ethiopian_orthodox | Unsorted

Telegram-канал ethiopian_orthodox - የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

30344

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Subscribe to a channel

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሐዋርያት ተባበሩ፤
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ፤
ቃሉን አስተማሩ።

ካረገ በኋላ በአስረኛው ቀን፤
ወደ አለም ላከው ጰራቅሊጦስን።

በዝግ ቤት ውስጥ ቆዩ ቀኑን ሲጠብቁ፤
የተሰጣቸውን ተስፋውን እስኪያውቁ።

ቀኑም ደረሰና በሃምሳኛው እለት፤
ተሰብስበው ሳሉ በአንድነት ፀሎት፤
መንፈስ ቅዱስ ታየ በነደ እሳት።

ያ የተነገረው ያ የተስፋ ቃል፤
ወረደ ከሰማይ በእሳት አምሳል።

ጴጥሮስ አሳመነ ሶስት ሺ ነፍሳት፤
ያን ጊዜ ገሊላ በሰጠው ትምህርት።

ከሶስት አካል አንዱ መንፈስ ቅዱስን፤
ልኮ አናገራቸው ሁሉን በልሳን።

ሐዋርያት ተባበሩ፤
በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ፤
ቃሉን አስተማሩ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ስለተባለበትና ተስፋ በተሰጣቸው በኀምሳኛው ቀን ወርዶ ስለ ሠራው ሥራ እንዲህ በማለት ያብራራል። ‹‹ወመንፈስ ቅዱስኒ ኢተሰምየ ጰራቅሊጦስሃ ዘእንበለ አመ ይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ እፌኑ ለክሙ ካልአ ጰራቅሊጦስሃ። ጰራቅሊጦስ ብሂል ናዛዚ ብሂል በነገረ ጽርዕ ……መንፈስ ቅዱስም ጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሌላውን አጽናኝ እልክላችኋለሁ›› ከማለቱ በፊት ጰራቅሊጦስ አልተባለም ጰራቅሊጦስ ማለት በጽርዕ ቋንቋ አጽናኝ ማለት ነው ስለምን አጽናኝ ተባለ ደቀ መዛሙርቱ ወልድ ካረገበት ቀን ጀምሮ ጰራቅሊጦስ እስከ ወረደበት ቀን ድረስ ያለቅሱ ነበረና ስለዚህም ወልድ መንፈስ ቅዱስን ጰራቅሊጦስ አለው። የስሙ ትርጓሜ ግን አስቀድመን እንደተናገርነው አጽናኝ ማለት ነው። (ዮሐ. ፲፬፥፲፭)

በዓለ ጰራቅሊጦስ የሚከበረው ርደተ መንፈስ ቅዱስን መሠረት በማድረግ በመሆኑ ምክንያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል ነው፤ በዕለቱም ኢየሩሳሌም በተባለችው ቤተክርስቲያን ስለመጽናት፤ ከግለኝነት ይልቅ መንፈሳዊ አንድነትን ስለማስቀደም እና ስለመጸለይ እንማራለን፡፡
በዓለ ትንሣኤውን በቸርነቱ በሰላም እንድናሳልፍ ፈቅዶ እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ጠበቀን፣ አሁን ደግሞ በጾም፣ በጸሎት ሆነን እርሱን የምናመሰግንበትን ወቅት ስላመጣልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁን፤ አሜን፡፡
ምንጮች፤

መዝገበ ታሪክ፣ ክፍል ፪፤ መምህር ኅሩይ ኤርምያስ፤ ፲፱፻፺፭ ዓ.ም፤ ገጽ ፹፬-፹፭፡፡

መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፲፰ ቀን፣ መጽሐፈ ምሥጢር፡፡

መጽሐፈ ግጻዌ፡፡

ማኅቶተ ዘመን፣ መምህር በሙሉ አስፋው፤ ፳፻፩ ዓ.ም፤ ገጽ ፻፺፭-፪፻፬፡፡


ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የትምህርት ጥቅም
መማር የሚኖርብህ ልጅ በመሆንህ ተገደህ ወይም ምንም ምርጫ ስላጣህ መሆን የለበትም፡፡ ትምህርት ብዙ ጥቅም እንዳለው ዐውቀህ ከልብ በመነጨ ፍላጐትና ጥረት ብትማር ለወደፊት ኑሮኽ ምን ዓይነት ባልንጀራ ማፍራት እንዳለብህ፣ ምን ብትሠራ እንደምትጠቀምና በሕይወትህ ዙሪያ ለሚፈጠሩ የሕሊና ጥያቄዎች በቀላሉ መልስ እንድታገኝ ጥሩ መሠረት ይጥልልሃል።
ትምህርት ሌሎች ሰዎች ክዚህ በፊት የሠሩትን ወይም አሁን በመሥራት ላይ ያሉትን ነገሮች ለማወቅ ያስችላል፡፡ በሥራቸውም የተሳካላቸውንና ውድቀት ያስከተለባቸውን አካሄድ በመለየት በሙከራ ጊዜ ሳታጠፋና በእነርሱ ላይ የደረሰውም ውድቀት ሳይደርስብህ የትኛ ውን ጐዳና መከተል እንዳለብህ ለመወስን ይረዳሃል፡፡
ከልብ የተማረ ሰው ጊዜውን ጠብቆ መጠቀሙ አይቀርም።የተማረውን ትምህርት ለሌሎች ለማስተማር፤ የፈጠራ ሥራዎችን በመሥራት፣ ወይም ተምሮ ባገኘው ሙያ ምንደኛ ሆኖ በሚያገኘው ግቢ ራሱን ማስተዳደር ይችላል ። ከዚህም በተጨማሪ የሙያ ተሰጥኦቹን በመጠቀም ያለአግባብ የሚያወጣውን ወጪ መቀነስና ለራሱ የተመቻቸ ሁኔታን ሊፈጥር ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡- የምግብ አዘጋጃጀት ትምህርትን የተከታተለ አንድ ሰው የሚፈልገውንና የሚስማማውን የምግብ ዓይነት በማዘጋጀት ጤናውን ለመጠበቅ ከመቻሉም በላይ መመገብያ ቤቶችን (ሆቴሎችን) በመጠቀም የሚያወጣውን ያልተመጣጠነ ወጪ በመቀነስ ራሱን ለመርዳት ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ እንድ የቴክኒክ ሙያ ሥልጠና የወሰደ ሰው በዙሪያው ከሚገኙ ነገሮች በመጠቀምና ወጪ ሳያስፈልገው ልዩ ልዩ መገልገያዎችን ለራሱ ማበጀት ወይም የተበላሹ ንብረቶቹን ያለተጨማሪ ወጪ ራሱ ሊጠግናቸውና ሊያድሳቸው መቻሉም ከመማር የሚገኝ ጉልህ ጥቅም ተደርጐ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
አንድ ሰው የተማረውን ትምህርት በቀጥታ በሥራ ላይ ለማዋል በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ቢገኝ እንኳን ትምህርት አይጠቅምም ለማለት አይቻልም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰው ምንም እንኳን በተማረው ትምህርት በቀጥታ ገቢ አግኝቶ ተጠቃሚ ባይሆንም ትምህርቱ በሌላ አቅጣጫ ተጠቃሚ እንደሚያደርገው ማስተዋል ይገባል:: ምክንያቱም መማር ለመማር ከተዘጋጀንበት መደበኛ ትምህርት ውጭ በሂደቱ ትዕግሥትን፣ ትጋትን፣ ሐሳብን ሰብስቦ የመከታተል ችሎታን፣ መጠየቅንና የማንበብ ልምድን እንድናዳብር ከማድረጉም በላይ አእምሮአችን እንዲሰፋ ያደርጋል።የሠሩበት አካል እንደሚጠነክር ሁሉ የተማሩበትም አእምሮ መዳበሩ አይቀርም። ይህም በዋጋ ሊተመን የማይችል የትምህርት ሁለ ገብ ጥቅም ነው።
ቀጣይ ምዕራፍ ዐሥር ክፍል ሦስት :
👉«በትምህርት መኖር ጥበቃ ነው»
👉«የመንፈሳዊ ትምህርት ጥቅም »
👉«ትምህርት ጉዳት ይኖረዋል »
በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

መንፈሳዊ ትምህርት እንደ ራት ሲሆን ሥጋዊ ትምህርት ግን እንደ ዳረጎት ነው:: ከእራትና ከዳረጐት ዳረጎትን የሚመርጥ ማንም የለም:: ዳረጐት እራት አይሆንምና፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ጊዜያዊ እንጂ ዘለዓለማዊ ጥቅም የሌላት ሥጋዊ ጥበብ ከመንፈሳዊ ጥበብ መቅደም የለባትም፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንኛውም ሰው በሕይወት ዘመኑ ማስቀደም ያለበት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት የሚረዳውን ነገር መሆን እንዳለበት ሲገልጽ «አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል» በማለት ተናግሯል:: ማቴ6÷33
ሠለስቱ ምዕት ልጆችና ወጣቶች አስቀድመው ምን መማር እንዳለባቸው በትእዛዝ መልክ እንዲህ ብለዋል- «ቅድመ መሀርዎሙ ለውለድክሙ መጽሐፈ ሲራክ ወሰሎሞን ወመዝሙረ ዳዊት» ይህም «አስቀድማችሁ ለልጆቻችሁ የሲራክን የሰለሞንን መጻሕፍትና የዳዊትን መዝሙር አስተምሯቸው» ማለት ነው:: ይልቁንም «አስቀድማችሁ» እና «አስተምሯቸው» የሚሉት ቃላት ልጆች ከዘመናዊ ትምህርት አስቀድመው መንፈሳዊውን ትምህርት እንዲማሩ የማድረግ ኃላፊነት የወደቀው በወላጆች ላይ መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡
ይህ የአበው ትዕዛዝ መንፈሳዊው ትምህርት ከሥጋዊው ትምህርት መቅደም እንዳለበት ብቻ ሳይሆን ከመንፈሳዊ መጻሕፍትም ለወጣቶች ከላይ የተጠቀሱት መጻሕፍት መቅደም እንዳለባቸው ያስረዳል።ምክንያቱም እነዚህ መጻሕፍት ወጣቶች በአእምሮ የበሰሉ እንዲሆኑ ከማድረጋቸውም በላይ ሥጋዊውንና መንፈሳዊውን ጥበብ አጣምረው ለመረዳት እንዲችሉ ያደርጓቸዋል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎሰ ለሃይማኖት ልጁ ለጢሞቴዎስ በላከው መልእክቱ «ማንም ባልቴት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሩአት፥ እነርሱ አስቀድመው ለገዛ ቤተሰቦቻቸው እግዚአብሔርን መምሰል ያሳዩ ዘንድ ለወላጆቻቸውም ብድራትን ይመልሱላቸው ዘንድ ይማሩ» በማለት ልጆችና ወጣቶች አስቀድመው ምን መማር እንዳለባቸው በግልጽ ተናግሯል፡፡ መማር ያለባቸውም ተገልጦ ሊታይ የሚችል «እግዚአብሔርን መምሰል›› እና ወላጆቻቸውን በመጦር መንከባክብ ማለትም «ብድራትን መመለስ»መሆን እንደሚገባው አስረድቷል።ወላጆችን መርዳትና እግዚአብሔርን መምሰል የሚገኝበት ትምህርት መንፈሳዊ ትምህርት መሆኑ ግልጽ ነው።ይህን ተረድቶ መንፈሳዊውን ትምህርት አስቀድሞ መማር ምን ያህል እግዚአብሔርን እንደሚያስደስተው «ይህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና የተወደደ ነውና» በማለት ጨምሮ ገልጧል፡፡ 1ጢሞ5፡4
አንድ ክፉ ሱስ ከተጸናወተህ በኋላ ምንም እንኳን ጐጂነቱን በበቂ ሁኔታ ብታውቅ ካንተ ለማራቅ እጅግ ይቸግርሃል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ዓለማዊ ትምህርትን አስቀድመህ ተምረህ ከሃይማኖትህ ጋር የሚጣረሱትን ጽንሰ ሐሳቦች ከተለማመድካቸው በኋላ እነዚህን አስወግደህ ሃይማኖተኛ ለመሆን መቸገርህ አይቀርም።ዘመናዊ ትምህርት ለማመን ዳተኛ ያደርጋል፣ የሕሊና ሙግት ይፈጥራል፣ ጥያቄ እንድታበዛ ያደርጋል፤ ከማመን ይልቅ እንድትመራመር ይገፋፋሃል፡፡ እነዚህ ነገሮች ደግሞ በመንፈሳዊ እይታ መጠነኛ ጥቅም ሲኖራቸው የሚያመዝነው ግን ጉዳታቸው ነው፡፡ እንኳን ዘመናዊ አስተሳሰብና ትምህርት ወደ ውስጥህ ቀድሞ ገብቶ ይቅርና ትምህርተ ሃይማኖትን አስቀድመህ ከተማርክ በኋላ እንኳን ዘመናዊውን ትምህርት ስትማረው በመንፈሳዊነትህ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድርብሃል፡፡ ለዚህ ምስክር የሚሆኑ በመጀመሪያ በሃይማኖት ትምህርት ከተደላደሉ በኋላ በዘመናዊ ትምህርት መርሕና አስተሳሰብ ተውጠው ሃይማኖተኛ እንደነበሩ ይቅርና ስለሃይማኖት ሰምተው እንኳን ማወቃቸው የሚያጠራጥሩ በርካታ ሰዎች በዙሪያህ ይገኛሉ።ስለዚህ ከምንም በላይ የሚጠቅመው ትምህርተ ሃይማኖትን አስቀድሞ መማር ነው።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የትምህርት ዓይነቶች
ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ምድራዊና ሰማያዊ፣ ሥጋዊና መንፈሳዊ በማለት ጥበብን በሁለት በመክፈል ጽፏል። ስለምድራዊ ጥበብ ሲናገር «ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፣ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው» በማለት ሲገልጸው ሰማያዊውን ጥበብ ደግሞ «ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፡ በኋላም ታራቂ፣ ገር፡ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት፡፡›› በማለት ይገልጻታል። ያዕ3፥15(17) ጥበብ ለሁለት ወገን ተከፈለች ማለት ትምህርትም ለሁለት ይከፈላል። ምክንያቱም ጥበብ የሚገኝ ከትምህርት ነውና፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ትምህርትን ትምህርተ ክርስቶስና ትምህርተ ሰብእ (የሰው ትምህርት) በማለት ለሁለት ክፍለ አስረድቷል፡፡ ይህም «እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓላማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ::» ባለው ይታወቃል።ቆላ2÷8
ስለዚህ መንፈሳዊውን ትምህርት የክርስቶስ ትምህርት፣ መንፈሳዊ፣ የቤተክህነት፣ ሰማያዊ፤ ጥንታዊ በማለት ስንጠራው ዘመናዊውን ትምህርት ደግሞ ዓለማዊ፣ ምድራዊ ፣ሰብአዊ፣ ወግ፣ ፍልስፍና፣ ሥጋዊ ትምህርት በማለት ልንጠራው እንችላለን፡፡
ከቤተ ክርስቲያን የጸሎት መጻሕፍት መካከል አንዱ የሆነው መስተብቁዕ መንፈሳዊውን ትምህርት «የመለኮት ትምህርት» በማለት ይጠራዋል፡፡ «ወሴሲ ልበነ በመለኮተ ትምህርት ወበለብዎ ዘእምኀቢከ» ፍችውም «በመለኮት ትምህርት ልቡናችንን መግብ፡ ከአንተ ዘንድ የሚገኘውንም ማስተዋል» ማለት ነው። (መስተብቁዕ በእንተ ዝናማት)
በአሁኑ ጊዜ ሥጋዊውን ትምህርት በሀገራችን ለማዳረስ ኃላፊነት የተሰጠው ክፍል በሚኒስቴሮች መሥሪያ ቤት የትምህርት ሚኒስቴር ሲሆን እውነተኛውን መንፈሳዊ ትምህርት ለዓለም እንድታዳርስ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሙሉ ኃላፊነትና ትዕዛዝ የተቀበለች ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ይሁን እንጂ ቤተ ክርስቲያን በሀገራችን ለመንፈሳዊውም ሆነ ለሥጋዊው ትምህርት መሠረት እንደ መሆኗ መጠን ዘመናዊውንም ትምህርት በሀገራችን ከማስፋፋት የቦዘነችበት ጊዜ የለም።
በሀራችን በኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርት በማይታወቅበት ጊዜ እንኳን ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቷን በአስደናቂ መልኩ ቀርጻ ከፍልስፍና (ከዘመናዊ ጥበብ) ጋር ጐን ለጐን ስታስተምር ቆይታለች።ከዚህም በተጨማሪ ለሀገርና ለአህጉር መኩሪያ የሆነ ብቁ ፊደል ቀርጻ ማስረከቧ ሳያንሳት የፊደላቱን ምሥጢር፣ መልክና ቅርጽ በማስለየት እስከዛሬ ድረስ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች ነው።ይህን ሁሉ የመረመረ ሰው ቤተ ክርስቲያን ለመንፈሳዊ ትምህርት ብቻ ሳይሆን ለሥጋዊ ትምህርት መሠረት መሆኗን ለማወቅ አይቸገርም፡፡
ሕንፃ ከማነጽ፣ ፍትሕት ከመፍታት፣ ከማጥመቅ፣ ከመቀደስ ይልቅ ቀዳሚው የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ማስተማር ነው:: ማስተማርና ማሳመን ከሌለ እነዚህ ምሥጢራት በሙሉ ላላመነ ሰው የሚፈጸሙ አይደሉምና፡፡ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችው በትምህርተ ወንጌል ነው። «ሊቀ ማኅበር» የሚባል ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለትም ሦስትም ሆነን በምንሰበሰብበት ጊዜ በመካከላችን ይገኛል፡፡ «ያዘዝኋችሁንም እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ» ማቴ28፥20፤18፥20 በማለት ከቃል ኪዳን ጋራ ቤተ ክርስቲያን በትምህርተ ወንጌል እንድትመሠረት የፈቀደ ራሱ ነውና፡፡
ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ማስተማር የዘወትር ሥራዋ ነው፡፡ ትምህርቷም የሕይወት ትምህርት ነው።ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ «እናት አባት ልጆቻቸውን የእነርሱ ለማድረግ ቢፈልጉ ለቤተ ክርስቲያን ይስጡ፡፡ ከደግ በቀር ክፉ ነገር አታስተምራቸውምና፡፡›› በማለት የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ለልጆች ያለውን ጠቀሜታ አስረድቷል፡፡
የትምህርተ ወንጌልን አገልግሎት ቸል በማለት ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች ቅድሚያ የሚሰጡ የቤተ ክርስቲያን አካላት ቢኖሩ ዋናውን ጉዳይ ቸል ስላሉ ከዚህ ቀጥሎ ባለው የወንጌል ቃል ይገሠጻ።«በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፡ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህንን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር፡፡ እናንተ ዕውሮች መሪዎች ፡ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ፡፡» ማቴ 23፥23
ዋናው የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ መንፈሳዊ ትምህርት ማስተማር ነውና።
ከቤተ ክርስቲያን ባሻገር ወላጆች ልጆቻቸውን «በተግሣጽና በምክር» የማሳደግ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ኤፌ6፥4 ሠለስቱ ምዕትም በሃይማኖተ አበው «ለልጆችህ አርምሞንና ጸጥታን አስተምራቸው፤ ሰነፍ አትሁን።›› በማለት ወላጆችን መክረዋል፡፡ ልጆቻችውን የማያስተምሩ ወላጆች ቅጣት እንደሚገባቸው ቅዱስ ባስልዮስ «ልጆችን መልካም ትምህርት ከማስተማር ቸል የሚሉ ወላጆች በሌላ በኩል ለልጆቻቸው ደግ ቢሆኑ በዚህ ብቻ ሊቀጡ ያስፈልጋቸዋል» በማለት ተናግሯል፡፡ አስቀድሞ እንደተገለጸው ሥጋዊና መንፈሳዊ ጥበባት በምድሪራችን ይገኛሉ፡፡ ሁለቱም በአቀራረባቸው፣ በዓላማቸውና በሚሰጡት ጠቀሜታ እጅግ ይለያያሉ። አንዳንድ ጊዜ የሚስማሙበት የጋራ ነጥብ ሲኖራቸው ብዙ ጊዜ ደግሞ እጅግ የሚቃረኑበት ቦታ አለ።ታዲያ ሰው አስቀድሞ መማር የሚኖርበት የትኛውን ትምህርት ነው?

ቀጣይ ምዕራፍ ዐሥር ክፍል ኹለት:
👉 «የትኛው ይቅደም»
👉«በሚገባ መማር»
👉«የትምህርት ጥቅም»
በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ዐሥር ክፍል አንድ
.................................................
➺ወጣቶችና ትምህርት

ትምህርት ዕድሜን አይወስንም። ለመማር ፍላጎት ያለው ሰው ሁሉ ለመማር ይችላል፡፡ ወጣቶች ግን ከሁሉ ይልቅ ባገኙት አጋጣሚ ተጠቅመው መማር ይኖርባቸዋል። ምክንያቱም ወጣትነት በሁሉም አቅጣጫ ለትምህርት ምቹ ወቅት ስለሆነ ነው።
በወጣትነት ዘመን ሰውነት እየጠነከረ የመሄዱን ያህል አእምሮ'ም እየሰፋና እየዳበረ ይሄዳል፡፡ መጽሐፍ ስለ ወጣቶች ሲናገር «በሠላሳ ዘመን ናላ ይመላል አእምሮ ይደላደላል» ይላል።(ሕዝቅኤል ትርጓሜ) ከዚህ ትርጓሜ ወጣትነት በራስ ቅል ውስጥ የሚገኝ የዕውቀት መገኛ (አንጐል) ወደ መጨረሻ የእድገት ደረጃው የሚደርስበት ጊዜ መሆኑን እንረዳለን፡፡ ስለዚህ ወጣቶች ለመማር ፈቃደኛ ከሆኑ ለማወቅ የተመቻቸ ተፈጥሮ አላቸው፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቆጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ።» በማለት የተናገረው ቃል በልጅነት ዘመን ያለው ዐላዋቂነት በጎልማስነት ዘመን እንደሚሻርና በወጣትነት ዘመን ኣእምሮ እንደሚዳብር ያስረዳል፡፡ 1ቆሮ13:11 ይህ የዳበረ የወጣቶች አእምሮ ደግሞ የትምህርት ሂድትን ቀላል ያደርግላቸዋል፡፡
መጽሐፍ ጻድቃንን ከዕውቀት አንጻር በወጣት ሊመስላቸው ኃጥአንን ደግሞ በሕፃናት ይመስላቸዋል፡፡ ሕፃናት ፍትፍትና እሳት ለይተው እንደማያውቁ ኃጥአንም ክፉና በጎን ለይተው በማወቅ አይሠሩም:: ወጣቶች ግን ክፉና ደግን ለይተው እንደማያውቁ ጻድቃንም ጽድቅና ኃጢአትን ለይተው በማወቅ ይሠራሉ። ስለዚህ ወጣቶች ከዕውቀት አንጻር በጻድቃን ተመስለዋል፡፡ (ምሳ 1፣ 4 ትርጓሜ)

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ስለ ወንድ «ወንድ ፀጉሩን ቢያስረዝም ነውር እንዲሆንበት፡ ሴት ግን ጠጉርዋን ብታስረዝም ክብር እንዲሆንላት ተፈጥሮ እንኳን አያስተምራችሁምን" በማለት ቅዱስ ጳውሎስ ተናግሯልና ወንድ ፀጉሩን ማስረዘም አይገባውም።ሠለስቱ ምዕትም ስለ ፀጉር በተናገሩበት በፍትሐ ነገሥት " ኢታስተርኢ ስእርተከ በአፍኣ» ብለዋል፡፡ ይህም ፀጉርህን ስበህ እስክታየው ድረስ አታሳድገው» ማለት ነው::
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስእለት ስለ ነበረበትና አይሁድም ስለ እርሱ ያላቸውን የተዛባ አመለካከት አስተካክለው ሥርዓትና ሕግ ኣክባሪ መሆኑን እንዲያውቁ ለማድረግ ሁለት ጊዜ ፀጉሩን ተላጭቷል፡፡ የሐዋ21፥24፤ 18÷18 ሠለስቱ ምዕት ከዚህ ተነሥተው ወንዶች ይልቁኑም ካህናት ፀጉራቸውን እንዳያሳድጉ ሥርዓት ሠርተዋል።
ቅዱስ ጳውሎስ ስእለት ስለነበረበት ተላጨ እንጂ ተላጩ ወይም ጸጉራችሁን አሳጥሩ የሚል ሥርዓት የለም ማለት አይገባም።በእርግጥ ቅዱስ ጳውሎስ የተላጨው ለትሩፋት ብሎ ነው።ምክንያቱ ስእለት የነበረ ቢሆንም «የቅዱስ ጳውሎስ ሥራ ሥርዓት ለመሆን አያንስም።» በማለት አበው ሠለስቱ ምዕት ወንዶች ፀጉራቸውን እንዳያስረዝሙ ሥርዓት አድርገው ጠቅሰውታል፡፡
ወንዶች ይልቁኑም ካህናት ፀጉራቸውን አያሳድጉ የሚለው ትእዛዝ ናዝራውያንን አይመለከትም። በመጽሐፍ ቅዱስ እንደ መልከ ጼዴቅ፣ ሶምሶን፣ ነቢዩ ኤልያስና መጥምቁ ዮሐንስን የመሳሰሉት ናዝራውያን ጸጉራቸውን አይላጩም ነበር፡፡ ዘኁ6፥5፤ መሳ13÷5
ወንዶች ፀጉራችንን እንድናሳጥረው ብቻ ሳይሆን በምናሳጥረበት ጊዜም ጋሜ፣ ቁንጮ እያልን ጌጥና ልዩ ልዩ ቅርጽ እንዳናወጣ ታዘናል። አበው ወኢትኅድግ ላዕሊከ ሥርጋዊ እም ጸጉረ ርእስከ» ብለዋል። ይኽም «በፀጉርህ ላይ ጌጥ አትተው» ማለት ነው።
በሐዋርያት ዘመን የነበሩ ሴቶች ረጅም ፀጉራቸውን በመጠቀም እንደ ስጋጃ በመሥራትና ለጣዖት በመጋረድ ለባዕድ አምልኮ እስከ መጠቀም ደርሰው ነበር። ይህ የሚያሳየው ፀጉር ተገቢ ላልሆነ ልዩ ልዩ አላማ ሊውል መቻሉን ነው። ስለዚህ ወንዶች ፀጉራቸውን በማስረዘም ትኩረት ለመሳብና ለልዩ ልዩ ዓላማ ቢጠቀሙበት መጨረሻቸው ላያምር ይችላል፡፡
አቤሴሎም የተባለው የንጉሥ ዳዊት ልጅ ቆንጆ መልኩን ፀጉሩን ከማስረዘም ጋር አስተባብሮ የብዙዎችን ቀልብ ለመሳብ ችሎ ነበር። ይህንኑ ማራኪነት ደግሞ የገዛ አባቱን ከዙፋኑ ለማባረርና ብዙ ድምፅ ለማግኘት ተጠቅሞበታል።ሙከራው ለጊዜው የተሳካለት ቢመስልም በመጨረሻ ግን መጥፊያው የሆነው ወዶ ያስረዘመው የራሱ ፀጉር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ የአቤሴሎምን አሟሟት እንዲህ ይተርከዋል።«አቤሴሎም በበቅሎ ተቀምጦ ነበር ፣ በቅሎውም ብዙ ቅርንጫፍ ባለው ከታላቅ ዛፍ በታች ገባ፣ ራሱም (ፀጉሩም) በዛፉ ተያዘ ፤ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠለጠለ።..... ኢዮአብም.... ሦስት ጦሮች በእጁ ወስደ፣ አቤሴሎምም ገና በዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ሕያው ሳለ በልቡ ላይ ተከላቸው ዐሥሩም የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬዎች ከበቡት አቤሴሎምንም መትተው ገደሉት::» 20ሳሙ 18÷9-15
ከዚህ መንፈሳዊ ታሪክ በመነሣት ወጣት ወንዶችና ሴቶች ስለ ፀጉራቸው በሚገባ ማሰብና ሥርዓት ባለው መልኩ መያዝ ይኖርባቸዋል።ከዚህ አልፎ ግን ከዘመኑ ፋሽን ጋር እንደፈለጉ ፀጉራቸውን ቢለዋውጡ በኅብረተሰብ ዘንድ በብልሹ ስም ከመታወቅ አንሥቶ በልዩ ልዩ መንገድ ሳይጎዱበት አይቀርም።እንደ አለባበስ ሁሉ የፀጉር አያያዝም ስለማንነት አፍ አውጥቶ ይናገራልና።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ" ሁሉ በእናንተ ዘንድ በአግባብና በሥርዓት ይሁን" በማለት መክሮናል። በክርስትና ሥርዓት የሌለው ነገር የለም።ነገር ግን አንዳንዶች ስለ አመጋገብ፣ አለባበስ፣ ፀጉር አበጣጠርና የመሳሰሉ ነገሮች የተሠሩትን ሥርዓቶችና መመሪያዎች ሲመለከቱ በሥርዓት መኖርን ያልለመዱ ከሆነ ነጻነት እንደማጣት፣ መብትን እንደመገፈፍና ብዙ አማራጮች እንደማጣት አድርገው ይቆጥሩት ይሆናል።ነገር ግን በመንፈሳዊ ዓይን ለሚመለከተው ደግሞ ምልከታው የተገላቢጦሽ ነው።ክርስቲያኖች በሥርዓት አየኖሩ ነገር ግን ስለ ፀጉር አበጣጠርና ስለ አለባበስ እጅግ ብዙ ከሥርዓት ውጭ አማራጭ እንዳለ ያውቃሉ። ጥያቄውንም የመንፈሳዊነት እንጂ የመብት ጉዳይ አለመሆኑን ይረዳሉ፡፡ ምክንያቱም ለፈጣሪ ስለ መገዛት ንቆ በመተው እንጂ እንደ ክርስቲያኖች ነጻ ፍጥረት ሊኖር እንደማይችል ያስተውላሉና።
ወጣቶች በሙሉ ለማንኛውም ነገር ከመንፈሳዊነት ሳይናወጹ ሊያገኙት የሚችሉት ብዙ አማራጭ መኖሩን ማወቅ ይገባቸዋል።ይልቁንም ብዙ ነገሮች በዓይነትም ሆነ በመጠን በብዛት በሚገኙበት በዚህ ዘመን የክርስትና ጎዳና ጠባብ አይደለችም። እንደ ዓለማዊ ነገሮች ሁሉ መንፈሳዊ ነገሮችም መሠረታቸውን ሳይለቁ ዘመናዊና ምቹ ሆነው በቀላሉ እንደሚገኙ ከማንም የተሠወረ አይደለም። ልዩነቱ የምርጫ ጉዳይ ብቻ ነው።ስለዚህ መንፈሳዊነት የኑሮ አማራጮችን ያጠባል ማለት አሮጌ አስተሳሰብና ጊዜ ያለፈበት ስለሆን በዘመናዊ አስተሳሰብ መለወጥ አለበት።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ስለ መጋጌጫ ነገሮች ምን ይባላል?
ሰዎች ልብስ የሚለብሱት በዋናነት ሰውነታቸውን ለመሸፈን ቢሆንም በሌላ ዘንድ አምሮ ለመታየት መርጦ መልበስም ተቆጥሮለታል፡፡ የጥንት ዕብራውያን የሚጠጋቸውን ሁሉ ለመማረክ አዘወትረው ሽቶ ይቀቡ፣ ቅባቶችንና መኳኳያዎችን ይጠቀሙ እንደ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል።
ሆኖም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ የሚያመጣላቸውን ነገር ማድረግ የሚፈልጉ ወጣት ሴቶች ዋና ጌጣቸው «በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ» መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ምንም ነገር ቢሆን በልክና እጅግ ባልተጋነነ መልኩ መሆን እንዳለበት አለመዘንጋት ይጠቅማል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ «ነገርን ሁሉ በልክ» እንድናደርግ መክሮናል፡፡ 2ጢሞ4÷5
ሌላው ወጣት ሴቶች ሁሉ ማወቅ ያለባቸው ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው እንደሚያመዝን ነው።መዋቢያ ቅባቶች ጥሩውን ደም ግባት ሊያበላሹ ወይም መልከ ጥፉነትን የባሰ መጥፎ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም መጋጌጫ ቅባቶች ከማሳመር በስተጀርባ የሚበልጠውን የተፈጥሮ የወጣትነትን የፊት ጥራት፣ ወዝንና ቁንጅናን የሚደብቅና የሚያበላሽ ጎጂ ጎን አላቸው::
ልጃገረዶች በመዋቢያ ቅባቶች ያለ ልክ መጠቀማቸው ወደ ደካማ ጎናቸው ትኩረትን ከመሳብ ያለፈ ጠቀሜታ የለውም።በተጨማሪም እንዲህ ማድረጋቸው በአንድ በኩል በሌሎች ዘንድ በመጥፎ እንዲተረጎምባቸው ሲያደረግ በሌላ በኩል ደግሞ ከጊዜ በኋላ በውጫዊ መልካቸው ባስተዋወቁት ወይም ባሳዩት ርካሽ አምሳል ጠባያቸው እንዲቀረጽ ተፅዕኖ ሊያደርግባቸው ይችላል።
ኩል፣ ቅባት፣ የጥፍርና የፀጉር ቀለም፣ እንሶሰላና የመሳሰሉትን ነገሮች በሚመለከት እንዲጠቀምባቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ነገሮች ባይኖሩም ጥሩ ጥሩ መመሪያዎች ግን ተሰጥተዋል፡፡ ሌሎች ቅዱሳት አዋልድ መጻሕፍትም የሚሻለውን መንገድ ሳይጠቁሙ አላለፉም።ለምሳሌ፦ የመልክዓ ማርያም ደራሲ ድንግል ማርያምን ሲያወድሱ «ሰላም ለአጽፍረ እግርኪ ዘኢፈቀዳ ለሥርጋዌ ጥምዓታተ ኅምር ምድራዊ » ብለዋል፡፡ ትርጓሜው «እንሶስላ መሞቅና ሌላ ምድራዊ ጌጥን ላልፈቀዱ የእግር ጥፍሮችሽ ሰላምታ ይገባል» ማለት ሲሆን ይህም አፍአዊ ጌጣጌጥን አለመሻት የሚያስመሰግን ቁጥብነትና ግብረ ገብነት በሆኑን ያስረዳል፡፡ ስለዚህ ልጃገረዶች ይህን በተመለከተ ሚዛናዊ ሆኖ መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ (መልክዐ ማርያም)
መጋጌጫን በተመለከተ ወላጆች ለልጆቻቸው ተጨማሪ መመሪያዎች የማወጣት ተገቢ የወላጅነት መብት አላቸው።አንድ ቤት ባለቤቶችን ከሚወክለው በላይ ልጆች ወላጆችን ይወክላሉ።በወላጆቻቸው ስም ይጠራሉና፡፡ ስለዚህ ልጆች የሚሠሩት ሥራ በሙሉ አሳዳጊዎቻቸው ምን ዓይነት ስብእና እንዳላቸው ሊናገር ይችላል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን ክርስቲያን ነን እስካሉ ድረስ በስሙ የተጠሩበትን ኢየሱስ ክርስቶስንም ይወክላሉ፡፡ ስለሆነም ወጣቶች «አለባበሴና የሰውነቴ አቋም ከወላጆቼ ክብርና ማንነት ይልቁንም ከክርስቲያንነቴ ጋር ይስማማልን?› በማለት ራሳቸውን መጠየቅ አለባቸው። አንድ ቤት ፈርሶና ተላልጦ ቢታይ ባለቤቱን አንደሚያስነቅፍ የክርስቲያኖች ሕይወት ቤተ ክርስቲያንንና ወላጆቻቸውን ሊያስነቅፍ ይችላል፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች አባል ለሆኑበት ሰንበት ትምህርት ቤት ደንብና ሥርዓት ተገዢ ቢሆኑና ባያምፁ እጅግ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ አንዳንድ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ስለ አለባበስና ስለመሳሰሉት ሥነ ምግባራት ደንብ እንዳላቸው የታወቀ ነው።

ቀጣይ ምዕራፍ ዘጠኝ ክፍል ስድስት:
👉 ክርስቲያናዊ ፀጉር አያያዝ እንዴት ነው?
👉 ስለ <መልክ> ሊኖር የሚገባ ተገቢ አመለካከት
በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

«ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ› ሲል ሱሪ አትልበስ ማለቱ ብቻ ከሆነ ከሁለት ዓይነት ነገር (ቀለም) የተሠራ ልብስ አትልበስ›› ሲልስ ምን ማለቱ ነው? የሚል ጥያቄ ያስነሣል፡፡ እስኪ ንባቡን ቆም አድርገውና ከላይ እስከ ታች የለበስከው ልብስ ስንት ዓይነት ነገር (ቀለም) እንዳለው ቁጠረው:: ታዲያ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ያለው ይህን አለባበስህን ለመንቀፍ ነውን? አይደለም።«ከሁለት ዓይነት ነገር (ቀለም) የተሠራ ልብስ አትልበስ› ማለቱ ሁለት ዓይነት ሰብእና አትላበስ፡፡ በተጨማሪም «በአንድ ራስ ሁለት ምላስ› እንደሚባለው ቃሉና ሐሳቡ ተለዋዋጭ የሆነ ሁለት ዓይነት ሰው አትሁን ማለቱ ነው።ይህን የመሰለ «ከተልባ እግርና ከበግ ጠጉር በአንድነት የተሠራ ልብስ አትልበስ» የሚል ትእዛዝም አለ፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ አርእስትና ኅዳጉ እየታየ በሚገባ ይተረጎማል እንጂ በዘፈቀደ የሚነገር አይደለምና መጠንቀቅ ያሻል። ዘዳ22፥11፣ Ηሌ19:19
ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በዚህ መልኩ በመተርጎሙ ጠባብ አመለካከት ያላቸው እጅግ በጣም በርካታ ሴቶች ሱሪ ለመልበስ መግቢያ ያገኙ ይመስላቸው ይሆናል፡፡ ምክንያቱም አብዛኞቹ ሴቶች «ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ› የሚለውን ቃል የሚረዱት "ሴት ሱሪ መልበስ አይገባት"እንደሚል ብቻ አድርገው በመሆኑ ነው።ከዚህ ቀደም «ሱሪ» የማይለብሱ ሆነው ይህን ትርጓሜ በማወቃቸው ብቻ «ሱሪ» ለመልበስ የሚነሣሡ ሴቶች እውነት አይነገረን ከተነገረን ግን ዋ! የሚል ዓላማ አንግቦ ሰልፍ የሚወጣን ሰነፍ ሰው ይመስላሉ፡፡
ከላይ የተጠቀሰው ቃል ትርጓሜውን በዚህ መልኩ በግልጽ ማስቀመጥ ያስፈለገበት ምክንያት የቃሉን ምሥጢራዊ ፍቺ ባለማወቅ ብዙዎች «ሱሪ» በሚለብሱ ሴቶች ላይ ያላቸው አመለካከት የተዛባ በመሆኑ አመለካከታቸውን ለማረም እንዲችሉ ነው።አንዲህ ዓይነት ሰዎች ፍርድና ትችት ስለሚያበዙ የእነርሱን አስተሳሰብ ለመገሠጽ ትርጓሜው ተጻፈ እንጂ ሴቶች ሱሪ ይልበሱ ለማለት እንዳልሆነ ልብ ማለት ይገባል።አሁንም ቢሆን ሴቶች ሱሪ አለመልበሳቸው በብዙ መንገድ ጠቃሚ መሆኑንና የመልካም ማንነታቸው መሆኑን መዘንጋት የለባቸውም። በማኅበረሳባችን ዘንድ ሱሪ የወንዶች ልብስ መሆኑ በአብዛኛው ሰው ዘንድ ታምኖ ሳለ ሴቶች ሱሪ ቢለብሱ አርአያን መለወጥ ስለሆነ ስሕተት ከመሆኑም ባሻገር ተረማማጅ (ተለዋዋጭ) ዐመልንና ባሉበት ነገር ያለመወሰንን ሁኔታ የሚያመለክት ነው።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ማርያም አንቲ"
ማርያም አንቲ ደመና ሰማይ ዘአኃዝኪ ዝናመ(፪)
ተክላተ መሬት አዳም ወሔዋን ዘፈረዩ ብኪ ዳግመ(፪)

ከመሬት የተገኙ አዳምና ሔዋን ሕይወት ያገኙብሽ(፪)
ዝናምን የያዝሽ የሰማይ ደመና ማርያም አንቺ ነሽ(፪)
በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ግንቦት ፳፩
ደብረ ምጥማቅ


ከሠላሳ ሶስቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ነው። ደብረ ምጥማቅ በግብፅ ሀገር በምኔተ ገምኑዲ አቅራቢያ የምትገኝ ቦታ ናት። እመቤታችን በስደት ሳለች ጌታ በዚህ ቦታ በስምሽ ዐብይ ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ ስሙንም ደብረ ምጥማቅ ይሉታል ብሎ ነግሯት ነበር። ይኸውም አልቀረ፤ በዚሁ ቦታ በእመቤታችን ስም ቤተክርስቲያን ታንጾ ስሙ ደብረ ምጥማቅ ተብሏል።

በዚህም ዕለት እመቤታችን ከፀሐይ ሰባት እጅ አብርታ ከጉልላቱ ላይ በመንበረ ብርሃን ተቀምጣ መላእክት ሊቃነ መላእክት ከበው ሲያመሰግኗት ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት እጅ ሲነሷት ታይታለች። “እንዘ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኃምሰ ዕለታተ” እንዳለ ደራሲ በልጇ የመለኮት ብርሃን አሸብርቃ መላእክት: ሊቃነ መላእክት: ኪሩቤል: ሱራፌል ከበዋት ነቢያት: ሐዋርያት: ሰማዕታት: ደናግላን: መነኮሳት ሄሮድስ ያስፈጃቸው ሕፃናት ይመጣሉ። ሱራፌል ማዕጠንት ይዘው በእያንዳንዱ እያመሰገኑ ያጥኑ ነበር። ከሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ተከትሎ ቅዱስ መርቆርዮስ በጥቁር ፈረስ በየተራ እየመጡ ይሰግዱላታል።

ከፊቷ ብርሃን የተነሣ 5 ቀን ሌሊቱና ቀኑ አይታወቅም ነበር። በዚህ ጊዜ ልብሳቸውን ወደ ላይ ሲወረውሩላት የፈቀደችውን ተቀብላ ትልክላቸዋለች። ከዚያም ለበረከት ይካፈሉታል። ከተሰበሰቡትም እስኪ እገሌን አስነሺልን እያሉ ሲለምኗት አስነሥታ በሕይወተ ሥጋ ታሳያቸው ነበር። እንዲህ እየሆኑ በፍጹም ደስታ ሰንብተዋል። እስከ አምስት ቀንም ምዕመናኑን አረማውያኑንም አንድ ወገን አድርጋ ስትባርክ ሰንብታለች። ከዚህም በኋላ ምዕመናኑም አረማውያኑም በየዓመቱ እኚህን አምስት ዕለታት በደብረ ምጥማቅ ተሰብስበው የሚያከብሩ ሆነዋል። የበዓሉ መታሰቢያ ከግንቦት 21 እስከ 25 ቀን ነው።

ግንቦት 21 በደብረ ምጥማቅ በገሃድ ተገልጻ ታላቅ ተአምር ያደረገችበት፡፡

ግንቦት 22 በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡

ግንቦት 23 በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡

ግንቦት 24 እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ይዛ ከአረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በመሰደድ ግብፅ አገር የገባችበት ዕለት፡፡

ግንቦት 25 ተወዳጅ ልጇ የደረቁ በትሮችን ተክሎ በተአምራት ያለመለመበት ዕለት፡፡

በዚህ ዕለትም እናታችን፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ለ5 ቀን በግልጽ መታየቷ የሞቱት መነሳታቸው ብርሃን መሆኑ ጨለማ መጥፋቱ የሰውን ልመና መቀበሏ ወዘተ ይነገራል። የቅድስት እናታችን ረድኤት በረከቷ አማላጅነቷ አይለየን፣ ጣዕሟን ፍቅሯን አይለይብን። የዓመት ሰው ይበለን፣ አሜን!
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
“ድንግል ሆይ በሁሉ አንደበት መመስገን የተገባሽ ስለሆነ በሰማይ ካሉ መላእክትና በምድር ከሚኖሩ ደቂቀ አዳም ሁል ጊዜ ምስጋና ይቀርብልሻል።” ቅዳሴ ማርያም

“ሰላም ለእለ ርእዩኪ ከመ ዐይነ ወለት ኀበ እማ፣
መዋዕል ኃምስ እስከ ይትፌጸማ፣
ማርያም ንግስት ዘደብረ ምጥማቅ ከተማ፣
ብፁዓት አዕይንት ዘነጸራኪ በግርማ፣
ወብፁዓት አእጋር ቅድሜኪ ዘቆማ።” እን ዐርኬ
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ምንጭ፡ መዝገበ ታሪክ 2 ገጽ 87፣ መድብለ ታሪክ ገጽ 383

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ምስባክ፦
ዐረገ እግዚአብሔር በይባቤ ፤
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን፤
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

አፍአዊ ጌጥን መውደድ «አምልኮ ጣዖት ነው!» የሚባለው ለምንድር ነው?
መታበይ፣ መኩራራት፣ ማማረርና፣ ተስፋ መቁረጥን የመሳሰሉ ኃጢአቶች በሙሉ በአብዛኛው አፍአዊ ጌጽን ከመውደድ ይወለዳሉ:: ሰዎች ይህን ሲያገኙ እንደሚኮሩና ደስ እንደሚላቸው ሁሉ ያጡትም እንደ ሆነ በሕይወታቸው አንድ ታላቅ ነገርን እንዳጡ በመቁጠር ያለ መጠን ሲማረሩና ሲያዝኑ ይገኛሉ:: አልፎ ተፈርሞ በተገቢው መንገድ የሚሹትን አፋአዊ ጌጽ ካላገኙ በመስረቅ፣ በመዋሸትና ፍላጎታቸውን ሊያሟሉ ለሚችሉ ሀብታም ሰዎች በመገዛት ያሟሉታል።ይህ መገዛታቸው ልክ በማጣቱ ሐሳባቸው ይሟላላቸው ዘንድ ለዝሙት ከመንበርከክና ከመግደል አንሥቶ ለማንኛውም የኃጢአት ተግባር ወደ ኋላ አይመለሱም፡፡ ሊያገቡት የመረጡትንና ያጩትንም ሰው የጌጥ አምሮታቸውን ባለሟሟላቱ ብቻ እስከ መካድ የሚደርሱበት አጋጣሚ እጅግ ብዙ ነው:: በዚህ ምክንያት አፍአዊ ጌጽ መውደድን እንደ ጨካኝ ጌታ ስንቆጥረው ጌጽ ወዳጅዋን ሴት ደግሞ የሥጋና የዓለም ታማኝ ሎሌ እንላታለን፡፡ ለምን ቢባል ጌጥ በመውደዷ ብቻ የማትፈልገውን ኃጢአት ሁሉ ትሠራለችና፡፡
አንቺ ሴት እንደ ሌሎች ሴቶች ለማጌጥ አቅም በማጣትሽ ለምን ታዝኛለሽ? ፈጣሪሽ ለጌጣጌጥ በባርነት ከመገዛት ነጻ ስላወጣሽ ታዝኛለሽን? አንድ ሰው መዝገቡን ተግተሽ አንድትጠብቂ ቢያዝሽ እጅግ ታዝኚ ነበር፡፡ ከዚህ ይልቅ ግን የጌጣጌጥሽን ጉዳይ ለመሟላት የምታደርጊው ጥንቃቄና ዝግጅት ይከብዳል፡፡ ታዲያ ለጌጣጌጥ በመገዛት ራስሽን በጽኑ ማሠሪያ ለምን ታሥሪዋለሽ? ጠፍቶብሽ ከመደንገጥ፣ እዘረፋለሁ ከማለት፣ ግድ ለማያስፈልግ ነገር ከፍተኛ ባጀት ከመመደብ፣ ጊዜ ከማባከን፣ በጌጥ ምክንያት የሰው እጅ ከማየት፣ ወዘተ ነጻ እንደ መሆን ምንም አይገኝም:: ማጌጫ አጣሽ ማለት ከእነዚህ ሁሉ ክፉ ነገሮች ነጻ ወጣሽ ማለት ነውና፡፡
ጌጽ መውደድ ባርነት ብቻ ሳይሆን <ጣዖት አምልኮ> ም ነው።ነፍስ በጽኑ ፍቅር የታሠረችበት ከሆነ ሁሉም ነገር ወደ አምልኮት ይሄዳልና፡፡ ታዲያ አንቺ ያለ ጌጽ ምንም ነገር የማይሆንልሽ፣ ጌጥሽን ልጆችሽና አገልጋዮችሽ አንኳን ሊነኩት ሊያዩት የማታደርሻቸው ከሆነ፣ ለራስሽ እንኳን ልታጌጭበት የምትሳሽለት፣ ለሌላ ማዋስማ ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ከሆነብሽ ከዚህ የበለጠ «ጣዓት አምልኮ» ከወዴት ይመጣል? በቀን ዐሥር ጊዜ ሣጥን ከፍተሽ የምትመለከቺው፣ ዕጣን የምታጥኚው፣ ሽቶ የምትቀቢው፣ አጥፈሽ የምትዘረጊው፣ የምታናፍሽው፣ ብታውሺው እንኳን ጠባይሽን ዐውቀው «ያጅሪት ገንዘብ» እያሉ ያዋስሻቸው ሰዎች እንዳንቺ የሚጠነቀቁ ከሆነ ትንሽ ቢበላሽባቸው ደግሞ ጥፋታቸውን የማትታገሻቸው ከሆነ ያ ነገር ላንቺ «ጣዖት» ነው ቢባል ይበዛበታልን? በፍጹም አይበዛበትም:: ምክንያቱም መምለኪያነ ጣዖታት (ጣፆታትን የሚያመልኩ ሰዎች) ጣዖትን እንደሚንከባከቡት አንቺም ጌጣጌጥሽን የምትንከባከቢው እንደነርሱ ነውና።
በተመሳሳይ መልኩ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለአፍአዊ ጌጽ የሚሳሱ ሰዎች ከጣዖት አምላኪ ጋር እንደሚቆጠሩ የቅዱስ ጳውሎስን ቃል ጠቅሶ ተናግሯል፡፡ «እስኩ ንግረኒ ኢኮነሁ ርቱዐ ቃለ ሐዋሪያ ሶበ ይሰምዮ ለስሱዕ ከመ መምልኬ ጣዖት» ይህም ወደ አማርኛ ሲመለስ «እስኪ ንገረኝ ሐዋሪያው ጣዖት የሚያመልኩትን በነቀፈበት አንቀጽ «አው ዐማፂ (ዐመፀኛም ቢሆን)» ብሎ በምንዝር ጌጥ (በትውዝፍት) እና በፍቅረ ንዋይ የታሠሩትን ሰዎች አያይዞ መንቀፉ የሚገባ አይደለምን? ጣዖት አምላኪዎች ጣዖታትን እንደሚያከብሯቸው «ከማሁ እሉሂ ያከብሩ አልባስ ወንዋየ፤ እንዲሁ እነዚህም ልብስንና ገንዘብን ያከብራሉና›› ማለት ነው:: ተግሣጽ ዘዮሐ አፈ.20
እስራኤላዊያን ጭቃ በመርገጥ ኖራ በመውቀጥ ለግብፅ ንጉሥ ይገዙ ነበር፡፡ እኅቶቻችንም ርጉም ሰይጣንን ለማስደሰት ለአፋዊ ጌጣጌጥ ብዙ ይጨነቃሉ፡፡ ከፈርዖን አገዛዝ ለአፋአዊ ጌጣጌጥ መገዛት ይከፋል።ያ ሥጋዊ ነውና፤ ለጌጣጌጥ መገዛት ግን በቀጥታ ለዲያብሎስ መገዛት ነው።ሆኖም እግዚአብሔር የራሔልን ዕንባ ተመልክቶ እስራኤላዊያንን እንደታደጋቸው እኛም ንስሐ ብንገባና ስለ ኃጢአታችንም መሪር ዕንባን ብናነባ የነፍሳችንን ኀዘን ተመልክቶ ለቁሳቁስ ከመገዛት ፈጣሪያችን ነጻ ያወጣናል፡፡ ዕንባችንን አይቶ የሚልክልን ጸጋም ሊቁ «ይፌኑ ለነ ቃሎ ወረድኤቶ ወፈሪሆተ ) ዚአሁ» እንዳለ «ቃሉን ትእዛዙን ፣ ረድኤቱን እርሱን መፍራትንና ሰውን ማፈርን ያሳድርብናል እንጂ ፤ ሙሴና አሮንን አይደለም፡፡» በዚህ ጊዜ በግብፅ ከተመሰለች ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ነጻ እንወጣለን ፤ መልካምና ክፉንም ለይተን እናውቃለን፡፡
ቀጣይ ምዕራፍ ዘጠኝ ክፍል አምስት :
👉 «ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ» ሲል ምን ማለቱ ነው?
👉 ሴቶች ሱሪ መልበስ ይችላሉ?
👉 ስለ መጋጌጫ ነገሮች ምን ይባላል?
በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ዘጠኝ ክፍል ዐራት
.................................................

➺አለባበስሽ ስለ አንቺ በደንብ ይናገራል!
አለባበስሽና ውጫዊ ቁመናሽ ከውስጥሽ ምን ዓይነት ሰው አንደ ሆንሽ መቶ በመቶ ባያስረዳም የቀረበ ግምት ለመስጠት ይረዳል፡፡ ሕፃን ሳለሽ አለባበስሽ ምን ዓይነት ሰው እንደሆንሽ ብዙም አይናገር ኖሮ ይሆናል፡፡ ልብሶችሽን የሚመርጡልሽና ፀጉርሽንም የሚያበጥሩልሽ አሳዳጊዎችሽ ናቸውና፡፡ እያደግሽ ስትሄጂ ግን ልብስ ስለ መምረጥ፣ ስለ ፀጉር አያያዝና ስለመሳሰሉት የራስሽን ምርጫ እንድትከተዪ ይተውሻል፡፡ ከዚያ ወዲያ የራስሽ ምርጫ መታየት ጀመረ ማለት ነው።ስለዚህ ቁመናሽና አለባበስሽ በውስጥሽ ምን ዓይነት ሰው እንደሆንሽ ማንጸባረቅ ጀምሯል፡፡ እስኪ ይህን ንባብ ገታ በማድረግ የሰውነትሽ አቋምና አለባበስስ ስለ አንቺ ምን እንደሚናገር ለአፍታ ቆም ብለሽ አስቢው።
አለባበስሽ በእርግጥ ስለ አንቺ ስለሚናገር ከአንድ ዓይነት ቡድን ወይም ክፍል ጋር ያስመድብሻል።ብዙ ሺህ ዓመታት ወደኋላ መለስ ብለን ብንመለከት ይህንን እውነታ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንረዳለን፡፡ ለምሳሌ በነገሥት መጽሐፍ ውስጥ የንጉሥ አካዝያስ መልእክተኞች እርሱ ከላካቸው በኋላ አንድ ዓይነት ሰው ማግኘታቸውንና አርሱም በበኩሉ መልሶ መልእክት እንደላካቸው ተመልሰውም ለንጉሡ እንደተናገሩ ተጽፏል:: ንጉሡም « የሰውየው መልክ ምን ይመስላል» ብሎ ጠየቃቸው አለባበሱን በገለጹለት ጊዜ ወዲያውኑ «ኤልያስ ነው» አለ፡፡ እንዴት ዐወቀው ቢሉ ኤልያስ ነቢያት የሚለብሱትን ዓይነት ልብስ ይለብስ ስለነበረ ነው።2ነገ1÷2-6

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጾመ ሐዋርያት
ሰኔ 2
ጾመ ሐዋርያት በወርኃ ሰኔ ስለሚጾም በምእመናን ዘንድ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፤ ከሰባቱ የዐዋጅ አጽዋማትም አንዱ ነው፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡
ይህም ጾም ከበዓለ ኀምሳ በኋላ የሚጾም ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ቅዱሳን ሐዋርያት በጸሎት ይተጉ ወደ ነበረበት ቤት በመሄድ ደቀመዛሙርቱን ይዟቸው ከቤት በመውጣት መንገድ ጀመረ፡፡ እርሱ ከፊት እየመራቸው እነርሱ እየተከተሉት ወደ ረጅሙና በረጃጅም ዛፎች ወደ ተሞላው ደብረ ዘይት ተራራ ይዟቸው ወጣ፡፡ ይህንንም እየነገራቸው ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ፤ከፍ አለ፡፡ ነጭ የሆነች ብሩህ ደመናም አምላካችንን ተቀበለችው፡፡ከዓይናቸውም እየራቀ፤ከእይታቸው በርቀት ሳይሆን በርኅቀት ተሰወረባቸው፡፡ሐዋርያትም ኢየሱስ ክርስቶስን በጣም ይወዱት ስለነበር ሲለያቸው አዝነው አተኩረው ሰማዩን ለረጅም ሰዓት ተመለከቱ፡፡ ድንገትም ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ቅዱሳን መላእክት በአጠገባቸው ቆመው ታዩአቸው፡፡መላእክትም ሐዋርያትን እንዲህ አሏቸው፤ ‹‹እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን  ቆማችኋል፡፡ ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል›› አሏቸው፤ (ሐዋ. ፩፥፰-፲፩)፡፡ ሐዋርያትም የመላእክትን ማረጋጊያ ቃል ከሰሙ በኋላ  በኢየሩሳሌም ወደ ምትገኘው ቤተ መቅደስ በመሄድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገራቸው እስኪፈጸም ድረስ ቀን ከሌሊት በአንድነት ሆነው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከመካከላቸው አድርገው በጾምና በጸሎት እየተጉ ቆዩ፡፡
የጾመ ሐዋርያት የጊዜ ቀመር ሥሌት በዓለ ጰራቅሊጦስ እንደ ገባ ባለው የመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ በዚህም መሰረት የዘንድሮ ጾመ ሐዋርያት ሰኔ ፪(2) ይገባል። ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት እንዲህ ተናግሮ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። ‹‹እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት›› (ማቴ.፱፥፲፬)።  ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ ጌታችን እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር፡፡‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው  ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ያንጊዜም ይጾማሉ›› (ማቴ.፱፥፲፭)፡፡
እኔ ሳለሁ አይጾሙም ማለቱ እርሱ ካልሞተና ካላረገ፤ መንፈስ ቅዱስም ካልተሰጣቸው በመንፈስ ቅዱስ ባልታደሰ ሰውነት ጾመው ድል መንሳት ስለማይቻላቸው ነው፡፡ ይህን ጾም የምንጾመው ሐዋርያት ጾመው ጸልየው ድል ያደረጉትን ዓለም እኛም የምናሸንፍበት ኃይል እንዲሰጠን ፈጣሪያችንን አምላከ ሐዋርያት ተለመነን እያልን ለመማጸን ነው፡፡
ይህን ጾም እንደ ሌሎቹ አጽዋማት ሁሉ እያንዳንዱ ምእመን ሊጾመው የሚገባ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን አብዛኛው ምእመን ‹‹የቄስ ጾም›› ነው በማለት ከጾሙ ሽሽት ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተክርስትያንን መሠረት ያደረገ ባለመሆኑ መስተካከል ይገባዋል፡፡
ሐዋርያትን አብነት በማድረግ ጾመን በረከትን ልናተርፍ ይገባናል፡፡
የአምላካችን የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት፣
የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣
የቅዱሳን ሐዋርያት በረከት፣
የጻድቃን የሰማዕታት ጸሎት እና ምልጃ አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን፡፡

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በዓለ ጰራቅሊጦስ

መንፈስ ቅዱስ ከሚጠራባቸው ስሞች አንዱ ጰራቅሊጦስ ናዛዚ መጽንዒ መስተፍሥሒ፤ የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ የሚል ትርጉም አለው፡፡ አጽናኝም የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ‹‹አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል፤ እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋ›› ብሎ ተናግሯል፡፡ በሌላም በኩል ደግሞ ‹‹እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ ጰራቅሊጦስ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል›› እንዲል። (ዮሐ.፲፬፥፳፮፤ ፲፭፥፲፮)

ጰራቅሊጦስ የሚለው የመንፈስ ቅዱስ ስም የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ መሆኑም ከማሳየት በላይ፤ ፍጹም አካል ያለው አምላክ እንደሆነ አመልካች ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጰራቅሊጦስ ማለት መሪ፣ አጽናኝ፣ ረጂ ማለት መሆኑን በስፋት ካስተማሩ ሊቃውንት በቀዳሚነት ይነሳል። ጰራቅሊጦሰ የተባለው መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው። ሐዋርያዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ያላትን እምነቷን ስትገልጥ ‹‹ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማኅየዊ ዘሠረፀ እም አብ ንሰግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ››፤ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረፀ ከአብ ከወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን፣ እናመሰግነዋለን፤›› የሚል ነው።
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ፤ የቅድስናም ምንጭ ነው። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ‹‹ወስመ መንፈስ ቅዱስ ነቅዐ ቅድሳትየ፤ የመንፈስ ቅዱስም ስም የቅድስናየ መገኛ ነው›› በማለት ገልጾታል። (መጽሐፈ ምሥጢር)
ቅዱስ ባስልዮስም በቅዳሴው ‹‹ሃሌ ሉያ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር መንፈስ ቅዱስ ንጹሕ ክቡር ልዩ ነው›› በማለት አምላካዊ ስሙን ጠርቶ አመስግኖታል። ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ዕለት ዕለት በምታከናውነው ሥርዓተ ቅዳሴ ‹‹መንጽሒ ወመጽንዒ የሚሆን መንፈስ ቅዱስ ክቡር ምስጉን ነው›› እያለች የአምላክነት ስሙን ጠርታ ታመሰግነዋለች።
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ሊያጸኑ ከሓድያንን ሊለዩ (ሊያወግዙ) ሲሰባሰቡ በመካከላቸው ተገኝቶ ውሳኔ ያስወስናቸው የነበረው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ሲገልጹ ጰራቅሊጦስ የተባለ ስሙን ጠርተው እንዲህ ብለዋል፣ ‹‹ወሀሎ ምስሌሆሙ ኅብረ መንፈስ ቅዱስ …. ጰራቅሊጦስ የሚያነጻና የሚያጸና መንፈስ ቅዱስም በጉባኤያቸው ነበረ፡፡›› (መጽሐፈ ምሥጢር)
ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ሰባ ሁለቱ አርድእት እና ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ሆነው በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ‹‹እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤›› ሲል ለሐዋርያቱ በሰጣቸው የተስፋ ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል (ሉቃ. ፳፬፥፵፱)፡፡ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በሁሉም ላይ አረፉባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሁላቸውም መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየሀገሩ ቋንቋዎች ሁሉ ተናገሩ፡፡ (ሐዋ.፪፥፩-፬)

ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ዐሥራቱን፣ በኵራቱን፣ ቀዳምያቱን ካህናተ ኦሪት ስለሚቀበሉበት በብሉይ ኪዳን በዓለ ሠዊት ተብሎ ይከበር ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ስለ ተቀበሉበት በበዓለ ሠዊት ምትክ በዓለ ጰራቅሊጦስ ተብሎ ይከበራል፡፡ የበዓለ ትንሣኤ መነሻው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ማለትም በግብጽ፣ እስራኤል ከሞት የዳኑበት የመታሰቢያ በዓል እንደ ሆነው ሁሉ፣ ለበዓለ ጰራቅሊጦስም መነሻው ይኸው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ነው፡፡ የአይሁድ ፋሲካ ከተከበረ ከሰባት ሳምንታት በኋላ በኀምሳኛው ቀን የሩቆቹ ከከተሙበት ወጥተው፣ የቅርቦቹ ከተሰባሰቡበት ተገናኝተው ለበዓሉ ፍጻሜ የሚሆነውን በዓለ ሠዊት (የእሸት በዓል) ያከብሩ ነበር፡፡
ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰባስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጐልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ሆነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል፡፡ ቀድሞ ይናገሩት ከነበሩት ቋንቋ በተጨማሪ ፸፩ ቋንቋዎች ተገልጠውላቸው ምሥጢራትን በልዩ ልዩ ቋንቋ መተርጐም ጀምረዋል፡፡ ሐዋርያት በየሀገሩ ቋንቋ ሲናገሩ የሰሙ በዚያ የነበሩ ሰዎችም በሐዋርያት ተገረሙ፡፡ አንዳንድ የአይሁድ ወገኖች ግን በሐዋርያት ላይ ያዩት ክሥተት አዲስ ነገር ስለሆነባቸው ‹‹ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ሰክረው የሆነ ያልሆነውን ይቀባጥራሉ›› እያሉ ሐዋርያትን ያሟቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ይህንን ሐሳባቸውን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ‹‹ሰክረዋል የምትሉ እናንተ እንደምትጠራጠሩት አይደለም፡፡ ጊዜው ማለዳ፣ ሰዓቱም ገና ሦስት ሰዓት ነውና፡፡ ግን በነቢዩ ኢዩኤል ‹ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ፣ ይህንን ድንቅ ተአምር ያደረገው እናንተ የሰቀላችሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤››በማለት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥቷቸዋል፡፡ (ኢዩ.፪፥፳፰)
በትምህርቱም ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት፣ምሳሌ የመሰሉለት አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ማረጉንና ዳግም በክብር በምስጋና መጥቶ በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈረድ መሆኑን ሐዋርያት እንደሚመሰክሩ በአይሁድ ፊት አሰምቶ ተናገረ፡፡በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም ‹‹ምን እናድርግ?››ብለው በጠየቁት ጊዜ ከክፋታቸው ተመልሰው፣ንስሓ ገብተው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ ነገሯቸዋል፡፡ በዚያችም ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ተጠምቋል፡፡(ሐዋ.፪፥፩-፵፩)
ቅዱሳን ሐዋርያት፤ ‹‹በዚህች ቀን በሦስት ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና በላያችን ኃይልን ሞላ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን እንዳለው በአዲስ ቋንቋ ተናገርን፤›› በማለት በዕለቱ ያዩትንና የተደረገላቸውን፣ እንደዚሁም የበዓሉን ታላቅነት ከመሰከሩ በኋላ ይህንን በዓል ማክበር እንደሚገባ አዝዘዋል፤ በዚህ ወቅት መጾምና ማዘን ተገቢ አለመሆኑንም ተናግረዋል፡፡ (ዲድስቅልያ ፴፥፴፰-፴፱፤ ፴፩፥፷፱-፸)
ቅዱሳን ሐዋርያትም ‹‹ከአብ የሠረፀ የሁላችንም መጽናኛ የሚሆን ዓለሙንም ሁሉ ያዳነ ከአብና ከወልድ ጋር ህልው የሚሆን መንፈስ ቅዱስን ላከልን፡፡ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስም አንድ ነው›› ብለዋል። በሌላም ነቢዩ ዳዊት ስለመንፈስ ቅዱስ ‹‹መንፈስህን ከእኔ አታርቅ አለ፤ ዳግመኛም በሰውነቴ እውነተኛ መንፈስን አጽናልኝ፣ ከሁሉ በሆነ መንፈስ ቅዱስ አጽናኝ አለ›› በማለት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መንፈስ ቅዱስን ጰራቅሊጦስ አጽናኝ መካሪ መባሉን አስተምሯል። (መዝ. ፶፥ ፲-፲፪፤ መጽሐፈ ምሥጢር)
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በበዓለ ኀምሳ ምንባብ ላይ እግዚአብሔር

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በሚገባ መማር
ትምህርትን ሲከታተሉ በፍቅርና በሙሉ ኃይል ጥረት ከማድረግ ጋር ከሆነ ውጤቱ ያማረ ይሆናል። ብዙ ወጣቶች ለትምህርት የተነሣሣ ልብ ስለሌላቸው በሚገባ አይማሩም፡፡ በትምህርት ገበታቸው ላይ እንኳን የሚገኙት ሌላ ምክንያት ሲኖራቸው ወይም ደስ ሲላቸው ብቻ ነው። ማጥናቱንም ቢሆን የሚያከናውኑት ፈተና ለማለፍ ያህል ነው፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለው በጣም ተግተዋል ከተባለ ነው።አንተስ የምታጠናው እንዴት ነው? ስልቹ ሰው የቆረሰውን እንጀራ ለመጉረስም ይታክታልና፡፡ ስልቹ ሰው አትሁን! ደግሞም «መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት›› ገላ6÷9፣2ተሰ3፡13 የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል እንደ ስንቅ ብትይዘው ከመሰልቸት ያድንኃል፡፡
በምንም ምክንያት በሚያስተምርህ መምህር ጥላቻ እንዲያድርብህ ተጠንቀቅ፡፡ ይህ በትምህርትህ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አለውና፡፡ ከመምህራን ጋር በፍቅር ለመኖር የምታደርገው ጥረት ባይሳካልህ እንኳን ተግቶ ከመማር ግን ተስፋ ሊያስቆርጥህ አይገባም።እንደ ምንም ተቸግረህና ለፍተህ ተማር! ጊዜ ጠብቆ የለፋበትን መስጠት የእግዚአብሔር ድርሻ ነውና ተግተህ መማርህን እንጂ ውጤትህን አታሰላስል፡፡
በሚገባ ብትማር ዕውቀት ካንተ ጋር ትሆናለች፣ ስትሰንፍ ደግሞ ትለይሃለች፡ ከጎበዝ ተማሪ እየቀዳህ (እየኮረጅህ) ለማለፍ አትሞክር፡፡ ይህ ለዘለቄታው የሚጠቅም አይደለምና፡፡ በዚህ ሁኔታ ካሰብክበት ለመድረስ አትችልም። ብትደርስም እንኳን የሚስጥህን ኃላፊነት በብቃት መወጣት አትችልም። በራስ የመተማመን ስሜትህ ይጠፋል። ደግሞም በኩረጃ ማለፍ ሁልጊዜ የሚሳካ ነገር አይደለም፤ ቢሳካም እንኳን ሌብነትንና ኃጢአትን መለማመድ ነው፡፡ ደግሞስ ራስህን ጐበዝ ማድረግ ካላወቅህበት ወደፊት ለሚያጋጥሙህ የሕይወት ጥያቄዎች ማን ሊያስኮርጅህ ይችላል? ለዚህ ችግር መፍትሔው ራስን ጐበዝ ማድረግ ብቻ ነውና ጠንክሮ መማር ይኖርብሃል፡፡
በመደበኛ ክፍለ ጊዜ የምትከታተለውን ትምህርት በሚገባ ካልተወጣኸው በኋላ ለመማር ቁጭት ቢያድርብህ እንኳን ብዙ እንቅልፋቶች ያጋጥሙሃል፡፡ በመጀመሪያ የምትፈልጋቸው ሥልጠናዎች እንተ ባለህ ውጤት በቀላሉ ላይገኙ ይችላሉ፡፡ ቢገኙም ብዙ ገንዘብ የሚያስወጡህ ሆነው ነው። ታዲያ መደበኛ ተማሪ እያለህ በሚገባ በመማር ዕድልህን ለምን አትጠቀምበትም? ተግተህ በመማርህ የምትጠቀመው አንተ ራስህ ነህ፡፡ «ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና» የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንዲሁ የሚቀር አይደለምና፡፡ ገላ6፥7
ዕውቀት የሚገነባው ሌሎች ሰዎችን መሠረት በማድረግ ነው። ስለዚህ ከሌሎች ሰዎች ጋር ሳትነጋገር፣ የጻፉትን ሳታነብ፣ ወይም ትምህርትን ዓላማ አድርገህ ሲሠሩ ሳትከታተል ሌሎች ያገኙትን ዕውቀትና ልምድ ልትቀስም አትችልም፡፡ ይህን ሁሉ ለማድረግ ደግሞ በቂ ጊዜ ያስፈልግሃል:: ማወቅ የሚገባህን ነገሮች ሳታውቅ ከተቃራኒ ጾታ ጋር ወዳጅነት ብትፈጥር ምን እንደሚያስከትልብህ ታውቃለህ? ዕውቀት ከምትገበይባቸው ሰዎችና ነገሮች ጋር ያለህ ግንኙነት እንዲጠብ ወይም እንዲቋረጥ በማድረግ ትኩረትህ ወደ አንድ ፆታዊ አቅጣጫ ብቻ እንዲሆን ያደርግና በዕውቀት እንዳታድግ ትሆናለህ፡፡ ስለዚህ ይህን ከመሳሰለ አካሄድ ለጊዜው ብትቆጠብ እዕቀትን ከመራብ ትድናለህ:: ለሁሉም ጊዜ አለውና፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ዐሥር ክፍል ሁለት
.................................................

የትኛው ይቅደም?
በዚህ ዘመን ለሚከሠቱ ልዩ ልዩ ወንጀሎች መበራከት መንሥኤው የዕውቀት ማነስ ሳይሆን የግብረ ገብነት መጉደል ነው፡፡ ይህንን ችግር በመጠኑም ቢሆን መንግሥት የተረዳው ይመስላል፡፡ ምክንያቱም እንደ ድሮው ሁሉ ዛሬም በየትምህርት ቤቱ የሥነ ዜጋ ትምህርት (ሲቪክ ኤጁኬሽን) እና የሥነ ምግባር ትምህርት መሰጠት ተጀምሯል፡፡ ይህም ቢሆን እግዚአብሔርን መፍራት አያሳድርምና ብቻውን ዓላማውን ሊመታ አይችልም፡፡
ሰው ሁሉ የመልካም ሥነ ምግባር ባለቤት እንዲሆን በመጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ይኖርበታል፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት የሚገኘው ደግሞ ከመንፈሳዊ ትምህርት ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት «ልጆቼ ኑ ስሙኝ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ» መዝ33፥11 በማለት የተናገረው ቃል ለዚህ ምስክር ነው፡፡ «ከእሾህ ወይን ከኩርንችትም በለስ» እንደማይለቀም ሁሉ ሰው ሁሉ እግዚአብሔርን እንዲፈራ ለማድረግ ዓላማ ይዞ ያልተቀረጸ ትምህርት ሁሉ እግዚአብሔርን ስለመፍራት ሊያስተምር አይችልም፡፡ ስለዚህ በጥሩ ሥነ ምግባር ተኮትኩቶ ለማደግ አስቀድሞ መንፈሳዊ ትምህርትን መማር ይገባል፡፡ «የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነውና›› ምሳ1÷7፤ መዝ110 ፥ 10

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ሥርዓተ መንግሥተ ሰማያትን በተናገረበት አንቀጽ ‹ሕፃናት ተወልደው እስከ ሰባትና አሥራ ሁለት ዓመታቸው ድረስ የሚያውቁት ዕውቀት ጻድቃን ከበቁ በኋላ እንደማያውቁት ዕውቀት ነው፡፡ እስከ ሃያና ሠላላ ዓመታቸው የሚያውቁት ዕውቀት ጸድቃን ከሞቱ በኋላ በገነት እንደሚያውቁት ዕውቀት ነው፡፡ እስከ ዓርባና ሃምሳ ዓመታቸው የሚያውቁት ዕውቀት ደግሞ ጻድቃን መንግሥተ ሰማያት ገብተው እንደሚያውቁት ዕውቀት ነው፡፡› በማለት በሃያዎቹና በሠላሳዎቹ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ኸዕውቀት አንጻር በሞት ለሄዱና በገነት ላሉ ጻድቃን ምሳሌ እንደሚሆኑ አስረድቷል።(ዮሐ.አፈ.ተግ.8)
ይህ የወጣቶች ለጻድቃን ምሳሌ መሆን ወጣቶች ብሩህ አእምሮ እንዳላቸው የሚያመለክት ነው።ቀን ላለ በብርሃን መመላለስ ይሉሃል በወጣትነት መማር ነው።ወጣትነት ብሩህ ወቅት ነው። ኃላፊነቶች ያልበዙበት ሰው በመሆንህ ያለህን ነጻነት ለመማር ተጠቀምበት። ራስህን ጊዜው ባልሆነ የተቃራኒ ጾታ ግንኙ ነት ውስጥ ሳታስገባ ለመማር ጥረት አድርግ፡፡ በተጨማሪም ሌሎች ልዩ ልዩ ሱሶችና ልማዶች የወጣትነት ብሩህ አእምሮህን በአጉል ተስፋ እንደሚያጨልሙብህ አትጠራጠር።
ምንም እንኳን ሁሉም ወጣቶች ተመሳሳይ ዕድል ባይኖራቸው በሀገራችን ብዙ ወጣቶች ወላጆችና ትልልቅ ሰዎች ያሉባቸው ዓይነት ኃላፊነት የለባቸውም:: እንዲያውም አብዛኞቹ ወጣቶች በቤተሰቦቻቸው ትከሻ እየኖሩ እንክብካቤ የሚደረግላቸውና «የሚጦሩ» ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ወጣቶች ከብዙ ኃላፊነት ነጻ መሆናቸውን ዐውቀው ዕድላቸውን ቢጠቀሙበት ለመማርና ዕውቀት ለመሰብሰብ ሰፊ ጊዜ ይኖራቸዋል። ሆኖም አብዛኞቹ ወጣቶች ያን ያህል ሰፊ ጊዜ እንደነበራቸው የሚያስተውሉት ጊዜው ካለፈ በኋላና ለመጠቀም የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሊገኙ መሆኑ እጅግ ያስቆጫቸዋል።
ትምህርት ትግልን ይጠይቃል፡፡ መታገሉን ብትሰለች ከትግሉ በኋላ የምታገኘውን ዘለቄታዊ ጥቅም ታጣለህ:: ስለዚህ ወጣት ከሆንክ ኋላ የምትቆጭበትና ከሰው የምታንስበት ጫወታና መዝናናት አታሎኽ ከመማር አትቦዝን። ለጊዜያዊ ደስታ ብለህ ዘለቄታዊ ጥቅምን ለምን ታጣለህ? መዝናናትና መደሰት ድሮም ነበሩ፣ የሚያልቁ ነገሮች አይደሉምና ወደፊትም ይኖራሉ፡፡ ስለዚህ በሌላ ጊዜ የምትደርስባቸው እነዚህ ነገሮች እንዳያዘናጉህ ተጠንቀቅ:: የወደፊት የሥጋህና የነፍስህ ዕጣ ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ በጥንቃቄ አስብበት። ነቢዩ ኢሳይያስ «ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል?» ብሏልና ከወሬነት ለማያልፉ ነገሮች እየጓጓህ ትምህርትን ቸል እትበል፡፡ ኢሳ28÷9
ጠቢቡ ሰሎሞን ታካች ሰው ብትልከው «አንበሳ በመንገድ አለ» ይላል በማለት እንደተናገረው ላለ መማር ምክንያት አታብዛ። ምክንያት የሚያልቅ ነገር አይደለም። ለምንም ነገር ምክንያት ሊቀርብ ይችላል:። ከዚያ ይልቅ ለሰው የሚያዋጣው ምክንያትን በብርታት አሸንፎ ጠንክሮ መማር ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ቀዳማዊ አንዱን ወጣት ያለ ሥራ ስላዩት «ልጄ ለምን አትማርም?» ቢሉት እርሱም «አባታችን- ምን በልቼ?›› በማለት መለሰላቸው። ብፁዕነታቸውም ምክንያተኝነት እንደማይጠቅም በሚያስረዳ ቃል «ታዲያ አሁን እየደነቆርህ ያለኸው ምን እየበላህ ነው?›› በማለት መለሱለት ይባላል።
ላለመማር የትምህርት ፖሊስን፣ መምህራንን፣ ወላጆችን (ቤተሰብን)፣ ጾታን፣ የሥራ ጫናን፣ የጤና ሁኔታንና የመሳሰሉትን መኮነን ለማንም አልጠቀመም።የተሻለው መንገድ በራስ በኩል ያሉትን ድክመቶች አስወግዶ ተገቢውን ጥረት ማድረግ ብቻ ነው።ጥሮ በመማር መጠቀም እንጂ ቁጭ ብሎ ሌላውን ማማትና መተቸት ዐዋቂነት አይደለም።ስለዚህ በተቻለህ ሁሉ ጠንክረህ ተማር ከዐቅምህ በላይ የሆነውን ደግሞ ፈቃዱን አታውቅምና ለፈጣሪህ ተወው፡፡
እንኳን ከጨዋታና ከመዝናናት ይቅርና ከሥራም ቢሆን መቅደም ያለበት ትምህርት ነው።ዕውቀት ያልደገፈው ሥራ መሠረት እንደሌለው ቤት ነውና፡፡ ሥራ ያለህም ሰው ብትሆን የየዕለት መሠረታዊ ፍጆታህን ካገኘህ በኋላ ሐሳብህ ወደ ትምህርት ይሁን። ከተግባረ ሥጋም ሆነ ክተግባረ ነፍስ መቅደም ያለበት መማር ነውና፡፡
በራስ አነሣሽነት ከትምህርት ይልቅ ዋዛ ፈዛዛንና በልምድ የሚገኝ ዕለታዊ ተግባርን የመረጠ ሰው የኋላ ኋላ የሚያዝንበትና የሚያፍርበት ነገር ሳያጋጥመው አይቀርም:: ጠቢቡ ሰሎሞን ትምህርትን በልዩ ልዩ ምክንያት ሳይማር የቀረ ሰው ዘግየት ብሎ የሚሰማውን ስሜት እንዲህ በማለት ይገልጸዋል:- «በመጨረሻም ሥጋህና ሰውነትህ በጠፉ ጊዜ ታለቅሳለህ፡ ትላለህም፥ እንዴት ትምህርትን ጠላሁ ልቤም ዘለፋን ናቀ! የአስተማሪዎቼንም ቃል አልሰማሁም፡ ጀሮቼንም ወደ አስተማሪዎቼ አላዘነበልሁም።»ምሳ5:11-13
ይልቁንም ለመማር የሚያስችል ሁኔታ ተመቻችቶ ሳለ ለመሥራትና ንብረት ለማካበት መሽቀዳደም የከበረች ጥበብን ዋጋ ማሳጣት ነው፡፡ ከገንዘብ ተግሣጽ ይበልጣልና:: ተግሣጽ ደግሞ ጥበብም ትምህርትም ነው፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ «ተግሣጹን እንጂ ብርን አትቀበሉ፡ ከምዝምዝ ወርቅም ይልቅ ዕውቀትን ተቀበሉ፣ ጥበብ ከቀይ ዕንቁ ትበልጣለችና የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም፡፡» ምሳ8፥10-11 በማለት ትምህርት በገንዘብ እንደማይለካ ምስክርነቱን ይሰጣል፡፡ ሲራ6፥ 18-37

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ስለ «መልክ» ሊኖር የሚገባ ተገቢ አመለካከት!
በኮረዳነት ወቅት የሚከሠቱ አካላዊ ለውጦች የስሜት ለውጦችን ሊያስከትሉ ይችላል፡፡ አንዲት ልጃገረድ አንድ ጊዜ በኃይልና በብርታት የተሞላች ጤናማ ወጣት የሆነች ይመስላትና በሌላ ቅጽበት ደግሞ ድክምክም ብላ ፍጹም ጤና እንደሌላት እንደሚሰማት ሁሉ ስለማንኛውም ነገር የሚሰማት ስሜትም በዚያው ልክ በጣም ተለዋዋጭ ሊሆንባት ይችላል፡፡ ከዚህ የተነሣ ብዙ ብሩህና የደስታ ወቅቶች በትካዜና በተስፋ መቁረጥ ተሞልተው ይታያል፡፡ አሁን የወደደችውን ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ያለ ምንም ተጠቃሽ ምክንያት መሰልቸትና መጥላት ትጀምራለች።በዚህ ምክንያት የወሰነቻቸው ውሳኔዎችና የወሰደቻቸው እርምጃዎች የማይሽር ጸጸት ሊያስከትሉባት ይችላሉ፡፡
በዚህ ተለዋዋጭ ስሜት ላይ ነገሮች በሙሉ በሽማኔ መወርወሪያ ፍጥነት የሚቀያየሩበት ዘመናዊው የኢንዱስትሪ ዓለም ሲጨመርበት ወጣት ልጃገረዶችን ለከፍተኛ ጭንቀትና ግራ መጋባት ሊዳርጓቸው ይችላሉ።በእርግጥ ጤናማ መሆኗንና ወደፊት ምን ዓይነት ሰው እንደሚወጣት ሊያሳስባት ይችላልደበዚህ ያለመረጋጋት ሁኔታ በቀላሉ ላለመሸነፍ ብዙ ብቸኛና ዝምተኛ ወይም በጣም ትምክህተኛና እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ማለት አያዋጧትም::
ወጣት ልጃገረዶች ስለመልካቸው መሳሳትና መጨነቃቸው ከዘመነ ሔዋን ጀምሮ እንደ ነበር በመጻሕፍት ተገልጧል። ይሁን እንጂ የሴቶች ጠቅላላ የወደፊት ሕይወት በመልክ ላይ የተመረኮዘ ይመስል ሰለ ፊትና ቁመና ከመጠን በላይ መጨነቅ አይገባም፡፡ በዙሪያሽ የሚገኙና በብዙ መንገድ የምትቀኚባቸውን ታላላቅ ሰዎች አስተውለሽ ተመልከቻቸው። አብዛኞቹ ተራ መልክ ያላቸው አይደሉምን? ስለዚህ ወደፊት ለሚኖርሽ ደስተኛ ኑሮ እውነተኛ ቁልፉ የቁመና ማራኪነት አለመሆኑን ለምን አታስተውዪም?
አካላዊ ውበትን የተላበስሽ ልጃገረድም ብትሆኚም ሐቁ ከዚህ አይዘልም፡፡ ብዙ ቆንጆ ሴቶች በጣም ከንቱና ይልቁኑም የብልግና ኑሮ የሚኖሩ ሆነው እንደቀሩ መገንዘብ ይኖርብሻል፡፡ ይህ ኑሮ ኀዘንና «ምነው ባልተፈጠርኩ?» የሚያሰኝ ጸጸት የሞላበት እንደሆነ ግልጽ ነው።መልከ ጥፉ ሴት ከሆንሽ ብታስተውዪው ብዙ ቆንጆ ሴቶች ሕይወታቸው መና የቀረበት ፈተና ላንቺ እንደቀረልሽ ትረጃለሽ፡፡
ውስጣዊ ማንነት እንጂ ውጫዊ ቁመና ከንቱና ጠፊ መሆኑን ማወቅ ካቃተሽ ምንም ቆንጆ ብትሆኚ ትልቅ ጥበብ ጎሎሻል ማለት ነው።በዓለም ኣስቀያሚ ፍጥረት የሚባለው ደግሞ ጥበብ የጎደለው ነው።መጽሐፍ ቅዱስ «የወርቅ ቀለበት በእሪያ አፍንጫ እንደሆነ ከጥበብ የተለየች ቆንጆ ሴትም እንዲሁ ናት» ይላል፡፡ ምሳሌ 11÷22 በተጨማሪም «ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፣ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች» የሚል ቃል ይገኛል።ምሳ31፥30 አንቺ ምን ያህል እግዚአብሔርን ትፈሪዋለሽ? በፆታሽና በቁመናሽ ምን ያህል ደስተኛ ነሽ? ያለሽን ሕዋሳት በሙሉ እግዚአብሔር ባሉበት ሁኔታ ዐውቆ እንደሰጠሽ አስበሽ በደስታ ተቀብለሻል? እንዲህ ከሆነ በጣም ቆንጆ ሴት ነሽ ማለት ነዋ!

ቀጣይ ምዕራፍ ዐሥር ክፍል አንድ:
👉 "ወጣቶችና ትምህርት "
👉"የትምህርት ዓይነቶች "
በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ዘጠኝ ክፍል ስድስት
.................................................

ክርስቲያናዊ ፀጉር አያያዝ እንዴት ነው?
ፀጉርን ማሳመር የሚችሉ ብዙ የፀጉር አያያዝ ዘዴዎች አሉ፡፡ ከእነዚያም ውስጥ ክርስቲያኖች ሊቀበሉት የማይገባ የፀጉር አያያዝ መንገድ አይጠፋምና መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ለፀጉር አሠራር ደግሞ ማንኛውንም መንገድ ብከተል ምን አለበት? ማለት ጥሩ አይደለም፡፡ የሰው የልቦና ክፋት ከልክ ያለፈና ለመንፈሳዊነት ተፃራሪ የሆነ የፀጉር አያያዝን አስከትሏልና፡፡ ስለዚህ ሐዋርያት በተለያየ ስፍራ ስለ ፀጉር አያያዝ የሚበጅ መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡
ለምሳሌ፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስና ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ክርስቲያን ሴቶች ከልክ እንዳያልፉ ወይም ለፀጉር አያያዝ ከመጠን ያለፈ ትኩረት እንዳይሰጡ መምከር አስፈላጊ ሆኖ ስላገኙት «ለእናንተ ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁላችሁ» በማለት ተመሳሳይነት ያለውን መልእክት ጽፈዋል።1ጴጥ3፥3፤ 1ጢሞ2፥10
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ተናገረው ለሴት «ፀጉርዋ መጎናጸፊያ ሊሆን ተሰጥቶአታል» 1ቆሮ11:15 ስለዚህ ፀጉሯን ማስረዘም ተገቢ ነገር ነው:: ፀጉሯን «መቁረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር» መስሎ ካልተሰማት መቁረጥ ወይም መላጨት መብቷ ነው:: ፀጉሯን ካስረዘመች ግን በጸሎት ጊዜ «ራሷን ትሸፍን» ወይም ትከናነብ፡፡ 1ቆሮ11÷6

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሴቶች «ሱሪ» መልበስ ይችላሉ?
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ወንድና ስለ ሴት ኣለባበስ ብዙ መግለጫዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ከወንዶች አልባሳት ተርታ ከተጠቀሱት ውስጥ መታጠቂያ፣ መደረቢያ፣ መጎናጸፊያ፣ ስናፊል፣ ቀሚስ፣ እጀ ጠባብ፣ ካባና ድግ ይገኙበታል፡፡ 1ሳሙ18፥4፤2፥19 ዳን3፥21 ምሳ31፥24፤ ዮሐ19፥23፥ ኢያ7:21 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት የሴቶች አልባሳት መካከል ደግሞ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡ እነርሱም: ልግም በገላ፣ መታጠቂያ፣ መጎናጸፊያ፤ ራስ ማሠሪያ፣ ቀጸላና ዓይነ ርግብ ናቸው:: ኢሳ3÷20-24
«ሱሪ» ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለወንዶች ይልቁንም ለካህናት ብቻ ተጠቅሶ እናገኘዋለን፡፡ ዘጸ39፥29 ያም ቢሆን በተለይ በሀገራችን አብዛኛው ማኅበረ ስብአ «ሱሪ»ን ያለ አንዳች ተደራቢ ነገር መልበስ የወንዶች መደበኛ አለባበስ አድርጎ መቀበሉን ማረጋገጫ አያስፈልገውም፡፡ ስለዚህ ተገቢ ያልሆነን አለባበስ መርምሮ እንኳን «ሱሪ» ይቅርና ቀሚስም ቢሆን አለመልበስ ለሴቶች የተገባ ነው። ወንዶችም ቢሆኑ ሱሪ ስለ ሆነ ብቻ ሳይሆን በልዩ ልዩ መንገድ መዝኖ ሊያደርጉት የማይገባ ከሆነ መተው ይጠበቅባቸዋል።
በተረፈ ሴቶች «ሱሪ» መልበሱን ካልተውት ሲብስ ነው እንጂ «ሱሪ» በመሆኑ ብቻ ለባሾቹን ከመተቸት መተው ይመረጣል። እንዲህ የተባለው «ሴቶች ሱሪ መልበስ አይተዉም» በማለት ተስፋ ከመቁረጥ የመነጨ ሳይሆን «ሱሪ» መልበስ እጅግም የሚነቅፉት ነገር ባለመሆኑ ነው:: ምክንያቱም እንደኛ አርአያን መለወጥ ከሚለው ምሥጢር ከመነሣት ካልሆነ በቀር ሱሪ በመሆኑ ብቻ «ሱሪ› መልበስን ለመንቀፍ በቂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት አይኖረንም። ሁለተኛ ሁሉም ባይሆኑ አንዳንድ ሴቶች ሱሪ የሚለብሱበት የጤና መታወክን ጨምሮ አፍን የሚያሲዝ በቂ ምክንያት አላቸው።ሦስተኛ ደግሞ መሠረት በሌለው ነገር ለመተቸት መሞከር የሚጎዳው የሚለብሱትን ሳይሆን ሐሜተኞቹንና እንተቻለን ባዮቹን በመሆኑ ነው።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ዘጠኝ ክፍል አምስት
.................................................

«ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ» ሲል ምን ማለቱ ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ «ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ ወንድም የሴትን ልብስ አይልበስ ይላል።» ዘዳ22፥5 ይህን የእግዚአብሔር ቃል «ሴት ሱሪ አትልበስ ማለቱ ነው» በማለት የሚፈቱት አንዳንዶች ኣሉ።ነገር ግን ይህ ቃል ምሥጢሩ ከዚህም በላይ ከፍ የሚልና «ሴት ወንድነትን አትላበስ ወንድ ደግሞ ሴትነትን አይላበስ ሁለቱም በተፈጠሩበት ጾታ ጸንተው ይገኙ» ማለትም ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ሴትነታቸውን የሚያማርሩ «ዘር ላቀብል » እስከ ማለት የሚደርሱ እጅግ ብዙ «ወንዳ ገረድ» ሴቶች መኖራቸው ይታወቃል።ከወንዶችም ደግሞ «ዘር ልቀበል፣ ላምጥ፡ ልውለድ የሚሉ ወንዶች በርካታ ናቸው። ይህ ጎዳና «በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና» መጽሐፍ ቅዱስ ሴት የወንድን ወንድ ደግሞ የሴትን ልብስ አይልበስ ማለቱ እውነት ነው፡፡ ዘዳ 22፥5

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ዐረገ በስብሀት ዐረገ በእልልታ :
ሞትን ድል አድርጎ የሠራዊት ጌታ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ዕርገት

ከጌታችን ፱ቱ አበይት በዓላት ውስጥ አንዱ ዕርገት ነው፡፡

“እያዩት ወደሰማይ ዐረገ”(ሉቃ 24÷50 የሐዋ 1÷9)

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ ለሰላሳ ዘጠኝ ቀናት ያህል ለሐዋርያቱ በተለያየ ጊዜ እየተገለጠ ለአገልግሎት ሲያዘጋጃቸው እና ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምስጢር እያስተማራቸው ከቆየ በኋላ በ፵ኛው ቀን በሐዋርያቱ ፊት አርጓል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው የጌታችን አበይት በዓላት አንዱ ዕርገት ነው።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተነሣ በ፵ኛው ቀን ወደ ሰማይ አረገ ያረገበትም ቦታ ቢታንያ አጠገብ የሚገኘው ደብረ ዘይት የሚባለው ተራራ ነው። አሥራ አንዱ ሐዋርያትን እዚያ ድረስ ከወሰዳቸው በኋላ ባርኳቸው እያዩት ዐረገ። ደመና ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቀደመ ክብሩ፤ በመለኮታዊ ክብሩ ወደ ሰማይ አርጎ በአባቱ ቀኝ ተቀመጧል። ጌታችን ያረገውም በለበሰው ሥጋ በመሆኑ እና ለሁለተኛ ጊዜ ለፍርድ በሚመጣበት ጊዜ ይህን ክብር እኛም እንድናገኝ ምሳሌ ሲሆነን ነው።

በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ኤፌ . ፪፡፮ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዕርገቱ አስመልክቶ ከተናገራቸው ሦስት ነገሮች ውስጥ፦

#የመጀመሪያው፤ እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ። ዮሐ . ፲፪፡፴፪
#ሁለተኛው ደግሞ፤ ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ዮሐ .፲፬፡፲፰
#ሶስተኛው፤ እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። ዮሐ . ፲፮፡፯

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ለእኛ ትልቅ ተስፋ ነው ስለዚህም ሐዋርያት ጌታችን ሲያርግ ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ይመለከቱት እንደነበር እኛም በታላቅ ተስፋ የጌታን ነገር ልናስብ ይገባል። ነቢዩ ዳንኤል ስለ ጌታችን ዕርገት እና በአብ ቀኝ ስለመቀመጡ እንዲህ ሲል በትንቢት ተናግሮ ነበር፤ "በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የሰው ልጅየሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ
በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።" ዳን. ፯፡፲፫ - ፲፬ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ስንል ጌታ ከአብ ጋር እኩል ነው ማለታችን ነው።

ከ፬ቱ ወንጌላት ውስጥ ይህን የዕርገቱን ታሪክ የመዘገቡት የማርቆስ ወንጌልና የሉቃስ ወንጌል ናቸው። ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ። እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው፤ እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርሷም እንደታያት ሲሰሙ አላመኑም። ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ባላገር ሲሄዱ በመንገድ በሌላ መልክ ተገለጠ፤ እነርሱም ሄደው ለሌሎቹ አወሩ፤ እነዚያንም ደግሞ አላመኑአቸውም። ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ተገለጠ፥ ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ። እንዲህም አላቸው። "ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥ የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ። ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።" ማር. ፲፮፡፱-፲፱ "እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ። እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ። እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየወደ ሰማይም ዐረገ።" ሉቃ. ፳፬፡፵፰-፶፩

ቅዱስ ሉቃስ የሐዋርያት ሥራን ሲጽፍ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት አብራርቶ ጽፎታል። እንዲህ ሲል፦ ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው። ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፥ ነገር ግን።" ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ፤ ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ" አለ። እነርሱም በተሰበሰቡ ጊዜ። "ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሥትን ትመልሳለህን?" ብለው ጠየቁት። እርሱም "አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድርዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ" አለ። ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤ "ደግሞ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል" አሏቸው። ሐዋ. ፩፡፫-፲፩

ክርስቲያኖች በሰማያት ስፍራ ከጌታችን ከመድሃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረው እንደሚቀመጡ የእርሱ ዕርገት ያረጋግጥልናል። ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ጌታችን እርገት እንዲህ ሲል ይመክረናል፤ "እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ። በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና። ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበትጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።" ቆላ. ፫፡፩-፬

ኖርንም ሞትንም የክርስቶስ ነንና ዘላለማዊ ሕይወትን እንወርስ ዘንድ አምላካችን ይርዳን። ልዑል እግዚአብሔር በኑሮአችን ሁሉ ባርኮን፤ ቀድሶን፤ በእርሱ ፈቃድ እንድንኖር ይርዳን። የምንሻትን መንግስተ ሰማያትን ያወርሰን ዘንድ የእናቱ የድንግል ማርያም አማላጅነት፤ ስለ እርሱ ክብር ሲሉ ሕይወታቸውን ሰውተው ያለፉት ቅዱሳን ሰማዕታት ምልጃ እና ጸሎት አይለየን አሜን።

[በዲያቆን ንጋቱ አበበ]
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በእርግጥ በነቢይነት መታወቅ ክብር ያለው ነገር ነው።ይሁን እንጂ ቀጥሎ የሚጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ምሳሌ አለባበስ አንድን ሰው በወራዳና በተነወረ ተግባርም ሊያሳውቀው እንደሚችል ያሳያል።የይሁዳ ምራት ትዕማር የፈለገችውን ለማግኘት ዓላማ አድርጋ የመበለትነት ልብሷን አወለቀችና መጎናጸፊያና መሸፈኛ ለብሳ ከመንገድ ዳር ተቀመጠች።አማቷ ይሁዳ በዚያ መንገድ ሲያልፍ «ጋለሞታ መሰለችው ፊትዋን ሸፍና ነበርና» በማለት መጽሐፍ ቅዱስ ይተርካል፡፡ ትዕማርን አለባበሷ በጊዜው የነበሩትን ጋለሞታዎች አስመስሏት ነበር።ዘፍ38 ፥ 13-15
እንደ ቀድሞ ጊዜ ሁሉ ዛሬም ምንም እንኳን ያን ልብስ የሚለብሱ ሰዎች የሚያደርጉትን ባናደርግና የሚያምኑትንም ባናምን አለባበሳችን ግን እንደ እነርሱ ከሆነ ከእነርሱ ጋር በአንድ ሊያስመድበን ይችላል፡፡ ሌሎች ከአለባበሳችን ተነሥተው ስለ እኛ እንዲህ በማሰባቸውና በመገመታቸው ልንፈርድባቸው እንችላለንን? ሌሎች አሳባቸውን እንዲለውጡ ከማድረግና እኛ አለባበሳችንን ከማስተካከል የቱ ይቀላል? በቀላሉ ሲገለጽ አሳብን ከመቀየር ልብስን መቀየር አይቀልምን?
ልብስ የሕግ አስከባሪዎች (ፖሊሶች)፣ ፈሊጠኞችና የሥነ መንግሥት ሰዎች (ፖለቲከኞች)፣ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ወይም የሕክምና ባለሙያዎችና የወታደሮች ብቻ መለያ አይደለም፡፡ በረከሰ ተግባር የተሰማሩ ሰዎችም በአለባበሳቸው ተለይተው ሊታወቁ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፡ ብዙ ዝሙት አዳሪዎች የሚለብሱት አካልን የሚያጋልጥና ምንዝርን የሚያሳስብ ልብስ ይበልጥ ግልጽ በሆነ ሁኔታ የተሰማሩበትን ተግባር ያመለክታል፡፡ እንደ መልካሞቹ ሁሉ ግብረ ሰዶም ፈጻሚዎች፣ በዝርፊያ ተግባር የተሰማሩ ሰዎች፣ ወንበዴዎችና በልዩ ልዩ መጥፎ ተግባር የተሰማሩ ሰዎች ተለይተው የሚታወቁበትን የፋሽን ልብስ ይለብሳሉ። አንቺስ ከእነዚህ እንደ አንዱ ሆነሽ ለመታየት ትፈልጊያለሽ?
በማኅበረሰቡ ዘንድ የሚነቀፍ፣ ወይም መጥፎ ግብርን የሚያመለክት አለባበስ ብትከተይና ሥራ ለመቀጠር ወይም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንፈሳዊ ተግባር ለማከናወን ወይም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ አገልግሎት ለማግኘት በምትሞክሪበት ጊዜ ችግር ቢያጋጥምሽ ልትደነቂ ይገባል? እርግጠኛ ነኝ አለባበስሽ ዘወትር ግብረ ገብነት ይጎደለው ከሆነ የዚህ ዓይነት አንድ አጋጣሚ ሳይኖርሽ አይቀርም፡፡ ግን በማን ፈረድሽ? በናቁሽ፣ በተጸየፉሽ፣ መብትሽንና የመሰለሽን እንዳታደርጊ በከለከሉሽ፣ ባንጓጠጡሽና ፊት በነሡሽ ወይስ በራስሽ? እርግጥ ነው እንዲህ ማድረጋቸው ትክክል አይሆን ይሆናል ግን የችግሩ ዋና ምንጭ አንቺ መሆንሽን ለምን ትዘነጊዋለሽ?
በዚህ አንቀጽ ነውረኛ አለባበስ በእጅጉ ቢነቀፍና ስለአለባበስ ከልክ ያለፈ ጭንቀት እንደማያስፈልግ ቢጻፍም ስለ መልካም የአለባበስ ልማድ ለማስተማር ነው እንጂ በጥቅሉ ልብስን ለመኮነን አይደለም፡፡ በተገቢው መንገድ ከሆነ አንዲት ሴት በአለባበሷ ብቻ ሳይሆን በቤት አያያዟና በኑሮ'ዋ ሁለ ጠንቃቃ መሆን ያስፈልጋታል፡፡ ቤቷን ንጹሕና ስንዱ አድርጎ መያዝ፣ በእንቅልፍ፣ በአመጋገብና በሥራ ወቅት ሰዓት አክባሪ መሆን፣ ለግልፍተኝነት፣ አክብሮት ለጎደለውና ለሻካራ ንግግር አለመሸነፍ ይኖርባታል፡፡ እንዲህ ባደረገች ቁጥር ጸጥታ፣ ከጸጸት የመዳን፣ የመረጋጋትና የአሸናፊነት ስሜት ይሰማታል፡፡ ይህም የሚያጋጥማትን ሌሎች የስሜት ጫናዎች ቀላል ለማድረግ ይረዳታል፡፡
ሴት ልጅ ከአለባበሷ ጀምሮ ቸልተኛ፣ ሰነፍና ዝርክርክ ብትሆን ብዙ ልትጎዳ ትችላለች።ዝርክርክነት ቀላልና ብዙ ዋጋ የማያስወጣ ይመስላል። ይሁን እንጅ በሌሎች መንገዶች ብዙ ነገር ሊያስቀር ይችላል።አንዲት ሴት ልብሶቿ በውድ ዋጋ የተገዙና የዘመኑን ፋሽን የተከተሉ ባይሆኑም ንጹሕና በሥርዓት የተያዙ ከሆኑ ጠንቃቃ መሆኗን ያሳያሉ፡፡ እንዲህ ከሆነ ሌሎች ሰዎች በይበልጥ ያከብሯታል ፤ በእርሷም ላይ የበለጠ እምነት ያሳድራሉ፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

በ. ስለራሳቸው በጣም የሚኮሩ ሰዎች ኩራታቸውን የሚያሳዩት ብዙ ጊዜ ስለ አለባበሳቸው ከመጠን በላይ በመጨነቅ ነው፡፡ በልብሳቸው ወይም በመልካቸው ሁል ጊዜ «ሌሎችን አስንቀው» ለመታየት ይፈልጋሉ።ይህንንም ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንዲህ ሲል ገልጾታል፦ «ከመ ትዘኀሪ መትትመክሒ በላዕለ ብዙኃት አንስት ነዳያት ወትትዐበዪ በቅድመ አዕይንቲሆን ወትምስዊ አልባቢሆን ወታድውዪ ነፍሳቲሆን ወትወስኪዮን ንዴተ በዲበ ንዴቶን» ይህም አንቺ ሴት አጊጠሽ መውጣት የምትፈልጊው «ልብስ በሌላቸው በድሆች ላይ ልትመኪ፣ በፊታቸው ልትታበዪ፣ ልቡናቸውን በቅንአት እንደ ሰም ልታቀልጪ፣ ሰውነታቸውን በቅንአት ልታሳምሚና በኃዘናቸው ላይ ኃዘን ልታመጪባቸው ወደሽ ነው እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም።» ማለት ነው:: አንቺ ራስሽ «ዝንጥ» ያልሽ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ስሜት ተሰምቶሽ አያውቅም? ተግ.ዮሐ28
ውድና ጌጠኛ ልብስ መልበስ ያኮራሻል? ይህ የሚያኮራሽና ከሌላው ሰው የበለጥሽ መስሎ የሚሰማሽ ከሆነ ሰነፍ ሴት ነሽ፡፡ አላዋቂ በመሆንሽም ታሳዝኛለሽ እንጂ አታስጎመጂም፡፡ ምክንያቱም እንኳን ዐዋቂው የሰው ልጅ ይቅርና ፈረስና በቅሎ እንኳን የሰው ያህል ዕውቀት ሳይኖራቸው በጣም የሚደሰቱት ጌጣጌጥ አድርገውላቸው ከሚነዷቸው ይልቅ አራግፈው ሲያቀሉላቸው ነው።ስለዚህ ዐዋቂ የሚባል የሰው ልጅ ወርቁን ሐሩን በራሱ ቢሸከመው በወገቡ፣ በደረቱ፣ በእጁና በጣቱ ቢያጠልቀው በአንገቱም ቢያንጠለጥለው ሊያፍር እንጂ ሊኮራ አይገባውም ነበር፡፡
ያደረገው የወርቅና የሐር ጌጥ ዕወቀትና ሕይወት የሌለው ፍጡር በመሆኑ ነው እንጂ ኩራት የሚገባው ለእርሱ ነበር። ለባሕርይው የማያሻው ነገር ከተጫነበት ሰው ይልቅ ጌጡ ቢከብር ምን ይደንቃል? በላዩ የተቀመጠበት ሳይኮራ ተሸካሚው የሰው ልጅ መኩራቱና መደሰቱ እጅግ የሚያሳዝንና ዐላዋቂነት ነው። ተመልካቾችም ስለዚህ ሽክም ምክንያት ሊያዝኑለት ሲገባቸው ቢቀኑበት ወይም ቢያከብሩት ቅዱስ ያዕቆብ ለወርቅና ለብር በመሳሳታቸው የነቀፋቸው ከንቱዎች ናቸውና አይመሰገኑም፡፡ ዐዋቂ ግን ሌላውን ባለው ወርቅና ብር ብዛት አያከብርም።ለራሱም ቢሆን በሀብቱ ብዛት እናደሚከበር አያስብም አይቀበለውምም፡፡
በሌላ አቅጣጫ ስንመለከተው ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ስለ ልብስ «ግድ የለሽ» መሆንም ኩራትን ወይም ራስ ወዳድነትን ሊያሳይ ይችላል፡፡ በአለባበሱ የተዝረከረከው ግለሰብ ስለ አለባበሱ ግድ የለሽ የሆነው በስንፍና ምክንያት ሊሆን ቢችልም አለባበሱ በሌሎች ላይ ለሚያሳድረው ተጽዕኖ «ምን ቸገረኝ!» የሚል ዓይነት ዝንባሌ ያለው ሰው መሆኑን ሊጠቁም ይችላል፡፡
ተ. እኛ ራሳችንን ከምንመለከተው በላይ ሌሎች ሰዎች ይመለከቱናል፡፡ ታዲያ ሌሎች ሲመለከቱን መልካም ነገር ከእኛ እንዲያገኙ መጣር የለብንምን? ይህም ስለ ስሜታቸው እንደምንጠነቀቅላቸው የሚያሳይ መሆን አለበት፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች ግን ነገረ ሥራቸው በሙሉ ወዳጆቻቸው ስለራሳቸው በሚያስቡበት ጊዜ እንዲሸማቀቁ የሚያደርግ ነው:: በዚህም ተግባራቸው «እያንዳንዳችን እንድናንጸው እርሱን ለመጥቀም ባልጀራችንን ደስ እናሰኝ» በማለት ሐዋርያው የተናገረውን ምክር ቀኑን ሙሉ ሲሽሩት ይውላሉ፡፡ ሮሜ 12÷2
ቸ. አንቺ ሴት እስኪ ነፍስሽን ትሕትና አስተምሪያት።ሁልጊዜ ደምቆና አሽብርቆ መታየት ብቻ ሳይሆን ተራና መናኛ ልብስን መልበስንም ተለማመጂ።«ሞትን የምታለብስና ወደ ሲኦል የምታወርድ አፍአዊ ጌጥን» ከልክ በላይ አትውደጂ:: ይህ በነፍስ እንደ ማጌጥ በእግዚአብሔር ፊት አያኮራሽምና፡፡ ለአፍአዊ ጌጥ የማትጓጓ ሴት ዘውድ ከደፋ ንጉሥ ትበልጣለች፡፡ እንዴት? ቢባል ሰው ሁሉ ለቁሳቁስ ሲገዛ እሷ አትገዛምና፡፡
ነ. አንዳንድ ሰዎች ስለ አለባበስ ባይሰበክ ይመርጣሉ።ብዙዎች ደግሞ «ለምን ስለ ሌላ ነገር አታስተምሩም? ከዚህ ይልቅ ብዙ አንገብጋቢ ርእሰ ጉዳይ የለምን?» ይላሉ።አርግጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር ይኖር ይሆናል፣ ሆኖም የአለባበስ ጉዳይም በክርስትና ዐቢይ ነገር ነው።ያ ባይሆን ኖሮ ሐዋርያትም ሆኑ ሊቃውንት ስለ አለባበስ ብዙ ባልጻፉ ነበር፡፡ ይህ ጉዳይ ተራ ነው የምትዪ ከሆነ አለባበስሽን በማስተካከል ተራነቱን አንቺ ራስሽ አስቀድመሽ ማሳየት ይገባሻል፡፡ ካልሆነ በጉዳዩ በየጊዜው ላለመገሠጽ ብለሽ ትምህርቱን ማናናቅሽ አስተዋይ አያደርግሽም።

ቀጣይ ምዕራፍ ዘጠኝ ክፍል ዐራት :
👉አለባበስሽ ስለ አንቺ በደንብ ይናገራል!
👉አፋዊ ጌጥን መውደድ "አምልኮ ጣዖት ነው!" የሚባለው ለምንድር ነው?
በሚል ይቀጥላል .....
ለጥያቄና አስተያየት @Ethiopian_Orthodox_bot ተጠቀሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…
Subscribe to a channel