ልእልት ብራይዳል ሰርጋችሁን የሚያድምቁትን ቅሚሶች አስግብተን እየጠብቅናችሁ ነው።
አዳዲስ የሚገቡ ሰርጐትን የሚያሳምሩ ቀሚሶች ለማግኘት ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ
/channel/leeltbridal
Call us for early reservations
+251920017385
+251 97 899 5369
📍22 ከጐላጐል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ
ፀጋ የገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ C4A
የአፍሪካ አገር፣ ሚስጥራዊ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት ሆና እንደምታውቅ ስንቶቻችን እናውቃለን?
የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ከተፈጠረ 100 አመት ያልሞላው ቴክኖሎጂ ሲሆን እንደ ቦምቦቹ ብዛት ከከተሞች እስከሃገራት የሚደርስ ቦታን ማጥፋት የሚችል ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ ነው። አለም ላይ እስካሁን አስር ሃገራት የዚህ መሳሪያ ባለቤት መሆን ችለዋል ወይንም ችለው ነበር። እነዚህም ራሺያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ቻይና፣ ብሪታኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ህንድ፣ ፓኪስታን፣ እስራኤል፣ ሰሜን ኮሪያ እና በዚህ ቪዲዮ የምንመለከታት አፍሪካዊት ሀገር ናቸው። ይህንን ልዩ ዝግጅት ሊንኩን ተጭነው ይከታተሉት፤ መሰል ዝግጅቶችን በየጊዜው ለመከታተል ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
https://youtu.be/Va_GpklAY3I
የውጭ የሥራ ሥምሪት ኤጀንሲዎች 250 ሺሕ ዶላር ዋስትና እንዲያሲዙ የሚያስገድድ ሕግ ለፓርላማ ቀረበ!
ማንኛውም የውጭ የሥራ ሥምሪት ኤጀንሲ ከካፒታሉ በተጨማሪ ለሠራተኛው መብት፣ ክብርና ደኅንነት ዋስትና ማስከበሪያ የሚውል 250 ሺሕ ዶላር ዋስትና እንዲያሲዝ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ባካሄደው 36ኛ መደበኛ ስብሰባ የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ፣ ለሰው ሀብት ልማት ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ መርቷል፡፡
ረቂቅ አዋጁ ኤጀንሲዎች ከሚያስመዘግቡት ካፒታል በተጨማሪ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የባንክ ሒሳብ ተቀማጭ የሚሆን የዋስትና ገንዘብ እንደ ደረጃቸው ልዩነት እንዲያስቀምጡ የሚያስገድድ ሲሆን፣ በዚህም ደረጃ አንድ ፈቃድ ያለው ኤጀንሲ 250 ሺሕ ዶላር ዋስትና እንዲያስቀምጥ ይደነግጋል፡፡
ተጨማሪ : https://ethiopianreporter.com/142312/
@YeneTube @FikerAssefa
ልእልት ብራይዳል ሰርጋችሁን የሚያድምቁትን ቅሚሶች አስግብተን እየጠብቅናችሁ ነው።
አዳዲስ የሚገቡ ሰርጐትን የሚያሳምሩ ቀሚሶች ለማግኘት ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ
/channel/leeltbridal
Call us for early reservations
+251920017385
+251 97 899 5369
📍22 ከጐላጐል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ
ፀጋ የገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ C4A
የቴህራን ነዋሪዎች “ዋጋ ይከፍላሉ” ሲሉ የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ዛቱ
ኢራን ሌሊቱን በፈጸመችው ጥቃት አምስት ዜጎቿ ከተገደሉ እና በርካቶች ከቆሰሉ በኋላ ለጥቃቱ አጸፋ የኢራን ዋና ከተማ ነዋሪዎች “ዋጋ ይከፍላሉ” ሲሉ የእስራኤል የመለካከያ ሚኒስትር ሲሉ ዛቱ።
ሚኒስትሩ ኢዝራኤል ካትዝ “የኢራንን አቅም እያዳከመ ያለውን የእስራኤል ሠራዊት ከሚፈጽማቸው ጥቃቶች ለማደናቀፍ” የሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ አካባቢዎችን ዒላማ እያደረጉ ነው ሲሉ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ከስሰዋል።
የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር የኢራኑን የበላይ መሪ አያቶላ ኻሜኒን “ፈሪ ነፍሰ ገዳይ” እና “ጉረኛ አምባገነን” ሲሉ ተችተዋቸዋል።
አራተኛ ቀኑን በያዘው የእስራኤል እና የኢራን ድንበር ተሻጋሪ ግጭት በሁለቱም ወገን ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው እየተነገረ ሲሆን፣ ኢራን ሌሊቱን በእስራኤል ውስጥ ጥቃትን ፈጽማለች።
በተለያዩ የኢራን አካባቢዎች ላይ ጥቃቶችን እያደረሰች ያለችው የእስራኤል ሚኒስትር ሌሊቱን ለተፈጸመው ጥቃት “ሳይዘገይ” አጸፋ እንደምትመልስ ተናግረዋል።
Via BBC
@Yenetube @Fikerassefa
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 2 Sessions
We’re back with five expert-led sessions in Week 2 of our 14-part workshop series, continuing the dialogue between private sector professionals and code developers:
🏢 Building Facility Management
🧯 Fire Safety & OHS
🏗 Structural Design Fundamentals
🚿 Building Plumbing Systems
📐 Spatial Design in Buildings
📅 June 10, 12 & 14, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also, live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments
✨ Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.
📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
🔗 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.
Many thanks to our partners for making this possible!
#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #FireSafety #StructuralDesign #Plumbing #FacilityManagement #SpatialDesign
እየተወሳሰበ የመጣው የቀይ ባህር ጉዳይ
ከደቂቃዎች በፊት የኢራን ብሔራዊ ቴሌቪዥን በአወጣው መረጃ ኢራን ኢትዮጵያን በቀጥታ አደጋ ውስጥ ሊከት የሚችለውን እርምጃ ወስዳለሁ ስትል ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።
በዚህም መሰረት ኢራን "እስራኤልን እንዳላጠቃ ለመከላከል የሚሞክሩትን አሜሪካ ፣ዩኬ፣ የኢዩ ሀገራትን ወታደራዊ ጣቢያዎችንና መርከቦቻቸውን በቀጥታ ማጥቃት እጀምራለሁ" ስትል ይፋዊ መግለጫ የሰጠች ሲሆን ፤እንደሚታወቀው ሁሉም የተጠቀሱት ሀገራት የወታደራዊ ጣቢያና ባህር ሃይላቸው በአንድ ላይ ተከማችተው የሚገኙት እና የሚተላለፉባት የበሬ ግንባር የምታክለውና የ120 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ህልውና የኪራይ ወደባችን በሆነችው ጂቡቲ ነው።
ኢራን እንዳለችውምበ ጅቡቲ የሚገኘውን የአሜሪካ የጦር ቤዝ ለማጥቃት በቀጥታ የጦር ቀጠና ምታደርጋት ከሆነ ያለ አንዳች ጥርጥር ሀገራችን ከዚህ ቀድም ባህር በር በማጣታችን ስንፈራው የነበረውን ከባድ አደጋ ይዞ ይመጣል።
@Yenetube @Fikerassefa
እስራኤል ሌላ ዙር ጥቃት ፈፀመች።
በቴላቪቭ በርካታ ፍንዳታዎችን እና ውድመትን ያስከተለው ጥቃት በኢራን ላይ መፈፀሟ ተነገረ።
በቴህራን የኢራን መንግስት ቲቪ እንደዘገበው ከሆነ ዛሬ አመሻሹ ላይ እስራኤል ከ150 በላይ ቦታዎች ላይ ጥቃት መፈፀሟን እና በተፈፀመው ጥቃትም በኢራን ደቡባዊ ቡሻህር ግዛት ውስጥ ከጋዝ ማውጫ ጨምሮ በርካታ ቦታዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የገለፀ ሲሆን በጥቂቱም 20 ህጻናትን ጨምሮ ወደ 60 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን እና በመላ ሀገሪቱ ተጨማሪ ጥቃቶች መፈፀሙን ተዘግቧል።
@Yenetube @Fikerassefa
የደብረፂዮን ላፕቶፕ ጉዳይ
የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ላፕቶፕ ኮምፒተርን " ሰርቀዋል " ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት በዋስ እንዲፈቱ ቢወስንም አልተተገበረም።
6 የVIP የጥበቃ አባላት የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚከካኤል (ዶ/ር) ላፕቶፕ ኮምፒተርን " ሰርቀዋል " በመባል ተከሰዋል።
የመቐለ ዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ ፍርድ ቤት ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሊቀመንበሩ ላፕቶፕ ኮምፒተር ስርቆት የተጠረጠሩት ግለሰቦች በዋስ እንዲፈቱ ወስኗል።
ስድስቱ ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ በሰጠው ውሳኔ መሰረት ቤተሰቦቻቸው ብር ቢያስይዙም " ከላይ የመጣ ትእዛዝ " በሚል ከእስር አልተለቀቁም ብለዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ ምርጫ ቦርድ “ነጻና ገለልተኛ” ሆኖ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫው ለማስፈጸም “አንዳችም አስቻይ ሁኔታ የለም” አለ!
የስድስት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያካተተው የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “ነጻና ገለልተኛ ሆኖ” 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫው ለማስፈጸም “አንዳችም አስቻይ ሁኔታ የለም” ሲል ገለጸ።ኮከሱ፤ ሰኔ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ የምርጫ ቦርድን “በወገኝተኝነት” እና “ለገዢው ፓርቲ በታዛዥነት” ከሷል። በዚህም "የገዢው ፓርቲ አሸናፊነት አስቀድሞ የሚታወቅ ነው" ብሏል።
መግለጫው፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከነባር አመራሮቹ “ሶሰቱን (60 በመቶ) ለመቀየር ጫፍ መድረሱን እያሳወቀን ነው” ብሏል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ፤ “ልምድ በሌላችው ኮሚሽነሮችና በወቅታዊው የፖለቲካ ያለመረጋጋት፣ የግጭትና ጦርነት ውጥረትና ሁለንተናዊ ውስብስብ ተጨባጭ ሁኔታ” ውስጥ የሚደረግ ምርጫ “ጣጣና መዘዙ” እንደሚያስከትሉ አስጠንቅቋል።በመሆኑም በዚህ ተጨባጭ እውነታ ምርጫ ቦርድ "ነጻና ገለልተኛ" ሆኖ ምርጫውን ለማስፈጸም "አንዳችም አስቻይ ሁኔታ የለም" ያለው ኮከሱ፤ “ጉዳዩ ወደከፋ አደጋና ትርምስ እንዳንገባ በእጅጉ የሚያሳስብና የሚያሰጋ ነው” ሲል በአጽንዕኦት ገልጿል።
ኮከስ ከምርጫ ቦርድ በተጨማሪ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይም ትችት ሰንዝሯል። በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የቀረቡ የማሻሻያ ኃሣቦችና የተነሱ ጥያቄዎች “ቦታ ሳይሰጣቸው”፣ እንዲሁም የኮሚሽነሮች ሹመት “የብልጽግናውን አዋጅ እንኳ ያልተከተለና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍላጎትና ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነው” ብሏል።በመሆኑ የተሰጠውን ከፍተኛ ተግባርና ኃላፊነት “በህግ፣ በዕውቀትና እውነት በነጻነትና ገለልተኝነት በሚዛናዊነት ከአገራዊ ተልዕኮው አንጻር ለመፈጸም ይቸገራል” ሲል ገልጿል።
በተጨማሪም ኮሚሽኑ ከምስረታው ጀምሮ ኮሚሽኑ ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎችና ባከናወናቸው ተግባራት ኮከሱ ያነሳቸውን ችግሮች የሚያረጋግጡ አፈጻጸሞች፣ በተለይም የኮከሱን “የመፍትሄ ኃሳቦች ከመቀበል ይልቅ እንደተጻራሪና ተቃዋሚው በማየት ሲያገለኝ ቆይቷል” በማለት ከሷል፡፡አክሎም፤ “በያዘው አግላይ አካሄድ ቀጥሎ”፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ሥራውን “ሊያጠናቅቅ ቀርቶ አጀንዳ አሰባስቦ ባለመጨረሱ” የአንድ ዓመት ተጨማሪ ዕድሜ ተሰጥቶታል ሲል ተችቷል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
#ቴምር ሪልስቴት
⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች
‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
👉1 መኝታ 66ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
👉2መኝታ 71ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 745,500ብር
ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
👉2መኝታ 93ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 976,500ብር
ሙሉ ክፍያ 9,765,000ብር
👉3መኝታ 130ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው የሚጨርሱት
👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
/channel/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
ኢራን ዛሬ ከመሸ በኋላ በሁለት ዙር በቴልአቪቭ በ7 ቦታዎች ላይ የሚሳኤል ጥቃት ፈፅማለች።
በጥቃቱ የተነሳ የእስራኤል ዋና የጦር ማዘዣ አካባቢ እሳት መታየቱ ተዘግቧል።
Source: BBC
@Yenetube
አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ ቁጥጥር ስር ዋለ
ሲዳማ ክልል ሰላም እና ጸጥታው ቢሮ ሃላፊነት ላለፉት ሳባት አመታት በመምራት ያሳለፈዉ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ፤ ትናንትና ለፎርማልቲ የክልሉ ምክርቤት መንግስት ፍንቀላ እና በከፍተኛ ሙስና ወንጀል ማስረጃ በማቅረብ ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ይታወሳል።
@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው 100 ኪሎ ዋት ኃይል የሚያመነጭ የሶላር ፕሮጀክት ተመረቀ!
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው የተባለ100 ኪሎ ዋት ኃይል የሚያመነጭ የሶላር ፕሮጀክትን የውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር አስመረቀ።የሶላር ፕሮጀክቱ 200 ሺህ ዶላር ወጪ እንደተደረገበት እና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ መገንባቱ ተገልጿል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፤ እንደ ሀገር በዚህ ደረጃ ሀይል የማመንጨት አቅም ያለው የሶላር ፕሮጀክት አለመኖሩን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አለው ያሉት ፕሮጀክቱ 100 ኪሎ ዋት የሚያመርት መሆኑ የመጀመሪያው ያደርገዋል ብለዋል።ከሚመነጨው ኃይል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚፈልገውን ተጠቅሞ ስራ በማይኖር ጊዜ የተመረተውን ሀይል ወደ ብሔራዊ ግሪድ ማስገባት መቻሉ ፕሮጀክቱን ልዩ ያደርገዋል ሲል ገልጸዋል።
ሀብታሙ ኢተፋ፤ ፕሮጀክቱ ሌሎች ተቋማት በግቢያቸው ያለውን ቦታ ለዚህ ዓላማ ማዋል እንደሚቻል ትምህርት እንደሚሰጥ ጠቅሰው፤ በቀጣይ የሶላር ሀይልን በስፋት ለማምረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 2 Sessions
We’re back with five expert-led sessions in Week 2 of our 14-part workshop series, continuing the dialogue between private sector professionals and code developers:
🏢 Building Facility Management
🧯 Fire Safety & OHS
🏗 Structural Design Fundamentals
🚿 Building Plumbing Systems
📐 Spatial Design in Buildings
📅 June 10, 12 & 14, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also, live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments
✨ Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.
📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
🔗 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.
Many thanks to our partners for making this possible!
#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #FireSafety #StructuralDesign #Plumbing #FacilityManagement #SpatialDesign
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 3 Sessions
We’re continuing our 14-part expert-led workshop series with four important sessions in Week 3:
🧱 Geotechnical Properties & Structures
🌍 Seismic Design & Earthquake Resistance
🏗 Steel & Composite Structures
🪟 Aluminum & Glass Design
📅 June 17, 19, & 21, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also streaming live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments
✨ Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.
📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
📩 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.
A big thank you to all our partners for making this series possible!
#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #Geotech #SeismicDesign #StructuralEngineering #FacadeDesign
ዩኒሊቨር በአዲሱ የኢንቨስትመንት ህግ ቀዳሚ የአስመጪነት ፈቀድ የወሰደ የውጭ ኩባንያ ሆነ!
በፍጆታ እቃ ምርት ስሙ በአለም የገነነው የብሪታኒያ–ደች ኩባንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ አገራት ውስጥ የምርት ማእከል ያለው መሆኑ ይታወቃል።መንግስት እያላላ ባለው የኢንቨስትመንት ህግ መሰረት ኩባንያው በአስመጪነት ቢዝነስ ለመሰማራት ፈቃድ እንዲወስድ አስችሎታል።
ቀደም ሲል በነበረው ህግ በአገር ውስጥ አስመጪዎች ብቻ መግባት ይፈቀዱ የነበሩ ምርቶቹን እራሱ ማስገባት እንደሚጀምር የገለፀው ዩኒሊቨር የተለያዩ ቫዝሊን ምርቶቹን በማስገባት በአከፋፋዮቹ በኩል በቅርቡ ለገበያ እንደሚያቀርብም ነው ለፎርቹን ያስታወቅ።
የውጭ ኢንቨስተሮችን እንቅስቃሴ በማስፋት ኩባንየዎች በጅምላ፣ ችርቻሮ አስመጪ እና ላኪ ንግድ ውስጥ እንዲገቡ መንግስት ህጎቹን እያላላ መሆኑ ይታወሳል።ይህም የአለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል የሚረዳ መሆኑ ይታወቃል።
Via KGEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእስራኤል እና ኢራን ጦርነት የተነሳ ከአዲስአበባ ወደ ቴላቪቭ የሚያደርገዉን በረራ አቋረጠ!የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእስራኤል እና ኢራን ጦርነት የተነሳ ከአዲስአበባ ወደ ቴላቪቭ የሚያደርገዉን በረራ
ማቋረጡን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ እና በቴልአቪቭ መካከል በሁለቱም አቅጣጫ የሚደረጉ በረራዎች በአዉሮፓዉያን አቆጣጠር እስከ ሰኔ 22 ቀን 2025 ድረስ መቋረጣቸውን ባወጣዉ መግለጫ አሳዉቋል።
አየርመንገዱ ለተፈጠረዉ ችግር ይቅርታ ጠይቆ ደምበኞቹ የቲኬት መሸጫ ቢሮዎቹን እንዲያናግሩ መክሯል። አየርመንገዱ በረራዉን መቼ እንደሚጀምር እና አዲስ መረጃዎችን እንደሚያሳዉቅ ጠቅሷል።
እስራኤል እና ኢራን መጠነ ሰፊ ጦርነት ከጀመሩ ቀናት ተቆጥረዋል።እስካሁንም በሁለቱም ወገን የሰዉ ህይወትና ንብረት ላይ ትልቅ ጉዳት ደርሷል።
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስአበባ እና በስድስት ክልሎች የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ መከሰቱን ሪፖርት ገለፀ!
ኢንተርናሽናል ሜዲካል ኮርፕስ (IMC) በአዲስ አበባ እና በስድስት ክልሎች የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ(ኤምፖክስ) መከሰቱን አስታወቀ። ኢንተርናሽናል ሜዲካል ኮርፕስ ባሳለፍነው ሳምንት ሰኔ 6 ወን ባወጣው ሪፖርት፤ እስከ ሰኔ 3 ቀን በ አዲስ አበባ ከተማ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ሲዳማ፣ ሀረሪ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች 18 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው መረጋገጡን ገልጾ፤ የአንድ ሰው ይህወት ማለፉን አስታውቋል። ይህም የሞት መጠኑን ወደ 5.6 በመቶ ከፍ ያደርገዋል ብሏል።
በሽታው መጀመሪያ የተገኘው በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ የ27 ቀን ሕፃን ልጅ ላይ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር እና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ግንቦት 17 ቀን በጋራ አስታውቀዋል።ባሳለፍነው ሳምንትም በአማራ ክልል በመተማ እና ባሕርዳር ከተሞች በዝንጀሮ ፈንጣጣ (ኤምፖክስ) በሽታ የተያዙ ሁለት ሰዎች መገኘታቸውን የክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጿል።
በሽታው በመተማ አንድ ሰው እንዲሁም በባሕርዳር አንድ ሰው አጠቃላይ በሁለት ሰዎች ላይ የተገኘ ቢሆንም በሽተኞች በወቅቱ ተገቢውን ሕክምና አግኝተው በማገገም ላይ መሆናቸውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ36 አገራት ዜጎች ላይ የጉዞ ዕገዳ ልትጥል ነው!
የትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያን ግበፅ እና ናይጄሪያን ጨምሮ የ36 አገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ለማገድ ሃሳብ እንዳለው ሮይተርስ እና ዋሽንግተን ፖስት የተመለከቱት የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጣዊ ሰነድ አመለከተ።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ የተፈረመው ለዲፕሎማቶች የተዘጋጀው ሰነድ ላይ በቀጣይ ዜጎቻቸው ላይ ዕገዳ ሊጣልባቸው የታሰቡት 36 አገራት ዝርዝር የሰፈረ ሲሆን፣ አገራቱ ከዕገዳው ለመውጣት ማከናወን የሚጠበቁባቸው ማስተካከያዎችም ተካተውበታል።
ሰነዱ ዜጎቻቸው ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ሙሉ ወይም ከፊል ዕገዳ የሚጣልባቸው አገራት በመለየት ያሉባቸውን ችግሮች በማስቀመጥ፤ ይህ ዕገዳ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት አገራቱ የሚጠበቅባቸውን መመዘኛዎች እና ማስተካከያዎችን እንዲያደርጉ የሁለት ወራት ጊዜ እንደሚሰጣቸው ተጠቅሷል።
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ለሚመለከታቸው ዲፕሎማቶች የተሠራጨው ሰነድ "[የውጭ ጉዳይ] መሥሪያ ቤቱ የተቀመጡ መመዘኛዎች እና ግዴታዎችን በ60 ቀናት የማያሟሉ ከሆነ ሙሉ ወይም ከፊል የጉዞ ዕገዳ የሚጣልባቸውን አሳሳቢ የሆኑ 36 አገራትን ለይቷል" ማለቱን ሮይተርስ አመልክቷል።
ባለፈው ግንቦት ኤርትራ፣ ሱዳን እና ሶማሊያን ጨምሮ ሰባት የአፍሪካ አገራት ባሉባቸው 12 አገራት ላይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአገራቸውን እና የሕዝባቸውን ደኅንነት ለመጠበቅ በሚል ትዕዛዝ ፈርመው ተግባራዊ መሆኑ ይታወሳል።
(ቢቢሲ)
@YeneTube @FikerAssefa
#ቴምር ሪልስቴት
⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች
‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
👉1 መኝታ 66ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
👉2መኝታ 71ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 745,500ብር
ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
👉2መኝታ 93ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 976,500ብር
ሙሉ ክፍያ 9,765,000ብር
👉3መኝታ 130ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው የሚጨርሱት
👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
/channel/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
ኢራን አሜሪካን ኢላማ ካደረገች መዘዙ እንደሚከፋ የአሜሪካ ባለስልጣን አስጠነቀቀቁ
አሜሪካ ይህንን ያለችው ኢራን፤ አሜሪካ፣ ፈረንሳይ እና ዩኬ እስራኤልን የሚረዱ ከሆነ አጸፋውን እንደምትመልስ ማስጠንቀቋን ተከትሎ ነው።
እስራኤል በኢራን ላይ የፈጸመችውን ጥቃት በተመለከተ ከጥቃቱ በፊት አሜሪካ “ምክር ተጠይቃ” በምላሹ “ራሷን ለመከላከል መሰረታዊ ነው” የሚል ምላሽ እንደተሰጣት የአሜሪካ ባለስልጣን ተናግረዋል ።
“አሜሪካ ስለ ጥቃቱ ቀድሞ ቢነገራትም በነዚህ ጥቃቶች ላይ ወታደራዊ ተሳትፎ አልነበራትም” ሲሉ የአገሪቱ የአለም አቀፍ ድርጅት ጉዳዮች ቢሮ ከፍተኛ ባለስልጣን ማኮይ ፒት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ተናግረዋል።
"ዋነኛው ቅድሚያ የምንሰጠው በቀጣናው ውስጥ ያሉ የአሜሪካ ዜጎች፣ ሰራተኞች እና ኃይሎችን ጥበቃ ነው።" ብለዋል።
ኢራን በቀጣናው ያሉ የአሜሪካ ዜጎች፣ የጦር ሰፈሮችን ወይም መሰረተ ልማቶችን ዒላማ ካደረገች “የሚከተላት መዘዝ አስከፊ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
የአሜሪካ አቋም ኢራን ስምምነት ማድረግ አለባት የሚል እንደሆኑ ገልጸው አገራቸው “ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ” ትሻለች ብለዋል።
“የኢራን አመራሮች በዚህ ወቅት መደራደራቸው ብልህነት ነው” ብለዋል።
ኢራን በእስራኤል ላይ እየወሰደች ያለችን አጸፋዊ እርምጃ ለማስቆም አሜሪካ፣ ፈረንሳይ እና ዩናይትድ ኪንግደም እስራኤልን የሚረዱ ከሆነ ምላሹን እንደምትሰጥ ማስጠንቀቋን የኢራን መንግሥታዊ ሚዲያ ዘግቧል።
ሶስቱ አገራት ለእስራኤል ድጋፋቸውን ከሰጡ ኢራን በቀጣናው የሚገኙ የጦር ሰፈሮቻቸውን እና መርከቦችን ኢላማ እንደምታደርግ ዘገባዎች ወጥተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
“እኔ በሕይወት እያለሁ መምህራን መኪና ኖሯቸው ከማየት በላይ የሚያስደስተኝ ነገር የለም”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የመምህራን ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ የመምህራን ጥያቄዎች ሌሎችንም አካታች በሆነ ማዕቀፍ ሊታዩ የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የመጀመሪያው ሀገር ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን እንዳለበት ጠቅሰው፤ ከዚያ ውጭ የሚቀርበው ንጽጽር ግን ኢትዮጵያ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ ጋር ስለማይሄድ ዋጋ የለውም ብለዋል።
ነጻ ሕክምና፣ ነጻ ትምህርት፣ መኖሪያ ቤት የመሳሰሉት ጥያቄዎች ሲጠየቁ የወታደሩን፣ የሐኪሙን እና የሌላውንም ደምሮ ማየት እንደሚያስፈልገ አመላክተዋል።
"እኔ በሕይወት እያለሁ መምህራን መኪና ኖሯቸው፣ መኪናቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤታቸው በር ላይ አቁመው ሲያስተምሩ ከማየት በላይ ለኔ ደስታ የለም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ውስጥ ውስጡን እየተሠሩ ያሉት ሥራዎች ሲሳኩ የመምህራን ጥያቄዎች ምላሽ ያገኛሉ ብለዋል።
የመምህራን ጥያቄ በደመወዝ ጭማሪ ብቻ የማይመለስ መሆኑን አንስተው፣ የደመወዝ ጭማሪው ላይ ብቻ ትኩረት ከተደረገ ያለችው ተበልታ ታልቃለች በማለት የሚከተለውን መዛባት ጠቁመዋል።
ያለችውን በልቶ ከመጨረስ በራስ ላይ ጨክኖ ገበታን ማስፋት፤ ለዚህ ደግሞ ምርትን ማብዛት አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።
የመምህራን ጥያቄ ከሌሎች ጥያቄዎች ጋር ታይቶ ነገን ታሳቢ ባደረገ መልኩ መመለስ እንደሚቻል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
በለሚ ታደሰ
@Yenetube @Fikerassefa
"በኢራን የኒውክሌር መሰረተ ልማቶች ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰም"፦ የኢራን አቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ቃል አቀባይ
ከዓርብ ሌሊት ጀምሮ እስካሁን በቀጠለው የኢራንና የእስራኤል ግጭት በሁለቱም በኩል ጉዳት ደርሷል።
እስካሁን ይፋ የሆኑ አሀዞች እንደሚያመለክቱት እስራኤል በኢራን የተለያዩ ከተሞች ላይ ባደረገችው የቦንብ ድብደባ 320 ኢራናውያን ሲቆስሉ፤ ቁልፍ የሆኑ ወታደራዊ መሪዎችና አቶሚክ ሳይንቲስቶችን ጨምሮ 78 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።
በእስራኤል ወገን ደግሞ 3 ሰዎች መሞታቸውንና አርባ የሚሆኑ ቆስለው በሆስፒታል እንደሚገኙ እየተዘገበ ነው።
ጥቃትና አጸፋውን ተከትሎ የኢራን አቶሚክ ኢነርጂ ቃል አቀባይ ቤህሩዝ ካማልቫንዲ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም እስራኤል በናታንዝ፣ ፎርዶ እና ኢስፋሃን አቶሚክ ጣቢያዎች ላይ በፈፀመችው ድብደባ በኒውክሊየር ጣቢያዎቹ ላይ ከደረሰው መጠነኛ ጉዳት ውጭ በኒውክሊየር መሰረተ ልማት ላይ የደረሰ ምንም ዓይነት ጉዳት የለም ሲሉ ተናግረዋል።
ካማልቫንዲ አያይዘውም፥ ኢራን ቀደም ሲል በነበራት መረጃ በኒውክሊየር መሰረተ ልማቷ ላይ ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል በመገመት አብዛኛውን ወሳኝ ቁስ አስተማማኝ ወደሆነ ቦታ አዛውራለች ብለዋል።
በመሆኑም በኢራን አቶሚክ መሰረተ ልማት ላይ የደረሰ ጉዳት ምንም ዓይነት ጉዳት የለም ሲሉ መናገራቸውን የኢራን መንግስት ዜና አገልግሎት ኢርና ዘግቧል።
@Yenetube @Fikerassefa
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 2 Sessions
We’re back with five expert-led sessions in Week 2 of our 14-part workshop series, continuing the dialogue between private sector professionals and code developers:
🏢 Building Facility Management
🧯 Fire Safety & OHS
🏗 Structural Design Fundamentals
🚿 Building Plumbing Systems
📐 Spatial Design in Buildings
📅 June 10, 12 & 14, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also, live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments
✨ Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.
📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
🔗 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.
Many thanks to our partners for making this possible!
#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #FireSafety #StructuralDesign #Plumbing #FacilityManagement #SpatialDesign
አሜሪካ የኢራን ሚሳኤሎችን በማምከን መሳተፏ ተገለፀ
የአሜሪካ ጦር ወደ እስራኤል ያቀኑትን የኢራን ሚሳኤሎችን ለመምታት ረድቷል ሲሉ ሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናት ለሮይተርስ ተናግረዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት ባለስልጣናቱ፣ ተዋጊ ጄቶች ወይም የጦር መርከቦች በመጠቀም የመከላከል ሥራውን ስለመፈጸማቸው ጨምሮ ተጨማሪ መረጃ አልሰጡም።
@Yenetube @Fikerassefa
እስራኤል አዲስ ጥቃት መፈፀሟ ተነገረ !
የእስራኤል አየር ሃይል አመሻሹ ላይ በኢራን መአከላዊ ክፍል በመዝለቅ ጥቃት መፈፀሙን አስታወቀ ።
የእስራኤል የስለላ ድርጅት እንደገለፀዉ ከሆነ አመሻሹ ላይ የፈፀመዉ ጥቃት የኢራንን የጸጥታ ተቋም ልብ ውስጥ ዘልቆ በመግባት ከኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ጋር ግንኙነት ያላቸውን ቦታዎች ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን የአየር መከላከያ እና የባለስቲክ ሚሳኤል ማዕከላትን ኢላማዎች መምታቱን ገልጿል ።
የእስራኤል ፕሬዘዳንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "ለኢራን ህዝብ ምንም ነገር እንደሌለን በቀጥታ እየነገርኳቸው ነው። እየተሰቃዩ መሆናቸውን እናውቃለን። የሚኖሩበትን ሁኔታ አይተናል… ትግላችን ከኢራን ህዝብ ጋር አይደለም ። ጥቃቱ የተካሄደው (ቦታው) ሰዎች በጎዳና ላይ በማይገኙበት ጊዜ ነው ፣ እናም በሲቪሎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የተቻለንን ሁሉ አድርገናል" ብለዋል ።
ጥቃቱን በተመለከተ ከቴህራን በኩል በተገኘ መረጃ በተራራ ውስጥ በጥልቀት የተገነባው ፎርዶ የኑክሌያር ማብሊያ ጣቢያ ጨምሮ በርካታ ሰዉ የሚኖርባቸዉ አካባቢዎች በቦንብ መደብደቡን በጥቃቱ 78 ሰዎች መሞታቸውን እና ከሟቾቹ መካከል ህጻናትን ጨምሮ ሲቪሎች እንደሚገኙበት የኢራን መንግስት ቲቪ ገልጿል ።
አንድ የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ሶማሊላንድ እንደሀገር እውቅና እንድታገኝ ሐሳብ አቀረቡ!
የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ስኮት ፔሪ ዛሬ የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ የነጻነት ህግን አስተዋውቀዋል። ይህም ሶማሊላንድን ከሶማሊያ ተነጥላ ነጻ ሀገር እንድትሆን በይፋ እውቅና ለመስጠት ያለመ ደፋር እርምጃ ነው። ዛሬ ላይ ይፋ የሆነው ይህ ምክረ ሃሳብ፣ ሶማሊላንድ ለ30 ዓመታት ያስመዘገበችውን የራስ ገዝ አስተዳደር፣ መረጋጋት እና ዲሞክራሲያዊ እድገት የሚያደንቅ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የ2001 ህገ መንግስቷ እና ነጻ ምርጫዎችን ማድረጓን ያነሳል።
@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በስድስተኛው ቀን ከእስር ተፈታ!
የ'ኢትዮጵያ ኢንሳይደር' የበይነመረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ወልደየስ ከእስር መፈታቱን ጠበቃው አቶ ቤተማርያም አለማየሁ ለቢቢሲ ተናገሩ።ተስፋለም ከእስር የተፈታው ዛሬ አርብ፣ ሰኔ 6/2017 ዓ.ም እስጢፋኖስ አካባቢ ከሚገኘው የፖሊስ መምሪያ መሆኑን ቤተማሪያም ገልጸዋል።
ባለፈው ማክሰኞ ሰኔ 3/ 2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ የቄርቆስ ምድብ ችሎት በ15 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ወስኖ ነበር። ሆኖም ፖሊስ ለአዲስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቤቱታ በማቅረቡ ሳይፈታ ቀርቷል።ይግባኝ ሰሚ ችሎት ሰኔ 4/ 2017 ዓ.ም. ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ የፖሊስን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማጽናት ጋዜጠኛው የዋስትና መብቱ እንዲጠበቅለት በድጋሚ በይኗል።
ነገር ግን ፖሊስ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔን በመቃወም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰበር ሰሚ ችሎት በድጋሜ አቤቱታ አቅርቧል።ሰበር ሰሚ ችሎቱ ትላንት ሐሙስ የፖሊስ ይግባኝ አቤቱታ "አያስቀርብም" በሚል መወሰኑን የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ባለቤት ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
#ቴምር ሪልስቴት
⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች
‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
👉1 መኝታ 66ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
👉2መኝታ 71ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 745,500ብር
ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
👉2መኝታ 93ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 976,500ብር
ሙሉ ክፍያ 9,765,000ብር
👉3መኝታ 130ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው የሚጨርሱት
👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
/channel/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177