ethiopian_orthodox | Unsorted

Telegram-канал ethiopian_orthodox - የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

30344

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Subscribe to a channel

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሠ. ስለወር አበባ በተጻፈበት አንቀጽ እንደተገለጸው በወቅቱ ልዩ ልዩ የሕመም ስሜት እንደሚኖር የታወቀ ነው። በዚህ ጊዜ ሕመሙ የጠና ከሆነ ወደ ሐኪም ዘንድ መሄድ ግድ ይላል፡፡ አብዛኞቹ የሕክምና ባለሙያዎች ከሚሰጡት ሙያዊ እገዛ በተጨማሪ «ከወንዶች ጋር ሩካቤ ማድረግ ስትጀምሪ ሕመሙ ይቀንሳል ወይም ይተውሻል» የሚል የመፍትሔ ምክር መደመጡ አይቀርም፡፡
አስቀድሞ በውስጣቸው ከነበረው ተቃራኒ ጾታን የመፈለግ ግፊት በተጨማሪ ይህን ለመሰለ ሕመማቸው ሩካቤ መፈጸም መፍትሔ እንደሆነ ሲነገራቸው ዔሳው «ብኩርናዬ ለኔ ምኔ ናት?» እንዳለ «ድንግናዬ ምን ያደርግልኛል?» በማለት ለዝሙት የተጋለጡም ሰዎች አልጠፉም፡፡ ስለዚህ ይህን የመሰለ ክብር እንድናጣ በብዙ መልኩ መፈተን አይቀርልንም፡፡ ለጊዜው የሚሆን መጠነኛ የሕመም ስሜትን መታገሥ አቅቶን ለማያልፍ ጸጸት አንጋለጥ፡፡ በዚህ መልኩ እንኳን ሐኪም መክሮን ይቅርና አዞንም ቢሆን ሕገ ወጥ ሩካቤ ማለትም ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ሩካቤን መሞከር የለብንም፡፡
ረ. ድንግልና ያላትን ሴት አጭተሃል እንበል፡፡ ምንም ሳትደርስባት ራሳችሁን ጠብቃችው እየኖራችሁ ሳለ በድንገት ተለያያችሁ:: የዚህ ጊዜ ምን ይሰማሃል? ወይኔ ሕጓን እንኳን በገሠሥኩ ኖሮ እያልክ ትቆጫለህን? ሊቆጭህ አይገባም! በእርግጥ ይህንን የሚያውቁ ጓደኞችህ አሁን አንተ ወንድ ነህ? እያሉ ሊዘባበቱብህ ይችላሉ:: አንተ ግን መመካት አይገባህም እንጂ ከወንድም ወንድ መሆንህን እመን፡፡ ምክንያቱም ከጋብቻ በፊት ድንግልናን መግሠሥ የዘማውያን ሙያ እንጂ የወንድነት መታወቂያ አይደለም፡፡ እንዲያውም ወንድ የሚያሰኘው ራስን በንጽሕና ለመጠበቅ መቻል ነው።
ደግሞስ አንተን ብቻ ድንግልና ወሳጅ ማን አደረገኽ? አንተ የሷን ድንግልና በምትወስድበት ጊዜና ጎዳና ያንተም ድንግልና እንደሚገሠሥ አታውቅምን? እኔ እንኳን ድንግልናዬን ቀደም አጥፍቼው ነበር ብትል እንኳን ኃጢአት እየሠራኽ መሆኑን ማን በነገረኽ? ዝሙት መሥራት ስልጣኔ፣ ችሎታና ዘመናዊነት አይደለም:: ከሰብአ ትካት፣ ከሰብኣ ሰዶምና ከሰብኣ ገሞራ ጊዜ ጀምሮ የነበረ ዘማዊነት በምን ምክንያት ስልጣኔና ዘመናዊነት ይሆናል፡፡

ሰ. ሊጋቡ ሲቃረቡ ድንግልናቸውን እንደሚያጡ ሰዎች ሁሉ የተጫጩ ወንድና ሴት የሚለያዩበት ሁኔታም ሲፈጠር ድንግልናቸውን ያጡ ብዙዎች አሉ፡፡ ሁለቱ ተፈቃቃሪዎች ራሳቸውን ጠብቀው ከኖሩ በኋላ የሚያለያያቸው አለመግባባት ሲፈጠር «ንጽሕናቸውን ሳላስፈርስ?» በማለት ሰይጣን በቁጣ ይነሣሣባቸዋል፡፡ ይህ ርኩስ መንፈስ በሁለቱም ወይም ለጥፋት ሐሳቡ በተመቸው በአንደኛው ያድርና ሲሆን በውዴታና በማባበል ካልሆነ ደግሞ አስገድዶ በመድፈርም ቢሆን እንዲፈጽመው ሊገፋፋው ይችላል፡፡
ፍቅረኛሞች የሚለያዩበት ጊዜ እጅግ ፈታኝ ወቅት ነው፡፡ ስለዚህ በፍቅር ከሚኖሩበት ጊዜ ይልቅ በሚለያዩበት ጊዜ ንጽሕናን ጠብቆ ለመቆየት የበለጠ ጥንቃቄ ይጠይቃል:: በሚለያዩበት ወቅት ሁለቱም ወይም ከሁለቱ አንዱ መከፋታቸው አይቀርም ስለዚህ እንክብካቤ ባላደርግ «ግፍ» ይሆንብኛል የሚል ሐሳብ ይፈጠርና ቢያንስ አንዱ ወገን መንከባከብ እንዳለበት ይሰማዋል፡፡ የተጎዳን ሰው መንከባከብ ባልከፋ ነበር ነገር ግን መሰናክልና ድንግልናን ማጣት የሚፈጠረው በዚህ የመንከባከብ ሂደት ውስጥ ነው:: ስለዚህ ይህን በመሰለ ጊዜ ጠንቀቅ ማለት ይበጃል::
ከሁሉ የሚያስደንቀውና የሚያሳዝነው እንዲህ ባለ የመለያየት ዋዜማ ፍቅራቸው ለሁልጊዜ መሆኑን የገለጡና ማስታወሻ ያኖሩ እየመሰላቸው ድንግልናቸውን የሚጥሉ ሴቶች መኖራቸው ነው:: አንዳንዶችማ «ለሌላ ከምሰጠው» እስከ ማለት ደርሰው ለሚለያቸው ወንድ ድንግልናቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ:: እንዲህ የምታስቢ ከሆነ እስኪ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ሞክሪ፡፡ እየተለየሽ ያለው ወንድ ኋላ ከምታገቢው ወንድ የበለጠ ተፈቃሪ መሆኑን በምን አረጋገጥሽ? ከበለጠስ ለምን ትለይዋለሽ? ለሚመጣው ባልሽስ ያስቀረሽለት ምን ስጦታ አለሽ? ምን ላድርግለት የሚያሰኝ እጅግ ተወዳጅ ባልስ ብታገኚ የቀድሞ ሥራሽ ጸጸት አያስከትልብሽምን? የምታገቢው ባል ከቀድሞ ፍቅረኛሽና ወደ ፊት ልታገኚው ከምትችይው ማንኛውም ወንድ የበለጠ ልታፈቅሪው ካልቻልሽ ማግባትሽ መቼም ቢሆን ፍጹም ትክክል አይሆንም፡፡ ስለዚህ ድንግልናን ጨምሮ ምርጥ ነገሮች ሁሉ ሊያገባ ላጨሽ ወይም አጭቶሽ ለነበረ ሰው ሳይሆን ላገባሽው ወንድ ብቻ መሆን ይኖርበታል:: በተጨማሪም ዝሙት ምጽዋት ሊሆን እንደማይችል «ዜና ሥላሴ» ይናገራል፡፡ ስለዚህ ዝሙት ሠርተሽ «አሳዝኖኝ ነው!» ብትዩ የሚሰማሽ የለም፡፡
ሸ. የመለያየት ነገር ሲነሣ ሙሉ ለሙሉ ላለመገናኘት የሚደረግ መለያየት ሳይሆን በሥራና በትምህርት ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ ርቆ የመሄድ ዓይነት መለያየት በሚፈጠርበት ጊዜ ወንድና ሴት ተፋቃሪዎች ሩካቤ መፈጸምን ሻይ፣ ቡና እንደ ማለት እየቆጠሩት ይገኛል፡፡ በዚህ ዓይነት አጋጣሚ ክብረ ድንግልናቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ይህም ሰው ስለ ድንግልና አጠባበቅ ያለውን የተዛባ አመለካከት ያሳያል፡፡
ቀ. ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «ስለ ድንግልናው ያፈረ ሰው ቢኖር» 1ኛ ቆሮ 7÷36 በድንግልና መኖራቸው የሚያሳፍራቸው፣ ያልሠለጠነ፤ አላዋቂ፣ ጤና ቢስ፣ ወንድነት የሌላቸውና ተፈላጊነትን ያጡ ተደርገው እንደሚቆጠሩ አድርገው ሚያስቡ ብዙዎች አሉ፡፡ እንደዚህ ያሉ ሰዎች ማንኛውም ሰው አብሮአቸው ቢተኛ ተፈላጊነታቸው፣ አዋቂነታቸውና ሥልጡን መሆናቸው የተረጋገጠ ይመስላቸዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ ሐሳብ በተገኘው ተራ አጋጣሚ ንጽሕናችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ከማድረግ ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡ ስለሆነም ይህን ከመሰለ ደካማ አመለካከት ተላቆ ንጽሕናን መጠበቅ ተገቢ ነገር ነው፡፡

በ. ሰው ወደዚህ ዓለም ከመጣ ጀምሮ በልዩ ልዩ ጊዜ በተለያየ ደዌ ሲሠቃይ ይታያል።በዚህ ጊዜ የታመሙትን በሚገባ ማስታመም ለመንግሥተ ሰማይ የሚያበቃ የጽድቅ ሥራ ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ ክፉ መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች ታማሚዎችን በማስታመም ሰበብ ዝሙት ሲፈጽሙባቸው መስማት ለጆሮ የሚዘገንን ቢሆንም ይህ አስነዋሪ ተግባር በተለያየ ጊዜ ተፈጽሟል። በዚህ ድርጊታቸው ክስ የተመሠረተባቸው ብዙ የሕክምና ባለሙያዎችም ይገኛሉ።
እንዲህ ባሉ ቦታዎች የበለጠ ለዝሙት ተግባር የሚያነሣሡ ምክንያቶች አይጠፉም:: አንደኛ ቦታው መጠመቂያ ወይም የሕክምና ቦታ እስከ ሆነ ድረስ ሰዎች ከልብስ ተራቁተው የሚታዩበት ጊዜ አለ፡፡ሌላው በተለይ በጸበል መጠመቂያ ስፍራዎች ደግሞ ሰይጣን ታማሚዎችን እያወራጨ ከልብስ ያራቁታቸውና አካላቸውን እያዩ ሌሎች በዝሙት እንዲፈተኑ ያደርጋል፡፡ ከዚህም አልፎ ተርፎ ታማሚዎቹን «ሮጠን እናመልጣለን›› እያሰኘ ከአስታማሚዎቻቸው ጋር እንዲጓተቱና እንዲታገሉ ያደርጋል:: ታማሚዋና አስታማሚው የተለያየ ፆታ እስካላቸው ድረስ ይህ መላፋት በአስታማሚው ላይ የሚፈጥረው የፍትወት መነሣሣት በምንም ለመመለስ የሚያስቸግር ይሆናል፡፡ ይህን አጋጣሚ እንደ ምቹና እንደ አስደሳች ነገር በመቁጠር ማስታመም ጸጋቸው ሳይሆን ለመላፋትና የሰዎችን ገላ ለመመልከት ከጠበል ስፍራ የማይጠፉ ሰዎች እንዳለ አስተውለው ያውቃሉ? እንዲህ ከሆነ ከየትም ቦታ ይልቅ በጠበል ቦታዎች በይበልጥ ከሰይጣነ ዝሙት መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ አያጠራጥርም።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሕይወተ ወራዙት(የወጣቶች ሕይወት)
 ምዕራፍ ስምንት ክፍል አምስት

.................................................
ድንግልናን የሚያሳጡ አደገኛ ወቅቶች፣ ቦታዎችና አጋጣሚዎች
ሕጋዊ ባልሆነ ሩካቤ ምክንያት ሰዎች ድንግልናቸውን የሚያጡት በተለያየ የዕድሜ ደረጃ ላይ እያሉ ነው፡፡ አንዳንዶች ገና በልጅነትና በመጀመሪያዎቹ የወጣትነት አፍላ ጊዜያት ድንግልናቸውን ያጣሉ። ሌሎች ደግሞ አስቸጋሪውን የወጣትነት ዕድሜ አጋምሰው ክብራቸውን የሚያጡበት ሁኔታ ይፈጠራል፤ጥቂቶች ደግሞ ያን ሁሉ የወጣትነት ፈተና ካገባደዱ በኋላ ወደ መጨረሻ ሲደርሱ ክብራቸውን የሚያጡበት ጊዜ አለ፡፡ በዚህ መልኩ ከፍጻሜ ሲደርሱ ለክብር አለመብቃት በእጅጉ ያስቆጫል።
ይህ የሚሆነው ልጆች ስለተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ከሚኖራቸው የአመለካከት ልዩነት፣ ለዚህ ዓይነቱ ግንኙነት ከሚኖራቸው መጋለጥ፣ ከራሳቸው መንፈሳዊና አካላዊ ጥንካሬ፣ ከባሕልና ከአስተዳደግ ልዩነት ወዘተ የተነሣ ነው:: ሆኖም ግን ብዙ ነገር ተቋቁመው ካለፉ በኋላ የፈተናው መጠን በሚቀንስበትና ወደ ጋብቻ በሚቃረቡበት ሰዓት ሳያገቡ ድንግልናን ማጣት ከሁሉ የበለጠ የሚያስቆጭ ነው።

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተገልጾ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ በምድር መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ እኔ ኃጢአቱን ሁሉ እደመስሳለሁ በመከራም ውስጥ ሁኖ በባሕርም ሆነ በየብስ ወይም በደዌ በስምህ የሚለምነኝን እኔ ፈጥኜ ከመከራው አድነዋለሁ ይህንንም ጌታችን ተናግሮ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ፡፡

ከዚህ በኋላ ራሱን ዘንበል አድርጎ በሰይፍ ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያት አክሊላትን ተቀበለ፡፡ ከአገልጋዮቹም የቀሩት ሥጋውን ወስደው በልብስ ጠቀለሉት ወደ ሀገሩ ልዳም ወሰዱት፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው በውስጥዋ አኖሩት ከእርሱም ቍጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ፡፡

የሰማዕቱ ረድኤትና በረከት አይለየን!
©ስንክሳር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

2. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “ማርያም ቤዛዊተ ዓለም” አትባልም በማለት ከቤተ ክርስቲያናችን የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ የሰጡት ሕጸጽ ያለበት ትምህርት በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በሚገባ ተመርምሮና ተጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ በአስቸኳይ እንዲቀርብ ብፁዕነታቸውም ጉዳዩ ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በተአቅቦ እንዲቆዩ፣

3. ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት እና ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፏቸው የስሕተት ትምህርቶችና በሌሎችም መምህራን የተላለፉ ነቀፋ ያለባቸው ትምህርቶች ካሉ የሊቃውንት ጉባኤ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ አንጻር በሚገባ መርምሮና አጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብ፣

4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኝ ብዙኃን ስርጭት ድርጅት ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር ሚዲያ የአየር ሰዓት የሰጠበትን ዝርዝር ሁኔታና ከማኅበሩ ጋር በተያያዘ አየር ላይ ያዋላቸውን ትምህርቶች የሚያሳይ ሪፖርት እንዲያቀርብ ይደረግ በማለት ቋሚ ሲኖዶስ ወስኖ የዕለቱን ጉባኤ በቅዱስነታቸው ጸሎተ ቡራኬ አጠናቋል።

ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም:
ተነስቷል በዚህ የለም(2):
መድኃኔዓለም
ሞት የማይችለው የበረታ:
ኃያል ነው ማይረታ ማኅተሙን የፈታ:
የትንሳኤው ጌታ።
*አዝ*
ገዳዩ ሞት በእርሱ ድል መንሳት ተዋጠና:
ሰንሰለቴን ቀንበሬን ተካው በበገና:
ሞት ሆይ መውጊያህ የታል እያልን ምንዘምረው:
መስቀልህ ጦር ስምህ ጋሻችን ሆኖልን ነው :
ዳንን የምንልው።
*አዝ*
ተሻግረናል ስላሻገርከን ለዘለዓለም:
በመቃብር ሞት ይይዝህ ዘንድ ከቶ አልቻለም:
ኃይለኛውን በኃይል አስረኸው ላይፈታ:
ዘመርንልህ አሸናፊ ነህ የእኛ ጌታ:
ከፍ በል በእልልታ።
*አዝ*
ሞቶ ማዳን ለማን ተችሏል ካንተ በቀር:
ጌትነትህ ሥራህ ይኖራል ሲመሰከር:
ወዳጄ ሆይ ውበትህ ውብ ነው የሚያበራ:
ተጨነቀ ተንቀጠቀጠ ጠላት ፈራ:
ዕፁብ ያንተ ሥራ።
*አዝ*
መስክሩለት የምስራች ነው ታላቅ ዜና:
መላዕክቱ ነጭ ለብሰዋል ድል ነውና:
ከተማዋ አንዳች ሆናለች በለሊቱ:
በዝማሬ ተንቀጠቀጠ ወኅኒ ቤቱ:
ከበሮውን ምቱ።

በዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
እሁድ
ዳግማይ ትንሣኤ

ዳግማይ ትንሣኤ ማለት ጌታችን በተደጋጋሚ ለሐዋርያቱ እና ለተለያዩ ሰዎች በተለያየ ሥፍራ መገለጡን የምናስብበት ሳምንት ነው፡፡
ቤተክርስቲያን ከትንሣኤው እስከ ዳግማይ ትንሣኤው ያለውን ሳምንት እንደ አንድ ቀን ነው የምታየው ክብር ይግባውና የትንሣኤው ጌታ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው ዕለት ጀምሮ ከመግደላዊት በመጀመር ለልዩ ልዩ ሰዎች ተገልጧል፡፡
፩. ለመግደላዊት ማርያም ተገልጧል፡፡(ዮሐ፳፡፲፩)
፪. ለሴቶች ተገልጧል፡፡(ማቴ፳፰፡፱)
፫. ለሐዋርያው ጴጥሮስ ተገልጧል፡፡(ሉቃ፳፬፡፴፬)
፬. ለኤማውስ መንገደኞች ተገልጧል፡፡(ሉቃ፳፬፡፲፫)
፭. ከሐዋርያው ቶማስ በቀር ለሐዋርያት ተገልጧል፡፡(ዮሐ፳፡፲፱)
፮. ሐዋርያው ቶማስ ባለበት ለደቀ መዛሙርቱ በዝግ ቤት ተገልጧል፡፡(ዮሐ፳፡ ፳፮)
፯. በጥብርያዶስ ለሰባቱ ሐዋርያት ( ጴጥሮስ ቶማስ ናትናኤል ሉቃስ ኒቆዲሞስ ይሁዳ ያዕቆብ ) ተገልጧል፡፡
፰. ለአምስት መቶ ሰዎች ተገልጧል፡፡(፩ቆሮ፲፭፡፮)
፱. ለሐዋርያው ያዕቆብ ተገልጧል፡፡(፩ቆሮ፲፭፡፯)
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተገለጠባቸው በእያንዳንዱ መገለጦች ውስጥ ለሐዋርያቱ ሦስት አደራዎችን ሰጥቷቸዋል፡፡ እነዚህም :-
በመጀመሪያው የትንሣኤ ዕለት የኃጢአት ስርየት የማድረግን ሥልጣን ሰጥቷቸዋል(ዮሐ፳፡፳፫)
በሁለተኛው ደግሞ የማስተማር ጸጋ ሰጥቷቸዋል(ማቴ፳፰፡፲፮-፳)
በሦስተኛው ሕጻናትን ፤ ወጣትን እና ሽማግሌዎችን የመጠበቅና የመምራት ኃላፊነት ሰጥቷቸዋል፡፡(ዮሐ፳፩፡፲፭-፲፰)
በዚህም ሐዋርያዊት ወይም የሐዋርያትን ፍኖት የተከተለች በሐዋርያት በኩል ይህንን ሁሉ ጸጋ ያገኘች ቅድስት ፣ አንዲት ፣ ኩላዊት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ሁሉንም አደራ እና መመሪያ ተግባራዊ እያደረገች ትገኛለች፡፡
ሐዋርያዊት የሆነች ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በዚህ ዕለት ልክ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ጋር በነበሩበት ዘመን ይሰማቸው የነበረውን ደስታ በማሰብ ሥርዓተ አምልኮቷን ትፈጽማለች፡፡
በግጻዌው መሰረት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናትም ሆነ ገዳማት የሚዘመረው
መዝሙር "ይትፌሳህ ሰማይ ወትትሐሰይ ምድር" ትርጉም "ሰማይ ይደሰታል ምድርም ሐሴት ታደርጋለች" የሚለው ሲሆን ምስባኩ ደግሞ "ይትነሣእ እግዚአብሔር ወይዘረው ጸሩ ወይጎይዩ ጸላእቱ እምቅድመ ገጽ ከመ የሀልቅ ጢስ ከማሁ የሀልቁ" ትርጉም እግዚአብሔር ይነሳ ጠላቶቹ ይበተኑ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ ጢስ እንደሚበን እንዲሁ ይብነኑ" (መዝ፷፯(፷፰)፩-፪)
ቅዳሴው የዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ሲሆን ወንጌሉ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ሃያ ከቁጥር አሥራ ዘጠኝ እስከ ፍጻሜ ነው፡፡ በዚህ ወንጌል ላይ ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ ያላቸውን ሐዋርያት እናገኛለን፡፡ "ጌታን ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው፡፡" (ዮሐ፳፡፳)
ያም ቀን ዕለተ እሑድ ማታ ላይ ነበር፤ የጨለማው መጨለም ፤ የአይሁድ ዛቻና ማስፈራራት ሐዋርያትን እጅጉን አስጨንቋቸዋል ከአሁን አሁን ገደሉን ፤ በቃ ጠፋን፤ይህን እና ይህን ብቻ እያሰቡ በራቸውን እንዳይከፍቱት በጠንካራ ቁልፍ ቆልፈው የጭንቀታቸው መጠን እየጨመረ እየጨመረ... ባለበት በዚህ ጊዜ ምንም እንኳን ከመከራው እና ከጭንቀቱ ብዛት በሩን ዘግተው ሞታቸውን ቢጠባበቁም በሞት ላይ ስልጣን ያለው ተስፋን መቀጠል የሚችል አምላክ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ብሎ መካከላቸው ሲቆም ከመቅጽበት ጌታን ባዩ ጊዜ በሐዘን የጨፈገገው ፊታቸው በደስታ በራ፡፡ ክብር ለአምላካችን ይሁን፡፡ የእኛንም የተዘጋ ቤታችንን ከፍቶ ገብቶ በሐዘን እና በጭንቀት የጨፈገገው ፊታችንን በደስታ አብርቶ ሰላማችንን ይመልስልን፡፡ አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

" የጌታ ትንሣኤ "

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ እና ዘማሪ ዲያቆን ሄኖክ ሞገስ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ ክ/የማኅበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር  አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ።

ሚያዚያ ፲፮/ ፳፻፲፯ ዓ.ም

መምሪያው ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር በጻፈው ደብዳቤ ማኅበሩ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ ርቱዕ እምነትን ከሥነ ምግባር ጋር ይዞ የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያን ያሳዘነ፣ እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ለጠላት መሳለቂያ እንድትሆን ያደረገ፣ ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ጋር የሚቃረን እመቤታችን ቤዛ አይደለችም የሚል ጤናማ ያልሆነ ትምህርት ሚያዝያ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በማኅበሩ ሚዲያ ማስተላለፉን እንደተመለከተ ገልጾ የማኀበራት ምዝገባ ክትትል እና ቁጥጥር መምሪያው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ጸድቆ በተሰጠው ደንብ መሠረት በማኅበራት መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮች ሲፈጠሩ ተገቢውን ክትትልና አስፈላጊውን እርምት የመስጠት ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ በደብዳቤው ለተጠቀሱ አምስት ነጥቦችን በማኅበሩ በኩል አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥባቸው በጥብቅ አሳስቧል።

መምሪያው በጻፈው ደብዳቤ ላይም  በዕለተ ስቅለት የተላለፈው ትምህርት ቪዲዩ በአስቸኳይ ከማኅበሩ ዩቲዩብ እንዲወርድ እንዲያደርግና በዕለቱ የተላለፈውን ትምህርት ሙሉ ቪዲዮ ቅጂ ለመምሪያው እንዲያቀርብ ጥብቅ መመሪያ ሰጥቷል።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
ሐሙስ
አዳም
ይባላል
ይህ ዕለት አዳም ሐሙስ (አዳም) የተባለበት ምክንያት አምላካችን እግዚአብሔር ለአዳም "ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ቃል የገባበት ዕለት በመሆኑ ይህንን ስያሜ አግኝቷል፡፡(ዘፍ፫፡ ፲፭) ፤ (መጽሐፈ ቀለሜንጦስ አንቀጽ ፰ እና መጽሐፈ አክሲማሮስ ዘዓርብ ቁ. ፲፫) ቤተክርስቲያን በዋናነት ለአዳም የተሰጠውን የተስፋ ቃል አምላካችን መፈጸሙንና የሰው ልጆች ሁሉ በትንሣኤው ከሞት ነጻ እንደወጡ በዚህ ዕለት ታስተምራለች፡፡
በዚህ ዕለት በአባታችን በአዳም በእናታችን በሔዋን አንጻር:-
፩. ከውድቀታችን ይልቅ መነሳታችንን
፪. ከባርነታችን ይልቅ ነጻነታችንን
፫. ከለቅሶአችን ይልቅ መጽናናታችንን
፬. ከሀዘናችን ይልቅ ደስታችንን
፭. ከመሰበራችን ይልቅ መጠገናችንን
፮. ከመታመማችን ይልቅ መፈወሳችንን
፯. ከድካማችን ይልቅ ኃይላችንን
፰. ከመረሳታችን ይልቅ መታወሳችንን
፱. ከጨለማችን ይልቅ ብርሃናነችንን
፲. ከፍርሃታችን ይልቅ ድፍረታችንን
፲፩. ከክህደታችን ይልቅ እምነታችንን
፲፪. ከጥላቻችን ይልቅ ፍቅራችንን
፲፫. ከመታወካችን ይልቅ ሠላማችንን
፲፬. ከሞታችን ይልቅ ሕይወታችንን
፲፭. ከመቃብራችን ይልቅ ትንሣኤአችንን የምናስብበት ዕለት ነው፡፡
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ብርሃን ወጣ ከመስቀሉ የሚያንጸባርቅ"

በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

✞"ክርስቶስ ህያው ነው"✞

ክርስቶስ ህያው ነው ሞት ይዞ ያላስቀረው
የለም ከመቃብር ተነስቷል በክብር(፪)

በገዛ ፈቃዱ ነፍሱን ስለሰጠ
የጨለመው ዓለም በብርሃን ተዋጠ
ሲኦል ድል መንሳቱ መውጊያውም ታጠፈ
የሞት ሥልጣን በሞት ስለተሸነፈ

አዝ---

የጥሉ ግድግዳ በሞቱ ፈረሰ
የነፍሳችን ቁስል በእርሱ ተፈወሰ
ከቶ አላስቀረውም የመቃብር ድንጋይ
ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ኤልሻዳይ

አዝ---

ዓለሙን እንዲሁ እግዚአብሔር ወዶ
የሰው ልጅ ከበረ ዲያብሎስ ተዋርዶ
ይገዛን ይነዳን ያስጨንቀን ነበር
በሞት ላይ ተራመድን አምላካችን ይክበር

አዝ---

ህይወት ይሰጠን ዘንድ ስለኛ የሞተው
ቤዛችን ክርስቶስ ሞትን ድል አረገው
የሞተው ተነሳ በመቃብር የለም
ዳግመኛም ይመጣል ሊፈርድ በዓለም

አዝ---
  በዘማሪ ዲ/ን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከትንሳኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
ማክሰኞ
ቶማስ
ይባላል
እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሲፈጥረው የሚያንቀላፋና የሚነቃ አድርጎ ፈጥሮታል፡፡
ማንቀላፋቱ የሞት ፤ መንቃቱ ደግሞ የትንሣኤ ምሳሌ መሆኑን ስናስብ ሁሌም ይደንቃል፡፡ አባቶቻችን የትንሣኤውን ምሥጢር በአበው እና በስነፍጥረትም ይመስሉታል፤ አቤል ከሞተ በኋላ በደሙ መናገሩ እና የሔኖክ ሳይሞት በእግዚአብሔር መሰወሩ የትንሣኤ ምሣሌ ናቸው፡፡ በተፈጥሮ ፀሐይ መውጣቷ የመወለዱ ፤ መጥለቋ የሞቱ እና ዳግመኛ መውጣቷ የትንሣኤው ምሣሌ ነው፡፡
አምላካችን ክብር ይግባውና በእርሱ ያመንን ሁላችን እንደምንነሳ የእርሱ ከሙታን መካከል በሥልጣኑ መነሳት ለሁላችን መነሳት በኩር መሆንና ማረጋገጫም እንደሆነ በቃሉም በተግባሩም ያስተማረን የትንሣኤ ጌታ ነው፡፡
በቃሉ "በመቃብር ያሉት ሁሉ ድምጹን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል ፤ መልካም
ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ፤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ " (ዮሐ፭፡፳፱) እንዲሁም በተግባር የአራት ቀን ሬሳ አልዓዛርን አስነስቷል፡፡(ዮሐ፲፩፡፵፫)
የትንሣኤው ምሥጢር ሁላችን አምላክ የሆንበት ፤ በሁሉ ላይ ሥልጣን ያገኘንበት ፤ነጻ ወጥተን ነጻ አውጪ የሆንበት ፤ ከማይጠፋ ዘር እንደተወለድን ያረጋገጥንበት ፤ ሞትን የተዘባበትንበት ፤ ጨለማን የረታንበት ከዓለም እና ከዲያብሎስ እስራት ነጻ የወጣንበት ልዩ ክብር ኃይል እና ጸጋን ያገኘንበት ምሥጢር ነው፡፡

ይህቺ ዕለትም ይህንኑ ምሥጢር ነው የምትገልጥልን ሐዋርያው #ቶማስ ተብሎ ለምን ተሰየመ የሚለውን ከማየታችን በፊት ማነው የሚለውን ማየት ነገርን ከስሩ እንድንረዳው ይረዳናልና እውነት ሐዋርያው ቶማስ ማነው?
ሐዋርያው ቶማስ
ሐዋርያው ቶማስ የስሙ ትርጓሜ ፀሐይ ማለት ሲሆን የቀድሞ ስሙ ዲዲሞስ ይባላል ትርጉሙም ጨለማ ማለት ነው፡፡ ቁጥሩ ከ፲፪ ሐዋርያት ነው፡፡ (ማቴ፲፡፫)
(መዝገበ ታሪክ ክፍል ሁለት ገጽ፹፱) ፤ ሐዋርያ ማለት ደጅ አዝማች ፤ ቀላጤ ፤ ምጥው ፤ ፍንው ፤ ሂያጅ ማለት ነው፡፡(ወንጌል ቅዱስ ገጽ፻፶፱)
ሐዋርያው ቶማስ አልዓዛር በሞተ ጊዜ ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም አቅራቢያ ወደነበረው መቃብሩ ለመሄድ በተነሳ ጊዜ አይሁድ ሊገሉት ስለሚፈልጉ ሌሎቹ ሐዋርያት ክርስቶስ እንዳይሄድ ቢፈልጉም ቶማሰ ሌሎቹን ሐዋርያት በድፍረት እኛም ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ አብረን እንሂድ ያለ የእምነት ሐዋርያ ነው፡፡ (ዮሐ፲፩ ÷ ፲፮)
ሐዋርያው ቶማስ ጌታችንን በእውነት እስከ ሞት ድረስ ያመነው ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ በ8ኛው ቀን እሁድ ሲሆን ሐዋርያት የነገሩትን ካላየው አላምንም ብሎ የተወጋ ጎኑን ከዳሰሰ በኋላ ነው፡፡ የእምነት ምስክርነቱም ጌታዬ አምላኬም ብሎ የገለጠው፡፡(ዮሐ፳፡፳፬)
ሐዋርያው ቶማስ መንፈስ ቅዱስን ከሐዋርያት ጋር ከተቀበለ በኋላ በ፵፮ ዓ.ም ገደማ በፋርስና በሕንድ እንዳስተማረ የተለያዩ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይገልጣሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ ፤ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ፤ ቅዱስ አምብሮስ ተጠቃሾች ናቸው፡፡በመጨረሻም ብዙ ተአምራት እና ድንቅን አድርጓል፡፡ የሐዋርያው ቶማስ ተአምር እና አገልግሎት ብዙ ተአምራትን ቢያደርግም ለአሁኑ አንዱን ብቻ እናያለን፡፡ የኸውም የሉክዮስ አገልጋይ ሆኖ በሕንጻ ማነጽ እና በሐውልት መስራት ተቀጥሮ በሚሰራበት ወቅት የሉክዮስን ሚስት ከእነ ልጆቿ እና አገልጋዮቿ አሳምኖ ያጠመቀ ሐዋርያ ነው፡፡
ሐዋርያው ቶማስ ለሕንጻ እና ለሐውልት ማሰሪያ ከሉክዮስ የተቀበለውን ገንዘብና ወርቅ ሁሉ ለነዳያን በመመጽወቱ ንጉሡ እጅና እግሩን አሥሮ ቆዳውን አስገፍፎ ስልቻ አሰፍቶ በአሸዋ ሞልቶ አሸክሞት ገበያ ለገበያ ሲያዞረው የሉክዮስ ሚስቱ አርሶንዋ ተመልክታ በድንጋጤ ሞታለች፡፡ ንጉሡም ለሚስቴ መሞት ምክንያት አንተ ነህ ካዳንካት እኔም በአምላክህ አምናለው ሲለው ጌታችን ቁስሉን እንደ ውኃ አቀዝቅዞለት ካለችበት ሄዶ ስልቻውን ቢያስነካት ተነስታለች በዚህም ሉክያኖስ አምኖ ተጠምቋል፡፡
ሐዋርያው ቶማስ በራሱ ቆዳ በተሰራ ስልቻ እየተዘዋወረ ሙት አስነስቷል ፤ ድውያንን ፈውሷል አሕዛብን አሳምኖ አጥምቋል ፤ በቀንጦፍያ አንድ ሽማግሌ ሰባት ልጆቹን ገድለውበት ሰባቱንም ከሞት አስነስቷል ፤ በኢናስም በቃሉ ትምህርት እና በእጁ ተአምራቱ ብዙዎችን አሳምኖ አጥምቋል፡፡
የሐዋርያው ቶማስ ሰማእትነት
በሕንድ የነበሩት የብራሕማን እምነት ተከታዮች የቶማስ ትምህርት የእነርሱን እምነት የሚጻረር እና የሚያጠፋ መሆኑን ተገንዝበው ተነሱበትና በብዙ ስቃይ አሠቃይተው በ፸፪ዓ.ም በሰማዕትነት አርፏል፡፡ በሶርያ ትውፊት መሠረት የሐዋርያው የቶማስ አጽም በአንድ የሶርያ ነጋዴ ተወስዶ በኤዴሳ በክብር አርፏል፡፡ (የእግዚአብሔር መንግሥት ታሪክ በምድር ላይ አንደኛ መጽሐፍ ገጽ ፺፪)
ሐዋርያው ቶማስ ለምን ሰምቶ አላመነም?
እንደ ወንጌል ትርጓሜ ሐዋርያው ቶማስ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዝግ ቤት ገብቶ ሰላም ለእናንተ ይሁን ባለ ጊዜ አልነበረም ፤ በነገሩት ጊዜም አላመነም ያለማመኑ ምክንያት ሰዱቃዊ ስለነበር እና ሐዋርያቱ አይተው እርሱ ሰማው ብሎ ከሚያስተምር ማየት ወዶ ነው፡፡

"ጌታዬ አምላኬም" (ዮሐ፳:፳፰)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከሁሉ የሚያሳዝነው «ድንግልናዬን ያጣሁበትን መንገድ ምንም እንኳን በመንፈሳዊ ዓይን ሳየው ሥራዬ እጅግ ቢያስቆጨኝም በወቅቱ ግን ያን በማድረጌ ደስተኛ ነበርኩኝ› በማለት ለመናገር የሚደፍሩ ጥቂቶች ብቻ መሆናቸው ነው:: ምክንያቱም የብዙዎች ሰዎች ድንግልና ማጣት በአንድ ወገን ጫናና ፍላጎት ብቻ የተፈጸመ ከመሆኑም በላይ በቦታ ዐቅም እንኳን ጎንን ማሳረፊያ በሌለበት በየሜዳውና በየፈፋው፣ በአጥር ጥግና በመኪና ውስጥ፣ በፊልም ቤት፣ በምግብ ማብሰያና በመጸዳጃ ቤት፣ በየትምህርት ተቋማት ማደሪያዎች፣ በቢሮዎችና በየኮሪደሩ፣ በድብደባ፣ በጉተታና በልዩ ልዩ መንገድ የተፈጸሙ በመሆናቸው ነው:: ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በምንም ዓይነት ምቾት ቢሆን ድንግልናን ያህል ነገር ከጋብቻ ውጭ ማጣት የሚያሳዝን ነገር ቢሆንም በዚህ መልኩ መሆኑ ደግሞ ሲታሰብ እንኳን ይዘገንናል፡፡
ከዚህ በታች ድንግልናን ለማጣት የሚዳርጉ ወሳኝ ወቅቶች፣ ቦታዎችና ሁኔታዎች ተዘርዝረዋል። የተነሡት ነጥቦች አብዛኞቹ እውነተኛ ታሪኮች ናቸው:: ሆኖም «ታሪክ ራሱን ይደግማል›› እንደሚባለው እነዚህ ሰዎች በተጓዙበትና በተጎዱበት የስሕተት ጐዳና የሚሯሯጡ ብዙ ሰዎች ዛሬም ይገኛሉ፡፡ ብልህ ሰው ከሰው ጉዳት ብዙ ይማራል፡፡ በራስ ላይ ክፉ ነገር ሳይደርስ በሌሎች ከደረሰ ጉዳት መማር ታላቅ ዕድል ነው፡፡
ሀ. ብዙዎች ክብረ ድንግልናቸውን ያጡበት መንገድ ተገድዶ መደፈር ነው፡፡ ይህ ጉዳይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዐቢይ መነጋገሪያ እየሆነ ከመጣ ዘመናትን አስቆጥሯል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስም ስለ አስገድዶ መድፈር ተጽፏል፡፡ በወቅቱ በደፋሪነት የሚታወቀው ወንድ ተደፋሪዋ ደግሞ ሴት በመሆኗ ደፋሪው ስለሚገባው ቅጣት ተደፋሪዋ ማድረግ ስላለባት ነገር በዝርዝር ተጽፎ ነበር፡፡ ዘዳ22፥23-27
እንደ ሥርዓተ ኦሪት ከሆነ ተደፋሪዋ ሴት ድርጊቱን መቃወሟ የሚታወቀው ቢያንስ ‹መጮኽ›› በሚቻላት ጊዜ ሁሉ ‹‹መጮኽ› ከቻለች ብቻ ነበር፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በድርጊቱ እንደተስማማች ይቆጠርና ከደፋሪዋ ጋር እርሷም አብራ በድንጋይ ትወገር ነበር፡፡ ለምን ቢባል «በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና» በማለት ቅዱስ መጽሐፍ መልስ ይሰጠናል፡፡ ዘዳ22 ፥ 24
ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ሥርዓት የሚያስተምረው ከመደፈር ለመዳን ሴቶች ከ‹መጮኽ›› አንሥቶ በአለባበስ፣ በድርጊት፣ በቦታ፣ ወንዶች ሥጋ እንዳየ አንበሳ በኃይል እንዲነሡባቸው ከማድረግ በመቆጠብ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለባቸው ነው፡፡ ‹‹መብቴ ነው» እያሉ እንደፈቀዱ መሆን ይቻል ይሆናል፡፡ መብትሽ ከሰው በታች የሚያደርግሽ ከሆነ ምን ይረባሻል? በመንፈስ፣ በሥነ ልቦናና በአካል ጉዳት ላይ ከወደቅሽ በኋላ ለዚህ ያበቃሽ ሰው በሕግ መቀጣቱ ተገቢ ነገር ነው:: ቢሆንም ላንቺ ግን እንኳን መታሰሩ ብቻ ይቅርና በስቅላት የሚቀጣም ቢሆን ምንም አይጠቅምሽም፡፡ላንቺ የሚበጅሽ ከመጀመሪያው ጉዳት ባይደርስብሽ ነውና፡፡ ስለዚህ ከወዲሁ ራስሽን ለአስገድዶ መደፈር አታጋልጪው፡፡
ለ. መደፈር በኃይል በመገደድ ብቻ አይደለም፡፡ ከመነሻው ከወንዶች ጋር የሚኖርሽን ግንኙነት በጥንቃቄ አድርጊ፡፡ እርዳታ ካስፈለገሽ አቋምሽን ገልጸሽ በቀና የመረዳዳት መንፈስ እርዳታ ተቀበይ፡፡ አንቺም ሌሎችን ስትረጂ በዚሁ መንገድ አድርጊው:: በእርዳታና በውለታ ብዛት መደፈር አለና ያለ አግባብ እርዳታ ብታገኚ ሳትወጂ በግድ ራስሽን ትሰጪያለሽ፡፡ ስለዚህ እርዳታ ከመጠየቅ ወይም ከመቀበልሽ በፊት በውኑ ይህን ዓይነት እርዳታ የሚያስፈልገኝ ሰው ነኝን? የሚረዳኝስ ሰው ምን ዓይነት ነው? ፆታው፣ እድሜው፣ የኑሮ ሁኔታው፣ ቅርርባችንስ ምን ያህል ነው? ወይም ምን ይመስላል? ለምን ይረዳኛል? ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ አግኚላቸው።ይህ ሰው ለኔ የሚያደርገውን ያህል እርዳታ የሚያስፈልጋቸውና ከኔ ይልቅ የሚቀርቡት ሌሎች ወገኖች የሉምን? ታዲያ እኔ በምን ምክንያት ቀዳሚያቸው ሆንኩኝ? በመጨረሻም ምን አልባት በመጨረሻ ከዚህ ሰው ያላሰብኩት ፆታዊ ጥያቄ ቢሰነዘርብኝ በምን መልኩ መልስ መስጠት እችላለሁ? ብለሽ አስቢበት።
እግዚአብሔር ስለ ንጽሕና ከሰው የሚፈልገው ንጽሕናን ብቻ ነው:: ዝሙት በንስሓ እንጂ በምጽዋት ሊሠረይ አይችልም፡፡ ንጽሕና በዋጋ የሚሸምቱት ሸቀጥ አይደለምና፡፡ ምጽዋት ተቀባይነት የሚኖረው ከንጽሕና ሥራ ጋር ሲተባበር ነው:: እንዲህ ከሆነ በምንም ዓይነት መንገድ ቢሆን ለተዋለልን ውለታ በሰውነታችን ለመክፈል ማሰብ ሞኝነት ነው:: ውለታ ከተቻለ በዚያው መንገድ ሊከፈል ይገባል:: ካልሆነም «እግዚአብሔር ይስጥልኝ» ማለት ብቻ ውለታን ሊመልስ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ውለታ ብድር አይደለምና። ሆኖም ይህ ምስጢር ሳይገባቸው ቀርቶ ለማግኘት ስለሚፈልጉት ነገር ወይም አስቀድሞ ስለተደረገላቸው ውለታ ሰውነታቸውን ለዝሙት አሳልፈው የሚሰጡና ድንግልናቸውንም በዚህ መንገድ እያጡ ያሉ ሴቶች ቁጥር እጅግ ብዙ ነው:: አንቺስ በሕይወትሽ የምትመኚውን ትልቅ ነገር ሊያደርግልሽ የሚችል ወንድ ብታገኚ በድንግልናሽ እንደማትዋዋዪ ምን ያህል እርግጠኛ ነሽ?
ሐ. ከለላ ለማግኘት ስትዪ ከአንዱ ወንድ ጋር እጅግ አትጣበቂ፡፡ ከፈራሻቸው ሌሎች ይልቅ መጥፊያሽ የተማመንሽበት እንዳይሆን ተጠንቀቂ፡፡ እንዲህ ባለ ጐዳና ብዙዎች ተሰናክለዋልና፡፡ እጅግም በሰው መተማመን አይገባም፡፡ እርሱ ራሱ ሸክላ ነውና፡፡ ለምሳሌ:- በሚያስፈራ ጭለማ ብትሄጂ በራስሽ መመዘኛ ከሰከረ ያልሰከረውን ከእብድ ይልቅ ደግሞ ያልቀወሰውን ተማምነሽ ትጠጊ ይሆናል፡፡ እነዚህን ግን ማን የተሻሉ አረጋቸው? ብሰውስ ይገኙ እንደ ሆን ምን ታውቂያለሽ ? ስለዚህ ይህን በመሳሰለ ጥርጣሬ ብትሄጂ ሊያገኝሽ የሚችለው ጉዳት በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ ሰውን ማመን አያጸድቅምና፡፡

መ. የሰው ባሕርይ እንደ ተቀጠቀጠ ሸንበቆ ነው፡፡ ብዙ ሲደገፉት መሰበሩና መውጋቱ አይቀርም:: በራስም ሆነ በሌላ ሰው ብዙ መተማመን አይገባም:: ብዙ ጊዜ ስሜት ከዕውቀት ይልቅ ይበረታል:: መጥፎነቱን እያወቅን ማድረግ የማንፈልገውን ነገር ደጋግመን ለመሥራት የምንገደደው ስሜት ከዕውቀት ይልቅ ስለሚበረታ ነው።
ብዙ ሰዎች ድንግልናቸውን ሲጠብቁ ኖረው ከዚህ ክብር የሚወድቁት ጋብቻቸውን ለመፈጸም ጥቂት ቀናት ወይም ሰዓታት ሲቀራቸው ነው:: ይህም የሚሆነው ከላይ እንደተገለጸው ቀኑ በቀረበ ቁጥር የኔነት ስሜት እየተሰማቸው በሚፈጥሩት መቀራረብና መተማመን ምክንያት ስለሚዘናጉ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን አስቸጋሪ ወቅት እንደወትሮው ሁሉ መቀራረብን በልክ አድርጐ በጥንቃቄ መጓዝ ያስፈልጋል:: እንዲህ ካልሆነ የአንዲት ቅፅበትን ስህተት በዕድሜ ልክ እንባ ማጥራት ሊሳነን ይችላል፡፡
ከላይ የተጠቀሰውን የማሳሳቻ ዘዴ (ማዘናጋት) በመጠቀም እንጋባ የሚል ሐሳብ ሲነሣ ጆሮአቸውን ይይዙ የነበሩ ወንዶች ከጋብቻ በፊት የሩካቤ ጥያቄ አንሥተው ውድቅ ሲሆንባቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማግባት እንደወሰኑ ቃል መግባትና መሐላ መደርደር ይጀምራሉ፡፡ ይህን የሚያደርጉት «የሚያገባኝ ከሆነ ምን አስጨነቀኝ» በማለት አቋምሽ እንዲላላና እንድትዘናጊ ለማድረግ ነው፡፡ ይህንን በመሰለ ጊዜ አለመፈታትና አቋምን ጥብቅ አድርጐ በመያዝ እስከ ጋብቻ ዕለት ድንግልናን ጠብቆ መቆየት አግባብ ነው፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

📌 በደንብ ይነበብ 📌
          ቅዱሳን በአጸደ ነፍስ ያማልዳሉ☑️

ማስረጃ 2 ይቀጥላል🙌
join በማለት እናበረታታው 🙏
/channel/KM_thoughts
/channel/KM_thoughts

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሚያዝያ ፳፫
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕት


ሚያዝያ ሃያ ሦስት በዚህች ቀን ፀሐይና የአጥቢያ ኮከብ የተባለ ታላቅና ክቡር የሆነ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ የምስክርነት ፍጻሜ ሆነ። የዚህም ቅዱስ አባቱ መስፍን ነው ስሙም አንስጣስዮስ ይባላል ከቀጰዶቅያ አገር ነው የእናቱም ስም ቴዎብስታ ይባላል ከፍልስጥዔም አገር ናት ታናሽ ሆኖ ሳለ አባቱ አረፈ።

ሃያ ዓመትም በሆነው ጊዜ የአባቱን ሹመት ሊቀበል ወደ ንጉሥ ዱድያኖስ ዘንድ ሔደ፡፡ ንጉሡም ጣዖት አቁሞ ጣዖትን እንዲአመልኩ ሰዎችን ሁሉ ሲያስገድዳቸው አገኘው። ይህንንም አይቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ እጅግ አዘነ በእርሱ ዘንድ ያለውን ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች ለምስኪኖች ሰጠ ባሮቹንም ነፃ አወጣቸው።

ከዚህ በኋላ በንጉሥ ፊት ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። ንጉሡም አባበለው ብዙ ቃልኪዳንም ገባለት እርሱ ግን አልተቀበለውም። ለመስማት እንኳ የሚያስጨንቅ ሥቃይን አሠቃየው ጌታችን ግን ያጸናዋል ቍስሉንም ያድነዋል ሦስት ጊዜም እንደ ሚሞት እርሱም እንደሚአሰነሣው በአራተኛውም የምስክርነት አክሊልን እንደሚቀበል ነገረው። ቃል ኪዳንም ሰጠው ስሙ በዓለሙ ሁሉ የተገለጠ ይሆን ዘንድ በተጋድሎና መከራ በመቀበልም ጽኑዕ በሆነ ሥቃይም ሰባት ዓመት እንደሚኖር መላእክትም እንደሚአገለግሉት ነገረው።

ንጉሡም ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለመታዘዙና ባለመመለሱ እጅግ አዘነ ስለዚህም አትናስዮስ የሚባል ታላቅ ሥራየኛ አመጣ እርሱም መርዝን ቀምሞ በጽዋ መልቶ አስማት ደግሞ እንዲጠጣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው። ወዲያውኑ የሚሞት መስሎት ነበር። ቅዱሱም ያንን ጽዋ ጠጣው ምንም ጉዳት አልደረሰበትም።

ያ መሠርይም በክብር ባለቤት በጌታ ኢየሱስ አምኖ በሰማዕትነት ሞተ። ከእርሱም ጋራ ሌሎች ብዙዎች ሰዎች በሰማዕትነት ሙተው የሕይወት አክሊል ተቀበሉ ቍጥራቸውም ሠላሳ ሺህ ሰባት መቶ ነፍስ ነው።

ቅዱስ ጊዮርጊስም በዱድያኖስና በሰባ ነገሥታት ፊት በቆመ ጊዜ በዚያም የተቀመጡባቸው የዕንጨት ወንበሮች ነበሩ። ቅዱሱንም እሊህን የተቀመጥንባቸውን ወንበሮች እንዲበቅሉ እንዲአብቡና እንዲአፈሩ ታደርጋቸው ዘንድ ከአንተ እንሻለን አሉት። በዚያን ጊዜ ጸለየ እንዳሉትም አደረጋቸው ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው ቍጥር የሌላቸው ብዙ አሕዛብ በጌታችን አመኑ።

ከዚህም በኋላ ቅዱሱን ወስደው በጐድጓዳ ብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት። አቃጥለው አሳርረውም ሥጋውንና አጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው ከረጅም ተራራ ላይ በተኑት። ጌታችንም ነፍሱን ወደ ሥጋው መልሷት ደግሞ አስነሣው። ወደ ነገሥታቱም ተመልሶ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ስም ሰበከ ቁጥር የሌላቸው አሕዛብ አይተው አደነቁ በጌታችንም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ።

ነገሥታቱም ደግመው ሙታኖችን ብታሥነሣ አምላክህ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ እናውቃለን በእርሱም እናምናለን አሉት። ቅዱሱም ጸለየ ከጉድጓድም ውስጥ ወንዶችና ሴቶች ጎልማሶችንም አስነሣላቸው እነዚያም በክብር ባለቤት በጌታችን ስም አስተማሩ የገሀነምንም ወሬ ተናገሩ ጥምቀትንም ተቀብለው ተመልሰው አረፉ።

ከሀድያን ነገሥታት ግን ሙታንን ያስነሣህ አይደለም የረቀቁ ሰይጣናትን አሳየህ እንጂ ብለው ተከራከሩ። ከዚያም ከጭንቀታቸው ብዛት የተነሣ ከአንዲት ድኃ ሴት ዘንድ አስጠበቁት እርሷም እንጀራ ልትለምንለት ወጣች የእግዚአብሔርም መልአክ በላዩ ከበጎ ነገር ሁሉ የተመላ ማዕድን አቀረበላት። የዚያች መበለትም የቤቷ ምሰሶ ቅርንጫፍን አበቀለ ታላቅ ዛፍም ሆነ። ያቺም መበለት በተመለሰች ጊዜ የቤቷ ምሰሶ ቅርንጫፍ አብቅሎ ታላቅ ዛፍ እንደሆነ ስለ ማዕዱም ይህን ታላቅ ምልክት አይታ የክርስቲያኖች አምላክ ሰው ተመስሎ ወደእኔ መጣ አለች።

ቅዱሱም እኔ አምላክ አይደለሁም የአምላክ ባሪያ ነኝ እንጂ አላት። እርሷም እንዲህ ብላ ለመነችው የአምላክ አገልጋይ ከሆንክ ቸርነትህ እንድትደርሰኝ አለምንሃለሁ። ዕውር ደንቆሮ ዲዳ ጐባጣ የሆነ ልጅ አለኝና ታድንልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ። ስለ ጌታችን እምነትም አስተማራትና በመስቀል ምልክት አማተበው ያንጊዜም አየ። ቅዱሱም በሌላ ጊዜ እንዲሰማ እንዲናገርና እንዲሔድ እንዲአገለግለኝም እኔ እሻለሁ አላት።

በዚያን ጊዜ ንጉሡ በአገሩ ሜዳ ውስጥ ሲዘዋወር ያቺን ዛፍ አይቶ አደነቀ ስለ እርሷም ጠየቀ ቅዱስ ጊዮርጊስ በእርሷ ዘንድ የተቀመጠባት የዚያች መበለት የቤቷ ምሰሶ እንደሆነ ነገሩት። ንጉሡም ተቆጣ ቅዱሱንም ከዚያ ወስዶ አሰገረፈው በመንኰራኩርም አበራዩት ሙቶም ከከተማ ውጭ ጣሉት ጌታም ከሞት አስነሣው ወደ ነገሥታቱም ተመለሰ ንጉሡም አይቶ ደነገጠ ስለ ሕይወቱም አደነቀ።

ከዚህም በኋላ ይሸነግለው ዘንድ ጀመረ በመንግሥቱ ላይም ሁለተኛ ያደርገው ዘንድ ቃል ገባለት ቅዱስ ጊዮርጊስም እየዘበተበት ነገ በጥዋት ለአማልክቶችህ መሥዋዕትን አቀርባለሁ አንተም ሕዝቡ እንዲሰበሰቡ እዘዝ እኔ ስሠዋ እንዲአዩ አለው፡፡ ንጉሡም ዕውነት የሚሠዋ መስሎት ደስ አለው ወደ ቤተ መንግሥቱም እልፍኝ አስገብቶ አሳደረው፡፡

ለጸሎትም ተነሣ የዳዊትንም መዝሙር አነበበ የዱድያኖስ ሚስቱ እለስክንድርያ ንግሥት ሰምታ ቃሉ ደስ አሰኛት የሚያነበውንም ይተረጒምላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ሰው እስከሆነበት ጊዜ የሆነውን ሁሉ ሊያስረዳትና ሊያስገነዝባት ጀመረ ትምህርቱም በልቡዋ ተቀርጾ በክብር ባለቤት በጌታችን አመነች፡፡

በማግሥቱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአማልክት ሲሠዋ ለማየት ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብ ዐዋጅ ነጋሪ ዞረ የቤቷን ምሰሶ ያበቀለላት ያቺ መበለት ሰምታ ዕውነት መስሏት እጅግ እያዘነች ልጅዋን ተሸክማ እያለቀሰችም ወጣች፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስም በአያት ጊዜ ፈገግ አለ ልጅሽን በምድር ላይ አኑሪው አላት ከዚያም ልጅዋን ጠርቶ ወደ አጵሎን ሒድ ወደእኔም ይመጣ ዘንድ በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ስም እዘዘው አለው፡፡ ያን ጊዜ ያ ልጅ ድኖ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዳዘዘው ወደ ጣዖቱ ቦታ ሒዶ አዘዘው፡፡ በጣዖቱ ያደረ ያ ርኵስ መንፈስም ከማደሪያው ወጥቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አለበት መጥቶ እኔ ሰውን ሁሉ የማስት እንጂ አምላክ አይደለሁም ብሎ በሕዝቡ ሁሉ ፊት አመነ፡፡ ቅዱሱም ትውጠው ዘንድ ምድርን አዘዛትና ወዲያውኑ ዋጠችው ጣዖታቱንም ከአገልጋዮቻቸው ጋራ አጠፋቸው ንጉሡም ከወገኖቹ ጋር አፈረ፡፡

ብስጭትና ቁጣንም እንደተመላ ወደ ንግሥት ሚስቱ ዘንድ ገባ፡፡ እርሷም አምላካቸው ጽኑዕና ኃያል ነውና ክርስቲያኖችን አትጣላቸው አላልኩህምን አለችው፡፡ ይህንንም ከእርስዋ ሰምቶ በእርሷ ላይ እጅግ ተቆጣ ወደ ክብር ባለቤት ክርስቶስ እምነት የከበረ ጊዮርጊስ እንደአስገባት አወቀ፡፡

ከዚህም በኋላ ከከተማ ውጭ እንዲጐትቷትና በመጋዝም እንዲሰነጥቋት አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች፡፡ በዚያም ጊዜ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሥራ ነገሥታቱ ሁሉም ደነገጡ ኀፍረት ደግሞ እንዳይጨምርባቸው ከእርሱም እንዲአርፍ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ እንዲጽፍ ንጉሥ ዱድያኖስን መከሩት፡፡

ያን ጊዜም የክቡር ጊዮርጊስን ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ድል አድራጊ ጊዮርጊስም እጅግ ደስ አለው እሳት ከሰማይ አውርዶ ሰባውን ነገሥት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያን ወገን ጸጥ ይል ዘንድ ጌታችንን ለመነው፡፡ ወዲያው እሳት ወርዶ ከሠራዊታቸው ጋር ሰባውን ነገሥታት አቃጠላቸው፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቋሚ ሲኖዶስ ልዩልዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ።

ሚያዚያ ፳፪/ ፳፻፲፯ ዓ.ም

ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከቤተክርስቲያናችን የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ በፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር አዳራሽ የሰጡትን ትምህርትና በማኅበሩ ሚዲያ የተላለፈበትን ሁኔታ በተመለከተ በዛሬው መደበኛ ጉባኤው በሰፊው ተወያይቶ ለመወሰን በያዘው ቀጠሮ መሠረት በጉዳዩ ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ካደረገ በኋላ የሚከተሉትን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

1. ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር በተለያዩ ጊዜያት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ውጪ በሚዲያው ያስተላለፈው የስሕተት ትምህርት የቤተክርስቲያናችንን አባቶች፣ሊቃውንቱንና መላው ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሳዘነ በመሆኑ በማኅበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ በኩል ጊዜያዊ የእገዳ ደብዳቤ እንዲደርሰው እና በመምሪያው በኩል አስፈላጊው ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ ሆኖ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ መስጠት ይቻል ዘንድ አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ እንዲቋቋም አድርጓል።

በዚህም መሠረት ቋሚ ሲኖዶስ ያቋቋማቸው አጣሪ ልዑካን አጠቃላይ የማህበሩን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እና በሚዲያው ያስተላለፋቸውን የስህተት ትምህርቶች በተመለከተ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ከማህበራት ምዝገባ፣ ቁጥጥርና ክትትል መምሪያ ጋር በመነጋገር በሚገባ መርምርውና አጣርተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከውሳኔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርቡ፣

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

💠ከሰማያት ወርዶ💠

ከሰማያት ወርዶ ሥጋን በመልበሱ
በዓለም መድኃኒት ነጻ ወጣን በእርሱ
የጨለማው ገዢ ዲያብሎስ አፈረ
በጌታ ትንሣኤ የሞት ኃይል ተሻረ(፪)

እልል እልል ደስ ይበለን(፪)
ሞትን ድል ነስቶ ተነሣልን(፪)

አዳም ሆይ በሲኦል ለዘመናት ኖረ
ዛሬ በትንሣኤው ብርሃንን አገኘ
የተስፋው ቃልኪዳን ይኸው ተፈጽሟል
ላንተም ለልጆችህ ዛሬ ሰላም ሆኗል(፪)

አዝ---

የአጋንንት ግዛት ሲኦል ባዶ ቀረ
ነፍሳት ነጻ ወጡ ጠላትም ታሰረ
የብርሃን ግርማ ጸዳል ምድርን ሞላት
በትንሣኤው ብርሃን አገኘን ድኅነት(፪)

አዝ---

የድኅነትን ሥራ በሞቱ ፈጸመ
የዲያብሎስ ሴራ ሥልጣኑ አከተመ
በዕለተ ሰንበት ክርስቶስ ተነሥቷል
የሲኦል እስራት ገመዱ ተፈትቷል(፪)

እልል እልል ደስ ይበለን(፪)
ሞትን ድል ነስቶ ተነሣልን(፬)
በማኅበረ ሰላም መዘምራን

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
ቅዳሜ
ቅዱሳት አንስት
ይባላል
በወንጌል ተጽፎ እንደምናነበው ፍቅሩን
በማሰብ ጨለማውን ሳይፈሩ ወደ መቃብር ስለመጡት መግደላዊት ማርያም እና ማርያም ባውፍልያ በስፋት ቤተክርስቲያን እንድናስብ ስለምታስተምረን ቅዱሳት አንስት ተብሏል።
ወንጌሉ ስለዚህ ዕለት እንዲህ ብሎ ይገልጻል :- "ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን መግደላዊት ማርያም ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብር መጣች ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች።
እየሮጠችም ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ኢየሱስ ይወደው ወደ ነበረው ወደ ሌላው ደቀ መዝሙር መጥታ፦ ጌታን ከመቃብር ወስደውታል ወዴትም እንዳኖሩት አናውቅም አለቻቸው።
ስለዚህ ጴጥሮስና ሌላው ደቀ መዝሙር ወጥተው ወደ መቃብሩ ሄዱ። ሁለቱም አብረው ሮጡ፤ ሌላው ደቀ መዝሙርም ከጴጥሮስ ይልቅ ፈጥኖ ወደ ፊት ሮጠና አስቀድሞ ከመቃብሩ ደረሰ፤ ዝቅም ብሎ ቢመለከት የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ፥ ነገር ግን አልገባም። ስምዖን ጴጥሮስም ተከትሎት መጣ ወደ መቃብሩም ገባ፤ የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ፥ ደግሞም በራሱ የነበረውን ጨርቅ ለብቻው በአንድ ስፍራ ተጠምጥሞ እንደ ነበረ እንጂ ከተልባ እግሩ ልብስ ጋር ተቀምጦ እንዳልነበረ አየ። በዚያን ጊዜ አስቀድሞ ወደ መቃብር የመጣውም ሌላው ደቀ መዝሙር ደግሞ ገባ፥ አየም፥ አመነም፤ ከሙታን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው የሚለውን የመጽሐፉን ቃል ገና አላወቁም ነበርና። ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቤታቸው ደግሞ ሄዱ።
ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተ ውጭ ቆማ ነበር። ስታለቅስም ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች፤ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶበት በነበረው አንዱ
በራስጌ ሌላውም በእግርጌ ተቀምጠው አየች።
እነርሱም፦ አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ? አሉአት። እርስዋም፦ ጌታዬን ወስደውታል ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም አለቻቸው።
ይህንም ብላ ወደ ኋላ ዘወር ስትል ኢየሱስን ቆሞ አየችው፤ ኢየሱስም እንደ ሆነ አላወቀችም።
ኢየሱስም፦ አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊያለሽ? አላት።
እርስዋም የአትክልት ጠባቂ መስሎአት፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ወስደኸው እንደ ሆንህ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ አለችው።
ኢየሱስም፦ ማርያም አላት። እርስዋ ዘወር ብላ በዕብራይስጥ፦ ረቡኒ አለችው፤
ትርጓሜውም፦ መምህር ሆይ ማለት ነው።
ኢየሱስም፦ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።
መግደላዊት ማርያም መጥታ ጌታን እንዳየች ይህንም እንዳላት ለደቀ መዛሙርቱ ነገረች። (ዮሐ፳:፩-፲፰)
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
አርብ
ቅድስት ቤተክርስቲያን/ነፍሳት/
ይባላል
በዚህ ዕለት ቅድስት ቤተክርስቲያን ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት በጥቂቱ በቤተክርስቲያን ዙሪያ ሰባት ነገሮችን እንድናስብ ነው፡፡ እነዚህም፡-
፩. ቅድስት ቤተክርስቲያን በሞቱ እና በትንሣኤው መመስረቷን እናስባለን፡፡
፪. አምላካችን ራሱን አሳልፎ እንደሰጣት እናስባለን፡፡
፫. እርሱ ራሷ እርሷ ደግሞ አካሉ እንደሆነች እናስባለን፡፡
፬. ቅድስት ቤተክርስቲያን መሰረቷ የነብያት እና የሐዋርያት ቃል መሆኑን እናስባለን፡፡
፭. በደሙ ስለመታጠቧ እናስባለን።
፮. ከነገድ ከቋንቋ ሁሉ ስለመመረጧ እናስባለን፡፡
፯. ለዘላለም እንዳትናወጽ በእርሱ ላይ ስለመታነጽዋ እናስባለን፡፡ (ሥርዓተ አምልኮ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ገጽ፻፰፯)

ነፍሳት ከሲዖል የወጡበት ጌታችን በዕለተ ዓርብ በመልዕልተ መስቀል ቅዱስ ሥጋውን ቆርሶ ክቡር ደሙን አፍስሶ በአካለ ነፍስ ወደ ሲዖል ወርዶ በሲዖል ያላችሁ ውጡ በጨለማ ያላችሁ ተገለጡ ብሎ ግእዛነ ነፍስን ( የነፍስን ነፃነት ) ሰበከላቸው ሰይጣንን አሰረው ሲዖልን መዘበረው ነፍሳትን ነፃ አወጣቸው ልምላሜ ገነትን አወረሳቸው ይህ ዕለት በቀጣዩ በትንሣኤ ሳምንት ዓርብ እንዲታሰብ ነፍሳት የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል ፡፡

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"እምይእዜሰ ይኩን ሰላም"

በዘማሪ ብሩክ መኩሪያ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቅድስት ድንግል ማርያምን በማስመልከት ባስተላለፉት ትምህርት ዙሪያ መወያየታቸው ተገለጸ።

ሚያዚያ ፲፭/ ፳፻፲፯ ዓ.ም

ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ ማለዳ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ባለፈው አርብ በስቅለት ዕለት በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በቅድስት ድንግል ማርያም ዙሪያ ያስተላለፉትን ትምህርት በተመለከተ ውይይት መደረጉ ተገልጿል።

በብፁዕነታቸው  የተላለፈውን ትምህርት ዝርዝር ሁኔታ በመመርመርም ውሳኔ ለማስተላለፍ  ይቻል ዘንድ ሁሉም የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምልዓት በተገኙበት  ለረቡዕ ሚያዝያ 22 ቀን 2017 ዓ/ም ቀጠሮ ተይዟል።

በተያያዘ ዜና የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በሆኑት በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ፍራንሲስ ስርዓተ ቀብር ላይ፦ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ(ዘአውሮፓ) ቤተክርስቲያናችንን በመወከል እንዲገኙ ተወስኗል።

ምንጭ :- የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከትንሳኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
ረቡዕ
አልዓዛር
ይባላል
በዚህች ዕለት አምላካችን ትንሣኤ እና ሕይወት መሆኑን በተግባር በታላቅ ተአምራቱ ማሳየቱን የምናስብበት በመሆኑ ስያሜው አልዓዛር ተብሏል፡፡
የአራት ቀን ሬሳን ሕይወት ይዘራበት ዘንድ የፍቅር አምላካችን በሞት በሚፈልጉት በጠላቶቹ ሰፈር ተመላለሰ ፤ የደቀ መዛሙርቱን ክልከላ አልሰማም ፤ የመንገዱ ርቀት አላዘለውም ግን በፍቅር ስለ ፍቅር ሰው ሁሉ ተስፋ የቆረጠበትን ወዳጁ አልዓዛርን ከሞት ሊያስነሳ ወደ ቢታኒያ በፍቅር ተጓዘ ፤ እውነት ነው ሞት ለታወጀብን ለእኛ ለመመላለሱ ምሳሌ ነው ፤ ሞት ድል ያላደረገው የትንሣኤውን ጌታ አምላካችንን በእውነት እንደተነሳ እንድናስብ ቤተክርስቲያን በዚህ ዕለት በአልዓዛር አንጻር ትንሣኤ እና ሕይወት እርሱ እንደሆነ ታስተምረናለች፡፡

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

✞ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ✞

ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ
ክርስቶስ ተነሳ እሰይ እሰይ
እኛንም ከሞት ሊያስነሳ/፪
ክርስቶስ ከሙታን ተነሳ

ሰላም/፬
ለሰው ልጆች በምድር ሆነ ሰላም/፪

ነፍሳትን ነፃ አወጣ ከጨለማ ኑሮ/፪
እሰይ እሰይ
የሲኦልን በር ሰብሮ/፪
ኃይሉንም በኃይሉ ሽሮ

ሰላም/፬
ለሰው ልጆች በምድር ሆነ ሰላም/፪

ሞት በትነሳኤ ተሻረ የሰው ልጅ ከበረ/፪/
እሰይ እሰይ
ጠላት ዲያቢሎስ አፈረ/፪
እጅና እግሩንም ታሰረ

ሰላም/፬
ለሰው ልጆች በምድር ሆነ ሰላም/፪/

እንዳይኖር ለዘላዓለም ሞት በአዳም ላይ
ነግሶ/፪ እሰይ እሰይ
ክርስቶስ ተነሳ ሞትን ደምስሶ/፪
ግርማ መለኮቱን ለብሶ

ሰላም/፬
ለሰው ልጆች በምድር ሆነ ሰላም/፪
በዘማሪት ማርታ ኃይሉ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
ሰኞ
ሰኑይ ማእዶት
ይባላል
እንደ ቤተክርስቲያን ይትባሕል ከትንሣኤ እስከ ዳግማዊ ትንሣኤ ያለውን ሳምንት እንደ አንድ እሁድ እናከብራለን። ለዚህም ነው ዕለታቱን እንደ ሰንበት እናከብራቸው ዘንድ በፍትሐ ነገሥት ላይ አባቶቻችን ትእዛዝ የቀረጹልን።
ማእዶት ማለት መሻገር ማለት ነው። አደወ ማለት ተሻገረ ማለት ሲሆን ማእዶት መሸጋገሪያ ማለት ሊሆን ነው።
ማእዶት የትንሣኤ እሑድ ማግስት ጌታ ክርስቶስ በትንሣኤው ምዕመናንን ከሞት ወደ ሕይወት ያሻገረበት ቀን የትንሣኤው ማሳሰቢያ ነው። (ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ገጽ ፻፶)
መሻገር በዕብራይስጥ ፓሳሕ ከሚባለው ቃል ይመሳሰላል ትርጉሙም ፋሲካ መሻገር ማለፍ የሚል ትርጉም ይሰጣል። ሁላችን እንደምናውቀው እስራኤላውያን ከሚያክብሯቸው አበይት በዓላት አንዱም ፋሲካ ነው። ምክንያታቸው ደግሞ እግዚአብሔር ከሞተ በኩር ያሳለፋቸውን ዕለት ያስቡበታል።
ቤተክርስቲያናችንም ይህንን በዓለ ትንሣኤን የፋሲካ በዓል የማክበሯ ምሥጢር ወይም የትንሣኤው ምሥጢር ነፍሳት በአምላካችን ትንሣኤ ከሞት ወደ ሕይወት ፣ ከአሳር ወደ ክብር ፣ ከሲዖል ወደ ገነት መሻገራቸውን በማሰብ አማናዊው ፋሲካ ወይም አሸጋጋሪው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብላ ታምናለች። እናምናለን።
ቅዱስ ጳውሎስ በብሉይ ኪዳን በታረደው የፋሲካ በግ (ዘዳ፲፮:፮) ምትክ አማናዊው ክርስቶስ እንደታረደልን እና ሞት ላያገኘን በሕይወት ለሕይወት እንዳሸጋገረን ሲገልጥ እንዲህ ብሏል:-"" እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ
አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤" (፩ ቆሮ ፭:፯)
ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እርሾም ሆነ ስለ አዲሱ ሊጥ በምሳሌ የሚነግረን እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ፋሲካ ሲያከብሩ ያደርጉት የነበረ ስርዓትን ነው።
ይኸውም ፋሲካን ያከበሩት ገና ከነጻነት በፊት ነው። ምክንያቱ ደግሞ ከላይ እንዳየነው ከሞተ በኩር መቅሰፍት ለመዳን እና ከእግዚአብሔር ፍርድ ለመዳን ነበር።
በአዲስ ኪዳንም ያለን ክርስቲያኖች በተለይ ይህንን ዕለት ወይም ማእዶትን ስናስብ አምላካችን ከሞት ወደ ሕይወት እንዳሻገረን ፣ ከአሳር ወደ ክብር እንዳሳለፈን ፣ ከድካም ወደ ኃይል እንዳሻገረን ፣ ሁላችን ወደ መንግሥተ
ሰማያት ፋሲካችን በሆነው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሸጋገርን በማመን ሊሆን ይገባል።
የፋሲካው ጌታ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞት ላይ እንድንዘባበትበት ሞትን ፣ ፍርሃትን ፣ ጭንቀትን ፣ ተስፋ መቁረጥን ፣ ሐዘንን ፣ ለቅሶን ፣ ትካዜን ፣ ድካምን ፣ ሥጋትን እና መቃብርን ሁሉ አጥፍቶ አሻግሮናል። ክብር ማዕዶታችን ለሆነ ለእርሱ ይሁን። አሜን ክብር ይግባውና አምላካችን የሰው ልጅ ሞትን እንዲሻገር ሁለት ነገሮች(እምነት እና ምግባር ) እንደሚያስፈልጉት በመዋለ ስብከቱ እንዲህ ሲል አስተምሮናል:-
"እውነት እውነት እላችኋለሁ ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።" (ዮሐ፭:፳፬-፳፭)
ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ዕለቷ ፋሲካ እንደሆነችና እንደሰትባት ዘንድ የተገባች እንደሆነች እንዲህ ሲል በመዝሙሩ አዚሞታል:- " ፋሲካ ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ (ይህቺ የፋሲካ ዕለት ልዩ ናት) ፣ ዛቲ ዕለት ንትፈሳሕ በቲ (በዚህ ዕለት ሐሴት እናድርግባት)..."

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…
Subscribe to a channel