት አያሰኝምን? ይህ ምሳሌ ነጭ ልብስ መልበስና ትዕቢተኛነት ያላቸውን ረቂቅ ትሥሥር ያስረዳል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የምንለብሰው ልብስ፣ የምንጠጣው መጠጥ፣ የምንሄድበት ቦታ ወዘተ እንዴት ለዝሙት ሊያጋልጠን እንደሚችል ተረድተን መጠንቀቅ ይገባናል፡፡
  ፍጻሜውን ባለማስተዋል፣ በመታለልና በመሞኘት ክብረ ንጽሕናቸውን አጥተው የሚቆጩ ሴቶች ብዙ ናቸው:: አንድ ሹፌር የመኪና ሞተር ለማስነሣት ቁልፍ አስገብቶ ማዞሩን እንጂ በውስጡ የሚካሄዱትን ነገሮች በውል ላይረዳ ይችላል:: አንድ የቴክኒክ ባለሙያ ግን ከቁልፉ መዞር ባሻገር ምን ምን ነገሮች ተካሂደው በመጨረሻ ሞተሩ እንደ ተነሣ በተሻለ ይረዳዋል:: የአንድን ነገር ሂደት በዚህ መልኩ በጥልቀት መረዳት ከስሕተት ያድናል:: ወጣቶች እንኳን የሚሠሩት የሚመኙት ነገር በአንክሮ ቢጤን አንድ ጾታዊ ጉዳይ አይታጣበትም፡፡ የሚመርጡት የሥራ ዓይነት፣ የሚመኙት ቤትና መኪና፣ የሚሹት ታዋቂነት፣ ዝንባሌያቸው ወዘተ መጨረሻው ከፆታዊ ጉዳይ ጋር ቁርኝት ያለው ሆኖ ይገኛልና ራስን መመርመር ያስፈልጋል፡፡

ነ. ድንግል ነሽ? አይደለሽም? ዓይነት ውርርድና ጨዋታ መቼም ቢሆን የሚያስፈልግ አይደለም:: ወደ ግል ሕይወትሽ የሚያመራ ይህን የመሰለ ጨዋታ መሸሽ ይገባሻል፡፡ ለማንም ድንግል ነኝ አትበይ እንደውም ግድ መናገር ካስፈለገ ሁኔታውን አይቶ ድንግል አይደለሁም ማለት ሳይሻል አይቀርም:: ምክንያቱም ድንግል ነኝ በማለታቸው ብዙዎች ካላሰቡት ወጥመድ ውስጥ ገብተዋልና፡፡
የሚያገባሽ ሆኖ ስለ አኗኗርሽ በግድ ማወቅ ከሚያሻው ሰው በቀር ለማንም ስለ ራስሽ ድንግል መሆንም ሆነ አለመሆን አታውሪ፡፡ ብታወሪ ግን ለጊዜው ሊያኮራሽ ይችል ይሆናል:: ዘግይቶ ግን ሳታዝኚበት አትቀሪም፡፡ ምክንያቱም ከድንግል ሴት ጋር መተኛት ንጹሕ መሥዋዕት የማቅረብን ያህል የሚያስደስታቸው ሰዎች ብዙ ናቸውና፡፡ ስለዚህ ድንግል ነኝ በማለትሽ በራስሽ ላይ የፈተና ትብትብ ትሸከሚያለሽ፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከሁሉ የሚያሳዝነው «ድንግልናዬን ያጣሁበትን መንገድ ምንም እንኳን በመንፈሳዊ ዓይን ሳየው ሥራዬ እጅግ ቢያስቆጨኝም በወቅቱ ግን ያን በማድረጌ ደስተኛ ነበርኩኝ› በማለት ለመናገር የሚደፍሩ ጥቂቶች ብቻ መሆናቸው ነው:: ምክንያቱም የብዙዎች ሰዎች ድንግልና ማጣት በአንድ ወገን ጫናና ፍላጎት ብቻ የተፈጸመ ከመሆኑም በላይ በቦታ ዐቅም እንኳን ጎንን ማሳረፊያ በሌለበት በየሜዳውና በየፈፋው፣ በአጥር ጥግና በመኪና ውስጥ፣ በፊልም ቤት፣ በምግብ ማብሰያና በመጸዳጃ ቤት፣ በየትምህርት ተቋማት ማደሪያዎች፣ በቢሮዎችና በየኮሪደሩ፣ በድብደባ፣ በጉተታና በልዩ ልዩ መንገድ የተፈጸሙ በመሆናቸው ነው:: ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በምንም ዓይነት ምቾት ቢሆን ድንግልናን ያህል ነገር ከጋብቻ ውጭ ማጣት የሚያሳዝን ነገር ቢሆንም በዚህ መልኩ መሆኑ ደግሞ ሲታሰብ እንኳን ይዘገንናል፡፡
ከዚህ በታች ድንግልናን ለማጣት የሚዳርጉ ወሳኝ ወቅቶች፣ ቦታዎችና ሁኔታዎች ተዘርዝረዋል። የተነሡት ነጥቦች አብዛኞቹ እውነተኛ ታሪኮች ናቸው:: ሆኖም «ታሪክ ራሱን ይደግማል›› እንደሚባለው እነዚህ ሰዎች በተጓዙበትና በተጎዱበት የስሕተት ጐዳና የሚሯሯጡ ብዙ ሰዎች ዛሬም ይገኛሉ፡፡ ብልህ ሰው ከሰው ጉዳት ብዙ ይማራል፡፡ በራስ ላይ ክፉ ነገር ሳይደርስ በሌሎች ከደረሰ ጉዳት መማር ታላቅ ዕድል ነው፡፡
ሀ. ብዙዎች ክብረ ድንግልናቸውን ያጡበት መንገድ ተገድዶ መደፈር ነው፡፡ ይህ ጉዳይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዐቢይ መነጋገሪያ እየሆነ ከመጣ ዘመናትን አስቆጥሯል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስም ስለ አስገድዶ መድፈር ተጽፏል፡፡ በወቅቱ በደፋሪነት የሚታወቀው ወንድ ተደፋሪዋ ደግሞ ሴት በመሆኗ ደፋሪው ስለሚገባው ቅጣት ተደፋሪዋ ማድረግ ስላለባት ነገር በዝርዝር ተጽፎ ነበር፡፡ ዘዳ22፥23-27
እንደ ሥርዓተ ኦሪት ከሆነ ተደፋሪዋ ሴት ድርጊቱን መቃወሟ የሚታወቀው ቢያንስ ‹መጮኽ›› በሚቻላት ጊዜ ሁሉ ‹‹መጮኽ› ከቻለች ብቻ ነበር፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በድርጊቱ እንደተስማማች ይቆጠርና ከደፋሪዋ ጋር እርሷም አብራ በድንጋይ ትወገር ነበር፡፡ ለምን ቢባል «በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና» በማለት ቅዱስ መጽሐፍ መልስ ይሰጠናል፡፡ ዘዳ22 ፥ 24
ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ሥርዓት የሚያስተምረው ከመደፈር ለመዳን ሴቶች ከ‹መጮኽ›› አንሥቶ በአለባበስ፣ በድርጊት፣ በቦታ፣ ወንዶች ሥጋ እንዳየ አንበሳ በኃይል እንዲነሡባቸው ከማድረግ በመቆጠብ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለባቸው ነው፡፡ ‹‹መብቴ ነው» እያሉ እንደፈቀዱ መሆን ይቻል ይሆናል፡፡ መብትሽ ከሰው በታች የሚያደርግሽ ከሆነ ምን ይረባሻል? በመንፈስ፣ በሥነ ልቦናና በአካል ጉዳት ላይ ከወደቅሽ በኋላ ለዚህ ያበቃሽ ሰው በሕግ መቀጣቱ ተገቢ ነገር ነው:: ቢሆንም ላንቺ ግን እንኳን መታሰሩ ብቻ ይቅርና በስቅላት የሚቀጣም ቢሆን ምንም አይጠቅምሽም፡፡ላንቺ የሚበጅሽ ከመጀመሪያው ጉዳት ባይደርስብሽ ነውና፡፡ ስለዚህ ከወዲሁ ራስሽን ለአስገድዶ መደፈር አታጋልጪው፡፡
ለ. መደፈር በኃይል በመገደድ ብቻ አይደለም፡፡ ከመነሻው ከወንዶች ጋር የሚኖርሽን ግንኙነት በጥንቃቄ አድርጊ፡፡ እርዳታ ካስፈለገሽ አቋምሽን ገልጸሽ በቀና የመረዳዳት መንፈስ እርዳታ ተቀበይ፡፡ አንቺም ሌሎችን ስትረጂ በዚሁ መንገድ አድርጊው:: በእርዳታና በውለታ ብዛት መደፈር አለና ያለ አግባብ እርዳታ ብታገኚ ሳትወጂ በግድ ራስሽን ትሰጪያለሽ፡፡ ስለዚህ እርዳታ ከመጠየቅ ወይም ከመቀበልሽ በፊት በውኑ ይህን ዓይነት እርዳታ የሚያስፈልገኝ ሰው ነኝን? የሚረዳኝስ ሰው ምን ዓይነት ነው? ፆታው፣ እድሜው፣ የኑሮ ሁኔታው፣ ቅርርባችንስ ምን ያህል ነው? ወይም ምን ይመስላል? ለምን ይረዳኛል? ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ አግኚላቸው።ይህ ሰው ለኔ የሚያደርገውን ያህል እርዳታ የሚያስፈልጋቸውና ከኔ ይልቅ የሚቀርቡት ሌሎች ወገኖች የሉምን? ታዲያ እኔ በምን ምክንያት ቀዳሚያቸው ሆንኩኝ? በመጨረሻም ምን አልባት በመጨረሻ ከዚህ ሰው ያላሰብኩት ፆታዊ ጥያቄ ቢሰነዘርብኝ በምን መልኩ መልስ መስጠት እችላለሁ? ብለሽ አስቢበት።
እግዚአብሔር ስለ ንጽሕና ከሰው የሚፈልገው ንጽሕናን ብቻ ነው:: ዝሙት በንስሓ እንጂ በምጽዋት ሊሠረይ አይችልም፡፡ ንጽሕና በዋጋ የሚሸምቱት ሸቀጥ አይደለምና፡፡ ምጽዋት ተቀባይነት የሚኖረው ከንጽሕና ሥራ ጋር ሲተባበር ነው:: እንዲህ ከሆነ በምንም ዓይነት መንገድ ቢሆን ለተዋለልን ውለታ በሰውነታችን ለመክፈል ማሰብ ሞኝነት ነው:: ውለታ ከተቻለ በዚያው መንገድ ሊከፈል ይገባል:: ካልሆነም «እግዚአብሔር ይስጥልኝ» ማለት ብቻ ውለታን ሊመልስ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ውለታ ብድር አይደለምና። ሆኖም ይህ ምስጢር ሳይገባቸው ቀርቶ ለማግኘት ስለሚፈልጉት ነገር ወይም አስቀድሞ ስለተደረገላቸው ውለታ ሰውነታቸውን ለዝሙት አሳልፈው የሚሰጡና ድንግልናቸውንም በዚህ መንገድ እያጡ ያሉ ሴቶች ቁጥር እጅግ ብዙ ነው:: አንቺስ በሕይወትሽ የምትመኚውን ትልቅ ነገር ሊያደርግልሽ የሚችል ወንድ ብታገኚ በድንግልናሽ እንደማትዋዋዪ ምን ያህል እርግጠኛ ነሽ?
ሐ. ከለላ ለማግኘት ስትዪ ከአንዱ ወንድ ጋር እጅግ አትጣበቂ፡፡ ከፈራሻቸው ሌሎች ይልቅ መጥፊያሽ የተማመንሽበት እንዳይሆን ተጠንቀቂ፡፡ እንዲህ ባለ ጐዳና ብዙዎች ተሰናክለዋልና፡፡ እጅግም በሰው መተማመን አይገባም፡፡ እርሱ ራሱ ሸክላ ነውና፡፡ ለምሳሌ:- በሚያስፈራ ጭለማ ብትሄጂ በራስሽ መመዘኛ ከሰከረ ያልሰከረውን ከእብድ ይልቅ ደግሞ ያልቀወሰውን ተማምነሽ ትጠጊ ይሆናል፡፡ እነዚህን ግን ማን የተሻሉ አረጋቸው? ብሰውስ ይገኙ እንደ ሆን ምን ታውቂያለሽ ? ስለዚህ ይህን በመሳሰለ ጥርጣሬ ብትሄጂ ሊያገኝሽ የሚችለው ጉዳት በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ ሰውን ማመን አያጸድቅምና፡፡

መ. የሰው ባሕርይ እንደ ተቀጠቀጠ ሸንበቆ ነው፡፡ ብዙ ሲደገፉት መሰበሩና መውጋቱ አይቀርም:: በራስም ሆነ በሌላ ሰው ብዙ መተማመን አይገባም:: ብዙ ጊዜ ስሜት ከዕውቀት ይልቅ ይበረታል:: መጥፎነቱን እያወቅን ማድረግ የማንፈልገውን ነገር ደጋግመን ለመሥራት የምንገደደው ስሜት ከዕውቀት ይልቅ ስለሚበረታ ነው።
ብዙ ሰዎች ድንግልናቸውን ሲጠብቁ ኖረው ከዚህ ክብር የሚወድቁት ጋብቻቸውን ለመፈጸም ጥቂት ቀናት ወይም ሰዓታት ሲቀራቸው ነው:: ይህም የሚሆነው ከላይ እንደተገለጸው ቀኑ በቀረበ ቁጥር የኔነት ስሜት እየተሰማቸው በሚፈጥሩት መቀራረብና መተማመን ምክንያት ስለሚዘናጉ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን አስቸጋሪ ወቅት እንደወትሮው ሁሉ መቀራረብን በልክ አድርጐ በጥንቃቄ መጓዝ ያስፈልጋል:: እንዲህ ካልሆነ የአንዲት ቅፅበትን ስህተት በዕድሜ ልክ እንባ ማጥራት ሊሳነን ይችላል፡፡
ከላይ የተጠቀሰውን የማሳሳቻ ዘዴ (ማዘናጋት) በመጠቀም እንጋባ የሚል ሐሳብ ሲነሣ ጆሮአቸውን ይይዙ የነበሩ ወንዶች ከጋብቻ በፊት የሩካቤ ጥያቄ አንሥተው ውድቅ ሲሆንባቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማግባት እንደወሰኑ ቃል መግባትና መሐላ መደርደር ይጀምራሉ፡፡ ይህን የሚያደርጉት «የሚያገባኝ ከሆነ ምን አስጨነቀኝ» በማለት አቋምሽ እንዲላላና እንድትዘናጊ ለማድረግ ነው፡፡ ይህንን በመሰለ ጊዜ አለመፈታትና አቋምን ጥብቅ አድርጐ በመያዝ እስከ ጋብቻ ዕለት ድንግልናን ጠብቆ መቆየት አግባብ ነው፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

📌 በደንብ ይነበብ 📌
          ቅዱሳን በአጸደ ነፍስ ያማልዳሉ☑️

ማስረጃ 2 ይቀጥላል🙌
join በማለት እናበረታታው 🙏
/channel/KM_thoughts
/channel/KM_thoughts

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሚያዝያ ፳፫
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕት


ሚያዝያ ሃያ ሦስት በዚህች ቀን ፀሐይና የአጥቢያ ኮከብ የተባለ ታላቅና ክቡር የሆነ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ የምስክርነት ፍጻሜ ሆነ። የዚህም ቅዱስ አባቱ መስፍን ነው ስሙም አንስጣስዮስ ይባላል ከቀጰዶቅያ አገር ነው የእናቱም ስም ቴዎብስታ ይባላል ከፍልስጥዔም አገር ናት ታናሽ ሆኖ ሳለ አባቱ አረፈ።

ሃያ ዓመትም በሆነው ጊዜ የአባቱን ሹመት ሊቀበል ወደ ንጉሥ ዱድያኖስ ዘንድ ሔደ፡፡ ንጉሡም ጣዖት አቁሞ ጣዖትን እንዲአመልኩ ሰዎችን ሁሉ ሲያስገድዳቸው አገኘው። ይህንንም አይቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ እጅግ አዘነ በእርሱ ዘንድ ያለውን ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች ለምስኪኖች ሰጠ ባሮቹንም ነፃ አወጣቸው።

ከዚህ በኋላ በንጉሥ ፊት ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። ንጉሡም አባበለው ብዙ ቃልኪዳንም ገባለት እርሱ ግን አልተቀበለውም። ለመስማት እንኳ የሚያስጨንቅ ሥቃይን አሠቃየው ጌታችን ግን ያጸናዋል ቍስሉንም ያድነዋል ሦስት ጊዜም እንደ ሚሞት እርሱም እንደሚአሰነሣው በአራተኛውም የምስክርነት አክሊልን እንደሚቀበል ነገረው። ቃል ኪዳንም ሰጠው ስሙ በዓለሙ ሁሉ የተገለጠ ይሆን ዘንድ በተጋድሎና መከራ በመቀበልም ጽኑዕ በሆነ ሥቃይም ሰባት ዓመት እንደሚኖር መላእክትም እንደሚአገለግሉት ነገረው።

ንጉሡም ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለመታዘዙና ባለመመለሱ እጅግ አዘነ ስለዚህም አትናስዮስ የሚባል ታላቅ ሥራየኛ አመጣ እርሱም መርዝን ቀምሞ በጽዋ መልቶ አስማት ደግሞ እንዲጠጣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው። ወዲያውኑ የሚሞት መስሎት ነበር። ቅዱሱም ያንን ጽዋ ጠጣው ምንም ጉዳት አልደረሰበትም።

ያ መሠርይም በክብር ባለቤት በጌታ ኢየሱስ አምኖ በሰማዕትነት ሞተ። ከእርሱም ጋራ ሌሎች ብዙዎች ሰዎች በሰማዕትነት ሙተው የሕይወት አክሊል ተቀበሉ ቍጥራቸውም ሠላሳ ሺህ ሰባት መቶ ነፍስ ነው።

ቅዱስ ጊዮርጊስም በዱድያኖስና በሰባ ነገሥታት ፊት በቆመ ጊዜ በዚያም የተቀመጡባቸው የዕንጨት ወንበሮች ነበሩ። ቅዱሱንም እሊህን የተቀመጥንባቸውን ወንበሮች እንዲበቅሉ እንዲአብቡና እንዲአፈሩ ታደርጋቸው ዘንድ ከአንተ እንሻለን አሉት። በዚያን ጊዜ ጸለየ እንዳሉትም አደረጋቸው ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው ቍጥር የሌላቸው ብዙ አሕዛብ በጌታችን አመኑ።

ከዚህም በኋላ ቅዱሱን ወስደው በጐድጓዳ ብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት። አቃጥለው አሳርረውም ሥጋውንና አጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው ከረጅም ተራራ ላይ በተኑት። ጌታችንም ነፍሱን ወደ ሥጋው መልሷት ደግሞ አስነሣው። ወደ ነገሥታቱም ተመልሶ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ስም ሰበከ ቁጥር የሌላቸው አሕዛብ አይተው አደነቁ በጌታችንም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ።

ነገሥታቱም ደግመው ሙታኖችን ብታሥነሣ አምላክህ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ እናውቃለን በእርሱም እናምናለን አሉት። ቅዱሱም ጸለየ ከጉድጓድም ውስጥ ወንዶችና ሴቶች ጎልማሶችንም አስነሣላቸው እነዚያም በክብር ባለቤት በጌታችን ስም አስተማሩ የገሀነምንም ወሬ ተናገሩ ጥምቀትንም ተቀብለው ተመልሰው አረፉ።

ከሀድያን ነገሥታት ግን ሙታንን ያስነሣህ አይደለም የረቀቁ ሰይጣናትን አሳየህ እንጂ ብለው ተከራከሩ። ከዚያም ከጭንቀታቸው ብዛት የተነሣ ከአንዲት ድኃ ሴት ዘንድ አስጠበቁት እርሷም እንጀራ ልትለምንለት ወጣች የእግዚአብሔርም መልአክ በላዩ ከበጎ ነገር ሁሉ የተመላ ማዕድን አቀረበላት። የዚያች መበለትም የቤቷ ምሰሶ ቅርንጫፍን አበቀለ ታላቅ ዛፍም ሆነ። ያቺም መበለት በተመለሰች ጊዜ የቤቷ ምሰሶ ቅርንጫፍ አብቅሎ ታላቅ ዛፍ እንደሆነ ስለ ማዕዱም ይህን ታላቅ ምልክት አይታ የክርስቲያኖች አምላክ ሰው ተመስሎ ወደእኔ መጣ አለች።

ቅዱሱም እኔ አምላክ አይደለሁም የአምላክ ባሪያ ነኝ እንጂ አላት። እርሷም እንዲህ ብላ ለመነችው የአምላክ አገልጋይ ከሆንክ ቸርነትህ እንድትደርሰኝ አለምንሃለሁ። ዕውር ደንቆሮ ዲዳ ጐባጣ የሆነ ልጅ አለኝና ታድንልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ። ስለ ጌታችን እምነትም አስተማራትና በመስቀል ምልክት አማተበው ያንጊዜም አየ። ቅዱሱም በሌላ ጊዜ እንዲሰማ እንዲናገርና እንዲሔድ እንዲአገለግለኝም እኔ እሻለሁ አላት።

በዚያን ጊዜ ንጉሡ በአገሩ ሜዳ ውስጥ ሲዘዋወር ያቺን ዛፍ አይቶ አደነቀ ስለ እርሷም ጠየቀ ቅዱስ ጊዮርጊስ በእርሷ ዘንድ የተቀመጠባት የዚያች መበለት የቤቷ ምሰሶ እንደሆነ ነገሩት። ንጉሡም ተቆጣ ቅዱሱንም ከዚያ ወስዶ አሰገረፈው በመንኰራኩርም አበራዩት ሙቶም ከከተማ ውጭ ጣሉት ጌታም ከሞት አስነሣው ወደ ነገሥታቱም ተመለሰ ንጉሡም አይቶ ደነገጠ ስለ ሕይወቱም አደነቀ።

ከዚህም በኋላ ይሸነግለው ዘንድ ጀመረ በመንግሥቱ ላይም ሁለተኛ ያደርገው ዘንድ ቃል ገባለት ቅዱስ ጊዮርጊስም እየዘበተበት ነገ በጥዋት ለአማልክቶችህ መሥዋዕትን አቀርባለሁ አንተም ሕዝቡ እንዲሰበሰቡ እዘዝ እኔ ስሠዋ እንዲአዩ አለው፡፡ ንጉሡም ዕውነት የሚሠዋ መስሎት ደስ አለው ወደ ቤተ መንግሥቱም እልፍኝ አስገብቶ አሳደረው፡፡

ለጸሎትም ተነሣ የዳዊትንም መዝሙር አነበበ የዱድያኖስ ሚስቱ እለስክንድርያ ንግሥት ሰምታ ቃሉ ደስ አሰኛት የሚያነበውንም ይተረጒምላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ሰው እስከሆነበት ጊዜ የሆነውን ሁሉ ሊያስረዳትና ሊያስገነዝባት ጀመረ ትምህርቱም በልቡዋ ተቀርጾ በክብር ባለቤት በጌታችን አመነች፡፡

በማግሥቱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአማልክት ሲሠዋ ለማየት ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብ ዐዋጅ ነጋሪ ዞረ የቤቷን ምሰሶ ያበቀለላት ያቺ መበለት ሰምታ ዕውነት መስሏት እጅግ እያዘነች ልጅዋን ተሸክማ እያለቀሰችም ወጣች፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስም በአያት ጊዜ ፈገግ አለ ልጅሽን በምድር ላይ አኑሪው አላት ከዚያም ልጅዋን ጠርቶ ወደ አጵሎን ሒድ ወደእኔም ይመጣ ዘንድ በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ስም እዘዘው አለው፡፡ ያን ጊዜ ያ ልጅ ድኖ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዳዘዘው ወደ ጣዖቱ ቦታ ሒዶ አዘዘው፡፡ በጣዖቱ ያደረ ያ ርኵስ መንፈስም ከማደሪያው ወጥቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አለበት መጥቶ እኔ ሰውን ሁሉ የማስት እንጂ አምላክ አይደለሁም ብሎ በሕዝቡ ሁሉ ፊት አመነ፡፡ ቅዱሱም ትውጠው ዘንድ ምድርን አዘዛትና ወዲያውኑ ዋጠችው ጣዖታቱንም ከአገልጋዮቻቸው ጋራ አጠፋቸው ንጉሡም ከወገኖቹ ጋር አፈረ፡፡

ብስጭትና ቁጣንም እንደተመላ ወደ ንግሥት ሚስቱ ዘንድ ገባ፡፡ እርሷም አምላካቸው ጽኑዕና ኃያል ነውና ክርስቲያኖችን አትጣላቸው አላልኩህምን አለችው፡፡ ይህንንም ከእርስዋ ሰምቶ በእርሷ ላይ እጅግ ተቆጣ ወደ ክብር ባለቤት ክርስቶስ እምነት የከበረ ጊዮርጊስ እንደአስገባት አወቀ፡፡

ከዚህም በኋላ ከከተማ ውጭ እንዲጐትቷትና በመጋዝም እንዲሰነጥቋት አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች፡፡ በዚያም ጊዜ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሥራ ነገሥታቱ ሁሉም ደነገጡ ኀፍረት ደግሞ እንዳይጨምርባቸው ከእርሱም እንዲአርፍ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ እንዲጽፍ ንጉሥ ዱድያኖስን መከሩት፡፡

ያን ጊዜም የክቡር ጊዮርጊስን ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ድል አድራጊ ጊዮርጊስም እጅግ ደስ አለው እሳት ከሰማይ አውርዶ ሰባውን ነገሥት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያን ወገን ጸጥ ይል ዘንድ ጌታችንን ለመነው፡፡ ወዲያው እሳት ወርዶ ከሠራዊታቸው ጋር ሰባውን ነገሥታት አቃጠላቸው፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቋሚ ሲኖዶስ ልዩልዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ።

ሚያዚያ ፳፪/ ፳፻፲፯ ዓ.ም

ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከቤተክርስቲያናችን የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ በፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር አዳራሽ የሰጡትን ትምህርትና በማኅበሩ ሚዲያ የተላለፈበትን ሁኔታ በተመለከተ በዛሬው መደበኛ ጉባኤው በሰፊው ተወያይቶ ለመወሰን በያዘው ቀጠሮ መሠረት በጉዳዩ ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ካደረገ በኋላ የሚከተሉትን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

1. ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር በተለያዩ ጊዜያት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ውጪ በሚዲያው ያስተላለፈው የስሕተት ትምህርት የቤተክርስቲያናችንን አባቶች፣ሊቃውንቱንና መላው ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሳዘነ በመሆኑ በማኅበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ በኩል ጊዜያዊ የእገዳ ደብዳቤ እንዲደርሰው እና በመምሪያው በኩል አስፈላጊው ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ ሆኖ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ መስጠት ይቻል ዘንድ አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ እንዲቋቋም አድርጓል።

በዚህም መሠረት ቋሚ ሲኖዶስ ያቋቋማቸው አጣሪ ልዑካን አጠቃላይ የማህበሩን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እና በሚዲያው ያስተላለፋቸውን የስህተት ትምህርቶች በተመለከተ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ከማህበራት ምዝገባ፣ ቁጥጥርና ክትትል መምሪያ ጋር በመነጋገር በሚገባ መርምርውና አጣርተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከውሳኔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርቡ፣

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

💠ከሰማያት ወርዶ💠

ከሰማያት ወርዶ ሥጋን በመልበሱ
በዓለም መድኃኒት ነጻ ወጣን በእርሱ
የጨለማው ገዢ ዲያብሎስ አፈረ
በጌታ ትንሣኤ የሞት ኃይል ተሻረ(፪)

እልል እልል ደስ ይበለን(፪)
ሞትን ድል ነስቶ ተነሣልን(፪)

አዳም ሆይ በሲኦል ለዘመናት ኖረ
ዛሬ በትንሣኤው ብርሃንን አገኘ
የተስፋው ቃልኪዳን ይኸው ተፈጽሟል
ላንተም ለልጆችህ ዛሬ ሰላም ሆኗል(፪)

አዝ---

የአጋንንት ግዛት ሲኦል ባዶ ቀረ
ነፍሳት ነጻ ወጡ ጠላትም ታሰረ
የብርሃን ግርማ ጸዳል ምድርን ሞላት
በትንሣኤው ብርሃን አገኘን ድኅነት(፪)

አዝ---

የድኅነትን ሥራ በሞቱ ፈጸመ
የዲያብሎስ ሴራ ሥልጣኑ አከተመ
በዕለተ ሰንበት ክርስቶስ ተነሥቷል
የሲኦል እስራት ገመዱ ተፈትቷል(፪)

እልል እልል ደስ ይበለን(፪)
ሞትን ድል ነስቶ ተነሣልን(፬)
በማኅበረ ሰላም መዘምራን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መጽሐፍ ቅዱስ በየዘመኑ ብዙ ደናግላን መኖራቸውን ገልጾ ይናገራል፡፡ ለምሳሌ፦ «በስድስተኛው ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨት ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ›› ይላል፡፡ ይህን የወንጌላዊ ቃል መምህራን ሲተረጉሙ ብዙ ገሊላዎች አሉና ከእነዚያ ለመለየት «የናዝሬት ከተማ» ሲል ብዙ ዮሴፎች አሉና አረጋዊ ዮሴፍን «ከዳዊት ወገን ለሆነው» በማለት ለይቶ ጠቅሶታል:: በዚያው ዘመን ደግሞ ብዙ ደናግል ነበሩና ከእነዚያ ለመለየት «ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል» በማለት ተናገረ ይላሉ፡፡ ይህም ትርጓሜ በየዘመኑ ብዙ ደናግላን መኖራቸውን ያስረዳል። ሉቃ 1÷26-27
ሐቁ ይህ ሆኖ ሳለ ይህ ትውልድ ግን ዛሬ ዛሬ ደናግላንን ማግኘት ጭንቅ እንደሆነ ይናገራል፡፡ የዚህ ነገር ዐቢይ ምክንያት ይህ ትውልድ አመንዝራ በመሆኑና ሁሉን የሚመለከተው እንደ ራሱ ስለሆነ ነው:: ይህ ሐሳብ የተጋባባቸው አንዳንድ ደናግላንም ድንግልናቸውን እነሱ ብቻ ጠብቀው እንደሚኖሩ ይሰማቸዋል:: ነገር ግን የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና ድንግልናዊ አኗኗርን ከምታወድስ ከቤተ ክርስቲያን ዘልቀው ቢመለከቱ በየጊዜው እንደ ዕንቁ የሚያበሩ ደናግላን ምእመናንን በዐፀዷ ዙሪያ ተኮልኩለው መመልከት ይቻላል:: በዚህ ምክንያት ሰይጣን ብዙ ሴሰኞች ዓይኖቻቸውን በቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ እንዲያነጣጥሩ ማድረጉ ሊታወቅ ይገባል::
ዛሬ ዛሬ ድንግልና የሚገኘው በማዋለጃ ሆስፒታል ውስጥ በሚገኙ ሕፃናት ዘንድ ብቻ እንደሆነ ተደርጎ የሚናኘው ቀልድ መሰል አሉባልታ እጅግ የተጋነነ የሰይጣን ወሬ ነው፡፡ ይህ ዓይነት የተጋነነ ወሬ ድንግልናቸውን ያፈረሱ ሰዎች ከመጸጸትና ንስሐ ከመግባት ይልቅ «በእኔ አልተጀመረ» እያሉ እንዲጽናኑ ሲያደርጋቸው፣ ሌሎችን ደግሞ «በድንግልና የምገኝ እኔ ብቻ ነኝ» በማለት በትዕቢት እንዲወደቁ አድርጓቸዋል።
ደናግላን በቁጥር ብዙ መሆናቸው መታወቁ ማንም በድንግልናው እንዳይመካ ያደርጋል። ብዙ ሰው በያዘው ነገር መመካት አይመችምና፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በድንግልናው የሚመካ ሰው ራሱን ቢመረምር አንዳይመካ የሚያደርገውና ለድንግልናዊ ኑሮው የማይስማማ እጅግ በጣም ብዙ የልቡና ርኩሰት ይገኝበታል፡፡ ለምሳሌ፡- መመካት፣ በሌላው መፍረድ፣ መታበይ፣ ማማት፣ ክፉ ፍትወት፣ ሰዶማዊነት፣ ትምክህት የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ታዲያ ከእነዚህ ሁሉ የረከሱ ሥራዎች ጋር እንደ ትኋን ተጣብቀው እየኖሩ «ድንግል ነኝ እኮ!» እያሉ መመካት አያሳፍርም?
አንዳንዶች ደግሞ በድንግልናቸው ይመኩ እንጂ እነርሱ ራሳቸው በልዩ ልዩ መንገድ ሲያቃልሉት ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ፡- ድንግልና በገንዘብ የማይተመን ሆኖ ሳለ አንዲት ልጃገረድ «ድንግል ነኝኮ» እያለች የሚመጣላትን ባል «አንዱን ዕውቀት፣ አንዱን ሹመት፣ አንዱን ገንዘብ፣ አንዱን ንብረት ሌላውን ደግሞ ማራኪ ቁመናና ውበት የለውም» በማለት ከድንግልና ጋር የማይወዳደሩ ነገሮችን ብታማርጥበት ንጽሕናዋን ለተጠቀሱት ነገሮች እንደ መሸጥ አይቆጠርባትምን? ስለ ንጽሕናዋ ንጽሕናን መሻትና መመልከት ሲገባት የሀብትን መጠንና ሌሎች ነገሮችን በማየቷ ድንግልናን እንደሚገባው መጠን ታከብራለች ለማለት አያስደፍርም፡፡ ስለ ድንግልና እንዲህ ዓይነት የተዛባ አመለካከት ይዞ በድንግልና መመካት እንዴት ያሳፍራል?
በመጨረሻም ማስተዋል ያለብን ድንግልናችንን ለመጠበቅ የመጀመያዎቹ ተጠቃሾች እኛው ራሳችን ብንሆንም ዐስበ ድንግልናችንን (የድንግልናችንን ዋጋ) ለማግኘት ያህል ነው እንጂ ድንግልናችንን የሚጠብቅልን ራሱ እግዚአብሔር ነው:: መጽሐፈ አርጋኖን ስለ መንፈስ ቅዱስ "ንጹሐን ደናግልን ያበረታቸው እርሱ ነው።"ይልና «በድንግልናም ጊዜ የንጽሕና መንፈስ ነው» በማለት ይናገራል፡፡ (አርጋኖን ዘእሁድ) ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ደግሞ «እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂ በከንቱ ይደክማል» መዝ126÷1 በማለት ተናግሯል፡፡ ትርጓሜውም እግዚአብሔር በከተማ የሚመስለውን ሰውነትን በንጽሕና በድንግልና ካልጠበቀ ራሴን ጠብቄ ድንግልናዬን እቆያለው ማለት ከንቱ ድካም ነው ይለናል፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ዛሬ ለምን ንፍሮ እንበላለን?

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በደጅ መወለድሽ - በገዛ እጅሽ አንቺን የሚሸከም ቤት በዚህ ዓለም አልተገኘምና ልደትሽ በውጭ ኾነ። ቅዱስ ያዕቆብ የሰማይ ደጅ እንዳለሽ ትዝ ይለናል። ድሮስ ሰማይን የሚችል ምን ቤት በዚህ ዓለም ይኖራል? ከምድር እስከ ሰማይ የተዘረጋሽ መሰላል ይልሻል። እናስ አንቺን ምን ዓይነት ቤት ያስተናግድሻል?
ደግሞ ስትመጪ ብቻሽን አይደለም። የራቀንን እግዚአብሔርን ከአሽከሮቹ መላእክት ጋር ይዘሽ እንጅ። እኮ ለአንችም ቤት አላገኘን ስንኳን ለምሉዕ በኩለሄው። እስከዛሬ የሚመጥንሽን ቤት ልንሠራ አልተቻለንም። ያ ወንጌላዊ ስፍራ አልተገኘላቸውም ያለን ለዚህ ነበር ለካ።
አንች ግን ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረው ሰማይና ምድር ለማይችሉት ቤቱ ኾንሽ።
ለወለዱሽ ለተራሮች መልሰሽ እናት ኾንሻቸው። ያ ዶኪማስ እንኳን ልጅሽ ተጨምሮ ለአንችም ቤቱ እንዳይበቃ ዐውቆ በአዳራሽ በድንኳን ቢያስቀምጥሽ ከመንበርሽ ሳለሽ ጓዳውን ዐየሽበት። ቤቱን ከባዶነት ወደ መትረፍረፍ ለወጥሽው።
አክስትሽ ቅድስት ኤልሳቤጥም ቤቷ እንዳይበቃሽ ዐውቃ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይኾናል? ብላ ተርበተበተች። አንቺ ግን ገና በደጅ ሳለሽ በቤት በነበረችው በአክስትሽ ማኅፀን ላለው ጽንስ ታየሽ። በረድኤትሽ ቀርበሽዋልና ጠብ እርግፍ ብሎ ሰገደልሽ። የኾነው ሁሉ የተገለጠላት ቅድስት ኤልሳቤጥ እኛ ሁሉ እንሰማው ዘንድ በታላቅ ድምፅ ዐወጀችሽ። ከቤቷ በላይ ነሽና።
ሰማይ ነሽ ብለን ስንደነቅ ምድር ኾነሽ ያለ ዘር ታበቅያለሽ። ምድር ነሽ ስንል ሰማይ ቤት ደርሰሽ ዙፋን ትዘረጊያለሽ። በሰማይ አንድ ልጅ ብቻ ቢኖር የእርሱም እናቱ ኾንሽ። አብ አንድ ዘር ቢኖረው ሙሽራው አደረገሽ። ያለ እናት ቢወልደው ያለአባት ወለድሺው። ታዲያ ምን ዓይነት ቤት ይችልሽ ኖሯል? እመቤታችንሆይ በደጅ የተወለድሽው በገዛ እጅሽ ከአቅማችን ስለገዘፍሽ ነው።
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ልደትሽ ልደታችን ነው❤️

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

🌿 🌿 ግንቦት ፩ 🌿 🌿
🌿 ልደታ ለማርያም 🌿
የፍጥረት ሁሉ ደስታ

ግንቦት አንድ ቀን የእመቤታችን የንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት ስለሆነ የደስታችን ቀን ነው፡፡ የቀደሙ አባቶቻችን ሁሉ በፍጹም ደስታ ያሳለፉት ቀን ነው፡፡
የልደቷ ቀን የሐና የደስታ ዕለት ነበር፤ "አንች ያልወለድሽ መካን ሆይ ደስ ይበልሸ የሚለውን ቃል ሰምታበታለችና" ኢሳ 54፤1/፡፡ የልደቷ ቀን የኢያቄም የደስታ ዕለት ነበር፡፡ ከዕሴይ ግንደ በትር ይወጣል /ኢሳ 11፤1/ የሚለው ቃለ ነቢይ በውድ ልጁ ሲፈጸምና በበትሩ ሠራዊተ አጋንንትን ሲርቁ አይቷልና፡፡
በእርሷ ልደት ነቢያት ሁሉ ተደስተዋል። ትንቢታቸው ፍጻሜ ሲደርስ ፤ የንባባቸው መንፈሰ ሲገለጥ፣ ሕግ ለጸጋ፣ ኦሪት ለወንጌል ሊያስረክቡ፣ ነገደ ሌዊ ሊቀ ካህንነቱን ለነገደ ይሁዳ ሊያስረክብ ሲሰላለፉ አይተዋልና፡፡ የእርሷ ልደት የያዕቆብ ፍጹም ደስታ ነበረ፡፡ በሕልሙ ከመሬት እስከ ሰማይ ተዘርግታ ያያት መሰላል በእውን ከምድር ወደ ላይ በቅድስና ስትደርስ ለማየት በቅቷልና። ራስዋ ላይ እግዚአብሔር የተቀመጠባት እውነተኛዋ መሰላላችን በርግጥም ድንግል ማርያም ናት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የሴት ሁሉ ራስ ወንድ ነው/1ኛ ቆሮ 11፤1/ አለ፡፡ የእርሷ ራስ ግን ያዕቆብ እንዳየው እግዚአብሔር ነው፡፡ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል ያለችው ቅዱስ ጳውሎስ የሴት ሁሉ ራሰ ያለው ወንድ በእርሷ ዘንድ ስላልነበረ ነውና፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ልዩ መሆኗን ስለሚያውቅ አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሸ የተባረክሽ ነሺ፤ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ጽንስሽም እንደ ሌሎቹ ሴቶች አይደለም እያለ ሲሰግድላትና ሲያመሰግናት እርሱን አልፋ ለእግዚአብሔር መቀመጫ ዙፋን ማደሪያ መቅደስ መሆኗን ያየው አባታችን ያዕቆብ በእውነት ደስ አለው፡፡
አብርሃም ልጁን ይስሐቅን የተቤዠለትን አማናዊ በግ ይዛለት የምትወርደውን ዕፀ ሳቤቅ ተወልዳ አይቶ ደስ አለው፡፡ እርሷ ስትወለድ ያች ያያት ቀን መድረሷን አውቆ ፍጹም ደስ አለው፡፡ ይስሐቅም ከታሰረበት ያስፈታችውን ስለእርሱ ፋንታ ቤዛውን ይዛለት ከች ያለችውን ስትወለድ አይቶ በደስታ ቃል ዘለለ፡፡ ከሲኦል እስራት የሚፈታበት ቀንም እንደ ደረሰ በእርሷ ልደት ደወሉን ሰምቷልና ፈነደቀ፡፡ ሙሴ በእርሷ ልደት በደስታ ብዛት ቦረቀ፡፡ ከሩቅ ያያት የማትቃጠል ቁጥቋጦ በሐና ጭን ቁጭ ብላ ሲያይ እንደገነና ወደ እርሷ ሊገሰግስ ወደደ፤ ያኔ ጫማህን አውልቅ ያለውን ድምጽ አቃጨለበትና ባለበት ቆሞ ያያት ጀመር፡፡ ሲያያት ሕብረ ብዙ ሆና አስደነቀችው፡፡ ኦሪትን በሥነ ፍጥረት ሲጀምር በሁለተኛው ቀን ሰኞ እግዚአብሔር ከውኃ ጠፈር ያለውን ሰማይ እንዳሳየው ዛሬ ደግሞ ከመሬት አዳም የተወለደችውን ድንግል አዲስ ሰማይ ሁለተኛ ሰማይ አድርጎ ሲያሳየው ተገረመ፡፡ ያኛው ሰማይ ለዚህ ዐለም ፀሐይ ሲዘጋጅ ወደ ኋላ እንዳየ አሁን ደግሞ የአማናዊው የጽድቅ ፀሐይ መውጫ ስትወለድ ፀሐዩን ሊሞቅ ጊዜው መድረሱን አይቶ ተደሰተ፡፡ እንደገና ሲያያት ደግሞ አሁንም ሕብሯን ለውጣ ታየችው፡፡ ምድር ከመረገሟ በፊት ያለ ዘር ዕፀዋት አዝርእትን ስታበቅል አይቶ የነገረን ሙሴ
ከእናቱ ከሔዋን ልጆች ሆና መርገም ያላረፈባት ያለወንድ ዘር የሕይወት እንጀራ ሆኖ የሚሰጠውን ፍሬ የምታስገኘውን አማናዊት ገራኅተ ሠሉስ አይቶ እንደገና አደነቀ፡፡
ሙሴ ከተመስጦ አልተመለሰም፡፡ መንፈስ ቅዱስን እንደ ጣት አድርጎ በጽላት ላይ ቃሉን ጽፎ የሰጠው እርሱ አካላዊ ቃል ሰው ሆኖ የሚታይባትን ጽሌ ተወልዳ ሲያይ ተገረመ፡፡ ፊትህን አሳየኝ ሲለው ፊቴን ልታይ አትችልም ነገር ግን ጀርባዬን ታያለህ ያለው አምላክ የሚወልደባትን ተወልዳ ሲያይ የጌታን ጀርባ በደብረታቦር የሚያይበት ቀን መድረሱን አውቆ በደስታ ዘለለ፡፡ የመገናኛውን ድንኳን የተከለው ሙሴ ከድምፁ በቀር ያላገኘውን አምላክ የሚያገኝባት እውነተኛዋ የመገናኛው ድንኳን ተተክላ ባያት ጊዜ ደስ አለው። መቅረዝ ፣ ሙዳየ መና፣ ታቦትና የሥረየት መክደኛ ላይ ደም እየረጨ ሲያመልክ የነበረው ሙሴ አማናዊው ብርሃን የሚበራባት መቅረዝ፣ እውነተኛው መና የሚገኝባት ሙዳይ፣ እውነተኛው የሥረየት ደም የሚረጭባት ምሥዋዕ፤ አካላዊ ቃል የተቀረጸባት በሁለተናዋ ጽሩይ ወርቅ በተባለ ፍጹም ንጽሕና ተጊጣ ድንግሊቱን ባያት ጊዜ መደነቁን አበዛ፡፡ ድንኳኑን ሲያስብ እርሷ፣ ታቦቱንም ሲያስብ እርሷ፣ ጽላቱን ሲያስብ እርሷ፣ ሙዳየ መናውንም ሲያስብ እርሷ፣ መቅረዙንም ሲያስብ እርሷ፣ ማዕጠንተ ወርቁንም ሲያስብ እርሷ ስትሆንበት እንዴት አይደነቅ በእውነት፡፡ ሙሴ በዚህ አላበቃም፡፡ ሕግ የተቀበለበትን የጨሰውን ተራራ አስታወሰና ልጁን ዳዊትን ጠራው። ዳዊትም የአባቱን ሙሴን ጥሪ ሰምቶ ሲነሣ የረጋችው ተራራ ተወልዳ አያትና እርሱም በደስታ ዘለለ፡፡ አዎ "የእግዚአብሔር ተራራ የለመለመ ተራራ ነው፤ የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ፤ እግዚአብሔር ይህን ተራራ ያድርበት ዘንድ ወደደው " /መዝ 68 ፤ 16/ ብሎ የተናገረላት ተራራ ስትወለድ አይቶ ደስ አለዉ፡፡
ሐላፊውን ብሉይ ኪዳን አባቱ ሙሴ ሲቀበል በነጓድጓድ ድምጽ በረዓድና በፍርሃት ነበረ፡፡ የማያልፈው ሐዲሱ ኪዳን ግን በጸና ተራራ እንደሚሰጥ የተናገረላት ያድርባት ዘንድ የወደደዳት አማናዊት የንጽሕና የቅድስና ተራራ ተወልዳ አይቶ ደስ እያለው መዝሙሮችን በአናት በአናት አከታተለ፡፡ ልጁ ሰሎሞንም "ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው፤ ጠጕርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ እንደ ፍየል መንጋ ነው" /መኃ 4 ፤ 1/ እያለ በምስጋና ተከተለው። ኢሳይያስም ንጹሕ ወረቀቱን አይቶ ደስ አለው፡፡ እንደ ታሸገች የተጻፈባት ሀዝብም አህዛብም ይህን ደብዳቤ ልናንብበው አንችልም ያሏት አካላዊ ቃል በድንግልና የሚጻፍባትን ንጹሕ ወረቀት /ኢሳ 29;11/ አይቶ ተደነቀ። ሕዝቅኤልም ሁለንተናዋ ዝግ ሆኖ እግዚአብሔር ብቻ ገብቶ የወጣባት መቅደሱን ተሠርታ አይቶ ደስ አለው፡፡
ተራ በተራ ሁሉም ነቢያት ትንቢቶቻቸውን ይዘው ስለእርሷ ያዩትን ራእይ፣ ምሳሌና ትንቢት ፍጻሜውን እያዩ ተደነቁ። መሐንዲስ የሕንጻውን ንድፍና የሚሠራውን ሕንጻ እንደሚያስተያይ እነርሱም በልደቷ ትንቢታቸውን ከፍጻሜው መጀመሪያ መሠረት ጋር እያስተያዩ ተደሰቱ፡፡
በመጨረሻም የፍጥረት ሁሉ አባት አዳም ከልጆቹ ጋር ደስ አለው፡፡ አዳም ሆይ መሬት ነህና ወደ መሬት ትመለሳለህ ያለው ጌታው ከጨለማ ሲኦል ሊያውጣው ልጁን ከመሬት ባሕርዩ አንሥቶ እርሷን ሰማይ አድርጎ ሲያያት በእርሷም ላይ እርሱ ፀሐይ ሆኖ ሊወጣ ወገግታውን ሲያሳየው በደስታ አነባ። የሰጠኸኝ ሴት አሳተችኝ ብሎ የከሰሳት ሔዋንን ተክታ የሚያመሰግናት ሌላ ሔዋን ተወልዳ ሲያይ ደስስስ አለው፡፡ ምሳሌና የሚተካከላት እንደሌለም ሲያይ ልጁን ሰሎሞንን ጠርቶ "ለእኗቷ አንዲት ናት፣ ለወለደቻትም የተመረጠች ናት" የሚለውን ዘምር አለው፡፡
ልጆቹ ሁሉ ከመረገሙ በፊት ያለ ክብሩን ስላላዩ በተገቢው መጠን የማያደንቁለትን ከስሕተት በፊት የነበረ ክብሩንና ጸጋውን ይዛ ስትወለድ በደስታ ተንሰቀሰቀ። የአዳምን ለቅሶ ሰምታ ሔዋን እናቷ የመርገም ጨርቋን ጥላ ብድግ አለች። አንድ ልጇን እያየች በደስታ አለቀሰች። በልጆቿ ሳይቀር ምነው እባብን ሰማሽው የሚል ወቀሳ እየሰማች ስታዝን የኖረች ምስኪን እናት መርገሟን ወርውራ በቅድስና ከብራ መላአክትን በልጣ እንደ ጨረቃ ስታበራ ስታያት መካሷን አይታ ፈነደቀች፡፡......

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሰይጣንም ቢሆን ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ደናግላን ክብራቸውን ሲያጡለት ጻድቃንን ያስኮነነ ያህል እጅግ ደስ ይሰኛል:: ስለዚህ ለትዳር ያሰብሽው ሰውም ቢሆን እስከ ጋብቻ ድረስ ከሩካቤ ተጠብቆ መኖር እንደሚገባ የማያምን ሆኖ ካገኘሽው ስለ ድንግልናሽ አታውሪለት፡፡ ብዙ ካጠናሽውና መልካም ሰው ሆኖ ካገኘሽው አንቺ እንኳን ብትሰንፊ እርሱ ሊረዳሽ ይችላልና መጠንቀቅሽ እንዳለ ሆኖ አኗኗርሽን ቢያውቅ መልካም ነው። ድንግል ሳይሆኑ ድንግል ነኝ ማለት ይጎዳል እንጂ ድንግል ሆነው ድንግል መባል አይገባኝም ወይም አይደለሁም ማለት ምንም አይጐዳም፡፡
ኘ. ድንግልና ማጓጓቱ አይቀርም ይልቁንም ድንግል የሆነ ሰው የበለጠ ድንግልን ይፈልጋል፡፡ ታዲያ እንዲህ ዓይነት ሰው ሆነህ ሳለ ተፈትሖ ያገኛት (ድንግል ያልሆነች) ሚስት ብታጭ ሕሊናህ ድንግል ወደ ሆነች ሌላ ሴት እንዳይሳብ መጠንቀቅ አለብህ:: መጀመሪያ ድንግል የሆነች ሴት ብታጭ መልካም ነበር፡፡ ያ ካልሆነ ግን በያዝከው መጽናት አለብህ እንጂ ከሚስትህ ጋር ክብር በማጣት ለመተካክል ስትል ድንግልናህን ለሌላ አትስጥ፡፡ ወይም ሌላ ድንግልን በመሻት አታመነዝር! ብዙዎች በዚህ ምክንያት ስተዋልና፡፡ ድንግል ሴት አጓጉታኽ እንዳታመነዝር ተጠንቀቅ።
አ. ኢዮናዳብ የተባለው ሰው ከትዕማር ጋር እንዲተኛ አምኖንን እንደ መከረው ይህን እንድታደርግ የሚመክሩህ ብዙ ባልንጀሮች ሊኖሩህ ይችላሉ፡፡ ቢሆንም ምክራቸውን በመቀበል ክብርህን መጣልህ ተገቢ አይደለም፡፡ በእንዲህ ዓይነቱ ምክር አምኖንም ቢሆን በሰይፍ ከመገደል በቀር የተጠቀመው ምንም ነገር የለም:: ለሰዎች ግፊት በቀላሉ መረታት አያስፈልግም፡፡ ከሰዎች ግፊት በላይ ደግሞ የመጠጥ ግፊት ተጠቃሽ ነው። ብዙዎች በመጠጥ ግፊት ንጽሕናቸውን አሳድፈዋል:: ስለዚህ ከዝሙት ለመጠበቅ ከስካር መጠበቅ ዋነኛ መንገድ ነው፡፡
ከ. ለብዙዎች ሰዎች ከክብር ማነስና ለንጽሕናቸው መጉደፍ ሌላው ዓቢይ ተጠቃሽ ነገር ቢኖር ግብዣ ነው፡፡ በልዩ ልዩ ምክንያት የሚከናወኑ የራት ግብዣዎች ብዙዎችን ይህን ለመሰለ ጥፋት ዳርገዋል፡፡ ስለዚህ ይህን በመሰሉ ፓርቲዎች፣ የራት ግብዣዎችና መዝናኛ ኘሮግራሞች ከቻልክ ጨርሶ ተሳታፊ አለመሆን መልካም ነው፡፡ ካልሆነም እንዴት በጥንቃቄ ራስህን ማስተናገድ እንዳለብህ የራስህን እቅድ ነድፈህ በጊዜ ወደ ቤትህ የምትገባበትን መንገድ ማመቻቸት ይኖርብሃል፡፡ በግብዣው ቦታ ሳለኽም ጥበቃ ባለው መልኩ መንቀሳቀስ፣ ከምታፍረውና ከሚታፈር ሰው ጋር መቀመጥ በእጅጉ ይጠቅማል፡፡ በጣም ማምሸትንና ከቤት ውጭ ማደርን ግን በጭራሽ መሞከር የለብህም:: ይህ የብዙዎች መጥፊያ ሆኗልና::
ወ. ወንድ ከሆንክ ብዙ ጓደኞችህ ሴቶች አይሁኑ፡፡ ይህ ማለት ግን ሴት ጓደኞች አይኑሩህ ማለት አይደለም:: ይልቁኑም ሴቶችን በዙሪያህ አታብዛ ወይም ልክ ሳይኖርህ ወንዶችን የምታቀርበውን ያህል ሴቶችን ምሥጢረኛ አታድርግ ማለት ነው:: ይህ አካሄድ በንጽሕና ለመኖር ለፈለገ ሰው የበለጠ ይጠቅመዋልና:: ሴትም ከሆንሽ እንዲሁ የቅርብ ጓደኞችሽ ወንዶች አይሁኑ:: እንዲሁም ከብዙ ወንዶች ጋር ያለ ውድ በግድ እንዳትቀራረቢና ክብርሽን ለሚያሳጣ የዝሙት ተግባር እንዳትጋለጪ ተማሪ ሳለሽ እንኳን የምትመርጪው የትምህርት ዘርፍ ወደ ሥራ ዓለም ስትመጪ በይበልጥ የሚያቀራርብሽ ከወንዶች ጋር እንዳይሆን ተጠንቀቂ:: ይህ ሐሳብ የሕይወት ጎዳናን ጠባብ የሚያደርግ ኋላ ቀር ሐሳብ ሊመስል ይችላል:: ሆኖም በንጽሕና መኖር ከምንም ነገር በልጦ የሚታየው ሰው የዚህ ምክር ጥቅም ይገባዋል፡፡
ወንዶችና ሴቶች ባልንጀራሞች ቢሆኑ የሚገኘውን ጥቅም ማንም ይረዳዋል:: ነገር ግን ሴቶች ሴቶችን እየራቁ ከወንዶች ጋር በተወዳጁ ቁጥር የሚያጡትንም ሴትነትና ወንዶችም ሴቶችን ብቻ በመቅረባቸው የሚመጣውን የአርአያ ለውጥ ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡ አንዲት ሴት ሴቶችን እየነቀፈች «ወንዶች ይሻሉኛል» በማለት ብዙ ወንዶችን እጅግ ብትላመድ የሴትነት መገለጫዎቿን እያጣች ከመሄዷም ሌላ ለዝሙት የተጋለጠች ትሆናለች:: ክብረ ድንግልናዋንም በቀላሉ ታጣለች:: ወንዱም ቢሆን እንዲሁ ነው:: ታዲያ ለተፈጥሮአችን በሚስማማ መልኩ ብዙውን ጊዜ ባለንጀሮቻችን ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው እንዲሆኑ ለምን ጥረት እናደርግም? በተረፈ ግን የመቀራረባችን ሁኔታ ልክ ይኑረው እንጂ ተቃራኒን ጾታ ባለንጀራ ማድረግ ስሕተት አይደለም፡፡
ዐ. በዚህ ዘመን ንጽሕናውን ጠብቆ መኖር የሚሻ ሰው ራሱን ደብቆ ካልሆነ እጅግ ይቸገራል:: ስለዚህ ሴቶች እኅቶቻችን ከአለባበስ አንሥቶ ትሑት መሆን ይኖርባቸዋል:: ልይ! ልታይ! እና ልወቅ! ልታወቅ ! ማለት ድንግልናን ያሳጣል፡፡ ያለ ምክንያትም አደባባይ መውጣትም እንዲሁ ነው:: በዚህ ዓይነት አካሄድ ድንግልናን ጠብቆ መኖር እንደማይቻል ማር ይስሐቅ እንዲህ ብሏል፡- «ወኢትትዐወቅ ድንግል በውስተ ጉባኤያት ወትዕይንታት» ይህም «ወንዶች መኻል እየዋለች ከተማ እየዞረች በድንግልና የምትገኝ ሴት የለችም›› እንደ ማለት ነው፡፡ (ማር.ይስ.አን.28 ምዕ.2) ስለዚህ ክብርን ለማጣት ከሚያጋልጡ ሁኔታዎች አንዱ ወጣ! ወጣ! ማለትና እግርን አለመሰብሰብ ነው ማለት ነው።

በቀጣይ ምዕራፍ ስምንት ክፍል ስድስት :
👉 ድንግልና ያስመካል? በሚል ይቀጥላል....

ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሠ. ስለወር አበባ በተጻፈበት አንቀጽ እንደተገለጸው በወቅቱ ልዩ ልዩ የሕመም ስሜት እንደሚኖር የታወቀ ነው። በዚህ ጊዜ ሕመሙ የጠና ከሆነ ወደ ሐኪም ዘንድ መሄድ ግድ ይላል፡፡ አብዛኞቹ የሕክምና ባለሙያዎች ከሚሰጡት ሙያዊ እገዛ በተጨማሪ «ከወንዶች ጋር ሩካቤ ማድረግ ስትጀምሪ ሕመሙ ይቀንሳል ወይም ይተውሻል» የሚል የመፍትሔ ምክር መደመጡ አይቀርም፡፡
አስቀድሞ በውስጣቸው ከነበረው ተቃራኒ ጾታን የመፈለግ ግፊት በተጨማሪ ይህን ለመሰለ ሕመማቸው ሩካቤ መፈጸም መፍትሔ እንደሆነ ሲነገራቸው ዔሳው «ብኩርናዬ ለኔ ምኔ ናት?» እንዳለ «ድንግናዬ ምን ያደርግልኛል?» በማለት ለዝሙት የተጋለጡም ሰዎች አልጠፉም፡፡ ስለዚህ ይህን የመሰለ ክብር እንድናጣ በብዙ መልኩ መፈተን አይቀርልንም፡፡ ለጊዜው የሚሆን መጠነኛ የሕመም ስሜትን መታገሥ አቅቶን ለማያልፍ ጸጸት አንጋለጥ፡፡ በዚህ መልኩ እንኳን ሐኪም መክሮን ይቅርና አዞንም ቢሆን ሕገ ወጥ ሩካቤ ማለትም ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ሩካቤን መሞከር የለብንም፡፡
ረ. ድንግልና ያላትን ሴት አጭተሃል እንበል፡፡ ምንም ሳትደርስባት ራሳችሁን ጠብቃችው እየኖራችሁ ሳለ በድንገት ተለያያችሁ:: የዚህ ጊዜ ምን ይሰማሃል? ወይኔ ሕጓን እንኳን በገሠሥኩ ኖሮ እያልክ ትቆጫለህን? ሊቆጭህ አይገባም! በእርግጥ ይህንን የሚያውቁ ጓደኞችህ አሁን አንተ ወንድ ነህ? እያሉ ሊዘባበቱብህ ይችላሉ:: አንተ ግን መመካት አይገባህም እንጂ ከወንድም ወንድ መሆንህን እመን፡፡ ምክንያቱም ከጋብቻ በፊት ድንግልናን መግሠሥ የዘማውያን ሙያ እንጂ የወንድነት መታወቂያ አይደለም፡፡ እንዲያውም ወንድ የሚያሰኘው ራስን በንጽሕና ለመጠበቅ መቻል ነው።
ደግሞስ አንተን ብቻ ድንግልና ወሳጅ ማን አደረገኽ? አንተ የሷን ድንግልና በምትወስድበት ጊዜና ጎዳና ያንተም ድንግልና እንደሚገሠሥ አታውቅምን? እኔ እንኳን ድንግልናዬን ቀደም አጥፍቼው ነበር ብትል እንኳን ኃጢአት እየሠራኽ መሆኑን ማን በነገረኽ? ዝሙት መሥራት ስልጣኔ፣ ችሎታና ዘመናዊነት አይደለም:: ከሰብአ ትካት፣ ከሰብኣ ሰዶምና ከሰብኣ ገሞራ ጊዜ ጀምሮ የነበረ ዘማዊነት በምን ምክንያት ስልጣኔና ዘመናዊነት ይሆናል፡፡

ሰ. ሊጋቡ ሲቃረቡ ድንግልናቸውን እንደሚያጡ ሰዎች ሁሉ የተጫጩ ወንድና ሴት የሚለያዩበት ሁኔታም ሲፈጠር ድንግልናቸውን ያጡ ብዙዎች አሉ፡፡ ሁለቱ ተፈቃቃሪዎች ራሳቸውን ጠብቀው ከኖሩ በኋላ የሚያለያያቸው አለመግባባት ሲፈጠር «ንጽሕናቸውን ሳላስፈርስ?» በማለት ሰይጣን በቁጣ ይነሣሣባቸዋል፡፡ ይህ ርኩስ መንፈስ በሁለቱም ወይም ለጥፋት ሐሳቡ በተመቸው በአንደኛው ያድርና ሲሆን በውዴታና በማባበል ካልሆነ ደግሞ አስገድዶ በመድፈርም ቢሆን እንዲፈጽመው ሊገፋፋው ይችላል፡፡
ፍቅረኛሞች የሚለያዩበት ጊዜ እጅግ ፈታኝ ወቅት ነው፡፡ ስለዚህ በፍቅር ከሚኖሩበት ጊዜ ይልቅ በሚለያዩበት ጊዜ ንጽሕናን ጠብቆ ለመቆየት የበለጠ ጥንቃቄ ይጠይቃል:: በሚለያዩበት ወቅት ሁለቱም ወይም ከሁለቱ አንዱ መከፋታቸው አይቀርም ስለዚህ እንክብካቤ ባላደርግ «ግፍ» ይሆንብኛል የሚል ሐሳብ ይፈጠርና ቢያንስ አንዱ ወገን መንከባከብ እንዳለበት ይሰማዋል፡፡ የተጎዳን ሰው መንከባከብ ባልከፋ ነበር ነገር ግን መሰናክልና ድንግልናን ማጣት የሚፈጠረው በዚህ የመንከባከብ ሂደት ውስጥ ነው:: ስለዚህ ይህን በመሰለ ጊዜ ጠንቀቅ ማለት ይበጃል::
ከሁሉ የሚያስደንቀውና የሚያሳዝነው እንዲህ ባለ የመለያየት ዋዜማ ፍቅራቸው ለሁልጊዜ መሆኑን የገለጡና ማስታወሻ ያኖሩ እየመሰላቸው ድንግልናቸውን የሚጥሉ ሴቶች መኖራቸው ነው:: አንዳንዶችማ «ለሌላ ከምሰጠው» እስከ ማለት ደርሰው ለሚለያቸው ወንድ ድንግልናቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ:: እንዲህ የምታስቢ ከሆነ እስኪ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ሞክሪ፡፡ እየተለየሽ ያለው ወንድ ኋላ ከምታገቢው ወንድ የበለጠ ተፈቃሪ መሆኑን በምን አረጋገጥሽ? ከበለጠስ ለምን ትለይዋለሽ? ለሚመጣው ባልሽስ ያስቀረሽለት ምን ስጦታ አለሽ? ምን ላድርግለት የሚያሰኝ እጅግ ተወዳጅ ባልስ ብታገኚ የቀድሞ ሥራሽ ጸጸት አያስከትልብሽምን? የምታገቢው ባል ከቀድሞ ፍቅረኛሽና ወደ ፊት ልታገኚው ከምትችይው ማንኛውም ወንድ የበለጠ ልታፈቅሪው ካልቻልሽ ማግባትሽ መቼም ቢሆን ፍጹም ትክክል አይሆንም፡፡ ስለዚህ ድንግልናን ጨምሮ ምርጥ ነገሮች ሁሉ ሊያገባ ላጨሽ ወይም አጭቶሽ ለነበረ ሰው ሳይሆን ላገባሽው ወንድ ብቻ መሆን ይኖርበታል:: በተጨማሪም ዝሙት ምጽዋት ሊሆን እንደማይችል «ዜና ሥላሴ» ይናገራል፡፡ ስለዚህ ዝሙት ሠርተሽ «አሳዝኖኝ ነው!» ብትዩ የሚሰማሽ የለም፡፡
ሸ. የመለያየት ነገር ሲነሣ ሙሉ ለሙሉ ላለመገናኘት የሚደረግ መለያየት ሳይሆን በሥራና በትምህርት ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ ርቆ የመሄድ ዓይነት መለያየት በሚፈጠርበት ጊዜ ወንድና ሴት ተፋቃሪዎች ሩካቤ መፈጸምን ሻይ፣ ቡና እንደ ማለት እየቆጠሩት ይገኛል፡፡ በዚህ ዓይነት አጋጣሚ ክብረ ድንግልናቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ይህም ሰው ስለ ድንግልና አጠባበቅ ያለውን የተዛባ አመለካከት ያሳያል፡፡
ቀ. ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «ስለ ድንግልናው ያፈረ ሰው ቢኖር» 1ኛ ቆሮ 7÷36 በድንግልና መኖራቸው የሚያሳፍራቸው፣ ያልሠለጠነ፤ አላዋቂ፣ ጤና ቢስ፣ ወንድነት የሌላቸውና ተፈላጊነትን ያጡ ተደርገው እንደሚቆጠሩ አድርገው ሚያስቡ ብዙዎች አሉ፡፡ እንደዚህ ያሉ ሰዎች ማንኛውም ሰው አብሮአቸው ቢተኛ ተፈላጊነታቸው፣ አዋቂነታቸውና ሥልጡን መሆናቸው የተረጋገጠ ይመስላቸዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሐሳብ በተገኘው ተራ አጋጣሚ ንጽሕናችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ከማድረግ ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡ ስለሆነም ይህን ከመሰለ ደካማ አመለካከት ተላቆ ንጽሕናን መጠበቅ ተገቢ ነገር ነው፡፡

በ. ሰው ወደዚህ ዓለም ከመጣ ጀምሮ በልዩ ልዩ ጊዜ በተለያየ ደዌ ሲሠቃይ ይታያል።በዚህ ጊዜ የታመሙትን በሚገባ ማስታመም ለመንግሥተ ሰማይ የሚያበቃ የጽድቅ ሥራ ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ ክፉ መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች ታማሚዎችን በማስታመም ሰበብ ዝሙት ሲፈጽሙባቸው መስማት ለጆሮ የሚዘገንን ቢሆንም ይህ አስነዋሪ ተግባር በተለያየ ጊዜ ተፈጽሟል። በዚህ ድርጊታቸው ክስ የተመሠረተባቸው ብዙ የሕክምና ባለሙያዎችም ይገኛሉ።
እንዲህ ባሉ ቦታዎች የበለጠ ለዝሙት ተግባር የሚያነሣሡ ምክንያቶች አይጠፉም:: አንደኛ ቦታው መጠመቂያ ወይም የሕክምና ቦታ እስከ ሆነ ድረስ ሰዎች ከልብስ ተራቁተው የሚታዩበት ጊዜ አለ፡፡ሌላው በተለይ በጸበል መጠመቂያ ስፍራዎች ደግሞ ሰይጣን ታማሚዎችን እያወራጨ ከልብስ ያራቁታቸውና አካላቸውን እያዩ ሌሎች በዝሙት እንዲፈተኑ ያደርጋል፡፡ ከዚህም አልፎ ተርፎ ታማሚዎቹን «ሮጠን እናመልጣለን›› እያሰኘ ከአስታማሚዎቻቸው ጋር እንዲጓተቱና እንዲታገሉ ያደርጋል:: ታማሚዋና አስታማሚው የተለያየ ፆታ እስካላቸው ድረስ ይህ መላፋት በአስታማሚው ላይ የሚፈጥረው የፍትወት መነሣሣት በምንም ለመመለስ የሚያስቸግር ይሆናል፡፡ ይህን አጋጣሚ እንደ ምቹና እንደ አስደሳች ነገር በመቁጠር ማስታመም ጸጋቸው ሳይሆን ለመላፋትና የሰዎችን ገላ ለመመልከት ከጠበል ስፍራ የማይጠፉ ሰዎች እንዳለ አስተውለው ያውቃሉ? እንዲህ ከሆነ ከየትም ቦታ ይልቅ በጠበል ቦታዎች በይበልጥ ከሰይጣነ ዝሙት መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ አያጠራጥርም።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ስምንት ክፍል አምስት

.................................................
ድንግልናን የሚያሳጡ አደገኛ ወቅቶች፣ ቦታዎችና አጋጣሚዎች
ሕጋዊ ባልሆነ ሩካቤ ምክንያት ሰዎች ድንግልናቸውን የሚያጡት በተለያየ የዕድሜ ደረጃ ላይ እያሉ ነው፡፡ አንዳንዶች ገና በልጅነትና በመጀመሪያዎቹ የወጣትነት አፍላ ጊዜያት ድንግልናቸውን ያጣሉ። ሌሎች ደግሞ አስቸጋሪውን የወጣትነት ዕድሜ አጋምሰው ክብራቸውን የሚያጡበት ሁኔታ ይፈጠራል፤ጥቂቶች ደግሞ ያን ሁሉ የወጣትነት ፈተና ካገባደዱ በኋላ ወደ መጨረሻ ሲደርሱ ክብራቸውን የሚያጡበት ጊዜ አለ፡፡ በዚህ መልኩ ከፍጻሜ ሲደርሱ ለክብር አለመብቃት በእጅጉ ያስቆጫል።
ይህ የሚሆነው ልጆች ስለተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ከሚኖራቸው የአመለካከት ልዩነት፣ ለዚህ ዓይነቱ ግንኙነት ከሚኖራቸው መጋለጥ፣ ከራሳቸው መንፈሳዊና አካላዊ ጥንካሬ፣ ከባሕልና ከአስተዳደግ ልዩነት ወዘተ የተነሣ ነው:: ሆኖም ግን ብዙ ነገር ተቋቁመው ካለፉ በኋላ የፈተናው መጠን በሚቀንስበትና ወደ ጋብቻ በሚቃረቡበት ሰዓት ሳያገቡ ድንግልናን ማጣት ከሁሉ የበለጠ የሚያስቆጭ ነው።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተገልጾ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ በምድር መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ እኔ ኃጢአቱን ሁሉ እደመስሳለሁ በመከራም ውስጥ ሁኖ በባሕርም ሆነ በየብስ ወይም በደዌ በስምህ የሚለምነኝን እኔ ፈጥኜ ከመከራው አድነዋለሁ ይህንንም ጌታችን ተናግሮ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ፡፡

ከዚህ በኋላ ራሱን ዘንበል አድርጎ በሰይፍ ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያት አክሊላትን ተቀበለ፡፡ ከአገልጋዮቹም የቀሩት ሥጋውን ወስደው በልብስ ጠቀለሉት ወደ ሀገሩ ልዳም ወሰዱት፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው በውስጥዋ አኖሩት ከእርሱም ቍጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ፡፡

የሰማዕቱ ረድኤትና በረከት አይለየን!
©ስንክሳር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

2. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “ማርያም ቤዛዊተ ዓለም” አትባልም በማለት ከቤተ ክርስቲያናችን የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ የሰጡት ሕጸጽ ያለበት ትምህርት በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በሚገባ ተመርምሮና ተጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ በአስቸኳይ እንዲቀርብ ብፁዕነታቸውም ጉዳዩ ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በተአቅቦ እንዲቆዩ፣

3. ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት እና ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፏቸው የስሕተት ትምህርቶችና በሌሎችም መምህራን የተላለፉ ነቀፋ ያለባቸው ትምህርቶች ካሉ የሊቃውንት ጉባኤ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ አንጻር በሚገባ መርምሮና አጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብ፣

4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኝ ብዙኃን ስርጭት ድርጅት ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር ሚዲያ የአየር ሰዓት የሰጠበትን ዝርዝር ሁኔታና ከማኅበሩ ጋር በተያያዘ አየር ላይ ያዋላቸውን ትምህርቶች የሚያሳይ ሪፖርት እንዲያቀርብ ይደረግ በማለት ቋሚ ሲኖዶስ ወስኖ የዕለቱን ጉባኤ በቅዱስነታቸው ጸሎተ ቡራኬ አጠናቋል።

ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም:
ተነስቷል በዚህ የለም(2):
መድኃኔዓለም
ሞት የማይችለው የበረታ:
ኃያል ነው ማይረታ ማኅተሙን የፈታ:
የትንሳኤው ጌታ።
*አዝ*
ገዳዩ ሞት በእርሱ ድል መንሳት ተዋጠና:
ሰንሰለቴን ቀንበሬን ተካው በበገና:
ሞት ሆይ መውጊያህ የታል እያልን ምንዘምረው:
መስቀልህ ጦር ስምህ ጋሻችን ሆኖልን ነው :
ዳንን የምንልው።
*አዝ*
ተሻግረናል ስላሻገርከን ለዘለዓለም:
በመቃብር ሞት ይይዝህ ዘንድ ከቶ አልቻለም:
ኃይለኛውን በኃይል አስረኸው ላይፈታ:
ዘመርንልህ አሸናፊ ነህ የእኛ ጌታ:
ከፍ በል በእልልታ።
*አዝ*
ሞቶ ማዳን ለማን ተችሏል ካንተ በቀር:
ጌትነትህ ሥራህ ይኖራል ሲመሰከር:
ወዳጄ ሆይ ውበትህ ውብ ነው የሚያበራ:
ተጨነቀ ተንቀጠቀጠ ጠላት ፈራ:
ዕፁብ ያንተ ሥራ።
*አዝ*
መስክሩለት የምስራች ነው ታላቅ ዜና:
መላዕክቱ ነጭ ለብሰዋል ድል ነውና:
ከተማዋ አንዳች ሆናለች በለሊቱ:
በዝማሬ ተንቀጠቀጠ ወኅኒ ቤቱ:
ከበሮውን ምቱ።

በዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
እሁድ
ዳግማይ ትንሣኤ

ዳግማይ ትንሣኤ ማለት ጌታችን በተደጋጋሚ ለሐዋርያቱ እና ለተለያዩ ሰዎች በተለያየ ሥፍራ መገለጡን የምናስብበት ሳምንት ነው፡፡
ቤተክርስቲያን ከትንሣኤው እስከ ዳግማይ ትንሣኤው ያለውን ሳምንት እንደ አንድ ቀን ነው የምታየው ክብር ይግባውና የትንሣኤው ጌታ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው ዕለት ጀምሮ ከመግደላዊት በመጀመር ለልዩ ልዩ ሰዎች ተገልጧል፡፡
፩. ለመግደላዊት ማርያም ተገልጧል፡፡(ዮሐ፳፡፲፩)
፪. ለሴቶች ተገልጧል፡፡(ማቴ፳፰፡፱)
፫. ለሐዋርያው ጴጥሮስ ተገልጧል፡፡(ሉቃ፳፬፡፴፬)
፬. ለኤማውስ መንገደኞች ተገልጧል፡፡(ሉቃ፳፬፡፲፫)
፭. ከሐዋርያው ቶማስ በቀር ለሐዋርያት ተገልጧል፡፡(ዮሐ፳፡፲፱)
፮. ሐዋርያው ቶማስ ባለበት ለደቀ መዛሙርቱ በዝግ ቤት ተገልጧል፡፡(ዮሐ፳፡ ፳፮)
፯. በጥብርያዶስ ለሰባቱ ሐዋርያት ( ጴጥሮስ ቶማስ ናትናኤል ሉቃስ ኒቆዲሞስ ይሁዳ ያዕቆብ ) ተገልጧል፡፡
፰. ለአምስት መቶ ሰዎች ተገልጧል፡፡(፩ቆሮ፲፭፡፮)
፱. ለሐዋርያው ያዕቆብ ተገልጧል፡፡(፩ቆሮ፲፭፡፯)
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተገለጠባቸው በእያንዳንዱ መገለጦች ውስጥ ለሐዋርያቱ ሦስት አደራዎችን ሰጥቷቸዋል፡፡ እነዚህም :-
በመጀመሪያው የትንሣኤ ዕለት የኃጢአት ስርየት የማድረግን ሥልጣን ሰጥቷቸዋል(ዮሐ፳፡፳፫)
በሁለተኛው ደግሞ የማስተማር ጸጋ ሰጥቷቸዋል(ማቴ፳፰፡፲፮-፳)
በሦስተኛው ሕጻናትን ፤ ወጣትን እና ሽማግሌዎችን የመጠበቅና የመምራት ኃላፊነት ሰጥቷቸዋል፡፡(ዮሐ፳፩፡፲፭-፲፰)
በዚህም ሐዋርያዊት ወይም የሐዋርያትን ፍኖት የተከተለች በሐዋርያት በኩል ይህንን ሁሉ ጸጋ ያገኘች ቅድስት ፣ አንዲት ፣ ኩላዊት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ሁሉንም አደራ እና መመሪያ ተግባራዊ እያደረገች ትገኛለች፡፡
ሐዋርያዊት የሆነች ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በዚህ ዕለት ልክ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ጋር በነበሩበት ዘመን ይሰማቸው የነበረውን ደስታ በማሰብ ሥርዓተ አምልኮቷን ትፈጽማለች፡፡
በግጻዌው መሰረት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናትም ሆነ ገዳማት የሚዘመረው
መዝሙር "ይትፌሳህ ሰማይ ወትትሐሰይ ምድር" ትርጉም "ሰማይ ይደሰታል ምድርም ሐሴት ታደርጋለች" የሚለው ሲሆን ምስባኩ ደግሞ "ይትነሣእ እግዚአብሔር ወይዘረው ጸሩ ወይጎይዩ ጸላእቱ እምቅድመ ገጽ ከመ የሀልቅ ጢስ ከማሁ የሀልቁ" ትርጉም እግዚአብሔር ይነሳ ጠላቶቹ ይበተኑ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ ጢስ እንደሚበን እንዲሁ ይብነኑ" (መዝ፷፯(፷፰)፩-፪)
ቅዳሴው የዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ሲሆን ወንጌሉ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ሃያ ከቁጥር አሥራ ዘጠኝ እስከ ፍጻሜ ነው፡፡ በዚህ ወንጌል ላይ ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ ያላቸውን ሐዋርያት እናገኛለን፡፡ "ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው፡፡" (ዮሐ፳፡፳)
ያም ቀን ዕለተ እሑድ ማታ ላይ ነበር፤ የጨለማው መጨለም ፤ የአይሁድ ዛቻና ማስፈራራት ሐዋርያትን እጅጉን አስጨንቋቸዋል ከአሁን አሁን ገደሉን ፤ በቃ ጠፋን፤ይህን እና ይህን ብቻ እያሰቡ በራቸውን እንዳይከፍቱት በጠንካራ ቁልፍ ቆልፈው የጭንቀታቸው መጠን እየጨመረ እየጨመረ... ባለበት በዚህ ጊዜ ምንም እንኳን ከመከራው እና ከጭንቀቱ ብዛት በሩን ዘግተው ሞታቸውን ቢጠባበቁም በሞት ላይ ስልጣን ያለው ተስፋን መቀጠል የሚችል አምላክ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ብሎ መካከላቸው ሲቆም ከመቅጽበት ጌታን ባዩ ጊዜ በሐዘን የጨፈገገው ፊታቸው በደስታ በራ፡፡ ክብር ለአምላካችን ይሁን፡፡ የእኛንም የተዘጋ ቤታችንን ከፍቶ ገብቶ በሐዘን እና በጭንቀት የጨፈገገው ፊታችንን በደስታ አብርቶ ሰላማችንን ይመልስልን፡፡ አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…
Subscribe to a channel