yenetube | Unsorted

Telegram-канал yenetube - YeneTube

122182

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Subscribe to a channel

YeneTube

🖐 በትርፍ ሰዓትዎ ተጨማሪ ገቢ 💵 የሚያስገኝ ስራ ይፈልጋሉ?

🚀 አዎን ከሆነ  በካሪስ አድቨርታይዚንግ እጅግ አዋጭ የሆነ የስራ ዕድል ተመቻችቷል!

💡ብቁ እና ልምድ ባላቸዉ ዲጂታል ማርኬተሮች ዘመኑን የሚመጥን የዲጂታል ማርኬቲንግ ዕዉቀት እንዲሁም የዘመናዊ ሽያጭ ጥበብ በአጭር ጊዜ አሰልጥነን ብቁ እናደርጎታለን!

  📚  መሰረታዊ የሆነ ስልጠና

💡Digital Marketing
💡Branding
💡Graphics design
💡Video editing አሰራር

✨ በአንድ ፓኬጅ በመሰልጠን የተፈላጊ ሙያ ባለቤት በመሆን ተጨማሪ ገቢ ያግኙ!

1⃣ በስልጠናው በቂ እውቀት ያካብታሉ

2⃣ ስልጠናውን ሲወስዱ በተግባር የታገዘ ልምምድ እንዲሁም ሲጨርሱ ከእኛ ጋር 100% የስራ እድል ይመቻቻል!

3⃣ በሰሩት ስራ ልክ የሚያድግ የገቢ ምንጭ!

4⃣ የተለያዩ ኘሮጀክቶችን በመስራት ልምድ ይቀስማሉ

5⃣ የተለያዩ ኦንላይን ኮርሶችን በነፃ በቤቶ የሚማሩበት እድል እንሰጣለን!

6⃣ የቢዝነስ እና ሶፍት ስኪል ትሬኒንግን ያካተተ

▫️ለአዳዲስ ተመራቂ ተማራዎች
▫️ለኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች
▫️በተለያዪ ድርጅቶች ዉስጥ ተቀጥረው ለሚሰሩ ሰዎች በትርፍ ሰዓት ሊሰሩት የሚችሉትን የስራ ዕድል አመቻችተንሎታል!

ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነዉ ይመዝገቡ!!

🔈ለተጨማሪ መረጃ
☎️ 0954742475 
☎️ 0926738676 ይደውሉ
Telegram : @Charistechnology

አድራሻ : 22 ጎላጉል ጀርባ ኖህ ፕላዛ 3 ተኛ ፎቅ

Читать полностью…

YeneTube

አቶ ደመቀ መኮንን ከመንግስት እና ከገዢው ፓርቲ ከነበራቸው ኃላፊነት ተሰናበቱ!

ላለፉት 11 ዓመታት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ደመቀ መኮንን፤ ከመንግስት እና በገዢው ፓርቲ ከነበራቸው ኃላፊነት መሰናበታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለ”ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። አቶ ደመቀ በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትነት በነበራቸው የኃላፊነት ቦታ ላይ፤ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ መተካታቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

አሜሪካዊው ፍርደኛ በናይትሮጂን ጋዝ በሞት በመቀጣት የመጀመሪያው ሰው ሆነ!

በግድያ ወንጀል ጥፋተኛ የተባለው ኬነት ዩጂን ስሚዝ በአሜሪካ በናይትሮጂን ጋዝ የሞት ቅጣት የተፈጸመበት የመጀመሪያው ሰው ሆነ።በአልባማ ግዛት የሞት ቅጣቱ የተፈጸመው።የ58 ዓመቱ ኬነት አንድ ግዜ ለፌደራል ፍርድ ቤት፤ ሁለት ግዜ ደግሞ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት በናይሮጂን ጋዛ የሞት ቅጣት መፈጸም ጭካኔ የተሞላበት እና ከዚህ ቀደም ተሞክሮ የማያውቅ ነው ሲል ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም።

እአአ በ2022 የአልባማ ግዛት ግለሰቡን በመርፌ በሞት ለመቅጣት ያደረገው ሙከራ ደም ስሩን ማግኘት ባለመቻላቸው ሳይሳካ ቀርቶ ነበር።ግለሰቡ በ1989 በቅጥረኛ ገዳይነት ተሰማርቶ የሰባኪ ሚስት ገድሎ ነበር የተከሰሰው።እንደ ዴዝ ፔናሊቲ ኢንፎርሜሽን ሴንተር ከሆነ ግለሰቡ በአሜሪካ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም በናይሮጂን ጋዛ ዘዴ የተገደለ የመጀመሪያው ሰው ሆኗል።

ናይትሮጂንን ለገድያ ለመጠቀም አልባማን ጨምሮ አንድ የአሜሪካ ግዛትም ፈቅዷል።የኬነት ግድያ ሲፈጸም አምስት ጋዜጠኞች ተገኝተዋል።ኬነትም “ዛሬ አልባማ ሰብአዊነትን ወደኋላ የጎተተችበት ቀን ነው። ስለደገፋችሁኝ አመሰግናለሁ። ሁላችሁንም እወዳችኋላሁ” ብሏል።ቢያንስ ከሁለት እስከ አራት ደቂቃ እንደተንፈራገጠ የዐይን እማኞች ተናግረዋል።ናይትሮጂን ያለ ኦክስጅን ወደሰውነት ሲገባ በደም ሕዋሳት ላይ ጉዳት አድርሶ ሞት ያስከትላል።

የአልባማ አገረ ገዥ ኬይ ሌቪ ግድያው ሲፈጸም ለመገኘት አልፈቀዱም።“ከ30 ዓመታት ሙከራ በኋላ ለአስከፊ ወንጀሉ ተቀጥቷል” ሲሉ ግን ገልጸዋል። የተገደለችው ኤልዛቤት ሴኔት ቤተሰቦች በስተመጨረሻ እረፍት እንደሚያገኙም አክለዋል።ስሚዝ የ45 ዓመቷን ኤልዛቤት አንድ ሺህ ዶላር ተከፍሏቸው ከገደሏት ሁለት ወንጀል ፈጻሚዎች መካከል አንዱ ነው።

ተደብድባ ደረቷ እና አንገቷ ላይ በጩቤ ተወግታ ሕይወቷ አልፏል። ሕይወቷ ያለፈው በቤት ዘረፋ ወቅት እንዲመስል ተሞክሮ ነበር።በዕዳ የተዘፈቀውና ሰባኪ የነበረው ባለቤቷ የኢንሹራንስ ገንዘብ ለማግኘት ግድያውን ማስፈጸሙ ታውቋል። መርማሪዎች ሊደርሱበት መሆኑን ሲያውቅ ራሱን አጥፍቷል።ከኬነት ጋር በተባባሪነት ወንጀሉን የፈጸመው ጆን ፎረስት ፓርከር በ2010 በሞት ተቀጥቷል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

🎄ዮም ፎቶ ቬሎ ሜካፕ ሀዋሳ መጀመራችንን ምክኒያት በማድረግ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ አድርገናል

       ከ18000 ብር ጀምሮ

❄️የመስክ እና ስቱዲዮ ፎቶ
ቬሎ፣ሱፍ፣ካባ፣ሜካፕ፣ጥፍር፣ፀጉር
እና ሌሎች የያዙ ጥቅሎች

📞0919868065 / 0992997458

➡️አድራሻ :- ሀዋሳ ፒያሳ ዳሽን ባንክ ፊትለፊት ጋሜ ህንጻ 1ኛ ፎቅ

🟢1st package  
👍Laminate Album 20 page
✔️Board photo 50 x 80 1 pc
✔️Signboard 1 pc
✔️Thank you card 200 pc
🔼Save The Date 5 pc
➕Slideshow
   🆕 የሠርግ አልባሳት  
👍ከለር ቬሎ በመረጡት አይነት
💯የመስክ ቬሎ በመረጡት አይነት
🟢የስቱዲዮ ቬሎ በመረጡት አይነት
♾ሜካፕ
⏰ጥፍር
📌ፀጉር
🔥ካባ
➡️የሙሽራ ሱፍ 2
💸28,000Birr

Читать полностью…

YeneTube

“አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን ለጦርነት እየተዘጋጁ ነው” - ላቭሮቭ

“አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን ከሰሜን ኮሪያ ጋር ጦርነት ለማድረግ እየተዘጋጁ ነው” ሲሉ የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ትናንት ረቡዕ ክስ አሰምተዋል።ሶስቱ አገራት በበኩላቸው፤ በጋራ የሚያደርጉት ወታደራዊ ልምምድ በመከላከል ላይ ያተኮረ እና ከሰሜን ኮሪያ በመምጣት ላይ ያለውን የኑክሌር ስጋት ለመቋቋም ያለመ መሆኑን ይናገራሉ።

በተመድ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት ላቭሮቭ፤ ከደቡብ ኮሪያ የሚሰማው ትርክት፣ ድንገት ሰሜን ኮሪያ ላይ አነጣጥሯል ብለዋል።በተመሳሳይ ከጃፓን የሚሰማው መልዕክትም "ተንኳሽ" እንደሆነ ላቭሮቭ አመልክተዋል።“የወታደራዊ ትብብሩ ዓላማ፣ ከኮሪያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጋር ለውጊያ መዘጋጀት እንደሆነ ግልጽ ሆኗል” ብልዋል ላቭሮቭ።

ሶስቱ አገራት፣ የአሜሪካንን አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ያሳተፈ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ፣ ባለፈው ሳምንት አድርገዋል።የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጁንግ ኡን በበኩላቸው፣ ተከታታይ የሚሳዬል ሙከራዎችን በማድረግ ላይ ናቸው።ሩሲያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላት ግንኙነት በጥሩ ሁኔታ እያደገ መሆኑን ላቭሮቭ ጠቁመዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 የስኳር ፋብሪካ ምርት ማምረት መጀመሩ ተገለፀ!

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 የስኳር ፋብሪካ ዓመታዊ የአጠቃላይ ጥገና እና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቹን አጠናቅቆ ምርት ማምረት መጀመሩ ተገልጿል፡፡ፋብሪካው በበጀት ዓመቱ በ3 ሺህ 600 ሔክታር ላይ የለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት በመጠቀም 151 ሺህ 200 ኩንታል ስኳር እንደሚያመርት ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ከ8 ሺህ 402 ቶን በላይ ሞላሰስ እና ሌሎች ተረፈ ምርቶችን ለማምረት አቅዶ ወደሥራ መግባቱ ተጠቅሷል፡፡

ፋብሪካው የ2016 በጀት ዓመት ዕቅዱን ለማሳካት የሚያስችሉ ዓመታዊ የአጠቃላይ ጥገና እና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማጠናቀቅ በቅርቡ ወደምርት መግባቱን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ መረጃ አመልክቷል፡፡ፋብሪካው በ2015 የምርት ዓመት 88 ሺህ 720 ኩንታል ስኳር ማምረቱ ይታወሳል፡፡

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰኞ እለት ተቋቁሟል የተባለውን " መንበረ ጴጥሮስ " አወገዘች፡፡

አሁን በሕገወጥ ድርጊታቸው የቀጠሉትን ቡድኖች በፍርድ እንደምትጠይቅ አሳውቃለች፡፡ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያን " ሕገወጥ " ባለችው መንገድ በጵጵስና ተሹመናል ካሉት እና በኃላም በእርቅ ወደቤተክርስቲያን ሳይመለሱ ከቀሩት መካከል አባ ገብረማርያም ነጋሳን ጨምሮ 4 አባቶች ትላንት በሰጡት መግለጫ " የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት መንበረ ጴጥሮስ " አቋቁመናል ብለዋል።

ይህ በ2015 ዓ/ም ተቋቁሟል ላሉት የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንበር መሰየም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ሲሉ ተናግረዋል።ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቋሚና ጊዜያዊ ፕሮጀክት መምሪያ ኃላፊ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ወ/ኢየሱስ ሰይፉ መግለጫ ሰጥተው ነበር።በዚህ መግለጫ ፤ " ግለሰቦቹ በሌላቸው ክህነት ነው መግለጫ እየሰጡ ያሉት " ብለዋል።

እነዚህን አካላት ያደረጉት ከቀኖና ውጭ ስለሆነ ዛሬም ቤተክርስቲያን አጥብቃ ታወግዛለች ሲሉ ተናግረዋል።"ቤተክርስቲያን በሕግ በፍርድ ቤት ትጠይቃችለች ፤ በፍትህ መንፈሳዊ ከዚህ ቀደም እንዳወገዘችው አሁንም ህጌ፣ ስርዓቴ፣ ልብሴ ፣ ዶግማዬ ይከበር ትላለች " ሲሉ አክለዋል።"ከዚህ ቀደም በፍ/ቤት ከቤተክርስቲያን እውቅና ውጭ የትም እንዳይንቀሳቀሱ ፣ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደው ነበር ያንን ተላልፈዋል ከዚህ በኃላ በፍርድ እንጠይቃቸዋለን፤ የለበሱት ልብስም የቤተክርስቲያን ስለሆነ እናስወልቃቸዋለን፤ ህገወጥ ናቸው " ብለዋል።

"ከዚህ ባለፈ ይህ የሕገወጥ የሹመት እንቅስቃሴ ጉዳይ ከኦሮሚያ ወገን የተነሱትን ብቻ ሳይሆን ከትግራይ ወገን የተነሱትንም የሚመለከት ነው " ያሉ ሲሆን ሲመቱ ትክክለኛ አይደለም ቅዱስ ሲኖዶስም አይቀበለውም ብለዋል።

በሌላ ዜና

“የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስትያን መንበረ ጴጥሮስ” ሲሉ የሰየሙትን ሲኖዶስ ማቋቋማቸውን ይፋ ካደረጉ የሃይማኖት አባቶች መካከል ሦስቱ ትላንት፤ ማክሰኞ መታሠራቸውን የእንቅስቃሴው አስተባባሪዎች ገልፀዋል።አቡኖቹ የታሠሩት መግለጫውን ከሰጡ በኋላ ሸገር ከተማ አስተዳደር በሚገኘው ቢሯቸው ውስጥ እንዳሉ መሆኑን ከ“መንበር” ምሥረታው አስተባባሪዎች አንዱ መሆናቸውን ለቪኦኤ የተናገሩት ዲያቆን አክሊሉ ዓለሙ ገልፀዋል።

ስለሁኔታው ከሸገር ከተማ አስተዳደርና ከፖሊስ መምሪያው ምላሽ ለማግኘት ያደረኩት ጥረት አልተሳም ብሏል፡፡
ባለፈው ዓመት ተቀስቅሶ የነበረ ተመሳሳይ ውዝግብ ለሰው ህይወት መጥፋት ለንብረት ውድመት ምክንያት እንደነበረ የሚታወስ ነው፡፡በኃላም ችግሮን ውይይት ተካሂዶ መቋጨቱ በወቅቱ ተዘግቦ ነበር።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

🎄ዮም ፎቶ ቬሎ ሜካፕ ሀዋሳ መጀመራችንን ምክኒያት በማድረግ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ አድርገናል

       ከ18000 ብር ጀምሮ

❄️የመስክ እና ስቱዲዮ ፎቶ
ቬሎ፣ሱፍ፣ካባ፣ሜካፕ፣ጥፍር፣ፀጉር
እና ሌሎች የያዙ ጥቅሎች

📞0919868065 / 0992997458

➡️አድራሻ :- ሀዋሳ ፒያሳ ዳሽን ባንክ ፊትለፊት ጋሜ ህንጻ 1ኛ ፎቅ

🟢1st package  
👍Laminate Album 20 page
✔️Board photo 50 x 80 1 pc
✔️Signboard 1 pc
✔️Thank you card 200 pc
🔼Save The Date 5 pc
➕Slideshow
   🆕 የሠርግ አልባሳት  
👍ከለር ቬሎ በመረጡት አይነት
💯የመስክ ቬሎ በመረጡት አይነት
🟢የስቱዲዮ ቬሎ በመረጡት አይነት
♾ሜካፕ
⏰ጥፍር
📌ፀጉር
🔥ካባ
➡️የሙሽራ ሱፍ 2
💸28,000Birr

Читать полностью…

YeneTube

Printer Head ለ Epson L382, L3110 , L3150 L3250 የሚሆን የምትፈልጉ በውስጥ መስመር ያናግሩን @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከዚህ ዓመት ጀምሮ የኬጂ ተማሪዎች እንግሊዝኛ እንዳይማሩ ከልክሏል

በከተማዋ የሚገኙ የመንግስት የግል ትምህርት ተቋማት የኬጂ ተማሪዎች እንግሊዝኛ እንዳይማሩ ክልከላ መጣሉ ተሰምቷል።

የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ምንም እንኳን ክልከላውን በሁሉም ትምህርት ቤቶች እንዲሆን ቢልም የግል ትምህርት ተቋማት በድብቅ ለተማሪዎቻቸው እየሰጡ መሆኑን ለካፒታል የደረሰው መረጃ ያመላክታል።

ክልከላው ከተጣለ 2 ወር ገደማ መሆኑን የሚናገሩት መምህራን እና የተማሪ ወላጆች የግል ትምህርት ተቋማት ከመንግሥት የሚለያቸው ተጨማሪ ትምህርቶችን ሲሰጡ እንደሆነና ለዚህም ሲባል የተለያዩ ቋንቋዎችን በትምህርት ስርዓት ዉስጥ አካተዋል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በሰጠዉ ትዕዛዝ አሁን ላይ የመንግስት ትምህርት ተቋማት ለኬጂ ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ትምህርትን መስጠት ማቆማቸው ለማወቅ ተችሏል።

@Yenetube @Fikerassefa

Читать полностью…

YeneTube

🖐 በትርፍ ሰዓትዎ ተጨማሪ ገቢ 💵 የሚያስገኝ ስራ ይፈልጋሉ?

🚀 አዎን ከሆነ  በካሪስ አድቨርታይዚንግ እጅግ አዋጭ የሆነ የስራ ዕድል ተመቻችቷል!

💡ብቁ እና ልምድ ባላቸዉ ዲጂታል ማርኬተሮች ዘመኑን የሚመጥን የዲጂታል ማርኬቲንግ ዕዉቀት እንዲሁም የዘመናዊ ሽያጭ ጥበብ በአጭር ጊዜ አሰልጥነን ብቁ እናደርጎታለን!

  📚  መሰረታዊ የሆነ ስልጠና

💡Digital Marketing
💡Branding
💡Graphics design
💡Video editing አሰራር

✨ በአንድ ፓኬጅ በመሰልጠን የተፈላጊ ሙያ ባለቤት በመሆን ተጨማሪ ገቢ ያግኙ!

1⃣ በስልጠናው በቂ እውቀት ያካብታሉ

2⃣ ስልጠናውን ሲወስዱ በተግባር የታገዘ ልምምድ እንዲሁም ሲጨርሱ ከእኛ ጋር 100% የስራ እድል ይመቻቻል!

3⃣ በሰሩት ስራ ልክ የሚያድግ የገቢ ምንጭ!

4⃣ የተለያዩ ኘሮጀክቶችን በመስራት ልምድ ይቀስማሉ

5⃣ የተለያዩ ኦንላይን ኮርሶችን በነፃ በቤቶ የሚማሩበት እድል እንሰጣለን!

6⃣ የቢዝነስ እና ሶፍት ስኪል ትሬኒንግን ያካተተ

▫️ለአዳዲስ ተመራቂ ተማራዎች
▫️ለኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች
▫️በተለያዪ ድርጅቶች ዉስጥ ተቀጥረው ለሚሰሩ ሰዎች በትርፍ ሰዓት ሊሰሩት የሚችሉትን የስራ ዕድል አመቻችተንሎታል!

ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነዉ ይመዝገቡ!!

🔈ለተጨማሪ መረጃ
☎️ 0954742475 
☎️ 0926738676 ይደውሉ
Telegram : @Charistechnology

አድራሻ : 22 ጎላጉል ጀርባ ኖህ ፕላዛ 3 ተኛ ፎቅ

Читать полностью…

YeneTube

50/50   ባንክ

    ቤት   በ299ሺ(5%) ብር
"በአልሙኒየም ፎርም ወርክ የግንባታ ጥበብ የሚሰሩ""

"እስከ 6,000,000ልዩ ቅናሽ 30%
❇️ከ27ዓመት በላይ በኮንስትራክሽን ላይ ልምድ ያካበተ

• ሀዋሳ ፡ አርባምንጭ ፡ ባህዳር  መንገድ ስራ  በከፍተኛ ጥራት ሠርቶ ያስረከበ
ሀሮሚያ ዩኒቨርሲቲ ግንባታወችን የሰራ
በማርብል እና ጠጠር ፋብሪካ የተሰማራ

❇️አፍሪካ CDC 2ኪ.ሜ ርቀት፡ ቻድ ኢምባሲ  አጠገብ

🌻 65,395 ካሬ  ላይ ያረፈ ሰፊ መንደር ፡

""ኮምፓውንድ አፓርትመንት ፡
✅ መክፈል ባይችሉ በመሀል አትርፈው ይሸጣሉ
✅ 5% ብቻ ቅድመ ክፍያ በመክፈል፡ ቀሪውን በ3ዓመት ፡ ተጨማሪ 5% ልዩ ቅናሽ

ስትድዮ 56.6ካሬ
       👉56.6ካሬ=299ሺ ብር
      👉57.4ካሬ=300ሺ ብር
አንድ መኝታ
    👉77.7ካሬ,=411ሺ ብር
    👉85.6ካሬ=453ሺ ብር
   👉98.10ካሬ=519ሺ ብር
ሁለት መኝታ
     👉123.3ካሬ=650ሺ ብር
     👉134.5ካሬ=710ሺ ብር
ሶስት መኝታ
    👉146.8ካሬ=775ሺብር
   👉151.6ካሬ=800ሺ ብር
አራት መኝታ
     👉177.1ካሬ =937ሺ ብር
      👉186.9ካሬ=988ሺ ር
👉 ቀሪውን በ3 አመት በ 9 ዙር 
ወይም  50/50 የባንክ አማራጭ

  ቤቶች ተጨማሪ የእንግዳ ክፍል እስከ ባዝሩም አላቸው

የንግድ ሱቆች ከ28ካሬ እስከ 1000 ካሬ ድረስ ለሽያጭ ዝግጁ ናቸው

ለበለጠ መረጃ
+251988887676
+251988885656

Читать полностью…

YeneTube

ባስቸኳይ እርምጃ ካልተወሰደ በትግራይ ያለው የረሀብ አደጋ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ አሳሰቡ።

አቶ ጌታቸው በተመ የሕጻናት መርጃ ድርክት UNICEF የምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪካ አካባቢ ዳይሬክተር ኤትሌቫ ካዲሊ ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት በትግራይ ባለፉት አስር ወራት የምግብ እርዳታ በመቋረጡ ምክንያት ያንዣበበውን አስከፊ ሰብአዊ እልቂት ለመቀልበስ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የ10 ወራት እገዳው ያስከተለውን ከፍተኛ ጉዳት በማመልከት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስበዋል። በክልሉ የምግብ እርዳታው መቋረጡን በመቶ ሺህዎች ላይ የተበየነ «የሞት ቅጣት» ነው ያሉት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ዘግይቶ የሚቀርብ ማንኛውም እርዳታ በኋላ ትርጉም አልባ እንዳይሆን ያላቸውን ስጋት መግለጻቸውን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ኤትሌቫ ካዲሊ በበኩላቸው በክልሉ የድርቅ ሁኔታ መባባሱ አሳሳቢ መሆኑን በማረጋገጥ፤ አስቸኳይ እርምጃ ተወስዶ ለሕጻናትም ሆነ ለማኅበረሰቡ የምግብ እርዳታ ካልደረሰ መዘግየቱ የከፋ ጠኔ ሊያስከትል እንደሚችል ተናግረዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

በጸጥታ ችግሮች ሳቢያ “የገቢ ጉድለት” እንደገጠመው ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ!

ከጸጥታ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ ችግሮች፤ በኢትዮ ቴሌኮም ገቢ ማመንጨት ላይ ችግሮች እየፈጠሩበት መሆኑን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ተናገሩ። ኩባንያው በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት ያጣው ገቢ፤ በቅርቡ በአንድ ዓለም አቀፍ ሪፖርት የተጠቀሰውን ያህል እንዳልሆነም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚዋ የኢትዮ ቴሌኮምን የ2016 በጀት ዓመት የመንፈቅ የስራ አፈጻጸም በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረጉበት ወቅት፤ ኩባንያው በግማሽ ዓመቱ ካጋጠሙት ተግዳሮቶች መካከል አንዱ “በተለያዩ አካባቢዎች ይሰጥ የነበረው አገልግሎት መቋረጥ” መሆኑን ጠቅሰዋል። መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ አገልግሎቱን ለማቋረጥ የተገደደው በአካባቢዎቹ ባጋጠመው “የጸጥታ ችግር ምክንያት” መሆኑ የገለጹት ፍሬሕይወት፤ በዚህም ሳቢያ ኩባንያው “የገቢ ጉድለት” እንዳጋጠመው አስታውቀዋል።

“ተዘዋውረን ካልሰራን እና ጥገና ማድረግ ካልተቻለ፤ የተዘረጉ መሰረተ ልማቶችን አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ካላደረግን ጉድለት ያመጣል። ወይም ያቀድነውን ዕቅድ ሙሉ ለሙሉ እንዳናሳካ የራሱ የሆነ ተጽዕኖ አለው” ሲሉ ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ችግሩን ለጋዜጠኞች አስረድተዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፈው ግማሽ ዓመት 43 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ!

መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ኢትዮ ቴሌኮም፤ ባለፈው መንፈቅ ዓመት 42.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። ኢትዮ ቴሌኮም በዚሁ ጊዜ ውስጥ የደንበኞቹ ቁጥር 74.6 ሚሊዮን መድረሱንም ገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም ይህን የገለጸው የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ ዛሬ ማክሰኞ ጥር 14፤ 2016 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ተቋሙ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያስገባው ገቢ፤ ከእቅዱ 98 በመቶውን ያሳካ መሆኑን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ገቢው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር 26 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል። ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ያገኘው ገቢ 33.8 ቢሊዮን ብር ሲሆን በወቅቱ ያስመዘገበው ትርፍ ደግሞ 9.72 ቢሊዮን ብር ነበር። ተቋሙ ዘንድሮ በግማሽ ዓመት ብቻ 11 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን ፍሬሕይወት ይፋ አድርገዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

🎉Good News for Ethiopian Undergraduate and Masters Program Students !

✅STUDY IN EUROPE ! 🇪🇺 🇮🇹

⭐️ በዚህ Full scholarship ማግኘት አስቸጋሪ  በሆነበት ሰዐት 💯 ወጪዎ ተሸፍኖ በተጨማሪም እየከፈሉ ሳይሆን በአመት እስከ € 11,000 (Euro) እየተከፈሎ በጣሊያን 🇮🇹(Europe) ከፍተኛ ትምህርቶን መከታተል ይፈልጋሉ ?

ታዲያ ምን ይጠብቃሉ ❔

ኑ ወደ Ethio-Genuine-Consultancy ከ Application process እሰከ Visa Process ሙሉ በሙሉ ሀሳባቹን በእኛ ላይ ጥላቹ Europe ትገባላቹ። እኛ እንደስማችን Genuine ነው ስራችን።

⭐️ 100% Application and Visa Success rate !

✅ Requirements for undergraduate students:

1. Passport,
2. High school transcripts,
3. Grade 10 & 12 Matric result.


✅ Requirements for Masters Students :

1. Passport,
2. Bachelor degree certificate,
3. Student Copy
.

Students who have 500+ Entrance Score will be offered big discount.

 ✅ ለበለጠ መረጃ : -

🔵 @Gossa07

☎️ +251935343325 /+393444355194

✅ ቴሌግራም ገፅዓችንን መቀላቀል እንዳይረሱ 👇👇👇:
@Ethiogenuine1
@Ethiogenuine1

📍 Address : Addis Ababa, 22, Tsega Business Center, 7th Floor, Office No - H04 .

🌐 Www.Ethio-Genuine-Consultancy.com

Читать полностью…

YeneTube

ሐብት ካስመዘገቡ 41 ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ውስጥ አንዱ ብቻ ነው ትክክለኛ ተባለ!

ሐብት ካስመዘገቡ 41 ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች መካከል ትክክለኛ ሆኖ የተገኘው አንዱ ብቻ መሆኑን የፌደራል የሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

ባለፉት ስድስት ወራት 41 ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ያስመዘገቡትን ሐብት እውነተኝነት ለማረጋገጥ በተደረገው ማጣራት ትክክለኛ ሆኖ የተገኘው አንድ ብቻ መሆኑን በኮሚሽኑ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ገዛኽኝ ጋሻው መናገራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግቧል።

አዲስ ማለዳ የተመለከተችው ዘገባ እንዳመላከተው ከ41ዱ 24ቱ ከፍተኛ ልዩነት እንዲሁም 16 የሚሆኑት መካከለኛ ልዩነት የተገኘባቸው ሲሆን ትክክለኛ ሆኖ የተገኘው አንድ ብቻ ነው።

ጉዳዩም ለፍትህ አካላት ደርሶ የማጣራት ስራ እየተከናወነ ይገኛል የተባለ ሲሆን በቀጣይ ስድስት ወራት የ55 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የተመዘገበ ሐብት የማረጋገጥ ስራ እንደሚከናወን ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

🖐 በትርፍ ሰዓትዎ ተጨማሪ ገቢ 💵 የሚያስገኝ ስራ ይፈልጋሉ?

🚀 አዎን ከሆነ  በካሪስ አድቨርታይዚንግ እጅግ አዋጭ የሆነ የስራ ዕድል ተመቻችቷል!

💡ብቁ እና ልምድ ባላቸዉ ዲጂታል ማርኬተሮች ዘመኑን የሚመጥን የዲጂታል ማርኬቲንግ ዕዉቀት እንዲሁም የዘመናዊ ሽያጭ ጥበብ በአጭር ጊዜ አሰልጥነን ብቁ እናደርጎታለን!

  📚  መሰረታዊ የሆነ ስልጠና

💡Digital Marketing
💡Branding
💡Graphics design
💡Video editing አሰራር

✨ በአንድ ፓኬጅ በመሰልጠን የተፈላጊ ሙያ ባለቤት በመሆን ተጨማሪ ገቢ ያግኙ!

1⃣ በስልጠናው በቂ እውቀት ያካብታሉ

2⃣ ስልጠናውን ሲወስዱ በተግባር የታገዘ ልምምድ እንዲሁም ሲጨርሱ ከእኛ ጋር 100% የስራ እድል ይመቻቻል!

3⃣ በሰሩት ስራ ልክ የሚያድግ የገቢ ምንጭ!

4⃣ የተለያዩ ኘሮጀክቶችን በመስራት ልምድ ይቀስማሉ

5⃣ የተለያዩ ኦንላይን ኮርሶችን በነፃ በቤቶ የሚማሩበት እድል እንሰጣለን!

6⃣ የቢዝነስ እና ሶፍት ስኪል ትሬኒንግን ያካተተ

▫️ለአዳዲስ ተመራቂ ተማራዎች
▫️ለኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች
▫️በተለያዪ ድርጅቶች ዉስጥ ተቀጥረው ለሚሰሩ ሰዎች በትርፍ ሰዓት ሊሰሩት የሚችሉትን የስራ ዕድል አመቻችተንሎታል!

ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነዉ ይመዝገቡ!!

🔈ለተጨማሪ መረጃ
☎️ 0954742475 
☎️ 0926738676 ይደውሉ
Telegram : @Charistechnology

አድራሻ : 22 ጎላጉል ጀርባ ኖህ ፕላዛ 3 ተኛ ፎቅ

Читать полностью…

YeneTube

50/50   ባንክ

    ቤት   በ299ሺ(5%) ብር
"በአልሙኒየም ፎርም ወርክ የግንባታ ጥበብ የሚሰሩ""

"እስከ 6,000,000ልዩ ቅናሽ 30%
❇️ከ27ዓመት በላይ በኮንስትራክሽን ላይ ልምድ ያካበተ

• ሀዋሳ ፡ አርባምንጭ ፡ ባህዳር  መንገድ ስራ  በከፍተኛ ጥራት ሠርቶ ያስረከበ
ሀሮሚያ ዩኒቨርሲቲ ግንባታወችን የሰራ
በማርብል እና ጠጠር ፋብሪካ የተሰማራ

❇️አፍሪካ CDC 2ኪ.ሜ ርቀት፡ ቻድ ኢምባሲ  አጠገብ

🌻 65,395 ካሬ  ላይ ያረፈ ሰፊ መንደር ፡

""ኮምፓውንድ አፓርትመንት ፡
✅ መክፈል ባይችሉ በመሀል አትርፈው ይሸጣሉ
✅ 5% ብቻ ቅድመ ክፍያ በመክፈል፡ ቀሪውን በ3ዓመት ፡ ተጨማሪ 5% ልዩ ቅናሽ

ስትድዮ 56.6ካሬ
       👉56.6ካሬ=299ሺ ብር
      👉57.4ካሬ=300ሺ ብር
አንድ መኝታ
    👉77.7ካሬ,=411ሺ ብር
    👉85.6ካሬ=453ሺ ብር
   👉98.10ካሬ=519ሺ ብር
ሁለት መኝታ
     👉123.3ካሬ=650ሺ ብር
     👉134.5ካሬ=710ሺ ብር
ሶስት መኝታ
    👉146.8ካሬ=775ሺብር
   👉151.6ካሬ=800ሺ ብር
አራት መኝታ
     👉177.1ካሬ =937ሺ ብር
      👉186.9ካሬ=988ሺ ር
👉 ቀሪውን በ3 አመት በ 9 ዙር 
ወይም  50/50 የባንክ አማራጭ

  ቤቶች ተጨማሪ የእንግዳ ክፍል እስከ ባዝሩም አላቸው

የንግድ ሱቆች ከ28ካሬ እስከ 1000 ካሬ ድረስ ለሽያጭ ዝግጁ ናቸው

ለበለጠ መረጃ
+251988887676
+251988885656

Читать полностью…

YeneTube

ድምጻዊ ሮፍናን " ዘጠኝ " የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበም ለአድማጮች ሊያደርስ ነው!

ከዚህ ቀደም በለቀቃቸው የነጠላ ዜማ እና የአልበም ስራዎቹ ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጣው ድምጻዊ ሮፍናን፤ "ዘጠኝ" የተሰኘ አዲስ አልበም ለአድማጮቹ ሊያደርስ መሆኑን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

የሙዚቃ አልበሙ በዓይነቱ ለየት ያለ በውስጡ "ሀራቤ" እና "ኖር" የተሰኙ ሁለት አልበሞችን እንደሚይዝም ነው ድምጻዊው የገለጸው።አልበሙ ከ3 ሳምንት በኋላ እንደሚለቀቅ የገለጸው ሮፍናን፤ አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ብዙ እንደለፋበትም ተናግሯል።ድምጻዊው ከዚህ ቀደም "ሶስት" እና "ስድስት" የተሰኙ የሙዚቃ አልበሞችን ለአድማጮች ማድረሱ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

በሶማሌ ክልል 75 ሺህ ልጆች ትምህርት አልገቡም!

በሶማሌ ክልል ውስጥ ጥቅምትና ኅዳር ውስጥ በነበረው ጎርፍ ምክንያት ትምህርት ያቋረጡ ከሰባ አምስት ሺህ በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ አለመመለሳቸውን የክልሉ የትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

116ት ትምህርት ቤቶች አሁንም እንዳልተከፈቱና የከፋ ጉዳት ከደረሰባቸው ሃያ ትምህርት ቤቶች በቀር ሌሎቹ በሁለተኛው ወሰነ ትምህርት እንዲከፈቱ ጥረት እንደሚደረግ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አመልክቷል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

🖐 በትርፍ ሰዓትዎ ተጨማሪ ገቢ 💵 የሚያስገኝ ስራ ይፈልጋሉ?

🚀 አዎን ከሆነ  በካሪስ አድቨርታይዚንግ እጅግ አዋጭ የሆነ የስራ ዕድል ተመቻችቷል!

💡ብቁ እና ልምድ ባላቸዉ ዲጂታል ማርኬተሮች ዘመኑን የሚመጥን የዲጂታል ማርኬቲንግ ዕዉቀት እንዲሁም የዘመናዊ ሽያጭ ጥበብ በአጭር ጊዜ አሰልጥነን ብቁ እናደርጎታለን!

  📚  መሰረታዊ የሆነ ስልጠና

💡Digital Marketing
💡Branding
💡Graphics design
💡Video editing አሰራር

✨ በአንድ ፓኬጅ በመሰልጠን የተፈላጊ ሙያ ባለቤት በመሆን ተጨማሪ ገቢ ያግኙ!

1⃣ በስልጠናው በቂ እውቀት ያካብታሉ

2⃣ ስልጠናውን ሲወስዱ በተግባር የታገዘ ልምምድ እንዲሁም ሲጨርሱ ከእኛ ጋር 100% የስራ እድል ይመቻቻል!

3⃣ በሰሩት ስራ ልክ የሚያድግ የገቢ ምንጭ!

4⃣ የተለያዩ ኘሮጀክቶችን በመስራት ልምድ ይቀስማሉ

5⃣ የተለያዩ ኦንላይን ኮርሶችን በነፃ በቤቶ የሚማሩበት እድል እንሰጣለን!

6⃣ የቢዝነስ እና ሶፍት ስኪል ትሬኒንግን ያካተተ

▫️ለአዳዲስ ተመራቂ ተማራዎች
▫️ለኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች
▫️በተለያዪ ድርጅቶች ዉስጥ ተቀጥረው ለሚሰሩ ሰዎች በትርፍ ሰዓት ሊሰሩት የሚችሉትን የስራ ዕድል አመቻችተንሎታል!

ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነዉ ይመዝገቡ!!

🔈ለተጨማሪ መረጃ
☎️ 0954742475 
☎️ 0926738676 ይደውሉ
Telegram : @Charistechnology

አድራሻ : 22 ጎላጉል ጀርባ ኖህ ፕላዛ 3 ተኛ ፎቅ

Читать полностью…

YeneTube

50/50   ባንክ

    ቤት   በ299ሺ(5%) ብር
"በአልሙኒየም ፎርም ወርክ የግንባታ ጥበብ የሚሰሩ""

"እስከ 6,000,000ልዩ ቅናሽ 30%
❇️ከ27ዓመት በላይ በኮንስትራክሽን ላይ ልምድ ያካበተ

• ሀዋሳ ፡ አርባምንጭ ፡ ባህዳር  መንገድ ስራ  በከፍተኛ ጥራት ሠርቶ ያስረከበ
ሀሮሚያ ዩኒቨርሲቲ ግንባታወችን የሰራ
በማርብል እና ጠጠር ፋብሪካ የተሰማራ

❇️አፍሪካ CDC 2ኪ.ሜ ርቀት፡ ቻድ ኢምባሲ  አጠገብ

🌻 65,395 ካሬ  ላይ ያረፈ ሰፊ መንደር ፡

""ኮምፓውንድ አፓርትመንት ፡
✅ መክፈል ባይችሉ በመሀል አትርፈው ይሸጣሉ
✅ 5% ብቻ ቅድመ ክፍያ በመክፈል፡ ቀሪውን በ3ዓመት ፡ ተጨማሪ 5% ልዩ ቅናሽ

ስትድዮ 56.6ካሬ
       👉56.6ካሬ=299ሺ ብር
      👉57.4ካሬ=300ሺ ብር
አንድ መኝታ
    👉77.7ካሬ,=411ሺ ብር
    👉85.6ካሬ=453ሺ ብር
   👉98.10ካሬ=519ሺ ብር
ሁለት መኝታ
     👉123.3ካሬ=650ሺ ብር
     👉134.5ካሬ=710ሺ ብር
ሶስት መኝታ
    👉146.8ካሬ=775ሺብር
   👉151.6ካሬ=800ሺ ብር
አራት መኝታ
     👉177.1ካሬ =937ሺ ብር
      👉186.9ካሬ=988ሺ ር
👉 ቀሪውን በ3 አመት በ 9 ዙር 
ወይም  50/50 የባንክ አማራጭ

  ቤቶች ተጨማሪ የእንግዳ ክፍል እስከ ባዝሩም አላቸው

የንግድ ሱቆች ከ28ካሬ እስከ 1000 ካሬ ድረስ ለሽያጭ ዝግጁ ናቸው

ለበለጠ መረጃ
+251988887676
+251988885656

Читать полностью…

YeneTube

የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ ወደጥር 20 ተራዘመ!

የትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ እስከ 20 ቀን 2016 ዓ.ም መራዘሙን አስታውቋል፡፡በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመፈተን ተገልጾ የነበረው የምዝገባ ጊዜ ከጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ጥር 15 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑ ይታወሳል፡፡ይሁን እንጂ በተፈታኞች ጥያቄ መሰረት የምዝገባ ጊዜው እስከ ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም የተራዘመ ሲሆን÷ ሌሎች ሁኔታዎች ግን ቀደም ሲል በተገለጸው አግባብ እንደሚከናወኑ ተገልጿል፡፡

የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለሚፈተኑ አመልካቾችም ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ለዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና እየተሰጠ ነው ተብሏል፡፡በ2016 አጋማሽ ላይም የመውጫ ፈተናን ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ላሉ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናው ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ይሰጣል መባሉን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ስለሆነም በሐምሌ 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን ተፈትነው ላላለፉ እና ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የመውጫ ፈተናውን በድጋሚ (Re-exam) ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ላሉ ተፈታኞች በሙሉ ምዝገባ የሚያካሂዱትና የመፈተኛ ተቋም (የመንግስት ዩኒቨርሲቲ) የሚመርጡት በዚህ ማስፈንጠሪያ (Link) (https://exam.ethernet.edu.et) መሆኑም ተጠቅሷል፡፡በዚሁ መሠረትም ከጥር 8 እስከ ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የምዝገባ ክፍያ 500 ብር በቴሌ ብር ብቻ በመክፈል መመዝገብ ይቻላል ነው የተባለው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

ለዳሰነች ልዩ ወረዳ የጎርፍ ተፈናቃዮች የተቀናጀ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳሰነች ልዩ ወረዳ፣ የኦሞ ወንዝ ሙላት ባስከተለው ጎርፍ ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች የሚቀርበው ድጋፍ የተቀናጀ እንዲኾን፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጥሪ አቅርቧል።

ማኅበሩ፣ የ44 ሚሊዮን ብር ያህል ድጋፍ እንዳደረገም አስታውቋል። የልዩ ወረዳዋ ተፈናቃይ አርብቶ አደሮች ተወካዮች ደግሞ፣ እየቀረበ ያለው ድጋፍ በቂ እንዳልኾነና ከፍተኛ የውኃ እጥረት መኖሩን አመልክተዋል።

Photo: File
Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

🎄ዮም ፎቶ ቬሎ ሜካፕ ሀዋሳ መጀመራችንን ምክኒያት በማድረግ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ አድርገናል

       ከ18000 ብር ጀምሮ

❄️የመስክ እና ስቱዲዮ ፎቶ
ቬሎ፣ሱፍ፣ካባ፣ሜካፕ፣ጥፍር፣ፀጉር
እና ሌሎች የያዙ ጥቅሎች

📞0919868065 / 0992997458

➡️አድራሻ :- ሀዋሳ ፒያሳ ዳሽን ባንክ ፊትለፊት ጋሜ ህንጻ 1ኛ ፎቅ

🟢1st package  
👍Laminate Album 20 page
✔️Board photo 50 x 80 1 pc
✔️Signboard 1 pc
✔️Thank you card 200 pc
🔼Save The Date 5 pc
➕Slideshow
   🆕 የሠርግ አልባሳት  
👍ከለር ቬሎ በመረጡት አይነት
💯የመስክ ቬሎ በመረጡት አይነት
🟢የስቱዲዮ ቬሎ በመረጡት አይነት
♾ሜካፕ
⏰ጥፍር
📌ፀጉር
🔥ካባ
➡️የሙሽራ ሱፍ 2
💸28,000Birr

Читать полностью…

YeneTube

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአይነቱ የመጀመሪያ ነዉ ያለዉን "ዲጂታል ቀበሌ የሞባይል መተግበሪያ" ወደ ስራ ሊያስገባ ነዉ!

የመንግስት አገልግሎት አሰራር ዉስንነትና ብልሹ አሰራር በሚገለፅበት እንዲሁም ብዙ ቅሬታዎች በሚነሱበት ስያሜ ስም ተሰይሟል የተባለዉ" ዲጅታል ቀበሌ የሞባይል መተግበሪያ" በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወራት በኃላ ወደ ስራ እንደሚገባ ተሰምቷል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኢኖቬሽኝና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ባለቤትነት የኤሌክትሮኒክ እና የሞባይል መታወቂያ (Electronic-ID and Mobile-ID) ሲስተም ለማልማት ከሁለት የሶፍትዌር አበልፃጊ ካምፓኒዎች ጋር ስምምነት ያደረገ ሲሆን በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚያስችል ታምኖበታል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

#ትግራይ

ትግራይ ክልል ውስጥ በ5 መጠለያ ጣቢያዎች ከ900 በላይ ሰዎች ከምግብ እጦት እና ከመድሃኒት እጥረት ጋር በተያየዝ ሞተዋል ሲል የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳውቋል።

የተቋሙ የመቐለ ቅርንጫፍ ፤ ረሃብ የሰው ህይወት መንጠቅ ከጀመረ ወራቶች መቆጠሩንም ገልጿል።
* በሽረ
* አክሱም
* በአብይአዲ
* በመቐለ
* ዓዲግራት ባሉ መጠለያ ጣቢያዎች የሰው ህይወት በረሃብ እና በመድሃኒት እጥረት እያለፈ መሆኑን የሚገልጸው ተቋሙ አንድ ዓመት ከሁለት ወር ምንም እርዳታ ያላገኘ ተፈናቃይ መኖሩንም አሳውቋል።

የዕንባ ጠባቂ ተቋም የመቐለ ቅርንጫፍ ፤ ከህዳር በፊት ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ነበር ግን መንግሥት እርምጃ ባለመውሰዱ የከፋ ችግር ደርሷል ብሏል።

በሽረ የተፈናቃዮች ጣቢያ ፤ 309 አረጋዊያን እና 118 ህፃናት የሚገኙበት 849 ሰዎች ሞተዋል ይህ ሁሉ ሰው በአንድ IDP የሞተው በረሃብ እና በመድሃኒት እጦት ነው ሲል አሳውቋል።

በአክሱም 93 ሰዎች፣ በአብይአዲ 35 ሰዎች፣ በአይደር 4 ሰዎች፣ በሞሞና 2 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንም ተቋሙ አደረኩት ባለው ክትትል ማረጋገጡን ገልጿል።

በአጠቃላይ ክትትል በተደረገባቸው መጠለያዎች 980 ሰዎች ላይ ሞት ማጋጠሙን አክሏል።

ከመጠለያ ጣቢያ ውጭም ያሉ በርካታ ዜጎችም በድርቅ ምክንያት እየተሰቃዩና በተከሰተው የምግብ እጥረት ህይወት እየጠፋ ነው ብሏል።

ፅ/ቤቱ በረሃብ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርት አቋርጠው እንዲሰደዱ ፣ ከ600 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ለመራው ጫፍ ላይ ደርሰዋል ሲል ይፋ አድርጓል።

" አሁንም በርካታ ትምህርት ቤቶች በተፈናቃዮች ተሞልተዋል   እዛ ያሉ ተማሪዎችም ድንኳን ሰርተው ለመማር ተገደዋል " ብሏል።

ምንም እኳን የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ረሃብ አልተከሰትም ቢልም የህዝብ ዕንባ ጠባቂ የመቐለ ቅርንጫፍ ረሃብ መከሰቱን አረጋጫለሁ ብሏል። በፌዴራልም ይሁን በክልል እየተሰጠ ያለው ትኩረትና ድጋፍም የሞተ በመሆኑ በቀጣይ አደጋው የከፋ ይሆናል ሲል አስጠንቅቋል። ህዝቡ ቀጣይ ክረምት አምርቶ እራሱን እስኪመግብ እርዳታ ማግኘት አለበትም ብሏል።

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ባለሃብቶች፣ድጋፍ አድራጊ ተቋማት፣ አቅም ያላቸው ክልሎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ በድርቅ ምክንያት ረሃብ አንዣቧል ፌዴራል መንግሥት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የህግና የሞራል ግዴታቸውን ይወጡ ማለቱ ይታወሳል።

የፌዴራል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ደግሞ በትግራይ ረሃብ ስለመከሰቱ አለመከሰቱ በመዘኛ መስፈርቶች መዝኖ መናገር የሚችለው የፌዴራል መንግሥት ተቋም ነው "ረሃብ የሚባለው ሀሰት ነው" ማለቱ አይዘነጋም።

ከቀናት በፊት ደግሞ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፤ 'ድርቁ ወደ ረሃብ እየተቀየረ ነው' የሚለው ሃሳብ የተሳሳተ ድምዳሜ መሆኑን በማስረዳት ሠብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም በመቻልና የልማት ስራዎችን በማስፋፋት፣ ትርፍ አምራች ለመሆን ይሰራል ብሏል።

በተጨማሪ ከሳምንታት በፊት ኮሚሽኑ በሰጠው ቃል በረሃብ ምክንያት የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ ማረጋገጫ እንደሌለው አሳውቆ ነበር።

የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብ ተቀይሮ የሰውን ህይወት የሚያጠፋበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የሀገሪቱ መዋቅራዊ አደረጃጀት የሚፈቅድ እንዳልሆነም ነው የገለፀው።

የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ከድርቅ ጋር ተያይዞ በክልልና በፌዴራል መንግሥት መካከል አለመግባባት እንዳለ ጠቁመው፤ በድርቅ ምክንያት ስለደረሰ ጉዳት ቁጥጥር እንዳካሄዱና በቅርብ እውነቱን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

Via Sheger Radio
@Yenetube @Fikeryassefa

Читать полностью…

YeneTube

ግብፅ ሶማሊያን እደግፋለሁ ማለቷን ተከትሎ ሶማሊላንድ ‘የውጭ ጣልቃ ገብነት’ እንደምትቃወም ገለጸች!

ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ባደረገችው ስምምነት ዙሪያ ማንኛውንም የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደምትቃወም ገለጸች።የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰኞ ጥር 13/2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ “በስምምነቱ ዙሪያ የሚነሱ ማንኛውንም የውጭ ጣልቃ ገብነትን እንቃወማለን” ብሏል።ከሶማሊያ ተለይታ ነጻ አገርነቷን ያወጀችው ሶማሊላንድ አቋሟን የገለጸችው ግብፅ ከሶማሊያ ጎን እንደምትቆም መግለጿን ተከትሎ ነው።

ግብፅ፣ ከኢትዮጵያ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባችው ሶማሊያ ጥያቄ ካቀረበች ከጎኗ ለመቆም ጣልቃ እንደምትገባ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ መናገራቸው ይታወሳል።ሶማሊላንድ ይህንን ተክትሎ በሰጠችው መግለጫ፣ ከግብፅ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት ከፍ አድርጋ እንደምትመለከት ገልጻለች።ይሁን እንጂ በሶማሊላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ከተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ማንኛውንም አይነት የውጭ ጣልቃ ገብነቶችን እንድምትቃወም አስታውቃለች።

በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ላይ ያላትን ስጋትም እውቅና እንደምትሰጥም ገልጻለች።ሶማሊላንድ “እንደ ሉዓላዊ አገር በተቋቋመ ዓለም አቀፍ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች አከብራለሁ” በማለት ገልጻለች።በቀጠናው ፍላጎት ያላቸው አካላት “ቀጠናዊ መረጋጋትን እና አጋርነትን” በማረጋገጥ ላይ እንዲያተኩሩም ጠይቃለች።

ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር በባሕር በር አጠቃቀም ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነት ላይ ከደረሰች በኋላ ሶማሊያ ተቃውሞ ያቀረበች ሲሆን፣ ግብፅም በተደጋጋሚ የሶማሊያን አቋም ደግፋ አስተያየት ስትሰጥ ቆይታለች።

የሶማሊያውን ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ከግብፅ መንግሥት በቀረበላቸው ግብዣ ወደ ካይሮ በመጓዝ ከፕሬዝዳንት አል ሲሲ ጋር ከተወያዩ በኋላ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው ሁለቱ አገራት ከኢትዮጵያ አንጻር በጋራ እንሚቆሙ የተገለጸው።ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ አገራቸው በሶማሊያም ሆነ በፀጥታዋ ላይ ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት እንዲፈጠር እንደማትፈቅድ እና ለዚህም ግብፅ ጣልቃ እንድትገባ ከተጠየቀች ከሶማሊያ ጎን ትሰለፋለች ሲሉ ተናግረዋል።የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ስምምነቱ በሶማሊያ ላይ የደኅንነት ስጋት የሚፈጥር አለመሆኑን ገልጸው፤ በቀጠናው ያሉ አንዳንድ ኃይሎች አጀንዳ በአፍሪካ ቀንድ ቀውስ መፍጠር ነው ብለዋል።

አምባሳደር ሬድዋን በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት “ኢትዮጵያ ለሰላምና ደኅንነት ቁርጠኛነቷ የሚገለጸው በውድ ልጆቿ ደምና ላብ ነው” ብለዋል።አያይዘውም “ኢትዮጵያና ሶማሊያ ጎረቤት ብቻ አይደሉም። ድንበርም ይጋራሉ። ቋንቋና ባህል የሚጋሩ ወንድማማች አገሮች ናቸው” ሲሉ አክለዋል።የሶማሊላንድ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ደግሞ “ግብፅ በቀጠናው ሰላምና ምርታማ ግንኙነት ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት እንጋራለን” ብሏል።

ከስምምነቱ መፈረም በኋላ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በቀጣናው ከሚገኙ መሪዎች ጋር ተከታታይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ወደ አሥመራ እና ካይሮ ጉዞዎችን አድርገዋል።የሶማሊላንድ መንግሥት በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ልማትን ለማስፈን ከሁሉም ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን እና ትብብር እንደሚያደርግም መግለጫው አክሏል።ሆኖም ግን ውጫዊ ጣልቃ ገብነትን “አጥብቀን እንቃወማለን” ሲል የሶማሊላንድ መንግሥት አቋሙን ገልጿል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…

YeneTube

በእፎይታ የገበያ ማዕከል ጀርባ በደረሰ የእሳት አደጋ ሰባት የንግድ ሱቆችና ሁለት መጋዘኖች ሙሉ በሙሉ ወደሙ!

ትላንት ምሽት 2:47 በአዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኙ የንግድ ሱቆች እና መጋዘኖች ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል።የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን እንደተናገሩት በእሳት አደጋዉ  ሰባት የንግድ ሱቆችና ሁለት መጋዘኖች በዉስጣቸዉ ካሉ ንብረቶች ጋር ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።

በእሳት አደጋዉ በሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሱ ሲሆን በሰባቱ የንግድ ሲቆች የተለያ የልብስ መስፊያ በርካታ ሲንጀሮች ሚሊ በሚሊ የወደሙ ሲሆን በሁለቱ መጋዘን  ውስጥ የነበሩ ጨርቃ ጨርቆችን እና ስፖንጆችም መውደማቸው ተነግራል፡፡ የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 11 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች ከ60 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉ በአካባቢዉ ባሉ የንግድ ሱቆች ተዛምቶ በገበያ ማዕከላቱ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ከሶስት ሰዓት በላይ መፍጀቱን አቶ ንጋቱ ጨምረው ነግረውናል፡፡ አካባቢዉ በከተማ ደረጃ ለእሳት አደጋ ከተለዩ የገበያ ቦታዎች አንዱ ሲሆን በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ አጋጥሞ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።የገበያ ማዕከላቱ የተገነቡበት ግብዓትና የዉስጥ አደረጃጀቱና ስራዎች የሚከናወኑበት ሁኔታ እንዲሁም ለአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች መግቢያ መንገድ ከአጋላጭ ሁኔታዎቹ የሚጠቀሱ ናቸዉ ተብላል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa

Читать полностью…
Subscribe to a channel