እንኳን ደህና መጡ። በቴሌግራም ውስጥ የታዋቂ ሰዎች ማለትም 💥አርስቶትል 💥አብርሀም ሊንከን 💥አልበርት አንስታይን 💥ማህተመ ጋንዲ... እንዲሁም የሌሎችም አባባል የሚያገኙበት ቻናል🎯 ሲሆን አላማችንም ሰዎች በሚያነብቡት ጥቅስ የአስተሳሰባቸውን አድማስ ማስፋት ነው። ስለመረጡን እናመሰግናለን 🙏 Contact፦ @onajonah
« ጦርነት ሲጀምር ፖለቲከኞች ጥይት ያቀብላሉ፡፡ባለፀጎች ምግብ ያቀርባሉ፡፡ድሆች ልጆቻቸውን ይለግሳሉ፡፡ጦርነቱ ሲያበቃ ፖለቲከኞች ቀሪ ጥይቱን ይሰበስባሉ፡፡ባለፀጎች ከጦርነቱ በተረፈው ሐብታቸው ማደግ ይጀምራሉ፡፡ድሆች ግን ልጆቻቸውን በመቃብር ስፍራ ይፈልጋሉ »💔
Читать полностью…በአንድ ወቅት የሪቻርድ ፓንክረስት ወዳጅ የሆነው ኤድዋርድ ኡሉንዶርፍ ወደ አንዱ የኢትዮጵያ ገጠራማ ክፍል ለጥናት ሄደ፡፡ አንድ ገበሬ ቤት ገባ፡፡ እግሩን ሊያጥቡት ሲሉ አንገራገረ፡፡ አስተርጓሚው ባህል እንደሆነ ነገረው፡፡ በደንብ ታጠበ፡፡ እግሩን ተሳመ። እንግዳ ክቡር ነው። ያ እንግዳ በረከት ነው ብለው ያምናሉ። ቤቱም የእግዜር ነው።
ምሳ አበሉት፡፡
"ስንት እንከፈላቸው" ብሎ ጠየቀ
"ነፃ ነው" ብሎ ነገረው አስተርጓሚው።
መሸ፡፡ መጠጥ ይዘው አምሽተው እንደገና እራት በሉ።
ማታ ባልና ሚስት አልጋቸውን ለእንግዶች ለቀው መሬት ላይ ተኙ፡፡
ጥዋት ቁርስ በሉ፡፡
"የአልጋ እና የቁርስ እንከፈል" አለ ኡሉንዶርፍ
"ነውር ነው" አለው አስተርጓሚው፡፡
ከዚያ ስመው ተሰናብተው ወደሚሄዱበት ሀገር በራሳቸው በቅሎ ሸኟቸው፡፡
በመጨረሻ ኡሉንዶርፍ አንድ ታላቅ ነገር ተናገረ-እንዲህ ሲል <<ዓለም መፅሐፍ ቅዱስን ያነበዋል፥ ኢትዮጵያውያን ግን ይኖሩታል>>
መንፈሳዊ ስልጣኔ፣ ሰብአዊነት፣ ሰውነት!
የላይኛው ያስባችሁ!
#መልካም_ቀን
SHARE||@ethio_tksa_tks
«የማዋረድ ሩጫ» ‼የእንግሊዙ መሪ የነበሩት ዊንስተን ቸርችል እጅግ አንደበተ ርቱዕ፥ ሲናገሩ የሚያፈዙ፥ ጨዋታም ጭምር አዋቂ ናቸው ይባልላቸዋል። እርሳቸው ንግግር ሊያደርጉ ነው የተባለ እንደሆነ፥ ሰው ሁሉ ካለበት መጥቶ ተሰብስቦ ያዳምጣቸው ነበር።
በአንድ ወቅት አንድ ጋዜጠኛ ሲጠይቃቸው፥ “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር፥ እርስዎ ንግግር ሲያደርጉ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተሰብስቦ የሚያዳምጥዎት መሪ ነዎት። ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስቦ ሲያዳምጥዎት ምን ይሰማዎት ይኾን?” ብሎ ጠየቃቸው። እርሳቸው ግን የሰውን ስነልቡና በደንብ ጠንቅቀው የተረዱ ብልህ ስለነበሩ፤ “ተፈርዶበታል ይሰቀል ቢባል ከዚህ በላይ ሕዝብ አይሰበሰብም ብለህ ነው?” ብለው መለሱለት ይባላል።
ታላቁ ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ ወልደሕይወት ሲመክር «እንደ ንብ ሁኑ» ይላል። ንብ መልካም መልክ እና መዓዛ ካላቸው አበቦች ስትደክም ውላ ማር ትሠራለች። እርሷ የሠራችው ማር፥ ከራሷ አልፎ ሌላውን ይመግባል። የራሷን እድሜ ተሻግሮ ከአንድ ሺህ ዓመት በላይም ሳይበላሽ ይቆያል። በዚህ ‘ዘመናዊ’ በተባለው ዘመን ግን የሰው ልጅ ከንብ ይልቅ የዝንብን ጠባይ እየተዋረሰ መሄዱን ማሰብ ያሳዝናል። ይህንን ለማወቅ ወደ ዩቲዩብ ጎራ ብሎ በብዙ መቶ ሺህ እይታዎች ያላቸውን ቪዲዮዎች ርእስ ማንበብ በቂ ነው።ከሚጠቅመን ምክር ይልቅ የሚጎዳንን አሉባልታ፥ ከሚያንጸን ትምህርት ይልቅ የሚያውከንን ዜና ለመስማት እንከጅላለን። የተወደዱት ሲጠሉ፥ የተከበሩት ሲዋረዱ፥ የተመረቁት ሲረገሙ ለማየት ያለን ጉጉት ያስፈራል። የሰው ልጅ በታሪኩ ውስጥ የተከበሩትን ለማዋረድ የሮጠበት ጊዜ ብዙ ነው። ሰው አንዳንዴ ለጌታም አይመለስም።
“ሆሳዕና”
ያለ ሕዝብ መልሶ “ይሰቀል” ለማለት ብዙ ጊዜ እንዳልፈጀበት ማስታወስ መልካም ነው።
አንድ መምህር ወረቀት ላይ ነጥብ አስቀምጦ “ምን ይታያችኋል?” ብሎ ተማሪዎቹን ሲጠይቅ፤ እነርሱም “ጥቁር ነጥብ” ብለው መለሱለት። ሰፊ ቦታ የያዘው ነጩ ወረቀት ሆኖ ሳለ፥ ተማሪዎቹ ግን ያዩት ጥቁሩን ነጥብ ነው። ከብዙው መልካም ትንሿን ሕጸጽ አጉልቶ ማየት የሚያስገርም ነው። እኛም ብዙ ሰዎች ከመልካም ጎናቸው ሰዋዊ ድካማቸው ጎልቶ ይታየናል። የብዙ ዓመት ድካማቸውን በአንድ ቀን የተዛነፈ ሚዛን አሽቀንጥረን እንጥላለን። በመረቅናቸው አፍም መልሰን ስንረግማቸውም ለነገ አንልም። ዛሬ የመረቀ አንደበት፥ ነገ ተሳዳቢ ሆኖ ሲገኝ ያሳፍራል።
ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ “ከአንድ አፍ በረከት እና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።” (ያዕ 3፡10)
መምህር ኤስድሮስ የተባሉት ሊቅ ያስተማሩትን የመንፈስ ልጃቸዉን ሲመክሩ እንዲህ አሉት፡፡
"ልጄ ከመሃይም አትጣላ ፣ ደጋፊው ብዙ ስለሆነ ያሸንፍሃል"
© Yismake Worku
SHARE||@ethio_tksa_tks
"በተማርኩ ቁጥር ምን ያህል እንደማላውቅ እገነዘባለሁ።
🙏 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ 🙏
"የምንኖረው መኖር ስለምንችል ሳይሆን የሚያኖር አምላክ ስላለን ነው"
እስቲ ለደቂቃ ሁላችንም ፀጥ እንበልና ወደ ውስጣችን በትዝታ እንንጎድ፡፡ እውነት በእኛ እውቅት ብቻ አጥንተን ስንቱን ፈተና እየሰራን ተምረን ተመረቅን?
እስቲ በእኛ የንግድ ችሎታ ተጠቅመን ስንቱን ነግደን አተረፍነው?
እስቲ በእኛ የመናገር ችሎታ ታግዘን ስንቱን አሳምነን መሪ ሆንን?
እስቲ በእኛ የህክምና እውቀት ተጠቅመን ስንቱን ከበሽታ አዳነው?
እስቲ በእኛ መልካም ስነ-ምግባር ታግዘን ስንቱን መልካም ወዳጅ አፈራነው?
እስቲ በእኛ እውቀትና ጥበብ ተጠቅመን ስንቱን ችግር አለፍነው?
✍ ብቻ ምን አለፋችሁ እግዚአብሔርንም አመንን አላን እስከዛሬ የኖርነውም ሆነ አሁን እየኖርን ያለነው የሚያኖር አምላክ ስላለን እንጂ እኛ መኖር ስለምንችል አይደለም፡፡
ጎበዝ ተማሪ ብንሆን በእሱ ነው፤ እጅግ የተፈራ መሪ ብንሆን በእሱ ነው፤ የናጠጠ ሃብታም ነጋዴ ብንሆን በእሱ ነው፤ በሰዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅና ተፈቃሪ ብንሆን በእሱ ነው፡፡
እናም ወዳጄ የትኛውንም እምነት ተከተል ነገር ግን ፈጣሪክ ለአንተ ያደረገውን ለማሰብና ለማመስገን ጊዜ አትጣ፡፡
እስከዛሬ ላደረክልኝ፤ ወደ ፊትም ለምታረግልኝ ሁሉ አመሰግናለሁ በለው ፡፡
SHARE||@ethio_tksa_tks
#ኦፕራን_ተመልከታት
👉 ልጅ ሳለች
- ከድንች ማዳበሪያ የተሰራ ልብስ ለብሳለች።
👉 ለዓመታት ስትደፍር ቆይታ
በ13 ዓመቷ ከቤቷ ወጥታ ጠፍታለች
👉 በ14 ዓመቷ ተደፍራ አርግዛለች
👉 በ20 ዓመቷ ራሷን ልታጠፋ ነበር
👉 በ30 ዓመቷ ትልቅ ድብርትና
ሱስ ውስጥ ወድቃ ነበር!
ዛሬስ?
ዛሬ ያን ሁሉ አሸንፍ የዓለማችን ቁንጮ የሚዲያ ሰው ናት።
ችግርና ፈተና ቢያደክምህም እንዲረታህ አትፍቀድለት።Читать полностью…
ፓኪስታናዊ ጸሓፊ አዲብ ሚርዛ እንዲህ ይላል፦
አባቴ ሁሌ ይደበድበኛል እናቴም ከእሱ ምት እንዳዳነችኝ ነበር። ስለዚህ ለራሴ አልኩ፦ “አንድ ቀን እናቴ ብትደበድበኝ አባቴ ምን ያደርጋል?”
እና ይህን ለማየት እናቴ ወተት ከገበያ አምጣ ብላ ስትልከኝ አልታዘዝም አልሄድም አልኳት። ለምሳ ቁጭ ስንል ሳህኔ ላይ የተመለደውን መጠን ያህል ምግብ አደረገችልኝ። ሁሌ ትንሽ ነው የምታደርጊልን ጨምሪልኝ ብዬ ጮሁኩባት። እሷም እየጨመረችልኝ ‹‹ወንበር ላይ ቁጭ ብለህ ብላ›› አለችኝ። እኔ ግን አውቄ መሬት ላይ ቁጭ ብዬ ልብሴን እያቆሸሽኩ ባለመደችው ቃና ማውራት ጀመርኩ። እናቴ ትመታኛለች ብዬ ስጠብቅ እሷ ግን አጥብቃ እቅፍ አድርጋኝ ‹‹ልጄ ምን ሆነ ነው አሞሃል እንዴ?›› አለችኝ። ያኔ መቆጣጠር የማልችለው የሀዘን ስሜቴን አይኔን በእንባ ሞላው።
እናቴ ለዘለአለም ኑሪልኝ❤️
SHARE||@ethio_tksa_tks
💎ከክፉ ትናንትህ ፊትህን አዙር!!
Let it go the past!
💡ሰው በዓለም እያለ በፈተና መኖሩ የታየና የተረጋገጠ እውነታ ነው፡፡ ማንም በሕይወት መንገዱ ላይ እንቅፋት አያጣውም፡፡ የሰው ልጅ በእድሜ መሰላል ወደ ላይ ሲወጣ፤ ወይ መጀመሪያው ላይ፣ ወይ መጨረሻው አካባቢ፤ አልያም ደግም መካከሉ የዕድሜ ዘመን ላይ አንሸራትቶት የሚፈጠፍጠው አዳላጭ አይጠፋውም፡፡ ድሃ ይሁን ሐብታም፤ ተራ ይሁን ባለስልጣን፤ ሊቅ ይሁን ደቂቅ፣ ብቸኛ ይሁን ባለብዙ ዘመድ ሕይወቱ የሚፈተንበት፣ ኑሮው የሚደናቀፍበት እክል አያጣም፡፡ ሰው ነዋ!
💡አንዳንዱ በማጣት ይፈተናል፤ አንዳንዱ በማግኘት ይፈተናል፤አንዳንዱ በጥጋብ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በረሃብ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በገንዘብ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በዕውቀቱ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በውበቱ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በሀዘን ይፈተናል፤ አንዳንዱ በደስታ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በጤናው ይፈተናል፤ አንዳንዱ በፍቅሩ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በዓመሉ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በገዛ ልጁ ይፈተናል፡፡ ሰው ይፈተንበት ዘንድ የተሰጠው ፈተና ሺ ነው፡፡ እስትንፋሱ እስካለች ድረስ ፈተናው አያልቅም፡፡ ተረጋጋሁ ሲል የሚረበሽ፤ አረፍኩ ሲል እንከን የማያጣው ጥቂት አይደለም፡፡ ኑሮዬ ተስተካከለ፤ ሕይወት ሰመረልኝ፤ ጎጆዬ ሞቀ፤ ሁሉ ነገር አማረልኝ ሲል የሚበላሽበት፣ በብዙ የሚጎድል፤ ደስታውን ሳይጨርስ ሐዘን የሚገባው ዕድለቢስ ብዙ ነው፡፡ ሰው ነዋ!
ፕሮፌሰሩ ለተማሪዎቻቸው ምሳሌ የሚሆን አንድ ብርጭቆ ውሃ አዘጋጁ፡፡ ብርጭቆውን አንስተው፡-‹‹የዚህ ብርጭቆ ውሃ ክብደቱ ምን ያሕል ነው?›› ብለው ጠየቁ፡፡ ተማሪዎቹም የራሳቸውን ግምት መመለስ ጀመሩ፡፡ አንዱ 8 ኦዝ ነው፤ ሌላኛው 12 ነው፤ ሌሎቹ 16፣ 10፣ 8፣ ወዘተ አሉ፡፡
🕯ፕሮፌሰሩ የመላሾቹን ተማሪዎች እጆች እየጨበጡ ለሁሉም አድናቆታቸውን ገለፁ፡፡ ጥያቄው ስለፊዚክስ አይደለም፡፡ ጥያቄው ክብደቱን የማወቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ጥያቄው ዋናው ትኩረቱ ስለብርጭቆው ውሃ አልነበረም፡፡ ፕሮፌሰሩ የጥያቄውን ዋና ቁምነገር ማብራራት ጀመሩ፡-
‹‹ትክክለኛው የብርጭቆው ክብደት ትርጉም አያመጣም፡፡ ቁምነገሩ ያለው ብርጭቆውን ለምን ያህል ጊዜ ይዘነዋል የሚለው ላይ ነው››
በማለት የፍሬ ነገሩን ጭብጥ ተናገሩ፡፡
💎‹‹ለምሳሌ ይሄን ብርጭቆ ለጥቂት ደቂቃ ብቻ ብይዘው ክብደቱ ያን ያህል አይደለም፤ ነገር ግን ለሰዓታት ብይዘው ግን ክንዴ ይዝላል፤ እጆቼም ይደክማሉ፡፡ ለቀናት ብይዘው ደግሞ ክንዴ ሽባ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የብርጭቆው ውሃ ክብደት ባይለወጥም የምይዝበት ጊዜ ግን ብርጭቆውን ከባድም ሆነ ቀላል ያደርገዋል፡፡›› ሲሉ አስረዱ፡፡
ተማሪዎቹም በሃሳባቸው መስማማታቸውን ጭንቅላታቸውን በማወዘወዝ ገለፁ፡፡ ፕሮፌሰሩ ስለብርጭቆው ሚስጥር ገለፃቸውን ቀጠሉ፡፡
🔑‹‹ጭንቀትም ልክ እንደብርጭቆው ውሃ ነው፡፡ ጭንቀታችንን ለትንሽ ጊዜ ብቻ ከያዝነው ብዙ ችግር አይፈጥርም፡፡ የምንጨነቅበት ሰዓት እየረዘመ ሲመጣ ግን ጉዳት ያስከትላል፡፡ ጭንቀታችን ለቀናት፣ ለወራት አልፎ ተርፎ ለዓመታት ሲሆን ደግሞ በጣም ይጎዳናል፡፡ በጤናችን ላይ፣ በኑራችን ላይ፣ በአስተሳሰባችን ላይ ችግር ያመጣል፡፡ የማሰብ አቅማችን ሽባ ያደርጋል፡፡ አዲስ ሕይወት ለመጀመር የሚያስችል ብቃት እናጣለን፡፡ በአጠቃላይ አቅመ ቢስ እንሆናለን›› በማለት የብርጭቆውን ምሳሌ አብራሩ፡፡
በመጨረሻም ፕሮፌሰሩ የያዙትን ብርጭቆ ጠረጴዛቸው ላይ እያስቀመጡ፡-
‹‹ሁልጊዜም ቢሆን ብርጭቆውን ከመያዝ ይልቅ ማስቀመጣችሁን አትርሱ›› ... በማለት የዕለቱ ትምህርታቸውን ጨረሱ፡፡
💎እውነት ነው! ብዙዎቻችን በትናንት እየተብከነከንን፣ ባለፈው እየቆሰልን ዛሬን እንገድላለን፤ ነጋችንንም እናጨልማለን፡፡ አንዳንድ ክፉ ቀንን ‹‹ይሁን እንግዲህ ካመጣው›› ብሎ ማሳለፍ መልካም ነው፡፡ የመጣው ሊያስተምረን እንደሆነ ራሳችንን በማሳመን እንደመጣው ሁሉ እንዲሄድ ልንፈቅድለት ይገባል፡፡ አባቶቻችን ‹‹መተው ነገሬን ከተተው!›› የሚሉት ልንለውጥጠው የማንችለውን ነገር መተው ጭንቀትን ጠቅልሎ እንደመጣል ነው ማለታቸው ነው፡፡ ፈረንጆቹም ቢሆን የመጣባቸውን የህይወት ሳንካ የሚያሸንፉት ከችግሩ ጋር በመቋሰል ሳይሆን ‹‹Let it go›› በማለት ነው፡፡
💡ወዳጄ ሆይ... በራስህም ይሁን በሌላ ምክንያት የመጣብህን ፈተና ከቻልክ ለውጠው፡፡ ልትለውጠው ካልቻልክ ደግሞ ተቀበለውና ትምህርት ውሰድበት፡፡ የሆነውን መቀየር ባትችልም አንተ ግን ተለወጥ፡፡ ከክፉ ትናንትህ ፊትህን አዙር!! ያለፈውን ቁስልህን እየነካካህ ራስህን አታሳምም፡፡ ከትናንትህ ነፃ ውጣ፡፡ ይዘኸው የቆየኸውን የዘመን ሸክም ከጫንቃህ አውርድና ትከሻህን አሳርፍ፤ ራስህን ፍታ! ጭንቀትህን ጣልና የአዕምሮ ሠላምህን ተጎናፀፍ!!
የትናንትህን ጣጣ አስቀምጠህ ቆልፍበት እንጂ ተሸክመኸው አትዙር! (Always remember: put the glass down)
ነፃ ማንነት! አዲስ ሰውነት!
SHARE||@ethio_tksa_tks
🐎 እንደ ፈረስ እሩጥ (Run like a horse🐴)
🪽 አንድ አትሌት በልምምድ ሰዓት በተደጋጋሚ ይደክመውና ሩጫውን ማጠናቀቂያው ጋር ሳይደርስ ያቆማል።
🪽 ከዛ ሚስቱ አንድ ምክር ሰጠቸው "እንደ ፈረስ 🐎 እሩጥ!"ስትል፤
🪽 "ምን ማለት ነው እንደ ፈረስ እሩጥ?" ስለመጨረሻው አታስብ አሁን ላይ ሆነህ (present) እሩጥ። ፈረስ ሲሮጥ የመጨረሻውን መዳረሻ እያሰበ አይደለም፤ የቻለውን ያህል ይጋልብ ይጋልብ እና ከአቅሙ በላይ ሲሆንና ሲደክመው ያቆማል።
🪽 አንተም እንደ ፈረሱ መጨረሻ ላይ መድረስ ሪከርዱን መበጠስ ሚለውን ትተህ አሁን ላይ አንድ እርምጃዋን ውሰድ ከዛም ሌላኛውን..
🪽 ይህ ምክር ለአትሌቶች ብቻ አይደለም፤ ለእኛም ይሆናል ብዙ ጊዜ ግባችን ላይ እናተኩርና ትልቅ ሆኖ ከባድ ሆኖ ሲታየን ተስፉ እንቆርጣለን፣ እናቆማለን።
🪽 ግን ትልቁ ግብ ላይ ማተኮር ትተን ወደ ግባችን ሚያደርሰንን ትንሹን ስራ ብንሰራ ግባችን ጋር መድረሳችን አይቀርም።🐴
SHARE||@ethio_tksa_tks
ማይክል አንጀሎ ታላቅ የሆነ የዕምነበረድ ቅርፅ ሰርቶ አስመረቀ፤ ሰዎች ተገረሙ አንዳንዶች በእጅ ጥበቡ ውበት ተደንቀው 'ታይቶ የማይታወቅ' አሉ። እሱ ግን ተጠየቀ "ይሄን የዳዊትን ቅርፅ እንዴት እንዲህ ድንቅ አርገህ ሰራኸው" ተባለ፤ ከዛ መለሰ "አንድ ትልቅ ዕምነበረድ አመጣሁና የማያስፈልገውን ሁሉ ገፍፌ ፈቅፍቄ ከላዩ አነሳሁለት፤ ምንም የተለየ ነገር አለሰራሁም" አለ።
አንዳንዴ ከህይወትህ ተቆርጠው ተገፈው የሚወጡ ሰዎች ሁኔታዎች ትዝታዎች ሁሉ ታላቁ ማንነትህን ግልጥ አድርገው ሊያወጡት ስለሚችሉ በዚህ አለም ፈተናዎች በፍፁም አትደንግጥ!
=>ስህተትን ከተረዱ በኃላ መመለስ
ተሳስቼ ነበር ለማለትም አለመግደርደር
=>በችግር ግዜ ተስፋ አለመቁረጥ
በሀዘንም ግዜ አለመደንገጥና
እራስን መቆጣጠር
=>የተጣሉትን ወዳጅ ሚስጥር አለማባከን
መልካም ውለታውንም አለመርሳት
=>ሳይመች ተለማማጭ ሲመች ተሳዳቢ አለመሆን ነው!
SHARE||@ethio_tksa_tks
"ፈጣሪ የት ነው..?"
(ሩሚ)
የክርስቲያን መስቀል ላይ ልፈልገው ሞከርኩኝ ነገር ግን ከዛ የለም! የሒንዱስ ጥንታዊ ቤተ-መቅደስ ፓጎዳ ጎራ አልኩኝ ቢሆንም ዱካውን የትም ላገኘው አልቻልኩኝም!
ከተራራው እና ከሸለቆው አሰስኩት ግን በከፍታም፣ በዝቅታም ለማግኘት አልተቻለኝም! መካ ውስጥ ካዕባም ተጓዝኩኝ በተመሳሳይ እዛም ቢሆን የለም!
ጠበብቶች እና ፈላስፎችን ጠየኩኝ ዳሩ ግን እሱ (ፈጣሪ) ከመረዳታቸው በላይ ነው!
በመጨረሻ ከልቤ ስፍራ ማተርኩኝ፣ ማረፊያውን ያፀናው እዛ ነው፤ አየሁትም! እናም ሊገኝ ሚችልበት ሌላ ቦታ የለም!
Charlie Chaplin once lost his own lookalike contest, and some say this is a lesson about the difficulty of imitating someone else.
ቻርሊ ቻፕሊን አንድ ጊዜ ቻርሊ ቻፕሊን የማስመሰል ውድድር ላይ ተሸንፏል። 😄
አንዳንዶች ይህ ሌላን ሰው ለመምሰል የመሞከር ከባድነት የሚያሳይ ትምህርት ነው ይላሉ.
/channel/ethio_tksa_tks
(ካነበብኳቸውና ከሚረብሹኝ ነገሮች አንዱ💔)
―ዶክተሩ፡- የስኳር በሽታው ጸንቶብሻል ሌላኛውን እጅሽን ለመቁረጥ እንገደዳለን..
እሷም እንዲህ አለችው፦ “ አንድ ሳምንት መጠበቅ እንችላለን። ልጄ ጉዞ ሊያደርግ ነው። እና በአውሮፕላኑ ውስጥ ሲገባ ለመጨረሻ ግዜ እጄን ማወዛወዝ እፈልጋለሁ!”
―ዊልሰን እንዲህ ይላል፡-
“ከለሊቱ 8 ሰአት ላይ የእግዚአብሄርን መኖር የካድኩበትን ፅሁፍ ጨረስኩ እና ስተኛ እግዚአብሔር ምን ያደርገኛል በሚል ፍርሃት መብራቱን ማጥፋት አልቻልኩም ነበር።
―በትምህርት ቤት ደካማ ተሳትፎ የነበረው አንድ ልጅ ወደ እናቱ መቃብር ሄዶ፡- መች ነው እኔ ጋር የምትመጪው? መምህሩ በተማሪዎቹ ፊት ሁሌ እየመታኝ እንዲህ ይለኛል፦ “እናትህ ግድ የለሽ ናት ስለ አንተ ደንታ የላትም!”
― “ባሌ ቸልተኛ ይለኛል ምክንያቱም ፀጉሬ ሁል ጊዜ የምሰራው ምግብ ላይ ስለሚረግፍ። እንዴት ብዬ ነው ካንሰር እንዳለብኝ የምነግረው!”
― “የእናቴን ሬሳ ከመጠቅለሌ በፊት አፍንጫዋ ውስጥ ጥጥ ማስገባት ነበረበኝ። እና ጥጡን ከጓዳ ለማምጣት ስላልተመቸኝ ሁሉንም ዘንግቼ ጮክ ብዬ ተጠራሁ “እማዬ ከጓዳ ጥጥ አምጪልኝ..”
💔
|እነዚህ የእውነት ክስተቶች ናቸው የትኛው የበለጠ ያማል?|
ብዙ ሰዎች ያውቁናል ግን
የሚረዱን ጥቂቶች ናቸው!
አንዳንዴ ህይወት ልክ እንደ ሊፍት ነው ወደ ከፍታ እየወጣን ባለንበት ሰአት አቁመን መውረድ ያለባቸው ሰዎች እንዲወርዱ ማድረግ አለብን።Читать полностью…
ሁሉም ሰው ዓለምን ስለመቀየር ያስባል፤ ነገር ግን ማንም ራሱን ስለመቀየር አያስብም።
ፍቅር እንደ ጦርነት ነው ለመጀመር ቀላል ነው ፣ ግን ለማቆም በጣም ከባድ ነው ።
ህይወት እየኖርን ነው ብለን በሙሉ አፋችን የምናወራ ሰዎች ካለን በኪስ ማበጥ ሳይሆን በሰብዓዊነት መጋመድ ውስጥ ነው ህይወት የምታምረው🥰
ከታች በምስሉ ላይ የምታዩት ወጣት abinetmg በሚል user name የሚታወቅ የዋቻሞ ዩንቨርስቲ ተማሪ ነው።
ታዲያ ሰሞኑን በተከበረው የገና በዓል ላይ በሚማርበት ዩንቨርሲቲ ዶርም ውስጥ ሆኖ
"ሁሉም ለበዓል ወደ ቤት ሄደው ዶርም ውስጥ ብቻዬን ቀረሁ....ለማንኛውም እንኳን አደረሳችሁ" የሚል እና አንጀት የሚበላ ቪዲዮ በቲክቶክ ሰርቶ ለቀቀ። ከዛስ❓
ከዛማ....በብዙ ጫናዎች ምክንያት ሞቶ የተቀበረ የመሠለን #የኢትዮጵያዊነት_ፍቅር መቃብሩን ፈንቅሎ ዘራፍ ብሎ ወጣ። ኢትዮጵያዊ ወንድምና እህቶች፣ አባቶችና እናቶች..ከጋምቤላ፣ ከሀረር፣ ከድሬ፣ ከወለጋ፣ ከጅማ፣ ከባህርዳር፣ ከሀሩማያ፣ ከጎንደር...እያሉ አይዞህ እኔ አለሁህ አካውንትህን ላክ፣ ያለህበትን አሳውቀንና በአሉን አብረን ፈታ እንበል፣ እኔ አስተምርሃለሁ ወዘተ፣ ወዘተ የሚል ከልብ የመነጨ የፍቅር መልዕክት ጎረፈ።
ከሁሉም የገረመኝ አንድ ወጣት "በውትድርና ላይ ተሰማርቼ እየሰራሁ ነው....ያለህበትን ንገረኝና ቤተሰብ ለበአል የላከልኝ አንድ ሺብር አለችኝ በሷ ፈታ እንላለን.." ያለውን ሳነብ ያጋመደን፣ ያስተሳሰረንን፣ ያዋደደንን #ኢትዮጵያዊነት_ጥልቅ_ፍቅር በማየቴ የደስታ እንባ አነባሁ።
ሁሉም ሰዎች በቃላቸው መሰረት በአካውንቱ ብር ያስገቡለት abinetmg (❓) ሌላ አስደማሚ ተግባር ሰራ። "ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በለገሱኝ ገንዘብ ብቻዬን በዓሉን አልደሰትም" ብሎ ለጎዳና ህፃናትም ያገኘውን አካፈለ።
ምን አይነት ድንቅ አጋጣሚ መሰላችሁ...
ግዴላችሁም ወደቀልባችን እየተመለስን የመሆናችን ምልክት ነው...ከንግዲህ የምንዋደድበት፣ በጋራ የምንቆምበት፣ አንተትብስ፣ አንቺ ትብስ የምንባባልበት የጥንቱ የፍቅር ዘመን ተመልሶ እየመጣ ነው❤❤
ከያንዳንዳችን የሚጠበቀው በዙሪያችን ላሉ ሁሉ ፍቅርን መዝራት ነው!!
✍️አለበል ንጋቱ
//__
በፍቅር-በደስታ ዋሉ🙏
SHARE||@ethio_tksa_tks
መክብብ እንዳለው «ከእውቀትም ብዛት ትካዜ ይበዛል!» በዓለም የቱንም ያህል ከእውቀት እውቀትን ብጨምር "እውነትን" ግን አላክላትም። ምክንያቱም ፈጣሪዬን የሚያስክደኝ ጥበብ የመውደቂያዬ ከፍታ ነው!።
ስለመጣውም ስለሄደውም፣ ስለ መከራና ደስታ፣ ስለምኖረው ህይወት ብሎም ስለምሞተው ሞት ሁሉ አንደበቴ ፈጣሪዬን ታመሰግናለች።
ፈጣሪ ይመስገን 🙏🏼
SHARE||@ethio_tksa_tks
ዶይስቶይቭስኪ አንድ እውነት ልንገራችሁ ብሎ ይጀምራል፦
‹‹ዓለም እንደ እናታችሁ አይደለችም ንዴታችሁን የመታገስ አመል የላትም፤ ቢርባችሁ ደርቃችሁ ትቀራላችሁ እንጂ ማንም ግድ አይሰጠውም!። እናት ግን ቀን ላይ ተናዳችሁ ትጮኹባታላችሁ፤ እናም ማታ በቀኑ መጨረሻ ሁሉንም እረስታ እራት ታቀርብላችኋለች..›› ❤🩹
SHARE||@ethio_tksa_tks
ስኬትህ የሚወሰነው በሌላው ሳይሆን በአንተ አመለካከት ነው።
SHARE||@ethio_tksa_tks
⚠️ ማሳሰቢያ !! ይድረስ ለቻናሉ አባላት በሙሉ
✅ በአዲሱ የቴሌግራም ፖሊሲ መሠረት ይህን ከታች unmute ሚለው ላይ የሚያደርጉ አባላት ቻናሉ ላይ እንደሌሉ ይቆጠራሉ ፡፡ ይህንን ማድረግ የሚፖሰቱትን መረጃዎች #VIEW ይቀንሰዋል።
ምንም እንኳን የምንፖስተውን እየተመለከቱ ቢሆንም ቻናሉ ላይ እንዳሉም አይቆጠርም ፤ ስለዚህ...
✅ ከታች #MUTE የሚለው ላይ ከሆነ ምንም አይንኩት ነገር ግን
✅ #UNMUTE ላይ ከሆነ 1 ግዜ በመንካት MUTE የሚለው ላይ አድርጉት
🙏 ስለ ትብብርዎ እናመሰግናለን 🙏
✌️ Share & React 🤞❤️
sʜᴀʀᴇ ☛ @ethio_tksa_tks
Bruce lee የተባለው ታዋቂው የሆሊውድ አክተር በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር..
✅"የምትጓዝበት መንገድ ወደ ጥሩ አሊያም ወደ መጥፎ የሚመራው አንተን እንጂ ተመልካችህን አይደለም...
✅የምትለብሠው ልብስ የሚያሞቀውም ሆነ የሚያበርደው አንተኑ እንጂ የሚያይህን አይደለም...
የምትበላው ምግብ የሚጣፍጠው ወይም የሚመረው አንተን እንጂ ሌላውን አይደለም።
✅እናም አንድን ነገር ለታይታ ማድረግ ሞኞች የፈለሠፉት የመከበር ሙከራ መሆኑን ተረድተህ" በቀጥተኛው መንገድ ለመጓዝ ሞክር...❤
እንማር
SHARE||@ethio_tksa_tks
አሳ አጥማጆች ሁልጊዜ ላይቀናቸው ይችላል አይደል?
👇🏾
አሳ አጥማጆች ማእበል ሲያስቸግራቸው: አሳዎች የሚፈልግ ቦታ ላይ ሳይመጡላቸው: ንፋስ ሆኖ በቂ የሆነ ቀዘፋ ማድረግ ሳይችሉ ሌሎች ተግባራቶች አሏቸው
ከማእበል እና ንፋስ ጋር ታግለው ለማጥመድ አይጋጋጡም
.
ሁኔታውን እያወቁት "አሳ ካልያዝኩኝ ሞቼ እገኛለሁ" ብለው መረባቸውን አይጥሉም
.
አሳ መያዝ አልቻልኩም ብለው አይቆዝሙም
👇🏾
ባህሩ እስኪሰክን እና ንፋሱ ገለል እስኪል ድረስ ሌሎች ስራዎችን ይከውናሉ
መረባቸውን ያጠናክራሉ: ይጠግናሉ: ይሰፋሉ
.
ጀልባቸውን ያጠባብቃሉ: ቀዳዳዎችን ይደፍናሉ
.
ማእበሉ ሲበርድ እና አሳዎች ሲገኙ ለማጥመድ ይዘጋጃሉ
……………….
አንዳንድ ጊዜ አለ አይደል?🤔
👇🏾
ቁጭ ማለት የሚገባን: ነገሮች የማይሆኑበት
.
ያሰብነው የማይሳካበት: ብንታገልም ድካም የሆነበት
አሳ አጥማጁን መሆን !!!
❤️🙌🏼
ትናንሽ ነገሮች ትንሽ ናቸው ብለህ አትዘናጋ ትኩር ብለህ ተመልከት። ትልቅ መርከብ እንዲሰምጥ የሚያደርገው ትንሽ ቀዳዳ ነውና።