ethio_tksa_tks | Unsorted

Telegram-канал ethio_tksa_tks - ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

6061

እንኳን ደህና መጡ። በቴሌግራም ውስጥ የታዋቂ ሰዎች ማለትም 💥አርስቶትል 💥አብርሀም ሊንከን 💥አልበርት አንስታይን 💥ማህተመ ጋንዲ... እንዲሁም የሌሎችም አባባል የሚያገኙበት ቻናል🎯 ሲሆን አላማችንም ሰዎች በሚያነብቡት ጥቅስ የአስተሳሰባቸውን አድማስ ማስፋት ነው። ስለመረጡን እናመሰግናለን 🙏 Contact፦ @onajonah

Subscribe to a channel

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

What do you need ¿¿¿¿¿¿¿¿¿?¿???
👀👀👀👀⚠️⚠️🌐

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ዝናብ እንደምትወድ ትናገራለህ፤ ነገር ግን ለመጠለል ጃንጥላ ትጠቀማለህ። ፀሀይን እንደምትወድ ትናገራለህ፤ ነገር ግን ስትበራ መጠለያ ትፈልጋለህ። ንፋስን እንደምትወድ ትናገራለህ፤ ነገር ግን ሲመጣ መስኮቶችህን ትዘጋለህ። ስለዚህ እንወድሃለን ስትሉኝ የምፈራው ለዛ ነው።"


©Bob Marley

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

#ፈጣሪህን_አውራው

1- ስለድክመቶችህ
2- ስለሕልሞችህ
3- ስለምትፈራው ነገር
4- እየተማርከው ስላለ ነገር
5- እየተጋፈጥከው ሰላለ ውሳኔ
6- አቅምህን ስለሚያደክሙት ነገሮች
7- ስለምን ይቅርታው እንደሚያስፈልግህ
8- ምን ያህል እንደባረከህ
9- ለእሱ ስላለህ ፍቅር

ስለሁሉም ንገረው!

መልካም አዳር🙏


Share @ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

#ለፈገግታ

እናቴ መርፌ ውስጥ ክር እንዳስገባላት ጠራችኝ።
በዚሁ ቅፅበት የአንድ ሰው ምክር ትዝ አለኝ ፦

«እናትህ መርፌ ውስጥ ክር እንድታስገባላት ከጠየቀችህ ተቀብለህ ወዲያውኑ አታስገባው። ይልቁንም ያረጀችና እድሜዋ የገፋ  እንዳይመስላትና  ቀልቧ እንዳይሰበር አውቀህ ታግለህ ታግለህ አስገባው» ብሎ መክሮኝ ነበር ።

እኔም ማስገባቱ  ቀላል እንዳልሆነ እየነገርኳት ጥቂት ደቂቃዎችን ታገልኩ ። በድንገት አንድ ጥፊ ፊቴ ላይ አረፈ 👋


«ድሮውንም እውር ያደረገህ ይሄ ሞባይልና ፌስቡክ ነው»  😊


Share @ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

✅ ምንጊዜም በሰው ሳይሆን #በፈጣሪ መመካት ይበጃል ........

✔️ሰው ቢገፋህ~~~ፈጣሪ ይደግፈሀል
✔️ ሰው ቢጠላህ~~~ፈጣሪ ያነሳሀል
✔️ሰው ቢንቅህ~~~ፈጣሪ ያከብርሀል
✔️ሰው ቢያቀልህ~~~ፈጣሪ ያከብድሀል
✔️ሰው ቢያዋርድህ~~~ፈጣሪ ከፍ ያደርግሀል
✔️ብትንገዳገድ~~~~ፈጣሪ ይደግፍሃል
✔️ብትደክም~~~~ምርኩዝ ይሆንሃል
✔️ሰው ቢረሳህ~~~ፈጣሪ ያስታውሰሃል


ፈጣሪ ከተወህ ግን ማንን ትደግፋለህ በማንስ ትመካለህ ምርኩዛችሁን ፈጣሪ ብቻ አድርጉ .......
         የሰው አለኝታነቱ ከንቱ ነው::
በህይወታችን ሁሉ የፈጣሪ አብሮነት አይለየን🙏🙏
 
#መልካም_ቀን

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

“….. ዘርፈህ ቤት ብትሰራ  ይጨበጨብለሃል፡፡ ሰርቀህ ብትመጸዉት ትመረቃለህ÷ 100 ሚሊዮን የሀገር ሃብት ዘርፈህ አንድ ሚሊዮን ለቤተክርስቲያን ወይም ለመስጊድ ብትሰጥ ምዕምናን እልል በሉላቸዉ ይባልለሃል፡፡ ቢሊዮን አጭበርብረህ መልሰህ ሚሊዮን ለመንግስት ፕሮጀክት ብትሰጥ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጎን ተቀምጠህ የቁርጥ ቀን ልጅ ትባላለህ፡፡ ገንዘብ መያዝክን እንጅ ከየት አመጣኸዉ የሚልህ የለም እና ትከበርበታለህ፡፡ …”
“… በስርቆት በጎ ነገር መስራት አይቻልም፡፡ የተዘረፈን ሃብት መመጽወት አይቻልም፡፡ በተዘረፈ ሃብት ቤት መቅደስ ወይም መስጊድ ሰርቶ መጽደቅ አይቻልም፡፡ “አትስረቅ” ያለን አምላክ ሰርቀን መስዋዕት አድረግን ብናቀርብለት የስርቆታችን ተባበሪ እንዳደረግነዉ ይቆጠራል፡፡

 " ሚትራሊዮን - ከገጽ180-181"

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

#አትፍቀድ!

👉 ዓለም
- መራራ እንድታደርግህ

👉 የሰዎች ድርጊት
- ቀዝቃዛ እንዲያደርግህ

👉 የሞኞች ክፋት
- ክፉ እንዲያደርግህ

👉 በደል
- ሳቅህን እንዲነጥቅህ

አትፍቀድ!!!

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ማይክል ጃክሰን ብዙ ተወርቶለታል ብዙ ተብሎለታል፤ ግን ከላይ በፎቶ እንደምታዮት ጉዳይ በብዛት የተወራለት ድርጊት የለም። ነገሩ ሳይንስ ይሁን ድግምት፣ ብቃት ይሁን ሽወዳ እስከአሁን ብዙወች የሚነታረኩበት ጉዳይ ነው። Smooth Ccriminal የተባለ ዘፈኑ ላይ እንደምታዮት 45 ድግሪ ወደፊት አዝምሞ "በአፉ ወድቆ ጥርሱን ለቀመ" ሲባል ተመልሶ ቆመ! ይሄ ዳንሱ ቁጥር ስፍር የሌለው መላምት ተፅፎበታል ፣ ከፊዚክስ ባለሙያወች እስከጫማ ሰሪወች ተከራክረውበታል፣ ስለአጥንት አብጠርጥረው የሚያጠኑ ባለሙያወች /Osteologist?/  በየሚዲያው እየተጋበዙ ብዙ ብለዋል! ያዘመመ ሐውልት ሁሉ ቁሞለታል!

የሆነ ሆኖ ምኑ ነው እንዲህ ለአመታት ዓለምን ያነጋገረው? ማይክል ወደፊት ማዝመሙ ነው? አይደለም! መደነሱ ነው? ከአርጋው በዳሶ በላይ ማን ደነሰ ወገኖቸ? ማዝመም ሁላችንም እንችላለንኮ፤ ግን አንመለስም!  በዛው እንደደመራ ቋሚ እንገነደሳለን! የማይክልን ነገር አነጋጋሪ ያደረገው

አ.  ለ.  መ.  ው.  ደ. ቁ.  ነው !  አለመውደቁ! ቢወድቅ የአንድ ሰሞን ዜና ሁኖ ይረሳ ነበር!

ጓዶች! ኑሮም ይሁን ሰው አልያም ማንኛውም ነገር ገፍቷችሁ አዝምማችኋል? እንዳትወድቁ! እንደምንም ቀና በሉ፣ ወደፅናታችሁ ተመለሱ!! ያኔ ማዝመማችሁ ሳይሆን አለመውደቃችሁ ታሪካችሁ ይሆናል!!

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

በዚህ ዓለም ውስጥ ምንም ዘላለማዊ ነገር የለም፣ ችግሮቻችንም ጭምር።

     
      ©ቻርሊ ቻፕሊን

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

መሉ አቅምህን ተጠቀም!

አንድን ነገር ስትሰራ በሙሉ አቅምህ ተጠቅመህ ስራ ያ ነው እንድታድግ የሚረዳህ በግማሽ ልብ ሆነህ ምትሰራው ነገር ብዙም ለውጥ አያመጣልህም።

ስራውን አንተ ብቻ አይደለህም ምትሰራው ስራው በራሱም አንተን ይሰራሃል - Buruk


አንተ ምርጥ አድርገህ ስትሰራው ስራው ደግሞ አንተን የተመረጠ ሰው ፣ ተፈላጊ ሰው ያደርግሃል።

መልካም ቀን

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ጠዋትህን ጠብቃት!

ህይወት የምርጫ ጉዳይ ናት ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነቃ ቀናችንን የሚወስን አማራጭ ይቀርብልናል ፤ ያኔ ግን ተጠንቅቀን መወሰን የእኛው ምርጫ ነው ቀናችን ብሩህ እንዲሆን ከተመኘን ጠዋታችንን በፍቅር እና ደስ በሚል መንፈስ  ከእኛ አልፈን ለሌሎች ሰላምን ፍቅርን እና መልካምነትን በመስጠት እንጀምረዋለን ያኔ ቀኑ የእኛ ሲሆን እና በእኛ ላይ ሲያበራ ይውላል በተቃራኒውም ከመረጥን እንደዛው ስለዚህ ቀናችንን እንድንገዛው እና የእኛ እንድናረገው ጠዋታችንን እናስተካክለው!

መልካም ቀን ተመኘን🙏

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

#እንሞታለን
አንድ ቀን ለዘላለም ዝም ትላላችሁ
አንድ ቀን ለዘላለም ትሄዳላችሁ አንድ ቀን እስከወዳኛው ተረስታችሁ ትዝታ ትሆናላችሁ
አንድ ቀን ዳግመኛ እድል አይሰጣችሁም
        ያላችሁ አሁን ነው።
የናፈቃችሁ ጋር ደውላችሁ አውሩ
ያስቀየማችሁትን ይቅርታ ጠይቁ
አሁን.....😊😊
              

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

የፈረስ ውድድር አይታችሁ ታውቃላችሁ

ፈረስ ሩጫውን ለምን እንደሚሮጥ አያውቅም  ግን በቃ ሲመታ ይሮጣል።ሲመታ ህመሙ የበለጠ እንዲሮጥ(እንዲያሸንፍ) ያደርገዋል።

በቃ ሕይወትም  እንዲሁ ሩጫ ነው
ፈጣሪ ግን ጋላቢያችን ነው ❤ ️

ስለዚህ በህይወት ሩጫ በህመም ውስጥ ከሆናችሁ ፈጣሪ እንድታሸንፉ ፈልጎ ነውና ደስ ይበላችሁ።


share @ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

📖 100 ግመሎች!

በድሮ ግዜ በ እንዲት ትንሽዬ ከተማ ውስጥ የሚኖር ወጣት ነበረ:: ታድያ ይህ ሰው በህይወቱ ደስተኛ አልነበረም ፤ ምክንያቱ ደግሞ ህይወቴ በችግር የተሞላ ነው ብሎ ስለሚያስብ ነበር::

ታድያ በ አንድ ወቅት በዛች ትንሽዬ ከተማ እጅግ የተከበሩ ትልቅ ሰው እንደመጡ ይሰማል:: እርሱም በዛው እለት ምሽት እሳቸው ወዳረፉበት ቦታ ሄዶ እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው...

" እንዴት አመሹ አባቴ? ዛሬ እርስዎ ጋር  የመጣሁት በህይወቴ ደስተኛ ስስላልሆንኩ ነው፤ ምክንያቱ ደግሞ ሁሌ በ ችግሮች የተከበብኩ ሰው ነኝ:: የቤት ውስጥ ችግር፣ የስራ ቦታ ውጥረት፣ እንዳንዴም መታመም ብቻ በጣም ነው የደከመኝ:: ስለዚህ ከእርሶ ምፈልገው እንዚህን ሁሉ ችግሮች እንዴት እንደማሸንፍና እንዴት ደስተኛ ህይወት መኖር እንደምችል እንዲነግሩኝ ነው::"...

እርሳቸውም:- "ልጄ ዛሬ ስለመሸ፤ ነገ ማለዳ ምን ማድረግ እንዳብህ እነግርሃለሁ:: ባይሆን እንዚህን 100 ግመሎች ለዛሬ ምሽት ብቻ ጠብቅልኝ:: ሁሉም ግመሎች ቁጭ ሲሉልህ መተኛት ትችላለህ::" እርሱም ተስማማ...

በሚቀጥለው ቀን ማለዳ መጥተው "ልጄ እንዴት አደርክ?" ሲሉት "አይ አባት ለ አንድ ደቂቃ እንኳን አልተኛሁም፤ግመሎቹ ግማሾቹ እራሳቸው ቁጭ ሲሉ፣ ሌሎቹን ደግሞ እኔው እየዞርኩ አስቀመጥኳቸው ፤ የተቀሩት ግን እንዲሁ ሲያስቸግሩኝ ቁጭ ብዬ ነው ያደርኩት" አላቸው...

እርሳቸውም "ትላንት ያየህው ነገር  ነው የጥያቄህ መልሱ::አንዳንድ የህይወት ችግሮች በራሳቸው ጊዜ ይፈታሉ፤ ገሚሶቹ ደግሞ ባንተ ጥረት ፤ የተቀሩት ደግሞ ምንም ያህል ብትጥር አትፈታቸውም::ችግሮች የህይወታችን አንድ አካል ናቸዉ::

ህይወት ወጀቡ እስኪያልፍ መጠበቅ ሳትሆን፤ በዝናቡም ውስጥ ሆኖ መደሰትን ይጨምራል::”


@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ሶቅራጥስን ስኬት ምስጢር ምን እንደሆን እንዲነግረው ጠየቀው ሶቅራጥስ ከወጣቱ ጋር በነጋታው ጠዋት ከወንዙ ዳርቻ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዘ በነጋታው ሁለቱም እየተራመዱ ወደ ወንዙ ገቡ። ውሃው አንገታቸው ላይ ሲደርስ በድንገት ሶቅራጥስ ልጁን ገፍትሮ ውሃው ውስጥ ደፈቀው። ልጁ ለወጣት ቢታገልም ጉልበቱ ከሶቅራጥስ ጋር ሲመጣጠን ስላልቻለ ጥረቱ አልተሳካስትም። በመጨረሻ በጣቱ ፊቱ ሰማያዊነት መቀየር ሲጀምር ለቀቀው።ልጁ አየር ስቦ ከተረጋጋ በኋላ ሶቅራጥስ ጥያቄውን አቀረበለት ለመሆኑ ውሃ ውስጥ ሳለህ ከምንም ነገር በላይ አስፈስጎህ የነበረው ነገር ምንድነው? ልጁ ሳያማታ አየር ሲል መለሰለት። የስኬትም መስጥር ይህ ነው።ልክ አየር የፈለግከውን ያህል ስኬትንም ፈልገውና ታገኘዋለህ ሌላ ምስጢር የለውም አለው ሶቅራጥስ።
ክልብ መሻት የውጤታማ ጉዞ ዋነኛ መነሻ ነጥብ ነው፡፡ በፍንጣሪ እሳት በቂ ሙቀት ማግኘት እንደማይቻል ሁሉ ደካማ ፍላጐትም ታላቅ ውጤትን ሊያስገኝ አይችልም፡


መልካም ቀን ይሁንልን🙏

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

“ስለእንስሳት ባህሪ እና ሕክምና አላጠናሁም። ነገር ግን ክርክር ከመጀመሬ በፊት አህያው የቱ እንደሆነ የማወቅ ብቃት አለኝ።”

   ©ማርክ ትዌይን

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

መኖር ማለት የሶስት ቀናት ጥምር ውጤት ነው። ትናንት፣ዛሬ እና ነገ ወይም ትዝታ፣ ሕይወትና ተስፋ። ሕይወት ማለት በትናንት ትዝታህ ተመርኩዘህ በነገ ተስፋ ዛሬን መኖር መቻል ነው። ማንም ሰው ትዝታህን አጥፍቶ ተስፋህን እንዲነጥቅህ አትፍቀድለት ያ ከሆነ ግን የዛሬ መኖርህ ህልም ብቻ ነው። ምክንያቱም ትዝታና ተስፋን ያላዘለ ሕይወት ባዶና መድረሻ አልባ ነው። አስታውስ ትዝታና ተስፋህ ለዛሬ ሕይወትህ ምርኩዞች ናቸው።

ሰናይ ቀን


@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

«የምትማረው ሰው ሁሉ እውቅና በሰጠው መንገድና ቦታ መተዳደሪያ ልታገኝ ነው። የምታነበው ግን በሕይወት አንተ ብቻ እውቅና የሰጠኸው ደረጃ ላይ ለመድረስ ነው።»

©አለማየሁ ገላጋይ

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

አፍህን ዝጋ ከማለት...

አዞ ከምድራችን እንስሳት ሁሉ እጅግ ሀይለኛ የመንከስ አቅም ያለው ፍጥረት ነው። ለምሳሌ የሰው ልጅ በመጨረሻ አቅሙ ቢናከስ 162 PSI ( pounds per square inch) የመንከስ ሀይል አለው።  አንበሳ ፣ ጅብ ወዘተ 1000 pSI!  ይታያችሁ. በዚህ ንክሻ ነው አጥንት የሚሰባብሩት፣ እንስሳትን የሚገነጣጥሉት!  አጅሬው አዞ በአንዴ የሚያሳርፍባችሁ ሀይል 5000 Psi ይደርሳል።  የአንበሳን 5 እጥፍ ማለት ነው!

የሚገርመው ታዲያ አዞ ንክሻው እንዲህ ሀይለኛ ቢሆንም የመንጋጋ ጡንቻው  ደካማ ስለሆነ አፉን እንዳይከፍት ሰው በእጁ አፍኖ ሊይዘው ወይም በተልካሻ ክር ሊያስረው ይችላል። አንዴ አፉን እንደምንም  ከከፈተ ግን የተጠጋውን ሰው ይሁን እንስሳ እንጨት ይሁን ድንጋይ ብትንትኑን ነው የሚያወጣው። በሌላ አባባል አዞ አፉን እንዳይከፍት ማድረግ በጣም ቀላልና ትንሽ አቅም የሚጠይቅ ሲሆን፣ ከከፈተ በኋላ ማዘጋት ግን ህይወትን ጭምር ሊያስከፍል ይችላል።

ምን ለማለት ነው?  ለራሳችንም ቢሆን አንዴ የከፈትነውን አፍ ለመዝጋት ከመታገል ይልቅ መጀመሪያውኑ አለመክፈት ቀላሉ መንገድ ነው። አፍ ካለነገሩ  ከተከፈተ የሌሎችንም የራሳችንንም  አጥንትና ሕይወት ካልሰባበረ በቀላሉ አይዘጋም። እንግዲህ ታዘቡ፣ በየሶሻል ሚዲያው በየመድረኩ ጨዋ የሚባሉ፣ የፖለቲካ ፣ የእምነት ወዘተ  ሰወች አንዴ አፋቸውን መተሳሳተ መንገድ ከከፈቱ ስንቱን የሞራል አጥንት እንደሚሰባብሩት። ከከፈቱት በሰላም አይዘጋም። ራሳቸውንም ሌላውንም በልቶና አባልቶ፣ ደቀው እና አድቅቀው ወይ እንደከፈቱት ያልፋሉ አልያም ክፍታፍነትን መሳሪያቸው፣ ማስፈራሪያና መኖሪያቸው አድርገውት ይቀጥላሉ።


©አሌክስ አብርሃም

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

መስታወት ፊት ቆመህ ስትመለከት አለም ላይ ከተፈጠሩ ፍጡሮች ውብ የሆነውን ታያለህ"


©ቻርሊን ቻፕሊን

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

የሰው ልጅ
እንደ #አቦሸማኔ_መሮጥ ባይችልም
እንደ #ንስር አይኑ #አርቆ ባያይም
እንደ አንደ #አንበሳ_ጉልበት ባይኖረውም

ከሁሉ የበለጠ ሁሉን ሚገዛበት ድንቅ አእምሮ አለው።#አእምሯችንን_ለመልካም_ነገር_እንጠቀምበት።

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ለፈገግታ

አንድ የህግ ባለሙያ በባቡር እየተጓዘ ሳለ አንድ በጣም ቆንጆ የሆነች ልጅ መጥታ ፊት ለፊቱ ከሚገኘው ወንበር ላይ ተቀመጠች። በዚህም የህግ ባለሙያው ደስ አለው። ቀና ብሎ ሲመለከታት አይን ለአይን ተያዩ ከዛም ፈገግ አለች። አሁን ደግሞ በይበልጥ ደስ አለው። ትንሽ ቆይታ አጠገቡ ሄዳ ተቀመጠች።

በዚህን ጊዜ እጅግ በጣም ደስ አለው። ትንሽ ቆየችና ወደ ጆሮው ጠጋ ብላ በሹክሹክታ "ያለህን ገንዘብ; የATM ካርድህን ከነፓስ ዎርዱ እና የሞባይል ቀፎህን አሁኑኑ ካልሰጠኸኝ ስትጎነትለኝ እንደ ነበረና ፆታዊ ትንኮሳ እንደደረሰብኝ እዚህ ባቡር ውስጥ ላሉት ሁሉ በመንገር እጮኃለሁ።" አለችው።

የህግ ባለሙያው በቸልተኝነት ቀና ብሎ ተመለከታትና ከቦርሳው ውስጥ ወረቀትና እስክሪብቶ አውጥቶ እንዲህ ብሎ ፃፈላት "ይቅርታ መናገርና መስማት የተሳነኝ ነኝ። እባክሽን ማለት የፈለግሽውን ሁሉ እዚህ ወረቀት ላይ ፃፊልኝ።" ልጅቷም ቀደም ብላ ስትነግረው የነበረውን ሁሉ ጽፋ ሰጠችው። የህግ ባለሙያው ወረቀቱን ተቀብሏት በጥሩ ሁኔታ አጥፎ ኪሱ ከከተተው በኋላ ከተቀመጠበት ተነስቶ ጎርነን ባለ ድምጽ ምን ቢላት ጥሩ ነው "አሁን እንደፈለግሽ መጮህ ትቺያለሽ።"😁

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ስሜታዊ ሆኖ ለተናገረን ፣ ሊረዳን ፈልጎ ለሳተ ፣ ኑሮ አስክሮት ለገፋን ፣ ንዴት ገፍቶት ላጠፋ ፣ ግዜ አጣሁ ብሎ ላልጎበኘን ፣ ስናሸንፍ ላላጨበጨበ፣ ስንወድቅ ላላነሳን ፣ ስናስብለት ላልተረዳን ፣ ማደጋችንን ላላየ...

...."ትንሽ ቦታ ለይቅርታ..." ማዘጋጀት ይጠበቅብናል።

አማረልን ብለን ላሳዘንን ፣ አጉል ተስፋ ለሰጠነው ፣ ውድቀቱ ላይ ለሳቅነው ፣ ማድረግ ችለን ላላደረግነው ፣ ችለን ለተጣመምነው ።

ለራሳችንስ ይቅርታ አደርገናል...?

መልካም ቀን!

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ጥሩ ተናጋሪዎች ንግግራቸውን ካልተገበሩት፣ልክ እንደ ሙዚቃ መሳሪያ ድምጽ ብቻ ነው የሚያሰሙት።"


  © Diogenes

@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

አንድ ጊዜ የሞት መልክተኛ ወደ አንዲት ሴት ጋ ይመጣና
"እኔ የሞት መላእክት ነኝ ዛሬ አንቺ ተራሽ ሰለሆነ ነው ልወስድሽ መጥቻለሁ" ይላታል
ሴትየዋም ተደናግጣ "ግን እኮ አልተዘጋጀሁም" ብላ ትነግረዋለች ።
የሞት መልክተኛውም
እንግዲህ ምንም ማድረግ አልችልም ሊስቴ ላይ ያለው የመጀመሪያ ስም ያንቺ ነው" አላት። ሴትየዋም ምን ማምጣት እንማትችል ሲገባት ተስፋ በመቁረጥ "እሺ በቃ ትንሽ አረፍ በል የሚበላ ነገር ላምጣልህ እኔም ቤተሰቦቼን እና ጓደኞቼን ልሰናበት ከዛ ይዘኸኝ ትሄዳለህ" አለችው።
መልክተኛውም በሴትየዋ ሀሳብ ተስማምቶ ቁጭ አለ። ሴትየዋም አንድ ሀሳብ መጣለትና ምግቡ ውስጥ የእንቅልፍ መድኃኒት ጨምራ ለመልክተኛው ምግቡን ሰጠችው። መልክተኛውም ምግቡን በልቶ ከጨረሰ በኃላ ወዲያው ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ሲወድቅ ሴትየዋ በፍጥነት መልክተኛው ስም ዝርዝር የፃፈበትን ሊስት አንስታ የሷን ስም ከመጀመሪያው አጥፍታ መጨረሻ ላይ አደረገችው።
መልክተኛው ከጥልቅ እንቅልፍ ሲነሳ ሊስቱን ያነሳና " እንግዲህ ስላደረክልኝ እንክብካቤ በጣም አመሰግናለሁ።ሰለተንከባከብሽኝ በጥሩ ሁኔታ ስላስተናገድሽኝ ለዛሬ ላንቺ ብዬ ከመጨረሻ እጀምራለሁ😂

ማንም ሰው ከቀኑ አያልፍም
‼️

Share @ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

በህይወት ጎዳና ውስጥ ሁሉም ይቀየራል.....


ከእናት ፍቅር በስተቀር


ከተስማማችሁ ♥️

share @ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ልዩነት ለመፍጠር ትንሸ እንደሆንክ ካሰብክ ትንኝ ባለበት ለመተኛት ሞክር!


©Dalai Lama

በቅንነት like share እያደረጋችሁ
@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

Do you love wallpapers? 🌇❤️
What kind of wallpapers do you like?

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

በመሠረቱ ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ ። ነገሮችን የሚያከናውኑ ሰዎችና ነገሮችን እንዳከናወንኩ የሚናገሩ ሰዎች። የመጀመሪያው ቡድን ብዙም አይጨናነቀውም ።


© Mark Twain

SHARE||@ethio_tksa_tks

Читать полностью…

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

ዋጋችሁን እወቁ

አንድ መምህር የሀምሳ ብር ኖት ወደ ላይ ከፍ አድርጎ በመያዝ ለተማሪዎቹ ማን ነው ይህን የሚፈልግ አላቸው። ሁሉም እጃቸውን በማውጣት ቲቸር እኔ..... እኔ ..... ማለት ጀመሩ። መምህሩ ብሯን በእጁ ጭምድድ ካደረጋት በኋላ ዳግም ወደላይ ከፍ አድርጎ አሁንስ ማነው መውሰድ የሚፈልግ አላቸው። ሁሉም ተማሪዎች አሁንም እጃቸውን በማውጣት ልክ እንደመጀመሪያው እኔ..... እኔ እያሉ ጩኸታቸውን ቀጠሉ። መምህሩ ብሯን መሬት ላይ ከጣላት በኋላ በጫማው እየረጋገጠ አቆሸሻት። ከዚያ ወደ ላይ ከፍ በማድረግ አሁንስ ማነው መውሰድ የሚፈልግ አላቸው። ተማሪዎቹ ብሯን በዋዛ ሊያሳልፏት ስላልፈለጉ ልክ እንደመጀመሪያዎቹ ጊዜያት እጆቻቸውን በማውለብለብ ቲቸር እኔ..... እኔ.... ማለታቸውን ቀጠሉ።
መምህሩ ብሯን (ልጆቹን በማስጎምጀት እንዳይከሰስ እንጂ) ወደ ኪሱ በመመለስ የዛሬው ትምህርታችሁ እዚህ ላይ ያበቃል። ቀዳደህ ካልጣልካት በስተቀር በማሸት፡ በማቆሸሽና በመረጋገጥ የዚህችን ወረቀት ዋጋ መቀነስ እንደማይቻለው ሁሉ እናንተንም ሰዎች ሊያንቋሽሿችሁ፡ ሊያሳንሷችሁ፡ ሊያዋርዷችሁ፡ ሊያፌዙባችሁ፡.......ጥረት ቢያደርጉም ትክክለኛ ዋጋችሁን ሊቀንሱ እንደማይችሉ እወቁ። ይህን ካወቃችሁ ከውድቀት በኋላም መነሳት ትችላላችሁ። ሁሉም ትክክለኛ ዋጋችሁን እንዲያውቅ ማድረግ ትችላላችሁ። ነገር ግን ትክክለኛ ዋጋችሁን የረሳችሁ እና በራስ መተማመናችሁን ያጣችሁ ቀን ሁሉንም ነገር ማጣታችሁን እወቁ!!

Share @ethio_tksa_tks

Читать полностью…
Subscribe to a channel