#AmazonFashion #አማዞንፋሽን
🕴የሙሉ ልብስ ኪራይ እና ሽያጭ ከአማዞን!
🔔 እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ!
ሙሉ ልብስ ኪራይ ከ1500 ብር ጀምሮ
ሙሉ ልብስ ሽያጭ ከ6000 ብር ጀምሮ
ለተመራቂ ተማሪዎች እና ለሚዜዎች የሚሆኑ ሱፎች፣ ሸሚዞ፣ ጫማዎች፣ ከረባቶች በብዙ አማራጭ ያገኛሉ! ይምጡና መርጠው ይውሰዱ!
አድራሻ፦
ፒያሳ Down Town ህንጻ ምድር ላይ
ለበለጠ መረጃ፦
0919339250 / 0911072936
የ Amazon Fashion ቻናልን ይቀላቀሉ 👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w
#RemedialExam
የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከግንቦት 25-30/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
መርሐግብሩ እንደሚያሳየው ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ ግንቦት 25/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጠው የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና ይጀመራል፡፡
በኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት ፈተናው አርብ ግንቦት 29/2017 ዓ.ም የማይሰጥ መሆኑን መርሐግብር ያሳያል፡፡
ፈተናው ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጠው የእንግሊዝኛ ትምህርት ፈተና እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡
የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ግምገማ ከ100% ከማዕከል ብቻ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል፡፡
@tikvahuniversity
እስከ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለም እንዲሁም ዘመኑ ያፈራቸውን የላብራቶሪና የስቱዲዮ እቃዎች በማሟላት ምዝገባ ጀምረናል።
ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!
የብዙ ዓመት ልምድ እና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!
ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ያለው ሰርተፊኬት ይውሰዱ!
🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Fullstack Web app development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯 Foreign & Local Languages
አድራሻ
#1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ) (0991929303)
#2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (2ኛው ሊፍት) (0991929304)
#3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ (0991926707)
ለኦንላይን ስልጠና፦ 0910317675
Telegram: /channel/topinstitutes
TokTok: topinstitute" rel="nofollow">https://Tiktok.com/@topinstitute
Facebook: https://www.facebook.com/Topinstitutes
ከ1500 በላይ በኢትዮጵያ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች ከመኖሪያ ፈቃድ ክፍያ ጋር በተያያዘ ችግር እንደገጠማቸዎ ተገለፀ፡፡
በቀን 10 ዶላር የነበረው የመኖሪያ ፈቃድ ክፍያ ወደ 30 ዶላር ማደጉ በርካታ የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች የገንዘብ እጥረት እንዲገጥማች አድርጓል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሰጠው ስኮላርሺፕ የትምህርት እና ማረፊያ ወጪዎችን ብቻ የሚሸፍን መሆኑ የተማሪዎቹን ተጋላጭነት እንደጨመረው የአዲስ ፎርቹን ዘገባ ያሳያል፡፡
ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በጂኦሎጂ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀው ሞሰስ አኪይ በቀላሉ ወደቤተሰቦቹ እንደሚመለስ አስቦ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከ3 ሺህ ዶላር በላይ ባልተከፈለ የኢሚግሬሽን ቅጣት ምክንያት አሁንም ከኢትዮጵያ ሳይወጣ ይገኛል፡፡ ምግብ እና መኖሪውንም በጓደኛው ቤት አድርጓል፡፡
በቅርቡ የሚመረቁ 200 የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች ተመሳሳይ የመኖሪያ ፈቃድ ክፍያ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪ የሆነው ዳንኤል ድዮክ ይገልጻል፡፡ ይህም ተመራቂዎቹ በኢትዮጵያ እንዲቆዩ የሚያስገድዳቸውና ተጋላጭነታቸውን የሚጨምረው መሆኑን ጠቁሟል፡፡
ተማሪዎቹ ቅጣቱ እንዲነሳላቸው እና ወደሀገራቸው መመለስ እንዲችሉ የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ እና የኢትዮጵያ መንግሥትን ድጋፍ ቢጠይቁም ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በቅርቡ ለ500 የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል በመስጠት የተቀበለች ሲሆን፤ ትምህርት ሚኒስቴር 20 ሚሊዮን ብር በመመደብ የተማሪዎቹን የቪዛ ወጪ መሸፈኑ ተሰምቷል ይህም በተቋሙ በጀት ላይ ጫና የፈጠረ መሆኑ ታውቋል፡፡ #Fortune
@tikvahuniversity
የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ነገ ግንቦት 20/2017 ዓ.ም መደበኛ የትምህርት ቀን እንደሆነ ገልጿል።
ሁሉም ትምህርት ቤቶች ዝግ እንዳይሆኑና መደበኛ የትምህርት እንቅስቃሴ እንዲቀጥል ቢሮው በክልሉ ለሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ባስተላለፈው መልዕክት አሳስቧል።
@tikvahuniversity
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሚያዘጋጀው 4ኛ ዙር ሀገር አቀፍ የሳይበር ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ እሑድ ግንቦት 24/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል።
በ4ኛው ዙር የሰመር ካምፕ ፕሮግራም ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ልዩ ታለንት ያላቸው ታዳጊዎች ለመመልመል ዝግጅት መጠናቀቁን በአስተዳደሩ የሳይበር ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር ቢሻው በየነ ገልፀዋል።
የ2017 ዓ.ም የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ቻሌንጅ ፕሮግራም ምዝገባ እየተካሔደ ሲሆን፤ ፍላጎት ያላችሁ እስከ ግንቦት 24/2017 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።
ለሰመር ካምፕ ፕሮግራሙ የተለዩ መስኮች፦
- ሳይበር ደህንነት
- ሳይበር ዴቨሎፕመንት
- ኢምቤድድ ሲስተም
- ኤሮስፔስ
ባለ ልዩ ተሰጥኦ ከሆኑ ይመዝገቡ 👇 https://talent.insa.gov.et
@tikvahuniversity
#HawassaUniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 7ኛ ዙር ዓለም አቀፍ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና (IELTS) ፈተና ሰጥቷል፡፡
ፈተናውን ለመውሰድ የተመዘገቡ በተለይ በሀዋሳ እና አካባቢዋ የሚኖሩ ተፈታኞች ለሁለት ቀናት የተሰጠውን ምዘና ወስደዋል፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ IELTS ፈተና ማዕከል በየሦስት ወሩ የIELTS ፈተና የሚሰጥ ሲሆን፤ ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባ በኦንላይን በብሪቲሽ ካውንስል ድረ-ገጽ ይከናወናል፡፡ ፈተናው በወረቀት የሚሰጥ ሲሆን፤ ተፈታኞች በአካል በዩኒቨርሲቲው መገኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 8ኛ ዙር ዓለም አቀፍ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና (IELTS) ፈተና ነሐሴ 01/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ ምዝገባው ሲጀመር የምናሳውቃችሁ ይሆናል፡፡
@tikvahuniversity
#ጥቆማ
የአውሮፕላን አብራሪነት ስልጠናዎን በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ይከታተሉ።
በዩኒቨርሲቲው የ Commercial Pilot License ፕሮግራም የሚሰጡ ስልጠናዎች፦
- Multi Crew Pilot License
- Commercial Pilot License
- Private Pilot License (PPL)
- Dispatcher Training
ለማመልከት 👉 https://eau.edu.et
ለተጨማሪ መረጃ 👇
Email: etauinfo@ethiopianairlines.com | eaainfo@ethiopianairlines.com
Phone: +251115174600 / 8598
@tikvahuniversity
#DireDawaUniversity
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ፌስቲቫል ተካሔደ።
የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር መመስረት የቀድሞ እና የአሁን ተማሪዎችን እና ዩኒቨርሲቲውን በማቀራረብ እንዲሁም ድጋፎችን በማሰባሰብ የጎላ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል።
በዕለቱ የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር መመስረቻ ሰነድ (By-law) ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፤ አምስት አባላት ያሉት አመቻች ኮሚቴ ተቋቁሞ ሥራ ጀምሯል።
ኮሚቴው በዋናነት የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር መመስረቻ ሰነድ አዘጋጅቶ ማፅደቅ፣ አባላትን ማሰባሰብ እና ቀጣዩን ፌስቲቫል ከዩኒቨርሲቲው ጋር በትብብር የማዘጋጀት ኃላፊነት ተሰጥቶታል።
በፌስቲቫሉ ላይ በድሬዳዋ ከተማ በግል የኮንስትራክሽን ድርጅት ሥራ ላይ የተሰማራው ወጣት ኢንጂነር ሳቢት በድሩ የ2018 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው አልሙናይ አምባሳደር በመሆን ተመርጧል።
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ1999 ዓ.ም የመማር ማስተማር አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወቃል።
@tikvahuniversity
#MoH
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በAnesthesia ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የጽሁፍ ፈተና ያለፋችሁና የተግባር ፈተና (OSCE) ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ ተፈታኞች፥ የተግባር ፈተናው ግንቦት 22/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።
በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርብችኋል።
ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ ወደ ፈተና ማዕከል መግባት አይፈቀድም።
ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ማዕከል ሲሔድ ሲስተሙ የሚሰጠውን QR Code ያለው የፈተና መግቢያ /ስሊፕ/ Print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ አይችልም ተብሏል።
ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ አይፈቀድም፡፡
የተፈታኞች ሙሉ ስም እና የፈተና ማዕከል ለማየት 👇
https://drive.google.com/file/d/1L1x3jJrmZrhOTzCWpecAi0LtM-mcVzAw/view?usp=sharing
@tikvahuniversity
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።
መንግሥት ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የ12ኛ ክፍል ሀገረ አቀፍ ፈተናን ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ በማድረግ ፈተናውን ሲሰጥ ቆይቷል።
ይህም የፈተና ስርቆትና ኩረጃ እንዲቀንስ ማድረጉን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢቢሲ ተናግረዋል።
ዘንድሮ ከ608 ሺህ በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል።
ሀገር አቀፍ ፈተናው በወረቀት እና በበይነ መረብ የሚሰጥ ሲሆን፤ ፈተናውን በተሳካ መልኩ ለመስጠት የትምህርት ተቋማት የቁሳቁስ እና ሌሎች ዝግጅቶችን አጠናቀው ተማሪዎችን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
ፈተናውን በብይነ መረብ የሚፈተኑ 150 ሺህ ተማሪዎች በየትምህርት ቤታቸው ልምምድ በማድረግ ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
@tikvahuniversity
#SalaleUniversity
አዲስ የተመደቡት የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሥራ ጀምረዋል።
አዲሱ ተሿሚ ፈየራ ዲንሳ (ዶ/ር) የትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች በተገኙበት ከቀድሞው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት የሥራ ርክክብ ፈፅመዋል።
ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ ከዩኒቨርሲቲው ካውንስል ጋር በተለያዩ ተቋማዊ ጉዳዮች ምክክር አድርገዋል።
ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ገናናው ጎፌ (ዶ/ር) ከሐምሌ 2009 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ስምንት ዓመታት የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግለዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሪፎርም አካል የሆነ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ለውጥ እና ዝውውር ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።
@tikvahuniversity
#AmazonFashion #አማዞንፋሽን
🕴የሙሉ ልብስ ኪራይ እና ሽያጭ ከአማዞን!
🔔 እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ!
በ6 ሺህ፣ በ7 ሺህ እና በ13 ሺህ ብር ብቻ!
ለተመራቂ ተማሪዎች እና ለሚዜዎች የሚሆኑ ሱፎች፣ ሸሚዞ፣ ጫማዎች፣ ከረባቶች በብዙ አማራጭ ያገኛሉ! ይምጡና መርጠው ይውሰዱ!
አድራሻ፦
ፒያሳ Down Town ህንጻ ምድር ላይ
ለበለጠ መረጃ፦
0919339250 / 0911072936
የ Amazon Fashion ቻናልን ይቀላቀሉ 👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w
#ጥቆማ
5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠናን ለመከታተል ይመዝገቡ።
ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ባሉበት ሆነው ይውሰዱ።
የስልጠና ዘርፎች፦
► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ
► አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፋንዳሜንታልስ
ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/
በተሰጠው ስምንት ሳምንት ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ፥ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይበረከትልዎታል።
@tikvahuniversity
በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አገልግሎት ለማግኘት የምትሔዱ ተገልጋዮች ከዛሬ ግንቦት 15/2017 ዓ.ም ጀምሮ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባችኋል።
የፋይዳ መታወቂያ የሌላቸው ተገልጋዮች ከዛሬ ጀምሮ በተቋሙ የማይስተናገዱ በመሆኑ የሚጠበቅባችሁን ቅድመ ሁኔታ አሟልታችሁ እንድትቀርቡ ባለሥልጣኑ አሳስቧል።
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና 25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም
የጋዜጠኝነት ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆች
👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት እና የዶክመንተሪ ዝግጅት
👉 የሞባይል ጋዜጠኝነት እና የ YouTube Journalism አካቷል፡፡
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
ሁለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኢትዮጵያን ወክለው በዓለም አቀፉ የቻይና ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ ውድድር ሊካፈሉ ነው፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሰልጠና ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከቅድስት ማሪያም ዩኒቨርሰቲ በተውጣጡ 14 ተማሪዎች መካከል የቻይና ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ የተማሪዎች ዓመታዊ ውድድር ተካሒዷል።
በአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዓመት የቻይና ቋንቋ ተማረ የሆነው ማንደፍሮ ስመኘው ውድድሩን በአንደኝነት ማሸነፉ ታውቋል።
በውድድሩ ከፍተኛውን ውጤት በማስመዝገብ አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡት የአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኢትዮጵያን በመወከል በቻይና በሚደረገው ዓለም አቀፍ የቻይና ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ ውድድር (International Chinese Language and Arts Competition / "Chinese Bridge") ተካፋይ ይሆናሉ ተብሏል።
@tikvahuniversity
#ETA
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ሚሽከን ኮሌጅ ላይ አስፈላጊው የህግ እርምጃ እንዲወሰድበት ጠየቀ፡፡
ባለሥልጣኑ ከዚህ ቀደም በኮሌጁ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ የትምህርት ተቋሙ ተግባራዊ ባለማድረጉ የህግ እርምጃ እንዲወሰድበት መጠየቁ ታውቋል፡፡
ሚሽከን ኮሌጅ በዋና ማዕከሉ አዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ማለትም በባሌ ሮቤ፣ ሀዋሳ፣ አርባምንጭ፣ ሳውላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ጋምቤላ፣ ጊምቢ፣ ጅማ፣ ሆሳዕና፣ ነቀምቴ፣ ቴፒ፣ ጀግጅጋ፣ ቻግኒ እና ባህር ዳር ቅርንጫፎቹ በቅድመ-ምረቃ ደረጃ ከሐምሌ 2004 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2007 ዓ.ም ፈቃድ ባገኘባቸው ከተሞች እና የትምህርት መስኮች በርቀት መርሐግብር ሲያስተምር መቆየቱን ባለሥልጣኑ አስታውሷል፡፡
በፈፀመው የህግ ጥሰት ምክንያት ማስተማሩን አንዲያቋርጥ ተደርጎ እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ የተቀበላቸውን ተማሪዎች እንዲያስጨርስና በህጋዊ አግባብ የተመረቁ ተማሪዎችን መረጃ ፈቃድ ወዳለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በማዘዋወር ለባለሥልጣኑ ሪፖርት እንዲያደርግ በተደጋጋሚ መጠየቁን ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡
ይሁን እንጂ "ኮሌጁ ከባለሥልጣኑ የተወሰነበትን ውሳኔ ተግባራዊ ባለማድረግ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ተሰማርቶ ዜጎች ላይ ሁለንተናዊ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ" ከዚህ ተግባሩ እንዲቆጠብ እና የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት መስጠት እንዲያቆም አስፈላጊው የህግ እርምጃ እዲወሰድበት ባለሥልጣኑ ለሁሉም ክልላዊ መንግሥታት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤቶች፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ጽ/ቤት፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቨል ሰርቪስ ኮሚሽን እና ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ከ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት በጻፈው ሰርኩላር ጠይቋል፡፡
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና 25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም
የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Advanced Graphic + Video Editing + Motion Graphic + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ነገ ግንቦት 20/2017 ዓ.ም መደበኛ የትምህርት ቀን እንደሆነ ገልጿል።
ሁሉም ትምህርት ቤቶች ዝግ እንዳይሆኑና መደበኛ የትምህርት እንቅስቃሴ በተለመደው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መቀጠል እንዳለባቸው ቢሮው በአስተዳደሩ ስር ለሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ባስተላለፈው መልዕክት አሳስቧል።
@tikvahuniversity
#AAEB
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች በነገው ዕለት (ግንቦት 20/2017 ዓ.ም) መደበኛ የመማር መስተማር ሥራ የሚቀጥል መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡
@tikvahuniversity
#AmazonFashion #አማዞንፋሽን
🕴የሙሉ ልብስ ኪራይ እና ሽያጭ ከአማዞን!
🔔 እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ!
በ6 ሺህ፣ በ7 ሺህ እና በ13 ሺህ ብር ብቻ!
ለተመራቂ ተማሪዎች እና ለሚዜዎች የሚሆኑ ሱፎች፣ ሸሚዞ፣ ጫማዎች፣ ከረባቶች በብዙ አማራጭ ያገኛሉ! ይምጡና መርጠው ይውሰዱ!
አድራሻ፦
ፒያሳ Down Town ህንጻ ምድር ላይ
ለበለጠ መረጃ፦
0919339250 / 0911072936
የ Amazon Fashion ቻናልን ይቀላቀሉ 👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና 25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም
የድረ-ገጽ እና የሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 ፕሮግራሚንግ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ
👉 በተግባር ድረ ገጾችን እና ሞባይል መተግበሪያዎችን እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
እስከ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለም እንዲሁም ዘመኑ ያፈራቸውን የላብራቶሪና የስቱዲዮ እቃዎች በማሟላት ምዝገባ ጀምረናል።
ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!
የብዙ ዓመት ልምድ እና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች!
ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ያለው ሰርተፊኬት ይውሰዱ!
🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Fullstack Web app development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯 Foreign & Local Languages
አድራሻ
#1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ) (0991929303)
#2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (2ኛው ሊፍት) (0991929304)
#3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ (0991926707)
ለኦንላይን ስልጠና፦ 0910317675
Telegram: /channel/topinstitutes
TokTok: topinstitute" rel="nofollow">https://Tiktok.com/@topinstitute
Facebook: https://www.facebook.com/Topinstitutes
#ETA
የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃዎን ማረጋገጫ አገልግሎት ለማግኘት ሊያሟሏቸው የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎችን ከተያያዘዎ ምስል ይመልከቱ።
በምስሉ ላይ የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች ካሟሉ በኋላ የሁሉንም ማስረጃዎች አንድ ኮፒ ስካን በማድረግ ባሉበት ሆነው በበይነ መረብ https://neta.gov.et በመጠቀም ማመልከት ይችላሉ።
@tikvahuniversity
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና 25% ቅናሽ እስከ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም
ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀምራል።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
ሰላም ሚኒስቴር በአምስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው 13ኛ ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ስለጠና ተጀምሯል።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ መቱ ዩኒቨርሲቲ፣ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ እና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 13ኛ ዙር ስልጠና የሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው።
5 ሺህ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ለ22 ቀናት በሚሰጠው 13ኛ ዙር ስልጠና እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
ሰላም ሚኒስቴር ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማሳተፍ በሥነ ምግባር፣ በክሕሎት እና በሥራ ፈጠራ ግንዛቤ የሚያዳብር ስልጠና በመስጠት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በማሰማራት የብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
@tikvahuniversity
#DireDawaUniversity
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ፌስቲቫል ተካሒዷል።
በፌስቲቫሉ ላይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር የመመስረቻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ማኅበሩ በይፋ ተመስርቷል።
@tikvahuniversity
8ኛ ዙር የኢንቴሪየር ዲዛይን (Interior Design) ስልጠና በፒያሣ ካምፓስ ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 16/2017 ዓ.ም ይጀምራል።
👉 Sketch-Up, Revit, Rhino, 3D Max እና Lumion ሶፍትዌሮችን በአንድ ላይ
👉 ከንድፈ ሀሳብ እና ሶፍትዌር ስልጠና በተጨማሪ በተግባር በወርክሾፕ የሚሰጥ ስልጠና
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#HaramayaUniversity
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በአንድ የፒ.ኤች.ዲ.፣ በአምስት የማስተርስ እና በአንድ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርት መስጠት ለመጀመር የስርዓተ ትምህርት የውጭ ግምገማ አካሒዷል።
አዲስ የሚከፈቱ ፕሮግራሞች፦
- PhD in History of Ethiopia and the Horn;
- MA in Culture and Heritage Studies,
- MA in Teaching English as a Foreign Language,
- MA in Teaching Afan Oromo,
- MA in Afan Oromo Linguistics,
- MA in Afan Oromo Literature;
- BA in Political Science and International Relations (PSIR).
ፕሮግራሞቹ በ2018 የትምህርት ዘመን ወደ ትግበራ ይገባሉ ተብሏል።
@tikvahuniversity