29777
በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
የቅዱሳን አባቶችን ትምህርት በአጭሩ
"ለባልንጀራህ ያለህ ፍቅር ሲቀዘቅዝ ከእግዚአብሔር ጋር ያለህ ግንኙነትም አደጋ ላይ መውደቁን እውቅ።" ( ቅዱስ ባስልዮስ)
\\በፆም ትትፌወስ//
በጾም ትትፌወስ ቁስለ ነፍስ
ወበጸሎት ትትሀሰይ መንፈስ /2/
አዝ………….
መአልትና ሌሊት በጾም ጸሎት ተግቶ
አሳይቷል ጌታ ስርዓትን ሰርቶ
አይቀርም ፈተናው ትጋት ከሌለበት
ስጋ ካልደከመች በጾምና ጸሎት
አዝ………….
ሙሴ የተባለው ያ የእግዚአብሔር ሰው
ፊቱን የበራለት አርባ ቀን ጾሞ ነው
በሲና ተራራ ተቀብሎ ህግን
እርሙን እንድንተው አሳየን መንገድን
አዝ………….
የጸሎት እናቷ ስለሆነች ጾም
ትህትናን ይዘን ደግሞም አንድ ሆነን
ብንተጋ በጸሎት ከንስሀ ጋራ
ጾም ታደርሰናለች ከጽዮን ተራራ
አዝ………….
አንድበትም ይጹም ኃይልም ይረጋጋ
ጆሮም ክፉ ሰምቶ ነፍሱን እንዳይወጋ
ድኅን ከመበደል ልብም ተመልሶ
መጾምስ እንዲህ ነው የበደለን ክሶ......
በዘማሪ አቤል ተስፋዬ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ኅዳር ፲፭
ጾመ ነቢያት
ጾም በሃይማኖት ምክንያት ከምግብና መጠጥ ተጠብቀው (ተከልከለው) ከአምላክ ጋር የሚነጋገሩበት መንፈሳዊ ዘር የሚዘራበት የአምላክ ፈቃድ ብቻ የሚፈፀምበት የጽድቅ (የሕይወት) በር ነው። ከቤተክርስቲያናችን የሥርዓተ ቀኖና መጽሐፍ የፆምን ትርጉም አንዲህ ብሎ ይተረጉመዋል። 'ሰው ህግን ለሰራለት ለክርስቶስ እየታዘዘ ኃጢአቱን ለማስተስረይ ብዙ ዋጋ ለማግኘት ፈልጎ የፍትወት ሃይል ደካማ ሥጋ ለነባቢት ነፍስ ይገዛለት ዘንድ በሕግ በታወቁ ጊዜያት ከመብል መከልከል ማለት ነው።'
ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ለልጆቿ ከምታስተምራቸውና ለመንፈሳዊ ተጋድሎ ለሥጋዊ ፈቃድ መግቻ ልጓም ለፈቃደ ነፍስ መፈፀሚያ መንገድ ሆኖ ለአማኒያኖቿ ከሰራቻቸው ስርዓቶች አንዱ ጾም ነው። ይህም የድኅነት በር ነው። የጽድቅ መንገድ ነው። ይህም ለአንድ ኦርቶዶክሳዊ አማኝ በሃይማኖት ሲኖር ራሱን እየመረመረና እየፈተነ (2ኛ ቆሮ. 13፥5) የዲያብሎስን ሃይል ድል መንሻ የመንግሰተ ሰማያት መውረሻ ስንቁን ትጥቁን የሚያሳድግበት ብርቱ ጥሩር እንደሆነ ቤተክርስቲያን ሥርዓት ሰርታ ልጆቿን ታስተምራለች።
የጾም ወቅት መንፈሳዊ ተጋድሎ የሚበዛበት የጌታን ፍቅር የምንገልፅበት ዲያብሎስን ተዋግተን ድል የምናገኝበት የጦር እቃ የምንለብስበት እግዚአብሔርን በንስሃ ምሕረት ቸርነት የምንጠይቅበት አባታዊ ፍቅርን ቤተሰባዊ ግንኙነታችንን የምናዳብርበት የውስጣችንን ምስጢር ለአምላካችን የምንነግርበት እንዲሁም ምህረትን የምናደርግበት፣ ድሃ አደጎችን ፣ የታመሙትን፣ የሞቱ ነፍሳትን የምናስብበትን ጊዜ ሲሆን በአጠቃላይ በጾም አማካይነት ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ መውደዳችንን የምናሳይበት ከፈቃደ ሥጋ ይልቅ ፈቃደ ነፍስን የምንፈፅምበት ወቅት ነው።
የነቢያት ጾም የሚገባው ኅዳር ፲፭ (15) ቀን ሲሆን ጾሙ የሚፈታው በገና በዓል ታኅሣሥ ፳፱ (29) ነው:: ወይም ደግሞ በአራት ዓመት አንዴ በዘመነ ዮሐንስ ታኅሣሥ ፳፰(28) ቀን ይፈታል።
ጾመ ነቢያት የተባለበትም ምክንያት ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለ ተፈጸመበት እንዲሁም በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምሥጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ የረቀቀው ገዝፎ እየተመለከቱ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ስለ ጾሙ ስለ ጸለዩ ነው፡፡
እንዲሁም ነቢያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ፣ እና ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍጻሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑት፡፡ በየዘመናቸው «አንሥእ ኃይለከ፣ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ እጅህንም ላክ» እያሉ ጮኹ (መዝ 143/144/:7-8)፡፡ በጾምና በጸሎት ተወስነውም ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ ... ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር «የማያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር» ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ፡፡ ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩት እነ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋልም (ኢሳ 58:1)፡፡ በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለ ተፈጸመበት ይህ ጾም «የነቢያት ጾም» ይባላል፡፡
ስለ ጾሙ መግቢያ የእኛ ቤተ ክርስቲያን የሥርዓታችን መጽሐፍ ፍትሐ ነገሥታችን እንዲህ ይላል፦ <<ወይከውን ከመ ረቡዕ ወዓርብ፤ ወውእቱ ጾም ዘይቀድም እምልደት፤ ወጥንተ ዚኣሁ መንፈቀ ሕዳር ወፋሲካሁ በዓለ ልደት። /የነቢያት ጾም እንደ ረቡዕና እንደ ዓርብ የሆነ፤ ይኸውም ከልደት አስቀድሞ የሚጾም መጀመሪያው የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል የሆነ ጾም ነው።>> (ፍት.ነገ. ፲፭፥፭፻፷፰)::
እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን በረከት የምናገኝበት ያድርግልን! አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ኅዳር ፲፪
ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላዕክት
ኅዳር ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
ዳግመኛ በዚህች ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን የተራዳበት ቀን ነው።
ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሁኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው ከእኛ ሰዎች ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ አለው። እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወዳንተ መጥቻለሁ አለው ።
ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል አለው ። የእግዚአብሔር የሠራዊቱም አለቃ ሚካኤል ኢያሱን የቆምክባት ምድር የከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው ኢያሱም እንዳለው አደረገ ።
እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው በውስጧ ያለውን ንጉሧን ከኃያላኑና ከአርበኞቹ ጋር በእጃችሁ ኢያሪኮን እነሆ አስገባታለሁ ። ይህም የከበረ መልአክ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር በመሆን ገድላቸውን እስከ ሚፈጽሙ የሚያጸናቸውና የሚያስታግሣቸው ነው ።
ስለዚህም ስለ ልዕልናውና ስለ አማላጅነቱ በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠራለት እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲአወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲአደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲአደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናልና። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ይማረን የቅዱስ ሚካኤል በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ደም ወማይ
ደም ወማይ ወሐሊብ እምነ ክሳዱ ፈልፈለ/፪/
ሶበ ተከለለ/፪/ጊዮርጊስ ሶበ ተከለለ/፪/ኧኸ/፫/
ትርጉም፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰይፍ አንገቱን በተሰየፈ ጊዜ ደም ውኃና ወተት ፈሰሰ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ኅዳር ፯
የቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕት ቅዳሴ ቤቱ ከበረች
ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን የልዳ ሀገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ።
ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ሊአፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው፤ ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ። በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲያኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዱው ራስ ደርሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልንጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጐሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ ሀገራቸው አፍረው ተመለሱ።
ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ ሀገር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሔደ በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ።
ክብር ይግባውና ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቁስጠንጢኖስን በእግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
✞ንብ ሁኑ ዝንብ አትሁኑ!
አንዳንድ ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚመለከቱት ትክክል ያልሆኑ ነገሮች እጅግ ሐፍረት እንደሚሰማቸው በማዘን ይነግሩኛል። ለነዚህ ሰዎች እንዲህ ብዬ እነግራቸዋለሁ:- ዝንብን “እዚህ አካባቢ አበቦች ይታዩሻል” ብላችሁ ጠይቋት።
ዝንቧም “ ስለ አበባዎች አላውቅም። ነገር ግን እዚያ ጋር ትልቅ የቆሻሻ ክምር አለ በዚያ የምትፈልጉትን አይነት የሚሸት ቆሻሻ ታገኛላችሁ” ብላ ትመልስላችኋለች። ካስፈለገ ስለ ቆሻሻው ዝርዝርና በቦታው ስለሚገኝ ንጹህ ያልሆነ ነገር በቂ ማብራሪያ ትሰጣችኋለች። ንብን ደግሞ “በዚህ አካባቢ ንጹሕ ያልሆነ ቆሻሻ ቦታ ታውቂያለሽ” ብላችሁ ብትጠይቋት “ ቆሻሻ? በጭራሽ! እዚህ አካባቢ አይቼም አላውቅም! ይህ ቦታ እጅግ ውብ በሆኑ ቆንጆ መዓዛ ባላቸው አበቦች የተሞላ ነው” ብላ ትመልስላችኋለች። በአትክልት ስፍራውና በሜዳው ስላሉ አበቦች ውበትና ዝርዝርም ትነግራችኋለች። አስተዋላችሁ? ዝንብ የምታውቀው ቆሻሻንና ቆሻሻ ያለበትን ቦታ ነው ንቢቱ ግን ውብ አበቦች እና ሰናይ መዓዛ ያለበትን ቦታ ነው የምታውቀው።
አንዳንድ ሰው እንደ ዝንብ ነው። አንዳንድ ሰው ደግሞ እንደ ንብ። እንደ ዝንብ የሚያስቡት በሁሉም አጋጣሚ የሚያዩት መጥፎውን ሲሆን በመጥፎው ሃሳብም ቀድመው የተሞሉ ናቸው። መልካም ቢኖር እንኳ አይታያቸውም። ንቦቹ ግን በሚመለከቱት ነገር ውስጥ ሁሉ መልካሙን ያያሉ። ስሑት የሆነ እና በጎ ሕሊና የሌለው ሰው ሁሉን ነገር ስሑት አድርጎ ያስባል። ሁሉንም ነገር በመጥፎ መንገድ ይመለከታል። በጎ ሕሊና ያለው ሰው ግን ምንም ዓይነት ነገር ቢመለከት ምንም አይነት ነገር ብትነግሩት መልካምና ቀና ሀሳብን እንደያዘ ይቀጥላል።
አንድ ጊዜ የሆነ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪ ወደኔ በዓት መጣና በበሩ ላይ ባለው የመጥሪያ ብረት አንኳኳ። በወቅቱ በርግጥ ብዙ ደብዳቤዎችን እያነበብኩ ቢሆንም ምን እንደፈለገ ወጥቼ ለማየት ወሰንኩ። “ ምን ፈለግክ የኔልጅ?” አልኩት። “ የአባ ፓይሲዮስ በዓት ነው?” ሲል ጠየቀኝ። አክሎም “አባ ፓይሲዮስን ላገኛቸው እፈልጋለሁ” አለኝ። “በርግጥ የአባ ፓይሲዮስ በዓት ነው ነገር ግን አባ ፓይሲዮስ ሲጋራ ሊገዛ ወጥቷል” ስል መለስኩለት። “ የሆነ ሰው ሊረዱ ነው የሄዱት በርግጠኝነት” ሲል መለሰልኝ። “አይ ለራሱ ነው የሚገዛው ሲጋራውን” አልኩት። “የነበረውን በሙሉ አጭሶ ጨርሷቸዋል። ሲጋራ በጣም ነው የሚወደው። እኔን እዚህ ብቻዬን ትቶኝ ነው የሄደው መቼ እንደሚመለስ እንኳን አላውቅም። የሚቆይ ከሆነ እኔ ራሱ ጥዬ መሄዴ ነው” አልኩት። የተማሪው ዐይን እንባን አቅርሮ ውስጣዊ ስሜቱን አሳበቀበት። ነገር ግን አሁንም በበጎ ሕሊና እና በቀና ሀሳብ “አባ ፓይሲዮስን እንደኔ ያለነው ነን ያሰቃየናቸው” ሲለኝ “ ቆይ ለምን ልታገኘው ፈለግህ” አልኩት “ቡራኬ ልቀበል ነው” አለኝ “ አንተ ሞኝ ከእርሱ ምን አይነት ቡራኬ ነው የምትጠብቀው ለራሱ የተታለለ ሞኝ ነውኮ! እኔ በደንብ አውቀዋለሁ። በርሱ ውስጥ ምንም ጸጋ እግዚአብሔር የለም። ይመለሳል ብለህ እሱን በመጠበቅ ጊዜህን አታባክን ጠጥቶም ሊሆን ይችላል የሚመጣው በጣም ጠጪም ነው በዛ ላይ” አልኩት። ይህንን ሁሉ እየነገርኩት ሁሉ ያ ወጣት ልጅ አሁንም መልካም ማሰቡንና በጎ ሕሊናውን አልጣለም። በመጨረሻም “ ይኸውልህ እኔ እስኪመጣ ጥቂት እጠብቀዋለሁ ምን ልንገርልህ ንገረኝና ሂድ” ስለው “ የምሰጣቸው ደብዳቤ አለ በዚያም ላይ ሲመጡ ቡራኬ ተቀብዬ ነው የምሄደው” ብሎ ከነገርኩት ከዚህ ሁሉ ቆሻሻ ውስጥ መልካም ነገር ብቻ እንዴት እንዳየ ተመለከታችሁ? ምንም ያህል መጥፎ ነገር ብነግረው በመልካም ሀሳብ ነበር የሚወስዳቸው። ስለ ሲጋራ እንኳ እየነገርኩት አይኑ እንባ አቅርሮ “የሆነ ሰው ሊረዱ ሄደው ነው” ብሎ ያስብ ነበር። ብዙ የተማሩና ታላላቅ ነገሮችን ያነበቡ ሰዎች እንኳ የዚህን ወጣት ተማሪ ያህል በጎ ሕሊና የላቸውም። መልካም ሀሳቡን በመጥፎ ስታጠፉበት ደግሞ ሌላ በጎ ሀሳብ ይፈጥርና በዚያም ተመስርቶ በጎ ድምዳሜ ላይ ይደርሳል። በርሱ በጣም ተደነቅሁ እንዲህ ያለ ነገር ሳይ የመጀመሪያዬ ነው።
ንብ እንሁን ዝንብ አንሁን!
ንብ እንሁን ዝንብ አንሁን!
ንብ እንሁን ዝንብ አንሁን!
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
<<ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማኅበረ ጻድቃን ተወደሰ። ወፈድፋደሰ በላዕለ ኃጥአን ነግሠ። እስመ አንሥአ (አሕየወ) ሙታነ ወሕሙማነ ፈወሰ። ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ። ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ።>>
<<ማርያም ሆይ የፍቅርሽ ተአምር በጻድቃን ማኅበር ዘንድ ተመሠገነ። ይልቁንም በኃጢያተኞች ላይ ነገሠ። ሙታንን አድኗልና ፤የታመሙትንም ፈውሷልና። "የደረቀውን እንዲያብብ አድርጓል" የሚል አለ። "ተራሮችን አፈለሰ የሚልም "አለ።>>
እንኳን አስፈጸመን!🙏
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
" የጴጥሮስን እንባ "
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"በቁስሌ ላይ"
ዲ/ን ዘማሪ በኃይሉ ተበጀ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ጥቅምት ፳፯
መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ
ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት::
¤ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::
ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት::
¤ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት::
¤ራሱንም በዘንግ መቱት::
¤እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::
¤በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት::
በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት::
ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: 6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት::
7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን
ተናገረ:: ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ::
በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ::
11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ::
ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::
ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::
+በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱ ይማረን ለሀገራችን ሰላሙን ይላክልን፤ አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"ማርያም ጎየይኪ"
ማርያም ጎየይኪ እምገጸ ሄሮድስ/፪/
ለአርእዮ/፬/ ተአምረ ግፍዕኪ/፪/
ትርጉም፦ ማርያም ሆይ የግፍሽን ተአምር ለማሳየት ከሄሮድስ ፊት ሸሸሽ ፡፡
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
የ፳፻፲፰ ዓ.ም የጥቅምት ፲፮(የሦስተኛው ሰንበት) የጽጌ ማኅሌት
ዘሣልሳይ ሰንበት
መልክአ ሥላሴ
ዚቅ
ዓዲ ዚቅ
፩ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ዚቅ
፪ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ዚቅ
፫ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ዚቅ
ዓዲ ዚቅ
፬ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ዚቅ
ዓዲ ዚቅ
፭ኛ. ሰቆቃወ ድንግል
ዚቅ
መዝሙር በ፫
#ጾም
#የጽድቅ_ሥራ
ከ 600 አመት በላይ የሆናት የደብረ መድኃኒት አሾረና ኪዳነምህረት አንድነት ገዳም እርዱኝ ትላለች።
ገዳሟ ምንም እንኳን ጥንታዊና የብዙ ቅርሶች ባለቤት ብትሆንም አካባቢዉ ከመሰረተ ልማት የራቀ በመሆኑ የገዳሙ አባቶችና አገልጋይ አርድዕት የእለት ምግብና አልባሳት በማጣት : ከገዳሟ ለብዙ ጊዜ ለመቆየት : ቅርሱን በተሻለ ቦታ ለማስቀመጥና ለመጠበቅ መቸገራቸዉን ገልፀዋል።
ከአለም ርቀው ስለፍቅሩ ሲሉ በየበርሀው እና በየገዳማቱ ባዕታቸውን ቀልሰው ሌት ከቀን ለሚማፀኑልን ሰርክ የሚጸልዩ ስለ ዓለሙ ምልጃ የሚተጉ የሚያነቡ ገዳማውያን የልጆቻቸውን እጅ ናፍቀው ተጨነቁ ቢባል እግዜሩስ እንዴት ያየናል?!
ስለእኛ ለነፍሳችን በመድከም በመንፈሳዊ ህይወት መምህር የሚሆኑን የክርስቶስ እውነተኛ ሙሽሮች ገዳማውያን፣ ዛሬ ላይ ባለው ሰው ሰራሽም ሆነ ተፈጥሯዊ ነባራዊ ሁኔታዎች የሚቀመስ እፍኝ ቆሎም ጠፍቶ ረሀብ ጥማቱ በብርቱ እየተፈታተናቸው ለጾም ለጸሎት መቆም ተስኗቸው ከተፈጥሮ ጋር ግብ ግብን ይዘዋል።
እግዚአብሔርን የምትወዱ እርሱን ለመምሰል የምትተጉ ብጹዓን ጥቂት በመራራት የቸርነት እጃችሁን ለእነዚህ ገዳማውያን በመዘርጋት በረከተ እግዚአብሔርን ታገኙ ዘንድ እንጠይቃቹኋለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- የደብረ መድኃኒት አሾረና ኪዳነምህረት አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000719392419
አሾረና ኪዳነምህረት አንድነት ገዳም
ወይም
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:- 0945351250
ወረብ
አንተኑ ሚካኤል መና/፪/ ዘአውረድከ{፪}
ወአንተኑ ለእስራኤል መና ዘአውረድከ{፪}
.
"ኦ አንተኑ ሚካኤል"
በዘማሪ ዲ/ን ሙሉቀን ከበደ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
አርባዕቱ እንስሳ
አንቅዕተ ማኅሌት አንቅዕተ ውዳሴ
ምግባቸው ምስጋና ልብሳቸው ቅዳሴ
ዘወትር ይቀኛሉ ለቅድስት ሥላሴ /፪/
ዐይኖቻቸው ብዙ ክንፎቻቸው ስድስት የሥላሴን መንበር የሚሸከሙት
ሱራፌል ኪሩቤል መገብተ ስብሐት /፪/
አዝ.....
ሰአሉ ለነ አርባዕቱ እንስሳ ገጸ ሰብእ ወገጸ አንበሳ
ገጸ ላሕም ወገጸ ንስር /፪/
አዝ.....
ዘወትር አይለዩም ከመንበሩ ዙሪያ ያመሰግናሉ ብለው ሃሌ ሉያ
ይሏታል ድንግልን እኅትነ ነያ /፪/
አዝ.....
ኪሩቤል ሱራፌል ምሉዓነ ግርማ ምስጋናቸው ሲፈስ ድምፃቸው ሲሰማ
ልብን ይመስጣል የምስጋናው ዜማ /፪/
አዝ.....
ሰአሉ ለነ አርባዕቱ እንስሳ ገጸ ሰብእ ወገጸ አንበሳ
ገጸ ላሕም ወገጸ ንስር /፪/
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ኅዳር ፰
አርባዕቱ እንስሳ
ኅዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው የአርባዕቱ እንስሳ በዓላቸው ሆነ።
እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።
የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።
የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።
ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።
የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።
ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።
በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።
እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።
ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።
ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።
በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።
ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው። ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።
ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።
©ስንክሳር
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ገሊላ እትዊ
በቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ኅዳር ፮
እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ደብረ ቁስቋም የገባችበት
ኅዳር ስድስት በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡
አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገርን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡
ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡
ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡
ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡
ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡
እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡
ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡
እመቤታችን ማርያም የአስራት ሀገሯን ሀገራችንን ኢትዮጵያን ከገባችበት መአት ታውጣልን።
~ አሜን ~
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ንግስተ ሰማያት ወምድር ማርያም ድንግል (2):
ተፈጸመ(5) ማኅሌተ ጽጌ።🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹 @Ethiopian_Orthodox 🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
የ፳፻፲፰ ዓ.ም የጥቅምት ፴(የመጨረሻ ሰንበት) የጽጌ ማኅሌት
ዘኀምስ ሰንበት/ዘተፈጸመ/
መልክአ ሥላሴ
ዚቅ
ዓዲ ዚቅ
፩ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
፪ኛ.ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
፫ኛ.ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
፬ኛ.ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
ሰቆቃወ ድንግል
ወረብ
ዚቅ
መዝሙር በ፮
«ኢየሱስም ዘወር ብሎ ተመለከተው»
ጴጥሮስ ጌታውን ለሦስተኛ በካደበት ጊዜ ጌታችን ከሸንጎው ታስሮ ወደሚያድርበት ምድር ቤት እየተወሰደ ነበር፡፡ ጴጥሮስ «ሰውዬውን አላውቀውም» እያለ ሲምልና ሲገዘት «ያንጊዜ ዶሮ ጮኸ፡፡ ጌታም ዘወር ብሎ ጴጥሮስን ተመለከተው ፤ ጴጥሮስም፦ ዛሬ ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ እንዳለው የጌታ ቃል ትዝ አለው፡፡ ጴጥሮስም ወደ ውጪ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቃሰ።» ሉቃ፳፪፥፰-፳፪
የዋሑ ጴጥሮስ በሎሌዎች ተከብቦ ሰውየውን አላውቀውም እያለ በሚያስረዳበት ሰዓት መምህሩ ክርስቶስ ዘወር ብሎ ተመለከተው።ጴጥሮስ ሦስት ጊዜ አላውቀውም ብሎ የካደው ጌታ «እኔ ግን አውቅሃለሁ» ሲል ዘወር ብሎ ተመለከተው።ክርስቶስ እንደታሰረ በዓይኖቹ ተመለከተው 'ጴጥሮስ ሆይ አታውቀኝምን? በገሊላ ባሕር ዓሣ ስታጠምድ የጠራሁህ፤ በባሕር ላይ እንድትራመድ ያደረግኩህ ፤ ከዓሣው ሆድ ውስጥ ገንዘብ አውጥተህ ለእኔ እና ለአንተ ግብር ክፈል ያልኩህ፤ከሰዓታት በፊት እግርህን ያጠብሁህ... እኔን አታውቀኝም?'የሚሉ ዓይኖች ጴጥሮስን ተመለከቱት።
ጴጥሮስ በካደባት በዚያች ቅጽበት የጌታን ዓይኑን ሲመለከት ምን ተሰምቶት ይሆን? እስከ ልብ ድረስ ዘልቀው የሚያዩት አምላካዊ ዓይኖች ለዚህ ሐዋርያ ምን መልእክትን ተናግረው ይሆን? ይህን ሐዋርያ አግኝቶ ማን ጠይቆ በነገረን? እሱ ያየውን ጌታ ከሦስት ጊዜ አልፈን ሦስት ሺህ ጊዜ በኃጢአታችን ለካድነው ለእኛ ማን ጠይቆ በነገረን? እንደ ጴጥሮስ ስንክደው ዘወትር የሚያየንን ጌታ ማየት ለተሳነን ለእኛ የጌታን የዓይኑን መልእክት ማን ጠይቆ በነገረን?
ጴጥሮስ የጌታን ዓይን ባየበት ቅጽበት ልቡ ድረስ የሚወጋው፤ በኀዘን የሚያቃጥለው ጸጸት ተሰማው።የጌታ ዓይኖች በቁጣ የተሞሉ አልነበሩም። ጴጥሮስን ግን በጸጸት ጦር ልቡን የሚወጉት ሆኑ።ቀድሞ ያልተሰማው የዶሮ ጩኸት አሁን ዘልቆ ተሰማው « ሌሎች ቢክዱህ እኔ አልክድህም» ብሎ ተናግሮ ሦስት ጊዜ መካዱን አሰበ 'ከሁሉ ይልቅ ስወደው ከሁሉ ቀድሜ እክደው ?' ብሎ ተንገበገበ። ስለዚህም ለክህደት ከዳረገው እሳት ከሚሞቅበት ግቢ በሕሊናው ዓይን የጌታን ዓይኖች በሕሊናው ጆሮ የዶሮውን ጩኸት እየሰማ ወጣ ከአጥር ውጪ ወጥቶም ምርር ብሎ አለቀሰ።
ጴጥሮስ 'ጌታ ሆይ ይቅር በለኝ፤ በድንገት ፈርቼ ነው ነው የካድኩህ ፤ሎሌዎቹ ሲያዋኩብኝ ነው' እያለ ይቅርታ አልጠየቀም። «አለቀሰ እንጂ ይቅርታ አልለመነም ምክንያቱም የዕንባ ዘለላዎች ይቅርታን ያገኛሉ እንጂ ይቅርታን አይለምኑም»እንዳለ ሊቁ አምብሮስ። ስለዚህ የዋሁ ጴጥሮስ ቃል ሳይተነፍስ በጨለማ ውስጥ ብቻውን ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡ ጌታ አይቶታል እና ስለ በደሉ ምርር ብሎ አለቀሰ። "ጌታችን ሆይ ወደ እኛም ተመልከት ስለ ኃጢአታችንም እንድናለቅስ አድርገን።" ይላል ሊቁ አክሎ።
ዕንባ በእርግጥም ኃይል አለው፡፡ የሰው ልጅ ኃያሉን እግዚአብሔር የሚያሸንፈው በዕንባው ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚያለቅሱ ዓይኖች ላይ ኣይጨክንም፡፡ በፍጹም ጸጸት የምታለቅስን ነፍስ አይቶ እግዚአብሔር “አውከውኛልና ዓይኖችሽን ከእኔ መልሺ" ይላል።(መኃ ፮፥፭) ስለዚህ እንዲህ ዓይነቱን ዕንባ ለማፍሰስ በጌታችን ዓይን መታየት ይፈልጋል።
ጴጥሮስ“ በዕንባ ውኃ ክህደቱን አጠበው" (ወሐጸቦ ለክህደቱ በማየ አንብዑ) ይህንን ዕንባ እንዲሰጠን በአባቶቻችን እና በእናቶቻችን ዕባ በራሰው የቤተ ክርስቲያን ቅጽር እንዲህ ኢያልን በዘወትር ጸሎት ተሰብስበን ወደ ጴጥሮስ አምላክ ላይ እንጮኻለን፦
« አቤቱ በደሌንና ነውሬን የሚያጥብ ዕንባ ስጠኝ፤
አቤቱ አንተን የሚያገለግል ዕንባን ሥጠኝ
አቤቱ የሚያቃጥል ዕንባን ሥጠኝ፤
አቤቱ ከዓይኔ ፈስሶ የአካሌን እድፍ የሚያጥብልኝ ዕንባ ሥጠኝ፤
የተጸጸቱ ሰዎችን ዕንባ የምትቀበል ጌታ ሆይ አንተ የተቀበልከውን ጽኑ ለቅሶ እንዳለቀሰ እንደ ጴጥሮስ ያለ ዕንባን ሥጠኝ፤
አቤቱ እንደ ባሕርም በምትፈስስ ዕንባ እጠበኝ፤
የማያቋርጥ የዕንባን ጎርፍ አፍስስልኝ።»(ውዳሴ አምላክ ዘእሑድ)
[ ሕማማት - በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ]
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
የ፳፻፲፰ ዓ.ም የጥቅምት ፳፫(የዐራተኛው ሰንበት) የጽጌ ማኅሌት
ዘራብዓይ ሳምንት
ለገባሬ ኵሉ
ዚቅ
፩ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
፪ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
፫ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
ዓዲ ዚቅ
፬ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
ሰቆቃወ ድንግል
ወረብ
ዚቅ
መዝሙር በ፭
«ድንግል ሆይ አንቺን ያሳደደሽ ሄሮድስ እኔን የማያሳድደኝ ጌታ በእቅፌ ስለሌለ ነው። እኔ በልቤ ያነገሥሁት 'የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ' ስላልሆነ ሄሮድስ ከእኔ ጋር ጠብ የለውም ። የሄሮድስን ስልጣን አደጋ ላይ የሚጥል ንጉሠ ሰላም በእኔ እቅፍ የለም። አሁን ግን ፍቀጂልኝና ሄሮድስን ማስደሰት ትቼ ልጅሽን በልቤ ልቀበለው ።የልቤን ክርስቶስ ሄሮድስ እንዳይገድልብኝ እኔም እንዳንቺ ልሰደድ።እርሱን አቅፌ መከራን ቢደርስብኝ እንኳን ጽናት እንደማገኝ በአንቺ አይቻለሁ እና የልጅሽን ፍቅር በልቤ አኑሪልኝ። ለሦስት ቀናት ከፊትሽ ዘወር ቢል ፍለጋ የወጣሽዋ ድንግል ሆይ ከእኔ ሕይወት ልጅሽ ከተሠወረ ቆይቶአልና ያለ እርሱ መሰንበት የማልችል የፍቅሩ ምርኮኛ አድርጊኝ ።»
[የብርሃን እናት-በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ]
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"አቡነ አረጋዊ"
ጽድቅህ ጠርቶናል አባትነትህ
በቅድስና ያማረ ሕይወትህ
ጌጥ ውበታችን አባ አረጋዊ
መናኝ መነኩሴ መልአክ ምድራዊ (፪)
ተቃኝተህ ስላደግክ በመንፈስ ቅዱስ
ወደ ፅርዕ ተጓዝክ ወደ አባ ጳኩሚስ
ተዘጋጅተህ ነበር ለችግር ፈተና
ዘሚካኤል አለህ ሰጥቶህ ምንኩስና (፪)
አዝ---
ለኢትዮጵያ ምእመናን አባት ተብለሃል
ወንጌል በማስተማር ብዙ አትርፈሃል
መጻሕፍት ተርጉመህ ያበረከትክ ለአበው
የአንተስ ትሩፋት እፁብ ነው ድንቅ ነው (፪)
አዝ---
የዓለም ጨው ሆነህ አጣፈጥካት ምድርን
በልባችን ሳልካት ቤተ ክርስቲያንን
ደብረ ሀሌ ሉያ ደብረ ዳሞ ቅድስት
የፈውስ ቦታ ናት መካነ ትኅርምት (፪)
አዝ---
ልክ እንደ አባቶችህ አስተዋይ ስለሆንክ
ገና ወጣት ሳለህ አረጋዊ ተባልክ
የሥጋን ሞት ሳታይ ተሰውረህ ከምድር
ብሔረ ሕያዋን ተቀላቀልክ በክብር (፪)
አዝ---
በቦሌ ደብረ ገነት ቅ/ጊዮርጊስ እና ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox