ethio_tksa_tks | Unsorted

Telegram-канал ethio_tksa_tks - ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

6061

እንኳን ደህና መጡ። በቴሌግራም ውስጥ የታዋቂ ሰዎች ማለትም 💥አርስቶትል 💥አብርሀም ሊንከን 💥አልበርት አንስታይን 💥ማህተመ ጋንዲ... እንዲሁም የሌሎችም አባባል የሚያገኙበት ቻናል🎯 ሲሆን አላማችንም ሰዎች በሚያነብቡት ጥቅስ የአስተሳሰባቸውን አድማስ ማስፋት ነው። ስለመረጡን እናመሰግናለን 🙏 Contact፦ @onajonah

Subscribe to a channel

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

Relax!!!

•  ያመለጣችሁን “እድል” ስታሰላስሉ፣ በፊታችሁ ያለውን ድንቅ ነገር እንዳታባክኑት!

•  ትተዋችሁ ስለሄዱት ሰዎች ስታወጡና ስታወርዱ፣ አጠገባችሁ ያሉትን አስገራሚ ሰዎች እንዳታቷቸው!

•  ገና ለገና ይሆንብኛል ብላችሁ ስለምትሰጉት ነገር ስትጨነቁ፣ ለሚመሆንላችሁ ድንቅ ነገር ሳትዘጋጁ ጊዜ እንዳያልፍባችሁ!

•  ሰዎች ሊያዝኑባችሁ ስለሚችሉት ነገር በማሰብ እነሱን ለማስደሰት ስትታገሉ ራሳችሁን እንዳታጡት!


እስቲ ትንሽ ፈታ፣ ዘና በሉ!

መልካም ቀን

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ስህተትህን ....

ቶማስ ኤዲሰን ብዙ ተሳስቶ አምፖልን ፈጠረ። ስለስህተቶቹ ሲያወራ ግን እንዲህ ይላል 'እኔ ብዙ ስለሞከርኩ ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ሁሌም ስሞክር ወይ ልክ ነኝ ወይ ደግሞ ተምሬበታለው' ይለናል።

ያለፉ ስህተቶቻችንን ለከፍታችን መጠቀም አለብን፤ ሰሞኑን ካጋጠመኝ ችግር ምን ተማርኩበት እንበል። ሁለቴ መውደቅ የሚፈልግ የለም መቼም...አሸናፊ ማለት የማይወድቅ አይደለም፤ ቢወድቅም መልሶ የሚነሳ ነው። የሆነ ነገር አልሳካ ሲለን እስኪ ምንድነው ያጎደልኩት ብለን ጊዜ ወስደን ማሰብ አለብን።

ከስህተት በላይ ምን አስተማሪ ነገር አለ? እንደውም ምርጥ አድርጌ ደግሜ እንድሰራው እድል ተሰቶኛል ማለት አለብን።

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

አንድ Caps NFT በ 71 TON እየተሸጠ ነው ያለው የሚፈጠረው አይታወቅም 6ቀን ነው የቀረው

መጀመር የምትፈልጉ ➜
/channel/DurovCapsBot/caps?startapp=7682786416

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

#አስተማሪ ታሪክ

የአስራ ሶስት አመት ልጅ ነው፡፡ በእናቱ ላይ ፊቱን ካኮማተረና ካኮረፈ ሰንበት ብሏል፡፡ ለምን ጸባዩ እንደተቀያየረ ለማወቅ ብዙ ብትጠይቀውም መልስ አልሰጥ ስላላት፣ “ጉርምስና” ጀምሮታል” ብላ ተወት አድርጋዋለች፡፡ አንድ ቀን ወደ እናቱ መጣና አንድን ደብዳቤ ሰጣት፡፡ በእንደዚህ መልኩ ደብዳቤን ከልጇ ተቀብላ ስለማታውቅ ለማንበብ ቸኩላ ስትመለከተው እንዲህ የሚል ጸሑፍ አገኘች፡፡

ይህንን ደብዳቤ ለመጻፍ የፈለኩት ያለብሽን እዳ ላስታውስሽና እንድትከፍለኝ ለመጠየቅ ነው፡፡

• ግቢ ውስጥ ያደገውን ሳር የቆረጥኩበት = 5 ብር

• ክፍሌን ያጸዳሁበት = 2 ብር

• ወደ ሱቅ የተላላኩበት = 3 ብር

• ሱቅ ስትሄጂ ወንድምህን ጠብቅ ብልሽኝ የጠበቅኩበት = 4 ብር

• ቆሻሻ የደፋሁበት = 5 ብር

• ትምህርት ቤት ጥሩ ውጤት ያመጣሁበት = 5 ብር

ያለብሽ እዳ ጠቅላላ ድምር = 24 ብር

ብዙ ውለታ ያደረገችለትና በጣም የምትወደው ልጇ ሁኔታውን በዚህ መልኩ ማየቱና ያደረገውን ሁሉ እንደ እዳ መቁጠሩ በጣም አስገረማት፡፡ ሁኔታውን በምን መልክ እንደምትይዘው ካሰበች በኋላ ወረቀቱን ገለበጠችና እንዲህ የሚል የምላሽ ደብዳቤ ጻፈችለት፡-

እዳዬን ስላስታወስከኝ አመሰግናለሁ፡፡ በመጀመሪያ አንተ ያለብህን እዳ ላስታውስህና አሁንም እዳ አለብሽ ካልከኝ እከፍልሃለሁ፡፡

• ዘጠኝ ወር ሙሉ ማህጸኔ ውስጥ የተሸከምኩበት = ከክፍያ ነጻ

• በታመምክ ጊዜ ሁሉ ወደ ሃኪም ቤት ያመላለስኩበትና ገንዘብ ከፍዬ ያሳከምኩበት = ከክፍያ ነጻ

• ሌሊት ስታለቅስ ቁጭ ብዬ በመንከባከብ ያደርኩበት = ከክፍያ ነጻ

• ከልጅነትህ ጀምሮ ጡት ያጠባሁበትና በየቀኑ ምግብ ሰርቼ ያበላሁበት = ከክፍያ ነጻ

• መጫወቻ፣ ልብስና ጫማ የገዛሁበት = ከክፍያ ነጻ

• አንድ ነገር እንዳይደርስብህ ወደ ፈጣሪ ጸሎት በማድረግ ያሳለፍኳቸው ቀናትና ሰዓታት = ከክፍያ ነጻ

ያለብህ እዳ ጠቅላላ ድምር = 0

ይህንን የእናቱን ደብዳቤ ያነበበው ይህ የአስራ ሶስት አመት ልጅ ሳያስበው አይኖቹ በእንባ ተሞሉ፡፡ እስከዛሬ የታየው እሱ አደረኩኝ የሚለው እንጂ የተደረገለት ነገር አልነበረም፡፡ የእናቱ ምላሽ እድሜ ልኩን የማይረሳ ትዝታን ተወለት፡፡

አንዳንድ ሰዎች እነሱ የከፈሉትን መስዋእትነት ብቻ የመቁጠር ዝንባሌ አላቸው፡፡ ካለፈው ሁኔታቸው አልፈው እዚህ ለመድረሳቸው ምክንያት የሆናቸው ሰውና ሁኔታ እንዳለ ለማሰብ ጊዜም የላቸው፡፡

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ስፔናዊው አትሌት ኢቫን ፈርናንዴዝ እና ኬንያዊው አትሌት አቤል ሙታይ በአንድ የሀገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር ላይ ለሜዳልያ ፉክክር እያደረጉ ነበር።

ኬንያዊው አቤል ሙታይ ውድድሩን እየመራ ስፔናዊው ኢቫን ፈርናንዴዝ ደግሞ ሁለተኛ ሆኖ እየተከተለው ትንቅን ላይ ነበሩ።

በድንገት ግን ከውድድሩ ፍጻሜ መስመር ላይ ሊደርሱ በግምት 10 ሜትር ገደማ ሲቀራቸው ኬንያዊው የውድድሩ መሪ አቤል ሙታይ ውድድሩን ያጠናቀቀ መስሎት በስህተት ውድድሩን አቋርጦ ቆመ:: ይህንን ክስተት የተመለከተው ስፔናዊው ሯጭ አቤል ሙታይ ውድድሩን እንዲቀጥል እና መስመሩን እንዲያቋርጥ ከኃላው ሆኖ ይጮህበት ጀመር

የስፓኒሽ ቋንቋ ጆሮውን ቢቆርጡት የማይሰማው አቤል ሙታይ ምን እንደተፈጠረ ሊገባው አልቻለም:: በመሆኑም ስፔናዊው ሯጭ ኢቫን መስመሩን አቋርጦ ውድድሩን ከማሸነፍ ይልቅ አቤል ሙታይን በመግፋት ውድድሩን አሸንፎ የወርቅ ሜዳልያውን እንዲያሸንፍ አደረገው።

ውድድሩ መጠናቀቁ ተከትሎ አንድ ጋዜጠኛ ለኢቫን ጥያቄ አቀረበለት ...

"ለምን እንደዚያ አደረግክ?"

"የእኔ የህይወት ህልም አንዳችን ሌላችንን በመግፋት አሸናፊ እንድንሆን ማገዝ ነው:: ህልሜ እርስ በእርሱ ተደጋግፎ አሸናፊ የሚሆን ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ነው" ሲል መለሰለት።

"ለምን ኬንያዊው እንዲያሸንፍ አደረግክ ?" ደግሞ ጠየቀው

"እኔ እንዲያሸንፍ አላደረግኩትም:: እሱ መጀመርያም ሊያሸንፍ ነበር"

"ግን እኮ አሸንፈህ የወርቅ ሜዳልያውን ማጥለቅ ትችል ነበር" ጋዜጠኛው አሁንም ጠየቀው

"ድል የማድረግ መርሁ እና ጣእሙ ምንድነው? እንዲህ ሆኖ የማሸንፈው ሜዳሊያ ክብሩ ምንድነው? እናቴ ይህንን ስታይ ምን ትለኛለች?" ሲል ጋዜጠኛውን
አስደመመው

Moral of the story 👉አሸንፍ...ሌሎችም እንዲያሸንፉ አድርጉ



@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

/channel/DurovCapsBot/caps?startapp=8003440176

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

#አታብዛው!!!

አብዝተህ ካፈቀርክ— ትካዳለህ!

አብዝተህ ካሰብክ— ትደበራለህ!

ብዙ ካወራህ— ትዋሻለህ!

ብዙ ከጠበቅክ— ቅር ትሰኛለህ!

ብዙ ከበላህ— ትዝረከረካለህ!

ብዙ ካጠፋህ— ትደኸያለህ!

ሕይወትን አብዝተህ ካሳደድካት— ሁሉንም ነገር ታጣለህ

ከዚህ ሁሉ የምትድነው— በሚዛን ነው!

ሚዛናዊነት የተሟላ ሕይወት ቁልፍ ነው።

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ዛሬም ተሰጥቶናል !

ነቅተናል ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን ፤ የሰው ልጅ ከነቃ አዲስ ቀን ከተሰጠው እድል አለው ማለት ነው ረፍዷል የሚባል ነገር የለም!

እድሜዬ ሄዷል አቅም የለኝም ከዚህ በኋላማ ምን ሊፈጠር ብሎ ነገር የለም ዛሬም እስካለህ ድረስ ማድረግ የምትፈልገውን መልካም ነገር ሁሉ መጀመር ትችላለህ !

"ፈጣሪን የምናመሰግነው በአፋችን ብቻ ሳይሆን በምግባራችንም ነው !"

መልካም ቀን

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

የሆነ ጊዜ ጓደኛዬ  እግሩን ተሰብሮ ሆስፒታል ተኝቶ ነበር

ውጪ በር ላይ የተቀመጠው ወንበር ላይ  ነበርኩ ፣ ፋዘሩ እንባቸውን እየጠረጉ ከተኛበት ክፍል ሲወጡ አየኋቸው

ተደናግጬ

ዘው ብዬ ገባው ያቃስታል ፤  ምን ሆንክ?  አመመህ ? ስለው እያቃሰተ ስለነበረ ገላመጠኝ እያየኸኝ አይደል አይነት

ፋዘር ጋ ምን አወራቹ ? እ ?

"እሱ ባክህ  ...... ወንድ ልጅ አይደለህ ጠንከር በል ፣ ቀላል ነገር ነው ብሎኝ ነው ኮስተር ብሎ የወጣው" አለኝ መሃል መሃል ላይ  እያቃሰተ
አባትነት መውለድ ብቻ ሳይሆን መሰዋትነት መክፈልም ለልጆቻቸው ሲሉ ጠንክረው ይገኛሉ

አባትነት ❤

በቅንነት SHARE & React እያደረጋችሁ

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

💡ሁሌም ቢሆን ጥቁር ብቻ መስሎ ከሚታይህ ቀን ጀርባ የታዘለ ደማቅ ብርሃን አለ፣ ሊገፈትሩህ ከበረቱ እልፍ ክንዶች ኋላ ሊያቀኑህ የቆሙ ልስልስ መዳፎች አሉ፣ አንሸራትተው ከሚደፉህ ሃሳቦች ባሻገር በተስፋ ሞልተው የሚያቆሙህ ቅን ሀሳቦች ተሰልፈዋል።

💎 ያላየኸው ነገ ብዙ አዲስ የህይወት ገፆችን ይዞ ይጠብቅሃል ካጎነበስክበት ቀና ትላለህ ሀዘንህ በሳቅ ይተካል፣ ጉስቁልናህን ወዝ ይሽረዋል፣ ይህ እንዲሆን ግን ነገን ጠብቀው ፦ ተስፋ አትቁረጥ ነገ ያንተ ሲሆን ብቻ አሸናፊ ነህ::

መልካም ምሽት

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

Pt 2...

ከእንቅልፌ ተነስቼ ውሃ ልጠጣ እቃ ቤት ስገባ እናቴ እኔን ላለመቀስቀስ ብላ ስታለቅስ አገኘዋት። ቅደም ባልኳት ነገር እንደሆነ ገባኝ። አሳዘነችኝ ድምፄን ሰምታ ቀና ስትል ከአንዱ አይኗ የሚወርዱ እንባዎቿን አየዋቸው። አይኗ በእንባ ተሞልቶ ሳየው ይበልጥ ጠላዋት! በዛው ቅፅበት ለራሴ አንድ ነገር ቃል ገባው አድጌ ስኬታማ ስሆን አንድ አይናማዋን እናቴን ጥያት እንደምሄድ! ከዛን ቀን ጀምሮ ጠንክሬ መማር ጀመርኩ።
እናቴን ትቻት ወደ ከተማ አለ በሚባል ዩኒቨርስቲ ውስጥ ስኮላርሺፕ አግኝቼ በነፃ ትምህርቴን ተከታትዬ ጨረስኩ። ጥሩ ስራ ይዝኩ የራሴን ቪላህ ቤት ገዛው ሚስት አግብቼም ልጆች ወለድኩ። አሁን የተመኘሁትን የልጅነት ህይወት እየኖሩኩ እገኛለሁ። በጣም ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ገንዘብ💵 አለኝ ፣ ቆንጆ ቤት አለኝ ፣ 😃ደስተኛ 👨‍👩‍👧ቤተሰብ አለኝ ከሁሉም በላይ ግን የምጠላትን እናቴን የማላገኝበት ሩቅ ቦታ ነኝ። አንድ ቀን ግን ያላሰብኩት ዱብዳ መጣብኝ ቤታችን ተንኳኳ "ማነው!? ማነው!?" እናቴ ነበረች ፀጉሮቿ ሸብተው  ከስታ እና የተቀዳደዱ ቆሻሻ ልብሶችን ለብሳ መጣች ላምን አልቻልኩም ቤቴን እንዴት አወቀችው? 👶ህፃኗ ልጄ ፈርታት ሮጣ ወደ ቤት ገባች እንዳላወቀ በመምሰል "ሴትዬ ምን ፈልገሽ ነው? የሰው ቤት ዘው ተብሎ አይገባም እሺ ውጪልኝ ከቤቴ!!" አልኳት ኮስተር ብዬ እናቴ ደነገጠች "ይቅርታ ጌታዬ አድራሻ ተሳስቼ ነው ብላኝ ወጣች. . . ተመስገን አላወቅኸኝም። ይህ ከሆነ ከ አንድ ወር በኃላ ለድሮ ት/ቤቴ የመዋጮ ተዘጋጅቶ የት/ቤቱ ዳይሬክተር ደውለው ጠሩኝና ሄድኩ። ፕሮግራሙ ሲያልቅ በዛውም ያደኩበት ቤት ምን እንደሚመስል ለማየት ስሄድ
. . . .

ይቀጥላል.....

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ልብ የሚነካ ታሪክ >>>>>

እናቴ አንድ አይን ብቻ ነው ያላት በዛም የተነሳ በጣም እጠላታለው። አባቴ ደግሞ የአራስ ልጅ እያለሁ ነው የሞተው እሱ ከሞተ በኃላ እናቴ እና እኔ በደሳሳ ጎጆዋችን ከድህነት ጋር መኖር ጀመርን። አባዬ ያስቀመጠው ገንዘብ ሲያልቅ እናቴ በራችን ጋ ትንሽ ሱቅ ከፍታ መስራት ጀመረች እማ ለኔ የማታረግልኝ ነገር የለም እኔ ግን በሷ አፍር ነበር። ትዝ ይለኛል 5ተኛ ክፍል የወላጆች ቀን እናቴ 🏫ትምህርት ቤት አበባ ይዛልኝ መጣች "እንዴት እንዲ ታደርገኛለች? ማን ነይ አላት? ተሸማቀኩ በጥላቻ አይን ገልምጫት እየሮጡኩ አዳራሹን ለቂቄ ወጣው🚶‍። በሚቀጥለው ቀን ት/ቤት ስመጣ ጓደኞቼ "እናቱ አንድ አይን👁 ነው ያላት" እያሉ ሲያወሩ ሰማዋቸው በውስጤ ምናለ እናቴ ከዚህ አለም ብትጠፋ ብዬ ተመኘሁ። እቤት ስደርስም "ደስ ይበልሽ በጓደኞቼ አሳቅሽብኝ ቆይ አንድ አይንሽ የት ሄዶ ነው? ሁሌ እንዲህ ከምታሸማቅቂኝ ለምን አትሞቺም? ብዬ ጮሁኩባት🗣
ምንም መልስ ሳትሰጠኝ ወጣች እንዲህ ማለቴ ስሜቴን ቢኮረኩረኝም ለረጅም ጊዜ ልላት ያሰብኩትን በማለቴ ውስጤን ቀለል አለኝ ብዙም ስሜቷን የጎዳሁት አልመሰለኝም ነበር ያን ቀን ማታ ከእንቅልፌ ተነስቼ ውሃ ልጠጣ እቃ ቤት ስገባ እናቴ
.....ከ20 like❤️ በኃላ ይቀጥላል ...

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

Which Unlocks The World Secrets?¿😐

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

መጥፎ ሰው ማለት እየፈለከው የማይፈልግህ ሳይሆን ሳትፈልገው ፈልጎህ የመፈለግ ስሜት ፈጥሮ የማይፈለግህ ሰው ነው!

ይኼው ነው!

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

«ያለፈውን ጊዜህን ያለጸጸት ተቀበል፤ አሁን ያለህበትን ጊዜ በልበሙሉነት ተቆጣጠር፤ እና የወደፊትህን ጊዜ ያለ ፍርሃት ፊት ለፊት ተጋፈጥ!»

©ዴል ካርኒጌ

SHARE||
@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ከዚህ ታሪክ ምን ተማራችሁ ሃሳባችሁን ግለጹልን

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

የአንገት ጌጡ

አንድ ውብ ወጣት ሴት ነበረች። ነገር ግን ከድሀ ወገን ስለነበረች አንድ ተራ ፀሀፊ አገባች።በህይወቷ ደስተኛ አልነበረችም።

*ታዲያ ባሏ የትምህርት ሚኒስትሩ ከሚገኙበት ታላቅ ግብዣ ተጠራ።ዜናው ያስደስታታል ብሎ ሮጦ መጥቶ ቢነግራት እንደጠበቀው አልተደሰተችም።**

"ምነው?" ቢላት
"ምን ለብሼ እሄዳለሁ?" አለችው።

ትንሽ አሰበና ለአስፈላጊ ጊዜ ይሆናል ብሎ አስቀምጦት ከነበረ ብር ላይ 300 ፍራንክ ቀንሶ ሰጣት
ደስ እያላት ሄዳ አዲስ ቀሚስ አሰፋች።

ቀሚሱ ካለቀ በኋላ ደግሞ ለካ ስታስበው ምንም የሚረባ ጌጣ ጌጥ የለት።ባሏ ግን አንድ ሀሳብ አቀረበላት።አንድ ሀብታም ጓደኛ ነበረቻት።

"እና ለምን ከሷ አትዋሺም?" አላት።

በማግስቱ ጓደኛዋ ጋር ሄደች።
መረጠችና በጣም የተዋበ የአንገት ሉል ተዋሰች
አሁን ሁሉም ሙሉ ሆነ።ወደ ግብዣው ሄደች።ሰዎች ምን ያህል ውብ እንደሆነች አዩ።ሁሉም ሰው ከሷ ጋር መደነስ ፈለገ።ሚኒስትሩ ሳይቀሩ አነጋገሯት።በህይወቷ በጣም የተደሰተችበት ቀን ሆነ።

ግብዣው አልቆ ከባሏ ጋር በሰረገላ ተሳፍራ ወደ ቤቷ ሄደች።ቤት ስትደርስ ሉሉን ከአንገቷ ላይ ብትፈልገው አጣችው።በጣም ደነገጠች።ከባሏ ጋር ሆነው በመጡበት መንገድ ተመልሰው ሌሊቱን ሁሉ ሲፈልጉት አደሩ።ሊያገኙት አልቻሉም።በማግስቱም በብርሀን ፈለጉት። ምንም ፍንጭ ጠፋ። ተስፋ ቆረጡ።

በመጨረሻ ጌጣ ጌጥ ሰሪ ቤት ሄደው ተመሳሳዩን ለመግዛት ጠየቁ።17000 ፍራንክ ተባሉ።ድሀ ቤተሰብ ናቸው!እድሜ ልካቸውን ከፍለው የማይጨርሱት የአራጣ ብድር ተበድረው ሉሉን ገዝተው ለባለቤቷ መለሱ።ከዚያ ያንን ብድር ለመክፈል ሁለቱም ከአቅማቸው በላይ ሶስት አራት ስራ እየሰሩ በ10 አመት ብድሩን ከፍለው ጨረሱ። በድካሟ መሀልም፣ ያን ሌሊት ያ ጌጥ ባይጠፋ ፣ ህይወቷ ምን ሊመስል ይችል እንደነበር ታልማለች።

ታዲያ ያች ውብ ወጣት ሴት በስራ ብዛት ምክንያት ያለእድሜዋ ገርጅፋ ወዟ መልኳ ጠፍቶ አስቀያሚ አሮጊት መስላለች።አንድ ቀን መንገድ ላይ ያች ሀብሉን ያዋሰቻትን ሴት ታገኛታለች።

አሁን ያለፈ ስለሆነ ስለ ሉሉ ወይም ስለ ጌጡ መጥፋት ልንገራት ትልና ሰላምታ ትሰጣታለች።ሀብታሟ ሴት ግን ልታውቃት አልቻለችም፦

"እኔ ማቲልዳ ነኝ"
"ውይ ምነው አረጀሽ?"
"ባንቺ ምክንያት ነው!"
"በኔ? እንዴት?"
"ታስታውሻለሽ ውድ ጌጥ አውሰሽኝ ነበር"
"አዎ"
"እና ጠፋብኝ"
"እንዴ መልሰሽልኛል እኮ"
"አዎ!ግን በምትኩ ሌላ በ17000 ፍራንክ ገዝቼ ነው የመለስኩልሽ"
ጓደኛዋ በጣም አዘነች።
"እኔ ያዋስኩሽ እኮ አርቴ ነበር,,,ዋጋውም 500 ፍራንክ አይሞላም!!!"😐

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

በህይወታችን እንደ ኳስ ተጫዋች እንጂ
እንደ ዳኛ አንሁን ምክንያቱም ተጫዋች
ለእድል ሲሮጥ ዳኛ ግን ስህተት ለማግኘት ይሮጣል።
...... ስለዚህ ምን ግዜም ለእድላችን እንጂ የሰዎች ስህተት ለማየት አንሩጥ።


መልካም ቀን🙏

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

አንድ ሰው ካህሊል ጂብራንን ጠየቀው፡-

"በሰዎች ውስጥ በጣም አስደናቂው ነገር ምንድነው?"

እርሱም፡

“ሰዎች በልጅነት ጊዜ ይሰለቻቸዋል ለማደግ ይቸኩላሉ፤ ከዚያም እንደገና ልጅ ለመሆን ይናፍቃሉ። ስለ ወደፊቱ ጊዜ በጭንቀት ያስባሉ እና የአሁኑን ይረሳሉ። ስለዚህ በአሁንም ሆነ በወደፊቱ ውስጥ አይኖሩም፤ የማይሞቱ መስለው ይኖራሉ ያልኖሩም ሆነው ይሞታሉ..። ”
     

.... ያለችህን ትንሿ ጊዜህን ባግባቡ ተጠቀም ራስህንና በዙሪያ ያሉትን ደስተኛ አርግ......" መሄጃችን አይታወቅምና "

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ደስተኛ ለመሆን ሁልጊዜ እውነትን ተናገር ትንሽ የመርዝ ጠብታ ወተትን እንደምታበላሽ ሁሉ ትንሽ የምትባል ውሸትም ሰዎችን የማጥፋት ሃይል አላት

©Mahatma Gandi

በቅንነት Share & react እያደረጋችሁ
@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ለጉዞ ከተዘጋጀህ ቤቱን ለቆ ከማያቅ ምክር አትጠብቅ!


©Rumi

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

'ጉድለትህን' ወደ ሙላት ትለውጣለህ?... ወይስ 'በጉድለትህ' ላይ እየተብሰለሰልክ በጽልመት ውስጥ ትቀጥላለህ?


ሌሎች 'ጉድለትህን' አይተው እንዲሳለቁ ትፈቅዳለህ?... ወይስ 'ጉድለትህን' በሞላህበት ትጋት የራሳቸውን ባዶነት አይተው እንዲነቁ ታደርጋለህ?


'ጉድለትህ' ሸክም እንዲያደርግህ አሜን ትላለህ?... ወይስ 'ጉድለትህ' ያዳፈነውን ብርታት ገልጸህ ለሌሎች ትጸልያለህ?

ህይወት ምርጫ ነው

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

አንድ ቀን አንድሰውዬ መንገድ ላይ ሲሄድ ከኪሱ ጉድጓድ ውስጥ ብር ገባበት ከዛ ብሩን ማውጣት ብዙ ቢታገልም ጉድጓዱ ጠባብ ስለነበር አልቻለም ከዛ አድ ህፃን ልጅ አየና

አባ ና ይሄን ብር አውጣና ግማሹን እሰጥሀለው
አለው ልጁም በጣም ተደሰተ ።

ከዛ ልጁ ቢሞክርም ቁመቱ ስላጠረ መግባት አልቻለም ከዛ ሰውዬው በገመድ አድርጌ ልያዝህ አለው ከዛ ልጁ ቆይ አባዬን ጠርቼው ልምጣ አለው።

ሰውየውም በአግራሞት ለምን እኔ አለው አደል ሲለው ልጁ መልሶ

አንተ እኔ ብከብድህ ትለቀኛለህ አባቴ ግን አይለቀኝም አለው
@ethio_tksa_tks 😍😘
ክብር ለአባቶች

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

🎀🎀 እንደምን አመሻችሁ!🎀🎀

....

If egg is broken by outside force, life ends, if broken by inside force, life begins.

     Great things always begin from inside.


      እንቁላል ከውስጥ ሲሰበር ነፍስ ይዘራል ፤ ከውጪ  ከተሰበረ ሕይወት ያቆማል!


     ✍✍✍ ታላላቅ ነገሮች ሁሉ  ሁሌ ከውስጥ ይጀምራሉ! ሰዎች ስላሉ፣ የሚያበላ ስለሆነ፣ አዋጭ ነው ስለተባለ ፣አቋራጭ በመሆኑ.... ነገሮችን ከመስራት ይልቅ ከውስጣችን ፍላጎት የመነጨ መነሳሳት ሲኖረን ሁሌም ውጤታችን አንጸባራቂ ለውጣችን ዘላቂ ይሆናል። ረጅም ርቀት መጓዝ ከፈለግን ውስጣችንን ማድመጥ ይኖርብናል እንጂ ሰዎች 'ያዋጣል!' በሚሉት መመርኮዝ የለብንም።
   
      የኋላ ኋላ የሆነ ነገር ቢፈጠር ... ድሮም'ኮ እነ እንትና ብለውኝ ነው ፤ ዕድሜ ለነ እገሊት እነሱ ጀምሪ ባይሉኝ ኖሮ ይህ ባልደረሰብኝ... ከምንል ሐሳብ ፣ ምክር ... ከሰዎች እንጠይቅ ውሳኔ ግን በራሳችን ይሁን!!


❤️❤️❤️ የነገ ሰዎች ይበለን!!❤️❤️❤️

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

Pt 3...

ፕሮግራሙ ሲያልቅ በዛውም ያደኩበት ቤት ምን እንደሚመስል ለማየት ስሄድ እናቴ መሬት ላይ ተዘርራ አገኘዋት። ሞታለች!! ምንም አላለቀስኩም። እጇ ላይ ወረቀት አየውና አንስቼ ማንበብ ጀመርኩ ለኔ የተፃፈ ደብዳቤ ነበር  እንዲህ ይላል "ወድ ልጄ ከአሁን በኃላ ህይወት ማለት ለኔ ምንም አይደለችም። አንተ ወደምትኖርበት ከተማም ተመልሼ አልመጣም። ልጄ ከምንም በላይ ግን ናፍቆትህ ሊገለኝ ነው ለምን አንድ አይን👁 ብቻ እንዳለኝ ጠይቀከኝ አልነገርኩክም ነበር እውነታው ይሄ ነው... ልጄ ልጅ እያለክ ከባድ የመኪና🚌 አደጋ የደርስብክና አንድ አይንህ ይጠፋል። እንደማንኛውም እናት በአንድ አይን ስታድግ ማየት አልችልምና የኔን አይን አውጥተው ላንተ እንዲያደርጉልህ ዶክተሮችን ጠይቄ ፈቃደኛ ሆነው አደረጉልህ... ለዚህ ነው አንድ አይናማ የሆንኩብህ። አይዞህ ልጄ ባደረካቸው ነገሮች ተቀይሜክ አላውቅም ነበር ባለፈው ቤትክ መጥቼ የልጅ ልጄን በማየቴ በጣም ተደስቻለሁ። ለወደፊቱም በደስታ እንደምትኖር ተስፋ አደርጋለሁ። ልጄ እናትህ በጣም ትወድሃለች🥰"
አንብቤ ስጨርስ በሁለት እግሬ መቆም አቃተኝ። እማ. .እማ. .😢እንባዬን እየዘራው ምስኪኗን እናቴን አቅፌ ተንሰፈሰፍኩ😭 ለኔ ብላ ህይወቷን የሰጠችውን እናቴን በራሴ እጅ ገደልኳት😭

እናት ማለት እውነተኛ ፍቅር ናት። ክብር ይገባታል የሷን ብድር በምድር ላይ ማንም ሊከፍለው አይችልምና ከሞቷ በፊት የሚገባትን ክብር እንስጣት።



ከወደዳችሁት ❤️like comment📝
          ➥Share እያደረጋችሁ

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

በጨረፍታ የተሰማ ፀሎት

አምላኬ ሆይ፦  ፀሃይ ከመንገድ ወጥቼ
ይቀጥቅጠኝ ፤ዶፍ ዝናብ መጠለያ አጥቼ ይደብድበኝ ፤ የታክሲ ሰልፍ ያማረኝ ፤ የቀጠርኳት እንስት ቀርታብኝ ሰፈሯ ሄጄ ልንጎራደድ ይሄ ሁሉ እንዲሆንብኝ ከዚ አልጋ ብቻ አላቀኝ እንደሰው ልራመድ 🙏
.
.
የብዙ ሰው ምሬት ላንዳንዱ የሰርክ ፀሎቱ ነው።

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ከእለታት በአንዱ ቀን የቡጢ ተፋላሚው መሀመድ አሊ አንድ ራሱን ሊያጠፋ ከድልድይ ላይ የቆመን ሰው ያናግራል

👇🏾

"ነገ መልካም ሊሆን ነገር ለምን ይህንን ውሳኔ ትወስናለህ?"

"ስራ የለኝም: ገንዘብ የለኝም: ደህና የምለው ወዳጅ የለኝም: የገዛ ቤተሰቤ እንኳ ከቁብ የሚቆጥረኝ ሰው አይደለሁም"

"እኔ ግን እወድሃለሁ: እኔ ግን አለሁልህ" ሲል አሊ መለሰለት

"ለምንድነው ስለ እኔ እንዲህ የተጨነቅከው? ምን ገዶህ ነው? እኔ እኮ ምንም ያልሆንኩ አንድ ተራ ሰው ነኝ"

"እንዲህ እናደርጋለን - ከእኔ ጋር እንሄድና ልብስ እና ጫማ እንገዛለን: እናት እና አባትህ ቤት አብረን እንሄዳለን:: ከእኔ ጋር ሲያዩህ ትልቅ ሰው እንደሆንክ እና ተራ ሰው እንዳልሆንክ ይረዳሉ”

ይህንን እያወራ መሀመድ አሊ እንባው በጉንጩ ላይ መፍሰስ ጀመረ

ራሱን ሊያጠፋ የነበረው ሰው "ይህንን ያህል ሰው ስለ እኔ ሊጨነቅ እና ግድ ሊለው ይችላል እንዴ?" ብሎ ከድልድዩ ላይ ወረደ

አንድ ህይወት ተረፈች: አንድ ሰው ዋጋውን አወቀ!!

👇🏾

ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነው

❤️🙌🏼

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

Nelson Mandela በዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት በሚማሩበት ወቅት አንድ ዘረኛ የሆነ ዴክላርክ የሚባል፣ ነጭ መምህር ነበራቸዉ።

  አንድ ቀን ኘሮፌሰር ዴክላርክ ፣በአንድ ምግብ ቤት ምግብ እየበላ ሳለ ፣ማንዴላ በአጋጣሚ ምግብ ይዘው ከአጠገቡ ይቀመጣሉ።ዘረኛው ዴክላርክ "አቶ ማንዴላ አሳማ ና ወፍ አብረው ለምግብ  አይቀመጡም!!!"አላቸዉ።ብልሁ ማንዴላም "አይጨነቁ ፕሮፌሰር በርሬ እሄዳለሁ"ብለዉት ሌላ ወንበር ላይ ተቀመጡ።

  በማንዴላ መልስ የተናደደው ዴክላርክ፣ በሌላ ቀን ክፍል ዉስጥ "ማንዴላ ሁለት ቦርሳዎች ወድቀው ብታገኝና በአንዱ ቦርሳ ብር በሌላው ደግሞ ጥበብ ቢኖር፣ የትኛውን በቅድሚያ ትወስዳለህ ?" በማለት ይጠይቃል።ማንዴላም "እኔ ገንዘብ ያለዉን ቦርሳ እወስዳለሁ" በማለት ይመልሳሉ።

ፕሮፌሰሩ ማንዴላን በንቀት እየተመለከተ "አንተ ሞኝ ነህ!!!እኔ አንተን ብሆን የምወስደው ጥበብ ያለበትን ቦርሳ  ነበር።"ይላል

ነገር አዋቂዉ ማንዴላ ፈገግ በማለት "ልክ ነህ ማንም ቢሆን የሌለዉን ነዉ የሚወስደው "ሲሉ መለሱለት።

በማንዴላ መልስ እጅጉን የተበሳጨዉ ፕሮፌሰር ዴክላርክ በማንዴላ የፈተና ወረቀት ላይ "ደደብ "ብሎ ይፅፋል።
ማንዴላም ደደብ የሚለዉን ተመልክቶ በመገረም ወደ ፕሮፌሰሩ በመሄድ "ቲቸር ፊርማህን ብቻ ነዉ ያስቀመትክልኝ ዉጤቴን ፃፍልኝ"በማለት በቅኔ እንደዘለፉት ይነገራል።

ከተመቻችሁ like share እያደረጋችሁ ቤተሰብ

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

አንድ የገጠር መንደርን ከሚያስተዳድሩት አንዱ ባለስልጣን ለገጠር የኮሪደር ልማት ንድፍ ለማውጣት መንደሩን እየጎበኘ ነው። እና በድንገት የድንጋይ ወፍጮ አየ። ከወፍጮ አለፍ ብሎ ደግሞ አንድ አህያ ከድንጋይ ጋር ታስራ ይመለከታል። በአህያዋ እና በድንጋዩ መካከል ገመድ ታስሯል። ስለዚህ አህያዋ መንቀሳቀስ ስትጀምር ድንጋዩ ይሽከረከራል። በዚህ ቀላል ተግባር ገበሬው እህሉን ይፈጫል። ነገር ግን በአህያዋ አንገት ላይ ትልቅ ደወል ተንጠልጥሏል።

አስተዳዳሪው በዚህ ድርጊት በመገረም የስልጣን እኩዮቹን ጠራና ይህ ድንቅ ዘዴ አሳያቸው። ከሁሉም በስልጣን የሚበልጠው ዋና አስተዳዳሪ እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ “ለምንድነው በአህያዋ አንገት ላይ ደወል የሰቀልከው?”

ገበሬው፡- “ብዙ ስራ አለብኝ እናም አህያዋ በምትሰራበት ጊዜ ተቀምጬ ማየት አልችልም። ለዛም ነው ደውሉን አንገቷ ላይ የሰቀልኩት። ስለዚህ የደወሉን ድምፅ ሰማው ማለት አህያዋ እየተሽከረከረች ነው ማለት ነው። በዚህም የወፍጮ ድንጋይም አብሮ ይሽከረከራል”

አስተዳዳሪው፡- “አህያዋ መሽከርከሯን ትታ አንገቷን ብቻ ብታወዛውዝስ?”

ገበሬው፡- “ለዚህ አሳብህ ፈጣሪህ ያክብርህ ገዢያችን። ነገር ግን ይህ ሃሳብ በአህያዋ በአእምሮ ቢመጣ ኖሮ አህያ ባልተባለች ይልቁንም የመንደራችን አስተዳዳሪ በሆነች ነበር።” 🙄🤗

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ሳንቲም ብዙ ድምፅ ያሰማል:: ገንዘብ ግን ምንም አያሰማም:: ስለዚህ ዋጋህ ሲጨምር ወሬህን እየቀነስክ ና!"


  ©William Shakespeare

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…
Subscribe to a channel