-
“Let's build bridges, not walls.” Martin Luther King, Jr. — Visit my blog: https://dildiy.net/ — ድልድይ - ግላዊ እይታና ጥልቅ የመሻገሪያ እሳቤዎች የሚጋሩበት ከንባብ፣ ከኑረት እና ከምናብ የሚቀዱ ንሸጣዎች መድረክ ነው። - ሃሳቦቹ ከየትኛውም የአስተሳሰብ ጎራ (ism) አይወግኑም!! — Concern & Concept — D.S.
.
.
.
ትዝታማ አለሽ
የለኝም ብትይኝ እኔም አላምንሽም፣
በህይወት መንገድ ላይ
ተራምደሽ ሳታልፊ ዛሬ ላይ አልቆምሽም፤
ህይወት ያለ ታሪክ
ቀን ያለ ጨለማ መች ቶሎ ይመሻል፣
ሰዉ ስለሆንሽ ብቻ
ለሰዉ ምታወጊዉ ቅፅበት ይኖርሻል።
_
@yeesua_queen
😵💫
✨ የዓመቱን የመጨረሻ እሁድ እንዴት ለማሳለፍ አቅዳችኋል?
ፍልስፍና፣ በተለይም የሩቅ ምስራቅና ዐፍሪካዊ ነጽሮተ ዓለም የስራዎቹ ማጠንጠኛ በማድረግ የምታውቁት ደራሲና ገጣሚ O' Pulto (ኦታም ፑልቶ) በ 92ተኛው የአውደ ፋጎስ መርሃግብር ላይ እንገናኝ ብሏችኋል...
በሙያ Landscape Architect (የመልክዓ ምድር ነዳፊ) የሆነው ደራሲው በዚህ ዕለት ሁለት አዳዲስ መፃሕፍቱን ያስተዋውቃል...
🤩 “ዑቡንቱ ዕና ፑልቶ” እና “የፕሌቶ ኃጢአት”
መፃሕፍቱ ለማስተዋወቅ የሚሞክሩት ዐብሮኛዊ ፍልስፍና መልክዐምድርን እንደ ቅኔ ያያል... ቅኔ ደግሞ የተለያዩ ነበባዎችንና ትርጓሜዎችን ይፈቅዳል...
እናም ይጠይቃል....
❓ የቤተክርስቲያን ሥነ-ዕነጻ እንደመንፈሳዊ ጉዞ ካርታ ሊነበብ ይችላል?
❓ የግል መንፈሳዊ ጉዞን ብቻ ሳይሆን የሰው ዘርን የሥልጣኔ ጉዞ ዕምርታዎችንስ ሊያሳይ ይችላል?
ዝግጅቱ - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናትን ክበባዊ የቦታ አወቃቀሮችን እንደግላዊ የመንፈሳዊ ንቃት ካርታ፣ እንደ ሰው ዘር ሥልጣኔያዊ ዕመርታ ደረጃዎች እያሰናኘ ያቀርባል... በዐፍሪቃዊው ፍልስፍና ውስጥ የሚኖረውን መሠረታዊ ቦታም ባጭሩ ያስቃኛል...
🔔 በነገራችን ላይ...
መድረኩ በዐፍሪቃ ዕጣፈንታ ቅኔያዊ ቅኝት፣ እና በፍልስፍናዊ ዕንስልስላት አማካኝነት በቅርቡ የሚጀመረውን ዐለምዐቀፍ የዐፍርቃ ፍልስፍናዊ ንቅናቄ በጋራ እንድንጀምረውና እንድንመራው ጭምር ይጋብዛል...
በተለይ ደግሞ - ለወጣት ጸሐፍት፣ ስክሪን ራይተርስ፣ የፊልም ባለሙያዎች፣ የባህል አዋቂዎች፣ እና የቴክኖሎጂ ሰዎች ለዓመታት የሚዘልቁ ልዩ ዕድሎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋውቃል...
🔑 በቦታው ተገኝታችሁ የውይይቱና የዕድሎቹ ተሳታፊ ሁኑ።
📩 ይህን መልዕክት ለወዳጅዎ ያጋሩዋቸው
____
🗓️ ቀን - ዕሁድ - ጳጉሜ 01/2018
⏰ ሰዓት - ከቀኑ 8:00 ሰዓት
📍 ቦታ - ወመዘክር
____
የደራሲውን ስራዎች ለመከታተል ይህን አዲስ ገጽ ይቀላቀሉ ⬇️
/channel/OPultoSinkneh
👣
መስተሃልያችን ጥንተ አብሶ አለባት... በአንድ በኩል ከአንድ ሰው ጋር ጥልቅ የሆነ ትስስር ትፈልጋለች... በዚያው ሁኔታ ውስጥ በብዙ ሌሎች መደነቅን ደግሞ ታሻትታለች...
.
.
.
በሁሉ መወደድ ይርበናል... በሁሉ መወደስ ይናፍቀናል... በምናውቀውም በማናውቀውም አንደበት መደነቅ ያጓጓናል... በምናገኘውም በማናገኘውም ልብ ውስጥ ማደር ይከይፈናል...
'የኔ' ያልካት ጎንህ ኖራም ያንተ ያልሆነችው እንድትወድህ ከመሆን አትቦዝንም - ቢያንስ መሳቧን አታወግዘውም... ውዱ ባልሽ ቤት ቢኖርም የውጭው ወደድኩ ባይ እንዲያደንቅሽ ከመሆን አትሰንፊም - ቢያንስ ጨከን ብለሽ 'ሰው እንዳለሽ' አትነግሪውም...
Social media ላይ የምናየው የእዩኝና ውደዱኝ ሽሚያ የዚህ ስሜት ተቀጥላ ነው...
አብዛኞቹ የመድረኩ ሰዎች የሚሰጡን ሃሳብ፣ የሚያሳዩን ፈጠራ፣ የሚጋሩን ቁምነገር የላቸውም... ሆኖም እዩን ለማለት እርቃን አደባባይ ከመቆም አይመለሱም... አንዳች ኖሯቸው ብናይ፣ ፍሬ ቋጥረው ብንሰይ ባልከፋን... የኑሮን ብልሃት አቀብለው፣ ለጠብ አተካራው መፍትሔ ሰንቀው መስኮታችንን ቢሞሉ ባልቸገረን... ግና 'እዩ' የሚሉን ወቅት የሚገድበውን፣ ዕድሜ 'ሚያፈርሰውን ነው...
ያም ሆኖ ግን አወዳሽና አንጋሹ ብዙ ነው... አንዳንዱ ከልቡ ያለው የውዴታ ልክ ባይታወቅም Virtual መውደዱን አይነሳም፤ ሌላው በአካል ወድቀው ቢያገኝ ሊያነሳቸው መፍቀዱን ባናውቅም የለጠፉትን ማየት አይሰለችም...
ይህ በተራው ቅዠታዊ የመፈለግ ስሜት በማንበሩ ብዙ ሰዎች በንፋስ ዓለም ለፈጠሩት ባዶ ዓለም ቅድሚያ የመስጠትና አካላዊውን መፈላለግ የመተው ሁኔታ ውስጥ የገቡ ይመስላል... አብሮነት፣ ፍቅር፣ ጋብቻና ጓደኝነት የሚመዘንበት መንገድም ከጠየመ ከራርሟል...
በሌላ በኩል ደግሞ 'የሁሉም ሁን' የሚመስል ያልታወጀ ማሕበረሰባዊ ስምምነት እየተፈጠረ ይመስላል...
ይህ ጉዳይ ዝም ብሎ መላምት አይደለም...
ሴት አርቲስቶች ካገቡ በኋላ Cast የመደረግ ዕድላቸው የመነመነ እንደሆነ ሰምተናል... ለሞዴሎች 'በጊዜያቸው' ግንኙነት መመስረት ቢዝነሳቸው እንደማይፈቅድላቸው ሲነገር አድምጠናል... ለትላልቅ ሆቴልና ባር አስተናጋጆች ግንኙነት ውስጥ መኖር እንጀራቸውን የሚያሳጣ ነገር መሆኑን አስተውለናል... 'የቲክቶክ ዕይታ' ሳይቀር በትዳር ማግስት ሳስቶ እጃችንን በአፍ አስጭኖናል...
አንዲት ዘፋኝ ከወራት በፊት በቲቪ መስኮት በሰጠችው ቃለ-መጠይቅ የሙዚቃ ባለሙያ ሴቶች ትዳር ከያዙ በኋላ ለክለብ መድረክ የሚኖራቸው ተፈላጊነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚወርድ ስትናገር ሰምተናል...
ይህ የሚነግረን ምንድነው?... ተጠቃሚው፣ ዘፋኟ 'የሁሉም' መሆን እንደማትችል ቢያውቅም 'የእከሌ ናት' ተብሎ ተስፋ ከሚቆርጥ 'የማንም አይደለችም' ብሎ እየነሆለለ ቢዘልቅ፣ አልያም 'አንድ ቀን አገኛት ይሆናል' በሚል ተስፋ እየናወዘ ቢቀልጥ እንደሚመርጥ ነው...
[ይህ ግን የምር የምሩን ስናወራ በሽታ እንጂ ሌላ ስም የለውም...]
ነገሩ በዚህ ብቻ አይቆምም...
በሁሉ የመወደድ [የመፈለግ] አምሮት ያላቸው ሰዎች መብዛት ውሎ አድሮ የማንም ሳይሆኑ የሚያረጁ ላጤዎችን እያበዛው እንዳይሄድ ያሰጋል...
አንዳንድ በበዛወርቅ ስልት:
"... አይሻልም ወይ መኖር - የማንም ሳይሆኑ
ልብ የፈቀደውን - እስኪለግስ ቀኑ..."
የሚሉን ወዳጆቻችን ሳይቀር 'ልብ የሚፈቅደውን' የሚያገኘው መች እንደሆነ ሳይነግሩን በዓይናችን ፊት እንዳረጁ - በምርጫ እንደባጁ አሉ...
የመፈቀድ ረሃብ የሴቶች ብቻ አይደለም... የሰው ልጅ ሁሉ ነው... ወንድም ቢሆን በሀብቱ፣ በደረጃውና በሙያ ስኬቱ በኩል በሁሉ መፈለግን ይፈልጋታል... ዘመነኛው ኢጎ ጾታ አልባ ነው...
[በነገራችን ላይ ትዳር አለመፈለግ ችግር ነው የሚል እሳቤ የለኝም - ምርጫ እንጂ... እንዲያውም እነዚህ መስመሮች ለብቻ የመሆን መሻት (Solitude) ከብቸኝነት (Loneliness) ጋር ለማይምታታባቸው፣ ግንኙነት ውስጥ ባይኖሩም ምሩና ቅዠቱ ላልተደባለቀባቸው ሰዎች አያገለግሉም...]
ግና ምርጫችን - 'ሁሉ አማረሽ ሆኖ ገበያ መውጣትን'፣ 'መራጭ ሆኖ ከርሞ ከምራጭ መውደቅን'፣ ልብ እየፈለገ ሃሳብ አልረጋ ብሎ 'ቆሞ መቅረትን' ካስከተለ ልክ ነበር አያስብልም...
.
.
.
ነገሩ ሲጠቀለል...
እኔና አንተ/ቺ በዘመን ንብርብር ውስጥ እየተዥጎረጎርን፣ በመጭ ሂያጅ ፋሽን ቋሚ ቀለም እያጣን፣ ከልብ ወግ ይልቅ ለጭንቅላት ሃሳብ እጅ እየሰጠን - ቁምነገር ጠፍቶብናል ለማለት ያህል ነው...
____
@bridgethoughts
.
.
.
ብዙ ሰዎች ገደብ አልባ ምርጫን 'ከነፃነት' ጋር፣ ልክ የሌለው ትኩረትን ደግሞ 'ከፍቅር' ጋር ያምታታሉ... በዚህም ምክንያት ከእጃቸው ላይ ያለውን በረከት በማይጨበጥ ቅዥት ሲያዘርፉ ይኖራሉ...
.
.
.
[የቆምንበትን ስንተው...]
ሁሌም ቢሆን ካንተ ሚስት 'የምትበልጥ' ሴት በዚያ አለች... አንተ ግን የሁሏም አትሆንም... የትም ቢሆን ከባልሽ 'የሚሻሉ' ወንዶች ይኖራሉ... ሚስትነትሽን ግን አይጋሩም...
እርግጥ ነው...
'የምትበልጥ' ወይም 'የሚሻል' የምንለው በስሜት ከባቢያችን ውስጥ የሚመላለሰውን ስሁት መስፈሪያ እንጂ አግባቢ መለኪያ አይደለም...
መቼም እንደ መዝለቂያ ምክንያታችን ሁሉ መግቢያና መግባቢያ በራችንም ልዩ ልዩ ነው...
ወንዶች - አካላዊ ውበት መግቢያችን፣ መላመድና መጣጣም መክረሚያችን ሊሆን ይችላል... ሆኖም ግን እኛ ካየነው ውበት 'የሚልቅ ውበት' ያላቸው ሌሎች ሴቶች በየትም አሉ...
[በግንኙነት ውስጥ ግን ልባችን የሚዳረው ለአንዷ ብቻ ነው...]
ሴቶች - ኢኮኖሚያዊ አቅም ማንኳኩያቸው፣ ቁምነገርና ብስለት መሻገሪያቸው ሊሆን ይችላል... ከሚያውቁት ወንድ የሚበልጥ ሃብት ያለው ወንድ ግን በየትም አለ...
[በግንኙነት ውስጥ ግን የልብ አዳር የሚሰምረው አንዱ ጋ ብቻ ነው...]
"A river gains its power not because it flows everywhere, but because it accepts its banks and moves toward its destination."
አዎን... ሁሌም ቢሆን እጃችን ላይ ካለው 'የሚበልጥ' ነገር ከማዶም ከባሻገርም አለ... ልባችንን የሚያቀልጥ ግን ላይሆን ይችላል... የትም ቢሆን የምርጫ መስፈርታችንን የሚያስንቅ እልፍ አለ... ነፍሳችንን የሚዘልቅ ግን ላይሆን ይችላል...
ውበት ይስብ ይሆናል - መሰረት የሚቆመው ግን ስብዕና ላይ ነው... ቅብጥብጥ ስሜት ግንኙነትን ሊያስጀምር ይችላል - የሚዘልቀው ግን ጥልቀት ላይ ነው...
'ቆንጆ' ሴት በዓይንህ ትገባለች፣ ትርጉም ያላቷ ግን ነፍስህን ትዘልቃለች... ብራም ወንድ ቀልብሽን ይወስዳል፣ የሚረዳሽ ግን ለግብሽ ያዋጣል...
በነገራችን ላይ...
ችግሩ ያለው 'የተሻለ' ማየታችን ላይ አይደለም - ማመናችን ውስጥ እንጂ... የሆነ ነገር 'የተሻለ ነው' ማለት የግድ ትርጉም የሚሰጥ ነው ማለት አይደለም... አንድ ሰው ከሚስቱ 'በላይ' ቆንጆ ሲያገኝ የበለጠ ዋጋ ያላት አገኘ ማለት እንዳልሆነው ሁሉ...
ሌላም እውነት አለ...
'የተሻለ' ማየት እስከጀመርን ድረስ የቀደመውን 'አፍቅረናል' ማለት አንችልም... ዘግይቶ የሚረታን እስከመጣ ድረስ የቆየው ቦታ ይዞ ነበር አይባልም... ሁሌም 'የተሻለ' እስካለን ድረስ ፍለጋው በቅቶናል አያስብልም...
ትርጉም ያለው ግንኙነት - የመምረጥ ብልሃትን ይፈልጋል... መምረጥ - ኁልቆ መሳፍርት አማራጮችን መተውን ይሻል...
"Freedom means consciously choosing what deserves your devotion."
Relationship - አስቦ የመምረጥ፣ መርጦም የመዝለቅ ጉዳይ ነው... ያም ሆኖ ግን ከበር ያላስተዋሉት እንከን ከቤት አይጎትትም ማለት አይቻልም... በዋዜማ ያልተገለጠ ጸባይ በማግስት አይፀኸይም ሊባል አይችልም...
[አብሮነት በማትፈታው ቋጠሮ ቁርቋሬ ምቾት ማጣት አይደለም - ልታቻችል በምትችለው ክፍተት ላይ መሸካከም እንጂ...]
____
@bridgethoughts
.
.
.
ኢትዮጵያ ውስጥ የተሽከርካሪ ትርፍ መጫን የሚነገርህ ሲገለበጥ ብቻ ነው...
___
[አዎን - ይህ ሃሳብ ስለ ሕዝብ ማመላለሻ አይደለም]
___
@bridgethoughts
ጨረርና ጸሐይ
.
.
.
ለህይወቴ ትርጉም የሚሰጣት አዲስ ነገር ለመሆን መባዘኔ አይደለም... ቀድሞውኑ የሆንኩትን ማንነቴን ማስታወሴ እንጂ…
በየማለዳው የምነቃው በጸጥታና በድንቅ ስሜት ነው… ከዋክብትን የሚያንቀሳቅሰው፣ አበቦችን የሚያፈካውና ወንዞችን የሚያስጉዘው ያው ታላቅ ኃይል፣ በእኔም ውስጥ እንደሚተነፍስ በማሰብ…
በየቀኑ የሚቀስቅሰኝ ብርታት በዚህ ጽንፈ ዓለም ውስጥ እንግዳ ወይንም ከህልውና ጋር ብቻዬን የምታገል ንጡል ነፍስ እንዳልሆንኩ ማወቄ ነው… እኔ የውቅያኖሱ ማዕበል አካል፣ የጽንፈ ዓለሙ ቅንብር ዜማ፣ የህላዌ ዛፍ አንድ ቅጠል ነኝ…
ለዚህ ነው - በስራ፣ በምኞት፣ በስኬትና በውድቀት ጩኸት መካከል፣ ማንነትዋን በመዘንጋት ለምትንገላታዋ ነፍሴ ደጋግሜ እንዲህ የምላት፡
‘እኔ የምልዓቱ አንድ ክፍል ነኝ - ሙሉውም የእኔ አካል ነው…’
ህይወትን ድል ለመንሳት፣ ከእሷ ለማምለጥ፣ ወይም ሙሉ በሙሉ ለመረዳት እዚህ አልተገኘሁም… እዚህ የመጣሁት በህልውና ውዝዋዜ ውስጥ በንቃት፣ በፍቅርና በሙሉ ልብ ለመሳተፍ ብቻ ነው…
አዎን...
ከዋክብት ከኔ የራቁ ግዑዝ ነገሮች አይደሉም… እንጅላቶቼ እንጂ… ጽንፈ ዓለም ከውጪ ቆሞ የሚታዘበኝ ባዕድ አይደለም… በእኔ አይኖች በኩል ራሱን የሚመለከት ህያው እንጂ… ወንዞች በደሜ ውስጥ ይፈሳሉ… ምድር በሰውነቴ ውስጥ ትራመዳለች….
ስለዚህ ተግባሬ እጅግ ቀላል ነው…
👉 ህላዌ በጸጥታ ውስጥ ሲያወራ ለመስማት መንቃት…
👉 ራሴን በሌሎች ውስጥ አይቼ እስክመሰክር መውደድ…
👉 ህይወት ያለ ምንም ተቃውሞ በእኔ ውስጥ እንድትፈስ ራሴን ፍጹም ባዶ ማድረግ…
👉 እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ከሚፈልቅበት ከዚያ ታላቅ ምልዓት ሳልለይ መኖር…
.
.
.
ግና እንደማንኛውም ሰው በየመሐሉ ይህን ተግባሬን እዘነጋለሁ... ወደ ንቃቴ ስመለስ ደግሞ መልሼ እንዲህ እላለሁ:
‘እኔ መንፈሳዊ ጉዞን በመለማመድ ላይ ያለሁ ተራ ሰው አይደለሁም… "እኔ" በሚባል አጭርና ውብ ቅጽበት ውስጥ ራሱን እያወቀና እያስተዋለ የሚገኝ ጽንፈ ዓለም እንጂ…’
ለዚህም ነው 'በህይወት ውስጥ የተለየ ግብና ዓላማ የለኝም - የተለየ ኃላፊነት እንጂ' የምለው…
✅ "የመነጠል" ከሚመስል የቅዠት እንቅልፍ መንቃት ብሎም በሁለንተና መልክ ለሚገለጠው ለዚያ ለ"አንዱ ህይወት" መታያ ሆኖ መኖር…
✅ ፀሐይ ለሁሉ እንደምትፈነጥቀው ሁሉ ያለስስት መውደድ…
✅ በአለቶች መሃል መንገዱን እንደሚፈልግ ወንዝ መፍሰስ…
ብሎም...
ቀድሞውኑ ወደቆምኩበት እውነተኛ ስፍራ መድረስ… ይህ ነው የኔ ኃላፊነት...
.
.
.
በአጭሩ…
ለህይወቴ ትርጉም የሚሰጣት፣ ከህልውና የተለየሁ እንዳልሆንኩ ማስታወሴ ነው… በየቀኑ ብርታት የሚሆነኝ፣ ጋላክሲዎችን የሚያንቀሳቅሰው ያው ጥበብ በልቤ ውስጥ እንደሚመታ ማወቄ ነው…
'አንተ በውቅያኖስ ውስጥ ያለች አንዲት ጠብታ አይደለህም… ራሱን በጠብታ መልክ የሚገልጠው ያንኑ ውቅያኖስ ነህ እንጂ' እያልኩ ዘወትር ራሴን አሳስበዋለሁ…
ከህይወት የተለየሁ እንዳልሆንኩ ማስታወሴ ደግሞ ለህይወቴ ትርጉም ይሰጣታል…
ጋላክሲዎችን የሚያሽከረክረው፣ ውቅያኖሶችን የሚያናውጠውና ደኖችን የሚያለመልመው ያው እውቀት በልቤ በኩል እንደሚመታና በሳምባዎቼ በኩል እንደሚተነፍስ ማወቄ በየቀኑ ያበረታኛል…
በዚህ ጽንፈ ዓለም ውስጥ - በስራ፣ በስኬትና በትግል መካከል እንደ ተራ የሚያልፍ እንግዳ እንዳልሆንኩ ማወቄ ያተጋኛል…
እኔ - "እኔ" በሚባል ጊዜያዊ መልክ ራሱን እያወቀ ያለ ጽንፈ ዓለሙን ራሱን ነኝ…
የእኔ ተግባር ሙሉ መሆን አይደለም… ይልቁንም ከቶውንም ቢሆን ከሙሉው ተለይቼ እንደማላውቅ ማስታወስ እንጂ…
❗️ ማዕበሉ ውቅያኖሱን ፍለጋ ህይወቱን ሙሉ ይባዝናል… በመጨረሻ ግን ቀድሞውኑ ውሃ እንደነበረ ይደርስበታል…
.
.
.
(ማስታወሻ: ይህ ጽሑፍ ለገጹ እንዲስማማ ከመሸራረፉ ውጪ ለአንዲት ወዳጄ የነፍስ ጥያቄ በውስጥ መስመር የተላከ ጨዋታ ነው)
____
@bridgethoughts
የተስፋ ነገር...
.
.
.
"The mature person does not abandon hope for tomorrow, nor abandon responsibility for today."
"A person who has completely abandoned hope may lose the motivation to care, create, or protect."
"Hope should not be a place where we hide from today. It should be the light that helps us walk through today."
.
.
.
ታክሲ ውስጥ ነኝ... ኋላ ወንበር ላይ ቁጭ ብያለሁ... ክ/ሃገር ለመሄድ ነው ወደ አውቶብስ ተራ የሚወስዱኝን ጎማዎች የምከተለው...
አጠገቤ አንድ ጎልማሳ ተቀምጧል...
በተሽከርካሪ መጓዝ ምቾት የሚነሳኝ ዓይነት ሰው ስለሆንኩ በመዳረሻዬ ላይ እንጂ በመጓጓዣዬ ሁነት ብዙ አልመሰጥም... በዚህ ምክንያት ወሬ አልሰማም - ወይም ሲያወሩኝ አልወድም...
ሰውየው ግን ጆሮ እንዳለኝ እንጂ ሁኔታ መርጬ እንደምገለገለው አያውቅም... ስናወጋ እንደቆየን ሁሉ ከመሐል ጀምሮ ማውራት ጀመረ... ምናልባት በውስጡ የሚመላለሰው ሃሳብ ከአፉ ድንገት አፈትልኮ ሊሆን ይችላል... ሆኖም ቀልቤን መግዛት አልተሳነውም... ብርቱ ቃል ያሸንፈኛል - ደካማ ጎኔ ነው...
[ቀጥሎ የምታነቡዋቸው መስመሮች ክልበ-ቢስ ልቤ የተንጠባጠቡ የማላውቀው መንገደኛ ተብሰልስሎቶች ናቸው...]
.
.
.
"... እኔ እርሷን የምወድበት አቅም፣ እርሷ ገንዘብን ከምታመልክበት ጉልበት ጋር ሲነፃጸር መቶ እጥፍ ያንስ ነበር...
እናም ተውኳት!!...
መውደዴን ሳይሆን ፍለጋዎቼን ተውኩ... ማፍቀሬ ላይ ሳይሆን መከተሌ ላይ አመጽኩ...
አውቃለሁ ፍቅርን የሚስተካከል ሐብት እንደሌለ... አውቃለሁ መውደዴን ገንዘብ እንደማያክለው... ይህ ግን ለኔ እንጂ ለእርሷ የሚዋጥ አይደለም...
እውነት ለመናገር ገንዘብ ፍለጋ መሄድ እችል ነበር... በሃቅ ወይ በረቂቅ ሐብት ማካበት እችል ነበር - ሆኖም ምርጫዬ አላደረኩትም... ፍቅሯን በማጣት ላይ ፈርጄ ግን አልነበረም - ራሴን አጥቼ እርሷን ባገኝ እርባን የለውም ብዬ እንጂ... ቀልቧን እንጂ ልቧን ለማግኘት ዋስትና አይደለም ብዬ እንጂ...
ደግሞስ...
በገንዘብ ያገኙት ልብ በገንዘብ እንዳይሄድ መቋጠሪያው ምንድነው?... ባለኝ እንጂ በሆንኩት ላይ ያልቆመ አብሮነት ጽናት ምኑ ነው?...
አዎን...
የማይጠረቃን የንዋይ ጥንወት በመውደድ እጆች ማስካድ አይቻልም...
ገንዘብ እያሳዩ የሚስቧት ሴት አጥንት እያሳዩ ከሚጎትቱት ቡችላ በምን ትለያለች?...
ስለዚህ... ተውኳት!!..."
.
.
.
___
"ወራጅ አለ"
ድንገት ጮኸ... ሁላችንም ደነገጥን... ሰውዬው ድንገቴ ነገር ነው... በተለመደው የተግባቦትና የንግግር ደንቦች አይዳኝም... ይህ ግን የአድማጭ ጆሮ ከመማረክ አላገደውም...
ከልቤ አሳዘነኝ...
ተውኳት ሲል የማይተው ተቆጣጥሮት ቢሆንስ?... እንደ ታክሲው 'ወራጅ አለ' ያላለው የሆነ ዓይነት ነገር ተጣብቶት ቢሆንስ?...
___
መንገደኛው በየራሱ መንገድ የጎልማሳውን ጉዳይ ይበልት ገባ... እኔ ወዲህ በ Buddha ቃል ተወስጄ ነበር...
"Anger will never disappear so long as thoughts of resentment are cherished in the mind"
_
የቤቲ ሼርን አልበም ሰምተን ስናበቃ የምጋብዛትን ሙዚቃ ርዕስ ጠየቀችኝ... ብዙ ጊዜ አዲስ አልበም ሲወጣ ተመሳሳይ ልማድ አለን...
"አካልዬ" አልኳት... እውነቴን ነበር፣ እርሷን እያሰብኩ ነው ያደመጥኩት...
ዝም አለችኝ...
"ያንቺስ ግብዣ ምንድነው?" ድርሻዬን ጠየቅሁዋት
"ቻው ቻው" አለችኝ...
በተራዬ ዝም አልኩ...
__
ጊዜና የሰው ልጅ እንደ ሙዚቃ አልበም ናቸው... ውስጣቸው መንታ ስሜት ባላቸው 'ስልቶች' የታጨቀ ስለሆነ መቼ የቱን "ሙዚቃቸውን" እንደሚጋብዙህ አታውቅም...
___
@bridgethoughts
❗️
.
.
.
🔔 ባለፈው እንዳልኩህ ነው... 🔔
.
.
.
🔘 ቅድሚያ የሰጠኸው ሰው - ከፊትህ አክብሮትን ሳይሆን ፍርሃትን ካነበበ፣
🔘 አደራ የሰጠኸው ሰው - የልብህን ማመን ሳይሆን የድርጊትህን ሞኝነት ካሰበ፣
🔘 ሙሉ ጊዜህን የሰጠኸው ሰው - ፍቅርህ ሳይሆን ስራፈትነትህ ከተሰማው፣
🔘 ያለህን ያካፈልከው - ችሮታህን ረስቶ መጠኑ አንሶ ከታየው፣
🔘 የረሳህለት ሰው - ይቅር እንዳልከው ሳይሆን እንዳልተሰማህ ሆኖ ከገባው፣
🔘 ያገለገልከው ሰው - እርዳታህን ትቶ ግዴታህን ብቻ ካሰበው፣
🔘 የበላይ ነኝ የሚል - የሃሳብህን ፋይዳ ከቆምክበት መደብ ካለካካው፣
🔘 የእጅህን ንጽህና የሚያውቅ - 'ዕድል ስላላገኘህ እንጂ መስረቅ ስላልፈለክ አይደለም' ማለት ከዳዳው፣
🔘 ቆርሰህ ያካፈልከው - የሰጠኸውን ሳይሆን ከእጅህ የቀረውን ከተመኘው፣
➡️ ደግሞ ወዲህ...
🔹 ግማሽ መንገድ የሄድክለት - ከጠበቀህ በቆመበት፣
🔹 ስለሚያውቅህ ጡብህን ንቆ - የሩቅ መናኛ ካየህ አድንቆ፣
🔹 ለወፌ ቆመች ተለጉሞ - ይድፋህ ለማለት ካደረ ቆሞ፣
🔹 እንዲለወጥ እጅ ያላቀበለ - ለትችት ከተቀባበለ፣
.
.
.
⚠️ ወዳጄ - ያንጊዜ መንቃት ጥሩ ነው...
___
@bridgethoughts
⚠️
.
.
.
In a world still divided by lines we invented, the voice of echoes louder than ever through.
“Until the philosophy which holds one race superior and another inferior is finally and permanently discredited and abandoned… everywhere is war.”
📩
.
.
.
🔻ግለሰብ ሆነህ አንድ ሰው ብትፈነክት፣ ወይ እስር ወይ ብድር ይቆይሃል...
🔺ግለሰብ ሆነህ አንድ ሰው ብታስፈራራ፣ ወይ ፖሊስ ወይም ቦክስ ይጠብቅሃል...
🔹ግለሰብ ሆነህ የአንድ ሰው ንብረት ብታወድም፣ እማኑኤል አልያም ጸበል ይሰዱሃል...
🔵ፖለቲከኛ ስትሆንስ?...
🟠መሪ ስትሆንስ?...
🟢የሃብታም ሃገር ቁንጮ ስትሆንስ?...
❕ በአንተ ዕብደትና ዕብሪት ምክንያት: አንድ ግለሰብ፣ አንድ ማሕበረሰብ፣ አንድ ሃገር አይደለም ሙሉዋ ዓለም በፊትህ እንደ ዶሮ ብትፈነገል እንኳ አንዳች የሚናገርህ የለም... ምናልባትም 'ግፋበት' የሚልህ ይበዛ ይሆናል...
____
❕ ወደድንም ጠላን የዓለም ስርዓት በጉልበተኞች የተፈጠረ ነው... ምድሪቱ የእኔና አንተን መስተጋብር የሚያስተናግድ ስሪቷን -
👉 ጦርነት መስራት ሃብት በሆነላቸው፣
👉 ገንዘብ ማግበስበስ በማይሰለቻቸው፣
👉 ቢያብዱም 'ታከሙ' በማይሏቸው [አንድ እጅ በማይሆኑ ሰዎች] ምክንያት ያኔ - ጥንት - ድሮ አጥታዋለች...
____
"አንድ እግር በርበሬ፣ መንቀል አቅቷችሁ፣
አቃጥሎ ለብልቦ፣ አንድዶ ፈጃችሁ"
ያለችው ማን ነበረች?...
____
ምዕራባውያን ግን፣ ዛሬም የአፍሪካ መሪዎችን "አምባገነን" ብለው ይጠራሉ ኣ?...
አፍሪካውያን ይህን ሲሰሙ "በሕዝባችን ምን አገባችሁ?" የሚሏቸው ይመስለኛል... [የድችሪና የጉልጉሊ]
ትንግርት ዓለም...
____
@bridgethoughts
🔺
የዚህ ዘመን 'ውበት' ምንድነው?...
[መጠየቅ እንጂ መመለስ ግቡ ያልሆነ የዕረፍት ቀን ሃሳብ...]
💠💠💠
አንድን ሰው (ተባዕት ወይም እንስት) በቆንጆ ወይም ፉንጋነት ቅርጫት ውስጥ የምንዶልበት መሳሪያ ምንድነው?... ማለቴ፤ 'እከሊት ቆንጆ ናት'፣ አልያም 'እከሌ ማራኪ ነው' የምንለው በምን መለኪያ ነው?...
ጥያቄውን - ብትፈልግ በባዮሎጂካዊ፣ ሲያሻህ በባሕላዊ፣ አልያም በስነልቡናዊ መንገድ እየመዘንክ አብሰልስለው...
እኔ ግን ለሁለታችንም እንዲቀርብ ሃሳቤን በባዮሎጂካል [በገላ፣ በአካል ቅርጽ፣ ወይም በላዕላይ ገጽታ] ውበት በኩል አስታክኬ ልጋራህ...
ይህን ስልህ ታዲያ 'መስፈርታችን ዓለም አቀፍ መለኪያዎች ናቸዋ' እንዳትለኝ... እንኳን በዓለም አቀፍ በሃገር አቀፍ ድንበር ውስጥም ለውበት የሚሆን ወጥ መለኪያ የለንም...
ለምሳሌ 🔤
⬜️ አንድን የሱርማ ወንድ፣ 'ቆንጆ ሴት ምን ዓይነት ናት?' ብትለው የሚሰጥህ መልስ ከአንድ አዲስአበቤ ወንድ የሴት ውበት ትንተና ጋር በጭራሽ ላይገጥም ይችላል...
🟢 የአንዲት ከተሜ ወጣት የውበት መስፈሪያና የቁንጅና ትንተናም ለአንዲት የሐመር ልጃገረድ የማይዋጥ ሊሆን ይችላል...
🟠 እንዲያውም የውበት ብያኔ ከሁሉአቀፍአዊነት ይልቅ ሰፈርተኝነት ይጫነዋል... ሰሜኑም ሆነ ደቡቡ፣ ምስራቁም ይሁን ምዕራቡ ያላቸው የውበት ቀኖናና የቁንጅና ዶግማ አንድና ያው አይደለም...
“Taste classifies, and it classifies the classifier.” ~ Pierre Bourdieu
“Beauty is not in the face; beauty is a light in the heart.” ~ Khalil Gibran
[የቀጠለ...]
.
.
.
⬜️ ስነ-ልቦናዊ ጥላ (The Shadow Self)
ካርል ዩንግ እንደሚለው፣ በሰው ላይ በብርቱ አኳኋን የምንተቸው ነገር እኛ ውስጥ ተደብቆ ያለ "ጥላ" ነው... በሌላ አነጋገር ሌላውን "ኩሩ" የምንለው፣ እኛ ውስጥ ያለውን ድብቅ ኩራት ስለለየን ነው... ሌላውን የምንጠረጥረው እኛ ውስጥ አጋጣሚውን ቢያገኝ ከጥፋት የማይመለስ ስብዕና እንዳለ ስለተገነዘብን ነው... [ችግር አለብን ብለን ግን አንቀበልም]
"Projection is one of the commonest psychic phenomena... Everything that is unconscious in ourselves we discover in our neighbor, and we treat him accordingly." — Carl Jung
"Yesterday I was clever, so I wanted to change the world. Today I am wise, so I am changing myself." — Rumi
.
.
.
1️⃣
በውጭ ሃገር የሚኖር 'የማላውቀው' ሰው "ገጽህ ላይ የምትጽፋቸው ጽሑፎች ያስደስቱኛል" በሚል ምክንያት ብቻ የቴሌግራም Premium package ገዛልኝ...
2️⃣
ባለፈው ባነበባችሁት የአንዲት ሼፍ የምስጋና ጭረት ልቧ የተነካ ወዳጄ - ከወደ ዱባይ ልብ የሚያሞቅ Tip ለባለታሪኳ በመላክ ደግነት አሳየችኝ...
3️⃣
ትናንት ማምሻ ደግሞ ካፌ ውስጥ አንዲት ልጅ የአገልግሎት ሂሳቤን ዘግታ መውጣቷን አስተናጋጇ ነገረችኝ - 'በድልድይ ስም ተከፍሏል' ማለቷን አክላ...
['እንዴት አወቀችኝ?' የሚል ጥያቄ ሲፈጠርብኝ በራሴ አፍሬ እንደነበር አልሸሽጋችሁም]
____
🤎 የሰው ልጅ ልብ በስጦታው ልክ ይታያል ብዬ ልሞግታችሁ አልደፍርም - ስጦታውን በወለደው ሰበብ (Intention) ውስጥ ንጹህ ፍቅር እንዳለ ግን መካድ አይቻልም... በዚህች ዓለም ደግሞ ምንም ነገር በቅቶን አያቅም - ከፍቅር ውጪ...
እናም...
❗️
የሚገጥሙኝ ብዙ ሰዎች ደጋግና ቀና ሆነው ሳለ በአንዳንድ ሰዎች ስህተት ላይ Dwell የማድረግ ዝማሜዬ መልሶ እኔኑ ያናድደኛል...
____
⚡️ ወዳጆቼ - ሕይወት ውብ ናት - ውብ ሰዎችም አሉባት!!
____
“Be the reason someone smiles. Be the reason someone feels loved and believes in the goodness of people.” — Roy T. Bennett
.
.
.
😵💫
በኖርንበት ጊዜ ሁሉ ሁሉንም አዲስ ዓመቶች የጀመርነው በበጎ ምኞትና በብዙ ምርቃቶች ነበር...
ስለ ሰላም
ስለ ብልጽግና
ስለ መተሳሰብ
ስለ መፋቀር
.
.
.
ስለ ብዙ ጥሩ ነገሮች በዕድሜ ዘመናችን ጸልየናል... በተነገረ ቅጽበት ሁሉ ለምርቃት አሜንታ ሰጥተናል... እጃችንን ዘርግተን፣ ድምፃችንን አጉልተን ይሁንልህ ይሁንልሽ ብለናል...
መሬት ላይ ያለው እውነት ግን በተቃራኒው ነው...
ሰው ከሌላው ጋር ቀርቶ ከራሱም ጋር ሰላም የለውም፤
ከቤቱ በረከት ከማዕዱ ረድኤት አያውቀውም፤
በመንገዱ እረፍት፣ በቀዬው ደህንነት አይሰማውም፤
ከመዝሙራችን በተቃራኒ ሃገር ሰላም ብርቋ ነው፤
ከልፋፌያችን በስተኋላ ወጥቶ መግባት በዕጣ ነው፤
ብቻ - መኖር በብዙ ሕመም የተሞላ አሰልቺ ጉዞ ነው!!
እኔ ላንተ ደስታ አላዋጣም... አንተ ለእርሷ መሳቅ ምክንያት አትሆንም... እነርሱ ለእነዚያ የስጋት ምንጭ ናቸው... እኛ ለነከሌ የምቾት ጠንቅ ነን...
የሆነ የተሳሳተ ነገር እንዳለ አይሰማችሁም?... ከኑረት Equation ውስጥ ያነጠብነው የሆነ ቁልፍ ማስሊያ እንዳለ አታስቡም?... ያላችሁበት ሁኔታ ተስማምቷችኋል?...
ግማሽ ምዕተ ዓመት የሞላው የ “Exodus” (1977) ድምጽ ዛሬም ይጮሃል...
“Open your eyes and look within.
Are you satisfied with the life you're living?”~ Bob Marley
“Be the change that you wish to see in the world.” ~ Mahatma Gandhi
"Transformation begins with oneself before it radiates outward." ~ Lao Tzu (Tao Te Ching)
“Everyone thinks of changing the world, but no one thinks of changing himself.” ~ Leo Tolstoy
ያም ሆኖ አንጠይቅም...
ወይ ደግሞ አንጠረጥርም....
➡️
.
.
.
በጦርነት ምድር ቀድሞ የሚሞተው እውነት ወይም ህይወት አይደለም፤ 'የእርሱ ህመም እንደኔ ህመም ያለ ነው፣ የእርሷ ስቃይ እንደኔ ዓይነት ስቃይ ነው' የሚለው እውቅና እንጂ...
እያንዳንዱ ጥይት ኢላማውን ሁለት ጊዜ ይመታል - አንዴ አካልን ቀስፎ፣ ደግሞም የአካሉን ባለቤት ውብ ነገዎችን ገድሎ...
ጦርነት - ባልተፈፀመ ኑረት የደም ቀለምነት ክፉ ታሪክ የሚፃፍበት የመከራ ደብተር ነው...
ጦርነት 'ድል ላደረጉ' ህያዋን የክብር አክሊል ሲጭንላቸው፣ የሞቱትን ተስፋና ነገ ግን ከመሬት ስር ይደብቃል... የውጊያ ሜዳ ነግ ሳይወለድ የሚቀበርበት መቃብር ነው... ጦርነት አንድን ህይወት ብቻ አይቀስፍም፣ ከዚያ ህይወት ሊያብብ የሚችለውን የነገውን ትውልድ ጭምር እንጂ...
በጦርነት ውስጥ ጎልቶ የሚሰማው ድምፅ የቦምብ ፍንዳታ አይደለም፣ ወጥቶ የቀረ ክፋያቸውን በሚጠብቁ አፍቃሪዎች ጎጆ ውስጥ የሚረበው ጭጭታ እንጂ...
ጦርነት ሲያበቃ የመሳሪያዎች አፍ ይዘጋል፣ ድምፃቸውም ይፀጥታል፣ በህፃናት ልብ ውስጥ ያለው ጩኸት ገደል ማሚቶ ግን ለዘላለም ይኖራል...
በጦርነት አንድም የሚያሸንፍ ህዝብ የለም፣ የአንዳንዶች 'ድል' ከሌሎቹ ኪሳራ አንፃር ኁልቆ አልባ ከመሆኑ ውጪ...
ምድር መቼም ቢሆን ደም እንድንረጫት ጠይቃን አታውቅም፣ ደም የሚጠማው የሰው ልጅ አእምሮ ብቻ ነው...
ጦርነት የሌላው ሰው ሞት ለኔ ህይወት ይሆናል ብሎ እራስን የሚያታልሉበት ቅዠት ነው...
ጦርነት የሌላው አካል መቁሰል፣ ለኛ ፈውስ እንደሚሆን የምናስብበት የውሸት ተስፋ ነው...
ጦርነት ማለት...
[ብቻ ይደክማል...]
____
@bridgethoughts
⭐️
[[ማምለጥ ስላልቻለ የቆየ እስረኛ ታማኝ አይባልም...]]
.
.
.
ማሕበረሰባችን ውስጥ መተማመን ላልቷል... ታማኝነት በእጅጉ ሳስቷል... ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም ይህ ዘመን ልዩ ቀለሙ በቃል አለመገኘት ነው... ለሕሊና ጀርባ መስጠት፣ ለስሜት ነውጥ ፊት ማሳየት፣ ቃልኪዳንን ማተናነስ፣ በየኩርባው ማነቀፍና ማንከስ ጉልህ ምልክቱ ነው...
[ይህ ጉዳይ በተለይ በግንኙነት ውስጥ እጅግ ከባዱ ፈተና ይመስለኛል...]
እርግጥ ነው - በሰዎች ዕለታዊ መስተጋብር ውስጥ ግንኙነትን እንደ ይዞታ የማሰብ አዝማሚያ መኖሩን መካድ አይቻልም... 'እከሊት የእንትና ናት'፣ 'እከሌ የእኔ ነው'፣ 'እርሷ የኔ ናት' እያልን ሰውነትን እንደ ቁስ ለመቁጠር መዳዳታችን እውቅ ነው... ጥንዶች ለየብቻ ሕይወት እንደሌላቸው ሁሉ የአንድ ሰው እስረኛ እንደሆኑ አድርገን እናስባለን... ይህ ግን ፍቅር አይደለም...
ይልቅ እርሷ ሁሌም ነፃ ሆና እርሱን ትመርጣለች - ሌላ ምርጫ ባላት ጊዜም ቢሆን... እርሱ ሁሌም ነፃ ሆኖ እርሷን ይላል - ብዙ ሴቶች ዙሪያው ሳሉም ጭምር... [ልዩነቱ ግልጽ ነው...]
ማምለጥ ስላልቻለ የቆየ እስረኛ ታማኝ አይባልም... የመተው ምርጫ እያለው ሁሌም በዚያ ያለ ሰው ግን እርሱ ፍቅርን ያውቃታል...
[ይህ በእንዲህ እንዳለ - ይላል ራዲዮን...]
ፍቅርን የሚያዘልቁት ከባዱን ዳገት መርጠው እንጂ ቀላሉን ቁልቁለት አቋርጠው አይደለም... ስለዚህ መታመን ጥንካሬን ይፈልጋል... ጽናትን ይፈልጋል... ምርጫ ነፃነት ቢሆንም ዳሩ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ለቃል ማደር ብርታትን ይጠይቃል... ሲታዩም ሳይታዩም ለአቋም መገዛት የሞራል ልዕልናን ይፈልጋል...
እኔና እርሷ 'ሚጋራና 'ሚከለከለውን ካለየን... 'ሚገለጥ 'ሚሸፈነውን ካልመረጥን... በነ'ከሌ ድርሻና በራስ ሰው ድብቅ ላይ - ድንበር ካላኖርን ታማኝነት ውሉን ይስታል... ስብዕና ይተናነሳል...
ያም ብቻ አይደለም፣ እኔ 'ጨዋ ነው ቀሚሷ' ለማለት ሳመነታ፣ እርሷ 'ልቡ የኔ ብቻ ናት' ለማለት ድፍረት ታጣለች...
[ይሄኔ... ያልታሰረ ልብ ይዞ ጣትን በቀለበት የማሰር ልማድ ትርጉም ያጣል...]
"... ማተብን ቢያጠብቁ - የአንጀት ፍቅር ሽረው
በቁርባን ቢጋቡ - ቃልኪዳን ሸርሽረው
ለአፍ ዓመል ካልሆነ - ማ'ላው ከምን ሊያስጥል
በቀለበት ታስሮስ - ፍቅር ምን ሊቀጥል..." እንዲል ከያኒው
እንደ ሰው ማሕበራዊ ተጋልጦ (Exposure) ቢኖረንም እንደ ቤተሰብ ደግሞ የማይነካ ግዛት አለን... ካርታ ባይኖረውም ቅሉ ቤተሰብ ሃገር ነው፣ የማይቆረስ ስስ ገላ - የሚከለል እውነት፣ የማይደራደሩበት ልዓላዊነት አለው...
[ለቤት ከምንገልጠው ገጽ ላይ ገመና ባይኖረንም ለውጭ ከምንጋራው ላይ ግን ደስታና ሃዘናችንም ቁጥብ ነው...]
ከገበያ ብንሸምትም የምናበስለውን የምናውቀው እኛ ነን... (የሸመትነውን ያወቀ ሁሉ የበላነውን መለየት የለበትም!)... ከአደባባይ ብንውልም አዳር የሁለታችን ብቻ ምስጢር ነው... (ያገኘን ሁሉ ልባችንን ማግኘት የለበትም)...
[ከሳቅም ሸርፈው ይስቁታል፣ ከቃልም መርጠው ያወጉታል...]
ለባልሽ ብቻ የምትስቂውን ሳቅ የምትስቂለት እስካለ ድረስ ታማኝነትሽ ከንቱ ነው... ለሚስትህ ብቻ በሚመጥን ቃል የምታወራት እስካለች ድረስ ሴሰኛነትህ ግልጽ ነው...
____
"Lust is a strong need. Love is not a need but a longing. When you love, you settle down – nothing more is needed." ~ Sadhguru
👍
ከመስበቅዎ በፊት...
የተወረወረ ጦር የሚያውቀው አንድ አቅጣጫ ብቻ ነው፤ ንግግር ግን መሄድን ብቻ ሳይሆን መመላለስንም ያውቃል...
ሰሞኑን አንድ ፊልም እያየሁ ነበር… "Man of War" የተሰኘ የ 2026 የጦርነት ፊልም ነው…
ፊልሙ በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት መሃል በቅጥረኛ ወታደሮች የታገተችን እንስት ለማዳን በጦርነት ቀውስ ውስጥ ወደምትገኘው ዩክሬን የተጓዘን አንድ ጡረተኛ የአሜሪካ ልዩ ኃይል (Special Forces) ወታደርን ጀብዱ ያትታል…
ፊልሙ ሲጀምር - ቀደም ሲል በተሰማራባቸው የጦር ሜዳዎች የደከመውን፣ በከባድ የስነ-ልቦና ቀውስ (Trauma) ውስጥ የሚገኘውን እና ራሱን የማጥፋት ሃሳብ የሚታገለውን ሰው እናያለን... ይህ ሰው ጡረተኛው የባህር ኃይል ልዩ ተዋጊ (Navy SEAL) እና የ CIA ወኪል ማይክል ኮነር ሲሆን በአፓርታማው ውስጥ በከፍተኛ የስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ እንደተቀመጠ ይቀላቀለናል…
ኮነር (በመዝገብ ስሙ LaMonica Garrett) ራሱን ለማጥፋት በሚዳዳበት ቅጽበት በዩክሬን ካርኪቭ በሚገኝ የህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ረዳት ሰራተኛ ሆና ከምትሰራውና የማደጎ ልጁ ከሆነችው ራይሊ አስቸኳይ የቪዲዮ ጥሪ ይደርሰዋል…. የተጨነቀች ሴት ድምጽ፣ በፍርሃት የተዋጠች እንስት ፊት፣ በፈንጂዎች የምትናጥ ከተማ ድምጽ…
"Mike, I'm in trouble. I need your help."
"I'm still in Kharkiv."
"I couldn't leave them, Mike. The Russians just crossed the border. They're bombing the city."
“War is a monster that chews up everything in its path.” ~ Connor
When we have lived with a problem for a long time, the first thing that exposes the problem may appear to be the cause of the problem.
.
.
.
እንደምታውቀው ጥርሱን ሳይፍቅ/ ሳይቦርሽ ለረጅም ጊዜ የቆየ ሰው የአፉ ጠረን እንደሚያስቀይም ለመረዳት ሩቅ ነው...
እንዲህ ዓይነት ሰው ለተወሰኑ ቀናት የጥርስ ሳሙና መጠቀም ቢጀምርና መልሶ ቢተዉ እንኳ የአፉን ሽታ በተለየ መንገድ ለማስተዋል ዕድል ስለሚያገኝ 'በምን ምክንያት ነው ይህ ሽታ የተፈጠረብኝ?' ብሎ መጠየቁ አይቀርም...
ሁኔታው በቅርብ ከጀመረው የጥርስ መቦረሽ ጉዳይ ጋር ስለሚያያዝበት ወደ አዕምሮው ቶሎ የሚመጣለት ድምዳሜ ‘የጥርስ ሳሙና አፍ ያሸታል’ የሚል ነው…
ስለምን?...
ነገሩ ወዲህ ነው...
ብሩሽ ከመጠቀሙ በፊት የአፉን መጥፎ ጠረን ተላምዶት ስለቆየ ‘አፍህ ይሸታል’ ቢሉት እንኳ አይሰማም ነበር… ወይም ደግሞ እንደ ችግር ለመቀበል ይከብደው ነበር... ብሩሹ ካለመደው ንጽህና በኋላ ግን የትኛውንም ሽታ መረዳትና መለየት ስለሚጀምር፣ ሽታውን እንደ አዲስ ክስተት ወስዶ ሰበቡ 'አዲሱ እንግዳ ነው' በሚል የጥርስ ሳሙናን ለማውገዝ አንደኛ ይሆናል…
"Sometimes the thing that disturbs your comfort is the thing that restores your clarity."
"The first enemy of transformation is not the problem itself; it is our attachment to what has become familiar. We often reject the hand that cleanses us because cleanliness makes us aware of the dirt we had learned to ignore."
📌
.
.
.
በውዳሴ ወቅት የምታሳየው ፈንጠዝያ፣ በወቀሳ ጊዜ ለመሰበር ያለህን ፍጥነት አመልካች ነው... ለሙገሳ ፈጥኖ እጅ የሚሰጥ ሰው በውግዘት ወቅት በፍጥነት ይፈራርሳል...
ብልህ ሰው ግን ሲያሞግሱት በዝምታ ያልፋል - ከቁምነገር አይጽፈውም... ሲያወግዙትም አንዳች ሳይረበሽ ጸንቶ ይጓዛል - በግሉ አይወስደውም...
ዓለሚቱን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ፣ ሰውንም ከእጁ መዳፍ በላይ በማንበብ ስለሚራቀቅ እያንዳንዱ አጋጣሚ በቀላሉ አሻራውን የሚያትምበት የመንገድ ላይ ሸራ ከመሆን ነፃ ወጥቷል...
ስለምን ቢሉ... ብልህ መሆን ማለት "ይህም ያልፋል!!" ይሉትን ብሂል መገንዘብ ነውና...
___
The moment you are disturbed by insult or pleased by praise, you are still slave ~ Osho
.
.
.
"ይህን ነገር እያመለክሽው አልመሰለሽም?"
"ገንዘብ አልወድም እያልከኝ ባልሆነ"
"አልጠላም፤ ነገርግን አገልጋዬ ላይ ጥገኛ መሆን አልፈልግም"
"ተገልጋይ በአገልጋዩ ፍቅር አይወድቅም ያለህ ማነው?"
"እኔ ጌታ ነኝ፣ ከአገልጋዬ ጋር በፍቅር ወድቄ ክብሬን ማጣት አልፈልግም"
"ያለ ሃብት ክብር የለም ባክህ"
"ከማንነትሽ የማይመነጭ ክብር - ክብር አይደለም"
"ስለየትኛው ክብር ነው የምታወራው?"
"ስለ ሁሌያዊው ክብር፤ በስብዕናሽ ጥራት ብቻ ስለሚገነባው ክብር፤ ሰዎች ሊሰጡሽ ወይም ሊከለክሉሽ ስለማይችሉት ክብር፤ በሁኔታዎች ላይ ስለማይንጠለጠለው ክብር፤ አንቺ ስለራስሽ ባለሽ ግንዛቤ እንጂ ሌሎች ስላንቺ ባላቸው ግምት የማይቆመው ክብር..."
"ሌሎች ካላከበሩኝ እኔ ዋጋዬን ብቆልል ምን ያደርጋል?"
"ለራሱ ክብር የሌለውን ሰው ሌሎች አያከብሩትም፤ ክብር ውስጣዊ ነው"
"እርሱ ቅዠት ነው፣ ክብር አይደለም"
"ያልተረዱትን ማኮሰስ የተለመደ ስንፍና ነው"
"ኖረው ያላዩትን ድሎት ማጥላላትም ያው ነው"
"ያለኝ ይበቃኛል ማለትን ማወቅ ግን የስብዕና ከፍታ ነው"
"ለብቻህ ፃድቅ መሆን አትችልም ባክህ"
"ለብቻ መቆም ነው ጽድቄ"
"ግትር ተብሎ መገለል አያስፈራህም?..."
"በራስ ፊት ማፈር ብቻ ነው የሚያስፈራኝ"
"ለምን ባሕታዊ አትሆንም ታዲያ?"
"እዚህ ያለሁት ራሴን ብቻ ለመሆን ነው"
"በዚህ አቋምህ እኮ ነው ሰው ሁሉ የሚሸሽህ"
"ከእኔ አይደለም የሸሸው ከህሊናው ሙግት ነው"
"ህሊና ህሊና አትበለኝ ባክህ... ድሃ ሆኜ ህሊናዬ ባይወቅሰኝ ሆዴ ዝም ይለኛል?"
"አፍሽ የሚጎርሰውን እጅሽ መመጠን እስካልቻለ ድረስ ሆድ መቼም በቃኝ አያውቅም"
"ሃብት እኮ አይጠገብም"
"በቃኝ ማለት ግን ይቻላል"
"ትንሽ ነገር አያረካማ..."
"ከእጅሽ ያለው ትንሽ እንደሆነ ማሰብ ካላቆምሽ ምድር ሙሉዋን ሃብትሽ ብትሆንም አትረኪም"
"ከጓደኞቼ አንሼ መታየት አልፈልግም"
"ፉክክር እስካለ ድረስ ለራስ መኖር አይቻልም"
"ካልተፎካከርክማ መጨመር አትችልም"
"መኖር የሚመዘነው ባገኘነው ሃብት መጠን ሳይሆን ለራሳችን በፈጠርነው አፍታ ልክ ነው፤ በማግኘት ላይ ብቻ ከተመሰጥሽ ለመኖር ጊዜ ስለማትሰጭ ምንም ማድረግ የማትችይባቸው ቀናት ሲመጡ ጸጸት ይቆጣጠርሻል፤ ፉክክር ጉድለትሽን ብቻ እንጂ ሙላትሽን እንድታይ ዕድል አይሰጥም... ሃብት ይኑርሽ፣ ግን ደግሞ ኑሪበት"
"ኑሪበት ስትል..."
"አፍታ ፍጠሪበት፣ ቆም ብለሽ ስክነት ግዢበት፣ ወደፊት አገኘዋለሁ ከምትይው ላይ ዓይንሽን ንቀይና ባገኘሽው ላይ ትንሽ አተኩሪ፣ አጣጥሚው... ወደድሽም ጠላሽ ከዚህች ቅጽበት ውጪ እርግጠኛ ጊዜ የለንም... አንዳንዴ ከእጅሽ ያለው ሁሉ ያንቺ እንዳልሆነም አስቢ - ለሌሎች በኛ በኩል እንዲደርስ እጃችን የሚገባ አደራም ይኖራል - እርሱን ለሚገባው ማድረስንም ልመጅ"
"አደራ"
"አዎን አደራ... አስር ቤቶች ቢኖሩሽ የምትኖሪው በአንዱ ብቻ ነው፣ መቶ መጫሚያ ቢኖርሽ በአንድ ጊዜ የምታደርጊው አንዱን ነው፣ አስር መኪና ቢኖርሽ በአንድ ጊዜ የምታሽከረክሪው አንዱን ብቻ ነው... አንዳንድ ነገሮች እጃችን ላይ ሲበዙ ሁለት ነገር ማሰብ ይቻላል፤ የመጀመሪያው የእርካታ እጦታችን ነው፣ የነበረን ሲያንስብን ለመጨመር እንሮጣለን፣ መጨመሪያውን ለማግኘት መኖርን እንገብራለን... ሁለተኛው መጋራት አለማወቅ ነው፣ አንቺ አንዱን በሌላው ላይ ለመደረብ ስትከንፊ የነገዋን ጸሐይ ማየት ብርቅ የሆነበት ደግሞ በየዕለቱ ይረግፋል..."
"ሰርቶ አይበላም ታዲያ?"
"ሳይሞክር ቀርቶ አይደለም - የላቡን ያህል ማግኘት ምጥ ሆኖበት እንጂ... የማይገባቸውን በሚሰበስቡ ጥቂቶች ምክንያት የሚገባቸውን የማያገኙ እልፎች መብዛት፣ ዓለማችን ያነበረችው ዕብድ የገበያ ስርዓት ውጤት ነው"
"ገበያው ምን አደረገ?..."
"አግበስባሽነትን አበረታ፣ ከሰው ሁሉ እጅ ላይ ያለውን እያንኳሰሰ የሌለን በመጨመር ውጥረት ውስጥ ከተተ፣ ትናንት በብዙ ውዳሴ አማልሎ ከእጅሽ ያስገባውን ቁስ ዛሬ ከፈጠረው ሌላ ቁስ ጋር እያነፃፀረ ያሳንስብሻል፤ እርሱን ለመቀየር ስትሮጪ ደግሞ ሌላ አዲስ መጥቷል... የዘመኑን ሩጫ በነባር ፍጥነት መስተካከል አልሆንላቸው ያለ በማግኘት ላይ ብቻ ተመስጠው የማይገባቸውን ይመኛሉ፤ ይሄኔ ገበያው ማጭበርበርና የራስ ያልሆነን መሰብሰብ በሚፈቅዱ ሰዎች ይሞላል... ይህ በሌላ ጎኑ ጥሪት አልባውን ይገፋል..."
"ሃብትን ታወግዛለህ ልበል?"
"ሃብትን አናወግዝም፣ ከሃብት ብዛት የሚመጣውን ትዕቢት እንጂ - ይላል ዮሃንስ አፈወርቅ"
"ትዕቢተኛ ነሽ እያልከኝ ነው?"
"አንቺ አልሽ!"
"በኑሮህ ግን ደስተኛ ነህ?"
"ከባድ ጥያቄ ነው፤ ግን ደግሞ ያለኝ ስለሚበቃኝ በጎደለኝ ላይ ለማተኮር ብዙ ዕድል አልሰጥም"
"እኔ ግን ደስተኛ አትመስለኝም"
"ደስተኝነት ለራስ እንደሚሰማው ነው፣ ለሌሎች እንደሚታየው አይደለም"
"እኔ ግን ከስንት አንዴ ነው ደስታ የሚሰማኝ"
"ይህንን ነው ያልኩሽ፣ ደስታ የሃብት ውጤት አይደለም፤ አዕምሮአዊ ቅኝት ነው"
"እና ምን ላድርግ?"
"ዓይኖችሽን ከጉድለት ገጾችሽ ላይ ንቀይ... በረከቶችሽን ቁጠሪ፣ እዚህና አሁን ኑሪ"
"እርሱ ደግሞ ምን ማለት ነው?"
"ደስታ የምናጣው በእልፊት ጸጸትና በመፃኢ ፍርሃት ውስጥ ስለምንቦራጨቅ ነው፤ ሁለቱም ከአንቺ ቁጥጥር ውጪ ናቸው... አሁንና እዚህ ግን ምርጫዎችሽን እንጂ ስህተትና ስጋትሽን አትኖሪም..."
"ስለ ነገ ካላሰብኩ ምኑን ኖርኩት?"
"የተሰጠሽ ዛሬ ላይ ሳትኖሪ በሌለ ነገ ውስጥ መኖር አትችይም፤ ነገም ሲደርስ ያው ዛሬ ነው፣ ካልኖርሽበት ሌላ ነገ ያስጠብቅሻል፣ ከተገለገልሽው ግን የአፍታ ዘላለማዊነትን ሃቂቃ ይገልጥልሻል"
"ሃብታሞች ሁሉ እየኖሩ አይደለም ብለህ ነው የምታስበው?"
"የፍርድ ወንበር ላይ አልተቀመጥኩም፤ ግን አስታውሽ፣ የሁላችንም የመኖር ትርጉም አንድና ያው አይደለም"
"ስለነገ የሚያስቡ እየኖሩ አይደለም እያልከኝ..."
"ለመኖር ጊዜ ካልሰጡ አዎን፣ እየኖሩ አይደለም"
"ጊዜ መስጠት ስትል..."
"ወደ ተራራው ጫፍ ለመውጣት የሚያስቡ መንገዳቸው ላይ በየመሐሉ አረፍ ማለትን ይማሩ ማለቴ ነው... የሰበሰብሽውን ለመብላትም ጊዜ ያስፈልግሻል"
"ተራራው ግን ጫፍ የለውም"
"ልክ ነሽ፣ በሄድሽ ቁጥር የአንዱ ተራራ ጫፍ የሌላኛው ተራራ መነሻ መሆኑ ይገለጥልሻል"
"ፍለጋው አያልቅማ"
"አዎን - ትርፉ መባከን ነው፤ ባገኙት መብቃቃት ግን ነፃ ያወጣል"
"መጨመር ሲያስፈልግስ?..."
"ላለው የሚያስፈልገው ሁሉ ይጨመርለታል"
"ምን ላለው?"
"ምስጋና!!"
_
@bridgethoughts
.
.
.
👍
ታዘባርቀኛለች.... አልደርስባትም... በየቀኑ ቅኔ ትሆናለች... “እንደዚህም መኖር ይቻላል እንዴ?” የምታስብለኝ ብዙ ነው... ለማኅበረሰብ ወግና ሥርዓት ስትገዛ አላውቃትም...
➡️
‘ሰው ግን እንዴት እንዲህ በሚያምር መንገድ ያምፃል?’ ታስብላለች... ያውም ‘እንዲህ የማደርገው ለዚህ ነው’ በሚል ማብራሪያ ሳታጅበው... ያውም ክብሯን እንደ በትረ መንግሥት ይዛ... በዙሪያዋ ያሉ ሁሉ እንዲህ መኖር አለባት የተባለውን ሳይሆን የምትኖረውን ልክነት እየተነተኑላት… ድርጊት የተሻለ ያሳምናልና - ፍሬዎቿ ውስጥ የቀሰሙት እውነት ልዕለ ስብዕናዋ ሆኖላት...
➡️
እጇ ከመስጠት አይሰንፍም... ለመቀበል ግን ሩቅ ናት... ስታማርር አልሰማሁም... የተሸከመችው ጓዝ እኔን እያንሻፈፈኝ እርሷ ፈገግታዋ ሳይነጥፍ በሚዳሰስ ኃይል መንገዷን ትቀጥላለች... ለራሷ ያላት ቦታ በየትኛውም ውጪያዊ ክስተት የማይነካካባት እርሷ!...
➡️
ደግሞ ለስላሳ ትሆናለች... ጥል ቀርቶ በጎኗ ያለፈ ሁሉ ከፍቶት እንዲያልፍ የማትሻ፣ ሁለት ፀጉር ያላቸው የዘመን ባለፀጎችን ሳይቀር እንደ ህፃን አባብላ መሸኘት የምትችል.... ደግሞም ተዋጊ… ድንበሯን ያለፈ ሁሉ ያቺን ቀን እስኪረግም፣ "የሞተ ገድሎ አይፎከርም" እንዲሉ አሸንፋ ይቅር ብላ እስክትመለስ የማታቆም....
➡️
ታስገርመኛለች… እንደ እርሷ መሆን ያማልለኛል… ታዘባርቀኛለች…
➡️
እንደዋዛ የምትኖረውን የህይወት ፍልስፍና ሞክሬ በእርሷና በራሴ መሃል የጠፋሁት ጥቂት አይደለም... ታስፈራኛለች… ተነጥዬ ልተነትናት ላያት አልችልም፣ ትፈትነኛለች… ‘እንዴት ቻልሽበት?’ ጥያቄዎቼን ብዙ ሳታብራራ ታተናቸዋለች...
➡️
‘የምር የሚኖረው እንዲህ ይሆን እንዴ?’.... እንጃ!?!?
➡️
የሆነው ሆኖ በዘመኔ ሁሉ ዓይኖቼ እርሷ ላይ ነበሩና በደመነፍሴ ነው የማውቃት... እርሷን!!
➡️👈
ተፃፈ - በእሙዬ
➡️👈
✈️ @yeesua_queen
❗️
.
.
.
"ጥቃትን እየለመድንና ለሺዎች ሞት ግድ የለሾች እየሆንን መጥተናል" ~ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ
__
መጋቢት 27/2018
___
@bridgethoughts
📣 Today's Reminder
➡️ Don't Escape Life - Experience it.
🟢🟢🔴
@bridgethoughts
🎸🎸🎸
.
.
.
🎶
"አልጋ ከመያዛችሁ" በፊት ልትሰሙት የሚገባ ጉልበታም ሙዚቃ [መልዕክት ወዜማ]...
🌨🌨🌨
በዝናቡ ድባብ ውስጥና በጊዜ ሄድ መለስ መሐል ሆኜ እየሰማሁት ያለ ሙዚቃ ነው...
Things they told me before they left.
መንደርደሪያ...
___
✔️የምንተቸው የማናደርገውን ነው ወይስ ዕድሉን ብናገኝ የማንዘለውን?... ✔️
ክህደት፣ ኩራት፣ ንቀት፣ ህሊናቢስነት ወዘተ፣ የየራሳቸው ብዙ ጥቅስ፣ ብዙ አባባል፣ ብዙ ምሳሌና ብዙ ተረቶች አሉዋቸው... ትናንት ወላጆቻችን በቡና ላይ ሐሜት ይኖሩት ነበር... ዛሬ ደግሞ በዘመን መድረክ እኛ እየኖርነው ነው...
ሰው ማማት ደስ ስለሚል የሐሜት አድናቂው ብዙ ነው፤ ሁሉም አንገቱን ይነቀንቃል፣ 'ልክ ነህ፣ ልክ ነሽ' ይላል... Like share repost ያደርጋል...
ሁሉ ተቺ ከሆነ - ማነው 'ንጹህ' ሰው?... ሰው ሁሉ ችግር ካለበት ታዲያ ልክነትን እንዴት አወቅነው?... በጎነት ከሌሎች ብቻ የምንጠብቀው ከሆነ እኛ መች ነው የምንኖረው?...
ድራማው በአባባል የተሞላ ነው... ቲክቶክ በዚህ የሰለጠነ ነው... ሬዲዮው፣ ቲቪው፣ ጋዜጣው፣ ውይይቱ፣ ጓደኝነቱ... ሁሉም እየተነሳ የሰው ልጅ እንዲህ ነው፣ የሰው ልጅ እንዲያ ነው በማለት የሚበይን ነው...
ለመሆኑ እኛ ምንድን ነን?... ሰው አይደለንም እንዴ?...
የሆነ ሰው እንዲህ ሲል 'ደስ የሚለን፣ አሃ፣ ልክ ነው እኮ...' ምናምን የሚያሰኘን በተወቃሾቹ ዝርዝር ውስጥ እራሳችንን እያየን ነው?... የወቃሹንስ እንዲያውነት እያመንን ነው?... የሰው ልጅ በሙሉ እንዲህ ከሆነ ሰውነት አብቅቶለታል ማለት ነው?... ታዲያ ምን እንሁን?...
.
.
.
እንዳልኳችሁ ነው...
ሁላችንም መተቸት እንወዳለን... [እርግጥ በኑሮአችን ውስጥ ትችት ቀላሉ ተግባር ነው... የማቅናት ዓላማ የሌለው አስተያየት ዕውቀትም ሆነ ልምድ አይፈልግም...] እናም፣ ሁሏንም ነገር እናብጠለጥላለን... ጓደኝነትን፣ ማህበራዊ ግንኙነትንና የሰው ልጅ ምንነትን በየቀኑ በሂስ ሚዛን ላይ እናስቀምጣለን... "ሰው ተበላሸ፣ ክህደት በዛ፣ ንቀት ነገሰ" ወዘተ እንላለን... ነገር ግን ይህ የምንተቸው "ክፋት" የት ነው ያለው?... ከእኛ ውጭ ወይስ በእኛም ውስጥ?...
ነገሩን ከፈትፈት ለማድረግ - "ሰው እኮ!" የሚለው ድምጸታችን ውስጥ ሰውነታችን አለ ወይ?... ነው ወይስ ራሳችንን ከዓለም ንጡል አድርገን ነው የምናስበው?...
[ይህንን ሃሳብ በቅጡ ለማንጸር እንዲያስችለን የተለያዩ መነጽሮችን እንዋስ...]
⬜️ ሚስቲሲዝም (Oneness)
በተማላዮች (Mysticism) እይታ፣ ዩኒቨርሱ አንድ ነው... "እኔ" እና "ሌላው" የሚባል መስመር፣ እዚህና እዚያ የሚባል ድንበር ወይም ደግሞ ዓይነታዊ (ሰው፣ እንስሳ፣ ተራራ፣ ሰማይ... ወዘተ) የሚል ተናጥሎ የለም... ስለዚህም ሌላውን ስንተች፣ በእውነቱ የምንተቸው የራሳችንን ነጸብራቅ ነው...
'The eye with which I see God is the same eye with which God sees me." — Meister Eckhart
"In quantum physics, the observer creates the reality." — Amit Goswami
“Now, there is one thing you might have noticed I don’t complain about: politicians. Everybody complains about politicians. Everybody says they suck. Well, where do people think these politicians come from? They don’t fall out of the sky. They don’t pass through a membrane from another reality… it’s what our system produces: Garbage in Garbage out. If you have selfish, ignorant citizens you’re going to get selfish & ignorant leaders…” ~ George Carlin