#ETA
ከውጭ ሀገር ላገኙት የትምህርትና ስልጠና ማስረጃ በኢትዮጵያ ብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ተቃኝቶ የአቻ ግመታ የምስክር ወረቀት ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለማግኘት ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶችን ባለሥልጣኑ ይፋ አድርጓል።
ለመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃዎች (Bachelor’s Degree)፣ ለሁለተኛ ዲግሪ (Master’s Degree) እንዲሁም ለሦስተኛ ዲግሪ (Ph.D. Degree) የትምህርት ማስረጃ የአቻ ግመት ለማሠራት የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና
25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.
የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ እና ዳታቤዝ (Computer Programming and Database) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!
✍️ ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
✍️ C++, Java እና Python ፕሮግራሞች በ Advanced Level በጋራ የሚሰጡበት
✍️ ፕሮጀክቶችን እየሠሩ የሚሰለጥኑበት
✍️ ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#ቢያስፈልግዎ
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥና የአቻ ግመታ ለማግኘት ከሙያ ብቃት ምዘና የተያያዙ መረጃዎችን ግልፅ አድርጓል።
➻ እስከ 2009 ዓ.ም መጨረሻ ባለው ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያ ዲግሪዎን ተምረው የጨረሱ ከሆነ ያለ ብቃት ምዘና የትምህርት ማስረጃዎን ማረጋገጥ ይችላሉ።
➻ በ2008 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርትዎን የጀመሩ ከሆነ፥ ዲግሪዎን ከማረጋገጥዎ በፊት የደረጃ አራት የሙያ ምዘና ማቅረብ ይኖርብዎታል። በመማር ላይ እያሉ ያገኙት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት/COC/ ተቀባይነት ይኖረዋል።
➻ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ የሚቀርቡ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬቶች ተማሪው የመጀመሪያ ዲግሪውን ለመማር ከመመዝገቡ በፊት የተጠናቀቁ መሆን አለባቸው፡፡ #ETA
@tikvahuniversity
#RemedialExam
የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከዛሬ ግንቦት 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት ይሰጣል።
ፈተናው በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና በሦስት ክፍለ ጊዜ ይሰጣል።
@tikvahuniversity
በመውጫ ፈተና ውጤት ምክንያት 90 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተዘግተዋል። - ትምህርት ሚኒስቴር
የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ ባወጣው መመሪያ መሠረት፣ 90 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚያስፈትኗቸው ተማሪዎች 75 በመቶ ያህሉን ማሳለፍ ባለመቻላቸው መዘጋታቸው ተሰምቷል፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ደኤታ ኮራ ቱሹኔ ይህን ያሉት፥ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ባዘጋጀው የአፍሪካ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዓለም አቀፍ ጉባዔ መድረክ ላይ ነው።
"መመሪያው ከተላለፈ በኋላ ራሳቸው ላይ ዕርምጃ የወሰዱ ተቋማት አሉ፡፡ በተለይ ከግሎቹ 90 ያህል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተዘግተዋል፡፡ አብዛኞቹ መመሪያውን ካዩ በኋላ ራሳቸውም እየዘጉ ናቸው" ብለዋል፡፡
ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እስካሁን የተዘጋ ባይኖርም ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተቋማት እንዳሉም ሚኒስትር ደኤታው ተናግረዋል፡፡ ተዘግተዋል የተባሉት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሲያስተምሩ የነበሩ ቢሆኑም ስማቸው አልተጠቀሰም፡፡
"የእኛ ሥራ ሔዶዶ መዝጋት ሳይሆን፥ ተቋማቱ ያሉበትን ሁኔታ መግለፅና መማር ለሚፈልጉ ዜጎች ለውሳኔ እንዲረዳቸው ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ ነው" ያሉት ሚኒስትር ደኤታው፤ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የወጡ መመሪያዎችን በማየት ብቻ በራሳቸው ከገበያ የወጡ ተቋማት መኖራቸውንም ገልፀዋል፡፡ #ሪፖርተር
@tikvahuniversity
#DebarkUniversity
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ከ570 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው ሦስት ዘመናዊ የመምህራን መኖሪያ አፓርትመንቶችን አስመርቋል።
መኖሪያ ቤቶቹ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑ የተቋሙ መምህራንን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አስማማው ዘገየ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
መኖሪያ ቤቶቹ አጠቃላይ 216 ክፍሎች ሲኖሯቸው ባለሦስት፣ ባለሁለት እና ባለአንድ መኝታ ሆነው የተሠሩና የሳሎን፣ የመኝታ ቤት፣ የማብሰያ፣ የመታጠቢያ እና የመፀዳጃ ክፍሎች እንደተሟላላቸው ተገልጿል።
ግንባታዎቹ የመምህራንን የቤት ችግር ከመቅረፍ ባሻገር ምቹ የማስተማሪያ ሁኔታ ይፈጥራል ተብሏል።
@tikvahuniversity
#AmazonFashion #አማዞንፋሽን
🕴የሙሉ ልብስ ኪራይ እና ሽያጭ ከአማዞን!
🔔 እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ!
ሙሉ ልብስ ኪራይ ከ1500 ብር ጀምሮ
ሙሉ ልብስ ሽያጭ ከ6000 ብር ጀምሮ
ለተመራቂ ተማሪዎች እና ለሚዜዎች የሚሆኑ ሱፎች፣ ሸሚዞ፣ ጫማዎች፣ ከረባቶች በብዙ አማራጭ ያገኛሉ! ይምጡና መርጠው ይውሰዱ!
አድራሻ፦
ፒያሳ Down Town ህንጻ ምድር ላይ
ለበለጠ መረጃ፦
0919339250 / 0911072936
የ Amazon Fashion ቻናልን ይቀላቀሉ 👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w
በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች የሙያ ብቃት የጽሑፍ ምዘና ተሰጠ።
የጽሑፍ ምዘናው በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በ10 የምዘና ጣቢያዎች ተሰጥቷል።
የሙያ ብቃት የጽሑፍ ምዘናው መምህራኑ በተመረቁበት የትምህርት አይነት እና የሚያስተምሩበትን የክፍል ደረጃ መሰረት አድርጎ በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
በዛሬው ምዘና ከ9,700 በላይ የሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀውን ፈተና ወስደዋል።
ለጽሑፍ ምዘናው የተቀመጠውን የማለፊያ ነጥብ የሚያመጡ ተመዛኞች በቀጣይ የማህደረ ተግባር ምዘና እንደሚሰጣቸው ከአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ያሳያል።
@tikvahuniversity
የመምህራን የሙያ ብቃት ምዘና
የመምህራን የሙያ ብቃት ምዘና ዛሬ ግንቦት 23/2017 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ ይሰጣል፡፡
የአንደኛ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።
ምስል፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና!
25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም
የዓለም አቀፍ ግብይት (Import and Export Business) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አሰራሮች የሚተነተኑበት
👉 በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች የሚሰጥ
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#WerabeUniversity
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ከ3ኛ-5ኛ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተከታታይ መርሐግብር ተማሪዎች የሁለተኛ ሴሚስቴር ምዝገባ የሚካሔደው ግንቦት 25 እና 26/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።
በተጠቀሱት ቀናት ምዝገባ ማድረግ የማትችሉ ተማሪዎች ረቡዕ ግንቦት 27/2017 ዓ.ም ብቻ በቅጣት በቅጣት መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል።
(ተጨማሪ የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)
@tikvahuniversity
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎቹ ከቀጣሪ ተቋማት ጋር የሚገናኙበት የመጀመሪያ የሥራ አውደ ርዕይ አዘጋጅቷል፡፡
አውደ ርዕዩ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ግንቦት 25 እና 26/2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ይካሔዳል፡፡
በአውደ ርዕዩ ላይ 24 ያህል ተቋማት እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ)፣ የግል ባንኮች እና ሌሎች አምራች ኩባንያዎች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡
ዕጩ ተመራቂዎቹ በሥራ አውደ ርዕዩ ላይ ጠንካራ ተሳትፎ እንዲያደርጉ፣ ቀጣሪዎችን በብቃት እንዲያሳምኑና ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር መልካም ግንኙነትን መፍጠር እንዲችሉ አጠቃላይ ገለፃ በዩኒቨርሲቲው ዛሬ አርብ ግንቦት 22/2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው አዲሱ የመመረቂያ አዳራሽ ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
@tikvahuniversity
#DebreTaborUniversity
አዲስ የተመደቡት የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሥራ ጀምረዋል።
በቅርቡ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመደቡት ሰለሞን አበጋዝ (ዶ/ር) የሥራ ርክክብ ያደረጉ ሲሆን፤ ከዩኒቨርሲቲው የማኔጅመንት አባላት ጋር ትውውቅ አካሒደዋል።
አነጋግረኝ ጋሻው (ዶ/ር) የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን ላለፉት ዓመታት ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል።
ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሪፎርም አካል የሆነ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ለውጥ እና ዝውውር ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።
@tikvahuniversity
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በበይነ መረብ ለሚፈተኑ ተፈታኞች የቴክኒካል ድጋፍ የሚሰጥ ቡድን ተቋቁሟል።
በበይነ መረብ ፈተና ለመውሰድ እየተዘጋጁ የሚገኙ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ማንኛውንም ድጋፍ በመጀመሪያ በትምህርት ቤታቸው ቀጥሎም በመፈተኛ ማዕከላት ካሉ የትምህርት አመራር እና ቴክኒክ ድጋፍ ሰጪዎች ማግኘት እንደሚችሉ ይታወቃል።
ተጨማሪ ድጋፍ ለተፈታኝ ተማሪዎቹ የሚሰጥ ቴክኒካል ቡድን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል።
ዘጠኝ አባላት በውስጡ የያዘው ቴክኒካል ቡድኑ፤ በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተከፋፍሎ የተደራጀ ነው።
(የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ቡድኑን ድጋፍ ለማግኘት ከላይ የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ።)
@tikvahuniversity
ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይዘጋጁ!
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
ለሀገር አቀፍ ፈተናው እየተዘጋጁ ነው?
ተፈታኝ ተማሪ ከሆኑ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ለፈተናው በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችሉ ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ።
በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጁ የቲቶርያል ቪዲዮዎችን ለማግኘት 👇
https://examinfo.moe.gov.et/guides
@tikvahuniversity
#TVTI
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የገበያ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ አዳዲስ ፕሮግራሞች ሊከፍት ነው፡፡
አዲስ የሚጀመሩ የስልጠና መስኮች፦
➫ Bio-Medical Technology
➫ Coal Mining Technology
➫ Finishing Construction Works
➫ Plastic Technology
➫ Horticulture
➫ Poultry
➫ Electric Vehicle
➫ Leather and Leather products Technology
በተጨማሪም Emerging Skills ተብለው በተለዩ መስኮች ላይ የስርዓተ-ስልጠና ተዘጋጅቶ፥ በአጫጭር ወይም/እና በመደበኛ ፕሮግራሞች ስልጠና እንደሚጀመር ተገልጿል።
@tikvahuniversity
#RemedialExam
77 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች የሪሚዲያል ፈተና እየወሰዱ ነው። - ትምህርት ሚኒስቴር
በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታቸውን ለተከታተሉ 77 ሺ ለሚሆኑ ተማሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ የማጠቃለያ የሪሚዲያል ፈተና መሠጠት መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
የሪሚዲያል ፈተናው በ41 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተዘጋጁ 64 የፈተና ማዕከላት መሠጠት መጀመሩን በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ኢዶሳ ተርፋሳ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል ብቻ ከ25 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ 3,528 ተማሪዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ መሆናቸውን ተገልጿል፡፡
ፈተናው ከግንቦት 25-30/2017 ዓ.ም ለአምስት ቀናት ይሰጣል። በኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት ፈተናው አርብ ግንቦት 29/2017 ዓ.ም የማይሰጥ መሆኑ ታውቋል፡፡ #MoE
@tikvahuniversity
የ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ መርሐግብር (Remedial Program) ፈተና እየተሠጠ ነው።
ፈተናው ከዛሬ ግንቦት 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ለአምስት ቀናት ይሰጣል። በኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት ፈተናው አርብ ግንቦት 29/2017 ዓ.ም የማይሰጥ መሆኑ ታውቋል፡፡
የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ግምገማ ከ100% ከማዕከል ብቻ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል፡፡
ምስል፦ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የልጆች የክረምት ስልጠና (25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.)
👉 ስልጠናው ዕድሜያቸው ከ 7-18 ዓመት ላሉ ልጆች የሚሰጥ
👉 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሠሩ የሚሰለጥኑበት
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
የስልጠና ዓይነቶች፦
👉 Computer Programming and Website Development
👉 AI and Robotics
👉 Graphic Design, Video Editing and Animation
👉 Art (Film Acting, Writing and Modeling)
👉 Painting, Drawing and Sculpture
👉 Language and Basic Computer
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
በዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊነት ህግጋት ላይ ትኩረት ያደረገው 8ኛው ሀገር አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች አሸናፊነት አጠናቀዋል፡፡
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሁለተኛነት እንዲሁም የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
የምስለ ችሎት ውድድሩ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ቤት እና የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ትብብር የተዘጋጀ ነው።
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ጥሩ የክርክር ጽሁፍ አቅራቢ ዘርፍ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪ የሆነችው ተማሪ ንያማል ቲቢትሀ ጥሩ ተናጋሪ በሚል ዘርፍ ልዩ ተሸላሚ ሆናለች፡፡
አሸናፊዎች በአፍሪካ ደረጃ ኬኒያ ናይሮቢ ላይ በሚካሄደው አህጉራዊ፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊነት ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡
@tikvahuniversity
እስከ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለም እንዲሁም ዘመኑ ያፈራቸውን የላብራቶሪና የስቱዲዮ እቃዎች በማሟላት ምዝገባ ጀምረናል።
ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!
የብዙ ዓመት ልምድ እና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!
ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ያለው ሰርተፊኬት ይውሰዱ!
🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Fullstack Web app development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯 Foreign & Local Languages
አድራሻ
#1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ) (0991929303)
#2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (2ኛው ሊፍት) (0991929304)
#3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ (0991926707)
ለኦንላይን ስልጠና፦ 0910317675
Telegram: /channel/topinstitutes
TokTok: topinstitute" rel="nofollow">https://Tiktok.com/@topinstitute
Facebook: https://www.facebook.com/Topinstitutes
የመምህራን የሙያ ብቃት ምዘና ዛሬ ግንቦት 23/2017 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ ተሰጥቷል፡፡
የአንደኛ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘናውን ወስደዋል።
ምዘናው መምህራኑ በተመረቁበት የትምህርት አይነት እና የሚያስተምሩበትን የክፍል ደረጃ መሰረት አድርጎ በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ከ9,700 በላይ ለሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የጹሑፍ ምዘና ይሰጣል፡፡
ምዘናው ዛሬ ግንቦት 23/2017 ዓ.ም በአስር የምዘና ጣቢያዎች ከጠዋት 2፡30 ጀምሮ ይከናወናል ተብሏል፡፡
በከተማዋ በሚገኙ የግል የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ምዘናውን ይወስዳሉ።
ምዘናው ለመምህራን እና ለትምህርት ቤት አመራሮች የሚሰጠው በሚያስተምሩት ትምህርትና በተመረቁበት የትምህርት ዘርፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ምዘናው በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የሚሠጥ ይሆናል፡፡ ፈተናው በሃገር አቀፍ ደረጃ በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ ነው።
@tikvahuniversity
#AmazonFashion #አማዞንፋሽን
🕴የሙሉ ልብስ ኪራይ እና ሽያጭ ከአማዞን!
🔔 እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ!
ሙሉ ልብስ ኪራይ ከ1500 ብር ጀምሮ
ሙሉ ልብስ ሽያጭ ከ6000 ብር ጀምሮ
ለተመራቂ ተማሪዎች እና ለሚዜዎች የሚሆኑ ሱፎች፣ ሸሚዞ፣ ጫማዎች፣ ከረባቶች በብዙ አማራጭ ያገኛሉ! ይምጡና መርጠው ይውሰዱ!
አድራሻ፦
ፒያሳ Down Town ህንጻ ምድር ላይ
ለበለጠ መረጃ፦
0919339250 / 0911072936
የ Amazon Fashion ቻናልን ይቀላቀሉ 👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w
#MockExam
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በኦንላይን የሚወስዱ ተማሪዎች #ሞዴል ፈተና በተለያዩ ተቋማት ተሰጥቷል።
#ሞዴል ፈተናው ለሁለት ቀናት እንዲሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባዘጋጀው መርሐግብር መሠረት፤ በርካታ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞቹ የኦንላይን ልምምድ እንዲያገኙ አድርገዋል።
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ ዘንድሮ 150 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ፈተናውን በብይነ መረብ ይወስዳሉ።
@tikvahuniversity
እስከ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለም እንዲሁም ዘመኑ ያፈራቸውን የላብራቶሪና የስቱዲዮ እቃዎች በማሟላት ምዝገባ ጀምረናል።
ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!
የብዙ ዓመት ልምድ እና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!
ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ያለው ሰርተፊኬት ይውሰዱ!
🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Fullstack Web app development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯 Foreign & Local Languages
አድራሻ
#1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ) (0991929303)
#2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (2ኛው ሊፍት) (0991929304)
#3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ (0991926707)
ለኦንላይን ስልጠና፦ 0910317675
Telegram: /channel/topinstitutes
TokTok: topinstitute" rel="nofollow">https://Tiktok.com/@topinstitute
Facebook: https://www.facebook.com/Topinstitutes
#AASTU
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ Smart City Development የማስተርስ ፕሮግራም ለመጀመር የስርዓተ ትምህርት ግምገማ አካሒዷል።
በስርዓተ ትምህርት ግምገማው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ገምጋሚዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ስርዓተ ትምህርቱ በዩኒቨርሲቲው እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ በጋራ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
ፕሮግራሙ እጅግ እየዘመነ ለመጣው የከተማ ልማት ፍላጎቶችና ፈተናዎች ምላሽ መስጠት የሚችል ሁለንተናዊ ክህሎት ያለው ባለሙያ ለማፍራት ያስችላል ተብሏል።
ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሲሆን፤ በሀገሪቱ ስማርት ከተሞች ለመገንባት የሚደረረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተገልጿል።
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና 25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም
የኮምፒውተር ጥገና እና ኔትዎርኪንግ (Computer Maintenance and Networking) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና
👉 የሶፍትዌር ጥገናን አካቶ የሚሰጥ
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
የበለጠ ይጠብቁ ...
ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#ModelExam
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በኦንላይን ለሚወስዱ ተማሪዎች #ሞዴል ፈተና በተለያዩ ቦታዎች እየተሰጠ ነው፡፡
#ሞዴል ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት እንዲሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መርሐግብር ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡
ሞዴል ፈተናው መልቀቂያ ፈተናውን በሁለት ዙር በኦንላይን የሚወስዱ ተማሪዎች አስቀድመው በተለያዩ የመፈተኛ ጣቢያዎች በመገኘት ልምምድ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
ምስል፦ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
@tikvahuniversity
#ModelExam
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሞዴል ፈተና መሰጠት ጀምሯል፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2017 ዓ.ም በበይነ መረብ ለሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ለሁለት ቀናት የሚቆይ #ሞዴል ፈተና አዘጋጅቷል፡፡
ፈተናው ዛሬ መሰጠት የጀመረ ሲሆን፤ በጠዋት እና ከሰዓት መርሐግብር የሚከናወን ይሆናል፡፡
የትምህርት አመራርና መምህራን እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተሳካ የሞዴል ፈተና እንዲኖርና በሂደቱም ተፈታኞቻችን ከሲሰተሙና ከፈተና ማዕከላቱ ጋር በአግባቡ እንዲተዋወቁ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ ዘንድሮ 150 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ፈተናውን በብይነ መረብ ይወስዳሉ።
@tikvahuniversity