wegoch | Unsorted

Telegram-канал wegoch - ወግ ብቻ

18304

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch ✔ @zefenbicha Creator @leul_mekonnen1

Subscribe to a channel

ወግ ብቻ

የቆሰለ ነገር ፣የከሳ ፣የኮሰመነ እንሰሳ እሚያድን አውሬ ያስጠላኛል ምቹ ግዜ እየጠበቀ ድምፁን እና ሁኔታውን የሚቀያይር ሰው ግን ያስፈራኛል።

ስዩም ፦

ጓደኛው ነኝ ጓደኛዬ ግን አይደለም።
ብዙኅ አሳልፈናል ። ቢሰማብኝ የማፍረውን ነገር ወይ ቢሰማብኝ ጉድ የሚያደርግብኝን ነገር አልነግረውም ።

እፈራዋለሁ። ቋሚ ወዳጅ ስለሌለው እና
ዋሉልኝ ያለቸውን ሰዎች ሁሉ በየምክንያቱ ስለሚተዋቸው እፈራዋለሁ ።

ከጓደኞቹ X ስር ስለማይጠፋ ስሜቱን ሁሉ የተሰማው ሰዓት ስለማያንፀባርቅ

አብሬው ሆኜ አይጥ ለመያዝ ትክ ብላ እንደምታደባ ድመት ነው የማየው። እሱ እንደድመቷ ትኩረት ሲያደርግ ሁኔታው እንደድመቷ አይነት አይደለም አያስታውቅበትም ።

ዘና እያለ እየሳቀ ሚስጥር እየነገረ ነው
ሚስጥር የሚያስወጣው ።

ስዩምን እፈራው ነበረ .....!

ችግር ገጠመኝ ከሁሉም በላይ አብሮኝ ሆነ ያለውን ሁሉ ሰጠኝ አሰጣጡ ስሙልኝ እዩልኝ ያለው አልነበረም

በችግሬ አብረውኝ ያልነበሩትን ስወቅሳቸው እያገዘ አላባባሰብኝም... "ተዋቸው አልሞላ ብሎቸው ነው" አለኝ ....ከነሱ ጋ ሆኜ ያጣጣልኩት ስዩም አብሮኝ ቆመ ....

ተፀፀትኩ ...!

ከብዙ ግዜያት በኋላ ስዩምን በየወሬው እንደዚ አትመስለኝም ነበር እያልኩ እሱ ላይ ያለኝን አቋም ተናዘዝኩ

አልተናደደም ሳቀ

ስልከው እና ሲላከኝ እንደኩያ አይደለም እንደታናሽ ነው ሲተማመንብኝ እንደታላቅ ነው ...!

እሚያግዘን እና የሚኮራብን ወዳጅ የኛ ሲሆን የሚሰማውን ምቾት አሰማኝ

ከጥቂት ግዜ በኃላ ...

ስራ በዛብኝ ብዬ የሰጠሁንት ላግዝ ብሎ የወሰደውን ሙሉ ውክልና ተጠቅሞ መኪናዬን ሸጦ አውሮፓ መግባቱን ከሳምንት በሆላ ሰማሁኝ ...

ስስቅ ላየኝ ሰው ተታልዬ አልመስልም ነበር ...

ማመን ከመጠራጠር በላይ ዋጋ ያስከፍላል ማለት ነው ??
መፍራት ከመድፈር በላይ አቅም አለው ማለት ነው ??
ኮቴ በሰማን ቁጥር እየባነንን የት ድረስ እንሄዳለን ??

የሄድንበትን መንገድ እየጠየቅን መሄድ የሰውነት እጣ ፈንታ ነው ??....

በርግጥ
የግዜ ጉዳይ እንጂ
ከተካደ ሰው የከዳ ሰው ያሳዝናል!!

By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

የ ሥዓሊ እና መምህር ኃይሉ ክፍሌ

"ተገማች፡ ዋዜማ" የሥዕል አውደርዕይ

እዚህ ትርዒት ላይ ተገኝቼ፣ በከተማ ዝመና ውስጥ የማንነትንና የትዝታን ትርጉም የሚፈትሹ ስራዎችን ተመልክቻለሁ። የጥበብ ስራዎቹ የሚጠቀሟቸው ቁሶችና የሚያነሷቸው ሰብአዊ ጥያቄዎች ቆም ብሎ ለማሰብ ትልቅ እድል ይሰጣሉ። የለውጥ ሂደቱ ወዴት እየወሰደን ነው? የጋራ ትዝታችንን እያካተትን ነው ወይስ እየረሳን?
እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን የሚመልስ ድንቅ ትርዒት ነው። እድሉ ያላችሁ እንዳያመልጣችሁ!

📍 እስከ ግንቦት 24 ድረስ ክፍት ነው


@Seiloch


#Hailukifle #artExhibition.

Читать полностью…

ወግ ብቻ

ሶምሶማ የአጫጭር ልቦለዶች መጽሐፍ
-በጃፋር መጽሐፍት መደብር(ለገሀር)
-አብዱ book delivery (ፒያሳ)
- +251994886247 ሰለሞን አራት ኪሎ ያገኙታል።@sirakoo
@wegoch
@wegoch
@wegoch

Читать полностью…

ወግ ብቻ

📌 በሀዋሳ ከተማ አዲስ የስነ-ጥበብ ትምህርት ቤት የምዝገባ ጥሪ!
ጥበብን ለሚወዱ እና ተሰጥኦአቸውን ማሳደግ ለሚፈልጉ ሁሉ ታላቅ እድል! በሀዋሳ ከተማ ከዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር አዲስ የስነ-ጥበብ (ስዕል) ትምህርት ቤት ስራ ሊጀምር ዝግጅቱን አጠናቋል።
🎨 ለምን ይመዘገባሉ?
• በዘርፉ ብቁ በሆኑ ባለሙያዎች የታገዘ ስልጠና ለማግኘት።
• ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በተቀናጀ መልኩ እውቀትን ለማዳበር።
• የፈጠራ ስራዎትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር።
🌟 የእርስዎ ድርሻ፦
ጥበብ የሀገር መገለጫ ናት! ይህ መልዕክት እንዲደርሳቸው የሚገባቸው ወጣቶች እና ፍላጎቱ ያላቸው ግለሰቦች እንዲያውቁት በማጋራት (Share በማድረግ) ማህበራዊ ሀላፊነትዎን ይወጡ።
ምዝገባው ተጀምሯል!👇👇 link ይጫኑ
https://tally.so/r/D4Jjrl.

Читать полностью…

ወግ ብቻ

የሳሪሱ ወጣት እና የቱርኳ Player
-------------------------------------

ምነው ባላወቅኳት ያልኩበት ጊዜ ነበር...! at that time She gave me a Trauma. የደግነት ማስኳን አጥልቃ ነገር ግን የክ-ፋት ሀሳቧንም በውስጧ ሰቅዛ ተለሳልሳ ስትቀርበኝ ምን ነበር አይኔን የጋረደው..? 😁
.
.
እንዴት ልታሳየኝ የፈቀደችውን ብቻ ተመለከትኩላት..? ልትደብቅ የሞከረችውን ማንነት እንዴት ማየት አቃተኝ..? ወቅቱ 2014 ዓ.ም ነው። ወርሀ መጋቢት። ክስተቱ ዛሬ ድፍን አራት አመት ሞላው። በአንዲት የቢሾፍቱ ቆንጆ የተታለልኩበት ሁኔታ እና አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር። አጃጃለችኝ። አሞኘችኝ። አጭበ-ረበረችኝ። አወጫበረችኝ። የምትኖረው ቱርክ ነው። በወቅቱ Turkey መኖር ከጀመረች 3 አመታትን ያህል አስቆጥራለች። የተዋወቅነው በ Facebook ነው። Long Distance Relationship መሆኑ ነው እንግዲህ። ከ Messanger ወደ Telegram ባደገው የስልክ ልውውጣችን - በየቀኑ ለሰአታት በ Video call እናወራ ነበር። አስታውሳለሁ የሆነ ሰአት ላይ እንዲሁ በ Telegram - Video call አውርተን ስንጨርስና መጨረሻ ላይ ቻው ስንባባል - ስልኩን "አንተ ዝጋው..አንቺ ዝጊው..አንተ ዝጋው.." ተባብለን እናውቃለን። ከአንዴም ብዙ ጊዜ። Straight 5 ሰአት ያህል በስልክ የምናወራበትም ጊዜም ነበር።
.
እንደ እኔ እንደ እኔ ይህ ፍቅር የሚባለው ነገር መጃጃል ነው የሚመስለኝ።It is all Imagination. Glazing a person without any valid reason. There is no reason to glaze someone like that. ይህ ጉዳይ በሳይንሳዊው ዓለም Limerence ወይም ደግሞ Halo Effect ተብሎ ይጠራል። አንድ ሰው ሲያፈቅር አንጎሉ ውስጥ የሚረጩት Dopamine እና Oxytocin ልክ እንደ እ-ፅ ናቸው። እነዚህ ኬሚካሎች ሲበዙ ደግሞ... የወደድነውን ሰው ድክመት እንዳናይ ያደርገናል፣ የማይረቡ ነገሮችን እንደ ትልቅ ቁምነገር እንድንቆጥር ያደርገናል፣ በዚህ ሰዓት የምንወስነው ውሳኔ Logic የለውም።
.
ለማንኛውም.. የባለታሪካችንን ስም R እንበለው። R እሳት ነች ፤ ዛሬ ላይ ሁሉም ነገር አልፎ ሳስበው አድናቂዋ ነኝ። እንዴት እንዳወጫበረችኝ ሳጤነው በራሴ ሽምቅቅ እላለሁ። ቢሾፍቱ ተወልዳና አድጋ የመሀል ከተማ ልጅ [ የአዲስአበባ ልጅ ] ለዛውም የሳሪስ ልጅ ላይ ድራማ የሰራች እሳት ናት። መጀመርያ ከእኔ ጋር የፍቅር ግንኙነት ስትጀምር ሌላ ያላለቀ ግንኙነት ላይ እያለች ነው። እኔ ይህንን አላውቅም ነበር። መጨረሻ ላይ ነው የደረስኩበት። መጀመርያውኑ ፍቅረኛ እያላት ለምን ከእኔ ጋር መሆን ፈለገች..?
.
ከእኔ ጋር እንደተዋወቅን እንዲሁም ለረጅም ጊዜ [ ለ 4 ወር ያህል ] in Contact እያለን የበፊት ፍቅረኛዋን ሙሉ ለሙሉ አልተወችውም። በሳምንት 1ዴ ወይም 2ቴ እየደወለች ታወራዋለች። ከእኔ በፊት የነበረውን ልጅ ከመተዋወቋ በፊት ደግሞ ሌላ ፍቅረኛ ነበራት - unfortunately ያንንም አልተወችውም። ከዛ በፊትም ሌላ ፍቅረኛ ነበራት - ያንንም አልተወችውም። ሁላችንንም አልተወችንም። እንደ የቤት አውቶሞቢል [ የቤት መኪና ] በአንድ ጊዜ 4 ሰው አሳፍራ ነበር ስትጓዝ የነበረው። ልጅቷ Multi-tasking ትችላለች። በአንድ እጇ ለኔ ቴክስት እየፃፈች፣ በሌላኛው እጇ ደግሞ ከሌላው ጋር ቪዲዮ ኮል ታደርጋለች። 4 መኪና በአንድ ጊዜ የምትነዳ Formula 1 ድራይቨር ናት። ይሄን ሁሉ መጨረሻ ላይ ነው የማውቀው። ከአንድ ወንድ ጋር ሆና - ወደ ሌላ ወንድ። እኔን አስምጣ ወደ ሌላ - ያኛውንም አስምጣ ወደ ሌላ - ይሄኛውንም አስምጣ ወደ ሌላ። She is a player type of sh-it.
.
በአንድ ጊዜ አራት ወንዶችን እንደ ቼዝ ጠጠር እያገላበጠች ስታጫውት አንዱ ለሌላው እንቅፋት እንዳይሆን ያደረገችው Scheduling የሚገርም ነበር። እኔ ስልኩን "አንቺ ዝጊው.. አንተ ዝጋው" እየተባባልኩ በቪዲዮ ኮል ስሟገት፣ እሷ ግን ለካ በሌላ ስልኳ ሌላኛውን "አንተ ዝጋው.." እያለችው ነበር። ፍቅር ሳይሆን ለካ የኔትወርክ መጨናነቅ ውስጥ ነበርኩ..😁 በነገራችን ላይ.. እኔ በጣም ጠንቃቃ ነኝ። እንደ እኔ ተጠራጣሪ ሰው አልነበረም / አሁንም የለም። ማንንም አላምንም። መጨረሻ ላይ ይሄ ባህሪዬ ወይም ጥርጣሬዬ [ my Gut felling ] ነው እውነታው ላይ እንድደርስ ያደረገኝ። እኔ ጥላዬንም አላምንም። እሷን ግን እንዴት ላምናት እንደቻልኩና - ሙሉ ሀሳቤን እንደሰጠኋት ሳስብ ይገርመኛል። እንኳን ክፉ ድርጊት ሊያደርግ ያሰበን ሰው ይቅርና ያላሰበን ሰው ራሱ የምጠራጠር አይነት ሰው ነኝ።
.
ልባችሁ የሆነ ነገር ሲነግራችሁ አትናቁት። ልባችሁ የሚነግራችሁን አትናቁ። እኔ ተጠራጣሪው የሳሪስ ልጅ፣ በውበቷ ምክንያት እውነታው ተጋርዶብኝ Gut Fellingኤን አላዳመጥኩም ነበር። ቆንጆ ፊትና የተረጋጋ አንደበት ሁልጊዜም ቅንነትን አይወክሉም። አንዳንዴ እጅግ Calculated የሆነ አቀራረብ ከጀርባው የተቆፈረ ጥልቅ ጉድጓድ እንዳለው ማወቅ ነበረብኝ። እኔ ተጠራጣሪ ነኝ እያልኩ ግን የእኔ Gut feeling የሚሰጠኝን ምልክት ውበቷ ሸፍኖብኝ ነበር። ጥርጣሬ መጥፎ አይደለም። መጠርጠር ማለት ነፍስህ ራስህን እንድታድን የምትሰጥህ Alarm ማለት ነው። Infact በመጀመርያዎቹ ሳምንታት ያሳየችኝ እጅግ Calculated የሆነ - እንዲሁም የተጠና አቀራረብ አውሮኝ ነበር።
.
በውበቷ አሻፍዳኝ፣ በምላሷ አታላኝ የገባሁበት የ 6 ወር የፍቅር ህይወት በመጠኑም ቢሆን Scar ጥሎብኝ አልፏል። ፍቅር እውር ነው ይላሉ። እኔ ግን ሽፍድናዬ ነው ያሳወረኝ እላለሁ። ልጅቷ ቆንጆ ናት። በተለምዶ ቀይ የምንለው ወይም Light skinned የሆነው የቆዳ ቀለሟ - እንዲሁም ሰላም ተስፋዬን የሚመስለው መልኳ - ጨዋ ጨዋ የምትጫወተው ነገር - ምሁር ምሁር አንባቢ አንባቢ የሚያደርጋት ነገር - ይሄ ሁሉ ተደማምሮ አስምጣኝ ነበር። በኋላ ላይ ግን ሁሉንም ነገር ስደርስበት እኔ ብቻ አይደለሁም የተጣላኋት። እያንዳንዱ ስታወራቸው የነበሩ ወንዶችን ሰብስቤ እስካሁን እየተጫወተችብን እንደሆነ ነግሬያቸው አስረድቻቸው እነሱም አይንሽን ለአፈር ብለው ተለይተዋታል።
.
ታዲያ በመጨረሻ ሁሉንም መኪናዎች በአንድ ጊዜ ለማሽከርከር የሞከረችው Formula 1 ድራይቨራችን፣ በራሷ ስህተት Crash አደረገች። እያንዳንዱን ተሳፋሪ / ተበዳይ ሰብስቤ እውነታውን ሳስረዳቸው፣ ለካ ሁላችንም በአንድ ቃል ተገዝተን፣ በአንድ መስመር ስንታለል የነበርን ምስኪኖች ነን። ፍቅር እውር አይደለም ፤ ፍቅር አስተዋይ ነው ፤ እውር የሚያደርገን ግን የምናየው ውበት ሳያንስ የምንመኘው ህልም ነው። ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው ግን ይሄ ራሱ አንድ ትልቅ ትምህርት ነው። አሁን የገዛ ጥላዬንም ቢሆን ፋይዳ መታወቂያ / National ID ካላሳየኝ አላምነውም..! 😁

By Fraol Habesha

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

ከአንዲት ቆንጅዬ ልጅ ጋ ነበርኩ። መኪና ውስጥ ነበርን ፒዛ እየጋበዝኳት አስተናጋጁ ሲያልፍ በእጄ ቢል እንዲያመጣልኝ ነገርኩት

ቢል ይዞ መጣ

እያየኝ ከፊት ከኃላ ኪሴ አውጣጥቼ ሂሳብ ከፈልኩ ...
ሄደ .... መልስ መጠበቅ ጀመርኩ አልመጣም ጠበኩት አልመጣም ተበሳጭቼ ክላክስ አስጮህኩ

(ሱሰኛ ይመስላል ፣ የቀረውን ገንዘብ ለማስቀረት አስቦ ነው ፣ ጉርሻ በፍቃደኝነት የሚሰጥ እንጂ በብልጠት የሚዘገን አይደለም ፣ ሲቆይብን ሰልችቶን እንድንሄድ ነው )

ያስጮኩትን ክላክስ ሰምቶ መጣ

"መልስ ስጠን እንጂ ጌታው "አልኩት

"የሰጠኸኝ ስድስት መቶ ነው ሂሳቡ ደሞ ስድስት መቶ ሰላሳ አምስት ብር ነው "አለኝ ( ስበረብር ስላየኝ የለው ይሆናል በማለት ተሳቆ ነው እንዳልገረጣ ይጎላል ያላለው )

ከሌለህ ብዬ ነው አይነት ፊት አሳየኝ ። አንዳንድ አድራጎት የሚያገዝፈው አደራረጉ ነው ።

ይቅርታ ቢሉን በደንብ ስላላስተዋልኩት ነበር።
በጣም አመሰግናለሁ አልኩት

እንደገና ኪሴን በርብሬ ድፍን ሁለት መቶ ብር ሰጠሁት እንዲመጣልኝ እንዳልቸኮልኩ እንዲሄድልኝ ቸኮልኩ
መልስ ሊያመጣልኝ ሄደ

ሳይነግሩን ለዋሉልን እየነገርን መዋል ነውር ነው አይደል ?
ሳይመጣብኝ ሄድኩኝ ።

By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

ሳሯን . . .
-----------

አንድ ድሮ መቀለ መካነ ኢየሱስ ቤ/ክርስቲያን አንድ "ገበሬ ነኝ" ይሉን የነበሩ ከአድዋ? ይመጡ የነበሩ አባት ስለ ዕምነት የነገሩን ምሳሌ አለች። ሰውዬው ተንሸራተው ወድቀው ከገደል አፋፍ ላይ ተንጠልጥለዋል። ወደገደሉ ከመውደቅ ያዳነቻቸው አንዲት ገደሉ አፋፍ ላይ የበቀለች ሳር ነች። እሷን ይዘው ጥቂት እንደቆዩ እጃቸው ዛለ። ሊወድቁ ሆነ። ይሄኔ ድምፅ አውጥተው ፀለዩ።

"ጌታ ሆይ አድነኝ!"

ይሄኔ መልዓክ ብቅ አለና ሰውዬውን "በአምላክህ አዳኝነት ካመንክ ላድንህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኬ የመጣሁ ነኝ!" ይላቸዋል።

ሰውዬውም "ታዲያ ምን ትጠብቃለህ፣ አምናለሁ! አድነኝ!" ይላሉ።

መልዓኩም "መጀመሪያ የያዝካትን ሳር ልቀቅና!" አላቸው።

* * *

ሳሯን አስለቅቀኝ 🤲

By gemechu merera fana

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

''ማንቺስተር ያሸነፈ ቀን !''

ትናንት ማንቺስተር አሸንፎ ደጋፊዎቹ መሬት አልበቃቸው ብሎ ሳይ እንደሁሌውም ትዝያለኝ ያ ራሱን 'የአርሰናል ቁልፍ ሰው' አድርጎ ይቆጥር የነበረው ታናሽ ወንድሜ ነው

በፍቃዱ ብርሃኑ ይባላል… እማዬ “ፍቃዴ” ትለው ነበር፡፡ እኔን ጨምሮ እሱን የሚያውቁት ሁሉ “ፍቄ” ብለው ነበር የሚጠሩት፡፡ በህጻን አዛውንቱ ተወዳጅ የነበረ ወንድሜ .... ዛሬ በህይወት የለም።

ፍቄ ሁሌም ማታ የጠንቋይ መጣፍ የመሰለ ደቃቅ ጽሁፍ የታጨቀበትን ሊብሮ ጋዜጣ ይዞ ወደቤት ይመጣል። ገና ጎረምሳ ነው፡፡ ረጅም ...1 ሜትር ከ87 ሳ.ሜ ቁመቱን በአሮጌው ሶፋ ላይ ዧ አድርጎ እንሩን አንፈራጦ ይቀመጥና …. ፊቱን ጋዜጣው ውስጥ ቀብሮ …ኮስተር ፈታ እያለ ‘የነቡናን እና የነአርሴን' ወግ ይጨመጭማል።

“… ምንድነው ግን የምታነበው?” ትለዋለች እማዬ፡፡ ”ስፖርት ነው እማ.. ብዙም አታውቂውም” ይላታል።

”ኡኡቴ! አዋቂ ነኝ ብለህ ሞተሃል..ደሞ ለቅሪላ ወሬ!” ትላለች።

” ጭንቅላትህን በኳስ ዕወቀት ከምትሞላ ትምህርትህ ላይ አትበረታም ነበር? …ደደብ!! …ነገ አርሰናል መጥቶ ይፈተንልህ መሰለህ? ..” ብዬ ልጮህበት እፈልጋለሁ።

ግን ብዙ ጊዜ ይህንን ብዬው ጉሮሮዬን አመመኝ እንጂ ያመጣሁት ለውጥ የለም።

እማዬ ማለዳ ወደቤተክርስቲያን በምትሄድባቸው ቀናት ወደእግዜር ከምትወስደው የራሷ ጥያቄዎች በተጨማሪ ፍቄ የሚያዛት ተጨማሪ ፀሎት አለ። ጨዋታ ያለ ቀን ወይ ቡና… ወይ አርሰናል እንዲያሸንፍ እንድትጸልይለት ይነግራታል፡፡

የሆነ ጊዜ የቡና ረከቦቷን የምትሸፍንበትን ጨርቅ አነስቶ ጥሎ በምትኩ ሁለት የቡና አርማ ያለበትን ባንዲራ አሰርቶ አመጣና አንዱን “የቡና ስኒ በቡና አርማ ነው መሸፈን ያለበት” ብሎ ሰጣት፡፡ አንዱን ደግሞ የቤታችን ግድግዳ ላይ በሚስማር መትቶ ሰቀለው፡፡ ቤት ስገባና የሆነውን ሳይ ተናደድኩና ገንጥዬ ጣልኩበት፡፡ የረከቦቱን ግን እማዬ ከለከለችኝ፡፡ "ይሁን፣በገዛ ሲኒዬ ምን አገባህ" ብላ ፡፡ እነዚያ ጨርቆች ዛሬም ድረስ ቤታችን አሉ፡፡

እማዬን “ እሙ!” ነበር የሚላት፡፡ የሚተኛው ከሷ ጋር ነው፡፡ የመጨረሻ ልጅ ስለሆነ ነው መሰለኝ እንደነፍሷ ትወደዋለች፡፡ ጨዋታ ያለ ቀን ታዲያ እማዬ ማለዳ ወደቤተክርስቲያን ለመሄድ ስትነሳ የተሸፈነበትን ብርድልብስ ገለጥ ያደርግና “እሙ! ዛሬ የኔ ቡድን ይጫወታል።እንዲያሸንፍ ጸልዪልኝ ...ካሸነፍን ስለት ታስገቢልኛለሽ! ” ይላታል፡፡

“አይ እዳዬ!..... ደሞ ዛሬ አቡነ ተክለሃይማኖት እንዴት ያረጉኝ ይሆን” ትላለች ። እማዬ ስትምልም ስትለምንም በአቡነ ተክለሃይማኖት ነው፡፡

አንድ ቀን 'የምር ስለሱ ኳስ ጨዋታ ትጸልያለሽ?' ብዬ ጠየቅኳት፡፡ “እንዴ አዎና!...ተክልዬ !! የዚህን ልጅ ልብ የበሉት ባለኳሶች እንዲያሸንፉ እርዱልኝ…..ጉድ እንዳይሰሩኝ ኋላ! እላቸዋለሁ” አለችና አሳቀችኝ።

ምን ታድርግ? የርሱ ክለብ የተሸነፈ’ለታ ቤታችን የሚፈጠረውን ነገር ስለማውቅ አልፈረድኩባትም፡፡

ጨዋታ ያለ ቀን ገና በጠዋቱ አጠገቤ ቆም ይልና…”መላ’ዬ …ጨዋታው 3 ከ 45 ይጀምራል። ከዚያ በፊት ሃይላይት አለ። ወደ አምስት ሰዓት አካባቢ ያልቃል። እንደጨረስኩ ወዲያው እመጣለሁ።” ይላል።

ማስፈቀዱ ነው፡፡ ዝም እላለሁ።ቆሞ ያየኛል።ዝም እላለሁ። አይሄድም፡፡ እኔ ጥዬው እሄዳለሁ።

አንዳንዴ የሆነ ልቡን ስልብ አድርጎ ራሱን የሚያስተው ነገር አለ፡፡ ሲጨነቅ ወይም ሲበሳጭ እንዲያ ይሆናል፡፡

አርሰናል የተሸነፈ’ለት ታዲያ ብዙ ጊዜ ያ ህመም ይነሳበታል፡፡ ቤት እንደገባ በዚያ ቁመቱ ሶፋ ላይ ዧ ብሎ ይወድቃል፡፡ ጸጥ ነው የሚለው፡፡ አንዳንዴ ሞተ ብለን የምንጮህበት ቀን አለ።ውሃም ጸበልም ደፋፍተንበት ነፍስ ከዘራ በኋላ “ደህና ነኝ እኮ” ሲል ደግሞ የኔ ንዴት በተራው አናቴ ላይ ይወጣል።

“አንተ በማይረባ ኳስ እየመጣህ ትዘረጋለህና እኛ መጨነቅ አለብን?” ብዬ እጮህበታለሁ፡፡ መልስ አይሰጠኝም፡፡ሌላ ቀንም እንዲሁ ይሆናል፡፡

የሆኑ ከሌላ ሰፈር የሚመጡ የጊዮርጊስ ይሁኑ የማንቺስተር ደጋፊዎች እሱን ሁሌም እንደተቃረኑት ነበር። ኳስ የሚያዩት አብረው መሰለኝ ፡፡

ጨዋታ ያለ ቀን ታዲያ...ብዙ ጊዜ እኩለ ሌሊት ከእንቅልፌ የሚያባንነኝ በራችን አቅራቢያ የምሰማው የብዙ ልጆች ዘፈን የሚመስል ጫጫታ ነበር። እኛ ቤት በር ላይ አርሰናልን የሚሳደብ ዘፈን ከሰማሁ በቃ ነገር አለ ማለት ነው !።

ፍቄን ለማብሸቅ የሚዘፈን ዘፈን መሆኑን አውቃለሁ።
ልጆቹ የሚሉት ነገር አይገባኝም። ግን ሁለቱ ቡድኖች ከማንም ጋር ይጫወቱ ብቻ አርሰናል ከተሸነፈ ወይም ማንቺስተር ካሸነፈ እሱን ለማብሸቅ እኩለ ሌሊት በራችን ላይ ይመጡና ይጨፍራሉ።

አንድ ቀን ከነሱ ጋር ሲደባደብ ፖሊሶች ደረሱና ብዙዎቹን ያዟቸው፡፡ እሱንም ይዘውት መኪና ላይ ከጫኑት በኋላ የኔ ወንድም መሆኑን ሲነግራቸው ደውለው ጠርተውኝ ፊቴ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ለቀቁት፡፡ ለእማዬ ብዬ እንጂ እስር ቤትን ትንሽ ቢቀምሳት ቅር አይለኝም ነበር፡፡

እሱ የሚደግፈው ቡድን ያሸነፈ’ለት ደግሞ ታሪክ ይገለበጣል፡፡እማዬ ይህንን ስትሰማ ወደሰማይ እያንጋጠጠች “ዛሬስ ተክለሃይማኖት ገላገሉኝ !” ትላለች።

የዚያን ቀን ታዲያ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ አይወስደውም። ብቻውን ይስቃል። አልጋው ራስጌ ፎቷቸውን የሰቀለውን ማንነታቸውን የማላውቃቸውን ተጨዋቾች በተኛበት አንጋጦ ያያቸዋል፡፡ ጸጥ ባለው ሌሊት ድንገት ይነሳና “ይሄ የተረገመ ልጅ! ሰራላቸው እኮ!” ብሎ በሳቅ ፍርስ ይላል።

አንዳንዴ ዝም ብዬ ሳየው ጤነኛ ሁሉ አይመስለኝም ነበር ።እማዬ ግን “ተወው ልጅ አይደል? ብቻ አይመመው እንጂ ሲለፈልፍ ቢያድር እኔ ምን ቸገረኝ…ሲያድግ ይተወዋል” ትላለች፡፡

ፍቄ ገና በ21 ዓመቱ አንድ እሁድ ቀን ድንገት ራሱን ስቶ ወደቀ፡፡ ሆስፒታል በገባ በሶስተኛ ቀኑ …እኛንም የሚወዳቸውን ቡናና አርሰናልንም ሳይሰናበት በዚያው ሄደ።

የቀብሩ ዕለት የነበረው ህዝብ ብዛት እስካሁን ሳስበውም ይገርመኛል። በዚያ እድሜው ትምህርቱን ትቶ በሚሰራው ስራ የሚያገኘውን ደመወዝ ሁሉ የሰፈር አቅመደካሞችን ፣ ልጅ ያላቸው የኔ ቢጤዎችን ወዘተ በቋሚነት ይረዳበት እንደነበር ያወቅኩት የለቅሶው ሰሞን ሰዎች ስለርሱ ሲያወሩ በሰማኋቸው ታሪኮች ነው፡፡

በስሙ ትልቅ የእግር ኳስ ግጥሚያ ተዘጋጅቶለትም ነበር፡፡ የዋንጫው ቀን አሸናፊውን ቡድን ስሸልም ስሜቴን መቆጣጠር አቅቶኝ ነበር ፡፡

አሁንም ታዲያ ኳስ በሚታይባቸው ቤቶች በኩል ሳልፍ የደጋፊዎችን ጩኸት ስሰማ ፊቴ ላይ ድቅን የሚልብኝ አሱ ነው ። ምን ያደርጋል ያንን ምድር የማይበቃው የሚመስል ዋልያ …ያች ቀዝቃዛ ቀን እንደዋዛ ይዛው ሄደች....የርሱ መጉደል በቤታችን ይዞት የመጣው ከባድ ሃዘን እናቴን ህመምተኛ አድርጓት ኖሯል፡፡ ባሰብኩት ቁጥር የሚናፍቀኝ ከፊቱ የማይጠፋው ፈገግታ ነው፡፡

ፍቄ ወንድሜ ! ….ነፍስህ በሰላም ትረፍ !!

By Melaku Berhanu

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

እውነት ሁሉም ነገር 'upgrade' ያረጋል! ህይወት፣ ኑሮው፣ ሳሩ፣ ቅጠሉ፣ ሰፈሩ፣ መንደሩ፣ ሰዉ ሁሉ  'upgrade' ያረጋል!

እብድ ነው። ከሰፈሬ ሁለት አቋራጭ ራቅ ብሎ የሚኖር። በልጅነቴ ወደትምህርት ቤት ስሄድ ነው ማየው።  በጫት ገረባ የተሞላው አፉ፣ ያገኘውን ከብስኩት ልጣጭ እስከ አፉን እስካስጌጠባት ገረባ ድረስ እጁ ለመያዝ ከልካይ የለውም። በተለይም ከተማውን በእርቃኑ ማካለሉ የሱ ትልቁ መለያ ነው። ወንዱን ሴቱን አዛውንት ጨቅላ ሳይለይ ያለከልካይ  ያስኮመኩመናል።  ወንዶቹ በሱ ባዶ ገላነት ደስተኛ እንዳልሆኑ አውቃለው (እኔስ እንደው ልጅ ነኝ)  ይህ ነገራቸው ለሱ ከማዘን የመነጨ ሳይሆን በእንትኑ ምክንያት ነው። ረዥም ነው ከረዥምም ረዥም። በምን ይሉኛል ብሂል  አቀርቅሮ  ከማለፍና በእጆቻቸው አይናቸውን ከመከለል በዘለለ ለአፍታ እንኳ ቢሆን ድንገት በእይታ ይህንን በረከት የተቋደሱ ሴቶች የከተማውን ወንድ በዛ ልክ ይጠብቁታል የሚለው ስጋት እንጂ።

 ጊዜያት ነጎዱ። እኔም አደኩ ወደ ወንዶቹ ጎራ። ከብዙ ጊዜያት በኋላ ያንን እብድ አየሁት። ተለውጧል። መላ መላውን የማውቀው  አሁን ላይ ከላይ እስከታች ታጥቋል። ቲሸርት ሱሪ አልቀረው። ከአንዴም ሁለቴ ለብሶ  አየሁት። ያ በእጁ የሚይዛት በአፉ የሚያጣጥማት ገረባው ግን አሁንም የሱ ነች። upgrade መሆኑ ነው። ወንድ ነኝ ያልኩት እኔ እራሴን አየሁት። በዘመኑ ኑሮና ህይወት እየተራቆትኩኝ ነው። የፊተኞች ኋለኞች የኋለኞች ፊተኞች ነው መሰል ነገሩ። እኔንስ የሚያሳስበኝ  ግን እንደው ውል ብሎኝ ብራቆትስ? በብዙ እብዶች መሀል ያለው አንድ ጤነኛ ነኝ ሚሉትን ቅኔ ብቀኝስ? የኔውን እንደሆነ በማይዳሰሱ ቅርፆች UNESCO ላይ አስመዝግቤዋለው። የከተማው ወንዶች ነን ባዮችንስ አስገምት ይሆን?  አቤ...ት! በሰላም ማይታበድባት ሀገር ...

By 乃丨丂尺卂ㄒ

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

የደራሲ ቅጣት ...

የሆነ ሰውዬ ይሞትና ገነትንም፣ ሲዖልንም ይጎበኛል፡፡ ገነት ሲደርስ በጎ ምግባሮች እንደቀጠሉ ናቸው። መልካም ሰርተው የፀደቁትንም አስተዋለ፡፡ ይልቅ የገረመው አንዲት ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ የሚፅፍ ሰው ተመለከተ። ገረመውና ምን እንደሆነ ቢጠይቅ "ደራሲ ነው" አሉት። እየተደነቀ “አይ ደራሲ ፀድቆም አያርፍ፣ አሁኑም ይፅፋል” ሲል ተደመመ።

ከሚንቀለቀል የእሳት እቶትን ውስጥ የሲዖልም ሕይወት ቀጥላለች። አመፅ፣ ግርግሩ፣ ጦርነቱ…ኃጥያቱ አናት ባናቱ ይደራረባል። አሁንም አንድ ሰውዬ ከእሳት ዛፍ ስር አረፍ ብሎ በእሳት ብዕር፣ በእሳት ወረቀት ይቸከችካል። ተመልካቹ ሰውዬ ግራ ተጋባም ምን ሊሆን ይችላል ሲል እያሰበ ጠየቀ "ደራሲ ነው፣ ይከትባል" አሉት።

እየተገረመ፣ እየተደነቀ መልዓኩን "ቆይ ደራሲ እዚህም ሲፅፍ አይቼዋለሁ… እዛም ሲቸከችክ ተመልክቼዋለሁ ካዲያ ገነትም ገባ፣ ሲዖልም ወረደ ምን ቀረበት? ምንድነው ቅጣቱ? ምን ተጎዳ?" ሲል ጠየቀው።

መልዓኩም መለሰለት “ገነት ያሉት ይታተምላቸዋል"

By Alemayew Gelagay

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

ሰውዬው በድመቱ ይበሳጭና አውጥቶ ይጥላታል። ምሽት ላይ ድመቷ ወደ ቤት ትመለሳለች።በማግስቱ እንደገና ራቅ ወዳለ ስፍራ ወስዶ ይጥላታል። ይሁንና እሱ እቤቱ ሳይደርስ ድመቷ ቀድማው ደርሳ አገኛት። ንዴቱ የባሰ ጨመረ፣ ደሙ ፈላ። ከዚያ በጆኒያ አድርጎ እርሱ ራሱ ወደማያውቀው ሌላ ከተማ ወስዶ በጣም ውስብስብ ባለ ሰፈር ውስጥ አዙሮ፣ አሽከርክሮ ጣላት። ይሁንና  ይህን እርምጃ ከወሰደ በኋላ እሱ ራሱ እንዴት ወደ ቤቱ ይመለስ? ቢዞር፣ ቢሽከረከር መንገዱ ጠፍቶት ወደ ቤቱ መመለስ አቃተው። የመጨረሻ ሲጨንቀው ወደ ቤቱ ስልክ ደወለና ባለቤቱ ስልኩን አነሳች   ....
ባል: ሄሎ ሃኒ

ሚስት: ሄሎ የት ጠፋህ የኔ ማር?

ባል: ትንሽ ለጉዳይ ወጣ ብዬ ነው። ድመቷ አለች?

ሚስት: አዎ  ምነው?

ባል: አንዴ አቅርቢልኝ  😅

By hasan enjamo

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

እንደቆመብኝ ዓለም አይቶኝ ቢሆንስ ?
(አሌክስ አብርሃም)

ይሄ የተረገመ ኮሮና ሳያጠፋፋን በፊት አንድ ሶሪያዊ ጓደኛ ነበረኝ …ከመሬት ተነስቶ ኢትዮጲያን ይወዳል …በተገናኘን ቁጥር ግብፅን ተባብረን እንረግማለን እናማለን ! አገሩ የዩኒቨርስቲ መምህር ነበር ፣ወሬን እሱ ያውራት! ስንትና ስንት መከራ አልፎ ነው አሜሪካ የገባው ግን ሁልጊዜ ሳቅ ከፊቱ ላይ አይጠፋም አወራሩ ራሱ የሆነ ድራማ ነው የሚመስለው ….

‹‹ሚስቴ ጋር የተለያየነው የጋብቻችን ቀን ማታ ነው ›› አለኝ

‹‹አግብተህ ነበር ?››

‹‹ታዲያ! ያውም አይኖቿ እንደዳይመንድ የሚያንፀባርቁ ….ሳቋ ልብህን እንደሳሙና አኩረፍርፎ የሚጨርስ …የእጆቿ ጣቶች እንደባህር እንጉዳይ የሚስልከለኩ ….ከንፈሯ …የሚሳም ሳይሆን እንደአቮካዶ ጁስ በወፍራሙ ፉት የሚባል ዓይነት ….››
አገላለፁ አማሎኝ ‹‹እህት አላት ?›› ልል አስቤ ከአፌ ላይ መለስኩትና

‹‹እድለኛ ነህ ›› አልኩት

‹‹አይደለሁም ባክህ !››

‹‹ምነው? ››

‹‹የጋብቻችን ቀን ማታ … ከተማችን ውስጥ አለ ወደሚባል ኢንተርናሽናል ሆቴል ነበር የሄድነው …እዛ ነው ክፍል የተያዘልን …ሰፊ ይሄን አዳራሽ የሚያክል ክፍል ! በአበባ በተሞላ ክፍላችን ውስጥ ገብተን …የጓጓሁለትን ሰውነቷን በምኞት እየተቃጠልኩ አያለሁ !ጫማወቿን ስታወልቅ በሂና የተዋቡ በወርቅ አልቦ ተተሸቆጠቆጡ ከአንተ የእጅ ጣት የረዛዘሙ ውብ የእግር ጣቶቿ ….ሽፍንፍኗን ከፀጉሯ ላይ ስታነሳው ወገቧ ላይ የሚገማሸር ከክረምት ጨለማ የጠቆረ ውብ ፀጉሯ ….የሙሽራ ቀሚሷን ስትከፍተው የወርቅ ሃብል የሚጫወትበት የብርሃን ሜዳ የመሰለ ሰፊ ደረቷ ….ግራና ቀኝ ሙሉ ጨረቃቃ የመሳሰሉ ክብ ጡቶቿ …ከተፈጠረች እህል ቀምሳ ታውቃለች ወይ የሚያስብል እንዲህ በአንድ አጅ መዳፍህ የምትከበው ውብ ሽንጥ ….ወረድ ስትል በእቅፍ የማትደርሰው ኩርት ያለ ዳሌ ….

ምራቄን ዋጥኩና ‹‹እና ምን ተፈጠረ ?›› አልኩት

‹‹በቃ ያደረገችውን የወርቅ ጌጣጌጥ ሁሉ አወላልቃ ራቁቷን ስትሆን …ወርቅኮ ውበት ይቀንሳል አልኩ …ወርቁን ስታወላልቅ ውበቷ ወጣ ….በቃ እሷን ፈዝዠ ስመለከት የራሴን ልብስ ማውለቅ ረስቸ ነበር ….ወላሂ ! ስልምልም እያለች ‹‹አውልቅ እንጅ ›› ስትለኝ የድምፅዋ ፍስስስ ማለትና መለስለስ እንኳን ልብስ ቆዳን ማውለቅ ያስመኛል .... የአልጋ ልብስና አንሶላውን ገለጥ ሳደርገው የገነት በር የተከፈተ ነበር የሚመስለው …ሽቶው …በቃ በሽቶ የታጠበ አንሶላ በለው ….በባህላችን እንደዛ ነው ….ቀስ ብላ በነዛ ረዣዥምና ውብ እግሮቿ ወደአልጋው ሳብ ሳብ ሳብ እያለች …ስትመጣ በቃ እንደዚህና እንደዛ ጠረጴዛ …ነበር ርቀታችን ….. ፈገግ ብየ ስመለከታት ጅስሜ ሁሉ እንደእሳት እየነደደ ወንድነቴ ሁሉ ከተፈጠረ እንደዛ ቁሞ አያውቅም …እንኳን ሌላ ጆሮየ ቁሞ ነበር …ፀጉሬ ቁሞ ነበር ….

ድንገት አልጋው ጋ ልትደርስ አንድ ሁለት እርምጃ ሲቀር ያለንበት ሆቴል ምድር በሚያናጋ ፍንዳታ ወደፍርስራሽነት ተቀየረ …. የማስታውሰው እነዛ ውብ አበቦች በአየር ላይ ሲንሳፈፉ ነው .... ክፍሉ በአቧራ ብናኝና በሚፈነጣጠር እቃ ሲሞላ ነው …በቃ !!›› ብሎ ትክዝ አለ

‹‹ምን ተፈጠረ ከዛ …ባለቤትህ ….?››

‹‹እኔጃ ! የነቃሁት ከምንኖርበት ከተማ ውጭ ቃሬዛ ላይ ተሸክመውኝ ሲሮጡ ነበር …ከተማችን በጦርነት እየተናጠች ነው …ከሳምንት በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ካምፕ ገባን …ሚስቴ ትኑርም ትሙትም አላወቁም አላገኟትም …ከሶስት ዓመት በኋላ እዚህ ያሉ ቤተሰቦቸ ጋር መጣሁ …ፈለኩ አስፈለኩ በቃ አልተገኘችም …. የአላህ ....ህልም ነበር የምትመስለው ! ከሁሉም ግን እስካሁን ሳስበው የሚያስቀኝ ....›› ወዲያው ከትካዜው ወጥቶ መሳቅ ጀመረ

‹‹የሚያስቀኝ ምን መሰለህ? …ከፍንዳታው በኋላ ሲያገኙኝ …እንደዛ እንደቆመብኝ ይሆን ?….እያልኩ እስቃለሁ …ሃሃሃሃሃሃሃሃ ›› ጎርናና ሳቁ አካባቢውን ሞላው ...የነበርንበት ኮፊሾፕ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ዙረው አዩን ...ማን ያምናል ያሳቀውን ነገር ቢሰማ …

‹‹…አስበኸዋል ? አልጀዚራ ፍንዳታውን ሲዘግብ እኔ ራቁቴን ከፍርስራሽ ውስጥ እንትኔን ሚሳኤል አስመስየ ተጎትቸ ስወጣ ….የአላህ ! ጦርነት ክፉ ነው ...አገርህንም አንተንም ከነገመናህ ነው ለአለም የሚያሰጣህ ››

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

ገደልኩት

ወሎ መስታወትን "መታዘቢያ" ይለዋል።

ራስን መመልከቻ፣ እድፍን ጉድፍን ማያ፣ ከራስ ጋር ማውጊያ መሆኑን አይቶ።

እውነት ነው !

ወርሃ ግንቦት  ከረጅምና አሰልቺ ቀን በኃላ
እቤቴ ውስጥ ካለው ሙሉ ገፅታዬን ከሚያሳየው መስታወት ፊት እርቃኔን በትካዜ ቆምኩ ፍዝዝ ብዬ እራሴን በእዝነት ተመለከትኩት ።

እኔ ለእኔ አዘንኩ መስታወቱ ውስጥ ያለው የራሴው ምስል አይኑ እንባ አቅርሮ ታየኝ በአይኑ የሆነ ነገር ይለኛል መናገር ማይቻል ቡቡ ልጅ ፊት እያሳየ ሆዴን ያባባኛል::


መስታወቱ:- እባክህ ዛሬም በዛ ባማይረባ ፍቅር በሚሉት ዝባዝንኬ ወሬ እኔንም ልብህንም ማሰልቸት ተውና ስለ ካሳኖቫ እናውራ ስለቬነስ ፈገግ እያልክ አጫውተኝ አለኝ ? ..........
ደሞ መጪው ክረምት ነው ፊትህን አታዝንበው !

እኔ :-የኔና የሲፈን የፍቅር ህይወት እራሱ እኮ ሃምራዊ ቀለም ነው ስለሱ እናውራ አልኩት::

መስታወቱ :-እንዴት አንድ ሰው  ጥንካሬም ድክመትም ይሆናል ?
ሲልህ ትልፈሰፈሳለህ ሲልህ ዘራፍ አርበኛው አያቴ ተጉሉት ምናምን ትላለህ ምንድነው ችግርህ ?

እኔ:- እኔ አላውቅም ....ብቻ እኔ ማውቀው የማትደራደርባቸው ነገሮች ተብዬ ብጠየቅ ከመልሶቼ መሃል  አንዱ እሷ ነበረች።

ሲፈን  እንዴት እወዳት ነበር መተው በማልችልበት ልክ እወዳት እደ'ነበር አተም ታውቃለህ !

እራስ ወዳድ እንዳልባል እየፈራው እንጂ አሁንም ድረስ እኮ እወዳታለሁ የእኔ እንድትሆን እፈልጋለሁ !
ለዘግ ላለ አመታትም አብረን ብንቆይ ሳልጠግባት ነው የተለያየነው::

መስታወቱ:-ምን ለያችሁ ታዲያ ?

እኔ:- ሁኔታዎች ድንግት ኑሮ ሚሉት ደራሽ ወንዝ ወሰደብኝ አልኩ እያቀረቀርኩ::

ከውጪ ሚሰማው ዝናብ የኔን ሃዘን የሚስደርስ የቅርብ ወዳጄ ነው ሚመስለው ሰማዩ ያነባዋል  ያንዠቀዥቀዋል !


መስታወቱ :- አንዳንዴ መለያየት ሳይኖርብህ ሁኔታዎች ይለዩሃል" እጣ ፍንታ ነው ምርጫ"የሚያስብሉ የህይወት መንታ መንገድ ጋር ትቆማለህ !

እሱን መረዳት አለብህ !

ከልክ እና ከስህተት ባሻገር አንድ ሜዳ አለ - እዛ እንገናኝ ትልሃለች  ዓለም ዱላዋ ይሰብርሃል ::
 
ስለዚህ እውነታውን መቀበል ነው ያለብህ ብትሸሽም ሲከተልህ ይኖራል እንጂ አታመልጠውም አለኝ ጎርነን ባለ ድምፅ ::

መብረቁ ተስረቀረቀ  የራሴው የሳግ ድምፅ መሰለኝ ።

ሳለላስበው በጉንጮቼ እንባ እየወረደ ነበር የአለም ዱላ ልቤን ቀጠቀጠው ::

መስታወቱ:-በአሽሙር አፉን አጣሞ ፈገግ አለ ደስ አለው ይህን ቀን እንደሚመጣ ነግሬህ ነበር አልሰማኽኝም ነበር አለኝ ::

ይሁን አሁንም ዋናው ምክር መስማትህ ነው እ'ውስጥህ ያለውን አንተነትህን ግደለው መሞት ይፋልጋል ፣ሸኘው አለኝ ...

እኔ:- በመስኮት አሻግሬ ተመለከትኩ ያንን ብዙአየሁን ከውስጤ ልገለው ተመኘው !


ዛሬዬ የተሰራው በእሷ ትላንትናዬ ውስጥ በመኖር ነው :: 

እንዴት ላርግ ያኛው ቡዙአየሁ እኮ መልካም ሰው ነው ፈገግታ ከፊቱ ማይጠፋ እምነት ፣ተስፍ ፣ፍቅር አብረው ፀንተው ይኖራሉ የሚል ደግ ሰው ነው አልኩት ::

መስታወቱ:- አየኽው ያኛው ብዙአየሁ ምን እንደሰህ?

ለማንም አልሆነም ላንተም አልበጀህም  እሷንም ለሰቀቀን እና እራሷን እንድትጠላ ነው ያረካት  ::

መስታወቱ:-ተዋታ በቃ ትቅርብህ

እኔ:- እንዴት ልተዋት

መስታወቱ:- ወንድ ልጅ አይደለህ ?
ቁረጥ ምድነው ገብርዬን ያጣ ካሳ ምትሆነው ቆፍጠን በል !

የነገን ማን ያውቃል ምን ይዞልህ እንደሚመጣ ?

እኔ:- አቤት እ/ር ግን ማኖር ሲያውቅበት !

ተመስገን🤲 በረጅሙ ተነፈስኩ::

እኔ:-አብቅቷል ካልኩ በኃላ ወጣልኝ ባልኩ ማግስት የትዝታ ፈረስ የኃሊት እያስጋለበ ከተጓዝኩት መንገድ ዳዴ እያስባለ ይመልሰኛል

አብረን የሆነው ሁሉ ይናፍቀኛል

መስታወቱ:-ብትመጣስ  ?

እኔ:- አላውቅም ግራ ያጋባል ግን ሲመስለኝ እንደዛ የሚል ተስፋ አይደል የሚያኖረኝ አንዳንዴ ህይወት የምታምረው ፣እንደ ሲፈን ጡት ምታጓጓው ከፊት ተስፋ ከኃላ ትዝታ ሲኖራት ነው ::

መስታውቱ:- ተስፋ እና ህልም ብቻውን እኮ እንደቆመ ውሃ ነው ይሸታል!


በልብህ ያለው ፍቅር የማይሞት ህልም ቢመስልህ ፣ ብትውተረተርም፥ የሚጨበጥ ያለ መስሎህ ብትዋትትም ፥ ምናልባትም እሷ ቆይታ ይሆናል ከገደለችህ ፤

ውስጥህ ያለው ፍቅር እኮ እድትገለው እየቃተተ ነው  ! አለኝ ለመተንፈስ መቸገሬን አይቶ ...


እኔ :-

ተለያየለን ፣ገደልኩት ፤መስታወቱን ሰበርኩት።

ከዚህ ቀን በኃላ የዚህ የህይወቴ ገፅ እንደመስታወቱ ፊቴንም ቆንጥሬ እንደማይበት ሁሉ የሲፈንም ታሪክ ቁንፅል ነው ታሪኳ፣ሽርፍራፊ ነው ትዝታዋ፣የደበዘዘ ነው መልኳ።

ጊዜ የዳበሰው ትዝታ !

ከኤርምያስ ፍሬው

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

መፈቀር ደስ ይላል

ለስለስ አርጌ ነው ማልወደውን ተይ የምላት በትህትና እሺ ትለኛለች እሺታዋ ውስጥ መብትህ ነው ስልጣን አለህ ስትለኝ የሚሰማኝ ስሜት ጥልቀቱን እወድላታለሁ ::

አስሬ እየደወለች እንደልጅ እየተፍነከነከች  ሲያሻትም እያጉረመረምች እየተበሳጨች ያጋጠማትን ነገር ትኩስ ዜና ደውላ ስትነግረኝ ድምፆ ላይ ያለው ቃና እውነተኛ ስለሆነ በፍፁም ልቤ ነበር ምቀበላት ::

ማታ ማታ

ጀንበር ከመሰለው ከንፈሯ መንፈስን ቀላቅላ እፍፍፍ ትልብኛለች እንደ ቡችላላ ስፍስፍ ትላለች ከነብሴ ትጣበቃለች እኔ ደሞ እፉዬ ገላ እሆናለሁ ፍፍፍ ባለችኝ ቁጥር ወደሰማይ በነፍሴ እቃትታለሁ::


እንደምትወደኝ ስለምታሳየኝ የሚሰማኝ ሰላም ወደር አልነበረውም አንዳንድ ቀንማ ስትንከባከበኝ "ከክሽ ክሽ”በኃላ ቢሆንም ንጉስ ባልጋው ሳለ ሚጎማለለውን ምተውን ይመስለኛል ::

ስትጨነቅልኝ ደሞ ደበረኝ ካልኳት አመመህ እንዴ ብላ ፊቷ  ላይ ያለው መረበሽ አንጀቴን ይበላዋል እንደ ታናሽ ወንድሟ ስትሳሳልኛለች እንደ ቆሎ ጓደኛዋ ስታሾፍብኛለች እንደ እናቷ (አባቷ )  ስትሰማኝ አይይይይይ... እላለሁ እናቴ የመረቀችኝ ምርቃት ደርሶ እንጂ እንደኔ አመል እንደኔ መደመር መቀነስ ሚጢሚጣ በቃሪያ የሆነች ልጅ ነበር ሚገባኝ ።

የሆነው ሆኖ መፈቀር ደስ ይላል ::

By ኤርምያስ ፍሬው

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

ታረቂኝ ። በቃ ታረቂኝ አልኩሽ ታረቂኝ ። ዝም ብሎ ሆድ እየባሰኝ ነው ታረቂኝ ። ያለ ምክንያት እየከፋኝ ፥ እንዲሁ እየደበረኝ ነው ታረቂኝ ። ጥላቢስ ከውካዋ ሆኛለሁ ታረቂኝ ። ከቦሌ መገናኛ እንዲህ ሩቅ ነው እንዴ ታረቂኝ ። መንገድ ስሻገር ሾፌር ጮኸብኝ እኮ ታረቂኝ ። የዛ ቤት አስተናጋጅ "ጓደኛህስ የት ሄደች" አለኝ ታረቂኝ ። የታጠቡ ልብሶቼን መች ልልበሳቸው ታረቂኝ ። ገማሁልሽ እኮ ታረቂኝ ። ከነጋ 15ኛ ሲጋራዬን እያጨስኩ ነው ታረቂኝ ። የዛሬው ፍርፍር ደሞ ሲያስጠላ ታረቂኝ ። ጫማዬን ካስጠረግኩ በጣም ቆየሁ ታረቂኝ ። የሆነ ልጅ ዝም ብሎ እየተራመደ ነው ፤ ሄጄ ላጋጨው እንዴ ታረቂኝ ። ና ማነህ የ11 ደብል ጂን ሒሳብ ውሰድ ታረቂኝ ። ፀሐይ ነው ብዬ በቲሸርት ወጥቼ ዝናብ ቀጠቀጠኝ ታረቂኝ ። በፍቅር ያዘነ በምን ይደሰታል ታረቂኝ ። ከዚህ አገር ብን ብዬ ልጥፋ ወይ ታረቂኝ ። ዘፈን የሚባል ነገር ነው ያስጠላኝ ታረቂኝ ። ቱ !...ትፍ ሚሪንዳና ነው ሬት ? ታረቂኝ ። የእናትምስ ነው አቢይ አህመድ ታረቂኝ ። ቅዳሜና እሁድ አስጠላኝ ታረቂኝ ። እግዚአብሔር መልካም ነው - ወለሂ ? በቃ ታረቂኝ ። ወደ ማን ልደውል ነበር ስልኬን ያወጣሁት ? ታረቂኝ ። ሶስት ሲደመር አራት ሰባት ነው ስምንት ? ታረቂኝ ። ኧረ በህግ አምላክ ታረቂኝ ። ያምሻል እንዴ ታረቂኝ ።

By Hab Hd

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

🌄 We’re Back And We’re Hiking Again
Hey Sunset community 🌄

Life happened. The city got louder.

And for a while, the sunsets were quieter without us.

Sunset Hiking is officially back with a stronger team, clearer plan, and a growing 4,000+ hiking community ready to move again.

Over the next weeks, we’ll be sharing:
🥾 Upcoming sunset hikes
🌅 Community moments
🧭 Safe, well-organized experiences

If you’re still here, it means you love nature as much as we do.
Let’s start again one sunset at a time. 🌄👣

Читать полностью…

ወግ ብቻ

ሰው ብቻ አይደለሽም!

Sirak Wondemu

እናትነት ዓለምን አምጦ መውለድ ነው።
በምጥ ጣር ተይዞ ለሚቃትት ነፍስ የውልደት እልልታን በከንፈሩ ሰማይ ይዞ እንደሚዞር ደመና ነው።
ሰው እውነትን መፃፊያ ጠመኔ ሲሆን እናት የጠመኔው መዳረሻ ሰፊ ሰሌዳ ናት። ትሁንልህ መወደሻ ተብላ በባርኮት የተሰጠች ስጦታ!
በግምባሯ መስመር ላይ ዘመን ፅፋለች። በመዳፏ ስር ሕይወት ወልዳለች። ሽብሽብ ቆዳዋ እድሜን ዘምሯል። ዳሳሽ ጣቶቿ ቀንን ፈክሯል።

ሰው ብቻ አይደለችም!

በወዟ ጠፈፍ ከራሰ የሻሿ ጨርቅ የበለጠ የዓለም ታሪክ የለም። ጊዜና የሕይወት ዑደት አዳውረው በጥቁር ጸጉሯ መሀል እንደበተኑት የሽበት ተክል ያህል መቆዘሚያ ሀሳብ አልነበረም።
እማማ ንፁህ ፈገግታሽ የንግስ ቀን ነው። የእሺታ ደጅሽ የዓለም ብርሃን ነው። ሁሉን ቻይ ልብሽ ዕፁብ ተምሳሌት ... በጊዜ ጣይ ፊት የማይሞት አይነት ፤ ነው።
ኩርፊያሽ ውስጥ እንደነገሩ የወለድሽው ልጅ ፈገግታሽ ያጫውተኛል። የውሸት ተኮሳትረሽ ከሸበሸብሽው የግምባርሽ መስመር ላይ መጥምቁ ዮሐንስ እየሱስን ባጠመቀበት ቅፅበት ትከሻው ላይ ያረፈችውን ፀዓዳ እርግብ እመለከታለሁ። አለሀሳብ መከደን ካማረው መንታ ዓይኖችሽ ውስጥ ፍቅር ጠምቃለሁ። ሰው ይርበኛል።

ተስፋ ጠምጄ... እምነት አርሳለሁ!

እማማ ልጄ ሰው ሆነልኝ ዩኒቨርስቲ ገባልኝ ብለሽ ግማሽ ደስታ ግማሽ ሀዘን ሆነሽ የሸኘሽኝ ቀን ትምህርትን ለዘላለም ረገምኩ። ከእነዚያ ብርሃናማ ዓይኖች ብርቅ ... ከህመም ፈዋሽ ጠረኖችሽ ብሸሽ ... ከሞት መላሽ ዳሳሽ ጣቶችሽ ብሰደድ ፤ ማወቅ የገሀነም ፀሎት ሆነብኝ። ክረምቱ መጥቶ ጉያሽ ውስጥ ሽሽግ እንድል አርጩሜ ቆርጠሽ በጋውን አባሪልኝ። ኮስተር ብለሽ ሀምሌን ጥሪው። ነሀሴም ይምጣ! አንቺ ከተቆጣሽ ሁሉም ቀና ይሆናል!
እማማ እምባ አርግዞ በስስት የሚያየኝ ክርትት አይኖችሽ እንዴት ናቸው? ዛሬም ለመንገደኛ እንዳዘኑ ነው? ለነፍሰጡር ላም እንደተንሰፈሰፉ ነው? በቅርሻቴ ያረጠብኩት ጀርባሽ ... ዓለሜን የተሸከመው ጫንቃሽ ዛሬም ከመቻሉ አልተፈታም?
እኔማ እነሱን ለማየት ለመንካት በስንት ቀናትና ወራቶች ደረት ላይ ተሳብኩ!
ሺህ ናፍቆት ከፊቴ ሺህ ጉጉት ከኋላዬ አጅቦኝ በርሽ ለመቆም ተሳልኩ!
ለስንት ንጋቶች ለፈፍኩ!

ሰው ብቻ አይደለሽም። ብትይኝም አላምንሽም!

ሞገስሽ ልክ እንደታቦት ነው። ቁጣሽ ሀገር ያርማል። የወደቀ ቀዬን አንስቶ በውል ያቆማል። ዝምታሽ እንደፍርድ ቀን ይጨንቃል። ይጠባል። ሳቅሽ እንደእሸት ባቄላ ታኝኮ አይጠገብም። መርቀሽ የሳምሽኝ ግንባሬ ዛሬም በብርሃን እንደታጀበ ነው። ኑርልኝ ብለሽ የመረቅሽኝ ምርቃት እኔ ካልሰለቸኝ ከሞት እንደሚታደገኝ ቃል ገብቶልኛል።
እማዬ ከእንግዲህ ይራባል ብለሽ አትስጊ! ይልቅ የስጋት በርሽን ዝጊ! ያኔ በጨቅላነቴ ዘመኔ እንደወፍ ልጅ ከአፍሽ ነጥቄ የጎረስኩት እስከ እለተ ሞቴ ከአንጀቴ ይኖራል።
አምሳያ የሌለው ውዴታሽ ሞትን ማምለጫዬ ነው። የአንቺ ትካዜ የሀገር መፍረስ ነው። ያ ልዝብ ቃልሽ የንጋት ቀን ነው።

ሰው ብቻ አይደለሽም!

በነጠላሽ ጫፍ የሰው ልጅ ቋንቋ የማይገልፀው የእረፍት ዋኔ - በመቀነትሽ ስር ያልታየ ያልተሰማ ስውር ቅኔ ተቋጥሯል።
ከአንቺ ጋር አይደለም አስር ሀያዬን ሰባ ሰማኒያዬን መሰንበት እፈልጋለሁ።
እማ አንቺ ወዳጅ የለሽም ወዳጅሽ እኔ ነኝ። እኔም የአንቺን ያህል ግምት ሰጥቶ የሚቀበለኝ ወዳጅ የለኝም። ወዳጄ አንቺ ነሽ!
ቀሚስሽን በለጋ ጣቶቼ ጨብጬ የቆምኩባቸው የጎረቤት ቡና ቅፅበቶች አይረሱኝም። ገበያ ሄደሽ እስክትመለሺ መንገድ መንገዱን እያየሁ ጉበን ታቅፌ የተኮራመትኩባቸው ወቅቶች አይኔ ላይ ናቸው። አባቴ ነጥቆሽ ዓመት ከዓይንና ድምፅሽ ርቄ የተመለስኩ ቀን ዘማች በህይወት ተርፎ እንደመጣልሽ ሁሉ በስስት ያነባሽው ዕምባ አንቺ ብትፈቅጂ ወንዝ ሆኖ ይወስደኝ ነበር።
ሰውነትን የለካሁብሽ ፤ የፍቅርን ትርጉም የሰፈርኩብሽ ፤ ትናንትን ፣ ዛሬንና ነገን የመዘንኩብሽ ሚዛኔ ነሽ።
ሳቅሽ ውሎ ሳይገባ እንዳይመሽ እፀልያለሁ። ስጋትሽ ስጋት በልቶት ሳይጠፋ ዘመን እንዳያልፍ እፈልጋለሁ።
በትከሻሽ ላይ ቆሜ ጎበዝ ተብያለሁ። አንድ የናፍቆትሽ ዘለላ አንገቴ ላይ ቢታሰር ይዞኝ ጥልቅ እንደሚወርድ ግን የተረዳኝ የለም።

አድጌ አንቺን ረሳለሁ? ቤት ይኖረኛል? እሸሽሻለሁ? አመመኝ ብትይ እረጋጋለሁ? ልቤ ይሰክናል?
እኔ'ንጃ !

ልጅ ሆኜ አጎቴ ሞቶ በሀዘን ቅስምሽ ስብር ሲል ፤ ማቅ ስትለብሺ እግዜር ከትምህርት ቤታችን ዳገት በላይ ያለ እየመሰለኝ ሄጄ «አንተ አትችልም እናቴ ትሁን! » ብዬ መኮሳተር ያምረኛል።
ሰፈር ሰው ሞቶ ለቅሶ ስትሄጂ መንደርተኛው እርር ሲል ... ምርር ብሎ እምባውን በጉንጩ በራፍ ሲደፋ ያ አባባሌ እውነት ሆኖ እታዘባለሁ።
« በቃ እሱ አይችልም እናቴ ትሁን! » እላለሁ በልቤ።
እዝነት እንደሌለው ሁሉ ፤ ምህረትን እንደማያውቅ ዝንጉ አባት ፍፁምነቱን እንድጠራጠር ያደረገኝ ፍቅርሽ ነው።
ለሁሉም ነገር ሆደ ባሻ የሚሆነው አዛኝ አንጀትሽ ነው። አንቺ እኮ እግዜርን ብትሆኚ የሰፈራችን ሰዎች በሙሉ ማሪያም ቤተክርስቲያን እንዳሉ ዛፎች ሰማይ ጠቀስ እንደሆኑ ይሸብቱ ነበር።
እማማ እርጅና በአንቺ ላይ ስልጣን እንዳይኖረው የአንቺን ቁጣ ኮርጄ እቆጣዋለሁ። ሞት በሰፈርሽ እንዳያልፍ በርሽ ላይ አያ-ጅቦ እንዳለ ነግሬ አስፈራራዋለሁ። እማማዬ ቃል የእምነት እዳ ነው ይላል ፀጋዬ። ቃል የእምነት ዕዳ መሆኑን የተረዳሁት ግን በአንቺ ነው። ዛሬም በሰው ሀገር ሆኜ የተቆላ ቡና ሲሸተኝ ትዝ ትይኛለሽ። ትኩስ ሽሮ ሲሸተኝ ፤ ጠይም ፈገግታም እናት ስመለከት ዓይኔ በእምባ ይሞላል።
ማን ያውቃል ዛሬም ህፃን ልጅ ሲጮህ ትደነግጫለሽ አይደል? በሌለሁበት ቀዬ ተጋደሉ ሲሉሽ እግርሽን ብርክ ብርክ ይልሻል አይደል?

እማዬ ጌሾ ያልወቀጠልሽ እጄን እጠላዋለሁ። ስታዢኝ በእምቢታ የሰበቅኳቸውን ትከሻዎቼን እጠየፋቸዋለሁ።
ለእነዚያ ጊዜ ... ለእነዚያ ወቅቶች መዳፍሽ ስር ፊቴን ቀብሬ ማልቀስ እፈልጋለሁ።
ስትገርፊኝ ያኮረፍኩባቸውን ቀኖች ባገኛቸው እንደልጅነቴ ድንጋይ ወርውሬባቸው ሮጣለሁ።
ማጀትሽ በጥጋብ ይሙላ! ... ሰላምሽ እንደአሸን ይፍላ! የጦር ቃል ጆሮው ይደፈን ... በደጅሽ ፍቅር ይሸመን!
ማሳሽ ላይ አዝዕርት ይብቀል! ... ይመር ሰማዩ እንደምንጭ ይጥለል።
አዛኝ ነሽና መርቂኝ አለሁ... ክፉሽን ከቶ አልስማ ሳለሁ! ገብያሽን ጥጋብ ይውረሰው አይጉደል ዘመኑን ሙሉ... የተኳረፈም ይታረቅ ሁሉ! አካል ነሽና ለምድሩ ለሰው... ስሁት ደስታሽን ቀን ይደግሰው!

ብቻ እማማ አንቺ
ሰው ብቻ አይደለሽም ፤ እግዜር ነሽ ለልጅሽ ... ሚዛን ነሽ ለምድሩ.. ባርኮት ነሽ ለሰማይ አድባር ነሽ አውጋር ነሽ የኔ አድባር። መላዕክ ነሽ ልዩ ሰው! የአጥቢያ ዳኛ የአንቺን ያህል ፍትሕ አያውቅም! ውብ አዝማሪ ከእሽሩሩሽ የተሻለ ዜማ አይደርስም። በዓይኖችሽ ስር የፀነስሽው የተስፋ እምባ ለመኖሬ ለመዳኼ ሆኗል መባ! አለው ዋጋ! አለው ፀጋ።

አስራቴ ነሽ ጃኖ ጥለት... ወደር የለሽ የሰው ቁመት።
ብቻ ብቻ . . .

አንቺ ሰው ብቻ አይደለሽም... ብትይኝም አላምንሽም።
. . .
መልካም የእናቶች ቀን ❤
@wegoch
@wegoch
@sirakoo

Читать полностью…

ወግ ብቻ

ADDIS ABABA — FOR SUDAN

Voices From Sudan

On April 21, join us for a powerful evening where film, music, and community come together to mark the 3rd anniversary of the Sudan war.

The night opens with a special live performance by The Tana Quintet by Hazim Alshafei, bringing the rhythm, soul, and resilience of Sudan to life—followed by a screening of the acclaimed film Khartoum.

✨ Free Entrance

This is more than a screening.
It’s a gathering.
It’s a shared moment.
It’s solidarity in action.

Expect a full house, a powerful atmosphere, and a night that will stay with you.

📅 Tuseday, April 21, 2026
📍 Bata Complex 22, around Golagul
🕠 5:30 PM

Bring your friends. Be present. Stand with Sudan.

#Khartoum #Sudan #AddisAbaba #InDeepCultures #FilmScreening #LiveMusic #1960Films #AddisCinemaClub

Читать полностью…

ወግ ብቻ

ፖስታዬንና ክርታሴን አንጠልጥዬ እንትና በሰጠኝ አድራሻ ታክሲ ይዤ አዲስአባ አስራምስት ቀን ያህል ቆይተን ለመመለስ ሁለት ቀኖች ሲቀረን ሄድኩ። ስድስት ኪሎ አፍንጮ በር አካባቢ ነበር።

በር ሳንኳኳ የከፈቱልኝ ጥምጥም ያደረጉ፤ ፂማቸውን የተላጩ፣ ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት ገፅ ያላቸው መልከ መልካም ጠይም ሽማግሌ ነበሩ፡፡

መምጣቴን ቀደም ብዬ ስልክ ደውዬ ነግሬአቸው ስለነበር፣ በስሜ ጠርተው በትህትና እንድገባ ጋበዙኝ፡፡

ቤት ውስጥ እሳቸውና ፊታቸው ብቻ እስኪቀር የተከናነበ ሌላ ሴት ነበሩ፡፡ ገና እንደተቀመጥኩ ራት በልቼ (ማታ ላይ ነበር የደረስኩት) እንድሄድ ሲጠይቁኝ፣ በሥነስርዓት ተከላክዬ ፖስታውንና እቃቸውን በእጃቸው ሰጠኋቸው።

ስለ ልጃቸው ጤንነት ከጠየቁኝ በኋላ፤ የሚያበረታታቸውን መልስ ሰጥቼ ከተቀመጥኩበት ስነሳ፣ አንድ የሚያጫውቱኝ ነገር ስላለ በጥሞና እንድሰማቸው አግባቡኝና ተመልሼ በመመቻቸት ተቀመጥሁ።

«እግዚአብሄር አንድ ነው፣ አየህ፤ ስሙን ሰዎች ይለያዩታል እንጂ አላህ ብትል፣ እግዚአብሄር ብትል አንድ ነው።

ቅድመ አያቴ እስላም ነበሩ።

ልጃቸው ክርስቲያን አገባና ከዚያ በኋላ ክርስትናው ቤታችን ገባ። የድሮ ሰዎች ናቸው። ለምን? በለኝ አላህ በለው እግዜር በለው ያው ነው። ልጄ ሆላንድ የቤተክርስቲያን አመራር ይሠራል ሲባል ሰምቼአለሁ፣ እሱም አንዴ ሰላም ሊል ደውሎ አጫውቶኛል።

ልክ ነው? (‘ኧረ የማይገባበት ቦታ የለም’)

አንድ ነገር ልንገርህ፤ እኔ ወደ ቅድመ አያቶቼ ሐይማኖት ተመልሼአለሁ»

ግድግዳ ላይ በመስታወት ውስጥ ሆኖ የተሰቀለ ዳንቴል የመሰለ የዐረብኛ ነገር የተፃፈበት ነገር አሳዩኝ፡፡

«ዐረብኛውን ባላውቀውም አላህ ከሰዎች ጋር በሚገባቸው ቋንቋ ይናገራል፡፡ ነቢዩም እንዲህ ነው የሚያስተምሩት፤ ስማቸው ይባረክና፡፡

ግን ልጄ እንዲከፋው አልፈልግም፡፡

‛አባቱም እናቱም ሰለሙ' ተብሎ ቢሰማ ያዝናል፣ ይበሳጫል፡፡ (ኧረ ካሽ ካገኘ ግድ የለውም)፡፡

ግን እዚያም ስገዱ ነው፣ እዚህም ስገዱ ነው።

'አለማየሁ' የተባለ ስሜን ‛አብዱላሂ' አሰኝቼአለሁ፡፡ የሰፈር ሰው ገና አለማየሁ' ነው የሚለኝ፡፡ ክፋት የለውም፡፡

እንዲህ ያደረግነው ለጥቅም አይደለም፡፡ ለእሱ ነው። ለእምነቱ ነው።

ታዲያ ከልጄ ጋር ተገናኝታችሁ ድንገት ወሬ ቢነሳ መነሳቱ መቼም አይቀር፣ እንደ ሰለምኩ አትንገረው፡፡ ይኼን ቃል ግባልኝ፡፡ ያለዛሬ አይቼህ አላውቅም፡፡

መቼም ታምነህ የተላክህ ሰው ስለሆንክ፣ ብትግባቡ ነው መቼም (‛ከቴም ተግባባን')

ቢሰማ ችግርይኖረዋል? እንጃ እንግዲህ ባትነግረው ባታወራው ግን ይመረጣል፡፡ እንዳይሳትህ ብዬ ነው»

ሴትዮዋ/ባለቤታቸው ከእኛ ራቅ ብለው በጋቢያቸው ተሸፋፍነው ታስረው የተቀመጡ መስለዋል፡፡ ቃል አውጥተው አይንገሩኝ እንጂ ከአስተያየታቸው፣ ከአንገት አደፋፋቸው እየተለማመጡኝ እንደሆነ ይገባኛል፡፡

ለሰውዬው ከአፌ ቃል እንደማይወጣኝ፣ በተፈጥሮዬ (ምናልባት ስወለድ ጀምሮ ወይም ከእናቴ ሆድ ጀምሮ ለሐይማኖት ግድ እንደሌለኝ፤ እንደውም እሳቸው ያሉት የእግዜር መመሳሰል ትልቁ እውነት እንደ ሆነ አንስቼ) ሳይሆን አይቀርም ሚስጢር ቀርቃሪ በመሆኔ ትንፍሽ እንደማልል፣ አንዲት ቃል ከአፌ ጠብ እንደማትል ቃሌን ሰጠኋቸው፡፡

ክርስቶስን ጠርተው መረቁኝ፡፡

ከተቀመጡበትም ተነስተው ትከሻዬ ላይ ሳሙኝ፡፡

ሲሰናበቱኝና ሲሸኙኝ ሽማግሌው ዐይኖች ውስጥ ሊሸፍኑት ያልቻሉት ወፍራም እፍረት ነበር፡፡

ለመቅደስ ይሄን ሁሉ አልነገርኳትም፡፡

***

By | አዳም ረታ/ 📖 ይመያመ

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

ወግ ብቻ ቻናል ቤተሰቦች በሙሉ

ተረት ተረት
(የመሠረት)
አንድ ልጅ ነበረ።(እሺ) ሲኖር . . .  ሲኖር . . . ሥነ ጽሑፍ የሚባል ነገር ለመደ። (እሺ) ሲያነብ ወረቀት ላይ ሲፅፍ ሲፅፍ . . . ጊዜያት ጥለውት እልፍ!
ወራት ቀናት ረስተውት ጥድፍ ጥድፍ አሉ። እሱም አንድ ቀን ጽሑፌ ታትሞ ይነበብልኛል ብሎ ያስብ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀን ጽሑፎቹን ሰበሰበና ማተሚያ ቤት ኼደ። (እሺ) «አትሙልኝ ብያለሁ አትሙልኝ ካልሆነ ለአያ ጅቦ እናገራለሁ» ብሎ አስፈራራቸው። እነርሱም አተሙለት።
ቅዳሜ መጋቢት 12 ከ10፡30 ጀምሮ በወመዘክር ጊቢ ተገኝታችሁ መጽሐፉን ካልመረቃችሁለት እውነቴን ነው ለአያ ጅቦ ይነግርባችኋል። እኔ ተናግሬያለሁ! ብትቀሩ እኔ የለሁበትም።
ደግሞ ደግሞ እናቱ የምትቆጣው ካለ እኔ እነግርለታለሁ እሺ😀
ደግሞ ቶሎ ከጨረስን እቃቃ እንጫወታለን እሺ ኑ😊

@wegoch

@wegoch

Читать полностью…

ወግ ብቻ

ያች ከልታማ ወለተ ስላሴ ናት አሉ እንደዛሬው ሁዳዴ ፆም ሊገባ ሲል እሁድ ማታ ቅበላ ተብሎ ድስት ሙሉ ወጥ ተሰርቶ ሲዛቅ አምሽቶ ትንሽ ተርፎባቸው አደረ።

በበነጋታው ፆሙ ገብቶ እቃ ልታጥብና የፆም ምግብ ልትሰራ ስትል ያደረውን ስጋ ወጥ ለመድፋት አንዤቷ አልችል አለ።እንጀራዋን እጥፍ አርጋ ድስቱን ጠራርጋ በልታ በሳምንቱ ንስሃ ገባችና ስግደት ታዘዘላት።

ይችው ሴትዮ ደግሞ ፆሙን ፆማ ጨርሳ ፋሲካ እሁድ ሊሆን ቅዳሜ ማታ ዶሮ ሰርታ አሻቦውን ለመቅመስ ብላ እንጀራዋን መዥረጥ አድርጋ አንዱን ክንፍ አቀላጠፈችው።

በበነጋው ለንሰሐ አባቷ ድጋሚ ተሳሳትኩኝኮ ብላ ሀፅያቷን ስትነግራቸው አባ ግራ ገብቷቸው እንዲህ አሏት:-ምነው ወለተ ስላሴ ይሄንን ፆም አላስገባ አላስወጣ አልሽው?

እና ይሄንን ያረጀ ወግ ለምን አወጋኋችሁ መሰላችሁ ምነው ግን ፆሙን አላስገባ አላስወጣ አላችሁት?
ሊገባ ሲልም ዳንኪራ፣ዝሙት እና ስጋ ሊወጣ ሲልም ዳንኪራ፣ዝሙት እና ስጋ እስኪ ቢያንስ ወይ በመግቢያው ወይ በመውጫው በኩል ሰከን ብላችሁ አስተናግዱት!

By koan Ad

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

የክብራን ገብርኤል መናኝ ገጠመኝ

በዕለታት በአንዱ ቀን ከኪዳን ፀሎት በኋላ ንፋስ ለመቀበል ወደ ሀይቅ ዳርቻ አመሩ፡፡ ተፈጥሮን ያስተውሉ ጀመር፡፡ ሀይቁ፣ ንፋሱ፣ አዕዋፋት፣ በሀይቁ ዳርቻና በደኑ ጥግ የሚራወጡት አርጃኖዎች ብዙ ናቸው፡፡

ጠላቂ አዕዋፋት ሰምጠው ቆይተው የዕለት ምግባቸውን ራሳቸውን ወደ ፈጣሪ አንጋጠው አንገታቸውን ቀጥ አድርገው የዕለት ምግባቸውን ወደ ሆዳቸው ያወራርዳሉ፤ ሁሉም የአቅሙን ይጥራል፣ የመጠኑን ያገኛል፣ ይመገባል፤ ትርፍ ማግበስበስ የለም፤ የአቅምን የድርሻን ብቻ፡፡

በዚህ ትዕይንት መካከል አንድ ንሥር ከገዳሙ ረጅም ዛፍ ጫፉ ላይ ተቀምጦ በንሥር ዓይኖቹ የዓሣዎችን እንቅስቃሴ በንቃት ያማትራል፤ በድንገት በተመለከተው ትልቅ ዓሣ ጓጉቶ ተወርውሮ ወደ ሀይቁ ወረደ፡፡ እንደ ሰንጢ የሾሉ ጥፍሮቹን ከመቅፅበት በዓሣው ገላ /ጐን/ ላይ ሰገሠገ፡፡ የተለመደው ድርጊት ከዚህ በኋላ ረጃጅም ክንፎቹን እያማታ ወደ ላይ መነሣትና ወደ ረጅሙ ዛፍ አልያም ወደ ሀይቁ ዳርቻ በርሮ የዕለቱን ሢሣይ ማጣጣም ነበር፡፡

በዕለቱ መነኩሴው የተመለከቱት ግን አስገራሚ ነበር፡፡ ንሥሩ አድኖ የያዘው ዓሣ እጅግ ትልቅ ከመሆኑ የተነሣ ተሸክሞ መብረር አልቻለም፡፡ ጥፍሮቹ ጫፋቸው ላይ ቆልመም ያሉና እንደ ሜንጦ ያሉ ስለነበር ከዓሣው ለማላቀቅም አልቻለም፡፡

መጨረሻ ክንፎቹን አማትቶ ሲደክመው ሀይቁ ላይ ተመልሶ አረፈ፡፡ ዓሣው ነፍስ ዘራና ወደ ሀይቁ ንሥሩን ይዞት ሰጠመ፡፡

የንሥሩ እጣ ፈንታ መሞት እንደነበር ግልፅ ነው፣ እርግጥ ዓሣውም ከጐኑ የተሰካውን ጥፍር ባለቤት ትልቅ ንሥርን ያህል ተሸክሞ መኖር አይችልም፡፡ ሁለቱም አዳኝና ታዳኝ እጣ ፈንታቸው ሞትና ለሌላ አውሬ ሢሣይ መሆን ነው፡፡

መነኩሴው ባዩት ትዕይንት ተመስጠው ለራሣቸው “ለዐይን የሚያስጎመጅ ሁሉ አይበላም፤ ምናልባት ሞት ያለውም በሚያሰጎመጅ ነገር ውስጥ ይሆናል” አሉ፡፡
ነገሩ እስከ አሁን ድረስ እንደሚደንቃቸውም አጫወቱኝ፡፡

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Alemayehu wassie

Читать полностью…

ወግ ብቻ

የማባልጋት ባለትዳር ነበረች ።

ዋና ተግባራችን ወሲብ ነው ። የምንቀጣጠረው ለወሲብ ብቻ ነው ። የምናወራው ስለ ወሲብ ነው ። አንዳችን አንዳችንን የምንፈልገው ወሲብ ሲያምረን ነው ።

አጠገቤ ሆና ባሏ ደውሎ ያውቃል: "ሰውዬሽ ደወለ" ብዬ ስልኳን አቀብያት አቃለሁ ። ምንም እንዳልተፈጠረ ስታወራው እርቃኗን አትመስልም ነበር። ይገርመኛል ድድብናችን ።

ነውራችን ስለተደጋገመ ተግባራችን ብልግና መሆኑ ተሰወረብን ።

ቢሮዋ እሄዳለሁ፣ ቢሮዬ ትመጣለች ። ጓደኛዬ ቤት፣ እኔ ቤት፣ የሆነ ኮስመን ያለ ሰዋራ ቦታ ፣የሆነ ድብቅ ፅድት ያለ ስፍራ ፣ መኪና ውስጥ ... ብዙ ብዙ ቦታ ትመጣለች እንዋሰባለን ። የታሪካችን መነሻ እና መድረሻው ወሲብ ነው ።
አንድ ቀን በደነገጠ: ተስፋ በቆረጠ ድምፅ "ባሌ አወቀብን" አለችኝ .....ደነገጥኩ ።

ጠፋሁኝ ...ጠፋች

ከአስራ ሰባት ቀን በኋላ ጓደኞቼ "ገኒ ሃዘን ላይ ነች፣ ሙሉ ከላይ እሰከታች ጥቁር ለብሳለች፣ ከስታለች" አሉኝ

"ምን ሆነች?" አልኩ

"ባሏ ሞቶባት ነው፤ ራሱን አጥፍቶ ነው የሞተው" አሉ።

ስደነግጥ፣ ፊቴ ሲቀያየር ፣ እምባዬ ሲያመልጠኝ አዝኜለት ነው የመሰላቸው ። እኔ እንደገደልኩት አልጠረጠሩም ።

የጥፋተኝነት ስሜት ሊገለኝ ሲል ማምለጫ መፅሃፍ ቅዱስ ገለጥኩ።

"ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል " የሚለው ከሁሉም ጎልቶ ተነበበኝ ።
..
ሰው ይዞ መውደቅ ፤ ማስተካከል የማይቻል አወዳደቅ ፣ ሲያስታውሱት የሚያስነክስ አይነት አወዳደቅ፣ እነሳለሁ የማይሉት አወዳደቅ ፣ ወድቄ ነበር የማይሉት አወዳደቅ። በግዜ ምክንያት የማይደበዘዝ አወዳደቅ ...
እንደዚህ አይነት መውደቅ ሲ..ያ...ስ..ጠ..ላ !! !

By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

አስፈሪወቹ ሌሊቶች!

የሆነ ጊዜ የሚከራይ ቤት ስፈልግ አንድ ክልፍልፍ ደላላ "ግራውንድ ፕላስ 2 " ቪላ አጠገብ ያለች ቆንጆ የብሎኬት ቤት አሳየኝ። ለታክሲ ቅርብ፣ ፅድት ያለች በዚያ ላይ ዋጋዋ የማይታመን ርካሽ! ቤት። እድሌን አመስግኘ ወዲያው ተስማማሁ። መስኮቷን ስከፍት ፊት ለፊት የተንጣለለው ውብ ቤት ይታየኛል። መሀል አዲስ አበባ እንደዛ ሰፊ ግቢ ውብ ህንፃ...ዙሪያውን ያለ ደካማ መንደርተኛ እያየሁ "ወይ አዲስ አባባ የኑሮ ልዮነት..." እያልኩ እሁድ ገብቸ እስከማክሰኞ አለሜን ቀጨሁ።

ማክሰኞ እኩለ ሌሊት አካባቢ ነበር ድንገት ከአልጋየ የሚያነጥር ድምፅ እንደሰፌድ ቆሎ አንቀርቅቦ ያስነሳኝ። መድፍ ነበር የመሰለኝ። ደንግጨ ብነሳ ሀድራው ደርቷል ጭብጨባው፣ ጉሪያው፣ ከበሮው.... ሌላ ነገር ነው። በተለይ ከበሮው የአደዋ ዘማችን ነጋሪት ያስንቃል...ይነዝራል!
ድዝዝ ድዝዝ ድዝዝ ...
ጨብ ጨብ ጨብ
እሰይ እስይ እሰይ እሰይ
ሁርርርርር፣ ሁይይይ፣ አሀይ ..... እህህህህህህ !
ግርጭው ብርጭው አፍከኸከት ግራጭገት
አጉዛራ
ቀወዢራ
ጆቢጃራ
እሁይይይይ ....ደግሞ በጎች በመሀል ይጮሃሉ! ባኣኣኣኣ! ዜማውን ሁሉ እስካሁን አስታውሰዋለሁ።

መስኮቴን በቀስታ ከፍቸ ባጮልቅ ያ ቪላ ቤት ዙሪያውን በቆሙ የቤት መኪኖች ተጥለቅልቆ ሰፈሩ በከርቤ ጭስ ታፍኗል። በሩ ላይ ነጠላ ያደገደጉ ሰወች ቁመዋል፣ መብራቱ ፀሐይ ይመስላል። እንዳለ በሩ ቄጤማ ተጎዝጉዞበታል። ህልም ነበር የሚመስለው። በኋላ ስሰማ የታዋቂ ጠንቋይ ቤት ሆኖ ተገኘ። የተከራየሁት ቤት ለሰባት ወር ባዶውን እንደከረመ አንዲት ያለሁበት ግቢ ልብስ የምታጥብ ልጅ ነገረችኝ።

ድምጿን ቀንሳ በፍርሃት "ጥሩ አይደለም የገባው ሁሉ ተጥመልምሎ ነው የሚወጣው ቶሎ ልቀቅ ይሄን ቤት...ከአንተ በፊት ተከራይቶ የነበረው ልጅ፣ ሌሊት አያለሁ ብሎ በመስኮት ብቅ ሲል አፉ ወደግራ አፍንጫው ወደቀኝ ተጠነጋግሮ እግሩም ተጥመልምሎ ቁጭ! " አለችኝ....። አንች ለምን አልተጥመለመልሽም ልላት ፈልጌ ከአፌ መለስኩት። ውስጤ ቢፈራም "ሳለ መድሃኒያለም ለጠንቋይማ ርስቴን አለቅም" ብየ ጧት ጧት አፌና አፍንጫየ አለመጣመሙን በእጀ እየዳሰስኩ መኖሬን ቀጠልኩ። አንድ ቀን ጧት ቁርሴን ስበላ በአጋጣሚ ወደአፌ የላኩት ማንኪያ አፌን ሳተው። የደነገጥኩት መደንገጥ። መስተዋት ፊት ቁሜ ሳይግን አልተጣመምኩም። ነፍሴ መለስ አለች።

እና ማክሰኞና ሐሙስ "ላይቭ ባንድ በሚያቀርበው ጭፈራ እየተዝናናሁ መኖር አዝናኝ ሆነልኝ። አንድ ሐሙስ እንደውም ፀጥ ብሎብኝ ማዛጋት ጀምሮኝ ማንን ልጠይቅ ስል? ያችው ልብስ አጣቢ "ግንቦት ገባ፣ በዚህ ወር ሁልጊዜ ሰውየው የሆነ ቦታ ስለሚሄድ ሰላም እናድራለን" አለችኝ። እውነትም ጠንቋዮ ሙሉ ግንቦትን ጠፍቶ ሰኔ ላይ ተመለሰ። ሰፈሩም ትንሽ ዘና ብሎ ከረመ። በሳምንትም በወርም ከመንደርተኛው አንዱ ጠንቋዮን የተሳፈጠ ይጣመማል የሚል ወሬ ስለነበር እነዛ ሌሊቶች አስጨናቂ ነበሩ። ጠንቋይ እንዲህ ተፈሪ መሆኑን ያኔ ነው ያወኩት። በሹክሹክታ በሚደርሰን ስጋት ብዙ አስፈሪ ሌሊቶች የምናሳልፍ ህዝቦች ነን።

እንግዲህ በሳምንት ሁለት ቀን ማክሰኞና ሐሙስ ሌሊት እንዲቹ ሲቀወጥ ያድራል። የገረመኝ ይሄ አይደለም! ብዙ ባለሀብትና ታዋቂ ሰው የሚሰግድለትን፣ ስንቱን ሐብት በሐብት ያደረገ ነው የሚባለው ይሄ ጠንቋይ ለማየት ስመኝ አንድ ቀን በሁለት ሰወች ታጅቦ ሲወጣ አየሁት! ...(ጠንቋይ ከዛ በፊት አይቸ ስለማላውቅ ፤ የሆነ ፍጥረት ነበር የጠበኩት) ....ምን ገጠመኝ? መናኛ ሙሉ ልብስ ለብሶና ከዘራውን ይዞ የሚያዘግም ሽማግሌ። ያችው ወሬ ወዳድ ልብስ አጣቢ እየተጣደፈች መጥታ ነበር "ወጣልህ ና እየው" ያለችኝ። ...እና ምን አለችኝ?
"ጡረታውን ሊቀበል እየሄደኮ ነው"
ጡረታ?
"አወ ...ወታደር ነበር...ቢሞት ጡረታውን አያሳልፍም ከቤት የሚወጣውም በዚቹ ቀን ነው" 😀

By Alex abrham

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

"አንድ ሽበት ታያለህ ፀጉሬ ላይ?" አለኝ አንገቱን ጎንበስ አድርጎ

"አይይይ..." አልኩ አንገቴን ከግራ ወደቀኝ እየነቀነኩ

"አየህ... የእኔ ሚስት እናት በላት። ያኖረችኝ እንደ እናት ነው። ተግሳፅዋም፣ ፍቅሯም፣ እንክብካቤዋም፣ አሳቢነቷም ልክ እንደ እናት...ይገርምሀል ሳገባት ለብዙ ሰው መሳለቂያ ሆኜ ነበር...የሆነ ማዕበል ነው የተነሳብኝ..."

ለምን?

"በእኔና በእሷ መካከል ያለው የዕድሜ ልዩነት የተለመደ አልነበረም። 13 ዓመት ትበልጠኝ ነበር። እኔ የ27 ዓመት እያለሁ እሷ 40 ዓመቷ ላይ ነበረች። ይህ ነገር ብዙ ሰውን አስገረመ፣ ቤተሰብ ተንጫጫ (እናቴን ጨምሮ)፣ ጓደኞቼ በሙሉ አሽሟጠጡ አሾፉ፤ በሄድኩበት ሁሉ "ምነው ምነው አንተ?፤ ምነው ብጤህን ብትፈልግ?" እያለ አሸማቃቂው በዛ፤ ደግነቱ እኔ ላመንኩበት ነገር ምድር ከፍ ሰማይ ዝቅ ቢል አንድም ለውጥ አላደርግም። እናም እሷ ትበልጥብኛለች ብዬ 'አዲዮስ' አልኳቸው። አኮረፉ... ፍጡር የተባለ ሁላ ነው ያኮረፈኝ ከሚስቴ ውጪ፤ ርቀን ብቻችንን መኖር ጀመርን። በሄድንበት ሁሉ ባለትዳር መሆናችንን አይቶ ተገራሚው ቢበዛም 'ወይ ፍንክች' አልን፤ ኃላ ኃላ ነገሩን ተላመድነው። በዓመቱ መንታ ልጆች ወለድን ሁለት ወንድ፤ እነሱ በተወለዱ በሁለተኛው አመት አንድ ሴት ልጅ ደሞ ደገምን።

በስመአብ እንዴት ደስ ይላል...አሁን ስንት ዓመትህ ነው?" አልኩት ነገሩ እያስገረመኝ።

"አሁን 50 አለፍኩ...ልጆቼም ጎርምሰዋል"

"ኦ አትመስልም ግን...ልጆችህ አብረውህ ነው የሚኖሩት"

"ሴቷ ከእኔው ጋ ነች ወንዶቹ ውጪ ሀገር ሄደዋል።...ባለቤቴ የተረጋጋ ህይወት ነበር ያኖረችኝ...በጣም ነው የምወዳት፤ እሷ ደሞ ስትወደኝ የእኔን ሺ እጥፍ አይበቃውም፤ ብዙ እንክብካቤ ነበረኝ። እኔም በሁሉም ነገር እጅግ እታመንላታለሁ (ታምነኛለች) ፣ ከሰው ሀሜታ ሁሉ በፍቅር እሸፍናታለሁ...ቅንጣት እንዲከፋት አልፈልግም። ለነገሩ ቀስ በቀስ ሰዉም ስለእኛ ማውራቱን እርግፍ አድርጎ ተወ...ያው ተረቱ "ጉድ አንድ ሰሞን ነው" ይባል የለ። የሚገርምህ ያኔ ሲስቁብኝ የነበሩ ጓደኞቼ ዛሬ ከፊሎቹ በህይወታቸው የተረጋጉ አይደሉም...አንዳንዱ ቤተሰቡን በትኖ ጤና የማይሰማው አለ...አንዳንዱ ኑሮ እና ሚስቱ አቃጥለው ጠብሰውት ዕድሜው ትንሽ ሆኖ ግርጅፍ ያለ አለ... አንዳንዱ ያለ ትዳርም የሚኖር አለ። ብቻ ምን ልበልህ..."

"ይገርማል ...ባለቤትህስ ታድያ?"
"አልፋለች። ሁለት ዓመት ሊሞላት ነው ካለፈች።"

ይቅርታ

"የጤና ረዳት ነበረች። ክፍለ ሀገር ለስራ እንደሄደች በወባ ምክንያት ታማ ነው የሞተችው።የሚገርምህ ስትሄድ ውስጤን ብዙም ደስ አላለውም ነበር።ያው የስራ ነገር ሆነና ሄደች በህይወት አልተመለሰችም።" ትክዝ አለ። ፊቱ ላይ ጥልቅ የሆነ ሀዘን አ ሳየኝ

"ይቅርታ...መጥፎ ትዝታ ጣልኩብህ " አልኩ

"አይ ምንም አይደል...ባይገርምህ አሁን ጎኔ እንዳለች ነው የሚሰማኝ...ከህልፈቷ በኃላ የመጀመሪያ ዓመት ላይ እጅግ ከብዶኝ ነበር። ኋላ በልጆቼ ተፅናናሁ በተለይ ሴቷ ልጄ የእናቷን መልክ ከነ ልቧ ነው የወረሰችው...ይመስገን በእነሱ ተፅናናሁ።...ትዳር ውስጥ ስትገባ አብዛኛው የሚስማማበትን ሳይሆን...ለአንተ የምትስማማህ ላይ ወስን...ያኔ ምንም መናወጥ የሌለበት ባህር ላይ ታንኳህን እንዳሳረፍክ ይገባሀል። ምክንያቱም ከታደልክ የዘላለም ህይወትህ ነው።" ቀና ብሎ አየኝ። ባለ ሙሉ ልብነቱ ከአወራሩ ያስታውቃል። ስልኩ ጠራ "ህምምም ...አየህ እቺ የእናቷ ቢጤ ደወለች..." ፈገግ እያለ ስልኩን አንስቶ ስፒከር ላይ አደረገና በዓይኑ ስማት ብሎ ምልክት አሳየኝ
"ሄሎ አባቢ...የት ነህ?"
"አለሁ...እዚሁ መናፈሻው አካባቢ ቁጭ ብዬ ነው..." ልክ በዓይኑ እንደሚመለከታት ነው ድምፅዋን በስስት ነው የሚሰማው

"አይ ይሁን ...አትገባም ወደ ቤት ንፋስ እንዳይመታህ... ምግብም አስቀምጬልሀለሁ ቡና ከፈለክ አለልህ ሞቅ አድርገህ መጠጣት ነው...ወይ በዛው ሳልፍ ላግኝህ እንዴ?"አለች። ስታወራ በፍጥነት ነው መልስ እስኪመልስላት አትጠብቅም
"ነይ እሺ...ትላንት የጠየቅሽኝንም ትወስጃለሽ በዛው"
"መጣሁ እሺ..."ብላ ስልኩ ተዘጋ።
"ተመለከትክልኝ በዚህ ሁሉ ፍቅር መሀል ሆኜ እርጅና ከየት ይመጣል ብለህ? ሀ ሀ ሀ ሀ😊... እስካሁን ግን እኮ አልተዋወቅንም...ስምህን ማን ልበል?" አለኝ። ለካ ድንገት እራሴን ላናፍስ ብዬ በገባሁበት መናፈሻ ቦታ ነው ድንገት ከዚህ ሰው ጋር አብረን ተቀምጠን ወግ የጀመርነው።

"አብርሃም እባላለሁ...እኔስ ማን ልበል?"

"እኔ አድማሱ እባላለው። እዚህ አካባቢ አይቼህ ግን አላውቅም... እዚህ ነዋሪ ነህ?" በደንብ ልብ ብሎ እያየኝ ጠየቀኝ...
"አይ እኔ እንኳን ለዘመድ ጥየቃ ከዝዋይ ነው የመጣሁት በዛውም አንድ ጉዳይ ነበረኝ...እዚህ ፀሀዩም ከረር ሲልና ቦታውን ሳልፍ ስለወደድኩት ገብቼ ቁጭ አልኩና ተገጣጠምን። "
"ግሩም ነው።እኔም ቦታውን እጅግ ነው የምወደው ለቤቴም ቅርብ ነው።ብዙ ጥሩ ጥሩ ተጨዋወትን!...ያቿትልህ አበባዬ መጣች..." ቀና አልኩኝ... እውነትም አበባ እየተራመደ መጣ። ከቁመቷ ዘልግ ማለት፣ከመልኳ ጥራት፣ከዓይኗ፣ከጥርሷ፣ከአፍንጫዋ ምኗንም ጥንቅቅ አድርጎ ነው የሰራት...ቅልጥፍናዋ ከአረማመዷ ያስታውቃል። ደነገጥኩ።
አባቷን አቅፋ ሳመች። ወደ እኔ እጇን ዘረጋች "አብርሃም ይባላል። የዝዋይ ልጅ ነው።" አላት አባቷ ትከሻዬን ነካ አድርጎ እያስተዋወቃት። እኔ ዝም ብዬ እጄን ዘረጋሁ። ከአባቷ ጋ የረጅም ግዜ ግንኙነት እንጂ፤ ፈፅሞ ዛሬ የተገናኘን አንመስልም።
"አበባ..." አለችኝ። ውበቷ በጣም ነው ያስደነገጠኝ። አባቷ ሳይታዘበኝ አይቀርም። በራሴ አፈርኩ።"ታድያ እቤት ይዘኸው አትመጣም ነበር? ከአንድ ሰዓት በፊት ብትመጡ እኮ ቡና አፈላላችሁ ነበር።ደሞ ምግብም አብ ስዬ ነበር። ቅድም በስልክ አልኩህ አ? አስቀምጬልሀለው። ቡናውንም እንዳልኩ" አለች ሁለታችንንም እያየች...ስታወራ ምንም መልስ እንደማትጠብቅ አሁን ይበልጥ ተረዳሁ።

"እሱም ተፈጥሮ ወዳጅ እኔም ተፈጥሮ ወዳጅ...ጨዋታ ይዘን ከዚህ ቦታ መነሳቱ እንዴት ይሁንልን ብለሽ ..." ብሎ በዓይኑ ተመለከተኝ። ጭንቅላቴን በአዎንታ ነቀነኩ...

"እሺ ይሁን በቃ ሌላ ቀን ...አሁን ስጠኝና ልሂዳ ረፈደ...ጓደኛዬም እየጠበቀችኝ ነው።"አለች። ብር አውጥቶ ሰጣት ወይ የትራንስፖርት ይሆናል፣ ወይ የትምህርት ቤት አልያም ለሌላ ይሆን ይሆናል።ከተቀበለችው በኃላ ተሰናብታን በፍጥነት ሄደች። ከዓይናችን እስክትሰወር በዓይኑ ተከተላት።ዓይኑ ላይ ጥልቅ ትዝታ አለ።
"...እና መች ነው ወደ ከተማህ የምትመለሰው?" አለኝ ከዓይናችን ከተሰወረች በኃላ ወደእኔ ተመልሶ

"አይ ትንሽ መቆየቴ እንኳን አይቀርም። የምጨርሳቸው ጉዳዮች አሉኝ።" አልኩ

"የምረዳህ ነገር ካለ አለሁ፤ ብዙ ግዜ ከዚህ ቦታ አልጠፋም። እሁድ እንደውም ቤት ብትመጣ ደስ ይለኛል።በዚህ አቅጣጫ 100 ሜትር ሄደህ በግራ ስትዞር አንድ ሱቅ አለ፤ ከእሱ ቀጥሎ ያለው ሰማያዊ በር የኔ ነው።እንዳትቀር አጠብቅሀለው።በል ሰላም ሁን ልሂድ" ብሎ ከመቀመጫው ተነሳ።
"እሺ...መልካም ቀን..." ብዬ ቆሜ ተሰናበትኩትና ቁጭ ብዬ ከዓይኔ እስኪሰወር ከጀርባው አስተዋልኩት። ተክለ ሰውነቱ በእርጅና አንድም ንክች አላለም። የሚመስለው ገና የ 40 ዓመት ወጣት ነው።ለካ ዙሪያችን አድርገን የምንሸከማቸው ሰዎች ናቸው የሚያጎብጡንም፤ የሚያቃኑንም።

by Abrham. F Yekedas

@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

ጫካ ውስጥ አንዱ ዝንጀሮ ዛፍ ላይ ሆኖ ቅንዝርርር ይልበታል; እናም ካቅሙ በላይ ሲሆንበት ታች ያለው አንበሳ ጀርባ ላይ ጉብ ብሎ ፀጉሩን እንቅ አርጎ ይሰርረዋል …

አንበሳው ከጀርባው ለማውረድ በዚህ በዛ ሲታገል ዝንጀሮ እንቅ እንዳረገ ይጨርስና ወርዶ ላጥ ይላል …
አንበሳውም ተደፈርኩ ብሎ ሲያባርረው ዝንጀሮ ሆዬ በሆነች ቅያስ እጥፍ ብሎ ሌላ ዝንጀሮ በመምሰል ዱቅ ብሎ ጋዜጣ ማንበብ ይጀምራል፦

አንበሳው ይደርስና "የሆነ ዝንጀሮ በዚህ ሮጦ ሲያልፍ አይተሃል" ሲለው

"አንበሳውን የነፋው?" ይለዋል …

ይሄኔ አንበሳው ድንግጥ ብሎ ፦

"ከመቼው ጋዜጣ ላይ አወጡት? 🤔"

By hasen enjamo

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

ቦግ እልም!
(አሌክስ አብርሃም)

በደርጉ ዘመን «ዕድገት በህብረት » የሚባል ዘመቻ ታውጆ ነበር አሉ። በየዩኒቨርስቲው ያለው ተማሪ በየገጠሩ እየሄደ ህዝቡን እንዲያስተምር፣ እንዲያነቃ ነበር ዘመቻው! ከዘማቾቹ ፍልስፍና ቢጤ ያነበበ ተማሪ ይሄድና አንዱን በሰላም የሚኖር አርሶ አደር "ፈጣሪ የሚባል ነገር የለም አጉል እምነት ነው» ይለዋል! ማለት ብቻ አይደለም የተማረ የሚታመንበት ዘመን ነበርና በመረጃና በማስረጃ ያንን ሚስኪን ገበሬ ራሱን አዙሮ አሳመነው! ገበሬው «በቃ ፈጣሪ የሚባል ነገር የለም » አለና ከቤተክርስቲያን ጠፋ! ለሌለ ሲኦል በከንቱ ነው ስፈራና ስጋየን ስጨቁን የኖርኩት አለና ጠጁን እየጠጣ፣የስጋ ነገሩን እንዳማረው እየፈፀመና እርሻውን እያረሰ ሲኖር ሲኖር ሲኖር ዘመቻው አልቆ ልማት የሚያለሙ ሚሽነሪዎች እዛው ገጠር ሄደው ያንኑ ሰው አገኙት «ፈጣሪ አለ፣ እንደውም ለአንተ ብሎ ሙቶ ተሰቅሎ . . . » ብለው ክፉኛ ሰበኩት፣ አመነ! ቤተክርስቲያን በስንት ጊዜው ሲሄድ «ምነው ከግዚሃር ቤት ጠፋህ» ቢሉት
«እኔማ ምን መጥፊያ አለኝ፣ እግዜሩ ራሱ በየተራ ሰው እየላከ ቦግ እልም ያደርጉብኛ እንጅ» አለ አሉ!

By Alex abrham

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

"እናቴ ሁልጊዜ 'ደህና ነህ? ደህና ነህ?' ማለት ታበዛለች" አለኝ። ገና ከመግባቱ ። ጓደኛየ ነው፣ አብረን እንሰራለን። እናቱ ጋር አውርቶ ገና ስልክ መዝጋቱ ነበር። ሁልጊዜ ጧት ጧት ያወራሉ።

"እናት አይደሉ" ከማለቴ ፈጠን ብሎ
"ኖ ኖ ከኖርማሉ በዛ ይላል የሷ! በኋላ ስትነግረኝ በተወለድኩ በሁለት ወሬ አንዲት ደንቃፋ ሰራተኛ ትልቁ ባለአበባው የቡና ስኒ ታውቀዋለህ? ያ ስኒ አምልጧት ጭንቅላቴን ነርቶኝ ነበር። እና እናቴ የሆነ የአዕምሮ ችግር ይፈጠርብኛል ብላ ስትጨነቅ ነው የኖረችው። እንደምታየኝ ተርፊያለሁ! እሷ ግን እስከአሁን አታምንም። አለና ተሳሳቅን።

ወደቡና ማሽኑ ሄዶ ሁለት ቡና ይዞ መጣ ...አንዱን ዘረጋልኝ። ቡና ማቆሜን ለሃያኛ ጊዜ ትላንት ነግሬው ነበር። እንደገና ሳስታውሰው ሳቀና "እናቴ እውነቷን ነው መሰል አንተ?" አለ።

"እንደገና ደውልላቸውና ሰራተኛዋ የቡና ስኒ ነው ወይስ ዘነዘና የጣለችብኝ ብለህ ጠይቅ" ዝም አለ። የመልስ ምት እያሰበ ነው። ሲያስብ ትንሽ ይዘገያል ስኒው መሰለኝ። ቆይቶ

"ሰራተኛ ነበራችሁ" አለኝ
የለንም
ስኒስ ?
የለንም
ዘነዘናስ?
የለንም
በቃ አንተ ራስህ ሲያቅፉህ አምልጠህ በጭንቅላትህ መሬት ላይ ወድቀህ ነበር። 😁

By alex abrham


@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

ማሪታ ሎሬንዝ

ዘመድ አይጥፋ ባለፈው ዙምባቤ ሐረሬ ዞር ዞር ስል ትንሽ ሃገሬ ብትናፍቀኝም ጓድ መንግስቱም እንኳን ተወለዱ ለማለት  እቤታቸው ጎራ አልኩኝ ።

ፍልቅልቋ ባለቤታቸው ወ/ሮ ውብባንቺ ቡና  አፍልተው እያጫጫሱ ሳለ በአይኔ የፊደል ካስትሮን እና  የጓድ መንግስቱ  ፎቶ ስቀላውጥ አይተው "ጥቁር ነብር " ሚላቸው በአሉ ግርማ  ጓድ መንግስቱ ፊታቸውን ጠቆር አርገው የማየውን ካጤኑ በኃላ

ይገርምሃል  ያኔ ሁለታችንም የበዛ የሃገር ፍቅራችን እራሳችን ላይ ወቶ ካቲካላ እንደጠጣ ሰው በሰከርንበት ጊዜ ነበር ይሄን ፎቶ የተነሳነው ብለው ላፍታ ትክዝ አሉ።

እንግዲ ወዳጄም አይደል እቺ ሰዓት ምን እያወራን መሰለክ ብለው የትዝታ ፈገግታ ብልጭ አረጉና ጉሮሮዋቸውን ጠራርገው እንዲ ሲሉ ጀመሩ ....

ስለ ሴት እያወራን ነበር ለዛውም ስለ ጉደኛ ሴት ...

ካስትሮ ሞት በቃኝ ካንተ ጋር ትግል ደከመኝ ስለተባለለት ከ600 በላይ ጊዜ የግድያ ሙከራ ስለተደረገበት የኔ ወዳጅ ፣ የህፃናት አንባ ልጆች አጎት፣ የኤርኔስቱ ቼ ጉቬራ የትግል ጎደኛ  ፣  ፣የሶሻሊስት አጥማቂ፣ የአሜሪካ ራስ ምታት ፣ ከከበርቴ ቤተሰብ የተገኘው የበኩር ልጅ ፣ የውቧ ኩባ ባላባት፣የራሁል ወንድም ፣ ፊደል ካስትሮ እንዴት ከሞት አፋፍ ስንት ጊዜ እንዳመለጠ አጫውትሃለሁ አሉኝ በኩራት ።

  በተለይ ደሞ ከሴት ወጥመድ እንዴት እንዳመለጠ ብታይ ብለው ወደጣሪያው እያዩ ወገባቸውን ወደ መደገፊያው አሳረፋ።

ነገር ጎንጓኟ አሜሪካ ልታስገድለው ያልቆፈረችው ጉድጓድ አልነበርምና

በEisenhower 38 ጊዜ፣በKennedy 42 ጊዜ፣በJohnson ፣በNixon፣በReagan ፣እንዲሁም በBush እና በClinton ጊዜ ጨምሮ ከ635 ጊዜ ሚሆን የግድያ ሙከራ የተደረገበት ብርቱው ሶሻሊት ነበር ፊደል ካስትሮ የኃላ ኃላ አሜሪካ ሴት ላከችበት!

አሉና ወደባለቤታቸው ዞር ብለው የፍቅር አዪዋት

ወ/ሮ ውብባንቺ አሄሄሄሄ ስለዛች ጉደኛ ስለ"ማሪታ" ልታወጋው ነው አሉ ፊታቸው ሙሉ እየሳቀ ።

"marita lorenz" እቺ ሴት  የጀምስ ቦንድን ሴቶች ምታስንቅ ቆንጆና በ25 ዓመታት የስለላ ታሪኳ ገዳዬ ገዳዬ ተብሎ የተዘፈነላት ቀላች እንጂ የሙት መንፍስ ስጋ ለብሶ በላት ።

ከጀርመን አባቷና ከአሜሪክዊት እናት የተወለደች የCIA ግርፍ ነች ብለው አከሉበት ።

ማሪታ ሎሬንዝ ምንትስ በተባለ መርስ ልትገለው ባንድ ክፍል ውስጥ እራሷን ከቁመተ ለግላጋው ከፊደል ካስትሮ ጋር ተገናኘች ቀድሞውኑ ቀልቡ የነገረው ፊደል ካስትሮ ቁልቁል እያያት እንድትገይኝ  ነው አይደል የላኩሽ አላት ፀጉሩዋን እየደባበሰ ።

" ቼ" አለችው በስፖኒች ቋንቋ "የኔ" ማለት ነው አሉ ጓድ መንግስቱ በእንክሮት ቃሉን ረገጥ አርገው ።

ማሪታ ሎሬንዝ ተንሰፈሰፈች ልገልህ አልችል   አለችው
( Quiero esta noche contigo un gastado papi ) አለችው

ትንሽ ማስተካከያ ታክሎበት

"ካንተ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት"

ማለቷ ነው ብላ ከደረቱ ተለጥፋ ትኩስ እንባ በጉንጮቿ አወረደች ።

ጓድ መንግስቱ ወደኔ እየተጠጉና ሚስታቸውን አፈር እያሉ  "የኩባ ሴቶች በደንብ ካረካቸው እና የልባቸውን ካደረሱ
የእርካተ ጣሪያ ላይ ሲወጡ በነሱ ቋንቋ  "Carico papi"  ይላሉ አሉኝ ይህም ነጮቹ Am coming ሚሉት ነው ብለው በሳቅ ፈነዱ ።

እትዬ ውብአንቺም አንቱ !

ዘንድሮም አላረጁ አሉ በባላቸው ቅብጥብጥነት አየሳቁ።

ከነዚህ ሁላ የግድያ ሙከራዎች መክሸፍ ምን እንዳዳነው ገምት እስኪ ጃል ? አሉኝ

አይናቸውን አጨንቁረው መልሴን በመጠባበቅ።

እኔም የግል ጠባቂዎቻቸው ብርቱና ንቁ ናቸው ብዬ አስባለሁ አልኩ ጥርጣሬ ባዘለ ድምፅ

ልክ ነክ አሉ ጓድ መንግስቱ ፈገግ እያሉ አንዱ እሱ ሲሆን ግን ዋነኛው የሱ ደመ ነፍስ ነበር ።

ደመ ነፍስ ? አልኩ ጥያቄ ባላው ድምፀት

ጓድ መግስቱም ቀጠል አረገው ፊደል ካስትሮ ቡና ይወዳል እሱን ካልጠጣ እና ያንን ግንድ ሚያክል ወይራ ወይራ ሚል ሲጋሩን(Cigar)አፋ ላይ ካላረገ ስራ አይሰራም ።

አይኑም አይገለጥለትም አሉ ጥቁሩ ነብር ።

የነሱ ቡና እ'ንደኛ እንዳይመስልህ ቦንብ ነው ፣ቦንብ ሚጠጣው እራሱ ባረቄ መለኪያ ነው ።

አንዴ እሷን ቋ  ካረገ ሁሉ ነገር ወገግ ብሎ ይታየኛል ይላል ፤ አሉ ጓድ መንግስቱ  አይናቸውን ወደ ፎቶው ቡዝዝ አርገው ።

እናሳ በምን ተቋጨ የሲቲቱ ጉዳይ አልኩ መጨረሻውን ለመስማት ጓጉቼ

በዚህ ሰዓት ሁሉ ነገሬ ጆሮ ሆኖ ነበር ።

ሳትገለው የፍቅሩን አዙሪት አልቻልኩም ብላ ወደ ሃገሯ አሜሪካ ሄደች ።

ማሪታ ሎፔዝ ልገለው አልቻልኩም ብላ CIA ን ግን ዋሸች ።

አንድ ልጅ ወልዳለታለች ይባላል አሉ እሱ ግን ውሸት ነው ይላል አሉ ጥቁሩ ነብር ።

የጊዜ ጀግና እንጂ የሰው የለው ብለው ሚስታቸው ውብባንቺ በነገር ጎሸም አርጓቸው ።

ጓድ መንግስቱም ዞር ብለው ሚስታቸውን እስቲ ተይ ...ተይው ዓለሜ አሏትና በረጅሙ ተነፈሱ ።

የራሳቸው ትዝ ሳይላቸው አልቀረም

ብቻ አሜሪካም ልትገለው እንደቋመጠች በ90 ዓመቱ ዓረፈ አሉኝ ጥቁሩ ነብር ደግመው ፎቶውን እያዩ።

እኔም ፎቶውን ደግሜ ሳየው ፊደል ካስትሮ

"ገደገድኩባት " ሚሉ ነው ሚመስሉት ።

By Ermias frew

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…

ወግ ብቻ

በሁሉም ቀናት ከሰዓት አንድ ጉዳይ አስባለሁ። መኖራችንን። ከመሰደድ፣ ከመጋደልና ከመቧደን የተረፈ ቀናችንን። ኖረናል?! እንጃ?! እንደ Virginia Woolf አባባል ቀን ተቀን ከማውቀው ህይወታችን ወዲያ የምመኘውና በስሜት የሚንጠኝ አለ።(I have a deeply hidden and inarticulate desire for something beyond the daily life)። ያልደረስኩበት ሰላም፣ ያላሸተትኩት መውደድ፣ ያልኖርኩበት አንድነት፣ እንዳሻኝ የምዞርባት ሀገር ትናፍቀኛለች። እንደ መንግስቱ ኃይለማርያም ሀገርየምታምስ "ሰብአዊነት ይፋፋም" የምትል ቃል ብዬ የምወረውረው ነጭ ርግብ የያዘች ጠርሙስ አሊያም እንደ ቀይ ሽብር ፍቅር፣ ሰላም፣አንድነትና ነጻነት ይፋፋምብኝ ብላ የሞቷ ምክንያት ከጀርባዋ የተለጠፈባት ወጣት ። እንደ ህዝብ በሀዘን አንጀቴን አስሬና ተለጉሜ ከኖርኩባቸው ቀናት ወዲያ የሰላምና የደስታ አብዮት በታሪኬ እንዲጻፍ አልማለሁ።
በሰላም መኖርን

@wegoch
@wegoch
@paappii

Читать полностью…
Subscribe to a channel