zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

311892

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የዐማራ ፋኖ በወሎ… የዛሬ ውሎ

"…የብራኑ ጁላ ጦር በተደጋጋሚ በእግረኛ ሠራዊቱ ወደ ቃሊም ለመግባት ሙከራ ቢያደርግም ሠራዊቱን ከማስጨረስና ከማስመራክ በቀር ያገኘው አንዳችም ትርፍ እንደሌለው ያወቀው ሰው በላው መከላከያ ተብዬ በመጨረሻም ወልዲያ ተቀምጦ ወደ ቃሊም ከመድፍ ጀምሮ አለኝ ያለውን ከባድ መሳሪያ ሁሉ ያገኘውን ያግኝ በማለት ፍጹም ከጦርነት ሕግ ባፈነገጠ መልኩ ሕዝቡም ቢሆን ያው ፋኖ ነው በሚል ሒሳብ የመድፍ አረሩን እንደ ዶፍ ዝናብ ሲያዘንበው ውሏል። ይሄንን ተከትሎም።

"…አንድ ሰው ሲሞት በጣም ብዙ ሰዎች ቆስለዋል። እጅግ በጣም ብዙ ከብቶች፣ ፍየሎች እና የተለያዩ እንስሳቶችም ሞተዋል። ብዙ መኖሪያ ቤቶች በከባድ መሳሪያ ተመትተው ፈራርሰዋል። "እስራኤል በጋዛ ፍልስጤም ላይ እንደወሰደችው ዓይነት የማውደም እርምጃ የኦሮሞ ብልጽግናም ውጤቱ ምንም ይሁንምን በእስራኤል መንገድ ሄደን የዐማራን ሕዝብ እንደ ጋዛ ማውደም ነው ያለብን እያሉ ነው ተብሏል። ሕዝቡን እግዚአብሔር ጠብቆት ነው እንጂ እንደዛሬው ውሎ እና እንደ አገዛዙ እሳቤ የቃሊምን ሕዝብ የሚያልቀው ዘሬ ነበር ይላሉ ሲተኮስ የዋለውን እሳት ሲያዩ የዋሉ የዓይን ምስክሮች።

• በመጨረሻም ከፋኖ ምት ከሞት የተረፉት እና ጥይት የጨረሱት የምርኮኛው የጁላ አረመኔ ሠራዊት እንዲህ እንደከፍት በዐማራ ፋኖ ይነዳል።

"…የቀን ጉዳይ ነው ዐማራ ብቻውን ፈርሶ አይቀርም። መዝግብልኝ። የዐማራ በቀሉ፣ ቂሙ እየጨመረ ነው የመጣው። ሌላው ግን ጥጋብ፣ ትእቢት ላይ ስለሆነ አይታወቀውም። ይሄ ጥጋብ አንድ ቀን ይገለበጣል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③ ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …ሄደ። በወሎም የወሎ ፋኖዎችን አግኝቶ ገምግሟል። በመጨረሻም ወደ ሸዋ በመምጣት በራሳ የነበሩትን የአሰግድ እና የመከታውን ፋኖ ጎብኝቷል። ገምግሟል። በነገራችን ላይ በወቅቱ አሰግድና መከታው አባትና ልጅ ሆነው አንድላይ ነበሩ።

"…እስክንድር ነጋ በአራቱም የዐማራ ግዛት የነበረውን የዐማራ ፋኖ አደረጃጀት ከገመገመ በኋላ ነው በቀጥታ ወደ አሜሪካ የበረረው። በአሜሪካም ለጥቂት ቀናት ከሚስቱም ጋር፣ በዚያ ካሉት ጓደኞቹም ጋር ሳይገናኝ የት እንደከረመ ሳይታወቅ ብቅ በማለት ከእነዚያው ከግንቦቴዎች ጋር መታየት ጀመረ። ለገጽታ ግንባታም አቶ ሙሉጌታንና አቶ ኤርሚያስን አስከትሎ በኢትዮጵያ ኤንባሲ ፊት ለፊት ለሦስት ሆነው መግለጫ ሰጥተው ሲያበቁ እስኬው በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ። እስክንድር አሜሪካ በነበረ ጊዜ የዐማራ ፋኖ ቀድሞ ተደራጅቶ ቦታ ቦታውን በመያዝ ትግሉን ጀምሯል። እስክንድር አሜሪካ በቆየ ጊዜ ለአሜሪካ መንግሥት የፋኖን አደረጃጀት፣ የሰው ኃይልና አቅም ሪፖርት ሳያቀርብ እንዳልቀረ የሚጠረጥሩ አካላትም አሉ። የአሜሪካ መንግሥትም ለኢትዮጵያው አገዛዝ ለእስክንድር እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥር ሳያስገድዱት እንዳልቀረም ነው የሚነገረው። ለዚህ ነው እስክንድር አሜሪካ ሆኖ ለብዙ ሰው ከአሜሪካ እንደተመለሰ ወደ ትጥቅ ትግል እንደሚገባ ሲናገር አይፈራ የነበረው። እስክንድር ጫካ እገባለሁ እያለ እየሰማ አቢይ አሕመድም ምንም ዓይነት እንቅፋት ሳይፈጥርበት የድራማው አካል ሆኖ እስኬው ፈነነ።

"…በእስክንድር ግምገማ መሠረት ጎንደር መቀመጥን አልመረጠም። ሪሶርሱ ደካማ ነው ብሎ ነው የገመገመው። ከኤንባሲም የራቀ ነው። ከአሜሪካም፣ ከእንግሊዝ ኤምባሲዎች ርቆ መቆየትን አልፈለገም የሚሉም አሉ። ወሎ ቤተ ዐምሓራም አስተማማኝ አልሆነለትም። ጎጃም ጠንካራ ነው። አደረጃጀቱ ያስፈራል። የተማረም ሰው ይበዛበታል። እንደ ሕዝብም ነው የጎጃም እንቅስቃሴ። እናም እስኬው በጎጃም መሆኑንም እንብዛም እንደማያዛልቀው ዐውቋል። ስለዚህ ምርጫው ሸዋ ሆነ። ሸዋ ለአሜሪካና ለእንግሊዝ ኤምባሲዎች ቅርብ ነው። ሸዋ ላይ የፋኖ አደረጃጀት በወቅቱ እጅግ ደካማ ስለነበር፣ ብዙ የተማረ የሰው ኃይልም የሸዋ ፋኖን በወቅቱ ስላልተቀላቀለ፣ አቶ አሰግድና አቶ መከታውም በጋራ አንድላይ ስለነበሩ፣ የራሳና የይፋት ተኳሽ ፋኖዎች እንጂ ምሑራኑ በሙሉ እንደዛሬው በሸዋ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እያደረጉ ስላልነበር እስክንድር ሸዋን መርጦ ሸዋ ገባ። ሸዋ ከገባ በኋላ ደራሲና ጋዜጠኛ በውትድርናውም ዓለም ኮሎኔል የነበረውን አቶ አሰግድንና ማይሙን መከታውን እርስ በርስ አጋጭቶ አለያየ። አለያይቶም ሸዋን ከሁለት ቦታ ከፍሎ መከታውን ይዞ ተገንጥሎ ሄደ። በዚያውም ከአሜሪካ ማን እንደላከው ባይታወቅም የፋኖን አደረጃጀት ለሁለት መክፈሉን አሀዱ ብሎ በሸዋ ፋኖ ላይ ጀመረ። የሸዋ ፋኖን እንደ አሜባ ከከፈለ በኋላ ወደ ጎጃም እንዲገባ አጋጣሚውን አገዛዙ አመቻቸለት። ዘመነ ካሤ ታሠረ፣ እነ መስከረምም ታሠሩ፣ የጎጃም ፋኖን ብአዴን በታተነው። በዚህ ጊዜ እስክንድር ነጋ ጎጃም ምድር ላይ በሸነና ይል ጀመር። በነፃነት አንዴ ምሥራቅ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ምዕራብ ጎጃም ሆኖ ይንሸራሸርበት ጀመር። በአንድ ወገን ጎጃሜ ስለሆነ ሜዳው ተመቸው። አቢይ አሕመድ ዘመነ ካሤን አሥሮ እስክንድርን የ3 ወር የእግር መንገዱን በግማሽ ቀን እያሳጠረለት በጎጃም ምድር እንዲምነሸነሽ አደረገው። እንዲያውም በደንብ ለማጀገን ሲልም ደንበጫ ላይ በቁጥጥር ስር ያዋለውን እስክንድር ነጋን ለመንግሥቱ አሸባሪ የተባለን አደገኛ ሰው እስከ ደጀን ከተማ ድረስ አዙሮት፣ በመላው ጎጃም ብቻ ሳይሆን በመላው ዐማራ ጀግና ጀግና አጫውቶት፣ በብቸና በሞጣ አዙረው ባህርዳር አስገብተው፣ በሕዝብ ትግል እንደተፈታ አስመስለው በመታወቂያ ዋስ ለቀውት ተመለስና ጫካ ገብተህ ውጋኝ ብለውም ለቀቁት። ስንታየሁን በካቴና አስሮ ከባህርዳር አዲስ አበባ በአውሮጵላን ያመጣው አገዛዙ የስንታየሁን አለቃ አጀግኖ መልሶ ወደ ጫካ ላከው። በእውነት በእስክንድር ነጋ ጉዳይ እንደ አቢይ አሕመድ ጻድቅ ከወዴት ይገኛል? እስኬውም ምኑ ሞኝ ነው ወዲያው ጎንደር በመሄድ ከዶር ወንደሰን ጋር በመገናኘት ተመለሰ። ዶ/ር ወንደሰንም ይኸው እስክንድርን አግኝቶት ከተመለሰ በኋላ ከርቸሌ ወረደ። በዚያውም ቀልጦ ቀረ።

"…እስክንድር ነጋ ዘመነ በታሰረበት ጎጃም እንዳሻው ሆነ። ዘመነ ሲፈታ ግን እስክንድር በግማሽ ቀን የእግር ጉዞ በተአምር ሸዋ ገባ ተባለ። እስክንድር ውሎ ያደረበት ቤት እስክንድር ከሄደ በኋላ በድሮን ይመታል። እስክንድርን የሚከተል ባጃጅ ተለይቶ ይመታል። እስክንድር እና መከታው ተሰብስበው ከሕዝብ ጋር የተመካከሩበት አዳራሽ፣ ትምህርት ቤት እስክንድር ዞር ካለ በድሮን ይመታል። ደብረ ኤልያስ የስላሴ ገዳም እስክንድር አለበት ተብሎ እንዴት እንደወደመ የምታውቁት እውነት ነው። አዎ እስክንድር እንዲያ ነው። በጎጃም አብሮት የታሰረው ልጅ ተገድሏል። እስክንድር ግን አለ። በጎጃም ግንባሩን ለእስክንድር ያደራጀው ልጅ ወሎ ስብሰባ ውሎ ሲመለስ ብቻውን በድሮን ተመትቶ ሞቷል። እስክንድር ለዚህ ልጅ ነፍስ ይማር እንኳ አላለም። እስኬው ከደንበጫ ሸዋ ለበረታ መንገደኛ ሁለት ወር፣ ወንዙን ለመሻገርም በጋ ተጠብቆ የሚፈጀውን መንገድ በግማሽ ቀን ሸዋ እየገባ አስደመመን። በአደባባይ መግለጫ እየሰጠ፣ ከራሳ ይፋትም በእግሩ እየተመላለሰ ምንም አይሆን። ይሄ የጸሎቱ ውጤት ነው አይደል?

"…ከዘመነ መፈታት በኋላ በጎጃም ችግርም ዕድልም ተፈጠረ። ሁለት ቦታ ተከፍሎ የነበረው የጎጃም ዐማራ ፋኖ ወደ አንድነት መጣ። በዝናቡ እና በዘመነ ይመሩ የነበሩ አደረጃጀቶችም ወደ አንድነት መጡ። እስክንድር በዝናቡ ላይ ኢንቨስት አድርጎ የነበረ ቢሆንም ጎጃሜዎቹ ተፋጭተው አንድ ሆኑ። ይሄ አንድነት ለእስክንድር ነጋና ለቡድኑ አልተዋጠለትም። ስለዚህ ትግል አቋርጦ የራሱን ኑሮ ይኖር የነበረን ማስረሻ ሰጤ የተባለን የእነ ዘመነን ጓደኛ ገንጥለው አመጡ። ኮሎኔል ጌታሁንንም የራሱ አደረገ። ጎጃም ግን ሁለቱንም ወደ መስመር ግቡ ብሎ አዘዘ። በአንድ ቤት አንድ አባወራ ብቻ ብሎ ዐወጀ። ኮሎኔሉ ተዋግቶ ተሸነፈ። ማስረሻ ወደ ወሎ ፈረጠጠ። ጎጃም ብቻውን ወጥ አቋም ይዞ አመለጠ። የጎጃም ሲከሽፍ ጎንደርን ሦስት ቦታ፣ ወሎን ሁለት ቦታ ከፈለ ታናሹ እስክንድር። የኦሮሙማው አገዛዝ ሊያደርግ የማይችለውን ነገር ነው እስክንድር ያሳካው። ፋኖ መሃል ሽብልቅ በመክተት፣ ፋኖ እርስ በእርሱ እንዳይተማመን በማድረግ፣ ፋኖ ተዋጊ ኃይል ነው። ፖለቲካውን ይዘን ሥልጣን መያዝ ያለብን እኛ ጋዜጠኞቹ ነን በማለት የዐማራ ፋኖን አመሰው። ዳያስጶራው ባዋጣው ዶላር እስክንድር ነጋ ከፋፍሎት ቁጭ አደረገው።

"…በነገው ዕለት ይቀጥላል…

• በዐማራ ትግል ላይ ደንቃራ የሆኑትን ሾተላዮች በሙሉ በጋራ ሆነን በእውነት ሰፌድ እናበጥራቸው…!

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

•••

ሻሎም.!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ህዳር 3/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

• ሃሎ…አበበ በለው ነኝ።
~ ሃሎ አቤ ሰላም ነው?
• ሰላም ነኝ እንዴት ናችሁ?
~ አለን፣ አለን እግዚአብሔር ይመስገን አቤ። ምን እንታዘዝ?
• ኧረ ይሄን ነገር እንዴት እያያችሁት ነው?
~ የቱን ነገር አቤ…?
• ይሄ የዘመድኩንን አካሄድ፣ እጅግ አደገኛ አካሄድ እኮ ነው እየሄደ ያለው። ፋኖዎች መሬት ላይ መግለጫ እያወጡበት ነው። ባለፈው ጎንደር አሁን ደግሞ ሸዋ እነ መከታው መግለጫ አውጥተውበታል። በጎጃምም፣ በወሎም እንዲሁ መግለጫ ሊያወጡበት ነው። እኛም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የዐማራ ማኅበራት በዚህ ሰውዬ ላይ ዝምታችን እስከመቼ ነው? በቃ ዝም ብለን እያየነው ያፈራርሰን? ይሄ ለእኛ ትልቅ ውርደት ነው። እናም የእናንተም ማኅበር፣ የሌሎቹም ማኅበራት ሰብሰብ ብለን መግለጫ እናውጣበት። እኛ እንደ MDV በዋ ዐማራ በኩል መግለጫ ለማውጣት በዝግጅት ላይ ነን። እናም አስቡበት። እንወስን። በአቶ ዘመድኩን እና በመረጃ ቴሌቭዥን ላይ አቋም ልንይዝ ይገባል ይልልኛላ አቤ በለው በአንዳንድ የዐማራ ማኅበራት መሪዎች ስልክ ላይ እየደወለ። ይሄ ማለት ራሱ በለኮሰው እሳት ውስጥ ሌሎች እንዲገቡ እና አብረውት እንዲቃጠሉ ፈልጎ እያስጨነቃቸው ነው ማለት ነው። በእኔ በመረጃ ቲቪና፣ በኤልያስ መካከል እንዲገቡና እኔን ከአየር ላይ እንዲያስወርዱ ነው ፍላጎቱ። አበበም ሆነ ሌሎች ያልገባቸው ግን መረጃ ቲቪ የእኔም ላብ የፈሰሰበት፣ የእሁድ ምሽት አየሩ የግሌ የሆነ፣ ኤልያስ ክፍሌም ሆኑ ሌሎች ጣልቃ የማይገቡብኝ፣ በምሠራው ሥራ ሓላፊነትን ከተጠያቂነት ጋር አስተባብሬ በመያዝ አስሬ ለክቼ አንዴ የምቆርጥ መሆኑን ነው። ቅሬታ ያለው ወደ ኤልያስ ሳይሆን የቅሬታ ደብዳቤውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽጎ ወደ እኔ ነው ማቅረብ ያለበት። ኤልያስ ምንአገባው ስለእኔ ፕሮግራም? እነ አበበ፣ እነ ሀብታሙ መረጃ ቴቪ ላይ በነበሩ ጊዜ ኤልያስ እነሱ በሚሠሩት ፕሮግራም እንደማያገባው ሁሉ እኔም በምሠራው ፕሮግራም አያገባውም። ከምኔው ረሱት ግን?

"…አበበ በለውን ከሌሎች የዐማራ ተወላጆች፣ አክቲቪስቶች፣ አርቲስቶች፣ ኮሜዲያኖች፣ ጋዜጠኞች በተለየ መልኩ እንዲህ ያንገበገበው ምን ቢሆን ነው? የሚል ጠያቂ አይጠፋም። አበበ መሀይም ስለሆነ ነው እንጂ ሌሎቹ ጮጋ ብለው ተኩሱንም፣ ቅዝምዝሙንም ለጥ ብለው ሲያሳልፉ እሱ እንዲህ የሚያንቀዠቅዠው ተንኮሉ ነው። እስከዛሬ በዐማራ ትግልና ታጋዮች ላይ የሠራው ግፍ ነው። አበበ እኔን መጣላት የጀመረው እኔ ግንባሩ የተባለውን የእስክንድር የዶላር ማለቢያ ማሽን ግንባሩን ብዬ እንደ ጎልያድ ካጋደምኩት ጊዜ ጀምሮ ነው። እኔ ዘመዴ በገንባሩ ላይ ጥያቄ ሳነሣም ጥያቄውን የጠየቅኩት የግንባሩን የውጭ አስተባበሪ ሻለቃ ዳዊትን እና የግንባሩ ሊቀመንበር የሆነውን እስክንድር ነጋን ነው። መቼም ትልቅ ሰው ሁልጊዜ ትልቅ ነው። ቀለም የዘለቀው፣ ፊደል የቆጠረ፣ የተማረ ሰው አንዳንዴ ጥሩ ነው፣ የሥራ ልምድ፣ ዕድሜ፣ መሰልጠን ተጨምሮበት እንደ አንድ ግለሰብ ግንባሩን በተመለከተ ላነሣሁት ጥያቄ በአስቸኳይ ምላሽ የሰጡኝ ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ናቸው። እስክንድር ነጋ በጋዜጠኛ ጌጥዬ በኩል ለኤልያስ ክፍሌ ደውሎ ምላሽ እሰጣለሁ ካስባለ በኋላ ትንሽ ሰው ሁሌ ትንሽ ነውና ትንሹ እስክንድር በዚያው እልም ብሎ ጠፍቷል። እኔም ሻለቃ ዳዊትን አመስግኜ፣ እስክንደር ነጋን ግን እሞግተው ዘንድ ወስኜ ጥያቄዎቼን ይዤ ወደፊት ቀጠልኩ።

"…ጭራሽ የሚልዮን ዶላሩ ዶሴ ሳይዘጋ ሀብታሙ አያሌው እና አበበ በለው ወደ አዳራሽ መግቢያ ብቻ የሆነ መቶ ዶላሮች የተቆረጡበት ድል ያለ ዝግጅት በዋሽንግተን ከተማ አዘጋጅተው፣ ያንኑ ላሜ ቦራ የዐማራን ሕዝብ ወደ አዳራሹ ጠርተው የዐማራ ሕዝባዊ ሠራዊት የሚልም ማቋቋማቸውን ይፋ አደረጉ። የዚህ ድርጅት መቋቋምን ተከትሎ አሁንም የዚህ ድርጅት መሪ የሆኑት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና በውጪው ዓለም ደግሞ ሻለቃ ዳዊት ናቸው ተብሎ ታወጀ። የገንዘብ ያዡ ደግሞ ያው የማይቀየረው የእስክንድር ካዝና ተብሎ የሚገለፀው ዶር አምሳሉ አስናቀ መሆኑ ተነግሮ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶችም በድጋሚ ያው የፈረደበትን ዐማራን እንደለመዱት ዶላር ሊግጡት ጥርሳቸውን አሹለው፣ ጥፍራቸውንም ሞርደው ተነሡ። እኔም መልሼ ቀላል ጥያቄ ጠየቅኩ። ሲጀመር ግንባሩ መፍሩሱን ሳትነግሩን እንዴት ሠራዊቱ ብላችሁ ተከሰታችሁ? የግምባሩ መሪም ሻለቃ፣ አሁንም የሠራዊቱ መሪ ሻለቃ ይሄ እንዴት ይሆናል? የበፊቱ ገንዘብ ሳይወራረድ፣ ኦዲት ሳይደረግ፣ እንዴት አሁን ደግሞ ሌላ ገንዘብ ትሰበስባላችሁ ብዬ ጥያቄ አቀረብኩ። ለዚህም ጥያቄዬ ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ አሁንም ወዲያው ነው ፈጣን ምላሻቸውን የሰጡኝ። "ዘመዴ እኔ በአዲሱ ሠራዊቱ በሚባለው ውስጥ የለሁበትም። እንዲያውም ሠራዊቱ የሚባለው ሲመሠረት አበበ በለው እንዳትመጣ ብሎ ነው የከለከለኝ። ለገቢ ማሰባሰቢያ ብለው ባዘጋጁት ፖስተር ላይ ፎቶዬን መለጠፋቸውም አግባብ አይደለም ብዬ ተቃውሜአለሁ በማለት አሁንም ታላቅነታቸውን በሚያስመሰክር መልኩ ምላሻቸውን ሳይንቁኝ ሰጡኝ። እኔም የሻለቃን ምላሽ ለሕዝብ ይፋ አድርጌ ወደፊት ቀጠልኩ።

"…ዓሣ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል እንዲሉ ወደ ኋላ ሄጄ የእስክንድርን የኋላ ታሪክ ፋይሎች ከመዝገብ ቤት አውጥቼ መመርመር፣ ማገላበጥም ጀመርኩ። ታላቁ ያስባለው ነገር ምንድነው? እስክንድር እስከዛሬ ስንት ድርጅት መስርቶ አፈረሰ? የእስክንድር ስኬት ተብሎ የሚጠቀስ፣ የሚቆጠር ተግባሩ ምንድነው? በማለት ምርመራዬን ጀመርኩ። እናም በምርመራዬ እኔ ብቻ የደረስኩበትን ውጤት አገኘሁ። በውጤቱም፣ በግኝቴም መሠረት ከገንዘብ እና ድርጅት ፈጥሮ ከማፍረስ ጋር በተያያዘ የእስክንድር ነጋን እልል የተባለለት አፍራሽ፣ ሾተላይ፣ የተጨበጨበለት ዘራፊ፣ ሰርተፊኬት ያለው አጭበርባሪ መሆኑን የሚያረጋግጡ ማሳያዎችን አገኘሁ። እስክንድር ነጋ ግንባሩ ጋር ሲደርስ እኔን ጣልቃ አስገብቶ በይፋ እግዚአብሔር ሰብሮ አጋለጠው እንጂ የኋላ ታሪኩ በሙሉ የሚያሳያው ትኩስ፣ አማላይ የሆነ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማና በኢትዮጵያ ስም የተጠቀለለ አጀንዳ በመፍጠር የዐማራ ዳያስጶራን ሙልጩን ሲያወጣ የኖረ ዘራፊ መሆኑን ደረስኩበት። እስክንድር ለዚህ ዘረፋው ብቻውን ሳይሆን በአሜሪካም የዘረፋው ተባባሪ ወኪሎች እንዳሉትም አረጋገጥኩ። ከእነዚህ ገንዘብ አሰባሳቢዎች መሃልም ባለቤቱ ወሮ ሠርካለም ፋሲል እና አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ፣ የቅንጅቱ አቶ መስፍን አማን፣ እንዲሁም እነ አቶ ገለታው ዘለቀ እና አቶ ሙልጌታ የማይቀየረው ዶር አምሳሉ አስናቀንም አገኘኋቸው። ከሴቶች ያው ያለችው ሕይወት ናት።

"…በዚህ የገንዘብ ማሰባሰብ የተደራጀ የማፍያ ሥራ ዘረፋ ውስጥ አበበ በለው ከጀርባ ሆኖ በዙም ስብሰባ ወቅት ነጭ ላብ እስኪፈሰው ድረስ ያስተባብር ነበር። ቪድዮውም አለ። ከግንቦት 7 መፍረስና መክሰም በኋላ የዳያስጶራውን ኪስ ለማጠብ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኖ የተገኘው የአዲስ አበባ ጉዳይ ስለነበረ ለዚህ አጀንዳ ብቁ ነው የተባለው እስክንድር ነጋ መጀመሪያ ባላደራው የሚባል የገንዘብ ማለቢያ ድርጅት መሠረቱ። ቀደም ሲል እስክንድር ዘብጥያ እያለ በእስክንድር ፎቶ ሸቅሎ ገንዘቡን የበሉት ግንቦት 7ቶች ስለነበሩ አሁን ከግንቦት 7 መክሰም በኋላ በግንቦት 7 የዘረፋ ወቅት ከፍተኛ የዘረፋ ልምድ ያላቸው ዘራፊዎች ሙሉ ለሙሉ ተሰብስበው በእስክንድር ነጋ እግር ስር ተኮለኮሉ።…👇① ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…አሁንስ ምሳር ደግሞ በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።” ሉቃ 3፥9

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የስብሰባ ጥሪ ነው…❗️

• እኔ ገብቻለሁ፣ እናንተም ግቡ። ገንዘቡን የት አደረሳችሁ ብላችሁ ጥያቄም ጠይቁ።

"…በቦስተን እና አካባቢው ለምትገኙ የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አሕፋድ) የእስክንድር ነጋ አባላት እና ደጋፊዎች በሙሉ የዐማራው የዘር ጭፍጨፋ ይቁም በሚል ሊካሄድ ስለታሰበው የተቃውሞ ሰልፍ ለመወያየት ዛሬ ማክሰኞ 11/12/2024 በ 7:00 PM በዙም ስብሰባ ስለሚኖረን ከታች የተጠቀሰውን የዙም መግቢያ ሊንክ ወይም ስልክ ቁጥር በመጠቀም እንድትገኙሉን ስንል በአክብሮት ጠርተኖታል።

ድል ለፋኖ !
መነሻችን የአማራ ሕልውና መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት !

በስልክ ለመግባት 
Phone Number: 646 558 8656
Meeting ID: 856 3553 4107
Passcode: 039519

Amhara Fano is inviting you to a scheduled Zoom meeting.

Topic: Stop Amhara Genocide
Time: Nov 12, 2024 07:00 PM Eastern Time (US and Canada)

Join Zoom Meeting
https://us06web.zoom.us/j/85635534107?pwd=LtpQqcYB5NiBXKo9yaRJhiDny2Ceuz.1

Meeting ID: 856 3553 4107
Passcode: 039519

---

One tap mobile
+13052241968,,85635534107#,,,,*039519# US
+13092053325,,85635534107#,,,,*039519# US

---

Dial by your location
* +1 305 224 1968 US
* +1 309 205 3325 US

Meeting ID: 856 3553 4107
Passcode: 039519

Find your local number: https://us06web.zoom.us/u/kdUbYSdW1A

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…በርእሰ አንቀጻችን ላይ አስተያየት መስጠታችሁ እንደተጠበቀ ነው። ነገር ግን እኔ ደግሞ ተወት አድርጌው የነበረውን የቲክቶክ መንደሬን ሞቅ ለማድረግ፣ በዚያውም ጥቃቅን ቀበሮቹን ድባቅ ለመምታት ስል እንደ ቲክቶክ አንበሳ እያገሳሁ ወደ ቲክቶክ መንደራችን እየመጣሁ ነኝና እናንተም ከያላችሁበት ወደ መንደራችን በመሄድ አበባና ኮፍያ በማያዝ ገባ ገባ ብላችሁ እንደትጠብቁኝ እኔ ፊልድ ማረሻው ዘመዴ አዝዤአችኋለሁ።

• ሰምታችኋል አይደል…?

zemedkun.b" rel="nofollow">http://tiktok.com/@zemedkun.b

"…ኣ… ላችሁ…  አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከመጀመሪያው ጀምሮ እስክንድርን ተጠግቶ እንደ አዝማሪ እስክስ እያለ ሆዱን፣ ቀፈቱን ሲሞላ የነበረው ከርሶ አበበ በለው እንዴት ሰርካለም ፋሲል ስሟን ዘመድኩን ያነሣዋል ብሎ ሲበጠረቅ የነበረው። እንዴት ገንዘቡን ሲሰበስቡ እንደነበር በቪድዮ ይዤ እቀርባለሁ።

"…አሁን የዐማራ የወይን እርሻ አብቧል። አጥሩም ጠባብቆ ስለታጠረ፣ በእሾህም፣ በጋሬጣም ስለታጠረ ወፋፍራሞቹም ጥቃቅኖቹም ቀበሮዎች መግባት አልቻሉም። ኢትዮ 360፣ አዲስ ድምጽ፣ ጣና ቲቪ የሚባለው የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው ቡድንም እንደፈለገ ቢዘበዝብ ወፍ የለም። ዐማራው አጥሩን አጠባብቆ ማጠር ጀምሯል። ዐማራ ለዐማራ ብቻ። ዐማራን መምራት ያለበት ዐማራው ብቻ። ከዚህ ቀደም በአንድም በሌላም መልኩ በኢትዮጵያም፣ በዐማራም ስም ኪስ የማውለቅ፣ የዐማራን ካዝና የማራቆት ሥራ ሲሠሩ የነበሩ ቀበሮች በምንም ዓይነት መልኩ አሁን በዐማራው የደረሰ የወይን እርሻ ውስጥ በምንም መንገድ መግባት የለባቸውም። በምንም መልኩ አልኳችሁ። አትፍቀዱ። እናንተ ብትፈቅዱ እንኳ እኔ ለኅሊናዬ ሥር ቀበሮቹን እዋጋቸዋለሁ። አልምራቸውም።

"…ያለ ታማኝ በየነ፣ ያለ ግንቦቴው፣ ያለ ባልደራሱ፣ ያለ ግምባሩ የሰልፍ አስተባባሪነት ይኸው እኮ ዓለም አቀፍ የዐማራ ሰልፍ ማዘጋጀት ተችሏል። ክብር ለለንደኖች፣ ለዋሽንግተን፣ ለሲያትል ዐማሮች፣ ክብር ለፍራንክፈርት፣ ለደቡብ አፍሪቃ ዐማሮች ይኸው አሳዩ እኮ። አዲስ ሰው፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ አደረጃጀት ነው የሚያስፈልገው። የመርዝ ብልቃጦቹን አርቆ ማስቀመጥ ነው። ደቡብ አፍሪካ የእኔ ወንድም ደጉ ነው 600 ኪሎሜትር እየነዳ ባስ ሙሉ ዐማራ እስከ ፕሪቶሪያ ድረስ ይዞ ለሰልፉ የደረሰው። የዲሲው ሰልፍ በእነ መንጌ፣ በእነ ሰሌ የተመራ ነው። የለንደኑ፣ በእነ ወርቁ፣ በእነ አዲስ፣ የተመራ ነው። የፍራንክፈርቱም እንደዚሁ በአዲሱ የወይን ጠጅ አቁማዳ የተዘጋጀ ወይን ነው። አሮጌው አቁማዳ አዲሱን አቁማዳ ሊሸከመው አይችልም። ጥፋ በለው።

"…ቀበሮዎቹ አሁን ሌላ ዘዴ አምጥተዋል። ሁለት ነው ዘዴው። የመጀመሪያው ዋናውን ቀጩኑን ቀበሮ መደበቅ። ቀጭኑ ቀበሮ እስክንድርን መሸሸግ። በእስክንድ ምትክ ሰካራሙን ሀብታሙ ነው ያለው። ሰካራሙን ማስረሻ ሰጤን ወደፊት አምጥቶ በእሱ ስም ከዐማራው ላይ ማዳበሪያውን መግፈፍ ነው የፈለጉት። በጣና ቲቪ ሰበብ ከዐማራው ላይ ለመሰብሰብ የታቀደውን ገንዘብ እግር በእግር ተከታትዬ አድርቄዋለሁ። በመማር አለባቸው በኩል ያሰቡትን አይደለም ራሳቸውን መማር አለባቸውን አብሬ አሹቅ አድርጌያታለሁ። እነ ኪሩቤል ባለ ከበሮው፣ እነ እሸቱ ገጠሬው፣ እነ ዶፍቶር ደረጄ፣ እነ ሙላት አድኖ ወዘተ በቁማቸው ነው በረዶ ውስጥ የቀበርኳቸው። ዐማራን መጋጥ አይታሰብም። ከእንግዲህ ማንም እየተነሣ ኪሱን አያጥበውም። ጨርቅህን ጥለህ እበድ።

"…የሚገርመው አሁን አሁን ከብዙ ልፋት በኋላ ቀበሮዎቹ ጋር እኔም ራሴ ቀበሮ የመሰሉ የቀበሮ ቆዳ የለበሱ በግ ዐማሮችን፣ ጦጣ ዐማሮችን፣ ብልጥ፣ ንቁ የሆኑ ዐማሮችን አብሬ በማሰማራት አጀንዳቸውን በመቀማት፣ ምስጢራቸውን በመበዝበዝ ጥላቸውን እንዲጠራጠሩ አድርጌአቸዋለሁ። በየትኛውም የዙም ስብሰባቸው እኔ አለሁ። እኔ ባልኖር የእኔ ወፎች አሉ። እኔ በምተኛ ሰዓት እኔን ተክተው የሚሠሩ የትየለሌ ንስር ዐማሮችን አፍርቼአለሁ። በዚህ አምላኬን ልዑል እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ። ምስጋናው አንዷለም አሁን አሁን መናገር እስኪሳቀቅ ድረስ ነው የማስደነብረው። ስለምቀዳ መናገር ይቅርብኝ እስኪል ድረስ። የዐማራ ካባ ለብሰው ፋኖን ለምን መስቀል አንጠለጠለ? ለምን ዳዊት ደገመ? የሚሉትን ፓስተር ምስጋናው አንዷለምን ዛሬ ላይ ብቻውን እንዲያወራ ነው ያደረግኩት። ሚኪ ጠሽን ሰንደል ጆሮው ላይ ሰክቶ ፍራንክፈርት ባንሆፍ ላይ እንዲለፈልፍ ያደረግኩት እኔ ነኝ። ምስኪን ዐማራን ሲግጥ የከረመው ቀበሮው ሚኪ ዛሬ ብቻውን እያወራ የጆብ ሴንተር ጡረተኛ ሆኖ ዘርፏል። አልለቃቸውም። ሠርተህ ብላ።

"…እነዚህ ቀበሮዎች አሁን መገለጥ የፈለጉት ሌላው መንገድ ደግሞ ከአዲሱ የዐማራ ትውልድ ጋር ተመሳስሎ መቅረብ። አንድ ላይ እንስራ ብሎ መምጣት። ሰልፍ እናዘጋጅ፣ ከዚያ በኋላ ወደ ኪስ አጠባው መሄድ ነው ያሰቡት። ሰልፍ መውጣት ይችላሉ ሰልፉን ግን መምራት አይፈቀድም። በፍጹም በጭራሽ አይፈቀድም። ከዚያ ገንዘብ ልሰብስብ ማለት በፍጹም፣ በጭራሽ አይታሰብም። ካካ ነው። እፉ ነው። እነዚህ የዐማራን የወይን እርሻ ማዳበሪያ ሌቦች ወደ እርሻው አካባቢ ማቅረብ በፍጹም አይሞከርም። ሲንጫጫ ውሎ ቢያድር ወፍ የለም። ቀበሮዎቹ ያላቸው አማራጭ ጎንደር ባሉ የጌታ አስራደ ታዛዥ ጥቂት ቀበሮ ፋኖ መሳይ ቀበሮዎች እኔን ማሰደብ ነበር። አደረጉት፣ ሞከሩት፣ ብሩክ ይባስ ሂርጶም ዜና አድርጎ፣ እስክክስ አበበ በለውም ለማጯጯህ ሞክረው ነበር። ነገር ግን አልተቻለም። ቀጥሎ ያደረጉት በሸዋ ፋኖ በማይሙ መከታውና በአበበ ጢሞ፣ በቀውሷ በኩል ነበር። እሱም አልተሳካም።

"…የሸዋ ተወላጅ ኮሚቴዎች ይፋት ተራራ መሽጎ የሚቀለበውን የእነ መከታውን እና የእነ እስክንድርን ጦር በሳምንት 10 ሺ፣ 20 ሺ፣ 30 ሺ ዶላር እየላኩ ደግፈውት ነበር። ከልባቸው መዋጋት የሚፈልጉ ቢኖሩም ነገር ግን ከብልፅግና ጋር የሚሞዳሞደው ስለሚበዛ አንዳች ነገር ጠብ ሳያደርጉ በሚላከው ዶላር በሸነና እያሉ፣ አንዲት የገጠር ቀበሌ ሳያስለቅቁ፣ ሳይዙ በይፋት ሸለቆ ውስጥ ሚስትና ገርልፍሬንዶቻቸውን፣ እቁባቶቻቸውንም ይዘው እየተምነሸነሹ፣ በስቴኪኒ ጥርሳቸውን እየጎረጎሩ፣ የፎቶ፣ የቪዲዮ ትርኢት እያሳዩ ሲቀፍሉ ኖረዋል። አሁን ያ የዶላር ማዳበሪያ ቀጥ ብሎ እንዲቆም ተደርጓል። መሬት ላይ በእነ መከታው በኩል ይሄድ የነበረው ዶላር ነጥፏል። ምን ይበላ? የገበሬ ፍየል፣ በግና በሬ እያረደ መብላትን የትግል ስልት አድርጎ የነበረው የሆድ ፋኖ ቡድን አሁን ፍርክርኩ ወጥቷል። ኩላሊቱ እየፈረጠ ለእነ መከታው ዶላር እየላከ እነ መከታው የቅቤ ቅል መስለው እያብለጨለጩ የሚኖሩበት አግባብ ላይመለስ ተቋርጧል። ከነመከታው ቡድን እንለያለን ላሉ በቀደም ዕለት ከተላከው 4ሺ ዶላር በቀር አንድም ዶላር ወደ ይፋት ጫካ ጎረምሶች መሄድ አቁሟል። 24 ሰዓት ሜካፗን ተለቅልቃ ትግል ላይ ነኝ እያለች ስትሳደብ የከረመችው ፎንፏኒትም የአሸቦ ዕቃ ወደ መምሰሉ ተቃርባለች። አለቀ። ለምን መግለጫ አይደለም ማጋጫ አያወጡም። እኔ መስሚያዬ ጥጥ ነው። በፎቶ ትርኢት ዐማራን መቀፈል ጊዜው አልፎበታል።

"…ባለፈው ባልደራስ ሲቋቋም ገንዘብ ያዥ የሆኑት በሙሉ በመላው ዓለም በፊት ግንቦት ሰባት፣ ቅንጅት የነበሩቱ ነበሩ። ጀርመን ፍራንክፈርት ተሯሩጠው መጥተው ቦታውን ያዙት። ግንባሩ ሲቋቋምም እነዚሁ ሰዎች ናቸው የመጡት። ቶሎ ብለውም ሊቀመንበር፣ ሰብሳቢ ነው የሚሆኑት። አሁንም ሰልፍ መዘጋጀት ሲጀምር እነዚሁ ሰዎች ናቸው ጥፍራቸውንም፣ ጥርሳቸውን አሹለው ከቻሳ ለማለት የመጡት። እስከአሁን ለንደኖች ነአዲስ ጉልበት፣ በአዲስ ኃይል ቀዳዳ ላለመክፈት እየጣሩ ነው። አሜሪካም እንደዚያው። የጀርመኖቹን ግን አላውቅም። በዐማራ አዲሱ የትግል ማዕቀፍ ውስጥ የወይኑን እርሻ የሚያጠፉት ስመጥር ቀበሮዎች አሁንም ሰልፉን ከመሩት አደጋ ነው። ተመልሶ መንቦራጨቅ ነው። ስለዚህ በምንም ዓይነት መንገድ በአዲሱ የዐማራ ትግል አሮጌዎቹን የወይን መያዣ አቁማዳ መክተት አይገባም። ወይን ጠጁም ይፈሳል፣ አቁማዳውም ይቀደዳል። ስለዚህ እነዚህን መርዞች፣ እነዚህን ቫይረሶች፣ እነዚህን የኋላ ታሪካቸው ደርግ፣ ኢህአዴግ፣

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…ድፍርሱ ውኃ እየጠራ ነው። የክረምቱ ጎርፍ፣ አፈር ጭቃ፣ ቆሻሻ ሁሉ ይዞ በሰፈር መንደራችን ሲያልፍ የነበረው ጎርፍ እየጠራ ነው። እንኳን ደካማ ክንደ ብርቱ ወጠምሻ ጎሮምሳ አላሳልፍ ብሎ፣ ከወዲያማዶ ወዲህ ማዶ አላሻግር ብሎ ሲፎገላ የነበረው ከላይ ሰፈር የጣለው ዶፍ ዝናብ ጎርፉ አሁን እየሰከነ ነው። እንኳን ብርቱው ደካማው ሁሉ ያለ ምርኩዝ መሻገር ጀምሯል። ሕፃናት አይፈሩትም ጭራሽ ሊንቦራጨቁበት ሁላ ይችላሉ፣ ከወንዙ ዳር ሴቶችም ወንዶችም ልብሳቸውን ተረጋግተው ይጠጣሉ፣ ከብቶችም እንደዚያው፣ በወንዙ፣ ኩልል ብሎ በጠራው ወንዝ ልብስም ገላም ይታጠባሉ። አዎ ወንዙ ሲጠራ እንዲያ ነው የሚሆነው። ጠልፎ ለመስኖ ማድረግ ሁላ ይቻላል።

"…በመስኖው ውኃ፣ በገራሙ ውኃ፣ በታዛዡ ውኃ የለመለመው፣ የጸደቀው፣ ያበበውና ያፈራው ወይናችን ደግሞ ሌላ አደጋ አለበት። ቀበሮ። ቀበሮ የተባለ አደጋ አለበት። ቀበሮ የወይን ጠላት ነው። በስንት ጣጣና፣ በስንት ልፋት፣ ከተባይ፣ ከአእዋፋት ጥፋት የተረፈውን የደረሰ ወይን የሚያጠቃው ቀበሮ ነው። ለዚህ ነው ጠቢቡ ሰሎሞን መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕራፍ 2፣15 ላይ "…ወይናችን አብቦአልና የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮች፥ ጥቃቅኑን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን።" መኃልየ 2፣15 የሚለን።

"…ብዙ ጊዜ ወደ ወይን አትክልት ስፍራው ቀበሮች እንዳይገቡ የሚሠራው አጥር ትላልቅ ቀበሮችን እንዳያስገባ፣ እንዳያሳልፍ ተደርጎ ነው። እንዲያም ሆኖ ወይኑ በቀበሮ መጥፋቱ አልቀረም። ወፎቹ ወይኑንን እንዳያበላሹት በላስቲክ፣ በወረቀት ወይኑ ይጠቀለላል። በዚያ በኩል ስጋት የለም። አስቸጋሪው ቀበሮ ነው። ቀበሮ ወይኑን በላስቲክ፣ በወረቀት፣ በጋዜጣም ብትጠቀልለው ወደ ወይን እርሻው ከገባ ዘንጥሎ ነው የሚያረግፈው። ለዚያ ነው አጥር የሚሠራው የወይን ገበሬ። ጠቢቡ ሰሎሞን ግን ምን አለ? "…ወይናችን አብቦአልና የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮች፥ ጥቃቅኑን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን።" መኃልየ 2፣15። ቀበሮች ካለ በኋላ ነው ቀጥሎ "ጥቃቅኑን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን።" መኃልየ 2፣15 ያለው። አያችሁ መልእክት ሙሉ ሲሆን ደስ ይላል።

"…የወይን ገበሬዎቹ የሚሠሩት አጥር ወፋፍራም ቀበሮች ብቻ የሚያጠምድ ከሆነ ይከስራሉ፣ ትኩረታቸውን፣ ታርጌታቸውን ወፋፍራም የሚታዩ፣ የሚታወቁ አጥፊ፣ የወይን እርሻ የማውደም ልምድ ባላቸው፣ ሰርተፊኬት ዲፕሎማና ዲግሪ ባላቸው ቀበሮች ላይ ብቻ የሚያተኩሩ ከሆነ ይሸወዳሉ። ትላልቅ ባለበት ትናንሽ፣ ግዙፍ ባለበት ጥቃቅን፣ ደቃቃ፣ ወፋፍራም በላበት ቀጫጭን ቀበሮ አይጠፋም እና ወደ ወይን እርሻ እንዳይገባ ለቀበሮ ማገጂያ ተብሎ የሚሠራው አጥር ጥቃቅኖቹን ቀበሮች የሚያጠምድ፣ የሚይዝ መሆን አለበት። ቀበሮ ቀበሮ ነው። ቀበሮ ወፍራም ሆነ ቀጭን ያው ቀበሮ ነው። ቀበሮ ትልቅ ሆነ ትንሽ ሕፃን ሙጭቅላ ያው ቀበሮ ነው። እናም የወይን እርሻው ባለቤቶች ስለ ወይን እርሻቸው አጥር ማጠር ሲያስቡ ትኩረት ማድረግ ያለባቸው ትላልቆቹ ቀበሮች ላይ ብቻ ሳይሆን ትናንሽ፣ ቀጫጭን፣ ጥቃቅን ቀበሮዎች ጭምር ላይ መሆን አለበት።

"…በራሴ ትርጓሜ አሁን በዚህ ዘመን እኔ የወይን እርሻ ነው ብዬ የማስበው የዐማራውን የፋኖ ትግል ነው። የዐማራ ፋኖን ትግል እንደ ደረሰ የወይን እርሻ ነው የማየው። አድካሚ፣ አሰልቺ፣ የሚያለፋውን የተራራ ላይ የወይን እርሻ መድረስ ተከትሎ ወደ ወይን እርሻው በመግባት የዐማራ የገበሬውን ድካምና ልፋት መና ለማስቀረት የቀበሮ መንጋ ከየስፍራው ተንጋግቶ ይመጣል የሚል ስጋት ነበረኝ። ከዚህ በፊት ልምድ ያላቸው ቀበሮች፣ ወፋፍራሞቹ፣ ቀያይ፣ ሲያዩዋቸው መኳንንት የሚመስሉት ቀበሮች ዐማራው ለእርሻው ጥንቃቄ ባለማድረጉ የወይን እርሻው ወድሞ ነበር። አውድመውት ነበር። አሁን ግን እንደዚያ አይደለም። የዐማራ የወይን እርሻ ልምድ ባለው በግባብዳ፣ በወፋፍራም፣ በተላላቅ ቀበሮች አይወድምም። ምክንያቱም የወይኑ እርሻ ባለቤት ዐማራው የቀበሮቹን መግቢያ አጥር ከርችሞ ዘግቷልና። በዚያ በኩል ወፍ የለም።

"…ለዐማራ የወይን እርሻ የሰማይ ግሪሳም አሁን ላይ አያሰጋውም። በሆነ ባልሆነው፣ በረባ ባልረባው፣ ለዐማራው ማስለቀሻ ፕሮጀክት ቀርጸው የዶላር መለመኛ አቁፋዳቸውን ይዘው መጥተው ያጥቡት፣ ይቦጠቡጡት የነበሩት የሰማይ በራሪ ግሪሳ ወፎችም፣ በምድር ዘላይ ቀበሮችም የዐማራ ወይን በዋዛ የማይገኝ ሆኖ ተከርችሟል። የዐማራ ኪሱ በቀላሉ የሚፈታ፣ የሚበረበር መሆን አቁሟል። የወይን እርሻውን ከግሪሳ ወፍ ለመጠበቅ በጋዜጣ፣ በላስቲክ እንደሚጠቀለለው ሁሉ የዐማራ ዳያስጶራም ኪስ ከግሪሳዎቹ ልማደኛ ኪስ አውላቂዎች ዘመዴ በሚባል ፀረ ተባይ፣ ፀረ ግሪሳ መድኃኒት አማካኝነት ተጠብቋል። አለቀ።

"…ወፋፍራም ልምድ ያላቸው ግሪሳ ቀበሮችም አሁን መግቢያ፣ መውጫ ቀዳዳ አጥተው በመቅበዝበዝ ላይ ይገኛሉ። በአየር ላይ ቢዘሉ፣ ቢፈርጡ፣ ቢወጡ፣ ቢወርዱ ወፍ የለም። ከዘመነ ደርግ ጀምሮ በተቃውሞ ጎራ መሪነት በኢትዮጵያ ስም ሲገረፍ፣ ሲገፈፍ፣ ሲበዘበዝ የነበረው ዐማራም አሁን መጀመሪያ ለራሴ፣ ቅድሚያ ለራሴ በማለት ወደራሱ መመልከት ጀምሯል። ከ1983 ዓም ጀምሮ በዘመነ ወያኔ ኢህአዴግ ዘመነ መንግሥትም እንዲሁ በተቃውሞ ስም ተደራጅተው ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ሲጦሩበት ከርመዋል የዐማራን ትግል። ከ1997 ዓም ጀምሮ፣ አንዴ ቅንጅት፣ ሌላ ጊዜ፣ ኢድሀቅ፣ ኢድህን፣ ኢዴድ፣ ኢዳድ፣ ኢዶድ፣ ኢዲድ፣ ብቻ ምን አለፋችሁ ሰዎቹ ሳይቀየሩ ስምና አርማ እየቀየሩ በተለየ ሁኔታ ዐማራውን የወይን እርሻውን ቦጥቡጠው፣ ቦጥቡጠው አክስረውታል። ከቅንጅት መፍረስ በኋላም እነዚያው ሰዎች ጫካ እንገባለን በማለት ከዐማራው ኪስ ፈረንካውን ሙልጭ አድርገው ኤርትራ በረሃ የሻአቢያን ፍየል ሲጠብቁ ከርመው አንዳችም ሥራ ሳይሠሩ ርቃኑን ሲያስቀሩት ቆይተዋል።

"…የቀበሮቹን ስም ዘርዝሩ እስቲ። ግንቦት 7፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ መድኅን፣ መድን፣ ኢድህን፣ ኢዳቅ፣ ኢሳቅ፣ ይሳቅ፣ ኧረ ስንቱ በስንቱ ቀበሮ ድራሹ ጠፋ ዐማራው። ትግሬ ተደራጅቶ መስመር ሲይዝ፣ ኦሮሞ ተደራጅቶ መስመር ሲይዝ፣ ዐማራው እንዳይደራጅ ጉራጌው ብራኑ ነጋ ዐማርኛ እያወራ ጋጠው፣ አደነዘዘው፣ አጠበው። በዐማራው ገንዘብ ጉራጌው ብራኑ ነጋ የኦሮሙማው መንግሥት የትምህርት ሚንስትር ሆኖ አረፈው። ቀበሮው ብራኑ በዐማራ ገንዘብ፣ በዐማራ ዶላርና ዩሮ ሲዝናና፣ ሲምነሸነሽ ከርሞ በመጨረሻ ሚንስትር ሲሆን የዐማራን ተማሪ ረፍርፎ፣ ሸክሽኮ ጥሎ ለብራኑ ጁላ የማረጃ ቄራ አቅራቢ ሆነ። ዛሬ እንደ ብራኑ ነጋ ዐማራ ላይ የሚያላግጥ፣ የሚያሾፍ፣ የሚላግድ አንድም ኦሮሞ፣ ትግሬ እንኳ የለም። ቢያንስ አደብ እየገዙ ነው። ዐማራ ይሄን ወፍራም ቀበሮ አሁን አጥሩን ዘግቶበታል። ብራኑ ነጋ ወደ ወይን እርሻው እንዳይገባ አጥሩ ቢያግደውም የብራኑ ነጋ ጥቃቅን ቀበሮዎች ግን አሁንም አሉ። የመርዝ ብልቃጥ ያው መርዙ ቢደፋም መርዝነቱ አይቀርም። የቀበሮ ልጅ ቀበሮ ነው። አጥሩን ጠበቅ ማድረግ ነው መፍትሄ መድኃኒቱ።👇ከታች ① ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…መልካም…

"…በወዳጅም፣ በጠላትም፣ ተማርኩ፣ ተመራመርኩ፣ ፍሮፌሰርም፣ ዶፍቶርም ነኝ፣ ፎሎቴካዬን ማንም አይደርስበትም፣ ዐዋቂ ነኝ፣ ብዙ ወረቀቶች አሉኝ የሚለውንም ሆነ እንደ እኔ ማይም፣ "ሀ" ገደሉ፣ የእንግልጣር አፍ የማይችል፣ የማይሰማውንም ደግሞም ካህን ነኝ ሼክ ነኝ፣ ፓስተር ነኝ፣ እልል የተባለለኝ የተቃዋሚ ፎለቲካ መሪ፣ ገዢው ባርቲ ነኝ የሚለው ሁላ በጉጉት የሚጠብቀውና ዘወትር በዕለተ ማክሰኞ ተጀምሮ በዕለተ አርብ የሚያበቃውን ተወዳጁ እና ተናፋቂውን ርእሰ አንቀጻችን መጻፍ አሁን እጀምራለሁ።

"…ባይገርምላችሁ ዛሬ እየጻፍኩላችሁ ያለሁት የዐማራን የደረሰ የወይን እርሻ ለማውደም ስላሰፈሰፉና መልካቸውን ቀይረው ተዘጋጅተው ስለተቀመጡ ሾተላይ፣ ጽንስ የማጨናገፍ፣ የደረሰም የወይን ፍሬ የማውደም ልምድ ስላላቸው ትግል ጠላፊ ግሪሳዎችና ጥቃቅን ቀበሮዎች ነው።

"…እናም ዛሬ ከዕውቀቴ አንጣር የደረሰ አጓጊ የወይን እርሻ አውዳሚ ስለሆኑት ወፋፍራሞቹና ስለሚታወቁት ቀበሮች ሳይሆን ስለ የጥቃቅን ቀበሮዎች አጠማመድ ላስተምራችሁ ነኝና ተዘጋጁ። እናንተም ጎበዝ ተማሪዎች ሆናችሁ ስለ ጥቃቅን ቀበሮዎች አጠማመድም ተምራችሁ የደረሰ፣ የሚያስጎመጀውን የወይን እርሻችሁን አጥር ለማጠባበቅ ዝግጁ ናችሁ ወይ…?

• በተለይ ለሜቦራ ዳያስጶራ ዝግጁ ነህ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ይነበብ…

"…የ24/7 ዕረፍት አልባ ጩኸቴ ፈር እየያዘ ነው። አሁን ብቻዬን እንደ እብድ አልጮህም። ብቻዬን ዘመዴ ምን ነካው አልባልም። በማንም መንገደኛ፣ ክፍትአፍም ስሰደብ ውዬ አላድርም። አሁን ዘመን ተቀይሯል። ላንቃዬ እስኪሰነጠቅ፣ እንጥሌ እስኪወርድ፣ ከምላሴ ላይ ምራቅ እስኪጠፋ ድረስ የምጮህበት ጉዳይ አደማጭና ጆሮ የሚሰጡት ብቻ ሳይሆን ከእኔ በላይ በያገባኛል ስሜት የሚጮሁ የትየለሌ የጉዳዩ ባለቤቶች ከተኙበት ጥልቅ እንቅልፍ ነቅተው ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ከሰኞ እስከ ሰኞ፣ ከነግህ እስከ እኩለ ሌሊት፣ ከክረምት እስከ በጋ ድረስ ድሮ ድሮ በፌስቡክ፣ አሁን ደግሞ በቴሌግራም ዓይኔ ዕንባ እስኪያፈስ፣ ጣቴ እስኪደነዝዝ፣ ችክ፣ ምንችክ ብዬ፣ ብዙዎች ቋቅ ብለው እስኪጸየፉኝ ድረስ ያለመሰልቸት ስጽፍ፣ ስቸከችክ ቆይቻለሁ። ዩቱዩብ እና ፌስቡኬ ሲዘጉ በኢትዮ ቤተሰብ፣ በመረጃ ቴቪ ዩቱዩብ፣ ከዚያም በቲክቶክ፣ በመረጃ ቴሌቭዥንም ጭምር እንደ እብድ ውሻ ስጮህ መክረሜ ይታወሳል።

"…ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የርእሰ አንቀጽ ጦማሬን ከ7 ቀን ወደ 5 ቀናት ቀንሻለሁ። ቅዳሜ፣ እሁድና ሰኞን ቀንሼ ከማክሰኞ እስከ አርብ ብቻ አድርጌአለሁ። ዕለተ ሰኞን ደግሞ ከፈጣሪ ምስጋና በቀር በኢንተርኔቱ ዓለም ብቅ ሳልል ለመዋል ወሰንኩ። ሰኞና ረቡዕ ትምህርት ሁላ ጀመርኩ። ከቤተሰቤና ከልጆቼም ጋር ተቀላቀልኩ። ይሄ ሁላ የሆነው የምጮህለት የዐማራ ጉዳይ ገዢ ስላገኘና የጉዳዩ ባለቤቶችም ከፊት መስመር መሰለፍ ስለጀመሩ ነው።

"…ትንሣኤው እስኪበሠር ድረስ ለራሴ የገባሁትን ቃል ለመፈጸም ስል ደረጃውን ከፍ አድርጌ የጀመርኩትን ትግል እንደተለመደው ከዛሬው የዕለተ ሰኞ ዕረፍቴ በኋላ ነገጠዋት ከምስጋና በኋላ በሚጀምረው ርእሰ አንቀጻችን እንደንስር ሆኜ እጀምረዋለሁ።

• የነገ ሰው ይበለን…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በትእግስት ጠብቁን…

"…መላቀቅ የለም ብለው ከሳታላይቱ ጋር እየታገሉ ነው ቴክኒሽያኖቹ። ወደ 2ሺ ሰው ዩቱዩብ ላይ እየጠበቀ ነው። ቀጥሎ የማቀርበው ነው ጣጣ ያመጣብኝ። ከዛሬ በኋላ መርሀ ግብሬን ቀድሞ ማስተዋወቅ አቆማለሁ።

• ወይ ንቅንቅ…💪 አላችሁ አይደል?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ምሽት 2:30 ላይ ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ዛሬ ግሩም ግሩም የሆኑ መርሀ ግብሮች ናቸው የሚጠብቋችሁ።

• ዩቲዩብ 👉 https://youtu.be/f9fnW5M3AUk
• ትዊተር 👉 https://twitter.com/MerejaTV
• Mereja TV: https://mereja.tv
• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mereja/live

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሻሎም…!  ሰላም…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ይገደል…✊✊✊

"…ይሄ ከወለጋ ናዝሬት ድረስ የመጣው የዋቃ ጉራቻ አራጅ ምን ዓይነት አሰቃቂና አረመኔያዊ ወንጀል ቢሠራ ነው የናዝሬት ሕዝብ እንዲህ አውራ ጎዳና ላይ ወጥቶ ይገደል፣ ይገደል፣ ይገደል ብሎ የሚጮኸው?

• የምሽት 2:00 ሰዓት ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር የመረጃ ቴሌቭዥን የቀጥታ ስርጭቴ ምላሹን ይዞላችሁ ይጠብቃችኋል።

• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁኝ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር
🌹🌹🌹…🌹🌹🌹…🌹🌹🌹

"…ድንግል ሆይ…! ርጉም በኾነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ ጋራ ካገር ወደ አገር ስትሸሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ረኀቡንና ጥሙን፣ ችግሩንና ጒዳቱን ከርሱ ጋራ የደረሰብሽን ጸዋትወ መከራ ኹሉ አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ከዐይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ፤ ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ፣ መዐትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ፤ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥኣን አሳስቢ ለንጹሓን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ።

"…ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ሆይ ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን፤ አእምሮውን ጥበቡን ፍቅርሽን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን፡፡"

"…የእመቤታችንን ፍቅሯን በልቦናችን ጣዕሟን በአንደበታችን ያሳድርብን። ምልጃና ጸሎቷ ረድኤት በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን። የአሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያን በምልጃዋ ትጠብቅልን።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…7

"…አየህልኝ ይሄን ጎንደሬ የቴዲ ልጅ…!

"…የሕዝብ ብዛቷ 2 ሚልዮን የማይሞላው የተባበሩት ኤምሬትስ አቢይ አሕመድን አቅፋ ደግፋ ድሮንና ቦንብ እየሰጠች የዐማራን ሕዝብ እያስፈጀችው ነው። ትግሬን አስፈጅታ ከጨረሰች በኋላ ወደ ዐማራው ነው የዞረችው።

"…ትናንት ዐመዳም ደሀ፣ የግመል ቂጥ ተከታይ የነበረ ሕዝብ ባለቤት የነበረችው ሚጢጢዋ አረብ ለኦሮሙማው አገዛዝ አግዛ በተለይ ጥንታዊውን እስልምናና፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮችን ለማጥፋት ቆርጣ የተነሣች ብር ልቧን የደፈነባት ሀገር ናት።

"…ይህቺ ሚጢጢ ደፋር ሀበሻን አትንኩ የሚልውን የነቢዩአን ቃል ችላ በማለት ሀገሬ ላይ ቦንብ ማዝነብ ከጀመረች ውላ አድራለች። ይሕቺን ጥገበኛ፣ ደፋር የአረመኔ አራጅ ደጋፊ ነው ለንደን ላይ ሁለት የለንደን ፋኖዎች እንዲህ ብጥብጥ ያደረጓት።

"…ተመልከት ዐማራን፣ ተመልከተው ልቡን፣ ተመልከተው ድፍረቱን፣ ተመልከተው ይሄን ግልብ ብር ልቡን የደፈነው ዊጢምጢማም ዓረብ መግቢያ ሲያሳጣው? አንበሳ የለንደን ፋኖ። 👏👏👏

"…እንግዲህ እኒህ ሁለት ዐማሮች ዐረቦቹን ለንደን ላይ እንዲህ ብጥብጥ ካደረጉ ለንደን ላይ የሚኖረው በመቶ ሺ የሚቆጠር ዐማራ ቢወጣ ብላችሁ አስባችሁታል?

"…አሁን ዶናልድ ትራምፕን በደንብ መጠቀም ነው። የታረዱ የዐማራ ቄሶችና፣ የታረዱ የዐማራ ሼኮችን፣ ቤተ ክርስቲያንና መስጊድ በቪድዮ ማሳያት ነው። አሁን ወደ ኋላ ማለት የለም። ገፋ ማድረግ ነው። ይሄን ኢትዮጵያ ዐማራ ገድሎ ዋሽንግተን ለሾፒንግ የሚመጣ የብልፅግና አራጁ እንዲህ ማንቆራጠጥ ነው።

• እስቲ በማርያም… ለለንደን ፋኖ ለአፄ ቴዎድሮስ ልጆች አንደዜ ሞራል። 👏👏👏👏👏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…መልካም…!

"…አሁን ደግሞ 15 ሰው አንብቦት 14 ፍሬ ሰው ብቻ 😡 ብው ብሎ የተናደደበትን ርእሰ አንቀጽ በእናንተ ወደማስተቸቱ እናመራለን። ተራው የእናንተ ነው።

"…ርእሰ አንቀጹ ረጅም ነው። በይቀጥላል ነው የቆመው። ነገ ጠዋት ካቆምንበት እንቀጥላለን። በደንብ እንተቻለን። አበጥረን እንመረምራለን። በድፍረት መወያየት እንጀምራለን። የሚበሳጭ እስክስ ማለት ይችላል። መብቱ ነው።

"…አበበ በለው ተነካብኝ፣ ተተቸብኝም ብሎ በጎጥ ተወሽቆ፣ የደንቢያ ልጅ ነኝም ብሎ፣ በዐማራነቱ ተሳስቦ በእኔ በሐረርጌው መራታ በዘመዴ ላይ ስህተት ካለብኝ እኔን ስህተቴን ከሚያርም ጨዋ አስተያየት በቀር ከመስመር ያለፈ ክፍት አፉን የሚከፍትብኝን፣ በአበበ ጭቅጨቃ ክፍት አፉን የሚከፍትብኝ የዐማራ ማኅበር ካለ እኔም በአፀፋው ምላሽ ለመስጠት የምገደድ መሆኔ ይታወቅልኝ።

• በሉ ጀምሩ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ …የጉዳዩ ባለቤትም፣ መሪም፣ ተቆጣጣሪም፣ አዛዥም እስክንድር ነጋ ያለምንም ተቀናቃኝ ብቸኛው ሰው ሆነ። ጉራጌው ብርሃኑ ነጋ ዐማራን አልቦ፣ አልቦ፣ እጥብ አድርጎ ሲያበቃ፣ አናቱ ላይ ተጸዳድቶ ወደ አቢይ ዘንድ ገሌ ስለገባ፣ እነ ነአምን ዘለቀ፣ እነ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ እነ ኤፍሬም ማዴቦ፣ እነ ታማኝ በየነም የዐቢይ መንገድ ያዋጣናል ብለው በማሰብ በእስክንድር የስም ሽያጭ  የሚገኝን ዶላር ንቀው ዞር ከዚህ ዘራፊ ቡድና ክለብ ዞር ስላሉ ወደ አዲስ አበባ የታከለ ኡማ ኮንዲሚንየም ቃል ተገብቶለት ከተሸበለሉ ጥቂት የዲሲ ግብረ ኃይል አባላት የተረፉትን ይዞ እስክንር ወደ ግልጽ ዘረፋው ገባ። በዚህ ዘረፋ ላይ ሚስቱም ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል በግልፅ ተሳታፊ ነበረች። ቪድዮው አለኝ። ባል እስክንድር ኢትዮጵያ ሆኖ፣ ሚስት አሜሪካ ሆና ይሄንን ምስኪን ዐማራ አለበቱ አይገልጸውም። አጠቡት። ለዘረፋ ዓይናቸውን በጨው ታጥበው ነው የሞለጩት።

"…ዘረፋው ሀ ተብሎ የተጀመረው በባላደራው ነው። ባላደራው ብዙም ሳይቆይ ባልደራስ ተብሎ ስሙን ቀይሮ ከች አለ። ሰናይ ቲቪም ምሥረታ ተብሎ፣ አክስዮን ሁሉ እንሸጣለን ብሎ እስክንድር ውርውር ብሎ ነበር። በእነዚህ ሁሉ ከላይ የጠቀስኳቸውን ጆፌ አሞሮች ሰብስቦ በአዲስ አበባ ስም ዳያስጶራውን በተስፋ እየሞላ፣ ለልመናው የሚሆን አጫጭር ቪድዮ እንደ ቲክቶከር እና እንደ ዩቱዩበር እሠራ እየላከ ይሄን ምስኪን ዳያስጶራ እንደ ጉድ ይሄን ዶላር ያልበው ጀመር። ኢትዮ 360፣ እኔን ጨምሮ፣ አበበ በለው፣ ፌስቡከርና ቲክቶከር፣ ዩቱዩበሩ ሁላ "ታላቁ እስክንድር" እያልን እንድንጮህ ተደረግን። እነ ኢሣት፣ እነ መሳይ፣ እነ ሲሳይ አጌና በተራቸው የቀድሞ እንጀራቸው የነበረውን እስክንድርን ይጠሉት፣ በግልፅም ይወርፉት ጀመር። ነገር ግን የኃይል ሚዛኑ ወደ እስክንድር መንደር ሰዎች ስላጋደለ ያኛው መንደር ተሸናፊ ሆነ። በተለይ የታከለ ኡማ አስተዳደር ቄሮዎችን ወደ እስክንድር ቢሮ እየላከ ሁከት በመፍጠር እስክንድር ነጋን ማጀገኑን ተያያዘው። ዳያስጶራውም፣ ሀገር ቤት ያለውም ሕዝብ እልህ ውስጥ ገባ። እስክንድር የኦሮሙማው አገዛዝ ብቸኛው ተቃዋሚ ሆኖ ወጣ። ቀድመው የነበሩት ተቃዋሚዎች በአቢይ አስተዳደር ውስጥ ተካተው ስለበለፀጉ፣ ቀድመው የነበሩት ተቃዋሚዎች እንደነ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ እንደ ብራኑ ነጋ የመሳሰሉት የሥርዓቱ አጋር ስለሆኑ፣ እነ አብንም ተስፋ የሚጣልባቸው ስላልሆነ፣ እነ ልደቱ አያሌውም አፍቃሬ ወያኔ ናቸው ተብለው በሕዝቡ ዘንድ ስለተገመገሙ፣ የተቃዋሚው መንደር በተቃዋሚ መሪ እጦት እየተሰቃየ፣ እየቃተተ በነበረ ሰዓት ነው በወያኔ በተደጋጋሚ ታስሮ መፈታቱ እንደ ጥሩ ሪከርድ ተቆጥሮለት እሱ ራሱ ሳያስበው፣ ሳይጠብቀውም ያለምንም ተቀናቃኝ እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ከተማ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሆኖ አረፈው።

"…ባላደራው ሲቋቋም ገንዘብ ያዦቹ አቶ ሙሉጌታ፣ ሕይወት፣ ኤርሚያስና ዶር አምሳሉ ሆነው በእስክንድር ነጋ ተመርጠው ተሾሙ። አንድ በሉ። ባላደራው መፍረሱ ሳይነገር ባልደራስ ተቋቋመ። ባልደራስ ሲቋቋምም ገንዘብ ያዦቹ አቶ ሙሉጌታ፣ ወሮ ሕይወት፣ አቶ ኤርሚያስና ዶር አምሳሉ ሆነው በእስክንድር ነጋ ተመርጠው ተሾሙ። ባልደራስ ሳይፈረወስ እስክንድር ፈነንኩ ብሎ ጫካ ገባ። ጫካ ገባሁ ብሎም ግንባሩ የሚባል ድርጅት መመሥረቱን በይፋ ዐወጀ። አሁንም ገንዘብ ያዦቹ አቶ ሙሉጌታ፣ ሕይወት፣ ኤርሚያስና ዶር አምሳሉ ሆነው በእስክንድር ነጋ ተመርጠው ተሾሙ። ግንባሩ መፍረሱ ሳይነገር ሠራዊቱ የሚባል መቋቋሙ ታወጀ። አሁንም ገንዘብ ያዦቹ አቶ ሙሉጌታ፣ ሕይወት፣ ኤርሚያስና ዶር አምሳሉ ሆነው በእስክንድር ነጋ ተመርጠው ተሾሙ። ሠራዊቱ ተመሥርቶ ወር ሳይቆይ የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የሚባል መመሥረቱ ታወጀ። አሁን ጭንቅ መጣ። ገንዘብ ያዦቹም ተደበቁ። ትናንት የዙም ማስታወቂያ ብሠራላቸውም ለሕዝብ ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጡ ተደበቁ።

"…ለባልደራስ ተብሎ ሚልዮን ፈሪ ዶላር ተዋጣ። ያ በአሜሪካ ተሰብስቦ ወደ አዲስ አበባ ይላካል ተብሎ ይጠበቅ የነበረ ዶላር ወደ አዲስ አበባ ሳይላክ የእስክንድር ነጋ ሚስት በቅርብ ርቀት እየተቆጣጠረችው በዚያው በአሜሪካ እንደ ጨው ሟሙቶ እንደ በረዶም ቀልጦ ቀረ። አዲስ አበባ የነበሩት የባልደራስ አመራሮችም ስለ ኦዲት፣ ስለ ተሰበሰበው ገንዘብ ሲጠይቁት አንድም መልስ ሳይሰጣቸው፣ ኦዲትም ሳይደረግ እስክንድር ነጋ እንደ ቦዘኔ፣ እንደ ዋልጌ ልጅ እንደወጣ ቀረ። እንዲያውም ከአሁን በኋላ ፋኖ ሆኛለሁ በቃ ብሎ ብጣሽ ወረቀት ለባልደራስ ጽሕፈት ቤት ለአስቴር (ቀለብ) ስዩም ልኮ እሱ ሰሜን ሸዋ ራሳ መከታው ጋር ሄዶ በዚያው ፈነነ። የነገው ቢሳካለት ሀገር ለመምራት የሚታትረው እስክንድር በትንሹ በባልደራስ ያልታመነ፣ ተመዝኖም የቀለለ ሰው ሆኖ ተገኘ። ይሄን አሁኑኑ ደፍረን ካልሞገትነው፣ ሕጋዊ ጥያቄውንም በድፍረት ካላነሣን አደጋ ነው። ይታያችሁ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሆን ከአረመኔው አብይ አሕመድ የባሰ ዘራፊ፣ ነፍሰ ገዳይ ነው የሚሆነው። ልጓም የግድ ነው። ኋላ ላይ በሬ መስረቅ ጀምሮ ተይዞ ሊሰቀል ሲል ብናለቅስ እስክንድር የሚለን ምነው እናቴ በእንቁላሉ ጊዜ በቀጣሽኝ ነበር። የማይጠቅም፣ የማያድን ለቅሶ ነው የሚለን።

"…እስክንድር ነጋ በአሜሪካ ባልደራስን ሲያቋቁም ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራን ይዞ ነው። ኤርሚያስ ዋቅጅራ ደግሞ ኢህአዴግ ነው። እስክንድር ኢህአዴጉን ኤርሚያስ ለገሰን ከመረጠው በኋላ የተፈጠረው ቀውስ ቀላል አይደለም። እስክንድር የአዲስ አበባን ጉዳይ አጀንዳው ካደረገ በኋላ ብዙ የአዲስ አበባ ወጣቶች፣ ምሁራንም ባልደራስን ለማገዝ ተቀላቅለውት ነበር። የባልደራስ አባላት መብዛታቸው ሲታይ እንደተለመደው በኢትዮጵያ ፖሊስ፣ በወያኔም ጊዜ ሆነ በኦህዴድ ጊዜ ሲታሰር ጫፉን የማይነካው፣ ዝንቡ እሽ የማይባለው፣ በእስር ብቻ የሚጀግነው እስክንድር ነጋ የሀጫሉን ሞት ተከትሎ የእነ ጃዋር፣ የጓደኛው የበቀለ ገርባ ማባያ ተደርጎ ታሰረ። እስክንድር በእስር ዘመኑ ሃይላንድ በብልቱ ላይ  አልተንጠለጠለበትም። ጨለማ ቤት ገብቶም አልተሰቃየም። እንደሌላው የዓይኑን ብርሃንም፣ እግሩንና እጁንም አላጣም። ብቻ ይታሠራል። ይፈታል። ከተፈታ በኋላ የዶላር ማለቢያ ድርጅት ያቋቁማል። የአዲስ አበባ፣ በተለይ የፈረንሳይ ወጣቶች በመዝገቡ ተለቅመው ታሠሩ። ገሚሱ ተሰደደ፣ ገሚሱ ተገደለ።

"…እስክንድር ከእስር እንደተፈታ በቀጥታ ወደ አሜሪካ ነው የሄደው። ድል ለዲሞክራሲ ሲል የነበረው እስክንድ አሜሪካ ከመሄዱ በፊት ግን ይመስለኛል በትግራዩ ጦርነት ጊዜ ከኢትዮጵያ ወገን ሆነው ለተዋጉ የፋኖና የአፋር ክልል መንግሥት ምስጋና ለማቅረብ የባልደራስ ቲምን አስከትሎ ሄዷል። እስክንድር በዚህ ጉዞው ፋኖ በሚገባ መዘጋጀቱን፣ ጦርነትም አይቀሬ መሆኑን ተረድቷል። የባልደራስ አባላትን ይዞ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎና በሸዋም የፋኖ አደረጃጀቶችን በተመስጦ ጎብኝቷል። ገምግሟልም። በጎንደር ጋሽ መሳፍንት ጋር በመሄድ ከጋሼ ጋር መክሯል። በውለታም፣ በመሃላም አስሮት ተመልሷል። በጎጃም ከኢንጂነር ይልቃል ጋር፣ ከነ ዘመነ እና ማስረሻ ሰጤ ጋር በመሆን መክሯል። የጎጃምን ፋኖ አደረጃጀት እና አያያዙንም ገምግሟል። ጎጃሜዎቹን ጋዜጠኞች ጌጥዬንና ወግደረስንም መልምሎ የባልደራስ አካል አድርጓቸዋል። ከዚያ ወደ ወሎ…👇②ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ዛሬም ቆሻሻ አመለካከት መጥረጊያዬን ይዤ፣ ወንፊትና ሰፌድንም ይዤ፣ ይሄን ዘራፊ፣ አጭበርባሪ የደም ነጋዴ ሁላ ልጠርገው፣ ለበጥረው፣ በዚያውም በጭቃ ዥራፌ እየዠለጥኩ፣ በእሳት አርጩሜ ብዕሬ እሸነቆጥኩ፣ በዐማራ ትግል ጫንቃ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው፣ እንደ አልቅት ደሙን እየመጠጡ ዐማራን ነጭ የአሸቦ ዕቃ አስመስለው ያስቀሩትን መዥገሮች ላራግፍ ነኝና ጮጋ ብላችሁ ጠብቁኝ።

"…ደጋግመው ፋውል የሠሩ፣ የዐማራ ትግል በገንዘብ እጦት እንዳይፋፋ፣ እንዳይመራ ሳንካ ሆነው ያስቸገሩ፣ እንደ ጋሬጣም የተጋረጡ፣ እንደ ሾተላይ የትግሉን ጽንስ ማጨናገፍ ቋሚ ሥራቸው ያደረጉ ሰው መሳይ በሸንጎዎችን ፋስ መዶሻ ሆኜ ልነቅል ነኝና ጫ ብላችሁ ጠብቁኝ።

"…እንደ ቴሌ የግድግዳ ስልክ ያለ ገንዘብ፣ ያለሳንቲም የማይሠሩ። እፍረት፣ ነውር፣ ሼም የሚባል ነገር የማያውቁ፣ አርጅተው በዳይፐር እየሄዱም እንኳ አሁንም ንስሀ ለመግባት ወኔ የሌላቸው የፖለቲካ ጋለሞቶችን ንስሀ እንዲገቡ ልሰብክ ነኝና ምእመናን ተዘጋጁ።

"…ይሄን ያፈጠጠና በጥቂት ግለሰቦች ተይዞ፣ በሕዝብ ትግል የግል ኑሮና ቤተሰብ የሚጦርበት፣ ከዳያስጶራው ተሰብስቦ ብልፅግና የሚቀለብበትን የአጭበርባሪ፣ የነውረኞችን የእንጀራ ገመድ በድፍረት ልበጥሰው ነኝና ተዘጋጁ። አዲስ ዐማራዊ ወጣት፣ አዲስ ዐማራዊ አስተሳሰብ፣ አዲስ ግልፅ የሆነ ተጠያቂነት ከሓላፊነት ጋር አስተባብሮ የያዘ ዘመናዊ ዐማራዊ አሠራር እንዲዘረጋ መጀመሪያ እነዚህን የዕድር ዳኞች፣ ዕቁብ ሰብሳቢዎች መቀየር፣ ከትግሉ ሜዳም ዞር ማድረግ ያስፈልጋል። ያለበለዚያ ወፍ የለም።

"…እህሳ የቲም እስክንድርን ነጋን የዶላር ዘራፊ ቡድን የዘረፋ ስልት ለማንበብ፣ አንብባችሁም የራሳችሁን አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ ናችሁ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አይባልም…!

"…ለምን ዘመድኩን ቤት ሄዳችሁ ይባላል እንዴ? በፍጹም አይባልም። የኡጋንዳው ወንዴ አፍንጮ ግን ሲበዛ ክፉ ሰው ነው። አሽቆጠቆጣቸው እኮ። ይኸው እኔ ማሙሼ ጉልቻው ቤት ገብቼ እየሰማኋችሁ አይደል እንዴ? ሰው እኔ ቤት ገብቶ ቢያዳምጠኝ ምንድነው ችግሩ? በእውነት ትክክል አይደለም። ወንዴ የእስክንድር የአክስት ልጅ ነው ብለው ለምን እንዲህ እንደሚፈሩት ነው እኔ የሚገርመኝ።

"…ያፈነዳሁት የቲክቶክ ፈንጂ ስንቱን እንደረፈረፈ እየቃኘሁ ነው። በሁሉም ቤት ዘወር፣ ዘወር እያልኩ ሳይ በሁሉም ቤት አጀንዳው እኔ ነኝ። እኔ ዘመዴ እኮ በቃ ይሄን አይደል እንዴ የምፈልገው? አጥንት እወረውልሃለሁ እሱ ላይ ለሃጭህን እያዝረበረብክ ስትለፋ እኔ ጋደም ብዬ እየከለምኩህ ፈታ እላለሁ።

• እስቲ እነ ዳማከሴ ቤት ልግባ ደግሞ። 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…በሉ ቤተሰብ… በርእሰ አንቀጹ ላይ አስተያየት እየሰጣችሁ ወደ ቲክቶክ መንደራችን እናምራ።

• እየሄዳችሁ ኮምቱ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ግንቦት 7፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ ኢህአፓ፣ ቅንጅት፣ ብአዴን፣ ወያኔ፣ ግንባሩ፣ ባልደራስ፣ ባላደራ፣ አፋህድ፣ አመድ ወዘተ ጋር የተነካኩትን እንደ ኢቮላ ቫይረስ ቆጥራችሁ ከአመራር እና ከገንዘብ ስፍራ አርቋቸው። የመርዝ ብልቃጥ ሕፃናት በማይቀመጡበት ስፍራ ነው መቀመጥ ያለበት። ተናግሬአለሁ።

"…አሁን ዘመኑ የወንፊት ዘመን ነው። የማበጠሪያ ዘመድ። ሰፌድ ላይ ትወጣለህ ትበጠራታለህ። ሚዛን ላይ የግድህን ትወጣለህ ትመዘናለህ ቀለህ ከተገኘህ ትወገዳለህ። እብቅ ነህ። መሬት ላይ ያሉት ፋኖዎች አሁን ችግር ላይ ናቸው አዎ ናቸው። ችግሩ እንደ ወንፊት ነው። ለሆዱ ብሎ የገባው ፋኖ ዶላሩ ሲቀር ወደ ዘረፋ፣ ከዚያ ወደ ቤቱ፣ አልያም ወደ ብልጽግና ይሄዳል። ለዓላማ የገባው ፋኖ ግን አፈር ደቼ እየበላ ተጋድሎውን በይፋ ይቀጥላል። የወሎ ዐማራ ፋኖ የእነ ምሬ ወዳጆ፣ የእነ ባዬ ቀናው የጎንደር ፋኖ፣ የእነ ዘመነ ካሤ የጎጃም ፋኖ፣ የሸዋው የእነ ኢንጂነር ደሳለኝ ፋኖ እነደነ መከታው ፋኖ ዶላር አላገኘም። እነ መከታው እኮ እስከ 500 ሺ ዶላር በአጭር ጊዜ ተሰጥቷቸዋል። አበበ በለው እኛ ምን ሠርተን እንብላ ብሎ እስኪያለቃቅስ ድረስ በጥበብ፣ ውስጥ ለውስጥ ተሠርቶ ነበር የደረሳቸው። እነሱ ግን የፂማቸውን ቁርጥ እያሳዩ ከመቀፈል በቀር ነቅነቅ አላሉም። ሥራ ፈት ጎሮምሳ ጫካ አስቀምጦ መቀለብ ደግሞ ግፍ ነው። ሳይረዱ፣ እርዱንም ብለው ሳይለምኑ ይኸው እነ ምሬ ጠላትን ይነዱት የለም እንዴ? ለእነሱ ቢረዳ እሺ። ሳይሠራ ምንአባቱ ስለሆነ ነው ግማሽ ሚልዮን ዶላር የሚቀለበው? ጥፋ በለው። ታነቅ። ስትሰድበኝ፣ መግለጫ ስታወጣብኝ ዋል። ሚልኢላል ኢሄ?

"…አሁን ምድር ላይ ያሉትን ፋኖዎች ትቼአለሁ። አሁን እኔ ሰቀቀን ውስጥ መክተት የምፈልገው የአየር ላዮቹን ጥቃቅን ቀበሮዎች ነው። ዋናዎቹ እዚያ አሜሪካ ያሉት ናቸው። እነ አምሳሉ አስናቀ፣ ምስጋናው አንዷለም፣ ሙሉጌታ አያሌው ደስታ፣ ኤርሚያስ እሹሹ ሽበሺ፣ ሕይወት በላቸው፣ ኢዮብ የቦስተኑ፣ ሃብታሙ ነጋሽ፣ ወንደሰን መኮንን፣ ሃብታሙ አያሌው፣ አበበ በለው፣ ዱኒ ተስፋዬ፣ ክንፉ ወዳጄ፣ ዶ/ር ደረጀ ተሾመ፣ ዩሐንስ ሙሉነህ፣ እንግዳሸት፣ ገነት ረታ፣ ቴዎድሮስ ከበደ፣ የሺ ወንድሙ፣ ወሮ እቴነሽ እና ወሮ ሸዊት ናቸው። (ሸዊት ማለት እንዴት ያለች እናቴ ነበረች መሰለቻችሁ። እስክንድር ነው የለያየን። በእስክንድር ምክንያት ነው እኔን መደገፍ ሁላ ያቆመችው። በየወሩ መቶ ዶላር ነበር ሚዲያዬን የምትደግፈው። ዘመዴ እስክንድርን ስለነካህብኝ ከዛሬ ጀምሮ አቁሚያለሁ ሳትለኝ ነበር ቀጥ ያደረገችው) በሉ አንድ ሰው በወሮ ሸዊት ቦታ 100 ዶላር ይዞ ይቅረብ። እነዚህን የወይኑን እርሻ ሊያበላሹ የሚችሉ ቀበሮችን አጥሩን ልናጠብቅባቸው ይገባል።

"…ከባላደራው እና ባልደራስ ጀምሮ፣ በገንዘብ ስብሰባው ላይ የነበሩትን የእስክንድር ነጋ ባለቤት ከወሮ ሰርካለም እና መስፍንን ጀምሮ እነ አበበ በለው እንዴት በዙም ገንዘብ ይሰበስቡ እንደነበር በቪድዮ ይዤ እመጣለሁ። ከግምባሩ ሙልጌታ ጋር እንዴት ዶላር ሲቀፍል እንደነበረም አጋልጠዋለሁ። አበበ ፀረ ሸዋ ነው። አበበ ሸዋን እንደ ጉድፍ ነው የሚፀየፈው። አበበ እስክንድርን ይዞ አቅም የለውም እንጂ ሸዋን ለማድቀቅ የማይቆፍረው መሬት የለም። አለማፈሩ ለሸዋ ሰዎች እየደወለ ይዘበዝባል። በሙሉ የደወለላቸው እየደወሉ እንዲህና እንዲህ እያለን ነው ይሉታል።

"…አበበ በለው ከእስክስ ወጥቶ የዐማራን ትግል ማዳበሪያ ዶላር ክስክስ ነው ያደረገው። በዋ ዐማራ ማኅበር በኩል የዘረፈውን ፈጣሪ ይወቅ። ቤት ገዝቷል። ቶዮታ መኪናውን በቴስላ ቀይሯል። ከእስክንድር ተጠግቶ፣ ከእነ ሀብታሙ ተጠግቶ፣ ከግንቦቴም፣ ከባልደራስም፣ ከስኳድም ተጠግቶ ዋነኛ ዓላማው ቁጢ፣ ዶላሩ ላይ ነው። አበበ በለው እንደ ሴተኛ አዳሪ ለከፈለው ሁሉ የሚተኛ ነውረኛ ሰው ነው። አበበ በለው ሆቴል ገብቶ ሒሳብ እንደማይከፍል የሆቴል ባለቤቶች በምሬት የሚያወሩት ነው። አበበ በለው በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር በዐማራ ስም በግልፅ እየሰበሰበ ሆቴል ገብቶ ለበላበት፣ ለጠጣው ሻይ የማይከፍል፣ ለአስተናጋጆች ጭምር ቲፕ የማይሰጥ ስቁንቁናም ነው። አስተናጋጆች እያሳሳቀን ሒሳብ ሳይከፍለን፣ ቲፕም ሳይሰጠን ነው የሚወጣው። እባክህ ዘመዴ ይሄን ሰው አንድ በልልን እስኪሉኝ ድረስ ነው ማፈሪያ የሆነው። አልፋታውም። ቪድዮ እየቆራረጠ የሚልክለት ልጅ አሁን ኡጋንዳ ገብቶ ሥራ አስጀምሮታል። ይሄም አያዋጣውም። እኔ በዐማራ ጉዳይ ድርድር፣ ቀልድ አላውቅም።

"…በመጨረሻም እላለሁ"…ወይናችን አብቦአልና የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮች፥ ጥቃቅኑን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን።" መኃልየ 2፣15። የምታስታውሷቸውን አሮጌም፣ ቀጭንም፣ ሽማግሌም፣ ወጣት፣ ጎልማሳ፣ ጥቃቅን ቀበሮችን ሁሉ እስቲ በስም ዝርዝር ጻፏአቸው። አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ እስያ፣ አውሮጳ፣ እስራኤል፣ በአረቢያ ምድር፣ በአፍሪካም አዲስ አበባም እንዳለው እንደ ፌስቡከር ጥላሁን ጽጌ ዓይነት የፈትለ የጭን ገረድ ፍርፋሪ ለቃቃሚ የስኳድ ቀበሮ ዓይነቶቹን አጋልጡ። እናጋልጥ።

• ዛሬ ቲክቶክ ገባ ብዬ እወጣለሁ እና ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁኝ።

• ጥቃቅን ቀበሮዎቹን በጋራ እናጥምድ…!

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

•••

ሻሎም.!  ሰላም.!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ.!
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ህዳር 3/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ.!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆② ከላይኛው የቀጠለ…✍✍✍ "…ዐማራው በኢትዮጵያ ስም ኢሣት የሚባል እሳት የሆነ ሚድያ ከፍቶ ላቡንም፣ ደሙንም አፍስሶ ሲጦረው፣ ሲቀልበው ነበር የከረመው። የኢሳት ጋዜጠኞች እየወፈሩ፣ እየደለቡ፣ እየቀሉ፣ የኢሳት ደጋፊ፣ ለኢሳት የሳታላይት ጣቢያ ገንዘቡን ሲያዋጣ የነበረው ዐማራው ግን እየከሳ፣ እየሟሟ፣ እየመነመነ፣ እየጫጫ ነበር የሄደው። የቤቱን ኪራይ፣ አሮጌ መኪናውን ሽጦ፣ እቁብ ጥሎ፣ ኩላሊቱ እስኪፈርጥ፣ በእንቅልፍ እጦት እስኪናውዝ ድረስ ጡዞ ያገኘውን ዶላርና ዩሮ ለኢሳት ለቀበሮዋ ሲቀልብ ከርሞ በመጨረሻም ኢሳት ቀበሮዋ አውላላ ሜዳ ላይ በትናው እሷ የኦሮሙማው ገሌ፣ ገረድ ሆና አረፈችው። እነ ደረጄ ሀብተወልድ እየተንተባተቡ ለአቢይ አህመድ ተገረዱ፣ እነ መሳይ መኮንን የለመደ ግርድናቸውን ዐወጁ፣ እነ ሲሳይ አጌና ጠቅልለው ተገርደው ገቡ። ዐማራው ተራራው በኢትዮጵያዊነት ስም ተሸወደ፣ ተበላ፣ ተጠጣም።

"…ልብበሉ፣ በኢትዮጵያዊነት ካባ ተጠቅልለው ከዐማራው ጋር አብረውት የነበሩት በሙሉ የማታ ማታ የቀበሮ ልጅ ቀበሮ ነውና ወደ ቀበሮነታቸው ሲሄዱ በጉ ዐማራ ብቻውን አውላላ ሜዳ ላይ ቀረ። እነርሱ በራሱ በዐማራው ገንዘብ ጎጆአቸውን ሲሠሩ አያውቅም ነበር። ዐማራነቱ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ሲገባው ገንዘቡን ለኤፍሬም ማዴቦ ሲቀልብ ከረመ። ለሲሳይ አጌና ሲገብር ከረመ፣ ንገሩኝ የዐማራ መሪ ሆነው ከርመው በስተመጨረሻ ዐማራውን እግርህን ብላ ያሉትን፣ አምጧቸው። ዐማራውን ያልበላ ቀበሮ አለ እንዴ? ተጫወቱበት እኮ። ኦሮሞው መስፍን ፈይሳ ሮቢ እንኳ በአቅሙ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ እያሳየ ዐማራውን ዶላሩን እጥብ ነው እኮ ያደረገው። ከሚስቴ ጋር ተጣላሁ፣ ጎፈንድሚ ክፈቱልኝ ብሎ ስንቱን ዐማራ ነው ያሾቀው። አፈር ከደቼ ያበላው። የዋህ በጉ ዐማራን በዐማራነቱ ተደራጅቶ የወይን እርሻውን ኮትኩቶ እንዳያሳድግ እንዴት እንደተጫወቱበት የግድ ወደኋላ ተመልሳችሁ ማየት ነው መፍትሄ የሚያመጣው። ዛሬ መስፍን ፈይሳ በዐማራ የሚያሾፍ፣ የሚያላግጥ ፀረ ዐማራነቱን የገለጠ ወፍራም ቀበሮ ነው። ደግሞ በመስፍብ ፈይሳ የሚሸወድ ያለ አይመስለኝም። ደግሞም አይጠፋም። ዝንጉ አእምሮ ያለው ዐማራ አይጠፋም ብዬ ነው።

"…የወይን እርሻው ደርሷል። ወፋፍራም ቀበሮዎች እየተጋለጡ መግቢያ መውጫ ቀዳዳም አጥተዋል። የዐማራ ገበሬም ነቅቷል። እግዚአብሔር ይመስገን። ተረፈ ቅንጅቶች፣ ፌክ ኢትዮጵያኒስቱ ሁላ ቆዳ ቀይሮ ቢመጣም የዘመኑ ትንታግ ዐማራ ድራሽህ ይጥፋ፣ ጥፋ ከዚህ ብሎ ድራሽ አባቱን አጥፍቶታል። እነ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ እነነአምን ዘለቀ፣ እነታማኝ በየነ ወፋፍራም ቀበሮ ስለሆኑ ወደ ዐማራው የደረሰ የወይን እርሻ ለመግባት አልተቻላቸውም። አጥሩ ጠብቋል። አያሳልፍም። ይሄ በቀላሉ የመጣ አይምሰልህ። ተሰድቤ፣ ተገፍቼ ፣ ተዋርጄ፣ እንደ ክረምት ዝናብ እንደ ዶፉ፣ እንደ በረዶው የሚዘንበውን ስድባቸውን ችዬ፣ ተቋቁሜ፣ እንደ በጋ ፀሐይ የሚያቃጥለውን፣ የሚለበልበውን፣ የሚያልበውን ጩኸታቸውን፣ ድንፋታቸውን ችዬ በድፍረት ቀበሮዎቹን ተጋፍጬ የወይኑን እርሻ ባለቤቶች ስላነቃሁ ነው። በዚህ አልፀፀትም። እኮራለሁ።

"…ዐማራው በኢትዮጵያዊነት ካባ ከተጠቀለሉት ከእነማዴቦ ልጅ፣ ከእነነጋ ቦንገር ልጅ ሲላቀቅ የወደቀው በእነ ዋቅጅራ የልጅ ልጆች በእነ ኤርሚያስ፣ በእነአፍራሳ የልጅ ልጅ በእነ ሀብታሙ፣ በእነ ሂርጶ የልጅ ልጅ በእነ ብሩኬ እጅ ነው። መረገም እኮ ነው አንዳንዴ። ተቀባብለው ጋጡት። ወይኑን ተጫወቱበት፣ መካከለኛ ጎረምሳ ቀበሮች ፈነጩበት። እነዚህን ተከትሎ ዐማራው አዚሙ እየተገፈፈለት፣ ሾተላዩ እየተነቀለለት ሲመጣ ደግሞ የእነዚያ የወፋፍራም ቀበሮዎች ሃይ ኮፒ ልጆች የበግ ለምድ ለብሰው የዐማራን የደረሰ፣ የሚያስጎመዥ የወይን እርሻ ለማውደም ተሰማሩ። የቅንጅት፣ የግንቦት ሰባቶቹ ቀበሮች ግንባሩ፣ ሰራዊቱ፣ ታፋው፣ ጭኑ፣ ቁርጭምጭሚቱ በማለት ተከሰቱ። ቀበሮቹ ባላደራ ብለው፣ ከዚያ ባልደራስ፣ ባልደራስ ብለው ከዚያ ግንባሩ፣ ግንባሩ ብለው ወዲያው ሠራዊቱ፣ ሠራዊቱ ብለው ወዲያው በፍጥነት ዐፋሕድ ብለው ተገለጡ። የዐማራውን ኪስ አጠቡት። አራቆቱት። እንደፈረደብኝ እኔው ጣልቃ ገብቼ አስቆምኩት። እየተሰደብኩ፣ እየተወገዝኩ፣ ፎቶዬ ተዘቅዝቆ እየተረገምኩም ቢሆን ዘልዬ ገብቼ ቀበሮቹ ጉሮሮ ላይ ቆሜ ቢያንስ የዐማራው ዳያስጶራ እንደ በፊቱ ገንዘቡን እንዳይበላ አደረግኩ። በዚህም እኮራለሁ።

"…ወፋፍራም ቀበሮዎቹ መፈራገጥ ላይ ናቸው። በዚያ ሲዘጋባቸው በዚህ ዊኒጥ ዊኒጥ እያሉ መንደፋደፋቸው አልቀረም። እኔም የዋዛ አይደለሁም እና ቀበሮዎቹ የሚገበቡበትን ቀዳዳ ሁሉ ድፍን በማድረግ ከዐማራ ኪስ የለመዱትን ዶላር፣ የዶላር ምንጭም አደረቅኩት። ከባላደራው፣ ከባልደራስ ጀምሮ ከእስክንድር ጋር በዐማራ ዳያስጶራ ገንዘብ ሕይወቱን ሲመራ የከረመው እንደ እስክስ አበበ በለው ዓይነቱ ወፍራም ቀበሮ አሁን አሁን ላይ ጠብ የሚልለት ነገር አጥቶ እየቃዠ፣ እየባዘነ ይገኛል። ዐማራ ከምንግዜውም በላይ ኪሱን ከግሪሳ፣ ወይኑን ከቀበሮች ጠብቆ ፍሬውን ለመብላት፣ ለመጠጣትም ከፈለገ አጥሩን ማጥበቅ ያለበት አሁን ነው።

"…የዐማራ ፋኖ፣ የዐማራ ትግል ማዳበሪያው ዶላር ነው። ማዳበሪያው ዩሮ ነው። ማዳበሪያው ሪያል፣ ሸክሉ ነው። ፓውንዱ ነው። ይሄን የዐማራን የወይን እርሻ ማዳበሪያ ዐማሮች ለዐማራ እርሻ ማከፋፈል፣ በወይኑ እርሻ ላይ መበተን ሲገባቸው የዐማራን ማዳባሪያ ጠልፈው ሲሸጡ፣ የዐማራ ወይን እንዲጫጫ፣ አፍሬ እንዳያፈራ ሲያደርጉ የነበሩ ሁሉ አሁን እጃቸው ተቆርጧል። መሬት ላይ ኦሮሙማው ነበር በብአዴን በኩል ለዐማራ ገበሬ ማዳበሪያ የከለከለው፣ በአየር ላይ ደግሞ ለዐማራ ፋኖ የወይን እርሻ ማዳበሪያው እንዳይደርስ ያደረጉት የአየር ላይ ቀበሮዎች ነበሩ። አሁን እነሱን ወደ ወይን እርሻው መግቢያ መንገዱን ጠረቃቅመን ስለዘጋንባቸው እንደ አበደ ውሻ ነው እየሆኑ ያሉት። አጥሩ ጠብቆ ታጥሯል። ወፋፍራሙም፣ ጥቃቅኑም ቀበሮ ወደ ዐማራ የወይን እርሻ እንደ ድሮው ሰተት፣ መሰስ ብሎ አይገባም። ዘበኛው፣ ጥበቃው እኔ ዘመዴ እንደ ገነት በር ጠባቂው ሱራፊ የእሳት ሰይፍ የመሰለ ጦማሬንና ምላሴን ስዬ ስለምጠብቃቸው ወፍ የለም። ዐማራው ጠብቅልኝ አላለኝም፣ ዐማራው አላዘዘኝም፣ ዐማራው አልቀጠረኝም። በፈቃደኝነት ነው የቆምኩት። ክፍያ የለውም፣ ደሞዝ የለውም። ማዘእረግ ሹመትም የለውም። የሚከፈለኝ አንዳች ነገር የለም። በነፃ ነው ለዐማራው የወይን እርሻ የቆምኩት። መብቴ እኮ ነው። አይደለም እንዴ?

"…የዐማራን ትግል በመጥለፍ፣ የደረሰ የወይን እርሻውን በማውደም፣ ለእርሻው የሚያስፈልገውን ማዳበሪያ ዶላር፣ ዩሮና ፓውንድ እንደ ሾተላይ ሲሰበስብ የከረመውንም አንድ የበግ ለምድ የለበሰ ሾተላይ እንዲደበቅ አድርጌዋለሁ። ቀበሮ ግንቦት ሰባቶችን ማርጀት ተከትሎ በኢትዮጵያኒስት ካባ ወደ ዐማራ የደረሰ የወይን እርሻ ሰተት ብሎ የገባው ቀጭኑ ቀበሮ እስክንድር ነጋ ነበር። እስክንድር ነጋ ትግሬዋን ሚስቱን ሰርካለም ፋሲልን፣ ኦሮሞውን ሻንጣውን ኤርሚያስ ዋቅጅራን፣ የሆላንዱን የቅንጅት ቋሚ የፊት መስመር ተሰላፊ መስፍን አማንን። (መስፍኔ ግን ዐማራ ነው?) ጠይቄው ስለማላውቅ ነው። ሙልጌታን፣ የጎንደር ስኳድ ሚስቱ የትግሬ ጁንታ ገንዘብ አሰባሳቢየሆነችው ዶር አምሳሉን ወዘተ ይዞ ነበር መጀመሪያ ባላአደራው ብሎ አዲስ አበባን በአዲስ አበባ ስም ዐማራውን ጋጠ። ዐማራንም ያለማዳበሪያ አስቀረ። ለዚህ ነው እኔ የእስክንድር ሚስት ገንዘብ አሰባሳቢ ነበረች ስል…👇② ከታች ይቀጥላል…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…የዘገየሁት ቀበሮዎቹን እያጠመድኩ ሰረለሆነ ነው። መጣሁ። እስከዚያው ድረስ እስክስ እያላችሁ በትእግስት ጠብቁኝ እሺ…?

• እሺ በሉኛ በማርያም…! ሃኣ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ወይናችን አብቦአልና የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮች፥ ጥቃቅኑን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን።" መኃልየ 2፣15

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለች…። ” ማቴ 27፥64

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አላችሁ አይደል…?

• እስቲ ገባ ገባ በሉ ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ይሄ የለንደን ፋኖ ነው…!

"…እንደ እከደከን ማንችሎት፣ በብልጠትም ሆነ በጉልበት አበጀ ጥላሁን ጉግሣ ቤት ገብቶ ለሽ ብሎ ተኝቶ የነበረው ዐማራ የእንቅልፍ አዚሙ ተወግዶለት በመጨረሻው ሰዓት ከጥልቅ እንቅልፉ ነቅቶ በት በት እያለ ነው። እኔም ስለቴን ለለንደኗ ማርያም ላስገባ ነኝ ማለት ነው። የለንደኗ ማርያም አሁንም የቀረውን ዝንጉ፣ ዳተኛ፣ አለቅላቂ፣ ወሬኛ፣ ሸውከኛ፣ ፈሪ፣ አስመሳይ፣ ገተት፣ ሆዳም፣ ማይም፣ የወገኑ ስቃይ የማይሰማው፣ ራስወዳድ ዐማራን አዚሙን አስወግደሽ አንድ ላይ እንዲህ ካቆምሽው ስለቴን አስገባለሁ።

"…እነ አዲስ፣ እነ ወርቁ ብቻቸውን ይጮሁበት፣ እነ ያየሽህራድ ብቻቸውን ዋይዋይ ይሉለት የነበረው ዐማራ ከፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ጉያ በተአምራት ተፈልቅቆ ወጥቶ እንዲህ ሲቀውጠው እንደማየት ምን የሚያስደስት ሌላ ነገር አለ?

"…አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አወሮጳ፣ አፍሪካም በሙሉ ይቀጥላል። ዐማራ ለመነሣት የፈጀውን ማገዶ ቢፈጅም መነሣቱ አይቀሬ እንደሆነ ዐውቅ ነበር። አሁንም ይቀራል። በዛሬ ምሽት የመረጃ ቲቪ መርሀ ግብሬ ይሄም ይዳሰሳል።

• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁኝ…!✊✊✊

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ይሄ መረገም ነው…

"…ደግነት መልክ ቢኖረው እሷን ነው የሚመስለው ተብሎ በያያ፣ ኢትዮጵያዊቷ ማዘርትሬዛ በፓስተር ምስጋናው አንዷለም ተብሎ ፕሮፓጋንዳ የተሠራላት፣ በእናቷ አዲስ ዘመን ግማሽ ቅማንቴ በአባቷ ኦሮሞ የደርግ ወታደር ልጅ እንደሆነች በሚነገርላትና ልክ እንደ እስክንድር ነጋ ስሟንም መልኳንም ፀረ ዐማራው ቡድን ቀባብቶ የዐማራ ሾተላይ አድርጎ ያዘጋጃት፣ የኢንተርኔት ላይ ማፍያዋ በተደራጁ የጎንደር ፀረ ዐማራ ኔትወርኮች አማካኝነት በተቸገሩ ዐማሮች ስም በቲክቶክ ወዘተ ዶላር ከዳያስጰራው በመግፈፍ ለተቸገሩት ዐማሮች ሳያደርሱ ይበሉ፣ ይሸቅጡ የነበሩት ቡድኖች በግፍ የሰበሰቡትን ብር ሳይበሉ በአገዛዙ ቁጥጥር ስር መዋል ጀምረዋል።

"…በተለይ ጎንደር ቀበሮ ሜዳ ላይ ፈስሰው በቁማቸው ትል የሚረግፍባቸውን የዐማራ ተፈናቃዮች ታስታውሳላችሁ። እነ መማር አለባቸው እና በእሷ ጀርባ የነበሩት የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎች 1ሚልዮን ብር ሰብስበው እንዳስቀሩባቸውም እንደነገርኳችሁ ታስታውሳላችሁ። ዋነኛው የመማር አለባቸው የጎንደር የዘረፋ ወኪልንም እነ አያሌው መንበር ለተፈናቃዮቹ መርዳትን እንደ ነውር ቆጥረው አፋቸውን በከፈቱብኝ ወቅት የጎንደሩን ወኪላቸውን ቢያንስ እግዚአብሔር ፍርዱን እስኪሰጥህ ዝም በል ማለቴም ይታወሳል።

"…ይህው ዛሬ በጎንደር የእነ መማርን ተወካይ በባንኩ ውስጥም ከ14 ሚልዮን ብር በላይ ዘጭ ብሎ፣ የተለያዩ መኪኖችንም በስሙ ገዝቶ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል። በተፈናቃይ ብቻ ሳይሆን በፋኖዎችም ስም የተሰበሰበ ገንዘብ አለና ፋኖዎችም ገንዘባችንን ስጠን እያሉት፣ ለድሆቹም የተዋጣውን ብር ሳይሰጥ ብሩ የአገዛዙ ቀለብ ሆነ።

• እነ ምስጋናው አንዷለም ሆይ…! አቦ እግዚአብሔር አምላክ የእጃችሁን ይስጣችሁ። በማታው የመረጃ ቴቬ የነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ በሰፊው እመጣበታለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…9

"…በመጨረሻም…በመጨረሻም ያ ሞኝ መስሎ፣ ሀገር መውደዱ እንደ ፈሪም እንደ ፋራም፣ አንዳንዴም እንደ አድርባይ አስቆጥሮት፣ ታላቋን ሀገር ኢትዮጵያን ይመራ ዘንድ ሕፃን መሆኑን ያልተማረ ማይም መሆኑንም እያወቀ፣ ጨቅላ ቢሆንም ግድየለም እየታገዘ ያድጋል፣ ይሁን ብሎ ድጋፍ ሰጥቶ፣ አንድም ኢትዮጵያን ስሟን እየጠራ፣ ሰንደቋን ለብሶ እየማለ እየተገዘ ቢያየው አያታለለኝማ አይሆንም፣ ግድየለም ጊዜ መስጠትም አይከፋም፣ አያስከፋም፣ ሽግርም የለውም፣ በማለት ለበሸሻሻው አራዳ ለአራጁ አቢይ አሕመድና ለአረመኔ ግሩፖቹ ዕድል የሰጠው፣ ያ በጊዜ አልነቃ ብሎ ጭራሽ እየሰደበኝ ጨጓራዬን ሲልጠኝ የከረመው ታላቁ የዐማራ ሕዝብ አሁን ትእግስቱ አልቆ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማድረግ ማስታወቂያ ለጥፎ ቀጠሮ ይዞ ተነሥቷል።

"…ሰልፉ ዓለም አቀፍ ነው። ትግል ጠላፊ ግንቦቴ፣ ፌክ ኢትዮጵያኒስቶች፣ ግንባሩና ታፋና ጭኑም ግን ሰልፉን ሊመሩት አይገባም። አይፈቀድላቸውምም። ሰልፉን ዐማሮችን ይመለከታል፣ ዐማሮችም ይመሩታል። ለዐማራ ያዘኑ፣ ነግ በኔ ብለው ያሉም ቤርቤረሰቦች ግን በሰልፉ ላይ በመሳተፍ ለዐማራ ሕዝብ አጋርነታቸውን ያሳዩታል ተብሎም ይጠበቃል።

• መግደርደር የለም፣ ወጥር ዐማራ…! 💪💪🏿💪🏿👏

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ተቀበል…6

"…ዐማራ እንዲህ ጥርሱን ነክሶ በባዶ እጁ ከቱርክ፣ ከሳዑዲ፣ ከኢራንና ከሳዑዲ አረቢያ በሚላክ የአቢይ አሕመድ ድሮን ጋር የሚዋጋው የሚሳፈጠው ለቄንጥ አይደለም። አሁን ተሰልፈህ ብትስቅበት፣ በቲክቶክ ስትሰድበው፣ ስትፎትተው ውለህ ብታድር መስሚያው ጥጥ ነው። ደንታውም አይደለም። አባቴ አሁን እሱ ጥርሱን ነክሶ፣ ወገቡን ታጥቆ ለይመለስ ተነሥቷል። የቀን፣ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው እንጂ እመነኝ ዐማራ ድብን አድርጎ በዝረራ ያሸንፋል።

"…አልሙት፣ አልፈናቀል፣ ደመከልብ አልሁን፣ አልዘረፍ፣ የዜግነት መብቴም የሕግ የበላይነትም ይከበር ብሎ በመጠየቁ እነ ትግሬው አባ ሰረቀ ሳይቀሩ "ዐማራ የሚባል ዘር የለም፣ ከዚያም ከዚህም ተለቃቅሞ የመጣ ልቅምቃሚ ነው ብለው ፍትህ ስለጠየቀ ብቻ ከፍ ዝቅ አድርገው በድፍረት አፋቸውን ሞልተው ሰደቡት። ተላገዱበት። ወዳጄ ያ "የለም" የሚሉትን ዐማራ ግን ቤቱ ድረስ ሄደው ሊያጠፉት ሲፈልጉ "ዐማራ የት ነው? ሂድ ወደ ክልልህ በማለት ሲጨፈጭፉት ይታያሉ። እንደ ጫጩት እኮ ነው የፈጁት። ይሄ አልበቃ ብሏቸው በሦስት ሳምንትም ሱሪውን እናስፈታዋለን ብለው ቤቱ ደጃፉ ድረስ ቢሄዱም ይኸው አጅሬው ዐማራ ለኅልውናው ሲል የእህቱን፣ የሚስት የእናቱን በግፍ መታረድ እያሰበ እንዲህ እንደከፍት እየነዳው ይገኛል።

"…የጊዜ፣ የቀን ጉዳይ ነው እንጂ ማርያምን ስልህ ዐማራው ድብን አድርጎ ያሸንፋል።

• እየኮመታችሁ…✍✍✍

Читать полностью…
Subscribe to a channel