tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ ግሎባል ውድድርን አንደኛ በመሆን አሸነፉ።

ውድድሩ ከመጋቢት 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ በቻይና ቤጂንግ እና ሼንዘን የቴክኖሎጂ ማዕከሎች ጉብኝትና የተግባር ስልጠናዎች በማካተት እየተካሄደ ይገኛል።

በስድስት ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን ተማሪዎቹን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አሰባስቧል።

በውድድሩ (Huawei’s Tech4Good Global Competition 2025) ከመላው ዓለም ከተውጣጡ 12 ቡድኖች ጋር ተወዳድሯል።

የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ግሎባል አምባሳደር የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ አሲያ ከሊፋም በዝግጅቱ በእንግድነት ተገኝታለች።

ተማሪዎቹ የእንስሳትን ህመሞች አስቀድሞ ለመለየት የሚያስችልና በአርተፊሻል አስተውሎት በጎለበተው ኤርሊ ቬት (EarlyVet) በተሰኘው ፕሮጀክታቸው መወዳደራቸው ተገልጿል።

የፈጠራ ፕሮጀክቱ ከተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) በተለይም ግብ 2 "ዜሮ ርሃብ" እና ግብ 15 "ህይወት በምድር" ከሚለው ጋር የተጣጣመ መሆኑና በግብርናና በእንስሳት ጤና ላይ ያሉ ፈተናዎችን ይፈታል ተብሎ እንደሚታመን በውድድሩ ተብራርቷል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2008 የተጀመረው የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ፕሮግራም በአገር ውስጥ ያለውን ውድድር ከኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚያዘጋጅ ሲሆን፤ ለተሳታፊ ተማሪዎች ከውድድር ባለፈ የሰው ሰራሽ አስተዉሎት (AI)፣ ክላውድ ኮምፒውቲንግ እና ቢግ ዳታን ጨምሮ በሌሎች ቴክኖሎጂዎች ላይ አጠቃላይ ስልጠና የሚወስዱበት ዕድል ያመቻቻል። #MoE

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🚨 Attention influencers with 5,000+ followers! 🌟

Join our exciting competition for a chance to win up to 300,000 Birr by promoting climate action! 🌍💚

Get ready for training to enhance your skills and creativity! Be one of the top 5 impactful posts to win fantastic prizes! 🎉

Make your voice heard and help us make a difference together! 🎤✨

Читать полностью…

Tikvah-University

#AAU #GAT

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ የመግቢያ ፈተና (GAT) ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ ዛሬ ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃቀል።

ለ'GAT' ይመዝገቡ፦
https://Portal.aau.edu.et ይግቡ።
➫ Exam Application የሚለውን ይጫኑ።
➫ Test Taker Registration የሚለውን ቅፅ ይሙሉ።
➫ የፓስፖርት መጠን ፎቶ ያለው ፎቶ ያስገቡ።
➫ Submit የሚለውን ይጫኑ።
➫ ሲስተሙ የሚሰጠዎን መለያ ቁጥር ይያዙ።
➫ ቴሌብር በመጠቀም የምዝገባ ክፍያ 750 ብር ይክፈሉ።
➫ አድሚሽን ቲኬትዎን በማውረድ ፕሪንት ብለው ይያዙ።

🔔 የ'GAT' ፈተና ፊታችን ማክሰኞ ሚያዝያ 7/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

የባለፈው ዓመት የ 'GAT' ውጤት ለዘንድሮ ስለማይሰራ፣ ፈተናውን ባለፈው ዓመት ወስዳችሁ ያለፋችሁ ዘንድሮ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ለመከታተል ፈተናውን በድጋሜ መውሰድ ይኖርባችኋል፡፡

የ 'GAT' ፈተና ካለፋችሁ በኋላ ሰነዶች የማስገቢያ ቀናት ከሚያዝያ 8-10/2017 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ቅበላ ቢሮ፣ ሬጅስትራር ህንጻ ቢሮ ቁ. 203

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🚨 Attention influencers with 5,000+ followers! 🌟

Join our exciting competition for a chance to win up to 300,000 Birr by promoting climate action! 🌍💚

Get ready for training to enhance your skills and creativity! Be one of the top 5 impactful posts to win fantastic prizes! 🎉

Make your voice heard and help us make a difference together! 🎤✨

Читать полностью…

Tikvah-University

#Digital_ID

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ማውጣት ይጠበቅባቸዋል።

ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች እና ሰራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ እንዲይዙ እና የሀገር አቀፍ ፈተናዎችን ደኅንነት ለማስጠበቅ ጠቀሜታ አለው ተብሏል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ኮራ ጡሹኔ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፉት ሰርኩላር፤ በዚህ ዓመት ሰኔ 2017 ዓ.ም ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ሁሉም የግል እና የመንግሥት ዕጩ ተመራቂዎች የፋይዳ መታወቂያ እንደ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠ መሆኑን አስታውሰዋል።

በመሆኑም ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂ ተማሪዎቻቸው የፋይዳ መታወቂያ እንዲያወጡ እንዲያደርጉ እና የተማሪዎቹን የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ቁጥር በኤሜል አድራሻ eyobie2002@yahoo.com በኩል እንዲልኩ አሳስበዋል።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ ማድረግ መጀመራቸው ይታወቃል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ በመሆን ከግንቦት 8-10/2017 ዓ.ም የሚቆይ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖና ኮንፍረንስ ያዘጋጃሉ፡፡

በአይነቱ የመጀመሪያ በሆነው በዚህ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖና ኮንፍረንስ ላይ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎች ጥናታዊ ወረቅት እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል፡፡

ኤክስፖና ጉባኤው ከግንቦት 8-10/2017 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል ይካሔዳል።

🎯 Thematic Areas:

🔹 Cybersecurity in the AI Era
🔹 Cybersecurity in Smart Cities
🔹 Quantum Computing
🔹 Fintech
🔹 Trustworthy AI

Submission Details:

Deadline: April 20, 2025
✅ Acceptance Notification:
April 30, 2025
✅ Submission Mode: Email
✅ Paper Template: IEEE Format

Incentives:
Selected papers will receive special recognition!

Submit your papers: Etexconference@insa.gov.et

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

47ኛ ዙር የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሳ እና በመገናኛ ካምፓስ በምዝገባ ላይ ነን። 

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Advanced Graphic + Video Editing + Motion Graphic + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1:
ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

በአዲስ አበባ ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለው አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር እንዲሆን ተወሰነ፡፡

ውሳኔው በአካባቢው ያሉትን አገልግሎቶች አካቶ የትምህርት፣ የምርምር፣ የዕውቀት እና የባህል ልህቀትን በከተማዋ ለማሳደግ የሚያስችል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ገልጿል፡፡

የምስረታ ዕቅዱ በፕላንና ልማት ቢሮ እና በትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ተጠንቶ የቀረበ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመንደሩ ወስጥ የሚገኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውሳኔው ከፍ ያለ ጥቅም ያስገኝልኛል ያለ ሲሆን፤ በቀጣይ ኮሪደሩ ሲለማ ከዓለም አቀፍ የምርምር ተቋማት፣ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ከአገር ውስጥ አልሚዎች ጋር ለመስራት ምቹ ሁኔታ ይፈጠርልኛል ብሏል፡፡

@tikvauniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

⭐️ የማኅበረሰብ አንቂ ነዎት?
እንግዲያውስ ይህ ውድድር ለእርስዎ ነው!

'አየሩ እየሞቀ ነው!' 'ፀሐይዋ በረታች!' 'ቃጠሎ ሆነ!' ማለት ያዘወተርነው ለምን ይመስልዎታል? ጉዳዩ ያሳስብዎታል?

🔔 ይወዳደሩ!! እስከ 300 ሺህ ብር ይሸለሙ!

የሚያስፈልገው 5 ሺህ እና ከዚያ በላይ ተከታይ ያለው የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂ መሆን ብቻ ነው፡፡

ከዚያ በተከታይ ቁጥር ብዛት የተመረጡ 25 አመልካቾች ስልጠና ይወስዳሉ፡፡

ከስልጠናው በኋላ በሚታወቁበት የሶሻል ሚዲያ ጥራት ያለው፣ ሳቢ እና ማራኪ መልዕክት አስተላልፈው ብዙ ተከታይ በርካታ ላይክ እና ሼር ያገኙ ከ1-5 የወጡ ተወዳዳሪዎች እስከ 300 ሺህ ብር ይሸለማሉ፡፡

1ኛ - ደረጃ 300,000 ብር
2ኛ - ደረጃ 200,000 ብር
3ኛ - ደረጃ 100,000 ብር
4ኛ - ደረጃ 50,000 ብር
5ኛ - ደረጃ 40,000 ብር

በተከታዩ የጉግል ቅጽ አማካኝነት ይመዝገቡ 👇
https://docs.google.com/.../1FAIpQLSdnunm8XYs.../viewform

⏰ ምዝገባው የሚጠናቀቀው 👇
ሚያዝያ 11/2017 ዓ.ም ከለሊቱ 6:00

ይመዝገቡ! ይወዳደሩ! ያሸንፉ!
መልካም ዕድል!!

Читать полностью…

Tikvah-University

በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት "በኢትዮጵያ መልቀቂያ የብሔራዊ ፈተና ውጤት የቅርብ ጊዜ ተለዋዋጭነት ግምገማ" በሚል ርዕስ ለአንድ ዓመት የቆየ ጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል።

ኢንስቲትዩቱ ካቀረባቸው የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦች መካከል፣ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይሰጥ የሚለው ይገኝበታል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የማኅበራዊ ልማትና አካታችነት ማዕከል ኃላፊና ከፍተኛ ተመራማሪ ደሳለኝ አንጭሶ (ዶ/ር)፥ የተማሪዎች ውጤት እንዲቀንስ ካደረጉ ቁልፍ ምክንያቶች መካከል የፈተና አሰጣጥ ስርዓቱ መቀየር በተለይ ከከተሞች ራቅ ካሉ አካባቢዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚመጡ ተማሪዎች ላይ የፈጠረው የስነ-ልቦና ችግር ተጠቃሽ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተፈጠረው የስነ-ልቦና ችግር ምክንያት ጥሩ ውጤት ማምጣት የነበረባቸው ተማሪዎች ውጤት ሳያመጡ መቅረታቸው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

"ተማሪዎች የባዮሜትሪክ መረጃዎች እንዲሞሉ በማድረግ እንዲሁም በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የደኅንነት ካሜራዎችን በመግጠም የቁጥጥር ስራ በመስራት፣ ተማሪዎች ከሚኖሩበት አካባቢ ሳይርቁ ፈተናውን እንዲፈተኑ ትምህርት ሚኒስቴር የረዥም ጊዜ ዕቅድ ይዞ እንዲሠራ" ምክረ ሐሳብ መቅረቡን ገልፀዋል።

የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ማሻሻል እና ከታች ጀምሮ ጥራት ላይ ሊሰራ እንደሚገባ የገለፁት ኃላፊው፤ የትምህርት ቤት አመራሮች ዕውቀትን መሠረት ባደረገ ሁኔታ ሊመደቡ እንደሚገባም ምክረ ሐሳብ መቅረቡን ተናግረዋል።

በማኅበረሰቡ ዘንድ "ትምህርት ምን ያደርጋል" የሚል ዕሳቤ መቀየር ላይ አፅንኦት ሰጥቶ የለውጥ ሥራ መስራት ይገባል የሚለው በጥናቱ የተለየ ምክረ ሐሳብ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ጥናቱ በፀጥታ ችግር ምክንያት የአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችን እንዳላካተተ ተገልጿል። #Reporter

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#TVTI

በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በደረጃ 7 (2ኛ ዲግሪ) ስልጠና ለመከታተል አመልክታችሁ በተቋሙ የተሰጠውን ምልመላ ያለፋችሁ እስከ አርብ ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም ድረስ በኢንስቲትዩቱ በመገኘት ምዝገባ አድርጉ ተብሏል።

የምዝገባ ጥሪው ከየክልሎቻችሁ ተመልምላችሁ የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተፈትናችሁ ያለፋችሁ፣ በግላችሁ የመግቢያ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፋችሁ፣ በኢንስቲትዩቱ ከፍላችሁ ለመሰልጠን የምትፈልጉ እንዲሁም በኢንስቲትዩቱ የነጻ የስልጠና ዕድል ተሰጥቷችሁ የመግቢያ ፈተና ያለፋችሁን ይመለከታል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች፦

➫ የመጀመሪያ ዲግሪ ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ NGAT ውጤት፣
➫ ከሚሰሩበት ተቋም የድጋፍ ደብዳቤ፣
➫ የማመልከቻ ክፍያ ደረሰኝ፣
➫ የቅርብ ጊዜ ሁለት ፎቶግራፍ፣
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ ትራንስክሪፕት በአንድ ወር ውስጥ መቅርብ አለበት።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#JimmaUniversity

በ2017 ዓ.ም ጅማ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ የሚያበቃው ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በመያዝ እስከ አርብ ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም ምዝገባ እንድታደርጉ ተብሏል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

22ኛ ዙር የድረ-ገፅ እና ሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።   

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 ፕሮግራሚንግ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ
👉 በተግባር ድረ-ገፆችን እና ሞባይል መተግበሪያዎችን እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1:
ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#Update

ከሚያዝያ 1-3/2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ አመልካቾች፥ የፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (Orientation) እና የሙከራ ፈተና (Mock Exam) ማክሰኞ መጋቢት 30/2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት የሚሰጥ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#AmboUniversity

በ2017 ዓ.ም አምቦ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ ሚያዝያ 5 እና 6/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ሙሉ የትምህርት ማስረጃ፣ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ፣ የቀድሞ የሥራ ተቋም መልቀቂያ እና ጉርድ ፎቶግራፍ ስካን በማድረግ በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ፖርታል estudent.ambou.edu.et ላይ መጫን ይጠበቅባችኋል፡፡

ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ለአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት በፖ.ሳ.ቁ. 240 ማስላክ ይጠበቅባችኋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውንና የማይመለስ አንድ ኮፒ መያዝ ያስፈልጋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ArsiUniversity

አርሲ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ400 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በስፔሻሊቲ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው 32 ተማሪዎች በስፔሻሊቲ፣ 98 ተማሪዎች በሕክምና ዲግሪ፣ 32 በፋርማሲ ዲግሪ እንዲሁም 242 በድኅረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

4ኛ ዙር የህንፃ ኤሌክትሪክ እና የዲሽ መስመር ዝርጋታ ስልጠና በምዝገባ ላይ ነን!

🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 የሳተላይት ዲሽ መስመር ዝርጋታ በተጨማሪነት የሚሰጥበት 
👉 ከትምህርት ቢሮ የ 'COC' ምዘና የተዘጋጀለት

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ

ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#የፌሎውሺፕ_ጥቆማ

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የ Obstetrics and Gynecology ትምህርት ክፍል ብቃት ያላቸው አመልካቾችን ለ2025 የትምህርት ዘመን ፌሎውሺፕ ፕሮግራም መቀበል ይፈልጋል፡፡

የፌሎውሺፕ ፕሮግራሙ ክፍት የሆነባሀቸው መስኮች
➫ Maternal and Fetal Medicine - ሁለት
➫ Urogynaecology - ሁለት

መስፈርቶች፦


➫ ዕውቅና ካለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በሕክምና የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ያላት
➫ በ'Obstetrics and Gynecology' የሬዚደንሲ ስልጠና ያጠናቀቀ/ያጠናቀቀች
➫ ለሁለት ዓመት በ'Obstetrics and Gynecology' የገለገለ/ያገለገለች
➫ የኮሌጁን የቅበላ ሒደት (የመግቢያ ፈተናን ጨምሮ) ማጠናቀቅ የሚችል/የምትችል
➫ በኢትዮጵያ በ'Gynecology and Obstetrics' ሙያተኝነት የተመዘገበ እና ፈቃድ ያለው/ያላት
➫ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ያለፈ/ያለፈች

የተራዘመው የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ሚያዝያ 10/2017 ዓ.ም

(ስታመለክቱ ልታሟሏቸው የሚገቡ ሰነዶችና ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

6ኛ ዙር የጋዜጠኝነት ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!

👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆች የተካተቱበት
👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት እና ዶክመንተሪ ዝግጅት
👉 የሞባይል ጋዜጠኝነት እና YouTube Journalism አካቷል
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) አካቷል

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1:
ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና እየተሰጠ ይገኛል።

ፈተናው ለሦስት ተከታታይ ቀናት እስከ ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ትናንት ሚያዝያ 1/2017 ዓ.ም ሲሰጥ የነበረው የምዘና ፈተና በቴክኒክ ችግር ምክንያት በተወሰኑ ተቋማት መቋረጡን ሰምተናል።

በዚህም ትናንት የተሰጠውን ፈተና ያልወሰዱ ተመዛኞች ቅዳሜ ሚያዝያ 4/2017 ዓ.ም ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ቀጥሎ በዛሬው ዕለት የፋርማሲ፣ ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ እና ሚድዋይፈሪ ተመዛኞች ፈተናውን እየወሰዱ ነው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

⭐️ የማኅበረሰብ አንቂ ነዎት?
እንግዲያውስ ይህ ውድድር ለእርስዎ ነው!

'አየሩ እየሞቀ ነው!' 'ፀሐይዋ በረታች!' 'ቃጠሎ ሆነ!' ማለት ያዘወተርነው ለምን ይመስልዎታል? ጉዳዩ ያሳስብዎታል?

🔔 ይወዳደሩ!! እስከ 300 ሺህ ብር ይሸለሙ!

የሚያስፈልገው 5 ሺህ እና ከዚያ በላይ ተከታይ ያለው የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂ መሆን ብቻ ነው፡፡

ከዚያ በተከታይ ቁጥር ብዛት የተመረጡ 25 አመልካቾች ስልጠና ይወስዳሉ፡፡

ከስልጠናው በኋላ በሚታወቁበት የሶሻል ሚዲያ ጥራት ያለው፣ ሳቢ እና ማራኪ መልዕክት አስተላልፈው ብዙ ተከታይ በርካታ ላይክ እና ሼር ያገኙ ከ1-5 የወጡ ተወዳዳሪዎች እስከ 300 ሺህ ብር ይሸለማሉ፡፡

1ኛ - ደረጃ 300,000 ብር
2ኛ - ደረጃ 200,000 ብር
3ኛ - ደረጃ 100,000 ብር
4ኛ - ደረጃ 50,000 ብር
5ኛ - ደረጃ 40,000 ብር

በተከታዩ የጉግል ቅጽ አማካኝነት ይመዝገቡ 👇
https://docs.google.com/.../1FAIpQLSdnunm8XYs.../viewform

⏰ ምዝገባው የሚጠናቀቀው 👇
ሚያዝያ 11/2017 ዓ.ም ከለሊቱ 6:00

ይመዝገቡ! ይወዳደሩ! ያሸንፉ!
መልካም ዕድል!!

Читать полностью…

Tikvah-University

#AksumUniversity

በ2017 ዓ.ም አክሱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የስፔሻሊቲ ሬዚደንሲ ተማሪዎች ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የመግቢያ ቀናት ከሚያዝያ 5-8/2017 ዓ.ም መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።

በተጠቀሱት ቀናት አክሱም ከተማ በሚገኘው በዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ግቢ በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ተብሏል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

➫ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስድስት 3×4 ፎቶግራፍ፣
➫ ማንነታችሁ የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ፣
➫ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ወደ ዩኒቨርሲቲው ዋናው ሬጅስትራር ማስላክ።

@tikvauniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በኢትዮጵያ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክፍል ጋር በመተባበር “የአየር ንብረት ብክለት በአፍሪካ ጤና እና ምጣኔ ሀብት ላይ የደቀነው ስጋት” በሚል ጭብጥ ላይ የፓናል ውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

የፓናል ውይይቱ በጉምቱ ምሁራን አቅራቢነትና አወያይነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ ሐሙስ ሚያዝያ 02/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00-12፡00 ሰዓት ይካሔዳል፡፡

በአካል ተገኝተው ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሰው የዙም አድራሻ በቀጥታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

Join Zoom Meeting: https://us06web.zoom.us/j/84982334618...
Meeting ID: 849 8233 4618
Passcode: 831700

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በተካሄደ ስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ በትናንትናው ዕለት ተሸላሚ ሆኗል።

በዚህ ሽልማት የተሰማንን ደስታ እየገለፅን በቀጣይ ከዚህ በበለጠ ውጤታማ ለመሆን የምንተጋ ይሆናል።

የበለጠ ይጠብቁ ...
ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TiktTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ሁነቶች ሊያከብር ነው፡፡

75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ሁነቶች እንደሚከበር የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ዛሬ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

የአልማዝ እዮቤልዩ በዓሉ፤ ዩኒቨርሲቲው ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲነት ከሚያደረገው ሽግግር ጋር መግጠሙን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ ዩኒቨርሲቲው የመጣበትን መንገድና የወደፊት ጉዞውን በሚዘክር መልኩ ለማክበር ዝግጅት መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉ በምርምር ኮንፈረንሶች፣ ኤግዚቢሽን፣ የኪነ-ጥበብ ስራዎች፣ ስፖርታዊ ውድድሮች እንዲሁም በቀድሞ ምሩቃን ሳምንት ዝግጅቶች እንደሚከበር ገልፀዋል፡፡

በሀገሪቱ የመጀመሪያው ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ የመልሶ ማደራጀት ሥራዎችን በማከናወን፣ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ አውጥቶ እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ሰባት አስርት ዓመታት ከ280 ሺህ በላይ ምሩቃንን አፍርቷል፡፡ #ኢፕድ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#WallagaUniversity

በ2017 ዓ.ም ወለጋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ የሚያበቃው ሚያዝያ 6/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች፦

➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ፣
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ ሰርተፊኬት፣
➫ ፕሮፌሽናል የሙያ ፈቃድ
➫ የመልቀቂያ ደብዳቤ ይሰሩበት ከነበረው ተቋም፣
➫ የ NGAT ሰርተፊኬት
➫ ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ለወለጋ ዩኒቨርሲቲ ማስላክ ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

⭐️ የማኅበረሰብ አንቂ ነዎት?
እንግዲያውስ ይህ ውድድር ለእርስዎ ነው!

'አየሩ እየሞቀ ነው!' 'ፀሐይዋ በረታች!' 'ቃጠሎ ሆነ!' ማለት ያዘወተርነው ለምን ይመስልዎታል? ጉዳዩ ያሳስብዎታል?

🔔 ይወዳደሩ!! እስከ 300 ሺህ ብር ይሸለሙ!

የሚያስፈልገው 5 ሺህ እና ከዚያ በላይ ተከታይ ያለው የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂ መሆን ብቻ ነው፡፡

ከዚያ በተከታይ ቁጥር ብዛት የተመረጡ 25 አመልካቾች ስልጠና ይወስዳሉ፡፡

ከስልጠናው በኋላ በሚታወቁበት የሶሻል ሚዲያ ጥራት ያለው፣ ሳቢ እና ማራኪ መልዕክት አስተላልፈው ብዙ ተከታይ በርካታ ላይክ እና ሼር ያገኙ ከ1-5 የወጡ ተወዳዳሪዎች እስከ 300 ሺህ ብር ይሸለማሉ፡፡

1ኛ - ደረጃ 300,000 ብር
2ኛ - ደረጃ 200,000 ብር
3ኛ - ደረጃ 100,000 ብር
4ኛ - ደረጃ 50,000 ብር
5ኛ - ደረጃ 40,000 ብር

በተከታዩ የጉግል ቅጽ አማካኝነት ይመዝገቡ 👇
https://docs.google.com/.../1FAIpQLSdnunm8XYs.../viewform

⏰ ምዝገባው የሚጠናቀቀው 👇
ሚያዝያ 11/2017 ዓ.ም ከለሊቱ 6:00

ይመዝገቡ! ይወዳደሩ! ያሸንፉ!
መልካም ዕድል!!

Читать полностью…

Tikvah-University

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በአንጋፋው ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝነት ጉዞ ዙሪያ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ክፍል ፩ እንድትከታተሉ ጋበዝናችሁ 👇
https://youtu.be/mfR_fLZXYuE?si=pIJXssnk8pBxtDiI

Читать полностью…

Tikvah-University

#WachemoUniversity

በ2017 ዓ.ም ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ የሚካሄደው ሚያዝያ 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች፦

➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስፖንሰር ለተደረጋችሁ)፣
➫ ከ8-12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት እና ከ9-10ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➫ የመልቀቂያ ደብዳቤ ይሰሩበት ከነበረው ተቋም፣
➫ ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ለዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በፖ.ሳ.ቁ. 667 እንዲሁም በኢሜል registrarpos@wcu.edu.et ማስላክ ይኖርባችኋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሕንጻ ቁ. 144

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#Update

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና (EHPLE) ከሚያዝያ 1-3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

እያንዳንዱ ተፈታኝ 200 ጥያቄዎች ይቀርቡለታል፦ 100 ጥያቄዎች በጠዋት መርሐግብር እና 100 ጥያቄዎች በከሰዓት መርሐግብር፡፡

ተፈታኞች ፈተና ማዕከል እንዲደርሱ የሚጠበቀው ጠዋት 1፡30 እና ከሰዓት 7፡00 ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

(የፈተና መርሐግብር፣ የጊዜ ሰሌዳ፣ የሚያስፈልጉ ሰነዶች እንዲሁም ወደ ፈተና ማዕከል ይዞ መምጣት የተከለከሉ ነገሮች እና ሌሎች መረጃዎች ከላይ ተያይዘዋል፡፡)

ለተጨማሪ መረጃ፦
952 ወይም 0115186275 / 0115186276

@tikvahuniversity

Читать полностью…
Subscribe to a channel