yenetube | Unsorted

Telegram-канал yenetube - YeneTube

113382

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Subscribe to a channel

YeneTube

ከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

ድርጅታችን አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋሲሁን በኮንትራት ውል በዜና አቅራቢነት እንዲሁም በቅርቡ በጣቢያችን ‹‹ሶፊ ሾው›› ሲል በሰየመው የመዝናኛ ዝግጅቱ በአሻም የቴሌቪዥን እና በዩትዩብ ገፅ እያዘጋጀ ሲያቀርብ እንደነበረ ይታወቃል፡፡

ይህ በሆነበት ከትላንት ሕዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ አማራጮች ስለ ጋዜጠኛው ከኢትዮጵያዊነት ባሕል፣ ወግ እንዲሁም ሃይማኖት ያፈነገጠ ተግባር ሲፈጽም የሚያሣይ መረጃ በድምጽ፣ በጽሁፍና በተንቀሳቃሽ ምስል ጭምር ሲዘዋወር ተመልክተናል፡፡

አሻም ይህንኑ በማህበራዊ ሚዲያ ስለ ጋዜጠኛው የተሰራጨውን መረጃ ተከትላ ስለ ተሰራጨበት መረጃ ሶፎኒያስን ማብራሪያ እንዲሰጥበት ጠይቃለች፡፡ በዚህም ሶፎኒያስ <<አሁን ራሴን ለማስተካከል፤ለማከም ፀበል ገብቻለሁ>> የሚል አጭር ምላሽ ከመስጠት ውጭ ተጨማሪ ያለው ነገር የለም።
ስለሆነም አሻም ሚድያ ትሬዲንግ አ.ማ. የኢትዮጵያን ባህል እና ወግ እንዲሁም የህብረተሰቡን እሴት እና ሃይማኖት ያከበረ የምትመራበት ኤዲቶሪያል አላት፡፡ ይሁን እንጂ ጋዜጠኛው የሚዲያውን ኤዲቶሪያልም ሆነ የማህበረሰቡን እምነት ፣ እሴት፣ ወግ፣ ባህልና ሃይማኖት የሚጻረር ተግባር ተሰራጭቶበት በመመልከቷ እጅጉን እያዘነች ድርጊቱ የሚዲያ ተቋሟን የማይወክል ይልቁንም በጽኑ የምታወግዘው መሆኑን ለውድ ተመልካቾቻችን እና ተከታታዮቻችን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አሻም ሚዲያ ትሬዲን አክሲዮን ማህበር ጋዜጠኛ ሶፎኒያስ ዋሲሁን በፈጸመው ከባድ የማህበረሰባዊ እሴት እና ኤዲቶሪያል ጥሰት ጭምር የነበራትን የስራ ውል ከዛሬ ሕዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ማቋረጡዋን ለመግለጽ ትወዳለች፡፡

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

በጎንደር የሰዓት እላፊ ገደብ ተነሳ

"ያለምንም የፀጥታ ስጋት 24 ስዓት መንቀሳቀስ ይቻላል"

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ፣ በከተማዋ ተጥሎ የቆየው የስዓት እላፊ የእንቅስቃሴ ገደብ መነሳቱን አስታውቋል፡፡

በከተማው አስተማማኝ ሰላም መፈጠሩን ተከትሎ፣ የስዓት እላፊ ገደብ የተነሳ መሆኑን የጎንደር ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ አለልኝ ዓለም የገለጹ ሲሆን፤ ህብረተሰቡ ያለምንም የፀጥታ ስጋት 24 ስዓት መንቀሳቀስ እንደሚችል መናገራቸውን የከተማዋ ኮሚኒኬሽን ጠቁሟል።

ህብረተሰቡም ሆነ ተሽከርካሪዎች 24 ስዓት መንቀሳቀስ እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፤ የማታ አገልግሎት የሚሰጡ ባጃጆች ደግሞ እውቅና ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

Samsung A06 5G
Memory: 128/6GB
Condition: Brand New
Battery: 5000mAh
Price: 17500ETB
Call: 0924769665
DM: @adagioandante

Читать полностью…

YeneTube

"የነዳጅ ዋጋ አልጨመረም"

የአቅርቦት ችግርም የለም።


የነዳጅ ሰልፍ የተከሰተው ከአቅርቦት እጥረት ሳይሆን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን በሚሰራጭ የተሳሳተ መረጃ ነው ተብሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ ሰሞኑን የሚስተዋል የነዳጅ ሰልፍ በአቅርቦት ችግር ሳይሆን በተሳሳተ መረጃ ምክንያት መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን የነዳጅ ሰልፍ ተከትሎ ባለስልጣኑ የማጥራት ስራ መስራቱን እና በዚህም የአቅርቦት እጥረት አለመኖሩን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ በቀለች ኩማ ተናግረዋል።

በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን አማራጮች ከዋጋና አቅርቦት ጋር በተገናኘ የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎችን ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች የነዳጅ ሰልፎች እንደሚስተዋሉም ገልፀዋል።

ባለስልጣኑ በከተማዋ በተለመደው መሰረት ነዳጅ  እያቀረበ እንደሚገኝ ያስታወቁት ሀላፊዋ በቀጣይ ቀናትም ምንም አይነት የአቅርቦት ችግር እንደማይፈጠር አስታውቀዋል፡፡

ተጠቃሚው ትክክለኛውን መረጃ በማረጋገጥ  አማራጭ የነዳጅ ማደያዎችን በመጠቀም አላስፈላጊ ሰልፎች እንዳያጋጥሙ ሊያደርግ እንደሚገባም ሃላፊዋ አመላክተዋል፡፡

አክለውም በከተማዋ በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች በየእለቱ ከ1 ሚሊየን ሊትር በላይ የቤንዚን አቅርቦት መኖሩን ገልጸዋል።

የከተማዋ ንግድ ቢሮ በበኩሉ የነዳጅ አቅርቦት ችግር ሳይኖር በህገ ወጥ አሰራር ተጠቃሚውን የሚያጉላሉ አካላት ላይ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢብራሂም
ትራኦሬ "ጥሩ መሪ አይደለም" አሉ


የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የቡርኪናፋሶው ኢብራሂም ትራኦሬ ጥሩ መሪ አይደለም ሲሉ ትችት ሰንዝረዋል፡፡

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ፣ ስለ ቡርኪናፋሶ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ የሰነዘሩት የሰላ ትችት እያነጋገረ ነው፡፡

ሙዳቫዲ በንግግራቸው፤ አንድ ትክክለኛ መሪ በወገቡ ላይ ሽጉጥ መታጠቅ ወይም በጠረጴዛው ላይ የጦር መሳሪያዎችን ማሳየት የለበትም፤ ብለዋል፡፡ እንደ እሳቸው አባባል፤ አመራር በተቋማት፣ በዴሞክራሲና በተጠያቂነት ላይ መገንባት አለበት - በኃይል ሳይሆን።

መሪዎችን መሪ የሚያደርጋቸው መሣሪያ ሳይሆን ርዕይ፣ ህግና ኃላፊነት ነው ሲሉም አክለዋል፤ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፡፡

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

QR code ወይም ነባሩ ደረሰኝ የሌለው  ከታህሳስ 30/2018 በኋላ የማያገለግል በመሆኑ ፤ እስካሁን QR code ያለውን የማንዋል ደረሰኝ ህትመት ያላቀረባችሁ ግብር ከፋዮች በ10 ቀናት ውስጥ የትዕዛዝ ደብዳቤ ውሰዱ ተብላችኋል፣ደብዳቤው ተያይዟል።

Via:- አዩዘሀበሻ
@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

የጠለፋ እና የእገታ ተግባር የፈፀሙ አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በምዕራብ ሸዋ እና  በሰሜን ሸዋ  ሁለት ዞኖች ውስጥ የጠለፋና የእገታ ተግባር የፈፀሙ አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።እንደ ምዕራብ ሸዋ ዞን የአደአ በርጋ ወረዳ አቃቢ ሕግ ፅህፈት መግለጫ 1ኛ ተከሳሽ ግርማ ሳሕሉ 2ኛ ተከሳሽ ፀጋ ሐይሉ 3ኛ ተከሳሽ  ቶሊ ደጉ የተባሉ ሶስት ተከሳሾች ጥቅምት 11 ቀን 2018ዓም ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት ላይ ለአንደኛው ተከሣሽ በግዳጅ የትዳር አጋሩ ለማድረግ የአስራ አራት ዓመቷን ታዳጊ ከወፍጮ ቤት ስትመለስ ጠብቀው የጠለፋ ተግባር ፈፅመው ለማምለጥ ሲሞክሩ ተጠላፊዋ ባሰማችው የድረሱልኝ ጩኸት ስልጠና ላይ የነበሩ የፀጥታ አካላት ሰምተው ተከታትለው በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

ሶስቱም ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኃላ በፖሊስ የምርመራ መዝገባቸው  በበቂ ማስረጃ ተጣርቶ ለአቃቤ ሕግ የተላከ ሲሆን አቃቤ ሕግም በወንጀል ሕግ ቁጥር 587 ንዑስ አንቀፅ 1 ሴትን በመጥለፍ ወንጀል ክስ መስርቷል፡፡ ክሱን ሲከታተል የቆየው የአደአ በርጋ ወረዳ ፍርድ ቤት ጥቅምት 24-2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሶስቱም ተከሣሾች ላይ በእያንዳዳቸው ላይ በሉለት አመት ከሶስት ወር እስራት እንደተወሰነባቸው የአቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫው አመልክቷል።

በተመሳሳይ በወረጃርሶ ወረዳ ሌንጮ ቦርሱ ቀበሌ የጦር መሣርያ በመታጠቅ የእገታ ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጠተዋል።እንደ ወረጃርሶ ወረዳ አቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫ  ደሬሣ ተሾመ እና ጀማል ደምሴ የተባሉ ሑለት ተከሳሾች ለግዜው እጃቸው ካልተያዙ ሑለት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን የጦር መሣርያ በመታጠቅ  መስከረም 25 ቀን 2018 ዓም ሁለት ግለሰቦችን አግተው አፍነው ለመውሠድ ሲሞክሩ በፀጥታ ስራ ላይ በተሠማሩ አካላት በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

ፖሊስም በሁለቱ ተከሣሾች ላይ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሠባሰብ አጠናክሮ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ሕግ የላከ ሲሆን አቃቤ ሕግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በጦር መሣርያ በመታገዝ የእገታ ተግባር መፈፀምን ጠቅሶ ክስ የመሠረተ ሲሆን ክሱን ሲከታተል የቆየው የወረጃርሶ ወረዳ ፍርድ ቤት ሕዳር 24 ቀን 2018ዓም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሣሽ ደሬሣ ተሾመ ስምንት አመት ከአራት ወር  እስራት ሁለተኛ ተከሳሽ ጀማል ደምሴ በስድስት አመት ከስድስት ወራት እስራት እንዲቀጡ የወሠነ መሆኑን የአቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫ አመላክቷል።

Via :- ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

በሀዲድ ገበያ የደረሰው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል

ዛሬ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 9:45 ሰአት ላይ ሀዲድ ገበያ 
እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በንግድን መኖሪያ ቤቶች ላይ  ተከስቶ የነበረዉ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የእሳት አደጋው የተከሰበት ቦታ ለአደጋ መቆጣጠር ስራ ምቹ ያልሆነ ፣ ቤቶቹ የተገነቡበት ግብዓቶች ፈጣን ተቀጣጣይ ከሆኑ ከቆርቆሮና ከእንጨት የተገነቡ በመሆኑ እሳቱ ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በፍጥነት  መቆጣጠር ተችሏል።

የእሳት  አደጋው መንስኤ በፖሊስ እየተጣራ ሲሆን  አደጋው በሠው ላይ ያስከተለው ጉዳት የለም ።

አሁን ያለንበት ሞቃታማና ነፈሻማ የአየር ንብረት ለእሳት መከሰትና መባባስ አስተዋጾኦ የሚያደርግ
በመሆኑ ህብረተሰቡ እሳትና የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጮችን ሲጠቀም ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ማሳሰቡን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

ሰኔ ላይ የሚጀመረው የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫ ዕጣ ማውጣት ስነስርአት ዛሬ በአሜሪካ ይካሄዳል

እጣ ማውጣት ፕሮግራሙ ዛሬ 11 ሰአት የሚካሄድ ይሆናል።

48 ብሔራዊ ቡድኖች እጣ ውስጥ የሚገቡ ሲሆን
ፕሮግራሙ የሚካሄደው በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው በኬኔዲ የኪነ ጥበባት ማዕከል ነው።

Читать полностью…

YeneTube

ባሉበት ፎቶ አንስተው በመላክ ያገለገለ እቃዎትን ይሽጡ - መግዛትም ይቻላል

✅ ልብ ይበሉ ሁላችንም ቤት አንድ የማንፈልገውና የማንጠቀምበት ያገለገለ እቃ አለ በተቃራኒው ደግሞ ያንን እቃ የሚፈልጉ ግን የት እንደሚገኝ የማያውቁ ሰዎች አሉ።

አላማችን እርሶ የማይጠቀሙበትን ያገለገለ እቃ በቀላሉ ካሉበት ሆነው ፖስት በማስደረግ እንዲሸጡ ማስቻል ሲሆን ያገለገለ እቃ መግዛት ሲፈልጉ ደግሞ በቀጥታ ከእቃው ባለቤት በጥሩ ዋጋ እንዲገዙ ማስቻል ነው።

ስለሆነም እርሶም ቤት አገልግሎት ሳይሰጥ ቦታ ይዞ የተቀመጠ ያገለገለ እቃ ካሎት ፎቶ አንስተው ይላኩልን ወይም በሌሎች ሰወች ፖስት የተደረጉ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ

✅ JOIN 👉 /channel/ET_Creatives_Family

ET Creatives

Читать полностью…

YeneTube

🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉



እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ

Читать полностью…

YeneTube

የትግራይ ኃይሎች ከምክትል ፕሬዝዳንቱ ጋር ንግግር ቢያደርጉም የፕሬዚዳንት ጽ/ቤትን ለቀው ለመውጣት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተገለፀ!

መቀሌ፡ የትግራይ ኃይሎች ዛሬ ሐሙስ ጠዋት በመቀለ የሚገኘውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ዙሪያ ለአጭር ጊዜ ከበባ አድርገው በቅጥር ግቢው ዙሪያ እንቅስቃሴና ትራንስፖርት ተስተጓጎለ።

አዲስ ስታንዳርድ እንዳረጋገጠው፣ ኃይሎቹ ወደ ጽህፈት ቤቱ የሚወስደውን መንገድ በመዝጋት ጽ/ቤቱን ከበዋል። በዚህም የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት እና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሰራተኞች እንዳይገቡ ከልክለው ውጪ እንዲቆዩ አስገድደዋል።

የአዲስ ስታንዳርድ ምንጮች እንደጠቆሙት፣ ወደ 70 የሚጠጉ የአርሚ 31 ወታደሮች በክስተቱ ውስጥ ተሳትፈዋል።

በስፍራው የሚገኝ የአዲስ ስታንዳርድ ዘጋቢ እንዳረጋገጠው፣ ኃይሎቹ በኋላ ላይ የከበቡትን አካባቢ መንገዶች ለቀው በመውጣታቸው ትራፊክ እና መደበኛ እንቅስቃሴ እንዲቀጥል የተደረገ ሲሆን ከፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት መግቢያ በር ግን ለወው አልወጡም።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት አማኑኤል አሰፋ ከኃይሎቹ ጋር መነጋገራቸው የተገለፀ ቢሆንም፤ ኃይሎቹ ከፕሬዝዳንቱ ጋር ስብሰባ ለማድረግ ካልተፈቀደላቸው በስተቀር ለመልቀቅ ፍቃደኛ አልሆኑም ሲሉ ምንጮች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል፡፡

@Yentube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈረመ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ስምምነቱን የክልሉ ርዕሰ መሰተዳድር አረጋ ከበደ እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን በመወከል ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ተፈራርመዋል።

በአፍሪካ ህብረት እና በኢጋድ አደራዳሪነት ወይይት እና ድርድር ሲካሄድ መቆየቱ የተገለጸ ሲሆን፥ በዚሁ መሰረት የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ርዕሰ መሰተዳድሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ ዛሬ ለክልላችን ህዝብ የመጀመሪያው ትልቅ የሰላም ኩነት የተካሄደበት ቀን ነው ብለዋል።

ከግጭት አሸናፊም ተሸናፊም የለም፥ ከሰላም ሁሉም ያተርፋል፥ ስምምነቱ ለሰላም ወዳድ ህዝባችን ትልቅ እፎይታን ይሰጣል ነው ያሉት፡፡

የህዝብና የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ለመጡ ወንድሞቻችን እንደ መንግስት አድናቆትና ክብር አለኝ ብለዋል፡፡

የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትን (አፋሕድ) በመወከል ስምምነቱን የተፈራረሙት ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ባደረጉት ንግግር፥ ማንኛውም ግጭት መጨረሻው ውይይትና ድርድር ነው ብለዋል።

ችግሮችና የሀሳብ ልዩነትን በንግግር መፍታት ፖለቲካዊ ሽንፈት ሳይሆን ጥበብና ብልጠት መሆኑን ገልጸው፥ ችግሮችን ለመፍታት ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ማበር ተገቢ አለመሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊካ አዳዲ በበኩላቸው፥ ስምምነቱ የሀገሪቱን ቀጣይ መዳረሻ የሚያቃና ነው ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉



እስከ 30% በተሻለ ዋጋ የተሻለ ጉዞ በYango ይጓዙ

Читать полностью…

YeneTube

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተወያዩ!

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ "የአፍሪካ ቀንድ ሰላም" እና "ቀጣናዊ መረጋጋትን" በተመለከተ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የዋሽንግተን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስታወቀ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው አጭር መገለጫ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይት የተደረገው ረቡዕ ኅዳር 24/2018 ዓ.ም. መሆኑን አመልክቷል።

ይህ የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ውይይት በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ ሁለቱ ባለሥልጣናት፤ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ መረጋጋት ያላቸውን ቁርጠኝነት እና ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም መሠረት በመጣል ዙሪያ መነጋገራቸውን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መግለጫ አሳውቋል። የኢትዮጵያን ውስጣዊ ጉዳዮች በተመለከተ ንግግር ስለማድረጋቸው በመግለጫው ላይ አልተጠቀሰም።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩቢዮ መካከል የተደረገውን ውይይት በተመለከተ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ምክትል ቃል አቀባይ በኩል የተላለፈው መልዕክት በአንድ አረፍተ ነገር የተጠቃለለ እና ዝርዝር ጉዳዮችን ያልያዘ ነው።

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር የተደረገውን ንግግር በተመለከተ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጽሕፈት ቤት በኩል እስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር የለም።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩቢዮ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቀጣናዊ የሰላም ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያው አይደለም።

https://www.bbc.com/amharic/articles/c14vk5nplrdo

@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

የዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ መስጫ ቀን ግንቦት 24 ቀን ሆኖ ፀደቀ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተያዘው ዓመት የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ መስጫ ቀን ግንቦት 24/2018 ዓ.ም እንዲሆን መወሰኑን አስታወቀ።ቦርዱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል። የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ባለፉት ወራት በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው፣ የፓርቲዎች እንዲሁም በግል የሚወዳደሩ እጩዎች እና መራጮች የሚመዘገቡበትን የዲጂታል ስርዓት መዘርጋቱን አስታውቀዋል።

ሰብሳቢዋ ለእጩዎች ምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ማስገባት እና የእጩዎች ምዝገባ ማካሄድ እንደሚለያይ ገልፀው ምርጫ ቦርድ ከህዳር 8- ህዳር 23/2018 ዓ.ም ድረስ የጠየቀው ፓርቲዎች የምዝገባ ሰነዶቻቸውን እንዲያቀርቡ እንደሆነ ጠቁመዋል።የእጩዎች ምዝገባን በተመለከተም የሚከናወነው ከታህሳስ 1- ጥር 1/2018 ዓ.ም መሆኑን ገልፀዋል።

ከሰሞኑ የምርጫ ክልል ፅህፈት ቤት ሥራ አስፈፃሚዎችን የመመልመል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው፣ 131ሺህ አመልካቾች በአሁኑ ወቅት የፅሁፍ እና የቃል ፈተና እየወሰዱ መሆኑን ተናግረዋል።

ምርጫውን ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ መኖሩን በተመለከተ ማብራርያ የሰጡት ሰብሳቢዋ አስቻይ ሁኔታ በአንድ ቀን፣ በሶስት ቀን፣ በአምስት ቀን የሚሰራ አይደለም ቀጣይነት ያለው እና እስከ ምርጫው ዕለት ድረስ የሚከናወን ስራ ነው ብለዋል።

አስቻይ ሁኔታ ሲባል የፀጥታ ሁኔታዎች ብቻ አለመሆናቸውን የገለፁት ሰብሳቢዋ መሬት ላይ ያለውን የፖለቲካ ምህዳርን እንደሚያካትት ገልፀዋል።በዚህም ፓርቲዎች እንደልባቸው ይንቀሳቀሳሉ ወይ የሚለውም ላይ ቦርዱ ዕለት ዕለት እየሰራበት መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።

[AS]
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በሚቀጥለው ሳምንት ኢትዮጵያን ሊጎበኙ እንደሚጠበቅ ተነገረ። ይህ ጉዞ የህንድ መሪ ለአፍሪካ ቀንድ አገር ከአሥር ዓመት በላይ በኋላ የሚያደርጉት የመጀመሪያው ሲሆን፣ ኒው ዴሊ ከአኅጉሪቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያላትን አዲስ ቁርጠኝነት ያሳያል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከታኅሣሥ 7 እስከ 8፤ 2018 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ ሊቆዩ እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ዮርዳኖስን (ታኅሣሥ 6 እና 7) እና ኦማንን (ታኅሣሥ 8 እና 9) የሚያካትተው የሶስት አገራት ጉብኝት አካል ነው። ለመጨረሻ ጊዜ ኢትዮጵያን የጎበኙት የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንሞሃን ሲንግ ሲሆኑ እሱም እ.ኤ.አ. በ2011 ዓ.ም. እንደነበር መረጃዎች ይጠቀማሉ።

ህንድ እና ኢትዮጵያ በደቡብ-ደቡብ ትብብር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የልማት አጋርነት አላቸው። አዲስ አበባ ከአኅጉሪቱ ከፍተኛ የህንድ የቅናሽ ብድር ተቀባዮች አንዷ ስትሆን፣ ፕሮጀክቶችም የባቡር መስመር፣ የሸንኮራ ፋብሪካዎችና የኃይል ማስተላለፊያን ያካትታሉ።

ይህ ባለብዙ አገራት ጉዞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው G20 ስብሰባ እና በቅርቡ በቡታን ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ከተሳተፉ በኋላ የሚደረግ ሲሆን፣ ህንድ በተለያዩ ክልሎች ያሉ ግንኙነቶቿን ለማጠናከር የምታደርገውን ጥረት ያመለክታል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጰያ በሚያደርጉት ጉዞ በዲጂታል የህዝብ መሠረተ ልማት፣ በግብርና ቴክኖሎጂ፣ በንጹህ ኃይል፣ በባቡር ዘመናዊነት፣ በማምረት፣ በመከላከያ ትብብር እና በትምህርት ዘርፎች ላይ አዳዲስ ስምምነቶችን ያስከትላል ተብሎ ይጠበቃል።

በአሁኑ ጊዜ ከ650 በላይ የህንድ ኩባንያዎች ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሲሆን፣ ይህም የሕንድ ኢንተርፕራይዞች የአገሪቱ ትላልቅ የግል ቀጣሪዎች እንዲሆኑ አድርጓል።በተጨማሪም፣ በቴክኖሎጂ አጋርነት እና በዲጂታል ለውጥ ላይ አዲስ ተነሳሽነት መፍጠር የሞዲ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ቀደምት ውይይቶች ውጤት መሆኑ ተጠቁሟል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

በቅርቡ በአዲስ አበባ በተካሄደው 3ኛው የ«ጂ-ፓወር ቲክቶክ ሽልማት» (G-Power TikTok Creative Award) ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ የኢትዮጵያን ባህልና የህዝብ ሞራል የሚጋፋ አለባበስ ለብሰው ቀርበዋል የተባሉ ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ ፊቶች እና የዝግጅቱ አስተባባሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ በዝግጅቱ ላይ የተስተዋለው አለባበስ "ከኢትዮጵያ ህዝብ ባህል እና ሥነ-ምግባር ያፈነገጠ፣ እንዲሁም ሰውነትን በዝርዝር የሚያሳይ አስነዋሪ ድርጊት" ነው። ይህ ድርጊት በአደባባይ ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ለሚሊዮኖች መሰራጨቱ ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ እንዳደረገው ተገልጿል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት እነማን ናቸው? ፖሊስ በጉዳዩ ላይ እያደረገ ባለው ምርመራ፣ አለባበሱ በቀጥታ ከሚመለከታቸው ግለሰቦች በተጨማሪ ዝግጅቱን በስፖንሰርነት የደገፉ እና ያቀነባበሩ አካላትንም አካቷል። በዚህም መሰረት፡-

1. ወንጌላዊት ገብረ እንድርያስ በርሄ፣
2. በረከት ፀጋዬ ጅፋር፣
3. መቅድም ደረጄ መንግስቱ፣
4. ግሩም ገዛሀኝ ቀጭኔ፣ እና
5. ዮሃንስ መኮንን ሀ/ማርያም

የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን ፖሊስ አረጋግጧል።

የፖሊስ ቀጣይ እርምጃ እና ማስጠንቀቂያ

ፌደራል ፖሊስ አክሎ እንደገለጸው፣ መሰል "መጤ ባህሎች እና ከእሴት ያፈነገጡ አለባበሶች" በሀገር ተረካቢው ትውልድ ላይ ስነ-ልቦናዊ እና ሞራላዊ ውድቀት እንዳያስከትሉ ስጋት አለ። በመሆኑም የህዝብን ሥነ-ምግባር ለመጠበቅና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ተጠያቂነትን እንደሚያሰፍን ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የአክሲዮን ምዝገባ ቀነ ገደብ በህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም. መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ያልተመዘገቡ ሰነደ ሙአለ ንዋዮች (አክሲዮኖች) ላይ የሚካሄዱ ማናቸውም ግብይቶች ከባድ የወንጀል ተጠያቂነት እንደሚያስከትሉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል።

ባለስልጣኑ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአዋጅ ቁጥር 1248/2013 አንቀጽ 75 መሰረት ለህዝብ የሚሸጥ ሰነደ ሙአለ ንዋይ ለገበያ ከመቅረቡ በፊት መመዝገብ ግዴታ ነው።

ቀነ ገደቡ ካለፈ በኋላ ያልተመዘገቡ አክሲዮኖችን ለግብይት ማቅረብ ወይም መገበያየት በአዋጁ አንቀጽ 106 (5) መሰረት በወንጀል የሚያስቀጣ ተግባር ሲሆን፣ ቅጣቱም ከ7 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከ150 ሺህ እስከ 300 ሺህ ብር በሚደርስ መቀጮ ነው።

ይሄን ተከትሎ፣ አክሲዮኖቻቸውን ያላስመዘገቡ አክሲዮን ማህበራት ከአዲስም ሆነ ነባር አክሲዮኖች ሽያጭና ግብይት ጋር የተያያዘ ማንኛውንም እንቅስቃሴ እና ማስተዋወቅ እንዲያቆሙ፣ እንዲሁም አክሲዮን የሚያገበያዩ ቢሮዎች ያሏቸው ኩባንያዎችም የማገበያየት ሥራ እንዲያቆሙ በጥብቅ አሳስቧል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

ቲክቶክ በናይጄሪያ የምሽት የቀጥታ ስርጭቶች እንዳይደረጉ አገደ።

የቻይናው የማህበራዊ ሚዲያ ተቋም ቲክቶክ በናይጄሪያ በምሽት የሚደረጉ የቀጥታ ስርጭቶችን በጊዜያዊነት ማገዱን ገልጿል።

ቲክቶክ በናይጀሪያ ከምሽቱ 5 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት የሚደረጉ የቀጥታ ስርጭቶችን ማቆሙን ይፋ ያደረገው ወሲባዊ ይዘት ያላቸው ስርጭቶች መብዛታቸውን ተከትሎ ነው።

ይህ የወሲብ ይዘት በብዛት ይሰራጭበታል በተባለው በዚህ ሰዓትም በናይጄሪያ የቀጥታ ስርጭቶችን ማሰናዳት ወይም መመልከት አይቻልም።

"የይዘት ደህንነትና ተጠቃሚዎቼን እጠብቃለሁ" ያለው ቲክቶክ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ምክንያት ከ49,000 በላይ የቀጥታ ውይይቶችን ከናይጄሪያ አጥፍቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቲክቶክ እውቅና እና ትኩረት ለማግኘት በሚል ወሲባዊ ይዘት ያላቸውን ነገሮች ማሰራጨት እየተለመደ ሲሆን ቲክቶክ በተደጋጋሚ ቁጥጥር እንዲያደርግ በተለያዩ አካላት ሲጠየቅ ቆይቷል።

ቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት እገዳው ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ያሳወቀው ነገር የለም።

መረጃው የDW ነው።
@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

ትራምፕ  የቅርብ ጊዜውን የሰላም እቅድ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ባለማንበባቸዉ መበሳጨታቸዉን ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የምታደርገውን ጦርነት እንዴት ማስቆም እንደሚቻል የሚያትተዉን የቅርብ ጊዜውን እቅድ የዩክሬን አቻቸዉ ቮልዲሚር ዜለንስኪ አላነበቡትም ሲሉ ተናግረዋል ።በኬኔዲ ማእከል ዋሽንግተን ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ትራምፕ እንደተናገሩት የዜለንስኪ ሰዎች በፍሎሪዳ ከዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ጋር ሲነጋገሩ የቆዩት እቅዱን ወደዉት ነበረ ሲሉ አጥብቀው ተናግረዋል ።

ትራምፕ “ሩሲያ ጥሩ ናት” ብለዋል ። "ሩሲያ ዩክሬንን በሙሉ ብትይዝ እንደምትመርጥ እገምታለሁ። ነገር ግን፣ ጥሩ ነች፣ ዘሌንስኪ ጥሩ ስለመሆኑ ግን እርግጠኛ አይደለሁም።" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ዘሌንስኪ ቀደም ሲል ዩክሬን ግዛትን ለሩሲያ አሳልፋ እንድትሰጥ እና የመከላከያ አቅሟን እንድትገድብ የቀረበውን ሀሳብ ተቃውመዋል።ሰኞ ማለዳ ለዩክሬን ህዝብ ባደረጉት ሳምንታዊ ንግግር ዘሌንስኪ ከትራምፕ ልዑካን ጋር "ጠቃሚ ውይይት" መደረጉን ተናግረዋል።አክለውም "የአሜሪካ ልዑካን የዩክሬንን ዋና አቋም ያውቃሉ እና ውይይቱ ቀላል ባይሆንም ገንቢ ነበር፤ ስራችንን እንቀጥላለን አንዳንድ ጉዳዮችን በአካል ብቻ መወያየት ይኖርብናል" ብለዋል፡፡

በቀጠለዉ ዉጊያ በሱሚ ክልል ሰሜን ምስራቅ በምትገኘው ኦክቲርካ ከተማ ሩሲያ በፈጸመችዉ ጥቃት ቢያንስ ሰባት ሰዎች በአንድ ሌሊት ቆስለዋል ሲሉ የክልሉ አስተዳዳሪ ኦሌግ ግሪጎሮቭ ተናግረዋል።ይህ የሆነው ሰው አልባ አውሮፕላኖች አፓርተማዎችን ከመተ በኋላ ነው። በተጨማሪም በቼርኒሂቭ እና ዲኒፕሮፔትሮቭስክ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል፡፡እሁድ እለት በሩሲያ ጥቃቶች አራት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸዉ ይታወሳል። ባለፈው ሳምንት ብቻ በ1,600 የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና 70 የሚጠጉ ሚሳኤሎች ጥቃት ዩክሬን ደርሶባታል ሲሉ ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ ተናግረዋል።

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

ለም ሆቴል አካባቢ ተደራራቢ አውቶቡስ የቀላል ባቡር የኤሌክትሪክ ገመድ በመበጠሱ አገልግሎት አቆመ!

በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት መስመር ላይ የሚገኘው ከሃያት ወደ ጦር ኃይሎች የሚወስደው መስመር አገልግሎት መገናኛ አካባቢ ለም ሆቴል መሻገሪያ ላይ በተፈጠረ ብልሽት ምክንያት መቋረጡ ታውቋል።

ብልሹቱ የተከሰተው ለም ሆቴል አቅራቢያ በቅርቡ ለመተላለፊያነት በተሰራ መንገድ ላይ ሲሆን፣ በተለይም ተደራራቢ የአንበሳ አውቶቡስ መንገዱን ሲያቋርጥ የቀላል ባቡሩን ማስተላለፊያ የኤሌክትሪክ ገመድ በመበጠሱ አደጋው እንደደረሰ ተገልጿል።

በዚህ አደጋ ምክንያት የባቡር አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ፣ በወቅቱ በመስመሩ ላይ የነበረው ባቡርም ተሳፋሪዎችን ለማውረድ መገደዱን ካፒታል ተመልክቷል።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት ይህን መሰል የባቡር መሠረተ ልማት ብልሽት (የኤሌክትሪክ ገመድ መበጠስ) ከዚህ በፊት አጋጥሞ አያውቅም።

የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የኤሌክትሪክ ገመዱን በአስቸኳይ ለመጠገን ጥረት እያደረገ ነው። የሃያት-ጦር ኃይሎች መስመር ተጠቃሚዎችም አገልግሎቱ ወደ መደበኛ ሥራው እስኪመለስ ድረስ የትራንስፖርት አማራጮችን እንዲጠቀሙ ተጠይቀዋል።

ባለሥልጣናት በአሁኑ ወቅት የደረሰውን ጉዳት መጠን በመገምገም ላይ ሲሆኑ፣ አገልግሎቱ በፍጥነት ወደ መደበኛ ሥራው እንዲመለስ የሚያስችላቸውን ጥረት እያደረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

የቀድሞው የሠላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ጥፋተኛ በተባሉበት ክስ የ7 ዓመት ከ2 ወር እስር ተፈረደባቸው።

አቶ ታዬ ዛሬ አርብ ኅዳር 26/2018 ዓ.ም. የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት ጥፋተኛ በተባሉበት ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ነው።

የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን እና የክልል ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ታዬ ሕገ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት እንዲሁም ፍቃድ ሳይኖራቸው በቤታቸው ውስጥ አንድ ታጣፊ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ60 ጥይቶች ጋር ተገኝቷል በሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

የኤርትራ መንግሥት ያለፍርድ ለ18 ዓመታት አስሯቸው የነበሩ 13 ሰዎችን ለቀቀ!

የኤርትራ መንግሥት በወታደራዊ እስር ቤት ያለ ፍርድ ለ18 ዓመታት ያህል አስሯቸው የነበሩ 13 ሰዎችን መልቀቁን ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ ትግርኛ ተናገሩ።አስራ ሦስቱ ግለሰቦች ታስረው የነበረው በአስቸጋሪ አነወኗር ማይ ስርዋ ተብሎ በሚጠራ ጥብቅ ቁጥጥር በሚደረግበት ወታደራዊ እስር ቤት ነው።

ከእስር የተለቀቁት ሰዎች ነጋዴዎች፣ የፖሊስ አባላት እንዲሁም በተለያየ የሙያ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው የነበሩ ባለሙያዎች ሲሆኑ፣ ያለ ምንም ማብራሪያ ሐሙስ ኅዳር 25/2018 ዓ.ም. ተለቀው ከቤተሰባቸው ጋር ተቀላቅለዋል።በማይ ስርዋ ወታደራዊ እስር ቤት ታስረው የነበሩ እና ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ ግለሰብ ለቢቢሲ ትግርኛ እንደተናገሩት ጥቅምት 2000 ዓ.ም. ላይ በወቅቱ የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊ ከነበሩት ከኮሎኔል ስምኦን ገብረድንግል መገደል ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልፀዋል።አክለውም የተያዙት ከሁለት ነጋዴዎች ጋር በተያያዘ መሆኑን አብራርተዋል።

መጀመሪያ ላይ 30 የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው የነበረ ሲሆን፣ የተወሰኑት ከዓመታት እስር በኋላ ተለቅቀው 20ዎቹ ብቻ በአስቸጋሪው እስር ቤት ውስጥ ቆይተዋል።ከተለቀቁት መካከል የቀድሞው የኦሊምፒክ ብስክሌተኛ እና ነጋዴ ዘርአግብር ገብረሕይወት፣ በንግድ ሥራቸው ታዋቂ የሆኑት ተስፋለም መንግሥተአብ እና በኩረ መብርሃቱ እንዲሁም ኢንጂነር ዳዊት ኃብተማሪያም እና ማቲዮስ ኃብተማሪያም የተባሉ ሁለት ወንድማማቾች ይገኙበታል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሰባተኛው ሃገራዊ ምርጫ የእጩዎች የድጋፍ ፊርማ ግዴታ የሚያነሳዉን ማሻሻያ አፀደቀ፣ ሁለት አለም አቀፍ የብድር ስምምነቶችም ጸድቀዋል!

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሰባተኛው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የእጩ ተወዳዳሪዎች የድጋፍ ፊርማ የማሰባሰብ ግዴታን በአንድ ድምፅ የሚያስቀር ማሻሻያ አፀደቀ።

በስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሦስተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዋጅ ቁጥር 1397/2018 የጸደቀው ይህ አዋጅ ፣ ቀደም ሲል የጸደቀውን አዋጅ ቁጥር 1162/2014 አንቀጽ 32(2) እና አዲስ የተጨመረውን ንዑስ አንቀጽ 8 ከሥራ ውጪ ያደርጋል።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ፣ የድጋፍ ፊርማው ግዴታ ከዚህ ቀደም ለስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ በአዋጅ ቁጥር 1235/2014 መሠረት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ገደቦች ምክንያት መነሳቱን አውስተዋል።

ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አማካኝነት፣ ጊዜው ውስን መሆኑና ቀጣይነት ያለው የምርጫ ዝግጅት የፊርማ አሰባሰቡን አዳጋች እንዳደረገው በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ሲገልጹ መቆየታቸውን አስረድተዋል።

አፈ-ጉባዔው አክለውም “የድጋፍ ፊርማ ሕጉን አሁን ማስፈጸም ፓርቲዎች በምርጫው ተወዳድረው የመሳተፍ ብቃታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ስለሚፈጥር ይህንን ማስቀረት የግድ አስፈላጊ ነው”ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

የውድቀት አዋጅ! በድሉ ዋቅጅራ

እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮጵያውያን ለደህንነታቸው የቆመ፣ ሀላፊነት የሚሰማው አስተዳዳሪ የሚያገኙት መቼ ነው?! (በድሉ ዋቅጅራ)


በመጀመሪያ
ከአርባ በላይ በሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተምረውም/ሳይማሩም ተመርቀው፣ወይም ትምህርታቸውን 12ኛ ላይ አቁመው፣ እዚህ ግባ የሚባል የስራ እድል በሌለባት ሀገር የሚበተኑ ወጣቶች፣ ማህበራዊ ሚዲያን እንደስራ ፈጠራ/እድል በመጠቀም እራሳቸውን በገቢ ለመደጎም የሚያደርጉትን ጥረት በጅምላ አልቃወምም፡፡

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆኑኝ በቁጥር ጥቂት የማይባሉት፣ ለይዘት ፈጠራ ያጠራቸውን እውቀትና የህይወት ልምድ ድንቁር፣ የአእምሮና የስነልቦና ችግር በወለደው ድፍረትና ንቀት ተክተው ‹‹የደደቡትና የሰገጡት›› ናቸው፡፡ እንደሰመረ ባሪያው አሌክስ አብረሀም ወዘተ. ያሉ ሰዎች በቲክቶ በሚሰሩት ጠቃሚ ይዘት ስማቸው እንኳን ሳይጠራ፣ አለመለወጥን፣ አእምሮን ያለመጠቀምን አርማ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ወጣቶችን መኪና የሚሸልሙ፣ በሚሊየን የሚቆጠር ተከታዮች እንዲያገኙ የሚያግዙ ተቋማትን መመልከት እጅግ በጣም ይሸማቅቃል፤ በሀገርና በማህበረሰብ ላይ ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ይሁን እንጂ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፣ ‹‹በሀገር እና በማህበረሰብ ላይ ተስፋ መቁረጥ፣ ሀገርን ለደንቆሮዎች፣ ለደፋሮችና ለአንባገነኖች አሳልፎ መስጠት ነው፡፡›› ይሉ እንደነበረው፣ ይህን ‹‹እንዳሻው›› ብሎ ማለፍ ያዳግታል፡፡

ምን አይነት ተቋማት ናቸው ይህን የሽልማት ፕሮግራም የሚያዘጋጁትና በገንዘብ የሚደግፉት? ለነዚህ ተቋማት ሀገርና ማህበረሰብ ከሸቀጣቸው ማራገፊያነት የዘለለ ትርጉም የላቸውም ማለት ነው? በነገራችን ላይ የከሳቴ ብርሀን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ ‹ሰገጠ› የሚለውን ቃል፣ ‹‹ክፉ ሰው፤ ሞገደኛ፤ የሰውን ነገር የማይቀበል፤ . . .›› ሲል ይፈታዋል፡፡

የሽልማቱ ሲገርመን፣‹‹ሰግጥ - ፈምስ›› የሚባል ሀገራዊ ጉዞ፣ አዶናይን ይዞ፣ ድንቁርናን ተመርኩዞ፣ ሊዘጋጅ ስለመሆኑ ጋዜጣዊ መግለጫ መሰጠቱን ተመለከትኩ፡፡ ‹‹በኤ.አይ የተሰራ ነው በሉኝ›› ብዬ፣ ሰዎች ጋ ደወልኩ፡፡ የተመኘሁት ሳይሆን ቀርቶ እውነት ነው፡፡

ልጆችና ወጣቶች በተለያየ ምክንያት የነዚህ ቲክቶከሮች ተከታይ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እኔን እንቅልፍ የነሳኝ ፈጽሞ በማልጠብቀው ሁኔታ፣ የጋዜጣዊ መግለጫው ተናጋሪ ወይዘሮና የሰራዊት ፍቅሬ ጉዳይ ነው፡፡ ይህች ሴት ለልጆችዋ፣ ‹ደድቡ፣ ሰግጡ› ትላለች ማለት ነው? በአፍለኛው የሬዲዮ ድራማ አሀዱ ብሎ፣ ብዙ ውጣውረዶችን አልፎ፣ እዚህ የደረሰው ሰራዊት ፍቅሬ፣ የመጣበት የሙያ ትግል ጉዞ ላይ ውሀ ከልሶ፣ ‹ሰግጥ - ፈምስ› የሚል ሀገራዊ ዘመቻ ፊታውራሪ ለመሆን የተነሳው ምን አስልቶ ነው? ለመሆኑ ሰራዊት የዚህ አካል መሆኑ ለልጆቻችን የሚያስተላልፈው መልእክት፣ ‹እዚህ የደረስኩት፣ ‹ደድቤ - ሰግጬ ነው› የሚል እንደሆነ ያውቃል?

የትምህርት ስረአታችን ማጥ ውስጥ ነው!
በሙስና ተጨማልቀናል!
የሀይማኖት ተቋሞቻችን ረክሰው አለማዊ መድረኮችን እየመሰሉ ነው! . . . ይህ ሁሉ አልቆረቆራቸውም፤ ለዘመቻ አላነሳሳቸውም፡፡ ‹‹ወርቅ በወርቅ›› ብሎ ፊልም የሰራበት፣ ሀገራችን የምትታወቅበት አትሌቲክስ ተዋርዶ፣ ከአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያለ ወርቅ መመለሳችን እንኳን ሰራዊት ፍቅሬን በቁጭት ለተግባር አላነሳሳውም፡፡ ሰራዊትን ለሀገራዊ ዘመቻ ያነሳሳው የሀገሪቱ የደደቦች፣ የሰገጤዎች ማነስ ነው፡፡

በመጨረሻ
ይህ ጉዞ የሀገራዊና ማህበረሰባዊ ውድቀታችን ይፋዊ አዋጅ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርና ህዝብ አስተዳድራለሁ የሚል መንግስት፤
ባህል ሚንስቴር፣ ትምህርትት ሚኒስቴር፣ በወጣቶች፣ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ሚንስቴሮች፣ ካሉ (አሉ ብዬ አምናለሁ) ይህ ጉዞ መታገድ አለበት፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በሀይማኖት ስም፣ በአነቃቂ ንግግር ስም፣ በይፋ ማህበረሰባዊ እሴቶቻችንን የሚቃረኑና የዘቀጡ፣ ለማጭበርበር የቀረቡ ይዘቶች በማቅረብ፣ በህዝብ በተለይ ባልተማረው ማህበረሰብ ስነልቦና ላይ የሚጫወቱ የማህበራዊ ሚድያ ይዘት አቅራቢዎች ላይ ህጋዊና ተገቢ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል።

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

መደበኛ ሎተሪ 1752ኛ ዛሬ ህዳር  25 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በእድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል።

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

ማስታገሻ በሚል ማንኛውም መድኃኒት ከሃኪም ትዕዛዝ ውጪ ከመውሰድ ህብረተሰቡ ሊጠነቀቅ እንደሚገባ ተነገረ

መድሃኃኒቶችን ያለ ሀኪም ትዕዛዝ መጠቀም እንዲሁም ከታዘዘው መጠን በላይ መውሰድ ለጸረ ተህዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድ እንደሚያስከትል በወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የላብራቶሪ ዳይሬክተር እና የጸረ ተህዋሲያን መላመድ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ  የሆኑት ባህረዲን ዳሪ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች በጀርሞች መለመድ ምክንያት ታማሚዎች ታክመው መሄድ ከሚገባቸው በላይ በጤና ተቋማት እንዲቆዩ ላልተፈለገ ወጪ እንዲሁም ለከፋ የጤና ችግር ተጋላጭ እንደሚያደርጉ  እና በሽታ የመከላከል አቅም እንደሚቀንሱ   ተጠቁሟል ።

የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ከህክምና ባለሙያ  ትዕዛዝ ውጪ መውሰድ የጎንዮሽ  ጉዳቶች እንደሚያስከትል ተጠቁሟል።  ሰዎች ለራስ ምታት እና ለተለያዩ ህመሞች ከፓራስታሞል ጀምሮ ዳይክሎፌን እያሉ የሚወስዷቸው መድሃኒቶች  ደረጃቸው ከፍ እያለ በሄደ ቁጥር የሚያስከትለው ችግርም እንደሚጨምር ተጠቁሟል።በተጨማሪም በንጽህና ጉድለት የጸረህዋሲን ጀርሞች መላመድ  ከታማሚ ወደ ታማሚ ስለሚተላለፉ ንጸህናን መጠበቅ እንደሚገባ ተነግሯል።

በአለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ በሰዎች ፣በአካባቢ እንዲሁም በእንስሳት ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳትን የሚያስከትል ሲሆን ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር እንዲሁም ሌሎች ጉዳቶችንም ለመቆጣጠር  የሚመለከተው አካል ሁሉ በትኩረት ለለሰራበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑ ተጠቁሟል።ማንኛውም ሰው ህመም ስለተሰማው ብቻ ማስታገሻ በሚል ማንኛውንም አይነት መድሃኒቶች  መውሰድ እንደሌለበት እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሃገራት ላይ ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት  እንደሚያደርስ  በወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የላብራቶሪ ዳይሬክተር  የጸረ ተህዋሲያን መላመድ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ  የሆኑት ባህረዲን ዳሪ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በወራቤ ሆስፒታል በሽታወን የመከላከል ስራ በትኩረት በኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

ተጨማሪ መረጃ ከመቀሌ

የትግራይ የጸጥታ ኃይሎች አባላት የጊዜያዊ አስተዳደሩን ቢሮ መክበባቸውን ለቢቢሲ ትግርኛ ገልፀዋል።

የትግራይ የጸጥታ ኃይሎች አባላት “የደመወዝ ክፍያ ዘገየ” በሚል ቅሬታቸውን መሳሪያዎቻቸውን ይዘው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ህንፃን ከበውታል።

የአርሚ 31 ጦር 71 አባላት ትናንት ረቡዕ ምሽት ከአራጉሬ (እንደርታ) አካባቢ ወደ መቀሌ መጥተው አመፅ እንዳስነሱ ታውቋል። ዛሬ ጠዋት የአስተዳደር ህንፃውን ከበውታል። ከዚህ በተጨማሪ የ “አርሚ 31 ኮር 312 ክፍለ ጦር ረመፅ የሚባለው ዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም 5:05 የመሳሪያ ማስቀመጫ መጋዘን በመስበር ትጥቃቸውን በመታጠቅ ከነሩበት ቦታ ወደ መቀሌ በመገስገስ ላይ መሆናቸውን ምንጮች ጠቁመዋል። የፌደራል መንግሥቱ በጀት በወቅቱ ባለመልቀቁ በትግራይ ክልል ደመወዝ በወቅቱ መክፈል እንዳልተቻለ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲሁም ህወሃት በተናጠል ለፌደራል መንግስቱ ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

ሰበር ዜና

ባሁኑ ሰአት በመቀሌ የጀነራል ታደሰ ወረደ ቢሮ በአርሚ 31 ታጣቂዎች መከበቡ ተሰምቷል። በትናንትናው ዕለት አንዳፍታ ሚዲያ ጀነራሉ ጫና ውስጥ መግባታቸውን ዘግቦ ነበር።

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…
Subscribe to a channel