እንኳን ደህና መጡ። በቴሌግራም ውስጥ የታዋቂ ሰዎች ማለትም 💥አርስቶትል 💥አብርሀም ሊንከን 💥አልበርት አንስታይን 💥ማህተመ ጋንዲ... እንዲሁም የሌሎችም አባባል የሚያገኙበት ቻናል🎯 ሲሆን አላማችንም ሰዎች በሚያነብቡት ጥቅስ የአስተሳሰባቸውን አድማስ ማስፋት ነው። ስለመረጡን እናመሰግናለን 🙏 Contact፦ @onajonah
ፈጣሪ
👉በሀዘን ውስጥ
ፈገግ የምትልበት
👉ተከድተህ
የምታምንበት
👉በቀውስ ውስጥ
ሰላም የምታገኝበት
👉በድክመት
የምትበረታበት
👉ፈርተህም
ወደ ፊት የምትጓዝበት
ምክንያት ይሁንልህ!!!
አሜን
@ethio_tksa_tks
ሁሌም ከቀን ላይ ቀን ሲጨመርልህ ይህንን የፈጣሪ መልእክት አሰላስለው
💬 ሁልጊዜ ካንተ ጋር ነኝ
💬 ሕልምህን የሰጠሁህ በምክንያት ነው
💬ከእኔ ጋር ሁሉም ይቻላል
💬 አትጨነቅ፤ በእኔ ተማመን
💬 መቼም አልተውህም
💬 ጊዜው ሲደርስ፤ ያኔ አደርግልሃለሁ
💬 ናፍቀኸኛል፤ አዋራኝ
💬 ጭንቀትህን ለእኔ ስጠኝና ተኛ
መልካም ቀን🙏
@ethio_tksa_tks
> አንድ ሰው በበረሃ እየተጓዘ እያለ የያዘው ውሃ አልቆበት በውሃ ጥም ይያዛል ቀስ በቀስ ውሃ ጥሙ ሰውዬውን እያደከመው ይመጣል በስተመጨረሻ ከአንድ የውሃ ጉርጓድ ጋር ይደርሳል ጉርጓዱ በጣም ጥልቅ ነበረ ውሃ ይኑረው አይኑረው አይታይም፡፡
ከዚያም ከጉርጓዱ ጎን አንድ አሮጌ የውሃ መሳቢያ ሞተር አለ ሞተሩ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ሰፍሯል፡፡ <<ይህ የውሃ መሳቢያ ሞተር የሚሰራው በውሃ ነው›› ይላል፡፡
ከሞተሩ ጎን አንድ ጆግ ሙሉ ውሃ ተቀምጧል ጆጉ ላይ እንዲሁ አንድ ፅሁፍ ሰፍሯል ‹‹ወዳጄ ሆይይህንን ጆግ ውሃ ሞተሩ ውስጥ ጨምረው ሞተሩ ብዙ ውሃ ያወጣልሃል ታዲያ አደራ አንተም እንዳንተ ላለ ሌላ መንገደኛ ይጠቅማልና ውሃው ከጉርጓዱ ሲወጣልህ ጆጉን ሞልተህ ማስቀመጥን አትርሳ›› ይላል፡፡
በጆግ ያለውን ውሃ ሞተሩ ውስጥ ይጨምረው ወይስ ይጠጣው? እዚጋር ሰውዬው በሁለት ሃሳብ ተወጠረ ‹‹አንደኛ ይህ ሞተር አርጅቷል ጨምሬው ባይሰራ ይህንንም ውሃ አጣሁ ማለት ነው ሞትኩ ማለት ነው ስለዚህ ልጠጣውና ህይወቴን ላድን ፡ ደሞ ማሳሰቢያውስ ውሃው ያለሞተር አይሰራም እንደኔ ውሃ የተጠማ ሰው ቢመጣ ይህንን ማንቀሳቀሻ ከጠጣሁት ይሞታሉ›› ብሎ ለራሱም ለሌሎቹም አሰበና በሃሳብ ተወጠረ በስተመጨረሻ በብዙ ጭንቀት ተወጥሮ ትልቅ ውሳኔ ወሰነ እንዲህ አለ <<ውሃውን ወደሞተሩ ብጨምረው ይሻላል ከሰራ ጥሩ ካልሰራ ግን እሞታለሁ እንጂ በፍፁም ይህንን ጆግ ውሃ ጠጥቼ ሄጄ ዛላለሜን ስለዚህ ጉርጓድና ይህንን ውሃ አተው ስለሚሞቱ ሰዎች እያብኩ መኖር አልፈልግም›› አለ፡፡
ከዚያም የጆጉን ውሃ ወደ አሮጌው ሞተር ውስጥ ጨመረውና የሞተሩን ማስነሻ ተጫነው፡፡ ሞተሩም ድምፅ እያሰማ ውሃ የማውጣት ስራውን ጀመረ፡፡ ሰውዬው ተደነቀ የሚፈልገውን ያህል ጠጣ አካባቢው በሙሉ በውሃ እራሰ ከጠበቀው በላይአካባቢው ሁሉ ውሃ በውሃ ሆነ ከዚያም በተባለው መሰረት እሱም ጆጉን በውሃ ከሞላው ቦሃላ ጆጉ ላይ ፅሁፍ ጨመረበት <<እመኑኝ በትክክል ይሰራል›› አለ፡፡
እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ለራስ ማሰብ በህይወት መኖር ነው ለሌላው ማሰብ ግን ሰው መሆን ነው፡፡ ያለህን በሙሉ ሳትሰስት ከሰጠህ በእጥፍ ድርቡ ፈጣሪ ይሰጥሃል። ሰውዬው ጆግ ውሃ ሰቶ አካባቢን የሚያርስ ውሃ እንደተቸረው አንተም የምትሰጣት ጠብታ ከልብህ ከሆነ በእጥፉ ይሰጥሃል፡፡ በምትሰፍረው መስፈሪያ ይሰፈርልሃል በሰጠኸው ልክ ይሰጥሃል ስለዚህ <<አመድ አፋሽ ሆንኩ›› ከማለትህ በፊት አመድ ሰተህ ከሆነስ፡፡ መስጠትን ብቻ ሳይሆን አሰጣጥህ ወሳኝነት አለው፡፡
@ethio_tksa_tks
ለራስህ ካላሰብክ ማንም ላንተ አይጨነቅም!
ካልሰራህ ደሃ እንደሆንክ ትቀራታለህ እንጂ ማንም አንተን ሃብታም አያረግም😊
ካላጠናህ ትወድቃለህ እንጂ ማንም አያስጠናህም
ገንዘብ ካልሰራህ ትቸገራለህ እንጂ ማንም እሱ ገንዘብ የለውም ቆይ በደንብ ልስራና ልስጠው አይልም
ለምንድነው እነዚህን ነገሮች ማስታውስህ እንዳትረሳው ነው።
እነዚህን መርሳት ስትጀምር ሰነፍ መሆን ትጀምራለህ
#አስታውስ እኔ ካልሰራው ማንም መጥቶ ከድህነት አያወጣኝም በል ፣ እኔ ካልሞከርኩ ማን ይጨነቃል ስለኔ ትዝም አልላቸው በል።
ደግሞም ውሸት አይደለም ትዝም አትለንም🤨
እንትና አለልኝ አትበል እሱም የራሱ ህይወት አለው።
ገንዘብ ቸግሮሃል?
ድብርት ውስጥ ነህ?..
ማን የራሱን ችግር ትቶ ያንተ ያሳስበዋል? ማንም!
ሁሉም ላይፉን ይኖራል እንጂ ያንተን ላይፍ አያስተካክልም።
"ለራስህ ያለኸው ራስህ ነህ!"
በርትተህ ቀጥል ወይም ተስፉ ቆርጠህ ተቀመጥ! 2ኛው ግን የሰነፎች ምርጫ ነው!
እንደውም ሰው ስላንተ ማሰብ ሚጀምረው ደሃ እያለህ ፣ ጭንቀታም እያለህ ፣ ሰነፍ እያለህ አይደለም ስኬታማ ስትሆን ፣ ደስተኛ ስትሆን ነው ሰው ስላንተ ሚያስበው። ደስታው ግን ከየት መጣ ይላሉ ምንሆኖ ነው ያላሉህ ስትጨነቅ ፣ ደሃ ሆነህ ያልጠየቁህ ገንዘብ ስትይዝ ከ10 አመት በፊት እንደምትተዋወቁ ትዝ ይላቸዋል🤔
አለም እንዲ ናት! ሁሉም የራሱን የሚያሳድድባት!
በርትተህ ቀጥል🔥
ፈተናን ተጋፈጥ ⚡️
ጠንካራ ሁን 💪
ጀግና ሁን👏
ወደፊት ገስግስ ⏩
በጽናት ቀጥል እስኪሳካ ድረስ!👍
መልካም ምሽት
share @ethio_tksa_tks
በቻናላችን የምትገኙ ሙስሊም ቤተሰቦቻችን እንኳን ለ1446ኛ የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! 🌙
መልካም በዓል ፤ መልካም ቀን ❤️
@ethio_tksa_tks
መሞት ትፈልጋለህ❓
ራስህን ወንዝ ውስጥ ክተትና እንዴት ራስህን ለማዳን እንደምትፍጨረጨር ታየዋለህ
ራስህን ከማጥፋት ይልቅ ውስጥህ ያለውን ነገር ለማጥፋት ሞክር።
Share @ethio_tksa_tks
#repost
ፓኪስታናዊ ጸሓፊ አዲብ ሚርዛ እንዲህ ይላል፦
አባቴ ሁሌ ይደበድበኛል እናቴም ከእሱ ምት እንዳዳነችኝ ነበር። ስለዚህ ለራሴ አልኩ፦ “አንድ ቀን እናቴ ብትደበድበኝ አባቴ ምን ያደርጋል?”
እና ይህን ለማየት እናቴ ወተት ከገበያ አምጣ ብላ ስትልከኝ አልታዘዝም አልሄድም አልኳት። ለምሳ ቁጭ ስንል ሳህኔ ላይ የተመለደውን መጠን ያህል ምግብ አደረገችልኝ። ሁሌ ትንሽ ነው የምታደርጊልን ጨምሪልኝ ብዬ ጮሁኩባት። እሷም እየጨመረችልኝ ‹‹ወንበር ላይ ቁጭ ብለህ ብላ›› አለችኝ። እኔ ግን አውቄ መሬት ላይ ቁጭ ብዬ ልብሴን እያቆሸሽኩ ባለመደችው ቃና ማውራት ጀመርኩ። እናቴ ትመታኛለች ብዬ ስጠብቅ እሷ ግን አጥብቃ እቅፍ አድርጋኝ ‹‹ልጄ ምን ሆነ ነው አሞሃል እንዴ?›› አለችኝ። ያኔ መቆጣጠር የማልችለው የሀዘን ስሜቴን አይኔን በእንባ ሞላው።
እናቴ ለዘለአለም ኑሪልኝ❤️
SHARE||@ethio_tksa_tks
" በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል። ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!"
©ጋሽ ስብሀት ገብረእግዚአብሔር
Share @ethio_tksa_tks
የገበሬው ሚስት
አንድ ገበሬ ቆንጆ ልባምና አስተዋይ ሚስት አገባ። በጣም ተዋደውና ተከባብረው ይኖራሉ፡፡ ነገር ግን አንዲት ነገረኛ ጎረቤትም ነበረቻቸው።
እቺህ ጎረቤታቸው የገበሬውን ሚስት ስለምትጠላት ስሜቷን የሚጎዱ ነገሮችን ታደርግባት ነበር፡፡
ሁልጊዜም በየቀኑ ቤት በገባችና በወጣች ቁጥር ስድብ ታከናንባታለች። በአንዱ ቀን አጋጣሚም እቺው መከረኛ ጎረቤቷ እንዲህ ትላታለች
"ምን አይነት ማፈሪያ ሴት ነሽ! አባትሽ የተሻለ ሰው አግብተሸ ደህና ቦታ ትደርሻለሽ ብሎ እያሰበ አንቺ ግን አሁን የምታደርጊው ነገር ቢኖር በእርሻው ውስጥ ለረጅም ሰአት በመቆየት እጅግ የኮሰሱ ላሞችን መንከባከብ ብቻ ነው። አንቺ የከሰርሽ ሴት ነሽ! "
በተለያየ ጊዜ ስታገኛትም ለማናደድ እና ሙድ ለመያዝ የማታደርገው ጥረት የለም። ነገር ግን የገበሬዋ ሚስት በጣም የተረጋጋች እና ስድቧም የሚረብሻት ሰው አይደለችም። ስትሰደብም ከመበሳጨት ይልቅ ሳቅ ትላለች፡፡ ሰላማዊ ነችና ሁልጊዜ ፈገግታዋን ተላብሳ ትታያለች።
ታዲያ በዚህ መሃል ጎረቤቷ የገበሬውን ሚስት ለማስቆጣት ያደረገችው ጥረት ሳይሳካላት ስለቀረና ስድቦቿን ለምን ከቁም ነገር እንዳልቆጠረቻቸው ሊገባት አልቻለም። አንድ ቀን ታዲያ ወደ እርሷ ቀረበችና እንዲህ አለቻት፡-
"ስሰድብሸ ነበር የኖርኩት። ለምንድን ነው ግን የማትናደጅውና መልስ የማትሰጪኝ? " ስትል ትጠይቃታለች።
የገበሬው ሚስትም አንድ
ጥያቄ ልጠይቅሽ? እስቲ የሆነ ነገር ሰጥተሸኝ አልቀበልም ካልኩ ማን ጋር ነው የሚቀረው? " በማለት ጥያቄዋን በጥያቄ አፋጠጠቻት።
ጎረቤት ምላሽ ሰጠች
እኔ ጋር ይቀራል።
የገበሬው ሚስትም ፈገግ ብላ ስድብሽን እስካልተቀበልኩ ድረስ አንቺው ጋር ይቀራሉ ማለት ነው ብላ ነጉሩን ቋጨችው።
ይህች ዓለም እርስ በእርስ በመበላላት፣ በጭቅጭቅ፣ ጥላቻ እና በአጠቃላይ በአሉታዊ ሁነቶች የተሞላች ስፍራ ሆናለች። እነዚህን ነገረኞች ማስቀረት አንችልም። እነዚህ ነገሮች በዙሪያችን እለት በእለት ህይወታችን ውስጥ ያጋጥሙናል። ሆኖም ግን ሰዎች ሲሰድቡን፣ ሲሳለቁብን ወይም ሲነቅፉን መበሳጨት የለብንም፡፡ ሁሌም ቢሆን ስድብ ከተሳዳቢው ዘንድ ቀሪ መሆኑን አስታውስ። ንብረትህ አይደለምና ሲያመጡብህ ተበሳጭተህ አትቀበል።
Share @ethio_tksa_tks
ጦርነት ክፉ በሽታ ነው !!!
ይህ የሆነው በሁለተኛው የአለም ጦርነት ነው ይህ የጀርመን ወታደር ሌሎችን ለማጥቃን ቤተሰቡን ቤቱን እና ንብረቱን ጥሎ ወደ ጦርነቱ ይዘምታል ..ይዋጋል ..ሌሎችን ያጠቃል ..በሄደበት ጦርነት ብዙ ድል ቢያደርግም በመጨረሻ በጦርነቱ ጀርመን በመሸነፏ እሱም እድለኛ በመሆኑ ሳይሞት በህይወት ወደ ሀገሩ ወደ ቤቱ ይመለሳል።
ግን ይሁን እንጅ ወደ ቤቱ ቢመለስም የጠበቀውን አላገኘም በጦርነቱ ቤቱ ፈራርሷል ..ሚስቱና ልጆቹ በሙሉ አልቀዋል
ኸረ ሰፈሩ ሁሉ ጠፍቷል እሱ ሌሎችን ለማጥፋት እንደሄደው የእሱን ቤተሰቦች ደግሞ ሌሎች አጥፍተዋቸዋል የጦርነት መጨረሻው ይህው ነው አሸናፊና ተሸናፊ በሌለበት ሁኔታ መጠፋፋት።
ምን ለማለት ነው ጦርነት በሽታ ነው.... በስግብግብ አእምሮ የሚጸነስ ....አሸናፊንም ተሻናፊንም የሚያጠፋ....ከራስ ወዳድነት አስተሳሰብ የሚነሳ የአለም ክፉ በሽታ ነው ጦርነት መቼም ቢሆን ለማንም ቢሆን ለማንም ጠቅሞ አይውቅም ሰላም ይሻለናል ..ከሆነ በሁዋላ ዋይ ዋይ ከማለት ይልቅ ነገሮችን ሰከን ባለ መልኩ መመልከት ይበጀናል ለማለት ነው ምክንያቱም ከዚህ በፊት ሞክረነው ሞክረነው ከጉዳት በቀር ምንም ያተረፍነው ነገር የለምና !!!
share @ethio_tksa_tks
ስልኩን አንሥቶ ቅርብ ጓደኛው ጋር ደወለና ''እናቴ ስለታመመችብኝ ለመድኃኒት የሚሆን ገንዘብ አበድረኝ" ብሎ
ጓደኛውን ጠየቀው።ጓደኛውም "እማማ ምን ሆኑ?" አለ።
"አቅም አንሷታል መድሀኒቱ የግድ ያስፈልጋታል" በማለት
አስረዳው።ጓደኛውም "እሺ እፈልጋለሁ ከአንድ ሰአት በኋላ ደውልልኝ" ብሎት ስልኩ ተዘጋ።
ልቡ በእናቱ ህማም ጭንቀት ተወጥሮ ደቂቃዎችን በስስት እየቆጠረ አንድ ሰዓት ሆነ። በቀጠሯቸው መሠረት ደወለለት።
ነገር ግን የጓደኛው ስልክ ዝግ ነበር! ደጋግሞ ደወለ ስልኩ ግን አይሰራም። ያ ለችግር ቀን መደገፊያ ይሆነኛል ያለው የቅርብ ጓደኛው ችግሩን አስረድቶት እያለ ስልኩን ጠርቅሞ መዝጋቱ ቅስሙን ሰበረው። አማራጭ እንደሌለኝ እያወቀ እንዴት ስልኩን ዘግቶ ይጠልፋ ሲል ራሱን በአግራሞት ጠየቀ። ቢያንስ አልቻልኩም አይለኝም ነበር ብሎ በጓደኛው በጣም አዘነ።ምድር ጠበበችው። የሚደገፍበት ሰው አጣ። የሚወዳትን እናቱን እንዴት ይታደጋት?! ምድር ተከፍታ ብትውጠው ተመኘ።በአጽናፈ ሰማይ መጠለል እንደማይችል ያህል ተሰማው።
ስለእናቱ በጣም አዘነ። አምርሮም አለቀሰ.......
ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ እየተጋባ በጓደኛው አለመታመን ብስጭትና እናቱን መድሀኒት ገዝቶ መታደግ ባለመቻሉ በሐዘን ተሞሎቶ በዕንባ እየታጠበ ወደ ቤት ተመለሰ።እናቱ በሰላም ተኝታለች። ፊቷ ላይ የእረፍት ስሜት ይነበባል።አጠገቧ ሊገዛው ፈልጎ ገንዘብ በማጣቱ ምክንያት ሳይገዛው
የተመለሰው የመድሀኒት ብልቃጥ ተቀምጧል።ሁኔታው ግራ ቢገባው እህቱን "መድሃኒቱን ማን ገዛው?" አላት
ብሎ ጠየቃት።
"ጓደኛህ እየሮጠ መጥቶ ማዘዣውን ወስዶ መድሀኒቱን ገዝቶ አመጣው። እማም መድሀኒቱን ስትወስድ ወዲያው ተሻላት።" አለችው።
ዓይኖቹ የደስታ እንባን አቀረሩ።ድብልቅልቅ እያለበት ወደ ጓደኛው ቤት በሩጫ ገሰገሰ።በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ ገባ። ደግሜ ደጋግሜ ብደውልልህም ስልክህ ግን ዝግ ነበር?አለው።
ጓደኛውም አዎ ስልኬን ሽጬ ለእማማ መድኀኒት ስለገዛሁበት ነው ዝግ የሆነው ሲል መለሰለት
ለሁላችሁም እንዲህ ያለ ልባዊ ጓደኛ ይስጣችሁ!!!
🙌♥️
@ethio_tksa_tks
በውስጥህ የምትይዛቸው እንደ ቂም፣ ቁጣና ጥላቻ ያሉ ስሜቶች አንተ ጠጥተሃቸው ሌላ ሰው እንዲሞት የምትጠብቅባቸው መርዞች ናቸው።
📓የሕይወት ኬሚስትሪ
✍️ሳድጉሩ ጃጋዲሽ
Share @ethio_tksa_tks
ተቆጣጠር!
ብቻህን ስትሆን አስተሳሰብህን
ከጓደኞችህ ጋር ስትሆን አንደበትህን
ስትናደድ ቁጣህን
ከሰው ጋር ስትሆን ባህሪህን
በችግር ውስጥ ስትሆን ስሜቶችህን
ፈጣሪ አንተን መባረክ ሲጀምር፣
ጉራህን ተቆጣጠር!
መልካም ቀን
@ethio_tksa_tks
አያወራም ዝምተኛ ነው ፣ እንደሚወደኝ ነግሮኝ አያውቅም ፣ ሳጠፋ እነግርብሃለሁ እያሉ በእሱ ነው የሚስፈራሩልኝ ፣ እንዳላጠፋ ቀድሞ ይገስፀኛል ፣ አጥና እያለ ያዘኛል።
ደብተር ካለቀብኝ ጠጅ ሊጠጣበት ያሰበውን ወይ ለባስ ብሎ ያስቀመጠውን ገንዘብ አልያም የእድር ክፍያውን አዛሎ ደብተር ይገዛልኝ ነበር ።
ሲያመኝ ከወትሮ በተለየ ይቆዝማል ፤ እንዴት ነህ እያለ ትኩሳቴን በእጁ ግንባሬ ላይ መዳፉን እየስቀመጠ ይለካል ፤ እናቴን አሁንም አሁንም ደህና ነው ምንም አይሆንም እያለ እየነገረ ራሱንም እሷንም ያፅናናል ። ጠንከር ካለብኝ ጤና ጣቢያ ይወስደኛል
እያንዳንዱ እንቅስቃሴው ፣ ትኩረቱ ፣ ቁጣው ፣ ትዕግስቱ ፣ ግሳፄው ፍቅር እንደነበር ፤ ነገዬን ለመስራት ሲውተረተር ፣ ሲጨናነቅ ፣ ሲመታኝ ፣ ሲጨቃጨቅ እንደነበር ገብቶኛል
አባቴ ሆይ ያንተን ያህል ባይሆንም እኔም እወድሃለሁ ❤🙏
©️ Adhanom meteku
SHARE @ethio_tksa_tks
በአንድ ወቅት ቦብ ማርሌይ ፍጹም ሴት አለች ብለህ ታስባለህ ተብሎ ሲጠየቅ
"ፍፁምነትን ማን ያስባል?
በመሸ ጊዜ የምናያትና የምታምረው ጨረቃ እንኳን ፍፁም አይደለችም፣ አንዳንዴ ግማሽም ትሆናለች።
ባህሩ በጣም ቆንጆ ነው፣ ነገር ግን ጨዋማ እና ወደ ጥልቅ ከገባህ ደሞ ጨለማ ነው።
ስለዚህ የሚያምር ሁሉ ፍጹም አይደለም፣ ልዩ ነው።
ስለዚህ እያንዳንዱ ሴት ለአንድ ሰው ልዩ ልትሆን ትችላለች።
'ፍፁም' መሆንን አትችልም። ነፃ ለመሆን እና ለመኖር ሞክሩ፣ ሌሎችን ለማስደመም ሳይሆን የምትወዱትን ነገር በማድረግ።"
SHARE||@ethio_tksa_tks
"አስራ አምስት ብር አለህ "??
አለኝ የሰፈራችን ቀፋይ ከ2ቀናት በፊት
"ለምንህ ነው"?አልኩት የሁልጊዜ ሰበቡ ስለሚያስቀኝ
"ባክህ እራሴን ላጠፋ ፈልጌ አሪፍ ገመድ መግዛት ፈልጌ ነው "አለኝ እየሳቀ
ከኪሴ ድፍን 50ብር አውጥቸ እየሰጠሁት"ከሚል ሱቅ አሪፍ ሲባጎ አለልህ 2ሜትሩን በ10ብር ይሸጥልሀል "አልኩት
"ታድያ ለምን 50ብር ለምን ትሰጠኛለህ"?አለኝ ግራ በመጋባት
"በ 20ሲጋራ ግዛበት በ10መናዘዣ ወረቀትና እስክርቢቶ .."ብየው ላልፍ ስል
"የቀረውን 10ብር ምን ላርጋት"?ሲለኝ
"ባክህ ወንድ ልጅ ባዶ ኪሱን አይሞትም።"አልኩት ኮስተር ብየ።
ከስአት ቡሀላ ቀፋየ እራሱን ማጥፋቱን ሰማሁ ።ዛሬ በሰልስቱ ድንኳን ውስጥ ካርታ እየተጫወትኩ ሳስበው የገረመኝ ነገር በኑዛዜው ማብቂያ አካባቢ ሞቱን ስፖንሰር ስላደረግኩ ማመስገኑ ነበር።
ስቀልድ ነው ከምትለዋ ቃል ጀርባ እውነት አለ
የስንቱ ህመም በፈገግታ ሽፋን ስር ሰዶ ይሆን?
እኛስ የስንቱ ሞት ስፖንሰር ሁነን ይሆን?
የስንቱ ቤት ሳናስተውል በወረወርነው ጠጠር ንደን ይሆን ?
ስንቱን ቀለድን ብለን በወረወርናቸው ቃላት ልቡን ሰብረን ይሆን??
አንዳንዴ አጠገባችን ያሉ ስወች ስለሳቁ ብቻ ደስተኛ ናቸው ብለን እናስባለን ህመማቸውን እየነገሩን እንኳን እየቀለዱ ነው ሚመስለን አንዴ እንኳን ቆም ብለን ደህንነታቸውን ብንጠይቅኮ ብዙ የተደበቀ ህመም ያልታየ ስብራት ይኖራል።
ጓደኝነታችን አብሮ ከመዝናናት ያለፈ ነው ??
ምን ያህል ትተዋወቃላችሁ ??
ከሳቁ ከጨዋታው ትንሽ አረፍ ብላችሁ እስኪ የልብ የልባችሁን አውሩ የሰው መድሀኒቱ ሰው አይደል..
ሰናይ ቀን🙏
ቢያንስ አንድ ሰው ያስተምራል ካላችሁ Share @ethio_tksa_tks
እንዲህ ማን ነው ሚያስደነግጠኝ!!
ኒውዚላንድ ውስጥ ነው ። ኤፕሪል አንድ ቀን ፡ በሀገሪቱ ተነባቢ የሆነ አንድ ጋዜጣ እንዲህ የሚል ማስታወቂያ ይዞ ወጣ ።
መኪናዎት ምን አይነት ነው ? አሮጌ መኪና እየነዱ ለመቀየር ግን አቅሞት ስለማይፈቅድ አዝነዋል ? እንግዲያውስ አሮጌ መኪናዎን ይዘው በመምጣት ምንም ያልተነዳ አዲስ ሞዴል BMW መኪና በነጻ ይውሰዱ ። የሚል ማስታወቂያ ነበር ።
እናም ያንን April -1 ( የኤፕሪል ዘ ፉል ቀን) በጋዜጣ የወጣ ማስታወቂያ ሺዎች አነበቡት ። እና ሺዎቹም ፡ ሞኝህን ፈልግ ፡ ማንን መሳቂያ ለማድረግ ነው ብለው ፡ ካምፓኒው ያወጣውን ማስታወቂያ ስቀው አለፉት ።
እና ግን ከብዙ ሺህ ሰወች መሀል አንድ ሴት ፡ በተለየ አይነት መልኩ አሰበች ። ይሄ ነገር እውነት ቢሆንስ ፡ ለምንድነው ሄጄ የማልሞክረው በማለት ማስታወቂያው የወጣበትን ጋዜጣ ይዛ ፡ BMW ካምፓኒ ወደሚገኝበት ቦታ ሄደች ።
ከትልቁ ካምፓኒ እንደደረሰችም ለተቀበለቻት ፀሀፊ ሚስተር ቶምን ፈልጌ ነው አለቻት ፡ ሰውየው መጣ ፡ ሰላምታ ካቀረበላት በኋላም ምን ልርዳሽ አላት .....
" በነጻ መኪና ይሰጣል የሚል ማስታወቂያ አይቼ ነው "
ሰውየው ልክ ይህን ሲሰማ ፡ ልብ በሚያሞቅ መልኩ ፈገግ እያለ Ok መኪናሽ ምን አይነት ነው ሲል ጠየቃት
" አሮጌ ሞዴል ኒሳን " ስትል መለሰች
በጣም ጥሩ በይ የአሮጌ መኪናሽን ቁልፍ ስጭን ፡ አንቺ ደግሞ ይህን የአዲስ ሞዴል BMW ቁልፍ ተረከቢ ብሎ ፡ ከፊት ለፊት ሸራ ለብሳ የተሸፈነችውን BMW መኪና ቁልፍ ሰጣት ።
ሺዎች ባሰቡበት መንገድ ሳይሆን ፡ በተለየ መንገድ አሰበች ። የተለየ ሽልማት ጠበቃት ።
በተለየ መንገድ አስብ !
«ድንጋይ ከሆንክ ተገንባ »
«ዛፍ ከሆንክ ፍሬ ስጥ »
ሰው ከሆንክ አስብ !
©ደራሲ እና ሐያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ
በአንድ ወቅት አንድ ቀልጣፋ እንጨት ቆራጭ በአንድ የስራ መስክ በጥሩ ደሞዝ ተቀጠረ።ስለዚህም እንጨት ቆራጩ የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ እና ጥሩ ስራ ለመስራት ይወስናል።
በመጀመሪያው ቀን ሃላፊው መፍለጫ ሰጠውና የሚሰራበትን ቦታ አሳየው። መቁረጥ የሚችላቸው ዛፎች እነዚህ እንደሆኑ አስረድቶት ሄደ።በርግጥም እንጨት ቆራጩ በመጀመሪያው ቀን 15 ዛፎችን ቆርጦ ማስተካከል ቻለ።
በሁለተኛው ቀን የበለጠ ለመስራት ወስኖ ቢሞክርም ከ10ዛፍ በላይ መቁረጥ አልቻለም ነበር።
በሶስተኛው ቀን ከሁለቱ ቀናት የበለጠ ቢተጋም ከ7 ዛፍ በላይ መቁረጥ አልቻለም።
ቀናቶች ባለፋ ቁርጥ የሚቆርጣቸው ዛፎች መጠን እያነስ እያነስ መሄድ ጀመረ። በስተመጨረሻም አንዲትን ዛፍ መቁረጥ ከበደው። ሞከረ ሞከረ ሊሳካለት አልቻለም።
ይሄኔ ሃይሉን እንዳጣ ተሰማው። ጉልበቴም ከዳኝ ብሎ በማሰብ ላይ ሳለ የሆነ ሌላ ሰው ሲያልፍ ይህንን ሰው አንዲትን ዛፍ ያለጥቅም ሲደበድብ ይመለከተዋል።
"ሰውየው ወደ እንጨት ቆራጩ ጠጋ አለና አንድ ምክር ልምከርህ ትፈቅድልኛለህ?" አለው።
እንጨት ቆራጩም "አሁን ስራ ላይ ስለሆንኩ ምንም መስማት አልፈልግም" ይለዋል።
ሰውየውም እንዲህ አለው" እየፈለጥክበት ያለከው ፋስ(መፍለጫ) ስለት የለውም ዶምድሟል። ከጥቅም ውጭም ሆኗል። ይህን አውቀህ እረፍት በማድረግ የምትሰራበትን #ፋስ ልታስለው ይገባል" አለው።
ይሄኔ ይህ እንጨት ቆራጭ ቆም ብሎ አሰበ። እንዲህም አለ"እውነትም ፋሴን አሞረድኩትም። ዛፎችን በመቁረጥ ቢዚ ስለነበርኩ" ብሎ ፋሱን በእርጋታ ሞረደና ከድሮ በተሻለ መልኩ ስራውን በአግባቡ ማከናወን ቀጠለ።
በህይወትህ ውስጥ መለወጥ ያለብህን ነገር ለመለወጥ ግዜ አትስጥ። ሁሉንም ነገር በጊዜ ለማከናወን ሞክር።
@ethio_tksa_tks
እናትህን እያት!
ፊቷ ላይ ያለ እያንዳንዱ ጥቁረት ላንተ የተከፈለ ነው!
የመሸነፍ መብት የለህም!
የማቋረጥ መብት የለህም!
አኩራት!
አንድ ቀን " ይህን ሁሉ ያደረግኩት ላንቺ ነው!"
ትላታለህ!
ድካሟን በከንቱ አታስቀረው!
ተነስ! ተፋለም! አሸንፍ!
በቅንነት Share በማድረግ ይተባበሩን
@ethio_tksa_tks
አንድ ድሀ ሰውዬ እድሜ ልኩን ለፍቶ ያጠራቀመውን ሁሉ አፍስሶ ለብዙ አመታት ቤት ሲሰራ ይቆይና ያጠናቅቀዋል።
ሆኖም ግን በቀጣዩ ቀን ቤተሰቦቹን ይዞ ሊገባው ሲዘጋጅ ቤቱ ተደርምሶ ወድሞ ያድራል።
በነጋታው ጠዋት የአካባቢው ሰዎች በቦታው ተሰባስበው የሰውየውን የብዙ አመት ልፋትና በቤቱ ውስጥ ለመኖር የነበረውን ጉጉት ስለሚያውቁ እያዘኑ አንዳንዶች ሲያየው እጅግ በጣም ያዝናል! ሌሎች ደግሞ አይ ራሱን ያጠፋል! ሲባባሉ ድሀው ሰውዬ ደረሰ።
ሰውዬው ከፍርስራሹ ፊት በርከክ አለና ድምፁን ከፍ አድርጎ "ጌታ ሆይ ዛሬ እንዲወድም ስላደረግከው አመሰግንሀለሁ! በእጅጉ እንደምትወደኝም አረጋግጫለሁ!" እያለ በደስታ ማመስገን ጀመረ።
ያዝናል ወይም ራሱን ያጠፋል ብለው ሲጨነቁ በደስታ ተሞልቶ ሲያመሰግን ያዩት የአካባቢው ሰዎችም "ለምንድን ነው በደስታ ተሞልተህ የምታመሰግነው? የወደመው እኮ ከልጅነት እስከሽምግልና ያጠራቀምከውን ገንዘብ፣ ብዙ ጉልበትና ጊዜ አፍስሰህ የሰራኸው ቤትህ ነው?" ብለው ጠየቁት።
ሰውዬውም በደስታ እንደተሞላ እንዲህ አላቸው፦
"አያችሁ ወገኖቸ! አስባችሁታል ይህ ውድመት ነገ ማታ ከገባንበት በኃላ ቢከሰት ኖሮ ምን እንደሚፈጠር?
እኔም፣ ልጆቸም፣ ባለቤቴም፣ የቤት ዕቃየም፣ የቤት እንስሳቶቸም ይህኔ አንኖርም ነበር እኮ!" አላቸው። ያኔ የደስታው ምክንያት ሲገለጥላቸው እነሱም በሰውየው አስተዋይነት ተደንቀው አብረው ፈጣሪን አመሰገኑ ይባላል።
ባጣነው ነገር ከማልቀስ ይልቅ በአተረፍነው ነገር መደሰት ይሻላል። በጎውን ነገር ስለማናስተለው ነው እንጅ ሁሉም ነገር የሚሆነው ለበጎ ነው! አስተዋይ አእምሮ ይስጠን 🙏።
SHARE @ethio_tksa_tks
ፈጣሪህን ዘወትር እንዲህ በለው፦
ፈጣሪዬ ሆይ፦
የተጣልኩ ሲመስለኝ👉 ፍቅር
ጉልበቴ ሲዝል👉 ብርታት
ስፈራ👉 ድፍረት
ሞኝ ስሆን👉 ብልሃት
ብቸኛ ስሆን👉 ምቾት
ስገፋ👉 መጠጊያ
ስናወጥ👉 ስክነት
ሁነኝ።
አሜን!
@ethio_tksa_tks
Lao tzu በአንድ ዘመን ይህንን ድንቅ ንግግር ተናግሮ ነበር ።
ሀሳብህን ልብ በል ። ምክንያቱም ሀሳብህ ንግግርህ ይሆናል ። ንግግርህን ልብ በል ምክንያቱም ንግግርህ ተግባርህ ይሆናል።ተግባርህን ልብ በል ምክንያቱም ተግባርህ አመልህ ይሆናል። አመልህን ልብ በል ምክንያቱም አመልህ መገለጫህ ይሆናል። መገለጫ ባህሪህን ልብ በል ምክንያቱም ባህሪህ የአንተነትህ ወይም የመኖርህ ምክንያት ይሆናል ።
የመንገድህን አቅጣጫ ካልቀየርክ የመረጥከው መንገድ መጨረሻህ ሆኖ ልትቀር ትችላለህ። ጊዜ የተፈጠረ ነገር ነውና "ጊዜ የለኝም" ብለህ ስትናገር አልፈልግም አያልክ አንደሆነ ነው የሚቆጠረው።አይምሮህ አስኪረጋጋ ፣ የተናወጠውም ውቂያኖስ አስኪረጋ ለመጠበቅ ትግስቱ ይኑርህ።
አውነትም ራሷን አስክትገልፅስ በተስፋ ጽና።
መድረስን ትመኛለህ?
አንግዲአውስ መቆምህን አቁምና ሩጥ።
መገኘት ትፈልጋለህ?
አንግዲአውስ መሮጥህን አቁም።
ማውራት በሌለብህ ሰዓት አፍህን ዝጋ። ስሜቶችህም በመንገድህ አንዳይገቡ ከልክላቸው።ዱልዱምነትህን ሳለው ፣ አስራቶችህም ፍታ፣ አቧራውንም አፅዳ። ህይወት የተፈጥሮና የድግግሞሽ ክትትል ነች።
አነዚህን ለዉጦች አትግፋቸው ። ምክንያቱም መለወጥ ባለብህ ሰዓት ካልተለወጥክ ሁአላ* ቀር ሆነህ ትቀራለህ።ስለዚህ አውነታው አውነት አንዲሆን ፍቀድለት።
ነገሮች በራሳቸው መንገድ ወደየትኛውም አቅጣጫ ቢሆን ይነፍሱም ዘንድ ልቀቃቸው ።
@ethio_tksa_tks
አንዳንድ ፎቶ ደግሞ አለ 🙌🏼
👇🏾
በህይወትህ አድካሚ ናቸው ብለህ የፈረጅካቸውን ነገሮች ዋጋ የሚያሳጣ
ከአልጋህ ተነስተህ በእግርህ ለመቆም የያዘህን የስንፍና መንፈስ የሚሰብር
ዙርያህን አይተህ ጎሎብኛል ብለህ በተነጫነጭክበት ነገር አምላክህን ይቅርታ ጠይቀህ ለምስጋና ቀና የምትልበት
ምን ያህል ብርቱ ነሽ?
ምንድነው የጥንካሬህ ልኬትስ?
❤️🙌🏼
@ethio_tksa_tks
አንስታይን ያለ መነፅሩ ማንበብ ይቸግረዋል። አንድ ጊዜ ወደ ምግብ ቤት ገብቶ እንደተቀመጠ መነፅሩ እንዳልያዘ ይረዳል። በመሃል አስተናጋጁ የሚያነብበትን ሜኑ አምጥቶ የፈለገውን እንዲመርጥ ነገረው። አንስታይን ግን ለአስተናጋጁ መልሶ አንተ አንብብልኝ በማለት ይሰጠዋል። ይሄኔ አስተናጋጁ አንስታይን ላይ እየሳቀ “ይቅርታ ጌታዬ እኔም እንዳንተ መሀይም ነኝ!” 🤭
አርምሞ
Share @ethio_tksa_tks
አንድ የሀብታም ልጅ እናቱ ከድሀ ጎረቤቶቻቸው አንድ ስኒ ጨው እንዲሰጧት ስትጠይቅ ሰማና ቤታቸው ከተመለሱ በኃላ.....
ልጁ፡- "እንዴ እማየ! ትላንት ለአንድ ወር የሚበቃ ጨው ገዝተሽ እያለ እንዴት እነዚያ ምስኪን ጎረቤቶቻችንን ጨው ትጠይቂያቸዋለሽ?" አላት።
እናቱም፡- "አየህ ልጀ! እነሱ ድሆች ስለሆኑ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ሁሌም ከኛ ይጠይቃሉ። አንድ ስኒ ጨው የጠየኳቸው ጨው ርካሽ ስለሆነ እንደማያጡና እንደማይጎዳቸው ስለማውቅና እኔም ከነሱ የምፈለገው ነገር እንዳለ ተሰምቷቸው ከኛ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ሳይሸማቀቁ ዘና ብለው እንዲጠይቁን ለማስቻል ነው!" አለችው።
ፈጣሪ እንዲህ ያለውን አስተዋይ አእምሮና ደግ ልብ ይስጠን!🙏
@ethio_tksa_tks
ነገ የማን ተራ እንደሆነ አታውቅም 👦
በአንድ ወቀት እንስሳቶች በሚኖሩበት ፖርክ ውስጥ አንዲት በግ በሆነ አካባቢ ስታልፍ አንድ አንበሳ በሆነ ኬጂ ተቆልፎበት በጓ እንድታድነው ለመናት። በጓ ግን ጥያቄውን አልተቀበለችውም። አንበሳው ደጋግሞ ሲለምናትና እንደማይነካት ሲያረጋግጥላት በመጨረሻ እሺ በማለት ቁልፉን ከፈተችለት።
ነገርግን አንበሳው ያለ ምግብ ብዙ ቀን ስለቆየ እርቦት ነበርና በግዋን ሊበላት ያዛት። በግዋ ግን ፈጥና ቃልኪዳናቸውን አስታወሰችው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉ ሌሎቹ እንስሳቶች በዚያ ሲያልፉ የሆነውን መጠየቅ ጀመሩ። ሁለቱም የየራሳቸውን መከራከሪያ ሃሳብ አቀረቡ። ነገርግን ሁሉም እንስሳት በአንበሳው ፊት ሞገስ ለማግኘትና ለመወደድ እንዲሁም አንበሳውን በመፍራት ከአንበሳው በኩል ወገኑ። በመጨረሻም ኤሊ መጣች።ሆኖም እሷም የሆነውን ሁሉ ከሰማች በኋላ ከሌሎቹ በተለየ መልኩ ጥያቄ መጠየቅ ጀመረች።
አንበሳውን በግዋን ሳታድንህ በፊት የት እነደነበር ጠየቀችው? አንበሳውም ታስሮበት ወደነበረው ቦታ አሳያት። ከዚያም ቀጥላ በጉ የነበረበትን ቦታ ጠየቀች። ያንንም አሳያት። ከዚያም በመቀጠል ለአንበሳው እስኪ ምንያህል አስቸጋሪ እንደነበር መጀመሪያ የነበርክበት ቦታ ግባ እና እንይ አለችው። አንበሳውም እንደገባ ወዲያው ኤሊዋ አንበሳው ላይ ቆለፈችበት።
ሌሎቹ እንስሳቶች ተገርመው ኤሊዋ ለምን እነደዚያ እንዳደረገች ጠየቋት? እሷም ምላሺ ሰጠች። ዛሬ በግዋን እንዲበላ ከፈቀድናለት ነገ ደግሞ ሲርበው ከመሃከላችን ማንን እንደሚበላ አናውቅም አለች።
ብዙሃን ናቸው ብለህ ፍትህን አጉድለህ ከግፈኞች ጋር አትወግን። ምንም እንኳ እውነት ሃብታም ባታደርግህም ነጻ ግን ታወጣሃለች።
ዛሬ አንተን በቀጥታ ስለማይነካ ክፋትን ብትደግፍም ነገ የማን ተራ እንደሆነ አታውቅም..🤔
እናስተውል
Share @ethio_tksa_tks
የህይወት 3ቱ አስተማሪዎች
✔️የተሰበረ ልብ
✔️ባዶ ኪስ
✔️ወድቀት
SHARE||@ethio_tksa_tks
ፀሎቴ አልተሰማም
~~
አንዲት ልጅ ንሰሀ አባቷ ጋር ትሄድና " አባቴ ፈጣሪን ትዳር ስጠኝ ብዬ እፀልያለሁ ለዛውም ስፀልይ ከእሁድ እስከ እሁድ ከቤቴ ሳልወጣ ሳላቋርጥ እፀልያለሁ ግን አባቴ ፀሎቴ አልተሰማም እስካሁን ትዳር አልያዝኩም " አለቻቸው ።
ንሰሀ አባቷም ካዳመጧት በኋላ " ልጄ ከእሁድ እስከ እሁድ እየፀለይሽ ነው ታድያ ባልሽን የት ታገኝዋለሽ በይ ባይሆን እንኳን እሁድን ፍለጋ ውጪ " አሏት ፡
ሰዎች ፀሎታችን ከተግባር ጋር ካልታገዘ ከሰማይ የሚወርድ ነገር የለም ፡ ፈጣሪ የእጆቻችንን ፍሬ ነው የሚባርከው ፡ ስንንቀሳቀስ ነው።
~~
Share @ethio_tksa_tks
💡ሁሌም ቢሆን ጥቁር ብቻ መስሎ ከሚታይህ ቀን ጀርባ የታዘለ ደማቅ ብርሃን አለ፣ ሊገፈትሩህ ከበረቱ እልፍ ክንዶች ኋላ ሊያቀኑህ የቆሙ ልስልስ መዳፎች አሉ፣ አንሸራትተው ከሚደፉህ ሃሳቦች ባሻገር በተስፋ ሞልተው የሚያቆሙህ ቅን ሀሳቦች ተሰልፈዋል።
💎 ያላየኸው ነገ ብዙ አዲስ የህይወት ገፆችን ይዞ ይጠብቅሃል ካጎነበስክበት ቀና ትላለህ ሀዘንህ በሳቅ ይተካል፣ ጉስቁልናህን ወዝ ይሽረዋል፣ ይህ እንዲሆን ግን ነገን ጠብቀው ፦ ተስፋ አትቁረጥ ነገ ያንተ ሲሆን ብቻ አሸናፊ ነህ::