በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
ሰማዕታት
በገርጂ ጊዮርጊስ የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሦሰት ሲሆኑ እነዚህም ጣሊያኖችና የጦር ሹማምንቶች ናቸው፤ መካከለኛው ዳኛ ኮሎኔል ነበር፡፡ የቀረበባቸውም ወንጀል ‹ሕዝብ ቀስቅሰዋል፤ ራስዎም አምፀዋል፣ ሌሎችንም እንዲያምፁ አድርገዋል› የሚል ነበር፡፡ ዳኛውም ‹ካህናቱም ሆኑ የቤተ ክህነት ባለሥልጣኖች ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የጣሊያንን መንግሥት ገዥነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ እርስዎ ለምን አመፁ? ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ?› ሲል ጠየቃቸው፡፡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስም በቆራጥነት የሚከተለውን መለሱ፡- ‹‹አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵየዊ ነኝ፡፡ ሓላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፡፡ ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ፡፡ እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼን አትንኩ» አሉ፡፡ ‹‹ይህንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲመለከት ተጋብዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልእክት አስተላለፉ፡- ‹አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው፤ እንጂ በጎ ለመሥራት ስላልመጣ ለዚህ ለግፈኛ አትገዙ፡፡ ስለ ውድ ሀገራችሁ፣ ስለ ቀናች ሃይማኖታችሁ ተከላከሉ፡፡ ነጻነታችሁ ከሚረክስ ሙታችሁ ስማችሁ ቢቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ለጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ፤ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን፡፡ በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን› ብለው አወገዙ፡፡ ቀጥሎም ብፁዕነታቸው በፍጥነት ችሎት ላይ እንዳሉ ሕዝቡ ሁሉ ስለ እርሳቸው እያዘነ ሳለ መስቀላቸውን አውጥተው እየጸለዩ ሕዝቡን ባረኩ፡፡ ወዲያው የሞታቸው ፍርድ ሲሰማ ሕዝቡ በኢጣሊያ የእጅ ሰላምታ ዓይነት እጁን እንዲያነሳ ታዘዘ፡፡ በዚያን ጊዜ አቡነ ጴጥሮስ የሞታቸው ሰዓት መድረሱን ዐውቀው ሰዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ፡፡ በዚህን ጊዜ ምንም ፍርሃት አይታይባቸውም ነበር፡፡ የሞታቸውን ፍርድ ያነብ የነበረው ኢጣሊያዊው ዳኛ ግን ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ ታላቅ ፍርሃም በፊቱ ላይ ይታይ ነበር፡፡ የሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች ጸልየው በመስቀላቸው ባረኳቸው፡፡
የሀገራቸው በጠላት መወረር፣ የሕዝባቸው መገደልና መታሰር፣ የቤተክርስቲያናቸው መደፈር እስከ ሞት ያደረሳቸው እኒያ እውነተኛ ጳጳስ እንዲገደሉ ሲወሰዱ ጥይት አልፎ ሌላ ሰው እንዳይመታ ግንብ ይፈለግ ጀመር፡፡ ሩቅ ባለመሄድ ከመካነ ፍትሑ ዐሥር ሜትር ርቆ ግንብ ያለው መግደያ ቦታ ተገኘና ወደዚያ ተወሰዱ፡፡ ከገዳዮቹም አንዱ ‹ፊትዎን ለመሸፈን ይፈልጋሉን?› ሲል ጠየቃቸው፡፡ ‹ይህ ያንተ ሥራ ነው› ሲሉ ብፁዕነታቸው መለሱ፡፡
ከመግደያውም ቦታ እንደደረሱ ወንበር ቀረበላቸውና ፊታቸውን ወደ ግንቡ ጀርባቸውን ወደ ሕዝቡ አድርገው እንዲቀመጡ ሆኑ፡፡ ከዚያም በኋላ ስምንት ወታደሮች በስተ ጀመርባቸው ሃያ እርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተጠንቀቅ ቆሙ፣ ወዲያው አዛዡ ‹ተኩስ!› በማለት ትእዛዝ ሲሰጥ ስምንቱም ተኩሰው መቱዋቸው፡፡ ግን በስምንት ጥይት ሳይሞቱ ቀሩ፡፡ መሞታቸውንና አለመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ፡፡ ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ፡፡ ከዚያም በኋላ አንድ ወታደር በሦስት የሽጉጥ ጥይት ራስ ቅላቸውን መትቶ ገደላቸው፡፡ ብፁዕነታቸው የተገደሉበት ቦታ መሐል አዲስ አበባ ላይ ዛሬ መታሰቢያ ሐውልታቸው ቆሞ በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው›› በማለት የጋዜጣ ወኪልና የምሥራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛው ፖጃሌ ስለ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ ‹‹አቡነ ጴጥሮስ እንዴት ሞቱ?›› ሲል በወቅቱ አባታችን ሰማዕትነትን ሲቀበሉ በቦታው ላይ በአካል በመገኘት ሁኔታውን ይከታተሉ የነበሩትን ሙሴ ፓይላክን ጠይቋቸው እርሳቸውውም የሚከተለውን ተናረዋል፡- ‹‹አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ፡፡ መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት፡፡ ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት፡፡ ወዲያው ወታደሮቸ በሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው፡፡
ይህ እንደሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ፡፡ ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት ‹በዚህ ቄስ መገደልኮ ሕዝቡ ተደስቷል› አለኝ፡፡ ‹እንዴት?› ብለው ‹አላየህም ሲያጨበጭብ?› አለኝ፡፡ ‹ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል› አልኩት፡፡ ‹እንዴት?› ቢለኝ እጄን አጨብጭቤ አሳየሁት፡፡ ‹ከዚህ በኋላ የሆነው ቢሆን እኔ ትልቅ ማስታወሻ አግኝቻለሁ› ብሎ አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ ይዘውት የነበረውን መስቀልና መጽሐፍ ቅዱስ የኪስ ሰዓታቸውንም ጭምር አሳየኝ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ መሐል ለመሐል በጥይት ተበስቷል፡፡ መስቀሉም ልክ በመሐሉ ላይ ጥይት በስቶት ወጥቷል፡፡ የኪስ ሰዓታቸውንም እንዳየሁት እንዲሁ ጥይት በስቶታል›› ብለው በወቅቱ የተመለከቱትን መስክረዋል፡፡
ብፁዕ አባታችን በአደባባይ በሕዝብ ፊት የሰማዕትነት ጽዋቸውን ሲቀበሉ ከሕዝቡ ጋር ሆና ትመለከት የነበረች አንዲት ከድጃ የምትባል እስላም ሴት ማንም ሰው ያላየውን ታላቅ ነገር እርሷ ተመልክታለች፤ ይኸውም አባታችን ሰማዕትነትን ሲቀበሉ የብርሃን አክሊል በራሳቸው ላይ ሲቀዳጁ ተመልክታ በዚያው እርሷም ‹‹የእኚህን አባት ሃይማኖት እከተላለሁ›› ብላ በመጠመቅ ክርስቲያን ሆናለች፡፡ የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል በሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም ሰማዕቱን አቡነ ጴጥሮስን ገድሎ አስክሬናቸው አደባባይ ላይ ጥሎ ከዋለ በኋላ ቀብራቸው በምሥጢር መፈጸሙን አንዳንዶች ይናገራሉ፡፡ የእኚህን ታላቅ አባት ቀብር በምሥጢር የተፈጸመበት ቦታ ለማግኘት የተለያዩ ምሁራን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ የታሪክ ሰነዶችን ሲመረምሩ ቢቆዩም ‹‹ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በምሥጢር ቀበሯቸው›› ከሚል ከመላምት ያለፈ ነገር ምንም ዓይነት የተረጋገጠ ማስረጃ ሳይገኝ ቀርቷል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከአዲስ አበባ ከተማ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ‹‹ፉሪ ለቡ›› ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሰፈሩ ምዕመናን በአካባቢው ተወልደው ካደጉ አረጋውያን ጋር ባደረጉት ማኅበራዊ ግንኙነት ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፋሽስቶች በመኖርያነትና በእስር ቤትነት ይጠቀሙበት በነበረው ‹‹ሙኒሳ ጉብታ›› ላይ መቀበራቸውን ከወላጆቻቸው ሲሰሙ እንዳደጉ እየተነገረ ይገኛል፡፡ እንዲሁም የአቡነ ጴጥሮስን ሥጋ በተመለከተ ማንም እንዳይወስደው በአስቸኳይ ከአ.አ ውጭ ማንም በማያውቀው ቦታ በምሥጢር እንዲቀበር መደረጉ በትንሣኤ መጽሔት ቁ.58 1978 ዓ.ም ላይ የተገለጠ ቢሆንም ነገር ግን አንዳንድ የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች ቅዱሳን መላእክት የጻድቃንን በድን እያመጡ ወደሚያስቀምጡበትና በውስጡ የሚቀመጥ አስክሬን ወደማይፈርስበት አቡነ መልከ ጼዴቅ ዋሻ ገዳም መላእክት ወስደው እንዳስቀመጡትና በዚያም እንደታየ ይናገራሉ፡፡ ሰሜን ሸዋ ሚዳ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው በአቡነ መልከ ጼዴቅ ዋሻ ውስጥ የቅዳሱኑ አጽም ሳይፈርስና ሳይበሰብስ የአንገት ክራቸው ራሱ ሳይበጠስ እንደዛው እንደነበሩ ስለሚገኝ ቦታውም እጅግ ትልቅ የቃልኪዳን ቦታ ስለሆነ
በርሱ ምክንያትም ታንኳይቱ በምትሳፈርበት ባህር ላይ ማዕበል ታዘዘ በታንኳይቱም ውስጥ ያሉ ሁሉ ሊሰጥሙ ስለሆነ ተጨነቁ ዮናስ ግን በታንኳይቱ ውስጠኛ ከፍል ተኝቶ ነበር በቀሰቀሱት ጊዜ ንፋሱን ወጀቡንና ማዕበሉን ተመለከተ ከርሱ አመጽና ኃጢአት የተነሳ የሆነ መሆኑን ነግሮአቸው ወደ ባህሩ አውጥተው እንዲጥሉት ጠየቃቸው ሰዎቹ ግን ንጹሕ ደም በእጃችን እንዳይሆን ብለው ዕጣ ጣሉ በሚገርም ሁኔታ ዕጣው በዮናስ ላይ ወጣ በዚህ ምክንያት ከታንኳይቱ አውጥተው ወደ ባህሩ ጣሉት፡፡ ማዕበሉም ፀጥ አለ ዮናስንም የታዘዘ አሣንባሪ ዋጠው ሰዎቹም በደኅና ሄዱ ዮናስ ግን በአሣአንባሪ ሆድ ውስጥ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአቱን ይናዘዝ ነበር ቀጥለን እንመልከተው፡፡
"በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ
እርሱም ሰማኝ በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኸሁ
ቃሌንም አዳመጥU
ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ ፈሳሾችም በዙሪያዬ ነበሩ ማዕበልህና ሞግድህ ሁሉ በላዬ አለፉ
እኔም ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁ አልሁ
ውኆችም እስከ ነፍሴ ድረስ ከበቡኝ ጥልቁ ባሕር በዙሪያዬ ነበረ የባሕሩ ሣር በራሴ ተጠምጥሞ ነበር
ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ
በምድርና በመወርወሪያቸው ለዘላለም ተዘጋሁ
አንተ ግን አቤቱ አምላኬ ሕይወቴን ከጉድጓድ አወጣህ
ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብኩት
ጸሎቴ ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስ ገባች
ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምህረታቸውን ትተዋል
እኔ ግን በምስጋና ቃል እሠዋልሃለሁ የተሳልሁትንም እከፍላለሁ፡፡
ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው”
ዮና2÷3-11
ዮናስ ይህን ጸሎት በኑዛዜ ያቀረበው ያለበት ሁኔታ ከኃጢአት የተነሣ የመጣበት መሆኑን በማመን ወደ እግዚአብሔር በመመለስ በሕይወት እንዲያድነው በጸሎትና በስዕለት በመማለድ ነው፡፡
ይህን የኑዛዜ ጸሎት እንዲያደርግ ያበቃው ደግሞ በደሉን ማመኑ ነው፡፡በመርከቢቱ ውስጥ ሳለ በዙሪያው ባሉት ፊት ቆሞ በደሉን በማመን ሲናዘዝ “... ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንዳገኛችሁ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል አላቸው” /ዮናስ 1÷12/
ኑዛዜ የኃጢእትን ማዕበል ጸጥ ያደርጋል
በሰው ሕይወት ውስጥ ከሚነሱ ሁከቶች አብዛኞቹ በኃጢአት የሚመጡ ናቸው ሰይጣንም ኃጢአታችንን መሣሪያ አድርጎ ሰላማችንን ሲያሳጣን በሁከት ሊመታን ይችላል፡፡
ነቢዩ ዮናስ በሕይወቱ የሚያሰረዳን ይህንን ነው፡፡ “ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንዳገኛችሁ አወቃለሁ” ይላል፡፡ ብዙዎቻችን በሕይወታችን በኑሮአችን የተነሳብን ታላቅ ማዕበል የሚያተረማምሰን ማዕበል፣ እንቅልፍ የነሳን ማዕበል፣ ጭንቀት ውስጥ የዘፈቀን ማዕበል፣ ከምን የተነሣ እንደሆነ ማስተዋል ስለተሣነንና መመርመርም ስለማንፈልግ የሰማኒያ ቀን ዕድላችን አድርገን በመቀበል ማዕበሉ እንዳላጋን እንኖራለን ሕይወታችንም መራርነትን ተሞልቶ መኖራችንን እንደረገምን እያንዳንዱ ቀን ያልፋል፡፡
ነቢዩ ዮናስ በእርሱ ምከንያት በባህሩ ላይ ማዕበል ተነስቶ የውስጥ ሰላም በማጣት ለተጨነቁት ሰዎች ኃጢአቱ የእኔ ነው ብሎ ተናዞ “...አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል..” በማለት በኑዛዜውና ለሰራው በደል ቅጣት በመቀበል ማዕበሉ በጸጥታ እንዲተካ አድርጎአል፡፡
ቀጣይ ምዕራፍ አንድ ክፍል ዐራት :
👉 "የቀራጩ ሰው የዘኬዎስ ኑዛዜ" በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
እንዴት እና ምን ብዬ ልናዘዝ?
ምዕራፍ ፩ ክፍል ፫
.........................................
1.2 ኑዛዜ በመጽሐፍ ቅዱስ
በዚህ ክፍል ኑዛዜን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለማየት የምንሞክር ሲሆን ስለ ንስሐ የተጠቀሱ ጥቅሶችን በመጥቀስ የምንመለከትበት ከፍል ብቻ ሳይሆን በቀጥታ በኃጢአታቸው የተናዘዙ የተለያዩ የእግዚአብሔርን ሰዎች ሕይወት የምንዳሰስበትና ቃል በቃል አስፈላጊ ነው የምንለውን በኑዛዜ ላይ የተመሰረተውን ጸሎታቸውን ሙሉ ለሙሉ በዝርዝር እንዳለ በማስቀመጥ አንባቢዎች በጸሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምሪት የምንሰጥበት ክፍል ጭምር ይሆናል፡፡
ኑዛዜ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ሰፊውን ቦታ ይዞ እናገኘዋለን፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ኑዛዜ የጸሎትን ዋና ክፍል ይዞ ስለሚገኝ ጭምር ነው ተያይዞም ከላይ እንደተመለከትነው የኑዛዜ ጠቀሜታው መሠረታዊ ስለሆነም ነው፡፡
ሀ. የቅዱስ ዳዊት ኑዛዜ
መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት የእስራኤል ንጉሥ ነው፡፡ ለእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን ምርጫው ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሕዝብ የደረሰው ወይም እርሱ በፍላጎቱ ያገኘው አልነበረም፡፡
ነገር ግን ይህ ንጉሥ በሕይወት ዘመኑ በኃጢአት የተፈተነበት በተለያዩ ኃጢአቶች የተያዘበት ጊዜ ነበር። የጎልማሳ ሚስት ለራሱ አድርጓል ባሏንም አስገድሏል ንጹሕ ደም በማፍሰሱና ያከበረውን እግዚአብሔርን መበደሉ በነቢዩ ናታን ተነግሮት ከተገለጸ በኋላ ግን ስለ ልዩ ልዩ ኃጢአቶቹ በእግዚአብሔር ፊት እየተናዘዘ ንስሐ ገብቷል ከዚህ ቀጥሎ በዚህ ርዕስ ተስማሚ የሆነውን የኑዛዜ ጸሎቱን እንጠቅሳለን ይህ ደግሞ የዳዊት ኑዛዜ የሚለውን ርዕስ ያስረዳልናል፡፡
ሀ. ኑዛዜ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ስለመሆኑ
"ኢየሱስም... ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔር መንግስት ቀርባለች ንስሐ ግቡ…” /ማር1÷15/
“…በኃጢአታችሁ ብትናዘዙ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመጽም ሁሉ ሊያነጻን የታመነ ጻድቅ ነው።"/1ዮሐ 1÷8-9/
ሰው የሰራውን እና የኖረበትን ኃጢአት እንዲናዘዝና ንስሐ እንዲገባ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ፈቃዱ ብቻ ሳይሆን ትዕዛዙም ነው፡፡ ጌታችን በሐዲስ ኪዳን የትምህርቱ መጀመሪያ አድርጎታል፡፡ ዮሐንስም በመልከቱ እንዳስታወሰን በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመጽም ሁሉ ሊያነጻን የታመነ ጻድቅ /እውነተኛ/ ነው ያለን በኃጢአታችን መናዘዛችን ፈቃዱና ትዕዛዙ ስለሆነ ነው ይቅር ሊለንና ሊያነጻን የታመነ የሆነው፡፡
በዚህም መሠረት በእርሱ ፊት ስለሰራነው ኃጢአት በፍፁም ጸጸት ብንናዘዝ እርሱ ይቀበለናል፡፡ ቅዱስ ዳዊት በኃጢአት በተያዘበት ወቅት ኑዛዜን በሚወድ በእግዚአብሔር ፊት “አንተን ብቻ በደልኩ” በማለት ከበደሉ እንዲያነፃው በአምላኩ ፊት እየተናዘዘ ንስሐ መግባቱ ታላቅ ምሳሌ ነው፡፡
ለ. ስለ ኑዛዜ አስፈላጊነት
ኑዛዜ ለእግዚአብሔር የንስሐ ጥሪ መልስ የምንሰጥበት መንገድ ነው።ኑዛዜ ወደ ንስሐ ሕይወት የምንገባበት በር ስለሆነ በሰው ሕይወት ውስጥ አስፈላጊ ነው፡፡
እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሳ ሰው በኃጢአት እንዳይሞት የንስሐ ጥሪ ያደርግለታል፡፡ ነቢዩ “…..ስለምን ትሞታላችሁ? የሟቹን ሞት አልፈቅድምና ይላል ጌታ እግዚአብሔር ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ፡፡” /ሕዝ 18÷30-32/ ብሎ እንደመሠከረ፡፡
ስለዚህ በኃጢአት የዘላለም ሞት ካለ ከዚህ ሞት ለመዳን በንስሐ መመለስና ውጤቱ ሞት የሆነውን ኃጢአት በመናዘዝ ወደ ሕይወት መቀየር ስለሚቻል ኑዛዜ አስፈላጊያችን ነው።
በኑዛዜ ስለሚገኘውም የእግዚአብሔር ምላሽ ነቢዩ ኢሳይያስ ሲያስታውስ እንዲህ ብሎ ጽፏል፡፡ “ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ ክፉ ማድረጋችሁን ተዉ መልካም መሥራትን ተማሩ... ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጣለች እንደ ደምም ብትቀላ እንደባዘቶ ትጠራለች" / እ.ሳ 1÷16-18/ ይህን የነቢዩን ቃል በጥልቅ ስንመለከት ኑዛዜ ከተግባራዊ ምላሽ ጋር አብሮ የሚሄድ እንጂ የኖሩበትንና የሰሩትን ኃጢአት በቃል በመናገር ላይ ብቻ የተመሰረተ አለመሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ “…. ከፉ ማድረጋችሁን ተዉ መልካም መስራትን ተማሩ….” የሚለው ሀረግ ኑዛዜ ከተግባራዊ ምላሽ ጋር የሚሄድ መሆኑን ያረጋገጠበት ኃጢአትን ሳይተዉ መልካም ለመስራት ፍጹም ውሳኔ ሳይዙ ኃጢአትን መናዘዝም ሆነ የንስሐ ሕይወት መኖር አይቻልም፡፡
ሐ. የኑዛዜ ጠቀሜታ
ብዙ ጊዜ ሰዎች ስሕተትን ካደረኩ በኋላ ወይም ኃጢአትን አንዴ ካለፍኩበት በኋላ መናዘዙ ምን ጠቀሜታ አለው? ይላሉ በአስፈላጊነቱ ዙሪያ ከላይ ለማስረዳት እንደተሞከረው ጠቀሜታውንም እንመለከታለን፡፡
“..… የኢየሱስ ከርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነፃናል ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን እውነትም በእኛ ውስጥ የለም በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነ ጻድቅ ነው፡፡” /ዮሐ 1÷7-9/
ሰው የዘላለም ሞት የሚያገኘው ኃጢአት በመስራቱ ብቻ ሳይሆን የሰራውን ኃጢአት ባለመናዘዙና በንስሐ ባለመመለሱም ጭምር ነው፡፡ ቢናዘዝና ንስሐ ቢገባ ግን ኃጢአት ከሚያመጣበት ጥፋት ይድናል፡፡ መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ከርስቶስ “ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ” /ሉቃ 13÷3/ በማለት ብርቱ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ኃጢአቱን የሚናዘዝና ንስሐ የሚገባ ከፍርድና ሞት መዳኑን ያረጋግጣል፡፡
ስለዚህ ኃጢአታችንን መናዘዝና ንስሐ መግባት ከዘለዓለም ድህነት ጋር የተያያዘ ወሳኝ ነገር ስለሆነ ኃጢአትን መናዘዝ አስፈላጊነቱ አሌ የማይባል ስለሆነ ጠቃሚ ነው።
በዚህ መሠረት ኃጢአትን መናዘዝ ለምን ይጠቅማል ብለን ስናነሳ ቀዳሚውና ዋናው መልሳችን ለድህነት ነው ቅዱስ መጽሐፍም “… ለአሕዛብ ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሰጣቸው…” /የሐዋ 11÷18/ በማለት ያረጋግጥልናል፡፡ በኃጢአታችን ካልተናዘዝንና ንስሐ ካልገባን ግን የዘላለም ፍርድ ያገኘናል፡፡ ይህ ደግሞ የኑዛዜን ጠቀሜታ ካለመረዳት ሊከተል ይችላል፡፡
ሌላው የኑዛዜን ጠቀሜታ የተረዳ ሰው በአግባቡ ንስሐ እንዲገባ ይጠቅመዋል፡፡ ኃጢአቱን ሊናዘዝና ንስሐ ሊገባ የሚችለው ከማናቸውም ምስጢራተ ቤተክርስቲያን በፊት ንስሐ ያልገባ ሰው ምስጢራተ ቤተክርሲያን ቢካፈል ሊጠቀም አይችልም ስለዚህ ኃጢአትን መናዘዝ ከሌሎች ምስጢራተ ቤተከርስቲያን በፊት የሚካሄድ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “ንስሐ ግቡ ኃጢአታችሁም ይሠረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ" /የሐዋ2÷38/ በማለት አስተምሯል፡፡
ሐዋርያው ኃጢአታቸሁ ይሠረይ ዘንድ ንስሐ ግቡ ከዚያ በኋላ ደግሞ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ እያመናችሁ ተጠመቁ በማለት በግልጽ ኃጢአትን ከተናዘዙ በኋላ ወደሌሎች ምስጢራተ ቤተክርስቲያን መሸጋገር እንደሚገባ በሚገባ ያስረዳናል፡፡ ስለዚህ ኃጢአትን መናዘዝና ንስሐ መግባት ኃጢአትን በመደምሰስ ለምስጢራተ ቤተክርስቲያንና ለሰማያዊው የዘላለም ሕይወት ያበቃል፡፡ “ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም" /የሐዋ 3÷19/
ቀጣይ ምዕራፍ አንድ ክፍል ሦስት :
👉 "ኑዛዜ በመጽሐፍ ቅዱስ" በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
በሕይወተ ሥጋ ሳለን በተመላለስንበት በኖርንበትና እያደረግን ባለነው የኃጢአት ሥራ ጥልቅ ሀዘን ሲሰማን በመጸጸት የምናደርገው ነገር በደላችንን በዝርዝር መናገርና ቀሪ ዘመናችንን ለእግዚአብሔር በማስረከብ ከኃጢአት እስራት መፈታት ነው፡፡
ስለዚህ መናዘዝ ከኃጢአት ታጥቦ የንስሐ ሕይወት ለመኖርና የንስሐ ፍሬዎች የተባሉትን የመንፈስ ፍሬዎች ለማፍራት በእግዚአብሔር ቤት ተተክሎ ለመኖር መዘጋጀትንና መወሰንን ማረጋገጥ ነው /ማቴ3÷2 - ገላት 5÷17/
በዓለማችን ላይ ከባዱና እስቸጋሪው ነገር ጥፋተኛነትን ማመን በራስ ላይ መስካሪ ሆኖ ራስን በራስ መክሰስና መውቀስ ሲሆን ይህ በከርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ግን በመናዘዝ ሲፈፀም እናገኘዋለን፡፡ ይህ ደግሞ የሃይማኖት ሰውነትን ታላቅነትን የሚያሳይና የሚያረጋግጥ ነው፡፡
መናዘዝ እንዴት ይጀመራል? ደረጃዎቹስ ብንል ኑዛዜ የሚጀመረው ራስን በውስጣዊ ልቦና በመውቀስ በመኮነን ሲሆን በኋላም በደረጃው በእግዚአብሔር ፊትና ባገልጋዩ ካህን ፊት ለመውቀስና በራስ ለመፍረድ መቻል ነው፡፡
ይህ ሂደት ደግሞ ንስሐችንን ጥልቅ ከልብ የመነጨ ያለፈውን ሕይወት በፍጹም በመጥላት ላይ የተመሰረተ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ተነሳሒው ኑዛዜው ፍጹም ጸሎት ነውና የሚያውቀውን በደሉን አንዳች ሳይቀር በፍጹም ጥላቻ እየዘረዘረ በመናገር ንስሐ እንዲገባ ያደርገዋል፡፡
"...በአንተ ላይም ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኃጢአት እናዘዝልሃለሁ እኔና የአባቴም ቤት በድለናል፡፡ እኛም በአንተ ላይ እጅግ ክፉ ሠርተናል"እንዳለ ነህምያ /ነህ1÷6-7/
ሰው በኃጢአቱ እንዲናዘዝና በእግዚአብሔር እጆች ላይ እራሱን እንዲጥል የሚያደርጉትን ሁኔታዎች ጥቂቶቹን ስናነሳ:-
+እግዚአብሔር የፈጠረው ለክብሩ መሆኑ
+ ኃጢአት የማይስማማው ሆኖ መፈጠሩ
+ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ማደሪያ መሆኑ
+የሚሰራው ኃጢአት የሚያስከትልበት ውጤት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡
እግዚአብሔር የፈጠረው ለክብሩ መሆኑ
የሰው ተፈጥሮ ንጹህ ነው
እግዚአብሔርም በአምሳሉ ፈጥሮታል፡፡ ቅዱስ ዳዊት “ግሩምና ድንቅ አድርገህ ፈጥረኸኛልና አመሰግንሀለሁ" እንዳለው፡፡ እግዚአብሔር የፍቅሩ ማሳያ የክብሩ መግለጫ አድርጎ በዕለተ ዐርብ የፈጠረው እንደ ልምጭ መልምሎ እንደ እሸት ፈልፍሎ በጣቶቹ የሰራው ልዩ ፍጥረት ሰው ነው፡፡ በአዳም ምክንያት ይህ ክብር ከሰው ልጅ ቢለይና ሰው ከእግዚአብሔር ተጣልቶ ባሕርዩ ጎስቁሎ ቢኖር ከሰማያት ወርዶ በመስቀል ላይ ተሠውቶ በደሙ መፍሰስ ተቤዠቶታል፡፡ ስለዚህ “ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው አሮጌው ነገር አልፏል እነሆ ሁሉ አዲስ ሆኖአል፡፡" /2ቆሮ 5÷17/ ተብሎ ተጻፈ፡፡
ኃጢአት የእግዚአብሔር ከሰው መለየት የሰው ደግሞ ዘላለማዊውን ክብር ማጣት ምክንያት ስለሆነ ሰው ይህን በተረዳ ልክ ኃጢአቱን ሊናዘዝ በውስጡ ተነሳሽነት ይፈጠራል ይህንንም የንስሐ ጥሪ ልንለው እንችላለን፡፡
ኃጢአት የማይስማማው ሆኖ በመፈጠሩ
ሰው ኃጢአቱን ለእግዚአብሔር እንዲናዘዝ የሚገደደው በእግዚአብሔር አምሳል በመፈጠሩ ነው፡፡ በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጠረ ስንል በውስጡ ያለችውን ህያዊት ነባቢትና ልባዊት ነፍሱን ይመለከታል፡፡
ይህቺ ነፍስ በተፈጥሮዋ ንጽሕትና በባሕርይዋ ኃጢአት የማይስማማት ስለሆነች ሰው ሲበድልና በኃጢአት ባርነት ሲያዝ ሰላሟን ታጣለች፡፡ ሌላው ነፍስ በባሕርይዋ አዋቂ ስለሆነች ፈጽሞ በደሏን አትረሳም በሥጋዊ ባሕርይ በጊዜያዊ እርካታ የተሰወረ የተረሳ ኃጢአት እርስዋን ግን የእግዚአብሔር ሰላም ይነሳታል ስለዚህ ለእረፍቷ ፍጹም ንስሐና ልባዊ ኑዛዜ ትፈልጋለች፡፡
ይህን በመሰለው አጠቃላይ ገጽታ ሰውን ስንመለከተው በጥንቱ ተፈጥሮው ኃጢአት የማይስማማው ሆኖ በእግዚአብሔር እጆች ተበጅቷል በቅዱስ እስትንፋሱ ንጽሕት ቅድስት ህያዊት ነፍስ ተሰጥቶታል፡፡ /ዘፍ 2÷7/
የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ማደሪያ መሆኑ
“የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና ያውም እናንተ ናችሁ፡፡"/1ቆሮ 3÷16/
በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እና የእግዚአብሔረ ቃል በጥልቀት እንደተገለፀው እኛ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ማደሪያ ቤተ መቅደሱ እንደሆንን ተገልጿል፡፡ ይህ ደግሞ ኃጢአት እንዳንሰራ ይከለክለናል፡፡ በኃጢአት ብንሆን ደግሞ ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር እንድንናዘዝ ያስገድደናል፡፡ በበደል የተለየን ቅዱስ መንፈስ ወደኛ ሊመለስና የፈረሰው ቤተመቅደስ ሰውነታችን ሊታደስ የሚችለው ወደ ንስሐ ስንመለስና ኃጢአታችንን ስንናዘዝ ብቻ መሆኑን ያስገነዝበናል።
ስለዚህ ኑዛዜ ልብን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር ማቅረብና እንደገና ለመሰራት መወሰን ነው፡፡ ለዚህ ነው "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ" የሚል ጥሪ የቀረበልን /ምሳ 23÷26/ ስለዚህ ኃጢአታችንን በመናዘዝ ለእግዚአብሔር እንድንለይ ግድ ከሚሉን ምክንያቶች አንዱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤተ መቅደሱ መሆናችን ነው፡፡
ቀጣይ ምዕራፍ አንድ አንድ ክፍል ኹለት:
👉 "የምንሰራው ኃጢአት የሚያስከትለው ውጤት" በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሰውም ይህን ፍቅሩን የሚቀበልበትና ለዚህ ፍቅር የሚገዛበት መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን አንድነት ጠብቆ መኖር ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በጠላት የተከናወነው ጥቃት በዚህ አንፃር የተቀናበረ ስለነበር ሰው ከእግዚአብሔር ፍቅር እንዲወጣ ትዕዛዙን እንዲያፈርስ ከአምላኩ አንድነት እንዲለይ ተደረገ "ብትወዱኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ" /ዮሐ 14÷15 / ማለት ሰው በጠላት ምክር ተነዳ ከእግዚአብሔር ፍቅር ወጥቶ ሕጉን በመተላለፍ ከእግዚአብሔር አንድነት ተለይቶ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ በመቃብር መውርድ ሲኦል መውረድ አገኘው ባሕርይው አደፈ ሥነ ተፈጥሮው ጎሰቆለ በጠላት መዳፍ ላይ ለዘላለም በባርነት ወደቀ፡፡
እግዚአብሔር ግን ከኔ ካልጎደለ በገዛ እጁ ባመጣው ሳይል ሰውን ከፈጠረበት ጽኑ ፍቅሩ ተነስቶ የሰውን ልጅ ሊፈልገው ወደደ፡፡ እግዚአብሔር ቃል ሰው ሆነ ጸጋና እውነትን ተሞልቶ በእኛ አደረ ይህ ማለት እግዚአብሔር ሰውን አልተወውም ሊፈልገው መጣ ይህ ፍቅር ደግሞ ልዩ ነው ስለሆነም እግዚአብሔር ሰውን ከፈጠረበት ሰውን ያዳነበት ምስጢር ይበልጣል ይደንቃል ተባለ ይህ ፍቅር ከሰማይ እንዲወርድ አድርጎታል፣ ይህ ፍቅር ሰው እንዲሆን አድርጎታል፣ ይህ ፍቅር በአደባባይ እንዲከሰስ ያለበደሉ እንዲገረፍ ያለ ኃጢአቱ እንዲሰቀል ስለ ሰው እንዲሞት አድርጎታል፡፡ በዚህ ቤዛነቱ ሞታችንን በሞቱ ሽሮ በመነሳት ለእኛ ሕይወትና ትንሳኤ ሆኖናል፡፡
ከዚህ በኋላ ለሰው ልጅ በክርስቶስ ከሆነው ብዙ ጸጋ አንዱ ደግሞ ከበደል እንደገና መመለስ ከኃጢአት በመናዘዝ መንጻት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰው ከበደሉ በንስሐ ወደርሱ እንዲመለስ እድል መስጠቱ ንስሐ እግዚአብሔር በሰው ልጅ ላይ ያለውን የማያባራ ፍቅር ማረጋገጫ ሆኖ የተሰጠ ጸጋ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ እስከ ዓለም ማለፍ ቤተክርስቲያን መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለች እግዚአብሔር ለእርሷና ለአማኞች የሰጠውን ጸጋ ስታውጅ ትኖራለች፡፡
፨መግቢያ
በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአእምሮ ሕሙማን ሲኖሩ እነዚህን ሕሙማን ለማከምና ለማዳን የሚሰሩ ባለሙያዎች የሥነ አእምሮ ባለሙያዎች ይባላሉ፡፡ እነዚህ ባለሙያዎች ቁጥራቸው ጥቂት አይደለም በየዕለቱም ብዙ የአእምሮ እረፍትና ሰላም የሌላቸው ሰዎች ችግሮቻቸውን ሲናዘዙላቸውና እነርሱም በአጠፌታው ምክራቸውን ሲለግሷቸው ይውላሉ፡፡
አስገራሚው ነገር እነዚህ የሥነ አእምሮ ባለሙያዎች ባልተነሱበት ጊዜ ከአስራ ስምንተኛው ከፍለ ዘመን አስቀድሞ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ይህን መንገድ ስትሰራበት አማኞቿን ስታገለግልበት ቆይታለች፡፡
ለመሆኑ ሰዎች በውስጣቸው አንድ ነገር አፍነው ሲይዙና አፍነው በያዙት ሰላም የሚነሳ ጉዳይ ሲጎዱ ሁለንተናቸው እንዴት ይዘበራረቃል? የሚለውን ስንመለከት በሥጋ በነፍስ የኑዛዜ አስፈላጊነትን በሚገባ እንገነዘባለን፡፡
ኑዛዜ በቃል ብቻ የሚነገር እና ጥቅሙን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ሂደቱን የአፈፃፀም ደረጃውን መገንዘብ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ኑዛዜ ቀጣዩን አኗኗራችንን የመቀየር ቁርጠኝነትን የምናረጋግጥበት የትላንቱን ያደፈ ሕይወት ያስጠላን ቀሪ ሕይወታችንን ለአምላካችን አስረከቦ ለመኖር የሚያስችል ሰላማዊ ሕይወትን የሚያጎናጽፍ መንፈሳዊ ኃይል ነው፡፡
ይህ ደግሞ በትክክለኛ ጸጸት ያለፍንበትንና ያለንበትን ስህተት ከማመን ኃጢአትን በኃጢአትነቱ ተመልከቶ ከመጥላት የሚገኝ ነው፡፡ ስለዚህ ኑዛዜ የነፍስና ሥጋ ድህነት ዋስትና ሲሆን በቀጣዩ ዘላለማዊ ሕይወታችን ላይ ወሳኝ ስለሆነ ቀጠሮ የማይሰጠውና በሕይወተ ሥጋ ሳለን ሳናመነታ ልንፈጽመው የሚገባ የቀሪ ሕይወታችን እረፍትና ሰላም መጎናፀፊያ መንገድ ነው፡፡
“ወደ እኔ ኑ" /ማቴ 11÷28/ ሲል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊታችን ወዳቀረበው የዘላላም ተስፋና ሕይወት ከሚያደርሱን መንገዶች በአንዱና በዋነኛው የሕይወት መንገድ ከርሱ ጋር መመላለስ እንችላለን ማለት ነው፡፡ ይህን መረዳታችን ደግሞ ለኑዛዜ እንድንቀርብ የሚያበረታን ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የንስሐ ሕይወታችንንም ጽኑ ያደርግልናል፡፡
ቀጣይ ምዕራፍ አንድ ክፍል አንድ :
👉 "የኑዛዜ ምንነት" በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
“ኃይሌ ብርታቴ”
በዘማሪ ታዴዎስ ግርማ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሐምሌ ፯
ቅድስት ሥላሴ
ሐምሌ ሰባት በዚህች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡
አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡
ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡
እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሐምሌ ፭
ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ
1. ትውልዳቸው
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ፡-በገሊላ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው በቤተሳይዳ ተወለደ፡፡ የአባቱ ስም ዮና የእናቱ ስም ሃውኒን ይባላል፡፡ ከ 5 ዓመቱ ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ነው የመጀመሪያው ስሙ ስምዖን ሲሆን ይህንንም እናቱ በነገዷ ስም እንዳወጣችለት ይነገራል፡፡ ጴርቴዋ የምትባል ሚስት ነበረችው፡፡ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር ዓሣ በማጥመድ ይተዳደር ነበር፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፡- ከብንያም ነገድ ነው፡፡ አባቱ ዮስአል ሲሆን የተወለደውም ጌታ በተወለደ በ5 ዓመት በጠርሴስ ከተማ ነው፡፡ ጠርሴስ በንግድዋ የታወቀች የኬልቅያ ዋና ከተማ ናት፡፡ ሮማውያን በሥራቸው ለሚተዳደሩት ሕዝቦች ሮማዊ ዜግነት ይሰጡ ስለነበር የቅዱስ ጳውሎስ አባት በዜግነት ሮማዊ ነበር፡፡ ይህም ለቅዱስ ጳውሎስ ተላልፎለታል፡፡ ቀዳሚ ስሙ ሳውል ሲሆን ትርጓሜውም ጸጋ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በ15 ዓመት ዕድሜው ወደ ትውልድ ሐገሩ በመመለስ በኢየሩሳሌም ከታላቅ እኅቱ ቤት ተቀምጦ ከመምህር ገማልያል ሕገ ኦሪትን መጻሕፍተ ነቢያትን ሲማር አድጓል፡፡ በ3ዐ ዓመቱም የአይሁድን ሸንጐ አባል ሆኖ ተቆጠረ፡፡ ሐዋ22÷3
2. አጠራራቸው እና ሕይወታቸው
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ
በጐልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ ማሥገር ጀመረ፡፡ ለደቀመዛሙርትነት ሲመረጥ እድሜው 55 ዓመት ሲሆን ወደጌታችን ያመጣውም ወንድሙ እንድርያስ ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረውን መረቡን ታንኩዋውን እንዲህም አባቱን ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው፡፡ በቂሳርያ ከተማ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቀ ጊዜ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ ለአይሁድ ሊቃውንት የተሰወረ ምሥጢረ ተዋሕዶ ገልጦ በመመስከሩ ጌታችን አንተ ጴጥሮስ ነህ ብሎታል ትርጓሜውም «ዐለት» ማለት ነው በአረማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ይወድ ነበር፡፡ ፍቅሩ ግን ቅንዓት የተቀላቀለ በመሆኑ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የሞቱን ነገር ቀድሞ ሲነግራቸው አይሁንብህ በማለት ተከራክሯል፡፡ ማቴ 16፥23 በኋላም ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም ብሎ በራሱ ቅንዓት ተማምኖ ተናግሮ ነበር፡፡ ጌታችን ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ቢለው እንኳን ከአንተ ጋር መሞት እንኳ የሚያስፈልገኝ ቢሆን ከቶ አልክድህም በማለት የተናገረ ሰው ነው፡፡ ማቴ 26፥34
ቅዱስ ጴጥሮስ አስቀድሞ የተናገረውን ቃል ለመጠበቅ ሞክሮ ነበር፡፡ ጌታ የሰው ልጅ አሳልፎ ይሰጣል ብሎ አስተምሯቸው ነበር፡፡ ጌታ ተላልፎ የሚሰጥበት ሌሊት ቅዱስ ጴጥሮስ ጭፍሮችም ጌታን ለመያዝ ሲጠጉ የሊቀ ካህናቱን ባርያ ማልኮስ ጆሮውን በሰይፍ ቆረጠው፡፡ ዮሐ 18፥1ዐ ጌታችን ግን ሞቱ በፍቃዱ ለድኀነተ ዓለም ነውና ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ ሲል ገሠጸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታ በሐናና በቀያፋ በሮማ መኳንንትና ወታደሮች መከራን ሲቀበል በሩቅ ይከተለው ነበር፡፡ ጌታን ወደ ሊቀካህናት ቀያፋ ግቢ ባስገቡትም ጊዜ ተከትሎ ገባ፡፡
ነገር ግን አይሁድ ከሮም ወታደሮች ጋር አብረው በጌታ ላይ ያደርሱት የነበረው መከራ ለሰው ልጅ ህሊና የሚከብድ በመሆኑ እውነተኛ ፍርድ መጥፋቱን የተመለከተው ጴጥሮስ እሳት ወደሚሞቁት ተጠጋ፡፡ በዚያም እያለ የገባውን ቃል አጥፎ 3 ጊዜ አላውቀውም ብሎ ካደ፡፡ ያን ጊዜም ዶሮ ጮኸ፡፡ቅዱስ ጴጥሮስ የሚታወቅበት ሌላው ትልቁ ነገር ንስሐው ነው ጌታው የነገረው መድረሱን ቃል የገባለት አምላኩን መበደሉን እንዳወቀ ከግቢው ወጥቶ አለቀሰ፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ በዕድሜው ታላቅነት በሐዋርያት ዘንድ እንደ አባት ይታይ ስለነuር ጌታ በተለየው ጊዘ? ሐዋርያቱን ሊመግብ ወደሚያውቀው ሙያ ዓሣ ወደማስገሩ ተሠማራ ጌታም አስቀድሞ የመረጠው እርሱ ነውና ቢከዳው እንኳን በንስሐ በመመለሱ ንስሐውን መቀበሉን ዛሬም እንደሚወደው ይገልጽለትም ዘንድ በጥብርያዶስ ባሕር ተገለጠለት፡፡ አሁን ቅዱስ ጴጥሮስ በራስ መተማመኑ እንዳላዋጣው አውቆ ትወደኛለህ ተብሎ ሲጠየቅ አንተ ታውቃለህ ነበረ መልሱ የራሱ እውቀት የት እንዳደረሰው ያውቃልና ጌታችንም ኀዳጌ በቀል /በቀልን የሚተው/ ነውና ዛሬም እንደሚወደው በንሰሐ ተመልሷልና ዛሬም ለእርሱ የሰጠውን ክብር እንደማያጐልበት ሲነግረው ግልገሎቼን አሠማራ ጠቦቶቼን ጠብቅ በጐቼን አሠማራ በማለት አደራውን አስረከበው፡፡ ዮሐ 21፥15-17
ጌታ በዐረገ በ10ኛው ቀን መንፈስቅዱስን ተቀብሎ የሚያውቀው ጸንቶለት የማያውቀው ተገልጾለት በአንድ ቀን ስብከት 3000 ሕዝብ አሳምኗል፡፡ሐዋ2÷41
ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለጸሎት ወደ ምኩራብ ሲገቡ እግሩ ልምሾ ሆኖ የተወለደ አንድ ሰውን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነስ ተመላለስ ብሎ አድኅኖታል፡፡ በኢዮጴ ስምዖን ሰፋዬ አሣዕንን(ቁርበት ፋቂ)፣ ሊቀ ሐራ ቆርነሌዎስን አስተምሯል፣ጣቢታን ከሞት አስነሥቷል(ሐዋ9÷36)፣ በልዳም ኤንያ የተባለ የ8 ዓመት የአልጋ ቁራኛ ፈውሷል፡፡ ሐዋ9÷32 በሰማርያ ጸጋ እግዚአብሔርን በወርቅ በሀብቱ እገዛለሁ ያለውን ሲሞን መሠርይን ድል ነስቶታል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ስለነበረ በአይሁድ ሸንጐ አባልነት ለ2 ዓመታት በሠራበት ወቅት እምነቱ ቀናተኛ ፊሪሳዊ በመሆኑ ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣማ> ይቃወም ነበር፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ሲያርፍም የወጋሪዎችን ልብe ይጠብቅ የነበረው እርሱ ነው፡፡
በ32 ዓመት ዕድሜው ከኢየሩሳሌም 223 ኪ.ሜ ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ወደ ሊቀ ከህናቱ ቀርቦ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የሚያስችKውን የፈቃድ ደብዳቤ ጠይቆ ከአገኘ በኋላ ጭፍሮችን አስከትሎ ወደ ደማስቆ አመራ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ከተማዋ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው ነበር ከሰማይ የወረደው ብርሃን አካባቢውን ያለበሰውና ሳዖል ሳዖል ስለምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምጽ የሰማው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስም ጌታ ሆይ ማን ነህ? ብሎ ጠየቀ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል ሲል መድኃኒታችን ተናገረው፡፡ ያንን በወደቀበት ሆኖ እየተንቀጠቀጠ ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ ሲል ጠየቀው ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ወደ ደማስቆ እንዲገባ ተነገረው፡፡ የሐዋ 9፥1
የሐዋርያው ዓይኖች ለማየት አልቻሉም፡፡ እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ ለ3 ቀናት ያህልም እህል ሳይቀምስ ቆየ በዚያች ዕለት እግዚአብሔር አምላክ በደማስቆ ለሚገኘው እና ሐናንያ ለተባለው አባት በራዕይ ተገለጠለት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ያለበትን አድራሻ ነገረውና እንዲያጠምቀው አዘዘው፡፡ ሐናንያ አስቀድሞ የቅዱስ ጳውሎስን ማንነት ያውቃል፡፡ አብዛኞቹ በደማስቆ የሚገኙት ክርስቲያኖች ከኢየሩሳሌም በስደት ጊዜ የመጡ ናቸው፡፡ ያን ስደት ያስነሳው ደግሞ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ የደረሰው መከራ ነው፡፡ በዚህ በቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ደግሞ ዋናው ተዋናይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነበርና ነው፡፡ ሐናንያ ቅዱስ ጳውሎስን ካጠመቀውና ካስተማረውም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዓረብ ሐገር መሄዱን ራሱ ተናግሯል፡፡ ገላ 1÷17 ለሦስት ዓመታት በዓረቢያ በረሃ ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ፡፡ በዚያም በነበሩ አይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ፡፡ ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱና
◈ ያልተወለደው ባለ ቅኔ ◈
በእርግጥም መጥምቁ ዮሐንስ ገና ሳይወለድ በእናቱ ሆድ ጰራቅሊጦስ የተደረገለት ሐዋርያ ነው፡፡ ሐዋርያት 'እናንተ ግን ከላይ ኃይል አስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ' ተብለው እንደታዘዙ ዮሐንስም 'በአናትህ ማሕፀን ሳለህ ኃይልን አግኝ' የተባለ የእናቱ ሆድ ውስጥ ጸንቶ የቆየ ደቀ መዝሙር ነበር፡፡ ሉቃ. ፳፬፥፵፱ ሐዋርያት በአንድ ልብ ሆነው ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በወረደላቸው ጊዜ ድንግል ማርያም በመካከላቸው እንደነበረች ዮሐንስ እና እናቱ በመንፈስ በአንድ ልብ ሆነው ባመሰገኑባት በዚህች ዕለትም ድንግሊቱ ከመካከላቸው ነበረች፡፡ ሐዋ፩÷፲፬፣ ሉቃ ፩÷፵፩
ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ ከመካከላቸው ተነሥቶ ጴጥሮስ በሰበከው ስብከት ልባቸው የተነኩትን ሕዝቡን 'ምን እናድርግ' እንዳሰኘ ከእናቱ ጋር መንፈስ ቅዱስ የተቀበለው ዮሐንስም ከተወለደ በኋላ በሰበከው ስብከት ሕዝቡን 'ምን አናድርግ?' አሰኝቷል፡፡ ሐዋ.፪÷፴፯ ፣ሉቃ፫÷፲ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ የዮሐንስም የጴጥሮስም የስብከታቸው ርእስ 'ንስሓ ግቡ' ነበረ፡፡ ማቴ. ፫፥፩ ፣ ሐዋ. ፪፥፴፰
ቅዱስ አቡሊዲስ ዘሮሜ ስለ ዮሐንስ ሲናገር:- “እርሱም ማርያም ሰላምታ ስታቀርብላት ሰማ ፤ ደስ አያለውም በእናቱ ሆድ ውስጥ ዘለለ ፤ በድንግል ሆድ ውስጥ የፀነሰችውን የእግዚአብሔርን ቃል አይቶአልና'ሰምዐ : እንዘ፡ ትትአምኃ : ማርያም : አንፈራዓጸ : በከርሠ: እሙ : እንዘ ፡ ይትፌሣሕ፡ እስመ፡ ይሬኢ፡ ዘውስተ: ከርሠ : ድንግል፡ ዘፀንሰት፡ ቃለ፡ እግዚአብሔር' ብሏል፡፡
የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅም በዚህ በጨረሻው ሀሳብ ይስማማል፡፡
ሰማያዊ ክብርን የሚያስገኝ አኩሪ ገድል በመፈጸም የቤተክርስቲያን ታላቅ አለኝታ አባትና መሪ የሆኑት የዘመናችንን ታላቅ ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስን ትውልዱ የግድ ሊያስባቸውና ሊዘክራቸው ይገባል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (united nations) አቡነ ዼጥሮስን "የሺህ ዓመቱ ምርጥ ሰማዕት" ወይም በፈረንጅኛው አፍ (MARTYR OF THE MILLENIUM) በሚል መጠሪያ ሰይሟቸዋል፡፡ ላልተነገረላቸውና ላልተዘመረላቸው ለእኚህ ብርቅዬ የቤተ ክርስቲያናችን ድንቅ አባት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት 12 ቀን 1998 ዓ.ም እኚህን ሰማዕት ‹‹አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ›› ተብለው እንዲጠሩ ወስኗል፡፡ በስማቸውም መቅደስ እንዲታነጽ ፈቅዶ በመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዝ መሠረት (ኢሳ 56፡4) ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ጻድቁ በተወለዱበት ሥፍራ መታሰቢያ አቁማላቸዋለች፡፡ ግንቦት 1 ቀን 2001 ዓ.ም በስማቸው የተሰየመው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንና መታሰቢያ ሐውልታቸው ሲሠራ የፍቼ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ የእስልምና እምነት ተከታዮችም ጭምር ለግንባታ የሚሆን አሸዋ ከመርዳት አንስቶ በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ድንኳን እስከመትከል ተሳትፈዋል፡፡ በገንዘብም በጉልበትም ተባብረዋል፡፡ ጠላት ድል ተደርጎ ሀገራችን ነፃነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የአባታችንን እጅግ አኩሪ ታሪክ ሲያዘክራቸው እንዲኖር መታሰቢያ ይሆናቸው ዘንድ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት አሳሳቢነት ሐምሌ 16 ቀን 1938 ዓ.ም በአ.አ መሐል ከተማ ላይ ሐውልት ቆሞላቸዋል፡፡
የሰማዕት አባታችን በረከታቸው ትደርብን!
@Ethiopian_Orthodox
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ሊቀጳጳስ /1932 - 1982 ዓ.ም/
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በ1933 ዓ.ም በያኔው የወሎ ጠቅላይ ግዛት ደሴ ከተማ ከአባታቸው አቶ ገበየሁ እና ከእናታቸው ወ/ሮ አሰለፈች ተወለዱ። ብፁዕነታቸው መዓርገ ጵጵስናን ከመቀበላቸው በፊት አባ መዝገበሥላሴ ይባሉ ነበር።
ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰም በደሴ መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ መንፈሳዊ ትምህርታቸውን አጠናቀቁ። ከዚያም ትምህርታቸውን ለማስፋፋት ወደ ወሎ ላስታ ነአኩቶለአብ በመሔድ ከአባ ክፍሌ ዘንድ የውዳሴ ማርያም እና ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ አዕማደ ምሥጢርና ባሕረ ሐሳብ ተማሩ።
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በወቅቱ የወሎ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ከነበሩት ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ መዓርገ ዲቁናን ተቀበሉ። ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጥተው በመታሰቢያ ቤት ታዕካ ነገስት በኣታ ለማርያም ገዳም ገብተው ሐዲሳትን ተማሩ። ከዚያም ወደ ደብረሊባኖስ በመውረድ ምንኩስናን ተቀበሉ። በመቀጠል ወደአዲስዓለም በመሔድ አፈወርቅ መንገሻ ከተባሉ ሊቅ ቅኔን ከነአገባቡ ተማሩ።እንደገና ወደ ደብረሊባኖስ ተመልሰው መምህር ፍሥሐ ከተባሉ ሊቅ የሐዲሳት ትርጓሜ እና ትምህርተ ሃይማኖትን፣ መምህር ቢረሳው ከተባሉ ሊቅ ደግሞ መጽሐፈ ሊቃውንትን እንዲሁም ከመምህር ገብረ ሕይወት የሐዲሳት ትርጓሜን አደላድለው ተመረቁ።በዚሁ ደብርም ቅዳሴን ከነሥርዓቱ አጠናቀው ተመርቀዋል። ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ መዓርገ ቅስናን ተቀበሉ።
ከዚህ በኋላ ብፁዕነታቸው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን ለሁለት ዓመታት ካስተዳደሩ በኋላ በ1963ዓ.ም ወደ ግሪክ ተላኩ።በዚያም ፍጥሞ በተባለችው ደሴት ከሚገኘው ነገረሃይማኖት ትምህርት ቤት ተምረው በዲፕሎማ ተመረቁ ትምህርቱን በመቀጠልም ወደ አቴና ዩኒቨርሲቲ በማቅናት ለአራት ዓመታት የነገረ መለኮት ትምህርታቸውን በመከታተል በማስተርስ ተመርቀዋል። ወደ ስዊዘርላንድ በማቅናትም የፈረንሰኛ ቋንቋ አጥንተዋል።
ብፁዕነታቸው ወደኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ጥር ወር 1971 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ተክለሃይማኖት አንብሮተ ዕድ ከተሾሙት አባቶች አንዱ በመሆን መዓርገ ጵጵስና ተቀበሉ። የቅዱስ ፓትርያሪኩና የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ ሆነው አገልግለዋል።በነበራቸው ኃላፊነትም ምቅዋመ ሕግ/ሕገ ቤተክርስቲያን/ አርቅቀዋል። ዘመን የማይሽራቸው "የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ" የሚሉት መጻሕፍቶቻቸው ግሩም ሥራዎቻቸው ናቸው።
ከዚያም ሙሉ ትኩረታቸውን ብዙ ሥራ ወደሠሩበት የዝዋይ ገዳም አድርገዋል። ብፁዕነታቸው በዚያም ገዳሙንና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቱን በማስፋፋት ታላቅ ሥራ ሰርተዋል። በነበራቸው ወጣቱን ትውልድ የመያዝ ፍላጎትና ችሎታ በወቅቱ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ይማሩ የነበሩ ተማሪዎችን በክረምት ወደ ገዳሙ እንዲገቡ በማድረግ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት በመማር ዘመኑን እንዲዋጁ አድርገዋል ። እርሳቸው ለሁለት ለሦስት ክረምቶች ሰብስበው ያስተማሯቸውና የመከሯቸው ተማሪዎች ዛሬ ቊጥራቸውን አበራክተው በማኅበረ ቅዱሳን ደረጃ በመሰባሰብ በዕውቀታቸውና በገንዘባቸው ቤተ ክርስቲያንን እና አባቶችን እያገለገሉ ይገኛሉ።
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ለዐሥራ አንድ ዓመታት በዚህ ዓይነት ከፍተኛ እና አርአያነት ያለው አገልግሎት ካበረከቱ በኋላ ሐምሌ 22 ቀን 1982 ዓ.ም በመቂ ቅዱስ ሚካኤል ለሚገኙ ምእመናን አባታዊ ትምህርታቸውን ለመሠጠት ሲገሰግሱ በድንገት በደረሰባቸው የመኪና አደጋ በተወለዱ በኀምሳ ዓመታቸው ዐርፈዋል። የብፁዕነታቸው በረከት አይለየን።
©- ስንክሳር ዘወርኀ ሐምሌ
-ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሐምሌ ፳፪
✝አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ
✝ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
በዚህች ዕለት ኢትዮጵያዊው ሰማዕት ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት አረፉ፡፡ የ20ኛው ክ/ዘ ታላቅ ሰማዕት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ በ1875 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰላሌ አውራጃ ፍቼ ከተማ ተወለዱ፡፡ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት እንደሚሞቱ አስቀድመው መምህራቸው በትንቢት ነግረዋቸው ነበር፡፡ ‹‹አለቃ ተጠምቀ›› የተባሉ ቅድስናን ከሊቅነት ጋራ አስተባብረው የያዙ የቅኔ መምህራቸው አንድ ቀን አቡነ ጴጥሮስን ጠርተው «ኀይለ ማርያም አንተ ወደፊት ጳጳስ ትሆናለህ፤ በወቅቱም አረመኔ በዚህች ሀገር ይሠለጥናል፡፡ ታዲያ ያኔ አንተ ለነፍስህ ሳትሳቀቅ በሰማዕትነት እለፍ፤ ሰማዕትነት ክፍልህ ነው፣ አደራ›› ብለዋቸው ነበር፡፡ ይኸውም ትንቢት ደርሶ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት ለማረፍ በቅተዋል፡፡ ብፁዕ አባታችን የጵጵስና ስማቸውን ከማግኘታቸው በፊት መመህር ኀይለ ማርያም ይባሉ ነበር፡፡ በልጅነታቸው ወላጆቻቸው ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመውሰድ በሃይማኖትና በምግባር ተኮትኩተው እንዲያድጉ አድርገዋቸዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኗን ሥርዓተ ትምህርት ከንባብ እስከ ቅኔ ያሉትን ትምህርቶች በሚያስገርም ፍጥነት ከተማሩ በኋላ ወደ ቅኔው አውድማ ጎጃም በመሄድ በሸዋራ የቅኔ ትምህርታቸውን ፈጽመው መምህር ሆነዋል፡፡ የዜማውንም ትምህርት ወደ ጎንደር ሄደው ተምረዋል፡፡ በመቀጠልም ወሎ ቦሩ ሜዳ ላይ ወንበር ዘርግተው የመጻሕፍትን ምሥጢር ይመግቡ ወደነበሩት ወደ ሊቁ አካለ ወልድ ዘንድ በመሄድ ዋና ዋናዎቹን የመጻሕፍት ትርጓሜ ማለትም ብሉያትን፣ ሐዲሳትንና ሊቃውንትን በሚገባ አሒዱ፡፡ ከዚህ በኋላ በ1900 ዓ.ም ወሎ አምሐራ ሳይንት ሄደው በምስካበ ቅዱሳን ገዳም ገብተው ወንበር ዘርግተው ለ9 ዓመታት ቅኔንና መጻሕፍትን አስተማሩ፡፡ በ1910 ዓ.ም ወደ ደብረ ሊባኖስ መጥተው ሥርዓተ ምንኩስናን ፈጸሙ፡፡ ከዚያም መምህርነት ተሹመው ደብረ መንክራት ምሁር ኢየሱስ ገዳም ሄደው ለ6 ዓመታት ካስተማሩ በኋላ በ1916 ዓ.ም እንደገና በዝዋይ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ገዳም በመምህርነት ተሹመው ለ3 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በ1919 ዓ.ም ወደ አ.አ በመምጣት የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ መምህርና በቤተ መንግሥት የግርማዊ ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ የንስሓ አባት ሆኑ፡፡ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በራሷ ተወላጅ ጳጳሳት ልጆቿ እንድትመራ ከ1600 ዓመታት በኋላ ስለተፈቀደላት ከዚህ በኋላ በሃይማኖታቸውና በስነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸው አምስት ደጋግ አባቶች ሲመረጡ አንዱ አቡነ ጴጥሮስ ነበሩ፡፡ በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የራሷን ጳጳስ ስትሾም አቡነ ጴጥሮስ ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም ጵጵስና ተሾሙ፡፡ ከዚህም በኋላ ብፁዕ አባታችን ‹‹አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቀ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዐ›› ተብለው በያኔው መንዝና ወሎ ሀገረ ስብከት ተሾሙ፡፡
ብፁዕ አባታችንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያንንና ቅድስት ሀገራችን በጸሎታቸው፣ ሕዝቡን በትምህርታቸው እየጠበቁ በተጋድሎ እየኖሩ ሳለ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት በ1928 ዓ.ም በኢትዮጵያ ላይ የግፍ ጦርነትን አውጆ ሕዝቡን በግፍ ይገድል ቤተ ክርስቲያንን ያቃጥል ጀመር፡፡ በየገዳማቱ እጅግ በርካታ ካህናትና መነኮሳት ተገደሉ፣ ብርቅዬ የቤተ ክርስቲያን ቅርሶች ተዘረፉ፡፡ አቡነ ጴጥሮስም ይህንን ግፍ በማየታቸው ከሀገራችን አርበኞች ጋር በመሆን በጸሎታቸው ሊዋጉት ተነሡ፡፡ አባታችን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ተከትለው ወደ ሰሜን ጦር ግንባር ማይጨው ዘምተዋል፡፡ ፋሺስቱ በማይጨው በመርዝ የተደገፈ ጦርነት ከማድረጉ የተነሣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሲበታተንም ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ወደ አ.አ የተመለሱት አቡነ ጴጥሮስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደው ለአገርና ለነፃነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን ለሠላሌ አርበኞች በሚገባ አስተምረዋል፡፡ በደብረ ሊባኖስ ጫካዎች ውስጥ መሽጎ የነበረው የእነ ደጃዝማች አበራ ካሣ አርበኛ ጦር እና በሸንኮራ በኩል መሽጎ የነበረው የእነ ፍቅረ ማርያም አርበኛ ጦር እንደሁም በምዕራብ ይመራ ከነበረው የእነ ደጃዝማች አባ ነፍሶ ጦር ሦስቱም በአንድ ጊዜ ወደ መሐል አ.አ በመግት አ.አ ላይ መሽጎ የነበረውን ፋሽስትን ለመውጋት ታቅዶ የነበረው ዕቅድ በመረጃ ክፍተት ምክንያት ውጤታማ ሳይሆን ቀረ፡፡ በተለያየ ጊዜ መሐል አ.አ እየደረሱ ማለትም በመጀመሪያ የእነ ፍቅረ ማርያም አርበኛ ጦር ለብቻው በኮተቤ አድጎ የካ ሚካኤል ላይ ሲድርስ ተመቶ ተመለሰ፤ ይሄኛው እንዳለቀ ቀጥሎ የእነ አባ ነፍሶ ጦር በባቡር ጣቢያ መጣሁ ቢልም በጠላት ጦር ድካሚ ተመቶ ተመለሰ፤ መጨረሻ ላይ የእነ ደጃዝማች አበራ ካሣ አርበኛ ጦር በእንጦጦ በኩል ቢመጣም እርሱም በጠላት ጦር ተመቶ ተመለሰ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ሦስቱም የአርበኞች ጦር በመረጃ ክፍተት ምክንያት እየተመታ ወደመጣበት ሲመለስ አቡነ ጴጥሮስ አብረው ከአርበኛው ጦር ጋር መመለሱን አልፈለጉትም ይልቁንም ‹‹ብችል ጠላት በኢትዮጵያውያን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በቅርብ ርቀት ሆኖ የሚመለከተውን ሕዝብ በማትጋት በጠላት ላይ እንዲነሣ አደርገዋለሁ ካልሆነም ደግሞ እዚሁ እሞታለሁ›› በማለት አባታችን ከአርበኞቹ ተነጥለው አ.አ ቀሩ፡፡ ይሁን እንጂ ጠላት በመላዋ ከተማ ያሰማራቸው ባንዳዎች አባታችንን እንዳሰቡት ሊያነቀሳቅሷቸው አልቻሉም ነበር፡፡ በመሆኑም አባታችን ‹‹የሀገሬን ሕዝብ ለጠላት እንዳይገዛ በአደባባይ አውግዤ ጠላትን ረግሜ በሰማዕትነት ባልፍ ይሻለኛል›› ብለው ራሳቸውን ለጠላት አሳልፈው ለመስጠት ወሰኑና የፋሺስት ኢጣሊያ እንደራሴ ለሆነው ለራስ ኀይሉ ሄደው እጃቸውን ሰጡት፡፡ እርሱም ብፁዕ አባታችንን ወስዶ ለግራዚያኒ ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም አሳልፎ ሰጧቸው፡፡ ግራዚያኒም ግማሽ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዲገደሉ ወሰነባቸው፡፡ አቡነ ጴጥሮስ በፈቃዳቸው እጃቸውን አሳልፈው ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ በጠላት የጥይት እሩምታ በሰማዕትነት እስካለፉበት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሒደት ኮርየሬ ዴላሴራ የተባለው ጋዜጣ ወኪልና የምሥራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው ፖጃሌ የተባለው ጋዜጠኛ እ.ኤ.አ ሰኔ 15 ቀን 1936 ዓ.ም በአዲስ አበባ በነበረ ጊዜ በአቡነ ጴጥሮስ ላይ የተሰጠውን ፍርድና የተፈጸመውን የግፍ ግድያ ባየውና በተመለከተው መንገድ እንደሚከተለው ጽፎ ነበር፡-
‹‹ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም አቡነ ጴጥሮስ ተይዘው ወደ ግራዚያኒ ቀረቡ፡፡ በዚህ ጊዜ አቡነ ቄርሎስ የተባሉት ግብፃዊ ጳጳስ ቀርበው ‹ለእስክንድርያው መንበረ ፓትርያርክ ምክር ቤት ሳታሰማ በአቡነ ጴጥሮስ ላይ እንዳች ነገር ማድረግ አይገባህም››› ሲሉ ለግራዚያኒ ነገሩት፡፡ አቡነ ቄርሎስ ይህን ማለታቸው በዲፕሎማቲክ ደረጃ ለዓለም ለማሰማትና የአቡነ ጴጥሮስን ሕይወት ለማትረፍ አስበው ነበር፡፡ ነገር ግን ግራዚያኒ የአቡነ ጴጥሮስ የሞት ፍርድ እንኳንስ እስከ ግብጽ ከአ.አ ውጭ እንኳ ከመሰማቱ በፊት በግማሽ ቀን እንዲፈጸም መመሪያ አስተላላፈ፡፡ ወደ ምሥራቅ አፍሪካው ዜና መዋዕል አዘጋጁ ወደ ፖጃሌ ዘገባ እንመለስና የአቡነ ጴጥሮስን መልካቸውንና ተክለ ቁመናቸውን እንዲህ በማለት ይገልጸዋል፡- ‹‹ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረዘም፣ ፊታቸው ዘለግ ያለ፣ መልካቸው ጠየም ያለ፣ ዐዋቂነታቸውና ትሕትናቸው ከገጻቸው የሚነበብ ሲሆን በዚህ ጊዜ ለብሰውት የነበረው ልብሰ ጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የተበከለ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ችሎት ቀረቡ፡፡ ለፍርድ የተሰየሙት ዳኞች
አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ
እንደ ምህረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ፡፡
ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ
ከኃጢአቴም አንፃኝ፣
እኔ መተላለፌን አውቃለሁ
ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና፡፡
አንተን ብቻ በደልሁ
በፊትህም ክፋትን አደረግሁ
በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ
በፍርድህም ንፁህ ትሆን ዘንድ
እነሆ በዓመፃ ተፀነስሁ
እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ
እነሆ እውነትን ወደድህ
የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ በሂሶጵ እርጨኝ እነጻማለሁ
እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ፡፡ ሐሴትና ደስታን እሰማኝ
የሰበርሃቸወም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል፡፡ ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ
አቤቱ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ
የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ
ከፊትህ አትጣለኝ ቅዱስ መንፈስህንም
ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ
የማዳንህን ደስታ ስጠኝ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ
ለሕግ ተላላፎች መንገድህን አስተምራለሁ
ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ፡፡ የመድኃኒቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ
ከደም አድነኝ አንደበቴም በአንተ ጽድቅ ትደሰታለች፡፡
አቤቱ ከንፈሮቼን ክፈት
አፌን ምስጋናህን ያወራል፡፡
መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም፡፡
የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው
የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም፡፡
መዝ50(51)÷1-17
◈ሌላው የዳዊት ኑዛዜ
አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ
በመዓትህም አትገሥጸኝ
ፍላጻዎችህ ወግተውኛልና እጅህንም አከበደህብኛልና፡፡
ከቁጣህ የተነሣ ለሥጋዬ ጤና የለውም ከኃጢአቴም የተነሣ ለአጥንቶቼ ሰላም የላቸውም፡፡
ኃጢአቴ በራሴ ላይ ከፍ ከፍ ብሎአልና
እንደ ከባድ ሸክምም በላዬ ከብዶአልና፡፡ ከስንፍናዬ የተነሣ ቁስሌ ሸተተ በሰበሰም እጅግ ጎሰቆልሁ ተዋረድሁም
ሁልጊዜም በትካዜ እመላለሳለሁ
ነፍሴ ስድብን ተመልታለችና
ለሥጋዬም ጤና የላትምና
ታመምሁ እጅግም ተቸገርኩ
ከልቢ ውዝዋዜም የተነሳ ጮኹኩ፡፡
አቤቱ ፈቃዴ ሁሉ በፊትህ ነው
ጭንቀቴም ከአንተ አይሰወርም
ልቤም ደነገጠብኝ ኃይሌም ተወችኝ የዓይኖቼም ብርሃን ፈዘዘ
ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ከቁስሌ ገለል ብለው ቆሙ
ዘመዶቼም ርቀው ቆሙ
ነፍሴንም የሚሹአት በረቱብኝ መከራዬንም የሚፈልጉ ከንቱን ተናገሩ ሁልጊዜ በሽንገላ ይመከራሉ
እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቆሮ
አፉንም እንደማይከፍት ዲዳ ሆንኩ
አቤቱ በእንተ ታምኛለሁና
አቤቱ አምላኬ አንተ ትሰማኛለህ
ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ እንዳይላቸው ብያለሁና
እግሮቼ ቢሰናከሉ ራሳቸው በእኔ ላይ ከፍ ከፍ ያደርጋሉ፡፡
እኔስ ወደማንከስ ቀርቤአለሁ
ቁስሌም ሁልጊዜ በፊቱ ነውና
በደሌን እናገራለሁና /እናዘዛለሁ/ ስለኃጢአቴም እተከዛለሁ /እጸጸታለሁ/
መዝ 37/38/÷1-22
ለ.የነቢዩ ዮናስ ኑዛዜ
ነቢዩ ዮናስ ለእግዚአብሔር አልታዘዝም ብሎ በማመጹ የተለያየ ቅጣት የተቀጣ ሰው ነው፡፡ በበዛው ኃጢአቷ ምክንያት ፍርድና ጥፋት የደረሰባትን ነነዌን እንዲገስጽና ንስሐ እንዲገቡ እንዲያስተምር ቢላክ ከእግዚአብሔር ፊት ለመኮብለል ተነስቶ በታንኳ በመሳፈር ወደ ተርሴስ አቀና ተመልከቱ ምድር ሁሉ በፊቱ ከሆነችለት ጌታ ፊት ለመሸሽ ሞከረ፡፡
"የአርባብ አለቃ"
የአርባብ አለቃ ቅዱስ ገብርኤል
አብሳሪ ትስብዕቱ ለቀዳሚ ቃል
ምሕረት አሰጠን ከአምላክ ከልዑል
በሦስቱ ሰማያት በመላእክት ከተማ
ሳጥናኤል ተነሥቶ ክህደትን ሲያሰማ
ጽኑ ብለህ ያቆምክ መላዕክትን በዕምነት
እኛንም አድነን አጽናን በሃይማኖት
አዝ..
ቂርቆስ ኢየሉጣን ከመቃጠል ያዳንክ
በመልካሙ ዜና ድንግልን ያበሰርክ
ተስፋ በቆረጥን በተከፋን ጊዜ
አንተ ድረስልን አውጣን ከትካዜ
አዝ...
ከምግባር ለይቶ በዓለም ፍቅር ስቦ
የመስቀሉን ተስፋ ከልባችን ሰልቦ
ዲያብሎስ በምኞት ሊጥለን ነውና
ጠብቀን ገብርኤል ከስህተት ጎዳና
አዝ...
ሥልጣንህን አምነን የምልጃህን ጸጋ
አስታርቀን ስንልህ ዘወትር ስንተጋ
ፈቅደህ ተለመነን ድምጻችንን ስማ
የአርባብ አለቃ መልአክ ዘራማ
አዝ...
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሐምሌ ፲፱
ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ለቅዱስ ቂርቆስና ለቅድስት ኢየሉጣ ተራዳኢ የሆነበት ታላቅ ቀን
ቅድስት ኢየሉጣ በሮም ግዛት በሚገኝ አንጌቤን በሚባል አገር በፈሪሃ እግዚአብሔር፣ በክርስትና ሃይማኖት እና በበጎ ምግባር ጸንታ ትኖር የነበረች ደግ ሴት ናት፡፡ በሥርዓት ያሳደገችው ቂርቆስ የሚባል ሕፃን ልጅም ነበራት፡፡ ይህቺ ቅድስት የዘመኑን አረማዊ መኰንን እለእስክንድሮስን በመፍራቷ ከልጇ ጋር ከሮም ወደ ጠርሴስ በተሰደደች ጊዜ መኰንኑ እነርሱ ከሚገኙበት አገር ገብቶ ክርስቲያኖችን እያሳደደ መግደል ጀመረ፡፡ የንጉሡ ወታደሮችም እግዚአብሔርን እንዲክዱ፤ ለጣዖት እንዲሰግዱ ቅድስት ኢየሉጣንና ቅዱስ ቂርቆስን አስፈራሯቸው፡፡ ቅዱሳኑ ግን ሃይማኖታቸውን ለመለወጥ ፈቃደኛ አልሆኑም ነበር፡፡
በዚህም መኰንኑ ተቈጥቶ በዓይንና በአፍንጫቸው ውስጥ ጨውና ሰናፍጭ በመጨመር፤ በጋሉ የብረት ችንካሮች በመቸንከርና መላ ሰውነታቸውን በመብሳት በብዙ ዓይነት መሣሪያ አሠቃያቸው፡፡ እግዚአብሔርም የጋሉ ብረቶችን እንደ ውኀ ያቀዘቅዝላቸው፤ ሥቃያቸውንም ያቀልላቸው ነበር፡፡
በሌላ ጊዜም በገመድ አሳሥሮ ንጉሡ ሲያስጨንቃቸው ከቆየ በኋላ ራሳቸውን ከቆዳቸው ጋር አስላጭቶ እሳት አነደደባቸው፡፡ ዳግመኛም ከትከሻቸው እስከ እግራቸው ድረስ በሚደርሱ ችንካሮች ቸነከራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ከሥቃያቸው አድኗቸዋል፡፡
አሁንም ቀኑን ሙሉ በልዩ ልዩ የሥቃይ መሣሪያዎች ቢያስጨንቃቸውም የእግዚአብሔር ኃይልና የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት አልተለያቸውም ነበርና ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰባቸውም፡፡ እንደ ገናም በመጋዝ ሰንጥቀው በብረት ምጣድ በቆሏቸው ጊዜ ጌታችን ከሞት አነሣቸውና በመኰንኑ ፊት ድንቅ ተአምራትን አደረጉ፡፡ ከተአምራቱ መካከልም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ የመኰንኑን ጫማ በጸሎት ወደ በሬነት እንዲቀየር ማድረጉ ተጠቃሽ ሲሆን፣ መኰንኑ በተአምራቱ ተቈጥቶ የቅዱስ ቂርቆስን ምላስ አስቈርጦታል፤ ጌታችንም ምላሱን አድኖለታል፡፡
ዳግመኛም በፈላ የጋን ውኀ ውስጥ ቅዱሳን ቂርቆስና ኢየሉጣን ሊጨምሯቸው ሲሉ ቅድስት ኢየሉጣ በፈራች ጊዜ ቅዱስ ቂርቆስ ‹‹እናቴ ሆይ አትፍሪ፤ አናንያ፣ ዓዛርያና ሚሳኤልን ከእሳት ነበልባል ያዳናቸው እግዚአብሔር እኛንም ከዚህ የፈላ ውኀ ያድነናል›› እያለ ያረጋጋት በተጋድሎዋ እንድትጸና ወደ እግዚአብሔር ይጸልይላት ነበር፡፡
ከዚህ በኋላ ተያይዘው ወደ ጋኑ ውስጥ ገቡ፡፡ ያ ውኀም እንደ ውርጭ ቀዘቀዘ፡፡
ደግሞም ወታደሮቹ መንኰራኵር ባለበት የብረት ምጣድ ውስጥ አስገብተው ሥጋቸው እስኪቈራረጥ ድረስ በጎተቷቸው ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል አድኗቸዋል፡፡
በመጨረሻም ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ተቀብለው በመንፈቀ ሌሊት አንገታቸውን ተቈርጠው በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ እስከ ሞት ድረስ በታመኑበት ተጋድሏቸውም ከእግዚአብሔር ዘንድ የሕይወትን አክሊል ተቀብለዋል፡፡
በአጠቃላይ ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት ኢየሉጣ የዚህን ዓለም ጣዕም በመናቅ ‹‹ሞት ቢሆን፣ ሕይወትም ቢሆን፣ መላእክትም ቢሆኑ፣ ግዛትም ቢሆን፣ ያለውም ቢሆን፣ የሚመጣውም ቢሆን፣ ኃይላትም ቢሆኑ፣ ከፍታም ቢሆን፣ ዝቅታም ቢሆን፣ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ›› በማለት ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረውን ቃል በተግባር በማሳየት ለክርስቶስ ፍቅር ሲሉ ራሳቸውን ለመከራና ለሞት አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ ቅዱሳኑ ተጋድሏቸውን እስኪፈጽሙ ድረስም ቅዱስ ገብርኤል አልተለያቸውም፡፡ በቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት ቅድስት ኢየሉጣና ቅዱስ ቂርቆስ ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ምእመናንም ተጠቅመዋል፡፡ ስሙ በሚጠራባቸው ገዳማትና አድባራት መልአኩ የሚያደርጋቸው ድንቅ ድንቅ ተአምራት ለዚህ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ይህም ቅዱሳን መላእክት በእግዚአብሔር ስም መከራ የሚቀበሉ ምእመናንን እንደሚጠብቁና ከልዩ ልዩ ደዌ እንደሚፈውሱ የሚያስረዳ ታሪክ ነው፡፡ (ሮሜ. ፰፥፴፰-፴፱)
እኛም በሃይማኖታችን ምክንያት መከራ ባጋጠመን ጊዜ ቈራጥ ልብ ያለው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ‹‹እናቴ ሆይ አትፍሪ›› እያለ በእሳት ውስጥ ሊጣሉ ባሉበት ወቅት እናቱን እንድትጸናና ለሰማዕትነት እንድትበቃ እንዳደረጋት ሁሉ፣ ዘለዓለማዊውን የእግዚአብሔርን መንግሥት በአንድነት ለመውረስ እንድንችል ‹‹አይዞህ! አይዞሽ! አትፍራ! አትፍሪ›› በመባባል በዚህ ዓለም የሚገጥመንን መከራ ታግሠን፣ እስከ ሞት ድረስ በሃይማኖታችን ጸንተን መኖር ይገባናል፡፡
ክርስትና ለብቻ የሚጸደቅበት መንገድ ሳይሆን በጋራ ዋጋ የሚያገኙበት የድኅነት በር ነውና፡፡ ከዚሁ ሁሉ ጋርም ቅዱስ ቂርቆስንና ቅድስት ኢየሉጣን የተራዳው የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በአማላጅነቱ እንዲጠብቀን ‹‹በተአምኖ ንሴፎ ትንባሌ ዚአከ መዓልተ ወሌሊተ፤ በእግዚአብሔር ታምነን በቀንም በሌሊትም የአንተን ልመና ተስፋ እናደርጋለን›› እያልን ዘወትር ልንማጸነው ያስፈልጋል፡፡ እርሱ ከፈጣሪው ከእግዚአብሔር በተሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት ከሚደርስብን ልዩ ልዩ መከራና ሥቃይ ያድነናልና፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙርያ ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (መዝ. ፴፬፥፯)፡፡ ይህን እንድናደርግም የቅዱሳን ተራዳኢነት አይለየን፡፡ የቅዱስ ገብርኤል፣ ቅድስት ኢየሉጣ እና ቅዱስ ቂርቆስ ጸሎታቸው፣ ምልጃቸው ይጠብቀን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
©ስንክሳር ዘወርኀ ሐምሌ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
እንዴት እና ምን ብዬ ልናዘዝ?
ምዕራፍ ፩ ክፍል ፪
.........................................
የምንሰራው ኃጢአት የማያስከትለው ውጤት
የምንሰራው ወይም የምንኖርበት የኃጢአት ሕይወት የሚያስከትለው ውጤት በኃጢአታችን እንድንናዘዝ ያስገድደናል፡፡ ይህ ማለት የምንሰራው ኃጢአት ዋጋ ምን እንደሚሆን መገንዘባችን ለኑዛዜና ለንስሐ ያስወሰነናል ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ አንድ ጠጪ ሰው በሚሰከርበት ጊዜ ስቶ እየተወላገደ ሲብስም እየወደቀና እየተነሳ ይሄዳል፡፡ ይህ የሚሆነው ሕጌን ጥሰሀል አትስከር ብዬህ ነበር አልሰማ ብለኸኛል ብሎ እግዚአብሔር ከኃላው ሆኖ እየገፈተረው ሳይሆን የኃጢአቱ ጠባይ ያስከተለበት የስካር ውጤት ነው፡፡ ሰው በማመንዘርም በሽታ በስንፍናም ድህነት እነዚህን የመሰሉት ኃጢአትን የሚከተሉ የኃጢአት ውጤቶችና ዋጋዎች ናቸው።
ስለዚህ በዚህ ምክንያት ሰው ወደ ንስሐ እንዲመለስና በኃጢአቱ እንዲናዘዝ ይገደዳል።
እንዴት እና ምን ብዬ ልናዘዝ?
ምዕራፍ ፩ ክፍል ፩
.........................................
1.1 የኑዛዜ ምንነት
፨ኑዛዜ፡- የሰሩት ኃጢአት እንዲሠረይ የፈፀሙት በደል እንዲደመሰስ የተላለፉት መተላለፍ እንዲቀር በመቆጨት በመጸጸት በማዘን በራስ አንደበት ራስን ወቃሽ ሆኖ ኃጢአትን ለእግዚአብሔርና ለአገልጋዩ ካህን መናገር ማለት ነው። /መዝ32÷1-2/
በዚህ መሠረታዊ ትርጉም መነሻነት ኑዛዜ+ የሰሩትን ኃጢአት እየረገሙ ሲሰሩት ስለኖሩ ወይም ስለፈፀሙት መጸጸት ነው፡፡ ኑዛዜ+ ኃጢአትን ላለመሥራት መነሣትን የሰሩትንም በመግለጥ ላለመመለስ መርገም ነው። ኑዛዜ+ በጌታችን በኢየሱስ ከርስቶስ ደም እንደሚነጹ በማመን በገዛ አንደበት መቆሸሽን አምኖ ራስን ለእግዚአብሔር ማቅረብ ነው /ኤር 33÷8/ ኑዛዜ+ በዮርዳኖስ ዙሪያ የንስሐ ጥምቀት ያጠምቅ ለነበረው ዮሐንስ መጥምቅ ኃጢአታቸውን ይነግሩት እንደነበር የካህኑ ስልጣን የእግዚአብሔር መሆኑን አምኖ እራስን እያዋረዱ ሲሰሩት የኖሩትን በደል መናገር ነው። /ማቴ 2+8/ ባጠቃላይ ኑዛዜ መናገር፣ ራስን መውቀስ፣ ድብቁን መግለጥ፣ ተጸጸትኩ፣ ተሳሳትኩ፣ በደልኩ፣ አጠፋሁ፣ ይህንንና ያን አደረግኩ፣ አላበጀሁም እያሉ ራስን ማዋረድና በደለኛ ማድረግ ነው።
፨መናዘዝ፡- መናዘዝ ራስን ለእግዚአብሔርና ለፈቃዱ ለማውረስ በራስ ፍላጎትና በሙሉ ተነሳሽነት የሰራናቸውን ስህተቶችና ኃጢአቶች ለመርገምና ለመኮነን ውስጣችንን ሙሉ ለሙሉ በደለኛ መሆንን በማሳመን በእግዚአብሔርና በካህኑ ፊት ንስሐ የምንገባበት መንገድና ለኃጢአት ዓለም ራሳችንን ምውት የምናደርግበት መንፈሳዊ ምስጢር ነው፡፡
📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚
ሰላም ውድ የ"የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች" ቻናል ተከታታዮች በኃያሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንደምን ሰነበታችሁ? ከዚህ በፊት በመጻሕፍት አምዳችን "ተግባራዊ ክርስትና" እና "ሕይወተ ወራዙት ፩" የተሰኙ መጻሕፍትን ወደ እናንተ ማድረሳችን ይታወቃል። እነሆ አሁን ደግሞ "እንዴትና ምን ብዬ ልናዘዝ?" በሚል ርዕስ በመ/ር የሺጥላ ሞገስ የተዘጋጀውን እጅግ ጠቃሚ መጽሐፍ በመጽሐፉ ምዕራፍ መሠረት በክፍል ከፋፍለን ወደ እናንተ ማድረስ እንጀምራለን። ስለሆነም አንብባችሁ ትጠቀሙበት ዘንድ እንዲሁም ለሌሎችም ያነበባችሁትን ታጋሩ ዘንድ እናሳስባለን። ይልቁንም ደግሞ ያነበብነውን ወደ ተግባራዊ ህይወት ቀይረን እንኖረው ዘንድ መልዕክታችን ነው።
መልካም ንባብ!
==================================
እንዴትና ምን ብዬ ልናዘዝ?
...............................................
፨መቅድም
ንስሐ እግዚአብሔር በሰው ልጅ ላይ ያለው የማያባራ ፍቅር ማረጋገጫ ሆኖ የተሰጠ ጸጋ ነው
የሰው ተፈጥሮ እራሱ የእግዚአብሔር ፍቅር መግለጫና ውጤት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ብቻውን መኖር አቅቶት አልያም ለህልውናው ከሰው ልጅ የሚፈልጋቸው ግብዓቶች ኖረው አልያም ያለ እኛ መኖር ስለማይችል አይደለም ፍቅር የሆነው እግዚአብሔር ፍቅሩ በሚፈጥረው ሰው ላይ እንዲገለጽ ሽቶ እንጂ፡፡ “ሰውን በመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር፡፡” /ዘፍ 2÷18/
"ወይቤሎሙ ሑሩ"
በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰብክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት፡፡ በዚያም የተነሣ የደማስቆ ክርስቲያኖች በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ አይሁድ ጳውሎስን እንደሚያውቁት እና እንደለመዱት ሆኖ ስላላገኙት ሊገድሉት ተነሱ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቲያኖች የቅዱስ ጳውሎስን መመለስ ሊያምኑ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻ ግን በርናባስ ወደ ሐዋርያት ዘንድ ወስዶ የጳውሎስን መመለስ በመተረክ እንዲያምኑት አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም በድፍረት በማስተማሩ አይሁድ ስለተቃወሙት ከተማዋን ትቶ በቂሳርያ በኩል ወደ ትውልድ ሐገሩ ጠርሴስ ተመለሰ፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጠርሴስ ከተማ ለ9 ዓመታት ቆይቷል፡፡ ከኢየሩሳሌም ውጭ የአሕዛብ ከተማ በነበረችው በአንጾኪያ የክርስትና ሃይማኖት ተስፋፋ፡፡ ከዚህም በኋላ ሐዋርያው ሦስት ታላላቅ ሐዋርያዊ ጉዞዎችን አድርጓል፡፡ በመጀመሪያው ጉዞው ወደ 2ዐዐዐ ኪ.ሜ የሚደርስ መንገድ በእግር ተጉዟል፡፡ ይህም የተከናወነው በ46 ዓ.ም ነው፡፡ በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከ18 በላይ ከተሞችን ሸፍኗል፡፡ ጉዞውም በ5ዐ ዓ.ም የተደረገ ነው፡፡ በሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከ2ዐ በላይ ከተሞችን ሸፍኗል፡፡ ጉዞውም በ54 ዓ.ም የተደረገ ነው፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በጥበብ ነበር የሚያስተምረው፡፡ ጣዖት የሚያመልኩትን መምለኬ ጣዖት መስሎ፣ ሕሙማንን ሕሙም መስሎ አስተምሯል፡፡ 1ኛ ቆሮ9÷21 በአንጾኪያ ከሞተ 2 ወር ያለፈውን የንጉሡን ልጅ ከሙት አስነሥቷል፡፡ ብዙም ጊዜ በቁም እሥር በብዙም መከራ ሥቃይ እንግልት ያለፈ ታላቅ ሐዋርያ ነው፡፡
3. ዕረፍታቸው
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ
ንጉሡ ኔሮን ቄሣር መምለኬ ጣዖት ነበር፡፡ በሃይማኖት ምክንያት አስሮት ነበር፡፡ ወደ ጦር ግንባር ዘምቶ ጠላቱን ድል ነሥቶ ሲመለስ ለጣዖት ስገድ ቢለው አልሰግድም አለ፡፡ በችንካር ተቸንክሮ በመስቀል ተሰቅሎ ይሙት ብሎ ፈረደበት፡፡ ከዚያ በፊት አሕዛብ ሊጣሉት ሲነሱ ወደ ጌታ ሲያመለክት እሳት ከሰማይ ወርዳ ታጠፋለት ነበር፡፡ አሁንም ትብላቸው ብሎ ወደ ጌታ ቢያመለክት ጌታ በመስቀል ተሰቅሎ ታየው ዳግመኛ በሮም ሰቀሉህን አለ አንተ ብትፈራ እንጂ አለው፡፡ ፈቃድህስ ከሆነ ብሎ እንደ ጌታዬ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ስቀሉኝ አላቸው ፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ በጨካኙ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት ቁልቁል በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ሥጋውንም ደቀመዝሙሩ መርቄሎስ ከመስቀሉ አውርዶ በወተት አጥቦ ሽቱ ቀብቶ በነጭ ሐር ገንዞ እንዳይፈርስ በማር በተመላ ሣጥን አድርጎ ቀብሮታል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
ለ 2 ዓመት ከ6 ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ከቆየ በኋላ በ74 ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት አንገቱን በሠይፍ ተሠይፎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም በሰማዕትነት አረፈ፡፡
አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ረድኤት በረከታቸው ይክፈለን፡፡ አሜን!!!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የድንግል ማርያምን ድምፅ ሲሰማ የተሰማውን ደስታ መናገር ባይችልም ፣ 'የተባረክሽ ነሽ' ብሎ ለማመስገን ባይታደልም እናቱ ኤልሳቤጥ ግን ልጅዋን ወክላ 'በደስታ ዘለለ' ብላ ተናገረችለት፡፡ እርሱ ቃል አውጥቶ ማመስገን ባይችልም እናቱ የጌታን እናት አመስግና የልቡን አደረሰችለት፡፡ እርሱ በመዝለልና በመስገድ እናቱ ደግሞ በታላቅ ድምፅ በማመስገን ድንግል ማርያምን ተቀበሏት፡፡
በእናቱ ሆድ ውስጥ ያለ ሕፃን 'ኖር' ብሎ እጅ ነሥቶ የሚቀበላት ክብርት እንግዳ ከድንግል ማርያም በቀር ወዴት አለች? ገና ያልተወለደ ልጅ ድምፅዋን ሰምቶ ከእናቱ ሆድ ለመውጣት ከጓጓላት ማርያም ስም በቀርስ ሴት ልጅ ምጥ ላይ በሆነች ጊዜ ልጁን ልውጣ ልውጣ ለማሰኘት ሊጠራ የሚገባው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስም ምን አለ?
ዮሐንስ በእናቱ ሆድ ሳለ የድንግል ማርያምን ድምፅ ስለሰማ ከተወለደ በኋላ የዓለምን ድምፅ መስማት አስጠልቶት ወደ በረሃ ሸሸ፡፡
አረጋዊው ስምዖን 'ዓይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ' እንዳለ ዮሐንስም 'ጆሮዎቼ የእናትህን ድምፅ ሰምተዋልና ባሪያህን አሰናብተኝ' ብሎ ለዓለም የሞተ ሆኖ በበረሃ ኖረ፡፡ ድንግሊቱን የሰሙ ሰዎች ልባቸው ወደ ምናኔ ሕይወት ያዘነብላል፡፡ ወደ ምድረ በዳ ሔደው ድንጋይ ተንተርሰው ሲተኙ ደግሞ እንደ ያዕቆብ እግዚአብሔር በላይዋ የተቀመጠባትን መሰላል ያያሉ፡፡
በማሕፀን የነበረውን ዮሐንስን በትኩረት ሳስበው በቤተ ክርስቲያን ያሉ የዋሀን ምእመናንን ይመስለኛል፡፡ በድንግል ማርያም ፍቅር ልባቸው እየነደደ ስምዋን ሲሰሙ ፣ ምስጋናዋን ሲያዩ የሚናገሩት የሚጠፋቸው ፣ እመብርሃንን እየወደዷት ቃላት አሳክተው ስለ እርስዋ ለመናገር ግን አንደበት የሚያጥራቸው ምእመናን ይታዩኛል፡፡ በቅኔ ማኅሌቱ ዳር ቆመው ማኅሌት ሲቆም ለጌታና ለእናቱ ምስጋና ሲቀርብ እንደ ዮሐንስ የሚይዙት የሚጨብጡትን አጥተው በደስታ የሚዘልሉ ፣ አንድም ቃል ከአፋቸው ሳይወጣ በሐሴት የሚሰግዱ ብዙ የዋሃን ምእመናን ትዝ ይሉኛል፡፡
ወዳጄ አንተም ድንግሊቱን ለማመስገን እንደ ዮሐንስ መናገር ካቃተህ ብዙ አትጨነቅ፡፡ መንፈስ ቅዱስን የተመላች እናትህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከኤልሳቤጥ በላይ ለድንግሊቱ የሚሆን ብዙ ምስጋና አላትና ለንግግርህ ሳትጨነቅ በደስታ እየዘለልህ አጅባት፡፡ በእናትህ ቤተ ክርስቲያን ሆድ ውስጥ እንደ ያዕቆብና ኤሳው ለብኵርና እየተጣላህ ሆድዋን መርገጥህን ትተህ እንደ ዮሐንስ ለምስጋናና ስግደት ከተጋህ ቤተ ክርስቲያን ፍቅርህን አይታ ምስጋናን ታስተምርህና እርስዋ 'የጌታዬ እናት አንዴት ወደ እኔ ትመጣለች' እንዳለች አንተም ነፍስ ስታውቅ እንደ ዮሐንስ 'ጌታ ሆይ አንተ አንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?' ብለህ ለመናገር ትበቃለህ፡፡
እዚህ ላይ ለዘጠኝ ወር ዲዳ የነበረው የሊቀ ካህናቱ ዘካርያስን ነገር ሳስበው እጅግ አሳዘነኝ፡፡ ድንግሊቱ በቤታቸው ሦስት ወራት ስትቆይ ዘካርያስም የማገልገሉ ወራት ተፈጽሞአልና በዚያ ነበረ፡፡ ሆኖም የድንግል ማርያምን ድምፅዋን እንዳይሰማ መልአኩ ጆሮውን ዘግቶታል፡፡ የድንግል ማርያም ድምፅ በኤልሳቤጥ ጆሮ ሲንቆረቆርና ዮሐንስን ሲያዘልል ዘካርያስ ግን ከማየት በቀር አምላክን ፀንሳ የመጣችዋን ድንግል ድምፅ ለመስማት አልቻለም፡፡ ስለ እርስዋ ለመናገር እና ገብርኤል እንደነገረው የዘለለው ሕፃን ዮሐንስ ለጌታ መንገድ የሚያሰናዳ መሆኑን እንዳይናገር አንደበቱ ተይዞአል፡፡ የዘካርያስ ሁኔታ ጊዜያዊም ቢሆን እጅግ ያሳዝናል፡፡ በኋላ ግን ተአምረኛው ልጁ 'የሚጮኽ ሰው ድምፅ' የተባለ ዮሐንስ ሲወለድ ስሙን በመጻፍ ብቻ ልሳኑ ተከፍቶለት ከድንግሊቱ መዝሙር ጋር የሚመሳሰል ምስጋናን ቢያቀርብም ድንግል ማርያም ቤቱ በከረመችበት ጊዜ ስለእርስዋ ቤቱ እያለች መናገርም ሆነ እርስዋን መስማትም አለመቻሉ ያሳዝናል፡፡
ዘካርያስስ ተይዞ ነው ፤ የበለጠ የሚያሳዝኑት ግን ስለ ድንግል ማርያም መናገርም ፣ መስማትም የማይወድዱ ሰዎች ናቸው፡፡ የድንግል ማርያምን ድምፅ ሰምተው እንደ ዮሐንስ የሚዘልሉትንና በታላቅ ድምፅ የሚጮኹትን በትዝብት እያዩ ምንም ተሳትፎ የሌላቸው ! ልሳን እያላቸው ስለ ድንግል ማርያምና ልጅዋ የማይናገሩ ፣ ጆሮ እያላቸው ውዳሴዋን የማይሰሙ ሰዎች ግን መልአክ ሳይቀሥፋቸው ራሳቸውን የቀሠፉ ናቸው ብል እንደ መሳደብ ይሆንብኝ ይሆን? ከሆነስ ይቅር፡፡
("የብርሃን እናት" /በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ/ ከሚል የተወሰደ)
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"በተራራማው"
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሰኔ ፴
ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
ሰኔ ሠላሳ በዚህች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ። ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው። በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጐረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው።
በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን አይሆንም ዮሐንስ ይባል አለች። ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም አሏት። አባቱንም ጠቅሰው ማን ሊባል ትወዳለህ አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም 'የልዑል ነቢይ' እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ።
ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው።
ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ።
"የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ" እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እነሆ ብሎ ኢሳይያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለሱ እንዲህ አለ። "በፊትህ ጐዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልእክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ።'
ራሱ መድኃኒታችንም ስለርሱ ሲናገር "ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም" ብሏል። ይህ የእግዚአብሔርን ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና።
ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ፡፡
©ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox