በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
የኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የማኅበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ።
ሚያዚያ ፲፮/ ፳፻፲፯ ዓ.ም
መምሪያው ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር በጻፈው ደብዳቤ ማኅበሩ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ ርቱዕ እምነትን ከሥነ ምግባር ጋር ይዞ የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያን ያሳዘነ፣ እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ለጠላት መሳለቂያ እንድትሆን ያደረገ፣ ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ጋር የሚቃረን እመቤታችን ቤዛ አይደለችም የሚል ጤናማ ያልሆነ ትምህርት ሚያዝያ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በማኅበሩ ሚዲያ ማስተላለፉን እንደተመለከተ ገልጾ የማኀበራት ምዝገባ ክትትል እና ቁጥጥር መምሪያው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ጸድቆ በተሰጠው ደንብ መሠረት በማኅበራት መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮች ሲፈጠሩ ተገቢውን ክትትልና አስፈላጊውን እርምት የመስጠት ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ በደብዳቤው ለተጠቀሱ አምስት ነጥቦችን በማኅበሩ በኩል አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥባቸው በጥብቅ አሳስቧል።
መምሪያው በጻፈው ደብዳቤ ላይም በዕለተ ስቅለት የተላለፈው ትምህርት ቪዲዩ በአስቸኳይ ከማኅበሩ ዩቲዩብ እንዲወርድ እንዲያደርግና በዕለቱ የተላለፈውን ትምህርት ሙሉ ቪዲዮ ቅጂ ለመምሪያው እንዲያቀርብ ጥብቅ መመሪያ ሰጥቷል።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
ሐሙስ
አዳም ይባላል
ይህ ዕለት አዳም ሐሙስ (አዳም) የተባለበት ምክንያት አምላካችን እግዚአብሔር ለአዳም "ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ቃል የገባበት ዕለት በመሆኑ ይህንን ስያሜ አግኝቷል፡፡(ዘፍ፫፡ ፲፭) ፤ (መጽሐፈ ቀለሜንጦስ አንቀጽ ፰ እና መጽሐፈ አክሲማሮስ ዘዓርብ ቁ. ፲፫) ቤተክርስቲያን በዋናነት ለአዳም የተሰጠውን የተስፋ ቃል አምላካችን መፈጸሙንና የሰው ልጆች ሁሉ በትንሣኤው ከሞት ነጻ እንደወጡ በዚህ ዕለት ታስተምራለች፡፡
በዚህ ዕለት በአባታችን በአዳም በእናታችን በሔዋን አንጻር:-
፩. ከውድቀታችን ይልቅ መነሳታችንን
፪. ከባርነታችን ይልቅ ነጻነታችንን
፫. ከለቅሶአችን ይልቅ መጽናናታችንን
፬. ከሀዘናችን ይልቅ ደስታችንን
፭. ከመሰበራችን ይልቅ መጠገናችንን
፮. ከመታመማችን ይልቅ መፈወሳችንን
፯. ከድካማችን ይልቅ ኃይላችንን
፰. ከመረሳታችን ይልቅ መታወሳችንን
፱. ከጨለማችን ይልቅ ብርሃናነችንን
፲. ከፍርሃታችን ይልቅ ድፍረታችንን
፲፩. ከክህደታችን ይልቅ እምነታችንን
፲፪. ከጥላቻችን ይልቅ ፍቅራችንን
፲፫. ከመታወካችን ይልቅ ሠላማችንን
፲፬. ከሞታችን ይልቅ ሕይወታችንን
፲፭. ከመቃብራችን ይልቅ ትንሣኤአችንን የምናስብበት ዕለት ነው፡፡
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"ብርሃን ወጣ ከመስቀሉ የሚያንጸባርቅ"
በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
✞"ክርስቶስ ህያው ነው"✞
ክርስቶስ ህያው ነው ሞት ይዞ ያላስቀረው
የለም ከመቃብር ተነስቷል በክብር(፪)
በገዛ ፈቃዱ ነፍሱን ስለሰጠ
የጨለመው ዓለም በብርሃን ተዋጠ
ሲኦል ድል መንሳቱ መውጊያውም ታጠፈ
የሞት ሥልጣን በሞት ስለተሸነፈ
አዝ---
የጥሉ ግድግዳ በሞቱ ፈረሰ
የነፍሳችን ቁስል በእርሱ ተፈወሰ
ከቶ አላስቀረውም የመቃብር ድንጋይ
ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ኤልሻዳይ
አዝ---
ዓለሙን እንዲሁ እግዚአብሔር ወዶ
የሰው ልጅ ከበረ ዲያብሎስ ተዋርዶ
ይገዛን ይነዳን ያስጨንቀን ነበር
በሞት ላይ ተራመድን አምላካችን ይክበር
አዝ---
ህይወት ይሰጠን ዘንድ ስለኛ የሞተው
ቤዛችን ክርስቶስ ሞትን ድል አረገው
የሞተው ተነሳ በመቃብር የለም
ዳግመኛም ይመጣል ሊፈርድ በዓለም
አዝ---
በዘማሪ ዲ/ን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ከትንሳኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
ማክሰኞ
ቶማስ ይባላል
እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሲፈጥረው የሚያንቀላፋና የሚነቃ አድርጎ ፈጥሮታል፡፡
ማንቀላፋቱ የሞት ፤ መንቃቱ ደግሞ የትንሣኤ ምሳሌ መሆኑን ስናስብ ሁሌም ይደንቃል፡፡ አባቶቻችን የትንሣኤውን ምሥጢር በአበው እና በስነፍጥረትም ይመስሉታል፤ አቤል ከሞተ በኋላ በደሙ መናገሩ እና የሔኖክ ሳይሞት በእግዚአብሔር መሰወሩ የትንሣኤ ምሣሌ ናቸው፡፡ በተፈጥሮ ፀሐይ መውጣቷ የመወለዱ ፤ መጥለቋ የሞቱ እና ዳግመኛ መውጣቷ የትንሣኤው ምሣሌ ነው፡፡
አምላካችን ክብር ይግባውና በእርሱ ያመንን ሁላችን እንደምንነሳ የእርሱ ከሙታን መካከል በሥልጣኑ መነሳት ለሁላችን መነሳት በኩር መሆንና ማረጋገጫም እንደሆነ በቃሉም በተግባሩም ያስተማረን የትንሣኤ ጌታ ነው፡፡
በቃሉ "በመቃብር ያሉት ሁሉ ድምጹን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል ፤ መልካም
ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ፤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ " (ዮሐ፭፡፳፱) እንዲሁም በተግባር የአራት ቀን ሬሳ አልዓዛርን አስነስቷል፡፡(ዮሐ፲፩፡፵፫)
የትንሣኤው ምሥጢር ሁላችን አምላክ የሆንበት ፤ በሁሉ ላይ ሥልጣን ያገኘንበት ፤ነጻ ወጥተን ነጻ አውጪ የሆንበት ፤ ከማይጠፋ ዘር እንደተወለድን ያረጋገጥንበት ፤ ሞትን የተዘባበትንበት ፤ ጨለማን የረታንበት ከዓለም እና ከዲያብሎስ እስራት ነጻ የወጣንበት ልዩ ክብር ኃይል እና ጸጋን ያገኘንበት ምሥጢር ነው፡፡
ይህቺ ዕለትም ይህንኑ ምሥጢር ነው የምትገልጥልን ሐዋርያው #ቶማስ ተብሎ ለምን ተሰየመ የሚለውን ከማየታችን በፊት ማነው የሚለውን ማየት ነገርን ከስሩ እንድንረዳው ይረዳናልና እውነት ሐዋርያው ቶማስ ማነው?
ሐዋርያው ቶማስ
ሐዋርያው ቶማስ የስሙ ትርጓሜ ፀሐይ ማለት ሲሆን የቀድሞ ስሙ ዲዲሞስ ይባላል ትርጉሙም ጨለማ ማለት ነው፡፡ ቁጥሩ ከ፲፪ ሐዋርያት ነው፡፡ (ማቴ፲፡፫)
(መዝገበ ታሪክ ክፍል ሁለት ገጽ፹፱) ፤ ሐዋርያ ማለት ደጅ አዝማች ፤ ቀላጤ ፤ ምጥው ፤ ፍንው ፤ ሂያጅ ማለት ነው፡፡(ወንጌል ቅዱስ ገጽ፻፶፱)
ሐዋርያው ቶማስ አልዓዛር በሞተ ጊዜ ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም አቅራቢያ ወደነበረው መቃብሩ ለመሄድ በተነሳ ጊዜ አይሁድ ሊገሉት ስለሚፈልጉ ሌሎቹ ሐዋርያት ክርስቶስ እንዳይሄድ ቢፈልጉም ቶማሰ ሌሎቹን ሐዋርያት በድፍረት እኛም ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ አብረን እንሂድ ያለ የእምነት ሐዋርያ ነው፡፡ (ዮሐ፲፩ ÷ ፲፮)
ሐዋርያው ቶማስ ጌታችንን በእውነት እስከ ሞት ድረስ ያመነው ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ በ8ኛው ቀን እሁድ ሲሆን ሐዋርያት የነገሩትን ካላየው አላምንም ብሎ የተወጋ ጎኑን ከዳሰሰ በኋላ ነው፡፡ የእምነት ምስክርነቱም ጌታዬ አምላኬም ብሎ የገለጠው፡፡(ዮሐ፳፡፳፬)
ሐዋርያው ቶማስ መንፈስ ቅዱስን ከሐዋርያት ጋር ከተቀበለ በኋላ በ፵፮ ዓ.ም ገደማ በፋርስና በሕንድ እንዳስተማረ የተለያዩ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይገልጣሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ ፤ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ፤ ቅዱስ አምብሮስ ተጠቃሾች ናቸው፡፡በመጨረሻም ብዙ ተአምራት እና ድንቅን አድርጓል፡፡ የሐዋርያው ቶማስ ተአምር እና አገልግሎት ብዙ ተአምራትን ቢያደርግም ለአሁኑ አንዱን ብቻ እናያለን፡፡ የኸውም የሉክዮስ አገልጋይ ሆኖ በሕንጻ ማነጽ እና በሐውልት መስራት ተቀጥሮ በሚሰራበት ወቅት የሉክዮስን ሚስት ከእነ ልጆቿ እና አገልጋዮቿ አሳምኖ ያጠመቀ ሐዋርያ ነው፡፡
ሐዋርያው ቶማስ ለሕንጻ እና ለሐውልት ማሰሪያ ከሉክዮስ የተቀበለውን ገንዘብና ወርቅ ሁሉ ለነዳያን በመመጽወቱ ንጉሡ እጅና እግሩን አሥሮ ቆዳውን አስገፍፎ ስልቻ አሰፍቶ በአሸዋ ሞልቶ አሸክሞት ገበያ ለገበያ ሲያዞረው የሉክዮስ ሚስቱ አርሶንዋ ተመልክታ በድንጋጤ ሞታለች፡፡ ንጉሡም ለሚስቴ መሞት ምክንያት አንተ ነህ ካዳንካት እኔም በአምላክህ አምናለው ሲለው ጌታችን ቁስሉን እንደ ውኃ አቀዝቅዞለት ካለችበት ሄዶ ስልቻውን ቢያስነካት ተነስታለች በዚህም ሉክያኖስ አምኖ ተጠምቋል፡፡
ሐዋርያው ቶማስ በራሱ ቆዳ በተሰራ ስልቻ እየተዘዋወረ ሙት አስነስቷል ፤ ድውያንን ፈውሷል አሕዛብን አሳምኖ አጥምቋል ፤ በቀንጦፍያ አንድ ሽማግሌ ሰባት ልጆቹን ገድለውበት ሰባቱንም ከሞት አስነስቷል ፤ በኢናስም በቃሉ ትምህርት እና በእጁ ተአምራቱ ብዙዎችን አሳምኖ አጥምቋል፡፡
የሐዋርያው ቶማስ ሰማእትነት
በሕንድ የነበሩት የብራሕማን እምነት ተከታዮች የቶማስ ትምህርት የእነርሱን እምነት የሚጻረር እና የሚያጠፋ መሆኑን ተገንዝበው ተነሱበትና በብዙ ስቃይ አሠቃይተው በ፸፪ዓ.ም በሰማዕትነት አርፏል፡፡ በሶርያ ትውፊት መሠረት የሐዋርያው የቶማስ አጽም በአንድ የሶርያ ነጋዴ ተወስዶ በኤዴሳ በክብር አርፏል፡፡ (የእግዚአብሔር መንግሥት ታሪክ በምድር ላይ አንደኛ መጽሐፍ ገጽ ፺፪)
ሐዋርያው ቶማስ ለምን ሰምቶ አላመነም?
እንደ ወንጌል ትርጓሜ ሐዋርያው ቶማስ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዝግ ቤት ገብቶ ሰላም ለእናንተ ይሁን ባለ ጊዜ አልነበረም ፤ በነገሩት ጊዜም አላመነም ያለማመኑ ምክንያት ሰዱቃዊ ስለነበር እና ሐዋርያቱ አይተው እርሱ ሰማው ብሎ ከሚያስተምር ማየት ወዶ ነው፡፡
"ጌታዬ አምላኬም" (ዮሐ፳:፳፰)
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
" ክርስቶስ ተንስአ እሙታን"
በዘማሪ ሊቀ ዲያቆናት ነቢዩ ሣሙኤል
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
✝ "ሞታችንን ሻረ" ✝
አልተቻለም ሞት ይዞት ሊያስቀር
ክርስቶስ ተነሣ ከህቱም መቃብር{፪}
ክርስቶስ በሞቱ ሞታችንን ሻረ
ነፍሳትን አውጥቶ ሰይጣንን አሰረ
የሲኦል እስር ቤት ባዶ ሆኖ ቀረ
በትንሣኤው ብርሃን ሰላም ተበሰረ።
አዝ---
ሙስና መቃብርን በሥልጣኑ ሽሮ
የሲኦልን መዝግያ የሞት ቁልፍን ሰብሮ
ብርሃን ተጎናጽፎ ሰላምን አብስሮ
ክርስቶስ ተነስቷል አልቀረም ተቀብሮ።
አዝ---
የሰንበት ጌታዋ ክርስቶስ ሲነሳ
መርገማችን ጠፋ ቀረልን አበሳ
እርቅ ሆነ በሰማይ እርቅ ሆነ በምድር
ነፍሳት ተሻገሩ ወደ ገነት ምድር።
አዝ---
ለዘመናት ሰፍኖ የኖረው ጨለማ
የጥሉ ግድግዳ የሞት ጥላ ግርማ
ሸሸ ተወገደ በመስቀሉ ዓላማ
የትንሣኤው ብስራት በዓለም ተሰማ።
አዝ---
በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"ትንሣኤከ ለእለ አመነ
ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ"
በቀሲስ ይስሐቅ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
እንደሚመጡና ‘ሰማይና ምድር ያልፋል፤ ጌታ ይመጣል፤ ትንሣኤ ሙታን ይደረጋል፤ ያላችሁት የት አለ?’ እያሉ የሚክዱና የሚያስክዱ ሰዎች እንደሚመጡ አስቀድሞ ነግሮናል። (2ኛ ጴጥ 3፥1-18)። እንዲሁም ጌታችን በወንጌሉ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ”(ዮሐ 11፥25)። ብሎ የሰበከውን ህያው ቃል ያልተገነዘቡ የቅዱስ ጴጥሮስንና የቅዱስ ጳውሎስን ትምህርት እንዳቃለሉና እንዳፌዙ ሁሉ ዛሬም በዘመናችን ስለትንሣኤ ሙታን፣ ስለ ዘላለማዊ ህይወት ሲነገራቸውና ሲሰበክላቸው የማያምኑ ብዙ ሰዎች መኖራቸው እንግዳ ነገር እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባናል። እኛ ግን ይልቁንም ቅዱሳት መጻፍትን በማንበብና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን በመጠየቅ ይበልጥ ስለትንሣኤ ልንረዳና በመጨረሻው ስዓት የክብር ትንሣኤ ባለቤት እንድንሆን መትጋት ይኖርብናል። በትንሣኤ የምናምንም የማያምኑም ለፍርድ መነሣታችን አይቀርምና። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ሙታን ትንሣኤ በሚገባ ቋንቋ አብራርቶ በምሳሌ ሲያስተምር «ነገር ግን ሰው፥ ሙታን እንዴት ይነሣሉ? በምንስ ዓይነት አካል ይመጣሉ? የሚል ይኖር ይሆናል፡፡» ብሎ ከጠየቀ በኋላ፥ «አንተ ሞኝ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም፡፡» ብሏል፡፡ ከዚህም አያይዞ «የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው፡፡ በመበስበስ ይዘራል÷ ባለመበስበስ ይነሣል፤ በውርደት ይዘራል በክብር ይነሣል፤ በድካም ይዘራል÷ በኃይል ይነሣል፤ ፍጥረታዊ አካል ይዘራል÷ መንፈሳዊ አካል ይነሣል ፤ ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ፡፡ እንዲሁ ደግሞ፡- ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም (ክርስቶስ) ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ ፍጥረታዊው ቀጥሎም መንፈሳዊው ነው እንጂ መንፈሳዊው መጀመሪያ አይደለም። የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው። ሁለተኛው ሰው ( ክርስቶስ ) ከሰማይ ነው፡፡ መሬታዊው እንደሆነ መሬታውያን የሆኑት ደግሞ እንዲህ ናቸው÷ ሰማያዊው እንደ ሆነ ሰማያውያን የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው ፡፡ የዚያንም የመሬታዊውን መልክ እንደ ለበስን የሰማያዊውን መልክ ደግሞ እንለብሳለን፡፡» ብሏል። ፩ኛቆሮ ፲፭÷፴፭-፵፱፡፡ በአጠቃላይ መድኃኔዓለም ክርስቶስ እኛን የወደደበት ሕይወቱን እስከ መስጠት ደርሶ ቤዛ የሆነበትን ምሥጢር የሰው ሕሊና መርምሮ ሊደርስበት የሚችል አይደለም፡፡ ተነጻጻሪ ተወዳዳሪ አቻ ወይም አምሳያ የሌለው ልዩ ነውና፡፡ ስለሆነም የትንሣኤ ሙታንን ምሥጢር ተረድተን በክርስቲያናዊ ምግባር መኖር አለብን። በትንሳኤ ሙታን ጊዜ ስንነሣ በጌታችን ፊት እንዳናፍር በትዕዛዙና በሕጉ ጸንተን ጌታችን "ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፣ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ" (ዮሐ 6፥54)፤ እንዳለ የክብር ትንሣኤ አግኝተን ከምርጦቹ ጋር በቀኙ እንዲያቆመን የጌታችንን ትንሣኤ ስናከብር ንስሐ ገብተን፣ ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን በመቀበል ለክብር ትንሣኤ ተዘጋጅተን ሊሆን ይገባል። ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች እንደጻፈልን በ፩ኛቆሮ ፲፭÷፳-፳፫፡፡«አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቷል፡፡ ሞት በሰው (በቀዳማዊ አዳም) በኵል ስለመጣ፥ ትንሣኤ ሙታን በሰው (በተዋሕዶ ሰው በመሆኑ ዳግማዊ አዳም በተባለ በክርስቶስ) በኩል ሆኗልና፡፡ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኵራት ነው፤» እንዲል የትንሣኤያቸን በኩር ክርስቶስን አብነት አድርገን፣ ቃሉን ሰምተን፣ ሕጉን ጠብቀን፣ ትዕዛዙን አክብረን፣ ትንሣኤ ልቡና ተነሥተን፣ ሥጋውን በልተን፣ ደሙን ጠጥተን፣ በንስሐ ተሸልመን፣ በፍቅረ እግዚአብሔርና በፍቅረ ቢፅ (ወንድምን በመውደድ) ጸንተን ብንኖር የትንሣኤውን ትርጉም አውቀነዋል፣ ገብቶናል ማለት ነው፡፡ ከትንሣኤ ሥጋ ትንሣኤ ልቡና ተነሥተን፣ በንስሐ ታጥበን ሥጋውና ደሙን ተቀብለን፣ ተዘጋጅተን እንድንኖር የአምላካችን ቸርነት የወላዲተ አምላክ የድንግል ማርያም፣ የቅዱሳንና የቅዱሳን መላእክት አማልጅነትና ተራዳኢነት አይለየን። አሜን!
🌿መልካም በዓል!🌿
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሥርዓተ ማኅሌት ዘትንሣኤ
ደወል እንደተደወለ ከሁሉ አስቀድሞ ነቢያት ተደግሞ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል።
"ተፈሥሂ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ" ይባላል። መልክአ ስዕል አይባልም።
ከዚያም ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስ ይነበባል። ቀጥሎም ወተንሥአ ይሰበክና አራቱም ወንጌላት ተነበው "አርያም" በተባለው ምስጋና ማኅሌቱ ይጀመራል።
ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፸፯ : ፷፭
ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም፤
ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን፤
ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ።
አርያም
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ቀዳሚ ዜማ ግበሩ በዓለ ትፍሥሕት እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ፤ ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ።
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ይገብሩ በዓለ ሰማያት፤ ይገብሩ በዓለ ደመናት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።
አንገርጋሪ
ዮም ፍሥሃ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን፤ እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን፤ ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል አልዓላ፤ አማን ተንሥአ እምነ ሙታን።
አመላለስ
'አማን በአማን'/፪/ ተንሥአ 'አማን በአማን'/፪//፩/
ተንሥአ እምነ ሙታን/፬/
ወረብ
ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን/፪/
ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል/፪/
እስመ ለዓለም
ትንሣኤከ ለእለ አመነ፤ ብርሃንከ ፈኑ ዲቤነ።
አመላለስ
ትንሣኤከ ለእለ አመነ/፪/
ፈኑ ዲቤነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ/፪/
ከእስመ ለዓለሙ ጋር ተያይዞ የኪዳን ሰላም ይዘመማል፣ ይመረገዳል።
የኪዳን ሰላም
ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ይእቲ ማርያም እምነ፤ ወእሙ ለእግዚእነ፤ ሰአሊ በእንቲአነ፤ ከመ ይምሐረነ ወይሣሐለነ፤ ያስተርኢ ኂሮቶ ላዕሌነ፤ ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ።
አመላለስ
ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ/፬/
መዝሙር
ትትፌሣሕ ሰማይ ወትትኃሠይ ምድር፤ ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ፤ ወይበውኡ አድባር ወአውግር፤ ወኲሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዓባይ ፍሥሐ በሰማያት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።
ሰላም
ፍጹመ ንጉሠ ኮነንዎ አይሁድ፤ ተካፈሉ አልባሲሁ ሐራ ሠገራት፤ ወኮርዕዎ ርእሶ በኅለት፤ ረገዝዎ ገቦሁ በኲናት፤ ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት፤ ሰላመ ለነገሥት፤ ለአሕዛብ ወለበሐውርት።
መልካም በዓል!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ቀዳም ስዑር
የማይሞተው አምላካችን በፈቃዱ ቅድስት ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ሰማይና ምድር የማይችሉት አምላካችን እኛን ያስነሳ እና ነጻነት ይሰብከን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ነጻ ሲያወጣ በአካለ ሥጋም ያለመለያየት በመቃብር ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት ሙስና መቃብር ሳያገኘው ቆይቷል።
ይህንን ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ሲያስረዳ እንዲህ ይላል"ነፍሱን በሲኦል አልተወም ሥጋውንም ሙስና መቃብርን አላየም መለኮቱ ከሁለቱም አልተለየም ሁለንተናው ከነፍስ ጋር በሲኦል ነበር። በሲኦል ለጻድቃን የምሥራችን አበሰረ፤ ሁለንተናው ከሥጋ ጋር በመቃብር ነበር እንጂ በቦታው ሁሉ ምሉዕ ነውና" (ሃይ. አበ ዘቄርሎስ ፸፩:፲፭-፲፮)
ለሁላችን የማያልፍ ድኅነትን ፣ ሥርየተ ኃጢአትን ፣ ቅድስናን ፣ አሸናፊነትን እና ይቅርታን ይሰጠን ዘንድ ሞታችንን ሞተ፤ የነገረንን ትንቢት ፈጸመ።" ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።" እንዲል። (ማቴ፲፪:፵)
ጌታችን ከዐርብ ሠርክ እስከ እሁድ መንፈቀ ሌሊት ድረስ ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት በመቃብር ዐርፏል። እነዚህ ቀንና ሌሊት የራሳቸው ትርጉም አላቸው። የነገረ ክርስቶስ መጽሐፍ ጸሐፊ መጋቤ ሐዲስ ክቡር ዶክተር ሮዳስ ስለ ሶስት ምክንያት እንደሆነ ይጠቅሳሉ:-
፩. ለአዳም ፣ ለሔዋን ፣ ለሕጻናቱ ሊክስ
፪. ለሥጋ ፣ ለነፍስ ፣ ለደመ ነፍስ ሊክስ
፫. ሞትን ፣ ፍዳን ፣ ኃጢአትን ሊያጠፋ ጌታችን ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት በመቃብር ዐርፏል። (ነ.ክርስቶስ ገጽ፻፸፰)
ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት
ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሠ መቃብር 3 ቀንና 3 ሌሊት አደረ፡፡ ይኸውም ነቢዩ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ እንዳደረው (ዮና 2÷1-2) ራሱም መድኅን ዓለም ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በ3 ኛው ቀን አነሣዋለሁ ብሏል፡፡ (ዮሐ2÷19-22 ) የተሰቀለ አርብ 6 ሰዓት ነፍሱን ከሥጋው የለየው አርብ 9 ሰዓት ወደ መቃብር የወረደ አርብ 11 ሰዓት የተነሣ ቅዳሜ ለእሁድ ሌሊት 6 ሰዓት ነው፡፡ ይህ 3 ቀንና 3 ሌሊት እንዴት ተባለ? ቢሉ የመጀመሪያው ብርሃኑን “ቀን” ጨለማውን “ሌሊት” በማለት የሚቆጠረው አቆጣጠር ነው፡፡ ይኸውም
ሦስቱ ቀኖች:-
🕕 አርብ ከነግህ/ጠዋት እስከ ቀን 6 ሰዓት ብርሃን ነበር
🕘 ከ9 ሰዓት እስከ ሰርክ ብርሃን ነበር
🕛 ቅዳሜ መዐልት/ቀን
ሦስቱ ሌሊቶች:-
🕕 አርብ ከቀን 6 ሰዓት እስከ ቀን 9 ሰዓት አምላክ በመስቀል ላይ ሳለ ጨለማ ሆነ
🕛 አርብ ለቅዳሜ ሌሊት
🕛 ቅዳሜ ለእሁድ ሌሊት
ሌላው በእዕብራውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት ዓርብ ሌሊቱን እሁድ ቀኑን ይስቡና ይቆጠራል፡፡ ይኸውም:- ሌሊቶቹ
⌛ሐሙስ ለአርብ
⌛ አርብ ለቅዳሜ
⌛ ቅዳሜ ለእሁድ
ቀኖቹ ደግሞ
⌛ አርብ ቀኑን
⌛ ቅዳሜ ቀኑን
⌛ እሁድ ቀኑን ቆጥሮ ነው፡፡
ጌታችን ቀድሞ አዳምን፤ ሔዋንን አርብ ፈጥሮ ቅዳሜ እንዳረፈ ሁሉ አሁንም ያጡትን ገነትን ባጡበት አርብ ዕለት ሰጥቶ ቅዳሜ በመቃብር አርፎባታል ስለዚህም የተለየች ቅዳሜ ናት።
አራቱ ስያሜዎች፦
፩. ቀዳም ስዑር
ስዑር ማለት የግእዝ ግስ ሆኖ በአማረኛ የተሻረ ማለት ሲሆን በአንድ ላይ ሲነበብ የተሻረ ቅዳሜ የሚል ትርጓሜ እናገኛለን። ምክንያቱ እንደ ቀደመቺቱ ሰንበት የማናርፍባት ይልቁንም ደቀመዛሙርቱን አብነት አድርገን በጾም በሀዘን ህማሙን እያሰብንባት የምናሳልፋት ቀን በመሆኗ ቀዳም ስዑር ተብላለች።
፪. ዐባይ ሰንበት
አምላካችን ሃያ ሁለቱን ስነ ፍጥረት ፈጥሮ እንዳረፈባት የማዳኑንም ስራ በመስቀል ላይ ፈጽሞ በአዲስ መቃብር ዐርፎ ውሎባታልና ዐባይ ሰንበት ተብላለች።
፫. ቅዱስ ቅዳሜ
በአካለ ነፍስ ወደ ሲዖል ወርዶ ነፍሳትን አድኖበታል ፣ ሲዖልን በዝብዟል ፣ ምርኮን ለራሱ ጨምሯል ፣ ዲያብሎስን አሳፍሯል ፣ የዕዳ ደብዳቤያችንን ደምስሷል ከሌሎች ቀናት ሁሉ የተለየች በመሆኗ ቅዱስ ቅዳሜ ተብላለች።
፬. ለምለም ቅዳሜ 🌿🕊
በዚህ ዕለት በኖኅ ዘመን የጥፋቱ ውኃ ማለቁን የሰላም አብሳሪ እርግብ ለኖኅ ቄጤማ እንዳመጣችለት አሁንም የጥፋቱ ሞት ራቀልን ፣ ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋገርን ፣ አንቀጸ ገነት ተከፈተልን ሲሉ ካህናት አባቶቻችን የቅዳሜው የነግህ ጸሎት ከተጠናቀቀ በኋላ ለምዕመኑ ለምለም ቄጤማ ስለሚሰጡ ምዕመናንም በግንባራችን ላይ አድርገን ትንሣኤውን ስለምናከብር ለምለም ቅዳሜ ተብላለች።
🔔"ዲያብሎስ ታሰረ ጌታ ተመረመረ"🔔
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
Your precious blood bought- በደምህ ተገዛ
https://youtu.be/lxJnGYp8XRM?si=pfeyVGLl6rTVIspB
©Canada Toronto Debre Genet Abune Teklehaymanot Church Sunday School
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሥርዓተ ጸሎት ዘዓርብ ፫
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሥርዓተ ጸሎት ዘዓርብ ፩
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"እምይእዜሰ ይኩን ሰላም"
በዘማሪ ብሩክ መኩሪያ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቅድስት ድንግል ማርያምን በማስመልከት ባስተላለፉት ትምህርት ዙሪያ መወያየታቸው ተገለጸ።
ሚያዚያ ፲፭/ ፳፻፲፯ ዓ.ም
ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ ማለዳ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ባለፈው አርብ በስቅለት ዕለት በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በቅድስት ድንግል ማርያም ዙሪያ ያስተላለፉትን ትምህርት በተመለከተ ውይይት መደረጉ ተገልጿል።
በብፁዕነታቸው የተላለፈውን ትምህርት ዝርዝር ሁኔታ በመመርመርም ውሳኔ ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ ሁሉም የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምልዓት በተገኙበት ለረቡዕ ሚያዝያ 22 ቀን 2017 ዓ/ም ቀጠሮ ተይዟል።
በተያያዘ ዜና የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በሆኑት በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ፍራንሲስ ስርዓተ ቀብር ላይ፦ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ(ዘአውሮፓ) ቤተክርስቲያናችንን በመወከል እንዲገኙ ተወስኗል።
ምንጭ :- የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ከትንሳኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
ረቡዕ
አልዓዛር ይባላል
በዚህች ዕለት አምላካችን ትንሣኤ እና ሕይወት መሆኑን በተግባር በታላቅ ተአምራቱ ማሳየቱን የምናስብበት በመሆኑ ስያሜው አልዓዛር ተብሏል፡፡
የአራት ቀን ሬሳን ሕይወት ይዘራበት ዘንድ የፍቅር አምላካችን በሞት በሚፈልጉት በጠላቶቹ ሰፈር ተመላለሰ ፤ የደቀ መዛሙርቱን ክልከላ አልሰማም ፤ የመንገዱ ርቀት አላዘለውም ግን በፍቅር ስለ ፍቅር ሰው ሁሉ ተስፋ የቆረጠበትን ወዳጁ አልዓዛርን ከሞት ሊያስነሳ ወደ ቢታኒያ በፍቅር ተጓዘ ፤ እውነት ነው ሞት ለታወጀብን ለእኛ ለመመላለሱ ምሳሌ ነው ፤ ሞት ድል ያላደረገው የትንሣኤውን ጌታ አምላካችንን በእውነት እንደተነሳ እንድናስብ ቤተክርስቲያን በዚህ ዕለት በአልዓዛር አንጻር ትንሣኤ እና ሕይወት እርሱ እንደሆነ ታስተምረናለች፡፡
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
✞ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ✞
ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ
ክርስቶስ ተነሳ እሰይ እሰይ
እኛንም ከሞት ሊያስነሳ/፪
ክርስቶስ ከሙታን ተነሳ
ሰላም/፬
ለሰው ልጆች በምድር ሆነ ሰላም/፪
ነፍሳትን ነፃ አወጣ ከጨለማ ኑሮ/፪
እሰይ እሰይ
የሲኦልን በር ሰብሮ/፪
ኃይሉንም በኃይሉ ሽሮ
ሰላም/፬
ለሰው ልጆች በምድር ሆነ ሰላም/፪
ሞት በትነሳኤ ተሻረ የሰው ልጅ ከበረ/፪/
እሰይ እሰይ
ጠላት ዲያቢሎስ አፈረ/፪
እጅና እግሩንም ታሰረ
ሰላም/፬
ለሰው ልጆች በምድር ሆነ ሰላም/፪/
እንዳይኖር ለዘላዓለም ሞት በአዳም ላይ
ነግሶ/፪ እሰይ እሰይ
ክርስቶስ ተነሳ ሞትን ደምስሶ/፪
ግርማ መለኮቱን ለብሶ
ሰላም/፬
ለሰው ልጆች በምድር ሆነ ሰላም/፪
በዘማሪት ማርታ ኃይሉ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
ሰኞ
ሰኑይ ማእዶት ይባላል
እንደ ቤተክርስቲያን ይትባሕል ከትንሣኤ እስከ ዳግማዊ ትንሣኤ ያለውን ሳምንት እንደ አንድ እሁድ እናከብራለን። ለዚህም ነው ዕለታቱን እንደ ሰንበት እናከብራቸው ዘንድ በፍትሐ ነገሥት ላይ አባቶቻችን ትእዛዝ የቀረጹልን።
ማእዶት ማለት መሻገር ማለት ነው። አደወ ማለት ተሻገረ ማለት ሲሆን ማእዶት መሸጋገሪያ ማለት ሊሆን ነው።
ማእዶት የትንሣኤ እሑድ ማግስት ጌታ ክርስቶስ በትንሣኤው ምዕመናንን ከሞት ወደ ሕይወት ያሻገረበት ቀን የትንሣኤው ማሳሰቢያ ነው። (ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ገጽ ፻፶)
መሻገር በዕብራይስጥ ፓሳሕ ከሚባለው ቃል ይመሳሰላል ትርጉሙም ፋሲካ መሻገር ማለፍ የሚል ትርጉም ይሰጣል። ሁላችን እንደምናውቀው እስራኤላውያን ከሚያክብሯቸው አበይት በዓላት አንዱም ፋሲካ ነው። ምክንያታቸው ደግሞ እግዚአብሔር ከሞተ በኩር ያሳለፋቸውን ዕለት ያስቡበታል።
ቤተክርስቲያናችንም ይህንን በዓለ ትንሣኤን የፋሲካ በዓል የማክበሯ ምሥጢር ወይም የትንሣኤው ምሥጢር ነፍሳት በአምላካችን ትንሣኤ ከሞት ወደ ሕይወት ፣ ከአሳር ወደ ክብር ፣ ከሲዖል ወደ ገነት መሻገራቸውን በማሰብ አማናዊው ፋሲካ ወይም አሸጋጋሪው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብላ ታምናለች። እናምናለን።
ቅዱስ ጳውሎስ በብሉይ ኪዳን በታረደው የፋሲካ በግ (ዘዳ፲፮:፮) ምትክ አማናዊው ክርስቶስ እንደታረደልን እና ሞት ላያገኘን በሕይወት ለሕይወት እንዳሸጋገረን ሲገልጥ እንዲህ ብሏል:-"" እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ
አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤" (፩ ቆሮ ፭:፯)
ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እርሾም ሆነ ስለ አዲሱ ሊጥ በምሳሌ የሚነግረን እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ፋሲካ ሲያከብሩ ያደርጉት የነበረ ስርዓትን ነው።
ይኸውም ፋሲካን ያከበሩት ገና ከነጻነት በፊት ነው። ምክንያቱ ደግሞ ከላይ እንዳየነው ከሞተ በኩር መቅሰፍት ለመዳን እና ከእግዚአብሔር ፍርድ ለመዳን ነበር።
በአዲስ ኪዳንም ያለን ክርስቲያኖች በተለይ ይህንን ዕለት ወይም ማእዶትን ስናስብ አምላካችን ከሞት ወደ ሕይወት እንዳሻገረን ፣ ከአሳር ወደ ክብር እንዳሳለፈን ፣ ከድካም ወደ ኃይል እንዳሻገረን ፣ ሁላችን ወደ መንግሥተ
ሰማያት ፋሲካችን በሆነው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሸጋገርን በማመን ሊሆን ይገባል።
የፋሲካው ጌታ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞት ላይ እንድንዘባበትበት ሞትን ፣ ፍርሃትን ፣ ጭንቀትን ፣ ተስፋ መቁረጥን ፣ ሐዘንን ፣ ለቅሶን ፣ ትካዜን ፣ ድካምን ፣ ሥጋትን እና መቃብርን ሁሉ አጥፍቶ አሻግሮናል። ክብር ማዕዶታችን ለሆነ ለእርሱ ይሁን። አሜን ክብር ይግባውና አምላካችን የሰው ልጅ ሞትን እንዲሻገር ሁለት ነገሮች(እምነት እና ምግባር ) እንደሚያስፈልጉት በመዋለ ስብከቱ እንዲህ ሲል አስተምሮናል:-
"እውነት እውነት እላችኋለሁ ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።" (ዮሐ፭:፳፬-፳፭)
ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ዕለቷ ፋሲካ እንደሆነችና እንደሰትባት ዘንድ የተገባች እንደሆነች እንዲህ ሲል በመዝሙሩ አዚሞታል:- " ፋሲካ ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ (ይህቺ የፋሲካ ዕለት ልዩ ናት) ፣ ዛቲ ዕለት ንትፈሳሕ በቲ (በዚህ ዕለት ሐሴት እናድርግባት)..."
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!"
ይህ ሰላምታ ለሃምሳ ቀናት ይዘልቃል። የዚህ ሰላምታ ልውውጥ ታሪክ የሚጀምረው ከመጀመሪያዋ ምዕተ ዓመት ከነበረችው ከጥንት ክርስቲያኖች ጀምሮ ሲሆን ለትንሳኤ በዓል ብቻ ሳይሆን ሁሌም ሲገናኙ አይሁዳውያን "ሻሎም" ወይም ሰላም ብለው ሰላምታ እንደሚለዋወጡት ሁሉ ክርስቲያኖቹም "ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷል" ብለው ሰላምታ ሲሰጡ መላሹ ደግሞ "በአማን ተንስአ እሙታን ፤በእውነት ከሙታን ተለይቶ ተነስቷል" በማለት ይመልሳል።
ይህ ሰላምታ በሁሉም በምስራቁም በምዕራቡም ኦርቶዶክሳውያን ብሎም በአንግሊካንም ቤተክርስቲያን ከትንሳኤው ጋር የፋሲካ ሰሞን ሰላምታ እንደሆነ ቆይቷል። አሁንም የሚተገበር ሰላምታ ነው። ነገር ግን መቼ እንደሆነ ባይታወቅም ሰላምታው ከዘወትር ሰላምታ ወደ ዘመነ ፋሲካ ብቻ ሰላምታ ተለወጠ።
በምዕራቦቹ ክርስቲያኖች ሰላምታ ሰጪው Christ is Risen!" ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ወይም "The Lord is Risen!" እግዚእ ተንስአ እሙታን ሲል ሰላምታ መላሹም "Truly, He is Risen," በአማን ተንስአ፤በእውነት ተነስቷል "Indeed, He is Risen," ወይም በእርግጥ ተነስቷል "He is Risen Indeed እርግጥ ነው ከሙታን ተነስቷል ይላል።
Christ is Risen!" or "The Lord is Risen!", and the response is "Truly, He is Risen," "Indeed, He is Risen," or "He is Risen Indeed.
ይህ ሰላምታ ከሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት የእኛ ቤተክርስቲያን የሚለየው ረዘም ብሎ "ክርስቶስ ተንስአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ ዓግአዞ ለአዳም፤ ሰላም፤ እምይእዜሰ፤ ኮነ ፍሰሀ ወሰላም በማለት በጥልቅ ሚስጢር ሰላምታ ላይ ይውላል።
በዚህም የሀገርኛ ነገረ ክርስቶስ ትምህርት (Ethiopic Christology)እድገትን አንድ ማሳያም አድርገን መውሰድ እንችላለን። የጌታ ሞትና ትንሳኤ በቤተክርስቲያን ታሪክም ይሁን በነገረ መለኮት አስተምህሮ እድገት(Development of theological teachings) ትልቁን ስፍራ ይይዛል። በስልታዊ ነገረ መለኮት (Systematic Theology) ትምህርት ውስጥ "ዶግማ አይቀየርም ነገር ግን ያድጋል" የሚባለው ለዚህ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስ አትናቴዎስ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ በ367 ዓ.ም በዛሬዋ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ባስተላለፈው ቃለ ምዕዳን (ልፋፈ ጽድቅ) በ45ኛ ደብዳቤው የኦርቶዶስክ ቤተክርስቲያን በቀኖና የምትቀበላቸውን በዝርዝር 27 የሐዲስ ኪዳን መጻህፍትን መሆኑን ያወጀበት ቀን ነው። ከዚያም ወደ ሁሉም መንበረ ፕትርክናዎች (Patriarchate) ልኳል።
Priest : Christ is risen from the dead!
ካህን : ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!
People : By the highest power and authority!
ሕዝብ : በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን!
Priest : He chained Satan!
ካህን : አሰሮ ለሰይጣን!
People : Freed Adam!
ሕዝብ : አግዐዞ ለአዳም!
Priest : Peace!
ካህን : ሰላም!
People : Henceforth!
ሕዝብ : እምይእዜሰ!
Priest : Is!
ካህን : ኮነ!
People : Joy and Peace!
ሕዝብ : ፍስሐ ወሰላም
መልካም በዓል!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን፤ቀደሳ ወአክበራ እምኵሎን መዋዕል አልዓላ አማን ተንሥአ እምነ ሙታን!"
-ቅዱስ ያሬድ
"ክርስቶስ ተነሣ፥ አጋንንትም ድል ተነሡ !
ክርስቶስ ተነሣ፥ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፥ ሕይወትም በሰው ልጆች ላይ ሰፈነች!"
-ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ተነሥቷል!
Just risen!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
☦ ትንሣኤ ☦
✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሓ ወሰላም
✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በከብቶች በረት ከተወለደበት ሰዓት ጀምሮ ለሰው ልጅ ድኅነት ሲል ከመሰደድ እስከ ሞት፤ ጽኑ መከራና ስቃይን ተቀብሏል። በተለይ በመጨረሻው ሰዓት ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ የሆነ ስቃይ፣ መከራ፣ እንግልትና ግርፋትን ተቀብሎ፤ በጲላጦስ ከወንበዴዎች ጋር ተፈርዶበት፤ በቀራንዮ አደባባይ በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፤ ነፍሱን በፈቃዱ ሰጥቶ አዳምንና ዘሩን ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከባርነት ወደ ነፃነት መልሶ በሦስተኛው ቀን መቃብር ክፈቱልኝ፣ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል፤ በማቴ28፥5 ላይ “እነሆም የጌታ መልአክ ከሰማይ ወረደ፣ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፣ እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና። እንደ ተናገረው ተነስቷልና በዚህ የለም ኑና እዩ አላቸው።” ተብሎ እንደ ተገለጸው፤ ብርሃንን ተጎናጽፎ በታላቅ ኃይልና ስልጣን በክብር ተነስቷል። ማጽናናትና የምሥራችን ለሰው ልጆች ማብሰር ልማዳቸው የሆኑ መላእክት ለእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በመለአኩ በቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት አምላክን እንደምትወልድ እንዳበሰራት ሁሉ እነሆ ጌታም ሞቶ በተቀበረ በሦስተኛው ቀን የትንሣኤውን ብስራት በሌሊት ወደ መቃብሩ ስፍራ ለመጡ የገሊላ ሰዎች በእግዚአብሔር መለአክ አማካኝነት ተነገረ። አስቀድሞ በነብዩ ቅዱስ ዳዊት አማካኝነት ስለ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በመዝ.77፥6 “እግዚአብሔር ይነሣል ጠላቶቹም ይበተናሉ፤ እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው ጠላቶቹንም በኋላው መታ” እንዲሁም በመዝ.3፥5 “እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም እግዚአብሔር አሥነስቶኛልና ተነሣሁ” በማለት የክርስቶስን ከሙታን መነሣት በትንቢት ተናግሯል፡፡ ሌሎች ነብያትም ክርስቶስ እንዲሞት በ3ኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ በተለያየ ጊዜያት በትንቢትና በምሳሌ ገልጸዋል፡ ፡ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ሥጋዌው ስለትንሳኤው በምሳሌ አስተምሯል እንዲሁም በመጨረሻም እንደተናገረው በተግባር መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በስልጣኑ ተነስቷል። ሐዋርያትም በስብከታቸው እና በመጽሐፋቸው ስለ ትንሣኤው ምስክርነት በመስጠት አረጋግጠው አስፍተውና አምልተው አስተምረዋል፤ ጽፈዋል። (ዮና.2፥1፣ ሆሴ.13፥14፣ ማቴ.12፥4ዐ ማቴ 28፣ ማር 16፣ ሉቃ 24፣ ዮሐ 20 ወዘተ)። ይሁን እንጂ የጌታችን ትንሳኤ በነዚህ ሁሉ ትንቢታትና ምሳሌዎች፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት፣ እንዲሁም በጌታችን በራሱ በትምህርትም በተግባርም የተገለፀ ቢሆንም ስለ ትንሣኤው ለማመን ያዳግታቸው ብዙ ሰዎች ነበሩ። ከሐዋርያትም መካከል የሆነው ቅዱስ ቶማስ የተቸነከሩትን እጆቹንና እግሮቹን፣ በጦር የተውጋውን ጎኑን ካላየሁ፣ ካልዳሰስሁ የክርስቶስን መነሣት አላምንም ብሎ ጌታችን በዝግ ቤት ሰላም ለእናንተ ይሁን ብሎ የተወጋውን ጎኑን አሳይቶ በክብር መነሣቱን እስከሚያረጋግጥለት ድረስ የጌታችንን ትንሣኤ ለማመን እንደተቸገረ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል (ዮሐ 20፥24) ይሁን እንጂ የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በስሙ ላመኑ ክርስቲያኖች ሁሉ ትንሣኤ ነው፡፡ ክርስቶስ ለሙታን ሁሉ በኲር ሆኖ ተነሥቶአል፡፡ የሙታንን ሁሉ መነሣት የሚያረጋግጥልን የጌታ ትንሣኤ ነው፡፡ የክርስቶስም ትንሣኤ መርገመ ሥጋ፥ መርገመ ነፍስ፤ ሞተ ሥጋ፥ ሞተ ነፍስ የተሻረበት ርደተ ገሃነም ጠፍቶ፥ በአዳም የተፈረደው ፍርድ ሁሉ ተደምስሶ፤ ፍጹም ነፃነት፣ የማይለወጥ ደስታ፣ የተገኝበት ስለሆነ ፋሲካ ይባላል፡፡ ፋሲካ ደስታ ነው እስራኤል ከግብጽ ባርነት ነፃ የወጡበትን ቀን ፋሲካ ብለውታል፡፡ የእርቅ፣ የሰላም፣ የድኅነት ቀን ነው። ከሞት ከመነሣት ከመቃብር ጨለማ ከመውጣት ከዲያብሎስ ቁራኝነት ከመላቀቅ፥ ከሲኦል እስራት ከመፈታት የሚበልጥ ምንም ደስታ ሊኖር አይችልምና ፋሲካችን እንለዋለን። ስለሆነም የጌታችን ትንሣኤ ለኛ በኩራችን ነው፡፡ እርሱን በኩር አድርገን እንነሣለንና። ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ሰዎች እንደጻፈው በ1ኛ ቆሮ.15፥20 “አሁንም ክርስቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስቀድሞ ተነሥቶአል በመጀመሪያው ሰው ሞት መጥቶአል በሁለተኛው ሰው ትንሣኤ ሙታን ሆነ” እንዳለ የጌታችንን የትንሣኤውን በዓል ስናከብር የእኛም ትንሣኤያችን መሆኑን አውቀንና ተረድተን በትንሣኤ ልቡና ተነሥተን መልካም ሥራ በመሥራት መሆን አለበት። እኛ ትንሣኤ ልቡናን ሳንነሣ በየዓመቱ ትንሣኤን ብናከብር ፈሪሳውያንን ወይም ትንሣኤ የለም ፈርሰን በስብሰን እንቀራለን ብለው የሚያምኑ ሰዱቃውያንን መምሰል ይሆናል፡፡ እንደሁም በቆላ.3፥1-4 “ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኛ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ የላይኛውን አስቡ በምድር ያለውንም አይደለም እናንተ ፈጽማችሁ ሞታችኋልና ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ የተሠወረች ናትና ሕይወታችሁ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ያን ጊዜ ከእርሱ ጋር በፍጹም ክብር ትገለጣላችሁ” ተብሎ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆላስያስ ሰዎች እንደተጻፈው የክርስቶስ ትንሣኤ ትንሣኤያችን ነው ብለን ለምናምን ሁሉ ከምድራዊ ሀሳብ ነጻ ሆነን ተስፋ የምናደርገው ትንሣኤ እንዳለን በማሰብ ከሞት በኋላ ሕይወት ከትንሣኤም በኋላ የዘለዓለም ሞት መኖሩን ሳንዘነጋ መኖር እንደሚገባን ይመክረናል፡፡ በተጨማሪም በዮሐ.5፥28 እንደተገለጠው በትንሳኤ ለማያምኑ ወይም ከሞት በኋላ ስላለ ሕይወት ስለማያስቡ፣ መልካም ሥራ ለማይሰሩ ሰዎች ትንሣኤ ምን እንደሚመስል ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያስተምር “በመቃብር ያሉ ሁሉ ቃሉን የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ስለዚህ አታድንቁ መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ ክፉ የሠሩም ለፍርድ ትንሣኤ ይነሣሉ” ብሏል፡፡ ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች የቅዱስ ቶማስን ዓይኖች ዓይኖቻችን አድርገን፤ የእርሱን ጆሮዎች ጆሮቻችን አድረገን፤ የእርሱን እጆች እጆቻችን አድርገን ትንሣኤውን በፍጹም ልባችን አምነን መኖር ይገባናል። እንዲሁም ጌታችን ለቶማስ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው ብሎ እንደ ተናገረ እኛም ትንሣኤውን በመንፈስ የተረዳን ሁሉ ከትንሣኤው ብርሃን በረከትን ለማግኘት የጌታችንን ትንሣኤ ላልተረዱ ሁሉ እነርሱም እንደኛ የትንሣኤውን ብርሃን እንዲያዩ በሕይወታችን በቃልም በምግባርም ልንመሰክርላቸው ይገባል። በዘመናችንም በትንሳኤው የማያምኑ እንዳሉ ይልቁንም፤ ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ትንሣኤ በአቴና ከተማ ሲያስተምር ትምህርቱን ባለመረዳት እንዳፌዙበት ሁሉ በአሁኑም ወቅት የሙታን ትንሣኤ ሲነገር የሚቀልዱና የሚዘብቱ ብዙዎች አሉ። (የሐዋ 17፥32)። ቅዱስ ጳውሎስ የአቴና ሰዎችን ከአምልኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር እንዲመለሱ፣ በጌታችን ትንሣኤ አምነው በትንሣኤው ክብርን እንዲወርሱ ቢያስተምራቸውም ብዙዎቹ ግን ድኅነትን ከመፈለግ ይልቅ ፌዝን መረጡ። ቅዱስ ጳውሎስ “ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?” (ገላ 3፥1)። ብሎ እንደ ተናገረው ዛሬም የትንሣኤውን እውነት መስማትም ሆነ መናገር የማይፈልጉ ተረፈ ሰዱቃውያን አሉ፤ ወደፊትም ይኖራሉ። እንደነዚህ ስላሉት ሰዎች ቅዱስ ጴጥሮስም በመጨረሻው በዚህ ዘመን ብዙዎች ዘባቾች
የሰሙነ ሕማማት ዕለታት-ቅዳሜ
✅ ቀዳም ስዑር
✅ ዐባይ ሰንበት
✅ ቅዱስ ቅዳሜ
🌿 ለምለም ቅዳሜ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊
ለይሁዳ ወልዱ ወለ ዉሉደ ወልዱ ይደምሰስ!
ለይሁዳ ወልዱ ወለ ዉሉደ ወልዱ ይደምሰስ!
ለይሁዳ ወልዱ ወለ ዉሉደ ወልዱ ይደምሰስ!
(የይሁዳ ልጁና የልጅ ልጁም ይደምሰስ!)
ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ!
🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሥርዓተ ጸሎት ዘዓርብ ፬
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሥርዓተ ጸሎት ዘዓርብ ፪
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🩸"ሕሙም ስላዳነ" 🩸
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን፤
ወአኀዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን፤
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ፤
ወኈለቊ ኲሎ አዕጽምትየ።
ሕሙም ስላደነ በእጆቹ ዳስሶ፤
ሙትን ስላስነሳ በእጆቹ ዳስሶ፤
ይህም በደል ሆኖበት ለአምለክ ኖላዊ ሔር፤
በዕጸ መስቀሉ ላይ ዘርግቶ በፍቅር፤
ቀኝ እጁን በሳዶር ግራውን በአላዶር፤
ተቸነከረልን ጌታ በሁለት ችንካር፤
አምንስቲቲ ሙኬርያ አንቲ ፋሲልያሱ
ቤተመቅደስ ምኩራብ በተመላለሱ፤
ባሕር ላይ በሄደ ልክ እንደበየብሱ፤
ለአምላክ ቤዛ ኲሉ ይህ ወንጀል ሆኖበት፤
በዕፀ መስቀሉ ላይ ተላልፎ ለመሞት፤
ሁለቱን በአንድ ላይ እግሮቹን በዳናት፤
ተቸነከረልን አምላክ የኛ ሕይወት፤
አምንስቲቲ ሙአግያ አንቲ ፋሲልያሱ
በልቡ አስቦ ድኅነቴን ሊያመጣ፤
ከበጎ ልቦናው በጎ የሚያወጣ፤
ይኽ ወንጀል ሆኖበት ለአምላክ መድኅንዓለም፤
በዕጸ መስቀሉ ላይ ተዘርግቶ ለዓለም፤
ልቡን በአዴራ ደረቱን በሮዳስ፤
ተቸነከረልን ወልደ አምላክ ክርስቶስ፤
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
በዘማሪ ቀሲስ ዳዊት ፋንታዬ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox