zemedkunbekelez | Unsorted

Telegram-канал zemedkunbekelez - Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

311892

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Subscribe to a channel

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ቤቲሻ ጋር እየሄድን…!

"…የዋን ዐማራው ትግሬው ወንድሜ አፄ ዘርአያዕቆብ ነቤክስ የቤቴ የሥራ አለቃዋ ማለት ነው። "ዘመዴ ቤቲ እየጠራችህ ነው ብሎ" መልእክት አድርሶኛል። ጠርታሃለች እያለኝ ነው። ሥራዬን ልጨርስና እስቲ ሄጄ ኮንሰርቷን ለመሳተፍ እሞክራለሁ። ያውም አረጋዊ አዛውንት ጠርተውኝ በፍጹም አልቀርም።

"…ረስቼው ትልቅ ሰው ይፈራል እንዴ…? ጀምሬሻለሁ አሳይሻለሁ። እኔ ዘመዴ፣ የሐረርጌው ቆቱ እጅሽ ላይ ያለውን ደም አስልስሻለሁ። ብአዴን አያድንሽም፣ ተመስገን ጥሩነህ፣ ጥላሁን አበጀም አያድንሽም። ለጋለሞታማ እኔ ዘመዴ መድኃኒቱ እኮ ነኝ።

"…ወዳጆቼ እኔ መረቤን ዘርግቻለሁ። ወጥመዴን አስተካክዬ አጥምጃለሁ፣ ልፋጭ ቁራጭ የአጀንዳ ሥጋዬን ወርውሬአለሁ፣ በቃ እስቲ ሄጄ ፈታ ልበል። እስክስ ነው ቅዳሜ ገበያ። ሂዳችሁ ፈታ በሉ። በነገራችን ላይ ጋለሞታዋ የጎጃም ዐማራ አትመስለኝም። እኔ እንዲህ ዓይነት ዐማራ በፍጹም አላውቅም። ለማንኛውም…

"…እየሄድን…🚶🚶‍♀‍➡️🚶‍➡️🚶🚶‍♂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በጣም ነው የመረገተው አይደል…?

"…ተመስገን ስኳድ እንኳ አደብ ገዛ እኮ። በጎንደር ዐማራ ስም ሲነጠነጥ የከረመው የትግሬው ልጅ ስኳድ አምደማርያም እዝራ በትግራዩ ጦርነት ትግሬ ሲገድል፣ መሳሪያ ሲሸጥ ከርሞ በመጨረሻ ጠና ያሉ ሴትዮ አጋብተውት ላሽ ብሏል አሉኝ። 🙏🙏🙏 ተመስገን ነው።

"…አሥራት ሚዲያን አፍርሶ፣ እንደ ጉድ ተጨማልቆበት፣ በመጨረሻም አምዴ እስኳዱ ደሰጶረ።

"…ይኸው ዛሬ ደግሞ ዓመታዊውን የቅዱስ ገብሬአልን በዓል ምክንያት በማድረግ መርግቶልን አረፈው። 😂😂 አሁንም ተመስገን ነው። ቶማስ ጃጀው አንተስ መቼ ነው የሆኑ ሴትዮ ድረውልህ የሚያሳርፉህ?

• ወእዘ ትፈትል፣ ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ አስተራአያ ገብርኤል ግብተ፣ ወይቤላ: ወይቤላ እስመ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር። እልልልል

• ወደ ጎጃም እመለሳለሁ…

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጨዋታውን ልጀምር ነኝ።

"…ይሄን ጀግና ወንድ እናቱ የወለደችውን የጎጃም ዐማራ ጀግና፣ በተደጋጋሚ ኢንጂባራ ከተማ እየገባ ከዐማራ አድማ ብተና እና ከዐማራ ሚሊሻ ጋር እየተፋለመ፣ አፈር ከደቼ እያበላ፣ መከላከያን ራሱ እያደባየ ቁም ስቅሉን ያሳይ የነበረ ጀግና እንዴትና በማን ሞተ…?

"…አርበኛ አሳየ ይሁኔ የተመታው ከኋላው ነው። የተመታው ከጀርባው ነው። አሳየ ዐማራ ነው። አሳየ ዐማራ ብቻ ሳይሆን እንደምታዩት ባለማዕተብ ኦርቶዶክስ የተዋሕዶ ልጅ ነው። ዐማራው አሳየ የካቲት 16/2016 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ከኋላው ተመታ። ጀግናው ወደቀ። አሳየ ከሞተ፣ ከተወገደ በኋላ ግን ኢንጂባራን የሚደፍራት የጎጃም ፋኖ እንዴት፣ ለምን ጠፋ? አሳየን ማነው የገደለው?

"…በጎጃም የዐማራንና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶውን አማኙን ቁጥር ለመቀነስ የተያዘው አደገኛ ቀፋፊ የዘር ማጥፋት ፕሮጀክት ከወዲሁ መክሸፍ አለበት።

"…እየጠበቅኳችሁ ነው ወጣ ወጣ በሉ እንጂ ሸንጎዎች። ዲቃሎች፣ ፀረ ዐማራው የበድኑ ብአዴን ቫይረስ ተሸካሚዎች፣ ተናግራችሁ አናግሩኝ አጫውቱኝ እንጂ። እንደ አዲሱ ጌታነህ ብቅ ብቅ በሉ እንጂ። በቀላሉ እለቅህ መስሎሃል

• ይደፈርሳል ግን ደግሞ ይጠራል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በጥያቄ መልክ ልምጣ እስኪ…

"…እሾሁን ለመንቀል መግሉ ማበጥ አለበት። ቁስሉ እስኪመግል የሚጠበቀውም ለዚያ ነው። አሁን ሳፈርጠው ትንሽ ህመም ይኖረዋል። ግን ከዘላቂ ጥዝጠዛና ስቃይ ይታደጋል። ያበጠ መግላም የቁስል ቦታ ያሳክካል ሁላ። እናም አከክ፣ አከክ እያደረግሁ ቆይቼ የሆነ ቀን አፈርጠዋለሁ።

"…አሁን ወደ ጥያቄው ልምጣማ…

፩ኛ፦ አንድ ጊዜ በቅርቡ አንድ ነጭ ጋዜጠኛ የተባለው ፈረንጅ በጎጃም ጉብኝት አድርጎ የሆነ ዘገባ መሥራቱ ይታወቃል። ፈረንጁ ምርኮኞቹን ከጎበኘ በኋላ ምንድነው የሆነው? ፈረንጁ አገዛዙ ፋኖን አይችለውም አለ። ዐማራ ሁላ ጮቤ ረገጠ። አቢይ አሕመድ ደግሞ በአደባባይ ወጥቶ በመረጃው ሠሰርቶበት ይሁን ሌላ አይታወቅም "አንድ ሺ ዓመት ቢዋጉ አያሸንፉም" አለ። አቢይ ከምን ተነሥቶ እንዲህ ሊል ቻለ?… አጉል ባዶ ፉከራ ነው ብዬ አሁን ላይ ማለፍ አልፈለግኩም።

"…ከፈረንጁ የምርኮኛ ጉብኝት ዜና በኋላ በጎጃም ውጊያም ምርኮኛ መማረክም ቀረ መሰለኝ። ጥያቄው ፈረንጁ የሠራው ሴራ ይኖር ይሆን? ደግሞስ ማን ነበር ፈረንጁን ጎጃም ያስገባው? ከፈረንጁ ጋር የከረመውስ የፋኖ መሪ ማን ነበር?

"…የራሱን ዐማራ ወገኖቹን ብአዴን ናችሁ እያለ ያለ ምህረት የሚረሽነው የጎጃም ፋኖ በተቃራኒው ደግሞ የጎጃም ዐማራን ያረደ፣ የደፈረ፣ የጨፈጨፈ የኦሮሙማውን ምርኮኛ አጥቦ፣ አብልቶ፣ የኪስ ገንዘብ ሁላ ሰጥቶ የሚሸኘው ዐማራሩን ራሱ አያስጠረጥርም ወይ?

"…አሁንስ በጎጃም ምርኮኛ የጠፋው እና እንይያዝ የተደረገዉ ምን አልባት አሁን ላይ መከላከያው ኦሮሞ ስለሚበዛው ኦሮሞዎቹ እንዳይሞቱ፣ ተይዘው በኦሮሚኛ ፋኖ ያሸንፋል እያሉ በፋኖ ትእዛዝ እየጨፈሩ፣ የሌላውን የኦሮሞ መከላከያ ሀሞት እንዳይፈስ ለማድረግ ይሆን? ይኸው ብትማረኩ አይገድሏችሁም። እናንተ ግን ጨፍጭፉ ተብለውስ ይሆን?

•እቀጥላለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ጎጃም ላይ እቆያለሁ።

"…ነገርየውን ሳየው እጅግ ከባድ ነው። ውስብስብም ነው። ማርያምን፣ አዛኜን ቅዱስ ገብርኤል ምስክሬ ነው ውዬ ሳድር የጎጃሙ ሾተላይ ከጎንደር ስኳድም የከፋ ሰንኮፍ ሆኖ እያገኘሁት ነው። የመድኃኔዓለም ያለህ እኔ የጎንደር፣ ስኳድ ስኳድ ስል ዋነኛው ጉድ ያለው እዚህ ጎጃም ውስጥ አይደል እንዴ? እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ። የአንተ ያለህ። ምንጉድ ነው የማየው? ምን ጉድ ነው የምመለከተው? ምንጉድ ነው የምሰማው። ስኳድ ማረኝ ነው የሚያስብለው የጎጃሙ።

"…ብታምኑም፣ ባታምኑም የጎንደር ዐማራ በፖለቲካው ቅማንት፣ የየጎጃም ዐማራም በፖለቲካው አገው ሸንጎ ተጠርንፏል። ተተብትቧል። የጎንደርም፣ የጎጃምም ዐማራ በዚሁ ከቀጠለ፣ ሴራውን ለመቀልበስ በፍጥነት ካልተንቀሳቀሰ እመኑኝ እንደ ኩርድ ሀገር አልባ የመሆኛ ጊዜው እጅግ በጣም ቅርብ ጊዜ ነው። በጣም ቅርብ ጊዜ።

"…አዝናለሁ፣ እያለቀስኩ ነው የምጽፈው፣ ዐማራው በሲስተም፣ በዘዴ ከጎንደርና ከጎጃም ምድር በሃላል እየጸዳ ነው። ወዳጄ ምንም መደባበቅ፣ መሸፋፈንም አያስፈልግም። እውነታውን መዋጥ፣ መጨለጥና ለመፍትሄ መንቀሳቀስ ብቻ ነው የሚያስፈልገው። በቃ መፍትሄው እሱ ብቻ ነው።

"…ቢያንስ ቢያንስ የጎንደሩ በጸሎትም፣ በገዳማውያኑ ርብርብም፣ በሽማግሌም መስመር ወደመያዝ መጥቷል። እነ ሀብቴና እነ ባዬ ቀሪ የቤት ሥራቸውን ሠርተው ከጨረሱ ቢያንስ የጎንደር ዐማራ እልቂቱ ይቀንስለታል። የጎጃሙን ግን እንጃ። ማርያምን እንጃ። አባቴ ይሙት፣ ወላዲተ አምላክ ምስክሬናት እንጃ።

"…ሆኖም ግን ከመጋፈጥ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም። በአንደዜ አይደለም ግን የምምረው የለም። ይደፈረሳል ግን ደግሞ ይጠራል።

• አልወጣም፣ የትም አልሄድም። ጎጃም ላይ እቆያለሁ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ስኳድ አፈር ልሳ ልትነሣ…😂

• በሕልሜ ይመስለኛል…

"…ዐማራ ባንክን የትግሬና የኦሮሞ መፈንጫ፣ የዐማራ ባንኩን ባለሙያ ቀጥቅጠው ገድለው አስከሬኑን ያአስረክም ይመስለኛል። ደግሞም የዐማራ ባንክን ተቀማጭ ገንዘብ ለአዳነች አበቤና ለአቢይ አሕመዱ ገንዘብ ማጠቢያ መሽን ኦሺድ ኖ ኦቪድ በብድር ስም አስረክቦ ሲያበቃ አጅሬ አገኘሁ ተሻገር ይመስለኛል አይተ መላኩን ጠርቶ ኧረ ሞትነ፣ አለቀልነ በልበል መሌ የሆነች ቢዝነስ ፍጠርና ገንዘብ መሰብሰቢያ ብሮጀክት ውለድ እያለ ሲጨቀጭቀው ይመስለኛል አይተ መሌም እሺ ብሎ ከች ሲል እነ ፓስተር ምስጋናው ጮቤ ሲረግጡ እያየሁ፣ ሙንኡኖው ነው እያልኩ ጥላሁን አበጀን ስጠይቀው የሆነች አስቀያሚ ዐማራ አሰዳቢ የቲክቶክ ጋለሞታ መግቢያ መውጫው ጠፍቷት ኢትዮ ፎረም የሚባል መዚቃ ከፍታ ስትንበጫበጭ እያየሁ ይመስለኛል ድንገት ብንን ብዬ ተነሣሁ።

• ጎጃም ነኝ። አየሩ ሸጋ ነው። ጎጃም በሚገርም ሆኔታ እየተናበበ ነው። ከየወረዳው፣ ከየቀበሌው የምሰማው ዜና፣ የሚደርሰኝ መልእክት እጅግ ገራሚ፣ ልብም የሚያሞቅ ነው። ጎጃም ቆሻሻው ይጠራል፣ ዘራፊው ይጠራል፣ ደፋሪው ይቀጣል፣ ሴረኛው፣ አገው ሸንጎው፣ ሌባው፣ በላተኛው በሙሉ ልክ ይገባል።

• የነገው የተቀበል መርሀ ግብራችንም ጎጃም ላይ ነው የሚያቆየን። እዚያው ነው የዋሸራን ቅኔ የመሰለ ግጥም ስንገጥም፣ የቲክቶክ ላይ ጎጃም አሰዳቢ ስድአደግ ክፍታፍ ባለጌዎችን ስንነቁር፣ ስናበሽቅ፣ ስናስነቅል፣ ጨርቅ ስናስጥል የምንውለው።

• እኔ ዘመዴ ነኝ። ጃል ወያ ወይም ሞጣ ቀራንዮ አይደለሁም። እኔ ማለት ዘመዴ ነኝ ከባድ ሚዛን ነኝ። ጋለሞታ ጆሮ ቆንጥጬ ነው ልክ የማስገባው። ዘርዓ ያዕቆብ ትግሬው የሚነዳት ጋለሞታ የጎጃም አሰዳቢ የቲክቶክ ኮማሪት ብቻዋን እንድታወራ ነው የማደርጋት። ለነፍሰ ገዳይ ምህረት የለኝም።

•መጣሁልሽ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆④ ✍✍✍ …አስቀያሚ ገጽታ ተላብሶ ቀፋፊ መስሎ መታየት ጀምሯል። ፋኖነት በብዙ ቦታ እንደ ገቢ ማግኛ መንገድ ሁሉ እየሆነ ነው። ትግሉ ገንዘብ ያስፈልገዋል አዎ ምንም ጥያቄ የለውም። ነገር ግን የሰፈር ጎረምሳ ቂጡን የጣለው ዱርዬ ሁላ የፋኖ መሪ ነኝ እያለ የ30  እና 60 ሚሊዮን ብር ባለቤት የሚሆንበት ምክንያት የለም። በወታደራዊ ቁመናም በለው በትጥቅም ጭምር ታንክና ጀት ድሮን ሲቀረው አሁን ላይ በተለይ የጎጃሙ ፋኖ ከመከላከያ የተሻለ ነገር ያለው። እና ይሄ ከተወሰነ ከ ዙ 23 ውጭ ሁሉ ነገር ያለው ፋኖ አሁን ላይ ለምንድነው አንዲት የቀበሌ ከተማ እንኳን ማስለቀቅ ያቃታቸው? ብሎ መጠየቅ ሞኝ አያስብልም። እውነት ለመናገር አሁን እኮ ሕዝቡ ራሱ በፋኖ ማማረር ጀምሯል። እንዴ ምንድን ነው ነገሩ? ለምሳሌ መራዊ፣ አማሪት፣ ቢኮሎ፣ ወተት ዓባይ አካባቢ ያለው ፋኖ ከሕዝብ ሊነጠሉ ምንም እኮ አልቀራቸውም። የአቸፈር ፋኖስ ቢሆን የመንግሥት ኃይል አለኝ ከሚለው መሳሪያ እና ትጥቅ በጣም በተሻለ እና ጥራት ባለው መልኩ የተደራጁ ናቸው። ነገር ግን የትኛውን ቦታ ተቆጣጥረው ሕዝቡን ዋስ ሆኑት? ይገባሉ ከዚያ ይወጣሉ። እነሱ ሲገቡ ሕዝብ ደስ ይለዋል፣ ይገብርላቸዋልም። እነሱ ሲወጡ በተራው መከላከያ ይገባል። ይዘርፋል፣ ይደበድባል። እነሱ ሲገቡ ብአዴን ነው፣ የመከላከያ አቃጣሪ ነው ብለው ዐማራውን ይረሽናሉ፣ እነርሱ ሲወጡ ደግሞ መከላከያው የፋኖ ደጋፊ ነህ፣ ረጂ ነህ እያለ ይረሽናል። ሕዝቡ ከላይ እሳት፣ ከታች እሳት የገና ዳቦ ነው የሆነው። ይሄ በቃ ሊባል ይገባል።

"…የአቸፈር ፋኖ ያለውን መሣሪያ መንግሥት እራሱ በወረዳው አንድም የቡድን መሳሪያ የለውም። የዚህ አካባቢ ፋኖ ግን የትየለሌ የቡድን መሳሪያ ነው ያላቸው። ነገር ግን ምን ሠሩበት ብሎ ሕዝቡ ይጠይቃል? እሺ ለዚህ ጥያቄ ማን መልስ ይስጥ። ለምሳሌ በምን ምክንያት እንደሆነ ባይታወቅም ዛሬ ከብዙ ቦታዎች ላይ መከላከያ ለቅቆ እየወጣ ነው። አብዛኞቹ ትንንሽ ከተሞችም በሚሊሺያ እና በአድማ ብተና ስር ነው ያሉት። የአካባቢው ኅብረተሰብ የሚለው መከላከያ ከክልሉ ሊወጣና ከዚያ ክልሉ ራሱን በራሱ ሊያስተዳድር ነው ብሎ ነው የሚያወራው። የሆነው ሆኖ መከላከያ ግን ለቅቆ መውጣት ጀምሯል። ለምሳሌ ወተት አባይ፣ ቢኮሎ፣ አማሪት፣ መራዊ አካባቢ እንዲሁም ደቡብ ሜጫ ዳጊ አካባቢ መከላከያ ለቅቆ እየወጣ ነው። በዚህም ፋኖዎች በጠዋቱ ከች ብለው ከመራዊ በቅርብ ርቀት ኬላ ጥለው የጭነት መኪኖችን ገንዘብ ሲቀበሉ ነበር። የሚያስቀው በአጠገባቸው ደግሞ ሚሊሺያ እና አድማ ብተናዎች አሉ። ይተያያሉ። ነገር ግን መከላከያ ስለሌለ ተኩሰው ለማስቆም አልደፈሩም። ይልቁንም እኛ እኮ ግራ ገባን እሺ አሁን ምንድን ነው የሚሻለን? እያሉ ነው። ምናልባት የምር መከላከያ ከክልሉ ሙሉ በሙሉ ለቅቆ እየወጣ ይሆን የእኔም ጥያቄ ነው። ከዚያስ አስባችሁታል? ከአሁን ሥርዓትና ሕግ የማይገዛው፣ መጠላለፍ ያለበት፣ በካምፕ ያልተጠረነፈ፣ ወታደራዊ ሥነ ምግባርን ያልተላበሰ በፋኖ ስም የተሰገሰገ ዘራፊ ምን ሊፈጥር እንደሚችል?

"…ጎጃምን መጎብኘቴ፣ መመርመሬን እቀጥላለሁ። የደከመውን አበርትቼ፣ በእልህ ምላጭ አስውጬ፣ የተኛውን ቀስቅሼ አሯሩጠዋለሁ። እንደዚያ አደርጋለሁ። አሁን በተለያዩ የጎጃም ክፍሎች ውጊያ መቀስቀሱን እየሰማሁ ነው። ሕዝባዊ የነበረውን ትግል ጎረምሶች ይዘው ገደሉት ከመባልና ከመተቸት መገላገል አለባቸው። በቲክቶክ እነመራዋለን የሚሉ የቲክቶክ ጋለሞቶችን ከጎጃም ዐማራ ትግልም ዠልጬ አስወጣቸዋለሁ። እኔ እተቻለሁ። ትችቱ ተገቢ ከሆነ ያስተካክላሉ። ተገቢ ካልሆነ ወደ ጋርቤጅ ይወርውሩት። የዐማራ ፋኖ ትግል መዳኛዬ ስለሆነ ከጋለሞቶች በበለጠ ይመለከተኛል። የሚያስቆመኝም አንዳች ኃይል የለም። መከላከያ ለቅቆ የወጣውን ሁላ ጥላሁን አበጀ ፋኖ ተቆጣጠረው ብትል አልሰማህም።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…

• ይደፈርሳል… ግን ደግሞ ይጠራል…✊

•••

ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ታሕሳስ 18/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆②✍✍✍ …ወጥተው ከቁምነገር በቀር ሌላ የማያወሩ ምሁራን ሆነው ነው ያገኘኋቸው። መማር ማለት ይሄ ነው። መብሰል ማለት ይሄ ነው። ስክን ብሎ አዳምጦ ከእኔ ስህተት ቢገኝ እንኳ ዘመዴ ይሄ ስህተት ነው ይታረም የሚሉ ሆነው ነው ያገኘኋቸው። ተደምሜባቸዋለሁ። ዓለሙ በባዶ በርሜሎች ሲንጫጫ፣ ሲታወክ እነሱ ረጋ ብለው "ስለ ክርስቲያን ታደለ ሕክምና መከልከል ነበር ሲያወሩ፣ ሲወያዩ፣ ትዊት ሲያደርጉ የነበረው። ከምር አከበርኳቸው።

"…ገና ጎጃም ስመጣ፣ እግሬ ዓባይን ሲሻገር በጎጃም ምን ተከሰተ? አዎ ልክ እንደ ጎንደሩ የፖለቲካው ቅማንት የጎጃሙም የፖለቲካው አገው ሸንጎ ተጠራርጎ ወደ ኢንጂባራ ነካው። ኢንጂባራ እነ መቶ አለቃ ማርቆስ የማይገቡት ለምንድነው ብዬ ለጠየቅኩት ጥያቄ መልስ ባይሆንም ከእንግዲህ አይገቡም ብዬ ግን አልጠብቅም። ይገባሉ፣ ወደው ሳይሆን በግዳቸው ይገባሉ። የጎጃምን አጀንዳ ስጀምር ሌላው ምን ተከሰተ? የዋን አዋራዎች የ24/7 የቲክቶክ ላይ ጫጫታ ቀነሰ። አኪላም ከቲክቶኳ ብልጽግና ሥር ሄዶ በትዊተር እስፔስ ኮኦ ሆስት ሆኖ አረፈው። አይደክሜው የትግራዩ ልጅ ዘርዓያዕቆብ ነቤክስም ደከመው፣ ሰለቸው፣ የዘርዓ ያዕቆብን ትግሬነት ያወራችው አብራው ያደገችው፣ አብራው የተማረችው ልዕልና ናት። ለእኔም የሰፈሬ ልጅ አክባሪዬ ናት፣ ብልጽግና ያውብ ብአዴን መሆኗን አክብሬላት፣ በጨዋ ደንብ ሃሳቧን በነፃነት የምትሸጥ ልጅ ናት። አኪላ ኤልያስ ታደሰ እዚያ ነው እንግዲህ ዘሎ ገብቶ ሆስት ሆኖ ሲራቀቅ የዋለው። መያዣ መጨበጫ ነው ያሳጣኋቸው። ለመጀመሪያ ጊዜ ቲክቶክ ሩም ሳይከፍቱ በየቤቱ ሲንቀዠቀዡ ነው ያመሹት። ቤተ ልሄም ዳኛቸውን ለመጋለብ፣ ማይም ናት አልተማረችም ብለው ጃስ ለማለት ነቢዩ እየገባ ዘመዴ እንዲህ ብሎሻል፣ እንዲህ በዪው ቢሉ ወፍ የለም። እኔ ስይዝ ማንቁርት ስለሆነ ውልፍት የለም።

"…አየሩ ተረብሿል። ፈስ ያለባቸው ሁሉ መዝለል አቅቷቸዋል። እንቡር፣ እንቡር ይሉ የነበሩ በሙሉ አደብ እየገዙ ነው። የጎጃም ትግል መስመር የያዘ ቢሆንም በኔትወርክ፣ በሰፈር ልጅነት፣ በጓደኝነት፣ በቤተሰብ ተጠፍሮ የተያዘው አደረጃጀት መከለስ አለበት። ደሀው እየሞተ እነ ጥላሁን አበጀ ድራማ የሚሠሩበት አግባብ የለም። ሌብነቱ፣ ዘረፋው፣ እንደ ሱማሌ ተራ መኪና ማረጃ ሥፍራ በጎጃም ውስጥ የከፈቱ የፋኖ አመራሮች አሉ ቢባል ማን ያምናል? እየመረረህ ነው የማውጥህ? የውባንተን ሚስት የሥራ መኪና ያፈኑ፣ ብትለምናቸው እንኳ እንቢ ያሉ ወንበዴዎች በጎጃምም፣ በጎንደርም ምድር እንዴት ይኖራሉ? ገና ጆሮ ያልሰማውን ጉድ ነው የምዘረግፍልህ። አባት ፊት ሕፃን ልጃገረድ ታዳጊ የሚደፍር አረመኔ እንዴት በጎጃም ምድር ፋኖ ነው ተብሎ ይከበራል፣ ይመራል? ሌባ፣ ወራዳውን መች እለቀዋለሁ።

"…ጎጃም ከገባሁ ምን ቀነሰ በሉኛ? አዎ ዘመነ ካሤን በኔትወርክ ተደራጅተው ያሰድቡ የነበሩ አፈ ቅቤ ልበ ጩቤዎች እየተንጋጉ ሚዲያውን ሞሉት። የእናቱ ጸሎት፣ የዋሕነቱና የአብዛኛው ኢትዮጵያዊም፣ ዐማራም ጸሎት የሚታደገው አርበኛ ዘመነ ካሴን አመስጋኙ፣ መሪዬ ባዩ በዛ። አቶ ተመስገን ጥሩነህ ማንን ተማምኖ፣ ከማን ሰምቶ ነው በእርግጠኝነት ባሕር ዳር በነበረው የብአዴን ስብሰባ ላይ "ዘመነ ካሴ ተገድሏል። ሞቷል" በማለት አፉን ሞልቶ የተናገረው? ማን ምን ብሎት ነው? እነ ናትናኤል መኮንን ዘመነ ሞቷል፣ እነ ጌትነት አልማው ዘመነ ተወግዷል ብለው የተንጫጩት ማን ምን ቃል ቢገባላቸው ነው? ፓስተር ምስጋናው አንዷለም፣ ይሄ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ መናፍቅ ድልብ ፀረ ጎጃም ዐማራ የሆነ ግለሰብ አፉን ሞልቶ፣ ቲክቶክ ላይ ወጥቶ "ዘመነ ተመቷል፣ ቆስሏል" ብሎ አፉን የከፈተው ከየት ሰምቶ ነው? እየተዋወቅን። በዘመነ ሥር የተኮለኮለውን ኮልኮሌ በሙሉ ሥርዓት ያላስያዝኩት እንደሆነ እኔ ዘመዴ አይደለሁም። ማርያም አዛኜን ብያለሁ።

"…ዘመነ ካሴና ሻለቃ ዝናቡ ብቻ በሚያውቁት ሥልክ ተደዋውለው፣ ተቀጣጥረው፣ ሊገናኙ 3 ኪሎ ሜትር ሲቀረው እኮ ነው የጎንደሩ የአርበኛ ባዬ የሳይበር ሴኪዩሪቲ የደኅንነት ክፍል ለዝናቡና ለዘመነ ደውሎ ከድሮን ሞት ያዳናቸው። ይሄን የምናውቀው እኔ የባዬ ደኅንነቶች ዝናቡና ዘመነ ካሤ ብቻ እኮ ነን። ብልፅግና ሂሊኮፍተር እና ጋዜጠኛ ባህርዳር አዘጋጅቶ፣ ዝናቡንና ዘመነን አንድ ላይ ገድሎ፣ እስክንድርን እና የጎጃም የእነ ተመስገን ጥሩነህን ግሩፕ ይዞ፣ ሊደራደር ነበር የቋመጠው። ለድርድሩ እንቅፋት ናቸው የተባሉትን ዘመነን እና ዝናቡን በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ሊፈጩ የነበረውን ነው የታደግነው። ምድረ ፈዳላ ሁላ። እኔ የምሠራውን ነጥብ ያህል ለዐማራ ለነገዳችሁ ብትሠሩ የት በደረሳችሁ። ምድረ ፎከታም። ባወራ መሰለህ እንዴ? እርጥብ ሁላ። አይተሃል በአንድ ጊዜ ጎጃም የድርጅት መሪዋንና የጦር መሃንዲሷን ስታጣ ሊፈጠር የሚችለውን። በካርታ የተደገፈ የደረሰኝን መረጃ ለአንዱ የጎጃም ፋኖ ልኬ ከፍቶ ያየው ቆይቶ ነው። ካለፈ በኋላ ነው የሚነግረኝ። ጎንደሮች ቀድመው ግን ዘመነን ታደጉት። ዝናቡን አተረፉት። ይሄን የምጽፈው ፈጠራ ከመሰለህ ስም ጠቅሼ እኮ ነው እየጻፍኩ ያለሁት።

"…እነ ዋን አዋራ፣ ወያኔ፣ ብልፅግና፣ ግንቦት ሰባት፣ ኢዜማ፣ የአገው ሸንጎ ከጎጃም የዐማራ ፋኖ ትግል ውስጥ ሳይወዱ በግዳቸው ይጸዳሉ። ትእቢተኛ፣ ሌባ፣ ደፋሪ፣ ቀማኛ፣ ጉልቤ፣ ባንዳ ይጸዳል። የማንንም ርዳታ ሳልፈልግ እኔ ብቻዬን እገጥማቸዋለሁ። እሺ ካሉ ከተስተካከሉ እሰየው እምቢ ካሉ ግን የሚዘገንኑ ወንጀሎቻቸውን አሰጣዋለሁ። በውስጥ ለአመራሮቹም እልክላቸዋለሁ። ማንም ሁን ማን በፎቶ ቦለጢቃ ትግሉን መሸወድ አትችልም። የዘመነ ብብት ስር እየተወሸቅክ ፎቶ በመለጠፍ መሪዬ፣ አለቃዬ እያል ሕዝቡን ማሞኘት አትችልም። በሚሊዮን ብር የሚቆጠር ገንዘብ የዘረፍክ ባንዳ፣ ባህርዳር፣ አዲስ አበባ ማርቆስ፣ የገጠር ከተማ ሁላ ሕንፃ የገነባህ፣ ሕዝቡን በኬላ ያማረርክ፣ የጆሮ ጉትቻ፣ የአንገት ሀብል፣ አምባር፣ ሞባይል ሳይቀር እየገፈፍክ የምትቀማ ነጭ አለሌ ዱርዬ ሌባ አንተን በምንም ተአምር አልፋታህም። ባደረ ቂም ፋኖ ስለሆንክ ብቻ ሰው እያገትክ መልሰህ ዐማራውን የምታስመርር ማጅራት መቺ አንተን አልፋታህም። በደም መላሽነት ፋኖ ስለሆንክ ንፁሐንን እየረሸንክ የአያቴን ገዳይ ዘሮች ተበቀልኩ የምትል ነፍሰገዳይ አረመኔን አልፋታህም። ነገርኩህ እበድ የፈለግከውን በለኝ። ለደንታህ ነው። ይህን እታገላለሁ በማለቴ የምትቃወም ካለህ ታነቅ። ሞት።

"…አሁን በቀጣይ የሚሆነውን ተመልከቱ። ጠብቁማ። ጥላሁን አበጀ ይሄን ከተማ ተቆጣጠርን፣ ይሄን ከተማ ያዝን፣ ገባን ወጣን እያለ ይፏልላል። ምን አለ በሉኝ ከመደንገጡ የተነሣ የማይለጥፈው ነገር አይኖርም። አምናለሁ የጎጃም ዐማራ ጠንካራ ነው ነገር ግን አሁን ላይ በሙስና፣ በዘመዳ ዘመድ፣ በሰፈር ልጅነት፣ በጓደኝነት ተሳስቦ እየገማ፣ እየሸተተ፣ ጠረኑን እየለወጠ ነው። ማኅበረሰቡ በፋኖ እየተማረረ ነው። ብአዴን ምን አደረገን እያለ ነው። ይሄ የሆነው ደግሞ የፋኖን የአመራርነት ሥፍራ ጠላት ባንዳ ስለተቆጣጠረው ነው። እነሱ በሚሠሩት ግፍ ሕዝቡ ፋኖን እየጠላው ነው። እያንገሸገሸው ነው። ከሚሊሻው፣ አድማ ብተናው ጎን ተሰልፎ ድራሽ አባትክን ሳያጠፋው በቶሎ ግምገማ ተቀመጥ። በቶሎ አፅዳ። ሌባውን አጋልጥ፣ ዘርፎ ሆቴል፣ ሥጋ ቤት የከፈተውን እከካም ሌባ አጋልጥ። ትግሉ ካለቀ የምበላው አይኖረኝም በሚል ትግሉ ላይ የተኛውን አስወግድ። እምቢ ካልክ ከሕዝቡ ጎን እቆማለሁ። እኔም…👇②✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

• አላችሁ ኣ…?

😂😂😂

• አባ አሯሩጥ እኔ ዘመዴ አለሁ። እናንተ አላችሁ ኣ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ከተማን በደም ለሚሠራ፥ ከተማንም በኃጢአት ለሚመሠርት ወዮለት!” ዕን 2፥12  …“…በድሀ የሚያላግጥ ፈጣሪውን ይሰድባል፤ በጥፋትም ደስ የሚለው ሳይቀጣ አይቀርም።” ምሳ 17፥5

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ወዴት ወዴት…

• አዛኜን ብያለሁ እኮ…

"…የነብሩን ጅራት እኮ ይዤዋለሁ። የጀመርኩት ከዳር ሳላደርስ ነክሼ ሳላደማው መች እፋታህና አባቴ። አሄሄሄ… የአርበኛ ዘመነ ካሤን ስም ሲያጠፋ፣ ሲያስጠፋ፣ ዘመነ ካሤ በሁሉም ዐማራ ዘንድ እንዲጠላ፣ ጥያቄም እንዲነሣበት ሲደረግ የቆየውን ዘንዶ አንገቱ ላይ ቆምኩ እኮ።

"…ሸበል በረንታ ውስጥ እዚህ ግባ የሚባል ሥራ ሳይሠራ፣ ሸበል በረንታ የጥላሁን አበጀ ቤዝ ነበር። የጎጃም ሰዉ እኮ እያለ ያለው የበላይ ዘለቀን ሀገር አሰደቡት፣ የበላይ ዘለቀን ሃውልት ከቢቸና ያንሱት ወይም ቀሚስ ያልብሱት እያለ እኮ ነው አባቴ።

"…ከእናርጅ እናውጋው ሶማ ብርጌድ ውጭ ሌላው እየተዋጋ ነው ማለት አይቻልም። ዝርዝር መረጃውን አረፍ እያልኩ አፈነዳዋለሁ። ጎበዝ የዛምብራ ብርጌድ አመራሮች ባለፈው ወር በድሮን ተገድለዋልም እኮ። አሁን ላይ ሸበል በረንታን የብአዴን ሚሊሻ ሥልጠና እየሠለጠነ፣ እየፈነጨበት ከምሥራቅ ሸሽቶ ምዕራብና ሰሜን ጎጃም ላይ መከማቸት ፌር አይደለም።

"…የቆየ ሞላ ትናንት ደውሎልኝ ሁሉን ያዝ፣ አድምጥ ብሎ እውነቴ ነው የሚለውን አፍርጦ ነግሮኛል። ሸበል በረንታን ያስበላው አሳልፎ ለብአዴን የሰጠው ግንቦቴው ጥላሁን አበጀ ወለጋ ድረስ ሄዶ እንዴት በወለጋ ፋኖን አደራጀ? ሃኣ…? መሳይ መኮንን እና ደረጀ ሀ/ወልድ፣ እነ ፋሲል የኔዓለም ለምን አጮሁት…?

"…ከጎንደር የነቀልኩትን የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ የጎንደር እስኳድ ከጎጃምም የፖለቲካው ቅማንት የትግሬና የኦሮሞ ዲቃላውን ገረዱን የአገው ሸንጎ፣ የብአዴን ሴል፣ የግንቦት ሰባት፣ የግንባሩን ርዝራዥ በሙሉ እዠልጠዋለሁ። አጸዳዋለሁ።

"…ይሄ ማባያ ነው። አፒታይዘር…! ዝም ብሎማ መበርታት የለም። አበደን ዝም ብሎማ አይበረታም። የግድ አናግርህሃለሁ።

• መዝግቡልኝ። ይደፈርሳል ግን ይጠራል✊💪🏿

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③✍✍✍ …ሜካፓቸውን ተለቅልቀው፣ በአደረ አፋቸው 24/7 ያለማቋረጥ የሚለፈልፉ፣ ምንም ቁምነገር የማይገኝባቸው፣ እንደ ቁጭራ ሰፈር ሴት ሐሜት፣ ነውረኛ ስድብ፣ አግቦ፣ ሲዘሩ የሚውሉ አሉ። እንዲያውም እነ አርበኛ ዘመነ ካሤ በሌሎች እንዲጠሉ፣ እነ ሀብቴ፣ እነ መከራው፣ እነ ምሬ እንዲጠሉ የሚያደርጉ አሉ። እናም እነዚህን ከጨዋታው ለማስወጣት ዋነኛው መፍትሄ እነሱን ተከትላችሁ በእነሱ ቤት የምትለፋደዱ ዐማሮች አይመጥኗችሁምና የራሳችሁን ቤት ከፍታችሁ የዐማራን ዐዋቂነት፣ የዐማራን ከፍታ ለዓለሙ ሁሉ አሳዩ። እነ መሀመድ ሀሰንም ከፌስቡክ ውጡና በቲክቶክ ተገለጡ። ዐማሮች መድረኩን ተቆጣጠሩ። ሁሌ እኔን አትጠብቁ። ሰው ፍጠሩ። የመንደር ሴት መሃይም ሀሜተኛ፣ ተሳዳቢ የዐማራ ስብዕና የሌላቸውን በዐማራ ስም የሚያቀረሹ የቲክቶክ ላይ ጋለሞቶችን ገለል፣ ገሸሽ አድርጉ። 

"…ጎጃሜ ሆነው ከፀረ ዐማራው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ጋር የሚሠሩ፣ ከጎንደሩ ስኳድ ጋር የሚሠሩ፣ ከወያኔ ጋር የሚሠሩ፣ ማረፊያ ካጡት ዋን አማራዎች ጋር አጀንዳ ተቀባብለው አንቺ እንዲህ በይ፣ እኔ እንዱህ እላለሁ የሚባባሉ እስስቶችም አሉ። እነ አርበኛ አሰግድን ከእነ መከታውና ከብልፅግና ጋር ተመሳጥረው ያስያዙ፣ እነ ውባንተን ያስገደሉ አሉ። የሳተላይት ስልክ ልከው ስልኩ በተደወለ ቁጥር ቅጂውን የሚቀዱ ፀረ ዐማራ አክቲቪስቶችም አሉ። እነዚህ ሁሉ እንጭጭ ያልበሰሉ ተራ መንደሬ ቲክቶክ ያገነናቸው ጋለሞቶች አደብ የሚገዙት ኢግኖር ሲገጩ ብቻ ነው። ትኩረት ስትነፍጓቸው ብቻ ነው። መዋጮ ብለው ኪስ ጎተራቸውን መሙላት ስታቆሙ ብቻ ነው። የሜካፕ መግዢያ ስትነፍጓቸው ብቻ ነው። ያኔ ነው አደብ የሚገዙት፣ ሥርዓት የሚይዙት። እኔም በቀጣይ አልፋታቸውም። አስነጥሳቸዋለሁ። አጨልላቸዋለሁ።

"…ብታምኑም ባታምኑም እነዚህ የቲክቶክ ሴቶች በእነሱ ስር ሆኖ ለእነሱ እንዲታዘዝ ነግረውት እምቢ ያላቸውን ምስኪን ፋኖ ገንዘብ ከፍለው በሌሎች ፋኖዎች ሲያስገድሉ የኖሩ አሉ። በሸዋና በጎጃም፣ በጎንደርም ይሄ ሲደረግ ሰምቻለሁ። በተለይ በጎጃም 16 ወጣት ዐማሮችን አንዲት የቲክቶክ የዩቲዩብ ጋለሞታ የሆነች ሴት ከእነ ተመስገን ጥሩነህ ጋር ስትሠራ፣ በሰነድ ስለደረሱባት ለምንድነው እንዲህ የምታደርጊው ስላሏት ብቻ 16ቱን አሳስራ 3ቱ ሲያመልጡ 13ቱን ሙሉ ለሙሉ አስረሽናለች። ከሦስቱም ሁለቱ ያመለጡ ሲሆን አንዱ ብቻ ተመልሶ ተይዟል ይባላል። እሱም ይረሸን አይረሸን አላውቅም። እንደነዚህ ዓይነት ጋለሞቶች በቶሎ ትግሉን ከማንቦራጨቅ ካልወጡ አደጋው ከፍ ያለ ነው የሚሆነው። መሬት ላይ ያለ ፋኖ ውጭ ሀገር ያለ ጓደኛው ጋር ደውሎ ይሄን ያህል ብር አበድረኝ ይለዋል። የለኝም ይላል የተጠየቀው። መልሶ ግን ያ ፋኖ ነኝ ባይ ወንበዴ መሬት ላይ ያሉ ቤተሰቦቹን አግቶ ከምገድላቸው ብሩን ትልካለህ አትልክም ብሎ ጓ ነው የሚለው። እግዚአብሔር ያሳያችሁ የምጽፈው ራሴ በሽምግልና የተሳተፍኩበትን ጉድ ነው። ይሄን ስጽፍ ጉዳዩን የሚያውቁ የፋኖ አለቆችና ምስክሮችም አሉ። እናም ጓዶች ጠንከር ማለት ያስፈልጋል።

"…እኔ ዘመዴ የሐረርጌ ቆቱ መራታ የምሥራቅ ሰው መሆኔን ተናግሬአለሁ። አሳውቄአለሁ። የትግሉ መሪ አይደለሁም። የትግሉ አማኝ ነኝ። የፋኖ ትግል ያድነኛል ብዬ የማምን ሰው ነኝ። እናም ይሄ እምነቴ ሊከበር ይገባል። ሌላው ደግሞ እኔ ፋኖን ስተች እንደ ስዩም ተሾመ፣ እንደ ፓስተር ደሳለኝ የመሃል ሜዳ አህያ፣ እንደ ኮሮና ዳዊት፣ እንደ ገሌው ፕሮፌሰር ጌትነት አልማው፣ እንደ ቶማስ ጃጃው፣ እንደ ናቲ አንደግምም ወይ ዓይነት ያለ ትችት አይደለም የምተቸው። ነው እንዴ? እኔ እምነቴን አላፈርስም፣ ቃልኪዳኔንም አላፈርስም። እንቅልፍ አጥቼ ተጯጩሄ፣ ላንቃዬ እስኪሰነጠቅ፣ ከምላሴ ላይ ምራቅ፣ ከአይኔ ላይ እንቅልፍ እስኪጠፋ ድረስ፣ ትንፋሽ አጥሮኝ ደረቴን እየወጋኝ ያለምንም ክፍያ እዚህ ያደረስኩትን የዐማራ ፋኖ እንደ ዓይኔ ብሌን ነው የምጠብቀው። ምክንያቱም እምነቴ ነዋ። የፋኖ ትግል መዳኛዬ ነው ብዬ ነዋ የማምነው። እና ብጮህ ብቆጣ መብቴ ነው። ይሄንን ሁሉም ይወቅ። ተው ብትለኝ አልተወውም፣ አቁም ብትለኝ አላቆመውም። በአካል እስከሌለሁ ድረስ በጽሑፌ እና በንግግር በዲስኩሬ ለማቀርበው ሓሳብ ከልካይ፣ ተቆጪም የለኝ። መሬት ላይ ያሉት የእኔ ሓሳብ ገዢ ሆነው ካገኙት መሸመት መብታቸው ነው። ካልጣማቸው ግን የሚያስገድዳቸው የለም። የእኔን ሓሳብ መተቸት፣ መሞገት ደግሞ የተፈቀደ ነው። የተፈቀደ። ሞግቱ፣ ተቹ።

"…በመጨረሻም እንዲህ እላለሁ በጎጃም የጀመርኩትን ትችት እቀጥላለሁ። ጎጃም ቤቱን ሠርቶ ቀለም እየቀባ ያለ ነው። ያንን ቀለም ሲቀባ ደግሞ እንቅፋት የሚሆንበትን የሸረሪት ድር፣ ጥቀርሻ፣ ቆሻሻ፣ አዋራ እኔ ዘመዴ አራግፍለታለሁ፣ እጠርግለታለሁ። ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ አይደል ጆሮ እሆንለታለሁ። የሚመጣ የሕዝብ ሮሮ ድምጽ ሆኜ የጎጃም የዐማራ ፋኖ እንዲያርመው፣ እንዲያስተካክለው እጮሃለሁ። የእኔ ጩኸት ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም። በፋኖ ስም የሚዘርፈውን እስክንደርም ሆነ ሌላ ፋኖ መገሰጽ ካለበት ይገሰጻል። ጎንደርን ስተች ልክ፣ ብራቮ ዘመዴ፣ ወሎን ስተች ልክ፣ ብራቮ ዘመዴ፣ ሸዋን ስተች ልክ፣ ብራቮ ዘመዴ፣ ጎጃምን ስተች ጓ ገርገጭ አይሠራም። ከጎንደር የፖለቲካውን ቅማንት የትግሬ ዲቃላውን ታግዬ ስብርብሩን እንዳወጣሁት፣ ከሸዋም የፌክ ኢትዮጵያኒስቱን፣ የስኳድ አሽከር፣ የዶላር ዕዙን እንኩትኩቱን እንዳወጣሁት በጎጃምም የአገው ሸንጎውን እና የብአዴንን ሴል ጎትቼ፣ ጎትቼ፣ መዝዤ አወጣዋለሁ። ማንም አያስቆመኝም። እስቲ ትፈነዳ እንደሁ አያታለሁ። ምንም አባክ አታመጣም። ገበሬ እያስለቀስ፣ እየደበደብክ፣ ከመከላከያ ጋር ተመሳጥረህ ጎጃምን እያስወደምክ፣ የአንተ የአገው ሸንጎ ቁጥርህ ጥቂት ስለሆነ የጎጃም ዐማራውንና አገዉን ለመጨፍጨፍ፣ ቁጥሩን ለማመናመን በሲስተም፣ በተጠና መልኩ በጎጃም ዐማራ ላይ የምትሠራውን ሴራ ካላከሸፍኩማ ሞቻታለሁ።

"…የትግሬውን የኮሎኔል ያሬድ ኪሮስን በበላይነት ተደራድረው ያስመለጡት በአገው ሸንጎ በኩል እነ ዘለቀ ከፋለ የአዊ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እንደሆነ ነው የሰማሁት። ለኮሎኔሉ ሴትና ጫት ሲያቀርቡለት ከርመው፣ ስታሊን ከአሜሪካ ደውሎ፣ ተደራድሮ፣ ብር ተከፍሎለት፣ ከአዲስ ቅዳም የአገው ሸንጎ ወጣቶች በሞተር ሳይክል 30 ኪሎሜትር ተጉዘው መጥተው ይዘውት ሲወጡ ያናድዳል። አሁን ሁሉም የፋኖ አመራሮች ሳይቀሩ መሳሪያ አውርደው በቁጥጥር ስር ውለው እየተመረመሩ መሆናቸውን ሰምቻለሁ። ድርጅቱም ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። በተያያዘ ዜና ይኸው እነዚሁ የአገው ሸንጎ አባላት መሪያቸውን ገድለው ዛሬ የዳንግላ አካባቢ ፋኖዎች ብሬንና ስናይፐርና ሌሎችን መሳሪያዎችን ጭምር ይዘው እንጅባራ ድረስ ሄደው አገዛዙን ተቀላቅለዋል። እንጅባራ ግቡ ሲባሉ አይ አንገባም የሚሉትም ለምን እንደሆነ አሁን በደንብ እየተገለጸልህ ይመጣል። ነገርኩህ አልፋታህም። ከነከስኩ ሳላደማ፣ የነብር ጭራ ይዤ ስለቅ አይተኸኝ ታውቃለህ?

• ይደፈርሳል… ግን ደግሞ ይጠራል…✊

•••

ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ታሕሳስ 17/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…ከትናንት ወዲያ በዕለተ ማክሰኞ ጠዋት በቴሌግራም፣ ምሽት በቲክቶክ፣ ትናንት ደግሞ በርእሰ አንቀጼ ላይ የጎጃም ፋኖን በተመለከተ የተጠራቀመ የሕዝብ ብሶትንና እሮሮን መነሻ ምክንያት በማድረግ ሓሳብና ትችት፣ ሸንቆጥም፣ ዠለጥም የሚያደርግ ሓሳብ ሳራምድ፣ መልእክት ሳስተላልፍ መዋል ማደሬ ይታወቃል። ያን የእኔን የዐማራ ፋኖ በጎጃምን መተቸት ተከትሎ ቀላል የማይባል ቁጥር ባላቸው የዐማራ ፋኖ በጎጃም አደረጃጀት ወዳጆች ዘንድ ድንጋጤ፣ መረበሽ፣ ስጋት መፈጠሩን አይቻለሁ። የስጋታቸው መነሻም የፋኖ አደረጃጀቱ በተሻለ ቁመና ላይ ስለሚገኝ እንደው ዘመዴ ዐሳብ ስታነሳ ችት ስታቀርብ ጠላት እንዳይጠቀምበት፣ በውስጥ ቢያልቅ ወዘተ የሚልና የፋኖ አደረጃጀት አሁናዊ ተቋማዊ ገጽታ ምን እንደሚመስል ካለማወቅ የመጣ ስጋት ያንጸባረቁ ነበሩ። ስጋታቸው ስለሚገባኝ፣ ክፋትም ስለሌለው እነሱን "አይዞኝ" ብሎ ማለፉ በቂ ነበር።

"…ሌሎች ደግሞ ለእኔ ቀን የሚጠብቁልኝ ተረፈ ብአዴኖች፣ ዐማራ መሳይ አሞሮች፣ በጎጃም የተሰገሰጉ ያልተገለጡ የፋኖ ወዳጅ መሳይ ብአዴኖች፣ ዐማራ ሆነው በሃይማኖቴ የሚጠሉኝ፣ ኦርቶዶክስ መሆኔ የሚያንገበግባቸው አንዳንዶች የወሃቢይ እስላምና የብልፅግና ወንጌል አማኝ ዐማሮች አንዳንዶቹ ደፍረው፣ ፈራ ተባ እያሉ ሲጽፉ፣ ሌሎች ደግሞ ፈራ ተባ እያሉ በእነዚህ ሰዎች የተጦመረውን ጦማር ሼር ሲያደርጉ ነበር የዋሉት። እጠቅሳለሁ። በብዕር አጣጣሉ፣ ባለማቋረጥ በሚሰጠው መረጃ፣ በአጫጭር ግን ግልጽ መልእክት በመጻፍ በሚታወቀው፣ በተለይም የእስልምናው አማኝ ዐማራወረ ፋኖን እንዲወድ፣ እንዲቀርብ የበኩሉን አስተዋጽኦ ሲወጣ የከረመው እጅግ የማከብረው ዐማራው ብዕረኛ አቶ መሀመድ ሐሰን አንደኛው ነው። መሐመድ ሐሰን ትናንት ባቀረብኩት ሓሳብ ቢተቸኝ መልካም ነበር። ማሜ ግን እኔን ወስዶ ከእነ ሀብታሙ አያሌውና፣ ከእነ አበበ በለው ጋር አብሮ አጃምሎ ግልጽ ያልሆነ ትችት በማንፀባረቁ እኔን ራሴን ባስደነገጠኝ መልኩ ከወዳጅ ዘመዶቹ የትችት ናዳ ሲወርድበት፣ እርሱም ከድንጋጤ የተነሣ አንዳንድ ኮመንቶችን ሲደልት ለመዋል ተገዷል። በእውነት መሀመድ ሀሰን እንዲህ ያለ ወጣ ያለ ስድብ መሰደብ የሚገባው ዓይነት ሰው አይደለም። ከምር የማከብረው ዐማራ ነው። አንዳንዶች እንዳሉት የወሃቢይ እስልምናው ተጽዕኖ አድርጎበት እኔን ክርስቲያን ስለሆንኩም ነው ወስዶ ከእነ አበበ በላው ጋር የጀመለህ እንዳሉትም አይመስለኝም። ወሃቢይ ስለመሆኑም ማረጋገጫም የለኝም። እንዲያውም ፋኖነትን ከእስልምና ነጥለው በሌላ ጠርዝ ላይ ለቆሙ ለዐማራ እስላሞች ፋኖነት ዐማራነት እንጂ እስላም ክርስቲያን እንዳልሆነ ሲያሳይ፣ ሲያስረዳ የኖረ ወንድም ነው። ማሜ አዝናለሁ። ያነሣሁትን ዐሳብ ብቻ ብትተች ጥሩ ነበር። እናንተም ተቺዎች በአንደዜ እንዲህ ከመዘርጠጥ፣ አንሥቶ ከማፍረጥ ተቆጠቡ። ለማሜ የተሰጠውን ኮመንት ዓይቼ "ነግ በእኔ" ነው ያልኩት። በቃ አፉ በሉት።

"…ሌሎች ደግሞ አሉ። እነሱ ቢናገሩት ጠላት እንደሚበዛባቸው ዐውቀው፣ ፈርተው ሌላ ሰው የጻፈውን ፈልገው በገጻቸው ላይ ሼር አድርገው ጸሐፊውም እነርሱም ሲወቁ፣ ሲወቀጡ ውለው ያደሩ። የABC ጋዜጠኛዋ ውቃቢዋም፣ ቀልቧም ከድሮ፣ ከጥንት ጀምሮ የማይወደኝ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አባሏ የወይንሸት ሞላ እህት የምትመስለኝ መልካም ሰላም ሞላ የመሀመድ ሀሰንን ጦማር በገጿ ሼር አድርጋ፣ ዐሳቡን የምትገዛው መሆኑን በማወጇ የደረሰባትን ተቃውሞም አዓይቼ ለእሷም አዝኛለሁ። ይሄ የእሷ ዐሳብ እንጂ የABC የተቋሙ እንዳልሆነ ግን መገመት እችላለሁ። መልካም ከድሮ ፌስቡክ ላይ ሳለሁ ጀምሮ ቀልቧ፣ ውቃቢዋና ቆሌዋ አይወደኝም። አንድ ጊዜ ብቻ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ቀውጢ ተፈጥሮ ዝም ስል "ለዚህ ጊዜ ነበር እንደ ዘመድኩን ዓይነት ሰው የሚያስፈልገው" ብላ መጻፏን አስታውሳለሁ። ሆኖም ግን እሷም ቢሆን በራሷ ዐሳብ አልሞገተችኝም፣ በመሀመድ ሀሰን ላይ ተንጠላጥላ ነው ውርውር ያለችው።

"…ሌላው ከአርበኛ ዘመነ ካሤ ጋር አብሮ ፎቶ በመነሣቱ፣ አርበኛ ዘመነ ካሤን በተለየ እቀርበዋለሁ ብሎ ራሱን የሚያሻሽጠው የጎጃሙ ይኼነው የሸበሉ ነው። ይኼነው የሸበሉም ከድሮ ጀምሮ ቀልቡም፣ ውቃቢውም እንደማይወደኝ ዐውቃለሁ። እሱም እንደ መልካም የመሀመድ ሀሰንን ዐሳብ ነው የገዛው። እሱን ነው አምጥቶ በገጹ ያጋራው። ሆኖም ግን ይኼነውም ያልጠበቀው ግብረ መልስ ነው የገጠመው። አርበኛ ማንችሎትን ተችቶ ጽፎ እነ ተስፋዬ ለምነው ያስነሡትን ረስቶ አሁን የእኔን ሓሳብ ከአበበ በለውና ከሀብታሙ አያሌው ጋር ደምሮ መውቀጥ አግባብ አይደለም ነበር ያሉት ጎጃሞች። እሱ ይኼነው የሸበሉ ከአርበኛ ዘመነ ካሤ ጋር አብሮ የተነሣውን ፎቶ ስለለጠፈ እኔ ከዘመነ ካሤ ጋር የተነሣሁት ፎቶ ስለሌለኝ ዘመነ ካሤን አልቀርበውም ማለት እኮ አይደለም። እሱ ይኼነው ጎጃሜ ነኝ ስላለ እኔ የሐረርጌ ቆቱው ዘመዴ ለጎጃሞች ሩቅ ነኝ ማለትም አይደለም። ከይሄነው በላይ በምድር ያሉት ጎንደርም፣ ጎጃምም፣ ሸዋና ወሎም ያሉት የፋኖ አመራሮች ከሚገመተው በላይ ወዳጆቼ ናቸው።  ለምሳሌ ፋኖ ማርሸት ፀሐዩን በግልጽ የተቸሁት እኔ ነኝ። ትችቴን ተከትሎ በእኔ ትችት ባይሆንም ማርሸት ወዲያው ነበር ከሁለት ሓላፊነቶች የተነሣው። ፋኖ ማርሸት ግን እስከአሁኗ ደቂቃና ሰከንድ ድረስ ያልተቋረጠ ወዳጄ ነው። መማር ደጉ ማለት ይኸነዜ ነው። ማርሸትን ለከፍተኛ ማዕረግ የምጠብቀውም ከዚህ ተነሥቼ ነው። ሓሳቤን ስሸጥ ሓሳቤን የሚገዛ ካገኘሁ የሌላው ነጋዴ መንፈራገጥ ከቅናት የዘለለ ሌላ ነገር የለውም። ይሄነው የሸበሉም ብዙም ባይወቀጥ ደስስ ይለኛል።

"…ሌላው መንቆረር ኢንሳይደር በሚባለው የፌስቡክ ፔጅ ሲያንጸባርቀው የዋለው ሓሳብ ነው። ከጎጃም ፋኖዎች መንደር ሲንጨረጨር ያየሁት ይሄንን ፔጅ ብቻ ነው። የፔጁ አስተዳዳሪ በፎቶው ላይ የምታዩት አቶ ጥጋቡ መኮንን ይባላል። ጥጌክስ በግል የማርሸት ጓደኛ ነው። በግል እኔ ከማርሸት ጋር ያወራነውን ዐሳብም በገጹ ላይ አስፍሮ አይቼዋለሁ። መረጃ ለዘመዴ የሚሰጡት ላይ እርምጃ እንወስዳለን ብሎም ሲፎገላ ነበር ያየሁት። ስምን መልአክ ያወጣዋል እንዲሉ አበው አቶ ጥጋቡም ከአሁኑ ምኑንም ሳይያዝ ጥጋብ ደረቱን ነፍቶት ከአሁኑ ደርግና ወያኔን አስንቆ እንደ ሳዳም፣ እንደ ጋዳፊ፣ እንደ ኤዲአሚን ዳዳ ወጠጤ አምባገነን ለመምሰል ሲፎገላ አይቼው ስስቅበት ነው ያመሸሁት። ይሄ የፋኖነት መገለጫ አይደለም። ነገር ግን ጥጌክስ ትተነፍሳለህ፣ ጥጋብህም ይበርዳል እንጂ እንደፎገላህ አትቀርም። ጥጌክስ ጥጋቡ ከጎጃም አልፎ ወሎና ሸዋ ውስጥ ባሉ ታጋዮች ጭምር ላይ ነው ሲፎገላ፣ ሲዝት የዋለው። እኔ ደግሞ እንዲህ ዓይነት ደንቆሮ ሳገኝ ማገዶ ፈጅቼም ቢሆን ሊቅ ነው የማደርገው። ይሄን ፋኖ አሰዳቢ ጥጋበኛ ጎጃም አሰዳቢ ነውረኛ ሰገጤ ጊዜ ወስጄ አበርደዋለሁ። ሰከን አደርገዋለሁ። ጥጋቡ ጠግበህ ጠብቀኝማ።

"…ሌሎች ግን ገና እኔ በጎጃም ዐማራ ፋኖ ላይ የትችት፣ የተግሳጽ፣ የጭቃ ዥራፌን እመዛለሁ በማለት ቀጠሮ ሲያዝ ጮቤ ረግጠው፣ ፌሽታ በፌሽታ ሆነው፣ እየጨፈሩ አዋራ ሲያስነሱ የዋሉም ነበሩ። ስኳድ ጌትነት ይስማውና ሙላት አድኖ የፈራ ይመለስ በቃ የሴራ ቦለጢቃ ሠራን ብለው ብብታቸውም፣ ብሽሽታቸውንም እስኪያልባቸው ነበር የተወራጩት። ቁናስ በቁናስ ሲያደርጉን ነበር የዋሉት። እነሱ በሴራ ሚሳኤል፣ በሴራ ፈንጅ፣ በሴራ ቦንብ፣ በሴራ መድፍ፣ በስድብ፣ በሀሜት፣ በቲክቶክ፣ በፌስቡክ፣…👇①✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…የዕለቱን አፍራሽ፣ አደፍራሽ ድማሚት፣ ቆሻሻውን ማንጠሪያ፣ ወንፊት፣ ሰፌድ የሆነውን ርእሰ አንቀጼን ልለጥፍ ነኝ።

"…የፈረንሳዩና የኢትዮጵያው መሪ በአዲስ አበባ መስቀል ረግጠው፣ የአዲስ አበባው በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በራብና በሽንፈት ሲሰቃይ፣ የፈረንሳዩ አማኑኤል ማክሮን ወደ ፈረንሳይ ሳይመለስ የፈረንሳይ ምልክት የሆነው አይፊልታወር በእሳት ስለመንደዱ አይደለም የምጽፍላችሁ።

"…4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ የተነጠፈው መስቀል የዛሬ እንዳይደለ፣ አፄ ኃይለ ሥላሴ ያስነጠፉት እንደሆነና ካቴድራሉ ለእድሳት ሲነሣ የኢትዮጵያ መንግሥትና ቅዱስ ፓትርያርኩ አንዳች ነገር እንዳይነካ በደብዳቤ ማዘዛቸውን፣ መስቀሉ ሲረገጥ ኖሮ አሁን ለእድሳቱ ምንጣፉ ሲነሣ መታየቱን፣ አፄ ኃይለሥላሴ በማን ትእዛዝ እንዳሠሩት ፈጣሪ ይወቀውና ይኸው እሳቸውም መስቀል ሲረግጡ ኖረው በመጨረሻም በትራስ ታንቀው፣ ያዋረዱት መስቀል አዋርዷቸው፣ ሌባ ሌባ አስብሎአቸው፣ ደርግ ሽንት ቤት ቀብሮ በላዩ ላይ ቢሮ ሠርቶ እንዴት እንዳጠፋቸው፣ አሁን ሥላሴ የተቀበረው አጽም የጃንሆይ ስለመሆኑ ማረጋገጫ እንደሌለ፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ መስቀሉ አይነሣም ስለማለታቸው፣ ምእመናንም መስቀሉን መርገጥ ይቀጥላሉ ስለመባሉ። ኢትዮጵያም በመከራ መረገጧ፣ ስለመቀጠሉ፣ ስለ ፀሐይ ደም መልበስም አይደለም የጻፍኩት።

"…የጻፍኩት የጎጃሙን የዐማራ ፋኖ ከተቸሁ በኋላ በማኅበራዊ ሚዲያው እነማን ተንጫጩ፣ እነማን ስሜታቸውን በምን መልክ ገለጹ፣ የጎጃም ዐማራ ሕዝብም፣ የማኅበራዊ ሚዲያው ሠራዊትም ትችቱን እንዴት ተመለከተው? እነ ስኳድ፣ እነ ፌክ ኢትዮጵያኒስት፣ እነ ግንቦቴስ ምን አሉ? ምን ተሰማቸው የሚለውን ነው ዳስሼ ለውይይት ያቀረብኩት።

"…እህሳ ለማንበብ፣ አንብቦም አስተያየት ለመስጠት ዝግጁ…? አንድ 100 ያህል ሰው ዝግጁ ነነ ዘመዴ ይበል እስቲ።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የሆነ ጊዜ ነው አሉ…

"…መምህሩ ዐውደ ምህረት ላይ ቆመው ወንጌል ይሰብካሉ። በስብከታቸውም መሃል "…የአቦን መገበሪያ የበላ ሳይጠይቁት ይለፈልፋል" በማለት ታሪክ ጠቅሰው ይሰብካሉ አሉ። ኋላ ላይ አንዱ ተሰባኪ ምእመን ማንም ሳያስገድደው፣ ሳይዘተይቀውም ድንገት ብድግ አለላችሁና ጥያቄ አለኝ፣ ጥያቄ አለኝ መመሩ አይል መሰላችሁ?

• ጠይቅ ምንድነው ጥያቄህ አሉታ መምህሩ?

"…መምሬ አሁን ያስተማሩት ትምህርት ልክ አይደለም። ለምሳሌ እኔ የጊዮርጊስን መገበሪያ በልቻለሁ። ይኸው እስከአሁን ድረስ ግን አለፈለፍኩም በማለት ሙግት ጀመራቸው።

"…መለሱለታ መምህሩ። "…እና አሁን ምን እያደረገህ ነው? ማንስ ጠይቆህ ነው እንዲህ በአደባባይ የቲክቶክ አክቲቪስት ይመስል የምታወራልን? ዥል… አሉት አሉ።

"…ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ… የአቦን መገበሪያ የበላ ቆርፋዳ ቁርፍድፍድ የደም ነጋዴ ሁላ በየስፍራው እየተንጫጫ ነው አሉ።

• ጩህ፣ እበድ፣ እሪ በል… ምንአባህ ልታመጣ…ዝተት ሁላ… ደግሞ ሰደብከን ብለህ አጓራ አሉህ። 😂😂😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ለዘመነ ካሤ አድርሱለት…

"…ይሄን መልእክት እንደ ቀልድ እንዳታዩት። የጥላሁን አበጀ ወዳጅ ኮማሪቷ አዝዛለችና ዘመነ ካሤን የተለየ ጥበቃ አድርጉለት። ተናግሬአለሁ የጋለሞታ፣ የማይም የአዝማሪ ወሬ ነው ብላችሁ ንቃችሁ እንዳታልፉት። ዘመነን ለማዘዝ የሚሞክረው በቲክቶክ ገንዘብ አጠራቅሞ የራሱ ገዳይ ፋኖ ያዘጋጀ አካል ብቻ ነው።

"…የእኔ ሥራ ቅዳሜ በገበያውም ቀን ሆነ በሌላው በአዘቦቱም ቀን ቢሆን አቅሙን በማያውቅ በማንም ወፈፊት ዐማራ አሰዳቢ ክብረ ቢስ ጋለሞታ የማይመራ፣ የማይታዘዝም ጥርት ያለ የዐማራ ፋኖ ትግል መፍጠር ነው።

"…አይደለም ኮመንት መስጫ ሰንዱቅሽን ገና ክፍት ልቅ ስድ የጎጃም ዐማራ አሰዳቢ ሸታታ አፍሽን ነው ጥርቅም እንድታደርጊ የማደርግሽ። የጎጃም ዐማራ ስንትና ስንት ሊቃውንት ሞልተውት በማንም ያረጠች፣ ምራቋ ከምላሷ ላይ በደረቀ ጋለሞታ አይወከልም። አይመራም።

"…በዚህች የተነሣ ዐማራ እንዲህ ነው እንዴ ብለው ሌሎች ሲታዘቡት እንደማየት የሚያም ነገር የለም። እነ እመሆይ ገላነሽ ከወጡበት ሀገር እንዲህች ዓይነት ስድ አደግ አሳዳጊ የበደላት ትወጣለች ቢባል አሁን ማን ያምናል? ስሜ ልክ ነው የማስገባሽ። ሥርዓት ነው የማስይዝሽ አንች አቦሬ አፍ። ጠብቂኝ።

"…አንቺንና ወንድሜን፣ አክባርዬን ዩሪን ደውዬ ሁለታችሁንም በስልክ በመረጃና በማስረጃ አነጋግሬአለሁ። ሥነ ሥርዓት ያዢም ብዬ ዩሪ ፊት ነግሬሻለሁ። እምቢ ብለሻል፣ ጨርቅሽን አስጥዬ ብቻሽን እንድታወሪ ነው የማደርግሽ። እጅሽን ከጎጃም ፋኖ ላይ በግድ ታነሺያለሽ። በግድ አልኩሽ።

• እኔ ዘመዴ ነኝ። እኔ ጃል ወያ አይደለሁም። ዮኒ ማኛም፣ ጂጂ ኪያም አይደለሁም። እኔ ቤታዮም ሞጣም አይደለሁም። እኔ ዘመዴ ነኝ። የዳዊት ጠጠር። ቤተሰቦችሽ ወዳጆቼ፣ አክባሪዎቼ ስለሆኑ እንጂ አሳይሽ ነበር።

• ጎጃም ነኝ ተከተሉኝ…🏃‍♂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የጎጃም ጉብኝቴ ቀጥሏል።

"…ጎጃም መግባቴን የሰማው አርበኛ ጠበቃ አስረስ ማረ በአካል ባንገናኝም በስልክ ደውሎልኝ ረዘም ላሉ ደቂቃዎች አውርተናል። በጎጃም ጉብኝቴ ወቅት እንዳይርበኝ፣ እንዳይጠማኝ ሁላ ነው ሲጨነቅልኝ ያመሸው። ወቅቱ የጦም ወቅት ስለሆነ የጎጃምን ቅቤ፣ ብርንዶ ቁርጥ ሥጋውን ለመብላት እንዳልታደልኩ ቢነግረኝም እኔም ጉብኝቴን እስከ ጥምቀት፣ አልፌም አስተርዮ ማርያም ድረስ ላራዝም እንደምችል አውርተናል

"…በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ከጠበቃ አርበኛ አስረስ ማረ ጋር ሳወራ። የሕግ ሰው ስለሆነ ከጠበቃ ጋር ማውራት በጣም ከባድ ስለሆነ ነበር የምሸሸው። አሁን ግን የግድ አወራሁት። በጉብኝቴም ደስተኛ ነው። የሚናገረው ነገር የሚገባ፣ ደግሞም አድማጭ፣ ለእኔም እንጨት እንጨት ለሚለው ቀልዴ ከልቡ እየሳቀ እኔን ያላሳፈረኝ ሰው ነው። እጅግ ነው ያከበርኩት።

"…ጎጃም ምርመራዬ ይቀጥላል። የስህተቱ፣ የጥፋቱ ክር እየተመዘዘ የማከብረው አርበኛ ዘመነ ካሤም ሆነ አርበኛ ጠበቃ አስረስ ማሬ ጋር ካደረሰኝ አዛኜን አልምራቸውም። አልፋታቸውም። እኔ ቋሚ ወዳጅም፣ ቋሚ ጠላትም የለኝም። ይኸው ነው።

"…የጎጃም ዳያስጶራ ምሁራንን ሳላደንቅም አላልፍም። እስከአሁን በሥራዬ ጣልቃ የገባ የጎጃም ዐማራ አላየሁም። አልገጠመኝምም። በጎጃም ስም ጎጃም ስለተወለዱ ብቻ እንደ ጠላት የሚቆጥሩኝ የሸንጎ አባላትና ፀረ ዐማራዎቹ ብአዴኖች ብቻ ናቸው ውርውር ሲሉ የማያቸው። በተለይ የጎንደር ስኳድ ደክሞት ስለ ሰኔ 15 ጉዳይ ማውራት ጀምሯል። 😂

"…የጎጃም ጉብኝቴ ይቀጥላል። እስከአሁን ግሩም መስተንግዶ ነው እየተደረገልኝ ያለው። ለጠበቃ አስረስ አጋር፣ መድኅን፣ ወዳጅ ለመምሰል የደከማችሁም አረፍ በሉ። ወይም ተኙ። እሺ… ስንት አይነት ቃጥራ አለ በማርያም…

• ይደፈርሳል ግን ደግሞ ይጠራል…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አዛኜን አልኩህ ሴራውን አፈርሰዋለሁ…!

"…አዲስ ጌታነህ ዘመነ ከመታሰሩ 1ቀን ቀደም ብሎ ከጠበቃ አስረስ ማረና ከመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ጋር ይህችን ፎቶ ለጠፈ። ዘመነ ወዲያው በማግሥቱ ወደ ዘብጥያ እንዲወርድ ተደረገ። ያነዜ እኔ እየሳቅኩ ነበር። ነገርየው ልክ እንደ እስክንድር "ከጎጃምም ይሄን ጥገኛ የዐማራ አቀንጭራ እስር ያገነነው ጀግና ለማድረግ ነበር።😂

"…ቆየና የዐማራ ፋኖ በጎጃም ሲጠናከር ወጣቶቹ እነሻለቃ ዝናቡ ሰማይ ምድሩን ሲያናጉት፣ አገዛዙ የማያውቀው ኃይል፣ የዐማራ ልጆች የሚመሩት ቡድን መፈጠሩን ሲታወቅ ብአዴኖች ከወሎ ዘሪሁን ገሠሠን፣ ከጎጃም አዲሱ ጌታነህን በምህረት ፈቱ። 😂 እኔም ልክ የተፈቱ ቀን ድራማው ተጀመረ ብዬ ጦመርኩ። የጎጃሙ የፖለቲካ አገው ፀረ ዐማራና ፀረ አገው ሸንጎ ሊንጫጫብኝ ቢሞክርም አልገፉበትም።

"…አርበኛ ዘመነ ካሤ ሁሉን አልፈልግም፣ በቃኝ፣ ሰው የለም ብሎ ትግሉን ትቶ ከሰው ርቆ ከተቀመጠበት ድረስ ሄደው መሪ ሁነን ብለው እግሩ ላይ ወድቀው ወደ ትግሉ ያመጡት አርበኛ ማርሸት ጠበቃ አስረስ ናቸው። አስረስ በድርድር ጉዳይ ለቢቢሲ በሰጠው ቃለመጠይቅ ድንብርብሩ ሲወጣ ጊዜ ነው ዘመነን ወደ መፈለግ የሄዱት። ሌላ ጊዜ በሰፊው እሄድበታለሁ።

"…እናንላችሁ ወየንቲቲው አዲስ ጌታነህ ልክ እኔ ጎጃም ገብቼ ሟሟቅ ስጀምር አድፍጣ ከተደበቀችበት ጎሬ ወጥታ "አንድ ደንቆሮ ግልብ ግለሰብ" ብላ አረፋ ደፍቃ እየሰደበችኝ ተከሰተችላችሁ። እኔ ደንቆሮው፣ ግልቡ፣ መሃይሙ፣ ማይሙ፣ መራታው ዘመዴ የክሩን ጫፍ ይዤዋለሁ እንዴት እንደምተለትለው ጠብቀኝ።

• ከባድ ይመስላል ግን ደግሞ ለፈጣሪ የሚሳነው ነገር የለም። እጅግ ቀላል ነው። እኔ የሀረርጌው ቆቱ ዘመዴ እኮ ዐማራ ያልሆነውን በጆሮው ቅርጹ ሁላ ነው የምለየው። 😂😂😂

• በነገራችን ላይ በጎጃም ሥራ ገና አልጀመርኩም።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ማሳሰቢያም… ማስጠንቀቂያም ነው።

"…እኔ ቀላል ነው ብዬ ገምቼ የነበረው የጎጃም ጉዳይ እንዳሰብኩት ቀላል አልሆነም። በቃ ቀላል አይደለም ስል ቀላል አይደለም ነው። የጎጃም ዐማሮች፣ እና የጎጃም አገዎች ከተባበሩ፣ ከተቀናጁና ከተግባቡ፣ ከተማመኑም፣ በመሃላ ጭምር በቃል ኪዳን ከተሳሰሩ ብቻ ነው የጎጃም ጋንግሪኑ፣ ካንሠሩ የሚቆረጠው። ያለበለዚያ እመኑኝ የጎጃሙ ከሌላው የዐማራ ክፍል ከምትገምቱትና ከምታስቡት በላይ የከፋ፣ የከረፋ፣ የሸተተ፣ የገማ፣ የጠነባ፣ የተግማማ ሸታታ የሆነ ሴራ ነው ያለው። ወደ ውስጥ ስገባ ያገኘሁት እሱን ነው።

"…ስለዚህ የሸዋን ሴረኛና ባንዳ ስናገር፣ የወሎን ሾተላይ ስቀጠቅጥ፣ የጎንደርን ስኳድ ስወግር፣ ስፋለም ከዳር ቆመህ ስታጨበጭብልኝ፣ በርታ ዘመዴ፣ ብራቮ ዘመዴ ስትለኝ የከረም የጎጃም ሾተላይ፣ ሰንኮፍ፣ ካንሰር፣ ጋንግሪን አሁን ወደ ጎጃም ስመጣ እንበጫበጫለሁ ብትል አልሰማህም። አንተ ከሌላው ዐማራ ሰንኮፍ አትበልጥም፣ አታንስም። ሥነ ሥርዓት ይዘህ ትቀመጣለህ።

"…በጀመርኩት የጎጃም ዐማራንና አገውን የመታደግ ጉዳይ ዐማራ ዐማራ እጫወታለሁ ብለህ ወደ ፔጄ ገብተህ እኔንም ሆነ፣ በእኔ ፔጅ ላይ በጨዋ ደንብ የመሰላቸውን ሓሳብ የሚሰጡትን የቤቴን ሰዎች እሰድባለሁ፣ እዘልፋለሁ ስትል ባይህ እንድትናፍቀኝ አድርጌ ነው ወገብ ዛላህን ቆርጬ ቀስፌ እገላግልህሃለሁ።

• ማሳሰቢያ፦ አገውና ዐማራ አንድ ነው። አገው ማለት የቅዱስ ላሊበላ ዘር ማለት ነው። ፍልሚያው ከፖለቲካው አገው ሸንጎው ከፀረ አገውና ዐማራው ጋር ነው። ስለዚህ አስተያየት ስትሰጡ ሸንጎንና አገውን እየለያችሁ ይሁን።

• በተረፈ አንት ክፍታፍ ሸንጎ፣ ቅዘናም ብአዴን፣ ፀረ ጎጃም ሾተላይ ሁላ ማስጠንቀቂያዬን አክብር። እመነኝ የነብሩን ጭራ ይዤዋለሁ፣ ሳላደማው አልመለስም። ማርያምን አልኩ እኮ። ፈሳሙ ስምተሃል።

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ገብርኤል ሆይ ከጭንቅና ከመከራ ለማውጣት የተላክህ መልአክ ነህና ሠለስቱ ደቂቅ በእሳት ጉድጓድ በተጣሉ ጊዜ ሁለቱ ክንፎችህን ጋርደህ ከመቃጠል እንዳዳንሃቸው እኔንም አገልጋይህን በረድኤትህ ኃይል አድነኝ" መልክአ ገብርኤል

• እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል በሰላም አደረሰን።

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ጎጃም ከገባሁ ገና አራተኛ ቀኔ ነው። በነገራችን ላይ የጣና አየር የገነት ነፋስ ነው። እናም እሱን እየማግኩ በወፍ በረር ጎጃምን እየቃኘኋት፣ እየመረመርኳት ነው። በጎጃም ትንሽ ሳልከርም አልቀርም።

"…ዋሸራ ሄጄ ቅኔ ባልቀኝ እንኳ የሚቀኙትን ሰምቼ፣ አድምጬ፣ ዲማ ጊዮርጌስ፣ መርጦ ለማርያም፣ ደብረ ማርቆስ የድሮዋ መንቆረር ደረስ ብዬም እመጣለሁ። ሶማ በረሃውም ላይ ወረድ ለማለት አስቤአለሁ። ደብረወርቅ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ቡሬ፣ ቲሊሊም ደረስ ብዬ፣ ዘንገና ሀይቅን ጎብኝቼ እመለሳለሁ። ፍኖተ ሰላም፣ ዳንግላም ገብቼ ሸንኮራአገዳ ሸምቼ ነው የምመለሰው።

"…ባይገርምላችሁ የተማረ ይግደለኝ አይደል የሚባለው ቁስሉ፣ በሽታው ያለበት እከካም ሸታታ ብቻ ነገሩ ሳይገባው፣ መዳረሻዬን ሳያውቅ ክፍት አፉን ከፍቶ እኔ ላይ ለማጓራት ሲባትት፣ እንደ አበበ ዶላር በላው የትግሬ ዲቃላውም ሰገጤ ገጠሬ እሱም አራዳ ሆኖ ከጎጃም ጋር ሊያቀሳስረኝ ሲንተባተብ ይታያል። ጎጄ መለኛው ግን ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኖ ትዊተርን በክርስቲያን ታደለ ፎቶ አጥለቅልቆ "ለክርስቲያን ታደለ ህክምና ያገኝ ዘንድ፣ የታሰሩት ሁሉም የዐማራ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ዘንድ "በትዊተር ስፔስ ከፍተው Save ChristianTaddele & all Amhara Poltical Perisoners እያለ ይታገላል። ጋለሞቶቹና ጎጃም አሰዳቢ ክፍት አፍ መንደሬ የቲክቶክ ለዛቢስ ቀዳዶቹ ደግሞ የኮመንት ሰንዱቃቸውን ዘግተው በአቦሬ ልቅ አፋቸው ሲንጫጩ ይታያሉ። ጎጄ መለኛው ግን እሱ እቴ ሥራም አላጣ። አቦ የተስተማረ ይግደለኝ። እንደ ስኳድ ቀፎ፣ ባዶ ቆርቆሮ እኮ አይደለም። በማርያም ተቀላቀሏቸው።

• የጎጃም ጉብኝቴ አልተጀመረም። ይደፈርሳል ነገር ግን ይጠራል። አዛኜን እነ ዘመዴ አደርገዋለሁ።

• እስቲ እናንተ ደግሞ ተንፒሱ…!

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆③✍✍✍ …እዋጋሃለሁ። ምንአባክ ታመጣለህ? ምንም አባክ አታመጣም።

"…ለምሳሌ ቢዛሞ ሚዲያ የሚባለውን ተመልከቱ። እኔ ስለወለጋ የተናገርኩት በስሱ ነው። ምንም ፍንጭም አልሰጠሁም። ገና ለገና ምን ሊናገር ነው ብሎ ከወዲሁ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ መሳቂያ መሳለቂያ እየሆነ ነው። ለዐማራ ተስፋ ይሆናሉ የምላቸው ሚዲያዎች ሁሉ አቅመቢስ፣ የብላኔ እየሆኑ ባይ ለዐማራ ከምር አዘንኩ። ቢዛሞ ሚዲያ እንዲህ አለ። " ዘመድኩን በቀለ የወለጋን ፋኖ ለመተቼት ለፊታችን እሁድ ቀጠሮ መያዙን ተናግሯል። እንደምክናየት ያነሳው ደግሞ በዋናነት ሌሎች ጋዜጠኞች የወለጋ ፋኖ መመስረቱን በሰበር ዜና ሲያንሸራሽሩት እኔ ከበላይ ማናዬ ከፋሲል የኔአለምና ከመሳይ መኮነን በምን አንሼ ነው መጀመርያ መረጃው ያልተሰጠኝ የሚል ጥያቄ ለወለጋ ፋኖ አመራሮች እንዳቀረበላቸውና በዋናነት ንጉሴ ዋለልኝን (የዕዙ ሰብሳቢ) ወቀሳ እንዳቀረበበትና በዋናነትም እሱን እንደሚተቸው ተናግሯል ብሎ ጓ ብሎ አየሁት። እኔና ንጉሤ የቆየ ወዳጅነትና ትውውቅ ነው ያለን፣ ስጋቴን እናገራለሁ አልኩ እንጂ ሌላ ነገር አልወጣኝም። ለምሳሌ ዛሬ እንኳ እኔና ንጉሤ ከ30 ደቂቃ በላይ ነው ደውሎልኝ ያወራነው። ዘመዴ ወለጋዎች ምስረታቸውን በተመለከተ ለኔ ቀድመው ለምን አልነገሩኝም በማለት ነው ያኮረፈው ማለት ምንማለት ነው? እኔ እንዲህ ብዬ የጻፍኩት ጦማር የለም። ምናልባት የውስጥ ልቦናዬን ኡጋንዳ ተቀምጦ መርምሮ እንዳይሆን እዚህ መደምደሚያ ላይ የደረሱት። ለማንኛውም የጎጃም ጉዳይ ተጀመረ እንጂ ገና ምኑንም አልነካሁም።

"…የቆየ ሞላ ደውሎልኝ ሰፊ ጊዜ ወስደን አውርተናል። ተጠያቂነት ይስፈን፣ የሚስተካከለው ይስተካከል፣ የአንተን የዘመዴን ምክረ ሓሳብ የማይቀበል የዐማራ ፋኖ አደረጃጀት የለም። እኔም ያጠፋሁት ካለ መተቸት፣ መጠየቅ አለብኝ፣ ለዚህ ደግሞ ዝግጁ ነን ዘመዴ ነው ያለኝ። የሰከነ፣ ሃቅ ላይ የተመሠረተ፣ በኮሎኔሉ መጥፋት ዙሪያም ምንም ሳያለባብስ ማስታወሻ ያዝማ ዘመዴ ብሎ አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት ብሎ ቆጥሮ ሁሉን ነገር ያስረዳኝ ሰው ነው። የሚያውቁኝ ያውቁኛል። የሚጠቅም፣ የሚያንጽ ሓሳቤን ነው የሚቀበሉት። ኡጋንዳ ተቀምጦ የካናዳ ወረቀት እየጠበቀ፣ ፋኖ ወንድሙ የዐማራ ገበሬን፣ ነጋዴን አስለቅሶ ዘርፎ ያገኘውን ገንዘብ እየላከለት ፖለቲካ ልሠራ ነኝ፣ ቦለጢቃ እየሠራሁ ነው የሚለውን ጋጠወጥ፣ ረኸጥ አልፋታውም። ዐማራስ ባልሆን፣ ሶማሊያዊ፣ ፓክስታኒያዊ፣ የላኦስ ሰው፣ ጃማይካዊ፣ ወይም ፔሩአዊ ብሆንስ ሌባን፣ ነፍሰገዳይን መቃወሜ ዘሬን፣ ማንነቴን ጠቅሶ ለምን ያስብላል እንዴ? በፍጹም። የተነሣው ሓሳብ ላይ ብቻ ተሟገት። ስለመልኬ፣ ስለ ዕድሜዬ፣ ስለ ቁመቴ፣ ስለ ውፍረት ቅጥነቴ ማን ሞግተኝ አለህ? ገና ለገና እንዲህ ሊናገር ነው ብሎ አስቀድሞ መለፍለፍስ ምን ይባላል?

"…አሁንም እላለሁ ምሥራቅ ጎጃምን ያስበሉት እነ ጥላሁን አበጀ ምዕራብ ጎጃም ተደብቀው፣ ሥልጣን ይዘው ቀለብ መጨረስ የለባቸውም። የራሱን ቀጠና ለጅቡ ብአዴን ሰጥቶ ሲያበቃ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ጎጃም ሰፍሮ የገበሬ እህል መጨረስ ወንድነት አይደለም። ሽንታም ሁላ። አስነጥስህሃለሁ። አሁን ምሥራቅ ጎጃም ውስጥ ካሉት ክፍለ ጦሮች መካከል በዓባይ ተፋሰስ አቅራቢያ በላይ ዘለቀ እና ሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦሮች ይገኛሉ። ከበላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ውስጥ ዛምብራ ብርጌድ የሚባለው በደጀን ጉበያ እና ዛምበራ በርሀ ውስጥ የሚገኘው እንዲሁም የእነማዩ አባኮስትር ብርጌድ እና የእናርጅ እናውጋው ሶማ ብርጌድ በጥሩ ይዋጋሉ። በተለይ ሶማ ብርጌድ ትዕግስት ጫንያለው ተረፈ ያለችበት ብርጌድ ስለሆነ አኩሪ ገድል ፈጽመው ታይተዋል። ጋዜጠኛ ወግደረስንም ያለምንም ደም መፋሰስ በጥበብ ይዘዋል። ተመስግነዋልም። ሌሎች ግን ተጃጅለዋል።.አሉ ማለት አይቻልም።

"…ልብ በሉ የበላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር የሕዝብ ግንኙነት ግንቦቴው ይሁዳው ጥላሁን አበጀ ነበር። እሱ በመስከረም ከቦታው ሲነሳ የአባኮስትር ብርጌድ ጠቅል ሻለቃ ህዝብ ግንኙነት የነበረው ይበልጣል ጌቴ ነው የተተካው። በቅርቡ ይበልጣልም ተሻረ። በይበልጣል ጌቴ ምትክ ደግሞ የዛምበራው ሕዝብ ግንኙነት ዓባይነህ ምህረት ተመደበ። አባይነህ ከተሾመ በኋላ 1 ቀን በኢትዮ 251 ሚዲያ እንደሰማነው በማግሥቱ ጓዶቹ ጋር ምሳ ሲበሉ በድሮን ተገደሉ። ይሄን መዝግቡልኝ። ሠራዊቱ እነ ዓባይነህ በድሮን የተገደሉት በሴራ እንደሆነ ደርንበታል ነው የሚሉት። እስከአሁን ድረስ የሚገርመው ነገር አስተኳሽ የተባሉት ሰዎች አለመጠየቃቸው ነው። (በአፋጎም) ብዙዎች ተስፋ እንዲቆርጡ እያደረጋቸው ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የነቃውን ቲም አስገድለው የዛምብራ ብርጌድ ሪፎርም ብለው የቀረውን አመራር በሴራ ገልብጠው ቀደም ሲል በጎበዝ አመራሮች እንዲታሰሩ የተደረጉት ሌባዎችን እና ንፁሀንን የሚረሽኑትን ሰብስበው አምጥተው ሾሟቸው። ልብ በሉ አሁንም አምጥተው የሾሙት ሕዝብን ያስመረሩትን ወንበዴ ሌቦችን ነው። አሁን ላይ የተሻለ አመራር ስለሌለ እነዛ ሌቦች ዛምብራ ብርጌድን ተቆጣጥረውታል። ለምሳሌ የብርጌዱ ሰብሳቢ የሆነው አቶ በረደድ እልም ያለ ሌባ ነው። ፈንዳ ምን ታመጣለህ። ዝርዝር ከፈለግክ እዘረግፍልሃለሁ።

"…በነገራችን ላይ የበላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሰብሳቢ ሻለቃ በላይነህ ዋልተንጉሥ የሚባል ጀግና ሲሆን በፊት የእነ ዝናቡ ዕዝ የምስራቅ ጎጃም ክንፍ መሪ ነበር። አሁንም ክፍለ ጦሩን በሀቅ እየመራ ነው ግን ከስር ያሉ ጥቅመኞች ግን ፈተና ሆነው አላላውስ ብለውት እጅከወርች ታስሮ ነው የተቀመጠው። ለምሳሌ የአባ ኮስትር ብርጌድ ሻለቃዎች እርስበርስ አይስማሙም ነበር። ጥላሁን አበጀ የመሰረተው ሽፈራው ገርባው ብርጌድም ውስብስብ ችግር አለበት። ለችግር የተደራጀ ብርጌድ ነው የሚመስለው። ወደ ሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦርም ስንመጣ በመርጦለማርያም በኩል ያለው አባይ ሸለቆ ብርጌድ ጥሩ ይሠራል። የእስክንድርን ሚሊሾችም ጠራርጓል። ሻለቃ ይንገሥ የሚባል ጀግና መሪ ያለው ብርጌድም ነው። ሌሎች ብርጌዶች ግን እንደሌሉ ይቆጠራሉ።

• ዓባይነህ እንዴት ሞተ…?

"…ዓባይነህ በድሮን ከመገደሉ በፊት ከአርበኛ ዘመነ ካሤ ጋር ተገናኝቶ እሱ የክፍለ ጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ወይም ቃልአቃባይ ሊሆን ተነጋግረው፣ በስብሰባውም ተመርጦ ነበር። ከዚያ መልስ ግን አብረውት የነበሩት የብአዴን ባንዳዎች ስለነበሩ አብረውት አድረው ጠዋት ላይ ቆይ አንድ ጊዜ እዚህ ጠብቀን የሆነ ቦታ ደርሰን እንመጣለን ብለውት ከተለዩት ከጠቂት ደቂቃዎች በኋላ ነው ድሮኗ መጥታ ቦንብ ጥላ ጀግናው ዓባይነህ ተበጣጥቆ የሞተው፣ የተገደለው። ውሸት ነው የሚል ኡጋንዳ የተቀመጠ የሌባ ተካፋይ ፊትለፊት ይሞግተኝ። የሕዝቡ ሰቆቃ ይብቃ። የጎጃም ሕዝብ በኦሮሙማው መከላከያ፣ በአገው ሸንጎም መጨፍጨፉ ይቁም። የጎጃም ዐማራ በሴራ ልክ እንደ ጎንደር ዐማራ እየተጨፈጨፈ ነው። አገውን ክልል ለማድረግ፣ ጎጃምን ኦሮሞና አገው ሊካፈል ዐማራው በፋኖ መሳይ ፋኖዎች መጨፍጨፍ የለበትም።

"…እየመረረህ ዋጠው። የምናገረው ከጠቀመህ ተቀብለህ አስተካክለው። ካልጣመህ አንቅረህ ትፋው። እኔ ግን እጽፋለሁ። በሸዋ፣ በእስክንድር፣ በምሬ፣ በኮሎኔል ፈንታሁን፣ በጎንደር ስኳድ፣ በወዳጄ በፕሮፌሰር እያሱና በደረጀ በላይ ላይ እንደጻፍኩት እጽፋለሁ። ዘመነ ካሤን ሕዝብ እንዲጠላው፣ የጎንደር ስኳድ እንዲጠምደው ያደረጉትን የጎጃም ነቀርሳዎች እሞግታቸዋለሁ። እውነት ለመናገር አሁን ላይ የፋኖ አጠቃላይ ገፅታ እየተቀየረ መጥቷል። በቶሎ እርምጃና ሪፎርም ካልተደረገ በቀር…👇③✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"ርእሰ አንቀጽ"

"…ዛሬም ጎጃም ላይ ነኝ። እዚያው ነው ስንሸራሸር የምውል የማድረው። ልክ ሸዋ እንደነበርኩት፣ ወሎም ተሻግሬ እንደጎነበኘሁት፣ በጎንደርም ከላይ እስከታች ስምነሸነሽ እንደነበረው ነው አሁን ደግሞ ጎጃም በበላይ ዘለቀ ሀገር፣ በእነ እማሆይ ገላነሽ ሀገር፣ በእነ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ፣ በእነ ሊቀሊቃውንት አለቃ አያሌው ሃገር፣ በእነ የኔታ ዮፍታሄ ንጉሴ ሀገር፣ በእነ ዶር ሀዲስ አለማየሁ ሀገር ያለከልካይ ልምነሸነሽ ዓባይን ተሻግሬ ዘና፣ ፈታ እያልኩ ጎጃም ምድር የገባሁት። ተከተሉኝ። አስጎበኛችኋለሁ።

"…ሸዋ ለጉብኝት ስገባ፣ በዚያም ያየሁትን፣ የታዘብኩትን ስጽፍልህ፣ ስደሰኩርልህ ብራቮ ዘመዴ፣ ወንድ የወንዶች ቁና፣ ጀግናዬ፣ እናት ወለደች አንተን፣ አንበሳዬ፣ ነብር፣ ጎሽና ጥንቸል ሲለኝ የከረመ ገልቱ፣ ገንገበት መንጋ ሁሉ ዛሬ ጎጃም ስገባ ለምን? እንዴት ሲለኝ ብስቅበት፣ ባፍር ብሳለቅበት ደግሞም ብንቀው እንጂ በመቼም ቢሆን ከቁምነገርም አልቆጥረውም። ሸዋ ገብቼ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን፣ ፋኖ መከታው ሞሞን፣ እነ አቤ ጢሞን ጢማቸውን ይዤ ስመረምር፣ ሳስመረምር ልክነህ፣ ያለአንተ ማንአለ ስትለኝ ከርመህ ዛሬ ጎጃም ገብቼ ግንቦቴውን፣ እደግመዋለሁ አርበኛ ዘመነ ካሤን ለእስር የዳረገውን ተውሳክ፣ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ሾተላይ የሆነውን ተውሳክ ጥላሁን አበጀን ገና ሳልነካው ስዞረው አይተህ እሪሪ ቁርሪ እምቡር ብትል ይብስብኝ ይሆን እንጂ ምንአባህ ልታመጣ ፈለግህ? ወሬያም።

"…ወሎ ተሻግሬ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሃቤ ልክ አይደለም፣ በአንድ ወቅት ምሬ ወዳጆ ሠራዊቱን ሳያስፈቅድ ከመከላከያ ጋር ስምምነት መፍጠሩ ልክ አይደለም ብዬ ስናገር ወንዳታ ዘመዴ ብለህ የሙገሳ መዓት ስታዘንብብኝ፣ ወንድ ወንዳታ ስትለኝ ከርመህ አሁን ወደ ጎጃም ጎራ ብዬ በመንገዴ የታዘብኩትን፣ የአገው ሸንጎ፣ የወዳጅ ዘመድ መሳሳብ፣ የብአዴን ብልፅግና እግሩን መትከል፣ የጎጃም ፋኖ አመራሮችን እንዝህላልነት በስሱ ልናገር ስሞክር እንደ ብራቅ እየጮህክ ልታደነቁረኝ መሞከርህ ልክ አይደለም። ሸዋም፣ ወሎም ገብቼ እንዳስጎበኘሁህ፣ ጎጃምም ገብቼ ስለማስጎበኝህ ከአንተ የሚጠበቀው በትእግስት መጠባበቅ እንጂ ዋይዋይ ማለት ለእኔ አጃቢ ሙዚቃ ሆኖ ይበልጥ እንድስፈነጠር ከማድረግ በቀር የሚፈጥረው ምንም ነገር የለም።

"…ወደ አፄ ቴዎድሮስ ሀገር ወደ እምዬ እናት ዓለም ጎንደር ኑ ላስጎብኛችሁ ብዬ ዘው ብዬ ስገባ ብራቮ ዘመዴ፣ ብራቮ ወንድምዓለም፣ ይሄነው ዘመዴ ማለት፣ አቤት አንተ እኮ እያልክ እጅህ እስኪላጥ እያጨበጨብክ፣ ከንፈርህና ምላስህ እስኪጣመም እስኪቆለመም ድረስ እያፏጨህ፣ ላንቃህ እስኪሰነጠቅ፣ ጉሮሮህ እስኪደፈን፣ ልሣንህ እስኪጋ ድረስ ስትቶፍዘኝ ከርመህ አሁን ወደ ጎጃም ልወስድህ ነኝ ስል ምንአባህ ሆነህ ነው ዛር እንዳለበት ወባ እንደያዘው ሰው የምትንቀጠቀጠው? የምትንዘፈዘፈው? ጎንደርስ አለቀልህ፣ የመጨረሻህ ነው፣ አትችላቸውም ስትለኝ እኮ ችዬ አሰያሁህ፣ አቅሜን አሳየሁህ። አይነኬ፣ አይዳሰሴ፣ በአጠገቡ አይደረሴ፣ በአጠገቡ አይታለፌ የሚመስለውን የጎንደር የፖለቲካው ቅማንት፣ የትግሬ ዲቃላውን ስኳድ እኮ ቀጠቅጬ፣ ቀጥቅጬ አቅልጬ ድራሽ አባቱን አጥፍቼ አሳየሁህ። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን አግለብልቤ ማን እንደሆነ እኮ አሳየሁህ እና ምንአባህ ሆነህ ነው አሁን ጎጃም ስገባ አዋራ ላስነሣ ነኝ የምትለኝ? ሃኣ…? ተናገራ አባቴ።

"…መጀመሪያ መጠርጠር ነበረብህ እኮ። ሸዋ ስገባ በዚያው ይቆማል ብለህ ብታስብ እንኳ እሺ አይፈረድብህም። ሸዋን ጨርሼ ወደ ወሎ ስሄድ በዚያው ይመለሳል ብለህ ብታስብ እንኳ እሺ አይፈረድብህም፣ ወሎን ተሻግሬ ጎንደር ስገባ ዘመዴ በቃ ጎጃምም ይገባል ብለህ የማትጠረጥር ምንአባህ ሆነህ ነው? እንዴት ያለ ደደብ፣ የደደብ ደደብ ብትሆን ነው ግን በእናትህ። እንዴት ጎንደር ደርሼ ጎጃምን ሳልጎበኝ፣ ጎጃምንም ሳላይ፣ ሳልመረምር፣ በጣና ሃይቅ ላይ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በቡሬ ፍኖተሰላም፣ በሞጣ ደብረወርቅ፣ በብቸና ሳልንሸራሸር እመለሳለሁ? በአንተ ቤት በቃ ተቀናቃኝህ ስኳድ ተመትቶ አንተ የአገው ሸንጎው የምትታለፍ መስሎሃል? አንት ሰገጤ መሃይም፣ አንት እርጥብ 100 ኪሎ ፋራ ከየት የመጣህ ሰጋቱራ ነህ በአባ ጃሌው? እንዴት ብታስበኝ፣ እንዴት ብትንቀኝ ነው ግን እንዲህ ልትለፋደድ የደፈርከው? ሥነ ሥርዓት ያዝ።

"…እንኳን አንተ ገገማ ፋራው እነ እስክስ አበበ በላው፣ እነ እውይ ሙላት አድኖ፣ እነ ሃሬ አያሌው መንበር፣ እነ ጋንጃው ሚኪ ጠሽ፣ እነ ማንትስዮና ቅብጥርስዮ ራሱ ዐውቀዋል፣ አስቀድመው ተናግረዋልም። ዘመዴ የእኛን ሲጨርስ ወደ ጎጃም ይዞራል፣ ጠብቁ፣ ዛሬ በእኛ የሳቃችሁ ነገ ደም እንባ ታለቅሳላችሁ ብለው አስቀድሞ የሚታወቅ ነገር እንደ ትንቢትና ኋላ ላይ ይኸው አላልንም ነበር? አልነገርናችሁም ነበር? ተናግረን እኮ ነበር ለማለት እዩ ጩፋን፣ ዮናታንና እስራኤል ዳንሳን አስንቀው ሲተነብዩ መጠርጠር ነበረብህ እኮ። የጎንደርን ስጨርስ ወደ ሸገር፣ ወደ ሀረር በጎጃም ካልሆነ በየት አልፋለሁ? ጎጃም ገብቼ ነጭ ማኛ እንጀራ፣ ያን ግሩም የሆነ ጠላ ሳልጠጣ እንዴት በአየር ላይ እመለሳለሁ? ነውር አይደለም ወይ? ጎጄስ ምን ይለኛል? ዝም ብዬው ባልፍስ አይቀየመኝም ወይ? እኔ እኮ አስባለሁ። እንዳንተ ንፍጥ ጭንቅላቴን የሞላው ሰው አይደለሁም። እኔ በሐረር ጂማ ጭማቂ ያደግሁ እንደ ፍየሏ እባብ ገድዬ በልቼ መርዙ የማይጎዳኝ፣ መድኃኒቱን ማርከሻውን ማንም ሳያየኝ የምውጥ፣ የምበላ እልም ያልኩ ሐረር ተወልጄ አዲስ አበባ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ማርገጃው ጋር ያደግኩ፣ ኋላ ላይ ደጃች ውቤ፣ ገዳም ሰፈር፣ ዶሮማነቂያ ያረጀሁ፣ አሁን ደግሞ ከራየን ወንዝ ማዶ ሆኜ ተአምር እየሠራሁ የምገኝ ሀገሬን የምወድ፣ ሃይማኖተኛ አማኝ ባለማዕተብ የተዋሕዶ ልጅ፣ አራዳ የገባው የፒያሳ ልጅ ነኝ። ደግሞ ለሰገጤ። እንዴት ሙድ እንደምይዝብህ ባወቅክ። አይገባህማ።

"…እኔ ስለጎጃም ጉብኝቴ ማውራት ስጀምር በጎጃም ውስጥ የመሸገው ሌባ፣ ዘራፊ፣ ደፋሪ፣ ሸርሙጣው፣ ጋለሞታው፣ ቋንጃ ቆራጩ፣ ማጅራት መቺው፣ ወንበዴው ሁላ ተንጫጫ፣ ያስቆመኝ ይመስል ምን ልናገር እንደሆነ ያልገባው ሁላ እሪሪ አለ። ያዙኝ ልቀቁኝ። ጎጃም ልሄድነኝ ስላልኩ ብቻ "ዘመነን ሊነካብን ነው፣ አስረስን ሊወቅስብን ነው ብላብላ እሪሪ አሉ። ምን ያለበት ምን አይችል ሆኖ እኮ ነው። የምጽፈውን፣ የምናገረውን የማውቀው እኔው ሆኜ ሳለ ገና ለገና እገሌን ይናገረው ይሆናል ብሎ መቅዘን፣ ቀዝኖም ሱሪውን ሳያጥብ በግማት፣ በጥንባት አደባባይ ወጥቶ መሽተት ምን ይባላል? ምንም ሳልናገር መገበሪያ እንደበላ ሌባ የምን መለፍለፍ ነው። ስሙ ሳይጠራ አቤት የሚል ሌባ እኮ አያድርስ ነው። ገና ጎጃም ስል የምን መፈርጠጥ፣ መበጥበጥ ነው። በስሱ እየዝሃለሁ፣ ልፋጭ ቁራጭ የአጀንዳ ሥጋ እወረውርልሃለሁ፣ ከዚያ እሱን ለመብላት ከጎሬህ ተርመስምሰህ ስትወጣ አንቄ እይዝሃለሁ። አለቀ።

"…ሳላደንቃቸው የማላልፋቸውን ልንገራችሁ። 0.001% የሆኖ ባዶ ጀሪካን፣ ድኩማን ማይሞች ባልገባቸው ነገር ሲንጫጩ፣ በእኔ ላይ ያደረ ቂም ያላቸው ዐማራ መሳይ አሞሮች ሲንጫጩ 99.9% የጎጃም ዐማራ ስክን ብሎ፣ የሚነገረውን መጀመሪያ እንስማ፣ ከዚያ ወደ መፍትሄው እንሂድ ነው ሲሉ ያየኋቸው። የጎጃም ዐማሮች የተማሩ፣ የተመራመሩ ሆነው ነው ያገኘኋቸው። ለዶክትሬት 12 ዓመት ያልፈጀባቸው፣ የሰከኑ፣ እንደ ወጠጤ፣ እንደ ጎረምሳ ቲክቶክ ላይ…👇①✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሃሎ ሃሎ…

"…መልካም… ሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር የነበረኝን ጉብኝትና ምርመራ ጨርሼ፣ በዚያ የነበረን ባንዳ፣ የዐማራ ትግል ጠላፊ ሾተላይ፣ የሕዝብ ነቀርሳ፣ እሾሁን ሁሉ ነቃቅዬ፣ ከፖለቲካው ቅማንት ከትግሬ ዲቃላው የጎንደር እስኳድ፣ ከፋሕፍዴኑ፣ ከግንቦቴው፣ ከስሁላውያኑ፣ ከብልጽግናውና ከብአዴን ሴል፣ ከፌክ ኢትዮጵያኒስቱና ከግንባሩ፣ ከጣፊያ፣ ከጉበቱ ጋር ስፋለም ከርሜ፣ ወጥ በወጥ አድርጌ አሸንፌአቸው፣ ብትንትናቸውን አውጥቼ፣ ጎንደርን ወደ አንድነት አምጥቼ ከጎንደር ወጥቼ ሰሞኑን ከማክሰኞ ጀምሮ ለተመሳሳይ ጉብኝት እና ምርመራ በዚያውም የሚፋለመኝ ካለ ልገጥመው ጎጃም የበላይ ሀገር እንደገባሁ ታውቃላችሁ አይደል? አዎ…! ታውቃላችሁ እንጂ…

"…ጎጃም ገና ከመግባቴ የጎጃም ዐማራ አበባ ይዞ፣ የዘንባባ ዝንጣፊም ተሸክሞ፣ ቄጤማ ጎዝግዞ በዐማራዊ ደንብና ባሕል መሠረት ማርና ጠጁን፣ ማኛ ነጭ ሀጫ በረዶ የመሰለ ለምለም እንጀራውን ተሸክሞ ነው የተቀበለኝ። በእውነት በጣም ነው የተደሰትኩት።

"…ያው ወሎም፣ ሸዋና ጎንደርም ስገባ ለበዓሉ ድምቀት ይንጫጩ የነበሩ ቁጫጮች እንዳሉ ሁሉ ጎጃምም ስገባ ቁጥራቸው እዚህ ግባ የማይባሉ ቁጫጮች በየቦታው እሪሪ ሲሉ እያየኋቸው በጣም ሙድ እየያዝኩባቸው ዘና ፈታ እያልኩ ነው።

"…ጎጃም ገና ከመግባቴ የጎጃም ዐማራና አገው እንቅፋቶች ሌቦቹ፣ ዘራፊዎቹ በራሳቸው ግዜ ወደ ኢንጂባራ እየነኩት ነው። አሁን ኢንጂባራ ለመግባት ምክንያት አይኖርም። እኔ ቁራጭ ሥጋ ነው ጣል ያደረግኩት፣ ቁጫጮቹ ሰፍ ብለው እየመጡ ነው። የእኔ ሥራ እስኪከመሩ፣ ሁሉም ከጎሬአቸው እስኪወጡ ድረስ እየጠበቅኩ ማጫወት ነው።

"…እስከዚያው ድረስ ግን የጌሙ መጫወቻ ካርዴ ጥሌ ነው። ጥሌ ይሁዳው፣ ጥሌ ከሃዲው፣ ጥሌ መሰሪው፣ እሱን ይዤ ነው የምጫወተው።

• ገባችሁ ኣ…? አላችሁ ኣ…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

አይቼዋለሁ…!

"…እኔ የማውቀው አማኑኤል አብነትም ከኡጋንዳ እስከ… ድረስ ወዳጄ እንደነበረ ነው። ሊባኖስ ዮሐንስም እንደዚሁ፣ መዓዛ መሐመድም እንደዚያው። ወዳጆቼ ላይክ ያደረጉት በራሳቸው መስመር እንጂ ከእኔ ጋር ምንም የሚያገናኛቸው ነገር የለም።

"…እኔን በተመለከተ ከጥላሁን ጋር የጀመርኩትን ዥለጣ አላቋርጥም። እኔ ከጥላሁን ጋር ብቻ እየተላተምኩ ሌላ ቦታ የሰፈረውን የተደራጀ ሴራ አፈርሰዋለሁ። ፍርስርሱን ነው የማወጣው። መዓዛ ለየከች፣ ሊባኖስ ሸረረው፣ አማኑ ጦመረው ደንታዬ አይደለም። ምን እየሠራሁ፣ ወዴት እያመራሁ እንደሆነ ጥሌና ጀማው በደንብ ይገባቸዋል።

"…በነገራችን ላይ አርበኛ ዘመነ ካሤ ለ5 ተኛ ጊዜ ከድሮን ጥቃት ተርፏል። ለአርበኛ ምሬ ወዳጆ የተተኮሰው ድሮን የጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድን የሥጋ ወንድም እና ፋኖዎችን ነው ብትንትናቸውን ያወጣው፣ የገደለው። አስተኳሹ ደግሞ 3ሺ ብር ነው ተከፍሎት ይሄን አዋራጅ ሥራ የፈጸመው። የምለው ይገባችኋል።

"…እናም ዘመዴ መዓዛ አንተን የሚሰድቡትን እየዞረች ላይክ ታደርጋለች የምትሉኝ ሰዎች እናንተ እንጂ እንዲያ የምትሉኝ መዓዛ ወዳጄ እንደሆነች ነው የማውቀው። ስጠራት እንኳ የእኔ ሲአይኤ እንደምነሽ ብዬ ነው። እንደዚያ ነው።

"…የጥላሁን አበጀ ጋሽ አሰግድን ከዘመነ ጋር አቆላምጦ መጥራት፣ ጠርቶም መፖሰት እኔን የገባኝ ነገር ገብቶኛል። አይ የዘሜ ታላቅ ወንድም…? 😂 ለማያውቅሽ ጥልዬ።

"…የሆነ ነገር ስጀምር መደንገጣችሁ፣ መረበሻችሁ የተለመደ ነው። እኔ የሆነ ነገር ስጀምር ሊሰድበኝ፣ ሊነቅፈኝ የሚንበጫበጭ በሙሉ የበሽታው ተጠቂ ስለሆነ ቀን ጠብቄ አስተነፍሰዋለሁ። ቁራጭ ሥጋ እወረውራለሁ፣ ከዚያ ቁጫጭና ጉንዳኑን እሰበስብታለሁ። ለጭፍለቃ የሚመቸች እንደዚያ ነው። ገባቹ…ኣ…?😂

• ጥሌ ደኅና ነህ አይደል…?

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…14 ሺ ሰው አንብቦት 14 ፍሬ ሰው ጓ 😡 ብው ያለበትን ርእሰ አንቀጽ እናንተ ደግሞ የራሳችሁን ሓሳብ የምትሰጡበት ሰዓት ነው። ክፍለ ጊዜውን በአግባቡ ተጠቀሙበት።

"…ጥላሁን አበጀ አሁንም አትንቀዥቀዥ፣ እኔና አንተ በደንብ ነው የምንተዋወቀው። አንተን ብሎ ለፋኖ ጋሽ አሰግድ አዛኝ። እረፍ ብዬሃለሁ። መገለጥህ ላይቀር አትድከም። ለማያውቅህ ታጠን። እኔና ጥላሁን መስመር ላይ ስለተገናኘን አንላቀቅም። ሌሎቻችሁ ጣልቃ አትግቡ። ግን እረፍ።

"…በተቀረው ጎጃም ከአገው ሸንጎ ይጸዳል። የጎጃም አገውና የጎጃም ዐማራም ያሸንፋል። ይደፈርሳል ግን ደግሞ ይጠራል። ገብቼበታለሁ እንደ ፀሐይ ጨረሬን እየረጨሁ፣ ቀስ በቀስ ሙቀቴን እየለቀቅኩ፣ የተከናነበውን ክንብንብ ሁሉ እገላልጠዋለሁ። ወበቀኝ ብለህ ጭንብልህን እንድታወልቅ ነው የማደርግህ።

"…የሥልጣን ጥመኛ የብአዴን ሴል በሙሉ ይራገፋል፣ የበሬ ሌባ፣ የአምባር የጣት ቀለበት ሳይቀር ዘራፊውን እለጋዋለሁ። ምሥራቅ ጎጃምን ለብልፅግና አስረክቦ ብልፅግና ሚሊሻ እንዲያሰለጥንበት በሲስተም፣ በዘዴ ቦታ ለቅቆ ወደ ምዕራብና ሰሜን ጎጃም ፈርጥጦ በዚያም የፋኖ መሪ ካልሆንኩ ብሎ መከራ የሚዘራውን አስመሳይ ሽንታም አስነጥሰዋለሁ።

"…አርበኛ ዘመነ ካሤን በመክበብ በአርበኛ በዘመነ ካሤ ስር መደበቅ አይቻልም። የጎጃም ፋኖ በጠንካራ አለት ላይ ተመሥርቷል። ሌባው፣ ዘማዊው፣ አቅመቢሱ፣ አውርቶ አደሩ፣ ዘራፊው፣ ከሃዲው ምርኮኛ ሻጩ በሙሉ ግን መገምገም አለበት። ይህ አቋሜ ነው። ስታሊን ገ/ሥላሴ ተደራድሮ ገንዘብ ከፍሎ እስረኛ አመለጠ የሚለውን አልሰማውም። እንደ በፊቱ መፍታት እየቻሉ ለመሸወድ መሞከር ነውር ነው።

"…ስለ ጎጃም ፋኖ ሳወራ ስኳድ ዝም በል። መከታው ኮሎኔሉን፣ የዩኒቨርሰቲ ፕሬዘዳንቱን በስንት ሚልዮን ብር ነው የሸጠው? ሃኣ

•በሉ ተንፒሱ…✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

👆②✍✍✍ …በቴሌቭዥን፣ በመግለጫ፣ በመላላጫ ብለው ብለው ማፍረስ አይደለም መነቅነቅ ያቃታቸውን የዐማራ ፋኖ በጎጃምን በዘመዴ በኩል ሊፈርስልን ነው፣ ሊወቀጥልን ነው በማለት እንቅልፍ አጥተው ነበር ያደሩት። "ብለን ነበር" ስኳድን ሲጨርስ ወደ ጎጃም ነው የሚዞረው ቻሉት ብለው አስቀድመው ሲቦርቁ ነበር። አርበኛ ዘመነንማ አትነካብንም ብለው ድራማ ለመሥራት ስኳድ ሲላላጥ እንደማየት የሚያስቅ ሌላ ምን አለ? መቼም ለጉድ ነበር ዋይ ዋይታው። እስኪመሽ፣ እስኪነጋ ድረስ ምጥ እንደያዛት ሴት ሲንቆራጠጡም ውለው ያደሩም ነበር። እንደ እነሱ አርበኛ ዘመነ ካሤን ሳዋርድ፣ እነ ማርሸትን ሳንጓጥጥ፣ እነ አስረስን ስመዠልጥ ዓይተው ስለት ለታቦት ለማስገባት የቋመጡ ሁላ ነበሩ። ስንቱን ታዘብኩት። ማይም ሁላ…

"…በተለይ ፌክ ኢትዮጵያኒስቱ፣ በጎጃም ዐማራ ፋኖ አደረጃጀት ውስጥ በግልጽ ጣልቃ መግባት ያቃተው የግምባሩ፣ የጣፊያው፣ የዶላር ዕዙ ሠራዊት በወይራና በጡንጂት ታጥኖ ሁላ ነበር አሰፍስፎ የጠበቀኝ። መቼም እንደ ትናንት የፖለቲካው ቅማንት የትግሬው ዲቃላ የጎንደሩ ስኳድ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ድል ለማግኘት የቋመጠበት ቀን አልነበረም። ጎንደር የሚገኘውን የስኳድ ምሽግ ፍርስርሱን በመዋጣቴ፣ የእስክንድር ነጋን የፖለቲካ አካሄድ በቁሙ እንዲሞት በማድረጌ ነበር በቃ አሁን ጎጃምንም እንደዚያው ያደርግልናል ብለው ስለት ለታቦት አስገብተው የጠበቁኝ። እንዲያውም አንዳንዱ እስኳድ እንደ ጌትነት ይስማው ዓይነቱ ቀባጣሪ ዘመድኩንን ተባብረን ከትግሉ የምናስወጣበት ወቅቱ አሁን ነው በማለት በድፍረት እስከመጻፍ ደርሶ ነበር። እነ ዝናቡን፣ ዘመነን፣ አስረስን በስም ጠቅሰው አይዟችሁ በማለት አዛኝ ቅቤ አንጓች በመሆን የአዞ እንባቸውን ሲያፈስሱ እያየሁ ነበር። ለማጯጯህ ሞከሩ። ወደቁ ተነሡ። ስኳድ ሲነካ በጎንደር ዐማራ ስም የተንጫጫው የትግሬ ዲቃላ ሁላ አሁንም ጎጃም ሲተች የአገው ሸንጎ እንኳ በጫጫታ ሊያግዛቸው አልፈቀደምም። ከምር አከሰሯቸው። እነ ሀራ ሀራ ብቻ ዋን አቧራዎች ጋር ገብተው አይዞኝ ጎጃሞች ዘመድኩን ይውጣ እንጂ አንድ ነን። እየበጠበጠን ያለው ዘመድኩን ነው በማለት የሰገጤ ድልብ ምሁራዊ ትንተና ሲሰጡ ነበር ያየሁት። እንዲያውም የመድረኩ መሪ አይታክቴው፣ አይሰለቼው፣ ሼምየለሹ ዘርአ ያዕቆብ ነቤክስ ሀራ ሀራ ተናግሮ ሲጨርስ "አመሰግናለሁ ሞጣ" ብሎት በሳቅ ነበር ያፈረሰኝ። ምንም ቢባል አጀንዳውን የሚገዛ ጠፋ፣ ጭራሽ ማታ ላይ "በላይ ዘለቀ ባንዳ ነው፣ ኃይለሥላሴ የገደለው ለዚህና ለዚያ ነው ብለው" አዲስ አጀንዳ ለመፍጠ ቢላላጡም ወፍ። ኖ ሞር አጀንዳ ለዐማራ።

"…የጎጃም ዐማራ ልጆችስ? እነሱማ ተደመምኩባቸው። ትንፍሽ አላሉም። ዝም፣ ጭጭ፣ ክትት ነው ያሉት። ጭራሽ ምንም እንዳልተፈጠረ ቲውተር ስፔስ ከፍተው "ስለ የተከበሩት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ስለ አቶ ዮሐንስ ቧ ያለው" ውይይት ያደርጉ ነበር። እንዲያውም ስኳዶች ግራ ቢገባቸው "ጎጃሞቹ ዐውቀው ነው በዘመድኩን በኩል አጀንዳ ሰጥተውን እኛን የሚያንጫጩን፣ እንዲያ ባይሆንማ እኛ ብቻችን ስንንጫጫ እንዴት አንድ ጎጃሜ አያግዘንም? በማለት የሆነ ፊንታ እንደተሠሩ አዝነው ሲናገሩም ሰምቻቸዋለሁ። ምስጋናው አንዷለም ጎጃሜ ገፀባህሪ ሰጥቶት እንዲተውን ወደ ሜዳው ያስገባው አንድ የማውቀው የጎንደር እስኳድ እንኳ ዋን ዐማራዎች ጋር ገብቶ ዘመድኩንን ብጠላውም የዛሬ ያነሳው ሓሳብ ገዢ ነው ብሎ ውኃ ነው የቸለሰባቸው። መማር፣ ዐማራነት ማለት እንዲህ እንደ ጎጃሞች ነው። ትችቱ ተገቢ ሲሆን ሰብሰብ ብሎ በመመካከር እንዴት የተነሣውን ትችት ተቀብለን በአግባቡ አስተናግደን እናስተካክል በማለት ለመፍትሄው ወደ መድከም ነው የገቡት። መብሰል ማለት ይሄ ነው። ጎጃሞች ዐማራ ስለሆኑ በዐማራ መንፈስ ወደ መመካከር ነው የሄዱት። የጎንደር ዐማራውም ቢሆን በቆርቆሮው፣ በባዶ በርሜሉ፣ በጯሂው በፖለቲካ ቅማንቱ በትግሬ ዲቃላው ስኳድ ስለተዋጠ ነው እንጂ የጎንደር ዐማራም ከእኔ ጎን ነበር የቆመው። ቆሞም ይሄው እነ ሀብቴ ወልዴ ወደ አንድነት፣ እነ ጋሽ መሳፍንት ወደ እውነት መጥተው ዓለሙን ሁሉ አስደስተዋል። በዚህ የተበሳጩት በሙሉ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ጎንደሮች ስኳዶች ናቸው።

"…በዐማራ ትግል ውስጥ አምርሮ የሚጠላኝ ጎንደር ጎንደሬ ነኝ የሚል ሰው ካለ እርሱ በእርግጠኝነት እናገራለሁ ቆርቆሮ ባዶ ጀሪካን፣ የማንነት ቀውስ ያለበት የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ ነው። የጎንደር ብአዴን ሆኖ ዐማራ ከሆነ እንኳ አይጠላኝም። ጎንደር ሆኖ የሚጠላኝ ስኳዱ ብቻ ነው። ጎጃሜ ነኝ የጎጃም ዐማራ ብሎ እኔን የሚጠላ ካለ እሱ ፀረ ዐማራው የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላው የስኳድ ገረድ፣ አሽከር፣ ኦሮሙማው በባርነት የገዛው የአገው ሸንጎ ነው። ተለጣፊ ጎጃም የገባ የኦሮሞ ዲቃላም ሊወደኝ አይችልም፣ የህወሓት የወያኔ፣ የበረከት ስምኦን ሴልም ሊወደኝ አይችልም። ወሎ ሆኖም የሚጠላኝ የስኳድ ገረድ፣ ፀረ ዐማራው ቡድን ነው። በሸዋም የስኳዱ ርዝራዥ ነው። ዐማራ ሆኖ የሚጠላኝ ሌላው የዐማራ የወሃቢይ እስላም፣ ጎጃሙ ቅባት፣ የሸዋው ፀጋ፣ የወሎው ወሃቢይ እስላም ነው። ዐማራ ሆኖ ፅንፈኛ የብልፅግና ወንጌል አማኝም ሲሰማኝ፣ ሲያየኝ አጋንንቱ ይነሣበታል። ይንበጫበጫል። ያጓራል። ዋይዋይም ይላል። ደግሞ ለአጋንንት እኔም አናት አናቱን በቃሌ፣ በብዕሬ እበጠርቀዋለሁ። ይጩህ። ይውጣለት።

"…ሌላው የዐማራ አክቲቪዝም ጉዳይ ነው። አዎ አሁን አሁን የዐማራው አክቲቪዝም እየሰከነ ነው። እነ ጠሽ፣ እነ ገጠሬው የሚመሩት የዐማራ ፋኖ አክቲቪዝም ጊዜው እያለፈበት ነው። እነ ዮኒ ማኛው እነ ቀላቅሌ ሞጣ ቀራንዮ የሚመሩት ትግል ቀኑም፣ ጊዜውም አልፎበታል። ሰዳቢ፣ ተሳዳቢ በዶላር ተፈልጎ የሚንጫጫበት ዘመን አልፏል። አሁን ጊዜው ስክን ያሉ የጎጃም፣ የሸዋ፣ የጎንደርና የጎጃም፣ የአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያና በመላው ኢትዮጵያ የተወለዱ፣ በአውሮጳ፣ በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአፍሪካ፣ በአረብ ሀገር ያሉ ዐማሮች በዕውቀት የሚመሩት እየሆነ መጥቷል። እኔ ጩኸቴ ፍሬ እያፈራ እንደመጣ አድርጌ ነው የምቆጥረው። በእውነት የሚያኮራ ነገር ነው የሚታየው። በቲክቶክ እንኳ ከጥቂት ጋለሞቶች፣ ስድአደግ የብአዴን ኔትወርኮች በቀር ጨዋ ነው የበዛው። ሜካፓም ለፍላፊ የመንደር ሴት፣ ጋለሞታ አሳዳጊ የበደለው፣ የዐማራን ስብዕና የማይገልጥ፣ የዐማራን ክብር ዝቅ የሚያደርግ፣ ዐማራ በእንደዚች ዓይነቷ ክፍት አፍ፣ በእንደዚህ ዓይነቱ ወራዳ ነው እንዴ ትግሉ የሚመራው ብለው ሌሎች ሰዎች ዐማራን በእነሱ ቁመናና እውቀት ልክ እንዲመዘን የሚያደርጉ ጥቂቶች ቢቀሩም እነሱም እየከሠሩ እየመጡ ነው። በትግሉ ስም ከዓረብ ሀገር ሴቶች የሚቃርሙት ብርም እየነጠፈ ስለሆነ በጊዜ ሂደት ቁርጣቸውን ዐውቀው አርፈው ይቀመጣሉ ብዬ አምናለሁ። 

"…የግል ፋኖ አደራጅተው ለመምራት የሚላላጡ ብኩን ጋለሞታ የዐማራ ሴት አክቲቪስት ነን ባዮችም አሉ። የፋኖ መሪዎች ጋር እየደወሉ የሚዝቱ፣ የሚያስጨንቁ የሴተኛ አዳሪ ገፀ ባህሪ ተላብሰው የሚተውኑም አሉ። የዐማራ ፋኖዎችን አግብቼህ ነው የምወስድህ ብለው ነገ ይኑር ይሙት የማያውቀውን ፋኖ በሙሉ ልቡ እንዳይታገል አድርገው አውሮጳና ካናዳን እያለመ ትግሉን የሚጎትቱ አሉ። በዲስኮ ሰዓት የሚዋጋውን ጀግና የወርቅ ቅብ ውድ ሰዓት ልከው አደንዝዘው እና አፍዘው የሚያስቀምጡ አሉ። የደቡብ ጎንደሩ ፋኖ ተሾመ፣ የሸዋው ፋኖ መከታው የዚህ ሰለባ ናቸው። ጭናቸውን ከፍተው፣…👇②✍✍✍

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ገና ሳልጀምረው አገው ሸንጎ ተናደላችሁ።

"…ትናንት ምን ብዬ ነበር? አዎ ጎጃም የመሸገውን፣ ዘራፊ፣ ቀማኛ፣ ፀረ ዐማራውን የአገው ሸንጎን እፋለመዋለሁ ብዬአችሁ ነበር። ይኸው ገና ሳልነካው የአገው ሸንጎ ሌባ መናድ፣ መፈርጠጥ ጀመረላችሁ።

"…ባለፈው ጎንደር የሚገኘውን የፖለቲካ ቅማንት የትግሬ ዲቃላውን ስኳድ ስፋለመው፣ የጎንደር ዐማራ ነቅቶ ወደ አንድነት ሲመጣ፣ እነጋሽ መሳፍንት እና ሀብቴ ወልዴ ከእነ ባዬ ቀናው ጋር አንድ ሲሆኑ፣ የወልቃይቴው ስኳድ ደመቀ ዘውዱ ያሰማራቸው የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎች ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑቱ ለአገዛዙ እጃቸውን ሰጡ ተብሎ፣ ቢሮአቸው መቀሌና አዲግራት የሆኑ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃሎች ቅማንት የቅማንት ነፃ አውጪ ነነ የሚሉትም እጃቸውን ሰጡ ተብሎ ሲለፈፍ ሀብታሙ አያሌው እና አበበ በላው ደራጇቸው እነ ሰለሞን አጠናው እና እነ ደረጀ በላይ ግን አንድነቱን ጠልተው ለብቻቸው ቆሙ።

"…ይኸው ዛሬም ትላንት ገና ወደ አገው ሸንጎ ምድር ለማራገፍ ስመጣ የጎጃም ዐማራ ፋኖዎችን ሲያሰድቡ፣ በስሙ ሲዘርፉ የነበሩት ዘራፊ አገው ሸንጎዎቹ መሪያቸውን ገድለው ከነትጥቃቸው ለብልፅግና እጅ ሰጥተዋል። የዐማራ ፋኖ በጎጃም መሬቱን ሲቆጣጠር ፈርጥጠው ወደ ላካቸው ሄደዋል።

• ዘመነን ጠብቁት ብያለሁ። የፋኖ መሪዎች ራሳችሁን ጠብቁ። ፍልሚያው እየተጀመረ ነውና ነቃ በሉ። የፈለከውን በለኝ፣ ፈንዳ ጧ በላት እንጂ አልፋታቸውም። ገና አስደንጋጭ መረጃ ሁላ ነው የሚወጣው። ሌቦች፣ ዘራፊዎች ምድር ላይ ቦታ አይኖራቸውም። ስኳድም፣ አገው ሸንጎም ይደመሰሳል። አለቀ።

"…የቆየሁት ይሄን ሳጣራ ነው። አላችሁ አይደል? ርእሰ አንቀጹን ለማንበብም ዝግጁ ናችሁ አይደል? 😂

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

“…ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፤ ኀጥኣን በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል።” ምሳ 29፥2

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

Читать полностью…

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም…

"…ርእሰ አንቀጹን 15 ሺ ሰዎች አንብበውት 5 ፍሬ ግማሽ ደርዘን እንኳ ያልሞሉ ግማሽ ሰዎች ብቻ ብው ብለው በሰጭተውበት ታይቷል።

"…እናንተ አስተያየት ከመስጠታችሁ በፊት የገረመኝን ነገር ልንገራችሁ። ከትናንት ጀምሮ አጀንዳውን ካነሣሁበት ጊዜ ጀምሮ የጎጃም ዐማራዎች፣ አገው ሸንጎ ያልሆኑት አገዎች አንዳች ሳይተነፍሱ፣ በውስጥ መስመርም እየመጡ "ልክ ነው ዘመዴ፣ ችግሮች አሉ፣ ችግሮቹ ይስተካከላሉ" በማለት ከፍ ባለ ሞራልና ከፍ ባለ በራስ መተማመን ነበር ሲያወሩኝ የዋሉት፣ ያደሩት።

"…በአንጻሩ የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተልባ የጎንደሩ ስኳድ የጎጃምን ጉዳይ አጀንዳው አድርጎ ሲንጫጫ ሳይ በሳቅ ወደቅኩ። አንዳንድ ጎጃም በመወለድ ብቻ ጎጃሜ መሳይ ጎጆ ፊት ጎልጃጃ የጎጃም ብአዴን አገው ሸንጎዎችም ከስኳድ እኩል ሲወበሩ እያየሁ በሳቅ ነፈርኩ፣ አፈርኩላቸውም።

"…ኮሎኔሉን ያስመለጡት አመራሮች በሙሉ መሳሪያ አውርደው ዘብጥያ መውረዳቸውን፣ ምርመራ መጀመሩንም የጎጃም ዐማራ ፋኖ የሚመለከተው ክፍል አረጋግጦልኛል። ወቀሳው ይቀጥላል። ምንጣሮውም ይቀጥላል። የዐማራ አንድነቱም ይበሠራል። ሌላህ ፈንዳ። የበሬው እንትን ይወድቅልኛል ብለህ ከበሬው ቂጥቂጥ ሱክሱክ በል። ሶክሳካ ሁላ። ማፈሪያዎች፣

"…ጎጃም ማለት ይሄ ነው። ሲወቀስ ክትት፣ ሁሉን በውስጥ ጭርስ፣ እንደ ስኳድ አናሳ፣ የበታችኝነት የማይሰማው፣ የበሰሉ፣ ቋ ያሉ ስለሆነ በቲክቶክ በለው፣ በዩቲዩብ አልተንጫጩም። መቀስ ይዘው ለማራገብ አልተራወጡም። ስኳድ ከጎጃሞች ተማር። አየሩን አትበክል።

"…ተራው የእናንተ ነው። የእናንተ የአንባቢያን። በጨዋ ደንብ ሓሳባችን ስጡ፣ እኔ ሌባ፣ ትግል ጠላፊ ሾተላዩን ሁላ መዠለጤን እቀጥላለሁ። ማንም አያስቆመኝም። ከሌባ ጋር ቆሞ የሚሞግተኝን አብሬው ነው የምጠርገው።

• ተንፒሱ እስቲ…✍✍✍ ጻፉ

Читать полностью…
Subscribe to a channel