በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
የ ጸሎትና ምሕላ አዋጅ
++++++++++++++++++++++++++++++++
በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየተከሠተ ያለው ችግርና ፈተና የሚወገደው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በአንድነትና በሕብረት ለችግሮቹ መፈታት ድርሻ እንዳለን አውቀን እንደየእምነታችን አስተምህሮ በጸሎትና በምሕላ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር በንስሓ መመለስ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም ስለ ሀገራችን ሰላምና ስለ ቤተ ክርስቲያናችን አንድነት በመላው ዓለም በሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ከህዳር 15 ቀን 2016 እስከ ታህሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸምና መላው ሕዝበ ክርስቲያንም በአንድነትን በሕብረት ከላይ በተጠቀሱት ዕለታት በቤተ ክርስቲያን በመገኘት የበረከቱና የሥርዓተ ጸሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
©የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷
የጥቅምት ፲፰(ሰንበት) ግጻዌ
✞ መልእክታት ዘቅዳሴ
፩. ሮሜ ፯፥፩-፲፬/17፥1-14
፪. ራእ ዮሐ ፳፩፥ ፳፩ - ፍጻሜ/21፥21-ፍጻሜ
፫. ግብረ ሐዋርያት ፳፪፥፩- ፮/22፥1-6
✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
መዝ ፸፫ ፥ ፲፯ -፲፰/73፥17-18
"አንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኀ።
ወአንተ ገበርከ አድባረ ምድር ኵሎ ፤
ክረምተ ወሐጋየ ዘአንተ ፈጠርከ። "
"አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀህ። አንተ የምድርን ዳርቻ ሁሉ ሠራህ፤ በጋንም ክረምትንም አንተ አደረግህ።"
✞ ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ፮፥፳፭ - ፍጻሜ/6፥25-ፍጻሜ
" ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን? ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን? ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው? ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤ አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም። እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት? እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።"
✞ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷
የትምህርት ዕድል ያመለጠህ መስሎህ ነው? ገና ሺህ የትምህርት ዕድሎች አሉህ:: ዕድሜህ ያመለጠህ መስሎህ ነው? ነገ የሚጠብቁህ ብሩሕ ዘመናት እኮ ቁጭ ብለው አሉ? የሚረዳኝ ሰው የሚያስብልኝ ሰው አጥቼያለሁ? ብለህ ከሆነም ካልሰሙህ ጥቂቶች በላይ ልንሰማህ የምንሻ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ"
መከራ ጸናብኝ ኑሮ ጨለመብኝ የሀገሪቱ ሁኔታ ተስፋ አሳጣኝ ብለህ ይሆን? እኛስ አብረንህ አይደልንም? አብረን ከገባንበት ችግር አብረን ብንወጣ አይሻልም? ከአንተ በባሰ ሁኔታ የታሰርንና የተገረፍን ጳውሎሶችና ሲላሶች "ሁላችን በዚህ አለንና በራስህ ክፉ አታድርግ" ስንልህ ስማን::
ይልቅ አንተም እንደ ወኅኒው ጠባቂ "እድን ዘንድ ምን ላድርግ ብለህ?"ነፍስህን የምታድንበትን መንገድ ወደ መቅደሱ ቀርበህ ጠይቅ::
ወዳጄ ይህንን ጽሑፍ ያነበብኸውም በሕይወት ስላለህ ነው:: የአንተን ዓይን የሚጠብቁ ብዙ ጽሑፎች ፣ የአንተን ጆሮ የሚፈልጉ ብዙ ድምፆች ፣ የአንተን መሐረብ የሚፈልጉ ብዙ ዕንባዎች ፣ የአንተን ሳቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀልዶች ... ገና ብዙ ብዙ አሉ::
ስለዚህ ሰይጣንን አሳፍረው:: እንዲህ በለው :-
"ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ" ሚክ. 7:8
©ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷
የጥቅምት ፲፩(ሰንበት) ግጻዌ
✞ መልእክታት ዘቅዳሴ
፩. ፩ኛ ቆሮ ፲፥፩-፲፬/10፥1-14
፪. ራእ ዮሐ ፲፬: ፩ - ፮/14፥1-6
፫. ግብረ ሐዋርያት ፬ : ፲፱ - ፴፩/4፥19-31
✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
መዝ ፺፩ ፥ ፲፪ -፲፫/91፥12-13
"ጻድቅሰ ከመ በቀልት ይፈሪ ፤ ወይበዝኀ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ ፤ ትኩላን እሙንቱ ውስተ እግዚአብሔር ። "
"ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል። በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል።"
✞ ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ፲፪:፩ - ፴፪/12፥1-32
" በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በሰንበት ቀን በእርሻ መካከል አለፈ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተራቡና እሸት ይቀጥፉ ይበሉም ጀመር።
ፈሪሳውያንም አይተው፦ እነሆ፥ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ማድረግ ያልተፈቀደውን ያደርጋሉ አሉት።
እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት በተራቡ ጊዜ፥ እርሱ ያደረገውን፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ ካህናትም ብቻ እንጂ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሊበሉት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕቱን ኅብስት እንደ በላ አላነበባችሁምን?
ካህናትም በሰንበት በመቅደስ ሰንበትን እንዲያረክሱ ኃጢአትም እንዳይሆንባቸው በሕጉ አላነበባችሁምን?
ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከመቅደስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።
ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደሆነ ብታውቁስ ኃጢአት የሌለባቸውን ባልኰነናችሁም ነበር።
የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።
ከዚያም አልፎ ወደ ምኩራባቸው ገባ።
እነሆም፥ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤ ይከሱትም ዘንድ። በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን? ብለው ጠየቁት።
እርሱ ግን፦ ከእናንተ አንድ በግ ያለው በሰንበት በጉድጓድ ቢወድቅበት፥ ይዞ የማያወጣው ሰው ማን ነው?
እንግዲህ ሰው ከበግ ይልቅ እንደምን አይበልጥም! ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዶአል አላቸው።
ከዚያም በኋላ ሰውየውን፦ እጅህን ዘርጋ አለው። ዘረጋትም፥ እንደ ሁለተኛይቱም ደህና ሆነች።
ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት።
ኢየሱስም አውቆ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፥ ሁሉንም ፈወሳቸው፥ እንዳይገልጡትም አዘዛቸው፤
በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል፦
እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል።
አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም።
ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጥዋፍ ክርም አያጠፋም።
አሕዛብም በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ።
ከዚህም በኋላ ጋኔን ያደረበትን ዕውር ዲዳም ወደ እርሱ አመጡ፤ ዕውሩም ዲዳውም እስኪያይና እስኪናገር ድረስ ፈወሰው።
ሕዝቡም ሁሉ ተገረሙና፦ እንጃ ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆንን? አሉ።
ፈሪሳውያን ግን ሰምተው፦ ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ።
ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፥ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም።
ሰይጣንም ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ፥ እርስ በርሱ ተለያየ፥ እንግዲህ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች?
እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል።
እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።
ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።
ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፥ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል።
ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም።
በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።"
✞ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷
🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷
የጥቅምት ፬(ሰንበት) ግጻዌ
✞ መልእክታት ዘቅዳሴ
፩. ኤፌ ፮፥፩-፲/6፥1-10
፪. ራእ ዮሐ ፲፪: ፩ - ፲፫/12፥1-13
፫. ግብረ ሐዋርያት ፮ : ፳፫ - ፴/6፥፳፫-30
✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
መዝ ፻፪ ፥ ፲፬ -፲፭/102፥14-15
"ተዘከር ፡ እግዚኦ ፡ ከመ ፡ መሬት ፡ ንሕነ ፡፡ ወሰብእሰ ፡ ከመ ፡ ሣዕር ፡ መዋዕሊሁ ፤ ወከመ ፡ ጽጌ ፡ ገዳም ፡ ከማሁ ፡ ይፈሪ ። "
" ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፤ አቤቱ፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን አስብ። ሰውስ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤ እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል፤"
✞ ወንጌል ዘቅዳሴ
የሉቃስ ወንጌል ፲፪: ፲፮ - ፴፪/12፥16-32
" ምሳሌም ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ አንድ ባለ ጠጋ ሰው እርሻ እጅግ ፍሬያም ሆነችለት። እርሱም፦ ፍሬዬን የማከማችበት ስፍራ አጥቻለሁና ምን ላድርግ? ብሎ በልቡ አሰበ። እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጐተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፥ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤ ነፍሴንም፦ አንቺ ነፍሴ፥ ለብዙ ዘመን የሚቀር ብዙ በረከት አለሽ፤ ዕረፊ፥ ብዪ፥ ጠጪ፥ ደስ ይበልሽ እላታለሁ አለ። እግዚአብሔር ግን፦ አንተ ሰነፍ፥ በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል? አለው። ለራሱ ገንዘብ የሚያከማች፥ በእግዚአብሔር ዘንድም ባለ ጠጋ ያልሆነ እንዲህ ነው። ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ለነፍሳችሁ በምትበሉት ወይም ለሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ። ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና። ቍራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም፥ ዕቃ ቤትም ወይም ጎተራ የላቸውም፥ እግዚአብሔርም ይመግባቸዋል፤ እናንተስ ከወፎች እንዴት ትበልጣላችሁ? ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው? እንግዲህ ትንሹን ነገር ስንኳ የማትችሉ ከሆናችሁ፥ ስለ ምን በሌላ ትጨነቃላችሁ? አበቦችን እንዴት እንዲያድጉ ተመልከቱ፤ አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዲቱ አለበሰም። እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን በሜዳ የሆነውን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጐደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት? እናንተም የምትበሉትን የምትጠጡትንም አትፈልጉ፥ አታወላውሉም፤ ይህንስ ሁሉ በዓለም ያሉ አሕዛብ ይፈልጉታልና፤ የእናንተም አባት ይህ እንዲያስፈልጋችሁ ያውቃል። ዳሩ ግን መንግሥቱን ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። አንተ ታናሽ መንጋ፥ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።"
✞ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷
"በዙሪያችን ካሉ ድንቅ ምስክሮች" | ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
መስከረም ፳፱
ሰማዕት ቅድስት አርሴማ
የቅድስት አርሴማ አባቷ ቴዎድሮስ ከሌዋውያንና ከኃያላን ነገሥታት ወገን ሲሆን እናቷ አትኖስያ ደግሞ ከጳጳሳት አለቆች ወገን ናት፡፡ ወላጆቿ በሃይማኖት በምግባር ያጌጡ በበጎ ትሩፋት የተመሰገኑ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡ በጾም፣ በጾሎት፣ በምጽዋትና ዓሥራት በኩራትን በማውጣት በመንፈሳዊ ሥራ ሁሉ እየተጉ ቢኖሩም ነገር ግን እስክ እርጅናቸው ዘመን ድረስ ልጅ ስላልነበራቸው ያዝኑ ነበር፡፡ እናቷ ቅድስት አትኖስያ እንደ ነቢዩ ሳሙኤል እናት ሐና ጠዋት ማታ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ በእግዚአብሔር ፊት ታለቅስ ነበር፡፡ እግዚአብሔር የልቧን ፈቃድ ይፈጽምላት ዘንድ ወደደና የቂሣርያውን ሊቀ ጳጳሳት ልድዮስን ስለ እርሷ ይጸልይላት ዘንድ አዘዘው፡፡
ሊቀ ጳጳሳቱም ስለ ቅድስት አትኖስያ ጸለየላት፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የሊቀ ጳጳሳቱንና የቅድስት አትኖስያን ጸሎት ሰምቶ መልኳ እጅግ ያማረችን ሴት ልጅ ቅድስት አርሴማን ሰጣት፡፡ እናቷም እየተንከባከበች አሳድጋት ዕድሜዋ ከፍ ሲል አምላክን በወለደች በእመቤታችን ስም ወደተሠራች ቤተ ክርስቲያን ታገለግል ዘንድ ሰጠቻት፡፡ ቅድስት አርሴማ ወጣት በሆነች ጊዜ ወላጆቿ ባል ያጋቧት ዘንድ ወደዱ ነገር እርሷ ይህንን ፈጽሞ አልወደደችምና ወላጆቿን ‹‹እኔ የሰማያዊው የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ እንጂ ምድራዊ ሙሽራ አይደለሁም›› አለቻቸው፡፡
ቅድስት አርሴማ ከእርሷ በፊትም ሆነ ከእርሷ በኋላ በመልክና በውበት የሚመስላት የለም፡፡ ይህን ዓለም እንደትቢያ በመቁጠርና ፍጹም በመናቅ ጌታችንን ከተከተሉት ቅዱሳት ደናግል አንስት ውስጥ በመልክና በውበት ቅድስት አርሴማን የሚመስል የለም፡፡ አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን በቀር የሚበልጣት ማንም የለም፡፡ እርሷም በምግባር በሃይማኖት ያጌጠች በመንፈሳዊ ተጋድሎ የበረታች በትሩፋት የበለጸገች ናት፡፡ ብሉይን ከሐዲስ አጠናቃ ተማረች፡፡ የአገሮችንም (የሮምያን፣ የጽርዕን፣ የሶርያን፣ የኪልቅያን) ቋንቋዎች ታውቅ ስለነበር ቅዱሳት መጻሕፍትንም ወደ ተለያዩ አገራት ቋንቋዎች ትተረጉማለች፡፡
ቅድስት አርሴማ 15 ዓመት በሆናት ጊዜ ከሃዲውን ዲዮቅልጥያኖስን ሰይጣን አስነሥቶት ነገሠ፡፡ ይኸውም ከሃዲ ንጉሥ ሚስት ያባ ዘንድ በመልኳ ውብ የሆነች ሴት ልጅን ይመርጡለት ዘንድ በሀገሩ ሁሉ እንዲሄዱ ጭፍሮቹን አዘዘ፡፡ ያገኟትንም ውብ የሆነችን ሴት መልኳን ሥለው ያመጡለት ዘንድ ሠዓሊዎችንም አብሮ ላከ፡፡ የተላኩትም ሰዎች ወደ ሮሜ አገር በደረሱ ጊዜ ቅድስት አርሴማ ያለችበትን የደናግል ገዳም አገኙ፡፡ ወደ ገዳሙም ገብተው ቅድስት አርሴማን አይተዋት በመልኳ ማማር እጅግ ተደስተው ‹‹ለንጉሡ ሚስት የምትሆነው ይህች ናት›› ብለው መልኳን በሥዕል ቀርጸው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ንጉሡም ሥዕሏን በተመለከተ ጊዜ ፈጽሞ ተደሰተ፡፡ ስለ ሠርጉ ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ ሕዝቡን ይጠሩአቸው ዘንድ ወደ ነገሥታቱና ወደ መኳንንቱ ሁሉ ላከ፡፡
እሊያ ደናግልም ይህን ነገር በአወቁ ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ ድንግልናቸውንም ይጠብቅ ዘንድ አልቅሰው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ። ከዚህም በኋላ ተነሥተው በሥውር ሸሹ የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነ ወደ አርማንያ ሀገርም ደርሰው በአንድ ቦታ ተቀመጡ ከእርሳቸውም ጋር የተሰደዱ ቁጥራቸው ሰባ አምስት የሆነ ወንዶች፣ ሴቶችም ሠላሳ ዘጠኝ የሆኑ ከእርሳቸው ጋራ አሉ። ምግባቸውን አያገኙም ነበርና በታላቅ ችግር ውስጥ ኖሩ ከእነርሱም መብራት የምትሠራ አንዲት ሴት ነበረች ከእርሷም የእጅ ሥራ ከሚገኘው በየጥቂቱ ይመገባሉ።
ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም የከበረች አርሴማን በፈለጋት ጊዜ አላገኛትም ግን በአርማንያ አገር እንዳለች ስለርሷ ሰማ። ደግሞ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ ስለርሷ ከዲዮቅልጥያኖስ ሸሽታ እንደ መጣች የአርሴማን ሥራ ነገሩት እርሱም አንዱን የአርማንያ መኰንን ለእኔ ጠብቃት ወደ እኔም ላካት ብሎ አዘዘው።
ደናግሉም ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሠወሩ ወደ ንጉሥም ወነጀሉአቸው ንጉሡም ቅዱስት አርሴማን በክብር አድርገው ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ወደ እርሱ መምጣትን እምቢ በአለች ጊዜ እየጎተቱ ወስደው ወደርሱ አደረሷት።
የቅድስት አርሴማንም ላህይና ደም ግባቷን በአየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ እናቷ አጋታን አባብላ እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት አጋታም ወደርሷ ሒዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት። ዕወቂ ይህ ርኲስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ሙሽራሽን እንዳትተዪ እርሱም ክብር ይግባውና የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው ክርስቶስ ነው።
ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት። በዚያንም ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለ ነበር በታናሽ ሴት ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ። ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት ከዚህም በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው አጋታ ጋር ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ።
አንዲት የታመመች ድንግል ነበረች በዐልጋዋ ላይም እንደተኛች ወደ ወታደሮች ጮኸች መጥተውም እንደ እኅቶቿ ራሷን ቆረጡ ሁሉም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ እነዚያንም ከሮሜ አገር አብረው የመጡ ወንዶችን ገደሏቸው ቁጥራቸውም ሰባ አምስት ናቸው ሥጋቸውም በተራራ ላይ የተጣለ ሁኖ ቀረ።
ሰማዕታትም ከተገደሉ በኋላ በንጉሡ ላይ ጋኔን ተጫነበት መልኩም ተለውጦ እንደ እርያ ሆነ። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደርሱ መጥቶ በላዩ ጸልዮ እስከ አዳነው ድረስ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። የቅዱሳን ሰማዕታትንም ሥጋቸውን ከተጣለበት ሰብስበው በአማረ ቦታ አኖሩአቸው ያማረች ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራችላቸው። ከእነርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።
የእናታችን ቅድስት አርሴማ ምልጃዋ ይጠብቀን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"አክሊለ ጽጌ"
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
“ጽጌ መዓዛ ሠናይ”
🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ያለውን ወቅት ወርኃ ጽጌ ትለዋለች። ወርኃ ጽጌ የእመቤታችን ስደት የሚታሰብበት ወቅት ነው። ስደት አድካሚ ጉዞ አለው። ረኀብና ጥምም መገለጫው ነው። ጠቢቡ "እነሆ ክረምት ዐለፈ ዝናቡም አልፎ ሔደ፤ አበቦችም በምድር ላይ ተገለጡ፤ የዜማም ጊዜ ደረሰ፤ የቁርዬም ቃል በምድራችን ተሰማ" (መኃ. ፪÷፲፩-፲፪) ብሏል። “ክረምት ዐለፈ” ያለው የአዳም የመከራ ዘመን ማለፉን ሲናገር ነው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድም እመቤታችንን መዓዛ ባላቸው ጽጌያት መስሎ "መዓዛሆሙ ለቅዱሳን " ብሏታል።
አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፈ ምሥጢር" አዳም እንኳን ተሳሳተ ፣አዳም እንኳን ወደቀ በገነት ውስጥ ቢኖር ኑሮ አዳም ከሔዋን ጋር ዕፀ-ሕይወትን እየበላ ይኖር ነበር እንጂ እኛ አናገኛትም ነበር።፣አዳም ባይሳሳት ኑሮ አንቺ አትወለጅም ነበር። ስለዚህ በገነት የተነፈግነውን ዕፀ-ሕይወት አንቺ ሰጥተሽናልና እናመሰግንሻለን” ብሏታል።
ቅዱስ ዮሐንስ "ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ፤ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች። እርስዋም ፀንሳ ነበር፤ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች። ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት፤ በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ"(ራእ. ፲፪÷፫) ብሏል። ፀሐይ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ በቀንም፣ በሌሊትም የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን ነው። ፲፪ የክብር አክሊል የተባሉት ፲፪ ሐዋርያት ናቸው። ቅዱሳን ሐዋርያት ለድንግል ማርያም ጌጦች በመናቸው አክሊል አላቸው። ድንግል ማርያምም ለሐዋርያት ጌጣቸው ናት። "ሞገሶሙ ለሐዋርያት" እንዲል ቅዳሴ ማርያም። በጨረቃ የተመሰለው ዮሐንስ መጥምቅ ነው። ጨረቃ ሠርቅ ካደረገችበት ጀምሮ ብርሃኗ እየጨመረ በ፲፭ኛው ቀን ሙሉ ትሆናለች። ቅዱስ ዮሐንስም አንገቱን ከተቆረጠ በኋላ ፲፭ ዓመት አስተምሯል። ጨረቃን ተጫምታ ነበር ማለት ዮሐንስ ገና ከእናቱ ማኅፀን ሁኖ ለድንግል ማርያም ሰገደ ማለት ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ "ምጥ" ያለው ድንግል ማርያም የገጠማትን ጭንቅ ነው። ቅዱስ አትናቴዎስ " ያለ ዘር ፣ያለ ምጥ ወለደችው" (ሃይ.አበው ምዕ•፳፰ ክ፲፬ ቊ ፲፱) በማለት የወለደችው ያለ ምጥ መሆኑን ተናግሯል። እመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሦስት ነገሮች ብትጨነቅም ክርስቶስን ስለመውለድ አልተጨነቀችም። ድንግል ማርያም የተጨነቀችው ልጇ በቀራንዮ በተሰቀለ ጊዜ፣ ስለ ኃጥአን ለመከራ መዳረግ እና የሦስት ዓመቱ የግብፅ በረሃ ስደቷ ያስጨንቃት ነበር።
እርሷም "ከእንግዲህ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል” በማለት ትውልደ ሴም፣ ትውልደ ካም፣ ትውልደ ያፌት እንደሚያመሰግናት ተናግራለች። “እነሆ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ሁኖ ወደ ምድረ ግብፅ ይመጣል፤ የግብፅ ጣዖታትም በፊቱ ይርዳሉ"(ኢሳ ፲፱÷፩) ተብሎ የተነገረው በስደቷ ወቅት የተፈጸመውን ነው። ሆሴዕም "ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድኩት፤ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት"(ሆሣ ፲፩÷፩:) ብሏል። ጌታችን የተሰደደው ግብፅን እና ኢትዮጵያን ለመባረክ ነው። አንድም ሰይጣንን ከሰው ልቡና አስወጥቶ ለመስደድ ነው።
በድንግል ማርያም ስደት ምክንያት ክርስቲያኖች የሰማዕትነትን በረከት አግኝተዋል። ሰሎሜ ጌታን በማዘል ድንግል ማርያምን ስትረዳ የመከራዋ ተካፋይ በመሆን አብራ ተንከራታለች። ጥጦስም ጌታን በትከሻው ተሸክሞ ሸኝቷቸዋል። በቅዳሴያችን "በቀኝ የተሰቀለውን ሽፍታ በመስቀል ላይ እንዳሰብከው አቤቱ እኛንም በመንግሥትህ አስበን" በማለት እንማጸናለን። በእመቤታችን ስደት በረከትን ያጡት ሄሮድስ፣ ትዕማር፣ዳክርስ እና መሰሎቻቸው ናቸው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ የድንግል ማርያምን ስደት በማሕሌት፣ በዝክርና በቅዳሴ ታስባለች። በዚህ ምክንያት ድንግል ማርያምን “አንቲ ውእቱ ጽጌ መዓዛ ሠናይ” በማለት እናመሰግናታለን። 🌺
የእመቤታችን ፍቅሯ በልባችን ምስጋናዋ በአንደበታችን እጥፍ ድርብ ሆኖ በእኛ በምናምን ክርስቲያኖች ላይ ይደርብን!
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ ኡራኤል"
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የብፁዕ አቡነ ሰላማ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል !
የብፁዕነታቸው በረከት አይለየን !
@Ethiopian_Orthodox
" እሰይ አበራ መስቀሉ " ዘማሪት ትርሃስ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ስለ ስደት የበገና መዝሙር
በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"መናኝ መነኩሴ አባ አረጋዊ"
በገርጂ ጊዮርጊስ የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ጥቅምት ፲፬
ጻድቁ አቡነ አረጋዊ
ጥቅምት ዐሥራ አራት በዚህችም ቀን ታላቁና የከበረው አባታችን አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) የተሰወሩበት ነው።
እኚህ አባት ከ፱(9) ቅዱሳን አባቶች አንዱ ሲሆኑ
አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉስ ነበሩ፡፡ እናታቸው ንግስት እደና ይባሉ ነበር፡፡ የመጀመሪያ ስማቸው ዘሚካኤል ነው፡፡ ጥበብ መንፈሳ ሲማሩ አድገው ወደ እስክንድርያ ገዳም ገቡ፡፡ አበምኔቱ አባ ጳኩሚስ በፈቃደ እግዚአብሔር የመጡ መሆናቸውን አውቀው መዓረገ ምንኩስና ሰጥተዋቸዋል፡፡
የንጉሳዊ የቅንጦት ኑሮ ንቀው ትተው ገዳም ገብተው በምንኩስና ተወስነዋል፡፡ አባታችን በተጋድሏቸውም ከአባ እንጦንስ፣ ከአባ ጳውሊ እና ከአባ መቃርስ ቀጥሎ በአራተኛ ማዕረግ አበ መነኮሳት ሆነው ተመርጠዋል።
በገዳመ ዳውናስ ፯ ዓመት ከቆዩ በኋላ ወደ ሮም ተመልሰው ሲያስተምሩ የሀገራችን ኢትዮጵያን ዜና ሰምተው ለመምጣት በ፬፻፹ ዓ.ም ከአባ ፍሬምናጦስ በኋላ መንገድ ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በክንፉ ተሸክሞ አክሱም አድርሷቸዋል፡፡
ተመልሰውም ሄደው ስለ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መስክረዋል፡፡ ሐዋርያ ሳይላክላት በሃይማኖት በምግባር ጸንታ ትኖራለች ብለው ለሰባቱ ዘመዶቻቸው አበው መነኮሳት ነገሯቸው፡፡ ስምንቱም ጓዛቸውን ጠቅልለው በሮም ነግሶ የነበሩ ይስሐቅን (አባ ገሪማን) ጨምረው ንጉስ አልአሜዳ በነገሰ በአምስተኛ ዓመት ማለትም በ፬፻፹ ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ዘጠኝ ሆነው መጥተዋል፡፡
አባ አረጋዊ እናታቸው ቅድስት እድናን ደቀ መዝሙራቸውን ማትያስን አስከትለው እግረ መንገዳቸውን እያስተማሩና ድውያንን እየፈወሱ ደብረ ዳሞ ደርሰዋል፡፡
ከእግረ ደብር ሆነው አሁን ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግሩ ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነቢዩ ዳዊት ላይ አድሮ በመዝሙር ፺/፺፩፥፲፩-፲፮ ላይ “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። እንዳለው የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስደሳ ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ ሚካኤል ሰይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል፡፡
ወዲያው ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው አመስግነዋል፡፡ ቦታውም ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሏል፡፡ በዚያ ዕለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምድራዊ ሕብስት አልተመገቡም፡፡ በሰንበተ ክርስታያን ከቅዳሴ በኋላ ሕብስተ ሰማያዊ እያመጡላቸው ይመገቡ ነበር እንጂ፡፡ ኋላም ዜና ጽድቃቸውን ሰምተው ከስድስት ሺህ ያላነሱ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበውላቸዋል፡፡
ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁ ብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም ብለው ነግረዋቸው አበምኔት ሾመውላቸው በዚህች ዕለት በዚያው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ ተሰውረዋል፡፡
በረከታቸው ይድረሰን!
©ስንክሳር
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
+ በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ +
ይድረስ ለተከፋኸው ወንድሜ መኖር ለደከመህ ፣ ሕይወት ለታከተህ ፣ የሚሰማህ ላጣኸው ፣ የሚረዳህ ሰው ላላገኘኸው መከረኛው ወዳጄ!
ከሞት ውጪ ሌላ መፍትሔ አልታይ ካለህ የአንተ ቢጤ መከረኞቹ ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት ውስጥ ሆነው እንዲህ ይሉሃል::
"በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" ሐዋ. 16:28
አውቃለሁ ዙሪያው ገደል ሆኖብሃል:: ምነው ባልተፈጠርሁ እስክትል ድረስ ተጨንቀሃል::
ግን ይህ ስሜት በአንተ አልተጀመረም:: ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ኑሮ ያልመረረው ማን አለ? መሞት ያልተመኘስ ማን አለ?
ሞት ያማረህ አንተን ብቻ መሰለህ?
" ስለ ምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዓይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ" ያለውን ጻድቅ ኢዮብ አልሰማህም? (ኢዮ. 10:18)
"ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ" ብሎ እንዲሞት የለመነውን ኤልያስን አላየኸውም? 1ነገሥ. 19:4
ዮናስንስ "አሁንም፥ አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ፥ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ፡ አለው" ሲል አልሰማኸውም? (ዮናስ 4:3)
ወንድሜ እመነኝ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን መኖር ያላስጠላው ሰው በታሪክ ፈልገህ አታገኝም::
ሞት ሞት የሸተተው ልቡ የተሰበረ ብዙ ነው:: አንተ ላይ ብቻ የደረሰ ልዩ ፈተና የለም:: "ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል" ይላል መጽሐፍ:: 1ኛ ቆሮ. 10:13
ምናልባት የልብህን መሰበር የኀዘንህን ጥልቀት አይቶ ምቹ ጊዜ አገኘሁ ብሎ ራስህን እንድትጎዳ ሰይጣን ሊገፋፋህ ይችላል:: እንዴት እንዲህ ዓይነት ሃሳብ በልቤ ሊመጣ ቻለ ብለህ አትረበሽ:: ሰይጣን ይህንን ክፉ ሃሳብ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለክርስቶስም አቅርቦለታል::
"የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር" ብሎ ክርስቶስን እንኳን [ማንነቱን ሳያውቅ] ራሱን እንዲወረውር ሊገፋፋው የሞከረ ደፋር ነው:: የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ግን ራሱን አይጎዳም:: "ጌታ አምላክህን አትፈታተነው" "ሒድ አንተ ሰይጣን" ብለህ ሰይጣንን ገሠፀው::
ሰይጣን ክርስቶስን "ከሕንፃ ጫፍ በመወርወር የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን አሳይ" ሲለው ክርስቶስ ሰይጣንን ሒድልኝ ብሎ በመገሠጹ በክብር ወደ ሰማይ ዐርጎ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ::
ወንድሜ ሆይ አንተም ሰይጣንን አትስማው ሃሳቡ ራስህን ጎድተህ ከፈጣሪህ እንድትጣላ ሊያደርግህ ነው:: ሰይጣንን ከገሠጽከው በእግዚአብሔር ቀኝ ከበጎቹ ጋር ትቆማለህ::
አሁን ያለህበት ችግር ያልፋል:: የሚሰማህ ክፉ ስሜት መቼም የማይለወጥ አይምሰልህ:: ኀዘኑም ፣ ብቸኝነቱም ፣ ተስፋ ቢስነቱም ያልፋል:: ጨለማው ይነጋል:: የተዘጋው በር ይከፈታል:: ችግሩ ሲፈታ አንተ ከሌለህ ግን ትርጉም የለውም::
ስለዚህ ለሚፈታ ችግር የማይቀለበስ ውሳኔ አትወስን:: ራስን ማጥፋት ከጊዜያዊ ችግር ለመሸሽ ሲሉ ዘላቂ ችግር ውስጥ መግባት ነው:: ጊዜያዊ ሕመምን ለማስታገስ የዘላለም ሕመምን ለምን ትመርጣለህ? "የሞተ ተገላገለ" ሲሉ ሰምተህ እንዳትታለል ሞት ዕረፍት የሚሆነው ራሱ እግዚአብሔር ሲጠራህ ብቻ ነው::
"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ" ያለው ጌታ ሳይጠራህ ራስን ማጥፋት የዘላለም ስቃይ ያመጣል::
ወዳጄ "በራስህ አንዳች ክፉ አታድርግ"
የሕይወትህን ዋጋ ታውቅ ይሆን? አንተ እኮ የእግዚአብሔር ልጅ ለአንተ ሲል የሞተልህ ነህ:: ሊፈውስህ የቆሰለ ፣ ሊያከብርህ የተዋረደ ፣ ሊያረካህ የተጠማ ፣ ሊያለብስህ የተራቆተ ለአንተ እኮ ነው::
ክርስቶስ ስለ አንተ ሞቶአል:: አንተን ግን የጠየቀህ እንድትሞትለት ሳይሆን እንድትኖርለት ነው::
ለሞተልህ አምላክ እንዴት መኖር ያቅትሃል?
ወዳጄ ሆይ ሰውነትህ በአምላክ ደም የተገዛ ክቡር ሰውነት ነው:: አካልህ "አንተ" እንጂ "ያንተ" አይደለም:: "በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ" ይላል
ስለዚህ በከበረ የእግዚአብሔር ልጅ ደም የተገዛ ሰውነትህን ለሰይጣን በርካሽ አትሽጠው:: አትግደል የሚለው ሕግ ራስህንም ይጨምራል:: ቤተ መቅደስ የሆነ ሰውነትህን ለማፍረስ አታስብ::
"ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ" 1ኛ ቆሮ. 3:17
ሰዎች አስቀይመውህ ይሆን?
"አሳያቸዋለሁ ፤ ስሞት የእኔን ነገር ይገባቸዋል" ብለህ በሰዎች ተቀይመህ ራስህን አትጉዳ:: እመነኝ ብትሞት ሰዎች ከሳምንት በላይ አያስታውሱህም:: ለሕይወትህ ዋጋ ያልሠጡ ሰዎች ለሞትህ ዋጋ አይሠጡም:: ፈጥነውም ይረሱሃል:: ለሚረሱህ ሰዎች ብለህ የማይረሳህን አምላክ አታሳዝን:: ሰው ስለ አንተ ግድ የለውም እግዚአብሔር ግን የራስህን ቁጥር ሳይቀር በቁጥር ያውቀዋል :: እንኳንስ ራስህን ልትጎዳ አንዲት ጸጉር እንኳን ከአንተ እንድትወድቅ አይፈልግም::
እግዚአብሔርን በኃጢአት ብታሳዝነው እንኳን ኖረህ ንስሓ እንድትገባ እንጂ እንድትሞት አይፈልግም:: አባትህ ነውና ከእርሱ ጋር ባትሆንም እንድትኖር ይፈልጋል:: በምሳሌ ልንገርህ :-
ሁለት ሴቶች አንድን ሕፃን "የኔ ልጄ ነው" ብለው እየተከራከሩ ጠቢቡ ሰሎሞን ፊት ቀረቡ:: ጠቢቡ ሰሎሞን ሰይፍ አመጣና "ልጁን ቆርጬ ለሁለት ላካፍላችሁ" አላቸው:: አንደኛዋ ሴት "እሺ እንካፈል" ስትል እውነተኛዋ እናት ግን "ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" አለች:: እናት መሆንዋም በዚህ ታወቀ::
ወዳጄ ያንተም ኑሮህ ከእግዚአብሔር ጋር ላይሆን ይችላል:: ዓለም የራስዋ አድርጋህም ይሆናል:: በሱስ ውስጥ ትዘፍቀህ ፣ እንደ ሶምሶን በደሊላ እቅፍ ፣ እንደ ዴማስ በተሰሎንቄ ውበት ተማርከህ ይሆናል:: እግዚአብሔር ግን አባትህ ነውና ሞትህን አይፈልግም::
"ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" እንዳለችው እናት ፈጣሪህ ከነኃጢአትህም ቢሆን እንድትሞት አይፈልግም:: ከእርሱ ጋር ባትኖርም መኖርህን ይፈልጋል:: "የሟቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ" ሕዝ. 18:32
የይሁዳ ኃጢአቱ ጌታውን መሸጡ አልነበረም:: ራሱን መግደሉ ነው:: እግዚአብሔር የሚያዝነው ከበደልህ በላይ በእርሱ ተስፋ ቆርጠህ ራስህን ስትጎዳ ነው::
ወዳጄ የአንተን መኖር የሚፈልጉ ብዙ ናቸው:: ፈጣሪ ወደዚህች ዓለም ያለ ምክንያት አላመጣህም:: በአንተ አለመኖርም የሚጎድል ነገር አለ:: አንተን የሚመስል ሌላ ሰው አልፈጠረምና ለዚህ ዓለም አንተን የሚተካ የለም:: በክብር ወደዚህ ዓለም ያመጣህ አምላክ በክብር ወደራሱ እስኪወስድህ ድረስ "በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርግ"
"የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።
ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ፡ ብሎ ጮኸ" ሐዋ. 16:27-28
ይህ ሰው እስረኛ ያመለጠ መስሎት ራሱን ሊያጠፋ ሲል ጳውሎስ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" አለው::
ወዳጄ አንተስ ተስፋ የቆረጥኸው ምን ያመለጠ መስሎህ ነው?
"የአምላክ አቃቤ ሕግ"
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ጥቅምት ፭
የታላቁ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት) የዕረፍታቸው መታሰቢያ
ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሏቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው። የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አንደበት ይኖራል? እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል? ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?
አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ፭፻፷፪(562) ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ /ምግባቸው ምስጋና ነውና/ ልብስ ያልለበሱ /ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና/ ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት፤ ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል።
ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ። በ፭፻፷፪ ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮጵያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም በሚሊዮን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል።
ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል። እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል። ለ'የ'ት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው፤ ከዕልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና።
የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቀር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ፻(100) ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።
ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ፳፻(2,000) በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት። በ፰(8)ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ፲፬(14)ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዝዘው መጋቢት ፭(5) ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።
ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ። "ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ: ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ: ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ: ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ: ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ።" እንዲል።
ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት ፭(5) ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው። ፍትሃ ነገስት አንቀጽ ፲፭(15) ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ :የመጋቢት ፳፯(27) ስቅለት ጥቅምት ፳፯ ቀን እንደሚከበረው ሁሉ የአባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው ወደ ጥቅምት ፭ ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡
የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከታቸው በእኛ በምናምን ላይ ይደርብን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የአሜሪካ ሕክምናቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸውና ወደ መንበረ ክብራቸው
በሰላም ተመለሱ።
*******
ጥቅምት ፩ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
****
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
""""""""""""""""""""
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሰሜን አሜሪካ ሲያደርጉት የቆዩትን ሕክምና አጠናቀው ዛሬ ማለዳ ወደ አገራቸውና ወደ ወንበረ ክብራቸው በሰላም ተመለሱ።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ዛሬ ማለዳ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዩወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ክቡር መልአከ ሕይወት አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ደማቅ አቀባበል ከድርገውላቸዋል።
በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳምም ለቤተክርስቲያንና ለቅዱስነታቸው ክብር የሚመጥን የእንኳን ደህና መጡ መርሐ ግብር ከሰዓታት በኋላ የሚከናወን ይሆናል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ አሜሪካ ያቀኑት ከአንድ ዓመት በፊት ተይዞላቸው በነበረ የህክምና ቀጠሮ ምክንያት ነው።
አንዳንድ የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ከቅዱስነታቸው ጉዞ ጋር በተያያዘ ቅዱስነታቸው ተመርዘው ወደ አሜሪካን ለህክምና እንደ ተጓዙ አስመስለው መሰረተ ቢስና ከእውነት የራቀ መረጃዎችን በማስተላለፍ ሕዝበ ክርስቲያኑን ሲያደናግሩ መክረማቸውም ይታወሳል።
©EOTCDoPR
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷
የመስከረም ፳፰(ሰንበት) ግጻዌ
✞ መልእክታት ዘቅዳሴ
፩. ወደ ሮሜ ፭ : ፳፩ - ፍጻሜ
፪. ራእ ዮሐ ፩ : ፩ - ፱
፫. ግብረ ሐዋርያት ፳፩ : ፴፩ - ፍጻሜ
✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
መዝ ፻፳፯ : ፪ -፫/127:2-3
" ፍሬ ፃማከ ተሰሴይ። ብፁዕ አንተ ወሠናይ ለከ።
ብእሲትከ ከመ ወይን ሥሙር ውስተ ጽርሐ ቤትከ።"
"የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ፤ ምስጉን ነህ መልካምም ይሆንልሃል።ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት።"
✞ ወንጌል ዘቅዳሴ
የዮሐንስ ወንጌል ፫: ፳፭ - ፍጻሜ /3:25-ፍጻሜ
"ስለዚህም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል ስለ ማንጻት ክርክር ሆነ።
ወደ ዮሐንስም መጥተው፦ መምህር ሆይ፥ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው አንተም የመሰከርህለት፥ እነሆ፥ እርሱ ያጠምቃል ሁሉም ወደ እርሱ ይመጣሉ አሉት።
ዮሐንስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ ከሰማይ ካልተሰጠው ሰው እንዳች ሊቀበል አይችልም።
እናንተ፦ እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፥ ነገር ግን፦ ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ እንዳልሁ ራሳችሁ ትመሰክሩልኛላችሁ።
ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ።
እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል።
ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው።
ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፥ ምስክሩንም የሚቀበለው የለም።
ምስክሩን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ።እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።አባት ልጁን ይወዳል ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል።በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።"
✞ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷
🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤
በኦሮሚያ አዳማ ዙሪያ ወረዳ ሁለት ካህናት በቤተክርስቲያን ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ 2 አገልጋዮች ታፍነው ተወስደዋል።
***
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙርያ ወረዳ በምትገኘው በመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያንን አገልጋይ የነበሩት አባ ተክለ አብ እና ቀሲስ መሠረት የተባሉ ካህናት አባቶች በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን እንዲሁም መርጌታ ፍሰሐ እና መርጌታ ተቅዋም የተባሉ አገልጋዮች ታፍነው ሸኔ ተብሎ በሚታወቀው አከባቢው ላይ በሚንቀሳቀሰው ኃይል ተወስደዋል፡፡
ሰማዕትነት የተቀበሉ አባቶችም ስርዓተ ቀብራቸው በሚያገለግሉት እና በተገደሉበት አጥቢያ ተከናውኗል።
የሰማዕታቱ በረከት ይደርብን !!!
🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤🖤
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ትምክህተ ዘመድነ ማርያም እምነ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
መስከረም ፳፩
ብዙኃን ማርያም
በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው።
ጉባዔ ኒቅያ
በ፫፻፳፭ ዓ.ም አርዮስ የሚባል መናፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡
በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡
ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ (2348) መካከል ፫፻፲፰ (318) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡
፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "ብዙኃን ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡
@Ethiopian_Orthodox
ዕፀ መስቀል/ግሸን ማርያም
በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤
ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡
ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡
መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡
ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡ መጽሐፉ እንደሚለው በሃገራችን ያለው ግማደ መስቀሉ (የቀኝ እጁ) ብቻ ሳይሆን ሙሉው ዕፀ መስቀል ነው።
የእመቤታችን ማርያም ምልጃና ጥበቃ አይለየን!
©ማኅበረ ቅዱሳን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ዜና እረፍት
መስከረም ፲፰ቀን፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
*
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።
*
የታዕካ ነገስት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል ገዳማት የበላይ ጠባቂ ጸሎተኛው፣ደጉ፣ሩህሩሁና ታጋሹ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዛሬ መስከረም ፲፰ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።ብፁዕ አባታችን ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።የብፁዕነታቸውን ሽኝት መርሐ ግብር በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ እንደተወሰነ ዝርዝሩን የምናሳውቅ ይሆናል።
የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን
©EOTCPR
@Ethiopian_Orthodox
መስከረም 17 ቀን ማለትም የደመራ በዓል ማግስት የምናከብረው የመስቀል በዓል ደግሞ ንግሥት እሌኒ ደመራ አስደምራ እጣን አጢሳ (አስጢሳ) የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ #ቁፋሮውን_ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤ በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ አጋዥነት ቁፋሮ በተጀምረ ከ5 ወር ከ23 ቀን በኋላ መስቀሉ መጋቢት 10 ተገኝቷል፤ ከ10 ዓመት በኋላም ቤተ መቅደሱ ታንጾ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡ መስቀሉም እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽባዎችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡ ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡ ይህ የጌታ #ዕፀ መስቀልም በዓፄ #ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በተለያዩ ቅዱሳት መካናት (እንጦጦ #ማርያም፣ ጋራ #መድኃኔዓለም፣…..) ሲያርፍ ቆይቶ በስተመጨረሻው ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል›› ተብሎ ለዓፄ #ዘርዓ ያዕቆብ በተነገረው መሠረት በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም በክብር አርፏል፡፡ እኛንም በመስቀሉ ፈዋሽነት ይማረን የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ይሳልብን አሜን፡፡
* "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" /ሊቁ ቅዱስ #ያሬድ/
* ‹‹ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።›› /ብርሃነ ዓለም ቅዱስ #ዻውሎስ ገላ.6፥14፣ 1ኛቆሮ.1፥18/
የመስቀል ክብረ በዓላት
መስከረም 16 የደመራ በዓል
መስከረም 17 የመስቀል በዓል
መስከረም 10 ተቀጸል ጽጌ
መጋቢት 10 መስቀሉ የተገኘበት በዓል
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox