tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እና ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች ቅዳሜ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ያስመርቃሉ።

በዕለቱ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 17ኛ ባች፥ ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ 5ኛ ባች ሰልጣኝ ተማሪዎቻቸውን ያስመርቃሉ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በ15 ዩኒቨርሲቲዎች 109 መምህራን የውል ግዴታቸውን ሳይወጡ በመልቀቃቸው ከ40 ሚልዮን ብር በላይ ሀብት ባክኗል፡፡ - የፌዴራል ዋና ኦዲተ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር የፌዴራል መስሪያ ቤቶች የ2016 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት እንደተገለፀው፤ ዩኒቨርሲቲዎች ለስልጠና የላኳቸውን ባለሙያዎች በውልና ግዴታ መሰረተ ተመልሰው አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ ክፍተት አለባቸው ተብሏል።

በዚህም በ15 ዩኒቨርሲቲዎች 109 መምህራን የውል ግዴታቸውን ሳይወጡ ዩኒቨርሲቲውን በመልቀቃቸው ከ40 ሚልየዮን ብር በላይ ሀብት ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ ተናግረዋል።

አርባ ምንጭ፣ መቐለ፣ አክሱም፣ ጂንካ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛውን ድርሻ የያዙ ሲሆን፤ ተቋማቱ መምህራን በውል ግዴታ መሰረት አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ወይም ሀብቱን ተመላሽ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ዋቸሞ፣ ባህርዳር፣ ሐረማያ እና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ የተገኘባቸው ሲሆን፤ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ዋና ኦዲተሯ አሳስበዋል። #ኢፕድ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በአዲስ አበባ ከተማ በ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ዛሬ መለቀቁ ይታወቃል።

ውጤት ኦንላይን ለመመልከት 👇
https://aa.ministry.et/#/resu

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራም ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ከ60 ዓመታት በላይ ዕድሜ በትምህርት ተቋምነት ያስቆጠረው ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፤ በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን ስድስት ምሁራን ሰሞኑን አስመርቋል። ከስድስቱ ተመራቂዎች አንድ ሴት ይገኙበታል።

በመስከረም 2014 ዓ.ም በአዲስ መልክ የተደራጀው ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፤ የመጀመሪያዎቹን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የትምህርት ተመራቂዎች ዘንድሮ ማስመረቁም ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 13 በሦስተኛ ዲግሪ እና 22 በስፔሻሊቲ የተመረቁ ይገኙበታል።

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በጊምቢ እና በሻምቡ ካምፓሶች ያስተማራቸውን 536 ተማሪዎች ትናንት ማስመረቁ ይታወቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለምና ዘመኑ ያፈራቸውን ሙሉ የስቱዲዮ እቃዎችን በማሟላት የምንሰጠውን ስልጠና ይውሰዱ።

ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር! የብዙ ዓመት ልምድና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe photoshop
🎯 Fullstack Webapp Development 
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign & Local Languages

አድራሻ
1. መገናኛ መተባበር ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)  ☎️ 0991929303
2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929304
 3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707

Telegram: /channel/topinstitutes
TikTok: topinstitute" rel="nofollow">https://Tiktok.com/@topinstitute
Facebook: https://www.facebook.com/Topinstitutes

Читать полностью…

Tikvah-University

#ETA

በአዲስ አበባ የሚገኙ 73 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዳግም ምዝገባ መረጃ ይፋ ሊደረግ ነው።

በሀገሪቱ የሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዳግም ምዝገባ እየተካሔደ እንደሚገኝ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቢኒያም ኤሮ ለፋና ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከ375 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ 85 ተቋማት አስፈላጊውን መስፈርት ባለማሟላታቸው ተማሪዎቻቸውን ከነማስረጃቸው ሥራ ላይ ለሚገኙ ተቋማት እያስተላለፉ ነው ብለዋል።

አብዛኞቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከአጠቃላይ የትምህርት መሰረተ ልማት እና ከሰው ኃይል አንጻር ከፍተኛ ክፍተት እንዳለባቸው ኃላፊው አንስተዋል።

መንግስት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከትምህርት ስርዓቱ የማስወጣት ፍላጎት እንደሌለውና በማብቃት ዕውቅና እንዲያገኙ እንደሚሠራ የገለፁት ኃላፊው፤ ከትምህርት ስርዓቱ የወጡ ተቋማት መስፈርቱን ሲያሟሉ በድጋሚ መመለስ እንደሚችሉ አስረድተዋል። ተቋማቱ 50 በመቶ የዳግም ምዝገባ መስፈርቶችን ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል፡፡

አሁን ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ 73 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዳግም ምዝገባ መረጃ እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ድረስ ይፋ እንደሚሆንም ገልፀው፤ በክልሎች የተጀመረው የዳግም ምዝገባ ሥራም በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡ #FMC

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ሰኔ 21 የሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የምስረታ ቀን!

በማህበራዊ ገፆቻችን በሙሉ እየተከታተላችሁን ለዘለቃችሁ ቤተሰቦቻችን በሙሉ ምስጋናችን ከልብ ነው።

የምስረታ በዓላችንን ምክንያት በማድረግ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ድረስ በሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ለምትመዘገቡ በሙሉ 25% ቅናሽ ሊጠናቀቅ የቀረው አራት ቀናት ብቻ በመሆኑ ቀድመው እንዲመዘገቡ እየጠየቅን፤ በየጊዜው እያሳየን የመጣናቸውን ለውጦች አስጠብቀን ለመቀጠል እንጥራለን።

Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1 ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

                 የበለጠ ይጠብቁ ...

Читать полностью…

Tikvah-University

#AksumUniversity
#ClassOf2025
#CommencementPhotos

‎አክሱም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 1155 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ 191 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

‎በዩኒቨርሲቲው የኢሌክትሪካልና ኮምፕዩተር ምህንድስና ፋካሊቲ ተማሪ የሆነው አክሊሉ አብርሃ አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.96 በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ተማሪ የሆነችው ይብራለም ተኽላይ አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.95 በማምጣት ከሴቶች ከፍተኛውን ውጤት በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሐግብር ያስተማራቸውን ተማሪዎች ነገ ሰኔ 17/2017 ዓ.ም ያስመርቃል፡፡

ተመራቂዎቹ በሦስተኛ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በጋምቤላ ክልል ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በ2017 ዓ.ም በክልሉ ከ900 በላይ ተማሪዎች ፈተናቸውን በበይነ መረብ እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ኡኩኝ ኡኬሎ ተናግረዋል።

ፈተናውን በበይነ መረብ ለሚወስዱ ተፈታኞች በቂ ልምምድ መሰጡትን የገለፁት ኃላፊው፤ በፈተና ወቅት የመብራትና የኔትዎርክ መቋራጥ እንዳይፈጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ዝግጅት መደረጉን ገልፀዋል።

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል። ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

46 A+ ያሳካው ተመራቂ

ዶ/ር ትዕዛዙ አሰፋ ይባላል። በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና የ2017 ዓ.ም ተመራቂ ነው።

አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.97 እና 46 A+ በማምጣት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የዓመቱ የሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ዓመት የመውጫ ፈተና ከወሰዱ ዕጩ ተመራቂዎች 86% ማሳለፍ ችሏል። ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ መርሐግብሮች ያሰለጠናቸውን 983 ተማሪዎች አስመርቋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#GambellaUniversity

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 701 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 115ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#TVTI
#ClassOf2025
#CommencementPhotos

ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ በቴክኒክ ሙያ ዘርፍ በሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቋል። - የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ (Level 6) እና በሁለተኛ ዲግሪ (Level 7) ያሰለጠናቸውን 2000 ተማሪዎች አስመርቋል።

ከዛሬ ተመራቂዎች መካከል 120 ሰልጣኞች በሁለተኛ ዲግሪ ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በቴክኒክ ሙያ ዘርፍ በሦስተኛ ዲግሪ (Level 8) ትምህርትና ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን የምረቃ ስነ-ስርዓቱ የክብር እንግዳ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገልፀዋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#MattuUniversity

መቱ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በመቱ እና በበደሌ ካምፓሶች ያስተማራቸውን 2157 ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ 32ቱ የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለቋሚ የሥራ ቅጥር መደቦች የቀን ሠራተኞችን በመቅጠር ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ ፈፅመዋል ተባለ፡፡

የፌዴራል ዋና አዲተር የመንግሥት ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት የበጀት ኦዲት አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት እንደጠቀሰው፤ 12 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሳይፈቀድላቸው ለቋሚ የሥራ መደቦች ላይ የቀን ሠራተኞችን ቀጥረው ተገኝተዋል ብሏል፡፡

ተቋማቱ በጠቅላላው 61,882,081 ብር ለቀን ሠራተኞች ክፍያ እንደፈጸሙ የገለጸው የፌዴራል ዋና አዲተር፤ ጅማ ዩኒቨርሲቲ 25,310,211 ብር፣ አምቦ ዩኒቨርሲቲ 10,938,834 ብር፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 7,888,374 ብር፣ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 5,170,600 ብር እና ዲላ ዩኒቨርሲቲ 4,414,974 ብር በመክፈል ዋነኞቹ እንደሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሰዋል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የፊታችን እሑድ ሰኔ 22/2017 ዓ.ም ጠዋት 02:00 በፒያሣ ካምፓስ የጋዜጠኝነት ስልጠና ተማሪዎች የመመረቂያ ፕሮጀክታቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፤ ጋዜጠኛ ዳዊት አለሙ እና ጋዜጠኛ ውቢት ያረጋል በመርሐግብሩ ላይ በመገኝት የጋዜጠኝነት ሕይወታቸውን እና ልምዳቸውን የሚያካፍሉ ይሆናል።

በመርሐግብሩ ላይ በመገኘት የተመራቂ ተማሪዎቻችንን የመመረቂያ ሥራዎች እንዲከታተሉ እንዲሁም ለጋዜጠኛ ዳዊት አለሙ እና ጋዜጠኛ ውቢት ያረጋል መጠየቅ የሚፈልጉትን በማንሳት በልምድ ልውውጡ ላይ እንዲካፈሉ ጋብዘንዎታል።

መግቢያ: በነፃ

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥

Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute

Читать полностью…

Tikvah-University

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የዋንጫ ተሸላሚዎች 👏

በ2017 ዓ.ም ከወሎ ዩኒቨርሲቲ የሰርጅካል ነርሲንግ ትምህርት ክፍል ተመራቂው ተማሪ ፋንታሁን ስመኘው ከአጠቃላይ ተመራቂዎች አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.959 በማምጣት የሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የፐብሊክ ሄልዝ ትምህርት ክፍል ተመራቂዋ ተማሪ ያብስራ አማረ ከሴት ተማሪዎች አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.955 በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን ከ1 ሺህ በላይ ተማሪዎች ማስመረቁ ይታወቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በ 10 ሳምንታት ፣ ተፈላጊ ይሁኑ!

HaHuMuya ባዘጋጀው የክረምት ኮርስ በሳምንት 3ቀን ብቻ እየተማሩ በ2 ወር ከ15 ቀን ውስጥ የሰርተፊኬት ባለቤት ይሁኑ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን ይደውሉ +251988007773/75/05 ወይም በአድራሻችን መገናኛ ወደ ሾላ በሚወስደው መንገድ ግሬስ ሲቲ ሞል አጠገብ ሲሳይ ፕላዛ 3ኛ ፎቅ መምጣት ይችላሉ!

@hahujobs | @hahujobs_bot
HaHuJobs, ለሀገር ልጅ በሀገር ልጅ!


#HaHuJobs #HaHuMuya #summerclass #summercourse #skillup #trainings #skills #careergoals

Читать полностью…

Tikvah-University

በአዲስ አበባ በ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 88.8 በመቶ የሚሆኑት ማለፋቸውን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በወሩ መጀመሪያ የተሰጠውን ፈተና ከወሰዱ 70,525 ተማሪዎች መካከል 88.8 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት በማምጣት ማለፋቸውን የቢሮው ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

ዘንድሮ በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ 20 ተማሪዎች መካከል 13ቱ በእቴጌ መነን የልጃገረዶች እና በገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤቶች የተማሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በ2016 ዓ.ም ያለፉ ተማሪዎች 78.9 በመቶ እንደነበር ያስታወሱት ኃላፊው፤ በከተማ አስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በየዓመቱ መሻሻል እያሳየ ነው ብለዋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ1700 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሐግብሮች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 32 የህክምና ዶክተሬት እና 32 የስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በ2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 86% የሚሆኑት ማለፋቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትጉቼ ጉሌ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በአዲስ አበባ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል።

የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 3 እና 4/2017 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 194 የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠቱ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% እንዲሆን ወስኗል።

በከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም 70,525 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተናን ወስደዋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🚀 ቤት-ዋይፋይ መጥቷል!

እጅግ ፈጣኑ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ቤት-ዋይፋይ አገልግሎት በኮዬ ፈቼ፣ ቡልቡላ እና አያት ኮንዶሚኒየሞች ተጀምሯል! በቀጣይም ወደ ሁላችሁም ሰፈር እየመጣን ስለሆነ በትዕግስት ይጠብቁን!

#SafaricomEthiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በጊምቢ እና በሻምቡ ካምፓሶች ያስተማራቸውን 536 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ጊምቢ ካምፓስ 360 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ እና ስድስት ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ በአጠቃላይ 366 ተማሪዎችን አስመርቋል።

በተመሳሳይ የዩኒቨርሲቲው ሻምቡ ካምፓስ 161 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ ስምንት ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም አንድ ተማሪ በሦስተኛ ዲግሪ በአጠቃላይ 170 ተማሪዎችን አስመርቋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

በአዲስ አበባ ከተማ ከ51 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ ይወስዳሉ።

በከተማዋ የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

ተፈታኞቹ በቀን፣ በማታ እና በርቀት መርሐግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ እንዲሁም የመከላከያ እና የግል ተፈታኞች መሆናቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ዲናኦል ጫላ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ሁሉም የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን እንደሚወስዱ የገለፁት ኃላፊው፤ ተማሪዎቹ ፈተናውን በኦንላይን በትክክል እንዲወስዱ የሚያስችል ልምምድ እንደተሰጣቸው ገልፀዋል።

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል። ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የሁለት ወር የክረምት ስልጠና!
25% ቅናሽ 5 ቀን ቀረው
!

ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን። 

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 ስልጠና የሚጀመረው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ነው።

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1:
ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#SamaraUniversity

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 768 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በማታ እና ክረምት መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

የእንሰሳት ህክምና ትምህርት ክፍል ተመራቂው ዶ/ር አብዱ ኢብራሒም አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.94 በማምጣት የሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የሕግ ትምህርት ክፍል ተመራቂዋ ሜሮን ክንፈ አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.87 በማምጣት የሜዳሊያ እና የወርቅ ሀብል ተሸላሚ ሆናለች።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#MizanTepiUniversity

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ምስኮች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 638 ተማሪዎች በሚዛን አማን ካምፓስ ዛሬ አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በግብርናና ተፈጥሮ ሀብት፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጆች እና በህግ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ትናንት 249 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን በቴፒ ካምፓስ ማስመረቁ ይታወቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

37 A+ ያሳካችው ተመራቂ

ፈቲሃ አህመድ ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል በዛሬው ዕለት ተመርቃለች።

ከአጠቃላይ ተመራቂዎች አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 4.00 እና 37A+ በማምጣት የሁለት ዋንጫዎች ተሸላሚ ሆናለች።

የ2017 ዓ.ም የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ውጤት ተሸላሚዋ ፈቲሃ፤ ይህን ውጤት ለማሳካት ከቤተሰቦቿ ጀምሮ ብዙ ዋጋ እንደተከፈለቀት ገልጻለች። እንደሷ ያሉ እህቶቿ ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ምክሯን ለግሳለች።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#DebreBerhanUniversity

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ39 የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 1359 ተማሪዎች አስመረቀ።

ከተመራቂዎቹ 251ዱ የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…
Subscribe to a channel