ethiopian_orthodox | Unsorted

Telegram-канал ethiopian_orthodox - የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

30344

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Subscribe to a channel

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

አርባዕቱ እንስሳ

አንቅዕተ ማኅሌት አንቅዕተ ውዳሴ
ምግባቸው ምስጋና ልብሳቸው ቅዳሴ
ዘወትር ይቀኛሉ ለቅድስት ሥላሴ /፪/

ዐይኖቻቸው ብዙ ክንፎቻቸው ስድስት የሥላሴን መንበር የሚሸከሙት
ሱራፌል ኪሩቤል መገብተ ስብሐት /፪/
አዝ.....
ሰአሉ ለነ አርባዕቱ እንስሳ ገጸ ሰብእ ወገጸ አንበሳ
ገጸ ላሕም ወገጸ ንስር /፪/
አዝ.....
ዘወትር አይለዩም ከመንበሩ ዙሪያ ያመሰግናሉ ብለው ሃሌ ሉያ
ይሏታል ድንግልን እኅትነ ነያ /፪/
አዝ.....
ኪሩቤል ሱራፌል ምሉዓነ ግርማ ምስጋናቸው ሲፈስ ድምፃቸው ሲሰማ
ልብን ይመስጣል የምስጋናው ዜማ /፪/
አዝ.....
ሰአሉ ለነ አርባዕቱ እንስሳ ገጸ ሰብእ ወገጸ አንበሳ
ገጸ ላሕም ወገጸ ንስር /፪/

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ኅዳር ፰

አርባዕቱ እንስሳ

ኅዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው የአርባዕቱ እንስሳ በዓላቸው ሆነ።

እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።

የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።

የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።

ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።

የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።

ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።

በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።

እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።

ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።

ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።

በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።

ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው። ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።

ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።

©ስንክሳር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ገሊላ እትዊ"
እመቤቴ እስከ መቼ በባዕድ ሀገር ትኖሪያለሽ/2/
ገሊላ ግቢ/4/ ሀገርሽ ገሊላ ግቢ /2/

ገሊላ እትዊ /4/ ሀገረኪ ገሊላ እትዊ /2/

እመቤቴ ማርያም ገሊላ እትዊ
ስደቱ ይበቃሻል    ገሊላ እትዊ
ሄሮድስ ሞቷል ብሎ ገሊላ እትዊ
ገብርኤል ነግሮሻል  ገሊላ እትዊ
በእሳት ሰረገላ        ገሊላ እትዊ
ዑራኤል ይመራሻል  ገሊላ እትዊ
ሀገረኪ ገሊላ እትዊ /2/

የዝናቡን ጌታ       ገሊላ እትዊ
እናቱ ሆነሽ ሳለ     ገሊላ እትዊ
ሰይጣን በሰዉ አድሮ ገሊላ እትዊ
እያስከለከለ          ገሊላ እትዊ
ዉሃ ጥም ጸንቶብሽ ገሊላ እትዊ
አፍሽ ደርቆ ዋለ       ገሊላ እትዊ
ይበቃል እናቴ          ገሊላ እትዊ
ርሀብ ጥማትሽ       ገሊላ እትዊ
ሂጂ ወደ ገሊላ       ገሊላ እትዊ
ወደ ዘመዶችሽ        ገሊላ እትዊ

ሀገረኪ ገሊላ እትዊ /2/

የሰማዕታት አክሊል ገሊላ እትዊ
የፃድቃን እናት         ገሊላ እትዊ
ባርከሽ ሰጠሻቸዉ   ገሊላ እትዊ
መከራን ስደት         ገሊላ እትዊ
እኛም ይታደገን       ገሊላ እትዊ
የአንቺዉ በረከት      ገሊላ እትዊ

ሀገረኪ ገሊላ እትዊ /2/

ገፅሽ ብሩህ መልካም ገሊላ እትዊ
ልክ እንደ ፀሐይ    ገሊላ እትዊ
እግዚትነ ማርያም   ገሊላ እትዊ
እሙ ለአዶናይ       ገሊላ እትዊ
አይገባም ለአንቺ    ገሊላ እትዊ
መከራ ሲቃይ         ገሊላ እትዊ

ሀገረኪ ገሊላ እትዊ /2/
ገሊላ ግቢ /4/ ሀገረሽ ገሊላ ግቢ/2/
በቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ኅዳር ፮

እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ደብረ ቁስቋም የገባችበት


ኅዳር ስድስት በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡

አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡

ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡

ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡

ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡

ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡

እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡

ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡

እመቤታችን ማርያም የአስራት ሀገሯን ሀገራችንን ኢትዮጵያን ከገባችበት መአት ታውጣልን።
~ አሜን ~

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

✞ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ [ ዘጸ 20÷3]

አንዳንድ ሰዎች ይህንን ትዕዛዝ በሚያነቡበት ወይም በሚሰሙበት ጊዜ "ይህ ከእኔ ጋር ምን ግንኙነት አለው ? ይህ ሊነገር የሚገባው ለከሐድያንና ለመናፍቃን ወይም ከሥጋዊ ዕውቀታቸው የተነሳ አለበለዚያም ከፍልስፍና በመነጨ ሁኔታ ከሃይማኖት ያፈነገጡትን ነው ። እኔ ግን በሳምንት ይህን ያህል ቀን እጾማለሁ አሥራት አወጣለሁ በየሰዓቱ እጸልያለሁ ከልብ ሆኜ እዘምራለሁ ፤ የቤተ ክርስቲያን መርሐ ግብሮችን ያለማቋረጥ እከታተላለሁ ስለሆነም ይህ ትእዛዝ አይመለከተኝም " ይሉ ይሆናል ።
ነገር ግን ይህ ትእዛዝ ሁሉንም የሚመለከት ነው ። " ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ " ተብሎ መነገሩ በሰው ልጅ እጅ የተጠረቡትንና የለዘቡትን ሰው ያቆማቸውንና በባሕር ወይም በፀሐይ ወይም በእሳት ወዘተ የተመሰሉትንና በተለያዩ ስያሜዎች የሚታወቁትን ጣኦታትን ብቻ ማለት አይደለም ።
በዚህ አንጻር ሰዎች ሀይላቸውን ያመልካሉ ፤ ገንዘባቸውን፤ ውበታቸውን ፤ ዝናቸውን ወዘተ ያመልካሉ ። እንዲህ አይነቶቹ ሰዎች በየፊናቸው የየራሳቸው ጣዖታትና አማልክት አሏቸው ማለት ነው ። እንደዚህም ሆነው እየኖሩ ደግሞ እነዚህ ሁሉ " በእውነት እግዚአብሔርን እናመልካለን በእርሱም እናምናለን ።" ሲሉ ይደመጣሉ ።በእነርሱ ዘንድ ግን እውነትም ሃይማኖትም ፈጽሞ የለም ።
➺ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ !!


@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

🥀🌷🌺🥀🌷🌺🥀🌷🌺🥀🌷🌺
<<ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማኅበረ ጻድቃን ተወደሰ። ወፈድፋደሰ በላዕለ ኃጥአን ነግሠ። እስመ አንሥአ (አሕየወ) ሙታነ ወሕሙማነ ፈወሰ። ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ። ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ።>>

<<ማርያም ሆይ የፍቅርሽ ተአምር በጻድቃን ማኅበር ዘንድ ተመሠገነ። ይልቁንም በኃጢያተኞች ላይ ነገሠ። ሙታንን አድኗልና ፤የታመሙትንም ፈውሷልና። "የደረቀውን እንዲያብብ አድርጓል" የሚል አለ። "ተራሮችን አፈለሰ የሚልም "አለ።>>

እንኳን አስፈጸመን!😍
🥀🌷🌺🥀🌷🌺🥀🌷🌺🥀🌷🌺

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ዘሳድስ ሣምንት ጽጌ በዓለ ልደታ ወራጉኤል ሊቀ መላእክት ስርዓተ ማኅሌት
🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀

ለማንኛውም ወርኃዊ እና ዓመታዊ ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
.....................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም።

ዚቅ፦
አሠርገወ ገዳማት ስን በመንክር ኪን አርአያሁ ዘገብረ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ በኩሉ ክብሩ ከመ አሎን ጽጌያት ኢቀደምት ወኢያኃርት :ዓራዛተ ሰርጎ ነሢኦሙ ኢክህሉ ከመ ክርስቶስ መዊሃ

ወቦ መልክዓ ሥላሴ(ሌላ)፦
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡

ዚቅ፦
እምሥርወ ዕሤይ ሠሪፃ ዘእምዘርዓ ዳዊት ተወሊዳ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ከመ ፍህሶ ቀይህ ከናፍሪሃ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ወከመ ሮማን መላትሒሃ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ኅብስተ ሕይወት በየማና ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ወጽዋዓ ወይን በጸጋማ ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር ትቤ ድንግል ሳይዳ ጸሎታ ወበረከታ ይኩነነ ወልታ

ማኅሌተ ጽጌ
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ዘኢየኃልቅ ስብሐተኪ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ፡፡

ወረብ
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌ ረዳ አመ ኃለቀ/፪/
ዘኢየኃልቅ ስብሐተ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ/፪/

ዚቅ
እለትነብሩ ተንሥኡ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውዑ፤ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል ፤መርዓተ አብ ወእመ በግዑ፡፡

ወረብ
እለ ትነብሩ ተንስኡ ወእለ ተረምሙ አውስዑ ማርያምሀ በቃለ ስብሐት ፀውኡ/፪/
ጸልዩ ቅድመ ስዕል ለቅድስት ድንግል እመ በግ ወመርዓተ አብ/፪/

ማኅሌተ ጽጌ
ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ፤በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ፤ማዕከለ ማኅበር ፍሡሓን ተአምረኪ ዘይነቡ፤እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዓፅ እሌቡ፤ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ።

ወረብ፦
እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዓፅ እሌቡ ፍኖተ ነፈርዓፅ/፪/
ማዕከለ ማኅበር እዜምር ማዕከለ ማኅበር/፪/

ዚቅ
ሰሎሞን ይቤላ ለማርያም፤ወለተ ሐና ወኢያቄም፤ ጽጌ ደመና ዘብርሃን።

ዓዲ ዚቅ፦
ወትወፅእ እምግበበ አናብስት ፤ እምታዕካ ዘነገሥት እምቅድመ ሃይማኖት ፤ንዒ ርግብ ሠናይት፤ኵለንታኪ ሠናይት አልብኪ ነውር ፤ወኢምንትኒ ላዕሌኪ፤ንዒ ርግብ ሠናይት፤ንዒ ርግብየ።

ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ

ወረብ፦
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/፪/

ዚቅ
ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ

ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ  ጽሩይ ዘየኃቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/ 
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ መንግሥቱ ለመፍቀሬ አምላክ/፪/

ዚቅ፦
አክሊል ዘእምጳዝዮን ተደለወ :ጌራ ባሕሪይ ወቀጸላ ወርቅ ጽሩይ በቤተልሔም ተወልደ እምድንግል በብስራትክሙ መሐይምናን እምአፈ ዮሐንስ ሥርግው ተቀሰመ አፈው ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማዕከለ አኃው

ማኅሌተ ጽጌ፦
ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ
አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፤ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡

ወረብ
ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ናሁ ማኀሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ/፪/
አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት/፪/

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጥቀ አዳም መላትሕኪ ከመ ማዕነቅ ይግበሩ ለኪ
ኰሰኰሰ ወርቅ፡፡

ሰቆቃወ ድንግል
ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፤ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ፡፡

ወረብ
ተመየጢ ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ/፪/
ወኢትጎንድዪ በግብፅ በግብፅ ከመ ዘአልብኪ ቤተ/፪/

ዚቅ
ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት
ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት፤እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ ከመ መድበለ ማኅበር፤ሑረታቲሃ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ።

መዝሙር ፦
በ፮ ሃሌታ-
ክርስቶስ ሠረዓ ሰንበት፤ክርስቶስ ሠረዓ ሰንበት ወጸገወነ ዕረፍት ከመ ንትፌሳሕ ኅቡረ።አዕፃዳተ ወይን ጸገዩ ቀንሞስ ፈረይ፤ማ- ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ፤ከመ አሐዱ እምእሉ

አመላለስ፦
ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ/፪/
ከመ አሐዱ እምእሉ/፬/

©ያሬዳውያን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ስለ ስደት የበገና መዝሙር
     በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የአራተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ
🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀

ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
........................................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም ፣
ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፡፡
መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢት ዓለም ፣
መልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም ፣
እም አምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም፡፡

ዚቅ:
ፈጠርካሆሙ ለመላእክት ከመ ይትለአኩከ ፣
ግብረ እደዊከ አዳም አሠርጎከ ለሰማይ በከዋክብት ፣
ወለምድርኒ በስነ ጽጌያት ፣
ግብረ እደዊከ አዳም ፣
እግዚኦ ፈድፋደ ቃልከ ጥዑም ፡፡

ማኅሌተ ጽጌ:
ናሁ ጸገየ ወወሀበ መዓዛ ፣
ተአምርኪ ናርዶስ ለቤተክርስቲያን ዘይውሕዛ ፡፡
እንዘ ታረውጽኒ ቦቱ ማርያም ፍኖተ ቤዛ ፣
አጉይዪኒ ከመ ወይጠል ወከመ ኃየል ወሬዛ ፣
እምገጸ ኃጢአት አጎተ አርዌ ዘይቀትል ኀምዛ፡፡
ትርጉም፦ ቤተክርስቲያንን የሚያስጌጣት ናርዶስ የተባለ ተዓምርሽ እነሆ አብቦ መዓዛን ሰጠ ማርያም ሆይ በድኅነት ጎዳና እያስሮጥሽኝ እንደ ፌቆና እንደ ዋልያ አውራ አሽሺኝ፡፡

ወረብ:
ናሁ ጸገየ ወወሀበ መዓዛ ተአምርኪ ናርዶስ (2) ይሐውዛ ለቤተክርስቲያን (2)
እንዘ ታረውጽኒ ቦቱ ፍኖተ ቤዛ (2) ማርያም ፍኖተ ቤዛ (2)

ዚቅ:
ነፍሳተ ጻድቃን እውያን አመ ይሁቡ መዓዛ ፣
ለዘምግባረ ጽድቅ አልብነ ይኩነነ ቤዛ ፣
ንግደትኪ ማርያም እስከ ደብረ ቁስቋም እምሎዛ፡፡

ማኅሌተ ጽጌ:
እእሚርየ ማርያም ከመ ዘልፊ ታፈቅሪ ፣
ሰላም መልአከ ለኪ አንተ ጽጌረዳ ትፈሪ፡፡
ለለአማኅኩኪ ባቲ ከመ ገብርኤል አብሣሪ ፣
አፈዋተ ጽጌ እምልሳንየ ትፀርሪ ፣
ትእምርቶ ለሠናይትኪ ምስሌየ ግበሪ ፡፡

ወረብ:
እእሚርየ ማርያም (ከመ) ዘልፊ ታፈቅሪ ሰላመ መልአክ (2)
አንተ ጽጌረዳ ትፈሪ ሰላመ (2) መልአክ (2)
(ለለአማኅኩኪ ከመ ገብርኤል አብሣሪ አፈዋተ ጽጌ (2) )

ዚቅ:
ሃሌ ሉያ ጸረሐ ገብርኤል ልዑለ ቃል ወይቤ ፣
ጽገዩ ገዳም ተፈሥሒ ገዳም ፣
እስመ ናሁ ናርዶስ ወሀቦ መዓዛሁ ፡፡

ማኅሌተ ጽጌ:
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስት ወራብዕተ ፣
ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ ፣
ካዕበ ትመስል ሰብእተ ዕለተ ፣
እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ ፣
ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኩ ዕረፍተ ፡፡
ትርጉም፦ ማርያም እናትሽ አበባን ያስገኘች ሦስተኛይቱ ቀን ማክሰኞን ትመስላለች ዳግመኛም ሰባተኛይቱ ቀን ቀዳሚትን ትመስላለች በሰማይና በምድር ላሉ ፍጥረታት ዕረፍት የሆንሽ የነፃነት ምልክት አንቺን አፍርታለችና አስገኝታለችና፡፡

ወረብ:
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እምኪ (2)
ዘወለደት ጽጌ (2) ወፀሐየ ዓለም (2)

ዚቅ:
እምኩሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ፣
ወእምኩሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ፣
ከመ ትኩኖ ማሕደረ ለመንፈስ ቅዱስ ፣
ወምስጋድ ለኩሉ ዓለም፡፡

ወረብ:
እምኩሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ (2)
ወእምኩሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ከመ ትኩኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ (2)

ማኅሌተ ጽጌ:
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፣
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ ፡፡
ትርጉም፦ ነጭና ቀይ መልክ ያለው አበባ ልጅሽን ታቅፈሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ርግቤ ከሐዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነይ የእኔ አዛኝ ደስ ካለው ከገብርኤል እንደ አንቺ ሩኅሩኅ ከሚኾን ከሚካኤል ጋር ነይ፡፡

ወረብ:
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ (2)
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ ሠናይትየ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ (2)

ዚቅ:
ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን ፣
ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን ፣
ንዒ ርግብየ ሠናይት ፣
ወይቤላ መልአክ ተፈሥሒ ፍሥሕት ፣
ቡርክት አንቲ እም አንስት ፣
ንዒ ርግብየ ሠናይት፡፡

ወረብ:
ንዒ ርግብየ (2) ምስለ ሚካኤል (2)
ወንዒ ሠናይትየ (2) ምስለ ገብርኤል ፍሱሕ (2)

ማኅሌት
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፣
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፣
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፣
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፣
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
ትርጉም፦ በስሙ ምልክትና የሞቱ መታሰቢያ የታነፀብሽ ከሚያበራ ወርቅ ይልቅ እንደ ዕንቁ የጠራ ንጽህና ያለሽ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ኹሉን ለእርሱ ታሰግጂለታለሽ እርሱም ለአንቺ ይሰግዳል፡፡

ወረብ:
ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየኀቱ እምዕንቁ ባሕርይ (2)
ማርያም አክሊለ ጽጌ ለጊዮርጊስ ቀፀላ መንግሥቱ (2)

ዚቅ:
ይእቲ ተዓቢ እም አንስት ፣
አሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት ፣
መድኃኒቶሙ ለነገሥት አክሊል ንፁህ ለካህናት ፣
ብርሃኖሙ ለከዋክብት፡፡

ወረብ:
ይእቲ ተዓቢ እም አንስት እሞሙ ለሰማዕት ተዓቢ (2)
መድኃኒቶሙ ለነገሥት ፋሲለደስ ወኢያሱ መድኃኒቶሙ (2)

ሰቆቃወ ድንግል:
አይቴኑ መልአክ ዘአብሠረኒ ፣
ብካይየ ይርአይ ወይርድአኒ ፣
ወአልብየ ሰብእ ዘየአምረኒ ፣
እንዘ ትብሊ ድንግል እራኅራኅከኒ ፣
በገዳም አመ ነሥኡኪ ልብሰ ወልድኪ ረቡኒ ፣
ጸላኢ ወተቃራኒ ፈያታይ ማኅዘኒ ፡፡

ወረብ:
አይቴኑ መልአክ ዘአብሰረኒ (2) ገብርኤል ወይርድአኒ (2)
እንዘ ትብሊ ድንግል እራኅርከኒ አልብየ ሰብእ ዘየአምረኒ (2)

ዚቅ:
አመ ወጽአት በፍርሃት እም ሀገረ ዳዊት ዘይሁዳ ፣
በብሥራተ መልአከ እንግዳ ፣
ኢረከበት ማየ በፍኖት ዘታሰቅዮ ለወልዳ፡፡

መልክአ ውዳሴ:
ለኪ ይደሉ ውዳሴ ወስባሔ ፣
በአፈ መላእክት ወሰብእ እለ ይነብሩ ውስተ ኩለሄ ፣
ማርያም ድንግል ማርያም አመ ኤሎሄ ፣
ከመ ሰብሐዊ ፍቁርኪ አቀረብኩ እማኄ ፣
ለዝክረ ስምኪ ዘይምዕዝ እምርኄ፡፡
 
ዚቅ:
ለኪ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወስግደት ፣
እምኀበ ሰብእ ወመላእክት ፡፡

መዝሙር:
ሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት ፣
ኩሉ ነባሪ ወቀናዪ ያዕርፉ ባቲ ፣
ግብረ እደዊከ አዳም ፣
ለሐኮ ለሰብእ በአርአያከ ወበአምሳሊከ ፣
ግብረ አደዊከ አዳም ፣
ፈጠርካሆሙ ለመላእክት ከመ ይትለአኩከ ፣
ግብረ እደዊከ አዳም ፣
አሠርጎከ ለሰማይ ወለከዋክብት ፣
ወለምድርኒ በስነ ጽጌያት ፣
ግብረ እደዊከ አዳም ፣
እግዚኦ ፈድፋደ ቃልከ ጥዑም፡፡

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

#ዘጠኙ ቅዱሳን
(በ5ኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ ክርስትናን ለማስፋፋት የተሰደዱ ክርስቲያን ሚሲዮናውያን)

ዘጠኙ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት አከፋፈል መሰረት “ ጥንታዊው የታሪክ ዘመን” ተብሎ በሚጠራው ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ዘጠኝ የውጭ ሀገር ታላላቅ የክርስትና ሃይማኖት አባቶች ናቸው ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ የሆነ መንፈሳዊ አስተዋጽኦን ማለትም በመንፈሳዊ ህይወት ፣ በስብከተ ወንጌል፣ገዳማዊ እና የምንኩስና ሕይወትን በማስፋፋት ፣ መጽሐፍትን በመተርጎም፣ አበርክተዋል፡፡

ለአገራችን ሥነ-ፅሑፍ እድገት ጉልህ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ ከደጋግ ነገስታት ጋር በመሆን ለትምህርት ፣ ለማህበራዊ ኑሮ ወዘተ መሠረት የሆኑ ገዳማትን ከመመስረት ከቤት ክርስቲያን አልፎ ለአገራችን ኢትዮጵያ አያሌ አበርክቶት አድርገው አልፈዋል፡፡ በአገራችን ለቅድስናና ምንኩስና ፣ ለመፈንሳዊነት ትልቅ አብነት አላቸው፡፡ ከሮም ፣ ታናሽ እስያ፣ቁስጥንጥንያ ፣ ቂሳሪያ እና ሌሎች የእስያና ኤሮፓ አገሮች ቢመጡም ግዕዝን አጥንተው የአገሩን ባህልና አኗኗር ለምደው ክርስትናን በምድረ ኢትዮጵያ አስፋፍተዋል፡፡

ክርስትናን ወሰን አይገድበውምና ፣ ክርስቲያን ሃይማኖት እንጂ የድንበር አገር የለውምና የመጡበትን ቦታ ሳይሆን ህዝቡ መንፈሳዊ አባትነታቸውን ተቀብሎ! ቤተክርስቲያንም ውለታቸውን ቆጥራ የቅድስና ማዕረግ ሰጥታ ታከብራቸዋለች፡፡ ዕለት ተሰይሞላቸውም ክብር ይደረግላቸዋል፡፡

ከተለያዩ አካባቢ መምጣታቸውም ከየመጡበት አገር ወደ ግዕዝ መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ አያሌ መንፈሳዊ መጽሐፍትን እንዲተረጉሙ አስችሏቸዋል፡፡ በዚህች ትንሽ ርዕስ ስለተሰዓቱ ቅዱሳን ይህን ያክል ካነሳን በሚከተለው አንቀጽ ደግሞ ማንነታቸውን እናስተዋውቃችኋለን፡፡ ስም የመጡበት አገር የገደሙበት ቦታ የመታሰቢያቸው ቀን:-

፩- አቡነ አረጋዊ ሮም ደብረዳሞ ጥቅምት ፲፬

፪- አቡነ ጰንጤሌዎን ሮም አክሱም ጥቅምት ፮

፫- አቡነ የማታ ቆስይ ገርዓልታ ጥቅምት ፳፰

፬- አቡነ ገሪማ ሮም መደራ/ዓድዋ/ ሰኔ ፲፯

፭- አባ ጽሕማ አንጾኪያ እንደ አባ ድሕማ/ይዲያ ጥር ፲፮

፮- አባ አፍፄ ታናሽ እስያ የሓ ግንቦት ፳፱

፯- አባ ሊቃኖስ ቁስጥንጥንያ አክሱም ህዳር ፳፰

፰- አባ አሌፍ ቂሳርያ ደብረ ሃሌሉያ መጋቢት ፲፩

፱- አባ ጉባ ኪልቂያ አድዋ አጠገብ ግንቦት ፳፱

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ደም ወማይ
ደም ወማይ ወሐሊብ እምነ ክሳዱ ፈልፈለ/፪/
ሶበ ተከለለ/፪/ጊዮርጊስ ሶበ ተከለለ/፪/ኧኸ/፫/

ትርጉም፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰይፍ አንገቱን በተሰየፈ ጊዜ ደም ውኃና ወተት ፈሰሰ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ኅዳር ፯
የቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕት ቅዳሴ ቤቱ ከበረች


ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን የልዳ ሀገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ሊአፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው፤ ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ። በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲያኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዱው ራስ ደርሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልንጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጐሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ ሀገራቸው አፍረው ተመለሱ።

ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ ሀገር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሔደ በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ።

ክብር ይግባውና ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቁስጠንጢኖስን በእግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ።


ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ "

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ንግስተ ሰማያት ወምድር ማርያም ድንግል (2):
ተፈጸመ(5) ማኅሌተ ጽጌ።🌷🌹🌸🌺


🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹 @Ethiopian_Orthodox 🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"የአብርሃም አምላክ"
የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ቤዛ/፪/
ወገኖቹን ሁሉ በራሱ ደም ገዛ/፪/

የሐሰት ምስክር አቁመው ከሰሱት/፪/
በሞት እንዲቀጣ ሁሉም ፈረዱበት/፪/

ጲላጦስ ገረፈው በሰንሰለት አስሮ/፪/
ከሮማዊው መንግስት እንዲኖር ተፋቅሮ/፪/
 
ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ/፪/
እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ/፪/

በብርሃን ዙፋን ላይ የቆሙት እግሮቹ/፪/
በችንካር ላይ ቆሙ ምንም ሳይሰለቹ/፪/
 
የብርሃን አክሊል ለሰማዕታት ያደለ /፪/
የእሾህ አክሊል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ/፪/
በዘማሪ ዳንኤል ጥበበሥላሴ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጥቅምት ፳፯
መድኃኔዓለም ክርስቶስ

ጌታችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት::

¤ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::

ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት::
¤ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት::
¤ራሱንም በዘንግ መቱት::
¤እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::
¤በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት::

በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6666 ገረፉት::

ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: 6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት::

7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን ተናገረ:: ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ::

በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ::

11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ::

ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::

ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::

+በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::

አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱ ይማረን ለሀገራችን ሰላሙን ይላክልን፤ አሜን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ማኅሌተ ጽጌ ዘሐምሳይ ሳምንት በዓለ ተክለሃይማኖት
🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀🌺🥀

ለማንኛውም ወርኃዊ እና ዓመታዊ ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
.....................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

ገባሬ ኩሉ-
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።

ዚቅ
ዛቲ ይእቲ እኅተ ትጉሃን መላእክት፤ ወለተ ኄራን ነቢያት፤ እሞሙ ለሐዋርያት፤ ሞገሶሙ ለጻድቃን ወሰማዕት።

ወቦ መልክዓ ሥላሴ(ሌላ)

ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ
ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤ወተክለ ሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዐጽሙ፡፡

ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ንዕዱ ማዕዶተ ንትካፈል ርስተ ኀበ ጽጌ ዘሠምረ ኀበ አስተዳለወ ዓለመ ክቡረ ምስለ ተክለሃይማኖት ንትፈሳሕ ሀገረ

ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ

ወረብ፦
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሠናይትየ  ምስለ ገብርኤል ገብርኤል ፍሡሕ ሊቀ መላእክት/፪/

ዚቅ፦
በሰላም ንዒ ማርያም፤ትናዝዝኒ ኃዘነ ልብየ፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሱራፌል ወኪሩቤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ኲሎሙ ቅዱሳን፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ወልድኪ አማኑኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ለናዝዞ ኩሉ ዓለም።

ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘይኀቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/

ዚቅ፦
ሰአሊ ለነ ማርያም አክሊለ ንጹሐን ብርሃን  ቅዱሳን።

ዓዲ ዚቅ፦
አክሊሎሙ ለሰማዕት ተስፋ መነኮሳት ሠያሚሆሙ ለካህናት፤ነያ ጽዮን መድኃኒት

ማኅሌተ ጽጌ፦
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማህበረ ጻድቃን ተወደሰ፤ ወፈድፋድሰ በላዕለ ኃጥአን ነግሠ፤ እስመ አንሥአ ሙታነ ወሕሙማነ ፈውሰ፤ ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ፤ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ

ወረብ፦
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማህበረ ጻድቃን ተወደሰ ተአምረ ፍቅርኪ/፪/
ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ/፪/

ዚቅ፦
ይዌድስዋ ኵሎሙ ወይብልዋ እኅትነ ነያ ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ በሰማያት ኵሎሙ መላእክት

ማኅሌተ ጽጌ፦
ለምንት ሊተ ኢትበሊ እምአፈ ኃጥእ ውዳሴ፤ ይበቁዓኒ ዘብየ እምአፈ ጻድቃን ቅዳሴ፤ጽጌ መድኃኒት ማርያም ዘሠረፅኪ እምሥርወ እሴ፤ እመ ተወከፍኪ ኪያየ አባሴ፤ተአምረኪ የአኵት ብናሴ

ወረብ-
ለምንት ሊተ ኢትበሊ ድንግል ውዳሴ እምአፈ ኃጥእ/፪/
ይበቁዓኒ ዘብየ ቅዳሴ እምአፈ ጻድቃን/፪/

ዚቅ፦
አዘክሪ ለኃጥአን ወአኮ ለጻድቃን አዘክሪ ለርሱሐን ወአኮ ለንጹሐን

ሰቆቃወ ድንግል
እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሔልዊ፤ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤ለክብረ ቅዱሳን በከመይቤ ኦዝያን ዜናዊ፤እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።

ወረብ
በከመ ይቤ ኦዝያን ኦዝያን ክብረ ቅዱሳን/፪/
እምግብጽ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡ/፪/

ዚቅ
ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን ጸዋዕክዎ

መዝሙር በ5-
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ጸገየ ወይን ወፈረየ ሮማን፤ወፈረዩ ኩሉ ዕጽወ ገዳም ቀንሞስ ዕቁረ ማየ ልብን፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ጸገዩ ጽጌያት ጸገዩ ደንጎላት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር በስነ ጽጌያት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ ምሕረት፤ማ፦ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ።

አመላለስ፦
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ወለመድኃኒት/፬/

©ያሬዳውያን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እም፤
ዘወለደት ጽጌ(፫) ወፀሐየ ዓለም።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከአቡነ አረጋዊ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ የተገኘ በ፲፯ኛው ክፍለ ዘመን የተሳለ የቅዱሳኑ ምስል

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"አቡነ አረጋዊ"
ጽድቅህ ጠርቶናል አባትነትህ
በቅድስና ያማረ ሕይወትህ
ጌጥ ውበታችን አባ አረጋዊ
መናኝ መነኩሴ መልአክ ምድራዊ (፪)

ተቃኝተህ ስላደግክ በመንፈስ ቅዱስ
ወደ ፅርዕ ተጓዝክ ወደ አባ ጳኩሚስ
ተዘጋጅተህ ነበር ለችግር ፈተና
ዘሚካኤል አለህ ሰጥቶህ ምንኩስና (፪)
     አዝ---
ለኢትዮጵያ ምእመናን አባት ተብለሃል
ወንጌል በማስተማር ብዙ አትርፈሃል
መጻሕፍት ተርጉመህ ያበረከትክ ለአበው
የአንተስ ትሩፋት እፁብ ነው ድንቅ ነው (፪)
    አዝ---
የዓለም ጨው ሆነህ አጣፈጥካት ምድርን
በልባችን ሳልካት ቤተ ክርስቲያንን
ደብረ ሀሌ ሉያ ደብረ ዳሞ ቅድስት
የፈውስ ቦታ ናት መካነ ትኅርምት (፪)
   አዝ---
ልክ እንደ አባቶችህ አስተዋይ ስለሆንክ
ገና ወጣት ሳለህ አረጋዊ ተባልክ
የሥጋን ሞት ሳታይ ተሰውረህ ከምድር
ብሔረ ሕያዋን ተቀላቀልክ በክብር (፪)
  አዝ---

በቦሌ ደብረ ገነት ቅ/ጊዮርጊስ እና ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት መዘምራን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጥቅምት ፲፬
ጻድቁ አቡነ አረጋዊ


‹‹ወበዛቲ ዕለት ኮነ ተዝካሩ ለዐብይ ወክቡር አቡነ አረጋዊ ዘይሰመይ ዘሚካኤል››
‹‹በዚህች ቀን የታላቁ እና የከበረ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዘሚካኤል የሚባለው መታሰቢያ ነው››


አባታችን ‹‹አቡነ አረጋዊ›› በሀገራችን ስም አጠራራቸው ከከበሩ አባቶች አንዱ ጻድቅ ናቸው፡፡ ጻድቁ የተወለዱት በ5ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አከባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው አባታቸው ንጉሥ ይስሐቅ እናታቸው ደግሞ ቅድስት እድና ይባላሉ፡፡ የተወለዱት ደግሞ በታላቋ ሮም ነው፡፡ ስማቸው ብዙ አይነት ነው ወላጆቻቸው ‹‹ ዘሚካኤል›› ሲሏቸው፣ በበረሀ ‹‹ገብረ አምላክ ››ተብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ደግሞ ‹‹አረጋዊ›› ይባላሉ፡፡ አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጽሐፍ ተምረዋልና ጠፍተው ገዳም ገቡ፡፡ በዚያም በገዳሙ ዳውንስ (ግብፅ) የታላቁ ቅዱስ "ጳኩሚስ" ደቀ መዛሙርት ሆነው ከነአባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል፡፡ ከመነኮሱ ከዓመት በኋላ ወደ ሀገራቸው ሮም ተመልስው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግሥት ስዎች ወደ ምናኔ ማርከዋል ፡፡
451 ዓ.ም በተካሄደው የኬልቄዶን ጉባዔ ላይ የሁለት ባሕርይ ትምህርት አንቀበልም በማለታቸው በቤዛንታይን ነገሥታት ስቃይ እና መከራ ፀናባቸው :: በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ ከሁለት ባሕርይ ትምህርት የፀዳች እና ታላቅ አምልኮተ እግዚአብሔር እንደሚፈፀምበት ስለ አወቁ ከሌሎች ስምንት ቅዱሳን ጋር በሁለተኛው የኢትዮጲያ ጳጳስ በአባ ሚናስ ጊዜ በንጉሥ አልዓሜዳ ዘመነ መንግሥት በ5ተኛው መቶ ክ/ዘመን ማብቂያ 480/81 ዓ.ም ወደ ሀገራችን ገቡ፡፡ ከአባታችን ከአቡነ አረጋዊ ጋር የነበሩት ስምንቱ ቅዱሳን ከሮም ፤ከቤዛንታይን ፤ ታናሿ እስያ፤ሶሪያ ግዛትና አካባቢዎች የመጡ ናቸው፡፡ ስማቸውም አባ ገሪማ (አባ ይስሐቅ) ፣ አባ ጰንጠሌዎን፣ አባ አፍፄ፣ አባ ጉባ ፣አባ ሊቃኖስ ፣ አባ ይምዓታ ፣አባ ጽሕማ፣አባ አፍጼ ናቸው :: ስለ ተሰዓቱ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ የገቡበት መንገድ ሁለት ዓይነት ምንጮች ይገኛሉ፡፡ የመጀመሪያው አምደ ሃይማኖት ኢትዮጲያዊው ቄርሎስ የሚባለው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ቅዱሳኑ ወደ ኢትዮጲያ ሲመጡ ነገሥታት እና መኳንንትን አስከትለው መጽሐፍትን ይዘው ስለነበር የመጡት ሀገር ለመውረር መስሏቸው ኢትዮጲያውያን ደንግጠው ነበር ፡፡ ነገር ግን በእጃቸው የተለያየ ተአምራትን ማየት ስለቻሉ ለመንፈሳዊ ተልዕኮ መምጣታቸውን ተረዱ ከተአምራቱ መካከል በዕራፈ የእሳት ፍም የቋጠሩ፣ ጠዋት ዘርተው ለሠርክ ቅዳሴ ማድረሳቸው (አቡነ ገሪማ)፣ በወንፊት ውሃ ተሸክመው መሄዳቸው፣ አሥሩ የእጅ እና የእግር ጣቶቻቸው እንደ ፀሐይ ያበሩ መሆናቸውን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጠቅሰዋል ሁለተኛው ምንጭ አባታችን አቡነ አረጋዊ መጀመሪያ ብቻቸውን መጥተው የኢትዮጲያውያንን ደግነት እና ታማኝነት ስለተረዱ ተመልሰው ሄደው ለ8ቱ ቅዱሳን በመግለፅ ይዟቸው መጥተዋል የሚሉ ምንጮች ናቸው ::
አባታችን አቡነ አረጋዊ ሲመጡ እናታቸው ቅድስት እድና እና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ :: ንጉሡም ተቀብለው በቤተ ቀጢን ( አክሱም) አሳረፏቸው በዚያ ተቀምጠው መጽሐፍትን እየተረጎሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል፡፡ አባታችን ለብዙ ጊዜ በዓት ፍለጋ ደክመዋል በመጨረሻም ደብረዳሞ ማርካቸዋለች ፡፡ፃድቁ አባታችን እያስተማሩ ደብረዳሞ ሲደርሱ ወደሰማይ ቀጥ ያለች ተራራ ሰው በምንም መንገድ ሊደርስበት ወይም ሊወጣበት የማይቻለውን ቦታ እሳቸው ተመኙ፡፡ ‹‹ አሁን ይህንን ተራራ በምን ልወጣ እችላለሁ›› እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግር ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነብዩ ዳዊት ላይ አድሮ እንደተናገረ ( መዝ 90 (91) ÷11-16) የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስድስት ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ ሚካኤል ሠይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል ፡፡ ወዲያው “ሀሌ ሉያ ለአብ ሀሌ ሉያ ለወልድ ሀሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው አመስግነዋል። ቦታውም <<ደብረ ሀሌ ሉያ>> ተብሏል ፡፡ በዚህችም እለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ምድራዊ ህብስትን አልበሉም፡፡ በሰንበተ ክርስቲያን ከቅዳሴ በኋላ ህብስተ ሰማይ እያመጡላቸው ይመገቡ ነበር ፡፡
ፃድቁ አባታችን የምንኩስና ኑሮ ሥነ ሥርዓት በማስተማራቸውና በማስፋፋታቸው <<አቡሆሙ ለመነኮሳት ዘኢትዮጵያ፤ የኢትዮጵያ መነኮሳት አባት>> ይባላሉ። ግዕዝን በመማር መጽሐፍ ወደ ግዕዝ ቋንቋ ተርጉመዋል። ከአፄ ገ/መስቀል እና ከቅዱስ ያሬድ ጋርም ወዳጆች ነበሩ፡፡ በደብረዳሞ ተራራ ግርጌ የኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ለሴቶች ገዳም አድርገው ሰጥተዋል። ቀዳሚ መነኩሴም የሆኑት እናታቸው ቅድስት እድና ናቸው፡፡ በመጨረሻም ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስማቸውን ለሚጠራ መታሰቢያቸውን ለሚያደርግ ቃልኪዳን ተቀበሉ፡፡ በመምህራቸው አባ ጳኩሚስ እንደተማሩት ለልጆቻቸው መነኮሳት ሥርዓተ ማኅበርን ሰሩላቸው፤ ከዚያ በኋላ በእግዚአብሔር ቸርነት እንደሄኖክ እንደ ኤልያስ ከሞት ገፅ ጥቅምት 14 ቀን በደብረ ዳሞ ተሰወሩ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በፃድቁ ጸሎት ይማረን፤ በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…
Subscribe to a channel