ethio_tksa_tks | Unsorted

Telegram-канал ethio_tksa_tks - ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

6061

እንኳን ደህና መጡ። በቴሌግራም ውስጥ የታዋቂ ሰዎች ማለትም 💥አርስቶትል 💥አብርሀም ሊንከን 💥አልበርት አንስታይን 💥ማህተመ ጋንዲ... እንዲሁም የሌሎችም አባባል የሚያገኙበት ቻናል🎯 ሲሆን አላማችንም ሰዎች በሚያነብቡት ጥቅስ የአስተሳሰባቸውን አድማስ ማስፋት ነው። ስለመረጡን እናመሰግናለን 🙏 Contact፦ @onajonah

Subscribe to a channel

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

አልበርት አንስታይን የካቲት 5 1930 ዓ.ም ላይ ለልጁ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ላከለት፦

“ህይወት ብስክሌት እንደመንዳት ናት ሚዛንህን ለመጠበቅ መንቀሳቀስህን መቀጠል አለብህ። የስኬት ሰው ብቻ ለመሆን አትሞክር ይልቅ ዋጋ ያለው ሰው ለመሆን ሞክር። ምክንያቱም ስኬት የሚለካው በምትወስደው ነገር ሲሆን ዋጋ የሚለካው ደግሞ በምትሰጠው ነገር ነው።

ሞኝ ማለት አንድ አይነት ነገርን ደጋግሞ ሰርቶ የተለየ ውጤት የሚጠብቅ ነው። የተለየውን መንገድ ተከተል አዲስ ነገር ታገኛለህ። አትቀመጥ ምክንያቱም ምድራችን አደገኛ የሆነችው በክፉ ሰዎች ስራ ሳይሆን ምንም በማይሰሩ ሰዎች ውጤት ነው።

ትምህርት እውነትን አያስተምርም ይልቅ የአእምሮ አስተሳሰብን ማበልጸጊያ ልምምድ ነው። የሌሎች ጫጫታ የአንተን የውስጥ ድምፅ እንዲውጠው ማድረግ የለብህም። ማንም ሰው ባንተ ላይ ገደቦች እንዲጥል አትፍቀድ፤ ገደብህ በራስህ ያወጣኸው የህይወት መመርያ መሆን አለበት!።”


(📷 ፎቶው በ1993 አንስታይን በ54 አመቱ ብስክሌት እየነዳ የሚያሳይ ማስታወሻ ነው)

አርምሞ

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

"ቅቤ፣ ቅቤ።.....ቅቤ!"
"ባለ ቅቤ"
"አቤት"
"ሁለት ኪሎ ቅቤ ለቅዳሜ አምጣልኝ"
"እሺ"
"አደራህን"
"ኧረ ግዴለም፣ ደንበኝነት ለመቼ ነው?"
"አደራህን፣ አደራህን"
"ምን ሆነዋል? ግዴለም እያልኮት"
"አደራ ያልኩህ ለምን እንደሆነ አላወከውማ"
"ለምንድንነው?"
"ሙዙን ጠቃጠቆ አድርገው"

ውልብታ /በዓለማየሁ ገላጋይ/

Share @ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ስብዕና በልጅነት እንደተቦካ ሲሚንቶ፣ በአዋቂነት ደግሞ እንደደረቀ አርማታ ነወ።

የብዙ ሰው ስብዕና እንደተቦካ ሲሚንቶ በልጅነቱ በትክክል የሚቀርፀው ካላገኘ ተንሻፎና ተዛብቶ ያድጋል። እድሜው ከገፋ በሁዋላ ደርቆ ስለሚጠነክር፣ ብዙ ጊዜ ለመከራ መዶሻና ለምክር መጥረቢያ አዳግቶ አገር ያጠፋል።

ዶክተር ምህረት ደበበ

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ያለማቋረጥ ሌላ ነገር እንድትሆን በሚጥር ዓለም ውስጥ ራስህን መሆን ትልቁ ስኬት ነው።"


©Ralph Waldo Emerson

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ያለፈውን መለወጥ አይችሉም ፣ ግን ዛሬ ብልህ ውሳኔዎችን በማድረግ ለወደፊቱ ጥሩ ስጦታዎችን መላክ ይችላሉ።


Share||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ድርጊት ሁልጊዜ ደስታን ላያመጣ ይችላል፣ ነገር ግን ያለ ድርጊት ምንም ደስታ የለም።"

©William James

SHARE @ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ይችላል

"እውነት ነው።
ብዙ ነገር ተስፋ ያስቆርጣል።
ስራ አታገኝም!
ብታገኝም ብሩ አይበቃህም!
ዙሪያው ሁሉ ጨልሞ
ተስፋ የሌለህ መስሎሃል።

እና በቃ አልችልም ብለሃል።

ግን ከዚህ ሁሉ በላይ ፈጣሪ አለ!

ፈጣሪ አይችልም ትላለህ?
አትልም።

ይችላል!

ያመንከው ላይ ተስፋ አትቁረጥ።"

ፈጣሪን ተማምነህ ወደህልምህ መጓዝን ቀጥል

መልካም ቀን

share @ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ቀይሩ

👉 ክፉን በጥሩ
👉መጥፎ ሐሳቦችን የንጽህና ነገሮችን በማሰብ
👉ኃጢአትን በንስሐ
👉አድልኦን ሁሉንም በመውደድ
👉ኩራትን በትህትና


ሰናይ ቀን

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

Some goodbyes set you free

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ፈጣሪህን እንዲህ በለው

ፈጣሪዬ ኾይ

በማይታወቀው ነገ ውስጥ
"መልካሙን"

በክፉ ዘመን
" ተስፋ ማድረግን"

በደስታ ጊዜ
"መረጋጋትን"

ላለፈው ትናንት
"ይቅር ባይነትን"


ስጠኝ!!!

አሜን።

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ሞኝ ሰው በሩቅ ደስታን ይፈልጋል; ጠቢብ ከእግሩ በታች ያበቅላል.


© James Openheim

    SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

አንድ ዛፍ ጫካን ማስጀመር ይችላል

አንድ ፈገግታ ወዳጅነትን ይችላል

አንድ እጅ አንዲት ነፍስን ሊያነሳ ይችላል

አንድ ሻማ ሙሉ ጨለማን ሊገፍፍ ይችላል

ዛሬ ያንን አንድ ሰው ሁን

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

#ለፈገግታ

ከእናቱ ጋር ፊልም ሲያይ የቆየው ልጅ ወደ እናቱ ዞር ብሎ ''እናቴ አኔ ሳድግ እንደ አክተሩ 7 ሚስት ነው ማገባው" አላት እተተኮላተፈ። እናት ፈገግ ብላ "ምን ያረጉልሀል ሰባት ምታገባው አንድ አይበቃህም?" አለችው።
"አይ እናቴ ሰባት ነው ማገባው። የመጀመሪያዋ ምግብ ታበስልልኛለች፣ ሁለተኛዋ ልብሴን ታጥብልኛለች ......... እያለ ሲዘረዝር እናት ግራ ተጋብታ "ታድያ የትኛዋ ናት አብራህ የምትተኛው?' አለችው። ልጁም ወዲያው ያለምንም ማንገራገር "የምተኛውማ ካንቺ ጋር ነው ከእናቴ ጋ" አላት .
እናት ደስ አላት የኔ ልጅ እያለች እቅፍ አርጋ ሳመችውና "ታዲያ ሚስቶች ከማን ጋር ሊተኙ ነው?'' አለችው በስስት እያየችው።
"እነሱማ ከአባቴ ጋር ይተኛሉዋ : አላት
እናት
ስራ ይዞ ወሬውን ሲከታተል የተበረው አባት ደሞ ብድግ ብሎ ልጁን አቀፈውና "ተባረክ ልጄ ብሩክ ሁን ያሰብከው ይሳካልህ'
😂

Share @ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ምላሽ የመስጠት ጥበብ


አንድ አህያ ከመስጂድ ፊት ለፊት ሞቶ ተገኘ። ይህን የተመለከቱት ኢማም ከንቲባውን ጠርተው እንዲህ አሉት፡-“ክቡር ፕሬዝዳንት አንድ አህያ ከመስጂድ ፊት ለፊት ሞታለች”

ከንቲባው፡-“ሼኽ ሆይ ከኔ ምን ፈልገው ነው ታድያ?”

ኢማሙም መለሱ፡-“የማዘጋጃ ቤቱ ሃላፊዎችን ጥራቸው። ሰራተኞቹ መጥተው አህያውን ከመስጂዱ ያንሱልን።”

ከንቲባው በኢማሙ ላይ እየተሳለቀ፡-“ያ ሼይኹ እኔ በሃይማኖታችን እንደተማርኩት ከሆነ እናንተ ናችሁ ሟችን አጥባችሁ የመቅበር ግዴታ ያለባችሁ”

ኢማሙም በተረጋጋ መንፈስ መለሱ፡-“ልጄ የተናገርከው ሁሉ እውነት ሆኖ ሳለ አህያዋ መሞቷን ግን ለአንተ መናገር ነበረብኝ ምክንያቱም እኛ አጥበን የመቅበር ግዴታ እንዳለብን ሁሉ፤ የሟች ቤተሰብ የቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ ለመጨረሻ ግዜ ሬሳውን እንዲሰናበት የማሳወቅ ግዴታም አለብን”
🙂

አርምሞ

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ለፈገግታ

ፍልስፍና ሲማር የነበረው ልጅ ትምህርቱን አጠናቆ ቤተሰቡ ለመዘየር ወደ ቀየው ይሄዳል። አባትም ደስተኛ ሁነው ዶሮ አርደውና አዘጋጅተው ይጠብቁታል። ቃለ ምልልሳቸው ከብዙ በጥቂቱ ይህ ነው።

አባት፦ እና አሁን በቃ ዶክተር ሁነሀልና የታመሙ ሰዎችን ማከም ጀመርክ እንዴ?

ልጅ፦ አይደለም አባቴ እኔ ዶክትሬቴን የያዝኩት በፍልስፍና ነው፤ ከህክምና ጋር አይያያዝም።

አባት፦ ደግሞ የሱ ጥቅም ምንድን ነው?

ልጅ፦ ላስረዳህ አሁን እዚህ ጋ የምታየው ዶሮ አንድ ዶሮ ብቻ ነው አይደል?

አባት፦ አዎ

ልጅ፡- በፍልስፍና እውቀቴ መሠረት ግን እዚህ ላይ ያለው ዶሮ አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት ናቸው ብየ ላሳምንህ እችላለሁ።

አባት፦ "ማሻአላህ ልጄ ቀድመህ ካሁኑ አሳመንከኝ እኮ"

ልጅ፦ እንዴት?

አባት :- ጠረንጴዛው ላይ ያለውን አንድ ዶሮ እያነሱ "እኔ ይህኛውን ዶሮ እበላለሁ አንተ ካገኘኸው ሁለተኛውን ዶሮ መብላት ትችላለህ 😂።


@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

#ለፈገግታ

..ሙላ ነስሩዲን በአንድ ወቅት ከወዳጁ ትልቅ ማሰሮ ተበደረ።ልክ በ3ተኛው ቀን ማሰሮውን ሲመልስ ግን ከሌላ ትንሽዬ ማሰሮ ጋር ነበር።ግራ የተጋባው ጓደኛው ምን እንደሆነ ሲጠይቀው ነስረዲን ቀልጠፍ ብሎ"ማሰሮህ እኔ ጋር እያለች ልጅ ወልዳ ነው አሳድገው"አለው።በሞኝነቱ የተገረመው ጓደኛው በደስታ ተቀበለው። ልክ በሣምንቱ ነስረዲን በድጋሚ ትልቁን ማሰሮ ተበደረ፤አሁን ግን ሳይመልስ ቀረ። ይህ ያሳሰበው ጓደኛው ቤቱ ሄዶ ማሰሮውን መልስ ሲለው ሙላ እያዘነ"ማሰሮህን እኮ ሞታ ቀበርኳት"አለው። በንዴት የጦፈው ጓደኛው ለድብድብ ሲጋበዝ ነስሩዲን እየሳቀ" ማሰሮህ ወለደች ስትባል ስቀህ ከተቀበልክ ሞተች ስትባል ምን አናደደህ?" ብሎ ጥሎት ገባ።
የአያ ሙላ የህይወት ፍልስፍና ዎች ሁሌም ተዝናኖት ይፈጥራሉ!

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

የሰራህበትን ታገኛለህ !

ነገሮች ሁሉ የሚሆኑት በምክንያት ነው ነገ የተሻለ እንጂ የባሰ እንዳይሆን የቻልነውን ሁሉ ካደረግን ዛሬን በዚህ መልኩ ያለፍነው መልካሙን ነገ ለመስራት እንደሆነ አንጠራጠር !

"ፈጣሪ ለሁሉም የለፋበትን እና የምኞቱን ይሰጠዋል "

መልካም ቀን

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

Everything you need 🔥🔥🔥

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ማቴ 21:9 የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም፡— ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም፡ እያሉ ይጮኹ ነበር።


እንኳን አደረሳችሁ ቤተሰብ ❤️

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

እውነተኛው ጥያቄ ከሞት መኋላ ሂወት አለ ወይ አይደለም፣ትክክለኛው ጥያቄ ከመሞትህ በፊት በህይወት አለህ ወይ የሚለው ነው

አለመኖር
ዳዊት ወንድምአገኝ🤌🏿

@wlbta
@wlbta

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

#ለፈገግታ

ሰውዬው ጠዋት ወደ ስራ ሲሄድ ሚስቱ የረሳቸውን ነገሮች ሁሌም ታስታወሰዋለች። አንዳንዴ የመኪና ቁልፍ ሌላ ጊዜ መንጃ ፈቃድ መጣሉን ትነግረዋለች። ብዙ ጊዜ ግን ሞባይሉን ትቶ እየሄደ ጠርታ ትሰጠዋለች። «በቃ አረጀህ ማለት ነው !» እያለች ታፌዝበታለች።

«እንዲህ የሷ መቀለጃ ሆኜ መቀጠልማ አልችልም» ብሎ ለችግሩ መፍትሄ ለማበጀት ቆረጠ። ከዚህ በፊት የሚረሳቸውን ነገሮች አንድ በአንድ በዝርዝር ማስታወሻ ደብተር ላይ አሰፈረ። ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ ማስታወሻ ደብተሩን ከፍቶ የጻፋቸውን ዕቃዎች መፈተሽ ጀመረ። ምንም የረሳው ነገር እንደሌለ ሲያረጋግጥ በፈገግታ ታጅቦ ቤቱን ለቆ ወጣ። የድል ስሜት ተሰማው። መኪናውን አስነስቶ ገና ከመንቀሳቀሱ ባለቤቱ እንደወትሮው ደወለችበት። «እባክሽን ዛሬ አንድም የረሳሁት ነገር ስለሌለ ሆን ብለሽ ከስራዬ እንዳታስተጓጉሊኝ» ሲላት ምን ብትለው ጥሩ ነው ?? ...

«ባክህ ዛሬ እሁድ ነው ስራ የለም ወደ ቤትህ ተመለስ» 😂

share @ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

Try it out 😕😕😕
😤😤😤😤😤

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ህይወት አጭር ናት

አንዲት አሮጊት ሴት አውቶብስ ላይ ወጥተው ተቀመጡ። በቀጣዩ ማቆሚያ ላይ አንዲት ወጣት ሴት ብዙ ቦርሳዎችን ይዛ እየተጣደፈች ገባች። ከአሮጊቷ ሴት አጠገብ ተቀምጣ በቦርሳዎቿ ገጨቻቸው።

አሮጊቷ ዝም አሉ፣ ነገር ግን ወጣቷ አስተውላ "በቦርሳዎቼ ስገጭዎት ለምን ምንም አላሉም?" ብላ ጠየቀች።

አሮጊቷ ፈገግ ብለው "እንዲህ ላለው ትንሽ ነገር መጨቃጨቅ አያስፈልግም። ከአንቺ ጋር ያለኝ ጉዞ አጭር ነው - በቀጣዩ ማቆሚያ እወርዳለሁ።" አሉ።

ይህ መልስ ሊታወስ የሚገባው ነው፡
"አብረን የምንቆየው ጊዜ በጣም አጭር ስለሆነ በትናንሽ ነገሮች መጨቃጨቅ አያስፈልግም።"

ህይወት በንዴት፣ በቅናት፣ ቂም በመያዝ ወይም አላስፈላጊ በሆኑ ክርክሮች ጊዜን ለማባከን በጣም አጭር ናት።

አንድ ሰው ስሜታችሁን ጎዳው/ጎዳሽ? ተረጋጉ። ህይወት በጣም አጭር ናት።

አንድ ሰው ከዳችሁ፣ዋሻችሁ ወይም አሳፈራችሁ በጥልቀት ተንፍሱ።ተዉት ህይወት በጣም አጭር ናት።

አንድ ሰው ያለ ምክንያት ሰደባችሁ ጉልበታችሁን አታባክኑ። ችላ በሉት። ህይወት በጣም አጭር ናት።

ጎረቤት መጥፎ ነገር ተናገሩ? ይዛችሁ አትቀመጡ ይቅር በሉ ቀጥሉ። ህይወት በጣም አጭር ናት።

በዚህ ዓለም ላይ የማንም ሰው ጉዞ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ማንም አያውቅም። የማቆሚያው ጊዜ መቼ እንደሚመጣ ማንም አያውቅም። ለዚህ ነው በዙሪያችን ያሉትን ሰዎች ማድነቅ፣ ደግ መሆን እና በቀላሉ ይቅር ማለት ያለብን።

ፍቅርን፣ ትዕግስትን እና ደስታን እንምረጥ - ምክንያቱም አብረን የምናደርገው ጉዞ በጣም አጭር ነው።

ፈገግታችሁን አካፍሉ… ምክንያቱም ህይወት አጭር ናት። ❤️

መልካም ምሽት

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ይቺ ፍቅር የሆነች ሚጢጢ ህጻን የጋዛ ነዋሪ ናት። እና አይደለም ምግብ የፖሊዮ ክትባት እንኳን እንዳይገባ በከለከለው የእስራኤል ማእቀብ ምክንያት፣ የምግብ እጥረት ተከስቶ ርቧት ነበር ።
.....
እርቧት ስታለቅስ ቆይታ ይህን ምግብ ከማግኘቷ አንድ አለም አቀፍ ጋዜጠኛ የዚህች ምስኪን ህጻን ነገር አሳዝኗት ልታቅፋት ተጠጋቻት  ።
........
ጋዜጠኛዋ አይን ላይ እንባ ነበር ። እና ይህን ያየችው ህጻን ልክ እንደ እሷ፡ ርቧት የምታለቅስ ለመሰለቻት፣ ጋዜጠኛ ምግብ  ለመስጠት እጇን ዘረጋች ❤️

Share @ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ሰውየው ከስሩ እባብ እንዳለ አያውቅም።

ሴትየዋ ሰውየውን የሚጨፈልቅ ድንጋይ እንዳለ አታውቅም።

ሴትየዋ እንዲህ ታስባለች፦ “ልወድቅ ነው! እባቡ ሊነድፈኝ ስለሆነ መውጣት አልችልም! ሰውየው ትንሽ ተጨማሪ ጉልበት ተጠቅሞ ለምን ወደ ላይ አይጎትተኝም!”

ሰውየው እንዲህ ያስባል፦ “በጣም እየተሰቃየሁ ነው! ግን አሁንም በምችለው መጠን እየጎተትኩሽ ነው! አንቺስ ትንሽ አጥብቀሽ ለመውጣት ለምን አትሞክሪም!?”

ሞራሉ ወይም ትምህርቱ—ሌላው ሰው ምን ዓይነት ጫና ውስጥ እንዳለ ማየት አትችልም፣ ሌላው ሰው ደግሞ አንተ ውስጥ ያለውን ህመም ማየት አይችልም።

ይህ ህይወት ነው፣ በስራ፣ በቤተሰብ፣ በስሜት ወይም በጓደኞች መካከል ቢሆን፣ እርስ በርስ ለመረዳዳት መሞከር አለብን። በተለየ መንገድ፣ ምናልባትም በግልጽ እና በተሻለ ሁኔታ ማሰብን ተማሩ። ትንሽ ማሰብ እና ትዕግስት ትልቅ ለውጥ ያመጣል።


@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

https://vm.tiktok.com/ZMBQsCTwC/

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

አምልጥ፦
👉 ወደ ጥል ከሚያመራ ወሬ
👉 አቅደው ከሚያሳንሱህ ሰዎች
👉 ዋጋህ ከማይገባቸው ወዳጆች

ተው፦

👉 ሁሉንም ላስደስት ማለትህን
👉 መስዬ ልኑር ባይነትን
👉 አልችልም ማሰብን

ቻልበት፦
👉 ፈጣሪ ፈርቶ መኖርን
👉 ራስን ተቀብሎ
ለራስና የሚወዱት መኖርን

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

#ስብሃት ጫት ሲቅም የደረሰ አንድ ወጣት ነው አሉ “ይመክረዋል። ጋሽ ስብሃት አይቃሙ።መቃም ሱስ ያሲዛል።

#እኔ አልቅምም!

ስብሃት ዝም ይልና ሲጋራ ይለኩሳል።ወጣቱ ምክሩን

ይቀጥላል። 'ጋሽ ስብሃት አያጭሱ። ማጨስ ሡስ ያሲዛል።

እኔ አላጨስም!

ስብሃት ዝም ይልና ቡና ያዝዛል። "ትጠጣለህ?"

ወጣቱን ሊጋብዝ፡

"ቡና አልጠጣም ሱስ ያሲዛል!

ስብሃት ዝም ይለዋል። በመጨረሻ ሁሉም አልቆ መጠጣት ሲጀመር ወጣቱ "መጠጥ ሱስ ያሲዛል አይጠጡ። እኔ ሱስ እንዳዪዘኝ አልጠጣም' ሲለው

ስብሃት ገረፍ አድርጎ አይቶት "ከሱስ አላመለጥክም፤ሱስ የመፍራት ሱስ አለብህ” አለው፡፡


እኛም ምናልባት ሱስ የለብንም ብለን ሳናውቀው ሱስ የሆነብን ነገር አለ

share @ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

የሆስፒታል አልጋ ላይ አይደለህም!

እስር ቤት ውስጥ አይደለህም!

ከመሬት በታች አይደለህም!

እስኪ ለ1 ደቂቃ ፈጣሪህን አመስግን!!

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

አይገርምም የሆነ ግዜ እንቅልፋችንን ሰውተን ስናወራቸው የነበሩ ሰዎች አሁን ግን እነሱን ላለማየት በግዜ መተኛታችን ምክንያት ናቸው የሆነ ጊዜ በጣም ሰው የማመናችን ምክንያቶች አሁን እራሳችንን መውደዳችን ምክንያቶች ናቸው በጣም ልናያቸው የምንፈልጋቸው ሰዎች አሁን እነሱን አያሳየን ብለን የምንፀልይላቸው ሰው ሆነዋል💔

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…
Subscribe to a channel