wasulife | Unsorted

Telegram-канал wasulife - Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

221547

እንኳን ደህና መጡ‼ ✔ማስታወቂያ ለማሰራት እና ጥቆማ ለመስጠት በዚህ ይጠቀሙ ☞https://t.me/WasuMohammed ✔ ቻናሉን ለመቀላቀል Join ☞http://t.me/Wasulife ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏

Subscribe to a channel

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

ኢትዮጵያና ኡጋንዳ‼

የኡጋንዳ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙሆዚ ካኒሩግባ አዲስ አበባ ናቸው።ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መምከራቸውን ሰምተናል።

ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ከስደተኞች ጋር መሽገው ወንጀል የሚፈፅሙትን በጋራ ለመከላከልና ለመስራት መግባባት ላይ መድረሳቸውም ተሰምቷል።ዚህም ሁለቱ ሀገራት የፀጥታ መረጃ መቀያየር፣ ሁሉን አቀፍ ስልጠና እንዲሁም ለቀጣናው ሰላም በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት ማድረጋቸውን ተዘግቧል።
---------------------------------------------------
"በአማራ ክልሉ ጉዳይ በጣም አዝናለሁ።ለትግል ወጣሁ ባለው ወጣት አልፈርድም"  አቶ ጣሂር
👇እዚህ ይከታተሉት👇
https://youtu.be/p6asP2eF_U0
https://youtu.be/p6asP2eF_U0

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

ሶማሊያ ወታደሮቿን ከጁባላንድ አስወጣች።

ሶማሊያ ከማዕከላዊ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት ካቋረጠዉ የጁባላንድ ግዛት ከአካባቢዉ ሃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት የፌደራል ወታደሮችን ከደቡብ ምዕራብ የታችኛው ጁባ ክልል ማስወጣቷን  አሳውቃለች።

ጁባላንድ ባለፈው ወር በተመረጠው ድምጽ የጁባላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ መሀመድ ማዶቤን በድጋሚ ከመረጠ በኋላ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፌደራል ወታደሮች ወደ ስፍራው ሄው በራስ ካምቦኒ የባህር ዳርቻ ከተማ ዙሪያ ከባድ ጦርነት ተካሂዶ ሽንፈት ደርሶባቸዋል።

ከኬንያ እና ከኢትዮጵያ ጋር የምትዋሰነው ጁባላንድ ከሶማሊያ ከፊል ራስ ገዝ መንግስታት አንዷ ናት። ሶስት ክልሎችን ያቀፈ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የታችኛው ጁባ በህዝብ ብዛት ከፍተኛ ነው።
💎https://www.facebook.com/profile.php?id=61569879454961&mibextid=ZbWKwL
📌ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

ይህ በአዋሽ ኮምቦልቻ ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ላይ እየተፈፀመ ያለ ዝርፊያን የሚያሳይ ነው።ከየሳይቱ አቅራቢያ የሚደርሱኝ ጥቆማዎች በጣም ያሳዝናሉ።1.7 ቢሊየን ዶላር በወጣበት ፕሮጀክት እየቀለደ ያለው መንግስታዊው ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዛሬም ዝርፊያውን በዝምታ እየተመለከው ይገኛል።መንግስትም "እኛ ስላልጀመርነው አይመለከተንም "የሚል በሚመስል አካሄድ ዞሮ ለማየት አልፈለገም።
💎https://www.facebook.com/profile.php?id=61569879454961&mibextid=ZbWKwL
📌ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

የባስ አታምጣ ከማለት ውጭ ምን ይባላል‼

ጋናዊ ፓስተር ራሱን መልዓክ ነኝ ብሎ ሰይሟል ። እኔን አዝላችሁ እንድትወስዱ ጌታ አዟል በማለት ምዕመናኖቹን ጀርባ ላይ እንደ ህጻን ታዝሎ ወደ አምልኮ ስፍራው ይሄዳል።

ምዕመናኑም በረከት ለማግኘት በሚል ተሽቀዳድመው በነቢያቸው ይጋለባሉ። ነቢያቸውን አዝለው ወደ ቸርች የሚገቡ ምዕመናንም በልዩ ሁኔታ በጭብጨባ አቀባበል ይደረግላቸዋል።
ማሕበራዊ ሚዲያ የማያሳየን የለም።"
(Befekadu Abay)
ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተደረሰው ስምምነት “አይመለከተኝም” ስትል ሶማሊላንድ ገለጸች

በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና በሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ መካከል ቱርክ ውስጥ የተደረሰውን ስምምነት በሚመለከት ሶማሊላንድ አቋማን አስታወቀች።

የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ ዋዳኒ ፓርቲ ቃል አቀባይ ሞሐመድ ፋራህ አብዲ በሁለቱ አገራት ስምምነት ላይ የመንግሥታቸውን አቋም ለቢቢሲ ሶማሊኛ ተናግረዋል።

ስምምነቱን በተመለከተ በሶማሊላንድ በኩል ያለውን አስተያየት ቃል አቀባዩ እንደተናገሩት በሁለቱ አገራት መካከል አንካራ ላይ የተደረሰው ስምምነት የሁለቱ አገራት ጉዳይ መሆኑን እና ሶማሊላንድ ሌላ አገር በመሆኗ ይህ ጉዳይ የሚመለከታት እንዳልሆነ አስረድተዋል።

"የፈረሙት ሁለቱ አገራት ናቸው፣ እኛ ሶማሊላንድ ነን። ሁለቱ ወንድማማች አገራት የራሳቸውን ስምምነት ነው የተፈራረሙት። እነሱ ተነጋግረው ከስምምነት ላይ መድረሳቸው የተለመደ ነገር ነው። እኛን የሚመለከት አይደለም" ሲሉ የገዢው ዋዳኒ ፓርቲ ቃል አቀባይ ሞሐመድ ፋራህ አብዲ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ቀደም ሲል በሶማሊላንድ ሥልጣን ላይ የነበረው መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ ያለበትን ሁኔታን በተመለከተ ሲናገሩ አዲሱ መንግሥት ገና ሥልጣን መረከቡ በመሆኑ ጊዜ ወስዶ እንደሚመለከተው እና የሚወስንበት መሆኑን ገልጸዋል።

"ገና ሥልጣን መረከባችን ነው፤ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገውን ስምምነት አልተመለከትነውም። ነገር ግን የምናየው ይሆናል፤ አይተነው የሶማሊላንድን ጥቅም የሚያስጠብቅ ከሆነ እንሠራበታለን፤ ካልሆነ ግን የሚቀር ይሆናል። ስለዚህ ምን እንሚሆን ለማወቅ መጠበቅ አለብን፣ ከዚያ በኋላ ውሳኔ ይሰጥበታል" ብለዋል ቃል አቀባዩ።
ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

የፖሊስ አባል የሆነች ባለቤቱን  በመጥረቢያ እንጨት ደብድቦ የገደለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ አስተዳዳር  ነዋሪ  እና የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ የፖሊስ መኮንን የሆኑትን ረዳት ኢንስፔክተር ጀሚላ  ቢንዳ የተባለችው ባለቤቱ  ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ  በእስራት ተቀጥቷል።

ሟች በምዕራብ  አርሲ ዞን  በተለያዩ ወረዳዎች በከፍተኛ አመራርነት ሲሰሩ ቆይተዋል ።

በፖሊስ ሙያ እያገለገሉ ባሉበት  ወቅት ከአቶ ከድር ጅቦ ከተባለ የዶዶላ ከተማ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ  ጽ/ቤት ሰራተኛ ጋር ትዳር መስርተው ይኖሩ እንደነበር ተገልጿል ።

ጥንዶቹ በትዳር ከ30 ዓመት በላይ በመቆየት የአምስት ሴት ልጆች  እና የአንድ ወንድ ልጅ ማፍራት ችለው እንደነበር  የዶዶላ ከተማ አስተዳደር  የፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አብዱላዚዝ ጀማል በተለይ  ተናግረዋል።

ሟች በስራቸው ላይ ባሳዩት ብርታት አዋሽ ማሰልጠኛ ገብተው በመሰልጠን  የረዳት  ኢንስፔክተርንት ማዕረግ በማግኘት የሴቶች እና ህጻናት ክፍል ኃላፊ በመሆን  ሲያገለግሉ በነበረበት ሰዓት በትዳራቸው ላይ አለመግባባት እየተፈጠረ በሽምግልና  ለመፍታት ሲሞከር የነበረ  ቢሆንም ለልጆች ሲባል ትዳር ሳንበትን አብረን እንኖራለን በሚል ተስማምተው እንደነበረ ተነግሯል።

ሚያዚያ 13 ቀን 2016  ዓ.ም  ረዳት  ኢንስፔክተር ጀሚላ ስራ ውለው ደክሟቸው  ለማረፍ ገብተው ይተኛሉ። አቶ ከድር ከጓደኞቻቸው ጋር መጠጥ ጠጥተው  አምሽተው ወደ ቤት ሲገባ ሁሉም የቤተሰቡ አባል መተኛታቸው ያረጋግጣል ። ባል አልጋ ለይቶ ስለነበር  ሚስት ማንም ወደ እኔ ክፍል የሚገባ የለም በማለት በሩን ሳይዘጉ ነበር የተኙት ይሁን እና መተኛታቸውን ካረጋገጠ በኋላ የእንጨት መፍለጫ  መጥረቢያ ዛቢያ እንጨት አንስቶ  በእንቅልፍ ለይ ያለችውን ባለቤቱን አንገቷን እና ጭንቅላቷን በመምታት ከባድ ጉዳት አድርሷባታል ። 

ጉዳት ካደረሰባት በኋላ ተሸክሞ ወደ ጤና ተቋም  ካደረሳቸው በኋላ ከአካባቢው ይሰወራል ይሁን እና በህክምና እርዳታ ላይ የነበሩት ኢንስፔክተር ጀሚላ ህይወት ያልፋል።ይህንን ድርጊት ተከትሎ የኦሮሚያ ፖሊስ መምሪያ እና የምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ  አመራር አካላት  በአባሏ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን በመግለጽ  መኮንኗ ሚያዚያ 16 ቀን 2016  ዓ.ም  ወዳጅ ዘመድ እና የስራ ባልደረቦች ባሉበት ስርዓተ ቀብሯ መፈጸሙ ገልጿል ።

ፖሊስም  ባለቤቱን የገደለውን ግለሰብ  በማፈላለግ  ክትትል ሲያደርግበት ከቆየ በኋላ   ከ12 ቀናት ቆይታ በኋላ  ከተሸሸገበት በምዕራብ አርሲ  ዞን ገደብ አሳሳ  ወረዳ ሚያዚያ 28  ቀን 2016 ዓ.ም  በአንድ ግለሰብ ቤት ተሸሽጎ  በቁጥጥር  ስር ሊውል መቻሉ ፖሊስ ገልጿል ።

በዚህም ባለቤቱን ማለትም ረዳት ኢንስፔክተር ጀሚላ በተኙበት ጉዳት አድርሶ ህይወታቸው እንዲያልፍ  ማድረጉ በማመን ድርጊቱን የፈጸመው በሌላ ሰው ስለምትጠረጥረኝ ነው በማለት ቃሉን ለፖሊስ ይሰጣል።  ፖሊስ መዝገቡን በማጠናከር ለዓቃቢ ህግ ይልካል ። ዓቃቢህግ  በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ በመመስረት ለምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት  ይልካል ።

ፍርድ ቤትም ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም  በዋለው ችሎት በ18 ዓመት እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት ሲሆን ተከሳሹን ሸሽጎ ያስቀመጠው ግለሰብ ደግሞ 5ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ መወሰኑን የዶዶላ ከተማ  አስተዳደር  የፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል  ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር  አብዱላዚዝ ጀማል ጨምረው ተናግረዋል።
መረጃው የብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ነው
📌ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

አዲስ አበባ ዋና መስመር ላይ የአገልግሎት መስጫ ያለው ከምሽት 3:30 ቀድሞ መዝጋት ተከለከለ

መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ ፀደቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

የጸደቁ አጀንዳዎች:-

📌1ኛ. የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ብክለት መከላከል ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ለከተማዋ ነዋሪዎች ጤና፣ ፅዳት እና ውበት ወሳኝ እና ጠቃሚ መሆኑን በማረጋገጥ ደንቡን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

📌2ኛ. በከተማ ፕላን ልማት ቢሮ የተዘጋጁና የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጀት፣ አፈፃፀም ቁጥጥር እና ደንብ ማሻሽያን መርምሮ በመወያየት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

📌3ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ማቅረብ በመጀመሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ መነሻ ሀሳብ መርምሮ በጥልቅ በመወያየት በመንግስት እና  የግል አጋርነት (PPP) እንዲተዳደሩ ብሎም በከተማዋ የመንግስት እና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4፡00 ድረስ ግልጋሎት እንዲሰጡ እና በሁሉም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠቀሙ እንዲደረግ

📌4ኛ. በሁሉም የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ

📌5ኛ. ሁሉም ዋና መንገድ እና መጋቢ መንገድ ላይ ያሉ ተቋማት፣ ህንፃዎች እንዲሁም የግልና የመንግስት ቢሮዎች ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር  ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
💎https://www.facebook.com/profile.php?id=61569879454961&mibextid=ZbWKwL
📌ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

ሶሪያ-ደማስቆ-ጁሙዓ

ከአል-አሳድ ውድቀት በኃላ በሶርያ መዲና ደማስቆ የመጀመሪያዉ የጁማ ጸሎት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት በአደባባይ ተካሄደ

አል-አሳድ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ለሶሪያ የመጀመሪያ አርብ ጸሎት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በደማስቆ በሚገኘው የኡመያድ መስጊድ ተሰብስበዉ ታይተዋል።

የድል አድራጊዎቹ የሶሪያ ተቃዋሚ ቡድኖች ወታደራዊ ኦፕሬሽን አስተዳደር ዛሬ በደማስቆ በነበረዉ ክብረ በዓል ላይ የጸጥታ ኃይሎች "በከፍተኛ ሁኔታ መሰማራታቸዉን" ተናግረዋል::

"የህዝብ ደህንነት ላይ አደጋ የሚዳርግ ነገር ከተጋረጠ ማንኛውም ሰው ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወስዳል" ሲል ባወጣዉ መግለጫ ገልጿል።የሁሉንም ሰው ደህንነት ለመጠበቅ በሰላማዊ ሰልፎች ወቅት ሰላማዊ ባህሪን እንዲከተሉ እንጠይቃለን ።

በሌላ ዜና ፔንታገን በአሜሪካዋ ኒው ጀርዚ ግዛት አካባቢ የታዩት ድሮኖች ከኢራን የጦር መርከብ የተነሱ እንዳልሆኑ አስታውቋል።በቅርብ ሳምንታት በኒው ጀርዚ ሰማይ ላይ በርካታ ድሮኖች የታዩ ሲሆን አንዳንድ ድሮኖች ወታደራዊ ካምፖች እና የተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጎልፍ መጫወቻ አካባቢ ታይተዋል።

የአሜሪካ ኮንግረስ አባል የሆኑት ጄፍ ዳን ድሩ "ከፍተኛ አመኔታ ካላቸው" ምንጮቼ ሰማሁ ብለው ድሮኖቹ ከኢራን ጋር ግንኘነት እንዳላቸው ተናግረው ነበር።የኒው ጀርዚው ሪፐብሊካን ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ድሮኖች አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ከሚገኝ የኢራን የጦር አውሮፕላን የተነሱ ናቸው ብለዋል።

"መርከቧ የምትገኘው በዩናይትድ ስቴትስ ምስራቃዊ ጠረፍ አካባቢ ነው። ወደ ምናየው እና የምንሰማው ነገር ሁሉ ድሮኖች ለቀዋል" ሲሉ የኮንግረስ አባሉ ረቡዕ ተናግረው እንደነበር ይታወሳል።"ከፍተኛ አመኔታ ካላቸው ምንጮቼ ያገኘሁት መረጃ ነው። በቀላሉ የምወስደው ጉዳይ አይደለም።"አክለው አሜሪካ ድሮኖቹ ተኩሳ እንድትጥላቸው ምክረ ሐሳብ ሰጥተዋል።ነገር ግን የፔንታገን ምክትል ፕሬስ ሴክሬታሪ ሳብሪና ሲንግ የሰውየው አስተያየት ውሀ የሚያነሳ አይደለም ሲሉ አጣጥለውታል።(ስምኦን ደረጄ)
💎https://www.facebook.com/profile.php?id=61569879454961&mibextid=ZbWKwL
💎ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

ለአስተናጋጆች ዝቅተኛ የደሞዝ ተመንን ገቢዎች ይፋ አደረገ

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ለሆቴሎች፣ ለስጋ ቤቶች፣ ለመጠጥ ቤቶች እና ለተለያዩ የተመረጡ የንግድ ዘርፎች ለሰራተኞቻቸው አነስተኛ የደመወዝ ተመን ይፋ አድርጓል፡፡

ግብር ስወራን ለመከላከል በሚል ለንግድ ዘርፎቹ ስራ ላይ የዋለው የሰራተኛ ደመወዝ እና የሰራተኛ ቁጥር ተመን የህጋዊነት ጥያቄ አስነስቷል፡፡

አነስተኛ የደመወዝ ወለል በህግ ባልፀደቀበት ሁኔታ ‘’ዝቅተኛ መክፈል የምትችሉት ደመወዝ 5,000 ብር ነው ብሎ በመወሰን ግብር መሰብሰብ ህገ-ወጥ አሰራር ነው’’ ተብሏል፡፡

ዘገባው የሸገር ኤፍ ኤም102.1 ነው።
💎https://www.facebook.com/profile.php?id=61569879454961&mibextid=ZbWKwL
💎ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

."...ኤርትራውያን ስደተኞች... "

"ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የውጭ አገር ሰዎች ባልተፈቀደላቸው የሥራ መስክ ተሰማርተው ይገኛሉ" የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ለእስርና እንግልት እየተዳረጉ ነው በሚል የተሰሩ ዘገባዎችን አስመልክቶ በትላንትናው ዕለት የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት "ሕጋዊ የስደተኝነት ዕውቅና ኖሯቸው ለእስርና እንግልት የተዳረጉ ስደተኞች በሀገሪቱ የሉም" የሚል መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በበኩሉ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የህግ ጥሰት የፈፀሙ የውጭ ዜጎችን የተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ከጎረቤት አገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዜጎች ለ9ዐ ቀናት ያለ ቪዛ ክፍያ በቀን ማህተም ገብተው እንዲቆዩ መፈቀዱን አስታውሷል።

ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የውጭ አገር ሰዎች የስራ ፈቃድና መኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው ባልተፈቀደላቸው የሥራ መስክና ህገወጥ የማዕድን፣ የገንዘብ፣ አደገኛ እፅ፣ የሰዎች ዝውውርና መሰል ህገወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ ብሏል።

በተለይ በርካታ ኤርትራዊያን ወደ ሀገር የሚገቡት በህገወጥ መንገድ ነው ያለው መግለጫው ከተፈቀደላቸው የጊዜ ገደብ በላይ በመቆየት በህገ-ወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ሲል ከሷል።

በዚህም

📌ለውጭ አገር ዜጎች ባልተፈቀዱ የስራ መስኮች በመሰማራት በህገወጥ መንገድ ከትንሸ ሱቅ ችርቻሮ እስከ ያልተፈቀዱ ትላልቅ ስራዎች ተሰማርተው ሳለ፤

📌 በርካታ የኤርትራዊ ዜግነት ያላቸው ዘመድ ለመጠየቅ በማስመስል ከዱባይ፣ ከኤርትራ፣ ከኡጋንዳ በመመላለስ የኮንትሮባንድ እና ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲያከናውኑ፤

📌በተለያዩ አገራት ከሚገኙ ሌሎች ህገ-ወጥ ደላሎች ጋር በመተሳሰር ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሲሳተፉ፤

📌ለተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት የሚያገለገሉ ሐሰተኛና የተጭበረበሩ የጉዞና የይለፍ ሰነዶች፣ ማህተሞች፣ የባንክ ቡኮች በማዘጋጀትና በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባራት ሲፈጽሙ ተገኝተዋል ብሏል።

መግለጫው አክሎም ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የአገራችንን ህግ ተላልፎ ከተገኘ በህግ ተጠያቂ ይሆናል። ይህ ግን በአንድ ሀገር ዜጋ ብቻ ተፈጻሚ የሚደርግ አሰራር ተደርጎ በአንድ አንድ ሚድያዎች መዘገቡ ስህተት ነው ብሏል።

በተጨማሪም በስደተኝነት የተመዘገበ ማንኛውም የኤርትራዊ ዜግነት ያለው ሰው ያለ ፈቃዱ ከአገር እንዲወጣ እና ተገቢነት የሌለው ክፍያ እንዲክፍል የተደርግ ሰው የለም ብሏል።(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።)
💎https://www.facebook.com/profile.php?id=61569879454961&mibextid=ZbWKwL
💎ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

ዶናልድ ትራምፕ፤ የ2024 የዓመቱ ምርጥ ሰው ተባሉ

ተመራጩ የአሜሪካን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2024 «የዓመቱ ሰው» ተባሉ። ትራምፕን በዓመቱ ሰውነት የመረጠው ታይም መጽሔት ነው። ዶናልድ ትራምፕን ለሁለተኛ ጊዜ ነው ታይም መጽሔት ይህን ስፍራ ያገኙት። ቀደም ሲል በ2018 ዓ.ም. ከሁለት ዓመታት በፊት በተካሄደው ምርጫ ማሸነፋቸውን ተከትሊ በተመሳሳይ «የዓመቱ ሰው» ተብለዋል።

ታይም መጽሔት «የዓለም በጣም ኃያል ሰው» ያላቸው የ78 ዓመቱ ትራምፕ ዳግም ወደ ሥልጣን የመጡበትን መንገድም በአሜሪካ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ብሎታል። ታይም መጽሔት ሰማያዊ ሱፍ ሙሉ ልብስ ከቀይ ክራቫት ጋር መለያቸው ነው ያላቸው ዶናድል ትራምፕ፤ የመጀመሪያ የሥልጣን ዘመናቸው በጎርጎሪዮሳዊው 2020 ዓ.ም. የተካሄደውን የምርጫ ውጤት ለመቀልበስ ካፒቶል ላይ በተሞከረው ጥቃት ሳቢያ በውርደት መጠናቀቁን አስታውሷል።

ይህን ጨምሮ የተለያዩ ክሶች የቀረቡባቸው ትራምፕ ለእጩ ፕሬዝደንትነት እንደሚቀርቡ መግለጻቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤት ሲመላለሱ መክረማቸውን፣ ሆኖም በወንጀል መከሰሳቸው በምርጫው ድል ከማስመዝገብ እንዳላገዳቸውም አንስቷል። ትራምፕ ለድል ስኬታቸው የሕዝቡን መሠረታዊ ቅሬታዎች መጠቀማቸውን፤ ከታይም መጽሔት ጋር በነበራቸው ቃለመጠይቅ ገልጸዋል።

የታይም ዋና አዘጋጅ ሳም ጃኮብስ ስለውሳኔው ለአሜሪካው ኤንቢሲ መገናኛ ብዙሃን ሲገልጽ «በጥሩም ሆነ በመጥፎ ትራምፕ በ2024 በዜና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድረዋል» ነው ያለው። ባለፈው ኅዳር በአሜሪካ በተካሄደው ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ የዴሞክራቲክ እጩ ካማላ ሃሪስን በማሸነፍ 47ኛው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

ለዓመቱ ሰው ምርጫም፤ ተፎካካሪያቸው ዴሞክራቷ ካማ ሃሪስን ጨምሮ፤ የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት ክላውዲያ ሺንባም፣ እስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የሟቹ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አሌክሲ ናቫልኒ ባለቤት ሩሲያዊቷ የኢኮኖሚ ባለሙያ ዩሊያ ናቫልኒ እጩዎች ነበሩ።(DW)
💎https://www.facebook.com/profile.php?id=61569879454961&mibextid=ZbWKwL
💎ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

በተከለከለ አየር ክልል በረራ አድርገዋል የተባሉ የኢትዮጵያንና የ ኢትሃድ አየር መንገዶችን በአሜሪካ መቀጣታቸው ተሰምቷል።

የአሜሪካ የትራንስፖርት ክፍል የኢትዮጵያ አየር መንገድን 425,000 ዶላር እና የኢትሃድ አየር መንገድን 400,000 ዶላር  መቅታቱ ተገለጸ። 

አየር መንገዶቹ የተቀጡት ያለፍቃድ በተቀከለከለ አየር ክልል በረራ ማከናወናቸው በደንበኞች ጥበቃ አቪየሽን ቢሮ ምርመራ መደረጉን ተከትሎ ነው ተብሏል።

ምርመራው እንዳመለከተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጎርጎሮሳውያኑ 2020 እስከ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ እና በጂቡቲ መካከል የተባበሩት አየር መንገድ መለያ ኮዶችን የያዙ በረራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

አየር መንገዱ ከሀምሌ 2022 እስከ ሚያዚያ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ ጄትብሉ አየር መንገድን (B6) ኮድን በመጠቀም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስና አሜሪካ መካከል በረራዎችን አካሄዷል ሲል የአቪየሽን ድር ገጾች ዘግበዋል።

የአሜሪካ የትራንስፖርት ክፍል እነዚህ በረራዎች በአሜሪካ ደንቦች መሠረት ተገቢ ፈቃድ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጸ ሲሆን ምርመራው አየር መንገዶቹ ቀደም ብሎ ማሳወቂያ ቢሰጣቸውም በራራዎቹ መቀጠላቸውን ከአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ተመልክተናል።
📌አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

የመንግስት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑ ይፋ ተደርጓል‼️

ወላጆችም የልጆቻቸውን የምግብ ዝርዝር ይከታተላሉ።

📌 ቁርስ ላይ ፦ እንጀራ ፍርፍር / ሩዝ + ዳቦ + በሻይ ፣ ቅንጬ ፣ ስልስ ፣ ማካሮኒ ተካተለዋል።

📌 ምሳ ላይ ፦ ምስር/አተር ክክ/ሽሮ / አተር / ባቄላ / ድንች / አትክልት ማለትም ጎመን ፣ድንች፣ ካሮት የመሳሰሉ / ፓስታ / + እንጀራ / ዳቦ ፣ ከዚህ በተጨማሪም በሳምንት 1 ቀን ስጋ በምስር/በድንች/ በክክ (በዳቦ ወይም በእንጀራ) ተካተዋል።

📌 እራት ላይ ፦ ምስር/ክክ/ፓስታ / ሽሮ + በእንጀራ/ዳቦ ፣ ከዚህ በተጨማሪ በሳምንት 1 ቀን ስጋ በምስር/በድንች/ በክክ (በዳቦ ወይም በእንጀራ) ተካተዋል።

ዝርዝር መረጃው ከላይ ተያይዟል።

አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

ሐርጌሳ‼

አዲሱ የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ ስድስተኛው የራስ ገዟ ፕሬዝዳንት ኾነው ዛሬ በይፋ ሥልጣናቸውን ተረክበዋል።

ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ የባሕር በር ዙሪያ ከስምምነት በደረሱ ማግስት ሥልጣናቸውን የተረከቡት ፕሬዝዳንት አብዱላሂ፣ ሶማሌላንድ የአገርነት እውቅና እንድታገኝ ጥረት ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ባለፈው ዓመት የተፈራረመችው የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ዕጣ ፋንታው ምን እንደሚኾን ለጊዜው አልታወቀም።

ፕሬዝዳንቱ፣ በምሥራቃዊ ሶማሌላንድ የፑንትላንድ ራስ ገዝ አዋሳኝ በኾነው ሱል አውራጃ ለተከሰተው ግጭት ያለ ምንም ቅድመ ኹኔታ ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንደሚፈልጉም ቃል ገብተዋል።

በሶማሌላንድ ወታደሮችና ባካባቢው የጎሳ ታጣቂዎች መካከል ለወራት የዘለቀ ውጊያ ከተካሄደ በኋላ፣ የአካባቢው የጎሳ መሪውዎች ራሱን የቻለ የፌደራል ግዛት በመመስረት ከሱማሊያ ጋር ለመቀላቀል መወሰናቸው አይዘነጋም።

በፕሬዝዳንቱ በዓለ ሲመት ላይ፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሞሐመድ የኢትዮጵያ መንግሥትን ወክለው ተገኝተዋል።
💎https://www.facebook.com/profile.php?id=61569879454961&mibextid=ZbWKwL
💎ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

አስደሳች ዜና ከዶ/ር አብዱ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት -ደሴ

👉1ኛ.ደሴ ከተማ ገራዶ አዲሱ መናኸሪያ የንግድ ቦታ ለ1 አባል 2 ሱቅ በግል እና ሌሎች ከ3 ወለሎች በላይ በጋራ የሚጠቀሙበት የገባያ  ማእከል በ400 ሽህ ብር ሙሉ ክፍያ እና በ250 ሽህ ብር ግማሽ ክፍያ አማራጮች

👉2ኛ.150 ሺህ ብር አንድ ሱቅ እና ባለ 2 መኝታ አፓርታማ በ 3 ወር ውስጥ ግንባታ የምትጀምር ውሱን እጣ የቀረው ለ 5 ቀን ብቻ የሚቆይ

ማሳሰቢያ -የሁሉም ሳይቶች የግንባታ ወጪ በጋራ መዋጮ ነው

አድራሻ :-ደሴ ገራዶ አዲሱ መናኸሪያ መውጫ በር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት

ስልክ 0937411111
          0938411111
ዶ/ር አብዱ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት

ግሩፕ📍
/channel/+ACPCPoXDK4JlMjA0

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

በኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ አቅራቢያ የሚገነባው የባምዛ አል-ረህማን መስጂድ ግንባታ መጀመሩ ተገለፀ!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ጉባ ወረዳ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ በተመሰረተችው ባምዛ ከተማ ላይ 'አል-ረህማን' በሚል ስያሜ መስጅድ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ መቀመጡ የሚታወስ ሲሆን የመስጂዱ ግንባታ መጀመሩ ተሰምቷል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ኘሬዝዳንት ሸይኽ ኢብራሂም ሲራጅ በመስጂዱ የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሀግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት አካባቢው ላይ ያለው ማህበረሰብ የመስጂድ እጦት የተቸገረና አካባቢው የመዝናኝ ከተማ እየሆነ ስለሆነ መስጂዱን በአፋጣኝ እንዲሰራ መጠየቃቸው ይታወሳል።

ሙስሊሙ ማህበረሰብም ለዚህ ታሪካዊ መስጂድ ግንባታ ማሰባሰቢያ መርሀግብር ላይ በፍልውሀ ተውፊቅ መስጂድ እና ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው በአቡሁረይራ መስጂድ የጁመአ ሰላትን በመስገድ ለመስጂዱ ግንባታ የበኩላችንን እንድንወጣ አስተባባሪ ኮሚቴው ጥሪ አቅርቧል።
(ሀሩን ሚድያ)
💎https://www.facebook.com/profile.php?id=61569879454961&mibextid=ZbWKwL
📌ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

💥ሳር ቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ ለጥቂት ቀናት ብቻ የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ  ✅Jenboro real estate.
👉አፓርትመንት እና የንግድ ሱቆች በ10% ቅድመ ክፍያ ብቻ 📞 0909210806 / 0932610115

💥 የአፓርትመንት ዋጋ
👉108 ካሬ 2 መኝታ = 12,305,000
10% ቅድመ ክፍያ = 1,230,500
👉123 ካሬ 2 መኝታ = 14,145,000
10% ቅድመ ክፍያ = 1,414,500
👉150 ካሬ 3 መኝታ = 17,250,000
10% ቅድመ ክፍያ = 1,725,000
👉183 ካሬ 3 መኝታ = 21,045,000
10% ቅድመ ክፍያ = 2,104,500

💥 የሱቆች ዋጋ
👉16 ካሬ= ሙሉ ክፍያ 4,944,000 , 10% = 494,000
👉 18 ካሬ = ሙሉ ክፍያ 5,562,000 , 10% = 556,200
👉 20 ካሬ = ሙሉ ክፍያ 6,180,000 , 10% = 618,000
👉 23 ካሬ = ሙሉ ክፍያ 7,107,000 , 10% = 710,700
👉 25 ካሬ = ሙሉ ክፍያ 7,725,000 , 10% = 772,500
👉 28 ካሬ = ሙሉ ክፍያ 8,652,000 , 10% = 862,500

💥ከ30% በላይ ለሚከፍሉ ልዩ ቅናሽ አለው
👉ለጥቂት ቤቶች ብቻ የወጣ የማስታወቂያ ዋጋ ስለሆነ ፈጥነው ይጠቀሙ።
📞0909210806  /  0932610115

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

አስደሳች ዜና ከዶ/ር አብዱ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት -ደሴ

👉1ኛ.ደሴ ከተማ ገራዶ አዲሱ መናኸሪያ የንግድ ቦታ ለ1 አባል 2 ሱቅ በግል እና ሌሎች ከ3 ወለሎች በላይ በጋራ የሚጠቀሙበት የገባያ  ማእከል በ400 ሽህ ብር ሙሉ ክፍያ እና በ250 ሽህ ብር ግማሽ ክፍያ አማራጮች

👉2ኛ.150 ሺህ ብር አንድ ሱቅ እና ባለ 2 መኝታ አፓርታማ በ 3 ወር ውስጥ ግንባታ የምትጀምር ውሱን እጣ የቀረው ለ 5 ቀን ብቻ የሚቆይ

ማሳሰቢያ -የሁሉም ሳይቶች የግንባታ ወጪ በጋራ መዋጮ ነው

አድራሻ :-ደሴ ገራዶ አዲሱ መናኸሪያ መውጫ በር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት

ስልክ 0937411111
          0938411111
ዶ/ር አብዱ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት

ግሩፕ📍
/channel/+ACPCPoXDK4JlMjA0

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

የቀለሜ መነሻ ጥቅል

👉ከእርሳስ አያያዝ ችሎታ ጀምሮ ልጆችን ማንበብ ፣ መፃፍ ፣ ማዳመጥ እና ማንበብ  ችሎታቸውን በተቀናጀ መልኩ በምስል ፣ በድምፅና በተግባር የሚለማመዱበት አስደናቂ ጥቅል

👉በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተዘጋጀ
👉የልጆችን መማር ፍላጎት የሚያነሳሱ 68 መማሪያዎችን ግልፅ ከሆነ አጠቃቀም መመሪያ ጋር የያዘ


👉ደጋግመው የሚጠቀሙባቸው 11 መፃህፍት
👉 ባለ ድምፅ መማሪያ መነሻዬ ፓድ
👉 2 በ1 ሰሌዳ
👉 ኤሌክትሮኒክ ሰሌዳ
👉 የሰዓት መማሪያ ቦርድ
👉ከ20 በላይ ማርከሮችና ጠመኔዎች
👉 በዶ/ር ኢዮብ ማሞ ተዘጋጅቱ ለወላጆች ከመነሻዬ ከተበረከተ ስጦታ ጋር

ዋጋ 12000


የማህበራዊ ድረገፆቻችንን ይጎብኙ
https://linktr.ee/meneshaye

ይደውሉ 0989939393 ወይም 0930323334

አድራሻ፦ 1.ጉርድ ሾላ ሆሊ ሲቲ ሴንተር
               2. ፒያሳ ካንትሪ ታወር
በተጨማሪም 👉 ጀሞ ደሊና ሞል ፤ ገርጂ ከፋውንቴን ህንፃ ፊት ለፊት

#meneshaye #መነሻዬ #kidsmaths #kids #success #focus #children #education  #science #knowledge #math #maths #mathematics #concentration   #primaryeducation  #braindevelopment #kidsimagination

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

አፊያ ሙሀመድ ከፍተኛ የባህል ሕክምና እና ዘመናዊ የዋግምት አገልግሎት

  የምንሰጣቸው የባህል ህክምናዎች

➢ ለውጭና ለውስጥ ኪንታሮት
➢ ለማድያት
➢ ለሱኳር በሽታ
➢ለጉበት(ለወፍ በሽታ)
➢ለጨጎራ ህመም
➢ለስፈተወሲብ
➢ለደም ግፊት
➢ለአስም ወይም ሳይነስ
➢ለሚጥል በሺታ
➢ ለእሪህና ቁርጥማት
➢ለራስ ህመም (ማይግሪን)
➢ለቺፌ ና ለጭርት
➢ለቋቁቻና ፎረፎር
➢ለእጢና ለእባጭ
➢ለወገብ ህመም
➢ለመካንነት ለወድም ለሴትም
➢ለጆሮና ለአይን ህመም
➢ለሆድ ህመም
➢ዘመናዊ የዋግምት አገልግሎት በተቋማችን እንሰጣለን።
👉ከኢትዮጵያ ባህላዊ ህክምና አዋቂዎች ማህበር በዘርፉ ህጋዊ የባህል ህክምና ፍቃድ ያለን ነን።
አድራሻ:አዲስ አበባ አየር ጤና
   ስልክ ቁጥር   📲0927506650
                         📲0987133734
                         📲0956522222
ቴሌግራም ቻናላችን
/channel/+08vmUP_ntvE5NmM0

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

📌30% ከፍለው 25% ቅናሽ ያገኛሉ

📍ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ቀሪውን በ ረጅም ዙር የሚከፍሉት

በመሀል ፒያሳ ሊሴ ትምህርት ቤት ጀርባ በ 1200ካሬ ላይ ያረፈ በግንባታ ላይ ያሉ ቅንጡ አፓርትመንቶችን  በተመጣጣኝ ዋጋ ከ TEMER ሪል እስቴት ለሽያጭ አቅርበናል።

አፓርትመንቶች

👉 ከ ስቱዲዮ እስከ ባለ 3 መኝታ 46 - 141ካሬ
👉የንግድ ሱቆች ፒያሳ ላይ ከ20 ካሬ ጀምሮ
     
❇️ ቢኖሩባቸው ምቹ ፣ ቢያከራዩዋቸው በዶላር ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙባቸው እንዲሁም መልሰው መሸጥ ቢፈልጉ በብዙ የሚያተርፉባቸው ውብና ማራኪ አፓርትመት::

❇️ በዘመናዊ የግንባታ ጥበብ የሚገነባ

❇️በህንፃዎቻችን ላይ ያሉ ተጨማሪ አገልግሎቶች
☞ 4 ደረጃቸውን የጠበቁ ሊፍቶች
☞ አውቶማቲክ ጀነሬተር
☞የከርሰምድር ውሃ : የእሳት መቆጣጠሪያ
☞  ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ
☞ ለደስታ/ለሀዘን ለልዩ ዝግጅት የሚውል የተንጣለለ አዳራሽ
☞ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጅ ማድረጊያ ቦታ የተዘጋጀለት
☞የ24 ሰአት የካሜራ አገልግሎት(CCTV Service )
❇️በተጨማሪም

           👉 አያት
            👉ጋርመንት
            👉ሱማሌተራ አፓርትመንት ቤቶች

ዛሬ ነገ ሳይሉ ይምጡና ይጎብኙን አትርፈው ይመለሳሉ።

ለበለጠ መረጃ:
☎️ 0942996771

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

አዲስ አበባ‼

የአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሪደር ልማት ደንብ ከተላለፉ አካላት ከ103 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ዛሬ መግለፁን ሰምተናል።ቅጣቱ መንግስታዊ ተቋማትን ጭምር የነካ መሆኑም ተሰምቷል።ዘንባባ መግጨት ቅጣቱ ከ300 ሺህ በላይ ሲሆን አሁን ላይ ግጭቱ ሲከሰት አይስተዋልም።
💎https://www.facebook.com/profile.php?id=61569879454961&mibextid=ZbWKwL
📌ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

ደንባራዎቹ መገናኛ ብዙሃን

አዲስ መፅሀፍ በቅርብ ቀን

በጋዜጠኝነትና በመምህርነት ለረጅም አመታት ያገለገሉትና በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን መምህር የሆኑት የዶ/ር ጀማል ሙሀመድ አዲስ መፅሐፍ በቅርብ ቀን ገበያ ይውላል::

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

አስደሳች ዜና ከዶ/ር አብዱ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት -ደሴ

👉1ኛ.ደሴ ከተማ ገራዶ አዲሱ መናኸሪያ የንግድ ቦታ ለ1 አባል 2 ሱቅ በግል እና ሌሎች ከ3 ወለሎች በላይ በጋራ የሚጠቀሙበት የገባያ  ማእከል በ400 ሽህ ብር ሙሉ ክፍያ እና በ250 ሽህ ብር ግማሽ ክፍያ አማራጮች

👉2ኛ.150 ሺህ ብር አንድ ሱቅ እና ባለ 2 መኝታ አፓርታማ በ 3 ወር ውስጥ ግንባታ የምትጀምር ውሱን እጣ የቀረው ለ 5 ቀን ብቻ የሚቆይ

ማሳሰቢያ -የሁሉም ሳይቶች የግንባታ ወጪ በጋራ መዋጮ ነው

አድራሻ :-ደሴ ገራዶ አዲሱ መናኸሪያ መውጫ በር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት

ስልክ 0937411111
          0938411111
ዶ/ር አብዱ ዶ/ር ሙሀመድ እና ጓደኞቻቸው ሪልስቴት

ግሩፕ📍
/channel/+ACPCPoXDK4JlMjA0

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

💥Jenboro Real Estate ( ሳር ቤት ቫቲካን ኤምባሲ አጠገብ )
👉አፓርትመንት እና የንግድ ሱቆች በ10% ቅድመ ክፍያ ሽያጭ ጀምረናል 📞 0909210806 / 0932610115

💥 የአፓርትመንት ዋጋ
👉108 ካሬ 2 መኝታ = 12,305,000
10% ቅድመ ክፍያ = 1,230,500
👉123 ካሬ 2 መኝታ = 14,145,000
10% ቅድመ ክፍያ = 1,414,500
👉150 ካሬ 3 መኝታ = 17,250,000
10% ቅድመ ክፍያ = 1,725,000
👉183 ካሬ 3 መኝታ = 21,045,000
10% ቅድመ ክፍያ = 2,104,500

💥 የሱቆች ዋጋ
👉16 ካሬ= ሙሉ ክፍያ 4,944,000 , 10% = 494,000
👉 18 ካሬ = ሙሉ ክፍያ 5,562,000 , 10% = 556,200
👉 20 ካሬ = ሙሉ ክፍያ 6,180,000 , 10% = 618,000
👉 23 ካሬ = ሙሉ ክፍያ 7,107,000 , 10% = 710,700
👉 25 ካሬ = ሙሉ ክፍያ 7,725,000 , 10% = 772,500
👉 28 ካሬ = ሙሉ ክፍያ 8,652,000 , 10% = 862,500

💥ከ30% በላይ ለሚከፍሉ ልዩ ቅናሽ አለው
👉ለጥቂት ቤቶች ብቻ የወጣ የማስታወቂያ ዋጋ ስለሆነ ፈጥነው ይጠቀሙ።
📞0909210806  /  0932610115

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

አፊያ ሙሀመድ ከፍተኛ የባህል ሕክምና እና ዘመናዊ የዋግምት አገልግሎት

  የምንሰጣቸው የባህል ህክምናዎች

➢ ለውጭና ለውስጥ ኪንታሮት
➢ ለማድያት
➢ ለሱኳር በሽታ
➢ለጉበት(ለወፍ በሽታ)
➢ለጨጎራ ህመም
➢ለስፈተወሲብ
➢ለደም ግፊት
➢ለአስም ወይም ሳይነስ
➢ለሚጥል በሺታ
➢ ለእሪህና ቁርጥማት
➢ለራስ ህመም (ማይግሪን)
➢ለቺፌ ና ለጭርት
➢ለቋቁቻና ፎረፎር
➢ለእጢና ለእባጭ
➢ለወገብ ህመም
➢ለመካንነት ለወድም ለሴትም
➢ለጆሮና ለአይን ህመም
➢ለሆድ ህመም
➢ዘመናዊ የዋግምት አገልግሎት በተቋማችን እንሰጣለን።
👉ከኢትዮጵያ ባህላዊ ህክምና አዋቂዎች ማህበር በዘርፉ ህጋዊ የባህል ህክምና ፍቃድ ያለን ነን።
አድራሻ:አዲስ አበባ አየር ጤና
   ስልክ ቁጥር   📲0927506650
                         📲0987133734
                         📲0956522222
ቴሌግራም ቻናላችን
/channel/+08vmUP_ntvE5NmM0

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

ኑኑሻዬ አባቷ በገዛላት ድንቅ ስጦታ እንዲህ እየተማረች ትገኛለች. . . . . እርሶስ ለልጆዎ መማሪያ ምን አስበዋል ??

" በቀለሜ መነሻ ጥቅል  የልጆዎን የቀለመ መነሻ ያቅልሉ"

የማህበራዊ ድረገፆቻችንን ይጎብኙ
https://linktr.ee/meneshaye

ይደውሉ 0989939393 ወይም 0930323334

አድራሻ፦ 1.ጉርድ ሾላ ሆሊ ሲቲ ሴንተር
               2. ፒያሳ ካንትሪ ታወር
በተጨማሪም 👉 ጀሞ ደሊና ሞል ፤ ገርጂ ከፋውንቴን ህንፃ ፊት ለፊት

#meneshaye #መነሻዬ #kidsmaths #kids #success #focus #children #education  #science #knowledge #math #maths #mathematics #concentration   #primaryeducation  #braindevelopment #kidsimagination

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

📌30% ከፍለው 25% ቅናሽ ያገኛሉ

📍ከ10% ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ቀሪውን በ ረጅም ዙር የሚከፍሉት

በመሀል ፒያሳ ሊሴ ትምህርት ቤት ጀርባ በ 1200ካሬ ላይ ያረፈ በግንባታ ላይ ያሉ ቅንጡ አፓርትመንቶችን  በተመጣጣኝ ዋጋ ከ TEMER ሪል እስቴት ለሽያጭ አቅርበናል።

አፓርትመንቶች

👉 ከ ስቱዲዮ እስከ ባለ 3 መኝታ 46 - 141ካሬ
👉የንግድ ሱቆች ፒያሳ ላይ ከ20 ካሬ ጀምሮ
     
❇️ ቢኖሩባቸው ምቹ ፣ ቢያከራዩዋቸው በዶላር ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙባቸው እንዲሁም መልሰው መሸጥ ቢፈልጉ በብዙ የሚያተርፉባቸው ውብና ማራኪ አፓርትመት::

❇️ በዘመናዊ የግንባታ ጥበብ የሚገነባ

❇️በህንፃዎቻችን ላይ ያሉ ተጨማሪ አገልግሎቶች
☞ 4 ደረጃቸውን የጠበቁ ሊፍቶች
☞ አውቶማቲክ ጀነሬተር
☞የከርሰምድር ውሃ : የእሳት መቆጣጠሪያ
☞  ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ
☞ ለደስታ/ለሀዘን ለልዩ ዝግጅት የሚውል የተንጣለለ አዳራሽ
☞ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጅ ማድረጊያ ቦታ የተዘጋጀለት
☞የ24 ሰአት የካሜራ አገልግሎት(CCTV Service )
❇️በተጨማሪም

           👉 አያት
            👉ጋርመንት
            👉ሱማሌተራ አፓርትመንት ቤቶች

ዛሬ ነገ ሳይሉ ይምጡና ይጎብኙን አትርፈው ይመለሳሉ።

ለበለጠ መረጃ:
☎️ 0942996771

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

የፕሮፌሰርነት እድገት አሰጣጥ ለጊዜው መታገዱን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

📌"ከትምህርት ሚኒስቴር ሀምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም፣ በቁጥር 1/515/80/16 በተጻፈ ደብዳቤ ከጥቅምት 4/2013 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ የነበረውንና በትግበራ ወቅት በነበረበት ክፍተት ምክንያት እንደገና በመሻሻል ላይ የሚገኘው የአካዳሚክ ሰራተኞች የደረጃ እድገት መመሪያ ተጠናቅቆ እስከሚላክ ድረስ በሁሉም ተቋማት የፕሮፌሰርነት እድገት አሰጣጥ ለጊዜው መታገዱን መግለጻችን ይታወቃል"በማለት ሚንስቴር መ/ቤቱ ደብዳቤ ፅፏል።

📌"ይሁን እንጂ እንዳንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክልከላውን በመጣስ መመሪያውን ባልተከተለ፤ ግልጽነት በጎደለው፣ ወጥነት በሌለው እና ከትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ሪፎርሞች ጋር በሚጣረስ እኳ ኋን የፕሮፌሰርነት እድገት መስጠት መቀጠላቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡ በመሆኑም በእገዳ ደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም አማካኝነት የተሰጠ እና የሚስጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልጻለን "ያለው ት/ሚ የየተቋማቱ ከፍተኛ አመራር አካላት እና የስራ አመራር ቦርድም የተሻሻለው መመሪያ ተጠናቅቆ እስኪደርሳችሁ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ እየጠየቅን በጉዳዩ ላይ የቅርብ ክትትል በማድረግ፣ የተቀመጠውን አቅጣጫ በማክበር እና በማስከበር የተጣለባችሁን ከፍተኛ ሃላፊነትና አደራ በትጋት እንድትወጡ እናሳስባለን" ሲል ለዩኒቨርስቲዎች ፅፏል።
💎https://www.facebook.com/profile.php?id=61569879454961&mibextid=ZbWKwL
💎ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…

Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

የሶማሊያ መከላከያ ሰራዊት የጁባላንድ ከፊል ራስ ገዝ ክልልን ለቆ ወጣ።

በሶማሊያ መከላከያ ሰራዊት እና በጁባላንድ ከፊል ራስ ገዝ ኃይሎች መካከል ትናንት ረቡዕ ከተቀሰቀሰ ዉጊያ በኋላ የሶማሊያ መከላከያ ግዛቲቱን ለቆ መውጣቱን የሞቃዲሾ መንግስት ዛሬ አስታውቋል።

የመንግስት እና ወታደራዊ ባለስልጣናት  በራስ ካምቦኒ ከተማ እና አካባቢው ለበርካታ ሰዓታት ለቆየው ዉጊያ  አህመድ ማዶቤ የሚመሩት የከፊል ራስ ገዟ አስተዳደር  ጦር ትናንት ረቡዕ  ግጭት ቀስቅሷል በማለት ከሰዋል።

ባለስልጣናቱ "የሶማሌ ብሄራዊ  ሃይሎች ከጂሃዲስቶች ጋር እንጂ  ከሌላ ከማንም ጋር የትጥቅ ትግል የማድረግ መመሪያ አልተሰጣቸዉም"ብለዋል።

የጁባላንድ ባለስልጣናት ትናንት ረቡዕ ግጭቱ ሲቀሰቀስ ባወጡት መግለጫ የፌዴራል ኃይሎች በድሮን የታገዘ ጥቃት ፈጽመውብናል ሲሉ ለግጭቱ መቀስቀስ የፌዴራል መንግስቱን ተጠያቂ አድርገዋል።

ከጁባ ላንድ ዛሬ የተሰማው ዜና ግን ከዉግያው በኋላ የፌዴራል ኃይሎች ጁባ ላንድን ለቀው መውጣታቸውን ነው የሚያመለክተው።

የጁባ ላንድ ባለስልጣናት ይህንኑ በሚያረጋግጠው መግለጫቸው « የጦር ሰፈሩን መልሰን ተቆጣጥረናል» ፤ ብለዋል። የአካባቢው የፀጥታ ጥበቃ ምክትል ሚኒስትር አዳነ አህመድ«በመጨረሻም የጁባላንድ ወታደሮች ከቀትር በኋላ የራስ ካምቦኒ ከተማ ተቆጣጥረውታል» ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

በአንድ ቀን ዉግያው ከሁለቱም ወገኖች የተገደሉ ወታደሮች መኖራቸውን ያመለከተው የሮይተርስ ዘገባ ነገር ግን አኃዙን በተመለከተ መረጃ አለማግኘቱን ጠቅሷል።

በራስ ገዟ አስተዳደር የግንኙነት ችግር መፈጠሩንም ዘገባው አመልክቷል።
በጁባ ላንድ የተቀሰቀሰው ግጭት ከሶማሊያ ባሻገር ሶማሊያ ውስጥ አልሸባብን የሚዋጉት ኢትዮጵያ እና ኬንያን ያሳስባቸዋል።(DW)
💎https://www.facebook.com/profile.php?id=61569879454961&mibextid=ZbWKwL
💎ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
/channel/+WNLm9dbzuIlp9DF4
💎ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
/channel/wasumohammed

Читать полностью…
Subscribe to a channel