ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ - ዳይናሚክ አክሲዮን ማህበር
የስራ ቦታ፡ የሽያጭ እና የግብይት ኃላፊዎች (ብዛት 20 )
አካባቢ፡ አዲስ አበባ
🔹 ቁልፍ ኃላፊነቶች
የኩባንያ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ማስተዋውቁ እና መሽምጥ።
የመስክ ግብይት እና የደንበኛ ክትትል ማካሄድ።
ሳምንታዊ እና ወርሃዊ የሽያጭ ግቦችን ማሳካት።
የዕለታዊ እንቅስቃሴ እና የገበያ ግብረመልስ ሪፖርቶችን ማቅረብ።
🔹 መስፈርቶች
በማርኬቲንግ፣ በቢዝነስ፣ በኢኮኖሚክስ ወይም ተዛማጅ መስኮች ዲፕሎማ ወይም ዲግሪ።
እጅግ በጣም ጥሩ የመግባቢያ እና የማሳመን ክህሎቶች።
በጫና ስር የመስራት እና የሽያጭ ግቦችን የማሳካት ችሎታ።
በሽያጭ ወይም በማርኬቲንግ ልምድ መኖሩ ተጨማሪ ነው (ግዴታ አይደለም።)
ሐቀኛ፣ ታታሪ እና የመስክ ስራ ለመስራት ፈቃደኛ።
🔹 የምናቀርበው ነገር
ወርሃዊ ደሞዝ + ማራኪ ኮሚሽን
የአፈጻጸም ጉርሻዎች
የስልጠና እና የሙያ እድገት እድሎች
📩 እንዴት ማመልከት እንደሚቻል (የTalentHub ብቻ)
ሁሉም አመልካቾች በTalentHub በኩል ብቻ ማመልከት አለባቸው።
https://talenthubethiopia.com/
📍 የቢሮ አድራሻ
Megenagna፣ Hibire ህንፃ፣ 3ኛ ፎቅ፣ የቢሮ ቁጥር 312፣ አዲስ አበባ
📅 የማመልከቻ ቀነ-ገደብ፡
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ።
"አሰብን በጋራ መጠቀም አለብን'' ኤርትራኖች ሞኞች ናቸው! ''አምባሳደር ጀኔራል ባጫ ደበሌ።
የሚያስቡ ከሆነ አሰብን በጋራ ጥቅም ማዋል'' ለጋራ ጥቅም ካላዋልክ ደግሞ አይቀርም እናመጣዋለን። አሰብን አስቀራለሁ ስትል ይጠፋል። በውጊያ የመሄድ ፍላጎት የለንም፣ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንሄዳለን።
የነሱ ሃሳብ ኢትዮጵያን በማመስ ኤርትራ በሰላም ትኖራለች የሚል ፖሊሲ ነው ያላቸው። ይህ ደግሞ የሞኞች ፓሊሲ ነው አንተ የሰው ቤት እየበጠበጥክ በሰላም አትኖርም ሰውን ሰላም አሳጥተህ አንተ በሰላም አትኖርም።
አንተ መስታወት ቤት ውስጥ ቁጭ ብለህ ድንጋይ ብትወረውር ምን ሊያመጣ እንደሚችል ይታወቃልና የኢትዮጵያ የባህር በር የማገኘት ጉዳይ ምንም ጥርጥር የለውም"።
አምባሳደር ጀነራል ባጫ ደበሌ
@Yenetube @Fikerassefa
ኤርትራ ከኢጋድ አባልነቷ መውጣቷን አስታወቀች!
"ኢጋድ የቀጣናውን ሕዝቦች ምኞት የማያሳካ ሆኗል"
ኤርትራ ከድርጅቱ ለመውጣት የወሰነችውን ውሳኔ በይፋ ለኢጋድ ዋና ጸሐፊ አሳውቃለች ሲል የአገሪቱ የኢንፎሜሽን ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል፡፡
ኤርትራ እ.ኤ.አ. በ1993 የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) እንደገና ሲደራጅ ጀምሮ ቁልፍ ሚና መጫወቷን ያስታወሰው መግለጫው፣ ጥምረቱ በሂደት የቀጣናውን ሕዝቦች ምኞት የማያሳካ ሆኗል ሲል ተችቷል፡፡
“ከጎርጎሮሳውያኑ 2005 ዓ.ም ወዲህ፣ ኢጋድ የቀጣናውን ሕዝቦች ምኞት የሚያሟላ ሳይሆን፣ ጉዳት የሚያስከትል ሚና ተጫውቷል፡፡ በተለይም ኢላማ ለተደረጉ አባል አገራት፣ኤርትራ ላይ በልዩ ሁኔታ መሣሪያ ሆኗል። እነዚህ ያልተገቡ ድርጊቶች ኤርትራን እ.ኤ.አ. ሚያዚያ 2007 አባልነቷን እንድታግድ አስገድዷታል።” ብሏል መግለጫው፡፡
ኤርትራ ድርጅቱ ስህተቶቹን ያርማል በሚል ተስፋ እ.ኤ.አ. ሰኔ 2023 አባልነቷን ማስቀጠሏን የጠቀሰው መግለጫው፣ ኢጋድን በሕግ የተሰጡትን ግዴታዎች ባለመወጣት እንደሚከስ ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
የኤርትራ የኢንፎሜሽን ሚኒስቴር፤ “በዚህ ሁኔታ ኤርትራ ሕጋዊ ሥልጣኑንና ኃላፊነቱን ካጣ፣ ለሁሉም አባላቱ የሚታይ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ከማያስገኝ እንዲሁም ለቀጣናው መረጋጋት ጉልህ አስተዋጽኦ ካላደረገ ድርጅት አባልነቷን ለማቋረጥ ተገድዳለች።” ብሏል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ግሎባል ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል ከቀነ ገደቡ በፊት ማሟላቱን ገለጸ።
ግሎባል ባንክ የተከፈለ ካፒታሉን በማሳደግ ብር 5 ቢሊየን ማድረስ መቻሉን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ገልጸዋል፡፡
ካለፈዉ ዓመት ጋር ሲነፃፃር የ1መቶ2 በመቶ ዕድገት ማሳየት መቻሉንም ነዉ የተናገሩት፡፡
ባንኮች ካፒታላቸዉን 5 ቢሊየን ብር እንዲያደርሱ በብሔራዊ ባንክ የተቀመጠውን መመሪያ ከጊዜ ገደቡ በፊት ማሳካት መቻሉን አንስተዋል፡፡
ግሎባል ባንክ በ2024/25 በጀት ዓመት 5.56 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ የተገለጸ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት የተመዘገበው ከባለፈው ዓመት ከተመዘገበው ገቢ ጋር ሲነፃፀር የ37 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተነግሯል።
በተዘጋው በጀት ዓመት የባንኩ ጠቅላላ ሃብት 34.4 ቢሊየን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን፤ ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር የ42 በመቶ ዕድገት ማሳየት መቻሉንና በበጀት ዓመቱ 7.53 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰበሰብ መቻሉ ተገልጿል።
ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ41 በመቶ ብልጫ በማሳየት የባንኩን አጠቃላይ ተቀማጭ የገንዘብ መጠን ወደ ብር 25.75 ቢሊየን ማድረሱ ተነግሯል።
ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከታክስ፣ ከመጠባበቂያ እና ሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ1.17 ቢሊየን ብር በላይ ማትረፍ መቻሉን አስታዉቋል፡፡
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
መምህሯን አስገድደው የደፈሩ ሁለት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ሀርቡ ጂባት ቀበሌ ውስጥ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል የፈፀሙት ሁለት ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸውን ፖሊስ አስታወቀ
የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ታደሰ በዬራ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት 1ኛ ተከሳሽ ማሞ ዘነበ
2ኛ ተከሳሽ ቢቂላ ፍቃዱ የካቲት 27ቀን 2017 ዓ.ም ከለሊቱ 7ሰዓት ድርጊቱን መፈጸማቸው ተገልጿል ። ተጎጂዋ በመምህርነት ሞያ ስታገለግል የነበረች ሲሆን በር ሰብረው በመግባት የግብረ ስጋ ድፍረት በደል እንደፈፀሙባት በማስረጃ ተረጋግጧል።
ሁለቱ ተከሳሾች በመምህሯ ላይ ድርጊቱን ከፈፀሙ በኋላ ወዲያው ለፖሊስ ደውላ በማሳወቋ ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ተጎጂዋ የጤና ምርመራ የተደረገላት ሲሆን በውጤቱም የግብረ ስጋ ድፍረት በደል በግዳጅ እንደተፈፀመባት መረጋገጡም ከጤና ተቋም የተገኘው ማስረጃ ማረጋገጡን ገልፀዋል ።
ፖሊስ በመምህሯ ላይ የተፈፀመውን የግብረ ስጋ ድፍረት በደል በማስረጃዎች አጠናክሮ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቢ ህግ ልኳል።
አቃቢ ህግም ከፖሊስ የቀረበውን ማስረጃ ተመልክቶ በወንጀል ህግ ቁጥር 620 እና 605 መሰረት ክስ የመሰረተ ሲሆን ክሱን ሲከታተል የቆየው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 39ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች የሃይል ድርጊት በመጠቀም አስገድደው የግብረ ስጋ ድፍረት በደል መፈፀማቸውከፍተኛ የአእምሮ ጉዳት በማስከተላቸው እያንዳዳቸው በአስራ አንድ አመት እስራት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ታደሰ በዬራ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።
ብስራት FM
@Yenetube @Fikerassefa
የአሜሪካ ኮንግሬስ አባል ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና በሌሎች እምነት አማኞች ላይ እየተፈጸመ ነዉ ላሉት ጥቃት ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጠየቁ ተባለ
በአሜሪካ ኮንግሬስ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባሉ ኤርል በዲ ካርተር፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና ሌሎች የሓይማኖት ተከታይ ማኅበረሰቦች ላይ ይፈጽሙቸዋል ላሉት ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ አሜሪካ ማዕቀብ እንድትጥል የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አቀረቡ።
ረቂቅ የውሳኔ ሃሳቡ፣ በሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስቆም እና ባለስልጣናትን ተጠያቂ ለማድረግ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የተመረጡ ማዕቀቦችን ጨምሮ ሁሉንም ዲፕሎማሲ መሳሪያዎች እንዲጠቀሙ ይጠይቃል።
የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና የሌሎች ኃይማኖቶች ተከታዮች የጦር ወንጀልና ዘር ማጥፋትን ጨምሮ በርካታ ወንጀሎች እንደተፈጸሙባቸው የሚያሳዩ ሁኔታዎች መኖራቸውንም የውሳኔ ሃሳቡ ይገልጣል።
Via ዋዜማ
@Yenetube @Fikerassefa
የታጠቁ አካላት የሰላም መንገድን እንዲመርጡ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች ጥሪ አቀረቡ።
የአማራ ክልል ሕዝብ ከዚህ በላይ ጦርነት እያደረሰ ያለውን ችግር መሸከም ስለማይችል አሁንም ድረስ የታጠቁ አካላት የሰላም መንገድን እንዲመርጡ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ከፍተኛ አመራሮች ጥሪ አቅርበዋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ የአፋሕድ ከፍተኛ አመራሮች መግለጫ ሰጥተዋል።
የአማራ ሕዝብን ጥያቄ እናስመልሳለን ብለን ወደ ጫካ ብንገባም ትግላችን የአማራ ሕዝብ ጠል በሆኑ እና ኢትዮጵያ እንድትፈርስ በሚፈልጉ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ጠላቶች እጅ መውደቁ ድርጅቱ ወደ ሰላም ስምምነቱ መምጣቱን አመራሮቹ ገልጸዋል።
አፋሕድ ወደ ትጥቅ ትግል ከገባበት ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የአማራ ክልል ሕዝብ በሰላም መንቀሳቀስ የማይችልበት ደረጃ መድረሱን እና ከትምህርት፣ ከጤና እና ሌሎችም አገልግሎቶች ውጭ ሆኖ ከፍተኛ ችግር ማስተናገዱንም የአፋሕድ ምክትል የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ እና የወሎ ቤተ አማራ ጠቅላይ ግዛት እዝ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ኢያሱ አበራ ተናግሯል።
የትኛውም ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ እንጂ በጦርነት የሚፈታ ባለመሆኑ እንዲሁም የክልሉ ሕዝብ በሰላም እጦት ከሚደርስበት ችግር እንዲወጣ ድርጅቱ የሰላም ስምምነቱን መፈረሙንም ገልጿል።
“እስከመቼ ነው ጦርነት ውስጥ የምንቆየው?” የሚል ጥያቄ በድርጅቱ ውስጥ በየደረጃው ካሉ ሠራዊት አባላት ጥያቄ ሲነሣ እንደነበር የገለጸው የአፋሕድ የጎጃም ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ፋይናስ ኃላፊ፣ አሁን የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተገቢ መሆኑን አረጋግጧል። በተደረሰው ስምምነትም ሁላችንም ደስተኞች ነን ሲልም ገልጿል።
የድርጅቱ የጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የወሎ ቤተ አማራ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አስተዳደር እና ማኅበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ግርማ እጅጋየሁ፣ አማራ ጠል ወይም ኢትዮጵያ ጠል የሆኑት ህወሓት እና ሻዕቢያ ከግብጽ ተልዕኮ ተቀብለው የአማራ ክልልን የማተራመስ አጀንዳ ይዘው እየተንቀሳቀሱ በመሆኑ አካሄዳችን ትክክል አይደለም ብለን ወደ ድርድር መጥተናል ብሏል።
@Yenetube @Fikerassefa
ትራምፕ 1 ሚሊየን ዶላር 'ጎልደን ካርድ' ቪዛን በይፋ አስጀመሩ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቢያንስ 1 ሚሊየን ዶላር መክፈል ለሚችሉ ሐብታም የውጭ ሀገር ዜጎች የሚሰጥ ‘ጎልደን ካርድ’ ቪዛን በይፋ አስጀምረዋል።
ቪዛ ካርዱ አመልካቾች ብቁ መሆናቸው ከተረጋገጠ “በቀጥታ የአሜሪካ ዜጋ መሆን የሚችሉበትን መንገድ ይከፍትላቸዋል” ተብሏል።
ትራምፕ ቪዛውን ካስተዋወቁ በኋላ “እጅግ አስደናቂ ነገር” በማለት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
ቀደም ብሎ ይፋ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ይህ ቪዛ ካርድ ለአሜሪካ“ተጨባጭ ጥቅም” ያስገኛሉ የተባሉ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።
አዲሱ የትራምፕ ቪዛ ዋሺንግተን ከስደተኞች ጋር በተያያዘ ዘመቻ በጀመረችበት፣ ለሥራ ቪዛ የሚከፈለው ገንዘብ እንዲጨምር እና ሰነድ አልባ ስደተኞችን የማባረር እርምጃ በጀመረችበት ወቅት የተዋወቀ መሆኑን ዘገባው አስታውሷል።
@Yenetube @Fikerassefa
አሻም ቴሌቪዥን ሙሉ በሙሉ ስርጭት ማቆሙን አሳወቀ
📌 ከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር የቦርድ አባላት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል።
#Ethiopia | አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ከተመሰረተችበት ባለፉት 8 ዓመታት ጀምሮ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዜናና ወቅታዊ እንዲሁም በመዝናኛ ዝግጅቶች መረጃዎችን በቴሌቪዥን እና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ስታደርስ ቆይታለች፡፡
ይሁን እንጂ አሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ስራዋን ለመቀጠል አቅም ስለሌላት በቴሌቪዥንም ሆነ በየትኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ ከዛሬ ታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በይፋ ስርጭት ማቆሟን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ስለሆነም ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ የአሻም ሚዲያ መታወቂያ በመያዝ ወይም የሚዲያዋን ሎጎ በመጠቀም በየትኛውም ሁነት (Event) ፣ በእቅድ ዜና ወይም ፕሮግራም ፣ በስልጠና መድረክ ፣ ቃለ-መጠይቅ እና በመሰል ጉዳዮች ላይ የሚገኙ (የሚሳተፉ) ባለሞያዎች የሚዲያ ተቋሙን እንደማይወክሉ ለሁሉም የግልና መንግስታዊ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ጭምር በትህትና ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ባለፉት 8 ዓመታት ከአሻም ሚዲያ ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ጋር አብራችሁ ለዘለቃችሁ ለውድ ተመልካቶቻችንና ተከታታዮቻችን ልባዊ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
🥁 65% /35%
🌬እንኳን ደስ አላችሁ💫💫💫
🌬 አሁን ቀደም ያመለጣችሁ ደንበኞቻችን ወርቃማ እድል በዲፕሎማቲክ መንደር በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ ለውስን ቤቶች ብቻ
🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ
🌬 65% ሲከፍሉ 35% እኛ ልዩ ቅናሽ አቅርበናል።
🏠 80 ካሬ ሜትር ባለ ሁለት መኝታ
🥁ሙሉ ክፍያ 5,770,050ብር
🏠139 ካሬ ሜትር ባለሶስት መኝታ
🥁ሙሉ ክፍያ 9,938,,000 ብር
✅ መገልገያዎች
👉 ሁለት ዘመናዊ የሰው እና አንድ የእቃ ሊፍቶች
👉 የመኪና ማቆሚያ ቦታ
👉 ቴራስ
👉 ያልተገደበ የውሃ አቅርቦት
👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር
👉 የደህንነት ካሜራ
👉ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ እና ኢንተርኮም ሲስተም
እንዲሁም
⛳️ ገላን ኮንደምንየም
🗣ሱቆች ከ23 ካሬሜትር ጀምሮ
በ500,000ብር ቅድመ ክፍያ እንዲሁም 2.3 ሚሊዬን ሙሉ ክፍያ ለውስን ሱቆች ብቻ እየሸጥን እንገኛለን።
🚴🏿♂️ይፍጠኑ🚴🏽♀️
🕹ለበለጠ መረጃ:- 0931835733
ይደውሉ! በwhatsapp ያገኙናል።
Telegram @momsra16
ይፍጠኑ🗣
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል የተባለ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አሳወቀ!
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል የተባለ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል።
አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩት አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር በዋሉበት የወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
ዕውቅና እና ገንዘብ ለማግኘት ብቻ በማሰብ ሚዲያዎችን ኃላፊነት በጎደለው አኳሃን እየተጠቀሙ በተለይ ወጣቱ ትውልድ በመልካም ሥነ ምግባር ተቀርጾ ሀገርን የሚጠቅሙ ተግባራትን እንዳያከናውንና በተቃራኒው በትውልዱ ላይ ርካሽ ባህል ለመጫን የሚደረገው ተግባር ለመከላከል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል።
@YeneTube @FikerAssefa
በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል በቀን ከ3 እስከ 4 ለወሲባዊና አካላዊ ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች አገልግሎት ያገኛሉ ተባለ
አሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ካለፉት አምስት ዓመታት አንስቶ ከክልሉ ሴቶች ጉዳይ ጋር በመተባበር እንዲሁም ዩኒሴፍ በሚያገኘዉ ድጋፍ የአንድ መስኮት አገልግሎት በማቋቋም አካላዊና ወሲባዊ ጥቃት ለሚደርስባቸዉ ሴቶችና ህፃናት የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታዉቋል ።
የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር መርቀኒ አወድ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት ሆስፒታሉ በቀን ወሲባዊና አካላዊ ጥቃት ለሚደርስባቸዉ ከ3 እስከ 4 ለሚሆኑ ሴቶችና ህፃናት የአንድ መስኮት አገልግሎት ይሰጣል ።
ባለፉት 4 ወራት ለችግሩ ተጋላጭ ለሆኑ 218 ሴቶችና ህፃናት አገልግሎት መሰጠቱን ገልፀዉ ፤ከዚህ ዉስጥ ስድስቱ ህፃናት ሲሆን የተቀሩት ከ18 ዓመት የዕድሜ ክልል በታችና በላይ የሆናቸዉ ናቸዉ ብለዋል ።
ይህ የአንድ መስኮት አገልግሎት በዉስጡ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ፣ጠቅላላ ሀኪም ፣ነርስ ፣የፖሊስ አካል ፣አቃቤ ህግና ሌሎችንም ያካተተ ሲሆን የመደፈር ጥቃት የደረሰባቸዉ ሴቶች የእርግዝናና የኤችአይቪ ምርመራ እንዲሁም ሌሎችንም ህክምናዎች እንዲያገኙ ከተደረገ በኃላ ወዲያዉኑ ጉዳያቸዉ በህግ ይታይላቸዋል ተብሏል ።
ይህም መጉላላትን በማስቀረት ዉሳኔዎች በፍጥነት እንዲሰጡ የሚኖረዉ ሚና ከፍተኛ ነዉ ያሉት ዳይሬክተሩ አልፎ አልፎ የግብረሰዶም ጥቃት የሚደርስባቸዉ ወንዶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸዉን ገልፀዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
🥁 65% /35%
🌬እንኳን ደስ አላችሁ💫💫💫
🌬 አሁን ቀደም ያመለጣችሁ ደንበኞቻችን ወርቃማ እድል በዲፕሎማቲክ መንደር በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ ለውስን ቤቶች ብቻ
🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ
🌬 65% ሲከፍሉ 35% እኛ ልዩ ቅናሽ አቅርበናል።
🏠 80 ካሬ ሜትር ባለ ሁለት መኝታ
🥁ሙሉ ክፍያ 5,770,050ብር
🏠139 ካሬ ሜትር ባለሶስት መኝታ
🥁ሙሉ ክፍያ 9,938,,000 ብር
✅ መገልገያዎች
👉 ሁለት ዘመናዊ የሰው እና አንድ የእቃ ሊፍቶች
👉 የመኪና ማቆሚያ ቦታ
👉 ቴራስ
👉 ያልተገደበ የውሃ አቅርቦት
👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር
👉 የደህንነት ካሜራ
👉ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ እና ኢንተርኮም ሲስተም
እንዲሁም
⛳️ ገላን ኮንደምንየም
🗣ሱቆች ከ23 ካሬሜትር ጀምሮ
በ500,000ብር ቅድመ ክፍያ እንዲሁም 2.3 ሚሊዬን ሙሉ ክፍያ ለውስን ሱቆች ብቻ እየሸጥን እንገኛለን።
🚴🏿♂️ይፍጠኑ🚴🏽♀️
🕹ለበለጠ መረጃ:- 0931835733
ይደውሉ! በwhatsapp ያገኙናል።
Telegram @momsra16
ይፍጠኑ🗣
"በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚተገበር የ30 በመቶ ግብር የለም!"
ከታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚተገበር የ30 በመቶ ግብር እንደማይኖር፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ገለጸ።
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር)፣ ከታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች ላይየ30 በመቶ ግብር ይጣላል የሚል መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር መቆየቱን፣ ነገር ግን ይህ መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል።
ገንዘብ ሚኒስቴርን ጨምሮ በጉዳዩ ላይ በየትኛውም የመንግሥት አካል የተሰጠ መግለጫ እንደሌለ ማረጋገጣቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይጣላል የተባለው ግብር በማኅበራዊ ሚዲያው ላይየተፈጠረ እንጂ፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣንም የሚያውቀው ከዚህ ወር ጀምሮ የሚጣል ምንም ዓይነት የግብር ጭማሪ እንደማይደረግና መንግሥትም ይህን የማድረግ ዕሳቤ እንደሌለው መሆኑን ተናግረዋል።
‹‹በሐሰተኛ መረጃ የተነሳ ኅብረተሰቡ ላልተገባ ሠልፍና እንግልት እየተዳረገ ይገኛል፤›› ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ያለ ምንም ይፋዊ የመንግሥት ውሳኔ ከወጣው የነዳጅ ዋጋ ውጪ ያለ አግባብ ጭማሪ የሚያደርጉ የነዳጅ አከፋፍይ ኩባንያዎችና ማደያዎች ተጠያቂ እንደሚደረጉም አሳስበዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ በመደበኛ ሁኔታ ነዳጅ እየቀረበ መሆኑን፣ ነገር ግን በዚህ ሐሰተኛ መረጃ ምክንያት ፍጆታ ላይ ጭማሪ መፍጠሩን ገልጸዋል። የተናፈሰው መረጃ ስህተት መሆኑን ለነዳጅ ኩባንያዎችና ማደያዎች በተደጋጋሚ እያሳወቁ መሆናቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ኩባንያዎች ባልተፈለገ መንገድ ተታለው ከጂቡቲ የተረከቡትን ነዳጅ ላልተገባ ጥቅም የማዋል ዕሳቤ እንዳይፈጠርባቸው በድጋሚ አሳስበዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ - ዳይናሚክ አክሲዮን ማህበር
የስራ ቦታ፡ የሽያጭ እና የግብይት ኃላፊዎች (ብዛት 20 )
አካባቢ፡ አዲስ አበባ
🔹 ቁልፍ ኃላፊነቶች
የኩባንያ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ማስተዋውቁ እና መሽምጥ።
የመስክ ግብይት እና የደንበኛ ክትትል ማካሄድ።
ሳምንታዊ እና ወርሃዊ የሽያጭ ግቦችን ማሳካት።
የዕለታዊ እንቅስቃሴ እና የገበያ ግብረመልስ ሪፖርቶችን ማቅረብ።
🔹 መስፈርቶች
በማርኬቲንግ፣ በቢዝነስ፣ በኢኮኖሚክስ ወይም ተዛማጅ መስኮች ዲፕሎማ ወይም ዲግሪ።
እጅግ በጣም ጥሩ የመግባቢያ እና የማሳመን ክህሎቶች።
በጫና ስር የመስራት እና የሽያጭ ግቦችን የማሳካት ችሎታ።
በሽያጭ ወይም በማርኬቲንግ ልምድ መኖሩ ተጨማሪ ነው (ግዴታ አይደለም።)
ሐቀኛ፣ ታታሪ እና የመስክ ስራ ለመስራት ፈቃደኛ።
🔹 የምናቀርበው ነገር
ወርሃዊ ደሞዝ + ማራኪ ኮሚሽን
የአፈጻጸም ጉርሻዎች
የስልጠና እና የሙያ እድገት እድሎች
📩 እንዴት ማመልከት እንደሚቻል (የTalentHub ብቻ)
ሁሉም አመልካቾች በTalentHub በኩል ብቻ ማመልከት አለባቸው።
https://talenthubethiopia.com/
📍 የቢሮ አድራሻ
Megenagna፣ Hibire ህንፃ፣ 3ኛ ፎቅ፣ የቢሮ ቁጥር 312፣ አዲስ አበባ
📅 የማመልከቻ ቀነ-ገደብ፡
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ።
የአሜሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያውያን ሲሰጥ የነበረውን ከለላ አቋረጠ!
የአሜሪካ መንግሥት ከሦስት ዓመት በፊት ኢትዮጵያውያን በጊዜያዊ የሕግ ጥበቃ በአገሪቱ ውስጥ እንዲኖሩ የፈቀደበትን አሠራር እንዲያበቃ አደረገ።የአሜሪካ መንግሥት ይህንን ጊዜያዊ የሕግ ጥበቃ መብት የሚሰጠው በአገራቸው ግጭት፣ የተፈጥሮ አደጋ ወይም ሌላ ለደኅንነታቸው አስጊ የሆነ የተለየ ክስተት ካለባቸው አገራት ለመጡ ስደተኞች ነው።
በዚህ የጥገኝነት መብት ውስጥ ተቀባይነት የሚያገኙ ስደተኞች በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እንዲሠሩ እና ከአገር እንዳይባረሩ የሚያደርግ ጊዜያዊ ከለላን ያገኛሉ።
ይህ በትግራይ የተካሄደውን ጦርነት ተከትሎ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ለኢትዮጵያውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ሲሰጥ የነበረው ጊዜያዊ የሕግ ጥበቃ አሁን በስደተኞች ላይ ጠንከር ያለ አቋም በሚያራምዱት በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር እንዲያበቃ ተደርጓል።ውሳኔው ይፋ የተደረገው የአሜሪካ የአገር ውስጥ ደኅነንት መሥሪያ ቤት ኃላፊ ክሪስቲ ኖም የመንግሥት ውሳኔዎች በሚወጡበት የፌደራል መንግሥቱ መድረክ ላይ ባወጡት ማስታወቂያ ነው።
"የአገሪቱን ሁኔታ በመመርመር እና ከሚመለከታቸው የአሜሪካ መንግሥት አካላት ጋር በመመካከር ኃላፊዋ ኢትዮጵያ ለጊዜያዊ የሕግ ጥበቃ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን የማታሟላ ናት የሚል ውሳኔ አሳልፈዋል" በማለት ውሳኔውን አሳውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/clyddz42p4vo
@YeneTube @FikerAssefa
🥁 65% /35%
🌬እንኳን ደስ አላችሁ💫💫💫
🌬 አሁን ቀደም ያመለጣችሁ ደንበኞቻችን ወርቃማ እድል በዲፕሎማቲክ መንደር በሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ ለውስን ቤቶች ብቻ
🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ
🌬 65% ሲከፍሉ 35% እኛ ልዩ ቅናሽ አቅርበናል።
🏠 80 ካሬ ሜትር ባለ ሁለት መኝታ
🥁ሙሉ ክፍያ 5,770,050ብር
🏠139 ካሬ ሜትር ባለሶስት መኝታ
🥁ሙሉ ክፍያ 9,938,,000 ብር
✅ መገልገያዎች
👉 ሁለት ዘመናዊ የሰው እና አንድ የእቃ ሊፍቶች
👉 የመኪና ማቆሚያ ቦታ
👉 ቴራስ
👉 ያልተገደበ የውሃ አቅርቦት
👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር
👉 የደህንነት ካሜራ
👉ኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ እና ኢንተርኮም ሲስተም
እንዲሁም
⛳️ ገላን ኮንደምንየም
🗣ሱቆች ከ23 ካሬሜትር ጀምሮ
በ500,000ብር ቅድመ ክፍያ እንዲሁም 2.3 ሚሊዬን ሙሉ ክፍያ ለውስን ሱቆች ብቻ እየሸጥን እንገኛለን።
🚴🏿♂️ይፍጠኑ🚴🏽♀️
🕹ለበለጠ መረጃ:- 0931835733
ይደውሉ! በwhatsapp ያገኙናል።
Telegram @momsra16
ይፍጠኑ🗣
አንቶኒዮ ጉተሬዝ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለአልጄርስ ስምምነት ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቀረቡ!
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የአልጀርስ የሰላም ስምምነት 25ኛ ዓመት ክብረ በዓሉ በተከናወነበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለስምምነቱ ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ዋና ፀሐፊው በቃል አቀባያቸው ስቴፋን ዱጃሪክ በኩል የሰጡት መግለጫ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት እንደገና ባየለበት ወቅት ነው።
ታህሳስ 3 ቀን 1993 ዓ.ም የተፈረመው የአልጀርስ ስምምነት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የነበረውን ደም አፋሳሽ ጦርነት በይፋ ያስቆመ ሲሆን፣ የድንበር ማካለል ዘዴዎችን ከመዘርጋቱ በተጨማሪ የሁለቱንም ሀገራት ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት አረጋግጧል።
ዋና ጸሐፊው ስምምነቱን ለሩብ ምዕተ ዓመት ያህል ሰላማዊ ግንኙነትን መሠረት ያደረገ “ወሳኝ ማዕቀፍ” በማለት ገልጸውታል።
ጉተሬዝ በተጨማሪም፣ ከሰባት ዓመታት በፊት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጋራ መግለጫ አማካኝነት ለሰላም የገቡትን ቁርጠኝነት ያደሱበትን ሁኔታ አስታውሰው፣ ይህም የውይይትና የትብብርን ዋጋ የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው ብለዋል።
ውጥረቱ እንደገና እየጨመረ ባለበት ወቅት፣ ዋና ጸሐፊው ሁለቱም አገራት በአልጀርስ ስምምነት ውስጥ የተካተተውን ዘላቂ ሰላምና የሉዓላዊነት እንዲሁም የግዛት አንድነት ራዕይ ዳግም እንዲያረጋግጡ የጠየቁ ሲሆን የትብብርና የመልካም ጉርብትና ግንኙነቶችን ለመገንባት የሚያደርጉትን ጥረት እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያና ኤርትራ “ለሁሉም በሚጠቅም” መልኩ የልማት ትብብርን ለመከተል ከቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ አጋሮች ጋር መሥራታቸውን እንዲቀጥሉ አበረታተዋል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
"ከኢትዮጵያ ተገንጥለን እንደ ኤርትራ ነጻ አገር እንፈልጋለን" ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው
ከኢትዮጵያ ተገንጥለን እንደ ኤርትራ ነጻ አገር እንፈልጋለን ሲሉ የትግራዩ ጀነራል ተናገሩ። ለአመታት በአዲስአበባ ታስረው የነበሩት የቀድሞው የሜቴክ ሀላፊ ጀኔራል ክንፈ ዳኘው አነጋጋሪ አስተያየት ሰጥተው ተከስተዋል። “የትግራይ ህዝብ ሁለት ምርጫዎች ከኢትዮጵያ ጋር ባርነት ወይስ እንደ ኤርትራ ነፃነት” ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ጀነራል ክንፈ ዳኘው የትግራይ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ይልቅ ከኤርትራ ነፃነት እንደሚያገኝ አዲስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል፡፡ ጀነራሉ ብራኸ ከተሰኘ የዩቱዩብ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ “የትግራይ ህዝብ ሁለት ምርጫዎች ከኢትዮጵያ ጋር ባርነት ወይስ ኤርትራ ነፃነት” ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ከእስር ከተፈቱ በኋላ አልፎ አልፎ አነጋገሪ ሀሳቦችን በመሰንዘር የሚታወቁት ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ ትግራይ ነፃ ሀገር መሆን አለባት የሚለውን አቋማቸውን ደግመውታል፡፡ እንደ ጀነራሉ እምነት ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ሆና መቀጠል የሚበጃት ስላልፎነ፣ በአነስተኛ መስዋዕትነት ሀገር መሆን አለባት ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ወደ ቅድመ ጦርነት ሁኔታ እየተመለሰች ያለችው ትግራይ የኢትዮጵያ መንግሥት ቁጥጥር ስር መግባት እንደሌለባትም ጀነራሉ ተናግረዋል፡፡ በትግራይ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ብቸኛ የግንኙነት የፕሪቶሪያ ስምምነት ነው ያሉት ሲሆን፣ ከዚያ ውጭ ምንም አይነት ማሰሪያ የለም ብለዋል፡፡
አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የትግራይ ኃይሎች ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አስተዳደር ይልቅ፣ ከኤርትራ ጋር መወዳጀት እንደሚሻለቸውም ጠቁመዋል፡፡ የትግራይ ኃይሎች ከኤርትራም ይሁን ከፋኖ ኃይሎች ጋር ስለሚኖራቸው ግንኙነት፣ ስልታዊ ወይስ ቋሚ የሚለውን ጉዳይ በግልጽ መበየን እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል፡፡
ትግራይ በአነስተኛ መስዋዕትነት ሀገር መሆን አለባት ብለው የሚያምኑት ጀነራሉ፣ የሚፈጸመውን በፖለቲካዊ ቁርጠንነትና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 መሰረት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የትግራይን ሀገርነት ለማደናቀፍ የሚንቃቀስ አካል ካለ ለመመከት ወይም ለኃይል አማራጭ ለመጨረስ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግም ጀነራሉ ገልጸዋል፡፡
ስለ አሁናዊ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የትግራይና ኤርትራ ውጥረት የተጠየቀት ጀነራሉ፣ ግጭት ከተቀሰቀሰ የውክልና ጦርነት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መንግሥት መካከል በባህር በር ጉዳይ ጦርነት የሚቀሰቀስ ከሆነ፣ ሌሎች ኃይሎችን በውክልና የሚያሳትፍ እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡
በቀጠናው የሚቀሰቀስ ጦርነት በባህሪው የውክልና ጦርነት ያሉት ጀነራሉ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ያነሳው የቀይ ባህር ጥያቄ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ፍላጎት ነው ሲሊም ያጣጥላሉ፡፡ ምንም እንኳን ጀነራሉ ጥያቄ የውክልና ጉዳይ ነው ቢሉም፣ ኢትዮጵያ መፍትሔ ያላገኘ ታሪካዊ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ እንደላት ይታወቃል፡፡
|
ጀነራሉ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ሊቀሰቀስ ይችላል ያሉት ጦርነት፣ ትግራይን የወጊያ ማዕከል ሊያደርግ እንደሚችለም ጠቁመዋል፡፡ ትግራይ የኤርትራ እና ኢትዮጵያ የውክልና ጦር ሜዳ እንዳትሆን ከወዲሁ ስልታዊ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም ጀነራሉ መክረዋል፡፡
ሁሉም ፖለቲካ ኃይሎች ትግራይን ወደ ሀገርነት ለማሸጋገር በጋራ መቆም እንዳለባቸው ጀነራሉ መክረዋል፡፡ የትግራይ ፖለቲካ ኃይሎች ጌታቸው ረዳን ጨምሮ በሕዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ነው ያሉትን የመገንጠል አጀንዳ እንደሚያቀነቅኑ ይታወቃል፡፡
Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
በቁጥጥር ስር ውለዋል ቲክቶከሮቹ
ከሀገራችን ባህልና ወግ ባፈነገጠ መልኩ የማህበራዊ ሚዲያን ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ከማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርም አንዱ የሆነውን ቲክቶክ በመጠቀም ከሀገራችን ባህልና ወግ ያፈነገጡ መልዕክቶችና ምስሎችን ሲያስተላልፉ የነበሩ ግለሠቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።
በቲክቶክ ስሙ Lil_jay ወይም ጎይጋር ኮት ውይዋል እና ከእርሱ ጋር ያልተገባ አፀያፊ ድርጊት ስትፈጽም የነበረችው ኸሊሌ ጊቦ አያና የተባሉ ግለሠቦች የቲክቶክ አካውንት በመጠቀም ለመልካም ጠባይና ስነ ምግባር ተቃራኒ የሆነ መልዕክትንና ተንቀሳቃሽ ምስልን በቀጥታ ሲያስተላልፉ በመገኘታቸው ታህሳስ 02 ቀን 2018 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ፍሊንትስቶን ሆምስ ከሚባል ቦታ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በተመሳሳይ ዜና በቲክቶክ ስሙ ፕሬዚዳንት ማሜ ወይም ባህሩዲን ሙሰማ ከሀገራችን ባህልና ወግ ያፈነገጡ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ቦሌ ሚካኤል ጃፋር መስጅድ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባራትና ትውልድን ለማነጽ መጠቀም ሲገባ ትውልድን ወደ አላስፈላጊ ድርጊት እንዲገባ የሚያስተምሩና የሚገፋፉ መሠል እኩይ ተግባራትን በሚፈጽሙ ግለሠቦችና ቡድኖች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል ።
@Yenetube @Fikerassefa
አይ ኤም ኤፍ እና ኢትዮጵያ በባለሙያዎች ደረጃ የተራዘመ የብድር አቅርቦት ስምምነት ላይ ደረሱ፣ ይህም ኢትዮጵያ 261 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንድታገኝ ያስችላታል ተብሏል!
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የአራት ዓመት የተራዘመ የብድር አቅርቦት ፕሮግራም አራተኛው ዙር ውይይት ማድረጉን ተከትሎ በባለሙያዎች ደረጃ ስምምነት ላይ መደረሱን አስታወቀ።
ስምምነቱ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አመራርና የቦርድ አስፈጻሚ አካል የመጨረሻውን ይሁንታ ካገኘ በኋላ ወደ 261 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለኢትዮጵያ እንዲለቀቅ ያስችላል ተብሏል።
አይ.ኤም.ኤፍ ይህን ያስታወቀው ትናንት ታኅሣሥ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ነው። ስምምነቱ የተደረሰው ከጥቅምት 20 - ህዳር 4/2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ የተካሄዱትን ውይይቶች ተከትሎ ሲሆን፣ ከህዳር 24- 26/2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በበይነ-መረብና በአካል በተደረጉ ተጨማሪ ስብሰባዎች ተጠናቋል።
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እንዳስታወቀው፣ ስምምነቱ ቀደም ሲል በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም የጸደቀው እና 3.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተመደበለት የተራዘመ የብድር አቅርቦት ፕሮግራም አካል ነው። ቀጣዩ ዙር ብድር ሲለቀቅ፣ ተቋሙ ከአጠቃላይ ብድሩ ውስጥ እስካሁን ለአገሪቱ የለቀቀው የገንዘብ መጠን 2.134 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይደርሳል።
የአይ.ኤም.ኤፍ ልዑክ መሪ የሆኑት አልቫሮ ፒሪስ፣ በቅርቡ የወጡ መረጃዎች “ከ2024 አጋማሽ ወዲህ የተፋጠነ ዕድገት” መኖሩን እንደሚያሳዩ ገልጸዋል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
እጅ የሰጡ የፋኖ ታጣቂዎች በአዲስአበባ
ሰሞኑን በቡድን ከነትጥቃቸው ሰላም ይሽለናል በማለት እጃቸውን ለመከላኪያ ሰራዊት የሰጡት የፋኖ አመራሮችና ታጣቂዎች በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ መግለጭ እየሰጡ እንደሚገኝ ታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
እግድ ከተጣለባቸው ዘጠኝ የ #ዶቼ_ቬለ ዘጋቢዎች መካከል የሰባቱ ሲነሳ ሁለት ጋዜጠኞች በዘላቂነት መታገዳቸውን ጣቢያው አስታወቀ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ኢትዮጵያ ከሚገኙት የዶይቸቬለ ዘጠኝ ዘጋቢዎች መካከል በሰባቱ ላይ የጣለውን እገዳ ማንሳቱን ጣቢያው አስታወቀ።
ሆኖም ጣቢያው ሁለቱ ሠራተኞቹ በዘለቂነት ከሥራ መታገዳቸውን ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን መስማቱን ገልፆ "እርምጃውን አጥብቆ አውግዟል"።
አያይዞም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ስህተት አለባቸው ያላቸው ዘገባዎች አልያም የኢትዮጵያ ሕግን የሚጥሱ የሚላቸውን ማስረጃ እንዲያቀርብ ዶይቸ ቬለ በድጋሚ መጠየቁን ከጣቢያው የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ከተለያዩ የኢትዮጵያ አከባቢዎች ለ #ዶቸ_ቬለ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች ዘገባ እንዳይሰሩ ጊዜያዊ እግድ የተጣለባቸው ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም ነበር።
ጣቢያው በወቅቱ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ "የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በፃፈዉ ደብዳቤዉ ዶቼ ቬለና ወኪሎቹን የኢትዮጵያን ሕግና ደንብ ጥሰዋል፣ ሙያዊ ሥነ-ምግባርን አያከብሩም በማለት ወቅሷል" ሲል ገልፆ ነበር።
የዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን (IFJ) በበኩሉ ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የዶይቼ ቬለ አማርኛ ዘጠኝ ጋዜጠኞች በጊዜያዊነት ማገዱን በጽኑ ማውገዙ ይታወሳል። ውሳኔውም በአስቸኳይ እንዲቀለበስ ጥሪ አቅርቦ ነበር።
ፌዴሬሽኑ ይህንን እርምጃ የዶይቼ ቬለን ዘገባ “ዝም ለማሰኘትና በተለይም በአማራ ክልል ውስጥ ስላለው ግጭት ኢትዮጵያውያን ገለልተኛ መረጃ እንዳያገኙ ለመገደብ የታሰበ የማስፈራሪያ ድርጊት ነው” ሲል በወቅቱ ማስታወቁ አይዘነጋም።
@Yenetube @Fikerassefa
የትራንስፖርት ታሪፍ
የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች የታሪፍ ጭማሪ እንዲደረግ ያቀረቡት ጥያቄ ተፈፃኒ ሳይሆን መቆየቱን ተናገሩ‼️
“በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሺያ ይደረጋል” የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር
በአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች፤ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከሦስት ጊዜ በላይ ጭማሪ ቢደረግም የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ሳይደረግ መቆየቱን አስታውቀዋል። የታሪፍ ማሻሺያ እንዲደረግላቸው ለትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እስካሁን ተግባራዊ አለመደረጉንም ገልጸዋል።
የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች የታሪፍ ማሻሺያ የተደረገላቸው የአንድ ሊትር ነዳጅ ዋጋ 80 ብር በሚሸጥበት ወቅት እንደነበር ኢቲዮቲዩብ ያነጋገራቸው የታክሲ አሽከርካሪዎች አስታውቀዋል። ሆኖም የነዳጅ ዋጋ ከሦስት ጊዜ በላይ ጭማሪ ያደረገ ቢሆንም የታሪፍ ማሻሺያው ግን ሳይስተካከል መቆየቱን ገልጸዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡን የታክሲ አሽከርካሪ እንደገለጹት ከሆነ “ ታሪፉን እንዲያስተካክሉልን የትራንስፖርት ሚኒስቴርን ጠይቀናል። የነዳጅ ዋጋ ሦስት ጊዜ ተሻሽሏል። [በሦስቱ ዙሮች] ከ 80 ብር ወደ 121 ብር ጨምሯል። በዚህ ጊዜ ምንም የታክሲ ታሪፍ ማሻሺያ አልተደረገም” በማለት አስረድተዋል።
ዛሬ ታኀሳስ 1/2018 ዓ.ም የነዳጅ ዋጋ በድጋሚ ተሻሽሎ ቀርቧል። ከ ቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ 121 ብር ሲሸጥ የነበረውን አንድ ሊትር ቤንዚን 8 ብር ከ 12 ሳንቲም ጨምሮ በ 129.12 ብር መሸጥ ጀምሯል። ነጭ ናፍጣ እና ኬሮሲንም በተመሳሳይ ዋጋ እንዲሸጡ መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ይፋ ካደረገው መረጃ ላይ ተመልክተናል።
በዚህ ሁኔታ የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ የትራንስፖርት ታሪፍ ሳይሻሻል መቅረቱ ጫና ውስጥ ከትቶናል የሚሉት ጣቢያችን ያነጋገራቸው የታክሲ ሾፌሮች “በጥቂት ሳምንታት አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ይፋ ይደረጋል ብንባልም ተግባራዊ አልተደረገልንም” ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ዴኤታ አቶ በሪኦ ሐሰን “መጥተው ይጠይቁ እኔ ጋር” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተውናል። ሆኖም ኢትዮቲዩብ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያገኙው መረጃ እንደሚያመላክተው በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንት ወስጥ ዐዲስ የትራንፖርት ታሪፍ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገንዝቧል።
@Yenetube @Fikerassefa
ሁሉም ሰው እየሸጠ ነው - እርሶስ?
ያገለገለ እቃዎትን ባሉበት ፎቶ አንስተው በመላክ ይሽጡ። መግዛት ከፈለጉ ደግሞ ያገለገሉ እቃዎችን ፎቶ ፣ አድራሻ ፣ ዋጋ እና የእቃውን ባለቤት ስልክ ቁጥር በ ET Creatives በቀላሉ ያገኛሉ
✅ JOIN 👉 /channel/ET_Creatives_Family
ET Creatives
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከባንክ ሥርዓት ጋር የማጣመር ሥራ በይፋ ተጀመረ
የፋይናንስ ዘርፍ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ ምዕራፍ የሆነው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ከባንክ ሥርዓት ጋር የማጣመር ሥራ በይፋ ተጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጉዳዩን አስመልክቶ ለፋና ዲጂታል የላከው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ አጀንዳ እና በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ 2030 ውስጥ አንዱና ዋናው አስቻይ ምሰሶ ሆኖ ተቀምጧል።
ለተለያዩ ዘርፎች አገልግሎትን ለመስጠት አስቻይ ሁኔታን መፍጠር፤ ተደራሽነትን ማረጋገጥ እና ለዲጂታል የህዝብ መሠረተ ልማት መሠረት በመጣል በኢትዮጵያ የዲጂታላይዜሽን ሒደት ዋነኛ አስቻይ እንዲሆን ተዘጋጅቷል፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፋይዳን መሰረት አድርጎ የሚሰጡ የፋይናንስ ዘርፍ አገልግሎቶችን የማቀናጀት ሀገራዊ ግብን ለማሳካት በትግበራው ላይ በሰፊው እየሰራ እንደሆነም ይታወቃል።
በዛሬው እለትም ለፋይናንስ ዘርፉ ወሳኝ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞን አንድ ርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ ፋይዳ ዲጂታል የማንነት መረጃ ከሁሉም ባንኮች የደንበኞች ባንክ ሂሳብ ቁጥር ጋር የማጣመር (harmonization) ስራን በዛሬው እለት በይፋ አስጀምሯል።
@Yenetube @Fikerassefa
የቀድሞው የአደጋ ስጋት ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በሙስና ወንጀል በ13 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ!
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቀድሞ ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በከባድ የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
የፍትሕ ሚኒስቴር ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ፣ አቶ ምትኩ ከሌሎች ተባባሪዎች ጋር በመሆን የተረጂዎችን ቁጥር በማጋነን ከ601 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴን ጨምሮ በርካታ የምግብ እርዳታ ቁሳቁሶችን ከመጋዘን በማውጣት ለተረጂዎች ሳይደርስ ለዱቄት ፋብሪካዎችና ለሌሎች በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉ አስረድቷል።
በተጨማሪም፣ ከ472 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ እንዲከፈል በማድረግ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰዋል።ፍርድ ቤቱ አቶ ምትኩ ካሳን በተጨማሪም፣ በሕገ ወጥ መንገድ ያገኙትን ገንዘብ ምንጩን ደብቀው ሕጋዊ አስመስለው በማቅረብ ወንጀል ከልጃቸው ወ/ሮ ሚልካ ምትኩ እና ከባለቤታቸው ወ/ሮ ሶፊያ ጀማል ጋር ተከሰው ጥፋተኛ መሆናቸውን ወስኗል።
በዚህም መሰረት፣ ባለቤታቸው ወ/ሮ ሶፊያ ጀማል የ8 ዓመት ከ4 ወር እስራት ሲፈረድባቸው፣ ልጃቸው ወ/ሮ ሚልካ ምትኩ ደግሞ የ5 ዓመት እስራት ተበይኖባቸዋል።
Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር የዓለም የነዳጅ ዋጋን መነሻ በማድረግ ከታህሳስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋን ነው ይፋ ያደረገው።
የአውሮፕላን፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ አና የከባድ ጥቁር ናፍጣ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ የሚቀጥል ሲሆን ፤ የቤንዚን፣ የነጭ ናፍጣ እና የኬሮሲን ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ግን ጭማሪ ተደርጎበታል።
- ቤንዚን 129.12 ብር በሊትር
- ነጭ ናፍጣ 129.12 ብር በሊትር
- ኬሮሲን 129.12 ብር በሊትር እንዲሸጡ ተወስኗል
@Yenetube @Fikerassefa
የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ፡፡
በሕንድ፣ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ጥበቃ ኮሚቴ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ያቀረበችው የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በሰው ልጅ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ዝርዝር ስር ተመዝግቧል።
"ጊፋታ" በወላይታ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ በዓል ሲሆን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የሕዝቡ የማንነት መገለጫ የሆነ የአሮጌው ዓመት ማብቂያና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ የመሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡
ጊፋታ እድሜ፣ ጾታ፣ ሃይማኖት ወይም ሌላ ማኅበራዊ ደረጃ ሳይለይ ለሁሉም ሠላም እና ማኅበራዊ ትሥሥር አስተዋጽኦ በማድረግ በዩኔስኮ የተለዩትን ዘርፎች ያካተተ ሁሉን አቀፍ ተግባራትን በማበረታታት የሚከበር በዓል መሆኑ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ አስችሎታል።
@YeneTube @FikerAssefa
"ዘለንስኪ ከአሜሪካ 350 ቢሊዮን ዶላር ወስዶ ከአገሩ መሬት 25 ፐርሰንቱን ያጣ ሰው ነው" ሲሉ ትራፕም ተናገሩ፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ከፖለቲኮ ጋር ሰፋ ያለ ቃለምልልስ አድርገዋል፡፡
በዚህ ቃለምልልስ ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል ፕሬዝደንት ዘለንስኪን የሚመለከተው ይገኝበታል፡፡ ትራምፕ በቃለምልልሳቸው ዘለንስኪን ከታዋቂው አሜሪካዊው ትርኢት አቅራቢና ነጋዴ ፒቲ ባርኑም ጋር አመሳስለዋቸዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹ዩክሬይን ኔቶ ውስጥ እንደማትገባ ከፑቲን በፊት መግባባት ላይ የተደረሰበት ጉዳይ ነው፡፡ እናም ዘለንስኪ መጀመሪያ ፑቲንን እንዳገኘው ሁለት ጥያቄዎችን አቀረበ፡፡ እነዚህም ክሬሚያ ይመለስልኝና ኔቶ ውስጥ መግባት እፈልጋለሁ የሚሉ ናቸው›› ብለዋል፡፡
ሲቀጥሉም ‹‹ነገር ግን ሁለቱንም ጥያቄዎቹን አግባብ ባለው መንገድ አልጠየቀም›› ያሉት ትራምፕ በዚህም ከአሜሪካዊው ትርኢት አቅራቢና ስራ ፈጣሪ ፒቲ ባርኑም ጋር እንደሚያመሳስላቸው አስታውቀዋል፡፡
አባባላቸውን ሲያብራሩም ‹‹ፒቲ ባርኑም የአለማችን እጅግ ምርጥ ሰው ነበረ፡፡ ምርቱን በማንኛውም ጊዜ የትም ቦታ መሸጥ የሚችል ሰው ነበር፡፡ ምንም ሆነ ምን በእጁ ላይ ያለውን እቃ እንደፈለገው አድርጎ የሚሸጥ ነበር፡፡ ያ ሁኔታ አሁን ያለፈ ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን ዘለንስኪ ከፕሬዝደንት ጆ ባይደን 350 ቢሊዮን ዶላር ቢወስድም ከአገሩ ግዛት ውስጥ ግን 25 ፐርሰንቱን አጥቷል፡፡ እውነታው ይህ ነው›› በማለት ገልፀዋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa