yenetube | Unsorted

Telegram-канал yenetube - YeneTube

122182

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Subscribe to a channel

YeneTube

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ደህንነት ለመጠበቅ ያስችላል የተባለ ስምምነት ተፈረመ!

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል ስምምነት ከፌደራል ፖሊስ ጋር መፈራረሙን አስታወቀ።የፌደራል ፖሊስ ለባቡር ትራንስፖርት ደህንነት ትኩረት በመስጠት ራሱን የቻለ መምሪያ በማቋቋም የጥበቃ ስራ እንደሚሰራ አመላክቷል።የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ/ማ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር በጋራ ለመስራት የተፈራረሙት ስምምነት ሁለቱ ተቋማት ያላቸውን አቅም አቀናጅቶ በመጠቀም ውጤታማ የሆነ የጥበቃ ሥራ ለመስራት እንደሚያስችል ተገልጿል።

የፌደራል ፖሊስ ከተሰጠው ተልዕኮ ውስጥ አንዱ የሀገሪቱን መሰረታዊ ተቋማትን መጠበቅ መሆኑ ይታወቃል።የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እንዳሉት የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት የሀገሪቱ ገቢና ወጪ ንግድ ዋና መስመርና ከወደብም ጋር የሚያገናኝ በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።ኮሚሽነሩ ስምምነቱ በተናጠል ሲሰራ የነበረውን አሰራር በማስቀረት በትብብር ለመስራት የሚያስችል መሆኑን አንስተው የአገልግሎቱን ደህንነት ለማስጠበቅ በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አ/ማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢ/ር ታከለ ኡማ በበኩላቸው አክሲዮን ማህበሩ ትርፋማ እንዲሆን እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።ይህንን ለማሳካትም ዋነኛ የሆነውን የደህንነት ችግር ለመፍታት ስምምነቱ መደረጉን ገልጸው ስምምነቱ ተቋሙ በሙሉ አቅሙ እንዲሰራ የሚያስችል ነው ማለታቸውን ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮች በኅብረቱ ልዑክ ውስጥ የመካተታቸውን ጉዳይ “መልሳ ለማጤን” ዝግጁ መኾኗን አስታወቀች!

የሶማሊያ መንግሥት የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ኅብረት ልዑክ ውስጥ መካተታቸውን በተመለከተ “መልሶ ለማጤን” ዝግጁ መኾኑን አስታውቋል።በጉዳዩ ላይ ለመናገር ፈቃድ ስላልተሰጣቸው ስማቸውን ለመግለጽ ያልፈለጉ አንድ ከፍተኛ የሶማሊያ መንግሥት ባለሥልጣን በተለይ ለቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ እንዳስታወቁት፣ የሶማሊያ መንግሥት ለልዑኩ ኅይል ከሚያዋጡት ሀገራት ማለትም ዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ ጂቡቲ እና ቡሩንዲ ወታደሮችን ማግኘቷን እና መደልደሏን አስታውቀዋል።

ሁለቱ ሀገራት አንዱ የሌላውን ሉዐላዊነት፣ እንዲሁም የግዛት አንድነት እንደሚያከብር አንካራ፣ ቱርክ ላይ ባለፈው ሳምንት በፈጸሙት ስምምነት አስታውቀዋል። ስምምነቱ በመፈጸሙም ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮች በአዲሱ ልዑክ ውስጥ የመካተታቸውን ጉዳይ “እንደገና እንደምታጤን” ባለሥልጣኑ ለቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋራ የፈጸመችውንና የባሕር በርን የተመለከተውን የመግባቢያ ስምምነት የማትሰርዝ ከኾነ ወታደሮቿ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ሶማሊያ ስትጠይቅ ቆይታ ነበር። ሶማሊያ ይህን ብትልም የኢትዮጵያ መንግሥት ግን በሶማሊያ የሚገኙት ወታደሮቹ አል ሻባብን መዋጋት እንደሚቀጥሉ ሲያስታውቅ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ትኩረት አል ሻባብ ላይ መኾኑን የኢትዮጵያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በቅርቡ አስታውቀው ነበር።

የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላምና ጸጥታ ቡድን ባካሄደው ስብሰባ አል ሻባብ የደቀነው ስጋት እንደሚያሳስበው ገልጾ፣ በስማሊያም ኾነ በኅብረቱ ኅይሎች ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት አውግዟል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ለልዑኩ የገንዘብ ምንጭ አማራጮችን እንዲያጤን የአፍሪካ ኅብረት ጠይቋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

ጤናወ በእጀወ በቤትወ የጤና በረከት የተለያዩ መፍትሄ ያጡ ችግሮች እናም በሽታወችን እንዴት አባቶች እና እናቶች ባቆዩነን ቅመማቅመም ቅጠል ስር ፍሬ እና ጥበብ መታከም መፈወስ ከችግራችን መውጣት እንዴት እንደምንችል እምንረዳበት የምንችለው  ቻናል ነው ይቀላቀሉ በየቀኑ የምንለቃቸውን ጠቃሚ መረጃ ተካፋይ ይሑኑ ሸር ያድርጉ
    👇
https://vm.tiktok.com/ZMhNYSvDS/       ለበለጠ መረጃ
0912718883
0917040506 በቴሌግራም በውስጥ መስመር የሚፈልጉትን ያስቀምጡ
👉አድራሻችን አዲስ አበባ አየር ጤና ካራቆሬ ወደመድኀኒአለም 200ሜትር ገባ ይበሉ
ቁጥር 2ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በአሮየው 
አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት ያገኙናል ይምጡ
ይፈወሱ
     https://www.tiktok.com/t/ZMhN2XcBE/

በማንኛውም አገልግሎት ውጤቱን እንዳዪ ክፍያ ይፈፅማሉ

Читать полностью…

YeneTube

🔷 የአያትን አክሲዮን የገዛ ሁሌም ትርፋማ

በ 2015 ዓ.ም 51% ትርፍ /Dividend/ ለባለክሲዮኖች አከፋፍለናል

በቀላል አማርኛ የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የነበራቸው ባለአክሲዮኖች 510 ሺ ብር ትርፍ /Dividend/ አግኝተዋል

የ 5 ሚሊዮን ብር የገዙ 2.5 ሚሊዮን ብር አትርፈዋል

የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር ነው

ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን 2500 ነው

ዝቅተኛ የአክሲዮን ዋጋ 262,500 ብር ፣ 5% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ

ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን ገደብ የለውም

40% ከፍለው ቀሪውን በሶስት ዓመት መጨረስ ይችላሉ

አክሲዮኑን ከገዙ ከአንደኛው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ መሆን ይጀምራሉ

ለበለጠ መረጃ: በ 0967907669 ይደውሉ

Читать полностью…

YeneTube

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ከመሠረተ ልማቶቹ የተሠረቁ ብረቶች መዳረሻቸው ብረት አቅላጭ ፋብሪካዎች ናቸው በማለት መክሰሱን የመንግሥት ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ተቋሙ፣ ብረት አቅላጭ ፋብሪካዎች ለውስጥ መመሪያቸው ተገዥ እንዲኾኑና ከተቋሙ የተዘረፉ ብረቶቶችን መግዛት እንዲያቆሙ  ጠይቋል። በኃይል መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ የሚፈጸመው ዝርፊያ ባለፉት አምስት ዓመታት በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መሄዱን የጠቀሰው ተቋሙ፣ በ2015 እና 2016 በጀት ዓመቶች በመሠረተ ልማቶቹ ላይ በተፈጸሙ ሥርቆቶች 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር እንደከሠረ ገልጧል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

በአማራ ክልል "በመንግሥት ተጠርቷል" በተባለ ሰልፍ ላይ በ3 ከተሞች በተፈጸሙ የቦምብ ጥቃቶች የሰው ህይወት ማለፉ ተገለጸ!

በአማራ ክልል “በመንግሥት አስተባባሪነት” ትናንት ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሄድ በተባለ ሰልፍ ላይ በባሕር ዳር፣ ወልዲያና ደብረ ብርሃን ከተሞች “በተፈጸሙ የቦምብ ጥቃቶች የአንድ ሰው ህይወት ማልፉንና ሰልፈኞች መቁሰላቸውን” የአይን እማኞች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪ ትላንት የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ “በክልሉ መንግስት አስተባባሪነት” የተካሄደ ነው ሲሉ ገልጸው፤ በከተማዋ በሶስት ከፍለ ከተሞች “የቦምብ ጥቃቶች መፈጸማቸውን” ገልጸዋል።በጥቃቱም ከጠዋት ጀምሮ “ጥሩንባ እየነፋ ነዋሪው ሰልፍ እንዲወጣ ሲያስተባብር የነበረ ግለሰብ መገደሉን” ነዋሪው ገልጸዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ የሚኖሩ የአይን እማኝ በተመሳሳይ በወልድያ በተካሄደው ሰልፍ ላይ 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተብሎ በሚጠራው ሰፍር “ቦንብ መጣሉንና ሰልፈኞች መቁሰላቸውን” ተናግረዋል።

Via Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

በኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ባለስልጣናትን ከስልጣን እንዲነሱ አሜሪካዊቷ አምባሳደር ጠየቁ!

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የሀገሪቱ የሽግግር የፍትህ ሂደት አካል በመሆን በሰብአዊ መብት ጥሰት የተሳተፉና ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፍርድ ሂደት ላይ የሚገኙ ወታደራዊ አባላትን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ የሀላፊነት ቦታዎች የሚገኙ ባለስልጣናትን ከስልጣን እንዲያነሱ ሲሉ በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያካሄዱት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአለም አቀፍ የወንጀል ፍትህ አምባሳደር ቤትዝ ቫን ስካክ አሳሰቡ።

በተጨማሪም አምባሳደር ቤትዝ የሀገሪቱ መንግስት ለተፈጸሙ ግፎች እና በደሎች እውቅና ሊሰጥ ይገባል ሲሉ አሳሰቡ።በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሲቪክ ማህበራት ምህዳሩ እንደጠበበ ተረድተናል ሲሉ ቅሬታቸውን የገለጹት አምባሳደር በአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች እየተፈጸሙ ስላሉ አሰቃቂ ተግባራት የሚወጡ ዘገባዎችንም እየተከታተልን ነው ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

በሀረር፣ ጅግጅጋ እና ሌሎች የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለፀ!

በሀረር፣ ጅግጅጋ እና ሌሎች የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡ከድሬዳዋ ቁጥር ሁለት - ሀረር- ጅግጅጋ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ባልታወቀ ምክንያት ኃይል ማስተላለፍ ማቋረጡን የምስራቅ አንድ ሪጅን የኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች መምሪያ ገልጿል።

የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ወርዲ መሐመድ፤ በተከሰተው ችግር ምክንያት በሀረር፣ ጅግጅጋ እና በሌሎች የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች ኃይል ተቋርጧል ብለዋል። ችግሩን ለመለየት ፍተሻ መጀመሩን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩን በመጠገን አገልግሎቱን ዳግም ለማስቀጠል ይሰራል ነው ያሉት። በኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትግዕስት እንዲጠብቁ ኃላፊው መጠየቃቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

ጀዋር መሐመድ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ ምን አለ?

ጃዋር ከትውልድ አንስቶ በፖለቲካ ህይወቱ የተጓዘበትን ህይወቱ ላይ የሚያጠነጥን 'አልጸጸትም' የተሰኘውን መጽሐፍ ታህሳስ 10/ 2017 ዓ.ም በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ያስመርቃል።ጃዋር መሃመድ ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚኖረው ሚና፣ አገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ቢቢሲ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን እንደመጡ ብዙ በጎ ነገሮች በንግግርም፣ በተግባርም ታይቶ ነበር። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ የትግራይ ጦርነት ተከሰተ፤ አሁንም በኦሮሚያ እንዲሁም በአማራ ክልሎች ግጭቶች እንደቀጠሉ ነው። ረሃብ፣ መፈናቀል እንዲሁም የከተማ ኑሮ ውድነት የአገሪቱ ገጽታ ሆኗል። በአንተ እምነት ኢትዮጵያ መስመር ስታ እዚህ ውስጥ የገባችው የቱ ጋር ነው?

ጃዋር፡- ዐቢይ ከመጀመርያውም መስመር ላይ አልነበረም። . . . [መጀመርያ አካባቢ] እኛ ከህወሓቶች ጋር እንደራደር ነበር፤ ስልጣን እንደሚለቁ፤ ማዕከላዊ ስልጣን እንደሚለቁ፣ ስምምነት ላይ ከደረስን በኋላ፣ ስልጣን ከለቀቁ በኋላ ማን ይሁን? የሚለው ሲመጣ የዐቢይ ስም በመምጣቱ አነጋግሬው ነበር።ያኔ ለእኔ ግልጽ ነበር።ኢትዮጵያ ከኢህአዴግ አንድ ፓርቲ አገዛዝ፣ ወደ መድብለ ፓርቲ፣ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መሄድ፣ መሻገር ነበረባት፤ ወደ ግጭት የማያደርስ ያለው ብቸኛ አማራጭ እርሱ ብቻ ነበር።ገና ስልጣን ሳይይዝ፣ገና ስሙም ሳይታወቅ፣ለእኔ ከእርሱ ጋር በነበረኝ ውይይት የዲሞክራሲ ስርዓት የመገንባት ፍላጎት እንደሌለው ግልጽ ነበር።አምባገነናዊ ስርዓትን ከአንድ ፓርቲ ወደ አንድ ግለሰብ የማሻገር ህልም እንዳለው ለእኔ ግልጽ ነበር። ለዚያ ነው የተቃወምኩት።በወቅቱ ግን ሰዉ የሚያየው ነገር የለውጥ ስሜቱ ወያኔ [ህወሓት] ብቻ ትጥፋ እንጂ ማንም ይምጣ የሚለው ስሜት በጣም ጠንካራ ስለነበር እኔ ሰዉን ማሳመን አልቻልኩም። መጀመርያ ኦህዴዶችን፣ ቀጥሎ ሕዝቡን ማሳመን አልቻልኩም። በዚያ ምክንያት አቆምኩ እንጂ ለእኔ በጣም ግልጽ ነበር።ከዚያ በኋላ የመጀመርያው አንድ ዓመት ሲደረግ የነበረውን ሳየው ነበር። ተወያይተን ይህንን ሽግግር እንምራ የሚለው ሲመጣ እኔ አሻግራችኋለሁ ማለት፤ የጋራ ፍኖተ ካርታ ይምጣ ሲባል አያስፈልገንም የሚል ምላሽ ተሰማ።በጎ በጎው በሚታይበት ወቅት ራሱ በውስጥ በውስጡ ወደ ዲሞክራሲ የሚያሸጋግረው ኃዲድ ተስቶ ነበር። መጨረሻ ላይ የለየለት ወደ ምርጫ ሲገባ፣ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡ ኃይሎችን ወደ መምታት ሲገባ ነው ሰዉ የነቃው እንጂ ከጅምሩም ዐቢይ ኢትዮጵያን ወደ ዲሞክራሲ የማሻገር ፍላጎት ፈጽሞ ኖሮት አያውቅም።

ቢቢሲ፦በአገሪቱ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ጦርነቶች እንደቀጠሉ ናቸው፤ በትግራይ ክልልም ግጭትን በዘላቂነት የማቆም የፕሪቶርያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አልሆነም። . . . አሁንም ወደ ዲሞክራሲ የመመለስ፣ አገሪቱን ወደ መስመር የመመለስ እድል አለ ብለህ ታምናለህ?

ጃዋር፦ ቢጠብም እድል አለ። ግን አሁን እነ ዐቢይ በያዙት አመለካከት እና ትምክህተኛነት ወደ ትክክለኛው መስመር መመለስ የሚችሉ አይመስለኝም።ምክንያቱም ኢትዮጵያን አይረዷትም። ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ብሔር ብሔረሰቦች ያሉበትን (Multi ethnic) የሆነን አገር፣ አሁን ባለው ዓለም ተጨባጭ ሁኔታ እና ኢትዮጵያ ባለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አይረዱም። ለመረዳትም ፍላጎት የላቸውም። ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ የብልጽግና ደሴት የሚባል ተፈጥሯል። ዐቢይ እና እርሱ አካባቢ ያሉ ሰዎች ብቻ የሚንሸራሸሩበት፣ ሌላውን ሕዝብ ፈጽሞ ያገለለ፣ የሌላውን ሕዝብ አኗኗር የማይረዳ።በቅርቡ [አዲስ አበባ] ሄጄ የሆነ ነገር ፌስቡክ ላይ ጽፌ ነበር። 'ሕዘቡ ጠውልጓል እነርሱ ደንዝዘዋል' የሚል፤ እውነቴን ነበር። ሕዝቡን ተዘዋውሬ አየሁት። ከተማ ውስጥ ቀንም ማታም እየዞርኩ ሕዝቡን አየው ነበር። ከዚያ ደግሞ ቱባ ቱባ ሚኒስትሮችን አገኘኋቸው።ስለ ኢኮኖሚ ስታወራ፣ 'ኢኮኖሚውማ እንደዚህ አድጎ አያውቅም' ይሉሀል. . . በየቤቱ ማር እና ወተት በቧንቧ የሚፈስ ነው የሚያስመስሉት። ስለ ጦርነት ስታወራ አማራ ክልል. . እነሱ እኮ ተከፋፍለዋል፤ እየጠፉ ነው። ኦሮሚያ ክልል ምንም ችግር የለም። ትግራይ የራሳቸው ጉዳይ. . . ያምኑታል ደግሞ [ጠቅላይ ሚኒስትሩን]። . . . የራሳቸውን ውሸት ያምኑታል። እነርሱ በያዙት አመለካከት ወደ መስመር መመለስ አንችልም። ነገር ግን ዝም ብለን እንመለከታለን? ዝም ብለን ደግሞ አንመለከትም። አገራችን ነው ሕዝባችን ነው። የለፋንበት ነው፤ እድሜያችንን ያጠፋንበት ነው። We are not going let them take us down [ብልጽግናዎች ይዘውን እንዲጠፉ አንፈቅድላቸውም]። ራሳቸው ብቻ ሳይሆን አገር ይዘው ሊወድቁ ነው። እኛ ኢትዮጵያን ሕዝቦቿ ወደ መንገድ መመለስ እንችላለን? አዎ መመለስ እንችላለን። እነሱን ግን ይመልሱናል ብለን የምንጠብቅ ከሆነ ባለፉት ስድስት ዓመታት አገሪቷን ከከተተበት መከራ ወደባሰበት ነው ይዘውን እየሄዱ ያሉት።

ቢቢሲ፦ ጃዋርን ከመታሰሩ በፊት የሚያውቁት ሰዎች መንግሥት ላይ የሠላ ትችት ሲያቀርብ ፣ ፖለቲካው ላይ በነበረው ንቁ ተሳትፎ ነው ።ከእስር በኋላ ግን መሀል ላይ ያለ የአሸማጋይነት ሚና ያለውን ጃዋር ነው ያየነው። እስር ቤት አንተ ላይ ያመጣው ለውጥ ምንድን ነው?

ጃዋር፦በእስር ቤት ወቅት እኔ ብቻ እስር ቤት መሆኔ አይደለም ትልቁ ነገር። ባለፈውም እንዳልኩት እኔ ትቻት የታሰርኩት ኢትዮጵያ እና እኔ ከእስር ቤት ወጥቼ ያገኘኋት ኢትዮጵያ የተለያዩ ነበሩ።እስር ቤት ከመግባቴ በፊት የችግር ዳመናው፣ የጦርነት ዳመናው የተሰበሰበ ነበር። ከእስር ቤት ስወጣ እሳት በየቦታው ተቀጣጥሎ ነበር። ስለዚህ እንደ አንድ ተሰሚነት እንዳለው እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰው ምን ባደርግ ነው አገር እና ሕዝብ ማዳን የምችለው? ብዬ አሰብኩ። ወጥቼ ወደ አክቲቭዝም እና ወደ ትችት ብመለስ በእሳቱ ላይ ሌላ ቤንዚን መጨመር ሆኖ ታየኝ። ስለዚህ ያንን ተወት ላድርገው እና ያለኝን ተሰሚነት፣ ያለኝን ትስስር፣ መስተጋብር በማማከር፣ በመገሰጽ፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡም እንዲረባረብ፣ መስራት ላይ አተኮርኩ። ከእስር ከወጣሁም በኋላ ሕዝቡንም ወደ ዲያስፖራው ሄጄ ስለ ሠላም ስናገር ከፍተኛ ተቃውሞ ይደርስብኝ ነበር። ያንን ማድረግ የምችለው እኔ ብቻ ነበርኩ።ከትግሉ ጋር ተያይዞ ያለኝ የፖለቲካ ካፒታል ነበር።ያንን የፖለቲካ ካፒታል ውጪ አገር ሄጄ በመመንዘር፣ በወቅቱ ሕዝቡ በተለያየ ወገን ያለውን ጦር በመደገፍ በጣም ተከፋፍሎ ስለነበር፣የጦርነት ገበያ እንዲጠብ እና የሠላም ገበያ እንዲሰፋ፣ መንግሥትም ሆነ ጫካ ያሉት አማፂያን ጫና ተደርጎባቸው ወደ ሠላም ይመጣሉ በሚል ነበር ያንን ስሰራ የነበረው።
መጀመርያ ለሕዝቡ ስለ ሠላም በመናገር፣ ከዚያ ደግሞ ዲፕሎማቶቸን በመቀጠል ደግሞ የአገሪቱን ባለሥልጣናት የአማፂ አመራሮችን በማግኘት የተቻለኝን ሳደርግ ነበር። ብዙ ሞከርኩ። ግን እያየሁት የመጣሁት ነገር፣ ጊዜ ለመግዣ እንጂ አገሪቱን ወደ አጠቃላይ ሠላም፣ ሥር ነቀል ሠላማዊ ለውጥ ለማምጣት ቁርጠኝነቱም ፍላጎትም እንደሌለ፣ እንዳውም ነገሮች ረገብ ሲሉ ወደ ነበረበት ሲመለሱ ስላየሁ ይህ ነገር በዚሁ ከቀጠለ እየተባባሰ ነው የሚሄደው፤ ዝም ማለቱ እና መምከሩ፣ መለማመጡ፣ መለመኑ ብዙም አላስኬደም። . . . እኔ በዚያ መቀጠሉ ዋጋ ስለሌለው ነው።

Читать полностью…

YeneTube

በካሬ ከ 78,246 ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ። እንዳያመልጦ ለ 15 ቀናት ለ 50 ቤቶች ብቻ የወጣ እድል ነው።
  ከ 432,000ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

  ከ ስቱድዮ 56ካሬ- ባለ 4 መኝታ 177 ካሬ ድረስ
ባለ 1 መኝታ -69ካሬ,77ካሬ
ባለ 2 መኝታ-99ካሬ,104ካሬ
ባለ 3 መኝታ-139ካሬ,147.6ካሬ
ባለ 4 መኝታ-177ካሬ

    በ 8% ቅደመ ክፍያ
60% የባንክ ብድር ጋር
   ለ ቢሮ እና ሳይት ቀጠሮ

         በ +251994670888 ይደውሉ።

Читать полностью…

YeneTube

“የቪድዮ ማስታወቂያ ከ500 ብር ጀምሮ 😃
ከ 500-5000 ብር የተዘጋጁትን የስጦታ ካርዶች ሲወስዱ በውስጡ:-
  ✔️ለቤተሰብ ለጓደኛ እንዲሁም ሞዴሎች የሚሆን የቪድዮ እና የፎቶ መነሻ ስጦታ🎁
  ✔️ለ ጀማሪ ቢዝነስ ,ሱቆች, ካፌዎች, ድርጅቶች የገና giveaway እንዲሁም product photography እና ማስታወቂያ ማሰሪያ ስጦታ🎁
   ✔️ለ podcast ሰሪዎች, content creator, actor , music clip ሰሪዎችና ፎቶ ግራፈሮች የሚሆን የ studio rental ስጦታ ያገኛሉ።
ለራሶም ሆነ ለወዳጅዎ ካርዶቹን ይዘዙን። የነፃ ዴሊቨሪ አለን🤩።

ለተጨማሪ መረጃ
በቲክቶክ እና ኢንስታግራም Account @easyproduction1 ይመልከቱ።
በቴሌግራም Account @yabu721 or @M16192129
ወይም
📞0931719020
📞0923125196. ይደዉሉልን

Читать полностью…

YeneTube

ከ3 ሃኪሞች በስተቀር ሁሉም የካምባ ወረዳ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ሥራ በመልቀቃቸው ነዋሪዎች ለከፍተኛ እንግልት ተዳረጉ!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ካምባ ወረዳ የሚገኘው ብቸኛው የካምባ ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፤ በክፍያና ጥቅማጥቅም አለመፈጸም እንዲሁም “በወረዳው አመራር ያልተገባ ድርጊት” ምክንያት የሕክምና ባለሙያዎች ከሥራ በመልቀቃቸው በተከሰተ የባለሙያ እጥረት ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጉን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

ሆስፒታሉ በአከባቢው ብቸኛ የሕዝብ መገልገያ የጤና ተቋም በመሆን ለካምባና ለጋርዳ ማርታ ወረዳዎች ግልጋሎት ሲሰጥ ቢቆይም አሁን ላይ 3 ሃኪሞች በቻ በመቅረታቸው የሕክምና አገልግሎት ወደ ማቆም ተቃርቧል ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።ሆስፒታሉ ታካሚዎችን ከካምባ ወረዳ በ105 ኮሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው አርባምንጭ ሆስፒታል በመንግስት አንቡላንስ 7000 ብር በማስከፈል ሪፈር ያደርጋል ተብሏል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢዩኤል ቡጋ በበኩላቸው ከ2015 ዓ.ም የካቲት ወር ጀምሮ ችግሮች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ የድንገተኛ ቀዶጥገና ህክምና የሚሰጥ ባለሙያ ባለመኖሩ ሆስፒታሉ መስጠት የሚገባውን አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

Via Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ49 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ በመያዝ የኮንጎ አየር መንገድን ስራ ማስጀመሩ ተገለጸ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ መንግስት ጋር በጋራ በመሆን “ኤር ኮንጎ” የሚል ስያሜ የተሰጠው አየር መንገድ አቋቁሞ በይፋ ስራ ማስጀመሩን አስታወቀ።በይፋ ስራውን በጀመረው የኮንጎ አየር መንገድ የሀገሪቱ መንግስት 51 በመቶ የሚሆነውን አብላጫውን ድርሻ መያዙ የተገለጸ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ 49 በመቶ ድርሻ በመያዝ አየር መንገዱን እንደሚያስተዳድር ተጠቁሟል።

ኤር ኮንጎ በሁለት ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ሰባት ኤርፖርቶች በረራ በማድረግ አገልግሎት መጀመሩን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮንጐ ዜጎችን በአብራሪነት፣ በበረራ ሰራተኝነት፣ በሽያጭና አገልግሎት ሰራተኞች እና በቴክኒሻንነት አሰልጥኖ ለማብቃት በስምምነቱ ላይ መካተቱን መረጃው አመላክቷል።

ይህ ጥምረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራዕይ 2035 አንዱ አካል መሆኑን የጠቆመው መረጃው ከዚህም በፊት በሎሜ አስካይ አየር መንገድ፣ በሊሎንግዌ የማላዊ አየር መንገድ እንዲሁም በሉሳካ የዛምቢያ አየር መንገድን በጋራ ማቋቋሙን አስታውሷል።

@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል።

ፎቶ :- ባህር ዳር - ደሴ - ኮምቦልቻ

Читать полностью…

YeneTube

ጤናወ በእጀወ በቤትወ የጤና በረከት የተለያዩ መፍትሄ ያጡ ችግሮች እናም በሽታወችን እንዴት አባቶች እና እናቶች ባቆዩነን ቅመማቅመም ቅጠል ስር ፍሬ እና ጥበብ መታከም መፈወስ ከችግራችን መውጣት እንዴት እንደምንችል እምንረዳበት የምንችለው  ቻናል ነው ይቀላቀሉ በየቀኑ የምንለቃቸውን ጠቃሚ መረጃ ተካፋይ ይሑኑ ሸር ያድርጉ
    👇
https://vm.tiktok.com/ZMhNYSvDS/       ለበለጠ መረጃ
0912718883
0917040506 በቴሌግራም በውስጥ መስመር የሚፈልጉትን ያስቀምጡ
👉አድራሻችን አዲስ አበባ አየር ጤና ካራቆሬ ወደመድኀኒአለም 200ሜትር ገባ ይበሉ
ቁጥር 2ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በአሮየው 
አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት ያገኙናል ይምጡ
ይፈወሱ
     https://www.tiktok.com/t/ZMhN2XcBE/

በማንኛውም አገልግሎት ውጤቱን እንዳዪ ክፍያ ይፈፅማሉ

Читать полностью…

YeneTube

“የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበ መጥቶ ተኮማትሯል” - የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ

ኢትዮጵያን እያስተዳደረ የሚገኘው ገዥው ፓርቲ ብልጽግና ፍጹም አምባገነን እየሆነ መጥቷል ሲሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ ተቸ፤ “የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበ መጥቶ ተኮማትሯል” ብሏል።የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ኦፌከን ጨምሮ ስድስት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ ትላንት ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ባወጡት መግለጫ የብልጽግና መንግስት “ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ የአገራችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ከዕለት-ወደ ዕለት ‹‹ ከድጡ ወደ ማጡ›› በሚያስብል ደረጃ ለሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ እየዳረጉን ነው” ሲል አሳስቧል፡፡

“ሽግግር በሌለበት ስለሽግግር ፍትህ”፣ “ለመወያየትና ለድርድር ቁርጠኝነት በሌለበት” ስለ ምክክር ኮሚሽን “አብዝቶ ይደሰኩራል” ሲሉም ፓርቲዎቹ ገዢው ፓርቲን በመግለጫቸው ተችተዋል።በሺ ዓመትም ‹‹አታሸንፉኝም›› በማለት እየፎከሩ ‹እንመካከር› ማለትም ሆነ ‹በእኔ ሥር ሆናችሁ እንደራደር› ማለት ከባዶ ፕሮፖጋንዳ ያለፈ ትርጉም የለውም ሲሉ ወቀሳቸውን በገዢው ፓርቲ ላት ሰንዝረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

እናት ፓርቲ ያለ ሕግ ትዕዛዝ በእስር ላይ የሚገኙ አባላቱ ሰብዓዊ መብታቸው እየተጠበቀ አለመሆኑን ገለጸ!

እናት ፓርቲ "ሦስት የፓርቲ አባሎቼ በአርባ ምንጭ ከተማ  ያለምንም የሕግ ትዕዛዝ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው በወታደራዊ ካምፕ ውስጥም በእስር ላይ ይገኛሉ ያለ ሲሆን፤ የቤተሰብ ጉብኝትን ጨምሮ የሕግ ድጋፍ እንዲሰጣቸው ብጠይቅም ተከልክያለሁ" ሲል ለአሐዱ ተናግሯል።

የእናት ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ ጌትነት ወርቁ ፓርቲያቸው የአባላቱን ጉዳይ ለማጣራት ሲጥር አለአግባብ እንዳታሰሩ ማረጋገጡን ነግረውናል፡፡

ማንኛውም ተጠርጣሪ በሚታሰርበት ፖሊስ ጣቢያ ሳይሆን ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ መታሰራቸው የገለጹት አቶ ጌትነት፤ "በተገቢው ጊዜ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው እና ተያያዥ የመብት ጥሰቶች በመፈጸም የፓርቲውን አባላት ሆነ ብሎ የማሸማቀቅ ሥራ የተደረገ ነው" ብለው እንደሚያምኑም ይናገራሉ፡፡

አቶ ጌትነት ፓርቲያቸው ሰላማዊ ትግልን የሚከተልና በዚሁ መንገድ እየታገለ እንደሚገኝ ተናግረው፤ በአመራርና አባሎቹ ላይ በመንግሥት ኣካላት እየደረሰ ያለው እስርና አፈና እንዲሁም ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እንዲቆም፣ ፖሊስ የእስሩን ምክንያት እንዲያሳውቅ፣ ፍርድቤት እንዲያቀርባቸው እንዲሁም የቤተሰብ ጉብኝትን እንዲፈቅድ ጠይቀዋል፡፡

እናት ፓርቲ ታሕሳስ 6 ቀን 2017 ባወጣው መግለጫ የፓርቲው የአርባ ምንጭና አካባቢው ማስተባበሪያ ሰብሳቢ ቴዎድሮስ ፋንታዬ (ዕጩ ዶክተር)፣ የወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ክፍል ኃላፊ አቶ ኤፍሬም አበበ እንዲሁም የፋይናንስ ጉዳዮች ኃላፊ መ/ር ኃብተ ገብርኤል ቃይዳ ታሕሳስ 4 እና 5 ቀን 2017 ዓ.ም የእስር ትዕዛዝ ሳይደርሳቸው 'ከአዲስ አበባ የፌዴራል ደህንነት መሥሪያ ቤት እንደመጡ' በገለጹ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ማስታወቁ ይታወሳል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

በካሬ ከ 78,246 ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ። እንዳያመልጦ ለ 15 ቀናት ለ 50 ቤቶች ብቻ የወጣ እድል ነው።
  ከ 432,000ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

  ከ ስቱድዮ 56ካሬ- ባለ 4 መኝታ 177 ካሬ ድረስ
ባለ 1 መኝታ -69ካሬ,77ካሬ
ባለ 2 መኝታ-99ካሬ,104ካሬ
ባለ 3 መኝታ-139ካሬ,147.6ካሬ
ባለ 4 መኝታ-177ካሬ

    በ 8% ቅደመ ክፍያ
60% የባንክ ብድር ጋር
   ለ ቢሮ እና ሳይት ቀጠሮ

         በ +251994670888 ይደውሉ።

Читать полностью…

YeneTube

“የቪድዮ ማስታወቂያ ከ500 ብር ጀምሮ 😃
ከ 500-5000 ብር የተዘጋጁትን የስጦታ ካርዶች ሲወስዱ በውስጡ:-
  ✔️ለቤተሰብ ለጓደኛ እንዲሁም ሞዴሎች የሚሆን የቪድዮ እና የፎቶ መነሻ ስጦታ🎁
  ✔️ለ ጀማሪ ቢዝነስ ,ሱቆች, ካፌዎች, ድርጅቶች የገና giveaway እንዲሁም product photography እና ማስታወቂያ ማሰሪያ ስጦታ🎁
   ✔️ለ podcast ሰሪዎች, content creator, actor , music clip ሰሪዎችና ፎቶ ግራፈሮች የሚሆን የ studio rental ስጦታ ያገኛሉ።
ለራሶም ሆነ ለወዳጅዎ ካርዶቹን ይዘዙን። የነፃ ዴሊቨሪ አለን🤩።

ለተጨማሪ መረጃ
በቲክቶክ እና ኢንስታግራም Account @easyproduction1 ይመልከቱ።
በቴሌግራም Account @yabu721 or @M16192129
ወይም
📞0931719020
📞0923125196. ይደዉሉልን

Читать полностью…

YeneTube

#Update

በምስራቅ ኢትዮጵያ የተቋረጠው ኃይል መልሶ ተገናኝቷል!

የድሬዳዋ - ሀረር- ጅግጅጋ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የምስራቅ አንድ ሪጅን የኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ወርዲ መሐመድ እንደገለፁት ለሀረር፣ ጅግጅጋ እና ለሌሎች የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች ኃይል የተቋረጠው የማስተላለፊያ መስመሩ አንዱ ፌዝ በመበጠሱ ምክንያት ነበር።

ችግሩን ለመለየት አስቸጋሪውን የደንገጎን ተራራ በእግር በመጓዝ ፍተሻ መከናወኑን የተናገሩት ዳይሬክተሩ የተበጠሰውን የኃይል ማስተላለፊያ  መስመር በመጠገን አገልግሎቱን ዳግም መመለሱን ገልፀዋል።በማስተላለፊያ መስመሩ ላይ የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትግዕስት ስለጠበቁ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

አቶ ሰርፀ ፍሬስብሀት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፃፉት ደብዳቤ ከስራቸው ተሰናበቱ

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ሆነው ላለፉት ስድስት አመታት ያገለገሉትን አቶ ሰርፀ ፍሬስብሀትን ከስራቸው ማሰናበታቸውን መሠረት ሚድያ የደረሰው መረጃ ያሳያል።

አቶ ሰርፀ ከስራቸው የተነሱት በከንቲባዋ ህዳር 23/2017 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ ሲሆን ምክንያቱ ግን በደብዳቤ ላይ አልተገለፀም።

ይሁንና ሚድያችን ከውስጥ አዋቂዎች የደረሰው ተከታታይ ጥቆማ እንደሚያሳየው ጉዳዩ በከተማ አስተዳደሩ ሊደረግ ከታሰበው የሰራተኛ ቅነሳ ጋር የተያያዘ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ባህልና ቱሪዝም ስር በሚገኙት 4 ቴአትር ቤቶች ማለትም የአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ፣ አገር ፍቅር፣ ራስ ቴአትር እና ሕጻናትና ወጣቶች ቴአትር በስራቸው 800 ሰራተኞች አሉ።

ከእነዚህ ሰራተኞች 50 ከመቶው እንዲቀነሱ እንደተወሰነ የደረሰን መረጃ የሚጠቁም ሲሆን በምትካቸው ማለትም 50 ከመቶ የሚሆኑ ከተለያዩ የክልል አካባቢዎች በመጡ ሰዎች በቴአትር ቤቶቹ ምደባ ተከናውኗል ተብሏል።

ይህን ውሳኔ ያልተቀበሉ ላይ ወይም ተቃውሞ ያሰሙ ሰዎች ላይ ከስራ የማንሳት እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ የታወቀ ሲሆን የአቶ ሰርፀ ጉዳይም ከዚህ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።

ሚድያችን ከሰሞኑ በተደጋጋሚ በሰራዎች ዘገባዎቹ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች በቅርቡ ከስራ ሊቀነሱ እንደሆነ መዘገቡ ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

"የብልፅግና ፓርቲ አባላት ናችሁ" በሚል ደምወዛቸው ያለፈቃዳቸው የሚቆረጥባቸው ሠራተኞች መኖራቸው ተገለጸ!

በሲዳማ፣ በደቡብ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የሠራተኞችን ደሞዝ ያለፈቃዳቸው እየተቆረጠባቸው መሆኑን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለአሐዱ ገልጿል።በክልሎቹ በሕግ ባልተወሰነ መልኩ እና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የመንግሥት ሠራተኞችን ደምወዝ የሚቆርጡ የካቢኔ አባላት መኖራቸውን የገለጹት፤ በጽ/ቤቱ የአስተዳደር በደል ምርመራ ዳይሬክተር አቶ አበራ ንጉሴ ናቸው።

እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ፤ 'የብልፅግና ፓርቲ አባላት ናችሁ' እየተባሉ እና 'የልማት ሥራ ሊሰራ ነው' በሚሉ ምክንያቶች የሠራተኞች ደሞዝ ያለፈቃዳቸው እየተቆረጠባቸው ይገኛል።በክልሎቹ ያለውን ችግር ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግር መደረጉን እና እየተደረገም መሆኑን ተናግረዋል።

በእነዚህ ክልሎች የጤና ባለሙያዎች የረጅም ጊዜ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዳልተከፈላቸው እንዲሁም የመምህራን ደምወዝ ያለፈቃዳቸው የሚቆርጡ የወረዳ አስተዳደሮች መኖራቸው መገለጹን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል።

ችግሩ በሁሉም የመንግሥት ሠራተኞች ላይ ያለ እና ሠራተኞቹ ችግር ውስጥ እንዲወድቁ ያደረገ መሆኑም ነው የተገለጸው።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በተለያዩ አካላት የሚፈፀሙ በደሎችን አስመልክቶ የሚመጡለትን ቅሬታዎች በማጋለጥ ተጠያቂነትን ለማምጣት እየሰራ መሆኑን ቢገልጽም፤ ወደ ተቋሙ ከመጡ በኋላ ጉዳያቸውን አቋርጠው ወደ ፍርድ ቤት የሚሄዱ ቅሬታ አቅራቢዎች በርካቶች መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

"ቅሬታ አቅራቢዎች ለምን ወደ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ? በናንተ በኩል ያለውን ሂደት ለምን ያቋርጡታል?" ሲል አሐዱ አቶ አበራ ንጉሴን የጠየቀ ሲሆን፤ በምላሻቸውም አንዳንድ ተገልጋዮች 'የፍርድ ሂደታችሁ ፅኑና አስገዳጅ አይደለም' ብለው የሚያቋርጡ መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም "ፍርድ ቤት ማንኛውንም ለፍርድ የቀረበ አካል ተቋምም ቢሆን፤ ንብረት የማሳገድ እና አፋጣኝ ምላሽ የማሰጠት ስልጣን ስላለው ወደዛ ይሄዳሉ" ብለዋል፡፡"የኛ አሰራር የሚፈቅደው ምርመራ ማድረግ ለአካባቢው ወይም ለክልል ምክር ቤት ማቅረብ እያለ ስለሚጓተት ተገልጋዮች አፋጣኝ ምላሽ ስለሚፈልጉ ነው ይህን ያደርጋሉ" ሲሉም ተናግረዋል፡፡

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

...ከላይኛው ልጥፍ የቀጠለ

ቢቢሲ፡- ስለዚህ ወደ ቀደመው የነቃ የፖለቲካ ተሳትፎህ ተመልሰሃል?

ጃዋር፦ ወደ ቀደመው መመለስ አይቻልም። ወደፊት ብቻ ነው መሄድ የሚቻለው።(ሳቅ)

ቢቢሲ፡- ይህንን ያነሳሁት ቀጣዩ ምርጫ ብዙም ሩቅ አይደለም በሚል ነው። አንተ ደግሞ በኦፌኮ ውስጥ አባል እና አመራር ነህ፤ በቀጣይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ምን ሚና ይኖርሃል ለማለት ነው?

ጃዋር- ቀልጣፋ ሚና ይኖረኛል። እኔ አሁን መናገር እና መጻፍ የጀመርኩት እነዚህ ልጆች[የብልጽግና ሰዎች] በጣም አደገኛ ነገር ውስጥ ነው የገቡት። Total ignorance and arrogance (እልም ያለ ድንቁርና እና እብሪተኝነት)።

ቢቢሲ- የብልጽግና ሰዎች ማለትህ ነው?

ጃዋር-የብልጽግና ሰዎች ዐቢይ እና በአካባቢው ያሉ ሰዎች Total ignorance and arrogance[እልም ያለ ድንቁርና እና እብሪተኝነት] ውስጥ ናቸው። ይህ ነው የማይባል ጥጋብ ውስጥ ገብተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

ጤናወ በእጀወ በቤትወ የጤና በረከት የተለያዩ መፍትሄ ያጡ ችግሮች እናም በሽታወችን እንዴት አባቶች እና እናቶች ባቆዩነን ቅመማቅመም ቅጠል ስር ፍሬ እና ጥበብ መታከም መፈወስ ከችግራችን መውጣት እንዴት እንደምንችል እምንረዳበት የምንችለው  ቻናል ነው ይቀላቀሉ በየቀኑ የምንለቃቸውን ጠቃሚ መረጃ ተካፋይ ይሑኑ ሸር ያድርጉ
    👇
https://vm.tiktok.com/ZMhNYSvDS/       ለበለጠ መረጃ
0912718883
0917040506 በቴሌግራም በውስጥ መስመር የሚፈልጉትን ያስቀምጡ
👉አድራሻችን አዲስ አበባ አየር ጤና ካራቆሬ ወደመድኀኒአለም 200ሜትር ገባ ይበሉ
ቁጥር 2ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በአሮየው 
አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት ያገኙናል ይምጡ
ይፈወሱ
     https://www.tiktok.com/t/ZMhN2XcBE/

በማንኛውም አገልግሎት ውጤቱን እንዳዪ ክፍያ ይፈፅማሉ

Читать полностью…

YeneTube

🔷 የአያትን አክሲዮን የገዛ ሁሌም ትርፋማ

በ 2015 ዓ.ም 51% ትርፍ /Dividend/ ለባለክሲዮኖች አከፋፍለናል

በቀላል አማርኛ የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የነበራቸው ባለአክሲዮኖች 510 ሺ ብር ትርፍ /Dividend/ አግኝተዋል

የ 5 ሚሊዮን ብር የገዙ 2.5 ሚሊዮን ብር አትርፈዋል

የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር ነው

ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን 2500 ነው

ዝቅተኛ የአክሲዮን ዋጋ 262,500 ብር ፣ 5% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ

ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን ገደብ የለውም

40% ከፍለው ቀሪውን በሶስት ዓመት መጨረስ ይችላሉ

አክሲዮኑን ከገዙ ከአንደኛው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ መሆን ይጀምራሉ

ለበለጠ መረጃ: በ 0967907669 ይደውሉ

Читать полностью…

YeneTube

መንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል በቀጣይ ጥር 6 ቀን ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ!

ከተመሰረተ ከ81 ዓመታት በላይ የቆጠረው የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እድሳት ከ125 ሚልየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተከናውኖ፤ በቀጣይ ጥር 6 ቀን ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል።ካቴድራሉ ለአገልግሎት ክፍት ሊደረግ መሆኑን አስመልክቶ፤ ዛሬ ታሕሳስ 09 ቀን 2017 ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው የካቴድራሉ የሕንፃው እድሳት ወደ መጠናቀቁ ገደማ የደረሰ በመሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ የፊታችን ጥር 06 ቀን 2017 ታቦተ ሕጉን በክብር ወደ ነበረበት ካቴድራል ለማስገባት በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገልጿል።የእድሳት እና የጥገና ሥራው ከተጀመረ 773 ቀናት ማስቆጠሩ የተገለጸ ሲሆን፤ በወቅቱ በገጠመው የሲሚንቶ እጥረት ችግር እና በሌሎችም ምክንያቶች ተጨማሪ 225 ቀናት መውሰዱም ተነግሯል።

መግለጫውን የሰጡት የመበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ዋና አስተዳዳሪ ሊቀ ስልጣናት አባ ሲራክ አድማሱ፤ "የአንድ ሀገር ማንነት በሃይማኖት፣ በታሪክና በቅርስ ላይ የተመሰረተ ነው። እነዚህ የሌሉት ሀገር ማንነቱ ሊታወቅ አይችልም።" ብለዋል።

"በመሆኑም ብዙ ሀገሮች የአጭር ጊዜም ይሁን የረጅም ዘመን ታሪካቸውና ቅርሶቻቸውን ይንከባከባሉ፣ ይጠብቃሉ፣ ዜጎቻቸውንም በሥራው እንዲሳተፉ አጥበቀው ይቀሰቅሳሉ፣ ያስተምራሉ" ያሉ ሲሆን፤ የብዙ ሕዝቦች መኖሪያ የሆነችው ኢትዮጵያም በዓለም መድረክ ከፍ ያለ ታሪክ ያላት መሆኑን አንስተዋል።

"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያን በውስጧ በርካታ ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ቅርሶችን ይዛ በሀገር በቀል ዕውቀቶቿም ለሀገረችን ስልጣኔ አሻራ መሆኗ የሚታወቅ ነው" ያሉት የካቴድራሉ አስተዳዳሪ፤ "ከነዚህ መካከል የመንበረ ጸባዖት ቅድስ ስላሴ ካቴድራል አንዱ ነው" ብለዋል።

"ካቴድራሉ ሃይማኖታዊ አገልግሎትና ትርጉም ያላቸውን ቅዱሳት መካናትና ንዋያተ ቅዱሳትን፣ ቅዱሳት ሥዕላትንና ቅዱሳት መፃህፍትን ብቻም ሳይሆን የነገስታቱን፣ የመሳፍንቱን የሥርዓተ መንግሥት ማድረሻ ንዋያት፣ አልባሳትና የወግ እቃዎችን እና የባህል እቃዎችን በዕቃ ቤቷ ሸክፋ የያዘች ባለውለታ ናት" ሲሉም ገልጸዋል።

ካቴድራሉ በእድሜ እርዝማኔ ምክንያት እድሳት ሳይደረግለት በመቆየቱ፤ ይህን ታሳቢ በማድረግ ከ17 ወራት ጥናት በኋላ እድሳቱ መጀመሩን ተናግረዋል።አክለውም በአሁኑ ሰዓት የእድሳት ሥራው በተፋጠነ ሁኔታ ተሰርቶ የውስጥ ሥራዎች የውስጥ ሥራው ወደ ፍፃሜ በመድረሱ ጥር 06 ቀን 2017 ዓ.ም ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ እንደሚመለስ ጠቁመዋል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

ከሳምንት በፊት እገዳው ተነስቶለት የነበረው ካርድ በድጋሚ ታገደ

የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከልን (ካርድ) በድጋሚ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን መታገዱ ተገለጸ።

ከአንድ ሳምንት በፊት ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከልን (ካርድ) ጨምሮ በሶስት አገር በቀል ሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች ላይ ጥሎ የነበረውን  ዕግድ ማንሳቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ምንጭ ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል።

ባለስለጣኑ ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በጻፈው እና ለተቋሙ ትላንት ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በደረሰው ደብዳቤ የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከልን (ካርድ) በድጋሚ መታገዱን በተቋሙ እንደሚሰሩ ለአዲስ ስታንዳርድ የገለጹልን ምንጭ አስታውቀዋል።

ካርድ በድጋሚ ለመታገድ ያደረሰው ምክንያት ቀደም ሲል ተጥሎ የነበረው እገዳ ሲነሳ “የተገለጸለትን የእርምት እርምጃዎች ባለመውሰድ“ እንዲሁም “ለተሰጠው ማስጠንቀቂያ ትኩረት መንፈግ” የሚል መሆኑን ምንጫችን አመላክተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

ባንኮች ያለምን ማስያዣ ከብሔራዊ ባንክ እንዲበደሩ ይፈቅድ የነበረዉ ድንጋጌ ከረቂቅ አዋጁ ተሰረዘ

ብሔራዊ ባንክ ጊዜያዊ የገንዘብ እጥረት የገጠመው ሆኖ ዕዳውን ግን መክፈል ለሚችል ባንክ ጊዜያዊ ብድር ሊሰጥ እንደሚችል የሚገልጸው ድንጋጌ ከረቂቅ አዋጁ ላይ እንዲሰረዝ ተደርጓል።

በዚህም ማዕከላዊ ባንኩ ያለመያዣ ለባንኮች ይሰጥ የነበረዉ ብድር የሰረዘ ሲሆን እንደምክንያት ያስቀመጠዉ የመንግስትን ገንዘብ ያለ በቂ ዋስትና መስጠት ተገቢነት ያለው አሠራር ባለመሆኑ እና  የህዝብን ጥቅም እንደሚጎዳ ስለታሰበበት መሆኑን ጠቁሟል።

ይህን ተከትሎ ብሔራዊ ባንክ ያለመዣ ይሰጥ የነበረዉ የብድር አሰራር እንዲቀር የተደረገ ሲሆን ባንኮችም ብድር ሲፈልጉ ዋስትና ማቅረብ እንዳለባቸው በአዋጁ አሳስቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ረቂቁ ባንኮች ከብሔራዊ ባንክ የወሰዱትን ብድር የመመለሻ ጊዜ በ 6 ወራት ዉስጥ መሆን አለበት የሚል ሲሆን አሁን ግን " የብድር መመለሻ ጊዜ በአዋጅ ከመደንገግ ይልቅ በመመሪያ እንዲሆን መወሰኑን በተሻሻለዉ የብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ አስቀምጧል ።

Via Capital Newspaper
@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

ከግል የትምህርት ተቋማት የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ለመምህርነት እና ለጤና እንደማይፈቀድ በመገለጹ ቅሬታ እንደተፈጠረባቸዉ ባለሙያዎች ተናገሩ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዉስጥ በሚገኙ ሁሉም ዞኖች ከግል የትምህርት ተቋማት ተመርቀዉ ከ10 እስከ 15 ዓመታት የሚደረስ ጊዜ በትምህርቱ ዘርፍ ላይ በአመራርነት ሲያገለግሉ የነበሩ ግለሰቦች አሁን ላይ በክልሉ እየተተገበረ በሚገኘዉ ሪፎርም የተነሳ ከስራ ገበታቸዉ መፈናቀላቸዉንና ደሞዛቸዉም ያለአግባብ እየተቆረጠባቸዉ መሆኑን አመራሮቹ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

አመራሮቹም ለረጅም አመታት በሙያቸዉ ማህበረሰቡን በታማኝነት ሲያገለግሉ እንደቆዩ ገልፀው ከነሀሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ስራ እንዲያቆሙ ቤት ለቤት ደብዳቤ እንደተላከላቸዉ ገልጸዋል።የሪፎሪሙን ፈተና ለመፈተን ተመዝገብን ከምዝገባ በኃላ የመጨረሻዉ የምልመላ ቀን ላይ ከግል የዩኒቨርስቲ ተቋማት የተመረቁ አካላት በዚህ ፈተና ላይ  አይካተቱም ተብለን ከፈተና ዉጪ ተደርገናል ብለዋል።

አሁን ላይ በክልሉ እየተተገበረ የሚገኘዉ ሪፎርም ከፌደራልና ከሲቨል ሰርቪስ ሪፎርም ጋር የሚጣረስ መሆኑን ገልፀዉ እውቅና ካለዉ ዩኒቨርስቲ ተመርቀዉ 20 ዓመታትን በትምህርቱ ዘርፍ ላይ በርዕሰ መምህርነትና ሱፐርቫይዘርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ሆኖም ግን አሁን ላይ ከደረጃቸዉ ዝቅ በማለት በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ እንዲያስተምሩ ከመደረጋቸዉም በላይ ደሞዛቸዉ ያለአግባብ እየተቆረጠባቸዉ መሆኑን ገልፀዋል ።በዚህም የተነሳ ጉዳዩን ለትምህርት ሚኒስቴር ፣ለመምህራን ማህበር እና ለሲቪል ሰርቪስ ያሳወቅን ሲሆን በቃል ደረጃ ፈተናዉን እንድንፈተን ካልሆነም በሚሰጡን መደብ ደሞዛችን ሳይቀነስ እንድንሰራ ምላሽ ተሰጥቶናል ብለዋል።

ደሞዛችን በመቀነሱ ቤተሰባችንን ማስተዳደር አቅቶናል የሚመለከተዉ አካል ጉዳዩን ተመልክቶ መፍትሄ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ብለዋል።በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸዉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት አመራርና ሰራተኞች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተሾመ ኃይሉ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ከግል ተቋም በተገኘ የትምህርት ማስረጃ ለመምህርነት ሙያ እና ለጤና  እንደማይፈቀድ 2001 ዓ.ም ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር የህግ ማዕቀፍ ወይም መመሪያ በመዉጣቱ ያንን ታሳቢ በማድረግ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ባሉት አመታት በተሳሳተ መንገድ በየትምህርት ተቋማቱ ላይ በአመራርነት ሲያገለግሉ የነበሩትን እያረሙ እንደሚገኙ ገልፀዋል።j

በዚህም የተነሳ ከ2001 በፊት ተመዝግበዉ የሚመሩ ከሆኑ እንዲወዳደሩ ከ2001 በኃላ ተምረዉ ያጠናቀቁ ከሆነ ለትምህርት ጥራት የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚፈጥር በመሆኑ ከግል የትምህርት ተቋማት በተገኘ ማስረጃ ከመምህርነት ዉጪ ባሉ መደቦች ላይ ተወዳድረዉ መመደብ ይችላሉ ብለዉ ገልጸዋል ።ተከታታይነት ባለዉ መንገድ እንዲታረም ክልሉ አቅጣጫ ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዉ ይህም አሰራር ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ሲደረግ እንደነበር ገልፀዋል ።

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

በካሬ ከ 78,246 ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ። እንዳያመልጦ ለ 15 ቀናት ለ 50 ቤቶች ብቻ የወጣ እድል ነው።
  ከ 432,000ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

  ከ ስቱድዮ 56ካሬ- ባለ 4 መኝታ 177 ካሬ ድረስ
ባለ 1 መኝታ -69ካሬ,77ካሬ
ባለ 2 መኝታ-99ካሬ,104ካሬ
ባለ 3 መኝታ-139ካሬ,147.6ካሬ
ባለ 4 መኝታ-177ካሬ

    በ 8% ቅደመ ክፍያ
60% የባንክ ብድር ጋር
   ለ ቢሮ እና ሳይት ቀጠሮ

         በ +251994670888 ይደውሉ።

Читать полностью…
Subscribe to a channel