🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣ መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣ እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣ ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣ እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡ አብረን እንደግ !! @EthioHumanity @Ethiohumanity ✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot
❤️ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ:-
እንኳን ለጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!
በዓሉ፦ የሰላም ፣ የፍቅር፣ የደስታ ፣ የመተሳሰብ ፣ የአብሮነት እና የአንድነት በዓል እንዲሆን እንመኛለን።
(መልካም ትንሳኤ ፤ መልካም በዓል!)❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
📍ቡዳን እንዴት ማወቅ እንችላለን?
✍አሌክስ አብርሃም
♦️ሰሞኑን ስለቡዳ አብዝታችሁ ስታወሩ ነበር። ሁላችሁም ቡዳ ስለሚባል የሆነ ቦታ የሆነ ሰው ውስጥ ተደብቆ ሰወችን ስለሚበላ መንፈስ ነው "አለ የለም" ስትባባሉ የነበረው። መኖር አለ። እኔ የምላችሁ ግን... እናንተ ራሳችሁ ውስጥ የቡዳ መንፈስ እንደሌለ በምን እርግጠኛ ሆናችሁ? ለምን ምርመራውን ከራሳችሁ አትጀምሩም? ለማንኛውም የቡዳ መንፈስ እንዳለባችሁና እንደሌለባችሁ ለማወቅ የሚረዱ 5 ነጥቦችን ልንገራችሁ፤ ከዛ ((ቡዳ ፖዘቲቭ)) ወይም ((ቡዳ ኔጌቲቭ)) መሆናችሁን ራሳችሁ ወስኑ።
1ኛ:- ከምትወዱት ሰው ይልቅ የምትጠሉት ሰው ቁጥር ከበለጠ፣ ጥላቻችሁ በግል የማታውቁትን ሰው ከሆነ፣ ምንም ተበድላችሁ ሳይሆን ያ የጠላችሁት ሰው ቆንጆ፣ ሐብታም ወይም ታዋቂ፣ ወይም የተሳካለት ስለሆነ ብቻ ፀጉር የሚያስነጫችሁ ከሆነ ቡዳ ፖዘቲቭ ናችሁ።
2ኛ:- ሁልጊዜ ሰወችን የምትፈልጉት ለችግራችሁ ብቻ ከሆነና እናንተን ሲፈልጓችሁ የምትሸሹ፣ ችግር ውስጥ ሲገቡ እንደአቅማችሁ የማትረዷቸው ከሆነ ቡዳ ከነልጁ ውስጣችሁ ፈርሿል።
3ኛ:- የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀማችሁን ፈትሹ፤ በተደጋጋሚ የምትገኙት ምናይነት ወሬ ላይ ነው? ተጋደሉ፣ ተፋቱ፣ ሚስቱ ከዳችው ባሏ ካዳት፣ ተጣሉ፣ ተለያዮ ተሰዳደቡ ዝምታቸውን ሰበሩ ወዘተ ላይ ከሆነ ቡዳ ውስጣችሁ ተቀምጦ አይናችሁን እንደመስኮት እየተጠቀመ ነው።
4ኛ:- ሀሜተኛ፣ አሽሙረኞች፣ የሰወችን ስም በሐሰት የምታጠፉ፣ አቃጣሪወች፣ ተንኮለኛና አድመኞች፣ ቀናተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ሰውን በመዝለፍ ለማሸማቀቅ የምትሞክሩ (((ፌክ አካውንት ያላችሁ))) የሰው ላይክ የምትቆጥሩ ከሆናችሁ፣ ሌሎች ሲደነቁ "እኔምኮ..." ብላችሁ የድሮ ዝናችሁን በሰው ክፍለጊዜ የምትዘንቁ ከሆ...ነ ቡዳ ጢባጢቤ እየተጫወተባችሁ፤ እንደፈረስም እየጋለባችሁ ነው።
5ኛ:- አካውንታችሁን ሎክ አድርጋችሁ ሌሎችን የምታዮ 😀 ይሄ ቀለል ያለው ነው ፤ አንዳንዴም ኮንፊደንስ ማጣት፣ ወይም ፀጉር ቤት እስከምትሄዱ ኤክሳችሁ ተጎሳቁላችሁ እንዳያያችሁ ከመፈለግ ሊሆን ይችላል። የሆነ ሁኖ የራሳችሁን ቆልፋችሁ ሌሎች መቆለፋቸው ካበሳጫችሁ ግን... 😀😀
💎መፍትሄ፦ ጨክናችሁ ከጥላቻ ውጡ። የሌሎች ውድቀት አያጓጓችሁ። ፍቅር ቡዳን አይነጋጃውን ነው የሚያጠፋው።
ውብ ዛሬ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
✨
💫እንኳን ለ 1446ኛው የዒድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
♦️በመላው አለም የምትኖሩ የእስልምና እምነት ተከታይ ሙስሊም ወገኖቻችን እንኳን ለ1446ኛው የዒድ በአል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን።
✨ የዒድ በአል የእዝነት ÷ የመተሳሰብ ÷ አብሮ የመብላትና የመፈቃቀር በአል በመሆኑ በየ አካባቢያችን በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን እያሰብን እንዋል።
ዒድ ሙባረክ !!!❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
💡አንድ ወጣት ሰው ስለአርምሞ ሊቀስም ከZen መምህር ዘንድ መጥቶ ቢጠይቅ "ታግሰህ መጠብቅ ይቻልሃል ወይ?" አሉት ።
ወጣቱ "ምን ያህል ጊዜ?" መልሶ ጠየቀ።
መምህሩ "አንተን ለማባረር ይሄ መልስህ ብቻ በቂ ነበር። 'ምን ያህል ጊዜ' ብሎ መጠየቅ ማለት ለመጠበቅ ዝግጁ አይደለህም ማለት ነው። ከቻልክ 'ምን ያህል ጊዜ' ብለህ ሳትጠይቅ ዝም ብለህ ከጠብቅክ መጠበቅን ትችላለህ" አሉት።
📍ወጣቱ ነገሩ ገባውና እጅ ነስቶ ከመምህሩ ዘንድ ከረመ። ያለምንም ቀለም ዓመቱ ነጎደ። ሁለተኛው ተከተለ። ሶስተኛውም ተደገመ። 'አሁንስ በዛ! ምንም አልተጀመረም ፤ አንድ ክፍል እንኳን። ሰው ምን ያህል ጊዜ ነው መጠበቅ ያለበት?' ድጋሚ ጥያቄዎች ከአዕምሮው ቦታ ይዘው 'እስከ መቼ?' ብሎ ከመምህሩ ዘንድ አቅንቶ "ሶስት ዓመት ጠበኩኝኮ" ሲል ጠየቃቸው።
💡መምህሩ "እየቆጠርክ ነበር? በቀላሉ ይሄ የሚያሳየው እንዴት መጠበቅ እንዳለብህ አለማወቅህን ነው። መቁጠር? ከኔ ጋር ቀናትን መቁጠር? ላንተ ቀናቶች ዘላለም ሆነው ይሆናል፤ ለኔ ደግሞ ዘላለም ቀናት ሊመስሉ ይችላሉ። አንተ ከንቱ መጠበቅ አለብህ። መጠበቅ ማለት ምን እንደሆነ መማር ይኖርብሃል። ብቻ ተዘጋጅ ከነገ ጀምሮ ትምህርቱን እንጀምራለን" አሉት።
📍ትምህርቱ እንግዳ ነገር ነበር። ወጣቱ ወለል እያጸዳ እያለ መምህሩ ከጀርባው መጥቶ በያዘው ነገር ኋላውን ነረተው። ወጣቱ በርግጎ "ከሶስት ዓመት መጠበቅ በኋላ ይሄ ነው የአርምሞ መግቢያ?" አለው። መምህሩ "በሚገባ። አሁን ንቁ ሁን። በየትኛው ጊዜ፣ በየትኛው ወቅት ስለምጠልዝህ ንቁ ሁን። የራስህ ጠባቂ ሁን" አሉት።
ምቱ እና ንረታው ለወራት ቀጠለ። ምክንያቱም ሽማግሌው ቢያረጅም ኮቴ ቢስ ነበር፤ ድንገት ብቅ ይሉና ወጣቱን ያቀምሱታል። ይሄም በዝቶ ስለተደጋገመ የገላው ሕመም ምሽት ላይ ይጠዘጥዘው ነበር።
📍ሆኖም ቀስ በቀስ የወጣቱ ደመ-ነፍስ ነቃ። ከኋላም ቢሆን መምህሩ ሊመቱት ተቃርበው እያሉ ያመልጥ ጀመር። በሥራ ቢጠመድ እንኳ ቆሌው ይነግረዋል። የሕመሙ ሥቃይ የንቃት ግዴታ ጥሎበት ነበር።
💎ሕመም ለእድገት ግድ ነው። ሥቃይ ለማደግ ፍፁም አስፈላጊ ነው። ካልተሰቃየህ በስተቀር ንቃትህ ሊደምቅ አይችልም። ሥቃይ ልቦናን ያስገዛል፤ ፍቃደ-ስቃይም እልፍ አስተውሎትን ያሸምታል። [ Pain is a must for growth, suffering is absolutely necessary for growth. Unless you suffer you cannot be aware. Suffering brings awareness, and voluntary suffering brings tremendous awareness.]።
🔆ወጣቱ ማምለጥ ይችል ነበር፤ ማንም አላገደውም። ግን ሥቃዩን ፈቀደ። መምህሩን አስቀደመ። ምርጫው ሆነ። ለምን እንደሆነ አሁን ይገለጥለት ጀመር ለወጣቱ። "ይሄ የመምህሩ አስተምህሮ ነው። እንደዚህ ነው አርምሞን የሚያስተምረው" ከልቦናው ጣፈው። አብዝቶ አመሰገነ።
መምህሩ ከጀርባው እያደቡ መጥተው ሳይነርቱት በፊት ወጣቱ ተስፈንጥሮ ገሸሽ ቢል ዱላው ከመሬት ሲወድቅ በጣም ተደሰቱ። በወጣቱ ልቦና አዲስ አስተውሎት ፈነጠቀ፤ እናም መምህሩ ባረኩለት።
💡ዳሩ ግን ከዛን ዕለት ወዲህ ነገሮች ከበዱ። መምህሩ በውድቅት ጨለማ ወጣቱ ሲያሸልብ ይቆጉት ጀመር። 'አሁን ልኩን አለፈ። በጨለማ! ለዛውም በየትኛውም ሰዓት!' እንደውነቱ መምህሩ ስለጃጁ እምብዛም ማንቀላፋት አይችሉም። በየትኛው ጊዜ የነቃ ሲመስላቸው ሄደው ወጣቱን ይነርቱታል። 'ይሄ ቅጥ-አንባሩ የጠፋ ጅልነት ነው። ራሴን ቀን መከላከል አያዳግተኝም፤ መሮጥ፣ ማምለጥ፣ ዞር ማለት እችላለሁ። ግን ሳንቀላፋ ምን ማድረግ ይቻለኝ ይሆን?' አላለም፤ አልጠየቀም አሁን። ዝም ብሎ ተረዳ። 'ሒደቱ ላይገባኝ ይችላል ቢሆንም እነዛ የቀን ዱላዎች ብዙ ትሩፋት ስለነበራቸው ነው ይሄን ልውጠት (transformation) በኔ ላይ ያመጡት። ካለምንም ጥያቄ ይሄንንም እቀበለዋለሁ' አለ።
መምህሩም "ይሄ ጥሩ ምልክት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ እምነት ጥለህ ጥያቄ አላነሳህም። ሁለት ወይም ሶስት ወራት ሲደበደብ ገላው በየቀኑ ቁስል ቢሰማውም አንድ ዕለት ሆነለት፤ በፅልመት ራሱን መከላከል ቻለ። መምህሩም እክፍሉ ሲዘልቁ "ተረጋጉ…ነቅቻለሁ" አላቸው። እንደዚሁ ደጋግሞም ተከሰተ።
🔷 ወጣቱን መነረት የሚቻል አልሆነም። መምህሩ እክፍሉ እንደጠለቁ፣ ፈጽሞ የማይተኛ ይመስል አይኖቹ ፈጠዋል። ግን እንደዛ አልነበረም፤ ወጣቱ ሲያሸልብ በጣም ችኩል ነበር። ሆኖም እውስጥ እንደቀንዲል የበራች ትንሽ የበረዶ ግግር ጫፍ የመሰለች አለላ ንቃት ለቅኝት (watching)፣ ለጥበቃ (waiting) ከሽልብታ ዓለም አምልጣ ወጥታ ስለነበረ ነው ቀድማ ምታባንነው።
📍መምህሩ ተደሰቱ። በበነጋው ማለዳ መምህሩ ከአንድ ዛፍ ስር አርፈው ጥንታዊ መጻሕፍ ያነባሉ። ወጣቱ ያትክልት ሥፍራውን እያጸዳ 'ይሄ ሽማግሌ ለዓመት ያህል ጠዋት፣ ማታ ሲነርተኝ ነበር። እሱን አንዴ ብቻ ብደልቀው እንዴት ይሆናል? ባየው ደስ ይለኛል እንዴት እንደሚሆን?' የሚል ሐሳብ ብልጭ አለበት።
መምህሩም በዛው ቅፅበት መጻሕፉን ከደኑና "አንተ ቂል! ይሄ ከንቱ ሐሳብ ይቅርብህ፤ እኔ ለራሴ አቅመ ደካማ ነኝ" ብለው ለወጣቱ መለሱለት ....
❤️ውብ አሁን ለሁላችን😊
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
✨የትላንት ታሪኮቻችን የሚያስተምሩን ዛሬም ላይ ታሪክ መስራት እንደሚቻል ነው።
ታሪክን መዘከር እና ለትውልድ ማውረስ እንደተጠበቀ ሆኖ ከትናንት ታሪካችን ጽናትን፣ አብሮነትን እና አገራዊ አንድነትን በመላበስ ዛሬ ላይ የትላንቱን ምኒሊክን መሆን፣ በድህነት ላይ መዝመት፣ ኋላቀርነትን መታገል፣ ለመርህ ተገዥ ሆኖ መተባበር የአሁን አድዋ ድል ነው።
✨ታሪክ በራሱ ነፃ አያወጣም። ታሪክን ተመርኩዞ ጭቆናን አሸንፎ፣ ነፃነትን መቀናጀት ግን ይቻላል። አድዋ ! በጥቁር ህዝቦች ታሪክ ትልቁ የድል ማማ! ነውና። በአድዋ ጦርነት ከ100 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የውስጥ ልዩነቶቻቸውን እና ችግሮቻቸውን ወደ ጎን አድርገው ከ1000 በላይ ኪሎሜትር በእግራቸው በአንድነት ተጉዘው አገራቸውን ከጠላት ወራሪ በመከላከል ታሪካዊ ድል አስመዝግበዋል።
💎ክብር ሃገርን በደም መስዋዕትነት ላቆዩልን ጀግኖች አባቶቻችን።
🌟ይህ ትውልድ የአባቶቹን ጀግንነት ለመድገም የውጭ ወራሪን መጠበቅ የለበትም! እርስ በርስ መፋጀታችንን በማኅበራዊ ሰላም አክመን ÷ኃላቀርነትን በእውቀት ከትበን ÷ ዘመናችንን በይቅር ባይነት በአንድነት በመተሳሰብ አቃንተን፣ የእኛን አደዋን ለመስራት መንቃት አለብን፡፡አንዱ ካንዱ ልብለጥ ማለቱን ይተው፣አንዱ አንዱን ልግፈፍ ማለቱን ይርሳው፣ ያኔ የእኛን አደዋን እንሰራለን ፤ የእኛን አደዋን እናሸንፋለን፡፡
ሁለንተናዊ ኑሮአችን ያስጎመጀ እንዲሆን በማኅበራዊ ፣ በፓለቲካ ፣ በባህል በኢኮኖሚ የእኛን አደዋ ማበጀት አለብን፡፡ ሁላችንም የድል ታሪክን የመድገም ሀላፊነት አለብን።
በድጋሚ እንኳን ለ፻፳፱ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አደረሰን!❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
♦️እብድ ማለት ከተለመደው ውጪ የሚያስብ እና የሚራመድ ሳይሆን ከተለመደው ጋር ተጣብቆ እውነተኛ ማንነቱን ክዶ ከተወለደ በኋላ የሰማውን የመጨረሻ እውነት አድርጎ በተወለደበት አካባቢ ታጥሮ ብሄሩን ማንነቱ አድርጎ ሀገሩን ብቻ ሰውነቱ አድርጎ አምኖ የሚኖር ማለት ነው።
☯አንተ ሀገር ብቻ አደለህም አንተ አለም ነህ፣ አንተ ዘር ብቻ አደለህም አንተ የፈጣሪ አምሳል ነህ፣ በፈጠረህ አምላክ ውስጥ ስትሆን የፈጠራቸውን ፍጥረቶች ሁሉ በእኩሌታ ማየት እና ማክበር ትጀምራለህ የሰውነት መለኪያው ይህ ነውና። በዚህ አለም የተፈጠርከው እንደ ካርቦን የተፃፈብህን ለማስተላለፍ ወይንም በጉልቻ መሀል እንደ ተለኮሰ እሳት የተጣደብህን ሁሉ ለማብሰል አይደለም። ከቦክሱ ወጥተህ ለማሰብ እና አለምን ለማየት ሞክር በስሜት ድልቅታ ጋልበህ እንዳትባክን... አንተ ለሰውነት እንጂ ለማሽንነት አልተጠራህም።
♦️በሀይማኖት አጥር ታጥረህ ሌላውን አትንከስ በዘር ድንቁርና ሰክረህ ሌላውን አታራክስ በግለሰብ ጥፋት እልፎችን አትክሰስ፣ ይልቅ ወደ ልብህ ፍሰስ ተገኝ ወደ ፈጠረህ ንፁህ መቅደስ ወደ ሰራህ ፅኑ መንፈስ ክነፍ፣ በጥላቻ አትቁም ከወንዙ ጋር ፍሰስ ወደ አለም ፍለስ አቋርጥ ገስግስ መሬቴ አፈሬ አትበል አትከለል አለም'ም የአንተ ናት አንተም የአለም ነህ።
💡በሰሀራ በረሀ የሚኖሩ አልኬሚስቶች - ፔራሚዶቹን ከመጎብኘትህ በፊት ፔራሚዶቹን በልብህ ፈልገህ ልታገኛቸው ይገባል አለዛ በፔራሚዶቹ ስፍራም ብትሄድ ፔራሚዶቹን አታገኛቸውም!!'' ይላሉ! እውነትም በውጪ ያጣችሁት ሁሉ በውስጥ ያልፈለጋችሁት ጉዳይ ነው። አፅናፈ አለም እንዲህ ካሉት ጋር ነው ምትሰራው!
📍አሁን አሁን ሰዎች ከውስጣቸው አለም እየወጡ ከውጪ በሚመጣ የሰዎች አስተያየት ልክ ራሳቸውን ይመለከታሉ... ትክክለኛ የህይወት መስታዎታቹህ ነፍሳቹ ነች እናንተ ግን ከነፍሳቹ ቤት ወታቹህ አለምን ለማትረፍ ትጋጋጣላቹ. የመሰላቸውን በሚናገሩ ሰዎች እይታ የህይወት መልካችሁን ትቀርፃላቹህ።
ቡድሀም ይላል መጥፎ አጋጣሚ ከምዕራብም ሆነ ከምስራቅ አይመጣም። ከውስጥህ ነው የሚፈልቀው።
💎የሰው መልክ ተፈጥሮ ናት የምትነፍሰው እስትንፋስ ከልብህ ድልቅታ ጋር ልትጣመር ይገባል ስትኖር ከልብህ ኑር ፣ አታስመስል!! አለም በህብረት ቢደንስብህ እንኳን፣ አንተ ከነፍስህ በሚወጣው ሙዚቃ ብቻ ተወዛወዝ፣ እብድ ይበሉህ ይህ ማእረግህ ይሁን!
💡ጥላ አልባ ሁን በፍቅር ብርሀን ከነፍስህ ጋር አብራ፣ ጭንብልህን ቅደድ የፈጣሪም ብርሀን ከወስጥህ እንዲፈስ ፍቀድ የተሰመረን አድማቂ ለመሆን አልመጣህም፣ አንተ ካርቦን አይደለህም አንተ ከነበሩትም አሁን ካሉትም ወደፊትም ከሚፈጠሩትም የሰው ፍጥረቶች ሁሉ የተለየህ ነህ። ውስጥህን በታትነህ ከሌሎች ጋር አንድ ለመምሰል አትውተርተር።
✍ Dîž Âb
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanityBot
📍ስለ ህይወት
💡አንድ አባባል አለ በጣም የምወደው ''ቁም ነገሩ ምን ያህል እድሜ ኖረሀል ሳይሆን ምን አይነት ህይወት አሳልፈሀል'' ብዙዎቻችን ካለፍንባቸውን ህይወቶች የምንማረው እሩጫችንን ከጨረስን በኋላ በእርጅና ትናንትን ስንመለከት ነው። በወጣትነታችን ያለፍንባቸውን የህይወት ዱካዎች አስተውለን ማጥናት ምንችል ቢሆን ግን ነጋችንን ብሩህ የማድረግ ትልቅ እድል ይኖረናል።
"የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ" እንዲል ያገሬ ሰው... የዛሬው ህይወታችን ያለፍንባቸው የህይወት ውጣ ውረዶቻችን ቅጂዎች ናቸው ። እናም ስለ ህይወት የገባኝን ከትናንቶቼ የተማርኳቸውን እንደ አባት ልንገራቹህ.
💡በዚህ አለም ላይ ቋሚ ነገር የለም።
ዛሬ የወደዱህ ነገ ይጠሉሀል ዛሬ ያከብሩህ ነገ ይንቁሀል ዛሬ እንደ አስፈላጊ የተመለከቱህ ነገ አንተን ረስተው ሌላ ህይወትን ሲጀምሩ ታያለህ አየህ ሁሌም ቢሆን ለሰዎች አብዝተህ መጨነቅ የለብህም! ከሰዎች አብዝተህ መጠበቅ የለብህም! በዚህ አለም ቋሚ ነገር የለምና ያለህባትን ህይወት እና ግዜ ብቻ በተገቢው ማጣጣም እወቅበት!
📍ሰዎች ደስታ እና ሀዘንህን የሚፅፉልህ የህይወትህ ደራሲ እንዲሆኑ አትፍቀድላቸው! እነግርሀለው አሁንም ያለኸው አንተ እና አንተ ብቻ ናቹህ ስትሞትም የሚወዱህ ቀብረውህ ህይወትን ይቀጥላሉ... ሁሉም የመጣው ለህይወት እንጂ ለአንተ እንዳልሆነ ተረዳ!
ስለዚህም ለራስህ ክብርን ግዜን ፍቅርን መስጠት እወቅበት ከህይወት ጋር ተዛመድ!
አንድ እውነትን ተረዳ ማንም ሚወድህም ሆነ ሚንቅህ አንተ ላይ ካየው ነገር ተነስቶ ብቻ ነው ሰዎችን አብዝተህ ከማመንህ በላይ ራስህን እመን! ራስህ ላይ ስራ! ሌላው ከሰዎች የሚሰጡህን መልካም ነገሮችን ውደድላቸው አክብርላቸው ነገር ግን ይሄ የመጣው ለራስህ ካለህ ጥልቅ ክብር እንደሆነ ማስተዋል መቻል አለበህ!
♦️ስለዚህም የምትወዳቸውን ሰዎች እንዳታጣ የምትደውን ማንነትህን አትጣለው! ሌሎች ሰዎች ደግሞ ለአንተ ያሰቡ በመምሰል እነሱ በሚፈልጉት ልክ እንድትራመድ መንገድ ሊያመቻቹልህ ይችላሉ ይህ ማለት በሌላ ቋንቋ
(የግል ባርያዬ ላደርግህ እያሰብኩ ነው) እንደማለት ነው ። አንተም ስለምትወዳቸው ውለታም ስለዋሉልህ እነሱን ካለማጣት እና ለማስደሰት የራስህን ማንነት ትተዋለህ ሰዎችም ዙሪያህን እንደተቆጣጠሩ ሲሰማቸው ጥለውህ ይሄዳሉ ! አየህ በማንነትህ አትደራደር ማንም እንዲ ሁን ሊልህ ቢሞክር ከመስመሩ እንዳታሳልፈው! ሰዎች የአንተን ነገር ማክበር ሚጀምሩት ለራስህ ካለህ ፅኑ እምነት ተነስተው ነው።
💎ይቺን እወቅልኝ ማንም በዚህ አለም ያለምክኒያት አብሮህ ሊሆን አይችልም ''ማንም" ካላመንክ ይወዱኛል ብለህ ያሰብካቸውን ሰዎች ''ለምን ከኔ ጋር ሆንክ/ሽ?" በላቸው የሀገር ምክኒያቶችን ሲደረድሩልህ ትሰማለህ
💡ያለ አንዳች ምክኒያት አንተን የሚወድህ ፈጣሪህ ብቻ ነው። ሰዎች ሁኔታዊ እንደሆኑ እወቅ የቱንም ያህል ቢወዱህ እነሱ ሊያዩህ ከሚፈልጉበት ቦታ ወርደህ ካዩህ ይለዩሀል በቃ ይሄ የሰዎች ተፈጥሮ ነው። ከነፍስህ ጋር መፋቀርን ልመድ ሰዎች ሳይኖሩ ሙሉ መሆንን ልመድ ሁሉም ትቶህ ሄዶ መፈንደቅን ልመድ በህይወት ጭለማህ ውስጥ ብቻህን መሳቅን ልመድ! ለህይወት ቁስሎችህ ሁነኛ ዶ/ር መሆንን ልመድ!
📍ራስህን በወደድክ ቁጥር ህይወት አንተን በጥልቅ መንፈስ ማፍቀር ትጀምራለች... ሰዎችም የህይወት አንዷ አካል ስለሆኑ ወደ በአንተው መሳብ ይጀምራሉ። በሰዎች አትደገፍ ! በራስህ መቆም እስኪሳንህ ድረስ ለሰዎች ራስህን አሳልፈህ አትስጥ ሰዎችን ውደድ ግን በሰዎች አትደገፍ ዘወር ቢሉ መቆም እንደምትችል አሳያቸው!
💡ስትወድቅ አይቶ ሚያነሳህ ፈጣሪ እንጂ ሰዎች አይደሉም። ሰዎች ሁሌም የተሻለን ነገር በተፈጥሮዋቸው ይፈልጋሉ ስለዚህ አንተ ከነሱ ግዜ ጥሎህ አንሰህ ከተገኘህ ጥለውህ ይሄዳሉ እንዳትረሳ! በመጨረሻም አምላክህን ህይወትህን እና ራስህን አጥብቀህ አፍቅር ! ህይወት ያን ያህል ቀላል ትሆናለች ጀግናው!
✍Dîž Âb
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanityBot
🌍ምክር ለወዳጅ
📍ወዳጄ ሆይ
ድንቅ ሕይወት ለመኖርና ሕልምህን ለማሳካት ፣ ማንም አንዳች ነገር እስኪያደርግልህ መጠበቅ የለብህም ። ሕልሙ ያንተ ነው ፤ የታየህም ለአንተ ነው ። ስለዚህ መከፈል ያለበትን ዋጋ መክፈል ያለብህ አንተ ራስህ ነህ ። አንተ ለሕልምህ ምንም ዐይነት ዋጋ ሳትከፍል ፣ ሌሎች ሰዎች ለአንተ ሕልም ዋጋ እንዲከፍሉ መጠበቅ የለብህም ። አንተ ለሕልምህ የመጨረሻውን ዋጋ እና አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ሁሉ ስትከፍል ፣ ሌሎች ሰዎች መረዳት ይጀምራሉ ። ራስህን ስትቀይር ፣ ሌሎች ሰዎችም ሊቀየሩ ይችላሉ ። ራስህን ስትቀይር ፣ ሁሉም ነገር መቀየር ይጀምራል ። ሕይወትህ ፣ ቤተሰብህ ፣ ሥራህ ፣ ገቢህ ፣ ጤንነትህ እንዲሁም የምትፈልገው ነገር ሁሉ እንዲቀየር ፣ በመጀመሪያ አንተ መቀየር አለብህ ። ይህ ጥልቅ ምስጢር ነው ።
📍ወዳጄ ሆይ
ጓደኛ፣ወዳጅ፣ዘመዴ ያልከው ባስቀመጥከው ቦታ ባታገኘው እንደ ነብር በድንገት ተቆጥተህ እላፊ ነገር ውስጥ ዘለህ አትግባ!... ትርፍ ንግግር ሁሌም ቢሆን ሕሊናን ከማቆሸሽ ያለፈ ውጤት ከቶም የለውም፡፡ ይልቅስ ነገሮች ሁሉ ለበጎ ናቸው የሚባለውን የአባቶች ብሂል አስታውስና ነገሩን ናቅ አድርገህ እለፈው። በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ ፣ ክፉ አትመኝ ፣ በሃዘናቸውም አብረህ እዘን ሲያዝኑ አትደሰት ፣ ሰው ከሆንክ የሰው ነገር ይሰማህ ፣ ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ተደሰት ማለት አይደለም።
📍ወዳጄ ሆይ
ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም አንተም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት ፣ በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን ። የስራ ጉዳይ ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁ ፤ አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለችም እየኖረች ያለችው፣ በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት ፤ አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ አውጣው ፣ "ምን ይሻለኛል ?" እያልክ ጊዜህ እንዳያልቅ ፣ በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው።
📍ወዳጄ ሆይ
አስተውል ፣ መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን አይደለም ፣ ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀዪር ብቃት አለው ። ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል ፣አስተውል ። መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው ፣ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ አይኑርህ ። በመውደድ የተጠመደ ሰው ለመጥላት ጊዜ የለውም። መጥፎነት ከአንተ ይራቅ ፣ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም።
📍ወዳጄ ሆይ
የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "ሰው የዘራውን ያጭዳል " የሚለውን ስታውስ ፣ ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ ራስህን አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ ።
📍ወዳጄ ሆይ
እልህ ከራስ ጋር ገመድ መጓተት ነው ። የማይቀጥሉ ነገሮችን መሬት ላይ አስቀምጣቸው ፤ አየር ላይ ከተበተኑ ጉዳት ያመጣሉ ። “የጨዋ ልጅ ሲፋታ የሚጋባ ይመስላል” እንዲሉ ። የሃያ ዓመቱም የሰማንያ ዓመቱም ሁለቱም የዕድሜ ስስት አለባቸው ። በምናልባት መኖር ጉልበት ይጨርሳል ። ውሳኔ ማጣትም ዕድሜን ይፈጃል ። መኖርህ አለመኖር እንዳይሆን ተጠንቀቅ ። እንዳትዋረድ ክፉ ጠባይህን አርቅ እንጂ እንዳያዋርዱኝ ብለህ ግን እግርህን አታሳቅቅ።
📍ወዳጄ ሆይ
ያለ መጠን ማድረግ ጭንቀትን ፣ ሀዘንን
ውጥረትን ያስከትላል አፍ የሚችለውን እጅ ይመጥነዋል እንዲሉ ለሁሉ ነገር መጠን፣ልክ፣ገደብ አለው፡፡ በርሜል ውስጥ የተጠራቀመ ውሃ ከሞላ መፍሰሱ አይቀርም፡፡ መሬትህ በሚሸከመው መጠን ቤትህን ሥራ ፣ ወዳጅህ በሚችለው መጠን ምሥጢር ንገረው ፣ ተማሪህ ባደገበት መጠን መግበው ።
💎እናም ወዳጄ
ጎደለብኝ በምንለው ጎን ብቻ ነገሮችን ካየን ህይወት መቼም አትሞላም ! ያለንን የሞላውን ግን በደንብ ስንመለከተው ህይወት በራሷ እርካታን ትሰጠናለች ! ያለን የለንም ከምንለው ሁሉ ይበልጣል፣ የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ’ረስተን ፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ ነው ፣ ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል ። በማማረር መባረክ የለም ። ሰላምና ጤና ፣ ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንጊዜም ከዘመንህ አይለዪ።
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
🎄በመላው ዓለም ለምትኖሩ የክርስትና እመነት ተከታይ እህት ወንድሞቻችን እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ።
💛ይህንን ቀን ስናከብር በአንድነት፣ በርህራሄ የወደቀን የምናነሳበት፣ የታመመን የምንጠይቅበት፣ ለተቸገሩ የምንረዳበት የልግስናን መንፈስ በመቀበል ያገኘነውን በረከት የምናካፍል እንሆን ዘንድ መልካም ፈቃዱ ይሁን።
🎄በአሉ የሰላም የፍቅርና የደስታ እንዲሆን እንመኛለን።
🏑 መልካም የገና በአል 🏑
❤️ስብዕናችን❤️
@ETHIOHUMANITY
@ETHIOHUMANITY
🔴ትላንት ማታ የዓለምን ሚስጥር ይነግረኝ ዘንድ ጠቢቡን ለመንሁት
። ከብዙ እርጋታ በኋላም
“ፀጥ በል!... ምስጢሩ በዝምታ ተጠቅልሏልና ሊናገሩት አይቻልም!” ሲል አንሾካሾከልኝ
-ሩሚ
📍ዝምታ ፈጣኑ እርጋታ ነው። ዝምታ ዝ...ግ ነው ፡ ካለትዕግስት የማይከፈት ምስጢር ፤ ዝምታ ዝቅ ነው ፡ አውቃለሁ የማይል ትሁት፡ ዝምታ ወርቅ ነው ፡ ከልብ ተቆፍሮ የሚገኝ ውድ ሐብት ነው።"
🔆ከውጫዊ ገፅታ የበለጠ ውስጣዊ ማንነት ይኑርህ፤ መልክህ፣አለባበስህ፣የምትነዳው መኪና አልያም የምትኖርበት ቤት ያንተን ዋጋ አይተምኑ። እንኳንስ ቁሳቁስህና ሀብት ንብረትህ ቀርቶ ሥራህ፣ ማእረግና ቤተሰብህ እንኳን ያንተ አይደሉም። የእኔ የሚባል ነገር የለም ፣ እሱ ነው ያጠፋን።
♦️አንተ ወደዚህ አለም ከመምጣትህ በፊት የነበረህ እውነተኛ ማንነት አለ ፣ እሱም ህይወት ራሱ ነው፡፡ የዚህ አለም ማንነትህ ሁሉም የውሸት ናቸው፡፡ ለምሳሌ ይህ ሰውነትህ አፈር ነው፡፡ህይወት አይደለም፡፡ስምህም ሰዎች ተስማምተው የሰጡህ ጊዛዊ ታርጋ ነው፡፡ድግሪ ካለህም የሚናገረው ኮሌጅ ውስጥ ያሳለፍከውን ጊዜ ነው፡፡ ዝና፣ ትዳር፣ ስልጣንና እዚህ አለም ላይ እኔ ነኝ ብለህ የምታስባቸው ነገሮች ሁሉ አንተን አይደሉም፡፡
🔶እዚህ አለም ላይ አንተን የሆነ ነገር የለም፡፡ መከበርም፡ መዋረድም.... ድህነትም ፡ ሀብትም.... ዝናም ፡ መረሳትም..መማርም:አለመማር...መውለድም ፡ አለመውለድም ሆኑ ሁሉም የዚህ አለም ነገሮች ጊዛዊ ናቸው፡፡ይመጣሉ ይሄዳሉ፡፡ ጊዛዊ ያልሆነ ነገር አለ፡፡እሱን ያዘው፣ እሱም ህይወት ራሱ ነው፡፡ እውነተኛ ማንነትህ ይህ ነው፡፡
🔷"ያንን ማንንነት ለማግኘት ከጫጫታ መለየት አለብህ፡፡መጀመርያ አለም የጫነብህን ኮተት ከራስህ ላይ ልታራግፍ ያስፈልጋል፡፡ ትኩረትህን በውስጥህ ወዳለው ፈጣሪ ማይረግ አለብህ፡፡ህይወት አይታይም ፡ አይነካም፡ ቅርጽ የለውም፡ አይሞትም፡ አይገደብም አይገለጽም፡፡ህይወት ራሱ ፈጣሪ ነው፡፡ፈጣሪ አሁን ውስጥ ያለ የማይታይ ግንድ ነው፡፡አንተ ደግሞ የማይታይ ቅርንጫፍ ነህ፡፡ከዚህ ከማይታይ የፈጣሪ ግንድ ጋር ስትገናኝ ያንተ የማይታየው ቅርንጫፍ ያበራል፡፡ያለምንም ነገር መደሰት ትጀምራለህ
🌊በህብረተሰብ የጅምላ ጫጫታ ውስጥ የጠፋውን ግለሰባዊ የስብዕና ማንነትን ፈለገን እናግኝ። ጸጥታ፣ ዝምታ፣ እርጋታ ሀሴትን ፈጣሪ ልዩ ገፀ በረከቶቻችን ናቸው።የውስጥ ሰላሙን ያጣ ሰው፣ ውጫዊው ትርምስ ምኑ ነውን?ጠቢብ ግን ባንቀላፉት መኃል መንቃትን ፥ ከብዙ ሰው ጫጫታ ዝምታን ይመርጣል ... በእርጋታና በጸጥታ የተሞላች ነፍስ የተመረጠች ነች።
የሰከነ ልብ፣ አስተዋይ ልቦናን ፈጣሪ ያድለን!
ውብ ቅዳሚት ለሁላችን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
🔴ዛሬ ስለማለት መብት እንናገራለን... የምንለውን እንድንል የሚሉትን እንዲሉ ስለመፍቀድ እናወራለን...
🔷ምንድነው ግን እንዲህ አመክንዮ አልባ ያደረገን? ፣ የማለት በር ይከርቸም.. እኛ ብቻ እናውራ የሚያሰኘን ምን ይሆን?... የሌላውን የማለት መብት እግር ከእግር ተከትለህ ስታብጠለጥል የምትጠቀመውን መብት እኮ ነው ተተቺህ የተጠቀመው ፣ እንዳንተ አለማሰብን ስህተት ያደረገው ማን ነው?... እስኪ አንዳንዴ እንኳን ከተባለው ነገር በፊት ለመባሉ እውቅና ስጥ።......ከዚያ አባባሉን ከግለሰቡ ነጥለህ.. በማስረጃ አስደግፈህ.. ወይም ደግሞ ከእይታህ አዋቅረህ ተች... ገና ለገና 'ሃሳቡ ከሃሳቤ ተጣርሷልና .. ቅኝቱ ከቅኝቴ ተፋልሷልና እገሌ የያዘው የረዘዘው ምንትስ የነካው እንጨት ይሁን' ማለት የእውነት Fair አይደለም።
በግሌ የማለት መብት መጋፋታችን ብቻ አይደለም የሚያሳስበኝ አንዳንዴ ወደላይ ምን ካላልን የምንለው ነገር አለን። ያለሙያችን ፣ ያለሜዳችን... ይሄ እውነተኛን ሂስ በስሜት አረንቋ ውስጥ ይደብቅብናል። በዚህ መሃል ፍሬና ግርዱ ተቃቅፎ ይኖራል ፣ አንዳንዴ አንዳንዶች ራሳቸውን እንዲሰድቡ መፍቀድም ብልህነት ነው...
♦️ሌላ የምንረሳው ነገር ደግሞ ተቺውም ሆነ ተተቺው የትችት ሰበብ የሆነው ፣ ነገሩ ያብብ ..... እርስ በእርስ ያማምር ዘንድ አስፈላጊ መሆናቸውን ነው። እርስ በርስ ካልተያየን እንዴት ልናድግ እንችላለን?... የኔ ስህተት ባንተ ክህሎት ይቃናል... ያንተ ጥፋት በእርሷ ጥቁምት ይፋቃል እንጂ አትድረሱብኝ በሚል ስሜታዊነት እንዴት ይጎለምሳል?... 'አትንኩኝ የሹም ዶሮ ነኝ' ለማን ይበጃል?...
🔷የአንዳንድ ነገሮች ድጋፋችን ጭፍን ስሜት ይጫነዋል ፣ ዳንኤል ክብረት አንድ መድረክ ላይ ".. ወጣቱ ባዶ ቅናት ይቀናል..." ሲል ሰምቼዋለሁ... ባዶ ቅናት ስለጉዳዩ በቂ ግንዛቤ ሳይዙ በጥቅል ስሚያ ላይ ከመመስረት የሚመነጭ ስሜት ነው። አንድ ሳር ቅጠሉ ሆ.. የሚልለትን ሰው/ስራ ሌላው ሰው ሲተች የኛን ድንቅ የማሳየት መንገድ መከተል አይደለም የሚቀናን፣ እንዴት እነካለሁ በሚል ቅኝት መደንፋት እንጂ፣ በዚህም ምክንያት እኛም ስለነገሩ ሳናውቅ.. ተቺውም ከስህተቱ ሳይታረቅ ይቀራል... ከትችቱ ቁምነገር የመገብየቱ ነገርማ አይታሰብም.......።
♦️ምን ለማለት ነው?... የተባለው ነገር ፈጽሞ የማንቀበለው ሊሆን ይችላል... አለመቀበላችን ግን የመባል መብቱን መጋፋት የለበትም... ልክነትና ስህተት በመቀበል/መተዋችን ውስጥ ቦታ የለውም... በነገሩ ተፈጥሮ ውስጥ እንጂ...
🔶 ስለዚህም... 'እንዴት እንዲህ ትላለህ?' ሳይሆን 'እንዲህ ማለትህ ከዚህ ከዚህ አንፃር ስህተት ነበር' ማለትና ለውይይት በር መክፈት የተሻለ ነው... ለምን ቢባል ... አንዳንዴ ተመሳሳይ እሳቤንም በተለያየ ቋንቋ እያወሩ 'የተለያዩ' መምሰል አለ... አንዳንዴ ሽንጥ ገትረው የተሟገቱለትን ጉዳይ አድሮ መተውና በሌላኛው ሰው ጫማ ውስጥ መገኘት አለ... ደግሞ አንዳንዴ የትችቱ መልስ ዝምታ መሆን ተቺውን ወደራሱ እንዲያይ ዕድል ሰጥቶት መግባባት አለ...
📍ፈረንሳዊዉ ቮልቴር ለአንድ ጓደኛው በፃፈው ደብዳቤ ላይ ለማለት መብት መቆሙን ያሳየበት መንገድ ድንቅ ነበር... እንዲህ ብሏል:
"I disapprove of what you say, but I will defend to the death your right to say it."
<በሃሳብህ በፍጹም አልስማማም ~ በፍጹም... ነገርግን ሃሳብህን ለመግለጽ ላለህ መብት እስከሞት ድረስ እታገልልሃለሁ>
ፍቅርን ከመስጠት በላይ ዕዳ አይኑርባችሁ!!❤️
✍ ደምስ ሰይፉ
ፏ ያለች ቅዳሚት ለሁላችን😉
@BridgeThoughts
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
እዚህ የሃሳብ ድልድይ አለ...
እዚህ የመገናኛ ድልድይ አለ...
__
ድልድይ
-
ሰው ከራሱ እውነት የሚገናኝበት የቆምታ ታዛ ነው...
ከውክቢያ ተፋትቶ የሚያስተውልበት ፋታ ነው...
ከእልፊት ጸጸትና ከመፃኢ ስጋት ተላቆ ከአሁንታ እውነት የሚገናኝበት ከፍታ ነው...
__
ከሚተነፍግ የዓለም ጣጣ፣ ከማይሞላ የኑሮ ሩጫ እፎይ ማለት ሲሹ ጎራ ይበሉ... መልካም ማረፊያ ነው...
__
ይቀላቀሉ፣ ወዳጆችዎንም ይጋብዙዋቸው!!
_👇👇
@bridgethoughts
@bridgethoughts
💎የራስ ቀለም
"በዚህች አለም እንተን የሚመስል ሰው ተፈጥሮ አያውቅም ወደፊትም አይፈጠርም በቃ አንተ አንተን ሆነህ ብቻ አንዴ ተፈጥረሀል..." - ዴልካርኔጊ
💡 በራሳቹ ቀለም እጅግ ውብ ናቹህ በራሳቹ አለም እንደመልአክት ታብረቀርቃላቹህ በራሳቹህ መንገድ እንደንጉስ ትራመዳላቹህ ። ውበታቹህ እርሱ ነው እናንተነታቹህ የነፍሳቹህ ብርሀን መንገድ ነው። አለም በቀደደላቹህ ቦይ እንድትፈሱ ፈጣሪያቹህ አልተጠበበባችሁም በእናንተ የተጠበበ'በትን ህይወት ለመኖር ወደ ልባቹህ መቅደስ ብቻ ፍሰሱ... እግራቹህን ከልባቹህ ጋር አስተሳስሩ ልባቹህ ወደ መራቹህ ሂዱ ፣ ይሄ ነው ህይወት....... ይሄ ነው መተንፈስ..... ይሄ ነው መንቀሳቀስ.....
⏳በእግርህ ከመተማመንህ አስቀድሞ ፡ የምትጓዝበት መንገድ ይኑርህ ፤ ምክንያቱም በዚህች ተራራማ ፣ ሜዳማ ፣ በረሃማና ረግረጋማ ዓለም ላይ እግር ያላቸው ሁሉ አይጓዙም መንገድ ያላቸው እንጂ ፡ ስለሆነም ከርምጃህ መንገድህ ይቅድም !"። ህይወትህን ከፉክክር አልቀው ወደ ተፈጥሮ ዝለቅ በፀሀይ መውጣት እና መጥለቅ ተመሰጥ በከዋክብቶች ፊት ዳንስን ደንስ ከጨረቃዋ ጋር ተወያይ በፅጌሬዳ ፍካታዊ ውበት ነፍስህን ከስነፍጥረት ጋር አዋህደው።
የሕይወት ጎዳናህ ርዝማኔ ዕድሜህን የመወሰን አቅም ስለሚኖረው ፣በቀን ከፀሐይ ተዋህደህ አርቀው ፣ በምሽትም ከጨረቃ ተማክረህ አርቅቀው ፤ ስጋህን ከጀምበሯ ሙቀት አላምደው ፡ ነፍስህንም ከጨረቃዋ ብርሃን አስታርቀው ፤ፀሐይዋን የሚጋርድህ ፡ ከጨረቃዋም የሚደብቅህ አንዳችም ኃይል የለም ፤ ራስህ ካልሆንክ በቀር።
⌛️ተራራማ ፣ ሜዳማ ፣ በረሃማና ረግረጋማ የሕይወት ጎዳናህን ከጀምበሯ ዕለታዊ የብርሃን ዕድሜ አንፃር አንፅረህ በማስተዋል አስልተህ ቀምረው ፤ ተራራውን ፣ ሜዳውን ፣ በረሃማውንና ረግረጋማውን ምድራዊ ስፍራና የጎዳናህን አካል በጨረቃዋ ጥበባዊ ምስጢር መስጥረው ፤ ከጨረቃዋም የውበት ውቅያኖስ ቀለም በሰዓሊነት መንፈሳዊ ብሩሽህ እየጨለፍክ አስውበው።
📍ተፈጥሯዊ ነህና ስጋዊ ዓይንህ በቀን ብርሃን የመመልከት አቅም እንዳለው ሁሉ በምሽት የጨለማ ጊዜም መንፈሳዊ ዓይንህ የጠራ የማስተዋል ኃይልን ታድሏልና ሳትደናገጥ ሳትፈራ በራስ መተማመን ቀን ያየኸውን ተራራ ተንደርደረው ፣ የውቅያኖሱን ሞገድም ሰንጥቀህ ቅዘፈው ፣ በረሃማውን ረግረጋማውንም የጎዳና አካል፣ በእባብ ብልህነት በጊንጥም ፅናት በሌሊት ወፍ ምስጢራዊ አከናነፍ ተምሳሌታዊ ስልት በዝግታ በማስተዋል፣ ከጊዜም ሙዚቃዊ ስልተ-ምት ጋር ተዋህደህ በመዝናናት፣ መንፈሳዊ ክንፍህን እያርገበገብክ በዳንስህ ክነፍ-ብረር-ድረስ እንጂ ከአላማህ ፈፅሞ እትቁም።
💡ነፍስህን ለማደስ ከፀሐይዋ ብርሃን ሙቀት ውሰድ ፡ ከጨረቃዋም ብርሃን ውበትን ቅዳ ፤ልብ በል… ተፈጥሮ የሙዚቃ መሳሪያ ..... አንተ ዳንሰኛ.... ሕይወትም ሙዚቃ ናት። ፀሐይ ጨረቃና የሰማይ ከዋክብትም በጎዳናህ ክበባዊ ዙሪያ በሰልፍ እንደተኮለኮሉ በዳንስህ ለመዝናናት እንዳሰፈሰፉ ተመልካቾች መሆናቸውን ልብ በል።
🔑በተፈጥሯዊው ሕግ መሰረት ካንተ የሚጠበቀው የሕይወትን ሙዚቃ በነፍስ መንፈሳዊ ክንፍ እየደነስክ ጎዳናህን በዳንስ ልትበርበት እንደምትችል ብቻ ማመን ነው። ከሺ አመታት በፊት የተፃፈው ታላቁ መፅሃፍ ከሽህ አመታት ቡሃላም ይናገራል 'ዕመን እንጂ አትፍራ !' የትርጉሙ ምስጢር የጥበብ ተምሳሌትነቱም ይህ ነውና።
✍ Tupaca Ela
ውብ ሰንበት❤️
@Ethiohumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanitybot
📍ከ150 አመት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳችንም በህይወት አንገኝም። ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 አመት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም፡፡ ፈጽመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡
🕯በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት የነበሩ፡፡ የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ አላፊ ጠፊ ሆነው እናስተውላቸዋለን፡፡ ሌላው ይቅርና በሽታ እንኳን ሩቅህ አይደለም፣ የተዘረጋው እጅ አሁን በቅፅበት ማጠፍ ሊቸግርህ ይችላል። በሃብታችን በእውቀታችን በዝናችን .... አለን ባልነው ነገር ሁሉ መማፃደቁ ከንቱ ነው .... ሌላው ቢቀር የዘረጋነውን የምናጥፈው በፈጣሪ ቸርነት ነው።
💡ታላቁ እስክንድር ወደ ሞት አፋፍ መቃረቡን ሲያውቅ፤ ወዳጆቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸው "ስትቀብሩኝ፤ እጄን ወደ ላይ አርጋችሁ ቅበሩኝ" አለ። ሰዎቹም ግራ ገብቷቸው ለምን እንደሆነ ጠየቁት፤ እሱም መልሶ ፤ "እጄን ወደላይ አድርጋችሁ ቅበሩኝ ያልኩት፤ ስሞት ከምድር ምንም ነገር ይዤ እንዳልሄድኩኝ ሰዎች እንዲያዩ ነው " አለ። ይህንን ያለው እንግዲህ በጊዜው አለምን ያስገበረው ታላቁ እስክንድር ነው።
🔷ብርሌ በመሰለ ዓለም ፡ መጥፊያው ሰፊ መልሚያው ጠባብ በሆነ ኑሮ፣ በዙፋን ላይ ካለ ንጉስ በፈጣሪው የታቀፈ አማኝ ይበልጣል!! Impermanenceን በቅጡ የተረዳነው ያህል ሆኖ ያታልለናል። በሕይወት መንገድ ስለ ጤዛነት ብዙ እያየንም አልማር ብሎ የፈተነን አንጎላችን ብዙ ያነበብነና ያወቀ ይመስለዋል።
ማጠቃለያው፣
📍ህይወትን ቀለል አርገህ ኑር፡፡ ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡ከ150 አመታት በኋላ ዛሬ እንደ ትልቅ ሀብት የምናያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡
ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መከባበርን እናስቀድም፣ከጀርባ መወጋጋት፣ መጠላለፍ አክሳሪ ነው፡፡ ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡ የሰው ሕይወት በምድር ላይ በጣም አጭር ናት። ኑሮ ማለት ደግሞ በውልደት እና በሞት መካከል ያለ የመሸጋገሪያ ጊዜ ነው። በድንገት ተጀምሮ በድንገት የሚቆም የመሸጋገሪያ ጊዜ.......
💡ቃሉም እንደሚለው "ሕይወታችሁ ምንድን ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁና።ያዕ 4፡14
💡ሀዲሱም እንዲል "ምድር ላይ ስትኖር እንደ እንግዳ እንደ መንገደኛ እንደ አልፎ ሂያጅ ሆነህ ኑር" (ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ )
🔑 በዚህ ዓለም ላይ ምንም ቋሚ የሚባል ነገር የለም እንኩዋን ሰውና ግዑዝ ነገር ሁሉ አላፊ ነው . . . እንደ አልፎ ሂያጅ አልሆንም ብንልም ማለፋችን አይቀርምና መልካም ስራን ለነፍሳችን እናስቀድም ዘንድ ፈጣሪ ያግዘን።
ውብ አሁን❤️
@Ethiohumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanitybot
💫May this Serve as a living tribute,
To Fendika Art Center.
Words of wisdom,
Shared by Melaku Belay ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
✨ዛሬ በአስቸጋሪና ሊታለፍ የማይቻል የሚመስል ሁኔታ ውስጥ ከሆነ ያለኸው፤እመነኝ ይኼ ሁሉ ፈተና ይታለፋል!የሚገርመው ችግርህን አልፈኸውም ትረሳዋለህ።አሁን ብቻ መንፈስህን አጠንክርና የገጠመህን ፈተና ፊት ለፊት ተጋፈጠው፣ ፈርተህ ጥግህን ከያዝህማ መቼም ደረጃህን ከፍ ልታደርገው አትችልም።
🪐 ያለህ እድል በብልሀትና በጥበብ ከከበበህ የህይወት ፈተና ጋ በመጋፈጥ ለትግል መዘጋጀት ነው። ያኔ ድል ከአንተ ጋ ትቆማለች። ህይወትህም የጣፈጠ ይሆናል። ያኔ የድሮውን ህመም ትረሳዋለህ። ህይወትህንም እንድትጠላው አድርጎህ የነበረውን ስቃይ በአንድ ወቅት በህይወትህ ላይ መከሰቱንም ትዘነጋዋለህ።
🌪ይህ ማለት ግን ድሮ የደረሰብህን ህመም እረስተህ በሌሎች ላይ በአንተ ላይ የደረሰውን መንገላታት አድርግ ማለት አይደለም።እንዲያውም ምንም እንኳን አሁን ህመሙና ስቃዩ በላያችን ላይ ባይኖርም ሌሎች የኛ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሲገቡ ዝቅ በማለት ከጎናቸው በመሆንና ተስፋ በመስጠት ህይወታቸው የተቃናና በተስፋ የተሞላ እንዲሆን ማስቻል ነው።
📍የዕውቀት መገለጫው ብዙ ቢሆንም ሕይወትን በሙላት መኖር ዋነኛውና የሁሉ ነገር መሠረት ነው፡፡ ሕይወትን በእርግጠኝነት የምንኖረው ዛሬ ነውና ዛሬን በልቡ መሻት የሚኖር ሰው እሱ አዋቂና ነገ የእሱ እንዳልሆነች የተረዳ ነው። ለዚህ ማሳያ ደግሞ ቀጣይዋን ተረት እናስከትል።
አንድ ቀን በበረሃ የሚጓዝ ሰው እጅግ የሚያስፈራ ነብር በድንገት ከፊቱ ሲመጣ ተመሰከተ፡፡ በዚህ ጊዜ በድንጋጤ ወደኋላው ተመልሶ መሮጥ ይጀምራል። ጥቂት ርቀት ከሮጠ በኋላ ግን ትልቅ ገደል ከፊቱ ይጋረጣል፡፡ ነብሩ ከኋላው እየሮጠ እንደተከተለው የተረዳው ይኸ ሰው ራሱን ለማዳን አማራጭ ያደረገው በገደሉ ጫፍ ላይ የበቀለውን የወይን ሐረግ ተንጠልጥሎ ወደገደሉ መውረድ ነበረ።
🍇 የወይኑን ሐረግ በሁለት እጆቹ ጨብጦ ወደገደሉ ጥቂት ከወረደ በኋላ ቀና ሲል ሁለት አይጦች የተንጠለጠለበትን ሐረግ ግንድ በጥርሳቸው ሊገግዙ ተመለከተ፡፡ በዚያው ቅፅበት በእጆቹ ከጨበጠው ሐረግ አጠገብ የወይን ዘለላ በሌላ ቅርንጫፍ ላይ ተንዠርግጐ አየና ከዚያ እየቀጠፈ መብላት ሲጀምር እጅግ ጣፈጠው።ሁሉን ረስቶም ከሚጣፍጠው ወይን መብላቱን ቀጠለ፡፡ «ሕይወትም እንዲሁ ነች.....
[ The Enlightened One ] እውቀት የበራለት ሰው በዙሪያው ስለበዛው መከራ የሚጨነቅ ሳይሆን ዛሬ በአጠገቡ ባገኘው መልካም ነገርን አስተውሎ አመስግኖ ተደስቶ የሚያልፍ ነው።
📍እናም ወዳጄ
⏳ ያለፈው ላይ አትጨነቅ፣ እርሳው፤ አትኩሮትህ ዛሬ ላይ ይሁን፡፡ እውቀት ያለው ሰው በዚህ መንገድ ብቻ ሕይወትን መደሰት ይችላል፣ ስለ ሕይወትህ ችግር ከገጠመህ ወይም ጥያቄ ከተፈጠረብህ ዙርያህን አጥና... ያለህበት ሁኔታ ከሕይወትህ ጋር ያለውን መልካም አንድምታ መርምር በተለይ ትንሽ ትልቅ ሳትል በአቅራብያህ ያሉ ሰዎችን ህይወት በመመልከት ላንተ ምን መልእክት እንዳለው በትጋት ተከታተል ምክንያቱም የተፈጥሮ መንፈሳዊ አንደበት ናቸውና።
⌛️ከዘላለም አንፃር ስናየው የዚህ ዓለም ቆይታ አንዲት ሰዓት እንኳን አይሞላም፡፡ቢሆንም ትግል ባይኖር የድል ደስታ ፣ በሽታ ባይኖርበት የጤና ምስጋና አይኖርም ነበር፡፡ ጣፋጭን ያጎላው መራራ ነው።የሁሉን ሰው መከራ፣ ስደትና ስቃይ ፈጣሪ ይመለከታል። በጊዜው ፍቃድም የሰራውን የሚያፈርስ ራሱ የፈጠረው ነው።
🔑 ተስፋ አለና ትደርሳለህ ለዛሬ ብቻ አይደለም ነገንም ለማየት ነው ከትላንት ያለፍከው፡፡ በርታ ሰው ሁን ፣ ሰው መሆን ትግል ነው ፣ ግፋ! ፅና! ሰው የድካሙን ፍሬ ሲያይ እና ሲበላ እንዳለ ያለ ታላቅ ደስታ የለምና...... ሁሉም አንተ ውስጥ ነው፡፡ አንተነትህንም ጨምሮ፡፡ ማነህ? ለምን መጣህ? ማን ነው ይህንን ሊመልስልህ የሚችለው? አይታይህም ጥያቄውም መልሱም አንተ መሆንህ?
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
💡ቀስ እያለ ነጋ!
🔷አንዳንድ ቀን በጣም ከባድ ነው ሁሉም ነገር ይሰለቻል ከአልጋ ላይ ራሱ መነሳት ያስጠላል በጣም ደክሞኛል ስትል እንኳን ምን ለማለት ፈልገህ እንደሆነ ማንም አይረዳህም
በቃ............... ሁሉም ነገር ጭልምልም ይልብሀል ምን መስራት እንዳለብህ የት መሄድ እንዳለብህ ራሱ ግራ ይገባሀል ያስደስትህ የነበረዉ ሁሉ ያስጠላሀል በቃ መሀል ላይ ራስህን ታጣዋለህ፣ ሕይወት እንደ ደራሽ ማዕበል ይሆንብሃል፡፡ በሰላም ይሄዱ የነበሩ ነገሮች ልክ የተመካከሩ ይመስል በአንድ ላይ ይናጋሉ፡፡ የሁኔታዎች አልሳካ ማለት፣ ድንገተኛ ወጪዎች፣ የጉዳዮች መጥመም፣ የሰዎች ክህደት፣ስጋትን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች መከሰት፣ ልክ እንደ ማዕበል በአንድ ላይ ይመጣሉ፡፡
💎ህይወት ሁሌ ሙሉ አይደለችም ፣ ማጣት ማግኘት መደሰት ማዘን መጫወት መከፋት ማዉራት ዝም ማለት መሳቅ ማልቀስ ብዙ ብዙ ነገር ይገጥመናል ሰው ይፈተንበት ዘንድ የተሰጠው ፈተና ሺ ነው፡፡ እስትንፋሱ እስካለች ድረስ ፈተናው አያልቅም፡፡ ተረጋጋሁ ሲል የሚረበሽ፤አረፍኩ ሲል እንከን የማያጣው ጥቂት አይደለም፡፡
📍ጥያቄው ግን እኛ ሰዎች በጎ በጎዉን ትተን መጥፎው ላይ ብቻ ለምን እንከርማለን ነው??
አንድ እውነታ የሚመሰረተው እውነታ ካልሆነው ነገር ጋር ተነፃፅሮ ነው። ካልሆነ ግን እውነት ሚባል ስያሜም አይኖረውም። ጥሩ መጥፎ ከሌለ ሊኖር አይችልም። ጥንካሬ ድክመት ካሌለ ሊታወቅ አይችልም።ስለዚህም መከራን አትጥላው። የመከራ ዘር በውስጡ የማንነት እድገትን ይዟልና። ያሰብከው እና ያገኘህው ነገር ሊለያይ ይችላል። ነገር ግን የቱም ሁኔታ ትምህርትን ይዞ ይመጣል፣ የምንኖረው በአንፃራዊ አለም ውስጥ ነውና።
💡ለማንም ሰው ህይወት ስህተት ወይም ትክክል መሆኑን የሚያውቀው ሲፈተን ነው። ጫጩት ለማግኘት የእንቁላሉ ቅርፊት ማስወገድ ሽፋኑን መግለጥ ያስፈልጋል፣ ወርቅ የሚወጣው ከጭቃ ውስጥ ነው። ዝናብ ሊዘንብ ሲል ነጎድጓድና የመብረቅ ብልጭታ ቀድመው መታየት ይጀምራሉ። ሌቱ ሊነጋጋ ሲል በጣም ይጨልማል። ከከባድ ምጥ በኋላ ልጅ ይወለዳል። ይህ የተለመደ የሕይወት አካል የሆነ ክስተት በእኛም ላይ ሲደርስ መረጋጋት ወሳኝ ነው፡፡
እናም ወዳጄ
🔑ህይወት ሁሌም ለማንም የትም ሙሉ አይደለችም፡፡ ቀን አለና ቀና በል፣ አስብ ባሰብከው ሀሳብ ተፅናና በተፅናናህበትም ቃል ሌሎችን አፅናና!! በሕይወት ሩጫዎችህ መሀል ያለውን ውስብስብ የሕይወት ገፅ ጠንቅቀው የሚያውቁት ጥቂቶች ናቸው። ስለሆነም ባልተረዱህ ብዙ ሰዎች እየተናደድክ ሳይሆን በተገነዘቡህ ጥቂት ሰዎች እየተደሰትክ ኑር። አልሞላ ያለው ነገር ሁሉ ፈጣሪ በራሱ ግዜ አስተካክሎ ጨምሮ ያመጣዋል ።
ዛሬን ባለህ ነገር አመስግነህ ደስ ብሎህ ኑር። ባለህ የማትረካ ከሆንክ ሩጫህ ሁሌ ሌላ ነገር ፍለጋ ብቻ የሆናል፡፡ የሌለህን ነገር ብቻ ካሰብክ በማማረርህ ውስጥ ያለህንም ታጣዋለህ፡፡ ያለህን ነገር ካሰብክ ግን በምስጋናህ ውስጥ የሌለህንም ታገኘዋለህ፡፡
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
🛑ሠላም ከውስጣችን የሚመነጭ፣ ከቅን አስተሳሰባችን ተምጦ የሚወለድ፣ ከደግ ልቦናችን የሚፈለቀቅ ውስጣዊ ሐብት ነው፡፡ ሠዎች ሠላምን ፍለጋ የማያደርጉት ነገር የለም፡፡ አንዳንዶች ‹‹ሠላምን ማግኘት የምንችለው በጦርነት ነው›› በሚል ፈሊጥ ጠብመንጃ ያነሳሉ፡፡ ጥቂቶች ‹‹ካልደፈረሠ አይጠራም›› በሚል ሃሳብ አደፍርሠው ማጥራትን ይሻሉ፡፡ ነገር ግን ልፋታቸው ከንቱ ሲሆን እናያለን፡፡ በአሸናፊነትና ድል በመንሳት የሚገኝ ሠላም ዕረፍት የሚሠጠው ለጊዜው እንጂ ቋሚ ሠላም አያስገኝም፡፡ ተሸናፊዎቹ ጊዜ ጠብቀውና ዕድል ሲቀናቸው ሠላሙን ሊያደፈርሱት ይችላሉና፡፡
🔷ሠዎች ሠላምን መፈለግ ያለባቸው መጀመሪያ ከራሳቸው ነው፡፡ ጥቂቶች ሠላማዊ ሕሊናን መፍጠር አቅቷቸው ሠላምን ፍለጋ ሲዋትቱ እናያለን፡፡ ለራሳቸው እንኳን ቅድሚያ ሠላም አልሠጡትም፡፡ አዕምሯቸውን በሠላማዊ ሃሳብ አልሞሉትም፡፡ ልቦናቸውን ለሠላም አላስገዙትም፡፡ ስሜታቸውን በሠላማዊ አመለካከት አልገሩትም፡፡ ጥቂቶች እንደውም የሌሎችን ሠላም በመንሳትና ሠላማቸውን በማደፍረስ ሠላም የሚያገኙ ይመስላቸዋል፡፡
♦️ሠላም ከራስ፣ ከቤተሠብ፣ ከመንደር፣ ብሎም ሐገር ጋር ሊደርስ የሚችል እንጂ ከውጪ በጉልበት ወይም በገንዘብ ገዝተን የምናመጣው አይደለም፡፡ ሠላምን መፍጠር የሚችለው ራሱ ሠው ነውና፡፡ በግለሠብ ያለው ሠላም ተሰብስቦ የቤተሠብ፣ የመንደር ብሎም የሐገር ሠላም ይሆናል፡፡
አልበርት አንስታይን ስለሠላም ሲናገር እንዲህ ይላል፡-
‹‹ሠላምን በሃይል ማስጠበቅ አይቻልም፡፡ ሠላም ዕውን ሊሆን የሚችለው በጋራ መግባባት ብቻ ነው፡፡›› ይለናል፡፡
📍እውነት ነው! ሠላምን ማስፈን የሚቻለው በመግባባት፣ ሃሳብን በሃሳብ በማዋሃድ፣ የጋራን ጥቅም በእኩልነት በማስጠበቅ፣ ‹‹እኔ ብቻ ይድላኝ›› የሚሉትን ስግብግብ አስተሳሰብ ወደጎን በማለትና በማስወገድ ጭምር ነው፡፡ መግባባት ሲባል ሠጥቶ መቀበል፤ ተቀብሎ መስጠት ያለበት መርህ ነው፡፡ ለሌላው ሠላም ሳንፈጥር ለራሳችን ሠላም ማግኘት አንችልም!
💎ወዳጆች የሐገርም ሠላም ዕውን የሚሆነው እያንዳንዳችን በምናዋጣት የሠላም አስተሳሰብና ድርጊት ነው፡፡ ሠላማዊ ሠው ሌሎችን ያከብራል፣ ሠላማዊ ሠው የሌሎችን መብትና ነፃነት ያስጠብቃል፣ ሠላማዊ ሠው እሱ የሚያስፈልገው ሁሉ ሌሎችም እንደሚያስፈልጋቸው ቀድሞ ስለሚያውቅ ጥቅማቸውንና ሕይወታቸውን አይቀማም፡፡ ግና ግን ሠላምን በፖለቲካ አሻጥር፣ ጠልፎ በመጣል ሴራ እውን ማድረግ ፈፅሞ አይቻልም፡፡ ሌሎችን በመጣል የሚገኝ ሠላም እውነተኛ ሠላም አይባልም፡፡
ለዚህም እኮ ነው ዳላይ ላማ፡-
‹‹እያንዳንዱ ግለሠብ ሠላሙን በመፈለግ ሂደት ውስጥ የዓለም ሠላምን ይወስናል!›› የሚለን፡፡
ሠላም ምንጩ ግለሠብ ነው፤ መድረሻው ሐገር ነው፤ ወሠኑ ደግሞ ዓለም ነው፡፡ ሠላምን በመፈክር፣ በዘፈን፣ በግጥም፣ በቀረርቶ፣ ወዘተ ነገሮች ማስፈን አንችልም፡፡
💡እነዚህ ያለን ወይም የነበረን ሠላም ለማጎልበት ይጠቅሙ ይሆናል እንጂ የሠላም ምንጭ መሆን ግን አይችሉም፡፡ የሠላም ምንጩ ግለሠብ ነው፡፡ ያ ግለሠብ ደግሞ ለሠላም ካለው አመለካከት ጋር በተያያዘ የራሱንም ሆነ የአካባቢውን፣ አልፎ ተርፎም የሐገሩን ሠላም ይወስናል፡፡ በአንድ ሠላም በሌለው ግለሠብ ምክንያት ቤተሠብ፣ አካባቢ፣ ሐገር እንዴት እንደሚሸበር በዓለማችን እያየን ነው፡፡
🔑የሠላም መነሻው ግለሠብ ነውና እያንዳንዱ ሠው ሠላሙን ይፍጠር፣ ሠላሙን ያስጠብቅ፣ የሌሎችንም ሠላም ያረጋግጥ፡፡ በተለይ መጪው ትውልድ ሠላማዊ እንዲሆን ለልጆቻችን ሠላምን በተግባር እየከወንን ሠላምን እናስተምራቸው፤ እርስ በርስ በሠላም በመግባባትና በመተራረቅ የሠላም አብነት ሆነን እናሳያቸው፡፡
ሠላም ለዓለማችን! ሠላም ለሃገራችን!ዘመኑ ሠላማችንን የምናረጋግጥበት ይሁን።
ውብ ጊዜ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
✏️እርሳስነት
🔴እርሳስነት ለኑረት ስምረት የተመቸ ተምሳሌት ይመስላል፣ ለመስተጋብር ውበት የተስማማ ምልክት፣ ለመማር የተዘጋጀ ሰው በዙሪያው እልፍ መምህራን አሉለት።
“When the student is ready the master will appear” እንዲሉ…
🟡ተወዳጁ ደራሲ ፓውሎ ኩዌልሆ “Like the Flowing River” በተሰኘው መጽሐፉ ላይ የልጅ ልጃቸውን ታሪክ በሚጽፉ አያት አማካይነት ስለ እርሳስ ልዩ መገለጫዎች ይነግረናል፣ አንድ ሕፃን ሴት አያቱ የሚጽፉት ታሪክ የእርሱ ስለመሆኑ እንዲነግሩት ሲጠይቅ ከሚጽፉት ታሪክ በላይ በሚጽፉበት እርሳስ የተመሰጡት አያት “አዎን ልጄ ታሪኩ ስላንተ ነው… ግና ከምጽፈው ታሪክ ይልቅ የምጽፍበት እርሳስ የተለዩ ነገሮች አሉትና ስታድግ እንደዚህ እርሳስ እንደምትሆን ምኞቴ ነው” ይሉታል።
በአያቱ ንግግር የተገረመው ሕፃን እርሳሱን ትኩር ብሎ ይመለከትና ከሌሎች እርሳሶች የተለየ ነገር እንዳላየበት ለአያቱ መልሶ ይነግራቸዋል።
“አዎን ልክ ነህ” አሉት አያት፣ “የምታይበት መንገድ የምታየውን ነገር ዋጋ ይወስነዋል፣ በደንብ ተመልከት፣ እርሳስ ያሉትን ልዩ ጠባያት መገንዘብ የቻለ ሰው ከፍጥረተ-ዓለሙ ጋር ስሙር እንዲሆን የሚረዱትን አምስት ጥበባት ይማራል…” ሲሉ መለሱለት።
🔴እኒህን አምስት የኑረት መላዎች ከሌሎች አሰላሳዮች ጥልቅ ምልከታ ጋር ማዛነቅ ሻትኩ፣ ልክ እንደዚህ…
1️⃣‘First quality: you are capable of great things, but you must never forget that there is a hand guiding your steps. We call that hand God, and He always guides us according to His will.’
🔷“ታላላቅ ተግባራት የመፈጸም ሰዋዊ አቅም ቢኖርህም በመንገድህ ሁሉ የሚመራህ እጅ እንዳለ ግን መዘንጋት የለብህም፣ እርሱም መለኮት ነው። ሁልጊዜም እንደፈቃዱ ይመራሃል”
♦️ዓለም በስልጣኔ ብትረቅ፣ በቁስ ዕድገት ብታሸበርቅ፣ የሰው ልጅ ትንግርት በሚያስብሉ ተግባራት ቢራቀቅ ያለ መለኮታዊ ድጋፍ የትም ሊደርስ አይችልም። እያንዳንዲቷ እርምጃው መለኮታዊ እገዛ ያሻታል፣ ከራስ አቅም ጣሪያ በላይ ገደብ አልባ ጣሪያ መኖሩን አለመርሳት ደግ ነገር ነው። እብሪትና ማንአለብኝነት ከሚያመጡት አዙሪት ለመውጣትም ሆነ ከኑረት እልፍ ጉድጓድ ለመሻገር ሁነኛው መድኅን መለኮት ነው።
“I’ve forgotten all my learning’s but from knowing you I’ve become a scholar. I’ve lost all my strength, but from your power I am able.” ~ Rumi
2️⃣“በየቆምታዬ ታዛ መቅረጫ ተጠቅሜ እቀርጸዋለሁ፣ ይህ ተግባሬ እርሳሱ በመጠኑ እንዲጨቆን ቢያደርግም ስለቱ ለስራ ምቹ ያደርገዋል። አንተም ብትሆን በኑረት ውስጥ የተሻልክ ትሆን ዘንድ ጥቂት እንግልቶችን እና ጫናዎችን ማለፍ ይኖርብሃል”
🔶ብዙውን ጊዜ የገባንበትን ፈተና ጥልቀት እንጂ ከፈተናው በመውጣት ሂደት የሰነቅነውን ጥበብ አናስተውልም… በዚህም ምክንያት በርካታ የኑረት ክህሎቶች በማስተዋል እጦት ይቀጭጫሉ፣ የብዙ ስኬቶቻችን አሃዱ ግና የሕመማችን ማግስት ነው።
“The wound is the place where the Light enters you.” ― Rumi
3️⃣“እርሳስ ምንጊዜም ቢሆን የሰራነውን ስህተት በላጲስ አጥፍተን የማረም ዕድል ይሰጠናል ፣ ስህተትን ለማስተካከል መድፈር መጥፎ ነገር አይደለም። ይልቁን በቀናው መንገድ ጉዞአችንን እንድንቀጥል የሚረዳን አቅም እንጂ”
🔷በፊቶቻችን የተንኮታኮቱ ጅምሮች፣ የጨነገፉ ሕልሞች፣ ያልተሳኩ ሙከራዎች በርካታ ናቸው። የጅምር እንከን ለዳግም ጅማሬ እንቅፋት ሆኖባቸው ከመንገድ የቀሩ ጓደኝነቶች፣ ትዳሮችና መሰባሰቦች እልፍ ናቸው። ጥፋትን በይቅርታ ማንፃት የተሳናቸው ግትርነቶች፣ ትዕቢትን በአትሕቶ ርዕስ ማጠብ ያቃታቸው አምባገነንነቶች፣ ጭካኔን በአጥፍቻለሁ ዝቅታ ማረቅ የማይሹ ድርቅናዎች የየዕለት ገጠመኞቻችን ናቸው። ይህ ሁሉ ታዲያ መሳሳትን ለመቀበል ድፍረት ከማጣት የሚመጣ እንከን ነው። አልያም ‘ካፈርኩ አይመልሰኝ’ ከሚል አኞነት…
“A man should never be ashamed to own that he has been in the wrong, which is but saying in other words that he is wiser today than he was yesterday.” ― Alexander Pope
“O, happy the soul that saw its own faults.” ~ Rumi
4️⃣ “የእርሳስ ወሳኙ ክፍል ከውጭ የሚታየው እንጨት አይደለም፣ ከውስጥ ያለው መፃፊያ እንጂ፣ ስለሆነም ትኩረት ማድረግ ያለብህ በውስጣዊው ሁነትህ ላይ ነው”
♦️ወጭቱን በአፍአ ጽድት አድርገው የሚይዙ ውስጣቸው ግን በኖራ እንደተለሰነ መቃብር የሚገለሙ በርካታ የአዘቦት ተመሳስሎዎችን እናውቃለን፣ አለማወቁን በቃል ብልጠት የሚሸሽግ ከንቱ… ባዶነቱን በከፈን ድምቀት የሚከልል ሰነፍ ፣ መልከ-ጥፉ ልቡን በስም የሚደግፍ ነውረኛ፣ የነፍሱን እርቃን በመንፈሳዊነት ካባ የሚከፍን አስመሳይ… ቁጥሩ ብዙ ነው።
Beauty is not who you are on the outside, it is the wisdom and time you gave away to save another struggling soul like you.” ― Shannon L. Alder
5️⃣ “እርሳስ ሁልጊዜም አሻራውን ትቶ ያልፋል። አንተም ብትሆን በኑረት የምትሰራው ማንኛውም ነገር ምልክቱን እንደሚተው ልብ ልትል ይገባል። ስለዚህም ድርጊትህን ሁሉ በአስተውሎት ከውን። ለደቀመዛሙርቱ የሚሰጠውን የሚያውቅ መምህር ከራሱ የሚሻሉትን ያፈራል። ፍርሃቱን ከራስ አኑሮ ድፍረቱን የሚጋራ ሰው ለሌሎች ተስፋ ያተርፋል፣ ለዛሬው የሚጠነቀቅ ነገውን አሁን ይሰራል። በብርሃን ላይ የተመሰጠ የጽልመት አምካኝ መላ ያፈልቃል።
ምንህን እየሰጠህ ነው?… “What kind of footsteps will you leave for those who follow you?” ― Kathy Bee …
🔑ፍቅርን ነው ጥላቻ፣ ሰላምን ነው ጸብን፣ አንድነትን ነው መለያየትን፣ ስታልፍ የምናስብህ ለሰላማችን በጣልከው መሰረት ነው ወይስ ለግጭታችን በሰራኸው ሴራ? ለአብሮነታችን በገነባኸው ታዛ ነው ወይስ ለመቋሰላችን ባኖርከው ሰይፍ?
ለሚያነቡህ ምን እየፃፍክ ነው? ለሚሰሙህ ምን እየተናገርክ ነው? ወላጅ ላሉህ ምን ትተሃል? ከቶ አሻራህ ምን ይመስላል? ቅርስህሳ ምን ሸክፏል? ከኑረትህ ምን ተርፎናል?
በአያቱ ተግባር የሚያፍር ዘመነኛ – በተራው ልጁ እንዳያፍርበት ያለው ብቸኛ አማራጭ ልቡናውን ከቂም አንጽቶ የእርሱን ውብ ነገ ዛሬ ላይ መስራት ነው። ይህ ግን ከኢጎ የመላቀቅን ድፍረት ይሻል!!
“Take nothing but memories, leave nothing but footprints!” ― Chief Seattle
✏️በደምስ ሰይፉ
እርሳስነት – ምርጥ ብልሃት
ውብ አሁን❤️
💎ሃሳብ ፣ ንባብ፣ ኑረት፣ ሕይወት፣ፍቅር እና ምናብ! ድልድይ👇
@BridgeThoughts
@BridgeThoughts
✍ @EthioHumanitybot
📍እንኳን ለ129ኛው ለታሪካዊ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ነፃነት በር ለሆነው የጥቁር ህዝቦች ኩራት የአድዋ ድል በአል በሰላም አደረሰን።
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✨አሃ - /Aha Moment/
“What I always want is to have several little ‘aha’ moments where your brain is very happy.” – Scott Kim
ከመቶ ዓመት በፊት በአንዱ ዕለት ነው፣ ሰውየው የሚያማምሩ አበቦች ባሉበት የቤቱ የአትክልት ስፍራ ላይ ተቀምጦ የዕለቱን ጋዜጦች ያገላብጣል። ድንገት… ‘በሞት የተለዩ ሰዎች’ በሚለው አምድ ላይ የአንድን ሰው ዜና እረፍት አየና ክው ብሎ ደነገጠ፣ ጽሑፉን ሲያነብ ጋዜጣው እንደ መርዶ ነጋሪ ሹክክ ብሎ ቤቱ የተገኘ ጥላቢስ እንጂ ተራ ወረቀት አልመስልህ አለው፣ ክውታና ድንዛዜ፣ ደርሶ ጭውውውውው አለበት።
ብንን ብሎ ጋዜጣውን በድጋሚ ተመለከተው፣ አልተሳሳተም፣ በትክክል የሚያነበው የራሱን ዜና እረፍት ነው፣ Dynamite king dies ይላል። ‘የድማሚቱ ንጉስ አረፈ…’ ያ.. ተራራውን ገምሶ.. ቋጥኙን ፈልፍሎ.. አለታቱን ነድሎ መንገድ የሚተልመውን ድማሚት የፈጠረው ሰው አረፈ እያለ ነው… ሰውየው ራሱን ጠየቀ… ‘ይህን ዜና የማነበው በእውኔ ነው በሕልሜ?’ መልስ የለም።
💡ዜናው በዚህ ቢያበቃ ጥሩ አይደል… ስለ ‘ሟቹ’ ሌላም ነገር ይላል፣ And he was the merchant of death…(የሞት ነጋዴ እንደማለት ነው) ሳይሞት ሞተሃል ከመባሉ በላይ እንደ ሙት የሚታሰብበት መንገድ ሰውየውን የበለጠ አስደነገጠው፣ ተንቀጠቀጠ… ሰበበ ሞት ተደርጎ ነዋ የተገለጸው… የጅምላ ፍጅት ምክንያት ተደርጎ ነው የተሳለው… ‘እውነት ሞቼ ቢሆን ሰዎች የሚያስታውሱኝ እንደዚህ እያሉ ነው?’ ሲል ጠየቀ፣ ‘በፍጹም!!! ይህ ቅጽል መፋቅ አለበት!!’
🧨 ይህ ሰው አልፍሬድ ኖቤል ነው። ኖቤል ድማሚትን ‘በመፍጠሩ’ ይታወቃል፣ ግኝቱ ለመንገድ ስራ ያለው አስተዋጽዎ ጎልቶ የሚነገርለት ቢሆንም ኖቤልን ‘ነፍሰ ገዳይ’ ከሚል ስም አላስጣለውም… የፈረንሳይ ጋዜጦች “Le marchand de la mort est mort” (“The merchant of death is dead.”) ብለው ሲዘግቡ ዜናውን በዚያው ወቅት ፈረንሳይ ውስጥ ከሞተው የአልፍሬድ ኖቤል ወንድም ሉድቪግ ጋር አምታተውት ኖሯል፣ ሆኖም አጋጣሚው ኖቤልን ከጥልቅ እንቅልፉ የሚያነቃው ነበር… እናም ይህን ስም ለውጦ ማለፍ እንዳለበት የወሰነው እዚያው ነበር።
💎በፈጠራው ምክንያት ያገኘውን ሳንቲም ሰብስቦ ለበጎ ተግባር እንዲውል ሰጠ፣ በደህናው ዘመን ስለ ድንቅ ጥበቡ የተበረከተች ሳንቲም በችግሩ ጊዜ ስለ ስሙ መታደስ ወጣች፣ ያቺ ሳንቲም በዝታና በርክታ በዓለም ዙሪያ በሳይንስ፣ በስነጽሑፍ፣ በሰላም፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በፊዚክስና በሌሎችም በርካታ ዘርፎች ከፍ ያለ አስተዋጽዎ ለሚያደርጉ ግለሰቦች ሽልማት ሆና የምትቀርብ ሆነች።
ዛሬ ዛሬ የ Nobel Prize Winner መሆን የልዕልና መግለጫ ሆኗል፣ በዙርያችን ‘እከሌ የኖቤል ተሸላሚ ነው’ የሚለው ስያሜ ትልቅ ማዕረግ ሆኗል፣ ብዙ የምናደንቃቸው የዓለማችን ሰዎች የሽልማቱ አሸናፊ ሆነዋል፣ ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ጨምሮ ፣ አዎን… አሁን ኖቤልን ከሞት ጋር አያይዞ ስሙን የሚያነሳ፣ ከውድመት ጋር አቆራኝቶ ስራውን የሚያወሳ አንድ ስንኳ የለም።
ከ’ሞት’ በኋላ በበጎ መታወስ የሚል ቅዥት ሰከንዶችን ተጋርቶኝ አያውቅም፣ ግና ሰው በኑረት ብቻ ሳይሆን በእልፈቱም ለሌሎች መኖር ከቻለ ድንቅነቱ ይገባኛል፣ ያም ሆኖ የበለጠ የሚመስጠው የተረኩ ክፍል ‘በሌሎች ዘንድ የጠለሸን ስም’ ለማደስ የመቁረጡ ጉዳይ ነው።
🔷አስባችሁታል፣ መንግስት ‘ለካ ሕዝብ የሚረዳኝ እንዲህ ነው?’ ብሎ ስሙን ለማደስ ሲተጋ… ፣ ባል በጸጸት ውስጥ ሆኖ ‘ለካ በሚስቴ ዓይን የምመስለው ይህን ነው?’ ብሎ እንከኑን ሲነቅስ… አባት ‘ለካስ ለልጆቼ ጥሩ ወላጅ አልነበርኩም’ ብሎ መንገዱን ለመቀየር ሲወስን… ተቋማት ‘በደንበኞቻችን ዘንድ ያለን ገጽታ ጥሩ አይደለም ለካ’ ብለው ለምርትም ሆነ አገልግሎት መሻሻል ሲሰሩ… ትራፊኮች በአሽከርካሪ ዓይን፣ አሽከርካሪዎች በተሳፋሪ ዓይን…፣ አለቆች በሰራተኛ፣ መምህራን በተማሪ፣ ፍቅረኞች በተፈቃሪያቸው፣ ብቻ ሁሉም በየአንፃራቸው ቦታ ራሳቸውን አስቀምጠው ‘አሃ…’ ቢሉ
🔑አንዳንዴ በሌሎች መስታወት ውስጥ ካላየነው በቀር የማይገለጥ ቁሸት አያጣንም፣ በወዳጅ ምክር ውስጥ ካልሆነ የማይቀና ጉብጠትም እንዲሁ ፣ ‘ለሌሎች’ ሲባል ሁሉ ይፍረስ አይባልም መቼም… ሁሉን ማስደሰት አለመቻል ብቻ ሳይሆን ‘የራስ ጣዕም’ ማጣትም ልክ አይሆንምና
ግን አለ አይደል… ‘በልክ ነኝ’ ካብ ውስጥ ያደፈጠች ክፋት፣ በማናለብኝ ጎሬ ውስጥ የተሸጎጠች ትዕቢት፣ የሌላውን ምቾት የምትነሳ ክርፋት… ምናል.. ‘አሃ…’ እያልን ብናስወግዳት።
ውብ አሁን❤️
✍ ደምስ ሰይፉ
💯 በዚህ ውብ ድልድይ እንሻገር ፣ ሁላችንም ቻናሉን በአብሮነት እንቀላቀል 💯
👇
@BridgeThoughts
@BridgeThoughts
✍@EthioHumanitybot
📍ፍቅርን ለመስበክ እንደ ጦርነት መሳሪያ መደርደር ወታደር ማሰለፍ ፤ ግዳይ መጣል አያስፈልገንም ። ቅን እና በፍቅር የተሞላች ልብ ብቻ በቂ ነው ። ከጦርነት በኋላ የምናተርፈው ነገር የፈራረሰ ከተማና ማንነት ነው ። ጀግና ነኝ ብሎ ከሚፎክረው ገዳይ ልብ ውስጥ ጥልቅ ፍርሃት ፣ ጥላቻ ፣ ጥርጣሬና ትምክህት ነው የምታገኙት ።
ጦርነት እምቅ ሀብትን አውዳሚ
እምቅ እውቀትን በታኝ፣እምቅ ሀይል ያለው ትውልድን አጥፊ ስለሆነ አስተዋይ ነኝ የሚል ሰው ሊጫወተው የማይገባ ድራማ ነው።
ምላስ የጦርነቶች ሁሉ እናት ነው፡፡ ምላስ አዳኝ ነው፤ ምላስ ገዳይ ነው፡፡ ለአንዱ ንፁህ የሆነው ለሌላው መርዝ ነው፤ አንዱን የፈወሰው ሌላውን ይገድለዋል፡፡በአለም ላይ የተደረጉ ጦርነቶች በሙሉ በስተመጨረሻ ሁሉም ሰው በሰላም ለመፍታት ቢሞክር ይህ ሁሉ ባልሆነ ነበር የሚሉ አንድምታ ይፈጥራሉ።እኔ ነኝ ልክ ፣ እኔ ነኝ አሸናፊ በማለት የሚነሳ ትውልድ በእልህ የታነቀ ፣ቂምን ያረገዘ ሰለሆነ የሚመጣውን የሀገር ውድመት አያስተውልም።
የህይወት ለውጦችን ከመቃወም ይልቅ ራስን አስተጋብሮ መራመድ ጥበብ ነው ። ሕይወት ካንተ ውጪ ሳትሆን ከእናንተ ጋር ናት፡፡
📍እናም ወዳጄ
ራስህን ስጋት አታድርግ፡፡ መልካም ሰው ማንንም አያማርርም ። ያለፍቅር ሕይወት ዋጋ የለውም ፡፡ ፍቅር የሕይወት ውሃ ነው ፣ ፍቅርን የሚያቅ ሰው የነፍስ መብራት ነው። ሁሉም ነገር እና ሁሉም ሰው ከማይታዩ ብዙ ህብረቶች ጋር የተሳሰረ ነው።
የሰዎችን ልብ አትስበር ፡፡ከአንተ ይልቅ ደካማ እንደሆኑ አርገህ ቁልቁል አትመልከት፡፡በአንደኛው የዓለም ክፍል ውስጥ ያለ ሀዘን መላውን ዓለም ሊያሰቃይ ይችላል ፣በዛው ልክ ደግሞ የአንድ ሰው ደስታ እና ፈገግታ መላውን ዓለም ፈገግ ሊያደርገው ይችላል።
💡አብዛኛዎቹ ግጭቶች እና ውጥረቶች በቋንቋ ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው። በፍቅር የሚለመልም እንጂ የሚወድም ግለሰብም ማህበረሰብም ሆነ ሀገር አላየንም ።በፍቅር የተሞላች ልብ ውስጥ ጥንካሬ ፣ቅንነትና ለሁሉ አሳቢነት በአንድንት ጎጆ ሰርተው በፍቅር ሲኖሩ ታያላችሁ ።
ሰው ከፍቅር ውጭ ሊኖር እንዴት ይቻለዋል ! ስለ ፍቅር ስበክ ፣ ስለ ፍቅር ኑር !
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanityBot
📍በራስህ ችሎታ እና አቅም ለመሰራት ፈቃደኛ ከሆንክ፣ በሰሪህም ኃይል እና እርዳታ ካመነክ፣ በሌሎች እርዳታ እና ተግዳሮት ጠቀሜታ ላይም እምነት ካለህ፣ ከሁሉም በላይ በራስህ ላይ ከተማመንክ፣ ከወርቅ እና አልማዝ በላይ ደምቀህ ትታያለህ። እራስህን ሁን!! እራስህን መሆን የፈጠረህን አካል አምንህ መቅበል ነው።
💎አልማዝ ጠንካራ ነው። በድንጋይ ቀጥቅጡት አይሰበርም። በሰይፍ ምቱት አይሰነጠቅም። በመጋዝ ገዝግዙት አይቆረጥም። በአልማዝ ግን ብረት ይቆረጣል፣ በአልማዝ ግን ሰይፍ ይቆረጣል። በአልማዝ ግን ድንጋይ ይፈርሳል። አልማዝ የሚቆረጠው በሌላ አልማዝ ነው።
💡ከፍተኛ የማንጸባረቅ ባህሪ አለው። refractive index ይባላል። የተቀበለውን ብርሃን መልሶ የማብራት ባህሪ አለው። ያንጸባርቃል። አልማዝ ባህሪ የተቀበለውን የጸሐይ ብርሃን፣ ነጩን ብርሃን ወደ ተለያዩ በርካታ ቀለማት የመበተን ችሎታ አለው። የተሰሩ ሰዎች አልማዝ ናቸው ጠጠር ጠጠር ነው! ጠጠር ከመሬት በቅርብ ርቀት ይገኛል። አልማዝ በጥልቀት በጋለ ሙቀት እና በከፍተኛ pressure ላይ ይገኛል። ዋጋው ይታወቃል ፤ ድንጋይን ማን ይፈልጋል? አልማዝ ግን ይፈለጋል ምክንያቱም አልማዝ ጠንካራ ነው ፤ የእርሱ የሆነውን የሚያደምቅ ነው ፤ ከምንም ነገር በላይ ንፁህ እና ውድ ነው።
🔑 እናም ወዳጄ ሆይ
እንደ አልማዝ ውድና ተፈልገህ የምትገኝ ሁን። እንደ አልማዝ በሰዎች መካከል አብራ ፤ ሰዎችን ተስፋ ለግሳቸው ፤ ከቂም ቆሻሻ ነፃ ሁን፤ ይቅር በል ፤ከዘረኝነት ቆሻሻ ታጠብ፤ ከክፋት፤ ከተንኮል እና ከምቀኝነት ራቅ፣ የልብህን ንፅህናን ጠብቅ። ሁኔታዎች ችግር ፈተናዎች አይስበሩህ። ዋጋህ በጣም ውድ ይሁን።
📍የሰው ልጅ ልክ እንደእርሳስ ነው፡፡ እርሳስ ጠቃሚው ነገሩ ውስጡ ነው ያለው፡፡ ለዚህም ነው የሚቀረፀው፡፡ ተቀርፆ ሲያበቃ ታሪክ መፃፍ ሂሳብ መስራት ስእል መሳል ይችላል፡፡ አንተም እርሳስ ነህ በመከራ በፈተና ተቀርፀህ ስታበቃ ነው ታሪክ መፃፍ አለም ማስደመም የምትችለው፡፡ እርሳስ ያለመቅረጫ ዋጋ የለውም አንተም ያለፈተናዎችህ አንተነትህ አይታወቅም፡፡ አስታውስ ሽቶ አናት አናቱን ጫን ሲሉት ነው መልካም መአዛ የሚያወጣው፡፡ መከራህን ውደደው የሰውነትህን መአዛ የሚሰጥህ እሱ ነውና።
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
🔔የሚሸጥ የልብስ ቤት ቁልፍ
✅ዋጋ 230ሺ ብር
✅የቤቱ ኪራይ 22000 ብር ነው
✅ቦታው ቤተል አደባባይ ታክሲ መውረጃው ጋር
☎️ 0911410771
👉 @Nagayta
🟡ሲያነቃቁን ለምን አንነቃም? ሙተን ይሆን እንዴ?
(አሌክስ አብርሃም)
💡ለመጀመሪያ ጊዜ self-help book የሚሏቸውን ሳነብ በጣም ነቅቸ ነበር! አስታውሳለሁ የ Rhonda Byrne ን The secret ሳነብ በጣም ከመንቃቴ የተነሳ ለስራ እጀን ከመጠቀም ይልቅ አዕምሮየን ለመጠቀም ወስኘ ነበር። ለምሳሌ መብራት አጥፍቸ ከመተኛት ተኝቸ መብራቱ ልክ እንቅልፍ ሲወስደኝ ይጠፋል ብየ ለራሴ እነግረዋለሁ፤ጧት ስነሳ እንደበራ ባገኘው አልደነቅም፣ ከእንቅልፌ ከመንቃቴ አንድ ደይቃ በፊት በራሱ ጊዜ እንደበራ አምናለሁ። የወሩ የመብራት ሂሳብ ግን የነገረኝ ሌላ ሆነ፤ ተው ወንድሜ በጣም አትንቃ አለኝ። እናም እያጠፋሁ መተኛት ጀመርኩ። ከ1890 ዓ/ም ጀምሮ መብራት ሀይል መብራት ያላጠፋበት ብቸኛ ወር ነበር። ስንነቃ አይወዱ😀
🕯ኦሾን ያነበቡ የኔ ዘመን ወጣቶች ደግሞ "ሐይማኖት ባህል ገለመሌ ከጫነብን ፍዘት ወጣን" አሉና በየመንገዱ ፀጉራቸውን በመፍተል መቆዘም ጀመሩ፤ ይህንንም "ውስጣዊ ንቃት" አሉት። ከአመታት በኋላ ሁሉም ጠበል ገብተው እየጮሁ ከንቃታቸው በጣም ነቁ። በቀን አምስቴ ኡዱ የሚያደርጉ፣ ለጁመዓ የሽቷቸው መዓዛ ከሞያሌ የሚጣራ ፣ እንዴት ያሉ ንፁህ ሙስሊም ወዳጆቸ ሳይቀሩ ጀዝበው ገላቸውን መታጠብ አቁመው ነበርኮ! ስንት ተቀርቶባቸው ተመለሱ። የዛን ሰሞን ወጣቱ ሁሉ ውስጣችን በራልን እያለ ስንት ጨለማ ተከናነበ። ራሳቸውን ያጠፉም ነበሩ። ኦሾና አለቃ ገብርሃና ተረታቸው እንጅ ኑሯቸው አያምርም።
🔦ይሄው በዚህኛው ዘመን ደግሞ አነቃቂወች እንደአሸን ፈሉና "ያሰብከውን ትሆናለህ፣ ነኝ በል፣ አለኝ በል፣ ደርሻለሁ በል፣ እችላለሁ በል፣ በሀሳብህ መኪና አስነሳ፣ አሉ፤ ወጣቱ የሀሳብ መኪና አስነሳ፤ በሀሳብ ሲጋልብ ራሱ ጋር ተጋጨ፣ ቤተሰቡ ጋር ተጋጨ፣ አገሩ ጋር ተጋጨ፣ፈጣሪው ጋር ተጋጨ ። ከሆነስ ሆነና ለምንድነው በዚህ ዘመን ይሄ ሀሁሉ አነቃቂ ንግግር ያላነቃን? የእውነት የሆነ ጊዜ ያነቃን ነበርኮ፣ እየቆየ ግን እንኳን ሊያነቃን ያስተኛን ጀመረ፤ እኮ ለምን?
📍የህክምና ባለሙያወች ከተሳሳትኩ አፉ ብለው ያርሙኝና በእነሱ ሙያ Drug tolerance የሚሉት ነገር አለ አሉ፤ በትክክል ከተረዳሁት ለሆነ ህመም የተሰጣችሁ መድሀኒት ከሆነ ጊዜ በኋላ በሽታችሁ ጋር ይግባቡና ፍሬንድ ይሆናሉ። በሽታው መድሃኒቱን ይላመደዋል።ጉቦ እንደበላ ደንብ አስከባሪ በሽታችሁ መንገድ ዳር ሲያሰጣችሁ መድሀኒቱ እንዳላየ ያልፈዋል። ለምሳሌ የእንቅልፍ ችግር ገጠማችሁና በሐኪማችሁ የእንቅልፍ ኪኒን ታዘዘላችሁ እንበል ፤ የመጀመሪያ ሰሞን ድብን ያለ እንቅልፍ ያስወስዳችኋል፤ እየቆየ ሰውነታችሁ ሲላመደው መድሀኒቱን ውጣችሁም ቁልጭ ቁልጭ ስትሉ ታነጋላችሁ። ወይ አይነቱን ወይ መጠኑን ባለሙያ ካልቀየረው በቃ ለውጥ የለም። አይ መጠኑን ራሴ እቀይረዋለሁ ብላችሁ ጨመር አድርጋችሁ ከወሰዳችሁ ደግሞ ትተኙ ይሆናል ግን እንደገና ላትነሱ ትችላላችሁ።
🔑ወደህይወት ስናመጣው እኛ ኢትዮጵያዊያን በአሁኑ ሰዓት ማንኛውንም ማነቃቂያ ከመላመድ አልፈን እንደዘፈን ሸምድደነው አብረን እየደገምነው ነው። ገና ፊቱን ስታዮት አብራችሁ "ብሮሮሮሮሮ" አትሉም?! ለዛ ነው ከነዋሪ መካሪና ዘማሪ የበዛው። የፈለገ ብንመከር ብንዘከር ብንሰበክ ብንወገዝ ወይ ፍንክች። አሁን ሞራል፣ ሐይማኖት፣ የአገርም ይሁን የሰው ፍቅር፣ ይሉኝታ ፣መማር ፣ የራስ ክብር ወዘተ አእምሯችን ተላምዷቸው ተራ ነገር ሁነውብናል።
✨የሞራል ተቋሞቻችን በሞራል ድሽቀት ከተራው ህዝብ ቀድመው ባፍጢማቸው ተተክለዋል፤ የትዳር ሰባኪወቹ ማግባትና መፍታት መድረክ ላይ እንደመውጣትና መውረድ ቀሏቸዋል፤እንደውም የጓዳቸውን ውድቀት እንደባንዲራ በአደባባይ እየሰቀሉ እዮልን ባይ ሆኑ። አሁን እንደህዝብ ሁለት ነገሮች ብቻ ናቸው የሚያነቁን ወይ (((ብር ማጣት))) አልያም (((ብር ማግኘት))) ይሄ የመጨረሻው ዶዝ(መጠን) ነው!
💎ሰው ክብሬ፣ ገመናየ ፣ማንነቴ የሚለውን ነገር ሁሉ ይዞ ገበያ ከወረደ ምን ይመልሰዋል?! ከዚህ በኋላስ? ምን ያነቃን ይሆን? ምክንያቱም በብር የሚመጣ ንቃት በአንዴ አይረካም፤ እንደአደንዛዢ ዕፅ በየቀኑ መጠኑን እየጨመሩ ካልወሰዱት መጨረሻ የለውም። መመለስም መቀጠልም የማንችልበት አውላላ ሜዳ ላይ የሚያስቀር መርገምት ነው!! ምን ላድርግ ቸገረኝ፣ የማደርገው አጣሁ ልሙት እንዴ ታዲያ በሚል ሰበብ ከሰውነት ድንበር ከምንርቅ በየግላችን "ይሄንኛው ነገሬ ለገበያ ከሚቀርብ ሞቴን እመርጣለሁ" የምንልለት የሆነ መስመር ልናሰምር ግድ ነው። ሰው ራሱ ወስኖ ያሰመረውን መስመር ከሞት በስተቀር ምን ያሻግረዋል?!
✍አሌክስ አብርሃም
ሸጋ ቅዳሚትን ተመኘን!❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
🛑 The Golden Rule
ኢየሱስ በወንጌሉ ያስተማረው፤ ነብዩ ሙሀመድም በአስተምህሮቱ ፣ ቻይናዊው ፈላስፋ ኮንፊሽየስም በፍልስፍናው የሚመክረው ተመሣሣይ ሃሳብ ያለው አባባል አለ፡፡ ይሄ አባባል በየትኛውም እምነት ተከታይ አማኝ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሃሳብ ነው፡፡ አይደለም እምነት ላለው ሰው ቀርቶ በኢአማኙም ዘንድ የሚደገፍና የሚከበር ሃሳብ ነው፡፡ ሕሊና ያለው ሰው ሁሉ በዚህ ሃሳብ ይስማማል፡፡ ይሄ አባባልም ወርቃማው ህግ ይባላል፡፡ ወርቃማነቱ በሁሉም ሠዎች ዘንድ ተቀባይነቱን መሠረት ያደረገ በመሆኑ ያገኘው ስያሜ ነው፡፡
ሕጉም እንዲህ ይላል፡-
🔑‹‹ለራስህ የማትፈልገውንና የማትመርጠውን ነገር ሌሎች ላይ አትጫን!›› ወይም ‹‹አንተ ላይ ሊሆንብህ የማትፈልገውን ነገር ሌሎች ላይ አታድርግ! (“Never impose on others what you would not choose for yourself.")
🔷ይሄን ሕግ ተለማምዶ መተግበር የቻለ ሠው በሌሎች ሰዎች ላይ ስቃይ፣ እንግልት፣ ማፈናቀል፣ ማሰደድ፣ ግድያ አይፈፅምም፡፡ የወገኖቹን፣ የብጤዎቹን ንብረታቸውንና ጥቅማቸውን፣ መብታቸውንና ነፃነታቸውን ያከብራል፡፡ ‹‹ነግ በእኔ›› በሚል ሌሎችን እንደራሱ ይወዳል፡፡
📍‹‹ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ›› የሚለው ታላቅ ሕግ ወርቃማውን ህግ አቅፎና ደግፎ ይዟል፡፡ ራሳችንን የምንወድበትን ያህል ከፍታ ሌሎችን መውደድ ከቻልን ዓለም ሠላማዊና በፍቅር የተሞላች ትሆናለች፡፡ እኛ ላይ ሊሆን የማንፈልገውን ሌሎች ላይ እንዲደርስባቸው አንመኝምም፣ አናደርግምም፡፡
ነገር ግን በገሃዱ ዓለም የሚታየው እውነታ ከዚህ በተቃራኒ የቆመ ነው፡፡ ትዕዛዙ ሳቢና በሁሉም ሠዎች ዘንድ የተወደደ ቢሆንም የሠው ልጅ ግን በተግባር እየኖረበት አይደለም፡፡ የአንዱ መጥፋት ለሌላው መልማት ዋና ምክንያት እስኪመስል ድረስ በተንኮል፣ በሴራ ፖለቲካ፣ በጥላቻ ጥልፍልፍ ደባ መጠፋፋት የዘመናችን ልማድ ከሆነ ሠነባብቷል፡፡ ራስን መውደድ ብቻ የተጋነነበትና ሌሎችን እንደምንም በመቁጠር ሰውነትን እስከመዘንጋት ተደርሷል፡፡ የሰው ልጅ በራሱ ወገን እንደአውሬ እየተባረረ ይጨፈጨፋል፣ አካሉ ይጎድላል፣ ይገደላል፡፡ በጣም ብዙ በደልና ስቃይ በገዛ ብጤው የሰው ልጅ ይደርስበታል፣ በወገኑ ይጨቆናል፡፡
💡ነገር ግን የታላቅነት ሚስጥር፣ የአዋቂነት ጥጉ ሌሎችን በነጻ መውደድ እንጂ ጥቅምና መብታቸውን ጨፍልቆ ክፋትና ጭካኔን፣ ተንኮልና ሴራ መስራት አይደለም፡፡ በዚህ ዘመን የፖለቲከኝነት ጣሪያው፣ የታዋቂነት ዙፋኑ ሴራ ጎንጉኖ ሌሎችን መጣል እንጂ በሀሳብ ልዩነት ተከባብሮና ተግባብቶ መኖር አይደለም፡፡ መቼም ቢሆን ታላቅነትና ሊቅነት ሌሎችን በማቀፍ እንጂ በመገፍተር የሚገለፅ አይሆንም፡፡
ለዚህ ጉዳይ የኮንፊሽየስን ምክር ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ አንድ ቀን ኮንፊሽየስ ለተማሪዎቹ ምክር በመስጠት ላይ ሣለ፤ አንዱ ተማሪ አቋረጠውና፡-
‹‹ታላቅ መሆን እፈልጋለሁና መንገዱን አሳየኝ›› አለው፡፡ ኮንፊሽየስ ሲመልስ፡-
‹‹ታላቅ የሚባል መንገድ የለም፤ ነገር ግን ሰው መንገዱን ታላቅ ያደርጋል›› አለ፡፡
💡እውነት ነው! ሰው መንገዱን ታላቅ የሚያደርገው ሰውነቱን በማረጋገጥ ነው፡፡ የመጀመሪያው ስኬት ሰውነትህን ፈትነህ፣ ስሜትህን ገርተህ ፣ ልቦናህን አቅንተህ ፣ ማስተዋልን ተግብረህ ሰው መሆንህን ማስመስከር ነው፡፡ ሰው መንገዱን ታላቅ የሚያደርገው ወደ ሰውነቱ መመለስ ሲችል ብቻ ነው፡፡ ሰው ሰውነቱን አጥብቆ መያዝ ከጀመረ የሌሎችን ሰውነት ያከብራል፡፡ የሌላው ሰውነት የተሠራውና የተዋቀረው እሱ በተሠራበት የሠውነት አካል መሆኑን ይረዳል፡፡ ሌላውም እንደእሱ ፍቃድ፣ ፍላጎት፣ መብትና ነፃነት እንዳለው ይገነዘባል፡፡ በዚህም በሌላው ላይ ክፉ አያደርግም፤ ነጻነቱን፣ መብቱን፣ ጥቅሙን፣ ወዘተ ያከብራል፡፡
ወዳጆች ሠብዓዊነት ማለት ሰውን ሁሉ ያለአድሎ ማፍቀር ነው፡፡ ዕውቀትም ሠውን ጠንቅቆ ማወቅ ነው፡፡ ማወቁ ለፍቅር ይዳርገዋል፡፡ ሰውን ያህል ድንቅ ፍጥረት የተረዳ ሰው በገዛ ወገኑ ላይ ክፉ አያደርግም፡፡ በራሱ ሊደርስበት የማይሻውን በሌሎች ላይ አያደርግም፡፡ ይሄን ህግ ሁላችንም ብንለማመደውና ብንተገብረው ሠላም፣ ፍቅር፣ ደስታ፣ መስማማት፣ መተቃቀፍ፣ መግባባት ሀብቶቻችን ይሆናሉ፡፡
📍እናም ሰው ሆይ አንተ ላይ የማትፈልገውን ሁሉ ሌሎች ላይ አታድርግ፡፡ ምን ስልጣን ይኑርህ፣ ምን ሊቅ ሁን፣ ምን ሃብት ይኑርህ፣ ምን ዝነኛ ሁን፣ ምን ዘመድ ይኑርህ፣ ምን ባለጊዜ ሁን፣ ምን ተከታይ ይኑርህ ሌሎችን በእጆችህ እቀፋቸው አንጂ አትገፍትራቸው፡፡ እጆችህን ለማቀፍ፣ ልብህን ለመውደድ፣ ዓይንህን ቅን ለማየት፣ አንደበትህን ለበጎ ቃላት ተጠቀምበት፡፡ ሕሊናህን ሌሎችን ለማፍቀር እንጂ በመጥላት አታባክነው!
✍እሸቱ ብሩ ይትባረክ
ያማረች ቅዳሜን ተመኘን ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthiohumanityBot
ዛሬ ቅዳሜ ነው የኛ ሸሞንሟና ሸሞንሟኒት😊
የyoakin Bekele Pachiን ጹሁፍ
ጀባ እንበላችሁ........
💫ዕድሜያቸው 30+ የሆኑ ሴቶች ይፀዱኛል:: በቃ ይመቹኛል:: እንደ ሰው በጥልቅ ማውራት የሚቻለው ከእነሱ ጋር ነው:: የምታወራው ይገባታል ፣ የምታወራህ ይገባሃል ደርባባ ናቸው ፣ ሞገስ አላቸው ፣ አንደበታቸው ቁጥብ ነው የሚፈልጉትን ያውቃሉ:: ወዝጋባና ጢባራም አይደሉም:: ለጓደኝነት እና ለቁምነገር ምርጥዬ ናቸው::
💡አንባቢ እና አድማጭ ከሆኑ ደግሞ ክትት ያለ የበሰለ አቋም አላቸው:: ስለፈለከው አጀንዳ ቀለል ብሎህ ታወራታለህ ስለ ባይደን ፣ ስለራሺያ ፣ ስለ ሶሪያ ፣ ስለ ያ ትውልድ ፣ ስለ ጀብሃ ስለ ሻቢያ ፣ ስለ አድዋ ፣ ስለ ማይጨው ፣ ስለ ካራማራ:: ስለ Netflix ፣ ስለ አባ ገብረ ኪዳን ስብከት ፣ ስለ ሄኖክ ኃይሌ ትምህርት ፣ ስለ ምህረተአብ ቴቄል ፣ ስለ ተቀዳሚ ሙፍቲ መጅሊስ ፣
🔆ስለ ዮናታን መልካም ወጣት ፣ ስለ እመቤቴ ማርያም መራር ሃዘን ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ፣ ስለ አምኖን ቅንዝራምነት ፣ ስለ ዮናታን እና ዳዊት ወዳጅነት ፣ ስለ ቶማስ ስኬፕቲካልነት ፣ ስለ ቮልቴር ቡና ሱስ ፣ ስለ ቫንጎህ ስዕልና ቺስታነት ፣ ስለ ካህሊል ጂብራን ብዕር ፣ ስለ አዳም ረታ ፣ ስለ ስብአት ገብረ እግዚአብሔር ጠሊቅነት ፣ ስለ ፌሚኒዝም ፣ ስለ ካቲታሊዝም ስለ ሙላቱ አስታጥቄ ጃዝ ፣ ስለ ግርማ በየነ ፣ ስለ Nina Simon ፣ ስለ ኤልያስ መልካ ቅንብር ታወራሃለች ፣ ታወራታለህ!
ፊቷን ጥላው ካገኘሃት ደግሞ ምነው ውሃ ጠፋ ፣ አብሲት ተበላሸ ፣ የቂቤ ዋጋ ጨመረ? ፣ ጎረቤት ለቅሶ አለ? ፣ በርበሬ አልተፈጨም? ምናምን ምናምን ትላታለህ!
⚡️መሸት ብሎ እንደ ኡመር ኻያም ወይን ከቀማመሰች ደግሞ ስለ አንገት ስር Cuddle ፣ ስለ For Play ታወራታለህ ፤ አፏን ሸፍና ወፍራም ሳቅ እየሳቀችና (አታሳፍረኝ አይነት) ጎንህን ጉሽም እያደረገች እሷም ታወራሃለች:: ሃሳብ ትለዋወጣለህ ፣ ትስቃለህ ፣ ትዝታ ትፈጥራለህ።
💡ፍቅራቸው የሚቆየው እንደ ወሲብ ለአምስት ደቂቃ ሳይሆን ለዘለአለም ነው:: ምክንያቱም ፍቅራቸውን የሚተክሉት በእግሮቻቸው መሀል ሳይሆን ከዛ ከፍ ብለው በልቦቻቸው ውስጥ ብሎም በአዕምሯቸው ውስጥ ነው:: ፍቅር የሚይዝህ ከአካላዊ አቋሟ ሳይሆን ከአስተሳሰቧ ፣ ከስብዕናዋ ፣ ከነፍሷ ነው::
ፍቅር ሞልቶ የሚፈስበት
ደርባባ ቅዳሜ ተመኘን!❤️
@Ethiohumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanitybot
🔥አልትራ ቦንዳ
⚫️የስራ መደቡ:- የሽያጭ ሰራተኛ
⚫️የስራ ሰአት:- 3:00-1:00
⚫️የስራ ቦታ:- ፒያሳ
⚫️ደሞዝ :- በስምምነት
⚫️የሽያጭ የስራ ልምድ ያላት እና ለፒያሳ አቅራቢያ ቦታ የሆነች
⚫️ፆታ:- ሴት
⚫ብዛት:- 1
✅መስፈርቱን የማያሟሉ ከሆነ አይደውሉ
በዚህ ሊያናግሩኝ ይችላሉ 👉@Nagayta
📍ተከታይህ ከህሊና ድህነት አያድንህም፤ ሃብት ንብረትህ አስተሳሰብህን አይቀርፅም፤ ወዳጆችህ ውስጣዊ ሰላም አይሰጡህም። በእውነት ካልተመራህ፣ በስረዓት ማሰብ ካልቻልክ፣ ጥያቄህን ካልመረጥክ፣ ተግባርህን ካልቆጠብክ ጉዞህን እንጂ መውደቂያህን አታስተውልም፤ ጭብጨባውን እንጂ ስህተትህን አትረዳም፤ ድጋፍህ እንጂ ጥፋትህ አይገባህም።
አዕምሮህን ክፍት ማድረግህ ሚዛናዊ ማንነት እንዲኖርህ ያደርግሃል። መስማት የሚፈልግ ሰው ሁሉ ይሰማህ ይሆናል፤ የሚወድህም ይከተልህ ይሆናል፤ የሚያምንብህም እንዲሁ ሊያሽቃብጥልህ ይችላል። እውነታ በሌለበት ግን ማንም ሰው እስከመጨረሻው አብሮህ እንደማይቆይ እወቅ። ጥልቁ ማንነትህ እንጂ የያዝከው ጊዜያዊ ንብረትና ዝና ነፃ አያወጣህም።
🔷ስትታወቅና ከፊት ስትሆን በእውቀት እና በጥበብ ካልተጓዝክ ብዙ ነገር ታበላሻለህ፡፡ በሰዎች ሙገሳና አድናቆት በሞቅታ መስመር ትስታለህ፡፡ ዛሬ ላይ ሶሻል ሚዲያ ላይ ብዙ ተከታይ ለማግኘት ካሰብክ ካንተ ሚጠበቀው ለገንዘብ ተገዝተህ ወጣ ያለ አቋም መያዝ፣ ሌላ ፆታን ማራከስ፣ ሌላውን ብሄር በመጥፎ ማውገዝ ነው። ያኔ ማን ይሆን እሱ! እያለ ሁሉም ካለበት ቦታ እየሮጠ ይመጣልሃል።
♦️ወዲህ ግን ቁምነገር የሚጽፉ ተከታያቸው ጥቂት ብቻ የሆኑ ጠንካራ የማህበረሰብ አንቂዎች አሉ። ግና ሰው ስለራሱ ነውርና እንከን ለመስማት የሸሸበት የረሳበት ዘመን ላይ ነው ያለነው። ከዕውቀት ከጥበብ ይልቅ ስላቅና ፣ ዘለፋን ያስበለጠበት ዘመን ላይ እንገኛለን። እስቲ ይሄን ሥልጣኔ ያለንበትን ነገር በጥሞና ተመልከቱ። የዘመንኛው ቁሳዊ ሥልጣኔ ግኝቶችን ልብ እንበል። ዓለም ላለባት ችግር መፍትሔ ከመሻት ይልቅ፤ ግኝቶቹ ራሳቸው ከምንም የከፋ ችግር እየሆኑ እንዲያውም የቀደሙትን ችግሮች እስከማስረሳት ደርሰዋል። ግኝቶቹ ከሚያስከትሉት ጠንቅ ይልቅ በግኝቶቹ የሚገኘው ኃይል ገንዘብና ዝና ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶታል ።
🔑እናም ወዳጄ ቁምነገሩን ስንቅ አርግ
ዋናው ጉዳይ የሰው ክትትል ወይም ጭብጨባ አይደለም፤ ከፈጠረህ አምላክ አንፃር ትክክል ከሆንክ የፍጡራን ክትትል አያሳስብህ። ፊት መሆን በሚችል ስብዕና ከፊት ቁም፣ ጊዜህን አፍ በመካፈት አትብላው፣ አለምን የገዙ ፣ በአስተሳሰብ ሊቅነታቸው አርአያነታቸውን የምንከተላቸው ፈላስፎች ፣ ተመራማሪዎች፣ የህይወት መንገድ እያመቻቹልን እነሆ በዚህ ተጓዙ፣ ያኛው የብዝኋኑ መንገድ አሜኬላና እንቅፋት አለው። የዓለም ምስጢራት የሚገለጡት በስውር መስመር ነው እያሉ አመላክተውናል።
ለሰው ልጅ በተሰጠው ወንበር ላይ ቁጭ ብለን ሰው የመሆናችንን፣ ሰው የመባላችንን ልዩ ገፀ-በረከት የሚያጎናፅፉን ሀብቶቻችን እንከተል።
💡ህሊና ይፈርዳል፣ የእራሱን ብይንም ይሰጣል። ስለተጨበጨበልህ እውነት ተናግረሃል ማለት አይደለም፤ ተቃውሞ ስለበዛብህም ውሸት ተናግረሃል ማለት አይደለም። ለሁሉም ሰው የተሰጠው ህሊና የመንገድህ መሪ፣ የንግግርህ ቆንጣጭ፣ የተግባርህ አራሚ ነው። ለመፍረድ አትቸኩል፤ ለንግግር አትጣደፍ፤ እውነታውን በጥላቻህ አትሸፍን፤ በእውቅናህ ሰላምን አትግፋ፤ በተሰሚነትህ ክፍተትን አታስፋ። ውሸት የአብሮነት ምክንያት ሆኖ አያውቅም፤ ተንኮል ፍቅርን አንግሶ አያውቅም፤ ጥላቻም የሰላምን በር ከፍቶ አያውቅም።
♦️ሁሉን ያገኘህው በፈጣሪህ ሞገስ እንጂ አንተ አምጥተህው አይደለምና ለበጎ ተጠቀመው። እውነትን በፍቅር ያዝ፣ ለሰላም ግድ ይኑርህ፣ ለመከባበርም ቅድሚያ ስጥ። ትዕቢትን፣ ጉራን፣ ጀብደኝነትን፣ ጥቅመኝነትን ከውስጥህ አስወግደው የመልካምነትን ስብዕና ገንባ፣ ጥሩ መሪ ፣ ጥሩ ተከታይም ሁን።
ደርበብ ያለች ቅዳሚትን ተመኘን 😉
@Ethiohumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanitybot
📍ሰው አገሩ ሰፈሩ ነው ህዝቦቼ እያለ ያደገው ጎረቤቶቹን ነው ።ማንነቱ የተጎነጎነው ከጎረቤቶች ማንነት እየተውጣጣ ጭምር ነው። ከሰፈር አግብቶ መውጣት በስራ ሌላ ቦታ መሄድ እና ያደክበት ስፍራ ሲፈርስ ልዩነቱ የትዬለሌ ነው ።
እሚፈርሰው ሰፈር ውስጥ ትዝታ ልጅነት ታሪክ ተጠቅልሏል ። ማህበራዊ ህይወት ያቆመን ህዝቦች ማህበራዊ ህይወታችን ሲበተን ማየት ድባቴው ካቅም በላይ ነው።
ምን አልባት እኛ ያለን የሆነ ሰው ህልሙ ነው!
ምን አልባት እኛ ያለን የሆነ ሰው ፀሎቱ ነው !
ምን አልባት እኛ ያለፈን የማይጠቅመን ነው!
ምን አልባት ያሳመመን ሊያስተምረን ነው!
ምን አልባት የሆንነው የሆኑትን እንድንረዳ ነው !
ምን አልባት የተበለሻሸው እንድንቀያይረው ነው!
ምን አልባት አማራጭ ያጣነው አማራጭ እንድናመጣ ነው !
"እኛ በህይወት ካለን ሌላ ካዛንቺስ እንገነባለን ፣ መኖር እስከነ-ትግሉ እስከነ ፈተናው ደስ ይላል"።
✍አዳህኖም ምትኩ
የካዛንቺስ ውብ ፈርጥ አለማየሁ ገላጋይ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
@EthioHumanityBot