መልካም…
"…እዚያው መርጡለ ማርያም ነኝ። ምን የመሰለ የዶሮ ዓይን የመሰለ ጠላዬን እየለጋሁ ግሩም የሆነ ወግ ላይ ነኝ። አየር ላይ ሳለሁ የጀመርኩትን የቼዝ ጨዋታ ንጉሡን "ቼክ ሜት" አድርጌው ነው የመጣሁት። ጎጃም የመጨረሻው የዐማራ ትግል የሚነቀልበት ሰንኮፉ ያለበት ነው። እናም እዚያ ነው ያለሁት። ቢንጎ።
"…በእኔ በዘመዴ የተቀጠቀጡት እነ ብአዴን፣ ብልፅግና፣ አገው ሸንጎ፣ ኦነግ፣ የጎንደሩ ስኳድ በሙሉ ጮቤ ረገጣ ላይ ናቸው። እኔም የያዝኩትን ስለያዝኩ ተንፈራገጡ እያልኳቸው ነኝ።
• ደግሞ ልመጣ ነኝ። አንድ ለእናቱ ሺ ለጠላቱ እኔ ዘመዴ ላንጫጫቸው፣ አጀንዳም ልሆናቸው ልመጣ ነኝ።
"…በፔጄ ገብተህ እሳደባለሁ፣ ፀያፍ ቃል ሌላውንም እሰድባለሁ የምትል በረሮ፣ ቁጫጭ፣ ዘመመሚት፣ ጉንዳን ግሪሳ ካለህም ብሎክ ባን በሚባለው ሰይፌ ቀስፌ እንድትናፍቀኝ አደርግሃለሁ። ስድብ ላያስቆመኝ በጨዋ ደንብ አርፈህ የነገሩን ፍጻሜ ተከታተል። የእኔዎቹ እኔ ያላየሁት ባለጌ ስድአደግ እናንተ ካያችሁ ክፉ አትመልሱለት። ብቻ 👉🏿 እንዲህ እየጠቆማችሁ ዘመዴ Block ብቻ ብላችሁ አቃጥሩልኝ። ከዚያ ጨጓራ በሽታ፣ የደም ግፊቱ እንዲነሣበት አድርጌ እቀስፈዋለሁ።
• እኔ አጀንዳ ነኝ በቃ። ስለ እኔ ብቻ እንድታወራ፣ እንድትጽፍ የማድረግ አቅምም ችሎታም አለኝ። ከዘመዴ ቴሌግራም ውጡ ብለህም መልሰህ ቁጥሩ ቀነሰ ትለኛለህ። እኔ ዘመዴ ሱስ ነኝ። ልትፋታኝ አትችልም። እየጠላኸኝ እናፍቅህሃለሁ። እየዠለጥኩህ፣ እየወገርኩህ ከስሬ አትጠፋም። ምክንያቱም እኔ ዘመዴ ነኝ።
• ጃል ቆቱ ወዲ አስገዶም ነኝ። 😂 አላችሁ አይደል? ርእሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ አይደል?
• የጎጃሙን ሸንጎ፣ ቅባቴና ብአዴን አፍቃሬ ወያኔውን የኦሮሙማ ገረድ ላንጫጫቸው ነኝ።
• ቀድሜሃለሁ አባው…!
"…ወዳጄ አሁን ያለህ ምርጫ አንድና አንድ ብቻ ነው። ይሄ በኢንተርኔት ላይ የሚጮኸው ግሪሳ አያዋጣህም። ነገ ዛሬ ሳትል በሴራ ያፈራረስከውን የዐማራን አንድነት በቶሎ መልስ። እገሌ እምቢ ብሎ ነው፣ ብላ ብላ የሚለው ዝባዝንኬህ አይሠራም። ፍጠን ብዬሃለሁ፣ ነግሬሃለሁ። ለአንድነቱም ቢሆን የጎጃም አመራር በአስረስ ምትክ ሌላ የተማረ ሰው ይላክ። ያለበለዚያ አደጋ ነው።
"…አንት ሰው መሳይ በሸንጎ ከዚያ በኋላ በሰረቅከው ልክ እጠይቅሃለሁ። በገደልከው፣ ባስገደልከው ልክ እሞግትህሃለሁ። መርጡለ ማርያም ላይ ብቻ ያስጨፈጨፍካቸውን ወጣቶች ደም በፈጣሪ ስም እጠይቅሃለሁ።
"…እኔ አስረስን መሞገቴን እቀጥላለሁ። አገው ሸንጎ፣ የጎንደር ስኳድ፣ ብአዴን፣ ፀረ ዐማራው፣ ቅባቴው በሙሉ ተንጫጫ፣ ታነቅ። ሙት ስትፈልግ። እስቲ ስታስጥሉት አያለሁ። ዘመነ ካሤ ያለበትን ጭንቀት ፎቶዎችን አይቶ መገመት ይቻላል። እኔ አስረስን ለጠየቅኩት ዘመነን መግለጫ ስጥ የሚሉት ዘመነ ምን አገባውና ነው? እኔ ይሄን አፍቃሬ ትግሬ ወያኔ የብአዴን አሽከር ነው እየጠየቅኩ፣ እየተሟገትኩ ያለሁት። መዳን ያለበት የዐማራ ፋኖ በጎጃም እንጂ ግለሰብ አይደለም።
"…ደግሞ በላቤ፣ በወዜ፣ ለምኜ ያቆምኩት የመረጃ ቴሌቭዥንም ሆነ ቲክቶክ ራሱ ሳያስፈልገኝ፣ በቴሌግራም ጦማር ብቻ አሳይሃለሁ አልኩህ። ጎጃም የተተከለውን ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ተዋሕዶ ጨፍጫፊ ቡድን ብቻዬን ልክ አገባዋለሁ።
"…ቴዎድሮስ ትርፌ ፈረንጁን ልኮልህ የዐማራ ፋኖ የወልቃይት ጨፍጫፊ ነው ብለህ፣ መጀመሪያ እስረኛ የትግሬ መኮንኖችን፣ ቀጥሎም ምርኮኛ የትግሬ ኮሎኔሉን ፈትተህ ለወዳጅህ ህዋሓት አሳልፈህ ሰጠህ። ማርያምን አስረስ መዓረይ ሆይ አልፋታህም። ከእስክንደር ጋር የግል ጠብ እኮ አልነበረንም። ያጣላን የዐማራ ጉዳይ ነው።
•ቀድሜሃለሁ አልኩህ…🫡
መልካም…
"…አሁን ደግሞ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በርእሰ አንቀጹና ከርእሰ አንቀጹ ቀጥሎ በሰጠሁት ማብራሪያ ላይ እናንተ ደግሞ አስተያየታችሁን ስትሰጡ ታመሻላችሁ።
"…በኦሮሙማው ቤት የመረጃ ቴሌቭዥን ከአየር ለመወርድ መወሰን ጮቤ አስረግጧል። አልማዝ ባለጭራዋና ሴቭ ኦሮሚያም ርችት የመተኮስ ያህል ተደስተዋል። ሆኖም ግን አገልግሎቴም፣ ትግሌም በዚሁ ይቀጥላል።
"…በኋላ በማርያም በአላህ ጠጥቼ ነው፣ ተናድጄ ነው መልሰኝ ብሎ ጭቅጨቃ አይሠራም። ስድብ፣ ፀያፍ ቃል ያስቀስፋል። በጨዋ ደንብ ሓሳባችሁን ግለጹ። እርስ በእርስ መሰዳደብም፣ ለእኔ ተደርቦ መሳደብም አይቻልም። ፈጽሞ አይቻልም።
• 1…2…3… ✍✍✍ ጀምሩ።
መልካም…
"…23 ሺ ሰው አንብቦት 103 ሰው ብው ጓ ያለበትን የዛሬውን ርእሰ አንቀጽ አንብባችሁታል። አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ በጨዋ ደንብ፣ በሰለጠነ መንገድ የምታቀርቡት ዐሳብ የሚደመጥበት ወቅት ነው። ትተነፍሳላችሁ።
"…በዛሬው ርእሰ አንቀጽ ላይ መርዶ እንደሰማችሁ ይገባኛል። የጎጃም ጉብኝቴ ዓሣ ጎርጓሪ ሆኖ ዘንዶ ማውጣት መጀመሩም ታይቷል። ላለፉት 6 ዓመታት የዐማራ ሕዝብ ድምጽ በመሆን ሲያገለግል የከረመው መረጃ ቴቪም ጠበቃ አስረስ ባስነሣው አዋራ፣ እነ አዝማሪት አልማዝ ባለጭራዋ መገርሳ፣ እነ ወዲ ተስፋዬ ወልደሥላሴ ተስፋዬ፣ እነ ይኸነው የሸበሉ፣ እነ አማኑኤል አብነት ባስነሱት የስኒ ላይ ማዕበል ማኔጅመንቱ አጣብቂኝ ውስጥ በመግባቱ ምክንያት ተቋሙ እኔንም የጎጃሙን የሴራ አባት የአስረስ ጠበቆችንም ላለማስቀየም፣ አስረስ ከተተቸም ደም ሊፋሰስ ይችላል ያሉትንም ቃል ይዞላቸው በቃ ከሐሙስ ጀምሮ ከአየር ላይ እወርዳለሁ ብሎ እቅጩን ተናግሯል።
"…መረጃ ቴቪ እኔም ጠይቆኝ ነበር። ዘመዴ ይሄን የጎጃም ጉብኝትህን ለጊዜው ትተወው ወይም ደግሞ ልታዘገየው ትችል ይሆን ብሎኝም ነበር። እኔም ኧረ በፍጹም አልተወውም፣ አላዘገየውምም። በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎንደር ተዟዙሬ ስጎበኝ እንዲህ ተብዬ ያልተጠየቅኩ አሁን በጎጃም ምንም ሳልተነፍስ የምጠየቀው ለምንድነው? ጭንቀታችሁ ይገባኛል። ይልቅ እኔ ከአየር ላይ አውርዱኝ። እኔ እኮ በባዶ ሆዴ፣ ውኃ ሳልጠጣ ደርቄ ልቤን እስኪደክመኝ ስጮህ የማመሸው ለዚያ መከረኛ የዐማራ ሕዝብ ድምጽ ለመሆን ብዬ ነው። የሳታላይት ክፍያውን ገዳም እንደሚያሠራ ሰው ቁጭ ብዬ ስለማርያም፣ በሚካኤል እያልኩ የምለምነው ጢና ስባሪ ሳንቲም ተከፍሎኝ አይደለም። ዜሮ አምስት ሳንቲም አይከፈለኝም። እናም በእኔ ምክንያት የመረጃ ቴቪ ከአየር ላይ ወርዶ የዐማራ ብቸኛው ድምፅ የሚሆንለት ልሳን ከሚዘጋ የእኔ ነጭ ነጯን መርሀ ግብር ከአየር ላይ ይውረድ እና እነ አስረስ መዓረይ በሚመድቡት ሰው ካለም ቴሌቭዥኑ በሌሎች መርሀ ግብሮቹ የዐማራ ድምጽ ሆኖ ይቀጥል። እነ 251፣ እነ በለጠ ካሣ፣ እነ ሞገሴ፣ እነ ጋሽ አዲሱ አበበን የመሳሰሉ ባለሙያዎች ከአየር ላይ መውረድ የለባቸውም በማለት ጠይቄም ነበር። ተቋሙ ግን በፍጹም አናደርገውም አንተን ማውረድ አይሆንልንም፣ በእነዚያም ዛቻ ምክንያት ችግር ቢፈጠር መረጃ ቴቪ ስሙ እንዲነሣ አንፈልግም በማለት ውሳኔአቸውን እያዘኑ አሳውቀውኛል።
"…ባዳ ሁል ጊዜም ባዳ ነው። ዐውቃለሁ የሆነ ቀን በሆነ ዐማራ ነኝ በሚል አካል እንደምከዳ፣ በጎጃም ይሆናል ብዬ ግን ለአፍታም ታህል አስቤው አላውቅም። በጭራሽ አስቤው አላውቅም። የሆነው ሆኖ ግን እኔ ለዐማራ ሕዝብ ቃል ነው የገባሁት። ቃሌን አልሽርም። ቃልኪዳኔንም አላፈርስም። ማዕተቤንም አልበጥስም። እኔ ሸዋ ውስጥ አበበ ጢሞን አምበርክኬዋለሁ፣ ጋሽ አሰግድንም በሁሉም ፊት ገስጫለሁ፣ ቢያኮርፉኝም እንደ ጎጃም ሸንጎ አልሆኑብኝም። ወሎም ሄጄ ድሮ ጥንት አንዴ ምሬ ወዳጆን፣ ኋላ ላይ ኮሎኔል ፋንታሁን ላይ ጓ ብያለሁ። ምሬም አሁን ድረስ ወዳጄ ነው። ከጥቂት የደቡብ ወሎ በሃይማኖት ምክንያት ጓ ከሚሉብኝ የወሃቢይ እስላሞች በቀር የከፈ ነገር ከመሪዎቹ አልገጠመኝም። ጎንደርም ዘልቄ ከስኳድ ጋር ግብግብ ገጥሜአለሁ። ጋሽ መሳፍንትን በሽምግልና ወቅት ገስጫለሁ። ኤፍሬምን ጋሽ መሳፍንትን ያልተገባ ቃል ተናገርሃል ብዬ ከሽምግልናው ውይይት መድረክ አሰናብቼዋለሁ። ይቅርታ ጠይቆ ነበር የተመለሰው። ሳሚ በለድልን ተቆጭቼ ገስጬ በሁሉ ፊት ወደ መስመር መልሼዋለሁ። ቢዘገዩም ዛሬ ምርት ከገለባ ከግርድ ለይቶ እነ ባዬና ሀብቴ ወደ አንድ መጥተዋል። ገና እነ ደረጄ በላይም ወደ አንድ ይመጣሉም ብዬ ተስፋ የማደርግ ነኝ።
"…ይሄ ሁሉ ሲሆን ከባድ መግለጫና መረጃ ቴቪን ከሩዋንዳው የዘር ጭፈጨፋ ጋር አያይዞ በሀሰት በፋኖዎቹ ስም መግለጫ ያወጣብኝ የጎንደሩ ስኳድ ነው። ፓስተር ምስጋናው አንዷለም፣ የሀሰተኛው ኢየሱስ አምላኪ በሀሰት መረጃ ቴቬን እና እኔ ዘመዴን ከስሶን፣ እነ አበበ በለው፣ እነ ሲሳይ ሙሉ፣ እነ ዶር አምሳሉ፣ እነ ሀብታሙ አያሌው ሁላ ሰበር ዜና ብለው መግለጫ ሁላ እስኪያወጡ ድረስ ለፍተው ነበር። በወቅቱ እኔ ድርቅ ብዬ መግለጫው የውሸት ነው፣ መሬት ላይ ያሉ ፋኖዎች የፈለገ ቢቀየሙን የዚህን ያህል ስድና ባለጌ አይደሉም። ብዬ ተማግቼ ነበር። እኔ ልክ ነበርኩ፣ ሀብቴና ባዬ ውሸት ነው እኛ መግለጫ አልሰጠንም ብለው መግለጫ አወጡ። ይሄን ነውር የሠራው ፓስተር ምስጋናውም በሀፍረት ወጥቶ ይቅርታ እኔ ነኝ ያደረግኩት ብሎ አመነ። እኔም አሸነፍኩ።
"…አሁንም ወደ ጎጃም ስመጣ እንዲህ ዓይነት አዋራ ይነሣል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር። የሚበሳጩ ይኖራሉ እንጂ እንዲህ የመረጃ ቴሌቭዥንን አመራሮች እዬዬ ብለው የመረጃ ቴሌቭዥን ከአየር ላይ እስኪወርድ ያስጨንቁታል ብዬም አልገመትኩም ነበር። የሆነው ሆኖ ገና ለገና የተደበቀ ወንጀሌ፣ ግፌ፣ ኃጢአቴ በዘመዴ በኩል ለሕዝብ ይፋ ይሆንብኛል ብሎ ያሰበው ማፍያ የብአዴን ቡድን አዋራ አስነሥቶ ለዐማራ ሕዝብ ያለምንም ጥቅም ዋጋ የከፈለውን የመረጃ ቲቪ ከአየር ላይ እንዲወርድ ምክንያት ሆነው ተገኝተዋል። እርግጥ ነው በእኔ በዘመዴ ምክንያት ያለ ምንም ቤሳቢስቲን ክፍያ መረጃ ቲቪን የፈጠረው ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ በዋን ዐማራዎች በእነ አኪላና ዘርዓ ያዕቆብ ምክንያት ከራሱ አልፎ የአያቱ ፎቶ ተዘቅዝቆ ተሰድቧል። እውነት ነው በእኔ ምክንያት የመረጃ ቴቪ መሥራቾች የተከበሩት አቶ ሰለሞን እና ወሮ መሠረት በእነ አኪላና ዘርዓ ያዕቆብ ፎቶአቸው ተዘቅዝቆ ተስደበዋል። አበበ በለው ከእጃቸው የበላውን እነ ጋሽ ሰለሞንን በአየር ላይ ሰልፍ ጠርቶባቸዋል። ዘመድኩን ከመረጃ ቲቪ ይውረድ የሚለው በጎንደር ተሞክሮ የከሸፈው በጎጃም ተሳክቷል።
"…አንድ ተቋም ሳይኖር፣ አንድም ሰው ሲሞት ወይ ሲርቅ ነው ጥቅምና ጉዳቱ የሚታወቀው። መረጃ ቴቪ ከኪሱ ጭምር እየከፈለ ሕዝብን ያገለገለ ተቋም ነው። እናም የመረጃ ቴቪ ያለመኖር የሚጠቅማቸው ቢኖርም የሚጎዱት ግን ሚልዮኖች ናቸው። እንግዲህ ዐማራ አዝማሪት ቤተልሄም ዳኛቸው ድምጽ ትሁንለት። እነ አይተ ተስፋዬ ወልደሥላሴ ድምጽ ይሁኑለት። የጎጃም ዐማራ ፋኖ በዚህ ቆሻሻ አሳፋሪ የዐማራን ሕዝብ ድምጽና ልሣን በስዘጋ ተግባር ላይ በመጠቀሱም አዝናለሁ። ከምር አዝናለሁ። ቢያንስ እኔ የሆነ ከባድ ነገር አስቀርቻለሁ። በጣም ብሩቱ አደገኛ ነገር አፍርሻለሁ። አክሽፌአለሁም። ነገ ብርሃን ሲመጣ የሚገለጥ አደገኛ ነገርም አስቀርቻለሁ።
"…ዛሬ መረጃ ቴቪ ከአየር ላይ የመውረዱ ዜና በተሰማ ዕለት ጠበቃ አስረስ መዓረይ በማርሸት ፀሐዩ በኩል ሁለት የሚዲያ አካላትን ለቴሌቭዥን ዝግጅት እና ለማኅበራዊ ሚዲያ ሓላፊ አድርጎ መሾሙን አይቻለሁ። የተሾሙትም ፋኖ ጥጋቡ መኮንን እና ፋኖ ጋዜጠኛ ወግደረስ ናቸው። ፋኖ ጥጋቡም የመርጡለ ማሪያም ልጅ ነው። በሙያው የባንክ ሠራተኛ የነበረ የአስረስ ቀኝ እጅ ነው። ከአስረስ ጋር በወንጀል የሚከሰስ ሰው ነው። ወግደረስም የምሥራቅ ጎጃም ልጅ ነው። ጠበቃ አስረስም ሚዲያውን በምሥራቅ ጎጃም ልጆች አስይዞታል ማለት ነው። ጥያቄዬ እንዴት ነው የዐማራ ፋኖ በጎጃም በምሥራቅ ጎጃም ልጆች ብቻ ቁጥጥር ስር ሊወድቅ የቻለው? ቲክቶኩ ላይ፣ ፌስቡኩላይ እነርሱ ብቻ ሆነው በሌላውም እንደዚህ የሆኑት ለምንድነው? ምሥራቅ ጎጃምን ለብልጽግና እና ለሚሊሻ አስረክቦ መሸሽ፣ መፈረጠጡ ሳያንስ እነ ጥላሁን አበጀ ምዕራብ ጎጃምም ሄደው የሚሾሙት፣ የሚሸለሙት👇✍✍✍
👆③✍✍✍ "…በራሱ ጊዜ ውጊያ ጦርነት ከገጠመኝ ከወዳጄ ከአስረስ ማረ ዳምጤ ጋር ያለኝን ምርመራ ስጨርስ ሌሎቹንም እንደየ ድርሻቸው እጎበኛቸዋለሁ። መጀመሪያ ግን ዘሎ መጥቶ በጫጫታ ያስቆመኝ ይመስል ከተላተመኝ ከአስረስ መዓረይ ጋር እንጨርሳለን። በጨዋ ደንብ ነው የምጠይቀው። ለእኔ በቀጥታ ባይመልስም በዐማራ ክልል ኔትወርክ ተዘግቶ 24/7 በማይዘጋው ፌስቡኩ፣ ወይም ወዳጁ ሞገስ ዘውዱ፣ አልያም መሳይ "በፖለቲካዊ ድንግልና" ቋንቋ መሳይ መኮንን ጋር ደውሎ ይመልስልኛል። ሌላህ ብትንጫጫ ግን ምንም አባክ አታመጣም። ምንም አልኩህ። ምንም አታመጣም። ስሙኝማ እኔ ዘመዴ ብደነፋ፣ ሄጵ ብል በእጄ የያዝኩትን ይዤ ነው። አዳሜ እና ሔዋኔ ሆይ እኔ ዘመዴ አንድ ከባድ የሆነ መረጃ በእጄ ሳልይዝ ወደ አደባባይ እንደማልወጣ ታውቃለህ። የኋላ ታሪኬም የሚያሳየው ይሄንኑ ነው። እና መረጃውን ሳላወጣ ሟምቶ ወደ መስመር እንዲገባ ነው የማደርገው። እኔና አስረስ ለምንነጋገረው ዘመነ ካሤን ማስጨነቁስ ምን ይጠቅማል? ምነው ከዚህ በፊት ዘመነን ስጮህበት እንዲህ አልተሯሯጣችሁ? ምነው ንገሩኝ እንጂ? እነ ሞጣ፣ እነ አልማዝ ባለጭራው፣ ዋን አዋራዎች ዘመነን እስከዛሬ ሲወቅጡት ምነው ለዘመነ እንደ አስረስ አልተንፈራገጣችሁለት? የሆነው ሆኖ የሆነ ሴራማ አክሽፌአለሁ። አስረስም ሆንክ ሌላህ ለራስህ ስትል ከእንግዲህ ዘመንንም ሆነ ልጁን ሳል፣ ጉንፋን እንኳ እንዳይዛቸው ትጠነቀቅለታለህ። የነብሩን ጭራ ይዤዋለሁ። በዘንዶው፣ በድራጎኑ አንገትም ላይ ቆሜአለሁ።
"…ጎንደር ገብቼ ጉረሮ ለጉረሮ ስተናነቅ፣ የጎንደር ጠላት ነው። ጎጃሞች ገዝተውት ነው። ከፍለውት ነው ስባል አይደል እንዴ? ነበር አይደል? ትናንት እኮ ነው እንዲያ ስባል የነበረው። ሸዋም ገብቼ፣ ወሎም ገብቼ ስናገር በጠላትነት ስፈረጅ ነበር። እንዲያውም እኔ ጎጃም ስገባ እኮ ግርማ አየለ "ዘመድኩንን እንደ ኮንዶም ተጠቅመንበት ጥለነዋል፣ ጋርቤጅ ውስጥም ከትተነዋል፣ ከእንግዲህ ዘመድኩን አይጠቅመንም ነበር አይደል ብሎ የጻፈው?" ብዙ የጎንደር ስኳዶች ሲሉኝ የነበረውን ነበር የደገመው። እና እኔ በንፁሕ ህሊና ለማንም ሳላዳላ ጎንደር ስኳድ ላይ ያነሣሁትን ጎጃም ሸንጎ ላይ የማላነሣበት ምክንያት ምንድነው? እስቲ ከፋዮቼ ክፍያቸውን ያቋርጡብኝና እኔ ስጎዳ ልታይ፣ ስጎዳ ልገኝ። እኔ የማውቀው እስከአሁን ወደ እኔ የሚደውሉ የጎጃም ልጆች ከአፋቸው ክፉ ሲወጣ ያለማየቴ ነው። ሸንጎ በጎጃም ስም ቀውጢ እየፈጠረ ነው። በባህርዳር ዊኪሊክስ በኩል የከፈትክብኝንም አስጠሊታ፣ ቀፋፊ ሰገራ የመሰለ ዘመቻም ገትሮ ተጋፍጦ የመለሰልኝ፣ የመከተልኝም ባለ አእምሮው የጎጃም ሕዝብ ነው። ኮመንቶቹን ሳይ እንዴት እንባዬ እንደፈሰሰ እኔና አምላኬ ነን የምናውቀው። አሁን የጎጃም ዐማሮች ግን ነገሩን በጥሞና እያጤኑት ነው። መፍትሄውም ቀላል ነው። ተቋም እንጂ ሊገነባ የሚገባው ግለሰብ አይደለም። በግለሰብ ላይ የተንጠላጠለ ተቋም ፈራሽ ነው። ለእኔ ከአስረስም፣ ከዘመነም ይልቅ የጎጃም ዐማራ ፋኖ ነው መቅደም ያለበት። እነሱ ሰዎች ናቸው። ነገ ሊክዱ፣ ሊማረኩ፣ ሊሞቱ ይችላሉ። ድርጅቱ ከሰዎች ጋር አብሮ መፍረስ፣ መሞት የለበትም። እኔ የማስበው እንደዚያ ነው። ዐማራ ያሸንፋል።
"…ለወንድሜ ለአስረስ መዓረይ አሁንም ወንድማዊ መልእክቴን ከአክብሮት ጋር ልነግረው አፈልጋለሁ። በቴክስት ፈልገህ ያገኘኸኝ አንተው ነህ። ሁሉም የጎጃም ፋኖ አመራሮች አስረስን አውራው ሲሉኝ በፍጹም አላወራውም ስል እንደኖርኩ መረጃው አለህ። በስልክ ፈልገህ፣ ደውለህ ያገኘኸኝም አንተው ነህ። መልካም በሰላም እንኳን በሰላም መጣህ፣ እንግዲያው ከመጣህ አይቀር ምርመራዬን ልጀምርብህ፣ ቃልህን ልቀበልህ ብዬ ምርመራዬን ተቀብለህ ቃልህን የሰጠኸኝም አንተው እኮ ነህ። የምርመራዬን ጥያቄዎች ብዙውን መልሰህልኝ ስታበቃ ጥቂት ሲቀረኝ ለሰኞ ተቀጣጥረን በዚያው የጠፋኸውም አንተው ነህ። መጥፋትህ ሳያንስ በዚህ በኩል ባስቆመው፣ ባሸማቅቀው ብለህ በጋለሞታ እኔን ማሰደብህ ሳያንስ መሳይ መኮንን ጋር ቀርበህ ጥንብ ርኩሴን ያወጣኸኝም አንተው ነህ። ብዕር አላቸው ያልካቸውን የጎጃም አክቲቪስቶችን በሙሉ ያዘመትክብኝም አንተው ራስህ ነህ። በኡጋንዳ፣ በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውሮጳ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በዓረብ ዓለም ያሉ ኔትውርኮችህን በሙሉ አዝምተኽብኛል። ከእኔ አልፎ ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ መረጃ ቲቪም ጨቅጫቂ ሎቢስት ሠራዊት ቀጥረህ አዝምተህብኛል። ዐውቃለሁ የምጠይቅህ ጥያቄ ሾተላይነትህን ያበቃዋል። ግና አንተ የፈለገህን ሁን፣ ውጣም ውረድ፣ ዝለልም ፍረጥ ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ናት አታስቆመኝም።
"…እኔ ዘመዴ ለዐማራ ፋኖ በጎጃም ከተቋሙ ስል ስሜታዊ ላለመሆን እጥራለሁ። አንተንና መሰል የጭቃ ውስጥ እሾሆችን ግን ነጥዬ አወጣችኋለሁ። አንተ ከወዳጄና መምህሬ ይለኝ ከነበረው ከእስክንድር ነጋ፣ ከአበበ ጢሞ፣ ከመከታው ማሞ አትበልጥም፣ አታንስምም። አንተ ከወዳጆቼ ከእነ ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ፣ ከእነ ፕሮፌሰር ዲያቆን ኢያሱ አትበልጥም አታንስምም። አንተ ከወዳጄ አርበኛ ራስ ደረጄ በላይ አትበልጥም አታንስምም። አንተ ከወዳጆቼ ከእነ ሀብታሙ አያሌው፣ አበበ በለው፣ ብሩክ ይባስ አትበልጥም አታንስምም። አንተ ከአክባሪዬ፣ ሰርተፊኬት ሁላ ያለሁበት ሀገር ድረስ ከላከልኝ ከኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አትበልጥም አታንስምም። አንተ ከልብ ወዳጄ፣ ወንድሜ፣ መምህሬ ከነበረው ከባለውለታዬ ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከመምህር ምህረተ አብ አትበልጥም አታንስምም። አንተ ወዳጆቼ ከነበሩት ከእነ በጋሻው ደሳለኝ፣ ከእነ ትዝታው ሳሙኤል፣ ከእነ ዘርፌና አሰግድ ሳህሉ አትበልጥም አታንስምም። አንተ ከመንፈሳውያን አባቶቼ ከእነ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ፣ አቡነ ሩፋኤል፣ አቡነ ሳዊሮስ፣ አቡነ ዜና ማርቆስ፣ አቡነ ኤውስጣቴዎስ አትበልጥምም አታንስምም ብዬ ከእነርሱ ጋር አላወዳድርህም። ለእኔ አንተ ምንም ነህ። ቀለህ፣ ገለባ ሆነህ ነው የተገኘኸው። ራስህን ነው ያዋረድከው ወንድም ዓለም።
"…ግርማ አየለ አንድ ነገር ጽፎ አየሁት። ዘመዴ እኔንና አስረስን ሊያጣለ ነው እንደዚያ ያለኝ ሲል አየሁት። እመነኝ ግርማ አየለን አይደለም ሌሎች ላይ የዘበዘብከውን ትእግስቱን ፈጣሪዬ ይስጠኝ እንጂ ባሰጣው አደጋው ለድርጅቱ ጭምር ነው የሚሆነው። አስረስ ከገመትኩት በላይ ዝርክርክ፣ ምስጢር የማይቋጥር፣ ወንድሞቹን እየከሰሰ ራሱን ጻድቅ አድረጎ መታየት የሚፈልግ ሆኖ ነው ያገኘሁት። የሕግ ባለሙያ ነው ብዬ የካብኩት ሰው እንዴት እንደቀለለብኝ እኔ ነኝ የማውቀው። እኔ ደግሞ ተቋሙ በአንተ በመሰሪው አስረስ ምክንያት እንዲናጋ አልፈልግም። አንተን ነጥዬ ነው የማጋልጥህ። Bezabih Belachew ከዳሞት እንደከተበው ብለህ ሌላውን ሰው ልታጃጅል ትችል ይሆናል። በዛብህ በላቸው አንተ አስረስ መዓረይ (ማሬ) እንደሆንክ የማያውቁትን ሰዎች ብቻ ነው የምታሞኘው። ሌላ ጊዜ ራስህ እንደምትለጥፈው ዛሬም በግርማ አየለ በኩል ከምትለጥፍ አንተው ብትለጥፈው መልካም ነበር።…👇③ ✍✍✍
"ርእሰ አንቀጽ"
"…ዛሬም መርጡለ ለማርያም ነኝ።
"…የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ልደት ለማክበር ከነበርኩበት ከሊቃውንቱ ሀገር ከዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተነሥቼ በጠዋት ገስግሼ ወደ ምሥራቅ ጎጃም ርእሰ ርኡሳን መርጡለ ማርያም ሔጄ በዚያ ነው የልደትን በዓል ያከበርኩት። መቸም የእኔን የሐረርጌውን ቆቱ መራታው ዘመዴን መምጣት የሰሙ አበው ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቱ፣ ሴት አዛውንቱ ብቻ ሳይሆን ኩታራው ውሪው ሁላ አልቀረም ሆ ብሎ ወጥቶ ሲቀበለኝ። ይሄ ኩርማን የሆነ ድንክ ሰውዬ ነው እንዴ እንዲህ እሳት በሚተፋ አንደበቱ ሀገር የሚያምስ? የሚያተራምስ? ሲሉኝ ነበር የዋሉት ያመሹት።
"…እኔ ዘመዴ በአንደዜ ከሁሉም የዐማራ ሾተላዮች ጋር ያለመላተሜ በጣሙኑ ነው በእጅጉ የጠቀመኝ። ከሸዋው ስኳድ፣ ከወሎ የስኳድ ፍሬ፣ ከጎንደር ዋናው ስኳድ እና ከጎጃሙ ብአዴንና የአገው ሸንጎ ጋር በአንደዜ ብጣላ፣ ብናቸፍ ኑሮ ባያሸንፉኝም ግን ያዘገዩኝ ነበር። የገንዘብ አቅማቸውን፣ የአድማ ችሎታቸውን፣ በሴራ የዳበረ እምቅና ያልተነካ ያልተደፈረም ጥንታዊ ጩኸት እሪሪ ባይ መታወቂያቸውን ተጠቅመው ያለ የሌላ ኃይላቸውን ተጠቅመው የእኔን ኃይል ጎትተው ኃይሌን ያዝሉት፣ ይጎትቱኝም ነበር። እኔ ግን አራዳው የሐረሩ ዘመዴ፣ የማርገጃው የፒያሳ የአራዳ ጊዮርጊሱ የደጃች ውቤው ዘመዴ የፋራ አራዶቹን፣ ንክር ጀዝባዎቹን፣ ፀረ ዐማራ አሞራ ጩሉሌዎቹን የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎቹን ስኳድ እና አገው ሸንጎዎቹን ነጣጥዬ ዠለጥኳቸው። እረፍትም፣ ፋታም አልሰጠኋቸውም። በዐማራ ውስጥ ያለውን ሰንኮፍ ለመንቀል ከእኔ ዘዴ ውጪ ሌላ ምንም ዓይነት ዘዴና መፍትሄም አልነበረም። ተመራጩም የእኔ መንገድ ብቻ ነበር።
"…ከእሁዱ የመረጃ ተለቭዥን መርሀ ግብሬ በኋላ አጉብጦኝ የኖረ፣ መቼና እንዴት ነው የምጀምረው ብዬ ሳምጥ ስጨነቅበት የኖርኩትን ከባድ ሸክም ነው ከጫንቃዬ ላይ ያወረድኩት። በምጥ ተጨንቃ ቆይታ በሰላም እንደተገላገለችም ሴት ነው የሆንኩት። ለመጀመሪያ ጊዜ በጊዜ ተኝቼ አርፍጄ ተነሣሁ። ከእሁድ ጀምሮ የመኝታዬም ሰዓት ተስተካከለልኝ። በጊዜ እተኛለሁ፣ ልክ እንደዛሬው በጠዋት ተነሥቼ ሥራዬን፣ ትግሌን እጀምራለሁ። የማልክደው ከቤቴ የባለቤቴና የልጆቼም ጸሎት በግልጽ ነው የረዳኝ። ከውጭ በመላዋ ኢትዮጵያ ባሉ ገዳማትና አድባራት ስለእኔ ስለ ኃጢአተኛው ዘመዴ የሚጸልዩልኝ አባቶች ገዳማውያን፣ ባሕታውያን፣ አበው መነኮሳት፣ ካህናትና ዲያቆናት ጸሎት ነው የረዳኝ። በመላው ዓለም ያሉ ምእመናንም ጸሎት ነው የረዳኝ። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…የዐማራ ትግል ዋነኛ እንቅፋት ነገር ግን አይነኬው፣ ብረቱ ሰው ተብሎ ስሙ የተገነባው አቅመቢሱ፣ በሚዲያ፣ በፕሮፓጋንዳ እና በወያኔ የተጠና ሴራ አስር ጊዜ ታስሮ አስር ጊዜ እየተፈታ፣ ከዚያም የወያኔ አልጋ ወራሹም ኦህዴድ ልክ እንደወያኔ አስሮ እየፈታው፣ ደንበጫ ላይ ይዞት በሕዝብ ቁጣ የተፈታ በማስመሰል፣ ውጋኝ፣ አስወጋኝ ብሎ በመታወቂያ ዋስ ከእስር ለቅቆት በእስር ስሙን የገነነው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ነበር። እስክንድርን መንካት ከኢትዮ 360 ጋር መጋጨትን፣ ከእነ ሀብታሙ አፍራሳ ጋር መላተምን ያስከትል ነበር። እስክንድርን መንካት ከዲሲ ግብረ ኃይል፣ ከግንቦት 7፣ ከባልደራስና ከፌክ ኢትዮጵያኒስቶች ጋር ያፋጭ ነበር። እስክንድርን መንካት በእነዚህ ሰበካና ፕሮፓጋንዳ የደነዘዘውን፣ ደንዝዞም ያመነውን፣ አምኖም የተጠመቀውን፣ ተጠምቆም እስክንድርን እንደ ግል አዳኙ የተቀበለውን የዋሕ ሕዝብ ማስከፋት፣ ማሳዘን፣ ማስጨነቅን ይፈጥር ነበር። ብዙ ወዳጅ ያሳጣም ነበር።
"…እኔም መመረጥ ነበረብኝ። እስክንድርን ነክቼው እንደ እናት ከማያቸው ከወዳጆቼ ከእነ ወይዘሮ ሸዊት እና ከእህት ከወንድሞቻቸው ጋር መቆራረጥ ወይም እስክንድርን ነክቼው የዐማራን ሾተላይ መንቀል። ጠዋት ማታ የሚጠይቁኝ፣ ጉድለቴን የሚሞሉልኝ፣ በፈረሰው ቅጥሬ በኩል የሚቆሙልኝ ወዳጆቼን እንደማስከፋም ዐውቅ ነበር።ስለምንም መስማት የማይፈልጉ፣ ስለ እስክንድር ምንም ቢነገራቸው ጆሮአቸውን የሚደፍኑ ጭፍን ያሉ የእስክንድር አማኞች ጋር መላተሜ የግድ ነበር። በዚህ ደግሞ እኔ ዘመዴ በግል ብቻ ሳይሆን የምጎዳው እሁድ እሁድ ነጭ ነጯን የማቀርብበት የመረጃ ቲቪም ጭምር ነበር የሚጎዳው። ሕዝቡን የሚያደነዝዙበት፣ የሚዘርፉበት፣ በሐሰት ሰበር ዜና ሆዱን የሚቀበትቱበት ፕላት ፎርም ስለሆነ እስክንድር ሲመታ እነዚህ ሁሉ አብረው ጡሩግ ብለው እንደሚሄዱ የታወቀ ነበር። የሆነውም እንደዚያ ነው። እስክንድር ሲመታ ጭንብላሙ ሁሉ ከእኔ ከዘመዴም ጀርባ ሆነ ከመረጃ ቴቪ ጫንቃ ላይ ተራገፉ። ሌላ አማራጭ ግን አልነበረኝም። ደፍሬ ነካሁት። ነክቼም አደቀቅኩት። አፈረስኩት። ድምጥማጡንም አወጣሁት።
"…እኔ ሸዋ ገብቼ እስክንድርን ስተጋተግ የጎንደር ስኳድ አስክንድርን በድብቅ እየጋለበው ስለነበር ተነቃነቀ። የተደበቁት፣ ከጀርባም እስክንድርን ይዘውሩት የነበሩት የጎንደር ስኳዶች መገለጥ ጀመሩ። እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም ወደፊት መጡ። እነ አያሌው መንበር ፌስቡክ ጀመሩ። ቲክቶክ ላይ እነ ዶር ደረጄ፣ እነ ማሳፍንት ባዘዘው፣ እነ ሰሌ ባለ ሃውልቱ ይንዘባዘቡ ጀመር። እነ አበበ በለውም ዋይ ዋይ ማለት ጀመሩ። ሸዋ የገባውና ሸዋን ጠምዝዞ አንቆ የያዘው ስኳድ ጦርነቱን ሸዋ ላይ ጀመረኝ። ሸዋ ላይ እተጋተገው ጀመር። ስለእውነት ለመናገር በሸዋው ጦርነቴ ወቅት የጎንደሩ ስኳድ አካሄዴ ስለገባው፣ ቤዙን እንደማፈርስበት ስላወቀ፣ በሸዋ ዳያስፖራ ገንዘብ፣ በእስክንድር አድራሽ ፈረስነት፣ 4ኪሎ ለመግባት የቋመጠውን መቋመጥ ውኃ ስቸልስበት ከወሎ ከጥቂት በሃይማኖት ምክንያት ከሚጠሉኝ በቀር የተናገረኝ አልነበረም። ሙሉ ጎጃም ሸንጎው ጭምር ተቀናቃኛቸውን እስክንድርንና ስኳዱን ስለነበር የገጠምኩለት ጮቤ ይረግጥ ነበር። ቲክቶክ ስገባ አበባም አንበሳም ነበር ያወርዱልኝ የነበረው። ምርቃቱ መቼም ለጉድ ነበር። እኔም ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታን እየተረትኩ ጎጃምን እንዲህች ብዬ በክፉ አላነሳውም ነበር።
"…ከጎጃም ወሎ ስገባ በወሎ የገጠመኝ ጦርነት አልነበረም። የእስክንድር ሰበካ ሰለባ የነበረው ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባው ብቻ ስለነበር እሱን ብዙም ክፉ ደግ ሳልናገረው ነበር ከወሎ የወጣሁት። የወሎ ቀጠና ለእኔ አስጊ አልነበረም። እንብዛም የሚያጋጨኝ ነገር አልነበረም። ስለዚህ ከወሎ ወጥቼ፣ የወሎን፣ የሸዋ የአሸናፊውን ወገን ይዤ፣ ከጎጃም ሙሉ ድጋፌን ይዤ ወደ ጎንደር ገባሁ። ጎንደር ወልቃይት ከመሸገው ፀረ ዐማራ የትግሬ ዲቃላ ከኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አንሥቶ እስከ ጎንደር ስኳድ መዋቅራዊ፣ ሥርዓታዊ የሆነውን ኃይል ገጠምኩ። ከስሁል ሚካኤል ጀምሮ በጎንደር የተንሠራፋው ፀረ ጎንደር ኃይልን ገጠምኩ። ብቻዬን ገጠምኩ። ትግሬው ተንጫጫብኝ፣ ኦሮሙማው እሪሪ ቋ ቀምበጭ አለብኝ። አበበ በለው አረፋ ደፈቀ፣ እነ ፓስተር ምስጋናው በልሳን ማጓራት፣ ትንቢት መናገርም ጀመረ። ሰማይ ምድር ተደበላለቀ። እኔ ግን በአቋሜ ጸናሁ። ኤልያስ ክፍሌን አያሌው መንበር አናግሮት ቢንጫጫም ኤልያስ ክፍሌ በሥራዬ ጣልቃ ስለማይገባ በነፃነቴ ተጠቅሜ ፍልሚያውን በበላይነት አጠናቀቅሁ።…👇① ✍✍✍
"…የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን። መዝ 36፥9
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
መልእክቱ ደርሶኛል…!
"…ብዙ ሰዎች ይህን ዛሬ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የዋለ ቪድዮ ልክለውልኝ አይቼዋለሁ። ተመልክቼዋለሁም። ከቪድዮው የተመለከትኩት አካላዊ እንቅስቃሴ ለእኔ ለዘመዴ የገባኝ ነገር በደንብ ገብቶኛል። ግልፅም ነው። በፋኖ ስለሺ፣ በፋኖ ጠበቃ አስረስ እና በፋኖ ማርሸት የተከበበው አርበኛ ዘመነ ካሤም እንደወትሮው አንበሳ ሆኖ ስላላየሁት ያለበትንም ሁኔታ አሳምሬ እረዳለሁ። አሁን ላይ በዚህ ቪድዮ ዙሪያ ምንም አልልም። ምንም።
"…ሌላው ደስ ያለኝ የቀድሞው የአሚኮ ጋዜጠኛ ግማሽ ትግራዋዩና ግማሽ አገው ሸንጎው ወንድሜና ወዳጄ ጋዜጠኛ ተስፋዬ ወልደሥላሴ እንዲህ ጮቤ መርገጥ ነው። ከተስፍሽም ጋር ሒሳብ የምናወራርድበት ቀን ደረሰ ማለት ነው። እግዚአብሔር ይመስገን። ከጀመርነው አይቀር የበረከት ስምዖን ቀኘ እጅ ስለሆነው የራህናይ ሆቴል ባለቤት ስለ አገው ተወላጁ አበበ ይመኑ እና ስለ ሚስቱ መርድያ እንድሪስም እናወጋለን።
"…በቀደም ዕለት ድብቅ ስብሰባ ነበር። ስብሰባውን መሳተፍ የምትችለው የግዮን ልጆች በሚል ኮድ ነበር። ስብሰባውን የሰበሰበውና ያደራጀው ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ ሲሆን፣ የሰኔ 15ቱ አክተር አማኑኤል አብነት፣ ይኼነው የሸበሉ፣ ዳዊት ብዙነህ፣ ምስጋናው ዘግዮን፣ እነ ሄኖክ እና እኔ የዲማው ዘመዴ ነበርን። መጨረሻ ላይ ማን ቢመጣ ጥሩ ነው? አስረስ መዓረይ…? ሁሉንም ቀድቼአቸዋለሁ።
"…አስረስ ሲያወራ ዘሜን ተመልከቱት። ቢረፍድም ግን በሰዓቱ ደርሼአለሁ። መርጦለ ማርያም ዘግናኝ ጉድ እየሰማሁ ነው። ለጊዜው ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ በኮሚቴነት ላለበት የገንዘብ ስብሰባ ተጠንቀቁ እላለሁ።
"…አሄሄ ወዴት ወዴት አባዬ? ወዴት ወዴት? የዘንዶውን ራስ ረግጬዋለሁ። እኔ ዘመዴ እንደሁ አንደዜ ከነከስኩ ነከስኩ ነው። ጎጃም እቆያለሁ። የነገ ሰው ይበለን። ተስፍሽም ተዘጋጅተህ ጠብቀኝ።
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ…!
"…ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ? ቃልን ወሰነችው። ልደቱንም ዘር አልቀደመውም። በመወለዱም ድንግልናዋን አልለወጠም። ቃል ከአብ ያለ ድካም ወጣ። ከድንግልም ያለ ህማም ተወለደ። ሰብአሰገል ሰገዱለት። አምላክ ነውና ዕጣን አመጡለት። ንጉሥም ነውና ወርቅ አመጡለት። ስለኛ በፈቃዱ ለተቀበለው መዳኛችን ለሆነው ሞቱም ከርቤ አመጡለት። እርሱ ቸርና ሰውን ወዳጅ የሆነ አንድ እርሱ ብቻ ነው። ቅድስት ሆይ ለምኚልን።
"…ቤዛ ይስሐቅ በግዕ ከኅቱም ዕፀ ሳቤቅ እንደተገኘ፤ ለእስራኤልም በበረሀ ውስጥ ከኅቱም አለት ውኃ እንደ ፈለቀ፤ የተደነቀች የአሮን በትርም እንደለመለመችና እንደ አፈራች፤ በሶምሶንም እጅ ውስጥ ከአህያ መንጋጋ አጥንት ውኃ እንደ ፈሰሰ፤ እንዲሁ የጌታችን ልደት በኅቱም ድንግልና ሆነ። በዕፀ ጳጦስ ውስጥ እሳት እንደ ነደደች ዕፂቱም እንዳልተቃጠለች እንዲሁ የመለኮቱ እሳት ድንግልን አላቃጠላትም። ለእርሱም ከቸር አባቱ ከማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነት ክብር ምስጋና ሰጊድ ከርሱ ጋር በትክክልነት ይገባል ለዘላለሙ አሜን።
"…በዓለ ጌናን ስናከብር በኀዘን በመከራ፣ በጭንቅ፣ በራብና በጥም፣ በሰቀቀን፣ በስደት፣ በወኅኒ ቤት፣ በአልጋ ቁራኛ በደዌ ደኛ፣ በፅኑ ህመም ተይዘው፣ በየቤቱ፣ በየጎዳናው፣ በየሆስፒታሉና በፀበል ስፍራዎች ሁሉ ያሉትን፣ ከሞቀ ቤትና ንብረታቸው ተፈናቅለው በየጥሻው የወደቁትን በማሰብ፣ በመንከባከብ፣ በመጠየቅ፣ በመጎብኘትና ማዕድ በማጋራት ይሁን። ሀገራችን ኢትዮጵያንና ጎረቤቶቿን፣ መላውንም ዓለም ሁሉ ሰላማዊው ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ያድርግልን። አሜን።
"…እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለአምላካችንና ለፈጣሪያችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን‼
ማስታወቂያ…
"…በዛሬው የዕለተ እሁድ የመረጃ ቴቪ የነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ ላይ "የሻምበል መማር ጌትነት ጉዳይ እና የተጀመረው የጎጃም ጉብኝቴ ቀጣይ ክፍል ይቀርባል።
• ጠብቁኝ…!
"…ኢየሱስም መልሶ፡— ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤ በሌሊት የሚመላለስ ቢኖር ግን ብርሃን በእርሱ ስለ ሌለ ይሰናከላል፡ አላቸው። ዮሐ 11፥ 9-10
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…በነገራችን ታች…
"…እነዚህ ጎርጎራ ቲቪ ብለው የመጡ ናቸው መሀል ላይ ያለው እስማኤል ዳውድ ነው ፣ ቀዩ ከፍያለው ጌቱ ይባላል። የመርዓዊ ሰው ነው። ኡጋንዳ በወንድሙ የሆነ ካምፓኒ አለው ይባላል። ሦስተኛው አማኑኤል አብነት ነው። አማኑኤል አብነት እና እስማኤል ዳውድ ወዳጆቼ የነበሩ ናቸው። በተለይ አማኑኤል አብነት በሰኔ 15 ጉዳይ ፍዳውን ባየ ጊዜ እኔ ነበርኩ አጽናኙ። አሁን በቀደም ዕለት ለቤቲ አግዞ ሰድቦኝ፣ መልሶ አጠፋው። እስማኤልም የቅድስተ ማርያም ልጅ ነው። ወዳጄ ነው። ሰሞኑን ታሞ አልጋ ላይ የከረመ ልጅ ነው።
"… እነዚህ ሦስት ሰዎች ናቸው "በላይነህ ሰጣርጌ" በሚል የመንፈስ ስም የሚጽፉት። በላይነህ ሰጣርጌ የጋራ የብዕር ስም መሆኑ ነው። በላይነህ ወሎ ነው ያለው፣ ሸዋ ነው ያለው ብለው ብዙ ሰዎች ግራ ይጋባሉ። በላይዬ እነዚህ ናቸው። አሁን እነዚህ ሦስቱ ወፎች የጻፉትን ቆይቼ እለጥፍላችኋለሁ።
• ዘመነ ካሤን ግን ፈጣሪ ይጠብቀው።
"…ችግሩ እኮ ለእኔና ለጎጠኛ የሚታየው አንድ ያለመሆኑ ነው። ሆኖም ግን ማገዶ ቢፈጅ እንጂ ሳላበስለው አልቀር።
• አይደለም እንዴ…?
እስቲ አስተያየት ስጡበት።
• ገዳይ፣ አራጅ፣ የኦሮሙማን ጦር ነጭ ጤፍ እንጀራ አብልተው፣ አረቄና ጠላ አጠጥተው፣ ልብስ ቀይረው፣ መታወቂያም አውጥተው፣ የኪስ ገንዘብ ሁላ ሰጥተው የሚሸኙት የጎጃም ፋኖዎች በአገዛዙ ተጠርንፎ የተማረከ አባቷን የገደለችን ፋኖ ጀግና ማለት ተገቢ ነው ወይ…? ዜናውን እነሆ👇
አማራነት ከገባህ የማትጋፈጠዉ
ከሰማይ በታች ምንም የለም።
ጀግኒት ትግስት ውዱ!
ይህ ነው ታጋይነት!
ትግስት ውዱ የ9ኛ(ሳሙኤል አወቀ) ክፍለ ጦር አካል የሆነው የባይ ሸለቆ ብርጌድ የኮማንዶ አባል ናት።ጅግኒት ትግስት ውዱ የመከራ ዶፍ ለሚወርድበት የአማራ ሕዝብ ለመታገል ብትወጣም አባቷ ግን የመከራ ዶፍ ከሚያወርዱት ከነአብይ አህመድ ጎን በመሰለፍ ሚሊሻ ይሆናል።
ልጅ ፋኖ አባት ሚሊሻ ሁነው በተቃራኒ ጎራ ተሰለፈው ሳለ ልጅ ተው አባቴ ውጣ ብላ ደግማ ደጋግማ ብትመክረው በዘመድ ብታስመክረው አልሰማ ይላታል።
እየመራትና እያታገላት ያለው አባይ ሸለቆ ብርጌድ አባትሽ ሚሊሻ ስለሆነ እንዴት አባትሽን በሃሳብ ማሸነፍ ያቅትሻል በማለት ትጥቋን ይነጥቃታል።ጀግንነትን የግሏ ያደረገችው ትግስት ውዱ ግን ብርጌዷ በታህሳስ 7/2017 ባደሩገው ውጊያ በጀሌዋ ውጊያ ላይ በመሳተፍ የብርሃኑ ጁላን ቱልቱላ ሰራዊት በደቦል ደንጋይ አናቱን ፈጥፍጣ ክላሽ ትማርካለች።
ጀብደኛዋ ትግስት ውዱ ትናንት ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም አባይ ሸለቆ ብርጌድ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ በተለያዩ ቦታዎች በተደረገ ውጊያ ከፊት ሁና ስትዋጋ ደግማ ደጋግማ የነገረችው አባቷን ትማርከዋለች።
ደጋግሜ ውጣ ብየ ብነግርህ አልሰማ ስላልከኝ ዛሬ ግን የተገናኘነው አማራን እየገደልህ ግንባር ላይ ስለሆነ የማናግርህ በአፈሙዝ ቋንቋ ነው በማለት ግንባሩን በጥይት ፈልጣ ሬሳውን አጋድማ ትጥቁንና መሳሪያውን ማርካ ለብርጌዱ ገቢ አድርጋለች።
"…ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ እይዛቸዋለሁም፥ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም። አስጨንቃቸዋለሁ መቆምም አይችሉም፥ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ። ለሰልፍም ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፤ በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ። የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው። ጮኹ የሚረዳቸውም አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ አልሰማቸውም። እንደ ትቢያ በነፋስ ፊት እፈጫቸዋለሁ፥ እንደ አደባባይም ጭቃ እረግጣቸዋለሁ። ከሕዝብ ክርክር ታድነኛለህ፥ የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፥ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል። መዝ 18፥ 37-43
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
• ሰው ተርፏል…? 😂
"…ሰኞና ረቡዕ የሆነች የማምሽባት ክላስ ቢጤ አለችኝ። እዚያ ቆይቼ ገና አሁን መምጣቴ ነው። የቴሌግራም ሰንዱቄን ስከፍተው ዓለሙ ሁሉ ቀውጢ ሆኖ የለ እንዴ? ድብልቅልቅ ብሎ ጠበቀኝ እኮ። የኮመንቱ ብዛት ራሱ ለጉድ ነው። አሁን ምሽቴን በሙሉ ኮመንት እያነበብኩ፣ ቢንቢውን፣ ቁጫጩን፣ ጉንዳኑን፣ ግሪሳውን ሁሉ ሳጸዳ፣ ስቀስፍ ነው የማመሸው። ቀልድ የለም።
"…የቲዊተር መንደር ሁላ ቀውጢ ሆኖ የለ እንዴ? ኧረ ባባጃሌው። ምናቸውን እንደነካሁት እኔ ነኝ የማውቀው። አሁንም እንደመርፌ ጠቅ እያደርግሁ አንጫጫቸዋለሁ።
"…ሸዋን መጀመሪያ ያደረግኩት፣ እስክንድርን ከስኳድ ጋር አዳብዬ የወቀጥኩት ዐውቄ ነው። የጎጃሙ ብአዴን፣ አገው ሸንጎን ቀድሞ ነክቼው ቢሆን ሊፈጠር የሚችለውን አስባችሁታል? ለዚያ ነው ጎጃምን አጋሬ አድርጌ ስኳድንና ፌክ ኢትዮጵያኒስቱን ስቀጠቅጥ የነበረው። ሁሉን ጨርሼ ጎጃም ስገባ አዋራው ጨሰ። ጨሰ አዋራው ጨሰ።
"…የጎንደሩም ስኳድ፣ የጎጃሙም ሸንጎ፣ ከብአዴን ጋር ሆነው እንዴት እንዳጓሩ አያችሁልኝ? የዓድዋው ትግሬ ወያኔው ስታሊን እንኳ እኔና ዘመነ ካሤን ሲሰድበን ዋለ አሉ። ጉድ እኮ ነው። አበበ በለው፣ እነ አያሌው መንበሩ ሁላ ጮቤ ረገጣ ላይ ናቸውም አሉኝ።
"…እኔ መንፈሳዊ ሰው ባልሆንም መንፈሳውያን አባቶች እግር ስር ያደግኩ የተዋሕዶ ልጅ ነኝ። በሩቅ ሀገር ሆኜ የልብህን ጓዳ ምስጢር የምዘረግፈው እንዲሁ ዝም ብሎ ይመስልሃል አይደል? እኔ ዘመዴ አክሊለ ገብርኤል የጎጃሙን ዘንዶ ወግቼዋለሁ። አንገቱ ማንቁርቱ ላይ ነው የቆምኩት። አይደለም በቴቪና በቲክቶክ በቲጂ ብቻ አፈር ከደቼ አበላዋለሁ። የጎንደር ቅማንትና ዐማራን፣ የጎጃም ዐማራን አገውን አንቀው የያዙት የፖለቲካው ቅማንትና ሸንጎ የትግሬ ዲቃሎችን ብቻዬን እፋለማቸዋለሁ።
• በቴሌግራም ብቻ…✍✊💪
👆② ✍✍✍ …በየትኛው መስፈርት ነው? ብዬ መጠየቄን እቀጥላለሁ።
"…እኔ ግን ቃል ቃል ነውና ወደ መቃብር እስክወርድ ድረስ ለዐማራ ድምጽ መሆኔን አላቋርጥም። ብከዳው ቀኜ ትክዳኝ። ባላስበው ምላሴ ከጉረሮዬ ይጣበቅ። በቴሌግራም ፔጄና፣ በቲክቶክ ገጼ እስክሞት ድረስ በታማኝነት ለማንም ሳላዳላ ድምጽ መሆኔን፣ ዐማራን ከክልሉ ውጪም ሆነ በክልሉ ውስጥ ግፍ የሚፈጽሙበትን በመቃወም መፋለሜ አይቀርም። አይቀርም አልኳችሁ።
"…አዛኜን ዐማራ ያሸንፋል። ዐማራን መከላከያ አላሸነፈውም። አድማ ብተናም አላሸነፈውም። ዐማራን ተዋግቶ ያሸነፈው የለም። የዐማራ ትግል ከወራት በፊት ይጠናቀቅ ነበር። ዐማራን እንዳያሸንፍ አንቀው የያዙት ራሳቸው በፋኖ ውስጥ የተሰገሰጉ። መሰግሰግ ብቻ ሳይሆን የብአዴን፣ የትግሬና የኦሮሞ ቅጥረኛ የሆኑ ከሃዲዎች ስለሞሉት ነው። ተብትበው ስለያዙት ነው። የጎንደሩ ስኳድ እና ብአዴን፣ የጎጃሙ ሸንጎና ብአዴን ዋነኞቹ ናቸው። የጎጃሙ ማነቆና ቋጠሮ ከተፈታ ዐማራ በአጭር ጊዜ ያሸንፋል። ይኽንን ዐውቃለሁ።
"…አንድነቱ እንዳይሳካ ወግሞ የያዘው አስረስ መዓረይ አሁን ሲጨንቀው ሊሯሯጥ ይችላል። የጎጃም ፋኖ ለአንድነቱ ቀናኢ ነው። የሥልጣን ጥም ያንገበገበው፣ ናላውንም ያዞረው አስረስ ማረን እሺ ማሰኘት ቢችሉ ሰሞኑን ራሱ የምሥራች ልንሰማ ሁላ እንችላለን። እኔ ግን እቀጥላለሁ። ኃይልን ለብሼ፣ ፅናትን ተጎናፅፌ እቀጥላለሁ።
• በፔጄ ሓሳብን መስጠት የተፈቀደ ነው። ክፍት አፍህን እከፍታለሁ ብትል ግን እቀስፍሃለሁ።
• ቆይቼ የኮመንት ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። መልካም ቆይታ።
👆④✍✍✍ "…ዛሬ የልደት በዓል ማግስት ነው። በጎጃም መርጡ ለማርያም ሿ፣ ፏ ብትን እያልኩ ነው መዋል የምፈልገው። በቲክቶክም፣ በመረጃ ቲቪም አልመጣም። የቤተሰቦቼንም ደስታ አልሻማም። ከመረጃ ቴቪ ማኔጅመንትም ጋር መክረን ዘክረን ወስነናል። እኔ የጀመርኩትን የጎጃም ጉብኝቴን አላቋርጥም። መረጃ ቴሌቭዥንን ደግሞ የተደራጁ ጎጃም ኃይሎች ገሚሶቹ በየዋሕነት፣ ገሚሶቹ በተደበቀ የሸንጎ ማንነት አስጨንቀው ይዘውታል። እኔ አቋሜን የማልቀይር ከሆነ፣ የጎጃሙ ከአስረስ ማረም የተላከውም ሆነ ትግሉ ይጎዳል ብለው የሰጉ ምስኪኖች በፈጠሩት ፍትጊያ ምክንያት መረጃ ቲቪ በዚህ ፍትጊያ መሃል ሁለታችንንም ማስከፋት ስለማልፈልግ፣ የሚፈጠር ቀውስም ካለ እኔ ገለልተኛ እንደሆንኩ እንዲታወቅልኝ ስለምፈልግ ከነገ ሐሙስ ጀምሮ ከአየር ላይ እወርዳለሁ ብሎኛል። ያ ለብዙዎች ድምጽ፣ አይንና ጆሮ የነበረው የመረጃ ቲቪ በአስረስ ሠራዊት ውትወታ ምክንያት ከአየር ላይ ለመውረድ መወሰኑ ቢያሳዝነኝም እኔ ግን ወይ ንቅንቅ፣ ወይ ፍንክች። ሃቅን፣ እውነትን አልሸጣትም፣ አልለውጣትም። ብአዴንና ሸንጎ የመረጃ ቴቪን አስተዳደር ቢያሸንፍ፣ ቢያውክ እንጂ እኔን አያሸንፈኝም። ቃሌ ነው ዐማራን ላልከዳ መሃላዬ ነው። የድሆች ድምጽ ለመሆን መሃላዬ የጸና ነው። አንደ አረመኔው የኦሮሙማው አገዛዝ የጎጃም ዐማራን በካራ፣ በሳንጃ የሚያርድ፣ አሰልፎ የሚረሽን ጨካኝ፣ ሳዲስት ቡድን የምደግፍበት ምንም ምክንያት የለም። ዐማራን ነፃ አወጣለሁ ብሎ ጫካ የገባ ቡድን ሀብት ሲያከማች፣ ምሁራንን ሲረሽን፣ ሕዝብ ሲዘርፍ፣ ነፃ አወጣዋለሁ የሚለውን ሕዝብ ሰቆቃ ሲሆንበት እያየሁ ዝም አልልም። እኔ ዘመዴ እስከ ፍልሰታ ከጎጃም አልወጣም። በቴሌግራም ብቻ ተሳዳቢውን እያጸዳሁ፣ እየቀስፍኩ ተግትጌ ልክ አገባዋለሁ። ቲክቶክ በወር አንዴ ነው የምጠቀመው። ያለ ቴሌቭዥን በቴሌግራም ጦማር ብቻ እንዴት ልኩን እንደማስገባው አሳይሃለሁ። የአስረስንና የጥላሁን አበጀን መጨረሻ እስካይ ድረስ ከጎጃም አልወጣም። እኔ እንደሁ እንደ አልማዝ ባለጭራዋ ዓይነት ተናግሮ አናጋሪ እስካለልኝ ድረስ ጦሜን አላድርም። እሷ በለፈለፈች ቁጥር እንደ ኃይለኢየሱስ አዳሙ ዓይነቶቹን ገተት ሁላ እኮ ነው ያገኘሁት። የእኔ የወርቅ እንቁላል ጣይ ዶሮዬ ኑሪልኝ።
• ለዛሬ ግን ይህቺን አጀንዳ ሰጥቼአችሁ እንለያይ።
ሀ፦ የጎንደርና የጎጃም ፋኖ ቢጋጭ ተጠያቂው አስረስ መዓረይ ነው።
ሁ፦ የዐማራ አንድነት እንዳይመጣ ዋናው ማነቆ አስረስ መዓረይ ነው።
ሂ፦ አስረስ መዓረይ ከብፁዕ አቡነ አብርሃም ጋር ያለህን የሥጋ ዝምድና በመሳይ መኮንን በኩልም ቢሆን ብታሳውቀኝ ደስ ይለኛል።
"…መልካም የጌታችንና የአምላካችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ይሁንላችሁ። ቆይቼ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያው መልካም ንባብ?
• ማነህ እስኪ ከጠጁ ቅዳልኝ…! ፐ የጎጃም ጠጅ ደግሞ ይለያል።
• ይደፈርሳል ነገር ግን ይጠራል።
•••
ሻሎም…! ሰላም…!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ታህሳስ 30/2017 ዓም
👆②✍✍✍ "…የጎጃም ጉብኝቴ ሁሉ ከዚህ ሁሉ ጦርነት በኋላ የመጣ ነው። ዘመዴ ለጎጃም ፈርሟል። የጎጃም ባለሀብቶች ከፍለውት ነው የሚያጽፉት፣ ዘመነ ካሤ ነው የሚያሠራው፣ የጎጃም ፋኖን ዘመዴ የማይተቸው ጎጃሜ ስለሆነ ነው ሲባል ስለከረመ ጎጃሞቹም ያንን ዲስኩር ይዘው ከምርም የገዙኝ፣ የቀጠሩኝ መስሏቸው ምንም አይመጣብንም ብለው አርፈው፣ ዝርፍጥ ብለው ነበር የጠበቁኝ። ጭራሽ በዘመዴ ስም ብርጌድ፣ ጎጃም ውስጥ ሃውልት በስሙ ካልተከልንለት ሞተን እንገኛለን የሚሉ ሁላ ነበሩ። ውዳሴ ከንቱ፣ ማሽቃበጥ፣ ገንዘብ፣ ሴትና መጠጥ፣ ሆድም የማይደልለኝ እኔ ዘመዴ ግን ጥርሴን ብልጭ እያደርኩላቸው አብሬያቸው ነበር እንጀፍ፣ እንጀፍ ስል የነበረው። እኔ አራቱም አንድ ላይ አብረው ሥራና ሸክም እንዳይሆኑብኝ በማለት በዘዴ ይዣቸው እንደነበር አያውቁም። አሁን ጎጃም ገብቼ ብአዴንና አገው ሸንጎን ስወቅጥ አገው ሸንጎና ብአዴን እሪሪ ቢል የሚደርስለት አይኖርም። ሽባ፣ ዊልቸር ላይ ያዋልኩት ስኳድ ክራንች ይዞ እያነከሰ ቢመጣም አያግዘውም። እኛን ሲወቅጠን፣ ሲበታትነን፣ ዶግ አመድ ሲያደርገን የት በበራችሁ። እሰይ ይበላችሁ ነው እያሏቸው ያሉት። እነ አልማዝ ባለ ጭራ እንኳ ጎንደርን ሲናገር ዝም ማለታችን ትክክል አልነበረም ማለቷ እንዴት መሳቂያ፣ መሳለቂያ እንዳደረጋትም አይቻለሁ። ጎጃም ገብቻለሁ እጅ በእጅ ነው ፍልሚያው። ከሸዋም፣ ከወሎም፣ ከጎንደርም ሊያግዝ የሚመጣ የለም። ይለይልናል። አለቀ።
"…በጎጃም እስከ ፋሲካ ድረስ እቆያለሁ ያልኩትን እንዲያውም ሳላራዝመው አልቀርም። እስከ ጾመ ፍልሰታ ድረስ የምቆይ ይመስለኛል። እስኪዚያም ድረስ ጉብኝቴን ከጨረስኩ ነው። ግን ሳስበው፣ ሳስበው በቶሎ የምጨርስ አይመስለኝም። ርብርቡ እጅግ ከፍ ያለ ስለሆነ አይረን ዶሜን እያጠናከርኩ በጎጃም የምቆይ ይመስለኛል። በግል እኔ ከፋኖ ጠበቃ አስረስ ጋር ጠብ ያለን አስመስለው ውርውር የሚሉ ሰዎችንም እያየሁ ነው። እነዚሁ ሰዎችም አስረስንም ለማዳን የአየር ላይ የማያዋጣ ዘመቻ መጀመራቸውንም ዓይቻለሁ። ይሄ ማንንም አያዋጣም። አስረስንም ሆነ ጓደኞቹን አትራፊ አያደርጋቸውም። በእግዚአብሔር ስም ምዬ እናገራለሁ አስረስን ከእኔ ምርመራ አታድኑትም። አታዋጡትምም። ታፍራላችሁ። አንገታችሁንም ትቀብራላችሁ። ነገር ግን ከእሁድ በፊት የነበረው ግርግር እና ሁሉን አሳታፊ የነበረው ጫጫታ ቀንሷል ሳይሆን የለም ማለት ይቻላል። አሁን አስረስን የማዳን ዘመቻው በጥቂት የአስረስ ክሊኮች ብቻ ነው የቀጠለው። እነሱንም ግን በብእሬ ብቻ አሸንፋቸዋለሁ። ማርያምን አሸንፋቸዋለሁ።
"…አሁን በጎጃም ትኩረቴ ሁሉ የሚሆነው አስረስ መዓረይ ላይ ብቻ ይሆናል። አንዳንድ ሰዎች መዓረይ ስላልኩ አስረስ ትግሬ ነው እንዴ? ሲሉም ሰምቻለሁ፣ አቢይ አሕመድን (አቢቹ፣ ጠሚዶኮ) ኦነግ ሸኔን (ኦነግ ሽሜ) ዳንኤል ክብረትን (ዳንኤል ክስረት) እስክንድር ነጋን (እስክንድር ነጋበት፣ ጨለመ) አርበኛ መከታውን (መከራው) ወዘተ እንዲሉ ፌስቡከራውያን እኔም አስረስን ማረን፣ ማር የሚለውን የአማርኛ ቃል ነው በትግርኛ መዓረይ ብዬ ያልኩት። እንጂ አስረስ የታሰሩ ትግሬዎችን ፈትቶ ሲልክ፣ ሲያስመልጥ፣ አስረስ የወልቃይት ጭፍጨፋን ይሄኛው ፋኖ አይደለም የፈጸመው ከማለቱ በቀር ከትግሬነት ጋር የሚያገናኘው ነገር እንዳለ አላውቅም። ቢኖርም ደግሞ አይደንቅም። ኢትዮጵያዊ ሆኖ አይደለም ከትግሬ ከጣልያን፣ ከግሪክ፣ ከየመንና ከቱርክ የተዋለደ ሕዝብ አይደል እንዴ በምድሪቱ የሞላው? ጥቂቶች እንዲያ ሲሉ ስላየኋቸው ነው ይሄን የምለው። እኔንስ ዘመድኩን በቀለን (አመድኩን ነቀለ) ይሉኝ የለም እንዴ?
"…እነ ጥላሁን አበጀን፣ እና ሌሎችን ከአስረስ ማረ ቀጥሎ ነው የምመጣባቸው። መጀመሪያ ራሱ ሳይጠየቅ ስለተወራጨ፣ ስለተሯሯጠ፣ ስለፈነጨ ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም እንዲሉ ከአስረስ ጋር ነው የምጨርሰው። እኔምለው ትግልን እመራለሁ፣ ሕዝብን ነፃ አወጣለሁ የሚል ቡድን ከወዲሁ ለምን ጥያቄ እጠየቃለሁ ብሎ ጓ ካለ አያስገምተውም እንዴ? አያስጠረጥረውም እንዴ? የማከብረው አርበኛ ዘመነ ካሤስ እንኳ ቢሆን የማይተቸው ምን ስለሆነ ነው? ትችቱ ገንቢ እስከሆነ ድረስ ማንም ይተቻል። የጎጃም ዐማራ ፋኖ ከወሎ፣ ከሸዋ እና ከጎንደር ፋኖ የሚለየው በምንድነው? የጎጃም ፋኖ የመላእክት ስብስብ ነው እንዴ? ገና ትችት እንኳ ሳልጀምር ጎጃም ገባሁ ስላልኩ ብቻ እንደ ሰይጣን፣ እንደ አጋንንት አድፍጦ፣ ነጠላ ለብሶ የተቀመጠው መስቀል እንዳየ፣ ጠበል እንደነካው አጋንንታም ማጓራቱስ ከመመርመር ያድነዋል እንዴ? በፍጹም አያድነውም። ድብን አድርጎ ይተቻል። ይገመገማልም። እንኳን በእኔ በወዳጃቸው በጠላትስ ቢሆን ቢተቹ፣ ቢገመገሙ ምንድነው ችግሩ? የሌለ የተደበቀ ወንጀል ከሌለ በቀር መተቸት አንድን ተቋምም ሆነ ግለሰብ ቢያጠነክረው፣ ነጥሮ ቢያወጣው ነው እንጂ አይጎዳውም። እኔ ከየትኛውም የፋኖ አመራሮች ጋር የተለየ ወዳጅነትም ሆነ የተለየ የግል ጠብ ያለኝም። የፋኖ አመራሮቹ ፈልገውኝ፣ ደውለውልኝ እንጂ ፈልጌአቸው፣ ደውዬላቸው አላውቅም። ከደወሉልኝ ግን አወራቸዋለሁ። ከጻፉልኝም እመልስላቸዋለሁ። በቃ ግኑኝነታችን ይኸው ነው። ትግሉን ልምራ ብዬ አላውቅም። ኢትዮጵያዊ በመሆኔ ብቻ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ማንኛውንም ጉዳይ የመመልከት፣ አስተያየት የመስጠት፣ የመንቀፍ፣ የማወደስ ሁላ መብት አለኝ። ተፈጥሮአዊም፣ ሕገመንግሥታዊም፣ ሃይማኖታዊም መብት አለኝ። ወደድከኝ አልወደደከኝ ሓሳቤን እሸጣለሁ፣ አለመግዛት መብትህ ነው። ወዳጄ ትግሉ ቅዱስ ትግል ስለሆነ የረከሰ ተግባር ፈጻሚዎች በጊዜ ሊታረሙ፣ ንስሐም ሊገቡ፣ ወደ ቀልባቸው ሊመለሱ ይገባል። አሁን በእንቁላሉ ያልቀጣኸው ታጋይ ነገ በበሬው ጊዜ አይሰማህም። ያን ደግሞ ከእኔ በላይ ደፍሮ ለገስጽም፣ ሊመክርም የሚችል ሌላ ሰው የለም። በበረሃ የሚጮህ ድምጽ ነኝ እኔ ዘመዴ አክሊለ ገብርኤል።
"…የአስረስ ዳምጠን የብዕር ስሞች በሙሉ ጠንቅቄ አውቃቸዋለሁ። የአስረስ መዓረይን የእጅ ጽሑፎችና የፊደል አጣጣሎች በሙሉ ዐውቃቸዋለሁ። ለዓመታት ሳጠናው የከረምኩትን ሰው በድንገት መጥቼ ጓ እንዳልኩበትም የምታስቡ ሰዎች አትሳሳቱ። ራሱ ተመቻችቶ ስለገባልኝ፣ ስለመጣልኝ አስረስን መዓረይን አልፋታውም። ወጥሬ፣ ነጥዬ ነው የምመረምረው። እጠይቀዋለሁ ይመልስልኛል። በቃ ሌላ እኮ አይደለም። መርጦ ለማርያም ላይ የፈጸመውን አሰቃቂ ዓለምአቀፍ የጦር ወንጀል ገና አላነሣሁበትም። በእሰረስ ትእዛዝ ስለተረሸኑ ሳይሆን ስለታረዱ ንፁሕ የዐማራ ፋኖ ልጆች መረጃ ገና አላወጣሁም። ከ40 በላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የገዳማትና የአድባራት አለቆች፣ መስቀል እና ወንጌል አውጥተው ጠይቀውት እሺ እፈጽማለሁ ብሎ ሌሊቱን ከምሥራቅ ጎጃም ሸሽቶ ምዕራብ ጎጃም ሄዶ ስለተደበቀው አስረስ ገና ገና ብዙ እጠይቃለሁ። ስለ 35 ሚልዮን ብር፣ ስለ ማዳበሪያ ሽያጭ 5 ሚልዮን ብሮች ገና አወራለሁ፣ እጠይቀዋለሁ። ጆሮአችሁ እስኪቀላ ድረስ ነው የምጠይቀው። ይሄ ለምን ማንንም ያስከፋል? አያስከፋም። ጎሽ፣ በርታ፣ ቀጥልበት ዘመዴ ነው የሚያስብለው እንጂ የምን መደንበር፣ የምን ማጓራት ነው።👇② ✍✍✍
መልካም…
"…ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው።" ዮሐ 2፥ 10። ይሄ በዮሐንስ ወንጌል ላይ የተጻፈውን የቃና ዘገሊላውን የሰርግ ቤት ተአምር የሚተርከውን ኃይለቃል ሳነበው መቼም አርጎ እንዴት ደስስ እንደሚያሰኘኝ አትጠይቁኝ። ከሰከሩ በኋላ መናኛውን ማቅረብ የሌሎች ልማድ ነበር። የሆነች ትንሽ እውነት አቅምሶ ሰው በዚያ ጮቤ ሲረግጥ እና ማጣጣም፣ ማገናዘብ ሲያቅተው መናኛውን ሰበር ዜና በፎቶ እያቀረቡ፣ ወንጀለኛን ጻድቅ አድርጎ ማቅረብ የሌሎች ዩቱዩበሮች ልማድ ነው።
"…እኔ ግን ዘመዴ ነኝ አክሊለ ገብርኤል። በእስክንድር ነጋ፣ በፌክ ኢትዮጵያኒስቶች፣ በግንባሩና በበብቱ፣ በጎንደሩ የፖለቲካ ቅማንት የትግሬ ዲቃላ የጀመርኩትን እውነተኛ ወይን ሕዝቡ ሰክሯልና ምላሱን ማጣጣም አይችልም ብዬ መናኛውን የጎጃሙን የፖለቲካው አገው የትግሬ ዲቃላውን ሸንጎ አቅርቤ አላደነዝዘውም። አላጭበረብረውም። እኔ ከጌታ እግር ስር የተማርኩ ነኝ። መልካሙን ወይን፣ እውነት፣ ሃቅ የሆነውን ወይን እስከመጨረሻው እግትሃለሁ። አቀርብልሃለሁ።
"…መርጡለ ማርያም ነኝ። የጎጃም ጉዞዬ እንደቀጠለ ነው። በጎጃም ደስተኛ ነኝ። ጎጃም በመግባቴ ጥቂት የተቃጠሉና የሚሸቱ ፌስታሎች ከሚሰሙኝ በቀር ጉብኝቴ እንደቀጠለ ነው። የአስረስ መወራጨት ትዝብት ላይ እየጣለው ነው። በቁራጭ ልፋጭ የአጀንዳ ሥጋዋ ስኳድ አበበ በለው ሳይቀር ተንደርድሮ ወደ ወጥመዴ እየገባ ነው። በደብረ ብርሃን አድርጌ በጻድቃኔ ማርያም በኩል ወደ ግሸን ላሊበላ ሄጄ፣ ጎንደር ከርሜ አሁን ጎጃም የገባሁበትን አድካሚ መንገድ እያስታወስኩ መርጡለ ማርያም ደርሼ እየሰማሁ ያለሁት ታሪክ እያስደመመኝ ነው።
• ርእሰ አንቀጹ ይቀጥላል…አቤ እስክስ ግን ሙንኡኖኖ…?
ሙንኡኖው ግን…?
"…ለወቀጣ እንዲያመቸኝ ቁጫጮቹም፣ ጉንዳኖቹም ከያሉበት ተሰባሰቡ። የብአዴኖችም ዓመት በዓላቸው ተበላሸ። የካዝና ቁልፋቸውም ጠፋ። ዋይ ዋይ በል። ገና ምንም ሳልናገር እንዲህ የተረበሽክ መናገር ስጀምርማ፣ የወንጀሉን፣ ከአይሲስ የበለጠውን አሰቃቂ የጦር ወንጀል ስዘረግፈውማ ምን ልትሆን ነው? ታነቅ።
"…አስረስ ማረ ሆይ አይደለም አልማዝ ባለጭራዋን ድልብ ማይሟን፣ ሥጋ ቆራጩን ይኼነው የሸበሉን፣ የሰው አጋንንት ልቡሰ ሥጋ አጋንንት ጋኔሉን አማኑኤል አብነትን፣ አይደለም ዳቪድ በዛብህን፣ ግርማ አየለ፣ ከፍያለው ጌቱ፣ ፋኖ ስለሺ ደምሴ፣ እሸቱ ጌትነት፣ ወዘተረፈውንም ብታሰማራ አልፋታህም። የዘረፍከውን ብር አስተፋሃለሁ። ያሳረድካቸውን፣ ያስረሸንካቸውን የዐማራ ልጆች ደም ከእጅህ እቀበላለሁ።
"…አይደለም ዘመነ እግር ስር፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ቀሚስ ስር ብትገባም፣ አታመልጠኝም። አንላቀቅም። አንተ ተረብሸህ ሌላውን አትርብሽ። ትልቁን በደም እና ባጥንት የተገነባውን የዐማራ ፋኖ በጎጃምን የመሰለ ተቋም ስር አትደበቅ። ነገርኩህ አልለቅህም። አንት ዘራፊ፣ አዘራፊ፣ ቅጥረኛ ነፍሰ ጋዳይ። አልፋታህም።
• ዐማራ አንድ እንዳይሆን የተከልከውን መርዝ እነቅለዋለሁ።
• በጎጃምና በጎንደር መካከል ልታስነሣ የጨረስከውን ጦርነት አከሽፈዋለሁ።
• መርጦለ ማርያም ነኝ። ጉድህን፣ ወንጀልህን እየሰማሁ ነው። አንት አረመኔ። ምዕራብ ጎጃም ተደብቀህም አታመልጥም። ፎቶ፣ ቪድዮ እጠቀማለሁ። ዐማሮች አንተን ለፍርድ ሳያቀርቡህ ድልም የለም።
"…እስቲ በረከት ስምኦን፣ ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ፣ እንግሊዝ ያስቀምጥከው የስለሺ ወንድም ግርማ ያድንህ እንደሁ አያለሁ። አዳሜና ሔዋኔ የአስረስ ቁጫጮች ሆይ ስታንጫጩ እደሩልኝ። የያዝኩትን ስለያዝኩ ብቻዬን እበቃችኋለሁ።
• ጃል ቆቱ ነኝ ከዲማ…😂
የልደት በዓልን
"…ከአዲስ አበባ በስተ ሰሜን አቅጣጫ፣ በ364 ኪሜ ርቀት ላይ በአሁኑ ምሥራቅ ጎጃም በድሮው የጎጃም ክፍለ ሀገር በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ርእሰ ከተማ በሆነችው በመርጡለ ማርያም ገዳም እያከበርኩ ነው።
"…ሕገ ልቡናም፣ ሕገ ኦሪትም፣ የሀዲስ ኪዳንም ኪዳናት የተፈጸሙባት፣ ክብሯ ከአክሱም ጽዮን፣ ከተድባበ ማርያም፣ ከጣና ቂርቆስ እኩል በሆነው በአክሱማውያኑ የኢትዮጵያ ነገሥታት በአብርሃ ወአፅብሃ ድንቅ ሕንጻ ባጌጠችዋ ከተማ እያከበርኩ ነው።
"…መርጡለ ማርያም በኢትዮጵያ የከተሞች ታሪክ ሺ ዘመናትን ያስቆጠረች ጥንታዊት ከተማም ናት። በሺ ዘመናት ታሪኳ በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን በቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት ከእስራኤል ታቦተ ጽዮንን ተከትለው የመጡ የኦሪት ካህናት የሰፈሩባት። ህሩያን አብርሃ ወአጽብሃን ተከትለው የመጡት ከሳቴ ብርሃን ሰላማ ወንጌለ ክርስቶስን ሰብከው አጥምቀው ክህነት ሰጥተው የሾሙባትም ናት መርጡለ ማርያም።
"…መርጡለ ማርያም በዘመናት ውስጥ አራት ጊዜ ስሟን ቀይራለች።መጀመሪያ ሀገረ ሰላም ነበር ተብላ የምትጠራው፣ ቀጥሎ ሀገረ እግዚአብሔር፣ ከዚያም ጽርሐ አርያም በመጨረሻም አሁን የምትጠራበትን ርእሰ ርኡሳን መርጡለ ማርያም ተብላ ተጠርታ ይህ ስሟ ፀንቶላታል።
"…ዛሬ በዓል ነው። ጭቅጭቅ፣ ንትርክ፣ ንዝንዝም የለም። እኔም ከቤተሰቦቼ ጋር እዚያው በመንፈስ ሳከብር ነው የምውለው። ዛሬ ሰላም ነው። ቲክቶክም፣ ተለቭጅንም ላይ አልወጣም። የእሁድ ሰው ይበለን። ከነገ ጀምሮ ግን የጎጃም ጉብኝቴ መረር፣ ኮምጨጭ ብሎ በጎጃም ምድር በቴሌግራም ላይ ይቀጥላል። ርእሰ አንቀጻችንም መረር፣ ኮምጨጭ ብሎ ይቀጥላል። እስከዚያው ድረስ በያላችሁበት መልካም በዓል ይሁንላችሁ።
• ሻሎም…! ሰላም…!
"…እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን? እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን? የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል። የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፡— እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው፥ ባታንጐራጕርም፥ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፥ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፥ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል። እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ። ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም፡— ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድን አዳሽ ትባላለህ። ኢሳ 58፥ 6-12
“…ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።” ዕብ 13፥16
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…ምሽት 1:20 ላይ ይጀምራል። ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።
• የዛሬውም መርሀ ግብራችን እንደወትሮው ሁሉ ልዩ ነው። ሁለት መርሀ ግብር ነው የሚኖረኝ።
1ኛ፦ የሻምበል ማማር ጌትነት ጉዳይ።
2ኛ፦ የጎጃም ጉብኝቴ ቀጣይ ክፍል።
•ዩቲዩብ👉 https://youtu.be/bQtDz0gxlDw
• ሮኩ/ Roku: 👉 https://my.roku.com/account/add?channel=merejatv
•ትዊተር👉 https://twitter.com/MerejaTV
•Mereja TV: https://mereja.tv
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
• ሻሎም…! ሰላም…!
መልካም…
"…በክርስቶስ ቅዱስ መስቀል መረገጥ ኢትዮጵያ በመሬት መንቀጥቀጥ እየተናጠች ነው። በተለይ 4 ኪሎ በሚገኘው በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለጥር 7 ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና ምእመናን በተገኙበት በኢትዮጵያ ምድር በታላቅ ክብር የቆየውን ቅዱስ መስቀል በይፋ በመርገጥ ቤተ ክርስቲያን ፀረ ክርስቶስነቷን በይፋ የምታወጅበት ዕለት ይሆናል ተብሎ ስለሚጠበቅ የመሬት መንቀጥቀጡ ይቀጥላል። እርግፍግፍ፣ ውድም ያደርገናል። ምህላ የሚኖረው የሃይማኖት አባቶቹ በእግዚአብሔር መኖር ሲያምኑ እኮ ነው። ምህላም የለም ይቅርታ ምህረትም የለም። መስቀሉን እንዳዋረድነው እንዋረዳለን። በራብ፣ በጦርነት፣ በጭንቅም እንኖራለን።
"…ሌላው እኔ ዘመዴ ከሸዋ፣ ከወሎና ከጎንደር መልስ ጎጃም ለጉብኝት መግባቴ ሰማይ ምድሩን በአዋራ አንቀጥቅጦታል። ጫጫታው በዝቷል። ግን ምንም መፍጠር አይችሉም። ጎጃም እቆያለሁ። እበድ፣ ፍረጥ፣ ዝለል፣ ጩህ፣ አጓራ ደንታዬ አይደለም። "ደመቀ ዘውዱን፣ እስክንድር ነጋን፣ ሃብታሙ አያሌውን፣ አበበ በለውን፣ የጎንደርን ስኳድ ስነካ ከተፈጠረው ጫጫታና ግርግር አይበልጥም የጎጃሙ። በመጨረሻ ዘመዴ እውነቱን ነው ብለህ ልትፀፀት አጉል ደርሰህ አትንፈራገጥ። የእስክንድር ነጋ ጠባቂ ጎጃም ምን ይሠራል? እስክንድርስ ደቡብ ጎንደር ምን ይሠራል? አርበኛ ዘመነ ካሤ ይሄ ሁሉ ድራማ በዙሪያው ሲሠራ ያውቃል? የዛሬው የመረጃ ቲቪ ዝግጅቴ ልዩ ነው የሚሆነው። እስከዚያው ላታስቆሙኝ ተንጫጩ።
"…እያየኸኝ፣ እየሰማኸኝ በዝረራ አሸንፍህሃለሁ። ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ናት። የጎጃም ፋኖን ከከበበው ጭራቅ እታደገዋለሁ። ባህርዳር፣ ኢንጂባራና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ ጫካና አሜሪካ የመሸገውን ፀረ ጎጃም ዐማራ ሁሉ አውጥቼ አሰጣዋለሁ። ማርያምን ብዬ ማልኩ እኮ። አለቀ።
እህህ… አሄሄ… ምን አስባችሁ ኖ…?
• ጎርጎራ ቴቪዎች
• እስማኤል ዳውድ
• ከፍያለው ጌቱ
• አማኑኤል አብነት ነው በአጠቃላይ በብዕር ስማቸው "በላይነህ ሰጣርጌ" ከይኸነው የሸበሉ ጋር ምን አስበው እንደጻፉ ከላይ ገብታችሁ በፔጃቸው አንብቡ።
"…በቀደም ዕለት ናትናኤል መኮንን ተስፋዬ ወልደ ሥላሴን ጠቅሶ ስለ አበጀ በለው የጻፈው ለምን እንደሆነ ብትሰሙ ትስቃላችሁ። እሳቱ ብዕረኛስ ማን ይመስላችኋል። አዛኜን እመ አምላክ ምስክሬናት ዘመነ ካሤን የእናቱ ጸሎት ይሰውረው። ይከልለው።
"…እኔ እኮ የሆነች ሰቀዝ አድርጌ መታ የማደርጋትን ጉዳይ ከብሮግራሜ በፊት ትመጣለች ብዬ አልገመትኩም ነበር። አዴ አልማዝ ዳኛቾ መገርሳ እና ጠበቃ አስረስ ማዕረይ ደንግጠው አካሄዴ ስላላማራቸው ነገሮችን ሁሉ አፈጣጠነብኝ እንጂ እኔ እንኳን ትንሽ ዞር ዞር ብዬ፣ እየጎሻሸምኩ፣ ባህርዳር እና ደብረ ማርቆስ ኢንጂባራ ዩኒቨርሲቲ የመሸገውን የፖለቲካውን ቅማንት የትግሬ ዲቃላውን ስኳድ እና ሌላውን ፀረ ዐማራና ፀረ አገው አናሳ ገዳይ ሸንጎ ወቅጬ ነበር ወደ ዐማራ ፋኖ በጎጃም ሙሉ ዳሰሳ ልገባ፣ ነገሮች እንዲስተካከሉ ምክረ ሓሳብ ልሰጥ የነበረው። እነሱ ግን ይሄ ሰው አያያዙ አላማረንም ብለው አፈጣጠኑት። ብቻዬን እመታቸዋለሁ። አዛኜን እሰብራቸዋለሁ።
• አሁን ወደ እነ በላይነህ ሰጣርጌ ልጥፍ ልምጣ።
"…እነ Belayneh Setarge Gizaw እና ይኼነው የሸበሉ ወደለጠፏት ልጥፍ እንምጣ። እነ በላይነህ ሦስት ስለሆኑ ተውአቸው። ይኼነው የሸበሉን ግን የግድ እጠቅሰዋለሁ። ይኼነው የሸበል በረንታው የጥላሁን አበጀ አጋር ማለት ነው። ፕሮፋይል ፒክቸሩን በዘመነ ፎቶ አድርጎ የሚሸቅል፣ ለዘመነ ካሤ ብቻ እንዲደርስ የተሰጠውን "ጥብቅ ሰነድ ለአስረስ ማረ አሳልፎ ሲሰጥ የኖረ ከብት መሰሪ ነው። ሰነዱን ሌላ ቀን እመጣበታለሁ። "…በጠበቃው ጉዳይ የመጀመሪያም የመጨረሻም ፅሁፍ ነው ብለው እነ ሰጣርጌ በኅብረት የጻፉትን ሂዳችሁ አንብቡ። እነ አማኑኤል አብነት ጥላሁን አበጀን ነፃ ሲያወጡት ዋሉና በመጨረሻ በጦመሩት ጦማር ላይ በስተ መጨረሻው አንቀጽ ላይ ምን አሉ?
• እሱም ከአምስት ጊዜ በላይ ከድሮን እና ከጥይት በተአምር ተርፏል። [ ከማን ጋር አቻ ልታደርጉት? ]
• በተደጋጋሚ የዚህ ዘመቻ ዒላማ ተደርጎ ሲቀጠቀጥ አላስችለኝ ብሎ መረጃ ፈልፍየ የመጣሁት የአማራ ህዝብ እውነተኛ ልጆቹን እንዲያውቅ እና እንዲጠብቅ ስለምፈልግ ነው። [ ዘመነ ካሤ ሁለት ዓመት ሙሉ በአልማዜ ጭምር ሲቀጠቀጥ የጻፈለት አለ?]
• አሁን ደግሞ በኦርቶዶክስ ኃይማኖት ስር የተሰባሰቡ የስልጣን ጥመኞች አዲስ ዘመቻ ከፍተውበታል። [ አስረስ ኦርቶዶክስ አይደለም እንዴ?] ብቻ እንዲህና እንዲህ ሲሉ ይቆዩና በመጨረሻ ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል እንዲሉ ሰካራሞች የሸበሉና ሰጥ አድርጌ እንዲህ ይላሉ።
"…የእሱ [የአስረስ ማለታቸው ነው] መልካም ስም እና ዝና እንድሁም የፓለቲካ ስብዕና ተነካ ማለት እኛም ተነካን ማለት ነው። በዚህ ትግል በፓለቲካው ክንፍ ከራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ ቀጥሎ ቅቡልነት ያለው መሪ ነው። [ ከዘመነ ካሤ ቀጥሎ ቅቡልነት ያለው መሪ ነው] ሌሎች የሉም ማለት ነው? ከምሥራቅ ጎጃም ሸሽቶ ምዕራብ ጎጃም የከተመው እዚያም አለቃ መሆኑ ሳይረሳ።] ይቀጥሉና እነ የሸበሉ እንዲህ ይላሉ።
"…ራስ አርበኛው የሚበልጠውም [ አስረስን ማለት ነው] ዘለግ ላለ ጊዜ ጠብመንጃ ስለነከሰ እንጅ የንባብ አቅማቸው እና ንስርነታቸው ተመሳሳይ ነው:: የአማራ ፋኖ የፓለቲካ ክንፍ ከዚህ ንስር ሌላ በማን ሊዘወር ታስቦ የዚህን ያክል እንደተዘመተበት ግራ ነው የገባኝ ይላሉ እነ ሰጥ አድርጌ። ይሄ ማለት ለእኔ የሚገባኝ [ አስረስ መዓረይም ከዘመነ ካሤ አያንስም። እኩል ናቸው። ሌሎች በድሮን ቢሞቱም። ነገም ዘመነ አንድ ነገር ቢሆን የጎጃም ዐማራ ሆይ አትዘን፣ አትስጋ፣ ወንድ እናቱ የወለደችው አስረስን የመሰለ የዘመነ አቻ አለልህ እያሉት ነው። ፈረንሳይኛው ለእኔ በደንብ ነው የሚገባኝ።
"…አስረስ እለዋለሁ። አቤት ዘመዴ ይለኛል። አንድነቱ እንዳይመጣ ለምን ትጎትተዋለህ? ምን አስበህ ነው? እለዋለሁ። አስረስም መለሰልኝ። ብዙውን ትቼ ጥቂቷን ልንገራችሁ። "…ዘመዴ አንድነቱን እኔ አይደለሁም ያጎተትኩት። ከእኛ ውስጥ እነ እንትና ናቸው። የእኛ አመራሮችም አንድነቱ እንዲፈጥን አስጨንቀውናል። እኔም ዘመነ እስካለ ድረስ የትኛውም ሥልጣን ቢሰጠኝ ከሥሩ ስለሆንኩ አይተወኝም። እናም በቃ አዎ አዘግይተነዋል፣ እናፋጥነዋለን ነበር ያለኝ። ውሸት ይበል አስረስ ወጥቶ ለመሳይ መኮንን።
"…ቆይ እኔ የምለው ለድርጅቱ ነው መጨነቅ ወይስ ለግለሰቦቹ። የዐማራ ፋኖ በጎጃም ነው እንደ ተቋም መገንባት ያለበት ወይስ አስረስ መዓረይ? አርበኛ ዘመነ ካሤ ላይ ሀገር ምድሩ ሲዘምትበት ምነዋ የዚህን ያህል መንጋው ወጥቶ አልተከላከለለት? ምን እየተካሄደ እንዳለ አልገብቶኝም። ከምር አልገብቶኝም ልል አልኩና እኔማ ከገባኝ ቆየ። አይ የሸበሉና እነ ሰጣርጌ።
• እናንተስ ምን ትላላችሁ…? …ሊበላ…?
"…ይህቺን ነገር እያያችሁ ቆዩኝና የሆነች ጥያቄ ለጥፌላችሁ ቤቴን ቆልፌ ስትብሰለሰሉ ታድራላችሁ። ከዚያ ነገ በዕለተ ሰንበት ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ አስቀድሼ ከወጣሁ በኋላ እንገናኛለን።
• እያያችኋት ቆዩኝ። ከ10 ደቂቃ በኋላ ጥያቄዬን እለጥፍላችኋለሁ።
• ጥያቄ እኮ ነው የጠየቅኩት…
"…ትናንት ባሕርዳር ዊኪሊክ ለሀገሯ ልጅ ለጠበቃ አስረስ ማዕረይ ጥብቅና ቆማ እኔ ዘመዴን የሐረርጌ ቆቱ መራታ ነው፣ በጎጃም ከእኛ ሰፈር ዘመድም፣ ወገንም፣ ጓደኛም የለውም ብለ በስሱ ወቅሳኝ ነበር። እኔም ፈጣሪ ያውቅልኛል ብዬ እንባዬን ወደ ሰማይ ረጭቼ ዝም አልኩ። ብዙዎች ግን በኮመንት መስጫው ላይ ሲከራከሩልኝ ሳይ ግን ዐማራ ፍትሕ ዐዋቂ ነው የሚለውን ቃል አስታወሼ ተጽናናሁ።
"…ከወኪ ሊኪ ዘገባ ግን እኔን የሳበኝ "…ምናልባት ግላዊ ህይወቱንም መዳሰስ ካስፈለ… አስረስ ማረ ዳምጤ ጥሩ ገቢ የነበረው ጠበቃ ነበር። አስረስ ልጆቹና ሚስቱ ወዳሉበት አሜሪካን አገር ለመምጣት የአሜሪካ ኤምባሲ ቀጠሮው ደርሶ ቀናቶች ሲቀሩት ጫካን የመረጠ የትውልዱ የነጻነት ፋኖስ ነው።" የሚለው አረፍተ ነገር ነው። "በተለይ ልጆቹና ሚስቱ ወዳሉበት አሜሪካን አገር" የምትለዋ አፈዘዘችኝ።
"…አስረስ ቢያንስ ዘር ተክቷል። ሚስቱና ልጆቹንም አሽሽቷል ማለት ነው አይደል? መልካም የእኔ ጥያቄ አስረስን ትላንት አናድዶት መሳይ መኮንን ቤት ሄዶ እኔን እንዲሳደብ ያስገደደው ነገር "በጎጃም የዐማራ መምህራን ለምን ይገደላሉ? በጎጃም የሚፈጸመውን የመምህራን ግድያ አቁሙ ማለቴም ነው።
"…ዲግሪ አለው። የተስተማረ ነው። ፍልስስ ያለ መኪና ነበረው። ቆንጅዬም ውብም ነው ወዘተ ብሎ መከራከር ይበጃችኋል ወይ? ጥያቄው እኮ እሱ አይደለም።
• የመምህራን ግድያን አስረስ መዓረይ ያስቁም። ይሄ እናንተን ቢደብራችሁም የእኔ ጥያቄ ነው።
እስቲ ፍረዱ…
"…እስቲ ስለ እውነት ስለሃቅ ብላችሁ ፍረዱ። እንደ የሆነስ ሆነና፣ የፈለገ ቢሆን፣ ከፀረ ዐማራው ከግንቦቴው መሳይ መኮንን እና ከእኔ ከመራታው የሐረርጌ ቆቱ ከዘመዴ በእስነት ለዐማራው ትግል ማነው ቅርብ? ማነውስ ዋጋ የከፈለው እና ነው ድሮን የማይመታው የዐማራ ፋኖ በጎጃም የፖለቲካ ዘርፍ ሓላፊው አይተ አስረስ መዓረይ ወስዶ አሳልፎ ለፀረ ዐማራው መሳይ መኮንን የከሰሰኝ…? አይዞኝ ዘመዴ… አይዞኝ…ግድየለም። አይዞህ ዘመድዋ።
• ከምር አላሳዝንም ወይ…? 😂 እስቲ ፍረዱኝ አሁን እኔ በመሳይ ፊት እንዲህ የምሰደብ መራታ ነብርኩ? የለህማ የዲማው ጊዮርጊስ። የለህማ በእውነት።