ethiopian_orthodox | Unsorted

Telegram-канал ethiopian_orthodox - የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

30459

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Subscribe to a channel

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ምእራፍ ሁለት
ትምህርት ስለ ፈቃድ

ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛልና፥ነገር ግን በብልቶቼ ከአእምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋውንና በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝን ሌላ ሕግ አያለሁ። ›› ሲል ነግሮናል፡፡ ሮሜ. ፯÷፳፪—፳፫
አባቶች ይህንን ሲያብራሩ በእኛ ዘንድ ሁለት ፈቃዶች እንዳሉ ያስረዳሉ፡፡ ታላቅ የሆነውና የከበረው ፈቃዳችን ‹‹ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን የሚሻ›› የውስጣዊው ሰውነታችን ፈቃድ ነው፡፡ (ቆላ.፫÷፩) የተዋረደውና ታናሽ የሆነው ፈቃዳችን ደግሞ እርካታን ብቻ የሚሻው ፈቃዳችን ወይም ‹የኃጢአት ሕግ› ሲሆን ዓለምንና የሥጋ አምሮቱን ብቻ የሚከተል ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው እነዚህ ሁለት ፈቃዳት በውጊያ ላይ ናቸው፡፡ (ሮሜ. ፯÷፳፫)
በሚያሳዝን ሁኔታ ብዙውን ጊዜ ታላቅ የሆነውን ፈቃዳችንን የሚያሸንፈው የተዋረደውና ታናሽ የሆነው ፈቃዳችን ነው፡፡ ስለዚህ የኃጢአት ሕግ ወይም የተዋረደው ፈቃድ ወይም የራስን እርካታ ብቻ የሚሻው ፈቃዳችን የሚመራው በቀንደኛው ጠላታችን በዲያቢሎስ ነው እንዲሁም በልእልና ያለው ፈቃዳችን በጸጋው ይመራል ልንል ማለትም አያስፈልግም፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ኖላዊነ ሔር- መድኃኒዓለም " ዘማሪ ቀሲስ እስክንድር ወልደማርያም

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቸር ጠባቂ ለበጎቹ መልካም መሰማርያን ያዘጋጃል፤ ያሰማራቸዋልም።

ቸር ጠባቂ በጎቹን በመልካም ስፍራ ለማሰማራት መሰማርያን ያዘጋጃል። ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፤ የሚያሳጣኝም የለም፤ በለመለመ መስክ ይመራኛል(መዝ 22፡1)።›› እንዳለው ቸር ጠባቂ በጎቹን በለመለመ መስክ ያሰማራቸዋል።  ‹‹በሙሴና በአሮን እጅ ህዝብህን እንደ በጎች መራሀቸው›› መዝ 76፡20 እንደተባለም በበጎ ይመራል። የለመለመ መሰማርያ የተባለም የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ የአገልግሎት ዘርፍ ነው።

ምንደኛ ግን ራሱን ያሰማራል። በትንቢተ ሕዝቅኤል በምዕራፍ 43 ቁጥር 2 ላይ እንደተገለፀው ክፉ እረኛ ራሱን በበጎቹ መካከል ያሰማራል። ጠቦቶቹንም ያርዳቸዋል፤ ይበላቸዋልም። ‹‹ጮማውን ትበላላችሁ፤ ጠጉሩንም ትለብሳላችሁ፤ የወፈሩትንም ታርዳላችሁ፤ በጎቹን ግን አታሰማሩም (ሕዝ 34፡23)።›› እንዳለ መሰማርያውንና ውኃውን ይረግጣል፤ ያፈርሳልም። ለራሱና ለራሱ ብቻ መሰማርያን ያዘጋጃል። ለእኛ ግን ለነፍስም ለሥጋም የሚሆን መሰማርያን የሚያዘጋጅልን እርሱ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ቸር ጠባቂ በጎቹን ያበዛል።

ቸር ጠባቂ በበረት ያሉትንና በውጭ ያሉትን በጎች አንድ ለማድረግ ይተጋል። በውጭ ያሉትን በጎች ወደ በረት ለማስገባት ሌትና ቀን ይሠራል። ይህንንም መርህ በማድረግ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን ለዓለም በመስበክ በጎችን አብዝተዋል። ቅጥረኛ ግን በውጭ ያሉት በጎች በዚያው ቢቀሩ አይገደውም። በበረት ያሉትንም ጭምር በመከፋፈል ከበረት አስወጥቶ ይበትናል። እርሱ ስለራሱ ጥቅም እንጂ ስለበጎቹ ምንም የማይገደው ምንደኛ ነውና። ነገር ግን ‹‹የማሰማሪያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው (ኤር 23፡1)።›› እንደተባለ በመጨረሻው ቀን መጠየቁ አይቀርም። እኛ ግን የጠፉትን የሚፈልግ፣ ያሉትን የሚያፀና እውነተኛ ጠባቂያችን እርሱ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብለን እናምናለን።

ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት ‹‹እኔ ባሪያህ የአባቴን በጎች ስጠብቅ አንበሳና ድብ ይመጣ ነበር፥ ከመንጋውም ጠቦት ይወስድ ነበር።  በኋላውም እከተለውና እመታው ነበር፥ ከአፉም አስጥለው ነበር፤ በተነሣብኝም ጊዜ ጕሮሮውን ይዤ እመታውና እገድለው ነበር (1ኛ ሳሙ 17፡34)። ›› እንዳለው ከዲያብሎስ ጉሮሮ ከአንበሳም መንጋጋ ያዳነን እውነተኛው ጠባቂያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ቸር ጠባቂ ስለበጎቹ መስዋእት ይሆናል።

ቸር ጠባቂ ራሱን ስለ በጎቹ አሳልፎ ይሰጣል። ተኩላ ሲመጣ ጥሎ አይሸሽም፤ ከበጎቹ ቀድሞ ይዋጋል እንጂ። ‹‹ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከማኖር ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም (ዮሐ 15፡13)።›› እንደተባለ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ መስዋእት ይሆናል። ምንደኛ ግን በጎቹን ስለ ራሱ አሳልፎ ይሰጣል። ተኩላ ሲመጣም በጎቹን ጥሎ ይሸሻል፤ በጎቹም ለምድር አራዊት መብል ይሆናሉ።

‹‹ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ።  ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍሱን ይሰጣል።  ጠባቂ ያይደለ፥ በጎቹም ገንዘቡ ያልሆኑ ምንደኛ ግን ቅጥረኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም መጥቶ በጎቹን ይነጥቃቸዋል፤  ይበትናቸዋልም።  ምንደኛስ ይሸሻል፤ ስለ በጎቹም አያዝንም፤ ምንደኛ ነውና።  ቸር ጠባቂ እኔ ነኝ፥ የእኔ የሆኑትን መንጋዎቼን አውቃለሁ፡፡ የእኔ የሆኑትም ያውቁኛል፡፡ አብ እኔን እንደሚያውቀኝ እኔም አብን አውቀዋለሁ፤ ለበጎች ቤዛ አድርጌ ሰውነቴን አሳልፌ እሰጣለሁ (ዮሐ 10፡11-15)።›› እንዳለ  ነፍሱን ስለ በጎቹ አሳልፎ የሰጠ እውነተኛ ጠባቂያችን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እንደተናገረው ቸር ጠባቂ እርሱ ነው፤ በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎቹ ትልቅ ጠባቂ የሆነው እርሱ ነው (ዕብ 13፡20)። የነፍሳችን  ጠባቂ የሆነው እርሱ ነው (1ኛ ጴጥ 2፡23)። የእስራኤል ዘነፍስ ጠባቂ የሆነውም እርሱ ነው (መዝ 79፡1)። እውነተኛም ጠባቂ እርሱ ነው (ዮሐ 10፡7)።

በጎችን የመጠበቅ ኃላፊነትና ተጠያቂነት

በጎችን የመጠበቅ ኃላፊነት ከተጠያቂነት ጋር አብሮ ለጠባቂዎች (ለሐዋርያትና ከሐዋርያት ቀጥሎ እስከ ዕለተ ምጽዓት ለሚነሱ እውነተኛ መምህራን) ተሰጥቷል። ‹‹ግልገሎቼን አሰማራ፤ ጠቦቶቼን ጠብቅ፤ በጎቼን አሰማራ።›› ብሎ የመጠበቅ ኃላፊነትን በጴጥሮስ በኩል ለሐዋርት ሰጥቷል (ዮሐ 21፡15-17)። ‹‹በጎቼን ከጠባቂዎች እጅ እፈልጋለሁ›› ብሎም በጎችን የመጠበቅ አገልግሎት ተጠያቂነትም እንዳለበት ተናግሯል (ሕዝ 34፡10)። በጎች (ምዕመናን) የክርስቶስ ተከታዮች እንጂ የእረኞቹ ተከታዮች አይደሉም፤  ጠባቂዎችም ባለአደራዎች እንጂ የበጎቹ ባለቤቶች አይደሉምና።

ዛሬስ የጠባቂዎች  ድርሻ ምንድን ነው?

ጌታችን እንዳስተማረው የጠባቂዎች (የካህናትና የመምህራን) ድርሻ የሚከተሉትን ያጠቃልላል።

በበሩ መግባት፡- በተዋሕዶ ላይ መመሥረት፣ በሥርዓት መመራት፣ በእምነት መኖር

በጎቹን ማወቅ፡- በግና ተኩላን ለይቶ ማወቅ፣ የራስንና የሌላውን ለይቶ ማወቅ፣ ለበጎቹም ግልፅ መሆን

በጎቹን መጠበቅ፡- በጎችን ነቅቶ መጠበቅ (እንዳይነጠቁ)፣ ባክነው እንዳይጠፉ መንከባከብ

መሠማርያውን ማዘጋጀት፡- የሚያስፈልጋቸውን ትምህርት፣ ተግሳፅና ምክር መስጠት

በመልካም ስፍራ ማሰማራት፡- ከፊት ሆኖ በመምራት (በማገልገል) ለሥጋ ወደሙ ማብቃት

አንድነትን ማጠናከር፡- ከውጭ ያሉትን በማምጣትና ከውስጥ ያሉትን በማፅናት አንድነትን ማጠናከር

መስዋዕትነትን መክፈል፡- እውነትን በመመስከር መልካም አርአያ መሆን

የበጎች (የተጠባቂዎች) ድርሻስ ምንድን ነው?

በጌታችን ትምህርት መሠረት በጎች (ተጠባቂዎች) ጠባቂያቸውን በሚገባ ድምፁን ማወቅና እርሱንም መከተል፣ እውነተኛ ጠባቂ ያልሆነውን (ክፉውን እረኛ ወይም ምንደኛውን) መለየትና ከእርሱም  መራቅ፣ ዛሬ እውነተኛ የሆነው ጠባቂያቸው ወደ ምንደኛነት  ቢቀየር እንኳን ቶሎ ነቅቶ መለየት መቻልና ራሳቸውንም መጠበቅ ይኖርባቸዋል። እውነተኛና ቸር ጠባቂያችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም በጎች ያድርገን፤ አርአያ የሚሆኑ ደገኞች ጠባቂዎችንም አያሳጣን።

የኖላዊ ክብረ በዓል ከታህሳስ 21-27 ባለ እሁድ ቀን ብቻ የሚከበር ሲሆን ይህ በዓል በተለይም በምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በጣባ የጎደና ቀበሌ በኢትዮጵያ ብቸኛ በሆነው ጣባ ኖላዊ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ይከበራል ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

⛪️ኑ ሰንበትን በቤተ መቅደሱ ተገኝተን እናስቀድስ ⛪    
@Ethiopian_Orthodox
...................................................................

🔵የታኅሣሥ ፳፩(ሰንበት) ግጻዌ

✞ መልእክታት ዘቅዳሴ
፩. ዕብ ፲፫፥፲፮-ፍጻሜ/13፥16-ፍጻሜ
፪. ፩ኛ ጴጥ ፪፥፳፩-ፍጻሜ/2፥21-ፍጻሜ
፫. ግብረ ሐዋርያት ፲፩፥፳፪- ፍጻሜ/11፥22-ፍጻሜ

✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
መዝ ፸፱ ፥ ፩/79፥1
"ኖላዊሆሙ፡ ለእስራኤል፡ አጽምዕ፡፡
ዘይርዕዮሙ፡ ከመ፡ አባግዐ፡ ዮሴፍ፡፡
ዘይነብር፡ ዲበ(ላዕለ)፡ ኪሩቤል፡ አስተርአየ፡፡"
"ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ፡፡
የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፣ አድምጥ፡፡
በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ ተገለጥ፡፡"

✞ ወንጌል ዘቅዳሴ
የዮሐንስ ወንጌል ፲፥፩ - ፳፪/10፥1-22
"¹ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤
² በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።
³ ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል።
⁴ የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤
⁵ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና።
⁶ ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ምን እንደ ሆነ አላስተዋሉም።
⁷ ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።
⁸ ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም።
⁹ በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል።
¹⁰ ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።
¹¹ መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።
¹² እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል በጎቹንም ይበትናቸዋል።
¹³ ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።
¹⁴-¹⁵ መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።
¹⁶ ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።
¹⁷ ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል።
¹⁸ እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።
¹⁹ እንግዲህ ከዚህ ቃል የተነሣ በአይሁድ መካከል እንደ ገና መለያየት ሆነ።
²⁰ ከእነርሱም ብዙዎች፦ ጋኔን አለበት አብዶአልም፤ ስለ ምንስ ትሰሙታላችሁ? አሉ።
²¹ ሌሎችም፦ ይህ ጋኔን ያለበት ሰው ቃል አይደለም፤ ጋኔን የዕውሮችን ዓይኖች ሊከፍት ይችላልን? አሉ።
²² በኢየሩሳሌምም የመቅደስ መታደስ በዓል ሆነ"

✞ቅዳሴ ~ ዘእግዚእነ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ማመስገንን በአእምሮዬ ውስጥ ተክዬዋለሁ? የማይቻል ነገር ነው ልትሉ ትችላላችሁ ግን መሆን ያለበት ነው፡፡
   አቡነ ዮሐንስ የተባሉ አባት በየሳምንቱ ሐሙስ ሐሙስ በአቅራቢያቸው ወዳለ አንድ መንደር ለማስተማር ይሔዱ ነበር፡፡ በግብፅ እንደተለመደው ወደዚያች መንደር ለመሔድ ሲሳፈሩ ከአንድ ሌላ ሰው ጋር መዳበል ነበረባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ አንድ አክራሪ ሙስሊም ሁልጊዜ በተመሳሳይ ሰዓት  አብሯቸው ይሳፈር ነበር፡፡ ሊሳፈሩ ሲገቡ ታዲያ ፊቱን ዞር ያደርግና ይተፋ ነበር! ይህን አስነዋሪ ድርጊት ለዓመታት ይፈጽም ነበር፡፡ አንድ ቀን ጳጳሱ ሊሳፈሩ ሲመጡ ያ ሰው አልነበረም፡፡
   አቡነ ዮሐንስ ከልባቸው አዝነው እግዚአብሔርን መጠየቅ ጀመሩ ‹‹ጌታዬ ይህንን በረከት ለምን አስቀረህብኝ? ይህንን በረከት ከዚህ በላይ እቀበል ዘንድ እንደማልገባ የወሰንከው በኃጢአቶቼ መብዛት ይሆን?››

    ሌላው የተቀደሰ ትውስታ ባለቤት ደግሞ የማይታክቱት የእግዚአብሔር ሠራተኛ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤል ነበሩ፡፡ እኚህ አባት እንደተለመደው ብዙ ጠላቶች ነበሯቸው ፤ እጅግ አስጸያፊ መልእክቶችን እየጻፉ በደብዳቤ መልክ ይልኩላቸው ነበር፡፡ እሳቸውም እነዚህን አስጸያፊ ስድቦች በመሳቢያቸው ውስጥ ያስቀምጡአቸው ነበር፡፡ በሚከፋቸውና በሚተክዙ ጊዜ ማኅደራቸውን ከፍተው እነዚህን ደብዳቤዎች ያነብቡ ነበር ፤ ከዚህ በኋላ የመታደስ ስሜት ይሰማቸዋል ምክንያቱም ነቀፋዎቹን ሲያነብቡ በእያንዳንዱ ስድብ ውስጥ በረከት እንዳለ ስለሚያዩ ነበር፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የምናነብበውን በልባችን ውስጥ መትከል የምንለው እንግዲህ ይህንን ነው፡፡
  አባቶቻችን ስድብን የመቀበልና ምስጋናን ያለመቀበል ሥልጠናን በተገቢው መንገድ ወስደዋል፡፡ ‹ፓራዳይዝ ኦፍ ፋዘርስ› የተባለው መጽሐፍ አእምሮን ስለመግዛት ሁለት አስደናቂ ታሪኮችን ይነግረናል፡፡
  አንድ አባት ወጣኒ ደቀመዝሙሩን አለው ‹ሒድና ሙታንን ተሳደብ› ፤ ወደ መቃብር ሔዶ ቀኑን ሙሉ ሙታንን ሲሳደብ ዋለ፡፡ በቀጣዩ ቀን ደቀ መዝሙሩን አለው ‹ሒድና ሙታንን አመስግን!› ወደ መቃብር ሔዶ ምስጋናውን ሲያወርድ ዋለ፡፡ ማታ ሲመለስ መምህሩ ጠየቀው ‹‹በሰደብካቸው ጊዜ ሙታኑ ተሰማቸው?›› ‹‹የለም አልተሰማቸውም›› አለና መለሰ ፤ ደግሞ ጠየቀው  ‹‹ስታመሰግናቸውስ?›› አለው ፤ ‹‹የለም አልተሰማቸውም›› አለው፡፡  አረጋዊውም ‹‹ሒድ አንተም እንዲህ ሁን!›› ብሎ ነገረው፡፡
   ሌላው ታሪክ ደግሞ መነኩሴ ይሆን ዘንድ ወደ ገዳም ስለሔደ የሀብታም ቤተሰብ ልጅ ስለሆነ ወጣት ነው፡፡ መምህሩ ‹‹ስድብን በደስታ ለመቀበል ራስህን አስለምድ›› ብለው ነገሩት፡፡ ዙሪያውን ቢፈልግ በገዳሙ ውስጥ እርሱን የሚሰድበው የለም፡፡ ስለዚህ ወደ መንደር ሔዶ ወደ ገዳም መጥቶ ስድብን በደስታ መቀበልን እስከሚለምድ ድረስ እንዲሰድበው አንድ ሰው ቀጠረ፡፡
    አንድ ቀን ከሌሎች መነኮሳት ጋር ወደ ከተማ ተልኮ ሳለ አንድ ቁጡ ሰው የስድብ ናዳ ሲያወርድበት በደስታ መሳቅ ጀመረ፡፡ ሌሎቹ መነኮሳት ለምን እንደሚስቅ ቢጠይቁት ‹‹ለዚህ (ለመሰደብ) ስከፍል ነበር ፤ አሁን ግን በነፃ አገኘሁት!›› አላቸው፡፡

   መጽሐፍ ቅዱስ በ፩ዮሐ. ፪÷፲፭ ላይ እንዲህ ይለናል ፡- ‹‹ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።›› እንዲሁም በያእቆብ ፬÷፬፡- ‹‹ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።›› ይላል፡፡
   ይህንንስ በአእምሮአችን ውስጥ ተክለነው ይሆን? የፍጹምነት መንገድ ዓለምንና በዓለም ያሉትን ነገሮች ሁሉ መናቅ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ›› ብሏል፡፡ ፊል. ፫÷፲፰
    ቅዱስ ጳውሎስ በዓለም ያለውን ነገር ሁሉ እንደ ጉድፍ ቆጥሮ የክርስቶስን እውቀት ያገኝ ዘንድ ሁሉን አጣለሁ አለ፡፡ የቆሻሻ ገንዳ! በልባችሁ ውስጥ ይህች ዓለም ትልቅ የቆሻሻ ገንዳ እንደሆነችና በውስጧም ያሉት ሁሉ ቆሻሻና ጉድፍ መጣያ እንደሆኑ ታስባላችሁ? አሁንም መኪና ባየሁ ጊዜ የምመሰጥና በአድናቆት የማከብረው ከሆነ ይህ መኪና የማመልከው ጣኦት አልሆነብኝም ትላላችሁ?
   አስታውሳለሁ አንድ ቀን ወጣቶችን አሳፍሬ ከሚሲሳውጋ ወደ ኪችነር እያመጣኋቸው ነበር፡፡ ሁሉም የሚያወሩት ስለ መኪኖች ነበር፡፡ የመኪኖች የተጨራመተ አካል በጭነት መኪኖች ላይ ተጭኖ አይታችሁ ታውቃላችሁ? ወይም ዝጎ የወደቀ የተጣለ መኪና አላያችሁም? ለዓይን ያስቀይማል፡፡ ሁልጊዜ መኪና ስትመኙ አስቀያሚ የብረት ቁርጥራጭ እንደሚሆን አስቡ፡፡ አእምሮአችሁን ዓለማዊ (ምድራዊ ነገሮችን) እንዲንቅና መንፈሳዊውን ፍጹምነት እንዲመኝ አለማምዱት፡፡
   መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ፡- ‹‹ትእግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስዱ ይበልጣል።›› ምሳ. ፲፮÷፴፪
    ቁጣን መቆጣጠር ጥንካሬ እንጂ ደካማነት አለመሆኑን በአእምሮዬ ውስጥ ቀርጬዋለሁ? የቁጣን ቃላት በቁጣ ቃላት ወይም ክፉን በከፉ መመለስ ቀላል ነው ፤ ቀላሉና የደካሞች መንገድ ይህ ነው፡፡ ንዴትን መቆጣጠርና እንደ ክፉ አመጣጥ አለመመለስ ግን ጥንካሬና ታላቅነት ነው፡፡ አንዴ ሲመቱ ሌላን ጉንጭ መስጠትስ ፈሪነት ሳይሆን ጀግንነት እንደሆነ በአእምሮአችሁ ውስጥ ተተክሏል? እንደማይቻል ትነግሩኛላችሁ እኔ ግን ይቻላል እላችኋለሁ፡፡
በዘጠናዎቹ ውስጥ የተፈጸመ እውነተኛ ታሪክ እነሆ፡፡ አንድ መነኩሴ የገዳሙን አስፈላጊ እቃዎች ለማሳደስ ተልኮ ወደ ካይሮ መኪና እየነዳ ይሔዳል፡፡ ከካይሮ ጠባብ ጎዳናዎች በአንዱ እየነዳው የነበረው መኪና አንድ የቆመ መኪናን ጭሮት ያልፋል፡፡ መነኩሴው የመኪናውን ባለቤት አጠያይቆ ያገኘውና ይቅርታ ጠይቆ ለማሳደሻ ልክፈል ይለዋል፡፡ የመኪናው ባለቤት ግን አክራሪ ነበር ፤ በክርስቲያኖች ላይ ያለውን ጥላቻ ለመወጣት ጥሩ አጋጣሚ ሆነለት፡፡ ስለዚህም መነኩሴውን መሳደብ ጀመረ ፣ አልፎም በጥፊ መታው፡፡ መነኩሴው ምንም ሳይል ሌላኛውን ጉንጩን ሰጠው፡፡ በዚህን ጊዜ ሰውዬው ልቡ ተነክቶ ፣ አልቅሶም መነኩሴውን ይቅርታ ጠየቀ ፤ እንዲህም አለው ፡- ‹‹መጥፎዎች እንደሆናችሁ ይነግሩናል ፤ ነገር ግን ከእኛ ትሻላላችሁ!›› ወደ ካይሮ ለምን እንደመጣም ጠየቀው፡፡ እቃ ለማሳደስ እንደመጣ ሲነግረው እርሱም እንዲህ ዓይነቶቹ እቃዎች የሚሠሩበትና የሚታደሱበት የሥራ መስክ ላይ እንደተሠማራ ነገረው፡፡ ከዚህ በኋላ እቃዎችን በነፃ ከማደስ አልፎ ሁልጊዜ ለእድሳት ሲመጣ ወደሌላ ቦታ እንዳይሔድ ቃል አስገባው፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በፊል. ፩÷፳፫ ላይ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና›› እንዲሁም በፊል. ፩÷፳፩ ላይ ‹‹ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና›› በእርግጥ ሞት ጥቅም እንጂ ጉዳት አለመሆኑ በአእምሮአችሁ ውስጥ ተተክሎአል? መሔድ ከክርስቶስ ጋር መኖር ከሁሉ ይልቅ የሚሻል መሆኑስ? ዓይን ያላያትን ጆሮ ያልሰማትን በሰው ልብ ያልታሰበችውን የእግዚአብሔርን መንግሥት መመኘትንስ አእምሮአችሁ ለምዷል? የሞትና የሕይወት እውነተኛ ትርጉምንስ በተገቢው መንፈሳዊ አረዳድ ተረድታችሁታል?

ምዕራፍ ሁለት ይቀጥላል......
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መልስ ግን ‹‹አትዋሹ! ጉዳዩ የግል ጉዳይ መሆኑን ብቻ ንገሯቸው›› የሚል ነው፡፡ ከተቆጡና ሊያናግሯችሁ ካልወደዱ አትጨነቁ ፤ እውነተኛ ጓደኞቻችሁ አይደሉም ማለት ነው፡፡ እውነተኛ ጓደኞች ምሥጢርን ለማውጣጣት ከመገፋፋት ይልቅ የጓደኞቻቸውን የግል ጉዳዮች ያከብራሉ፡፡

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መግቢያ
ምእራፍ አንድና ሁለት የሰው ልጅ ሕሊናና ፈቃድ ምን መምሰል እንዳለበት  ያብራራሉ፡፡  ቀጣዮቹ ሦስት ምእራፋት በግብረ ገብ ሥርዓት እና ከኃጢአት ጋር በመዋጋት ላይ ያተኩራሉ፡፡ የስሜትና የአሳብ ኃጢአቶችም በዚህ ላይ ይዳሰሳሉ፡፡ ቀጥሎ ያለው ምእራፍ ደግሞ ስለ ድፍረት ኃጢአቶችና ስለተሠወሩ ኃጢአቶች ያትታል፡፡ የመጽሐፉ መጨረሻ ክፍል ደግሞ ወደ መንፈሳዊ ፍጹምነት ለመድረስ የሚደረገውን ጉዞ ለመጀመር አስፈላጊ የሆኑ ባሕርያትን ይዘረዝራል።

                         ምእራፍ አንድ
                    ትምህርት ስለ አእምሮ

፩. ሕሊናን ከጎጂና ጥቅም አልባ እውቀት ጠብቅ
፪. በሕሊናህ ውስጥ መንፈሳዊ እውቀትን ትከል


          ጥቅም አልባ እውቀት
  ክርስቲያናዊ ፍጹምነትን ለማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ሕሊናህን ለነፍስህ ከማይጠቅም ወሬ መጠበቅ አለብህ፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ዘመኑ የመረጃና የመረጃ ጥበብ ዘመን ነው፡፡ ዓለም በቲቪ ፣ በመጻሕፍት ፣ በጋዜጦች ብቻ ሳይሆን በመረጃ መረብ ጭምር የሚያጥለቀልቅ መረጃን ከምንጊዜው በላይ እያቀረበችልን ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ጥቅም የለሽ መረጃ እኔ የአእምሮ ብክለት ብዬ ለምጠራው ችግር ይዳርጋል፡፡ በዚህ ዘመን ለሥራቸው ውጤታማነት ቢጠቅምም ባይጠቅምም መረጃን በመረጃነቱ ብቻ የሚፈልጉ የመረጃ ሱሰኞች አሉ፡፡   ቅዱስ ጳውሎስ በ፩ቆሮ.፪÷፪ ላይ እንዲህ ይለናል፡- ‹‹በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር ላላውቅ ቆርጬ ነበር›› ቅዱስ ጳውሎስን የሚያሳስበው እውቀት ኢየሱስና ሕይወትን የሚሰጠው መሥዋእትነቱ ነው፡፡  መክ. ፩÷፲፰ ላይ ደግሞ ፡- ‹‹በጥበብ መብዛት ትካዜ ይበዛልና እውቀትንም የሚጨምር ኀዘንን ይጨምራልና›› ይላል፡፡ 

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

⛪️ኑ ሰንበትን በቤተ መቅደሱ ተገኝተን እናስቀድስ ⛪    
@Ethiopian_Orthodox
...................................................................

🔵የታኅሣሥ ፲፬(ሰንበት) ግጻዌ

✞ መልእክታት ዘቅዳሴ
፩. ሮሜ ፲፫፥፲፩-ፍጻሜ/13፥11-ፍጻሜ
፪. ፩ኛ ዮሐ ፩፥ ፩ - ፍጻሜ/1፥1-ፍጻሜ
፫. ግብረ ሐዋርያት ፳፮፥፲፪- ፲፱/26፥12-19

✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
መዝ ፵፪ ፥ ፫/42፥3
"ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ።
እማንቱ ይምርሓኒ ወይስዳኒ ደብረ መቅደስከ
ወውስተ አብያቲከ እግዚኦ።"
“ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።”

✞ ወንጌል ዘቅዳሴ
የዮሐንስ ወንጌል ፩፥፩ - ፲፱/1፥1-19
"¹ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
² ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።
³ ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።
⁴ በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።
⁵ ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።
⁶ ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤
⁷ ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ።
⁸ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ፥ እርሱ ብርሃን አልነበረም።
⁹ ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።
¹⁰ በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም።
¹¹ የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።
¹² ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
¹³ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።
¹⁴ ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።
¹⁵ ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ እንዲህም ብሎ ጮኸ፦ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ።
¹⁶ እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤
¹⁷ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።
¹⁸ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።
¹⁹ አይሁድም፦ አንተ ማን ነህ? ብለው ይጠይቁት ዘንድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።"

✞ቅዳሴ ~ ዘአትናቴዎስ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
⛪️ኑ ሰንበትን በቤተ መቅደሱ እናስቀድስ 
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
@Ethiopian_Orthodox

🔵የታኅሣሥ ፯(ሰንበት) ግጻዌ

✞ መልእክታት ዘቅዳሴ
፩. ዕብ ፩፥፩-ፍጻሜ/1፥1-ፍጻሜ
፪. ፪ኛ ጴጥ ፫፥ ፩ - ፲/3፥1-10
፫. ግብረ ሐዋርያት ፫፥፲፯- ፍጻሜ/3፥17-ፍጻሜ

✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
መዝ ፻፵፫ ፥ ፯ -፰/143፥7-8
"ፈኑ እዴከ እምአርያም።
አድኅነኒ ወባልሐኒ እማይ ብዙኅ።
ወእምእዴሆሙ ለደቂቀ ነኪር። "
“እጅህን ከአርያም ላክ አድነኝም ከብዙ ውኆች፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር።”

✞ ወንጌል ዘቅዳሴ
የዮሐንስ ወንጌል ፩፥፵፬ - ፍጻሜ/1፥44-ፍጻሜ
"በነገው ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊወጣ ወደደ፥ ፊልጶስንም አገኘና፦ ተከተለኝ አለው።
ፊልጶስም ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበረ።
ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፦ ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው።
ናትናኤልም፦ ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን? አለው። ፊልጶስ፦ መጥተህ እይ አለው።
ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ፦ ተንኰል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው እነሆ አለ።
ናትናኤልም፦ ከወዴት ታውቀኛለህ? አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ ፊልጶስ ሳይጠራህ፥ ከበለስ በታች ሳለህ፥ አየሁህ አለው።
ናትናኤልም መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ አለው።
ኢየሱስም መልሶ፦ ከበለስ በታች አየሁህ ስላልሁህ አመንህን? ከዚህ የሚበልጥ ነገር ታያለህ አለው።
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ አለው።"

✞ቅዳሴ ~ ዘእግዚእነ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የኤልያስ በረከቱ ይደርብኝ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ታኅሣሥ ፩
ቅዱስ ኤልያስ ርዕሰ ነቢያት


በዚህች በታኅሣሥ አንድ ቀን በእስራኤል ፊት ነቢይ ኤልያስ የተገለጠበት ነው። ይህ ቀናኢ ኤልያስ ከሌዊ ወገን የሆነ የአባቱ ስም ኢያስኑዩ የእናቱም ስሟ ቶና ነው።

ስለርሱም እንዲህ ተነገረ በተወለደ ጊዜ ብርሃንን የለበሱ አራት ሰዎች ሲሰግዱለትና ሕፃናት በሚጠቀለሉበት ጨርቅ ፈንታ በእሳት ሲጠቀልሉት አባቱ አየ። እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ይህን ለካህናቱ ነገራቸው እነርሱም ማደሪያው በብርሃን ውስጥ ይሆን፣ በቃሉም የሚቆርጥ ይሆን፣ ወይም እስራኤልን በሰይፍና በእሳት እየቀጣ ይገዛቸው ይሆን ተባባሉ።

በእስራኤል ንጉሥ በአክዓብና በሚስቱ በኤልዛቤል በልጁም በአካዝያስም ዘመን ያደረገው የተአምራቱ ዜና በመጽሐፈ ነገሥት ተጽፎአል ። ወደ ሰማይ ያረገበት ዜናው ግን በጥር ወር በስድስት ቀን ተጽፎአል።

በኋላ ጊዜም ስለሚሆነው ሞቱ ራእይን በሕይወቱ ያየ ዮሐንስ ከኄኖክ ጋር እንደሚመጣና ሐሳዊ መሲሕን እንደሚቃወሙት ተአምራትንም እንደሚያደርጉ ተናግሮአል። ሁለቱ የዘይት ዕንጨቶች በምድር ላይም የተሾሙ በእግዚአብሔር ፊት የሚያበሩ ሁለት መብራቶች ናቸው አለ።

ከጠላቶቻቸውም ወገን ሊጣላቸው የወደደውን እሳት ከአፋቸው ወጥታ ታጠፋቸዋለች የሚጠሏቸው እንዲህ ይጠፋሉ። ትንቢት በሚናገሩበት ወራት በምድር ላይ ዝናም እንዳይዘንም ይዘጓት ዘንድ በሰማይ ላይ ሥልጣን አላቸውና ዳግመኛም ደምን ያደርጉት ዘንድ በውኃው ላይ ሥልጣን አላቸው የፈለጉትን ያህል በመቅሠፍቱ ሁሉ ምድርን ያስጨንቋታል።

ምስክርነታቸውንና ትንቢታቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከባህር የወጣው አውሬ ከእሳቸው ጋር ይጣላል ድል ነስቶም ይገድላቸዋል ። አስከሬናቸውንም ፍጥሞ በምትባል በታላቂቱ አገር ያስጥለዋል ይችውም በምሥጢር ሰዶም ግብጽ የተባለች ጌታቸው የተሰቀለባት ናት።

አስከሬናቸውንም ሕዝብና አሕዛብ በሀገርም ያሉ ነገዶች ሦስት ቀን ተኩል ያዩታል አስከሬናቸውንም በመቃብር ይቀብሩት ዘንድ አያሰናብቱም። በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በእነርሱ ሞት ደስ ይላቸዋል እርስበርሳቸውም በደስታ እጅ መንሻ ይሰጣጣሉ እሊህ ሁለቱ ነቢያት በምድር በሚኖሩ ሰዎች መከራ አጽንተውባቸዋልና ይላሉ።

ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሕይወት መንፈስ መጥታ ታድርባቸዋለች ተነሥተውም በእግራቸው ይቆማሉ በሚያዩዋቸው ላይም ጽኑ ፍርሀት ይሆናል።

ከወደ ሰማይ ቃል መጥቶ ወደዚህ ውጡ ይላቸዋል ከዚህ በኋላ ጠላቶቻቸው እያዩአቸው በደመና ያርጋሉ። በዚያችም ሰዓት ጽኑ መነዋወጥ ይሆናል የዚያችም አገር ዐሥረኛ እጅዋ ይጠፋል በዚያም መነዋወጥ ሰባት ሽህ ሰዎች ይሞታሉ የቀሩት ግን ደንግጠው የሰማይ አምላክን ፈጽመው ያመሰግናሉ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን!
©ስንክሳር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሱ መርቆሬዎስ ለተማፀነበት ሁሉ ይማልዳልና ድንቆች የሆኑ ታላላቅ ተአምራትንም ያደርጋልና።

ያም ወጣት መጋቢውን መልኩ እንዴት ነው ምን ይመስላል አለው መጋቢውም አካሉ አንተን ይመስላል አለው ይህንንም ብሎ ወደ ሥዕሉ ወስዶ ገልጦ አሳየው ወጣቱም በእገሌ በረሀ የታየኝ በእውነት ይህ ነው። በፈረሱም ላይ አፈናጥጦ ወደዚህ ያደረሰኝ ይህ ነው። እነሆ ታጥቋት በወገቡ ላይ ያየኋት የወርቅ መታጠቂያው ይቺ ናት። ስማኝ ልንገርህ እኔ በዚች አገር የምኖር አባቴም ስሙ ረጋ የሚባል መስፍን የሆነ እስላም የሆንኩ ሰው ነኝ። ክርስቲያንም ለመሆን ይች ምልክት ትበቃኛለች አሁንም በቦታ ውስጥ ሠውረኝ ለማንም ሥራዬን አትግለጥ። የክርስትና ትምህርትን አስተምሮ የእግዚአብሔርን መንገድ የሚመራኝን አምጣልኝ አለው። እርሱም ያለውን ሁሉ አደረገለት የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቀው።

ከዚህም በኋላ ወደ ነቢያቸው መቃብር የሔዱ እሊያ እስላሞች በአንድ ወራቸው ደረሱ። ዘመዶቻቸውም ሊቀበሏቸው ወጡ። ይህን ወጣት የመስፍን ልጅ ግን አላገኙትም። አባቱም አደራ ያስጠበቀውን ወዳጁን በጠየቀው ጊዜ እርሱም በበረሀ ውስጥ ቀርቶ እንደ ጠፋ እያለቀሰ ነገረው አባቱም በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀዶ አለቀሰ እንዲሁም ቤተሰቦቹ ሁሉም አርባ ቀኖች ያህል አለቀሱለት።

ከዚህም በኋላ በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ሲወጣ ይህን ክርስቲያን የሆነውን ወጣት አንድ እስላም አየው። ወደ ወላጆቹም ሒዶ እንዲህ ብሎ ነገራቸው ልጃችሁ በበረሀ ውስጥ የሞተ ከሆነ በመርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ደጅ ያየሁት እርሱን ባልመሰለኝ ነበር፤ እስቲ ሒዳችሁ አረጋግጡ። በሰሙም ጊዜ በስውር ሒደው ፈለጉት አግኝተውትም ይዘው ወሰዱት። እንዲህም አሉት በወገኖቻችን መካከል ልታሳፍረን ይህ የሠራኸው ምንድን ነው አሉት። እርሱም እኔ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታዬና በፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የማምን ክርስቲያን ነኝ ብሎ መለሰላቸው።

ይህንንም ሲል ታላቅ ሥቃይን አሠቃይተው ከጨለመ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት። ሽንታቸውን በላዩ እየደፉ የቤት ጥራጊም እያፈሰሱበት ያለ መብልና ያለ መጠጥ በዚያ ሰባት ቀንና ሌሊት ኖረ። እናቱ ግን ቀንም ሌሊትም በላዩ የምታለቅስ ሆነች ከልቅሶዋም ብዛት የተነሣ ከጉድጓድ አውጥተው እኛ ወደማናይህ ቦታ ሒድ አሉት። ወዲያውኑ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሒዶ በዚያ እያገለገለና እየተጋደለ ሁለት ዓመት ኖረ።

ከዚህም በኋላ በላዩ የትንቢት ጸጋ ያደረበት አንድ መነኰስ ወደ ምስር ከተማ ሒደህ ሃይማኖትህን ከምትገልጽ በቀር በዚህ መኖር ለአንተ አይጠቅምህም አለው። ወዲያውኑ ተነሥቶ ወደ ምስር ከተማ ሔደ።

አባቱም በአየው ጊዜ ሐኪም ወደ ሚባል ንጉሥ ወስዶ ይህ ልጃችን ነበር የእስልምና ሃይማኖትን ትቶ ወደ ክርስቲያን ሃይማኖት ገብቷል አለው። ንጉሡም ስለአንተ የሚናገሩት ዕውነት ነውን አለው። እርሱም በበረሀ ውስጥ ሳለ በሌሊት ቅዱስ መርቆሬዎስ እንደ ተገለጸለትና ከእርሱ ጋር በፈረስ እንዳስቀመጠው፣ በምስር አገር ወዳለች ቤተ ክርስቲያኑ የሃያ ሁለት ቀን መንገድ እንደ ዐይን ጥቅሻ አድርሶ ከውስጥዋ እንዳስገባው፣ ሥዕሉንም አይቶ ያመጣው እርሱ መሆኑን እንደ ተረዳ ለንጉሡ ነገረው።

ንጉሡም በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ። ታላቅ ፍርሀትም አደረበት አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምነኝ አለው። እርሱም በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም ዳግመኛም በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን እንድሠራ ታዝልኝ ዘንድ እሻለሁ አለው።

ንጉሡም በአስቸኳይ እንዲታነፁለት አዘዘለት። በውስጣቸውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። እርሱም አበ ምኔት ሁኖ ወደርሱ ብዙዎች መነኰሳት ተሰበሰቡ። ሁለት ድርሳናትንም ደረሰ። ከሀዲያንንም አስተምሮ ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ ። ለዚህም መነኰስ የክርስትና ጥምቀትን በተቀበለ ጊዜ ያወጡለት ስም ዮሐንስ ነው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ መርቆሬዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

©ስንክሳር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"አብሠራ ገብርኤል"
ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ታኅሣሥ ፳፪
ብሥራተ ገብርኤል

ታኅሣሥ ሃያ ሁለት በዚህች ዕለት ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን አምላክን እንደምትወልድ ያበሰረበት መታሰቢያ ነው፡፡ ይኸውም ‹‹ልዑል እግዚአብሔር ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን ‹ሂድና ለጽዮን ልጅ ለድንግል የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ወደአንቺ መጥቶ ኃይለ ልዑል ወልድ ሥጋሽን ለብሶ ሰው ይሆናል፤ ይኸውም ካንቺ የሚወለደው ጽኑዕ ነው ብለህ ንገራት› አለው፡፡ ‹ደንቆሮዎች የሚሰሙበት፣ ድዳዎቸ የሚናገሩበት፣ ዕውራንም የሚያዩበት፣ ሙታን የሚነሡበት፣ ለምጻሞች የሚነጹበት፣ ሐንካሳዎች የሚሄዱበት፣ በጨለማ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ብርሃን የሚያዩበት ጊዜ እነሆ ደረሰ ብለህ ንገራት› አለው፡፡
ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ሰምቶ በግንባሩ ተደፍቶ ልዑል እግዚአብሔርን ‹ጌታ ሆይ! የምትነግረኝ ይደረግ ዘንድ እንደምን ይሆናል?› አለው፡፡ ጌታም ‹የጀመርኩትን ቸርነት ፈጸምኩ፣ የወይን ግንድ ይቆረጣል (ወልደ እግዚአብሔር ይሞታል)፣ ወይራም ከበለስ ጋር ይተከላል (መስቀል ይተከላል)፣ ቅጽሮችም ይቀጸራሉ (ምግባር ከሃይማኖት ጋር ይሠራል)፣ የኤልፍና የሌሚ ወገን ይነሣል፡፡ ገብርኤል ሆይ! ሄደህ ለዳዊት ልጅ ‹እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ› ብለህ አብሥራት› አለው፡፡ ‹ለዘለዓለም ነግሦ የሚኖረውን እነሆ ትፀንሳለሽ በላት› አለው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ሰምቶ ሰገደ፡፡ ልብሱንም በላዩ ይዞ በመስቀል ቀኝ ይወርድ ዘንድ ወደደ፡፡ ጌታም ‹መግባትህና መውጣትህ በፍቅር አንድነት ይሁን› አለው፡፡ ‹ዘካርያስን ረግመህ አንደበቱን እንዳሰርህ እርሷን እንዳታሳዝናት ይልቁንም አብዝተህ ደስ አሰኛት አንጂ› አለው፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ሰምቶ ፈጽሞ ደስ እያለው ሊባኖስ ከሚባል ተራራ እስኪሰማ ድረስ ክንፉን እያማታ ወረደ፡፡ በዚህም ጊዜ በዙሪያው ያሉ ሁሉ ‹ይህ የምንሰማው ምንድነው?› ይሉ ነበር፡፡ የተደረገበትንም ቦታ አላወቁትም ነበር፡፡››
እመቤታችንን በ3 ዓመቷ እናትና አባቷ ብፅዓት አድርገው ለእግዚአብሔር ሰጥተዋታልና ካህናትም በቤተ መቅደስ ከመካነ ደናግል አስገብተዋት በመልአኩ በቅዱስ ፋኑኤል አማካኝነት ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየመጣላት ያንን እየተመገበች ቅዱሳን መላእክት እየጎበኟት 12 ዓመት ኖራለች፡፡ በ15 ዓመቷ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ጌታችንን እንደምትወልድ በዚህች ዕለት አብሥሯታል፡፡ በመጀመሪያ እመቤታችን ውኃ ቀድታ ስትመለስ የጠተማ ውሻ እያለከለከ ሲመጣ ብታየው ለፍጥረት ሁሉ የምትራራ ናትና በወርቅ ጫማዋ ለዛ ለተጠማው ውሻ ውኃ ስታጠጣ አብሯት የነበሩ ሴቶች ‹‹ማድጋሽን አጎደልሺው፣ ቀድቼ እሞለዋለሁ እንዳትይ ጉድጓዱ ጥልቅ ነው መቅጃም የለሽም›› አሏት፡፡ ክብርት እመቤታችንም ‹‹ውሃ የሚገኘው ከወደላይ ነው እንጂ ከወደታች ነውን? ፍጥረቱን ያጠጣ ጌታ ይሞላልኛል›› አለቻቸው፡፡ ማድጋዋም በተአምራት ሞልቶ ተገኘ፡፡ ሴቶቹም ዳግመኛ ‹‹በዚህ ዘመን አምላክ ከድንግል ይወለዳል ይላሉ ካንቺ ይሆን?›› እያሉ ሲዘብቱባት ወዲያው ከወደኋላዋ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ‹‹እነሆ ትጸንሻለሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም ዞር ብትል የተናገራትን አጣችው፡፡ በዚህም ጊዜ ‹‹አባቴን አዳምን እናቴን ሔዋንን ያሳተ ጠላት ይሆናል›› ብላ ሄደች፡፡
ዳግመኛም እመቤታችን ከቤት ደርሳ ማድጋዋን ስታስቀምጥ መልአኩ አሁንም በድምፅ ‹‹እነሆ ትጸንሻለሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም ይህን ጊዜ ‹‹ምነው ይህስ ነገር ደጋገመኝ እንዲህ ያለውን ነገር ቤተ መቅደስ ሄደው ሊረዱት ይገባል›› ብላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዳ ወርቅና ሐር እያስማማች ስትፈት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እሁድ ቀን በ3 ሰዓት በገሃድ ተገለጸላትና እጅ እየነሳ እየሰገደ አበሠራት፡፡ ‹‹የዕውነተኛ ንጉሥ እናቱ እመቤታችን ላንቺ ፍቅር አንድነት ይባል›› አላት፡፡ ዳግመኛም ‹‹አንቺ ከሴቶች ይልቅ ተለይተሸ ንዕድ ክብርት ነሽ›› አላት፡፡ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናቸ ክብርት እመቤታችንም የብርሃናዊውን መአልክ የቅዱስ ገብርኤልን ቃል በሰማች ጊዜ ‹‹እንዲህ ያለውን ሰላምታ እንደምን ይቀበሏል! እንዴትስ መቀበል ይቻላል? እንጃ›› አለችው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ‹‹ማርያም ሆይ! መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፣ ኃይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ይለብሳልና አይዞሽ አትፍሪ›› አላት፡፡ ዳግመኛም ‹‹ይህ ካንቺ የሚወለደው ጽኑ ከሃሊ ነው፡፡ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ፣ እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፣ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፣ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፣ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም›› አላት፡፡ እመቤታችንም መልአኩን ‹‹ምድር ያለ ዘር ፍሬን አትሰጥምና እኔ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?›› አለችው፡፡ መልአኩም መልሶ ‹‹መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፣ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ እርሷ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፡፡ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፣ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና›› አላት፡፡ ክብርት እመቤታችንም ይህን ጊዜ ‹‹እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ›› አለችው፡፡ መልአኩም ከእርሷ ዘንድ ሄዶ ተሠወረ፡፡ አካላዊ ቃልም በማኅፀኗ አደረ፡፡ በዚያችም ቅጽበት የእመቤታችን የፊቷ መልክ ተለወጠ፣ እንደፀሐይም አሸበረቀ፡፡
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
‹‹እንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ ወሪዳ ምድረ ቆላ ገብርኤል መጽአ እንዘ ይረውጽ በሰረገላ ክንፎ ክንፎ ክንፎ ጸለላ ተፈስሒ ተፈስሒ ለድንግል ይቤላ፤
ትርጉም ፦ወደ ቆላው ምድር ወርዳ እመቤታችን ወርቅን ከሐር ጋር አስማምታ እየፈተለች ሳለች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ እየሮጠ መጣ፣ ክንፉንም እያማታ እየሰገደ ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ አላት››

"ተፈሥሒ ፍሥሒት ኦ ምልዕተ ጸጋ፤ ጸጋን የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ" ሉቃ 1፡28

…ደስ የተሰኘህ ሆነህ ምሥራችን የተናገርክ መልአኩ ገብርኤል ሆይ የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው። ወደኛ የመጣ የጌታን ልደት ነገርኸን ለድንግል ማርያም ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ ብለህ አበሰርኻት ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን ።…

እንኳን አደረሳችሁ!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ኖላዊ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የበዓላት ቀኖና መሠረት ከህዳር 15 እስከ ጌታችን ልደት (ታህሳስ 28/29) ድረስ ያለው ወቅት በዘመነ ብሉይ የነበሩ ቅዱሳን ነቢያት የጌታን ልደት በተስፋ እየጠበቁ የገቡትን ሱባኤ፣ የጾሟቸውን አጽዋማት በማሰብ ልዩ ልዩ ክብረ በዓላት ይከበራሉ። ለእያንዳንዱ በዓልም የተለየ የቅዱሳት መጻሕፍት ንባብና ትርጓሜ፣ የተለየ የምስጋና መዝሙር ይዘመራል። በጾመ ነቢያት ውስጥ ያሉት የመጨረሻዎቹ ሦስት ሣምንታት በተለየ መልኩ ይከበራሉ። ወቅቱም ትንቢተ ነቢያትን በማሰብ ዘመነ ስብከት ይባላል። የነቢያት የስብከታቸው ማዕከል የክርስቶስ ሰው የመሆን ተስፋ ነውና።

የዘመነ ስብከት የመጀመሪያው ሣምንት ስብከት ይባላል(ከታኅሣሥ 7-13)፤ ሁለተኛው ሣምንት ብርሃን ይባላል(ከታኅሣሥ 14-20)፤ ሦስተኛው ሳምንት ኖላዊ ይባላል(ከታኅሣሥ 21-27)። ኖላዊ ማለት ጠባቂ ማለት ሲሆን ቅዱሳን ነቢያት እውነተኛው ጠባቂ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ይገለጣል ብለው በትንቢት መናገራቸውና ኢየሱስ ክርስቶስም ቸር ጠባቂ መሆኑን እያሰበች ቤተክርስቲያን የምትዘምርበት፣ የምታመሰግንበትና የምታስተምርበት ዕለት በመሆኑ ኖላዊ ተብሎ ተሰይሟል።  በዚህ ዕለት ጌታችን በወንጌሉ እርሱ ቸር ጠባቂ እንደሆነ ያስተማረበት ዮሐ 10፡1-22 ያለው የወንጌል ክፍል ይነበባል፣ ከተያያዥ የቅዱሳት መጻሕፍት ምስጢራት ጋርም ይሰበካል፣ ይተረጎማል።

የዚህ የጌታችን ትምህርት መነሻ ‹‹እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች ስፍራ በበሩ የማይገባ በሌላም በኩል የሚገባ  ሌባ፥ ወንበዴም ነው፤ በበሩ የሚገባ ግን የበጎች ጠባቂ ነው።  ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ አውጥቶም ያሰማራቸዋል።  ሁሉንም  አውጥቶ ባሰማራቸው ጊዜ በፊት በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ቃሉን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ ከሌላው ግን ይሸሹታል እንጂ አይከተሉትም፥ የሌላውን ቃሉን አያውቁምና(ዮሐ 10፡1-5)። ›› የሚለው ነው።

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ‹‹ቸር ጠባቂ›› የተባውን ትምህርት ስለ ሦስት ምክንያቶች አስተምሯል። የቸር ጠባቂ መገለጫዎችን ለይቶ ለማሳወቅ፤  የቸር ጠባቂና የምንደኛን ልዩነት ለማስረዳትና ቸር ጠባቂ እርሱ መሆኑን ለመግለጽ ያስተማረው ነው። በትምህርቱም ሰባት የቸር ጠባቂ መገለጫዎችን አስቀምጧል።  እነዚህም፡-

ቸር ጠባቂ በበሩ ይገባል፤ በበሩም ይወጣል።

ቸር ጠባቂ ወደ በጎች በረት በበሩ ብቻ ይገባል፤ በበሩም ብቻ ይወጣል። በጎቹን ከበረታቸው አውጥቶ ሊያሰማራ በግልፅ በበሩ ይገባል፤ ይዟቸውም በግልፅ (በብርሃን) በበሩ ይወጣል። የሌሊት ጠባቂውም ይከፍትለታል። ሌባ ግን አጥር ጥሶ ቅጥር አፍርሶ ይገባል እንጂ በበሩ አይገባም፤  እንደዚያውም ይወጣል።  በጨለማ ይገባል እንጂ በግልፅ (በብርሃን) አይገባም።  ምንደኛ መምህርም እንደዚሁ እምነትን አጉድሎ ሥርዓትን አፍርሶ ወደ ቤተክርስቲያን በተንኮል ይገባል።

የበጎች በር የተባለውም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በእርሱ ያላመነ (በበሩ ያልገባ) እውነተኛ ጠባቂ ሊሆን አይችልምና። እምነትን ሥርዓትን ያልጠበቀ እውነተኛ ጠባቂ ሊሆን አይችልም። በበሩ የገባ (ተመስክሮለት የመጣ) በበሩም መግባትን ያስተማረን ጠባቂ እርሱ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የክርስቶስን አርዓያ የተከተሉ ደገኛ መምህራንም በበሩ ይገባሉ፤ በበሩ ይወጣሉ።

ቸር ጠባቂ በጎቹን ያውቃቸዋል፤ እነርሱም ያውቁታል።

ቸር ጠባቂ በጎቹን በየስማቸው ይጠራቸዋል። እነርሱም ድምፁን ይሰሙታል፤ ያውቁታልም። በትክክለኛው ስማቸው (ግብራቸውን በሚገልፅ) ይጠራቸዋል። እነርሱም ድምፁን ስለሚያውቁ ይሰሙታል። ቃሉን (አስተምህሮውን) ያዉቁታል። ወንበዴ ግን የበጎቹን ስም ከቶ አያውቅም፤። በጎቹም ድምፁን አያውቁትም።  እንደ ይሁዳ ዘገሊላ እንደ ቴዎዳስ ዘግብፅ ያሉት እንደዚህ ሐሰተኛ ጠባቂዎች ነበሩ (ሐዋ 5፡33-39)። አስተምህሮአቸው ከእግዚአብሔር ስላልሆነ ለጊዜው ተከታይ ቢያገኙም ምዕመናን አልሰሟቸውም። እነርሱም ጊዜአቸው ሲደርስ ጠፍተዋል። በጎቹን የሚያውቅ እነርሱም ድምፁን የሚያውቁት እውነተኛ እረኛችን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ‹‹ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ፥ የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድምጥ፤ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ፥ ተገለጥ (መዝ 79፡1)።›› እንደተባለ የቤተክርስቲያን ጠባቂዋ እርሱ ነው። የክርስቶስን አርዓያ የተከተሉ ደገኛ መምህራንም በጎች የተባሉ ምዕመናንን ሐዋርያዊ ትምህርትን እያስተማሩ በምግባር በሃይማኖት ያጸኗቸዋል።

ቸር ጠባቂ በጎቹን ይመራቸዋል፤ እነርሱም ይከተሉታል።

ቸር ጠባቂ በበጎቹ ፊት ፊት ይሄዳል። እነርሱም እርሱን እየተከተሉት ይሄዳሉ። እርሱ ቀድሞ በጎቹ ይከተሉታል። ወደ መሰማርያችውም ይመራቸዋል። አንድ በግ ቢቀርበት ወይም ቢጠፋበት እንኳን ሌሎቹን ትቶ የጠፋውን ይፈልጋል (ሉቃ 15፡2ሌባ ግን ከበጎቹ ኋላ ኋላ ይሄዳል፤ በጎቹንም ሊሠርቅ ከኋላ ሆኖ በጎቹን በአይነ ቁራኛ እየተመለከተ ይከተላል። በጎቹ ቢጠፉም አይገደውም፤ ሊሠርቅ እንጂ ሊመራቸው አልመጣምና። እኛን ወደ ለመለመ መስክ የሚመራን እኛም ድምፁን ሰምተን የምንከተለው እውነተኛ ጠባቂያችን እርሱ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

የሰቡትና የወፈሩት አንዳንድ በጎች፣ ምስኪኖችንና የከሱትን በጎች እየገፉ ከበረት ሲያስወጡአቸው፣ በቀንዳቸው ሲወጉአቸው፣ ሲያቆስሉአቸው፣ ሲያደሙአቸው፣ የሚጠጡትን ውኃ ሲያደፈርሱባቸው፣ ምግባቸውን ሲረግጡባቸው እያዩ ከመቀመጫቸው ላለመነሳት ዝም ብለው እንደሚያዩ ምንደኞች ያይደለ እውነተኛ እረኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የክርስቶስን አርዓያ የተከተሉ ደገኛ መምህራንም በጎች የተባሉ ምዕመናንን በእውነተኛ ትምህርት ይጠብቋቸዋል። ምንደኛ የሆኑ ክፉ መምህራን ግን በጎች የተባሉ ምዕመናንን አቁስለውና አድምተው ከበረት ያወጧቸዋል፤ በሌሎች ፈተናዎች ምዕመናንን ከመጠበቅ ቸል ይላሉ።

ቸር ጠባቂ በጎቹን ይጠብቃል፤ ይንከባከባቸዋልም።

ቸር ጠባቂ በጎቹን ከክፉ ሁሉ ይጠብቃል፤ የሚያስፈልጋቸውንም ነገር ሁሉ ያውቃል። ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማቸዋል። የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል (ኢሳ 40፡11)። ጭቃውን ሳይጠየፍ ይሸከማቸዋል፤ ይንከባከባቸዋል (ሉቃ 15፡6)። ምንደኛ የሆነ እረኛ ግን የራሱን ፍላጎት እንጂ የበጎቹን ፍላጎት አያውቅም፤ እነርሱም አያውቁትም። በጎቹን ይበትናቸዋል፤ በጎቹን ይጠቀምባቸዋል እንጂ አይጠብቃቸውም፤ አይጠቅማቸውምም። ጠፍተን ሳለ የፈለገን የሚንከባከበንና የሚመግበን ቸር ጠባቂያችን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

እንደ ምንደኛ (ቅጥረኛ) በጎቹን በማሰማራት ፈንታ ወደ እረፍት መስክ ራሱን ያላሰማራ፤ በአደራና በጠባቂነት የተሰጣቸውን በጎች እያረዱ እየበሉ አውሬ በላቸው እንደሚሉ ቅጥረኞች ያይደለ፤  በጎች እሰከሚበርዳቸው ድረስ ያለ አግባብ ፀጉራቸውን እንደሚሸልቱ ቅጥረኛ ያልሆነ፤ ታማሚ በጎችን እንዳላከሙ፤ ደካሞችን እንዳላዳኑ፤ ሰባራዎችን እንዳልጠገኑ፤ የጠፉትን በጎች ወደ መንጋው በመመለስ ፈንታ ወሬያቸውን በመሰለቅ በወንበራቸው ተቀምጠው እንዳልሰበሰቡ እረኞች ያይደለ የጠፉትን የሚሰበስብ  የቤተክርስቲያን ጠባቂዋ እርሱ ነው።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"የራማው ልዑል ገብርኤል"
የራማው ልዑል ገብርኤል (፪)
ተመላለስ መሐላችን ስምህን ጠርተን ና ስንልህ(፪)
      ብርሃን ልብሱ እሳታዊ መልአክ
      አንተ አማልደን ከመሐሪው አምላክ (፪)
              አዝ….
የምስራች ነጋሪ ድንቅ ልደት አብሳሪ
የጽድቅ ፋና የምሕረት ጎዳና (፪)
              አዝ….
      ላመኑብህ ለተማጸኑብህ
      ፈጥኖ ደራሽ አለኝታቸው ነህ (፪)
             አዝ….
የአናንያ የአዛርያ የሚሳኤል ከለላቸው
ከእሳት ነበልባል ያዳንካቸው (፪)
            አዝ….
     ምሰሶ አምዳችን መጠጊያችን
     ቅዱስ ገብርኤል ጠባቂያችን (፪)
            አዝ….
ዕለት ዕለት የምንማልድህ
ልጀችህን ይምራን መንፈስህ(፪)
አዝ....

©ዓምደ ሐይማኖት ሰንበት ት/ቤት
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ታኅሣሥ ፲፱

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል


ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ያዳነበት ነው፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር ከአባታቸው ከይሁዳው ንጉሥ ከኢዮአቄም ጋር የማረካቸው አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ እግዚአብሔር በዚህች ዕለት መልአኩን ልኮ ታላቅ ተአምር አድርጎላቸዋል፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር እነዚህን ወጣቶች በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ጥበብን እያስተማረ ካሳደጋቸው በኋላ በባቢሎን ሀገሮች ሁሉ ውስጥ ሾማቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ የወርቅ ምስል በሠራ ጊዜ መኳንንቱንና በግዛቱ ውስጥ ያሉ ሁሉ ለዚያ ምስል እንዲሰግዱ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ለጣዖቱ ባለመስገድ እግዚአብሔርን ብቻ በማምለክ የጸኑት እነዚህ ሦስት ወጣቶች ብቻ ነበሩ፡፡ ስለ እነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡-
‹‹ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው፡፡ ንጉሡም ናቡከደነፆር መኳንንትንና ሹማምቶችን፥ አዛዦችንና አዛውንቶችን፥ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፣ መጋቢዎችንም፣ አውራጃ ገዦችንም ሁሉ ይሰበስቡ ዘንድ፣ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ፡፡ በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምቶቹ፣ አዛዦቹና አዛውንቶቹ፣ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ፣ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዦቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰበሰቡ፤ ናቡከደነፆርም ባቆመው ምስል ፊት ቆሙ፡፡ አዋጅ ነጋሪውም እየጮኸ እንዲህ አለ፡- ‹ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የምትናገሩ ሆይ! የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፣ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል፡፡ ተደፍቶም የማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል፡፡› ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፣ የመሰንቆውንና የክራሩን፣ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፣ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፤ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ፡፡

በዚያን ጊዜም ከለዳውያን ቀርበው አይሁድን ከሰሱ፡፡ ለንጉሡም ለናቡከደነፆር ተናገሩ እንዲህም አሉ ‹ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ፡፡ አንተ ንጉሥ ሆይ የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ፤ ተደፍቶም የማይሰግድ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል ብለህ አዘዝህ፡፡ በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፤ አማልክትህን አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም፡፡› ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ፤ እነዚህንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው፡፡ ናቡከደነፆርም ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ! አምላኬን አለማምለካችሁ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን? አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው?›› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡን ‹ናቡከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም፡፡ የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! እርሱ ባያድነን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ› አሉት፡፡

የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፡፡ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፡፡ እርሱም ተናገረ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ፡፡ ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ፡፡ የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ፡፡ የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም ‹ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?› ብሎ ተናገራቸው፡፡ እነርሱም ‹ንጉሥ ሆይ! እውነት ነው› ብለው ለንጉሡ መለሱለት፡፡ እርሱም ‹እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል› ብሎ መለሰ፡፡ የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ ‹እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም! ኑ ውጡ› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ፡፡

መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፣ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡ ናቡከደነፆርም መልሶ ‹መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፣ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ፡፡ እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ፣ ቤቶቻቸውም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ› አለ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም በባቢሎን አውራጃ ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፡፡›› ትንቢተ ዳንኤል 3፡1-30፡፡

አምላካችን ከቅዱስ ገብርኤል ረድኤት በረከት ያካፍለን ፤ የመልአኩ ፈጣን ምልጃ አይለየን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ተግባራዊ ክርስትና"
ምዕራፍ ፩ ክፍል ፪
..............................
..................................
መንፈሳዊ እውቀት
  ሁላችንም መጽሐፍ ቅዱስን አንብበናል ጥቅሶችንም እናስታውሳለን ፤ ይህ ሆኖ ሳለ ግን በእርግጥ ጥቅሶቹ የያዟቸውን መንፈሳዊ ጽንሰ ሃሳቦች በአእምሮአችን ውስጥ ተክለናቸዋል? 
  በዘዳ. ፮÷፮—፱ ላይ ተነግሮናል ፡- ‹‹እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ።ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው።››
  ይህም ማለት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያነበብነው ነገር በሚገባ ቀስመን የአስተሳሰባችን ሒደት አካል እስከሚሆኑ ድረስ በልባችንና በአእምሮአችን ላይ ማተም አለብን ማለት ነው፡፡ እነዚህን ምሳሌዎች  እዩ፡-
   መጽሐፍ ቅዱስ በሉቃስ ፮÷፳፮ ላይ እንዲህ ሲል ነግሮናል  ‹‹ሰዎች ሁሉ መልካም ሲናገሩላችሁ፥ ወዮላችሁ፤ አባቶቻቸው ለሐሰተኞች ነቢያት እንዲሁ ያደርጉላቸው ነበርና።›› እንዲሁም በድጋሚ በሉቃስ ፮÷፳፪—፳፫ ላይ ‹‹ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ።እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና።›› ይላል፡፡
  በዚህም መሠረት ከመመስገን ይልቅ መነቀፍ የበለጠ ብፅእና ነው፡፡ ሰዎች ሲያመሰግኑኝ ለእኔ መንፈሳዊነት አደገኛ እንደሆነና ሰዎች ሲነቅፉኝና በሐሰት ክፉ ሲናገሩብኝ

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ለጥቅም አልባ እውቀት የመጀመሪያው ምሳሌ ዜናን ከመጠን በላይ መመልከት ነው፡፡ በዙሪያችን ባለው ዓለም ላይ ምን እየሆነ እንዳለ ማወቅ መልካም ነው ፤ ይሁንና ክርስቲያናዊውን ፍጹምነት የምትፈልጉ ከሆነ በየቦታው በእያንዳንዱ ደቂቃ የሚሆነውን እያንዳንዱን ነገር ስለማወቅ መጨነቅ ትርፍ ያለው ነገር አይደለም፡፡ ሰዎች ዜናን ለመስማት ካላቸው የማይረካ ጉጉትና ጥማት የተነሣ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሃያ አራት ሰዓት ዜና ሥርጭትን ሊጀምሩ ችለዋል ፣ የሬድዮ ጣቢያዎችም ቀጥለውበታል፡፡ ይህን ምሳሌ ውሰዱ የኦ ጄ ሲምትሰን ተከታታይ የፍርድ ሒደት በዓለም ዙሪያ የነበሩ እጅግ ብዙ ሰዎች ከማንኛውም ክስተት በላይ ተመልክተውታል፡፡ የገና ጨዋታንስ ይሁን እረዳለሁ ረዥም የፍርድ ሒደትን መከታተል ግን ምን ሊባል ይችላል? ከዚህ ምን ላገኝ እችላለሁ? ለነፍሴም ለሥጋዬም ለሕሊናዬም ምንም አላገኝም!  በአቢይ ጾም ወቅት የማደርገውን ልንገራችሁ ፤ በሬድዮ ዜናን ከመስማት ፣ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ከማንበብ እከለከላለሁ፡፡ (እንደምታውቁት ቲቪ በአቢይ ጾም ወቅት  እንዳንጠቀም ተስማምተናል፡፡) እመኑኝ! ምንም ነገር አያመልጠኝም ፤ አይጎድልብኝም ፤ ይልቁንስ ሕሊናዬ ከመረጃ ብክለት ነፃ ይሆናል ፤ ስለዚህ በትክክል እንደሚሠራ አምናለሁ፡፡
  የአንድ መነኩሴ ታሪክ ሰምተን ነበር ፤ ይህ መነኩሴ ከሌሎች መነኮሳት ጋር ሲነጋገር ቆይቶ ወደ በዓቱ ከሔደ በኋላ እጅግ በተደጋጋሚ በአቱን ሲዞር አንድ መነኩሴ ተመለከተውና ምን እያደረገ እንደሆነ ጠየቀው ፤ እርሱም መለሰ ‹‹ስናወራቸው የነበርናቸውን ዓለማዊ ወሬዎች እያስወገድኩ ነው ፤ ወደ በአቴ ይዤ መግባት አልፈልግም››  ሁለተኛው የማይጠቅም እውቀት ምሳሌ ደግሞ ከንቱ የማወቅ ፍላጎት ነው፡፡ አዋቂ ለመሆን ብቻ ሲባል ስለ ብዙ ነገሮች የማወቅ ጥማት፡፡ ይህ እንዴት ሊጎዳኝ ይችላል? መልካም አበው እንዳሉት ይህ በጠቅላላ እውቀት መሞላት (መጠቅጠቅ) ከሌሎች የተሻለ አዋቂ እንደሆንኩ ወደማሰብና ወደ ኩራትና ትእቢት ይመራኛል፡፡ እውቀቴንም በሌሎች ፊት ማሳየት ስለምፈልግ ወሬኛ እሆናለሁ፡ ፡ ባሕታዊው ቴዎፋን እንዳለው ከሆነ በመጨረሻ አእምሮአችን ራሱ የምናመልከው ጣኦት ይሆንብናል፡፡ ሃሳበ ግትር  እንሆናለን ፤ ሁሉን እስካወቅን ድረስም ሌሎችን ለማማከርም ሆነ ምክርን ለመቀበል ፈቃደኞች አንሆንም፡፡ ይህም በመንፈሳዊ ጉዳዮችም ጭምር በራስ ወደ መደገፍ የሚመራን የሕሊና ትእቢት ሲሆን እጅግ አደገኛ ነው፡፡  ክርስቲያናዊውን ፍጹምነት መከተል ከፈለጋችሁ ሕሊናችሁን ከዚህ ዓይነቱ የእውቀት ሱስ ማላቀቅ አለባችሁ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በ፩ቆሮ.፫÷፲፰—፲፱ ላይ ፡- ‹‹ማንም በዚህች ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ይሁን፡፡ የዚህች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና፡፡›› መንፈሳዊ ጥበብና ዓለማዊ ጥበብ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሊሔዱ አይችሉም፡፡ የዚህን ዓለም ጥበብ እጅግ የሚሹ ሰዎች ብዙ ጊዜ በእግዚአብሔር የማያምኑ ይሆናሉ፡፡ በትእቢተኛ አእምሮአቸው ተወጥረው አእምሮአቸውን የፈጠረውን እግዚአብሔርን ይክዳሉ፡፡ በዚህ የተነሣም ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጢሞቴዎስ ሆይ በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ ፤ ይህ እውቀት አለን ብለው አንዳንዶች ከእምነት ስተዋልና ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን አሜን!›› ፩ጢሞ. ፮÷፳— ፳፩  በመዝ. ፸፪÷፳፪—፳፬ ላይ ነቢዩ ዳዊት እንዲህ አለ ፡- ‹‹እኔ የተናቅሁ ነኝ አላወቅሁምም ፤ በአንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ሆንሁ፡፡ እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ፡፡ በአንተ ምክር መራኸኝ ፤ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ፡፡›› ጠቢብ ለመሆን ሲባል ሞኝ የመሆን ትርጉም ይህ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነትህን ከገለጥህ ቀኝ እጅህን ይይዝሃል ፣ በእርሱም ምክር ይመራሃል ፤ ከክብርም ጋር ይቀበልሃል፡፡  የማወቅ ፍላጎት የሎጥን ሚስት ለጥፋት ዳርጎአታል፡፡ እንዲሁም ጌታችን በሐሳዊው መሲሕ ጊዜ ስለማወቅ ጉጉት በተመሳሳይ ምሳሌ አስጠንቅቆናል፡፡ ‹‹እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፥በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።››  
ይህም ማለት ሐሳዊውን መሲህ ከማግኘት ወይም ከማየት ወይም ከመስማት አሻፈረኝ ማለትና መሸሽ ማለት ነው፡፡ በጠንካራ የማወቅ ፍላጎት ለማየት የሚሞክሩ ሰዎች ግን እንደ ሎጥ ሚስት ይጠፋሉ፡፡ ሉቃ. ፲፯÷፴፩ ተመሳሳይ አሳብ የሚነግረን ሲሆን በሎጥ ሚስት ስኅተት ዳግም እንዳንወድቅ ያሳስበናል፡፡ በዚያን እለት ‹‹በዚያም ቀን በሰገነት ያለ በቤቱ ያለውን እቃ ሊወስድ አይውረድ፥ እንዲሁም በእርሻ ያለ ወደ ኋላው አይመለስ።የሎጥን ሚስት  አስቡአት።››   በእነዚያ እለታት ሰው ቲቪ ለማየት ወይም ሬድዮ ለመስማት ወይም የቅስቀሳ ስብሰባዎቹን ወይም ስለእርሱ ማንኛውንም ነገር ከማወቅ ራስን መግታት አለበት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ያስጠነቅቀናል፡፡ ‹ሂዱ ግን አትመኑበት› አላለንም ፡፡ ነገር ግን አትሒዱ ከእርሱም ተለዩ አለን እንጂ ፤ ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ድንቅ ነገሮች እና ታላላቅ ተአምራት ይደረጋሉና ነው፡፡›› ይህንን ማስጠንቀቂያ ወደ ጎን ትተህ የራስህን የማወቅ ፍላጎት ከተከተልህ ትጠፋለህ፡፡ በአቢይ ጾም ወቅት ቴሌቪዥን ከመመልከት መከልከል መልካም የሆነው ለዚህ ነው፡፡ ራሳችንን መግታት ከለመድን ደግሞ ሐሳዊው መሲህ ቢመጣም ከማየት መከልከልና ወደ እርሱ ይሰበስበን ዘንድ በደመና የሚመጣውን ጌታ በመጠባበቅ ዓይናችንን ወደ ሰማይ ማቅናት ይቻለናል፡፡ 
  ሌላው የከፋ የማወቅ ፍላጎት ደግሞ ስለ አስማት ፣ ጥንቆላና ስለመሳሰሉት የማወቅ ፍላጎት ነው፡፡ ይህም በአጋንንት ወደ መያዝ ራስን ወደ ማጥፋትና ሰዎችን ወደ መግደል የሚያደርስ ነው፡፡ 
  እስከ አሁን ጥቅም ስለሌለው እውቀት ተነጋገርን ፤ አሁን ደግሞ እስቲ ስለ ጎጂ እውቀት እናውራ፡፡ ይህም ስለሌሎች ሰዎች የማወቅ ፍላጎት ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ‹በነገር የሚገባ› የሚለው ነው፡ ፡ ፩ጴጥ.፬÷፲፭ እንዲህ ይላል ፡- ‹‹ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጒዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል››  ስለሌሎች ሰዎች ጉዳይ የማወቅ ሱስ የአሉባልታና የሐሜት ሥር ነው፡፡ ዲያቢሎስ የሰውን ጉዳይ ለማወቅ የምትፈልጉት ልትረዷቸው ስለምትችሉ ነው ብሎ ሊያሳምናችሁ ይችላል፡፡ ነገር ግን በምን ዓይነት በሽታ እንደታመመ ሳላውቅ ለታመመ ሰው ልጸልይ እችላለሁ፡፡ አንድን ሰው ቤቱን በስንት እንደገዛው ሳላውቅ ወደ አዲስ ቤቱ ሲዘዋወር ላግዘው እችላለሁ፡፡ አንድን ሰው ምን ያህል ደመወዝ እንደሚከፈለው ሳላውቅ ስላገኘው አዲስ ሥራ እንኳን ደስ ያለህ ልለው እችላለሁ፡፡   ከሌሎች በተለየ ወጣቶች የጓደኞቻቸውን ምሥጢሮች የማወቅ ሱስ አለባቸው፡፡ ‹ምሥጢርህን ካልነገርከኝ ጓደኛዬ አይደለህም› ‹ምሥጢሬን ልነግርህ የምችለው የአንተን ከነገርከኝ ብቻ ነው› ይባባላሉ፡፡ ይህ ግን ጎጂ እውቀት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹በነገር መግባትን› ነፍሰ ገዳይ የመሆንና የመስረቅ ያህል ክፉ መሆኑን ይገልጻል፡፡   ብዙ ሰዎች ስለእነርሱ ማወቅ ስለሚፈልጉ ወዳጆቻቸው ተማርረው ይነግሩኛል፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንደውም ‹‹ሰዎች የግል ጉዳዮቼን እንዲያውቁብኝ ስለማልፈልግ ለመዋሸት እገደዳለሁ›› ብለውኛል፡፡ ለዚህ የምሰጠው

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚
ሠላም ውድ የቻናላችን ተከታታዮች በኃያሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንደምን ሰነበታችሁ? እነሆ በዚህ አምዳችን ከዛሬ ጀምሮ ዘወትር ሰኞ እና ሐሙስ ለክርስቲያናዊ ህይወታችን እጅጉን ጠቃሚ ከሆኑ መጻሕፍት መካከል መርጠን፤ በመጻሕፍቱ ምዕራፍ መሠረት በክፍል ከፋፍለን ለእናንተ ለማድረስ አስበናል። ስለሆነም መጻሕፍቱን አንብባችሁ ትጠቀሙባቸው ዘንድ እንዲሁም ለሌሎችም ያነበባችሁትን ታጋሩ ዘንድ እናሳስባለን።  ይልቁንም ደግሞ ያነበብነውን ወደ ተግባራዊ ህይወት ቀይረን እንኖረው ዘንድ መልዕክታችን ነው።

ከዛሬ ጀምሮ ለተወሰኑ ተከታታይ ሳምንታት ይዘንላችሁ የምንቀርበው አቡነ አትናስዮስ እስክንድር "Practical Spirituality" በሚል ጽፈውት ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የተረጎመውን "ተግባራዊ ክርስትና" የተሰኘ ድንቅ መጽሐፍ ይሆናል።

".......ሌላው ታሪክ ደግሞ መነኩሴ ይሆን ዘንድ ወደ ገዳም ስለሔደ የሀብታም ቤተሰብ ልጅ ስለሆነ ወጣት ነው፡፡ መምህሩ ‹‹ስድብን በደስታ ለመቀበል ራስህን አስለምድ›› ብለው ነገሩት፡፡ ዙሪያውን ቢፈልግ በገዳሙ ውስጥ እርሱን የሚሰድበው የለም፡፡ ስለዚህ ወደ መንደር ሔዶ ወደ ገዳም መጥቶ ስድብን በደስታ መቀበልን እስከሚለምድ ድረስ እንዲሰድበው አንድ ሰው ቀጠረ፡፡
    አንድ ቀን ከሌሎች መነኮሳት ጋር ወደ ከተማ ተልኮ ሳለ..............................."


መልካም ንባብ!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ሚካኤል እመላእክት"
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል
አስተምሕር ለነ ሰአልናከ
በአሠርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ{፪}
አዝ
ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ
ሐመልማለ ወርቅ{፪}
አዝ
ይሰግድ በብረኪሁ እስከ ይመጽእ ሥርየት
ለኃጥአን{፪}
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ክቡር
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል

መኑ ከማከ ክቡር መኑ ከማከ ልዑል{፪}

...........................................................................

ሚካኤል ከመላእክት እንዳንተ ያለ ማነው የአምላክ ባለሟል/2/
ለምንልን/2/ ለመንህ
በአሥራ አራቱ የጸሎት ሥርዓትህ /2/
አዝ
ዐይኑ የርግብ ነው የወርቅ ሐመልማል
ልብሱ የመብረቅ ነው/2/
አዝ
ይሰግዳል በጉልበቶቹ ለኃጥአን
እስኪሰጥ የአምላክ ሥርየቱ/2/
ሚካኤል ከመላእክት እንዳንተ ያለ ማነው የአምላክ ባለሟል/2/

እንዳንተ ያለ ማን አለ/2/

©ማኅበረ ቅዱሳን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ንጽህተ ንጹሀን ከዊና፣
ከመታቦት ዘዶር ዘሲና፣
ውስተ ቤተ መቅደስ፣
ነበረት(፪) በድንግልና፣
ሲሳይያ ሕብስተ መና፣
ወስቴሃኒ ስቴ ጽሞና።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ታኅሣሥ ፫

በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም

"ልጄ ሆይ፥ ስሚ፤ እዪ፤ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን፡ ያባትሽንም ቤት እርሺ፤ ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና።" መዝ ፵፭፥፲

ታኅሣሥ ሦስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው ። እርሷ ለእግዚአብሔር የስእለት ልጅ ነበረችና።

እናቷ ቅድስት ሐና ልጅ የሌላት ስለሆነች በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ከሴቶች ተለይታ ርቃ ትኖር ነበር ሽማግሌ ከሆነ ከኢያቄም ከባሏ ጋርም እጅግ የምታዝን ሆነች ። እግዚአብሔርም ኀዘናቸውን ሰማ ቅድስት ሐናም እንዲህ ብላ ለእግዚአብሔር ተሳለች የሰጠህኝን ፍሬ ለእግዚአብሔር አገልጋይ አደርገዋለሁ ።

ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምንም በወለደቻት ጊዜ ሦስት ዓመት በቤቷ ውስጥ አሳደገቻት ከዚህም በኋላ ከደናግል ጋር ትኖር ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደቻት በቤተ መቅደስም ምግቧን ከመላእክት እጅ እየተቀበለች ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረች ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም መጥቶ ከእርሷ ሥጋን እስከ ነሣ ድረስ።

ከሴቶች ሁሉ የተመረጠች ይቺ ናት በቤተ መቅደስም በመኖር ዐሥራ ሁለት ዓመት ሲፈጸምላት እርሷ ለእግዚአብሔር የተሰጠች የስዕለት ልጅ ናትና ለሚጠብቃት ይሰጧት ዘንድ ካህናት እርስበርሳቸው ተማከሩ በሴቶች ላይ የሚደርስ በርሷ ላይም ይደርስባታል ብለው ስለፈሩ በቤተ መቅደስ ውስጥ ይተዋት ዘንድ ለእርሱ ትክክል መስሎ አልታያቸውም ስለዚህም ሊጠብቃት ለሚገባው በእርሷ ላይ እጮኛ ሊአኖሩ ወደዱ።

ከዚህም አስቀድሞ ሊቀ ካህናት ዘካርያስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልጄ ማርያም ሆይ አንቺ እንዳደግሽና ለአካለ መጠን እንደደረስሽ ዕወቂ ልትታጪ ትወጃለሽን እግዚአብሔርን የሚፈራ መልካም የሆነ የተባረከ ጐልማሳ እንፈልግልሽን ወይም በሕይወትሽ ዘመን ሁሉ በቤተ መቅደስ ተቀምጠሽ እግዚአብሔርን ልታገለግዪው የምትሺ ከሆነ በሴቶች ላይ የሚደርሰው በሚደርስብሽ ወራት ወደ ቤተ መቅደስ ደጅ ከመግባት ትጠበቂ ዘንድ በኦሪቱ የተጸፈውን የርግማን ሥርዓት በአንቺ ላይ እንሠራለን አላት ።

ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምም እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋዩ በፊታችሁ ነኝ አባትና እናት የሉኝም ስሙ ቡሩክ ምስጉን ከሆነ ከእግዚአብሔር በታች በእናትና አባት ፈንታ እናንት ናችሁና የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንደምታውቁ አድርጉ ብላ መለሰች።

ካህናቱና ማኅበሩም ሁሉ ዘካርያስን ወደ ቤተ መቅደስ ገብተህ ስለዚች ብላቴና ማርያም ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት ዘካርያስም ገብቶ ሲጸልይ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው። ዘካርያስ ሆይ ወጥተህ ከዳዊት ወገን ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን ሁሉ ወንዶች ሰብስብ የየአንዳንዱንም በትር ከስሙ ጋር ውሰድ ወደ ቤተ መቅደስም በምሽት አግብተህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይበት በነጋ ጊዜም በትሮቻቸውን አውጣ እግዚአብሔርም በበትሩ ላይ ምልክት ለገለጠልህ ለዚያ ሰው ማርያምን ተቀብሎ ሊጠብቃት ይገባዋል።

ካህኑ ዘካርያስም ወጥቶ አንድነት ለተሰበሰቡት ሕዝብ የእግዚአብሔር መልአክ የነገረውን ነገራቸው በዚያንም ጊዜ ከዳዊት ወገን ጐልማሳም ቢሆን ሽማግሌም ቢሆን ሚስቱ የሞተችበት ሁሉ በኢየሩሳሌም ወደአለ ቤተ መቅደስ ይሒድ እያሉ ዓዋጅን ዙረው የሚናገሩ በእስራኤል አገር ሁሉ ላከ ።

ከዳዊት ወገን የሆነ ጠራቢው ዮሴፍም በሰማ ጊዜ በትሩን ይዞ ከናዝሬት ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ካህኑ ዘካርያስም የሁሉንም በትሮች ተቀብሎ ስማቸውን በላያቸው ጻፈ ቁጥራቸውም አንድ ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት ሆነ ዘካርያስም በትሮችን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እንዲሁም ሰዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ውጭ ቁመው ይጸልዩ ነበር ዘካርያስም ጸሎቱን በፈፀመ ጊዜ ለየአንዳንዱ በትራቸውን አውጥቶ ሰጠ ጠራቢው ዮሴፍም በትሩን ሊቀበል በቀረበ ጊዜ ከእርሷ ነጭ ርግብ የመሰለች ተገለጠች እየበረረችም ሒዳ በጠራቢው ዮሴፍ ራስ ላይ ተቀመጠች ካህናቱና ሕዝቡ ሁሉ አይተው እጅግ አደነቁ ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ።

ዘካርያስም ዮሴፍን ዮሴፍ ሆይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ እንደ ተናገረ ድንግል ማርያምን ወደ ቤትህ ወስደህ ጠብቃት አለው ዮሴፍም ቅድስት ድንግል ማርያምን ከካህናት እጅ ተቀበላት በእርሱም ዘንድ ኖረች ። ከዚህም በኋላ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ስለ እግዚአብሔር ልጅ ከእርሷ ሰው ሁኖ ስለመወለዱ በዮሴፍ ቤት አበሠራት።

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል
በዚችም ቀን የሊቀ መላእክት ፋኑኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።

ይህም ታላቅ መልአክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናት እና አባት ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም እግዚአብሔር አምላክ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ዘወትር ይማፀኑት ነበር፡፡ለእግዚአብሔር “ወንድ ልጅ ብንወልድ እርሱ ወጥቶ ወርዶ ያበላናል አንልም ያንተን ቤት ያገለግላል፤ ሴትም ብትሆን ጋግራ ታብላን ፈትላ ታልብሰን አንልም ሀርና ወርቅ እየፈተለች መሶበ ወርቅ እየሰፋች ቤተ መቅደስን ታገለግላለች እንጂ” ብለው ስዕለትንም ተስለው ነበር፡፡

ለአብርሀም እና ለሳራ ይስሐቅን (ዘፍ. 21፥1-8)፣ ለሕልቃና እና ለሐና ነብዩ ሳሙኤልን (1ኛ ሳሙ. 1፥1-21) የሰጠ አምላክ ዛሬም የእነዚህን ቅዱሳን እንባቸውንና ልመናቸውን ሰምቶ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሰጣቸው፡፡ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በእናት እና አባቷ ቤት እስከ 3 ዓመት ድረስ ከቆየች በኋላ በስእለታቸው መሰረት ለቤተ መቅደስ ሰጡ፡፡ ቤተ መቅደስ ከደረሱ በኋላ ስእለታቸውን ለሊቀ ካህኑ ለዘካርያስ በሰጡት ወቅት ሊቀ ካህኑ እና ሌሎች የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች (ካህናት) የምግቧ ነገር እንዴት ሊሆን ነው ብለው እጅግ ተጨነቁ፡፡ በዚህ ወቅት ከሰባቱ ሊቃነ መላዕክት አንዱ የሆነው መልዐኩ ቅዱስ ፋኑኤል ሰማያዊ ጽዋ አና ሰማያዊ ሕብስት ይዞ ረብቦ ታየ፡፡ ሊቀ ካህኑ ዘካርያስ ለኔ የመጣ ነው ብሎ ወደ መልአኩ ጠጋ ሲል፡፡ ያኔ ቅዱስ ፋኑኤል ወደ ላይ ከፍ አለ፡፡ የሊቀ ካህኑ ምክትል የነበረው ስምኦንም ሲቀርብ መልአኩ አሁንም ከፍ አለ፡፡ ከዛም ህፃኒቱን እስቲ ተጠጊ ብለዋት ስትጠጋው መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክፉን ጋርዶ በሰው ቁመት ከመሬት ከፍ አድርጎ መግቧት አረገ፡፡ ይህም የሆነው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደቤተ መቅደስ በገባችበት ዕለት ነው፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ት።

በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ስለ ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳይነሡበት ፈርቶ የቀጰዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ሆነች ወደ ቂሣርያ በብረት ማሠሪያ አሥሮ ላከው። በዚያም እንዲአሠቃዩት አዘዘ ከአሠቃዩትም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና ተጋድሎውን ፈጽሞ በመንግሥተ ሰማያት የሕይወት አክሊልን ተቀበለ።

የማይጠፋ ሰማያዊ አክሊልንም ተቀዳጅቶ ወደ ዘላለም ሕይወት ከገባ በኋላ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስተያናት ታነፁለት። እግዚአብሔርም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራትን በውስጣቸው ገለጠ።

#ተአምር_ዘቅዱስ_መርቆሬዎስ - ፩

ከተአምራቱም አንዲቱ ዑልያኖስ በነገሠ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ካደ። በዚያንም ወራት ቅዱስ ባስልዮስ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ነበረ ተአምራቱ በተጻፉበት መጽሐፍ እንደተጻፈ ምእመናን በጽኑዕ ሥቃይ ዑልያኖስ ባሠቃየ ጊዜ መክሮ አስተምሮ ከስሕተቱ ይመልሰው ዘንድ ቅዱስ ባስልዮስ ወደርሱ መጣ።

ዑልያኖስም ቅዱስ ባስልዮስን በአየው ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን ሰደበ። ቅዱስ ባስልዮስንም አሠረው። በዚያ በእሥር ቤትም የቅዱስ መርቆሬዎስን ሥዕል አይቶ በፊቱ ቅዱስ ባስልዮስ ጸለየ ሥዕሉም ከቦታው ታጣ። ያን ጊዜ ወደ ዑልያኖስ ሒዷልና በጦርም ወግቶ ገደለውና ወዲያውኑ ወደቦታው ተመለሰ ከጦሩም አንደበት ደም ይንጠፈጠፍ ነበር። ቅዱስ ባስልዮስም ከሀዲ ዑልያኖስን እንደገደለው አውቆ እንዲህ ብሎ ተናገረ የክርስቶስ ምስክር ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ሥዕሉ ራሱን ዘንበል አደረገ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ።

#ተአምር_ዘቅዱስ_መርቆሬዎስ - ፪

የዚህም የቅዱስ መርቆሬዎስ ሌላው ተአምር ከምስር አገር ከመሳፍንት ወገን የሆነ አንድ የእስላም ወጣት ነበረ የእስላሞችንም ሕጋቸውንና መጻሕፍቶቻቸውን ተምሮአል። በአንዲትም ዕለት ወደ ባሕር ዳርቻ በመንገድ አልፎ ሲሔድ አንድ የተፈረደበትን ሰው አገኘ። አስቀድሞ እስላም የነበረ አሁን የክርስትና ጥምቀትን የተጠመቀ የንጉሥ ጭፍሮችም ይዘውታል። ሊአቃጥሉትም ጉድጓድን ምሰው በውስጡ ታላቅ እሳት አንድደው አዘጋጅተውለታል። ብዙዎች ሰዎችም ሲቃጠል ለማየት ተሰብስበው ነበር።

ያም የመስፍን ልጅ ወጣት እስላም ወደ ተፈረደበት ሰው ቀረብ ብሎ "አንተ ከሀዲ ሰው ወደ ሲኦል ለመግባት ለምን ትሮጣለህ በኋላም በገሀነም እሳት ውስጥ ለመኖር አንተ እግዚአብሔርን ባለ ልጅ ታደርገዋለህና ሦስት አማልክትንም የምታምን ነህና ክፉ ነገር ነውና ይህን ስድብ ትተህ እኔን ስማኝ" አለው ።

ያ የተፈረደበትም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኛ የክርስቲያን ወገኖች ሦስት አማልክትን የምናመልክ ከሀድያን አይደለንም። አንድ አምላክን እናመልካለን እንጂ ይኸውም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነው። ወልድ ከአባቱ ከእግዚአብሔር ልዩ አይደለም። የራሱ ቃሉ ነው እንጂ። መንፈስ ቅዱስም ሕይወቱ ነው። የሃይማኖታችን ምሥጢር ከአናንተ የተሠወረ ድንቅ ነው። ዛሬ ለአንተ ልብህ ጨለማ ነው በውስጡ የሃይማኖት ብርሃን አልበራም በኋላ ግን ልብህ በርቶልህ እንደ እኔ ስለ ክርስቶስ ስም በመጋደል መከራውን ትቀበላለህ።"

ያም ወጣት እስላም በሰማው ጊዜ እጅግ ተቆጣ ጫማውንም ከእግሮቹ አውልቆ አፉን ፊቱንና ራሱን ጸፋው። ይህ የምትለው ከእኔ ዘንድ አይደረግም እያለ አብዝቶ አሠቃየ። የተከበረው ሰማዕትም ይህን ያልኩህን አስበህ የምትጸጸትበት ጊዜ አለህ አለው።

በዚያንም ጊዜ ራሱን በሰይፍ ቆርጠው ሥጋውን ከእሳት ማንደጃ ውስጥ ጨመሩ ከዚህም በኋላ እሳቱ ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ታላቅ አጥር ሆነ። የንጉሥም ወታደሮች እየጠበቁት ሦስት ቀን ኖረ። ከዚህም በኋላ ከቶ እሳት ምንም ሳይነካው እንደ ተፈተነ ወርቅ ሆኖ ሥጋውን አገኙት። ይህንንም ለንጉሥ ነገሩት። እርሱም እንዲቀብሩት አዘዘ።

ያ ወጣት እስላም ግን እያዘነ ወደ ቤቱ ገባ እርሱ ክርስቲያን እንደሚሆን ስለተናገረው ከኀዘኑ ብዛት የተነሣ የማይበላና የማይጠጣ ሆነ። እናቱና ወንድሞቹም ወደርሱ ተሰብስበው የማትበላ የማትጠጣ በአንተ ላይ የደረሰ ምንድን ነው አሉት። ክብር ይግባውና ለጌታችን ኢየሱስ ምስክር የሆነው የተናገረውን ነገራቸው። እነርሱም ይህ አሳች የተናገረውን ተወው በልብህ አታስበው እያሉ አጽናኑት። እርሱ ግን ከቶ ምንም አልተጽናናም።

በዚያም ወራት ወደሐሰተኛ ነቢያቸው መቃብር ለመሔድ የሚሹ ሰዎችን አይቶ ከእሳቸው ጋር መሔድ እፈልጋለሁ ብሎ ለአባቱ ነገረው። አባቱም እጅግ ደስ ብሎት የሚበቃውን ያህል የወርቅ ዲናር ሰጠው ለወዳጁም አደራ ብሎ ሰጠውና አብሮት ሔደ።

በሌሊትም ሲጓዙ እነሆ ብርሃን የለበሰ አረጋዊ መነኰስ ተገለጸለት በፊቱም ቁሞ ትድን ዘንድ ና ተከተለኝ አለው እንዲሁም ሁለተኛና ሦስተኛ ተገልጦ ተናገረው።

በደረሱም ጊዜ ሥራቸውን ፈጽመው ወደ አገራቸው ተመለሱ ሰባት ቀንም ያህል ተጓዙ። እነርሱም በሌሊት ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ ግዳጅ ያ ወጣት ከገመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ። ባልንጀሮቹም በበረሀ ውስጥ ትተውት ሔዱ ከእሳቸው ጋር የሚጓዝ መስሏቸዋልና በተነሣም ጊዜ ተቅበዘበዘ ወዴት እንደሚሔድ አላወቀምና አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ ደነገጠ።

በዘያንም ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕት የቅዱሰ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ እንዲህ አለ። ሰዎች ሁሉ በእርሷ ዘንድ እየተሳሉ ይፈጸምላቸዋል። በዚያንም ጊዜ የክርስቶስ ምስክር መርቆሬዎስ ሆይ በዚህ በረሀ ካሉ አራዊት አፍ በዛሬዋ ሌሊት ካዳንከኝና ያለ ጥፋት ካወጣኸኝ እኔ ክርስቲያን እሆናለሁ ብሎ ተሳለ።

ወዲያውኑ መልኩ የሚያምር ጎልማሳ የከበረ ልብስ የለበሰና የወርቅ መታጠቂያ በወገቡ የታጠቀ በፈረስ ተቀምጦ ወደርሱ መጣና አንተ ከወዴት ነህ እንዴት በዚህ በረሀ ውስጥ ጠፋህ አለው። ወጣቱም ስለ ሥጋ ግዳጅ ከገመል ላይ ወረድኩ ባልነጀሮቼ ትተውኝ ሔዱ አለው ባለ ፈረሱም ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ አለው በዚያንም ጊዜ ወደ አየር በረረ በምስር አገር ወዳለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች ከውስጧ አስገባው። ከፈረሱም ላይ አውርዶ በዚያ አቆመው ወደ መጋረጃ ውስጥም ገብቶ ከእርሱ ተሠወረ።

የቤተ ክርስቲያኑም መጋቤ በሌሊት በመጣ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከፍቶ ሲገባ ይህን ወጣት ከመካከል ቁሞ አገኘው። ደንግጦ ሊጮህ ፈለገ ጠቀሰውና ወደኔ ዝም ብለህ ና አለው ወደርሱም ሲቀርብ ይቺ ቦታ የማናት አለው የቤተ ክርስቲያኒቱ መጋቢም ይቺ በምስር አገር ያለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ናት። አንተን ግን ልቡ እንደ ጠፋ ሰው ስትናገር አይሃለሁ ከዚህ ምን አመጣህ አሁንም ንገረኝ አለው። ወጣቱም እንዲህ ብሎ መለሰለት ልቤ እንዴት አይጠፋ እኔ በዛሬው ሌሊት በእገሌ በረሀ ሳለሁ ፈረስ ላይ የተቀመጠ ሰው ተገለጠልኝና ከኋላው በፈረሱ አፈናጠጠኝ ከዚህም አድርሶ ተወኝ አለው።

መጋቢውም የዚያችን በረሀ ስም በሰማ ጊዜ አደነቀ እንዲህም አለው ልብህ ጠፍቷል በማለቴ መልካም የተናገርኩህ አይደለምን የምትናገረውን አታውቅምና የዚያ በረሀ መጠኑ የሃያ ሁለት ቀን ጉዞ የሚያስጉዝ ስለ ሆነ በእርግጥ አንተ ወንበዴ ነህ የቅዱስ ሰማዕት መርቆሬዎስ ኃይል ያለ ገመድ አሥሮሃል፣ እርሱ የዚህን ዓለም ክብር ንቆ የተወ፣ ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ ስም ከሀዲዎች ጽኑ ሥቃይ አሠቃይተው የገደሉት፣ ክርስቶስም በመንግሥቱ ውስጥ የተቀበለው፣ በቦታዎችም ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነፁለት በውስጣቸውም እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል። እር

Читать полностью…
Subscribe to a channel