እንኳን ደህና መጡ። በቴሌግራም ውስጥ የታዋቂ ሰዎች ማለትም 💥አርስቶትል 💥አብርሀም ሊንከን 💥አልበርት አንስታይን 💥ማህተመ ጋንዲ... እንዲሁም የሌሎችም አባባል የሚያገኙበት ቻናል🎯 ሲሆን አላማችንም ሰዎች በሚያነብቡት ጥቅስ የአስተሳሰባቸውን አድማስ ማስፋት ነው። ስለመረጡን እናመሰግናለን 🙏 Contact፦ @onajonah
"What’s more unbelievable: Words that move mountains, facts that defy logic, or images that seem unreal?"
Читать полностью…Part 2
ተጠራጠረና ወደ ሟቾ ፍርስራሽ ቤት እንደገና ተመለሰ።
አሁንም ተንበርክኮ ከሬሳው በታች ያለውን ትንሽ ቦታ በእጁ ሲፈትሽ የሆነ ነገር አገኘ። እሱም ህፃን ልጅ ነበር
የነብስ አድን የቡድን መሪው በድንገት እየጮኸ ፣ “ሕፃን! ልጅ አለ! "
አንድ የ3 ወር ሕፃን ልጅ በእናቱ ሬሳ ሥር በአበባማ ብርድ ልብስ ተጠቅልሎ ነበር።
በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ሴትየዋ ልጇን ለማዳን የመጨረሻውን መሥዋዕትነት ከፍላ ነበረ።.
ቤቷ በሚፈርስበት ጊዜ ልጇን ለመጠበቅ ስትል ሰውነቷን ሙሉ ለሙሉ ህፃኑ ልጇ ላይ አድርጋው ነበረ።
የቡድኑ መሪው ህፃኑን ልጅ አንስቶ ሲያየው ህፃኑ በሰላም ተኝቷል።
የሕክምና ቡድን ህፃኑን ልጅ ለመመርመር በፍጥነት ደርሶ ብርድ ልብሱን ሲከፍቱት ብርድ ልብሱ ውስጥ የሞባይል ስልክ ተመለከቱ።
በሞባይል ስክሪኑ ላይ እንዲህ የሚል የጽሑፍ መልእክት አነበቡ።
“
ከሞት ከተረፍክ እኔ እንደምወድህ ሁል ግዜም አስታውስ” ይላል።
ልብ የሚነካ ታሪክ💔
በአንድ ወቅት በጃፓን የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ቀዝቀዝ ካለ በኋላ የነብስ አድን ሰራተኞች በአንድ ፍርስራሽ ቤት ሲገቡ የአንዲት ሴትን እሬሳ ተመለከቱ።
ሴትየዋ በጉልበቷ ተንበርክካለች፤ ሰውነቷ ወደ ፊት ዘንበል ብሎ ነበር፣ ሁለቱ እጆቿ በአንድ ነገር ተደግፎ ነበረ። የፈራረሰው ቤት ጀርባዋ እና ጭንቅላቷ ላይ ወድቋል።
የነፍስ አድን ቡድን መሪው እጁን ወደ ሴቲቱ አካል ለመድረስ በግድግዳው ላይ ባለው ጠባብ ክፍተት ውስጥ እጁን ሴትየዋ ላይ አደረገው።
ሴትየዋ አሁንም በሕይወት ልትኖር እንደምትችል ተስፋ አድርጎ ነበር። ይሁን እንጂ ቀዝቃዛው እና ግትር ሰውነቷ በእርግጠኝነት እንደሞተች ነገረው💔።
እሱና የተቀሩት የቡድኑ አባላት ከሴትየዋ ቤት ወጥተው ቀጣዩን የፈራረሰውን ሕንፃ ለመፈተሽ ሄዱ።
የቡድን መሪው ግን የሆነ ነገር ተጠራጠረና ወደ......
ከ20♥️ like በኋላ ይቀጥላል
❤የፍቅር ጥግ!❤
አባትነት በልጅነቴ አይገባኝም ነበር።
በጠዋት የሚወጣ ኮስተር ያለ ሰውዬ ማታ ይመጣል።
አጥና ይላል , ሳጠፋ ይመክራል, ግዛልኝ ያልኩትን አይነት ጫማ እና ልብስ አይገዛም።
እንደሚወደኝ ነግሮኝ አያውቅም።
እንዳይቆጣኝ እርቄ አልሄድም ቤት ውስጥ ቁጭ ካለ እንደልቤ አልነጫነጭም። ካጠፋሁ , ላጠፋ ስል የሱን ስም እየጠሩ ያስፈራሩኛል።
አደኩኝ።
ሳድግ አባቴን አየሁት። ጨዋ ነው , ታታሪ ነው , ለፍቶ አዳሪ ነው። ሀላፊነቱን ይወጣል እንደሱ ደሀ እንዳልሆን ነበር የሚታገለው። ባለጌ እንዳልሆን ነው የሚመክረኝ። ከሱ የተሻለ እንድሆን ነው የታተረው። ፋብሪካ ሰርቶ እየዋለ ነው ደከመኝ ብሎ የማያውቀው። መዝናናት እያማረው ፍላጎቱን ቸል ብሎ ነው የቻለውን ሁሉ ለሚስቱ , ለልጆቹ , ለጎጆው የሚያሟላው።
ስሜቱን ስለሚቆጣጠር ነው የሚሰማውን ሁሉ የማይናገረው። ሲያመው አመመመኝ የማይለው እንዳንጨነቅ ነበር። ሲያመኝ የሆነውን, የምፈልገውን ለማሟላት የሄደበት መንገድ የፍቅሩን መገለጫዎች ሳያቸው መውደዴ ከማዘን ጋር ተጣበቀብኝ።
በቅንነት share & react እያደረጋችሁ
@ethio_tksa_tks
"ልብህ እንደ እሳተ ጎመራ ከሆነ፣አበቦች በእጆችህ ላይ እንዲፈኩ እንዴት ትጠብቃለህ??"
በስራ ዘመኔ 9,000 ኢላማዎችን ስቻለው።300ጨዋታዎችን ተሸንፊያለው። ሀያ ስድስት ግዜ የጨዋታውን ማሸነፊያ ግቦችን ያስገባል ተብዬ እምነት ተጥሎብኝ ኢላማዬን ስቻለው።በሂወቴ መልሼ መላልሼ ወድቂያለው።ለዚህም ነው ስኬታማ የሆንኩት።
መጀመሪያ አንተ ተቀየር!
ለሰዎች መምከርማ እንችልበታለን! ምን ቢያደርጉ እንደሚሻል ከነሱ በላይ እኛ እናውቃለን፤ ችግሩ እሱ አይደለም "ለራሴስ እንዴት ልወቅበት?" ነው ጨዋታው።
አንድ የማከብረው ሰው "አገሬን እቀይራለው ብዬ ተነሳው ብዙም ሳልቆይ እንደማይሆን ገባኝ፣ አይ መቀየር ያለብኝ ከተማዬን ነው አልኩ እሱም እንደማይሳካ ሲገባኝ ሰፈሬን አልኩ፣ ከዛ ቤተሰቦቼን አልኩ....በመጨረሻ የገባኝ ነገር መጀመሪያ ራሴን መቀየር እንዳለብኝ ነው" ይለናል።
@ethio_tksa_tks
«ከአውሬ ጋር የሚዋጋ ራሱ
አውሬ እንዳይሆን መጠንቀቅ
አለበት። ወደ ጥልቁ ገደል
ብዙጊዜ ስታይ ገደሉ ወደ
አንተ ደግሞ እንደሚመለከት
አስታውስ!»
I won’t burn myself out
just to bring warmth to others.
ንጉሱ ግጥም አነበበና እንዴት ነኝ¿ ብሎ ነስሩዲንን ጠየቀዉ
"ምንም አትችልም። ልክ እንደ ህፃን ነህ።"
ንጉሱ ተናደደና 3 ቀን አሳሰረው።
በአራተኛው ቀን አሶጣውና አነበበለት...ከዛም እ አሁንስ እንዴት ነኝ? አለው።
ነስሩዲን ዝም ብሎ ሄደ። ንጉሱ ተናዶ ወዴት እየሄድክ ነው? ሲለው
ነስሩዲን፦ "ወደ እስር ቤት.."😐
የህይወትን ምንነት የሚያጠቃልል አጭር ታሪክ ይህ ነው።
ልጅ አባቷን ጠየቀችው፦“ምርጥና ደግ ሰዎች ለምንድነው ቶሎ የሚሞቱት?”
አባትም ጥያቄዋን በጥያቄ መለሰ፦“የአትክልት ስፍራ ውስጥ ብትሆኚ የትኛውን አበባ ነበር የምትመርጪው?”
ይህ አሜሪካዊ ሰው ስሙ ኢሳያስ ማትዮስ ይባላል።
አሜሪካን አይዶል ላይ ቀርቦ አንዲህ አለ . . .
"ልጅ እያለሁ እንደማንኛውም ልጅ ምኞትና ተስፋ ነበረኝ። አድጌ፣ ተመርቄ፣ ስራ ይዤ፣ ሚስት አግብቼ፣ ልጆች ወልጄ፣ በቤተክርስቲያን ዘማሪነት እያገለገልኩ በደስታና በስኬት የመኖር ትልቅ ህልምና ተስፋ ነበረኝ። ነገር ግን ከዚህ ሁሉ አንዱም አልተሳካልኝም። ምክንያቱም 18 ዓመት ሲሆነኝ በአንድ በተረገመች እለት ምንም በማላውቀው🤷♂ ጉዳይ ፖሊሶች በዘረፋ ተጠርጥረሀል አሉኝና ያዙኝ። ኧረ ንፁህ ነኝ ብልም የሚሰማኝ👂ጠፋና ተዘርፈዋል የተባሉ ሰዎችም ሌባውን ይመስላል ስላሉ ብቻ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደብኝ። ያለ ጠያቂ ለ54 ዓመት በአንድ ክፍል ውስጥ ተቆለፈብኝ። መጀመሪያ አከባቢ ተስፋ ቆረጥኩ። ቆየት ብዬ ግን ይሄ ነገር የእግዚአብሔር አላም ሊሆን ይችላል ብዬ በፀጋ መቀበል ጀመርኩ። ከዚያ ያለ አጃቢ ባንድ፣ ያለ ሙዚቃ መሳሪያ🎹 በባዶ ክፍል ውስጥ በየቀኑ እግዚአብሔርን በመዝሙር ማመስገን ጀመርኩ። ብዙ አመታት ያለምን ለውጥ ነጎዱ . . .
ከ54 አመታት በኃላ መዝገቤን በአጋጣሚ ሲያየው አላግባብ እንደተፈረደብኝ የተገነዘበ አንድ ወጣት የህግ ባለሙያ ወደ እኔ መጣና ጉዳዬ እንደገና እንዲታይ(judicial review) ሊደረግ እንደሆነ ነገረኝ። ተስፋ ባላደርግም ይቅናህ አልኩት። በአጭር ጊዜ ውስጥ ጉዳዩን እንደገና አሳይቶ በ72 አመቴ በነፃ እንድለቀቅ አደረገኝ። ስወጣ ግን ምንም ነገር አላገኘሁም። ቢሆንም እግዚአብሔር ይመስገን እዚያ እያለው በነፃነት በመኖራቸው እቀናባቸው የነበሩት ብዙዎቹ በህይወት የሉም። እኔ ግን ዛሬ ላይ ንፁህ አየር እየተነፈስኩ🌬️ የማለዳ ፀሀይ በነፃነት እሞቅኩ በህይወት አለው። በህይወት መኖር ብቻ ሳይሆን አንድ ቀን በህዝብ ፊት እዘምራለሁ ብዬ ስመኘው የኖሩኩት ምኞቴ እውን ሆኖ ይሄው በእናንተ ፊት ቆሜ እግዘብሔርን ላመሰግን ደስተኛ ነኝ" አለና በለስላሳ ድምፁ . . .
"በሀሰት በከሰሱኝ ጊዜ፣ የሚሰማኝ አጥቼ በተፈረደብኝ ጊዜ፣ ከ50 ዓመት በላይ ያለ በቂ ምግብ እና ልብስ፣ ያለ ጠያቂ ወገን በአንድ ክፍል ውስጥ በተዘጋብኝ ጊዜ፣ አለም ሁሉ በረሳኝ ጊዜ፣ አበቃልኝ ብዬ ቀኑም ለሊቱም በጨለመብኝ ጊዜ ከጎኔ ያልተለየኸኝ አባቴና አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ ከልቤ አመሰግናለሁ!" እያለ በእንባ ታጅቦ መዝሙሩን ያንቆረቁረው ጀመር።
ይሄኔ ከአወዳዳሪዎች እስከመድረክ አስተባባሪዎች፣ ከታዳሚዎች እስከ ጥበቃዎች አዳራሹ በሙሉ በለቅሶ ተናጋ።
በርግጥ አንኳን እነሱ እኔም ሳየው አልቅሻለሁ
ጎበዝ እምነት ማለት ሲደላን የምናጠነክረው የምንጠብቀው ስንጣል ደግሞ የምንጥለው አይደለም🙅♂‼️ ፈጣሪን በመሸ በነጋ እንደ ኢሳያስ ከልብ ለማመስገን ምንም ባይኖር በእስር ቤትም ቢሆን ያለምንም ነገር መኖር ብቻ በቂ ነው።
አንድ ሰው ያስተምራል ካላቹ Please ➥Share
ለፈገግታ
አንድ በእድሜ ብዛት የጫጨ አዛውንት አልጋ ላይ ሊሞት እያጣጣረ ነው።
✔️አምስት የቤተሰቡ አባላት ቆንጅዬ ሚስቱና አራት ልጆችሁ ከአልጋው አጠገብ ቆመው የማይቀረውን ሞት እየጠበቁ ነበር።
✔️ ከልጆቹ መካከል ሦስቱ ታላላቆች ረጃጅሞች፣ ቆንጆዎች እና አትሌቲክስ ነበሩ፤ ነገር ግን አራተኛውና የመጨረሻው ልጅ የቤተሰቡ አስቀያሚ ነገር እንደነበር ጥርጥር የለውም።
ባልየው በሹክሹክታ "ውድ ሚስቴ ትንሹ ልጅ በእውነት የእኔ መሆኑን አረጋግጭልኝ። ከመሞቴ በፊት እውነቱን ማወቅ እፈልጋለሁ ሃቅ ከነገርሽኝ ይቅር እልሻለሁ" ሚስትየው በእርጋታ አቋረጠችውና "አዎ የኔ ውድ በፍፁም ምንም ጥያቄ የለውም በእናቴ መቃብር ላይ እምላለሁ አባቱ አንተ ነህ" አለችው። ሰውየው በመጨረሻ ለብዙ አመታት ያስጨነቀውን ጥያቄ በመጠየቁ ደስተኛ ሆኖ ሞተ።
ውድ ባል ትንፋሹ ፀጥ ካለ በኋላ ሚስትየው ቁና ቁና እየተነፈሰች "ፈጣሪ ይመስገን ስለ ሶስት ታላላቆች አልጠየቀኝም" 🤦🏼♀
ከመናገርህ በፊት ሁለቴ አስብ ምክኒያቱም የቃልህ ተፅእኖ በሌላው አዕምሮ ላይ የውድቀትም ሆነ የስኬት ዘር ሊያበቅል ይችላል !
#መቅደም ያለበት ነገር!!
#ማንንም ከመፍራታችሁ በፊት በቅድሚያ ፈጣሪን ፍሩ
#ማንንም ሰው ከማገዛችሁ በፊት በቅድሚያ ራሳችሁን አግዙ
#ማንንም ከማድመጣችሁ በፊት በቅድሚያ ትክክል እንደሆነ ህሊናችሁ የሚመሰክርላችሁን እውነት አድምጡ
#ስለማንም ሰው ሁኔታ ከሌሎች ሰዎች ጋር ከማውራታችሁ በፊት በቅድሚያ ስለራሳችሁ ጉዳይ ከራሳችሁ ጋር አውሩ
#ያልሆነላችሁንና የሆነባችሁን ከማሰላሰላችሁ በፊት በቅድሚያ የሆነላችሁንና ያልሆነባችሁን አሰላስሉ
#መልካም_ቀን
@ethio_tksa_tks
ከእንቅልፍህ ስትነቃ ፈጣሪህን ማመስገንን አትርሳ #ምክንያቱም እርሱ አንተን ማንቃትን አልረሳምና ።
አንዴ ልመርቃችሁ አሜን በሉኝ እንደ እናት ፈገግታ ያማረቀን ይሁንላችሁ 👋
ውሾቹ ይጮኻሉ ግመሉ ግን ጉዞውን ቀጥሏል >>> በነገራችን ላይ "ውሾቹም ይጮኻሉ ግመሎቹም ይሄዳሉ" የሚለው አባባል የአረብ ነጋዴዎች አባባል እንደሆነ "የኔ ጀግና" የሚለው የሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት መጽሐፍ ላይም ሰፍሮ እናገኛለን።
አረቦች በግመሎቻቸው የንግድ እቃዎቻቸውን ጭነው በሚሄዱበት ሰዓት የበረሃ ውሾት በጣም ቢጮሁባቸውም እነሱ ላይ ድንጋይ በመወርወር ጊዜን አያባክኑም፤ ምክንያቱም የውሾቹ መጮህ ግመሉን ከጉዞው አያቆመውምና።
በአንድ ወቅት የእንግሊዝ መሪ የነበረው ዊንስተን ቸርችልም ይህንን ብሎ ነበር...
"ባንተ ላይ ለሚጮህ ውሻ ሁሉ እየቆምክ ድንጋይ የምትወረውር ከሆነ ከአላማህ በቶሎ አትደርስም" ንግግሩ እውነታን ያዘለም ነው።
መልስ ለሚገባው እንጂ ለተናገረ ሁሉ መልስ መስጠት አግባብ አይደለም የጊዜ ብክነትም ነው። ምክንያቱም አንዳንዶች የሚጮሁት ትክክለኛ ጥያቄን እና መልእክትን ይዘው ሳይሆን እኛን ከመስመራችን አስወጥተው ከራሳቸው ጎራ ለመመደብ ነውና።
እንደ ንስር ሁኑ!
ንስርን የሚደፍር ሁነኛ ወፍ ቁራ ነዉ። ቁራ በንስሩ ጀርባ ላይ ይቀመጥ እና አንገቱን ይነክሰዋል።ንስሩ ምላሽ አይሰጥም፤ ከቁራ ጋር አይጣላም፤በቁራ ላይ ጊዜና ጉልበት አያጠፋም፤ ይልቁንም ክንፉን ከፍቶ ወደ ሰማይ ከፍ በማለት መብረር ይጀምራል።
በረራዉ ከፍ ባለ መጠን ቁራዉ ለመተንፈስ ይቸገራል እና በመጨረሻም ቁራዉ በኦክስጂን እጥረት ምክንያት ይወድቃል።
ዝቅ ብላችሁ ስላገኟችሁ፤ ጀርባችሁ ላይ እየወጡ ፣ ሥራችሁን እንዳትሰሩ የሚነቋቁሯችሁ ፣ ሠላም የሚነሷችሁ በዙሪያችሁ ቢኖሩም መፍትሄው መጣላት ፣ ማማረር፣ ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን ከፍ ብላችሁ መብረር,ነዉ!!
ራሳችሁን በእዉቀት አጠንክሩ፤ በሥራችሁም የበለጠ ታታሪ ፣ ጠንካራና ዉጤታማ ሁኑ!
በቅንነት share & react እያደረጋችሁ
@ethio_tksa_tks
ፍትህን አጓድሎ የማይፀፀት እውነተኛ ወንጀለኛ እሱ ነው!
"ትክክለኛው ጥያቄ :
ከሞት በሗላ ህይወት አለ ወይስ የለም የሚለው ሳይሆን ከመሞትህ በፊት እየኖርክ ነው ወይ??የሚለው ነው።"
ከወደድከው ሰው ልብ ውስጥ ሃዘንን ማስወገድ ካልቻልክ አብረኸው እዘን
ሀዘን የሚጠፋው አፍቃሪ ልቦች ሲጋሩት ነው።
እንግሊዝኛ ምን በአለም ቢነገር፣ ምን ቢሊዮኖች ቢመኙት .. እዚያው ከቻይና ብር ይበደሩበት እንጂ፤ ፊልም ይስሩበት እንጂ፤ እንደ እኔ ላለው መች እንደ አማርኛ የልብ ያደርሳል?
✔️እስቲ አሁን "አይዞህ"ን በእንግሊዝኛ ልበልህ ብለው እንዴት ይገለጻል?
እንግሊዘኛ እንደ ቋንቋ መተሳሰብን መች ይደግፋል? እስቲ አሁን እንግሊዝኛ "እኔን እኔን" ብሎ ነገር የት አባቱ ያውቃል? እሱን ተውት "የት አባቱ!" ማለትንስ የት አባቱ አውቆት? ሰው እንቅፋት ሲመታው "እኔን" በሚለው መተሳሰብ ፋንታ "ዋች አውት! አር ዩ ኦኬ? የት ያደርሳል? "ዋች አውት" አጠጋግተን ስንተረጉመው "ምን አባሽ ያደናብርሻል?" አይደለምን?
©ጋሽ ስብሃት ገ/እግዚያብሄር
SHARE||@ethio_tksa_tks
ማጂድ ካቮሲፋር፡ ዝርዝር ታሪክ
ስለ ማጂድ ካቮሲፋር የልጅነት እና የወጣትነት ህይወት ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም። በ20ዎቹ መጀመሪያ አመት የእድሜ ክልል ውስጥ እንደነበረ የሚገመት ሲሆን፣ ያደገው እና የኖረው በኢራን መሆኑ ይታወቃል። ከቤተሰቡ ጋር የነበረው ግንኙነት ምን እንደሚመስል በግልፅ አይታወቅም።
በማጂድ እና አጎቱ በሆሴን ካቮሲፋር የተፈፀመው የአቃቤ ህግ ማሶድ ሞላሳልታኒ ግድያ ዋና ምክንያት በይፋ የሚተታወቅ አይደለም። ሆኖም ብዙዎች ይህ ግድያ በፖለቲካዊ ወይም በግለሰባዊ በደል የተፈፀመ ነው ብለው ያምናሉ። አንዳንድ ወሬዎች ደግሞ ግድያው በሌሎች ወንጀሎች ውስጥ ከመሳተፋቸው ጋር የተገናኘ ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። ነገር ግን በምንም መልኩ እውነቱ በግልጽ አልታወቀም።
ማጂድ እና ሆሴን አቃቤ ህጉን የገደሉት በጥይት በመተኮስ እንደሆነ ታውቋል። ቦታውም በኢራን ዋና ከተማ በቴህራን መሃል ላይ ነበር። ግድያው በጠራራ ፀሀይ የተፈጸመ ሲሆን ይህም በወቅቱ ብዙ ሰዎችን አስደንግጦ ነበር።
ከግድያው በኋላ ሁለቱ ወንድማማቾች በፖሊስ ተይዘው ታሰሩ። በፍርድ ቤት ክስ ቀርቦባቸው ሁለቱም በግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው ተፈርዶባቸዋል። በወቅቱ በኢራን የነበረው የፍርድ ስርዓት ለግድያ ወንጀል የሚሰጠው ቅጣት ሞት ነበር። ስለዚህ ፍርድ ቤቱ ሁለቱንም ወንድማማቾች በሞት እንዲቀጡ ወሰነ።
በኢራን የሞት ፍርድ በተለያዩ መንገዶች ይፈፀማል። ከነዚህም ውስጥ አንዱ በአደባባይ ላይ በመስቀል ነው። የማጂድ እና የሆሴን የሞት ቅጣት የተፈፀመውም በዚሁ መንገድ ነበር። ከመገደላቸው በፊት በሰንሰለት ታስረው እና የሞት ገመድ አንገታቸው ላይ ተጠምጥሞ፣ በአደባባይ ታይተዋል። ይህ በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ትዝብት እና ሀዘን ፈጥሯል።
ከሁሉም በላይ የሚያነጋግረው የማጂድ ካቮሲፋር ፎቶግራፍ፣ በሞት ፍርድ ከመገደሉ በፊት ሲስቅ የሚያሳይ ነው። የዚህ ፈገግታ ትርጉም እስካሁን ድረስ ግልፅ ባይሆንም፣ ብዙ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል።
• ድፍረት እና ተቃውሞ፡ አንዳንዶች ማጂድ በሞት ፊት እንኳን ሳይንበረከክ ድፍረቱን ለማሳየት ፈገግ ብሏል ይላሉ። ለፍርድ ቤቱ እና ለስርዓቱ ተቃውሞውን የገለፀበት መንገድ እንደሆነ ያምናሉ።
• መጨረሻ ሰላምታ: ሌሎች ደግሞ የማጂድ ፈገግታ፣ ከዚህ ዓለም ለመሰናበት መዘጋጀቱን እና በመጨረሻም ሰላም ማግኘቱን ያሳያል ይላሉ።
• በጣም የተወሳሰበ ስሜት: አንዳንዶች ደግሞ ፈገግታው በጣም የተወሳሰበ ስሜት ሲሆን፣ ድብልቅልቅ ያለ ፍርሃት፣ ተስፋ መቁረጥና ተስፋ ማድረጉን ያሳያል ይላሉ።
ብቻ የምሆነ ይህ ማጂድ ካቮሲፋር በ2007 የተገደለ አንድ ኢራናዊ ወንጀለኛ ሲሆን ፈገግታው ግን ሁሉም ልብ ውስጥ ቀርቷል
ሌሎችን ለማሞቅ አትንደድ...ነደኽ ያለቅኽ ቀን የሚያስታውስህ የለም።ለሰው የከፈልኽው መስዋትነት በአንድ ስህተት ሊናድ ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ከእድሜ ልክ በጎነት የአንድ ቀን ስህተትህ ብቻ ይታያቸዋልና ሌሎችን ለማሞቅ ብለህ አትንደድ ። በእርግጥ በጎ ነገርን የሚያደርግ ለእግዚያብሔር ያበድራል ይላሉ ።ለሰው በጎ ማድረግ ካሰብኽም ያ ሰው በጎነቴን አስቦ ይከፍለኛል ብለህ አታድርገው ፤ ለፈጣሪ ብለህ አድርገው...እርሱ ጥቂት ጥረትህን የማይረሳ አምላክ ነውና ።Читать полностью…
✅️ በአንድ ወቅት ጋዜጣ በመሸጥ ደሃ ቤተሰቦቹን ለመርዳት ይታትር የነበረ አንድ የ ሰምንት አመት ልጅ፣ቀኑን ሙሉ ምግብ ሳይቀምስ በከተማዋ መንገዶች እየተዟዟረ ጋዜጣ ሲሸጥ ይዉላል።
ይሁን እንጂ ያገኘዉ ገንዘብ ምግብ ገዝቶ ለመብላት የሚበቃ አልነበረም ፣ከረሃቡ በላይ የዉሃ ጥሙ ቢበረታበት፣ በአካባቢው ከነበሩ ቤቶች ወደ አንዱ በመሄድ....
✅️ "የምጠጣው ዉሃ ስጡኝ??"ሲል ይለምናል።የቤቱ ባለቤት መልካም ሴት ስለነበረች፣ምንም እንኳን ህፃኑ የጠየቀዉ ዉሃ ቢሆንም በዉሃዉ ምትክ ወተት ትሰጠዋለች።
ህፃኑም በዝግታ ወተቱን ጠጥቶ ከጨረሰ በኋላ፣ወደ መልኳሟ ሴት እየተመለከተ "ስንት ብር ነዉ የምከፍለዉ?"ሲል ይጠይቃል።
✅️ "አይ ምንም አትከፍልም!!ለመልካም ስራ ክፍያ እንዳልቀበል ያስተማረችኝ እናቴ ነች።"በማለት ህፃኑን ወደ ቤቱ ትሸኘዋለች።
ከአመታቶች በኋላ ይህ ህፃን በአሜሪካ ታዋቂ በሆነዉ ጆን ሆፕኪንስ ሆስፒታል እጅግ ከሚከበሩ ዶክተሮች መሃል አንዱ በመሆን እያገለገለ በነበረበት ወቅት፤አንድ በጠና የተመመች ሴት ወደ ሆስፒታሉ ትመጣለች።
በጠና የታመመችዉ ሴት፣ዉሃ ጠይቆ ወተት የሰጠችዉ ያች መልካም ሴት እነደሆነች ለማወቅ አስታዋሽ አላስፈለገዉም ነበር።
ቀንና ለሊት ሳይሰለች ከህመሟ እንድታገግም እርዳታ ያደርግላታል።ምንም እንኳ እሷ ባታስታዉሰዉም ለሰጣት እንክብካቤ አጅግ ታመሰግነዋለች።
ለህክምና ወጪ የምትከፍለዉ ገንዘብ አልነበራትምና የገንዘብ መክፈያ ደረሰኙን ሲሰጧት በፍርሃት ነበር የከፈተችዉ፣በደረሰኙ ግርጌ በጉልህ የተፃፈ አንድ ፅሁፍን ተመለከተች፤ፅሁፉም እንዲህ የሚል ነበር.....
"በአንድ ብርጭቆ ወተት፣ሙሉ በሙሉ ተከፍሏል። "
"Paid in full with a glass of milk."
✅የዚህ እዉነተኛ ታሪክ ባለቤት የአሜሪካዉ ጆን ሆፕኪንስ ሆስፒታል መስራችና አሜሪካ ካፈራቻቸዉ ድንቅ ዶክተሮች መሃል አንዱ የሆነዉ የዶክተር ሃዋርድ ኬሊ ነዉ።
"ፈገግታህ አለምህን እንዲቀይር አድርግ እንጂ አለም ፈገግታህን እንዲቀይር አትፍቀድለት"Читать полностью…
🦅ንስርን ለመምታት የሚደፍር ብቸኛው ወፍ ቁራ ነው። በንስር ጀርባ ላይ ተቀምጦ አንገቱን በመንቁሩ ይነክሰዋል። ሆኖም ንስር ምላሽ አይሰጥም ወይም ቁራውን አይዋጋም። ንስር ከቁራ ጋር በመዋጋት ጊዜና ጉልበት አያባክንም። ንስር ክንፉን ከፍቶ ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ መብረር ይጀምራል። በረራው ከፍ ባለ ቁጥር ለቁራ መተንፈስ አስቸጋሪ ይሆናል እና በመጨረሻም ቁራ በኦክስጂን እጥረት ይወድቃል። ለዚያም ነው አንዳንድ ጊዜ ለሁሉም ጦርነቶች ምላሽ መስጠት አያስፈልግም።ለሰዎች ክርክር ወይም ትችት ምላሽ መስጠት አያስፈልግም። ስብዕናዎን ብቻ ያሳድጉ።
🗣 ኦሾ
በ 5 ዓመቱ አባቱ ሞተ
በ16 አመቱ ትምህርቱን አቋረጠ። በ17 ዓመቱ አራት ስራዎችን አጥቷል። በ18 ዓመቱ አገባ ከ18 እስከ 22 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በውትድርና አግልግሎት ውስጥ ተመዝግቧል፤ ከዚያም የባቡር አገልግሎት ሠርቷል በዚህም አልተሳካለትም። ለሕግ ፋኩልቲ አመልክቶ ማመልከቻውን ውድቅ ተደርጓል። የኢንሹራንስ ኩባንያ ሻጭ ሆነ እና እንደገና አልተሳካም። በ19 ዓመቱ አባት ሆነ። በ20 ዓመቱ ሚስቱ ትታው ልጃቸውን ወሰደችበት!እና በትንሽ ካፌ ውስጥ ሰሃን አጣቢ ሆነ። ሴት ልጁን ከሚስቱ ለመውሰድ ያደረገው ሙከራ አልተሳካለትም እና በመጨረሻም ሚስቱን ወደ ቤት እንድትመለስ አሳመነ። በ65 ዓመቱ የጡረታ ዕድሜ ላይ ለመድረስ ለጡረታ ተላከ በጡረታ የመጀመሪያ ቀን ከመንግስት 105 ዶላር ቼክ ተቀበለ።
ከዚህ በኋላ መኖር እንደማይገባው ስላየ ራሱን ለማጥፋት ወሰነ። ምክንያቱም ብዙ ውድቀቶችን አስተናግዷል የመጨረሻ ቃሉን ሊጽፍ ከዛፉ ስር ተቀምጦ ነበር፤ ነገር ግን በህይወቱ ያከናወናቸውን ነገሮች መጻፍ ጀመረ። እናም ጥሩ የሆነበት አንድ ነገር እንዳለ አወቀ እሱም "ምግብ ማብሰል" ነበር። 87 ዶላር ተበድሮ ድንች እና ዶሮ ገዛ በራሱ የፈጠራ ዘዴ ተጠቅሞ ከቤት ወደ ቤት ሄዶ ለኬንታኪ ጎረቤቶቹ መሸጥ ተያያዘው። በ88 አመቱ የኬንታኪ ብስል ዶሮ (KFC) ግዛት መስራች ቢሊየነር ሆነ።
በህይወት ውስጥ ተስፋ መቁረጥ አለ፤ ግን ደግሞ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ህይወት የለም!Читать полностью…