#MoE
በዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ውጤት በተከታታይ ሦስት ጊዜ ከ25 በመቶ በታች በሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል። - ትምህርት ሚኒስቴር
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር በተወያዩበት ወቅት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) እንዳሉት፥ "ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማድረግን ዋና ተግባራቸው አድርገው" ሊሠሩ ይገባል።
በዚህም በዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ውጤት በተከታታይ ሦስት ጊዜ ከ25 በመቶ በታች ካስመዘገቡ በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲዎች በተፈጥሮ የተሰጡ የአካባቢው ፀጋዎች ላይ ራዕይ ይዘው መሥራት እንደሚገባቸው አንስተዋል።
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በማዕድን ላይ ሰፊ ምርምር በማድረግ ሀገርን የሚጠቅም ሥራ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
@tikvahuniversity
#EthiopianAviationUniversity
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የአቪዬሽን ሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 974 ተማሪዎች አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው 43 የአውሮፕላን አብራሪዎች፣ 448 የበረራ መስተንግዶ፣ 184 የጥገና ዘርፍ፣ 44 የሆቴል ኦፕሬሽን እና 255 የኮሜርሻል ዘርፍ ሙያተኞችን አስመርቋል።
ተመራቂዎቹ ከኢትዮጵያ፣ ቻይና እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
@tikvahuniversity
Artificial Intelligence and Data Science ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።
👉 ከፍተኛ ልምድ ባላቸው መምህራን የሚሰጥ ስልጠና
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#ጥቆማ
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ "የኢትዮጵያ ሚና በዓለም አቀፍ ግንኙነቶች፡ ዲፕሎማሲ፣ አካባቢያዊ መሪነት እና የውጭ ፖሊሲ" በሚል ጭብጥ ላይ የሕዝባዊ ገለጻ መድረክ አዘጋጅቷል፡፡
የመድረክ ተናጋሪዎች፦
➫ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
ዲፕሎማት እና የሕ/ተ/ም/ቤት አባል
➫ አምባሳደር ቶፊቅ አብዱላሂ (ዶ/ር) ዲፕሎማት እና የሕ/ተ/ም/ቤት አባል
➫ ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር
መድረኩ ቅዳሜ ግንቦት 02/2017 ዓ.ም ጠዋት 2:30 በዩኒቨርሲቲው ሪሶርስ ማዕከል አዳራሽ ይካሔዳል።
@tikvahuniversity
#ETA
ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመዉጫ ፈተና ለመውሰድ ብቁ የሆኑ ዕጩ ተፈታኞች መረጃን እንዲልኩ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ጠይቋል፡፡
በመሆኑም ተቋማቱ ፈቃድ በተሰጣቸው ትምህርት መስኮች፣ ትምህርት ደረጃ፣ መርሐግብር እና ካምፓስ በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ዕጩ ምሩቃንን ዝርዝር መረጃ ከዛሬ ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 10/2017 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንዲልኩ አሳስቧል፡፡ (መረጃውን የመላኪያ ቅጽ ከላይ ተያይዟል፡፡)
@tikvahuniversity
#MoE
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ 50 ሺህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ከደረጃ በታች ናቸው፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር
ከደረጃ በታች የሆኑ ትምህርት ቤቶችን ለማሻሻልና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር ፕሮግራሞችና ጥራት ማሻሻያ ኃላፊ ዳዊት አዘነ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡
በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ እስካሁን ከ7,900 በላይ የቅድመ መደበኛ፣ 1ኛ ደረጃ እና 2ኛ ደረጃ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን የገለፁት ኃላፊው፤ የ29,900 ትምህርት ቤቶች እድሳትና ጥገና ሥራ መከናወኑን ገልፀዋል፡፡
@tikvahuniversity
በM-PESA ሩቁም ቅርብ ነው!
ከውጭ ሀገር ገንዘብ በM-PESA ስንቀበል 10% ስጦታ እና 1ጊ.ባ ኢንተርኔት ተጨማሪ አሁኑኑ እናግኝ! ቪዛ፣ ማስተርካርድ ወይም አሜክስ ካርድ በመጠቀም በካሽ ጎ በኩል እንላክ።
በምንዛሬ ተመን
1 USD = 143 ብር
ካሽ ጎን ይህን ሊንክ ተጠቅመን ማውረድ እንችላለን፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo
ገንዘብዎን በዳሽን ባንክ ዕለታዊ ምንዛሬ ያግኙ + 10% ስጦታ
#MPESAEthiopia #MPESASafaricom
#AASTU
በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በኒውክለር ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ለመጀመር የባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርጓል።
ዩኒቨርሲቲው ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከቻይናው Tsinghua ዩኒቨርሲቲ እና ከዓለም አቀፉ የአተሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ተወካዮች ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጉን ገልጿል።
ውይይቱ በፕሮግራሙ ስርዓተ ትምህርት፣ የባለሙያዎች ስልጠና እና አስፈላጊ መሰረተልማቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር ተብሏል።
ስምምነት ከተፈፀመ በኋላ በኒውክለር ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም መስጠት እንደሚጀመር ተገልጿል።
@tikvahuniversity
እንኳን ለላብ አደር ሠራተኞች ቀን አደረሳችሁ። መልካም የዕረፍት ቀን ይሁንላችሁ!
የበለጠ ይጠብቁ ...
ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#WolaitaSodoUniversity
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተገነባውና 20 ኪሎዋት የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም ያለው የባዮ-ጋዝ ፕሮጀክት ተመርቋል።
የባዮ-ጋዝ ማብለያ ፕሮጀክቱ 300 ሜ.ኪ. የማብላላት አቅም ያለው ሲሆን፤ የዩኒቨርሲቲውን የምግብ ማብሰል ሂደት ሙሉ በሙሉ በባዮ-ጋዝ ሲስተም ለመተካት የሚያስችለ ነው ተብሏል፡፡
የኤሌክትሪክ ሃይል ከተመረተ በኋላ የሚቀረው የባዮ-ጋዝ ተረፈ ምርት፣ የአፈር ማዳበሪያ ለማምረት እንደሚያስችል ተገልጿል።
@tikvahuniversity
#Reminder
የፋይዳ መታወቂያ አውጥተዋል?
በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ተፈታኞች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ሊያወጡ እንደሚገባ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።
የመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባውን በጊዜ በማድረግ የፋይዳ መታወቂያዎን ይያዙ።
@tikvahuniversity
Entrepreneurship, Leadership & Business Management ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!
👉 የሽያጭ መንገዶች እና ቢዝነስ ፕሮፖዛል አዘገጃጀት ብቃትን የሚያገኙበት
👉 ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በተግባር የሚሰጥበት
👉 በተጨማሪ የቢዝነስ አመራር እና ሥራ ፈጠራ ስልጠናን አካቷል
👉 ለመክፈት የሚያስቡትን ቢዝነስ ከስልጠና እስከ ማማከር አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና የተመቻቸለት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#ScholarshipTip
ለ University of Padua Scholarship 2025-26 ያመልክቱ!
የፓድዋ ዩኒቨርሲቲ የ2025-26 ስኮላርሺፕ ሙሉ ወጪዎ ተሸፍኖ በጣልያን ሀገር ትምህርትዎን እንዲከታተሉ የሚያስችል ነው፡፡
ነጻ የትምህርት ዕድሉ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በማስተርስ ደረጃ የሚሰጥ ሲሆን፤ የየትኛውንም ሀገር ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
አርብ ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም
ለማመልከት 👉 https://apply.unipd.it/
@tikvahuniversity
#ጥቆማ
ማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሚሰጣቸውን ነጻ የኦንላይን ኮርሶች ይውሰዱ!
'Introduction to Computer Science and Programming Using Python' ኢንስቲትዩቱ ያለምንም ክፍያ ከሚሰጣቸው የኦንላይን ስልጠናዎች መካከል አንዱ ነው፡፡
በዚህ ስልጠና የ Computation ፅንሰ ሃሳብ፣ Python Programming Language፣ ቀላል አልጎሪዝሞች፣ ዳታ ስትራክቸር እና ሌሎችም ተካተዋል፡፡
በነጻ በመመዝገብ ግንቦት 20/2017 ዓ.ም የሚጀምረውን የኦንላይን ስልጠና ይከታተሉ፡፡
ይመዝገቡ 👇
https://t.co/14aqyJYwXu
@tikvahuniversity
3ኛ ዙር የኮምፒውተር ጥገና እና ኔትዎርኪንግ (Computer Maintenance and Networking) ስልጠና በመገናኛ ካምፓስ የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 18/2017 ዓ.ም ይጀምራል።
👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
የበለጠ ይጠብቁ ...
ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Hackathon Alert! Are you ready to test your cyber skills on a next-gen, military-grade cyber range? 💥Join the CYBER RANGES Hackathon and choose your league:
🛡️ Expert League – Elite Blue & Red teams from top organizations and countries
⚔️ Advanced League – Pen testers and defenders from leading cybersecurity teams
🎯 Foundation League – Individuals eager to assess and level up their skills
Open to participants worldwide – from Africa to Asia, Europe to the Americas
Whether you're a student, a security pro, business, or academic institution, this is your chance to learn, train, test, and prove your digital resilience.
Sign up now, select your league, and let the cyber battle begin.
Register here: https://shorturl.at/oTC09
Don’t miss out—top performers will receive prestigious awards and recognition.
#ETEX #ETEX2025 #DigitalEthiopia #TechForAfrica #EthiopiaTech
#DigitalTransformation #CyberRanges #Hackathon2025 #CyberSecurityChallenge #CyberResilience #BlueTeam #RedTeam
#BahirDarUniversity
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ መርሐግብሮች ያሰለጠናቸውን 333 ተማሪዎች አስመርቋል።
ተመራቂዎቹ 64 በሁለተኛ ዲግሪ፣ 89 በስፔሻሊቲ፣ 2 በሰብ ስፔሻሊቲ እና 178 በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።
@tikvahuniversity
#AAUBookFair
17ኛው ዓመታዊ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመፅሐፍት አውደ ርዕይ ማክሰኞ ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም ይከፈታል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ የተዘጋጀው አውደ ርዕዩ፤ እስከ ግንቦት 04/2017 ዓ.ም ለስምንት ቀናት ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።
ቦታ፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ
@tikvahuniversity
እስከ ሚያዝያ 30/2017 ዓ.ም በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለም እንዲሁም ዘመኑ ያፈራቸውን የላብራቶሪና የስቱዲዮ እቃዎች በማሟላት ምዝገባ ጀምረናል።
ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!
የብዙ ዓመት ልምድ እና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች በመሰልጠን ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ያለው ሰርተፊኬት ይውሰዱ!
🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Fullstack Web app development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯 Foreign & Local Languages
አድራሻ
📍 መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929303
📍 ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሁለተኛውን ሊፍት) ☎️ 0991929304
📍 ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707
Telegram: /channel/topinstitutes
TokTok: topinstitute" rel="nofollow">https://Tiktok.com/@topinstitute
Facebook: https://www.facebook.com/Topinstitutes
#ScholarshipTip
ለ Fulbright African Research Scholars Program 2026-27 ያመልክቱ!
የዩኒቨርሲቲ መምህር ነዎት? በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ምርምርዎትን መስራት ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ ዓመታዊው Fulbright African Research Scholars Program 2026-27 ለርስዎ የሚሆን የተምህርት ዕድል ነው።
ፕሮግራሙ ሁለተኛ/ሦስተኛ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ ዲግሪ ያላቸው ምሁራን ማኅበራዊ ሳይንስ እና ስነ-ሰብን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች እጅግ ዘመናዊ ምርምር እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው።
አመልክተው ተቀባይነት ካገኙ የጉዞ ወጪዎ የሚሸፈን ሲሆን፤ የመኖሪያ ወጪ የገንዘብ ድጋፍ እና ወርሃዊ ክፍያ የሚያገኙ ይሆናል።
የማመልከቻ ጊዜ 👇
እስከ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም
ለማመልከት 👇
https:apply.iie.org/fvsp2026
በፕሮግራሙ ሁለት አይነት Grants ያሉ ሲሆን፤ ለእያንዳንዱ ግራንት የሚያስፈልግ የትምህርት ደረጃ እና ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahuniversity
6ኛ ዙር የጋዜጠኝነት ስልጠና በፒያሣ ካምፓስ ነገ ቅዳሜ ሚያዚያ 25/2017 ዓ.ም ይጀምራል።
👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆች ስልጠና
👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት እና ዶክመንተሪ ዝግጅት
👉 የሞባይል ጋዜጠኝነት እና YouTube Journalism አካቷል
👉 በተጨማሪም የሥራ ላይ ስልጠና ተመቻችቷል፡፡
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#ElectricalEngineeringExitExam
የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ዕጩ ተመራቂዎች በሰኔ ወር ከሚወሰዱት የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ ጥያቄያቸውን አድርሰውናል።
በጉዳዩ ዙሪያ ከትምህርት ሚኒስትቴር ጋር የተነጋገረው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ብዛት ላይ ምንም አይነት ለውጥ አለመደረጉን አረጋግጧል።
ከዚህ በፊት እንደነበረው የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ከ6 ኮርሶች የሚዘጋጅ መሆኑ ታውቋል።
በፈተናው የኮር ኮምፒተንስ እና ብሉ ፕሪንት ላይ ለውጥ እንደማይኖር የህብረቱ ፕሬዝዳንት ሐየሎም ስዩም ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግሯል።
@tikvahuniversity
🌐 እጅግ ፈጣን ማይፋይ በአዲስ ዋጋ! ሊያውም ከጉርሻ ጋር 🤗
💨⚡️ እስከ 6 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም!
🍰 ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር!
ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡️
#SafaricomEthiopia
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በቤተ-ሙከራ አገልግሎት ላይ የሚታዩበትን ክፍተቶች ሊቀርፍ እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ።
በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመስክ ምልከታና ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ጋር ውይይት አድርጓል።
የቋሚ ኮሚቴው ም/ሰብሳቢ ቤተልሔም ላቀው (ዶ/ር) የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ በተጨማሪ፤ ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎች በሚሰጣቸው ሌሎች አገልግሎቶች ላይ ለውጥ ለማምጣትና የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ሊሠራ ይገባል ብለዋል።
በተለይም ጥራት ያለውና በተግባር የተደገፈ ትምህርት ለመስጠት በቤተ-ሙከራ አገልግሎት ላይ የሚታዩበትን ክፍተቶች እንዲቀርፍ ጠይቀዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በሽር አብዱላሂ (ዶ/ር) የመምህራንን ብቃት ለማሳደግ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ጨምሮ በተቋሙ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎችን አብራርተዋል።
የቋሚ ኮሚቴው አባላት ከዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሥራዎች በተጨማሪ የአገልግሎት አሰጣጦች እና በዩኒቨርሲቲው እየተሠሩ ያሉ ግንባታዎችን ተመልክተዋል። #HPR
@tikvahuniversity
እስከ ሚያዝያ 30/2017 ዓ.ም በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው ስልጠናዎች በ Advanced Level እና 90% Practical በሆነ ካሪኩለም እንዲሁም ዘመኑ ያፈራቸውን የላብራቶሪና የስቱዲዮ እቃዎች በማሟላት ምዝገባ ጀምረናል።
ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!
የብዙ ዓመት ልምድ እና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች በመሰልጠን ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ያለው ሰርተፊኬት ይውሰዱ!
🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe Photoshop
🎯 Fullstack Web app development
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯 Foreign & Local Languages
አድራሻ
📍 መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929303
📍 ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሁለተኛውን ሊፍት) ☎️ 0991929304
📍 ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707
Telegram: /channel/topinstitutes
TokTok: topinstitute" rel="nofollow">https://Tiktok.com/@topinstitute
Facebook: https://www.facebook.com/Topinstitutes
#ArbaMinchUniversity
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የባዮ-ቴክኖሎጂ መምህርና ተመራማሪ አዲሱ ፈቃዱ (ዶ/ር) የሀገር አቀፍ የፈጠራ ሥራዎች ውድድር አሸናፊ ሆነዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ23ኛ ጊዜ በተከበረው የዓለም አእምሯዊ ንብረት ቀን የፈጠራ ሥራዎች አውደ ርዕይ ላይ በተደረገ የፈጠራ ሥራዎች ውድድር አዲሱ ፈቃዱ (ዶ/ር) 1ኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆነዋል።
በውድድሩ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን የወከሉት አዲሱ (ዶ/ር)፥ የእንሰት ማብላላትና አዘገጃጀት ሂደትን ለማዘመን በሠሯቸው አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች አሸናፊ መሆናቸው ታውቋል።
በውድድሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአእምሯዊ ንብረት ባለቤትነት የተሰጣቸው አሥር የፈጠራ ሥራዎችን ጨምሮ ሌሎች ከ70 የሚበልጡ የፈጠራ ሥራዎች ለውድድር ቀርበዋል።
@tikvahuniversity
ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ቅፅ አዘጋጅቶ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መላኩ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ኃላፊዎች ከትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሸኔ ጋር በመውጫ ፈተና እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል።
በዚህም ልኩ ሰርተፊኬቱ የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ወስደው የማለፍያ ነጥብ ላላመጡ ተማሪዎች ብቻ መሆኑን ገልፀዋል።
የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች አዲሱ ሰርተፊኬት የማይመለከታቸው ሲሆን፤ በፊት ይሰጥ በነበረው ፎርማት እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ከዘንድሮ ጀምሮ ማለትም በሰኔ 2017 ዓ.ም ከሚሰጠው የመውጫ ፈተና አስቀድሞ ሁለም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት #ሞዴል የመውጫ ፈተና በአስገዳጅነት ለተማሪዎቻቸው እንዲሰጡ ይደረጋል ብለዋል።
@tikvahuniversity
ልዩ የበዓል ቅናሹ እንደቀጠለ ነው! የበዓል ሰሞንን ከምንወዳቸው ጋር እየተገናኘን እናሳልፍ! ለቀን፣ ለሳምንት እና ለወር የሚያገለግሉ ያልተገደቡ የዳታ ጥቅሎችን በ50% ቅናሽ አዘጋጅተንላችኋል!
ቅናሹ እስከ ሚያዝያ 27/2017 ዓ.ም ብቻ የሚቆይ ይሆናል!
#SafaricomEthiopia
#Easter
#Furtheraheadtogether
የዩኤስ-ኤክስቼንጅ አልሙናይ በኢትዮጵያ (US-Exchange Alumni of Ethiopia) ሦስተኛ ምዕራፉን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አስጀምሯል፡፡
የድሬዳዋው ቡድን ሥራ መጀመር የበለጠ የዩኤስ-ኤክስቼንጅ አልሙናይ ትስስርና ልውውጥ እንዲኖር የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡
በድሬዳዋ የሚገኙ አለምናይን በመጠቀም የዩኤስ-ኤክስቼንጅ አልሙናይ በኢትዮጵያ ተጨማሪ የልማት፣ የትብብር እና ሜንተርሺፕ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ተገልጿል፡፡
በሀዋሳ እና በጅማ ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ቀደም የዩኤስ-ኤክስቼንጅ አልሙናይ መጀመሩ ይታወቃል፡፡
@tikvahuniversity
#ጥቆማ
የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ!
ብሪቲሽ ካውንስል ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ'IELTS' ፈተና ግንቦት 16/2017 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ይሰጣል፡፡
ሁለት አይነት የ'IELTS' ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) ይሰጣሉ፡፡
ዩኒቨርሲቲው ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉ አመልካቾች ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።
ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/.../dates-fees-locations
ምዝገባ ለማድረግ ስካንድ ፓስፖርት ወይም መታወቂያ እንዲሁም ኢሜይል አድራሻ ያስፈልጋል።
ለበለጠ መረጃ፦
ielts@hu.edu.et / 0925629589
@tikvahuniversity