tikvahuniversity | Unsorted

Telegram-канал tikvahuniversity - Tikvah-University

308824

Subscribe to a channel

Tikvah-University

🔥 Code. Compete. Conquer!
Safaricom Talent Cloud Capstone Challenge!
🔥

Ready to push your limits? Safaricom Talent Cloud brings to you the Capstone Project. If you are in Addis Ababa, team up and turn your idea into an MVP in just 6 weeks.

💰 Win BIG! 💰
🥇 Grand Prize: ETB 140,000
🥈 Second Place: ETB 85,000
🥉 Third Place: ETB 50,000

🔔 Are you are skilled in one of the following?

● Mobile (Kotlin/Flutter)
● Frontend (React)
● Backend (Java/Node.js)
● Fullstack
● DevOps
● UX/UI
● Product Ownership/Scrum Master

Form Your Dream Team! 🤝
● Assemble your 4–6-member squad and let one person apply, registering everyone.
● Note: All applicants must complete the TestGorilla assessment which will be sent through email!
Guided by expert advisors, you will collaborate, innovate, and compete for the prize.

Apply Here

Deadline: April 09, 2025

Читать полностью…

Tikvah-University

27ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን። 

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1:
ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህሕክምና ኮሌጅ በተለያዩ የጤና መስኮች ያሰለጠናቸውን 312 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በህሕክምና ቅድመ-ምርቃ፣ በስፔሻሊቲ እና በሰብ-ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#HaramayaUniversity

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በአካባቢ ሳይንስ የዶክትሬት ዲግሪ ፕሮግራም ሊጀምር ነው።

የዩኒቨርሲቲው ግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ በአካባቢ ሳይንስ የሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም መስጠት ለመጀመር የውስጥ ስርዓተ ትምህርት ግምገማ አካሒዷል።

የፕሮግራሙ መጀመሩ፥ ከፍተኛ የምርምር ክህሎት ያላቸውን ምሁራን በማፍራት አንገብጋቢ የአካባቢ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የብዝሀ ህይወት እና ዘላቂ የሀብት አያያዝ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር መሰረት አምዴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ኮሌጁ አስፈላጊውን ሒደት በመከተል በግምገማው ወቅት የተሰጡ አስተያየቶችን በማካተት ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከመጋቢት 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ የኦሪጅናል ዲግሪ ህትመት ማመልከቻ መቀበል ጀምሯል፡፡

ኦሪጅናል ዲግሪ እንዲሰራላችሁ የምትፈልጉ አመልካቾች ለዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ጥያቂያችሁን ማቅረብ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ Maxillofacial Surgery ስፔሻሊቲ መርሐግብር አመልካቾችን አወዳድሮ ማስተማር ይፈልጋል።

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ሚያዚያ 08/2017 ዓ.ም

የፈተና ቀን፦ ሚያዚያ 16/2017 ዓ.ም
የምዝገባ ቀን፦ ሚያዚያ 20/2017 ዓ.ም
ት/ት የሚጀምረው፦ ሚያዚያ 30/2017 ዓ.ም

መስፈርቶች፦
➫ ከታወቀ የመንግሥት ተቋም በ Dental Medicine (DDS OR DDM) የመረቀ/የተመረቀች
➫ ሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያለው/ያላት
➫ በጥሩ የጤና ሁኔታ የሚገኝ/የምትገኝ
➫ ዕድሜ ከ40 ዓመት በታች
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ ማምጣት የሚችል/የምትችል

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በተለያዩ የጤና መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች እሑድ መጋቢት 28/2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ያከናውናል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ከUK ገንዘብ በ M-PESA እንቀበል፣ 10% ስጦታ እና 1ጊ.ባ ኢንተርኔት ተጨማሪ አሁኑኑ እናግኝ! ቪዛ፣ ማስተርካርድ ወይም አሜክስ ካርድ በመጠቀም በካሽ ጎ በኩል እንላክ።

በምንዛሬ ተመን
1 GBP = 172 ብር

ካሽ ጎን ይህንን ሊንክ ተጠቅመን እናውርድ 👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo

ገንዘብዎን በዳሽን ባንክ ዕለታዊ ምንዛሬ ያግኙ +10% ስጦታ

#MPESAEthiopia #MPESASafaricom

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የህዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚዎች ፎረም ለሁለት ቀናት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ይካሔዳል፡፡

የሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የህዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚዎች የሚሳተፉበት ፎረም መጋቢት 27 እና 28/2017 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ይደረጋል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#MoH

በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች ፈተና ከሚያዚያ 1-3/ 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ጤና ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

ሚኒስቴሩ የመፈተኛ ጣቢያዎች ዝርዝርን ይፋ አድርጓል። ተፈታኞች የመፈተኛ ጣቢያችሁን መመልከት ትችላላችሁ። (ከላይ ተያይዟል)

ምንሊክ ጤና ሳይንስ ኮሌጂ የመረጣችሁ ተመዛኞች፥ የመፈተኛ ማዕከላችሁ ወደ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተቀየረ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የሰብል መውቂያ እና መፈልፈያ የሠሩ ወጣቶች 👏

ታምራት አለሙ ከሌሎች ሰባት ወጣቶች ጋር በመሆን እንደ በቆሎ፣ ጤፍ፣ ማሽላ እና ሩዝ የመሳሰሉ ሳራማ እና አገዳማ እህሎችን ለመውቃት እና ለመፈልፈል የሚያስችል ማሽን ሰርተዋል፡፡

ማሽኑ በኤሌክትሪክ ወይም በጀነሬተር የመስራት አማራጭን የያዘ ሲሆን፤ በቀላሉ ለማንቀሳቀስ በሚያስችል መልኩ የተሠራ ነው፡፡

Multi-Crop Threshing Machine የተሰኘው ፈጠራው፤ በተለይ አነስተኛ ማሳ ያላቸው አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡

ወጪ ቆጣቢ እና ችግር ፈቺ የሆነው ማሽኑ፤ በኪራይ እና በሽያጭ አማራጮች ለገበያ መቅረቡ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

46ኛ ዙር የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ የፊታችን ሰኞ መጋቢት 29/2017 ዓ.ም በቀን መርሐግብር ይጀምራል።

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Advanced Graphic + Video Editing + Motion Graphic + Digital Marketing በአንድ ላይ
👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ

ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

#HaramayaUniversity

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ኮሌጅ ተማሪዎች ቡድን በአሜሪካ፣ ዋሺንግተን ዲሲ JESSUP የምስለ ችሎት ውድድር ላይ ተሳትፏል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪዎች ማህደር እንደሻው፣ አያንቱ ደቻሳ እና አብዱራዛቅ ነቢ ኢትዮጵያን በመወከል በውድድሩ የተሳተፉ ሲሆን፤ መምህር ወንድሜነህ በየነ እና ሀብታሙ ሲዋያ ተወዳዳሪዎቹን በአሰልጣኝነት መርተዋል።

ተማሪዎቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተወዳዳሪ ቡድኖችን በማሸነፍ በ2025 PHILIP C. JESSUP ዓለም አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር ላይ ለመሳተፍ መቻላቸው ተገልጿል።

JESSUP በዓለም ትልቁ የምስለ ችሎት ውድድር ሲሆን ከመላው ዓለም 700 ከሚሆኑ የሕግ ትምህርት ቤቶች የሚወከሉ ተማሪዎች በውድድሩ ይሳተፋሉ።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🔥 ይጋብዙ፣ ይሸለሙ! 🔥
📣 አሁንም እንደቀጠለ ነው 📣

የቴሌግራም ቻናላችንን ያጋሩ!
💥 ትክክለኛውን ቦታችንን ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ🎁

ከእናንተ የሚጠበቀው የሳፋሪኮም መስመራችሁን በመጠቀም የተጠቀሱትን ቅደም ተከተሎች መተግበር ነው🫰🏽

👉🏽 ያስተውሉ፣ በዕርስዎ ጋባዥነት የሚቀላቀለው ሰው ቁጥር ሲጨምር የሚያገኙት የአየር ሰዓት መጠንም እየጨመረ ይሄዳል። እንዲሁም ተጋባዦቻችሁ ገፁን ከተቀላቀሉ በኋላ “Back” የሚለውን ተጭነው “Check Subscription” እንዲያደርጉ ያሳስቡ 🔥

የቴሌግራም ቻናላችን 👉🏽
/channel/Safaricom_Ethiopia_PLC

የቴሌግራም ቦታችን 👉🏽
/channel/official_safaricomet_bot

መልካም ዕድል 🎁💥

#SafaricomEthiopia #1Wedefit
#FurtherAheadTogether

Читать полностью…

Tikvah-University

#WolaitaSodoUniversity

በ2017 ዓ.ም ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ የሚካሄደው መጋቢት 29 እና 30/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስፖንሰር ለተደረጋችሁ)
➫ ከ8-12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ወረቀት እና ከ9-10ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
➫ የመልቀቂያ ደብዳቤ ይሰሩበት ከነበረው ተቋም
➫ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ሰርተፊኬት
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ለወላይታ ሶዶ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል በፖ.ሳ.ቁ. 200 ማስላክ
➫ ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#Residency_GAT_Registration

በ2017 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተመደባችሁ የሕክምና ስፔሻሊቲ ሬዚደንሲ አመልካቾች የትምህርት ማስጀመሪያ የገለጻ ፕሮግራም ረቡዕ ሚያዝያ 1/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

ገለጻው በዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዳራሽ አስተዳደር ሕንጻ አንደኛ ፎቅ፣ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሚያዝያ 1/2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ይሰጣል።

አመልካቾች ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ ፈተና (GAT) ለመውሰድ መመዘገብ ይኖርባችኋል።

ለ'GAT' ይመዝገቡ፦

https://Portal.aau.edu.et ይግቡ።

➫ Exam Application የሚለውን ይጫኑ።

➫ Test Taker Registration የሚለውን ቅፅ ይሙሉ።

➫ የፓስፖርት መጠን ፎቶ ያለው ፎቶ ያስገቡ።

➫ Submit የሚለውን ይጫኑ።

➫ ሲስተሙ የሚሰጠዎን መለያ ቁጥር ይያዙ።

➫ ቴሌብር በመጠቀም የምዝገባ ክፍያ 750 ብር ይክፈሉ።

➫ አድሚሽን ቲኬትዎን በማውረድ ፕሪንት ብለው ይያዙ።

የ'GAT' ፈተና ከሚያዝያ 6-10/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

መንትዮቹ ተመራቂዎች!

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ሕክምና ኮሌጅ ዛሬ ካስመረቃቸው 312 ተማሪዎች መካከል መንትዮቹ ዶክተሮች ይገኙበታል።

ዶ/ር ኃይማኖት ወልደሩፋኤል እና ዶ/ር ረድኤት ወልደሩፋኤል 🎓 👏

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#ExitExamCertificate

ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ቅፅ አዘጋጅቶ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልኳል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብሔራዊ የቅድመ-ምረቃ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።

በቅድመ-ምረቃ መውጫ ፈተናው የአፈጻጸም መመሪያ መሰረት፥ የመውጫ ፈተና ውጤት በተማሪዎች ሰርተፍኬት (Temporary Degree) ወይም ትራንስክሪፕት ላይ አልፏል (PASS) ወይም ወድቋል (FAIL) በሚል እንዲቀመጥ ሚኒስቴሩ አዟል።

በዚህም የመውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች የሚሰጡ ኮርሶችን ማጠናቀቃቸውን የሚያረጋገጥ ሰርተፊኬት የሚሰጣቸው ሲሆን፤ ጊዜያዊ ዲግሪ የሚሰጠው ተፈታኙ/ተፈታኟ የመውጫ ፈተናውን በድጋሚ ወስዶ/ወስዳ የማለፊያ ነጥብ ሲያስመዘግብ/ስታስመዘግብ ብቻ እንደሚሆን በሰርተፊኬቱ ይገለጻል።

(የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ እና የመውጫ ፈተና የውጤት ሰርተፍኬት ፎርማት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የአይነ ስውራን በትር የሠራው ወጣት 👏

ወጣት ንጉሥ አማረ ዘመናዊ እና ምቹ የሆነ የዐይነ ስውራን መንቀሳቀሻ በትር ሰርቷል፡፡

ዘመናዊ በትሩ ከፊት ያለን ማንኛውም እንቅፋትን በመለየት የማስጠንቀቂያ መልዕክት በድምፅ የሚናገር ነው፡፡ በድምፅ ጥቆማ መስጠቱ ከዚህ በፊት ከተሰሩ በትሮች ልዩ ያደርገዋል፡፡

ፈጠራው ተጠቃሚው በድምፅ አቅጣጫ እንዲቀይር ከማስቻሉ በተጨማሪ የገመድ አልባ የባትሪ ቻርጅ ማድረጊያ ስርዓት ተገጥሞለታል።

መጠቆሚያው ተጠቃሚው ግለሰብ አደጋ ቢያጋትመው ለተጠቃሚው ቤተሰብ ያለበትን ስፍራ የሚያሳውቅ GPS ስርዓት ተገጥሞለታል።

ወደፊት በትሩ ውሃን ለመለየት እንዲችል ይደረጋል የሚለው ወጣቱ፤ ተመጣጣኝ በሆነ 19 ሺህ ብር ዋጋ ለገበያ መቅረቡን ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

2ኛ ዙር መሰረታዊ የኮምፒውተር (Basic Computer) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!

👉 Microsoft Word, Excel, Access, PowerPoint, Publisher እና ሌሎች የኮምፒውተር አጠቃቀሞችን አካቶ የሚሰጥ ስልጠና
👉 ለሁለት ወር የሚቆይ ስልጠና

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ

ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…

Tikvah-University

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የኦንላይን ፈተና እየሰጠ ነው።

ፈተናው ተማሪዎቹ በቀጣይ ለሚወስዱት ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመዘጋጀት የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።

የ2017 ትምህርት ዘመን የሪሚዲያል ተማሪዎች የማዕከል ፈተና ከግንቦት 26-30/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

Capstone Project: Prize Pool EXPLODES! 🚀

You heard right! The Safaricom Talent Cloud Capstone Project is leveling up with a massive prize boost!

💰 Win BIG! 💰

🥇 Grand Prize: ETB 140,000
🥈 Second Place: ETB 85,000
🥉 Third Place: ETB 50,000

🔥 If you are skilled in one of the following:
● Mobile (Kotlin & Flutter)
● Frontend (React)
● Backend (Java & Node.js)
● Fullstack
● DevOps
● UX/UI
● Product Ownership/Scrum Master

Form Your Dream Team! 🤝
● Assemble your 4-6 member squad and let one person apply, registering everyone.
● Don’t you have a group? No problem! We will match you with a team.
● Note: All applicants must complete the assessment which will be sent through email!

Already applied: Check your inbox and spam for an email from TestGorilla to take the assessment

Located in Addis Ababa but haven’t Applied Yet? Apply Here

Deadline: April 09, 2025

💥 Six Weeks. One MVP. Infinite Possibilities! 💥

Читать полностью…

Tikvah-University

#ጥቆማ

የ3ኛ ዲግሪ መምህራን የዝውውር/የቅጥር ዕድል

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በቱሪዝምና ቅርስ አስተዳደር፣ በግብርናና አካባቢ ሳይንስ እንዲሁም በአትሌቲክስ ስፖርት ዘርፎች 3ኛ ዲግሪ ያላቸው መምህራንን ከዩኒቨርሲቲዎች እና ምርምር ተቋማት በዝውውር ወይም በቅጥር ወደ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ማምጣት ይፈልጋል።

በተጠቀሱት የትምህርት ዘርፎች በዝውውር ወደ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለሚሔዱ መምህራን ዩኒቨርሲቲው የመምህራን የመኖሪያ ቤት የሚያዘጋጅ መሆኑን አሳውቋል።

ለማመልከት የሚያስፈልጉ ሰነዶች፦

➫ ማመልከቻ
➫ ሲቪ
➫ የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማስረጃዎች
➫ በተገለፁት የትኩረት መስኮች ዙሪያ ያሳተሟቸው ህትመቶች እና የተሳተፉባቸው ፕሮጀክቶች ዝርዝር

የማመልከቻ ቀን፦
ከዛሬ መጋቢት 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) የሥራ ቀናት

ማመልከቻዎን በኢሜል አድራሻ president@dku.edu.et/asme2000@gmail.com መላክ ትችላላችሁ፡፡

ለበለጠ መረጃ፦ +251585558146

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

ፒስቺሪ አካውንቲንግ ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን! 

👉 ንድፈ ሀሳብን ከተግባር ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 በፒስቺሪ ላይ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institutep

Читать полностью…

Tikvah-University

#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዲጂታል ትምህርት እና ምርምር በተደራጀ መልኩ ለመስጠት የሚያስችል ዘመናዊ የድምጽ እና ምስል ሰቱዲዮ ሥራ አስጀምሯል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ጂኦስፓሺያል ዳታ እና ቴክኖሎጂ ማዕከል ውስጥ የተመረቀው ስቱዲዮው፤ በስትራቴጂክ አጋርነት ከኔዘርላንድሱ ትዌንቴ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተገነባ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስቱዲዮው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የዲጂታል ትምህርት፣ ምርምር እና ማኅበረሰብ ጉድኝትን ለማስፋት ያስችላል ተብሏል፡፡

የስቱዲዮው ሥራ መጀመር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት በመስጠት ቀዳሚ ከሆኑ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ለመሆን የሚያደርገውን ጥረት የሚደግፍ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

🌐 እጅግ ፈጣን ዋይፋይ በአዲስ ቅመም! ሊያውም ከጉርሻ ጋር! 🤗

💨⚡️ እስከ 6 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው ድረስ የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFI ‘ን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም!

🍰 ለ30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር

ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡️

#SafaricomEthiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

#MoE

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ ሊገደዱ ነው።

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።

ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ ጥናት አቅርበዋል።

ውይይት ሲደረግ ነበር።

በዚህም ወቅት በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል።

ላለፉት ዓመታት (እሳቸው በኃላፊነት ከተሾሙ ጀምሮ) ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅተኛ እንዲሆን ካደረጉ መንስዔዎች መካከል፣ የመምህራን ብቃትና የተነሳሽነት ማነስ ተጠቃሽ መሆናቸው ጠቁመዋል።

ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲቻል የተለያዩ ተግበራት እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

'' የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ '' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ " በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህም ሲሆን የተማሪዎቹ መሠረታዊ ወጪ የሚሸፈን እንደሚሆንም አክለዋል።

ይህ አሰራር ለተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።

ተማሪዎች የመምህርነትን ሙያ ተላብሰው በዚያው ወደ ሙያው እንዲያመሩ ዕድል በመፍጠር ለጊዜውም ቢሆን በዘርፉ እየቀነሰ የመጣውን ወደ ሙያው የሚገባ የአስተማሪን ቁጥር ለማሳግ እንደሚረዳም ሚንስትሩ አብራርተዋል።

በቅርቡ በመምህራን ላይ በተደረገ ግምገማ ፣ 100,000 የሚደርስ የመምህራን ዕጥረት መኖሩ መታወቁን የተናገሩት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ አሰራሩ በከፍተኛ ደረጃ ያለውን የመምህራን ዕጥረት እንዲቀንስ የበኩልን እንደሚወጣ አስረድተዋል።

ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎችን ክፍተት ለማስተካከል ከተያዙ ዘርፈ ብዙ የማትጊያ ሥርዓቶች አንዱ፣ መምህራን በአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸውና የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋሙ ለማድረግ፣ " የመምህራን ባንክ " ማቋቋም አንዱ እቅድ መሆኑን አንስተዋል።

ባንኩ " በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባዋል ብለን እንጠብቃለን " ያሉት ሚኒስትሩ፣ በ2019 ዓ.ም ደግም በእርግጠኝነት ወደ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ አሰራር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia

Читать полностью…

Tikvah-University

#TVTI

በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ውስጥ የፋሽን ስልጠና ማዕከል ሊከፈት ነው።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ከማፊ ፋሽን አካዳሚ ባለቤት ዲዛይነር ማህሌት አፈወርቅ (ማፊ) ጋር በኢንስቲትዩቱ ውስጥ የፋሽን ስልጠና ማዕከል ለመክፈት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የፋሽን ማሰልጠኛ ማዕከሉ የአጭር እና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

#የሥራ_ዕድል_ጥቆማ

የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት ብቁ የሕክምና መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ የሥራ መደብ፦ የሕክምና መምህራን
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 10
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ በሕክምና የመጀመሪያ ዲግሪ
➤ የሥራ ቦታ፦ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት

መስፈርቱን የምታሟሉ ባለሙያዎች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የሥራ ቀናት በዩኒቨርሲቲው የሰው ሃብት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 02 በመገኘት ወይም በኦንላይን humanresourcemgt@dadu.edu.et ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

(ዝርዝር የሥራ ማስታወቂያው ከላይ ተያይዟል፡፡)

ለተጨማሪ መረጃ፦ 0575553618

@tikvahuniversity

Читать полностью…

Tikvah-University

የፊታችን እሑድ መጋቢት 28/2017 ዓ.ም የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) የሦስት ወር ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ይጀምራል።

🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!

👉 ስልጠናው በተመረጡ የዩኒቨርሲቲ መምህራን የሚሰጥ ነው።
👉 በስልጠናው ሁሉም በፈተና ላይ የሚመጡ ኮርሶች ላይ ክለሳ ይደረጋል።
👉 ከ1000 በላይ ጥያቄዎችን በመስራት ለፈተናው ብቁ የምትሆኑበት።

☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ

ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

🌟 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት

Telegram: /channel/sagetraininginstitute
TikTok: sage_training_institute" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute

Читать полностью…
Subscribe to a channel